label
class label 4
classes | headline
stringlengths 17
80
| text
stringlengths 1
16.8k
| headline_text
stringlengths 28
16.8k
| url
stringlengths 36
49
|
---|---|---|---|---|
5sports
| ቼልሲ አሰልጣኙን ቶማስ ቱህልን አሰናበተ | የእንግሊዙ ፕሪሚየር ሊግ ክለብ ቼልሲ አሰልጣኙን ቶማስ ቱህልን አሰናበተ። አሰልጣኝ ቱህል የተሰናበቱት በ2022/23 የውድድር ዓመት በመጀመሪያ የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ከተሸነፉ በኋላ ነው። የጀርመናዊው አሰልጣኝ ቡድን ቼልሲ ትናንት ማክሰኞች ጳጉሜ 2/2014 ዓ.ም. ወደ ክሮሺያ ተጉዞ በዳይናሞ ዛግሬብ 1 ለ 0 ተሸንፏል። አሰልጣኙ በቼልሲ ቆይታቸው ቻምፒንስ ሊግ፣ ሱፐር ካፕ እና የክለቦች የዓለም ዋንጫን ማንሳት ችለዋል። ክለቡ የቱህልን መሰናበት አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ ለቼልሲ አዲስ አሰልጣኝ እስኪሰየም ድረስ የልምምድ እና ወደፊት የሚካሄዱ ጨዋታዎች ዝግጅትን የክለቡ አሰልጣኞች ቡድን ይመራዋል ብሏል። ቱህል 100ኛ የቼልሲ ጨዋታቸውን ነበር ትላንት ምሽት ያከናወኑት። ባለፉት 7 ጨዋታዎች ሦስቱን አሸንፈው በአንዱ አቻ ሲለያዩ በቀሪዎቹ ተሸንፈዋል። ቡድኑ በመጪው ቅዳሜ ከፉልሃም ጋር ይጫወታል። | ቼልሲ አሰልጣኙን ቶማስ ቱህልን አሰናበተ የእንግሊዙ ፕሪሚየር ሊግ ክለብ ቼልሲ አሰልጣኙን ቶማስ ቱህልን አሰናበተ። አሰልጣኝ ቱህል የተሰናበቱት በ2022/23 የውድድር ዓመት በመጀመሪያ የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ከተሸነፉ በኋላ ነው። የጀርመናዊው አሰልጣኝ ቡድን ቼልሲ ትናንት ማክሰኞች ጳጉሜ 2/2014 ዓ.ም. ወደ ክሮሺያ ተጉዞ በዳይናሞ ዛግሬብ 1 ለ 0 ተሸንፏል። አሰልጣኙ በቼልሲ ቆይታቸው ቻምፒንስ ሊግ፣ ሱፐር ካፕ እና የክለቦች የዓለም ዋንጫን ማንሳት ችለዋል። ክለቡ የቱህልን መሰናበት አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ ለቼልሲ አዲስ አሰልጣኝ እስኪሰየም ድረስ የልምምድ እና ወደፊት የሚካሄዱ ጨዋታዎች ዝግጅትን የክለቡ አሰልጣኞች ቡድን ይመራዋል ብሏል። ቱህል 100ኛ የቼልሲ ጨዋታቸውን ነበር ትላንት ምሽት ያከናወኑት። ባለፉት 7 ጨዋታዎች ሦስቱን አሸንፈው በአንዱ አቻ ሲለያዩ በቀሪዎቹ ተሸንፈዋል። ቡድኑ በመጪው ቅዳሜ ከፉልሃም ጋር ይጫወታል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cldz5xk91g2o |
0business
| ኮሮናቫይረስ፡ 300ሺህ አፍሪካውያን በኮቪድ-19 ምክንያት ሕይወታቸውን ሊያጡ ይችላሉ-የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን | የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ያለበቂ መከላከያ 300ሺህ አፍሪካውያን በኮሮና ምክንያት ህይወታቸውን እንደሚያጡ ይገመታል ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ ላይ አስታወቀ። የኮሮና ቫይረስ በአፍሪካውያን ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት በገመመገመበት በዚህ መግለጫ ከሰው ህይወት በተጨማሪ የአህጉሪቷን ምጣኔ ኃብት እያሽመደመደው እንደሆነም አስፍሯል። በዚህ አመት የአህጉሪቱ ምጣኔ ሃብት በ3.2 በመቶ ያድጋል ተብሎ የተገመተ ቢሆንም ቫይረሱ ባደረሰው ጫና ምክንያት ምናልባት 1.8 በመቶ ሊያድግ ይችላል ብሏል። ይህም ሁኔታ 27 ሚሊዮን ህዝብን ለረሃብ እንደሚያጋልጥ የኮሚሽኑ መግለጫ ጠቁሟል። • መንግሥታት ከተሜውን ከኮሮናቫይረስ ኢኮኖሚያዊ ጫና እንዲታደጉ ጥሪ ቀረበ • ኢትዮጵያ ከኮሮናቫይረስ ምጣኔ ሐብታዊ ጫና ትተርፋለች? • አገራትን ጭምብል እስከመሰራረቅ ያደረሳቸው የኮሮናቫይረስ ዲፕሎማሲ ኮሚሽኑ ነገ ይፋ በሚያደርገው ሪፖርት ቫይረሱ ካስተለው ቀውስ ጋር ተያይዞም ደካማ የሚባለው የአህጉሪቷጤና ስርዓት ለተጨማሪ ወጪ እንደሚዳረግም አስገንዝቧል። እስካሁን ባለው መረጃ በአህጉሪቷ ውስጥ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 16 ሺ ሲሆን 800 ሰዎችም ህይወታቸውን አጥተዋል፤ ይህ ቁጥር እየጨመረ ሊሄድ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ የአህጉሪቱ የጤና ስርአትም ጥያቄ ውስጥ እንደሚገባ መግለጫው አመላክቷል። ይህንንም ለመታደግ የመንግሥታት ቁርጠኝነት እንዲሁም ድጋፍ እንደሚገባም የኮሚሽኑ ዋና ፀሐፊ ቬራ ሶንግዌ ገልፀዋል። " የአህጉሪቱን የጋራ ብልጽግና ለመከላከልና ለመንባት፤ መንግሥታት ለዜጎቻቸው በአስቸኳይ መሰረታዊ ፍላጎታቸውን ማቅረብ እንዲችሉ 100 ቢሊየን ዶላር ያስፈልጋል" ብለዋል " የወረርሽኙ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ቫይረሱ በቀጥታ ከሚያደርሰው ጉዳት የበለጠ ነው" ያሉት ፀሐፊዋ በአፍሪካ አገራት በአጠቃላይ ምጣኔ ሃብታቸው ቫይረሱ እንደተከሰተ መጎዳት መጀመሩን ገልጠዋል። "ወረርሽኙን ለመከላከል ተብሎ የተቀመጠው አካላዊ ርቀትን መጠበቅ የኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን እግር ተወርች አስሯል" ሲሉ አስረድተዋል የኮሚሽኑ ሪፖርት አክሎም አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ድጋፍ ካልተደረገላቸው በስተቀር ሙሉ በሙሉ እንደሚዘጉ አትቷል። የአፍሪካን ምጣኔ ሃብት 40 በመቶ የሚሸፍነው ዘይት በግማሽ ዋጋው መቀነሱን፣ በዋነኝነት አፍሪካ ወደውጪ የምትልካቸው የጨርቃ ጨርቅና አበባ ምርቶችም መውደቃቸውን ጠቅሷል። ቱሪዝም የአንዳንድ የአፍሪካ አገራት አጠቃላይ ብሔራዊ ምርትን 38 በመቶ ቢይዝም አየር መንገዶች ስራቸውን በማቋረጣቸው ምክንያት ሙሉ በሙሉ ቆሟል ሲል ያትታል። የአፍሪካ ምጣኔ ሃብት የተሳሰረ ነው ያለው ሪፖርቱ ለቀውሱም የምንሰጠው ምላሽ " ወደ አንድ ሊያመጣን ይገባል" ብሏል። | ኮሮናቫይረስ፡ 300ሺህ አፍሪካውያን በኮቪድ-19 ምክንያት ሕይወታቸውን ሊያጡ ይችላሉ-የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ያለበቂ መከላከያ 300ሺህ አፍሪካውያን በኮሮና ምክንያት ህይወታቸውን እንደሚያጡ ይገመታል ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ ላይ አስታወቀ። የኮሮና ቫይረስ በአፍሪካውያን ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት በገመመገመበት በዚህ መግለጫ ከሰው ህይወት በተጨማሪ የአህጉሪቷን ምጣኔ ኃብት እያሽመደመደው እንደሆነም አስፍሯል። በዚህ አመት የአህጉሪቱ ምጣኔ ሃብት በ3.2 በመቶ ያድጋል ተብሎ የተገመተ ቢሆንም ቫይረሱ ባደረሰው ጫና ምክንያት ምናልባት 1.8 በመቶ ሊያድግ ይችላል ብሏል። ይህም ሁኔታ 27 ሚሊዮን ህዝብን ለረሃብ እንደሚያጋልጥ የኮሚሽኑ መግለጫ ጠቁሟል። • መንግሥታት ከተሜውን ከኮሮናቫይረስ ኢኮኖሚያዊ ጫና እንዲታደጉ ጥሪ ቀረበ • ኢትዮጵያ ከኮሮናቫይረስ ምጣኔ ሐብታዊ ጫና ትተርፋለች? • አገራትን ጭምብል እስከመሰራረቅ ያደረሳቸው የኮሮናቫይረስ ዲፕሎማሲ ኮሚሽኑ ነገ ይፋ በሚያደርገው ሪፖርት ቫይረሱ ካስተለው ቀውስ ጋር ተያይዞም ደካማ የሚባለው የአህጉሪቷጤና ስርዓት ለተጨማሪ ወጪ እንደሚዳረግም አስገንዝቧል። እስካሁን ባለው መረጃ በአህጉሪቷ ውስጥ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 16 ሺ ሲሆን 800 ሰዎችም ህይወታቸውን አጥተዋል፤ ይህ ቁጥር እየጨመረ ሊሄድ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ የአህጉሪቱ የጤና ስርአትም ጥያቄ ውስጥ እንደሚገባ መግለጫው አመላክቷል። ይህንንም ለመታደግ የመንግሥታት ቁርጠኝነት እንዲሁም ድጋፍ እንደሚገባም የኮሚሽኑ ዋና ፀሐፊ ቬራ ሶንግዌ ገልፀዋል። " የአህጉሪቱን የጋራ ብልጽግና ለመከላከልና ለመንባት፤ መንግሥታት ለዜጎቻቸው በአስቸኳይ መሰረታዊ ፍላጎታቸውን ማቅረብ እንዲችሉ 100 ቢሊየን ዶላር ያስፈልጋል" ብለዋል " የወረርሽኙ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ቫይረሱ በቀጥታ ከሚያደርሰው ጉዳት የበለጠ ነው" ያሉት ፀሐፊዋ በአፍሪካ አገራት በአጠቃላይ ምጣኔ ሃብታቸው ቫይረሱ እንደተከሰተ መጎዳት መጀመሩን ገልጠዋል። "ወረርሽኙን ለመከላከል ተብሎ የተቀመጠው አካላዊ ርቀትን መጠበቅ የኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን እግር ተወርች አስሯል" ሲሉ አስረድተዋል የኮሚሽኑ ሪፖርት አክሎም አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ድጋፍ ካልተደረገላቸው በስተቀር ሙሉ በሙሉ እንደሚዘጉ አትቷል። የአፍሪካን ምጣኔ ሃብት 40 በመቶ የሚሸፍነው ዘይት በግማሽ ዋጋው መቀነሱን፣ በዋነኝነት አፍሪካ ወደውጪ የምትልካቸው የጨርቃ ጨርቅና አበባ ምርቶችም መውደቃቸውን ጠቅሷል። ቱሪዝም የአንዳንድ የአፍሪካ አገራት አጠቃላይ ብሔራዊ ምርትን 38 በመቶ ቢይዝም አየር መንገዶች ስራቸውን በማቋረጣቸው ምክንያት ሙሉ በሙሉ ቆሟል ሲል ያትታል። የአፍሪካ ምጣኔ ሃብት የተሳሰረ ነው ያለው ሪፖርቱ ለቀውሱም የምንሰጠው ምላሽ " ወደ አንድ ሊያመጣን ይገባል" ብሏል። | https://www.bbc.com/amharic/52293148 |
2health
| እስካሁን በኮሮናቫይረስ ያልተያዙ ሰዎች ለምን ሳይያዙ ቆዩ? | የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ተከስቶ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ በሁሉም አገራት የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለህመም፣ ከተወሳሰበ የጤና ችግር እና ለሞት ዳርጓል። ይህ በሽታ ከተከሰተ ሁለት ዓመት ያለፈው ሲሆን ከመተላለፊያ መንገዶቹ አመቺነት የተነሳ በአጭር ጊዜ መላውን ዓለም አዳርሷል። አንዳንዶች እንዲያውም አብዛኛው የዓለም ሕዝብ በበሽታው የመያዝ ዕድል አለው ይላሉ። ከወረርሽኙ የስርጭት ፍጥነት እና ስፋት አንጻር በርካቶች ለቫይረሱ የተጋለጡ ቢሆንም፣ ተጋላጭ ቢሆኑም በርካቶች አስካሁን በሽታው አልያዛቸውም ይባላል። ለዚህ ምክንያቱ ምንድን ነው? | እስካሁን በኮሮናቫይረስ ያልተያዙ ሰዎች ለምን ሳይያዙ ቆዩ? የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ተከስቶ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ በሁሉም አገራት የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለህመም፣ ከተወሳሰበ የጤና ችግር እና ለሞት ዳርጓል። ይህ በሽታ ከተከሰተ ሁለት ዓመት ያለፈው ሲሆን ከመተላለፊያ መንገዶቹ አመቺነት የተነሳ በአጭር ጊዜ መላውን ዓለም አዳርሷል። አንዳንዶች እንዲያውም አብዛኛው የዓለም ሕዝብ በበሽታው የመያዝ ዕድል አለው ይላሉ። ከወረርሽኙ የስርጭት ፍጥነት እና ስፋት አንጻር በርካቶች ለቫይረሱ የተጋለጡ ቢሆንም፣ ተጋላጭ ቢሆኑም በርካቶች አስካሁን በሽታው አልያዛቸውም ይባላል። ለዚህ ምክንያቱ ምንድን ነው? | https://www.bbc.com/amharic/articles/ce9ne2g26qeo |
3politics
| ትግራይ፡ የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደና ጓደኛው በመቀለ ከተማ ተገደሉ | የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ የነበረው ዳዊት ከበደ አርአያ ወደ ሥራው ከተመለሰ ከቀናት በኋላ በመቀለ ከተማ ውስጥ ተገድሎ መገኘቱ ተዘገበ ። የሥራ ባልደረቦቹ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የትግራይ ክልላዊ መንግሥት በሚያስተዳድረው ቴሌቪዥን ጣቢያ በጋዜጠኝነት ይሰራ የነበረው ዳዊት ተገድሎ የተገኘው ረቡዕ ዕለት ጥር 12/ 2013 ዓ.ም በመኪና ውስጥ ነው። ከዳዊት ከበደም አርአያ በተጨማሪ አንድ ሌላ ጓደኛውም መቀሌ ውስጥ በምትገኝ አዲ ሃውሲ በምትባል ሰፈር መገደላቸውን ባልደረቦቹ ተናግረዋል። የቀይ መስቀል ሠራተኞች የዳዊትንና አብሮት የነበረውን ግለሰብ አስከሬን ካነሱ በኋላ በትግራይ ቴሌቪዥን ለሚሰሩ የሥረራ ባልደረቦቹ ማሳወቃቸውም ተጠቅሷል። ስለ ግድያው እስካሁን ድረስ ክልሉን ከሚያስተዳድሩት ባለስልጣናት የተሰጠ መረጃ የለም። አዲስ በተቋቋመው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የደኅንነት ኃላፊ የሆኑት አቶ ዋልታ ሐረጎትን ስለ ጋዜጠኛው አሟሟት ቢቢሲ በጠየቃቸው ወቅት ምንም መረጃ እንደሌላቸውና፤ መረጃዎችን ሰብስበውና አጠናቅረው ይፋ እንደሚያደርጉም ቃል ገብተዋል። ስሜ አይጠቀስ ያለ አንድ የዳዊት የሥራ ባልደረባ ለቢቢሲ ትግርኛ እንደተናገረው ሁለቱ ግለሰቦች የተገደሉት በተተኮሰባቸው ጥይት ነው። ይህንን መረጃ ከአካባቢው የፀጥታና ደኅንነት ኃላፊዎች ማረጋገጥ አልተቻለም። ሁለተኛው የተገደለው ግለሰብ ማንነትንም በተመለከተ ቢቢሲ ባደረገው ማጣራት በትግራይ ቴሌቪዥን የሚሰራ ሌላ ጋዜጠኛ ወንድም መሆኑን መረዳት ችሏል። ወደ ሥራ መመለስ በትግራይ ክልል ወታደራዊ ግጭት በተፋፋመበት በኅዳር ወር ሥራ አቋርጦ እንደነበር የተነገረው ዳዊት ከበደ አርአያ በቅርቡ ወደ ሥራው ተመልሶ ነበር ተብሏል። የመከላከያ ሠራዊት መቀለን መቆጣጠሩን ተከትሎ ተቋርጦ የነበረውም የክልሉ ቴሌቪዥን ፕሮግራም ስርጭት መተላለፍ የጀመረ ሲሆን ሠራተኞቹም ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ ጥሪ አድርጓል። ዳዊት ወደ ሥራ ተመልሶ ቢሮ በገባበት ወቅት ተይዞ ለቀናትም ያህል በቁጥጥር ስር የነበረ መሆኑን አንድ በቴሌቪዥን ጣቢያ የሥራ ባልደረባው አሳውቀዋል። እስሩን በተመለከተ የአካባቢው ባለስልጣናት ያሉት ነገር ባይኖርም የሥራ ባልደረባው ግን ከመገደሉ በፊት ለሦስት ቀናት በእስር ላይ እንደነበረ ተናግረዋል። "የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳዳሪዎች የቀድሞ ጋዜጠኞችንና የካሜራ ባለሙያዎችን እያናገሩ ነበር። ካናገሩዋቸው ጋዜጠኞች መካከል አንዱ ዳዊት ነው" በማለትም ባልደረባው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከህዳር 19/2013 ዓ.ም ጀምሮ በመከላከያ ቁጥጥር ስር ባለችው መቀለ የምሽት ሰዓት እላፊ የተጣለ ሲሆን በዚያ ሰዓትም በከተማው ማንኛውም እንቅስቃሴ የተከለከለ ነው። ዳዊት ከበደ አርአያ ማን ነው? ዳዊት በትግራይ ቴሌቪዥን ተቀጥሮ ከመስራቱ በፊት ለበርካታ ዓመታት በብሔራዊው የቴሌቪዥን ጣቢያ ኢቲቪ ሰርቷል። ኢቲቪን ከለቀቀ በኋላ የራሱን የትግርኛ መፅሔት በማቋቋም ለበርካታ ዓመታት ፅሁፍ ሲያበረክት ነበር። በኋላም ባለፈው ዓመት እስከ ተዘጋበት ድረስ አዲስ አበባ በሚገኘው የትግራይ ቴሌቪዥን ቅርንጫፍ ውስጥ እያገለገለ ነበር። የአዲስ አበባ ቅርንጫፉን መዘጋት ተከትሎ መቀለ ወደሚገኘውም ዋና ጣቢያ በመመለስ በቴሌቪዥን ጣቢያው ሲሰራ ነበር። የሁለቱ፣ የዳዊትና አብሮት የነበረው ግለሰብ የሥርዓተ ቀብር በትናንትናው ዕለት ጥር 12/ 2013 ዓ.ም አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን ተፈፅሟል። | ትግራይ፡ የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደና ጓደኛው በመቀለ ከተማ ተገደሉ የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ የነበረው ዳዊት ከበደ አርአያ ወደ ሥራው ከተመለሰ ከቀናት በኋላ በመቀለ ከተማ ውስጥ ተገድሎ መገኘቱ ተዘገበ ። የሥራ ባልደረቦቹ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የትግራይ ክልላዊ መንግሥት በሚያስተዳድረው ቴሌቪዥን ጣቢያ በጋዜጠኝነት ይሰራ የነበረው ዳዊት ተገድሎ የተገኘው ረቡዕ ዕለት ጥር 12/ 2013 ዓ.ም በመኪና ውስጥ ነው። ከዳዊት ከበደም አርአያ በተጨማሪ አንድ ሌላ ጓደኛውም መቀሌ ውስጥ በምትገኝ አዲ ሃውሲ በምትባል ሰፈር መገደላቸውን ባልደረቦቹ ተናግረዋል። የቀይ መስቀል ሠራተኞች የዳዊትንና አብሮት የነበረውን ግለሰብ አስከሬን ካነሱ በኋላ በትግራይ ቴሌቪዥን ለሚሰሩ የሥረራ ባልደረቦቹ ማሳወቃቸውም ተጠቅሷል። ስለ ግድያው እስካሁን ድረስ ክልሉን ከሚያስተዳድሩት ባለስልጣናት የተሰጠ መረጃ የለም። አዲስ በተቋቋመው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የደኅንነት ኃላፊ የሆኑት አቶ ዋልታ ሐረጎትን ስለ ጋዜጠኛው አሟሟት ቢቢሲ በጠየቃቸው ወቅት ምንም መረጃ እንደሌላቸውና፤ መረጃዎችን ሰብስበውና አጠናቅረው ይፋ እንደሚያደርጉም ቃል ገብተዋል። ስሜ አይጠቀስ ያለ አንድ የዳዊት የሥራ ባልደረባ ለቢቢሲ ትግርኛ እንደተናገረው ሁለቱ ግለሰቦች የተገደሉት በተተኮሰባቸው ጥይት ነው። ይህንን መረጃ ከአካባቢው የፀጥታና ደኅንነት ኃላፊዎች ማረጋገጥ አልተቻለም። ሁለተኛው የተገደለው ግለሰብ ማንነትንም በተመለከተ ቢቢሲ ባደረገው ማጣራት በትግራይ ቴሌቪዥን የሚሰራ ሌላ ጋዜጠኛ ወንድም መሆኑን መረዳት ችሏል። ወደ ሥራ መመለስ በትግራይ ክልል ወታደራዊ ግጭት በተፋፋመበት በኅዳር ወር ሥራ አቋርጦ እንደነበር የተነገረው ዳዊት ከበደ አርአያ በቅርቡ ወደ ሥራው ተመልሶ ነበር ተብሏል። የመከላከያ ሠራዊት መቀለን መቆጣጠሩን ተከትሎ ተቋርጦ የነበረውም የክልሉ ቴሌቪዥን ፕሮግራም ስርጭት መተላለፍ የጀመረ ሲሆን ሠራተኞቹም ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ ጥሪ አድርጓል። ዳዊት ወደ ሥራ ተመልሶ ቢሮ በገባበት ወቅት ተይዞ ለቀናትም ያህል በቁጥጥር ስር የነበረ መሆኑን አንድ በቴሌቪዥን ጣቢያ የሥራ ባልደረባው አሳውቀዋል። እስሩን በተመለከተ የአካባቢው ባለስልጣናት ያሉት ነገር ባይኖርም የሥራ ባልደረባው ግን ከመገደሉ በፊት ለሦስት ቀናት በእስር ላይ እንደነበረ ተናግረዋል። "የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳዳሪዎች የቀድሞ ጋዜጠኞችንና የካሜራ ባለሙያዎችን እያናገሩ ነበር። ካናገሩዋቸው ጋዜጠኞች መካከል አንዱ ዳዊት ነው" በማለትም ባልደረባው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከህዳር 19/2013 ዓ.ም ጀምሮ በመከላከያ ቁጥጥር ስር ባለችው መቀለ የምሽት ሰዓት እላፊ የተጣለ ሲሆን በዚያ ሰዓትም በከተማው ማንኛውም እንቅስቃሴ የተከለከለ ነው። ዳዊት ከበደ አርአያ ማን ነው? ዳዊት በትግራይ ቴሌቪዥን ተቀጥሮ ከመስራቱ በፊት ለበርካታ ዓመታት በብሔራዊው የቴሌቪዥን ጣቢያ ኢቲቪ ሰርቷል። ኢቲቪን ከለቀቀ በኋላ የራሱን የትግርኛ መፅሔት በማቋቋም ለበርካታ ዓመታት ፅሁፍ ሲያበረክት ነበር። በኋላም ባለፈው ዓመት እስከ ተዘጋበት ድረስ አዲስ አበባ በሚገኘው የትግራይ ቴሌቪዥን ቅርንጫፍ ውስጥ እያገለገለ ነበር። የአዲስ አበባ ቅርንጫፉን መዘጋት ተከትሎ መቀለ ወደሚገኘውም ዋና ጣቢያ በመመለስ በቴሌቪዥን ጣቢያው ሲሰራ ነበር። የሁለቱ፣ የዳዊትና አብሮት የነበረው ግለሰብ የሥርዓተ ቀብር በትናንትናው ዕለት ጥር 12/ 2013 ዓ.ም አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን ተፈፅሟል። | https://www.bbc.com/amharic/news-55745102 |
3politics
| ሩሲያ፡ የፑቲን ባላንጣ አሌክሴ አገሩ ሲገባ "የእስር አቀባበል" ተደረገለት | የሩሲያው ቭላድሚር ፑቲን የሰላ ተቺ ነው የሚባለው አሌክሴ ናቫልኒ ታሰረ። አሌክሴ የታሰረው ከጀርመን ወደ ሩሲያ በገባበት ቅጽበት ነው። አሌክሴ በአደገኛ መርዝ የግድያ ሙከራ ተደርጎበት በተአምር ከተረፈ ወዲህ ነው በድጋሚ ወደ አገሩ ሩሲያ የተመለሰው። ብዙዎች አሌክሴ ወደ ሩሲያ ከተመለሰ ሊገደል ስለሚችል ሐሳቡን እንዲቀይር ቢወተውቱትም እሱ ግን አሻፈረኝ ብሏል። የ44 ዓመቱ አሌክሴ ናቫልኒ ልክ ሼርሜትዯቮ አውሮፕላን ጣቢያ ሲደርስ፣ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሎታል። አብራው የነበረችው ሚስቱን ጉንጮቿን ስሞ በፖሊስ ታጅቦ ወዳልታወቀ ስፍራ ተወስዷል። አሌክሴ ወደ ሩሲያ ለመመለስ ሲወስን በሺህ የሚቆጠሩ ደጋፊዎቹ በሞስኮ አየር ማረፍያ በጉጉት ሲጠብቁትና ደማቅ አቀባበል ሊያደርጉለት ነበር። ሆኖም እሱ የተሳፈረበት ከጀርመን የተነሳው አውሮፕላን አቅጣጫውን እንዲቀይር ተገዷል። ይህም ከደጋፊዎቹ ጋር እንዳይገናኝ የሩሲያ ባለሥልጣናት ያደረጉት ነው። የቭላድሚር ፑቲን ተቀናቃኝ አሌክሴ ከ5 ወራት በፊት የመረዙኝ እሳቸው ናቸው ይላል። ክሬምሊን በበኩሉ እጄ የለበትም ሲል ያስተባብላል። አሌክሴ በአደገኛ የነርቭ መርዝ መመረዙን የጀርመን ሐኪሞች አረጋግጠዋል። ይህን ሊያደርጉ አቅሙ ያላቸው ቭላድሚር ፑቲንና አስተዳደራቸው ብቻ ስለመሆኑ ደግሞ በርካታ የምርመራ ጋዜጠኞች አረጋግጠዋል። የአሌክሴ ናቫልኒ ወደ ሩሲያ መመለስ ዓለምን ያስገረመ ጉዳይ ሆኖ የሚጠበቀው እስሩ እንደተሰማ ግን የአውሮጳ ኅብረት፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያንና ሌሎች በርካታ አገሮች ድርጊቱን አውግዘዋል። ከሰሞኑ ነጩ ቤተ መንግሥት የሚገቡት 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ተመራጭ ጆ ባይደን የመረጧቸው የደኅንነት አማካሪ ጃክ ሰሊቫን፣ የሩሲያ ድርጊት ያፈጠጠ የሰብአዊ መብት ጥሰት ብቻ ሳይሆን የሩሲያን ሕዝብ ድምጽ የማፈን ተግባር ነው ሲሉ ኮንነዋል። አሌክሴ ባለፈው ነሐሴ ወር የአገር ውስጥ በረራ ላይ ሳለ አውሮፕላን ውስጥ ራሱን ሲስት፣ በሰርቢያ ሕክምና ከጀመረ በኋላ ወደ ጀርመን ለተሻለ ሕክምና ተወስዶ ነበር። በርካቶች ግን ሕይወቱ ትተርፋለች አላሉም። ሆኖም ውጤታማ ሕክምና አድርጎ ነፍሱ ከተመለሰች በኋላ ትናንት እሑድ ወደ ሩሲያ ሲሳፈር ብዙዎችን አስደንግጧል። እሱ ወደ ሩሲያ የተሳፈረበት አውሮፕላን በርካታ ጋዜጠኞች ተሞልቶ ነበር። የኛ የቢቢሲ ዘጋቢ አንድሬ ኮዜንኮ ከተሳፋሪዎቹ አንዱ ነበር። ልክ አውሮፕላኑ ሊያርፍ ሲቃረብ ግን ፓይለቱ "የቴክኒክ ችግር ስለገጠመን" በሚል ከቭኑኮቮ አየር ማረፍያ ወደ ሼርሜትየቮ መዳረሻችንን ቀይረናል ሲል አስታውቋል። አሌክሴ አየር ማረፍያው እንደደረሰ ፖሊሶች ሲከቡት "ብዙ አስጠበቅኳችሁ እንዴ ሲል መቀለዱ ተዘግቧል። | ሩሲያ፡ የፑቲን ባላንጣ አሌክሴ አገሩ ሲገባ "የእስር አቀባበል" ተደረገለት የሩሲያው ቭላድሚር ፑቲን የሰላ ተቺ ነው የሚባለው አሌክሴ ናቫልኒ ታሰረ። አሌክሴ የታሰረው ከጀርመን ወደ ሩሲያ በገባበት ቅጽበት ነው። አሌክሴ በአደገኛ መርዝ የግድያ ሙከራ ተደርጎበት በተአምር ከተረፈ ወዲህ ነው በድጋሚ ወደ አገሩ ሩሲያ የተመለሰው። ብዙዎች አሌክሴ ወደ ሩሲያ ከተመለሰ ሊገደል ስለሚችል ሐሳቡን እንዲቀይር ቢወተውቱትም እሱ ግን አሻፈረኝ ብሏል። የ44 ዓመቱ አሌክሴ ናቫልኒ ልክ ሼርሜትዯቮ አውሮፕላን ጣቢያ ሲደርስ፣ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሎታል። አብራው የነበረችው ሚስቱን ጉንጮቿን ስሞ በፖሊስ ታጅቦ ወዳልታወቀ ስፍራ ተወስዷል። አሌክሴ ወደ ሩሲያ ለመመለስ ሲወስን በሺህ የሚቆጠሩ ደጋፊዎቹ በሞስኮ አየር ማረፍያ በጉጉት ሲጠብቁትና ደማቅ አቀባበል ሊያደርጉለት ነበር። ሆኖም እሱ የተሳፈረበት ከጀርመን የተነሳው አውሮፕላን አቅጣጫውን እንዲቀይር ተገዷል። ይህም ከደጋፊዎቹ ጋር እንዳይገናኝ የሩሲያ ባለሥልጣናት ያደረጉት ነው። የቭላድሚር ፑቲን ተቀናቃኝ አሌክሴ ከ5 ወራት በፊት የመረዙኝ እሳቸው ናቸው ይላል። ክሬምሊን በበኩሉ እጄ የለበትም ሲል ያስተባብላል። አሌክሴ በአደገኛ የነርቭ መርዝ መመረዙን የጀርመን ሐኪሞች አረጋግጠዋል። ይህን ሊያደርጉ አቅሙ ያላቸው ቭላድሚር ፑቲንና አስተዳደራቸው ብቻ ስለመሆኑ ደግሞ በርካታ የምርመራ ጋዜጠኞች አረጋግጠዋል። የአሌክሴ ናቫልኒ ወደ ሩሲያ መመለስ ዓለምን ያስገረመ ጉዳይ ሆኖ የሚጠበቀው እስሩ እንደተሰማ ግን የአውሮጳ ኅብረት፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያንና ሌሎች በርካታ አገሮች ድርጊቱን አውግዘዋል። ከሰሞኑ ነጩ ቤተ መንግሥት የሚገቡት 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ተመራጭ ጆ ባይደን የመረጧቸው የደኅንነት አማካሪ ጃክ ሰሊቫን፣ የሩሲያ ድርጊት ያፈጠጠ የሰብአዊ መብት ጥሰት ብቻ ሳይሆን የሩሲያን ሕዝብ ድምጽ የማፈን ተግባር ነው ሲሉ ኮንነዋል። አሌክሴ ባለፈው ነሐሴ ወር የአገር ውስጥ በረራ ላይ ሳለ አውሮፕላን ውስጥ ራሱን ሲስት፣ በሰርቢያ ሕክምና ከጀመረ በኋላ ወደ ጀርመን ለተሻለ ሕክምና ተወስዶ ነበር። በርካቶች ግን ሕይወቱ ትተርፋለች አላሉም። ሆኖም ውጤታማ ሕክምና አድርጎ ነፍሱ ከተመለሰች በኋላ ትናንት እሑድ ወደ ሩሲያ ሲሳፈር ብዙዎችን አስደንግጧል። እሱ ወደ ሩሲያ የተሳፈረበት አውሮፕላን በርካታ ጋዜጠኞች ተሞልቶ ነበር። የኛ የቢቢሲ ዘጋቢ አንድሬ ኮዜንኮ ከተሳፋሪዎቹ አንዱ ነበር። ልክ አውሮፕላኑ ሊያርፍ ሲቃረብ ግን ፓይለቱ "የቴክኒክ ችግር ስለገጠመን" በሚል ከቭኑኮቮ አየር ማረፍያ ወደ ሼርሜትየቮ መዳረሻችንን ቀይረናል ሲል አስታውቋል። አሌክሴ አየር ማረፍያው እንደደረሰ ፖሊሶች ሲከቡት "ብዙ አስጠበቅኳችሁ እንዴ ሲል መቀለዱ ተዘግቧል። | https://www.bbc.com/amharic/news-55700764 |
3politics
| የጀርመን አካል ሆና ለጀርመን ዕውቅና ያልሰጠቸው 'ቀበሌ' | ሰሞኑን በጀርመን መፈንቅለ መንግሥት ሴራ ተጎንጉኗል በሚል በርካቶች በቁጥጥር ሥር ውለዋል። ይህ የአፍሪካ ብቻ ዜና የሚመስለው ነገር እንዴት በጀርመን ተሰማ ያሉ ብዙ ናቸው። በምሥራቅ ጀርመን የምትገኘውን ‘ደችላንድ’ ስለማያውቋት ነው እንደዚያ ያሉት። የዚህ መንደር ልብ ተራራ ነው። ይቺ ትንሽ ቀበሌ ራሷን 'የጀርምን ሥርወ መንግሥት' እያለች ነው የምትጠራው። የሰሞኑ መፈንቅለ መንግሥት ጎንጓኞች የዚህች ቀበሌ አማኞች እንደሆኑ ይጠረጠራል። ወደዚች መንደር ስትጠጉ ያልተሰመረ ድንበር አለ፤ የማይታይ። በሰዎች ልብ ውስጥ ብቻ የሚኖር። ቀበሌዋ መግቢያ ላይ የተሰቀለው ማስታወቂያ ‘እንኳን ወደ ጀርመን ግዛት በሰላም መጡ’ ይላል። በአገሬው ቋንቋ እንዲህ ይላል። Königreich Deutschland- የደቾች አገር፤ የደቾች ምደር እንደማለት ነው። የጀርመን ሥርወ መንግሥት ብለው ራሳቸውን ሲጠሩ በታላቅ ኩራት ነው። ይህ ለብዙዎች ፌዝ ሊሆን ይችላል፤ ለቀበሌዋ ነዋሪዎች ግን የምር ነው። የራሳቸው ንጉሥ ሁሉ አላቸው። የንጉሡ ስም ‘ቀዳማዊ ንጉሥ ጴጥሮስ” ይባላል። ይህ ንጉሥ የቢቢሲ ጋዜጠኞች መሆናችንን አውቆ በታላቅ አክብሮት ጣሪያና ግድግዳው በጣውላ በተሠራ አዳራሽ ተቀበለን። ልብ ልትሉ የሚገባው ታዲያ 'ቀዳማዊ ጴጥሮስ' በዚህች ጠባብ አዳራሽ ነበር ከ12 ዓመት በፊት በዓለ ሲመቱ የተከናወነው። በዓለ ሲመቱን ያከናወኑለት መቶ የማይሞሉ የቀበሌዋ ነዋሪዎች ናቸው። በቃ ንጉሣችን አንተ ነህ አሉት። 'ዓለምን የተሻለች ላደርጋት ቃል ገብቻለሁ' አላቸው። ከዚያ ወዲያ ባሉ ዓመታት ታዲያ ለዋናዋ አገር ለጀርመን ብዙም ዕውቅና ሳይሰጥ፣ ብዙም ፊት ሳይሰጥ ራሱን 'ንጉሥ' አድርጎ ቀበሌዋን ቀጥ አድርጎ እየመራት ይገኛል። የራሱን መገበያያ ገንዘብ ሁሉ ማተም ጀምሯል። የቀበሌዋ ነዋሪዎች የራሳቸው ባንዲራ አላቸው። የራሳቸው የዜግነት መታወቂያም ማተም ጀምረዋል። ወደየትም ባይወስድም። ብዙዎቹ ጀርመናዊያን 'ቀዳማዊ ንጉሥ ጴጥሮስንና ተከታዮቹን የቀልድና ቧልት ምንጫቸው አድርገው ነበር የሚያይዋቸው። እስከባለፈው ሳምንት ድረስ። በጀርመን ሊፈጸም የነበረው መፈንቅለ መንግሥት ሴራው የተጠነሰሰው ከዚህ ንጉሥ ተከታዮች መካከል ባሉ ሴረኞች እንደሆነ ከተነገረ በኋላ ግን ከባድ ድንጋጤ ተፈጥሯል። ‘ንጉሥ ቀዳማዊ ጴጥሮስ’ ግን በነገሩ የለሁበትም፤ እጄ ንጹሕ ነው ብሏል። ይህ መንደርና ተከታዮቹ ዓለም በውሸታሞችና ገንዘብ አምላኪዎች እየተሽከረከረች ነው ብሎ ያምናል። በዓለም ላይ የሚመረቱ መድኃኒቶች ዉሸት ናቸው ብለው ያምናሉ። ለምሳሌ በመንደሪቱ ያሉ ‘ዜጎች’ አንዳቸውም የኮቪድ-19 ክትባት አልወሰዱም። እንዲያውም በካፒታሊዝም ሥርዓት በፍጹም አያምኑም። ቀዳማዊ ጴጥሮስ አሁን 'ዜጎቼ' የሚላቸው ተከታዮቹ 5ሺህ ደርሰውልኛል ይላል። የጀርመን ፖሊስ ግን እነዚህ ሰዎች አሻጥረኞች ናቸው ይላቸዋል። በሳይንስ አያምኑም። አሁን ዓለም ላይ በቆመው የአስተዳደር ሥርዓት አያምኑም። ካፒታሊዝም ጥቂቶችን ለማበልጸግ፤ ሰፊውን ሕዝብ ለማቆርቆዝ ነው የተዋቀረው ይላሉ። እነዚህ የማይጨበጥ ‘አሻጥር ሽረባ’ አማኞች 21ሺህ ደርሰዋል ይላል ፖሊስ። ባለፈው ሳምንት ፖሊስ 25 ሰዎችን በቁጥጥር ሥር አውሏል። የጀርመን ፓርላማን ለማውደም፤ መራሔ መንግሥቱንና ሚኒስትሮቻቸውን ለመግደል ሲያሴሩ ነበር ይላል ፖሊስ። የቢቢሲ ጋዜጠኞች ራሱን ‘ንጉሥ ጴጥሮስ ቀዳማዊ’ ብሎ ከሚጠራው ሰው ጋር ጉብኝት እያደረጉ ነው። ሆኖም አንድ ሰው እየተከታተለ ሁሉን ነገር ይቀርጻል። ለምን ሁሉ ነገር እንደሚቀረጽ ሲጠየቅ ቀሪው ዓለም ስለኛ የሚያሰራጨውን የሐሰት መረጃ ለመቋቋም ነው ይላል። የራሱን የቴሌቪዥን ጣቢያ ለመጀመርም እየተሰናዳ ነው። የዚህ ንጉሥ ነኝ ባይ ዕውነተኛ ስም ፒተር ፊዘር ነው። ከዚህ ቀደም ከንቲባ ለመሆን ተወዳድሯል። ፓርላማ ለመግባት ተወዳድሯል። አልተሳካለትም። ያልተሳካልኝ የተገነባዋው ሥርዓት እኔን ለመቀበል ዝግጁ ስላልሆነ ነው፤ ዓለም ለለውጥ ግዝጁ አይደለም ይላል። ከዚያ ወዲያ ነበር የራሱን 'ጀርመን' በራሱ አምሳያ ለመፍጠር የተነሳው። ለእሱ ትክክለኛዋ የጀርመን ሥርወ መንግሥት እሱ የመሠረታት መንደር ናት። እርግጥ ነው ጀርመን እንዲህ ዓይነት ራሱን የቻለ ትንሽ መንግሥት መመሥረትን አትፈቅድም። ነገር ግን መንደሪቱ የሕግ ክፍተቶችን በመጠቀም፣ የራሷ የጤና ሥርዓት እስከመመሥረት ደርሳለች። ፒተር መኪና ሲያሽከረክር ያለ መንጃ ፍቃድ በመሆኑ ብዙ ጊዜ ተከሷል። ለዓመታት እስር ቤት ተወርውሯል። ‘ዜጎቼ’ የሚላቸው ተከታዯቹን አጭበርብሯል በሚልም ዘብጥያ ወርዷል። ይህን ሁሉ አልፎ አዲስ ሥርዓት- አዲስ ግዛት ለመመሥረት ይታትራል። አሁን ቀን ተሌት የጀርመን ፖሊስ ይከታተለዋል። እሱ ግን የንግሥና ክብሩን ጠብቆ ‘ዜጎቼ’ ለሚላቸው፤ ለሚያምኑትና ለሚያምናቸው ሰዎች ማገልገሉን ቀጥሎበታል። ዜጎቼ የሚላቸው በካፒታሊዝም ሥርዓት ማመን የተውትን ነው። በተለይ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የተከታዮቹን ብዛት እጥፍ አድርጎለታል። ሰዎች ክትባት መከተብ እንደሌለባቸው ይመክራል። አሁን ባለው ገንዘብ ሰፋፊ መሬት እየገዛ 'የጀርመን ሥርወ መንግሥትን' እያፋፋ ነው። አዲሱ የጀርመን ሥርወ መንግሥት ሰዎች የማይበዘበዙበት፤ ደስታና ፍሰሐ የሚዘንብበት ይሆናል ይላል። ከነዚህ ግዛቴ ከሚላቸው አንዱ ባርዋልዴ መንደር ይባላል። ከበርሊን ወደ ደቡብ የአንድ ሰዓት የመኪና ጉዞ ነው። ቤቶቹ አሮጌና ጥንታዊ ናቸው። ሆኖም ነዋሪዎች ደስተኞችና ተስፈኞች ይመስላሉ። ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት አይልኩም። ግብር አይከፍሉም። በጀርመን ሁለቱም ከባድ ወንጀሎች ናቸው። እንዴት እንደሚያመልጧቸው እንጃ። 'ንጉሥ ጴጥሮስ ቀዳማዊ’ እንደሚለው አሁን የራሳቸውን የጤናና የሕግ ሥርዓት እያበጁ ነው። የርሱ አስተዳደር ለ 'ዜጎቹ' አስፈላጊውን ምግብ ያቀርባል። አሁን በቀጣይነት ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ተጠቅመው ዘላቂ አረንጓዴ ልማት ለማምጣት፤ የራሳቸውን መድኃኒት ለማምረት ዕቅድ አላቸው። “እኛን ብዙ ሰው የሴራ ተንታኞች አድርጎ እያሰበ ያወግዘናል፤ ስለ ዓለም በተጨነቅን፤ ስለ ሕዝብ ባሰብን እንወገዛለን፤ ነገር ግን ብዙዎቻችን ማታ ሲያቃዠን የሚውለው የግል ጉዳያችን ሳይሆን የኅብረተሰብ ችግር ነው” ይላል። እነ ‘ንጉሥ ጴጥሮስ ቀዳማዊ’ና ተከታዮቹ ለጀርመን ብሔራዊ ቧልቶች ሆነው ቆይተዋል። ከዚህ ወዲያ ግን እንዲያ አይቀጥልም። ምክንያቱም ሁሉም ነገር ሲጠነሰስ እንዲያ ነበር። ሒትለርም ከአንድ ስብሰባ ተነስቶ ነው ዓለምን በእሳት የቀቀለው። ይህ ደግሞ ለጀርመናዊያን የ80 ዓመት መጥፎ ትዝታ ነው። | የጀርመን አካል ሆና ለጀርመን ዕውቅና ያልሰጠቸው 'ቀበሌ' ሰሞኑን በጀርመን መፈንቅለ መንግሥት ሴራ ተጎንጉኗል በሚል በርካቶች በቁጥጥር ሥር ውለዋል። ይህ የአፍሪካ ብቻ ዜና የሚመስለው ነገር እንዴት በጀርመን ተሰማ ያሉ ብዙ ናቸው። በምሥራቅ ጀርመን የምትገኘውን ‘ደችላንድ’ ስለማያውቋት ነው እንደዚያ ያሉት። የዚህ መንደር ልብ ተራራ ነው። ይቺ ትንሽ ቀበሌ ራሷን 'የጀርምን ሥርወ መንግሥት' እያለች ነው የምትጠራው። የሰሞኑ መፈንቅለ መንግሥት ጎንጓኞች የዚህች ቀበሌ አማኞች እንደሆኑ ይጠረጠራል። ወደዚች መንደር ስትጠጉ ያልተሰመረ ድንበር አለ፤ የማይታይ። በሰዎች ልብ ውስጥ ብቻ የሚኖር። ቀበሌዋ መግቢያ ላይ የተሰቀለው ማስታወቂያ ‘እንኳን ወደ ጀርመን ግዛት በሰላም መጡ’ ይላል። በአገሬው ቋንቋ እንዲህ ይላል። Königreich Deutschland- የደቾች አገር፤ የደቾች ምደር እንደማለት ነው። የጀርመን ሥርወ መንግሥት ብለው ራሳቸውን ሲጠሩ በታላቅ ኩራት ነው። ይህ ለብዙዎች ፌዝ ሊሆን ይችላል፤ ለቀበሌዋ ነዋሪዎች ግን የምር ነው። የራሳቸው ንጉሥ ሁሉ አላቸው። የንጉሡ ስም ‘ቀዳማዊ ንጉሥ ጴጥሮስ” ይባላል። ይህ ንጉሥ የቢቢሲ ጋዜጠኞች መሆናችንን አውቆ በታላቅ አክብሮት ጣሪያና ግድግዳው በጣውላ በተሠራ አዳራሽ ተቀበለን። ልብ ልትሉ የሚገባው ታዲያ 'ቀዳማዊ ጴጥሮስ' በዚህች ጠባብ አዳራሽ ነበር ከ12 ዓመት በፊት በዓለ ሲመቱ የተከናወነው። በዓለ ሲመቱን ያከናወኑለት መቶ የማይሞሉ የቀበሌዋ ነዋሪዎች ናቸው። በቃ ንጉሣችን አንተ ነህ አሉት። 'ዓለምን የተሻለች ላደርጋት ቃል ገብቻለሁ' አላቸው። ከዚያ ወዲያ ባሉ ዓመታት ታዲያ ለዋናዋ አገር ለጀርመን ብዙም ዕውቅና ሳይሰጥ፣ ብዙም ፊት ሳይሰጥ ራሱን 'ንጉሥ' አድርጎ ቀበሌዋን ቀጥ አድርጎ እየመራት ይገኛል። የራሱን መገበያያ ገንዘብ ሁሉ ማተም ጀምሯል። የቀበሌዋ ነዋሪዎች የራሳቸው ባንዲራ አላቸው። የራሳቸው የዜግነት መታወቂያም ማተም ጀምረዋል። ወደየትም ባይወስድም። ብዙዎቹ ጀርመናዊያን 'ቀዳማዊ ንጉሥ ጴጥሮስንና ተከታዮቹን የቀልድና ቧልት ምንጫቸው አድርገው ነበር የሚያይዋቸው። እስከባለፈው ሳምንት ድረስ። በጀርመን ሊፈጸም የነበረው መፈንቅለ መንግሥት ሴራው የተጠነሰሰው ከዚህ ንጉሥ ተከታዮች መካከል ባሉ ሴረኞች እንደሆነ ከተነገረ በኋላ ግን ከባድ ድንጋጤ ተፈጥሯል። ‘ንጉሥ ቀዳማዊ ጴጥሮስ’ ግን በነገሩ የለሁበትም፤ እጄ ንጹሕ ነው ብሏል። ይህ መንደርና ተከታዮቹ ዓለም በውሸታሞችና ገንዘብ አምላኪዎች እየተሽከረከረች ነው ብሎ ያምናል። በዓለም ላይ የሚመረቱ መድኃኒቶች ዉሸት ናቸው ብለው ያምናሉ። ለምሳሌ በመንደሪቱ ያሉ ‘ዜጎች’ አንዳቸውም የኮቪድ-19 ክትባት አልወሰዱም። እንዲያውም በካፒታሊዝም ሥርዓት በፍጹም አያምኑም። ቀዳማዊ ጴጥሮስ አሁን 'ዜጎቼ' የሚላቸው ተከታዮቹ 5ሺህ ደርሰውልኛል ይላል። የጀርመን ፖሊስ ግን እነዚህ ሰዎች አሻጥረኞች ናቸው ይላቸዋል። በሳይንስ አያምኑም። አሁን ዓለም ላይ በቆመው የአስተዳደር ሥርዓት አያምኑም። ካፒታሊዝም ጥቂቶችን ለማበልጸግ፤ ሰፊውን ሕዝብ ለማቆርቆዝ ነው የተዋቀረው ይላሉ። እነዚህ የማይጨበጥ ‘አሻጥር ሽረባ’ አማኞች 21ሺህ ደርሰዋል ይላል ፖሊስ። ባለፈው ሳምንት ፖሊስ 25 ሰዎችን በቁጥጥር ሥር አውሏል። የጀርመን ፓርላማን ለማውደም፤ መራሔ መንግሥቱንና ሚኒስትሮቻቸውን ለመግደል ሲያሴሩ ነበር ይላል ፖሊስ። የቢቢሲ ጋዜጠኞች ራሱን ‘ንጉሥ ጴጥሮስ ቀዳማዊ’ ብሎ ከሚጠራው ሰው ጋር ጉብኝት እያደረጉ ነው። ሆኖም አንድ ሰው እየተከታተለ ሁሉን ነገር ይቀርጻል። ለምን ሁሉ ነገር እንደሚቀረጽ ሲጠየቅ ቀሪው ዓለም ስለኛ የሚያሰራጨውን የሐሰት መረጃ ለመቋቋም ነው ይላል። የራሱን የቴሌቪዥን ጣቢያ ለመጀመርም እየተሰናዳ ነው። የዚህ ንጉሥ ነኝ ባይ ዕውነተኛ ስም ፒተር ፊዘር ነው። ከዚህ ቀደም ከንቲባ ለመሆን ተወዳድሯል። ፓርላማ ለመግባት ተወዳድሯል። አልተሳካለትም። ያልተሳካልኝ የተገነባዋው ሥርዓት እኔን ለመቀበል ዝግጁ ስላልሆነ ነው፤ ዓለም ለለውጥ ግዝጁ አይደለም ይላል። ከዚያ ወዲያ ነበር የራሱን 'ጀርመን' በራሱ አምሳያ ለመፍጠር የተነሳው። ለእሱ ትክክለኛዋ የጀርመን ሥርወ መንግሥት እሱ የመሠረታት መንደር ናት። እርግጥ ነው ጀርመን እንዲህ ዓይነት ራሱን የቻለ ትንሽ መንግሥት መመሥረትን አትፈቅድም። ነገር ግን መንደሪቱ የሕግ ክፍተቶችን በመጠቀም፣ የራሷ የጤና ሥርዓት እስከመመሥረት ደርሳለች። ፒተር መኪና ሲያሽከረክር ያለ መንጃ ፍቃድ በመሆኑ ብዙ ጊዜ ተከሷል። ለዓመታት እስር ቤት ተወርውሯል። ‘ዜጎቼ’ የሚላቸው ተከታዯቹን አጭበርብሯል በሚልም ዘብጥያ ወርዷል። ይህን ሁሉ አልፎ አዲስ ሥርዓት- አዲስ ግዛት ለመመሥረት ይታትራል። አሁን ቀን ተሌት የጀርመን ፖሊስ ይከታተለዋል። እሱ ግን የንግሥና ክብሩን ጠብቆ ‘ዜጎቼ’ ለሚላቸው፤ ለሚያምኑትና ለሚያምናቸው ሰዎች ማገልገሉን ቀጥሎበታል። ዜጎቼ የሚላቸው በካፒታሊዝም ሥርዓት ማመን የተውትን ነው። በተለይ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የተከታዮቹን ብዛት እጥፍ አድርጎለታል። ሰዎች ክትባት መከተብ እንደሌለባቸው ይመክራል። አሁን ባለው ገንዘብ ሰፋፊ መሬት እየገዛ 'የጀርመን ሥርወ መንግሥትን' እያፋፋ ነው። አዲሱ የጀርመን ሥርወ መንግሥት ሰዎች የማይበዘበዙበት፤ ደስታና ፍሰሐ የሚዘንብበት ይሆናል ይላል። ከነዚህ ግዛቴ ከሚላቸው አንዱ ባርዋልዴ መንደር ይባላል። ከበርሊን ወደ ደቡብ የአንድ ሰዓት የመኪና ጉዞ ነው። ቤቶቹ አሮጌና ጥንታዊ ናቸው። ሆኖም ነዋሪዎች ደስተኞችና ተስፈኞች ይመስላሉ። ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት አይልኩም። ግብር አይከፍሉም። በጀርመን ሁለቱም ከባድ ወንጀሎች ናቸው። እንዴት እንደሚያመልጧቸው እንጃ። 'ንጉሥ ጴጥሮስ ቀዳማዊ’ እንደሚለው አሁን የራሳቸውን የጤናና የሕግ ሥርዓት እያበጁ ነው። የርሱ አስተዳደር ለ 'ዜጎቹ' አስፈላጊውን ምግብ ያቀርባል። አሁን በቀጣይነት ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ተጠቅመው ዘላቂ አረንጓዴ ልማት ለማምጣት፤ የራሳቸውን መድኃኒት ለማምረት ዕቅድ አላቸው። “እኛን ብዙ ሰው የሴራ ተንታኞች አድርጎ እያሰበ ያወግዘናል፤ ስለ ዓለም በተጨነቅን፤ ስለ ሕዝብ ባሰብን እንወገዛለን፤ ነገር ግን ብዙዎቻችን ማታ ሲያቃዠን የሚውለው የግል ጉዳያችን ሳይሆን የኅብረተሰብ ችግር ነው” ይላል። እነ ‘ንጉሥ ጴጥሮስ ቀዳማዊ’ና ተከታዮቹ ለጀርመን ብሔራዊ ቧልቶች ሆነው ቆይተዋል። ከዚህ ወዲያ ግን እንዲያ አይቀጥልም። ምክንያቱም ሁሉም ነገር ሲጠነሰስ እንዲያ ነበር። ሒትለርም ከአንድ ስብሰባ ተነስቶ ነው ዓለምን በእሳት የቀቀለው። ይህ ደግሞ ለጀርመናዊያን የ80 ዓመት መጥፎ ትዝታ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c6p6l5064pyo |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ የሱዳን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ሕይወታቸው አለፈ | የሱዳን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳዲቅ አል ማህዲ በኮሮናቫይረስ ሳቢያ በ84 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሦስት ሳምንታት ያህል በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ሆስፒታል ገብተው ሕክምና ሲደረግላቸው እንደነበር ቤተሰቦቻቸውና ብሔራዊው ኡማ ፓርቲያቸው ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። እዚያው ሕክምና ሲከታተሉ በነበሩበት ነው ሐሙስ ዕለት ሕይወታቸው ያለፈው። ማህዲ ሆስፒታል የገቡት በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ የአል ማህዲ 21 የቤተሰብ አባላት በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጠ በኋላ ነበር። የ84 ዓመቱ ማህዲ በአውሮፓውያኑ 1989 በቀድሞው የአገሪቷ ፕሬዚደንት ኦማር ኣል በሽር በተመራ መፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ሲወገዱ የአገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስትር ነበሩ። የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡ የመጨረሻው ጠቅላይ ሚኒስትር ነበሩ። እርሳቸው ይመሩት የነበረው ኡማ ፓርቲም በፕሬዚደንት አልበሽር አስተዳዳር ሥር ከነበሩ ጠንካራ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አንዱ ነበር። ማህዲ ምንም እንኳን አልበሽር ባለፈው ዓመት በተነሳ ሕዝባዊ ተቃውሞ ከሥልጣን ቢወገዱም በአገሪቷ ተፅእኖ ፈጣሪ ሰው እንደነበሩ ይነገርላቸዋል። ሕልፈታቸውን ተከትሎም አገሪቷን እያስተዳደረ ያለውና በሲቪልና ወታደራዊ የሥልጣን ከፍፍል የተቋቋመው የሽግግር መንግሥት የሦስት ቀናት የሃዘን ቀን ማወጁን ሮይተርስ ዘግቧል። እንደ ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ በሱዳን እስካሁን 16 ሺህ 052 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን 1 ሺህ 197 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ሕይወታቸውን አጥተዋል። | ኮሮናቫይረስ፡ የሱዳን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ሕይወታቸው አለፈ የሱዳን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳዲቅ አል ማህዲ በኮሮናቫይረስ ሳቢያ በ84 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሦስት ሳምንታት ያህል በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ሆስፒታል ገብተው ሕክምና ሲደረግላቸው እንደነበር ቤተሰቦቻቸውና ብሔራዊው ኡማ ፓርቲያቸው ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። እዚያው ሕክምና ሲከታተሉ በነበሩበት ነው ሐሙስ ዕለት ሕይወታቸው ያለፈው። ማህዲ ሆስፒታል የገቡት በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ የአል ማህዲ 21 የቤተሰብ አባላት በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጠ በኋላ ነበር። የ84 ዓመቱ ማህዲ በአውሮፓውያኑ 1989 በቀድሞው የአገሪቷ ፕሬዚደንት ኦማር ኣል በሽር በተመራ መፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ሲወገዱ የአገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስትር ነበሩ። የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡ የመጨረሻው ጠቅላይ ሚኒስትር ነበሩ። እርሳቸው ይመሩት የነበረው ኡማ ፓርቲም በፕሬዚደንት አልበሽር አስተዳዳር ሥር ከነበሩ ጠንካራ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አንዱ ነበር። ማህዲ ምንም እንኳን አልበሽር ባለፈው ዓመት በተነሳ ሕዝባዊ ተቃውሞ ከሥልጣን ቢወገዱም በአገሪቷ ተፅእኖ ፈጣሪ ሰው እንደነበሩ ይነገርላቸዋል። ሕልፈታቸውን ተከትሎም አገሪቷን እያስተዳደረ ያለውና በሲቪልና ወታደራዊ የሥልጣን ከፍፍል የተቋቋመው የሽግግር መንግሥት የሦስት ቀናት የሃዘን ቀን ማወጁን ሮይተርስ ዘግቧል። እንደ ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ በሱዳን እስካሁን 16 ሺህ 052 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን 1 ሺህ 197 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ሕይወታቸውን አጥተዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-55079316 |
5sports
| "40 ዓመትም ቢሆን ለማራቶን ውድድር ትልቅ አይደለም" ቀነኒሳ በቀለ | ኢትዮጵያዊው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በእሁዱ የበርሊን ማራቶን ሦስተኛ ሆኖ ካጠናቀቀ በኋላ ከስፖርቱ የመውጣት ዕቅድ እንደሌለው አፅንኦት በመስጠት ተናግሯል። ሰኔ ወር ላይ 39 ዓመቱን ያከበረው ቀነኒሳ በኬንያዊው ኤሊዩድ ኪፕቾጌ የተያዘውን ሁለት ሰዓት ከአንድ ደቂቃ ከ 39 ሰኮንድ የማራቶን ክብረ ወሰን ለመስበር እንዳቀደም ይናገራል። ሆኖም በባለፈው ሳምንት መጨረሻ በበርሊን በተደረገው ውድድር ከኪፕቾጌ የክብረ ወሰን ሰዓት ከአምስት ደቂቃዎች በላይ ዘግይቶ እንዲሁም ውድድሩን ካሸነፈው እና ከአገሩ ልጅ ጉዬ አዶላ አንድ ደቂቃ ዘግይቶ ነበር ውድድሩን በሦስተኛነት ያጠናቀቀው። የሦስት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮና ቀነኒሳ በአሁኑ ወቅት ትኩረቱ በሚቀጥለው ዓመት በጀርመን መዲና በርሊን በሚካሄደው የማራቶን ውድድር ክብረ ወሰኑን መስበር ቢሆንም በፓሪስ የሚደረገውን የ2024 ኦሎምፒክም እንደሚሳተፍ ፍንጭ ሰጥቷል። "ከበርካታ አትሌቶች በዚህ ዕድሜ፣ 40 ጥሩ ውጤት ሊያመጡ እንደሚችሉ መረጃ አለኝ። ለማራቶን ውድድር ትልቅ አይደለም" ብሏል። "ጤነኛ ከሆንኩ እና ከተዘጋጀሁ በበርሊን በሚደረገው የማራቶን ውድድር ክብረ ወሰን ለማሻሻል እሮጣለሁ" በማለት ተናግሯል። ከወራት በፊት በኮሮናቫይረስ ተይዞ ያገገመው ቀነኒሳ የበርሊኑ ማራቶን ውድድር ላይም ህመሙ ጥሎብት ባለፈው ጫና ያሰበውን ሳያሳካ እንደቀረም አስረድቷል። በአሁኑ ወቅት የኮሮናቫይረስ ህመም ምልክቶች ባይኖሩትም ከህመሙ በተጨማሪ በአጠቃላይ ከወረርሸኙ ጋር ተያይዘው የተከሰቱ ጉዳዮች በአትሌቱ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጥረዋል። "ለኔ ዋነኛው ችግር በወረርሽኙ ምክንያቱ ስልጠና አለመኖሩ ነው" በማለት ወረርሽኙ የደቀነውን ጉዳት አስረድቷል። በአትሌቲክስ ዘርፍ ምርጥ የረጅም ርቀት ሯጮች አንዱ የሆነው ቀነኒሳ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባለመመረጡ ብዙዎችን ባስገረመ መልኩ ያለፉት ሁለት የኦሎምፒክ ጨዋታዎች ላይ አልተወዳደረም። ቀነኒሳና ፌዴሬሽኑ ጥሩ ግንኙነት የሌላቸው ሲሆን በቅርቡም በነበረው የምርጫ ሂደት ላይ በማራቶን ውድድር ሁለተኛው ፈጣን አትሌት ቢሆንም ችላ ተብሏል። ቀነኒሳ ከሁለት አመት በፊት በበርሊን በተደረገው የማራቶን ውድድር ከኪፕቾጌ ክብረ ወሰን ጥቂት በሚባል፣ ሁለት ሰኮንዶችን ዘግይቶ በመግባት አሸናፊ ሆኗል። "በእርግጠኝነት ከሦስት አመት በኋላ በሚደረገው ፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ መሮጥ እፈለጋለሁ፤ ነገር ግን በኢትዮጵያ ፌዴሬሽን መሰረት መወሰን ከባድ ነው" በማለት ተናግሯል። "እኔ ያለኝ አንድ አገር ብቻ ነው። ወደ ፖሪስ መሄድ ብፈልግ እንኳን የፌዴሬሽኑን መስፈርቶች ስለማላውቅ አስቸጋሪ ይሆናል" ብሏል። | "40 ዓመትም ቢሆን ለማራቶን ውድድር ትልቅ አይደለም" ቀነኒሳ በቀለ ኢትዮጵያዊው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በእሁዱ የበርሊን ማራቶን ሦስተኛ ሆኖ ካጠናቀቀ በኋላ ከስፖርቱ የመውጣት ዕቅድ እንደሌለው አፅንኦት በመስጠት ተናግሯል። ሰኔ ወር ላይ 39 ዓመቱን ያከበረው ቀነኒሳ በኬንያዊው ኤሊዩድ ኪፕቾጌ የተያዘውን ሁለት ሰዓት ከአንድ ደቂቃ ከ 39 ሰኮንድ የማራቶን ክብረ ወሰን ለመስበር እንዳቀደም ይናገራል። ሆኖም በባለፈው ሳምንት መጨረሻ በበርሊን በተደረገው ውድድር ከኪፕቾጌ የክብረ ወሰን ሰዓት ከአምስት ደቂቃዎች በላይ ዘግይቶ እንዲሁም ውድድሩን ካሸነፈው እና ከአገሩ ልጅ ጉዬ አዶላ አንድ ደቂቃ ዘግይቶ ነበር ውድድሩን በሦስተኛነት ያጠናቀቀው። የሦስት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮና ቀነኒሳ በአሁኑ ወቅት ትኩረቱ በሚቀጥለው ዓመት በጀርመን መዲና በርሊን በሚካሄደው የማራቶን ውድድር ክብረ ወሰኑን መስበር ቢሆንም በፓሪስ የሚደረገውን የ2024 ኦሎምፒክም እንደሚሳተፍ ፍንጭ ሰጥቷል። "ከበርካታ አትሌቶች በዚህ ዕድሜ፣ 40 ጥሩ ውጤት ሊያመጡ እንደሚችሉ መረጃ አለኝ። ለማራቶን ውድድር ትልቅ አይደለም" ብሏል። "ጤነኛ ከሆንኩ እና ከተዘጋጀሁ በበርሊን በሚደረገው የማራቶን ውድድር ክብረ ወሰን ለማሻሻል እሮጣለሁ" በማለት ተናግሯል። ከወራት በፊት በኮሮናቫይረስ ተይዞ ያገገመው ቀነኒሳ የበርሊኑ ማራቶን ውድድር ላይም ህመሙ ጥሎብት ባለፈው ጫና ያሰበውን ሳያሳካ እንደቀረም አስረድቷል። በአሁኑ ወቅት የኮሮናቫይረስ ህመም ምልክቶች ባይኖሩትም ከህመሙ በተጨማሪ በአጠቃላይ ከወረርሸኙ ጋር ተያይዘው የተከሰቱ ጉዳዮች በአትሌቱ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጥረዋል። "ለኔ ዋነኛው ችግር በወረርሽኙ ምክንያቱ ስልጠና አለመኖሩ ነው" በማለት ወረርሽኙ የደቀነውን ጉዳት አስረድቷል። በአትሌቲክስ ዘርፍ ምርጥ የረጅም ርቀት ሯጮች አንዱ የሆነው ቀነኒሳ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባለመመረጡ ብዙዎችን ባስገረመ መልኩ ያለፉት ሁለት የኦሎምፒክ ጨዋታዎች ላይ አልተወዳደረም። ቀነኒሳና ፌዴሬሽኑ ጥሩ ግንኙነት የሌላቸው ሲሆን በቅርቡም በነበረው የምርጫ ሂደት ላይ በማራቶን ውድድር ሁለተኛው ፈጣን አትሌት ቢሆንም ችላ ተብሏል። ቀነኒሳ ከሁለት አመት በፊት በበርሊን በተደረገው የማራቶን ውድድር ከኪፕቾጌ ክብረ ወሰን ጥቂት በሚባል፣ ሁለት ሰኮንዶችን ዘግይቶ በመግባት አሸናፊ ሆኗል። "በእርግጠኝነት ከሦስት አመት በኋላ በሚደረገው ፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ መሮጥ እፈለጋለሁ፤ ነገር ግን በኢትዮጵያ ፌዴሬሽን መሰረት መወሰን ከባድ ነው" በማለት ተናግሯል። "እኔ ያለኝ አንድ አገር ብቻ ነው። ወደ ፖሪስ መሄድ ብፈልግ እንኳን የፌዴሬሽኑን መስፈርቶች ስለማላውቅ አስቸጋሪ ይሆናል" ብሏል። | https://www.bbc.com/amharic/news-58696684 |
2health
| በጎርፍ የተጥለቀለቁ የለንደን ሆስፒታሎች ታካሚዎችን 'አትምጡ' አሉ | ሁለት በምሥራቅ ለንደን የሚገኙ ሆስፒታሎች ድንገተኛ ክፍሎቻቸው በጎርፍ በመጥለቅለቃቸው ሳቢያ ታካሚዎች ወደ ሆስፒታሎቹ እንዳይሄዱ አስጠነቀቁ። ሁለቱ ሆስፒታሎች የጎርፍ አደጋ የደረሰባቸው ትላንት ነው። ዊፐርስ ክሮስ የተባለው ሆስፒታል የኤሌክትሪክ አቅርቦቱ ተቋርጧል። 100 ተኝተው የሚታከሙ ሰዎችን ከሆስፒታሉ ለማስወጣትም ተገዷል። ኒውሀም የተባለው ሆስፒታል ደግሞ ታካሚዎች ወደ ሌሎች የድንገተኛ ክፍሎች እንዲሄዱ ጠይቋል። የለንደን እሳት አደጋ መከላከያ ብርጌድ እንዳለው፤ ከ1,000 በላይ ከጎርፍ አደጋ ጋር የተያያዙ የስልክ ጥሪዎች ደርሰውታል። መኪና ውስጥ ሳሉ የጎርፍ አደጋው የገጠማቸውን ጨምሮ በመኖሪያ ቤታቸው ሆነው ከአደጋው ማምለጥ የተሳናቸው ሰዎችንም መታደግ ተችሏል። ሁለቱን ሆስፒታሎች የሚያስተዳድረው ማኅበር ቃል አቀባይ "ታካሚዎች ከኛ ሆስፒታሎች ውጪ ያሉ የሕክምና መስጫ አማራጮችን እንዲጠቀሙ እንጠይቃለን" ብለዋል። ለንደን ውስጥ የሚገኙ አውራ ጎዳናዎች በጎርፍ አደጋው ምክንያት ተዘግተዋል። ሴንት ፓርክ የተባለው ፓርክ ውስጥ የዝናቡ መጠን 41.6 ሚሊ ሜትር እንደደረሰና፤ ይህም ለንደን ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ በጎርፍ ከተጥለቀሉ ቦታዎች ቀዳሚ እንደሚያደርገው ተገልጿል። በምሥራቅ ለንደን የሚኖሩ ዜጎች ትላንት ጎርፉ ወደ ቤታቸው እንዳይገባ በመጥረጊያ ወይም የእንጨት ከለላ በመሥራት ሲከላከሉ ነበር። የሬስቶራንት አስተዳዳሪዋ ማርያ ፔቫ የጎረቤቷ መኝታ ቤት በጎርፍ እንደተዋጠ ተናግራለች። ልጇ ጎረቤቶቿን ከጎርፉ ለመታደግ እየሞከረ እንደነበረም ታክላለች። "ልጄ ምግብ ሊገዛ ወጥቶ ሲመለስ ሰፈራችን በጎርፍ ተጥለቅልቆ ጠበቀው። ጎርፉ ቤታችን ሊገባም ነበር" ብላለች የ46 ዓመቷ ማርያ። ሆስፒታሎቹ በመዘጋታቸው አምቡላንሶች ህሙማንን ወደ ሌሎች ሕክምና መስጫዎች ለመውሰድ ተገደዋል። ኒውሀም የተባለው ሆስፒታል አሁን አገልግሎት እየሰጠ ያለው በእናቶችና ሕፃናት ክፍሉ ነው። ይህ ክፍል በጎርፍ አልተጠቃም። የሆስፒታሉ ሬዚደንት ክሪስ ዴት "የጎርፍ ውሃው አስፋልቱን አጥለቅልቆት ነበር። መራመድም አይቻልም። ውሃው እስከ ጉልበቴ ድረስ ሞልቶ ስለነበር አውቶብስ ውስጥ ለመግባት ተቸግሬ ነበር" ሲል በትዊተር ገጹ ጽፏል። የ28 ዓመቱ የለንደን ነዋሪ ኤዲ ኤልየት "እንደዚህ አይነት ነገር ለንደን ውስጥ አይቼ አላውቅም። አውቶብሶች በጎርፍ ተይዘው ቆመው ነበር" ብሏል። | በጎርፍ የተጥለቀለቁ የለንደን ሆስፒታሎች ታካሚዎችን 'አትምጡ' አሉ ሁለት በምሥራቅ ለንደን የሚገኙ ሆስፒታሎች ድንገተኛ ክፍሎቻቸው በጎርፍ በመጥለቅለቃቸው ሳቢያ ታካሚዎች ወደ ሆስፒታሎቹ እንዳይሄዱ አስጠነቀቁ። ሁለቱ ሆስፒታሎች የጎርፍ አደጋ የደረሰባቸው ትላንት ነው። ዊፐርስ ክሮስ የተባለው ሆስፒታል የኤሌክትሪክ አቅርቦቱ ተቋርጧል። 100 ተኝተው የሚታከሙ ሰዎችን ከሆስፒታሉ ለማስወጣትም ተገዷል። ኒውሀም የተባለው ሆስፒታል ደግሞ ታካሚዎች ወደ ሌሎች የድንገተኛ ክፍሎች እንዲሄዱ ጠይቋል። የለንደን እሳት አደጋ መከላከያ ብርጌድ እንዳለው፤ ከ1,000 በላይ ከጎርፍ አደጋ ጋር የተያያዙ የስልክ ጥሪዎች ደርሰውታል። መኪና ውስጥ ሳሉ የጎርፍ አደጋው የገጠማቸውን ጨምሮ በመኖሪያ ቤታቸው ሆነው ከአደጋው ማምለጥ የተሳናቸው ሰዎችንም መታደግ ተችሏል። ሁለቱን ሆስፒታሎች የሚያስተዳድረው ማኅበር ቃል አቀባይ "ታካሚዎች ከኛ ሆስፒታሎች ውጪ ያሉ የሕክምና መስጫ አማራጮችን እንዲጠቀሙ እንጠይቃለን" ብለዋል። ለንደን ውስጥ የሚገኙ አውራ ጎዳናዎች በጎርፍ አደጋው ምክንያት ተዘግተዋል። ሴንት ፓርክ የተባለው ፓርክ ውስጥ የዝናቡ መጠን 41.6 ሚሊ ሜትር እንደደረሰና፤ ይህም ለንደን ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ በጎርፍ ከተጥለቀሉ ቦታዎች ቀዳሚ እንደሚያደርገው ተገልጿል። በምሥራቅ ለንደን የሚኖሩ ዜጎች ትላንት ጎርፉ ወደ ቤታቸው እንዳይገባ በመጥረጊያ ወይም የእንጨት ከለላ በመሥራት ሲከላከሉ ነበር። የሬስቶራንት አስተዳዳሪዋ ማርያ ፔቫ የጎረቤቷ መኝታ ቤት በጎርፍ እንደተዋጠ ተናግራለች። ልጇ ጎረቤቶቿን ከጎርፉ ለመታደግ እየሞከረ እንደነበረም ታክላለች። "ልጄ ምግብ ሊገዛ ወጥቶ ሲመለስ ሰፈራችን በጎርፍ ተጥለቅልቆ ጠበቀው። ጎርፉ ቤታችን ሊገባም ነበር" ብላለች የ46 ዓመቷ ማርያ። ሆስፒታሎቹ በመዘጋታቸው አምቡላንሶች ህሙማንን ወደ ሌሎች ሕክምና መስጫዎች ለመውሰድ ተገደዋል። ኒውሀም የተባለው ሆስፒታል አሁን አገልግሎት እየሰጠ ያለው በእናቶችና ሕፃናት ክፍሉ ነው። ይህ ክፍል በጎርፍ አልተጠቃም። የሆስፒታሉ ሬዚደንት ክሪስ ዴት "የጎርፍ ውሃው አስፋልቱን አጥለቅልቆት ነበር። መራመድም አይቻልም። ውሃው እስከ ጉልበቴ ድረስ ሞልቶ ስለነበር አውቶብስ ውስጥ ለመግባት ተቸግሬ ነበር" ሲል በትዊተር ገጹ ጽፏል። የ28 ዓመቱ የለንደን ነዋሪ ኤዲ ኤልየት "እንደዚህ አይነት ነገር ለንደን ውስጥ አይቼ አላውቅም። አውቶብሶች በጎርፍ ተይዘው ቆመው ነበር" ብሏል። | https://www.bbc.com/amharic/news-57972780 |
5sports
| ለተሰንበት ግደይ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ10 ሺህ ሜትር አሸናፊ ሆነች | ለተሰንበት ግደይ በአሜሪካ ኦሪገን እየተካሄደ ባለው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ10 ሺህ ሜትር አሸናፊ ሆነች። የ24 ዓመቷ አትሌት በዚህ ውድድር 30፡09፡94 ሰዓት በማስመዝገብ ነው የአንደኛነት ስፍራን በማግኘት የወርቅ ሜዳሊያዋን ያጠለቀችው። ፍጻሜው ላይ ከፍተኛ ትንቅንቅ በታየበት በዚህ ውድድር፣ ለተሰንበትን ተከትለው ኬንያውያን አትሌቶች ሄለን ኦቢሪ በሁለተኝነት እና ማርጋሬት ቼሊሞ ኪምኬምቦይ በሦስተኛነት አጠናቀዋል። ትውልደ ኢትዮጵያዊቷና ለሆላንድ የምትወደዳረው ሲፋን ሐሰን በዚህ ውድድር ላይ በአራተኝነት አጠናቃለች። በዚህ ውድድር ላይ ተሳታፊ የነበሩት ኢትዮጵያውያን አትሌቶቹ እጅጋዬሁ ታዬ 6ኛ፣ ቦሰና ሙላቴ 8ኛ ደረጃን ይዘው ውድድሩን አጠናቀዋል። ቀደም ሲል በ10 ሺህ ሜትር፣ በ5 ሺህ ሜትር እና በግማሽ ማራቶች ሦስት የዓለም ክብረ ወሰኖችን የያዘችው አትሌት ለተሰንበት በዚህ ዓለም አቀፍ ከፍተኛ ውድድር ላይ በመሳተፍም አሸናፊነቷን አስጠብቃለች። ለተሰንበት በቶኪዮ ማራቶን የአሸናፊነት ቦታ ትልቅ ግምት የተሰጣት ሲሆን 3ኛ በመሆን የነሐስ ተሸላሚ ሆናለች። እንዲሁም በአውሮፓውያኑ 2019 በኳታር ዶሃ በነበረው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ለተሰንበት በሁለተኝነት አጠናቃለች። ለተሰንበት ከውድድሩ በኋላም ለመገናኛ ብዙኃ በሰጠችው አስተያየት “ይህንን ውድድር ማሸነፍ ትልቁ አላማዬ ነበር። ህልሜም እውን ሆነ። ይህ ድል ከዓለም ክብረ ወሰን በበለጠ ለእኔ ትልቁ ነው። በውድድሩ በጣም ደስተኛ ነኝ” ብላለች። አትሌቷ በዚህ ዓመት ጥቅምት ወር ላይ ስፔን ቫሌንሺያ በተካሄደው ግማሽ ማራቶን ሩጫ የዓለም ክብረ ወሰን መስበሯ ይታወሳል። ለተሰንበት በኬንያዊቷ ሩት ቼፕንጌቲክ በ1 ሰዓት ከ04 ደቂቃ ከ02 ሰኮንድ ተይዞ የነበረውን የግማሽ ማራቶን ክብረወሰን በማሻሻል 1 ሰዓት ከ02 ደቂቃ ከ52 ሰኮንዶች በመግባት ክብረ ወሰን ጨብጣለች። በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ አምስት ሰዓት ላይ የወንዶች 10 ሺህ ሜትር ውድድር የሚካሄድ ሲሆን በሪሁ አረጋዊ፣ ሰለሞን ባረጋና ታደሰ ወርቁ እንደሚወዳደሩ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያስረዳል። ሰለሞን ባረጋ በጃፓን ቶኪዮ ኦሊምፒክ በ10 ሺህ ሜትር በማሸነፍ የወርቅ ሜዳሊያ ማግኘቱ ይታወሳል። ሰለሞን በዚህ ውድድር ያስመዘገበው ሰዓት 27፡43፡22 ሲሆን የዓለም ክብረወሰን ባለቤት የሆነውንም ጆሹዋ ቼፕቴጊን አስከትሎ ነው የገባው። በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ጉዳፍ ፀጋይ፣ ፍረወይኒ ኃይሉና ሂሩት መሸሻ ማጣሪያውን አልፈዋል። | ለተሰንበት ግደይ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ10 ሺህ ሜትር አሸናፊ ሆነች ለተሰንበት ግደይ በአሜሪካ ኦሪገን እየተካሄደ ባለው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ10 ሺህ ሜትር አሸናፊ ሆነች። የ24 ዓመቷ አትሌት በዚህ ውድድር 30፡09፡94 ሰዓት በማስመዝገብ ነው የአንደኛነት ስፍራን በማግኘት የወርቅ ሜዳሊያዋን ያጠለቀችው። ፍጻሜው ላይ ከፍተኛ ትንቅንቅ በታየበት በዚህ ውድድር፣ ለተሰንበትን ተከትለው ኬንያውያን አትሌቶች ሄለን ኦቢሪ በሁለተኝነት እና ማርጋሬት ቼሊሞ ኪምኬምቦይ በሦስተኛነት አጠናቀዋል። ትውልደ ኢትዮጵያዊቷና ለሆላንድ የምትወደዳረው ሲፋን ሐሰን በዚህ ውድድር ላይ በአራተኝነት አጠናቃለች። በዚህ ውድድር ላይ ተሳታፊ የነበሩት ኢትዮጵያውያን አትሌቶቹ እጅጋዬሁ ታዬ 6ኛ፣ ቦሰና ሙላቴ 8ኛ ደረጃን ይዘው ውድድሩን አጠናቀዋል። ቀደም ሲል በ10 ሺህ ሜትር፣ በ5 ሺህ ሜትር እና በግማሽ ማራቶች ሦስት የዓለም ክብረ ወሰኖችን የያዘችው አትሌት ለተሰንበት በዚህ ዓለም አቀፍ ከፍተኛ ውድድር ላይ በመሳተፍም አሸናፊነቷን አስጠብቃለች። ለተሰንበት በቶኪዮ ማራቶን የአሸናፊነት ቦታ ትልቅ ግምት የተሰጣት ሲሆን 3ኛ በመሆን የነሐስ ተሸላሚ ሆናለች። እንዲሁም በአውሮፓውያኑ 2019 በኳታር ዶሃ በነበረው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ለተሰንበት በሁለተኝነት አጠናቃለች። ለተሰንበት ከውድድሩ በኋላም ለመገናኛ ብዙኃ በሰጠችው አስተያየት “ይህንን ውድድር ማሸነፍ ትልቁ አላማዬ ነበር። ህልሜም እውን ሆነ። ይህ ድል ከዓለም ክብረ ወሰን በበለጠ ለእኔ ትልቁ ነው። በውድድሩ በጣም ደስተኛ ነኝ” ብላለች። አትሌቷ በዚህ ዓመት ጥቅምት ወር ላይ ስፔን ቫሌንሺያ በተካሄደው ግማሽ ማራቶን ሩጫ የዓለም ክብረ ወሰን መስበሯ ይታወሳል። ለተሰንበት በኬንያዊቷ ሩት ቼፕንጌቲክ በ1 ሰዓት ከ04 ደቂቃ ከ02 ሰኮንድ ተይዞ የነበረውን የግማሽ ማራቶን ክብረወሰን በማሻሻል 1 ሰዓት ከ02 ደቂቃ ከ52 ሰኮንዶች በመግባት ክብረ ወሰን ጨብጣለች። በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ አምስት ሰዓት ላይ የወንዶች 10 ሺህ ሜትር ውድድር የሚካሄድ ሲሆን በሪሁ አረጋዊ፣ ሰለሞን ባረጋና ታደሰ ወርቁ እንደሚወዳደሩ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያስረዳል። ሰለሞን ባረጋ በጃፓን ቶኪዮ ኦሊምፒክ በ10 ሺህ ሜትር በማሸነፍ የወርቅ ሜዳሊያ ማግኘቱ ይታወሳል። ሰለሞን በዚህ ውድድር ያስመዘገበው ሰዓት 27፡43፡22 ሲሆን የዓለም ክብረወሰን ባለቤት የሆነውንም ጆሹዋ ቼፕቴጊን አስከትሎ ነው የገባው። በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ጉዳፍ ፀጋይ፣ ፍረወይኒ ኃይሉና ሂሩት መሸሻ ማጣሪያውን አልፈዋል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cy7q9vn5pwyo |
2health
| በኒው ዚላንድ ሰዎች በፍቃዳቸው እንዲሞቱ የሚደነግግ ሕግ ሊወጣ ነው | በኒው ዚላንድ በጠና የታመሙ ሰዎች በፍቃዳቸው እንዲሞቱ የሚደነግግ ሕግ ሊወጣ ነው። ባለፈው ወር በተካሄደ ሕዝበ ውሳኔ 65.2% መራጮች የፍቃድ ሞትን ደግፈዋል። ዩትኔዝያ ወይም የፈቃድ ሞት በጠና የታመሙ ወይም ከስድስት ወር በላይ እንደማይኖሩ የተነገራቸው ሰዎች በህክምና እርዳታ ሕይወታቸው እንዲያልፍ የሚደረግበት ሂደት ነው። ሕጉ በቀጣዩ ዓመት ጥቅምት ወር ጸድቆ ይተገበራል ተብሎ ይጠበቃል። ኒው ዚላንድ ሕጉን ካጸደቀች የፈቃድ ሞት ከሚተገበርባቸው ጥቂት አገሮች አንዷ ትሆናለች። ዩትኔዝያ ከተፈቀደባቸው አገሮች ኔዘርላንድ እና ካናዳ ይጠቀሳሉ። ኒው ዚላንዳውያን ባለፈው ወር መሪያቸውን ሲመርጡ ስለ ፈቃድ ሞት እና ዕጸ ፋርስ ሕዝበ ውሳኔ አድርገዋል። ዕጸ ፋርስን ለመዝናኛ መጠቀም ሕጋዊ እንዲሆን ድምጽ የሰጡት 46.1% ብቻ ሲሆኑ፤ 53.1% ተቃውመዋል። የፈቃድ ሞትን ጠቅላይ ሚንስትር ጀሲንዳ አርደን እንዲሁም ተቀናቃኛቸው ጁዲት ኮሊንስም ይደግፉታል። ሕዝቡም ሕጋዊ ይሁን ብሎ እንደሚመርጥ ይጠበቅ ነበር። ባለቤቱ የሞተችበት ማት ቪከርስ "ርህራሄ እና ደግነት አሸንፈዋል። በጠና የታመሙ ኒው ዚላንዳውያን ሕይወታቸውን ማሳለፍ ስለሚችሉ ደስ ብሎኛል" ሲል የተሰማውን ገልጿል። ጠበቃ የነበረችው ባለቤቱ የአንጎል እጢ ሲገኝባት በፈቃዷ ለመሞት ክስ ብትመሠረትም ሳታሸንፍ በጠና ታማ ከአምስት ዓመታት በፊት ሞታለች። "ባለቤቴ መሞት አትሻም ነበር። ማንም ሰው መሞት አይፈልግም። ነገር ግን መኖር የምርጫ ጉዳይ ነው። ስቃይ እየበረታ ሲሄድ መሞት አንዱ ምርጫ መሆን አለበት" ብሏል። አንድ ሰው በፈቃዱ ለመሞት በጠና የታመመ ወይም ከስድስት ወር በላይ እንደማይኖር የተረጋገጠ መሆን አለበት። ሰውነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተዳከመ እንደሄደና ውሳኔው ላይ ለመድረስ በቂ መረጃ እንዳለው ማረጋገጥም ተገቢ ነው። ሂደቱ የሚመራው በዶክተር ወይም በነርስ ነው። አንድ ሰው እድሜው ስለገፋ፣ የአእምሮ ህመም ስላለበት ወይም የአካል ጉዳት ስላለበት የፍቃድ ሞት ሕግን መተግበር አይችልም። ሕጉን የሚቃወሙ ሰዎች "እንድንኖር እንጂ እንድንሞት አትርዱን" ሲሉ ምክር ቤት ሄደው ተቃውሞ አሰምተዋል። ሕጉ ለማኅበረሰቡ አስጊ እንደሆነ እና ራስን ማጥፋትን ለመግታት ከወጣ መርህ ጋር እንደሚቃረን ይናገራሉ። ሌላው መከራከሪያ ነጥብ በጠና የታመሙ ሰዎች የቤተሰብ ሸክም ላለመሆን ብለው በፈቃዳቸው ሊሞቱ ይችላሉ የሚለው ነው። ዩትኔዝያን አጥብቆ ሲተች የነበረ ቡድን "የኒው ዚላንድ ዜጎች የተሳሳተ ሕግ እንዲጸድቅ ድምጽ በመስጠታቸው አዝነናል" ሲል መግለጫ አውጥቷል። የፈቃድ ሞትን ሕጋዊ ያደረጉ አገሮች የኒው ዚላንድን ሕዝበ ውሳኔ በቅርበት ሲከታተሉ ነበር። ከነዚህ መካከል ቤልጄም፣ ካናዳ፣ ኮሎምቢያ፣ ሉግዘምበርግ እና ኔዘርላንድስ ይጠቀሳሉ። በኔዘርላንድስ በህክምና ታግዞ ራስን ማጥፋት ይቻላል። በአሜሪካ ያሉ ብዙ ግዛቶች እና የአውስትራሊያዋ ቪክቶሪያ በህክምና የታገዘ ሞትን ፈቅደዋል። | በኒው ዚላንድ ሰዎች በፍቃዳቸው እንዲሞቱ የሚደነግግ ሕግ ሊወጣ ነው በኒው ዚላንድ በጠና የታመሙ ሰዎች በፍቃዳቸው እንዲሞቱ የሚደነግግ ሕግ ሊወጣ ነው። ባለፈው ወር በተካሄደ ሕዝበ ውሳኔ 65.2% መራጮች የፍቃድ ሞትን ደግፈዋል። ዩትኔዝያ ወይም የፈቃድ ሞት በጠና የታመሙ ወይም ከስድስት ወር በላይ እንደማይኖሩ የተነገራቸው ሰዎች በህክምና እርዳታ ሕይወታቸው እንዲያልፍ የሚደረግበት ሂደት ነው። ሕጉ በቀጣዩ ዓመት ጥቅምት ወር ጸድቆ ይተገበራል ተብሎ ይጠበቃል። ኒው ዚላንድ ሕጉን ካጸደቀች የፈቃድ ሞት ከሚተገበርባቸው ጥቂት አገሮች አንዷ ትሆናለች። ዩትኔዝያ ከተፈቀደባቸው አገሮች ኔዘርላንድ እና ካናዳ ይጠቀሳሉ። ኒው ዚላንዳውያን ባለፈው ወር መሪያቸውን ሲመርጡ ስለ ፈቃድ ሞት እና ዕጸ ፋርስ ሕዝበ ውሳኔ አድርገዋል። ዕጸ ፋርስን ለመዝናኛ መጠቀም ሕጋዊ እንዲሆን ድምጽ የሰጡት 46.1% ብቻ ሲሆኑ፤ 53.1% ተቃውመዋል። የፈቃድ ሞትን ጠቅላይ ሚንስትር ጀሲንዳ አርደን እንዲሁም ተቀናቃኛቸው ጁዲት ኮሊንስም ይደግፉታል። ሕዝቡም ሕጋዊ ይሁን ብሎ እንደሚመርጥ ይጠበቅ ነበር። ባለቤቱ የሞተችበት ማት ቪከርስ "ርህራሄ እና ደግነት አሸንፈዋል። በጠና የታመሙ ኒው ዚላንዳውያን ሕይወታቸውን ማሳለፍ ስለሚችሉ ደስ ብሎኛል" ሲል የተሰማውን ገልጿል። ጠበቃ የነበረችው ባለቤቱ የአንጎል እጢ ሲገኝባት በፈቃዷ ለመሞት ክስ ብትመሠረትም ሳታሸንፍ በጠና ታማ ከአምስት ዓመታት በፊት ሞታለች። "ባለቤቴ መሞት አትሻም ነበር። ማንም ሰው መሞት አይፈልግም። ነገር ግን መኖር የምርጫ ጉዳይ ነው። ስቃይ እየበረታ ሲሄድ መሞት አንዱ ምርጫ መሆን አለበት" ብሏል። አንድ ሰው በፈቃዱ ለመሞት በጠና የታመመ ወይም ከስድስት ወር በላይ እንደማይኖር የተረጋገጠ መሆን አለበት። ሰውነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተዳከመ እንደሄደና ውሳኔው ላይ ለመድረስ በቂ መረጃ እንዳለው ማረጋገጥም ተገቢ ነው። ሂደቱ የሚመራው በዶክተር ወይም በነርስ ነው። አንድ ሰው እድሜው ስለገፋ፣ የአእምሮ ህመም ስላለበት ወይም የአካል ጉዳት ስላለበት የፍቃድ ሞት ሕግን መተግበር አይችልም። ሕጉን የሚቃወሙ ሰዎች "እንድንኖር እንጂ እንድንሞት አትርዱን" ሲሉ ምክር ቤት ሄደው ተቃውሞ አሰምተዋል። ሕጉ ለማኅበረሰቡ አስጊ እንደሆነ እና ራስን ማጥፋትን ለመግታት ከወጣ መርህ ጋር እንደሚቃረን ይናገራሉ። ሌላው መከራከሪያ ነጥብ በጠና የታመሙ ሰዎች የቤተሰብ ሸክም ላለመሆን ብለው በፈቃዳቸው ሊሞቱ ይችላሉ የሚለው ነው። ዩትኔዝያን አጥብቆ ሲተች የነበረ ቡድን "የኒው ዚላንድ ዜጎች የተሳሳተ ሕግ እንዲጸድቅ ድምጽ በመስጠታቸው አዝነናል" ሲል መግለጫ አውጥቷል። የፈቃድ ሞትን ሕጋዊ ያደረጉ አገሮች የኒው ዚላንድን ሕዝበ ውሳኔ በቅርበት ሲከታተሉ ነበር። ከነዚህ መካከል ቤልጄም፣ ካናዳ፣ ኮሎምቢያ፣ ሉግዘምበርግ እና ኔዘርላንድስ ይጠቀሳሉ። በኔዘርላንድስ በህክምና ታግዞ ራስን ማጥፋት ይቻላል። በአሜሪካ ያሉ ብዙ ግዛቶች እና የአውስትራሊያዋ ቪክቶሪያ በህክምና የታገዘ ሞትን ፈቅደዋል። | https://www.bbc.com/amharic/54744271 |
0business
| አንበጣ ፡ ኢትዮጵያ የአንበጣ መንጋን ለመቆጣጠር ምን ያህል አውሮፕላኖች አሏት? | የምሥራቅ አፍሪካ አገራትን በማዳረስ በተለይ የኢትዮጵያን ሰሜናዊና ሰሜን ምሥራቅ አካባቢዎችን ክፉኛ እያጠቃ የሚገኘውን ግዙፍ የበረሃ አንበጣ መንጋ ለመከላከል ከአየር ላይ ጸረ ተባይ መድኃኒት የሚረጩ ጥቂት አውሮፕላኖች ተሰማርተው ጥረት እየተደረገ ነው። የአንበጣ መንጋው ክፉኛ ባጠቃቸው አካባቢዎች የሚገኙ አርሶ አደሮች ብዙም ውጤታ ያልሆነውን ባህላዊ አንበጣን የመከላከያ መንገድ ጥረት እያደረጉ ሲሆን፤ ከዚሁ ጎን ለጎን አውሮፕላኖችም ተሰማርተው ጸረ ተባይ መድኃኒቶችን እየረጩ ቢሆንም እክል እየገጠማቸው የመከላከሉ ሥራ ላይ እክል እያጋጠመ ነው። ባለፈው የመስከረም ወር ሁለት የጸረ ተባይ መርቻ አውሮፕላኖች በሰሜንና በምሥራቅ ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ አካበቢዎች ተሰማርተው በነበረበት ጊዜ ወድቀው ከአገልግሎት ውጪ ሆነዋል። የመጀመሪያው አውሮፕላን በአማራ ክልል ወረባቦ ወረዳ ፍራንጉል በሚባል ቦታ ወድቆ የተከሰከሰ ሲሆን የወረዳው የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ሳዳም ሽመልስ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በአብራሪው ላይ ከደረሰው መጠነኛ ጉዳት ውጪ በሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም። ነገር ግን በአደጋው በአውሮፕላኑ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት የተነገረ ሲሆን በዚህም ሳቢያ አውሮፕላኑ ከአገልግሎት ውጪ ሊሆን ይችላል ተብሏል። ሁለተኛው አውሮፕላን ደግሞ በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ጃርሶ ወረዳ የአንበጣ መንጋ ለመከላከል ኬሚካል በመርጨት ላይ በነበረበት ጊዜ ጊደያ በሃ በምትበል ቀበሌ ውስጥ ነው የመውደቅ አደጋ የገጠመው። የወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አብዱል ቃድር ደዚ ለቢቢሲ በአደጋው ወቅት በአውሮፕላኑ ውስጥ አብራሪው ብቻ የነበረ ሲሆን እሱም ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰበትና በአውሮፕላኑ ላይም ቀላል ጉዳት እንዳጋጠመ ተናግረዋል። ስለዚህም የአንበጣው መንጋ ጥፋት የሚያደርስባቸውን አካባቢዎች እያሰፋ ባለበት በዚህ ወቅት በአገሪቱ ውስጥ አሉ ከሚባሉት የጸረ አንበጣ መድኃኒት መርጫ አውሮፕላኖች ሁለቱ በአንድ ወር ውስጥ ከአገልግሎት ውጪ ሆነዋል ማለት ነው። ለመሆኑ ኢትዮጵያ ስንት አውሮፕላኖች አሏት? የአፍሪካ ቀንድንና ደቡብ እስያን እያካለለ ያገኘውን ሰብል በማውደም የአካባቢውን ሕዝብ የምግብ አቅርቦትና ህይወት አደጋ ላይ ጥሎ የሚኘውን በ25 ዓመት ውስጥ ካጋጠሙት ሁሉ የከፋው ነው የተባለለትን የአንበጣ መንጋ ወረርሽን ለመከላከል ኢትዮጵያ ከምድር እና ከአየር ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል። የአንበጣ መንጋው ጥቃት ሰፊ ቦታን በሚሸፍን ቦታ ላይ እንደተከሰተ የግብርና ሚኒስቴር ግብርና ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት ማንደፍሮ ንጉሤ (ዶ/ር) የገለጹ ሲሆን፤ በአፋር፣ ሶማሊ፣ አማራ፣ ኦሮሚያና ትግራይ ክልሎችና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ ተከስቷል። ባለፉት ወራት በኢትዮጵያ ውስጥ የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል ስድስት አውሮፕላን እና ሁለት ሄሊኮፕተሮች ተሠማርተው የነበሩ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት በገጠማቸው አደጋና ለጥገና ወደ ውጭ የሄዱ በመኖራቸው በሥራ ላይ የሚገኘው አንድ አውሮፕላን ብቻ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ለቢቢሲ ገልጸዋል። የአንበጣ መንጋው በተከሰተባቸው አካባቢዎች ከዚህ ቀደም አውሮፕላኖቹ ተሰማርተው ባከናወኑት አንበጣውን የመከላከል ሥራ "በጣም ውጤታማ ነበሩ" የሚሉት ማንደፍሮ (ዶ/ር)፤ "በሰባት ክልሎች እና በአንድ ከተማ መስተዳድር የበረሃ አንበጣው ሲከሰት በተቀናጀ መልክ ተሠማርተው በመከላከል በሁለት ክልሎች ብቻ ሲቀር የሌሎቹን መቆጣጠር ችለው ነበር" ይላሉ። ነገር ግን ከወራት በፊት የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ በመቆጣጠር "የቀረውንም ተረባርበው ለማጥፋት ሲቃረቡ አዲስ የበረሃ አንበጣ መንጋ ከውጭ ገባ" የሚሉት ሚኒስትር ዲኤታው ሌላ ጫና መፈጠሩን አመልክተዋል። ስለዚህም አሁን የተከሰተውን የበረሃ አንበጣ መንጋ ለመቆጣጠር በተደረገው ጥረት ውስጥ ሁለቱ እክል ገጥሟቸው የወደቁ ሲሆን ሌሎች ደግሞ በጥገና ላይ በመሆናቸው የቀረው አንድ አውሮፕላን ብቻ ነው። ይህ ደግሞ በተለያዩ ክልሎች ውስጥ ካጋጠመው የአንበጣ መንጋ ወረራ አንጻር ከአቅም በላይ መሆኑን ጠቁመው፤ ለዚሁ ተግባር የሚውሉ አዳዲስ አውሮፕላኖች ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ ተብሎ እየተጠበቀ መሆኑን ተናግረዋል። አዲሶቹ የጸረ አንበጣ መድኃኒት መርጫ አውሮፕላኖች ስምንት ሲሆኑ የሚመጡትም በኪራይ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ማንደፍሮ (ዶ/ር) አመልክተው፤ ተባዩን ለመቆጣጠር በግብርና ሚኒስትሩ የሚመራ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ከአውሮፕላን በተጨማሪ በሰው ኃይልና በተሸከርካሪ በመታገዝ የጸረ ተባይ ርጭት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። አውሮፕላኖቹ ምን አጋጠማቸው? የአንበጣ መንጋው ወረራ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰበት ባለፈው የመስከረም ወር ላይ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ ጸረ አንበጣ መድኃኒት ለመርጨት ተሰማርተው የነበሩት አውሮፕኖች ላይ በተከታታይ የደረሰው አደጋ በአገሪቱ ውስጥ ያሉትን የጸረ ተባይ መርጫ አውሮፕላኖች ቁጥር አንድ ብቻ አድርጎታል። ለአደጋው መከሰት ምክንያቱ ምን እንደሆነ የተገለጸ ነገር ባይኖርም ሚኒስትር ዲኤታው ማንደፍሮ (ዶ/ር) ግን "ከፍ ብሎ ለመብረር መቸገራቸው ምክንያት ሳይሆን አይቀርም" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አደጋው የደረሰባቸው ሁለቱም አውሮፕላኖች በኪራይ የመጡና ንብረትነታቸውም የደቡብ አፍሪካ ሲሆኑ፤ አብራሪዎቹም ኢትዮጵያዊያን አለመሆናቸው ተገልጿል። አውሮፕላኖቹ የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዙ የመጡ ሲሆን የአደጋና የኢንሹራንስ ጉዳይ የግብርና ሚኒስቴርን የሚመለከት እንዳልሆነ ተጠቅሷል። አደጋው መድረሱ እንዳሳዘናቸው ነገር ግን "እኛ በውላችን መሠረት ኪራይ መከፈል እንጂ አደጋ ሲደርስ እንከፍላለን የሚል ውል የለም" ሲሉ ማንደፍሮ (ዶ/ር) ተናግረዋል። የግብርና ሚንስቴር የራሱ እንዲህ አይነቱ የተፈጥሮ ችግር በሚያጋጥምበት ጊዜ ፈጥነው በመሰማራት አገልግሎት ላይ የሚውሉ ሄሊኮፕተርም ሆነ አውሮፕላን እንደሌለው የጠቆሙት ሚንስትር ዲኤታው "አውሮፕላኖች ቢኖሩን ኖሮ አንበጣውን በፍጥነት ለመከላከል ይቻል ነበር" ብለዋል። ከዚህ አንጻርም የጎረቤት አገር ሱዳን የግብርና ሚንስቴር የአንበጣ እና የወፍ መከላከያ እንዲሁም ለሌሎች ሥራዎች የሚያገለግሉ ዘጠኝ አውሮፕላኖች እንዳሉት ጠቅሰው በኢትዮጵያም "ተመሳሳይ አቅም መገንባት" አስፈላጊነትን ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ ምን ያህል አውሮፕላኖች ያስፈልጓታል? በተለይ በኢትዮጵያ ምሥራቃዊ ክፍል በሚገኙ ክልሎች ላይ ተከስቶ ከባድ ውድመት እያስከተለ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር ያመለከተውን የአንበጣ መንጋ ወራረ ለመከላከል ከአየር ላይ የሚደረገው የጸረ ተባይ ርጭት ወሳኝ መሆኑን ከዓለም የምግብ ፕሮግራም መረጃ ያመለክታል። በተለይ ኢትዮጵያን በመሳሰሉ ተራራማ አገራት ውስጥ ከአየር ላይ የሚደረገው የጸረ አንበጣ መድኃኒት ርጭት አንበጣው የሚያደርሰውን ጉዳት በቶሎ ለመቆጣጠር ያስችላል። ነገር ግን አውሮፕላን ወይም ሄሊኮፕተር ለመግዛትም ሆነ ለመከራየት የሚያስፈልገው ገንዘብ ቀላል የሚባል አይደለም። ሚኒስትር ዲኤታው እንደሚሉት አንድ ሄሊኮፕተር ለመግዛት የሚያስፈልገው ገንዘብ ሁለት ሚሊዮን ዶላር እንደሚገመት ጠቁመው፤ ኢትዮጵያ አስር ብትገዛ ወደ 20 ሚሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚያስፈልጋት ተናግረዋል። አንበጣው በአገሪቱ ግብርና ላይ ከሚያደርሰው ጉዳትና ለተለያዩ ችግሮች ከሚያጋልጣቸው የአገሪቱ ዜጎች አንጻር የአውሮፕላኖቹ አስፈላጊነት አጠያያቂ አይደለም ብለዋል ሚኒስትር ዲኤታው። "በአገሪቱ ከዚህ በሚበልጥ ወጪ የሚሠሩ ፕሮጀክቶች መኖራቸውን እና በተመሳሳይ ለዚህም ግዢ ትኩረት ያስፈልጋል" ብለዋል። አንድ አውሮፕላን የአንበጣ መንጋ በተከሰተባቸው አካባቢዎች በአንድ ጉዞ አንድ ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ኬሚካል የመርጨት አቅም ሲኖረው፤ አንድ አውሮፕላን በቀን እስከ አምስት ምልልስ በማከለናወን የጸረ አንበጣ መድኃኒት መርጨት ከቻለ አምስት ሺህ ሄክታር መሬትን መሸፈን ይችላል። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በአንበጣ መንጋው የወረራ ስጋት ውስጥ ይሆናል ተብሎ እንደሚገመት ሚኒስትር ዲኤታው አመልከተው፤ ይህንንም ስፋት የጸረ ተባይ መድኃኒት ለመርጨት በትንሹ 10 አውሮፕላኖች ያስፈልጋሉ። የበረሃ አንበጣ መንጋው እስካሁን ስላደረሰው ጉዳት ጥናት ባለመደረጉ የተረጋገጠ መረጃ አለመኖሩን የተናገሩት ማንደፍሮ (ዶ/ር) አሁን ዋነኛ ትኩረት የተደረገው በመከላከል ሥራው ላይ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል። ሚኒስትር ዲኤታው ጨምረውም የበረሃ አንበጣውን ወረራ ለመከላከል ከአውሮፕላኖች በተጨማሪ በመቶዎች የሚቆጠሩ መኪኖች ጉዳቱ በከፋባቸው አካባቢዎች ተሰማርተዋል። ከ25 ዓመታት ወዲህ የከፋ ነው የተባለለት የበረሃ አንበጣ ለወራት ኢትዮጵያን ጨምሮ በምሥራቅ አፍሪካ ያሉ አገራት ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው። ከባለፈው ዓመት ጀምሮ አስካሁን በተከታታይ ለተከሰተው የአንበጣ መንጋ ምክንያቱ እንደ አውሮፓዊያኑ በ2018 እና 2019 ያጋጠመው ከባድ ነፋስና ዝናብ እንደሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ እንዳመለከተው ከሁለት ዓመት በፊት በደቡባዊ የአረብ ልሳነ ምድር ላይ የነበረው እርጥብና አመቺ የአየር ሁኔታ የአንበጣው ሦስት ትውልድ ሳይታወቅ እንዲራባ እድል ፈጥሮ በአካባቢው አገራት ላይ የሚታየውን የአንበጣ መንጋ ወረራ አስከትሏል። | አንበጣ ፡ ኢትዮጵያ የአንበጣ መንጋን ለመቆጣጠር ምን ያህል አውሮፕላኖች አሏት? የምሥራቅ አፍሪካ አገራትን በማዳረስ በተለይ የኢትዮጵያን ሰሜናዊና ሰሜን ምሥራቅ አካባቢዎችን ክፉኛ እያጠቃ የሚገኘውን ግዙፍ የበረሃ አንበጣ መንጋ ለመከላከል ከአየር ላይ ጸረ ተባይ መድኃኒት የሚረጩ ጥቂት አውሮፕላኖች ተሰማርተው ጥረት እየተደረገ ነው። የአንበጣ መንጋው ክፉኛ ባጠቃቸው አካባቢዎች የሚገኙ አርሶ አደሮች ብዙም ውጤታ ያልሆነውን ባህላዊ አንበጣን የመከላከያ መንገድ ጥረት እያደረጉ ሲሆን፤ ከዚሁ ጎን ለጎን አውሮፕላኖችም ተሰማርተው ጸረ ተባይ መድኃኒቶችን እየረጩ ቢሆንም እክል እየገጠማቸው የመከላከሉ ሥራ ላይ እክል እያጋጠመ ነው። ባለፈው የመስከረም ወር ሁለት የጸረ ተባይ መርቻ አውሮፕላኖች በሰሜንና በምሥራቅ ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ አካበቢዎች ተሰማርተው በነበረበት ጊዜ ወድቀው ከአገልግሎት ውጪ ሆነዋል። የመጀመሪያው አውሮፕላን በአማራ ክልል ወረባቦ ወረዳ ፍራንጉል በሚባል ቦታ ወድቆ የተከሰከሰ ሲሆን የወረዳው የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ሳዳም ሽመልስ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በአብራሪው ላይ ከደረሰው መጠነኛ ጉዳት ውጪ በሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም። ነገር ግን በአደጋው በአውሮፕላኑ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት የተነገረ ሲሆን በዚህም ሳቢያ አውሮፕላኑ ከአገልግሎት ውጪ ሊሆን ይችላል ተብሏል። ሁለተኛው አውሮፕላን ደግሞ በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ጃርሶ ወረዳ የአንበጣ መንጋ ለመከላከል ኬሚካል በመርጨት ላይ በነበረበት ጊዜ ጊደያ በሃ በምትበል ቀበሌ ውስጥ ነው የመውደቅ አደጋ የገጠመው። የወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አብዱል ቃድር ደዚ ለቢቢሲ በአደጋው ወቅት በአውሮፕላኑ ውስጥ አብራሪው ብቻ የነበረ ሲሆን እሱም ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰበትና በአውሮፕላኑ ላይም ቀላል ጉዳት እንዳጋጠመ ተናግረዋል። ስለዚህም የአንበጣው መንጋ ጥፋት የሚያደርስባቸውን አካባቢዎች እያሰፋ ባለበት በዚህ ወቅት በአገሪቱ ውስጥ አሉ ከሚባሉት የጸረ አንበጣ መድኃኒት መርጫ አውሮፕላኖች ሁለቱ በአንድ ወር ውስጥ ከአገልግሎት ውጪ ሆነዋል ማለት ነው። ለመሆኑ ኢትዮጵያ ስንት አውሮፕላኖች አሏት? የአፍሪካ ቀንድንና ደቡብ እስያን እያካለለ ያገኘውን ሰብል በማውደም የአካባቢውን ሕዝብ የምግብ አቅርቦትና ህይወት አደጋ ላይ ጥሎ የሚኘውን በ25 ዓመት ውስጥ ካጋጠሙት ሁሉ የከፋው ነው የተባለለትን የአንበጣ መንጋ ወረርሽን ለመከላከል ኢትዮጵያ ከምድር እና ከአየር ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል። የአንበጣ መንጋው ጥቃት ሰፊ ቦታን በሚሸፍን ቦታ ላይ እንደተከሰተ የግብርና ሚኒስቴር ግብርና ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት ማንደፍሮ ንጉሤ (ዶ/ር) የገለጹ ሲሆን፤ በአፋር፣ ሶማሊ፣ አማራ፣ ኦሮሚያና ትግራይ ክልሎችና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ ተከስቷል። ባለፉት ወራት በኢትዮጵያ ውስጥ የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል ስድስት አውሮፕላን እና ሁለት ሄሊኮፕተሮች ተሠማርተው የነበሩ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት በገጠማቸው አደጋና ለጥገና ወደ ውጭ የሄዱ በመኖራቸው በሥራ ላይ የሚገኘው አንድ አውሮፕላን ብቻ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ለቢቢሲ ገልጸዋል። የአንበጣ መንጋው በተከሰተባቸው አካባቢዎች ከዚህ ቀደም አውሮፕላኖቹ ተሰማርተው ባከናወኑት አንበጣውን የመከላከል ሥራ "በጣም ውጤታማ ነበሩ" የሚሉት ማንደፍሮ (ዶ/ር)፤ "በሰባት ክልሎች እና በአንድ ከተማ መስተዳድር የበረሃ አንበጣው ሲከሰት በተቀናጀ መልክ ተሠማርተው በመከላከል በሁለት ክልሎች ብቻ ሲቀር የሌሎቹን መቆጣጠር ችለው ነበር" ይላሉ። ነገር ግን ከወራት በፊት የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ በመቆጣጠር "የቀረውንም ተረባርበው ለማጥፋት ሲቃረቡ አዲስ የበረሃ አንበጣ መንጋ ከውጭ ገባ" የሚሉት ሚኒስትር ዲኤታው ሌላ ጫና መፈጠሩን አመልክተዋል። ስለዚህም አሁን የተከሰተውን የበረሃ አንበጣ መንጋ ለመቆጣጠር በተደረገው ጥረት ውስጥ ሁለቱ እክል ገጥሟቸው የወደቁ ሲሆን ሌሎች ደግሞ በጥገና ላይ በመሆናቸው የቀረው አንድ አውሮፕላን ብቻ ነው። ይህ ደግሞ በተለያዩ ክልሎች ውስጥ ካጋጠመው የአንበጣ መንጋ ወረራ አንጻር ከአቅም በላይ መሆኑን ጠቁመው፤ ለዚሁ ተግባር የሚውሉ አዳዲስ አውሮፕላኖች ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ ተብሎ እየተጠበቀ መሆኑን ተናግረዋል። አዲሶቹ የጸረ አንበጣ መድኃኒት መርጫ አውሮፕላኖች ስምንት ሲሆኑ የሚመጡትም በኪራይ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ማንደፍሮ (ዶ/ር) አመልክተው፤ ተባዩን ለመቆጣጠር በግብርና ሚኒስትሩ የሚመራ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ከአውሮፕላን በተጨማሪ በሰው ኃይልና በተሸከርካሪ በመታገዝ የጸረ ተባይ ርጭት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። አውሮፕላኖቹ ምን አጋጠማቸው? የአንበጣ መንጋው ወረራ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰበት ባለፈው የመስከረም ወር ላይ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ ጸረ አንበጣ መድኃኒት ለመርጨት ተሰማርተው የነበሩት አውሮፕኖች ላይ በተከታታይ የደረሰው አደጋ በአገሪቱ ውስጥ ያሉትን የጸረ ተባይ መርጫ አውሮፕላኖች ቁጥር አንድ ብቻ አድርጎታል። ለአደጋው መከሰት ምክንያቱ ምን እንደሆነ የተገለጸ ነገር ባይኖርም ሚኒስትር ዲኤታው ማንደፍሮ (ዶ/ር) ግን "ከፍ ብሎ ለመብረር መቸገራቸው ምክንያት ሳይሆን አይቀርም" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አደጋው የደረሰባቸው ሁለቱም አውሮፕላኖች በኪራይ የመጡና ንብረትነታቸውም የደቡብ አፍሪካ ሲሆኑ፤ አብራሪዎቹም ኢትዮጵያዊያን አለመሆናቸው ተገልጿል። አውሮፕላኖቹ የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዙ የመጡ ሲሆን የአደጋና የኢንሹራንስ ጉዳይ የግብርና ሚኒስቴርን የሚመለከት እንዳልሆነ ተጠቅሷል። አደጋው መድረሱ እንዳሳዘናቸው ነገር ግን "እኛ በውላችን መሠረት ኪራይ መከፈል እንጂ አደጋ ሲደርስ እንከፍላለን የሚል ውል የለም" ሲሉ ማንደፍሮ (ዶ/ር) ተናግረዋል። የግብርና ሚንስቴር የራሱ እንዲህ አይነቱ የተፈጥሮ ችግር በሚያጋጥምበት ጊዜ ፈጥነው በመሰማራት አገልግሎት ላይ የሚውሉ ሄሊኮፕተርም ሆነ አውሮፕላን እንደሌለው የጠቆሙት ሚንስትር ዲኤታው "አውሮፕላኖች ቢኖሩን ኖሮ አንበጣውን በፍጥነት ለመከላከል ይቻል ነበር" ብለዋል። ከዚህ አንጻርም የጎረቤት አገር ሱዳን የግብርና ሚንስቴር የአንበጣ እና የወፍ መከላከያ እንዲሁም ለሌሎች ሥራዎች የሚያገለግሉ ዘጠኝ አውሮፕላኖች እንዳሉት ጠቅሰው በኢትዮጵያም "ተመሳሳይ አቅም መገንባት" አስፈላጊነትን ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ ምን ያህል አውሮፕላኖች ያስፈልጓታል? በተለይ በኢትዮጵያ ምሥራቃዊ ክፍል በሚገኙ ክልሎች ላይ ተከስቶ ከባድ ውድመት እያስከተለ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር ያመለከተውን የአንበጣ መንጋ ወራረ ለመከላከል ከአየር ላይ የሚደረገው የጸረ ተባይ ርጭት ወሳኝ መሆኑን ከዓለም የምግብ ፕሮግራም መረጃ ያመለክታል። በተለይ ኢትዮጵያን በመሳሰሉ ተራራማ አገራት ውስጥ ከአየር ላይ የሚደረገው የጸረ አንበጣ መድኃኒት ርጭት አንበጣው የሚያደርሰውን ጉዳት በቶሎ ለመቆጣጠር ያስችላል። ነገር ግን አውሮፕላን ወይም ሄሊኮፕተር ለመግዛትም ሆነ ለመከራየት የሚያስፈልገው ገንዘብ ቀላል የሚባል አይደለም። ሚኒስትር ዲኤታው እንደሚሉት አንድ ሄሊኮፕተር ለመግዛት የሚያስፈልገው ገንዘብ ሁለት ሚሊዮን ዶላር እንደሚገመት ጠቁመው፤ ኢትዮጵያ አስር ብትገዛ ወደ 20 ሚሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚያስፈልጋት ተናግረዋል። አንበጣው በአገሪቱ ግብርና ላይ ከሚያደርሰው ጉዳትና ለተለያዩ ችግሮች ከሚያጋልጣቸው የአገሪቱ ዜጎች አንጻር የአውሮፕላኖቹ አስፈላጊነት አጠያያቂ አይደለም ብለዋል ሚኒስትር ዲኤታው። "በአገሪቱ ከዚህ በሚበልጥ ወጪ የሚሠሩ ፕሮጀክቶች መኖራቸውን እና በተመሳሳይ ለዚህም ግዢ ትኩረት ያስፈልጋል" ብለዋል። አንድ አውሮፕላን የአንበጣ መንጋ በተከሰተባቸው አካባቢዎች በአንድ ጉዞ አንድ ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ኬሚካል የመርጨት አቅም ሲኖረው፤ አንድ አውሮፕላን በቀን እስከ አምስት ምልልስ በማከለናወን የጸረ አንበጣ መድኃኒት መርጨት ከቻለ አምስት ሺህ ሄክታር መሬትን መሸፈን ይችላል። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በአንበጣ መንጋው የወረራ ስጋት ውስጥ ይሆናል ተብሎ እንደሚገመት ሚኒስትር ዲኤታው አመልከተው፤ ይህንንም ስፋት የጸረ ተባይ መድኃኒት ለመርጨት በትንሹ 10 አውሮፕላኖች ያስፈልጋሉ። የበረሃ አንበጣ መንጋው እስካሁን ስላደረሰው ጉዳት ጥናት ባለመደረጉ የተረጋገጠ መረጃ አለመኖሩን የተናገሩት ማንደፍሮ (ዶ/ር) አሁን ዋነኛ ትኩረት የተደረገው በመከላከል ሥራው ላይ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል። ሚኒስትር ዲኤታው ጨምረውም የበረሃ አንበጣውን ወረራ ለመከላከል ከአውሮፕላኖች በተጨማሪ በመቶዎች የሚቆጠሩ መኪኖች ጉዳቱ በከፋባቸው አካባቢዎች ተሰማርተዋል። ከ25 ዓመታት ወዲህ የከፋ ነው የተባለለት የበረሃ አንበጣ ለወራት ኢትዮጵያን ጨምሮ በምሥራቅ አፍሪካ ያሉ አገራት ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው። ከባለፈው ዓመት ጀምሮ አስካሁን በተከታታይ ለተከሰተው የአንበጣ መንጋ ምክንያቱ እንደ አውሮፓዊያኑ በ2018 እና 2019 ያጋጠመው ከባድ ነፋስና ዝናብ እንደሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ እንዳመለከተው ከሁለት ዓመት በፊት በደቡባዊ የአረብ ልሳነ ምድር ላይ የነበረው እርጥብና አመቺ የአየር ሁኔታ የአንበጣው ሦስት ትውልድ ሳይታወቅ እንዲራባ እድል ፈጥሮ በአካባቢው አገራት ላይ የሚታየውን የአንበጣ መንጋ ወረራ አስከትሏል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54495523 |
3politics
| የፊንላንዷ ጠቅላይ ሚኒስትር ‘ፓርቲ’ ላይ ሲጨፍሩ መታየታቸው ትችት አስከተለባቸው | የፊንላንዷ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳና ማሪን ሾልኮ በወጣ ቪዲዮ ‘ፓርቲ’ ላይ ሲጨፍሩ መታየታቸው ትችት አስከትሎባቸዋል። በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት እየተጋራ ባለው ተንቀሳቃሽ ምስል ጠቅላይ ሚኒስትሯ እና ዝነኛ ፊላንዳውያን ጓደኞቻቸው ሲጨፍሩ እና ሲዘፍኑ ታይተዋል። ይህ ተንቀሳቃሽ ምስል ከወጣ በኋላ የአገሬው መገናኛ ብዙኃን መነጋገሪያ የሆነ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ከተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ከፍተኛ ትችት ተሰንዝሮባቸዋል። ይባስ ብሎም አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ጠቅላይ ሚኒስትሯ "የአደንዛዥ እጽ ምረመራ ይደረግላቸው" ሲሉ ጠይቀዋል። የ36 ዓመቷ ጠቅላይ ሚኒስትር ግን አደንዛዥ እጽ አልወሰድኩም ካሉ በኋላ፣ አልኮል መጠጣታቸውን እና በሙሉ ኃይላቸው በፓርቲው ላይ መጨፈራቸውን ግን ተናግረዋል። የዓለማችን ወጣቷ ጠቅላይ ሚኒስትር ለጭፈራ ወደ ፓርቲ ቦታ ማቅናትን በምስጢር የሚይዙት ጉዳይ አይደለም። ከዚህ ቀደም በተለያዩ የሙዚቃ ፌስቲቫሎች ላይ በይፋ ታይተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሯ ባለፈው ዓመት እራሳቸውን ለኮቪድ-19 አጋልጠው ወደ ጭፈራ ቤት በመሄዳቸው ይቅርታ ጠይቀው ነበር። ባለፈው ሳምንት ተዋቂው የጀርመን መጽሔት ቢልድ ሳና ማሪን "የዓለማችን ምርጧ ጠቅላይ ሚኒስትር" ብሏቸው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቪዲዮ እየተቀረጹ መሆኑን እንደሚያውቁ ገልጸው ለሕዝብ ዕይታ መቅረቡ ግን ያበሳጫል ሲሉ ሾልኮ ስለወጣው ተንቀሳቃሽ ምስል አስተያየታቸውን ሲጥተዋል። "ደንሻለሁ፣ ዘፍኛለሁ እንዲሁም ፓርቲ አድርጊያለሁ ሁሉም ሕጋዊ ናቸው። እኔ ወይም በአካባቢዬ አደንዛዥ እጽ በሚወሰድበት ቦታ ሆኜ አላውቅም" ብለዋል የፊንላንዷ ጠቅላይ ሚኒስትር። ጠቅላይ ሚኒስትሯ እራሳቸውን ሲከላከሉ፤ "የቤተሰብ ሕይወት አለኝ፣ የሥራ ሕይወት አለኝ፣ እንዲሁም ከጓደኞቼ ጋር የማሳለፈው ነጻ የምሆንበት ጊዜ አለኝ። በእኔ የዕድሜ ክልል ውስጥ እንደሚገኙ ከሌሎች ሰዎች ጋር ተመሳሳይ ነው" ብለዋል። የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ሪካ ፑራ ጠቅላይ ሚኒስትሯ በገዛ ፍቃዳቸው የአደንዛዥ እጽ ምርመራ ያደርጉ ሲሉ ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን፤ ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ደግሞ ሌሎች አንገብጋቢ አገራዊ ጉዳዮች እያሉ ስለ ጭፈራ ማውራቱ ጊዜው አይደለም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሯን እና የአገሪቱን መገናኛ ብዙኃን ተችተዋል። መሪን ከእአአ 2019 መጨረሻ ጀምሮ ፊንላንድን ሲመሩ የቆዩ ሲሆን አሁንም ድረስ ከፓርቲያቸው ጠንካራ ድጋፍ አላቸው። | የፊንላንዷ ጠቅላይ ሚኒስትር ‘ፓርቲ’ ላይ ሲጨፍሩ መታየታቸው ትችት አስከተለባቸው የፊንላንዷ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳና ማሪን ሾልኮ በወጣ ቪዲዮ ‘ፓርቲ’ ላይ ሲጨፍሩ መታየታቸው ትችት አስከትሎባቸዋል። በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት እየተጋራ ባለው ተንቀሳቃሽ ምስል ጠቅላይ ሚኒስትሯ እና ዝነኛ ፊላንዳውያን ጓደኞቻቸው ሲጨፍሩ እና ሲዘፍኑ ታይተዋል። ይህ ተንቀሳቃሽ ምስል ከወጣ በኋላ የአገሬው መገናኛ ብዙኃን መነጋገሪያ የሆነ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ከተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ከፍተኛ ትችት ተሰንዝሮባቸዋል። ይባስ ብሎም አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ጠቅላይ ሚኒስትሯ "የአደንዛዥ እጽ ምረመራ ይደረግላቸው" ሲሉ ጠይቀዋል። የ36 ዓመቷ ጠቅላይ ሚኒስትር ግን አደንዛዥ እጽ አልወሰድኩም ካሉ በኋላ፣ አልኮል መጠጣታቸውን እና በሙሉ ኃይላቸው በፓርቲው ላይ መጨፈራቸውን ግን ተናግረዋል። የዓለማችን ወጣቷ ጠቅላይ ሚኒስትር ለጭፈራ ወደ ፓርቲ ቦታ ማቅናትን በምስጢር የሚይዙት ጉዳይ አይደለም። ከዚህ ቀደም በተለያዩ የሙዚቃ ፌስቲቫሎች ላይ በይፋ ታይተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሯ ባለፈው ዓመት እራሳቸውን ለኮቪድ-19 አጋልጠው ወደ ጭፈራ ቤት በመሄዳቸው ይቅርታ ጠይቀው ነበር። ባለፈው ሳምንት ተዋቂው የጀርመን መጽሔት ቢልድ ሳና ማሪን "የዓለማችን ምርጧ ጠቅላይ ሚኒስትር" ብሏቸው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቪዲዮ እየተቀረጹ መሆኑን እንደሚያውቁ ገልጸው ለሕዝብ ዕይታ መቅረቡ ግን ያበሳጫል ሲሉ ሾልኮ ስለወጣው ተንቀሳቃሽ ምስል አስተያየታቸውን ሲጥተዋል። "ደንሻለሁ፣ ዘፍኛለሁ እንዲሁም ፓርቲ አድርጊያለሁ ሁሉም ሕጋዊ ናቸው። እኔ ወይም በአካባቢዬ አደንዛዥ እጽ በሚወሰድበት ቦታ ሆኜ አላውቅም" ብለዋል የፊንላንዷ ጠቅላይ ሚኒስትር። ጠቅላይ ሚኒስትሯ እራሳቸውን ሲከላከሉ፤ "የቤተሰብ ሕይወት አለኝ፣ የሥራ ሕይወት አለኝ፣ እንዲሁም ከጓደኞቼ ጋር የማሳለፈው ነጻ የምሆንበት ጊዜ አለኝ። በእኔ የዕድሜ ክልል ውስጥ እንደሚገኙ ከሌሎች ሰዎች ጋር ተመሳሳይ ነው" ብለዋል። የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ሪካ ፑራ ጠቅላይ ሚኒስትሯ በገዛ ፍቃዳቸው የአደንዛዥ እጽ ምርመራ ያደርጉ ሲሉ ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን፤ ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ደግሞ ሌሎች አንገብጋቢ አገራዊ ጉዳዮች እያሉ ስለ ጭፈራ ማውራቱ ጊዜው አይደለም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሯን እና የአገሪቱን መገናኛ ብዙኃን ተችተዋል። መሪን ከእአአ 2019 መጨረሻ ጀምሮ ፊንላንድን ሲመሩ የቆዩ ሲሆን አሁንም ድረስ ከፓርቲያቸው ጠንካራ ድጋፍ አላቸው። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cmj3g8pezj1o |
0business
| መካከለኛ አፍሪካ ሪፓብሊክ ቢትኮይንን ይፋዊ መገበያያ አደረገች | መካከለኛ አፍሪካ ሪፓብሊክ ቢትኮይንን ይፋዊ መገበያያ በማድረግ ሁለተኛዋ አገር ሆነች። ቢትኮይንን አገር አቀፍ መገበያያ በማድረግ ኤል ሳልቫዶር የመጀመሪያዋ ናት። የሴንትራል አፍሪካን ሪፐብሊክ ሕግ አውጭዎች በሙሉ ድምጽ ቢትኮይን መገበያያ እንዲሆን ውሳኔ አሳልፈዋል። "ውሳኔው አገሪቷን ከዓለም ባለ ራዕይ አገሮች አንዷ ያደርጋታል" ብለዋል። ከአለማችን ድሃ አገራት አንዷ ብትሆንም በአልማዝ፣ ወርቅና ዩራንየም የበለጸገች ናት። የሩሲያ የቅርብ ወዳጅ የሆነችው መካከለኛ አፍሪካ ሪፐብሊክ (ካር) ለዓመታት በግጭት ስትናጥ ቆይታለች። የሩሲያ ቅጥረኛ ወታደሮች በአገሪቱ አማጽያንን እየተዋጉ ነው የሚለው ዜና ከወራት በፊት መውጣቱ አይዘነጋም። ኤል ሳልቫዶር እአአ መስከረም 2021 ላይ ቢትኮይንን መገበያያ ስታደርግ አይኤምኤፍን ጨምሮ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ውሳኔውን ተችተዋል። ቢትኮይንን ይፋዊ መገበያያ ማድረግ የፋይናንስ ሥርዓት አለመረጋጋት ይፈጥራል፣ ወንጀለኞች ሕገ ወጥ ገንዘብን ወደ ሕጋዊ መስመር እንዲያስገቡ መንገድ ይከፍታል፣ ሂደቱ በርካታ የኤሌክትሪክ ኃይል ስለሚወስድም አካባቢ ይበክላል ብለው ነበር የነቀፉት። የ2019 መረጃ እንደሚያሳየው፣ ሴንትራል አፍሪካን ሪፐብሊክ ውስጥ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ከአጠቃላይ ሕዝቡ 4 በመቶ ናቸው። ይህም ቢትኮይንን ለመጠቀም ፈታኝ ያደርገዋል። በአገሪቱ ጥቅም ላይ የሚውለው በፈረንሳዩ ሲኤፍኤ ባንክ የሚደገፈው ፍራንክ ነው። ባንኩ በማዕድን የበለጸገችው አገር ላይ የበለጠ ጫና እንዳያሳድር በሚል አገሪቱ ወደ ቢትኮይን ፊቷን አዙራለች የሚሉ አሉ። ቴሪ ቪርኮሉን የተባሉ ተንታኝ ለኤኤፍፒ እንደተናገሩት፣ በአገሪቱ ያለው መዋቅራዊ ሙስና እንዲሁም የአገሪቱ ወዳጅ አገር ሩሲያ ከሰሞኑ በምዕራባውን ማዕቀብ ሥር መውደቋ፣ ቢትኮይንን መገበያያ ለማድረግ እንዲወሰን ሳይገፋፉ አልቀሩም። በመዲናዋ ባኑጊ የሰዎች ስሜት የተደበላለቀ ነው። የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ያን ዳውሮ፣ በቢትኮይን መገበያየት ሕይወትን ቀላል ያደርጋል ሲሉ ለቢቢሲ አስተያየት ሰጥተዋል። "ነጋዴዎች ከዚህ በኋላ የሲኤፍኤ ፍራንክ ይዘው መጓጓዝ የለባቸውም። በቢትኮይን በስልክ መገበያየት ይቻላል። ቢትኮይንን ወደ ሌላ መገበያያ ገንዘብ በቀላሉ መቀየርም ይቻላል" ብለዋል። ሲኤፍኤ አፍሪካን የሚጠቅም አሠራር እንዳልዘረጋ ባለሙያው ይናገራሉ። ሌሎች የፈረንሳዩ ባንክ ጥገኛ የሆኑ የአፍሪካ አገራት መገበያያውን እንዲተውት የሚጠይቁም አሉ። መገበያያው ከቅኝ ግዛት የተወረሰና ፈረንሳይ ምጣኔ ሀብታዊ ጫና እንድታደርግ የሚረዳት ነው በሚል ይተቻል። ኮምፒውተር ሳይንቲስቷ ሲድኒ ቲካያ በበኩሉ፣ ቢትኮይንን መገበያያ ማድረግ ኃላፊነት የጎደለው ውሳኔ ነው ሲል ይከራከራል። "የኢንተርኔት ዝርጋታ ውስን ነው። ቢትኮይን ደግሞ ሙሉ በሙሉ ኢንተርኔት ላይ የተመሠረተ ነው። ወደ ቢትኮይን የመሸጋገሪያው ጊዜ አሁን አይደለም" ብሏል። አገሪቱ እንደ ትምህርት እና ንጹህ የመጠጥ ውሃ ያሉ መሠረታዊ አቅርቦቶችን ማሟላት ላይ ብታተኩር እንደሚሻልም ይመክራል። ሴንትራል አፍሪካን ሪፐብሊክ ከቅኝ ግዛት ነጻ ከወጣት በኋላ ከ1960ዎቹ ወዲህ በግጭት ስትናጥ ቆይታለች። በ2013 ሙስሊም አማጽያን በብዛት የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች የሚገኙባትን አገር ተቆጣጠሩ። ይህንን በመቃወም ሚሊሻዎች መደራጀት ጀመሩ። ይህም በሃይማኖት የተከፋፋለ ግጭትን አስከተለ። 2016 ላይ ፕሬዝዳንት ፋውስቲን አርቻንጌ ቶዋድራ ሥልጣን ከያዙ በኋላ አገሪቱ ከፈረንሳይ ወደ ሩሲያ ወዳጅነት ተሻግራለች። | መካከለኛ አፍሪካ ሪፓብሊክ ቢትኮይንን ይፋዊ መገበያያ አደረገች መካከለኛ አፍሪካ ሪፓብሊክ ቢትኮይንን ይፋዊ መገበያያ በማድረግ ሁለተኛዋ አገር ሆነች። ቢትኮይንን አገር አቀፍ መገበያያ በማድረግ ኤል ሳልቫዶር የመጀመሪያዋ ናት። የሴንትራል አፍሪካን ሪፐብሊክ ሕግ አውጭዎች በሙሉ ድምጽ ቢትኮይን መገበያያ እንዲሆን ውሳኔ አሳልፈዋል። "ውሳኔው አገሪቷን ከዓለም ባለ ራዕይ አገሮች አንዷ ያደርጋታል" ብለዋል። ከአለማችን ድሃ አገራት አንዷ ብትሆንም በአልማዝ፣ ወርቅና ዩራንየም የበለጸገች ናት። የሩሲያ የቅርብ ወዳጅ የሆነችው መካከለኛ አፍሪካ ሪፐብሊክ (ካር) ለዓመታት በግጭት ስትናጥ ቆይታለች። የሩሲያ ቅጥረኛ ወታደሮች በአገሪቱ አማጽያንን እየተዋጉ ነው የሚለው ዜና ከወራት በፊት መውጣቱ አይዘነጋም። ኤል ሳልቫዶር እአአ መስከረም 2021 ላይ ቢትኮይንን መገበያያ ስታደርግ አይኤምኤፍን ጨምሮ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ውሳኔውን ተችተዋል። ቢትኮይንን ይፋዊ መገበያያ ማድረግ የፋይናንስ ሥርዓት አለመረጋጋት ይፈጥራል፣ ወንጀለኞች ሕገ ወጥ ገንዘብን ወደ ሕጋዊ መስመር እንዲያስገቡ መንገድ ይከፍታል፣ ሂደቱ በርካታ የኤሌክትሪክ ኃይል ስለሚወስድም አካባቢ ይበክላል ብለው ነበር የነቀፉት። የ2019 መረጃ እንደሚያሳየው፣ ሴንትራል አፍሪካን ሪፐብሊክ ውስጥ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ከአጠቃላይ ሕዝቡ 4 በመቶ ናቸው። ይህም ቢትኮይንን ለመጠቀም ፈታኝ ያደርገዋል። በአገሪቱ ጥቅም ላይ የሚውለው በፈረንሳዩ ሲኤፍኤ ባንክ የሚደገፈው ፍራንክ ነው። ባንኩ በማዕድን የበለጸገችው አገር ላይ የበለጠ ጫና እንዳያሳድር በሚል አገሪቱ ወደ ቢትኮይን ፊቷን አዙራለች የሚሉ አሉ። ቴሪ ቪርኮሉን የተባሉ ተንታኝ ለኤኤፍፒ እንደተናገሩት፣ በአገሪቱ ያለው መዋቅራዊ ሙስና እንዲሁም የአገሪቱ ወዳጅ አገር ሩሲያ ከሰሞኑ በምዕራባውን ማዕቀብ ሥር መውደቋ፣ ቢትኮይንን መገበያያ ለማድረግ እንዲወሰን ሳይገፋፉ አልቀሩም። በመዲናዋ ባኑጊ የሰዎች ስሜት የተደበላለቀ ነው። የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ያን ዳውሮ፣ በቢትኮይን መገበያየት ሕይወትን ቀላል ያደርጋል ሲሉ ለቢቢሲ አስተያየት ሰጥተዋል። "ነጋዴዎች ከዚህ በኋላ የሲኤፍኤ ፍራንክ ይዘው መጓጓዝ የለባቸውም። በቢትኮይን በስልክ መገበያየት ይቻላል። ቢትኮይንን ወደ ሌላ መገበያያ ገንዘብ በቀላሉ መቀየርም ይቻላል" ብለዋል። ሲኤፍኤ አፍሪካን የሚጠቅም አሠራር እንዳልዘረጋ ባለሙያው ይናገራሉ። ሌሎች የፈረንሳዩ ባንክ ጥገኛ የሆኑ የአፍሪካ አገራት መገበያያውን እንዲተውት የሚጠይቁም አሉ። መገበያያው ከቅኝ ግዛት የተወረሰና ፈረንሳይ ምጣኔ ሀብታዊ ጫና እንድታደርግ የሚረዳት ነው በሚል ይተቻል። ኮምፒውተር ሳይንቲስቷ ሲድኒ ቲካያ በበኩሉ፣ ቢትኮይንን መገበያያ ማድረግ ኃላፊነት የጎደለው ውሳኔ ነው ሲል ይከራከራል። "የኢንተርኔት ዝርጋታ ውስን ነው። ቢትኮይን ደግሞ ሙሉ በሙሉ ኢንተርኔት ላይ የተመሠረተ ነው። ወደ ቢትኮይን የመሸጋገሪያው ጊዜ አሁን አይደለም" ብሏል። አገሪቱ እንደ ትምህርት እና ንጹህ የመጠጥ ውሃ ያሉ መሠረታዊ አቅርቦቶችን ማሟላት ላይ ብታተኩር እንደሚሻልም ይመክራል። ሴንትራል አፍሪካን ሪፐብሊክ ከቅኝ ግዛት ነጻ ከወጣት በኋላ ከ1960ዎቹ ወዲህ በግጭት ስትናጥ ቆይታለች። በ2013 ሙስሊም አማጽያን በብዛት የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች የሚገኙባትን አገር ተቆጣጠሩ። ይህንን በመቃወም ሚሊሻዎች መደራጀት ጀመሩ። ይህም በሃይማኖት የተከፋፋለ ግጭትን አስከተለ። 2016 ላይ ፕሬዝዳንት ፋውስቲን አርቻንጌ ቶዋድራ ሥልጣን ከያዙ በኋላ አገሪቱ ከፈረንሳይ ወደ ሩሲያ ወዳጅነት ተሻግራለች። | https://www.bbc.com/amharic/61253742 |
3politics
| አዲሷ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዝ ትረስ ማን ናቸው? | የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን የወግ አጥባቂው ፓርቲ መሪ ሆነው የተመረጡት ሊዝ ትረስ ከንግሥት ኤልዛቤጥ ጋር ከተገናኙ በኋላ በይፋ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዋል። ሊዝ ከየት ተነስተው አሁን ካሉበት ደረሱ? * * ሊዝ ትረስ ገና በ7 ዓመታቸው የቀድሞዋን ዝነኛ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርጋሬት ታቸርን በመወከል ተማሪ ሳሉ ተውነው ነበር። ሊዝ ትረስ ከ39 ዓመታት በኋላ በእውኑ ዓለም የወግ አጥባቂው ፓርቲ መሪ መሆን ችለዋል። እስካሁን ድረስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን እያገለገሉ ያሉት ሊዝ ትረስ፣ በተቀናቃኛቸው ሪሲ ሱናክ ለአምስት ዙሮች ሲመሩ ቢቆዩም በወግ አጥባቂ ፓርቲ አባላት ምርጫ በመጨረሻ አሸናፊ መሆናቸው ታውቋል። ሜሪ ኤልዛቤት ትረስ በሚለው ሙሉ የመዝገብ ስማቸው የሚታወቁት ፖለቲከኛዋ፣ ከሂሳብ ሊቁ አባታቸው እና ከነርስ እናታቸው እአአ 1975 በኦክስፎርድ፤ ኢንግላንድ ነበር የተወለዱት። የሊዝ ትረስ መሠረታዊ መረጃዎች ሊዝ ገና በልጅነት እድሜያቸው የዩናይትድ ኪንግደም አካል በሆነችው ስኮትላንድ መዲና ግላስጎ ውስጥ ኖረዋል። ከዚያም የቤተሰብ አባላቱ ወደ ሊድስ ተዘዋውሯል። ሊዝ ትረስ በወጣትነት እድሜያቸው ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ገብተው፤ ፍልስፍና፣ ፖለቲካ እና ምጣሄ ሃብት አጥንተዋል። በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው በተማሪዎች የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ንቁ ተሳትፎን ያደርጉ ነበር። አሁን ላይ የወግ አጥባቂ ፓርቲ መሪ ሆነው የተመረጡት ሊዝ ትረስ፤ በተማሪነት ዘመናቸው ግን ሊብራል ዴሞክራት ነበሩ። ሊዝ በፀረ ንጉሣዊ አስተዳደር ላይ በሚያንጸባርቁት ጠንካራ አቋም ይታወቁ ነበር። እአአ 1994 ላይ በሊብራል ፓርቲ ኮንፈረንስ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፤ “እኛ ሊብራል ዴሞክራቶች ለሁሉም መሰጠት ስላለበት ዕድል እናምናለን። ሰዎች ለመምረት ይወለዳሉ ብለን አናምንም” ሲሉ ተናግረው ነበር። ሊዝ ገና በኦክስፎርድ ሳሉ ነበር የፖለቲካ አቋም ለውጥ በማድረግ ፊታቸውን ወደ ወግ አጥባቂ ፓርቲ ያዞሩት። ከዩኒቨርሲቲ ከወጡ በኋላ ለሼል እንዲሁም ኬብል ኤንድ ዋየርለስ ለሚባል ኩባንያ የሂሳብ ባለሙያ ሆነው እያገለገሉ ሳለ ከሙያ አጋራቸው ጋር እአአ 2000 ላይ ትዳር መስርተዋል። ጥንዶቹ በእስራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ የሁለት ሴት ልጆች ወላጆች ናቸው። ትረስ እአአ 2001 ላይ በምዕራብ ዮርክሻየር የወግ አጥባቂ ፓርቲን ወክለው ተወዳድረው የነበረ ቢሆንም፣ ድል ሳይቀናቸው ቀርቷል። በተመሳሳይ 2005 ላይ በነበረ ምርጫም ተሸናፊ ነበሩ። ሊዝ ትረስ ከአንድም ሁለቴ ሽንፈት ቢገጥማቸውም ለፖለቲካ እጅ አልሰጡም። እአአ 2006 ላይ በደቡብ ምሥራቅ ለንደን ካውንስለር ሆነው ተመርጠው ነበር። እአአ 2010 ለነበረው ምርጫ የወግ አጥባቂው ፓርቲ መሪ ዴቪድ ካሜሩን ሊዝ ትረስን ለፓርቲው አጋርነት የመጀመሪያ ተመራጭ ዕጩ ዝርዝሮች ውስጥ ቢያካትቷቸውም፤ ወጣቷ ፖለቲከኛ ማርክ ፊልድ ከተባሉ የፓርላማ አባል ጋር የፍቅር ግንኙነት እንደነበራቸው ይፋ መሆኑን ተከትሎ ከፓርቲ አባላቶች ጫና በዝቶባቸው ነበር። ይሁን እንጂ የቀረበባቸውን ፈተና በማለፍ ተመራጭ ሆነው ነበር። ሊዝ ትረስ እአአ 2010 ላይ ከሌሎች አራት የወግ አጥባቂ ፓርቲ አባላት ጋር በመሆን ‘ብሪታኒያ አንቼንድ’ የተሰኘ ብዙ ያነጋገረ መጽሃፍ አሳትመው ነበር። በዛ መጽሐፍ ላይ ብሪታኒያውያን ሠራተኞችን፤ “በዓለማችን ካሉ ሰነፍ ሠራተኞች” ብለው መግለጻቸው ብዙ ያስተቻቸው ሲሆን፤ በቅርብ በነበሩ የክርክር መድረኮች ላይ ሊዝ ትረስ ይህን አስተያየት እንዳልጻፉ ተናግረዋል። ሊዝ የፓርላማ አባል በሆኑ በሁለት ዓመታት ውስጥ የትምህርት ሚንስትር ሆነው ተሾሙ። ከሁለት ዓመታት በኋላ ደግሞ በእድገት የአካባቢ ጥበቃ ሚንስትር በመሆን ሌላ ሹመት አግኝተዋል። ምናልባትም እአአ 2015 ከአውሮፓ ኅብረት የመውጣት ሕዝበ ውሳኔ በዚህ የዩኬ ትውልድ ትልቁ የፖለቲካ ክስተት ሊሆን ይችላል። ሊዝ ትረስ በብሬክዚት ላይ የነበራቸው አቋም ዩናይትድ ኪንግደም በአውሮፓ ኅብረት ውስጥ መቆየት አለባት የሚለው ነበር። ዘ ሰን ጋዜጣ ላይ አስፈረውት በነበረው መከራከሪያቸው፤ ዩኬ ከአውሮፓ ኅብረት ብትለይ ምርቶችን ለአውሮፓ ኅብረት ማቅረብ ፈታኝ ይሆናል ብለው ነበር። በሕዝበ ውሳኔው ዩኬ ከአውሮፓ ኅብረት ከተለየች በኋላ ሊዝ ትረስም አቋማቸውን በመቀየር፤ ዩኬ ከኅብረቱ መውጣቷ በበጎ መልኩ የአሰራር ሂደቶችን ቀይሯል ብለዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ አስተዳደር ውስጥ የፍትሕ ሚኒስትር፣ ከዚያም ደግሞ የግምጃ ቤት ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል። እአአ 2019 ላይ ቦሪስ ጆንሰን ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ወደ ሥልጣን ሲመጡ ደግሞ ሊዝ ትረስ የዓለም አቀፍ ንግድ ሚኒስትር ሆነው ማገልገል ጀምረዋል። ሊዝ የ46 ዓመት ጎልማሳ ሳሉ ነበር ትልቁን የመንግሥት ኃላፊነት የተረከቡት። እአአ 2021 ከዶሚኒክ ራብ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ሥልጣንን ተረክበዋል። የሊዝ ትረስ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ያደረጉት ጉዞ አልጋ ባልጋ አልነበረም። ከተቀናቃኛቸው ሪሺ ሱናክ ጋር በነበሯቸው ክርክሮች ላይ ባቀረቧቸው መከራከሪያዎች ሲተቹ ነበር። ይሁን እንጂ የምርጫ ውጤቱ ሊዝ ትረስ ከሪሺ ሱናክ ይልቅ በፓርቲ አባላት ዘንድ የተሻለ ተቀባይነት እንዳላቸው አሳይቷል። | አዲሷ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዝ ትረስ ማን ናቸው? የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን የወግ አጥባቂው ፓርቲ መሪ ሆነው የተመረጡት ሊዝ ትረስ ከንግሥት ኤልዛቤጥ ጋር ከተገናኙ በኋላ በይፋ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዋል። ሊዝ ከየት ተነስተው አሁን ካሉበት ደረሱ? * * ሊዝ ትረስ ገና በ7 ዓመታቸው የቀድሞዋን ዝነኛ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርጋሬት ታቸርን በመወከል ተማሪ ሳሉ ተውነው ነበር። ሊዝ ትረስ ከ39 ዓመታት በኋላ በእውኑ ዓለም የወግ አጥባቂው ፓርቲ መሪ መሆን ችለዋል። እስካሁን ድረስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን እያገለገሉ ያሉት ሊዝ ትረስ፣ በተቀናቃኛቸው ሪሲ ሱናክ ለአምስት ዙሮች ሲመሩ ቢቆዩም በወግ አጥባቂ ፓርቲ አባላት ምርጫ በመጨረሻ አሸናፊ መሆናቸው ታውቋል። ሜሪ ኤልዛቤት ትረስ በሚለው ሙሉ የመዝገብ ስማቸው የሚታወቁት ፖለቲከኛዋ፣ ከሂሳብ ሊቁ አባታቸው እና ከነርስ እናታቸው እአአ 1975 በኦክስፎርድ፤ ኢንግላንድ ነበር የተወለዱት። የሊዝ ትረስ መሠረታዊ መረጃዎች ሊዝ ገና በልጅነት እድሜያቸው የዩናይትድ ኪንግደም አካል በሆነችው ስኮትላንድ መዲና ግላስጎ ውስጥ ኖረዋል። ከዚያም የቤተሰብ አባላቱ ወደ ሊድስ ተዘዋውሯል። ሊዝ ትረስ በወጣትነት እድሜያቸው ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ገብተው፤ ፍልስፍና፣ ፖለቲካ እና ምጣሄ ሃብት አጥንተዋል። በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው በተማሪዎች የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ንቁ ተሳትፎን ያደርጉ ነበር። አሁን ላይ የወግ አጥባቂ ፓርቲ መሪ ሆነው የተመረጡት ሊዝ ትረስ፤ በተማሪነት ዘመናቸው ግን ሊብራል ዴሞክራት ነበሩ። ሊዝ በፀረ ንጉሣዊ አስተዳደር ላይ በሚያንጸባርቁት ጠንካራ አቋም ይታወቁ ነበር። እአአ 1994 ላይ በሊብራል ፓርቲ ኮንፈረንስ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፤ “እኛ ሊብራል ዴሞክራቶች ለሁሉም መሰጠት ስላለበት ዕድል እናምናለን። ሰዎች ለመምረት ይወለዳሉ ብለን አናምንም” ሲሉ ተናግረው ነበር። ሊዝ ገና በኦክስፎርድ ሳሉ ነበር የፖለቲካ አቋም ለውጥ በማድረግ ፊታቸውን ወደ ወግ አጥባቂ ፓርቲ ያዞሩት። ከዩኒቨርሲቲ ከወጡ በኋላ ለሼል እንዲሁም ኬብል ኤንድ ዋየርለስ ለሚባል ኩባንያ የሂሳብ ባለሙያ ሆነው እያገለገሉ ሳለ ከሙያ አጋራቸው ጋር እአአ 2000 ላይ ትዳር መስርተዋል። ጥንዶቹ በእስራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ የሁለት ሴት ልጆች ወላጆች ናቸው። ትረስ እአአ 2001 ላይ በምዕራብ ዮርክሻየር የወግ አጥባቂ ፓርቲን ወክለው ተወዳድረው የነበረ ቢሆንም፣ ድል ሳይቀናቸው ቀርቷል። በተመሳሳይ 2005 ላይ በነበረ ምርጫም ተሸናፊ ነበሩ። ሊዝ ትረስ ከአንድም ሁለቴ ሽንፈት ቢገጥማቸውም ለፖለቲካ እጅ አልሰጡም። እአአ 2006 ላይ በደቡብ ምሥራቅ ለንደን ካውንስለር ሆነው ተመርጠው ነበር። እአአ 2010 ለነበረው ምርጫ የወግ አጥባቂው ፓርቲ መሪ ዴቪድ ካሜሩን ሊዝ ትረስን ለፓርቲው አጋርነት የመጀመሪያ ተመራጭ ዕጩ ዝርዝሮች ውስጥ ቢያካትቷቸውም፤ ወጣቷ ፖለቲከኛ ማርክ ፊልድ ከተባሉ የፓርላማ አባል ጋር የፍቅር ግንኙነት እንደነበራቸው ይፋ መሆኑን ተከትሎ ከፓርቲ አባላቶች ጫና በዝቶባቸው ነበር። ይሁን እንጂ የቀረበባቸውን ፈተና በማለፍ ተመራጭ ሆነው ነበር። ሊዝ ትረስ እአአ 2010 ላይ ከሌሎች አራት የወግ አጥባቂ ፓርቲ አባላት ጋር በመሆን ‘ብሪታኒያ አንቼንድ’ የተሰኘ ብዙ ያነጋገረ መጽሃፍ አሳትመው ነበር። በዛ መጽሐፍ ላይ ብሪታኒያውያን ሠራተኞችን፤ “በዓለማችን ካሉ ሰነፍ ሠራተኞች” ብለው መግለጻቸው ብዙ ያስተቻቸው ሲሆን፤ በቅርብ በነበሩ የክርክር መድረኮች ላይ ሊዝ ትረስ ይህን አስተያየት እንዳልጻፉ ተናግረዋል። ሊዝ የፓርላማ አባል በሆኑ በሁለት ዓመታት ውስጥ የትምህርት ሚንስትር ሆነው ተሾሙ። ከሁለት ዓመታት በኋላ ደግሞ በእድገት የአካባቢ ጥበቃ ሚንስትር በመሆን ሌላ ሹመት አግኝተዋል። ምናልባትም እአአ 2015 ከአውሮፓ ኅብረት የመውጣት ሕዝበ ውሳኔ በዚህ የዩኬ ትውልድ ትልቁ የፖለቲካ ክስተት ሊሆን ይችላል። ሊዝ ትረስ በብሬክዚት ላይ የነበራቸው አቋም ዩናይትድ ኪንግደም በአውሮፓ ኅብረት ውስጥ መቆየት አለባት የሚለው ነበር። ዘ ሰን ጋዜጣ ላይ አስፈረውት በነበረው መከራከሪያቸው፤ ዩኬ ከአውሮፓ ኅብረት ብትለይ ምርቶችን ለአውሮፓ ኅብረት ማቅረብ ፈታኝ ይሆናል ብለው ነበር። በሕዝበ ውሳኔው ዩኬ ከአውሮፓ ኅብረት ከተለየች በኋላ ሊዝ ትረስም አቋማቸውን በመቀየር፤ ዩኬ ከኅብረቱ መውጣቷ በበጎ መልኩ የአሰራር ሂደቶችን ቀይሯል ብለዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ አስተዳደር ውስጥ የፍትሕ ሚኒስትር፣ ከዚያም ደግሞ የግምጃ ቤት ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል። እአአ 2019 ላይ ቦሪስ ጆንሰን ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ወደ ሥልጣን ሲመጡ ደግሞ ሊዝ ትረስ የዓለም አቀፍ ንግድ ሚኒስትር ሆነው ማገልገል ጀምረዋል። ሊዝ የ46 ዓመት ጎልማሳ ሳሉ ነበር ትልቁን የመንግሥት ኃላፊነት የተረከቡት። እአአ 2021 ከዶሚኒክ ራብ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ሥልጣንን ተረክበዋል። የሊዝ ትረስ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ያደረጉት ጉዞ አልጋ ባልጋ አልነበረም። ከተቀናቃኛቸው ሪሺ ሱናክ ጋር በነበሯቸው ክርክሮች ላይ ባቀረቧቸው መከራከሪያዎች ሲተቹ ነበር። ይሁን እንጂ የምርጫ ውጤቱ ሊዝ ትረስ ከሪሺ ሱናክ ይልቅ በፓርቲ አባላት ዘንድ የተሻለ ተቀባይነት እንዳላቸው አሳይቷል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cd1557wx3qyo |
3politics
| የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዊሊያም ሩቶን አሸናፊነት አጸና | የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባለፈው ነሐሴ 09/2014 ዓ.ም. በተካሄደው ምርጫ ላይ የቀረበውን ክስ ውድቅ በማድረግ የዊሊያም ሩቶን በፕሬዝዳንትነት መመረጥ አጸደቀ። ምርጫውን ተከትሎ ተፎካካሪ ዕጩ የነበሩት ራይላ ኦዲንጋ በምርጫው ሂደት ላይ ማጭበርበር መከሰቱን በመግለጽ ያቀረቡትን ክስ ተከትሎ ነው ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ያሳለፈው። ሰባት አባላት ያሉት የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀረበለትን ክስ ሲመለከት ቆይቶ ዊሊያም ሳሞይ ሩቶ አምስተኛው የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡበት ሂደትን ተቀብሎታል። ተቀናቃኙ ራይላ ኦዲንጋ እና አጋሮቻቸው በምርጫው ሂደት የውጤት መለወጥን ጨምሮ ከፍተኛ የማጭበርበር ድረጊቶች ተፈጽመዋል በማለት ነው ለአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ ያቀረቡት። ከፍተኛ ፉክክር በተካሄደበት ምርጫ 50.5 በመቶ የመራጮችን ድምጽ አግኝተው በጠባብ የድምጽ ብልጫ ነበር ዊሊያም ሩቶ ማሸነፋቸው የታወጀው። በአወዛጋቢው ምርጫ አሸናፊነታቸው በድጋሚ በፍርድ ቤት የጸናላቸው ዊሊያም ሩቶ የኬንያ አምስተኛው ፕሬዝዳንት በመሆን በሚቀጥለው ሳምንት ቃለ መሐላ ይፈጽማሉ ተብሎ ይጠበቃል። ነሐሴ መጀመሪያ ላይ የተካሄደውን የኬንያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተከትሎ በቀረበለት ቅሬታ ዙሪያ የአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚሰጠውን ውሳኔ በርካታ ኬንያውያን በጉጉት ሲጠበቅ ነበር። በምርጫው ሂደት ላይ ተፈጽመዋል የተባሉ የማጭበርበር ድርጊቶችን በተመለከተ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሰብሳቢ ማርታ ኮምቤ የቀረቡት ማስረጃዎች “ሐሰተኛ እና በስሜት ላይ የተመሰረቱ ናቸው” በማለት የሰባቱን ዳኞች ውሳኔ ይፋ አድርገው ውጤቱን አጽንተዋል። የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤትን ውሳኔ ተከትሎ በምርጫው የተሸነፉት ራይላ ኦዲንጋ እና ምክትላቸው ማርታ ካሩዋ በተሰጠው ብይን ደስተኛ እንዳልሆኑ ገልጸዋል። ኦዲናጋ ባወጡት መግለጫ ካሩዋ ደግሞ ትዊተር ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት ሁለቱም በተመሳሳይ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ እንደሚያከብሩ ነገር ግን “ፈጽሞ እንደማይስማሙበት” ገልጸዋል። ይህ ውሳኔ በምርጫው ውዝግብ ላይ የመጨረሻው ብይን በመሆኑ የዊሊያም ሩቶ ፕሬዝዳንትነት እውን ሆኗል። የአገሪቱ የምርጫ እና ድንበር ኮሚሽን የወቅቱ ምክትል ፕሬዝዳን ዊሊያም ሩቶን አብላጫ ድምጽ አግኝተዋል በማለት ተመራጭ ፕሬዝዳንት ሲል ማወጁ ይታወሳል። ይሁን እንጂ የሩቶ ተቀናቃኝ ራይላ ኦዲንጋ የምርጫ ውጤቱን በመቃወም ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስደውታል። የራይላ ኦዲንጋ ጠበቆች በምርጫው ሂደት ተአማኒነት የጎደላቸው አሠራሮች በማጋጠማቸው ፍርድ ቤቱ የምርጫ ውጤቱን ውድቅ እንዲያደርገው ጠይቀው ነበር። ለቀናት የሁለቱንም ወገን መከራከሪያ ሲያዳምጥ የነበረው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ በሰጠው ውሳኔ የቀደመውን ውጤት አጽድቆታል። የዊሊያም ሩቶ እና የምርጫ ኮሚሽኑ ጠበቆች በበኩላቸው ምርጫው ስለመጭበርበሩ ምንም ማስረጃ አልቀረበም በሚል ውጤቱ እንዲጸና ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል። ፍርድ ቤቱ እስካለፍነው አርብ ነሐሴ 27/2014 ዓ.ም. ድረስ የሁለቱንም ወገኖች ክርክር ሲያዳምጥ ቆይቶ፤ ዳኞች በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት የጋራ ውሳኔ ለማሳለፍ በአንድ ቦታ ተሰብስበው ሲሰሩ ቆይተዋል። ውሳኔው ከመተላለፉ በፊት የፀጥታ ኃይሎች ዋና ከተማዋ ናይሮቢን ጨምሮ በበርካታ የአገሪቱ ግዛቶች ውስጥ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ተሰማርተው እንደሚገኙ ታይቷል። ዛሬ ከጠዋት ጀምሮ በናይሮቢ ውስጥ በሚገኘው በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ህንጻ ዙሪያ ያሉ ዋና ዋና መንገዶች ለትራፊክ ዝግ ሆነዋል። ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ ጋር በተያያዘ የአደባባይ ተቃውሞ ሊከሰትባቸው ይችላሉ ተብለው በተለዩ አካባቢዎችም የፀጥታ ጥበቃው ጥብቅ እንዲሆን መደረጉን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ከአምስት ዓመት በፊት በነበረው ምርጫ ተመሳሳይ ውዝግብ ተከስቶ የአሁኑ ከሳሽ ራይላ ኦዲንጋ ጉዳዩን ወደ የአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መውሰዳቸው ይታወሳል። በወቅቱም ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ አሁን የሚሰናበቱት የፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታን የአሸናፊነት ውጤትን ውድቅ አድርጎ ምርጫው እንዲደገም ወስኖ ነበር። በተደገመው ምርጫም ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በድጋሚ አሸናፊ ሆነው ለሁለተኛ ዙር አምስት ዓመታት አገሪቱን ሲመሩ ቆይተዋል። | የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዊሊያም ሩቶን አሸናፊነት አጸና የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባለፈው ነሐሴ 09/2014 ዓ.ም. በተካሄደው ምርጫ ላይ የቀረበውን ክስ ውድቅ በማድረግ የዊሊያም ሩቶን በፕሬዝዳንትነት መመረጥ አጸደቀ። ምርጫውን ተከትሎ ተፎካካሪ ዕጩ የነበሩት ራይላ ኦዲንጋ በምርጫው ሂደት ላይ ማጭበርበር መከሰቱን በመግለጽ ያቀረቡትን ክስ ተከትሎ ነው ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ያሳለፈው። ሰባት አባላት ያሉት የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀረበለትን ክስ ሲመለከት ቆይቶ ዊሊያም ሳሞይ ሩቶ አምስተኛው የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡበት ሂደትን ተቀብሎታል። ተቀናቃኙ ራይላ ኦዲንጋ እና አጋሮቻቸው በምርጫው ሂደት የውጤት መለወጥን ጨምሮ ከፍተኛ የማጭበርበር ድረጊቶች ተፈጽመዋል በማለት ነው ለአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ ያቀረቡት። ከፍተኛ ፉክክር በተካሄደበት ምርጫ 50.5 በመቶ የመራጮችን ድምጽ አግኝተው በጠባብ የድምጽ ብልጫ ነበር ዊሊያም ሩቶ ማሸነፋቸው የታወጀው። በአወዛጋቢው ምርጫ አሸናፊነታቸው በድጋሚ በፍርድ ቤት የጸናላቸው ዊሊያም ሩቶ የኬንያ አምስተኛው ፕሬዝዳንት በመሆን በሚቀጥለው ሳምንት ቃለ መሐላ ይፈጽማሉ ተብሎ ይጠበቃል። ነሐሴ መጀመሪያ ላይ የተካሄደውን የኬንያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተከትሎ በቀረበለት ቅሬታ ዙሪያ የአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚሰጠውን ውሳኔ በርካታ ኬንያውያን በጉጉት ሲጠበቅ ነበር። በምርጫው ሂደት ላይ ተፈጽመዋል የተባሉ የማጭበርበር ድርጊቶችን በተመለከተ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሰብሳቢ ማርታ ኮምቤ የቀረቡት ማስረጃዎች “ሐሰተኛ እና በስሜት ላይ የተመሰረቱ ናቸው” በማለት የሰባቱን ዳኞች ውሳኔ ይፋ አድርገው ውጤቱን አጽንተዋል። የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤትን ውሳኔ ተከትሎ በምርጫው የተሸነፉት ራይላ ኦዲንጋ እና ምክትላቸው ማርታ ካሩዋ በተሰጠው ብይን ደስተኛ እንዳልሆኑ ገልጸዋል። ኦዲናጋ ባወጡት መግለጫ ካሩዋ ደግሞ ትዊተር ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት ሁለቱም በተመሳሳይ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ እንደሚያከብሩ ነገር ግን “ፈጽሞ እንደማይስማሙበት” ገልጸዋል። ይህ ውሳኔ በምርጫው ውዝግብ ላይ የመጨረሻው ብይን በመሆኑ የዊሊያም ሩቶ ፕሬዝዳንትነት እውን ሆኗል። የአገሪቱ የምርጫ እና ድንበር ኮሚሽን የወቅቱ ምክትል ፕሬዝዳን ዊሊያም ሩቶን አብላጫ ድምጽ አግኝተዋል በማለት ተመራጭ ፕሬዝዳንት ሲል ማወጁ ይታወሳል። ይሁን እንጂ የሩቶ ተቀናቃኝ ራይላ ኦዲንጋ የምርጫ ውጤቱን በመቃወም ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስደውታል። የራይላ ኦዲንጋ ጠበቆች በምርጫው ሂደት ተአማኒነት የጎደላቸው አሠራሮች በማጋጠማቸው ፍርድ ቤቱ የምርጫ ውጤቱን ውድቅ እንዲያደርገው ጠይቀው ነበር። ለቀናት የሁለቱንም ወገን መከራከሪያ ሲያዳምጥ የነበረው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ በሰጠው ውሳኔ የቀደመውን ውጤት አጽድቆታል። የዊሊያም ሩቶ እና የምርጫ ኮሚሽኑ ጠበቆች በበኩላቸው ምርጫው ስለመጭበርበሩ ምንም ማስረጃ አልቀረበም በሚል ውጤቱ እንዲጸና ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል። ፍርድ ቤቱ እስካለፍነው አርብ ነሐሴ 27/2014 ዓ.ም. ድረስ የሁለቱንም ወገኖች ክርክር ሲያዳምጥ ቆይቶ፤ ዳኞች በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት የጋራ ውሳኔ ለማሳለፍ በአንድ ቦታ ተሰብስበው ሲሰሩ ቆይተዋል። ውሳኔው ከመተላለፉ በፊት የፀጥታ ኃይሎች ዋና ከተማዋ ናይሮቢን ጨምሮ በበርካታ የአገሪቱ ግዛቶች ውስጥ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ተሰማርተው እንደሚገኙ ታይቷል። ዛሬ ከጠዋት ጀምሮ በናይሮቢ ውስጥ በሚገኘው በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ህንጻ ዙሪያ ያሉ ዋና ዋና መንገዶች ለትራፊክ ዝግ ሆነዋል። ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ ጋር በተያያዘ የአደባባይ ተቃውሞ ሊከሰትባቸው ይችላሉ ተብለው በተለዩ አካባቢዎችም የፀጥታ ጥበቃው ጥብቅ እንዲሆን መደረጉን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ከአምስት ዓመት በፊት በነበረው ምርጫ ተመሳሳይ ውዝግብ ተከስቶ የአሁኑ ከሳሽ ራይላ ኦዲንጋ ጉዳዩን ወደ የአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መውሰዳቸው ይታወሳል። በወቅቱም ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ አሁን የሚሰናበቱት የፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታን የአሸናፊነት ውጤትን ውድቅ አድርጎ ምርጫው እንዲደገም ወስኖ ነበር። በተደገመው ምርጫም ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በድጋሚ አሸናፊ ሆነው ለሁለተኛ ዙር አምስት ዓመታት አገሪቱን ሲመሩ ቆይተዋል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cgl00v5ymv7o |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ በዩናይትድ ኪንግደም ከ10ሺህ በላይ ተጨማሪ ሰዎች በኮቪድ -19 መያዛቸው ተገለፀ | ዩናይትድ ኪንግደም በስፋት ምርመራ ማካሄድ ከጀመረች ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ10 ሺህ ሰዎች በላይ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን አስታወቀች። በአገሪቷ ላለፉት 28 ቀናት በተደረገ ምርመራ 12 ሺህ 872 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የተገኙ ሲሆን፤ የ49 ሰዎች ሕይወትም አልፏል። በቴክኒክ ችግር ምክንያት በዚህ ሳምንት የተወሰኑ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ያልተመዘገበ ቢሆንም በቅዳሜ ዕለቱ መረጃ ላይ እንደተካተተ መንግሥት ገልጿል። መንግሥት ይህን ያለው በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የወጣው መረጃ የቫይረሱ ስርጭት ቀድሞ ከነበሩት ሳምንታት ቀስ በቀስ ሊጨምር እንደሚችል ካመላከተ በኋላ ነው። መረጃው በኢንግላንድ ምን ያህል ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው ለማወቅ ከማሕበረሰቡ ውስጥ በተወሰደ የአጋጣሚ ናሙና ላይ በተደረገ ሳምንታዊ ምርመራ ላይ የተመሰረተ ነበር። የአገሪቷ መንግሥት በየዕለቱ የሚወጡ መረጃዎችም የቫይረሱ ሥርጭት ያለበትን የቅርብ ሁኔታ ስለሚያሳዩ በየዕለቱ የሚመዘገቡ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥርም በቅርበት እየተከታተልኩ ነው ብሏል። ይሁን እንጅ በሚቀጥሉት ቀናት የሚወጣው መረጃ በቀደመው ሳምንት በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርን እንደሚያካትት አሳስቧል። የጤና መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ መረጃው በዚህ መልኩ መውጣቱ ሰዎች የምርመራ ውጤታቸውን ከመቀበል አያግዳቸውም ብለዋል። ውጤታቸውም በተለመደው አግባብ እንደሚገለፅላቸው ቃል አቀባዩ አክለዋል። በዩናይትድ ኪንግደም እስከ ቅዳሜ እለት ድረስ 480 ሺህ 017 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በዩናይትድ ኪንግደም የታየው የቫይረሱ ሥርጭት መስፋፋትም በሌሎች የአውሮፓ አገራት ላይ ታይቷል። ፈረንሳይ ቅዳሜ ዕለት 16 ሺህ 972 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን ይህም አዲስ የተመዘገበ ከፍተኛው ቁጥር ነው ተብሏል። በኔዘርላንድስ እና ቤልጂየም በቅደም ተከተል 3ሺህ 967 እና 3ሺህ 175 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ለአገራቱ ይህ በአንድ ቀን የተመዘገበ ከፍተኛው ቁጥር መሆኑ ተገልጿል። በአውሮፓ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ያላት ሩሲያም ከግንቦት ወዲህ ከፍተኛ የተባለውን 9 ሺህ 859 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር መዝግባለች። በተለይ በአውሮፓ ወረርሽኙ እንደገና እያገረሸ ነው። | ኮሮናቫይረስ፡ በዩናይትድ ኪንግደም ከ10ሺህ በላይ ተጨማሪ ሰዎች በኮቪድ -19 መያዛቸው ተገለፀ ዩናይትድ ኪንግደም በስፋት ምርመራ ማካሄድ ከጀመረች ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ10 ሺህ ሰዎች በላይ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን አስታወቀች። በአገሪቷ ላለፉት 28 ቀናት በተደረገ ምርመራ 12 ሺህ 872 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የተገኙ ሲሆን፤ የ49 ሰዎች ሕይወትም አልፏል። በቴክኒክ ችግር ምክንያት በዚህ ሳምንት የተወሰኑ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ያልተመዘገበ ቢሆንም በቅዳሜ ዕለቱ መረጃ ላይ እንደተካተተ መንግሥት ገልጿል። መንግሥት ይህን ያለው በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የወጣው መረጃ የቫይረሱ ስርጭት ቀድሞ ከነበሩት ሳምንታት ቀስ በቀስ ሊጨምር እንደሚችል ካመላከተ በኋላ ነው። መረጃው በኢንግላንድ ምን ያህል ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው ለማወቅ ከማሕበረሰቡ ውስጥ በተወሰደ የአጋጣሚ ናሙና ላይ በተደረገ ሳምንታዊ ምርመራ ላይ የተመሰረተ ነበር። የአገሪቷ መንግሥት በየዕለቱ የሚወጡ መረጃዎችም የቫይረሱ ሥርጭት ያለበትን የቅርብ ሁኔታ ስለሚያሳዩ በየዕለቱ የሚመዘገቡ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥርም በቅርበት እየተከታተልኩ ነው ብሏል። ይሁን እንጅ በሚቀጥሉት ቀናት የሚወጣው መረጃ በቀደመው ሳምንት በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርን እንደሚያካትት አሳስቧል። የጤና መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ መረጃው በዚህ መልኩ መውጣቱ ሰዎች የምርመራ ውጤታቸውን ከመቀበል አያግዳቸውም ብለዋል። ውጤታቸውም በተለመደው አግባብ እንደሚገለፅላቸው ቃል አቀባዩ አክለዋል። በዩናይትድ ኪንግደም እስከ ቅዳሜ እለት ድረስ 480 ሺህ 017 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በዩናይትድ ኪንግደም የታየው የቫይረሱ ሥርጭት መስፋፋትም በሌሎች የአውሮፓ አገራት ላይ ታይቷል። ፈረንሳይ ቅዳሜ ዕለት 16 ሺህ 972 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን ይህም አዲስ የተመዘገበ ከፍተኛው ቁጥር ነው ተብሏል። በኔዘርላንድስ እና ቤልጂየም በቅደም ተከተል 3ሺህ 967 እና 3ሺህ 175 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ለአገራቱ ይህ በአንድ ቀን የተመዘገበ ከፍተኛው ቁጥር መሆኑ ተገልጿል። በአውሮፓ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ያላት ሩሲያም ከግንቦት ወዲህ ከፍተኛ የተባለውን 9 ሺህ 859 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር መዝግባለች። በተለይ በአውሮፓ ወረርሽኙ እንደገና እያገረሸ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/news-54407550 |
3politics
| ኢራናዊው የዶናልድ ትራምፕ አማካሪን ለመግደል በማሴር ተከሰሰ | ኢራናዊው የዶናልድ ትራምፕ የቀድሞ ብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ጆን ቦልተንን ለመግደል በማሴር በአሜሪካ ክስ ቀረበበት። የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ (አይአርጂ) አባል የሆነው ሻህራም ፑርሳፊ በአሁኑ ወቅት ኢራን ውስጥ እንደሚገኝ እና በተጠረጠረው የግድያ ሴራ እንደሚፈለግ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ተናግረዋል። ግለሰቡ ግድያውን ያሴረው በአሜሪካ ጥቃት ለተገደሉት የኢራን ኃያል ወታደራዊ አዛዥ ቃሴም ሶለይማኒ የበቀል ምላሽ ሳይሆን እንዳልቀረም ተናግረዋል። ሶለይማኒ በመካከለኛው ምስራቅ የነበረውን የኢራን ወታደራዊ ዘመቻን መርተዋል። የ62 አመቱ ወታደራዊ አዛዥ የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃን ቡድን ኃይል የመሩ ሲሆን በአውሮፓውያኑ 2020 በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በኢራቅ፣ በባግዳድ አየር ማረፊያ መገደላቸው ይታወሳል። የግለሰቡን ክስ አስመልክቶ የኢራን መንግሥት ቃል አቀባይ “ክሱ መሰረተ ቢስ ነው” ሲሉ ለመንግሥት ሚዲያ ተናግረዋል። የአሜሪካ የፍትሕ ዲፓርትመንት ክሱን ይፋ ባደረገበት ወቅት እንዳሳወቀው መህዲ ሬዛይ በመባል የሚታወቀው የ45 አመቱ ፑርሳፊ በዋሽንግተን ዲሲ ወይም ሜሪላንድ ግድያው እንዲፈጸም አሜሪካ ላሉ ግለሰቦች 300 ሺህ ዶላር ከቴህራን ሆኖ ለመክፈል ሞክሯል። በተጨማሪም በክሱ ላይ ፑርሳፊ በኢንተርኔት ላይ ላገኘው አንድ አሜሪካዊ የቀድሞ ብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ጆን ቦልተንን ፎቶ እንዲያነሳው የጠየቀ መሆኑም ቀርቧል። ለዚህም እንደ ሽፋንነት የተጠቀመው "መጽሐፍ እየጻፍኩ ነው" የሚል እንደሆነ ተገልጿል። ይህ ስሙ ያልተጠቀሰ አሜሪካዊ ፑርሳፊን ሌላ ግለሰብ ጋር እንዳስተዋወቀው ያተተው ክሱ፣ ይህ ግለሰብ ጆን ቦልተንን እንዲገድል ለግድያው ማስረጃም ቪዲዮ እንዲልክ ተጠይቋል ብሏል። ጆን ቦልተን ኤፍ ቢ አይን እና የፍትሕ ክፍሉን ለዚህ ተግባራቸው አመስግነው መግለጫ አውጥተዋል። "የፍትሕ ክፍሉ ዜጎቻችንን ሊጎዱ ወይም ሊገድሏቸው ከሚፈልጉ ከጠላት መንግሥታት የመጠበቅ ትልቅ ኃላፊነት አለበት" በማለት ረዳት ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ማቲው ጂ ኦልሰን መናገራቸው ተዘግቧል። | ኢራናዊው የዶናልድ ትራምፕ አማካሪን ለመግደል በማሴር ተከሰሰ ኢራናዊው የዶናልድ ትራምፕ የቀድሞ ብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ጆን ቦልተንን ለመግደል በማሴር በአሜሪካ ክስ ቀረበበት። የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ (አይአርጂ) አባል የሆነው ሻህራም ፑርሳፊ በአሁኑ ወቅት ኢራን ውስጥ እንደሚገኝ እና በተጠረጠረው የግድያ ሴራ እንደሚፈለግ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ተናግረዋል። ግለሰቡ ግድያውን ያሴረው በአሜሪካ ጥቃት ለተገደሉት የኢራን ኃያል ወታደራዊ አዛዥ ቃሴም ሶለይማኒ የበቀል ምላሽ ሳይሆን እንዳልቀረም ተናግረዋል። ሶለይማኒ በመካከለኛው ምስራቅ የነበረውን የኢራን ወታደራዊ ዘመቻን መርተዋል። የ62 አመቱ ወታደራዊ አዛዥ የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃን ቡድን ኃይል የመሩ ሲሆን በአውሮፓውያኑ 2020 በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በኢራቅ፣ በባግዳድ አየር ማረፊያ መገደላቸው ይታወሳል። የግለሰቡን ክስ አስመልክቶ የኢራን መንግሥት ቃል አቀባይ “ክሱ መሰረተ ቢስ ነው” ሲሉ ለመንግሥት ሚዲያ ተናግረዋል። የአሜሪካ የፍትሕ ዲፓርትመንት ክሱን ይፋ ባደረገበት ወቅት እንዳሳወቀው መህዲ ሬዛይ በመባል የሚታወቀው የ45 አመቱ ፑርሳፊ በዋሽንግተን ዲሲ ወይም ሜሪላንድ ግድያው እንዲፈጸም አሜሪካ ላሉ ግለሰቦች 300 ሺህ ዶላር ከቴህራን ሆኖ ለመክፈል ሞክሯል። በተጨማሪም በክሱ ላይ ፑርሳፊ በኢንተርኔት ላይ ላገኘው አንድ አሜሪካዊ የቀድሞ ብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ጆን ቦልተንን ፎቶ እንዲያነሳው የጠየቀ መሆኑም ቀርቧል። ለዚህም እንደ ሽፋንነት የተጠቀመው "መጽሐፍ እየጻፍኩ ነው" የሚል እንደሆነ ተገልጿል። ይህ ስሙ ያልተጠቀሰ አሜሪካዊ ፑርሳፊን ሌላ ግለሰብ ጋር እንዳስተዋወቀው ያተተው ክሱ፣ ይህ ግለሰብ ጆን ቦልተንን እንዲገድል ለግድያው ማስረጃም ቪዲዮ እንዲልክ ተጠይቋል ብሏል። ጆን ቦልተን ኤፍ ቢ አይን እና የፍትሕ ክፍሉን ለዚህ ተግባራቸው አመስግነው መግለጫ አውጥተዋል። "የፍትሕ ክፍሉ ዜጎቻችንን ሊጎዱ ወይም ሊገድሏቸው ከሚፈልጉ ከጠላት መንግሥታት የመጠበቅ ትልቅ ኃላፊነት አለበት" በማለት ረዳት ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ማቲው ጂ ኦልሰን መናገራቸው ተዘግቧል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c90lvej7dq4o |
5sports
| ዓለም ዋንጫ፡ በሜሲ ድንቅ ጎል ታግዛ አርጀንቲና ወደ ድል ተመለሰች | ሜሲ የተለመደበትን ድንቅ ብቃት አሳይቶ ጎል ባስቆጠረበት ምሽት አርጀንቲና ከፍተኛ ውጥረት የነበረበትን ጨዋታ በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ዕድሏን አለምልማለች። በሳዑዲ አረቢያ ከደረሰባት አስደንጋጭ ሽንፈት በኋላ አርጀንቲና ሌላ ሽንፈት ቢያጋጥማት ከጥሎ ማለፉ ውጭ መሆኗን ታረጋግጥ ነበር። ሜክሲኮዎች በተለይም በመጀመሪያው አጋማሽ ሜሲን እና ጓደኞቹ ተጭነው ለመጫወት ችለዋል። ሜሲ በ64ኛው ደቂቃ ያገኛትን የግብ ዕድል ተጠቅሞ በተዓምረኛ ግራ እግሩ ኳሷን ጉሌርሞ ኦቾአ መረብ ላይ አሳርፏል። ሜሲ በተለይም በመጀመሪያው አጋማሽ በጨዋታው ውስጥ ያለው ተሳትፎ ዝቅ ብሎ ነበር። ሃይል የተቀላቀለበት ጨዋታ መረጋጋት ሲጀመር አጥቂው ተጽዕኖውን ማሳየቱን የጀመረው። ኤንዞ ፈርናንዴዝ ጨዋታው መገባደጃ ላይ ለቡድኑ እፎይታ የሰጠች ጎል አስቆጥሯል። አርጀንቲና ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን ለማረጋገጥ ከፖላንድ ጋር ጠንካራ ፍልሚያ ይጠብቃታል። በሌላ የምድቡ ጨዋታ ፖላንድ ሳዑዲ አረቢያን በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ተስፋዋን አሳድጋለች። ጨዋታው በፖላንድ 2 ለ 0 አሰናፊነት ተጠናቋል። ፒዮትር ዚየለንስኪ በመጀመሪያው አጋማሽ ፖላንድ ቀዳሚ ማድረግ ቻለ። በሁለተኛው አጋማሽ የሳዑዲ ተጫዋቾች የሰሩትን ስህተት ተጠቅሞ አምበሉ ሮበርት ሌዋንዶꬅውስኪ ሁለተኛ ኳስ ከመረብ ላይ አሳረፈ። ይህቺ ጎል ለጎል ቀበኛው ሌዋንዶውስኪ የመጀመሪያ የዓለም ዋንጫ ጎሉ ሆና ተመዝግባለች። የፖላንዱ አጥቂ ከጎሏ በኋላ ደስታውን በእንባ ታጅቦ ገልጿል። ሳዑዲዎች ያገኙትን ፍጹም ቅጣት ምት ወደ ጎል መቀየር ሳይችሉ ቀርተዋል። ከሁለት ጨዋታ በኋላ ፖላንድ ምድብ ሦስትን በአራት ነጥብ መምራት ጀምራለች። አርጀንቲና እና ሳዑዲ አረቢያ በእኩል ሦስት ነጥብ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል። በሚቀጥለው ሳምንት የሚደረጉ የምድቡ የመጨረሻ ጨዋታዎች ወደ ቀጣዩ ዙር የሚያልፉ ሃገራትን ይለያል። በምድብ ሦስት ደግሞ ፈረንሳይ ዴንማርክን በማሸነፍ ለጥሎ ማለፉ መብቃቷን አረጋግጣለች። ፈረንሳይ ዴንማርክን 2 ለ 1 በማሸነፍ ነው ሦስት ነጥብ ያሳካችው። ክሊያን ምባፔ የሰማያዊዎቹን ሁለት ጎሎች ከመረብ ማሳረፍ ችሏል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ እስከ 61ኛው ደቂቃ ድረስ ጎል አላስተናገደም። ምባፔ በ61ኛው ደቂቃ ፈረንሳይ ቀዳሚ አደረገ። አንድሪያስ ክርስቲያንሰን ከሰባት ደቂቃዎች በኋላ ዴንማርክን አቻ ማድረግ ቻለ። ጨዋታው በዚህ ውጤት ሊጠናቀቅ ነው ተብሎ ሲጠበቅ ምባፔ በ86ኛው ደቂቃ ሁለተኛዋን ጎል ከመረብ አሳርፎ ቡድኑን አሸናፊ ማድርግ ችሏል። በሌላ የምድቡ ጨዋታ ቱኒዝያ አውስትራሊያ ተሸንፋለች። ሚቼል ዱክ ብቸኛዋን ጎል ከመረብ አሳርፏል። በበርካታ ደጋፊዎች ታጅባ ወደ ሜዳ የገባችው ቱኒዝያው ውጤቱን መቀልበስ ሳትችል ቀርታለች። ከዚህኛው ምድብ ፈረንሳይ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋግጣለች። አውስትራሊያ በሦስት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች። ዴንማርክ እና ቱኒዝያ አንድ አንድ ነጥብ አላቸው። ፈረንሳይ ከቱኒዝያ እና ዴንማርክ ከአውስትራሊያ በሚያደርጉት ጨዋታ የምድቡ ሁለተኛ አላፊ ቡድን ይለያል። የዓለም ዋንጫው ዛሬም ቀጥሎ ይከናወናል። ዛሬ የምድብ አምስት እና የምድብ ስድስት ጨዋታዎች ይከናወናሉ። ጃፓን ከኮስታሪካ በሚያደርጉት ጨዋታ የምድብ አምስት ጨዋታ ውድድሩ ይቀጥላል። ስፔን ከጀርመን የሚያድርጉት የምድቡ ሌላኛው ጨዋታ በጣም ተጠባቂ ነው። ጀርመን ጨዋታውን ከተሸነፈች ከምድቡ መውደቋን ታረጋግጣለች። በምድብ ስድስት ደግሞ ቤልጂየም ከሞሮኮ እና ክሮሽያ ከካናዳ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ። | ዓለም ዋንጫ፡ በሜሲ ድንቅ ጎል ታግዛ አርጀንቲና ወደ ድል ተመለሰች ሜሲ የተለመደበትን ድንቅ ብቃት አሳይቶ ጎል ባስቆጠረበት ምሽት አርጀንቲና ከፍተኛ ውጥረት የነበረበትን ጨዋታ በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ዕድሏን አለምልማለች። በሳዑዲ አረቢያ ከደረሰባት አስደንጋጭ ሽንፈት በኋላ አርጀንቲና ሌላ ሽንፈት ቢያጋጥማት ከጥሎ ማለፉ ውጭ መሆኗን ታረጋግጥ ነበር። ሜክሲኮዎች በተለይም በመጀመሪያው አጋማሽ ሜሲን እና ጓደኞቹ ተጭነው ለመጫወት ችለዋል። ሜሲ በ64ኛው ደቂቃ ያገኛትን የግብ ዕድል ተጠቅሞ በተዓምረኛ ግራ እግሩ ኳሷን ጉሌርሞ ኦቾአ መረብ ላይ አሳርፏል። ሜሲ በተለይም በመጀመሪያው አጋማሽ በጨዋታው ውስጥ ያለው ተሳትፎ ዝቅ ብሎ ነበር። ሃይል የተቀላቀለበት ጨዋታ መረጋጋት ሲጀመር አጥቂው ተጽዕኖውን ማሳየቱን የጀመረው። ኤንዞ ፈርናንዴዝ ጨዋታው መገባደጃ ላይ ለቡድኑ እፎይታ የሰጠች ጎል አስቆጥሯል። አርጀንቲና ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን ለማረጋገጥ ከፖላንድ ጋር ጠንካራ ፍልሚያ ይጠብቃታል። በሌላ የምድቡ ጨዋታ ፖላንድ ሳዑዲ አረቢያን በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ተስፋዋን አሳድጋለች። ጨዋታው በፖላንድ 2 ለ 0 አሰናፊነት ተጠናቋል። ፒዮትር ዚየለንስኪ በመጀመሪያው አጋማሽ ፖላንድ ቀዳሚ ማድረግ ቻለ። በሁለተኛው አጋማሽ የሳዑዲ ተጫዋቾች የሰሩትን ስህተት ተጠቅሞ አምበሉ ሮበርት ሌዋንዶꬅውስኪ ሁለተኛ ኳስ ከመረብ ላይ አሳረፈ። ይህቺ ጎል ለጎል ቀበኛው ሌዋንዶውስኪ የመጀመሪያ የዓለም ዋንጫ ጎሉ ሆና ተመዝግባለች። የፖላንዱ አጥቂ ከጎሏ በኋላ ደስታውን በእንባ ታጅቦ ገልጿል። ሳዑዲዎች ያገኙትን ፍጹም ቅጣት ምት ወደ ጎል መቀየር ሳይችሉ ቀርተዋል። ከሁለት ጨዋታ በኋላ ፖላንድ ምድብ ሦስትን በአራት ነጥብ መምራት ጀምራለች። አርጀንቲና እና ሳዑዲ አረቢያ በእኩል ሦስት ነጥብ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል። በሚቀጥለው ሳምንት የሚደረጉ የምድቡ የመጨረሻ ጨዋታዎች ወደ ቀጣዩ ዙር የሚያልፉ ሃገራትን ይለያል። በምድብ ሦስት ደግሞ ፈረንሳይ ዴንማርክን በማሸነፍ ለጥሎ ማለፉ መብቃቷን አረጋግጣለች። ፈረንሳይ ዴንማርክን 2 ለ 1 በማሸነፍ ነው ሦስት ነጥብ ያሳካችው። ክሊያን ምባፔ የሰማያዊዎቹን ሁለት ጎሎች ከመረብ ማሳረፍ ችሏል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ እስከ 61ኛው ደቂቃ ድረስ ጎል አላስተናገደም። ምባፔ በ61ኛው ደቂቃ ፈረንሳይ ቀዳሚ አደረገ። አንድሪያስ ክርስቲያንሰን ከሰባት ደቂቃዎች በኋላ ዴንማርክን አቻ ማድረግ ቻለ። ጨዋታው በዚህ ውጤት ሊጠናቀቅ ነው ተብሎ ሲጠበቅ ምባፔ በ86ኛው ደቂቃ ሁለተኛዋን ጎል ከመረብ አሳርፎ ቡድኑን አሸናፊ ማድርግ ችሏል። በሌላ የምድቡ ጨዋታ ቱኒዝያ አውስትራሊያ ተሸንፋለች። ሚቼል ዱክ ብቸኛዋን ጎል ከመረብ አሳርፏል። በበርካታ ደጋፊዎች ታጅባ ወደ ሜዳ የገባችው ቱኒዝያው ውጤቱን መቀልበስ ሳትችል ቀርታለች። ከዚህኛው ምድብ ፈረንሳይ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋግጣለች። አውስትራሊያ በሦስት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች። ዴንማርክ እና ቱኒዝያ አንድ አንድ ነጥብ አላቸው። ፈረንሳይ ከቱኒዝያ እና ዴንማርክ ከአውስትራሊያ በሚያደርጉት ጨዋታ የምድቡ ሁለተኛ አላፊ ቡድን ይለያል። የዓለም ዋንጫው ዛሬም ቀጥሎ ይከናወናል። ዛሬ የምድብ አምስት እና የምድብ ስድስት ጨዋታዎች ይከናወናሉ። ጃፓን ከኮስታሪካ በሚያደርጉት ጨዋታ የምድብ አምስት ጨዋታ ውድድሩ ይቀጥላል። ስፔን ከጀርመን የሚያድርጉት የምድቡ ሌላኛው ጨዋታ በጣም ተጠባቂ ነው። ጀርመን ጨዋታውን ከተሸነፈች ከምድቡ መውደቋን ታረጋግጣለች። በምድብ ስድስት ደግሞ ቤልጂየም ከሞሮኮ እና ክሮሽያ ከካናዳ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ። | https://www.bbc.com/amharic/articles/crgzzdpnpkxo |
2health
| ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ አገራት ገበያ እንዲወጣ የተባለው የአፕል ጭማቂ | በደቡብ አፍሪካ የሚመረተው ሲረስ የተባለው ታሸገ ጭማቂ ከፍተኛ መጠን ያለው ለጤና ጎጂ የሆነ ንጥረ ነገር በውስጡ በመገኘቱ ከሰባት የአፍሪካ አገራት ገበያ እንዲሰበሰብ መደረጉ ተዘግቧል። የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን በበኩሉ ሲረስ አፕል ጁስ የተሰኘው ጭማቂ "በውስጡ ጎጂ የሆነ ከሻጋታ የመነጨ መርዛማ ኬሚካል ስለተገኘበት" ኅብረተሰቡ እንዳይጠቀም ማሳሰቢያ አውጥቷል። ባለስልጣኑ ስለተገኘው መርዛማ ንጥረ ነገር በአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን በኩል በሰጠው ማብራሪያ በፍራፍሬዎች ላይ የሚከሰት ማይኮቶክሲን ከሚባል ከሻጋታ የሚመነጭ መሆኑን አመልክቶ ኅብተሰቡ የተጠቀሰውን ምርት እንዳይጠቀም መክሯል። በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ተመርቶ ወደ ተለያዩ የአፍሪካ አገራት የሚሰራጨው ሲረስ የአፕል ጭማቂ በመበስበስና በመሻገት የሚከሰተው ፓቱሊን የተባለው ጎጂ ንጥረ ነገር ስለተገኘበት ከገበያ እንዲወጣ እየተደረገ ነው። በጭማቂው ላይ በተደረገ ቤተ ሙከራ ፍተሻ እንደተረጋገጠው ሲረስ በተባለው የአፕል ምርት ላይ በአንድ ሊትር ውስጥ እንዲኖረው ከተፈቀደው 50 ማይክሮ ግራም ከፍ ያለ መጠን መገኘቱ ተገልጿል። ይህ የማይኮቶክሲን ውጤት የሆነው ፓቱሊን የተባለው ጎጂ ንጥረ ነገር በአፕል እና በአፕል ምርቶች ውስጥ በሚከሰቱ በተለያዩ ሻጋታዎች አማካይነት የሚፈጠረው። በጭማቂው ውስጥ የተገኘው ንጥረ ነገር ፓቱሊን በተጠቃሚዎች ላይ ማቅለሽለሽና ማስታወክን በማስከተል ጤናን ሊያውክ ይችላል ተብሏል። ይህ ሲረስ የተባለው የአፕል ጭማቂ በኢትዮጵያ ገበያ ውስጥ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን አመልክቶ ኅብረተሰቡ እንዳይ ጠቀመውና በገበያ ላይ ከተገኘም ጥቆማ እንዲሰጠው ጥሪ አቅርቧል። ምርቱ በተጨማሪም በኬንያ፣ በዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ በዛምቢያ፣ ዚምብብዌ፣ ኡጋንዳ፣ ሲሸልስ እና ሞሪሺየስ ገበያዎች ውስጥ ተሰራጭቶ እንደሚገን ተነግሯል። የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ የንግድ ቀጠና (ኮሜሳ) የንግድ ውድድር ኮሚሽን በአገራቱ ውስጥ ያሉ የምርቱ ተጠቃሚዎች ባለፈው ሰኔ ወር ተመርተው የተሰራጩ የሲረስአፕል ጭማቂ ምርቶችን ከገበያ አስወጥተው ለአምራቹ እንዲመልሱ ጥሪ አቅርቧል። | ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ አገራት ገበያ እንዲወጣ የተባለው የአፕል ጭማቂ በደቡብ አፍሪካ የሚመረተው ሲረስ የተባለው ታሸገ ጭማቂ ከፍተኛ መጠን ያለው ለጤና ጎጂ የሆነ ንጥረ ነገር በውስጡ በመገኘቱ ከሰባት የአፍሪካ አገራት ገበያ እንዲሰበሰብ መደረጉ ተዘግቧል። የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን በበኩሉ ሲረስ አፕል ጁስ የተሰኘው ጭማቂ "በውስጡ ጎጂ የሆነ ከሻጋታ የመነጨ መርዛማ ኬሚካል ስለተገኘበት" ኅብረተሰቡ እንዳይጠቀም ማሳሰቢያ አውጥቷል። ባለስልጣኑ ስለተገኘው መርዛማ ንጥረ ነገር በአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን በኩል በሰጠው ማብራሪያ በፍራፍሬዎች ላይ የሚከሰት ማይኮቶክሲን ከሚባል ከሻጋታ የሚመነጭ መሆኑን አመልክቶ ኅብተሰቡ የተጠቀሰውን ምርት እንዳይጠቀም መክሯል። በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ተመርቶ ወደ ተለያዩ የአፍሪካ አገራት የሚሰራጨው ሲረስ የአፕል ጭማቂ በመበስበስና በመሻገት የሚከሰተው ፓቱሊን የተባለው ጎጂ ንጥረ ነገር ስለተገኘበት ከገበያ እንዲወጣ እየተደረገ ነው። በጭማቂው ላይ በተደረገ ቤተ ሙከራ ፍተሻ እንደተረጋገጠው ሲረስ በተባለው የአፕል ምርት ላይ በአንድ ሊትር ውስጥ እንዲኖረው ከተፈቀደው 50 ማይክሮ ግራም ከፍ ያለ መጠን መገኘቱ ተገልጿል። ይህ የማይኮቶክሲን ውጤት የሆነው ፓቱሊን የተባለው ጎጂ ንጥረ ነገር በአፕል እና በአፕል ምርቶች ውስጥ በሚከሰቱ በተለያዩ ሻጋታዎች አማካይነት የሚፈጠረው። በጭማቂው ውስጥ የተገኘው ንጥረ ነገር ፓቱሊን በተጠቃሚዎች ላይ ማቅለሽለሽና ማስታወክን በማስከተል ጤናን ሊያውክ ይችላል ተብሏል። ይህ ሲረስ የተባለው የአፕል ጭማቂ በኢትዮጵያ ገበያ ውስጥ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን አመልክቶ ኅብረተሰቡ እንዳይ ጠቀመውና በገበያ ላይ ከተገኘም ጥቆማ እንዲሰጠው ጥሪ አቅርቧል። ምርቱ በተጨማሪም በኬንያ፣ በዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ በዛምቢያ፣ ዚምብብዌ፣ ኡጋንዳ፣ ሲሸልስ እና ሞሪሺየስ ገበያዎች ውስጥ ተሰራጭቶ እንደሚገን ተነግሯል። የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ የንግድ ቀጠና (ኮሜሳ) የንግድ ውድድር ኮሚሽን በአገራቱ ውስጥ ያሉ የምርቱ ተጠቃሚዎች ባለፈው ሰኔ ወር ተመርተው የተሰራጩ የሲረስአፕል ጭማቂ ምርቶችን ከገበያ አስወጥተው ለአምራቹ እንዲመልሱ ጥሪ አቅርቧል። | https://www.bbc.com/amharic/news-58919812 |
3politics
| የአርጀንቲና ምክትል ፕሬዝዳንት በዕድል የተረፉበት የግድያ ሙከራ ቪዲዮ | የአርጀንቲና ምክትል ፕሬዝዳንት ክርስቲና ፈርናንዴዝ ዴ ኪሪችነር ባለፈው ሐሙስ ምሽት ከተሞከረባቸው ግድያ ለጥቂት አምልጠዋል። ምክትል ፕሬዝዳንቷ በጥይት ከመመታት የዳኑት የተኳሹ መሳሪያ በመንከሱ ነው ተብሏል። ዴ ኪሪችነር ከመኖሪያ ቤታቸው ውጪ ለተሰበሰቡ ደጋፊዎቻቸው ሰላምታ በመስጠት ላይ ሳሉ ነበር አንድ ግለሰብ ከሕዝቡ መካከል ወጥቶ ፊታቸው ላይ ሽጉጡን አነጣጥሮ ለመተኮስ የሞከረው። ቪዲዮውን ይመልከቱ . . . | የአርጀንቲና ምክትል ፕሬዝዳንት በዕድል የተረፉበት የግድያ ሙከራ ቪዲዮ የአርጀንቲና ምክትል ፕሬዝዳንት ክርስቲና ፈርናንዴዝ ዴ ኪሪችነር ባለፈው ሐሙስ ምሽት ከተሞከረባቸው ግድያ ለጥቂት አምልጠዋል። ምክትል ፕሬዝዳንቷ በጥይት ከመመታት የዳኑት የተኳሹ መሳሪያ በመንከሱ ነው ተብሏል። ዴ ኪሪችነር ከመኖሪያ ቤታቸው ውጪ ለተሰበሰቡ ደጋፊዎቻቸው ሰላምታ በመስጠት ላይ ሳሉ ነበር አንድ ግለሰብ ከሕዝቡ መካከል ወጥቶ ፊታቸው ላይ ሽጉጡን አነጣጥሮ ለመተኮስ የሞከረው። ቪዲዮውን ይመልከቱ . . . | https://www.bbc.com/amharic/articles/cxwrnvrj481o |
3politics
| ትግራይ፡ በአድዋ 'የኤርትራ ወታደሮች በከፈቱት ተኩስ' ነዋሪዎች መገደላቸው ተገለጸ | በአድዋ ከተማ ሚያዚያ 04/2013 ዓ.ም፣ ሰኞ ረፋድ አካባቢ የኤርትራ ወታደሮች በከፈቱት ተኩስ ነዋሪዎች እንደተገደሉና እንደቆሰሉ ተገለጸ። በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የአክሱምና የማዕከላዊ ዞን ጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ እንዳሉት ተኩሱ በኤርትራ ወታደሮች መከፈቱን ለቢቢሲ አረጋግጠው፤ በዚህም ሳቢያ ቢያንስ አንድ ሰው እንደሞተ ሲናገሩ ነዋሪዎች ግን ቁጥሩ ስምንት ነው ብለዋል። ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ደግሞ በክስተቱ ሦስት ሰዎች በኤርትራ ወታደሮች መገደላቸውንና ቢያነስ 19 ሰዎች መቁሰላቸውን ማረጋገጡን ለቢቢሲ ገልጿል። ድርጅቱ ጨምሮም ይህ ሁኔታ የኤርትራ ወታደሮች አሁንም በትግራይ ክልል ውስጥ እንደሚገኙ ያመለክታል ብሏል። ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቀው የአክሱም ሆስፒታል ዶክተር ከትናንት ረፋድ ጀምሮ እስከ ከሰዓት በኋላ ድረስ 20 የቆሰሉ ሰዎች ከአድዋ እንደመጡ ለቢቢሲ ተናግሯል። ዓለም አቀፉ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ማኅበር (ኤምኤስኤፍ) እንዳለው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችን ከአድዋ ሆስፒታል እንዳመጣቸው የሚናገረው ይህ ዶክተር "ሁለት ሴቶች የሚገኙባቸው 20 ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች እያከምን ነው" ብሏል። ኤምኤስኤፍ በበኩሉ ትናንት በትዊተር እንደገለጸው ሰኞ እለት 18 ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ አድዋ ኪዳነምህረት ሆስፒታል እንደመጡና እርዳታ እንደተደረገላቸው በመጥቀስ፤ 11 ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ለከፍተኛ ህክምና ወደ አክሱም ሆስፒታል ተልከዋል ብሏል። "ወታደሮቹ ጥቃት በደረሰባቸው ሰዎች ላይ መተኮሳቸው ነግረውኛል" ብሏል። የአካል ጉዳት ከደረሰባቸው ስድስቱ ከፍተኛ ጉዳት ስለ ደረሰባቸው በጽኑ የህክምና ክትትል ውስጥ ሲሆኑ፤ ከእነዚህ አንዷ ሴት እንደሆነች ቢቢሲ ያነጋገረው ሐኪም ገልጿል። የህክምና ባለሙያው እንደሚለው አንዳንዶቹ ሆዳቸው ላይ፤ የተቀሩት ደግሞ በተለያየ የሰውነታቸው ክፍል ጉዳት ደርሶባቸዋል። እነዚህ በ20ዎቹ መጀመሪያ የእድሜ ክልል የሚገኙ ሲሆን አንድ በ60ዎቹ የሚገኙ ግለሰብ እንደሆኑ ለማወቅ ችለናል። ጥቃቱ በአድዋ መናኽሪያ በመባል በሚታወቀው አካባቢ እንደሆነ ያረጋገጡልን በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የአክሱምና የማዕከላዊ ዞን ጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አስገዶም ስዩም፤ በመኪና ተጭነው ሲሄዱ የነበሩት የኤርትራ ወታደሮች "አንድ የባጃጅ አሽከርካሪ መንገድ ዘጋብን" በሚል ጥቃት እንደፈጸሙ ተናግረዋል። "ባለ ባጃጁ ጉዳት ደርሶበታል፤ አንድ ሰው እንደሞተም መረጃው ደርሶኛል። ሌሎች አምስት ሰዎች ደግሞ ተመትተው አክሱም ሪፈራል ሆስፒታል ይገኛሉ" ብለዋል። በተጨማሪም "የአክሱም ሕዝብም ሲሮጥ ነው የዋለው፤ የኤርትራ ወታደሮች ያገኙትን ሰው እየገደሉ እየመጡ ነው የሚል ስልክ ወደ አክሱም ተደወለ። ሕዝቡም ንብረቱን ትቶ፣ የከፈተው ሱቅ ሳይዘጋ ሸሸ" ሲሉ አቶ አስገዶም ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዚህ ጉዳይ የኤርትራ መንግሥት የሰጠው ማብራሪያ የለም። በጉዳዩ ላይ የትግራይ ግብረ ኃይል ኃላፊ ሌተናል ጀነራል ዮሐንስ ገብረመስቀልና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማብራሪያ እንዲሰጡን ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ባለፈው ሳምንት ግን የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግረው የገቡት የኤርትራ ወታደሮች መውጣት እንደጀመሩ የኢትዮጵያ መንግሥት ገልጾ ነበር። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ተጠቂዎችና ኗሪዎች እንደሚሉት የኤርትራ ወታደራዊ ልብስ የለበሱ ታጣቂዎች ጥቃት እንደፈፀሙ ነው። የአካል ጉዳት ደርሶበት አክሱም ሆስፒታል ላይ ከሚገኙት ታካሚዎች አንዱ የሆነው በጸጉር ሥራ ላይ የተሰማራው ወጣት፤ ሰኞ ጠዋት ወደ ሥራ እየሄደ ዲጋዲግ ተብሎ በሚጠራው የአውቶብሶች መናኽሪያ መኪና ላይ ሆነው የሚተኩሱ የኤርትራ ወታደር ልብስ የለበሱ ወታደሮች በጥይት እንደመቱት ለቢቢሲ ገልጿል። "ሁለት የኤርትራ ሠራዊት የጫኑ የጭነት መኪኖች አንበሳ ባንክ አካባቢ ሲደርሱ መተኮስ ጀመሩ። አጋጣሚ አጠገቤ አንድ ሱቅ ነበርና ወደ እዚያ ልገባ ስሮጥ ሦስት ጊዜ ተኮሱብኝ። ሁለት ከጀርባዬ አንድ ደግሞ ሆዴ ላይ መታኝ።" ተመሳሳይ ቆስሎ ሆስፒታል ውስጥ የሚገኘው ሌላ ታካሚ አምስት ጥይት እንደተተኮሰበት በመግለጽ "አንዱ አንገቴ አካባቢ፣ ሦስት ከጀርባዬ፣ አንድ ደግሞ እጄን መቶኛል" ብሏል። ሰኞ እለት ጥቃቱ ሲፈጸም አካባቢው ላይ ማን ነበር ብሎ ቢቢሲ የጠየቀው ሌላ የአድዋ ከተማ ኗሪ በበኩሉ" ወታደሮቹ ወደ ከተማዋ ሲገቡ፣ ጥቃቱ ከመፈጸሙ በፊት አድዋ ላይ ምንም አይነት ጦርነት አልነበረም" ብሏል። ከሰሞኑ የኤርትራ ሠራዊትን አስመልክቶ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች መልስና ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከትግራይ ክልል ግጭት ጋር ተያይዞ በተደጋጋሚ ሲነሳ ለነበረው የኤርትራ ሠራዊት ተሳትፎ ምላሽ ሰጥተዋል። በዚህም የኤርትራ ሠራዊት በድንበር አካባቢ "የደኅንነት ስጋት እንዳለበት" ገልጾ በዚያው አካባቢ ሠራዊቱ እንዳለ ያስረዱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ፣ ለዚህም ምክንያቱ "በኢትዮጵያ ሠራዊት ላይ በህወሓት የተፈጸመው ጥቃት እንደሆነ" ተናግረው ነበር። በዚሁ ወቅት በተጨማሪ ትግራይ ውስጥ የሰብአዊ መብት ጥሰትና በደሎች መፈጸማቸውን የሚያመለክቱ መረጃዎች መኖራቸውን ጠቅሰው መንግሥታቸው የድርጊቱ ፈጻሚዎች ላይ እርምጃ ይወስዳል ብለዋል። "እኛ ወታደሩን የላክነው ወንጀለኞችን እንዲቆጣጠር እንጂ እንዲደፍር አይደለም። በዚህ ወንጀል የተሰማራ ወታደር ካለ በሕግ ተጠያቂ ይደረጋል" ማለታቸው የሚታወስ ነው። በፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልልን ሲያስተዳድር በነበረው ህወሓት መካከል ለረዥም ጊዜ የዘለቀው መቃቃርና አለመግባባት ተካሮ የህወሓት ኃይሎች የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ፈጽመዋል በማለት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የፌደራሉን ጦር ወደ ትግራይ ማዝመታቸው ይታወሳል። በትግራይ ክልል ውስጥ በተካሄደው ወታደራዊ ግጭት ሳቢያ ምን ያህል ሰዎች እንደሞቱ የሚታወቅ ነገር ባይኖርም አሃዙ በበርካታ ሺዎች ሊሆን እንደሚችል የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ይናገራሉ። ከዚህ ባሻገርም በግጭቱ ውስጥ ተሳታፊ በሆኑ ኃይሎች ግድያዎች፣ ጾታዊ ጥቃቶች፣ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ ዘረፋና የንብረት ውድመቶች መፈጸማቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ባወጧቸው ሪፖርቶች ላይ አመልከተዋል። በተጨማሪም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዳለው በግጭቱ ሳቢያ ከሁለት ሚሊዮን ሰዎች በላይ ለመፈናቀል የተዳረጉ ሲሆን፤ ከአራት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ የሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ናቸው። | ትግራይ፡ በአድዋ 'የኤርትራ ወታደሮች በከፈቱት ተኩስ' ነዋሪዎች መገደላቸው ተገለጸ በአድዋ ከተማ ሚያዚያ 04/2013 ዓ.ም፣ ሰኞ ረፋድ አካባቢ የኤርትራ ወታደሮች በከፈቱት ተኩስ ነዋሪዎች እንደተገደሉና እንደቆሰሉ ተገለጸ። በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የአክሱምና የማዕከላዊ ዞን ጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ እንዳሉት ተኩሱ በኤርትራ ወታደሮች መከፈቱን ለቢቢሲ አረጋግጠው፤ በዚህም ሳቢያ ቢያንስ አንድ ሰው እንደሞተ ሲናገሩ ነዋሪዎች ግን ቁጥሩ ስምንት ነው ብለዋል። ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ደግሞ በክስተቱ ሦስት ሰዎች በኤርትራ ወታደሮች መገደላቸውንና ቢያነስ 19 ሰዎች መቁሰላቸውን ማረጋገጡን ለቢቢሲ ገልጿል። ድርጅቱ ጨምሮም ይህ ሁኔታ የኤርትራ ወታደሮች አሁንም በትግራይ ክልል ውስጥ እንደሚገኙ ያመለክታል ብሏል። ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቀው የአክሱም ሆስፒታል ዶክተር ከትናንት ረፋድ ጀምሮ እስከ ከሰዓት በኋላ ድረስ 20 የቆሰሉ ሰዎች ከአድዋ እንደመጡ ለቢቢሲ ተናግሯል። ዓለም አቀፉ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ማኅበር (ኤምኤስኤፍ) እንዳለው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችን ከአድዋ ሆስፒታል እንዳመጣቸው የሚናገረው ይህ ዶክተር "ሁለት ሴቶች የሚገኙባቸው 20 ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች እያከምን ነው" ብሏል። ኤምኤስኤፍ በበኩሉ ትናንት በትዊተር እንደገለጸው ሰኞ እለት 18 ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ አድዋ ኪዳነምህረት ሆስፒታል እንደመጡና እርዳታ እንደተደረገላቸው በመጥቀስ፤ 11 ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ለከፍተኛ ህክምና ወደ አክሱም ሆስፒታል ተልከዋል ብሏል። "ወታደሮቹ ጥቃት በደረሰባቸው ሰዎች ላይ መተኮሳቸው ነግረውኛል" ብሏል። የአካል ጉዳት ከደረሰባቸው ስድስቱ ከፍተኛ ጉዳት ስለ ደረሰባቸው በጽኑ የህክምና ክትትል ውስጥ ሲሆኑ፤ ከእነዚህ አንዷ ሴት እንደሆነች ቢቢሲ ያነጋገረው ሐኪም ገልጿል። የህክምና ባለሙያው እንደሚለው አንዳንዶቹ ሆዳቸው ላይ፤ የተቀሩት ደግሞ በተለያየ የሰውነታቸው ክፍል ጉዳት ደርሶባቸዋል። እነዚህ በ20ዎቹ መጀመሪያ የእድሜ ክልል የሚገኙ ሲሆን አንድ በ60ዎቹ የሚገኙ ግለሰብ እንደሆኑ ለማወቅ ችለናል። ጥቃቱ በአድዋ መናኽሪያ በመባል በሚታወቀው አካባቢ እንደሆነ ያረጋገጡልን በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የአክሱምና የማዕከላዊ ዞን ጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አስገዶም ስዩም፤ በመኪና ተጭነው ሲሄዱ የነበሩት የኤርትራ ወታደሮች "አንድ የባጃጅ አሽከርካሪ መንገድ ዘጋብን" በሚል ጥቃት እንደፈጸሙ ተናግረዋል። "ባለ ባጃጁ ጉዳት ደርሶበታል፤ አንድ ሰው እንደሞተም መረጃው ደርሶኛል። ሌሎች አምስት ሰዎች ደግሞ ተመትተው አክሱም ሪፈራል ሆስፒታል ይገኛሉ" ብለዋል። በተጨማሪም "የአክሱም ሕዝብም ሲሮጥ ነው የዋለው፤ የኤርትራ ወታደሮች ያገኙትን ሰው እየገደሉ እየመጡ ነው የሚል ስልክ ወደ አክሱም ተደወለ። ሕዝቡም ንብረቱን ትቶ፣ የከፈተው ሱቅ ሳይዘጋ ሸሸ" ሲሉ አቶ አስገዶም ለቢቢሲ ተናግረዋል። በዚህ ጉዳይ የኤርትራ መንግሥት የሰጠው ማብራሪያ የለም። በጉዳዩ ላይ የትግራይ ግብረ ኃይል ኃላፊ ሌተናል ጀነራል ዮሐንስ ገብረመስቀልና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማብራሪያ እንዲሰጡን ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ባለፈው ሳምንት ግን የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግረው የገቡት የኤርትራ ወታደሮች መውጣት እንደጀመሩ የኢትዮጵያ መንግሥት ገልጾ ነበር። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ተጠቂዎችና ኗሪዎች እንደሚሉት የኤርትራ ወታደራዊ ልብስ የለበሱ ታጣቂዎች ጥቃት እንደፈፀሙ ነው። የአካል ጉዳት ደርሶበት አክሱም ሆስፒታል ላይ ከሚገኙት ታካሚዎች አንዱ የሆነው በጸጉር ሥራ ላይ የተሰማራው ወጣት፤ ሰኞ ጠዋት ወደ ሥራ እየሄደ ዲጋዲግ ተብሎ በሚጠራው የአውቶብሶች መናኽሪያ መኪና ላይ ሆነው የሚተኩሱ የኤርትራ ወታደር ልብስ የለበሱ ወታደሮች በጥይት እንደመቱት ለቢቢሲ ገልጿል። "ሁለት የኤርትራ ሠራዊት የጫኑ የጭነት መኪኖች አንበሳ ባንክ አካባቢ ሲደርሱ መተኮስ ጀመሩ። አጋጣሚ አጠገቤ አንድ ሱቅ ነበርና ወደ እዚያ ልገባ ስሮጥ ሦስት ጊዜ ተኮሱብኝ። ሁለት ከጀርባዬ አንድ ደግሞ ሆዴ ላይ መታኝ።" ተመሳሳይ ቆስሎ ሆስፒታል ውስጥ የሚገኘው ሌላ ታካሚ አምስት ጥይት እንደተተኮሰበት በመግለጽ "አንዱ አንገቴ አካባቢ፣ ሦስት ከጀርባዬ፣ አንድ ደግሞ እጄን መቶኛል" ብሏል። ሰኞ እለት ጥቃቱ ሲፈጸም አካባቢው ላይ ማን ነበር ብሎ ቢቢሲ የጠየቀው ሌላ የአድዋ ከተማ ኗሪ በበኩሉ" ወታደሮቹ ወደ ከተማዋ ሲገቡ፣ ጥቃቱ ከመፈጸሙ በፊት አድዋ ላይ ምንም አይነት ጦርነት አልነበረም" ብሏል። ከሰሞኑ የኤርትራ ሠራዊትን አስመልክቶ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች መልስና ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከትግራይ ክልል ግጭት ጋር ተያይዞ በተደጋጋሚ ሲነሳ ለነበረው የኤርትራ ሠራዊት ተሳትፎ ምላሽ ሰጥተዋል። በዚህም የኤርትራ ሠራዊት በድንበር አካባቢ "የደኅንነት ስጋት እንዳለበት" ገልጾ በዚያው አካባቢ ሠራዊቱ እንዳለ ያስረዱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ፣ ለዚህም ምክንያቱ "በኢትዮጵያ ሠራዊት ላይ በህወሓት የተፈጸመው ጥቃት እንደሆነ" ተናግረው ነበር። በዚሁ ወቅት በተጨማሪ ትግራይ ውስጥ የሰብአዊ መብት ጥሰትና በደሎች መፈጸማቸውን የሚያመለክቱ መረጃዎች መኖራቸውን ጠቅሰው መንግሥታቸው የድርጊቱ ፈጻሚዎች ላይ እርምጃ ይወስዳል ብለዋል። "እኛ ወታደሩን የላክነው ወንጀለኞችን እንዲቆጣጠር እንጂ እንዲደፍር አይደለም። በዚህ ወንጀል የተሰማራ ወታደር ካለ በሕግ ተጠያቂ ይደረጋል" ማለታቸው የሚታወስ ነው። በፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልልን ሲያስተዳድር በነበረው ህወሓት መካከል ለረዥም ጊዜ የዘለቀው መቃቃርና አለመግባባት ተካሮ የህወሓት ኃይሎች የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ፈጽመዋል በማለት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የፌደራሉን ጦር ወደ ትግራይ ማዝመታቸው ይታወሳል። በትግራይ ክልል ውስጥ በተካሄደው ወታደራዊ ግጭት ሳቢያ ምን ያህል ሰዎች እንደሞቱ የሚታወቅ ነገር ባይኖርም አሃዙ በበርካታ ሺዎች ሊሆን እንደሚችል የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ይናገራሉ። ከዚህ ባሻገርም በግጭቱ ውስጥ ተሳታፊ በሆኑ ኃይሎች ግድያዎች፣ ጾታዊ ጥቃቶች፣ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ ዘረፋና የንብረት ውድመቶች መፈጸማቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ባወጧቸው ሪፖርቶች ላይ አመልከተዋል። በተጨማሪም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዳለው በግጭቱ ሳቢያ ከሁለት ሚሊዮን ሰዎች በላይ ለመፈናቀል የተዳረጉ ሲሆን፤ ከአራት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ የሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ናቸው። | https://www.bbc.com/amharic/news-56745429 |
3politics
| የእስራኤል ምርጫ ቅድመ ውጤት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ እየመሩ እንደሆነ አመላከተ | የቀድሞ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ትላንት ማክሰኞ በሀገራቸው በተከናወነው ምርጫ እየመሩ መሆናቸውን የቅድመ ምርጫ ውጤቶች አመላክተዋል። ከይፋዊ የምርጫ ውጤት በፊት ይፋ የሆኑ ቅድመ ውጤቶች እሳቸው የሚመሩት የቀኝ አክራሪ ፓርቲ በአነስተኛ አብላጫ ድምጽ እየመራ እንደሚገኝ አመላክቷል። ውጤቱም ለተከታታይ 12 ዓመታት በስልጣን ከቆዩ በኋላ ሃላፊነታቸውን ለቀው የነበሩትን ኔታንያሁ ወደ ፖለቲካው መድረክ የመለሰ ነው ተብሏል። በእየሩሳሌም ለደጋፊዎቻቸው ባደረጉት ንግግርም “ለታላቅ ድል ተቃርበናል” ብለዋል። ምርጫው ኔታንያሁን መደገፍ ወይመ አለመደገፍ ተደርጎ በስፋት ሲታይ ቆይቷል። ከሰዓታት በኃላ ይፋ እንደሚሆን የሚጠበቀው ዋናው ውጤት ከተጠበቀው በተቃራኒ ሊሆን የሚችልበት ዕድል አለ ተብሏል። ዋነኛ ተፎካካሪያቸው እና የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ያይር ላፒድ እስካሁን የተወሰነ ነገር የለም ብለዋል። የቅድመ ውጤቱ ይፋ ሲሆን በእየሩሳሌም ከሚገኘው የኔታናንያሁ ፓርቲ ቢሮ የተከፈተ ከፍ ያለ ሙዚቃ ተሰምቷል። የ73 ዓመቱ ኔታንያሁ በእስራኤል ፖለቲካ ውስጥ በአወዛጋቢነት ከሚነሱ ፖለቲከኞች አንዱ ናቸው። ጠንካራ ተቺዎች እንዳሏቸው ሁሉ ሰፊ ድጋፊም አላቸው። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1967 ከመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በኃላ እስራኤል በተቆጣጠረችው ዌስት ባንክ ላይ የዘረጉት የሰፈራ ፕሮግራም ጠንካራ ድጋፍ አስገኝቶላቸዋል። ምንም እንኳን እስራኤል ባትቀበለውም ይህ የሰፈራ ፕሮግራም ከዓለም አቀፍ ህግ አንጻር ህገ ወጥ እንደሆነ ይገመታል። የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር በዌስት ባንክ እና በጋዛ ሰርጥ የፍልስጤምን እንደ ሀገር መመስረት የእስራኤል እና ፍልስጤምን ግጭት ለመፍታት የቀረበውን እና የባይደን አስተዳደርን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ድጋፍ የሚሰጠውን የመፍትሄ ሃሳብ ይቃወሙታል። ኔታናንያሁ በጉቦ፣በማጭበርበር እና የተጣለባቸውን እምነት በማፍረስ ተከሰው ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት እየተከታተሉ ሲሆን የሚቀርብባቸውን ክስ በሙሉ አይቀበሉትም። በእስራኤል ቴሌቪዥን የተላለፉ የቅድመ ምርጫ ውጤቶች በሀገሪቱ ፓርላማ ካለው 120 መቀመጫ የሳቸው ፓርቲ 61 ወይም 62ቱን እንዳገኘ ይፋ አድርገዋል። | የእስራኤል ምርጫ ቅድመ ውጤት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ እየመሩ እንደሆነ አመላከተ የቀድሞ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ትላንት ማክሰኞ በሀገራቸው በተከናወነው ምርጫ እየመሩ መሆናቸውን የቅድመ ምርጫ ውጤቶች አመላክተዋል። ከይፋዊ የምርጫ ውጤት በፊት ይፋ የሆኑ ቅድመ ውጤቶች እሳቸው የሚመሩት የቀኝ አክራሪ ፓርቲ በአነስተኛ አብላጫ ድምጽ እየመራ እንደሚገኝ አመላክቷል። ውጤቱም ለተከታታይ 12 ዓመታት በስልጣን ከቆዩ በኋላ ሃላፊነታቸውን ለቀው የነበሩትን ኔታንያሁ ወደ ፖለቲካው መድረክ የመለሰ ነው ተብሏል። በእየሩሳሌም ለደጋፊዎቻቸው ባደረጉት ንግግርም “ለታላቅ ድል ተቃርበናል” ብለዋል። ምርጫው ኔታንያሁን መደገፍ ወይመ አለመደገፍ ተደርጎ በስፋት ሲታይ ቆይቷል። ከሰዓታት በኃላ ይፋ እንደሚሆን የሚጠበቀው ዋናው ውጤት ከተጠበቀው በተቃራኒ ሊሆን የሚችልበት ዕድል አለ ተብሏል። ዋነኛ ተፎካካሪያቸው እና የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ያይር ላፒድ እስካሁን የተወሰነ ነገር የለም ብለዋል። የቅድመ ውጤቱ ይፋ ሲሆን በእየሩሳሌም ከሚገኘው የኔታናንያሁ ፓርቲ ቢሮ የተከፈተ ከፍ ያለ ሙዚቃ ተሰምቷል። የ73 ዓመቱ ኔታንያሁ በእስራኤል ፖለቲካ ውስጥ በአወዛጋቢነት ከሚነሱ ፖለቲከኞች አንዱ ናቸው። ጠንካራ ተቺዎች እንዳሏቸው ሁሉ ሰፊ ድጋፊም አላቸው። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1967 ከመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በኃላ እስራኤል በተቆጣጠረችው ዌስት ባንክ ላይ የዘረጉት የሰፈራ ፕሮግራም ጠንካራ ድጋፍ አስገኝቶላቸዋል። ምንም እንኳን እስራኤል ባትቀበለውም ይህ የሰፈራ ፕሮግራም ከዓለም አቀፍ ህግ አንጻር ህገ ወጥ እንደሆነ ይገመታል። የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር በዌስት ባንክ እና በጋዛ ሰርጥ የፍልስጤምን እንደ ሀገር መመስረት የእስራኤል እና ፍልስጤምን ግጭት ለመፍታት የቀረበውን እና የባይደን አስተዳደርን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ድጋፍ የሚሰጠውን የመፍትሄ ሃሳብ ይቃወሙታል። ኔታናንያሁ በጉቦ፣በማጭበርበር እና የተጣለባቸውን እምነት በማፍረስ ተከሰው ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት እየተከታተሉ ሲሆን የሚቀርብባቸውን ክስ በሙሉ አይቀበሉትም። በእስራኤል ቴሌቪዥን የተላለፉ የቅድመ ምርጫ ውጤቶች በሀገሪቱ ፓርላማ ካለው 120 መቀመጫ የሳቸው ፓርቲ 61 ወይም 62ቱን እንዳገኘ ይፋ አድርገዋል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c84g3yj3x3lo |
2health
| የቀዶ ህክምና ባለሙያዎች ለመጀመሪያ ጊዜ የ3ዲ ቴክኖሎጂን ተግባራዊ አደረጉ | በእንግሊዝ የ11 ዓመት ታዳጊ የ3ዲ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የኩላሊት ቀዶ ህክምና ተደረገላት። በአገሪቷ የ3ዲ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የኩላሊት ቀዶ ህክምና ሲደረግ የዚች ታዳጊ የመጀመሪያው ነው። በእንግሊዟ ዋቼት ግዛት ነዋሪ የሆነችው ሊቢ በኩላሊት እና በፊኛ ችግሮች እየተሰቃየች የነበረች ሲሆን ለረዥም ጊዜም በከፋ ህመም ትሰቃይ ነበር። ከሰሞኑም የቀዶ ህክምና ባለሙያዎች የ3ዲ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ትንሽ ቀዳዳ አበጅተው ፈጣን በሆነ እና በተሳካ መንገድ ቀዶ ህክምና በሊቢ ላይ ማድረግ ችለዋል። በመላ አገሪቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተጨማሪ ልጆች በቀጣዩ ፈጣን የቀዶ ህክምና ሊደረግላቸው እንደሚችል ተነግሯል። ከ200 ህፃናት መካከል አንዱ ከተለጠጡ ኩላሊቶች ጋር የሚወለዱ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ቀዶ ህክምና የተደረገላት ሊቢ አደግ እስክትል ድረስ ሁኔታዋ አልታወቀም ነበር። ኩላሊቷን ከፊኛዋ ጋር የሚያገናኘው የሽንት ቱቦ በመዘጋቱም ከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ገብታ ነበር። ህመሟም እየከፋ በመጣ ቁጥር የሊቢ ሁኔታ ለቤተሰቡ "በጣም አስጨናቂ ነበር" ሲሉ እናቷ ተናግረዋል። 4 ሚሊሜትር ስፋት ያለው እና ለአእምሮ ቀዶ ህክምና በአብዛኛው ጥቅም ላይ የሚውለውን የ3ዲ ቴክኖሎጂን መሳሪያ በመጠቀም ያለባት እክል ተስተክሏል። ቀዶ ህክምናው የተደረገላት በብሪስቶል የህጻናት ሆስፒታል ነው። ሊቢ ላይ ቀዶ ህክምና ያደረጉላት ዶክተር ማርክ ዉድዋርድ እንደተናገሩት 20 ሺህ ፓውንድ የሚያወጣው የ3ዲ መሳሪያ በቀዶ ጥገናው ወቅት ትክክለኛ ምስል እንዲያገኙና እንዲሁም በተቀላጠፈና በተሳካ መንገድ ቀዶ ህክምናውን ለማካሄድ አስችሎኛል ብለዋል። ዶክተሩ አክለውም የ3ዲ መሳሪያው በትክክል ቀዶ ህክምና ማድረግ የሚያስችል ሲሆን ሰልጣኝ የቀዶ ህክምና ባለሙያዎችም በፍጥነት እንዲማሩ ያግዛል ብለዋል። የሊቢ ቀዶ ህክምና በተለምዶ ከሁለት እስከ ሶስት ሰአታት ይወስድ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን 3ዲ መሳሪያዎችን በመጠቀም ዶክተሮች በ 20 በመቶ መቀነስ እንደሚቻልም ተናግረዋል። | የቀዶ ህክምና ባለሙያዎች ለመጀመሪያ ጊዜ የ3ዲ ቴክኖሎጂን ተግባራዊ አደረጉ በእንግሊዝ የ11 ዓመት ታዳጊ የ3ዲ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የኩላሊት ቀዶ ህክምና ተደረገላት። በአገሪቷ የ3ዲ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የኩላሊት ቀዶ ህክምና ሲደረግ የዚች ታዳጊ የመጀመሪያው ነው። በእንግሊዟ ዋቼት ግዛት ነዋሪ የሆነችው ሊቢ በኩላሊት እና በፊኛ ችግሮች እየተሰቃየች የነበረች ሲሆን ለረዥም ጊዜም በከፋ ህመም ትሰቃይ ነበር። ከሰሞኑም የቀዶ ህክምና ባለሙያዎች የ3ዲ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ትንሽ ቀዳዳ አበጅተው ፈጣን በሆነ እና በተሳካ መንገድ ቀዶ ህክምና በሊቢ ላይ ማድረግ ችለዋል። በመላ አገሪቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተጨማሪ ልጆች በቀጣዩ ፈጣን የቀዶ ህክምና ሊደረግላቸው እንደሚችል ተነግሯል። ከ200 ህፃናት መካከል አንዱ ከተለጠጡ ኩላሊቶች ጋር የሚወለዱ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ቀዶ ህክምና የተደረገላት ሊቢ አደግ እስክትል ድረስ ሁኔታዋ አልታወቀም ነበር። ኩላሊቷን ከፊኛዋ ጋር የሚያገናኘው የሽንት ቱቦ በመዘጋቱም ከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ገብታ ነበር። ህመሟም እየከፋ በመጣ ቁጥር የሊቢ ሁኔታ ለቤተሰቡ "በጣም አስጨናቂ ነበር" ሲሉ እናቷ ተናግረዋል። 4 ሚሊሜትር ስፋት ያለው እና ለአእምሮ ቀዶ ህክምና በአብዛኛው ጥቅም ላይ የሚውለውን የ3ዲ ቴክኖሎጂን መሳሪያ በመጠቀም ያለባት እክል ተስተክሏል። ቀዶ ህክምናው የተደረገላት በብሪስቶል የህጻናት ሆስፒታል ነው። ሊቢ ላይ ቀዶ ህክምና ያደረጉላት ዶክተር ማርክ ዉድዋርድ እንደተናገሩት 20 ሺህ ፓውንድ የሚያወጣው የ3ዲ መሳሪያ በቀዶ ጥገናው ወቅት ትክክለኛ ምስል እንዲያገኙና እንዲሁም በተቀላጠፈና በተሳካ መንገድ ቀዶ ህክምናውን ለማካሄድ አስችሎኛል ብለዋል። ዶክተሩ አክለውም የ3ዲ መሳሪያው በትክክል ቀዶ ህክምና ማድረግ የሚያስችል ሲሆን ሰልጣኝ የቀዶ ህክምና ባለሙያዎችም በፍጥነት እንዲማሩ ያግዛል ብለዋል። የሊቢ ቀዶ ህክምና በተለምዶ ከሁለት እስከ ሶስት ሰአታት ይወስድ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን 3ዲ መሳሪያዎችን በመጠቀም ዶክተሮች በ 20 በመቶ መቀነስ እንደሚቻልም ተናግረዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59782208 |
3politics
| አሜሪካ ፡ የፕሬዝደናት ዶናልድ ትራምፕን መከሰስ የፓርቲያቸው አባላት ጭምር እየደገፉ ነው | ዲሞክራቶች ፕሬዝዳንት ትራምፕን ጥቂት ቀናት ከቀረው ሥልጣናቸው ለማባረር የሚያደርጉት ጥረት ከሪፐብሊካን ፓርቲ አባላትም ድጋፍ እያገኘ መሆኑ ተነገረ። የፓርቲያቸው አባል ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከሥልጣን እንዲባረሩ የሚጠይቀው ክስ እንዲመሰረትባቸው ድጋፋቸውን ከገለጹት መካከል በተወካዮች ምክር ቤት ከፍተኛዋ የሪፐብሊካን ፓርቲ እንደራሴ ሊዝ ቼኒ፤ ባለፈው ሳምንት ዋሺንግተን ውስጥ ከነበረው ግርግር ጋር በተያያዘ ፕሬዝዳንቱ እንዲከሰሱ ድምጽ እንደሚሰጡ በይፋ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንት ለሳምንት ያህል ድምጻቸውን አጥፍተው ከቆዩ በኋላ ማከስኞ ምሽት በሰጡት ቃል ደጋፊዎቻቸው በአገሪቱ ምክር ቤት ላይ ለፈጸሙት ጥቃት ኃላፊነቱን እንደማይወስዱ ገልፀዋል። የዛሬ ሳምንት በአዲሱ ተመራጭ ፕሬዝዳንት የሚተኩት ዶናልድ ትራምፕን ከቀሯቸው የሥልጣን ቀናት በውርደት እንዲባረሩ ዲሞክራቶች ግፊት እያደረጉ ነው። የአገሪቱ ምክር ቤት በፕሬዝዳንቱ ላይ አመጽ በማነሳሳት በሚቀርብባቸው ክስ ላይ ዛሬ ረቡዕ ድምጽ የሚሰጥ ሲሆን፤ በዚህም ፕሬዝዳንት ትራምፕ በአሜሪካ ታሪክ በስልጣን ዘመናቸው ሁለት ጊዜ የተከሰሱ መሪ ይሆናሉ። የቀድሞው የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ዲክ ቼኒ ሴት ልጅ የሆኑት ሊዝ ቼኒ በማለት የአንድ ፓርቲ መሪ የእራሳቸውን አባል ለመክሰስ መስማማታቸው በርካቶችን አስደንቋል። ባወጡት መግለጫ ላይ ትራምፕ "በሕገ መንግሥቱና በገቡት ቃል ላይ ክህደት ፈጽመዋል" ብለዋል። የዋዮሚንግ ግዛት ተወካይ የሆኑት ሊዝ ጨምረውም ፕሬዝዳንቱን "አመጸኞቹን ጠርተው በማሰባሰብ የጥቃቱን እሳት ለኩሰዋል" ሲሉ ከሰዋቸዋል። ሁለት ተጨማሪ የፕሬዝዳንቱ ፓርቲ አባላትም በትራምፕ ላይ የሚከፈተውን ክስ በመደገፍ ድምጻቸውን እንደሚሰጡ ተናግረዋል። በምክር ቤቱ የሪፐብሊካን ፓርቲ መሪ የሆኑትና የትራምፕ ወዳጅ ኬቭን ማካርቲ ክሱን እንደሚቃወሙት የገለጹ ሲሆን፤ ነገር ግን የፓርቲያቸው አባላት በሙሉ በምክር ቤቱ ውስጥ የተቃውሞ ድምጽ እንዲሰጡ ጥሪ እንደማያደርጉ ተናግረዋል። ኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ በሕግ መወሰኛው ምክር ቤት የሪፐብሊካን ፓርቲ መሪ የሆኑት ሚች ማኮኔል ለቅርብ ሰዎቻቸው ተናገሩት ብሎ እንደዘገበው፤ ፕሬዝደንቱን በዲሞክራቶች መከሰሳቸው ትራምፕን ከፓርቲው ለማስወገድ ይረዳል ብለው እንደሚያምኑ አመልክቷል። ማኮኔል ለተባባሪዎቻቸው ጨምረው እንደተናገሩት ፕሬዝደንት ትራምፕ ሊያስከስስ የሚችል ጥፋት ፈጽመዋል ብለው እንደሚያምኑ ዋሽንግተን ፖስት ዘግቧል። | አሜሪካ ፡ የፕሬዝደናት ዶናልድ ትራምፕን መከሰስ የፓርቲያቸው አባላት ጭምር እየደገፉ ነው ዲሞክራቶች ፕሬዝዳንት ትራምፕን ጥቂት ቀናት ከቀረው ሥልጣናቸው ለማባረር የሚያደርጉት ጥረት ከሪፐብሊካን ፓርቲ አባላትም ድጋፍ እያገኘ መሆኑ ተነገረ። የፓርቲያቸው አባል ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከሥልጣን እንዲባረሩ የሚጠይቀው ክስ እንዲመሰረትባቸው ድጋፋቸውን ከገለጹት መካከል በተወካዮች ምክር ቤት ከፍተኛዋ የሪፐብሊካን ፓርቲ እንደራሴ ሊዝ ቼኒ፤ ባለፈው ሳምንት ዋሺንግተን ውስጥ ከነበረው ግርግር ጋር በተያያዘ ፕሬዝዳንቱ እንዲከሰሱ ድምጽ እንደሚሰጡ በይፋ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንት ለሳምንት ያህል ድምጻቸውን አጥፍተው ከቆዩ በኋላ ማከስኞ ምሽት በሰጡት ቃል ደጋፊዎቻቸው በአገሪቱ ምክር ቤት ላይ ለፈጸሙት ጥቃት ኃላፊነቱን እንደማይወስዱ ገልፀዋል። የዛሬ ሳምንት በአዲሱ ተመራጭ ፕሬዝዳንት የሚተኩት ዶናልድ ትራምፕን ከቀሯቸው የሥልጣን ቀናት በውርደት እንዲባረሩ ዲሞክራቶች ግፊት እያደረጉ ነው። የአገሪቱ ምክር ቤት በፕሬዝዳንቱ ላይ አመጽ በማነሳሳት በሚቀርብባቸው ክስ ላይ ዛሬ ረቡዕ ድምጽ የሚሰጥ ሲሆን፤ በዚህም ፕሬዝዳንት ትራምፕ በአሜሪካ ታሪክ በስልጣን ዘመናቸው ሁለት ጊዜ የተከሰሱ መሪ ይሆናሉ። የቀድሞው የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ዲክ ቼኒ ሴት ልጅ የሆኑት ሊዝ ቼኒ በማለት የአንድ ፓርቲ መሪ የእራሳቸውን አባል ለመክሰስ መስማማታቸው በርካቶችን አስደንቋል። ባወጡት መግለጫ ላይ ትራምፕ "በሕገ መንግሥቱና በገቡት ቃል ላይ ክህደት ፈጽመዋል" ብለዋል። የዋዮሚንግ ግዛት ተወካይ የሆኑት ሊዝ ጨምረውም ፕሬዝዳንቱን "አመጸኞቹን ጠርተው በማሰባሰብ የጥቃቱን እሳት ለኩሰዋል" ሲሉ ከሰዋቸዋል። ሁለት ተጨማሪ የፕሬዝዳንቱ ፓርቲ አባላትም በትራምፕ ላይ የሚከፈተውን ክስ በመደገፍ ድምጻቸውን እንደሚሰጡ ተናግረዋል። በምክር ቤቱ የሪፐብሊካን ፓርቲ መሪ የሆኑትና የትራምፕ ወዳጅ ኬቭን ማካርቲ ክሱን እንደሚቃወሙት የገለጹ ሲሆን፤ ነገር ግን የፓርቲያቸው አባላት በሙሉ በምክር ቤቱ ውስጥ የተቃውሞ ድምጽ እንዲሰጡ ጥሪ እንደማያደርጉ ተናግረዋል። ኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ በሕግ መወሰኛው ምክር ቤት የሪፐብሊካን ፓርቲ መሪ የሆኑት ሚች ማኮኔል ለቅርብ ሰዎቻቸው ተናገሩት ብሎ እንደዘገበው፤ ፕሬዝደንቱን በዲሞክራቶች መከሰሳቸው ትራምፕን ከፓርቲው ለማስወገድ ይረዳል ብለው እንደሚያምኑ አመልክቷል። ማኮኔል ለተባባሪዎቻቸው ጨምረው እንደተናገሩት ፕሬዝደንት ትራምፕ ሊያስከስስ የሚችል ጥፋት ፈጽመዋል ብለው እንደሚያምኑ ዋሽንግተን ፖስት ዘግቧል። | https://www.bbc.com/amharic/news-55631984 |
0business
| የዩናይትድ ኪንግደም ፓውንድ የመግዛት አቅም ከዶላር አንጻር ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ዝቅ አለ | ከአውሮፓውያኑ 1971 በኋላ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ የዩናይትድ ኪንግደም ፓወንድ ከአሜሪካ ዶላር ጋር ሲነጻጸር ያለው ዋጋ ማሽቆልቆሉ ተነገረ። ፓውንድ ስተርሊንግ በእስያ ገበያ ያለው የመግዛት አቅም በ4 በመቶ የወረደ ሲሆን አንዱ ፓውንድ ዋጋ ቀደም ሲል ከነበረው ከ1.05 ወደ 1.0327 ዶላር ዝቅ ብሏል። ይህ የተሰማው የዩናይትድ ኪንግደም ቻንስለር ካዋሲ ከዋርቴነግ በከፍተኛ የብድር ድጋፍ የታገዘ ታሪካዊ የታክስ ቅነሳን ይፋ ካደረጉ በኋላ ነው። በአሜሪካ ማዕከላዊ ባንክ እየተደረገ ያለው ዶላርን የማጠናከር እና የወለድ ምጣኔ ጭማሪ የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ፓወንድ ከዶላር አንጻር ያለው የመግዛት አቅም ጫና ውስጥ እንዲገባ ምክንያት ሆኗል። በተጨማሪም ከዶላር አንጻር የዩሮ የመግዛት አቅም ከ20 ዓመት ወዲህ በእስያ ገበያ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ዝቅ ብሏል። ይህም በዩክሬን የተቀሰቀሰው ጦርነት ያስከተለው የነዳጅ ቀውስ መቼ እንደሚፈታ ምልክት አለማሰየቱ ባለሃብቶችን አሳስቧል ተብሏል። በአሁኑ ወቅት ሁሉም የመገበያያ ገንዘብ አይንቶች ከዶላር አንጻር ያላቸው አቅም እየተዳከመ ነው። ስለዚህ የአሜሪካ ዶላር ከፍተኛ ጥንካሬ እያሳየ ነው። ፓውንድን በታክስ ቅነሳ ለመደፍ መታሰቡ ማሽቆልቆሉን እንዲባባስ ያደርገዋል ሲሉ የአንድ የንግድ ተቋም ተባባሪ መስራች የሆኑት ፒተር ኢስኮ ተናግረዋል። “የኃይል አቅርቦት ላይ በቅርቡ የተደረገው ድጎማ እና የዩኬ ባንክ የአደጋ ጊዜ የዋጋ ጭማሪ ሊኖር እንደሚችል የሚጠቁመው ዜና የፍርሃት ምልክት ነው” ሲሉም አክለዋል። ባለፈው ሳምንት የአሜሪካ የፌደራል ጠባባቂያ እና የዩኬ ባንክን ጨምሮ የበርካታ አገራት ማዕከላዊ ባንኮች የዋጋ ጭማሪን ለመከላከል የወሰዱት የወለድ ምጣኔን የመጨመር እርምጃ የዓለም ገበያን እንዲቀዘቅዝ አድርጓል። ፓውንደ ከዶላር በታች ሀኖ የሚቆይ ከሆነ ጋዝ እና ነዳጅ ዘይትን ጨምሮ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶች ዋጋ አሁን ካለው በላይ ሊወደደዱ ይቸላሉ። ከአሜሪካ ወደ ዩኬ የሚገቡ ሌሎች ምርቶችም ሊወደዱ እንደሚችሉ የሚጠበቅ ሲሆን በበአላት ወደ አሜሪካ የሚጓዙ የብርታኒያ ቱሪስቶች ቁጥር ከዚህ ቀደም ከነበረው ሊወርድ ይችላል ተብሏል። | የዩናይትድ ኪንግደም ፓውንድ የመግዛት አቅም ከዶላር አንጻር ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ዝቅ አለ ከአውሮፓውያኑ 1971 በኋላ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ የዩናይትድ ኪንግደም ፓወንድ ከአሜሪካ ዶላር ጋር ሲነጻጸር ያለው ዋጋ ማሽቆልቆሉ ተነገረ። ፓውንድ ስተርሊንግ በእስያ ገበያ ያለው የመግዛት አቅም በ4 በመቶ የወረደ ሲሆን አንዱ ፓውንድ ዋጋ ቀደም ሲል ከነበረው ከ1.05 ወደ 1.0327 ዶላር ዝቅ ብሏል። ይህ የተሰማው የዩናይትድ ኪንግደም ቻንስለር ካዋሲ ከዋርቴነግ በከፍተኛ የብድር ድጋፍ የታገዘ ታሪካዊ የታክስ ቅነሳን ይፋ ካደረጉ በኋላ ነው። በአሜሪካ ማዕከላዊ ባንክ እየተደረገ ያለው ዶላርን የማጠናከር እና የወለድ ምጣኔ ጭማሪ የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ፓወንድ ከዶላር አንጻር ያለው የመግዛት አቅም ጫና ውስጥ እንዲገባ ምክንያት ሆኗል። በተጨማሪም ከዶላር አንጻር የዩሮ የመግዛት አቅም ከ20 ዓመት ወዲህ በእስያ ገበያ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ዝቅ ብሏል። ይህም በዩክሬን የተቀሰቀሰው ጦርነት ያስከተለው የነዳጅ ቀውስ መቼ እንደሚፈታ ምልክት አለማሰየቱ ባለሃብቶችን አሳስቧል ተብሏል። በአሁኑ ወቅት ሁሉም የመገበያያ ገንዘብ አይንቶች ከዶላር አንጻር ያላቸው አቅም እየተዳከመ ነው። ስለዚህ የአሜሪካ ዶላር ከፍተኛ ጥንካሬ እያሳየ ነው። ፓውንድን በታክስ ቅነሳ ለመደፍ መታሰቡ ማሽቆልቆሉን እንዲባባስ ያደርገዋል ሲሉ የአንድ የንግድ ተቋም ተባባሪ መስራች የሆኑት ፒተር ኢስኮ ተናግረዋል። “የኃይል አቅርቦት ላይ በቅርቡ የተደረገው ድጎማ እና የዩኬ ባንክ የአደጋ ጊዜ የዋጋ ጭማሪ ሊኖር እንደሚችል የሚጠቁመው ዜና የፍርሃት ምልክት ነው” ሲሉም አክለዋል። ባለፈው ሳምንት የአሜሪካ የፌደራል ጠባባቂያ እና የዩኬ ባንክን ጨምሮ የበርካታ አገራት ማዕከላዊ ባንኮች የዋጋ ጭማሪን ለመከላከል የወሰዱት የወለድ ምጣኔን የመጨመር እርምጃ የዓለም ገበያን እንዲቀዘቅዝ አድርጓል። ፓውንደ ከዶላር በታች ሀኖ የሚቆይ ከሆነ ጋዝ እና ነዳጅ ዘይትን ጨምሮ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶች ዋጋ አሁን ካለው በላይ ሊወደደዱ ይቸላሉ። ከአሜሪካ ወደ ዩኬ የሚገቡ ሌሎች ምርቶችም ሊወደዱ እንደሚችሉ የሚጠበቅ ሲሆን በበአላት ወደ አሜሪካ የሚጓዙ የብርታኒያ ቱሪስቶች ቁጥር ከዚህ ቀደም ከነበረው ሊወርድ ይችላል ተብሏል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cv21qlrlx4po |
3politics
| በጦርነቱ ከአፋር ክልል የተፈናቀሉ ሰዎች ከ112 ሺህ በላይ መድረሱ ተገለጸ | በአፋር ክልል ካለው ጦርነት ጋር ተያይዞ የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ112 ሺህ በላይ መሆኑን የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ አስታውቋል። የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ ከአፋር ክልል እና ከፌደራል መንግሥት ጋር በመሆን አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እያደረስኩ ነው ብሏል። እስካሁን ድረስ ባለው 30 ሺህ ለሚሆኑና በአምስት ወረዳዎች ላሉ ቤተሰቦች ስንዴ፣ የጥራጥሬና የአትክልት ዘይት ማድረስ መቻሉንም የማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ አስፍሯል። በትግራይ ኃይሎችና በፌደራሉ መንግሥት መካከል የተነሳው ጦርነት አስረኛ ወሩን ያስቆጠረ ሲሆን ወደ አጎራባች ክልሎችም ተዛምቶ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎችን አፈናቅሏል። የኢትዮጵያ መንግሥትና ህወሓት ከጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ጀምሮ ባደረጉት ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎችና ቁጥራቸው የማይታወቅ ተዋጊዎች ተገድለዋል። ከወራት በፊት የፌደራሉ መንግሥት የተናጠል የተኩስ አቁም በማወጅ ወታደሮቹን ከመዲናዋ መቀለ እንዳስወጣ ቢገልፅም ህወሓት በበኩሉ መቀለን በኃይል እንደተቆጣጠረ ተናግሯል። የፌደራሉ መንግሥት የተኩስ አቁም በማወጅ ከትግራይ ለቆ ከወጣበት ምክንያቶች መካከል አብዛኛዎቹ የህወሓት የፖለቲካ እና ወታደራዊ መሪዎች በመገደላቸውና በመታሰራቸው እንዲሁም የቀሩትን ጥቂት የህወሓት አመራሮች ለመያዝ ሲባል ጦርነቱን መቀጠል አስፈላጊ ባለመሆኑ ነው ተብሏል። በክልሉ ያሉ ነዋሪዎች የግብርና ወቅታቸውን እንዳይስተጓጎል፣ የረድዔት ድርጅቶች የበርካቶችን ህይወት እንዲያድኑ እድል ለመስጠት ነው የሚል መሆኑንም አስታውቋል። ህወሓት በስምምነት ላይ የተደረሰ የተኩስ አቁም እንደሚቀበል ያስታወቀ ሲሆን ካስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች መካከል ከክልሉ የኤርትራ ወታደሮችና የአማራ ክልል ኃይሎች ወጥተው ከጦርነቱ በፊት ወደነበሩበት እንዲመለሱ የሚጠይቀው ይገኝበታል። ባለፉት ወራት ጦርነቱን ተከትሎ በክልሉ ውስጥ ተፈጽመዋል የተባሉት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በገለልተኛ ወገን እንዲመረመሩ እንዲሁም ቴሌኮም፣ መብራትና የአውሮፕላን በረራን ጨምሮ የተቋረጡ የመሠረተ ልማት አገልግሎቶች እንዲጀመሩም ጠይቋል። በአሁኑ ወቅት የጦርነት ክተት ጥሪ በየቦታው በሚቀርብበት በዚህ ወቅት ግጭቱ ወደ አዲስ እና ይበልጥ ደም አፋሳሽ ወደ ሆነ ምዕራፍ ሊያመራ ይችላል ተብሎ ተሰግቷል። | በጦርነቱ ከአፋር ክልል የተፈናቀሉ ሰዎች ከ112 ሺህ በላይ መድረሱ ተገለጸ በአፋር ክልል ካለው ጦርነት ጋር ተያይዞ የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ112 ሺህ በላይ መሆኑን የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ አስታውቋል። የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ ከአፋር ክልል እና ከፌደራል መንግሥት ጋር በመሆን አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እያደረስኩ ነው ብሏል። እስካሁን ድረስ ባለው 30 ሺህ ለሚሆኑና በአምስት ወረዳዎች ላሉ ቤተሰቦች ስንዴ፣ የጥራጥሬና የአትክልት ዘይት ማድረስ መቻሉንም የማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ አስፍሯል። በትግራይ ኃይሎችና በፌደራሉ መንግሥት መካከል የተነሳው ጦርነት አስረኛ ወሩን ያስቆጠረ ሲሆን ወደ አጎራባች ክልሎችም ተዛምቶ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎችን አፈናቅሏል። የኢትዮጵያ መንግሥትና ህወሓት ከጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ጀምሮ ባደረጉት ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎችና ቁጥራቸው የማይታወቅ ተዋጊዎች ተገድለዋል። ከወራት በፊት የፌደራሉ መንግሥት የተናጠል የተኩስ አቁም በማወጅ ወታደሮቹን ከመዲናዋ መቀለ እንዳስወጣ ቢገልፅም ህወሓት በበኩሉ መቀለን በኃይል እንደተቆጣጠረ ተናግሯል። የፌደራሉ መንግሥት የተኩስ አቁም በማወጅ ከትግራይ ለቆ ከወጣበት ምክንያቶች መካከል አብዛኛዎቹ የህወሓት የፖለቲካ እና ወታደራዊ መሪዎች በመገደላቸውና በመታሰራቸው እንዲሁም የቀሩትን ጥቂት የህወሓት አመራሮች ለመያዝ ሲባል ጦርነቱን መቀጠል አስፈላጊ ባለመሆኑ ነው ተብሏል። በክልሉ ያሉ ነዋሪዎች የግብርና ወቅታቸውን እንዳይስተጓጎል፣ የረድዔት ድርጅቶች የበርካቶችን ህይወት እንዲያድኑ እድል ለመስጠት ነው የሚል መሆኑንም አስታውቋል። ህወሓት በስምምነት ላይ የተደረሰ የተኩስ አቁም እንደሚቀበል ያስታወቀ ሲሆን ካስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች መካከል ከክልሉ የኤርትራ ወታደሮችና የአማራ ክልል ኃይሎች ወጥተው ከጦርነቱ በፊት ወደነበሩበት እንዲመለሱ የሚጠይቀው ይገኝበታል። ባለፉት ወራት ጦርነቱን ተከትሎ በክልሉ ውስጥ ተፈጽመዋል የተባሉት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በገለልተኛ ወገን እንዲመረመሩ እንዲሁም ቴሌኮም፣ መብራትና የአውሮፕላን በረራን ጨምሮ የተቋረጡ የመሠረተ ልማት አገልግሎቶች እንዲጀመሩም ጠይቋል። በአሁኑ ወቅት የጦርነት ክተት ጥሪ በየቦታው በሚቀርብበት በዚህ ወቅት ግጭቱ ወደ አዲስ እና ይበልጥ ደም አፋሳሽ ወደ ሆነ ምዕራፍ ሊያመራ ይችላል ተብሎ ተሰግቷል። | https://www.bbc.com/amharic/news-58391134 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ ደቡብ ኮሪያ በስፖርት ማዘውተሪያዎች ውስጥ ፈጠን ያሉ ሙዚቃዎች መጫወትን አገደች | በደቡብ ኮሪያ የሰውነት ማጎልመሻ ማዕከላት ወይም በጂም ውስጥ የሚከፈቱ ሙዚቃዎች ለስለስ ያሉ እንዲሆኑ ደንብ ተላለፈ፡፡ ይህም የሆነው ፈጣን ምት ያላቸው ሙዚቃዎች ላብ እንዲፈጠር ስለሚያደርጉ፣ እንዲሁም ሰዎች ቶሎ ቶሎ እንዲተነፍሱ ምክንያት ስለሚሆኑ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ በዋናነት የኮቪድ ሥርጭትን ሊያስፋፋ ስለሚችል ለስላሳ ሙዚቃዎች ማጫወት በተዘዋዋሪ ኮቪድን ሊገታ ይችላሉ ተብሎ የተዘየደ መላ ነው ተብሏል፡፡ በዚህ መመርያ መሰረት 120 ቢት በደቂቃ እና ከዚያ በታች የሆነ ምት ያላቸው ሙዚቃዎች ናቸው ተገቢ የሚሆኑትና በሰውነት ማጎልመሻዎቹ ውስጥ መጫወት የሚችሉት፡፡ ተንቀሳቃሽ ያልሆነ የመሮጫ መም (ትሬድሚል) ደግሞ ቢበዛ በሰዓት 6 ኪሎ ሜትር ብቻ እንዲፈጥን እንዲደረግ ታዟል፡፡ የጤና ባለሞያዎች እንደሚሉት ይህ መመሪያ ተግባራዊ ሲደረግ በስፖርት ማጎልመሻ ማዕከላት ውስጥ የሚገኙ ሰዎች አተነፋፈሳቸው ከልክ በላይ እንዳይሆን፣ ላባቸውም እንዳይንቆረቆር ያስችላል፡፡ ይህም የኮቪድ ስርጭትን ይቀንሳል ብለዋል፡፡ ደቡብ ኮሪያ ከትናንት በስቲያ እሑድ አንድ ሺህ አንድ መቶ አዳዲስ ሰዎች በኮቪድ መያዛቸው ከተረጋገጠ በኋላ ድንጋጤ ተፈጥሯል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አርብ ዕለት እንዳስጠነቀቁት አገሪቱ በኮቪድ ምክንያት ትልቅ ምስቅልቅል ውስጥ ገብታለች፡፡ ከዚህ በላይ ጭንቅ መሸከም አትችልም፡፡ በዚህም የተነሳ መመርያዎቹ በጥብቅ እንዲተገበሩ አዘዋል፡፡ በዚህ መመሪያ ይበልጥ ተጸእኖ የሚደርስባቸው የዙምባና የኤሮቢክስ ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ እነዚህ የእንቅስቃሴ አይነቶች ፈጠን ያለ ሙዚቃን የሚሹ በመሆናቸው፡፡ በአዲሱ መመሪያ መሰረት ሰውነት ማጎልማሻ ማዕከላት ገብተው ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የሚያዘወትሩ ሁሉ ቢበዛ መቆየት የሚችሉት ለሁለት ሰዓታት ብቻ ሲሆን ገላቸውን መታጠብ የሚችሉት ደግሞ ቤታቸው ሄደው ነው፡፡ የጂም ባለቤቶች በበኩላቸው አዲሱ መመሪያ ግራ እንደሆነባቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል፡፡ እንዴት ነው ለስላሳ ሙዚቃ ማጫወት ኮቪድን የሚከላከለው ሲሉም ጠይቀዋል፡፡ ጨምረውም፣ በርካታ ሰዎች ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ‹ጂም› ውስጥ በሚሰሩ ጊዜ በግል ድምጽ ማጫወቻ ነው ሙዚቃ የሚሰሙት፡፡ እነዚህ ሰዎች ታዲያ መንግሥት ያዘዘውን ለስላሳ ሙዚቃ እየሰሙ እንደሆነ መከታተል የሚችለውስ እንዴት ነው ሲሉ መሰረታዊ ጥያቄን አንስተዋል፡፡ | ኮሮናቫይረስ፡ ደቡብ ኮሪያ በስፖርት ማዘውተሪያዎች ውስጥ ፈጠን ያሉ ሙዚቃዎች መጫወትን አገደች በደቡብ ኮሪያ የሰውነት ማጎልመሻ ማዕከላት ወይም በጂም ውስጥ የሚከፈቱ ሙዚቃዎች ለስለስ ያሉ እንዲሆኑ ደንብ ተላለፈ፡፡ ይህም የሆነው ፈጣን ምት ያላቸው ሙዚቃዎች ላብ እንዲፈጠር ስለሚያደርጉ፣ እንዲሁም ሰዎች ቶሎ ቶሎ እንዲተነፍሱ ምክንያት ስለሚሆኑ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ በዋናነት የኮቪድ ሥርጭትን ሊያስፋፋ ስለሚችል ለስላሳ ሙዚቃዎች ማጫወት በተዘዋዋሪ ኮቪድን ሊገታ ይችላሉ ተብሎ የተዘየደ መላ ነው ተብሏል፡፡ በዚህ መመርያ መሰረት 120 ቢት በደቂቃ እና ከዚያ በታች የሆነ ምት ያላቸው ሙዚቃዎች ናቸው ተገቢ የሚሆኑትና በሰውነት ማጎልመሻዎቹ ውስጥ መጫወት የሚችሉት፡፡ ተንቀሳቃሽ ያልሆነ የመሮጫ መም (ትሬድሚል) ደግሞ ቢበዛ በሰዓት 6 ኪሎ ሜትር ብቻ እንዲፈጥን እንዲደረግ ታዟል፡፡ የጤና ባለሞያዎች እንደሚሉት ይህ መመሪያ ተግባራዊ ሲደረግ በስፖርት ማጎልመሻ ማዕከላት ውስጥ የሚገኙ ሰዎች አተነፋፈሳቸው ከልክ በላይ እንዳይሆን፣ ላባቸውም እንዳይንቆረቆር ያስችላል፡፡ ይህም የኮቪድ ስርጭትን ይቀንሳል ብለዋል፡፡ ደቡብ ኮሪያ ከትናንት በስቲያ እሑድ አንድ ሺህ አንድ መቶ አዳዲስ ሰዎች በኮቪድ መያዛቸው ከተረጋገጠ በኋላ ድንጋጤ ተፈጥሯል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አርብ ዕለት እንዳስጠነቀቁት አገሪቱ በኮቪድ ምክንያት ትልቅ ምስቅልቅል ውስጥ ገብታለች፡፡ ከዚህ በላይ ጭንቅ መሸከም አትችልም፡፡ በዚህም የተነሳ መመርያዎቹ በጥብቅ እንዲተገበሩ አዘዋል፡፡ በዚህ መመሪያ ይበልጥ ተጸእኖ የሚደርስባቸው የዙምባና የኤሮቢክስ ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ እነዚህ የእንቅስቃሴ አይነቶች ፈጠን ያለ ሙዚቃን የሚሹ በመሆናቸው፡፡ በአዲሱ መመሪያ መሰረት ሰውነት ማጎልማሻ ማዕከላት ገብተው ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የሚያዘወትሩ ሁሉ ቢበዛ መቆየት የሚችሉት ለሁለት ሰዓታት ብቻ ሲሆን ገላቸውን መታጠብ የሚችሉት ደግሞ ቤታቸው ሄደው ነው፡፡ የጂም ባለቤቶች በበኩላቸው አዲሱ መመሪያ ግራ እንደሆነባቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል፡፡ እንዴት ነው ለስላሳ ሙዚቃ ማጫወት ኮቪድን የሚከላከለው ሲሉም ጠይቀዋል፡፡ ጨምረውም፣ በርካታ ሰዎች ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ‹ጂም› ውስጥ በሚሰሩ ጊዜ በግል ድምጽ ማጫወቻ ነው ሙዚቃ የሚሰሙት፡፡ እነዚህ ሰዎች ታዲያ መንግሥት ያዘዘውን ለስላሳ ሙዚቃ እየሰሙ እንደሆነ መከታተል የሚችለውስ እንዴት ነው ሲሉ መሰረታዊ ጥያቄን አንስተዋል፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/news-57796207 |
0business
| የአውሮፕላን በረራ የሚጀመረው መቼ ይሆን? | የአውሮፕላን በረራ የሚጀመረው መቼ ይሆን? የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት አገራት ከወሰዷቸው እርምጃዎች መካከል አንዱ በሆነው በአየር ትራንስፖርት እገዳ ምክንያት ዘርፉ ክፉኛ ተዳክሟል። በየዕለቱ በዓለም ዙሪያ ይደገሩ የነበሩ በሺህዎች የሚቆጠሩ በረራዎች በመሰረዛቸው የንግድ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት በአብዘኛው ተቋርጧል። በዚህ ዓመት በዓለም ደረጃ የአየር ትራንስፖርቱ ዘርፍ 84 ቢሊዮን ዶላር ይከስራል ተብሎ ተገምቷል። በዚህም ሳቢያ አየር መንገዶች እከሰሩ ሠራተኞቻቸውን ከመቀነስ በተጨማሪ የተዘጉም አሉ። ለወራት በወረርሽኙ ምክንያት የተስተጓጎለው የአየር ትራነስፖርት መቼ ይጀምራል? የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው። ባለሙያዎች በረራዎችን መልሶ ለማስጀመር የሚያስፈልጉ ያሏቸውን ጉዳዮች ያነሱበትን ይህን ቪዲዮ ይመልከቱ። | የአውሮፕላን በረራ የሚጀመረው መቼ ይሆን? የአውሮፕላን በረራ የሚጀመረው መቼ ይሆን? የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት አገራት ከወሰዷቸው እርምጃዎች መካከል አንዱ በሆነው በአየር ትራንስፖርት እገዳ ምክንያት ዘርፉ ክፉኛ ተዳክሟል። በየዕለቱ በዓለም ዙሪያ ይደገሩ የነበሩ በሺህዎች የሚቆጠሩ በረራዎች በመሰረዛቸው የንግድ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት በአብዘኛው ተቋርጧል። በዚህ ዓመት በዓለም ደረጃ የአየር ትራንስፖርቱ ዘርፍ 84 ቢሊዮን ዶላር ይከስራል ተብሎ ተገምቷል። በዚህም ሳቢያ አየር መንገዶች እከሰሩ ሠራተኞቻቸውን ከመቀነስ በተጨማሪ የተዘጉም አሉ። ለወራት በወረርሽኙ ምክንያት የተስተጓጎለው የአየር ትራነስፖርት መቼ ይጀምራል? የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው። ባለሙያዎች በረራዎችን መልሶ ለማስጀመር የሚያስፈልጉ ያሏቸውን ጉዳዮች ያነሱበትን ይህን ቪዲዮ ይመልከቱ። | https://www.bbc.com/amharic/52891046 |
3politics
| ሶማሊላንድ ሕገ ወጥ ስደተኞች እንዲወጡ ቀነ ገደብ አስቀመጠች፣ ኢትዮጵያውያን ሰግተዋል | ዓለም አቀፍ እውቅና የሌላት እና ከሶማሊያ ተነጥላ የወጣችው ሶማሊላንድ ሕጋዊ ፈቃድ የሌላቸው የውጭ ዜጎች አገሪቱን በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ አሳሰበች። የአገሪቱ የኢሚግሬሽን አገልግሎት ሐምሌ 21/2014 ዓ.ም. ባወጣው ማሳሰቢያ እስከ መጪው ነሐሴ 11/2014 ዓ.ም. ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ለቀው እንዲወጡ ያሳስባል። በተጨማሪም ሕገ ወጥ ስደተኞችን በሚያሰሩ ዜጎች ላይም እርምጃ እንደሚወስድ አሳስቧል። ከሌሎች አገራት ዜጎች በተለየ በርካታ ኢትዮጵያውያን በሶማሊላንድ ውስጥ በተለያዩ መስኮች ተሰማርተው የሚገኙ በመሆናቸው ይህ ውሳኔ እንደሚያሳስባቸው ተናግረዋል። በሶማሊላንድ የኢትዮጵያ ወኪል የሆኑት አቶ ሰኢድ መሐመድ ጂብሪል ጉዳዩን ቆንስላ ጽህፈት ቤታቸው እየተከታተለው እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግረዋል። “ከሶማሊላንድ መንግሥት ጋር እየተነጋገርን ነው። በመጪው ሦስት ቀናት ውስጥ ለውጥ ይኖራል ብለን እንገምታለን። እስካሁን ድረስ ግን በቁጥጥር ስር የዋለ ኢትዮጵያዊ የለም” ብለዋል። ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ በቀጥታ እውቅና ባትሰጥም ተጎራባች ግዛት በመሆኗ ግንኙነት ካላቸው ጥቂት አገራት መካከል አንዷ ናት። የሶማሊላንድ አምባሳደር በአዲስ አበባ እንዲሁም ኢትዮጵያም በሃርጌሳ ቆንስላ ጽህፈት ቤት አላቸው። ይህንን ተከትሎም ኢትዮጵያ የሶማሊላንድ የቅርብ አጋሮች ዝርዝር ውስጥ ትገኛለች። ኢትዮጵያ ከዓመታት በፊት ከዱባዩ ዲፒ ወርልድ ጋር የበርበራ ወደብን ለማልማት የሚያስችላትን 19 በመቶ ድርሻ መውሰዷ ብሎም ስምምነቱን የሶማሊላንድ ፓርላማ እንዳጸደቀው ይታወሳል። ይህ ስምምነት በያዝነው ዓመት ኢትዮጵያ ያላት ድርሻ መቋረጡን የሚያሳዩ መረጃዎች ከሶማሊላንድ መንግሥት ዘንድ የወጡ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ሂደቱን አስተባብሏል። ጉዳዩም ገና መቋጫ ያልተበጀለት እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገልጾ ነበር። መቀመጫቸውን በሶማሊላንድ ያደረጉት እና ከሚሰሩበት ተቋም ፖሊሲ ጋር ተያይዞ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈቀዱት ተንታኝ እንደሚሉት፣ ይህ አዲስ እርምጃ እንዳልሆነ እና ከአራት ዓመት በፊት ተመሳሳይ ውሳኔ ተላልፎ እንደነበር ለቢቢሲ ገልጸዋል። አክለውም ይህ የሶማሊላንድ ውሳኔ ከጫት ንግድ እና ከሌሎች የደኅንነት እንዲሁም የፀጥታ ጉዳዮች ጋር የተያያዘ ነው ብለው እንደሚያምኑ ይናገራሉ። “በሶማሊላንድ ያሉ ስደተኞች” ሲል የኢሚግሬሽን መሥሪያ ቤቱ በድፍን ይናገር እንጂ ኢትዮጵያውያንን ኢላማ ያደረገ ነው በማለት፣ ለዚህም በአገሪቱ ከኢትዮጵያውያን ውጪ ያሉ የሌሎች አገራት ስደተኞች ጥብቅ የሰነድ ቁጥጥር እንደሚደረግባቸው ጠቅሰዋል። “ለምሳሌ ፓኪስታኖች አሉ። ነገር ግን ቪዛቸው ጊዜው ካለፈ ራሱ ይቀጣሉ” ሲሉ ያክላሉ። “በሶማሊላንድ ያሉ ኢትዮጵያዊውን እንደ መደራደሪያ ናቸው። በሁለቱ መንግሥታት መካከል የጫት ንግድን የተመለከቱ ያለመግባባቶች አሉ። ከዛም ባሻገር በቅርቡ የተፈረመው የደኅንነት ስምምነት ለችግሩ ምክንያት ነው ብዬ አምናለሁ” ሲሉ ይናገራሉ። ኢትዮጵያ በበርበራ ወደብ ልማት ላይ የወሰደችው ድርሻ መሰረዙ ከተሰማ ወዲህ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣናትን የያዘ ልዑክ ወደ ሃርጌሳ ተልኮ ነበር። የትራንስፖርት ሚንስትሯ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ እንዲሁም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አቶ ሬድዋን ሁሴን ልዑኩን በሐምሌ ወር መጀመሪያ መርተው ተጉዘውም ነበር። በዚህ ሳምንት አጋማሽም በአገር መከላከያ የደኅንነት ሹም የተመራ ልዑክ ሃርጌሳ መግባቱን የሶማሊያ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ታዲያ እነዚህ የንግድ ጉዳዮች እንዳሉ ሆነው ሁለቱ አገራት በቅርቡ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን በሃርጌሳ መቀመጫቸውን ያደረጉት የሰላም እና የደኅንነት ተንታኝ የሆኑት ግለሰብ ይናገራሉ። የሶማሊላንድ እና የኢትዮጵያ ድንበር በቀጭን ገመድ የሚለይ እና ሰፊ የንግድ እና ማኅበራዊ ልውውጦች ያሉበት ነው። እንዲሁም ኢትዮጵያውያን ያለጥብቅ የድንበር ቁጥጥር ሶማሊላንድ ገብተው ይወጣሉ፤ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉትም በተለያዩ ሥራዎች ላይ ተሰማርተው ይኖራሉ። በተለይም የቤት ውስጥ ሥራ፣ ፀጉር ቤቶች እንዲሁም አነስተኛ ምግብ ቤቶችን ከፍተው ይሰራሉ። በቶግ ወቻሌ ከተማም በርካታ የኢትዮጵያ ባንኮች ቅርጫፎቻቸውን ከፍተው ይሰራሉ። በኢትዮጵያ እና በሶማሊላንድ አዋሳኝ አካባቢዎችና ድንበር ተሻግሮ ባሉ ስፍራዎች ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ የሚደረግ ሲሆን፣ በሁለቱም በኩል ተንካራ የሆነ ግንኙነት እንዳለ ይታመናል። የሶማሊያ ታጣቂ ቡድን አል ሻባብ ከሳምንት በፊት ወደ ኢትዮጵያ ዘልቆ በመግባት ጥቃት ከፈጸመ በኋላ የኢትዮጵያ ሠራዊት እና የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል በቡድኑ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መውሰዳቸውና ከፍተኛ አመራሮቹ መገደላቸው መነገሩ ይታወሳል። ኢትዮጵያ በሶማሌላንድ ድንበር በኩል አስካሁን ይህ ነው የሚባል የፀጥታ ስጋት ያልገጠማት ሲሆን፣ ይህንንም ለማጠናከር የአገሪቱ መከላከያ ሠራዊት ባለፉት ቀናት በሃርጌሳ ጉብኝት ማድረጋቸው ተዘግቧል። | ሶማሊላንድ ሕገ ወጥ ስደተኞች እንዲወጡ ቀነ ገደብ አስቀመጠች፣ ኢትዮጵያውያን ሰግተዋል ዓለም አቀፍ እውቅና የሌላት እና ከሶማሊያ ተነጥላ የወጣችው ሶማሊላንድ ሕጋዊ ፈቃድ የሌላቸው የውጭ ዜጎች አገሪቱን በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ አሳሰበች። የአገሪቱ የኢሚግሬሽን አገልግሎት ሐምሌ 21/2014 ዓ.ም. ባወጣው ማሳሰቢያ እስከ መጪው ነሐሴ 11/2014 ዓ.ም. ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ለቀው እንዲወጡ ያሳስባል። በተጨማሪም ሕገ ወጥ ስደተኞችን በሚያሰሩ ዜጎች ላይም እርምጃ እንደሚወስድ አሳስቧል። ከሌሎች አገራት ዜጎች በተለየ በርካታ ኢትዮጵያውያን በሶማሊላንድ ውስጥ በተለያዩ መስኮች ተሰማርተው የሚገኙ በመሆናቸው ይህ ውሳኔ እንደሚያሳስባቸው ተናግረዋል። በሶማሊላንድ የኢትዮጵያ ወኪል የሆኑት አቶ ሰኢድ መሐመድ ጂብሪል ጉዳዩን ቆንስላ ጽህፈት ቤታቸው እየተከታተለው እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግረዋል። “ከሶማሊላንድ መንግሥት ጋር እየተነጋገርን ነው። በመጪው ሦስት ቀናት ውስጥ ለውጥ ይኖራል ብለን እንገምታለን። እስካሁን ድረስ ግን በቁጥጥር ስር የዋለ ኢትዮጵያዊ የለም” ብለዋል። ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ በቀጥታ እውቅና ባትሰጥም ተጎራባች ግዛት በመሆኗ ግንኙነት ካላቸው ጥቂት አገራት መካከል አንዷ ናት። የሶማሊላንድ አምባሳደር በአዲስ አበባ እንዲሁም ኢትዮጵያም በሃርጌሳ ቆንስላ ጽህፈት ቤት አላቸው። ይህንን ተከትሎም ኢትዮጵያ የሶማሊላንድ የቅርብ አጋሮች ዝርዝር ውስጥ ትገኛለች። ኢትዮጵያ ከዓመታት በፊት ከዱባዩ ዲፒ ወርልድ ጋር የበርበራ ወደብን ለማልማት የሚያስችላትን 19 በመቶ ድርሻ መውሰዷ ብሎም ስምምነቱን የሶማሊላንድ ፓርላማ እንዳጸደቀው ይታወሳል። ይህ ስምምነት በያዝነው ዓመት ኢትዮጵያ ያላት ድርሻ መቋረጡን የሚያሳዩ መረጃዎች ከሶማሊላንድ መንግሥት ዘንድ የወጡ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ሂደቱን አስተባብሏል። ጉዳዩም ገና መቋጫ ያልተበጀለት እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገልጾ ነበር። መቀመጫቸውን በሶማሊላንድ ያደረጉት እና ከሚሰሩበት ተቋም ፖሊሲ ጋር ተያይዞ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈቀዱት ተንታኝ እንደሚሉት፣ ይህ አዲስ እርምጃ እንዳልሆነ እና ከአራት ዓመት በፊት ተመሳሳይ ውሳኔ ተላልፎ እንደነበር ለቢቢሲ ገልጸዋል። አክለውም ይህ የሶማሊላንድ ውሳኔ ከጫት ንግድ እና ከሌሎች የደኅንነት እንዲሁም የፀጥታ ጉዳዮች ጋር የተያያዘ ነው ብለው እንደሚያምኑ ይናገራሉ። “በሶማሊላንድ ያሉ ስደተኞች” ሲል የኢሚግሬሽን መሥሪያ ቤቱ በድፍን ይናገር እንጂ ኢትዮጵያውያንን ኢላማ ያደረገ ነው በማለት፣ ለዚህም በአገሪቱ ከኢትዮጵያውያን ውጪ ያሉ የሌሎች አገራት ስደተኞች ጥብቅ የሰነድ ቁጥጥር እንደሚደረግባቸው ጠቅሰዋል። “ለምሳሌ ፓኪስታኖች አሉ። ነገር ግን ቪዛቸው ጊዜው ካለፈ ራሱ ይቀጣሉ” ሲሉ ያክላሉ። “በሶማሊላንድ ያሉ ኢትዮጵያዊውን እንደ መደራደሪያ ናቸው። በሁለቱ መንግሥታት መካከል የጫት ንግድን የተመለከቱ ያለመግባባቶች አሉ። ከዛም ባሻገር በቅርቡ የተፈረመው የደኅንነት ስምምነት ለችግሩ ምክንያት ነው ብዬ አምናለሁ” ሲሉ ይናገራሉ። ኢትዮጵያ በበርበራ ወደብ ልማት ላይ የወሰደችው ድርሻ መሰረዙ ከተሰማ ወዲህ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣናትን የያዘ ልዑክ ወደ ሃርጌሳ ተልኮ ነበር። የትራንስፖርት ሚንስትሯ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ እንዲሁም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አቶ ሬድዋን ሁሴን ልዑኩን በሐምሌ ወር መጀመሪያ መርተው ተጉዘውም ነበር። በዚህ ሳምንት አጋማሽም በአገር መከላከያ የደኅንነት ሹም የተመራ ልዑክ ሃርጌሳ መግባቱን የሶማሊያ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ታዲያ እነዚህ የንግድ ጉዳዮች እንዳሉ ሆነው ሁለቱ አገራት በቅርቡ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን በሃርጌሳ መቀመጫቸውን ያደረጉት የሰላም እና የደኅንነት ተንታኝ የሆኑት ግለሰብ ይናገራሉ። የሶማሊላንድ እና የኢትዮጵያ ድንበር በቀጭን ገመድ የሚለይ እና ሰፊ የንግድ እና ማኅበራዊ ልውውጦች ያሉበት ነው። እንዲሁም ኢትዮጵያውያን ያለጥብቅ የድንበር ቁጥጥር ሶማሊላንድ ገብተው ይወጣሉ፤ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉትም በተለያዩ ሥራዎች ላይ ተሰማርተው ይኖራሉ። በተለይም የቤት ውስጥ ሥራ፣ ፀጉር ቤቶች እንዲሁም አነስተኛ ምግብ ቤቶችን ከፍተው ይሰራሉ። በቶግ ወቻሌ ከተማም በርካታ የኢትዮጵያ ባንኮች ቅርጫፎቻቸውን ከፍተው ይሰራሉ። በኢትዮጵያ እና በሶማሊላንድ አዋሳኝ አካባቢዎችና ድንበር ተሻግሮ ባሉ ስፍራዎች ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ የሚደረግ ሲሆን፣ በሁለቱም በኩል ተንካራ የሆነ ግንኙነት እንዳለ ይታመናል። የሶማሊያ ታጣቂ ቡድን አል ሻባብ ከሳምንት በፊት ወደ ኢትዮጵያ ዘልቆ በመግባት ጥቃት ከፈጸመ በኋላ የኢትዮጵያ ሠራዊት እና የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል በቡድኑ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መውሰዳቸውና ከፍተኛ አመራሮቹ መገደላቸው መነገሩ ይታወሳል። ኢትዮጵያ በሶማሌላንድ ድንበር በኩል አስካሁን ይህ ነው የሚባል የፀጥታ ስጋት ያልገጠማት ሲሆን፣ ይህንንም ለማጠናከር የአገሪቱ መከላከያ ሠራዊት ባለፉት ቀናት በሃርጌሳ ጉብኝት ማድረጋቸው ተዘግቧል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/clmk47ley75o |
3politics
| የዩክሬን የህዋ ሮኬቶች ፋብሪካ መመታትና የአሜሪካ ተጨማሪ የሳዑዲን ነዳጅ ፍለጋ | ባለፈው አርብ አመሻሽ ላይ ሩሲያ በማዕከላዊ ዩክሬን በምትገኘው ዲኒፕሮ ከተማ ላይ በፈጸመችው የረዥም ርቀት የሚሳኤል ጥቃት ሦስት ሰዎች ተገድለዋል። የአከባቢው ባለሥልጣናት እንዳሳወቁት ሚሳኤሎቹ የጠፈር ሮኬቶችን እና ሳተላይቶችን የሚያመርት ፋብሪካን እንዲሁም በአቅራቢያው የሚገኝ ጎዳናን መትተዋል። የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ ይህ ፋብሪካ ለዩክሬን የሚሳኤል ግብአቶችን እና የተለያዩ ክፍሎችን ይሰራ ነበር ብሏል። የዲኒፕሮ ከተማ ሩሲያ ኃይሏን ባሰባሰበችበት ምሥራቃዊ ክፍል ጦርነቱን ሸሽተው የመጡ ዩክሬናውያን መጠለያም መሆኑ ተነግሯል። ክላቭዲያ የተባለች ነዋሪ አንድ ሮኬት ከመስኮቷ ፊት ለፊት እንደወደቀ ተናግራለች። “እንደዚህ ያሉ ጥቃቶችን ለማምለጥ የት መጠለል እንዳለብን ማወቅ ፈታኝ ነው። በቤታችን በታችኛው ክፍል፣ በቤቶች ጀርባ ሁሉም ነገር በጥቃቱ ይወድቃል፣ ይፈራርሳል” ስትል ለሮይተርስ የዜና ወኪል ተናግራለች። ሩሲያ በምሥራቅ ዩክሬን ዶንባስ አካባቢ የምታደርገው የምድር ጥቃት ቀዝቀዝ እያለ በአየር ላይ የምታደርሰው ጥቃት እየጨመረ መጥቷል። እነዚህ ጥቃቶች አብዛኛውን ጊዜ እየደረሱ ያሉት በከተሞች ማዕከላት ላይ ነው ተብሏል። ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ከኪዬቭ በስተምዕራብ በምትገኘው ቪኒትሲያ ከተማ ሩሲያ ባደረሰችው የሚሳኤል ጥቃት 24 ሰዎች ተገድለዋል። ጆ ባይደን የአሜሪካ ፕሬዚዳንትነቱን መንበር በተቆጣጠሩበት የመጀመሪያዎቹ ሳምንታት የሳዑዲ አረቢያን ገዥ ልዑል አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ሳልማንን ለማነጋገር ፈቃደኛ አልነበሩም። የአሜሪካ የደኅንነትና የስለላ ድርጅት ልዑል አልጋ ወራሹ በሳዑዲው ተቃዋሚ ጋዜጠኛ ጀማል ኻሾግጂ ላይ የተፈፀመውን አሰቃቂ ግድያ እጃቸው አለበት ብሎ ያምናል። የጋዜጠኛው ግድያ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ ድንጋጤን እንዲሁም ውግዘት ማስከተሉ ይታወሳል። ነገር ግን ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችው ጦርነት ያስከተለው ከፍተኛ መዘዝ ማሳያ የፕሬዚዳንቱ በመካከከለኛው ምሥራቅ ጉብኝት ለማድረግ ወደ ሳዑዲ አረቢያ መጓዛቸው ነው። ሁለቱ መሪዎች በጀዳ በሚገኘው ንጉሣዊ ቤተ መንግሥት ግቢ ውስጥ ወዳጅነት ባለው መልኩ በጡጫ ሲነካኩ የሚያሳይ ፎቶ ወጥቷል። እንዲህ ፕሬዚዳንቱን ውሳኔያቸውን ያስቀለበሰው ጉዳይ ምንድን ነው? ዋነኛ ማጠንጠኛው የነዳጅ ዋጋ ነው። የዘይት፣ የነዳጅ በአጠቃላይ የኃይል ዋጋ በተወሰነ መልኩ ከዩክሬን ባለው ጦርነት ምክንያት እያሻቀበ መጥቷል። አሜሪካ ያንን ዋጋ ዋጋ ለማውረድ ሳዑዲ አረቢያ የነዳጅ ምርቷን እንድትጨምር ፍላጎት አላት። | የዩክሬን የህዋ ሮኬቶች ፋብሪካ መመታትና የአሜሪካ ተጨማሪ የሳዑዲን ነዳጅ ፍለጋ ባለፈው አርብ አመሻሽ ላይ ሩሲያ በማዕከላዊ ዩክሬን በምትገኘው ዲኒፕሮ ከተማ ላይ በፈጸመችው የረዥም ርቀት የሚሳኤል ጥቃት ሦስት ሰዎች ተገድለዋል። የአከባቢው ባለሥልጣናት እንዳሳወቁት ሚሳኤሎቹ የጠፈር ሮኬቶችን እና ሳተላይቶችን የሚያመርት ፋብሪካን እንዲሁም በአቅራቢያው የሚገኝ ጎዳናን መትተዋል። የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ ይህ ፋብሪካ ለዩክሬን የሚሳኤል ግብአቶችን እና የተለያዩ ክፍሎችን ይሰራ ነበር ብሏል። የዲኒፕሮ ከተማ ሩሲያ ኃይሏን ባሰባሰበችበት ምሥራቃዊ ክፍል ጦርነቱን ሸሽተው የመጡ ዩክሬናውያን መጠለያም መሆኑ ተነግሯል። ክላቭዲያ የተባለች ነዋሪ አንድ ሮኬት ከመስኮቷ ፊት ለፊት እንደወደቀ ተናግራለች። “እንደዚህ ያሉ ጥቃቶችን ለማምለጥ የት መጠለል እንዳለብን ማወቅ ፈታኝ ነው። በቤታችን በታችኛው ክፍል፣ በቤቶች ጀርባ ሁሉም ነገር በጥቃቱ ይወድቃል፣ ይፈራርሳል” ስትል ለሮይተርስ የዜና ወኪል ተናግራለች። ሩሲያ በምሥራቅ ዩክሬን ዶንባስ አካባቢ የምታደርገው የምድር ጥቃት ቀዝቀዝ እያለ በአየር ላይ የምታደርሰው ጥቃት እየጨመረ መጥቷል። እነዚህ ጥቃቶች አብዛኛውን ጊዜ እየደረሱ ያሉት በከተሞች ማዕከላት ላይ ነው ተብሏል። ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ከኪዬቭ በስተምዕራብ በምትገኘው ቪኒትሲያ ከተማ ሩሲያ ባደረሰችው የሚሳኤል ጥቃት 24 ሰዎች ተገድለዋል። ጆ ባይደን የአሜሪካ ፕሬዚዳንትነቱን መንበር በተቆጣጠሩበት የመጀመሪያዎቹ ሳምንታት የሳዑዲ አረቢያን ገዥ ልዑል አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ሳልማንን ለማነጋገር ፈቃደኛ አልነበሩም። የአሜሪካ የደኅንነትና የስለላ ድርጅት ልዑል አልጋ ወራሹ በሳዑዲው ተቃዋሚ ጋዜጠኛ ጀማል ኻሾግጂ ላይ የተፈፀመውን አሰቃቂ ግድያ እጃቸው አለበት ብሎ ያምናል። የጋዜጠኛው ግድያ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ ድንጋጤን እንዲሁም ውግዘት ማስከተሉ ይታወሳል። ነገር ግን ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችው ጦርነት ያስከተለው ከፍተኛ መዘዝ ማሳያ የፕሬዚዳንቱ በመካከከለኛው ምሥራቅ ጉብኝት ለማድረግ ወደ ሳዑዲ አረቢያ መጓዛቸው ነው። ሁለቱ መሪዎች በጀዳ በሚገኘው ንጉሣዊ ቤተ መንግሥት ግቢ ውስጥ ወዳጅነት ባለው መልኩ በጡጫ ሲነካኩ የሚያሳይ ፎቶ ወጥቷል። እንዲህ ፕሬዚዳንቱን ውሳኔያቸውን ያስቀለበሰው ጉዳይ ምንድን ነው? ዋነኛ ማጠንጠኛው የነዳጅ ዋጋ ነው። የዘይት፣ የነዳጅ በአጠቃላይ የኃይል ዋጋ በተወሰነ መልኩ ከዩክሬን ባለው ጦርነት ምክንያት እያሻቀበ መጥቷል። አሜሪካ ያንን ዋጋ ዋጋ ለማውረድ ሳዑዲ አረቢያ የነዳጅ ምርቷን እንድትጨምር ፍላጎት አላት። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cjq9ev834l0o |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ የኮሮና ተሕዋሲ መከላከያ መጠጥን ያበረታቱት የሲሪሊንካ ሚኒስትር በቫይረሱ ተያዙ | ከዕፅዋት የተሰራ የኮሮና ተሕዋሲ መከላከያ መጠጥን አገራቸው እድትጠቀም ያበረታቱት የሲሪላንካ የጤና ሚኒስትር በቫይረሱ ተያዙ። የጤና ሚኒስትሯ ፓቪትራ ዋኒያራቺቺ በዚህ ሳምንት በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን የመስሪያ ቤታቸው ሚዲያ ዘርፍ ፀሐፊ ለቢቢሲ አስታውቀዋል። የአገሪቱ የባህል ህክምና አዋቂ ለህይወት ዘመን የሚሆን የኮሮና ተሕዋሲ መከላከያ መጠጥ ማምረታቸውን ተከትሎ ሚኒስትሯም አገራቸው እንድትጠቀም ሲያበረታቱ ነበር። ፓቪትራ ዋኒያራቺቺ የኮሮና ተሕዋሲ መከላከያ መጠጡን በይፋ ሲጠጡም ታይተዋል። ወረርሽኙ ከተከሰተ ጀምሮ በሲሪሊንካ 56 ሺህ 76 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 276 ዜጎቿንም አጥታለች። በቅርብ ወራትም በከፍተኛ ሁኔታ እያገረሸ ነው ተብሏል። የጤና ሚኒስትሯ በኮሮቫይረስ የተያዙ አራተኛ ሚኒስትር ሆነዋል። የኮሮና ተሕዋሲ መከላከያ መጠጡ ማርና ገውዝን ጨምሮ ከሌሎች ንጥረ ነገሮች የተቀመመ ሲሆን ውህዱም በህልም እንደተሰጣቸው የባህል ሃኪሙ ተናግረዋል። የአገሪቱ የጤና ባለሙያዎች የኮሮና ተሕዋሲ መከላከያው ፍቱንነት አልተረጋገጠም ቢሉም በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የባህል ሃኪሙ ወደሚገኝበት መንደር ይጎርፉ ነበር ተብሏል። የጤና ሚኒስትሯ ሁለት የኮቪድ-19 ምርመራ ቢያደርጉም ሁለቱም በቫይረሱ መያዛቸውን እንደሚያሳይ የሚዲያ ፀሃፊው ቪራጅ አብይሲንጌ ተናግሯል። ሚኒስትሯ ራሳቸውን አግልለው እንዲቆዩና የቅርብ ቤተሰባቸውም እንዲሁ ራሳቸውን እንዲያገሉ ተጠይቀዋል። ሲሪላንካ ለድንገተኛ ጊዜ የሚሆነውን የኦክስፎርዱን አስትራዜኔካ ክትባት ዜጎቿ እንዲከተቡ ፈቃድ ሰጥታለች። የመጀመሪያ ዙር ክትባት በሚቀጥለው ወር ይደርሳል ተብሏል። ፍቱንነቱ ያልተረጋገጠ የኮሮና ተሕዋሲ መከላከያ መጠጥ የአንድ አገር ባለስልጣን ሲያበራታቱ እሳቸው የመጀመሪያ አይደሉም። ባለፈው አመት የማዳጋስካሩ ፕሬዚዳንት አንድሪ ራጆሊና ከዕፅዋት የተቀመመ የኮሮና ተሕዋሲ መከላከያ ተገኝቷል ማለታቸው ከፍተኛ ትችትን እንዲያስተናግዱ አድርገዋቸዋል። በመዲናዋ መጠጡን ሲያከፋፍሉ ታይተዋል። ወረርሽኙ ከተከሰተ በኋላ የአለም መሪዎች፣ ሚኒስትሮችና ባለስልጣናት በቫይረሱ ተይዘዋል። የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፣ የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንና ዶናልድ ትራምፕ በቫይረሱ ተይዘው ማገገማቸው ይታወሳል። | ኮሮናቫይረስ፡ የኮሮና ተሕዋሲ መከላከያ መጠጥን ያበረታቱት የሲሪሊንካ ሚኒስትር በቫይረሱ ተያዙ ከዕፅዋት የተሰራ የኮሮና ተሕዋሲ መከላከያ መጠጥን አገራቸው እድትጠቀም ያበረታቱት የሲሪላንካ የጤና ሚኒስትር በቫይረሱ ተያዙ። የጤና ሚኒስትሯ ፓቪትራ ዋኒያራቺቺ በዚህ ሳምንት በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን የመስሪያ ቤታቸው ሚዲያ ዘርፍ ፀሐፊ ለቢቢሲ አስታውቀዋል። የአገሪቱ የባህል ህክምና አዋቂ ለህይወት ዘመን የሚሆን የኮሮና ተሕዋሲ መከላከያ መጠጥ ማምረታቸውን ተከትሎ ሚኒስትሯም አገራቸው እንድትጠቀም ሲያበረታቱ ነበር። ፓቪትራ ዋኒያራቺቺ የኮሮና ተሕዋሲ መከላከያ መጠጡን በይፋ ሲጠጡም ታይተዋል። ወረርሽኙ ከተከሰተ ጀምሮ በሲሪሊንካ 56 ሺህ 76 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 276 ዜጎቿንም አጥታለች። በቅርብ ወራትም በከፍተኛ ሁኔታ እያገረሸ ነው ተብሏል። የጤና ሚኒስትሯ በኮሮቫይረስ የተያዙ አራተኛ ሚኒስትር ሆነዋል። የኮሮና ተሕዋሲ መከላከያ መጠጡ ማርና ገውዝን ጨምሮ ከሌሎች ንጥረ ነገሮች የተቀመመ ሲሆን ውህዱም በህልም እንደተሰጣቸው የባህል ሃኪሙ ተናግረዋል። የአገሪቱ የጤና ባለሙያዎች የኮሮና ተሕዋሲ መከላከያው ፍቱንነት አልተረጋገጠም ቢሉም በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የባህል ሃኪሙ ወደሚገኝበት መንደር ይጎርፉ ነበር ተብሏል። የጤና ሚኒስትሯ ሁለት የኮቪድ-19 ምርመራ ቢያደርጉም ሁለቱም በቫይረሱ መያዛቸውን እንደሚያሳይ የሚዲያ ፀሃፊው ቪራጅ አብይሲንጌ ተናግሯል። ሚኒስትሯ ራሳቸውን አግልለው እንዲቆዩና የቅርብ ቤተሰባቸውም እንዲሁ ራሳቸውን እንዲያገሉ ተጠይቀዋል። ሲሪላንካ ለድንገተኛ ጊዜ የሚሆነውን የኦክስፎርዱን አስትራዜኔካ ክትባት ዜጎቿ እንዲከተቡ ፈቃድ ሰጥታለች። የመጀመሪያ ዙር ክትባት በሚቀጥለው ወር ይደርሳል ተብሏል። ፍቱንነቱ ያልተረጋገጠ የኮሮና ተሕዋሲ መከላከያ መጠጥ የአንድ አገር ባለስልጣን ሲያበራታቱ እሳቸው የመጀመሪያ አይደሉም። ባለፈው አመት የማዳጋስካሩ ፕሬዚዳንት አንድሪ ራጆሊና ከዕፅዋት የተቀመመ የኮሮና ተሕዋሲ መከላከያ ተገኝቷል ማለታቸው ከፍተኛ ትችትን እንዲያስተናግዱ አድርገዋቸዋል። በመዲናዋ መጠጡን ሲያከፋፍሉ ታይተዋል። ወረርሽኙ ከተከሰተ በኋላ የአለም መሪዎች፣ ሚኒስትሮችና ባለስልጣናት በቫይረሱ ተይዘዋል። የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፣ የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንና ዶናልድ ትራምፕ በቫይረሱ ተይዘው ማገገማቸው ይታወሳል። | https://www.bbc.com/amharic/news-55785136 |
3politics
| ፕሬዝዳንት ባይደን የ6 ትሪሊየን ዶላር ዕቅድ አውጡ | የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የ2022 የበጀት ዕቅዳቸው 6 ትሪሊየን ዶላር እንዲሆን ሲያረቁ፤ በዕቅዱ በዓመቱ ከፌዴራል በጀት ጉድለት ጋር በተያያዘ በየዓመቱ ከአንድ ትሪሊየን ዶላር በላይ ይጨምራል፡፡ ባለፈው ዓመት በዶናልድ ትራምፕ ከቀረበው የ4.8 ትሪሊየን ዶላር ዕቅድ የሚበልጥ ሲሆን የመሰረተ ልማት ማዘመኛ እና የተስፋፋ ማኅበራዊ የደኅንነት መረብን እንደሚያካትት ተስፋ ተደርጓል፡፡ ሐሳቡ ለኮንግረሱ የሚሰጥ ሲሆን እንዲተገበር ድጋፍ ይፈልጋል፡፡ ከጸደቀም አሜሪካን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ወጪዋን ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ከፍ ያደርገዋል፡፡ በጀቱ ፕሬዚዳንቱ ቅድሚያ የሚሰጡትን ነገሮች የሚያሳይ ፍንጭ ይሰጣል፡፡ በዚህም ባይደን ያቀረቡት ሐሳብ ተዛማጅ የሆነ የወጪ ደረጃዎች እና የተስፋፋ መንግሥት ራዕይ እንዳላቸው የሚያንፀባርቅ ነው፡፡ ባይደን በጀቱ "በቀጥታ በአሜሪካ ሕዝብ ላይ የሚውል እና የአገራችንን ኢኮኖሚ የሚያጠናክር እና በረዥም ጊዜም አጠቃላይ ኢኮኖሚውን የሚያሻሽል ነው" ብለዋል፡፡ የፕሬዚዳንት ባይደን ዕቅዶች ለመንገዶች፣ ድልድዮች፣ የብሮድባንድ ኢንተርኔት እና የውሃ ዘርፍ ተጨማሪ ገንዘብን ያካትታሉ፡፡ የአዲሱ የወጪ ጭማሪ በመጪዎቹ 10 ዓመታት ለሦስት እና ለአራት ዓመት ሕጻናት ነጻ የቅድመ ትምህርት ቤት ለማቅረብ 200 ቢሊዮን ዶላር ይመድባል። 109 ቢሊዮን ዶላር ደግሞ ሁሉም አሜሪካውያኖች የሁለት ዓመት ነጻ የኮሚኒቲ ኮሌጅ እንዲያገኙ ያግዛል፡፡ ዴሞክራቱ ፕሬዝዳንት በርካታ የግብር ጭማሪዎችን እና ሌሎች ገቢ ለማሳደግ የሚያስችሉ ዘዴዎችን ቢያቀርቡም ዕቅዱ በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ የብድር ዕዳውን ወደ ከፍተኛ ደረጃ ያሳድገዋል፡፡ በሪፐብሊካኖች ከፍተኛ ነው የተባለለት በጀት በኋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ "ከጊዜ በኋላ በተሻለ የፋይናንስ ደረጃ ላይ ያደርሰናል" ተብሎለታል፡፡ ኮንግረሱ አዳዲስ የወጪ ሒሳቦችን ለማፅደቅ እስከ መስከረም መጨረሻ ድረስ ጊዜ አለው፡፡ አዲሱን በጀት ማሳለፍ ካልቻሉ የመንግሥት ሥራ በከፊል ሊዘጋ ይችላል፡፡ ዴሞክራቶች በምክር ቤቱ ውስጥ ጠባብ የአብላጫ ድምፅ አላቸው። | ፕሬዝዳንት ባይደን የ6 ትሪሊየን ዶላር ዕቅድ አውጡ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የ2022 የበጀት ዕቅዳቸው 6 ትሪሊየን ዶላር እንዲሆን ሲያረቁ፤ በዕቅዱ በዓመቱ ከፌዴራል በጀት ጉድለት ጋር በተያያዘ በየዓመቱ ከአንድ ትሪሊየን ዶላር በላይ ይጨምራል፡፡ ባለፈው ዓመት በዶናልድ ትራምፕ ከቀረበው የ4.8 ትሪሊየን ዶላር ዕቅድ የሚበልጥ ሲሆን የመሰረተ ልማት ማዘመኛ እና የተስፋፋ ማኅበራዊ የደኅንነት መረብን እንደሚያካትት ተስፋ ተደርጓል፡፡ ሐሳቡ ለኮንግረሱ የሚሰጥ ሲሆን እንዲተገበር ድጋፍ ይፈልጋል፡፡ ከጸደቀም አሜሪካን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ወጪዋን ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ከፍ ያደርገዋል፡፡ በጀቱ ፕሬዚዳንቱ ቅድሚያ የሚሰጡትን ነገሮች የሚያሳይ ፍንጭ ይሰጣል፡፡ በዚህም ባይደን ያቀረቡት ሐሳብ ተዛማጅ የሆነ የወጪ ደረጃዎች እና የተስፋፋ መንግሥት ራዕይ እንዳላቸው የሚያንፀባርቅ ነው፡፡ ባይደን በጀቱ "በቀጥታ በአሜሪካ ሕዝብ ላይ የሚውል እና የአገራችንን ኢኮኖሚ የሚያጠናክር እና በረዥም ጊዜም አጠቃላይ ኢኮኖሚውን የሚያሻሽል ነው" ብለዋል፡፡ የፕሬዚዳንት ባይደን ዕቅዶች ለመንገዶች፣ ድልድዮች፣ የብሮድባንድ ኢንተርኔት እና የውሃ ዘርፍ ተጨማሪ ገንዘብን ያካትታሉ፡፡ የአዲሱ የወጪ ጭማሪ በመጪዎቹ 10 ዓመታት ለሦስት እና ለአራት ዓመት ሕጻናት ነጻ የቅድመ ትምህርት ቤት ለማቅረብ 200 ቢሊዮን ዶላር ይመድባል። 109 ቢሊዮን ዶላር ደግሞ ሁሉም አሜሪካውያኖች የሁለት ዓመት ነጻ የኮሚኒቲ ኮሌጅ እንዲያገኙ ያግዛል፡፡ ዴሞክራቱ ፕሬዝዳንት በርካታ የግብር ጭማሪዎችን እና ሌሎች ገቢ ለማሳደግ የሚያስችሉ ዘዴዎችን ቢያቀርቡም ዕቅዱ በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ የብድር ዕዳውን ወደ ከፍተኛ ደረጃ ያሳድገዋል፡፡ በሪፐብሊካኖች ከፍተኛ ነው የተባለለት በጀት በኋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ "ከጊዜ በኋላ በተሻለ የፋይናንስ ደረጃ ላይ ያደርሰናል" ተብሎለታል፡፡ ኮንግረሱ አዳዲስ የወጪ ሒሳቦችን ለማፅደቅ እስከ መስከረም መጨረሻ ድረስ ጊዜ አለው፡፡ አዲሱን በጀት ማሳለፍ ካልቻሉ የመንግሥት ሥራ በከፊል ሊዘጋ ይችላል፡፡ ዴሞክራቶች በምክር ቤቱ ውስጥ ጠባብ የአብላጫ ድምፅ አላቸው። | https://www.bbc.com/amharic/57291564 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ ኩባ የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማምረት የምታደርገው ጥረት ይሳካ ይሆን? | በኩባዋ ዋና ከተማ ሃቫና የሚገኘው ፊንሌይ የክትባት ኢንስቲትዩት ምናልባት ከሌሎች የዓለማችን ማዕከላት አንጻር ሲታይ ያረጀና ጊዜ ያለፈበት ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን በዚህ ማዕከል የሚሰራው የምርምር ሥራ እጅግ ዘመናዊ ነው። የአገሪቱ ከፍተኛ ተመራማሪዎች እረፍት አልባ ረጅም ፈረቃዎችን ጭምር በመስራት ለኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ መፍትሄ ለማግኘት ደፋ ቀና እያሉ ነው። የክትባቱ ስም 'ሶቤሬና 2' የሚባል ሲሆን በኩባ ተመራማሪዎች ኩባ ውስጥ የተሰራ ነው። ይህ ክትባት በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ በጎ ፈቃደኞች ላይ ይሞከራል። ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት ባለፉት ሳምንታት በተደረጉ ክሊኒካዊ ሙከራዎች በጣም አመርቂ የሚባል ውጤት የተመዘገበ ሲሆን ይህ አገሪቱ ክትባቱን ለማግኘት በምታደርገው ጥረት ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የኢንስቲትይቱ ዳይሬክተር ዶክተር ቪሴንቴ ቬሬዝ ቤንኮሞ ገልጸዋል። በኩባ መንግሥት እቅድ መሰረት ክትባቱ ክሊኒካዊ ሙከራውን ከጨረሰ በኋላ በያዝነው የአውሮፓውያኑ ዓመት መጨረሻ አካባቢ ለሁሉም ዜጎች መሰጠት ይጀመራል። "የእኛ እቅድ በመጀመሪያ ሕዝባችንን መከተብ ነው'' ይላሉ ዶክተር ቪሴንቴ። "ከሕዝባችን በኋላ ምናልባት ለሌሎች አገራት መላክ ልንጀምር እንችላለን። ከ2021 መጨረሻ በኋላ ምናልባት 100 ሚሊየን የክትባት ብልቃጦችን አምርተን ሕዝባችን ሙሉ በሙሉ ለመከተብ እቅድ ይዘናል።" ይህ ክትባት የአሜሪካም ሆነ የየትኛውም አገር እርዳታ አልተደረገለትም። ኩባ በባዮቴክኖሎጂ ከ30 ዓመታት በላይ ልምድ ያላት አገር እንደመሆኗ ይህ ምንም የሚገርም ነገር አይደለም። በ1980ዎቹ መጨረሻ አካባቢ የኩባ ሳይንቲስቶች ለማጅራት ገትር ቢ (ሚኒንጃይተስ) ክትባት ካመረቱ የመጀመሪያዎቹ ሲሆኑ የወቅቱ የአገሪቱ መሪ ፊደል ካስትሮ መሰል ሥራዎችን ለማበረታታት ነበር ፊንሌይ የክትባት ኢንስቲትዩት እንዲቋቋም ያደረጉት። በአሜሪካ መድኃኒት አምራች ኩባንያዎች የሚሰሩ መድኃኒቶች ወደ ኩባ እንዳይገቡ ሲደረግ አገሪቱ በራሷ መንገድ መድኃኒቶቹን ማምረት ትችላለች በማለት ፊደል ካስትሮ ይከራከሩ ነበር። ነገር ግን አሁን ባለው ቴክኖሎጂ እና ዘመናዊ አሰራር እንኳን ያለ ሌሎች አገራት ድጋፍና እርዳታ 100 ሚሊዮን የክትባት ብልቃጦችን አምርቶ ሕዝቡን መከተብ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። "ክትባቱን በማምረት ሂደቱ ላይ ግንኙነት የፈጠርነው ከአውሮፓ አገራትና እና ካናዳ ጋር ነው። ከጣልያን እና ፈረንሳይ የመጡ ተመራማሪዎችም በሂደቱ ላይ ይሳተፋሉ" ብለዋል ዶክተር ቪሴንቴ ቬሬዝ። አክለውም "በሚያሳዝን ሁኔታ እስካሁን ድረስ ምንም አይነት የአሜሪካ ተሳትፎ የለም። ምናልባት ወደፊት በመሰል ሂደቶች ላይ ትብብር ሊኖረን እንደሚችል ተስፋ እናደርጋለን" ብለዋል። እንደ ፓን አሜሪካን ሄልዝ ኦርጋናይዜሽን መሰል ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ኩባ ለኮሮረናቫይረስ የሚሆነውን ክትባት በማግኘት የመጀመሪያዋ የላቲን አሜሪካ አገር እንደምትሆን ተስፋ ያደርጋሉ። "ኩባ ክትባቱን እንደምታገኝ ተስፋ እናደርጋለን'' ይላሉ በኩባ የድርጅቱ ተወካይ ዶክተር ሆዜ ሞቫ። ''የሶብሬና 2 ክትባት ሁለተኛ ደረጃ ሙከራ ውጤትን ከሰማን በኋላ ሂደቱን በቅርበት ስንከታተለው ነበር። ካለፈው ዓመት መጨረሻ አካባቢ ጀምሮ ኩባ የክትባቱን ውጤታማነትና ደኅንነት ስትመረምር እንደነበርም እናውቃለን።'' በአሁኑ ጊዜ በክትባቱ ዙሪያ ያለው ጉጉት ትልቅ ነው። በመጀመሪያ አገሪቱ በየቀኑ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ ነው። ወረርሽኙ በጀመረበት የመጀመሪያዎቹ ወራት ውስጥ በየቀኑ ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ እየተያዙ የነበረ ሲሆን ከብራዚልና ሜክሲኮ ጋር ሲነጻጸር ግን ቁጥሩ ብዙም አስፈሪ አይደለም። ነገር ግን የአገሪቱን የጤና ሥርዓት በእጅጉ ፈትኖታል። ባሳለፍነው የአውሮፓውያኑ ዓመት አጋማሽ ላይ ኩባ የወረርሽኙን ስርጭት መግታት ችላ ነበር። በዋነኛነት አየር ማረፊያዎችን በመዝጋትና የማኅበረሰቡን እንቅስቃሴ በመገደብ ነበር ይህንን ማሳካት የቻለችው። ሐምሌ እና ነሐሴ ላይ በጣም ዝቅተኛ የሚባል ስርጭትና ሞት ነበር የተመዘገበው። የፓን አሜሪካን ሄልዝ ኦርጋናይዜሽን ተወካዩ በአሁኑ ጊዜ ያለው የቫይረሱ ስርጭት መቆጣጠር ከማይቻልበት ደረጃ ላይ አልደረሰም ብለው ያስባሉ። ነገር ግን ኩባ ውስጥ በወረርሽኙ ምክንያት በርካታ እንቅስቃሴዎች በመገደባቸው በጣም ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ መላሸቅ አጋጥሟታል። እንደውም ከቀዝቃዛው ጦርነት በኋላ ከፍተኛው የኢኮኖሚ መድቀቅ ነው እየተባለ ነው። ክትባቱ በአገር ውስጥ የሚገኝ ከሆነ ደግሞ ሕዝቡን ከመክተብ ባለፈ ከሽያጭ ሊገኝ የሚችለው ገቢ ኢኮኖሚውን በከፍተኛ ሁኔታ ሊረዳው ይችላል ተብሎ ይታመናል። በተጨማሪም ከትባቱን ከሌሎች አገራት ማስመጣት ሊያስከትለው የሚችለውን ወጪ ይቀንሳል። ኮሮረናቫይረስን ተከትሎ በኩባ በተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት ባለፈው ዓመት ብቻ ኢኮኖሚው 11 በመቶ ኪሳራ አጋጥሞታል። በተጨማሪም የምግብ ሱቆችና ሱፐር ማርኬቶች አካባቢ ከፍተኛ ሰልፍና ግፊያም ታይቷል። በዚህ ወቅት ሁሉም ህጻናት ከትምህርት ቤት ቀርተዋል፣ የንግድ እንቅስቃሴዎች በእጅጉ ተቀዛቅዘዋል፣ የእንቅስቃሴ ገደቦችም ቢሆን የዜጎችን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ አስቸጋሪ አድርጎታል። ስለዚህ የክትባቱ ዜና በርካቶች በጉጉት እንዲጠብቁት አድርጓቸዋል። የዚህ ክትባት ውጤታማ መሆን የዜጎችን ጤንነት ከመጠበቅ ባለፈ ለጎረቤት አገራት ከሚደረገው ሽያጭ የሚገኘው ገቢ ኢኮኖሚውን እንደሚያነቃቃው ይታመናል። | ኮሮናቫይረስ፡ ኩባ የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማምረት የምታደርገው ጥረት ይሳካ ይሆን? በኩባዋ ዋና ከተማ ሃቫና የሚገኘው ፊንሌይ የክትባት ኢንስቲትዩት ምናልባት ከሌሎች የዓለማችን ማዕከላት አንጻር ሲታይ ያረጀና ጊዜ ያለፈበት ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን በዚህ ማዕከል የሚሰራው የምርምር ሥራ እጅግ ዘመናዊ ነው። የአገሪቱ ከፍተኛ ተመራማሪዎች እረፍት አልባ ረጅም ፈረቃዎችን ጭምር በመስራት ለኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ መፍትሄ ለማግኘት ደፋ ቀና እያሉ ነው። የክትባቱ ስም 'ሶቤሬና 2' የሚባል ሲሆን በኩባ ተመራማሪዎች ኩባ ውስጥ የተሰራ ነው። ይህ ክትባት በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ በጎ ፈቃደኞች ላይ ይሞከራል። ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት ባለፉት ሳምንታት በተደረጉ ክሊኒካዊ ሙከራዎች በጣም አመርቂ የሚባል ውጤት የተመዘገበ ሲሆን ይህ አገሪቱ ክትባቱን ለማግኘት በምታደርገው ጥረት ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የኢንስቲትይቱ ዳይሬክተር ዶክተር ቪሴንቴ ቬሬዝ ቤንኮሞ ገልጸዋል። በኩባ መንግሥት እቅድ መሰረት ክትባቱ ክሊኒካዊ ሙከራውን ከጨረሰ በኋላ በያዝነው የአውሮፓውያኑ ዓመት መጨረሻ አካባቢ ለሁሉም ዜጎች መሰጠት ይጀመራል። "የእኛ እቅድ በመጀመሪያ ሕዝባችንን መከተብ ነው'' ይላሉ ዶክተር ቪሴንቴ። "ከሕዝባችን በኋላ ምናልባት ለሌሎች አገራት መላክ ልንጀምር እንችላለን። ከ2021 መጨረሻ በኋላ ምናልባት 100 ሚሊየን የክትባት ብልቃጦችን አምርተን ሕዝባችን ሙሉ በሙሉ ለመከተብ እቅድ ይዘናል።" ይህ ክትባት የአሜሪካም ሆነ የየትኛውም አገር እርዳታ አልተደረገለትም። ኩባ በባዮቴክኖሎጂ ከ30 ዓመታት በላይ ልምድ ያላት አገር እንደመሆኗ ይህ ምንም የሚገርም ነገር አይደለም። በ1980ዎቹ መጨረሻ አካባቢ የኩባ ሳይንቲስቶች ለማጅራት ገትር ቢ (ሚኒንጃይተስ) ክትባት ካመረቱ የመጀመሪያዎቹ ሲሆኑ የወቅቱ የአገሪቱ መሪ ፊደል ካስትሮ መሰል ሥራዎችን ለማበረታታት ነበር ፊንሌይ የክትባት ኢንስቲትዩት እንዲቋቋም ያደረጉት። በአሜሪካ መድኃኒት አምራች ኩባንያዎች የሚሰሩ መድኃኒቶች ወደ ኩባ እንዳይገቡ ሲደረግ አገሪቱ በራሷ መንገድ መድኃኒቶቹን ማምረት ትችላለች በማለት ፊደል ካስትሮ ይከራከሩ ነበር። ነገር ግን አሁን ባለው ቴክኖሎጂ እና ዘመናዊ አሰራር እንኳን ያለ ሌሎች አገራት ድጋፍና እርዳታ 100 ሚሊዮን የክትባት ብልቃጦችን አምርቶ ሕዝቡን መከተብ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። "ክትባቱን በማምረት ሂደቱ ላይ ግንኙነት የፈጠርነው ከአውሮፓ አገራትና እና ካናዳ ጋር ነው። ከጣልያን እና ፈረንሳይ የመጡ ተመራማሪዎችም በሂደቱ ላይ ይሳተፋሉ" ብለዋል ዶክተር ቪሴንቴ ቬሬዝ። አክለውም "በሚያሳዝን ሁኔታ እስካሁን ድረስ ምንም አይነት የአሜሪካ ተሳትፎ የለም። ምናልባት ወደፊት በመሰል ሂደቶች ላይ ትብብር ሊኖረን እንደሚችል ተስፋ እናደርጋለን" ብለዋል። እንደ ፓን አሜሪካን ሄልዝ ኦርጋናይዜሽን መሰል ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ኩባ ለኮሮረናቫይረስ የሚሆነውን ክትባት በማግኘት የመጀመሪያዋ የላቲን አሜሪካ አገር እንደምትሆን ተስፋ ያደርጋሉ። "ኩባ ክትባቱን እንደምታገኝ ተስፋ እናደርጋለን'' ይላሉ በኩባ የድርጅቱ ተወካይ ዶክተር ሆዜ ሞቫ። ''የሶብሬና 2 ክትባት ሁለተኛ ደረጃ ሙከራ ውጤትን ከሰማን በኋላ ሂደቱን በቅርበት ስንከታተለው ነበር። ካለፈው ዓመት መጨረሻ አካባቢ ጀምሮ ኩባ የክትባቱን ውጤታማነትና ደኅንነት ስትመረምር እንደነበርም እናውቃለን።'' በአሁኑ ጊዜ በክትባቱ ዙሪያ ያለው ጉጉት ትልቅ ነው። በመጀመሪያ አገሪቱ በየቀኑ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ ነው። ወረርሽኙ በጀመረበት የመጀመሪያዎቹ ወራት ውስጥ በየቀኑ ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ እየተያዙ የነበረ ሲሆን ከብራዚልና ሜክሲኮ ጋር ሲነጻጸር ግን ቁጥሩ ብዙም አስፈሪ አይደለም። ነገር ግን የአገሪቱን የጤና ሥርዓት በእጅጉ ፈትኖታል። ባሳለፍነው የአውሮፓውያኑ ዓመት አጋማሽ ላይ ኩባ የወረርሽኙን ስርጭት መግታት ችላ ነበር። በዋነኛነት አየር ማረፊያዎችን በመዝጋትና የማኅበረሰቡን እንቅስቃሴ በመገደብ ነበር ይህንን ማሳካት የቻለችው። ሐምሌ እና ነሐሴ ላይ በጣም ዝቅተኛ የሚባል ስርጭትና ሞት ነበር የተመዘገበው። የፓን አሜሪካን ሄልዝ ኦርጋናይዜሽን ተወካዩ በአሁኑ ጊዜ ያለው የቫይረሱ ስርጭት መቆጣጠር ከማይቻልበት ደረጃ ላይ አልደረሰም ብለው ያስባሉ። ነገር ግን ኩባ ውስጥ በወረርሽኙ ምክንያት በርካታ እንቅስቃሴዎች በመገደባቸው በጣም ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ መላሸቅ አጋጥሟታል። እንደውም ከቀዝቃዛው ጦርነት በኋላ ከፍተኛው የኢኮኖሚ መድቀቅ ነው እየተባለ ነው። ክትባቱ በአገር ውስጥ የሚገኝ ከሆነ ደግሞ ሕዝቡን ከመክተብ ባለፈ ከሽያጭ ሊገኝ የሚችለው ገቢ ኢኮኖሚውን በከፍተኛ ሁኔታ ሊረዳው ይችላል ተብሎ ይታመናል። በተጨማሪም ከትባቱን ከሌሎች አገራት ማስመጣት ሊያስከትለው የሚችለውን ወጪ ይቀንሳል። ኮሮረናቫይረስን ተከትሎ በኩባ በተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት ባለፈው ዓመት ብቻ ኢኮኖሚው 11 በመቶ ኪሳራ አጋጥሞታል። በተጨማሪም የምግብ ሱቆችና ሱፐር ማርኬቶች አካባቢ ከፍተኛ ሰልፍና ግፊያም ታይቷል። በዚህ ወቅት ሁሉም ህጻናት ከትምህርት ቤት ቀርተዋል፣ የንግድ እንቅስቃሴዎች በእጅጉ ተቀዛቅዘዋል፣ የእንቅስቃሴ ገደቦችም ቢሆን የዜጎችን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ አስቸጋሪ አድርጎታል። ስለዚህ የክትባቱ ዜና በርካቶች በጉጉት እንዲጠብቁት አድርጓቸዋል። የዚህ ክትባት ውጤታማ መሆን የዜጎችን ጤንነት ከመጠበቅ ባለፈ ለጎረቤት አገራት ከሚደረገው ሽያጭ የሚገኘው ገቢ ኢኮኖሚውን እንደሚያነቃቃው ይታመናል። | https://www.bbc.com/amharic/news-56088539 |
5sports
| ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በፓራሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ በትዕግስት ገዛኸኝ አገኘች | ትዕግስት ገዛኸኝ በፓራሊምፒክ ውድድር ላይ ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ በማግኘት ታሪክ አስመዘገበች። ይህ በአትሌት ትዕግስት የተገኘው የወርቅ ሜዳሊያ በኢትዮጵያ የፓራሊምፒክ ተሳትፎ ታሪክ ውስጥ አገሪቱ ያገኘችው የመጀመሪያው የወርቅ ሜዳልያ ነው። በጃፓን፣ ቶኪዮ እየተካሄደ ባለው የፓራሊምፒክ ውድድር ላይ በአንድ ሺህ አምስት መቶ ሜትር የሩጫ ውድድር ላይ አንደኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የመጀመሪያው የወርቅ ሜዳሊያ ተመዝግቧል። በዚህ ውድድር ከትዕግስት በመከተል አሜሪካዊት አትሌት ሁለተኛ እንዲሁም ከአፍሪካ ቱኒዚያዊት ደግሞ በሦስተኛነት አጠናቀዋል። በዘንድሮው ፓራሊምፒክ ላይ ኢትዮጵያን በመወከል ሦስት አትሌቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ። ባለፈው ማክሰኞ ነሐሴ 18/2013 ዓ.ም በተጀመረው በዚህ ውድድር ኢትዮጵያ በትዕግስት ገዛኽኝ ባገኘችው የወርቅ አማካይነት በሜዳሊያ ሰንጠረዡ ላይ ከተወዳዳሪ አገራት መካከል የ35ኛ ደረጃን ለጊዜው ይዛለች። በዚህም በቶኪዮው የፓራሊምፒክ ውድድር ላይ ከሚሳተፉ የአፍሪካ አገራት ከደቡብ አፍሪካ፣ ከአልጄሪያ፣ ከቱኒዚያ እና ከናይጄሪያ በመቀጠል አምስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በፓራሊምፒክ የተሳተፈችው እስራኤል፣ ቴል አቪቭ ውስጥ እ.አ.አ በ1968 በተካሄደው ውድድር ላይ ነበር። በ2012 በተካሄደው ፓራሊምፒክ ላይ አትሌት ወንድዬ ፍቅሬ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የብር ሜዳልያ አስመዝግቦ ነበር። ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የብር ሜዳልያ ያገኘችው በ2016 በሪዮ ደ ጄኔሮ የወንዶች 1500 ሜትር ሩጫ በአትሌት ታምሩ ደምሴ አማካይነት ነው። የቶኪዮ ኦሊምፒክን ጨምሮ ኢትዮጵያ በፓራሊምፒክ ውድድር እስካሁን ስምንት አትሌቶችን አሳትፋለች። ዛሬ ትዕግስት ገዛኸኝ ያስመዘገበችው የወርቅ ሜዳልያ በፓራሊምፒክ ታሪክ ለኢትዮጵያ ትልቁና ቀዳሚው ውጤት ነው። ማክሰኞ ነሐሴ 18/2013 ዓ.ም የተጀመረው የቶኪዮ ፓራሊምፒክ ውድድር ለ13 ቀናት ይካሄዳል። ኢትዮጵያን በፓራሊምፒክ ውድድር የሚወክሉት አትሌት ታምሩ ከፍያለው፣ አትሌት ገመቹ አመኑ እና አትሌት ትዕግስት ገዛኸኝ ናቸው። ቱኒዚያ ላይ በ1500 ሜትር በተደረገው የማጣሪያ ውድድር አትሌት ትዕግስት ገዛኸኝ 4:31:53 በመግባት አንደኛ በመሆን ማጠናቀቋ ይታወሳል። | ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በፓራሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ በትዕግስት ገዛኸኝ አገኘች ትዕግስት ገዛኸኝ በፓራሊምፒክ ውድድር ላይ ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ በማግኘት ታሪክ አስመዘገበች። ይህ በአትሌት ትዕግስት የተገኘው የወርቅ ሜዳሊያ በኢትዮጵያ የፓራሊምፒክ ተሳትፎ ታሪክ ውስጥ አገሪቱ ያገኘችው የመጀመሪያው የወርቅ ሜዳልያ ነው። በጃፓን፣ ቶኪዮ እየተካሄደ ባለው የፓራሊምፒክ ውድድር ላይ በአንድ ሺህ አምስት መቶ ሜትር የሩጫ ውድድር ላይ አንደኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የመጀመሪያው የወርቅ ሜዳሊያ ተመዝግቧል። በዚህ ውድድር ከትዕግስት በመከተል አሜሪካዊት አትሌት ሁለተኛ እንዲሁም ከአፍሪካ ቱኒዚያዊት ደግሞ በሦስተኛነት አጠናቀዋል። በዘንድሮው ፓራሊምፒክ ላይ ኢትዮጵያን በመወከል ሦስት አትሌቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ። ባለፈው ማክሰኞ ነሐሴ 18/2013 ዓ.ም በተጀመረው በዚህ ውድድር ኢትዮጵያ በትዕግስት ገዛኽኝ ባገኘችው የወርቅ አማካይነት በሜዳሊያ ሰንጠረዡ ላይ ከተወዳዳሪ አገራት መካከል የ35ኛ ደረጃን ለጊዜው ይዛለች። በዚህም በቶኪዮው የፓራሊምፒክ ውድድር ላይ ከሚሳተፉ የአፍሪካ አገራት ከደቡብ አፍሪካ፣ ከአልጄሪያ፣ ከቱኒዚያ እና ከናይጄሪያ በመቀጠል አምስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በፓራሊምፒክ የተሳተፈችው እስራኤል፣ ቴል አቪቭ ውስጥ እ.አ.አ በ1968 በተካሄደው ውድድር ላይ ነበር። በ2012 በተካሄደው ፓራሊምፒክ ላይ አትሌት ወንድዬ ፍቅሬ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የብር ሜዳልያ አስመዝግቦ ነበር። ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የብር ሜዳልያ ያገኘችው በ2016 በሪዮ ደ ጄኔሮ የወንዶች 1500 ሜትር ሩጫ በአትሌት ታምሩ ደምሴ አማካይነት ነው። የቶኪዮ ኦሊምፒክን ጨምሮ ኢትዮጵያ በፓራሊምፒክ ውድድር እስካሁን ስምንት አትሌቶችን አሳትፋለች። ዛሬ ትዕግስት ገዛኸኝ ያስመዘገበችው የወርቅ ሜዳልያ በፓራሊምፒክ ታሪክ ለኢትዮጵያ ትልቁና ቀዳሚው ውጤት ነው። ማክሰኞ ነሐሴ 18/2013 ዓ.ም የተጀመረው የቶኪዮ ፓራሊምፒክ ውድድር ለ13 ቀናት ይካሄዳል። ኢትዮጵያን በፓራሊምፒክ ውድድር የሚወክሉት አትሌት ታምሩ ከፍያለው፣ አትሌት ገመቹ አመኑ እና አትሌት ትዕግስት ገዛኸኝ ናቸው። ቱኒዚያ ላይ በ1500 ሜትር በተደረገው የማጣሪያ ውድድር አትሌት ትዕግስት ገዛኸኝ 4:31:53 በመግባት አንደኛ በመሆን ማጠናቀቋ ይታወሳል። | https://www.bbc.com/amharic/58366879 |
0business
| ሩሲያ ቢትኮይንን ለውጭ ንግድ ግብይት ለመቀበል እያሰበች መሆኑ ተነገረ | ሩሲያ ወደ ውጭ አገራት ለምትልካቸው የነዳጅ ዘይትና ጋዝ ምርቶች ክፍያዎችን በቢትኮይን ለመቀበል እያሰበች መሆኑን አንድ የአገሪቱ ከፍተኛ የሕግ አውጪ ምክር ቤት አባል ገለጹ። ፓቬል ዛቫልኒይ እንዳሉት የሩሲያን የኃይል ምርቶች የሚገዙ "ወዳጅ" አገራት ክፍያቸውን በክሪፕቶከተንሲ ወይም በራሳቸው የመገበያያ ገንዘብ እንዲከፍሉ ሊፈቀድላቸው ይችላል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን "ወዳጅ ያለሆኑ" አገራት የአገራቸውን የጋዝ ምርት ሲገዙ በሩሲያ ገንዘብ (ሩብል) እንዲከፍሉ ለማድረግ እንደሚፈልጉ ገልጸው ነበር። ይህ እርምጃቸውም በዚህ የፈረንጆች ዓመት ብቻ ከ20 በመቶ በላይ ዋጋውን ያጣውን ሩብል ጥንካሬ ለመመለስ እንደሆነ ተገምቷል። በዚህም ሩብል በከፍተኛ ሁኔታ ማንሰራራት አሳይቷል። ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወረራ መፈጸሟን ተከትሎ በዩናይትድ ኪንግደም፣ በአሜሪካ እና በአውሮፓ ሕብረት የተጣሉባት ማዕቀቦች በአገሪቱ የመገበያያ ገንዘብ ላይ ጫናን የፈጠረ ሲሆን የኑሮ ውድነትንም አንሮታል። ነገር ግን አሁንም ቢሆን ሩሲያ ለዓለም ገበያ ከፍተኛ መጠን ያለው የተፈጥሮ ጋዝን በማቅረብ ቀዳሚ ስትሆን በነዳጅ ዘይትም ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። በሩሲያ ምክር ቤት ዱማ ውስጥ የኢነርጂ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ፓቬል ዛቫልኒይ እንዳሉት፣ አገራቸው ወደ ውጪ ለምትልካቸው የነዳጅና የጋዝ ምርቶች መገበያያ አማራጭ የክፍያ መንገዶችን እያፈላለገች እንደሆነ አመልክተዋል። ጨምረውም ቻይናና ቱርክ በሩሲያ ላይ እየተደረገ ባለው "የማዕቀቦች ጫና ውስጥ ያልተሳተፉ ወዳጅ" አገራት ናቸው በማለት ጠቅሰዋል። "ለረጅም ጊዜ ከቻይና ጋር የሚደረገውን የንግድ ልውውጥ በየአገሮቻችን መገበያያ ገንዘብ በሩብል እና በዩዋን እንድናደርገው ሃሳብ ስናቀርብ ቆይተናል" ያሉት ዛቫልኒይ "ከቱርክ ጋር በሊራ የምንገበያይ ይሆናል" ብለዋል። ባለሥልጣኑ ጨምረውም ከአገራቱ የመገበያያ ገንዘብ በተጨማሪ "በቢትኮይንም መገበያየት ይቻላል" ብለዋል። ተንታኞች እንደሚሉት ግን አደጋዎች ሊኖሩት ቢችሉም ሩሲያ በታዋቂ ክሪፕቶከረንሲዎች መገበያየት ከጀመረች ተጠቃሚ ልትሆን ትችላለች። ነገር ግን ከተለመዱት የግብይት ገንዘቦች በተቃራኒ የቢትኮይን ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ተለዋዋጭ በመሆኑ የራሱ የሆነ አደጋን ሊያስከትል እንደሚችል በኢነርጂው ዘርፍ ባለሙያ የሆኑት ዴቪድ ብሮድስቶክ ይናገራሉ። የሩሲያ ከበርቴዎች በምዕራባውያን የሚጣሉ ማዕቀቦችን ለማምለጥ ሲሉ እነዚህ ክሪፕቶከረንሲዎች ሊጠቀሙ ይችላሉ በሚል የዩክሬን፣ የአሜሪካና የአውሮፓ ፖለቲከኞች የክሪፕቶከረንሲ የመገበያያ መድረኮች የሩሲያ ተጠቃሚዎችን እንዲያግዱ ጠይቀዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ ይህንን ጥያቄ ውድቅ አድርገውታል። | ሩሲያ ቢትኮይንን ለውጭ ንግድ ግብይት ለመቀበል እያሰበች መሆኑ ተነገረ ሩሲያ ወደ ውጭ አገራት ለምትልካቸው የነዳጅ ዘይትና ጋዝ ምርቶች ክፍያዎችን በቢትኮይን ለመቀበል እያሰበች መሆኑን አንድ የአገሪቱ ከፍተኛ የሕግ አውጪ ምክር ቤት አባል ገለጹ። ፓቬል ዛቫልኒይ እንዳሉት የሩሲያን የኃይል ምርቶች የሚገዙ "ወዳጅ" አገራት ክፍያቸውን በክሪፕቶከተንሲ ወይም በራሳቸው የመገበያያ ገንዘብ እንዲከፍሉ ሊፈቀድላቸው ይችላል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን "ወዳጅ ያለሆኑ" አገራት የአገራቸውን የጋዝ ምርት ሲገዙ በሩሲያ ገንዘብ (ሩብል) እንዲከፍሉ ለማድረግ እንደሚፈልጉ ገልጸው ነበር። ይህ እርምጃቸውም በዚህ የፈረንጆች ዓመት ብቻ ከ20 በመቶ በላይ ዋጋውን ያጣውን ሩብል ጥንካሬ ለመመለስ እንደሆነ ተገምቷል። በዚህም ሩብል በከፍተኛ ሁኔታ ማንሰራራት አሳይቷል። ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወረራ መፈጸሟን ተከትሎ በዩናይትድ ኪንግደም፣ በአሜሪካ እና በአውሮፓ ሕብረት የተጣሉባት ማዕቀቦች በአገሪቱ የመገበያያ ገንዘብ ላይ ጫናን የፈጠረ ሲሆን የኑሮ ውድነትንም አንሮታል። ነገር ግን አሁንም ቢሆን ሩሲያ ለዓለም ገበያ ከፍተኛ መጠን ያለው የተፈጥሮ ጋዝን በማቅረብ ቀዳሚ ስትሆን በነዳጅ ዘይትም ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። በሩሲያ ምክር ቤት ዱማ ውስጥ የኢነርጂ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ፓቬል ዛቫልኒይ እንዳሉት፣ አገራቸው ወደ ውጪ ለምትልካቸው የነዳጅና የጋዝ ምርቶች መገበያያ አማራጭ የክፍያ መንገዶችን እያፈላለገች እንደሆነ አመልክተዋል። ጨምረውም ቻይናና ቱርክ በሩሲያ ላይ እየተደረገ ባለው "የማዕቀቦች ጫና ውስጥ ያልተሳተፉ ወዳጅ" አገራት ናቸው በማለት ጠቅሰዋል። "ለረጅም ጊዜ ከቻይና ጋር የሚደረገውን የንግድ ልውውጥ በየአገሮቻችን መገበያያ ገንዘብ በሩብል እና በዩዋን እንድናደርገው ሃሳብ ስናቀርብ ቆይተናል" ያሉት ዛቫልኒይ "ከቱርክ ጋር በሊራ የምንገበያይ ይሆናል" ብለዋል። ባለሥልጣኑ ጨምረውም ከአገራቱ የመገበያያ ገንዘብ በተጨማሪ "በቢትኮይንም መገበያየት ይቻላል" ብለዋል። ተንታኞች እንደሚሉት ግን አደጋዎች ሊኖሩት ቢችሉም ሩሲያ በታዋቂ ክሪፕቶከረንሲዎች መገበያየት ከጀመረች ተጠቃሚ ልትሆን ትችላለች። ነገር ግን ከተለመዱት የግብይት ገንዘቦች በተቃራኒ የቢትኮይን ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ተለዋዋጭ በመሆኑ የራሱ የሆነ አደጋን ሊያስከትል እንደሚችል በኢነርጂው ዘርፍ ባለሙያ የሆኑት ዴቪድ ብሮድስቶክ ይናገራሉ። የሩሲያ ከበርቴዎች በምዕራባውያን የሚጣሉ ማዕቀቦችን ለማምለጥ ሲሉ እነዚህ ክሪፕቶከረንሲዎች ሊጠቀሙ ይችላሉ በሚል የዩክሬን፣ የአሜሪካና የአውሮፓ ፖለቲከኞች የክሪፕቶከረንሲ የመገበያያ መድረኮች የሩሲያ ተጠቃሚዎችን እንዲያግዱ ጠይቀዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ ይህንን ጥያቄ ውድቅ አድርገውታል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60871774 |
0business
| ከ20 ሺህ ብር በላይ የሚወጣበት የኢትዮጵያ ዘመናዊ የንቅሳት ገበያ | ሰውነታቸው ላይ ንቅሳት ለማሳረፍ ወደ ንቅሳት ቤቶች ጎራ ከሚሉ ሰዎች መካከል በፍቅር ወይም በትዳር የተጣመሩ ጥንዶች ይገኙበታል። "ጥንዶቹ ፍቅራቸውን ለመግለጽ ሴቷ የወንዱን፣ ወንዱ ደግሞ የሴቷን ስም አሊያም የስም መጀመሪያ ፊደላትን መነቀስ የተለመደ ሆኗል" ይላል የንቅሳት ባለሙያው (ታቱ አርቲስት) ሔኖክ ጥላሁን። ሆኖም በጥንዶቹ መካከል ንፋስ ገብቶ መራራቅ ሲመጣ "ለየብቻ ይመጡና ንቅሳቱን ቀይርልኝ" ብለው እንደሚጠይቁት ይናገራል። ይህንን በመሰሉ አጋጣሚዎች የተሞላውን የንቅሳት ሥራ፤ ሰዎች ሐሳባቸውን ለማንጸባረቅ ያውሉታል። ዮሴፍ ተስፍዬ ይባላል። 28 ሺህ ብር አውጥቶ በሁለቱም እጆቹ ከትከሻው እስከ መዳፉ አንጓ 'የውስጤን ሐሳብ ይገልጹልኛል' ያላቸውን የተለያዩ ምስሎችና ጽሁፎች ተነቅሷል። ለእሱ የደስታ ምንጭ የሆነው ንቅሳቱ በተመልካቾች ዘንድ ሁለት ዓይነት አስተያየት ይቀርብበታል። አንዱ "ምን ነካህ?" ሲሆን ሌላኛው ደግሞ "ያምራል" የሚል ነው ይላል። ነገር ግን በሚሠራበት አካባቢ ንቅሳቱ እንዳይታይ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያደርግም ይናገራል። ሳምራዊት ተስፋዬ እና ኤልኤዘር ሙሴም በተመሳሳይ መነሻ የተለያዩ የሰውነት ክፍላቸውን ተነቅሰዋል። ለመሆኑ በአዲስ አበባ ምን አይነት ንቅሳቶች ይዘወተራሉ? ምን ያህል ገንዘብስ ይወጣባቸዋል? የንቅሳቶች ይዘት እና ምክንያት የንቅሳት ባለሙያው ሔኖክ ጥላሁን ቀደም ሲል ሥዕሎችን ይስል እንደነበር ይናገራል። እንደ ባለሙያው ገለጻ ንቅሳትም አንድ የጥበብ ዘርፍ በመሆኑ 'ሄና ታቱ' የሚል ድርጅት በመክፈት ንቅሳትን መተዳዳሪያው ካደረገ ከስምንት ዓመታት በላይ ተቆጥሯል። ንቅሳት የሚፈልጉ ሰዎች ከተዘጋጀ የንቅሳት ዝርዝር ውስጥ መርጠው ወይም የፈለጉትን ማንኛውንም አይነት ምስል አሊያም ጹሁፍን ወደ ንቅሳት መቀየር ይቻላል ይላል። በብዛት ወደ እሱ የሚመጡ ሰዎች ሰውነታቸው ላይ እንዲያርፍ የሚርጡት ይዘት ሐይማኖታዊ መሆኑን ይናገራል። በተጨማሪም ጥንዶች ፍቅራቸውን ለመግለጽ ተመሳሳይ ንቅሳት ወይም አንዱ የሌላውን ስም ይነቀሳሉ። የእናታቸውን ወይም የአባታቸውን ምስል ወይም ስም የተነቀሱ ደንበኞች እንዳሉት የሚጠቅሰው ሔኖክ፤ በሌላ በኩል መስቀል፣ የቅዱሳን ሥዕሎችና መሰል ሐይማኖታዊ ይዘቶች በብዛት እንደሚዘወተሩ ያስረዳል። ብዙዎች ንቅሳትን "የሚወዱትን ነገር መግለጫና ማሳያ አድርገው ነው የሚያዩት" ሲል ይጠቅሳል። ሳምራዊት የግራ እጇ ከክንዷ በታች ያለው ክፍል ሙሉ በሙሉ በንቅሳት የተሸፈነ ነው። "ስለ ወደደኝ አዳነኝ" እና "Be Happy" የሚሉ ጽሁፎች፣ ሳቅን የሚገልጽ የስሜት ነጸብራቅ ምስል (emoji)፣ አበባ እንዲሁም ሌሎች ምስሎች አሉ። ደረቷ ላይ "blessed" የሚል ጽሁፍና አንገቷ ላይ ደግሞ መስቀል ተነቅሳለች። ኤልዜር የደረቱ አብዛኛው ክፍል ንቅሳት ያረፈበት ሲሆን፤ የነብርና ንስር ምስሎችን ነው የተነቀሰው። ዮሴፍ ደግሞ ሰዓት፣ አበባ፣ ኮምፓስና መሰል ምስሎችን በቀይና ጥቁር ቀለሞች በእጆቹ ላይ ተነቅሷል። ሳምራዊት ለሐይማኖቷ ያላትን ፍቅር ለመግለጽና ውስጧ ያለውን የተለያየ ሰሜት ለማንጸባረቅ እንደተነቀሰች ትገልጻለች። ዮሴፍ እና ኤልኤዘር ውስጣቸው የሚያምንበትና የሚወዱት ሐሳብ ሰውነታቸው ላይ እንዲታይ በማለም ነው አካላቸውን በንቅሳት የሸፈኑት። በተለይ ኤልኤዘር ለቤተሰቦቹ ያለውን ፍቅር ለመግለጽ መነቀሱን ተናግሯል። እነ ሳምራዊት በጠቀሷቸው ምክንያቶች ይነቀሱ እንጂ ሰውነታቸው ላይ ያለ ጠባሳን ለመሸፈን ወይም ባህላዊ ንቅሳቶችን ወደ ዘመነኛ ለመቀየር ወደ ንቅሳት ቤቶች የሚያመሩ ሰዎች እንዳሉም ሔኖክ ይገልጻል። የንቅሳት ገበያ ኤልኤዘር ንቅሳቱን በተለያየ ጊዜ ማድረጉን ያስረዳል። ለዚህም እስከ 20 ሺህ ብር አውጥቷል። ሳምራዊት ደግሞ 15 ሺህ ብር በመክፈል ነው ንቅሳቷን ያሠራችው። ዝቅተኛው የንቅሳት ርዝመት አምስት ወይም ስድስት ሴንቲ ሜትር እንደሚረዝምና 500 ብር እንደሚያስወጣ ሔኖክ ይገልጻል። ንቅሳቱ ከፍ እያለ ሲሄድ ዋጋ እንደሚጨምር እንዲሁም ጀርባ ላይ የሚሠሩ ንቅሳቶች በአንድ ጊዜ እንደማያልቁና እስከ ሦስት ቀናት ሊፈጁ እንደሚችሉ ተናግሯል። ይህም እስከ 15 ሺህ ብር የሚወጣበት ነው። ታዲያ ይህ ሥራ ዋና የገቢ ምንጬ ነው የሚለው ሔኖክ "በየቀኑ ሥራ አለ" ሲል አስረድቷል። ንቅሳት ለመሥራት የሚውሉ መሣሪያዎች ከዘመኑ ጋር እየተጓዙ ነው የሚለው የንቅሳት ባለሙያው፤ ግብዓቶችን አገር ውስጥ ማግኘት ግን ፈታኝ መሆኑን እና የንቅሳት መርፌ ሳይቀር ከውጪ አገራት እንደሚገባ ይገልጻል። "ንቅሳት ላይ ከቴክኖሎጂው በላይ የአርቲስቱ ጉዳይ [የባለሙያው አቅም] ነው ትልቁ ነገር" ሲልም ጨምሯል። የተመልካቾች አስተያየት እና ልዩ ገጠመኞች ዮሴፍ ንቅሳቴን ሲያዩ "የሚያማትቡ አሉ" ይላል። ኤልኤዘር ደግሞ "አንዳንድ ሰው የሚያየኝ እንደ ዱርዬ ነው። ባንክ ስገባ አንዳንድ ሰዎች ቦርሳቸውን የሚደብቁበት ጊዜ አለ" ሲል ገልጾታል። "ሁሉም ሰው አንድ አይደለም። ወጣቶቹ ይወዱታል። 'በጣም ያምራል' ይላሉ። ሌላው ደግሞ 'ኔጌቲቭ' አስተያየት ነው የሚሰጠው። 'ለምን እንዲህ አደርግሽ?' 'በሐይማኖት አይፈቀድም' ይላሉ" ያለችው ደግሞ ሳምራዊት ናት። የንቅሳት ባለሙያው ሔኖክም በሥራው ብዙ ነገሮች እንደሚገጥሙት ይገልጻል። ፍቅረኞች ወይም ባለትዳሮች ፍቅራቸውን 'ለማጠንከር' በማሰብ ለመነቀስ ወደኛ ይመጣሉ የሚለው ሔሄኖክ፤ ከተሠራላቸው በኋላ ግን ተመልሰው የሚመጡ እንዳሉ ጠቅሷል። "ይመጡና ይሄን ነገር አልፈለኩትም። የዚያን ጊዜ በደንብ አላሰብኩበትም። ይሄን ነገር ማጥፋት እፈልጋለሁ ይላሉ። ያው ማጥፋት ከባድ ስለሆነ በሌላ ዲዛይን ይሸፈናል።" በሌላ በኩል ፊታቸው ላይ ንቅሳት ለማሠራት መጥተው እድሜያቸው ትንሽ ከሆነ "በኋላ እንዳይጸጽታቸው" ብለን እንመክራለንም ብሏል። "አንዳንዴ ሰዎች ንቅሳተቱን ሳይጨርሱ የሚሄዱበት አጋጣሚ አለ - አመመኝ በሚል" ሲልም ተናግሯል። አንዱን አጋጣሚ ሲያስታውስ፤ አንድ ደንበኛው "የቅዱስ ሚካኤልን ምስል ጀርባው ላይ ለመነቀስ መረጠ" ይላል። እናም ንቅሳቱ ተጀመረ። "ሥዕሉ መልአኩ ሰይጣኑን ሲረግጥ የሚያሳየው ነው። እኛ ከሥር እየሠራን ነው ወደ ላይ የምንሄደው። ሰይጣኑን ወደ ማገባደድ ደርሰን ወደ ላይ እየወጣን ስንሄድ 'በቃ አልቻልኩም ይቅርብኝ' አለ። ለመጨረስ በተከታታይ ብደውልለትም አልመጣም። እስካሁን ሰይጣኑን ይዞ ነው የሚዞረው" ሲል ያስታውሳል። ንቅሳቱ ሲሠራ በሚፈጠረው ህመም ምክንያት ንቅሳት ጀምረው ከሚያቋርጡ በተቃራኒው የንቅሳቱ መሣሪያ በሚፈጥው መጠነኛ ህመም 'እንደሚደሰት' ዮሴፍ አስረድቷል። ኤልኤዘር ደግሞ "አንድ ጊዜ ፀበል ለጠመቅ ሄጄ ቄሱ አልጠምቅህም ብለውኝ ነበር [ንቅሳቱን አይተው]" ብሏል። በሌላ በኩል ዮሴፍ "ሰዎች እንደ ቁም ነገረኛ ስለማይቆጥሩኝ፤ ሥራ ቦታ 'ታቱ' እንዳለኝ የማያውቅ ብዙ ሰው አለ" ሲል ገልጿል። ሳምራዊት በመነቀሷ ከቤተሰቧ አሉታዊ አስተያየት እንዳልገጠማትና እንዲያውም ስትነቀስ 15 ሺህ ብሩን ቤተሰቧ እንደከፈለላት ስትናገር፤ ከዚህ በተቃራኒ ኤልኤዘርና ዮሴፍ ቤተሰቦቻቸው ብዙም በአወንታዊ መንገድ አልተቀበሏቸውም። ንቅሳት እና ጤና የቆዳና የአባላዘር በሽታዎች ስፔሻሊስት ሐኪሙ ዶክተር ድጋፌ ጸጋዬ "ዘመናዊም ይሁን ባህላዊ ንቅሳት ሹል በሆኑ ነገሮች እየወጉ ቀለምን ቆዳ ውስጥ በመጨመር ጌጦችን የመፍጠር ልምድ ነው ብለን ልንገልጸው እንችላለን" ሲሉ ያስረዳሉ። ታዲያ ይህ ልምድ ከጤና አኳያ ሊታዩ የሚችሉ ጉዳዮች አሉትም ብለዋል። እንደ ዶ/ር ድጋፌ ገለጻ፤ ንቅሳት ቋሚ ሲሆን ሰዎች ግን ቀድመው ለንቅሳት የተነሱበት ፍላጎትና ስሜት በጊዜ ብዛት ሊቀየር ይችላል። በዚህም ምክንያት የተነቀሱ ሰዎች ከ40 ዓመታቸው በኋላ የሚጸጸቱበት አጋጣሚ ሊፈጠር ይችላል። በሌላ በኩል "ንቅሳት ያለበት ሰው ደም እንዲሰጥ አይመከርም" ያሉት ሀኪሙ፤ ለዚህም ምክንያቱ የንቅሳት መሣሪያዎች ለተላላፊ በሽታ ስለሚያጋልጡ ነው ብለዋል። ንቅሳት የቆዳ መቆጣት [allergic reactions] ሊፈጥር እንደሚችል ዶ/ር ድጋፌ ጠቅሰዋል። "የሰውነት አለርጂው ከብዙ ጊዜ በኋላ ይመጣል። ከተነቀሱ ከሳምንታት ብሎም ከ10 ወይም ከ15 ዓመታት በኋላ የቆዳ መቆጣት፣ የማሳከክ ወይም የማበጥ ስሜትን ሊያመጣ ይችላል" ብለዋል። ንቅሳት የሚደረግበት ስፍራና የመሣሪያው ንጽህና ካልተጠበቀ ለተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች ሊዳርግም ይችላል። "ንቅሳት ያደረገ ሰው ኤምአርአይ የሚባለውን ምርመራ ማድረግ ቢፈልግ እንደ ንቅሳቱ አይነትና የቀለም አይነት ንቅሳቱ ባለት ቦታ ላይ የቃጠሎ ቁስል ሊያጋጥም ይችላል" ሲሉም ያክላሉ። ቋሚ ንቅሳት መጥፋት ይችላል? አዎ መጥፋት ይችላል። "አብዛኛውን ንቅሳት በሌዘር [በጨረር] ማሽን ማጥፋት የሚቻልበት ዕድል አለ" ሲሉ ገልጸዋል - ዶ/ር ድጋፌ። ሕክምናው የብርሃንን ኃይል ወደ ሙቀት በመቀየር የሚሠራ መሆኑን የሚስረዱት ሐኪሙ፤ ጨረሩ ቆዳው ውስጥ ያለውን ቀለም በመሰባበር በደም አማካይነት እንዲወገድ ያደርጋል ብለዋል። ሕክምናው ተከታታይ ሲሆን፤ ለዘመናዊ ንቅሳት ከ6 እስከ 10 ጊዜ ቢሰጥ "ከፍተኛ ለውጥ ሊመጣ የሚችልበት አጋጣሚ አለ" ብለዋል - ቆዳን ሙሉ በሙሉ ወደነበረበት ባይመልሰውም። ሕክምናው በእያንዳንዱ የክትትል ዙር እስከ 2500 ብር ሊያስወጣ እንደሚችል የሚገልጹት ሐኪሙ፤ ሰዎች ንቅሳት ከማሠራታቸው በፊት ደጋግመው እንዲያስቡበት መክረዋል። | ከ20 ሺህ ብር በላይ የሚወጣበት የኢትዮጵያ ዘመናዊ የንቅሳት ገበያ ሰውነታቸው ላይ ንቅሳት ለማሳረፍ ወደ ንቅሳት ቤቶች ጎራ ከሚሉ ሰዎች መካከል በፍቅር ወይም በትዳር የተጣመሩ ጥንዶች ይገኙበታል። "ጥንዶቹ ፍቅራቸውን ለመግለጽ ሴቷ የወንዱን፣ ወንዱ ደግሞ የሴቷን ስም አሊያም የስም መጀመሪያ ፊደላትን መነቀስ የተለመደ ሆኗል" ይላል የንቅሳት ባለሙያው (ታቱ አርቲስት) ሔኖክ ጥላሁን። ሆኖም በጥንዶቹ መካከል ንፋስ ገብቶ መራራቅ ሲመጣ "ለየብቻ ይመጡና ንቅሳቱን ቀይርልኝ" ብለው እንደሚጠይቁት ይናገራል። ይህንን በመሰሉ አጋጣሚዎች የተሞላውን የንቅሳት ሥራ፤ ሰዎች ሐሳባቸውን ለማንጸባረቅ ያውሉታል። ዮሴፍ ተስፍዬ ይባላል። 28 ሺህ ብር አውጥቶ በሁለቱም እጆቹ ከትከሻው እስከ መዳፉ አንጓ 'የውስጤን ሐሳብ ይገልጹልኛል' ያላቸውን የተለያዩ ምስሎችና ጽሁፎች ተነቅሷል። ለእሱ የደስታ ምንጭ የሆነው ንቅሳቱ በተመልካቾች ዘንድ ሁለት ዓይነት አስተያየት ይቀርብበታል። አንዱ "ምን ነካህ?" ሲሆን ሌላኛው ደግሞ "ያምራል" የሚል ነው ይላል። ነገር ግን በሚሠራበት አካባቢ ንቅሳቱ እንዳይታይ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያደርግም ይናገራል። ሳምራዊት ተስፋዬ እና ኤልኤዘር ሙሴም በተመሳሳይ መነሻ የተለያዩ የሰውነት ክፍላቸውን ተነቅሰዋል። ለመሆኑ በአዲስ አበባ ምን አይነት ንቅሳቶች ይዘወተራሉ? ምን ያህል ገንዘብስ ይወጣባቸዋል? የንቅሳቶች ይዘት እና ምክንያት የንቅሳት ባለሙያው ሔኖክ ጥላሁን ቀደም ሲል ሥዕሎችን ይስል እንደነበር ይናገራል። እንደ ባለሙያው ገለጻ ንቅሳትም አንድ የጥበብ ዘርፍ በመሆኑ 'ሄና ታቱ' የሚል ድርጅት በመክፈት ንቅሳትን መተዳዳሪያው ካደረገ ከስምንት ዓመታት በላይ ተቆጥሯል። ንቅሳት የሚፈልጉ ሰዎች ከተዘጋጀ የንቅሳት ዝርዝር ውስጥ መርጠው ወይም የፈለጉትን ማንኛውንም አይነት ምስል አሊያም ጹሁፍን ወደ ንቅሳት መቀየር ይቻላል ይላል። በብዛት ወደ እሱ የሚመጡ ሰዎች ሰውነታቸው ላይ እንዲያርፍ የሚርጡት ይዘት ሐይማኖታዊ መሆኑን ይናገራል። በተጨማሪም ጥንዶች ፍቅራቸውን ለመግለጽ ተመሳሳይ ንቅሳት ወይም አንዱ የሌላውን ስም ይነቀሳሉ። የእናታቸውን ወይም የአባታቸውን ምስል ወይም ስም የተነቀሱ ደንበኞች እንዳሉት የሚጠቅሰው ሔኖክ፤ በሌላ በኩል መስቀል፣ የቅዱሳን ሥዕሎችና መሰል ሐይማኖታዊ ይዘቶች በብዛት እንደሚዘወተሩ ያስረዳል። ብዙዎች ንቅሳትን "የሚወዱትን ነገር መግለጫና ማሳያ አድርገው ነው የሚያዩት" ሲል ይጠቅሳል። ሳምራዊት የግራ እጇ ከክንዷ በታች ያለው ክፍል ሙሉ በሙሉ በንቅሳት የተሸፈነ ነው። "ስለ ወደደኝ አዳነኝ" እና "Be Happy" የሚሉ ጽሁፎች፣ ሳቅን የሚገልጽ የስሜት ነጸብራቅ ምስል (emoji)፣ አበባ እንዲሁም ሌሎች ምስሎች አሉ። ደረቷ ላይ "blessed" የሚል ጽሁፍና አንገቷ ላይ ደግሞ መስቀል ተነቅሳለች። ኤልዜር የደረቱ አብዛኛው ክፍል ንቅሳት ያረፈበት ሲሆን፤ የነብርና ንስር ምስሎችን ነው የተነቀሰው። ዮሴፍ ደግሞ ሰዓት፣ አበባ፣ ኮምፓስና መሰል ምስሎችን በቀይና ጥቁር ቀለሞች በእጆቹ ላይ ተነቅሷል። ሳምራዊት ለሐይማኖቷ ያላትን ፍቅር ለመግለጽና ውስጧ ያለውን የተለያየ ሰሜት ለማንጸባረቅ እንደተነቀሰች ትገልጻለች። ዮሴፍ እና ኤልኤዘር ውስጣቸው የሚያምንበትና የሚወዱት ሐሳብ ሰውነታቸው ላይ እንዲታይ በማለም ነው አካላቸውን በንቅሳት የሸፈኑት። በተለይ ኤልኤዘር ለቤተሰቦቹ ያለውን ፍቅር ለመግለጽ መነቀሱን ተናግሯል። እነ ሳምራዊት በጠቀሷቸው ምክንያቶች ይነቀሱ እንጂ ሰውነታቸው ላይ ያለ ጠባሳን ለመሸፈን ወይም ባህላዊ ንቅሳቶችን ወደ ዘመነኛ ለመቀየር ወደ ንቅሳት ቤቶች የሚያመሩ ሰዎች እንዳሉም ሔኖክ ይገልጻል። የንቅሳት ገበያ ኤልኤዘር ንቅሳቱን በተለያየ ጊዜ ማድረጉን ያስረዳል። ለዚህም እስከ 20 ሺህ ብር አውጥቷል። ሳምራዊት ደግሞ 15 ሺህ ብር በመክፈል ነው ንቅሳቷን ያሠራችው። ዝቅተኛው የንቅሳት ርዝመት አምስት ወይም ስድስት ሴንቲ ሜትር እንደሚረዝምና 500 ብር እንደሚያስወጣ ሔኖክ ይገልጻል። ንቅሳቱ ከፍ እያለ ሲሄድ ዋጋ እንደሚጨምር እንዲሁም ጀርባ ላይ የሚሠሩ ንቅሳቶች በአንድ ጊዜ እንደማያልቁና እስከ ሦስት ቀናት ሊፈጁ እንደሚችሉ ተናግሯል። ይህም እስከ 15 ሺህ ብር የሚወጣበት ነው። ታዲያ ይህ ሥራ ዋና የገቢ ምንጬ ነው የሚለው ሔኖክ "በየቀኑ ሥራ አለ" ሲል አስረድቷል። ንቅሳት ለመሥራት የሚውሉ መሣሪያዎች ከዘመኑ ጋር እየተጓዙ ነው የሚለው የንቅሳት ባለሙያው፤ ግብዓቶችን አገር ውስጥ ማግኘት ግን ፈታኝ መሆኑን እና የንቅሳት መርፌ ሳይቀር ከውጪ አገራት እንደሚገባ ይገልጻል። "ንቅሳት ላይ ከቴክኖሎጂው በላይ የአርቲስቱ ጉዳይ [የባለሙያው አቅም] ነው ትልቁ ነገር" ሲልም ጨምሯል። የተመልካቾች አስተያየት እና ልዩ ገጠመኞች ዮሴፍ ንቅሳቴን ሲያዩ "የሚያማትቡ አሉ" ይላል። ኤልኤዘር ደግሞ "አንዳንድ ሰው የሚያየኝ እንደ ዱርዬ ነው። ባንክ ስገባ አንዳንድ ሰዎች ቦርሳቸውን የሚደብቁበት ጊዜ አለ" ሲል ገልጾታል። "ሁሉም ሰው አንድ አይደለም። ወጣቶቹ ይወዱታል። 'በጣም ያምራል' ይላሉ። ሌላው ደግሞ 'ኔጌቲቭ' አስተያየት ነው የሚሰጠው። 'ለምን እንዲህ አደርግሽ?' 'በሐይማኖት አይፈቀድም' ይላሉ" ያለችው ደግሞ ሳምራዊት ናት። የንቅሳት ባለሙያው ሔኖክም በሥራው ብዙ ነገሮች እንደሚገጥሙት ይገልጻል። ፍቅረኞች ወይም ባለትዳሮች ፍቅራቸውን 'ለማጠንከር' በማሰብ ለመነቀስ ወደኛ ይመጣሉ የሚለው ሔሄኖክ፤ ከተሠራላቸው በኋላ ግን ተመልሰው የሚመጡ እንዳሉ ጠቅሷል። "ይመጡና ይሄን ነገር አልፈለኩትም። የዚያን ጊዜ በደንብ አላሰብኩበትም። ይሄን ነገር ማጥፋት እፈልጋለሁ ይላሉ። ያው ማጥፋት ከባድ ስለሆነ በሌላ ዲዛይን ይሸፈናል።" በሌላ በኩል ፊታቸው ላይ ንቅሳት ለማሠራት መጥተው እድሜያቸው ትንሽ ከሆነ "በኋላ እንዳይጸጽታቸው" ብለን እንመክራለንም ብሏል። "አንዳንዴ ሰዎች ንቅሳተቱን ሳይጨርሱ የሚሄዱበት አጋጣሚ አለ - አመመኝ በሚል" ሲልም ተናግሯል። አንዱን አጋጣሚ ሲያስታውስ፤ አንድ ደንበኛው "የቅዱስ ሚካኤልን ምስል ጀርባው ላይ ለመነቀስ መረጠ" ይላል። እናም ንቅሳቱ ተጀመረ። "ሥዕሉ መልአኩ ሰይጣኑን ሲረግጥ የሚያሳየው ነው። እኛ ከሥር እየሠራን ነው ወደ ላይ የምንሄደው። ሰይጣኑን ወደ ማገባደድ ደርሰን ወደ ላይ እየወጣን ስንሄድ 'በቃ አልቻልኩም ይቅርብኝ' አለ። ለመጨረስ በተከታታይ ብደውልለትም አልመጣም። እስካሁን ሰይጣኑን ይዞ ነው የሚዞረው" ሲል ያስታውሳል። ንቅሳቱ ሲሠራ በሚፈጠረው ህመም ምክንያት ንቅሳት ጀምረው ከሚያቋርጡ በተቃራኒው የንቅሳቱ መሣሪያ በሚፈጥው መጠነኛ ህመም 'እንደሚደሰት' ዮሴፍ አስረድቷል። ኤልኤዘር ደግሞ "አንድ ጊዜ ፀበል ለጠመቅ ሄጄ ቄሱ አልጠምቅህም ብለውኝ ነበር [ንቅሳቱን አይተው]" ብሏል። በሌላ በኩል ዮሴፍ "ሰዎች እንደ ቁም ነገረኛ ስለማይቆጥሩኝ፤ ሥራ ቦታ 'ታቱ' እንዳለኝ የማያውቅ ብዙ ሰው አለ" ሲል ገልጿል። ሳምራዊት በመነቀሷ ከቤተሰቧ አሉታዊ አስተያየት እንዳልገጠማትና እንዲያውም ስትነቀስ 15 ሺህ ብሩን ቤተሰቧ እንደከፈለላት ስትናገር፤ ከዚህ በተቃራኒ ኤልኤዘርና ዮሴፍ ቤተሰቦቻቸው ብዙም በአወንታዊ መንገድ አልተቀበሏቸውም። ንቅሳት እና ጤና የቆዳና የአባላዘር በሽታዎች ስፔሻሊስት ሐኪሙ ዶክተር ድጋፌ ጸጋዬ "ዘመናዊም ይሁን ባህላዊ ንቅሳት ሹል በሆኑ ነገሮች እየወጉ ቀለምን ቆዳ ውስጥ በመጨመር ጌጦችን የመፍጠር ልምድ ነው ብለን ልንገልጸው እንችላለን" ሲሉ ያስረዳሉ። ታዲያ ይህ ልምድ ከጤና አኳያ ሊታዩ የሚችሉ ጉዳዮች አሉትም ብለዋል። እንደ ዶ/ር ድጋፌ ገለጻ፤ ንቅሳት ቋሚ ሲሆን ሰዎች ግን ቀድመው ለንቅሳት የተነሱበት ፍላጎትና ስሜት በጊዜ ብዛት ሊቀየር ይችላል። በዚህም ምክንያት የተነቀሱ ሰዎች ከ40 ዓመታቸው በኋላ የሚጸጸቱበት አጋጣሚ ሊፈጠር ይችላል። በሌላ በኩል "ንቅሳት ያለበት ሰው ደም እንዲሰጥ አይመከርም" ያሉት ሀኪሙ፤ ለዚህም ምክንያቱ የንቅሳት መሣሪያዎች ለተላላፊ በሽታ ስለሚያጋልጡ ነው ብለዋል። ንቅሳት የቆዳ መቆጣት [allergic reactions] ሊፈጥር እንደሚችል ዶ/ር ድጋፌ ጠቅሰዋል። "የሰውነት አለርጂው ከብዙ ጊዜ በኋላ ይመጣል። ከተነቀሱ ከሳምንታት ብሎም ከ10 ወይም ከ15 ዓመታት በኋላ የቆዳ መቆጣት፣ የማሳከክ ወይም የማበጥ ስሜትን ሊያመጣ ይችላል" ብለዋል። ንቅሳት የሚደረግበት ስፍራና የመሣሪያው ንጽህና ካልተጠበቀ ለተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች ሊዳርግም ይችላል። "ንቅሳት ያደረገ ሰው ኤምአርአይ የሚባለውን ምርመራ ማድረግ ቢፈልግ እንደ ንቅሳቱ አይነትና የቀለም አይነት ንቅሳቱ ባለት ቦታ ላይ የቃጠሎ ቁስል ሊያጋጥም ይችላል" ሲሉም ያክላሉ። ቋሚ ንቅሳት መጥፋት ይችላል? አዎ መጥፋት ይችላል። "አብዛኛውን ንቅሳት በሌዘር [በጨረር] ማሽን ማጥፋት የሚቻልበት ዕድል አለ" ሲሉ ገልጸዋል - ዶ/ር ድጋፌ። ሕክምናው የብርሃንን ኃይል ወደ ሙቀት በመቀየር የሚሠራ መሆኑን የሚስረዱት ሐኪሙ፤ ጨረሩ ቆዳው ውስጥ ያለውን ቀለም በመሰባበር በደም አማካይነት እንዲወገድ ያደርጋል ብለዋል። ሕክምናው ተከታታይ ሲሆን፤ ለዘመናዊ ንቅሳት ከ6 እስከ 10 ጊዜ ቢሰጥ "ከፍተኛ ለውጥ ሊመጣ የሚችልበት አጋጣሚ አለ" ብለዋል - ቆዳን ሙሉ በሙሉ ወደነበረበት ባይመልሰውም። ሕክምናው በእያንዳንዱ የክትትል ዙር እስከ 2500 ብር ሊያስወጣ እንደሚችል የሚገልጹት ሐኪሙ፤ ሰዎች ንቅሳት ከማሠራታቸው በፊት ደጋግመው እንዲያስቡበት መክረዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-57390536 |
3politics
| የጤና እክል ገጥሟቸዋል የተባሉት የጂቡቲው ፕሬዝዳንት ከፈረንሳይ ተመለሱ | የጂቡቲው ፕሬዝደንት እስማኤል ኦማር ጉሌህ ከፈረንሳይ ወደ ጂቡቲ መመለሳቸውን ንብረትነቱ የመንግሥት የሆነው ቴሌቪዝን ጣቢያ አርቲዲ ጂቡቲ ዘገበ። ፕሬዝደንቱ ወደ ፈረንሳይ የሄዱት የጤና እክል ገጥሟቸው ነው የሚል ጭምጭምታ ለሳምንታት ሲሰማ ነበር። ነገር ግን የጂቡቲ መንግሥት ጭምጭምታውን አጣጥሎታል። የ73 ዓመቱ እስማኤል ኦማር ጉሌህ ፈረንሳይ ውስጥ እየታከሙ ነው የሚለውን የማኅበራዊ ሚዲያ ወሬ መንግሥት ሐሰት ነው ሲል አስተባብሎት ነበር። ትላንት ፕሬዝደንቱ ከአውሮፕላን ሲወርዱ እንዲሁም አቀባበል ላደረጉላቸውን የመንግሥት ባለሥልጣናት ሰላምታ ሲሰጡ በብሔራዊው ቴሌቭዥን ጣቢያ ታይቷል። እንደ አርቲዲ ጂቡቲ ዘገባ፤ ፕሬዘደንቱ ወደ ፈረንሳይ ያቀኑት ለግል ጉብኝት ነው። ተቃዋሚ ፓርቲው ራሊ ፎር አክሽን ዴሞክራሲ ኤንድ ኢኮሎጂካል ዴቨሎፕመንት (አርኤዲዲኢ) ፕሬዝደንት እስማኤል ኦማር ጉሌህ ከሳምንት በላይ ለሆነ ጊዜ ከሕዝብ ዕይታ መጥፋታቸው አጠራጣሪ ነው ብሏል። መሪው ከዕይታ ከመጥፋታቸው ባሻገር ስለ ጤና ሁኔታቸው ግልጽ መረጃ አለመሰጠቱንም ተቃዋሚ ፓርቲው ተችቷል። እአአ ከ1999 አንስቶ ሥልጣን ላይ የቆዩት ፕሬዝደንቱ ለአምስተኛ ጊዜ የተመረጡት ባለፈው ግንቦት ወር ላይ እንደነበር ይታወሳል። ተቃዋሚዎች ፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ተቀባይነት የለውም ብለውም ነበር። ጂቡቲ ለወደብ አልባዋ ኢትዮጵያ የወጪና ገቢ ንግድ ዋነኛ መተላለፊያ ስትሆን ከወደብ ኪራይ ከፍተኛ ገቢን ታገኛለች። የፈረንሳይ ቅኝ ግዛት የሆነችው ጂቡቲ ቁልፍ በሚባለው የቀይ ባሕር ስልታዊው ስፍራ ላይ የምትገኝ ሲሆን በርካታ የዓለማችን ወታደራዊ ኃያል አገራት በአገሪቱ ውስጥ ወታደራዊ ሰፈር አላቸው። | የጤና እክል ገጥሟቸዋል የተባሉት የጂቡቲው ፕሬዝዳንት ከፈረንሳይ ተመለሱ የጂቡቲው ፕሬዝደንት እስማኤል ኦማር ጉሌህ ከፈረንሳይ ወደ ጂቡቲ መመለሳቸውን ንብረትነቱ የመንግሥት የሆነው ቴሌቪዝን ጣቢያ አርቲዲ ጂቡቲ ዘገበ። ፕሬዝደንቱ ወደ ፈረንሳይ የሄዱት የጤና እክል ገጥሟቸው ነው የሚል ጭምጭምታ ለሳምንታት ሲሰማ ነበር። ነገር ግን የጂቡቲ መንግሥት ጭምጭምታውን አጣጥሎታል። የ73 ዓመቱ እስማኤል ኦማር ጉሌህ ፈረንሳይ ውስጥ እየታከሙ ነው የሚለውን የማኅበራዊ ሚዲያ ወሬ መንግሥት ሐሰት ነው ሲል አስተባብሎት ነበር። ትላንት ፕሬዝደንቱ ከአውሮፕላን ሲወርዱ እንዲሁም አቀባበል ላደረጉላቸውን የመንግሥት ባለሥልጣናት ሰላምታ ሲሰጡ በብሔራዊው ቴሌቭዥን ጣቢያ ታይቷል። እንደ አርቲዲ ጂቡቲ ዘገባ፤ ፕሬዘደንቱ ወደ ፈረንሳይ ያቀኑት ለግል ጉብኝት ነው። ተቃዋሚ ፓርቲው ራሊ ፎር አክሽን ዴሞክራሲ ኤንድ ኢኮሎጂካል ዴቨሎፕመንት (አርኤዲዲኢ) ፕሬዝደንት እስማኤል ኦማር ጉሌህ ከሳምንት በላይ ለሆነ ጊዜ ከሕዝብ ዕይታ መጥፋታቸው አጠራጣሪ ነው ብሏል። መሪው ከዕይታ ከመጥፋታቸው ባሻገር ስለ ጤና ሁኔታቸው ግልጽ መረጃ አለመሰጠቱንም ተቃዋሚ ፓርቲው ተችቷል። እአአ ከ1999 አንስቶ ሥልጣን ላይ የቆዩት ፕሬዝደንቱ ለአምስተኛ ጊዜ የተመረጡት ባለፈው ግንቦት ወር ላይ እንደነበር ይታወሳል። ተቃዋሚዎች ፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ተቀባይነት የለውም ብለውም ነበር። ጂቡቲ ለወደብ አልባዋ ኢትዮጵያ የወጪና ገቢ ንግድ ዋነኛ መተላለፊያ ስትሆን ከወደብ ኪራይ ከፍተኛ ገቢን ታገኛለች። የፈረንሳይ ቅኝ ግዛት የሆነችው ጂቡቲ ቁልፍ በሚባለው የቀይ ባሕር ስልታዊው ስፍራ ላይ የምትገኝ ሲሆን በርካታ የዓለማችን ወታደራዊ ኃያል አገራት በአገሪቱ ውስጥ ወታደራዊ ሰፈር አላቸው። | https://www.bbc.com/amharic/news-58628570 |
3politics
| ምርጫ 2013፡ የድምጽ መስጫ ቀን ላይ ለውጥ ሊኖር ይችላል ተባለ | የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ በርቱካን ሚደቅሳ የ2013 አጠቃላይ ምርጫ የመራጮች ድምጽ መስጫ ቀን ላይ ለውጥ ሊደርግ እንደሚችል ተናገሩ። የቦርዱ ሰብሳቢዋ የስድሰተኛው ሃገራዊ ምርጫ የድምጽ መስጫ ቀን "አስፈላጊ ከሆነ የተወሰኑ ቀናት ወደፊት ወደ ኋላ ሊል" ይችላል ሲሉ ተናግረዋል። ሰብሳቢዋ ቦርዱ በጉዳዩ ላይ እስካሁን የወሰነው ምንም ዓይነት የቀን ለውጥ አለመኖሩን አረጋግጠው፤ በመራጮች ምዝገባ እና በድምጽ መስጫ ቀናት መካከል መከናወን ያለባቸው ተግባራት መኖራቸውን አስረድተዋል። ኢትዮጵያ በአንድ ዓመት የተራዘመውን አጠቃላይ ምርጫ ግንቦት 28 እና ሰኔ 5 ለማድረግ አቅዳለች። ባሳለፍነው ቅደሜ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት፤ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢዋ ብርቱካን ሚደቅሳ የሎጂስቲክ እና የደህንነት ጉዳዮችን እንደምክንያት በመጥቀስ፤ የድምጽ መስጫው ቀን "አስፈላጊ ከሆነ የተወሰኑ ቀናት ወደፊት ወደ ኋላ ሊል ይችላል ብዬ እገምታለሁ" ሲሉ ተናግረዋል። ቦርዱ እስካሁን ድረስ ከ31 ሚሊዮን በላይ መራጮች መመዝገባቸውን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። የምርጫ ቁሳቁሶችን ማከፋፈል፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች ምልመላ እና ስልጣና እንዲሁም የፓርቲዎች ግብዓት ማግኘት የሚሉት ተግባራት የመራጮች ምዝገባ ተጠናቆ እስከ ድምጽ መስጫ እለት የሚተገበሩ መሆናቸውን አስረድተዋል። "እነዚህን አይተን በሁለቱ መካከል ለማስገባት እንሠራለን። የሚያስፈልገው ነገር የሚወስደው ጊዜ ከታወቀ በኋላ አስፈላጊ ከሆነ የተወሰኑ ቀናት ወደፊት ወደ ኋላ ሊል ይችላል ብዬ እገምታለሁ" ብለዋል። በአዲስ አበባ እና በሌሎች ህዝብ በብዛት የሰፈረባቸው ቦታዎች የምርጫ ጣቢያ አለመኖሩን ያረጋገጡት የቦርዱ ሰብሳቡቢ "ይህ የአሰራር ክፍተት ነው። ችግር በመሆኑ ኃላፊነትም የወሰድንበትም ጉዳይ ነው" ብለዋል። የሕዝብ ቆጠራ አለመደረጉ እና ያለው መረጃ የቆየ መሆኑ የመራጮች ምዝገባ ግምት አስቸጋሪ ማድረጉን በምክንያትነት አስቀምጠዋል። ችግሩን ለመቅረፍ እየተሠራ መሆኑን በመጠቆም "አዲስ አበባ ላይ ብዙ ቦታዎች ላይ በተለይም ኮንዶሚኒየም አካባቢዎች ላይ ከህዝብ ቁጥር አንጻር ያለመመጣጠን ነበር። በቀረው ጊዜ ብዙ ሰው እንመዘገባል ብለን እንገምታለን። የተሻለ ምዝገባ እንጠብቃልን" ብለዋል። የመራጮች ምዝገባ የተራዘመባቸው ስፍራዎች የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢዋ ብርቱካን፤ በደህንነት ስጋት የመራጮች ምዝገባ ዘግይቶ በነበረባቸው አካባቢዎች የመራጮች ምዝገባ መጀመራቸውን ተናግረዋል። በኦሮሚያ በአራቱ የወላጋ ዞኖች፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ካማሺ እንዲሁም በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ምዝገባ መጀመሩን ተናግረዋል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን በተመለከተም "በመተከል ዙሪያ ቦርዱ በትኩረት እየተከታተለው ነው። የደህንነት እና የተፈናቃዮች ሁኔታን ከግምት በማስገባት ምዝገባ ለማስጀመር እያየነው እንገኛለን" በማለት እስካሁን መተከል ላይ የመራጮች ምዝገባ አለመጀመሩን ተናግረዋል። በሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ 3 የምርጫ ክልሎችም አሁንም ምዝገባ አልመጀመሩን ጠቅሰው ከአባቢው የተፈናቀሉ ወደቦታቸው ስላልተመለሱ እና የደህንንነት ስጋት በመሆኑ ምዝገባ አለመጀመሩን አስረድተዋል። በደቡብ ክልል ደግሞ የሱርማ ልዩ እና ዲዚ ልዩ እስካሁን ምዝገባ አለመጀመሩ እንዲሁም በሶማሌ ክልል የምርጫ ምዝገባ ግድፈት ተፈጸሞባቸዋል በተባሉ አካባቢዎች ቦርዱ ምዝገባውን መታገዱን አስታውቀዋል። የአውሮፓ ሕብረት ታዛቢዎቸን አልክም ስለማለቱ የአውሮፓ ሕብረት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር መግባባት በለመቻሉ የምርጫ ታዛቢዎቹን እንደማይልክ ባሳለፍነው ሳምንት ማስታወቁ ይታወሳል። የአውሮፓ ሕብረት ታዛቢዎችን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ "የውጭ ታዛቢዎች ሁለት ደረጃዎች አሉት። የመጀመሪያው ከመንግሥት ጋር የሚያልቅ ነው። . . . በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የሚጠናቀቅ ነው። [ሁለተኛው] በውጭ ጉዳይ ማረጋገጫ መሠረት ዕውቅና በመስጠት እናሰማራለን። አውሮፓ ህብረት ታዛቢዎችን ባለመላኩ ቦርዱ አዝኗል። ከእኛ በፊት ከመንግሥት ጋር ያለውን ግንኙነት ሳይጨርስ ነው ይህ ነገር የተፈጠረው። ቢመጡ እንደምንወድ ለሂደቱም የሚጨምረው ነገር እንዳለ አረጋግጠንላቸው ነበር። በእነሱም በኩል ተመሳሳይ ግምት እና እምነት ነበር። . . . ቢመጡ መልካም ነበር። ከዚህ ያለፈ ሃሳብ መስጠትል አልችልም" ብለዋል። ኢትዮጵያ ምርጫ ለመታዘብ ካቀደው የአውሮፓ ሕብረት ጋር ያልተስማማቸው ሕብረቱ ሉዓላዊነትን የሚጻረር ጥያቄን በማቅረቡ ነው ሲሉ የውጪ ጉዳይ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ መናገራቸው ይታወሳል። ሕብረቱ ኢትዮጵያ የሌላትን የኮሚኒኬሽን ስርዓት ወደ አገር ውስጥ ይዞ መግባትን እንደ ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጡ እና የምርጫ ውጤትን ይፋ የማድረግ እኔ ነኝ ማለቱን ተከተሎ ከስምምነት መድረስ አለመቻሉን የውጪ ጉዳይ ቃል አቀባይ ተናግረዋል። | ምርጫ 2013፡ የድምጽ መስጫ ቀን ላይ ለውጥ ሊኖር ይችላል ተባለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ በርቱካን ሚደቅሳ የ2013 አጠቃላይ ምርጫ የመራጮች ድምጽ መስጫ ቀን ላይ ለውጥ ሊደርግ እንደሚችል ተናገሩ። የቦርዱ ሰብሳቢዋ የስድሰተኛው ሃገራዊ ምርጫ የድምጽ መስጫ ቀን "አስፈላጊ ከሆነ የተወሰኑ ቀናት ወደፊት ወደ ኋላ ሊል" ይችላል ሲሉ ተናግረዋል። ሰብሳቢዋ ቦርዱ በጉዳዩ ላይ እስካሁን የወሰነው ምንም ዓይነት የቀን ለውጥ አለመኖሩን አረጋግጠው፤ በመራጮች ምዝገባ እና በድምጽ መስጫ ቀናት መካከል መከናወን ያለባቸው ተግባራት መኖራቸውን አስረድተዋል። ኢትዮጵያ በአንድ ዓመት የተራዘመውን አጠቃላይ ምርጫ ግንቦት 28 እና ሰኔ 5 ለማድረግ አቅዳለች። ባሳለፍነው ቅደሜ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት፤ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢዋ ብርቱካን ሚደቅሳ የሎጂስቲክ እና የደህንነት ጉዳዮችን እንደምክንያት በመጥቀስ፤ የድምጽ መስጫው ቀን "አስፈላጊ ከሆነ የተወሰኑ ቀናት ወደፊት ወደ ኋላ ሊል ይችላል ብዬ እገምታለሁ" ሲሉ ተናግረዋል። ቦርዱ እስካሁን ድረስ ከ31 ሚሊዮን በላይ መራጮች መመዝገባቸውን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። የምርጫ ቁሳቁሶችን ማከፋፈል፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች ምልመላ እና ስልጣና እንዲሁም የፓርቲዎች ግብዓት ማግኘት የሚሉት ተግባራት የመራጮች ምዝገባ ተጠናቆ እስከ ድምጽ መስጫ እለት የሚተገበሩ መሆናቸውን አስረድተዋል። "እነዚህን አይተን በሁለቱ መካከል ለማስገባት እንሠራለን። የሚያስፈልገው ነገር የሚወስደው ጊዜ ከታወቀ በኋላ አስፈላጊ ከሆነ የተወሰኑ ቀናት ወደፊት ወደ ኋላ ሊል ይችላል ብዬ እገምታለሁ" ብለዋል። በአዲስ አበባ እና በሌሎች ህዝብ በብዛት የሰፈረባቸው ቦታዎች የምርጫ ጣቢያ አለመኖሩን ያረጋገጡት የቦርዱ ሰብሳቡቢ "ይህ የአሰራር ክፍተት ነው። ችግር በመሆኑ ኃላፊነትም የወሰድንበትም ጉዳይ ነው" ብለዋል። የሕዝብ ቆጠራ አለመደረጉ እና ያለው መረጃ የቆየ መሆኑ የመራጮች ምዝገባ ግምት አስቸጋሪ ማድረጉን በምክንያትነት አስቀምጠዋል። ችግሩን ለመቅረፍ እየተሠራ መሆኑን በመጠቆም "አዲስ አበባ ላይ ብዙ ቦታዎች ላይ በተለይም ኮንዶሚኒየም አካባቢዎች ላይ ከህዝብ ቁጥር አንጻር ያለመመጣጠን ነበር። በቀረው ጊዜ ብዙ ሰው እንመዘገባል ብለን እንገምታለን። የተሻለ ምዝገባ እንጠብቃልን" ብለዋል። የመራጮች ምዝገባ የተራዘመባቸው ስፍራዎች የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢዋ ብርቱካን፤ በደህንነት ስጋት የመራጮች ምዝገባ ዘግይቶ በነበረባቸው አካባቢዎች የመራጮች ምዝገባ መጀመራቸውን ተናግረዋል። በኦሮሚያ በአራቱ የወላጋ ዞኖች፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ካማሺ እንዲሁም በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ምዝገባ መጀመሩን ተናግረዋል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን በተመለከተም "በመተከል ዙሪያ ቦርዱ በትኩረት እየተከታተለው ነው። የደህንነት እና የተፈናቃዮች ሁኔታን ከግምት በማስገባት ምዝገባ ለማስጀመር እያየነው እንገኛለን" በማለት እስካሁን መተከል ላይ የመራጮች ምዝገባ አለመጀመሩን ተናግረዋል። በሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ 3 የምርጫ ክልሎችም አሁንም ምዝገባ አልመጀመሩን ጠቅሰው ከአባቢው የተፈናቀሉ ወደቦታቸው ስላልተመለሱ እና የደህንንነት ስጋት በመሆኑ ምዝገባ አለመጀመሩን አስረድተዋል። በደቡብ ክልል ደግሞ የሱርማ ልዩ እና ዲዚ ልዩ እስካሁን ምዝገባ አለመጀመሩ እንዲሁም በሶማሌ ክልል የምርጫ ምዝገባ ግድፈት ተፈጸሞባቸዋል በተባሉ አካባቢዎች ቦርዱ ምዝገባውን መታገዱን አስታውቀዋል። የአውሮፓ ሕብረት ታዛቢዎቸን አልክም ስለማለቱ የአውሮፓ ሕብረት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር መግባባት በለመቻሉ የምርጫ ታዛቢዎቹን እንደማይልክ ባሳለፍነው ሳምንት ማስታወቁ ይታወሳል። የአውሮፓ ሕብረት ታዛቢዎችን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ "የውጭ ታዛቢዎች ሁለት ደረጃዎች አሉት። የመጀመሪያው ከመንግሥት ጋር የሚያልቅ ነው። . . . በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የሚጠናቀቅ ነው። [ሁለተኛው] በውጭ ጉዳይ ማረጋገጫ መሠረት ዕውቅና በመስጠት እናሰማራለን። አውሮፓ ህብረት ታዛቢዎችን ባለመላኩ ቦርዱ አዝኗል። ከእኛ በፊት ከመንግሥት ጋር ያለውን ግንኙነት ሳይጨርስ ነው ይህ ነገር የተፈጠረው። ቢመጡ እንደምንወድ ለሂደቱም የሚጨምረው ነገር እንዳለ አረጋግጠንላቸው ነበር። በእነሱም በኩል ተመሳሳይ ግምት እና እምነት ነበር። . . . ቢመጡ መልካም ነበር። ከዚህ ያለፈ ሃሳብ መስጠትል አልችልም" ብለዋል። ኢትዮጵያ ምርጫ ለመታዘብ ካቀደው የአውሮፓ ሕብረት ጋር ያልተስማማቸው ሕብረቱ ሉዓላዊነትን የሚጻረር ጥያቄን በማቅረቡ ነው ሲሉ የውጪ ጉዳይ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ መናገራቸው ይታወሳል። ሕብረቱ ኢትዮጵያ የሌላትን የኮሚኒኬሽን ስርዓት ወደ አገር ውስጥ ይዞ መግባትን እንደ ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጡ እና የምርጫ ውጤትን ይፋ የማድረግ እኔ ነኝ ማለቱን ተከተሎ ከስምምነት መድረስ አለመቻሉን የውጪ ጉዳይ ቃል አቀባይ ተናግረዋል። | https://www.bbc.com/amharic/57056780 |
5sports
| ቡልጋሪያ ከ እንግሊዝ፡ የዩሮ 2020 ማጣሪያ ውድድር በደጋፊዎች ዘረኛ ስድብ የተነሳ ሁለቴ መቋረጡ ተሰማ | እንግሊዝ ለዩሮ 2020 ማጣሪያ በቡልጋሪያ፤ ሶፊያ ከተማ እያደረገች የነበረው ግጥሚያ ላይ የታደሙ የቡልጋሪያ ደጋፊዎች ዘረኛ የሆኑ ምልክቶችን በማሳየታቸውና ድምጾችን በማሰማታቸው የተነሳ ጨዋታው ሁለት ጊዜ መቋረጡ ተሰማ። በስታዲየሙ የነበሩት ደጋፊዎች የናዚ ሰላምታ ምልክት ያሳዩ ሲሆን እንደ ዝንጀሮ ይጮሁ እንደነበርም ተነግሯል። ጨዋታው መጀመሪያ የተቋረጠው እንግሊዝ 2 ለ 0 እየመራች ሳለ በ28ኛው ደቂቃ ላይ ነበር። • ዕድሜያችን የማቱሳላን ሲሶ እንኳ መሄድ የተሳነው ለምን ይሆን? • አሜሪካ ቱርክ ላይ ማዕቀብ ጣለች • "የተርባይኖች መቀነስ በሚመነጨው ኃይል ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም" የህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ በዚህ መካከል ስታዲየሙ ውስጥ በድምፅ ማጉያ ደጋፊዎች ከእንደዚህ አይነት ተግባራቸው እንዲታቀቡ መልዕክት የተላለፈ ቢሆንም፤ ነውጠኛ ደጋፊዎቹ ግን በድርጊታቸው ገፍተውበታል። በ43ኛው ደቂቃ ላይ ጨዋታው በድጋሚ ተቋርጧል። በዚህ ጨዋታ እንግሊዝ 6 ለ 0 የረታች ሲሆን ምድብ ሀ ላይ በመሪነት ስፍራውን ይዛ ትገኛለች። የእንግሊዝ የእግር ኳስ ማህበሩ ሊቀመንበር ግሬክ ክላርክ በስፍራው የነበሩ ሲሆን የተፈጠረውንም መታዘብ ችለዋል። የቡልጋሪያ ደጋፊዎች ተግባር በርካታ እንግሊዛዊያን ተጫዋቾችንና የቡድኑን አባላት ያስቆጣ ነው ብለዋል። "በርካታ ዘረኛ የሆኑ ድምጾችን ሰምቻለሁ" ካሉ በኋላም "50 የሚሆኑ ሰዎች በቡድን በመሆን ጥቁር ለብሰው የፋሺስት ምልክት ሲያሳዩ ተመልክቻለሁ፤ እርግጠኛ መሆን ባልችልም ካለሁበት በ100 ሜትር ርቀት ላይ ነበር ምልክቱን የሚያሳዩ ደጋፊዎች የነበሩት" ብለዋል። አክለውም የአውሮፓ እግር ኳስን የሚያስተዳድረው አካል በእለቱ ስለተፈጠረው ጉዳይ ጥልቅ ምርመራ ማድረግ እንዳለበትም ሃሳባቸውን ሰጥተዋል። በጨዋታው ወቅት የተፈጠረው ምን ነበር? የእንግሊዙ ተከላካይ በቁጥጥሩ ስር የነበረውን ኳስ ካሻገረ በኋላ ከደጋፊዎች የሰማው ድምፅ ምን እንደሆነ ለማጣራት ዞረ፤ ከዚያም በደቂቃዎች ውስጥ ጨዋታው ቆመ። አጥቂው ሀሪ ኬን ከጨዋታው ዳኛ ኢቫን ቤቤክ ጋር ከተነጋገረ በኋላ በስታዲየሙ ውስጥ የተሰማውን ዘረኛ ንግግር የሚያወግዝ መልዕክት በድምፅ ማጎያ ተላለፈ። በዚሁ ሰዓት የቡድኑ ኃላፊ የተወሰኑ ተጫዋቾችን እያነጋገሩ ነበር። ከዚያም ጨዋታው እንዲቀጥል ቢደረግም የእረፍት ሰዓት ከመድረሱ አስቀድሞ በድጋሚ ሊቋረጥ ችሏል። ጨዋታው እንደገና ከመጀመሩ በፊት የቡድኑ ኃላፊ ከተጫዋቾቹ ጋር ተነጋግረዋል። የተወሰኑ ፊታቸውን የሸፈኑና ጥቁር የለበሱ የቡልጋሪያ ቡድን ደጋፊዎች፤ ጨዋታው ከእረፍት ከመመለሱ በፊት ስታዲየሙን ጥለው ወጥተዋል። ቢቢሲ ሬዲዮ 5 እንደዘገበው የተወሰኑት ዘረኛ እና የቀኝ ክንፍ አክራሪ ምልክቶችን ሲያሳዩ ነበር። እንግሊዝ በ2020 የአውሮፓ ማጣሪያ ጨዋታ ወቅት ዘረኛ መልዕክቶችን ስታስተናግድ ይህ የመጀመሪያዋ አይደለም። ከሞንቴኔግሮ ጋር በነበራትና 5 ለ 1 ባሸነፈችበት ጨዋታም እንዲሁ ዘረኛ የሆኑ መልዕክቶች በእንግሊዝ ተጫዋቾች ላይ ተሰንዝሯል። በዚህም የተነሳ ሞንቴኔግሮ 20ሺህ ዩሮና ሁለት ጨዋታዎችን ደጋፊዎቿ በሌሎበት ዝግ ስታዲየም እንድታካሄድ ተቀጥታለች። | ቡልጋሪያ ከ እንግሊዝ፡ የዩሮ 2020 ማጣሪያ ውድድር በደጋፊዎች ዘረኛ ስድብ የተነሳ ሁለቴ መቋረጡ ተሰማ እንግሊዝ ለዩሮ 2020 ማጣሪያ በቡልጋሪያ፤ ሶፊያ ከተማ እያደረገች የነበረው ግጥሚያ ላይ የታደሙ የቡልጋሪያ ደጋፊዎች ዘረኛ የሆኑ ምልክቶችን በማሳየታቸውና ድምጾችን በማሰማታቸው የተነሳ ጨዋታው ሁለት ጊዜ መቋረጡ ተሰማ። በስታዲየሙ የነበሩት ደጋፊዎች የናዚ ሰላምታ ምልክት ያሳዩ ሲሆን እንደ ዝንጀሮ ይጮሁ እንደነበርም ተነግሯል። ጨዋታው መጀመሪያ የተቋረጠው እንግሊዝ 2 ለ 0 እየመራች ሳለ በ28ኛው ደቂቃ ላይ ነበር። • ዕድሜያችን የማቱሳላን ሲሶ እንኳ መሄድ የተሳነው ለምን ይሆን? • አሜሪካ ቱርክ ላይ ማዕቀብ ጣለች • "የተርባይኖች መቀነስ በሚመነጨው ኃይል ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም" የህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ በዚህ መካከል ስታዲየሙ ውስጥ በድምፅ ማጉያ ደጋፊዎች ከእንደዚህ አይነት ተግባራቸው እንዲታቀቡ መልዕክት የተላለፈ ቢሆንም፤ ነውጠኛ ደጋፊዎቹ ግን በድርጊታቸው ገፍተውበታል። በ43ኛው ደቂቃ ላይ ጨዋታው በድጋሚ ተቋርጧል። በዚህ ጨዋታ እንግሊዝ 6 ለ 0 የረታች ሲሆን ምድብ ሀ ላይ በመሪነት ስፍራውን ይዛ ትገኛለች። የእንግሊዝ የእግር ኳስ ማህበሩ ሊቀመንበር ግሬክ ክላርክ በስፍራው የነበሩ ሲሆን የተፈጠረውንም መታዘብ ችለዋል። የቡልጋሪያ ደጋፊዎች ተግባር በርካታ እንግሊዛዊያን ተጫዋቾችንና የቡድኑን አባላት ያስቆጣ ነው ብለዋል። "በርካታ ዘረኛ የሆኑ ድምጾችን ሰምቻለሁ" ካሉ በኋላም "50 የሚሆኑ ሰዎች በቡድን በመሆን ጥቁር ለብሰው የፋሺስት ምልክት ሲያሳዩ ተመልክቻለሁ፤ እርግጠኛ መሆን ባልችልም ካለሁበት በ100 ሜትር ርቀት ላይ ነበር ምልክቱን የሚያሳዩ ደጋፊዎች የነበሩት" ብለዋል። አክለውም የአውሮፓ እግር ኳስን የሚያስተዳድረው አካል በእለቱ ስለተፈጠረው ጉዳይ ጥልቅ ምርመራ ማድረግ እንዳለበትም ሃሳባቸውን ሰጥተዋል። በጨዋታው ወቅት የተፈጠረው ምን ነበር? የእንግሊዙ ተከላካይ በቁጥጥሩ ስር የነበረውን ኳስ ካሻገረ በኋላ ከደጋፊዎች የሰማው ድምፅ ምን እንደሆነ ለማጣራት ዞረ፤ ከዚያም በደቂቃዎች ውስጥ ጨዋታው ቆመ። አጥቂው ሀሪ ኬን ከጨዋታው ዳኛ ኢቫን ቤቤክ ጋር ከተነጋገረ በኋላ በስታዲየሙ ውስጥ የተሰማውን ዘረኛ ንግግር የሚያወግዝ መልዕክት በድምፅ ማጎያ ተላለፈ። በዚሁ ሰዓት የቡድኑ ኃላፊ የተወሰኑ ተጫዋቾችን እያነጋገሩ ነበር። ከዚያም ጨዋታው እንዲቀጥል ቢደረግም የእረፍት ሰዓት ከመድረሱ አስቀድሞ በድጋሚ ሊቋረጥ ችሏል። ጨዋታው እንደገና ከመጀመሩ በፊት የቡድኑ ኃላፊ ከተጫዋቾቹ ጋር ተነጋግረዋል። የተወሰኑ ፊታቸውን የሸፈኑና ጥቁር የለበሱ የቡልጋሪያ ቡድን ደጋፊዎች፤ ጨዋታው ከእረፍት ከመመለሱ በፊት ስታዲየሙን ጥለው ወጥተዋል። ቢቢሲ ሬዲዮ 5 እንደዘገበው የተወሰኑት ዘረኛ እና የቀኝ ክንፍ አክራሪ ምልክቶችን ሲያሳዩ ነበር። እንግሊዝ በ2020 የአውሮፓ ማጣሪያ ጨዋታ ወቅት ዘረኛ መልዕክቶችን ስታስተናግድ ይህ የመጀመሪያዋ አይደለም። ከሞንቴኔግሮ ጋር በነበራትና 5 ለ 1 ባሸነፈችበት ጨዋታም እንዲሁ ዘረኛ የሆኑ መልዕክቶች በእንግሊዝ ተጫዋቾች ላይ ተሰንዝሯል። በዚህም የተነሳ ሞንቴኔግሮ 20ሺህ ዩሮና ሁለት ጨዋታዎችን ደጋፊዎቿ በሌሎበት ዝግ ስታዲየም እንድታካሄድ ተቀጥታለች። | https://www.bbc.com/amharic/news-50052020 |
0business
| መካከለኛው ምሥራቅ ፡ ከእስራኤል ወደ አረብ ኤምሬትስ የመጀመሪያው የንግድ በረራ ሊደረግ ነው | ከእስራኤል ወደ አረብ ኤምሬትስ ለመጀመሪያ ጊዜ የንግድ በረራ ሊካሄድ ነው። ይህም በሁለቱ መካከል ያለው ግንኙነት ጤናማ እየሆነ ስለመምጣቱ ጠቋሚ ነው ተብሏል። የእስራኤሉ ኤል አል አየር መንገድ የእስራኤል ልዑካንን እንዲሁም የአሜሪካ ባለሥልጣኖችን ይዞ የሦሰት ሰዓት በረራ ያካሂዳል። አውሮፕላኑ በሳዑዲ አየር ክልል እንዲበር ይፈቀድለታል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህ ቀደም የእስራኤል አውሮፕላን በአየር ክልሉ ማለፍ አይችልም ነበር። በመካከለኛው ምሥራቅ፤ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እስራኤል ከተመሠረተች ወዲህ እውቅና የሰጠ ሦስተኛው የአረብ አገር ናት። አረብ ኤምሬትስ እስራኤል ላይ ከ1972 አንስቶ ተጥሎ የነበረውን ገደብ ቅዳሜ አንስታለች። በወሩ መባቻ ላይ ቀጥታ የስልክ መስመር ለመጀመሪያ ጊዜ ሥራ መጀመሩ ይታወሳል። በእስራኤል እና በአረብ ኤምሬትስ መካከል ያለው ግንኙነት የተለሳለሰው በአሜሪካ አሸማግይነት ሲሆን፤ ነሐሴ 13 ነበር ወዳጅነታቸውን ይፋ ያደረጉት። በአብዛኛው የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ ይህ ዜና በመልካም ቢወሰድም፤ ፍልስጤም ግን ተቃውሞዋን ገልጻለች። በተለይም የአረብ ኤምሬትስ ለፍልስጤም እውቅና ካልሰጠችው እስራኤል ጋር ግንኙነት መፍጠራቸው፤ ፍልስጤምን መክዳት ነው ተብሏል። የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፤ ከአረብ ኤምሬትስ ጋር ዳግመኛ መወዳጀታቸውን አስታከው በወረራ የተያዘውን ዌስት ባንክ በግዳጅ የእስራኤል ይዞታ የማድረግ እቅዳቸውን ለማዘግየት ተስማምተዋል። ፍልስጤም ይዞታው አገር የምመሠርትበት ነው ትላለች። | መካከለኛው ምሥራቅ ፡ ከእስራኤል ወደ አረብ ኤምሬትስ የመጀመሪያው የንግድ በረራ ሊደረግ ነው ከእስራኤል ወደ አረብ ኤምሬትስ ለመጀመሪያ ጊዜ የንግድ በረራ ሊካሄድ ነው። ይህም በሁለቱ መካከል ያለው ግንኙነት ጤናማ እየሆነ ስለመምጣቱ ጠቋሚ ነው ተብሏል። የእስራኤሉ ኤል አል አየር መንገድ የእስራኤል ልዑካንን እንዲሁም የአሜሪካ ባለሥልጣኖችን ይዞ የሦሰት ሰዓት በረራ ያካሂዳል። አውሮፕላኑ በሳዑዲ አየር ክልል እንዲበር ይፈቀድለታል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህ ቀደም የእስራኤል አውሮፕላን በአየር ክልሉ ማለፍ አይችልም ነበር። በመካከለኛው ምሥራቅ፤ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እስራኤል ከተመሠረተች ወዲህ እውቅና የሰጠ ሦስተኛው የአረብ አገር ናት። አረብ ኤምሬትስ እስራኤል ላይ ከ1972 አንስቶ ተጥሎ የነበረውን ገደብ ቅዳሜ አንስታለች። በወሩ መባቻ ላይ ቀጥታ የስልክ መስመር ለመጀመሪያ ጊዜ ሥራ መጀመሩ ይታወሳል። በእስራኤል እና በአረብ ኤምሬትስ መካከል ያለው ግንኙነት የተለሳለሰው በአሜሪካ አሸማግይነት ሲሆን፤ ነሐሴ 13 ነበር ወዳጅነታቸውን ይፋ ያደረጉት። በአብዛኛው የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ ይህ ዜና በመልካም ቢወሰድም፤ ፍልስጤም ግን ተቃውሞዋን ገልጻለች። በተለይም የአረብ ኤምሬትስ ለፍልስጤም እውቅና ካልሰጠችው እስራኤል ጋር ግንኙነት መፍጠራቸው፤ ፍልስጤምን መክዳት ነው ተብሏል። የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፤ ከአረብ ኤምሬትስ ጋር ዳግመኛ መወዳጀታቸውን አስታከው በወረራ የተያዘውን ዌስት ባንክ በግዳጅ የእስራኤል ይዞታ የማድረግ እቅዳቸውን ለማዘግየት ተስማምተዋል። ፍልስጤም ይዞታው አገር የምመሠርትበት ነው ትላለች። | https://www.bbc.com/amharic/news-53972550 |
5sports
| የኢራን ብቸኛዋ ሴት የኦለምፒክ ሜዳሊያ ባለቤት ሃገር ጥላ መሸሿን አሳወቀች | የኢራን ብቸኛዋ ሴት የኦለምፒክ ሜዳሊያ ባለቤት ኪሚያ አሊዛዴህ ሃገር ጥላ እንደሸሸች አሳወቀች። የ21 ዓመቷ አሊዛዴህ በማሕበራዊ ድር-አምባ ገጿ ይፋ እንዳደረገችው፤ 'ሃገሬን ጥዬ የሸሸሁት በዋናነት ኢራን ውስጥ ያለው ግብዝነት፣ ውሽትና ኢ-ፍትሃዊነት አካል መሆን ባለመፈለጌ ነው' ብላለች። አሊዛዴህ ራሷን ኢራን ውስጥ ከሚገኝ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተጨቋኝ ሴቶች አንዷ ስትል ትገልፃለች። አሊዛዴህ ያለችበትን ሥፍራ በይፋ ባታሳውቅም ኔዘርላንድስ ውስጥ ልምምድ ታደርግ እንደነበር ተነግሯል። 2016 ብራዚል በተካሄደው የሪዮ ኦለምፒክ ላይ በቴኳዋንዶ የስፖርት ዓይነት ብር በማምጣት ታሪክ ሠርታለች። ነገር ግን የኢራን ባለሥልጣናት ድሌን ለፕሮፖጋንዳቸው ተጠቅመውባታል ስትል በማሕበራዊ ገጿ መልዕክት ላይ አስፍራለች። ኢራን፤ በስህተት የዩክሬን አውሮፕላንን መትቼ ጥያለሁ ብላ ካመነች በኋላ ይህ ያበሳጫቸው ኢራናውያን አደባባይ ወጥተው ተቃውሞ ማሰማት በጀመሩበት ወቅት ነው አሊዛዴህ ሃገር ጥላ መሸሿን ያሳወቀችው። «ልበሽ ያሉኝን ለብሻለሁ፤ በይ ያሉኝን ብያለሁ። እያንዳንዷን ቃል አነብንብያለሁ። እኛ ማለት ለእነሱ [ለኢራን ባለሥጣናት] ግዑዝ ነን።» ምንም እንኳ መንግሥት የሷን ድል ለፕሮፖጋንዳ ቢያውለውም ባለሥልጣናቱ 'ሴት ልጅ እግሯን ማንሳት የለባትም' በማለት ያንጓጥጧት እንደነበር ይፋ አድርጋለች። አሊዛዴህ ወደ የትኛው ሃገር እንደሸሸች ይፋ ማድረግ አልፈቀደችም፤ አውሮጳ ናት ተብሎ የተነገረውንም አስተባብላለች። የኢራናውያን የአሊዛዴህን መሸሽ ሲሰሙ መደናገጣቸው አልቀረም። ፖለቲከኛው አብዶልካሪም ሆሴንዛዴህ 'አቅም የሌላቸው ፖለቲከኞች የሰው ኃይል እንዲሸሽ እያደረጉ ነው' ሲል ወቀሳውን አሰምቷል። አሊዛዴህ ቶክዮ በሚካሄደው ኦለምፒክ ላይ እንደምትሳተፍ ይጠበቃል። የኢራንን ባንዲራ ማውለብለቧ ግን እርግጥ አልሆነም። ሃገር ጥላ የሸሸችው አሊዛዴህ ስለ ወደፊት ዕቅዷ ምንም ያለችው ነገር ባይኖርም 'ሁልጊዜም የኢራን ልጅ ነኝ' ስትል መልዕክቷን ቋጭታለች። | የኢራን ብቸኛዋ ሴት የኦለምፒክ ሜዳሊያ ባለቤት ሃገር ጥላ መሸሿን አሳወቀች የኢራን ብቸኛዋ ሴት የኦለምፒክ ሜዳሊያ ባለቤት ኪሚያ አሊዛዴህ ሃገር ጥላ እንደሸሸች አሳወቀች። የ21 ዓመቷ አሊዛዴህ በማሕበራዊ ድር-አምባ ገጿ ይፋ እንዳደረገችው፤ 'ሃገሬን ጥዬ የሸሸሁት በዋናነት ኢራን ውስጥ ያለው ግብዝነት፣ ውሽትና ኢ-ፍትሃዊነት አካል መሆን ባለመፈለጌ ነው' ብላለች። አሊዛዴህ ራሷን ኢራን ውስጥ ከሚገኝ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተጨቋኝ ሴቶች አንዷ ስትል ትገልፃለች። አሊዛዴህ ያለችበትን ሥፍራ በይፋ ባታሳውቅም ኔዘርላንድስ ውስጥ ልምምድ ታደርግ እንደነበር ተነግሯል። 2016 ብራዚል በተካሄደው የሪዮ ኦለምፒክ ላይ በቴኳዋንዶ የስፖርት ዓይነት ብር በማምጣት ታሪክ ሠርታለች። ነገር ግን የኢራን ባለሥልጣናት ድሌን ለፕሮፖጋንዳቸው ተጠቅመውባታል ስትል በማሕበራዊ ገጿ መልዕክት ላይ አስፍራለች። ኢራን፤ በስህተት የዩክሬን አውሮፕላንን መትቼ ጥያለሁ ብላ ካመነች በኋላ ይህ ያበሳጫቸው ኢራናውያን አደባባይ ወጥተው ተቃውሞ ማሰማት በጀመሩበት ወቅት ነው አሊዛዴህ ሃገር ጥላ መሸሿን ያሳወቀችው። «ልበሽ ያሉኝን ለብሻለሁ፤ በይ ያሉኝን ብያለሁ። እያንዳንዷን ቃል አነብንብያለሁ። እኛ ማለት ለእነሱ [ለኢራን ባለሥጣናት] ግዑዝ ነን።» ምንም እንኳ መንግሥት የሷን ድል ለፕሮፖጋንዳ ቢያውለውም ባለሥልጣናቱ 'ሴት ልጅ እግሯን ማንሳት የለባትም' በማለት ያንጓጥጧት እንደነበር ይፋ አድርጋለች። አሊዛዴህ ወደ የትኛው ሃገር እንደሸሸች ይፋ ማድረግ አልፈቀደችም፤ አውሮጳ ናት ተብሎ የተነገረውንም አስተባብላለች። የኢራናውያን የአሊዛዴህን መሸሽ ሲሰሙ መደናገጣቸው አልቀረም። ፖለቲከኛው አብዶልካሪም ሆሴንዛዴህ 'አቅም የሌላቸው ፖለቲከኞች የሰው ኃይል እንዲሸሽ እያደረጉ ነው' ሲል ወቀሳውን አሰምቷል። አሊዛዴህ ቶክዮ በሚካሄደው ኦለምፒክ ላይ እንደምትሳተፍ ይጠበቃል። የኢራንን ባንዲራ ማውለብለቧ ግን እርግጥ አልሆነም። ሃገር ጥላ የሸሸችው አሊዛዴህ ስለ ወደፊት ዕቅዷ ምንም ያለችው ነገር ባይኖርም 'ሁልጊዜም የኢራን ልጅ ነኝ' ስትል መልዕክቷን ቋጭታለች። | https://www.bbc.com/amharic/51087784 |
5sports
| ሰሜን ኮሪያ ለቶክዮ ኦሎምፒክ "እንዳትጠብቁኝ አልመጣም" አለች | ሰሜን ኮሪያ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት በሚደረገው የቶክዮ ኦሎምፒክ አልሳተፍም ብላለች፡፡ የማልሳተፈውም ‹ስፖርተኞቼ በኮቪድ ይለከፉብኛል ብዬ ስለምሰጋ ነው› ብላለች፡፡ ይህ የሰሜን ኮሪያ ውሳኔ ከየትኛው አገር በላይ ልቧን የሰበረው የደቡብ ኮሪያን ነው፡፡ ምክንያቱም ደቡብ ኮሪያ ይህን የኦሎምፒክ ጨዋታዎችን አጋጣሚ በመጠቀም ከባላንጣዋ ጋር የመቀራረብ ፍላጎትና ተስፋን አሳድራ ስለነበረ ነው፡፡ በ2018 ሁለቱ አገሮች ለዊንተር ኦሎምፒክ የጋራ ቡድን ማሰለፋቸው አይዘነጋም፡፡ ያ አጋጣሚ ሁለቱን አገሮች እንዲቀራረቡ ረድቷቸው ነበር፡፡ ፒዮንግያንግ አሁንም ድረስ ቫይረሱ ወደ አገሬ ድርሽ አላለም ብላ ትሟገታለች፡፡ የወረርሽኝና ተያያዥ የጤና ጉዳዮችን በውል የሚያውቁ ባለሙያዎች ግን ይህ የማይመስል ነገር ነው ይላሉ፡፡ የሰሜን ኮሪያ ቴሌቪዥን ይህን ‹ከኦሎምፒክ ወጥተናል› ውሳኔ ይፋ ያደረገው በመጋቢት 25 የሰሜን ኮሪያ የኦሎምፒክ ኮሚቴው ያደረገውን ስብሰባ ተከትሎ ነው፡፡ ባለፈው ዓመት የወረርሽኙን መቀስቀስ ተከትሎ ሰሜን ኮሪያ ጥብቅ እርምጃዎችን መውሰድ ጀምራ ነበር፡፡ ድንበሮቿን የዘጋችው ቀደም ብላ በጥር ወር ነበር፡፡ ወደ አገሯ የሚገቡ የውጭ ዜጎችንም ለይታ ማዋል ማሳደርም ጀምራ ነበር፡፡ በርካታ ድንበር ተሻጋሪ ባቡሮችና የሕዝብ ማመላለሻ መኪናዎች ወደ አገሯ እንዳይገቡ እግድ አስቀምጣ ነበር፡፡ በሁለቱ ወንድም-እህት ሕዝቦች መካከል በ1953 የኮሪያዎች ጦርነት ሲያበቃ የሰላም ስምምነት ባለመደረሱ ሰሜን ኮሪያ አሁንም ከደቡብ ኮሪያ ጋር በጦርነት ላይ እንዳለች ነው የምታምነው፡፡ | ሰሜን ኮሪያ ለቶክዮ ኦሎምፒክ "እንዳትጠብቁኝ አልመጣም" አለች ሰሜን ኮሪያ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት በሚደረገው የቶክዮ ኦሎምፒክ አልሳተፍም ብላለች፡፡ የማልሳተፈውም ‹ስፖርተኞቼ በኮቪድ ይለከፉብኛል ብዬ ስለምሰጋ ነው› ብላለች፡፡ ይህ የሰሜን ኮሪያ ውሳኔ ከየትኛው አገር በላይ ልቧን የሰበረው የደቡብ ኮሪያን ነው፡፡ ምክንያቱም ደቡብ ኮሪያ ይህን የኦሎምፒክ ጨዋታዎችን አጋጣሚ በመጠቀም ከባላንጣዋ ጋር የመቀራረብ ፍላጎትና ተስፋን አሳድራ ስለነበረ ነው፡፡ በ2018 ሁለቱ አገሮች ለዊንተር ኦሎምፒክ የጋራ ቡድን ማሰለፋቸው አይዘነጋም፡፡ ያ አጋጣሚ ሁለቱን አገሮች እንዲቀራረቡ ረድቷቸው ነበር፡፡ ፒዮንግያንግ አሁንም ድረስ ቫይረሱ ወደ አገሬ ድርሽ አላለም ብላ ትሟገታለች፡፡ የወረርሽኝና ተያያዥ የጤና ጉዳዮችን በውል የሚያውቁ ባለሙያዎች ግን ይህ የማይመስል ነገር ነው ይላሉ፡፡ የሰሜን ኮሪያ ቴሌቪዥን ይህን ‹ከኦሎምፒክ ወጥተናል› ውሳኔ ይፋ ያደረገው በመጋቢት 25 የሰሜን ኮሪያ የኦሎምፒክ ኮሚቴው ያደረገውን ስብሰባ ተከትሎ ነው፡፡ ባለፈው ዓመት የወረርሽኙን መቀስቀስ ተከትሎ ሰሜን ኮሪያ ጥብቅ እርምጃዎችን መውሰድ ጀምራ ነበር፡፡ ድንበሮቿን የዘጋችው ቀደም ብላ በጥር ወር ነበር፡፡ ወደ አገሯ የሚገቡ የውጭ ዜጎችንም ለይታ ማዋል ማሳደርም ጀምራ ነበር፡፡ በርካታ ድንበር ተሻጋሪ ባቡሮችና የሕዝብ ማመላለሻ መኪናዎች ወደ አገሯ እንዳይገቡ እግድ አስቀምጣ ነበር፡፡ በሁለቱ ወንድም-እህት ሕዝቦች መካከል በ1953 የኮሪያዎች ጦርነት ሲያበቃ የሰላም ስምምነት ባለመደረሱ ሰሜን ኮሪያ አሁንም ከደቡብ ኮሪያ ጋር በጦርነት ላይ እንዳለች ነው የምታምነው፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/news-56645978 |
2health
| የዓለም ጤና ድርጅት ለደሃ አገራት ክትባቱ እስኪዳረስ ሶስተኛው የኮቪድ ክትባት እንዲገታ ጠየቀ | የዓለም ጤና ድርጅት ቫይረሱን የመከላከለል አቅም መጠን ለመጨመር በሚል የማበረታቻ ወይም ሶስተኛ የኮቪድ-19 ክትባት ቢያንስ እስከ መጪው መስከረም መገባደጃ ድረስ ገታ እንዲደረግ ጠይቋል። የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም እንዳሉት መሰል እርምጃ ቢያንስ 10 በመቶ የሚሆነው የዓለማችን ህዝብ ክትባቱን እንዲያገኝ ያስችላል። እንደ እስራኤልና ጀርመን ያሉ አገራት ደግሞ ሶስተኛ የኮቪድ-19 ክትባት ለዜጎቻቸው ለመስጠት ማሰባቸውን ማስታወቃቸው የሚታወስ ነው። ነገር ግን ኃላፊው ደሃ የሚባሉት አገራት በክትባት ሂደቱ ወደኋላ እየቀሩ እንደሆነ አሳስበዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ያወጣው መረጃ መሰረት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው አገራት ካለው የክትባት እጥረት አንጻር ለእያንዳንዱ 100 ሰው 1.5 ክትባቶችን ብቻ ማቅረብ እንደሚችሉ ያሳያል። ዶክተር ቴድሮስ ክትባቶቹ ተመልሰው መሰብሰብ እንዳለባቸውና ከተሰበሰበው ክትባት አብዛኛው ደግሞ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው አገራት መሰራጨት እንዳለበት አሳስበዋል። አክለውም ''ሁሉም መንግስታት ዜጎቻቸውን ከአዲሱ የዴልታ ዝርያ ለመከላከል እያደረጉ ያሉትን ነገር እረዳለሁ። ነገር ግን በዓለማችን ያለውን አብዛኛውን ክትባት የተጠቀሙት አገራት መልሰው አሁንም ክትባቱን እንዲጠቀሙት መፈቀድ የለበትም'' ብለዋል። ከፍተኛ ገቢ ባላቸውና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው አገራት መካከል ያለውን የክትባት ልዩነት ለመቀነስ እየሰራ የሚገኘው የዓለም ጤና ድርጅት የአሁኑ ጥያቄው ከበድ ያለ እንደሆነ እየተነገረ ነው። ድርጅቱ በሁሉም አገራት ከሚገኙ ዜጎች መካከል ቢያንስ 10 በመቶ የሚሆኑት እስከሚቀጥለው ወር መጨረሻ ድረስ ክትባቱን እንዲያገኙ እቅድ ያወጣ ቢሆንም ነገሮች አሁን እየሄዱበት ካለው ፍጥነት አንጻር ግን ላይሳካ እንደሚችል ተገምቷል። እንደ ሄይቲ እና ዴሞክራቲክ ኮንጎ ባሉ አገራት እስካሁን ድረስ ሁለተኛውን ዙር ክትባት የወሰደ ሰው የለም። ኢንዶኔዢያ ውስጥ ደግሞ ባለፈው ወር እንደ አዲስ በቫይረሱ የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረ ሲሆን አገሪቱ ግን መከተብ የቻለችው 7.9 በመቶ የሚሆነውን ህዝቧን ብቻ ነው። በሌላ በኩል እስራኤል እድሜያቸው ከ60 ዓመት በላይ የሆኑ አዋቂዎች ተጨማሪ ክትባት እንዲያገኙ እያሰራጨች ሲሆን ጀርመን ደግሞ ሞደርና እና ፋይዘር ክትባቶችን ለሶስተኛ ዙር ለማሰራጨት ማሰቧን ማክሰⶉ ዕለት አስታውቃለች። ከዚህ በተጨማሪ በዩናይትድ ኪንግደም ተጋላጭ ናቸው ተብለው የተለዩ ዜጎች ከመጪው ወር ጀምሮ ማጠናከሪያ ክትባቶችን እንደሚያገኙ ተገልጿል። አሜሪካ እስካሁን የማጠናከሪያ ክትባቶችን በተመለከተ ምንም ያለቸው ነገር ባይኖርም ዋይት ሃውስ ግን ረቡዕ ዕለት አሜሪካውያን በሙሉ እንዲከተቡ የሚያስችልና ለሌሎች አገራት ጭምር የሚላክም ክምችት እንዳለ አስታውቋል። ዶክተር ቴድሮስ ሀብታም አገራት ክትባቶችን ወደ ድሃ አገራት መላክ እንዲጀምሩ ሲጠይቁ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም። ግንቦት ወር ላይ ሀብታም አገራት ለህጻናትና ለታዳጊዎች ሚሰጡትን ክትባት ቀነስ አድርገው ወደ ደሃ አገራት ክትባቶቹን መላክ እንዲጀምሩ ጠይቀው ነበር። ኃላፊው ያደጉት አገራት ኮቫክስ በተሰኘው ዓለም አቀፍ ጥምረት በኩል በፍትሀዊነት ክትባቶቹን ለማድረስ እንዲሰሩ ቢጠይቁም እንደ ዩኬ ያሉ በርካታ አገራት ግን ህጻናትና ታዳዊቾን የመከተብ እቅዳቸውን በፍጥነት እየገፉበት ይገኛሉ። | የዓለም ጤና ድርጅት ለደሃ አገራት ክትባቱ እስኪዳረስ ሶስተኛው የኮቪድ ክትባት እንዲገታ ጠየቀ የዓለም ጤና ድርጅት ቫይረሱን የመከላከለል አቅም መጠን ለመጨመር በሚል የማበረታቻ ወይም ሶስተኛ የኮቪድ-19 ክትባት ቢያንስ እስከ መጪው መስከረም መገባደጃ ድረስ ገታ እንዲደረግ ጠይቋል። የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም እንዳሉት መሰል እርምጃ ቢያንስ 10 በመቶ የሚሆነው የዓለማችን ህዝብ ክትባቱን እንዲያገኝ ያስችላል። እንደ እስራኤልና ጀርመን ያሉ አገራት ደግሞ ሶስተኛ የኮቪድ-19 ክትባት ለዜጎቻቸው ለመስጠት ማሰባቸውን ማስታወቃቸው የሚታወስ ነው። ነገር ግን ኃላፊው ደሃ የሚባሉት አገራት በክትባት ሂደቱ ወደኋላ እየቀሩ እንደሆነ አሳስበዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ያወጣው መረጃ መሰረት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው አገራት ካለው የክትባት እጥረት አንጻር ለእያንዳንዱ 100 ሰው 1.5 ክትባቶችን ብቻ ማቅረብ እንደሚችሉ ያሳያል። ዶክተር ቴድሮስ ክትባቶቹ ተመልሰው መሰብሰብ እንዳለባቸውና ከተሰበሰበው ክትባት አብዛኛው ደግሞ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው አገራት መሰራጨት እንዳለበት አሳስበዋል። አክለውም ''ሁሉም መንግስታት ዜጎቻቸውን ከአዲሱ የዴልታ ዝርያ ለመከላከል እያደረጉ ያሉትን ነገር እረዳለሁ። ነገር ግን በዓለማችን ያለውን አብዛኛውን ክትባት የተጠቀሙት አገራት መልሰው አሁንም ክትባቱን እንዲጠቀሙት መፈቀድ የለበትም'' ብለዋል። ከፍተኛ ገቢ ባላቸውና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው አገራት መካከል ያለውን የክትባት ልዩነት ለመቀነስ እየሰራ የሚገኘው የዓለም ጤና ድርጅት የአሁኑ ጥያቄው ከበድ ያለ እንደሆነ እየተነገረ ነው። ድርጅቱ በሁሉም አገራት ከሚገኙ ዜጎች መካከል ቢያንስ 10 በመቶ የሚሆኑት እስከሚቀጥለው ወር መጨረሻ ድረስ ክትባቱን እንዲያገኙ እቅድ ያወጣ ቢሆንም ነገሮች አሁን እየሄዱበት ካለው ፍጥነት አንጻር ግን ላይሳካ እንደሚችል ተገምቷል። እንደ ሄይቲ እና ዴሞክራቲክ ኮንጎ ባሉ አገራት እስካሁን ድረስ ሁለተኛውን ዙር ክትባት የወሰደ ሰው የለም። ኢንዶኔዢያ ውስጥ ደግሞ ባለፈው ወር እንደ አዲስ በቫይረሱ የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረ ሲሆን አገሪቱ ግን መከተብ የቻለችው 7.9 በመቶ የሚሆነውን ህዝቧን ብቻ ነው። በሌላ በኩል እስራኤል እድሜያቸው ከ60 ዓመት በላይ የሆኑ አዋቂዎች ተጨማሪ ክትባት እንዲያገኙ እያሰራጨች ሲሆን ጀርመን ደግሞ ሞደርና እና ፋይዘር ክትባቶችን ለሶስተኛ ዙር ለማሰራጨት ማሰቧን ማክሰⶉ ዕለት አስታውቃለች። ከዚህ በተጨማሪ በዩናይትድ ኪንግደም ተጋላጭ ናቸው ተብለው የተለዩ ዜጎች ከመጪው ወር ጀምሮ ማጠናከሪያ ክትባቶችን እንደሚያገኙ ተገልጿል። አሜሪካ እስካሁን የማጠናከሪያ ክትባቶችን በተመለከተ ምንም ያለቸው ነገር ባይኖርም ዋይት ሃውስ ግን ረቡዕ ዕለት አሜሪካውያን በሙሉ እንዲከተቡ የሚያስችልና ለሌሎች አገራት ጭምር የሚላክም ክምችት እንዳለ አስታውቋል። ዶክተር ቴድሮስ ሀብታም አገራት ክትባቶችን ወደ ድሃ አገራት መላክ እንዲጀምሩ ሲጠይቁ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም። ግንቦት ወር ላይ ሀብታም አገራት ለህጻናትና ለታዳጊዎች ሚሰጡትን ክትባት ቀነስ አድርገው ወደ ደሃ አገራት ክትባቶቹን መላክ እንዲጀምሩ ጠይቀው ነበር። ኃላፊው ያደጉት አገራት ኮቫክስ በተሰኘው ዓለም አቀፍ ጥምረት በኩል በፍትሀዊነት ክትባቶቹን ለማድረስ እንዲሰሩ ቢጠይቁም እንደ ዩኬ ያሉ በርካታ አገራት ግን ህጻናትና ታዳዊቾን የመከተብ እቅዳቸውን በፍጥነት እየገፉበት ይገኛሉ። | https://www.bbc.com/amharic/news-58089449 |
0business
| ኢትዮጵያ ያለባት ዕዳ ስንት ነው? ዕዳዋን ባትከፍልስ ምን ይከተላል? | የኢትዮጵያ ዕዳ ከዓመት ዓመት በፍጥነት እያደገ መምጣት ይዟል። የዓለም ባንክ መረጃ እንደሚያመለክተው ደርግ ከሥልጣን ሲወርድ የኢትዮጵያ ዕዳ 9 ቢሊዮን ዶላር ነበር። ነገር ግን በ2006 የፈረንጆቹ ዓመት ይህ ዕዳ ወርዶ 2.2 ቢሊዮን ወርዶ የነበረ ቢሆንም፣ ከዚያ በኋላ ግን የኢትዮጵያ ዕዳ ከዓመት ዓመት በቢሊዮን ዶላሮች ይጨምር ያዘ። የዓለም ባንክ በፈረንጆቹ 2020 ባወጣው መረጃ የአገሪቱ ዕዳ 30.36 ቢሊዮን ዶላር ነበረ። እነሆ ከሁለት ዓመታት በኋላ ኢትዮጵያ ከአገር ውስጥና ከውጭ የወሰደችው ብድር 56.6 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል ይላል የገንዘብ ሚኒስቴር። የኢትዮጵያ ዕዳ ከአገሪቱ አጠቃላይ ምርት ግማሽ ያክል መሆኑን ተከትሎ ባሉ ወቅታዊ የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ሁኔታዎች ምክንያት አበዳሪዎች በኢትዮጵያ እና በሌሎች አገራት የብድር አከፋፈሉ ዙሪያ ውይይት ይዘዋል። ከኢትዮጵያ የውጭ አበዳሪዎች የአንበሳውን ድርሻ የምትይዘው ቻይና እንዲሁም ፈረንሳይ ናቸው ስብሰባውን የሚመሩት። የኢትዮጵያ አበዳሪዎች ዕዳ ስለማሸጋሸግ ውይይት ማድረግ የጀመሩት ባለፈው ዓመት ነበር። ነገር ግን በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ግጭት ጉዳዩን አጓተተው። ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ)፣ የዓለም ባንክ፣ ሌሎች የገንዘብ ተቋማት ቻይና እና ሌሎች አበዳሪዎች ኢትዮጵያ፣ ቻድ እና ዛምቢያ ላለባቸው ዕዳ አስተያየት እንዲያደርጉ በመወትወት ላይ ናቸው። የአይኤምኤፍ ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ ዕዳ ኖሮባቸው ተጨማሪ ፈተና እየገጠማቸው ላሉ አገራት መፍትሔ መበጀት አለበት ሲሉ ለሮይተርስ ዜና ወኪል ተናግረዋል። ለመሆኑ ዕዳ ማሸጋሸግ ምንድን ነው? ኢትዮጵያ ዕዳዋን መክፈል ባትችል ምን ይፈጠራል? ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ2010 ዓ.ም. ወደ ሥልጣን ከመምጣታቸው በፊት ኢትዮጵያ የነበረባት ዕዳ 28 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ነበር ይላሉ አየለ ገላን (ዶ/ር)። የምጣኔ ሃብት ተንታኙ እንደሚሉት በወቅቱ የተፈጠረውን የፖለቲካ ለውጥ የተመለከቱ አበዳሪዎች ለኢትዮጵያ ልገሳና ብድር ሰጥተዋል። “ሁኔታው የተበላሸው ከተፈጠረው ትልቅ ተስፋ አንፃር መንግሥት የተበደረውን ገንዘብ ጥቅም ላይ አለማዋሉ ነው” ይላሉ ተንታኙ። “ብድሩን ተጠቅሞ ተጨማሪ ገቢ ማስገባት አለመቻሉ፤ በቂ ሥራ አለመፈጠሩና ገንዘቡ የውጭ ምንዛሬ አለማምጣቱ ችግር ፈጥሯል።” ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መንግሥት በፊት የነበረው አስተዳደር የወሰደው ብድር ሳይመለስ እስከ 2012 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ቢያንስ ተጨማሪ 10 ቢሊዮን ዶላር ብድር መንግሥት መውሰዱ የዕዳውን መጠን እንዳሻቀበው ያምናሉ። “ብድር መክፈል ከዚህ ቀደም ከነበረው ይልቅ አሁን አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል።” ለኢትዮጵያና ሌሎች በርካታ የአፍሪካ አገራት ብድር ከሚሰጡ መካከል አንዱ የሆነው አይኤምኤፍ፣ በፈረንጆቹ 2020 ለኢትዮጵያ 3 ቢሊዮን ዶላር ብድር አፅድቋል። ሌሎች አበዳሪዎችና የዓለም ባንክም እንዲሁ ተጨማሪ 6 ቢሊዮን ዶላርመስጠታቸውን ተከትሎ አሁን ኢትዮጵያ ያለባት ዕዳ መጠን ከ38 ቢሊዮን ዶላር አያንስም ይላሉ ተንታኙ። አይኤምኤፍ ብድሩን ከማፅደቁ በፊት በ2019 ኢትዮጵያ ብድር ለመመለስ ከሚቸገሩ አገራት መካከል እንደሆነች ገልጦ ነበር። “ይህ ማስጠንቀቂያ የኢትዮጵያ ዕዳ መጠን በ2 ቢሊዮን ዶላር ቀንሶ በነበረ ጊዜ የወጣ ነው።” የዐቢይ አሕመድ መንግሥት አበዳሪዎች ለኢትዮጵያና ለሌሎች የአፍሪካ አገራት የዕዳ ሽግሽግ [ዴት ሪስትራክቸሪንግ] እንዲያደርጉ ተደጋጋሚ ጥያቄ ሲያቀርብ ቆይቷል። ከሰሞኑ አበዳሪዎችና ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት በዚህ ጥያቄ ዙሪያ ውይይት ጀምረዋል። የምጣኔ ሃብት ሙያተኛው አየለ ገላን፣ መንግሥት የ2015 ዓ.ም. በጀትን አስመልክቶ ባቀረበው ሪፖርት በቀዳሚነት ያሰፈረው ጉዳይ ብድር መመለስ መሆኑን ያወሳሉ። ኢትዮጵያ ከሰሜኑ ጦርነት በፊት ጀምሮ የዕዳ ሽግሽግ ጥያቄ ስታቀርብ ብትቆይም በጦርነቱ ወቅት ከአበዳሪዎች ጋር የነበራት የሻከረ ግንኙነት ችግር እንደፈጠረ ተንታኙ ይገልጣሉ። “መንግሥት በበጀት ድልድል ውስጥ ብድር መክፈልን ከላይ ሲያስቀምጥ አይቼ አላውቅም” የሚሉት ተንታኙ፤ ይህ የዕዳ ጫናው ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ያሳያል ባይ ናቸው። “አሁን የቀረበው የዕዳ ሽግሽግ ጥያቄ በአጭሩ ‘ብድሩ ከአቅም በላይ ስለሆነብኝ ማሻሻያ ይደረግልኝ’ ማለት ነው።” እንደ ተንታኙ ገለፃ ሽግሽጉ በዋናነት ሦስት መንገዶች አሉት። “አንደኛው ብድሩ ከአቅሜ በላይ ስለሆነ ይሰዘርልኝ ብሎ አበዳሪን ለማስማማት መሞከር ነው። ሁለተኛው፤ የብድሩ ወለድ ከፍተኛ ስለሆነብኝ ይቀነስልኝ የሚል ሊሆን ይችላል፤ ሦስተኛው ደግሞ ብድሩን ከፍዬ የምጨርስበት ጊዜ ይራዘም የሚል ነው።” አየለ (ዶ/ር) በዓለም አቀፍ ደረጃ ብድር ወስዶ በጊዜው አለመመለስ ወንጀል ነው ይላሉ። “ከዚህ ለመራቅ አገራት አበዳሪዎቻቸው ብድሩን እንዲሽሩላቸው የሚቻላቸውን ያደርጋሉ። ይህ ካልሆነ ጥቁር መዝገብ ውስጥ ይገባሉ። ይህ ደግሞ ችግሩን የከፋ ያደርገዋል።” ከዚህ ቀደም ብዙ ጊዜ አበዳሪ ድርጅቶች የኢትዮጵያን ብድር እንደ ሰረዙ የሚያስታውሱት ተንታኙ በአሁኑ ድርድር ሊሆን የሚችለው የክፍያ ጊዜን ማራዘም እንደሚሆን ግምት አላቸው። የመሳካት ዕድል የሚያገኘው የክፍያውን ጊዜ ማርዘም ነው። “የክፍያ ጊዜን በማራዘም የሚደረግን ሽግሽግ የኢትዮጵያ መንግሥት እንደ መልካም ዜና ቢያየውም አደጋ አለው። ጊዜያዊ መፍትሔ ሊሆን ቢችልም የክፍያ ጊዜው በረዘመ ቁጥር የወለድ መጠኑም እየጨመረ ይመጣል። ይህ ለበለጠ ድህነት የሚዳርግ ነው። ‘ሾርት ተርም ጌይን፤ ሎንግ ተርም ፔይን’ (አጭር ጊዜ ጥቅም፤ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ጉዳት) ይሆናል።” በርካታ የልማት ተቋማት 40 በመቶ የሚሆኑ ከሰሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገራት ከባድ የብድር ቀውስ ውስጥ እንደሚገኙ ይገልጻሉ። ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) በፈረንጆቹ 2018 ባወጣው መረጃ አፍሪካ የዕዳ ቀውስ ውስጥ እየገባች ነው ሲል አስጠንቅቆ ነበር። ተቋሙ እንደሚለው ባለፉት አምስት ዓመታት የዕዳ ስጋት ያለባቸው የአፍሪካ አገራት ቁጥር በእጥፍ ጨምሯል። ቻይና ለአፍሪካ አገራት ብድር ከሚሰጡ መካከል ቁንጮዋ ናት። ከአፍሪካ መንግሥታት መካከል 20 በመቶው የቻይና ዕዳ አለባቸው። 35 በመቶ ብድር የሚገኘው እንደ ዓለም ባንክ ካሉ ተቋማት ሲሆን፣ 32 በመቶ ደግሞ ከግል አበዳሪዎች ነው። ባለፉት 11 ወራት [እስከ ግንቦት ወር 2014 ዓ.ም ባለው ጊዜ] መንግሥት 330 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 309 ቢሊዮን ብር ብቻ መሰብሰቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ ተናግረው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕዝብ እንደራሴዎች ፊት ቀርበው ባሰሙት ንግግር መንግሥት 500 ቢሊዮን ዶላር ወጭ አድርጓል ብለዋል። የኢትዮጵያ ወጪ ከገቢዋ አንጻር ያለው ልዩነት እንደህ እንዲሰፋ ያደረገው አገሪቱ ያለባት ዕዳ ነው። “በዚህ ዓመት 1.7 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ ከፍለናል። ይህ መቶ ቢሊዮን ብር አካባቢ ማለት ነው” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለኢትዮጵያ የ2015 በጀት እንዲሆን የመደበው ገንዘብ 786.6 ቢሊዮን ብር ነው። በወቅቱ ከዚህ ገንዘብ መካከል አብዛኛው ለዕዳ ክፍያ፣ ለመልሶ ማቋቋምና ለመከላከያ ግንባታ የሚውል መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር ጠቅሶ ነበር። የምጣኔ ሃብት ሙያተኛው አብዱልመናን አሕመድ ኢትዮጵያን ወደ ኋላ ከሚጎትቱ ፈተናዎች መካከል አንደኛው አገሪቱ ያለባት ዕዳ ነው ይላሉ። አብዱልመናን መንግሥት የግል ዘርፉን የሚያበረታታ ፖሊሲ ካልቀረፀ ምጣኔ ሃብቱን ማሳደግ ሊከብደው ይችላል ብለው ያምናሉ። “የአገሪቱ የፖለቲካ ሁኔታ፣ የማክሮ ኢኮኖሚው ጉዳይ [ለምሳሌ የዋጋ ግሽበት] እና መንግሥት ያለበት የተጠራቀመ ዕዳ ማነቆ ሆነዋል።” ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግሥት ያለበትን የዕዳ መጠን እንዲሁም ከአገሪቱ በጀት ገዘፍ የሚለው ለዕዳ ክፍያ መሆኑን ባስረዱበት ወቅት በርካታ እንደራሴዎች ጥያቄ አንስተው ነበር። የመንግሥት የበጀት አጠቃቀም ችግርና ብክነት እንዲሁም የአገር ውስጥ ገቢ የመሰብሰብ አቅም አለመጎልበት ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ይላሉ እንደራሴዎቹ። የኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት ከ2011-13 ዓ.ም. ባለው ዘመን ከዕቅድ በታች የሆነ 7.1 በመቶ ዕድገት አስመዝግቧል። ኢትዮጵያ ካለባት ዕዳ 97 በመቶ የሚሆነውን ድርሻ የሚይዘው የረጅም ጊዜ ብድርና ‘ፐብሊክና ፐብሊክሊ ጋራንቲንድ’ የተሰኘ የብድር ዓይነት እንደሆነ ኢኮኖሚስቱ አየለ ገላን ይተነትናሉ። “የረጅም ጊዜ ብድር ማለት ክፍያው ከ30 እስከ 50 ዓመታት ባለው ጊዜ ውስጥ የሚከፈል ነው። ይህ ማለት ብድሩን መመለስ አሁን የተበደረው መንግሥት ኃላፊነት ላይሆን ይችላል ማለት ነው።” ‘ፐብሊክና ፐብሊክሊ ጋሪንቲንድ’ [በሕዝብ ንብረት ዋስትና የተገኘ ብድር] የተሰኘው ደግሞ ክፍያው መመለስ ባለበት ሰዓት የመመለስ ኃላፊነት ያለበት የኢትዮጵያ ሕዝብ ሲሆን፣ ብድሩን የሚመልሰው የአሁኑ ትውልድ አይሆንም ማለት ነው ይላሉ ተንታኙ። ዓለም አቀፍ አበዳሪዎች ሲያበድሩ ብድሩ በጊዜው የማይመለስ ከሆነ እንደ ዋስትና የሚይዙት ሃብት አሊያም ንብረት ይኖራል። አገራት ብድራቸውን መከፍል ሲሳናቸው ፕሮጀክቶቻቸው እንደ መያዣ ሲያዙ መስማት የተለመደ ሆኗል። ለምሳሌ ብቸኛው የዚምባቡዌ አየር መንገድ ለደቡብ አፍሪካ መንግሥት መክፈል የነበረበትን ዕዳ ባለመክፈሉ እስከ 2019 ተይዞ ቆይቷል። አየር መንገዱ በ2019 በረራ ሲጀምር 2017 በተከማቸበት ከፍተኛ ውዝፍ ዕዳ ምክንያት ከግማሽ በላይ ሠራተኞቹን ለማሰናበት ተገዶ ነበር። ይህ ሳያንሰው ኤይር ዚምባብዌ በደኅንነት ስጋት ምክንያት በአውሮፓ አገራት አየር ክልል የመብረር ፈቃዱን ተነጥቋል። አንጎላ ደግሞ መክፈል ያለባትን 100 ሚሊዮን ዶላር ዕዳ በገንዘብ መመለስ ባለመቻሏ ለቦትሰዋና ከብቶች በመስጠት ጭምር እየከፈለች መሆኑን በ2020 የአገሪቷ ጋዜጣ አስነብቦ ነበር። የምጣኔ ሃብት ተንታኙ አየለ ገላን እንደሚሉት ኢትዮጵያ ምን አስይዛ ብድር እንደምትወስድ እስካሁን በግልፅ አይታወቅም። የሌሎች አገራትም ልምድ ተመሳሳይ መሆኑን የሚገልጡት ባለሙያው አገራት ምን አስይዘው ብድር እንደሚወስዱ የሚታወቀው በተበዳሪውና በአበዳሪው መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ ወደ ሕግ ሲያመሩ እንደሆነ ያስረዳሉ። “መንግሥት ሲበደር በእጁ የሚገኘውን የትኛውንም ሃብት አስይዞ ነው። ምንድነው የሚለው ግን ምስጢር ነው።” ተንታኙ በኬንያ እና ቻይና መካከል የተፈጠረውን በምሳሌነት ይጠቅሳሉ። “ኬንያ ከቻይና ወስዳ በነበረው ብድር ዙሪያ አለመግባባት ተፈጥሮ የሞምባሳ ወደብ እንደ ዋስትና ተይዞ እንደነበር ግልፅ የሆነው ቻይና ወደቡ የእኔ ነው ማለት ስትጀምር ነው። “ዛምቢያም እንዲሁ ከቻይና ተበድራ ለነበረው ገንዘብ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ተቋሟን ማስያዣ አድርጋ እንደ ነበር አለመግባባት ሲፈጠር ነው ያወቅነው።” ኢትዮጵያ ከአበዳሪዎቿ ጋር ግልፅ የሆነ አለመግባባት ውስጥ ስላልገባች ምን እንዳስያዘች ማወቅ አዳጋች ነው ይላሉ። | ኢትዮጵያ ያለባት ዕዳ ስንት ነው? ዕዳዋን ባትከፍልስ ምን ይከተላል? የኢትዮጵያ ዕዳ ከዓመት ዓመት በፍጥነት እያደገ መምጣት ይዟል። የዓለም ባንክ መረጃ እንደሚያመለክተው ደርግ ከሥልጣን ሲወርድ የኢትዮጵያ ዕዳ 9 ቢሊዮን ዶላር ነበር። ነገር ግን በ2006 የፈረንጆቹ ዓመት ይህ ዕዳ ወርዶ 2.2 ቢሊዮን ወርዶ የነበረ ቢሆንም፣ ከዚያ በኋላ ግን የኢትዮጵያ ዕዳ ከዓመት ዓመት በቢሊዮን ዶላሮች ይጨምር ያዘ። የዓለም ባንክ በፈረንጆቹ 2020 ባወጣው መረጃ የአገሪቱ ዕዳ 30.36 ቢሊዮን ዶላር ነበረ። እነሆ ከሁለት ዓመታት በኋላ ኢትዮጵያ ከአገር ውስጥና ከውጭ የወሰደችው ብድር 56.6 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል ይላል የገንዘብ ሚኒስቴር። የኢትዮጵያ ዕዳ ከአገሪቱ አጠቃላይ ምርት ግማሽ ያክል መሆኑን ተከትሎ ባሉ ወቅታዊ የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ሁኔታዎች ምክንያት አበዳሪዎች በኢትዮጵያ እና በሌሎች አገራት የብድር አከፋፈሉ ዙሪያ ውይይት ይዘዋል። ከኢትዮጵያ የውጭ አበዳሪዎች የአንበሳውን ድርሻ የምትይዘው ቻይና እንዲሁም ፈረንሳይ ናቸው ስብሰባውን የሚመሩት። የኢትዮጵያ አበዳሪዎች ዕዳ ስለማሸጋሸግ ውይይት ማድረግ የጀመሩት ባለፈው ዓመት ነበር። ነገር ግን በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ግጭት ጉዳዩን አጓተተው። ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ)፣ የዓለም ባንክ፣ ሌሎች የገንዘብ ተቋማት ቻይና እና ሌሎች አበዳሪዎች ኢትዮጵያ፣ ቻድ እና ዛምቢያ ላለባቸው ዕዳ አስተያየት እንዲያደርጉ በመወትወት ላይ ናቸው። የአይኤምኤፍ ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ ዕዳ ኖሮባቸው ተጨማሪ ፈተና እየገጠማቸው ላሉ አገራት መፍትሔ መበጀት አለበት ሲሉ ለሮይተርስ ዜና ወኪል ተናግረዋል። ለመሆኑ ዕዳ ማሸጋሸግ ምንድን ነው? ኢትዮጵያ ዕዳዋን መክፈል ባትችል ምን ይፈጠራል? ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ2010 ዓ.ም. ወደ ሥልጣን ከመምጣታቸው በፊት ኢትዮጵያ የነበረባት ዕዳ 28 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ነበር ይላሉ አየለ ገላን (ዶ/ር)። የምጣኔ ሃብት ተንታኙ እንደሚሉት በወቅቱ የተፈጠረውን የፖለቲካ ለውጥ የተመለከቱ አበዳሪዎች ለኢትዮጵያ ልገሳና ብድር ሰጥተዋል። “ሁኔታው የተበላሸው ከተፈጠረው ትልቅ ተስፋ አንፃር መንግሥት የተበደረውን ገንዘብ ጥቅም ላይ አለማዋሉ ነው” ይላሉ ተንታኙ። “ብድሩን ተጠቅሞ ተጨማሪ ገቢ ማስገባት አለመቻሉ፤ በቂ ሥራ አለመፈጠሩና ገንዘቡ የውጭ ምንዛሬ አለማምጣቱ ችግር ፈጥሯል።” ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መንግሥት በፊት የነበረው አስተዳደር የወሰደው ብድር ሳይመለስ እስከ 2012 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ቢያንስ ተጨማሪ 10 ቢሊዮን ዶላር ብድር መንግሥት መውሰዱ የዕዳውን መጠን እንዳሻቀበው ያምናሉ። “ብድር መክፈል ከዚህ ቀደም ከነበረው ይልቅ አሁን አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል።” ለኢትዮጵያና ሌሎች በርካታ የአፍሪካ አገራት ብድር ከሚሰጡ መካከል አንዱ የሆነው አይኤምኤፍ፣ በፈረንጆቹ 2020 ለኢትዮጵያ 3 ቢሊዮን ዶላር ብድር አፅድቋል። ሌሎች አበዳሪዎችና የዓለም ባንክም እንዲሁ ተጨማሪ 6 ቢሊዮን ዶላርመስጠታቸውን ተከትሎ አሁን ኢትዮጵያ ያለባት ዕዳ መጠን ከ38 ቢሊዮን ዶላር አያንስም ይላሉ ተንታኙ። አይኤምኤፍ ብድሩን ከማፅደቁ በፊት በ2019 ኢትዮጵያ ብድር ለመመለስ ከሚቸገሩ አገራት መካከል እንደሆነች ገልጦ ነበር። “ይህ ማስጠንቀቂያ የኢትዮጵያ ዕዳ መጠን በ2 ቢሊዮን ዶላር ቀንሶ በነበረ ጊዜ የወጣ ነው።” የዐቢይ አሕመድ መንግሥት አበዳሪዎች ለኢትዮጵያና ለሌሎች የአፍሪካ አገራት የዕዳ ሽግሽግ [ዴት ሪስትራክቸሪንግ] እንዲያደርጉ ተደጋጋሚ ጥያቄ ሲያቀርብ ቆይቷል። ከሰሞኑ አበዳሪዎችና ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት በዚህ ጥያቄ ዙሪያ ውይይት ጀምረዋል። የምጣኔ ሃብት ሙያተኛው አየለ ገላን፣ መንግሥት የ2015 ዓ.ም. በጀትን አስመልክቶ ባቀረበው ሪፖርት በቀዳሚነት ያሰፈረው ጉዳይ ብድር መመለስ መሆኑን ያወሳሉ። ኢትዮጵያ ከሰሜኑ ጦርነት በፊት ጀምሮ የዕዳ ሽግሽግ ጥያቄ ስታቀርብ ብትቆይም በጦርነቱ ወቅት ከአበዳሪዎች ጋር የነበራት የሻከረ ግንኙነት ችግር እንደፈጠረ ተንታኙ ይገልጣሉ። “መንግሥት በበጀት ድልድል ውስጥ ብድር መክፈልን ከላይ ሲያስቀምጥ አይቼ አላውቅም” የሚሉት ተንታኙ፤ ይህ የዕዳ ጫናው ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ያሳያል ባይ ናቸው። “አሁን የቀረበው የዕዳ ሽግሽግ ጥያቄ በአጭሩ ‘ብድሩ ከአቅም በላይ ስለሆነብኝ ማሻሻያ ይደረግልኝ’ ማለት ነው።” እንደ ተንታኙ ገለፃ ሽግሽጉ በዋናነት ሦስት መንገዶች አሉት። “አንደኛው ብድሩ ከአቅሜ በላይ ስለሆነ ይሰዘርልኝ ብሎ አበዳሪን ለማስማማት መሞከር ነው። ሁለተኛው፤ የብድሩ ወለድ ከፍተኛ ስለሆነብኝ ይቀነስልኝ የሚል ሊሆን ይችላል፤ ሦስተኛው ደግሞ ብድሩን ከፍዬ የምጨርስበት ጊዜ ይራዘም የሚል ነው።” አየለ (ዶ/ር) በዓለም አቀፍ ደረጃ ብድር ወስዶ በጊዜው አለመመለስ ወንጀል ነው ይላሉ። “ከዚህ ለመራቅ አገራት አበዳሪዎቻቸው ብድሩን እንዲሽሩላቸው የሚቻላቸውን ያደርጋሉ። ይህ ካልሆነ ጥቁር መዝገብ ውስጥ ይገባሉ። ይህ ደግሞ ችግሩን የከፋ ያደርገዋል።” ከዚህ ቀደም ብዙ ጊዜ አበዳሪ ድርጅቶች የኢትዮጵያን ብድር እንደ ሰረዙ የሚያስታውሱት ተንታኙ በአሁኑ ድርድር ሊሆን የሚችለው የክፍያ ጊዜን ማራዘም እንደሚሆን ግምት አላቸው። የመሳካት ዕድል የሚያገኘው የክፍያውን ጊዜ ማርዘም ነው። “የክፍያ ጊዜን በማራዘም የሚደረግን ሽግሽግ የኢትዮጵያ መንግሥት እንደ መልካም ዜና ቢያየውም አደጋ አለው። ጊዜያዊ መፍትሔ ሊሆን ቢችልም የክፍያ ጊዜው በረዘመ ቁጥር የወለድ መጠኑም እየጨመረ ይመጣል። ይህ ለበለጠ ድህነት የሚዳርግ ነው። ‘ሾርት ተርም ጌይን፤ ሎንግ ተርም ፔይን’ (አጭር ጊዜ ጥቅም፤ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ጉዳት) ይሆናል።” በርካታ የልማት ተቋማት 40 በመቶ የሚሆኑ ከሰሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገራት ከባድ የብድር ቀውስ ውስጥ እንደሚገኙ ይገልጻሉ። ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) በፈረንጆቹ 2018 ባወጣው መረጃ አፍሪካ የዕዳ ቀውስ ውስጥ እየገባች ነው ሲል አስጠንቅቆ ነበር። ተቋሙ እንደሚለው ባለፉት አምስት ዓመታት የዕዳ ስጋት ያለባቸው የአፍሪካ አገራት ቁጥር በእጥፍ ጨምሯል። ቻይና ለአፍሪካ አገራት ብድር ከሚሰጡ መካከል ቁንጮዋ ናት። ከአፍሪካ መንግሥታት መካከል 20 በመቶው የቻይና ዕዳ አለባቸው። 35 በመቶ ብድር የሚገኘው እንደ ዓለም ባንክ ካሉ ተቋማት ሲሆን፣ 32 በመቶ ደግሞ ከግል አበዳሪዎች ነው። ባለፉት 11 ወራት [እስከ ግንቦት ወር 2014 ዓ.ም ባለው ጊዜ] መንግሥት 330 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 309 ቢሊዮን ብር ብቻ መሰብሰቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ ተናግረው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕዝብ እንደራሴዎች ፊት ቀርበው ባሰሙት ንግግር መንግሥት 500 ቢሊዮን ዶላር ወጭ አድርጓል ብለዋል። የኢትዮጵያ ወጪ ከገቢዋ አንጻር ያለው ልዩነት እንደህ እንዲሰፋ ያደረገው አገሪቱ ያለባት ዕዳ ነው። “በዚህ ዓመት 1.7 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ ከፍለናል። ይህ መቶ ቢሊዮን ብር አካባቢ ማለት ነው” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለኢትዮጵያ የ2015 በጀት እንዲሆን የመደበው ገንዘብ 786.6 ቢሊዮን ብር ነው። በወቅቱ ከዚህ ገንዘብ መካከል አብዛኛው ለዕዳ ክፍያ፣ ለመልሶ ማቋቋምና ለመከላከያ ግንባታ የሚውል መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር ጠቅሶ ነበር። የምጣኔ ሃብት ሙያተኛው አብዱልመናን አሕመድ ኢትዮጵያን ወደ ኋላ ከሚጎትቱ ፈተናዎች መካከል አንደኛው አገሪቱ ያለባት ዕዳ ነው ይላሉ። አብዱልመናን መንግሥት የግል ዘርፉን የሚያበረታታ ፖሊሲ ካልቀረፀ ምጣኔ ሃብቱን ማሳደግ ሊከብደው ይችላል ብለው ያምናሉ። “የአገሪቱ የፖለቲካ ሁኔታ፣ የማክሮ ኢኮኖሚው ጉዳይ [ለምሳሌ የዋጋ ግሽበት] እና መንግሥት ያለበት የተጠራቀመ ዕዳ ማነቆ ሆነዋል።” ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግሥት ያለበትን የዕዳ መጠን እንዲሁም ከአገሪቱ በጀት ገዘፍ የሚለው ለዕዳ ክፍያ መሆኑን ባስረዱበት ወቅት በርካታ እንደራሴዎች ጥያቄ አንስተው ነበር። የመንግሥት የበጀት አጠቃቀም ችግርና ብክነት እንዲሁም የአገር ውስጥ ገቢ የመሰብሰብ አቅም አለመጎልበት ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ይላሉ እንደራሴዎቹ። የኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት ከ2011-13 ዓ.ም. ባለው ዘመን ከዕቅድ በታች የሆነ 7.1 በመቶ ዕድገት አስመዝግቧል። ኢትዮጵያ ካለባት ዕዳ 97 በመቶ የሚሆነውን ድርሻ የሚይዘው የረጅም ጊዜ ብድርና ‘ፐብሊክና ፐብሊክሊ ጋራንቲንድ’ የተሰኘ የብድር ዓይነት እንደሆነ ኢኮኖሚስቱ አየለ ገላን ይተነትናሉ። “የረጅም ጊዜ ብድር ማለት ክፍያው ከ30 እስከ 50 ዓመታት ባለው ጊዜ ውስጥ የሚከፈል ነው። ይህ ማለት ብድሩን መመለስ አሁን የተበደረው መንግሥት ኃላፊነት ላይሆን ይችላል ማለት ነው።” ‘ፐብሊክና ፐብሊክሊ ጋሪንቲንድ’ [በሕዝብ ንብረት ዋስትና የተገኘ ብድር] የተሰኘው ደግሞ ክፍያው መመለስ ባለበት ሰዓት የመመለስ ኃላፊነት ያለበት የኢትዮጵያ ሕዝብ ሲሆን፣ ብድሩን የሚመልሰው የአሁኑ ትውልድ አይሆንም ማለት ነው ይላሉ ተንታኙ። ዓለም አቀፍ አበዳሪዎች ሲያበድሩ ብድሩ በጊዜው የማይመለስ ከሆነ እንደ ዋስትና የሚይዙት ሃብት አሊያም ንብረት ይኖራል። አገራት ብድራቸውን መከፍል ሲሳናቸው ፕሮጀክቶቻቸው እንደ መያዣ ሲያዙ መስማት የተለመደ ሆኗል። ለምሳሌ ብቸኛው የዚምባቡዌ አየር መንገድ ለደቡብ አፍሪካ መንግሥት መክፈል የነበረበትን ዕዳ ባለመክፈሉ እስከ 2019 ተይዞ ቆይቷል። አየር መንገዱ በ2019 በረራ ሲጀምር 2017 በተከማቸበት ከፍተኛ ውዝፍ ዕዳ ምክንያት ከግማሽ በላይ ሠራተኞቹን ለማሰናበት ተገዶ ነበር። ይህ ሳያንሰው ኤይር ዚምባብዌ በደኅንነት ስጋት ምክንያት በአውሮፓ አገራት አየር ክልል የመብረር ፈቃዱን ተነጥቋል። አንጎላ ደግሞ መክፈል ያለባትን 100 ሚሊዮን ዶላር ዕዳ በገንዘብ መመለስ ባለመቻሏ ለቦትሰዋና ከብቶች በመስጠት ጭምር እየከፈለች መሆኑን በ2020 የአገሪቷ ጋዜጣ አስነብቦ ነበር። የምጣኔ ሃብት ተንታኙ አየለ ገላን እንደሚሉት ኢትዮጵያ ምን አስይዛ ብድር እንደምትወስድ እስካሁን በግልፅ አይታወቅም። የሌሎች አገራትም ልምድ ተመሳሳይ መሆኑን የሚገልጡት ባለሙያው አገራት ምን አስይዘው ብድር እንደሚወስዱ የሚታወቀው በተበዳሪውና በአበዳሪው መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ ወደ ሕግ ሲያመሩ እንደሆነ ያስረዳሉ። “መንግሥት ሲበደር በእጁ የሚገኘውን የትኛውንም ሃብት አስይዞ ነው። ምንድነው የሚለው ግን ምስጢር ነው።” ተንታኙ በኬንያ እና ቻይና መካከል የተፈጠረውን በምሳሌነት ይጠቅሳሉ። “ኬንያ ከቻይና ወስዳ በነበረው ብድር ዙሪያ አለመግባባት ተፈጥሮ የሞምባሳ ወደብ እንደ ዋስትና ተይዞ እንደነበር ግልፅ የሆነው ቻይና ወደቡ የእኔ ነው ማለት ስትጀምር ነው። “ዛምቢያም እንዲሁ ከቻይና ተበድራ ለነበረው ገንዘብ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ተቋሟን ማስያዣ አድርጋ እንደ ነበር አለመግባባት ሲፈጠር ነው ያወቅነው።” ኢትዮጵያ ከአበዳሪዎቿ ጋር ግልፅ የሆነ አለመግባባት ውስጥ ስላልገባች ምን እንዳስያዘች ማወቅ አዳጋች ነው ይላሉ። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cn0gy1yvdpzo |
2health
| ከሥነ ልቦና አማካሪ ጋር የተወራ ሚስጥርን ለማጋለጥ የሚያስፈራሩት መዝባሪዎች | ፊንላንድ ውስጥ የሥነ ልቦና ምክር የሚወስዱ ሰዎች ለሀኪማቸው የተናገሩት ሚስጥር እየተሰረቀ ነው። የኮምፒውተር መረጃ መዝባሪዎች ይህን ሚስጥር ሰርቀው፤ ገንዘብ ካልተከፈላቸው ሚስጥሩን አደባባይ እንደሚያወጡት ያስፈራራሉ። በፊንላንድ የሚገኝ ትልቅ የሥነ ልቦና አማካሪ ክሊኒክ ውስጥ ህክምና ይከታተሉ የነበሩ ሰዎች ግላዊ መረጃ ተመዝብሯል። ቫስታሞ የተባለው ክሊኒክ ከ20 በላይ ቅርንጫፎችና በሺዎች የሚቆጠሩ ታካሚዎች አሉት። የግል መረጃቸው የተመዘበረባቸው ሰዎች ለፖሊስ እንዲያስታውቁም ክሊኒኩ አሳስቧል። የክሊኒኩ የመረጃ ቋት የተመዘበረው በጎሮጎሳውያኑ በኅዳር 2018 እና በሚያዝያ 2019 እንደሆነ ይገመታል። "መረጃ መዝባሪዎቹ ሀፍረተ ቢስ ናቸው" ክሊኒኩ ከፖሊስ ጋር ተባብሮ እየሠራ እንደሆነ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። አሁን ላይ የመገናኛ ብዙኃን ክፍሉ የኢሜል አድራሻ አይሠራም። እስካሁን የ300 ታካሚዎች ግላዊ መረጃ ተሰርቆ በስውሩ ድረ ገጽ 'ዳርክ ዌብ' መታተሙን አሶሽየትድ ፕሬስ ዘግቧል። ክሊኒኩ የታካሚዎች መረጃ መመዝበሩ "ከባድ ቀውስ ነው" ብሏል። ቫስታሞ፤ ታካሚዎች እርዳታ የሚያገኙበት ነጻ የስልክ መስመር ከፍቷል። ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች አንድ ነጻ የምክር አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን፤ የምክር አገልግሎቱ እንደማይቀረጽ አስታውቋል። የፊንላንድ መንግሥት ባለፈው እሑድ አስቸኳይ ስብሰባ አካሂዷል። የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትር ማርያ ኦሳሎ "ልዩ ሁኔታ ነው" ብለዋል። የበይነ መረብ ደህንነት ድርጅት የሆነው ኤፍ-ሰክዩር ሠራተኛ ሚኮ ሀፖነን "መረጃ መዝባሪዎቹ ሀፍረተ ቢስ ናቸው። አንዳንዶቹ ታካሚዎች 18 ዓመት እንኳን አልሞላቸውም" ሲል ተናግሯል።። ግላዊ መረጃቸው ከተሰረቀባቸው አንዱ የሆነው ጄሪ ለቢቢሲ እንደገለጸው፤ 'ዘ ራንሰም ጋይ' በሚል ራሱን የሚጠራ ሰው በቢትኮይን (ዲጂታል ገንዘብ) ጉቦ እንዲከፍል ጠይቆታል። መጀመሪያ ላይ የተጠየቀው 40 ዩሮ ቢሆንም፤ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ስላልከፈለ 200 ከዛም 500 ዩሮ ክፈል ተብሏል። ክፍያውን ካልፈጸመ ግን ወጣት ሳለ ከሥነ ልቦና ሀኪም ጋር ያደረገው ንግግር ይፋ እንደሚወጣም ተነግሮታል። "ከሥነ ልቦና አማካሪዬ ያደረግኳቸው ንግግሮችን የያዘ ጽሑፍ በመረጃ መዝባሪዎች እጅ መግባቱ አስጨንቆኛል" ብሏል ጄሪ። አያይዞም "በጽሑፍ የተቀመጡትን ነገሮች ከተቀረው ዓለም ጋር ለመጋራት ዝግጁ አይደለሁም" ሲል ስሜቱን ገልጿል። ከሀኪሙ ጋር ያወራው ነገር በማስታወሻ ደብተር ላይ ነበር የተጻፈው። ጽሑፉ ወደ ኮምፒውተር እንደሚሸጋገር አልተነገረውም ነበር። መረጃ መዝባሪው እንዲከፍል ያዘዘውን ገንዘብ የመክፈል አቅም እንደሌለው የሚናገረው ጄሪ፤ "ብከፍልም እንኳን የግል መረጃዬ አደባባይ እንደማይወጣ ማረጋገጫ የለኝም" ብሏል። መረጃቸው የተጋለጠባቸው 300 ሰዎች እጣ ፈንታ ይደርሰኛል ብሎ ይሰጋል። ግላዊ መረጃቸው ከመነበቡ ባሻገር ለማንነት ስርቆት ሊጋለጡ እንደሚችሉም ስጋት አለ። | ከሥነ ልቦና አማካሪ ጋር የተወራ ሚስጥርን ለማጋለጥ የሚያስፈራሩት መዝባሪዎች ፊንላንድ ውስጥ የሥነ ልቦና ምክር የሚወስዱ ሰዎች ለሀኪማቸው የተናገሩት ሚስጥር እየተሰረቀ ነው። የኮምፒውተር መረጃ መዝባሪዎች ይህን ሚስጥር ሰርቀው፤ ገንዘብ ካልተከፈላቸው ሚስጥሩን አደባባይ እንደሚያወጡት ያስፈራራሉ። በፊንላንድ የሚገኝ ትልቅ የሥነ ልቦና አማካሪ ክሊኒክ ውስጥ ህክምና ይከታተሉ የነበሩ ሰዎች ግላዊ መረጃ ተመዝብሯል። ቫስታሞ የተባለው ክሊኒክ ከ20 በላይ ቅርንጫፎችና በሺዎች የሚቆጠሩ ታካሚዎች አሉት። የግል መረጃቸው የተመዘበረባቸው ሰዎች ለፖሊስ እንዲያስታውቁም ክሊኒኩ አሳስቧል። የክሊኒኩ የመረጃ ቋት የተመዘበረው በጎሮጎሳውያኑ በኅዳር 2018 እና በሚያዝያ 2019 እንደሆነ ይገመታል። "መረጃ መዝባሪዎቹ ሀፍረተ ቢስ ናቸው" ክሊኒኩ ከፖሊስ ጋር ተባብሮ እየሠራ እንደሆነ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። አሁን ላይ የመገናኛ ብዙኃን ክፍሉ የኢሜል አድራሻ አይሠራም። እስካሁን የ300 ታካሚዎች ግላዊ መረጃ ተሰርቆ በስውሩ ድረ ገጽ 'ዳርክ ዌብ' መታተሙን አሶሽየትድ ፕሬስ ዘግቧል። ክሊኒኩ የታካሚዎች መረጃ መመዝበሩ "ከባድ ቀውስ ነው" ብሏል። ቫስታሞ፤ ታካሚዎች እርዳታ የሚያገኙበት ነጻ የስልክ መስመር ከፍቷል። ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች አንድ ነጻ የምክር አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን፤ የምክር አገልግሎቱ እንደማይቀረጽ አስታውቋል። የፊንላንድ መንግሥት ባለፈው እሑድ አስቸኳይ ስብሰባ አካሂዷል። የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትር ማርያ ኦሳሎ "ልዩ ሁኔታ ነው" ብለዋል። የበይነ መረብ ደህንነት ድርጅት የሆነው ኤፍ-ሰክዩር ሠራተኛ ሚኮ ሀፖነን "መረጃ መዝባሪዎቹ ሀፍረተ ቢስ ናቸው። አንዳንዶቹ ታካሚዎች 18 ዓመት እንኳን አልሞላቸውም" ሲል ተናግሯል።። ግላዊ መረጃቸው ከተሰረቀባቸው አንዱ የሆነው ጄሪ ለቢቢሲ እንደገለጸው፤ 'ዘ ራንሰም ጋይ' በሚል ራሱን የሚጠራ ሰው በቢትኮይን (ዲጂታል ገንዘብ) ጉቦ እንዲከፍል ጠይቆታል። መጀመሪያ ላይ የተጠየቀው 40 ዩሮ ቢሆንም፤ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ስላልከፈለ 200 ከዛም 500 ዩሮ ክፈል ተብሏል። ክፍያውን ካልፈጸመ ግን ወጣት ሳለ ከሥነ ልቦና ሀኪም ጋር ያደረገው ንግግር ይፋ እንደሚወጣም ተነግሮታል። "ከሥነ ልቦና አማካሪዬ ያደረግኳቸው ንግግሮችን የያዘ ጽሑፍ በመረጃ መዝባሪዎች እጅ መግባቱ አስጨንቆኛል" ብሏል ጄሪ። አያይዞም "በጽሑፍ የተቀመጡትን ነገሮች ከተቀረው ዓለም ጋር ለመጋራት ዝግጁ አይደለሁም" ሲል ስሜቱን ገልጿል። ከሀኪሙ ጋር ያወራው ነገር በማስታወሻ ደብተር ላይ ነበር የተጻፈው። ጽሑፉ ወደ ኮምፒውተር እንደሚሸጋገር አልተነገረውም ነበር። መረጃ መዝባሪው እንዲከፍል ያዘዘውን ገንዘብ የመክፈል አቅም እንደሌለው የሚናገረው ጄሪ፤ "ብከፍልም እንኳን የግል መረጃዬ አደባባይ እንደማይወጣ ማረጋገጫ የለኝም" ብሏል። መረጃቸው የተጋለጠባቸው 300 ሰዎች እጣ ፈንታ ይደርሰኛል ብሎ ይሰጋል። ግላዊ መረጃቸው ከመነበቡ ባሻገር ለማንነት ስርቆት ሊጋለጡ እንደሚችሉም ስጋት አለ። | https://www.bbc.com/amharic/54703285 |
2health
| እንግሊዛዊው 35 ኪሎግራም የሚመዝኑ ኩላሊቶቹ በቀዶ ህክምና ተወገዱለት | በአንግሊዝ ነዋሪ የሆነ አንድ ግለሰብ ሁለቱም ኩላሊቶች በከፍተኛ ደረጃ ትልቅ መሆናቸውን ተከትሎ እንዲወጡለት መደረጉን ሐኪሞች ተናገሩ። የ 54 ዓመቱ ዋረን ሂግስ በአጠቃላይ 35 ኪሎ ግራም የሚመዝኑትን የአካል ክፍሎቹን ለማስወገድ የሁለት ሰዓት ቀዶ ጥገና አድርጓል። ግለሰቡ ኩላሊቶቹ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ትልቅ ከመሆናቸው የተነሳ ክብረ ወሰንም ይዟል ተብሏል የአንድ ወድ ልጅ አባት የሆነው እና ፖሊሲስቲክ የተባለ የኩላሊት በሽታ ያለበት ግለሰቡ "በየትኛውም መንገድ ቢለካ" ትልቅ ኩላሊት ያለው በመሆን ክብረ ወሰን እንደሚሰብር ሐኪሞቹ እንደነገሩት አስታውቋል። በሆዱ መጠን ላይ ያለውን ልዩነት "አስገራሚ ነው" ብሏል። ከእንግሊዟ ዊንድሶር የመጣው ሂግስ ትልቁ የቀኝ ኩላሊቱ 15 ኪሎ ሲመዝን ተጨማሪ 5 ኪሎ የሚመዝን ፈሳሽም በላዩ ላይ ነበር ብሏል። ቀደም ሲል በዓለም ላይ ትልቅ የነበረው ኩላሊት በሕንድ በቀዶ ጥገና የተወገደው እና 7.4 ኪ.ግ የሚመዝነው እንደሆነ ይታመን ነበር። "የቀዶ ጥገና ሐኪሙ ሁሉንም አረጋግጦ ነበር። እናም አዎ በእያንዳንዱ መለኪያ ክብረ ወሰኑን አሻሽለነዋል።" ብሏል። "ርዝመቱ በሚለካበት ጊዜ፣ ከያዘው ፈሳሽ ጋር ሲመዘን እና ፈሳሹ ከተወገደ በኋላም አሻሽዬዋለሁ።" ያለው ግለሰቡ ሆኖም "ይህ የምኮራበት ነገር አይደለም።" ይላል ፒኬዲ በኩላሊት ውስጥ ሲስቲክ የሚባሉ ትናንሽ ፈሳሽ የተሞሉ ከረጢቶች እንዲፈጠሩ ያደርጋል። ከአምስት ዓመት በፊት በውርስ የሚመጣው ህመም ኩላሊቶቹ ከሚገባው በላይ አምስት እጥፍ እንዲያድጉ አድርጓቸዋል ሲሉ ዶክተሮቹ ተናግረዋል። ኩላሊቶቹ ሳንባውን፣ ሆዱን እና ልቡን መጉዳት ስለጀመሩ "ሕይወት አድን" ቀዶ ጥገና መደረጉ አስፈላጊ መሆኑ እንደተነገረው ሂግስ አስታውቋል። በተጨማሪ ትልቅ የሆድ እብጠት እንዲኖረው ምክንያት ሲሆን እብጠቱ ከሐምሌው ቀዶ ጥገና በኋላ "አስደናቂ" ለውጥ አምጥቷል ብሏል። ግለሰቡ በአሁኑ ወቅት ወደ ጂምናዚየም የተመለሰ ሲሆን በሚቀጥለው ዓመትም በኤሌክትሪክ ብስክሌት ትሪያትሎን (ሩጫ፣ ዋና እና ሳይክልን ያካተት ውድድር) ላይ ለመወዳደር በጉጉት እየተጠበቀ ነው። የቀድሞው የሂሳብ ባለሙያው በየሁለት ቀኑ የዲያሊሲስ ማድረጉ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰበት መሆኑን ጠቅሷል። "በዲያሊሲስ ማለፍ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ መግለጽ አልችልም" ብሏል። በሚቀጥለው ዓመት ለኩላሊት ንቅለ ተከላ ብቁ ለመሆን በመዝገቡ ውስጥ እንደሚገባ ተስፋ ያደርጋል። | እንግሊዛዊው 35 ኪሎግራም የሚመዝኑ ኩላሊቶቹ በቀዶ ህክምና ተወገዱለት በአንግሊዝ ነዋሪ የሆነ አንድ ግለሰብ ሁለቱም ኩላሊቶች በከፍተኛ ደረጃ ትልቅ መሆናቸውን ተከትሎ እንዲወጡለት መደረጉን ሐኪሞች ተናገሩ። የ 54 ዓመቱ ዋረን ሂግስ በአጠቃላይ 35 ኪሎ ግራም የሚመዝኑትን የአካል ክፍሎቹን ለማስወገድ የሁለት ሰዓት ቀዶ ጥገና አድርጓል። ግለሰቡ ኩላሊቶቹ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ትልቅ ከመሆናቸው የተነሳ ክብረ ወሰንም ይዟል ተብሏል የአንድ ወድ ልጅ አባት የሆነው እና ፖሊሲስቲክ የተባለ የኩላሊት በሽታ ያለበት ግለሰቡ "በየትኛውም መንገድ ቢለካ" ትልቅ ኩላሊት ያለው በመሆን ክብረ ወሰን እንደሚሰብር ሐኪሞቹ እንደነገሩት አስታውቋል። በሆዱ መጠን ላይ ያለውን ልዩነት "አስገራሚ ነው" ብሏል። ከእንግሊዟ ዊንድሶር የመጣው ሂግስ ትልቁ የቀኝ ኩላሊቱ 15 ኪሎ ሲመዝን ተጨማሪ 5 ኪሎ የሚመዝን ፈሳሽም በላዩ ላይ ነበር ብሏል። ቀደም ሲል በዓለም ላይ ትልቅ የነበረው ኩላሊት በሕንድ በቀዶ ጥገና የተወገደው እና 7.4 ኪ.ግ የሚመዝነው እንደሆነ ይታመን ነበር። "የቀዶ ጥገና ሐኪሙ ሁሉንም አረጋግጦ ነበር። እናም አዎ በእያንዳንዱ መለኪያ ክብረ ወሰኑን አሻሽለነዋል።" ብሏል። "ርዝመቱ በሚለካበት ጊዜ፣ ከያዘው ፈሳሽ ጋር ሲመዘን እና ፈሳሹ ከተወገደ በኋላም አሻሽዬዋለሁ።" ያለው ግለሰቡ ሆኖም "ይህ የምኮራበት ነገር አይደለም።" ይላል ፒኬዲ በኩላሊት ውስጥ ሲስቲክ የሚባሉ ትናንሽ ፈሳሽ የተሞሉ ከረጢቶች እንዲፈጠሩ ያደርጋል። ከአምስት ዓመት በፊት በውርስ የሚመጣው ህመም ኩላሊቶቹ ከሚገባው በላይ አምስት እጥፍ እንዲያድጉ አድርጓቸዋል ሲሉ ዶክተሮቹ ተናግረዋል። ኩላሊቶቹ ሳንባውን፣ ሆዱን እና ልቡን መጉዳት ስለጀመሩ "ሕይወት አድን" ቀዶ ጥገና መደረጉ አስፈላጊ መሆኑ እንደተነገረው ሂግስ አስታውቋል። በተጨማሪ ትልቅ የሆድ እብጠት እንዲኖረው ምክንያት ሲሆን እብጠቱ ከሐምሌው ቀዶ ጥገና በኋላ "አስደናቂ" ለውጥ አምጥቷል ብሏል። ግለሰቡ በአሁኑ ወቅት ወደ ጂምናዚየም የተመለሰ ሲሆን በሚቀጥለው ዓመትም በኤሌክትሪክ ብስክሌት ትሪያትሎን (ሩጫ፣ ዋና እና ሳይክልን ያካተት ውድድር) ላይ ለመወዳደር በጉጉት እየተጠበቀ ነው። የቀድሞው የሂሳብ ባለሙያው በየሁለት ቀኑ የዲያሊሲስ ማድረጉ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰበት መሆኑን ጠቅሷል። "በዲያሊሲስ ማለፍ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ መግለጽ አልችልም" ብሏል። በሚቀጥለው ዓመት ለኩላሊት ንቅለ ተከላ ብቁ ለመሆን በመዝገቡ ውስጥ እንደሚገባ ተስፋ ያደርጋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-58825476 |
5sports
| አንጋፋው የስፖርት ሰው ፍቅሩ ኪዳኔ ሲታወሱ | በኢትዮጵያ የተለያዩ ስፖርቶች ውስጥ አሻራቸውን ካሳረፉ ሰዎች መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ። በአገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያውን የእግር ኳስ ግጥሚያ በሬዲዮ ከማስተላለፍ አንስቶ፣ በሬዲዮና በጋዜጣ ላይ ስፖርትን የሚመለከቱ ዘገባዎች ቦታ እንዲያገኙ አድርገዋል። በአህጉራዊ እና በዓለም አቀፍ የስፖርት ተቋማት ውስጥ ጉልህ ሚና ካላቸው ጥቂት ኢትዮጵያውያን መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ። በ87 ዓመታቸው ያረፉት አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ እንዴት ይታወሳሉ? በኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኝነት ሙያ የመጀመሪያው የእግር ኳስ ግጥሚያ በሬዲዮ ከማሰራጨት እስከ ፀሐፊ እና የስፖርት ሕትመቶች ዋና አርታዒነት ደርሰዋል። በስፖርት እውቀታቸው ዓለም አቀፍ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ሴክሬታሪያት ፀሐፊ ሆነው አገልግለዋል። በዘረፉ ለስመዘገቡት አስተዋጽኦ በዓለም አቀፉ የስፖርት ፕሬስ ማኅበር የሕይወት ዘመን ስኬት ሽልማትን ተቀብለዋል። ጥቅምት 01/2015 ዓ.ም. ፈረንሳይ ውስጥ በ87 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን አንጋፋውን የስፖርት ሰው ፍቅሩ ኪዳኔን ታዋቂው የስፖርት ጋዜጠኛው ገነነ መኩሪያ “የሕይወት ዘመናቸውን በሙሉ ለኢትዮጵያ ስፖርት ያዋሉ” ሲል ይገልጻቸዋል። አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ እአአ 2016 ላይ ለሲቢሴስ አማርኛ ሲናገሩ፤ በኢትዮጵያ የሕትመት ውጤቶች እና የሬዲዮ ስርጭት ውስጥ የስፖርት ፕሮግራሞች እንዲከፈቱ ጥረት ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል። አቶ ፍቅሩ እርሳቸው በጀመሩት የመጀመሪያው የሬዲዮ ፕሮግራም የኢትዮጵያ እና የሱዳን ብሔራዊ ቡድኖችን የእግር ኳስ ግጥሚያ ለመጀመሪያ ጊዜ ማሰተላለፋቸውን ይገልጻሉ። አቶ ፍቅሩ ይህን ጨዋታ እንዴት በሬዲዮ እንዲያስተላለፉ የተደረገው በድንገትና ሳያስቡት ነበር። ይህም ጨዋታውን ለሕዝብ ጆሮ እንደሚያደርሱ ሳይነገራቸው እና ምንም አይነት ዝግጅት ሳያደርጉ ነበር የመጀመሪያውን የቀጥታ ሥርጭት ያስተላለፉት። አቶ ፍቅሩ ይህን ጨዋታ እንዴት በሬዲዮ እንዲያስተላለፉ የተደረገው በድንገትና ሳያስቡት ነበር። ይህም ጨዋታውን ለሕዝብ ጆሮ እንደሚያደርሱ ሳይነገራቸው እና ምንም አይነት ዝግጅት ሳያደርጉ ነበር የመጀመሪያውን የቀጥታ ስርጭት ያስተላለፉት። ሱዳኖች የእግር ኳስ ጨዋታውን ከአዲስ አበባ በቀጥታ በሬዲዮ እንደሚያስተላልፉ የተረዱት አቶ ይደነቃቸው ተስማ፣ እኛስ ለምን አናስተላልፍም? በማለት ሐሳቡን በድንገት እንዳመጡት ጋዜጠኛ ገነነ ይናገራል። ከዚያም ከኢትዮጵያ ሬዲዮ ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር የቀጥታ ሥርጭቱ በመፈቀዱ ጨዋታው ከመጀመሩ ከደቂቃዎች በፊት አቶ ፍቅሩ እንደሚፈለጉ በድምጽ ማጉያ ተጠርተው ነበር በድንገት ተጠርተው የቀጥታ ሥርጭት ማይክሮፎን የቸበጡት ይላል ገነነ። አቶ ፍቅሩም “ጨዋታው ሊጀመር 10 ደቂቃዎች ብቻ ሲቀሩት ትፈለጋለህ ተብዬ ተጠርቼ ስሄድ፣ አቶ ይድነቃቸው አንተ እኮ ነው የምትፈለገው ብሎ የተጫዋቾችን አሰላለፍ ሰጥቶ ጨዋታውን እንዳስተላልፍ ነገረኝ” ሲሉ አስታውሰዋል። “ጨዋታው ሊጀመር 10 ደቂቃዎች ብቻ ሲቀሩት ትፈለጋለህ ተብዬ ተጠርቼ ስሄድ፣ አቶ ይድነቃቸው አንተ እኮ ነው የምትፈለገው ብሎ የተጫዋቾችን አሰላለፍ ሰጥቶ ጨዋታውን እንዳስተላልፍ ነገረኝ።” ከዚያ በኋላ በኢትዮጵያ የስፖርት ውድድር ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ ስታዲዮም (በ1948 ዓ.ም.) የእግር ኳስ ጨዋታ በሬዲያ በቀጥታ በሬዲዮ በማስተላከፍ አቶ ፍቅሩ ቀዳሚው ሆኑ። በሕትመት ውጤቶች ላይም ቢሆን ስፖርታዊ ጉዳዮችን መዘገብ የተጀመሩት በአቶ ፍቅሩ ጥረት ነበር። ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ ለቢቢሲ ሲናገር፤ “በጋዜጦች ላይም ስፖርት የሚባል አይታወቅም ነበር። ከ1950 በኋላ ፍቅሩ ነበር መጻፍ የጀመረው።” ገነነ እንደሚለው በባዶ እግሩ የኢሊምፒክ ማራቶንን በማሸነፍ የሚታወቀው የዓለማችን ታላቁ የማራቶን ሯጭ አበበ ቢቂላ በጫማ እንዲሮጥ ያደረጉት አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ ናቸው። “ፍቅሩ ከአንድ ጫማ አምራች ድርጅት ጋር ተነጋግሮ ለአበበ በነጻ የመሮጫ ጫማ እንዲሰራለት አስደርጓል። ጫማ አምራቹም በአበበ ስም ታዋቂነትን ለማግኘት ችሏል።” በኒውዮርክ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ውስጥ ሲሰሩ የቆዩት አቶ ፍቅሩ፣ ወታደራዊው መንግሥት ወደ ሥልጣን በመጣበት ጊዜ እንደወጡ ቀርተው ለበርካታ ዘመናት በተለያዩ አገራት ውስጥ ኖረዋል። ነገር ግን ባሉበት ሆነው በኢትዮጵያ የተለያዩ ስፖርቶች እንዲጎለብቱ የሚችሉትን አስተዋጽኦ ሲያበረክቱ ቆይተው፤ አብዛኛውን እድሜያቸውን በቆዩባቸው የውጭ አገራት ውስጥ ሆነው እንኳን ለኢትዮጵያ ስፖርት ሲሰሩ እንቆዩ ገነነ ገልጿል። አቶ ፍቅሩ በኢትዮጵያ የተለያዩ ስፖርቶች ውስጥ ፍቅሩ ያልገቡበት ዘርፍ የለም የሚለው ገነነ፣ አሁን ትኩረትን እየሳበ ያለው የሴቶች እግር ኳስ እንዲጎለበት የአቶ ፍቅሩ ሚና ጉል እንደነበር ይጠቅሳል። ፍቅሩ ከእግር ኳስ ባሻገር በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ውስጥ ኢትዮጵያ ውክልና እንዲኖራት በግሉ የቻለውን ሁሉ ሲያደርግ እንደቆየ የሚናገረው ጋዜጠኛ ገነነ፤ ብዙም አቅም የሌላቸው የስፖርት ፌዴሬሽኖችን በመወከል በእራሱ ወጪ በዓለም አቀፍ ስብሰባዎች ላይ ይሳተፍ ነበር። እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ የነበረውን የዘር መድልዎ (አፓርታይድ) ሥርዓት በመቃወም አገሪቱ ከዓለም አቀፍ የስፖርት ውድድሮች እንድትታገድ ከአቶ ይድነቃቸው ተሰማ ጋር ከፍተኛ ጥረት ከማድረግ ባሻገር፤ በዓለም አቀፍ ሕትመቶች ላይ ፀረ አፓርታይ የቅስቀሳ ጽሁፎችንም ያቀርብ እንደነበር ገነነ አስታወሷል። አቶ ፍቅሩ ስፖርት በመገናኛ ብዙኃን ላይ ቦታ እንዲያገኝ ከመጣራቸው ባሻገር፣ ቴሌቪዥን ባልተስፋፋበት በዚያ ዘመን ከአዲስ አበባ ውጪ ያለው ስፖርት አፍቃሪ ታላላቅ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን እንዲመለከትም አስችለዋል። ለዚህም እአአ 1958 በስዊዲን አገር ተካሂዶ የፔሌ ትውልድን የያዘው የብራዚል ብሔራዊ ቡድን ዋንጫ የወሰደችበትን ግጥሚያ አቶ ፍቅሩ በክፍለ አገር ከተሞች እየተጓዙ በፕሮጀክተር ጨዋታውን ያሳዩ እንደነበረ ጋዜጠኛ ገነነ ይናገራል። “እኛ ፔሌ፣ ጋሪንቻ የሚባሉትን በስም እንኳ አናውቃቸውም ነበር። እሱ በየክፍለ አገሩ ዞሮ ካሳየ በኋላ ነው ተጫዋቾቹ ኢትዮጵያ ውስጥ የታወቁት።” አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ በስፖርት ጋዜጠኝነት ሙያ ከማገልገላቸው በተጨማሪ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ፣ የማስታወቂያ ባለሙያ ሆነውም ሠርተዋል። በተጨማሪም በመንግሥታቱ ድርጅት በኩል ኢትዮጵያ ወደ ኮንጎ ጦሯን ባሰማራችበት ወቅት ጦሩን የሚመሩት የኢትዮጵያ ጄኔራሎች ፈረንሳይኛ የሚናገር ወጣት በመፈለጋቸው፣ ፍቅሩ የመቶ አለቃ ማዕረግ ይዘው ወደ ኮንጎ መዝመተውም ነበር። ይህ አጋጣሚ ነበር አቶ ፍቅሩ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ የሥራ ዕድል በር ከፍቶላቸው የማስታወቂያ ባለሙያ ሆኖ የመስራት ዕድልን እንደከፈተላቸው ጠቅሰው ነበር። አቶ ፍቅሩ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ስለኦሊምፒክ ጨዋታዎች ያለው እውቀት እምብዛም ባልነበረበት ወቅት ውድድሩን ለአገሬው ለማስተዋወቅ መጽሐፍ እስከ ማሳተም ደርሰው ነበር። “የኦሊምፒክ ጨዋታ የሚል መጽሐፍ በ1960 አሳተምኩ። ይህን መጽሐፍ ያዘጋጀሁት ሕዝቡ ስለ ኦሊምፒክ ጨዋታዎች እውቀት እንዲኖረው ነው።” ይህን መጸሐፍም ለትምህርት ሚኒስቴር በመስጠት በአገሪቱ ባሉ ትምህርት ቤቶች እንዲታደሉ በማድረግ ወደ ወጣቶች እንዲደርስ አድርገዋል። አቶ ፍቅሩ ከስፖርት ጋር በተቆራኘው ሕይወታቸው በበርካታ ኃላፊነቶች ላይ አገልግለዋል። በኢትዮጵያ የወቅቱ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ውስጥ ተቀጥተው የኢትዮጵያ የብስክሌት ፌዴሬሽን፣ የቴኒስ ፌዴሬሽን፣ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ዋና ፀሐፊ እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል። አቶ ፍቅሩ የመጀመሪያውን የኢትዮጵያ የስፖርት ጋዜጠኞች ማኅበርን አቋቁመው የማኅበሩ ፕሬዝዳንት በመሆንም ሠርተዋል። ከኢትዮጵያም ውጪ አቶ ፍቅሩ ከኦሊምፒክ ውድድር ጋር ባላቸው ቁርኝት ትልቅ የሥልጣን ደረጃ ላይ መድረስም ችለው ነበር። ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ አቶ ፍቅሩ የመጀመሪያው ጥቁር የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ እና የፕሬዝዳንቱ ልዩ አማካሪ ሆነው ተሹመው እንደነበረ ይገራሉ። የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን የፕሬዝዳንቱ ልዩ አማካሪ፣ የአፍሪካ የሰፖርት ጋዜጠኞች ማኅበር ዋና ፀሐፊ በመሆን አገልግለዋል። የፊፋ የፕሬስ ኮሚቴ አባል የነበሩ ሲሆን እንደ ቢቢሲ፣ የአሜሪካ ድምጽ፣ ሬዲዮ ፍራንስ ኢንተርናሽናል ላሉ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ዘገባዎችን ይሰሩም ነበር። | አንጋፋው የስፖርት ሰው ፍቅሩ ኪዳኔ ሲታወሱ በኢትዮጵያ የተለያዩ ስፖርቶች ውስጥ አሻራቸውን ካሳረፉ ሰዎች መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ። በአገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያውን የእግር ኳስ ግጥሚያ በሬዲዮ ከማስተላለፍ አንስቶ፣ በሬዲዮና በጋዜጣ ላይ ስፖርትን የሚመለከቱ ዘገባዎች ቦታ እንዲያገኙ አድርገዋል። በአህጉራዊ እና በዓለም አቀፍ የስፖርት ተቋማት ውስጥ ጉልህ ሚና ካላቸው ጥቂት ኢትዮጵያውያን መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ። በ87 ዓመታቸው ያረፉት አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ እንዴት ይታወሳሉ? በኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኝነት ሙያ የመጀመሪያው የእግር ኳስ ግጥሚያ በሬዲዮ ከማሰራጨት እስከ ፀሐፊ እና የስፖርት ሕትመቶች ዋና አርታዒነት ደርሰዋል። በስፖርት እውቀታቸው ዓለም አቀፍ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ሴክሬታሪያት ፀሐፊ ሆነው አገልግለዋል። በዘረፉ ለስመዘገቡት አስተዋጽኦ በዓለም አቀፉ የስፖርት ፕሬስ ማኅበር የሕይወት ዘመን ስኬት ሽልማትን ተቀብለዋል። ጥቅምት 01/2015 ዓ.ም. ፈረንሳይ ውስጥ በ87 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን አንጋፋውን የስፖርት ሰው ፍቅሩ ኪዳኔን ታዋቂው የስፖርት ጋዜጠኛው ገነነ መኩሪያ “የሕይወት ዘመናቸውን በሙሉ ለኢትዮጵያ ስፖርት ያዋሉ” ሲል ይገልጻቸዋል። አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ እአአ 2016 ላይ ለሲቢሴስ አማርኛ ሲናገሩ፤ በኢትዮጵያ የሕትመት ውጤቶች እና የሬዲዮ ስርጭት ውስጥ የስፖርት ፕሮግራሞች እንዲከፈቱ ጥረት ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል። አቶ ፍቅሩ እርሳቸው በጀመሩት የመጀመሪያው የሬዲዮ ፕሮግራም የኢትዮጵያ እና የሱዳን ብሔራዊ ቡድኖችን የእግር ኳስ ግጥሚያ ለመጀመሪያ ጊዜ ማሰተላለፋቸውን ይገልጻሉ። አቶ ፍቅሩ ይህን ጨዋታ እንዴት በሬዲዮ እንዲያስተላለፉ የተደረገው በድንገትና ሳያስቡት ነበር። ይህም ጨዋታውን ለሕዝብ ጆሮ እንደሚያደርሱ ሳይነገራቸው እና ምንም አይነት ዝግጅት ሳያደርጉ ነበር የመጀመሪያውን የቀጥታ ሥርጭት ያስተላለፉት። አቶ ፍቅሩ ይህን ጨዋታ እንዴት በሬዲዮ እንዲያስተላለፉ የተደረገው በድንገትና ሳያስቡት ነበር። ይህም ጨዋታውን ለሕዝብ ጆሮ እንደሚያደርሱ ሳይነገራቸው እና ምንም አይነት ዝግጅት ሳያደርጉ ነበር የመጀመሪያውን የቀጥታ ስርጭት ያስተላለፉት። ሱዳኖች የእግር ኳስ ጨዋታውን ከአዲስ አበባ በቀጥታ በሬዲዮ እንደሚያስተላልፉ የተረዱት አቶ ይደነቃቸው ተስማ፣ እኛስ ለምን አናስተላልፍም? በማለት ሐሳቡን በድንገት እንዳመጡት ጋዜጠኛ ገነነ ይናገራል። ከዚያም ከኢትዮጵያ ሬዲዮ ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር የቀጥታ ሥርጭቱ በመፈቀዱ ጨዋታው ከመጀመሩ ከደቂቃዎች በፊት አቶ ፍቅሩ እንደሚፈለጉ በድምጽ ማጉያ ተጠርተው ነበር በድንገት ተጠርተው የቀጥታ ሥርጭት ማይክሮፎን የቸበጡት ይላል ገነነ። አቶ ፍቅሩም “ጨዋታው ሊጀመር 10 ደቂቃዎች ብቻ ሲቀሩት ትፈለጋለህ ተብዬ ተጠርቼ ስሄድ፣ አቶ ይድነቃቸው አንተ እኮ ነው የምትፈለገው ብሎ የተጫዋቾችን አሰላለፍ ሰጥቶ ጨዋታውን እንዳስተላልፍ ነገረኝ” ሲሉ አስታውሰዋል። “ጨዋታው ሊጀመር 10 ደቂቃዎች ብቻ ሲቀሩት ትፈለጋለህ ተብዬ ተጠርቼ ስሄድ፣ አቶ ይድነቃቸው አንተ እኮ ነው የምትፈለገው ብሎ የተጫዋቾችን አሰላለፍ ሰጥቶ ጨዋታውን እንዳስተላልፍ ነገረኝ።” ከዚያ በኋላ በኢትዮጵያ የስፖርት ውድድር ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ ስታዲዮም (በ1948 ዓ.ም.) የእግር ኳስ ጨዋታ በሬዲያ በቀጥታ በሬዲዮ በማስተላከፍ አቶ ፍቅሩ ቀዳሚው ሆኑ። በሕትመት ውጤቶች ላይም ቢሆን ስፖርታዊ ጉዳዮችን መዘገብ የተጀመሩት በአቶ ፍቅሩ ጥረት ነበር። ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ ለቢቢሲ ሲናገር፤ “በጋዜጦች ላይም ስፖርት የሚባል አይታወቅም ነበር። ከ1950 በኋላ ፍቅሩ ነበር መጻፍ የጀመረው።” ገነነ እንደሚለው በባዶ እግሩ የኢሊምፒክ ማራቶንን በማሸነፍ የሚታወቀው የዓለማችን ታላቁ የማራቶን ሯጭ አበበ ቢቂላ በጫማ እንዲሮጥ ያደረጉት አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ ናቸው። “ፍቅሩ ከአንድ ጫማ አምራች ድርጅት ጋር ተነጋግሮ ለአበበ በነጻ የመሮጫ ጫማ እንዲሰራለት አስደርጓል። ጫማ አምራቹም በአበበ ስም ታዋቂነትን ለማግኘት ችሏል።” በኒውዮርክ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ውስጥ ሲሰሩ የቆዩት አቶ ፍቅሩ፣ ወታደራዊው መንግሥት ወደ ሥልጣን በመጣበት ጊዜ እንደወጡ ቀርተው ለበርካታ ዘመናት በተለያዩ አገራት ውስጥ ኖረዋል። ነገር ግን ባሉበት ሆነው በኢትዮጵያ የተለያዩ ስፖርቶች እንዲጎለብቱ የሚችሉትን አስተዋጽኦ ሲያበረክቱ ቆይተው፤ አብዛኛውን እድሜያቸውን በቆዩባቸው የውጭ አገራት ውስጥ ሆነው እንኳን ለኢትዮጵያ ስፖርት ሲሰሩ እንቆዩ ገነነ ገልጿል። አቶ ፍቅሩ በኢትዮጵያ የተለያዩ ስፖርቶች ውስጥ ፍቅሩ ያልገቡበት ዘርፍ የለም የሚለው ገነነ፣ አሁን ትኩረትን እየሳበ ያለው የሴቶች እግር ኳስ እንዲጎለበት የአቶ ፍቅሩ ሚና ጉል እንደነበር ይጠቅሳል። ፍቅሩ ከእግር ኳስ ባሻገር በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ውስጥ ኢትዮጵያ ውክልና እንዲኖራት በግሉ የቻለውን ሁሉ ሲያደርግ እንደቆየ የሚናገረው ጋዜጠኛ ገነነ፤ ብዙም አቅም የሌላቸው የስፖርት ፌዴሬሽኖችን በመወከል በእራሱ ወጪ በዓለም አቀፍ ስብሰባዎች ላይ ይሳተፍ ነበር። እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ የነበረውን የዘር መድልዎ (አፓርታይድ) ሥርዓት በመቃወም አገሪቱ ከዓለም አቀፍ የስፖርት ውድድሮች እንድትታገድ ከአቶ ይድነቃቸው ተሰማ ጋር ከፍተኛ ጥረት ከማድረግ ባሻገር፤ በዓለም አቀፍ ሕትመቶች ላይ ፀረ አፓርታይ የቅስቀሳ ጽሁፎችንም ያቀርብ እንደነበር ገነነ አስታወሷል። አቶ ፍቅሩ ስፖርት በመገናኛ ብዙኃን ላይ ቦታ እንዲያገኝ ከመጣራቸው ባሻገር፣ ቴሌቪዥን ባልተስፋፋበት በዚያ ዘመን ከአዲስ አበባ ውጪ ያለው ስፖርት አፍቃሪ ታላላቅ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን እንዲመለከትም አስችለዋል። ለዚህም እአአ 1958 በስዊዲን አገር ተካሂዶ የፔሌ ትውልድን የያዘው የብራዚል ብሔራዊ ቡድን ዋንጫ የወሰደችበትን ግጥሚያ አቶ ፍቅሩ በክፍለ አገር ከተሞች እየተጓዙ በፕሮጀክተር ጨዋታውን ያሳዩ እንደነበረ ጋዜጠኛ ገነነ ይናገራል። “እኛ ፔሌ፣ ጋሪንቻ የሚባሉትን በስም እንኳ አናውቃቸውም ነበር። እሱ በየክፍለ አገሩ ዞሮ ካሳየ በኋላ ነው ተጫዋቾቹ ኢትዮጵያ ውስጥ የታወቁት።” አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ በስፖርት ጋዜጠኝነት ሙያ ከማገልገላቸው በተጨማሪ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ፣ የማስታወቂያ ባለሙያ ሆነውም ሠርተዋል። በተጨማሪም በመንግሥታቱ ድርጅት በኩል ኢትዮጵያ ወደ ኮንጎ ጦሯን ባሰማራችበት ወቅት ጦሩን የሚመሩት የኢትዮጵያ ጄኔራሎች ፈረንሳይኛ የሚናገር ወጣት በመፈለጋቸው፣ ፍቅሩ የመቶ አለቃ ማዕረግ ይዘው ወደ ኮንጎ መዝመተውም ነበር። ይህ አጋጣሚ ነበር አቶ ፍቅሩ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ የሥራ ዕድል በር ከፍቶላቸው የማስታወቂያ ባለሙያ ሆኖ የመስራት ዕድልን እንደከፈተላቸው ጠቅሰው ነበር። አቶ ፍቅሩ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ስለኦሊምፒክ ጨዋታዎች ያለው እውቀት እምብዛም ባልነበረበት ወቅት ውድድሩን ለአገሬው ለማስተዋወቅ መጽሐፍ እስከ ማሳተም ደርሰው ነበር። “የኦሊምፒክ ጨዋታ የሚል መጽሐፍ በ1960 አሳተምኩ። ይህን መጽሐፍ ያዘጋጀሁት ሕዝቡ ስለ ኦሊምፒክ ጨዋታዎች እውቀት እንዲኖረው ነው።” ይህን መጸሐፍም ለትምህርት ሚኒስቴር በመስጠት በአገሪቱ ባሉ ትምህርት ቤቶች እንዲታደሉ በማድረግ ወደ ወጣቶች እንዲደርስ አድርገዋል። አቶ ፍቅሩ ከስፖርት ጋር በተቆራኘው ሕይወታቸው በበርካታ ኃላፊነቶች ላይ አገልግለዋል። በኢትዮጵያ የወቅቱ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ውስጥ ተቀጥተው የኢትዮጵያ የብስክሌት ፌዴሬሽን፣ የቴኒስ ፌዴሬሽን፣ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ዋና ፀሐፊ እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል። አቶ ፍቅሩ የመጀመሪያውን የኢትዮጵያ የስፖርት ጋዜጠኞች ማኅበርን አቋቁመው የማኅበሩ ፕሬዝዳንት በመሆንም ሠርተዋል። ከኢትዮጵያም ውጪ አቶ ፍቅሩ ከኦሊምፒክ ውድድር ጋር ባላቸው ቁርኝት ትልቅ የሥልጣን ደረጃ ላይ መድረስም ችለው ነበር። ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ አቶ ፍቅሩ የመጀመሪያው ጥቁር የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ እና የፕሬዝዳንቱ ልዩ አማካሪ ሆነው ተሹመው እንደነበረ ይገራሉ። የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን የፕሬዝዳንቱ ልዩ አማካሪ፣ የአፍሪካ የሰፖርት ጋዜጠኞች ማኅበር ዋና ፀሐፊ በመሆን አገልግለዋል። የፊፋ የፕሬስ ኮሚቴ አባል የነበሩ ሲሆን እንደ ቢቢሲ፣ የአሜሪካ ድምጽ፣ ሬዲዮ ፍራንስ ኢንተርናሽናል ላሉ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ዘገባዎችን ይሰሩም ነበር። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cx76v13n28eo |
5sports
| በሩዋንዳ መንግሥት ስፖንሰር በሚደረገው የአርሰናል ክለብ ሽንፈት ፕሬዚዳንት ካጋሜ ብስጭታቸውን ገለፁ | የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት እና የአርሰናሉ ደጋፊ ፖል ካጋሜ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን መክፈቻ ቀን በክለቡ አስደንጋጭ ሽንፈት ብስጭታቸውን ገልፀዋል። ለ74 ዓመታት ያህል በከፍተኛ ሊጎች ውስጥ ያልነበረው ብሬንትፎርድ አርሰናልን 2-0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። በሩዋንዳ መንግሥት ስፖንሰር የሚደረገው አርሰናል ክለብን በተመለከተ ፕሬዚዳንት ካጋሜ ስለ መድፈኞቹ በርካታ ጊዜ አስተያየታቸውን ይሰጣሉ። አርብ ዕለት ከተደረገው ጨዋታ በኋላ ፕሬዚዳንት በትዊተር ገፃቸው "ለሁኔታዎች ይቅርታ እያደረግን ወይም የማይረቡ ነገሮችን መቀበል የለብንም። አንድ ቡድን መገንባት ያለበት ለማሸነፍና ለማሸነፍ ዓላማ ብቻ ነው" ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ በሁለት ተጨማሪ የትዊተር መልዕክቶቻቸው ክለቡ ስኬታማ የሚያደርገውን ዕቅድ እንዲያመጣ የጠየቁ ሲሆን "አድናቂዎች እንዲህ አይነት ሁኔታዎችን መልመድ አይገባቸውም" ብለዋል። ከአውሮፓውያኑ 2018 ጀምሮ የሩዋንዳ መንግሥት ከ 42 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጣ የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ከክለቡ ጋር አድርጓል። ይህም በአርሴናል የመለዮ ሸሚዝ እጀታ ላይ የሚታየውን "ሩዋንዳን ጎብኙ" አርማ ያካትታል። ተቺዎች ለሀብታም የእግር ኳስ ክለብ ድጎማ የሚሰጡ የደሃ አፍሪካዊት ሀገር አምባገነናዊ መሪ ምሳሌ ናቸው ቢሉም ነገር ግን የሩዋንዳ መንግሥት በበኩሉ የስፖንሰር ገቢው በቀጥታ ከሚገኘው በቱሪዝም ገቢው ነው በማለት ይከራከራል። በፕሬዚዳንት ካጋሜ አገዛዝ ዘመን ወደብ አልባዋ አገር በአውሮፓውያኑ 1990 ዎቹ ከተከሰተው የብሔር ግጭትና ዘር ማጥፋት አገግማለች። በአውሮፓውያኑ 2018 የዓለም ባንክ ሃገሪቱ እያከናወነች ያለውን "አስደናቂ የልማት ስኬቶች" አመስግኗል። ነገር ግን ፕሬዚዳንቱ በፖለቲካ እና በሰብአዊ መብቶች አያያዝ በአገር ውስጥ እና በውጭ ትችት ይገጥማቸዋል። | በሩዋንዳ መንግሥት ስፖንሰር በሚደረገው የአርሰናል ክለብ ሽንፈት ፕሬዚዳንት ካጋሜ ብስጭታቸውን ገለፁ የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት እና የአርሰናሉ ደጋፊ ፖል ካጋሜ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን መክፈቻ ቀን በክለቡ አስደንጋጭ ሽንፈት ብስጭታቸውን ገልፀዋል። ለ74 ዓመታት ያህል በከፍተኛ ሊጎች ውስጥ ያልነበረው ብሬንትፎርድ አርሰናልን 2-0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። በሩዋንዳ መንግሥት ስፖንሰር የሚደረገው አርሰናል ክለብን በተመለከተ ፕሬዚዳንት ካጋሜ ስለ መድፈኞቹ በርካታ ጊዜ አስተያየታቸውን ይሰጣሉ። አርብ ዕለት ከተደረገው ጨዋታ በኋላ ፕሬዚዳንት በትዊተር ገፃቸው "ለሁኔታዎች ይቅርታ እያደረግን ወይም የማይረቡ ነገሮችን መቀበል የለብንም። አንድ ቡድን መገንባት ያለበት ለማሸነፍና ለማሸነፍ ዓላማ ብቻ ነው" ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ በሁለት ተጨማሪ የትዊተር መልዕክቶቻቸው ክለቡ ስኬታማ የሚያደርገውን ዕቅድ እንዲያመጣ የጠየቁ ሲሆን "አድናቂዎች እንዲህ አይነት ሁኔታዎችን መልመድ አይገባቸውም" ብለዋል። ከአውሮፓውያኑ 2018 ጀምሮ የሩዋንዳ መንግሥት ከ 42 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጣ የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ከክለቡ ጋር አድርጓል። ይህም በአርሴናል የመለዮ ሸሚዝ እጀታ ላይ የሚታየውን "ሩዋንዳን ጎብኙ" አርማ ያካትታል። ተቺዎች ለሀብታም የእግር ኳስ ክለብ ድጎማ የሚሰጡ የደሃ አፍሪካዊት ሀገር አምባገነናዊ መሪ ምሳሌ ናቸው ቢሉም ነገር ግን የሩዋንዳ መንግሥት በበኩሉ የስፖንሰር ገቢው በቀጥታ ከሚገኘው በቱሪዝም ገቢው ነው በማለት ይከራከራል። በፕሬዚዳንት ካጋሜ አገዛዝ ዘመን ወደብ አልባዋ አገር በአውሮፓውያኑ 1990 ዎቹ ከተከሰተው የብሔር ግጭትና ዘር ማጥፋት አገግማለች። በአውሮፓውያኑ 2018 የዓለም ባንክ ሃገሪቱ እያከናወነች ያለውን "አስደናቂ የልማት ስኬቶች" አመስግኗል። ነገር ግን ፕሬዚዳንቱ በፖለቲካ እና በሰብአዊ መብቶች አያያዝ በአገር ውስጥ እና በውጭ ትችት ይገጥማቸዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-58220075 |
2health
| አዘውትሮ ምሽት አራት ሰዓት አካባቢ መተኛት ለልብ ችግር የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል- ጥናት | ከምሽቱ 4 ሰዓት እስከ 5 ሰዓት ባለው ጊዜ አዘውትሮ መተኛት ለተሻለ የልብ ጤንነት እንደሚረዳ በ88 ሺህ በጎ ፈቃደኞች ላይ ጥናት ያደረጉ ተመራማሪዎች አስታወቁ። በዩናይትድ ኪንግደም ባለ አንድ ቡድን በተደረገ ጥናት እንቅልፍ ከውስጣዊው የሰውነት ክፍላችን የጊዜ አቆጣጠር ጋር እንዲጣታም ማድረግ ለልብ ድካም እና ለስትሮክ የመጋለጥ እድልን እንደሚቀንስ ጠቁሟል። የሰውነት ተፈጥሯዊ የ24-ሰዓት ምት ለደኅንነት እና ንቁ ለመሆን አስፈላጊ መሆኑን የሚገልጸው ጥናቱ እንደ የደም ግፊት ባሉ ሂደቶች ላይም ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል ይላል። በአውሮፓ የልብ ጤና ጆርናል ላይ በታተመው በዚህ ጥናት ተመራማሪዎቹ በሰባት ቀናት ውስጥ በእንቅልፍ እና በእንቅልፍ ጊዜ ላይ ከጥናቱ ተሳታፊዎች መረጃን ለማሰባሰብ የእጅ ሰዓት የሚመስል መሳሪያ እንዲያጠልቁ አድርገዋቸዋል። በመሳሪያው አማካኝነት በአማካይ በስድስት ዓመታት ውስጥ በልብ እና በደም ዝውውር ጤና ላይ ያለውን ሁኔታ ተከታትለዋል። በዚህም ከ3,000 በላይ የሚሆኑ ተሳታፊዎች የልብ ችግር [የካርዲዮቫስኩላር] በሽታ ተገኝቶባቸዋል። በጥናቱ መሰረት ለዚህ ችግር የተጋለጡት ከምሽቱ 4 ወይም 5 ሰዓት ቀደም ብለው ወይም ዘግይተው ወደ አልጋ የማምራት ልምድ ያላቸው ሰዎች ላይ ነው። ተመራማሪዎቹ እንደ ዕድሜ፣ የሰውነት ክብደት እና የኮሌስትሮል መጠን ያሉ የአንድን ሰው ለልብ ስጋት የሆኑ ሌሎች ነገሮችን ለማየት ሞክረዋል። ነገርግን ጥናታቸው መንስኤውንና ውጤቱን ማረጋገጥ አልቻለም። ተመራማሪዎቹ እንደ ዕድሜ፣ የሰውነት ክብደት እና የኮሌስትሮል መጠን ያሉ አንድን ሰው ለልብ ችግር የሚያጋልጡ ሌሎች ነገሮችን ለማየት የሞከሩ ሲሆን ጥናታቸው መንስኤና ውጤቱን ማረጋገጥ እንዳልቻለ አስረድተዋል። "በጥናታችን መንስኤው ላይ መደምደሚያ መስጠት ባንችልም በውጤቱ መሰረት ከመደበኛው የመኝታ ሰዓት ቀደም ብሎ ወይም ዘግይቶ መተኛት የሰውነትን አቆጣጠርን ሊያስተጓጉል ስለሚችል የልብና የደም ሥር ጤና ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያስከትል ጥናቱ አመላክቷል" ሲሉ አጥኚው ዶ/ር ዴቪድ ፕላን ገልጸዋል። "በጣም ችግር የማስከተል ዕድል ያለው የእንቅልፍ ጊዜ ከእኩለ ሌሊት በኋላ ያለው ነው። ምክንያቱ ዘግይቶ የተኛው ሰው የጠዋት ብርሃንን የማየት እድሉን ሊቀንስ ስለሚችል የሰውነት አቆጣጠር እንደገና ይጀምራል" ሲሉም አክለዋል። በብሪቲሽ የልብ ፋውንዴሽን ከፍተኛ የልብ ነርስ የሆኑት ራይጃና ጊብሊን "ይህ ትልቅ ጥናት እንደሚያመለክተው ከምሽቱ 4 እስከ 5 ሰዓት መተኛት ለብዙ ሰዎች ልባቸው ለረጅም ጊዜ ጤናማ እንዲሆን ምቹ ሊሆን ይችላል" ብለዋል። "ሆኖም ይህ ጥናት መንስኤውን እና ውጤቱን ማረጋገጥ እንዳልቻለ ማስታወስ አስፈላጊ ነው። የእንቅልፍ ጊዜ እና ቆይታ ከልብ እና ደም ዝውውር በሽታዎች ጋር ስላለው ተያያዥነት ምርምሮች ያስፈልጋሉ" ሲሉ ገልጸዋል። ነርሷ በቂ እንቅልፍ ማግኘታችን ለአጠቃላይ ጤንነታችን ብሎም ለልባችን እና ለደም ዝውውር ጤናማነት ጠቃሚ ነው። አብዛኞቹ ጎልማሶች ከሰባት እስከ ዘጠኝ ሰዓታት መተኛት ይጠበቅባቸዋል ሲሉም አስረድተዋል። "ይህ ማለት ግን እንቅልፍ የልብ ጤና ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር የሚችል ብቸኛው ምክንያት ነው ማለት አይደልም። የደም ግፊት እና የኮሌስትሮል መጠንን ማወቅ፤ ጤናማ ክብደትን መጠበቅ እና በመደበኛነት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፤ የጨው እና አልኮል መጠጦችን በመቀነስ የአኗኗር ዘይቤን ማጤን በጣም አስፈላጊ ነው። በተጨማሪም የተመጣጠነ ምግብ መመገብ የልብን ጤንነት ለመጠበቅ ይረዳል" ሲሉ ነርስ ራይጃና ጠቅሰዋል። | አዘውትሮ ምሽት አራት ሰዓት አካባቢ መተኛት ለልብ ችግር የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል- ጥናት ከምሽቱ 4 ሰዓት እስከ 5 ሰዓት ባለው ጊዜ አዘውትሮ መተኛት ለተሻለ የልብ ጤንነት እንደሚረዳ በ88 ሺህ በጎ ፈቃደኞች ላይ ጥናት ያደረጉ ተመራማሪዎች አስታወቁ። በዩናይትድ ኪንግደም ባለ አንድ ቡድን በተደረገ ጥናት እንቅልፍ ከውስጣዊው የሰውነት ክፍላችን የጊዜ አቆጣጠር ጋር እንዲጣታም ማድረግ ለልብ ድካም እና ለስትሮክ የመጋለጥ እድልን እንደሚቀንስ ጠቁሟል። የሰውነት ተፈጥሯዊ የ24-ሰዓት ምት ለደኅንነት እና ንቁ ለመሆን አስፈላጊ መሆኑን የሚገልጸው ጥናቱ እንደ የደም ግፊት ባሉ ሂደቶች ላይም ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል ይላል። በአውሮፓ የልብ ጤና ጆርናል ላይ በታተመው በዚህ ጥናት ተመራማሪዎቹ በሰባት ቀናት ውስጥ በእንቅልፍ እና በእንቅልፍ ጊዜ ላይ ከጥናቱ ተሳታፊዎች መረጃን ለማሰባሰብ የእጅ ሰዓት የሚመስል መሳሪያ እንዲያጠልቁ አድርገዋቸዋል። በመሳሪያው አማካኝነት በአማካይ በስድስት ዓመታት ውስጥ በልብ እና በደም ዝውውር ጤና ላይ ያለውን ሁኔታ ተከታትለዋል። በዚህም ከ3,000 በላይ የሚሆኑ ተሳታፊዎች የልብ ችግር [የካርዲዮቫስኩላር] በሽታ ተገኝቶባቸዋል። በጥናቱ መሰረት ለዚህ ችግር የተጋለጡት ከምሽቱ 4 ወይም 5 ሰዓት ቀደም ብለው ወይም ዘግይተው ወደ አልጋ የማምራት ልምድ ያላቸው ሰዎች ላይ ነው። ተመራማሪዎቹ እንደ ዕድሜ፣ የሰውነት ክብደት እና የኮሌስትሮል መጠን ያሉ የአንድን ሰው ለልብ ስጋት የሆኑ ሌሎች ነገሮችን ለማየት ሞክረዋል። ነገርግን ጥናታቸው መንስኤውንና ውጤቱን ማረጋገጥ አልቻለም። ተመራማሪዎቹ እንደ ዕድሜ፣ የሰውነት ክብደት እና የኮሌስትሮል መጠን ያሉ አንድን ሰው ለልብ ችግር የሚያጋልጡ ሌሎች ነገሮችን ለማየት የሞከሩ ሲሆን ጥናታቸው መንስኤና ውጤቱን ማረጋገጥ እንዳልቻለ አስረድተዋል። "በጥናታችን መንስኤው ላይ መደምደሚያ መስጠት ባንችልም በውጤቱ መሰረት ከመደበኛው የመኝታ ሰዓት ቀደም ብሎ ወይም ዘግይቶ መተኛት የሰውነትን አቆጣጠርን ሊያስተጓጉል ስለሚችል የልብና የደም ሥር ጤና ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያስከትል ጥናቱ አመላክቷል" ሲሉ አጥኚው ዶ/ር ዴቪድ ፕላን ገልጸዋል። "በጣም ችግር የማስከተል ዕድል ያለው የእንቅልፍ ጊዜ ከእኩለ ሌሊት በኋላ ያለው ነው። ምክንያቱ ዘግይቶ የተኛው ሰው የጠዋት ብርሃንን የማየት እድሉን ሊቀንስ ስለሚችል የሰውነት አቆጣጠር እንደገና ይጀምራል" ሲሉም አክለዋል። በብሪቲሽ የልብ ፋውንዴሽን ከፍተኛ የልብ ነርስ የሆኑት ራይጃና ጊብሊን "ይህ ትልቅ ጥናት እንደሚያመለክተው ከምሽቱ 4 እስከ 5 ሰዓት መተኛት ለብዙ ሰዎች ልባቸው ለረጅም ጊዜ ጤናማ እንዲሆን ምቹ ሊሆን ይችላል" ብለዋል። "ሆኖም ይህ ጥናት መንስኤውን እና ውጤቱን ማረጋገጥ እንዳልቻለ ማስታወስ አስፈላጊ ነው። የእንቅልፍ ጊዜ እና ቆይታ ከልብ እና ደም ዝውውር በሽታዎች ጋር ስላለው ተያያዥነት ምርምሮች ያስፈልጋሉ" ሲሉ ገልጸዋል። ነርሷ በቂ እንቅልፍ ማግኘታችን ለአጠቃላይ ጤንነታችን ብሎም ለልባችን እና ለደም ዝውውር ጤናማነት ጠቃሚ ነው። አብዛኞቹ ጎልማሶች ከሰባት እስከ ዘጠኝ ሰዓታት መተኛት ይጠበቅባቸዋል ሲሉም አስረድተዋል። "ይህ ማለት ግን እንቅልፍ የልብ ጤና ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር የሚችል ብቸኛው ምክንያት ነው ማለት አይደልም። የደም ግፊት እና የኮሌስትሮል መጠንን ማወቅ፤ ጤናማ ክብደትን መጠበቅ እና በመደበኛነት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፤ የጨው እና አልኮል መጠጦችን በመቀነስ የአኗኗር ዘይቤን ማጤን በጣም አስፈላጊ ነው። በተጨማሪም የተመጣጠነ ምግብ መመገብ የልብን ጤንነት ለመጠበቅ ይረዳል" ሲሉ ነርስ ራይጃና ጠቅሰዋል። | https://www.bbc.com/amharic/59230351 |
2health
| ኢትዮጵያ የጤናማ አመጋገብ መመሪያን ይፋ ልታደርግ ነው | በኢትዮጵያ የጤናማ አመጋገብ መመሪያ [dietary guideline] ከአንድ ወይም ከሁለት ወር በኋላ ይፋ እንደሚሆን በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የምግብ ስርዓት እና ስነ ምግብ ምርምር ዳይሬክተሩ ዶ/ር ማስረሻ ተሰማ ለቢቢሲ ገለጹ። ሃላፊው ለሶስት ዓመታት ሲዘጋጅ የቆየው የጤናማ አመጋገብ መመሪያ ወደ መጠናቀቁ መደረሱን ገልጸው በጤና ሚኒስቴር እና በሌሎች ሚኒንስቴር መስሪያ ቤቶች የተዘጋጀ መሆኑን ጠቁመዋል። ዶ/ር ማስረሻ የመመሪያውን አስፈላጊነት ሲገልጹ "ህብረተሰቡ በኢትዮጵያ ውስጥ ምንድን ነው መብላት ያለብኝ? በሚል ብዙ ሰው ይጠይቃል የተማረም ያልተማረም ሰው ስለዚህ ይህንን በዘላቂነት ለመመለስ" የተዘጋጀ መሆኑን አስረድተዋል። መመሪያው ለማዘጋጀት 'ሰፊ ጥናት' እንደተደረገበትም ገልጸዋል። እድሜያቸው ከሁለት ዓመት በላይ ለሆኑ ሰዎች የተዘጋጀ ሲሆን ምን አይነት ምግቦች እና አመጋገቦች ለጤናማ ህይወት እንደሚረዳ የሚያመላክት ነው ብለዋል። በተጨማሪም በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎችን እንዲሁም በሀገሪቱ ዙሪያ ያሉ ባህላዊ እሴቶችን ታሳቢ አድርጎ የተዘጋጀ ነው ሲሉ አክለዋል። ጤናማ የአመጋገብ መመሪያ ምንድን ነው? እንደ ዓለም ምግብ እና እርሻ ድርጅት ትርጓሜ ጤናማ የአመጋገብ መመሪያ በሀገራት ውስጥ ጤናማ የአመጋገብ እና የኑሮ ዘይቤም ለመገንባት የሚወጡ ናቸው። በውስጣቸውም ከስነ ምግብ አኳያ ጠቃሚ የሆኑ ምግቦችን እና አመጋገቦችን በተለያዩ የእድሜ ክልል ለሚገኙ ዜጎቻቸው በምክረ ሃሳብ መልክ የሚያቀርቡበት ነው። በተጨማሪም እርሻና የምግብ ዝግጅትን በተመለከተ የሚያትት ነው። በሌላ በኩል ጤናን ለማጎልበት እና አሳሳቢ በሽታዎችን ለመከላከል የሚረዱ ንጥረ ነገርን ያዘሉ ምግቦች የአመጋገብ ዘይቤዎች ላይ ምክር ሃሳብ ይሰጣሉ። እንደ ድርጅቱ መረጃ በዓለም ከአንድ መቶ በላይ ሀገራት የጤናማ አመጋገብ መመሪያ አላቸው። በአፍሪካ ሰባት ሀገራት ይህ መመሪያ ያላቸው ሲሆን ከሌሎች አህጉራት አንጻር ዝቅተኛው ነው። በአህጉሪቱ ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሲሼልስ፣ ናይጄሪያ፣ ቤኒን፣ ናሚቢያና ሴራሊዮን የአመጋገብ መመሪያ አላቸው። ከሁለት ወር በታች በሆነ ጊዜ የጤናማ አመጋገብ መመሪያን ይፋ ለማድረግ ያቀደችው ኢትዮጵያ 8ኛዋ የአፍሪካ ሀገር እንደምትሆን ይጠበቃል። | ኢትዮጵያ የጤናማ አመጋገብ መመሪያን ይፋ ልታደርግ ነው በኢትዮጵያ የጤናማ አመጋገብ መመሪያ [dietary guideline] ከአንድ ወይም ከሁለት ወር በኋላ ይፋ እንደሚሆን በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የምግብ ስርዓት እና ስነ ምግብ ምርምር ዳይሬክተሩ ዶ/ር ማስረሻ ተሰማ ለቢቢሲ ገለጹ። ሃላፊው ለሶስት ዓመታት ሲዘጋጅ የቆየው የጤናማ አመጋገብ መመሪያ ወደ መጠናቀቁ መደረሱን ገልጸው በጤና ሚኒስቴር እና በሌሎች ሚኒንስቴር መስሪያ ቤቶች የተዘጋጀ መሆኑን ጠቁመዋል። ዶ/ር ማስረሻ የመመሪያውን አስፈላጊነት ሲገልጹ "ህብረተሰቡ በኢትዮጵያ ውስጥ ምንድን ነው መብላት ያለብኝ? በሚል ብዙ ሰው ይጠይቃል የተማረም ያልተማረም ሰው ስለዚህ ይህንን በዘላቂነት ለመመለስ" የተዘጋጀ መሆኑን አስረድተዋል። መመሪያው ለማዘጋጀት 'ሰፊ ጥናት' እንደተደረገበትም ገልጸዋል። እድሜያቸው ከሁለት ዓመት በላይ ለሆኑ ሰዎች የተዘጋጀ ሲሆን ምን አይነት ምግቦች እና አመጋገቦች ለጤናማ ህይወት እንደሚረዳ የሚያመላክት ነው ብለዋል። በተጨማሪም በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎችን እንዲሁም በሀገሪቱ ዙሪያ ያሉ ባህላዊ እሴቶችን ታሳቢ አድርጎ የተዘጋጀ ነው ሲሉ አክለዋል። ጤናማ የአመጋገብ መመሪያ ምንድን ነው? እንደ ዓለም ምግብ እና እርሻ ድርጅት ትርጓሜ ጤናማ የአመጋገብ መመሪያ በሀገራት ውስጥ ጤናማ የአመጋገብ እና የኑሮ ዘይቤም ለመገንባት የሚወጡ ናቸው። በውስጣቸውም ከስነ ምግብ አኳያ ጠቃሚ የሆኑ ምግቦችን እና አመጋገቦችን በተለያዩ የእድሜ ክልል ለሚገኙ ዜጎቻቸው በምክረ ሃሳብ መልክ የሚያቀርቡበት ነው። በተጨማሪም እርሻና የምግብ ዝግጅትን በተመለከተ የሚያትት ነው። በሌላ በኩል ጤናን ለማጎልበት እና አሳሳቢ በሽታዎችን ለመከላከል የሚረዱ ንጥረ ነገርን ያዘሉ ምግቦች የአመጋገብ ዘይቤዎች ላይ ምክር ሃሳብ ይሰጣሉ። እንደ ድርጅቱ መረጃ በዓለም ከአንድ መቶ በላይ ሀገራት የጤናማ አመጋገብ መመሪያ አላቸው። በአፍሪካ ሰባት ሀገራት ይህ መመሪያ ያላቸው ሲሆን ከሌሎች አህጉራት አንጻር ዝቅተኛው ነው። በአህጉሪቱ ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሲሼልስ፣ ናይጄሪያ፣ ቤኒን፣ ናሚቢያና ሴራሊዮን የአመጋገብ መመሪያ አላቸው። ከሁለት ወር በታች በሆነ ጊዜ የጤናማ አመጋገብ መመሪያን ይፋ ለማድረግ ያቀደችው ኢትዮጵያ 8ኛዋ የአፍሪካ ሀገር እንደምትሆን ይጠበቃል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60101546 |
0business
| በ2012 ጎልተው የወጡ ምጣኔ ኃብታዊ ጉዳዮች | ከሁለት ዓመት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን ወደ ስልጣን ያመጣው ለውጥ ይፋ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ከፖለቲካው በተጨማሪ ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያዎችም እንደሚደረጉ ሲነገር ቆይቷል። እነዚህን ማሻሻያዎች ተግባራዊ ለማድረግ ያስችላሉ የተባሉ እርምጃዎች እየተጠናቀቀ ባለው 2012 የተወሰደ ሲሆን፤ የአገሪቱ ምጣኔ ሀብት ግን ከተለያዩ ፈተናዎች አሁንም አልተላቀቀም። በዓመቱ በአገሪቱ ውስጥ የተከሰቱ አለመረጋጋቶች፣ ዓለም አቀፉ የኮሮናወረርሽኝ እንዲሁም ሌሎች ምክንያቶች በአገሪቱ ምጣኔ ሀብት ላይና በሕዝቡ የዕለት ከዕለት ህይወት ላይ ቀላል የማይባል ጫናን አሳድረዋል። በተጠናቀቀው ዓመት በኢትዮጵያ የምጣኔ ሀብት ገጽታ ላይ ጎልተው ከታዩ ጉዳዮች መካከል ከጊዜ ወደ ጊዜ እጠነከረ የመጣው የዋጋ ግሽበት፣ የብር የምንዛሪ ዋጋ በገበያ ይወሰናል መባል እንዲሁም የግል ባንኮች ከውጪ ባንኮች በውጭ ምንዛሪ እንዲበደሩ መፈቀዱን መልስ ብለን ለመቃኘት እንሞክራለን። በአገሪቱ በተከታታይ ከፍ እያለ የመጣው የዋጋ ግሽበት ከመስከረም እስከ ሐምሌ 2012 ባሉት 11 ወራት ውስጥ የመቀነስ ምልክት እንዳልታየበት ከማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ የሚወጡት መረጃዎች ይጠቁማሉ። ለዋጋ ግሽበት መጠን አለመቀነስ እንደ ዋነኛ ምክንያት የሚቀመጠው በፍላጎት እና በአቅርቦት መካከል ያለው ልዩነት ሰፊ መሆኑ እንደሆነ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች የሚስማሙበት ሃቅ ነው። ከማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት መጠኑ በ18.6 በመቶ እና በ22.9 በመቶ መካከል ሲዋዥቅ ቆይቷል። የምግብ ዋጋ ግሽበት ደግሞ ከ20 በመቶ ሳይወርድ ቆይቷል። ዝቅተኛ የምግብ ዋጋ ግሽበት የተመዘገበው በጥር 2012 ሲሆን የምግብ ግሽበት መጠኑም 20 በመቶ ነበር። መጋቢት 2012 ደግሞ የዋጋ ግሽበቱ ዋጋ 26.7 በመቶ በመሆን በዓመቱ የምግብ ግሽበት ዋጋ ጣራ የነካበት ወቅት ወር ሆኖ አልፏል። ምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበትም ቢሆን ባለፉት 11 ወራት ከ10.3 በመቶ እስከ 19.7 በመቶ መካከል ሆኖ ተመዝግቧል። ከብሔራዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ በተገኘው አሃዝ መሰረት ከመስከረም እስከ ሐምሌ 2012 ድረስ የተመዘገበው የምግብ የዋጋ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ እና አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት መጠኑ እንደሚከተለው ቀርቧል። ሌላ በዚህ ዓመት አነጋጋሪ ሆኖ ያለፈው ብሔራዊ ባንክ ከሦስት ዓመታት በኋላ የብር የምንዛሪ ዋጋ ተመን በገበያ ዋጋ ይወሰናል ማለቱ ነበር። ባንኩ የብር የውጭ ምንዛሪ ፍላጎትን መሠረት በማድረግ የብር ዋጋ በገበያ ተመን እንዲወሰን ማድረግ ተገቢ ነው በማለት ኢትዮጵያ በሦስት ዓመታት ውስጥ ብርን ወደ ፍሎቲንግ ካረንሲ ሥርዓት (የገንዘብን ተመን በገበያ ዋጋ ላይ መመስረት) እንደምትሸጋገር ሐምሌ ወር ማገባደጃ ላይ ገልጿል። ብር በአሁኑ ወቅት ከሚገባው በላይ ዋጋ እንዳለው የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች የሚስማሙበት ጉዳይ ነው። ስለዚህም የብር ዋጋ በገበያ ወደሚተመንበት ሥርዓት ሲሸጋገር ዋጋው አሁን ካለው እንደሚቀንስ ወይም በብር እና በዶላር መካከል ያለው ልዩነት እንደሚሰፋ ይታመናል። ቢቢሲ በጉዳዩ ላይ ያነጋገራቸው የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች የምንዛሪ ሥርዓት በገበያ ዋጋ መወሰን እንዳለበት ይሚስማሙበት ጉዳይ ሆኖ፤ አካሄዱ ግን ቀስ በቀስ መሆን እንደሚገባው አመልክተዋል። ብሔራዊ ባንክም በመጪዎቹ ሦስት ዓመታት ውስጥ መከናወን ያለባቸው ነገሮችን መሰራት እንደሚኖርበትና ለዚህ ደግሞ የዘርፉ ሙያተኞችን የያዘ ተቋም ያስፈልጋል የሚል አስተያየት ሰጥተዋል። የብር የዋጋ በገበያው መሠረት ሲተመን ከውጭ አገራት ገንዘብ ጋር የሚኖረው ልዩነት እንደሚሰፋ ሙያተኞች ይናገራሉ፤ ለምሳሌ አንድ የአሜሪካ ዶላር ዛሬ ላይ በባንኮች 35 ብር የሚመነዘር ከሆነ፤ በትክክለኛው የገበያ ዋጋ ይተመን ቢባል አንድ ዶላር እስከ 45 ብር ድረስ ሊመነዘር ይችላል። ይህም የዋጋ ግሽበትን ያስከትላል። በሌላ በኩል ብር በአሁኑ ወቅት ከሚገባው በላይ ዋጋ እንዳለው የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች የሚስማሙበት ጉዳይ ነው። ስለዚህም የብር ዋጋ በገበያ ወደሚተመንበት ሥርዓት ሲሸጋገር ዋጋው አሁን ካለው እንደሚቀንስ ወይም በብር እና በዶላር መካከል ያለው ልዩነት እንደሚሰፋ ይታመናል። በዚህም ኢትዮጵያ የምታመርታው ምርት ዋጋ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ርካሽ ይሆናል፤ ይህም የአገር ውስጥ አምራቾችን ተወዳዳሪ እንደሚያደርግ በመጥቀስ መልካም አጋጣሚ ሊሆን እንደሚችል ያስረዳሉ። ባንኮች በውጭ ምንዛሪ እንዲበደሩ መፈቀዱ ብሔራዊ ባንክ ከሳምንታት በፊት ይፋ ካደረጋቸው መመሪያዎች መካከል የግል ባንኮች በራሳቸው ጊዜ በውጭ ምንዛሪ ገንዘብ ይበደሩ የሚለው ይገኝበታል። ይህ የባንኩ ውሳኔ ኢትዮጵያ ጥብቅ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደሯን እያላላች ስለመምጣቷ የሚያመላክት ሲሆን፤ ባንኮች በውጭ ምንዛሪ ከአገር ውጭ እንዲበደሩ መፍቀዱ ለላኪዎች መልካም አጋጣሚን ይዞ የሚመጣ እንደሆነ እየተነገረ ነው። የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት እንዲጎለብትም ይህ ውሳኔ ከፍተኛ አስተጽኦ ይኖረዋል ተብሏል። የውጭ ኢንቨስተሮች በአንድ አገር ኢንቨስት ለማድረግ ከመሰናቸው በፊት ኢንቨስት በሚያደርጉበት አገር ግብዓቶችን ከውጭ ለማስገባት እንዲሁም ትርፋቸውን ይዘው ለመውጣት በቂ የውጪ ምንዛሬ መኖሩን ቀድመው ያረጋግጣሉ። ከፍተኛ የሆነ የውጪ ምንዛሪ እጥረት ባለባት ኢትዮጵያ ሌላ የውጭ ምንዛሪ ማግኛ መንገድ መኖሩ ምልካም አጋጣሚ እንደሚሆን በአንዳንድ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ይታመናል። በሌላ በኩል ደግሞ ባንኮች በውጭ ምንዛሪ የሚበደሩትን ገንዘብ ከእነ ወለዱ በውጭ ምንዛሪ እንደመመለሳቸው የምንዛሪ ተመን መዋዠቅ በአገር ውስጥ ባንኮች ላይ አሉታዊ ጫና ሊፈጥር ይችላል። | በ2012 ጎልተው የወጡ ምጣኔ ኃብታዊ ጉዳዮች ከሁለት ዓመት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን ወደ ስልጣን ያመጣው ለውጥ ይፋ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ከፖለቲካው በተጨማሪ ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያዎችም እንደሚደረጉ ሲነገር ቆይቷል። እነዚህን ማሻሻያዎች ተግባራዊ ለማድረግ ያስችላሉ የተባሉ እርምጃዎች እየተጠናቀቀ ባለው 2012 የተወሰደ ሲሆን፤ የአገሪቱ ምጣኔ ሀብት ግን ከተለያዩ ፈተናዎች አሁንም አልተላቀቀም። በዓመቱ በአገሪቱ ውስጥ የተከሰቱ አለመረጋጋቶች፣ ዓለም አቀፉ የኮሮናወረርሽኝ እንዲሁም ሌሎች ምክንያቶች በአገሪቱ ምጣኔ ሀብት ላይና በሕዝቡ የዕለት ከዕለት ህይወት ላይ ቀላል የማይባል ጫናን አሳድረዋል። በተጠናቀቀው ዓመት በኢትዮጵያ የምጣኔ ሀብት ገጽታ ላይ ጎልተው ከታዩ ጉዳዮች መካከል ከጊዜ ወደ ጊዜ እጠነከረ የመጣው የዋጋ ግሽበት፣ የብር የምንዛሪ ዋጋ በገበያ ይወሰናል መባል እንዲሁም የግል ባንኮች ከውጪ ባንኮች በውጭ ምንዛሪ እንዲበደሩ መፈቀዱን መልስ ብለን ለመቃኘት እንሞክራለን። በአገሪቱ በተከታታይ ከፍ እያለ የመጣው የዋጋ ግሽበት ከመስከረም እስከ ሐምሌ 2012 ባሉት 11 ወራት ውስጥ የመቀነስ ምልክት እንዳልታየበት ከማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ የሚወጡት መረጃዎች ይጠቁማሉ። ለዋጋ ግሽበት መጠን አለመቀነስ እንደ ዋነኛ ምክንያት የሚቀመጠው በፍላጎት እና በአቅርቦት መካከል ያለው ልዩነት ሰፊ መሆኑ እንደሆነ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች የሚስማሙበት ሃቅ ነው። ከማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት መጠኑ በ18.6 በመቶ እና በ22.9 በመቶ መካከል ሲዋዥቅ ቆይቷል። የምግብ ዋጋ ግሽበት ደግሞ ከ20 በመቶ ሳይወርድ ቆይቷል። ዝቅተኛ የምግብ ዋጋ ግሽበት የተመዘገበው በጥር 2012 ሲሆን የምግብ ግሽበት መጠኑም 20 በመቶ ነበር። መጋቢት 2012 ደግሞ የዋጋ ግሽበቱ ዋጋ 26.7 በመቶ በመሆን በዓመቱ የምግብ ግሽበት ዋጋ ጣራ የነካበት ወቅት ወር ሆኖ አልፏል። ምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበትም ቢሆን ባለፉት 11 ወራት ከ10.3 በመቶ እስከ 19.7 በመቶ መካከል ሆኖ ተመዝግቧል። ከብሔራዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ በተገኘው አሃዝ መሰረት ከመስከረም እስከ ሐምሌ 2012 ድረስ የተመዘገበው የምግብ የዋጋ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ እና አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት መጠኑ እንደሚከተለው ቀርቧል። ሌላ በዚህ ዓመት አነጋጋሪ ሆኖ ያለፈው ብሔራዊ ባንክ ከሦስት ዓመታት በኋላ የብር የምንዛሪ ዋጋ ተመን በገበያ ዋጋ ይወሰናል ማለቱ ነበር። ባንኩ የብር የውጭ ምንዛሪ ፍላጎትን መሠረት በማድረግ የብር ዋጋ በገበያ ተመን እንዲወሰን ማድረግ ተገቢ ነው በማለት ኢትዮጵያ በሦስት ዓመታት ውስጥ ብርን ወደ ፍሎቲንግ ካረንሲ ሥርዓት (የገንዘብን ተመን በገበያ ዋጋ ላይ መመስረት) እንደምትሸጋገር ሐምሌ ወር ማገባደጃ ላይ ገልጿል። ብር በአሁኑ ወቅት ከሚገባው በላይ ዋጋ እንዳለው የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች የሚስማሙበት ጉዳይ ነው። ስለዚህም የብር ዋጋ በገበያ ወደሚተመንበት ሥርዓት ሲሸጋገር ዋጋው አሁን ካለው እንደሚቀንስ ወይም በብር እና በዶላር መካከል ያለው ልዩነት እንደሚሰፋ ይታመናል። ቢቢሲ በጉዳዩ ላይ ያነጋገራቸው የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች የምንዛሪ ሥርዓት በገበያ ዋጋ መወሰን እንዳለበት ይሚስማሙበት ጉዳይ ሆኖ፤ አካሄዱ ግን ቀስ በቀስ መሆን እንደሚገባው አመልክተዋል። ብሔራዊ ባንክም በመጪዎቹ ሦስት ዓመታት ውስጥ መከናወን ያለባቸው ነገሮችን መሰራት እንደሚኖርበትና ለዚህ ደግሞ የዘርፉ ሙያተኞችን የያዘ ተቋም ያስፈልጋል የሚል አስተያየት ሰጥተዋል። የብር የዋጋ በገበያው መሠረት ሲተመን ከውጭ አገራት ገንዘብ ጋር የሚኖረው ልዩነት እንደሚሰፋ ሙያተኞች ይናገራሉ፤ ለምሳሌ አንድ የአሜሪካ ዶላር ዛሬ ላይ በባንኮች 35 ብር የሚመነዘር ከሆነ፤ በትክክለኛው የገበያ ዋጋ ይተመን ቢባል አንድ ዶላር እስከ 45 ብር ድረስ ሊመነዘር ይችላል። ይህም የዋጋ ግሽበትን ያስከትላል። በሌላ በኩል ብር በአሁኑ ወቅት ከሚገባው በላይ ዋጋ እንዳለው የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች የሚስማሙበት ጉዳይ ነው። ስለዚህም የብር ዋጋ በገበያ ወደሚተመንበት ሥርዓት ሲሸጋገር ዋጋው አሁን ካለው እንደሚቀንስ ወይም በብር እና በዶላር መካከል ያለው ልዩነት እንደሚሰፋ ይታመናል። በዚህም ኢትዮጵያ የምታመርታው ምርት ዋጋ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ርካሽ ይሆናል፤ ይህም የአገር ውስጥ አምራቾችን ተወዳዳሪ እንደሚያደርግ በመጥቀስ መልካም አጋጣሚ ሊሆን እንደሚችል ያስረዳሉ። ባንኮች በውጭ ምንዛሪ እንዲበደሩ መፈቀዱ ብሔራዊ ባንክ ከሳምንታት በፊት ይፋ ካደረጋቸው መመሪያዎች መካከል የግል ባንኮች በራሳቸው ጊዜ በውጭ ምንዛሪ ገንዘብ ይበደሩ የሚለው ይገኝበታል። ይህ የባንኩ ውሳኔ ኢትዮጵያ ጥብቅ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደሯን እያላላች ስለመምጣቷ የሚያመላክት ሲሆን፤ ባንኮች በውጭ ምንዛሪ ከአገር ውጭ እንዲበደሩ መፍቀዱ ለላኪዎች መልካም አጋጣሚን ይዞ የሚመጣ እንደሆነ እየተነገረ ነው። የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት እንዲጎለብትም ይህ ውሳኔ ከፍተኛ አስተጽኦ ይኖረዋል ተብሏል። የውጭ ኢንቨስተሮች በአንድ አገር ኢንቨስት ለማድረግ ከመሰናቸው በፊት ኢንቨስት በሚያደርጉበት አገር ግብዓቶችን ከውጭ ለማስገባት እንዲሁም ትርፋቸውን ይዘው ለመውጣት በቂ የውጪ ምንዛሬ መኖሩን ቀድመው ያረጋግጣሉ። ከፍተኛ የሆነ የውጪ ምንዛሪ እጥረት ባለባት ኢትዮጵያ ሌላ የውጭ ምንዛሪ ማግኛ መንገድ መኖሩ ምልካም አጋጣሚ እንደሚሆን በአንዳንድ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ይታመናል። በሌላ በኩል ደግሞ ባንኮች በውጭ ምንዛሪ የሚበደሩትን ገንዘብ ከእነ ወለዱ በውጭ ምንዛሪ እንደመመለሳቸው የምንዛሪ ተመን መዋዠቅ በአገር ውስጥ ባንኮች ላይ አሉታዊ ጫና ሊፈጥር ይችላል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54084794 |
0business
| የሲሚንቶ ግብይት መመሪያ ተነስቶ ወደ ነፃ ገበያ አሰራር እንዲገባ ተወሰነ | በሲሚንቶ ግብይት ላይ ይነሱ የነበሩ ቅሬታዎችን ለመፍታትና፣ የዋጋ ንረት እንዳይከሰትና የተረጋጋ የሲሚንቶ ግብይት እንዲኖር ለማድረግ በሚል ወጥቶ የነበረው የሲሚንቶ ግብይት መመሪያ ላልተወሰነ ጊዜ መነሳቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ። መንግሥት የሲሚንቶ አቅርቦት እና ግብይት መመሪያን ማውጣቱን ተከትሎ ከፌደራል ጀምሮ እስከ ወረዳ ድረስ በገበያው ላይ የዋጋ ቁጥጥር ሥራን እንዲሁም ያለውን ተደራሽነት ክትትል ይሰራ ነበር። ከረቡዕ ሐምሌ 7/2013 ዓ.ም ጀምሮ የወጣው መመሪያና ከዚያ ጋር ተያይዘው የወጡ የሰርኩላር ማስፈጸሚያ ደብዳቤዎች እንዲነሱና ወደ ቀደመው የግብይት ሥርዓት፣ የነፃ የገበያ አስራር እንዲመለስ ተወስኗል ተብሏል። የሲሚንቶ ግብይትን በተመለከተ ከዚህ በፊት መንግሥት ከፌደራል ጀምሮ እስከ ወረዳ ያለውን የተደራሽነትና የዋጋ ቁጥጥር ተቋርጦ ፋብሪካዎች ራሳቸውና በሰንሰለቱ የሚገኙ አከፋፋዮችና ቸርቻሪዎችን በመቆጣጠር ራሳቸው ማስፈፀም እንደሚችሉ ከፋብሪካ ባለቤቶችና ሥራ አስኪያጆች ጋር ስምምነት መደረሱም ተገልጿል። የፋብሪካዎች የምርት መሸጫ ዋጋ ከሚኒስቴሩ ጋር በመተባበር በተጠና መልክ እንዲሆን ስምምነት ላይ መደረሱ ተነግሯል። "ፋብሪካዎች የሲሚንቶ መሸጫ ዋጋቸውን ከመሥሪያ ቤቱ ጋር በመነጋገር በተጠናና ባልተጋነነ ዋጋ እንዲወስኑና እንዲያቀርቡ ስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን ሙሉ ኃላፊቱን ለፋብሪካዎችና በተለያየ ደረጃ ላይ ላሉ የንግድ አካላት እየተቆጣጠሩ እንዲያሰሩ ተወስኗል" ብለዋል በሚኒስቴሩ የንግድ እቃዎች ዋጋ ጥናት፣ ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ሙላት። ቀድሞ በነበረው የግብይት ሥርዓት እንዲሆን የተወሰነበትንም ምክንያትም አቶ ካሳሁን አስረድተዋል። በክረምት ወቅት የግንባታ ሁኔታ ዝቅተኛ ስለሚሆን የሲሚንቶ ፍላጎትም ማነስ ስለሚከሰት፣ አምራች ኢንዱስትሪዎች አከፋፋዮችና ቸርቻሪዎች ሲሚንቶ ባልተጋነነ ዋጋ ለመሸጥ በመስማማታቸው እንደሆነም ጠቅሰዋል። ከዚህም በተጨማሪ ፋብሪካዎች የበኩላቸውን ቁጥጥር ከደንበኞቻቸው ጋር እንደሚያደርጉ ስምምነት ላይ በመደረሱ እንዲሁም በአቅርቦትና በፍላጎት ያለውን ክፍተት ለመሸፈን በአገር ውስጥ ያሉ ፋብሪካዎችን አቅም አሁን ካለው በበለጠ በማጠናከር ምርታቸውን እንዲጨምሩ በማድረግና በተለይም እንደ አስፈላጊነቱ ከውጭ ተጨማሪ የሲሚንቶ ምርት ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት መንግሥት በመወሰኑ ነው። መመሪያው ከነሐሴ 25 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የነበረ ሲሆን የአምራች፣ የአስመጪ፣ የአከፋፋይ፣ የቸርቻሪ ግዴታዎችን የያዘ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ የተከለከሉ ተግባራትንም በዝርዝር አስቀምጧል። የሲሚንቶ አምራቾች ያለበቂ ምክንያት ከእቅድ በታች ማምረት፣ ከመደበኛው የግበይት ሰንሰለት ውጪ የሲሚንቶ ምርትን ማከፋፈል፣ አከፋፋይ ለአከፋፋይ እና ለቸርቻሪ የሚደረግ የጎንዮሽ ግብይትን ይከለክል ነበር። ከዚህም በተጨማሪ የዋጋ ንረት እንዲፈጠር ማድረግ፣ የሲሚንቶ ምርትን መደበቅ፣ ማከማቸት እና በሕገ ወጥ መንገድ ማዘዋር፣ በዝምድና የሚከናወን የሲሚንቶ ንግድንም ይከለክልም ነበር። ከዚህ ቀደም መንግሥት ካስቀመጠው የሲሚንቶ የዋጋ ተመን በላይ የሚሸጡ አከፋፋዮች እንዲሁም ምርት በመደበቅ፣ በማከማቸት፣ አየር በአየር በመሸጥ፣ ከንግድ አድራሻ ውጪ በመሸጥ፣ እንዲያከፋፍሉ ወይም እንዲሸጡ ከተፈቀደላቸው ውጪ ለሌላ አካል በመሸጥ የተገኙ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እንደተወሰደ ይታወሳል። | የሲሚንቶ ግብይት መመሪያ ተነስቶ ወደ ነፃ ገበያ አሰራር እንዲገባ ተወሰነ በሲሚንቶ ግብይት ላይ ይነሱ የነበሩ ቅሬታዎችን ለመፍታትና፣ የዋጋ ንረት እንዳይከሰትና የተረጋጋ የሲሚንቶ ግብይት እንዲኖር ለማድረግ በሚል ወጥቶ የነበረው የሲሚንቶ ግብይት መመሪያ ላልተወሰነ ጊዜ መነሳቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ። መንግሥት የሲሚንቶ አቅርቦት እና ግብይት መመሪያን ማውጣቱን ተከትሎ ከፌደራል ጀምሮ እስከ ወረዳ ድረስ በገበያው ላይ የዋጋ ቁጥጥር ሥራን እንዲሁም ያለውን ተደራሽነት ክትትል ይሰራ ነበር። ከረቡዕ ሐምሌ 7/2013 ዓ.ም ጀምሮ የወጣው መመሪያና ከዚያ ጋር ተያይዘው የወጡ የሰርኩላር ማስፈጸሚያ ደብዳቤዎች እንዲነሱና ወደ ቀደመው የግብይት ሥርዓት፣ የነፃ የገበያ አስራር እንዲመለስ ተወስኗል ተብሏል። የሲሚንቶ ግብይትን በተመለከተ ከዚህ በፊት መንግሥት ከፌደራል ጀምሮ እስከ ወረዳ ያለውን የተደራሽነትና የዋጋ ቁጥጥር ተቋርጦ ፋብሪካዎች ራሳቸውና በሰንሰለቱ የሚገኙ አከፋፋዮችና ቸርቻሪዎችን በመቆጣጠር ራሳቸው ማስፈፀም እንደሚችሉ ከፋብሪካ ባለቤቶችና ሥራ አስኪያጆች ጋር ስምምነት መደረሱም ተገልጿል። የፋብሪካዎች የምርት መሸጫ ዋጋ ከሚኒስቴሩ ጋር በመተባበር በተጠና መልክ እንዲሆን ስምምነት ላይ መደረሱ ተነግሯል። "ፋብሪካዎች የሲሚንቶ መሸጫ ዋጋቸውን ከመሥሪያ ቤቱ ጋር በመነጋገር በተጠናና ባልተጋነነ ዋጋ እንዲወስኑና እንዲያቀርቡ ስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን ሙሉ ኃላፊቱን ለፋብሪካዎችና በተለያየ ደረጃ ላይ ላሉ የንግድ አካላት እየተቆጣጠሩ እንዲያሰሩ ተወስኗል" ብለዋል በሚኒስቴሩ የንግድ እቃዎች ዋጋ ጥናት፣ ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ሙላት። ቀድሞ በነበረው የግብይት ሥርዓት እንዲሆን የተወሰነበትንም ምክንያትም አቶ ካሳሁን አስረድተዋል። በክረምት ወቅት የግንባታ ሁኔታ ዝቅተኛ ስለሚሆን የሲሚንቶ ፍላጎትም ማነስ ስለሚከሰት፣ አምራች ኢንዱስትሪዎች አከፋፋዮችና ቸርቻሪዎች ሲሚንቶ ባልተጋነነ ዋጋ ለመሸጥ በመስማማታቸው እንደሆነም ጠቅሰዋል። ከዚህም በተጨማሪ ፋብሪካዎች የበኩላቸውን ቁጥጥር ከደንበኞቻቸው ጋር እንደሚያደርጉ ስምምነት ላይ በመደረሱ እንዲሁም በአቅርቦትና በፍላጎት ያለውን ክፍተት ለመሸፈን በአገር ውስጥ ያሉ ፋብሪካዎችን አቅም አሁን ካለው በበለጠ በማጠናከር ምርታቸውን እንዲጨምሩ በማድረግና በተለይም እንደ አስፈላጊነቱ ከውጭ ተጨማሪ የሲሚንቶ ምርት ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት መንግሥት በመወሰኑ ነው። መመሪያው ከነሐሴ 25 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የነበረ ሲሆን የአምራች፣ የአስመጪ፣ የአከፋፋይ፣ የቸርቻሪ ግዴታዎችን የያዘ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ የተከለከሉ ተግባራትንም በዝርዝር አስቀምጧል። የሲሚንቶ አምራቾች ያለበቂ ምክንያት ከእቅድ በታች ማምረት፣ ከመደበኛው የግበይት ሰንሰለት ውጪ የሲሚንቶ ምርትን ማከፋፈል፣ አከፋፋይ ለአከፋፋይ እና ለቸርቻሪ የሚደረግ የጎንዮሽ ግብይትን ይከለክል ነበር። ከዚህም በተጨማሪ የዋጋ ንረት እንዲፈጠር ማድረግ፣ የሲሚንቶ ምርትን መደበቅ፣ ማከማቸት እና በሕገ ወጥ መንገድ ማዘዋር፣ በዝምድና የሚከናወን የሲሚንቶ ንግድንም ይከለክልም ነበር። ከዚህ ቀደም መንግሥት ካስቀመጠው የሲሚንቶ የዋጋ ተመን በላይ የሚሸጡ አከፋፋዮች እንዲሁም ምርት በመደበቅ፣ በማከማቸት፣ አየር በአየር በመሸጥ፣ ከንግድ አድራሻ ውጪ በመሸጥ፣ እንዲያከፋፍሉ ወይም እንዲሸጡ ከተፈቀደላቸው ውጪ ለሌላ አካል በመሸጥ የተገኙ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እንደተወሰደ ይታወሳል። | https://www.bbc.com/amharic/news-57837774 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ ዶናልድ ትራምፕ በፍጥነት ያገገሙበት መድሃኒት እውቅና ተሰጠው | አሜሪካ በኮቪድ-19 ታምመው ሆስፒታል ለሚገቡ ግለሰቦች ሬምዴስቪር የተሰኘውን ፀረ ቫይረስ መድሃኒት ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቀደች። የአሜሪካ ምግብና መድሃኒት አስተዳደር (ኤፍዲኤ) እንዳለው መድሃኒቱ በክሊኒክ ውስጥ ሙከራ ላይ ባለበት ወቅት በቫይረሱ የተያዙ ሕሙማንን ማገገሚያ ጊዜ በአምስት ቀናት ውስጥ ያሳጥራል። በቅርቡ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ በኋላ መድሃኒቱ የተሰጣቸው ሲሆን በፍጥነትም እንዲያገግሙ ረድቷቸዋል መባሉ ይታወሳል። ይህ ቬክለሪ በሚል የብራንድ ስያሜ የሚታወቀው መድሃኒት የአሜሪካ መድሃኒትና ምግብ አስተዳደር ፈቃድ ሲያገኝ የመጀመሪያው መድሃኒት መሆኑን በመግለጫው ላይ ተመልክቷል። ባለፈው ሳምንት የዓለም ጤና ድርጅት ሬምዴሲቪር በቫይረሱ ተይዘው የታመሙ ግለሰቦች ላይ ያለው ውጤት አነስተኛ ነው ብሎ ነበር። የዓለም ጤና ድርጅት በሰራው ጥናት እዚህ ድምዳሜ ላይ መድረሱን ቢናገርም የመድሃኒት አምራቹ ገሌድ ግን ውጤቱን ሊቀበለው አልፈለገም። ሬምዴሲቪር በአሜሪካ ከግንቦት ወር ጀምሮ ለድንገተኛ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ እንዲውል ተፈቅዶ ነበር። እንደ አሜሪካ መድሃኒት እና ምግብ ቁጥጥር ባለስልጣን ከሆነ መድሃኒቱ ለአዋቂዎችና እድሜያቸው 12 ለሞላ ሕጻናት እንዲሁም ክብደታቸው 40 ኪሎ ግራም ለሆነ ግለሰቦች በሆስፒታል የኮቪድ-19 ሕክምና በሚከታተሉበት ወቅት ለማከም ጥቅም ላይ መዋል ይችላል። የባለስልጣኑ ኮሚሽነር የሆኑት ስቴፈን ሃሃን እንዳሉት ተቋሙ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ተደጋጋሚ የክሊኒክ ሙከራዎችን ካደረገ እና በሚገባ ከፈተሸ በኋላ ነው። ከተደረጉ የተለያዩ ጥናቶች መካከል አንዱ የማገገሚያ ቀናቱ ከ15 ቀናት 10 ማድረሱ ተገልጿል። | ኮሮናቫይረስ፡ ዶናልድ ትራምፕ በፍጥነት ያገገሙበት መድሃኒት እውቅና ተሰጠው አሜሪካ በኮቪድ-19 ታምመው ሆስፒታል ለሚገቡ ግለሰቦች ሬምዴስቪር የተሰኘውን ፀረ ቫይረስ መድሃኒት ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቀደች። የአሜሪካ ምግብና መድሃኒት አስተዳደር (ኤፍዲኤ) እንዳለው መድሃኒቱ በክሊኒክ ውስጥ ሙከራ ላይ ባለበት ወቅት በቫይረሱ የተያዙ ሕሙማንን ማገገሚያ ጊዜ በአምስት ቀናት ውስጥ ያሳጥራል። በቅርቡ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ በኋላ መድሃኒቱ የተሰጣቸው ሲሆን በፍጥነትም እንዲያገግሙ ረድቷቸዋል መባሉ ይታወሳል። ይህ ቬክለሪ በሚል የብራንድ ስያሜ የሚታወቀው መድሃኒት የአሜሪካ መድሃኒትና ምግብ አስተዳደር ፈቃድ ሲያገኝ የመጀመሪያው መድሃኒት መሆኑን በመግለጫው ላይ ተመልክቷል። ባለፈው ሳምንት የዓለም ጤና ድርጅት ሬምዴሲቪር በቫይረሱ ተይዘው የታመሙ ግለሰቦች ላይ ያለው ውጤት አነስተኛ ነው ብሎ ነበር። የዓለም ጤና ድርጅት በሰራው ጥናት እዚህ ድምዳሜ ላይ መድረሱን ቢናገርም የመድሃኒት አምራቹ ገሌድ ግን ውጤቱን ሊቀበለው አልፈለገም። ሬምዴሲቪር በአሜሪካ ከግንቦት ወር ጀምሮ ለድንገተኛ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ እንዲውል ተፈቅዶ ነበር። እንደ አሜሪካ መድሃኒት እና ምግብ ቁጥጥር ባለስልጣን ከሆነ መድሃኒቱ ለአዋቂዎችና እድሜያቸው 12 ለሞላ ሕጻናት እንዲሁም ክብደታቸው 40 ኪሎ ግራም ለሆነ ግለሰቦች በሆስፒታል የኮቪድ-19 ሕክምና በሚከታተሉበት ወቅት ለማከም ጥቅም ላይ መዋል ይችላል። የባለስልጣኑ ኮሚሽነር የሆኑት ስቴፈን ሃሃን እንዳሉት ተቋሙ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ተደጋጋሚ የክሊኒክ ሙከራዎችን ካደረገ እና በሚገባ ከፈተሸ በኋላ ነው። ከተደረጉ የተለያዩ ጥናቶች መካከል አንዱ የማገገሚያ ቀናቱ ከ15 ቀናት 10 ማድረሱ ተገልጿል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54612591 |
3politics
| ፕሬዚዳንት ባይደን የሱዳን የሲቪል አገዛዝ በአስቸኳይ እንዲመለስ አሳሰቡ | የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የሱዳን ወታደራዊ መሪዎች የሲቪል አገዛዙን በአስቸኳይ እንዲመልሱ እና ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ አሳስበዋል። በጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን የተመራውን መፈንቅለ መንግስት በመቃወም አደባባይ ላይ የወጡ ሰልፈኞች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት እንዲቆምም ፕሬዚዳንቱ ጠይቀዋል። "ለሱዳን ወታደራዊ ባለስልጣናት የምናስተላልፈው መልእክት በርካታ እና ግልፅ ነው። የሱዳን ህዝብ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞውን እንዲያሰማ እና በሲቪል የሚመራ የሽግግር መንግስት ወደነበረበት መመለስ አለበት" ሲሉም በመግለጫቸው አስተላልፈዋል። የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የሱዳንን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት በመቃወም የአረብ ሊግ እና የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ የአለም አቀፍ ማህበረሰቡን ውግዘት ተቀላቅለዋል። በሱዳን በቅርብ ጊዜ የተከሰቱት ክስተቶች ሃገሪቷን በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ኋላ የሚጎትቱ ናቸው ያሉት ፕሬዚዳንት ባይደን ነገር ግን "የሱዳንን አብዮት አላማ ለማራመድ ከሱዳን ህዝብ እና ከሰላማዊ ትግል ጋር እንቆማለን" በማለት የመንግሥታቸውን አቋም ገልጸዋል። በተቃውሞው የተገደሉት ሰዎች ቁጥር 11 መድረሱንም የህክምና ምንጮች ገልጸዋል። በአውሮፓውያኑ 2019 ለአስርት ዓመታት ሱዳንን አንቀጥቀው የገዙት ኦማር አልበሽር ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ በሲቪል መሪዎች እና በወታደራዊ አቻዎቻቸው መካከል አለመግባባት ተፈጥሯል። በሲቪል እና በወታደራዊ መሪዎች መካከል የተደረገው የሥልጣን ክፍፍል ስምምነት ሱዳንን ወደ ዲሞክራሲ ለመምራት የተነደፈ ቢሆንም ከባለፈው አንድ ወር በፊት የተደረጉ በርካታ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራዎች ግን በተፃራሪው አገሪቷ በተቃራኒው አቅጣጫ እየሄደች እንደሆነ ያመላከተ ነው። የስልጣን መጋራት ምክር ቤት መሪ የነበሩት ጄኔራል ቡርሐን ሱዳን ወደ ሲቪል አስተዳደር ለመሸጋገር ቁርጠኛ መሆኗን ገልፀው ምርጫው በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር 2023 ሐምሌ ወር ሊካሄድ እንደታቀደም ተናግረዋል። | ፕሬዚዳንት ባይደን የሱዳን የሲቪል አገዛዝ በአስቸኳይ እንዲመለስ አሳሰቡ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የሱዳን ወታደራዊ መሪዎች የሲቪል አገዛዙን በአስቸኳይ እንዲመልሱ እና ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ አሳስበዋል። በጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን የተመራውን መፈንቅለ መንግስት በመቃወም አደባባይ ላይ የወጡ ሰልፈኞች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት እንዲቆምም ፕሬዚዳንቱ ጠይቀዋል። "ለሱዳን ወታደራዊ ባለስልጣናት የምናስተላልፈው መልእክት በርካታ እና ግልፅ ነው። የሱዳን ህዝብ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞውን እንዲያሰማ እና በሲቪል የሚመራ የሽግግር መንግስት ወደነበረበት መመለስ አለበት" ሲሉም በመግለጫቸው አስተላልፈዋል። የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የሱዳንን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት በመቃወም የአረብ ሊግ እና የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ የአለም አቀፍ ማህበረሰቡን ውግዘት ተቀላቅለዋል። በሱዳን በቅርብ ጊዜ የተከሰቱት ክስተቶች ሃገሪቷን በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ኋላ የሚጎትቱ ናቸው ያሉት ፕሬዚዳንት ባይደን ነገር ግን "የሱዳንን አብዮት አላማ ለማራመድ ከሱዳን ህዝብ እና ከሰላማዊ ትግል ጋር እንቆማለን" በማለት የመንግሥታቸውን አቋም ገልጸዋል። በተቃውሞው የተገደሉት ሰዎች ቁጥር 11 መድረሱንም የህክምና ምንጮች ገልጸዋል። በአውሮፓውያኑ 2019 ለአስርት ዓመታት ሱዳንን አንቀጥቀው የገዙት ኦማር አልበሽር ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ በሲቪል መሪዎች እና በወታደራዊ አቻዎቻቸው መካከል አለመግባባት ተፈጥሯል። በሲቪል እና በወታደራዊ መሪዎች መካከል የተደረገው የሥልጣን ክፍፍል ስምምነት ሱዳንን ወደ ዲሞክራሲ ለመምራት የተነደፈ ቢሆንም ከባለፈው አንድ ወር በፊት የተደረጉ በርካታ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራዎች ግን በተፃራሪው አገሪቷ በተቃራኒው አቅጣጫ እየሄደች እንደሆነ ያመላከተ ነው። የስልጣን መጋራት ምክር ቤት መሪ የነበሩት ጄኔራል ቡርሐን ሱዳን ወደ ሲቪል አስተዳደር ለመሸጋገር ቁርጠኛ መሆኗን ገልፀው ምርጫው በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር 2023 ሐምሌ ወር ሊካሄድ እንደታቀደም ተናግረዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59078937 |
5sports
| ነጥብ የተቀነሰበት የዋይኒ ሩኒ ቡድን ወደ ሶስተኛው ሊግ ወረደ | አንጋፋው እንግሊዛዊ እግር ኳስ ተጫዋች ዋይኒ ሩኒ የሚያሠልጥነው ደርቢ ካውንቲ ወደ ሶስተኛው ሊግ ወረደ። ራምስ በተሰኘው ቅጥል ስማቸው የሚታወቁት ደርቢዎች በኪውፒአር ተረተው ወደ ሶስተኛው ሊግ ወርደዋል። ደርቢ ካውንቲ በፈረንጆቹ 1986 ወደ ላይኛው ሊግ ከወጣ በኋላ ወደ ሶስተኛው ሊግ ሲወርድ ይህ የመጀመሪያው ነው። ደርቢ ካውንቲ ለዚህ ቀውስ የተዳረገው የቀድሞው ባለቤቱ ሜል ሞሪስ ክለቡን ማስተዳደር አልችልም ብለው ለመንግሥት አሳልፈው ከሰጡት በኋላ ነው። ወደ ሶስተኛው ሊግ የወረደው ዋይኒ ሩኒ "መቼም ባለቤቱ ይህን እያዩ እንቅልፍ ባይነሳቸው ነው የሚገርመኝ" ሲል መረር ያለ አስተያየት ሰጥቷል። ደርቢ ካውንቲ ባለፈው መስከረም 12 ነጥብ ተቀንሶበት ከነበረበት 12ኛ ደረጃ ወደ ወራጅ ቀጣና መውረዱ ይታወሳል። ነገር ግን የዋይኒ ሩኒ ልጆች ከረዥምና አድካሚ ትግል በኋላ እጅ ሰጥተዋል። "ክለቡን አመሰቃቅሎት ነው የሄደው። ሜል ሞሪስ የደርቢ ደጋፊ እንደሆነ አውቃለሁ። በብስጭት እየጨሰ እንደሆነ አልጠራጠርም" ሲል ሩኒ ቃሉን ለቢቢሲ ሰጥቷል። "ይህ እንዳይሆን የቻልነውን ሁሉ አድርገናል። ከሚገባው በላይ ለፍተናል። ብስጭታችን የሚበርድ አይደለም።" ደርቢ ካውንቲ መስከረም ላይ ከተጣለበት የ12 ነጥብ ቅጣት በተጨማሪ ባለፈው ኅዳር ተጨማሪ 9 ነጥብ ተቀንድቦበታል። የዋይኒ ሩኒ ቡድን 21 ነጥብ ባይቀነስበት ኖሮ 24 ቡድኖች ባሉት ሁለተኛው የእንግሊዝ ሊግ 17ኛ ደረጃ ላይ ይቀመጥ ነበር። "በዚህኛው ሊግ የሚያቆየን ነጥብ ነበረን። በዚያ ላይ በጣም ጥሩ ብቃት ያላቸው እዚሁ ያደጉ ተጫዋቾች አፍርተን ነበር" ሲል ውጤቱ ያንገበገበው ሩኒ ተናግሯል። "በጣም ተበሳጭቻለሁ። እጅግ አዝኛለሁ። ነገር ግን በክለቡ በጣም እኮራለሁ። ተስፋ ያለው ቡድን ሠርተናል።" የእንግሊዝና ማንችስተር ዩናይት ቁጥር አንድ ጎል አስቆጣሪው ሩኒ ጫማ የሰቀለው ባለፈው የውድድር ዘመን ነበር። ሩኒ ወደ ደርቢ ካውንቲ የመጣው በአሠልጣኝነትና ተጫዋችነት ቢሆንም ሙሉ በሙሉ የአሠልጣኝነት ወንበሩን ተቆጣጥሮ ክለቡን ሲመራ ቆይቷል። ባለፈው የውድድር ዘመን እንዲሁ ከመውረድ ያዳነውን ክለብ ታሪክ ዘንድሮ ግን ሊደግመው አልቻለም። ነገር ግን ቀውስ ያለ ቡድንን መንፈሰ ጠንካራና ታጋይ እንዲሆን በማድረጉ ብዙዎች ያወድሱታል። ያደገበት ክለብ ኤቨርተን ባለፈው ጥር አሠልጣኝ አድርጎ ይቀጥረዋል ተብሎ ቢታማም ሩኒ ግን ከደርቢ ጋር መቆየትን መርጧል። የአንጋፋው ተጫዋች ስም አሁን ደግሞ አሠልጣን ሾን ዳይሽን ካሰናበተው በርንሊ ጋር እየተያያዘ እየተነሳ ነው። ነገር ግን አዲሱ የደርቢ ካውንቲ ባለቤት ክሪስ ክሪችነር ሩኒ ከክለባቸው ጋር እንደሚቆይ ተናግረዋል። ከደርቢ ጋር የአንድ ዓመት ውል የሚቀረው ሩኒም በሚቀጥለው ዓመት ለሚገጥመው ፈተና እንደተዘጋጀ ጠቆም አድርጓል። አሜሪካዊው አዲሱ የደርቢ ባለቤት ክሪስ ክሪችነር ከጥቂት ሳምንታት በፊት ክለቡን ለመግዛት የተስማሙት። የደርቢ ካውንቲ ሜዳ የሆነው ፕራይድ ፓርክ አሁንም ባለቤትነቱ በሜል ሞሪስ እጅ ነው። | ነጥብ የተቀነሰበት የዋይኒ ሩኒ ቡድን ወደ ሶስተኛው ሊግ ወረደ አንጋፋው እንግሊዛዊ እግር ኳስ ተጫዋች ዋይኒ ሩኒ የሚያሠልጥነው ደርቢ ካውንቲ ወደ ሶስተኛው ሊግ ወረደ። ራምስ በተሰኘው ቅጥል ስማቸው የሚታወቁት ደርቢዎች በኪውፒአር ተረተው ወደ ሶስተኛው ሊግ ወርደዋል። ደርቢ ካውንቲ በፈረንጆቹ 1986 ወደ ላይኛው ሊግ ከወጣ በኋላ ወደ ሶስተኛው ሊግ ሲወርድ ይህ የመጀመሪያው ነው። ደርቢ ካውንቲ ለዚህ ቀውስ የተዳረገው የቀድሞው ባለቤቱ ሜል ሞሪስ ክለቡን ማስተዳደር አልችልም ብለው ለመንግሥት አሳልፈው ከሰጡት በኋላ ነው። ወደ ሶስተኛው ሊግ የወረደው ዋይኒ ሩኒ "መቼም ባለቤቱ ይህን እያዩ እንቅልፍ ባይነሳቸው ነው የሚገርመኝ" ሲል መረር ያለ አስተያየት ሰጥቷል። ደርቢ ካውንቲ ባለፈው መስከረም 12 ነጥብ ተቀንሶበት ከነበረበት 12ኛ ደረጃ ወደ ወራጅ ቀጣና መውረዱ ይታወሳል። ነገር ግን የዋይኒ ሩኒ ልጆች ከረዥምና አድካሚ ትግል በኋላ እጅ ሰጥተዋል። "ክለቡን አመሰቃቅሎት ነው የሄደው። ሜል ሞሪስ የደርቢ ደጋፊ እንደሆነ አውቃለሁ። በብስጭት እየጨሰ እንደሆነ አልጠራጠርም" ሲል ሩኒ ቃሉን ለቢቢሲ ሰጥቷል። "ይህ እንዳይሆን የቻልነውን ሁሉ አድርገናል። ከሚገባው በላይ ለፍተናል። ብስጭታችን የሚበርድ አይደለም።" ደርቢ ካውንቲ መስከረም ላይ ከተጣለበት የ12 ነጥብ ቅጣት በተጨማሪ ባለፈው ኅዳር ተጨማሪ 9 ነጥብ ተቀንድቦበታል። የዋይኒ ሩኒ ቡድን 21 ነጥብ ባይቀነስበት ኖሮ 24 ቡድኖች ባሉት ሁለተኛው የእንግሊዝ ሊግ 17ኛ ደረጃ ላይ ይቀመጥ ነበር። "በዚህኛው ሊግ የሚያቆየን ነጥብ ነበረን። በዚያ ላይ በጣም ጥሩ ብቃት ያላቸው እዚሁ ያደጉ ተጫዋቾች አፍርተን ነበር" ሲል ውጤቱ ያንገበገበው ሩኒ ተናግሯል። "በጣም ተበሳጭቻለሁ። እጅግ አዝኛለሁ። ነገር ግን በክለቡ በጣም እኮራለሁ። ተስፋ ያለው ቡድን ሠርተናል።" የእንግሊዝና ማንችስተር ዩናይት ቁጥር አንድ ጎል አስቆጣሪው ሩኒ ጫማ የሰቀለው ባለፈው የውድድር ዘመን ነበር። ሩኒ ወደ ደርቢ ካውንቲ የመጣው በአሠልጣኝነትና ተጫዋችነት ቢሆንም ሙሉ በሙሉ የአሠልጣኝነት ወንበሩን ተቆጣጥሮ ክለቡን ሲመራ ቆይቷል። ባለፈው የውድድር ዘመን እንዲሁ ከመውረድ ያዳነውን ክለብ ታሪክ ዘንድሮ ግን ሊደግመው አልቻለም። ነገር ግን ቀውስ ያለ ቡድንን መንፈሰ ጠንካራና ታጋይ እንዲሆን በማድረጉ ብዙዎች ያወድሱታል። ያደገበት ክለብ ኤቨርተን ባለፈው ጥር አሠልጣኝ አድርጎ ይቀጥረዋል ተብሎ ቢታማም ሩኒ ግን ከደርቢ ጋር መቆየትን መርጧል። የአንጋፋው ተጫዋች ስም አሁን ደግሞ አሠልጣን ሾን ዳይሽን ካሰናበተው በርንሊ ጋር እየተያያዘ እየተነሳ ነው። ነገር ግን አዲሱ የደርቢ ካውንቲ ባለቤት ክሪስ ክሪችነር ሩኒ ከክለባቸው ጋር እንደሚቆይ ተናግረዋል። ከደርቢ ጋር የአንድ ዓመት ውል የሚቀረው ሩኒም በሚቀጥለው ዓመት ለሚገጥመው ፈተና እንደተዘጋጀ ጠቆም አድርጓል። አሜሪካዊው አዲሱ የደርቢ ባለቤት ክሪስ ክሪችነር ከጥቂት ሳምንታት በፊት ክለቡን ለመግዛት የተስማሙት። የደርቢ ካውንቲ ሜዳ የሆነው ፕራይድ ፓርክ አሁንም ባለቤትነቱ በሜል ሞሪስ እጅ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/news-61151826 |
5sports
| የእንግሊዝ ክለቦች ለተጫዋች ግዥ 1.6 ቢሊዮን ዶላር አወጡ | ትናንት ብሪታኒያ ውስጥ ሁለት ክስተቶች በተመሳሳይ ሰዓት እልባት አግኝተው በብዙዎች ዘንድ ግርምትን አጭሯል። ሁለቱም የተጠናቀቁት በየራሳቸው መንገድ ቢሆንም ትናንት እኩለ ሌሊት ስፖርትና ፖለቲካ ተመሳሳይ ሰዓት ላይ ተገጣጥመዋል፤ በእንግሊዝ ሰዓት አቆጣጠር 23፡00 ላይ። ለሦስት ዓመታት ሲንከባለል የነበረው የብሪታኒያ ከአውሮፓ ሕብረት የመውጣት ሂደት ፍጻሜውን አግኝቶ በመላዋ ብሪታኒያ ሲበሰር፤ በዚያችው ቅጽበትም የእንግሊዝ ፕሪሜየር ሊግ የጥር የዝውውር መስኮት ተዘግቷል። የዝውውር ወሩ ስም ያላቸው ተጫዋቾችን ብዙም ሳይዳፈር በአብዛኛው አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ፕሪሜር ሊጉ በማምጣት ተጠናቋል። • አሠልጣኝ አብርሃም መብራህቱ፡ "የመጣውን በጸጋ መቀበልና መዘጋጀት ነው" በማጠናቀቂያ ሰዓቱ ላይ የፈረሙት ጃሮድ ቦውን እና ኦዲዮ ኢጋሎ በመጨረሻዋ ቀን በከፍተኛ የዝውውር ገንዘብ የተገዙ ተጫዋቾች ናቸው። በመጨረሻዋ ቀን ዌስትሃም ዩናይትድ የሃል ሲቲውን አጥቂ ጃሮድ ቦውን በ18 ሚሊዮን ፓውንድ አስፈርሟል። በውድድር ዘመኑ በጥር የዝውውር የመዝጊያ ዕለት ብቻ የወጣ ከፍተኛ ገንዘብ ሆኖም ተመዝግቧል። ይሁን እንጂ በጥር የዝውውር ወር የመጨረሻ ቀን እስከዛሬ ከወጣው ከፍተኛ ገንዘብ ጋር ሲነጻጸር ከ2010 እ.አ.አ ወዲህ ትንሹ ገንዘብ ሆኖ ተመዝግቧል። • «የኔ ትውልድ ታሪክ እንደሚሠራ እምነት አለኝ» ሎዛ አበራ በወሩ አጠቃላይ የእንግሊዝ ክለቦች 230 ሚሊዮን ፓውንድ ወጪ አድርገው ተጫዋቾችን የገዙ ሲሆን በታሪክ ሁለተኛው ከፍተኛ ገንዘብ ነው። ከዚህ ገንዘብ መካከል ታዲያ በመጨረሻዋ ቀን 25 ሚሊዮን ፓውንድ ብቻ ነው ወጪ የተደረገው። እንደአጠቃላይ ደግሞ በዚህ የውድድር ዘመን የእንግሊዝ ክለቦች ተጫዋች ለመግዛት 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ፓውንድ አውጥተዋል። ይህም 1 ነጥብ 9 ቢሊዮን ፓውንድ ከወጣበት የ2017/18 የውድድር ዘመን ቀጥሎ በታሪክ ከፍተኛ ገንዘብ የወጣበት ሁለተኛው የውድድር ዘመን ያደርገዋል። ከዚህ የውድድር ዘመን ውጪ በጥር የዝውውር ወር በዝውውሩ የመዝጊያዋ ዕለት ከ30 ሚሊዮን ፓውንድ በታች ወጪ የተደረገበት የውድድር ዘመን 2010 እ.አ.አ ነው። 10 ሚሊዮን ፓውንድ ብቻ ነበር ወጪ የተደረገበት። • የአውሮፓን እግር ኳስ የሚዘውረው ሃብታሙ 'ደላላ' ከፍተኛው ደግሞ 2018 እ.አ.አ ሲሆን በመዝጊያው ዕለት ብቻ 180 ሚሊዮን ፓውንድ ወጪ ተደርጎበታል። በዚህ የዝውውር ወር ቼልሲ ምንም ተጫዋች ባለማስፈረም ብቸኛው ክለብ ነው። ማንችስተር ዩናይትድ የስፖርቲንግ ሊዝበኑን ብሩኖ ፈርናንዴዝን በ47 ሚሊዮን መነሻ ዋጋ ያሰፈረመ ሲሆን በሂደት ግን የተጫዋቹ ዋጋ እስከ 67.7 ሚሊዮን ፓውንድ ያድጋል ተብሏል። ሸፊልድ ዩናይትዶች ሳንዴር በርግን በ22 ሚሊዮን ፓውንድ በማስፈራም የራሳቸውን ክብረወሰን አሻሽለዋል። • ቢጫና ቀይ ካርዶች እንዴት ወደ እግር ኳስ ሜዳ መጡ? በአሁኑ ወቅት አብዛኞቹ የአውሮፓ ታላላቅ ክለቦች የዝውውር ጊዜያቸውን አጠናቅቀዋል። ስፔን፣ ጀርመን፣ ጣልያን፣ ፈረንሳይና ሆላንድ እንደ እንግሊዝ ሁሉ የዝውውር ጊዜያቸውን በፈረንጆቹ ጥር 31 ትናንት ሌሊት የብሪታኒያ ከአውሮፓ ሕብረት መውጣት ጋር እኩል የዘጉ ናቸው። የፖርቱጋል ክለቦች ደግሞ በገበያው እስከ ፈረንጆቹ የካቲት ሁለት (በኢትዮጰያ እስከ ጥር 24) ድረስ ይቆያሉ። በተጨማሪም የሩሲያ፣ የቻይናና የአሜሪካ ክለቦች አሁንም አዲስ ተጫዋቾችን መቀበል ከሚችሉት መካከል ናቸው። | የእንግሊዝ ክለቦች ለተጫዋች ግዥ 1.6 ቢሊዮን ዶላር አወጡ ትናንት ብሪታኒያ ውስጥ ሁለት ክስተቶች በተመሳሳይ ሰዓት እልባት አግኝተው በብዙዎች ዘንድ ግርምትን አጭሯል። ሁለቱም የተጠናቀቁት በየራሳቸው መንገድ ቢሆንም ትናንት እኩለ ሌሊት ስፖርትና ፖለቲካ ተመሳሳይ ሰዓት ላይ ተገጣጥመዋል፤ በእንግሊዝ ሰዓት አቆጣጠር 23፡00 ላይ። ለሦስት ዓመታት ሲንከባለል የነበረው የብሪታኒያ ከአውሮፓ ሕብረት የመውጣት ሂደት ፍጻሜውን አግኝቶ በመላዋ ብሪታኒያ ሲበሰር፤ በዚያችው ቅጽበትም የእንግሊዝ ፕሪሜየር ሊግ የጥር የዝውውር መስኮት ተዘግቷል። የዝውውር ወሩ ስም ያላቸው ተጫዋቾችን ብዙም ሳይዳፈር በአብዛኛው አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ፕሪሜር ሊጉ በማምጣት ተጠናቋል። • አሠልጣኝ አብርሃም መብራህቱ፡ "የመጣውን በጸጋ መቀበልና መዘጋጀት ነው" በማጠናቀቂያ ሰዓቱ ላይ የፈረሙት ጃሮድ ቦውን እና ኦዲዮ ኢጋሎ በመጨረሻዋ ቀን በከፍተኛ የዝውውር ገንዘብ የተገዙ ተጫዋቾች ናቸው። በመጨረሻዋ ቀን ዌስትሃም ዩናይትድ የሃል ሲቲውን አጥቂ ጃሮድ ቦውን በ18 ሚሊዮን ፓውንድ አስፈርሟል። በውድድር ዘመኑ በጥር የዝውውር የመዝጊያ ዕለት ብቻ የወጣ ከፍተኛ ገንዘብ ሆኖም ተመዝግቧል። ይሁን እንጂ በጥር የዝውውር ወር የመጨረሻ ቀን እስከዛሬ ከወጣው ከፍተኛ ገንዘብ ጋር ሲነጻጸር ከ2010 እ.አ.አ ወዲህ ትንሹ ገንዘብ ሆኖ ተመዝግቧል። • «የኔ ትውልድ ታሪክ እንደሚሠራ እምነት አለኝ» ሎዛ አበራ በወሩ አጠቃላይ የእንግሊዝ ክለቦች 230 ሚሊዮን ፓውንድ ወጪ አድርገው ተጫዋቾችን የገዙ ሲሆን በታሪክ ሁለተኛው ከፍተኛ ገንዘብ ነው። ከዚህ ገንዘብ መካከል ታዲያ በመጨረሻዋ ቀን 25 ሚሊዮን ፓውንድ ብቻ ነው ወጪ የተደረገው። እንደአጠቃላይ ደግሞ በዚህ የውድድር ዘመን የእንግሊዝ ክለቦች ተጫዋች ለመግዛት 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ፓውንድ አውጥተዋል። ይህም 1 ነጥብ 9 ቢሊዮን ፓውንድ ከወጣበት የ2017/18 የውድድር ዘመን ቀጥሎ በታሪክ ከፍተኛ ገንዘብ የወጣበት ሁለተኛው የውድድር ዘመን ያደርገዋል። ከዚህ የውድድር ዘመን ውጪ በጥር የዝውውር ወር በዝውውሩ የመዝጊያዋ ዕለት ከ30 ሚሊዮን ፓውንድ በታች ወጪ የተደረገበት የውድድር ዘመን 2010 እ.አ.አ ነው። 10 ሚሊዮን ፓውንድ ብቻ ነበር ወጪ የተደረገበት። • የአውሮፓን እግር ኳስ የሚዘውረው ሃብታሙ 'ደላላ' ከፍተኛው ደግሞ 2018 እ.አ.አ ሲሆን በመዝጊያው ዕለት ብቻ 180 ሚሊዮን ፓውንድ ወጪ ተደርጎበታል። በዚህ የዝውውር ወር ቼልሲ ምንም ተጫዋች ባለማስፈረም ብቸኛው ክለብ ነው። ማንችስተር ዩናይትድ የስፖርቲንግ ሊዝበኑን ብሩኖ ፈርናንዴዝን በ47 ሚሊዮን መነሻ ዋጋ ያሰፈረመ ሲሆን በሂደት ግን የተጫዋቹ ዋጋ እስከ 67.7 ሚሊዮን ፓውንድ ያድጋል ተብሏል። ሸፊልድ ዩናይትዶች ሳንዴር በርግን በ22 ሚሊዮን ፓውንድ በማስፈራም የራሳቸውን ክብረወሰን አሻሽለዋል። • ቢጫና ቀይ ካርዶች እንዴት ወደ እግር ኳስ ሜዳ መጡ? በአሁኑ ወቅት አብዛኞቹ የአውሮፓ ታላላቅ ክለቦች የዝውውር ጊዜያቸውን አጠናቅቀዋል። ስፔን፣ ጀርመን፣ ጣልያን፣ ፈረንሳይና ሆላንድ እንደ እንግሊዝ ሁሉ የዝውውር ጊዜያቸውን በፈረንጆቹ ጥር 31 ትናንት ሌሊት የብሪታኒያ ከአውሮፓ ሕብረት መውጣት ጋር እኩል የዘጉ ናቸው። የፖርቱጋል ክለቦች ደግሞ በገበያው እስከ ፈረንጆቹ የካቲት ሁለት (በኢትዮጰያ እስከ ጥር 24) ድረስ ይቆያሉ። በተጨማሪም የሩሲያ፣ የቻይናና የአሜሪካ ክለቦች አሁንም አዲስ ተጫዋቾችን መቀበል ከሚችሉት መካከል ናቸው። | https://www.bbc.com/amharic/sport-51338567 |
5sports
| አትሌት ሻምበል አበበ ቢቂላ ሲታወስ | በዛሬው ዕለት ጥቅምት 25 ታዋቂው የማራቶን ሯጭ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየ 41 ዓመታትን አስቆጥሯል። አትሌቱ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመላው አፍሪካውያን በአትሌቱ ዘርፍ በር ከፋች ነበር። የዚህ ታላቅ ሰው መካነ መቃብር አዲስ አበባ በሚገኘው ቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርስትያን ይገኛል። ድሉ ደግሞ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ ታትሟል። የአበበን ታሪክ የታሪክ ሰነዶች፣ የስፖርት መዛግብት፣ የዓለም መገናኛ ብዙኀንና ኢትዮጵያውያን በጉልህ ያስታውሱታል። ከድሎቹ ሁሉ ደምቆ የሚታወሰው ደግሞ በሮም ኦሎምፒክ በባዶ እግሩ ሮጦ ለአገሩ ኢትዮጵያ እና ለጥቁር ህዝቦች ያስመዘገበው ድል ነው። 17ኛው የዓለም ኦሎምፒክ ውድድር እኤአ በ1960 በጣልያን መዲና ሮማ ነበር የተካሄደው። በዚህ ውድድር ከ83 ሀገራት የተወጣጡ ከ5 ሺህ በላይ ስፖርተኞች መሳተፋቸው ይነገራል። በሮም ኦሎምፒክ ከተሳተፉ ጥቁሮች መካከል ግን ሌላ ባለድልም አለ። መሐመድ ዓሊ በቀላል ሚዛን የወርቅ ሜዳልያ ተጎናፅፎ ነበር። ቢሆንም ኦሎምፒኩ በመሐመድ ዓሊ ወርቅ ሜዳልያ እምብዛም የደመቀ አልነበረም። በወቅቱ ታሪክ የሚያስታውሰው ሌላ ክስተትም ነበር። ጊዜው ደቡብ አፍሪካ በአህጉራዊ ውድድሮች ለመጨረሻ ግዜ ተሳትፋ የታገደችበት ነበር። የእገዳዋ ምክንያት ደግሞ ትከተለው በነበረ የአፓርታይድ ስርአት መሆኑ ነው። ቢሆንም የያኔ የሮሙ ኦሎምፒክ በመሐመድ ዓሊ የወርቅ ሜዳልያም ብሎም በደቡብ አፍሪቃ መታገድ አይደለም የሚታወሰው። ታድያ በምን ይታወሳል ያሉ እንደሆነ በውድድር ዘመኑ የማራቶን ሩጫ ያለ ጫማ ሮጦ የርቀቱ አዲስ ክብረወሰን ባስመዘገበው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሻምበል አበበ በቂላ ነው። በወቅቱ በርካታ ሊጠቀሱ የሚችሉ ነገሮች ቢከናወኑም አበበ ግን ታሪኮችን ሁሉ ልቆ የሚታወስ ድንቅ ታሪክ አስመዘገበ። ያኔ፣ አይደለም አበበ በቂላ የሚባል አትሌት፣ ኢትዮጵያ ተብላ ስለምትጠራ ሀገርም የሚያውቅ የውጭ ዜጋ ቁጥር እዚህ ግባ የሚባል አልነበረም። ይሁን እንጂ ውድድሩ በጣልያን መካሄዱ እና የጣልያን ወረራ በኢትዮጵያ ድል አድራጊነት ተጠናቅቆ ነጻነቷን የማግኘቷ ወሬ ገና ከዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች የወሬ አጀንዳነት ባለመረሳቱ፣ የአበበ ቢቂላ ድል ገነነ። የዓለም አቀፍ ሚድያዎች ሳይቀር ባልተጠበቀው የአትሌት አበበ በቂላ ድል ተደምመው ደጋግመው፣ በባዶ እግር ሮጦ የወርቅ ሜዳልያ ስላገኘው ኢትዮጵያዊው አትሌት ተናገሩ። "ሙሶሎኒ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች አሰልፎ እና መድፍ እና መርዛማ ጋዝ ተጠቅሞ ኢትዮጵያን ሲወር፣ አንድ ኢትዮጵያዊ ወታደር ግን ጣልያንን ብቻ ሳይሆን መላውን አለም አሸነፈ" የሚል ዘገባዎች ተሰራጩ። የኦሎምፒክ ውድድር እየተካሄደ በነበረበት ግዜ ጥቂት ኢትዮጵያውያን በጣልያን ሮም ይኖሩ ነበር። እነዚህ ኢትዮጵያውያን በካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን አማካኝነት የሥነ መለኮት ትምህርት እንዲማሩ ተብለው ከኢትዮጵያ የተላኩ ናቸው። እኤአ በ1960 አንዲት እናት በስራ ምክንያት ከአስመራ ወደ ሮም ተጉዘው ነበር። እኚህ ወ/ሮ ሳራ ሰለባ፣ የተሰኙ እናት "የጥቁሮች ፊት ሳላይ እኖራለሁ፣ ያቺ ተወልጄ ያደግኩባት አስመራም በምናቤ ትመላለስ ነበር። አልፎ አልፎ እነዛ የተባረኩ የሥነ መለኮት ተማሪዎች ብቸኝነቴ ተረድተው እየመጡ ይጠይቁኝ ነበሩ" ብለው ያጫውቱት እንደነበር ልጃቸው ያስታውሳል። ወ/ሮ ሳራ፣ አበበ በቂላ ሮጦ ድል ያደረገበ ዕለት ውደድሩ በቴሌቭዥን መስኮት ተከታትለዋል። አብረዋቸው የነበሩ ነጮች ተሰብስበው "የሀገርሽ ልጅ አሸንፏል" እያሉ ይጮሁ እንደነበር ያስታውሳሉ። ታድያ ወ/ሮ ሳራ አብረዋቸው ከመደሰት ይልቅ ማልቀስን መረጡ። ለወ/ሮ ሳራ የለቅሶ ምክንያት የነበረው ደግሞ የአበበ ባዶ እግር መሮጥ ነበር። አበበ ቢቂላ ነሐሴ 30 ቀን 1925 ዓ.ም በሸዋ ጠቅላይ ግዛት በደብረ ብርሃን አውራጃ፣ ደነባ ልዩ ስሟ ጃቶ በምትባል ሥፍራ ከአባቱ አቶ ቢቂላ ደምሴና ከእናቱ ከወይዘሮ ውድነሽ መንበሩ ተወለደ። ወጣቱ አበበ እንደአካባቢው ልምድ በእረኝነት ቤተሰቡን አገልግሏል። በአሥራ ሁለት ዓመቱም የቄስ ትምህርቱን አጠናቋል። በዚህ በጨቅላ ዕድሜው ስመ ጥር የገና ተጫዋች እንደነበር ይነገርለታል። በ1944 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ በመሄድ በክብር ዘበኛ ሰራዊት በወታደርነት ተቀጥሮ በገና ጨዋታ እና በስፖርት እየዳበረ ቆየ። ስዊድናዊው ኦኒ ኒስካነን [1910-1984] የክብር ዘበኛ ስፖርት ክፍል አስልጣኝ ነበር። በወቅቱ የስፖርት ክፍሉ ባልደረቦች ከነበሩት መካከል የሁለቱ አበበዎች የሩጫ ልምድ ትኩረቱን ስቦት እንደነበር ትቶት የሄደው ማስታወሻ ያሳያል። አበበ በቂላ ወደ አትሌቱ መንደር የተቀላቀለው በ24 አመቱ ነበር። ኦኒ ኒስካነን አበበን ወደ ሩጫ እንዲገባ ባያደፋፍረው አትሌትም ላይሆን ይችል እንደነበር ይነገራል። እርግጥ ነው አበበ እግር ኳስ እና ቅርጫት መጫወት ይወድ ነበር። አስለጣኝ ኦኒ ኒስካነን አበበ የሩጫ ውድድር እንዲሞካክር ይገፋፋው ነበር። በአራራጡ እና በራስ መተማመኑ ይወድለት ስለነበር በክቡር ዘበኛ ውድድሮች ሲያሳትፈው ጥሩ ውጤት ያመጣ ጀመር። ኒስካነን የአበበ በቂላ እና አበበ ዋቅጅራ የሩጫ ልምድ አይቶ ሮም ላይ በተካሄደው የዓለም ኦሎሚፒክ ውድድር እንዲሳተፉ አዘጋጃቸው። አበበ ዋቅጅራ ከአበበ ቢቂላ በ10 ዓመት ያህል የሚበልጥ ሲሆን በሮም ኦሎምፒክ ላይ እንደ አበበ ሁሉ በባዶ እግሩ ሮጦ ሰባተኛ መውጣቱን ድርሳናት ያሳያሉ። በሮም ኦሊምፒክ አበበ ቢቂላ በባዶ እግሩ የሮጠበት ምክንያት በተመለከተ የተለያዩ አስተያየቶች ሲንፀባረቁ ተሰምተዋል። በርካታ መዛግብት ለአበበ የሚስማማ ጫማ መጥፋቱን፣ የሞከረውም ጫማ ስለጠበበው ያለጫማ መሮጥን መምረጡን ጽፈዋል። እነዚህ መዛግብት አበበ ዋቅጅራም በባዶ እግሩ ስለመሮጡ ያነሱት አንዳች ነገር የለም። ይሁን እንጂ እውነታውን በተመለከተ የአበበ ቢቂላ ልጆች እንዲሁም አሰልጣኙ ትተዋቸው ያለፉ ድርሳናትና የይድነቃቸው ተሰማ እሸቴ ማስታወሻዎች ይህንን ይናገራሉ። ኦኒ ኒስካነን እነ አበበን ይዞ ወደ ሮም ከተጓዘ በኋላ እዚያው ሮም የሩጫ ልምምድ ያደርጉ ነበር። ልምምዱ የሚካሄደውም ጫም ተጫምተው እና በባዶ እግር ነበር። ኦኒ ኒስካነን በልምምዱ ሂደት ታድያ አንድ ነገር አስተዋለ። ሁለቱም አትሌቶች በባዶ እግር ሲሮጡ የተሻለ ፍጥነት ማስመዝገብ ችለው ነበር። ውድድሩን በድል ያጠናቅቁ እንጂ እንደ ፍላጎታቸው መሮጥ እንዲችሉ ፈቀደላቸው። አበበ ቢቂላ ጫማ ተጫምቶ ሲሮጥ በአንዲት ደቂቃ ከ5-6 ስንዝር ይዘገይ እንደነበርም አሰልጣኙ ኦኒ ኒስካነን መስክሯል። ከውድድሩ በኋላ ስለ ሁኔታው የተጻፉት እውነታነት እንዳልነበራቸውም ኒስካነን ተናግሮ ነበር። 'ጫማ ስላልተገዛላቸው ነው' እና 'የተገዛላቸው ጫማ ስለጠበባቸው ነው' የሚሉ ሀሳቦች ሀቅ አይደሉም ብሏል ኒስካነን። ኦኒ ኒስካነን እንደሚተርከው ሁለቱም ተወዳዳሪዎች ወደ ሮም ከመሄዳቸው በፊት ስለ ውድድሩ በቂ መረጃ ተሰጥቷቸው ነበር። በውድድሩ የተሻለ ፍጥነት ያላቸው ተወዳዳሪዎች እነማን ሊሆኑ ይችላሉ ከሚለው ጀምሮ እስከ የመወዳደርያ ማልያ ቁጥራቸው በሚገባ ተነግሯቸዋል። እነ አበበ ቢቂላን ከሚፎካከሩት መካከል ደግሞ ሞሮኳዊው ሯጭ ራዲ ቢን አብደልሰላም ይገኝበታል። ስለራዲ እነ አበበ መረጃ ቢኖራቸውም የመወዳደሪያ ቁጥሩ መቀየሩን ግን አያውቁም ነበር። ራዲ ቀድሞ የተሰጠው የመወዳደርያ ቁጥር ስላልተገኘ ነበር ሌላ አዲስ ቁጥር የተሰጠው። እነ አበበ ግን ራዲ አዲስ ቁጥር እንደተሰጠው መረጃው የላቸውም። አበበ ከቀሪዎቹ ተወዳዳሪዎች በሰፊ ርቀት ፈንጠር ብሎ በሚሮጥበት ግዜ ሞሮኳዊው ራዲ ግን በቅርብ ርቀት ይከተለው ነበር። በወቅቱ ሞሮኮ በውድድሩ ሶስት ተወዳዳሪዎች አሰልፋ ስለነበር፣ አበበ ከሶስቱ አንዳቸው ይሆናሉ በሚል ሮም የሚገኘው የአክሱም ሀውልት እስኪደርሱ ድረስ ብዙም ግምት አልሰጠውም ነበር። አበበ በውድድሩ በአስልጠኙ እንዲያደርጋቸው ከተነገሩት ነገሮች መካከል አንዱ የአክሱም ሀውልት ሲደርስ ፍጥነቱ እንዲጨምር ነበር። አበበም በተሰጠው ትእዛዝ መሰረት ውድድሩ ሊያልቅ 2 ኪሎ ሜትር ሲቀረው ሮም ፒያሳ በተተከለው አክሱም ሀውልት ሲደርስ በፍጥነት ተፈተለከ። አበበ ያኔ ለጥቂትም ቢሆን ቢዘናጋ ኖሮ ራዲ የማሸነፍ እድል እንደነበረው ይነገራል። እንደ አስልጣኙ ኦኒ ገለጻ ከሆነ አበበ 40 ኪሎ ሜትር ድረስ አብሮት የተጓዘው ራዲ መሆኑን ቢያውቅ ኖሮ ቀድሞት ሊሮጥ ምናልባትም ያስመዘገበው ክብወሰን በተሻለ ያሻሽለው ነበር ይላል። ሻምበል አበበ በቂላ በ1964 በቶክዮ ጃፓን በተካሄደው ውድድርም የራሱን ክብረወሰን በማሻሻል አሸናፊ ሆነ። ከውድድሩ አንድ ወር በፊት ግን ቀዶ ጥገና ተደርጎለት የነበረ ቢሆንም ውድድሩ በአስደናቂ ሁኔታ ለማጠናቀቅ ችሏል። በ1968 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ36 ዓመቱ በኦሎሚፒክ ውድድር ለ3ኛ ግዜ የተሳተፈ ቢሆንም በጉዳት ምክንያት ሳይጨርስ የቀረ ሲሆን፣ ውድድሩ በሌኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ማሞ ወልዴ አሸናፊነት ተጠናቀቀ። አለምን በባዶ እግር ሮጦ በማሸነፍ አንቱታ ያተረፈውን ሻምበል አበበ በቂላ በገጠመው የመኪና አደጋ ምክንያት በ41 ዓመቱ ከዚህ አለም ተለየ። | አትሌት ሻምበል አበበ ቢቂላ ሲታወስ በዛሬው ዕለት ጥቅምት 25 ታዋቂው የማራቶን ሯጭ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየ 41 ዓመታትን አስቆጥሯል። አትሌቱ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመላው አፍሪካውያን በአትሌቱ ዘርፍ በር ከፋች ነበር። የዚህ ታላቅ ሰው መካነ መቃብር አዲስ አበባ በሚገኘው ቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርስትያን ይገኛል። ድሉ ደግሞ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ ታትሟል። የአበበን ታሪክ የታሪክ ሰነዶች፣ የስፖርት መዛግብት፣ የዓለም መገናኛ ብዙኀንና ኢትዮጵያውያን በጉልህ ያስታውሱታል። ከድሎቹ ሁሉ ደምቆ የሚታወሰው ደግሞ በሮም ኦሎምፒክ በባዶ እግሩ ሮጦ ለአገሩ ኢትዮጵያ እና ለጥቁር ህዝቦች ያስመዘገበው ድል ነው። 17ኛው የዓለም ኦሎምፒክ ውድድር እኤአ በ1960 በጣልያን መዲና ሮማ ነበር የተካሄደው። በዚህ ውድድር ከ83 ሀገራት የተወጣጡ ከ5 ሺህ በላይ ስፖርተኞች መሳተፋቸው ይነገራል። በሮም ኦሎምፒክ ከተሳተፉ ጥቁሮች መካከል ግን ሌላ ባለድልም አለ። መሐመድ ዓሊ በቀላል ሚዛን የወርቅ ሜዳልያ ተጎናፅፎ ነበር። ቢሆንም ኦሎምፒኩ በመሐመድ ዓሊ ወርቅ ሜዳልያ እምብዛም የደመቀ አልነበረም። በወቅቱ ታሪክ የሚያስታውሰው ሌላ ክስተትም ነበር። ጊዜው ደቡብ አፍሪካ በአህጉራዊ ውድድሮች ለመጨረሻ ግዜ ተሳትፋ የታገደችበት ነበር። የእገዳዋ ምክንያት ደግሞ ትከተለው በነበረ የአፓርታይድ ስርአት መሆኑ ነው። ቢሆንም የያኔ የሮሙ ኦሎምፒክ በመሐመድ ዓሊ የወርቅ ሜዳልያም ብሎም በደቡብ አፍሪቃ መታገድ አይደለም የሚታወሰው። ታድያ በምን ይታወሳል ያሉ እንደሆነ በውድድር ዘመኑ የማራቶን ሩጫ ያለ ጫማ ሮጦ የርቀቱ አዲስ ክብረወሰን ባስመዘገበው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሻምበል አበበ በቂላ ነው። በወቅቱ በርካታ ሊጠቀሱ የሚችሉ ነገሮች ቢከናወኑም አበበ ግን ታሪኮችን ሁሉ ልቆ የሚታወስ ድንቅ ታሪክ አስመዘገበ። ያኔ፣ አይደለም አበበ በቂላ የሚባል አትሌት፣ ኢትዮጵያ ተብላ ስለምትጠራ ሀገርም የሚያውቅ የውጭ ዜጋ ቁጥር እዚህ ግባ የሚባል አልነበረም። ይሁን እንጂ ውድድሩ በጣልያን መካሄዱ እና የጣልያን ወረራ በኢትዮጵያ ድል አድራጊነት ተጠናቅቆ ነጻነቷን የማግኘቷ ወሬ ገና ከዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች የወሬ አጀንዳነት ባለመረሳቱ፣ የአበበ ቢቂላ ድል ገነነ። የዓለም አቀፍ ሚድያዎች ሳይቀር ባልተጠበቀው የአትሌት አበበ በቂላ ድል ተደምመው ደጋግመው፣ በባዶ እግር ሮጦ የወርቅ ሜዳልያ ስላገኘው ኢትዮጵያዊው አትሌት ተናገሩ። "ሙሶሎኒ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች አሰልፎ እና መድፍ እና መርዛማ ጋዝ ተጠቅሞ ኢትዮጵያን ሲወር፣ አንድ ኢትዮጵያዊ ወታደር ግን ጣልያንን ብቻ ሳይሆን መላውን አለም አሸነፈ" የሚል ዘገባዎች ተሰራጩ። የኦሎምፒክ ውድድር እየተካሄደ በነበረበት ግዜ ጥቂት ኢትዮጵያውያን በጣልያን ሮም ይኖሩ ነበር። እነዚህ ኢትዮጵያውያን በካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን አማካኝነት የሥነ መለኮት ትምህርት እንዲማሩ ተብለው ከኢትዮጵያ የተላኩ ናቸው። እኤአ በ1960 አንዲት እናት በስራ ምክንያት ከአስመራ ወደ ሮም ተጉዘው ነበር። እኚህ ወ/ሮ ሳራ ሰለባ፣ የተሰኙ እናት "የጥቁሮች ፊት ሳላይ እኖራለሁ፣ ያቺ ተወልጄ ያደግኩባት አስመራም በምናቤ ትመላለስ ነበር። አልፎ አልፎ እነዛ የተባረኩ የሥነ መለኮት ተማሪዎች ብቸኝነቴ ተረድተው እየመጡ ይጠይቁኝ ነበሩ" ብለው ያጫውቱት እንደነበር ልጃቸው ያስታውሳል። ወ/ሮ ሳራ፣ አበበ በቂላ ሮጦ ድል ያደረገበ ዕለት ውደድሩ በቴሌቭዥን መስኮት ተከታትለዋል። አብረዋቸው የነበሩ ነጮች ተሰብስበው "የሀገርሽ ልጅ አሸንፏል" እያሉ ይጮሁ እንደነበር ያስታውሳሉ። ታድያ ወ/ሮ ሳራ አብረዋቸው ከመደሰት ይልቅ ማልቀስን መረጡ። ለወ/ሮ ሳራ የለቅሶ ምክንያት የነበረው ደግሞ የአበበ ባዶ እግር መሮጥ ነበር። አበበ ቢቂላ ነሐሴ 30 ቀን 1925 ዓ.ም በሸዋ ጠቅላይ ግዛት በደብረ ብርሃን አውራጃ፣ ደነባ ልዩ ስሟ ጃቶ በምትባል ሥፍራ ከአባቱ አቶ ቢቂላ ደምሴና ከእናቱ ከወይዘሮ ውድነሽ መንበሩ ተወለደ። ወጣቱ አበበ እንደአካባቢው ልምድ በእረኝነት ቤተሰቡን አገልግሏል። በአሥራ ሁለት ዓመቱም የቄስ ትምህርቱን አጠናቋል። በዚህ በጨቅላ ዕድሜው ስመ ጥር የገና ተጫዋች እንደነበር ይነገርለታል። በ1944 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ በመሄድ በክብር ዘበኛ ሰራዊት በወታደርነት ተቀጥሮ በገና ጨዋታ እና በስፖርት እየዳበረ ቆየ። ስዊድናዊው ኦኒ ኒስካነን [1910-1984] የክብር ዘበኛ ስፖርት ክፍል አስልጣኝ ነበር። በወቅቱ የስፖርት ክፍሉ ባልደረቦች ከነበሩት መካከል የሁለቱ አበበዎች የሩጫ ልምድ ትኩረቱን ስቦት እንደነበር ትቶት የሄደው ማስታወሻ ያሳያል። አበበ በቂላ ወደ አትሌቱ መንደር የተቀላቀለው በ24 አመቱ ነበር። ኦኒ ኒስካነን አበበን ወደ ሩጫ እንዲገባ ባያደፋፍረው አትሌትም ላይሆን ይችል እንደነበር ይነገራል። እርግጥ ነው አበበ እግር ኳስ እና ቅርጫት መጫወት ይወድ ነበር። አስለጣኝ ኦኒ ኒስካነን አበበ የሩጫ ውድድር እንዲሞካክር ይገፋፋው ነበር። በአራራጡ እና በራስ መተማመኑ ይወድለት ስለነበር በክቡር ዘበኛ ውድድሮች ሲያሳትፈው ጥሩ ውጤት ያመጣ ጀመር። ኒስካነን የአበበ በቂላ እና አበበ ዋቅጅራ የሩጫ ልምድ አይቶ ሮም ላይ በተካሄደው የዓለም ኦሎሚፒክ ውድድር እንዲሳተፉ አዘጋጃቸው። አበበ ዋቅጅራ ከአበበ ቢቂላ በ10 ዓመት ያህል የሚበልጥ ሲሆን በሮም ኦሎምፒክ ላይ እንደ አበበ ሁሉ በባዶ እግሩ ሮጦ ሰባተኛ መውጣቱን ድርሳናት ያሳያሉ። በሮም ኦሊምፒክ አበበ ቢቂላ በባዶ እግሩ የሮጠበት ምክንያት በተመለከተ የተለያዩ አስተያየቶች ሲንፀባረቁ ተሰምተዋል። በርካታ መዛግብት ለአበበ የሚስማማ ጫማ መጥፋቱን፣ የሞከረውም ጫማ ስለጠበበው ያለጫማ መሮጥን መምረጡን ጽፈዋል። እነዚህ መዛግብት አበበ ዋቅጅራም በባዶ እግሩ ስለመሮጡ ያነሱት አንዳች ነገር የለም። ይሁን እንጂ እውነታውን በተመለከተ የአበበ ቢቂላ ልጆች እንዲሁም አሰልጣኙ ትተዋቸው ያለፉ ድርሳናትና የይድነቃቸው ተሰማ እሸቴ ማስታወሻዎች ይህንን ይናገራሉ። ኦኒ ኒስካነን እነ አበበን ይዞ ወደ ሮም ከተጓዘ በኋላ እዚያው ሮም የሩጫ ልምምድ ያደርጉ ነበር። ልምምዱ የሚካሄደውም ጫም ተጫምተው እና በባዶ እግር ነበር። ኦኒ ኒስካነን በልምምዱ ሂደት ታድያ አንድ ነገር አስተዋለ። ሁለቱም አትሌቶች በባዶ እግር ሲሮጡ የተሻለ ፍጥነት ማስመዝገብ ችለው ነበር። ውድድሩን በድል ያጠናቅቁ እንጂ እንደ ፍላጎታቸው መሮጥ እንዲችሉ ፈቀደላቸው። አበበ ቢቂላ ጫማ ተጫምቶ ሲሮጥ በአንዲት ደቂቃ ከ5-6 ስንዝር ይዘገይ እንደነበርም አሰልጣኙ ኦኒ ኒስካነን መስክሯል። ከውድድሩ በኋላ ስለ ሁኔታው የተጻፉት እውነታነት እንዳልነበራቸውም ኒስካነን ተናግሮ ነበር። 'ጫማ ስላልተገዛላቸው ነው' እና 'የተገዛላቸው ጫማ ስለጠበባቸው ነው' የሚሉ ሀሳቦች ሀቅ አይደሉም ብሏል ኒስካነን። ኦኒ ኒስካነን እንደሚተርከው ሁለቱም ተወዳዳሪዎች ወደ ሮም ከመሄዳቸው በፊት ስለ ውድድሩ በቂ መረጃ ተሰጥቷቸው ነበር። በውድድሩ የተሻለ ፍጥነት ያላቸው ተወዳዳሪዎች እነማን ሊሆኑ ይችላሉ ከሚለው ጀምሮ እስከ የመወዳደርያ ማልያ ቁጥራቸው በሚገባ ተነግሯቸዋል። እነ አበበ ቢቂላን ከሚፎካከሩት መካከል ደግሞ ሞሮኳዊው ሯጭ ራዲ ቢን አብደልሰላም ይገኝበታል። ስለራዲ እነ አበበ መረጃ ቢኖራቸውም የመወዳደሪያ ቁጥሩ መቀየሩን ግን አያውቁም ነበር። ራዲ ቀድሞ የተሰጠው የመወዳደርያ ቁጥር ስላልተገኘ ነበር ሌላ አዲስ ቁጥር የተሰጠው። እነ አበበ ግን ራዲ አዲስ ቁጥር እንደተሰጠው መረጃው የላቸውም። አበበ ከቀሪዎቹ ተወዳዳሪዎች በሰፊ ርቀት ፈንጠር ብሎ በሚሮጥበት ግዜ ሞሮኳዊው ራዲ ግን በቅርብ ርቀት ይከተለው ነበር። በወቅቱ ሞሮኮ በውድድሩ ሶስት ተወዳዳሪዎች አሰልፋ ስለነበር፣ አበበ ከሶስቱ አንዳቸው ይሆናሉ በሚል ሮም የሚገኘው የአክሱም ሀውልት እስኪደርሱ ድረስ ብዙም ግምት አልሰጠውም ነበር። አበበ በውድድሩ በአስልጠኙ እንዲያደርጋቸው ከተነገሩት ነገሮች መካከል አንዱ የአክሱም ሀውልት ሲደርስ ፍጥነቱ እንዲጨምር ነበር። አበበም በተሰጠው ትእዛዝ መሰረት ውድድሩ ሊያልቅ 2 ኪሎ ሜትር ሲቀረው ሮም ፒያሳ በተተከለው አክሱም ሀውልት ሲደርስ በፍጥነት ተፈተለከ። አበበ ያኔ ለጥቂትም ቢሆን ቢዘናጋ ኖሮ ራዲ የማሸነፍ እድል እንደነበረው ይነገራል። እንደ አስልጣኙ ኦኒ ገለጻ ከሆነ አበበ 40 ኪሎ ሜትር ድረስ አብሮት የተጓዘው ራዲ መሆኑን ቢያውቅ ኖሮ ቀድሞት ሊሮጥ ምናልባትም ያስመዘገበው ክብወሰን በተሻለ ያሻሽለው ነበር ይላል። ሻምበል አበበ በቂላ በ1964 በቶክዮ ጃፓን በተካሄደው ውድድርም የራሱን ክብረወሰን በማሻሻል አሸናፊ ሆነ። ከውድድሩ አንድ ወር በፊት ግን ቀዶ ጥገና ተደርጎለት የነበረ ቢሆንም ውድድሩ በአስደናቂ ሁኔታ ለማጠናቀቅ ችሏል። በ1968 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ36 ዓመቱ በኦሎሚፒክ ውድድር ለ3ኛ ግዜ የተሳተፈ ቢሆንም በጉዳት ምክንያት ሳይጨርስ የቀረ ሲሆን፣ ውድድሩ በሌኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ማሞ ወልዴ አሸናፊነት ተጠናቀቀ። አለምን በባዶ እግር ሮጦ በማሸነፍ አንቱታ ያተረፈውን ሻምበል አበበ በቂላ በገጠመው የመኪና አደጋ ምክንያት በ41 ዓመቱ ከዚህ አለም ተለየ። | https://www.bbc.com/amharic/news-54672466 |
3politics
| የኔዘርላንድሷ ልዕልት በደኅንነት ስጋት ከትምህርት ቤት ወጣች | የኔዘርላንድስ ንጉሥ እና ንግሥት የ18 ዓመት ልጃቸው ጥቃት ሊደርስባት ስለሚችል ከአሁን በኋላ በነጻነት መንቀሳቀስ እንደማትችል ገለጹ። ልዕልት አማሊያ አምስተርዳም ከሚገኘው የተማሪዎች መኖሪያ በመውጣት ዘ ሄግ ወደሚገኘው ቤት ተመልሳለች። ወላጆቿ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ በስዊድን ባደረጉት ጉብኝት ወቅት ነው በስሜታዊነት ዝርዝር ጉዳዮችን የገለጹት። ንግሥት ማክስማ “አስቸጋሪውን ሁኔታ” ሲገልጹ ዐይኖቻቸው በእምባ ተሞልቶ ነበር። “ለእሷ የተማሪነት ሕይወት እንደሌሎቹ ተማሪዎች አይደደለም” ብለዋል። ልዕልት አማሊያ እና የኔዘርላንድስ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩት ከተደራጁ ወንጀለኞች የተገኘ መረጃ ዒላማ ሊሆኑ እንደሚችሉ አመልክቷል። ባለፈው ወር በተሰራጨ ኦፊሴላዊ ፎቶ ልዕልት አማሊያን በመጀመሪያ የትምህርት ቀን በፈገግታ ተሞልታ ትታያለች። ወጣቷ ወደ ተማሪዎች መኖሪያ ቤት መግባቷ እና በአምስተርዳምስ ዩኒቨርሲቲ በፖለቲካ፣ በሥነ ልቦና፣ በሕግ እና በምጣኔ ሀብት የመጀመሪያ ዲግሪዋን መማር መጀመሯ በብዙዎች አድናቆት አትርፎላታል። ታኅሳስ ላይ 19 ዓመት የምትደፍነው አማሊያ ኔዘርላንድስ ውስጥ ብዙዎች በአንፃራዊነት ወደ ኅብረተሰቡ የቀረበች የንጉሣዊ ቤተሰብ ነች ሲሉ ይገልጿታል። ሞሂቶ የሚባል ፈረስ ያላት ሲሆን፤ በበጋ ወራት በሼቨኒንገን የባሕር ዳርቻ በሚገኝ መጠጥ ቤት ውስጥ መሥራቷ 'የኮክቴይል ንግሥት' የሚል ቅጽል ስም አስገኝቶላታል። ልዕልት አማሊያ ለ18ኛ ዓመት ልደቷ ባሳተመችው የሕይወት ታሪኳን በያዘው መጽሐፍ ስለ አእምሮ ጤንነቷ ተናግራ ብዙ ጊዜ የሥነ ልቦና ባለሙያዎችን እንደምትጎበኝ ተናግራለች። የመጀመሪያው የትምህርት ዘመንን በቅጡ ሳታጋምስ ነው የስለላ ተቋም ዘገባን ተከትሎ ልዕልት አማሊያ የምትወደውን እና የሚያስደስታትን የተማሪነት ሕይወት ለመተው የተገደደችው። የደኅንነት ጥንቃቄዎቹ ጊዜያዊ ብቻ እንደሆኑ ቤተሰቦቿ ተስፋ ያደርጋሉ። ንግሥት ማክስማ በስዊድን ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፣ ልዕልት አማሊያ ነገሩን የተቋቋመችበትን መንገድ እና ለጀግንነቷ ክብር እንደሚሰጡ ተናግረዋል። የአርጀንቲና ተወላጅና የቀድሞ ኢኮኖሚስት አባቷ አማሊያ አሁንም ዩኒቨርስቲ እንደምትማር ጠቁመው እንዲያውም ጥሩ ውጤት እያስመዘገበች ሊሆን ይችላል በማለት ቀልደዋል። ንጉሥ ቪለም-አሌክሳንደር እንደ አባት ጉዳዩን እንዲገልጹ ሲጠየቁ “ከባድ ሁኔታ” መሆኑን አምነው ተጽዕኖውን መግለጽ እንዳልቻሉ ተናግሯል። ለንጉሣዊው ቤተሰብ አባላት ወይም ለመንግሥት ባለሥልጣናት ስለደኅንነት ጉዳዮች ማውራት አልተለመደም። ፖሊስ፣ የሕዝብ ዐቃቤ ሕግ እና የመንግሥት ሚኒስቴር በንጉሣዊያኑ ጥንዶች መግለጫ ላይ አስተያየት ይሰጣሉ ተብሎ አይጠበቅም። | የኔዘርላንድሷ ልዕልት በደኅንነት ስጋት ከትምህርት ቤት ወጣች የኔዘርላንድስ ንጉሥ እና ንግሥት የ18 ዓመት ልጃቸው ጥቃት ሊደርስባት ስለሚችል ከአሁን በኋላ በነጻነት መንቀሳቀስ እንደማትችል ገለጹ። ልዕልት አማሊያ አምስተርዳም ከሚገኘው የተማሪዎች መኖሪያ በመውጣት ዘ ሄግ ወደሚገኘው ቤት ተመልሳለች። ወላጆቿ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ በስዊድን ባደረጉት ጉብኝት ወቅት ነው በስሜታዊነት ዝርዝር ጉዳዮችን የገለጹት። ንግሥት ማክስማ “አስቸጋሪውን ሁኔታ” ሲገልጹ ዐይኖቻቸው በእምባ ተሞልቶ ነበር። “ለእሷ የተማሪነት ሕይወት እንደሌሎቹ ተማሪዎች አይደደለም” ብለዋል። ልዕልት አማሊያ እና የኔዘርላንድስ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩት ከተደራጁ ወንጀለኞች የተገኘ መረጃ ዒላማ ሊሆኑ እንደሚችሉ አመልክቷል። ባለፈው ወር በተሰራጨ ኦፊሴላዊ ፎቶ ልዕልት አማሊያን በመጀመሪያ የትምህርት ቀን በፈገግታ ተሞልታ ትታያለች። ወጣቷ ወደ ተማሪዎች መኖሪያ ቤት መግባቷ እና በአምስተርዳምስ ዩኒቨርሲቲ በፖለቲካ፣ በሥነ ልቦና፣ በሕግ እና በምጣኔ ሀብት የመጀመሪያ ዲግሪዋን መማር መጀመሯ በብዙዎች አድናቆት አትርፎላታል። ታኅሳስ ላይ 19 ዓመት የምትደፍነው አማሊያ ኔዘርላንድስ ውስጥ ብዙዎች በአንፃራዊነት ወደ ኅብረተሰቡ የቀረበች የንጉሣዊ ቤተሰብ ነች ሲሉ ይገልጿታል። ሞሂቶ የሚባል ፈረስ ያላት ሲሆን፤ በበጋ ወራት በሼቨኒንገን የባሕር ዳርቻ በሚገኝ መጠጥ ቤት ውስጥ መሥራቷ 'የኮክቴይል ንግሥት' የሚል ቅጽል ስም አስገኝቶላታል። ልዕልት አማሊያ ለ18ኛ ዓመት ልደቷ ባሳተመችው የሕይወት ታሪኳን በያዘው መጽሐፍ ስለ አእምሮ ጤንነቷ ተናግራ ብዙ ጊዜ የሥነ ልቦና ባለሙያዎችን እንደምትጎበኝ ተናግራለች። የመጀመሪያው የትምህርት ዘመንን በቅጡ ሳታጋምስ ነው የስለላ ተቋም ዘገባን ተከትሎ ልዕልት አማሊያ የምትወደውን እና የሚያስደስታትን የተማሪነት ሕይወት ለመተው የተገደደችው። የደኅንነት ጥንቃቄዎቹ ጊዜያዊ ብቻ እንደሆኑ ቤተሰቦቿ ተስፋ ያደርጋሉ። ንግሥት ማክስማ በስዊድን ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፣ ልዕልት አማሊያ ነገሩን የተቋቋመችበትን መንገድ እና ለጀግንነቷ ክብር እንደሚሰጡ ተናግረዋል። የአርጀንቲና ተወላጅና የቀድሞ ኢኮኖሚስት አባቷ አማሊያ አሁንም ዩኒቨርስቲ እንደምትማር ጠቁመው እንዲያውም ጥሩ ውጤት እያስመዘገበች ሊሆን ይችላል በማለት ቀልደዋል። ንጉሥ ቪለም-አሌክሳንደር እንደ አባት ጉዳዩን እንዲገልጹ ሲጠየቁ “ከባድ ሁኔታ” መሆኑን አምነው ተጽዕኖውን መግለጽ እንዳልቻሉ ተናግሯል። ለንጉሣዊው ቤተሰብ አባላት ወይም ለመንግሥት ባለሥልጣናት ስለደኅንነት ጉዳዮች ማውራት አልተለመደም። ፖሊስ፣ የሕዝብ ዐቃቤ ሕግ እና የመንግሥት ሚኒስቴር በንጉሣዊያኑ ጥንዶች መግለጫ ላይ አስተያየት ይሰጣሉ ተብሎ አይጠበቅም። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c5164w2wxdqo |
5sports
| “በአምስት የዓለም ዋንጫዎች ወርቅ እንዲመጣ ምክንያት ነኝ” አትሌት ገብረእግዚአብሔር | አትሌት ገብረእግዚአብሔር ገብረማርያም ተወልዶ ያደገው በትግራይ ክልል በቀድሞዋ ሐውዜን፣ በአሁኗ ሳዕሲዕ ጻዕዳ እምባ ወረዳ ነው፤ ልዩ ስሟ ጻንቃኔት በተባለች አካባቢ ነው። በ1976 ዓ.ም. የተወለደው ገብረእግዚኣብሄር፤ ገና ታዳጊ እያለ በ16 ዓመቱ ጊዜውም በ1992 ዓ.ም ሩጫን ሀ ብሎ የጀመረው። በዓለም አቀፍ ደረጃ ለመጀመርያ ጊዜ 2003 ኒው ዮርክ በተካሄደው ማራቶን ላይ ተሳትፎ የወርቅ ሜዳልያ አገኘ። •"ሥልጣን ለደም ግፊት አጋልጦኛል" ኃይሌ ገብረሥላሴ ለቁጥር በሚያዳግቱ የተለያዩ ዓለም ዓቀፍ ውድድሮች በግሉም እንዲሁም በሃገርም ደረጃ ተሳትፎ ብዙ ወርቆችን ያስገኘ አትሌት ነው። በአሁኑ ወቅት ከሩጫው ባሻገር በአትሌቲክስ ፌዴሬሽንና በኦሎምፒክ ኮሚቴ ምክትል ኃላፊነት እያገለገለ ሲሆን፤በይፋ ጫማ ባይሰቅልም እምብዛም በሩጫ መድረክ ላይ ሲሳተፍ እየታየ አይደለም። ለዚህም ገብረእግዚአብሔር ምላሽ አለው "ሩጫ እንደሚታውቀው ብዙ ትኩረት የሚጠይቅ ነው። ቢዝነስን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እሳተፋለሁ። ከዚህ በተጨማሪም በዕድሜም እየገፋሁ ነው። በይፋ ጫማ ባልሰቅልም አሁን ወደዛው ነኝ።" በዚህና ወቅታዊ ስፖርታዊ ጉዳዮችን በማስመልከት ቢቢሲ ከገብረእግዚአብሄር ጋር ቆይታ አድርጓል። አትሌት ገብረእግዚአብሄር ሩጫ በጀመረበት ወቅት ሩጫ በአለም አቀፍ ደረጃ በውድድር ደረጃ ስላለው ስፍራ የጠለቀ እውቀት አልነበረውም። ትምህርቱን የተማረው እንደ ብዙው የኢትዮጵያ የገጠር ልጅ በእግሩ እየሄደ ነበር፤ አብዛኛውን ጊዜ ደግሞ ርቀቷን በሩጫ ፉት ይላታል። •ስለ አቶ ዱቤ ጅሎ ሽልማት ምን እናውቃለን? "እኔ የአርሶ አደር ልጅ ነኝ። ወላጆቼ ያዘዙኝን በሙሉ ሰርቼ በሰዓቱ ትምህርት ቤት ለመድረስ ስለማልችል እየሮጥኩ ነበር የምሄደው። ከትምህርት ቤት ስመለስም እንዲሁ በሩጫ ነበር።" ይላል ይሄ የአብዛኛው የአርሶ አደር ልጆች ታሪክ ቢሆንም ለገብረ እግዚአብሄር ግን የተለየ ዕድል እንደፈጠረለት ይናገራል። "አጋጣሚው ተፈጥሯዊ አቅምን ፈጥሮልኛል።" ሩጫን ከአንድ ቦታ ወደ አንድ ቦታ በፍጥነት ለመድረስ እንጂ በስፖርቱ አለም ያለውን ስፍራም አልተረዳውም ነበር። "በስፖርት ይሄን ያህል ታዋቂነት እንደሚገኝም አላውቅም ነበር" ይላል። ውድድር ማካሄድ የጀመረው በትምህርት ቤት በነበረበት ወቅት ሲሆን፤ የ9ኛ ክፍል ተማሪ ሆኖ በትምህርት ቤቱ በተጀመረው ውድድር ለመጀመርያ ጊዜ አንደኛ ወጥቶ የምስክር ወረቀትም አግኝቷል። •ጊነስ ዎርልድ ሪከርድስ፡ «ስለተተከሉት ዛፎች ከኢትዮጵያ የደረሰን መረጃ የለም» ከትምህርት ቤቱ በተጨማሪ ሌሎችን ውድድሮችን ማካሄድ የጀመረው ገብረእግዚአብሔር በ1993 ዓ.ም. የ11ኛ ክፍል ተማሪ ሆኖም አዲግራት አቅራብያ በምትገኘው ዕዳጋ ሐሙስ ከተማ ትምህርት ቤቱን ቀጢን ቃላይ' ወክሎ ነበር የተወዳደረው፤ አንደኛም ወጣ። ቀጥሎም ወረዳውን ወክሎ 1500 ኪሜ ተወዳደሮ ማሸነፉን ያስታውሳል። ለመጀመርያ ግዜ ከምስክር ወረቀት በተጨማሪ ሽልማት ያገኘበት መሆኑም ልዩ ያደርገዋል። አትሌት ገብረእግዚአብሄር አትሌት ገብረ እግዚአብሄር በተለይ ለእነዚህ ሶስቱ ድሎች [የአየርላንድ፣ የኒው ዮርክና አፍሪካ ሻምፒዮን] የተለየ ቦታ አለው። በተለይ ደግሞ የአፍሪካ ሻምፕዮን በኢትዮጵያ የተካሄደ በመሆኑና ከፍተኛ ዝናብ የጣለበት ፈታኝ ውድድርም ስለነበር ከፍ ያለ ትርጉም ይሰጠዋል። •"የት ይቀርልሃል!? አፈር ድሜ ትበላለህ...!" ጋሽ አበራ ሞላ "በኢትዮጵያ የመጀመርያ ውድድርም ስለ ነበር ሌሎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ወርቅ እንዲያመጡ ጉልበት የሆናቸው ይመስለኛል" የሚል እምነት አለው። የአትሌት ገብረ እግዚአብሄር አርአያ ማን ነው? ገብረእግዚአብሄር ሩጫን በአጋጣሚ ቢጀምርም በትምህርት ቤት ስለ እነ አትሌት ምሩጽ ይፍጠርና አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ የሩጫ ገድል ሲሰማ በሩጫ ላይ የተለየ ፍላጎት እንዳደረበት ይናገራል። አበበ ቢቂላም ሌላኛው የገብረእግዚአብሄር አርአያ ነው። ለሶስቱ አትሌቶች የተለየ ክብርና አድናቆት እንዳለው ነው የሚናገረው ገብረእግዚአብሄር፤ "ሩጫን ለዓለም በደንብ ያስተዋወቅነው እኛ ኢትዮጵያውያን ነን" የሚል አቋም አለው። ገብረእግዚአብሄር ከሁሉም በላይ ለኃይሌ ገብረ ስላሴ ያለው ቦታ ከፍ ያለ እንደሆነ ይናገራል። በሩጫ ማሸነፉ ብቻ ሳይሆን በሩጫው ለረዥም ግዜ የቆየበት ፅናቱን እንደ ምሳሌ ይቆጥረዋል። እንዲሁም ደግሞ ከሩጫው በተጨማሪ በቢዝነስ የሚያደርገው እንቅስቃሴና ስኬትም ሌላ የሚያደንቅበት ጉዳይ ነው። አትሌት ምሩጽ ይፍጠር በአንድ ኦሎምፒክ ሁለት የወርቅ ሜዳልያ ባለቤት መሆኑን ከፍተኛ ስፍራ ከመስጠቱ በተጨማሪ ለመጀመርያ ጊዜ ሩጫን በውድድርነት ሲሰማ የአትሌት ምሩጽ ይፍጠርን ድል ነበር የሰማው። የስድስተኛ ክፍል የሳይንስ መምህሩ ስለ አትሌት ምሩጽ ይፍጠር ማርሽ ቀያሪነት በሚነግሯቸው ወቅት መጀመርያ የሚያወሩት ስለመኪና ማርሽ ይመስለው እንደነደበር በፈገግታ ያስታውሰዋል። "ምሩጽ ስሙም ምርጥ ማለት ነው፤ ተግባሩም ምርጥ ነበር። በአካል ሳላውቀው ለረዥም ግዜ በውስጤ ይመላለስ ነበር፤ ምን ዓይነት ሰው ይሆን ብዬ ሁሌ አስብ ነበር" ይላል። በኋላም በአካል ተገናኝተው ከተዋወቁ በኋላ ያላቸው ግንኙነት ጠንክሮ እንደ ልጅና አባት ይተያዩ እንደነበር ይናገራል። • ዘሩባቤል ሞላና በአነቃቂ መንፈስ የታሸው 'እንፋሎት' አልበሙ "በህይወት ሳለ እንደ አብሮ አደጎችም ነበር የምንቀራረበው። እንደ አባቴ ነበር የማየው። የሃገሪቱም ሆነ ዓለም ክብር ነበር" በማለት በኃዘኔታ ያስታውሳል። ለተወሰኑ ዓመታት አሰልጣኙ እንደነበርም ይናገራል። በተለያዩ ማሕበራዊ ጉዳዮችም ያማክረው እንደነበር ገብረእግዚአብሄር ያስታወሳል። ተተኪ አትሌቶችን ከማፍራት ባለፈ የመቀሌ ከተማና ሌሎች በክልሉ የሚገኙ የቱሪዝም መስህቦችን ማስተዋወቅ አላማ ያለው 'ናትና ስፖት' በሚል ከባለቤቱ ከአትሌት ወርቅነሽ ኪዳነ ጋር ባቋቋሙት ተቋም አማካኝነት ሶስተኛው 'ናትና' የጎዳና ሩጫ ባለፈው ወር መቀሌ ላይ ተከናውኗል። "ትግራይ ክልል በደንብ ከተሰራበት ለስፖርት አመቺ የሆነ ሁኔታ አለ" የሚለው ገብረእግዚአብሄር ከሩጫው በሚገኘው ገቢ ሶስት የአትሌቲክስ መንደሮች ለማቋቋም አስቧል። የመቀሌ ሰብዓ እንደርታ እግር ኳስ ቡድን ዘንድሮ የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ዋንጫን ሲያነሳ በክልሉ የታየው መነቃቃትና መነሳሳት ደግሞ ስፖርት ምን ያህል ጉልበት እንዳለው የሚያሳይ እንደሆነም ያስረዳል። የስፖርት መርህ ሰላምና ፍቅር መሆኑን የሚናገረው አትሌት ገብሬ በተለያዩ ምክንያቶች የሚነሱ ግጭቶችና አለመግባቶች ስለስፖርት ምንነት ጠንቅቆ ካለማወቅ የመነጨ እንዳሆነ ይገልጻል። ከአትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ አገኘኋት በሚለው ተሞክሮ ባገኛት "ሳንቲም" ኢንቨስት ማድረጉን ይናገራል። አዲስ አበባ ውስጥ ሁለት ሕንጻዎች ሲኖሩት መቀሌ ከተማ ውስጥ ደግሞ ለሆቴል የሚሆን ሕንፃ እያስገነባ እንደሆነ ነግሮናል። ከዚህም በተጨማሪ የስፖርት አልባሳትን ከውጭ ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባት የተሰማራው ገብረእግዚአብሄር የመቀሌ ሰብዓ እንደርታ ማልያ በእርሱ ኩባንያ በኩል እንደሚመጣ ይናገራል። አትሌት ገብረ እግዚአብሄር በተለያዩ ሃገራዊ ኃላፊነቶችም በማገልገል ላይ ይገኛል። በአትሌቲክስ ፌዴሬሽንና በኦሎምፒክ ኮሚቴ ውስጥ በአመራርነት ይሳተፋል። •በአውሮፓ የኢትዮጵያዊያን ፌስቲቫል፡ ሙዚቃ፣ ኳስ፣ ፍቅርና ቡጢ.. ቢሆንም "በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መሳተፌ ውጤታማነቴ ላይ ድክመት እንዳያስከትልብኝ እፈራለሁ" ይላል። "ሆኖም በምሰራቸው ስራዎች ደስተኛ ነኝ። ሃገራዊ ግዴታዬን መወጣቴ ደስ ያሰኘኛል። የአንድ ሰው ህይወትም ቢሆን ከቀየርኩ ደስተኛ ነኝ።" ፖለቲካ ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳለው ጥያቄ የቀረበለት ገብረእግዚአብሄር ምላሹ አጠር እና ፈርጠም ያለ ነበር፤ "በፍጹም ፍላጎት የለኝም" የሚል። "ሆኖም" ይላል ገብረእግዚአብሄር "ሰዎች ለውጥ ያመጣል ብለው ካመኑብኝ እሠራለሁ። የወከለኝን ሰው አላሳፍርም። አቅም አለኝ ብየ ግን አይደለም።" 'ወርቄ' እያለ አቆላምጦ የሚጠራት ባለቤቱ ወርቅነሽ ኪዳኔም ከሩጫውም ከሚድያውም ርቃለች። "ወርቄ ለሀገሯ ብዙ ሠርታለች። ለዛውም ከፍተኛ መስዋዕትነትን እየከፈለች። አሁን ግን እኔም እሷም ወደ መተው ደረጃ ደርሰናል። የምንችለውን አድርገናል ብየ ነው የማስበው።" በተለያዩ የአትሌቲክስና ኦሎምፒክ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን በቡድን ስራ የተዋጣ ስራ ሲሰሩ እንደነበር አትሌት ገብረ እግአዚአብሄር ይናገራል። ሆኖም ወርቅ ላመጣ ብቻ የሚሰጠው እውቅናና ክብር ግን ያንን የቡድን ስራ ዋጋ እንዳይቀንሰው ይሰጋል። "እኛ፤ እኔም ሆነ ቀነኒሳ፤ ጥሩነሽ ሆነች ወርቅነሽ ሁላችንም የምንሰራው ኢትዮጵያ ወርቅ እንድታገኝ ነው። በእኛ ምክንያት ሃገር ማፈር የለባትም ብለን ነው። ስለሆነም ቀነኒሳ ወርቅ አምጥቶ ባንዲራ አንስቶ ሲሮጥ፤ ሁላችንም ተነስተን በደስታ እንጨፍራለን።"ይላል። ነገር ግን ወርቅ ያመጣው ላይ ብቻ ከፍተኛ ትኩረት ስለሚሰጥም በመንግሥትና በሚድያዎች ላይ መጠነኛ ቅሬታ እንዳለው ግን አልደበቀም። "ወደ አገር ስትመጣ ለእንዲህ ዓይነት የቡድን ስራ ክብር ሲሰጥ አይታይም። ወርቅ ላመጣ ብቻ ክብር መስጠት ራሱን የቻለ ችግር አለበት። ይህንን ደጋግመን ነግረናቸዋል" ይላል። አክሎም "በእርግጥ እኛ ተሰምቶን አያውቅም። የምንችለውን አድርገናል። መስዋዕትነት ነበር የምንከፍለው። ይሄ ከየት የመጣ ነው - ካልከኝ ከወከለን ህዝብ አደራ ነው።" "በአምስት የአለም ዋንጫዎች ተሳትፌያለሁ። በአምስቱም ወርቅ አላመጣሁም። ወርቅ እንዲመጣ ግን ምክንያት ነኝ። በሁለት ኦሎምፒክ ተሳትፌያለሁኝ። በሁለቱም ወርቅ እንዲገኝ ምክንያት ነኝ። ወርቄ [ወርቅነሽ] ደግሞ በተመሰሳይ በስድስት የዓለም ዋንጫና በሶስት የኦሎምፒክ ውድድሮች ላይ ተሳትፋለች። እሷም እንደዚሁ። ወርቅ እንዲመጣ የመጀመርያ ተጠሪ እሷ ነች። 'ዘ ካንትሪ ዉማን' ይሉዋታል። ወደፊት ወጥታ ለሁለትና ለሶስት ቆርጣ ደረጃ ታወጣባቸዋለች። ከተሸላሚዎቹ በላይ ወርቅ እንዲመጣ ምክንያት ነች። እነሱም ያምናሉ። ወደ መንግሥት ስትመጣ ግን ሌላ ነው፤ ይሄ የአስተሳሰብ ጠባብነት ነው የሚመስለኝ።" ይላል በሩጫ ውድድር ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ሌሎች አገራዊ ዘርፎችም እንደዚህ ዓይነት ተመሳሳይ ችግር እንዳለና መስተካከል እንዳለበት ያሳስባል ገብረእግዚአብሄር "ለሁሉም በተለይ ደግሞ መስዋዕትነት ለሚከፍለው ዕውቅና መስጠት አስፈላጊ ነው። ጥቅም አይፈልግም" በማለት ሃሳቡን ይቋጫል። | “በአምስት የዓለም ዋንጫዎች ወርቅ እንዲመጣ ምክንያት ነኝ” አትሌት ገብረእግዚአብሔር አትሌት ገብረእግዚአብሔር ገብረማርያም ተወልዶ ያደገው በትግራይ ክልል በቀድሞዋ ሐውዜን፣ በአሁኗ ሳዕሲዕ ጻዕዳ እምባ ወረዳ ነው፤ ልዩ ስሟ ጻንቃኔት በተባለች አካባቢ ነው። በ1976 ዓ.ም. የተወለደው ገብረእግዚኣብሄር፤ ገና ታዳጊ እያለ በ16 ዓመቱ ጊዜውም በ1992 ዓ.ም ሩጫን ሀ ብሎ የጀመረው። በዓለም አቀፍ ደረጃ ለመጀመርያ ጊዜ 2003 ኒው ዮርክ በተካሄደው ማራቶን ላይ ተሳትፎ የወርቅ ሜዳልያ አገኘ። •"ሥልጣን ለደም ግፊት አጋልጦኛል" ኃይሌ ገብረሥላሴ ለቁጥር በሚያዳግቱ የተለያዩ ዓለም ዓቀፍ ውድድሮች በግሉም እንዲሁም በሃገርም ደረጃ ተሳትፎ ብዙ ወርቆችን ያስገኘ አትሌት ነው። በአሁኑ ወቅት ከሩጫው ባሻገር በአትሌቲክስ ፌዴሬሽንና በኦሎምፒክ ኮሚቴ ምክትል ኃላፊነት እያገለገለ ሲሆን፤በይፋ ጫማ ባይሰቅልም እምብዛም በሩጫ መድረክ ላይ ሲሳተፍ እየታየ አይደለም። ለዚህም ገብረእግዚአብሔር ምላሽ አለው "ሩጫ እንደሚታውቀው ብዙ ትኩረት የሚጠይቅ ነው። ቢዝነስን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እሳተፋለሁ። ከዚህ በተጨማሪም በዕድሜም እየገፋሁ ነው። በይፋ ጫማ ባልሰቅልም አሁን ወደዛው ነኝ።" በዚህና ወቅታዊ ስፖርታዊ ጉዳዮችን በማስመልከት ቢቢሲ ከገብረእግዚአብሄር ጋር ቆይታ አድርጓል። አትሌት ገብረእግዚአብሄር ሩጫ በጀመረበት ወቅት ሩጫ በአለም አቀፍ ደረጃ በውድድር ደረጃ ስላለው ስፍራ የጠለቀ እውቀት አልነበረውም። ትምህርቱን የተማረው እንደ ብዙው የኢትዮጵያ የገጠር ልጅ በእግሩ እየሄደ ነበር፤ አብዛኛውን ጊዜ ደግሞ ርቀቷን በሩጫ ፉት ይላታል። •ስለ አቶ ዱቤ ጅሎ ሽልማት ምን እናውቃለን? "እኔ የአርሶ አደር ልጅ ነኝ። ወላጆቼ ያዘዙኝን በሙሉ ሰርቼ በሰዓቱ ትምህርት ቤት ለመድረስ ስለማልችል እየሮጥኩ ነበር የምሄደው። ከትምህርት ቤት ስመለስም እንዲሁ በሩጫ ነበር።" ይላል ይሄ የአብዛኛው የአርሶ አደር ልጆች ታሪክ ቢሆንም ለገብረ እግዚአብሄር ግን የተለየ ዕድል እንደፈጠረለት ይናገራል። "አጋጣሚው ተፈጥሯዊ አቅምን ፈጥሮልኛል።" ሩጫን ከአንድ ቦታ ወደ አንድ ቦታ በፍጥነት ለመድረስ እንጂ በስፖርቱ አለም ያለውን ስፍራም አልተረዳውም ነበር። "በስፖርት ይሄን ያህል ታዋቂነት እንደሚገኝም አላውቅም ነበር" ይላል። ውድድር ማካሄድ የጀመረው በትምህርት ቤት በነበረበት ወቅት ሲሆን፤ የ9ኛ ክፍል ተማሪ ሆኖ በትምህርት ቤቱ በተጀመረው ውድድር ለመጀመርያ ጊዜ አንደኛ ወጥቶ የምስክር ወረቀትም አግኝቷል። •ጊነስ ዎርልድ ሪከርድስ፡ «ስለተተከሉት ዛፎች ከኢትዮጵያ የደረሰን መረጃ የለም» ከትምህርት ቤቱ በተጨማሪ ሌሎችን ውድድሮችን ማካሄድ የጀመረው ገብረእግዚአብሔር በ1993 ዓ.ም. የ11ኛ ክፍል ተማሪ ሆኖም አዲግራት አቅራብያ በምትገኘው ዕዳጋ ሐሙስ ከተማ ትምህርት ቤቱን ቀጢን ቃላይ' ወክሎ ነበር የተወዳደረው፤ አንደኛም ወጣ። ቀጥሎም ወረዳውን ወክሎ 1500 ኪሜ ተወዳደሮ ማሸነፉን ያስታውሳል። ለመጀመርያ ግዜ ከምስክር ወረቀት በተጨማሪ ሽልማት ያገኘበት መሆኑም ልዩ ያደርገዋል። አትሌት ገብረእግዚአብሄር አትሌት ገብረ እግዚአብሄር በተለይ ለእነዚህ ሶስቱ ድሎች [የአየርላንድ፣ የኒው ዮርክና አፍሪካ ሻምፒዮን] የተለየ ቦታ አለው። በተለይ ደግሞ የአፍሪካ ሻምፕዮን በኢትዮጵያ የተካሄደ በመሆኑና ከፍተኛ ዝናብ የጣለበት ፈታኝ ውድድርም ስለነበር ከፍ ያለ ትርጉም ይሰጠዋል። •"የት ይቀርልሃል!? አፈር ድሜ ትበላለህ...!" ጋሽ አበራ ሞላ "በኢትዮጵያ የመጀመርያ ውድድርም ስለ ነበር ሌሎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ወርቅ እንዲያመጡ ጉልበት የሆናቸው ይመስለኛል" የሚል እምነት አለው። የአትሌት ገብረ እግዚአብሄር አርአያ ማን ነው? ገብረእግዚአብሄር ሩጫን በአጋጣሚ ቢጀምርም በትምህርት ቤት ስለ እነ አትሌት ምሩጽ ይፍጠርና አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ የሩጫ ገድል ሲሰማ በሩጫ ላይ የተለየ ፍላጎት እንዳደረበት ይናገራል። አበበ ቢቂላም ሌላኛው የገብረእግዚአብሄር አርአያ ነው። ለሶስቱ አትሌቶች የተለየ ክብርና አድናቆት እንዳለው ነው የሚናገረው ገብረእግዚአብሄር፤ "ሩጫን ለዓለም በደንብ ያስተዋወቅነው እኛ ኢትዮጵያውያን ነን" የሚል አቋም አለው። ገብረእግዚአብሄር ከሁሉም በላይ ለኃይሌ ገብረ ስላሴ ያለው ቦታ ከፍ ያለ እንደሆነ ይናገራል። በሩጫ ማሸነፉ ብቻ ሳይሆን በሩጫው ለረዥም ግዜ የቆየበት ፅናቱን እንደ ምሳሌ ይቆጥረዋል። እንዲሁም ደግሞ ከሩጫው በተጨማሪ በቢዝነስ የሚያደርገው እንቅስቃሴና ስኬትም ሌላ የሚያደንቅበት ጉዳይ ነው። አትሌት ምሩጽ ይፍጠር በአንድ ኦሎምፒክ ሁለት የወርቅ ሜዳልያ ባለቤት መሆኑን ከፍተኛ ስፍራ ከመስጠቱ በተጨማሪ ለመጀመርያ ጊዜ ሩጫን በውድድርነት ሲሰማ የአትሌት ምሩጽ ይፍጠርን ድል ነበር የሰማው። የስድስተኛ ክፍል የሳይንስ መምህሩ ስለ አትሌት ምሩጽ ይፍጠር ማርሽ ቀያሪነት በሚነግሯቸው ወቅት መጀመርያ የሚያወሩት ስለመኪና ማርሽ ይመስለው እንደነደበር በፈገግታ ያስታውሰዋል። "ምሩጽ ስሙም ምርጥ ማለት ነው፤ ተግባሩም ምርጥ ነበር። በአካል ሳላውቀው ለረዥም ግዜ በውስጤ ይመላለስ ነበር፤ ምን ዓይነት ሰው ይሆን ብዬ ሁሌ አስብ ነበር" ይላል። በኋላም በአካል ተገናኝተው ከተዋወቁ በኋላ ያላቸው ግንኙነት ጠንክሮ እንደ ልጅና አባት ይተያዩ እንደነበር ይናገራል። • ዘሩባቤል ሞላና በአነቃቂ መንፈስ የታሸው 'እንፋሎት' አልበሙ "በህይወት ሳለ እንደ አብሮ አደጎችም ነበር የምንቀራረበው። እንደ አባቴ ነበር የማየው። የሃገሪቱም ሆነ ዓለም ክብር ነበር" በማለት በኃዘኔታ ያስታውሳል። ለተወሰኑ ዓመታት አሰልጣኙ እንደነበርም ይናገራል። በተለያዩ ማሕበራዊ ጉዳዮችም ያማክረው እንደነበር ገብረእግዚአብሄር ያስታወሳል። ተተኪ አትሌቶችን ከማፍራት ባለፈ የመቀሌ ከተማና ሌሎች በክልሉ የሚገኙ የቱሪዝም መስህቦችን ማስተዋወቅ አላማ ያለው 'ናትና ስፖት' በሚል ከባለቤቱ ከአትሌት ወርቅነሽ ኪዳነ ጋር ባቋቋሙት ተቋም አማካኝነት ሶስተኛው 'ናትና' የጎዳና ሩጫ ባለፈው ወር መቀሌ ላይ ተከናውኗል። "ትግራይ ክልል በደንብ ከተሰራበት ለስፖርት አመቺ የሆነ ሁኔታ አለ" የሚለው ገብረእግዚአብሄር ከሩጫው በሚገኘው ገቢ ሶስት የአትሌቲክስ መንደሮች ለማቋቋም አስቧል። የመቀሌ ሰብዓ እንደርታ እግር ኳስ ቡድን ዘንድሮ የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ዋንጫን ሲያነሳ በክልሉ የታየው መነቃቃትና መነሳሳት ደግሞ ስፖርት ምን ያህል ጉልበት እንዳለው የሚያሳይ እንደሆነም ያስረዳል። የስፖርት መርህ ሰላምና ፍቅር መሆኑን የሚናገረው አትሌት ገብሬ በተለያዩ ምክንያቶች የሚነሱ ግጭቶችና አለመግባቶች ስለስፖርት ምንነት ጠንቅቆ ካለማወቅ የመነጨ እንዳሆነ ይገልጻል። ከአትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ አገኘኋት በሚለው ተሞክሮ ባገኛት "ሳንቲም" ኢንቨስት ማድረጉን ይናገራል። አዲስ አበባ ውስጥ ሁለት ሕንጻዎች ሲኖሩት መቀሌ ከተማ ውስጥ ደግሞ ለሆቴል የሚሆን ሕንፃ እያስገነባ እንደሆነ ነግሮናል። ከዚህም በተጨማሪ የስፖርት አልባሳትን ከውጭ ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባት የተሰማራው ገብረእግዚአብሄር የመቀሌ ሰብዓ እንደርታ ማልያ በእርሱ ኩባንያ በኩል እንደሚመጣ ይናገራል። አትሌት ገብረ እግዚአብሄር በተለያዩ ሃገራዊ ኃላፊነቶችም በማገልገል ላይ ይገኛል። በአትሌቲክስ ፌዴሬሽንና በኦሎምፒክ ኮሚቴ ውስጥ በአመራርነት ይሳተፋል። •በአውሮፓ የኢትዮጵያዊያን ፌስቲቫል፡ ሙዚቃ፣ ኳስ፣ ፍቅርና ቡጢ.. ቢሆንም "በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መሳተፌ ውጤታማነቴ ላይ ድክመት እንዳያስከትልብኝ እፈራለሁ" ይላል። "ሆኖም በምሰራቸው ስራዎች ደስተኛ ነኝ። ሃገራዊ ግዴታዬን መወጣቴ ደስ ያሰኘኛል። የአንድ ሰው ህይወትም ቢሆን ከቀየርኩ ደስተኛ ነኝ።" ፖለቲካ ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳለው ጥያቄ የቀረበለት ገብረእግዚአብሄር ምላሹ አጠር እና ፈርጠም ያለ ነበር፤ "በፍጹም ፍላጎት የለኝም" የሚል። "ሆኖም" ይላል ገብረእግዚአብሄር "ሰዎች ለውጥ ያመጣል ብለው ካመኑብኝ እሠራለሁ። የወከለኝን ሰው አላሳፍርም። አቅም አለኝ ብየ ግን አይደለም።" 'ወርቄ' እያለ አቆላምጦ የሚጠራት ባለቤቱ ወርቅነሽ ኪዳኔም ከሩጫውም ከሚድያውም ርቃለች። "ወርቄ ለሀገሯ ብዙ ሠርታለች። ለዛውም ከፍተኛ መስዋዕትነትን እየከፈለች። አሁን ግን እኔም እሷም ወደ መተው ደረጃ ደርሰናል። የምንችለውን አድርገናል ብየ ነው የማስበው።" በተለያዩ የአትሌቲክስና ኦሎምፒክ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን በቡድን ስራ የተዋጣ ስራ ሲሰሩ እንደነበር አትሌት ገብረ እግአዚአብሄር ይናገራል። ሆኖም ወርቅ ላመጣ ብቻ የሚሰጠው እውቅናና ክብር ግን ያንን የቡድን ስራ ዋጋ እንዳይቀንሰው ይሰጋል። "እኛ፤ እኔም ሆነ ቀነኒሳ፤ ጥሩነሽ ሆነች ወርቅነሽ ሁላችንም የምንሰራው ኢትዮጵያ ወርቅ እንድታገኝ ነው። በእኛ ምክንያት ሃገር ማፈር የለባትም ብለን ነው። ስለሆነም ቀነኒሳ ወርቅ አምጥቶ ባንዲራ አንስቶ ሲሮጥ፤ ሁላችንም ተነስተን በደስታ እንጨፍራለን።"ይላል። ነገር ግን ወርቅ ያመጣው ላይ ብቻ ከፍተኛ ትኩረት ስለሚሰጥም በመንግሥትና በሚድያዎች ላይ መጠነኛ ቅሬታ እንዳለው ግን አልደበቀም። "ወደ አገር ስትመጣ ለእንዲህ ዓይነት የቡድን ስራ ክብር ሲሰጥ አይታይም። ወርቅ ላመጣ ብቻ ክብር መስጠት ራሱን የቻለ ችግር አለበት። ይህንን ደጋግመን ነግረናቸዋል" ይላል። አክሎም "በእርግጥ እኛ ተሰምቶን አያውቅም። የምንችለውን አድርገናል። መስዋዕትነት ነበር የምንከፍለው። ይሄ ከየት የመጣ ነው - ካልከኝ ከወከለን ህዝብ አደራ ነው።" "በአምስት የአለም ዋንጫዎች ተሳትፌያለሁ። በአምስቱም ወርቅ አላመጣሁም። ወርቅ እንዲመጣ ግን ምክንያት ነኝ። በሁለት ኦሎምፒክ ተሳትፌያለሁኝ። በሁለቱም ወርቅ እንዲገኝ ምክንያት ነኝ። ወርቄ [ወርቅነሽ] ደግሞ በተመሰሳይ በስድስት የዓለም ዋንጫና በሶስት የኦሎምፒክ ውድድሮች ላይ ተሳትፋለች። እሷም እንደዚሁ። ወርቅ እንዲመጣ የመጀመርያ ተጠሪ እሷ ነች። 'ዘ ካንትሪ ዉማን' ይሉዋታል። ወደፊት ወጥታ ለሁለትና ለሶስት ቆርጣ ደረጃ ታወጣባቸዋለች። ከተሸላሚዎቹ በላይ ወርቅ እንዲመጣ ምክንያት ነች። እነሱም ያምናሉ። ወደ መንግሥት ስትመጣ ግን ሌላ ነው፤ ይሄ የአስተሳሰብ ጠባብነት ነው የሚመስለኝ።" ይላል በሩጫ ውድድር ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ሌሎች አገራዊ ዘርፎችም እንደዚህ ዓይነት ተመሳሳይ ችግር እንዳለና መስተካከል እንዳለበት ያሳስባል ገብረእግዚአብሄር "ለሁሉም በተለይ ደግሞ መስዋዕትነት ለሚከፍለው ዕውቅና መስጠት አስፈላጊ ነው። ጥቅም አይፈልግም" በማለት ሃሳቡን ይቋጫል። | https://www.bbc.com/amharic/49306146 |
2health
| የኮሮናቫይረስ ታማሚው ሆስፒታል ውስጥ ሌላ ታማሚን ገደለ | አሜሪካ፣ ካሊፎርንያ ውስጥ በኮሮናቫይረስ ተይዞ ሆስፒታል የነበረ ግለሰብ ሌላ ቫይረሱ ያለበትን ታማሚ ገደለ። የ37 ዓመቱ ግለሰብ ባለፈው ሳምንት ታማሚውን የገደለው በኦክስጅን መያዣ ታንክ ደብድቦት ነው። ግለሰቡ በግድያ እና በጥላቻ ወንጀል ተከሷል። ጀሲ ማርቲኔዝ የተባለው ግለሰብ የ82 ዓመት አዛውንት በኮሮናቫይረስ ተይዘው እሱ የሚገኝበት የሆስፒታል ክፍል ውስጥ ከገቡ በኋላ ነው ግድያውን የፈጸመው። ለሎስ አንጀለስ ፖሊስ በሰጠው ቃል መሠረት አዛውንቱ የሆስፒታሉ ክፍል ውስጥ እየጸለዩ ስለነበረ ተበሳጭቶባቸዋል። አዛውንቱ በኦክስጅን ታንክ ከተመቱ በኋላ በቀጣዩ ቀን ሕይወታቸው አልፏል። ፓሊስ እንዳለው፤ ሁለቱ ግለሰቦች በተመሳሳይ የሆስፒታል ክፍል ውስጥ ሕክምና ሲደረግላቸው ነበር። ከዚያ በፊትም አይተዋወቁም። አንቲሎፕ ቫሊ በተባለውና በደቡብ ካሊፎርንያ በሚገኝ ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግለት የነበረው ጀሲ "አዛውንቱ ሲጸልዩ ተበሳጨና በኦክስጅን ታንክ ገደላቸው" ሲል ፖሊስ መግለጫ አውጥቷል። ከግድያ በተጨማሪ የጥላቻ ወንጀል እና አረጋውያንን የማሰቃየት ክስም ተመስርቶበታል። ካሊፎርንያ ውስጥ በስድስት ሳምንት ብቻ አንድ ሚሊዮን ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። ሆስፒታሎች ህሙማንን ለማስተናገድ እየተጣጣሩም ነው። ወረርሽኙ ከጀመረ ወዲህ በግዛቲቱ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። ሆስፒታሎች የጤና ባለሙያዎች እጥረት ስለገጠማቸው ከአውስትራሊያ እና ታይዋን 3000 ባለሙያዎች ለመውሰድ አቅደዋል። የካሊፎርንያ የጤና ቢሮ ጸሐፊ ዶ/ር ማርክ ጋሊ በዚህ ወር መጨረሻ ለህሙማን አልጋ ላይኖር እንደሚችል ተናግረዋል። አገረ ገዢው ጋቪን ኒውሰም ዜጎች ከቤት እንዳይወጡ አዘዋል። እጅግ አስፈላጊ ከሆኑ አገልግሎቶች ውጪ ያሉ ተቋሞችም ተዘግተዋል። | የኮሮናቫይረስ ታማሚው ሆስፒታል ውስጥ ሌላ ታማሚን ገደለ አሜሪካ፣ ካሊፎርንያ ውስጥ በኮሮናቫይረስ ተይዞ ሆስፒታል የነበረ ግለሰብ ሌላ ቫይረሱ ያለበትን ታማሚ ገደለ። የ37 ዓመቱ ግለሰብ ባለፈው ሳምንት ታማሚውን የገደለው በኦክስጅን መያዣ ታንክ ደብድቦት ነው። ግለሰቡ በግድያ እና በጥላቻ ወንጀል ተከሷል። ጀሲ ማርቲኔዝ የተባለው ግለሰብ የ82 ዓመት አዛውንት በኮሮናቫይረስ ተይዘው እሱ የሚገኝበት የሆስፒታል ክፍል ውስጥ ከገቡ በኋላ ነው ግድያውን የፈጸመው። ለሎስ አንጀለስ ፖሊስ በሰጠው ቃል መሠረት አዛውንቱ የሆስፒታሉ ክፍል ውስጥ እየጸለዩ ስለነበረ ተበሳጭቶባቸዋል። አዛውንቱ በኦክስጅን ታንክ ከተመቱ በኋላ በቀጣዩ ቀን ሕይወታቸው አልፏል። ፓሊስ እንዳለው፤ ሁለቱ ግለሰቦች በተመሳሳይ የሆስፒታል ክፍል ውስጥ ሕክምና ሲደረግላቸው ነበር። ከዚያ በፊትም አይተዋወቁም። አንቲሎፕ ቫሊ በተባለውና በደቡብ ካሊፎርንያ በሚገኝ ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግለት የነበረው ጀሲ "አዛውንቱ ሲጸልዩ ተበሳጨና በኦክስጅን ታንክ ገደላቸው" ሲል ፖሊስ መግለጫ አውጥቷል። ከግድያ በተጨማሪ የጥላቻ ወንጀል እና አረጋውያንን የማሰቃየት ክስም ተመስርቶበታል። ካሊፎርንያ ውስጥ በስድስት ሳምንት ብቻ አንድ ሚሊዮን ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። ሆስፒታሎች ህሙማንን ለማስተናገድ እየተጣጣሩም ነው። ወረርሽኙ ከጀመረ ወዲህ በግዛቲቱ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። ሆስፒታሎች የጤና ባለሙያዎች እጥረት ስለገጠማቸው ከአውስትራሊያ እና ታይዋን 3000 ባለሙያዎች ለመውሰድ አቅደዋል። የካሊፎርንያ የጤና ቢሮ ጸሐፊ ዶ/ር ማርክ ጋሊ በዚህ ወር መጨረሻ ለህሙማን አልጋ ላይኖር እንደሚችል ተናግረዋል። አገረ ገዢው ጋቪን ኒውሰም ዜጎች ከቤት እንዳይወጡ አዘዋል። እጅግ አስፈላጊ ከሆኑ አገልግሎቶች ውጪ ያሉ ተቋሞችም ተዘግተዋል። | https://www.bbc.com/amharic/55438467 |
3politics
| ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን የመተማመኛ ድምጽ ሊሰጥባቸው ነው | የዩናይትድ ኪንግደሙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ዛሬ የመተማመኛ ድምፅ ሊሰጥባቸው ነው። መሰል ጉዳዮችን የሚመረምረው የላይኛው ምክር ቤት ኮሚቴ ሊቀ መንበር ሰር ግራሃም ብሬዴ ይህን ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ሥልጣን ይልቀቁ የሚሉ ድምፆች እየበረከቱ መጥተዋል። ቦሪስ የመተማመኛ ድምፅ ሊሰጥባቸው እንደሆነ የእንግሊዝ መገናኛ ብዙሃን ከውስጥ አዋቂዎች ሰምተናል ሲሉ ነው የከረሙት። ቦሪስ የመተማመኛ ድምፅ የሚሰጥባቸው 54 የገዥው ወግ አጥባቂ አባላትና የሕዝብ እንደራሴዎች [ቶሪስ] በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ያለን እምነት ተሟጧል የሚል ደብዳቤ ካስገቡ ነው። ባለፈው ሰንበት የትራንስፖርት ሚኒስትሩ ግራንት ሻፕስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመተማመኛ ድምፅ ቢወጣባቸውም ምንም እንደማይሆኑ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ባለፉት 10 ቀናት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከገዛ ፓርቲያቸው ያለመተማመን ድምፅ ሊሰጥባቸው እንደሚችል ሲነገር ቆይቷል። እስካሁን 28 ቶሪዎች [የገዥው ፓርቲ አባላትና የሕዝብ እንደራሴዎች] ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥልጣን እንዲለቁ በይፋ ጠይቀዋል። ቦሪስ በንግሥት ኤልሳቤጥ 70ኛ ዓመት የፕላቲኒዬም ኢዩቤልዩ ክብረ በዓል ላይ ሲገኙ ሕዝቡ ቁጣን ገልጦባቸዋል። በገዥው ወግ አጥባቂ ፓርቲ ሕግ መሠረት ቢያንስ 15 በመቶ የፓርቲው አባላትና የሕዝብ እንደራሴዎች ድምፅ መስጠት አለባቸው። ገዥው ፓርቲ በአሁኑ ወቅት በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት 54 አባላት አሉት። እኒህ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትሩን አንደገፍም ብለው ደብዳቤ መፃፍ አለባቸው። እስካሁን ምን ያህል አባላት ደብዳቤ እንዳስገቡ ግልፅ አይደለም። 54ቱም አባላት ደብዳቤ ካስገቡ ከፍተኛ ቶሪዎች በመሪያቸው ላይ በድብቅ የተማመኛ ድምፅ ይሰጣሉ። ይህ ከሆነ በኋላ ጉዳዩ ወደ ሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አምርቶ 180 አባላት አንተማመንም የሚል ድምፅ መስጠት አለባቸው። ቦሪስ ይህን የመተማመን ድምፅ ማለፍ ከቻሉ ሌሎችንም ፈተናዎች የማለፍ ዕድላቸው የሰፋ ነው። | ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን የመተማመኛ ድምጽ ሊሰጥባቸው ነው የዩናይትድ ኪንግደሙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ዛሬ የመተማመኛ ድምፅ ሊሰጥባቸው ነው። መሰል ጉዳዮችን የሚመረምረው የላይኛው ምክር ቤት ኮሚቴ ሊቀ መንበር ሰር ግራሃም ብሬዴ ይህን ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ሥልጣን ይልቀቁ የሚሉ ድምፆች እየበረከቱ መጥተዋል። ቦሪስ የመተማመኛ ድምፅ ሊሰጥባቸው እንደሆነ የእንግሊዝ መገናኛ ብዙሃን ከውስጥ አዋቂዎች ሰምተናል ሲሉ ነው የከረሙት። ቦሪስ የመተማመኛ ድምፅ የሚሰጥባቸው 54 የገዥው ወግ አጥባቂ አባላትና የሕዝብ እንደራሴዎች [ቶሪስ] በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ያለን እምነት ተሟጧል የሚል ደብዳቤ ካስገቡ ነው። ባለፈው ሰንበት የትራንስፖርት ሚኒስትሩ ግራንት ሻፕስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመተማመኛ ድምፅ ቢወጣባቸውም ምንም እንደማይሆኑ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ባለፉት 10 ቀናት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከገዛ ፓርቲያቸው ያለመተማመን ድምፅ ሊሰጥባቸው እንደሚችል ሲነገር ቆይቷል። እስካሁን 28 ቶሪዎች [የገዥው ፓርቲ አባላትና የሕዝብ እንደራሴዎች] ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥልጣን እንዲለቁ በይፋ ጠይቀዋል። ቦሪስ በንግሥት ኤልሳቤጥ 70ኛ ዓመት የፕላቲኒዬም ኢዩቤልዩ ክብረ በዓል ላይ ሲገኙ ሕዝቡ ቁጣን ገልጦባቸዋል። በገዥው ወግ አጥባቂ ፓርቲ ሕግ መሠረት ቢያንስ 15 በመቶ የፓርቲው አባላትና የሕዝብ እንደራሴዎች ድምፅ መስጠት አለባቸው። ገዥው ፓርቲ በአሁኑ ወቅት በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት 54 አባላት አሉት። እኒህ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትሩን አንደገፍም ብለው ደብዳቤ መፃፍ አለባቸው። እስካሁን ምን ያህል አባላት ደብዳቤ እንዳስገቡ ግልፅ አይደለም። 54ቱም አባላት ደብዳቤ ካስገቡ ከፍተኛ ቶሪዎች በመሪያቸው ላይ በድብቅ የተማመኛ ድምፅ ይሰጣሉ። ይህ ከሆነ በኋላ ጉዳዩ ወደ ሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አምርቶ 180 አባላት አንተማመንም የሚል ድምፅ መስጠት አለባቸው። ቦሪስ ይህን የመተማመን ድምፅ ማለፍ ከቻሉ ሌሎችንም ፈተናዎች የማለፍ ዕድላቸው የሰፋ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cgxyx74n2llo |
0business
| አሜሪካ የዓለም ንግድ ድርጅት ለመምራት የታጩትን አፍሪካዊት ልታግድ መሞከሯ ተገለፀ | የናይጄሪያ የቀድሞ የገንዘብ ሚኒስትር የዓለም ንግድ ድርጅትን እንዲመሩ መሾማቸው የአሜሪካ መቃወምን ተከትሎ ጥርጣሬ ውስጥ ወድቋል ፡፡ የዓለም ንግድ ድርጅት እጩዎች ኮሚቴ ንጎዚ ኦኮንጆ-ኢዊላ እንዲሾሙ ሀሳብ ያቀረበው ረቡዕ ነበር። የዓለም ንግድ ድርጅት የመሩ የመጀመሪያዋ ሴት እና የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ይሆናሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር ፡፡ ነገር ግን የዓለም ንግድ ድርጅት የዓለም ንግድን የመራበትን መንገድ አጥብቃ የነቀፈችው አሜሪካ ሌላ ሴት እያሰበች ነው- የደቡብ ኮሪያዋን ዮ ሚንግ ሂን፡፡ ኦኮንጆ-ኢዊላ በሹመቱ "እጅግ እንደተደሰቱ"ገልጸው ነበር፡፡ ለድርጅቱ አዲስ መሪ ለመፈለግ ለአራት ወራት የተደረገው ጉዞ ዋሺንግተን የደቡብ ኮሪያን የንግድ ሚኒስትርን እንደምትደግፍ በመናገሯ እንቅፋት አጋጠመው፡፡ የዓለም ንግድ ድርጅትን በመተቸት የአሜሪካ የንግድ ጽሕፈት ቤት ድርጅቱ "በእውነተኛ እና በመስኩ ልምድ ባለው ሰው መመራት አለበት" ብሏል ፡፡ ዮ "የድርጅቱን ውጤታማ መሪ ለመሆን የሚያስፈልጉ ብቃቶች ሁሉ አሏት" ይላል መግለጫው ፡፡ አክሎም "ይህ ለዓለም ንግድ ድርጅት እና ለዓለም ዓቀፍ ንግድ በጣም አስቸጋሪ ጊዜ ነው። በ 25 ዓመታት ውስጥ ሁለገብ የታሪፍ ድርድሮች አልተካሄዱም፤ የአለመግባባቶች መፍትሄ አሰጣጡ ሥርዓት ከቁጥጥር ውጭ ሆኗል። ግልፅነትን በተመለከተም በጣም ጥቂት አባላት ብቻ ግዴታቸውን እየተወጡ ነው፡፡ ደርጅቱ ትልቅ ለውጥ የሚያስፈልገው ነው" ብሏል። መግለጫው ኦኮንጆ-ኢያላ አልተጠቀሰም ፡፡ የድርጅቱ ቃል አቀባዩ ኪት ሮክዌል ስለውሳኔው ላይ ለመወያየት የዓለም ንግድ ድርጅት ልዑካን ከተሰበሰቡ በኋላ አንድ አባል ሀገር ብቻ ኦኮንጆ-ኢዊላን እንዳልደገፈ ተናግረው ነበር ፡፡ "ከአንድ ልዑክ በስተቀር ሁሉም ልዑካን ለሂደቱ ... ለውጤቱ ጠንካራ ድጋፍ አድርገዋል" ብለዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ የዓለም የንግድ ድርጅትን "አስፈሪ" እና ለቻይና ያደላ አድርገው የገለጹ ሲሆን በድርጅቱ ውስጥ ቁልፍ የተባሉ አንዳንድ ሹመቶች ቀድሞውኑም ታግደዋል ፡፡ የዓለም የንግድ ድርጅት በጉዳዩ ላይ ለመወያየት ከአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በኋላ ስብሰባ ጠርቷል ፡፡ የአሜሪካ መቃወም ናይጄሪያዊቷ እንዳይሾሙ ያግዳል ማለት አይደለም። ሆኖም ዋሽንግተን በውሳኔው ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማሳደር ትችላለች ፡፡ የ66 ዓመቷ ኦኮንጆ-ኢዊላ የናይጄሪያ የመጀመሪያዋ ሴት የገንዘብ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን በዓለም ባንክ ኢኮኖሚስት ሆነውአገልግለዋል። | አሜሪካ የዓለም ንግድ ድርጅት ለመምራት የታጩትን አፍሪካዊት ልታግድ መሞከሯ ተገለፀ የናይጄሪያ የቀድሞ የገንዘብ ሚኒስትር የዓለም ንግድ ድርጅትን እንዲመሩ መሾማቸው የአሜሪካ መቃወምን ተከትሎ ጥርጣሬ ውስጥ ወድቋል ፡፡ የዓለም ንግድ ድርጅት እጩዎች ኮሚቴ ንጎዚ ኦኮንጆ-ኢዊላ እንዲሾሙ ሀሳብ ያቀረበው ረቡዕ ነበር። የዓለም ንግድ ድርጅት የመሩ የመጀመሪያዋ ሴት እና የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ይሆናሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር ፡፡ ነገር ግን የዓለም ንግድ ድርጅት የዓለም ንግድን የመራበትን መንገድ አጥብቃ የነቀፈችው አሜሪካ ሌላ ሴት እያሰበች ነው- የደቡብ ኮሪያዋን ዮ ሚንግ ሂን፡፡ ኦኮንጆ-ኢዊላ በሹመቱ "እጅግ እንደተደሰቱ"ገልጸው ነበር፡፡ ለድርጅቱ አዲስ መሪ ለመፈለግ ለአራት ወራት የተደረገው ጉዞ ዋሺንግተን የደቡብ ኮሪያን የንግድ ሚኒስትርን እንደምትደግፍ በመናገሯ እንቅፋት አጋጠመው፡፡ የዓለም ንግድ ድርጅትን በመተቸት የአሜሪካ የንግድ ጽሕፈት ቤት ድርጅቱ "በእውነተኛ እና በመስኩ ልምድ ባለው ሰው መመራት አለበት" ብሏል ፡፡ ዮ "የድርጅቱን ውጤታማ መሪ ለመሆን የሚያስፈልጉ ብቃቶች ሁሉ አሏት" ይላል መግለጫው ፡፡ አክሎም "ይህ ለዓለም ንግድ ድርጅት እና ለዓለም ዓቀፍ ንግድ በጣም አስቸጋሪ ጊዜ ነው። በ 25 ዓመታት ውስጥ ሁለገብ የታሪፍ ድርድሮች አልተካሄዱም፤ የአለመግባባቶች መፍትሄ አሰጣጡ ሥርዓት ከቁጥጥር ውጭ ሆኗል። ግልፅነትን በተመለከተም በጣም ጥቂት አባላት ብቻ ግዴታቸውን እየተወጡ ነው፡፡ ደርጅቱ ትልቅ ለውጥ የሚያስፈልገው ነው" ብሏል። መግለጫው ኦኮንጆ-ኢያላ አልተጠቀሰም ፡፡ የድርጅቱ ቃል አቀባዩ ኪት ሮክዌል ስለውሳኔው ላይ ለመወያየት የዓለም ንግድ ድርጅት ልዑካን ከተሰበሰቡ በኋላ አንድ አባል ሀገር ብቻ ኦኮንጆ-ኢዊላን እንዳልደገፈ ተናግረው ነበር ፡፡ "ከአንድ ልዑክ በስተቀር ሁሉም ልዑካን ለሂደቱ ... ለውጤቱ ጠንካራ ድጋፍ አድርገዋል" ብለዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ የዓለም የንግድ ድርጅትን "አስፈሪ" እና ለቻይና ያደላ አድርገው የገለጹ ሲሆን በድርጅቱ ውስጥ ቁልፍ የተባሉ አንዳንድ ሹመቶች ቀድሞውኑም ታግደዋል ፡፡ የዓለም የንግድ ድርጅት በጉዳዩ ላይ ለመወያየት ከአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በኋላ ስብሰባ ጠርቷል ፡፡ የአሜሪካ መቃወም ናይጄሪያዊቷ እንዳይሾሙ ያግዳል ማለት አይደለም። ሆኖም ዋሽንግተን በውሳኔው ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማሳደር ትችላለች ፡፡ የ66 ዓመቷ ኦኮንጆ-ኢዊላ የናይጄሪያ የመጀመሪያዋ ሴት የገንዘብ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን በዓለም ባንክ ኢኮኖሚስት ሆነውአገልግለዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54729315 |
0business
| በዩኬ የተፈጠረውን የነዳጅ እጥረት ቀውስ ለማቃለል የሀገሪቱ ሰራዊት ዝግጁ ነው ተባለ | በዩኬ የተፈጠረውና አራተኛ ቀን ባስቆጠረው የነዳጅ አቅርቦት መስተጓጎል ምክንያት የተፈጠሩ ረጃጅም ሰልፎችንና መሰል ችግሮችን ለማቃለል ሰራዊቱ ዝግጁ መሆኑ ተገለጸ። በሀገሪቱ በተከሰተው የነዳጅ አቅርቦት ችግር የነዳጅ ማመላለሻ አሽከርካሪዎች እጥረትም ገጥሟል። አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ እስከ 150 የሚደርሱ የወታደር ነዳጅ ጫኝ አሽከርካሪዎች ሥልጠና በመሰጠት ማሰማራት እንደሚቻልም ተጠቅሷል። በርካታ የጭነት መኪና አሽከርካሪዎች የነዳጅ አቅርቦት ሊከሰት ይችላል በሚል ስጋት በርካታዎች በነዳጅ ማደያዎች በማጣሪያዎች በቁጥር በዝተው ይታያሉ። ዩናይትድ ኪንግደም ከ100 ሺህ በላይ የጭነት መኪና አሽከርካሪዎች ያስፈልጋታል ተብሎ የሚገመት ሲሆን ባለፉት ወራት የምግብ አቅራቢዎችን እና ሱፐርማርኬቶችን ጨምሮ የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ችግር አጋጥሟቸዋል። የሀገሪቱ ባለስልጣን በነዳጅ ማደያዎች ለሚታዩት ረጃጅም ሰልፎች ነዳጅ ሳያስፈልጋቸው ወደ ማደያዎች የሚሄዱ ሰዎችን ተጠያቂ አድርገዋል። ኤኤሲሲ የተባለ ኩባንያ እንዳስታወቀው ከዓርብ ጀምሮ የአንድ ሊትር ነዳጅ ዋጋ በአንድ ሳንቲም ጨምሯል ይህም ከስምንት ዓመት በኋላ የታየ ነው። ከፍተኛ ሰዎች በሚታዩባቸው ማደያዎች አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ቸርቻሪዎች ዋጋውን ከዚህም በላይ እየጨመሩ መሆኑን ተገንዝቤያለሁ ብሏል። በሌላ በኩል እንደ ጤና እና ማህበራዊ እንክብካቤ ላሉ ወሳኝ ሠራተኞች ቅድሚያ የነዳጅ ተደራሽነት እንዲያገኙ ጥሪዎችን እያደረጉ ነው። | በዩኬ የተፈጠረውን የነዳጅ እጥረት ቀውስ ለማቃለል የሀገሪቱ ሰራዊት ዝግጁ ነው ተባለ በዩኬ የተፈጠረውና አራተኛ ቀን ባስቆጠረው የነዳጅ አቅርቦት መስተጓጎል ምክንያት የተፈጠሩ ረጃጅም ሰልፎችንና መሰል ችግሮችን ለማቃለል ሰራዊቱ ዝግጁ መሆኑ ተገለጸ። በሀገሪቱ በተከሰተው የነዳጅ አቅርቦት ችግር የነዳጅ ማመላለሻ አሽከርካሪዎች እጥረትም ገጥሟል። አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ እስከ 150 የሚደርሱ የወታደር ነዳጅ ጫኝ አሽከርካሪዎች ሥልጠና በመሰጠት ማሰማራት እንደሚቻልም ተጠቅሷል። በርካታ የጭነት መኪና አሽከርካሪዎች የነዳጅ አቅርቦት ሊከሰት ይችላል በሚል ስጋት በርካታዎች በነዳጅ ማደያዎች በማጣሪያዎች በቁጥር በዝተው ይታያሉ። ዩናይትድ ኪንግደም ከ100 ሺህ በላይ የጭነት መኪና አሽከርካሪዎች ያስፈልጋታል ተብሎ የሚገመት ሲሆን ባለፉት ወራት የምግብ አቅራቢዎችን እና ሱፐርማርኬቶችን ጨምሮ የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ችግር አጋጥሟቸዋል። የሀገሪቱ ባለስልጣን በነዳጅ ማደያዎች ለሚታዩት ረጃጅም ሰልፎች ነዳጅ ሳያስፈልጋቸው ወደ ማደያዎች የሚሄዱ ሰዎችን ተጠያቂ አድርገዋል። ኤኤሲሲ የተባለ ኩባንያ እንዳስታወቀው ከዓርብ ጀምሮ የአንድ ሊትር ነዳጅ ዋጋ በአንድ ሳንቲም ጨምሯል ይህም ከስምንት ዓመት በኋላ የታየ ነው። ከፍተኛ ሰዎች በሚታዩባቸው ማደያዎች አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ቸርቻሪዎች ዋጋውን ከዚህም በላይ እየጨመሩ መሆኑን ተገንዝቤያለሁ ብሏል። በሌላ በኩል እንደ ጤና እና ማህበራዊ እንክብካቤ ላሉ ወሳኝ ሠራተኞች ቅድሚያ የነዳጅ ተደራሽነት እንዲያገኙ ጥሪዎችን እያደረጉ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/news-58716168 |
2health
| ጤና፡ የወጣቶች የወገብ ህመም መንስዔ እና መፍትሔው | አሁን አሁን የወገብ ህመም አጋጥሟቸው የህክምና ተቋማትን የሚጎበኙ ወጣቶች እየተበራከቱ ነው። በተለይ በማደግ ላይ ባሉ አገራት ለወገብ ህመም የሚጋለጡ ወጣቶች ቁጥርም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ጥናቶች ያመለክታሉ። ለመሆኑ ለዚህ መንስዔው ምንድን ነው? መፍትሔውስ? በዚህ ላይ በፓራጎን የፊዚዮቴራፒና ስፓርት ህክምና ስፔሻሊቲ ልዩ ክሊኒኮች ውስጥ ሥራ አስኪያጅ እና ሜዲካል ዳሬክተር ከሆኑት ዶ/ር ቴዎድሮስ ወ/ገብርኤል ጋር ቆይታ አድርገናል። ዶ/ር ቴዎድሮስ ሦስቱንም ድግሪያቸውን የተከታተሉት በአሜሪካ ሲሆን በፊዚዮቴራፒ በተለይ በስፖርት ህክምና እና ኦርቶፔዲክስ ህክምና ዶክትሬታቸውን አግኝተዋል። በሙያቸው በአሜሪካ ለ10 ዓመታት የሰሩ ሲሆን በኢትዮጵያ ደግሞ ላለፉት 12 ዓመታት እያገለገሉ ይገኛሉ። ከዚህም በተጨማሪ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ትምህርት ቤት ውስጥ ረዳት ፕሮፌሰር ናቸው። በጥቁር አንበሳ ህክምና ትምህርት ቤት በፊዚዮቴራፒ ዶክትሬት ፕሮግራም በመምህርነት ሠርተዋል። ብዙውን ጊዜ ወጣቶች ለወገብ ህመም ያጋለጣቸውን መንስዔ በውል አያውቁትም። እንዲሁ በደፈናው ድንገት አመመኝ ሲሉ ነው የሚሰማው። ለመሆኑ የወገብ ህመም መንስዔዎች ምንድን ናቸው? የሰውነት ማጎልመሻ እንቅስቃሴዎች፣ የምንጫማቸው ጫማዎች ፣ የምንተኛበት ፍራሽ ፣ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈፀምበት መንገድ ( Sex position) . . . ለወገብ ህመም ይዳርጉ ይሆን? ወደዚህ ዝርዝር ከማለፋችን በፊት ስለወገብ እና የወገብ ህመም ምንነት እናንሳ። ወገብ ቀበቷችን ወይም መቀነታችን የሚያርፍበት የሰውነታችን ክፍል ሲሆን በዚህ ላይ የሚከሰት ህመም የወገብ ህመም ይባላል። የወገብ ህመም ጽንሰ ሃሳቡ ሰፊና ጥልቅ ቢሆንም በቀላል አገላለጽ በወገብ አካባቢ በሚገኙ ጡንቻዎች ፣ የነርቭ ሥሮች፣ የአከርካሪ አጥንቶች፣ የጎን አጥንቶች እና ጅማቶች ላይ የሚደርስ ጉዳት ነው። ይህ ጉዳት ጊዜያዊ ወይም ዘለቄታዊ ሊሆን ይችላል። የወገብ ህመም ዓይነቶች እንደ መንስዔያቸው ይለያያሉ። ዋና ዋናዎቹ ግን እነዚህ ናቸው፦ ከመጨረሻው ነጥብ እንጀምር። የሰውነት በሽታ ተዋጊ ሂደት በመዛበት የሚከሰተው የወገብ ህመም የሚያጋጥመው ሰውነት በሽታን የሚከላከልበት ሂደት ሌሎች የሰውነት አካላትን ሲያጠቃ ነው። በእንግሊዝኛ አጠራሩ Ankylosing spondylitis ይባላል። የሰውነት የውስጥ ቁስለትን በመፍጠር ዘለግ ላለ ጊዜ የሚቆይ ህመም ነው። የዚህ ህመም ምክንያቱ ምን እንደሆነ በውል አይታወቅም። በተለይ በመገጣጠሚያዎች እና በአከርካሪ አጥንቶች መጋጠሚያ መካከል ቁስለትን ያስከትላል። ህመሙ እየጨመረ ሲሄድም የአከርካሪ አጥንቶች እንዲንቀሳቀሱ እንደ ሃዲድ የሚያገለግለው የሰውነት ክፍል ላይ አጥንቶቹ መንቀሳቀሳቸውን ትተው እርስ በእርሳቸው እንዲጣበቁ ያደርጋል። በዚህ ምክንያት አጥንቶቹ መንቀሳቀሳቸው ቀርቶ አንድ አካል ይሆናሉ። በዚህ ህመም የተጠቃ ሰው ማጎንበስ፣ ወደ ኋላ አሊያም ወደ ጎን መንቀሳቀስ አይችልም። የሌሎቹ የወገብ ህመም ዓይነቶች መንስዔዎችስ? ለወገብ ህመም የሚዳርጉን መንስዔዎች በርካታ ቢሆኑም ዶ/ር ቴዎድሮስ በ21 ዓመት የህክምና ልምዳቸው የተመለከቷቸውንና ዋና ዋና ያሏቸውን መንስዔዎች ያስረዳሉ። ከባድ ነገር ማንሳት፡ ማንኛውም ሰው በዕለት ተዕለት ክንውኑ ጥንቃቄ ካላደረገ ወገቡን ሊታመም ይችላል። በባልዲ ውሃ ቀድቶ ፎቅ ላይ መውሰድ፣ ክብደት ያላቸውን ሰዎች ከአልጋ ማንሳት እንዲሁም ማንኛውንም ከአቅም በላይ የሆነ ክብደትን ማንሳት ለወገብ ህመም ሊዳርግ ይችላል። ከልክ በላይ የሆነ የሰውነት ክብደት መኖር፡ በተለይ በአንድ ጊዜ የሚጨምር የሰውነት ክብደት የወገብ ህመም እንደሚያስከትል ዶ/ር ቴዎድሮስ ይናገራሉ። "በኮቪድ ወረርሽኝ ወቅት አካላዊ እንቅስቃሴ የሌለው ሥራ በመዘውተሩ በዚህ ሳቢያ የሚከሰት ህመም ተበራክቶ ነበር" ይላሉ። ረዘም ላለ ጊዜ ቆሞ፣ ተቀምጦ ወይም ቆሞ ጎንበስ ብሎ መስራት፡ ረዘም ላለ ጊዜ ቆመው፣ ተቀምጠው አልያም ቆመው ከአንገታቸው ተጎንብሰው በሚሰሩ ሙያዎች ላይ የተሰማሩ ሰዎች ለወገብ ህመም የመጋለጣቸው ዕድል ሰፊ ነው። ዶ/ር ቴዎድሮስ አንድ ሰው ቆሞ ከአንገቱ ጎንበስ ብሎ በሚሰራበት ጊዜ በሁለት አከርካሪ አጥንቶች መካከል ወደ 270 ኪሎ ግራም ግፊት እንዳለው ጥናቶችን ያጣቅሳሉ። ይህን በየቀኑ ማድረግ ደግሞ ከጊዜ በኋላ የከፋ ጉዳት ያስከትላል። ብዙ ጊዜ የቀዶ ህክምና ሐኪሞች በዚህ ሳቢያ ለሚከሰት የወገብ ህመም ሲጋለጡ ይስተዋላል። ብዙ መንገጫገጭ ያላቸው የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን ማሽከርከር፡ ብዙ ንዝረት ያላቸው የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን ማሽከርከር ወይም ምቹ ባልሆኑ መንገዶች ላይ መኪና ማሽከርከር ከጊዜ በኋላ የወገብ ህመም ያስከትላል። የዝላይ እና የሩጫ እንቅስቃሴዎች፡ በተለይ ከልክ በላይ የሰውነት ክብደት ያላቸው ሰዎች ሩጫ ወይም የመዝለል እንቅስቃሴ የሚያዘወትሩ ከሆነ ወገባቸው ሊጎዳ ይችላል። እንደ አስፓልት ያለ ጠንካራ የሆነ ቦታ ላይ የሚሮጡ ሰዎችም መሬቱ ላይ እግራቸውን በጣሉ ቁጥር መሬትም በአጸፋው ስለሚመታቸው ለጉዳት ሊዳርጋቸው ይችላል። ከዚህም በተጨማሪ ወጣ ገባ የሆነ መሬት ላይ የሚሮጡ ሰዎች እግራቸው በሚያርፍበት ሰዓት ሚዛናቸው እኩል ስለማይሆን ወገብ ላይ ጫና ይፈጠራል። ሰውነት ሳይለምድ በአንድ ጊዜ ከባድ የአካል እንቅስቃሴ መስራት፡ አሁን አሁን በወጣቶች ዘንድ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ እየተለመደ መጥቷል። የሚሰሯቸው እንቅስቃሴዎችንም ዩቲዩብ በማየት የሚመርጡም አሉ። ይህ ብቻም ሳይሆን ስፖርቱን ለምን ዓላማ እንደሚሰሩ የማያውቁ በርካቶች ናቸው። በዚህ ሳቢያ ተጎድተው ወደ ክሊኒካቸው የሚመጡ ወጣቶች መኖራቸውን ዶ/ር ቴዎድሮስ ይናገራሉ። "ችግሩ አካላዊ እንቅስቃሴ ከማድረግ የተከሰተ ሳይሆን ሰውነት ሳይለማመድ ከባድ የአካል እንቅስቃሴ መስራት ነው" ይላሉ። "ጂምናዚየም ውስጥ ለአሰልጣኝ ጉርሻ መስጠት የተለመደ ሆኗል" የሚሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ አንዳንድ አሰልጣኞች ጉርሻዋን ለማግኘት ደንበኞቻቸው የሚፈልጉት የሰውነት ለውጥ ላይ ቶሎ ማድረስ ላይ ብቻ ትኩረት እንደሚያደርጉ ይናገራሉ። አሰልጣኞቹ ስለስፖርታዊ እንቅስቃሴው እንጂ ስለጤና እውቀት ላይኖራቸውም ይችላል። አንዳንድ ሰልጣኞችም በአንድ ጊዜ በሰውነታቸው ላይ የሚፈልጉት ለውጥ እንዲመጣ ባልተገባ መልኩ ከልክ በላይ የሆነ አካላዊ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ። ዶ/ር ቴዎድሮስ ይህንን ሲገልጹት "ምንም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አድርጎ የማያውቅ ሰው ቅዳሜ እና እሁድ ጂምናዚየም ገብቶ አገር ይያዝልኝ እንደ ማለት ነው" ይላሉ። ዲስክ መንሸራተት፡ የዲስክ መንሽራተት ስሙ ለብዙዎቻችን ጆሮ እንግዳ አይደለም። ዶ/ር ቴዎድሮስም የዲስክ መንሸራተት ያለ ስሙ ብዙ ስም የተሰጠው በሽታ ነው ይላሉ። ዶ/ር ቴዎድሮስ እንደሚሉት የዲስክ ችግር ተብለው ወደ ክሊኒካቸው ከሚመጡት 100 ሰዎች ውስጥ 50 በመቶ የሚሆኑት ችግራቸው ሌላ ነው። በተለምዶ የህክምና ባለሙያዎች ህሙማንን ለዲስክ መንሸራተት ተዳርገዋል የሚሉት 'ኤምአርአይ' መመርመሪያ የሚያሳየው ውጤት ላይ ተመርኩዘው ነው። ይሁን እንጂ ዶ/ር ቴዎድሮስ "10 ሰዎችን እንዲሁ ከመንገድ ላይ በግምት ተመርጠው ኤምአርአይ ቢነሱ ቢያንስ 7ቱ የዲስክ መንሸራተት ሊያሳዩ ይችላሉ" ይላሉ። ይህ ማለት ግን ህመም አለባቸው ማለት አይደለም። "የዲስክ መንሸራተት ታይቷል ማለት የተዛባ ዲስክ አላቸው፤ ግን ዲስኩ ነርቩን ጨፍልቆ ህመም የሚያመጣበት ደረጃ ላይ አይደለም ማለት ነው" ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። በዚህ የምርመራ ውጤት ላይ ተመስርተው ቶሎ ቀዶ ህክምና አድርጉ ወደሚል ድምዳሜ የሚደርሱ የህክምና ባለሙያዎች መኖራቸውን የሚናገሩት ዶ/ር ቴዎድሮስ፤ ይህ ግን ስህተት ነው ብለዋል። ለመሆኑ ዲስክ ምንድን ነው? የሚገኘውስ የት ላይ ነው? ዲስክ በአከርካሪ አጥንቶች መካከል የሚገኝ በውስጡ ፈሳሽ ያለው ለስላሳ የሆነ እንደ ጎሚኒ (ሾክ አብሶርቨር) የምንጠቀምበት የአካል ክፍል ነው። ታዲያ ሰውነታችን ጫና በሚበዛበት ጊዜ በዲስኩ ውስጥ ያለው ፈሳሽ ሊወጣ ይችላል ወይም ደግሞ ፈሳሹ ሳይወጣ ዲስኩ ወደ አንድ በኩል አመዝኖ መውጣት ወደማይገባበት ቦታ ሊወጣ ይችላል። ዲስክ ያለበት አካባቢ የተጨናነቀ በመሆኑ አፈትልኮ በሚወጣበት ጊዜ ከጭንቅላታችን በሚወርደውና ህብለ ሰረሰር በሚባለው የነርቭ ግንድ እና ቅርንጫፎች ላይ በመተኛት ጫና ይፈጥራል። የዲስክ መንሸራተት በሚያጋጥምበት ጊዜ ቀዶ ህክምና ለማድረግ ከመጣደፍ በፊት ዲስኩ ተንሸራቶ ምን ሆነ? ወዴት አቅጣጫ ነው የተንሸራተተው? ምን ያህል ነው የተንሸራተተው? እየነካ ያለውስ ነርቭ የትኛውን ነው? ሊያስከትል የሚችለው የህመም ስሜት አለ ወይ? የሚሉትን ወሳኝ ጥያቄዎች መጠየቅ አስፈላጊ መሆኑን ዶ/ር ቴዎድሮስ ያሰምሩበታል። ወጣቶችን ለወገብ ህመም የሚያጋልጣቸው የተለየ ምክንያት ይኖር ይሆን? ከምንጊዜውም በላይ ብዙ ወጣቶች በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ላይ እየተሠማሩ መሆናቸው አንዱ ምክንያት ነው ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። ወጣቶች ረዘም ያለ ጊዜ መቆምን፣ መቀመጥን አሊያም ጎንበስ ብሎ መቆምን እንዲሁም ከባድ ነገር ማንሳትን፣ መሸከምን የሚጠይቁ ሥራዎችን ይሠራሉ። በሌላም በኩል ከዚህ ቀደሙ በተሻለ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማዘውተርም ሌላኛው ምክንያት መሆኑን ይናገራሉ። "ስለምንሰራው አካላዊ እንቅስቃሴ ጠለቅ ያለ እውቀት ከሌለን በስተቀር የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ጥቅም እንዳላቸው ሁሉ ጉዳት አላቸው።" ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። በተቃራኒው ደግሞ የሰውነት እንቅስቃሴ ማነስ ለወገብ ህመም መንስዔ ነው። የግብረ ሥጋ ግንኙነት ለወገብ ህመም ያጋልጣል? የግብረ ሥጋ ግንኙነት በሳይንስ እንደ ወገብ ህመም መንስዔነት ወይም እንደ ወገብ ህመም መነሻነት አይታወቅም ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። ይሁን እንጂ የወገብ ህመም ያለባቸው ሰዎች የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽሙበት መንገድ ህመማቸውን ሊያባብስባቸው ወይም የተሻላቸውን ህመም እንደገና ሊያስነሳባቸው እንደሚችል ይናገራሉ። "በተለይ በሴቶች ዘንድ ይህንን ለሐኪም የማስረዳት ልምድ የለም" የሚሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ አንዳንዶች ግን በስልክም ቢሆን ምክር የሚጠይቁ መኖራቸውን አልሸሸጉም። "እንደ የወገብ ህመማቸው ዓይነትም ለተወሰነ ጊዜ የግብረ ሥጋ ግንኙነት አደራረግ (Sex position) እንዲቀይሩ፣ እንዳያደርጉ ወይም ሊያደርጓቸው ስለሚችሉ የግብረ ሥጋ ግንኙነት አደራረግ ዓይነቶች ምክር የሚሰጣቸው ታማሚዎች አሉ" ይላሉ። የምንጫማው ጫማስ? የወገባችንን ጤንነት ለመጠበቅ የምንጫማው የጫማ ዓይነት ወሳኝነት አለው። ይህ ግን በአብዛኛው የሚገናኘው ከሴቶች ጋር ነው። ምክንያቱም በተለይ በፋሽንና መዝናኛ ኢንደስትሪው ሴቶች መንቀሳቀስ እስከሚቸገሩ ድረስ ረጃጅም ታኮ ያላቸውን ጫማዎች ተጫምተው ማየት የተለመደ ነው። ይህ ደግሞ በሰውነት ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራል። እንዴት? ዶ/ር ቴዎድሮስ ለዚህ ሳይንሳዊ ምላሽ አላቸው። ሰውነት የራሱን ሚዛን የሚጠብቅበት መንገድ አለው። ይህ የስበት ማዕከል (Center of gravity) ይባላል። ስንራመድ የማንወድቀው ወይም ደግሞ ቁጭ ብለን ስንነሳ ከግድግዳ ጋር የማንጋጨው ይህ የመሬት ስበት ማዕከል ሚዛናችንን ስለሚጠብቅልን ነው። ታዲያ ከፍ ያሉ ታኮዎች ያሏቸውን ጫማዎች ስንጫማ ሰውነት ተፈጥሯዊ የሆነውን የሰውነት ሚዛን ይለቃል። የሰውነታችን የመሬት ስበት ማዕከልም ይቀየራል። በመሆኑም ሰውነት ይህንን የስበት ማዕከል መልሶ ወደ ማዕከሉ ላይ ለማምጣት (ሚዛኑን ለመጠበቅ) የሚያደርጋቸው ማስተካከያዎች ወገብ ላይ ጫና ይፈጥራሉ። ጫናው ወገብ ላይ ብቻ ሳይሆን ጉልበት፣ እግርና የእግር መዳፍ ላይም ነው። ከዓመታት በፊት በዩናይትድ ኪንግደም በፖዲያትሪ ኮሌጅ የተሠራ ጥናት ሴቶች ህመም እንደተሰማቸው ሳይናገሩ ከፍ ያለ ታኮ ጫማ ተጫምተው መቆየት የሚችሉት በአማካይ ለአንድ ሰዓት ያህል ነው ይላል። በዚህ ጥናት ተሳታፊ የነበሩ ሴቶች ጫማውን ከተጫመቱ ከ10 ደቂቃ በኋላ በእግራቸው ላይ ህመም እንደተሰማቸው ተናግረዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ሰው የተፈጠረው በባዶ እግሩ ለመሄድ ነው በማለት ሰዎች በባዶ እግራቸው እንዲሄዱ የሚያበረታታ ሳይንስ አለ። በዚህም ምክንያት ሆነ ብለው በባዶ እግራቸው የሚሄዱ ሰዎች አሉ። በእርግጥ ዶ/ር ቴዎድሮስ በባዶ እግር መሄድ አሊያም በጣም አነስተኛ ታኮ ያላቸው ጫማዎች ማድረግ ጉዳት አለው ብለው አያምኑም። ይሁን እንጂ በተፈጥሮ 'የእግራቸው ቅርጽ ለየት ያለ' ሰዎች ከተረከዝ ሁለት ሴንቲ ሜትር ከፍ ያለ ታኮ ያለው ጫማ እንዲያደርጉ ይመክራሉ። "ተረከዝ በጫማ መሄድ ከለመደ በኋላ በባዶ እግር በብዛት መሄድ በተረከዝ ላይ አጥንት መብቀልን (Bone Spur) ሊያስከትልም ይችላል" ይላሉ። ይህ አጥንት የተረከዝን ስጋ እንደ ጩቤ የሚወጋ ነው። በመሆኑም በተለይ በባዶ እግር መሄድ ያልለመደ እና ተረከዝ ላይ በቂ የስብ ንጣፍ (Fat pad) የሌለው ሰው በባዶ እግሩ ቢሄድ ለእንዲህ ዓይነት ችግር ሊጋለጥ እንደሚችል ያሳስባሉ። ይህ ግን በስፋት የሚከሰት አይደለም። የወገብ ህመም እንዳጋጠመን እንዴት ማወቅ እንችላለን? እንደማንኛውም ህመም የወገብ ህመም ሲያጋጥም የሚታዩ ከቀላል እስከ ከባድ ምልክቶች አሉ። የህመም ማስታገሻ መድሃኒት የማያስወስዱ፣ ቁጭ ስንል የሚያስታውሱን፣ መድሃኒት እስከ መውሰድ የሚያደርስ የማቃጠልና መቆጥቆጥ ስሜት፣ ጎንበስ ብሎ ቀና ለማለት መቸገር፣ ለመነሳት ድጋፍ መፈለግ፣ የጡንቻ መኮማተር፣ ለመንቀሳቀስ መቸገር፣ ተኝቶ ለመገላበጥ ማቃት የተወሰኑት ምልክቶቹ ናቸው። የሚታዩት ምልክቶች ግን እንደ ህመሙ መንስዔዎች ይለያያሉ። ለምሳሌ ረዘም ላለጊዜ በመቆም ወይም በመቀመጥ የሚመጣ ህመም ከሆነ ተቀምጠን ቆይተን ድንገት ስንነሳ የሰውነት መያዝ ፣ ስንቀመጥ ወይ ስንቆም ህመም መሰማት፣ የመቀመጫ አካባቢ ህመም፣ መጠዝጠዝና ንዝረት ያጋጥማል። ንዝረቱ ከመቀመጫ አለፍ ብሎ ቁርጭምጭሚት ፣ ጣቶች እና የእግር መዳፍ ድረስ የሚሰማ የመደንዘዝና የማቃጠል ህመሞች እየባሰ ሲመጣም የእግር መክዳትና ደረጃ ለመውጣት አቅም እስከማጣት ሊደርስ ይችላል። እግርን ማዘዝ፣ ጣቶችን ወደ ላይ ቀና ማድረግ ካቃተን ግን ህመሙ የከፋ ደረጃ ደርሷል ማለት ነው። ምን አልባት ይህ ቀዶ ሕክምና የሚያስፈልግበት ደረጃ ሊሆን ይችላል። ያጋጠመንን የወገብ ህመም ለማስታገስ በቤት ውስጥ ምን ማድረግ እንችላለን? በአቅራብያ የህክምና ተቋም ከሌለ ለጊዜው የህመም ማስታገሻዎችን መውሰድ ይመከራል። ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን ሌላ የሚወስዱት መድሃኒት ከሌለ እና ከሚወስዱት መድሃኒት ጋር የማይጋጭ ከሆነ ነው። ዘላቂ መፍትሔ ግን አይደለም። የወገብ ህመሙ የተከሰተው በድንገተኛ አደጋ [መውደቅ] ከሆነ ደግሞ በመጀመሪያ ህክምና እርዳታ በረዶ ማድረግ ጥሩ ነው። "የቁስለት ሂደቱን ለመቀነስ፣ እብጠት እና ውስጥ የደም መፍሰስ እንዳይኖር ይረዳል" ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። ከዚህ በኋላም የጡንቻ መኮማተር የሚኖር ከሆነ ሙቀት ሰውነትን የማፍታታት ባህርይ ስላለው ሙቀት ማድረግ የተሻለ መሆኑን ይመክራሉ። እረፍት ማድረግም ህመማችንን በተወሰነ ደረጃ ሊያስታግስልን ይችላል። ይህን ሁሉ አድርገን የማይሻል ከሆነ ግን ሥር ሳይሰድ እንደ ምንም ወደ ህክምና ቦታ ሄዶ ትክክለኛ ህክምና ማድረግ አስፈላጊ ነው። "አንዳንድ ሰዎች ባህላዊ ቦታ ሄደው ባልተገባ ሁኔታ ህክምና ወስደው ተጎድተው የሚመጡ አሉ" ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። እንደዚህ ያሉ ቦታዎችን ከሚያዘወትሩ ሰዎች መካከል የተማሩ ሰዎችም ጭምር እንደሚገኙበት በመግለጽም ይህ ተገቢ አለመሆኑን ይናገራሉ። ህመሙን ለማስወገድ ሲባል ያልተገባ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግም ጉዳቱን ሊያባብሰው እንደሚችል ዶ/ር ቴዎድሮስ ያስጠነቅቃሉ። ወገባችንን በህክምና ቀበቶ ወይም በመቀነት ብንደግፈውስ? የወገብ ህመም የተለያዩ ደረጃዎች አሉት። መጀመሪያ አካባቢ ችግሩ እንደተፈጠረ፣ ከዚያ ከሁለት እስከ ሦስት ወር እና ከሦስት ወር በላይ የቆየ ህመም ናቸው። ህመሙ ከሦስት ወር በላይ የቆየ ከሆነ ሥር የሰደደ ችግር ይባላል። በመሆኑም ህመሙ እንደ ጀመረ አካባቢ እረፍት ማድረግን ጨምሮ በመቀነት ማሰር ወይም በቀበቶ መደገፍ ያገዘን ስለሚመስል በሥነ ልቦናም ሆነ አካላዊ በሆነ መልኩ ሊደገፍ ይችላል ይላሉ- ዶ/ር ቴዎድሮስ። ሆኖም ይህ ለረዥም ጊዜ የሚደረግ ከሆነ ችግር እንደሚያስከትል ይናገራሉ። ምክንያታቸውን ሲያስረዱም "ቀበቶ ተደረገ ወይም መቀነት ታሰረ ማለት እዚያ አካባቢ ያሉ ጡንቻዎች እረፍት ወጡ ማለት ነው።" ይላሉ። በዚህ ሳቢያም የጡንቻ መክሳት ችግር ይከሰታል። በመሆኑም ጡንቻችን ያለ ድጋፍ ሥራውን መሥራት ይቀንሳል፤ አልያም ያቆማል። ይህም ሰዎች በቀበቶ አሊያም በመቀነት ላይ ጥገኛ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። "በኢትዮጵያ በህክምና ባለሙያዎች ዘንድ የአንገት መደገፊያ [ኮላር] እና የወገብ መደገፊያ ቀበቶ የማዘዝ ችግር ጎልቶ እየታየ ነው" የሚሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ የችግሩ መንስዔ ሳይታወቅ እነዚህን ቁሶች ማዘዝ ተገቢ እንዳልሆነ ይናገራሉ። አንዳንድ ጊዜ ሐኪሞች ቀበቶ ማዘዛቸውን ሊዘነጉት የሚችሉበት አጋጣሚም ስለሚኖር ታማሚዎቹ ለረዥም ጊዜ ቀበቶውን ሊያደርጉት ይችላሉ። ይህ ደግሞ ጉዳት ያስከትላል ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። ምን ዓይነት ፍራሽ እና ትራስ ላይ እንተኛ ? መቼም በወገብ ህመም ሳቢያ ፍራሽ ያልቀያየረ፤ ከአልጋ መደብ ፣ ከመደብ አልጋ ያላለ አይኖርም። ትራስም ቢሆን እንዲሁ። ምን ዓይነት ፍራሽ ላይ እንተኛ ? ምን አይነት ትራስ እንጠቀም የበርካቶች ጭንቀት ነው። ለወገብ ህመም ፍቱን ናቸው የተባሉ ፍራሾችም ይቸበቸባሉ። በሰለጠነው ዓለም የተለያዩ ዓይነት ዘመናዊ ፍራሽና ትራሶች እየተመረቱ ነው። በአንድ አልጋ ላይ ባልና ሚስትን በመረጡት ፍራሽ ላይ የሚያስተኛ ቴክኖሎጂም ተፈልስፏል። ታዲያ የትኛው ላይ ብንተኛ የተሻለ ነው? ዶ/ር ቴዎድሮስ "ታማሚዎቹ ተመቸን ያሉትን ፍራሽ ትክክል አይደለም ማለት አስቸጋሪ ነው ምክንያቱም ሰውነታቸው ከመረጡት ፍራሽ ጋር ተመቻችቶ ሊሆን ይችላል" ይላሉ። ቢሆንም ግን ደረቅ ፍራሽ ላይ መተኛትን አይመክሩም። እርሳቸው የሚመክሩት ሰውነት ቅርጹን በጠበቀ መልኩ የሚያሳርፍን ፍራሽ ወይም ትራስ ነው። "ራቁታችንን በመስታዎት ብንመለከት ሰውነታችን እጥፋቶች (Curves) አሉት። ስንተኛ እነዚያ እጥፋቶች ቅርጻቸውን ጠብቀው በትክክል ማረፍ አለባቸው" ይላሉ። ለዚህም ነው በሰለጠነው ዓለም 'ሚሞሪ ፎም' የተመረተው። ሚሞሪ ፎም ስንተኛ የሰውነትን ቅርጽ ይዞ ስንነሳ ወደ ነበረበት መመለስ የሚችል ፍራሽ ነው። 'ስሊፕ ነምበር ቤድ' የሚባልም ባልና ሚስት አልጋቸውን ሳይለዩ ለየራሳቸው የሰውነት ቅርጽ በሚመቻቸው መልኩ ማስተካከል የሚችሉት ሳይንሳዊ ፍራሽም ተሰርቷል። በኢትዮጵያ ለወገብ ህመም ተብለው የሚሸጡ ፍራሾችስ? ዶ/ር ቴዎድሮስ እነዚህ ፍራሾች ሳይንሳዊ አይደሉም ይላሉ። "ሱቅ የተሰቀለን ልብስ በግምት አንስቶ ግባ ብሎ እንደመታገል ነው" ሲሉም በምሳሌ ያስረዳሉ። "በሰለጠነው ዓለም 30 ደቂቃ ፍራሹ ላይ እረፍት ወስደን ነው ፍራሽ የምንገዛው" የሚሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ በኢትዮጵያ አንዳንድ መሸጫዎች ውስጥ 'ፍራሾቹ ላይ መተኛት ክልክል ነው!' የሚልም ማስታወቂያ በመለጠፍ ምቾቱን ሞክሮ ለመግዛት የሚደረገውን ክልከላንም ተችተዋል። ዶ/ር ቴዎድሮስ ትራስን በተመለከተም ተመሳሳይ ሃሳብ ነው ያላቸው። ትራስ በጭንቅላታችን እና በአንገታችን ሥር መካከል ያለውን ክፍተት የሚሞላ መሆን አለበት ይላሉ። ነገር ግን ሰዎች ትራሳቸውን በአግባቡ ሲጠቀሙበት አይስተዋልም። በእርግጥ የሚመቸንንና ልካችንን ለማወቅ አዳጋች ነው። ገንዘባቸውን ትራስ በመግዛት የሚጨርሱም ጥቂት አይደሉም። ይህንን ችግር ለመፍታትም ይመስላል በሰለጠነው ዓለም 'ዎተር ፒሎው' [በውሃ የሚሞላ ትራስ] የተሰራው። ይህ የውሃውን መጠን በመቀነስ ወይም በመጨመር ትራሱን በልክ ለማሳነስና ለማተለቅ ያስችላል። በመሆኑም የምንጠቀመውን ትራስ ልክ ማወቅ እና በተገቢው መንገድ መጠቀም ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ይመክራሉ። የአኗኗር ዘይቤያችን ምን ይምሰል? የሰውነት ክብደታችንን መቆጣጠር ወሳኝ ነው። ይህን ማድረጋችን ከወገብ ብቻም ሳይሆን ከሌሎች በሽታዎችም ራሳችንን ለመጠበቅ ያስችለናል። "በሰውነታችን ላይ አንድ ኪሎ በጨመርን ቁጥር በእያንዳንዱ ኪሎ አንዱ ጉልበታችን ላይ 4 ኪሎ ጫና ይፈጠራል" የሚሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ የሰውነታችንን ክብደት መቆጣጠርን ቸል ልንለው እንደማይገባ ይመክራሉ። የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን በአቅማችን ልክ እና ቀስ በቀስ በተደረገ የሰውነት ልምምድ መስራት ሌላኛው ነው። የውሃ ዋና እና በሳምንት ለአራት ወይም ለሦስት ቀናት ለ45 ደቂቃ ያህል በእግር ፈጠን ያለ እርምጃ መሄድም ጥሩ ነው። የሥራ ሁኔታን ምቹ ማድረግም አስፈላጊነቱ የሚያጠያይቅ አይደለም። ቆመው የሚሰሩ ሰዎች እቃ ሲያነሱ እንዴት መጠንቀቅ እንዳለባቸው ማወቅ፣ የሚመች ጫማ ማድረግ እንዲሁም ብዙ የሚቆሙ ሰዎች አንድ እግራቸውን አንድ ነገር ላይ አሳርፈው (ሰቅለው) መቆም ለወገብ ህመም የመጋለጥ እድላቸውን ይቀንሳል። ከዚህም ባሻገር የወገብ ህመም መንስዔ ከሆኑ ድርጊቶች ራስን መጠበቅ እንደሚገባ ዶ/ር ቴዎድሮስ ይመክራሉ። | ጤና፡ የወጣቶች የወገብ ህመም መንስዔ እና መፍትሔው አሁን አሁን የወገብ ህመም አጋጥሟቸው የህክምና ተቋማትን የሚጎበኙ ወጣቶች እየተበራከቱ ነው። በተለይ በማደግ ላይ ባሉ አገራት ለወገብ ህመም የሚጋለጡ ወጣቶች ቁጥርም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ጥናቶች ያመለክታሉ። ለመሆኑ ለዚህ መንስዔው ምንድን ነው? መፍትሔውስ? በዚህ ላይ በፓራጎን የፊዚዮቴራፒና ስፓርት ህክምና ስፔሻሊቲ ልዩ ክሊኒኮች ውስጥ ሥራ አስኪያጅ እና ሜዲካል ዳሬክተር ከሆኑት ዶ/ር ቴዎድሮስ ወ/ገብርኤል ጋር ቆይታ አድርገናል። ዶ/ር ቴዎድሮስ ሦስቱንም ድግሪያቸውን የተከታተሉት በአሜሪካ ሲሆን በፊዚዮቴራፒ በተለይ በስፖርት ህክምና እና ኦርቶፔዲክስ ህክምና ዶክትሬታቸውን አግኝተዋል። በሙያቸው በአሜሪካ ለ10 ዓመታት የሰሩ ሲሆን በኢትዮጵያ ደግሞ ላለፉት 12 ዓመታት እያገለገሉ ይገኛሉ። ከዚህም በተጨማሪ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ትምህርት ቤት ውስጥ ረዳት ፕሮፌሰር ናቸው። በጥቁር አንበሳ ህክምና ትምህርት ቤት በፊዚዮቴራፒ ዶክትሬት ፕሮግራም በመምህርነት ሠርተዋል። ብዙውን ጊዜ ወጣቶች ለወገብ ህመም ያጋለጣቸውን መንስዔ በውል አያውቁትም። እንዲሁ በደፈናው ድንገት አመመኝ ሲሉ ነው የሚሰማው። ለመሆኑ የወገብ ህመም መንስዔዎች ምንድን ናቸው? የሰውነት ማጎልመሻ እንቅስቃሴዎች፣ የምንጫማቸው ጫማዎች ፣ የምንተኛበት ፍራሽ ፣ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈፀምበት መንገድ ( Sex position) . . . ለወገብ ህመም ይዳርጉ ይሆን? ወደዚህ ዝርዝር ከማለፋችን በፊት ስለወገብ እና የወገብ ህመም ምንነት እናንሳ። ወገብ ቀበቷችን ወይም መቀነታችን የሚያርፍበት የሰውነታችን ክፍል ሲሆን በዚህ ላይ የሚከሰት ህመም የወገብ ህመም ይባላል። የወገብ ህመም ጽንሰ ሃሳቡ ሰፊና ጥልቅ ቢሆንም በቀላል አገላለጽ በወገብ አካባቢ በሚገኙ ጡንቻዎች ፣ የነርቭ ሥሮች፣ የአከርካሪ አጥንቶች፣ የጎን አጥንቶች እና ጅማቶች ላይ የሚደርስ ጉዳት ነው። ይህ ጉዳት ጊዜያዊ ወይም ዘለቄታዊ ሊሆን ይችላል። የወገብ ህመም ዓይነቶች እንደ መንስዔያቸው ይለያያሉ። ዋና ዋናዎቹ ግን እነዚህ ናቸው፦ ከመጨረሻው ነጥብ እንጀምር። የሰውነት በሽታ ተዋጊ ሂደት በመዛበት የሚከሰተው የወገብ ህመም የሚያጋጥመው ሰውነት በሽታን የሚከላከልበት ሂደት ሌሎች የሰውነት አካላትን ሲያጠቃ ነው። በእንግሊዝኛ አጠራሩ Ankylosing spondylitis ይባላል። የሰውነት የውስጥ ቁስለትን በመፍጠር ዘለግ ላለ ጊዜ የሚቆይ ህመም ነው። የዚህ ህመም ምክንያቱ ምን እንደሆነ በውል አይታወቅም። በተለይ በመገጣጠሚያዎች እና በአከርካሪ አጥንቶች መጋጠሚያ መካከል ቁስለትን ያስከትላል። ህመሙ እየጨመረ ሲሄድም የአከርካሪ አጥንቶች እንዲንቀሳቀሱ እንደ ሃዲድ የሚያገለግለው የሰውነት ክፍል ላይ አጥንቶቹ መንቀሳቀሳቸውን ትተው እርስ በእርሳቸው እንዲጣበቁ ያደርጋል። በዚህ ምክንያት አጥንቶቹ መንቀሳቀሳቸው ቀርቶ አንድ አካል ይሆናሉ። በዚህ ህመም የተጠቃ ሰው ማጎንበስ፣ ወደ ኋላ አሊያም ወደ ጎን መንቀሳቀስ አይችልም። የሌሎቹ የወገብ ህመም ዓይነቶች መንስዔዎችስ? ለወገብ ህመም የሚዳርጉን መንስዔዎች በርካታ ቢሆኑም ዶ/ር ቴዎድሮስ በ21 ዓመት የህክምና ልምዳቸው የተመለከቷቸውንና ዋና ዋና ያሏቸውን መንስዔዎች ያስረዳሉ። ከባድ ነገር ማንሳት፡ ማንኛውም ሰው በዕለት ተዕለት ክንውኑ ጥንቃቄ ካላደረገ ወገቡን ሊታመም ይችላል። በባልዲ ውሃ ቀድቶ ፎቅ ላይ መውሰድ፣ ክብደት ያላቸውን ሰዎች ከአልጋ ማንሳት እንዲሁም ማንኛውንም ከአቅም በላይ የሆነ ክብደትን ማንሳት ለወገብ ህመም ሊዳርግ ይችላል። ከልክ በላይ የሆነ የሰውነት ክብደት መኖር፡ በተለይ በአንድ ጊዜ የሚጨምር የሰውነት ክብደት የወገብ ህመም እንደሚያስከትል ዶ/ር ቴዎድሮስ ይናገራሉ። "በኮቪድ ወረርሽኝ ወቅት አካላዊ እንቅስቃሴ የሌለው ሥራ በመዘውተሩ በዚህ ሳቢያ የሚከሰት ህመም ተበራክቶ ነበር" ይላሉ። ረዘም ላለ ጊዜ ቆሞ፣ ተቀምጦ ወይም ቆሞ ጎንበስ ብሎ መስራት፡ ረዘም ላለ ጊዜ ቆመው፣ ተቀምጠው አልያም ቆመው ከአንገታቸው ተጎንብሰው በሚሰሩ ሙያዎች ላይ የተሰማሩ ሰዎች ለወገብ ህመም የመጋለጣቸው ዕድል ሰፊ ነው። ዶ/ር ቴዎድሮስ አንድ ሰው ቆሞ ከአንገቱ ጎንበስ ብሎ በሚሰራበት ጊዜ በሁለት አከርካሪ አጥንቶች መካከል ወደ 270 ኪሎ ግራም ግፊት እንዳለው ጥናቶችን ያጣቅሳሉ። ይህን በየቀኑ ማድረግ ደግሞ ከጊዜ በኋላ የከፋ ጉዳት ያስከትላል። ብዙ ጊዜ የቀዶ ህክምና ሐኪሞች በዚህ ሳቢያ ለሚከሰት የወገብ ህመም ሲጋለጡ ይስተዋላል። ብዙ መንገጫገጭ ያላቸው የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን ማሽከርከር፡ ብዙ ንዝረት ያላቸው የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን ማሽከርከር ወይም ምቹ ባልሆኑ መንገዶች ላይ መኪና ማሽከርከር ከጊዜ በኋላ የወገብ ህመም ያስከትላል። የዝላይ እና የሩጫ እንቅስቃሴዎች፡ በተለይ ከልክ በላይ የሰውነት ክብደት ያላቸው ሰዎች ሩጫ ወይም የመዝለል እንቅስቃሴ የሚያዘወትሩ ከሆነ ወገባቸው ሊጎዳ ይችላል። እንደ አስፓልት ያለ ጠንካራ የሆነ ቦታ ላይ የሚሮጡ ሰዎችም መሬቱ ላይ እግራቸውን በጣሉ ቁጥር መሬትም በአጸፋው ስለሚመታቸው ለጉዳት ሊዳርጋቸው ይችላል። ከዚህም በተጨማሪ ወጣ ገባ የሆነ መሬት ላይ የሚሮጡ ሰዎች እግራቸው በሚያርፍበት ሰዓት ሚዛናቸው እኩል ስለማይሆን ወገብ ላይ ጫና ይፈጠራል። ሰውነት ሳይለምድ በአንድ ጊዜ ከባድ የአካል እንቅስቃሴ መስራት፡ አሁን አሁን በወጣቶች ዘንድ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ እየተለመደ መጥቷል። የሚሰሯቸው እንቅስቃሴዎችንም ዩቲዩብ በማየት የሚመርጡም አሉ። ይህ ብቻም ሳይሆን ስፖርቱን ለምን ዓላማ እንደሚሰሩ የማያውቁ በርካቶች ናቸው። በዚህ ሳቢያ ተጎድተው ወደ ክሊኒካቸው የሚመጡ ወጣቶች መኖራቸውን ዶ/ር ቴዎድሮስ ይናገራሉ። "ችግሩ አካላዊ እንቅስቃሴ ከማድረግ የተከሰተ ሳይሆን ሰውነት ሳይለማመድ ከባድ የአካል እንቅስቃሴ መስራት ነው" ይላሉ። "ጂምናዚየም ውስጥ ለአሰልጣኝ ጉርሻ መስጠት የተለመደ ሆኗል" የሚሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ አንዳንድ አሰልጣኞች ጉርሻዋን ለማግኘት ደንበኞቻቸው የሚፈልጉት የሰውነት ለውጥ ላይ ቶሎ ማድረስ ላይ ብቻ ትኩረት እንደሚያደርጉ ይናገራሉ። አሰልጣኞቹ ስለስፖርታዊ እንቅስቃሴው እንጂ ስለጤና እውቀት ላይኖራቸውም ይችላል። አንዳንድ ሰልጣኞችም በአንድ ጊዜ በሰውነታቸው ላይ የሚፈልጉት ለውጥ እንዲመጣ ባልተገባ መልኩ ከልክ በላይ የሆነ አካላዊ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ። ዶ/ር ቴዎድሮስ ይህንን ሲገልጹት "ምንም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አድርጎ የማያውቅ ሰው ቅዳሜ እና እሁድ ጂምናዚየም ገብቶ አገር ይያዝልኝ እንደ ማለት ነው" ይላሉ። ዲስክ መንሸራተት፡ የዲስክ መንሽራተት ስሙ ለብዙዎቻችን ጆሮ እንግዳ አይደለም። ዶ/ር ቴዎድሮስም የዲስክ መንሸራተት ያለ ስሙ ብዙ ስም የተሰጠው በሽታ ነው ይላሉ። ዶ/ር ቴዎድሮስ እንደሚሉት የዲስክ ችግር ተብለው ወደ ክሊኒካቸው ከሚመጡት 100 ሰዎች ውስጥ 50 በመቶ የሚሆኑት ችግራቸው ሌላ ነው። በተለምዶ የህክምና ባለሙያዎች ህሙማንን ለዲስክ መንሸራተት ተዳርገዋል የሚሉት 'ኤምአርአይ' መመርመሪያ የሚያሳየው ውጤት ላይ ተመርኩዘው ነው። ይሁን እንጂ ዶ/ር ቴዎድሮስ "10 ሰዎችን እንዲሁ ከመንገድ ላይ በግምት ተመርጠው ኤምአርአይ ቢነሱ ቢያንስ 7ቱ የዲስክ መንሸራተት ሊያሳዩ ይችላሉ" ይላሉ። ይህ ማለት ግን ህመም አለባቸው ማለት አይደለም። "የዲስክ መንሸራተት ታይቷል ማለት የተዛባ ዲስክ አላቸው፤ ግን ዲስኩ ነርቩን ጨፍልቆ ህመም የሚያመጣበት ደረጃ ላይ አይደለም ማለት ነው" ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። በዚህ የምርመራ ውጤት ላይ ተመስርተው ቶሎ ቀዶ ህክምና አድርጉ ወደሚል ድምዳሜ የሚደርሱ የህክምና ባለሙያዎች መኖራቸውን የሚናገሩት ዶ/ር ቴዎድሮስ፤ ይህ ግን ስህተት ነው ብለዋል። ለመሆኑ ዲስክ ምንድን ነው? የሚገኘውስ የት ላይ ነው? ዲስክ በአከርካሪ አጥንቶች መካከል የሚገኝ በውስጡ ፈሳሽ ያለው ለስላሳ የሆነ እንደ ጎሚኒ (ሾክ አብሶርቨር) የምንጠቀምበት የአካል ክፍል ነው። ታዲያ ሰውነታችን ጫና በሚበዛበት ጊዜ በዲስኩ ውስጥ ያለው ፈሳሽ ሊወጣ ይችላል ወይም ደግሞ ፈሳሹ ሳይወጣ ዲስኩ ወደ አንድ በኩል አመዝኖ መውጣት ወደማይገባበት ቦታ ሊወጣ ይችላል። ዲስክ ያለበት አካባቢ የተጨናነቀ በመሆኑ አፈትልኮ በሚወጣበት ጊዜ ከጭንቅላታችን በሚወርደውና ህብለ ሰረሰር በሚባለው የነርቭ ግንድ እና ቅርንጫፎች ላይ በመተኛት ጫና ይፈጥራል። የዲስክ መንሸራተት በሚያጋጥምበት ጊዜ ቀዶ ህክምና ለማድረግ ከመጣደፍ በፊት ዲስኩ ተንሸራቶ ምን ሆነ? ወዴት አቅጣጫ ነው የተንሸራተተው? ምን ያህል ነው የተንሸራተተው? እየነካ ያለውስ ነርቭ የትኛውን ነው? ሊያስከትል የሚችለው የህመም ስሜት አለ ወይ? የሚሉትን ወሳኝ ጥያቄዎች መጠየቅ አስፈላጊ መሆኑን ዶ/ር ቴዎድሮስ ያሰምሩበታል። ወጣቶችን ለወገብ ህመም የሚያጋልጣቸው የተለየ ምክንያት ይኖር ይሆን? ከምንጊዜውም በላይ ብዙ ወጣቶች በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ላይ እየተሠማሩ መሆናቸው አንዱ ምክንያት ነው ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። ወጣቶች ረዘም ያለ ጊዜ መቆምን፣ መቀመጥን አሊያም ጎንበስ ብሎ መቆምን እንዲሁም ከባድ ነገር ማንሳትን፣ መሸከምን የሚጠይቁ ሥራዎችን ይሠራሉ። በሌላም በኩል ከዚህ ቀደሙ በተሻለ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማዘውተርም ሌላኛው ምክንያት መሆኑን ይናገራሉ። "ስለምንሰራው አካላዊ እንቅስቃሴ ጠለቅ ያለ እውቀት ከሌለን በስተቀር የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ጥቅም እንዳላቸው ሁሉ ጉዳት አላቸው።" ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። በተቃራኒው ደግሞ የሰውነት እንቅስቃሴ ማነስ ለወገብ ህመም መንስዔ ነው። የግብረ ሥጋ ግንኙነት ለወገብ ህመም ያጋልጣል? የግብረ ሥጋ ግንኙነት በሳይንስ እንደ ወገብ ህመም መንስዔነት ወይም እንደ ወገብ ህመም መነሻነት አይታወቅም ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። ይሁን እንጂ የወገብ ህመም ያለባቸው ሰዎች የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽሙበት መንገድ ህመማቸውን ሊያባብስባቸው ወይም የተሻላቸውን ህመም እንደገና ሊያስነሳባቸው እንደሚችል ይናገራሉ። "በተለይ በሴቶች ዘንድ ይህንን ለሐኪም የማስረዳት ልምድ የለም" የሚሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ አንዳንዶች ግን በስልክም ቢሆን ምክር የሚጠይቁ መኖራቸውን አልሸሸጉም። "እንደ የወገብ ህመማቸው ዓይነትም ለተወሰነ ጊዜ የግብረ ሥጋ ግንኙነት አደራረግ (Sex position) እንዲቀይሩ፣ እንዳያደርጉ ወይም ሊያደርጓቸው ስለሚችሉ የግብረ ሥጋ ግንኙነት አደራረግ ዓይነቶች ምክር የሚሰጣቸው ታማሚዎች አሉ" ይላሉ። የምንጫማው ጫማስ? የወገባችንን ጤንነት ለመጠበቅ የምንጫማው የጫማ ዓይነት ወሳኝነት አለው። ይህ ግን በአብዛኛው የሚገናኘው ከሴቶች ጋር ነው። ምክንያቱም በተለይ በፋሽንና መዝናኛ ኢንደስትሪው ሴቶች መንቀሳቀስ እስከሚቸገሩ ድረስ ረጃጅም ታኮ ያላቸውን ጫማዎች ተጫምተው ማየት የተለመደ ነው። ይህ ደግሞ በሰውነት ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራል። እንዴት? ዶ/ር ቴዎድሮስ ለዚህ ሳይንሳዊ ምላሽ አላቸው። ሰውነት የራሱን ሚዛን የሚጠብቅበት መንገድ አለው። ይህ የስበት ማዕከል (Center of gravity) ይባላል። ስንራመድ የማንወድቀው ወይም ደግሞ ቁጭ ብለን ስንነሳ ከግድግዳ ጋር የማንጋጨው ይህ የመሬት ስበት ማዕከል ሚዛናችንን ስለሚጠብቅልን ነው። ታዲያ ከፍ ያሉ ታኮዎች ያሏቸውን ጫማዎች ስንጫማ ሰውነት ተፈጥሯዊ የሆነውን የሰውነት ሚዛን ይለቃል። የሰውነታችን የመሬት ስበት ማዕከልም ይቀየራል። በመሆኑም ሰውነት ይህንን የስበት ማዕከል መልሶ ወደ ማዕከሉ ላይ ለማምጣት (ሚዛኑን ለመጠበቅ) የሚያደርጋቸው ማስተካከያዎች ወገብ ላይ ጫና ይፈጥራሉ። ጫናው ወገብ ላይ ብቻ ሳይሆን ጉልበት፣ እግርና የእግር መዳፍ ላይም ነው። ከዓመታት በፊት በዩናይትድ ኪንግደም በፖዲያትሪ ኮሌጅ የተሠራ ጥናት ሴቶች ህመም እንደተሰማቸው ሳይናገሩ ከፍ ያለ ታኮ ጫማ ተጫምተው መቆየት የሚችሉት በአማካይ ለአንድ ሰዓት ያህል ነው ይላል። በዚህ ጥናት ተሳታፊ የነበሩ ሴቶች ጫማውን ከተጫመቱ ከ10 ደቂቃ በኋላ በእግራቸው ላይ ህመም እንደተሰማቸው ተናግረዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ሰው የተፈጠረው በባዶ እግሩ ለመሄድ ነው በማለት ሰዎች በባዶ እግራቸው እንዲሄዱ የሚያበረታታ ሳይንስ አለ። በዚህም ምክንያት ሆነ ብለው በባዶ እግራቸው የሚሄዱ ሰዎች አሉ። በእርግጥ ዶ/ር ቴዎድሮስ በባዶ እግር መሄድ አሊያም በጣም አነስተኛ ታኮ ያላቸው ጫማዎች ማድረግ ጉዳት አለው ብለው አያምኑም። ይሁን እንጂ በተፈጥሮ 'የእግራቸው ቅርጽ ለየት ያለ' ሰዎች ከተረከዝ ሁለት ሴንቲ ሜትር ከፍ ያለ ታኮ ያለው ጫማ እንዲያደርጉ ይመክራሉ። "ተረከዝ በጫማ መሄድ ከለመደ በኋላ በባዶ እግር በብዛት መሄድ በተረከዝ ላይ አጥንት መብቀልን (Bone Spur) ሊያስከትልም ይችላል" ይላሉ። ይህ አጥንት የተረከዝን ስጋ እንደ ጩቤ የሚወጋ ነው። በመሆኑም በተለይ በባዶ እግር መሄድ ያልለመደ እና ተረከዝ ላይ በቂ የስብ ንጣፍ (Fat pad) የሌለው ሰው በባዶ እግሩ ቢሄድ ለእንዲህ ዓይነት ችግር ሊጋለጥ እንደሚችል ያሳስባሉ። ይህ ግን በስፋት የሚከሰት አይደለም። የወገብ ህመም እንዳጋጠመን እንዴት ማወቅ እንችላለን? እንደማንኛውም ህመም የወገብ ህመም ሲያጋጥም የሚታዩ ከቀላል እስከ ከባድ ምልክቶች አሉ። የህመም ማስታገሻ መድሃኒት የማያስወስዱ፣ ቁጭ ስንል የሚያስታውሱን፣ መድሃኒት እስከ መውሰድ የሚያደርስ የማቃጠልና መቆጥቆጥ ስሜት፣ ጎንበስ ብሎ ቀና ለማለት መቸገር፣ ለመነሳት ድጋፍ መፈለግ፣ የጡንቻ መኮማተር፣ ለመንቀሳቀስ መቸገር፣ ተኝቶ ለመገላበጥ ማቃት የተወሰኑት ምልክቶቹ ናቸው። የሚታዩት ምልክቶች ግን እንደ ህመሙ መንስዔዎች ይለያያሉ። ለምሳሌ ረዘም ላለጊዜ በመቆም ወይም በመቀመጥ የሚመጣ ህመም ከሆነ ተቀምጠን ቆይተን ድንገት ስንነሳ የሰውነት መያዝ ፣ ስንቀመጥ ወይ ስንቆም ህመም መሰማት፣ የመቀመጫ አካባቢ ህመም፣ መጠዝጠዝና ንዝረት ያጋጥማል። ንዝረቱ ከመቀመጫ አለፍ ብሎ ቁርጭምጭሚት ፣ ጣቶች እና የእግር መዳፍ ድረስ የሚሰማ የመደንዘዝና የማቃጠል ህመሞች እየባሰ ሲመጣም የእግር መክዳትና ደረጃ ለመውጣት አቅም እስከማጣት ሊደርስ ይችላል። እግርን ማዘዝ፣ ጣቶችን ወደ ላይ ቀና ማድረግ ካቃተን ግን ህመሙ የከፋ ደረጃ ደርሷል ማለት ነው። ምን አልባት ይህ ቀዶ ሕክምና የሚያስፈልግበት ደረጃ ሊሆን ይችላል። ያጋጠመንን የወገብ ህመም ለማስታገስ በቤት ውስጥ ምን ማድረግ እንችላለን? በአቅራብያ የህክምና ተቋም ከሌለ ለጊዜው የህመም ማስታገሻዎችን መውሰድ ይመከራል። ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን ሌላ የሚወስዱት መድሃኒት ከሌለ እና ከሚወስዱት መድሃኒት ጋር የማይጋጭ ከሆነ ነው። ዘላቂ መፍትሔ ግን አይደለም። የወገብ ህመሙ የተከሰተው በድንገተኛ አደጋ [መውደቅ] ከሆነ ደግሞ በመጀመሪያ ህክምና እርዳታ በረዶ ማድረግ ጥሩ ነው። "የቁስለት ሂደቱን ለመቀነስ፣ እብጠት እና ውስጥ የደም መፍሰስ እንዳይኖር ይረዳል" ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። ከዚህ በኋላም የጡንቻ መኮማተር የሚኖር ከሆነ ሙቀት ሰውነትን የማፍታታት ባህርይ ስላለው ሙቀት ማድረግ የተሻለ መሆኑን ይመክራሉ። እረፍት ማድረግም ህመማችንን በተወሰነ ደረጃ ሊያስታግስልን ይችላል። ይህን ሁሉ አድርገን የማይሻል ከሆነ ግን ሥር ሳይሰድ እንደ ምንም ወደ ህክምና ቦታ ሄዶ ትክክለኛ ህክምና ማድረግ አስፈላጊ ነው። "አንዳንድ ሰዎች ባህላዊ ቦታ ሄደው ባልተገባ ሁኔታ ህክምና ወስደው ተጎድተው የሚመጡ አሉ" ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። እንደዚህ ያሉ ቦታዎችን ከሚያዘወትሩ ሰዎች መካከል የተማሩ ሰዎችም ጭምር እንደሚገኙበት በመግለጽም ይህ ተገቢ አለመሆኑን ይናገራሉ። ህመሙን ለማስወገድ ሲባል ያልተገባ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግም ጉዳቱን ሊያባብሰው እንደሚችል ዶ/ር ቴዎድሮስ ያስጠነቅቃሉ። ወገባችንን በህክምና ቀበቶ ወይም በመቀነት ብንደግፈውስ? የወገብ ህመም የተለያዩ ደረጃዎች አሉት። መጀመሪያ አካባቢ ችግሩ እንደተፈጠረ፣ ከዚያ ከሁለት እስከ ሦስት ወር እና ከሦስት ወር በላይ የቆየ ህመም ናቸው። ህመሙ ከሦስት ወር በላይ የቆየ ከሆነ ሥር የሰደደ ችግር ይባላል። በመሆኑም ህመሙ እንደ ጀመረ አካባቢ እረፍት ማድረግን ጨምሮ በመቀነት ማሰር ወይም በቀበቶ መደገፍ ያገዘን ስለሚመስል በሥነ ልቦናም ሆነ አካላዊ በሆነ መልኩ ሊደገፍ ይችላል ይላሉ- ዶ/ር ቴዎድሮስ። ሆኖም ይህ ለረዥም ጊዜ የሚደረግ ከሆነ ችግር እንደሚያስከትል ይናገራሉ። ምክንያታቸውን ሲያስረዱም "ቀበቶ ተደረገ ወይም መቀነት ታሰረ ማለት እዚያ አካባቢ ያሉ ጡንቻዎች እረፍት ወጡ ማለት ነው።" ይላሉ። በዚህ ሳቢያም የጡንቻ መክሳት ችግር ይከሰታል። በመሆኑም ጡንቻችን ያለ ድጋፍ ሥራውን መሥራት ይቀንሳል፤ አልያም ያቆማል። ይህም ሰዎች በቀበቶ አሊያም በመቀነት ላይ ጥገኛ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። "በኢትዮጵያ በህክምና ባለሙያዎች ዘንድ የአንገት መደገፊያ [ኮላር] እና የወገብ መደገፊያ ቀበቶ የማዘዝ ችግር ጎልቶ እየታየ ነው" የሚሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ የችግሩ መንስዔ ሳይታወቅ እነዚህን ቁሶች ማዘዝ ተገቢ እንዳልሆነ ይናገራሉ። አንዳንድ ጊዜ ሐኪሞች ቀበቶ ማዘዛቸውን ሊዘነጉት የሚችሉበት አጋጣሚም ስለሚኖር ታማሚዎቹ ለረዥም ጊዜ ቀበቶውን ሊያደርጉት ይችላሉ። ይህ ደግሞ ጉዳት ያስከትላል ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። ምን ዓይነት ፍራሽ እና ትራስ ላይ እንተኛ ? መቼም በወገብ ህመም ሳቢያ ፍራሽ ያልቀያየረ፤ ከአልጋ መደብ ፣ ከመደብ አልጋ ያላለ አይኖርም። ትራስም ቢሆን እንዲሁ። ምን ዓይነት ፍራሽ ላይ እንተኛ ? ምን አይነት ትራስ እንጠቀም የበርካቶች ጭንቀት ነው። ለወገብ ህመም ፍቱን ናቸው የተባሉ ፍራሾችም ይቸበቸባሉ። በሰለጠነው ዓለም የተለያዩ ዓይነት ዘመናዊ ፍራሽና ትራሶች እየተመረቱ ነው። በአንድ አልጋ ላይ ባልና ሚስትን በመረጡት ፍራሽ ላይ የሚያስተኛ ቴክኖሎጂም ተፈልስፏል። ታዲያ የትኛው ላይ ብንተኛ የተሻለ ነው? ዶ/ር ቴዎድሮስ "ታማሚዎቹ ተመቸን ያሉትን ፍራሽ ትክክል አይደለም ማለት አስቸጋሪ ነው ምክንያቱም ሰውነታቸው ከመረጡት ፍራሽ ጋር ተመቻችቶ ሊሆን ይችላል" ይላሉ። ቢሆንም ግን ደረቅ ፍራሽ ላይ መተኛትን አይመክሩም። እርሳቸው የሚመክሩት ሰውነት ቅርጹን በጠበቀ መልኩ የሚያሳርፍን ፍራሽ ወይም ትራስ ነው። "ራቁታችንን በመስታዎት ብንመለከት ሰውነታችን እጥፋቶች (Curves) አሉት። ስንተኛ እነዚያ እጥፋቶች ቅርጻቸውን ጠብቀው በትክክል ማረፍ አለባቸው" ይላሉ። ለዚህም ነው በሰለጠነው ዓለም 'ሚሞሪ ፎም' የተመረተው። ሚሞሪ ፎም ስንተኛ የሰውነትን ቅርጽ ይዞ ስንነሳ ወደ ነበረበት መመለስ የሚችል ፍራሽ ነው። 'ስሊፕ ነምበር ቤድ' የሚባልም ባልና ሚስት አልጋቸውን ሳይለዩ ለየራሳቸው የሰውነት ቅርጽ በሚመቻቸው መልኩ ማስተካከል የሚችሉት ሳይንሳዊ ፍራሽም ተሰርቷል። በኢትዮጵያ ለወገብ ህመም ተብለው የሚሸጡ ፍራሾችስ? ዶ/ር ቴዎድሮስ እነዚህ ፍራሾች ሳይንሳዊ አይደሉም ይላሉ። "ሱቅ የተሰቀለን ልብስ በግምት አንስቶ ግባ ብሎ እንደመታገል ነው" ሲሉም በምሳሌ ያስረዳሉ። "በሰለጠነው ዓለም 30 ደቂቃ ፍራሹ ላይ እረፍት ወስደን ነው ፍራሽ የምንገዛው" የሚሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ በኢትዮጵያ አንዳንድ መሸጫዎች ውስጥ 'ፍራሾቹ ላይ መተኛት ክልክል ነው!' የሚልም ማስታወቂያ በመለጠፍ ምቾቱን ሞክሮ ለመግዛት የሚደረገውን ክልከላንም ተችተዋል። ዶ/ር ቴዎድሮስ ትራስን በተመለከተም ተመሳሳይ ሃሳብ ነው ያላቸው። ትራስ በጭንቅላታችን እና በአንገታችን ሥር መካከል ያለውን ክፍተት የሚሞላ መሆን አለበት ይላሉ። ነገር ግን ሰዎች ትራሳቸውን በአግባቡ ሲጠቀሙበት አይስተዋልም። በእርግጥ የሚመቸንንና ልካችንን ለማወቅ አዳጋች ነው። ገንዘባቸውን ትራስ በመግዛት የሚጨርሱም ጥቂት አይደሉም። ይህንን ችግር ለመፍታትም ይመስላል በሰለጠነው ዓለም 'ዎተር ፒሎው' [በውሃ የሚሞላ ትራስ] የተሰራው። ይህ የውሃውን መጠን በመቀነስ ወይም በመጨመር ትራሱን በልክ ለማሳነስና ለማተለቅ ያስችላል። በመሆኑም የምንጠቀመውን ትራስ ልክ ማወቅ እና በተገቢው መንገድ መጠቀም ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ይመክራሉ። የአኗኗር ዘይቤያችን ምን ይምሰል? የሰውነት ክብደታችንን መቆጣጠር ወሳኝ ነው። ይህን ማድረጋችን ከወገብ ብቻም ሳይሆን ከሌሎች በሽታዎችም ራሳችንን ለመጠበቅ ያስችለናል። "በሰውነታችን ላይ አንድ ኪሎ በጨመርን ቁጥር በእያንዳንዱ ኪሎ አንዱ ጉልበታችን ላይ 4 ኪሎ ጫና ይፈጠራል" የሚሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ የሰውነታችንን ክብደት መቆጣጠርን ቸል ልንለው እንደማይገባ ይመክራሉ። የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን በአቅማችን ልክ እና ቀስ በቀስ በተደረገ የሰውነት ልምምድ መስራት ሌላኛው ነው። የውሃ ዋና እና በሳምንት ለአራት ወይም ለሦስት ቀናት ለ45 ደቂቃ ያህል በእግር ፈጠን ያለ እርምጃ መሄድም ጥሩ ነው። የሥራ ሁኔታን ምቹ ማድረግም አስፈላጊነቱ የሚያጠያይቅ አይደለም። ቆመው የሚሰሩ ሰዎች እቃ ሲያነሱ እንዴት መጠንቀቅ እንዳለባቸው ማወቅ፣ የሚመች ጫማ ማድረግ እንዲሁም ብዙ የሚቆሙ ሰዎች አንድ እግራቸውን አንድ ነገር ላይ አሳርፈው (ሰቅለው) መቆም ለወገብ ህመም የመጋለጥ እድላቸውን ይቀንሳል። ከዚህም ባሻገር የወገብ ህመም መንስዔ ከሆኑ ድርጊቶች ራስን መጠበቅ እንደሚገባ ዶ/ር ቴዎድሮስ ይመክራሉ። | https://www.bbc.com/amharic/news-60278142 |
5sports
| ለተሰንበት ግደይ የዓለም ግማሽ ማራቶን ክብረ ወሰንን ሰበረች | ኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ግደይ ስፔን ቫሌንሺያ ዛሬ በተካሄደው ግማሽ ማራቶን ሩጫ የዓለም ክብረ ወሰንን ሰበረች። ቫሌንሺያ ግማሽ ማራቶን ትሪኒዳድ አልፎንሶ ኢዲፒ የተሰኘ ስያሜ በተሰጠው የዘንድሮው ውድድር ላይ የተሳተፈችው ለተሰንበት 1 ሰዓት ከ02 ደቂቃ ከ52 በመግባት ነው ክብረ ወሰን የሰበረችው። ባለፈው ዓመት የ5 ሺህ ክብረ ወሰንን በሰበረችበት መድረክ ላይ ነው ለተሰንበት ዛሬ በኬንያዊቷ አትሌት የተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን ለማሻሻል የቻለችው። ኬንያዊቷ ሩት ቼፕንጌቲክ በያዝነው ዓመት ነበር የግማሽ ማራቶን ክብረ ወሰንን 1 ሰዓት ከ04 ደቂቃ ከ02 ሰኮንድ መግባት የያዘችው። የቶኪዮ ኦሊምፒክስ የነሐስ ባለቤቷ ለተሰንበት በዛሬው ውድድር ላይ የመጀመሪያውን 5 ኪሎ ሜትር በ15 ደቂቃ ነበር የሮጠችው። ለተሰንበት የውድድሩን 10 ኪሎ ሜትር በ29 ደቂቃ ስታጠናቅቅ ይህም በግማሽ ማራቶን ታሪክ ሦስተኛው ፈጣን ሰዓት ሆኖ ተመዝግቧል። ለተሰንበት በአስደናቂ ፍጥነት ቀጣዩን 5 ኪሎ ሜትር በመሮጥ 15 ኪሎ ሜትር በ44 ደቂቃ 29 ሰኮንድ ማጠናቀቅ ችላለች። ነገር ግን በመጨረሻው ሲሶ ፍጥነቷ በተነፃፃሪ ቢቀንስም በመጀመሪያዎቹ ኪሎ ሜትሮች ያስመዘገበችው ፈጣን ሰዓት ክብረ ወሰኑን እንድትሰብር አስችሏታል። በስተመጨረሻም 1 ሰዓት ከ02 ደቂቃ በ52 ሰኮንድ በመግባት በስሟ ሦስተኛውን ክብረ ወሰን ማስመዝገብ ችላለች። ለተሰንበት ግደይ በአሁኑ ወቅት የ10 ሺህ ሜትር፣ የ5 ሺህ ሜትርና ዛሬ ባስመዘገበችው ውጤት መሠረት ደግሞ የግማሽ ማራቶን ክብረ ወሰን ባለቤት ናት። በውድድሩ ላይ ተሳታፊ የነበረችው ሌላኛዋ ኢትዮጰያዊት የዓለምዘርፍ የኋላው ለተሰንበትን ተከትላ በ1 ሰዓት ከ03 ደቂቃ ከ52 ሰኮንድ ሁለተኛ ሆና አጠናቃለች። | ለተሰንበት ግደይ የዓለም ግማሽ ማራቶን ክብረ ወሰንን ሰበረች ኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ግደይ ስፔን ቫሌንሺያ ዛሬ በተካሄደው ግማሽ ማራቶን ሩጫ የዓለም ክብረ ወሰንን ሰበረች። ቫሌንሺያ ግማሽ ማራቶን ትሪኒዳድ አልፎንሶ ኢዲፒ የተሰኘ ስያሜ በተሰጠው የዘንድሮው ውድድር ላይ የተሳተፈችው ለተሰንበት 1 ሰዓት ከ02 ደቂቃ ከ52 በመግባት ነው ክብረ ወሰን የሰበረችው። ባለፈው ዓመት የ5 ሺህ ክብረ ወሰንን በሰበረችበት መድረክ ላይ ነው ለተሰንበት ዛሬ በኬንያዊቷ አትሌት የተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን ለማሻሻል የቻለችው። ኬንያዊቷ ሩት ቼፕንጌቲክ በያዝነው ዓመት ነበር የግማሽ ማራቶን ክብረ ወሰንን 1 ሰዓት ከ04 ደቂቃ ከ02 ሰኮንድ መግባት የያዘችው። የቶኪዮ ኦሊምፒክስ የነሐስ ባለቤቷ ለተሰንበት በዛሬው ውድድር ላይ የመጀመሪያውን 5 ኪሎ ሜትር በ15 ደቂቃ ነበር የሮጠችው። ለተሰንበት የውድድሩን 10 ኪሎ ሜትር በ29 ደቂቃ ስታጠናቅቅ ይህም በግማሽ ማራቶን ታሪክ ሦስተኛው ፈጣን ሰዓት ሆኖ ተመዝግቧል። ለተሰንበት በአስደናቂ ፍጥነት ቀጣዩን 5 ኪሎ ሜትር በመሮጥ 15 ኪሎ ሜትር በ44 ደቂቃ 29 ሰኮንድ ማጠናቀቅ ችላለች። ነገር ግን በመጨረሻው ሲሶ ፍጥነቷ በተነፃፃሪ ቢቀንስም በመጀመሪያዎቹ ኪሎ ሜትሮች ያስመዘገበችው ፈጣን ሰዓት ክብረ ወሰኑን እንድትሰብር አስችሏታል። በስተመጨረሻም 1 ሰዓት ከ02 ደቂቃ በ52 ሰኮንድ በመግባት በስሟ ሦስተኛውን ክብረ ወሰን ማስመዝገብ ችላለች። ለተሰንበት ግደይ በአሁኑ ወቅት የ10 ሺህ ሜትር፣ የ5 ሺህ ሜትርና ዛሬ ባስመዘገበችው ውጤት መሠረት ደግሞ የግማሽ ማራቶን ክብረ ወሰን ባለቤት ናት። በውድድሩ ላይ ተሳታፊ የነበረችው ሌላኛዋ ኢትዮጰያዊት የዓለምዘርፍ የኋላው ለተሰንበትን ተከትላ በ1 ሰዓት ከ03 ደቂቃ ከ52 ሰኮንድ ሁለተኛ ሆና አጠናቃለች። | https://www.bbc.com/amharic/news-59027278 |
0business
| ቲክቶክ ስደተኞች ለምነው ከሚያገኙት ገንዘብ ከፍተኛ ኮሚሽን እየሰበሰበ መሆኑ ተጋለጠ | በሶሪያ መጠለያዎች ውስጥ ያሉ ስደተኞች በቲክቶክ ላይ ድጋፍ እየለመኑ ከሚያገኙት ገቢ ኩባንያው እስከ 70 በመቶውን እንደሚወስድ የቢቢሲ ምርመራ አረጋገጠ። ልጆች ወደ ገንዘብ የሚቀየሩ ዲጂታል ስጦታዎችን ለማግኘት በማህበራዊ ሚዲያው ላይ ለሰዓታት በቀጥታ ስርጭት ሲማጸኑ ይቆያሉ። ስደተኞቹ ከቀጥታ ስርጭቶቹ በሰዓት እስከ 1,000 ዶላር እንደሚያገኙ ቢቢሲ ተመልክቷል። ስደተኞቹ ኪስ የሚገባው ግን በጣም ጥቂት ነው። ቲክቶክ "በልመና" ላይ አፋጣኝ እርምጃ እንደሚወስድ ተናግሯል። ኩባንያው በልመና ገንዘብ መሰብሰብን እንደማይፈቅድ ገልጾ ከዲጂታል ስጦታዎች የሚቀበሉ ደርሻ ከ70 በመቶ ያነሰ ነው ቢልም ትክክለኛውን መጠን ከመግለጽ ግን ተቆጥቧል። በፈረንጆቹ 2022 መጀመሪያ ላይ የቲክቶክ ተጠቃሚ ገጾች ከሶሪያ ካምፖች በሚገኙ የስደተኖች የቀጥታ ስርጭቶች ተሞልተው ነበር። በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ በሚገኙ መጠለያዎች ውስጥ ይህን ሁኔታ የሚያመቻቹ ‘የቲክቶክ ደላሎች’ መኖራቸውን ቢቢሲ አረጋግጧል። ለስደተኞቹ የቀጥታ ስርጭት የሚያገለግሉ ተንቀሳቃሽ ስልክ እና ቁሳቁስ እነዚህ ደላሎች ያቀርባሉ። ደላላዎቹ በበኩላቸው በቻይና እና በመካከለኛው ምስራቅ ከሚገኙና ከቲክቶክ ጋር ግንኙነት ካላቸው ድርጅቶች ጋር በመሥራት ስደተኞቹ የቲክቶክ አካውንት እንዲያገኙ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። እነዚህ ድርጅቶች የቀጥታ ስርጭቶችን ለማስፋት እና ተጠቃሚዎች በመተግበሪያው ላይ ተጨማሪ ጊዜ እንዲያሳልፉ ለማበረታታት ቲክቶክ በዓለም አቀፍ ደረጃ የጀመረው ስትራቴጂ አካል ናቸው። ቲክቶክ የሚሰራበት ሁኔታ (አልጎሪዝም) ይዘትን ይበልጥ የሚያስተዋውቀው የተጠቃሚውን የስልክ ቁጥር ጂኦግራፊያዊ አቀመጣጥ መሠረት በማድረግ ነው። በዚህም ደላላዎቹ የእንግሊዝ ሲም ካርዶችን መጠቀም እንደሚመርጡ ተናግረዋል። የዩናይትድ ኪንግደም ሰዎች በጣም ለጋሾች ናቸው ይላሉ። ሞና አሊ አል-ካሪም እና ስድስት ሴት ልጆቿ በየቀኑ በቲክቶክ የቀጥታ ስርጭት የሚያስተላልፉ ቤተሰቦች ናቸው። በድንኳናቸው ለሰዓታት ተቀምጠው የሚያውቁትን ጥቂት የእንግሊዘኛ ሐረጎች ይደጋግማሉ። "እባክዎ የመውደድ ምልክቱን ይጫኑ፣ ያጋሩ፣ እባክዎን ስጦታ ይስጡን" የሚሉ ቃላት ይደጋገማሉ። ሞና ባለቤቷ በአየር ድብደባ ወቅት ነው የተገደለው። የቀጥታ ስርጭቱን ተጠቅማ ማየት ለተሳናት ልጇ ሸሪፋ ቀዶ ህክምና የሚሆን ገንዘብ በማሰባሰብ ላይ ትገኛለች። የሚጠይቋቸው ስጦታዎች ምናባዊ ናቸው። ተመልካቾችን ግን እውነተኛ ገንዘብ ያስከፍላሉ። ከመተግበሪያውም በጥሬ ገንዘብ ማውጣት ይችላሉ። የቀጥታ ስርጭቱ ተመልካቾች ስጦታዎቹን ይልካሉ። ጥቂት ሳንቲሞችን ከሚያስወጡ ዲጂታል ጽጌረዳዎች እስከ 500 ዶላር ገደማ የሚያወጡ ምናባዊ አንበሶችን በስጦታ መልክ ይሰጣሉ። ለአምስት ወራት ያህል ቢቢሲ ከሶሪያ የስደተኞች ካምፖች በቀጥታ የሚተላለፉ 30 የቲክቶክ አካውንቶችን ተከታትሏል። ለዚሁ የሚሆን የኮምፒዩተር ስለተ ቀመር አዘጋጅቶ ባገኘው መረጃ እያንዳንዱ አካውንት በሰዓት እስከ 1,000 ዶላር የሚያወጡ ዲጂታል ስጦታዎችን እንዳገኘ ያሳያል። በካምፑ ውስጥ ያሉ ቤተሰቦች ግን በጣም ትንሽ ብቻ እያገኙ እንደሆነ ተናግረዋል ። ቲክቶክ ከስጦታዎች ምን ያህል እንደሚያገኝ አልገለጸም። ቢቢሲ ገንዘቡ የት እንደሚገባ ለማወቅ ሙከራ አድርጓል። በሶሪያ የሚገኝ አንድ ጋዜጠኛ በመጠለያ ጣብያ ውስጥ የሚኖር ስደተኛ መስሎ ከቲክቶክ ጋር ግንኙነት ወዳለው አንድ ኤጀንሲ ይቀርባል። አካውንት ይሰጠውና ቀጥታ ስርጭት ይጀምራል። በለንደን የሚገኙ የቢቢሲ ሠራተኞች በሌላ አካውንት 106 ዶላር የሚያወጣ የቲክ ቶክ ስጦታዎችን ላኩለት። የቀጥታ ስርጭቱ መጨረሻ ላይ በሶሪያው አካውንት ላይ ያለው ቀሪ ሒሳብ 33 ዶላር ነበር። ቲክቶክ ከስጦታዎቹ ዋጋ 69 በመቶውን ወስዷል። የቲክቶክ ተፅዕኖ ፈጣሪው እና የቀድሞው የራግቢ ተጫዋች ኪት ሜሰን በአንድ ቤተሰብ የቀጥታ ስርጭት ወቅት 330 ዶላር ለገሰ። አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ተከታዮቹም በተመሳሳይ አንዲለግሱ አበረታቷቸዋል። አብዛኛው ገንዘብ በማህበራዊ ድር አምባው ኩባንያ እንደሚወሰድ ከቢቢሲ ሲነገረው በሶሪያ ውስጥ ላሉ ቤተሰቦች ላይ የሚደረግ "አስገራሚ" እና "ፍትሃዊ ያልሆነ" ነገር ነው ብሏል። "ግልጽነት ሊኖር ይገባል። ለእኔ ይህ በጣም ስግብግብነት ነው። ስግብግብነት” ብሏል። ከቢቢሲ 106 ዶላር ስጦታ የቀረው 33 ዶላሩ ነው ብለናል። ይህን ገንዘብ ሲቀበሉ የሃገር ውስጥ የገንዘብ አስተላላፊዎች ደግሞ 10 በመቶ ይቀንሳሉ። የቲክ ቶክ ደላላዎቹ ደግሞ 35 በመቶውን ይወስዳሉ። ከዚህ ሁሉ በኋላ የስደተኛ ቤተሰቦቹ 19 ዶላር ብቻ ያገኛሉ። በካምፑ ውስጥ ከሚገኙ የቲክ ቶክ ደላላዎች አንዱ የሆነው ሃሚድ ከብቶቹን ሸጧል። በገንዘቡ ተንቀሳቃሽ ስልክ፣ ሲም ካርድ እና ዋይ ፋይ ገዝቷል። ይህንንም የቀጥታ ስርጭት ከሚያሰራጩ ቤተሰቦች ጋር ይሠራበታል። አሁን በቀን ለበርካታ ሰዓታት ከ12 የተለያዩ ቤተሰቦች ጋር ይሠራል። ሃሚድ እነዚህ ቤተሰቦች ለመተዳደሪያ የሚሆን ገቢ እንዲያገኙ ለመርዳት ቲክቶክን እንደሚጠቀም ይሞግታል። የራሱን ኮሚሽን ቀንሶ አብዛኛውን ገቢ እንደሚከፍላቸውም ገልጿል። ቻይና ውስጥ በቀጥታ ከቲክቶክ ጋር የሚሠሩ “ኤጀንሲዎች” ይደግፉናል ሲል ሃሚድም ሌሎችን ደላላዎች ሃሳብ ይጋራል። "በመተግበሪያው ላይ ችግር ካጋጠመን ይረዱናል። የታገዱ አካውንቶችን ያስከፍታሉ። የአካውንቱን ስም እና ምስል ስንሰጣቸው አካውንቱን ይከፍታሉ" ሲል ሃሚድ ያስረዳል። “የቀጥታ ስርጭት አጋዥ ” በመባል የሚታወቁት እነዚህ ኤጀንሲዎች በመላው ዓለም ይገኛሉ። ተጠቃሚዎች ይበልጥ ማራኪ የቀጥታ ስርጭቶችን እንዲያዘጋጁ ለመርዳት ከቲክቶክ ጋር የተስማሙ ናቸው። ቲክ ቶክ በቀጥታ ስርጭት የቆይታ ጊዜ እና በተቀበሉት ስጦታዎች ዋጋ መሠረት ኮሚሽን ይከፍላቸዋል ሲሉ ኤጀንሲዎቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የቆይታ ጊዜውን ለማሳደግ በሶሪያ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ያሉ ህጻናትን ጨምሮ ሌሎችም ቲክቶክ ላይ ለሰዓታት ይጣዳሉ። የዲጂታል መብቶች ድርጅት አክሰስ ናው ባለደረባ የሆኑት ማርዋ ፋፍታታ እነዚህ የቀጥታ ስርጭቶች ከቲኪ ቶክ ፖሊሲዎች ጋር የሚቃረኑ ናቸው ብለዋል። በተለይም ለአካለ መጠን ያልደረሱ ህጻናትን “ከጉዳት፣ አደጋ ወይም ብዝበዛ መከላከል” ከሚለው ፖሊሲ ጋር ይቃረናል ይላሉ። "ቲክቶክ ተጠቃሚዎቹ በግልጽ ስጦታዎችን እንዲጠይቁ እንደማይፈቀድላቸው ይናገራል። ስለዚህ ይህ የራሱን የአገልግሎት ውሎች እና የሰዎችን መብት መጣስ ነው" ይላሉ። ሰዎች "ድጋፍ እና ርህራሄን ለማግኘት" ታሪኮቻቸውን የማካፈል መብት እንዳላቸው ይገልጻሉ። እነዚህ የቀጥታ ስርጭቶች ግን "ክብር የሌላቸው እና የሚያዋርዱ ናቸው" ይላሉ። የቲክቶክ የቀጥታ ስርጭት ከመጀመር በፊት 1,000 ተከታዮች ሊኖሩዎት ይገባል ይላል። ስጦታዎችን በቀጥታ መጠየቅም አይፈቀድም። ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆችን “ከጉዳት፣ አደጋ ወይም ብዝበዛ መከላከል” አለብዎትም ይላል። ቢቢሲ መተግበሪያውን ተጠቅሞ ህፃናት የሚለምኑባቸውን 30 አካውንቶች ሪፖርት ቢያደርግም ቲክቶክ ፖሊሲው እንዳልተጣሰ ተናግሯል። ቢቢሲ አስተያየት ለማግኘት በቀጥታ ቲክቶክን ካነጋገረ በኋላ ኩባንያው ሁሉንም አካውንቶች አግዷል። በመግለጫውም “ቢቢሲ ያቀረበልን መረጃ እና ውንጀላ በጣም አሳስቦናል። ፈጣን እና ጥብቅ እርምጃም ወስደናል” ብሏል። "ይህ ዓይነት ይዘት በእኛ መድረክ ላይ ፈጽሞ አይፈቀድም። በበዝባዥ ልመና ዙሪያ ዓለም አቀፋዊ ፖሊሲያችንን የበለጠ እያጠናከርን ነው።" ቲክቶክ ፈጣን ዕድገት እያስመዘገበ የሚገኝ ማህበራዊ ድር አምባ ነው። ሴንሰር ታወር እንደተባለ አጥኚ ኩባንያ ከሆነ እአአ በ2017 ከተመሠረተ በኋላ 6.2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አግኝቷል። በቲክቶክ ቀጥታ ስርጭት ገንዘብ ማግኘትን እንደ አማራጭ ከመውሰድ በሶሪያ ውስጥ የሚሠሩ በጎ አድራጊ ድርጅቶች በመጠለያዎች ውስጥ ያሉ ቤተሰቦችን እንዲደግፉ ቢቢሲ ጠይቋቸዋል። ታካፉል አልሻም የተባለ የበጎ አድራጎት ድርጅት ልጆቹ ትምህርት እንዲያገኙ የትምህርት ወጪያቸውን በመሸፈን ለሚቀጥሉት ሦስት ወራት መሠረታዊ ቁሳቁሶችን እንደሚያቀርብ ተናግሯል። በካምፑ ውስጥ ላሉ ብዙ ቤተሰቦች ግን በቀጥታ ስርጭት ከመለመን ውጪ ገንዘብ የማግኛ ጥቂት አማራጮች ነው ያላቸው። በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦች በየቀኑ በቀጥታ ስርጭት መቅርባቸውን ቀጥለዋል። ከተለገሰው ገንዘብ አብዛኛውም ቲክቶክ መግባቱን ቀጥሏል። | ቲክቶክ ስደተኞች ለምነው ከሚያገኙት ገንዘብ ከፍተኛ ኮሚሽን እየሰበሰበ መሆኑ ተጋለጠ በሶሪያ መጠለያዎች ውስጥ ያሉ ስደተኞች በቲክቶክ ላይ ድጋፍ እየለመኑ ከሚያገኙት ገቢ ኩባንያው እስከ 70 በመቶውን እንደሚወስድ የቢቢሲ ምርመራ አረጋገጠ። ልጆች ወደ ገንዘብ የሚቀየሩ ዲጂታል ስጦታዎችን ለማግኘት በማህበራዊ ሚዲያው ላይ ለሰዓታት በቀጥታ ስርጭት ሲማጸኑ ይቆያሉ። ስደተኞቹ ከቀጥታ ስርጭቶቹ በሰዓት እስከ 1,000 ዶላር እንደሚያገኙ ቢቢሲ ተመልክቷል። ስደተኞቹ ኪስ የሚገባው ግን በጣም ጥቂት ነው። ቲክቶክ "በልመና" ላይ አፋጣኝ እርምጃ እንደሚወስድ ተናግሯል። ኩባንያው በልመና ገንዘብ መሰብሰብን እንደማይፈቅድ ገልጾ ከዲጂታል ስጦታዎች የሚቀበሉ ደርሻ ከ70 በመቶ ያነሰ ነው ቢልም ትክክለኛውን መጠን ከመግለጽ ግን ተቆጥቧል። በፈረንጆቹ 2022 መጀመሪያ ላይ የቲክቶክ ተጠቃሚ ገጾች ከሶሪያ ካምፖች በሚገኙ የስደተኖች የቀጥታ ስርጭቶች ተሞልተው ነበር። በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ በሚገኙ መጠለያዎች ውስጥ ይህን ሁኔታ የሚያመቻቹ ‘የቲክቶክ ደላሎች’ መኖራቸውን ቢቢሲ አረጋግጧል። ለስደተኞቹ የቀጥታ ስርጭት የሚያገለግሉ ተንቀሳቃሽ ስልክ እና ቁሳቁስ እነዚህ ደላሎች ያቀርባሉ። ደላላዎቹ በበኩላቸው በቻይና እና በመካከለኛው ምስራቅ ከሚገኙና ከቲክቶክ ጋር ግንኙነት ካላቸው ድርጅቶች ጋር በመሥራት ስደተኞቹ የቲክቶክ አካውንት እንዲያገኙ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። እነዚህ ድርጅቶች የቀጥታ ስርጭቶችን ለማስፋት እና ተጠቃሚዎች በመተግበሪያው ላይ ተጨማሪ ጊዜ እንዲያሳልፉ ለማበረታታት ቲክቶክ በዓለም አቀፍ ደረጃ የጀመረው ስትራቴጂ አካል ናቸው። ቲክቶክ የሚሰራበት ሁኔታ (አልጎሪዝም) ይዘትን ይበልጥ የሚያስተዋውቀው የተጠቃሚውን የስልክ ቁጥር ጂኦግራፊያዊ አቀመጣጥ መሠረት በማድረግ ነው። በዚህም ደላላዎቹ የእንግሊዝ ሲም ካርዶችን መጠቀም እንደሚመርጡ ተናግረዋል። የዩናይትድ ኪንግደም ሰዎች በጣም ለጋሾች ናቸው ይላሉ። ሞና አሊ አል-ካሪም እና ስድስት ሴት ልጆቿ በየቀኑ በቲክቶክ የቀጥታ ስርጭት የሚያስተላልፉ ቤተሰቦች ናቸው። በድንኳናቸው ለሰዓታት ተቀምጠው የሚያውቁትን ጥቂት የእንግሊዘኛ ሐረጎች ይደጋግማሉ። "እባክዎ የመውደድ ምልክቱን ይጫኑ፣ ያጋሩ፣ እባክዎን ስጦታ ይስጡን" የሚሉ ቃላት ይደጋገማሉ። ሞና ባለቤቷ በአየር ድብደባ ወቅት ነው የተገደለው። የቀጥታ ስርጭቱን ተጠቅማ ማየት ለተሳናት ልጇ ሸሪፋ ቀዶ ህክምና የሚሆን ገንዘብ በማሰባሰብ ላይ ትገኛለች። የሚጠይቋቸው ስጦታዎች ምናባዊ ናቸው። ተመልካቾችን ግን እውነተኛ ገንዘብ ያስከፍላሉ። ከመተግበሪያውም በጥሬ ገንዘብ ማውጣት ይችላሉ። የቀጥታ ስርጭቱ ተመልካቾች ስጦታዎቹን ይልካሉ። ጥቂት ሳንቲሞችን ከሚያስወጡ ዲጂታል ጽጌረዳዎች እስከ 500 ዶላር ገደማ የሚያወጡ ምናባዊ አንበሶችን በስጦታ መልክ ይሰጣሉ። ለአምስት ወራት ያህል ቢቢሲ ከሶሪያ የስደተኞች ካምፖች በቀጥታ የሚተላለፉ 30 የቲክቶክ አካውንቶችን ተከታትሏል። ለዚሁ የሚሆን የኮምፒዩተር ስለተ ቀመር አዘጋጅቶ ባገኘው መረጃ እያንዳንዱ አካውንት በሰዓት እስከ 1,000 ዶላር የሚያወጡ ዲጂታል ስጦታዎችን እንዳገኘ ያሳያል። በካምፑ ውስጥ ያሉ ቤተሰቦች ግን በጣም ትንሽ ብቻ እያገኙ እንደሆነ ተናግረዋል ። ቲክቶክ ከስጦታዎች ምን ያህል እንደሚያገኝ አልገለጸም። ቢቢሲ ገንዘቡ የት እንደሚገባ ለማወቅ ሙከራ አድርጓል። በሶሪያ የሚገኝ አንድ ጋዜጠኛ በመጠለያ ጣብያ ውስጥ የሚኖር ስደተኛ መስሎ ከቲክቶክ ጋር ግንኙነት ወዳለው አንድ ኤጀንሲ ይቀርባል። አካውንት ይሰጠውና ቀጥታ ስርጭት ይጀምራል። በለንደን የሚገኙ የቢቢሲ ሠራተኞች በሌላ አካውንት 106 ዶላር የሚያወጣ የቲክ ቶክ ስጦታዎችን ላኩለት። የቀጥታ ስርጭቱ መጨረሻ ላይ በሶሪያው አካውንት ላይ ያለው ቀሪ ሒሳብ 33 ዶላር ነበር። ቲክቶክ ከስጦታዎቹ ዋጋ 69 በመቶውን ወስዷል። የቲክቶክ ተፅዕኖ ፈጣሪው እና የቀድሞው የራግቢ ተጫዋች ኪት ሜሰን በአንድ ቤተሰብ የቀጥታ ስርጭት ወቅት 330 ዶላር ለገሰ። አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ተከታዮቹም በተመሳሳይ አንዲለግሱ አበረታቷቸዋል። አብዛኛው ገንዘብ በማህበራዊ ድር አምባው ኩባንያ እንደሚወሰድ ከቢቢሲ ሲነገረው በሶሪያ ውስጥ ላሉ ቤተሰቦች ላይ የሚደረግ "አስገራሚ" እና "ፍትሃዊ ያልሆነ" ነገር ነው ብሏል። "ግልጽነት ሊኖር ይገባል። ለእኔ ይህ በጣም ስግብግብነት ነው። ስግብግብነት” ብሏል። ከቢቢሲ 106 ዶላር ስጦታ የቀረው 33 ዶላሩ ነው ብለናል። ይህን ገንዘብ ሲቀበሉ የሃገር ውስጥ የገንዘብ አስተላላፊዎች ደግሞ 10 በመቶ ይቀንሳሉ። የቲክ ቶክ ደላላዎቹ ደግሞ 35 በመቶውን ይወስዳሉ። ከዚህ ሁሉ በኋላ የስደተኛ ቤተሰቦቹ 19 ዶላር ብቻ ያገኛሉ። በካምፑ ውስጥ ከሚገኙ የቲክ ቶክ ደላላዎች አንዱ የሆነው ሃሚድ ከብቶቹን ሸጧል። በገንዘቡ ተንቀሳቃሽ ስልክ፣ ሲም ካርድ እና ዋይ ፋይ ገዝቷል። ይህንንም የቀጥታ ስርጭት ከሚያሰራጩ ቤተሰቦች ጋር ይሠራበታል። አሁን በቀን ለበርካታ ሰዓታት ከ12 የተለያዩ ቤተሰቦች ጋር ይሠራል። ሃሚድ እነዚህ ቤተሰቦች ለመተዳደሪያ የሚሆን ገቢ እንዲያገኙ ለመርዳት ቲክቶክን እንደሚጠቀም ይሞግታል። የራሱን ኮሚሽን ቀንሶ አብዛኛውን ገቢ እንደሚከፍላቸውም ገልጿል። ቻይና ውስጥ በቀጥታ ከቲክቶክ ጋር የሚሠሩ “ኤጀንሲዎች” ይደግፉናል ሲል ሃሚድም ሌሎችን ደላላዎች ሃሳብ ይጋራል። "በመተግበሪያው ላይ ችግር ካጋጠመን ይረዱናል። የታገዱ አካውንቶችን ያስከፍታሉ። የአካውንቱን ስም እና ምስል ስንሰጣቸው አካውንቱን ይከፍታሉ" ሲል ሃሚድ ያስረዳል። “የቀጥታ ስርጭት አጋዥ ” በመባል የሚታወቁት እነዚህ ኤጀንሲዎች በመላው ዓለም ይገኛሉ። ተጠቃሚዎች ይበልጥ ማራኪ የቀጥታ ስርጭቶችን እንዲያዘጋጁ ለመርዳት ከቲክቶክ ጋር የተስማሙ ናቸው። ቲክ ቶክ በቀጥታ ስርጭት የቆይታ ጊዜ እና በተቀበሉት ስጦታዎች ዋጋ መሠረት ኮሚሽን ይከፍላቸዋል ሲሉ ኤጀንሲዎቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የቆይታ ጊዜውን ለማሳደግ በሶሪያ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ያሉ ህጻናትን ጨምሮ ሌሎችም ቲክቶክ ላይ ለሰዓታት ይጣዳሉ። የዲጂታል መብቶች ድርጅት አክሰስ ናው ባለደረባ የሆኑት ማርዋ ፋፍታታ እነዚህ የቀጥታ ስርጭቶች ከቲኪ ቶክ ፖሊሲዎች ጋር የሚቃረኑ ናቸው ብለዋል። በተለይም ለአካለ መጠን ያልደረሱ ህጻናትን “ከጉዳት፣ አደጋ ወይም ብዝበዛ መከላከል” ከሚለው ፖሊሲ ጋር ይቃረናል ይላሉ። "ቲክቶክ ተጠቃሚዎቹ በግልጽ ስጦታዎችን እንዲጠይቁ እንደማይፈቀድላቸው ይናገራል። ስለዚህ ይህ የራሱን የአገልግሎት ውሎች እና የሰዎችን መብት መጣስ ነው" ይላሉ። ሰዎች "ድጋፍ እና ርህራሄን ለማግኘት" ታሪኮቻቸውን የማካፈል መብት እንዳላቸው ይገልጻሉ። እነዚህ የቀጥታ ስርጭቶች ግን "ክብር የሌላቸው እና የሚያዋርዱ ናቸው" ይላሉ። የቲክቶክ የቀጥታ ስርጭት ከመጀመር በፊት 1,000 ተከታዮች ሊኖሩዎት ይገባል ይላል። ስጦታዎችን በቀጥታ መጠየቅም አይፈቀድም። ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆችን “ከጉዳት፣ አደጋ ወይም ብዝበዛ መከላከል” አለብዎትም ይላል። ቢቢሲ መተግበሪያውን ተጠቅሞ ህፃናት የሚለምኑባቸውን 30 አካውንቶች ሪፖርት ቢያደርግም ቲክቶክ ፖሊሲው እንዳልተጣሰ ተናግሯል። ቢቢሲ አስተያየት ለማግኘት በቀጥታ ቲክቶክን ካነጋገረ በኋላ ኩባንያው ሁሉንም አካውንቶች አግዷል። በመግለጫውም “ቢቢሲ ያቀረበልን መረጃ እና ውንጀላ በጣም አሳስቦናል። ፈጣን እና ጥብቅ እርምጃም ወስደናል” ብሏል። "ይህ ዓይነት ይዘት በእኛ መድረክ ላይ ፈጽሞ አይፈቀድም። በበዝባዥ ልመና ዙሪያ ዓለም አቀፋዊ ፖሊሲያችንን የበለጠ እያጠናከርን ነው።" ቲክቶክ ፈጣን ዕድገት እያስመዘገበ የሚገኝ ማህበራዊ ድር አምባ ነው። ሴንሰር ታወር እንደተባለ አጥኚ ኩባንያ ከሆነ እአአ በ2017 ከተመሠረተ በኋላ 6.2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አግኝቷል። በቲክቶክ ቀጥታ ስርጭት ገንዘብ ማግኘትን እንደ አማራጭ ከመውሰድ በሶሪያ ውስጥ የሚሠሩ በጎ አድራጊ ድርጅቶች በመጠለያዎች ውስጥ ያሉ ቤተሰቦችን እንዲደግፉ ቢቢሲ ጠይቋቸዋል። ታካፉል አልሻም የተባለ የበጎ አድራጎት ድርጅት ልጆቹ ትምህርት እንዲያገኙ የትምህርት ወጪያቸውን በመሸፈን ለሚቀጥሉት ሦስት ወራት መሠረታዊ ቁሳቁሶችን እንደሚያቀርብ ተናግሯል። በካምፑ ውስጥ ላሉ ብዙ ቤተሰቦች ግን በቀጥታ ስርጭት ከመለመን ውጪ ገንዘብ የማግኛ ጥቂት አማራጮች ነው ያላቸው። በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦች በየቀኑ በቀጥታ ስርጭት መቅርባቸውን ቀጥለዋል። ከተለገሰው ገንዘብ አብዛኛውም ቲክቶክ መግባቱን ቀጥሏል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c725qj2l2gko |
0business
| ኢትዮጵያ ለመጀመር ያቀደችው ‘ስቶክ ማርኬት’ ምን ይዞ ይመጣል? | ከጥቂት ሳምንታት በፊት በኢትዮጵያ የስቶክ ማርኬት ማስጀመር የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈርሟል። ‘ኢትዮጵያን ሴኪዩሪቲስ ኤክስቼንጅ’ (ESX) የተሰኘውን የአክሲዮን ገበያ በኢትዮጵያ ለማስጀመር የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት የተፈረመው በኢትዮጵያን ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ፣ በገንዘብ ሚኒስቴር እና በኤፍኤስዲ አፍሪካ መካከል ነው። አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ የፌርፋክስ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ሊቀ መንበር ናቸው። የኢትዮጵያን ምጣኔ ሀብታዊ ጉዳዮችም በቅርበት ይከታተላሉ። ለስቶክ ማርኬት ‘የድርሻ ገበያ’ የሚል አቻ የአማርኛ ትርጉም ልንሰጠው እንችላለን ይላሉ። ኩባንያዎች የኩባንያውን የባለቤትነት ድርሻ ለገበያ ያቀርባሉ። ሰዎችም ይህን ድርሻ ከገዙ በኋላ ኩባንያው ትርፋማ በሆነ መጠን ያላቸውን ድርሻ መልሰው በመሸጥ ወይም ከትርፍ ክፍፍል ትርፋማ የሚያደርግ አሠራር ነው። ስቶክ ማርኬት ለኢትዮጵያ ምን ይዞ ይመጣል? አቶ ዘመዴነህ ኢትዮጵያ የስቶክ ገበያ ለማቋቋም በዝግጅት ላይ ብትሆነም የስቶክ ገበያ ጽንሰ ሐሳብ ለአገሪቱ ገበያ አዲስ አይደለም ይላሉ። በመንግሥት እና በግሉ ዘርፍ ጥምረት የሚቋቋመው የስቶክ ገበያ በዋናነት የሚከተሉትን ጥቅሞች ለኢትዮጵያ ይዞ እንደሚመጣ ይገልጻሉ። በርካታ የአገር ውስጥ ባንክ እና ኢንሹራንሶች ሲመሠረቱ እና ከምሥረታቸውም በኋላ የአክሲዮን ድርሻዎችን ሲሸጡ መቆየታቸውን በማስታወስ፤ የስቶክ ገበያን ከዚህ የተለየ የሚያደርገው፤ ይፋዊ በሆነ መልኩ ተደራጅቶ ቁጥጥር እየተገደረገበት በግልጽ መገበያየት ማስቻሉ ነው ይላሉ። የኢትዮጵያን ሴኪዩሪቲስ ኤክስቼንጅ (ኢኤስኤክስ) እውን ሲሆን፤ ባንኮች እና ኢንሹራንሶች ሲቋቋሙም ሆነ ማስፋፋት ሲፈልጉ አክሲዮኖቻቸውን ለመሸጥ ይከተሉት የነበረውን ረዥም መንገድ እንደሚያሳጥርላቸው ያክላሉ። “እነዚህ ኩባንያዎች ሲቋቋሙ ስቶክ ኤክስቼንጅ ስላልነበረ በጣም ረዥም ሂደት በማለፍ ለእያንዳንዱ ሰው እየዞሩ ነው ሼር የሚሸጡት። ይህ ረዥም ጊዜ እና ገንዘብ ይወስዳል። አዋጭም አይደለም” ይላሉ ዘመዴነህ። የኢትዮጵያን ሴኪዩሪቲስ ኤክስቼንጅ መመሥረት አንዱ ጥቅም አዲስ ለመሚሠረቱም ሆነ ለነባር ኩባንያዎች የካፒታል ገበያን መፍጠሩ ነው ይላሉ። ካፒታል ማሰባሰብ ለሚፈልጉም ስቶክ ገበያ መልካም አማራጭ እንደሆነ አቶ ዘመዴነህ ያስረዳሉ። “ጥሩ ሐሳብ ኖሯቸው የካፒታል እጥረት ላለባቸው ሰዎች ይጠቅማል። ዛሬ ላይ ከባንክ ብድር ማግኘትም ቀላል አይለደም። ለዘመድ ወይም ለጓደኛ ሼር የመሸጥ ሂደት ቀላል አይደለም። ስቶክ ማርኬት አዲስ ለሆኑም ይሁን መስፋፋት ለሚፈልጉ ኩባንያዎች የካፒታል ገበያን ይፈጥራል።” የስቶክ ገበያ፣ ፍትሐዊ እና ተመጣጣኝ በሆነ ሁኔታ ሀብት ማከፋፈል የሚችል ሥርዓት እንደሆነ አቶ ዘመዴነህ ይገልጻሉ። በአሁኑ ጊዜ ግዙፍ መንግሥታዊ ኩባንያዎች ወደ ግሉ ዘርፍ እየተሸጋገሩ እንደሆነ በማስታወስ፣ እነዚህ ከመንግሥት ወደ ግሉ የሚዘዋወሩት ግዙፍ ኩባንያዎችን ሲገዙ የቆዩት ጥቂት ግለሰቦች እና ኮርፖሬሽኖች መሆኑን ይጠቅሳሉ። ኢኤስኤክስ ሲመጣ ግን መንግሥት የሕዝብን ሀብት ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ማከፋፈል ይችላል። “ስቶክ ማርኬት ላይ አንድ ሼር በአምስትም፣ በአሥርም ዶላር ሲሸጥ ሁሉም የየአቅሙን በመግዛት ኢትዮጵያ ያካበተችውን ሀብት ማከፋፈል ይቻላል” ሲሉ ያብራራሉ። እነዚህ ወደ ግሉ ዘርፍ የሚዘዋወሩ ኩባንያዎች ወደ ስቶክ ገበያው ሲገቡ፣ ሁሉም የአቅሙን ያህል ባለቤት እንደሚሆንና ይህም የሀብት ክፍፍልን እንደሚያመጣ ያክላሉ። የኢትዮጵያን ሴኪዩሪቲስ ኤክስቼንጅ እውን ሲሆን የቁጠባ ባህልን ከፍ እንደሚያደርግ አቶ ዘመዴነህ ይናገራሉ። ሰዎች በአሁኑ ጊዜ ኪሳራ አያስከትልም ብለው በሚያስቡት ዘርፍ ላይ ብቻ መዋዕለ ንዋያቸውን እያፈሰሱ ይገኛሉ። “ገንዘብ ያላቸው ሰዎች የቤት ልማት ላይ ብቻ ትኩረት ሲያደርጉ ይታያል። የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ደግሞ ተጎድቷል። ይህም ኢንቨስት የሚደረግባቸው ዘርፎችን ውስን በማድረግ የቁጠባ አለመመጣጠን ይፈጥራል። ስቶክ ማርኬቱ ግን ውጤታማ በሆነ መንገድ ካፒታል በሁሉም ዘርፎች ላይ ማሰራጨት ያስችላል” በማለት ያስረዳሉ። ሌላኛው መልካም አጋጣሚ የድርሻ ገበያዎችን በቀላሉ፣ ግልጸኝነት በሰፈነበት መልኩ መግዛት እና መሸጥ ማስቻሉ ነው። ምን ያህል ሼር በምን ያህል ዋጋ ለገበያ እንደቀረበ ግልጽ ነው። “ሰዎች ስልካቸው ላይ በሚጭኑት መተግበሪያ በቀላሉ የገበያ ድርሻዎችን መግዛት እና የገዙትንም መሸጥ ይችላሉ” ይላሉ አቶ ዘመዴነህ። የባንክ ባለ አክሲዮኖች ዓመት ጠብቀው ትርፍ ከመከፋፈል ውጪ በቀላሉ ያላቸውን አክሲዮን መሸጥ አይቻላቸውም። ኢኤስኤክስ እውን ሲሆን ግን በቀላሉ አክሲዮን የመሸጥ ዕድል ይዘረጋል። ከበርካታ አሥርት ዓመታት በፊት የተቋቋመው የኬንያው ‘ናይሮቢ ሴኪዩሪቲስ ኤክስቼንጅ’ ወደ 60 ገደማ የአገር ውስጥ እና የውጭ ኩባንያዎችን ይዟል። አቶ ዘመዴነህ የኢትዮጵያው ሴኪዩሪቲስ ኤክስቼንጅ በሁለት ዓመታት ውስጥ ከ50 ያላነሱ ኩባንያዎችን በውስጡ ይይዛል የሚል ተስፋ አላቸው። እሳቸው እንደሚሉት፣ የስቶክ ገበያውን ሊቀላቀሉ የሚችሉ ኩባንያዎችን ስናስብ በብሔራዊ ባንክ ጠንካራ ቁጥጥር የሚደርግባቸውን 18 ባንኮች እና ከ18 የማያንሱ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች መዘንጋት የለብንም ይላሉ። “ሁሉም የስቶክ ገበያውን ላይቀላቀሉ ይችላሉ። . . . ቁጥሩን 30 ብለን እንያዘው። 20ው ከየት ይመጣል? ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ባለቤትነታቸው በቤተሰብ ደረጃ የሆነ ግዙፍ ኩባንያዎች ስቶክ ማርኬት ላይ ለመግባት ዝግጁ የሆኑ ይኖራሉ። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ዓለም አቀፍ የሆኑ የውጭ ኩባንያዎች አሉ። ኮካ ኮላ፣ ሃይኒከን፣ ዩኒሊቨር እና ቶታልን ማንሳት ይቻላል። የእኔ ግምት ከ40 አስከ 70 ነው” በማለት ሐሳባቸውን ያጠናክራሉ። ይህ ማለት ግን ሁሉም ኩባንያዎች በአንድ ቀን ይገባሉ ማለት አይደለም። ቁጥራቸው በጊዜ ሂደት የሚጨምር ይሆናል። ይህንን ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት ስቶክ ገበያ ምንድን ነው? እንዴትስ መሸጥ እና መለወጥ ይቻላል? የሚለውን እንመልከት። ስቶክ ገበያን በቀላል ቋንቋ ለመረዳት የምጣሄ ሀብት ባለሙያዎች አዘወትረው የሚጠቀሙትን ቀላል ምሳሌ እንውሰድ። 'ሀ'፣ 'ለ' እና 'ሐ' የሚባሉ ሦስት ምናባዊ የሞባይል ስልክ አምራች ኩባንያዎችን አሉ አንበል። እርስዎ 6 ዶላር አውጥተው ከእያንዳንዱ ኩባንያ የሁለት ዶላር የገበያ ድርሻ ይገዛሉ። 'ሀ' ለገበያ ያቀረበው ሞባይል ስልክ ባትሪው እየፈነዳ ሰዎችን ለጉዳት እየዳረገ መሆኑን የሚያመለክት ሪፖርት መውጣት ይጀምራል። የ'ለ' ኩባንያ የሆነው ምርት ደግሞ ባትሪው በፍጥነት እያለቀ ከተጠቃሚዎች ቅሬታ ይደርሰዋል። የ'ሐ' ምርት የሆነው ሞባይል ስልክ ግን በአግባቡ ይሠራል። ይህ በገበያ ላይ ያጋጠመው ክስተት በሦስቱ ኩባንያዎች ስቶክ ገበያ ዋጋ ላይ ለውጥ ያመጣል። የአንድ ኩባንያ ምርት ጥራት ሲወርድ የዚያ ኩባንያ ፈላጊዎች ይቀንሳሉ። በተቀራኒው አንድ ኩባንያ ትርፍማ የሚያደርገውን ውሳኔ ወስኖ ትርፍ ሲያጋብስ፣ የትርፉ ተቋዳሽ መሆን የሚሹ ሰዎች ቁጥር ከፍ ይላል። በዚህ መሠረት ባትሪው እየፈነዳ ሰዎችን ለአደጋ እያጋለጠ ያለው የሞባይል ኩባንያ ድርሻ በከፍተኛ መጠን ሊወርድ ይችላል። በሁለት ዶላር የገዙትን ድርሻ መልሰው መሸጥ ቢፈልጉ ከግማሸ ባነሰ ዋጋ እንኳን የሚገዛዎትን ላያገኙ ይችላሉ። ይህ ሞባይል አምራች ኩባንያ ሲከስር እርስዎም የኩባንያው ባለድርሻ እንደመሆንዎ ኪሳራ ያጋጥምዎታል። ስለዚህ በኩባንያ 'ሀ' ላይ ያደረጉት ኢንቨስትመንት ኪሳራን ያስከትላል። የ 'ሐ' ምርት የሆነው ስልክ ግን በገበያ ተፈላጊነቱ ሲጨምር የኩባንያው ዋጋም ከፍ ይላል። ምናልባት በሁለት ዶላር የገዙትን የኩባንያውን ድርሻ፣ አሁን ላይ በ4 ዶላር ሸጠው ትርፍ ሊያገኙ ይችላሉ። | ኢትዮጵያ ለመጀመር ያቀደችው ‘ስቶክ ማርኬት’ ምን ይዞ ይመጣል? ከጥቂት ሳምንታት በፊት በኢትዮጵያ የስቶክ ማርኬት ማስጀመር የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈርሟል። ‘ኢትዮጵያን ሴኪዩሪቲስ ኤክስቼንጅ’ (ESX) የተሰኘውን የአክሲዮን ገበያ በኢትዮጵያ ለማስጀመር የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት የተፈረመው በኢትዮጵያን ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ፣ በገንዘብ ሚኒስቴር እና በኤፍኤስዲ አፍሪካ መካከል ነው። አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ የፌርፋክስ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ሊቀ መንበር ናቸው። የኢትዮጵያን ምጣኔ ሀብታዊ ጉዳዮችም በቅርበት ይከታተላሉ። ለስቶክ ማርኬት ‘የድርሻ ገበያ’ የሚል አቻ የአማርኛ ትርጉም ልንሰጠው እንችላለን ይላሉ። ኩባንያዎች የኩባንያውን የባለቤትነት ድርሻ ለገበያ ያቀርባሉ። ሰዎችም ይህን ድርሻ ከገዙ በኋላ ኩባንያው ትርፋማ በሆነ መጠን ያላቸውን ድርሻ መልሰው በመሸጥ ወይም ከትርፍ ክፍፍል ትርፋማ የሚያደርግ አሠራር ነው። ስቶክ ማርኬት ለኢትዮጵያ ምን ይዞ ይመጣል? አቶ ዘመዴነህ ኢትዮጵያ የስቶክ ገበያ ለማቋቋም በዝግጅት ላይ ብትሆነም የስቶክ ገበያ ጽንሰ ሐሳብ ለአገሪቱ ገበያ አዲስ አይደለም ይላሉ። በመንግሥት እና በግሉ ዘርፍ ጥምረት የሚቋቋመው የስቶክ ገበያ በዋናነት የሚከተሉትን ጥቅሞች ለኢትዮጵያ ይዞ እንደሚመጣ ይገልጻሉ። በርካታ የአገር ውስጥ ባንክ እና ኢንሹራንሶች ሲመሠረቱ እና ከምሥረታቸውም በኋላ የአክሲዮን ድርሻዎችን ሲሸጡ መቆየታቸውን በማስታወስ፤ የስቶክ ገበያን ከዚህ የተለየ የሚያደርገው፤ ይፋዊ በሆነ መልኩ ተደራጅቶ ቁጥጥር እየተገደረገበት በግልጽ መገበያየት ማስቻሉ ነው ይላሉ። የኢትዮጵያን ሴኪዩሪቲስ ኤክስቼንጅ (ኢኤስኤክስ) እውን ሲሆን፤ ባንኮች እና ኢንሹራንሶች ሲቋቋሙም ሆነ ማስፋፋት ሲፈልጉ አክሲዮኖቻቸውን ለመሸጥ ይከተሉት የነበረውን ረዥም መንገድ እንደሚያሳጥርላቸው ያክላሉ። “እነዚህ ኩባንያዎች ሲቋቋሙ ስቶክ ኤክስቼንጅ ስላልነበረ በጣም ረዥም ሂደት በማለፍ ለእያንዳንዱ ሰው እየዞሩ ነው ሼር የሚሸጡት። ይህ ረዥም ጊዜ እና ገንዘብ ይወስዳል። አዋጭም አይደለም” ይላሉ ዘመዴነህ። የኢትዮጵያን ሴኪዩሪቲስ ኤክስቼንጅ መመሥረት አንዱ ጥቅም አዲስ ለመሚሠረቱም ሆነ ለነባር ኩባንያዎች የካፒታል ገበያን መፍጠሩ ነው ይላሉ። ካፒታል ማሰባሰብ ለሚፈልጉም ስቶክ ገበያ መልካም አማራጭ እንደሆነ አቶ ዘመዴነህ ያስረዳሉ። “ጥሩ ሐሳብ ኖሯቸው የካፒታል እጥረት ላለባቸው ሰዎች ይጠቅማል። ዛሬ ላይ ከባንክ ብድር ማግኘትም ቀላል አይለደም። ለዘመድ ወይም ለጓደኛ ሼር የመሸጥ ሂደት ቀላል አይደለም። ስቶክ ማርኬት አዲስ ለሆኑም ይሁን መስፋፋት ለሚፈልጉ ኩባንያዎች የካፒታል ገበያን ይፈጥራል።” የስቶክ ገበያ፣ ፍትሐዊ እና ተመጣጣኝ በሆነ ሁኔታ ሀብት ማከፋፈል የሚችል ሥርዓት እንደሆነ አቶ ዘመዴነህ ይገልጻሉ። በአሁኑ ጊዜ ግዙፍ መንግሥታዊ ኩባንያዎች ወደ ግሉ ዘርፍ እየተሸጋገሩ እንደሆነ በማስታወስ፣ እነዚህ ከመንግሥት ወደ ግሉ የሚዘዋወሩት ግዙፍ ኩባንያዎችን ሲገዙ የቆዩት ጥቂት ግለሰቦች እና ኮርፖሬሽኖች መሆኑን ይጠቅሳሉ። ኢኤስኤክስ ሲመጣ ግን መንግሥት የሕዝብን ሀብት ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ማከፋፈል ይችላል። “ስቶክ ማርኬት ላይ አንድ ሼር በአምስትም፣ በአሥርም ዶላር ሲሸጥ ሁሉም የየአቅሙን በመግዛት ኢትዮጵያ ያካበተችውን ሀብት ማከፋፈል ይቻላል” ሲሉ ያብራራሉ። እነዚህ ወደ ግሉ ዘርፍ የሚዘዋወሩ ኩባንያዎች ወደ ስቶክ ገበያው ሲገቡ፣ ሁሉም የአቅሙን ያህል ባለቤት እንደሚሆንና ይህም የሀብት ክፍፍልን እንደሚያመጣ ያክላሉ። የኢትዮጵያን ሴኪዩሪቲስ ኤክስቼንጅ እውን ሲሆን የቁጠባ ባህልን ከፍ እንደሚያደርግ አቶ ዘመዴነህ ይናገራሉ። ሰዎች በአሁኑ ጊዜ ኪሳራ አያስከትልም ብለው በሚያስቡት ዘርፍ ላይ ብቻ መዋዕለ ንዋያቸውን እያፈሰሱ ይገኛሉ። “ገንዘብ ያላቸው ሰዎች የቤት ልማት ላይ ብቻ ትኩረት ሲያደርጉ ይታያል። የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ደግሞ ተጎድቷል። ይህም ኢንቨስት የሚደረግባቸው ዘርፎችን ውስን በማድረግ የቁጠባ አለመመጣጠን ይፈጥራል። ስቶክ ማርኬቱ ግን ውጤታማ በሆነ መንገድ ካፒታል በሁሉም ዘርፎች ላይ ማሰራጨት ያስችላል” በማለት ያስረዳሉ። ሌላኛው መልካም አጋጣሚ የድርሻ ገበያዎችን በቀላሉ፣ ግልጸኝነት በሰፈነበት መልኩ መግዛት እና መሸጥ ማስቻሉ ነው። ምን ያህል ሼር በምን ያህል ዋጋ ለገበያ እንደቀረበ ግልጽ ነው። “ሰዎች ስልካቸው ላይ በሚጭኑት መተግበሪያ በቀላሉ የገበያ ድርሻዎችን መግዛት እና የገዙትንም መሸጥ ይችላሉ” ይላሉ አቶ ዘመዴነህ። የባንክ ባለ አክሲዮኖች ዓመት ጠብቀው ትርፍ ከመከፋፈል ውጪ በቀላሉ ያላቸውን አክሲዮን መሸጥ አይቻላቸውም። ኢኤስኤክስ እውን ሲሆን ግን በቀላሉ አክሲዮን የመሸጥ ዕድል ይዘረጋል። ከበርካታ አሥርት ዓመታት በፊት የተቋቋመው የኬንያው ‘ናይሮቢ ሴኪዩሪቲስ ኤክስቼንጅ’ ወደ 60 ገደማ የአገር ውስጥ እና የውጭ ኩባንያዎችን ይዟል። አቶ ዘመዴነህ የኢትዮጵያው ሴኪዩሪቲስ ኤክስቼንጅ በሁለት ዓመታት ውስጥ ከ50 ያላነሱ ኩባንያዎችን በውስጡ ይይዛል የሚል ተስፋ አላቸው። እሳቸው እንደሚሉት፣ የስቶክ ገበያውን ሊቀላቀሉ የሚችሉ ኩባንያዎችን ስናስብ በብሔራዊ ባንክ ጠንካራ ቁጥጥር የሚደርግባቸውን 18 ባንኮች እና ከ18 የማያንሱ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች መዘንጋት የለብንም ይላሉ። “ሁሉም የስቶክ ገበያውን ላይቀላቀሉ ይችላሉ። . . . ቁጥሩን 30 ብለን እንያዘው። 20ው ከየት ይመጣል? ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ባለቤትነታቸው በቤተሰብ ደረጃ የሆነ ግዙፍ ኩባንያዎች ስቶክ ማርኬት ላይ ለመግባት ዝግጁ የሆኑ ይኖራሉ። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ዓለም አቀፍ የሆኑ የውጭ ኩባንያዎች አሉ። ኮካ ኮላ፣ ሃይኒከን፣ ዩኒሊቨር እና ቶታልን ማንሳት ይቻላል። የእኔ ግምት ከ40 አስከ 70 ነው” በማለት ሐሳባቸውን ያጠናክራሉ። ይህ ማለት ግን ሁሉም ኩባንያዎች በአንድ ቀን ይገባሉ ማለት አይደለም። ቁጥራቸው በጊዜ ሂደት የሚጨምር ይሆናል። ይህንን ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት ስቶክ ገበያ ምንድን ነው? እንዴትስ መሸጥ እና መለወጥ ይቻላል? የሚለውን እንመልከት። ስቶክ ገበያን በቀላል ቋንቋ ለመረዳት የምጣሄ ሀብት ባለሙያዎች አዘወትረው የሚጠቀሙትን ቀላል ምሳሌ እንውሰድ። 'ሀ'፣ 'ለ' እና 'ሐ' የሚባሉ ሦስት ምናባዊ የሞባይል ስልክ አምራች ኩባንያዎችን አሉ አንበል። እርስዎ 6 ዶላር አውጥተው ከእያንዳንዱ ኩባንያ የሁለት ዶላር የገበያ ድርሻ ይገዛሉ። 'ሀ' ለገበያ ያቀረበው ሞባይል ስልክ ባትሪው እየፈነዳ ሰዎችን ለጉዳት እየዳረገ መሆኑን የሚያመለክት ሪፖርት መውጣት ይጀምራል። የ'ለ' ኩባንያ የሆነው ምርት ደግሞ ባትሪው በፍጥነት እያለቀ ከተጠቃሚዎች ቅሬታ ይደርሰዋል። የ'ሐ' ምርት የሆነው ሞባይል ስልክ ግን በአግባቡ ይሠራል። ይህ በገበያ ላይ ያጋጠመው ክስተት በሦስቱ ኩባንያዎች ስቶክ ገበያ ዋጋ ላይ ለውጥ ያመጣል። የአንድ ኩባንያ ምርት ጥራት ሲወርድ የዚያ ኩባንያ ፈላጊዎች ይቀንሳሉ። በተቀራኒው አንድ ኩባንያ ትርፍማ የሚያደርገውን ውሳኔ ወስኖ ትርፍ ሲያጋብስ፣ የትርፉ ተቋዳሽ መሆን የሚሹ ሰዎች ቁጥር ከፍ ይላል። በዚህ መሠረት ባትሪው እየፈነዳ ሰዎችን ለአደጋ እያጋለጠ ያለው የሞባይል ኩባንያ ድርሻ በከፍተኛ መጠን ሊወርድ ይችላል። በሁለት ዶላር የገዙትን ድርሻ መልሰው መሸጥ ቢፈልጉ ከግማሸ ባነሰ ዋጋ እንኳን የሚገዛዎትን ላያገኙ ይችላሉ። ይህ ሞባይል አምራች ኩባንያ ሲከስር እርስዎም የኩባንያው ባለድርሻ እንደመሆንዎ ኪሳራ ያጋጥምዎታል። ስለዚህ በኩባንያ 'ሀ' ላይ ያደረጉት ኢንቨስትመንት ኪሳራን ያስከትላል። የ 'ሐ' ምርት የሆነው ስልክ ግን በገበያ ተፈላጊነቱ ሲጨምር የኩባንያው ዋጋም ከፍ ይላል። ምናልባት በሁለት ዶላር የገዙትን የኩባንያውን ድርሻ፣ አሁን ላይ በ4 ዶላር ሸጠው ትርፍ ሊያገኙ ይችላሉ። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cv2re4ddxgvo |
3politics
| ለ2ኛ ጊዜ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡት ማክሮን ሕዝቡን አንድ ለማድረግ ቃል ገቡ | ኢማኑኤል ማክሮን ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲያገለግሉ በድጋሚ ተመረጡ፡፡ ማክሮን ትናንት በተደረገ አገር አቀፍ ምርጫ ተቀናቃኛቸውን ማሪን ሌ ፔንን በሰፊ ልዩነት አሸንፈዋቸዋል፡፡ የቀኝ አክራሪዋ፣ ስደተኛ ጠል ናቸው የሚባሉት ማሪን ሌ ፔን ሊያሸንፉ የሚችሉበት ዕድል ስለነበረ የፈረንሳይ ምርጫ በተለይ በመላው አውሮጳ ከፍተኛ ትኩረት አግኝቶ ነበር፡፡ ሌ ፔን ሙስሊም ሴቶች ሒጃብ በአደባባይ እንዳይለበሱ ሕግ የማውጣት ፍላጎት ነበራቸው፡፡ ስደተኞችን የማባረር፣ ለአገሬው ሕዝብ በሁሉም ረገድ ቅድሚያ የመስጠት ፖሊሲም እንደሚከተሉ ቃል ገብተው ነበር፡፡ በተጨማሪም ፈረንሳይ ከኔቶ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት እንዲሁም ከአውሮጳ ኅብረት የምትወጣበትን ሁኔታ እንደሚያፈላልጉ ለደጋፊዎቻቸው ቃል ገብተው ነበር፡፡ ይህም በመሆኑ ነው የሳቸው አለመመረጥ በአውሮፓ ኅብረት አባል አገራት ዘንድ እፎይታን የፈጠረው፡፡ ማክሮን በድጋሚ ፕሬዝዳንትነቱን ያሸነፉት ከድምጽ ሰጪው ሕዝብ 58.55 ከመቶ በማግኘት ነው፡፡ ሌ ፔን ድምጽ ማግኘት የቻሉት ግን 41.45 የሚሆነውን ብቻ ነው፡፡ ይሁንና ለአንድ ቀኝ አክራሪ ፓርቲ መሪ ይህን ያህል ድምጽ ማገኘት እጅግ ከፍተኛ የሚባል ሲሆን አገሪቱ ምን ያህል እንደተከፋፈለች የሚያመላክት ነው ይላሉ ተንታኞች፡፡ ማክሮን ከድል በኋላ ባደረጉት ንግግር የተከፋፈለውን የፈረንሳይ ሕዝብ አንድ ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡ ኢማኑኤል ማክሮን በተለይ ለመካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች ደንታ የላቸውም፣ እሳቸው የሃብታም ፈረንሳዊያን ፕሬዝዳንት ናቸው በሚል ሲወቀሱ ቆይተዋል፡፡ ማክሮን የኑሮ ውድነትን መቆጣጠር አለመቻላቸውም ከፍተኛ ተቃውሞን አስነስቶባቸዋል፡፡ የምርጫ ውጤቱ ይፋ ከሆነ በኋላ ሌ ፔን ሽንፈታቸውን የተቀበሉ ሲሆን ያገኙት ድምጽ በራሱ ግን ለፓርቲያቸው ትልቅ ድል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በአውሮጳ ከሚንቀሳቀሱ ቀኝ አክራሪ ብሔርተኞች ሌ ፔን ከፍ ያለ ስምና ዝና ያላቸው ቢሆንም እሳቸውም እንደ ወላጅ አባታቸው በተደጋጋሚ ተወዳድረው ድል ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡፡ በተለይ በዚህኛው ዙር የሳቸው ፓርቲ ከሩሲያ ባንክ ብድር መውሰዱ፣ እሳቸውም ሩሲያ ክሪሚያን ጠቅልላ በወረራ ስትወስድ ድጋፍ ማሳየታቸውና ከቪላድሚር ፑቲን ጋር የተለየ ቅርበት ማሳየታቸው በምርጫ ክርክር ወቅት ከፍተኛ ነጥብ እንዲጥሉ ሳያደርጋቸው አልቀረም፡፡ የምርጫው ውጤት ከተሰማ በኋላ የአውሮጳ አባል አገራት ከፍተኛ እፎይታ ተሰምቷቸዋል፡፡ ምክንያቱም ሌ ፔን ምርጫውን አሸንፈው ቢሆን ሁነኛ የኔቶ አባልና የአውሮጳ ኅብረት አባል ፈረንሳይ ከኅብረቶቹ ልትወጣ የምትችልበት አጋጣሚ ይኖር ስለነበረ ነው፡፡ ሌ ፔን የፑትንን ወረራ የመደገፍ አዝማሚያ ማሳየታቸው የአውሮጳ ኅብረት አባላትን አስቆጥቶ ነበር፡፡ የማክሮንን ድል ተከትሎ የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን፣ የአውሮጳ ኅብረት ፕሬዝዳንት ቮን ደር ሌዮን እንዲሁም የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡ ዘለንስኪ ከምርጫው ቀደም ብሎም ቢሆን ፈረንሳዊያዊን በፍጹም ለማሪን ሌ ፔን ድጋፍ እንዳያሳዩ፣ ይለቅ ለማክሮን ድምጽ እንዲሰጡ ተማጽነው ነበር፡፡ ይህም የሆነው ተቀናቃኛቸው ማሪን ሌ ፔን ከፑቲን ጋር ያላቸው ቅርበት ስጋት ስለፈጠረባቸው ነበር፡፡ የመራጮች ቁጥር በታሪክ ዝቅተኛ ከሚባሉት አንዱ ሆኖ የተመዘገበ የትናንቱ ድምጽ አሰጣት፣ 3 ሚሊዮን የሚሆኑ መራጮች ባዶ ወረቀት ምርጫ ኮሮጆ ውስጥ ዶለዋል ተብሏል፡፡ ይህም የሚያመላክተው በርካታ መራጮች በሁለቱም እጩዎች ደስተኛ እንዳልነበረ ነው ይላሉ ተንታኞች፡፡ ማክሮን በ20 ዓመታት የፈረንሳይ የቅርብ ታሪክ ለ2ኛ ጊዜ የተመረጡ የመጀመርያው ፕሬዝዳንት ናቸው፡፡ | ለ2ኛ ጊዜ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡት ማክሮን ሕዝቡን አንድ ለማድረግ ቃል ገቡ ኢማኑኤል ማክሮን ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲያገለግሉ በድጋሚ ተመረጡ፡፡ ማክሮን ትናንት በተደረገ አገር አቀፍ ምርጫ ተቀናቃኛቸውን ማሪን ሌ ፔንን በሰፊ ልዩነት አሸንፈዋቸዋል፡፡ የቀኝ አክራሪዋ፣ ስደተኛ ጠል ናቸው የሚባሉት ማሪን ሌ ፔን ሊያሸንፉ የሚችሉበት ዕድል ስለነበረ የፈረንሳይ ምርጫ በተለይ በመላው አውሮጳ ከፍተኛ ትኩረት አግኝቶ ነበር፡፡ ሌ ፔን ሙስሊም ሴቶች ሒጃብ በአደባባይ እንዳይለበሱ ሕግ የማውጣት ፍላጎት ነበራቸው፡፡ ስደተኞችን የማባረር፣ ለአገሬው ሕዝብ በሁሉም ረገድ ቅድሚያ የመስጠት ፖሊሲም እንደሚከተሉ ቃል ገብተው ነበር፡፡ በተጨማሪም ፈረንሳይ ከኔቶ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት እንዲሁም ከአውሮጳ ኅብረት የምትወጣበትን ሁኔታ እንደሚያፈላልጉ ለደጋፊዎቻቸው ቃል ገብተው ነበር፡፡ ይህም በመሆኑ ነው የሳቸው አለመመረጥ በአውሮፓ ኅብረት አባል አገራት ዘንድ እፎይታን የፈጠረው፡፡ ማክሮን በድጋሚ ፕሬዝዳንትነቱን ያሸነፉት ከድምጽ ሰጪው ሕዝብ 58.55 ከመቶ በማግኘት ነው፡፡ ሌ ፔን ድምጽ ማግኘት የቻሉት ግን 41.45 የሚሆነውን ብቻ ነው፡፡ ይሁንና ለአንድ ቀኝ አክራሪ ፓርቲ መሪ ይህን ያህል ድምጽ ማገኘት እጅግ ከፍተኛ የሚባል ሲሆን አገሪቱ ምን ያህል እንደተከፋፈለች የሚያመላክት ነው ይላሉ ተንታኞች፡፡ ማክሮን ከድል በኋላ ባደረጉት ንግግር የተከፋፈለውን የፈረንሳይ ሕዝብ አንድ ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡ ኢማኑኤል ማክሮን በተለይ ለመካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች ደንታ የላቸውም፣ እሳቸው የሃብታም ፈረንሳዊያን ፕሬዝዳንት ናቸው በሚል ሲወቀሱ ቆይተዋል፡፡ ማክሮን የኑሮ ውድነትን መቆጣጠር አለመቻላቸውም ከፍተኛ ተቃውሞን አስነስቶባቸዋል፡፡ የምርጫ ውጤቱ ይፋ ከሆነ በኋላ ሌ ፔን ሽንፈታቸውን የተቀበሉ ሲሆን ያገኙት ድምጽ በራሱ ግን ለፓርቲያቸው ትልቅ ድል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በአውሮጳ ከሚንቀሳቀሱ ቀኝ አክራሪ ብሔርተኞች ሌ ፔን ከፍ ያለ ስምና ዝና ያላቸው ቢሆንም እሳቸውም እንደ ወላጅ አባታቸው በተደጋጋሚ ተወዳድረው ድል ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡፡ በተለይ በዚህኛው ዙር የሳቸው ፓርቲ ከሩሲያ ባንክ ብድር መውሰዱ፣ እሳቸውም ሩሲያ ክሪሚያን ጠቅልላ በወረራ ስትወስድ ድጋፍ ማሳየታቸውና ከቪላድሚር ፑቲን ጋር የተለየ ቅርበት ማሳየታቸው በምርጫ ክርክር ወቅት ከፍተኛ ነጥብ እንዲጥሉ ሳያደርጋቸው አልቀረም፡፡ የምርጫው ውጤት ከተሰማ በኋላ የአውሮጳ አባል አገራት ከፍተኛ እፎይታ ተሰምቷቸዋል፡፡ ምክንያቱም ሌ ፔን ምርጫውን አሸንፈው ቢሆን ሁነኛ የኔቶ አባልና የአውሮጳ ኅብረት አባል ፈረንሳይ ከኅብረቶቹ ልትወጣ የምትችልበት አጋጣሚ ይኖር ስለነበረ ነው፡፡ ሌ ፔን የፑትንን ወረራ የመደገፍ አዝማሚያ ማሳየታቸው የአውሮጳ ኅብረት አባላትን አስቆጥቶ ነበር፡፡ የማክሮንን ድል ተከትሎ የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን፣ የአውሮጳ ኅብረት ፕሬዝዳንት ቮን ደር ሌዮን እንዲሁም የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡ ዘለንስኪ ከምርጫው ቀደም ብሎም ቢሆን ፈረንሳዊያዊን በፍጹም ለማሪን ሌ ፔን ድጋፍ እንዳያሳዩ፣ ይለቅ ለማክሮን ድምጽ እንዲሰጡ ተማጽነው ነበር፡፡ ይህም የሆነው ተቀናቃኛቸው ማሪን ሌ ፔን ከፑቲን ጋር ያላቸው ቅርበት ስጋት ስለፈጠረባቸው ነበር፡፡ የመራጮች ቁጥር በታሪክ ዝቅተኛ ከሚባሉት አንዱ ሆኖ የተመዘገበ የትናንቱ ድምጽ አሰጣት፣ 3 ሚሊዮን የሚሆኑ መራጮች ባዶ ወረቀት ምርጫ ኮሮጆ ውስጥ ዶለዋል ተብሏል፡፡ ይህም የሚያመላክተው በርካታ መራጮች በሁለቱም እጩዎች ደስተኛ እንዳልነበረ ነው ይላሉ ተንታኞች፡፡ ማክሮን በ20 ዓመታት የፈረንሳይ የቅርብ ታሪክ ለ2ኛ ጊዜ የተመረጡ የመጀመርያው ፕሬዝዳንት ናቸው፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/news-61213148 |
5sports
| ታላቁ ሩጫ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት ተራዘመ | ህዳር 5/ 2014 ለ21ኛ ጊዜ ሊካሄድ የነበረው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከቀናት በፊት በታወጀው የአስቸኳያ ጊዜ አዋጅ ምክንያት መራዘሙን የውድድሩ አዘጋጅ አስታውቋል። 'ቶታልኢንርጂስ' የሚል ስያሜ የተሰጠው የ2014 ታላቁ ሩጫ መቼ እንደሚካሄድ አዘጋጁ ወደፊት እንደሚያሳውቅም በድህረ ገጹ ትናንት ማምሻውን አስታውቋል። ከ10 ቀናት በኋላ እንዲካሄድ ታቅዶ በነበረው ውድድር 25ሺ ሰዎች ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቅ ነበር። ባለፈው ዓመት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከተለመደው ጊዜ ውጪ ጥር ላይ በተከናወነው ታላቁ ሩጫ 12 ሺህ 500 ተሳትፈው ነበር። ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ላለፉት 20 ዓመታት ሲካሄድ የቆየ እና በርካታ ህዝብ የሚሳተፍበት የስፖርት ፌስቲቫል ነው። በዓለም የአትሌቲክስ ውድድር የገዘፈ ስም ባለው አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ 1994 የተመሰረተው ታላቁ ሩጫ፤ እስከ 2013 ዓ.ም ድረስ በድምሩ ወደ 600 ሺህ የሚጠጉ ተሳታፊዎችን አስተናግዷል። የመጀመሪያው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከ10 ሺህ ያነሱ ተሳታፊዎች የነበሩት ሲሆን ባለፉት ዓመታት ውድድሩ ከ40 ሺህ በላይ ተሳታፊዎችን አስተናግዶ ነበር። በአፍሪካ ትልቁ የጎዳና ላይ ሩጫ እንደሆነ የሚነገርለት ይህ ውድድር፤ ከኢትዮጵያውን ባሻገር ከተለያዩ ዓለም ክፍሎች የሚመጡ የውጪ አገራት ዜጎችም የሚሳተፉበት ሆኗል። ታላቁ ሩጫ ለጤና ከሚደረገውና አስር ሺዎች ከሚሳተፉበት ሩጫ በተጨማሪም፣ ለአሸናፊዎች የገንዘብ ሽልማት የሚያበርክትበት መደበኛ የውድድር ዘርፍም አለው። የዘንድሮ ታላቁ ሩጫ ሊካሄድ 11 ቀናት ሲቀሩት መራዘሙ የተገለጸው ባለፈው ማክሰኞ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ትናንት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጸደቀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። በስሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ተከትሎ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለሚቀጥሉት 6 ወራት ተፈጻሚ የሚሆን ነው። | ታላቁ ሩጫ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት ተራዘመ ህዳር 5/ 2014 ለ21ኛ ጊዜ ሊካሄድ የነበረው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከቀናት በፊት በታወጀው የአስቸኳያ ጊዜ አዋጅ ምክንያት መራዘሙን የውድድሩ አዘጋጅ አስታውቋል። 'ቶታልኢንርጂስ' የሚል ስያሜ የተሰጠው የ2014 ታላቁ ሩጫ መቼ እንደሚካሄድ አዘጋጁ ወደፊት እንደሚያሳውቅም በድህረ ገጹ ትናንት ማምሻውን አስታውቋል። ከ10 ቀናት በኋላ እንዲካሄድ ታቅዶ በነበረው ውድድር 25ሺ ሰዎች ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቅ ነበር። ባለፈው ዓመት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከተለመደው ጊዜ ውጪ ጥር ላይ በተከናወነው ታላቁ ሩጫ 12 ሺህ 500 ተሳትፈው ነበር። ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ላለፉት 20 ዓመታት ሲካሄድ የቆየ እና በርካታ ህዝብ የሚሳተፍበት የስፖርት ፌስቲቫል ነው። በዓለም የአትሌቲክስ ውድድር የገዘፈ ስም ባለው አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ 1994 የተመሰረተው ታላቁ ሩጫ፤ እስከ 2013 ዓ.ም ድረስ በድምሩ ወደ 600 ሺህ የሚጠጉ ተሳታፊዎችን አስተናግዷል። የመጀመሪያው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከ10 ሺህ ያነሱ ተሳታፊዎች የነበሩት ሲሆን ባለፉት ዓመታት ውድድሩ ከ40 ሺህ በላይ ተሳታፊዎችን አስተናግዶ ነበር። በአፍሪካ ትልቁ የጎዳና ላይ ሩጫ እንደሆነ የሚነገርለት ይህ ውድድር፤ ከኢትዮጵያውን ባሻገር ከተለያዩ ዓለም ክፍሎች የሚመጡ የውጪ አገራት ዜጎችም የሚሳተፉበት ሆኗል። ታላቁ ሩጫ ለጤና ከሚደረገውና አስር ሺዎች ከሚሳተፉበት ሩጫ በተጨማሪም፣ ለአሸናፊዎች የገንዘብ ሽልማት የሚያበርክትበት መደበኛ የውድድር ዘርፍም አለው። የዘንድሮ ታላቁ ሩጫ ሊካሄድ 11 ቀናት ሲቀሩት መራዘሙ የተገለጸው ባለፈው ማክሰኞ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ትናንት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጸደቀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። በስሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ተከትሎ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለሚቀጥሉት 6 ወራት ተፈጻሚ የሚሆን ነው። | https://www.bbc.com/amharic/news-59174005 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ በኦክስጅን እጥረት በምትታመሰው ዴልሂ ህይወት ምን ይመስላል? | የዴልሂ ሆስፒታሎች ከሁለት ሳምንት በፊት ነበር የኦክስጂን እጥረት ያጋጥማቸው የጀመረው። ቀውሱ የመቀነስ ምልክት አላሳየም። ቅዳሜ ብቻ በአንድ ታዋቂ ሆስፒታል ኦክስጅንን በማለቁ ሐኪምን ጨምሮ ቢያንስ 12 ታካሚዎች ሞተዋል። ከሆስፒታሎች ውጭ አልጋ ማግኘት የማይችሉ የሕመምተኞች ቤተሰቦች ተንቀሳቃሽ ሲሊንደሮችን ለማግኘት እየታገሉ ነው። አንዳንድ ጊዜ ለ12 ሰዓታት ድረስ ወረፋ ለመጠበቅ ይገደዳሉ። የዴልሂ ትልልቅ ሆስፒታሎች በየቀኑ በሚታደል የኦክስጅን እደላ ነው እየሰሩ የሚገኙት። አንድ ዶክተር ሁኔታውን አስፈሪ እንደሆነ ገልጸዋል። "ዋናውን ሲሊንደር አንዴ ከተጠቀሙ በኋላ የሚቀየርበት ምንም ነገር የለም" ብለዋል፡፡ የማጠራቀሚያ ታንከሮች በሌላቸው እና በትላልቅ ሲሊንደሮች በሚሠሩ አነስተኛ ሆስፒታሎች ሁኔታው የከፋ ነው። እሁድ ዕለት በዴልሂ ብቻ ከ25 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 412 ሰዎች መሞታቸውን ተዘግቧል። ሕንድ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ 400ሺህ በላይ አዳዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን በማስመዝገብ የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች። 'የዕለት ተዕለት ውጊያ ነው' የሽሪ ራም ሲንግ ሆስፒታልን አስተዳዳሪው ዶ/ር ጋውታም ሲንግ 16 የጽኑ ህሙማን እና 50 የኮቪድ ህሙማን አልጋዎች እንዳላቸው ገልጸዋል። የኦክስጅን አቅርቦት ዋስትና ስለሌላቸው ህሙማንን ለመቀበል ግን ፈቃደኛ አይደሉም። ሕይወት ለማትረፍ ኦክስጅን እንዲሰጣቸው በማሰብ ባለፉት ጥቂት ቀናት በርካታ የድረሱልን ጥሪዎችን አድርገዋል። "በየዕለቱ የምናደርገው ውጊያ ነው። ግማሾቹ የሆስፒታል ሠራተኞች ከቦታ ወደ ቦታ በመሄድ ሲሊንደሮች ለመሙላት በየቀኑ ሲንገላቱ ይውላሉ።" በሆስፒታሉ በኦክስጅን እጥረት የሚሞቱ ህመምተኞች ጉዳይ እንቅልፍ እንደሚነሳቸው ዶ/ር ሲንግ ይገልጻሉ። "ታካሚዎቼን ስለማከም እንጂ ኦክስጅን ለማግኘት መንገላታት አልነበረብኝም" ብለዋል። የሌሎች የሆስፒታሎችም እጣ ፈንታ ተመሳሳይ ነው። ቤተሰቧ ዴልሂ ውስጥ ሆስፒታል ያላቸው አንዲት ግለሰብም ቀውሱ ሲጀመር በባለስልጣናት መካከል ቅንጅት እንደሌለ ትናገራለች። "በእነዚያ ጥቂት ቀናት ውስጥ የሚመለከተው አካል ማን እንደሆነ እና ጉዳዩን የሚፈታው ማን እንደሆነ አናውቅም ነበር" ትላለች። ሁኔታው "አሁን በመጠኑ ተሻሽሏል" ትላለች። ይሁን እንጂ የኦክስጅን አቅርቦቱ ላይ እርግጠኛ መሆን ስለማይቻል ሆስፒታሎች ብዙ ታካሚዎችን የመቀበል አቅማቸው ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል። "የኦክስጅን አልጋ አለሽ ወይ ብለው ሲጠይቁኝ የለኝም በማለት ስመለስ በጣም ይሰማኛል" ትላለች። ኦክስጅን የሚያከፋፍለው የፌደራል መንግስት ነው። የደልሂ ዋና ሚኒስትር አርቪንድ ኬጅሪዋል ከተማዋ በቂ ኦክስጅንን እያገኘች አይደለም ሲሉ በተደጋጋሚ ተናግረዋል። የፌዴራል ባለሥልጣናት ደግሞ የኦክስጅን እጥረት የለም የቸገረን የትራንስፖርቱ ጉዳይ ነው ይላሉ። 'ሰዎች ዋጋ እየከፈሉ ነው' በመሬት ላይ ያለው ሁኔታ ግን አሁንም አስከፊ ነው። "በግዛቶች እና በፌዴራል መንግሥት መካከል በተፈጠረው የፖለቲካ ውዝግብ ሰዎች ዋጋ እየከፈሉ ነው። አንዳንድ ጊዜ ህይወታቸውን ነው የሚከፍሉት" ብለዋል አንድ ተንታኝ። በኦክስጅን እጥረት ምክንያት አልጋ ያገኙ ቤተሰቦችም በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ናቸው። ያለፉት 48 ሰዓታቶች ለአልታፍ ሻምሲ አሰቃቂ የሚባሉ ናቸው። እሱ እና መላው ቤተሰቡ ባለፈው ሳምንት ተመርምረው ኮቪድ -19 አለባችሁ ተባሉ። ነፍሰ ጡር ሚስቱ በጠና ታማ ሆስፒታል ተወሰደች። አርብ ዕለት ሴት ልጅ ተገላገለች። በተወሳሰበ ወሊድ ምክንያት ከጥቂት ሰዓታት በኋላ በመታመሟ ቬንትሌተር የተገጠመላት ሲሆን አሁን በአስጊ ሁኔታ ውስጥ ትገኛለች። አልታፍ አባቱ በሌላ ሆስፒታል ህይወታቸው እንዳለፈ ተነገረው። በጽኑ ህሙማን ማቆያ ውስጥ የሚገኙት ሚስቱ እና ሕጻኗ የሚገኙበት ሆስፒታል ኦክስጅን እያለቀ ነው ሲል አሳውቋቸዋል። ሆስፒታሉ ለአንድ ቀን የሚሆን ኦክስጅን ቢያገኝም አልታፍ ግን ዘላቂ መፍትሔ ባለመሆኑ እንደተጨነቀ ነው። "ነገ ምን እንደሚፈጠር ማን ያውቃል?" ይላል። ከኦክስጅን እጥረቱ በተጨማሪ ሆስፒታሉ በቂ የሰው ኃይል የለኝም በሚል ባለቤቱን ወደ ሌላ ተቋም እንዲያዛውር እየጠየቀው ነው። በዚህም ራሱ የባለቤቱን የኦክስጅን መጠን እና ትኩሳት ለመከታተል ተገደደ። "እያሳለፍኩ ያለሁትን ስቃይ መገመት እንኳን አትችሉም" ይላል። 'የአባቴ ኦክስጅን እያለቀ ነው' በዴልሂ በከባድ ሁኔታ ውስጥ ላሉት ታካሚዎች የሆስፒታል አልጋ ካላገኙ በቤታቸው ተንቀሳቃሽ የኦክስጂን ሲሊንደሮች መጠቀማው ብቸኛው መንገድ ነው። የአቢሼክ ሻርማ አባት የኦክስጅን መጠን ከቅዳሜ ጀምሮ እየወረደ ነው። ሲሊንደር ለመግዛት ወደ ገበያ በፍጥነት አቀና። ከደርዘን በላይ ሱቆችን ጎብኝቶ ለስድስት ሰዓታት ብቻ የሚቆይ ሲሊንደር አገኘ። በኋላ አንድ ትልቅ ሲሊንደር በ944 ዶላር ቢገዛም ባዶ ነበር። ሲሊንደሩን ለማስሞላት ወደ ብዙ መሙያ ጣቢያዎች ወስዶ አንዱ ብቻ ሊረዳው ፈቃደኛ የነበረ ቢሆንም ወረፋው በጣም ረጅም ነበር። "በወረፋው በቆምኩበት እያንዳንዱ ደቂቃው አባቴ ኦክስጂን እያለቀ ነበር። ሁሉም ሰው በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ስለነበረ እንዲያስቀድሙኝ ማንንም መጠየቅ አልቻልኩም ነበር። ሲሊንደሩን ከስድስት ሰዓታት በኋላ አስሞላሁ። ነገም ደግሞ ደጋሚ መሰለፍ አለብኝ" ይላል። የህዝብ ፖሊሲ እና የጤና ስርዓት ባለሙያ የሆኑት ዶክተር ቻንድራካንት ላሃሪያ መንግስት "ሊመጣ ስለሚችለው ቀውስ" ሕዝቡን ቢያስጠነቅቅም ምንም እርምጃ አልተወሰደም ይላሉ። የአገሪቱ ፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ በህዳር ወር ስለ ኦክስጅን አቅርቦት እና "በቂ ስላልሆነው የመንግሥት ሆስፒታል አልጋዎች ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር። እንደ ዶ/ር ላሃሪያ ከሆነ በሕንድ የተከሰተው የህክምና ኦክስጅን ቀውስ፤ የስርጭት እና የትራንስፖርት ኔትወርክን የማስተካከል ዕቅድ ባለመኖሩ ነው። 'የጦርነት ክፍል አዘጋጅተናል' በችግር ወቅት ዜጎች በችግር ውስጥ ያሉትን ለመርዳት ቅድሚያ ይሰጣሉ። ድጋፍ ከሰጡት ታዋቂ ሰዎች መካከል ማህበራዊ ጉዳይ ተሟጋች እና ፖለቲከኛው ተህሴን ፖናዋላ፣ ፖለቲከኛው ዲሊፕ ፓንዴይ፣ አክቲቪስት እና ፖለቲከኛ ስሪኒቫስ ቢ ቪ እና ተዋናይ ሶኑ ሶድ ይገኙበታል። ፖናዋላ መለስተኛ ሆስፒታሎች ኦክስጂን ሲያልቅባቸው ሲያግዙ ቆይተዋል። "የቸገራቸውን ለመርዳት ከሚችሉ ጋር እያገናኘሁ ነው" ብለዋል። "አንድ ትንሽ ቡድን ከእኔ ጋር አብሮ የሚሰራበትን የውጊያ ክፍል አቋቁመናል። የማውቃቸውን ሰዎች ጋር ብቻ እየደወልኩ ነው። አንዳንዶቹ በሌሎች ግዛቶች ቢኖሩም ለመርዳት ዝግጁ ናቸው" ይላሉ። "በእያንዳንዱ ቀን ሁኔታው ይበልጥ አስከፊ እየሆነ ነው። እንደ እኔ ያሉ ሰዎች እያንዳንዱን ሰው ወይም የተቸገረን ሆስፒታል ለማገዝ የሚረዳ ሃብት ስለሌላቸው መንግሥት ጣልቃ ገብቶ ኃላፊነቱን መውሰድ አለበት" ብለዋል። | ኮሮናቫይረስ፡ በኦክስጅን እጥረት በምትታመሰው ዴልሂ ህይወት ምን ይመስላል? የዴልሂ ሆስፒታሎች ከሁለት ሳምንት በፊት ነበር የኦክስጂን እጥረት ያጋጥማቸው የጀመረው። ቀውሱ የመቀነስ ምልክት አላሳየም። ቅዳሜ ብቻ በአንድ ታዋቂ ሆስፒታል ኦክስጅንን በማለቁ ሐኪምን ጨምሮ ቢያንስ 12 ታካሚዎች ሞተዋል። ከሆስፒታሎች ውጭ አልጋ ማግኘት የማይችሉ የሕመምተኞች ቤተሰቦች ተንቀሳቃሽ ሲሊንደሮችን ለማግኘት እየታገሉ ነው። አንዳንድ ጊዜ ለ12 ሰዓታት ድረስ ወረፋ ለመጠበቅ ይገደዳሉ። የዴልሂ ትልልቅ ሆስፒታሎች በየቀኑ በሚታደል የኦክስጅን እደላ ነው እየሰሩ የሚገኙት። አንድ ዶክተር ሁኔታውን አስፈሪ እንደሆነ ገልጸዋል። "ዋናውን ሲሊንደር አንዴ ከተጠቀሙ በኋላ የሚቀየርበት ምንም ነገር የለም" ብለዋል፡፡ የማጠራቀሚያ ታንከሮች በሌላቸው እና በትላልቅ ሲሊንደሮች በሚሠሩ አነስተኛ ሆስፒታሎች ሁኔታው የከፋ ነው። እሁድ ዕለት በዴልሂ ብቻ ከ25 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 412 ሰዎች መሞታቸውን ተዘግቧል። ሕንድ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ 400ሺህ በላይ አዳዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን በማስመዝገብ የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች። 'የዕለት ተዕለት ውጊያ ነው' የሽሪ ራም ሲንግ ሆስፒታልን አስተዳዳሪው ዶ/ር ጋውታም ሲንግ 16 የጽኑ ህሙማን እና 50 የኮቪድ ህሙማን አልጋዎች እንዳላቸው ገልጸዋል። የኦክስጅን አቅርቦት ዋስትና ስለሌላቸው ህሙማንን ለመቀበል ግን ፈቃደኛ አይደሉም። ሕይወት ለማትረፍ ኦክስጅን እንዲሰጣቸው በማሰብ ባለፉት ጥቂት ቀናት በርካታ የድረሱልን ጥሪዎችን አድርገዋል። "በየዕለቱ የምናደርገው ውጊያ ነው። ግማሾቹ የሆስፒታል ሠራተኞች ከቦታ ወደ ቦታ በመሄድ ሲሊንደሮች ለመሙላት በየቀኑ ሲንገላቱ ይውላሉ።" በሆስፒታሉ በኦክስጅን እጥረት የሚሞቱ ህመምተኞች ጉዳይ እንቅልፍ እንደሚነሳቸው ዶ/ር ሲንግ ይገልጻሉ። "ታካሚዎቼን ስለማከም እንጂ ኦክስጅን ለማግኘት መንገላታት አልነበረብኝም" ብለዋል። የሌሎች የሆስፒታሎችም እጣ ፈንታ ተመሳሳይ ነው። ቤተሰቧ ዴልሂ ውስጥ ሆስፒታል ያላቸው አንዲት ግለሰብም ቀውሱ ሲጀመር በባለስልጣናት መካከል ቅንጅት እንደሌለ ትናገራለች። "በእነዚያ ጥቂት ቀናት ውስጥ የሚመለከተው አካል ማን እንደሆነ እና ጉዳዩን የሚፈታው ማን እንደሆነ አናውቅም ነበር" ትላለች። ሁኔታው "አሁን በመጠኑ ተሻሽሏል" ትላለች። ይሁን እንጂ የኦክስጅን አቅርቦቱ ላይ እርግጠኛ መሆን ስለማይቻል ሆስፒታሎች ብዙ ታካሚዎችን የመቀበል አቅማቸው ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል። "የኦክስጅን አልጋ አለሽ ወይ ብለው ሲጠይቁኝ የለኝም በማለት ስመለስ በጣም ይሰማኛል" ትላለች። ኦክስጅን የሚያከፋፍለው የፌደራል መንግስት ነው። የደልሂ ዋና ሚኒስትር አርቪንድ ኬጅሪዋል ከተማዋ በቂ ኦክስጅንን እያገኘች አይደለም ሲሉ በተደጋጋሚ ተናግረዋል። የፌዴራል ባለሥልጣናት ደግሞ የኦክስጅን እጥረት የለም የቸገረን የትራንስፖርቱ ጉዳይ ነው ይላሉ። 'ሰዎች ዋጋ እየከፈሉ ነው' በመሬት ላይ ያለው ሁኔታ ግን አሁንም አስከፊ ነው። "በግዛቶች እና በፌዴራል መንግሥት መካከል በተፈጠረው የፖለቲካ ውዝግብ ሰዎች ዋጋ እየከፈሉ ነው። አንዳንድ ጊዜ ህይወታቸውን ነው የሚከፍሉት" ብለዋል አንድ ተንታኝ። በኦክስጅን እጥረት ምክንያት አልጋ ያገኙ ቤተሰቦችም በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ናቸው። ያለፉት 48 ሰዓታቶች ለአልታፍ ሻምሲ አሰቃቂ የሚባሉ ናቸው። እሱ እና መላው ቤተሰቡ ባለፈው ሳምንት ተመርምረው ኮቪድ -19 አለባችሁ ተባሉ። ነፍሰ ጡር ሚስቱ በጠና ታማ ሆስፒታል ተወሰደች። አርብ ዕለት ሴት ልጅ ተገላገለች። በተወሳሰበ ወሊድ ምክንያት ከጥቂት ሰዓታት በኋላ በመታመሟ ቬንትሌተር የተገጠመላት ሲሆን አሁን በአስጊ ሁኔታ ውስጥ ትገኛለች። አልታፍ አባቱ በሌላ ሆስፒታል ህይወታቸው እንዳለፈ ተነገረው። በጽኑ ህሙማን ማቆያ ውስጥ የሚገኙት ሚስቱ እና ሕጻኗ የሚገኙበት ሆስፒታል ኦክስጅን እያለቀ ነው ሲል አሳውቋቸዋል። ሆስፒታሉ ለአንድ ቀን የሚሆን ኦክስጅን ቢያገኝም አልታፍ ግን ዘላቂ መፍትሔ ባለመሆኑ እንደተጨነቀ ነው። "ነገ ምን እንደሚፈጠር ማን ያውቃል?" ይላል። ከኦክስጅን እጥረቱ በተጨማሪ ሆስፒታሉ በቂ የሰው ኃይል የለኝም በሚል ባለቤቱን ወደ ሌላ ተቋም እንዲያዛውር እየጠየቀው ነው። በዚህም ራሱ የባለቤቱን የኦክስጅን መጠን እና ትኩሳት ለመከታተል ተገደደ። "እያሳለፍኩ ያለሁትን ስቃይ መገመት እንኳን አትችሉም" ይላል። 'የአባቴ ኦክስጅን እያለቀ ነው' በዴልሂ በከባድ ሁኔታ ውስጥ ላሉት ታካሚዎች የሆስፒታል አልጋ ካላገኙ በቤታቸው ተንቀሳቃሽ የኦክስጂን ሲሊንደሮች መጠቀማው ብቸኛው መንገድ ነው። የአቢሼክ ሻርማ አባት የኦክስጅን መጠን ከቅዳሜ ጀምሮ እየወረደ ነው። ሲሊንደር ለመግዛት ወደ ገበያ በፍጥነት አቀና። ከደርዘን በላይ ሱቆችን ጎብኝቶ ለስድስት ሰዓታት ብቻ የሚቆይ ሲሊንደር አገኘ። በኋላ አንድ ትልቅ ሲሊንደር በ944 ዶላር ቢገዛም ባዶ ነበር። ሲሊንደሩን ለማስሞላት ወደ ብዙ መሙያ ጣቢያዎች ወስዶ አንዱ ብቻ ሊረዳው ፈቃደኛ የነበረ ቢሆንም ወረፋው በጣም ረጅም ነበር። "በወረፋው በቆምኩበት እያንዳንዱ ደቂቃው አባቴ ኦክስጂን እያለቀ ነበር። ሁሉም ሰው በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ስለነበረ እንዲያስቀድሙኝ ማንንም መጠየቅ አልቻልኩም ነበር። ሲሊንደሩን ከስድስት ሰዓታት በኋላ አስሞላሁ። ነገም ደግሞ ደጋሚ መሰለፍ አለብኝ" ይላል። የህዝብ ፖሊሲ እና የጤና ስርዓት ባለሙያ የሆኑት ዶክተር ቻንድራካንት ላሃሪያ መንግስት "ሊመጣ ስለሚችለው ቀውስ" ሕዝቡን ቢያስጠነቅቅም ምንም እርምጃ አልተወሰደም ይላሉ። የአገሪቱ ፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ በህዳር ወር ስለ ኦክስጅን አቅርቦት እና "በቂ ስላልሆነው የመንግሥት ሆስፒታል አልጋዎች ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር። እንደ ዶ/ር ላሃሪያ ከሆነ በሕንድ የተከሰተው የህክምና ኦክስጅን ቀውስ፤ የስርጭት እና የትራንስፖርት ኔትወርክን የማስተካከል ዕቅድ ባለመኖሩ ነው። 'የጦርነት ክፍል አዘጋጅተናል' በችግር ወቅት ዜጎች በችግር ውስጥ ያሉትን ለመርዳት ቅድሚያ ይሰጣሉ። ድጋፍ ከሰጡት ታዋቂ ሰዎች መካከል ማህበራዊ ጉዳይ ተሟጋች እና ፖለቲከኛው ተህሴን ፖናዋላ፣ ፖለቲከኛው ዲሊፕ ፓንዴይ፣ አክቲቪስት እና ፖለቲከኛ ስሪኒቫስ ቢ ቪ እና ተዋናይ ሶኑ ሶድ ይገኙበታል። ፖናዋላ መለስተኛ ሆስፒታሎች ኦክስጂን ሲያልቅባቸው ሲያግዙ ቆይተዋል። "የቸገራቸውን ለመርዳት ከሚችሉ ጋር እያገናኘሁ ነው" ብለዋል። "አንድ ትንሽ ቡድን ከእኔ ጋር አብሮ የሚሰራበትን የውጊያ ክፍል አቋቁመናል። የማውቃቸውን ሰዎች ጋር ብቻ እየደወልኩ ነው። አንዳንዶቹ በሌሎች ግዛቶች ቢኖሩም ለመርዳት ዝግጁ ናቸው" ይላሉ። "በእያንዳንዱ ቀን ሁኔታው ይበልጥ አስከፊ እየሆነ ነው። እንደ እኔ ያሉ ሰዎች እያንዳንዱን ሰው ወይም የተቸገረን ሆስፒታል ለማገዝ የሚረዳ ሃብት ስለሌላቸው መንግሥት ጣልቃ ገብቶ ኃላፊነቱን መውሰድ አለበት" ብለዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-56968683 |
5sports
| ኔይማር በማጭበርበር ተከሶ ፍርድ ቤት ሊቀርብ ነው | ታዋቂው ብራዚላዊ እግር ኳስ ተጫዋች ኔይማር ጁኒየር በዝውውሩ ወቅት ተፈጽመዋል ከተባሉ ሕገ ወጥ ድርጊቶች ጋር በተያያዘ በማጭበርበር ተከሶ ፍርድ ቤት ሊቀርብ ነው። አሁን ለፈረንሳዩ ፓሪ ሴን ዠርመን (ፒኤስጂ) የሚጫወተው ኔይማር፤ ለዓመታት በዘለቀ የፍርድ ቤት ጉዳይ በማጭበርበር እና በሙስና ክስ ቀርቦበታል። የኔይማር ጉዳይ በፍርድ ቤት የሚታየው ለሁለት ሳምንታት በመጪው ጥቅምት ወር የዓለም ዋንጫ ውድድር ኳታር ውስጥ መካሄድ ከመጀመሩ በፊት ነው። ከኔይማር በተጨማሪ ሌሎች ታዋቂ ሰዎችም ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ይጠበቃል። ሁለት የቀድሞዎቹ የባርሴሎና እግር ኳስ ቡድን ፕሬዝዳንቶች ጆሴፍ ማሪያ ባርቶሙ እና ሳንድሮ ሮሴል እንዲሁም የኔይማር ወላጆች በተመሳሳይ ክስ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ የስፔን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። በዚህ ክስ ውስጥ ስማቸው የተነሳው ግለሰቦች በሙሉ የቀረበባቸውን ውንጀላ አስተባብለዋል። ክሱን ያቀረበው ተቋም ኔይማር ከዓመታት በፊት ከብራዚሉ ሳንቶስ ክለብ ሲዘዋወር 40 በመቶ ገንዘብ ይገባኛል ብሏል። ኔይማር የተዘዋወረበት የገንዘብ መጠን እንዳይገለጽ በመደረጉ ከሳሽ ከዝውውሩ ሊያገኝ ከሚገባው ገንዘብ ያነሰ መቀበሉን ጠቅሷል። በጣም ከፍተኛ ነው የሚባለው የኔይማር የዝውውር ገንዘብ መጠን በሕጋዊ ውዝግብ የተከበበ እንደሆነ ይነገራል። ባርሴሎናን የተሰናበተው ኔይማር ከፍርድ ቤት ውጪ በሆነ ስምምነት በ222 ሚሊዮን ዩሮ ወደ ፒኤስጂ ነበር ያቀናው። ከዚህ ቀደም በነበረ የፍርድ ቤት ክርክር ባርሴሎና ኔይማርን ከሳንቶስ ባዘዋወረበት ሂደት ሕጋዊ ጉዳዮች ተጥሰዋል በሚል ባርሴሎና 5.5 ሚሊዮን ዩሮ እንዲከፍል ተፈርዶበት ነበር። | ኔይማር በማጭበርበር ተከሶ ፍርድ ቤት ሊቀርብ ነው ታዋቂው ብራዚላዊ እግር ኳስ ተጫዋች ኔይማር ጁኒየር በዝውውሩ ወቅት ተፈጽመዋል ከተባሉ ሕገ ወጥ ድርጊቶች ጋር በተያያዘ በማጭበርበር ተከሶ ፍርድ ቤት ሊቀርብ ነው። አሁን ለፈረንሳዩ ፓሪ ሴን ዠርመን (ፒኤስጂ) የሚጫወተው ኔይማር፤ ለዓመታት በዘለቀ የፍርድ ቤት ጉዳይ በማጭበርበር እና በሙስና ክስ ቀርቦበታል። የኔይማር ጉዳይ በፍርድ ቤት የሚታየው ለሁለት ሳምንታት በመጪው ጥቅምት ወር የዓለም ዋንጫ ውድድር ኳታር ውስጥ መካሄድ ከመጀመሩ በፊት ነው። ከኔይማር በተጨማሪ ሌሎች ታዋቂ ሰዎችም ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ይጠበቃል። ሁለት የቀድሞዎቹ የባርሴሎና እግር ኳስ ቡድን ፕሬዝዳንቶች ጆሴፍ ማሪያ ባርቶሙ እና ሳንድሮ ሮሴል እንዲሁም የኔይማር ወላጆች በተመሳሳይ ክስ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ የስፔን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። በዚህ ክስ ውስጥ ስማቸው የተነሳው ግለሰቦች በሙሉ የቀረበባቸውን ውንጀላ አስተባብለዋል። ክሱን ያቀረበው ተቋም ኔይማር ከዓመታት በፊት ከብራዚሉ ሳንቶስ ክለብ ሲዘዋወር 40 በመቶ ገንዘብ ይገባኛል ብሏል። ኔይማር የተዘዋወረበት የገንዘብ መጠን እንዳይገለጽ በመደረጉ ከሳሽ ከዝውውሩ ሊያገኝ ከሚገባው ገንዘብ ያነሰ መቀበሉን ጠቅሷል። በጣም ከፍተኛ ነው የሚባለው የኔይማር የዝውውር ገንዘብ መጠን በሕጋዊ ውዝግብ የተከበበ እንደሆነ ይነገራል። ባርሴሎናን የተሰናበተው ኔይማር ከፍርድ ቤት ውጪ በሆነ ስምምነት በ222 ሚሊዮን ዩሮ ወደ ፒኤስጂ ነበር ያቀናው። ከዚህ ቀደም በነበረ የፍርድ ቤት ክርክር ባርሴሎና ኔይማርን ከሳንቶስ ባዘዋወረበት ሂደት ሕጋዊ ጉዳዮች ተጥሰዋል በሚል ባርሴሎና 5.5 ሚሊዮን ዩሮ እንዲከፍል ተፈርዶበት ነበር። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cg3255v7pe4o |
5sports
| የኮንጎ ተወላጁ የስቱትጋርት አጥቂ በሐሰተኛ ስም ሲጫወት ነበር ተባለ | የዓመቱ ምርጥ አዲስ ተጫዋች በሚል ሽልማት የተቀበለውና በጀርመን ቡንደስሊጋ የሚሳተፈው የስቱትጋርት እግር ኳስ ክለብ ተጨዋች የሆነው ሲላስ ዋማንጊቱኪያስ በሐሰት መዝገብ ሲንቀሳቀስ ነበር ተባለ። የዴሞክራቲክ ኮንጎ ተወላጁ ሲላስ ዋማንጊቱኪያስ ትክክለኛ ስሙ ሲላስ ካቶምፓ ምቩምፓ ሲሆን የተወለደው ደግሞ በአውሮፓውያኑ ጥቅምት ወር 1998 ነበር። ይህ መረጃ ደግሞ እሱ ከተናገረውና መረጃ ካቀረበበት ጋር ሲነጻጸር በአንድ ዓመት እድሜውን ከፍ ያደርገዋል። ተጫዋቹ እንደሚለው ከሆነ እድሜውን ቀንሶ እንዲናገር ከፍተኛ ጫና ያደረሰበት የቀድሞ ወኪሉ ነበር። በዚህም ምክንያት 'በከፍተኛ ፍርሀት' ውስጥ እንደቆየ ተናግሯል። ስቱትጋርት እግር ኳስ ክለብ ደግሞ ጉዳዩን ካረጋገጠ በኋላ ከቡንደስሊጋ እና የጀርማን እግር ኳስ ማሕበር ጋር ንግግር ማድረግ ጀምሯል። ክለቡም ከ22 ዓመቱ ወጣት ተጨዋች እና አዲሱ ወኪሉ ጋር ንግግር እያደረገ እንደሆነና ጉዳዩን በጥልቀት እየመረመረው እንደሆነ አስታውቋል። ክለቡ ጨምሮም ከዴሞክራቲክ ኮንጎ ይፋዊ መረጃዎችን ከጥቂት ቀናት በፊት ማግኘቱን ገልጿል። ሲላስ ዋማንጊቱኪያስ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በጀርመን ቡንደስሊጋ 13 ግቦችን ማስቆጠር የቻለ ሲሆን ክለቡ ስቱትጋርትም ዘጠነኛ ሆኖ ማጠናቀቅ እንዲችል ረድቷል። በአውሮፓውያኑ 2017 ለቤልጂየሙ አንደርሌክትም ተጫውቶ የነበረ ሲሆን በቀድሞ ወኪሉ ገፋፊነት ደግሞ በፈረንሳይ ሁለተኛ ሊግ ወደሚጫወተው ፓሪስ እግር ኳስ ክለብ ተዘዋውሯል። 2019 ላይ ደግሞ ስቱትጋርትን በመቀላቀል ቡድኑ ወደ ጀርመን ቡንደስሊጋ እንዲያድግ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። "ባለፉት ጥቂት ዓመታት ኮንጎ ለሚገኙት ቤተሰቦቼ ጭምር እሰጋ ነበር" ብሏል ተጨዋቹ። "የግል ታሪኬን ለህዝብ ይፋ ለማድረግ መወሰን በጣም ከባድ ነገር ነበር። ነገር ግን ስቱትጋርት እግር ኳስ ክለብ እንደ ቤቴ የምቆጥረውና የማምነው ክለብ በመሆኑ ድፍረቱን አግኝቻለሁ" ብሏል። | የኮንጎ ተወላጁ የስቱትጋርት አጥቂ በሐሰተኛ ስም ሲጫወት ነበር ተባለ የዓመቱ ምርጥ አዲስ ተጫዋች በሚል ሽልማት የተቀበለውና በጀርመን ቡንደስሊጋ የሚሳተፈው የስቱትጋርት እግር ኳስ ክለብ ተጨዋች የሆነው ሲላስ ዋማንጊቱኪያስ በሐሰት መዝገብ ሲንቀሳቀስ ነበር ተባለ። የዴሞክራቲክ ኮንጎ ተወላጁ ሲላስ ዋማንጊቱኪያስ ትክክለኛ ስሙ ሲላስ ካቶምፓ ምቩምፓ ሲሆን የተወለደው ደግሞ በአውሮፓውያኑ ጥቅምት ወር 1998 ነበር። ይህ መረጃ ደግሞ እሱ ከተናገረውና መረጃ ካቀረበበት ጋር ሲነጻጸር በአንድ ዓመት እድሜውን ከፍ ያደርገዋል። ተጫዋቹ እንደሚለው ከሆነ እድሜውን ቀንሶ እንዲናገር ከፍተኛ ጫና ያደረሰበት የቀድሞ ወኪሉ ነበር። በዚህም ምክንያት 'በከፍተኛ ፍርሀት' ውስጥ እንደቆየ ተናግሯል። ስቱትጋርት እግር ኳስ ክለብ ደግሞ ጉዳዩን ካረጋገጠ በኋላ ከቡንደስሊጋ እና የጀርማን እግር ኳስ ማሕበር ጋር ንግግር ማድረግ ጀምሯል። ክለቡም ከ22 ዓመቱ ወጣት ተጨዋች እና አዲሱ ወኪሉ ጋር ንግግር እያደረገ እንደሆነና ጉዳዩን በጥልቀት እየመረመረው እንደሆነ አስታውቋል። ክለቡ ጨምሮም ከዴሞክራቲክ ኮንጎ ይፋዊ መረጃዎችን ከጥቂት ቀናት በፊት ማግኘቱን ገልጿል። ሲላስ ዋማንጊቱኪያስ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በጀርመን ቡንደስሊጋ 13 ግቦችን ማስቆጠር የቻለ ሲሆን ክለቡ ስቱትጋርትም ዘጠነኛ ሆኖ ማጠናቀቅ እንዲችል ረድቷል። በአውሮፓውያኑ 2017 ለቤልጂየሙ አንደርሌክትም ተጫውቶ የነበረ ሲሆን በቀድሞ ወኪሉ ገፋፊነት ደግሞ በፈረንሳይ ሁለተኛ ሊግ ወደሚጫወተው ፓሪስ እግር ኳስ ክለብ ተዘዋውሯል። 2019 ላይ ደግሞ ስቱትጋርትን በመቀላቀል ቡድኑ ወደ ጀርመን ቡንደስሊጋ እንዲያድግ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። "ባለፉት ጥቂት ዓመታት ኮንጎ ለሚገኙት ቤተሰቦቼ ጭምር እሰጋ ነበር" ብሏል ተጨዋቹ። "የግል ታሪኬን ለህዝብ ይፋ ለማድረግ መወሰን በጣም ከባድ ነገር ነበር። ነገር ግን ስቱትጋርት እግር ኳስ ክለብ እንደ ቤቴ የምቆጥረውና የማምነው ክለብ በመሆኑ ድፍረቱን አግኝቻለሁ" ብሏል። | https://www.bbc.com/amharic/news-57401439 |
3politics
| ሕዝቡ የማይመርጥበት የሶማሊያው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ | የሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ ጎዳናዎች እሁድ በሚካሄደው ምርጫ በሚወዳደሩት ፕሬዝዳንታዊ ዕጩዎች ትላልቅ የማስታወቂያ ሰሌዳዎች ተንቆጥቁጣለች። በመኪኖች በተጨናነቀው የትራፊክ እንቅስቃሴም አላፊው አግዳሚው ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው ምርጫ ከመድረሱ በፊት የተሰቀሉትን ፖስተሮችን ይቃኛሉ። ነገር ግን ሕዝቡ አይመርጥም። ሕዝብ የማይመርጥበት ምርጫ እንዴት? ልትሉ ትችላላችሁ። ለዚህም ምክንያቱ ሶማሊያ ውስብስብ እና ቀጥተኛ ያልሆነ የፖለቲካ ሥርዓት ስለምትከተል እና የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ስለማይወዳደሩ ነው። ይልቁንም 275 አባላት ያሉት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የሚመረጡት በክልል ባለሥልጣናት በተሰየሙ የጎሳ የአገር ሽማግሌዎችና የሲቪክ ማኅበራት አባላት ነው። በተጨማሪም የሶማሊያን አምስት ክልላዊ መንግሥታት የሚወክል 54 አባላት ያሉት ከፍተኛ ምክር ቤት (ሴኔት) አለ። ከዚያም የሁለቱም ምክር ቤቶች የፓርላማ አባላት 16.3 ሚሊዮን የሚሆነውን የሶማሊያን ሕዝብ የሚመራውን ፕሬዚዳንት ይመርጣሉ። ፕሬዚዳንታዊ ዕጩዎቹ እነማን ናቸው? ሶማሊያ ለረጅም ጊዜ የተጓተተውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዛሬ እሁድ ግንቦት 07/2014 ዓ.ም. ታካሂዳለች። ይህም መጀመሪያ ሊደረግ ከታቀደው ከአንድ ዓመት በላይ ዘግይቶ ነው። በሥልጣን ላይ የሚገኙትን መሐመድ አብዱላሂ መሐመድ ወይም ፋርማጆን ጨምሮ በፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ለመወዳደር 39 ዕጩዎች ቀርበዋል። በአውሮፓውያኑ 1991 በሲያድ ባሬ የሚመራው የሶሻሊስት መንግሥት ከተገረሰሰ ወዲህ ከፍተኛው ለፕሬዝዳንትነት የሚወዳደሩ ዕጩዎች ቁጥር ነው ተብሏል። ከዕጩዎቹ መካከል ሁለቱ የቀድሞ ፕሬዝዳንቶች፣ ሻሪፍ ሼህ አህመድ እና ሐሰን ሼክ መሐሙድ እንዲሁም የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሐሰን አሊ ኬሬ ይገኙበታል። ሌላኛዋ ዕጩ ፋውዚያ ዩሱፍ አደም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ያገለገሉ ሲሆን፣ ብቸኛዋ ሴት ዕጩ ተወዳዳሪ ናቸው። የወቅቱ የሶማሊያ ከፊል ራስ ገዝ የፑንትላንድ ክልል ፕሬዝዳንት ሰኢድ አብዱላሂ ዴኒም ውድድሩን ተቀላቅለዋል። የሚመረጠው ፕሬዚዳንት ለአራት ዓመታት የሚያገለግል ሲሆን እንደገና መመረጥም ይችላል። ይሁን እንጂ ቀጥተኛ ባልሆነ የድምፅ አሰጣጥ ሥርዓት በአውሮፓውያኑ 2000 ከተጀመረ ወዲህ አንድም የሶማሊያ ፕሬዝዳንት በድጋሚ አልተመረጠም። ለምን ተራ ዜጎች አይመርጡም? ይህ ሁኔታ በሶማሊያ ያለውን የጎሳ ኃይል የሚያሳይ ነው። የምዕራባውያን አይነት ዲሞክራሲ ባልሰፈነበት ማኅበረሰብም የጀርባ አጥንት ናቸው። በአውሮፓውያኑ 1991 በሶማሊያ የማዕከላዊ መንግሥት መውደቅን ተከትሎ አገሪቱ መንግሥት አልባ ሆና የቆየች ሲሆን ይህንንም ክፍተት የጎሳ መሪዎች ሞልተውታል። በሶማሊያ ጎሳዎች መካከል ከፍተኛ ፉክክር ስላለ ሥርዓቱ በሥልጣን ክፍፍል ቀመር ላይ የተመሰረተ ሲሆን፣ አራቱ ትላልቅ ጎሳዎች እኩል ቁጥር ያላቸው የፓርላማ መቀመጫዎችን ሲይዙ ቀሪዎቹ ጎሳዎች አንድ ላይ ተጣምረው ግማሹ የፓርላማ መቀመጫ ይሰጣቸዋል። ይህም ሁኔታ የሶማሊያ ጎሳ ተወካዮች በአገሪቱ አድራጊ ፈጣሪ እንዲሁም የአገሪቱን መሪ ወደ ሥልጣን የሚያመጡ ኃያላን ያደርጋቸዋል። የሁለቱን ምክር ቤቶች ምርጫ ተከትሎ ወደ 300 የሚጠጉ የፓርላማ አባላት ቃለ መሃላ ፈፅመዋል። ምርጫዎቹ መጠነ ሰፊ ሙስና፣ ሥልጣንን አላግባብ የተጠቀሙበት እና የምርጫ ሕግጋት ችላ የተባሉበት ነው ተብሏል። በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ልዑካንን ለመግዛት በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ወጪ ተደርጓል ተብሎ ይታመናል። እንደ አለመታደል ሆኖ አገሪቱ ሙስናን የሚቆጣጠሩ ተቋማት የሏትም። ኳታር በሶማሊያ ፖለቲካ መድረክ ዋና ተዋናይ ነች። ተንታኞች እንደሚናገሩት በአውሮፓውያኑ 2017 የፕሬዚዳንት ፋርማጆ የምርጫ ዘመቻን ወቅት ኳታር በብቸኝነት ከፍተኛ ድጋፍ ያደረገች ሲሆን ከአስተዳሩም ጋር ጠበቅ ያለ ግንኙነት ነበራት። ለምን ይህን ያህል ጊዜ ዘገዬ? የፕሬዚዳንት ፋርማጆ የሥልጣን ወቅት በአውሮፓውያኑ የካቲት 2021 ቢጠናቀቅም በነበረው የፖለቲካ አለመግባባት በሥልጣን ላይ ቆይተዋል። ለፓርላማ አባላት የነበረው ምርጫ ዝግጅት አለመኖር ምርጫውን ያዘገየው ሲሆን እሳቸውም ሆነ ሕግ አውጪዎች የመምራት ሥልጣን ባይኖራቸውም እየመሩ እንዲቆዩ አድርጓቸዋል። የፓርላማ ምርጫው በመጨረሻ የተካሄደው በምዕራባውያን ለጋሾች ግፊት ነው። አሜሪካ የምርጫውን ሂደት እያዘገዩ ነው ያለቻቸውን ባለሥልጣናት ቪዛ አግዳለች ። ምርጫው ከታኅሣሥ እስከ መጋቢት ድረስ አራት ወራትን አስቆጥሯል። በግንቦት ወር አጋማሽ ምርጫው ካልተጠናቀቀ ለሶማሊያ የሚሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ ሊያቆም እንደሚችል ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) አስታውቋል። አዲሱ መንግሥት ሥልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ ድርቅን ጨምሮ የሶማሊያን ተግዳሮቶች መፍታት ይኖርበታል። ድርቁ ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ የተባባሰ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የረድዔት ድርጅቶች ረሃብ ሊከሰት እንደሚችል እያስጠነቀቁ ነው። በአሁኑ ወቅት ከ3.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን 1.4 ሚሊዮን ህጻናት ለከፍተኛ የምግብ እጥረት ተጋልጠዋል። ምዕራባውያን በሶማሊያ ያላቸው ፍላጎት ምንድን ነው? ምዕራባውያን ዋናው ጭንቀታቸው የታጣቂ እስላማዊ ቡድን እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ ማንሰራራት ነው። ሶማሊያ የአል-ሸባብ ማዕከል ስትሆን የአልቃይዳ አጋር የሆነው አልሸባብ በአፍሪካ ውስጥ በጣም አደገኛ ነው ተብሎ ይታሰባል። ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት በአሜሪካ የሚደገፉ የኢትዮጵያ ወታደሮች የእስልምና ፍርድ ቤቶች ሕብረትን ከሥልጣን ለማውረድ ዋና ከተማይቱን ሞቃዲሾን ከወረሩ በኋላ የታጣቂ እስልምና እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ ተንሰራፍቶ ይገኛል። የእስልምና ፍርድ ቤቶች ሕብረት መሸነፍ አልሸባብን እንዲጠናከር ረድቶታል፤ የአልሻባብ ታጣቂዎች "ወራሪዎቹን" ለማባረርም ቃል ገቡ። በአሁኑ ወቅት አልሸባብ በርካታ የሶማሊያ አካባቢዎችን ተቆጣጥሮ የሚገኝ ሲሆን መንግሥትን ለመጣል እና እስላማዊ አገዛዝ ለመመስረት በማለም ተደጋጋሚ ጥቃቶችን ይፈጽማል። በአውሮፓውያኑ 2012 እና 2016 ምርጫ አልሸባብ የጎሳ ሽማግሌዎችን ከእስልምና እምነት ውጪ በሆነው ምርጫ ተሳትፈዋል በሚል ካወገዛቸው በኋላ የዛተባቸው ሲሆን አልፎ ተርፎም የታገቱም ነበሩ። በአሁኑ ምርጫ የአልሸባብ ድምጽ ያልተሰማ ሲሆን ምክንያቱ አባላቱ ወይም ደጋፊዎቹ በድብቅ የፓርላማ መቀመጫ ፈልገው ከውስጥ ሆነው ሥርዓቱን ለመናድ ሊገቡ ስለሚችል ስጋት እንዳይፈጠር በሚል ነው። ይህንንም ጉዳይ የጎረቤት አገር ጂቡቲ ፕሬዝዳንት ኦማር ጉሌህ ስጋታቸውን በይፋ ገልጸዋል "አልሸባብ በተዘዋዋሪ የሚቆጣጠረው ፓርላማ እንዳይኖር እሰጋለሁ፤ ምክንያቱም የአንዳንድ የፓርላማ አባላትን ድጋፍ ሊገዙ ይችላሉ" ብለዋል። አንዳንድ ተንታኞች ፕሬዚዳንት ጉሌህ አልሸባብ ፓርላማውን በተዘዋዋሪ ይቆጣጠረዋል ማለታቸው የተጋነነ ነው ያሉ ሲሆን፣ ነገር ግን በሶማሊያ ውስጥ ትልቅ የፖለቲካ ኃይል ስለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም። ሶማሊያ ዲሞክራሲያዊ አገር ልትሆን ትችላለች? በሶማሊያ የፖለቲካ ሥልጣን ክፍፍል ሂደት ውስጥ ተጽእኖ ያላቸው ወገኖች በዚህ ዓመት ሕዝብ የሚመርጥበት ሥርዓት በዘንድሮው ምርጫ እንደሚዘረጉ ከረጅም ጊዜ በፊት ተስማምተው የነበረ ቢሆንም ቃላቸውን ሳይፈጽሙ ቀርተዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና አዲስ ሕገ መንግሥት በሕዝበ ውሳኔ ማጽደቅን ጨምሮ ለዚህ የሚያስፈልጉ ዋና ዋና መስፈርቶች ባለሟሟላታቸው ይህ የሚያስደንቅ አልነበረም። በርካታ ግዙፍ ፈተናዎች የሚገጥሙት የቀጣዩ መንግሥት ቀዳሚ ጉዳይ ምን ያህል እንደሚሆን ግልጽ አይደለም። | ሕዝቡ የማይመርጥበት የሶማሊያው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ ጎዳናዎች እሁድ በሚካሄደው ምርጫ በሚወዳደሩት ፕሬዝዳንታዊ ዕጩዎች ትላልቅ የማስታወቂያ ሰሌዳዎች ተንቆጥቁጣለች። በመኪኖች በተጨናነቀው የትራፊክ እንቅስቃሴም አላፊው አግዳሚው ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው ምርጫ ከመድረሱ በፊት የተሰቀሉትን ፖስተሮችን ይቃኛሉ። ነገር ግን ሕዝቡ አይመርጥም። ሕዝብ የማይመርጥበት ምርጫ እንዴት? ልትሉ ትችላላችሁ። ለዚህም ምክንያቱ ሶማሊያ ውስብስብ እና ቀጥተኛ ያልሆነ የፖለቲካ ሥርዓት ስለምትከተል እና የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ስለማይወዳደሩ ነው። ይልቁንም 275 አባላት ያሉት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የሚመረጡት በክልል ባለሥልጣናት በተሰየሙ የጎሳ የአገር ሽማግሌዎችና የሲቪክ ማኅበራት አባላት ነው። በተጨማሪም የሶማሊያን አምስት ክልላዊ መንግሥታት የሚወክል 54 አባላት ያሉት ከፍተኛ ምክር ቤት (ሴኔት) አለ። ከዚያም የሁለቱም ምክር ቤቶች የፓርላማ አባላት 16.3 ሚሊዮን የሚሆነውን የሶማሊያን ሕዝብ የሚመራውን ፕሬዚዳንት ይመርጣሉ። ፕሬዚዳንታዊ ዕጩዎቹ እነማን ናቸው? ሶማሊያ ለረጅም ጊዜ የተጓተተውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዛሬ እሁድ ግንቦት 07/2014 ዓ.ም. ታካሂዳለች። ይህም መጀመሪያ ሊደረግ ከታቀደው ከአንድ ዓመት በላይ ዘግይቶ ነው። በሥልጣን ላይ የሚገኙትን መሐመድ አብዱላሂ መሐመድ ወይም ፋርማጆን ጨምሮ በፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ለመወዳደር 39 ዕጩዎች ቀርበዋል። በአውሮፓውያኑ 1991 በሲያድ ባሬ የሚመራው የሶሻሊስት መንግሥት ከተገረሰሰ ወዲህ ከፍተኛው ለፕሬዝዳንትነት የሚወዳደሩ ዕጩዎች ቁጥር ነው ተብሏል። ከዕጩዎቹ መካከል ሁለቱ የቀድሞ ፕሬዝዳንቶች፣ ሻሪፍ ሼህ አህመድ እና ሐሰን ሼክ መሐሙድ እንዲሁም የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሐሰን አሊ ኬሬ ይገኙበታል። ሌላኛዋ ዕጩ ፋውዚያ ዩሱፍ አደም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ያገለገሉ ሲሆን፣ ብቸኛዋ ሴት ዕጩ ተወዳዳሪ ናቸው። የወቅቱ የሶማሊያ ከፊል ራስ ገዝ የፑንትላንድ ክልል ፕሬዝዳንት ሰኢድ አብዱላሂ ዴኒም ውድድሩን ተቀላቅለዋል። የሚመረጠው ፕሬዚዳንት ለአራት ዓመታት የሚያገለግል ሲሆን እንደገና መመረጥም ይችላል። ይሁን እንጂ ቀጥተኛ ባልሆነ የድምፅ አሰጣጥ ሥርዓት በአውሮፓውያኑ 2000 ከተጀመረ ወዲህ አንድም የሶማሊያ ፕሬዝዳንት በድጋሚ አልተመረጠም። ለምን ተራ ዜጎች አይመርጡም? ይህ ሁኔታ በሶማሊያ ያለውን የጎሳ ኃይል የሚያሳይ ነው። የምዕራባውያን አይነት ዲሞክራሲ ባልሰፈነበት ማኅበረሰብም የጀርባ አጥንት ናቸው። በአውሮፓውያኑ 1991 በሶማሊያ የማዕከላዊ መንግሥት መውደቅን ተከትሎ አገሪቱ መንግሥት አልባ ሆና የቆየች ሲሆን ይህንንም ክፍተት የጎሳ መሪዎች ሞልተውታል። በሶማሊያ ጎሳዎች መካከል ከፍተኛ ፉክክር ስላለ ሥርዓቱ በሥልጣን ክፍፍል ቀመር ላይ የተመሰረተ ሲሆን፣ አራቱ ትላልቅ ጎሳዎች እኩል ቁጥር ያላቸው የፓርላማ መቀመጫዎችን ሲይዙ ቀሪዎቹ ጎሳዎች አንድ ላይ ተጣምረው ግማሹ የፓርላማ መቀመጫ ይሰጣቸዋል። ይህም ሁኔታ የሶማሊያ ጎሳ ተወካዮች በአገሪቱ አድራጊ ፈጣሪ እንዲሁም የአገሪቱን መሪ ወደ ሥልጣን የሚያመጡ ኃያላን ያደርጋቸዋል። የሁለቱን ምክር ቤቶች ምርጫ ተከትሎ ወደ 300 የሚጠጉ የፓርላማ አባላት ቃለ መሃላ ፈፅመዋል። ምርጫዎቹ መጠነ ሰፊ ሙስና፣ ሥልጣንን አላግባብ የተጠቀሙበት እና የምርጫ ሕግጋት ችላ የተባሉበት ነው ተብሏል። በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ልዑካንን ለመግዛት በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ወጪ ተደርጓል ተብሎ ይታመናል። እንደ አለመታደል ሆኖ አገሪቱ ሙስናን የሚቆጣጠሩ ተቋማት የሏትም። ኳታር በሶማሊያ ፖለቲካ መድረክ ዋና ተዋናይ ነች። ተንታኞች እንደሚናገሩት በአውሮፓውያኑ 2017 የፕሬዚዳንት ፋርማጆ የምርጫ ዘመቻን ወቅት ኳታር በብቸኝነት ከፍተኛ ድጋፍ ያደረገች ሲሆን ከአስተዳሩም ጋር ጠበቅ ያለ ግንኙነት ነበራት። ለምን ይህን ያህል ጊዜ ዘገዬ? የፕሬዚዳንት ፋርማጆ የሥልጣን ወቅት በአውሮፓውያኑ የካቲት 2021 ቢጠናቀቅም በነበረው የፖለቲካ አለመግባባት በሥልጣን ላይ ቆይተዋል። ለፓርላማ አባላት የነበረው ምርጫ ዝግጅት አለመኖር ምርጫውን ያዘገየው ሲሆን እሳቸውም ሆነ ሕግ አውጪዎች የመምራት ሥልጣን ባይኖራቸውም እየመሩ እንዲቆዩ አድርጓቸዋል። የፓርላማ ምርጫው በመጨረሻ የተካሄደው በምዕራባውያን ለጋሾች ግፊት ነው። አሜሪካ የምርጫውን ሂደት እያዘገዩ ነው ያለቻቸውን ባለሥልጣናት ቪዛ አግዳለች ። ምርጫው ከታኅሣሥ እስከ መጋቢት ድረስ አራት ወራትን አስቆጥሯል። በግንቦት ወር አጋማሽ ምርጫው ካልተጠናቀቀ ለሶማሊያ የሚሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ ሊያቆም እንደሚችል ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) አስታውቋል። አዲሱ መንግሥት ሥልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ ድርቅን ጨምሮ የሶማሊያን ተግዳሮቶች መፍታት ይኖርበታል። ድርቁ ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ የተባባሰ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የረድዔት ድርጅቶች ረሃብ ሊከሰት እንደሚችል እያስጠነቀቁ ነው። በአሁኑ ወቅት ከ3.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን 1.4 ሚሊዮን ህጻናት ለከፍተኛ የምግብ እጥረት ተጋልጠዋል። ምዕራባውያን በሶማሊያ ያላቸው ፍላጎት ምንድን ነው? ምዕራባውያን ዋናው ጭንቀታቸው የታጣቂ እስላማዊ ቡድን እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ ማንሰራራት ነው። ሶማሊያ የአል-ሸባብ ማዕከል ስትሆን የአልቃይዳ አጋር የሆነው አልሸባብ በአፍሪካ ውስጥ በጣም አደገኛ ነው ተብሎ ይታሰባል። ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት በአሜሪካ የሚደገፉ የኢትዮጵያ ወታደሮች የእስልምና ፍርድ ቤቶች ሕብረትን ከሥልጣን ለማውረድ ዋና ከተማይቱን ሞቃዲሾን ከወረሩ በኋላ የታጣቂ እስልምና እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ ተንሰራፍቶ ይገኛል። የእስልምና ፍርድ ቤቶች ሕብረት መሸነፍ አልሸባብን እንዲጠናከር ረድቶታል፤ የአልሻባብ ታጣቂዎች "ወራሪዎቹን" ለማባረርም ቃል ገቡ። በአሁኑ ወቅት አልሸባብ በርካታ የሶማሊያ አካባቢዎችን ተቆጣጥሮ የሚገኝ ሲሆን መንግሥትን ለመጣል እና እስላማዊ አገዛዝ ለመመስረት በማለም ተደጋጋሚ ጥቃቶችን ይፈጽማል። በአውሮፓውያኑ 2012 እና 2016 ምርጫ አልሸባብ የጎሳ ሽማግሌዎችን ከእስልምና እምነት ውጪ በሆነው ምርጫ ተሳትፈዋል በሚል ካወገዛቸው በኋላ የዛተባቸው ሲሆን አልፎ ተርፎም የታገቱም ነበሩ። በአሁኑ ምርጫ የአልሸባብ ድምጽ ያልተሰማ ሲሆን ምክንያቱ አባላቱ ወይም ደጋፊዎቹ በድብቅ የፓርላማ መቀመጫ ፈልገው ከውስጥ ሆነው ሥርዓቱን ለመናድ ሊገቡ ስለሚችል ስጋት እንዳይፈጠር በሚል ነው። ይህንንም ጉዳይ የጎረቤት አገር ጂቡቲ ፕሬዝዳንት ኦማር ጉሌህ ስጋታቸውን በይፋ ገልጸዋል "አልሸባብ በተዘዋዋሪ የሚቆጣጠረው ፓርላማ እንዳይኖር እሰጋለሁ፤ ምክንያቱም የአንዳንድ የፓርላማ አባላትን ድጋፍ ሊገዙ ይችላሉ" ብለዋል። አንዳንድ ተንታኞች ፕሬዚዳንት ጉሌህ አልሸባብ ፓርላማውን በተዘዋዋሪ ይቆጣጠረዋል ማለታቸው የተጋነነ ነው ያሉ ሲሆን፣ ነገር ግን በሶማሊያ ውስጥ ትልቅ የፖለቲካ ኃይል ስለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም። ሶማሊያ ዲሞክራሲያዊ አገር ልትሆን ትችላለች? በሶማሊያ የፖለቲካ ሥልጣን ክፍፍል ሂደት ውስጥ ተጽእኖ ያላቸው ወገኖች በዚህ ዓመት ሕዝብ የሚመርጥበት ሥርዓት በዘንድሮው ምርጫ እንደሚዘረጉ ከረጅም ጊዜ በፊት ተስማምተው የነበረ ቢሆንም ቃላቸውን ሳይፈጽሙ ቀርተዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና አዲስ ሕገ መንግሥት በሕዝበ ውሳኔ ማጽደቅን ጨምሮ ለዚህ የሚያስፈልጉ ዋና ዋና መስፈርቶች ባለሟሟላታቸው ይህ የሚያስደንቅ አልነበረም። በርካታ ግዙፍ ፈተናዎች የሚገጥሙት የቀጣዩ መንግሥት ቀዳሚ ጉዳይ ምን ያህል እንደሚሆን ግልጽ አይደለም። | https://www.bbc.com/amharic/news-61441549 |
5sports
| በኮሮናቫይረስ ስጋት ካናዳ እራሷን ከጃፓኑ የኦሊምፒክ ውድድር አገለለች | በዚህ ዓመት ይካሄዳል ተብሎ ከሚጠበቀው የጃፓን ኦሊምፒክ ካናዳ እራሷን አገለለች። የጨዋታው ዋነኛ ተሳታፊ ከሚባሉት መካከል የሆነችው ካናዳ እራሷን በማግለሏ በውድድሩ መካሄድ ላይ ተጨማሪ ጥርጣሬ ጥሏል። ካናዳ ይህንን ውሳኔዋን ያሳወቀችው የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ለመጀመሪያ ጊዜ የኦሊምፒክ ውድድሩ ለሌላ ጊዜ ሊተላለፍ ይችላል በማለት ከተናገሩ በኋላ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ የአውስትራሊያ የኦሊምፒክ ቡድን እንዳለው አሁን ባለው ሁኔታ ውድድሩ በተያዘለት ጊዜ እንደማይካሄድ "ግልጽ እየሆነ በመምጣቱ" ተሳታፊ አትሌቶች ለቀጣዩ ዓመት እንዲዘጋጁ ተነግሯቸዋል። ጃፓን ለማስተናገድ ለዓመታት ስትዘጋጅለት የነበረው የ2020ው ኦሊምፒክ ውድድር ከአራት ወራት በኋላ በሐምሌ ወር ላይ ነበር የሚካሄደው። የካናዳ የኦሊምፒክና ፓራኦሊምፒክ ኮሚቴ ውሳኔውን በተመለከተ እንዳለው፤ ከውድድሩ ለመውጣት "አስቸጋሪ" ካለው ውሳኔ ላይ ከመድረሱ በፊት ከአትሌቶች፣ ከስፖርት ቡድኖችና ከካናዳ መንግሥት ባለስልጣናት ጋር መመካከሩን ገልጿል። ኮሚቴው ጨምሮም ለዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ ለዓለም አቀፉ የፓራኦሊምፒክ ኮሚቴና የዓለም የጤና ድርጅት የኦሊምፒክ ውድድሩ በአንድ ዓመት እንዲዘገይ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል። "ውድድሩን ለሌላ ጊዜ በማሸጋገር ሂደት ውስጥ የሚያጋጥመውን ውስብስብ ሁኔታን ብንረዳውም፤ ምንም ነገር ከአትሌቶቻችንና ከዓለም ሕዝብ ጤናና ደኅንነት የሚበልጥ አይሆንም" ብሏል የካናዳ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ ላይ። | በኮሮናቫይረስ ስጋት ካናዳ እራሷን ከጃፓኑ የኦሊምፒክ ውድድር አገለለች በዚህ ዓመት ይካሄዳል ተብሎ ከሚጠበቀው የጃፓን ኦሊምፒክ ካናዳ እራሷን አገለለች። የጨዋታው ዋነኛ ተሳታፊ ከሚባሉት መካከል የሆነችው ካናዳ እራሷን በማግለሏ በውድድሩ መካሄድ ላይ ተጨማሪ ጥርጣሬ ጥሏል። ካናዳ ይህንን ውሳኔዋን ያሳወቀችው የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ለመጀመሪያ ጊዜ የኦሊምፒክ ውድድሩ ለሌላ ጊዜ ሊተላለፍ ይችላል በማለት ከተናገሩ በኋላ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ የአውስትራሊያ የኦሊምፒክ ቡድን እንዳለው አሁን ባለው ሁኔታ ውድድሩ በተያዘለት ጊዜ እንደማይካሄድ "ግልጽ እየሆነ በመምጣቱ" ተሳታፊ አትሌቶች ለቀጣዩ ዓመት እንዲዘጋጁ ተነግሯቸዋል። ጃፓን ለማስተናገድ ለዓመታት ስትዘጋጅለት የነበረው የ2020ው ኦሊምፒክ ውድድር ከአራት ወራት በኋላ በሐምሌ ወር ላይ ነበር የሚካሄደው። የካናዳ የኦሊምፒክና ፓራኦሊምፒክ ኮሚቴ ውሳኔውን በተመለከተ እንዳለው፤ ከውድድሩ ለመውጣት "አስቸጋሪ" ካለው ውሳኔ ላይ ከመድረሱ በፊት ከአትሌቶች፣ ከስፖርት ቡድኖችና ከካናዳ መንግሥት ባለስልጣናት ጋር መመካከሩን ገልጿል። ኮሚቴው ጨምሮም ለዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ ለዓለም አቀፉ የፓራኦሊምፒክ ኮሚቴና የዓለም የጤና ድርጅት የኦሊምፒክ ውድድሩ በአንድ ዓመት እንዲዘገይ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል። "ውድድሩን ለሌላ ጊዜ በማሸጋገር ሂደት ውስጥ የሚያጋጥመውን ውስብስብ ሁኔታን ብንረዳውም፤ ምንም ነገር ከአትሌቶቻችንና ከዓለም ሕዝብ ጤናና ደኅንነት የሚበልጥ አይሆንም" ብሏል የካናዳ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ ላይ። | https://www.bbc.com/amharic/news-52000794 |
3politics
| የፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ የሰላም ተደራዳሪዎች ወደ ደቡብ አፍሪካ ማቅናታቸው ተገለጸ | በሰሜን ኢትዮጵያ የርስ በርስ ጦርነት እየተፋለሙ ያሉት የፌደራል መንግሥት እና የትግራይ ኃይሎች ወኪሎች ዛሬ ጥቅምት 14፣ 2015 ዓ.ም ለሚጀመረው የሰላም ንግግር ወደ ደቡብ አፍሪካ ማቅናታቸው ተገለጸ። የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሕይወት፣ በአፍሪካ ኅብረት በሚመራው የሰላም ንግግር ላይ የሚሳተፈው የትግራይ ልዑክ ቡድን ደቡብ አፍሪካ ደርሷል ሲሉ ትናንት እሁድ ጥቅምት 13 ምሽት ላይ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስታውቀዋል። በተመሳሳይ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ ረፋድ ጥቅምት 14/2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ በሰላም ንግግሩ ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን ዛሬ ጠዋት ወደ ደቡብ አፍሪካ አምርቷል ብሏል። ሁለቱ ኃይሎች ልዩነቶቻቸውን በንግግር ለመፍታት በጠረጴዛ ዙሪያ የሚቀመጡት በትግራይ የሚካሄደው ጦርነት ተጠናክሮ በቀጠለበት ወቅት ነው። ባለፉት ቀናት የፌደራሉ መንግሥት ጥምር ኃይሎች በርካታ ከተማዎችን እና የትግራይ አካባቢዎችን ከትግራይ ኃይሎች አስለቅቋል የሚሉ ዘገባዎች እየወጡ ነው። ዛሬ ሰኞ ጥቅምት 14/2015 ዓ. ም. ጀምሮ በአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት በፌደራል መንግሥቱ እና በሕወሓት አመራሮች መካከል የሰላም ውይይት ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል። የአፍሪካ ኅብረት ተፋላሚ ኃይሎች ግጭት አቁመው ልዩነቶቻቸው በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲፈቱ ተደጋጋሚ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። ሁለቱ ተፋላሚ ኃይሎች ሊደራደሩባቸው የሚችሏቸውን ጉዳዮች በይፋ ባይገልጹም፤ የአፍሪካ ኅብረት እና ምዕራባውያን ግን ለግጭቱ ፖለቲካዊ መፍትሄ ለመስጠት ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል። ፕሮፌሰር ክንደያ፣ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር በሚደረገው ውይይት የትግራይ ኃይሎች የሚያነሷቸው አንገብጋቢ ጉዳዮች ግጭት በአስቸኳይ ማስቆም፣ ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብ እና የኤርትራ ኃይሎች ከትግራይ ማስወጣት የሚሉት መሆናቸውን አስታውቀዋል። የፌደራል መንግሥት ግን ከዚህ ቀደም "ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ" ለንግግር ዝግጁ መሆኑን ሲገልጽ ቆይቷል። ዛሬ በደቡብ አፍሪካ የሚጀመረው የሰላም ንግግር ለሁሉም ዜጎች መረጋጋትን የሚመልስ ነው ስትል አሜሪካ ያላትን ተስፋ ገልጻለች። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ጥቅምት 11፣ 2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ የሰላም ውይይቱን አሜሪካ እንደምትደግፍ ገልጾ፤ ድርድሩ በኢትዮጵያ ያለውን ውጊያ ይገታል ሲል ያለውን ተስፋ ጨምሮ ገልጿል። “ደቡብ አፍሪካ ይህንን ውይይት ለማስተናገድ በመፍቀዷ እናመሰግናለን። የአፍሪካ ኅብረት ልዩ ልዑክ ኦሉሴጎን ኦባሳንጆን እንዲሁም የአፍሪካ ኅብረት ፓናል አባል የሆኑትን ፑምዚሌ ማልምቦ ንግቹካ እና ኡሁሩ ኬንያታ የሰላም ስምምነት ላይ እንዲደረስ የሚያደርጉትን ጥረት እንደግፋለን” ይላል መግለጫው። በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ድረ ገጽ ላይ የወጣው መግለጫ “ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን መስከረም ላይ በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንዳሉት፣ በአፍሪካ ኅብረት ፓናል አባላቱ አማካይነት የሚደረሰው የሰላም ስምምነት፣ በኢትዮጵያ ያለውን ውጊያ ይገታል። ለሁሉም ዜጎች መረጋጋትንም ይመልሳል” ሲልም አክሏል። የፌደራሉ መንግሥት ከትግራይ ኃይሎች ጋር የሚነጋገሩ አባላት ከዚህ ቀደም ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ይህ ተደራዳሪ ቡድን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን የሚመራ ሲሆን ሰባት አባላትን ያካተተ ነው። ከአቶ ደመቀ በተጨማሪ የፌደራል መንግሥቱን የሚወክሉት የፍትሕ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር)፣ ብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ተመስገን ጥሩነህ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንት ጉዳዮች አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ የመከላከያ ሠራዊት የመረጃ ደኅንነት ኃላፊ ሌ/ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ፣ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ጌታቸው ጀምበር (ዶ/ር) እና በብልጽግና ፓርቲ የዴሞክራሲ ማዕከል ዘርፍ ውስጥ በከፍተኛ ኃላፊነት እየሰሩ የሚገኙት አምባሳደር ሐሰን አብዱልቃድር ናቸው። የትግራይ ኃይሎች በበኩላቸው ሁለት ተወካዮቻቸውን ለድርድር እንደሚልኩ ከዚህ ቀደም ገልጸው ነበር። የመጀመሪያው የህወሓት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና የፓርቲው ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ሲሆኑ ሁለተኛው ደግሞ የትግራይ ኃይሎችን ከሚመሩት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች መካከል አንዱ የሆኑት ጀኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳይ ናቸው። | የፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ የሰላም ተደራዳሪዎች ወደ ደቡብ አፍሪካ ማቅናታቸው ተገለጸ በሰሜን ኢትዮጵያ የርስ በርስ ጦርነት እየተፋለሙ ያሉት የፌደራል መንግሥት እና የትግራይ ኃይሎች ወኪሎች ዛሬ ጥቅምት 14፣ 2015 ዓ.ም ለሚጀመረው የሰላም ንግግር ወደ ደቡብ አፍሪካ ማቅናታቸው ተገለጸ። የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሕይወት፣ በአፍሪካ ኅብረት በሚመራው የሰላም ንግግር ላይ የሚሳተፈው የትግራይ ልዑክ ቡድን ደቡብ አፍሪካ ደርሷል ሲሉ ትናንት እሁድ ጥቅምት 13 ምሽት ላይ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስታውቀዋል። በተመሳሳይ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ ረፋድ ጥቅምት 14/2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ በሰላም ንግግሩ ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን ዛሬ ጠዋት ወደ ደቡብ አፍሪካ አምርቷል ብሏል። ሁለቱ ኃይሎች ልዩነቶቻቸውን በንግግር ለመፍታት በጠረጴዛ ዙሪያ የሚቀመጡት በትግራይ የሚካሄደው ጦርነት ተጠናክሮ በቀጠለበት ወቅት ነው። ባለፉት ቀናት የፌደራሉ መንግሥት ጥምር ኃይሎች በርካታ ከተማዎችን እና የትግራይ አካባቢዎችን ከትግራይ ኃይሎች አስለቅቋል የሚሉ ዘገባዎች እየወጡ ነው። ዛሬ ሰኞ ጥቅምት 14/2015 ዓ. ም. ጀምሮ በአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት በፌደራል መንግሥቱ እና በሕወሓት አመራሮች መካከል የሰላም ውይይት ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል። የአፍሪካ ኅብረት ተፋላሚ ኃይሎች ግጭት አቁመው ልዩነቶቻቸው በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲፈቱ ተደጋጋሚ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። ሁለቱ ተፋላሚ ኃይሎች ሊደራደሩባቸው የሚችሏቸውን ጉዳዮች በይፋ ባይገልጹም፤ የአፍሪካ ኅብረት እና ምዕራባውያን ግን ለግጭቱ ፖለቲካዊ መፍትሄ ለመስጠት ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል። ፕሮፌሰር ክንደያ፣ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር በሚደረገው ውይይት የትግራይ ኃይሎች የሚያነሷቸው አንገብጋቢ ጉዳዮች ግጭት በአስቸኳይ ማስቆም፣ ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብ እና የኤርትራ ኃይሎች ከትግራይ ማስወጣት የሚሉት መሆናቸውን አስታውቀዋል። የፌደራል መንግሥት ግን ከዚህ ቀደም "ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ" ለንግግር ዝግጁ መሆኑን ሲገልጽ ቆይቷል። ዛሬ በደቡብ አፍሪካ የሚጀመረው የሰላም ንግግር ለሁሉም ዜጎች መረጋጋትን የሚመልስ ነው ስትል አሜሪካ ያላትን ተስፋ ገልጻለች። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ጥቅምት 11፣ 2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ የሰላም ውይይቱን አሜሪካ እንደምትደግፍ ገልጾ፤ ድርድሩ በኢትዮጵያ ያለውን ውጊያ ይገታል ሲል ያለውን ተስፋ ጨምሮ ገልጿል። “ደቡብ አፍሪካ ይህንን ውይይት ለማስተናገድ በመፍቀዷ እናመሰግናለን። የአፍሪካ ኅብረት ልዩ ልዑክ ኦሉሴጎን ኦባሳንጆን እንዲሁም የአፍሪካ ኅብረት ፓናል አባል የሆኑትን ፑምዚሌ ማልምቦ ንግቹካ እና ኡሁሩ ኬንያታ የሰላም ስምምነት ላይ እንዲደረስ የሚያደርጉትን ጥረት እንደግፋለን” ይላል መግለጫው። በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ድረ ገጽ ላይ የወጣው መግለጫ “ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን መስከረም ላይ በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንዳሉት፣ በአፍሪካ ኅብረት ፓናል አባላቱ አማካይነት የሚደረሰው የሰላም ስምምነት፣ በኢትዮጵያ ያለውን ውጊያ ይገታል። ለሁሉም ዜጎች መረጋጋትንም ይመልሳል” ሲልም አክሏል። የፌደራሉ መንግሥት ከትግራይ ኃይሎች ጋር የሚነጋገሩ አባላት ከዚህ ቀደም ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ይህ ተደራዳሪ ቡድን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን የሚመራ ሲሆን ሰባት አባላትን ያካተተ ነው። ከአቶ ደመቀ በተጨማሪ የፌደራል መንግሥቱን የሚወክሉት የፍትሕ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር)፣ ብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ተመስገን ጥሩነህ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንት ጉዳዮች አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ የመከላከያ ሠራዊት የመረጃ ደኅንነት ኃላፊ ሌ/ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ፣ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ጌታቸው ጀምበር (ዶ/ር) እና በብልጽግና ፓርቲ የዴሞክራሲ ማዕከል ዘርፍ ውስጥ በከፍተኛ ኃላፊነት እየሰሩ የሚገኙት አምባሳደር ሐሰን አብዱልቃድር ናቸው። የትግራይ ኃይሎች በበኩላቸው ሁለት ተወካዮቻቸውን ለድርድር እንደሚልኩ ከዚህ ቀደም ገልጸው ነበር። የመጀመሪያው የህወሓት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና የፓርቲው ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ሲሆኑ ሁለተኛው ደግሞ የትግራይ ኃይሎችን ከሚመሩት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች መካከል አንዱ የሆኑት ጀኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳይ ናቸው። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cgxv4qge5e2o |
5sports
| እውቁ የቴኒስ ተጫዎች ጆኮቪች ከአውስትራሊያ ተባረረ | የዓለማችን ቁጥር አንድ የሜዳ ቴኒስ ኮኮብ ኖቫክ ጆኮቪች በአውስትራሊያ ለመቆየት ባደረገው የመጨረሻ ፍርድ ቤት ክርክር ተረትቶ አገሪቱን ለቆ እንዲወጣ ተደረገ። ክትባት ለመቀበል አሻፈረኝ ያለው የሜዳ ቴኒስ ተጫዋቹ፤ የአገሪቱ መንግሥት "በጤና እና ባልተገባ ስነምግባር" ምክንያት ቪዛውን መሰረዙን ተከትሎ ጆኮቪች ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ቢወስደውም ፍርድ ቤቱም ይግባኙን ውድቅ አርጎበታል። በውሳኔው "በጣም ቅር ብሎኛል" ያለው ጆኮቪች ውሳኔው ተቀበሎ ወደ ዱባይ አቅንቷል። አገሩ ሰርቢያ 'በአውስትራልያ ኦፕን' የቴኒስ ውድድር ላይ ተሳታፊ እንዲሆን ያደረገችው ጥረትም ፍሬ አልባ ሆኗል። የጆኮቪች ደጋፊዎች ከውድድሩ የመክፈቻ ጨዋታውን አንድ ቀን ቀደም ብሎ የተወሰነውን ውሳኔ ከችሎቱ ውጪ ሆነው በቁዘማ ተከታትለዋል። ከደጋፊዎቹ መካከል አንዷ በውድድሩ ላይ የዚህ ዝነኛ ተጫዎች አለመኖር የእረፍት ጊዜዋን "ባዶ" እንደሚያደርግባት ተናግራለች። የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን "ድንበሮቻችንን ለማጠናከር እና አውስትራሊያውያንን ለመጠበቅ የተደረገ ውሳኔ ነው" ሲሉ ውሳኔውን በአውንታ መቀበላቸው ገልጸዋል። ሆኖም ጠቅላይ ሚንስትሩ እና አስተዳደራቸው የጆኮቪችን ጉዳያ የያዙበት መንገድ በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ እያስተቻቸው ነው። የጆኮቪች ጉዳይ መነሻ የአውስትራሊያ ኢሚግሬሽን ሚኒስትር አሌክስ ሃውክ ስልጣናቸውን ተጠቅመው ቪዛውን ከሰረዙ በኋላ ነው። ምክንያት ያሉት ደግሞ በአገሪቱ የፀረ-ክትባት እንቅስቃሴን ሊያስፋፋ የሚችል ስሜት አንጸባርቋል በሚል ነው። ትላንት እሁዱ በተደረገው የፍርድ ቤት ችሎት የጆኮቪች ጠበቃ ተጫዋቹን ቪዛ ለመቀማት በመንግስት የተሰጡት ማብራሪያዎች ምክንያታዊ አይደሉም ያሉ ሲሆን የቴኒስ ኮከቡን ከአገር ማባረር የፀረ-ክትባት እንቅስቃሴን ያባብሳል ሲሉ አስረድተዋል። ዕውቁ ጆኮቪች በመጀመሪያ በፈረንጆቹ ታህሳስ ወር አጋማሽ ላይ በኮቪድ መያዙ ተረጋግጦ ነበር። ሆኖም ከዛ በኋላ በአውስትራሊያ የቴኒስ አስተዳደር እና በቪክቶሪያ የግዛት አስተዳደር ወደ አውስትራሊያ መግባት እንዲችል ፍቃድ ተሰጥቶት ነበር። ሆኖም የአውስትራሊያ የድንበር ዘብ የፌደራል የኮሮናቫይረስ መስፈርቶችን አላሟላም በሚል በፈረንጆቹ ጥር መግቢያ ላይ ቪዛው ተሰርዟል። የጠቅላይ ሚኒስትር ሞሪሰን መንግሥት "የአገሪቱን የግዛት አንድነት ለመጠበቅ አስፈላጊ የሆኑ ውሳኔዎች እና እርምጃዎችን ለመውሰድ ተዘጋጅቷል" ብሏል። ሆንም የተቃዋሚው ሌበር ፓርቲ አመራር እና ሴናተር የሆኑት ክሪስቲና ኬኔሊ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጆኮቪች ጉዳይን በተሳሳተ መንገድ በመምራት እራሳቸውን "በዓለም ፊት መሳቂያ" አድርገዋል ሲሉ ተችተዋቸዋል። | እውቁ የቴኒስ ተጫዎች ጆኮቪች ከአውስትራሊያ ተባረረ የዓለማችን ቁጥር አንድ የሜዳ ቴኒስ ኮኮብ ኖቫክ ጆኮቪች በአውስትራሊያ ለመቆየት ባደረገው የመጨረሻ ፍርድ ቤት ክርክር ተረትቶ አገሪቱን ለቆ እንዲወጣ ተደረገ። ክትባት ለመቀበል አሻፈረኝ ያለው የሜዳ ቴኒስ ተጫዋቹ፤ የአገሪቱ መንግሥት "በጤና እና ባልተገባ ስነምግባር" ምክንያት ቪዛውን መሰረዙን ተከትሎ ጆኮቪች ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ቢወስደውም ፍርድ ቤቱም ይግባኙን ውድቅ አርጎበታል። በውሳኔው "በጣም ቅር ብሎኛል" ያለው ጆኮቪች ውሳኔው ተቀበሎ ወደ ዱባይ አቅንቷል። አገሩ ሰርቢያ 'በአውስትራልያ ኦፕን' የቴኒስ ውድድር ላይ ተሳታፊ እንዲሆን ያደረገችው ጥረትም ፍሬ አልባ ሆኗል። የጆኮቪች ደጋፊዎች ከውድድሩ የመክፈቻ ጨዋታውን አንድ ቀን ቀደም ብሎ የተወሰነውን ውሳኔ ከችሎቱ ውጪ ሆነው በቁዘማ ተከታትለዋል። ከደጋፊዎቹ መካከል አንዷ በውድድሩ ላይ የዚህ ዝነኛ ተጫዎች አለመኖር የእረፍት ጊዜዋን "ባዶ" እንደሚያደርግባት ተናግራለች። የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን "ድንበሮቻችንን ለማጠናከር እና አውስትራሊያውያንን ለመጠበቅ የተደረገ ውሳኔ ነው" ሲሉ ውሳኔውን በአውንታ መቀበላቸው ገልጸዋል። ሆኖም ጠቅላይ ሚንስትሩ እና አስተዳደራቸው የጆኮቪችን ጉዳያ የያዙበት መንገድ በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ እያስተቻቸው ነው። የጆኮቪች ጉዳይ መነሻ የአውስትራሊያ ኢሚግሬሽን ሚኒስትር አሌክስ ሃውክ ስልጣናቸውን ተጠቅመው ቪዛውን ከሰረዙ በኋላ ነው። ምክንያት ያሉት ደግሞ በአገሪቱ የፀረ-ክትባት እንቅስቃሴን ሊያስፋፋ የሚችል ስሜት አንጸባርቋል በሚል ነው። ትላንት እሁዱ በተደረገው የፍርድ ቤት ችሎት የጆኮቪች ጠበቃ ተጫዋቹን ቪዛ ለመቀማት በመንግስት የተሰጡት ማብራሪያዎች ምክንያታዊ አይደሉም ያሉ ሲሆን የቴኒስ ኮከቡን ከአገር ማባረር የፀረ-ክትባት እንቅስቃሴን ያባብሳል ሲሉ አስረድተዋል። ዕውቁ ጆኮቪች በመጀመሪያ በፈረንጆቹ ታህሳስ ወር አጋማሽ ላይ በኮቪድ መያዙ ተረጋግጦ ነበር። ሆኖም ከዛ በኋላ በአውስትራሊያ የቴኒስ አስተዳደር እና በቪክቶሪያ የግዛት አስተዳደር ወደ አውስትራሊያ መግባት እንዲችል ፍቃድ ተሰጥቶት ነበር። ሆኖም የአውስትራሊያ የድንበር ዘብ የፌደራል የኮሮናቫይረስ መስፈርቶችን አላሟላም በሚል በፈረንጆቹ ጥር መግቢያ ላይ ቪዛው ተሰርዟል። የጠቅላይ ሚኒስትር ሞሪሰን መንግሥት "የአገሪቱን የግዛት አንድነት ለመጠበቅ አስፈላጊ የሆኑ ውሳኔዎች እና እርምጃዎችን ለመውሰድ ተዘጋጅቷል" ብሏል። ሆንም የተቃዋሚው ሌበር ፓርቲ አመራር እና ሴናተር የሆኑት ክሪስቲና ኬኔሊ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጆኮቪች ጉዳይን በተሳሳተ መንገድ በመምራት እራሳቸውን "በዓለም ፊት መሳቂያ" አድርገዋል ሲሉ ተችተዋቸዋል። | https://www.bbc.com/amharic/60020796 |
5sports
| ለቶኪዮ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያ ዝግጅት ምን ይመስላል? | ኢትዮጵያ በቶኪዮ ኦሎምፒክ ከአትሌቲክሱ በተጨማሪ በውሃ ዋና፣ በብስክሌት ውድድር እንዲሁም ለመጀመሪያ ጊዜ በቴኳንዶ ውድድር ትወከላለች። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 35 አትሌቶችን ይዞ ወደ ቶኪዮ የሚያመራ ሲሆን አትሌቶች በ7 የተለያዩ ርቀቶች ተወዳዳሪ ሆነው ይቀርባሉ። | ለቶኪዮ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያ ዝግጅት ምን ይመስላል? ኢትዮጵያ በቶኪዮ ኦሎምፒክ ከአትሌቲክሱ በተጨማሪ በውሃ ዋና፣ በብስክሌት ውድድር እንዲሁም ለመጀመሪያ ጊዜ በቴኳንዶ ውድድር ትወከላለች። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 35 አትሌቶችን ይዞ ወደ ቶኪዮ የሚያመራ ሲሆን አትሌቶች በ7 የተለያዩ ርቀቶች ተወዳዳሪ ሆነው ይቀርባሉ። | https://www.bbc.com/amharic/news-57913705 |
5sports
| “ኢትዮጵያውያን በኳታሮች ዘንድ ይከበራሉ” - የዓለም ዋንጫ ዶሃ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዐይን | ግሩም ሰይፉ ጋዜጠኛ ነው። አዲስ አድማስ ለተሰኘው ጋዜጣ ስፖርታዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮችን በመፃፍ ይታወቃል። ግሩም የኳታር የዓለም ዋንጫ ዝግጅትን ለመታደም ወደ ዶሃ ያቀናው ከመክፈቻው ጥቂት ቀናት ቀድሞ ነው። ዶሃ ከአዲስ አበባ 2200 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ ትገናለች። የኢትዮጵያ አየር መንገደ እና ኳታር ኤርዌይስ በየቀኑ መንገደኞችን ያመላልሳሉ። ግሩም፤ ነፋሻማዋን አዲስ አበባ ለቆ ወደ ዶሃ ሲያመራ የጠበቀው የግንቦት ሃሩር ነው። ነገር ግን ይህ ወቅት ለኳታሮች ቀዝቃዛው ወር ነው። “ዶሃ የቀትር ፀሐይ የሚባል የለም” ይላል። ምክንያቱም ቀኑን ሙሉ የዶሃን አሸዋማ መሬት የሚቀጠቅጠው ፀሐይ ሃሩር ነው። ኳታር፤ በሜትሬዎሎጂ ዘገባ አገላለፅ “በአብዛኛው ፀሐያማ” ናት። በአብዛኛው ከማለት ከንጋት እስከ ምሽት ማለት ሳይቀል አይቀርም። አሁን ባለው የአገሪቱ የአየር ሁኔታ ዝቅተኛው የሚባለው 23 ድግሪ ሴንትግሪድ የሚጀምረው ለሊት 10 ሰዓት ገደማ ነው። ዎርልድ ፖፑሌሽን ሪቪው የተሰኘው ድረ-ገፅ የኳታር ሕዝብ ብዛት በዚህ ዓመት 2.7 ሚሊዮን ይገመታል ይላል። ከእነዚህ መካከል ካታሪ የሚባሉት አረቦች 15 በመቶውን ይይዛሉ። ሕንዳዊያን፣ ፊሊፒናውያን እንዲሁም ሌሎች የእስያ አገራት ዜጎች ኑሯቸውን በኳታር ይኖራሉ። ከዚህ ባሻገር በርካታ ኢትዮጵያዊያን፣ ኤርትራዊያን እና ኬንያዊያን በዋና ከተማዋ ዶሃ እንዲሁም በአር ራያን ይገኛሉ። በነዳጅ ሃብት የበለፀገችው ኳታር እነሆ በአረቡ የዓለም ሲዘጋጅ የመጀመሪያው የሆነውን የዓለም ዋንጫ በማስተናገድ ላይ ትገኛለች። ግሩም፤ ካሜሩን ከሰርቢያ የሚያደርጉትን የቀን 7 ሰዓት የምድብ ጨዋታ ታድሞ ለመዘገብ እየተጓዘ ሳለ ነው በስልክ ያገኘነው። በየገባህበት ሥፍራ ሁሉ የአየር ማጤዣ ተገጥሟል የሚለው ግሩም፣ ይህ ቴክኖሎጂ ባይኖር ኳታር ለኑሮ ከባድ ትሆን እንደነበር ያምናል። “አሁን ለምሳሌ በአገሩ ሰዓት አቆጣጠር 5 ሰዓት ከምናምን ነው። እኛ አገር ግንቦት ወር ላይ ያለው የሚያማርረው ሙቀት ነው አሁን እዚህ ያለው።” ግሩም የኳታር ነዋሪዎችን ስለአየር ሁኔታው ሲጠይቃቸው “በብርድ ወቅት መጣህ” በሚል ዓይን እያዩት “ኧረ እንዲያውም ይሄ እኮ ቀዝቃዛው ጊዜ ነው” ይሉታል። ኳታር፤ ለዚህ ነው ይህንን ወቅት ለዓለም ዋንጫ የመረጠችው እንጂ ለወትሮው የዓለም ዋንጫ በሰኔ ነበር የሚዘጋጀው። ከፋርስ ባሕረ ሰላጤ የሚነሳው ነፋስ የኳታር ምሽትን ቀዝቀዝ አድርጎታል። ኳታር፤ ይህን የዓለም ዋንጫ ስታዘጋጅ ከምዕራቡ ዓለም ከፍተኛ ተቃውሞ ደርሶባት ነበር። አገሪቱ የሰብዓዊ መብት አይከበርባትም፣ ስታድየሞቹ ሲታነፁ በርካታ የጉልበት ሠራተኞች ሞተዋል፣ የአየር ሁኔታው ምቹ አይደለም. . . ብቻ ብዙ ነቀፋ አስተናግዳለች። ነገር ግን ጋዜጠኛ ግሩም ይህ ነቀፋ ተጋኗል የሚል እምነት አለው። “የኳታር ዜጎች በጣም ሰላምተኞች ናቸው። እንግዳ ተቀባይነታቸውን ማየት ችያለሁ። በአረቡ ዓለም መዘጋጀቱ የአረቡ የዓለም ለእግር ኳስ ያለውን ፍቅር ለማሳየት ልዩ አጋጣሚ ነው” ይላል። እንደሱ አመለካከት ዶሃ ወደፊት ልክ እንደ ዱባይ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚመጡ ጎብኚዎች የምታስናግድ መናኸሪያ እንደምትሆን አምነት አለው። ግሩም፤ በዶሃ በተዘዋወረባቸው ቦታዎች በርካታ ኢትዮጵያውያን ኑሮን ለማሸነፍ በተለያየ ሥራ ተሠማርተው ሲተጉ አይቷል። “ስታድየሞች ውስጥ በጎ ፈቃደኛ ኢትዮጵያውያን አግኝቻለሁ። አንድ የሥነ-ጥበብ ባለሙያ ኢትዮጵያዊም ተዋውቄያለሁ። በዓለም ዋንጫው ከትላልቅ የብሮድካስት ኩባንያዎች ጋር የሚሠራ ኢትዮጵያዊም ማግኘት ችያለሁ።” ጋዜጠኛው ባለኝ መረጃ መሠረት ከ20 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ኳታር ውስጥ ይኖራሉ ይላል። ስለአገሪቱ የተለያዩ መረጃዎችን የሚያወጣው ‘ኦንላይን ካታር’ የተሰኘው ገፅ ቢያንስ 25 ሺህ ኢትዮጵያዊያን እንደሚገኙ አስፍሯል። “በቤት ሠራተኝነት የሚሠሩ አሉ። የሚማሩ አሉ። የሕንፃ ግንባታ ባለሙያዎች፤ የታክሲ ሾፌሮች አሉ። በርካታ የኢትዮጵያ ሬስቶራንቶች ያሉበት አንድ አካባቢ አለ። አዲስ አበባ የሚል ስያሜ ያለው ፀጉር ቤት አይቻለሁ። እኔ ከጎበኘኋቸው ሬስቶራንቶች በአንዱ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ተሰባስበው አይቻለሁ።” ግሩም፤ “ኢትዮጵያውያን በኳታሮች ዘንድ ይከበራሉ። “የሥራ ሰዎች ናቸው ይባላሉ” ይላል። ጋዜጠኛ ግሩም ከዚህ ቀደም ወደ ደቡብ አፍሪካ እንዲሁም ሩሲያ ተጉዞ የዓለም ዋንጫን መታደም ችሏል። ነገር ግን የዶሃው በብዙ መልኩ እንደሚለይ ይገልጻል። አንደኛው ምክንያት ስታድየሞቹ የተቀራረቡ በመሆናቸው እሱና የሙያ አጋሮቹ በአንድ ቀን የተለያዩ ጨዋታዎችን መታደም መቻላቸው ነው። ለምሳሌ በሩሲያው የዓለም ዋንጫ ከዋና ከተማዋ ሞስኮው ወደ ሶቺ ለመሄድ 72 ሰዓታትን በባቡር ተጉዞ ነበር። አልፎም ከዚህ በፊት ከተመለከታቸው የዓለም ዋንጫዎች በተለየ በምድብ ጨዋታዎች የታየው ፉክክር፣ ተመልካቾች ብዛት፣ የስታድየሞቹ ልዩ ‘ዲዛይን’ ይህንን የዓለም ዋንጫ “ለየት አድርጎብኛል” ባይ ነው። መስከረም ዘውዴ በኳታር ከ15 ዓመታት በላይ ኖራለች። ዋና ከተማዋ ዶሃን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ተዘዋውራ ሠርታለች። አሁን ዶሃ ውስጥ አቢሲኒያ-ቢሾፍቱ የተሰኘ የቤተሰብ ሬስቶራንት ታስዳድራለች። የመስከረም ሬስቶራንት ከሰሞኑ ከተለያዩ ክፍለ ዓለማት በሚመጡ ተጠቃሚዎች መሞላቱን “ዕድሜ ለዓለም ዋንጫ” በሚመስል አንድምታ ትናገራለች። በርካታ ኢትዮጵያውያን እንግዶች፣ ኤርትራውያን፣ ሱዳናውያንን ጨምሮ የበርካታ አገራት ዜጎች ምግብ ቤቷን እንደሚጎበኙ ጠቅሳለች። ነገር ግን ብዙውን ጊዜ ኢትዮጵያውያን ተጠቃሚዎች የሌሎች አገራት ዜጎች ጓደኞቻቸውን ይዘው መጥተው የአገራቸውን ገበታ ሲቋደሱ ስታይ ደስ ይላታል። መስከረም ለአራት ዓመታት ያክል ያስተዳደረችው አቢሲኒያ-ቢሾፍቱ ሬስቶራንት፣ ዶሃ ውስጥ ኔአዘር የተሰኘ አካባቢ ይገኛል። ይህ መንደር በርካታ ኢትዮጵያውያን የሚኖሩበት ነው። መስከረም የዓለም ዋንጫ መጣ ሲባል ምናልባት አንዳንድ ቦታዎች ላይ ከመጠን በላይ መጨናነቅ ይኖራል የሚል ፍራቻ ነበራት። ነገር ግን ይህ በየአራት ዓመት የሚዘጋጅ ውድድር ደስታን ይዞላት ብቅ ብሏል። “ሰዉ በጣም ደስተኛ ነው። በነፃነት ነው የሚንቀሳቀሰው። ከዚህ በፊት ከምናውቀው የተለየ ነገር እያየን ነው። ሁሉም ሰው በሥነ-ሥርዓት ይስተናገዳል። ስሜቱም ለየት ይላል።” አቢሲኒያ-ቢሾፍቱ ሬስቶራንት የ32 አገራት ባንዲራዎች ይውለበለቡበታል። በዓለም ዋንጫ እየተሳተፉ ያሉ 32 አገራትን የሚወክል ነው። ሬስቶራንቱ ካለበት ቦታ ራቅ ብሎ ያለው ድባብ ልዩ እንደሆነ የምትናገረው መስከረም፣ እግር ኳስ እንዲህ ሰውን ሲያቀራርብ ማየቷ አስደንቋታል። “በቃ ኳስ ማለት ይሄ ነው። እግር ኳስ የዓለም ሰዎችን የሚያቀራርብ እንደሆነ ነው የገባኝ። በግሌ የተረዳሁት ይህንን ነው። በጣም ነው ደስ የሚለው። በጣም!” መስከረም፤ ሬስቶራንቱ ከሰሞኑ በደንበኞች በመጨናነቁ እንጂ በስታድየሞች ዙሪያ የኢትዮጵያ ገበታ ለተጠቃሚዎች አስባ ነበር። ለወትሮው ሙቀቷ ነፍስን የሚያስጨንቀው ኳታር ከሰሞኑ ቀዝቀዝ ማለቷ ለመስከረም አስደንቋታል። እንጂ የዶሃ ሙቀት የሚቋቋሙት አይደለም ትላለች። ለበርካታ ዓመታት በባሕረ ሰላጤዋ አገር የኖረችው መስከረም ኳታር ወግ አጥባቂ የአረብ አገር እንደመሆኗ እግር ኳስ ለመታደም የሚመጡ ሰዎች እንደልባቸው ላይዝናኑ ይችላሉ የሚል ስጋት ነበራት። ኳታር ስታዲዬሞች ውስጥ የአልኮል መጠጥ እንዳይሸጥ ከልክላለች። ነገር ግን በምሽት ክለቦች ሜክሲኮ እና የብራዚል ዜጎች ሲጨፍሩ ነው የከረሙት ትላለች መስከረም። ከሌሎች አገራት የሚመጡ ሰዎች የተለያየ ባሕርይ ይዘው ነው የሚመጡት። ነገር ግን አብዛኛዎቹ ጎብኚዎች ደስተኛ ሆነው በነፃነት ሲንቀሳቀሱ፣ ሲጫወቱ፣ ሲጨፍሩ ተመልክታለች። “አይቼው የማላውቀው ነው። በእውነት የተለየ ስሜት ፈጥሮብኛል።” ኢትዮጵያዊው አብዱልሃኪም አብዱልራህማን፤ በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ መኖር ከጀመረ አምስት ዓመታት አልፎታል። አብዱልሃኪም፤ ከዓለም ዋንጫው በጎ ፈቃደኞች አንዱ ነው። ወጣቱ፤ ከዶሃ ግዙፍ ስታዲዮሞች አንዱ በሆነው ኻሊፋ ዓለም አቀፍ ስታዲዬም የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። አብዱልሃኪም ዋነኛ ሥራው ጨዋታ ለመታደም ለሚመጡ ተመልካቾች አቅጣጫ መጠቆም፣ የሚያስፈልጋቸውን ነገር በመርዳት የበኩሉን ይወጣል። አልፎም በአገሪቱ ሕግ መሠረት የማይቻሉ ነገሮችን ጎብኚዎች ሲፈጽሙ ከተገኙ በማስረዳት የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱን ይወጣል። እያወቁ የሚያጠፉ ሰዎችን ደግሞ ለበላይ አካል ያሳውቃል። አብዱልሃኪም ይህን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መስጠት ከመጀመሩ በፊት የአጭር ጊዜ ሥልጠና ወስዷል። ወደ ስታዲዬም ጨዋታ ለመመልከት የሚመጡ ሁሉም ሰዎች ምግባረ-መልካም አይደሉም፣ የሚለው ወጣቱ አንዳንድ ጎብኚዎች በጎ ፈቃደኞችን እንደሚያንጓጥጡ ይናገራል። "ኳታር ሁለተኛ አገሬ ናት" የሚለው አብዱልሃኪም በዓለም ዋንጫው ብዙም ላልተሳካለት የኳታር ብሔራዊ ቡድን ድጋፉን ሲሰጥ ነበር። በምድብ አንድ ከኔዘርላንድስ፣ ከሴኔጋል እና ከኤኳዶር ጋር የተደለደለችው ኳታር ሦስቱንም ጨዋታዎች ተረትታ ተሰናብታለች። ቢሆንም አብዱልሃኪም እንደሚለው “ኳታር በብዙ ነገር አሸንፋለች።” “ከዓለም አገራት ብዙ መልክ እና ፍላጎት ያላቸው እንግዶችን ተቀብላ ማስተናገዷ እንደ አንድ ትልቅ ድል ነው የማየው።” | “ኢትዮጵያውያን በኳታሮች ዘንድ ይከበራሉ” - የዓለም ዋንጫ ዶሃ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዐይን ግሩም ሰይፉ ጋዜጠኛ ነው። አዲስ አድማስ ለተሰኘው ጋዜጣ ስፖርታዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮችን በመፃፍ ይታወቃል። ግሩም የኳታር የዓለም ዋንጫ ዝግጅትን ለመታደም ወደ ዶሃ ያቀናው ከመክፈቻው ጥቂት ቀናት ቀድሞ ነው። ዶሃ ከአዲስ አበባ 2200 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ ትገናለች። የኢትዮጵያ አየር መንገደ እና ኳታር ኤርዌይስ በየቀኑ መንገደኞችን ያመላልሳሉ። ግሩም፤ ነፋሻማዋን አዲስ አበባ ለቆ ወደ ዶሃ ሲያመራ የጠበቀው የግንቦት ሃሩር ነው። ነገር ግን ይህ ወቅት ለኳታሮች ቀዝቃዛው ወር ነው። “ዶሃ የቀትር ፀሐይ የሚባል የለም” ይላል። ምክንያቱም ቀኑን ሙሉ የዶሃን አሸዋማ መሬት የሚቀጠቅጠው ፀሐይ ሃሩር ነው። ኳታር፤ በሜትሬዎሎጂ ዘገባ አገላለፅ “በአብዛኛው ፀሐያማ” ናት። በአብዛኛው ከማለት ከንጋት እስከ ምሽት ማለት ሳይቀል አይቀርም። አሁን ባለው የአገሪቱ የአየር ሁኔታ ዝቅተኛው የሚባለው 23 ድግሪ ሴንትግሪድ የሚጀምረው ለሊት 10 ሰዓት ገደማ ነው። ዎርልድ ፖፑሌሽን ሪቪው የተሰኘው ድረ-ገፅ የኳታር ሕዝብ ብዛት በዚህ ዓመት 2.7 ሚሊዮን ይገመታል ይላል። ከእነዚህ መካከል ካታሪ የሚባሉት አረቦች 15 በመቶውን ይይዛሉ። ሕንዳዊያን፣ ፊሊፒናውያን እንዲሁም ሌሎች የእስያ አገራት ዜጎች ኑሯቸውን በኳታር ይኖራሉ። ከዚህ ባሻገር በርካታ ኢትዮጵያዊያን፣ ኤርትራዊያን እና ኬንያዊያን በዋና ከተማዋ ዶሃ እንዲሁም በአር ራያን ይገኛሉ። በነዳጅ ሃብት የበለፀገችው ኳታር እነሆ በአረቡ የዓለም ሲዘጋጅ የመጀመሪያው የሆነውን የዓለም ዋንጫ በማስተናገድ ላይ ትገኛለች። ግሩም፤ ካሜሩን ከሰርቢያ የሚያደርጉትን የቀን 7 ሰዓት የምድብ ጨዋታ ታድሞ ለመዘገብ እየተጓዘ ሳለ ነው በስልክ ያገኘነው። በየገባህበት ሥፍራ ሁሉ የአየር ማጤዣ ተገጥሟል የሚለው ግሩም፣ ይህ ቴክኖሎጂ ባይኖር ኳታር ለኑሮ ከባድ ትሆን እንደነበር ያምናል። “አሁን ለምሳሌ በአገሩ ሰዓት አቆጣጠር 5 ሰዓት ከምናምን ነው። እኛ አገር ግንቦት ወር ላይ ያለው የሚያማርረው ሙቀት ነው አሁን እዚህ ያለው።” ግሩም የኳታር ነዋሪዎችን ስለአየር ሁኔታው ሲጠይቃቸው “በብርድ ወቅት መጣህ” በሚል ዓይን እያዩት “ኧረ እንዲያውም ይሄ እኮ ቀዝቃዛው ጊዜ ነው” ይሉታል። ኳታር፤ ለዚህ ነው ይህንን ወቅት ለዓለም ዋንጫ የመረጠችው እንጂ ለወትሮው የዓለም ዋንጫ በሰኔ ነበር የሚዘጋጀው። ከፋርስ ባሕረ ሰላጤ የሚነሳው ነፋስ የኳታር ምሽትን ቀዝቀዝ አድርጎታል። ኳታር፤ ይህን የዓለም ዋንጫ ስታዘጋጅ ከምዕራቡ ዓለም ከፍተኛ ተቃውሞ ደርሶባት ነበር። አገሪቱ የሰብዓዊ መብት አይከበርባትም፣ ስታድየሞቹ ሲታነፁ በርካታ የጉልበት ሠራተኞች ሞተዋል፣ የአየር ሁኔታው ምቹ አይደለም. . . ብቻ ብዙ ነቀፋ አስተናግዳለች። ነገር ግን ጋዜጠኛ ግሩም ይህ ነቀፋ ተጋኗል የሚል እምነት አለው። “የኳታር ዜጎች በጣም ሰላምተኞች ናቸው። እንግዳ ተቀባይነታቸውን ማየት ችያለሁ። በአረቡ ዓለም መዘጋጀቱ የአረቡ የዓለም ለእግር ኳስ ያለውን ፍቅር ለማሳየት ልዩ አጋጣሚ ነው” ይላል። እንደሱ አመለካከት ዶሃ ወደፊት ልክ እንደ ዱባይ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚመጡ ጎብኚዎች የምታስናግድ መናኸሪያ እንደምትሆን አምነት አለው። ግሩም፤ በዶሃ በተዘዋወረባቸው ቦታዎች በርካታ ኢትዮጵያውያን ኑሮን ለማሸነፍ በተለያየ ሥራ ተሠማርተው ሲተጉ አይቷል። “ስታድየሞች ውስጥ በጎ ፈቃደኛ ኢትዮጵያውያን አግኝቻለሁ። አንድ የሥነ-ጥበብ ባለሙያ ኢትዮጵያዊም ተዋውቄያለሁ። በዓለም ዋንጫው ከትላልቅ የብሮድካስት ኩባንያዎች ጋር የሚሠራ ኢትዮጵያዊም ማግኘት ችያለሁ።” ጋዜጠኛው ባለኝ መረጃ መሠረት ከ20 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ኳታር ውስጥ ይኖራሉ ይላል። ስለአገሪቱ የተለያዩ መረጃዎችን የሚያወጣው ‘ኦንላይን ካታር’ የተሰኘው ገፅ ቢያንስ 25 ሺህ ኢትዮጵያዊያን እንደሚገኙ አስፍሯል። “በቤት ሠራተኝነት የሚሠሩ አሉ። የሚማሩ አሉ። የሕንፃ ግንባታ ባለሙያዎች፤ የታክሲ ሾፌሮች አሉ። በርካታ የኢትዮጵያ ሬስቶራንቶች ያሉበት አንድ አካባቢ አለ። አዲስ አበባ የሚል ስያሜ ያለው ፀጉር ቤት አይቻለሁ። እኔ ከጎበኘኋቸው ሬስቶራንቶች በአንዱ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ተሰባስበው አይቻለሁ።” ግሩም፤ “ኢትዮጵያውያን በኳታሮች ዘንድ ይከበራሉ። “የሥራ ሰዎች ናቸው ይባላሉ” ይላል። ጋዜጠኛ ግሩም ከዚህ ቀደም ወደ ደቡብ አፍሪካ እንዲሁም ሩሲያ ተጉዞ የዓለም ዋንጫን መታደም ችሏል። ነገር ግን የዶሃው በብዙ መልኩ እንደሚለይ ይገልጻል። አንደኛው ምክንያት ስታድየሞቹ የተቀራረቡ በመሆናቸው እሱና የሙያ አጋሮቹ በአንድ ቀን የተለያዩ ጨዋታዎችን መታደም መቻላቸው ነው። ለምሳሌ በሩሲያው የዓለም ዋንጫ ከዋና ከተማዋ ሞስኮው ወደ ሶቺ ለመሄድ 72 ሰዓታትን በባቡር ተጉዞ ነበር። አልፎም ከዚህ በፊት ከተመለከታቸው የዓለም ዋንጫዎች በተለየ በምድብ ጨዋታዎች የታየው ፉክክር፣ ተመልካቾች ብዛት፣ የስታድየሞቹ ልዩ ‘ዲዛይን’ ይህንን የዓለም ዋንጫ “ለየት አድርጎብኛል” ባይ ነው። መስከረም ዘውዴ በኳታር ከ15 ዓመታት በላይ ኖራለች። ዋና ከተማዋ ዶሃን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ተዘዋውራ ሠርታለች። አሁን ዶሃ ውስጥ አቢሲኒያ-ቢሾፍቱ የተሰኘ የቤተሰብ ሬስቶራንት ታስዳድራለች። የመስከረም ሬስቶራንት ከሰሞኑ ከተለያዩ ክፍለ ዓለማት በሚመጡ ተጠቃሚዎች መሞላቱን “ዕድሜ ለዓለም ዋንጫ” በሚመስል አንድምታ ትናገራለች። በርካታ ኢትዮጵያውያን እንግዶች፣ ኤርትራውያን፣ ሱዳናውያንን ጨምሮ የበርካታ አገራት ዜጎች ምግብ ቤቷን እንደሚጎበኙ ጠቅሳለች። ነገር ግን ብዙውን ጊዜ ኢትዮጵያውያን ተጠቃሚዎች የሌሎች አገራት ዜጎች ጓደኞቻቸውን ይዘው መጥተው የአገራቸውን ገበታ ሲቋደሱ ስታይ ደስ ይላታል። መስከረም ለአራት ዓመታት ያክል ያስተዳደረችው አቢሲኒያ-ቢሾፍቱ ሬስቶራንት፣ ዶሃ ውስጥ ኔአዘር የተሰኘ አካባቢ ይገኛል። ይህ መንደር በርካታ ኢትዮጵያውያን የሚኖሩበት ነው። መስከረም የዓለም ዋንጫ መጣ ሲባል ምናልባት አንዳንድ ቦታዎች ላይ ከመጠን በላይ መጨናነቅ ይኖራል የሚል ፍራቻ ነበራት። ነገር ግን ይህ በየአራት ዓመት የሚዘጋጅ ውድድር ደስታን ይዞላት ብቅ ብሏል። “ሰዉ በጣም ደስተኛ ነው። በነፃነት ነው የሚንቀሳቀሰው። ከዚህ በፊት ከምናውቀው የተለየ ነገር እያየን ነው። ሁሉም ሰው በሥነ-ሥርዓት ይስተናገዳል። ስሜቱም ለየት ይላል።” አቢሲኒያ-ቢሾፍቱ ሬስቶራንት የ32 አገራት ባንዲራዎች ይውለበለቡበታል። በዓለም ዋንጫ እየተሳተፉ ያሉ 32 አገራትን የሚወክል ነው። ሬስቶራንቱ ካለበት ቦታ ራቅ ብሎ ያለው ድባብ ልዩ እንደሆነ የምትናገረው መስከረም፣ እግር ኳስ እንዲህ ሰውን ሲያቀራርብ ማየቷ አስደንቋታል። “በቃ ኳስ ማለት ይሄ ነው። እግር ኳስ የዓለም ሰዎችን የሚያቀራርብ እንደሆነ ነው የገባኝ። በግሌ የተረዳሁት ይህንን ነው። በጣም ነው ደስ የሚለው። በጣም!” መስከረም፤ ሬስቶራንቱ ከሰሞኑ በደንበኞች በመጨናነቁ እንጂ በስታድየሞች ዙሪያ የኢትዮጵያ ገበታ ለተጠቃሚዎች አስባ ነበር። ለወትሮው ሙቀቷ ነፍስን የሚያስጨንቀው ኳታር ከሰሞኑ ቀዝቀዝ ማለቷ ለመስከረም አስደንቋታል። እንጂ የዶሃ ሙቀት የሚቋቋሙት አይደለም ትላለች። ለበርካታ ዓመታት በባሕረ ሰላጤዋ አገር የኖረችው መስከረም ኳታር ወግ አጥባቂ የአረብ አገር እንደመሆኗ እግር ኳስ ለመታደም የሚመጡ ሰዎች እንደልባቸው ላይዝናኑ ይችላሉ የሚል ስጋት ነበራት። ኳታር ስታዲዬሞች ውስጥ የአልኮል መጠጥ እንዳይሸጥ ከልክላለች። ነገር ግን በምሽት ክለቦች ሜክሲኮ እና የብራዚል ዜጎች ሲጨፍሩ ነው የከረሙት ትላለች መስከረም። ከሌሎች አገራት የሚመጡ ሰዎች የተለያየ ባሕርይ ይዘው ነው የሚመጡት። ነገር ግን አብዛኛዎቹ ጎብኚዎች ደስተኛ ሆነው በነፃነት ሲንቀሳቀሱ፣ ሲጫወቱ፣ ሲጨፍሩ ተመልክታለች። “አይቼው የማላውቀው ነው። በእውነት የተለየ ስሜት ፈጥሮብኛል።” ኢትዮጵያዊው አብዱልሃኪም አብዱልራህማን፤ በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ መኖር ከጀመረ አምስት ዓመታት አልፎታል። አብዱልሃኪም፤ ከዓለም ዋንጫው በጎ ፈቃደኞች አንዱ ነው። ወጣቱ፤ ከዶሃ ግዙፍ ስታዲዮሞች አንዱ በሆነው ኻሊፋ ዓለም አቀፍ ስታዲዬም የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። አብዱልሃኪም ዋነኛ ሥራው ጨዋታ ለመታደም ለሚመጡ ተመልካቾች አቅጣጫ መጠቆም፣ የሚያስፈልጋቸውን ነገር በመርዳት የበኩሉን ይወጣል። አልፎም በአገሪቱ ሕግ መሠረት የማይቻሉ ነገሮችን ጎብኚዎች ሲፈጽሙ ከተገኙ በማስረዳት የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱን ይወጣል። እያወቁ የሚያጠፉ ሰዎችን ደግሞ ለበላይ አካል ያሳውቃል። አብዱልሃኪም ይህን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መስጠት ከመጀመሩ በፊት የአጭር ጊዜ ሥልጠና ወስዷል። ወደ ስታዲዬም ጨዋታ ለመመልከት የሚመጡ ሁሉም ሰዎች ምግባረ-መልካም አይደሉም፣ የሚለው ወጣቱ አንዳንድ ጎብኚዎች በጎ ፈቃደኞችን እንደሚያንጓጥጡ ይናገራል። "ኳታር ሁለተኛ አገሬ ናት" የሚለው አብዱልሃኪም በዓለም ዋንጫው ብዙም ላልተሳካለት የኳታር ብሔራዊ ቡድን ድጋፉን ሲሰጥ ነበር። በምድብ አንድ ከኔዘርላንድስ፣ ከሴኔጋል እና ከኤኳዶር ጋር የተደለደለችው ኳታር ሦስቱንም ጨዋታዎች ተረትታ ተሰናብታለች። ቢሆንም አብዱልሃኪም እንደሚለው “ኳታር በብዙ ነገር አሸንፋለች።” “ከዓለም አገራት ብዙ መልክ እና ፍላጎት ያላቸው እንግዶችን ተቀብላ ማስተናገዷ እንደ አንድ ትልቅ ድል ነው የማየው።” | https://www.bbc.com/amharic/articles/cj59y335yj6o |
3politics
| "ጀዋር መሐመድ እናቱ ሊጠይቁት ሄደው ሊያውቃቸው አልቻለም" ኦፌኮ | የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) በረሀብ አድማ ላይ የሚገኙት እነ አቶ ጀዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ አሐምዛ አዳነ እና አቶ ሸምሰዲን ጠሃ የጤና ሁኔታ አሳሳቢ እንደሆነ ገልጾ መንግሥት "በአስቸኳይ ሕይወታቸውን አድኖ ግዴታውን ይወጣ" ሲል መግለጫ አውጥቷል። "ለሚጠፋው የዜጎቻችንና አባሎቻችን ሕይወት መንግሥት ኃላፊነቱን ይወስዳል" በማለት ሕዝቡ እንዲሁም ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም መንግሥት ላይ ጫና እንዲያሳድርም ፓርቲው አሳስቧል። የኦፌኮ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥሩነህ ገምታ የረሀብ አድማ ላይ የሚገኙት እስረኞች "ታመዋል። ከዚያም በላይ ሰው መለየት አይችሉም። መቆም አይችሉም። ሕይወታቸው አስጊ ደረጃ ነው" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ፊርማ በማሰባሰብ፣ አቤቱታ በማሰማት፣ ሰልፍ በማድረግ ወይም መንግሥታቸው በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ጫና እንዲያሳድር በማድረግ የእስረኞቹን ሕይወት እንዲያድን ጠይቀዋል። ያሳለፍነው ሰኞ፣ የካቲት 1/2013 ዓ.ም እስረኞቹን እንደጎበኟቸው የጠቀሱት አቶ ጥሩነህ፤ "ምንም ቃል ማውጣት አይችሉም። የሕክምና ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል" ብለዋል። አያይዘውም አቶ ጀዋር መሐመድን ሊጠይቋቸው የሄዱ እናታቸውን መለየት እንዳልቻሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል። "ሰኞ እለት አይቻቸዋለሁ። ቃል ማውጣት አይችሉም። መቆም አይችሉም። ጀዋር መሐመድን እናቱ ሊጠይቁት ሄደው ሊለያቸው አልቻለም። ጀዋር መሬት ይዞ እየዳኸ ነው ወደ እስር ክፍሉ የሄደው። አልቅሼ ነው የተለየሁት" በማለት ሁኔታውን ገልጸዋል። አቶ ጥሩነህ ዐቃቤ ሕግ፣ የሲቪል ማኅበራት፣ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶችና ሌሎችም አካላት እስር ቤት ሄደው እነ አቶ ጀዋርን እንዲያዩና መንግሥት ላይ ጫና እንዲያሳድሩም ጠይቀዋል። "በኢትዮጵያ ታሪክም ጥቁር ነጥብ መሆኑን በመገንዘብ ለመንግሥት አስፈላጊውን ማስጠንቀቂያ ምክርም መስጠት ይችላሉ" ብለዋል። የኦፌኮ አባላት በጅማ፣ በምዕራብ አርሲ ዞን፣ በምዕራብ ወለጋ፣ በምሥራቅ ወለጋ እና በሌሎችም የኦሮሚያ አካባቢዎች በተደጋጋሚ እንደሚታሰሩ፣ ታስረውም ፍርድ ቤት ያልቀረቡ እንዲሁም እንግልት የደረሰባቸው እንዳሉ ተናግረዋል። "ከሕግ አግባብ ውጪ የታሰሩ አባሎቻችንና ሌላው ሕዝብም መታሰሩ ያሳስበናል። ነገሮች ካልተሻሻሉ በሚደርስብን ጫና፣በግድያና በማስፈራሪያው ሳቢያ ኦፌኮ ሊዳረከም ሊፈርስም ይችላል" ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል። እነ አቶ ጀዋር በረሃብ አድማ ላይ ለረዥም ቀናት በመቆየታቸው የተነሳ የጤና ችግር እየተስተዋለባቸው መሆኑን የጤና ክትትል ከሚያደርጉላቸው ሐኪሞች መካከል አንዷ የሆኑት ዶ/ር ኢሊሊ ጀማል ለቢቢሲ መግለጻቸው አይዘነጋም። የረሃብ አድማውን እያደረጉ ያሉት በፖለቲከኞች ላይ የሚደርሰውን እንግልት እና እስር፣ እነሱን ለመጠየቅና የችሎት ሂደታቸውን ለመከታተል ወደ ፍርድ ቤት በሚሄዱ ሰዎች ላይ የሚፈጸም እስር እና ወከባ እንዲቆም ለመጠየቅ እንደሆነና ከ15 ቀናት በላይ እንዳለፋቸው ቢቢሲ ከጠበቆቻቸው ለመረዳት ችሏል። እነ አቶ ጃዋር እና አቶ በቀለን ጨምሮ በርካታ ፖለቲከኞች የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ ከተፈጠረው ሁከት ጋር ተያይዞ እጃችሁ አለበት ተብለው ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸው የሚታወስ ነው። ከቀረቡባቸው ተደራራቢ አስር ክሶች መካከል ስድስቱ እንዲቋረጡ ፍርድ ቤት ጥር ወር ላይ መወሰኑ ይታወሳል። የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ፣ የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል አዋጅ፣ የጦር መሣሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ የመተላለፍ ክሶች ከተመሰረቱባቸው ክሶች መካከል ሲሆኑ፤ እንዲቋረጡ የተደረጉት ክሶች የጦር መሣሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ 1177/2021 የተያያዙ ሲሆኑ በወቅቱ ውሳኔ እንዲቋረጡ የተደረጉት ክሶች የጦር መሳሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ 1177/2021 የተያያዙ መሆናቸውም የሚታወስ ነው። የቀሩት አራት ክሶች "በ1996 የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀፅ 240 በመተላለፍ ብሔርን እና ሐይማኖትን መሰረት ያደረገ የእርስ በርስ ግጭት በመቀስቀስ አንዱ ወገን በሌላው ወገን ላይ እንዲነሳሳ በማድረግ"፣ የፀረ ሽብር አዋጅ 1176/2012 እና የቴሌኮም ማጭበርበር አዋጅን 7061/2004 የሚመለከቱ ናቸው። | "ጀዋር መሐመድ እናቱ ሊጠይቁት ሄደው ሊያውቃቸው አልቻለም" ኦፌኮ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) በረሀብ አድማ ላይ የሚገኙት እነ አቶ ጀዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ አሐምዛ አዳነ እና አቶ ሸምሰዲን ጠሃ የጤና ሁኔታ አሳሳቢ እንደሆነ ገልጾ መንግሥት "በአስቸኳይ ሕይወታቸውን አድኖ ግዴታውን ይወጣ" ሲል መግለጫ አውጥቷል። "ለሚጠፋው የዜጎቻችንና አባሎቻችን ሕይወት መንግሥት ኃላፊነቱን ይወስዳል" በማለት ሕዝቡ እንዲሁም ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም መንግሥት ላይ ጫና እንዲያሳድርም ፓርቲው አሳስቧል። የኦፌኮ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥሩነህ ገምታ የረሀብ አድማ ላይ የሚገኙት እስረኞች "ታመዋል። ከዚያም በላይ ሰው መለየት አይችሉም። መቆም አይችሉም። ሕይወታቸው አስጊ ደረጃ ነው" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ፊርማ በማሰባሰብ፣ አቤቱታ በማሰማት፣ ሰልፍ በማድረግ ወይም መንግሥታቸው በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ጫና እንዲያሳድር በማድረግ የእስረኞቹን ሕይወት እንዲያድን ጠይቀዋል። ያሳለፍነው ሰኞ፣ የካቲት 1/2013 ዓ.ም እስረኞቹን እንደጎበኟቸው የጠቀሱት አቶ ጥሩነህ፤ "ምንም ቃል ማውጣት አይችሉም። የሕክምና ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል" ብለዋል። አያይዘውም አቶ ጀዋር መሐመድን ሊጠይቋቸው የሄዱ እናታቸውን መለየት እንዳልቻሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል። "ሰኞ እለት አይቻቸዋለሁ። ቃል ማውጣት አይችሉም። መቆም አይችሉም። ጀዋር መሐመድን እናቱ ሊጠይቁት ሄደው ሊለያቸው አልቻለም። ጀዋር መሬት ይዞ እየዳኸ ነው ወደ እስር ክፍሉ የሄደው። አልቅሼ ነው የተለየሁት" በማለት ሁኔታውን ገልጸዋል። አቶ ጥሩነህ ዐቃቤ ሕግ፣ የሲቪል ማኅበራት፣ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶችና ሌሎችም አካላት እስር ቤት ሄደው እነ አቶ ጀዋርን እንዲያዩና መንግሥት ላይ ጫና እንዲያሳድሩም ጠይቀዋል። "በኢትዮጵያ ታሪክም ጥቁር ነጥብ መሆኑን በመገንዘብ ለመንግሥት አስፈላጊውን ማስጠንቀቂያ ምክርም መስጠት ይችላሉ" ብለዋል። የኦፌኮ አባላት በጅማ፣ በምዕራብ አርሲ ዞን፣ በምዕራብ ወለጋ፣ በምሥራቅ ወለጋ እና በሌሎችም የኦሮሚያ አካባቢዎች በተደጋጋሚ እንደሚታሰሩ፣ ታስረውም ፍርድ ቤት ያልቀረቡ እንዲሁም እንግልት የደረሰባቸው እንዳሉ ተናግረዋል። "ከሕግ አግባብ ውጪ የታሰሩ አባሎቻችንና ሌላው ሕዝብም መታሰሩ ያሳስበናል። ነገሮች ካልተሻሻሉ በሚደርስብን ጫና፣በግድያና በማስፈራሪያው ሳቢያ ኦፌኮ ሊዳረከም ሊፈርስም ይችላል" ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል። እነ አቶ ጀዋር በረሃብ አድማ ላይ ለረዥም ቀናት በመቆየታቸው የተነሳ የጤና ችግር እየተስተዋለባቸው መሆኑን የጤና ክትትል ከሚያደርጉላቸው ሐኪሞች መካከል አንዷ የሆኑት ዶ/ር ኢሊሊ ጀማል ለቢቢሲ መግለጻቸው አይዘነጋም። የረሃብ አድማውን እያደረጉ ያሉት በፖለቲከኞች ላይ የሚደርሰውን እንግልት እና እስር፣ እነሱን ለመጠየቅና የችሎት ሂደታቸውን ለመከታተል ወደ ፍርድ ቤት በሚሄዱ ሰዎች ላይ የሚፈጸም እስር እና ወከባ እንዲቆም ለመጠየቅ እንደሆነና ከ15 ቀናት በላይ እንዳለፋቸው ቢቢሲ ከጠበቆቻቸው ለመረዳት ችሏል። እነ አቶ ጃዋር እና አቶ በቀለን ጨምሮ በርካታ ፖለቲከኞች የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ ከተፈጠረው ሁከት ጋር ተያይዞ እጃችሁ አለበት ተብለው ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸው የሚታወስ ነው። ከቀረቡባቸው ተደራራቢ አስር ክሶች መካከል ስድስቱ እንዲቋረጡ ፍርድ ቤት ጥር ወር ላይ መወሰኑ ይታወሳል። የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ፣ የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል አዋጅ፣ የጦር መሣሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ የመተላለፍ ክሶች ከተመሰረቱባቸው ክሶች መካከል ሲሆኑ፤ እንዲቋረጡ የተደረጉት ክሶች የጦር መሣሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ 1177/2021 የተያያዙ ሲሆኑ በወቅቱ ውሳኔ እንዲቋረጡ የተደረጉት ክሶች የጦር መሳሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ 1177/2021 የተያያዙ መሆናቸውም የሚታወስ ነው። የቀሩት አራት ክሶች "በ1996 የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀፅ 240 በመተላለፍ ብሔርን እና ሐይማኖትን መሰረት ያደረገ የእርስ በርስ ግጭት በመቀስቀስ አንዱ ወገን በሌላው ወገን ላይ እንዲነሳሳ በማድረግ"፣ የፀረ ሽብር አዋጅ 1176/2012 እና የቴሌኮም ማጭበርበር አዋጅን 7061/2004 የሚመለከቱ ናቸው። | https://www.bbc.com/amharic/news-56041932 |
0business
| “የኑሮ ውድነቱ ማህበራዊና ፖለቲካዊ መፍትሄ ያስፈልገዋል” | ነዋሪነቱ በአዲስ አበባ ከተማ የሆነውና መካከለኛ ገቢ ካለቸው ሰዎች ሊመደብ የሚችለው ግለሰብ በተለይ የኮቪድ-19 ወረረሽኝ ስጋትን ከመጣበት ከወርሃ ሚያዚያ አንስቶ የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋ መጨመር ህይወቱ ላይ የሚጨበጥ ተፅዕኖ ማምጣቱን ለቢቢሲ ይገልፃል። "ሃገር ውስጥ የሚመረቱ እንደ ሽንኩርት፣ ጤፍ፣ ቲማቲም የመሳሰሉት ላይ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ጭማሪ ታይቷል፤ ከዚያ ባሻገር ከውጭ የሚገቡ እንደ መዋቢያ ምርቶች፣ አልባሳት የመሳሰሉትም ከፍተኛ ጭማሪ ታይቷል" የሚለው ይሄው ግለሰብ ምናልባትም ከዓለም አቀፍ ወረርሽኙ ጋር በተያያዘ የንግድ እንቅስቃሴዎች መቀዛቀዛቸው፣ እንደ ወትሮውም በቀላሉ መጓጓዝ ባለመቻሉ የአቅርቦት እጥረት ማጋጠሙ ለዋጋ ጭማሪ ምክንያት ሳይሆን እንደማይቀር ግምቱን ሰንዝሯል። "ሽንኩርት በአስራዎቹ ብር ደረጃ ነበር የምንገዛው፥ አሁን ወደ አርባ ብር ደርሷል፤ ቲማቲምም እንደዚሁ ከፍ ብሏል፤ እንደዚሁ ሃያ ስምንት ብር ሃያ ዘጠኝ ብር [ገደማ] እየተሸጠ ነው ያለው በኪሎ" የሚለው ይህ ሰው ከዚህም የተነሳ እርሱና በማኅበራዊ ከባቢው የሚያውቃቸው ሌሎች ሰዎች አጠቃቀማቸውን ለማስተካከል መገደዳቸውን ይናገራል። የፍቼ ከተማ ነዋሪ የሆነችው ዘውዲቱ አሰፋም ከአዲስ አበባው ነዋሪ ጋር ተመሳሳይ ሃሳብ ነው ያላት። የኑሮ ውድነቱ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ መሆኑን ለቢቢሲ ስትገልጽ፤ "ለምሳሌ ሽንኩርት ከ45 እስከ 50 ብር እየተሸጠ ይገኛል። ሁሉም ነገር ጨምሯል። ጤፍ ከ4300 በላይ እየሆነ ነው። ዘይት ድሮ መንግሥት ያቀርብ ነበር፤ አሁን ግን አያቀርቡም፤ ስለዚህ ከነጋዴ እየገዛን ነው። ዋጋው ጨምሯል። የመንግሥት ሰራተኛ የሆነ፣ ደሞዙ አነስተኛ የሆነ፣ ቤተሰብ ያለው በጣም እየተቸገረ ነው።" ብላለች። የኑሮ ውድነቱ መናር በአኗኗሩ ላይ ያመጣውን ለውጥ የሚገልፀው የአዲስ አበባ ነዋሪ ". . .በምንጠቀማቸው ምግቦች ውስጥ ቲማቲም የምናዘወትር ከሆነ እርሱን እንተዋለን ማለት ነው፤ ሽንኩርትም የምንገዛውን እየቀነስን ሄደናል"፤ ስለዚህ "የምታገኘው ገቢና ለፍጆታዎችህ የምታወጣው ካልተመጣጠነልህ ፍጆታውን ወደ መቀነስ ብሎም ወደ ማቆም ነው የምንሄደው" ብሏል። ይኼው ሰው የኮቪድ-19 ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ እርግጥ የሆነበት ሰሞን በርካታ ሰዎች፣ የተለያዩ ምርቶችን በጅምላ ይሸምቱና ያከማቹ እንደነበር አስታውሶ፣ በወቅቱ አጋጣሚውን ለመጠቀም በፈለጉ አንዳንድ ነጋዴዎች የዋጋ ጭማሪ መደረጉን ይጠቅሳል።
"እኛ አገር የተለመደው ነገር ደግሞ ዋጋ አንድ ጊዜ ከፍ ካለ በኋላ ተመልሶ የመውረድ ዕድሉ በጣም አናሳ ስለሆነ" በዚያው ከፍ ብሎ ቀርቷል ይላል። የአርባምንጭ ነዋሪ የሆኑ ሌላ ግለሰብ ለቢቢሲ ሲናገሩ ገበያው "እሳት ነው" ይላሉ። ዋጋውን ለማነጻጸር ሩቅ መሄድ አልፈለጉም፤ "በቅርቡ እንኳ ቲማቲም እንገዛ የነበረው 20 ብር ነው አሁን ግን 30 ገብቷል" ካሉ በኋላ ሽንኩርት ደግሞ 30 ብር መግባቱን፣ ድንች በኪሎ 15 ብር፣ ነጭ ሽንኩርት 150 መሆኑን ለቢቢሲ ገልፀዋል። ነጋዴዎችም እንደ ከዚህ ቀደሙ ደፍረው የሚገዙ ደንበኞቻቸው እየቀነሱ መምጣታውን ለቢቢሰ ተናግረዋል። በላሊበላ የሚኖሩት ሌላው ቢቢሲ ያነጋገራቸው ግለሰብ ኑሯቸው የተመሰረተው ከተማዋን ለመገብኘት በሚመጡ ቱሪስቶች ላይ እንደነበር ተናግረው አሁን ግን በኮቪድ-19 ምክንያት ጎብኚ በመጥፋቱ ኑሯቸው ፈተና ውስጥ መውደቁን ለቢቢሲ አልሸሸጉም። ከዚህ ቀደም 30 እና 40 ብር ይገዙት የነበረውን ሽንኩርት አሁን 120 ብር እንደሚሸጥም አስረጅ በመጥቀስ ተናግረዋል። "ጤፍ ከ4000 ብር በላይ ገብቷል" በማለትም ኑሮ ከእለት ወደ እልት እየከበደ መምጣቱን ለቢቢሲ በሃዘን ስሜት ውስጥ ሆነው አስረድተዋል። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ዶ/ር ጉቱ ቲሶ በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም በኮሮናቫይረስ ምክንያት የሸቀጣሸቀጥ ዋጋ መጨመሩን ይገልፃሉ። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ በኮቪድ-19 እና በተጓዳኝ ችግሮች ምክንያት ምርትና አቅርቦት ላይ መስተጓጎል በመፈጠሩ መሆኑን ያስረዳሉ። ምሁሩ አክለውም ከየካቲት ወር ጀምሮ ይህ መከሰቱን እና እስካሁን መቀጠሉን ይናገራሉ። ዶ/ር ጉቱ በተለይ ደግሞ የአለማቸችን የሸቀጣሸቀጥ እቃዎች ዋነኛ አቅራቢ ቻይና በኮሮናቫይረስ ክፉኛ መጎዳቷ ምርቶችን ማስተጓጎሉንና በዚህም የተነሳ የዋጋ ንረት መከሰቱን ገልፀዋል። "አቅርቦት ሲቀንስ ዋጋ ይጨምራል" የሚሉት ባለሙያው፤ በተፈጠረው የአቅርቦት እጥረት ገበያ ውስጥ ያለውን መቀራመት በመፈጠሩ የምርት ዋጋ መናሩን አብራርተዋል። ሌላኛው ምርቶችን ከውጪ አገራት ገዝቶ ለማምጣት የውጭ ምንዛሬ በማስፈለጉ እና በበቂ ሁናቴ የውጪ ምንዛሬ ማግኘት አለመቻል ለዋጋ ግሽበቱ መናር አንዱ አስተዋጽኦ እንደሆነ ያስረዳሉ። በኮሮናቫይረስ ምክንያት አምራቾች የግብአት እጥረት ስለሚገጥማቸው የዋጋ ንረት ይከሰታል የሚሉት ዶ/ር ጉቱ፣ አምራቾች የማምረት ወጪያቸው ሲጨምር አብሮ የምርት ዋጋ ይጨምራል ይላሉ። አምራቹ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከትራንስፖርትና ከማምረት ጋር የተገናኘ የግብአት አቅርቦት እየተገታና እጥት እየተፈጠረ በመምጣቱ ለምርት እጥረቱ አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልፀዋል። "ግብአት አቅርቦት ቀነሰ ማለት፣ የግብአት ዋጋ ጨመረ ማለት ነው" በማለትም ናገራሉ። የማምረቻ ዋጋ ሲጨምር፣ በተዘዋዋሪ አምራቹ ዋጋውን ወደ ሸማቹ እንደሚያዞር የሚያስረዱት ዶ/ር ጉቱ፤ ዋጋው ወደ ተጠቃሚ ሲዞር ምርቱ ላይ ጭማሪ ያሳያል ሲሉ ይተነትናሉ። ከእነዚህ በተጨማሪ የስርጭት መሰተጓጎል መኖሩን ባለሙያው ጨምረው አስድተዋል። "በአንድ ቦታ የተመረተ ምርት በሚፈለግበት ወቅት ወደ ተለያየ የአገሪቱ ክፍል ማሰራጨት ሲያቅት፣ እጥረት ስለሚፈጠር ለተጨማሪ ወጪ ይዳረጋል፤ የዋጋ ጭማሪ ይከሰታል።" በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት የሰላምና መረጋጋት ጥያቄ ትልቅ ፈተና ውስጥ መውደቁን በማስታወስ፣ ይህ ሁሉ በምርት ሰንሰለት፣ በግብዓት አቅርቦት፣ በምርት ስርጭቶች ላይ ትልቅ መስተጓጎል መፍጠሩን ይናገራሉ። በሰላም እና መረጋጋት እጦቱ ፋብሪካዎች ምርታቸውን መቀነሳቸውን፣ ምርት ስርጭት ላይ የተሰማሩም መስተጓጎል ገጥሟቸዋል ሲሉ ይገልጻሉ። መኪናዎች ጭነት ጭነው መንገድ ላይ ከአንድ ቀን በላይ ተስተጓጉለው መቅረት፣ ለተጨማሪ ወጪ እና ኪሳራ ሲዳርጋቸው በተዘዋዋሪ ሸማቹ ላይ የምርቱ ዋጋ ከተገቢው በላይ ዋጋ እንዲጫን እንደሚያደርጉ ጨምረው ያስረዳሉ። እነዚህ ነገሮች በጥቅሉ ሲታዩ የሸቀጣ ሸቀጥ ዋጋ ላይ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም አገልግሎቶችና አቅርቦቶች ላይ የዋጋ ንረት እንደሚያሳዩ ዶ/ር ጉቱ ገልፀዋል። ለዋና ዋና ከተሞች የምግብ ፍጆታ ምርቶች የሚመጡት በከተሞቹ አቅራብያ ከሚገኙ የክልል ከተሞች መሆኑን በማስታወስ እነዚህ የግብርና ምርቶች ከየትኛውም ጊዜ ይልቅ የዋጋ ንረት ማሳየታቸውን ገልፀዋል። እነዚህ የፍጆታ እቃዎች አሳሳቢ በመባል ደረጃ ዋጋቸው እየጨመረ ነው የሚሉት ምሁሩ፣ ለዋጋ መናር ምክንያቱ ምን እንደሆነ ሲያስረዱም እነዚህ የእለት ፍጆታ ምርቶች ( እንደ ጥራጥሬ ያሉት) ለገበያ የሚቀርቡት ባለፈው አመት የተመረቱ መሆናውን በመጥቀስ ነው። ባለው አመት በተለያየ የአገሪቱ ክፍል አካባቢዎቹ የነበሩበት ሁናቴ የነበረውን ሁኔታም በማስታወስ፣ ለማምረት፣ ለመሰብሰብ፣ ለማሰራጨት አስቸጋሪ በሆነ ሁናቴ ውስጥ ማሳለፋቸውን ይጠቅሳሉ። በዚህ የተነሳ የምርት ማሽቆልቆል ተከስቶ ዘንድሮ ለገበያ ሲደርስ የዋጋ መናር መፈጠሩን ያስረዳሉ። ባለፉት ወራት የተከሰተውንም በተመለከተ ሲያስረዱም፣ ከድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዳሴ ግድያ በኋላም ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ ምርቶች ትልቅ መስተጓጎል እንደገጠማቸው ያብራራሉ። በተጨማሪም ነጋዴዎች ባለፈው አመት የገዙት ምርት እንኳ ቢሆን በእንዲህ አይነት ወቅት ዋጋ ከመጠን በላይ ጨምረው እንደሚሸጡ ሸማቾችም በገፍ ገዝው እንደሚያከማቹ ይህም ለዋጋ ንረቱ አስተዋጽኦ እንዳለው ይገልጻሉ። ወደ 80 በመቶ የሚጠጋው አትዮጵያዊ መደበኛ ባልሆነ ስራ ውስጥ ተሰማርቶ፣ ከእጅ ወደአፍ ገቢ እንደሚያገኝ የሚናገሩት ምሁሩ፤ በዚህም ለበርካታው ኢትዮጵያዊ ኑሮን ማክበዱን ይገልፃሉ። ገንዘብ ያለውም ቢሆን የፍጆታ እቃዎች ዋጋ በናረበት ቁጥር ያለውን ገቢው በአጠቃላይ ወደ ሚመገበው ነገር ለማዞር ይገደዳል ይላሉ። ይህም ቁጠባን፣ የወደፊት የማደግ ተስፋውንና ጥረቱን እንደሚያመክን ገልፀው፣ ይህ እንደ ግለሰብ ቢሆንም እንደ አገር ማህበረሳባዊ እድገትንም ፈተና ውስጥ እንደሚጥል ይገልፃሉ። እንደ ዶ/ር ጉቱ ከሆነ ለዋጋ ግሽበቱ መፍትሄ ለመስጠት ችግሩ ከምን መነጨ የሚለውን መለየት አስፈላጊ ነው። አንዳንድ ጊዜ ለምጣኔ ሃብት ችግር የምጣኔ ሃብት መልስ መስጠት ያስቸግራል የሚሉት ምሁሩ፣ የችግሩ መንስኤ ምጣኔ ሃብታዊ ሳይሆን ማህበራዊ አልያም ፖለቲካዊ ሊሆን ይችላል ይላሉ። ከኮሮናቫይረስ ጋር ተያይዞ የተከሰተን የዋጋ ንረት በፍጥነት በሽታውን በቁጥጥር ስር በማዋል፣ ህብረተሰቡ ወጥቶ ሰርቶ መግባት እንዲችል ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ይናገራሉ። ለዚህ ደግሞ የመንግሥት ብቻ ሳይሆን የሁሉም አካላት ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል። ይህን በፍጥነት መቆጣጠር ካልተቻለ የምጣኔ ሃብቱን ቀውስ እያባባሰው እንደሚሄድ ይናገራሉ። ሌላው በየዓመቱ ያለው የሰላም መደፍረስ ምክንያቱ ተጠንቶ እውነተኛ፣ አሳታፊ እና ግልጽ የሆነ ውይይት ተደርጎ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ምላሽ ሊሰጠው እንደሚገባ ይመክራሉ። በሶስተኛ ደረጃ እንደ ህዝብ ያሉትን ፖሊካዊ ብሶቶችና ጥያቄዎችን የምንገልፅበት መንገድን ቆም ብሎ መመልከት ተገቢ መሆኑን ይመክራሉ። ሁል ጊዜ የምጣኔ ሃብት ተቋማትን በማውደም፣ ምርትና ምርታማነትን በማስተጓጎል ብቻ ሳይሆን ሌሎች በተዘዋዋሪ ጫና መፍጠር የተፈለገው አካል ላይ ጫና መፍጠር የሚያስችሉ አማራጮችን መመልከትና መፈተሽ ተገቢ መሆኑን ያስታውሳሉ። ካልሆነ ግን አሁን የዋጋ ንረቱ እየሄድንበት ያለው ፍጥነትና መንገድ ከምጣኔ ሃብት አንፃር ሲታሰብ አገሪቷን መጥፎ ደረጃ ላይ እያደረሰ መሆኑን ለቢቢሲ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። | “የኑሮ ውድነቱ ማህበራዊና ፖለቲካዊ መፍትሄ ያስፈልገዋል” ነዋሪነቱ በአዲስ አበባ ከተማ የሆነውና መካከለኛ ገቢ ካለቸው ሰዎች ሊመደብ የሚችለው ግለሰብ በተለይ የኮቪድ-19 ወረረሽኝ ስጋትን ከመጣበት ከወርሃ ሚያዚያ አንስቶ የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋ መጨመር ህይወቱ ላይ የሚጨበጥ ተፅዕኖ ማምጣቱን ለቢቢሲ ይገልፃል። "ሃገር ውስጥ የሚመረቱ እንደ ሽንኩርት፣ ጤፍ፣ ቲማቲም የመሳሰሉት ላይ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ጭማሪ ታይቷል፤ ከዚያ ባሻገር ከውጭ የሚገቡ እንደ መዋቢያ ምርቶች፣ አልባሳት የመሳሰሉትም ከፍተኛ ጭማሪ ታይቷል" የሚለው ይሄው ግለሰብ ምናልባትም ከዓለም አቀፍ ወረርሽኙ ጋር በተያያዘ የንግድ እንቅስቃሴዎች መቀዛቀዛቸው፣ እንደ ወትሮውም በቀላሉ መጓጓዝ ባለመቻሉ የአቅርቦት እጥረት ማጋጠሙ ለዋጋ ጭማሪ ምክንያት ሳይሆን እንደማይቀር ግምቱን ሰንዝሯል። "ሽንኩርት በአስራዎቹ ብር ደረጃ ነበር የምንገዛው፥ አሁን ወደ አርባ ብር ደርሷል፤ ቲማቲምም እንደዚሁ ከፍ ብሏል፤ እንደዚሁ ሃያ ስምንት ብር ሃያ ዘጠኝ ብር [ገደማ] እየተሸጠ ነው ያለው በኪሎ" የሚለው ይህ ሰው ከዚህም የተነሳ እርሱና በማኅበራዊ ከባቢው የሚያውቃቸው ሌሎች ሰዎች አጠቃቀማቸውን ለማስተካከል መገደዳቸውን ይናገራል። የፍቼ ከተማ ነዋሪ የሆነችው ዘውዲቱ አሰፋም ከአዲስ አበባው ነዋሪ ጋር ተመሳሳይ ሃሳብ ነው ያላት። የኑሮ ውድነቱ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ መሆኑን ለቢቢሲ ስትገልጽ፤ "ለምሳሌ ሽንኩርት ከ45 እስከ 50 ብር እየተሸጠ ይገኛል። ሁሉም ነገር ጨምሯል። ጤፍ ከ4300 በላይ እየሆነ ነው። ዘይት ድሮ መንግሥት ያቀርብ ነበር፤ አሁን ግን አያቀርቡም፤ ስለዚህ ከነጋዴ እየገዛን ነው። ዋጋው ጨምሯል። የመንግሥት ሰራተኛ የሆነ፣ ደሞዙ አነስተኛ የሆነ፣ ቤተሰብ ያለው በጣም እየተቸገረ ነው።" ብላለች። የኑሮ ውድነቱ መናር በአኗኗሩ ላይ ያመጣውን ለውጥ የሚገልፀው የአዲስ አበባ ነዋሪ ". . .በምንጠቀማቸው ምግቦች ውስጥ ቲማቲም የምናዘወትር ከሆነ እርሱን እንተዋለን ማለት ነው፤ ሽንኩርትም የምንገዛውን እየቀነስን ሄደናል"፤ ስለዚህ "የምታገኘው ገቢና ለፍጆታዎችህ የምታወጣው ካልተመጣጠነልህ ፍጆታውን ወደ መቀነስ ብሎም ወደ ማቆም ነው የምንሄደው" ብሏል። ይኼው ሰው የኮቪድ-19 ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ እርግጥ የሆነበት ሰሞን በርካታ ሰዎች፣ የተለያዩ ምርቶችን በጅምላ ይሸምቱና ያከማቹ እንደነበር አስታውሶ፣ በወቅቱ አጋጣሚውን ለመጠቀም በፈለጉ አንዳንድ ነጋዴዎች የዋጋ ጭማሪ መደረጉን ይጠቅሳል።
"እኛ አገር የተለመደው ነገር ደግሞ ዋጋ አንድ ጊዜ ከፍ ካለ በኋላ ተመልሶ የመውረድ ዕድሉ በጣም አናሳ ስለሆነ" በዚያው ከፍ ብሎ ቀርቷል ይላል። የአርባምንጭ ነዋሪ የሆኑ ሌላ ግለሰብ ለቢቢሲ ሲናገሩ ገበያው "እሳት ነው" ይላሉ። ዋጋውን ለማነጻጸር ሩቅ መሄድ አልፈለጉም፤ "በቅርቡ እንኳ ቲማቲም እንገዛ የነበረው 20 ብር ነው አሁን ግን 30 ገብቷል" ካሉ በኋላ ሽንኩርት ደግሞ 30 ብር መግባቱን፣ ድንች በኪሎ 15 ብር፣ ነጭ ሽንኩርት 150 መሆኑን ለቢቢሲ ገልፀዋል። ነጋዴዎችም እንደ ከዚህ ቀደሙ ደፍረው የሚገዙ ደንበኞቻቸው እየቀነሱ መምጣታውን ለቢቢሰ ተናግረዋል። በላሊበላ የሚኖሩት ሌላው ቢቢሲ ያነጋገራቸው ግለሰብ ኑሯቸው የተመሰረተው ከተማዋን ለመገብኘት በሚመጡ ቱሪስቶች ላይ እንደነበር ተናግረው አሁን ግን በኮቪድ-19 ምክንያት ጎብኚ በመጥፋቱ ኑሯቸው ፈተና ውስጥ መውደቁን ለቢቢሲ አልሸሸጉም። ከዚህ ቀደም 30 እና 40 ብር ይገዙት የነበረውን ሽንኩርት አሁን 120 ብር እንደሚሸጥም አስረጅ በመጥቀስ ተናግረዋል። "ጤፍ ከ4000 ብር በላይ ገብቷል" በማለትም ኑሮ ከእለት ወደ እልት እየከበደ መምጣቱን ለቢቢሲ በሃዘን ስሜት ውስጥ ሆነው አስረድተዋል። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ዶ/ር ጉቱ ቲሶ በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም በኮሮናቫይረስ ምክንያት የሸቀጣሸቀጥ ዋጋ መጨመሩን ይገልፃሉ። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ በኮቪድ-19 እና በተጓዳኝ ችግሮች ምክንያት ምርትና አቅርቦት ላይ መስተጓጎል በመፈጠሩ መሆኑን ያስረዳሉ። ምሁሩ አክለውም ከየካቲት ወር ጀምሮ ይህ መከሰቱን እና እስካሁን መቀጠሉን ይናገራሉ። ዶ/ር ጉቱ በተለይ ደግሞ የአለማቸችን የሸቀጣሸቀጥ እቃዎች ዋነኛ አቅራቢ ቻይና በኮሮናቫይረስ ክፉኛ መጎዳቷ ምርቶችን ማስተጓጎሉንና በዚህም የተነሳ የዋጋ ንረት መከሰቱን ገልፀዋል። "አቅርቦት ሲቀንስ ዋጋ ይጨምራል" የሚሉት ባለሙያው፤ በተፈጠረው የአቅርቦት እጥረት ገበያ ውስጥ ያለውን መቀራመት በመፈጠሩ የምርት ዋጋ መናሩን አብራርተዋል። ሌላኛው ምርቶችን ከውጪ አገራት ገዝቶ ለማምጣት የውጭ ምንዛሬ በማስፈለጉ እና በበቂ ሁናቴ የውጪ ምንዛሬ ማግኘት አለመቻል ለዋጋ ግሽበቱ መናር አንዱ አስተዋጽኦ እንደሆነ ያስረዳሉ። በኮሮናቫይረስ ምክንያት አምራቾች የግብአት እጥረት ስለሚገጥማቸው የዋጋ ንረት ይከሰታል የሚሉት ዶ/ር ጉቱ፣ አምራቾች የማምረት ወጪያቸው ሲጨምር አብሮ የምርት ዋጋ ይጨምራል ይላሉ። አምራቹ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከትራንስፖርትና ከማምረት ጋር የተገናኘ የግብአት አቅርቦት እየተገታና እጥት እየተፈጠረ በመምጣቱ ለምርት እጥረቱ አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልፀዋል። "ግብአት አቅርቦት ቀነሰ ማለት፣ የግብአት ዋጋ ጨመረ ማለት ነው" በማለትም ናገራሉ። የማምረቻ ዋጋ ሲጨምር፣ በተዘዋዋሪ አምራቹ ዋጋውን ወደ ሸማቹ እንደሚያዞር የሚያስረዱት ዶ/ር ጉቱ፤ ዋጋው ወደ ተጠቃሚ ሲዞር ምርቱ ላይ ጭማሪ ያሳያል ሲሉ ይተነትናሉ። ከእነዚህ በተጨማሪ የስርጭት መሰተጓጎል መኖሩን ባለሙያው ጨምረው አስድተዋል። "በአንድ ቦታ የተመረተ ምርት በሚፈለግበት ወቅት ወደ ተለያየ የአገሪቱ ክፍል ማሰራጨት ሲያቅት፣ እጥረት ስለሚፈጠር ለተጨማሪ ወጪ ይዳረጋል፤ የዋጋ ጭማሪ ይከሰታል።" በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት የሰላምና መረጋጋት ጥያቄ ትልቅ ፈተና ውስጥ መውደቁን በማስታወስ፣ ይህ ሁሉ በምርት ሰንሰለት፣ በግብዓት አቅርቦት፣ በምርት ስርጭቶች ላይ ትልቅ መስተጓጎል መፍጠሩን ይናገራሉ። በሰላም እና መረጋጋት እጦቱ ፋብሪካዎች ምርታቸውን መቀነሳቸውን፣ ምርት ስርጭት ላይ የተሰማሩም መስተጓጎል ገጥሟቸዋል ሲሉ ይገልጻሉ። መኪናዎች ጭነት ጭነው መንገድ ላይ ከአንድ ቀን በላይ ተስተጓጉለው መቅረት፣ ለተጨማሪ ወጪ እና ኪሳራ ሲዳርጋቸው በተዘዋዋሪ ሸማቹ ላይ የምርቱ ዋጋ ከተገቢው በላይ ዋጋ እንዲጫን እንደሚያደርጉ ጨምረው ያስረዳሉ። እነዚህ ነገሮች በጥቅሉ ሲታዩ የሸቀጣ ሸቀጥ ዋጋ ላይ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም አገልግሎቶችና አቅርቦቶች ላይ የዋጋ ንረት እንደሚያሳዩ ዶ/ር ጉቱ ገልፀዋል። ለዋና ዋና ከተሞች የምግብ ፍጆታ ምርቶች የሚመጡት በከተሞቹ አቅራብያ ከሚገኙ የክልል ከተሞች መሆኑን በማስታወስ እነዚህ የግብርና ምርቶች ከየትኛውም ጊዜ ይልቅ የዋጋ ንረት ማሳየታቸውን ገልፀዋል። እነዚህ የፍጆታ እቃዎች አሳሳቢ በመባል ደረጃ ዋጋቸው እየጨመረ ነው የሚሉት ምሁሩ፣ ለዋጋ መናር ምክንያቱ ምን እንደሆነ ሲያስረዱም እነዚህ የእለት ፍጆታ ምርቶች ( እንደ ጥራጥሬ ያሉት) ለገበያ የሚቀርቡት ባለፈው አመት የተመረቱ መሆናውን በመጥቀስ ነው። ባለው አመት በተለያየ የአገሪቱ ክፍል አካባቢዎቹ የነበሩበት ሁናቴ የነበረውን ሁኔታም በማስታወስ፣ ለማምረት፣ ለመሰብሰብ፣ ለማሰራጨት አስቸጋሪ በሆነ ሁናቴ ውስጥ ማሳለፋቸውን ይጠቅሳሉ። በዚህ የተነሳ የምርት ማሽቆልቆል ተከስቶ ዘንድሮ ለገበያ ሲደርስ የዋጋ መናር መፈጠሩን ያስረዳሉ። ባለፉት ወራት የተከሰተውንም በተመለከተ ሲያስረዱም፣ ከድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዳሴ ግድያ በኋላም ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ ምርቶች ትልቅ መስተጓጎል እንደገጠማቸው ያብራራሉ። በተጨማሪም ነጋዴዎች ባለፈው አመት የገዙት ምርት እንኳ ቢሆን በእንዲህ አይነት ወቅት ዋጋ ከመጠን በላይ ጨምረው እንደሚሸጡ ሸማቾችም በገፍ ገዝው እንደሚያከማቹ ይህም ለዋጋ ንረቱ አስተዋጽኦ እንዳለው ይገልጻሉ። ወደ 80 በመቶ የሚጠጋው አትዮጵያዊ መደበኛ ባልሆነ ስራ ውስጥ ተሰማርቶ፣ ከእጅ ወደአፍ ገቢ እንደሚያገኝ የሚናገሩት ምሁሩ፤ በዚህም ለበርካታው ኢትዮጵያዊ ኑሮን ማክበዱን ይገልፃሉ። ገንዘብ ያለውም ቢሆን የፍጆታ እቃዎች ዋጋ በናረበት ቁጥር ያለውን ገቢው በአጠቃላይ ወደ ሚመገበው ነገር ለማዞር ይገደዳል ይላሉ። ይህም ቁጠባን፣ የወደፊት የማደግ ተስፋውንና ጥረቱን እንደሚያመክን ገልፀው፣ ይህ እንደ ግለሰብ ቢሆንም እንደ አገር ማህበረሳባዊ እድገትንም ፈተና ውስጥ እንደሚጥል ይገልፃሉ። እንደ ዶ/ር ጉቱ ከሆነ ለዋጋ ግሽበቱ መፍትሄ ለመስጠት ችግሩ ከምን መነጨ የሚለውን መለየት አስፈላጊ ነው። አንዳንድ ጊዜ ለምጣኔ ሃብት ችግር የምጣኔ ሃብት መልስ መስጠት ያስቸግራል የሚሉት ምሁሩ፣ የችግሩ መንስኤ ምጣኔ ሃብታዊ ሳይሆን ማህበራዊ አልያም ፖለቲካዊ ሊሆን ይችላል ይላሉ። ከኮሮናቫይረስ ጋር ተያይዞ የተከሰተን የዋጋ ንረት በፍጥነት በሽታውን በቁጥጥር ስር በማዋል፣ ህብረተሰቡ ወጥቶ ሰርቶ መግባት እንዲችል ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ይናገራሉ። ለዚህ ደግሞ የመንግሥት ብቻ ሳይሆን የሁሉም አካላት ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል። ይህን በፍጥነት መቆጣጠር ካልተቻለ የምጣኔ ሃብቱን ቀውስ እያባባሰው እንደሚሄድ ይናገራሉ። ሌላው በየዓመቱ ያለው የሰላም መደፍረስ ምክንያቱ ተጠንቶ እውነተኛ፣ አሳታፊ እና ግልጽ የሆነ ውይይት ተደርጎ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ምላሽ ሊሰጠው እንደሚገባ ይመክራሉ። በሶስተኛ ደረጃ እንደ ህዝብ ያሉትን ፖሊካዊ ብሶቶችና ጥያቄዎችን የምንገልፅበት መንገድን ቆም ብሎ መመልከት ተገቢ መሆኑን ይመክራሉ። ሁል ጊዜ የምጣኔ ሃብት ተቋማትን በማውደም፣ ምርትና ምርታማነትን በማስተጓጎል ብቻ ሳይሆን ሌሎች በተዘዋዋሪ ጫና መፍጠር የተፈለገው አካል ላይ ጫና መፍጠር የሚያስችሉ አማራጮችን መመልከትና መፈተሽ ተገቢ መሆኑን ያስታውሳሉ። ካልሆነ ግን አሁን የዋጋ ንረቱ እየሄድንበት ያለው ፍጥነትና መንገድ ከምጣኔ ሃብት አንፃር ሲታሰብ አገሪቷን መጥፎ ደረጃ ላይ እያደረሰ መሆኑን ለቢቢሲ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-53657254 |
3politics
| በሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን ለለውጥ ጎዳና ላይ ወጡ | በሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን ፖለቲካዊ ለውጥን በመሻት በተለያዩ ከተሞች ጎዳናዎች ለተቃውሞ ወጥተዋል። ባለፈው አመት የሱዳኑን ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር ከስልጣን መገርሰስ ተከትሎ ቃል የተገቡ ማሻሻያዎችና ለውጦች ምን ላይ እንደደረሱ ተቃዋሚዎች በመጠየቅ ላይ መሆናቸውን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አስታውቀዋል። በመዲናዋ ኻርቱምን ጨምሮ በአጎራባች ከተሞችና ወደ ጦር ኃይሉ ዋና መቀመጫ የሚያመሩ ጎዳናዎች ላይ የፀጥታ ኃይሎች ተሰማርተዋል። ተቃዋሚዎችም የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ እንዲሁም በዘፈኖች፣ የመኪና ጥሩምባ በማሰማት ተቃውሟቸውን እየገለፁ ነው። በአሁኑ ሰዓት እየተደረጉ ያሉ ተቃውሞዎች ባለፈው አመት ከነበረው፣ ለወራት ከዘለቀውና የኦማር አልበሽርን ረዥም የስልጣን ዘመን ማብቂያ ከሆነው አብዮትም ጋር ይመሳሰላል ተብሏል። የኦማር አልበሽር ከስልጣን መውደቅ ተከትሎም የሲቪልና ወታደራዊ ጥምር መንግሥት ተመስርቷል። ነገር ግን እውነተኛ የሲቪል መንግሥት እንዲሁም ፖለቲካዊ ለውጦች ይመጣሉ ወይ ለሚለው በርካቶች ስጋት አጭሮባቸዋል። በትናንትናው ዕለት በተደረጉ ተቃውሞችም የተንሰራፋው ሙስና እንዲጠፋ፣ በአልበሽር አገዛዝ ወቅት የተገደሉ ሰዎች ፍትህ እንዲያገኙ እንዲሁም ቃል የተገባው ፓርላማ እንዲመሰረት የሚጠይቁ ነበሩ። የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክም በበኩላቸው ቁልፍ የሚባሉ ማሻሻያዎችና ለውጦች በሃገሪቱ እንደሚካሄዱ ጠቅሰው በመጪዎቹ ቀናቶችም ይፋ ይሆናሉ ብለዋል። ሃገሪቱ በተፈጠረው የገበያ ግሽበት ምክንያት የምግብ እንዲሁም የነዳጅ ዋጋ መጨመር ጫናን ፈጥሮባታል። ከዚህም በተጨማሪ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ያስከተለው ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ቀጥ ማለትም ድቀትን እንዳይፈጥር ፍራቻን ደቅኗል። | በሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን ለለውጥ ጎዳና ላይ ወጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን ፖለቲካዊ ለውጥን በመሻት በተለያዩ ከተሞች ጎዳናዎች ለተቃውሞ ወጥተዋል። ባለፈው አመት የሱዳኑን ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር ከስልጣን መገርሰስ ተከትሎ ቃል የተገቡ ማሻሻያዎችና ለውጦች ምን ላይ እንደደረሱ ተቃዋሚዎች በመጠየቅ ላይ መሆናቸውን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አስታውቀዋል። በመዲናዋ ኻርቱምን ጨምሮ በአጎራባች ከተሞችና ወደ ጦር ኃይሉ ዋና መቀመጫ የሚያመሩ ጎዳናዎች ላይ የፀጥታ ኃይሎች ተሰማርተዋል። ተቃዋሚዎችም የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ እንዲሁም በዘፈኖች፣ የመኪና ጥሩምባ በማሰማት ተቃውሟቸውን እየገለፁ ነው። በአሁኑ ሰዓት እየተደረጉ ያሉ ተቃውሞዎች ባለፈው አመት ከነበረው፣ ለወራት ከዘለቀውና የኦማር አልበሽርን ረዥም የስልጣን ዘመን ማብቂያ ከሆነው አብዮትም ጋር ይመሳሰላል ተብሏል። የኦማር አልበሽር ከስልጣን መውደቅ ተከትሎም የሲቪልና ወታደራዊ ጥምር መንግሥት ተመስርቷል። ነገር ግን እውነተኛ የሲቪል መንግሥት እንዲሁም ፖለቲካዊ ለውጦች ይመጣሉ ወይ ለሚለው በርካቶች ስጋት አጭሮባቸዋል። በትናንትናው ዕለት በተደረጉ ተቃውሞችም የተንሰራፋው ሙስና እንዲጠፋ፣ በአልበሽር አገዛዝ ወቅት የተገደሉ ሰዎች ፍትህ እንዲያገኙ እንዲሁም ቃል የተገባው ፓርላማ እንዲመሰረት የሚጠይቁ ነበሩ። የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክም በበኩላቸው ቁልፍ የሚባሉ ማሻሻያዎችና ለውጦች በሃገሪቱ እንደሚካሄዱ ጠቅሰው በመጪዎቹ ቀናቶችም ይፋ ይሆናሉ ብለዋል። ሃገሪቱ በተፈጠረው የገበያ ግሽበት ምክንያት የምግብ እንዲሁም የነዳጅ ዋጋ መጨመር ጫናን ፈጥሮባታል። ከዚህም በተጨማሪ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ያስከተለው ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ቀጥ ማለትም ድቀትን እንዳይፈጥር ፍራቻን ደቅኗል። | https://www.bbc.com/amharic/53243266 |
3politics
| ትግራይ፡ የጸጥታው ምክር ቤት በትግራይ በቂ እርዳታ ባይቀርብም የመንግሥት ጥረት የሚበረታታ ነው አለ | የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል በቂ የሰብዓዊ እርዳታ ባይቀርብም የኢትዮጵያ መንግሥት ጥረት ግን የሚበረታታ ነው አለ። ምክር ቤቱ ኢትዮጵያን በተመለከተ ለመጀመሪያ ጊዜ ባወጣው መግለጫ፤ በክልሉ ተፈጽመዋል የተባሉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት አሳስቦኛል ያለ ሲሆን፣ የምክር ቤቱ አባል አገራት የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና የፖለቲካ ነጻነትን ያከብራሉ ብሏል። የመግለጫውን መውጣት ተከትሎ የተመድ የኢትዮጵያ ተወካይ፤ የጸጥታው ምክር ቤት አባላት ለሰጡት 'ገንቢ ምልከታ እና ድጋፍ' አድናቆቱን ገልጿል። የጸጥታው ምክር ቤት ምን አለ? የጸጥታው ምክር ቤት ትናንት ባወጣው መግለጫ ላይ፤ የምክር ቤቱ አባል አገራት በትግራይ ያለው የሰብዓዊ ቀውስ እንዳሳሰበው ገልጾ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት የሰብዓዊ እርዳታ ለማቅረብ እና የሰብዓዊ እርዳታ እንዲቀርብ እያደረገ ያለው ጥረት የሚበረታታ ነው ብሏል። የጸጥታው ምክር ቤት ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት በተባበሩት መንግሥታት መርህ መሠረት መቀጠል አለበትም ብሏል። በትግራይ ያለው የደኅንነት እጦት የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ሥራ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እያሳደረም ነው ብሏል። ጾታዊ ጥቃቶችን ጨምሮ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ያሳስቡኛል ያለው ምክር ቤቱ፤ ጥሰቶቹ በገለልተኛ አካል እንዲመረመሩ እና ተጠያቂዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቋል። በዚህ ረገድም የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን በጋራ የሚያደርጉትን ምርመራ በበጎ ጎኑ ተቀብሎታል። የጸጥታው ምከር ቤት ዓለም አቀፍ ሕግጋቶች መከበር አለባቸው ብሏል። ምክር ቤቱ እንደ የአፍሪካ ሕብረት እና ኢጋድ የመሳሰሉ አህጉራዊ እና ቀጣናዊ ተቋማት ለችግሩ መፍትሄ ለማምጣት ለሚኖራቸው ተሳትፎ ጠንካራ ድጋፍ እንዳለው ገልጿል። በመጨረሻም ምክር ቤቱ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ የፖለቲካ ነጻናትና የግዛት አንድነትን እንደሚያከብር ገልጿል። የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤቱ ኢትዮጵያን በተመለከተ መግለጫ ለማውጣት በርካታ ጊዜ ቢሰበሰብም ከስምምነት ሳይደርስ መቅረቱ ይታወሳል። የካቲት 25/2013 ዓ.ም የጸጥታው ምክር ቤት ኢትዮጵያን በተመለከተ ያደረገው ውይይት ከስምምነት ላይ ሳይደርስ መቅረቱን ኤኤፍፒ የዜና ወኪል የዲፕሎማቲክ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቦ ነበር። የዜና ወኪሉ የጸጥታው ምክር ቤት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ባረጋገጠ መልኩ በትግራይ አስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደረግ እና ግጭት እንዲቆም የሚጠይቅ መግለጫ ለማውጣት ያደረገው ስብሰባ በሩሲያ እና በቻይና ተቃውሞ ሳይወጣ ቀርቷል። ሩሲያ እና ቻይና መግለጫው በኢትዮጵያ "ውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ መግባት ነው" በማለት ነበር ተቃውሟቸውን ያሰሙት። በተመሳሳይ በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ አሜሪካ በሉአላዊ አገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ከመግባት እንድትቆጠብ ጠይቆ ነበር። ሩሲያና ቻይና በተቃወሙት ሰብሰባ ላይ ሌሎች አባላት ምን ብለው ነበር? የካቲት 25/2013 ዓ.ም ተካሂዶ በነበረው ውይይት ላይ በትግራይ ክልል ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ለሁለት ሰዓት ያህል የዘለቀ ውይይት ተካሂዶ እንደነበረ ቢቢሲ ያናገራቸው በውይይቱ ላይ የታደሙ አንድ ዲፕሎማት አስታውሰዋል። አስራ አምስቱም የጸጥታው ምክር ቤት አባላት በተገኙበት በተካሄደው በዚህ ስብሰባ ላይ ሁሉም በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ በተመለከተ ሐሳባቸውን ሰንዝረዋል። በዝግ በተካሄደው በዚህ ስብሰባ ላይ ሁሉም የምክር ቤቱ አባላት ሊባል በሚችል ደረጃ በትግራይ ክልል ውስጥ ያለው የሰብአዊ ሁኔታ እንደሚያሳስባቸው መግለጻቸውን ዲፕሎማቱ ተናግረዋል። ኬንያ፣ ቱኒዚያና ኒጀር እንዲሁም ሴንት ቪንሰንት እና ግሪናዲስ የኢትዮጵያ መንግሥት የእርዳታ ፈቃድ የመስጠት ሂደቱን በማፋጠንና የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በመመርመር በኩል እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀው ነበር። በስብሰባው ላይ በትግራይ ውስጥ ያለው ሁኔታ ለቀጠናው ብቻ ሳይሆን የዓለም አቀፍ ሰላም እና ደኅንነት ጉዳያ ሊሆን ይችላል ያለችው ፈረንሳይ ናት። ስለዚህም ምክር ቤቱ መፍትሔ ለማምጣት የሚደረጉ ቀጠናዊ ጥረቶችን ከመደገፍ በተጨማሪ ለመፍትሔው አስተዋጽኦውን እንዲያበረክት ጠይቃ ነበር። ዩናይትድ ኪንግደም በስበሰባው ላይ ፖለቲካዊ መፍትሔ ማማጣት ባለመቻሉ ውጥረቱ እየተባባሰ እንዲሄድ ምክንያት መሆኑን ጠቅሳ፤ የጸጥታው ምክር ቤት ይህ ቀውስ እንዲያበቃ ለማድረግ ተገቢውን ሚና መጫወት ይኖርበታል ብላለች። አሜሪካ በኢትዮጵያ ያለው የሰብአዊ እርዳታና የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ እንደሚያሳስባት ገልጻ ይህም ለቀጠናው ሰላምና ጸጥታ ቀጥተኛ ስጋት ስለሆነ በቶሎ መፍትሔ ሊሰጠው ይገባል ብላ ነበር። ሩሲያ፣ ቻይና፣ ሕንድና ቬትናም ያለው የሰብአዊ ሁኔታ እንደሚያሳስባቸው የገለጹ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ መንግሥት በዚህ ረገድ እርዳታ ለማቅረብ እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀው የኢትዮጵያ ሉአላዊነትና የግዛት አንድነት እንዲከበር ጥሪ አቅርበዋል። በተጨማሪም እነዚህ አገራትና የምክር ቤቱ አባል የሆኑ የአፍሪካ አገራት ለችግሩ መፍትሔ ለመፈለግ ኢጋድንና የአፍሪካ ሕብረትን የመሳሰሉ ተቋማት ሚና እንደሚደግፉ ገልጸዋል። የተባበሩት መንግሥታት የእርዳታ ማስተባበሪያ ግድያዎችን በተመለከተ የሚወጡት ሪፖርቶች አሳሳቢ እንደሆኑ ገልጾ፤ የሰብአዊ ሁኔታውን በተመለከተ ያለው መረጃ መሬት ላይ ያለው እውነታ ነጸብራቅ እንደሆነ ገልጿል። በተጨማሪም አስፈላጊውን እርዳታ ለማቅረብ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፉ ከፍ እንዲል ተጨማሪ ሐብት እንደሚያስፈልግም አመልክቷል። የጸጥታው ምክር ቤት አባል አገራት የትኞቹ ናቸው? የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት 15 አባል አገራት አሉ። ከ15ቱ አባል አገራት አምስቱ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት ያላቸው ቋሚ አባል አገራት ሲሆኑ፤ አስሩ ደግሞ በየዓመቱ የሚቀያየሩ እና ድምጽን በድምጽ የመሻር አቅም የሌላቸው አባል አገራት ናቸው። ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት ያላቸው የምክር ቤቱ አባላት አሜሪካ፣ ሩሲያ፣ ዩናይትድ ኪንግድ፣ ፈረንሳይ እና ቻይና ናቸው። ኢስቶኒያ፣ ሕንድ፣ አየርላንድ፣ ኬንያ፣ ሜክሲኮ፣ ኒጂር፣ ኖርዌይ፣ ሴንት ቪንሰንት ኤንድ ዘ ግሬናዲንስ፣ ቱኒዚያ እና ቬትናም ደግሞ አስሩ ተለዋዋጭ የምክር ቤቱ አባላት ናቸው። | ትግራይ፡ የጸጥታው ምክር ቤት በትግራይ በቂ እርዳታ ባይቀርብም የመንግሥት ጥረት የሚበረታታ ነው አለ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል በቂ የሰብዓዊ እርዳታ ባይቀርብም የኢትዮጵያ መንግሥት ጥረት ግን የሚበረታታ ነው አለ። ምክር ቤቱ ኢትዮጵያን በተመለከተ ለመጀመሪያ ጊዜ ባወጣው መግለጫ፤ በክልሉ ተፈጽመዋል የተባሉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት አሳስቦኛል ያለ ሲሆን፣ የምክር ቤቱ አባል አገራት የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና የፖለቲካ ነጻነትን ያከብራሉ ብሏል። የመግለጫውን መውጣት ተከትሎ የተመድ የኢትዮጵያ ተወካይ፤ የጸጥታው ምክር ቤት አባላት ለሰጡት 'ገንቢ ምልከታ እና ድጋፍ' አድናቆቱን ገልጿል። የጸጥታው ምክር ቤት ምን አለ? የጸጥታው ምክር ቤት ትናንት ባወጣው መግለጫ ላይ፤ የምክር ቤቱ አባል አገራት በትግራይ ያለው የሰብዓዊ ቀውስ እንዳሳሰበው ገልጾ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት የሰብዓዊ እርዳታ ለማቅረብ እና የሰብዓዊ እርዳታ እንዲቀርብ እያደረገ ያለው ጥረት የሚበረታታ ነው ብሏል። የጸጥታው ምክር ቤት ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት በተባበሩት መንግሥታት መርህ መሠረት መቀጠል አለበትም ብሏል። በትግራይ ያለው የደኅንነት እጦት የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ሥራ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እያሳደረም ነው ብሏል። ጾታዊ ጥቃቶችን ጨምሮ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ያሳስቡኛል ያለው ምክር ቤቱ፤ ጥሰቶቹ በገለልተኛ አካል እንዲመረመሩ እና ተጠያቂዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቋል። በዚህ ረገድም የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን በጋራ የሚያደርጉትን ምርመራ በበጎ ጎኑ ተቀብሎታል። የጸጥታው ምከር ቤት ዓለም አቀፍ ሕግጋቶች መከበር አለባቸው ብሏል። ምክር ቤቱ እንደ የአፍሪካ ሕብረት እና ኢጋድ የመሳሰሉ አህጉራዊ እና ቀጣናዊ ተቋማት ለችግሩ መፍትሄ ለማምጣት ለሚኖራቸው ተሳትፎ ጠንካራ ድጋፍ እንዳለው ገልጿል። በመጨረሻም ምክር ቤቱ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ የፖለቲካ ነጻናትና የግዛት አንድነትን እንደሚያከብር ገልጿል። የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤቱ ኢትዮጵያን በተመለከተ መግለጫ ለማውጣት በርካታ ጊዜ ቢሰበሰብም ከስምምነት ሳይደርስ መቅረቱ ይታወሳል። የካቲት 25/2013 ዓ.ም የጸጥታው ምክር ቤት ኢትዮጵያን በተመለከተ ያደረገው ውይይት ከስምምነት ላይ ሳይደርስ መቅረቱን ኤኤፍፒ የዜና ወኪል የዲፕሎማቲክ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቦ ነበር። የዜና ወኪሉ የጸጥታው ምክር ቤት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ባረጋገጠ መልኩ በትግራይ አስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደረግ እና ግጭት እንዲቆም የሚጠይቅ መግለጫ ለማውጣት ያደረገው ስብሰባ በሩሲያ እና በቻይና ተቃውሞ ሳይወጣ ቀርቷል። ሩሲያ እና ቻይና መግለጫው በኢትዮጵያ "ውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ መግባት ነው" በማለት ነበር ተቃውሟቸውን ያሰሙት። በተመሳሳይ በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ አሜሪካ በሉአላዊ አገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ከመግባት እንድትቆጠብ ጠይቆ ነበር። ሩሲያና ቻይና በተቃወሙት ሰብሰባ ላይ ሌሎች አባላት ምን ብለው ነበር? የካቲት 25/2013 ዓ.ም ተካሂዶ በነበረው ውይይት ላይ በትግራይ ክልል ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ለሁለት ሰዓት ያህል የዘለቀ ውይይት ተካሂዶ እንደነበረ ቢቢሲ ያናገራቸው በውይይቱ ላይ የታደሙ አንድ ዲፕሎማት አስታውሰዋል። አስራ አምስቱም የጸጥታው ምክር ቤት አባላት በተገኙበት በተካሄደው በዚህ ስብሰባ ላይ ሁሉም በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ በተመለከተ ሐሳባቸውን ሰንዝረዋል። በዝግ በተካሄደው በዚህ ስብሰባ ላይ ሁሉም የምክር ቤቱ አባላት ሊባል በሚችል ደረጃ በትግራይ ክልል ውስጥ ያለው የሰብአዊ ሁኔታ እንደሚያሳስባቸው መግለጻቸውን ዲፕሎማቱ ተናግረዋል። ኬንያ፣ ቱኒዚያና ኒጀር እንዲሁም ሴንት ቪንሰንት እና ግሪናዲስ የኢትዮጵያ መንግሥት የእርዳታ ፈቃድ የመስጠት ሂደቱን በማፋጠንና የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በመመርመር በኩል እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀው ነበር። በስብሰባው ላይ በትግራይ ውስጥ ያለው ሁኔታ ለቀጠናው ብቻ ሳይሆን የዓለም አቀፍ ሰላም እና ደኅንነት ጉዳያ ሊሆን ይችላል ያለችው ፈረንሳይ ናት። ስለዚህም ምክር ቤቱ መፍትሔ ለማምጣት የሚደረጉ ቀጠናዊ ጥረቶችን ከመደገፍ በተጨማሪ ለመፍትሔው አስተዋጽኦውን እንዲያበረክት ጠይቃ ነበር። ዩናይትድ ኪንግደም በስበሰባው ላይ ፖለቲካዊ መፍትሔ ማማጣት ባለመቻሉ ውጥረቱ እየተባባሰ እንዲሄድ ምክንያት መሆኑን ጠቅሳ፤ የጸጥታው ምክር ቤት ይህ ቀውስ እንዲያበቃ ለማድረግ ተገቢውን ሚና መጫወት ይኖርበታል ብላለች። አሜሪካ በኢትዮጵያ ያለው የሰብአዊ እርዳታና የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ እንደሚያሳስባት ገልጻ ይህም ለቀጠናው ሰላምና ጸጥታ ቀጥተኛ ስጋት ስለሆነ በቶሎ መፍትሔ ሊሰጠው ይገባል ብላ ነበር። ሩሲያ፣ ቻይና፣ ሕንድና ቬትናም ያለው የሰብአዊ ሁኔታ እንደሚያሳስባቸው የገለጹ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ መንግሥት በዚህ ረገድ እርዳታ ለማቅረብ እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀው የኢትዮጵያ ሉአላዊነትና የግዛት አንድነት እንዲከበር ጥሪ አቅርበዋል። በተጨማሪም እነዚህ አገራትና የምክር ቤቱ አባል የሆኑ የአፍሪካ አገራት ለችግሩ መፍትሔ ለመፈለግ ኢጋድንና የአፍሪካ ሕብረትን የመሳሰሉ ተቋማት ሚና እንደሚደግፉ ገልጸዋል። የተባበሩት መንግሥታት የእርዳታ ማስተባበሪያ ግድያዎችን በተመለከተ የሚወጡት ሪፖርቶች አሳሳቢ እንደሆኑ ገልጾ፤ የሰብአዊ ሁኔታውን በተመለከተ ያለው መረጃ መሬት ላይ ያለው እውነታ ነጸብራቅ እንደሆነ ገልጿል። በተጨማሪም አስፈላጊውን እርዳታ ለማቅረብ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፉ ከፍ እንዲል ተጨማሪ ሐብት እንደሚያስፈልግም አመልክቷል። የጸጥታው ምክር ቤት አባል አገራት የትኞቹ ናቸው? የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት 15 አባል አገራት አሉ። ከ15ቱ አባል አገራት አምስቱ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት ያላቸው ቋሚ አባል አገራት ሲሆኑ፤ አስሩ ደግሞ በየዓመቱ የሚቀያየሩ እና ድምጽን በድምጽ የመሻር አቅም የሌላቸው አባል አገራት ናቸው። ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት ያላቸው የምክር ቤቱ አባላት አሜሪካ፣ ሩሲያ፣ ዩናይትድ ኪንግድ፣ ፈረንሳይ እና ቻይና ናቸው። ኢስቶኒያ፣ ሕንድ፣ አየርላንድ፣ ኬንያ፣ ሜክሲኮ፣ ኒጂር፣ ኖርዌይ፣ ሴንት ቪንሰንት ኤንድ ዘ ግሬናዲንስ፣ ቱኒዚያ እና ቬትናም ደግሞ አስሩ ተለዋዋጭ የምክር ቤቱ አባላት ናቸው። | https://www.bbc.com/amharic/news-56855668 |
5sports
| የአፍሪካ ዋንጫ ፈር ቀዳጆቹ ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ ሲታወሱ | ከተጀመረ ሳምንት በሞላው የዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ በሜዳ ላይ ይህ ነው የሚባል ድምቀት ባይታይበትም የውድድር ፈር ቀዳጅ የሆኑት አገራት በአንድ ላይ ተሳታፊ በመሆናቸው በታሪካዊነቱ እየተጠቀሰ ነው። ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ በአውሮፓውያኑ 1957 የተጀመረውን የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ የጠነሰሱና የጀመሩ አገራት ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ ታሪክ ይዘክራቸዋል። ከ52 ዓመታት በኋላም የውድድሩ ሦስት የመጀመሪያ ተፎካካሪ አገራት ለመጀመሪያ ጊዜ ነው በአንድ ላይ በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ላይ ተሳታፊ የሆኑት። "የሦስቱም አገራት ቡድኖች በዚህ ውድድር አንድ ላይ መመለሳቸው ኩራትን እንዲሁም ጥልቀት ያለውን የውድድሩን ባህልን የሚያንጸባርቅ ነው" በማለት የስፖርት ጋዜጠኛው ባደርልዲን ባከይት ተናግሯል። በአፍሪካ ዋንጫ ቀዳሚ ስፍራ ያላቸው ሦስቱ አገራት ከፍተኛ ግምት የሚሰጠውን ዋንጫ አሸናፊ ቢሆኑም ግብፅ ሰባት ጊዜ በማሸነፍ ክብረ ወሰንን ጨብጣለች። ኢትዮጵያና እና ሱዳን ደግሞ አንዳንድ ዋንጫዎችን በስማቸው አስመዝግበዋል። እግር ኳስ በምሥራቅ አፍሪካ አገራቱ ኢትዮጵያና ሱዳን ከፍተኛ ተወዳጅነት ቢኖረውም እንዲሁም ከፍተኛ ተሰጥኦ ያላቸው ተጫዋቾች እንዳላቸው ቢነገርም ከነበራቸው ከ1960ዎቹና 70ዎቹ ታላቅነት ወደ ኋላ ቀርተዋል። ከምሥራቅ አፍሪካ አገራት በብቸኝነት ዋንጫውን ያነሱት ጎረቤት አገራቱ ኢትዮጵያ እና ሱዳን በጨዋታው ተመሳሳይ ታሪክ አላቸው። በአፍሪካ ዋንጫ ቀደምት ስፍራ ቢኖራቸውም ሁለቱም ድሎቻቸውን ያገኙት በአገራቸው መሬት ነበር። ኢትዮጵያ ለ31 ዓመታት ያህል ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ማለፍ አቅቷት በአውሮፓውያኑ 2013 ነበር ወደ ውድድሩ መመለስ የቻለችው፤ በተመሳሳይ ሱዳንም እንዲሁ ለ32 ዓመታት ያህል ርቃ በአውሮፓውያኑ 2008 ነበር ተሳታፊ የሆነችው። "በእግር ኳሱ ዘርፍ ሱዳንና ኢትዮጵያን ወደ ኋላ በመመለስ ረገድ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ሚና ተጫውተዋል" በማለት የሚቺጋን ስቴት ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰርና 'አፍሪካን ሶከርስኬፕስ፡ ሀው ኤ ኮንቲነንት ቼንጅድ ዘ ወርልድ'ስ ጌም' መጽሐፍ ደራሲ ፒተር አሌጊ ይናገራሉ። "ነገር ግን የአፍሪካ ዋንጫ እየተስፋፋና የዓለም ዋንጫ 2026 ማጣሪያ ባለበት በአሁኑ ወቅት የሁለቱ አገራት ቡድኖች አዎንታዊ ሁኔታዎችን እያሳዩ ያሉ ይመስላል" ሲሉ ያስረዳሉ። በሁለቱም አገራት የተራዘሙ የእርስ በርስ ጦርነቶች፣ የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ የኢኮኖሚ ውድቀት እና ተፈጥሯዊ አደጋዎች ተደማምረው በእግር ኳስ ጨዋታው እድገትና ሂደት ላይ በአሉታዊ መልኩ ተጽዕኖ አሳድረዋል። ይሁን እንጂ ሁለቱም አገራት ቀደም ባለው ስኬታቸው የተነሳ የሰፈነው ኩራት ለትውልዶች እንደ አስጨናቂ ማስታወሻና ማበረታቻ ሆኖም አገልግሏል። ኢትዮጵያ ካሜሩን እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ዋንጫ ባደረገቻቸው ሁለቱም ጨዋታዎች ሽንፈትን ማስተናገዷን ተከትሎ ለቀጣዩ ዙር የማለፊያ ዕድሏን አጥብቦታል። ነገር ግን ሱዳን ከጊኒ ቢሳዎ ጋር በነበረው ጨዋታ አቻ መውጣቷን ተከትሎ ወደ ቀጣዩ ዙር ልታልፍ ትችላለች። በናይጄሪያ ሽንፈት ያጋጠማት ግብፅም በቀጣዩ ከዚህ ማገገም አለባት። የአፍሪካ ዋንጫ ውልደት በአውሮፓውያኑ 1956 የኢትዮጵያ የግብፅና የሱዳን ባለሥልጣናት ከደቡብ አፍሪካ ተወካይ ጋር በመሆን የአፍሪካ አህጉራዊ ውድድርን ለመመስረት በፖርቹጋል በነበረው የዓለም እግር ኳስ አስተዳዳሪ ፊፋ አጠቃላይ ጉባኤ ላይ ተገኙ። የመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ በአውሮፓውያኑ 1957 በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም የተካሄደ ሲሆን ሲሆን የደቡብ አፍሪካ ፌደሬሽን ከተለያዩ ዘሮች የተውጣጣ ቡድን ለመላክ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ከውድድሩ ተገለለች። ሱዳንን የረታችው ግብፅ፣ ኢትዮጵያንም በፍፃሜው ጨዋታ 2 ለ 1 በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆነች። ነገር ግን የኢትዮጵያ ቡድን በአውሮፓውያኑ 1962 በተካሄደው በሦተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ያኔ አረብ ሪፐብሊክ ትባል የነበረችውን ግብፅ 4 ለ 2 በመርታት ሻምፒዮን በመሆን ድሏን አጣጣመች። የቡድኑ አምበል ኤርትራዊው ሉቺያኖ ቫሳሎ ዋንጫውን ከአፄ ኃይለሥላሴ እጅ የተቀበለ ሲሆን ይህ ውድድር ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ያዘጋጀችው ነበር። "ኢትዮጵያ በአትሌቲክሱ ዘርፍ በጣም ታዋቂ ናት፤ ነገር ግን በኢትዮጵያ በጣም ተወዳጅ ስፖርት እግር ኳስ ነው" በማለት በአዲስ አበባ የሱፐር ስፓርት ተንታኝ ሰይድ ኪያር ይናገራል። በመጀመሪያዎቹ ሁለት ውድድሮች ተሳታፊዎች የነበሩት የሦስት አገራት ቡድኖች ነበሩ ቀስ በቀስም ሌሎች አገራት መቀላቀል ጀመሩ። ይህንን በተመለከተ ሰይድ ኪያር እንደሚያምነው ያለፉትን ድሎችንም ቢሆን በጥልቀት ልንመረምረው ይገባል ይላል። "በተጫዋቾቻችን፣ በአሰልጣኞች፣ በታሪክ ሰሪዎቻችን ኩራት እና ክብር ይሰማናል። ነገር ግን እንደ አይቮሪኮስት፣ ናይጄሪያና ቱኒዝያ በርካታ የአፍሪካ አገራት በቅኝ ግዛት ውስጥ ነበሩ። ብሔራዊ ቡድኖቻቸውም አልነበሩም" በማለት የወቅቱን ፖለቲካዊና ታሪካዊ ዳራ ማጥናት እንደሚያስፈልግ ያስረዳል። ለሱዳን እክል የሆነው የአገር ውስጥ ፖሊሲ ሱዳን በአውሮፓውያኑ 1970 እነ አሊ ጋጋሪ፣ ጃክሳ በመባል የሚታወቀው ናስር ኤዲን ባካተተው ወርቃማ በሚባለው የእግር ኳስ ትውልዷ ጋናን 1 ለ ምንም በመርታት ብቸኛዋን ዋንጫ አሸንፋለች። የሱዳን ቡድን በዚያው ዓመት በሜክሲኮ በተካሄደው የዓለም ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ ተቃርቦ ነበር። ከሁለት ዓመት በኋላ ቡድኑ በአውሮፓውያኑ 1972 ሙኒክ ኦሊምፒክ ተሳትፎ በአንፃራዊነት ጥሩ አፈጻጸም አሳይቷል። ነገርግን በቀጣዮቹ ዓመታት 'ዘ ሴክሬታሪ በርድስ' ቡድን ውድቀት ገጠመው። "በወቅቱ አገሪቱ ውስጥ የነበረው መረጋጋት ለእግር ኳስ ማደግ ከፍተኛ ሚና ተጫውቶ ነበር። ነገር ግን የፖለቲካ አለመረጋጋት እና የምጣኔ ሀብት ችግሮች አገሪቱ በሌሎች ጉዳይ ላይ እንድታተኩር አድርጓታል" በማለት የወርቃማው ትውልድ ቡድን አባል የነበረው በአሁኑ ወቅት የ77 ዓመት እድሜ አዛውንቱ ጃክሳ ያስረዳል። በርካታ የመንግሥት ፖሊሲዎች በእግር ኳሱ ላይ የራሳቸውን ጥላ አጥልተውበታል። ከእነዚህም መካከል የ1976ቱ አል-ሪያዳ አል-ጃማሂሪያ ወይም የቀድሞው አምባገነን ጃፋር ኒሜሪ የብሔራዊ ሊግን በማገድ እግር ኳስን ወደ አካባቢያዊ ውድድር ያወረዱበት "ስፖርት ለሰፊው ሕዝብ" ፖሊሲዎች ይጠቀሳሉ። በምላሹም የሱዳን ታዋቂ ተጫዋቾች ወደ ጎረቤት አገራት እና ሊጎች በተለይም ወደ አረብ ባሕረ ሰላጤ አቀኑ። ከአንድ ዓመት በኋላ ፖሊሲው እንዲቀር ቢደረግም ከፍተኛ ጉዳት ካደረሰ በኋላ ነበር። "ሱዳን ማገገም ያልቻለችበት የትውልድ መቆራረጥ አጋጠመ" በማለት የኩራ ዶት ኮም ድረ ገፅ ጋዜጠኛ ባኬት ይናገራል። ጨዋታዎቹ አካላዊ እንዲሁም የታክቲክ ለውጦች በመጡበት ወቅት የምሥራቅ አፍሪካ ተጫዋቾች እና አሰልጣኞች ከዘመኑ ጋር መራመድ ወይ መላመድ አለመቻላቸው ከምዕራብ እና ሰሜን አፍሪካ አገራት ጋር መፎካከር አዳጋች እንዲሆን ያደረጉባቸው ሌሎች ምክንያቶችም ሊታሰብባቸው ይገባል። "የእኛን የአጨዋወት ዘይቤ ከአካላዊ ወደ አእምሯዊ መለወጥ ከቻልን ኳስን በመቆጣጠር፣ በአጫጭር ቅብብሎች፣ በቴክኒክ ችሎታዎች ጥሩ ነን" ሲል ሰይድ ያስረዳል። ከሜዳ ውጭ ያለው አደረጃጀት መስተከካል የተሻሻለ የጨዋታ አያያዝ እና የረጅም ጊዜ ስልቶችን መንደፍ ያስፈልጋል። ለምሳሌም ያህል እንደ ስፔን የማለፊያ ስታይል መተግበር ወይም በአውሮፓ ሻምፒዮና ደካማ ውጤቶችን ተከትሎ ጀርመን የታዳጊዎች የእግር ኳስ ፕሮግራሞችን ማዋቀር የመሳሰሉትን አይነት ፕሮግራሞች ልንከተል ያስፈልጋል። "ገንዘብ ማግኘት ወይም ጥሩ ተጫዎቾች እንዲኖረን ማድረግ ብቻ ሳይሆንን ይህንንም በአግባቡ ማስተዳደር እና ማቀድ ያስፈልጋል" ሲል የሞደርን ስፖርት ባልደረባ ሀሰን ኤል ሚስታዊ ይናገራል። አንጋፋው የስፖርት ጋዜጠኛ አሁንም ግብፅ ለመሻሻል ቦታ እንዳላት ያምናል። ለዚህም በአፍሪካ ዋንጫ በመሳተፍ ክብረ ወሰንን መጨበጥ ብቻ ሳይሆን ከአውሮፓውያኑ 2006-2010 ባለው ሦስት ተከታታይ ዋንጫዎችም ድሎችን በማስመዝገብ እንዲሁም በዓለም ዋንጫም ሦስት ጊዜ መሳተፏን ይጠቅሳል። ሌላኛው ባክሄት የሚጠቅሰው የሱዳን ትልልቅ ክለቦች የበላይነትን ሲሆን ይህም የሌሎችን ጉዳዮችንም እድገት የሚነካ ጉዳይ ነው። አል-ሂላል እና አል-ሜሪክ የተሰኙት ቡድኖች በአህጉር አቀፍ ውድድር በአንፃራዊነት ጥሩ ውጤት ያስመዘገቡ ቢሆንም ከሀብታም ደጋፊዎች የሚያገኙት ድጋፍ ውድድሮችን እያደናቀፈ ይገኛል። የምዕራብ እና የሰሜን አፍሪካ አገራትም ተጫዋቾቻቸው በከፍተኛ የአውሮፓ ክለቦች እና ሊጎች መጨዋታቸው ተጠቃሚ የሚያደርጋቸው ሲሆን ኢትዮጵያ እና ሱዳን በበኩላቸው በአብዛኛው በአገር ውስጥ የሚጫወቱ ተጫዎች ነው ያሏቸው። በካሜሮንም ለሚደረገው ውድድር እነዚህኑ ተጫዋቾችን ነው ይዘው የቀረቡት። "ለአውሮፓ ክለቦችና ሊጎች የሚጫወቱ ተጫዋቾቹ ልምዳቸውን ወደ አገራቸው ብሔራዊ ቡድኖቻቸው ያመጣሉ" ይላል ኤል ሚስታካዊ። ኢትዮጵያና ሱዳን ከአፍሪካ ዋንጫ ተፎካካሪነት ርቀው ቢገኙም በኢትዮጵያ በቀጠለው የርስ በርስ ጦርነትና በሱዳን ባለው መፈንቅለ መንግሥት ተመሳሳይ የፖለቲካ ፈተና ላይ ያሉት አገራት ደጋፊዎቻቸው በጨዋታቸው እንደሚያስደንቁ ተስፋን ሰንቀዋል። | የአፍሪካ ዋንጫ ፈር ቀዳጆቹ ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ ሲታወሱ ከተጀመረ ሳምንት በሞላው የዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ በሜዳ ላይ ይህ ነው የሚባል ድምቀት ባይታይበትም የውድድር ፈር ቀዳጅ የሆኑት አገራት በአንድ ላይ ተሳታፊ በመሆናቸው በታሪካዊነቱ እየተጠቀሰ ነው። ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ በአውሮፓውያኑ 1957 የተጀመረውን የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ የጠነሰሱና የጀመሩ አገራት ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ ታሪክ ይዘክራቸዋል። ከ52 ዓመታት በኋላም የውድድሩ ሦስት የመጀመሪያ ተፎካካሪ አገራት ለመጀመሪያ ጊዜ ነው በአንድ ላይ በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ላይ ተሳታፊ የሆኑት። "የሦስቱም አገራት ቡድኖች በዚህ ውድድር አንድ ላይ መመለሳቸው ኩራትን እንዲሁም ጥልቀት ያለውን የውድድሩን ባህልን የሚያንጸባርቅ ነው" በማለት የስፖርት ጋዜጠኛው ባደርልዲን ባከይት ተናግሯል። በአፍሪካ ዋንጫ ቀዳሚ ስፍራ ያላቸው ሦስቱ አገራት ከፍተኛ ግምት የሚሰጠውን ዋንጫ አሸናፊ ቢሆኑም ግብፅ ሰባት ጊዜ በማሸነፍ ክብረ ወሰንን ጨብጣለች። ኢትዮጵያና እና ሱዳን ደግሞ አንዳንድ ዋንጫዎችን በስማቸው አስመዝግበዋል። እግር ኳስ በምሥራቅ አፍሪካ አገራቱ ኢትዮጵያና ሱዳን ከፍተኛ ተወዳጅነት ቢኖረውም እንዲሁም ከፍተኛ ተሰጥኦ ያላቸው ተጫዋቾች እንዳላቸው ቢነገርም ከነበራቸው ከ1960ዎቹና 70ዎቹ ታላቅነት ወደ ኋላ ቀርተዋል። ከምሥራቅ አፍሪካ አገራት በብቸኝነት ዋንጫውን ያነሱት ጎረቤት አገራቱ ኢትዮጵያ እና ሱዳን በጨዋታው ተመሳሳይ ታሪክ አላቸው። በአፍሪካ ዋንጫ ቀደምት ስፍራ ቢኖራቸውም ሁለቱም ድሎቻቸውን ያገኙት በአገራቸው መሬት ነበር። ኢትዮጵያ ለ31 ዓመታት ያህል ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ማለፍ አቅቷት በአውሮፓውያኑ 2013 ነበር ወደ ውድድሩ መመለስ የቻለችው፤ በተመሳሳይ ሱዳንም እንዲሁ ለ32 ዓመታት ያህል ርቃ በአውሮፓውያኑ 2008 ነበር ተሳታፊ የሆነችው። "በእግር ኳሱ ዘርፍ ሱዳንና ኢትዮጵያን ወደ ኋላ በመመለስ ረገድ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ሚና ተጫውተዋል" በማለት የሚቺጋን ስቴት ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰርና 'አፍሪካን ሶከርስኬፕስ፡ ሀው ኤ ኮንቲነንት ቼንጅድ ዘ ወርልድ'ስ ጌም' መጽሐፍ ደራሲ ፒተር አሌጊ ይናገራሉ። "ነገር ግን የአፍሪካ ዋንጫ እየተስፋፋና የዓለም ዋንጫ 2026 ማጣሪያ ባለበት በአሁኑ ወቅት የሁለቱ አገራት ቡድኖች አዎንታዊ ሁኔታዎችን እያሳዩ ያሉ ይመስላል" ሲሉ ያስረዳሉ። በሁለቱም አገራት የተራዘሙ የእርስ በርስ ጦርነቶች፣ የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ የኢኮኖሚ ውድቀት እና ተፈጥሯዊ አደጋዎች ተደማምረው በእግር ኳስ ጨዋታው እድገትና ሂደት ላይ በአሉታዊ መልኩ ተጽዕኖ አሳድረዋል። ይሁን እንጂ ሁለቱም አገራት ቀደም ባለው ስኬታቸው የተነሳ የሰፈነው ኩራት ለትውልዶች እንደ አስጨናቂ ማስታወሻና ማበረታቻ ሆኖም አገልግሏል። ኢትዮጵያ ካሜሩን እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ዋንጫ ባደረገቻቸው ሁለቱም ጨዋታዎች ሽንፈትን ማስተናገዷን ተከትሎ ለቀጣዩ ዙር የማለፊያ ዕድሏን አጥብቦታል። ነገር ግን ሱዳን ከጊኒ ቢሳዎ ጋር በነበረው ጨዋታ አቻ መውጣቷን ተከትሎ ወደ ቀጣዩ ዙር ልታልፍ ትችላለች። በናይጄሪያ ሽንፈት ያጋጠማት ግብፅም በቀጣዩ ከዚህ ማገገም አለባት። የአፍሪካ ዋንጫ ውልደት በአውሮፓውያኑ 1956 የኢትዮጵያ የግብፅና የሱዳን ባለሥልጣናት ከደቡብ አፍሪካ ተወካይ ጋር በመሆን የአፍሪካ አህጉራዊ ውድድርን ለመመስረት በፖርቹጋል በነበረው የዓለም እግር ኳስ አስተዳዳሪ ፊፋ አጠቃላይ ጉባኤ ላይ ተገኙ። የመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ በአውሮፓውያኑ 1957 በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም የተካሄደ ሲሆን ሲሆን የደቡብ አፍሪካ ፌደሬሽን ከተለያዩ ዘሮች የተውጣጣ ቡድን ለመላክ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ከውድድሩ ተገለለች። ሱዳንን የረታችው ግብፅ፣ ኢትዮጵያንም በፍፃሜው ጨዋታ 2 ለ 1 በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆነች። ነገር ግን የኢትዮጵያ ቡድን በአውሮፓውያኑ 1962 በተካሄደው በሦተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ያኔ አረብ ሪፐብሊክ ትባል የነበረችውን ግብፅ 4 ለ 2 በመርታት ሻምፒዮን በመሆን ድሏን አጣጣመች። የቡድኑ አምበል ኤርትራዊው ሉቺያኖ ቫሳሎ ዋንጫውን ከአፄ ኃይለሥላሴ እጅ የተቀበለ ሲሆን ይህ ውድድር ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ያዘጋጀችው ነበር። "ኢትዮጵያ በአትሌቲክሱ ዘርፍ በጣም ታዋቂ ናት፤ ነገር ግን በኢትዮጵያ በጣም ተወዳጅ ስፖርት እግር ኳስ ነው" በማለት በአዲስ አበባ የሱፐር ስፓርት ተንታኝ ሰይድ ኪያር ይናገራል። በመጀመሪያዎቹ ሁለት ውድድሮች ተሳታፊዎች የነበሩት የሦስት አገራት ቡድኖች ነበሩ ቀስ በቀስም ሌሎች አገራት መቀላቀል ጀመሩ። ይህንን በተመለከተ ሰይድ ኪያር እንደሚያምነው ያለፉትን ድሎችንም ቢሆን በጥልቀት ልንመረምረው ይገባል ይላል። "በተጫዋቾቻችን፣ በአሰልጣኞች፣ በታሪክ ሰሪዎቻችን ኩራት እና ክብር ይሰማናል። ነገር ግን እንደ አይቮሪኮስት፣ ናይጄሪያና ቱኒዝያ በርካታ የአፍሪካ አገራት በቅኝ ግዛት ውስጥ ነበሩ። ብሔራዊ ቡድኖቻቸውም አልነበሩም" በማለት የወቅቱን ፖለቲካዊና ታሪካዊ ዳራ ማጥናት እንደሚያስፈልግ ያስረዳል። ለሱዳን እክል የሆነው የአገር ውስጥ ፖሊሲ ሱዳን በአውሮፓውያኑ 1970 እነ አሊ ጋጋሪ፣ ጃክሳ በመባል የሚታወቀው ናስር ኤዲን ባካተተው ወርቃማ በሚባለው የእግር ኳስ ትውልዷ ጋናን 1 ለ ምንም በመርታት ብቸኛዋን ዋንጫ አሸንፋለች። የሱዳን ቡድን በዚያው ዓመት በሜክሲኮ በተካሄደው የዓለም ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ ተቃርቦ ነበር። ከሁለት ዓመት በኋላ ቡድኑ በአውሮፓውያኑ 1972 ሙኒክ ኦሊምፒክ ተሳትፎ በአንፃራዊነት ጥሩ አፈጻጸም አሳይቷል። ነገርግን በቀጣዮቹ ዓመታት 'ዘ ሴክሬታሪ በርድስ' ቡድን ውድቀት ገጠመው። "በወቅቱ አገሪቱ ውስጥ የነበረው መረጋጋት ለእግር ኳስ ማደግ ከፍተኛ ሚና ተጫውቶ ነበር። ነገር ግን የፖለቲካ አለመረጋጋት እና የምጣኔ ሀብት ችግሮች አገሪቱ በሌሎች ጉዳይ ላይ እንድታተኩር አድርጓታል" በማለት የወርቃማው ትውልድ ቡድን አባል የነበረው በአሁኑ ወቅት የ77 ዓመት እድሜ አዛውንቱ ጃክሳ ያስረዳል። በርካታ የመንግሥት ፖሊሲዎች በእግር ኳሱ ላይ የራሳቸውን ጥላ አጥልተውበታል። ከእነዚህም መካከል የ1976ቱ አል-ሪያዳ አል-ጃማሂሪያ ወይም የቀድሞው አምባገነን ጃፋር ኒሜሪ የብሔራዊ ሊግን በማገድ እግር ኳስን ወደ አካባቢያዊ ውድድር ያወረዱበት "ስፖርት ለሰፊው ሕዝብ" ፖሊሲዎች ይጠቀሳሉ። በምላሹም የሱዳን ታዋቂ ተጫዋቾች ወደ ጎረቤት አገራት እና ሊጎች በተለይም ወደ አረብ ባሕረ ሰላጤ አቀኑ። ከአንድ ዓመት በኋላ ፖሊሲው እንዲቀር ቢደረግም ከፍተኛ ጉዳት ካደረሰ በኋላ ነበር። "ሱዳን ማገገም ያልቻለችበት የትውልድ መቆራረጥ አጋጠመ" በማለት የኩራ ዶት ኮም ድረ ገፅ ጋዜጠኛ ባኬት ይናገራል። ጨዋታዎቹ አካላዊ እንዲሁም የታክቲክ ለውጦች በመጡበት ወቅት የምሥራቅ አፍሪካ ተጫዋቾች እና አሰልጣኞች ከዘመኑ ጋር መራመድ ወይ መላመድ አለመቻላቸው ከምዕራብ እና ሰሜን አፍሪካ አገራት ጋር መፎካከር አዳጋች እንዲሆን ያደረጉባቸው ሌሎች ምክንያቶችም ሊታሰብባቸው ይገባል። "የእኛን የአጨዋወት ዘይቤ ከአካላዊ ወደ አእምሯዊ መለወጥ ከቻልን ኳስን በመቆጣጠር፣ በአጫጭር ቅብብሎች፣ በቴክኒክ ችሎታዎች ጥሩ ነን" ሲል ሰይድ ያስረዳል። ከሜዳ ውጭ ያለው አደረጃጀት መስተከካል የተሻሻለ የጨዋታ አያያዝ እና የረጅም ጊዜ ስልቶችን መንደፍ ያስፈልጋል። ለምሳሌም ያህል እንደ ስፔን የማለፊያ ስታይል መተግበር ወይም በአውሮፓ ሻምፒዮና ደካማ ውጤቶችን ተከትሎ ጀርመን የታዳጊዎች የእግር ኳስ ፕሮግራሞችን ማዋቀር የመሳሰሉትን አይነት ፕሮግራሞች ልንከተል ያስፈልጋል። "ገንዘብ ማግኘት ወይም ጥሩ ተጫዎቾች እንዲኖረን ማድረግ ብቻ ሳይሆንን ይህንንም በአግባቡ ማስተዳደር እና ማቀድ ያስፈልጋል" ሲል የሞደርን ስፖርት ባልደረባ ሀሰን ኤል ሚስታዊ ይናገራል። አንጋፋው የስፖርት ጋዜጠኛ አሁንም ግብፅ ለመሻሻል ቦታ እንዳላት ያምናል። ለዚህም በአፍሪካ ዋንጫ በመሳተፍ ክብረ ወሰንን መጨበጥ ብቻ ሳይሆን ከአውሮፓውያኑ 2006-2010 ባለው ሦስት ተከታታይ ዋንጫዎችም ድሎችን በማስመዝገብ እንዲሁም በዓለም ዋንጫም ሦስት ጊዜ መሳተፏን ይጠቅሳል። ሌላኛው ባክሄት የሚጠቅሰው የሱዳን ትልልቅ ክለቦች የበላይነትን ሲሆን ይህም የሌሎችን ጉዳዮችንም እድገት የሚነካ ጉዳይ ነው። አል-ሂላል እና አል-ሜሪክ የተሰኙት ቡድኖች በአህጉር አቀፍ ውድድር በአንፃራዊነት ጥሩ ውጤት ያስመዘገቡ ቢሆንም ከሀብታም ደጋፊዎች የሚያገኙት ድጋፍ ውድድሮችን እያደናቀፈ ይገኛል። የምዕራብ እና የሰሜን አፍሪካ አገራትም ተጫዋቾቻቸው በከፍተኛ የአውሮፓ ክለቦች እና ሊጎች መጨዋታቸው ተጠቃሚ የሚያደርጋቸው ሲሆን ኢትዮጵያ እና ሱዳን በበኩላቸው በአብዛኛው በአገር ውስጥ የሚጫወቱ ተጫዎች ነው ያሏቸው። በካሜሮንም ለሚደረገው ውድድር እነዚህኑ ተጫዋቾችን ነው ይዘው የቀረቡት። "ለአውሮፓ ክለቦችና ሊጎች የሚጫወቱ ተጫዋቾቹ ልምዳቸውን ወደ አገራቸው ብሔራዊ ቡድኖቻቸው ያመጣሉ" ይላል ኤል ሚስታካዊ። ኢትዮጵያና ሱዳን ከአፍሪካ ዋንጫ ተፎካካሪነት ርቀው ቢገኙም በኢትዮጵያ በቀጠለው የርስ በርስ ጦርነትና በሱዳን ባለው መፈንቅለ መንግሥት ተመሳሳይ የፖለቲካ ፈተና ላይ ያሉት አገራት ደጋፊዎቻቸው በጨዋታቸው እንደሚያስደንቁ ተስፋን ሰንቀዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59977329 |
3politics
| ቦሪስ በኮቪድ ወቅት ስላዘጋጁት ግብዣ ከእንደራሴዎች ጥያቄ ሊቀርብላቸው ነው | የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ነምበር ቴን በሚባለው መሥሪያ ቤታቸው ኮቪድ-19 ባየለበት ወቅት ስላዘጋጁት ድግስ ከሕዝብ እንደራሴዎች ጥያቄ ሊቀርብላቸው ነው። ነባር የእንግሊዝ መንግሥት ባለሥልጣን የሆኑት ሱ ጌሪ፤ ቦሪስ ጆንሰንን የተለመከተ አንድ ሪፖርት ያወጣሉ ተብሎ በጉጉት እየተጠበቀ ነው። ነገር ግን ሪፖርቱ ይፋ ከመደረጉ በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ከሕዝብ እንደራሴዎች ጋር ፍጥጫ ይጠብቃቸዋል። ፖሊስ በበኩሉ የራሱን ምርምራ አድርጎ ውጤቱን ማክሰኞ ዕለት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። የሜት ፖሊስ ኮሚሽነር ክሬሲዳ ዲክ እንዳሉት የቦሪስ አስተዳደር ኮቪድ-19ን ተከትሎ የእንቅስቃሴ ገደብ በጣለበት ወቅት በተለያዩ የመንግሥት ሕንፃዎች የመጠጥ ድግሶች ነበሩ። ይህ የፖሊስ የምርመራ ውጤት ለቦሪስ ጆንሰን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖባቸዋል። ዳውንኒንግ ስትሪት በተሰኘው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዋና መሥሪያ የሚገኝበት ሥፍራ በኮቪድ-19 ምክንያት ሰዎች ቤታቸው ሳሉ እሳቸው ግን የመጠጥ ድግስ አዘጋጅተዋል የተባሉት ቦሪስ ከሰሞኑ ከፍተኛ ጫና እየደረሰባቸው ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፈረንጆቹ ግንቦት 20/2020 የመጀመሪያው የእንቅስቃሴ ገደብ በተጣለበት ወቅት አንድ "ሥራ ነክ" ድግስ ተዘጋጅቶ በመገኘቴ ይቅርታ እጠይቃለሁ ብለው ነበር። ነገር ግን ሰኔ 2020ም በተመሳሳይ የልደት ድግስ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ተዘጋጅቶ ነበር የሚሉ ዘገባዎች ብቅ ማለት ጀምረዋል። አንዳንድ ወግ አጥባቂ የሕዝብ እንደራሴዎች ቦሪስ ከሥልጣን እንዲወርዱ ቢጠይቁም ሚኒስትሮች ደግሞ የሱ ጌሪ ምርመራ ውጤት ይፋ እስኪሆን እንጠብቅ እያሉ ነው። ወግ አጥባቂው ቶሪ ፓርቲ ምርመራው ይፋ ከተደረገ በኋላ በቦሪስ መንግሥት ላይ እምነት የለንም የሚል ደብዳቤ ሊፅፉ አቅደዋል። ይህ ደግሞ ቀጣዩ የዩኬ መንግሥት ማነው ወደሚል ሽኩቻ ሊያስገባ ይችላል። ኮመንስ ለተሰኘው የታችኛው ምክር ቤት አባላት መግለጫ የሚሰጡት ቦሪስ የምርመራውን ውጤት እየተጠባበቁ ሲሆን ውጤቱ ለሕዝብ መች ይፋ እንደሚሆን ግን አልታወቀም። ሌበር ፓርቲ በበኩሉ መንግሥት የሕዝብ እንደራሴዎች የምርመራውን ውጤት አንብበው እንዲያገናዝቡ ጊዜ እንዲሰጣቸው ጠይቋል። የታችኛው ምክር ቤት አባላት ኃላፊ የሆኑት ጃኮብ ሪስ-ሞግ የአሁኑ የእንደራሴዎችና የቦሪስ ፍጥጫ ከሌላው ጊዜ የተለየ እንደሚሆን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ጃኮብ አክለው የካቢኔው አባላት በሙሉ ቦሪስን የደገፉት "ያልደገፉ ሚኒስትሮች ሥልጣን እንዲለቁ ስለሚገደዱ ነው" ብለዋል። ትይዩ [ሻዶው] ዋና አቃቤ ሕግ የሆኑት ኤሚሊ ቶርንቤሪ እንደሚሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድግሶቹን በተለመከተ የቀረበባቸውን ወቀሳ ችላ ማለታቸው ትክክል አልነበረም። ኤሚሊ አክለው ቦሪስ ስለተካፈሏቸው ድግሶች በመዋሸታቸው ምክንያት አሁን ስላለው የኑሮ ውድነትም ሆነ ስለ ሩሲያ ወደ ዩክሬን መገስገስ የመወሰን ሥልጣን የላቸውም። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ከአንድም ሁለት ሶሥት አራቴ በቢሯቸው ድግሶች አዘጋጅተዋል ተብለው መወቀስ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። የዩናይት ኪንግደም ሕዝብን ያስቆጣው ጉዳይ ጠቅላዩ ድግስ ሲደግሱ ሕዝቡ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሎበት ቤቱ መከርቸሙ ነው። | ቦሪስ በኮቪድ ወቅት ስላዘጋጁት ግብዣ ከእንደራሴዎች ጥያቄ ሊቀርብላቸው ነው የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ነምበር ቴን በሚባለው መሥሪያ ቤታቸው ኮቪድ-19 ባየለበት ወቅት ስላዘጋጁት ድግስ ከሕዝብ እንደራሴዎች ጥያቄ ሊቀርብላቸው ነው። ነባር የእንግሊዝ መንግሥት ባለሥልጣን የሆኑት ሱ ጌሪ፤ ቦሪስ ጆንሰንን የተለመከተ አንድ ሪፖርት ያወጣሉ ተብሎ በጉጉት እየተጠበቀ ነው። ነገር ግን ሪፖርቱ ይፋ ከመደረጉ በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ከሕዝብ እንደራሴዎች ጋር ፍጥጫ ይጠብቃቸዋል። ፖሊስ በበኩሉ የራሱን ምርምራ አድርጎ ውጤቱን ማክሰኞ ዕለት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። የሜት ፖሊስ ኮሚሽነር ክሬሲዳ ዲክ እንዳሉት የቦሪስ አስተዳደር ኮቪድ-19ን ተከትሎ የእንቅስቃሴ ገደብ በጣለበት ወቅት በተለያዩ የመንግሥት ሕንፃዎች የመጠጥ ድግሶች ነበሩ። ይህ የፖሊስ የምርመራ ውጤት ለቦሪስ ጆንሰን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖባቸዋል። ዳውንኒንግ ስትሪት በተሰኘው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዋና መሥሪያ የሚገኝበት ሥፍራ በኮቪድ-19 ምክንያት ሰዎች ቤታቸው ሳሉ እሳቸው ግን የመጠጥ ድግስ አዘጋጅተዋል የተባሉት ቦሪስ ከሰሞኑ ከፍተኛ ጫና እየደረሰባቸው ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፈረንጆቹ ግንቦት 20/2020 የመጀመሪያው የእንቅስቃሴ ገደብ በተጣለበት ወቅት አንድ "ሥራ ነክ" ድግስ ተዘጋጅቶ በመገኘቴ ይቅርታ እጠይቃለሁ ብለው ነበር። ነገር ግን ሰኔ 2020ም በተመሳሳይ የልደት ድግስ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ተዘጋጅቶ ነበር የሚሉ ዘገባዎች ብቅ ማለት ጀምረዋል። አንዳንድ ወግ አጥባቂ የሕዝብ እንደራሴዎች ቦሪስ ከሥልጣን እንዲወርዱ ቢጠይቁም ሚኒስትሮች ደግሞ የሱ ጌሪ ምርመራ ውጤት ይፋ እስኪሆን እንጠብቅ እያሉ ነው። ወግ አጥባቂው ቶሪ ፓርቲ ምርመራው ይፋ ከተደረገ በኋላ በቦሪስ መንግሥት ላይ እምነት የለንም የሚል ደብዳቤ ሊፅፉ አቅደዋል። ይህ ደግሞ ቀጣዩ የዩኬ መንግሥት ማነው ወደሚል ሽኩቻ ሊያስገባ ይችላል። ኮመንስ ለተሰኘው የታችኛው ምክር ቤት አባላት መግለጫ የሚሰጡት ቦሪስ የምርመራውን ውጤት እየተጠባበቁ ሲሆን ውጤቱ ለሕዝብ መች ይፋ እንደሚሆን ግን አልታወቀም። ሌበር ፓርቲ በበኩሉ መንግሥት የሕዝብ እንደራሴዎች የምርመራውን ውጤት አንብበው እንዲያገናዝቡ ጊዜ እንዲሰጣቸው ጠይቋል። የታችኛው ምክር ቤት አባላት ኃላፊ የሆኑት ጃኮብ ሪስ-ሞግ የአሁኑ የእንደራሴዎችና የቦሪስ ፍጥጫ ከሌላው ጊዜ የተለየ እንደሚሆን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ጃኮብ አክለው የካቢኔው አባላት በሙሉ ቦሪስን የደገፉት "ያልደገፉ ሚኒስትሮች ሥልጣን እንዲለቁ ስለሚገደዱ ነው" ብለዋል። ትይዩ [ሻዶው] ዋና አቃቤ ሕግ የሆኑት ኤሚሊ ቶርንቤሪ እንደሚሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድግሶቹን በተለመከተ የቀረበባቸውን ወቀሳ ችላ ማለታቸው ትክክል አልነበረም። ኤሚሊ አክለው ቦሪስ ስለተካፈሏቸው ድግሶች በመዋሸታቸው ምክንያት አሁን ስላለው የኑሮ ውድነትም ሆነ ስለ ሩሲያ ወደ ዩክሬን መገስገስ የመወሰን ሥልጣን የላቸውም። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ከአንድም ሁለት ሶሥት አራቴ በቢሯቸው ድግሶች አዘጋጅተዋል ተብለው መወቀስ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። የዩናይት ኪንግደም ሕዝብን ያስቆጣው ጉዳይ ጠቅላዩ ድግስ ሲደግሱ ሕዝቡ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሎበት ቤቱ መከርቸሙ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/news-60136737 |
3politics
| 2020 በፎቶ ፡ ከኮሮናቫይረስ ጨረቃ ላይ ሰንደቅ አላማ እስከማስቀመጥ | ዓለም በኮሮናቫይረስ የተፈተነበት የፈረንጆቹ 2020 ሊያበቃ ነው። ዓመቱን ወደኋላ መለስ ብለን በፎቶ ስብስብ እንዲህ ቃኝተናል። ከጥር ወር እንጀምር። ጥር ቻይና ዉሃን ውስጥ የተቀሰቀሰው ኮሮናቫይረስን ለመከላከል የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ የግድ ነው። ከወራት በፊት በመላው ዓለም የጭምብል እጥረት ተከስቶ ነበር። የካቲት በከዋክብት ሳይንስ እጅግ አስደናቂ የሆነው ሙሉ ጨረቃ ቱርክ በሚገኘው ሰልሚዬ መስጂድ አቅራቢያ የታየው በዚህ ዓመት ነው። መጋቢት አብዛኛው ሰው ወዳጅ፣ ዘመድ፣ ጓደኛ ለማግኘት እንደ ዙም ያሉ የተለያዩ መተግበሪያዎችን ለመጠቀም ተገዷል። ይህ ፎቶ ሆንግ ኮንግ ውስጥ የሚገኝ መምህር ለተማሪዎቹ በበይነ መረብ ትምህርት ሲያስተላልፍ የተነሳ ነው። ሚያዝያ ወረርሽኙን ለመከላከል አካላዊ ርቀትን የመጠበቅ መርህ በዓለም ዙሪያ ተግባራዊ ሆኗል። አሜሪካ ውስጥ የሚኖሩ የካቶሊክ ቄስ ጸበል ለመርጨት ፈጠራ የተሞላበት መንገድን ተጠቅመዋል። ግንቦት ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ በፖሊስ እጅ መገደሉ በአሜሪካና በሌሎች አገራትም ዘረኝነትን የሚቃወም ንቅናቄ አስነስቷል። ሰኔ እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ከመጣሉ በፊት ባርሴሎና ውስጥ በሚገኘው ግሬን ቴትሬ ደል ሊሲዮ ከሁለት ሺህ ለሚበልጡ ችግኞች ሙዚቃ ቀርቧል። ሐምሌ ኢትዮጵያን ጨምሮ በሌሎችም የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች እንዲሁም በሕንድ፣ በፓኪስታን እና በኢራን ውስጥ የተስፋፋው የአንበጣ መንጋ ስጋት የሆነበት ዓመት ነው። በምስሉ ኬንያ ውስጥ አንዲት ሴት ሰብል በአንበጣ መንጋ ተወሮ ስትመለከት ይታያል። ነሐሴ በሊባኖስ መዲና በቤይሩት የተከሰተው ፍንዳታ ኒውክሌር ነክ ካልሆኑ ፍንዳታዎች ሁሉ ትልቁ ነው። ከ200 በላይ ሰዎች ሲሞቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ፎቶው የሚያሳየው ፒያኖ ተጫዋቹ ሬይመንድ ኢሳያም ከደረሰበት ጉዳት ባሻገር ቤቱን አጥቷል። መስከረም የብራዚል አማዞን ጫካ እጅግ በሚያስፈራ ሁኔታ የእሳት አደጋ ደርሶበታል። የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋቾች ቃጠሎው አሳስቧቸዋል። አንድ ጃጓር መዳፉ ተቃጥሎ ከእሳቱ ተርፏል። ጥቅምት ኮሮናቫይረስ ከፍተኛ ተጽዕኖ ካሳደረባቸው መካከል ነጋዴዎች በዋነኛነት ይጠቀሳሉ። በጣሊያን መዲና ሮም የሚገኘው ሬስቶራንት የንግዱ መቀዛቀዝ ተምሳሌት እንዲሆን አጽም አስቀምጧል። ኅዳር በታይላንድ ተቃውሞ ከሚሳተፉ አንዱ ሚትሬ ቺቲንዳ ነው። ጸጉሩን የተቆረጠው ተቃውሞውን እንደሚደግፍ በሚጠቁም የሦስት ጣት ምልክት ነው። ይህ ምልክት 'ሀንገር ጌምስ' ከተባለው ፊልም የተወሰደ ነው። ታኅሣስ ቻይና ጨረቃ ላይ ሰንደቅ አላማዋን በመትከል ከዓለም ሁለተኛዋ አገር ሆናለች። በተጨማሪም ቼንጅ-5 የተባለው የሕዋ ጉዞ ከ44 ዓመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጨረቃ አለት አምጥቷል። | 2020 በፎቶ ፡ ከኮሮናቫይረስ ጨረቃ ላይ ሰንደቅ አላማ እስከማስቀመጥ ዓለም በኮሮናቫይረስ የተፈተነበት የፈረንጆቹ 2020 ሊያበቃ ነው። ዓመቱን ወደኋላ መለስ ብለን በፎቶ ስብስብ እንዲህ ቃኝተናል። ከጥር ወር እንጀምር። ጥር ቻይና ዉሃን ውስጥ የተቀሰቀሰው ኮሮናቫይረስን ለመከላከል የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ የግድ ነው። ከወራት በፊት በመላው ዓለም የጭምብል እጥረት ተከስቶ ነበር። የካቲት በከዋክብት ሳይንስ እጅግ አስደናቂ የሆነው ሙሉ ጨረቃ ቱርክ በሚገኘው ሰልሚዬ መስጂድ አቅራቢያ የታየው በዚህ ዓመት ነው። መጋቢት አብዛኛው ሰው ወዳጅ፣ ዘመድ፣ ጓደኛ ለማግኘት እንደ ዙም ያሉ የተለያዩ መተግበሪያዎችን ለመጠቀም ተገዷል። ይህ ፎቶ ሆንግ ኮንግ ውስጥ የሚገኝ መምህር ለተማሪዎቹ በበይነ መረብ ትምህርት ሲያስተላልፍ የተነሳ ነው። ሚያዝያ ወረርሽኙን ለመከላከል አካላዊ ርቀትን የመጠበቅ መርህ በዓለም ዙሪያ ተግባራዊ ሆኗል። አሜሪካ ውስጥ የሚኖሩ የካቶሊክ ቄስ ጸበል ለመርጨት ፈጠራ የተሞላበት መንገድን ተጠቅመዋል። ግንቦት ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ በፖሊስ እጅ መገደሉ በአሜሪካና በሌሎች አገራትም ዘረኝነትን የሚቃወም ንቅናቄ አስነስቷል። ሰኔ እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ከመጣሉ በፊት ባርሴሎና ውስጥ በሚገኘው ግሬን ቴትሬ ደል ሊሲዮ ከሁለት ሺህ ለሚበልጡ ችግኞች ሙዚቃ ቀርቧል። ሐምሌ ኢትዮጵያን ጨምሮ በሌሎችም የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች እንዲሁም በሕንድ፣ በፓኪስታን እና በኢራን ውስጥ የተስፋፋው የአንበጣ መንጋ ስጋት የሆነበት ዓመት ነው። በምስሉ ኬንያ ውስጥ አንዲት ሴት ሰብል በአንበጣ መንጋ ተወሮ ስትመለከት ይታያል። ነሐሴ በሊባኖስ መዲና በቤይሩት የተከሰተው ፍንዳታ ኒውክሌር ነክ ካልሆኑ ፍንዳታዎች ሁሉ ትልቁ ነው። ከ200 በላይ ሰዎች ሲሞቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ፎቶው የሚያሳየው ፒያኖ ተጫዋቹ ሬይመንድ ኢሳያም ከደረሰበት ጉዳት ባሻገር ቤቱን አጥቷል። መስከረም የብራዚል አማዞን ጫካ እጅግ በሚያስፈራ ሁኔታ የእሳት አደጋ ደርሶበታል። የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋቾች ቃጠሎው አሳስቧቸዋል። አንድ ጃጓር መዳፉ ተቃጥሎ ከእሳቱ ተርፏል። ጥቅምት ኮሮናቫይረስ ከፍተኛ ተጽዕኖ ካሳደረባቸው መካከል ነጋዴዎች በዋነኛነት ይጠቀሳሉ። በጣሊያን መዲና ሮም የሚገኘው ሬስቶራንት የንግዱ መቀዛቀዝ ተምሳሌት እንዲሆን አጽም አስቀምጧል። ኅዳር በታይላንድ ተቃውሞ ከሚሳተፉ አንዱ ሚትሬ ቺቲንዳ ነው። ጸጉሩን የተቆረጠው ተቃውሞውን እንደሚደግፍ በሚጠቁም የሦስት ጣት ምልክት ነው። ይህ ምልክት 'ሀንገር ጌምስ' ከተባለው ፊልም የተወሰደ ነው። ታኅሣስ ቻይና ጨረቃ ላይ ሰንደቅ አላማዋን በመትከል ከዓለም ሁለተኛዋ አገር ሆናለች። በተጨማሪም ቼንጅ-5 የተባለው የሕዋ ጉዞ ከ44 ዓመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጨረቃ አለት አምጥቷል። | https://www.bbc.com/amharic/news-55472951 |
0business
| ኢትዮጵያ አይኤምኤፍን አዲስ የተራዘመ የብድር አቅርቦት ስምምነት ጠየቀች | ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉን የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) አዲስ የተራዘመ የብድር አቅርቦት (ኤክስቴንድድ ክሬዲት ፋሲሊቲ) ስምምነት መጠየቋን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ። በአሁኑ ወቅት የተራዘመው የብድር አቅርቦት ጊዜው ያለቀ ቢሆንም የተራዘመ የፈንድ አቅርቦት (ኤከስቴንድድ ፈንድ ፋሲሊቲ) የተባለው የተቋሙ የድጋፍ ማዕቀፍ ቀጥሏል ተብሏል። ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ለኢትዮጵያ አገር በቀል የኤኮኖሚ ማሻሻያ ድጋፍ የተራዘመ የብድር አቅርቦት እና የተራዘመ የፈንድ አቅርቦት በተባሉ ማዕቀፎች በኩል በአውሮፓውያኑ 2019፣ 2.9 ቢሊዮን ዶላር ማፅደቁ የሚታወስ ነው። አገሪቷ የተራዘመ የብድር አቅርቦት (ኤክስቴንድድ ክሬዲት ፋሲሊቲ) ማዕቀፍ ውስጥም ቃል ከተገባላት 1.7 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ እስካሁን የተቀበለችው ወደ 200 ሚሊዮን ዶላር ሲሆን 1.5 ቢሊዮን ዶላር ሳታገኝ ነው ጊዜው ያበቃው። ኢትዮጵያም የተራዘመው የብደር አቅርቦት በአዲስ ስምምነት እንዲቀጥልና የተፈጸመውን እንዲተካና ተመሳሳይም የገንዘብ መጠን እንዲሆን ተስፋ ተደርጎበታል። አዲሱ የተራዘመው የብድር አቅርቦት የቀድሞውን በመተካት በድህነት ቅነሳና የእድገት ፕሮግራሞች (PRGT)ን እንድታገኝም ጠይቃለች ተብሏል። የገንዘብ ሚኒስቴርም በመግለጫው የተራዘመ የብድር አቅርቦት እና የተራዘመ የፈንድ አቅርቦት ማዕቀፎች በኩል በኩል ለኢትዮጵያ የማሻሻያ ሂደት ያበረከተውን ድጋፍም እውቅና ሰጥቷል። አገሪቷ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋምን ጨምሮ ለሌሎች ተቋማትና አገራት ያላትን ዕዳ ለማሸጋሸጝ የአበዳሪዎች ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን የመጀመሪያውን የአበዳሪዎች ኮሚቴ ስብሰባ መስከረም 12/2014 ዓ.ም ተካሂዷል። የአበዳሪዎቹ ኮሚቴ የጋራ ሊቀመንበሮች የሆኑት ፈረንሳይና እና ቻይና ሲሆኑ ኮሚቴውን ለማቋቋም ያደረጉትን ያላሰለሰ ጥረት እንዲሁም አገሪቷ በስብሰባው ላይ ተገኝታ ጥያቄዋን እንድታቀርብ ለተመቻቸላት እድል ሚኒስቴሩ አመስግኗል። ኢትዮጵያ በቡድን 20 አገራት የጋራ ማዕቀፍ (G20's Common Framework) ያለባትን 30 በሊዮን ዶላር እዳ ማቃለያ በጊዜው ታሳካ ዘንድ በአበዳሪዎች ኮሚቴ የተወሰዱ አስፈላጊ እርምጃዎችን በበጎ መልኩ እንደምታያቸው አስታውቃለች። በዚህ ማዕቀፍ መሰረት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የደቀቀውን የዓለም ኢኮኖሚ እንዲያገግም በተለይም ለሚያድጉ አገራት የብድር እፎይታ ጊዜ የሰጡ ሲሆን ከዚህም ኢትዮጵያ አንዷ ተጠቃሚ ናት። የአበዳሪዎች ኮሚቴ የአገሪቱ የእዳ ሽግሽግ በአገሪቱ ካለው የምጣኔ ሀብት ጋር በተጣጣመ መልኩ እንዲሁም በመሠረታዊነት የማክሮ ኢኮኖሚውን መረጋጋትን ለማረጋገጥ ያደረገውን ጥረት አገሪቱ ደስተኛ መሆኗም ተገልጿል። በተለይም እርምጃዎቹ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከተፈጠረው ምጣኔ ሀብታዊ ተግዳሮቶች የመፍትሄ እፎይታን እንደሚሰጥና አገሪቷ ለልማትና ማህበራዊ አገልግሎት ይውል ዘንድ የገንዝብ ፍሰት ቦታን በመፍጠር እንዲሁም የአገሪቱን የእዳ መጠንም ለማሸጋሸግ ሚና ይጫወታል ተብሏል። አገሪቷ የእዳዋንም ሽግሽግ ሁኔታ ዝርዝሮችን ለማጠናቀቅ ከአበዳሪዎቿ ጋር ለመስራት ቁርጠኛ ናት ብሏል። የሃገር በቀሉን የኢኮኖሚ ማሻሸያ እየደገፈ ያለው ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አገሪቷ ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጫና እንድታገግም የሚያደርገውን የምጣኔ ሀብት ድጋፍ እንዲሁም ለተጋላጭ ማኅበረሰቦች አቅርቦትም ቀጣይ ተሳትፎ ወሳኝ እንደሆነም ሚኒስቴሩ አፅንኦት ሰጥቷል። ተቋሙ የገንዘብ እና እና የፋይናንስ ዘርፍ ፖሊሲ ማሻሻያዎችን የሚደግፍ የቴክኒክ ድጋፍ የኢኮኖሚያችንን አፈፃፀም በማጠናከር ረገድም ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ተብሏል። ከጥቂት አመታት በፊት የሃገር በቀል የምጣኔ ኃብት ማሻሻያ እየተገበረች ሲሆን ይህም የተረጋጋ የእድገት ጎዳና የማይናወጥ ምጣኔ ሀብት እንዲፈጠር እያደረገ መሆኑም ተገልጿል። ማሻሻያውም የማክሮ ኢኮኖሚ አስተዳደር፣ ዘላቂ የእዳ አስተዳደር ሥርዓት፣ የግሉ ዘርፍ በተሻለ ሁኔታ የሚሳተፍበት ከባቢ መፍጠር፣ የመንግሥት ልማቶች ድርጅቶች የተሻሻለ አፈፃፀም፣ የተሻሻለ የወጪ ንግድ እንዲሁም ገቢን መጨመርና ወጪዎችን ማስተካከል መቻሉንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ለኢትዮጵያ ዋነኛ አበዳሪ የሚባሉ የገንዘብ ተቋማት ከ11 ቢሊዮን ዶላር በላይ ተጨማሪ ብድር ለመልቀቅ እያንገራገሩ ነው ተብሏል። በዋነኝነትም የነዚህ ተቋማት ስጋት ተጨማሪ ብድር ለአገሪቱ መስጠት የበለጠ ጫና ውስጥ ይከታታል እንዲሁም መክፈል አቋሟን የበለጠ ሊያዳክም ይችላል ከሚል ስጋት ጋር የተያያዘ ነው። የቻይናው ኤክዚም ባንክ ለኢትዮጰያ ለመስጠት ቃል የገባውን 339 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆኑ ተነግሯል። ከዚህም በተጨማሪ የዓለም ባንክ አንድ አካል የሆነው የዓለም አቀፉ የልማት ትብብር ማኅበር (ኢንተርናሽናል ዴቨሎፕመንት አሶሲየሽን) 3.3 ቢሊዮን ዶላር፣ የዓለም የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) 2.7 ቢሊዮን ዶላር፣ የኢትዮጵያ ዋነኛ አበዳሪ ቻይና 1.4 ቢሊዮን ዶላርና ሌሎችም አበዳሪዎች ባለፈው አመት እስከ መጋቢት ድረስ ይሰጣሉ ተብሎ ቢጠበቅም እስካሁን አልተለቀቀም። | ኢትዮጵያ አይኤምኤፍን አዲስ የተራዘመ የብድር አቅርቦት ስምምነት ጠየቀች ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉን የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) አዲስ የተራዘመ የብድር አቅርቦት (ኤክስቴንድድ ክሬዲት ፋሲሊቲ) ስምምነት መጠየቋን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ። በአሁኑ ወቅት የተራዘመው የብድር አቅርቦት ጊዜው ያለቀ ቢሆንም የተራዘመ የፈንድ አቅርቦት (ኤከስቴንድድ ፈንድ ፋሲሊቲ) የተባለው የተቋሙ የድጋፍ ማዕቀፍ ቀጥሏል ተብሏል። ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ለኢትዮጵያ አገር በቀል የኤኮኖሚ ማሻሻያ ድጋፍ የተራዘመ የብድር አቅርቦት እና የተራዘመ የፈንድ አቅርቦት በተባሉ ማዕቀፎች በኩል በአውሮፓውያኑ 2019፣ 2.9 ቢሊዮን ዶላር ማፅደቁ የሚታወስ ነው። አገሪቷ የተራዘመ የብድር አቅርቦት (ኤክስቴንድድ ክሬዲት ፋሲሊቲ) ማዕቀፍ ውስጥም ቃል ከተገባላት 1.7 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ እስካሁን የተቀበለችው ወደ 200 ሚሊዮን ዶላር ሲሆን 1.5 ቢሊዮን ዶላር ሳታገኝ ነው ጊዜው ያበቃው። ኢትዮጵያም የተራዘመው የብደር አቅርቦት በአዲስ ስምምነት እንዲቀጥልና የተፈጸመውን እንዲተካና ተመሳሳይም የገንዘብ መጠን እንዲሆን ተስፋ ተደርጎበታል። አዲሱ የተራዘመው የብድር አቅርቦት የቀድሞውን በመተካት በድህነት ቅነሳና የእድገት ፕሮግራሞች (PRGT)ን እንድታገኝም ጠይቃለች ተብሏል። የገንዘብ ሚኒስቴርም በመግለጫው የተራዘመ የብድር አቅርቦት እና የተራዘመ የፈንድ አቅርቦት ማዕቀፎች በኩል በኩል ለኢትዮጵያ የማሻሻያ ሂደት ያበረከተውን ድጋፍም እውቅና ሰጥቷል። አገሪቷ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋምን ጨምሮ ለሌሎች ተቋማትና አገራት ያላትን ዕዳ ለማሸጋሸጝ የአበዳሪዎች ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን የመጀመሪያውን የአበዳሪዎች ኮሚቴ ስብሰባ መስከረም 12/2014 ዓ.ም ተካሂዷል። የአበዳሪዎቹ ኮሚቴ የጋራ ሊቀመንበሮች የሆኑት ፈረንሳይና እና ቻይና ሲሆኑ ኮሚቴውን ለማቋቋም ያደረጉትን ያላሰለሰ ጥረት እንዲሁም አገሪቷ በስብሰባው ላይ ተገኝታ ጥያቄዋን እንድታቀርብ ለተመቻቸላት እድል ሚኒስቴሩ አመስግኗል። ኢትዮጵያ በቡድን 20 አገራት የጋራ ማዕቀፍ (G20's Common Framework) ያለባትን 30 በሊዮን ዶላር እዳ ማቃለያ በጊዜው ታሳካ ዘንድ በአበዳሪዎች ኮሚቴ የተወሰዱ አስፈላጊ እርምጃዎችን በበጎ መልኩ እንደምታያቸው አስታውቃለች። በዚህ ማዕቀፍ መሰረት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የደቀቀውን የዓለም ኢኮኖሚ እንዲያገግም በተለይም ለሚያድጉ አገራት የብድር እፎይታ ጊዜ የሰጡ ሲሆን ከዚህም ኢትዮጵያ አንዷ ተጠቃሚ ናት። የአበዳሪዎች ኮሚቴ የአገሪቱ የእዳ ሽግሽግ በአገሪቱ ካለው የምጣኔ ሀብት ጋር በተጣጣመ መልኩ እንዲሁም በመሠረታዊነት የማክሮ ኢኮኖሚውን መረጋጋትን ለማረጋገጥ ያደረገውን ጥረት አገሪቱ ደስተኛ መሆኗም ተገልጿል። በተለይም እርምጃዎቹ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከተፈጠረው ምጣኔ ሀብታዊ ተግዳሮቶች የመፍትሄ እፎይታን እንደሚሰጥና አገሪቷ ለልማትና ማህበራዊ አገልግሎት ይውል ዘንድ የገንዝብ ፍሰት ቦታን በመፍጠር እንዲሁም የአገሪቱን የእዳ መጠንም ለማሸጋሸግ ሚና ይጫወታል ተብሏል። አገሪቷ የእዳዋንም ሽግሽግ ሁኔታ ዝርዝሮችን ለማጠናቀቅ ከአበዳሪዎቿ ጋር ለመስራት ቁርጠኛ ናት ብሏል። የሃገር በቀሉን የኢኮኖሚ ማሻሸያ እየደገፈ ያለው ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አገሪቷ ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጫና እንድታገግም የሚያደርገውን የምጣኔ ሀብት ድጋፍ እንዲሁም ለተጋላጭ ማኅበረሰቦች አቅርቦትም ቀጣይ ተሳትፎ ወሳኝ እንደሆነም ሚኒስቴሩ አፅንኦት ሰጥቷል። ተቋሙ የገንዘብ እና እና የፋይናንስ ዘርፍ ፖሊሲ ማሻሻያዎችን የሚደግፍ የቴክኒክ ድጋፍ የኢኮኖሚያችንን አፈፃፀም በማጠናከር ረገድም ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ተብሏል። ከጥቂት አመታት በፊት የሃገር በቀል የምጣኔ ኃብት ማሻሻያ እየተገበረች ሲሆን ይህም የተረጋጋ የእድገት ጎዳና የማይናወጥ ምጣኔ ሀብት እንዲፈጠር እያደረገ መሆኑም ተገልጿል። ማሻሻያውም የማክሮ ኢኮኖሚ አስተዳደር፣ ዘላቂ የእዳ አስተዳደር ሥርዓት፣ የግሉ ዘርፍ በተሻለ ሁኔታ የሚሳተፍበት ከባቢ መፍጠር፣ የመንግሥት ልማቶች ድርጅቶች የተሻሻለ አፈፃፀም፣ የተሻሻለ የወጪ ንግድ እንዲሁም ገቢን መጨመርና ወጪዎችን ማስተካከል መቻሉንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ለኢትዮጵያ ዋነኛ አበዳሪ የሚባሉ የገንዘብ ተቋማት ከ11 ቢሊዮን ዶላር በላይ ተጨማሪ ብድር ለመልቀቅ እያንገራገሩ ነው ተብሏል። በዋነኝነትም የነዚህ ተቋማት ስጋት ተጨማሪ ብድር ለአገሪቱ መስጠት የበለጠ ጫና ውስጥ ይከታታል እንዲሁም መክፈል አቋሟን የበለጠ ሊያዳክም ይችላል ከሚል ስጋት ጋር የተያያዘ ነው። የቻይናው ኤክዚም ባንክ ለኢትዮጰያ ለመስጠት ቃል የገባውን 339 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆኑ ተነግሯል። ከዚህም በተጨማሪ የዓለም ባንክ አንድ አካል የሆነው የዓለም አቀፉ የልማት ትብብር ማኅበር (ኢንተርናሽናል ዴቨሎፕመንት አሶሲየሽን) 3.3 ቢሊዮን ዶላር፣ የዓለም የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) 2.7 ቢሊዮን ዶላር፣ የኢትዮጵያ ዋነኛ አበዳሪ ቻይና 1.4 ቢሊዮን ዶላርና ሌሎችም አበዳሪዎች ባለፈው አመት እስከ መጋቢት ድረስ ይሰጣሉ ተብሎ ቢጠበቅም እስካሁን አልተለቀቀም። | https://www.bbc.com/amharic/news-58638143 |
5sports
| ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ ከተሞች የተካሄዱ ውድድሮችን አሸነፉ | በሳምንቱ መጨረሻ በተካሄዱ የተለያዩ የማራቶን ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸናፊ ሆነዋል። በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የማራቶን ውድድር በወንዶች ምድብ ኢትዮጵያዊው አትሌት ጫሉ ዴሶ ገልሜሳ ውድድሩን በ2 ሰዓት ከ5 ደቂቃ ከ7 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ አሸናፊ መሆን ችሏል። አትሌቱ ሰይፉ ቱራ ደግሞ 2ኛ ሆኖ በማጠናቀቅ በፓሪሱ ማራቶን የብር ሜዳሊያ አስገኝቷል። በሴቶች ምድብ ደግሞ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ፋንቱ ጂማ የቦታውን ሪከርድ ያሻሻለችውን ኬንያዊቷን አትሌት ጁዲት ጄፕቱምን ተከትላ በመግባት የብር ሜዳሊያ ስታሸንፍ አትሌት በሱ ሳዶ ደግሞ ውድድሩን በሦስተኝነት በማጠቀቅ የነሐስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆናለች። ስፔን ባርሴሎና ውስጥ በተደረገ የወንዶች ግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ሐፍቱ ተክሉ እና አትሌት ጫላ ረጋሳ አንደኛ እና ሁለተኛ ሆነው በመጨረስ የወርቅ እና የብር ሜዳሊያውን ወስደዋል። በተመሳሳይ በሴቶች ምድብ የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ጌጤ ዓለማየሁ ሁለተኛ፣ አትሌት አስናቀች አወቀ ሶስተኛ እና አትሌት ረድኤት ዳንኤል ደግሞ አራተኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቃቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። በሌላ ውድድር በ2022 የኮሪያ ዴጉ ዓለም አቀፍ ማራቶን ኢትዮጵያዊው አትሌት ሽፈራው ታምሩ 2:06:31 በሆነ ሰዓት አንደኛ በመውጣት አሸንፏል። በሴቶች ዴጉ ዓለም አቀፍ ማራቶን ኤርትራዊቷ ናዝሬት ወልዱ አሸናፊ ሆናለች። በጣልያን በተካሄደው የሚላኖ 2022 ማራቶን ውድድርም ኢትዮጵይውያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል። በሴቶች ምድብ አትሌት ስንታዬሁ ጥላሁን 2ኛ ሆና ስታጠናቅቅ ሌላኛዋ የአገሯ ልጅ አትሌት አታለል አንሙት የ3ኛ ደረጃን ይዛ ጨርሳለች። ከአራተኛ እስከ ስድስተኛ ያለውን ደረጃም ቢሆን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ናቸው የያዙት። | ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ ከተሞች የተካሄዱ ውድድሮችን አሸነፉ በሳምንቱ መጨረሻ በተካሄዱ የተለያዩ የማራቶን ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸናፊ ሆነዋል። በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የማራቶን ውድድር በወንዶች ምድብ ኢትዮጵያዊው አትሌት ጫሉ ዴሶ ገልሜሳ ውድድሩን በ2 ሰዓት ከ5 ደቂቃ ከ7 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ አሸናፊ መሆን ችሏል። አትሌቱ ሰይፉ ቱራ ደግሞ 2ኛ ሆኖ በማጠናቀቅ በፓሪሱ ማራቶን የብር ሜዳሊያ አስገኝቷል። በሴቶች ምድብ ደግሞ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ፋንቱ ጂማ የቦታውን ሪከርድ ያሻሻለችውን ኬንያዊቷን አትሌት ጁዲት ጄፕቱምን ተከትላ በመግባት የብር ሜዳሊያ ስታሸንፍ አትሌት በሱ ሳዶ ደግሞ ውድድሩን በሦስተኝነት በማጠቀቅ የነሐስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆናለች። ስፔን ባርሴሎና ውስጥ በተደረገ የወንዶች ግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ሐፍቱ ተክሉ እና አትሌት ጫላ ረጋሳ አንደኛ እና ሁለተኛ ሆነው በመጨረስ የወርቅ እና የብር ሜዳሊያውን ወስደዋል። በተመሳሳይ በሴቶች ምድብ የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ጌጤ ዓለማየሁ ሁለተኛ፣ አትሌት አስናቀች አወቀ ሶስተኛ እና አትሌት ረድኤት ዳንኤል ደግሞ አራተኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቃቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። በሌላ ውድድር በ2022 የኮሪያ ዴጉ ዓለም አቀፍ ማራቶን ኢትዮጵያዊው አትሌት ሽፈራው ታምሩ 2:06:31 በሆነ ሰዓት አንደኛ በመውጣት አሸንፏል። በሴቶች ዴጉ ዓለም አቀፍ ማራቶን ኤርትራዊቷ ናዝሬት ወልዱ አሸናፊ ሆናለች። በጣልያን በተካሄደው የሚላኖ 2022 ማራቶን ውድድርም ኢትዮጵይውያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል። በሴቶች ምድብ አትሌት ስንታዬሁ ጥላሁን 2ኛ ሆና ስታጠናቅቅ ሌላኛዋ የአገሯ ልጅ አትሌት አታለል አንሙት የ3ኛ ደረጃን ይዛ ጨርሳለች። ከአራተኛ እስከ ስድስተኛ ያለውን ደረጃም ቢሆን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ናቸው የያዙት። | https://www.bbc.com/amharic/news-60979076 |
2health
| ኮሮናቫይረስ ፡ የካናዳው ሚኒስትር በኮቪድ-19 ወቅት ሽርሽር በመሄዳቸው ምክንያት ሥልጣናቸውን ለቀቁ | የካናዳዋ ኦንታሪዮ ግዛት የገንዘብ ሚኒስትር የሆኑት ግለሰብ በኮቪድ-19 ወቅት ለመዝናናት ወደ ካሪቢያን በመጓዛቸው ምክንያት ሥራ ለቀዋል። የግዛቲቱ ገዥ ዶግ ፎርድ የገንዘብ ሚኒስትራቸው ሥልጣን እንዲለቁ ያደረጉት ኦንታሪዮ የእንቅስቃሴ ገደብ ላይ እያለች ሽርሽር ብለው በመጓዛቸው ነው። ሚኒስትር ሮድ ፊሊፕስ ይቅርታ ጠይቀዋል። ጉዟቸውንም "የሞኝ ሥራ" ብለውታል። የግዛቲቱ አስተዳዳሪ እንዳሉት "የፋይናንስ ሚኒስትሩ ሥልጣን መልቀቃቸው መንግሥታቸው ኃላፊነትን በአግባቡ የማይወጡ ሰዎችን እንደማይምር ማሳያ ነው" ብለዋል። በካናዳ ብዙ ሕዝብ የሚኖርባት የኦንታሪዬ ግዛት በኮሮናቫይረስ ምክንያት ጠበቅ ያለ የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሏ ይታወቃል። የፕሮግረሲቭ ኮንሰርቫቲቭ ፓርቲ አባል የሆኑት ሚኒስትር ሴይንት ባርትስ ወደ ተሰኘችው የካሬቢያን ደሴት ለሽርሽር የሄዱት በዚህ በታኅሣስ ወር ነው። በወቅቱ የኦንታሪዮ የጤና ባለሥልጣናት በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁትሩ በመጨመሩ ምክንያት ነዋሪዎች ከቤታቸው ንቅንቅ እንዳይሉ አዘው ነበር። ኦንታሪዮ ከቀናት በፊት እንደ አዲስ ጠበቅ ያለ የኮቪድ-19 ሕግ አውጥታለች። ባለፈው ሐሙስ ብቻ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከገባ በበሽታው የተያዙ ከፍተኛው የተባለው ቁጥር [3328] ተመዝግቧል። 56 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል። እንደ ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ከሆነ በካናዳ በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ582 ሺህ በላይ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ደግሞ 15 ሺህ 600 ደርሷል። ሚኒስትሩ ከሽርሽር ሲመለሱ ሥራቸውን ለመቀጠል አስበው የነበረ ቢሆንም የግዛቲቱ አስተዳደር ሥልጣናቸውን ቢለቁ የተሻለ እንደሆነ ነግረዋቸዋል። "እንምታዩት በጣም ከባድ ስህተት ፈፅሜያለሁ። ተጠያቂ መሆን ደግሞ አለብኝ። መሄድ በሌለብኝ ወቅት ነው የተጓዝኩት። ምንም ምክንያት መደርደር አይጠበቅብኝም" ብለዋል ስልጣናቸውን የለቀቁት ሚኒስትር። የኦንታሪዮ አስተዳዳሪ ሥልጣን በለቀቁት ሚኒስትር ምትክ ሌላ ሰው በጊዜያዊነት ሾመዋል። | ኮሮናቫይረስ ፡ የካናዳው ሚኒስትር በኮቪድ-19 ወቅት ሽርሽር በመሄዳቸው ምክንያት ሥልጣናቸውን ለቀቁ የካናዳዋ ኦንታሪዮ ግዛት የገንዘብ ሚኒስትር የሆኑት ግለሰብ በኮቪድ-19 ወቅት ለመዝናናት ወደ ካሪቢያን በመጓዛቸው ምክንያት ሥራ ለቀዋል። የግዛቲቱ ገዥ ዶግ ፎርድ የገንዘብ ሚኒስትራቸው ሥልጣን እንዲለቁ ያደረጉት ኦንታሪዮ የእንቅስቃሴ ገደብ ላይ እያለች ሽርሽር ብለው በመጓዛቸው ነው። ሚኒስትር ሮድ ፊሊፕስ ይቅርታ ጠይቀዋል። ጉዟቸውንም "የሞኝ ሥራ" ብለውታል። የግዛቲቱ አስተዳዳሪ እንዳሉት "የፋይናንስ ሚኒስትሩ ሥልጣን መልቀቃቸው መንግሥታቸው ኃላፊነትን በአግባቡ የማይወጡ ሰዎችን እንደማይምር ማሳያ ነው" ብለዋል። በካናዳ ብዙ ሕዝብ የሚኖርባት የኦንታሪዬ ግዛት በኮሮናቫይረስ ምክንያት ጠበቅ ያለ የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሏ ይታወቃል። የፕሮግረሲቭ ኮንሰርቫቲቭ ፓርቲ አባል የሆኑት ሚኒስትር ሴይንት ባርትስ ወደ ተሰኘችው የካሬቢያን ደሴት ለሽርሽር የሄዱት በዚህ በታኅሣስ ወር ነው። በወቅቱ የኦንታሪዮ የጤና ባለሥልጣናት በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁትሩ በመጨመሩ ምክንያት ነዋሪዎች ከቤታቸው ንቅንቅ እንዳይሉ አዘው ነበር። ኦንታሪዮ ከቀናት በፊት እንደ አዲስ ጠበቅ ያለ የኮቪድ-19 ሕግ አውጥታለች። ባለፈው ሐሙስ ብቻ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከገባ በበሽታው የተያዙ ከፍተኛው የተባለው ቁጥር [3328] ተመዝግቧል። 56 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል። እንደ ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ከሆነ በካናዳ በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ582 ሺህ በላይ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ደግሞ 15 ሺህ 600 ደርሷል። ሚኒስትሩ ከሽርሽር ሲመለሱ ሥራቸውን ለመቀጠል አስበው የነበረ ቢሆንም የግዛቲቱ አስተዳደር ሥልጣናቸውን ቢለቁ የተሻለ እንደሆነ ነግረዋቸዋል። "እንምታዩት በጣም ከባድ ስህተት ፈፅሜያለሁ። ተጠያቂ መሆን ደግሞ አለብኝ። መሄድ በሌለብኝ ወቅት ነው የተጓዝኩት። ምንም ምክንያት መደርደር አይጠበቅብኝም" ብለዋል ስልጣናቸውን የለቀቁት ሚኒስትር። የኦንታሪዮ አስተዳዳሪ ሥልጣን በለቀቁት ሚኒስትር ምትክ ሌላ ሰው በጊዜያዊነት ሾመዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-55505118 |
5sports
| ኢትዮጵያ ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ የምድብ ድልድሉን ተቀላቀለች | በ2022 ኳታር ለምታዘጋጀው የዓለም ዋንጫ ለማለፍ በአፍሪካ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎች ቅዳሜና እሁድ ተካሂደዋል። ከቀናት በፊት በባህር ዳር ስታዲየም ከሌሴቶ አቻዋ ጋር ያለምንም ግብ የተለያየችው ኢትዮጵያ፤ የመልስ ጨዋታዋን በሌሴቶ አድርጋ አንድ አቻ ተለያይታለች። ከሜዳ ውጭ ባገባ በሚለው ህግ መሰረትም ወደቀጣዩ ዙር በማለፍ የምድብ ድልድል ውስጥ መግባቷን አረጋግጣለች። ሃያ ተጫዋቾችን ይዘው ወደ ሌሴቶ ያቀኑት አሰልጣኝ አብራሃም መብራቱ በተቻለ መጠን አጥቅቶ በመጫወት ከሜዳቸው ውጪ ግብ ለማስቆጠር እንደሚጥሩ ገልጸው ነበር። በመጀመሪያው አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች ተጠንቅቀው የተጫወቱ ሲሆን ዋልያዎቹ የተሻለ የኳስ ቁጥጥር ነበራቸው። ነገር ግን ብዙም የግብ ዕድሎችን መፍጠር ሳይችሉ ቀርተዋል። በአንጻሩ ሁለተኛው አጋማሽ ፈጣንና ብዙ የግብ ሙከራዎች የታዩበት ነበር። 50ኛው ደቂቃ ላይ በቀኝ መስመር የሚጫወተው ቢንያም በላይ ያሻማውን ኳስ የሌሴቶው ንካይ ኔትሮሊ ሲመልሰው ኳሷ አቅጣጫዋን ቀይራ በራሱ መረብ ላይ ግብ አስቆጥሮ ኢትዮጵያ መምራት ጀመረች። ነገር ግን ከአምስት ደቆቃዎች በኋላ ሌሴቶዎች አቻ የምታደርጋቸውን ግብ በሴፖ ሴትሩማንግ አማካይነት ማግኘት ችለዋል። ጨዋታው በዚሁ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ቢጠናቀቅም ከሜዳ ውጭ ባገባ በሚለው ኢትዮጵያ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋግጣለች። በመጀመሪያ ዙር ጨዋታ አሥመራ ላይ ናሚቢያን አስተናግዳ በደጋፊዎቿ ፊት 2ለ1 የተሸነፈችው ኤርትራ ደግሞ የመልስ ጨዋታዋን የፊታችን ማክሰኞ ዊንድሆክ ላይ ታደርጋለች። • ሳሙኤል ኤቶ እግር ኳስ ሊያቆም ነው • 'አምብሮ' ከእግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር የአቅርቦት ውል ተፈራረመ ባለፈው ሐሙስ 1ለ0 በሆነ ጠባብ ውጤት ዚምባብዌን በማሸነፍ አስደናቂ ድል ያስመዘገቡት የሶማሊያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች፤ ለሁለተኛው ዙር ጨዋታ የፊታችን ማክሰኞ ወደ ሃራሬ ያቀናሉ። በሌላ በኩል ከአርብ ጀምሮ የአውሮፓ ቻምፒየንሺፕ ጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ተከሂደዋል። በዚህም መሰረት ሆላንድ ጀርመንን 4 ለ2 በማሸነፍ ጥሩ አጀማመር ያደረገች ሲሆን ቤልጂየም ሳን ማሪኖን 4 ለምንም አሸንፋለች። ክሮሺያም በተመሳሳይ ስሎቫኪያን 4 ለምንም ፤ አውስትራሊያ ደግሞ ላቲቪያን 6 ለባዶ ረምርማለች። ቅዳሜ በተደረጉ ጨዋታዎች ደግሞ እንግሊዝ ቡልጋሪያን 4 ለምንም፣ ፖርቹጋል ሰርቢያን 4 ለ2 እንዲሁም ፈረንሳይ አልባኒያን 4 ለ1 ማሸነፍ ችለዋል። ዕሁድ በተደረጉ ጨዋታዎች ደግሞ ጣልያን ፊንላንድን 2 ለ1 ፣ ስፔን ፋሮ አይላንድስን 4 ለምንም ሲያሸንፉ ጆርጂያና ዴንማርክ 0 ለ0 እንዲሁም ስዊድን እና ኖርዌይ 1 ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል። | ኢትዮጵያ ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ የምድብ ድልድሉን ተቀላቀለች በ2022 ኳታር ለምታዘጋጀው የዓለም ዋንጫ ለማለፍ በአፍሪካ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎች ቅዳሜና እሁድ ተካሂደዋል። ከቀናት በፊት በባህር ዳር ስታዲየም ከሌሴቶ አቻዋ ጋር ያለምንም ግብ የተለያየችው ኢትዮጵያ፤ የመልስ ጨዋታዋን በሌሴቶ አድርጋ አንድ አቻ ተለያይታለች። ከሜዳ ውጭ ባገባ በሚለው ህግ መሰረትም ወደቀጣዩ ዙር በማለፍ የምድብ ድልድል ውስጥ መግባቷን አረጋግጣለች። ሃያ ተጫዋቾችን ይዘው ወደ ሌሴቶ ያቀኑት አሰልጣኝ አብራሃም መብራቱ በተቻለ መጠን አጥቅቶ በመጫወት ከሜዳቸው ውጪ ግብ ለማስቆጠር እንደሚጥሩ ገልጸው ነበር። በመጀመሪያው አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች ተጠንቅቀው የተጫወቱ ሲሆን ዋልያዎቹ የተሻለ የኳስ ቁጥጥር ነበራቸው። ነገር ግን ብዙም የግብ ዕድሎችን መፍጠር ሳይችሉ ቀርተዋል። በአንጻሩ ሁለተኛው አጋማሽ ፈጣንና ብዙ የግብ ሙከራዎች የታዩበት ነበር። 50ኛው ደቂቃ ላይ በቀኝ መስመር የሚጫወተው ቢንያም በላይ ያሻማውን ኳስ የሌሴቶው ንካይ ኔትሮሊ ሲመልሰው ኳሷ አቅጣጫዋን ቀይራ በራሱ መረብ ላይ ግብ አስቆጥሮ ኢትዮጵያ መምራት ጀመረች። ነገር ግን ከአምስት ደቆቃዎች በኋላ ሌሴቶዎች አቻ የምታደርጋቸውን ግብ በሴፖ ሴትሩማንግ አማካይነት ማግኘት ችለዋል። ጨዋታው በዚሁ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ቢጠናቀቅም ከሜዳ ውጭ ባገባ በሚለው ኢትዮጵያ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋግጣለች። በመጀመሪያ ዙር ጨዋታ አሥመራ ላይ ናሚቢያን አስተናግዳ በደጋፊዎቿ ፊት 2ለ1 የተሸነፈችው ኤርትራ ደግሞ የመልስ ጨዋታዋን የፊታችን ማክሰኞ ዊንድሆክ ላይ ታደርጋለች። • ሳሙኤል ኤቶ እግር ኳስ ሊያቆም ነው • 'አምብሮ' ከእግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር የአቅርቦት ውል ተፈራረመ ባለፈው ሐሙስ 1ለ0 በሆነ ጠባብ ውጤት ዚምባብዌን በማሸነፍ አስደናቂ ድል ያስመዘገቡት የሶማሊያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች፤ ለሁለተኛው ዙር ጨዋታ የፊታችን ማክሰኞ ወደ ሃራሬ ያቀናሉ። በሌላ በኩል ከአርብ ጀምሮ የአውሮፓ ቻምፒየንሺፕ ጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ተከሂደዋል። በዚህም መሰረት ሆላንድ ጀርመንን 4 ለ2 በማሸነፍ ጥሩ አጀማመር ያደረገች ሲሆን ቤልጂየም ሳን ማሪኖን 4 ለምንም አሸንፋለች። ክሮሺያም በተመሳሳይ ስሎቫኪያን 4 ለምንም ፤ አውስትራሊያ ደግሞ ላቲቪያን 6 ለባዶ ረምርማለች። ቅዳሜ በተደረጉ ጨዋታዎች ደግሞ እንግሊዝ ቡልጋሪያን 4 ለምንም፣ ፖርቹጋል ሰርቢያን 4 ለ2 እንዲሁም ፈረንሳይ አልባኒያን 4 ለ1 ማሸነፍ ችለዋል። ዕሁድ በተደረጉ ጨዋታዎች ደግሞ ጣልያን ፊንላንድን 2 ለ1 ፣ ስፔን ፋሮ አይላንድስን 4 ለምንም ሲያሸንፉ ጆርጂያና ዴንማርክ 0 ለ0 እንዲሁም ስዊድን እና ኖርዌይ 1 ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል። | https://www.bbc.com/amharic/49625537 |
0business
| ሲሪላንካ ወሳኝ ላልሆኑ አገልግሎቶች ነዳጅ መሸጥ አቆመች | በአስር ዓመታት ውስጥ እጅግ የከፋ የኢኮኖሚ ቀውስ እያጋጠማት የምትገኘው ሲሪላንካ ወሳኝ ላልሆኑ ተሽከርካሪዎች ነዳጅ መሸጥን አቁማለች። በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ለህክምና አገልግሎት እና ምግብ ለማጓጓዝ የሚያገለግሉ ተሽከርካሪዎች፣ አውቶቡሶች፣ ባቡሮች እና ተሽከርካሪዎች ብቻ ነዳጅ እንዲሞሉ ተፈቅዶላቸዋል። መንግሥት በከተሞች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ ያደረገ ሲሆን፣ የአገሪቱ 22 ሚሊዮን ነዋሪዎች ከቤት እንዲሠሩ በባለሥልጣናት ተነግሯቸዋል። የደቡብ እስያዋ አገር እንደ ነዳጅ እና ምግብ ያሉ ከውጭ ለሚገቡ ምርቶች ክፍያ ለመፈጸም የሚያስችላትን ገንዘብ ለማግኘት እየተነጋገረች ነው። “በ1970ዎቹ የነዳጅ ቀውስ ተፈጥሮ በአሜሪካ እና በአውሮፓ ያለውን ፍላጎት ለመቀነስ የተሽከርካሪዎች የፍጥነት ገደብ እና የኮታ አቅርቦት ከተዋወቀ ወዲህ ስሪላንካ ለተራው ሰው የነዳጅ ሽያጭን በማስቆም ከባድ እርምጃ የወሰደች የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች” ሲሉ በኢንቨስቴክ የጋዝና ነዳጅ ምርምር ኃላፊው ናታን ፓይፐር ለቢቢሲ ተናግረዋል። እገዳው በሲሪላንካ ያለውን ከፍተኛ የነዳጅ ዋጋ መጨመር እና የውጭ ምንዛሪ ክምችት ውስን መሆኑን በግልጽ አሳይቷል። ብዙዎቹ የደሴቲቱ ነዋሪዎች ያለ ነዳጅ ኑሯቸውን እንዴት እንደሚገፉ ግራ ተጋብተዋል። ለወራት በስሪላንካ በሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ረዣዥም ሰልፎች ይታዩ ነበር። በዋና ከተማዋ ኮሎምቦ የታክሲ አሸከርካሪ የሆነው የ29 ዓመቱ ቺንታካ ኩማራ እገዳው “በሰዎች ላይ የበለጠ ችግር ይፈጥራል” ብሎ ያስባል። ለቢቢሲ ሃሳቡን ሲገልጽ “እኔ የቀን ደሞዝተኛ ነኝ። ወረፋ ይዤ ለሦስት ቀናት ቆይቻለሁ። መቼ ቤንዚን እንደማገኝ አላውቅም" ብሏል። አሽከርካሪዎች ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ የተነገረ ሲሆን የቀረ የነዳጅ ክምች ካለ ይከፋፈላል በሚል ቁጥር ተሰጥቷቸዋል። አንዳንዶቹ መሰለፋቸውን ቢቀጥሉም ሌሎች ግን ተመልሰዋል። የ52 ዓመቱ ኤስ ዊጄቱንጋ በበኩላቸው "ለሁለት ቀናት ወረፋ ይዤ ነበር። 11 ቁጥር ተሰጥቶኛል ግን ነዳጅ መቼ እንደምወስድ አላውቅም” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "አሁን ወደ ሥራ መሄድ ስላለብኝ ተሽከርካሪዬን እዚህ ትቼ በባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ ከመሄድ ውጪ ምንም አማራጭ የለኝም" ብለዋል። ኮሎምቦ ውስጥ ኮታሄና በሚባለው መንደር ባለ ሦስት እግር ተሸከርካሪ ያለው ኬናት እንደ እሱ ያሉ ሰዎች “ይበልጥ መጎዳታቸውን” ገልጿል። "ቤተሰባችን በቀን ሦስት ጊዜ ይመገብ ነበር። አሁን የምንበላው በቀን ሁለት ጊዜ ብቻ ነው። በዚሁ ከቀጠለ ደግሞ አንድ ጊዜ ወደ መብላት ይወርዳል" ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል። "ከባድ የኢኮኖሚ ቀውስ" በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተበት የኢኮኖሚ ቀውስ ሌላ የነደዳጅ ዋጋ መጨመር እና የታክስ ቅነሳ መደረጋቸው ተደማምረው ስሪላንካ አስፈላጊ ዕቃዎችን ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት የሚያስችላትን በቂ የውጭ ምንዛሪ እንድታጣ ምክንያት ሆኗል። ከፍተኛ የነዳጅ፣ የምግብ እና የመድኃኒት እጥረት የአገሪቱን የኑሮ ውድነት እንዲንር አድርጎታል። ብዙዎች ገቢያቸውን ከግል ሞተር ሳይክሎቻቸው ያገኛሉ። ሰኞ ዕለት የአገሪቱ መንግሥት እስከ ሐምሌ 10 ድረስ የግል ተሽከርካሪዎች ቤንዚን እና ናፍታ እንዳይገዙ እንደሚከለክል ተናግሯል። የአገሪቱ ካቢኔ ቃል አቀባይ ባንዱላ ጉኔዋርዴና በበኩላቸው ስሪላንካ “በታሪኳ እንደዚህ ያለ ከባድ የኢኮኖሚ ቀውስ ገጥሟት አያውቅም” ብለዋል። በገንዘብ ችግር የተሸበሸበችው አገር ርካሽ የነዳጅ አቅርቦት ለማግኘት ባለሥልጣናትን ወደ ነዳጅ አምራቾቹ ሩሲያ እና ኳታር ልካለች። በሳምንቱ መጨረሻ ባለሥልጣናቱ እንዳስታወቁት፣ በአገሪቱ በመጪዎቹ ቀናት አስፈላጊ አገልግሎቶችን ለመስጠት የሚያስችል 9,000 ቶን ናፍጣ እና 6,000 ቶን ቤንዚን ብቻ ነው ያለው። ክምችቱ በመደበኛ መንገድ ከተሰራጨ ከአንድ ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ እንደሚያልቅ ተገምቷል. የኃይል እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ካንቻና ዊጄሴኬራ እሑድ ዕለት ለጋዜጠኞች “ተጨማሪ ክምችት ለማግኘት የምንችለውን ሁሉ እያደረግን ነው። ይህ መቼ እንደሚሆን ግን አናውቅም” ሲሉ ተናግረዋል። አገሪቱ በግንቦት ወር በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ለዓለም አቀፍ አበዳሪዎች መክፈል ያለባትን ዕዳ ሳትከፍል ቀርታለች። ይህም በፕሬዚዳንት ጎታባያ ራጃፓክሳ መንግሥት ላይ ለሳምንታት የዘለቀውን ተቃውሞ ተከትሎ የተፈጠረ ነበር። የፕሬዝዳንቱ ወንድም ማሂንዳ የጠቅላይ ሚንስትርነቱን ቦታ ለቀዋል። ፕሬዝዳንቱ አሁንም ሥልጣን እንዲለቁ ግፊት እየተደረገባቸው ነው። በዋና ከተማው ነዳጅ ለመግዛት የሚጠባበቀው ካናን የተባለ አሸክርካሪ “መንግሥት ምንም ዓይነት እርምጃ የሚወሰድ አይመስልም” ሲል ለቢቢሲ ታሚል ተናግሯል። “እንድንታገስ እየጠየቁን ነው። ዶላር የለንም ይላሉ። እኔ ግን ለዚህ ተጠያቂው ማነው? ስል መንግሥትን እጠይቃለሁ” ብሏል። በምትኩ "የተማሩ ወጣቶች" አገሪቱን መምራት እንዳለባቸው ጠቁሟል። ባለፈው ሳምንት የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ቡድን በሦስት ቢሊዮን ዶላር የእርዳታ ስምምነት ላይ ለመነጋገር ወደ ሲሪላንካ አቅንቶ ነበር። መንግሥትም አስፈላጊ እቃዎች ለማስገባት ከሕንድ እና ቻይና እርዳታ እየጠየቀ ነው። አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር ራኒል ዊክሬሜሲንጌ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ እንደገለጹት እንደ ምግብ፣ ነዳጅ እና ማዳበሪያ ላሉ አስፈላጊ ዕቃዎች ለመክፈል አገሪቱ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ቢያንስ 5 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋታል። የምግብ እጥረት ሊከሰት ይችላል በሚልም ባለፉት ሳምንታት ሚኒስትሮች ገበሬዎች ብዙ ሩዝ እንዲያመርቱ ጠይቀዋል። መንግሥት በሲሪላንካ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ገቢ ከሚያስገኙት አንዱ የሆነው የቱሪስት ዘርፍ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ መጎዳቱን ለቀውሱ ተጠያቂ አድርጓል። ብዙ ባለሙያዎች ግን የመልካም አስተዳደር እጦት ለኢኮኖሚው ውድቀት ዋነኛው መንስኤ ነው ይላሉ። | ሲሪላንካ ወሳኝ ላልሆኑ አገልግሎቶች ነዳጅ መሸጥ አቆመች በአስር ዓመታት ውስጥ እጅግ የከፋ የኢኮኖሚ ቀውስ እያጋጠማት የምትገኘው ሲሪላንካ ወሳኝ ላልሆኑ ተሽከርካሪዎች ነዳጅ መሸጥን አቁማለች። በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ለህክምና አገልግሎት እና ምግብ ለማጓጓዝ የሚያገለግሉ ተሽከርካሪዎች፣ አውቶቡሶች፣ ባቡሮች እና ተሽከርካሪዎች ብቻ ነዳጅ እንዲሞሉ ተፈቅዶላቸዋል። መንግሥት በከተሞች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ ያደረገ ሲሆን፣ የአገሪቱ 22 ሚሊዮን ነዋሪዎች ከቤት እንዲሠሩ በባለሥልጣናት ተነግሯቸዋል። የደቡብ እስያዋ አገር እንደ ነዳጅ እና ምግብ ያሉ ከውጭ ለሚገቡ ምርቶች ክፍያ ለመፈጸም የሚያስችላትን ገንዘብ ለማግኘት እየተነጋገረች ነው። “በ1970ዎቹ የነዳጅ ቀውስ ተፈጥሮ በአሜሪካ እና በአውሮፓ ያለውን ፍላጎት ለመቀነስ የተሽከርካሪዎች የፍጥነት ገደብ እና የኮታ አቅርቦት ከተዋወቀ ወዲህ ስሪላንካ ለተራው ሰው የነዳጅ ሽያጭን በማስቆም ከባድ እርምጃ የወሰደች የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች” ሲሉ በኢንቨስቴክ የጋዝና ነዳጅ ምርምር ኃላፊው ናታን ፓይፐር ለቢቢሲ ተናግረዋል። እገዳው በሲሪላንካ ያለውን ከፍተኛ የነዳጅ ዋጋ መጨመር እና የውጭ ምንዛሪ ክምችት ውስን መሆኑን በግልጽ አሳይቷል። ብዙዎቹ የደሴቲቱ ነዋሪዎች ያለ ነዳጅ ኑሯቸውን እንዴት እንደሚገፉ ግራ ተጋብተዋል። ለወራት በስሪላንካ በሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ረዣዥም ሰልፎች ይታዩ ነበር። በዋና ከተማዋ ኮሎምቦ የታክሲ አሸከርካሪ የሆነው የ29 ዓመቱ ቺንታካ ኩማራ እገዳው “በሰዎች ላይ የበለጠ ችግር ይፈጥራል” ብሎ ያስባል። ለቢቢሲ ሃሳቡን ሲገልጽ “እኔ የቀን ደሞዝተኛ ነኝ። ወረፋ ይዤ ለሦስት ቀናት ቆይቻለሁ። መቼ ቤንዚን እንደማገኝ አላውቅም" ብሏል። አሽከርካሪዎች ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ የተነገረ ሲሆን የቀረ የነዳጅ ክምች ካለ ይከፋፈላል በሚል ቁጥር ተሰጥቷቸዋል። አንዳንዶቹ መሰለፋቸውን ቢቀጥሉም ሌሎች ግን ተመልሰዋል። የ52 ዓመቱ ኤስ ዊጄቱንጋ በበኩላቸው "ለሁለት ቀናት ወረፋ ይዤ ነበር። 11 ቁጥር ተሰጥቶኛል ግን ነዳጅ መቼ እንደምወስድ አላውቅም” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "አሁን ወደ ሥራ መሄድ ስላለብኝ ተሽከርካሪዬን እዚህ ትቼ በባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ ከመሄድ ውጪ ምንም አማራጭ የለኝም" ብለዋል። ኮሎምቦ ውስጥ ኮታሄና በሚባለው መንደር ባለ ሦስት እግር ተሸከርካሪ ያለው ኬናት እንደ እሱ ያሉ ሰዎች “ይበልጥ መጎዳታቸውን” ገልጿል። "ቤተሰባችን በቀን ሦስት ጊዜ ይመገብ ነበር። አሁን የምንበላው በቀን ሁለት ጊዜ ብቻ ነው። በዚሁ ከቀጠለ ደግሞ አንድ ጊዜ ወደ መብላት ይወርዳል" ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል። "ከባድ የኢኮኖሚ ቀውስ" በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተበት የኢኮኖሚ ቀውስ ሌላ የነደዳጅ ዋጋ መጨመር እና የታክስ ቅነሳ መደረጋቸው ተደማምረው ስሪላንካ አስፈላጊ ዕቃዎችን ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት የሚያስችላትን በቂ የውጭ ምንዛሪ እንድታጣ ምክንያት ሆኗል። ከፍተኛ የነዳጅ፣ የምግብ እና የመድኃኒት እጥረት የአገሪቱን የኑሮ ውድነት እንዲንር አድርጎታል። ብዙዎች ገቢያቸውን ከግል ሞተር ሳይክሎቻቸው ያገኛሉ። ሰኞ ዕለት የአገሪቱ መንግሥት እስከ ሐምሌ 10 ድረስ የግል ተሽከርካሪዎች ቤንዚን እና ናፍታ እንዳይገዙ እንደሚከለክል ተናግሯል። የአገሪቱ ካቢኔ ቃል አቀባይ ባንዱላ ጉኔዋርዴና በበኩላቸው ስሪላንካ “በታሪኳ እንደዚህ ያለ ከባድ የኢኮኖሚ ቀውስ ገጥሟት አያውቅም” ብለዋል። በገንዘብ ችግር የተሸበሸበችው አገር ርካሽ የነዳጅ አቅርቦት ለማግኘት ባለሥልጣናትን ወደ ነዳጅ አምራቾቹ ሩሲያ እና ኳታር ልካለች። በሳምንቱ መጨረሻ ባለሥልጣናቱ እንዳስታወቁት፣ በአገሪቱ በመጪዎቹ ቀናት አስፈላጊ አገልግሎቶችን ለመስጠት የሚያስችል 9,000 ቶን ናፍጣ እና 6,000 ቶን ቤንዚን ብቻ ነው ያለው። ክምችቱ በመደበኛ መንገድ ከተሰራጨ ከአንድ ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ እንደሚያልቅ ተገምቷል. የኃይል እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ካንቻና ዊጄሴኬራ እሑድ ዕለት ለጋዜጠኞች “ተጨማሪ ክምችት ለማግኘት የምንችለውን ሁሉ እያደረግን ነው። ይህ መቼ እንደሚሆን ግን አናውቅም” ሲሉ ተናግረዋል። አገሪቱ በግንቦት ወር በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ለዓለም አቀፍ አበዳሪዎች መክፈል ያለባትን ዕዳ ሳትከፍል ቀርታለች። ይህም በፕሬዚዳንት ጎታባያ ራጃፓክሳ መንግሥት ላይ ለሳምንታት የዘለቀውን ተቃውሞ ተከትሎ የተፈጠረ ነበር። የፕሬዝዳንቱ ወንድም ማሂንዳ የጠቅላይ ሚንስትርነቱን ቦታ ለቀዋል። ፕሬዝዳንቱ አሁንም ሥልጣን እንዲለቁ ግፊት እየተደረገባቸው ነው። በዋና ከተማው ነዳጅ ለመግዛት የሚጠባበቀው ካናን የተባለ አሸክርካሪ “መንግሥት ምንም ዓይነት እርምጃ የሚወሰድ አይመስልም” ሲል ለቢቢሲ ታሚል ተናግሯል። “እንድንታገስ እየጠየቁን ነው። ዶላር የለንም ይላሉ። እኔ ግን ለዚህ ተጠያቂው ማነው? ስል መንግሥትን እጠይቃለሁ” ብሏል። በምትኩ "የተማሩ ወጣቶች" አገሪቱን መምራት እንዳለባቸው ጠቁሟል። ባለፈው ሳምንት የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ቡድን በሦስት ቢሊዮን ዶላር የእርዳታ ስምምነት ላይ ለመነጋገር ወደ ሲሪላንካ አቅንቶ ነበር። መንግሥትም አስፈላጊ እቃዎች ለማስገባት ከሕንድ እና ቻይና እርዳታ እየጠየቀ ነው። አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር ራኒል ዊክሬሜሲንጌ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ እንደገለጹት እንደ ምግብ፣ ነዳጅ እና ማዳበሪያ ላሉ አስፈላጊ ዕቃዎች ለመክፈል አገሪቱ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ቢያንስ 5 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋታል። የምግብ እጥረት ሊከሰት ይችላል በሚልም ባለፉት ሳምንታት ሚኒስትሮች ገበሬዎች ብዙ ሩዝ እንዲያመርቱ ጠይቀዋል። መንግሥት በሲሪላንካ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ገቢ ከሚያስገኙት አንዱ የሆነው የቱሪስት ዘርፍ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ መጎዳቱን ለቀውሱ ተጠያቂ አድርጓል። ብዙ ባለሙያዎች ግን የመልካም አስተዳደር እጦት ለኢኮኖሚው ውድቀት ዋነኛው መንስኤ ነው ይላሉ። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cv2rdzdnevro |
2health
| ጤና፡ የወጣቶች የወገብ ህመም መንስዔ እና መፍትሔው | አሁን አሁን የወገብ ህመም አጋጥሟቸው የህክምና ተቋማትን የሚጎበኙ ወጣቶች እየተበራከቱ ነው። በተለይ በማደግ ላይ ባሉ አገራት ለወገብ ህመም የሚጋለጡ ወጣቶች ቁጥርም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ጥናቶች ያመለክታሉ። ለመሆኑ ለዚህ መንስዔው ምንድን ነው? መፍትሔውስ? በዚህ ላይ በፓራጎን የፊዚዮቴራፒና ስፓርት ህክምና ስፔሻሊቲ ልዩ ክሊኒኮች ውስጥ ሥራ አስኪያጅ እና ሜዲካል ዳሬክተር ከሆኑት ዶ/ር ቴዎድሮስ ወ/ገብርኤል ጋር ቆይታ አድርገናል። ዶ/ር ቴዎድሮስ ሦስቱንም ድግሪያቸውን የተከታተሉት በአሜሪካ ሲሆን በፊዚዮቴራፒ በተለይ በስፖርት ህክምና እና ኦርቶፔዲክስ ህክምና ዶክትሬታቸውን አግኝተዋል። በሙያቸው በአሜሪካ ለ10 ዓመታት የሰሩ ሲሆን በኢትዮጵያ ደግሞ ላለፉት 12 ዓመታት እያገለገሉ ይገኛሉ። ከዚህም በተጨማሪ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ትምህርት ቤት ውስጥ ረዳት ፕሮፌሰር ናቸው። በጥቁር አንበሳ ህክምና ትምህርት ቤት በፊዚዮቴራፒ ዶክትሬት ፕሮግራም በመምህርነት ሠርተዋል። ብዙውን ጊዜ ወጣቶች ለወገብ ህመም ያጋለጣቸውን መንስዔ በውል አያውቁትም። እንዲሁ በደፈናው ድንገት አመመኝ ሲሉ ነው የሚሰማው። ለመሆኑ የወገብ ህመም መንስዔዎች ምንድን ናቸው? የሰውነት ማጎልመሻ እንቅስቃሴዎች፣ የምንጫማቸው ጫማዎች ፣ የምንተኛበት ፍራሽ ፣ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈፀምበት መንገድ ( Sex position) . . . ለወገብ ህመም ይዳርጉ ይሆን? ወደዚህ ዝርዝር ከማለፋችን በፊት ስለወገብ እና የወገብ ህመም ምንነት እናንሳ። ወገብ ቀበቷችን ወይም መቀነታችን የሚያርፍበት የሰውነታችን ክፍል ሲሆን በዚህ ላይ የሚከሰት ህመም የወገብ ህመም ይባላል። የወገብ ህመም ጽንሰ ሃሳቡ ሰፊና ጥልቅ ቢሆንም በቀላል አገላለጽ በወገብ አካባቢ በሚገኙ ጡንቻዎች ፣ የነርቭ ሥሮች፣ የአከርካሪ አጥንቶች፣ የጎን አጥንቶች እና ጅማቶች ላይ የሚደርስ ጉዳት ነው። ይህ ጉዳት ጊዜያዊ ወይም ዘለቄታዊ ሊሆን ይችላል። የወገብ ህመም ዓይነቶች እንደ መንስዔያቸው ይለያያሉ። ዋና ዋናዎቹ ግን እነዚህ ናቸው፦ ከመጨረሻው ነጥብ እንጀምር። የሰውነት በሽታ ተዋጊ ሂደት በመዛበት የሚከሰተው የወገብ ህመም የሚያጋጥመው ሰውነት በሽታን የሚከላከልበት ሂደት ሌሎች የሰውነት አካላትን ሲያጠቃ ነው። በእንግሊዝኛ አጠራሩ Ankylosing spondylitis ይባላል። የሰውነት የውስጥ ቁስለትን በመፍጠር ዘለግ ላለ ጊዜ የሚቆይ ህመም ነው። የዚህ ህመም ምክንያቱ ምን እንደሆነ በውል አይታወቅም። በተለይ በመገጣጠሚያዎች እና በአከርካሪ አጥንቶች መጋጠሚያ መካከል ቁስለትን ያስከትላል። ህመሙ እየጨመረ ሲሄድም የአከርካሪ አጥንቶች እንዲንቀሳቀሱ እንደ ሃዲድ የሚያገለግለው የሰውነት ክፍል ላይ አጥንቶቹ መንቀሳቀሳቸውን ትተው እርስ በእርሳቸው እንዲጣበቁ ያደርጋል። በዚህ ምክንያት አጥንቶቹ መንቀሳቀሳቸው ቀርቶ አንድ አካል ይሆናሉ። በዚህ ህመም የተጠቃ ሰው ማጎንበስ፣ ወደ ኋላ አሊያም ወደ ጎን መንቀሳቀስ አይችልም። የሌሎቹ የወገብ ህመም ዓይነቶች መንስዔዎችስ? ለወገብ ህመም የሚዳርጉን መንስዔዎች በርካታ ቢሆኑም ዶ/ር ቴዎድሮስ በ21 ዓመት የህክምና ልምዳቸው የተመለከቷቸውንና ዋና ዋና ያሏቸውን መንስዔዎች ያስረዳሉ። ከባድ ነገር ማንሳት፡ ማንኛውም ሰው በዕለት ተዕለት ክንውኑ ጥንቃቄ ካላደረገ ወገቡን ሊታመም ይችላል። በባልዲ ውሃ ቀድቶ ፎቅ ላይ መውሰድ፣ ክብደት ያላቸውን ሰዎች ከአልጋ ማንሳት እንዲሁም ማንኛውንም ከአቅም በላይ የሆነ ክብደትን ማንሳት ለወገብ ህመም ሊዳርግ ይችላል። ከልክ በላይ የሆነ የሰውነት ክብደት መኖር፡ በተለይ በአንድ ጊዜ የሚጨምር የሰውነት ክብደት የወገብ ህመም እንደሚያስከትል ዶ/ር ቴዎድሮስ ይናገራሉ። "በኮቪድ ወረርሽኝ ወቅት አካላዊ እንቅስቃሴ የሌለው ሥራ በመዘውተሩ በዚህ ሳቢያ የሚከሰት ህመም ተበራክቶ ነበር" ይላሉ። ረዘም ላለ ጊዜ ቆሞ፣ ተቀምጦ ወይም ቆሞ ጎንበስ ብሎ መስራት፡ ረዘም ላለ ጊዜ ቆመው፣ ተቀምጠው አልያም ቆመው ከአንገታቸው ተጎንብሰው በሚሰሩ ሙያዎች ላይ የተሰማሩ ሰዎች ለወገብ ህመም የመጋለጣቸው ዕድል ሰፊ ነው። ዶ/ር ቴዎድሮስ አንድ ሰው ቆሞ ከአንገቱ ጎንበስ ብሎ በሚሰራበት ጊዜ በሁለት አከርካሪ አጥንቶች መካከል ወደ 270 ኪሎ ግራም ግፊት እንዳለው ጥናቶችን ያጣቅሳሉ። ይህን በየቀኑ ማድረግ ደግሞ ከጊዜ በኋላ የከፋ ጉዳት ያስከትላል። ብዙ ጊዜ የቀዶ ህክምና ሐኪሞች በዚህ ሳቢያ ለሚከሰት የወገብ ህመም ሲጋለጡ ይስተዋላል። ብዙ መንገጫገጭ ያላቸው የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን ማሽከርከር፡ ብዙ ንዝረት ያላቸው የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን ማሽከርከር ወይም ምቹ ባልሆኑ መንገዶች ላይ መኪና ማሽከርከር ከጊዜ በኋላ የወገብ ህመም ያስከትላል። የዝላይ እና የሩጫ እንቅስቃሴዎች፡ በተለይ ከልክ በላይ የሰውነት ክብደት ያላቸው ሰዎች ሩጫ ወይም የመዝለል እንቅስቃሴ የሚያዘወትሩ ከሆነ ወገባቸው ሊጎዳ ይችላል። እንደ አስፓልት ያለ ጠንካራ የሆነ ቦታ ላይ የሚሮጡ ሰዎችም መሬቱ ላይ እግራቸውን በጣሉ ቁጥር መሬትም በአጸፋው ስለሚመታቸው ለጉዳት ሊዳርጋቸው ይችላል። ከዚህም በተጨማሪ ወጣ ገባ የሆነ መሬት ላይ የሚሮጡ ሰዎች እግራቸው በሚያርፍበት ሰዓት ሚዛናቸው እኩል ስለማይሆን ወገብ ላይ ጫና ይፈጠራል። ሰውነት ሳይለምድ በአንድ ጊዜ ከባድ የአካል እንቅስቃሴ መስራት፡ አሁን አሁን በወጣቶች ዘንድ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ እየተለመደ መጥቷል። የሚሰሯቸው እንቅስቃሴዎችንም ዩቲዩብ በማየት የሚመርጡም አሉ። ይህ ብቻም ሳይሆን ስፖርቱን ለምን ዓላማ እንደሚሰሩ የማያውቁ በርካቶች ናቸው። በዚህ ሳቢያ ተጎድተው ወደ ክሊኒካቸው የሚመጡ ወጣቶች መኖራቸውን ዶ/ር ቴዎድሮስ ይናገራሉ። "ችግሩ አካላዊ እንቅስቃሴ ከማድረግ የተከሰተ ሳይሆን ሰውነት ሳይለማመድ ከባድ የአካል እንቅስቃሴ መስራት ነው" ይላሉ። "ጂምናዚየም ውስጥ ለአሰልጣኝ ጉርሻ መስጠት የተለመደ ሆኗል" የሚሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ አንዳንድ አሰልጣኞች ጉርሻዋን ለማግኘት ደንበኞቻቸው የሚፈልጉት የሰውነት ለውጥ ላይ ቶሎ ማድረስ ላይ ብቻ ትኩረት እንደሚያደርጉ ይናገራሉ። አሰልጣኞቹ ስለስፖርታዊ እንቅስቃሴው እንጂ ስለጤና እውቀት ላይኖራቸውም ይችላል። አንዳንድ ሰልጣኞችም በአንድ ጊዜ በሰውነታቸው ላይ የሚፈልጉት ለውጥ እንዲመጣ ባልተገባ መልኩ ከልክ በላይ የሆነ አካላዊ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ። ዶ/ር ቴዎድሮስ ይህንን ሲገልጹት "ምንም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አድርጎ የማያውቅ ሰው ቅዳሜ እና እሁድ ጂምናዚየም ገብቶ አገር ይያዝልኝ እንደ ማለት ነው" ይላሉ። ዲስክ መንሸራተት፡ የዲስክ መንሽራተት ስሙ ለብዙዎቻችን ጆሮ እንግዳ አይደለም። ዶ/ር ቴዎድሮስም የዲስክ መንሸራተት ያለ ስሙ ብዙ ስም የተሰጠው በሽታ ነው ይላሉ። ዶ/ር ቴዎድሮስ እንደሚሉት የዲስክ ችግር ተብለው ወደ ክሊኒካቸው ከሚመጡት 100 ሰዎች ውስጥ 50 በመቶ የሚሆኑት ችግራቸው ሌላ ነው። በተለምዶ የህክምና ባለሙያዎች ህሙማንን ለዲስክ መንሸራተት ተዳርገዋል የሚሉት 'ኤምአርአይ' መመርመሪያ የሚያሳየው ውጤት ላይ ተመርኩዘው ነው። ይሁን እንጂ ዶ/ር ቴዎድሮስ "10 ሰዎችን እንዲሁ ከመንገድ ላይ በግምት ተመርጠው ኤምአርአይ ቢነሱ ቢያንስ 7ቱ የዲስክ መንሸራተት ሊያሳዩ ይችላሉ" ይላሉ። ይህ ማለት ግን ህመም አለባቸው ማለት አይደለም። "የዲስክ መንሸራተት ታይቷል ማለት የተዛባ ዲስክ አላቸው፤ ግን ዲስኩ ነርቩን ጨፍልቆ ህመም የሚያመጣበት ደረጃ ላይ አይደለም ማለት ነው" ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። በዚህ የምርመራ ውጤት ላይ ተመስርተው ቶሎ ቀዶ ህክምና አድርጉ ወደሚል ድምዳሜ የሚደርሱ የህክምና ባለሙያዎች መኖራቸውን የሚናገሩት ዶ/ር ቴዎድሮስ፤ ይህ ግን ስህተት ነው ብለዋል። ለመሆኑ ዲስክ ምንድን ነው? የሚገኘውስ የት ላይ ነው? ዲስክ በአከርካሪ አጥንቶች መካከል የሚገኝ በውስጡ ፈሳሽ ያለው ለስላሳ የሆነ እንደ ጎሚኒ (ሾክ አብሶርቨር) የምንጠቀምበት የአካል ክፍል ነው። ታዲያ ሰውነታችን ጫና በሚበዛበት ጊዜ በዲስኩ ውስጥ ያለው ፈሳሽ ሊወጣ ይችላል ወይም ደግሞ ፈሳሹ ሳይወጣ ዲስኩ ወደ አንድ በኩል አመዝኖ መውጣት ወደማይገባበት ቦታ ሊወጣ ይችላል። ዲስክ ያለበት አካባቢ የተጨናነቀ በመሆኑ አፈትልኮ በሚወጣበት ጊዜ ከጭንቅላታችን በሚወርደውና ህብለ ሰረሰር በሚባለው የነርቭ ግንድ እና ቅርንጫፎች ላይ በመተኛት ጫና ይፈጥራል። የዲስክ መንሸራተት በሚያጋጥምበት ጊዜ ቀዶ ህክምና ለማድረግ ከመጣደፍ በፊት ዲስኩ ተንሸራቶ ምን ሆነ? ወዴት አቅጣጫ ነው የተንሸራተተው? ምን ያህል ነው የተንሸራተተው? እየነካ ያለውስ ነርቭ የትኛውን ነው? ሊያስከትል የሚችለው የህመም ስሜት አለ ወይ? የሚሉትን ወሳኝ ጥያቄዎች መጠየቅ አስፈላጊ መሆኑን ዶ/ር ቴዎድሮስ ያሰምሩበታል። ወጣቶችን ለወገብ ህመም የሚያጋልጣቸው የተለየ ምክንያት ይኖር ይሆን? ከምንጊዜውም በላይ ብዙ ወጣቶች በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ላይ እየተሠማሩ መሆናቸው አንዱ ምክንያት ነው ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። ወጣቶች ረዘም ያለ ጊዜ መቆምን፣ መቀመጥን አሊያም ጎንበስ ብሎ መቆምን እንዲሁም ከባድ ነገር ማንሳትን፣ መሸከምን የሚጠይቁ ሥራዎችን ይሠራሉ። በሌላም በኩል ከዚህ ቀደሙ በተሻለ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማዘውተርም ሌላኛው ምክንያት መሆኑን ይናገራሉ። "ስለምንሰራው አካላዊ እንቅስቃሴ ጠለቅ ያለ እውቀት ከሌለን በስተቀር የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ጥቅም እንዳላቸው ሁሉ ጉዳት አላቸው።" ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። በተቃራኒው ደግሞ የሰውነት እንቅስቃሴ ማነስ ለወገብ ህመም መንስዔ ነው። የግብረ ሥጋ ግንኙነት ለወገብ ህመም ያጋልጣል? የግብረ ሥጋ ግንኙነት በሳይንስ እንደ ወገብ ህመም መንስዔነት ወይም እንደ ወገብ ህመም መነሻነት አይታወቅም ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። ይሁን እንጂ የወገብ ህመም ያለባቸው ሰዎች የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽሙበት መንገድ ህመማቸውን ሊያባብስባቸው ወይም የተሻላቸውን ህመም እንደገና ሊያስነሳባቸው እንደሚችል ይናገራሉ። "በተለይ በሴቶች ዘንድ ይህንን ለሐኪም የማስረዳት ልምድ የለም" የሚሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ አንዳንዶች ግን በስልክም ቢሆን ምክር የሚጠይቁ መኖራቸውን አልሸሸጉም። "እንደ የወገብ ህመማቸው ዓይነትም ለተወሰነ ጊዜ የግብረ ሥጋ ግንኙነት አደራረግ (Sex position) እንዲቀይሩ፣ እንዳያደርጉ ወይም ሊያደርጓቸው ስለሚችሉ የግብረ ሥጋ ግንኙነት አደራረግ ዓይነቶች ምክር የሚሰጣቸው ታማሚዎች አሉ" ይላሉ። የምንጫማው ጫማስ? የወገባችንን ጤንነት ለመጠበቅ የምንጫማው የጫማ ዓይነት ወሳኝነት አለው። ይህ ግን በአብዛኛው የሚገናኘው ከሴቶች ጋር ነው። ምክንያቱም በተለይ በፋሽንና መዝናኛ ኢንደስትሪው ሴቶች መንቀሳቀስ እስከሚቸገሩ ድረስ ረጃጅም ታኮ ያላቸውን ጫማዎች ተጫምተው ማየት የተለመደ ነው። ይህ ደግሞ በሰውነት ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራል። እንዴት? ዶ/ር ቴዎድሮስ ለዚህ ሳይንሳዊ ምላሽ አላቸው። ሰውነት የራሱን ሚዛን የሚጠብቅበት መንገድ አለው። ይህ የስበት ማዕከል (Center of gravity) ይባላል። ስንራመድ የማንወድቀው ወይም ደግሞ ቁጭ ብለን ስንነሳ ከግድግዳ ጋር የማንጋጨው ይህ የመሬት ስበት ማዕከል ሚዛናችንን ስለሚጠብቅልን ነው። ታዲያ ከፍ ያሉ ታኮዎች ያሏቸውን ጫማዎች ስንጫማ ሰውነት ተፈጥሯዊ የሆነውን የሰውነት ሚዛን ይለቃል። የሰውነታችን የመሬት ስበት ማዕከልም ይቀየራል። በመሆኑም ሰውነት ይህንን የስበት ማዕከል መልሶ ወደ ማዕከሉ ላይ ለማምጣት (ሚዛኑን ለመጠበቅ) የሚያደርጋቸው ማስተካከያዎች ወገብ ላይ ጫና ይፈጥራሉ። ጫናው ወገብ ላይ ብቻ ሳይሆን ጉልበት፣ እግርና የእግር መዳፍ ላይም ነው። ከዓመታት በፊት በዩናይትድ ኪንግደም በፖዲያትሪ ኮሌጅ የተሠራ ጥናት ሴቶች ህመም እንደተሰማቸው ሳይናገሩ ከፍ ያለ ታኮ ጫማ ተጫምተው መቆየት የሚችሉት በአማካይ ለአንድ ሰዓት ያህል ነው ይላል። በዚህ ጥናት ተሳታፊ የነበሩ ሴቶች ጫማውን ከተጫመቱ ከ10 ደቂቃ በኋላ በእግራቸው ላይ ህመም እንደተሰማቸው ተናግረዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ሰው የተፈጠረው በባዶ እግሩ ለመሄድ ነው በማለት ሰዎች በባዶ እግራቸው እንዲሄዱ የሚያበረታታ ሳይንስ አለ። በዚህም ምክንያት ሆነ ብለው በባዶ እግራቸው የሚሄዱ ሰዎች አሉ። በእርግጥ ዶ/ር ቴዎድሮስ በባዶ እግር መሄድ አሊያም በጣም አነስተኛ ታኮ ያላቸው ጫማዎች ማድረግ ጉዳት አለው ብለው አያምኑም። ይሁን እንጂ በተፈጥሮ 'የእግራቸው ቅርጽ ለየት ያለ' ሰዎች ከተረከዝ ሁለት ሴንቲ ሜትር ከፍ ያለ ታኮ ያለው ጫማ እንዲያደርጉ ይመክራሉ። "ተረከዝ በጫማ መሄድ ከለመደ በኋላ በባዶ እግር በብዛት መሄድ በተረከዝ ላይ አጥንት መብቀልን (Bone Spur) ሊያስከትልም ይችላል" ይላሉ። ይህ አጥንት የተረከዝን ስጋ እንደ ጩቤ የሚወጋ ነው። በመሆኑም በተለይ በባዶ እግር መሄድ ያልለመደ እና ተረከዝ ላይ በቂ የስብ ንጣፍ (Fat pad) የሌለው ሰው በባዶ እግሩ ቢሄድ ለእንዲህ ዓይነት ችግር ሊጋለጥ እንደሚችል ያሳስባሉ። ይህ ግን በስፋት የሚከሰት አይደለም። የወገብ ህመም እንዳጋጠመን እንዴት ማወቅ እንችላለን? እንደማንኛውም ህመም የወገብ ህመም ሲያጋጥም የሚታዩ ከቀላል እስከ ከባድ ምልክቶች አሉ። የህመም ማስታገሻ መድሃኒት የማያስወስዱ፣ ቁጭ ስንል የሚያስታውሱን፣ መድሃኒት እስከ መውሰድ የሚያደርስ የማቃጠልና መቆጥቆጥ ስሜት፣ ጎንበስ ብሎ ቀና ለማለት መቸገር፣ ለመነሳት ድጋፍ መፈለግ፣ የጡንቻ መኮማተር፣ ለመንቀሳቀስ መቸገር፣ ተኝቶ ለመገላበጥ ማቃት የተወሰኑት ምልክቶቹ ናቸው። የሚታዩት ምልክቶች ግን እንደ ህመሙ መንስዔዎች ይለያያሉ። ለምሳሌ ረዘም ላለጊዜ በመቆም ወይም በመቀመጥ የሚመጣ ህመም ከሆነ ተቀምጠን ቆይተን ድንገት ስንነሳ የሰውነት መያዝ ፣ ስንቀመጥ ወይ ስንቆም ህመም መሰማት፣ የመቀመጫ አካባቢ ህመም፣ መጠዝጠዝና ንዝረት ያጋጥማል። ንዝረቱ ከመቀመጫ አለፍ ብሎ ቁርጭምጭሚት ፣ ጣቶች እና የእግር መዳፍ ድረስ የሚሰማ የመደንዘዝና የማቃጠል ህመሞች እየባሰ ሲመጣም የእግር መክዳትና ደረጃ ለመውጣት አቅም እስከማጣት ሊደርስ ይችላል። እግርን ማዘዝ፣ ጣቶችን ወደ ላይ ቀና ማድረግ ካቃተን ግን ህመሙ የከፋ ደረጃ ደርሷል ማለት ነው። ምን አልባት ይህ ቀዶ ሕክምና የሚያስፈልግበት ደረጃ ሊሆን ይችላል። ያጋጠመንን የወገብ ህመም ለማስታገስ በቤት ውስጥ ምን ማድረግ እንችላለን? በአቅራብያ የህክምና ተቋም ከሌለ ለጊዜው የህመም ማስታገሻዎችን መውሰድ ይመከራል። ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን ሌላ የሚወስዱት መድሃኒት ከሌለ እና ከሚወስዱት መድሃኒት ጋር የማይጋጭ ከሆነ ነው። ዘላቂ መፍትሔ ግን አይደለም። የወገብ ህመሙ የተከሰተው በድንገተኛ አደጋ [መውደቅ] ከሆነ ደግሞ በመጀመሪያ ህክምና እርዳታ በረዶ ማድረግ ጥሩ ነው። "የቁስለት ሂደቱን ለመቀነስ፣ እብጠት እና ውስጥ የደም መፍሰስ እንዳይኖር ይረዳል" ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። ከዚህ በኋላም የጡንቻ መኮማተር የሚኖር ከሆነ ሙቀት ሰውነትን የማፍታታት ባህርይ ስላለው ሙቀት ማድረግ የተሻለ መሆኑን ይመክራሉ። እረፍት ማድረግም ህመማችንን በተወሰነ ደረጃ ሊያስታግስልን ይችላል። ይህን ሁሉ አድርገን የማይሻል ከሆነ ግን ሥር ሳይሰድ እንደ ምንም ወደ ህክምና ቦታ ሄዶ ትክክለኛ ህክምና ማድረግ አስፈላጊ ነው። "አንዳንድ ሰዎች ባህላዊ ቦታ ሄደው ባልተገባ ሁኔታ ህክምና ወስደው ተጎድተው የሚመጡ አሉ" ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። እንደዚህ ያሉ ቦታዎችን ከሚያዘወትሩ ሰዎች መካከል የተማሩ ሰዎችም ጭምር እንደሚገኙበት በመግለጽም ይህ ተገቢ አለመሆኑን ይናገራሉ። ህመሙን ለማስወገድ ሲባል ያልተገባ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግም ጉዳቱን ሊያባብሰው እንደሚችል ዶ/ር ቴዎድሮስ ያስጠነቅቃሉ። ወገባችንን በህክምና ቀበቶ ወይም በመቀነት ብንደግፈውስ? የወገብ ህመም የተለያዩ ደረጃዎች አሉት። መጀመሪያ አካባቢ ችግሩ እንደተፈጠረ፣ ከዚያ ከሁለት እስከ ሦስት ወር እና ከሦስት ወር በላይ የቆየ ህመም ናቸው። ህመሙ ከሦስት ወር በላይ የቆየ ከሆነ ሥር የሰደደ ችግር ይባላል። በመሆኑም ህመሙ እንደ ጀመረ አካባቢ እረፍት ማድረግን ጨምሮ በመቀነት ማሰር ወይም በቀበቶ መደገፍ ያገዘን ስለሚመስል በሥነ ልቦናም ሆነ አካላዊ በሆነ መልኩ ሊደገፍ ይችላል ይላሉ- ዶ/ር ቴዎድሮስ። ሆኖም ይህ ለረዥም ጊዜ የሚደረግ ከሆነ ችግር እንደሚያስከትል ይናገራሉ። ምክንያታቸውን ሲያስረዱም "ቀበቶ ተደረገ ወይም መቀነት ታሰረ ማለት እዚያ አካባቢ ያሉ ጡንቻዎች እረፍት ወጡ ማለት ነው።" ይላሉ። በዚህ ሳቢያም የጡንቻ መክሳት ችግር ይከሰታል። በመሆኑም ጡንቻችን ያለ ድጋፍ ሥራውን መሥራት ይቀንሳል፤ አልያም ያቆማል። ይህም ሰዎች በቀበቶ አሊያም በመቀነት ላይ ጥገኛ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። "በኢትዮጵያ በህክምና ባለሙያዎች ዘንድ የአንገት መደገፊያ [ኮላር] እና የወገብ መደገፊያ ቀበቶ የማዘዝ ችግር ጎልቶ እየታየ ነው" የሚሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ የችግሩ መንስዔ ሳይታወቅ እነዚህን ቁሶች ማዘዝ ተገቢ እንዳልሆነ ይናገራሉ። አንዳንድ ጊዜ ሐኪሞች ቀበቶ ማዘዛቸውን ሊዘነጉት የሚችሉበት አጋጣሚም ስለሚኖር ታማሚዎቹ ለረዥም ጊዜ ቀበቶውን ሊያደርጉት ይችላሉ። ይህ ደግሞ ጉዳት ያስከትላል ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። ምን ዓይነት ፍራሽ እና ትራስ ላይ እንተኛ ? መቼም በወገብ ህመም ሳቢያ ፍራሽ ያልቀያየረ፤ ከአልጋ መደብ ፣ ከመደብ አልጋ ያላለ አይኖርም። ትራስም ቢሆን እንዲሁ። ምን ዓይነት ፍራሽ ላይ እንተኛ ? ምን አይነት ትራስ እንጠቀም የበርካቶች ጭንቀት ነው። ለወገብ ህመም ፍቱን ናቸው የተባሉ ፍራሾችም ይቸበቸባሉ። በሰለጠነው ዓለም የተለያዩ ዓይነት ዘመናዊ ፍራሽና ትራሶች እየተመረቱ ነው። በአንድ አልጋ ላይ ባልና ሚስትን በመረጡት ፍራሽ ላይ የሚያስተኛ ቴክኖሎጂም ተፈልስፏል። ታዲያ የትኛው ላይ ብንተኛ የተሻለ ነው? ዶ/ር ቴዎድሮስ "ታማሚዎቹ ተመቸን ያሉትን ፍራሽ ትክክል አይደለም ማለት አስቸጋሪ ነው ምክንያቱም ሰውነታቸው ከመረጡት ፍራሽ ጋር ተመቻችቶ ሊሆን ይችላል" ይላሉ። ቢሆንም ግን ደረቅ ፍራሽ ላይ መተኛትን አይመክሩም። እርሳቸው የሚመክሩት ሰውነት ቅርጹን በጠበቀ መልኩ የሚያሳርፍን ፍራሽ ወይም ትራስ ነው። "ራቁታችንን በመስታዎት ብንመለከት ሰውነታችን እጥፋቶች (Curves) አሉት። ስንተኛ እነዚያ እጥፋቶች ቅርጻቸውን ጠብቀው በትክክል ማረፍ አለባቸው" ይላሉ። ለዚህም ነው በሰለጠነው ዓለም 'ሚሞሪ ፎም' የተመረተው። ሚሞሪ ፎም ስንተኛ የሰውነትን ቅርጽ ይዞ ስንነሳ ወደ ነበረበት መመለስ የሚችል ፍራሽ ነው። 'ስሊፕ ነምበር ቤድ' የሚባልም ባልና ሚስት አልጋቸውን ሳይለዩ ለየራሳቸው የሰውነት ቅርጽ በሚመቻቸው መልኩ ማስተካከል የሚችሉት ሳይንሳዊ ፍራሽም ተሰርቷል። በኢትዮጵያ ለወገብ ህመም ተብለው የሚሸጡ ፍራሾችስ? ዶ/ር ቴዎድሮስ እነዚህ ፍራሾች ሳይንሳዊ አይደሉም ይላሉ። "ሱቅ የተሰቀለን ልብስ በግምት አንስቶ ግባ ብሎ እንደመታገል ነው" ሲሉም በምሳሌ ያስረዳሉ። "በሰለጠነው ዓለም 30 ደቂቃ ፍራሹ ላይ እረፍት ወስደን ነው ፍራሽ የምንገዛው" የሚሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ በኢትዮጵያ አንዳንድ መሸጫዎች ውስጥ 'ፍራሾቹ ላይ መተኛት ክልክል ነው!' የሚልም ማስታወቂያ በመለጠፍ ምቾቱን ሞክሮ ለመግዛት የሚደረገውን ክልከላንም ተችተዋል። ዶ/ር ቴዎድሮስ ትራስን በተመለከተም ተመሳሳይ ሃሳብ ነው ያላቸው። ትራስ በጭንቅላታችን እና በአንገታችን ሥር መካከል ያለውን ክፍተት የሚሞላ መሆን አለበት ይላሉ። ነገር ግን ሰዎች ትራሳቸውን በአግባቡ ሲጠቀሙበት አይስተዋልም። በእርግጥ የሚመቸንንና ልካችንን ለማወቅ አዳጋች ነው። ገንዘባቸውን ትራስ በመግዛት የሚጨርሱም ጥቂት አይደሉም። ይህንን ችግር ለመፍታትም ይመስላል በሰለጠነው ዓለም 'ዎተር ፒሎው' [በውሃ የሚሞላ ትራስ] የተሰራው። ይህ የውሃውን መጠን በመቀነስ ወይም በመጨመር ትራሱን በልክ ለማሳነስና ለማተለቅ ያስችላል። በመሆኑም የምንጠቀመውን ትራስ ልክ ማወቅ እና በተገቢው መንገድ መጠቀም ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ይመክራሉ። የአኗኗር ዘይቤያችን ምን ይምሰል? የሰውነት ክብደታችንን መቆጣጠር ወሳኝ ነው። ይህን ማድረጋችን ከወገብ ብቻም ሳይሆን ከሌሎች በሽታዎችም ራሳችንን ለመጠበቅ ያስችለናል። "በሰውነታችን ላይ አንድ ኪሎ በጨመርን ቁጥር በእያንዳንዱ ኪሎ አንዱ ጉልበታችን ላይ 4 ኪሎ ጫና ይፈጠራል" የሚሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ የሰውነታችንን ክብደት መቆጣጠርን ቸል ልንለው እንደማይገባ ይመክራሉ። የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን በአቅማችን ልክ እና ቀስ በቀስ በተደረገ የሰውነት ልምምድ መስራት ሌላኛው ነው። የውሃ ዋና እና በሳምንት ለአራት ወይም ለሦስት ቀናት ለ45 ደቂቃ ያህል በእግር ፈጠን ያለ እርምጃ መሄድም ጥሩ ነው። የሥራ ሁኔታን ምቹ ማድረግም አስፈላጊነቱ የሚያጠያይቅ አይደለም። ቆመው የሚሰሩ ሰዎች እቃ ሲያነሱ እንዴት መጠንቀቅ እንዳለባቸው ማወቅ፣ የሚመች ጫማ ማድረግ እንዲሁም ብዙ የሚቆሙ ሰዎች አንድ እግራቸውን አንድ ነገር ላይ አሳርፈው (ሰቅለው) መቆም ለወገብ ህመም የመጋለጥ እድላቸውን ይቀንሳል። ከዚህም ባሻገር የወገብ ህመም መንስዔ ከሆኑ ድርጊቶች ራስን መጠበቅ እንደሚገባ ዶ/ር ቴዎድሮስ ይመክራሉ። | ጤና፡ የወጣቶች የወገብ ህመም መንስዔ እና መፍትሔው አሁን አሁን የወገብ ህመም አጋጥሟቸው የህክምና ተቋማትን የሚጎበኙ ወጣቶች እየተበራከቱ ነው። በተለይ በማደግ ላይ ባሉ አገራት ለወገብ ህመም የሚጋለጡ ወጣቶች ቁጥርም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ጥናቶች ያመለክታሉ። ለመሆኑ ለዚህ መንስዔው ምንድን ነው? መፍትሔውስ? በዚህ ላይ በፓራጎን የፊዚዮቴራፒና ስፓርት ህክምና ስፔሻሊቲ ልዩ ክሊኒኮች ውስጥ ሥራ አስኪያጅ እና ሜዲካል ዳሬክተር ከሆኑት ዶ/ር ቴዎድሮስ ወ/ገብርኤል ጋር ቆይታ አድርገናል። ዶ/ር ቴዎድሮስ ሦስቱንም ድግሪያቸውን የተከታተሉት በአሜሪካ ሲሆን በፊዚዮቴራፒ በተለይ በስፖርት ህክምና እና ኦርቶፔዲክስ ህክምና ዶክትሬታቸውን አግኝተዋል። በሙያቸው በአሜሪካ ለ10 ዓመታት የሰሩ ሲሆን በኢትዮጵያ ደግሞ ላለፉት 12 ዓመታት እያገለገሉ ይገኛሉ። ከዚህም በተጨማሪ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ትምህርት ቤት ውስጥ ረዳት ፕሮፌሰር ናቸው። በጥቁር አንበሳ ህክምና ትምህርት ቤት በፊዚዮቴራፒ ዶክትሬት ፕሮግራም በመምህርነት ሠርተዋል። ብዙውን ጊዜ ወጣቶች ለወገብ ህመም ያጋለጣቸውን መንስዔ በውል አያውቁትም። እንዲሁ በደፈናው ድንገት አመመኝ ሲሉ ነው የሚሰማው። ለመሆኑ የወገብ ህመም መንስዔዎች ምንድን ናቸው? የሰውነት ማጎልመሻ እንቅስቃሴዎች፣ የምንጫማቸው ጫማዎች ፣ የምንተኛበት ፍራሽ ፣ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈፀምበት መንገድ ( Sex position) . . . ለወገብ ህመም ይዳርጉ ይሆን? ወደዚህ ዝርዝር ከማለፋችን በፊት ስለወገብ እና የወገብ ህመም ምንነት እናንሳ። ወገብ ቀበቷችን ወይም መቀነታችን የሚያርፍበት የሰውነታችን ክፍል ሲሆን በዚህ ላይ የሚከሰት ህመም የወገብ ህመም ይባላል። የወገብ ህመም ጽንሰ ሃሳቡ ሰፊና ጥልቅ ቢሆንም በቀላል አገላለጽ በወገብ አካባቢ በሚገኙ ጡንቻዎች ፣ የነርቭ ሥሮች፣ የአከርካሪ አጥንቶች፣ የጎን አጥንቶች እና ጅማቶች ላይ የሚደርስ ጉዳት ነው። ይህ ጉዳት ጊዜያዊ ወይም ዘለቄታዊ ሊሆን ይችላል። የወገብ ህመም ዓይነቶች እንደ መንስዔያቸው ይለያያሉ። ዋና ዋናዎቹ ግን እነዚህ ናቸው፦ ከመጨረሻው ነጥብ እንጀምር። የሰውነት በሽታ ተዋጊ ሂደት በመዛበት የሚከሰተው የወገብ ህመም የሚያጋጥመው ሰውነት በሽታን የሚከላከልበት ሂደት ሌሎች የሰውነት አካላትን ሲያጠቃ ነው። በእንግሊዝኛ አጠራሩ Ankylosing spondylitis ይባላል። የሰውነት የውስጥ ቁስለትን በመፍጠር ዘለግ ላለ ጊዜ የሚቆይ ህመም ነው። የዚህ ህመም ምክንያቱ ምን እንደሆነ በውል አይታወቅም። በተለይ በመገጣጠሚያዎች እና በአከርካሪ አጥንቶች መጋጠሚያ መካከል ቁስለትን ያስከትላል። ህመሙ እየጨመረ ሲሄድም የአከርካሪ አጥንቶች እንዲንቀሳቀሱ እንደ ሃዲድ የሚያገለግለው የሰውነት ክፍል ላይ አጥንቶቹ መንቀሳቀሳቸውን ትተው እርስ በእርሳቸው እንዲጣበቁ ያደርጋል። በዚህ ምክንያት አጥንቶቹ መንቀሳቀሳቸው ቀርቶ አንድ አካል ይሆናሉ። በዚህ ህመም የተጠቃ ሰው ማጎንበስ፣ ወደ ኋላ አሊያም ወደ ጎን መንቀሳቀስ አይችልም። የሌሎቹ የወገብ ህመም ዓይነቶች መንስዔዎችስ? ለወገብ ህመም የሚዳርጉን መንስዔዎች በርካታ ቢሆኑም ዶ/ር ቴዎድሮስ በ21 ዓመት የህክምና ልምዳቸው የተመለከቷቸውንና ዋና ዋና ያሏቸውን መንስዔዎች ያስረዳሉ። ከባድ ነገር ማንሳት፡ ማንኛውም ሰው በዕለት ተዕለት ክንውኑ ጥንቃቄ ካላደረገ ወገቡን ሊታመም ይችላል። በባልዲ ውሃ ቀድቶ ፎቅ ላይ መውሰድ፣ ክብደት ያላቸውን ሰዎች ከአልጋ ማንሳት እንዲሁም ማንኛውንም ከአቅም በላይ የሆነ ክብደትን ማንሳት ለወገብ ህመም ሊዳርግ ይችላል። ከልክ በላይ የሆነ የሰውነት ክብደት መኖር፡ በተለይ በአንድ ጊዜ የሚጨምር የሰውነት ክብደት የወገብ ህመም እንደሚያስከትል ዶ/ር ቴዎድሮስ ይናገራሉ። "በኮቪድ ወረርሽኝ ወቅት አካላዊ እንቅስቃሴ የሌለው ሥራ በመዘውተሩ በዚህ ሳቢያ የሚከሰት ህመም ተበራክቶ ነበር" ይላሉ። ረዘም ላለ ጊዜ ቆሞ፣ ተቀምጦ ወይም ቆሞ ጎንበስ ብሎ መስራት፡ ረዘም ላለ ጊዜ ቆመው፣ ተቀምጠው አልያም ቆመው ከአንገታቸው ተጎንብሰው በሚሰሩ ሙያዎች ላይ የተሰማሩ ሰዎች ለወገብ ህመም የመጋለጣቸው ዕድል ሰፊ ነው። ዶ/ር ቴዎድሮስ አንድ ሰው ቆሞ ከአንገቱ ጎንበስ ብሎ በሚሰራበት ጊዜ በሁለት አከርካሪ አጥንቶች መካከል ወደ 270 ኪሎ ግራም ግፊት እንዳለው ጥናቶችን ያጣቅሳሉ። ይህን በየቀኑ ማድረግ ደግሞ ከጊዜ በኋላ የከፋ ጉዳት ያስከትላል። ብዙ ጊዜ የቀዶ ህክምና ሐኪሞች በዚህ ሳቢያ ለሚከሰት የወገብ ህመም ሲጋለጡ ይስተዋላል። ብዙ መንገጫገጭ ያላቸው የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን ማሽከርከር፡ ብዙ ንዝረት ያላቸው የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን ማሽከርከር ወይም ምቹ ባልሆኑ መንገዶች ላይ መኪና ማሽከርከር ከጊዜ በኋላ የወገብ ህመም ያስከትላል። የዝላይ እና የሩጫ እንቅስቃሴዎች፡ በተለይ ከልክ በላይ የሰውነት ክብደት ያላቸው ሰዎች ሩጫ ወይም የመዝለል እንቅስቃሴ የሚያዘወትሩ ከሆነ ወገባቸው ሊጎዳ ይችላል። እንደ አስፓልት ያለ ጠንካራ የሆነ ቦታ ላይ የሚሮጡ ሰዎችም መሬቱ ላይ እግራቸውን በጣሉ ቁጥር መሬትም በአጸፋው ስለሚመታቸው ለጉዳት ሊዳርጋቸው ይችላል። ከዚህም በተጨማሪ ወጣ ገባ የሆነ መሬት ላይ የሚሮጡ ሰዎች እግራቸው በሚያርፍበት ሰዓት ሚዛናቸው እኩል ስለማይሆን ወገብ ላይ ጫና ይፈጠራል። ሰውነት ሳይለምድ በአንድ ጊዜ ከባድ የአካል እንቅስቃሴ መስራት፡ አሁን አሁን በወጣቶች ዘንድ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ እየተለመደ መጥቷል። የሚሰሯቸው እንቅስቃሴዎችንም ዩቲዩብ በማየት የሚመርጡም አሉ። ይህ ብቻም ሳይሆን ስፖርቱን ለምን ዓላማ እንደሚሰሩ የማያውቁ በርካቶች ናቸው። በዚህ ሳቢያ ተጎድተው ወደ ክሊኒካቸው የሚመጡ ወጣቶች መኖራቸውን ዶ/ር ቴዎድሮስ ይናገራሉ። "ችግሩ አካላዊ እንቅስቃሴ ከማድረግ የተከሰተ ሳይሆን ሰውነት ሳይለማመድ ከባድ የአካል እንቅስቃሴ መስራት ነው" ይላሉ። "ጂምናዚየም ውስጥ ለአሰልጣኝ ጉርሻ መስጠት የተለመደ ሆኗል" የሚሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ አንዳንድ አሰልጣኞች ጉርሻዋን ለማግኘት ደንበኞቻቸው የሚፈልጉት የሰውነት ለውጥ ላይ ቶሎ ማድረስ ላይ ብቻ ትኩረት እንደሚያደርጉ ይናገራሉ። አሰልጣኞቹ ስለስፖርታዊ እንቅስቃሴው እንጂ ስለጤና እውቀት ላይኖራቸውም ይችላል። አንዳንድ ሰልጣኞችም በአንድ ጊዜ በሰውነታቸው ላይ የሚፈልጉት ለውጥ እንዲመጣ ባልተገባ መልኩ ከልክ በላይ የሆነ አካላዊ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ። ዶ/ር ቴዎድሮስ ይህንን ሲገልጹት "ምንም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አድርጎ የማያውቅ ሰው ቅዳሜ እና እሁድ ጂምናዚየም ገብቶ አገር ይያዝልኝ እንደ ማለት ነው" ይላሉ። ዲስክ መንሸራተት፡ የዲስክ መንሽራተት ስሙ ለብዙዎቻችን ጆሮ እንግዳ አይደለም። ዶ/ር ቴዎድሮስም የዲስክ መንሸራተት ያለ ስሙ ብዙ ስም የተሰጠው በሽታ ነው ይላሉ። ዶ/ር ቴዎድሮስ እንደሚሉት የዲስክ ችግር ተብለው ወደ ክሊኒካቸው ከሚመጡት 100 ሰዎች ውስጥ 50 በመቶ የሚሆኑት ችግራቸው ሌላ ነው። በተለምዶ የህክምና ባለሙያዎች ህሙማንን ለዲስክ መንሸራተት ተዳርገዋል የሚሉት 'ኤምአርአይ' መመርመሪያ የሚያሳየው ውጤት ላይ ተመርኩዘው ነው። ይሁን እንጂ ዶ/ር ቴዎድሮስ "10 ሰዎችን እንዲሁ ከመንገድ ላይ በግምት ተመርጠው ኤምአርአይ ቢነሱ ቢያንስ 7ቱ የዲስክ መንሸራተት ሊያሳዩ ይችላሉ" ይላሉ። ይህ ማለት ግን ህመም አለባቸው ማለት አይደለም። "የዲስክ መንሸራተት ታይቷል ማለት የተዛባ ዲስክ አላቸው፤ ግን ዲስኩ ነርቩን ጨፍልቆ ህመም የሚያመጣበት ደረጃ ላይ አይደለም ማለት ነው" ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። በዚህ የምርመራ ውጤት ላይ ተመስርተው ቶሎ ቀዶ ህክምና አድርጉ ወደሚል ድምዳሜ የሚደርሱ የህክምና ባለሙያዎች መኖራቸውን የሚናገሩት ዶ/ር ቴዎድሮስ፤ ይህ ግን ስህተት ነው ብለዋል። ለመሆኑ ዲስክ ምንድን ነው? የሚገኘውስ የት ላይ ነው? ዲስክ በአከርካሪ አጥንቶች መካከል የሚገኝ በውስጡ ፈሳሽ ያለው ለስላሳ የሆነ እንደ ጎሚኒ (ሾክ አብሶርቨር) የምንጠቀምበት የአካል ክፍል ነው። ታዲያ ሰውነታችን ጫና በሚበዛበት ጊዜ በዲስኩ ውስጥ ያለው ፈሳሽ ሊወጣ ይችላል ወይም ደግሞ ፈሳሹ ሳይወጣ ዲስኩ ወደ አንድ በኩል አመዝኖ መውጣት ወደማይገባበት ቦታ ሊወጣ ይችላል። ዲስክ ያለበት አካባቢ የተጨናነቀ በመሆኑ አፈትልኮ በሚወጣበት ጊዜ ከጭንቅላታችን በሚወርደውና ህብለ ሰረሰር በሚባለው የነርቭ ግንድ እና ቅርንጫፎች ላይ በመተኛት ጫና ይፈጥራል። የዲስክ መንሸራተት በሚያጋጥምበት ጊዜ ቀዶ ህክምና ለማድረግ ከመጣደፍ በፊት ዲስኩ ተንሸራቶ ምን ሆነ? ወዴት አቅጣጫ ነው የተንሸራተተው? ምን ያህል ነው የተንሸራተተው? እየነካ ያለውስ ነርቭ የትኛውን ነው? ሊያስከትል የሚችለው የህመም ስሜት አለ ወይ? የሚሉትን ወሳኝ ጥያቄዎች መጠየቅ አስፈላጊ መሆኑን ዶ/ር ቴዎድሮስ ያሰምሩበታል። ወጣቶችን ለወገብ ህመም የሚያጋልጣቸው የተለየ ምክንያት ይኖር ይሆን? ከምንጊዜውም በላይ ብዙ ወጣቶች በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ላይ እየተሠማሩ መሆናቸው አንዱ ምክንያት ነው ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። ወጣቶች ረዘም ያለ ጊዜ መቆምን፣ መቀመጥን አሊያም ጎንበስ ብሎ መቆምን እንዲሁም ከባድ ነገር ማንሳትን፣ መሸከምን የሚጠይቁ ሥራዎችን ይሠራሉ። በሌላም በኩል ከዚህ ቀደሙ በተሻለ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማዘውተርም ሌላኛው ምክንያት መሆኑን ይናገራሉ። "ስለምንሰራው አካላዊ እንቅስቃሴ ጠለቅ ያለ እውቀት ከሌለን በስተቀር የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ጥቅም እንዳላቸው ሁሉ ጉዳት አላቸው።" ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። በተቃራኒው ደግሞ የሰውነት እንቅስቃሴ ማነስ ለወገብ ህመም መንስዔ ነው። የግብረ ሥጋ ግንኙነት ለወገብ ህመም ያጋልጣል? የግብረ ሥጋ ግንኙነት በሳይንስ እንደ ወገብ ህመም መንስዔነት ወይም እንደ ወገብ ህመም መነሻነት አይታወቅም ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። ይሁን እንጂ የወገብ ህመም ያለባቸው ሰዎች የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽሙበት መንገድ ህመማቸውን ሊያባብስባቸው ወይም የተሻላቸውን ህመም እንደገና ሊያስነሳባቸው እንደሚችል ይናገራሉ። "በተለይ በሴቶች ዘንድ ይህንን ለሐኪም የማስረዳት ልምድ የለም" የሚሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ አንዳንዶች ግን በስልክም ቢሆን ምክር የሚጠይቁ መኖራቸውን አልሸሸጉም። "እንደ የወገብ ህመማቸው ዓይነትም ለተወሰነ ጊዜ የግብረ ሥጋ ግንኙነት አደራረግ (Sex position) እንዲቀይሩ፣ እንዳያደርጉ ወይም ሊያደርጓቸው ስለሚችሉ የግብረ ሥጋ ግንኙነት አደራረግ ዓይነቶች ምክር የሚሰጣቸው ታማሚዎች አሉ" ይላሉ። የምንጫማው ጫማስ? የወገባችንን ጤንነት ለመጠበቅ የምንጫማው የጫማ ዓይነት ወሳኝነት አለው። ይህ ግን በአብዛኛው የሚገናኘው ከሴቶች ጋር ነው። ምክንያቱም በተለይ በፋሽንና መዝናኛ ኢንደስትሪው ሴቶች መንቀሳቀስ እስከሚቸገሩ ድረስ ረጃጅም ታኮ ያላቸውን ጫማዎች ተጫምተው ማየት የተለመደ ነው። ይህ ደግሞ በሰውነት ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራል። እንዴት? ዶ/ር ቴዎድሮስ ለዚህ ሳይንሳዊ ምላሽ አላቸው። ሰውነት የራሱን ሚዛን የሚጠብቅበት መንገድ አለው። ይህ የስበት ማዕከል (Center of gravity) ይባላል። ስንራመድ የማንወድቀው ወይም ደግሞ ቁጭ ብለን ስንነሳ ከግድግዳ ጋር የማንጋጨው ይህ የመሬት ስበት ማዕከል ሚዛናችንን ስለሚጠብቅልን ነው። ታዲያ ከፍ ያሉ ታኮዎች ያሏቸውን ጫማዎች ስንጫማ ሰውነት ተፈጥሯዊ የሆነውን የሰውነት ሚዛን ይለቃል። የሰውነታችን የመሬት ስበት ማዕከልም ይቀየራል። በመሆኑም ሰውነት ይህንን የስበት ማዕከል መልሶ ወደ ማዕከሉ ላይ ለማምጣት (ሚዛኑን ለመጠበቅ) የሚያደርጋቸው ማስተካከያዎች ወገብ ላይ ጫና ይፈጥራሉ። ጫናው ወገብ ላይ ብቻ ሳይሆን ጉልበት፣ እግርና የእግር መዳፍ ላይም ነው። ከዓመታት በፊት በዩናይትድ ኪንግደም በፖዲያትሪ ኮሌጅ የተሠራ ጥናት ሴቶች ህመም እንደተሰማቸው ሳይናገሩ ከፍ ያለ ታኮ ጫማ ተጫምተው መቆየት የሚችሉት በአማካይ ለአንድ ሰዓት ያህል ነው ይላል። በዚህ ጥናት ተሳታፊ የነበሩ ሴቶች ጫማውን ከተጫመቱ ከ10 ደቂቃ በኋላ በእግራቸው ላይ ህመም እንደተሰማቸው ተናግረዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ሰው የተፈጠረው በባዶ እግሩ ለመሄድ ነው በማለት ሰዎች በባዶ እግራቸው እንዲሄዱ የሚያበረታታ ሳይንስ አለ። በዚህም ምክንያት ሆነ ብለው በባዶ እግራቸው የሚሄዱ ሰዎች አሉ። በእርግጥ ዶ/ር ቴዎድሮስ በባዶ እግር መሄድ አሊያም በጣም አነስተኛ ታኮ ያላቸው ጫማዎች ማድረግ ጉዳት አለው ብለው አያምኑም። ይሁን እንጂ በተፈጥሮ 'የእግራቸው ቅርጽ ለየት ያለ' ሰዎች ከተረከዝ ሁለት ሴንቲ ሜትር ከፍ ያለ ታኮ ያለው ጫማ እንዲያደርጉ ይመክራሉ። "ተረከዝ በጫማ መሄድ ከለመደ በኋላ በባዶ እግር በብዛት መሄድ በተረከዝ ላይ አጥንት መብቀልን (Bone Spur) ሊያስከትልም ይችላል" ይላሉ። ይህ አጥንት የተረከዝን ስጋ እንደ ጩቤ የሚወጋ ነው። በመሆኑም በተለይ በባዶ እግር መሄድ ያልለመደ እና ተረከዝ ላይ በቂ የስብ ንጣፍ (Fat pad) የሌለው ሰው በባዶ እግሩ ቢሄድ ለእንዲህ ዓይነት ችግር ሊጋለጥ እንደሚችል ያሳስባሉ። ይህ ግን በስፋት የሚከሰት አይደለም። የወገብ ህመም እንዳጋጠመን እንዴት ማወቅ እንችላለን? እንደማንኛውም ህመም የወገብ ህመም ሲያጋጥም የሚታዩ ከቀላል እስከ ከባድ ምልክቶች አሉ። የህመም ማስታገሻ መድሃኒት የማያስወስዱ፣ ቁጭ ስንል የሚያስታውሱን፣ መድሃኒት እስከ መውሰድ የሚያደርስ የማቃጠልና መቆጥቆጥ ስሜት፣ ጎንበስ ብሎ ቀና ለማለት መቸገር፣ ለመነሳት ድጋፍ መፈለግ፣ የጡንቻ መኮማተር፣ ለመንቀሳቀስ መቸገር፣ ተኝቶ ለመገላበጥ ማቃት የተወሰኑት ምልክቶቹ ናቸው። የሚታዩት ምልክቶች ግን እንደ ህመሙ መንስዔዎች ይለያያሉ። ለምሳሌ ረዘም ላለጊዜ በመቆም ወይም በመቀመጥ የሚመጣ ህመም ከሆነ ተቀምጠን ቆይተን ድንገት ስንነሳ የሰውነት መያዝ ፣ ስንቀመጥ ወይ ስንቆም ህመም መሰማት፣ የመቀመጫ አካባቢ ህመም፣ መጠዝጠዝና ንዝረት ያጋጥማል። ንዝረቱ ከመቀመጫ አለፍ ብሎ ቁርጭምጭሚት ፣ ጣቶች እና የእግር መዳፍ ድረስ የሚሰማ የመደንዘዝና የማቃጠል ህመሞች እየባሰ ሲመጣም የእግር መክዳትና ደረጃ ለመውጣት አቅም እስከማጣት ሊደርስ ይችላል። እግርን ማዘዝ፣ ጣቶችን ወደ ላይ ቀና ማድረግ ካቃተን ግን ህመሙ የከፋ ደረጃ ደርሷል ማለት ነው። ምን አልባት ይህ ቀዶ ሕክምና የሚያስፈልግበት ደረጃ ሊሆን ይችላል። ያጋጠመንን የወገብ ህመም ለማስታገስ በቤት ውስጥ ምን ማድረግ እንችላለን? በአቅራብያ የህክምና ተቋም ከሌለ ለጊዜው የህመም ማስታገሻዎችን መውሰድ ይመከራል። ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን ሌላ የሚወስዱት መድሃኒት ከሌለ እና ከሚወስዱት መድሃኒት ጋር የማይጋጭ ከሆነ ነው። ዘላቂ መፍትሔ ግን አይደለም። የወገብ ህመሙ የተከሰተው በድንገተኛ አደጋ [መውደቅ] ከሆነ ደግሞ በመጀመሪያ ህክምና እርዳታ በረዶ ማድረግ ጥሩ ነው። "የቁስለት ሂደቱን ለመቀነስ፣ እብጠት እና ውስጥ የደም መፍሰስ እንዳይኖር ይረዳል" ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። ከዚህ በኋላም የጡንቻ መኮማተር የሚኖር ከሆነ ሙቀት ሰውነትን የማፍታታት ባህርይ ስላለው ሙቀት ማድረግ የተሻለ መሆኑን ይመክራሉ። እረፍት ማድረግም ህመማችንን በተወሰነ ደረጃ ሊያስታግስልን ይችላል። ይህን ሁሉ አድርገን የማይሻል ከሆነ ግን ሥር ሳይሰድ እንደ ምንም ወደ ህክምና ቦታ ሄዶ ትክክለኛ ህክምና ማድረግ አስፈላጊ ነው። "አንዳንድ ሰዎች ባህላዊ ቦታ ሄደው ባልተገባ ሁኔታ ህክምና ወስደው ተጎድተው የሚመጡ አሉ" ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። እንደዚህ ያሉ ቦታዎችን ከሚያዘወትሩ ሰዎች መካከል የተማሩ ሰዎችም ጭምር እንደሚገኙበት በመግለጽም ይህ ተገቢ አለመሆኑን ይናገራሉ። ህመሙን ለማስወገድ ሲባል ያልተገባ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግም ጉዳቱን ሊያባብሰው እንደሚችል ዶ/ር ቴዎድሮስ ያስጠነቅቃሉ። ወገባችንን በህክምና ቀበቶ ወይም በመቀነት ብንደግፈውስ? የወገብ ህመም የተለያዩ ደረጃዎች አሉት። መጀመሪያ አካባቢ ችግሩ እንደተፈጠረ፣ ከዚያ ከሁለት እስከ ሦስት ወር እና ከሦስት ወር በላይ የቆየ ህመም ናቸው። ህመሙ ከሦስት ወር በላይ የቆየ ከሆነ ሥር የሰደደ ችግር ይባላል። በመሆኑም ህመሙ እንደ ጀመረ አካባቢ እረፍት ማድረግን ጨምሮ በመቀነት ማሰር ወይም በቀበቶ መደገፍ ያገዘን ስለሚመስል በሥነ ልቦናም ሆነ አካላዊ በሆነ መልኩ ሊደገፍ ይችላል ይላሉ- ዶ/ር ቴዎድሮስ። ሆኖም ይህ ለረዥም ጊዜ የሚደረግ ከሆነ ችግር እንደሚያስከትል ይናገራሉ። ምክንያታቸውን ሲያስረዱም "ቀበቶ ተደረገ ወይም መቀነት ታሰረ ማለት እዚያ አካባቢ ያሉ ጡንቻዎች እረፍት ወጡ ማለት ነው።" ይላሉ። በዚህ ሳቢያም የጡንቻ መክሳት ችግር ይከሰታል። በመሆኑም ጡንቻችን ያለ ድጋፍ ሥራውን መሥራት ይቀንሳል፤ አልያም ያቆማል። ይህም ሰዎች በቀበቶ አሊያም በመቀነት ላይ ጥገኛ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። "በኢትዮጵያ በህክምና ባለሙያዎች ዘንድ የአንገት መደገፊያ [ኮላር] እና የወገብ መደገፊያ ቀበቶ የማዘዝ ችግር ጎልቶ እየታየ ነው" የሚሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ የችግሩ መንስዔ ሳይታወቅ እነዚህን ቁሶች ማዘዝ ተገቢ እንዳልሆነ ይናገራሉ። አንዳንድ ጊዜ ሐኪሞች ቀበቶ ማዘዛቸውን ሊዘነጉት የሚችሉበት አጋጣሚም ስለሚኖር ታማሚዎቹ ለረዥም ጊዜ ቀበቶውን ሊያደርጉት ይችላሉ። ይህ ደግሞ ጉዳት ያስከትላል ይላሉ ዶ/ር ቴዎድሮስ። ምን ዓይነት ፍራሽ እና ትራስ ላይ እንተኛ ? መቼም በወገብ ህመም ሳቢያ ፍራሽ ያልቀያየረ፤ ከአልጋ መደብ ፣ ከመደብ አልጋ ያላለ አይኖርም። ትራስም ቢሆን እንዲሁ። ምን ዓይነት ፍራሽ ላይ እንተኛ ? ምን አይነት ትራስ እንጠቀም የበርካቶች ጭንቀት ነው። ለወገብ ህመም ፍቱን ናቸው የተባሉ ፍራሾችም ይቸበቸባሉ። በሰለጠነው ዓለም የተለያዩ ዓይነት ዘመናዊ ፍራሽና ትራሶች እየተመረቱ ነው። በአንድ አልጋ ላይ ባልና ሚስትን በመረጡት ፍራሽ ላይ የሚያስተኛ ቴክኖሎጂም ተፈልስፏል። ታዲያ የትኛው ላይ ብንተኛ የተሻለ ነው? ዶ/ር ቴዎድሮስ "ታማሚዎቹ ተመቸን ያሉትን ፍራሽ ትክክል አይደለም ማለት አስቸጋሪ ነው ምክንያቱም ሰውነታቸው ከመረጡት ፍራሽ ጋር ተመቻችቶ ሊሆን ይችላል" ይላሉ። ቢሆንም ግን ደረቅ ፍራሽ ላይ መተኛትን አይመክሩም። እርሳቸው የሚመክሩት ሰውነት ቅርጹን በጠበቀ መልኩ የሚያሳርፍን ፍራሽ ወይም ትራስ ነው። "ራቁታችንን በመስታዎት ብንመለከት ሰውነታችን እጥፋቶች (Curves) አሉት። ስንተኛ እነዚያ እጥፋቶች ቅርጻቸውን ጠብቀው በትክክል ማረፍ አለባቸው" ይላሉ። ለዚህም ነው በሰለጠነው ዓለም 'ሚሞሪ ፎም' የተመረተው። ሚሞሪ ፎም ስንተኛ የሰውነትን ቅርጽ ይዞ ስንነሳ ወደ ነበረበት መመለስ የሚችል ፍራሽ ነው። 'ስሊፕ ነምበር ቤድ' የሚባልም ባልና ሚስት አልጋቸውን ሳይለዩ ለየራሳቸው የሰውነት ቅርጽ በሚመቻቸው መልኩ ማስተካከል የሚችሉት ሳይንሳዊ ፍራሽም ተሰርቷል። በኢትዮጵያ ለወገብ ህመም ተብለው የሚሸጡ ፍራሾችስ? ዶ/ር ቴዎድሮስ እነዚህ ፍራሾች ሳይንሳዊ አይደሉም ይላሉ። "ሱቅ የተሰቀለን ልብስ በግምት አንስቶ ግባ ብሎ እንደመታገል ነው" ሲሉም በምሳሌ ያስረዳሉ። "በሰለጠነው ዓለም 30 ደቂቃ ፍራሹ ላይ እረፍት ወስደን ነው ፍራሽ የምንገዛው" የሚሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ በኢትዮጵያ አንዳንድ መሸጫዎች ውስጥ 'ፍራሾቹ ላይ መተኛት ክልክል ነው!' የሚልም ማስታወቂያ በመለጠፍ ምቾቱን ሞክሮ ለመግዛት የሚደረገውን ክልከላንም ተችተዋል። ዶ/ር ቴዎድሮስ ትራስን በተመለከተም ተመሳሳይ ሃሳብ ነው ያላቸው። ትራስ በጭንቅላታችን እና በአንገታችን ሥር መካከል ያለውን ክፍተት የሚሞላ መሆን አለበት ይላሉ። ነገር ግን ሰዎች ትራሳቸውን በአግባቡ ሲጠቀሙበት አይስተዋልም። በእርግጥ የሚመቸንንና ልካችንን ለማወቅ አዳጋች ነው። ገንዘባቸውን ትራስ በመግዛት የሚጨርሱም ጥቂት አይደሉም። ይህንን ችግር ለመፍታትም ይመስላል በሰለጠነው ዓለም 'ዎተር ፒሎው' [በውሃ የሚሞላ ትራስ] የተሰራው። ይህ የውሃውን መጠን በመቀነስ ወይም በመጨመር ትራሱን በልክ ለማሳነስና ለማተለቅ ያስችላል። በመሆኑም የምንጠቀመውን ትራስ ልክ ማወቅ እና በተገቢው መንገድ መጠቀም ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ይመክራሉ። የአኗኗር ዘይቤያችን ምን ይምሰል? የሰውነት ክብደታችንን መቆጣጠር ወሳኝ ነው። ይህን ማድረጋችን ከወገብ ብቻም ሳይሆን ከሌሎች በሽታዎችም ራሳችንን ለመጠበቅ ያስችለናል። "በሰውነታችን ላይ አንድ ኪሎ በጨመርን ቁጥር በእያንዳንዱ ኪሎ አንዱ ጉልበታችን ላይ 4 ኪሎ ጫና ይፈጠራል" የሚሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ የሰውነታችንን ክብደት መቆጣጠርን ቸል ልንለው እንደማይገባ ይመክራሉ። የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን በአቅማችን ልክ እና ቀስ በቀስ በተደረገ የሰውነት ልምምድ መስራት ሌላኛው ነው። የውሃ ዋና እና በሳምንት ለአራት ወይም ለሦስት ቀናት ለ45 ደቂቃ ያህል በእግር ፈጠን ያለ እርምጃ መሄድም ጥሩ ነው። የሥራ ሁኔታን ምቹ ማድረግም አስፈላጊነቱ የሚያጠያይቅ አይደለም። ቆመው የሚሰሩ ሰዎች እቃ ሲያነሱ እንዴት መጠንቀቅ እንዳለባቸው ማወቅ፣ የሚመች ጫማ ማድረግ እንዲሁም ብዙ የሚቆሙ ሰዎች አንድ እግራቸውን አንድ ነገር ላይ አሳርፈው (ሰቅለው) መቆም ለወገብ ህመም የመጋለጥ እድላቸውን ይቀንሳል። ከዚህም ባሻገር የወገብ ህመም መንስዔ ከሆኑ ድርጊቶች ራስን መጠበቅ እንደሚገባ ዶ/ር ቴዎድሮስ ይመክራሉ። | https://www.bbc.com/amharic/news-60278142 |
5sports
| በደማቅ መክፈቻ እና በሜዳ ላይ ውዝግብ የጀመረው የኳታር የዓለም ዋንጫ | ኳታር ያዘጋጀችው የ2022 የዓለም ዋንጫ በአል-ባይት ስታዲም በድምቀት ተጀምሯል። አሜሪካዊው ፊልም ተዋናይ ሞርጋን ፍሪማን እና በዩቲዩብ ታዋቂነትን ያተረፈው ኳታራዊው ጋኒም አል-ሙፍታህ የመድረኩ ፈርጦች ነበሩ። የውድድሩ ዘፈን የሆነውን ድሪመርስ (ህልመኞቹ) የተሰኘውን ሙዚቃ ደቡብ ኮሪያዊው ፖፕ ኮከብ ጆንግ ኩክ እና የኳታሩ ፋሃድ አል ኩባሲ በስታዲየሙ ተገኝተው እየተቀባበሉ አቀንቅነዋል። ሞርጋን ፍሪማን በመከፍቻው ሥነ ሥርዓት ላይ እግር ኳስ ሰዎችን ለማቀራረብ ያለውን ኃይል ተርኳል። የዓለም ዋንጫ በመካከለኛው ምሥራቅ የሙስሊም አገር ሲዘጋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን፣ ኳታር የሠራተኞችን መብት ጨምሮ በብዙ ጉዳዮች ስትብጠለጠል ቆይታለች። በድንኳን ቅርጽ በተሠራው ስታዲየም ውስጥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊን ጨምሮ የቱርክ፣ የግብፅ እና የአልጄሪያ መሪዎች ታድመዋል። ለ30 ደቂቃ የዘለቀው የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት በርችት ደምቆ በመጠናቀቅ ሜዳውን ለዓለም ዋንጫው መጀመሪያ ጨዋታ ለቋል። ኳታር የደቡብ አሜሪካዋን ኢኳዶርን አስተናገደች። የዳኛው ፊሽካ ከተሰማበት ቅጽበት ጀምሮ የኳታር ብሔራዊ ቡድን ተበልጦ አምሽቷል። በደቂቃዎች ውስጥ የኢኳዶሩ ኤነር ቫሌንሽያ ኳስን እና መረብን ማገናኘት ቻለ። በቪዲዮ ምስሎች ድጋፍ ረዳት ዳኞች ኳሱ ከጨዋታ ውጪ ነው በሚል ሽረውታል። እፎይታ ለኳታር። ይህ ጎል የተሻረበት መንገድ ትክክል ነው አይደለም በሚል በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ መነጋጋሪያ ሆኗል። ነገሮች ግን አልተሻሻሉም። ቫሌንሽያ ከፍጹም ቅጣት ምት እና በጭንቅላት ባስቆጠራቸው ጎሎች ኢኳዶር ጨዋታውን 2 ለ 0 በመምራት ወደ መልበሻ ክፍል አመሩ። ከእረፍት መልስ ተጨማሪ ጎል ሳይቆጠር ጨዋታው ተጠናቀቀ። አሰልጣኝወ ሳንቼዝ ከጨዋታው በኋላ “ይህ የጠበቅነው ነገር አይደለም” ሲሉ ለስድስት ወር ካምፕ ገብተው ያደረጉትን ዝግጅት ውሃ እንደበላው ገለጹ። በመጀመሪያው አጋማሽ ብዙ ደጋፊዎች ሜዳውን ለቀው ወጥተዋል። ሳንቼዝ ተከፍቶ ከሜዳ ለወጣው የአገሬው ሰው በሚቀጥለው ጨዋታ “እንክሳችኋለን” ቢሉም ቀላል አይመስልም። በመጪው አርብ የአፍሪካ ሻምፒዮናዋ ሴኔጋልን ነው የሚገጥሙት። የምድቡን የመጨረሻ ጨዋታ ደግሞ ከብርቱካናማዎቹ ኔዘርላንድሶች ጋር። ኳታር በውዝግብ የጀመረችው የዓለም ዋንጫ በመክፈቻው ሥነ ሥርዓት ድምቀት የተሸፈነ ቢመስልም፣ ደጋፊዎች ሜዳ ውስጥ ባዩት ነገር አንገታቸውን ደፍተው ተመልሰዋል። የዓለም ዋንጫው ዛሬ በሚከናወኑ ሦስት ጨዋታዎች ይቀጥላል። በምድብ ለ ጨዋታዎች ውድድሩ ሲቀጥል አስር ሰዓት ላይ እንግሊዝ እና ኢራን ይጫወታሉ። በፖለቲካ ጉዳይ የሚቆራቆዙት ሁለቱ አገራት የሚያደርጉት ጨዋታ ከሜዳ ውጪ ባለው ጉዳይ ተጠባቂ ሆኗል። አህጉረ አፍሪካ ተወካይ ሴኔጋል በምድብ ሀ ከኔዘርላንድስ ጋር አንድ ሰዓት ላይ ይጫወታሉ። በምድብ ለ ሁለተኛ ጨዋታ አሜሪካ እና ዌልስ ምሽት አራት ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ። | በደማቅ መክፈቻ እና በሜዳ ላይ ውዝግብ የጀመረው የኳታር የዓለም ዋንጫ ኳታር ያዘጋጀችው የ2022 የዓለም ዋንጫ በአል-ባይት ስታዲም በድምቀት ተጀምሯል። አሜሪካዊው ፊልም ተዋናይ ሞርጋን ፍሪማን እና በዩቲዩብ ታዋቂነትን ያተረፈው ኳታራዊው ጋኒም አል-ሙፍታህ የመድረኩ ፈርጦች ነበሩ። የውድድሩ ዘፈን የሆነውን ድሪመርስ (ህልመኞቹ) የተሰኘውን ሙዚቃ ደቡብ ኮሪያዊው ፖፕ ኮከብ ጆንግ ኩክ እና የኳታሩ ፋሃድ አል ኩባሲ በስታዲየሙ ተገኝተው እየተቀባበሉ አቀንቅነዋል። ሞርጋን ፍሪማን በመከፍቻው ሥነ ሥርዓት ላይ እግር ኳስ ሰዎችን ለማቀራረብ ያለውን ኃይል ተርኳል። የዓለም ዋንጫ በመካከለኛው ምሥራቅ የሙስሊም አገር ሲዘጋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን፣ ኳታር የሠራተኞችን መብት ጨምሮ በብዙ ጉዳዮች ስትብጠለጠል ቆይታለች። በድንኳን ቅርጽ በተሠራው ስታዲየም ውስጥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊን ጨምሮ የቱርክ፣ የግብፅ እና የአልጄሪያ መሪዎች ታድመዋል። ለ30 ደቂቃ የዘለቀው የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት በርችት ደምቆ በመጠናቀቅ ሜዳውን ለዓለም ዋንጫው መጀመሪያ ጨዋታ ለቋል። ኳታር የደቡብ አሜሪካዋን ኢኳዶርን አስተናገደች። የዳኛው ፊሽካ ከተሰማበት ቅጽበት ጀምሮ የኳታር ብሔራዊ ቡድን ተበልጦ አምሽቷል። በደቂቃዎች ውስጥ የኢኳዶሩ ኤነር ቫሌንሽያ ኳስን እና መረብን ማገናኘት ቻለ። በቪዲዮ ምስሎች ድጋፍ ረዳት ዳኞች ኳሱ ከጨዋታ ውጪ ነው በሚል ሽረውታል። እፎይታ ለኳታር። ይህ ጎል የተሻረበት መንገድ ትክክል ነው አይደለም በሚል በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ መነጋጋሪያ ሆኗል። ነገሮች ግን አልተሻሻሉም። ቫሌንሽያ ከፍጹም ቅጣት ምት እና በጭንቅላት ባስቆጠራቸው ጎሎች ኢኳዶር ጨዋታውን 2 ለ 0 በመምራት ወደ መልበሻ ክፍል አመሩ። ከእረፍት መልስ ተጨማሪ ጎል ሳይቆጠር ጨዋታው ተጠናቀቀ። አሰልጣኝወ ሳንቼዝ ከጨዋታው በኋላ “ይህ የጠበቅነው ነገር አይደለም” ሲሉ ለስድስት ወር ካምፕ ገብተው ያደረጉትን ዝግጅት ውሃ እንደበላው ገለጹ። በመጀመሪያው አጋማሽ ብዙ ደጋፊዎች ሜዳውን ለቀው ወጥተዋል። ሳንቼዝ ተከፍቶ ከሜዳ ለወጣው የአገሬው ሰው በሚቀጥለው ጨዋታ “እንክሳችኋለን” ቢሉም ቀላል አይመስልም። በመጪው አርብ የአፍሪካ ሻምፒዮናዋ ሴኔጋልን ነው የሚገጥሙት። የምድቡን የመጨረሻ ጨዋታ ደግሞ ከብርቱካናማዎቹ ኔዘርላንድሶች ጋር። ኳታር በውዝግብ የጀመረችው የዓለም ዋንጫ በመክፈቻው ሥነ ሥርዓት ድምቀት የተሸፈነ ቢመስልም፣ ደጋፊዎች ሜዳ ውስጥ ባዩት ነገር አንገታቸውን ደፍተው ተመልሰዋል። የዓለም ዋንጫው ዛሬ በሚከናወኑ ሦስት ጨዋታዎች ይቀጥላል። በምድብ ለ ጨዋታዎች ውድድሩ ሲቀጥል አስር ሰዓት ላይ እንግሊዝ እና ኢራን ይጫወታሉ። በፖለቲካ ጉዳይ የሚቆራቆዙት ሁለቱ አገራት የሚያደርጉት ጨዋታ ከሜዳ ውጪ ባለው ጉዳይ ተጠባቂ ሆኗል። አህጉረ አፍሪካ ተወካይ ሴኔጋል በምድብ ሀ ከኔዘርላንድስ ጋር አንድ ሰዓት ላይ ይጫወታሉ። በምድብ ለ ሁለተኛ ጨዋታ አሜሪካ እና ዌልስ ምሽት አራት ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c1dg5g1zr5no |
0business
| ‘የክሪፕቶው ንጉሥ’ ሳም ባንክማን በባሃማስ በቁጥጥር ስር ዋለ | ግዙፉ የክሪፕቶከረንሲ ልውውጥ ኩባንያ 'ኤፍቲኤክስ' መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ ሳም ባንክማን ፍራይድ በባሃማስ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታወቀ። ኩባንያው መክሰሩን በቅርቡ በይፋ አውጆ ወጣቱ ቢሊየነር ከስልጣኑ ለቅቄያለሁ ማለቱ ይታወሳል። ‘የክሪፕቶው ንጉስ’ በባሃማስ በሚገኘው ፍርድ ቤት ማክሰኞ እለት እንደሚቀርብም ባለስልጣናቱ ገልጸዋል። ሳም ባንክማን በቁጥጥር ስር የዋለው የአሜሪካ እና የባሃማስ ህጎችን ተላልፎ “የፋይናንስ ጥፋቶች” በመፈጸሙ መሆኑን ፖሊስ ይፋ አድርጓል። ኤፍቲኤክስ በዓለም ላይ ግዙፍ ከሚባሉ የክሪፕቶ ከረንሲ ግብይት ኩባንያዎች አንዱ የነበረ ሲሆን እንዳልነበር ሆኖም በመንኮታኮቱ ባለፈው ወር ኪሳራ በይፋ መዋጁ ይታወሳል። በርካታ የክሪፕቶ ደንበኞች ዲጂታል ገንዘባቸውን በአንዳች ቁስ ወይም መደበኛ ገንዘብ ለመቀየር ሳይችሉ ቀልጦባቸው ቀርቷል። ኩባንያው ኪሳራ ማወጁን ተከትሎ በሚካሄደው የፍርድ ሂደት ምን ያህሎቹ ገንዛባቸውን እንደሚያገኙ ግልጽ አይደለም። ባለሙያዎች በበኩላቸው ካላቸው ገንዘብ ጥቂት ሊሆን እንደሚችልም አስጠንቅቀዋል። ኤፍቲኤክስ ክሪፕቶን በመሸጥ፣ ዲጂታል ገንዘብን የማለዋወጥ ሥራን የሚሠራ የዲጂታል ግብይት አሳላጭ ኩባንያ ነው። ኤፍቲኤክስ ኪሳራ ከመግጠሙ በፊት ሳም 'የክሪፕቶ ዋረን በፌት' ተብሎ ይወደስ ነበር። በኪሳራ የተንኮታኮተው ኤፍቲኤክስ የክሪፕቶ ግብይት ኩባንያ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ደንበኞች እና 15 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሃብት ነበረው። የ30 ዓመቱ ሳም በዓለም ላይ ሁለተኛውን ግዙፉን የክሪፕቶከረንሲ ልውውጥ ኩባንያን በበላይነት ሲያስተዳድር ነበር። “ዛሬ አመሻሽ ላይ የባሃማስ ለስልጣናት በአሜሪካ መንግሥት ጥያቄ ከደቡብ ኒውዮርክ በታሸገ የክስ መዝገብ መሰረት ሳሙኤል ባንክማን ፍራይድን በቁጥጥር ስር አውለዋል። የክስ መዝገቡን ጥዋት ከፍተን የምናየው ይሆናል በወቅቱም የበለጠ የምንለው ነገር ይኖራል” በማለት በማንሃተን የሚገኘው የአሜሪካ አቃቤ ህግ ፅህፈት ቤት በትዊተር ገፁ አስፍሯል። የዋል ስትሪት ተቆጣጣሪዎችም እንዲሁ በሳሙኤል ላይ እርምጃ እንደሚወስዱ ተናግረዋል። ባንክማን ፍራይድ በያዝነው ሳምንት ማክሰኞ በአሜሪካ ኮንግረስ ኤፍቲኤክስ ስላጋጠመው መንኮታኮት ምስክርነቱን ይሰጣል ተብሎ ነበር። ሆኖም በአሁኑ ወቅት ምስክርነቱን መስጠት እንደማይችል የምክር ቤት አባሏ ማክሲን ዋተርስ አስረድተው በቁጥጥር ስር መዋሉም እንዳስገረማቸው ተናግረዋል። የሳሙኤል ባንክማን ፍሪድ ጠበቃ ቢቢሲ ላቀረባላቸው ጥያቄ ምላሽ አልሰጡም። | ‘የክሪፕቶው ንጉሥ’ ሳም ባንክማን በባሃማስ በቁጥጥር ስር ዋለ ግዙፉ የክሪፕቶከረንሲ ልውውጥ ኩባንያ 'ኤፍቲኤክስ' መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ ሳም ባንክማን ፍራይድ በባሃማስ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታወቀ። ኩባንያው መክሰሩን በቅርቡ በይፋ አውጆ ወጣቱ ቢሊየነር ከስልጣኑ ለቅቄያለሁ ማለቱ ይታወሳል። ‘የክሪፕቶው ንጉስ’ በባሃማስ በሚገኘው ፍርድ ቤት ማክሰኞ እለት እንደሚቀርብም ባለስልጣናቱ ገልጸዋል። ሳም ባንክማን በቁጥጥር ስር የዋለው የአሜሪካ እና የባሃማስ ህጎችን ተላልፎ “የፋይናንስ ጥፋቶች” በመፈጸሙ መሆኑን ፖሊስ ይፋ አድርጓል። ኤፍቲኤክስ በዓለም ላይ ግዙፍ ከሚባሉ የክሪፕቶ ከረንሲ ግብይት ኩባንያዎች አንዱ የነበረ ሲሆን እንዳልነበር ሆኖም በመንኮታኮቱ ባለፈው ወር ኪሳራ በይፋ መዋጁ ይታወሳል። በርካታ የክሪፕቶ ደንበኞች ዲጂታል ገንዘባቸውን በአንዳች ቁስ ወይም መደበኛ ገንዘብ ለመቀየር ሳይችሉ ቀልጦባቸው ቀርቷል። ኩባንያው ኪሳራ ማወጁን ተከትሎ በሚካሄደው የፍርድ ሂደት ምን ያህሎቹ ገንዛባቸውን እንደሚያገኙ ግልጽ አይደለም። ባለሙያዎች በበኩላቸው ካላቸው ገንዘብ ጥቂት ሊሆን እንደሚችልም አስጠንቅቀዋል። ኤፍቲኤክስ ክሪፕቶን በመሸጥ፣ ዲጂታል ገንዘብን የማለዋወጥ ሥራን የሚሠራ የዲጂታል ግብይት አሳላጭ ኩባንያ ነው። ኤፍቲኤክስ ኪሳራ ከመግጠሙ በፊት ሳም 'የክሪፕቶ ዋረን በፌት' ተብሎ ይወደስ ነበር። በኪሳራ የተንኮታኮተው ኤፍቲኤክስ የክሪፕቶ ግብይት ኩባንያ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ደንበኞች እና 15 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሃብት ነበረው። የ30 ዓመቱ ሳም በዓለም ላይ ሁለተኛውን ግዙፉን የክሪፕቶከረንሲ ልውውጥ ኩባንያን በበላይነት ሲያስተዳድር ነበር። “ዛሬ አመሻሽ ላይ የባሃማስ ለስልጣናት በአሜሪካ መንግሥት ጥያቄ ከደቡብ ኒውዮርክ በታሸገ የክስ መዝገብ መሰረት ሳሙኤል ባንክማን ፍራይድን በቁጥጥር ስር አውለዋል። የክስ መዝገቡን ጥዋት ከፍተን የምናየው ይሆናል በወቅቱም የበለጠ የምንለው ነገር ይኖራል” በማለት በማንሃተን የሚገኘው የአሜሪካ አቃቤ ህግ ፅህፈት ቤት በትዊተር ገፁ አስፍሯል። የዋል ስትሪት ተቆጣጣሪዎችም እንዲሁ በሳሙኤል ላይ እርምጃ እንደሚወስዱ ተናግረዋል። ባንክማን ፍራይድ በያዝነው ሳምንት ማክሰኞ በአሜሪካ ኮንግረስ ኤፍቲኤክስ ስላጋጠመው መንኮታኮት ምስክርነቱን ይሰጣል ተብሎ ነበር። ሆኖም በአሁኑ ወቅት ምስክርነቱን መስጠት እንደማይችል የምክር ቤት አባሏ ማክሲን ዋተርስ አስረድተው በቁጥጥር ስር መዋሉም እንዳስገረማቸው ተናግረዋል። የሳሙኤል ባንክማን ፍሪድ ጠበቃ ቢቢሲ ላቀረባላቸው ጥያቄ ምላሽ አልሰጡም። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cz9yen17mzlo |
0business
| “የሚላስ የሚቀመስ እንኳን አልነበረንም” ብራዚላዊው ኮከብ ሪቻርሊሰን | ብራዚላዊው አጥቂ ሪቻርሊሰን እየተካሄደ ባለው የዓለም ዋንጫ ሰርቢያ ላይ ‘በመቀስ ምት’ ያስቆጠራት ጎል ስያሜ ታጥቶላታል። ብዙዎቹ ዐይናቸው ሌላኛው ብራዚላዊ የእግር ኳስ ማግኔት ኔይማር ላይ ነበር። ነገር ግን በዚህ ጨዋታ የሰዎችን ቀልብ የገዛው የ25 ዓመቱ ሪቻርሊሰን ነው። ሪቻርሊሰን፤ የሰርቢያ ብሔራዊ ቡድንን መረብ ሁለት ጊዜ በመጎብኘት የጨዋታው ኮከብ ሆኖ ተመርጧል። የቶተንሃሙ አጥቂ፣ ብራዚል በኳታሩ የዓለም ዋንጫ የጎል መዝገቧን የከፈተችባቸውን ሁለት ግቦች አስቆጥሯል። ይህ አጥቂ ሜዳ ላይ በሰራው ታሪክ ብቻ ሳይሆን ከሜዳ ውጪ በፈጸመው በጎ ምግባርም ስሙ ሲነሳ ከርሟል። ለመሆኑ ሪቻርሊሰን ማነው? ከሌሎች ብራዚላዊ ከዋክብትስ ምን ይለየዋል? ምንም እንኳ ሪቻርሊሰን ከአብዛኞቹ ብራዚላውያን ጋር የሚያመሳስለው ነገር ቢኖርም፣ እሱን ልዩ የሚያደርጉት ብዙ ነገሮች አሉት። ከአንዲት ትንሽዬ መንደር ኪሳቸው ካልዳበረ ወላጆች የተወለደው ሪቻርሊሰን በ16 ዓመቱ ትምህርት አቋርጦ ኳስ ማዘውተርን መረጠ። ሪቻርሊሰን ከሁሉ ትሻለኛለች ብሎ የመረጣ እግር ኳስ ወላጆቹን፣ ወንድም እና እህቶቹን ትደጉም ጀመር። ወደ እንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ከማምራቱ በፊት ለአትሌቲኮ ሚኔይሮ እና ለፍሉሚኒሴ ተጫውቷል። ወደ እንግሊዝ ከመጣ በኋላ መጀመሪያ ለዋትፈርድ ለጥቆ ደግሞ ብዙ ስምና ዝና ላተረፈረበት ኤቨርተን ተሰልፏል። እየተጠናቀቀ ባለው በዚህ የፈረንጆቹ ዓመት ለለንደኑ ክለብ ቶተንሃም የፈረመው ሪቻርሊሰን፣ ሳይንስና ተፈጥሮ ላይ ያተኮሩ ሥራዎች በመሥራት አልፎም ዘረኝነትን በመፋለም ይታወቃል። ተጫዋቹ በትውልድ አገሩ በሠራው የበጎ አድራጎት ተግባርም በፈረንጆቹ 2020 ከእንግሊዝ ፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ተጫዋቾች ማኅበር ሽልማት ተበርክቶለታል። ብራዚል ውስጥ “እግር ኳስ እና ፖለቲካ አንድ ላይ አይሄዱም” የምትል ከብዙዎች አፍ የማትይጠፋ አባባል አለች። ምንም እንኳ ብራዚላውያን የእግር ኳስ ጥበበኞች ፖለቲካን እንደተላጠ የኤሌክትሪክ ገመድ ቢፈሯትም ኔይማር የብራዚሉ ፕሬዝዳንት ጃይር ቦልሶናሮን በግልጽ ደግፎ ነበር። ሪቻርሊሰንም ሐሳቡን በይፋ ከመግለጽ ያገደው አንዳችም ኃይል አልነበረም። ብራዚል በኮቪድ ወረርሽኝ ትናጥ በነበረበት ወቅት ስለክትባት ጥቅም ለማወጅ የቀደመው አልተገኘም። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ 700 ሺህ ያህል ብራዚላውያንን ቀጥፏል። የቀድሞው የብራዚል ፕሬዝዳንት የኮቪድ ክትባትን ሲነቅፉ በነበረበት ወቅት፣ ሪቻርሊሰን በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ የማኅበራዊ ሚድያ ተከታዮቹ ይህን መልዕክት አስተላልፎ ነበር፡ “እባካችሁ! ከልቤ ልማፀናችሁ። ክትባት መውሰዳችሁን እንዳትዘነጉ. . . ክትባቱ የእናንተ ነው። መብታችሁ ነው። ይህ ዕድል እንዳያመልጣችሁ።” ሪቻርሊሰን፤ የሳኦ ፖሎ ዩኒቨርሲቲ አምባሳደር ከሆነ በኋላ የእግር ኳስ ጫማውን ለጨረታ አቅርቦ ገንዘቡን ለቤተ-ሙከራዎች ለግሷል። የብራዚልን የአካባቢ ሳይንስ ፖለሲ በጽኑ በመንቀፍ የሚታወቀው ሪቻርሊሰን በአገሩ ብራዚል የተነሳው እሣት የአገሪቱ ዋነኛ የብዘሃ ሕይወት መገኛ የሆነውን አካባቢ 30 በመቶውን ሲያወድም ድምፁን አሰምቷል። ይህ ስፍራ ፓንታናል የሚባል ሲሆን፣ በብራዚል የሚገኝ እጅግ ጠቃሚ የሥነ-ምኅዳር አካል ነው። አንድ ቃለ-መጠይቅ ሲያደርግ በእሣት ወደተጎዱት ሥፍራዎች ሄዶ በዐይኑ ያየውን ማመን እንዳቃተው ተናግሯል። ሪቻርሊሰን፤ ሰኔ 2022 ብሪታኒያዊው ጋዜጠኛ ዶም ፊሊፒስ ወደ አማዞን ጫካ ተጉዞ ደብዛው ከጠፋ በኋላ ባለሥልጣናት ፍለጋቸው እንዲያጠናክሩ ጠይቆ ነበር። ባለፈው መስከረም ብራዚል ከቱኒዚያ ጋር ፓሪስ ላይ በነበራት የወዳጅነት ግጥሚያ ላይ ጎል ያስቆጠረው ሪቻርሊሰን ደስታውን ሲገልጽ ሙዝ ይወረወርበታል። ዘረኝነትን ለመግታት “ሥልጣኑ ያላቸው ሰዎች ወሬ ብቻ ከሆኑ፤ ይህ ድርጊት ይቀጥላል” ሲል በትዊተር ገፁ ላይ አስፍሯል። “ዘረኝነት ሁሌም አብሮን የሚኖር ነገር ነው። በቃላት እና በድርጊት ብቻ ሳይሆን በማይታይ መልኩ ይገለጣል” ሲል በፈረንጆቹ 2020 ተናግሮ ነበር።” “ልጅ እያለሁ ከጓደኞቼ ጋር እግር ኳስ ስጫወት አንድ ሰው ምንም ሳላጠፋ ሽፍታ ሲል ሰደበኝ። ይህ ዘረኝነት ነው። ሰዎች ከፊት ለፊታቸው ጥቁር ሰው ሲመጣ አቅጣጫ ከቀየሩ ይህም ዘረኝነት ነው።” “እኒህ የማይታዩ የሚመስሉ ጉዳዮች ዘረኝነት ምን ያህል እንደሰረጸ ያሳያሉ” ሲል ድምፁን አሰምቷል። ሪቻርሊሰን፤ ጆርጅ ፍሎይድ የተሰኘው ጥቁር አሜሪካዊ አንድ ነጭ ፖሊስ አንገቱን በጉልበቱ ረግጦ ከገደለው በኋላ የተቃውሞ ድምፃቸውን ካሰሙ እግር ኳሰኞች መካከል አንዱ ነው። ሪቻርሊሰን፤ ኤስፒሪቶ ሳንቶ ከተባለችው ግዛት ድህነት ከደቆሳቸው ወላጆች ነው የተወለደው። ታዳጊ ሳለ ከረሜላ እና ማስቲካ እየሸጠ ወንድ አያቱ የቡና እርሻቸውን እንዲገፉበት ያግዛቸው ነበር። “አንዳንድ ጊዜ. . .” ይላል ሪቻርሊሰን፤ “የሚላስ የሚቀመስ እንኳን አልነበረንም።” ትምርህርቱን አቋርጦ ወደ እግር ኳስ ያመራበት ዋነኛው ምክንያት ቤተሰቡን ለመደጎምና ጠረጴዛቸው ላይ ምግብ ለማቅረብ ነው። “ይህ የእኔ ታሪክ ብቻ አይደለም። እኔ ባደግኩበት ከተማም ሆነ በሌሎች የብራዚል ከተሞች ያሉ ሕፃናትም ነው” ሲል ተናግሮ እንደነበር ይታወሳል። “ብዙዎች ትምህርታቸውን አቋርጠው ሥራ ፈልገው ቤተሰቦቻቸውን ያግዛሉ። ትምህርት ያቋረጠ ሕፃን ሳይ ልቤ ይሰበራል። ራሴን በእነሱ ውስጥ አየዋለሁ።” ቲክቶክ፣ ትዊተር፣ ኢንስታግራም እና ፌስቡክ በተሰኙት የማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር መድረኮች ላይ 19 ሚሊዮን ተከታዮች ያሉት ሪቻርሊሰን ከእግር ኳስ ሜዳ ውጪ ብዙዎችን ማነቃቃት ይፈልጋል። “የእግር ኳስ ሕይወቴን ከተመለከትኩ በኋላ በጣም ትልቅ ነገር ማድረግ እንደምችል እየገባኝ መጣ” ሲል ለኤቨርተን እየተጫወተ ሳለ ተናግሯል። “ይህ የገንዘብ ጉዳይ አይደለም። መጀመሪያ ለቤተሰቦቼ ቤት ሠርቶ መስጠት ነበር ዓላማዬ። አሁን ግን ከዚህ የተሻለ ብዙ ነገር ማድረግ እንደምችል አመንኩ።” | “የሚላስ የሚቀመስ እንኳን አልነበረንም” ብራዚላዊው ኮከብ ሪቻርሊሰን ብራዚላዊው አጥቂ ሪቻርሊሰን እየተካሄደ ባለው የዓለም ዋንጫ ሰርቢያ ላይ ‘በመቀስ ምት’ ያስቆጠራት ጎል ስያሜ ታጥቶላታል። ብዙዎቹ ዐይናቸው ሌላኛው ብራዚላዊ የእግር ኳስ ማግኔት ኔይማር ላይ ነበር። ነገር ግን በዚህ ጨዋታ የሰዎችን ቀልብ የገዛው የ25 ዓመቱ ሪቻርሊሰን ነው። ሪቻርሊሰን፤ የሰርቢያ ብሔራዊ ቡድንን መረብ ሁለት ጊዜ በመጎብኘት የጨዋታው ኮከብ ሆኖ ተመርጧል። የቶተንሃሙ አጥቂ፣ ብራዚል በኳታሩ የዓለም ዋንጫ የጎል መዝገቧን የከፈተችባቸውን ሁለት ግቦች አስቆጥሯል። ይህ አጥቂ ሜዳ ላይ በሰራው ታሪክ ብቻ ሳይሆን ከሜዳ ውጪ በፈጸመው በጎ ምግባርም ስሙ ሲነሳ ከርሟል። ለመሆኑ ሪቻርሊሰን ማነው? ከሌሎች ብራዚላዊ ከዋክብትስ ምን ይለየዋል? ምንም እንኳ ሪቻርሊሰን ከአብዛኞቹ ብራዚላውያን ጋር የሚያመሳስለው ነገር ቢኖርም፣ እሱን ልዩ የሚያደርጉት ብዙ ነገሮች አሉት። ከአንዲት ትንሽዬ መንደር ኪሳቸው ካልዳበረ ወላጆች የተወለደው ሪቻርሊሰን በ16 ዓመቱ ትምህርት አቋርጦ ኳስ ማዘውተርን መረጠ። ሪቻርሊሰን ከሁሉ ትሻለኛለች ብሎ የመረጣ እግር ኳስ ወላጆቹን፣ ወንድም እና እህቶቹን ትደጉም ጀመር። ወደ እንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ከማምራቱ በፊት ለአትሌቲኮ ሚኔይሮ እና ለፍሉሚኒሴ ተጫውቷል። ወደ እንግሊዝ ከመጣ በኋላ መጀመሪያ ለዋትፈርድ ለጥቆ ደግሞ ብዙ ስምና ዝና ላተረፈረበት ኤቨርተን ተሰልፏል። እየተጠናቀቀ ባለው በዚህ የፈረንጆቹ ዓመት ለለንደኑ ክለብ ቶተንሃም የፈረመው ሪቻርሊሰን፣ ሳይንስና ተፈጥሮ ላይ ያተኮሩ ሥራዎች በመሥራት አልፎም ዘረኝነትን በመፋለም ይታወቃል። ተጫዋቹ በትውልድ አገሩ በሠራው የበጎ አድራጎት ተግባርም በፈረንጆቹ 2020 ከእንግሊዝ ፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ተጫዋቾች ማኅበር ሽልማት ተበርክቶለታል። ብራዚል ውስጥ “እግር ኳስ እና ፖለቲካ አንድ ላይ አይሄዱም” የምትል ከብዙዎች አፍ የማትይጠፋ አባባል አለች። ምንም እንኳ ብራዚላውያን የእግር ኳስ ጥበበኞች ፖለቲካን እንደተላጠ የኤሌክትሪክ ገመድ ቢፈሯትም ኔይማር የብራዚሉ ፕሬዝዳንት ጃይር ቦልሶናሮን በግልጽ ደግፎ ነበር። ሪቻርሊሰንም ሐሳቡን በይፋ ከመግለጽ ያገደው አንዳችም ኃይል አልነበረም። ብራዚል በኮቪድ ወረርሽኝ ትናጥ በነበረበት ወቅት ስለክትባት ጥቅም ለማወጅ የቀደመው አልተገኘም። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ 700 ሺህ ያህል ብራዚላውያንን ቀጥፏል። የቀድሞው የብራዚል ፕሬዝዳንት የኮቪድ ክትባትን ሲነቅፉ በነበረበት ወቅት፣ ሪቻርሊሰን በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ የማኅበራዊ ሚድያ ተከታዮቹ ይህን መልዕክት አስተላልፎ ነበር፡ “እባካችሁ! ከልቤ ልማፀናችሁ። ክትባት መውሰዳችሁን እንዳትዘነጉ. . . ክትባቱ የእናንተ ነው። መብታችሁ ነው። ይህ ዕድል እንዳያመልጣችሁ።” ሪቻርሊሰን፤ የሳኦ ፖሎ ዩኒቨርሲቲ አምባሳደር ከሆነ በኋላ የእግር ኳስ ጫማውን ለጨረታ አቅርቦ ገንዘቡን ለቤተ-ሙከራዎች ለግሷል። የብራዚልን የአካባቢ ሳይንስ ፖለሲ በጽኑ በመንቀፍ የሚታወቀው ሪቻርሊሰን በአገሩ ብራዚል የተነሳው እሣት የአገሪቱ ዋነኛ የብዘሃ ሕይወት መገኛ የሆነውን አካባቢ 30 በመቶውን ሲያወድም ድምፁን አሰምቷል። ይህ ስፍራ ፓንታናል የሚባል ሲሆን፣ በብራዚል የሚገኝ እጅግ ጠቃሚ የሥነ-ምኅዳር አካል ነው። አንድ ቃለ-መጠይቅ ሲያደርግ በእሣት ወደተጎዱት ሥፍራዎች ሄዶ በዐይኑ ያየውን ማመን እንዳቃተው ተናግሯል። ሪቻርሊሰን፤ ሰኔ 2022 ብሪታኒያዊው ጋዜጠኛ ዶም ፊሊፒስ ወደ አማዞን ጫካ ተጉዞ ደብዛው ከጠፋ በኋላ ባለሥልጣናት ፍለጋቸው እንዲያጠናክሩ ጠይቆ ነበር። ባለፈው መስከረም ብራዚል ከቱኒዚያ ጋር ፓሪስ ላይ በነበራት የወዳጅነት ግጥሚያ ላይ ጎል ያስቆጠረው ሪቻርሊሰን ደስታውን ሲገልጽ ሙዝ ይወረወርበታል። ዘረኝነትን ለመግታት “ሥልጣኑ ያላቸው ሰዎች ወሬ ብቻ ከሆኑ፤ ይህ ድርጊት ይቀጥላል” ሲል በትዊተር ገፁ ላይ አስፍሯል። “ዘረኝነት ሁሌም አብሮን የሚኖር ነገር ነው። በቃላት እና በድርጊት ብቻ ሳይሆን በማይታይ መልኩ ይገለጣል” ሲል በፈረንጆቹ 2020 ተናግሮ ነበር።” “ልጅ እያለሁ ከጓደኞቼ ጋር እግር ኳስ ስጫወት አንድ ሰው ምንም ሳላጠፋ ሽፍታ ሲል ሰደበኝ። ይህ ዘረኝነት ነው። ሰዎች ከፊት ለፊታቸው ጥቁር ሰው ሲመጣ አቅጣጫ ከቀየሩ ይህም ዘረኝነት ነው።” “እኒህ የማይታዩ የሚመስሉ ጉዳዮች ዘረኝነት ምን ያህል እንደሰረጸ ያሳያሉ” ሲል ድምፁን አሰምቷል። ሪቻርሊሰን፤ ጆርጅ ፍሎይድ የተሰኘው ጥቁር አሜሪካዊ አንድ ነጭ ፖሊስ አንገቱን በጉልበቱ ረግጦ ከገደለው በኋላ የተቃውሞ ድምፃቸውን ካሰሙ እግር ኳሰኞች መካከል አንዱ ነው። ሪቻርሊሰን፤ ኤስፒሪቶ ሳንቶ ከተባለችው ግዛት ድህነት ከደቆሳቸው ወላጆች ነው የተወለደው። ታዳጊ ሳለ ከረሜላ እና ማስቲካ እየሸጠ ወንድ አያቱ የቡና እርሻቸውን እንዲገፉበት ያግዛቸው ነበር። “አንዳንድ ጊዜ. . .” ይላል ሪቻርሊሰን፤ “የሚላስ የሚቀመስ እንኳን አልነበረንም።” ትምርህርቱን አቋርጦ ወደ እግር ኳስ ያመራበት ዋነኛው ምክንያት ቤተሰቡን ለመደጎምና ጠረጴዛቸው ላይ ምግብ ለማቅረብ ነው። “ይህ የእኔ ታሪክ ብቻ አይደለም። እኔ ባደግኩበት ከተማም ሆነ በሌሎች የብራዚል ከተሞች ያሉ ሕፃናትም ነው” ሲል ተናግሮ እንደነበር ይታወሳል። “ብዙዎች ትምህርታቸውን አቋርጠው ሥራ ፈልገው ቤተሰቦቻቸውን ያግዛሉ። ትምህርት ያቋረጠ ሕፃን ሳይ ልቤ ይሰበራል። ራሴን በእነሱ ውስጥ አየዋለሁ።” ቲክቶክ፣ ትዊተር፣ ኢንስታግራም እና ፌስቡክ በተሰኙት የማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር መድረኮች ላይ 19 ሚሊዮን ተከታዮች ያሉት ሪቻርሊሰን ከእግር ኳስ ሜዳ ውጪ ብዙዎችን ማነቃቃት ይፈልጋል። “የእግር ኳስ ሕይወቴን ከተመለከትኩ በኋላ በጣም ትልቅ ነገር ማድረግ እንደምችል እየገባኝ መጣ” ሲል ለኤቨርተን እየተጫወተ ሳለ ተናግሯል። “ይህ የገንዘብ ጉዳይ አይደለም። መጀመሪያ ለቤተሰቦቼ ቤት ሠርቶ መስጠት ነበር ዓላማዬ። አሁን ግን ከዚህ የተሻለ ብዙ ነገር ማድረግ እንደምችል አመንኩ።” | https://www.bbc.com/amharic/articles/c4nrv477vg4o |
2health
| በዲሞክራቲክ ኮንጎ አንዲት ሴት በኢቦላ በሽታ ሕይወቷ አለፈ | በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ በኢቦላ በሽታ የሰው ሕይወት ማለፉን የአገሪቱ ጤና ሚንስቴር አስታወቀ። በአገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ቡቴምቦ በምትሰኝ ከተማ ነዋሪ የነበረች ሴት በኢቦላ በሽታ ከተያዘች በኋላ ሕይወቷ ማለፉ ተገልጿል። ቡቴምቦ ከዚህ ከቀደም የኢቦላ በሽታ ተቀስቅሶ በርካቶች ሕይወታቸውን ያጡባት ከተማ ነች። በኢቦላ በሽታ ሕይወቷ ያለፈው ይህች ሴት ከዚህ ቀደም በበሽታው ተይዞ ያገገመ ሰው ባለቤት ነች ተብሏል። የዓለም ጤና ድርጅት በበሽታው ሕይወቷን ካጣችው ሴት ላይ የተወሰደው ናሙና በኢቦላ በሽታ መያዟን አረጋግጧል ብሏል። የኢቦላ በሽታ ምልክትም ይታይባት ነበር ተብሏል። የአገሪቱ ጤና ሚንስቴር የበሽታውን ስርጭት ለመቆጣጠር የጤና ባለሙያዎች ቡድን ወደ ሥፍራው መላኩን አስታውቋል። የዓለም ጤና ድርጅትም ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ይሁን እንጂ በአከባቢው ያለው የደህንነት ስጋት የበሽታ መቆጣጠሩ ሥራ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እያሳደረ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ ለ10ኛ ጊዜ ተቀስቅስቅሶ የነበረው እና ለሁለት ዓመታት በዘለቀው የኢቦላ ወረርሽኝ 3481 ሰዎች በበሽታው ተይዘው 2299 ሰዎች ሞተዋል። በአገሪቱ የኢቦላ በሽታ ሲመዘገብ ይህ ለ12ኛ ጊዜ ነው። ከዚህ ቀደም በበሽታው የተያዘ ሰው የተገኘው ከወራት በፊት በምዕራባዊ የአገሪቱ ክፍል ነበር። ኢቦላ ቫይረስ ሲሆን ድንገተኛ እና አደገኛ የሆነ ትኩሳት፣ ድካም፣ የጡንቻ እና የጉሮሮ ሕመም ያስከትላል። በሽታው እየጠና ሲሄድ ትውከት፣ ተቅማጥ ይጀምራል። ባስ ሲል ውስጥ እና ወደ ውጪ መድማትን ያስከትላል። በበሽታው የሚያዙ ሰዎች በድርቀት እና የሰውነት አካላት መስራት ማቆም ምክንያት ሕይወታቸው ያልፋል። የዓለም ጤና ድርጅት በኢቦላ የሚያዝ ሰው በበሽታው የመሞቱ እድል 50 በመቶ ነው ይላል። አንድ ሰው በኢቦላ በሽታ ሊያዝ የሚችለው በኢቦላ በሽታ የተያዘ ሰው ደም፣ ትውከት፣ ሰገራ እና ፈሳሽ ወደ አፍና አፍንጫ አልያም ቁስለት ያለበት ቆዳ ላይ ካረፈ ነው። | በዲሞክራቲክ ኮንጎ አንዲት ሴት በኢቦላ በሽታ ሕይወቷ አለፈ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ በኢቦላ በሽታ የሰው ሕይወት ማለፉን የአገሪቱ ጤና ሚንስቴር አስታወቀ። በአገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ቡቴምቦ በምትሰኝ ከተማ ነዋሪ የነበረች ሴት በኢቦላ በሽታ ከተያዘች በኋላ ሕይወቷ ማለፉ ተገልጿል። ቡቴምቦ ከዚህ ከቀደም የኢቦላ በሽታ ተቀስቅሶ በርካቶች ሕይወታቸውን ያጡባት ከተማ ነች። በኢቦላ በሽታ ሕይወቷ ያለፈው ይህች ሴት ከዚህ ቀደም በበሽታው ተይዞ ያገገመ ሰው ባለቤት ነች ተብሏል። የዓለም ጤና ድርጅት በበሽታው ሕይወቷን ካጣችው ሴት ላይ የተወሰደው ናሙና በኢቦላ በሽታ መያዟን አረጋግጧል ብሏል። የኢቦላ በሽታ ምልክትም ይታይባት ነበር ተብሏል። የአገሪቱ ጤና ሚንስቴር የበሽታውን ስርጭት ለመቆጣጠር የጤና ባለሙያዎች ቡድን ወደ ሥፍራው መላኩን አስታውቋል። የዓለም ጤና ድርጅትም ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ይሁን እንጂ በአከባቢው ያለው የደህንነት ስጋት የበሽታ መቆጣጠሩ ሥራ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እያሳደረ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ ለ10ኛ ጊዜ ተቀስቅስቅሶ የነበረው እና ለሁለት ዓመታት በዘለቀው የኢቦላ ወረርሽኝ 3481 ሰዎች በበሽታው ተይዘው 2299 ሰዎች ሞተዋል። በአገሪቱ የኢቦላ በሽታ ሲመዘገብ ይህ ለ12ኛ ጊዜ ነው። ከዚህ ቀደም በበሽታው የተያዘ ሰው የተገኘው ከወራት በፊት በምዕራባዊ የአገሪቱ ክፍል ነበር። ኢቦላ ቫይረስ ሲሆን ድንገተኛ እና አደገኛ የሆነ ትኩሳት፣ ድካም፣ የጡንቻ እና የጉሮሮ ሕመም ያስከትላል። በሽታው እየጠና ሲሄድ ትውከት፣ ተቅማጥ ይጀምራል። ባስ ሲል ውስጥ እና ወደ ውጪ መድማትን ያስከትላል። በበሽታው የሚያዙ ሰዎች በድርቀት እና የሰውነት አካላት መስራት ማቆም ምክንያት ሕይወታቸው ያልፋል። የዓለም ጤና ድርጅት በኢቦላ የሚያዝ ሰው በበሽታው የመሞቱ እድል 50 በመቶ ነው ይላል። አንድ ሰው በኢቦላ በሽታ ሊያዝ የሚችለው በኢቦላ በሽታ የተያዘ ሰው ደም፣ ትውከት፣ ሰገራ እና ፈሳሽ ወደ አፍና አፍንጫ አልያም ቁስለት ያለበት ቆዳ ላይ ካረፈ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/55976626 |
0business
| 45 ሺህ ሹፌሮች ያሉት ኡበር የሎንዶን የሥራ ፍቃዱን ተነጠቀ | ኡበር የተሰኘው የታክሲ አገልግሎት ሰጭ ድርጅት በእንግሊዝ ከተማ ሎንዶን እንዲሠራ የተሰጠው ፈቃድ ተነጠቀ። 'ትራንስፖርት ፎር ሎንዶን' የተሰኘው የታክሲ አገልግሎት ኩባንያዎች ፈቃድ ሰጭ መሥሪያ ቤት ኡበር ሎንዶን ውስጥ ለመሥራት አቅምና አግባብነት የለውም ሲሉ ነው ፈቃዱን የነጠቁት። ኡበር፤ በግሪጎሪ አቆጣጠር 2017 ላይ በተመሳሳይ የሎንዶን የሥራ ፈቃዱን ተነጥቆ ነበር። ምክንያቱ ደግሞ የተጠቃሚዎች ደህንነት ነው። በጊዜው ይግባኝ የጠየቀው ኡበር የ15 ወራት ፈቃድ ተሰጥቶታል። ይህ ፈቃድ በ21 ቀናት ውስጥ የሚጠናቀቀው ኡበር የሥራ ፈቃዱ ድጋሚ እንደማይታደስ ያሳወቁት የትራንስፖርት ፎር ሎንዶን የሥራ ፈቃድ ሰጭ ሊቀመንበር ሄለን ቻፕማን ናቸው። «ደህንነት ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው። ምንም እንኳ ኡበር በጎ ለውጦችን ቢያመጣም ማንነታቸው የማይታወቅ ሰዎች ሹፌር ሆነው እንዲቀጠሩ መፍቀዱ አግባብ አይደለም» ሲሉ ኃላፊዋ ፈቃድ የነሱበትን ምክንያት ያስረዳሉ። ኡበር ይግባኝ እንደሚጠይቅ ይጠበቃል። 45 ሺህ ገደማ አሽከርካሪዎች ለኡበር ይሠራሉ። የኡበር የሥራ ፈቃድ ለዘለቄታው የሚሠረዝ ከሆነ እኒህ ሹፌሮች ከሥራ ውጭ ይሆናሉ የሚል ስጋት አለ። ነገር ግን ከዓለም አቀፍ ኡበር ጋር የተመሳሰለ ሥራ የሚሠሩ በርካታ ድርጅቶች በሎንዶን መኖራቸው ይታወቃል። 'ትራንስፖርት ፎር ሎንዶን' ለድርጅቶች ብዙ ጊዜ የአምስት ዓመት ፈቃድ በመስጠት ይታወቃል። ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፈቃድ መስጠት ላይ ቆጠብ ያለ ይመስላል። ድርጅቱ 'የተጠቃሚዎች ደህንነት' አደጋ ላይ ሊወድቅ እንዳይችል ነው ፈቃድ የነሳሁት ይላል። ውሳኔው ከሎንዶን ከንቲባ ሳዲቅ ካህን ድጋፍ አግኝቷል። ኡበር ሎንዶን ውሰስጥ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ከተሞችም ተቃውሞ ይገጥመዋል። ብዙ ቦታዎች ተቃውሞ የሞመጣው በባሕላዊ መንገድ የታክሲ ግልጋሎት ከሚሰጡ ሰዎች ነው። | 45 ሺህ ሹፌሮች ያሉት ኡበር የሎንዶን የሥራ ፍቃዱን ተነጠቀ ኡበር የተሰኘው የታክሲ አገልግሎት ሰጭ ድርጅት በእንግሊዝ ከተማ ሎንዶን እንዲሠራ የተሰጠው ፈቃድ ተነጠቀ። 'ትራንስፖርት ፎር ሎንዶን' የተሰኘው የታክሲ አገልግሎት ኩባንያዎች ፈቃድ ሰጭ መሥሪያ ቤት ኡበር ሎንዶን ውስጥ ለመሥራት አቅምና አግባብነት የለውም ሲሉ ነው ፈቃዱን የነጠቁት። ኡበር፤ በግሪጎሪ አቆጣጠር 2017 ላይ በተመሳሳይ የሎንዶን የሥራ ፈቃዱን ተነጥቆ ነበር። ምክንያቱ ደግሞ የተጠቃሚዎች ደህንነት ነው። በጊዜው ይግባኝ የጠየቀው ኡበር የ15 ወራት ፈቃድ ተሰጥቶታል። ይህ ፈቃድ በ21 ቀናት ውስጥ የሚጠናቀቀው ኡበር የሥራ ፈቃዱ ድጋሚ እንደማይታደስ ያሳወቁት የትራንስፖርት ፎር ሎንዶን የሥራ ፈቃድ ሰጭ ሊቀመንበር ሄለን ቻፕማን ናቸው። «ደህንነት ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው። ምንም እንኳ ኡበር በጎ ለውጦችን ቢያመጣም ማንነታቸው የማይታወቅ ሰዎች ሹፌር ሆነው እንዲቀጠሩ መፍቀዱ አግባብ አይደለም» ሲሉ ኃላፊዋ ፈቃድ የነሱበትን ምክንያት ያስረዳሉ። ኡበር ይግባኝ እንደሚጠይቅ ይጠበቃል። 45 ሺህ ገደማ አሽከርካሪዎች ለኡበር ይሠራሉ። የኡበር የሥራ ፈቃድ ለዘለቄታው የሚሠረዝ ከሆነ እኒህ ሹፌሮች ከሥራ ውጭ ይሆናሉ የሚል ስጋት አለ። ነገር ግን ከዓለም አቀፍ ኡበር ጋር የተመሳሰለ ሥራ የሚሠሩ በርካታ ድርጅቶች በሎንዶን መኖራቸው ይታወቃል። 'ትራንስፖርት ፎር ሎንዶን' ለድርጅቶች ብዙ ጊዜ የአምስት ዓመት ፈቃድ በመስጠት ይታወቃል። ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፈቃድ መስጠት ላይ ቆጠብ ያለ ይመስላል። ድርጅቱ 'የተጠቃሚዎች ደህንነት' አደጋ ላይ ሊወድቅ እንዳይችል ነው ፈቃድ የነሳሁት ይላል። ውሳኔው ከሎንዶን ከንቲባ ሳዲቅ ካህን ድጋፍ አግኝቷል። ኡበር ሎንዶን ውሰስጥ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ከተሞችም ተቃውሞ ይገጥመዋል። ብዙ ቦታዎች ተቃውሞ የሞመጣው በባሕላዊ መንገድ የታክሲ ግልጋሎት ከሚሰጡ ሰዎች ነው። | https://www.bbc.com/amharic/news-50545277 |
5sports
| የእግር ኳስ ኮከቡ ቦአቲንግ ፍቅረኛው ላይ ጥቃት በመፈጸም ጥፋተኛ ተባለ | ጀርመንናዊው የእግር ኳስ ኮከብ ዤሮም ቦአቲንግ የቀድሞ ፍቅርኛው ላይ ጥቃት በመፈጸም ጥፋተኛ ተባለ። የቀድሞ ፍቅረኛውን በማጥቃት ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘው ጀርመናዊው እግር ኳስ ተጫዋች ዤሮም ቦአቲንግ 1.8 ሚሊዮን ዩሮ ቅጣት እንዲከፍል ተበይኖበታል። ተጫዋቹ እአአ በ2018 በተፈጠረ አለመግባባት መንትያ ሴት ልጆቹን እናት ሼሪን ኤስን መጎዳቱን አስተባብሏል። የቀድሞው የባየርን ሙኒክ ተከላካይ እና የ2014 የዓለም ዋንጫ አሸናፊው ከሳሽ ለፍርድ ቤቱ በቡጢ በከፍተኛ ሁኔታ እንደመታት እና ለአፍታ እስትንፋሷን አጥታ እንደነበር ተናግራለች። በምስክርነቱ ወቅት ቦአቲንግ የተለየን የክስተቶች ሂደት ገልጿል። በጀርመን የቤት ውስጥ ጥቃት ሕጎች መሠረት እስከ አምስት ዓመት ድረስ በእስር ሊቆይ ይችል ነበር። ቦአቲንግ ጥቁር ሰማያዊ ሙሉ ልብስ ለብሶ በግል ጠባቂዎቹ እና በጠበቃው ካይ ዋልደን ተከቦ ነበር ፍርድ ቤት የደረሰው። ከችሎቱ በፊት ዐቃቤ-ሕግ በቦአቲንግ በሐምሌ 2018 በካሪቢያን ደሴት እረፍት ላይ በነበሩበት ወቅት በቀድሞው ፍቅረኛውአነስተኛ የማቀዝቀዣ ሣጥን በመወርወር ሆን ብሎ አካላዊ ጉዳት አድርሷል ብሏል። የቀድሞ ፍቅረኛው በፍርድ ቤት ምስክርነቷን ስትሰጥ በግጭቱ ወቅት ቦአቲንግ በቡጢ እንደመታት፣ ፀጉሯን መጎተቱን፣ ጭንቅላቷን መንከሱን እና እሷ እንደሰደበችው ተናግራለች። ቦአቲንግ በሰጠው ቃል በካርድ ጨዋታ ወቅት ውጥረቱ መባባሱን አምኗል። ጠበኛ መሆኗን እና እንደሰደበችው፣ እንደመታችው እና ከንፈሩን እንደጎዳችው ተናግሯል። ከላዩ ላይ ሲገፈትራትም መውደቋን ተናግሯል። ችሎቱ በታህሳስ ወር ሊካሄድ የነበረ ቢሆንም ምስክር ሊቀርብ ባለመቻሉ ለሌላ ጊዜ ተላልፏል። በእግር ኳስ ዓለም እና በማህበራዊ ሚዲያ ታዋቂ የሆነው ቦአቲንግ በክለብ እና በሀገር ደረጃ የተለያዩ ሽልማቶችን አንስቷል። ሁለት የሻምፒዮንስ ሊግና ዘጠኝ የቡንደስሊጋን ዋንጫን ጨምሮ ከሙኒክ ጋር 22 ዋንጫዎችን አንስቷል። በሙኒክ የነበረው ኮንትራት መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ ፈረንሳዩ ሊዮን በነጻ ዝውውር ተዛውሯል። ሌላኛዋ የቦአቲንግ የቀድሞ ፍቅረኛ የ25 ዓመቷ ሞዴል ካሲያ ሌንሃርትት በየካቲት ወር በርሊን ውስጥ በሚገኝ አንድ አፓርታማ የራሷን ሕይወት አጥፍታለች። | የእግር ኳስ ኮከቡ ቦአቲንግ ፍቅረኛው ላይ ጥቃት በመፈጸም ጥፋተኛ ተባለ ጀርመንናዊው የእግር ኳስ ኮከብ ዤሮም ቦአቲንግ የቀድሞ ፍቅርኛው ላይ ጥቃት በመፈጸም ጥፋተኛ ተባለ። የቀድሞ ፍቅረኛውን በማጥቃት ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘው ጀርመናዊው እግር ኳስ ተጫዋች ዤሮም ቦአቲንግ 1.8 ሚሊዮን ዩሮ ቅጣት እንዲከፍል ተበይኖበታል። ተጫዋቹ እአአ በ2018 በተፈጠረ አለመግባባት መንትያ ሴት ልጆቹን እናት ሼሪን ኤስን መጎዳቱን አስተባብሏል። የቀድሞው የባየርን ሙኒክ ተከላካይ እና የ2014 የዓለም ዋንጫ አሸናፊው ከሳሽ ለፍርድ ቤቱ በቡጢ በከፍተኛ ሁኔታ እንደመታት እና ለአፍታ እስትንፋሷን አጥታ እንደነበር ተናግራለች። በምስክርነቱ ወቅት ቦአቲንግ የተለየን የክስተቶች ሂደት ገልጿል። በጀርመን የቤት ውስጥ ጥቃት ሕጎች መሠረት እስከ አምስት ዓመት ድረስ በእስር ሊቆይ ይችል ነበር። ቦአቲንግ ጥቁር ሰማያዊ ሙሉ ልብስ ለብሶ በግል ጠባቂዎቹ እና በጠበቃው ካይ ዋልደን ተከቦ ነበር ፍርድ ቤት የደረሰው። ከችሎቱ በፊት ዐቃቤ-ሕግ በቦአቲንግ በሐምሌ 2018 በካሪቢያን ደሴት እረፍት ላይ በነበሩበት ወቅት በቀድሞው ፍቅረኛውአነስተኛ የማቀዝቀዣ ሣጥን በመወርወር ሆን ብሎ አካላዊ ጉዳት አድርሷል ብሏል። የቀድሞ ፍቅረኛው በፍርድ ቤት ምስክርነቷን ስትሰጥ በግጭቱ ወቅት ቦአቲንግ በቡጢ እንደመታት፣ ፀጉሯን መጎተቱን፣ ጭንቅላቷን መንከሱን እና እሷ እንደሰደበችው ተናግራለች። ቦአቲንግ በሰጠው ቃል በካርድ ጨዋታ ወቅት ውጥረቱ መባባሱን አምኗል። ጠበኛ መሆኗን እና እንደሰደበችው፣ እንደመታችው እና ከንፈሩን እንደጎዳችው ተናግሯል። ከላዩ ላይ ሲገፈትራትም መውደቋን ተናግሯል። ችሎቱ በታህሳስ ወር ሊካሄድ የነበረ ቢሆንም ምስክር ሊቀርብ ባለመቻሉ ለሌላ ጊዜ ተላልፏል። በእግር ኳስ ዓለም እና በማህበራዊ ሚዲያ ታዋቂ የሆነው ቦአቲንግ በክለብ እና በሀገር ደረጃ የተለያዩ ሽልማቶችን አንስቷል። ሁለት የሻምፒዮንስ ሊግና ዘጠኝ የቡንደስሊጋን ዋንጫን ጨምሮ ከሙኒክ ጋር 22 ዋንጫዎችን አንስቷል። በሙኒክ የነበረው ኮንትራት መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ ፈረንሳዩ ሊዮን በነጻ ዝውውር ተዛውሯል። ሌላኛዋ የቦአቲንግ የቀድሞ ፍቅረኛ የ25 ዓመቷ ሞዴል ካሲያ ሌንሃርትት በየካቲት ወር በርሊን ውስጥ በሚገኝ አንድ አፓርታማ የራሷን ሕይወት አጥፍታለች። | https://www.bbc.com/amharic/58507469 |
0business
| የዚምባብዌ አልማዝ ማዕድን ቁፋሮ በጉልበት ብዝበዛ ይሆን የሚካሄደው? | የአሜሪካ መንግሥት ከዚምባብዌ የሚመጣውን ያልተጣሩ የአልማዝ ምርቶችን በማዕድን ቁፋሮው ወቅት የጉልበት ብዝበዛን ይጠቀማሉ በሚል አግጃለሁ ብሏል። ዚምባብዌ ጉዳዩን ተራ ውንጀላ ነው በማለት አጣጥለዋለች። የመረጃ ሴክሬታሪው ኒክ ማንግዋና እንደሚሉት አሜሪካ ምንም ዓይነት መረጃ የላትም "መረጃ የላቸውም፤ ወይም ያሳሳታቸው አካል አለ" ብለዋል። • "የተርባይኖች መቀነስ በሚመነጨው ኃይል ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም" የህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ •የቀድሞው ፕሬዝደንት ልጅ በጉልበት ብዝበዛ ወንጀል ተፈረደባቸው የማዕድን ቁፋሮው በምስራቃዊቷ አገሪቷ ክፍል ማራንጅ ግዛት አካባቢ የሚካሄድ ሲሆን፤ በዓለም ላይ ካሉ ከፍተኛ የአልማዝ ምርት የሚገኝበት ሲሆን በኢኮኖሚ ቀውስ ለምትንገዳገደው ዚምባብዌም የውጭ ምንዛሬን በማስገኘት አገሪቷን የሚያንቀሳቅሳት ነው። የአሜሪካ ውንጀላ ምንድን ነው? የአሜሪካ ከተሞች የሥራ ልምዶችን የሚፈትሸው ድርጅት እንዳሳወቀው በማዕድን ቁፋሮ ሥራ ለመሰማራትና በተከለለው ቦታ ላይ ፍቃድ ለማግኘት ለፀጥታ ኃይሎች ጉቦ መክፈል ነበረባቸው። የአሜሪካ ጉምሩክና ድንበር ኤጀንሲ ተወካይ ብሬንዳ ስሚዝ እንደተናገሩት ሠራተኞች ያለ ፈቃድ የማዕድን ቁፋሮ አካባቢውን ለቀው መሄድ እንደማይችሉና፤ እምቢተኝነትን ያሳዩት ደግሞ አካላዊና ወሲባዊ ቅጣቶች እንዲሁም ለእስር ይዳረጋሉ ተብሏል። የአሜሪካ መንግሥት እንዳሳወቀው እንዲህ ዓይነት ጥቃቶችን በመረጃ አጠናቅረን ይዘናል ብለዋል። •ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ረቂቅ ህግ የሞት ቅጣት ተካቶበታል •"ሰልፍ የዜጎች መሰረታዊ መብት ነው" መስፍን ነጋሽ መረጃው ምንድን ነው? ጋዜጠኞችም ሆነ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ቡድን አካባቢውን እንዲጎበኙ የማይፈቀድላቸው ሲሆን፤ አካባቢውን ለማየትም ልዩ የሆነ ፍቃድ ያስፈልጋል። በማራንጌ የአልማዝ ቁፋሮ ቦታ ላይ የሥራ ሁኔታዎችን የሚቆጣጠረው ቡድን እንዳሳወቀው የጉልበት ብዝበዛ በተለይም የግዳጅ ሥራ እንደሚከናወን አሳውቋል። የቦቻ ዳይመንድ ትረስት ኩባንያ ሊቀመንበር ሞሰስ ሙክዋዳ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ የአካባቢው ሰዎች ተገደው በማዕድን ቁፋሮው ሥራ እንደተሰማሩ አጋልጠዋል። አንዳንድ ኩባንያዎች የግዳጅ ሥራ አለ ለማለት አልደፈሩም። ለማዕድን ቁፋሮ ሰራተኞች መብት የሚታገለው ዘ ሴንተር ፎር ናቹራል ሪሶርስስ ገቨርናንስ የተባለው ድርጅት ከአስራ ስምንት ዓመት በታች ያሉ ታዳጊዎች አካላዊ ጥቃት እንደደረሰባቸው ቢገልፅም ሰራተኞች በግዳጅ ተሰማርተዋል ከሚለው አስተያየት ተቆጥቧል። "ሰራተኞች በግዳጅ ተሰማርተዋል የሚለውን ሃሳብ ሙሉ በሙሉ አናጣጥለውም፤ ከአሜሪካ መንግሥትም ሆነ ከየትኛውም አካል በግዳጅ የተሰማሩ ሰራተኞች እንዳሉ መረጃ አልደረሰንም። ማን ማንን እያስገደደ ነው የሚለውንም የበለጠ ማወቅ እንፈልጋለን" በማለት የድርጅቱ ቃል አቀባይ ሲሚሶ ምሌቩ ተናግረዋል። በማራንጄ የማዕድን ቁፋሮ ቦታ ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ውንጀላዎች ሲቀርቡ የመጀመሪያው አይደለም። የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በተደጋጋሚ እንዳሳወቁት ከአካባቢው የሚመጣው አልማዝ "ከግጭት አካባቢ የተገኘ አልማዝ" ስለሆነ ወደ ውጭ የሚላከው የአልማዝ መጠን ሊገደብ ይገባል በሚል አሳውቀው ነበር። በጎርጎሳውያኑ 2011 ቢቢሲ ባደረገው ምርመራ በአካባቢው የከፋ ድብደባና ወሲባዊ ጥቃት እንደሚደርስም መረጃ ሰብስቧል። "በማራንጌም ሆነ ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ የአልማዝ ምርቶች በከፍተኛ ሁኔታ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ቢያጠላባቸውም ወደ አለም አቀፉ ገበያ መድረሳቸው አልቀረም" በማለት ዘ ሴንተር ፎር ናቹራል ሪሶርስስ ገቨርናንስ አስታውቋል። ሰራተኞች ላይ በሚደርሱ ጥቃቶች እንዲሁም ባለው የከፋ ሁኔታ አርባ ሰዎች በየአመቱ ይሞታሉ ተብሏል። •ቤይሩት፡ ባለፉት 7 ወራት 34 ኢትዮጵያዊያን ህይወታቸውን አጥተዋል •ጃፓን ያለ መሬትና ያለ አርሶ አደሮች የፈጠረችው የግብርና አብዮት የሰራተኞች መብት በዚምባብዌ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ነኝ የሚለው ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዋች ባለፈው ዓመት ባወጣው ሪፖርት በሃገሪቷ በሚገኙ የትምባሆ እርሻዎችም የግዳጅ ሥራ እንደተንሰራፋ ይፋ አድርጓል። የአሜሪካ መንግሥትም እንዲሁ ባለፈው አመት የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ እንደሚከናወን አንድ መረጃ አውጥቶ ነበር። ዚምባብዌ በበኩሏ የተባበሩት መንግሥታት የጉልበት ብዝበዛን ለማስቀረት ያፀደቃቸውን ሕጎች በዚህ ዓመት እንደተቀበለችና የግዳጅ ሥራ ልምድንም ለማስቀረት እየሞከሩ እንደሆነ ገልፃለች። | የዚምባብዌ አልማዝ ማዕድን ቁፋሮ በጉልበት ብዝበዛ ይሆን የሚካሄደው? የአሜሪካ መንግሥት ከዚምባብዌ የሚመጣውን ያልተጣሩ የአልማዝ ምርቶችን በማዕድን ቁፋሮው ወቅት የጉልበት ብዝበዛን ይጠቀማሉ በሚል አግጃለሁ ብሏል። ዚምባብዌ ጉዳዩን ተራ ውንጀላ ነው በማለት አጣጥለዋለች። የመረጃ ሴክሬታሪው ኒክ ማንግዋና እንደሚሉት አሜሪካ ምንም ዓይነት መረጃ የላትም "መረጃ የላቸውም፤ ወይም ያሳሳታቸው አካል አለ" ብለዋል። • "የተርባይኖች መቀነስ በሚመነጨው ኃይል ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም" የህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ •የቀድሞው ፕሬዝደንት ልጅ በጉልበት ብዝበዛ ወንጀል ተፈረደባቸው የማዕድን ቁፋሮው በምስራቃዊቷ አገሪቷ ክፍል ማራንጅ ግዛት አካባቢ የሚካሄድ ሲሆን፤ በዓለም ላይ ካሉ ከፍተኛ የአልማዝ ምርት የሚገኝበት ሲሆን በኢኮኖሚ ቀውስ ለምትንገዳገደው ዚምባብዌም የውጭ ምንዛሬን በማስገኘት አገሪቷን የሚያንቀሳቅሳት ነው። የአሜሪካ ውንጀላ ምንድን ነው? የአሜሪካ ከተሞች የሥራ ልምዶችን የሚፈትሸው ድርጅት እንዳሳወቀው በማዕድን ቁፋሮ ሥራ ለመሰማራትና በተከለለው ቦታ ላይ ፍቃድ ለማግኘት ለፀጥታ ኃይሎች ጉቦ መክፈል ነበረባቸው። የአሜሪካ ጉምሩክና ድንበር ኤጀንሲ ተወካይ ብሬንዳ ስሚዝ እንደተናገሩት ሠራተኞች ያለ ፈቃድ የማዕድን ቁፋሮ አካባቢውን ለቀው መሄድ እንደማይችሉና፤ እምቢተኝነትን ያሳዩት ደግሞ አካላዊና ወሲባዊ ቅጣቶች እንዲሁም ለእስር ይዳረጋሉ ተብሏል። የአሜሪካ መንግሥት እንዳሳወቀው እንዲህ ዓይነት ጥቃቶችን በመረጃ አጠናቅረን ይዘናል ብለዋል። •ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ረቂቅ ህግ የሞት ቅጣት ተካቶበታል •"ሰልፍ የዜጎች መሰረታዊ መብት ነው" መስፍን ነጋሽ መረጃው ምንድን ነው? ጋዜጠኞችም ሆነ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ቡድን አካባቢውን እንዲጎበኙ የማይፈቀድላቸው ሲሆን፤ አካባቢውን ለማየትም ልዩ የሆነ ፍቃድ ያስፈልጋል። በማራንጌ የአልማዝ ቁፋሮ ቦታ ላይ የሥራ ሁኔታዎችን የሚቆጣጠረው ቡድን እንዳሳወቀው የጉልበት ብዝበዛ በተለይም የግዳጅ ሥራ እንደሚከናወን አሳውቋል። የቦቻ ዳይመንድ ትረስት ኩባንያ ሊቀመንበር ሞሰስ ሙክዋዳ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ የአካባቢው ሰዎች ተገደው በማዕድን ቁፋሮው ሥራ እንደተሰማሩ አጋልጠዋል። አንዳንድ ኩባንያዎች የግዳጅ ሥራ አለ ለማለት አልደፈሩም። ለማዕድን ቁፋሮ ሰራተኞች መብት የሚታገለው ዘ ሴንተር ፎር ናቹራል ሪሶርስስ ገቨርናንስ የተባለው ድርጅት ከአስራ ስምንት ዓመት በታች ያሉ ታዳጊዎች አካላዊ ጥቃት እንደደረሰባቸው ቢገልፅም ሰራተኞች በግዳጅ ተሰማርተዋል ከሚለው አስተያየት ተቆጥቧል። "ሰራተኞች በግዳጅ ተሰማርተዋል የሚለውን ሃሳብ ሙሉ በሙሉ አናጣጥለውም፤ ከአሜሪካ መንግሥትም ሆነ ከየትኛውም አካል በግዳጅ የተሰማሩ ሰራተኞች እንዳሉ መረጃ አልደረሰንም። ማን ማንን እያስገደደ ነው የሚለውንም የበለጠ ማወቅ እንፈልጋለን" በማለት የድርጅቱ ቃል አቀባይ ሲሚሶ ምሌቩ ተናግረዋል። በማራንጄ የማዕድን ቁፋሮ ቦታ ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ውንጀላዎች ሲቀርቡ የመጀመሪያው አይደለም። የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በተደጋጋሚ እንዳሳወቁት ከአካባቢው የሚመጣው አልማዝ "ከግጭት አካባቢ የተገኘ አልማዝ" ስለሆነ ወደ ውጭ የሚላከው የአልማዝ መጠን ሊገደብ ይገባል በሚል አሳውቀው ነበር። በጎርጎሳውያኑ 2011 ቢቢሲ ባደረገው ምርመራ በአካባቢው የከፋ ድብደባና ወሲባዊ ጥቃት እንደሚደርስም መረጃ ሰብስቧል። "በማራንጌም ሆነ ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ የአልማዝ ምርቶች በከፍተኛ ሁኔታ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ቢያጠላባቸውም ወደ አለም አቀፉ ገበያ መድረሳቸው አልቀረም" በማለት ዘ ሴንተር ፎር ናቹራል ሪሶርስስ ገቨርናንስ አስታውቋል። ሰራተኞች ላይ በሚደርሱ ጥቃቶች እንዲሁም ባለው የከፋ ሁኔታ አርባ ሰዎች በየአመቱ ይሞታሉ ተብሏል። •ቤይሩት፡ ባለፉት 7 ወራት 34 ኢትዮጵያዊያን ህይወታቸውን አጥተዋል •ጃፓን ያለ መሬትና ያለ አርሶ አደሮች የፈጠረችው የግብርና አብዮት የሰራተኞች መብት በዚምባብዌ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ነኝ የሚለው ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዋች ባለፈው ዓመት ባወጣው ሪፖርት በሃገሪቷ በሚገኙ የትምባሆ እርሻዎችም የግዳጅ ሥራ እንደተንሰራፋ ይፋ አድርጓል። የአሜሪካ መንግሥትም እንዲሁ ባለፈው አመት የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ እንደሚከናወን አንድ መረጃ አውጥቶ ነበር። ዚምባብዌ በበኩሏ የተባበሩት መንግሥታት የጉልበት ብዝበዛን ለማስቀረት ያፀደቃቸውን ሕጎች በዚህ ዓመት እንደተቀበለችና የግዳጅ ሥራ ልምድንም ለማስቀረት እየሞከሩ እንደሆነ ገልፃለች። | https://www.bbc.com/amharic/news-50114465 |
5sports
| ሞ ፋራህ በኃይሌ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን አሻሸለ | ትውልደ ሶማሊያዊው ሞ ፋራህ በኃይሌ ገብረስላሴ ለ13 ዓመታት ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን አሻሸለ። ለግሬት ብሪቴን የሚሮጠው የአራት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮኑ ሞ ፋራህ የአንድ ሰዓት የዓለም ክብረ ወሰንን በዳይመንድ ሊግ ውድድር ነው ትናንት ምሽት ማሻሻል የቻለው። ፋራህ በአንድ ሰዓት ውስጥ 23.33 ኪሎ ሜትር በመሮጥ ነው የሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴን 21.285 ኪሎ ሜትር ርቀት ያሻሻለው። “የዓለም ክብረ ወሰንን መስበር ቀላል ነገር አይደለም። ይህን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ። ይህ ክብረ ወሰን ለረዥም ጊዜ ሳይሰበር ቆይቷል” ሲል ከውድድሩ በኋላ ሞ ፋራህ ተናግሯል። በዚህ ውድድር አትሌቶች በአንድ ሰዓት ውስጥ በተቻላቸው መጠን ረዥም ርቀትን ለመሸፈን ይወዳደራሉ። ከዛ ቀደም ብሎ በተካሄደ ተመሳሳይ የሴቶች ውድድርም ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፈን ሃሰን በተመሳሳይ የዓለም ክብረ ወሰንን ማሻሻል ችላለች። ለኔዘርላንድ የምትሮጠው ሲፈን ያሻሻለችው ክብረ ወሰን በኢትዮጵያዊቷ አትሌት ድሬ ቱኔ ተይዞ የነበረውን ነው። ሲፈን በአንድ ሰዓት ውስጥ 18.930 ኪሎ ሜትር በመሮጥ ከ14 ዓመታት በፊት ድሬ ቱኔ አስመዝግባ የነበረውን 18.517 ኪሎ ሜትር ማሻሻል ችላለች። | ሞ ፋራህ በኃይሌ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን አሻሸለ ትውልደ ሶማሊያዊው ሞ ፋራህ በኃይሌ ገብረስላሴ ለ13 ዓመታት ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን አሻሸለ። ለግሬት ብሪቴን የሚሮጠው የአራት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮኑ ሞ ፋራህ የአንድ ሰዓት የዓለም ክብረ ወሰንን በዳይመንድ ሊግ ውድድር ነው ትናንት ምሽት ማሻሻል የቻለው። ፋራህ በአንድ ሰዓት ውስጥ 23.33 ኪሎ ሜትር በመሮጥ ነው የሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴን 21.285 ኪሎ ሜትር ርቀት ያሻሻለው። “የዓለም ክብረ ወሰንን መስበር ቀላል ነገር አይደለም። ይህን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ። ይህ ክብረ ወሰን ለረዥም ጊዜ ሳይሰበር ቆይቷል” ሲል ከውድድሩ በኋላ ሞ ፋራህ ተናግሯል። በዚህ ውድድር አትሌቶች በአንድ ሰዓት ውስጥ በተቻላቸው መጠን ረዥም ርቀትን ለመሸፈን ይወዳደራሉ። ከዛ ቀደም ብሎ በተካሄደ ተመሳሳይ የሴቶች ውድድርም ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፈን ሃሰን በተመሳሳይ የዓለም ክብረ ወሰንን ማሻሻል ችላለች። ለኔዘርላንድ የምትሮጠው ሲፈን ያሻሻለችው ክብረ ወሰን በኢትዮጵያዊቷ አትሌት ድሬ ቱኔ ተይዞ የነበረውን ነው። ሲፈን በአንድ ሰዓት ውስጥ 18.930 ኪሎ ሜትር በመሮጥ ከ14 ዓመታት በፊት ድሬ ቱኔ አስመዝግባ የነበረውን 18.517 ኪሎ ሜትር ማሻሻል ችላለች። | https://www.bbc.com/amharic/news-54039364 |