Proverb
stringlengths 4
244
|
---|
ልጅ ሲያባብሉት ያለቅሳል። |
ልጅ ሳለህ አጊጥ፤ ሞል ሳይጋ ሸምት። ልጅ በልጅነት። |
ልጅ በቁንጮ፤ ወተት በጮጮ። ልጅ በጋሜ፤ አረም በጳጉሜ። |
ልጅ በጡት፤ እህል በጥቅምት (ይፋፋል)። |
ልጅ ቢያስብ ምሳውን፤ አዝማሪ ቢያስብ ጠላውን። ልጅ ቢያኮርፍ ቁርሱ ራት ይሆናል። |
ልጅ አባቱን ገደለ ቢለው፥ የእኔ ልጅ እንዳይሰማ አለው። ልጅ አይወልድ፤ እውነት አይፈርድ። |
ልጅ አባቱን፤ አይብ አቱን (ይመስላል)። |
ልጅ እንደ አባቱ፤ ሰው እንደቤቱ። ልጅ እንደ ወለደ፥ በበቅል ሰደደ። ልጅ ከአርጣጣ፤ እህል ከበጣ። ልጅ ከአበጀው፤ አባት ያበላሸው። ልጅ ከአባቱ፤ ሾተል ከአፎቱ። |
ልጅ ከዋለበት፥ ሽማግላ አይውልም። ልጅ ከደረሰ፥ ቤት ፈረሰ። |
ልጅ ከዕውር፤ እህል ከጉራንጉር። (ከዕውር ~ ከአጉል) ልጅ ከወረሰ፥ ቤት ፈረሰ። |
ልጅ ከጦረው፥ ጥርስ የጦረው። ልጅ፥ የቆል ትፋት ያምረዋል። ልጅ የአባቱን፤ ወቄራ የአፎቱን። |
ልጅ የጫረው እሳት፥ ለጎረቤት ይተርፋል። ልጅ ያለ፥ ልጅ አከለ። |
ልጅ ያለ እናት፤ ቤት ያለ ጉልላት ከፍ አይልም። |
ልጅ ያለ እናት፤ ቤት ያለ ጉልላት። |
ልጅ ያቦካው፥ ለራት አይበቃም። ልጅ ያቦካው፥ ለእራት አይሆንም። ልጅ ያቦካው፤ እብድ የነካው። |
ልጅ ይሮጣል እንጂ፥ አባቱን አይቀድምም። ልጅ ይወለዳል ከርጉዝ፤ ላም ይገዚል ከወንዝ። ልጅ ይወለዳል ከቦዝ፤ ላም ይገዚል ከወንዝ። ልጅ ደረሰ፤ ቤት ፈረሰ። |
ልጅ፥ ለእናቷ ምጥ አስተማረች። (ምጥ ~ ምጥን) ልጅ ለወለደው፤ ሙቅ ላሞቀው። |
ልጅም ከሆነ ይገፋል፤ ድንችም ከሆነ ይጠፋል። ልጅቷ፥ ለቤተሰቦቿ ንብ ናት። |
ልጅቱ፥ ለቤተሰቦቿ እንደንብ ናት። ልጅነት ጅልነት። |
ልጅና መስተዋት አይጠገብም። ልጅና ሴት፥ ወደ መሬት። ልጅና ቀራጭ ችግር አያውቅም። |
ልጅና ቄስ፥ በሰው ገንብ ያለቅስ። |
ልጅና አትክልትህን፥ ተጠባበቅ ጎረቤትክን። |
ልጅና እህል፥ እያደር ይበስላል። (ይበስላል ~ ይበስል) ልጅና እሳት፥ ባለቤቱ ያጠፋዋል። |
ልጅና ወረቀት የያውን አይለቅም። |
ልጅና ጉንዳን፥ ኹል ጊዛ እንደተጠቃ ነው። |
ልጅና ጥሬ፥ አይተጣጡም። (አይተጣጡም ~ አይተጣጣም) ልጅና ጦጣ፥ ውሃ(ውን) ይጠጣ። |
ልጅና ጫማ አልጋ ሥር። ልጅና ፊት አይበርደውም። |
ልጅን መርገምና፥ ራስጌ መሽናት ተመልሶ ጉዳት። ልጅን መቅጣት በጡት። |
ልጅን ሲወደ እስከነንፍጡ ነው። ልጅን በጡት፤ እህልን በጥቅምት። |
ልጅን በጡት ከአልጠበቁት፤ እህልን በጥቅምት ከአልቆጠቡት። ልጅን አሳዳጊ፤ እሳትን ውሃ ያጠፋዋል። |
ልጅን ከጡት፤ እህልን ከጥቅምት። ልጡ የተራሰ፤ መቃብሩ የተማሰ። |
ልፋ ያለው ሉስትሮ፥ እግር ሥር ይውላል። ልፋ ያለው ምረጡኝ አለ። |
ልፋ ያለው ቆዳ፥ ለመጫኛ ይሆናል። |
ልፋ ያለው በሬ፥ ቆዳው ለከበሮ (ይወጠራል)። ልፋ ያለው፥ አንድ ዕንጨት ያስራል። |
ልፋ ያለው፥ በሕልሙ ሲሸከም ያድራል። ልፋ ያለው፥ በሕልሙ ዳውላ ይሸከማል። |
ልፋት ቢያምርህ መሬት ግዚ፤ ችግር ቢያምርህ ልጅ አብዚ። ልላ ለስሕተት፤ ጌታ ለምሕረት። |
ሕልሙ አለሙ፥ የአገኙት ነገር ግን የለም። ሕልም ተፈርቶ፥ ሳይተኛ አይታደርም። ሕልም አለ ተብል፥ ሳይተኛ አይታደርም። ሕልም እልም ልበል። |
ሕልም እልም አድርግልኝ። |
ሕልም ፈርቶ፥ ሳይተኙ አያድሩም። ሕመሙ ቀርቶ፥ ሞቱን በሰጠኝ። ሕመሙ ቀርቶ፥ ሞቱን በተወኝ። |
ሕመሙን የሸሸገ፥ መድኀኒት አይገኝለትም። ሕመሙን የሸሸገ፥ መድኀኒት የለውም። ሕመሙን የሸሸገ በሽተኛ፥ ፈውሱ መጋኛ። ሕመሙን የደበቀ፥ መድኀኒቱም አልታወቀ። ሕመሙን የደበቀ፥ መድኀኒት የለውም። |
ሕንጻና ልጅ ስምን ያስጠራሉ። (ሕንጻና ~ ግንብና) ሕይወት እና ሽንኩርት ያስለቅሳሉ። |
ሕይወት፥ ከልብ ወለድ ይልቃል። ሕይወትም ሞትም በአፍ ይመጣሉ። ኅዳር መማረሪያ፥ ሠኔ መቃጠሪያ። |
ሕግ ይኖራል ተተክል፤ ሥርአት ይኖራል ተዚውሮ። ሕግ፥ ዝተትና ጃኖ ያቆራኛል። |
ሕግን መናቅ፤ በሽቦ መታነቅ። |
ሕፃን (ልጅ) ብሉ አይል፥ መቃብር ተነሡ አይል። ሕፃንን ምግብ እንጂ፥ ስሞሽ አያሳድገውም። ሆሆሆ፥ ሥቄ ልሙት አለ ሰውየው። |
መሀላ የማሉለት አይገባም፥ የካደለት ነው እንጅ። መሀይምነት ለድፍረት፤ ፍቀረ ንዋይ ለክህደት ይመቻል። መኼድ መኼድን እያደራጀኹ፤ እንደ ጉሬዚ ከእሬት አረጀኹ። መኼድ መመለስ፤ ከአሰቡት ለመድረስ። |
መላላጫ፥ ፊት መገለጫ። |
መላሰኛ ሴት፥ በጎረቤቷ ጠብ በተነሣ ጊዛ፥ መላሷን ትለምጥ ትጀምራለች። መላእክት የፈሩትን፥ ሞኞች ይደፍሩታል። |
መልከ ጥፉ፥ ቆንጆዋን አስናቀች። መልከ ጥፉ(ን)፥ በስም ይደግፉ። መልከኛ፥ ከአጤ ቤት ይገባል። |
መልከኛው ኮሶ ቢጠጣ፥ ጪሰኛው አስቀመጠው። መልኩ የእኔ፤ ግብሩ የአረመኔ። |
መልካም ላባ፥ ከመልካም ወፍ ይገኛል። መልካም፥ ልብ አይነካም። |
መልካም ሚስት፥ ለባሎ ውድ ናት። |
መልካም ሠሪ ለልጆቹ፥ የጨረቃ ንጋት በወፎቹ ይታወቃል። መልካም ሱሪ፥ ለተማሪ። (ለተማሪ ~ ከተማሪ) |
መልካም ሴት፥ ለባሎ ውድ ናት። መልካም ስም፥ ከመልካም ሽቶ ይበልጣል። |
መልካም ስም ከመቃብር በላይ ይቆማል። (ይቆማል ~ ይውላል) መልካም ቆንጆ፥ የላት መቀናጆ። |
መልካም በሬ ለዕርሻ፥ ድማም አያሻ። መልካም ባል፥ መጥፎ ሴት ይገራል። መልካም ተመኝ፥ መልካም እንድታገኝ። |
መልካም ንግግር ቁጣን ያበርዳል፤ መጥፎ ንግግር ልብን ያናድዳል። መልካም አባት፥ ለልጆቹ እጁን ኪሱ ይከታል። |
መልካም አድራጊ አበደረ፥ ክፉ አድራጊ ተግደረደረ። |
መልካም ወሬ አጥንት ያለመልማል፥ መጥፎ ወሬ ልብን ያደክማል። (ያደክማል ~ ይሰብራል) |
መልካም ወገን፤ የፀሓይ ወጋገን። (ወጋገን ~ ውጋገን) መልካም ወጥ፥ እጅን ያስመጥጥ። |
መልካም ጭራ ለደብተራ። |
መልካም ፈረስ ለሩጫ፤ ሰጋር በቅል ለኮርቻ። መልክ ስጠኝ እንጂ፥ ሙያ ከጎረቤቴ እማራለኹ። መልክ በግምት ይገኛል፤ ልብ ትልቅ ይመኛል። መልክ ታጥቦ አይጠጣም። |
መልክ ታጥቦ አይጠጣ? ወይ አይበላ? |
መልክተኛ ከአጤ፥ ቤት ይገባል። (መልክተኛ ~ መላክተኛ) መልክተኛ፥ ንጉሥ አይፈራም። |
መል ባያምር፥ አመሎ ይመር። መልፋት መድከም፥ የቆርበት የጉልበት። መመሳሰል የጋራ ነው። |
መመራመር ያደርሳል፥ (ከ)ቁም ነገር። መመራመር፥ ያገባል ከባሕር። (ያገባል ~ ይከታል) መመከት ጋሻ አንግቦ፤ መደለያ ዳዊት አቅርቦ። |
መመጽወት፥ ያድናል ከድህነት። (ከድህነት ~ ከጸጸት) መማለጃ እየበሉ፤ ወንድማቸውን እየበደሉ። |
መማር መሟር። |
መማር ይቅደም፥ ከመጠምጠም። መምህራን ከአሉ፥ አዋቂዎች ይበዚሉ። መምሩ፥ ያዩትን አይምሩ። |
መምሩ ገመሩ። |
መምሬ፥ አይበሉም ጥሬ። |
መምታት አያውቅ ራስ ይመታል፤ መስጠት አያውቅ የቁና ድርብብ ይሰጣል። መምከርማ ድሀ ይመክራል፥ ሰሚ አጥቶ ይቀራል። |
መሞት የፈለገ ግልገል፥ ቀበሮ ቤት ኼድ ይጨፍራል። መሠልጠን ወይስ መሰይጠን። |
መሠረትህ እውነት፤ መጨረሻህ ደግሞ ትዕግሥት ይኹን። መሰንበት፥ የማያሳየው ነገር የለም። |
መሥራት እንጂ፥ ማፍረስ አያቅትም። |
መሪ የላለው ጨንባሳ፤ ምርኩዝ የላለው አንካሳ። (ጨንባሳ ~ ጠንባሳ) መሪና ንፉግ እያደር ይቆጨዋል። |
መሪው ከተመታ፥ መንጋው ይበተናል። መራጭ ይወድቃል ከምራጭ። |
መሬት ለተሰደደ፥ እንዱያጎበድደ። መሬት ለአራሽ፤ ነፍጥ ለተሽ። |
መሬት ላይ ላለ ሥጋ፥ በሰማይ ያለ አሞራ ተጣላ። መሬት ሲያረጅ፥ መጭ ያበቅላል። |
መሬት በአቅጣጫ፤ መልክ በአፍንጫ። መሬት በአዋቂ፤ ጠጅ በፈላቂ። |
መሬት በወንዙ፤ እባብ በመርዙ። መሬት በድንበር፤ ውበት በከንፈር። መሬት እናት፤ ር አባት። |
መሬት ከሠባ፤ ግዳዩ ከሰለባ። |
መሬት ከደዳላብ፤ ውሃን ከናጌብ። (ከደዳላብ ~ ከኢየሩሳላም) መሬት የወደቀ ሥጋ፥ አፈር ሳይዝ አይነሣም። |
መርዝ መርዝን፥ ኮሶ ኮሶን ያፈራል። መርዝ ያፈላ፥ ሢሶው ለራሱ። መርጦ ይገዞል፥ ዋጋ ያበዞል። |
መርፌ መግቢያዋን እንጂ፥ መውጫዋን አታይም። መርፌ ሰርቆ ማረሻ ቢተኩ ልብ አይሞላም። መርፌ ሲለግም፥ ቅቤ አይወጋም። |
መርፌ ቢሰበሰብ፥ ማረሻ አይሆንም። መርፌ ውጦ፥ ማረሻ መትፋት። |
መርፌ የራሷን ቀዳዳ ሳታይ፥ ለብዙ ሰው ትጠቅማለች። መርፌ የራሷን ቀዳዳ ሳታይ፥ የላላውን ቀዳዳ ትጠቅማለች። |
መርፌ የጠፋው፥ ጋን ይፈነቅላል። |
መርፌ ፈላጊ፥ ማረሻ ቢያነቅፈው አያየውም። መሮጥ ሲበዚ ልብ ያፈርሳል። |
መሰስ ሲሉ፥ ምን ደስ ይሉ? መሰስ ሲል፥ ምን ደስ ይል? መሠረት ነዋሪ፤ መሪና አስተማሪ። |
መሳምን ወደሽ፥ ጢምን ጠልተሽ። መሣሣል የጋራ ነው። |
መሳሳሚያ ከንፈር፤ መገናኛ ድንበር (የለንም)። መሣሪያ ይዝ ጸልት፤ ካባ (ላንቃ) ለብሶ ማእድ ቤት። መስል ከመታየት፥ ሆኖ መገኘት። |
መስማት ማየትን አያሸንፍም። |
መስማት ሰለቸው ሕዝቡ ንድሮ፥ ምነው በሰጠው የዝኆን ጆሮ። መስማት ከማይወድ አንሶ፥ የሚሰማ የለም። |
መስተዋት ፊት ያሳያል፤ መሰንበት ዅሉን ያሳያል። |
መስከረም ሲጠባም ብንከፍተው፥ ያው ጎታው ሙሉ ገለባ ነው። መስከረም በአበባው፤ ሰርግ በጭብጨባው (ይታወቃል)። መስከረም የሚወልደው፤ ንጉሥ የሚፈርደው አይታወቅም። መስጠት ቤት አይፈታም። |
መስጠት አያውቅ ራት፤ መምታት አያውቅ አናት። መስጠት የማያውቅ፥ የቁና እኩል። |
መስጠትን የማያውቅ ሰው፥ መቀበልን ማን አስተማረው? መሶብ ሰፍቼ፥ ለአጤ አበርክቼ። |
መሸ መሰለኝ ሉጨልም፥ እንደቀን ጣይ የለም። |
መሸሽማ አንበሳም ይሸሻል፥ መለስ ያለ እንደሆን ሰውን ያበላሻል። መሸከም የለመደ ራስ፥ መናገር የለመደ ምላስ፥ ኹለቱ አንድ ናቸው። መሸጥ የለመደ፥ እናቱን ያስማማል። |