label
class label 4
classes | headline
stringlengths 17
80
| text
stringlengths 1
16.8k
| headline_text
stringlengths 28
16.8k
| url
stringlengths 36
49
|
---|---|---|---|---|
5sports
| የፀረ-አበረታች ኤጀንሲ በአትሌቲክስ ውስጥ የካናቢስን መታገድ ሊመረምር ነው | የዓለም ፀረ-አበረታች ንጥረ ነገሮች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ የሆነው ዋዳ በአትሌቲክስ ውስጥ የካናቢስን መከልከል ዳግም ሊመረምር ነው። ኤጀንሲው ይህን የሚያደርገው አሜሪካዊቷ የአጭር ርቀት ተወዳዳሪ የካናቢስ ምርመራ ማለፍ ባለመቻሏ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ሳትሳተፍ ከቀረች በኋላ ነው። የ21 ዓመቷ ሻካሪ ሪቻርደሰን የወላጅ እናቷን ሞት ተከትሎ ሐዘኗን ለመቋቋም ካናቢስ መጠቀሟን ይፋ አድርጋ ነበር። የዓለም ፀረ-አበረታች ንጥረ ነገሮች ኤጀንሲ በካናቢስ ዙሪያ ሳይንሳዊ ምርመራ በቀጣይ የፈረንጆች ዓመት እንደሚጀመር ገልጾ፤ ካናቢስ በአትሌቲክስ ውስጥ የተከለከለ ሆኖ አስከ 2022 ይቀጥላል ብሏል። የፀረ-አበረታች ኤንጀንሲው በካናቢስ ላይ ያለው ሕግ ዳግም ማጤን ያስፈለው "ከሚመለከታቸው በርካታ አካላት ጥያቄዎች በመቅረባቸው ነው" ብሏል። ሪቻርድሰን ሰኔ ወር ላይ ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ማጣሪያ በአሜሪካ በተደረገ ውድድር በ100 ሜትር ማሸነፍ ችላ ነበር። በዚህም በማጣሪው ግማሽ ፍጻሜ ውድድር ላይ ያጠናቀቀችበት ሰዓት 6ኛው በሴቶች የተመዘገበ ፈጣን ሰዓት ሆኖ ተመዝግቦ ነበር። የአትሌቷ የካናቢስ ምርመራ ውጤት 'ፖዘቲቭ' የሆነው በኦሊምፒክ ማጣሪያ ላይ ሲሆን፤ በማጣሪያ ውድድር ላይ ያስመዘገበችው ፈጣኑ ሰዓትም ውድቅ ተደርጎባታል። የአንድ ወር እገዳም ተጥሎባታል። ሪቻርድሰን የተካፈለችበት ማጣሪያ ውድድር የተካሄደው ከወላጅ እናቷ ሞት ከአንድ ሳምንት በኋላ ነበር። የአሜሪካ የትራክ እና መስክ እንዲሁም የአሜሪካ ፀረ-አበረታች ኤጀንሲ በአትሌቷ ወላጅ እናት ሞት ሐዘናቸውን በመግለጽ፤ አትሌቷ ዕጹን የተጠቀመችው የውድድር አቅሟን ከፍ ለማድረግ ባይሆንም ሕጉን ከመከተል ውጪ ሌላ አማራጭ የለንም ብለዋል። በአሁኑ ወቅት ካናቢስ ተጠቅሞ የተገኘ አትሌት እስካ አራት ዓመት እግድ ሊጣልበት ይችላል። ይሁን እንጂ እግዱ የተላለፈበት አትሌት ዕጹን ተጠቅመው ከተገኙ የውድድር አቅምን ከፍ ለማድረግ አለመሆኑን ማረጋገጥ የሚችሉ ከሆነ ቅጣቱ ወደ ሦስት ወራት ዝቅ ሊደረግ ይችላል። ከዚህ ውጪ አንድ አትሌት ለሕክምና ክትትል ፍቃደኛ ሆኖ የሚገኝ ከሆነ የትኛውም አይነት እግድ ወደ አንድ ወር ዝቅ ሊደረግ ይችላል። | የፀረ-አበረታች ኤጀንሲ በአትሌቲክስ ውስጥ የካናቢስን መታገድ ሊመረምር ነው የዓለም ፀረ-አበረታች ንጥረ ነገሮች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ የሆነው ዋዳ በአትሌቲክስ ውስጥ የካናቢስን መከልከል ዳግም ሊመረምር ነው። ኤጀንሲው ይህን የሚያደርገው አሜሪካዊቷ የአጭር ርቀት ተወዳዳሪ የካናቢስ ምርመራ ማለፍ ባለመቻሏ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ሳትሳተፍ ከቀረች በኋላ ነው። የ21 ዓመቷ ሻካሪ ሪቻርደሰን የወላጅ እናቷን ሞት ተከትሎ ሐዘኗን ለመቋቋም ካናቢስ መጠቀሟን ይፋ አድርጋ ነበር። የዓለም ፀረ-አበረታች ንጥረ ነገሮች ኤጀንሲ በካናቢስ ዙሪያ ሳይንሳዊ ምርመራ በቀጣይ የፈረንጆች ዓመት እንደሚጀመር ገልጾ፤ ካናቢስ በአትሌቲክስ ውስጥ የተከለከለ ሆኖ አስከ 2022 ይቀጥላል ብሏል። የፀረ-አበረታች ኤንጀንሲው በካናቢስ ላይ ያለው ሕግ ዳግም ማጤን ያስፈለው "ከሚመለከታቸው በርካታ አካላት ጥያቄዎች በመቅረባቸው ነው" ብሏል። ሪቻርድሰን ሰኔ ወር ላይ ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ማጣሪያ በአሜሪካ በተደረገ ውድድር በ100 ሜትር ማሸነፍ ችላ ነበር። በዚህም በማጣሪው ግማሽ ፍጻሜ ውድድር ላይ ያጠናቀቀችበት ሰዓት 6ኛው በሴቶች የተመዘገበ ፈጣን ሰዓት ሆኖ ተመዝግቦ ነበር። የአትሌቷ የካናቢስ ምርመራ ውጤት 'ፖዘቲቭ' የሆነው በኦሊምፒክ ማጣሪያ ላይ ሲሆን፤ በማጣሪያ ውድድር ላይ ያስመዘገበችው ፈጣኑ ሰዓትም ውድቅ ተደርጎባታል። የአንድ ወር እገዳም ተጥሎባታል። ሪቻርድሰን የተካፈለችበት ማጣሪያ ውድድር የተካሄደው ከወላጅ እናቷ ሞት ከአንድ ሳምንት በኋላ ነበር። የአሜሪካ የትራክ እና መስክ እንዲሁም የአሜሪካ ፀረ-አበረታች ኤጀንሲ በአትሌቷ ወላጅ እናት ሞት ሐዘናቸውን በመግለጽ፤ አትሌቷ ዕጹን የተጠቀመችው የውድድር አቅሟን ከፍ ለማድረግ ባይሆንም ሕጉን ከመከተል ውጪ ሌላ አማራጭ የለንም ብለዋል። በአሁኑ ወቅት ካናቢስ ተጠቅሞ የተገኘ አትሌት እስካ አራት ዓመት እግድ ሊጣልበት ይችላል። ይሁን እንጂ እግዱ የተላለፈበት አትሌት ዕጹን ተጠቅመው ከተገኙ የውድድር አቅምን ከፍ ለማድረግ አለመሆኑን ማረጋገጥ የሚችሉ ከሆነ ቅጣቱ ወደ ሦስት ወራት ዝቅ ሊደረግ ይችላል። ከዚህ ውጪ አንድ አትሌት ለሕክምና ክትትል ፍቃደኛ ሆኖ የሚገኝ ከሆነ የትኛውም አይነት እግድ ወደ አንድ ወር ዝቅ ሊደረግ ይችላል። | https://www.bbc.com/amharic/news-58571965 |
3politics
| ቻይና 'ወኪሏን' ወደ ዩኬ ፓርላማ አስገብታለች መባሉን አስተባበለች | የዩናይትድ ኪንግደም የደህንነት ተቋም (ኤምአይ5) ቻይና ወኪሏን የዩኬ ፓርላማ ውስጥ አስርጋ አስገብታለች ማለቱን ተከትሎ ቤይጂንግ ክሱን አጣጣለች። የደህንነት መስሪያ ቤቱ እንዳለው ክሪስቲን ቺንግ ኩይ የፓርላማ አባላት እና በቀጣይ አባል ለመሆን የሚፈልጉ ግለሰቦች ከቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ጋር "ግንኙነት እንዲመሠርቱ" አግዛለች ብሏል። ከ420,000 ፓውንድ በላይ ከግለሰቧ ድጋፍ የተደረገለት የሌበር ፓርቲ ተወካዩ ባሪ ጋርዲነርን ጨምሮ ለሌሎች ፖለቲከኞችም ድጋፍ አድርጋለች። መቀመጫውን ለንደን ያደረገው የቻይና ኤምባሲ ኤምአይ5 በእንግሊዝ በሚገኙ የቻይና ማህበረሰብ አባላትን 'ስም እያጠፋ እና እያስፈራራ ነው' ሲል ከሷል። የኤምባሲው ቃል አቀባይ በኤምባሲው ድረ-ገጽ ላይ በሰጡት መግለጫ "ቻይና በሌሎች አገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አለመግባት የሚለውን መርህ ሁሌም ትከተላለች" ብለዋል። "በማንኛውም አገር ፓርላማ ውስጥ 'ተጽዕኖ ለመፍጠር' ምንም ፍላጎት የለንም። በእንግሊዝ የቻይና ማህበረሰብ አባላት ላይ የሚደረገውን ስም ማጥፋት እና ማስፈራራት አጥብቀን እንቃወማለን" ብሏል። እንደ ኤምአይ5 ማስጠንቀቂያው ከሆነ ሊ ከፓርላማው ጋር የነበራት ግንኙነት "እንግሊዛዊ የሆኑ ቻይና ዝርያ ያላቸውን ለመወከል እና ብዝሃነትን ለማሳደግ" ነበር። ኤምአይ5 በኩሉ እንቅስቃሴው "ከዩናይትድ ፍሮንት ዎርክ ዲፓርትመንት (የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ አካል ነው) ጋር በድብቅ መካሄዱን አሰስታውቆ የገንዘብ ድጋፍ በቻይና እና ሆንግ ኮንግ በሚገኙ የውጭ አገር ዜጎች ተደርጓል" ብሏል። ዲፓርተመንቱ የዩናይትድ ኪንግደም የፖለቲካ ምህዳር ለኮሚኒስት ፓርቲው ምቹ መሆኑን ለማረጋገጥ እና የሰብዓዊ መብቶችን ጨምሮ በፓርቲው ላይ ስጋቶችን የሚያነሱትን ለመቃወም "ከተጽዕኖ ፈጣሪ ሰዎች" ጋር "ግንኙነትን ለማዳበር" ያለመ ነው ተብሏል። የደህንነት ቢሮው እንዳለው ግለሰቧ ቻይናዊያን በብሪታንያ ተብሎ የሚጠራውንና አሁን የተበተነውን ኦል ፓርቲ ፓርላመንተሪ ግሩፕን ጨምሮ "በዩናይትድ ኪንግደም ፖለቲካ ውስጥ ካሉ ግለሰቦች ጋር ሰፊ ግንኙነት ነበራት" ብሏል። ኤምአይ5 አክሎም "የቻይናን የኮሚኒስት ፓርቲን አጀንዳ ለማራመድ የፓርላማ ቡድኖችን ለማቋቋም ልትፈልግ ትችላለች" በማለት አስጠንቅቋል። ወግ አጥባቂ የህዝብ እንደራሴ እና የቀድሞ የፓርቲ ሊቀመንበር ሰር ኢይን ደንካን ስሚዝ ሐሙስ በፓርላማው ስለማስጠንቀቂያው ያነሱ ሲሆን ይህም በአፈ ጉባኤው ለፓርላማ አባላት እንደተላከ አረጋግጠዋል። "በጣም አሳሳቢ ጉዳይ ነው" ያሉ ሲሆን ሊ ከሃገራቸው እንድትባረር እና መንግሥት ለምክር ቤቱ መግለጫ እንዲሰጥ ጠይቀዋል። የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ፕሪቲ ፓቴል "የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲን ወክላ በፖለቲካ ጣልቃገብነት ተግባር ላይ የተሠማራች ግለሰብ የፓርላማ አባላት ላይ ማነጣጠሯ በጣም አሳሳቢ ነው" ብለዋል። ዩናይትድ ኪንግደም "የውጭ ጣልቃ ገብነትን ለመለየት" እርምጃዎች እንዳሏት ተናግረዋል። የሌበር ፓርቲ የህዝብ እንደራሴ ባሪ ጋርዲነር ከክርስቲን ቺንግ ኩይ ሊ የህግ ቢሮ ድጋፍ ማግኘት የጀመሩት እአአ ከ2014 ጀምሮ ነው። የሊ ልጅ ለህዝብ እንደራሴው በበጎ ፈቃደኝነት መሥራቱን እና በኋላም ቃለ ጉባኤ ያዥ ሆኖ ተቀጠሯል። ዠርሚ ኮርቢ የሌበር መሪ በነበሩበት ጊዜ የትይዩ ካቢኔ አባል የነበሩት ጋርዲነር ስለግለሰቧ "ለተወሰኑ ዓመታት ከደህንነት አገልግሎታችን ጋር ግንኙነት ሳደርግ ነበር" ብለዋል። ሊ የጥናት ባለሙያ ሆኖ በተሾመበት ወቅት ምንም ሚና ያልነበራት ሲሆን ሁሉም ልገሳዎችም "በትክክል ሪፖርት የተደረጉ ናቸው" ብለዋል። ጋርዲነር በኋላ ላይ ለስካይ ኒውስ "በእኔ እይታ ገንዘቡ በፓርላማ ውስጥ መሥራት የቻልኩትን ሥራ ለማሻሻል እና ለምርጫ ክልሌ ልሠራው የቻልኩትን ለማሻሻል የዋለ ነበር። ለግል ጥቅሜ የዋለ ገንዘብ የለም" ብለዋል። | ቻይና 'ወኪሏን' ወደ ዩኬ ፓርላማ አስገብታለች መባሉን አስተባበለች የዩናይትድ ኪንግደም የደህንነት ተቋም (ኤምአይ5) ቻይና ወኪሏን የዩኬ ፓርላማ ውስጥ አስርጋ አስገብታለች ማለቱን ተከትሎ ቤይጂንግ ክሱን አጣጣለች። የደህንነት መስሪያ ቤቱ እንዳለው ክሪስቲን ቺንግ ኩይ የፓርላማ አባላት እና በቀጣይ አባል ለመሆን የሚፈልጉ ግለሰቦች ከቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ጋር "ግንኙነት እንዲመሠርቱ" አግዛለች ብሏል። ከ420,000 ፓውንድ በላይ ከግለሰቧ ድጋፍ የተደረገለት የሌበር ፓርቲ ተወካዩ ባሪ ጋርዲነርን ጨምሮ ለሌሎች ፖለቲከኞችም ድጋፍ አድርጋለች። መቀመጫውን ለንደን ያደረገው የቻይና ኤምባሲ ኤምአይ5 በእንግሊዝ በሚገኙ የቻይና ማህበረሰብ አባላትን 'ስም እያጠፋ እና እያስፈራራ ነው' ሲል ከሷል። የኤምባሲው ቃል አቀባይ በኤምባሲው ድረ-ገጽ ላይ በሰጡት መግለጫ "ቻይና በሌሎች አገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አለመግባት የሚለውን መርህ ሁሌም ትከተላለች" ብለዋል። "በማንኛውም አገር ፓርላማ ውስጥ 'ተጽዕኖ ለመፍጠር' ምንም ፍላጎት የለንም። በእንግሊዝ የቻይና ማህበረሰብ አባላት ላይ የሚደረገውን ስም ማጥፋት እና ማስፈራራት አጥብቀን እንቃወማለን" ብሏል። እንደ ኤምአይ5 ማስጠንቀቂያው ከሆነ ሊ ከፓርላማው ጋር የነበራት ግንኙነት "እንግሊዛዊ የሆኑ ቻይና ዝርያ ያላቸውን ለመወከል እና ብዝሃነትን ለማሳደግ" ነበር። ኤምአይ5 በኩሉ እንቅስቃሴው "ከዩናይትድ ፍሮንት ዎርክ ዲፓርትመንት (የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ አካል ነው) ጋር በድብቅ መካሄዱን አሰስታውቆ የገንዘብ ድጋፍ በቻይና እና ሆንግ ኮንግ በሚገኙ የውጭ አገር ዜጎች ተደርጓል" ብሏል። ዲፓርተመንቱ የዩናይትድ ኪንግደም የፖለቲካ ምህዳር ለኮሚኒስት ፓርቲው ምቹ መሆኑን ለማረጋገጥ እና የሰብዓዊ መብቶችን ጨምሮ በፓርቲው ላይ ስጋቶችን የሚያነሱትን ለመቃወም "ከተጽዕኖ ፈጣሪ ሰዎች" ጋር "ግንኙነትን ለማዳበር" ያለመ ነው ተብሏል። የደህንነት ቢሮው እንዳለው ግለሰቧ ቻይናዊያን በብሪታንያ ተብሎ የሚጠራውንና አሁን የተበተነውን ኦል ፓርቲ ፓርላመንተሪ ግሩፕን ጨምሮ "በዩናይትድ ኪንግደም ፖለቲካ ውስጥ ካሉ ግለሰቦች ጋር ሰፊ ግንኙነት ነበራት" ብሏል። ኤምአይ5 አክሎም "የቻይናን የኮሚኒስት ፓርቲን አጀንዳ ለማራመድ የፓርላማ ቡድኖችን ለማቋቋም ልትፈልግ ትችላለች" በማለት አስጠንቅቋል። ወግ አጥባቂ የህዝብ እንደራሴ እና የቀድሞ የፓርቲ ሊቀመንበር ሰር ኢይን ደንካን ስሚዝ ሐሙስ በፓርላማው ስለማስጠንቀቂያው ያነሱ ሲሆን ይህም በአፈ ጉባኤው ለፓርላማ አባላት እንደተላከ አረጋግጠዋል። "በጣም አሳሳቢ ጉዳይ ነው" ያሉ ሲሆን ሊ ከሃገራቸው እንድትባረር እና መንግሥት ለምክር ቤቱ መግለጫ እንዲሰጥ ጠይቀዋል። የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ፕሪቲ ፓቴል "የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲን ወክላ በፖለቲካ ጣልቃገብነት ተግባር ላይ የተሠማራች ግለሰብ የፓርላማ አባላት ላይ ማነጣጠሯ በጣም አሳሳቢ ነው" ብለዋል። ዩናይትድ ኪንግደም "የውጭ ጣልቃ ገብነትን ለመለየት" እርምጃዎች እንዳሏት ተናግረዋል። የሌበር ፓርቲ የህዝብ እንደራሴ ባሪ ጋርዲነር ከክርስቲን ቺንግ ኩይ ሊ የህግ ቢሮ ድጋፍ ማግኘት የጀመሩት እአአ ከ2014 ጀምሮ ነው። የሊ ልጅ ለህዝብ እንደራሴው በበጎ ፈቃደኝነት መሥራቱን እና በኋላም ቃለ ጉባኤ ያዥ ሆኖ ተቀጠሯል። ዠርሚ ኮርቢ የሌበር መሪ በነበሩበት ጊዜ የትይዩ ካቢኔ አባል የነበሩት ጋርዲነር ስለግለሰቧ "ለተወሰኑ ዓመታት ከደህንነት አገልግሎታችን ጋር ግንኙነት ሳደርግ ነበር" ብለዋል። ሊ የጥናት ባለሙያ ሆኖ በተሾመበት ወቅት ምንም ሚና ያልነበራት ሲሆን ሁሉም ልገሳዎችም "በትክክል ሪፖርት የተደረጉ ናቸው" ብለዋል። ጋርዲነር በኋላ ላይ ለስካይ ኒውስ "በእኔ እይታ ገንዘቡ በፓርላማ ውስጥ መሥራት የቻልኩትን ሥራ ለማሻሻል እና ለምርጫ ክልሌ ልሠራው የቻልኩትን ለማሻሻል የዋለ ነበር። ለግል ጥቅሜ የዋለ ገንዘብ የለም" ብለዋል። | https://www.bbc.com/amharic/59991402 |
5sports
| በኢትዮጵያና ታንዛኒያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ግጥሚያ የተከሰተው ምንድን ነው? | ኡጋንዳ እየተካሄደ በሚገኘው የሴካፋ ውድድር የኢትዮጵያ ሴቶች ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የታንዛኒያ አቻዋን 2 ለ1 ረትታለች። የዚህ ጨዋታ ማብቂያ ግን እንደ ሌሎች ግጥሚያዎች ተጫዋቾች ተጨባብጠው የተለያዩበት አይደለም። ለመሆኑ የተፈጠረው ምንድን ነው? ኢትዮጵያ ሰኞ ዕለት ባደረገችው የመጀመሪያው ጨዋታዋ ጅቡቲን 7 ለምንም መርታቷ ይታወሳል። ቀጣይ ከጎረቤት ሃገር ኤርትራ ጋር ግጥሚያ የነበራት የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን 5 ለባዶ አሸንፋለች። ሶስተኛው የኢትዮጵያ ጨዋታ ከታንዛኒያ ጋር ትናንት ረቡዕ በኡጋንዳ ንጄሩ የተደረገ ሲሆን የዚህ ጨዋታ የመጀመሪያ አጋማሽ ጎል አላስተናገደም። በሁለተኛው አጋማሽ ተነቃቅታ የገባችው ኢትዮጵያ በ10 ደቂቃ ውስጥ ሁለት ጎል በማስቆጠር መሪነቱን ያዘች። ሁለቱን የኢትዮጵያ ጎሎች መሳይ ተመስገንና ይየን ኒያቦኒ ናቸው ያስቆጠሩት። ነገር ግን የታንዛንያዋ ሉቫንጋ አንድ ጎል አስቆጥራ የሃገሯን የጎል ዕዳ ወደ አንድ ዝቅ አደረገች። በዚህ ጎል የተነቃቁት ታንዛኒያዎች በተደጋጋሚ የጎል ማግባት ሙከራ ቢያደርጉም አልተሳካላቸውም። የጎል ሙከራቸውን የቀጠሉት ታንዛኒያዎች በጭማሪ ሰዓት ቅጣት ምት ያገኛሉ። ቅጣት ምቱ ወደ ጎል ከተሰነዘረ በኋላ የኢትዮጵያዋ ግብ ጠባቂ ቤቴልሄም በቀለ ኳሱን መቆጣጠር ባለመቻሏ የታንዛኒያዋ አጥቂ አይሻ ማሳካ ወደጎል ትቀይራታለች። ነገር ግን ይህ ጎል ከጨዋታ ውጪ ነው በማለት የመስመር ዳኛዋ አሊዳ ኢራዱካንዳ ባንዲራቸውን ያውለበልባሉ። በዚህ ውሳኔ ደስተኛ ያልሆኑት የታንዛኒያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አባላት ወደ መስመር ዳኛዋ በመሄድ ይከቧትና ይገፏት ጀመር። የታንዛኒያዋ ተከላካይ ፉሙካዚ የመስመር ዳኛዋን ገፍትራ በመጣሏ በቀይ ካርድ ከጨዋታው ታግዳለች። የታንዛኒያ ተጫዋቾች የመስመር ዳኛዋን በመግፋት በማዋከብ ብቻ ሳያልፉ ባንዲራዋን በመንጠቃቸው የካርድ ሰለባ ሆነዋል። የጨዋታው ማብቂያ ፊሽካ ከተነፋ በኋላም የታንዛኒያ ተጫዋቾች የጨዋታውን ዳኞች በማዋከባቸው ከሴካፋ ቅጣት ይጠብቃቸዋል እየተባለ ነው። በኡጋንዳ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ በምሕፃሩ ሴካፋ ከ20 ዓመት በታች ውድድር ባለፈው ቅዳሜ ነው የተጀመረው። ታንዛንያ፣ ኤርትራ፣ ጅቡቲ፣ ኢትዮጵያ፣ ቡሩንዲና ኡጋንዳ እየተሳተፉ ሲሆን ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ ሩዋንዳ፣ ኬንያና ሶማሊያ በውድድሩ አልተሳተፉም። ኢትዮጵያ እስካሁን ያደረገቻቸውን 3 ጨዋታዎች በማሸነፍ በ9 ነጥብ ውድድሩን እየመራች ትገኛለች። ሌላኛው በኡጋንዳ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው ቀጣናዊው የእግር ኳስ ውድድር አነጋጋሪ የሆነው ጉዳይ 5 ኤርትራዊያን መጥፋታቸው ነው። አምስቱ ተጫዋቾች ባለፈው ማክሰኞ ጠዋት ካረፉበት ሆቴል የተሰወሩ ሲሆን በሴካፋ ከ20 አመት በታች የሴቶች ሻምፒዮና የኤርትራ ብሄራዊ ቡድን አባል ነበሩ። የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ እግር ኳስ ማህበራት ምክር ቤት ሴካፋ] ባወጣው መግለጫ ጉዳዩ ለፖሊስ ሪፖርት እንደተደረገና ምርመራም በመካሄድ ላይ መሆኑን ገልጻል። ሴካፋ ከኡጋንዳ የእግር ኳስ ባለስልጣን ጋር የጠፉ ተጫዋቾችን ለማግኘት እንደሚሰራም ተናግረዋል። | በኢትዮጵያና ታንዛኒያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ግጥሚያ የተከሰተው ምንድን ነው? ኡጋንዳ እየተካሄደ በሚገኘው የሴካፋ ውድድር የኢትዮጵያ ሴቶች ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የታንዛኒያ አቻዋን 2 ለ1 ረትታለች። የዚህ ጨዋታ ማብቂያ ግን እንደ ሌሎች ግጥሚያዎች ተጫዋቾች ተጨባብጠው የተለያዩበት አይደለም። ለመሆኑ የተፈጠረው ምንድን ነው? ኢትዮጵያ ሰኞ ዕለት ባደረገችው የመጀመሪያው ጨዋታዋ ጅቡቲን 7 ለምንም መርታቷ ይታወሳል። ቀጣይ ከጎረቤት ሃገር ኤርትራ ጋር ግጥሚያ የነበራት የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን 5 ለባዶ አሸንፋለች። ሶስተኛው የኢትዮጵያ ጨዋታ ከታንዛኒያ ጋር ትናንት ረቡዕ በኡጋንዳ ንጄሩ የተደረገ ሲሆን የዚህ ጨዋታ የመጀመሪያ አጋማሽ ጎል አላስተናገደም። በሁለተኛው አጋማሽ ተነቃቅታ የገባችው ኢትዮጵያ በ10 ደቂቃ ውስጥ ሁለት ጎል በማስቆጠር መሪነቱን ያዘች። ሁለቱን የኢትዮጵያ ጎሎች መሳይ ተመስገንና ይየን ኒያቦኒ ናቸው ያስቆጠሩት። ነገር ግን የታንዛንያዋ ሉቫንጋ አንድ ጎል አስቆጥራ የሃገሯን የጎል ዕዳ ወደ አንድ ዝቅ አደረገች። በዚህ ጎል የተነቃቁት ታንዛኒያዎች በተደጋጋሚ የጎል ማግባት ሙከራ ቢያደርጉም አልተሳካላቸውም። የጎል ሙከራቸውን የቀጠሉት ታንዛኒያዎች በጭማሪ ሰዓት ቅጣት ምት ያገኛሉ። ቅጣት ምቱ ወደ ጎል ከተሰነዘረ በኋላ የኢትዮጵያዋ ግብ ጠባቂ ቤቴልሄም በቀለ ኳሱን መቆጣጠር ባለመቻሏ የታንዛኒያዋ አጥቂ አይሻ ማሳካ ወደጎል ትቀይራታለች። ነገር ግን ይህ ጎል ከጨዋታ ውጪ ነው በማለት የመስመር ዳኛዋ አሊዳ ኢራዱካንዳ ባንዲራቸውን ያውለበልባሉ። በዚህ ውሳኔ ደስተኛ ያልሆኑት የታንዛኒያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አባላት ወደ መስመር ዳኛዋ በመሄድ ይከቧትና ይገፏት ጀመር። የታንዛኒያዋ ተከላካይ ፉሙካዚ የመስመር ዳኛዋን ገፍትራ በመጣሏ በቀይ ካርድ ከጨዋታው ታግዳለች። የታንዛኒያ ተጫዋቾች የመስመር ዳኛዋን በመግፋት በማዋከብ ብቻ ሳያልፉ ባንዲራዋን በመንጠቃቸው የካርድ ሰለባ ሆነዋል። የጨዋታው ማብቂያ ፊሽካ ከተነፋ በኋላም የታንዛኒያ ተጫዋቾች የጨዋታውን ዳኞች በማዋከባቸው ከሴካፋ ቅጣት ይጠብቃቸዋል እየተባለ ነው። በኡጋንዳ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ በምሕፃሩ ሴካፋ ከ20 ዓመት በታች ውድድር ባለፈው ቅዳሜ ነው የተጀመረው። ታንዛንያ፣ ኤርትራ፣ ጅቡቲ፣ ኢትዮጵያ፣ ቡሩንዲና ኡጋንዳ እየተሳተፉ ሲሆን ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ ሩዋንዳ፣ ኬንያና ሶማሊያ በውድድሩ አልተሳተፉም። ኢትዮጵያ እስካሁን ያደረገቻቸውን 3 ጨዋታዎች በማሸነፍ በ9 ነጥብ ውድድሩን እየመራች ትገኛለች። ሌላኛው በኡጋንዳ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው ቀጣናዊው የእግር ኳስ ውድድር አነጋጋሪ የሆነው ጉዳይ 5 ኤርትራዊያን መጥፋታቸው ነው። አምስቱ ተጫዋቾች ባለፈው ማክሰኞ ጠዋት ካረፉበት ሆቴል የተሰወሩ ሲሆን በሴካፋ ከ20 አመት በታች የሴቶች ሻምፒዮና የኤርትራ ብሄራዊ ቡድን አባል ነበሩ። የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ እግር ኳስ ማህበራት ምክር ቤት ሴካፋ] ባወጣው መግለጫ ጉዳዩ ለፖሊስ ሪፖርት እንደተደረገና ምርመራም በመካሄድ ላይ መሆኑን ገልጻል። ሴካፋ ከኡጋንዳ የእግር ኳስ ባለስልጣን ጋር የጠፉ ተጫዋቾችን ለማግኘት እንደሚሰራም ተናግረዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59161580 |
5sports
| ለ39 ዓመታት እራሱን ስቶ የቆየው የቀድሞው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች አረፈ | ላለፉት 39 ዓመታት ኮማ ውስጥ የነበረው የቀድሞው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን እግር ኳስ ተጫዋች ዣን ፒየር አዳምስ በ73 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ሆስፒታል የገባው እአአ ግንቦት 1982 ለጉልበት ቀዶ ሕክምና ነበር። ማደንዘዣ ሲሰጠው በተፈጠረ ስህተት ምክንያት እራሱን ከሳተ በኋላ ለ39 ዓመታት ከኮማ አልነቃም። ሴኔጋል የተወለደው አጥቂው ዣን ፒየር፤ ለፓሪስ ሴንት ዠርሜን እና ኒይስ ቡድን ከ140 ጊዜ በላይ ተሰልፏል። ፓሪስ ሴንት ዠርመን (ፒኤስጂ) ባወጣው መግለጫ፤ "ግርማ ሞገስ ያለው፣ ልምድ ያካበተው እና የተከበረው" ሲል ነው ተጫዋቹን የገለጸው። ኒይስ በበኩሉ ለተጨዋቹ መታሰቢያ መርሃ ግብር እንደሚያዘጋጅ አስታውቋል። ዣን ፒየር እአአ ከ1972 እስከ 1976 ፈረንሳይ 22 ዋንጫዎችን እንድታገኝ አስችሏል። 84 ጊዜ ተጫዋቹን ያሰለፈው ኒምስ ቡድን "ለቤተሰቦቹና ለሚወዱት ሰዎች በአጠቃላይ መጽናናት እንመኛለን" ሲል የሐዘን መግለጫ አውጥቷል። ዣን ፒየር በልምምድ ላይ ሳለ ጉልበቱ ላይ ጉዳት ከደረሰበት በኋላ ነበር ወደ ሆስፒታል የተወሰደው። በእለቱ በሆስፒታሉ የነበሩ አብዛኞቹ ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማ ላይ ነበሩ። ማደንዘዣ የሚሰጡት ሐኪም ዣን ፒየርን ጨምሮ ለስምንት ህሙማን አገልግሎት እየሰጡ ነበር። ማደንዘዣ የሚሰጡትን ሐኪም የሚረዳ ተለማማጅ ባለሙያም ሆስፒታሉ ውስጥ ነበር። ተለማማጁ ባለሙያ ኋላ ላይ ለዣን ፒየር ሕክምና የመስጠት አቅም እንዳልነበረው ተናግሯል። "የተሰጠኝ ኃላፊነት ከአቅሜ በላይ ነበር" ብሏል። ማደንዘዣ የሚሰጡት ሐኪም እና ተለማማጁ ባለሙያ በሠሩት ስህተት ምክንያት ዣን ፒየር የልብ እና የአዕምሮ ጉዳት ደርሶበታል። ሁለቱ ባለሙያዎች እስከ 199ዎቹ አጋማሽ ድረስ ለስህተታቸው ሳይቀጡ ቢቆዩም፤ ኋላ ላይ 750 ዩሮ ቅጣት እንዲከፍሉ እና ለአንድ ወር እንዲታገዱ ተወስኗል። ዣን ፒየር ከ15 ወራት በኋላ ከሆስፒታል ወጥቶ ባለቤቱ በርንዴት በቤታቸው ውስጥ ስትንከባከበው ቆይታለች። ለአራት አስርት ዓመታት እራሱን ስቶ ቢቆይም፤ ባለቤቱ ግን እስትንፋስ የሚሰጠው መሣሪያ እንዲቋረጥ አልፈቀደችም። በየቀኑ ልብሱን እየቀየረችለት፣ ምግብ እያዘጋጀችለት፣ ስጦታ እየሰጠችው እና እያዋራችው 39 ዓመታትን አሳልፋለች። በእርግጥ ዣን ፒየር ኮማ ውስጥ ስለነበረ ለባለቤቱ ምንም ምላሽ አልሰጣትም። ይረዱት የነበሩ ነርሶች እንደሚሉት ከሆነ፤ በርንዴት ከአጠገቡ ስትለይ እራሱን ስቶ የቆየው ዣን ፒየር አንዳች የስሜት ለውጥ ይታይበት ነበር። የሕክምና ስህተት የሠራው ሆስፒታል እስከ ዛሬ ድረስ ይቅርታ አለመጠየቁ የዣን ፒየርን ባለቤት ዘወትር ያበሳጫታል። | ለ39 ዓመታት እራሱን ስቶ የቆየው የቀድሞው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች አረፈ ላለፉት 39 ዓመታት ኮማ ውስጥ የነበረው የቀድሞው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን እግር ኳስ ተጫዋች ዣን ፒየር አዳምስ በ73 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ሆስፒታል የገባው እአአ ግንቦት 1982 ለጉልበት ቀዶ ሕክምና ነበር። ማደንዘዣ ሲሰጠው በተፈጠረ ስህተት ምክንያት እራሱን ከሳተ በኋላ ለ39 ዓመታት ከኮማ አልነቃም። ሴኔጋል የተወለደው አጥቂው ዣን ፒየር፤ ለፓሪስ ሴንት ዠርሜን እና ኒይስ ቡድን ከ140 ጊዜ በላይ ተሰልፏል። ፓሪስ ሴንት ዠርመን (ፒኤስጂ) ባወጣው መግለጫ፤ "ግርማ ሞገስ ያለው፣ ልምድ ያካበተው እና የተከበረው" ሲል ነው ተጫዋቹን የገለጸው። ኒይስ በበኩሉ ለተጨዋቹ መታሰቢያ መርሃ ግብር እንደሚያዘጋጅ አስታውቋል። ዣን ፒየር እአአ ከ1972 እስከ 1976 ፈረንሳይ 22 ዋንጫዎችን እንድታገኝ አስችሏል። 84 ጊዜ ተጫዋቹን ያሰለፈው ኒምስ ቡድን "ለቤተሰቦቹና ለሚወዱት ሰዎች በአጠቃላይ መጽናናት እንመኛለን" ሲል የሐዘን መግለጫ አውጥቷል። ዣን ፒየር በልምምድ ላይ ሳለ ጉልበቱ ላይ ጉዳት ከደረሰበት በኋላ ነበር ወደ ሆስፒታል የተወሰደው። በእለቱ በሆስፒታሉ የነበሩ አብዛኞቹ ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማ ላይ ነበሩ። ማደንዘዣ የሚሰጡት ሐኪም ዣን ፒየርን ጨምሮ ለስምንት ህሙማን አገልግሎት እየሰጡ ነበር። ማደንዘዣ የሚሰጡትን ሐኪም የሚረዳ ተለማማጅ ባለሙያም ሆስፒታሉ ውስጥ ነበር። ተለማማጁ ባለሙያ ኋላ ላይ ለዣን ፒየር ሕክምና የመስጠት አቅም እንዳልነበረው ተናግሯል። "የተሰጠኝ ኃላፊነት ከአቅሜ በላይ ነበር" ብሏል። ማደንዘዣ የሚሰጡት ሐኪም እና ተለማማጁ ባለሙያ በሠሩት ስህተት ምክንያት ዣን ፒየር የልብ እና የአዕምሮ ጉዳት ደርሶበታል። ሁለቱ ባለሙያዎች እስከ 199ዎቹ አጋማሽ ድረስ ለስህተታቸው ሳይቀጡ ቢቆዩም፤ ኋላ ላይ 750 ዩሮ ቅጣት እንዲከፍሉ እና ለአንድ ወር እንዲታገዱ ተወስኗል። ዣን ፒየር ከ15 ወራት በኋላ ከሆስፒታል ወጥቶ ባለቤቱ በርንዴት በቤታቸው ውስጥ ስትንከባከበው ቆይታለች። ለአራት አስርት ዓመታት እራሱን ስቶ ቢቆይም፤ ባለቤቱ ግን እስትንፋስ የሚሰጠው መሣሪያ እንዲቋረጥ አልፈቀደችም። በየቀኑ ልብሱን እየቀየረችለት፣ ምግብ እያዘጋጀችለት፣ ስጦታ እየሰጠችው እና እያዋራችው 39 ዓመታትን አሳልፋለች። በእርግጥ ዣን ፒየር ኮማ ውስጥ ስለነበረ ለባለቤቱ ምንም ምላሽ አልሰጣትም። ይረዱት የነበሩ ነርሶች እንደሚሉት ከሆነ፤ በርንዴት ከአጠገቡ ስትለይ እራሱን ስቶ የቆየው ዣን ፒየር አንዳች የስሜት ለውጥ ይታይበት ነበር። የሕክምና ስህተት የሠራው ሆስፒታል እስከ ዛሬ ድረስ ይቅርታ አለመጠየቁ የዣን ፒየርን ባለቤት ዘወትር ያበሳጫታል። | https://www.bbc.com/amharic/news-58468255 |
3politics
| የጀርሲ ፍርድ ቤት የሮማን አብራሞቪችን 7 ቢሊየን ዶላር የሚገመት ንብረቶች አገደ | ከሩሲያዊው ቢሊየነር ሮማን አብራሞቪች ጋር የተያያዙ እና 7 ቢሊዮን ዶላር የሚገመቱ ንብረቶች በጀርሲ ፍርድ ቤት ታግደዋል። ከቀናት በፊት የጀርሲ ፖሊስ በደሴቲቱ ላይ ከባለሀሃብቱ አብራሞቪች የንግድ እንቅስቃሴ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብሎ በተጠረጠሩ ቦታዎች ፈተሻ ማድረጉን የጀርሲ የህግ መኮንኖች ጽህፈት ቤት አሳውቋል። ሩሲያ በዩክሬን ላይ በከፈተችው ጦርነት ምክንያት ቢሊየነሩ አብራሞቪች በዩኬ ማዕቀብ ውስጥ ከተካተቱበት ውስጥ ይገኛሉ። የደሴቲቱ ሀገር ጀርሲ የዩኬን በመከተል በተመሳሳይ ሰዎች ላይ ማዕቀብ ጥላለች። የሀገሪቱ ፍርድ ቤት ከ 7 ቢሊየን ዶላር በላይ የሚገመቱት ከአብራሞቪች ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው በተጠረጠሩት እና በጀርሲ የሚገኙ ወይም በባለቤትነት በተያዙ ንብረቶች እንዳይንቀሳቀሱ ትእዛዝ አስተላልፏል ሲል የደሲቲቱ የሕግ መኮንኖች ክፍል ገልጿል። ሮማን አብራሞቪች ባለፈው ወር ሩሲያ በዩክሬን ላይ በፈጸመችው ወረራ ምክንያት በዩኬ እና በአውሮፓ ህብረት ማዕቀብ ከተጣለባቸው በርካታ ባላሃብቶች መካከል አንዱ ናቸው። መንግስታትም የባለሃብቶቹን ውድ ጀልባዎች እና ሌሎች የቅንጦት ንብረቶችን ለመውሰድ እርምጃዎቸውን እያጠናከሩ ነው። ቢሊየነሩ ከወራት በፊት የቼልሲ እግር ኳስ ክለብን ለመሸጥ እንቅስቃሴ ጀምረው የነበረ ቢሆንም ማዕቀብ ከተጣለባቸው በኋላ ሂደቱ በመንግስት በእንግሊዝ መንግሥት እንዲቀጥል ተደርጓል። ከካሪቢያን ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው አንቲጓ እና ባርቡዳ ዩናይትድ ኪንግደም በአብራሞቪች ባለቤትነት የተያዙ ቅንጡ ጀልባዎችን እንድትይዝ ለመርዳት ፈቃደኛ ብላ ነበር። ባለሃብቱ በድምሩ በ1.2 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ዋጋ ያላቸው ቅንጡ ጀልባዎቻቸው በደቡብ ምዕራብ ቱርክ፣ በአውሮፓ ህብረት እና በዩኬ ስር ይገኛሉ። | የጀርሲ ፍርድ ቤት የሮማን አብራሞቪችን 7 ቢሊየን ዶላር የሚገመት ንብረቶች አገደ ከሩሲያዊው ቢሊየነር ሮማን አብራሞቪች ጋር የተያያዙ እና 7 ቢሊዮን ዶላር የሚገመቱ ንብረቶች በጀርሲ ፍርድ ቤት ታግደዋል። ከቀናት በፊት የጀርሲ ፖሊስ በደሴቲቱ ላይ ከባለሀሃብቱ አብራሞቪች የንግድ እንቅስቃሴ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብሎ በተጠረጠሩ ቦታዎች ፈተሻ ማድረጉን የጀርሲ የህግ መኮንኖች ጽህፈት ቤት አሳውቋል። ሩሲያ በዩክሬን ላይ በከፈተችው ጦርነት ምክንያት ቢሊየነሩ አብራሞቪች በዩኬ ማዕቀብ ውስጥ ከተካተቱበት ውስጥ ይገኛሉ። የደሴቲቱ ሀገር ጀርሲ የዩኬን በመከተል በተመሳሳይ ሰዎች ላይ ማዕቀብ ጥላለች። የሀገሪቱ ፍርድ ቤት ከ 7 ቢሊየን ዶላር በላይ የሚገመቱት ከአብራሞቪች ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው በተጠረጠሩት እና በጀርሲ የሚገኙ ወይም በባለቤትነት በተያዙ ንብረቶች እንዳይንቀሳቀሱ ትእዛዝ አስተላልፏል ሲል የደሲቲቱ የሕግ መኮንኖች ክፍል ገልጿል። ሮማን አብራሞቪች ባለፈው ወር ሩሲያ በዩክሬን ላይ በፈጸመችው ወረራ ምክንያት በዩኬ እና በአውሮፓ ህብረት ማዕቀብ ከተጣለባቸው በርካታ ባላሃብቶች መካከል አንዱ ናቸው። መንግስታትም የባለሃብቶቹን ውድ ጀልባዎች እና ሌሎች የቅንጦት ንብረቶችን ለመውሰድ እርምጃዎቸውን እያጠናከሩ ነው። ቢሊየነሩ ከወራት በፊት የቼልሲ እግር ኳስ ክለብን ለመሸጥ እንቅስቃሴ ጀምረው የነበረ ቢሆንም ማዕቀብ ከተጣለባቸው በኋላ ሂደቱ በመንግስት በእንግሊዝ መንግሥት እንዲቀጥል ተደርጓል። ከካሪቢያን ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው አንቲጓ እና ባርቡዳ ዩናይትድ ኪንግደም በአብራሞቪች ባለቤትነት የተያዙ ቅንጡ ጀልባዎችን እንድትይዝ ለመርዳት ፈቃደኛ ብላ ነበር። ባለሃብቱ በድምሩ በ1.2 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ዋጋ ያላቸው ቅንጡ ጀልባዎቻቸው በደቡብ ምዕራብ ቱርክ፣ በአውሮፓ ህብረት እና በዩኬ ስር ይገኛሉ። | https://www.bbc.com/amharic/news-61103519 |
5sports
| ጉዬ አዶሎ፡ "ቀነኒሳን ከመሰለ ጀግና ጋር በመወዳደሬ ትልቅ ደስታ ይስማኛል" | የበርሊን ማራቶን አሸናፊው አትሌት ጉዬ አዶላ "ቀነኒሳን ከመሰለ ጀግና ጋር መወዳደሬ ትልቅ ደስታ ይስማኛል" ሲል ተናገረ። አትሌት ጉዬ ውድድሩ እንደ አጠቃላይ ቆንጆ ነበር ያለ ካለ በኋላ፤ "በሰዓቱ ደስተኛ ባልሆነም አንደኛ በመውጣቴ ደስ ብሎኛል" ብሏል። በውድድሩ ጥሩ ሰዓት ያልተመዘገበው በበርሊን የነበረው ከፍተኛ ሙቀት እንደምክንያት ያነሳው አትሌቱ፤ በውድድር ላይ የሚያጋጥሙ ስህተቶችን በማራም በቀጣይ ውድድር የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል። "የማስበው የኤሊዩድ ሪኮርድ መስበር ነው" ትናንት በተካሄደው የበርሊን ማራቶን ላሌኛው ክስተት የሆነው ኢትዮጵያዊው ወጣት አትሌት አባቴ ታዱ ነው። አትሌት አባቴ ታዱ 4ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀ ሲሆን፤ "እንደ ጉዬ አዶላ እና ቀነኒሳ በቀለ ያሉ ልምድ ያላቸው ተወዳዳሪዎች ነበሩ። ከእነርሱ ጋር ተወዳድሬ ልምድ በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ" ብሏል። አትሌት አባቴ ታዱ "የወደፊት እቅዴ በደንብ ሰርቼ ይሄን የኤሊይድ ኪፕቾጌን ሪኮርድ መስበር አለብኝ ብዬ ነው ማስበው" ብሏል። | ጉዬ አዶሎ፡ "ቀነኒሳን ከመሰለ ጀግና ጋር በመወዳደሬ ትልቅ ደስታ ይስማኛል" የበርሊን ማራቶን አሸናፊው አትሌት ጉዬ አዶላ "ቀነኒሳን ከመሰለ ጀግና ጋር መወዳደሬ ትልቅ ደስታ ይስማኛል" ሲል ተናገረ። አትሌት ጉዬ ውድድሩ እንደ አጠቃላይ ቆንጆ ነበር ያለ ካለ በኋላ፤ "በሰዓቱ ደስተኛ ባልሆነም አንደኛ በመውጣቴ ደስ ብሎኛል" ብሏል። በውድድሩ ጥሩ ሰዓት ያልተመዘገበው በበርሊን የነበረው ከፍተኛ ሙቀት እንደምክንያት ያነሳው አትሌቱ፤ በውድድር ላይ የሚያጋጥሙ ስህተቶችን በማራም በቀጣይ ውድድር የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል። "የማስበው የኤሊዩድ ሪኮርድ መስበር ነው" ትናንት በተካሄደው የበርሊን ማራቶን ላሌኛው ክስተት የሆነው ኢትዮጵያዊው ወጣት አትሌት አባቴ ታዱ ነው። አትሌት አባቴ ታዱ 4ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀ ሲሆን፤ "እንደ ጉዬ አዶላ እና ቀነኒሳ በቀለ ያሉ ልምድ ያላቸው ተወዳዳሪዎች ነበሩ። ከእነርሱ ጋር ተወዳድሬ ልምድ በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ" ብሏል። አትሌት አባቴ ታዱ "የወደፊት እቅዴ በደንብ ሰርቼ ይሄን የኤሊይድ ኪፕቾጌን ሪኮርድ መስበር አለብኝ ብዬ ነው ማስበው" ብሏል። | https://www.bbc.com/amharic/news-58704717 |
3politics
| የአዲስ ዓመት ተስፋዬ 'ይህ በቃን' ብለን ወደ አዲስ ምዕራፍ የምንሸጋገርበት እንዲሆን ነው | የቀድሞው የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በመስከረም ወር 2005 ዓ. ም. ነበር የአቶ መለስ ዜናዊን ህልፈት ተከትሎ ኢትዮጵያን እንዲመሩ የተሾሙት። ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከመሾማቸው በፊት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል። የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደርነትን ጨምሮ በበርካታ የክልል ብሎም የፌደራል የሥራ ኃላፊነቶች ላይ ቆይተዋል። በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት በቦርድ አመራርነት ያገለግላሉ። እንዲሁም ከባለቤታቸው ወይዘሮ ሮማን ተስፋዬ ጋር ባቋቋሙት ፋውንዴሽን አማካኝነት በተለያዩ ተግባራትን ላይ እየተሳተፉ ነው። አቶ ኃይለማሪያም በአፍሪካ ምርጫዎችን የመታዘብ ሂደቶችን መርተዋል። ቢቢሲ ከአቶ ኃይለማሪያም ጋር የ2015 አዲስ ዓመት አስመልክቶ አጭር ቆይታ አደርጓል። ቢቢሲ፡ ጡረታ ወጥተዋል ወይስ አሁንም መደበኛ ሥራዎች አለዎት? ኑሮዎትስ የት ነው? አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው የምኖረው። ነገር ግን የሥራዬ ሁኔታ ወደ ተለያዩ አገራት በተደጋጋሚ ያመላልሰኛል። በሁለት መስኮች በዋናነት እሳተፋለሁ። የመጀመሪያው ሥራዬ በኃይለማሪያም እና ሮማን ፋውንዴሽን ከባለቤቴ ጋር በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ላይ እንሰራለን። ቅድሚያ የሚሰጣቸው የአየር ንብረት ለውጥ፣ ብሎም የተፈጥሮ ሃብት እና የብዝሃ ሕይወት ጥበቃ ላይ እንሰራለን። ይህም የደን፣ የአፈር እና የውሃ፣ የእጽዋት እንዲሁም የዱር እንስሳት ጥበቃ ሥራዎች ላይ እናተኩራለን። አገራችን በዚህ ጉዳይ በጣም የተጎዳች ናት። ከፍተኛ የሆነ የአየር ንብረት ለውጥ ቀውሶች አሉባት። ድርቅ እና ጎርፍ ተመላልሰው ያጠቋታል። ሥራችንን በኦሞ ስምጥ ሸለቆ ላይ እንጀምር ብለን እዚያ ጀምረናል። የአካባቢው ኅብረተሰብ በአብዛኛው አርብቶ አደር ነው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሕጻናት፣ የልጆች፣ የሴቶች ብሎም የወጣቶች ጉዳይ በጣም አንገብጋቢ ነው። ስለዚህም የጤና፣ የትምህርት እና የሥርዓተ ምግብ ሁኔታዎች እንዲሻሻሉ በዚሁ በኦሞ ስምጥ ሸለቆ አካባቢ እየሰራን እንገኛለን። ሌላኛው ግን የአየር ንብረት ለውጥን አስመልክቶ የማደርገው ተሳትፎ ነው። ይህ ከልጅነቴ ጀምሮ የሚያሳስበኝ ጉዳይ ስለሆነ ነው የትምህርት መስኬን ስመርጥ ወደዛው ያዘነበልኩት። ተፈጥሮን መሰረት ያደረጉ መፍትሔዎች ላይ የቅስቀሳ ሥራዎች (Advocacy) ላይ በሰፊው እሳተፋለሁ። እንዲሁም በሰላም እና ፀጥታ አጀንዳ ላይ በተለይም በአፍሪካ ውስጥ የሚደረጉ ውይይቶች ላይም ወረቀቶችን አቀርባለሁ እንዲሁም እሳተፋለሁ። በአንድ ወቅት የዓለም አቀፉ ክራይሲስ ግሩፕ የቦርድ አባል ሆኜ እሰራ ነበር። አሁን በሥራ መደራረብ ምክንያት ትቼዋለሁ። እንዲሁም በአፍሪካ የኢኮኖሚ ለውጥ ላይ፣ የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ፣ ዴሞክራሲ እና የአመራር ሥራን የማቀላጠፍ ሥራዎች ላይ እሳተፋለሁ። ቢቢሲ፡ አውደ ዓመትን እንዴት ያሳልፋሉ? አቶ ኃይለማሪያም ፡ ብዙ ጊዜ ከአውደ ዓመት በፊት በቤተክርስትያን ጾሞች አሉ። አዲሱም ዓመት ከመግባቱ 15 ቀናት ቀደም ብለን የጾም ጸሎት እናካሂዳለን። አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የልማት፣ የብልጽግና እንዲሆን ብሎም የተረጋጋ ሆኖ እንዲያልፍ እንጸልያለን። ነገር ግን በየትኛውም በዓል ወቅት ግርግር ሲኖር ብዙም ደስተኛ አይደለሁም። በእርግጥ በባሕሪዬ ብዙ ግርግር አልወድም። ይልቁንም ወደ ጫካ፣ ወንዝ ወይም ፓርኮች የመሄድ ልምድ አለኝ። ቤት ውስጥ የምናሳልፍ ከሆነ ግን ቁጭ ብለን የምንጫወትበት ነው። ከሁሉም በላይ ዋናው የቤተሰብ ነውና፤ ቤተሰብ አንድ ላይ ይሰበሰባል። በተለይም ማምሻ አካባቢ ሁሉም ሰው ከቸርችም ሆነ ከየቤታቸው ይሰበሰባሉ፤ እንጫወታለን። ቢቢሲ፡ ከዚህ በፊት አንድ ቃለ መጠይቅ ላይ ቁርጥ ሥጋ በጣም እንደሚወዱ ተናግረው ነበር። በአውደ ዓመት ላይ ቁርጥ ሥጋ እንዴት ነዎት? አቶ ኃይለማሪያም፡ አዎ በተገኘ መጠን ቁርጥ ሥጋ እመገባለሁ። በርግጥ ውፍረትን ለመቀነስም ሆነ ጤናማ የምግብ ሥርዓት ለመከተል ጭምር እንደ ሥጋ ያሉ ፕሮቲኖች ይመከራሉ። ከመጠን በላይ ሆነው ወደ ዩሪክ አሲድ እንዳይቀየሩ ጥንቃቄ ከተደረገ ማለት ነው። ከልጆቼም አንዷ በጣም ትወዳለች። ቢቢሲ፡ ስለዚህ በዓመት በዓል ወቅት ጥሬ ሥጋ ከቤታችሁ አይጠፋም? አቶ ኃይለማሪያም፡ አይጠፋም! ቢቢሲ፡ ለአዲስ ዓመት ለቤተሰብ ስጦታ መስጠት ላይ እንዴት ነዎት? አቶ ኃይለማሪያም ፡ በአውደ ዓመት እንኳን ብዙም ስጦታ በባሕላችንም አልተለመደም። ምናልባት ፖስት ካርድ ካልሆነ። ነገር ግን በተለያየ ጊዜ ስጦታ እንሰጣጣለን። ለእኛም ስጦታ ይመጣልናል። ከሚመጡልን ስጦታዎች መካከል አበባ፣ በግ እና መጠጦች ይገኛሉ። ነገር ግን እኛ መጠጥ ስለማንጠጣ አጠራቅመን ሸጠን ለሌላ ዓላማ እናውለዋለን። ቢቢሲ፡ በአዲሱ ዓመት ተስፋ እና ስጋትዎት ምንድን ነው? አቶ ኃይለማሪያም ፡ እኔ ሁልግዜ ተስፋዬ በእግዚአብሔር ላይ ነው። በእርሱ ተስፋ አደርጋለሁ፤ መቼም ተስፋ አልቆርጥም። መልካም ነገር ያደርጋል ብዬ አምናለሁ። ስጋት እና ተስፋ ግን የሰው ልጅ ዕለት ተቀን የሚፈራረቁበት ጉዳዮች ናቸው። ከእነሱ ውጪ ሆኖ መኖር የሚችል ሰው የለም። አንዳንዴ ተስፋ ያይላል አንዳንዴ ስጋት ያይላል። በአገራችንም ሆነ በግል ብዙ ተስፋ የሚሰጡ ነገሮች እንዳሉ ሁሉ፣ በዚያው ልክም ስጋት የሚያጭሩ፣ መፍታት ሲገባን ያልፈታናቸው የተጠራቀሙ ችግሮች አሉ። እነዚያን ከስሜት በጸዳ፣ በሰከነ ሁኔታ፣ አርቆ በማሰብ እንደዚሁም ፍቅርን ሰላምን እና መተሳሰብን ማዕከል አድርጎ ጥላቻን እና ምሬትን መፍታት ያስፈልጋል። በርካታ አገራት ብዙ ስጋቶች በተፈጠሩባቸው ጊዜ ያንን ትምህርት አድርገው ከእንግዲህ በቃኝ የሚሉበት ወቅት አለ። የአውሮፓ አገራት ሲመሰረቱ በብዙ ጣጣዎች ውስጥ አልፈው ነበር፤ ግን ያንን በቃን ብለው ነው ያመለጡት። እኛም አሁን ባለንበት ሁኔታ በቃን፣ ሰለቸን ከዚህ በኋላ አይደገም ብሎ ሕዝቡ በምሬት ያንን የሚስማማበት ወቅት እየደረሰ ይሆን? በሁሉም አቅጣጫ ያሉ መሪዎች የሚስማሙበት ጊዜ እየደረሰ ይሆን? ብዬ እጠይቃለሁ። ይህ ከሆነ ያለፈውን ለታሪክ አስቀምጦ ወደ አዲስ ምዕራፍ የመሸጋገር እድል አለ። ያ ካልሆነ ወደ ጥፋት የመሸጋገር ዕድል ይኖረዋል። ለእኔ ግን ተስፋዬ 'ይህ በቃን' ብለን ወደ አዲስ ምዕራፍ የምንሸጋገርበት ይሆናል የሚል ነው። ቢቢሲ፡ ኢትዮጵያ እና ሕዝቦቿ አሁን ያሉበት አስቸጋሪ ሁኔታ ይታወቃል። ይህንን ለማሻሻል ምን ሚና ይጫወታሉ? አቶ ኃይለማሪያም ፡ የእኔ ሚና ትልቅ ነው ብዬ ባልወስድም በታሪክ አጋጣሚ ኢትዮጵያን የሚያክል ትልቅ አገር እንደመራ ሰው ባገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ ጥረቶችን አደርጋለሁ። የሰላም፣ የመተባበር እና የፍቅር መንፈስ እንጂ የጥላቻ እና የጥሎ ማለፍ ስሜት የሚመራው እንዳይሆን ለማሳሰብ እና ለመምከር እሞክራለሁ። ይሄ በቃል ይባላል እንጂ በተግባር ሲተገበር ከባድ ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ በኢትዮጵያ ላይ ተጸዕኖ ማሳደር የሚችሉ ሰዎችን አገኛለሁ። በተለይም አፍሪካዊያን እና ምዕራባዊያን መሪዎችን በማግኘት ትክክለኛውን ኢትዮጵያ ያለችበትን ሁኔታ ለማብራራት እሞክራለሁ። አገሪቱ ካለችበት ችግር እንድትወጣ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥረት አደርጋለሁ። ያልተረዱት እውነታ ካለም ለማስረዳት እና በተለይም ደግሞ ትኩረታቸው ተፋላሚ ወገኖች ላይ ሳይሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እንዲሆን ለማድረግ እሞክራለሁ። ሕዝቡ ላይ ትኩረታቸውን ካላደረጉ ተፋላሚ ወገኖች በሚፈጥሩት ችግር ሕዝቡ ከፍተኛ ቅጣት እንዲደርስበት ይሆናል። ያ እንዳይሆን ሁሌም ሕዝቡን እንዲመለከቱ እና መንግሥታትንም እንዲመክሩ፤ ከሚያባብስ ነገር ይልቅ የሚያግባባ ነገር እንዲያደርጉ እመክራለሁ። የኢትዮጵያን ሕዝብ ከስቃይ የሚያስወጣ እንጂ ስቃዩን የሚያበዛ እርምጃ እንዳይወስዱ አሳስባቸዋለሁ። በተለይም ኢትዮጵያን የመሰለች ትልቅ አገር መሰረቷ የተናጋ እንደሆነ መላው አፍሪካ፣ ብሎም መካከለኛው ምሥራቅም ሆነ የአውሮፓ አገራት ድረስ የሚደርስ ቀውስ እንደሚመጣ አውቀው የተረጋጋ ፖሊሲ እንዲይዙ ጥረት አደርጋለሁ። ቢቢሲ፡ አዲስ ዓመት ሲመጣ በርካቶች ወደኋላ ሄደው ልጅነታቸውን ያስባሉ። እርስዎ አዲስ ዓመት ሲመጣ ወደ አዕምሮዎት የሚመጡ ትዝታዎች ምንድን ናቸው? አቶ ኃይለማሪያም ፡ አዲስ ዓመት ሲመጣ በተለይም አንድ መጥፎ ትዝታ አለኝ። ልክ 12ኛ ክፍል እንደጨረስኩ በነሐሴ ወር መጨረሻ ነበር አባቴ ሕይወቱ ያለፈው። አዲሱ ዓመት በለቅሶ ላይ ሳለን ነበር የደረሰው። ዩኒቨርሲቲም መግቢያ ወቅት ነበር እና ከለቅሶ እንደተነሳሁ ነበር ለምዝገባ የሄድኩት። ያ አዲስ ዓመት ለእኔ የከፋ አዲስ ዓመት ነበር። እሱን ሁልጊዜ ነው የማስታውሰው። አባታችን ለእኛ ሁሉም ነገር ስለነበረ ያ ስብራት የነበረ አዲስ ዓመት አልረሳውም። በሌላ በኩል ደግሞ ከባለቤቴ ጋር ሠርጋችን በነሐሴ መጨረሻ ላይ ነበር። እና በወጣትነት በአዲስ ዓመት ያሳለፍነው ሁልጊዜም ትዝ የሚለን መልካም ትዝታችን ነው። እና ሁለቱም ነገሮች ተፈራርቀው አይቻለሁ። ከዚያ በተረፈ ግን በእኛ አካባቢ በልጅነታችን አሁን በተለምዶ መስቀል የሚባለው ዓመት በዓል አለ። በእርግጥ በብሔሩ አጠራር 'ጊፋታ' ነው የሚባለው፤ ኋላ ከመስቀል ጋር ተገጣጠመ እንጂ። የዘመን መለወጫ ነው። መስከረም 17 ከሚውልበት ሳምንት ጀምሮ ለወራት ነው የሚከበረው። ያንን በጣም ከልቤ ያከበርኩበት ጊዜ ነው፤ እስከ 15 ዓመቴ ድረስ። ከዚያ በኋላ እሱም በተለያየ ምክንያት እየቀዘቀዘ መጥቷል። ቢቢሲ፡ ምንም አንኳን በአውደ ዓመት ዙሪያ ቢሆንም ቆይታችን ለማሳረጊያ አንድ ጥያቄ ላንሳ። ራስዎን ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ካገለሉ በኋላ፣ ለኢትዮጵያ ይመጣል ብለው ያሰቡት ለውጥ መጥቷል ብለው ያምናሉ? አቶ ኃይለማሪያም ፡ የእኔ ራሴን ከሥልጣን ማግለል በወቅቱ ተፈጥሮ የነበረውን ውጥረት እና ስጋት በማርገብ እና ሕዝቡ ተስፋ እንዲሰንቅ በማድረግ የራሱን ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። ከሥልጣን ወርዶ በሰላም የኖረ ሰው በአገራችን ባልነበረበት ሁኔታ ይህ እንደሚቻል አንድ ተምሳሌት መፈጠሩ አንድ ነገር ነው። እኔም የታደልኩ ነኝ ብዬ አምናለሁ። ይሄ በሁሉም መስክ የሚያስተላልፈው የራሱ መልዕክት አለው። አሁን በአመራር ላሉትም ይህ እንደሚቻል አሳይቷል። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይም "ልክ እንዳንተ ዕድል ቢገጥመኝ እና እኔም በጊዜዬ አስረክቤ በሰላም ከሕዝቡ ጋራ የምኖርበት ሁኔታ ቢፈጠርልኝ" ሲል ሰምተሽ ይሆናል። ከእኔ በኋላ ያሉ መሪዎች ሥልጣን የመጨረሻው ሕይወት እንዳልሆነ እና ከሥልጣን ወርዶ መኖር እንደሚቻል ያሳየ ነው ብዬ አስባለሁ። እንዲያውም የተሻለ አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሚቻል ያሳያል። ምንም እንኳን አስተዋጽኦ የምናደርገበት መንገድ ቢለያይም። ነገር ግን የአገራችን የኢትዮጵያ ችግር በጣም ጥልቅ ነው። በእኔ ወይም በአንድ ሰው ከሥልጣን መውረድ የሚፈታ አይደለም። የተወሰነ የራሱን መደላድል የሚፈጥር ሊሆን ይችላል። እኔ አሁን ወጥቼም ቢሆን ሳስበው የአገራችን ችግር ጥልቀቱን ባለመረዳት ብዙ እንጎዳለን። ኢትዮጵያ መግለጽ ከምችለው በላይ እጅግ የተወሳሰበ፣ የተደራረበ፣ እጅግ በጣም የቆየ፣ እንዲሁም አሁን የተፈጠሩ ችግሮች ውስጥ ያለች አገር ነገር ነች። ይሄ መፍትሄው እና መፍቻው ምንድን ነው ብሎ ማሰብን ይጠይቃል። ሌላው ቀርቶ አሁን ያለው አመራር ሁሉ ወረድኩ ቢል እንኳን የሚፈታ አይደለም። ችግሩ ከአመራር መለዋወጥ በላይ ነው። ይልቁንም አንድ ከፍተኛ የሥርዓት ለውጥ ይጠይቃል። በርካታ ቅሬታ እና ቁርሾ የሞላው ሕብረተሰብ ነው ያለን። ወጣቱ የራሱ አስተሳሰብ አለው፤ የቆየው ሰው የራሱ አሰተሳሰብ አለው። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በጣም ብዙ ምልክቶች አሳርፈው ያለፉ ትውልዶች አሉ። በእኛ አጠራር የ1960ዎቹ ትውልድ አሁንም በተለያዩ ፓርቲዎች ውስጥ ሆኖ እስካሁን ለሥልጣን እየተፎካከሩ ያሉ ሰዎችም ያሉበት ማለት ነው። ይሄ ትውልድ በወቅቱ የያዛቸው አቋሞች ኢትዮጵያን በመልካምም ሆነ በመጥፎው ጠባሳ ጥለው ያለፉ ናቸው። ከእነዚያ ውስጥ አንዱ የብሔር ጥያቄ የተመለሰበት መንገድ ነው። አሁን በደንብ እንደገባን ሁላችንም እንዳሰብነው የብሔሮችን መብት እና እኩልነት ከማምጣት አልፎ የመጠፋፊያ መንገድ ብሎም የጽንፈኝነት አዝማሚያ እያሳየ ነው። ከዚህ የተነሳ ብዙ መከራ ውስጥ ነው ያለነው። ይህንን በግልጽ ተወያይተን መካከለኛውን መንገድ መፈለግ አለብን። ከጽንፈኝነት የራቀ ነገር ግን የሃይማኖት እና የብሔር መብቶችን ጨምሮ የቡድን መብቶች ከዜግነት መብት በማይበልጡበት መንገድ መፍቻ አማራጮችን ቁጭ ብለን መፈለግ አለብን። ይህ በተለያየ መንገድ የተመሰረቱ እንደ ሶቪየት ኅብረት ያሉ አገራት በሚፈጠሩበት ጊዜ የመጣ ሃሳብ ነው። ኋላ ወደ ራሳችን ስናመጣው ሕዝባችን የተቀላቀለ መሆኑን በሚረሳ መንገድ ነበር ያስገባነው። እያንዳንዱ ብሔር ወጥ ነው ብለን በማሰብ ያስገባነው ነገር አሁን መላወሻ አሳጥቶናል። እንግዲህ እንደዚህ አይነት እና መሰል ያልተፈቱ ጥያቄዎች አሉ። የጋራ ፍቺ ለመስጠት የሃይማኖት እና የፖለቲካ መሪዎች እንዲሁም የሚመለከታቸውን በሙሉ ያሳተፈ ውይይት ተደርጎ ለእነዚህ ችግሮች መፍተሄ ማፈላለግ ያስፈልጋል። ለምሳሌ የእኔን ብሔር ወስደሽ ወላይታዎች በአጼ ምኒሊክ አገር የመመስረት ሂደት ውስጥ ተጨፍልቀናለን፣ በመቶ ሺዎች ተጨፍጭፈናል ብለው እስካሁን ይናገራሉ። እውነት ነው፤ ይሄ አልተደረገም አልልም። ነገር ግን ከአንድ ፊውዳል ንጉሥ ዴሞክራሲ እና የሰብአዊ መብት ጥበቃ የምናስብ ከሆነ ከታሪክ ጋር ግጭት እንገባለን። በወቅቱ ንጉሥ ጦናም ቢሆኑ ይሄንን ዕድል ቢያገኙ ንጉሥ ምኒሊክ ያደረጉትን ሊያደርጉ ይችላሉ ብዬ ነው የማምነው። ንጉሥ ጦናም በራሱ አካካቢ የፊውዳል ሥርዓት ጫና ፈጥሯል። ስለዚህ ሁሉም የፊውዳል ሥርዓቶች የሚፈጽሙት ነገር ነው። ነገር ግን ልክ አልነበረም። ያንን ቁርሾ ይዞ እርሳቸው የተፈጠሩበትን ጭቁኑ የአማራ ብሔር ይሄንን ችግር እንደፈጠረ ተደርጎ የሚሳልበት እና የተለያየ ስያሜ የሚሰጥበት መንገድ መፈታት አለበት። ይሄ አሁን ባለንበት ሁኔታ ያልተፈታ ቁርሾ ጥሎ ንጹሁ ሕዝብ እንዲጎዳ እና እንዲሞት ያደርጋል። የአገራችንን የበፊት ታሪክ በጎውን ይዘን፣ ሌላውን ደግሞ ሁለተኛ በማይደገምበት ሁኔታ እንዴት ነው መሻገር የሚቻለው የሚለው ላይ መስራት አለብን። ሁሉም የራሱን ያልሻረ ቁስል ተንፍሶ እና አንዳንዱን ደግሞ ልክ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ላይ ተስማምቶ ማለፍን ይጠይቃል። ጥልቅ እና አካታች የማኅበረሰብ ውይይት እና መግባባት መፈጠር አለበት። ይሄ ካልሆነ ግን ስጋታችን የበለጠ እየጨመረ መሄዱ አይቀርም። እናም የእኔ መውጣት ሁሉን ነገር የሚፈታ አይደለም። በወቅቱ የተወሰነ ተስፋ ጭሮ ነበር። ያ ተስፋ በሂደት እየቀዘቀዘ እና እየቀነሰ መምጣቱን ሁላችንም የምናየው ነገር ነው። ነገር ግን ወደ ትክክለኛው መንገድ እንድንገባ አሁንም ዕድል አለን። | የአዲስ ዓመት ተስፋዬ 'ይህ በቃን' ብለን ወደ አዲስ ምዕራፍ የምንሸጋገርበት እንዲሆን ነው የቀድሞው የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በመስከረም ወር 2005 ዓ. ም. ነበር የአቶ መለስ ዜናዊን ህልፈት ተከትሎ ኢትዮጵያን እንዲመሩ የተሾሙት። ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከመሾማቸው በፊት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል። የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደርነትን ጨምሮ በበርካታ የክልል ብሎም የፌደራል የሥራ ኃላፊነቶች ላይ ቆይተዋል። በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት በቦርድ አመራርነት ያገለግላሉ። እንዲሁም ከባለቤታቸው ወይዘሮ ሮማን ተስፋዬ ጋር ባቋቋሙት ፋውንዴሽን አማካኝነት በተለያዩ ተግባራትን ላይ እየተሳተፉ ነው። አቶ ኃይለማሪያም በአፍሪካ ምርጫዎችን የመታዘብ ሂደቶችን መርተዋል። ቢቢሲ ከአቶ ኃይለማሪያም ጋር የ2015 አዲስ ዓመት አስመልክቶ አጭር ቆይታ አደርጓል። ቢቢሲ፡ ጡረታ ወጥተዋል ወይስ አሁንም መደበኛ ሥራዎች አለዎት? ኑሮዎትስ የት ነው? አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው የምኖረው። ነገር ግን የሥራዬ ሁኔታ ወደ ተለያዩ አገራት በተደጋጋሚ ያመላልሰኛል። በሁለት መስኮች በዋናነት እሳተፋለሁ። የመጀመሪያው ሥራዬ በኃይለማሪያም እና ሮማን ፋውንዴሽን ከባለቤቴ ጋር በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ላይ እንሰራለን። ቅድሚያ የሚሰጣቸው የአየር ንብረት ለውጥ፣ ብሎም የተፈጥሮ ሃብት እና የብዝሃ ሕይወት ጥበቃ ላይ እንሰራለን። ይህም የደን፣ የአፈር እና የውሃ፣ የእጽዋት እንዲሁም የዱር እንስሳት ጥበቃ ሥራዎች ላይ እናተኩራለን። አገራችን በዚህ ጉዳይ በጣም የተጎዳች ናት። ከፍተኛ የሆነ የአየር ንብረት ለውጥ ቀውሶች አሉባት። ድርቅ እና ጎርፍ ተመላልሰው ያጠቋታል። ሥራችንን በኦሞ ስምጥ ሸለቆ ላይ እንጀምር ብለን እዚያ ጀምረናል። የአካባቢው ኅብረተሰብ በአብዛኛው አርብቶ አደር ነው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሕጻናት፣ የልጆች፣ የሴቶች ብሎም የወጣቶች ጉዳይ በጣም አንገብጋቢ ነው። ስለዚህም የጤና፣ የትምህርት እና የሥርዓተ ምግብ ሁኔታዎች እንዲሻሻሉ በዚሁ በኦሞ ስምጥ ሸለቆ አካባቢ እየሰራን እንገኛለን። ሌላኛው ግን የአየር ንብረት ለውጥን አስመልክቶ የማደርገው ተሳትፎ ነው። ይህ ከልጅነቴ ጀምሮ የሚያሳስበኝ ጉዳይ ስለሆነ ነው የትምህርት መስኬን ስመርጥ ወደዛው ያዘነበልኩት። ተፈጥሮን መሰረት ያደረጉ መፍትሔዎች ላይ የቅስቀሳ ሥራዎች (Advocacy) ላይ በሰፊው እሳተፋለሁ። እንዲሁም በሰላም እና ፀጥታ አጀንዳ ላይ በተለይም በአፍሪካ ውስጥ የሚደረጉ ውይይቶች ላይም ወረቀቶችን አቀርባለሁ እንዲሁም እሳተፋለሁ። በአንድ ወቅት የዓለም አቀፉ ክራይሲስ ግሩፕ የቦርድ አባል ሆኜ እሰራ ነበር። አሁን በሥራ መደራረብ ምክንያት ትቼዋለሁ። እንዲሁም በአፍሪካ የኢኮኖሚ ለውጥ ላይ፣ የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ፣ ዴሞክራሲ እና የአመራር ሥራን የማቀላጠፍ ሥራዎች ላይ እሳተፋለሁ። ቢቢሲ፡ አውደ ዓመትን እንዴት ያሳልፋሉ? አቶ ኃይለማሪያም ፡ ብዙ ጊዜ ከአውደ ዓመት በፊት በቤተክርስትያን ጾሞች አሉ። አዲሱም ዓመት ከመግባቱ 15 ቀናት ቀደም ብለን የጾም ጸሎት እናካሂዳለን። አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የልማት፣ የብልጽግና እንዲሆን ብሎም የተረጋጋ ሆኖ እንዲያልፍ እንጸልያለን። ነገር ግን በየትኛውም በዓል ወቅት ግርግር ሲኖር ብዙም ደስተኛ አይደለሁም። በእርግጥ በባሕሪዬ ብዙ ግርግር አልወድም። ይልቁንም ወደ ጫካ፣ ወንዝ ወይም ፓርኮች የመሄድ ልምድ አለኝ። ቤት ውስጥ የምናሳልፍ ከሆነ ግን ቁጭ ብለን የምንጫወትበት ነው። ከሁሉም በላይ ዋናው የቤተሰብ ነውና፤ ቤተሰብ አንድ ላይ ይሰበሰባል። በተለይም ማምሻ አካባቢ ሁሉም ሰው ከቸርችም ሆነ ከየቤታቸው ይሰበሰባሉ፤ እንጫወታለን። ቢቢሲ፡ ከዚህ በፊት አንድ ቃለ መጠይቅ ላይ ቁርጥ ሥጋ በጣም እንደሚወዱ ተናግረው ነበር። በአውደ ዓመት ላይ ቁርጥ ሥጋ እንዴት ነዎት? አቶ ኃይለማሪያም፡ አዎ በተገኘ መጠን ቁርጥ ሥጋ እመገባለሁ። በርግጥ ውፍረትን ለመቀነስም ሆነ ጤናማ የምግብ ሥርዓት ለመከተል ጭምር እንደ ሥጋ ያሉ ፕሮቲኖች ይመከራሉ። ከመጠን በላይ ሆነው ወደ ዩሪክ አሲድ እንዳይቀየሩ ጥንቃቄ ከተደረገ ማለት ነው። ከልጆቼም አንዷ በጣም ትወዳለች። ቢቢሲ፡ ስለዚህ በዓመት በዓል ወቅት ጥሬ ሥጋ ከቤታችሁ አይጠፋም? አቶ ኃይለማሪያም፡ አይጠፋም! ቢቢሲ፡ ለአዲስ ዓመት ለቤተሰብ ስጦታ መስጠት ላይ እንዴት ነዎት? አቶ ኃይለማሪያም ፡ በአውደ ዓመት እንኳን ብዙም ስጦታ በባሕላችንም አልተለመደም። ምናልባት ፖስት ካርድ ካልሆነ። ነገር ግን በተለያየ ጊዜ ስጦታ እንሰጣጣለን። ለእኛም ስጦታ ይመጣልናል። ከሚመጡልን ስጦታዎች መካከል አበባ፣ በግ እና መጠጦች ይገኛሉ። ነገር ግን እኛ መጠጥ ስለማንጠጣ አጠራቅመን ሸጠን ለሌላ ዓላማ እናውለዋለን። ቢቢሲ፡ በአዲሱ ዓመት ተስፋ እና ስጋትዎት ምንድን ነው? አቶ ኃይለማሪያም ፡ እኔ ሁልግዜ ተስፋዬ በእግዚአብሔር ላይ ነው። በእርሱ ተስፋ አደርጋለሁ፤ መቼም ተስፋ አልቆርጥም። መልካም ነገር ያደርጋል ብዬ አምናለሁ። ስጋት እና ተስፋ ግን የሰው ልጅ ዕለት ተቀን የሚፈራረቁበት ጉዳዮች ናቸው። ከእነሱ ውጪ ሆኖ መኖር የሚችል ሰው የለም። አንዳንዴ ተስፋ ያይላል አንዳንዴ ስጋት ያይላል። በአገራችንም ሆነ በግል ብዙ ተስፋ የሚሰጡ ነገሮች እንዳሉ ሁሉ፣ በዚያው ልክም ስጋት የሚያጭሩ፣ መፍታት ሲገባን ያልፈታናቸው የተጠራቀሙ ችግሮች አሉ። እነዚያን ከስሜት በጸዳ፣ በሰከነ ሁኔታ፣ አርቆ በማሰብ እንደዚሁም ፍቅርን ሰላምን እና መተሳሰብን ማዕከል አድርጎ ጥላቻን እና ምሬትን መፍታት ያስፈልጋል። በርካታ አገራት ብዙ ስጋቶች በተፈጠሩባቸው ጊዜ ያንን ትምህርት አድርገው ከእንግዲህ በቃኝ የሚሉበት ወቅት አለ። የአውሮፓ አገራት ሲመሰረቱ በብዙ ጣጣዎች ውስጥ አልፈው ነበር፤ ግን ያንን በቃን ብለው ነው ያመለጡት። እኛም አሁን ባለንበት ሁኔታ በቃን፣ ሰለቸን ከዚህ በኋላ አይደገም ብሎ ሕዝቡ በምሬት ያንን የሚስማማበት ወቅት እየደረሰ ይሆን? በሁሉም አቅጣጫ ያሉ መሪዎች የሚስማሙበት ጊዜ እየደረሰ ይሆን? ብዬ እጠይቃለሁ። ይህ ከሆነ ያለፈውን ለታሪክ አስቀምጦ ወደ አዲስ ምዕራፍ የመሸጋገር እድል አለ። ያ ካልሆነ ወደ ጥፋት የመሸጋገር ዕድል ይኖረዋል። ለእኔ ግን ተስፋዬ 'ይህ በቃን' ብለን ወደ አዲስ ምዕራፍ የምንሸጋገርበት ይሆናል የሚል ነው። ቢቢሲ፡ ኢትዮጵያ እና ሕዝቦቿ አሁን ያሉበት አስቸጋሪ ሁኔታ ይታወቃል። ይህንን ለማሻሻል ምን ሚና ይጫወታሉ? አቶ ኃይለማሪያም ፡ የእኔ ሚና ትልቅ ነው ብዬ ባልወስድም በታሪክ አጋጣሚ ኢትዮጵያን የሚያክል ትልቅ አገር እንደመራ ሰው ባገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ ጥረቶችን አደርጋለሁ። የሰላም፣ የመተባበር እና የፍቅር መንፈስ እንጂ የጥላቻ እና የጥሎ ማለፍ ስሜት የሚመራው እንዳይሆን ለማሳሰብ እና ለመምከር እሞክራለሁ። ይሄ በቃል ይባላል እንጂ በተግባር ሲተገበር ከባድ ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ በኢትዮጵያ ላይ ተጸዕኖ ማሳደር የሚችሉ ሰዎችን አገኛለሁ። በተለይም አፍሪካዊያን እና ምዕራባዊያን መሪዎችን በማግኘት ትክክለኛውን ኢትዮጵያ ያለችበትን ሁኔታ ለማብራራት እሞክራለሁ። አገሪቱ ካለችበት ችግር እንድትወጣ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥረት አደርጋለሁ። ያልተረዱት እውነታ ካለም ለማስረዳት እና በተለይም ደግሞ ትኩረታቸው ተፋላሚ ወገኖች ላይ ሳይሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እንዲሆን ለማድረግ እሞክራለሁ። ሕዝቡ ላይ ትኩረታቸውን ካላደረጉ ተፋላሚ ወገኖች በሚፈጥሩት ችግር ሕዝቡ ከፍተኛ ቅጣት እንዲደርስበት ይሆናል። ያ እንዳይሆን ሁሌም ሕዝቡን እንዲመለከቱ እና መንግሥታትንም እንዲመክሩ፤ ከሚያባብስ ነገር ይልቅ የሚያግባባ ነገር እንዲያደርጉ እመክራለሁ። የኢትዮጵያን ሕዝብ ከስቃይ የሚያስወጣ እንጂ ስቃዩን የሚያበዛ እርምጃ እንዳይወስዱ አሳስባቸዋለሁ። በተለይም ኢትዮጵያን የመሰለች ትልቅ አገር መሰረቷ የተናጋ እንደሆነ መላው አፍሪካ፣ ብሎም መካከለኛው ምሥራቅም ሆነ የአውሮፓ አገራት ድረስ የሚደርስ ቀውስ እንደሚመጣ አውቀው የተረጋጋ ፖሊሲ እንዲይዙ ጥረት አደርጋለሁ። ቢቢሲ፡ አዲስ ዓመት ሲመጣ በርካቶች ወደኋላ ሄደው ልጅነታቸውን ያስባሉ። እርስዎ አዲስ ዓመት ሲመጣ ወደ አዕምሮዎት የሚመጡ ትዝታዎች ምንድን ናቸው? አቶ ኃይለማሪያም ፡ አዲስ ዓመት ሲመጣ በተለይም አንድ መጥፎ ትዝታ አለኝ። ልክ 12ኛ ክፍል እንደጨረስኩ በነሐሴ ወር መጨረሻ ነበር አባቴ ሕይወቱ ያለፈው። አዲሱ ዓመት በለቅሶ ላይ ሳለን ነበር የደረሰው። ዩኒቨርሲቲም መግቢያ ወቅት ነበር እና ከለቅሶ እንደተነሳሁ ነበር ለምዝገባ የሄድኩት። ያ አዲስ ዓመት ለእኔ የከፋ አዲስ ዓመት ነበር። እሱን ሁልጊዜ ነው የማስታውሰው። አባታችን ለእኛ ሁሉም ነገር ስለነበረ ያ ስብራት የነበረ አዲስ ዓመት አልረሳውም። በሌላ በኩል ደግሞ ከባለቤቴ ጋር ሠርጋችን በነሐሴ መጨረሻ ላይ ነበር። እና በወጣትነት በአዲስ ዓመት ያሳለፍነው ሁልጊዜም ትዝ የሚለን መልካም ትዝታችን ነው። እና ሁለቱም ነገሮች ተፈራርቀው አይቻለሁ። ከዚያ በተረፈ ግን በእኛ አካባቢ በልጅነታችን አሁን በተለምዶ መስቀል የሚባለው ዓመት በዓል አለ። በእርግጥ በብሔሩ አጠራር 'ጊፋታ' ነው የሚባለው፤ ኋላ ከመስቀል ጋር ተገጣጠመ እንጂ። የዘመን መለወጫ ነው። መስከረም 17 ከሚውልበት ሳምንት ጀምሮ ለወራት ነው የሚከበረው። ያንን በጣም ከልቤ ያከበርኩበት ጊዜ ነው፤ እስከ 15 ዓመቴ ድረስ። ከዚያ በኋላ እሱም በተለያየ ምክንያት እየቀዘቀዘ መጥቷል። ቢቢሲ፡ ምንም አንኳን በአውደ ዓመት ዙሪያ ቢሆንም ቆይታችን ለማሳረጊያ አንድ ጥያቄ ላንሳ። ራስዎን ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ካገለሉ በኋላ፣ ለኢትዮጵያ ይመጣል ብለው ያሰቡት ለውጥ መጥቷል ብለው ያምናሉ? አቶ ኃይለማሪያም ፡ የእኔ ራሴን ከሥልጣን ማግለል በወቅቱ ተፈጥሮ የነበረውን ውጥረት እና ስጋት በማርገብ እና ሕዝቡ ተስፋ እንዲሰንቅ በማድረግ የራሱን ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። ከሥልጣን ወርዶ በሰላም የኖረ ሰው በአገራችን ባልነበረበት ሁኔታ ይህ እንደሚቻል አንድ ተምሳሌት መፈጠሩ አንድ ነገር ነው። እኔም የታደልኩ ነኝ ብዬ አምናለሁ። ይሄ በሁሉም መስክ የሚያስተላልፈው የራሱ መልዕክት አለው። አሁን በአመራር ላሉትም ይህ እንደሚቻል አሳይቷል። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይም "ልክ እንዳንተ ዕድል ቢገጥመኝ እና እኔም በጊዜዬ አስረክቤ በሰላም ከሕዝቡ ጋራ የምኖርበት ሁኔታ ቢፈጠርልኝ" ሲል ሰምተሽ ይሆናል። ከእኔ በኋላ ያሉ መሪዎች ሥልጣን የመጨረሻው ሕይወት እንዳልሆነ እና ከሥልጣን ወርዶ መኖር እንደሚቻል ያሳየ ነው ብዬ አስባለሁ። እንዲያውም የተሻለ አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሚቻል ያሳያል። ምንም እንኳን አስተዋጽኦ የምናደርገበት መንገድ ቢለያይም። ነገር ግን የአገራችን የኢትዮጵያ ችግር በጣም ጥልቅ ነው። በእኔ ወይም በአንድ ሰው ከሥልጣን መውረድ የሚፈታ አይደለም። የተወሰነ የራሱን መደላድል የሚፈጥር ሊሆን ይችላል። እኔ አሁን ወጥቼም ቢሆን ሳስበው የአገራችን ችግር ጥልቀቱን ባለመረዳት ብዙ እንጎዳለን። ኢትዮጵያ መግለጽ ከምችለው በላይ እጅግ የተወሳሰበ፣ የተደራረበ፣ እጅግ በጣም የቆየ፣ እንዲሁም አሁን የተፈጠሩ ችግሮች ውስጥ ያለች አገር ነገር ነች። ይሄ መፍትሄው እና መፍቻው ምንድን ነው ብሎ ማሰብን ይጠይቃል። ሌላው ቀርቶ አሁን ያለው አመራር ሁሉ ወረድኩ ቢል እንኳን የሚፈታ አይደለም። ችግሩ ከአመራር መለዋወጥ በላይ ነው። ይልቁንም አንድ ከፍተኛ የሥርዓት ለውጥ ይጠይቃል። በርካታ ቅሬታ እና ቁርሾ የሞላው ሕብረተሰብ ነው ያለን። ወጣቱ የራሱ አስተሳሰብ አለው፤ የቆየው ሰው የራሱ አሰተሳሰብ አለው። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በጣም ብዙ ምልክቶች አሳርፈው ያለፉ ትውልዶች አሉ። በእኛ አጠራር የ1960ዎቹ ትውልድ አሁንም በተለያዩ ፓርቲዎች ውስጥ ሆኖ እስካሁን ለሥልጣን እየተፎካከሩ ያሉ ሰዎችም ያሉበት ማለት ነው። ይሄ ትውልድ በወቅቱ የያዛቸው አቋሞች ኢትዮጵያን በመልካምም ሆነ በመጥፎው ጠባሳ ጥለው ያለፉ ናቸው። ከእነዚያ ውስጥ አንዱ የብሔር ጥያቄ የተመለሰበት መንገድ ነው። አሁን በደንብ እንደገባን ሁላችንም እንዳሰብነው የብሔሮችን መብት እና እኩልነት ከማምጣት አልፎ የመጠፋፊያ መንገድ ብሎም የጽንፈኝነት አዝማሚያ እያሳየ ነው። ከዚህ የተነሳ ብዙ መከራ ውስጥ ነው ያለነው። ይህንን በግልጽ ተወያይተን መካከለኛውን መንገድ መፈለግ አለብን። ከጽንፈኝነት የራቀ ነገር ግን የሃይማኖት እና የብሔር መብቶችን ጨምሮ የቡድን መብቶች ከዜግነት መብት በማይበልጡበት መንገድ መፍቻ አማራጮችን ቁጭ ብለን መፈለግ አለብን። ይህ በተለያየ መንገድ የተመሰረቱ እንደ ሶቪየት ኅብረት ያሉ አገራት በሚፈጠሩበት ጊዜ የመጣ ሃሳብ ነው። ኋላ ወደ ራሳችን ስናመጣው ሕዝባችን የተቀላቀለ መሆኑን በሚረሳ መንገድ ነበር ያስገባነው። እያንዳንዱ ብሔር ወጥ ነው ብለን በማሰብ ያስገባነው ነገር አሁን መላወሻ አሳጥቶናል። እንግዲህ እንደዚህ አይነት እና መሰል ያልተፈቱ ጥያቄዎች አሉ። የጋራ ፍቺ ለመስጠት የሃይማኖት እና የፖለቲካ መሪዎች እንዲሁም የሚመለከታቸውን በሙሉ ያሳተፈ ውይይት ተደርጎ ለእነዚህ ችግሮች መፍተሄ ማፈላለግ ያስፈልጋል። ለምሳሌ የእኔን ብሔር ወስደሽ ወላይታዎች በአጼ ምኒሊክ አገር የመመስረት ሂደት ውስጥ ተጨፍልቀናለን፣ በመቶ ሺዎች ተጨፍጭፈናል ብለው እስካሁን ይናገራሉ። እውነት ነው፤ ይሄ አልተደረገም አልልም። ነገር ግን ከአንድ ፊውዳል ንጉሥ ዴሞክራሲ እና የሰብአዊ መብት ጥበቃ የምናስብ ከሆነ ከታሪክ ጋር ግጭት እንገባለን። በወቅቱ ንጉሥ ጦናም ቢሆኑ ይሄንን ዕድል ቢያገኙ ንጉሥ ምኒሊክ ያደረጉትን ሊያደርጉ ይችላሉ ብዬ ነው የማምነው። ንጉሥ ጦናም በራሱ አካካቢ የፊውዳል ሥርዓት ጫና ፈጥሯል። ስለዚህ ሁሉም የፊውዳል ሥርዓቶች የሚፈጽሙት ነገር ነው። ነገር ግን ልክ አልነበረም። ያንን ቁርሾ ይዞ እርሳቸው የተፈጠሩበትን ጭቁኑ የአማራ ብሔር ይሄንን ችግር እንደፈጠረ ተደርጎ የሚሳልበት እና የተለያየ ስያሜ የሚሰጥበት መንገድ መፈታት አለበት። ይሄ አሁን ባለንበት ሁኔታ ያልተፈታ ቁርሾ ጥሎ ንጹሁ ሕዝብ እንዲጎዳ እና እንዲሞት ያደርጋል። የአገራችንን የበፊት ታሪክ በጎውን ይዘን፣ ሌላውን ደግሞ ሁለተኛ በማይደገምበት ሁኔታ እንዴት ነው መሻገር የሚቻለው የሚለው ላይ መስራት አለብን። ሁሉም የራሱን ያልሻረ ቁስል ተንፍሶ እና አንዳንዱን ደግሞ ልክ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ላይ ተስማምቶ ማለፍን ይጠይቃል። ጥልቅ እና አካታች የማኅበረሰብ ውይይት እና መግባባት መፈጠር አለበት። ይሄ ካልሆነ ግን ስጋታችን የበለጠ እየጨመረ መሄዱ አይቀርም። እናም የእኔ መውጣት ሁሉን ነገር የሚፈታ አይደለም። በወቅቱ የተወሰነ ተስፋ ጭሮ ነበር። ያ ተስፋ በሂደት እየቀዘቀዘ እና እየቀነሰ መምጣቱን ሁላችንም የምናየው ነገር ነው። ነገር ግን ወደ ትክክለኛው መንገድ እንድንገባ አሁንም ዕድል አለን። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cl5845y7v53o |
2health
| በኢትዮጵያ የኤችአይቪ ቫይረስ ስርጭት መቀነሱ ተገለጸ | በኢትዮጵያ በየዓመቱ በኤችአይቪ ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መቀነሱ ተገለጸ። በፌደራል ኤችአይቪ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ጽህፈት ቤት የሕዝብ ግነኙነት እና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዳንኤል በስረ በኢትዮጵያ የኤችአይቪ ቫይረስ ስርጭት መቀነሱን ጥናቶች ያመላክታሉ ብለዋል። በአገር አቀፍ ደረጃ አጠቃላይ የቫይረሱ የስርጭት ምጣኔ 0.86 በመቶ መሆኑን አቶ ዳንኤል ያስረዳሉ። "ይሄ ማለት በመላው አገሪቱ፤ በሁሉም ማሕበረሰብ ክፍል ተመሳሳይ ነው ማለት አይደለም። በገጠር እና በከተማ የስርጭት ምጣኔው የተለያየ ነው" የሚሉት ዳንኤል፤ በጋምቤላ ክልል እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስርጭት ምጣኔው ከፍተኛ መሆኑን ይናገራሉ። ዳንኤል የቫይረሱ ስርጭት በጋምቤላ 4.1 በመቶ እንዲሁም በአዲስ አበባ ከ3 በመቶ በላይ መሆኑን ያስረዳሉ። 3 በመቶ ምጣኔ ምን ማለት እንደሆን ሲያስረዱ፤ በቀላል ቋንቋ ከመቶ ሰዎች ሦስት ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው አለ ማለት ነው ይላሉ። በሶማሌ፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች፣ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች የስርጭት ምጣኔው ከ1 በመቶ በታች መሆኑን ይናገራሉ። የሶማሌ ክልል 0.01 በመቶ አነስተኛ የቫይረሱ ስርጭት የሚገኘበት ክልል መሆኑን ይናገራሉ። በአገሪቱ ክልሎች መካከል ከፍተኛ የሆነ የቫይረሱ ስርጭት ልዩነት እንዴት ሊፈጠረ ቻለ? ተብለው የተጠየቁት አቶ ዳንኤል፤ ለዚህ ጥያቄ ቁርጥ ያለ ምላሽ ለመስጠት በዝርዝር ጥናት ላይ መመርኮዝ እንደሚያስፈልግ ገልጸው፤ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል የተሰራ ሥራ ልዩነት ፈጥሮ ሳይሆን ዋናው ምክንያት ከባህል እና ሃይማኖታዊ ጉዳይ ጋር ሊያያዝ ይችላል ይላሉ። አቶ ዳንኤል ከዓመታት በፊት በኢትዮጵያ አጠቃላይ የቫይረሱ ስርጭት ምጣኔ ከ6 በመቶ በላይ ደርሶ የሚያውቅበት አጋጣሚ እንዳለ ይናገራሉ። በከተሞች አካባቢ ደግሞ የስርጭት ምጣኔው እስከ 10 በመቶ ስለመድረሱ ተመዝግቦ ነበር ይላሉ። "በአንድ አገር አጠቃላይ የስርጭት ምጣኔው ከ1 በመቶ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫይረሱ ስርጭት ወረርሽኝ ነው የሚባለው" የሚሉት አቶ ዳንኤል፤ ምንም እንኳ በአገር ደረጃ የስርጭት ምጣኔው ከ1 በመቶ በታች ቢሆንም የስርጭት መጠኑ ከ1 በመቶ በላይ የሆነባቸው ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች መኖራቸውን ይናገራሉ። የቫይረሱ ስርጭት በጾታ ተከፍሎ ሲታይ ደግሞ፤ ሴቶች ከወንዶች በላይ ተጋላጭ መሆናቸውን ይናገራሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ በሽታውን በመከላከል ረገድ የሚሰሩ ሥራዎች መቀነሳቸውን ዳንኤል አስረድተዋል። መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ቀደም ሲል ሲሰሩ በነበሩበት ልክ ቫይረሱን የመከላከል ሥራ እየሰሩ አይደለም ይላሉ። ለዚህም ምክንያቱ የስርጭቱ መጠን በየዓመቱ መቀነስ በማሳየቱ እና በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ከመከላከሉ ይልቅ ሕክምናው ላይ ትኩረት በመሰጠቱ ነው ይላሉ። በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች በአሁኑ ወቅት ከ622 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች በኢትዮጵያ የኤችአይቪ ቫይረስ በደማቸው ይገኛል። ከእነዚህ መካከል ወደ 500 ሺህ የሚሆኑ ጸረ-ኤችአይቪ መድሃኒት እየወሰዱ እንደሚገኙ ጥናቶች ያሳያሉ ብለዋል ዳንኤል። በየዓመቱ ከ11 ሺህ በላይ አዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች አሉ። "ይህን የከፋ የሚያደርገው ከእነዚህ ውስጥ 67 በመቶ ድርሻ የሚይዙት እድሜያቸው ከ30 ዓመት በታች የሆኑ ወጣቶች መሆናቸው ነው" ይላሉ ዳንኤል። የቫይረሱን ስርጭት መከላከል አስፈላጊነትን ከሚያረጋግጡት መካከል አንዱ በበሽታው የሚያዙት አብዛኛዎቹ ወጣቶች መሆናቸው ነው ይላሉ። "አምራች ኃይል ነው። እንደ ሀገር ተስፋ የሚጣልበት ነው። በዚህ እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ወጣቶች ላይ የስርጭት ምጣኔው ከፍ ብሎ መታየቱ እንደ አገር አደጋ ውስጥ እንዳለን የሚያሳይ ነው" ብለዋል። ዳንኤል፤ ሴተኛ አዳሪዎች፣ ባሎቻቸውን በሞት ያጡ እና ትዳራቸውን የፈቱ ሴቶች ዘንድ የቫይረሱ ስርጭት መጠን ከፍተኛ ነው ይላሉ። "በሴተኛ አዳሪዎች የስርጭት ምጣኔው 18 በመቶ ነው። ባሎቻቸውን በሞት ያጡ እና ትዳራቸውን የፈቱ ሴቶች አካባቢ የስርጭት ምጣኔው ወደ 20 በመቶ ሆኖ እናያለን" ይላሉ። ሕይወታቸው የሚያልፍ ሰዎች ከ12 ሺህ ባለይ ሰዎች ደግሞ በየዓመቱ በኤድስ እና ተያያዥ በሽታዎች ሕይወታቸው እያለፈ ነው። በአገሪቱ ቫይረሱ በደማቸው ይገኘባቸዋል ከተባለው ከ622 ሺህ ባለይ ሰዎች 61 በመቶውን የሚይዙት ሴቶች ናቸው ይላሉ። በአሁኑ ሰዓት የስርጭት ምጣኔው ከ1 በታች መሆኑ የስርጭት መጠኑ አነስተኛ እንደሆነ ነው የሚያሳየን የሚሉት አቶ ዳንኤል፤ የስርጭት መጠኑ ግን ሊያዘናጋን አይገባም ይላሉ። "መዘናጋቱ እና ቸልተኝነቱ በዚህ መንግድ የሚቀጥል ከሆነ፤ እንደ አገር ያልተገባ ዋጋ ሊያስከፍለን ይችላል" የሚሉት አቶ ዳንኤል፤ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ የልሆኑ ተቋማት እንዲሁም የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የድርሻቸውን መወጣት አለባቸው ይላሉ። ኮቪድ እና ኤችአይቪ የኮሮናቫይረስ መከሰት ኤችአይቪ በደማቸው በሚገኝባቸው እና መድሃኒት በሚወስዱ ሰዎች ላይ ተጽእኖ ፈጥሯል ይላሉ። "ትልቁ ችግር የነበረው ስነ-ልቦናዊ ተጽእኖ ነው" የሚሉት አቶ ዳንኤል፤ ኮቪድ-19 ተጓዳኝ በሽታ ያለባቸውን ሰዎችን ይጎዳል በሚል በስጋት ወደ ጤና ተቋም ያለመምጣት ሁኔታዎች እንደነበሩ ይናገራሉ። ከዚህ በተጨማሪም የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በማሰብ በመንግሥት የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሉን ተከትሎ ከሚኖሩበት ርቀው መድሃኒት ይወስዱ የነበሩ ሰዎች የትራንስፖርት አማራጭ ባለማግኘት መድሃኒታቸውን መውሰድ የማይችሉት ሁኔታ ነበር። "ለምሳሌ አዲስ አበባ ላይ ያለ ሰው አዳማ ሄዶ የሚወስድ ከሆነ . . . መንቀሳቀሱ ሲቆም መድሃኒቱን በትክክል ለመወሰድ መቸገር ነበር" ብለዋል። | በኢትዮጵያ የኤችአይቪ ቫይረስ ስርጭት መቀነሱ ተገለጸ በኢትዮጵያ በየዓመቱ በኤችአይቪ ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መቀነሱ ተገለጸ። በፌደራል ኤችአይቪ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ጽህፈት ቤት የሕዝብ ግነኙነት እና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዳንኤል በስረ በኢትዮጵያ የኤችአይቪ ቫይረስ ስርጭት መቀነሱን ጥናቶች ያመላክታሉ ብለዋል። በአገር አቀፍ ደረጃ አጠቃላይ የቫይረሱ የስርጭት ምጣኔ 0.86 በመቶ መሆኑን አቶ ዳንኤል ያስረዳሉ። "ይሄ ማለት በመላው አገሪቱ፤ በሁሉም ማሕበረሰብ ክፍል ተመሳሳይ ነው ማለት አይደለም። በገጠር እና በከተማ የስርጭት ምጣኔው የተለያየ ነው" የሚሉት ዳንኤል፤ በጋምቤላ ክልል እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስርጭት ምጣኔው ከፍተኛ መሆኑን ይናገራሉ። ዳንኤል የቫይረሱ ስርጭት በጋምቤላ 4.1 በመቶ እንዲሁም በአዲስ አበባ ከ3 በመቶ በላይ መሆኑን ያስረዳሉ። 3 በመቶ ምጣኔ ምን ማለት እንደሆን ሲያስረዱ፤ በቀላል ቋንቋ ከመቶ ሰዎች ሦስት ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው አለ ማለት ነው ይላሉ። በሶማሌ፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች፣ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች የስርጭት ምጣኔው ከ1 በመቶ በታች መሆኑን ይናገራሉ። የሶማሌ ክልል 0.01 በመቶ አነስተኛ የቫይረሱ ስርጭት የሚገኘበት ክልል መሆኑን ይናገራሉ። በአገሪቱ ክልሎች መካከል ከፍተኛ የሆነ የቫይረሱ ስርጭት ልዩነት እንዴት ሊፈጠረ ቻለ? ተብለው የተጠየቁት አቶ ዳንኤል፤ ለዚህ ጥያቄ ቁርጥ ያለ ምላሽ ለመስጠት በዝርዝር ጥናት ላይ መመርኮዝ እንደሚያስፈልግ ገልጸው፤ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል የተሰራ ሥራ ልዩነት ፈጥሮ ሳይሆን ዋናው ምክንያት ከባህል እና ሃይማኖታዊ ጉዳይ ጋር ሊያያዝ ይችላል ይላሉ። አቶ ዳንኤል ከዓመታት በፊት በኢትዮጵያ አጠቃላይ የቫይረሱ ስርጭት ምጣኔ ከ6 በመቶ በላይ ደርሶ የሚያውቅበት አጋጣሚ እንዳለ ይናገራሉ። በከተሞች አካባቢ ደግሞ የስርጭት ምጣኔው እስከ 10 በመቶ ስለመድረሱ ተመዝግቦ ነበር ይላሉ። "በአንድ አገር አጠቃላይ የስርጭት ምጣኔው ከ1 በመቶ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫይረሱ ስርጭት ወረርሽኝ ነው የሚባለው" የሚሉት አቶ ዳንኤል፤ ምንም እንኳ በአገር ደረጃ የስርጭት ምጣኔው ከ1 በመቶ በታች ቢሆንም የስርጭት መጠኑ ከ1 በመቶ በላይ የሆነባቸው ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች መኖራቸውን ይናገራሉ። የቫይረሱ ስርጭት በጾታ ተከፍሎ ሲታይ ደግሞ፤ ሴቶች ከወንዶች በላይ ተጋላጭ መሆናቸውን ይናገራሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ በሽታውን በመከላከል ረገድ የሚሰሩ ሥራዎች መቀነሳቸውን ዳንኤል አስረድተዋል። መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ቀደም ሲል ሲሰሩ በነበሩበት ልክ ቫይረሱን የመከላከል ሥራ እየሰሩ አይደለም ይላሉ። ለዚህም ምክንያቱ የስርጭቱ መጠን በየዓመቱ መቀነስ በማሳየቱ እና በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ከመከላከሉ ይልቅ ሕክምናው ላይ ትኩረት በመሰጠቱ ነው ይላሉ። በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች በአሁኑ ወቅት ከ622 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች በኢትዮጵያ የኤችአይቪ ቫይረስ በደማቸው ይገኛል። ከእነዚህ መካከል ወደ 500 ሺህ የሚሆኑ ጸረ-ኤችአይቪ መድሃኒት እየወሰዱ እንደሚገኙ ጥናቶች ያሳያሉ ብለዋል ዳንኤል። በየዓመቱ ከ11 ሺህ በላይ አዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች አሉ። "ይህን የከፋ የሚያደርገው ከእነዚህ ውስጥ 67 በመቶ ድርሻ የሚይዙት እድሜያቸው ከ30 ዓመት በታች የሆኑ ወጣቶች መሆናቸው ነው" ይላሉ ዳንኤል። የቫይረሱን ስርጭት መከላከል አስፈላጊነትን ከሚያረጋግጡት መካከል አንዱ በበሽታው የሚያዙት አብዛኛዎቹ ወጣቶች መሆናቸው ነው ይላሉ። "አምራች ኃይል ነው። እንደ ሀገር ተስፋ የሚጣልበት ነው። በዚህ እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ወጣቶች ላይ የስርጭት ምጣኔው ከፍ ብሎ መታየቱ እንደ አገር አደጋ ውስጥ እንዳለን የሚያሳይ ነው" ብለዋል። ዳንኤል፤ ሴተኛ አዳሪዎች፣ ባሎቻቸውን በሞት ያጡ እና ትዳራቸውን የፈቱ ሴቶች ዘንድ የቫይረሱ ስርጭት መጠን ከፍተኛ ነው ይላሉ። "በሴተኛ አዳሪዎች የስርጭት ምጣኔው 18 በመቶ ነው። ባሎቻቸውን በሞት ያጡ እና ትዳራቸውን የፈቱ ሴቶች አካባቢ የስርጭት ምጣኔው ወደ 20 በመቶ ሆኖ እናያለን" ይላሉ። ሕይወታቸው የሚያልፍ ሰዎች ከ12 ሺህ ባለይ ሰዎች ደግሞ በየዓመቱ በኤድስ እና ተያያዥ በሽታዎች ሕይወታቸው እያለፈ ነው። በአገሪቱ ቫይረሱ በደማቸው ይገኘባቸዋል ከተባለው ከ622 ሺህ ባለይ ሰዎች 61 በመቶውን የሚይዙት ሴቶች ናቸው ይላሉ። በአሁኑ ሰዓት የስርጭት ምጣኔው ከ1 በታች መሆኑ የስርጭት መጠኑ አነስተኛ እንደሆነ ነው የሚያሳየን የሚሉት አቶ ዳንኤል፤ የስርጭት መጠኑ ግን ሊያዘናጋን አይገባም ይላሉ። "መዘናጋቱ እና ቸልተኝነቱ በዚህ መንግድ የሚቀጥል ከሆነ፤ እንደ አገር ያልተገባ ዋጋ ሊያስከፍለን ይችላል" የሚሉት አቶ ዳንኤል፤ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ የልሆኑ ተቋማት እንዲሁም የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የድርሻቸውን መወጣት አለባቸው ይላሉ። ኮቪድ እና ኤችአይቪ የኮሮናቫይረስ መከሰት ኤችአይቪ በደማቸው በሚገኝባቸው እና መድሃኒት በሚወስዱ ሰዎች ላይ ተጽእኖ ፈጥሯል ይላሉ። "ትልቁ ችግር የነበረው ስነ-ልቦናዊ ተጽእኖ ነው" የሚሉት አቶ ዳንኤል፤ ኮቪድ-19 ተጓዳኝ በሽታ ያለባቸውን ሰዎችን ይጎዳል በሚል በስጋት ወደ ጤና ተቋም ያለመምጣት ሁኔታዎች እንደነበሩ ይናገራሉ። ከዚህ በተጨማሪም የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በማሰብ በመንግሥት የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሉን ተከትሎ ከሚኖሩበት ርቀው መድሃኒት ይወስዱ የነበሩ ሰዎች የትራንስፖርት አማራጭ ባለማግኘት መድሃኒታቸውን መውሰድ የማይችሉት ሁኔታ ነበር። "ለምሳሌ አዲስ አበባ ላይ ያለ ሰው አዳማ ሄዶ የሚወስድ ከሆነ . . . መንቀሳቀሱ ሲቆም መድሃኒቱን በትክክል ለመወሰድ መቸገር ነበር" ብለዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59515396 |
5sports
| አሜሪካ አበረታች መድኃኒት የሚጠቀሙ ስፖርተኞችን በወንጀል ልትከስ ነው | የአሜሪካ ምክር ቤት ሴኔት በዓለም አቀፍ የስፖርት ውድድሮች ላይ የአበረታች መድኃኒት የተጠቀመ ማንኛውንም ሰው የወንጀል ክስ እንዲመሰረትበት የሚያስችልን ረቂቅ ህግ አፀደቀ። የአበረታች መድኃኒት ጥሰቶችን ባጋለጠው በሩሲያዊው ግሪጎሪ ሮድቼንኮቭ ስም የሮድቼንኮቭ ፀረ-አበረታች አዋጅ ተብሎ የተሰየመ ሲሆን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሲፈርሙበት ሕግ ይሆናል ተብሏል፡፡ የአሜሪካ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ ዋና ኃላፊ ትራቪስ ታይጋርት ውሳኔውን “ንፁህ ስፖርት ለመፍጠር በሚደረገው ትግል ትልቅ” ነው ሲሉ ገልጸውታል፡፡ የዓለም ፀረ-አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ (ዋዳ) ግን ጉዳዩ እንዳሳሰበው አስታውቋል። ቀደም ሲል በተወካዮች ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ ከፀደቀ በኋላ ሰኞ ዕለት ሴኔቱ ያለተቃውሞ ያፀደቀው ሕግ ስፖርተኞችን፣ ስፖንሰር አድራጊዎችን እና ከአበረታች መድኃኒት መስፋፋት ጀርባ ያሉት ላይ አሜሪካ ክስ መመስረት ያስችላታል። ሕጉ ቀድም ሲል በዋዳ ቅጣት ካልተላፈባቸውን ስፖርተኞች ይልቅ አሰልጣኞች፣ ወኪሎች፣ ሥራ አስኪያጆች እና ባለሥልጣናትን ላይ ዒላማ ያደርጋል፡፡ ህጉን ተከላለፉ አካላት እስከ አንድ ሚሊዮን ዶላር ወይም እስከ 10 ዓመት የሚደርስ የእስር ቅጣትን ይጠብቃቸዋል ተብሏል፡፡ “ሕጉ ንፁህ ስፖርተኞችን ለመከላከል እንዲሁም ስፖርትን፣ ስፖንሰሮችን የሚያታልሉ እና ስፖርተረኞችን የሚጎዱ ዓለም አቀፍ የአበረታች መድኃኒት አሰራጮችን ተጠያቂ ያደርጋል” ብለዋል ታይጋርት፡፡ “በዓለም ዙሪያ ለንጹህ ስፖርት ለሚደረገው ትግል ታላቅ ቀን ነው። በቅርቡ ህግ ሆኖ ለማየት እና ለንጹህ ስፖርት በመፍጠር በኩል ለውት ያመጣል ብለን ተስፋ እናደርጋለን” ብለዋል። ዋዳ በበኩሉ ዓለም አቀፋዊ የፀረ-አበረታች መድኃኒት እርምጃዎችን ሊያዳክም ይችላል በሚል “ሥጋቶች” እንዳሉት ገልጿል። ሕጉ በረቂቁ ውስጥ ያካተታቸውን የአሜሪካ ፕሮፌሽናል እና የኮሌጅ ስፖርተኞችን ሳያካትት ለምን ቀረ ሲል ጠይቋል፡፡ “ለአሜሪካውያን ስፖርቶች ጥሩ ካልሆነ ለሌላው ዓለም ጥሩ የሆነው ለምንድነው?” ሲልም ያክላል። በተጨማሪ ይህ ረቂቅ ሕጉ መረጃ ሰጪዎች ወደ ፊት እንዳይመጡ ሊያግደው ይችላል የሚል ስጋት እንዳለው ዋዳ ገልጿል። ታይጋር ግን ህጉ “መረጃ ሰጪዎችን ይጠብቃል” ብሏል፡፡ የቀድሞው የሞስኮ የፀረ-አበረታች መድኃኒቶች ቤተ ሙከራ ኃላፊ የነበረው ሮድቼንኮቭ እ.ኤ.አ. በ2015 በሩሲያ መንግስት የተደገፈውን አበረታች መድኃኒት አጠቃቀም ዝርዝር ማስረጃ ይዘው ከሩስያ ተሰደዋል፡፡ በዚህ ምክንያትም ሩሲያ ከ2018ቱ ክረምት ኦሎምፒክ ታግዳለች። | አሜሪካ አበረታች መድኃኒት የሚጠቀሙ ስፖርተኞችን በወንጀል ልትከስ ነው የአሜሪካ ምክር ቤት ሴኔት በዓለም አቀፍ የስፖርት ውድድሮች ላይ የአበረታች መድኃኒት የተጠቀመ ማንኛውንም ሰው የወንጀል ክስ እንዲመሰረትበት የሚያስችልን ረቂቅ ህግ አፀደቀ። የአበረታች መድኃኒት ጥሰቶችን ባጋለጠው በሩሲያዊው ግሪጎሪ ሮድቼንኮቭ ስም የሮድቼንኮቭ ፀረ-አበረታች አዋጅ ተብሎ የተሰየመ ሲሆን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሲፈርሙበት ሕግ ይሆናል ተብሏል፡፡ የአሜሪካ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ ዋና ኃላፊ ትራቪስ ታይጋርት ውሳኔውን “ንፁህ ስፖርት ለመፍጠር በሚደረገው ትግል ትልቅ” ነው ሲሉ ገልጸውታል፡፡ የዓለም ፀረ-አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ (ዋዳ) ግን ጉዳዩ እንዳሳሰበው አስታውቋል። ቀደም ሲል በተወካዮች ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ ከፀደቀ በኋላ ሰኞ ዕለት ሴኔቱ ያለተቃውሞ ያፀደቀው ሕግ ስፖርተኞችን፣ ስፖንሰር አድራጊዎችን እና ከአበረታች መድኃኒት መስፋፋት ጀርባ ያሉት ላይ አሜሪካ ክስ መመስረት ያስችላታል። ሕጉ ቀድም ሲል በዋዳ ቅጣት ካልተላፈባቸውን ስፖርተኞች ይልቅ አሰልጣኞች፣ ወኪሎች፣ ሥራ አስኪያጆች እና ባለሥልጣናትን ላይ ዒላማ ያደርጋል፡፡ ህጉን ተከላለፉ አካላት እስከ አንድ ሚሊዮን ዶላር ወይም እስከ 10 ዓመት የሚደርስ የእስር ቅጣትን ይጠብቃቸዋል ተብሏል፡፡ “ሕጉ ንፁህ ስፖርተኞችን ለመከላከል እንዲሁም ስፖርትን፣ ስፖንሰሮችን የሚያታልሉ እና ስፖርተረኞችን የሚጎዱ ዓለም አቀፍ የአበረታች መድኃኒት አሰራጮችን ተጠያቂ ያደርጋል” ብለዋል ታይጋርት፡፡ “በዓለም ዙሪያ ለንጹህ ስፖርት ለሚደረገው ትግል ታላቅ ቀን ነው። በቅርቡ ህግ ሆኖ ለማየት እና ለንጹህ ስፖርት በመፍጠር በኩል ለውት ያመጣል ብለን ተስፋ እናደርጋለን” ብለዋል። ዋዳ በበኩሉ ዓለም አቀፋዊ የፀረ-አበረታች መድኃኒት እርምጃዎችን ሊያዳክም ይችላል በሚል “ሥጋቶች” እንዳሉት ገልጿል። ሕጉ በረቂቁ ውስጥ ያካተታቸውን የአሜሪካ ፕሮፌሽናል እና የኮሌጅ ስፖርተኞችን ሳያካትት ለምን ቀረ ሲል ጠይቋል፡፡ “ለአሜሪካውያን ስፖርቶች ጥሩ ካልሆነ ለሌላው ዓለም ጥሩ የሆነው ለምንድነው?” ሲልም ያክላል። በተጨማሪ ይህ ረቂቅ ሕጉ መረጃ ሰጪዎች ወደ ፊት እንዳይመጡ ሊያግደው ይችላል የሚል ስጋት እንዳለው ዋዳ ገልጿል። ታይጋር ግን ህጉ “መረጃ ሰጪዎችን ይጠብቃል” ብሏል፡፡ የቀድሞው የሞስኮ የፀረ-አበረታች መድኃኒቶች ቤተ ሙከራ ኃላፊ የነበረው ሮድቼንኮቭ እ.ኤ.አ. በ2015 በሩሲያ መንግስት የተደገፈውን አበረታች መድኃኒት አጠቃቀም ዝርዝር ማስረጃ ይዘው ከሩስያ ተሰደዋል፡፡ በዚህ ምክንያትም ሩሲያ ከ2018ቱ ክረምት ኦሎምፒክ ታግዳለች። | https://www.bbc.com/amharic/news-54978864 |
3politics
| የሱዳን መፈንቅለ መንግሥት፡ ቢያንስ ሦስት ተቃዋሚዎች ሲገደሉ በርካቶች ለጉዳት ተዳረጉ | በሱዳን ወታደራዊ ኃይሉ ሥልጣን መቆጣጠሩን ተቃውመው አደባባይ በወጡ ተቃዋሚዎች ላይ ወታደሮች በተኮሱት ተኩስ ቢያንስ ሦስት ሰዎች ሲገደሉ 80 የሚሆኑ ሰዎች ለጉዳት መዳረጋቸው ተዘገበ። ተቃዋሚዎቹ አደባባይ የወጡት ወታደራዊ ኃይሉ የሲቪል አስተዳደሩን ከበተነ፣ የፖለቲካ መሪዎችን ካሰረ እና በአገሪቷ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ካወጀ በኋላ ነው። ወታደሮች የተቃውሞውን አስተባባሪዎች ለመያዝ በዋና መዲናዋ ካርቱም የቤት ለቤት አሰሳ እያደረጉ እንደሆነም ተነግሯል። በሱዳን የተካሄደው መፈንቅለ መንግሥት በዓለም ዙሪያ የተወገዘ ሲሆን አሜሪካ ለእርዳታ የምትሰጠውን 700 ሚሊየን ዶላር አቁማለች። መፈንቅለ መንግሥቱን የመሩት ጀነራል አብደል ፈታህ ቡርሃን በአገሪቷ ለተፈጠረው ፖለቲካዊ ቀውስ ተጠያቂ ተደርገዋል። የሲቪል መሪዎችና አቻቸው የወታደራዊ መሪዎች ከሁለት ዓመት በፊት አገሪቷን ለረዥም ጊዜ ሲመሩ የነበሩት ኦማር አልበሽር ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ የፖለቲካ ሽኩቻ ውስጥ ገብተዋል። ሰኞ ምሽት በርካታ ቁጥር ያላቸው ተቃዋሚዎች በካርቱምና በሌሎች ከተሞች ጎዳናዎች ላይ በመውጣት የሲቪል አስተዳደሩ እንዲመለስ መጠየቃቸውን የቢቢሲ አረብኛ ዘጋቢ መሀመድ ኦስማን ዘግቧል። አንድ ጉዳት የደረሰበት ተቃዋሚ ከወታደራዊ ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውጭ እግሩ ላይ መመታቱን ለቢቢሲ የተናገረ ሲሆን ሌላኛው ተቃዋሚም ጦሩ መጀመሪያ ላይ ቦንብ እንደወረወረ እና ከዚያም በቀጥታ ጥይት መተኮሱን ተናግሯል። " ሁለት ሰዎች ሞተዋል ፤ ይህንንም በዐይኔ ተመልክቻለሁ" ብሏል አል ታይብ መሀመድ አህመድ። የሱዳን ሐኪሞች ማሕበር እና የማስታወቂያ ሚኒስቴር የተተኮሰው ከጦሩ መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውጭ መሆኑን በፌስቡክ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። በከተማዋ ካሉ ሆስፒታሎች የወጡ ምሥሎችም ሰዎች ልብሳቸው በደም ተነክሮ እና በርካቶች ጉዳት ደርሶባቸው ያሳያሉ። ተቃዋሚዎች የመኪና ጎማዎችን በማቃጠልና ድንጋይ በማስቀመጥ መንገድ ዘግተዋል። በርካታ ሴቶችም "ወታደራዊ አገዛዝ አንፈልግም" በማለት ድምጻቸውን አሰምተዋል። የከተማዋ አውሮፕላን ማረፊያም የተዘጋ ሲሆን ዓለም አቀፍ በረራዎችም ታግደዋል። ኢንተርኔትና የስልክ መስመሮችም ተዘግተዋል። የሴንትራል ባንክ ሰራተኞች በመላ አገሪቷ አድማ መትተዋል። ሒሞችም በጦሩ በሚመሩ ሆስፒታሎች ከድንገተኛ ሕክምና በስተቀር አንሰራም ብለዋል። የዓለም መሪዎች ጦሩ አገሪቷን መቆጣጠሩን ተከትሎ ስጋታቸውን ገልጸዋል። አሜሪካ በሱዳን በቁም እስር ላይ ያሉና የት እንዳሉ የማይታወቁ የፖለቲካ መሪዎች እንዲፈቱ በመጠየቅ ዩናይትድ ኪንግደምን፣ አውሮፓ ሕብረትን ፣ የተባበሩት መንግሥታት እና ሱዳን አባል የሆነችበትን የአፍሪካ ሕብረትን ተቀላቅላለች። በቤት ውስጥ እስር እንደሚገኙ ከተነገረው የፖለቲካ መሪዎች መካከል ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ እና ባለቤታቸው እንዲሁም የካቢኔ አባላቶቻቸው እና ሌሎች የሲቪል መሪዎች ይገኙበታል። የቢቢሲ ዘጋቢ እንዳለው ሰኞ ጠዋት ልዩ የደህንነት አባላት ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቤት በመሄድ ሃምዶክ በመፈንቅለ መንግሥቱ እንዲስማሙ ሞክረው የነበሩ ቢሆንም እርሳቸው ግን ሳይስማሙ ቀርተዋል። ሱዳን እአአ 2019 አገሪቷን ለረዥም ጊዜ የመሩት ኦማር አል ባሽር ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ የሲቪልና የወታደራዊ መሪዎች ሥልጣን በመጋራት ስምምነት አገሪቷን እየመሩ ነበር። ስምምነቱ አገሪቷን ወደ ዲሞክራሲ ለማሸጋገር ያለመ ቢሆንም ቀደም ብሎ በርካታ መፈንቅለ ሙከራዎች ተደርገዋል። ለመጨረሻ ጊዜ የተደረገው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ የተካሄደውም ከአንድ ወር በፊት ነበር። የሥልጣን መጋራት ስምምነቱን መሪ የነበሩት ጀነራል አብደል ፈታህ አልቡርሃን የአሁንን መፈንቅለ መንግሥት የመሩ ሲሆን መፈንቅለ መንግሥቱ በፖለቲካ ሽኩቻ ምክንያት የተፈጠረውን "የአብዮቱን አካሄድ ለማስተካከል" አስፈላጊ ነበር ብለዋል። | የሱዳን መፈንቅለ መንግሥት፡ ቢያንስ ሦስት ተቃዋሚዎች ሲገደሉ በርካቶች ለጉዳት ተዳረጉ በሱዳን ወታደራዊ ኃይሉ ሥልጣን መቆጣጠሩን ተቃውመው አደባባይ በወጡ ተቃዋሚዎች ላይ ወታደሮች በተኮሱት ተኩስ ቢያንስ ሦስት ሰዎች ሲገደሉ 80 የሚሆኑ ሰዎች ለጉዳት መዳረጋቸው ተዘገበ። ተቃዋሚዎቹ አደባባይ የወጡት ወታደራዊ ኃይሉ የሲቪል አስተዳደሩን ከበተነ፣ የፖለቲካ መሪዎችን ካሰረ እና በአገሪቷ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ካወጀ በኋላ ነው። ወታደሮች የተቃውሞውን አስተባባሪዎች ለመያዝ በዋና መዲናዋ ካርቱም የቤት ለቤት አሰሳ እያደረጉ እንደሆነም ተነግሯል። በሱዳን የተካሄደው መፈንቅለ መንግሥት በዓለም ዙሪያ የተወገዘ ሲሆን አሜሪካ ለእርዳታ የምትሰጠውን 700 ሚሊየን ዶላር አቁማለች። መፈንቅለ መንግሥቱን የመሩት ጀነራል አብደል ፈታህ ቡርሃን በአገሪቷ ለተፈጠረው ፖለቲካዊ ቀውስ ተጠያቂ ተደርገዋል። የሲቪል መሪዎችና አቻቸው የወታደራዊ መሪዎች ከሁለት ዓመት በፊት አገሪቷን ለረዥም ጊዜ ሲመሩ የነበሩት ኦማር አልበሽር ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ የፖለቲካ ሽኩቻ ውስጥ ገብተዋል። ሰኞ ምሽት በርካታ ቁጥር ያላቸው ተቃዋሚዎች በካርቱምና በሌሎች ከተሞች ጎዳናዎች ላይ በመውጣት የሲቪል አስተዳደሩ እንዲመለስ መጠየቃቸውን የቢቢሲ አረብኛ ዘጋቢ መሀመድ ኦስማን ዘግቧል። አንድ ጉዳት የደረሰበት ተቃዋሚ ከወታደራዊ ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውጭ እግሩ ላይ መመታቱን ለቢቢሲ የተናገረ ሲሆን ሌላኛው ተቃዋሚም ጦሩ መጀመሪያ ላይ ቦንብ እንደወረወረ እና ከዚያም በቀጥታ ጥይት መተኮሱን ተናግሯል። " ሁለት ሰዎች ሞተዋል ፤ ይህንንም በዐይኔ ተመልክቻለሁ" ብሏል አል ታይብ መሀመድ አህመድ። የሱዳን ሐኪሞች ማሕበር እና የማስታወቂያ ሚኒስቴር የተተኮሰው ከጦሩ መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውጭ መሆኑን በፌስቡክ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። በከተማዋ ካሉ ሆስፒታሎች የወጡ ምሥሎችም ሰዎች ልብሳቸው በደም ተነክሮ እና በርካቶች ጉዳት ደርሶባቸው ያሳያሉ። ተቃዋሚዎች የመኪና ጎማዎችን በማቃጠልና ድንጋይ በማስቀመጥ መንገድ ዘግተዋል። በርካታ ሴቶችም "ወታደራዊ አገዛዝ አንፈልግም" በማለት ድምጻቸውን አሰምተዋል። የከተማዋ አውሮፕላን ማረፊያም የተዘጋ ሲሆን ዓለም አቀፍ በረራዎችም ታግደዋል። ኢንተርኔትና የስልክ መስመሮችም ተዘግተዋል። የሴንትራል ባንክ ሰራተኞች በመላ አገሪቷ አድማ መትተዋል። ሒሞችም በጦሩ በሚመሩ ሆስፒታሎች ከድንገተኛ ሕክምና በስተቀር አንሰራም ብለዋል። የዓለም መሪዎች ጦሩ አገሪቷን መቆጣጠሩን ተከትሎ ስጋታቸውን ገልጸዋል። አሜሪካ በሱዳን በቁም እስር ላይ ያሉና የት እንዳሉ የማይታወቁ የፖለቲካ መሪዎች እንዲፈቱ በመጠየቅ ዩናይትድ ኪንግደምን፣ አውሮፓ ሕብረትን ፣ የተባበሩት መንግሥታት እና ሱዳን አባል የሆነችበትን የአፍሪካ ሕብረትን ተቀላቅላለች። በቤት ውስጥ እስር እንደሚገኙ ከተነገረው የፖለቲካ መሪዎች መካከል ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ እና ባለቤታቸው እንዲሁም የካቢኔ አባላቶቻቸው እና ሌሎች የሲቪል መሪዎች ይገኙበታል። የቢቢሲ ዘጋቢ እንዳለው ሰኞ ጠዋት ልዩ የደህንነት አባላት ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቤት በመሄድ ሃምዶክ በመፈንቅለ መንግሥቱ እንዲስማሙ ሞክረው የነበሩ ቢሆንም እርሳቸው ግን ሳይስማሙ ቀርተዋል። ሱዳን እአአ 2019 አገሪቷን ለረዥም ጊዜ የመሩት ኦማር አል ባሽር ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ የሲቪልና የወታደራዊ መሪዎች ሥልጣን በመጋራት ስምምነት አገሪቷን እየመሩ ነበር። ስምምነቱ አገሪቷን ወደ ዲሞክራሲ ለማሸጋገር ያለመ ቢሆንም ቀደም ብሎ በርካታ መፈንቅለ ሙከራዎች ተደርገዋል። ለመጨረሻ ጊዜ የተደረገው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ የተካሄደውም ከአንድ ወር በፊት ነበር። የሥልጣን መጋራት ስምምነቱን መሪ የነበሩት ጀነራል አብደል ፈታህ አልቡርሃን የአሁንን መፈንቅለ መንግሥት የመሩ ሲሆን መፈንቅለ መንግሥቱ በፖለቲካ ሽኩቻ ምክንያት የተፈጠረውን "የአብዮቱን አካሄድ ለማስተካከል" አስፈላጊ ነበር ብለዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59042602 |
5sports
| ኢትዮጵያውያኑ የሴቶችና የወንዶች የ5ሺህ ሜትር ውድድር ክብረ ወሰንን ሰበሩ | ኢትዮጵያውያኑ እጅጋየሁ ታዬ እና በሪሁ አረጋዊ የዓለም የአምስት ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድር ክብረ ወሰን መስበራቸውን የዓለም አትሌቲክስ የበላይ አካል አስታወቀ። ትናንት አርብ በፈረንጆቹ አቆጣጠር የዓመቱ የመጨረሻ ዕለት በአውሮፓዊቷ ስፔን ባርሴሎና ከተማ በኩርሳ ዴልስ ናሶስ በተካሄደ ውድድር ነው ሁለቱ ኢትዮጵያውያን ክብረ ወሰን የሰበሩት። በሴቶቹ እጅጋየሁ ታዬ ርቀቱን በ14 ደቂቃ ከ19 ሰከንድ እንዲሁም በወንዶቹ በሪሁ አረጋዊ በ12 ደቂቃ ከ49 ሰከንድ በማጣናቀቅ ነው ቀደም ሲል በርቀቱ የተያዙትን ክብረ ወሰኖች ያሻሻሉት። በሴቶቹ የአምስት ኪሎ ሜትር ርቀት የዓለምን ክብረ ወሰን ያሻሻለችው እጅጋየሁ ታዬ ቀደም ሲል ከነበረው ሰዓት ላይ በ24 ሰከንዶች ቀድማ ገብታለች። በሪሁ አረጋዊም ክብረ ወሰኑን ያሻሻለው በሁለት ሰከንዶች መሆኑን የዓለም አትሌቲስ አስታውቋል። የዓለም አትሌቲክስ በድረ ገጹ ላይ ባወጣው መረጃ የ21 ዓመቷ እጅጋየሁ ታዬ የኢትዮጵያ የ3ሺህ ሜትር ርቀት ባለ ክብረ ወሰን መሆኗን አስታውሶ፤ ክብረ ወሰኑን አስክታሻሽል ድረስም በአምስት ሺህ ሜትር ውድድር የዓለም ሁለተኛዋ ፈጣን ሯጭ ሆና ቆይታለች ብሏል። እጅጋየሁ የአምስት ኪሎ ሜትር ክብረ ወሰንን ያሻሻለችበት የባርሴሎናው ውድድር በሩጫ ዘመኗ ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የጎዳና ላይ የውድድር ተሳትፎዋ ነው። የሃያ ዓመቱ በሪሁ አረጋዊ በኅዳር ወር ሊል ውስጥ በተደረገው ተመሳሳይ ውድድር ላይ በኬንያዊው ጆሽዋ ቼፕቴጌ ተይዞ የቆየውን ክብረ ወሰን ለመስበር በአንድ ሰከንድ ተቃርቦ ነበር። ነገር ግን የፈረንጆቹ 2021 ከመጠናቀቁ በመጨረሻዋ ዕለት በመጨረሻው ውድድር በሪሁ ከወር በፊት ተቃርቦ የነበረውን ክብረ ወሰን ለማሻሻል ችሏል። በተለመደው የዓለም አትሌቲክስ አሰራር መሠረት ይህ በሁለቱ ኢትዮጵየውያን አትሌቶች የተሻሻለው ክብረ ወሰን የሚጸድቀው አስፈላጊው የማጣራት ሂደት ከተካሄደ በኋላ ነው። | ኢትዮጵያውያኑ የሴቶችና የወንዶች የ5ሺህ ሜትር ውድድር ክብረ ወሰንን ሰበሩ ኢትዮጵያውያኑ እጅጋየሁ ታዬ እና በሪሁ አረጋዊ የዓለም የአምስት ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድር ክብረ ወሰን መስበራቸውን የዓለም አትሌቲክስ የበላይ አካል አስታወቀ። ትናንት አርብ በፈረንጆቹ አቆጣጠር የዓመቱ የመጨረሻ ዕለት በአውሮፓዊቷ ስፔን ባርሴሎና ከተማ በኩርሳ ዴልስ ናሶስ በተካሄደ ውድድር ነው ሁለቱ ኢትዮጵያውያን ክብረ ወሰን የሰበሩት። በሴቶቹ እጅጋየሁ ታዬ ርቀቱን በ14 ደቂቃ ከ19 ሰከንድ እንዲሁም በወንዶቹ በሪሁ አረጋዊ በ12 ደቂቃ ከ49 ሰከንድ በማጣናቀቅ ነው ቀደም ሲል በርቀቱ የተያዙትን ክብረ ወሰኖች ያሻሻሉት። በሴቶቹ የአምስት ኪሎ ሜትር ርቀት የዓለምን ክብረ ወሰን ያሻሻለችው እጅጋየሁ ታዬ ቀደም ሲል ከነበረው ሰዓት ላይ በ24 ሰከንዶች ቀድማ ገብታለች። በሪሁ አረጋዊም ክብረ ወሰኑን ያሻሻለው በሁለት ሰከንዶች መሆኑን የዓለም አትሌቲስ አስታውቋል። የዓለም አትሌቲክስ በድረ ገጹ ላይ ባወጣው መረጃ የ21 ዓመቷ እጅጋየሁ ታዬ የኢትዮጵያ የ3ሺህ ሜትር ርቀት ባለ ክብረ ወሰን መሆኗን አስታውሶ፤ ክብረ ወሰኑን አስክታሻሽል ድረስም በአምስት ሺህ ሜትር ውድድር የዓለም ሁለተኛዋ ፈጣን ሯጭ ሆና ቆይታለች ብሏል። እጅጋየሁ የአምስት ኪሎ ሜትር ክብረ ወሰንን ያሻሻለችበት የባርሴሎናው ውድድር በሩጫ ዘመኗ ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የጎዳና ላይ የውድድር ተሳትፎዋ ነው። የሃያ ዓመቱ በሪሁ አረጋዊ በኅዳር ወር ሊል ውስጥ በተደረገው ተመሳሳይ ውድድር ላይ በኬንያዊው ጆሽዋ ቼፕቴጌ ተይዞ የቆየውን ክብረ ወሰን ለመስበር በአንድ ሰከንድ ተቃርቦ ነበር። ነገር ግን የፈረንጆቹ 2021 ከመጠናቀቁ በመጨረሻዋ ዕለት በመጨረሻው ውድድር በሪሁ ከወር በፊት ተቃርቦ የነበረውን ክብረ ወሰን ለማሻሻል ችሏል። በተለመደው የዓለም አትሌቲክስ አሰራር መሠረት ይህ በሁለቱ ኢትዮጵየውያን አትሌቶች የተሻሻለው ክብረ ወሰን የሚጸድቀው አስፈላጊው የማጣራት ሂደት ከተካሄደ በኋላ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/news-59845516 |
5sports
| ለኢትዮጵያውያንና ለአፍሪካውያን ፈር ቀዳጅ ድል ያስመዘገበችው ፋጡማ ሮባ | ፋጡማ ሮባ የመጀመሪያውን የሴቶች ማራቶን ፈር ቀዳጅ ድሏን እ.ኤ.አ. በ1996 በሞሮኮ ማራክሽ ነበር የተቀዳጀችው። በመቀጠልም ከሁለት ወር በኋላ በሮም ማራቶን አሸናፊ ሆነች። ከሮም አሸናፊነት በኋላም በ1996 በአትላንታ አሜሪካ በሚደረገው የኦሊምፒክ ውድድር በ2:26:05 በሆነ ሰዓት አንደኛ በመሆን አጠናቀቀች። በወቅቱ ፋጡማን በመከተል ሁለት ደቂቃ ዘግይተው የሩሲያዋ ቫለንቲና ይጎሮቫና ጃፓናዊቷ ዩኩ አርሞሪ 2ኛና 3ኛ በመሆን ተከታትለው ገብተዋል። ከ1997 እስከ 1999 የተካሄዱ የቦስተን ማራቶን ውድድሮች በተከታታይ ያሸነፈችውን ፋጡማ የ'ቦስተኗ ንግሥት' የሚል ቅጽል ስም አግኝታበታለች። ለአትሌት አበበ ቢቂላ ትልቅ ፍቅር እንደላት የምትናገረው አትሌት ፋጡማ ሮባ "አቤን በደንብ እወደዋለሁ፤ አደንቀዋለሁ። አቤን እኔ ብቻ ሳልሆን መላው ዓለም ያደንቀዋል" ትላለች። ለዓመታት ከአገርና ከአትሌቲክሱ መድረክ ርቃ የቆችው የኦሊምፒኳ ኮከብ አትሌት ፋጡማ ከቢቢሲ ጋር ባደረገችው ቆይታ ስለ ህይወቷ እንዲህ ብላለች። [የተጠቀሱት ዓመታት በሙሉ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ናቸው] ስለ አትሌቲክስ ምንም የማውቀው ነገር የለኝም በ1970 ዓ.ም በአርሲ ዞን ሌሙና ቢልቢሎ ወረዳ፣ ሁሉሌ ካራ በሚባል ስፍራ ተወለድኩ። ገጠር ውስጥ ከአርሶ አደር ቤተሰብ ነው የወጣሁት። ኑሮዬና ትምህርቴም እንደ ማንኛውም የገጠር ልጅ ነበር። በገጠር እንዳደጉት ልጆች ከብቶችን ስጠብቅና ቤተሰብን ስረዳ ስለቆየሁ ቶሎ ትምህርት ቤት አልገባሁም። ትምህርት ቤቱም ከቤተሰቤ ርቆ ስለሚገኝ በደንብ ካደግሁ በኋላ በደርሶ መልስ 14 ኪሎ ሜትር በእግር ተጉዤ እማር ነበር። ያደግኩበት ገጠር ቴሌቪዥንም ሆነ ሬዲዮ አልነበረም። ስለዚህ ስለአትሌቲከስ የማውቀው ነገር አልነበረም። ይሁን እንጂ በትምህርት ቤት ውስጥ እኣወዳደሩ ነጥብ ይይዙልን ነበር። አስተማሪያችን መሃረብ ይዞልን "ማን ቀድሞ ይነካል" እያለ ያወዳድረን ነበር። እኔ ከሴቶች ጋር ተወዳድሬ አሸንፋለሁ። ወንዶችንም ቢያመጡ አሸንፍ ነበር። ከዚያ በኋላ ከትምህርት ቤቴ ተመርጬ በወቅቱ አውራጃ ወደሚባለው፣ ከዚያ ደግሞ ክፍለ አገር ለሚባለው ተወክዬ መወዳደር ጀመርኩኝ። በዚሁ ነው እንግዲህ ወደ አዲስ አበባ መጥቼ የተለያዩ የስፖርት ቡድኖች መኖራቸውን ያወቅኩት። ክፍለ አገርን ወክዬ በተወዳደርኩበት ጊዜ የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ቡድን አይቶኝ ሃጂ ቡልቡላ የሚባለል ሰው ላከብኝ። እርሱም ቡድኑ እንደሚፈልገኝ፣ ትምህርቴንም እንድማር፣ ደሞዝም እንደሚከፍሉኝ ነገረኝ። እኔም ቤተሰቤን ሳማክር ብዙም ደስተኛ ስላልነበሩ ሊከለክሉኝ አሰቡ። ይሁን እንጂ ሃጂን ካዩ በኋላ ፈቀዱልኝ፤ ከዚያም ወደ አዲስ አበባ መጣሁ። በ1994 እኤአ ቤልጂየም አገር ነበርኩኝ። እዚያም በአገር አጭር ውድድሮች ላይ በመሮጥ ተሳተፍኩኝ። ቤልጂየም በቆሁበት ወቅት አንድ ማራቶን የምትሮጥ ሴትን በፓሪስ ማራቶን ለምን ካንቺ ጋር አልሮጥም ብዬ ጠየቅኳት። እርሷም ነይ አብረን እንሂድ አለችኝ። ከዚያም በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1994 በተካሄደው የፓሪስ ማራቶን ሳልዘጋጅ ተወዳደርኩ። ውድድሩ ሲጀመር ከሌሎች አትሌቶች ጋር መሮጥ አቃተኝ። ጥለውኝ ሄዱ፤ ይሁን እንጂ ወደ 35ኛው ኪሎ ሜትር ላይ ደረስኩባቸው። ከእነርሱ ጋር ግን መቀጠል አልቻልኩም ጥለውኝ ሄዱ። በጣም ደክሞኝ ስለነበር ውሃ ጠጣሁ። ውሃውም ሆዴን ወጥሮ ያዘኝ። ውድድሩንም ብጨርስም ሁለተኛ አልሮጥም ብዬ ነበር። ወደ አገር ቤት ስመለስ ግን ዶ/ር ወልደ መስቀል ኮስትሬ ማራቶን እንድሮጥ ጠየቁኝ። ከዚያ በኋላ ስልጠና ወስጄ እንዴት ማራቶን እንደምሮጥ ተማርኩ። ወደ ሞሮኮ ሄጄም ማራካሽ ላይ ማራቶን ተወዳደርኩ። በ1996 የማራካሽ ማራቶን ላይ ብዙም ስልጠናና ልምምድ ሳላደርግ ነበር የተሳተፍኩት። በውድድሩም 'ቢ ካታጎሪ' የሚባለውን አምጥቼ ተመለስኩ። ከሁለት ወር በኋላ በሮም ማራቶን ተወዳድሬ፣ 'ኤ ካታጎሪ' የሚባለውን ውጤት አምጥቼ በኦሊምፒክ ውድድር ለመሳተፍ የሚያስችለኝን ነጥብ አገኘሁ። በዚሁ ልምምድ አድርጌ በ1996 በተካሄደው የአትላንታ ኦሊምፒክ ለመሳተፍ ሄድኩኝ። ኦሊምፒክ ትልቅ ውድድር ነው። የአትላንታ ኦሊምፒክ ለእኔ ከተሳተፍኩባቸው ሁሉ ትልቁ ውድድር ነበር። ለውድድሩ በበቂ ተዘጋጅቼ ነበር። ግን ፍርሃት በውስጤ ስለነበረ አሸንፋለሁ የሚል ግምት አልነበረኝም። ካሸነፍኩ በኋላ ግን ትልቅ ደስታ ነው የተሰማኝ። አሰልጣኞቼም በውድድሩ ታሸንፋለች ብለው አልጠበቁም ነበረ። በኦሊምፒክ ማራቶን ውድደድር ላይ በማሸነፍ የመጀመሪያዋ ሴት አፍሪካዊት መሆኔ በጣም አስደሰተኝ። የሚረሳም አይደለም። ከአትላንታ በኋላ በ1997፣ 98፣ 99 በቦስተን ማራቶን ውድድሮች በተከታትዬ ለሦስት ጊዜ አሸንፌያለሁ። በ2004 ነበር ሩጫ ያቆምኩት። በዚያ ጊዜ ለመውለድ ብዬ ነበር ሩጫ ያቆምኩት፤ ከዚያ በኋላ ግን አልተመለስኩበትም። አሁን የሁለት ልጆች እናት ነኝ። የመጀመሪያው ልጄ 15 ዓመት ሁለተኛዋ ደግሞ 13 ዓመቷ ናቸው። ሩጫ ካቆምኩ በኋላ ምንም እየሰራሁ አልነበረም። ልጆቼን እያሳደኩ ነበር። ይሁን እንጂ እነርሱ ካደጉልኝ በኋላ አንደንድ ሥራዎችን ለመስራት እያሰብኩ ነው። የአሁኑን አትሌትክስ ብዙም አልከታተልም። ይሁን እንጂ በተለያዩ ውድድሮች ላይ ስመለከት ጠንካራ አትሌቶች አሉ። እኛ ስንገባበት የነበረውንም ሰዓት እያሻሻሉ ነው። ከአሰልጣኞቻቸው ጋር ከተስማሙ እና በደንብ ከሰሩ ከዚህ የበለጠ ነጥብ ማምጣት እንደሚችሉ ተስፋ አደርጋለሁ። | ለኢትዮጵያውያንና ለአፍሪካውያን ፈር ቀዳጅ ድል ያስመዘገበችው ፋጡማ ሮባ ፋጡማ ሮባ የመጀመሪያውን የሴቶች ማራቶን ፈር ቀዳጅ ድሏን እ.ኤ.አ. በ1996 በሞሮኮ ማራክሽ ነበር የተቀዳጀችው። በመቀጠልም ከሁለት ወር በኋላ በሮም ማራቶን አሸናፊ ሆነች። ከሮም አሸናፊነት በኋላም በ1996 በአትላንታ አሜሪካ በሚደረገው የኦሊምፒክ ውድድር በ2:26:05 በሆነ ሰዓት አንደኛ በመሆን አጠናቀቀች። በወቅቱ ፋጡማን በመከተል ሁለት ደቂቃ ዘግይተው የሩሲያዋ ቫለንቲና ይጎሮቫና ጃፓናዊቷ ዩኩ አርሞሪ 2ኛና 3ኛ በመሆን ተከታትለው ገብተዋል። ከ1997 እስከ 1999 የተካሄዱ የቦስተን ማራቶን ውድድሮች በተከታታይ ያሸነፈችውን ፋጡማ የ'ቦስተኗ ንግሥት' የሚል ቅጽል ስም አግኝታበታለች። ለአትሌት አበበ ቢቂላ ትልቅ ፍቅር እንደላት የምትናገረው አትሌት ፋጡማ ሮባ "አቤን በደንብ እወደዋለሁ፤ አደንቀዋለሁ። አቤን እኔ ብቻ ሳልሆን መላው ዓለም ያደንቀዋል" ትላለች። ለዓመታት ከአገርና ከአትሌቲክሱ መድረክ ርቃ የቆችው የኦሊምፒኳ ኮከብ አትሌት ፋጡማ ከቢቢሲ ጋር ባደረገችው ቆይታ ስለ ህይወቷ እንዲህ ብላለች። [የተጠቀሱት ዓመታት በሙሉ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ናቸው] ስለ አትሌቲክስ ምንም የማውቀው ነገር የለኝም በ1970 ዓ.ም በአርሲ ዞን ሌሙና ቢልቢሎ ወረዳ፣ ሁሉሌ ካራ በሚባል ስፍራ ተወለድኩ። ገጠር ውስጥ ከአርሶ አደር ቤተሰብ ነው የወጣሁት። ኑሮዬና ትምህርቴም እንደ ማንኛውም የገጠር ልጅ ነበር። በገጠር እንዳደጉት ልጆች ከብቶችን ስጠብቅና ቤተሰብን ስረዳ ስለቆየሁ ቶሎ ትምህርት ቤት አልገባሁም። ትምህርት ቤቱም ከቤተሰቤ ርቆ ስለሚገኝ በደንብ ካደግሁ በኋላ በደርሶ መልስ 14 ኪሎ ሜትር በእግር ተጉዤ እማር ነበር። ያደግኩበት ገጠር ቴሌቪዥንም ሆነ ሬዲዮ አልነበረም። ስለዚህ ስለአትሌቲከስ የማውቀው ነገር አልነበረም። ይሁን እንጂ በትምህርት ቤት ውስጥ እኣወዳደሩ ነጥብ ይይዙልን ነበር። አስተማሪያችን መሃረብ ይዞልን "ማን ቀድሞ ይነካል" እያለ ያወዳድረን ነበር። እኔ ከሴቶች ጋር ተወዳድሬ አሸንፋለሁ። ወንዶችንም ቢያመጡ አሸንፍ ነበር። ከዚያ በኋላ ከትምህርት ቤቴ ተመርጬ በወቅቱ አውራጃ ወደሚባለው፣ ከዚያ ደግሞ ክፍለ አገር ለሚባለው ተወክዬ መወዳደር ጀመርኩኝ። በዚሁ ነው እንግዲህ ወደ አዲስ አበባ መጥቼ የተለያዩ የስፖርት ቡድኖች መኖራቸውን ያወቅኩት። ክፍለ አገርን ወክዬ በተወዳደርኩበት ጊዜ የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ቡድን አይቶኝ ሃጂ ቡልቡላ የሚባለል ሰው ላከብኝ። እርሱም ቡድኑ እንደሚፈልገኝ፣ ትምህርቴንም እንድማር፣ ደሞዝም እንደሚከፍሉኝ ነገረኝ። እኔም ቤተሰቤን ሳማክር ብዙም ደስተኛ ስላልነበሩ ሊከለክሉኝ አሰቡ። ይሁን እንጂ ሃጂን ካዩ በኋላ ፈቀዱልኝ፤ ከዚያም ወደ አዲስ አበባ መጣሁ። በ1994 እኤአ ቤልጂየም አገር ነበርኩኝ። እዚያም በአገር አጭር ውድድሮች ላይ በመሮጥ ተሳተፍኩኝ። ቤልጂየም በቆሁበት ወቅት አንድ ማራቶን የምትሮጥ ሴትን በፓሪስ ማራቶን ለምን ካንቺ ጋር አልሮጥም ብዬ ጠየቅኳት። እርሷም ነይ አብረን እንሂድ አለችኝ። ከዚያም በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1994 በተካሄደው የፓሪስ ማራቶን ሳልዘጋጅ ተወዳደርኩ። ውድድሩ ሲጀመር ከሌሎች አትሌቶች ጋር መሮጥ አቃተኝ። ጥለውኝ ሄዱ፤ ይሁን እንጂ ወደ 35ኛው ኪሎ ሜትር ላይ ደረስኩባቸው። ከእነርሱ ጋር ግን መቀጠል አልቻልኩም ጥለውኝ ሄዱ። በጣም ደክሞኝ ስለነበር ውሃ ጠጣሁ። ውሃውም ሆዴን ወጥሮ ያዘኝ። ውድድሩንም ብጨርስም ሁለተኛ አልሮጥም ብዬ ነበር። ወደ አገር ቤት ስመለስ ግን ዶ/ር ወልደ መስቀል ኮስትሬ ማራቶን እንድሮጥ ጠየቁኝ። ከዚያ በኋላ ስልጠና ወስጄ እንዴት ማራቶን እንደምሮጥ ተማርኩ። ወደ ሞሮኮ ሄጄም ማራካሽ ላይ ማራቶን ተወዳደርኩ። በ1996 የማራካሽ ማራቶን ላይ ብዙም ስልጠናና ልምምድ ሳላደርግ ነበር የተሳተፍኩት። በውድድሩም 'ቢ ካታጎሪ' የሚባለውን አምጥቼ ተመለስኩ። ከሁለት ወር በኋላ በሮም ማራቶን ተወዳድሬ፣ 'ኤ ካታጎሪ' የሚባለውን ውጤት አምጥቼ በኦሊምፒክ ውድድር ለመሳተፍ የሚያስችለኝን ነጥብ አገኘሁ። በዚሁ ልምምድ አድርጌ በ1996 በተካሄደው የአትላንታ ኦሊምፒክ ለመሳተፍ ሄድኩኝ። ኦሊምፒክ ትልቅ ውድድር ነው። የአትላንታ ኦሊምፒክ ለእኔ ከተሳተፍኩባቸው ሁሉ ትልቁ ውድድር ነበር። ለውድድሩ በበቂ ተዘጋጅቼ ነበር። ግን ፍርሃት በውስጤ ስለነበረ አሸንፋለሁ የሚል ግምት አልነበረኝም። ካሸነፍኩ በኋላ ግን ትልቅ ደስታ ነው የተሰማኝ። አሰልጣኞቼም በውድድሩ ታሸንፋለች ብለው አልጠበቁም ነበረ። በኦሊምፒክ ማራቶን ውድደድር ላይ በማሸነፍ የመጀመሪያዋ ሴት አፍሪካዊት መሆኔ በጣም አስደሰተኝ። የሚረሳም አይደለም። ከአትላንታ በኋላ በ1997፣ 98፣ 99 በቦስተን ማራቶን ውድድሮች በተከታትዬ ለሦስት ጊዜ አሸንፌያለሁ። በ2004 ነበር ሩጫ ያቆምኩት። በዚያ ጊዜ ለመውለድ ብዬ ነበር ሩጫ ያቆምኩት፤ ከዚያ በኋላ ግን አልተመለስኩበትም። አሁን የሁለት ልጆች እናት ነኝ። የመጀመሪያው ልጄ 15 ዓመት ሁለተኛዋ ደግሞ 13 ዓመቷ ናቸው። ሩጫ ካቆምኩ በኋላ ምንም እየሰራሁ አልነበረም። ልጆቼን እያሳደኩ ነበር። ይሁን እንጂ እነርሱ ካደጉልኝ በኋላ አንደንድ ሥራዎችን ለመስራት እያሰብኩ ነው። የአሁኑን አትሌትክስ ብዙም አልከታተልም። ይሁን እንጂ በተለያዩ ውድድሮች ላይ ስመለከት ጠንካራ አትሌቶች አሉ። እኛ ስንገባበት የነበረውንም ሰዓት እያሻሻሉ ነው። ከአሰልጣኞቻቸው ጋር ከተስማሙ እና በደንብ ከሰሩ ከዚህ የበለጠ ነጥብ ማምጣት እንደሚችሉ ተስፋ አደርጋለሁ። | https://www.bbc.com/amharic/news-56156447 |
3politics
| ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ሦስት የተቃዋሚ አባላትን በካቢኔያቸው ውስጥ አካተቱ | ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በአዲሱ ካቢኔያቸው ውስጥ ሦስት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን በሚኒስተርነት እንዲያገለግሉ ለሕዝብ ተወካዮች አቅርበው አስሹመዋል። በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሊቀመንበር አቶ በለጠ ሞላ እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ምክትል ሊቀመንበር አቶ ቀጀላ መርዳሳ በሚኒስትር ተሹመዋል። ፕ/ሮ ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስትር፣ አቶ በለጠ ሞላ የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር፣ እንዲሁም አቶ ቀጀላ መርዳሳ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር በመሆን በጠቅላይ ሚኒስትሩ ካቢኔ ውስጥ ተካተዋል። ኢዜማ ከገዢው ብልጽግና ፓርቲ የቀረበውን የአብረን እንሥራ ጥያቄ አሁን ኢትዮጵያ ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ጥያቄውን ተቀብሎ አብሮ ለመሥራት በአብላጫ ድምጽ መወሰኑን ባሳለፍነው እሁድ አስታውቋል። ኢዜማ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ አራት መቀመጫዎች ያሉት ሲሆን አብን ደግሞ አምስት መቀመጫዎችን ለማሸነፍ ችሏል። በአቶ ዳውድ ኢብሳ በሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ውስጥ በተፈጠረ አለመግባባት ከግንባሩ ተለይቶ በመውጣት በአቶ አራርሳ ቢቂላ የሚመራው ግንባር በምርጫው ባይሳተፍም ምክትሩ በአዲሱ ካቢኔ ውስጥ ተካተዋል። በተመሳሳይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ባለፈው ሳምንት ሥራውን በጀመር ወቅት በከንቲባነት የተሾሙት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ 26 የካቢኔ አባሎቻቸውን አቅርበው ሲያስሾሙ ሁለቱ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን አመራሮችን አካተው ነበር። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅብራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አባል የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሲሾሙ፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ምክትል ሊቀመንበር የሱፍ ኢብራሂም ደግሞ የመንግሥት ንብረት አስተዳደር ባለሥልጣን ሆነው ተሹመዋል። የኦሮሚያ ክልልም ከሳምንት በፊት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀመንበር የሆኑትን አቶ አራርሳ ቢቂላን የቢሮ ኃላፊ አድርጎ የሾመ ሲሆን የአማር ክልልም ከተቃዋሚዎቹ አብንና ከአዴኃን ሁለት ሰዎችን በቢሮ ኃላፊነት ሹመት ሰጥተዋል። ከተፎካካሪ ፓርቲዎች በተጨማሪ ጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ አሕመድ እጩ የካቢኔ አባላቶቻቸውን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበው አስሾሙ። የጠቅላይ ሚንስትሩ የካቢኔ አባላት እና ኃላፊነቶቻቸው የሚከተሉት ናቸው። | ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ሦስት የተቃዋሚ አባላትን በካቢኔያቸው ውስጥ አካተቱ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በአዲሱ ካቢኔያቸው ውስጥ ሦስት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን በሚኒስተርነት እንዲያገለግሉ ለሕዝብ ተወካዮች አቅርበው አስሹመዋል። በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሊቀመንበር አቶ በለጠ ሞላ እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ምክትል ሊቀመንበር አቶ ቀጀላ መርዳሳ በሚኒስትር ተሹመዋል። ፕ/ሮ ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስትር፣ አቶ በለጠ ሞላ የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር፣ እንዲሁም አቶ ቀጀላ መርዳሳ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር በመሆን በጠቅላይ ሚኒስትሩ ካቢኔ ውስጥ ተካተዋል። ኢዜማ ከገዢው ብልጽግና ፓርቲ የቀረበውን የአብረን እንሥራ ጥያቄ አሁን ኢትዮጵያ ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ጥያቄውን ተቀብሎ አብሮ ለመሥራት በአብላጫ ድምጽ መወሰኑን ባሳለፍነው እሁድ አስታውቋል። ኢዜማ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ አራት መቀመጫዎች ያሉት ሲሆን አብን ደግሞ አምስት መቀመጫዎችን ለማሸነፍ ችሏል። በአቶ ዳውድ ኢብሳ በሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ውስጥ በተፈጠረ አለመግባባት ከግንባሩ ተለይቶ በመውጣት በአቶ አራርሳ ቢቂላ የሚመራው ግንባር በምርጫው ባይሳተፍም ምክትሩ በአዲሱ ካቢኔ ውስጥ ተካተዋል። በተመሳሳይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ባለፈው ሳምንት ሥራውን በጀመር ወቅት በከንቲባነት የተሾሙት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ 26 የካቢኔ አባሎቻቸውን አቅርበው ሲያስሾሙ ሁለቱ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን አመራሮችን አካተው ነበር። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅብራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አባል የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሲሾሙ፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ምክትል ሊቀመንበር የሱፍ ኢብራሂም ደግሞ የመንግሥት ንብረት አስተዳደር ባለሥልጣን ሆነው ተሹመዋል። የኦሮሚያ ክልልም ከሳምንት በፊት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀመንበር የሆኑትን አቶ አራርሳ ቢቂላን የቢሮ ኃላፊ አድርጎ የሾመ ሲሆን የአማር ክልልም ከተቃዋሚዎቹ አብንና ከአዴኃን ሁለት ሰዎችን በቢሮ ኃላፊነት ሹመት ሰጥተዋል። ከተፎካካሪ ፓርቲዎች በተጨማሪ ጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ አሕመድ እጩ የካቢኔ አባላቶቻቸውን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበው አስሾሙ። የጠቅላይ ሚንስትሩ የካቢኔ አባላት እና ኃላፊነቶቻቸው የሚከተሉት ናቸው። | https://www.bbc.com/amharic/58814095 |
0business
| የዩክሬኑ ጦርነት ባለፉት 50 ዓመታት ያልታየ የዋጋ ንረት እንደሚያስከትል ተገለጸ | የዩክሬን ጦርነት ከአውሮፓውያኑ 1970ዎቹ ወዲህ በዓለማችን ታይቶ የማይታወቅ የሸቀጦች እጥረት ሊያስከትል እንደሚችል የዓለም ባንክ አሳስቧል። የዓለም ባንክ ባወጣው ትንበያ መሠረት የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት በበርካታ ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ እያስከተለ ሲሆን ከነዚህ መካከል በዋነኛነት የተፈጥሮ ጋዝ፣ ስንዴ እንዲሁም ጥጥ ይገኙበታል። "የዋጋ ጭማሪው ከፍተኛ የሆነ ኢኮኖሚያዊና ሰብአዊ ጫናዎችን እያስከተለ ነው" ብለዋል ሪፖርቱን ካዘጋጁት መካከል አንደኛው የሆኑት ፒተር ኔግል። አክለውም "በመላው ዓለም የሚገኙ ቤተሰቦች ጫናውን በደንብ እያስተዋሉት ነው። እኛን በጣም የሚያሳስበን ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች ጉዳይ ነው። ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች ናቸው ምግብ ለማግኘት ከፍተኛ ጉልበትና ገንዘብ የሚያወጡት። የዋጋ ንረት ተከሰተ ማለት እነዚህን ቤተሰቦች ነው በቀጥታ የሚመለከተው" ብለዋል። የኃይል አቅራቢ ድርጅቶች ዋጋ ከ50 በመቶ በላይ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን ይህ ደግሞ ለድሃ ቤተሰቦችና አነስተኛ የንግድ ተቋማት መጥፎ ዜና ነው ይላል የዓለም ባንክ። ከፍተኛው የዋጋ ጭማሪ የሚኖረው አውሮፓ ውስጥ ሲሆን በዚህም ምናልባት ዋጋዎች ከሁለት እጥፍ በላይ ጨምረው ልንመለከት እንችላለን። የዋጋ ንረቱ በሚቀጥለው የፈረንጆቹ ዓመት እንዲሁም በ2024 ቅናሽ እንደሚያሳይ ተገምቷል። ነገር ግን ምንም እንኳን ቅናሽ ቢስተዋል ከዚህ በፊት ከነበሩት ዋጋዎች አንጻር እስከ 15 በመቶ የሚደርስ ጭማሪ ይኖረዋል ብሏል የዓለም ባንክ። የነዳጅ ዋጋም ቢሆን ጭማሪ እያሳየ እስከ 2024 ድረስ ሊቀጥል እንደሚችል የተገመተ ሲሆን ያልተጣራ ድፍድፍ በርሜል ነዳጅ በዚህ ዓመት እስከ 100 ዶላር ሊያወጣ ይችላል። ይህ ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ የዋጋ ንረትን ያባብሰዋል። ሩሲያ ዓለማችን ከምትጠቀመው ነዳጅ 11 በመቶ የሚሆነውን ታቀርባለች። ነገር ግን ጦርነቱ ቢቆም እንኳን ጦርነቱን ተከትሎ በርካታ ያደጉ አገራት ሩሲያ ላይ ማዕቀብ መጣላቸውና ትልልቅ የአውሮፓና አሜሪካ ድርጅቶች ሩሲያን ጥለው መውጣታቸው ለወደፊቱ በርካታ መዘዞችን ይዘው ይመጣሉ። በሌላ በኩል አውሮፓውያን ከሚጠቀሙት ጋዝ 40 በመቶ የሚሆነው ከሩሲያ ሲሆን፣ የሚመጣው 27 በመቶ የነዳጅ ፍላጎታቸውም ቢሆን የሚሟላው በሩሲያ ነው። ይህ ደግሞ በተለይ በአውሮፓ የዋጋ ንረቱ ከዕለት ወደ ዕለት እንዲጨምርና እጥረት እንዲከሰትም እያደረገ ነው። የዓለም ባንክ እንደሚለው ከነዳጅና ጋዝ በተጨማሪ የምግቦች ዋጋም ቢሆን በእጅጉ ይጨምራል። የተባበሩት መንግሥታትም ቢሆን በ60 ዓመታት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ የምግቦች ዋጋ ንረት መከሰቱን አስታውቋል። የስንዴ ዋጋ የ42 በመቶ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን ገብስም ቢሆን የ33 በመቶ ጭማሪ ታይቶበታል። የዶሮ ምርቶች የ41̇.8 በመቶ ጭማሪ እንዲሁም ሌሎች ጥራጥሬዎች የ29.8 በመቶ የዋጋ ጭማሪ ተስተውሎባቸዋል። እነዚህ ሁሉ ቁጥሮች የሚያሳዩት ደግሞ ሩሲያና ዩክሬን ምን ያህል ለዓለማችን ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ አገራት እንደሆኑ ነው። ከጦርነቱ በፊት ሁለቱ አገራት የዓለም ሕዝብ ከሚመገበው ስንዴ 28.9 በመቶ የሚሆነውን ያቀርቡ የነበረ ሲሆን፣ ዓለም ለማብሰል ይጠቀመው የነበረው የሱፍ ዘይትም ቢሆን 60 በመቶው የሚመጣው ከነዚሁ አገራት ነበር። | የዩክሬኑ ጦርነት ባለፉት 50 ዓመታት ያልታየ የዋጋ ንረት እንደሚያስከትል ተገለጸ የዩክሬን ጦርነት ከአውሮፓውያኑ 1970ዎቹ ወዲህ በዓለማችን ታይቶ የማይታወቅ የሸቀጦች እጥረት ሊያስከትል እንደሚችል የዓለም ባንክ አሳስቧል። የዓለም ባንክ ባወጣው ትንበያ መሠረት የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት በበርካታ ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ እያስከተለ ሲሆን ከነዚህ መካከል በዋነኛነት የተፈጥሮ ጋዝ፣ ስንዴ እንዲሁም ጥጥ ይገኙበታል። "የዋጋ ጭማሪው ከፍተኛ የሆነ ኢኮኖሚያዊና ሰብአዊ ጫናዎችን እያስከተለ ነው" ብለዋል ሪፖርቱን ካዘጋጁት መካከል አንደኛው የሆኑት ፒተር ኔግል። አክለውም "በመላው ዓለም የሚገኙ ቤተሰቦች ጫናውን በደንብ እያስተዋሉት ነው። እኛን በጣም የሚያሳስበን ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች ጉዳይ ነው። ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች ናቸው ምግብ ለማግኘት ከፍተኛ ጉልበትና ገንዘብ የሚያወጡት። የዋጋ ንረት ተከሰተ ማለት እነዚህን ቤተሰቦች ነው በቀጥታ የሚመለከተው" ብለዋል። የኃይል አቅራቢ ድርጅቶች ዋጋ ከ50 በመቶ በላይ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን ይህ ደግሞ ለድሃ ቤተሰቦችና አነስተኛ የንግድ ተቋማት መጥፎ ዜና ነው ይላል የዓለም ባንክ። ከፍተኛው የዋጋ ጭማሪ የሚኖረው አውሮፓ ውስጥ ሲሆን በዚህም ምናልባት ዋጋዎች ከሁለት እጥፍ በላይ ጨምረው ልንመለከት እንችላለን። የዋጋ ንረቱ በሚቀጥለው የፈረንጆቹ ዓመት እንዲሁም በ2024 ቅናሽ እንደሚያሳይ ተገምቷል። ነገር ግን ምንም እንኳን ቅናሽ ቢስተዋል ከዚህ በፊት ከነበሩት ዋጋዎች አንጻር እስከ 15 በመቶ የሚደርስ ጭማሪ ይኖረዋል ብሏል የዓለም ባንክ። የነዳጅ ዋጋም ቢሆን ጭማሪ እያሳየ እስከ 2024 ድረስ ሊቀጥል እንደሚችል የተገመተ ሲሆን ያልተጣራ ድፍድፍ በርሜል ነዳጅ በዚህ ዓመት እስከ 100 ዶላር ሊያወጣ ይችላል። ይህ ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ የዋጋ ንረትን ያባብሰዋል። ሩሲያ ዓለማችን ከምትጠቀመው ነዳጅ 11 በመቶ የሚሆነውን ታቀርባለች። ነገር ግን ጦርነቱ ቢቆም እንኳን ጦርነቱን ተከትሎ በርካታ ያደጉ አገራት ሩሲያ ላይ ማዕቀብ መጣላቸውና ትልልቅ የአውሮፓና አሜሪካ ድርጅቶች ሩሲያን ጥለው መውጣታቸው ለወደፊቱ በርካታ መዘዞችን ይዘው ይመጣሉ። በሌላ በኩል አውሮፓውያን ከሚጠቀሙት ጋዝ 40 በመቶ የሚሆነው ከሩሲያ ሲሆን፣ የሚመጣው 27 በመቶ የነዳጅ ፍላጎታቸውም ቢሆን የሚሟላው በሩሲያ ነው። ይህ ደግሞ በተለይ በአውሮፓ የዋጋ ንረቱ ከዕለት ወደ ዕለት እንዲጨምርና እጥረት እንዲከሰትም እያደረገ ነው። የዓለም ባንክ እንደሚለው ከነዳጅና ጋዝ በተጨማሪ የምግቦች ዋጋም ቢሆን በእጅጉ ይጨምራል። የተባበሩት መንግሥታትም ቢሆን በ60 ዓመታት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ የምግቦች ዋጋ ንረት መከሰቱን አስታውቋል። የስንዴ ዋጋ የ42 በመቶ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን ገብስም ቢሆን የ33 በመቶ ጭማሪ ታይቶበታል። የዶሮ ምርቶች የ41̇.8 በመቶ ጭማሪ እንዲሁም ሌሎች ጥራጥሬዎች የ29.8 በመቶ የዋጋ ጭማሪ ተስተውሎባቸዋል። እነዚህ ሁሉ ቁጥሮች የሚያሳዩት ደግሞ ሩሲያና ዩክሬን ምን ያህል ለዓለማችን ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ አገራት እንደሆኑ ነው። ከጦርነቱ በፊት ሁለቱ አገራት የዓለም ሕዝብ ከሚመገበው ስንዴ 28.9 በመቶ የሚሆነውን ያቀርቡ የነበረ ሲሆን፣ ዓለም ለማብሰል ይጠቀመው የነበረው የሱፍ ዘይትም ቢሆን 60 በመቶው የሚመጣው ከነዚሁ አገራት ነበር። | https://www.bbc.com/amharic/61240082 |
5sports
| ዛየን አሊ ሰልማን፡ በአርሰናል የእግር ኳስ ቡድን የተመለመለው የአራት ዓመቱ ታዳጊ | ዛየን አሊ ሰልማን የእንግሊዝ ትልቅ የእግር ኳስ ቡድንን ቀልብ ሲስብ ዕድሜው ገና አራት ነበር። ዛየን ያለው ችሎታ ከእድሜው በሁለት እጥፍ የላቀ ነው ሲሉ ይናገራሉ፤ አሰልጣኞቹ። የአርሰናል ቅድመ መደበኛ አካዳሚ እያሰለጠነው የሚገኘው ዛየን ገና ከአሁኑ ከሌሎች ስመ ገናና የእግር ኳስ ቡድኖች ጥሪ እየቀረበለት ይገናል። | ዛየን አሊ ሰልማን፡ በአርሰናል የእግር ኳስ ቡድን የተመለመለው የአራት ዓመቱ ታዳጊ ዛየን አሊ ሰልማን የእንግሊዝ ትልቅ የእግር ኳስ ቡድንን ቀልብ ሲስብ ዕድሜው ገና አራት ነበር። ዛየን ያለው ችሎታ ከእድሜው በሁለት እጥፍ የላቀ ነው ሲሉ ይናገራሉ፤ አሰልጣኞቹ። የአርሰናል ቅድመ መደበኛ አካዳሚ እያሰለጠነው የሚገኘው ዛየን ገና ከአሁኑ ከሌሎች ስመ ገናና የእግር ኳስ ቡድኖች ጥሪ እየቀረበለት ይገናል። | https://www.bbc.com/amharic/59047067 |
5sports
| ሴቶች ስታዲየም እንዲገቡ በቅርቡ የፈቀደችው ሳዑዲ የሴቶች ሊግን ልታስጀምር ነው | ሴቶች ስታዲየም ገብትው ኳስ እንዳይመለከቱ ትከለክል የነበረችው ሳዑዲ አራቢያ የሴቶች የእግር ኳስ ሊግን ልታስጀምር ነው። በሊጉ የሚሳተፉ ቡድኖች በመዲናዋ ሪያድ እና በሌሎች ሁለት ከተሞች ውድድሮችን ያካሂዳሉ። አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሰልማን በሳዑዲ እያካሄዱ ካለው የለውጥ እርምጃ መካከል ይህ ውሳኔ ተጠቃሽ ነው። የሰብዓ መብት ተሟጋቾች ግን አሁንም በሳዑዲ የሴቶች መብት ላይ ገደብ ተጥሏል ይላሉ። ባለስልጣናት የሴቶች የእግር ኳስ ሊግን ማቋቋም ያስፈለገው ሴቶች በስፖርት ያላቸው ተሳትፎ ለማሳዳግ ነው ብለዋል። ሴቶች ስታዲየም ገብትው እግር ኳስ እንዲመለከቱ የተፈቀደላቸው የዛሬ ሁለት ዓመት በፊት ነበር። በተመሳሳይ ዓመት ሳዑዲ ሴቶች መኪና ማሽከርከር አይችሉም የሚለውን ክልከላዋን አስቁማለች። ባሳለፍነው ዓመት ደግሞ ሴቶች ያለ ወንድ ጥበቃ ከአገር ውጪ ጉዞ ማድረግ እንዲችሉ እንደተፈቀደላቸው ይታወሳል። ይህ ይሁን እንጂ አሁንም ቢሆን በርካታ የሴቶች መብት ተከራካሪዎች በሳዑዲ እስር ቤቶች ውስጥ እየማቀቁ ይገኛሉ። | ሴቶች ስታዲየም እንዲገቡ በቅርቡ የፈቀደችው ሳዑዲ የሴቶች ሊግን ልታስጀምር ነው ሴቶች ስታዲየም ገብትው ኳስ እንዳይመለከቱ ትከለክል የነበረችው ሳዑዲ አራቢያ የሴቶች የእግር ኳስ ሊግን ልታስጀምር ነው። በሊጉ የሚሳተፉ ቡድኖች በመዲናዋ ሪያድ እና በሌሎች ሁለት ከተሞች ውድድሮችን ያካሂዳሉ። አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሰልማን በሳዑዲ እያካሄዱ ካለው የለውጥ እርምጃ መካከል ይህ ውሳኔ ተጠቃሽ ነው። የሰብዓ መብት ተሟጋቾች ግን አሁንም በሳዑዲ የሴቶች መብት ላይ ገደብ ተጥሏል ይላሉ። ባለስልጣናት የሴቶች የእግር ኳስ ሊግን ማቋቋም ያስፈለገው ሴቶች በስፖርት ያላቸው ተሳትፎ ለማሳዳግ ነው ብለዋል። ሴቶች ስታዲየም ገብትው እግር ኳስ እንዲመለከቱ የተፈቀደላቸው የዛሬ ሁለት ዓመት በፊት ነበር። በተመሳሳይ ዓመት ሳዑዲ ሴቶች መኪና ማሽከርከር አይችሉም የሚለውን ክልከላዋን አስቁማለች። ባሳለፍነው ዓመት ደግሞ ሴቶች ያለ ወንድ ጥበቃ ከአገር ውጪ ጉዞ ማድረግ እንዲችሉ እንደተፈቀደላቸው ይታወሳል። ይህ ይሁን እንጂ አሁንም ቢሆን በርካታ የሴቶች መብት ተከራካሪዎች በሳዑዲ እስር ቤቶች ውስጥ እየማቀቁ ይገኛሉ። | https://www.bbc.com/amharic/news-51641657 |
5sports
| ተጠባቂውን የሊቨርፑል እና የማንቸስተር ሲቲ ጨዋታ ማን በበላይነት ያጠናቅቃል? | በዚህ ሳምንትስ ከሊቨርፑል እና ከማንቸስተር ሲቲ ማን ያሸንፋል? “ወደ ኤሚሬትስ ስታዲም ከማቅናታቸው በፊት ሊቨርፑሎች ወደ ቀድሞ ብቃታቸው ይመለሳሉ በሚል ግምቴን ስሰጣቸው ቆይቻለሁ” ይላል ሱቶን። “ግን አልተሳካም። በቻምፒዮንስ ሊግ ሬንጀርስን 7 ለ 1 ማሸነፍ ቢችሉም ከፊታቸውን ከባድ ጨዋታ አለ።” ሱቶን ይህንን ጨዋታ ጨምሮ የ11ኛ ሳምንት ጨዋታዎችን ግምት አስቀምጧል። ብሬንትፎርድ ከ ብራይተን ውድድር ዓመቱን በድንቅ መንገድ የጀመሩት ብሬንትፎርዶች ከሰሞኑ ውጤት አልቀናቸውም። ባለፈው ሳምንት በኒውካስል ተደቁሰዋል። አዲስ አሰልጣኝ የሾሙት ብራይተኖች ደግሞ ምን ዓይነት ጉዞ እንደሚኖራቸው መገመት ከባድ ነው። ሁሌም ግን ጠንካራ ሆነው ስለሚቀርቡ ይህንን ጨዋታ ያሸንፋሉ ብዬ እገምታለሁ። ግምት፡ 1 - 2 ሌስተር ከ ክሪስታል ፓላስ ሌስተሮች በሜዳቸው ከኖቲንግሃም ፎረስት ጋር ባደረጉት ጨዋታ ድንቅ ሆነው ቢያመሹም ከብርንማውዝ ጋር ደግሞ ደካማ ነበሩ። ነገሮች የሚቀየሩ አይመስለኝም። የኋላ መስመራቸው ደካማ ሲሆን እነዊልፍሬድ ዛሃ ሊጠቀሙበት ይችላሉ። ፓላሶችም ሊድስ እስኪያሸንፉ ድረስ መንሸራተት ጀምረው ነበር። ሁለቱም ቡድኖች ነጥብ ተጋርተው ይወጣሉ ብዬ እገምታለሁ። ግምት፡ 2 - 2 ቶተንሃም ከ ኤቨርተን ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር በተለይም ጎል ካስቆጠሩ በኋላ ኤቨርተኖች ከሚገባቸው በታች ነበር የተንቀሳቀሱት። የቶፊዎቹ ተከላካይ መስመር መሻሻል ቢያሳይም አሁንም ክፍት መሆኑን ዩናይትድ አሳይቷል። ስፐርስን ማቆም ቀላል ቢሆንም ሃሪ ኬን እና ሶን ሄዩንግ-ሚን በጥሩ አቋም ላይ ይገኛሉ። ስለዚህ ቶተንሃም የሚሳካለት ሲሆን የጎሉ መጠን የሚወሰነው ግን የመጀመሪያወን ጎል በሚያስቆጥሩበት ደቂቃ ይሆናል። ግምት፡ 3 – 1 ፉልሃም ከ በርንዝማውዝ ፉልሃሞች ከዌስትሃም ጋር በነበራቸው ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ ጥሩ ነበሩ። አሰልጣኝ ማርኮ ሲልቫ ፍጹም ቅጣት ምት በመሰጠቱ ቢበሳጩም መናደድ ካለባቸው በተደጋጋሚ የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ አልሰማ ብሎ ስህተት በሠራው አንድሪያስ ፔሬራ ላይ መሆን ነበረበት። ሁሌም በርንማውዝን ይሸነፋል እያልኩ ትክክል አለመገመቴን ያሳዩኛል። ደጋፊዎችም ይህን ይወዱታል። በጋሪ ኦኒዬል ስር ብርንማውዞች ጥሩ ቢሆኑም ሦስቱን ነጥብ ለፉልሃም አሰጠላሁ። ግምት፡ 2 – 1 ዎልቭስ ከ ኖቲንግሃም ፎረስት ዎልቭሶች እስካሁን አሰልጣኝ ባይኖራቸውም በሚገባቸው መጠን መንቀሳቀስ ያልቻሉ ድንቅ ተጫዋቾችን ይዘዋል። በወራጅ ቀጠና ውስጥ ቢሆንም ብቃቱን ማሳየት እንዳልቻለ ቡድን ነው የምመለከተው። ኖቲንግሃም ፎረስትን ደግሞ ከዚህ በተለየ መልኩ የምመለከተው ሲሆን ባለፈው ሳምንት ከአስቶንቪላው ጨዋታ ነጥብ ማግኘታቸው ዕድለኛ ያደርጋቸዋል። የፎረስት ተጫዋቾች ያልተዋሃዱ ሲሆን በራሳቸው ላይ ያለቸው እምነትም እየተሸረሸረ ይመስለኛል። ግምት፡ 2 – 0 አስቶን ቪላ ከ ቼልሲ የአስልጣኝ ስቴቨን ዤራርድ ጉዳይ በአስቶን ቪላ ደጋፊዎች ዘንድ ቁርጥ ያለ ውሳኔ ያገኘ አይመስልም። ዋናው ምክንያት ደግሞ የሚመርጡት አጨዋወት ነው። ፒየር-ኤመሪክ ኦባሚያንግ ጎል እያስቆጠረ ሲሆን አሰልጣኝ ግርሃም ፖተርም የመላመድ ብቃታቸውን እያሳዩ ነው። ቪላ በሜዳው የማሸነፍ ጫና ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ተጫዋቾቹም ተጽዕኖው ያገኛቸዋል። ግምት፡0 – 2 ሊድስ ከ አርሴናል ሊድሶች ከፓላስ ጋር በነበራቸው ጨዋታ የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ ድንቅ ቢሆኑም አልዘለቁበትም። በዚህ ጨዋታም ሊድስ መጀመሪያ ላይ ተጭኖ ለመጫወት ቢሞክርም አይዘልቅበትም። ካላቸው ጥሩ እንቅስቃሴ እና ካለፈው ሳምንት ውጤት በኋላ አርሴናሎች ጨዋታውን በበላይነት እንደሚያጠናቅቁ እገምታለሁ። እንደምገምተው ሊድሶች አጥቅተው ለመጫወት ከሞከሩ ጋብርኤል ማርቲኔሊ እና ቡካዮ ሳካ የመጫወቻ ክፍተት ይገኛሉ። ለጋብርኤል ጂሰስም ዕድሎችን ይፈጥራል። ግምት፡ 1 – 3 ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ኒውካስል ይህን ጨዋታ ማንቸስተር ዩናይትድ ያሸንፋል ብዬ አልገምትም። ጥያቄው ኒውካስል አንድ ነጥብ ያገኛል ወይስ ሦስት ነጥብ የሚለው ነው። ማንቸስተር በኤሪክ ቴን ሃግ ስር እየተሻሻለ መሆኑን እቀበላለሁ። ከዚህ ይልቅ ኒውካስል በማጥቃት መጫወት በመጀመራቸው እና ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ዘጠኝ ጎሎችን ማስቆጠራቸው ነው። አሰልጣኝ ኤዲ ሃዊ በኦልትራፎርድ አጨዋወታቸውን ይቀይራሉ ብዬ አልገምትም። ይህ ደግሞ ቸዋታው ክፍት እንዲሆን ሲያደርግ ማንቸስተርንም ተጠቃሚ ያደርጋል። ግምት፡ 1 – 1 ሳውዝሃምፕተን ከ ዌስት ሃም ይህም ከባድ ጨዋታ ነው። ሳውዝሃምፕተንን በማንቸስተር ሲቲ ጨዋታ መገምገም ከባድ ነው። አሰልጣኝ ራልፍ ላይ ያንዣበበው ጫና ባለመቀነሱ ከዚህ ጨዋታ ውጤት ይጠብቃሉ። ጨዋታው በአቻ ውጤት ይጠናቀቃል ብዬ ብገምትም ነገሮች ወደ ዌስት ሃም ያደሉብኛል። ጂያንሉካ ስካማካን እወደዋለሁ። ዌስት ሃሞችም ወደ ድል መስመር ተመልሰዋል። ግምት፡ 1 – 2 ሊቨርፑል ከ ማንቸስተር ሲቲ ሊቨርፑልን ከዋንጫው ፉክክር ውጭ ማድረግ ከባድ ቢሆንም ሲቲ ወደ አንፊልድ አቅንቶ ማሸነፍ ከቻል ዕድል አይኖራቸውም። ሲቲዎች ይህንን ስለሚያውቁ ይጠቀሙበታል። ኤርሊንግ ሃላንድ በሳምንቱ አጋማሽ እረፍት በማግኘቱ ለዚህ ጨዋታ ዝግጁ ይሆናል። የሊቨርፑል አጨዋወት ለሃለንድ ስለሚመች ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ሊቨርፑሎች ዕድል መፍጠር ቢችሉም ማንቸስተር ሲቲ ባለው አቋም በላይ መሆኑ ግልጽ ነው። በ2021 የፔፕ ጋርዲዮላ ቡድን አራት ያስቆጠረ ሲሆን በዚህ ጨዋታም ተመሳሳይ ጎል እጠብቃለሁ። ግምት፡ 1 - 4 | ተጠባቂውን የሊቨርፑል እና የማንቸስተር ሲቲ ጨዋታ ማን በበላይነት ያጠናቅቃል? በዚህ ሳምንትስ ከሊቨርፑል እና ከማንቸስተር ሲቲ ማን ያሸንፋል? “ወደ ኤሚሬትስ ስታዲም ከማቅናታቸው በፊት ሊቨርፑሎች ወደ ቀድሞ ብቃታቸው ይመለሳሉ በሚል ግምቴን ስሰጣቸው ቆይቻለሁ” ይላል ሱቶን። “ግን አልተሳካም። በቻምፒዮንስ ሊግ ሬንጀርስን 7 ለ 1 ማሸነፍ ቢችሉም ከፊታቸውን ከባድ ጨዋታ አለ።” ሱቶን ይህንን ጨዋታ ጨምሮ የ11ኛ ሳምንት ጨዋታዎችን ግምት አስቀምጧል። ብሬንትፎርድ ከ ብራይተን ውድድር ዓመቱን በድንቅ መንገድ የጀመሩት ብሬንትፎርዶች ከሰሞኑ ውጤት አልቀናቸውም። ባለፈው ሳምንት በኒውካስል ተደቁሰዋል። አዲስ አሰልጣኝ የሾሙት ብራይተኖች ደግሞ ምን ዓይነት ጉዞ እንደሚኖራቸው መገመት ከባድ ነው። ሁሌም ግን ጠንካራ ሆነው ስለሚቀርቡ ይህንን ጨዋታ ያሸንፋሉ ብዬ እገምታለሁ። ግምት፡ 1 - 2 ሌስተር ከ ክሪስታል ፓላስ ሌስተሮች በሜዳቸው ከኖቲንግሃም ፎረስት ጋር ባደረጉት ጨዋታ ድንቅ ሆነው ቢያመሹም ከብርንማውዝ ጋር ደግሞ ደካማ ነበሩ። ነገሮች የሚቀየሩ አይመስለኝም። የኋላ መስመራቸው ደካማ ሲሆን እነዊልፍሬድ ዛሃ ሊጠቀሙበት ይችላሉ። ፓላሶችም ሊድስ እስኪያሸንፉ ድረስ መንሸራተት ጀምረው ነበር። ሁለቱም ቡድኖች ነጥብ ተጋርተው ይወጣሉ ብዬ እገምታለሁ። ግምት፡ 2 - 2 ቶተንሃም ከ ኤቨርተን ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር በተለይም ጎል ካስቆጠሩ በኋላ ኤቨርተኖች ከሚገባቸው በታች ነበር የተንቀሳቀሱት። የቶፊዎቹ ተከላካይ መስመር መሻሻል ቢያሳይም አሁንም ክፍት መሆኑን ዩናይትድ አሳይቷል። ስፐርስን ማቆም ቀላል ቢሆንም ሃሪ ኬን እና ሶን ሄዩንግ-ሚን በጥሩ አቋም ላይ ይገኛሉ። ስለዚህ ቶተንሃም የሚሳካለት ሲሆን የጎሉ መጠን የሚወሰነው ግን የመጀመሪያወን ጎል በሚያስቆጥሩበት ደቂቃ ይሆናል። ግምት፡ 3 – 1 ፉልሃም ከ በርንዝማውዝ ፉልሃሞች ከዌስትሃም ጋር በነበራቸው ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ ጥሩ ነበሩ። አሰልጣኝ ማርኮ ሲልቫ ፍጹም ቅጣት ምት በመሰጠቱ ቢበሳጩም መናደድ ካለባቸው በተደጋጋሚ የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ አልሰማ ብሎ ስህተት በሠራው አንድሪያስ ፔሬራ ላይ መሆን ነበረበት። ሁሌም በርንማውዝን ይሸነፋል እያልኩ ትክክል አለመገመቴን ያሳዩኛል። ደጋፊዎችም ይህን ይወዱታል። በጋሪ ኦኒዬል ስር ብርንማውዞች ጥሩ ቢሆኑም ሦስቱን ነጥብ ለፉልሃም አሰጠላሁ። ግምት፡ 2 – 1 ዎልቭስ ከ ኖቲንግሃም ፎረስት ዎልቭሶች እስካሁን አሰልጣኝ ባይኖራቸውም በሚገባቸው መጠን መንቀሳቀስ ያልቻሉ ድንቅ ተጫዋቾችን ይዘዋል። በወራጅ ቀጠና ውስጥ ቢሆንም ብቃቱን ማሳየት እንዳልቻለ ቡድን ነው የምመለከተው። ኖቲንግሃም ፎረስትን ደግሞ ከዚህ በተለየ መልኩ የምመለከተው ሲሆን ባለፈው ሳምንት ከአስቶንቪላው ጨዋታ ነጥብ ማግኘታቸው ዕድለኛ ያደርጋቸዋል። የፎረስት ተጫዋቾች ያልተዋሃዱ ሲሆን በራሳቸው ላይ ያለቸው እምነትም እየተሸረሸረ ይመስለኛል። ግምት፡ 2 – 0 አስቶን ቪላ ከ ቼልሲ የአስልጣኝ ስቴቨን ዤራርድ ጉዳይ በአስቶን ቪላ ደጋፊዎች ዘንድ ቁርጥ ያለ ውሳኔ ያገኘ አይመስልም። ዋናው ምክንያት ደግሞ የሚመርጡት አጨዋወት ነው። ፒየር-ኤመሪክ ኦባሚያንግ ጎል እያስቆጠረ ሲሆን አሰልጣኝ ግርሃም ፖተርም የመላመድ ብቃታቸውን እያሳዩ ነው። ቪላ በሜዳው የማሸነፍ ጫና ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ተጫዋቾቹም ተጽዕኖው ያገኛቸዋል። ግምት፡0 – 2 ሊድስ ከ አርሴናል ሊድሶች ከፓላስ ጋር በነበራቸው ጨዋታ የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ ድንቅ ቢሆኑም አልዘለቁበትም። በዚህ ጨዋታም ሊድስ መጀመሪያ ላይ ተጭኖ ለመጫወት ቢሞክርም አይዘልቅበትም። ካላቸው ጥሩ እንቅስቃሴ እና ካለፈው ሳምንት ውጤት በኋላ አርሴናሎች ጨዋታውን በበላይነት እንደሚያጠናቅቁ እገምታለሁ። እንደምገምተው ሊድሶች አጥቅተው ለመጫወት ከሞከሩ ጋብርኤል ማርቲኔሊ እና ቡካዮ ሳካ የመጫወቻ ክፍተት ይገኛሉ። ለጋብርኤል ጂሰስም ዕድሎችን ይፈጥራል። ግምት፡ 1 – 3 ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ኒውካስል ይህን ጨዋታ ማንቸስተር ዩናይትድ ያሸንፋል ብዬ አልገምትም። ጥያቄው ኒውካስል አንድ ነጥብ ያገኛል ወይስ ሦስት ነጥብ የሚለው ነው። ማንቸስተር በኤሪክ ቴን ሃግ ስር እየተሻሻለ መሆኑን እቀበላለሁ። ከዚህ ይልቅ ኒውካስል በማጥቃት መጫወት በመጀመራቸው እና ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ዘጠኝ ጎሎችን ማስቆጠራቸው ነው። አሰልጣኝ ኤዲ ሃዊ በኦልትራፎርድ አጨዋወታቸውን ይቀይራሉ ብዬ አልገምትም። ይህ ደግሞ ቸዋታው ክፍት እንዲሆን ሲያደርግ ማንቸስተርንም ተጠቃሚ ያደርጋል። ግምት፡ 1 – 1 ሳውዝሃምፕተን ከ ዌስት ሃም ይህም ከባድ ጨዋታ ነው። ሳውዝሃምፕተንን በማንቸስተር ሲቲ ጨዋታ መገምገም ከባድ ነው። አሰልጣኝ ራልፍ ላይ ያንዣበበው ጫና ባለመቀነሱ ከዚህ ጨዋታ ውጤት ይጠብቃሉ። ጨዋታው በአቻ ውጤት ይጠናቀቃል ብዬ ብገምትም ነገሮች ወደ ዌስት ሃም ያደሉብኛል። ጂያንሉካ ስካማካን እወደዋለሁ። ዌስት ሃሞችም ወደ ድል መስመር ተመልሰዋል። ግምት፡ 1 – 2 ሊቨርፑል ከ ማንቸስተር ሲቲ ሊቨርፑልን ከዋንጫው ፉክክር ውጭ ማድረግ ከባድ ቢሆንም ሲቲ ወደ አንፊልድ አቅንቶ ማሸነፍ ከቻል ዕድል አይኖራቸውም። ሲቲዎች ይህንን ስለሚያውቁ ይጠቀሙበታል። ኤርሊንግ ሃላንድ በሳምንቱ አጋማሽ እረፍት በማግኘቱ ለዚህ ጨዋታ ዝግጁ ይሆናል። የሊቨርፑል አጨዋወት ለሃለንድ ስለሚመች ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ሊቨርፑሎች ዕድል መፍጠር ቢችሉም ማንቸስተር ሲቲ ባለው አቋም በላይ መሆኑ ግልጽ ነው። በ2021 የፔፕ ጋርዲዮላ ቡድን አራት ያስቆጠረ ሲሆን በዚህ ጨዋታም ተመሳሳይ ጎል እጠብቃለሁ። ግምት፡ 1 - 4 | https://www.bbc.com/amharic/articles/c72d77v22xwo |
0business
| ትግራይ ውስጥ በረሃብ ሳቢያ ሰዎችና እንስሳት እየሞቱ ነው ተባለ | በጦርነት በተጎዳችው ትግራይ ክልል ሰዎች እና እንስሳት በረሃብ እና በመሠረታዊ የህክምና እንክብካቤ እጥረት እየሞቱ መሆኑን የክልሉ ግብርና ኃላፊ ገለጹ። "በመንደሮች እና በከተሞች ውስጥ የምግብ እና የመድኃኒት እጥረት አለ። እናም በክልሉ ውሰጥ እየተከሰተ ያለው ቀውስ እኛ ከምናውቀው የበለጠ ሊሆን ይችላል" ሲሉ ዶ/ር አትንኩት መዝገቦ ለቢቢሲ ትግርኛ ተናግረዋል። ህወሓትም ባወጣው መግለጫ ላይ የክልሉን አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኤጀንሲን ዋቢ አድርጎ በነሐሴ ወር 150 ሰዎች በረሃብ መሞታቸው ተመዝግቧል ብሏል። ረሃቡ የተከሰተው ማይ ቅኔጣል፣ ቆላ ተምቤን፣ ሃውዜን፣ በማዕከላዊ ዞን ታንኳ ምላሽ እንዲሁም ሽረ ውስጥ ባለ የተፈናቃዮች መጠለያ ካምፕ ውስጥ እንደሆነም ተገልጿል። በፌደራል መንግሥቱ እና በህወሓት መካከል እየተጠናቀቀ ባለው ዓመት ጥቅምት መጨረሻ በተቀሰቀው ጦርነት ሳቢያ ከባድ ሰብአዊ ቀውስ ተከስቷል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታንም አስመልክቶ "በአስርት ዓመታት ውስጥ በዓለም ላይ አስከፊው የረሃብ ሁኔታ" እንዲቀለበስ ከተፈለገ 5.2 ሚሊዮን ሰዎች የአስቸኳይ እርዳታ ሊቀርብላቸው እንደሚገባ አስታውቋል። ቀደም ሲልም 400 ሺህ የሚሆን ሕዝብ በረሃብ አፋፍ ላይ መሆናቸውን አስታውቋል። ነገር ግን ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፉት ሁለት ቀናት ውስጥ በክልሉ የደረሱትን 152 የጭነት መኪኖችን ጨምሮ 500 እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ክልሉ መግባታቸውን ገልጿል። ከዚህም በተጨማሪ የእርዳታ አቅርቦቱን ለማፋጠን የፍተሻ የደኅንነት ኬላዎች ቁጥርም መቀነሱ ተነግሯል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከነሐሴ 16 ጀምሮ አንድም እርዳታ የጫነ መኪና ወደ ትግራይ አልደረሰም ሲል ቅሬታ ያቀረበ ሲሆን በየቀኑም በ100 መኪኖች የተጫነ የእርዳታ አቅርቦት ለክልሉ ያስፈልጋሉ ብሏል። የግብርና ኃላፊው በተጨማሪ ምን አሉ? የግብርና ኃላፊው ዶ/ር አትንኩት መዝገቦ እንደሚናገሩት በምግብ ዕርዳታ ዕጥረት ምክንያት ረሃብ በመላው ክልሉ እየተስፋፋ ነው። "ከዚህ ቀደም ነዋሪዎች የነበረቻቸውን ይቋደሱ ነበር ነገር ግን በአሁኑ ወቅት የሚበሉት የላቸውም" ብለዋል። ለዚህም ደግሞ ነዳጅ አቅርቦት አለመኖሩ እንዲሁም የባንክ አገልግሎትና መብራት መቋረጥ ችግሩን በዋነኝነት እንዳባባሰው ያስረዳሉ። በዚህም የምግብ እጥረት ዋነኞቹ ተጠቂዎችና ከፍተኛ ድርሻውን የያዙት ሴቶችና ህፃናት መሆናቸውንም ይናገራሉ። በትግራይ ክልል በተጣለው መገናኛ አገልግሎት እገዳ ምክንያት እየተፈጠረ ያለውን የቀውስ መጠን በዝርዝር መረዳት አዳጋች ቢሆንም "ግለሰቦች በረሃብ ምክንያት ሲሞቱ በአይናችን እያየን ነው" ብለዋል። "በምግብ እና በመድኃኒት እጥረት ምክንያት ሰዎች እየሞቱ እና የህመም እባጭ ምልክቶችን እያሳዩ ነው" በማለትም ያስረዳሉ። የግብርና ቢሮ ኃላፊው እንደሚናገሩት በክልሉ ውስጥ እየተከሰተ ያለውን ቀውስ ለመግታት የምግብ ዕርዳታ እንደሚጠብቁ አስረድተዋል። ምንም እንኳን በአሁኑ ወቅት ያለው የዝናብ ጥሩ ቢሆንም አርሶ ለማምረት ከሦስት እስከ አራት ወራት ይወስዳል እንዲሁም በአንዳንድ አካባቢዎች የአንበጣ ወረራ መገኘቱንም እንደ ስጋት አንስተዋል። በተለይም የአንበጣ ወረራውን ለመግታት በሚደረገው ትግል የመገናኛ ዘዴዎች መዘጋታቸው አሳሳቢ አድርጎታል ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ እንስሳቱ ክትባት ባለማግኘታቸው በተለያዩ በሽታዎች እየሞቱ እንደሆነም አስረድተዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የእርዳታ ቁሳቁስ የጫኑ 100 የጭነት መኪናዎች ወደ ትግራይ ክልል መዲና መቀለ መግባታቸውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም በትናንትናው ዕለት አስታውቋል። 3500 ቶን ይመዝናሉ የተባሉት የጭነት መኪናዎች ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ሕይወት አድን ቁሶችን ጭነው ነው ወደ ክልሉ የገቡት። ባለፈው ሳምንት የተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ መንግሥት ለትግራይ የእርዳታ አቅርቦቶችን በጠበቀ መንገድ ዘግቷል ሲል ከሷል። በዚህም ምክንያት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ለአደጋ እየተጋለጡ መሆኑን አስጠንቅቋል። የፌደራሉ መንግሥት በበኩሉ ወደ ክልሉ የሰብዓዊ እርዳታ እንዳይገባ እክል የሆኑት የህወሓት አማጺያን ናቸው ይላል። | ትግራይ ውስጥ በረሃብ ሳቢያ ሰዎችና እንስሳት እየሞቱ ነው ተባለ በጦርነት በተጎዳችው ትግራይ ክልል ሰዎች እና እንስሳት በረሃብ እና በመሠረታዊ የህክምና እንክብካቤ እጥረት እየሞቱ መሆኑን የክልሉ ግብርና ኃላፊ ገለጹ። "በመንደሮች እና በከተሞች ውስጥ የምግብ እና የመድኃኒት እጥረት አለ። እናም በክልሉ ውሰጥ እየተከሰተ ያለው ቀውስ እኛ ከምናውቀው የበለጠ ሊሆን ይችላል" ሲሉ ዶ/ር አትንኩት መዝገቦ ለቢቢሲ ትግርኛ ተናግረዋል። ህወሓትም ባወጣው መግለጫ ላይ የክልሉን አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኤጀንሲን ዋቢ አድርጎ በነሐሴ ወር 150 ሰዎች በረሃብ መሞታቸው ተመዝግቧል ብሏል። ረሃቡ የተከሰተው ማይ ቅኔጣል፣ ቆላ ተምቤን፣ ሃውዜን፣ በማዕከላዊ ዞን ታንኳ ምላሽ እንዲሁም ሽረ ውስጥ ባለ የተፈናቃዮች መጠለያ ካምፕ ውስጥ እንደሆነም ተገልጿል። በፌደራል መንግሥቱ እና በህወሓት መካከል እየተጠናቀቀ ባለው ዓመት ጥቅምት መጨረሻ በተቀሰቀው ጦርነት ሳቢያ ከባድ ሰብአዊ ቀውስ ተከስቷል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታንም አስመልክቶ "በአስርት ዓመታት ውስጥ በዓለም ላይ አስከፊው የረሃብ ሁኔታ" እንዲቀለበስ ከተፈለገ 5.2 ሚሊዮን ሰዎች የአስቸኳይ እርዳታ ሊቀርብላቸው እንደሚገባ አስታውቋል። ቀደም ሲልም 400 ሺህ የሚሆን ሕዝብ በረሃብ አፋፍ ላይ መሆናቸውን አስታውቋል። ነገር ግን ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፉት ሁለት ቀናት ውስጥ በክልሉ የደረሱትን 152 የጭነት መኪኖችን ጨምሮ 500 እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ክልሉ መግባታቸውን ገልጿል። ከዚህም በተጨማሪ የእርዳታ አቅርቦቱን ለማፋጠን የፍተሻ የደኅንነት ኬላዎች ቁጥርም መቀነሱ ተነግሯል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከነሐሴ 16 ጀምሮ አንድም እርዳታ የጫነ መኪና ወደ ትግራይ አልደረሰም ሲል ቅሬታ ያቀረበ ሲሆን በየቀኑም በ100 መኪኖች የተጫነ የእርዳታ አቅርቦት ለክልሉ ያስፈልጋሉ ብሏል። የግብርና ኃላፊው በተጨማሪ ምን አሉ? የግብርና ኃላፊው ዶ/ር አትንኩት መዝገቦ እንደሚናገሩት በምግብ ዕርዳታ ዕጥረት ምክንያት ረሃብ በመላው ክልሉ እየተስፋፋ ነው። "ከዚህ ቀደም ነዋሪዎች የነበረቻቸውን ይቋደሱ ነበር ነገር ግን በአሁኑ ወቅት የሚበሉት የላቸውም" ብለዋል። ለዚህም ደግሞ ነዳጅ አቅርቦት አለመኖሩ እንዲሁም የባንክ አገልግሎትና መብራት መቋረጥ ችግሩን በዋነኝነት እንዳባባሰው ያስረዳሉ። በዚህም የምግብ እጥረት ዋነኞቹ ተጠቂዎችና ከፍተኛ ድርሻውን የያዙት ሴቶችና ህፃናት መሆናቸውንም ይናገራሉ። በትግራይ ክልል በተጣለው መገናኛ አገልግሎት እገዳ ምክንያት እየተፈጠረ ያለውን የቀውስ መጠን በዝርዝር መረዳት አዳጋች ቢሆንም "ግለሰቦች በረሃብ ምክንያት ሲሞቱ በአይናችን እያየን ነው" ብለዋል። "በምግብ እና በመድኃኒት እጥረት ምክንያት ሰዎች እየሞቱ እና የህመም እባጭ ምልክቶችን እያሳዩ ነው" በማለትም ያስረዳሉ። የግብርና ቢሮ ኃላፊው እንደሚናገሩት በክልሉ ውስጥ እየተከሰተ ያለውን ቀውስ ለመግታት የምግብ ዕርዳታ እንደሚጠብቁ አስረድተዋል። ምንም እንኳን በአሁኑ ወቅት ያለው የዝናብ ጥሩ ቢሆንም አርሶ ለማምረት ከሦስት እስከ አራት ወራት ይወስዳል እንዲሁም በአንዳንድ አካባቢዎች የአንበጣ ወረራ መገኘቱንም እንደ ስጋት አንስተዋል። በተለይም የአንበጣ ወረራውን ለመግታት በሚደረገው ትግል የመገናኛ ዘዴዎች መዘጋታቸው አሳሳቢ አድርጎታል ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ እንስሳቱ ክትባት ባለማግኘታቸው በተለያዩ በሽታዎች እየሞቱ እንደሆነም አስረድተዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የእርዳታ ቁሳቁስ የጫኑ 100 የጭነት መኪናዎች ወደ ትግራይ ክልል መዲና መቀለ መግባታቸውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም በትናንትናው ዕለት አስታውቋል። 3500 ቶን ይመዝናሉ የተባሉት የጭነት መኪናዎች ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ሕይወት አድን ቁሶችን ጭነው ነው ወደ ክልሉ የገቡት። ባለፈው ሳምንት የተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ መንግሥት ለትግራይ የእርዳታ አቅርቦቶችን በጠበቀ መንገድ ዘግቷል ሲል ከሷል። በዚህም ምክንያት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ለአደጋ እየተጋለጡ መሆኑን አስጠንቅቋል። የፌደራሉ መንግሥት በበኩሉ ወደ ክልሉ የሰብዓዊ እርዳታ እንዳይገባ እክል የሆኑት የህወሓት አማጺያን ናቸው ይላል። | https://www.bbc.com/amharic/news-58472069 |
5sports
| ለዓለም ዋንጫ ዝግጅት በርካታ የውጭ አገር ሠራተኞች የሞቱባት ኳታር የሠራተኞች አያያዝ | በጉጉት የሚጠበቀው የዓለም ዋንጫ ውድድሮች እሁድ ኅዳር 11/2015 ዓ.ም. ይጀመራል። ከተለያየ የዓለማችን ክፍሎች የሚተሙ የእግር ኳስ ደጋፊዎችም በአስር ሺዎች በሚቆጠሩ ስደተኛ ሠራተኞች አማካኝነት በተገነቡ ስታዲየሞች ጨዋታዎችን ይመለከታሉ። በሠራተኞች ላይ ሞትን ጨምሮ በርካታ የመብት ጥሰቶች ደርሰዋል በሚልም ኳታር ተደራራቢ ውግዘቶችን እያስተናገደች ትገኛለች። ኳታር ለዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ውድድር ሰባት ስታዲየሞችን እንዲሁም አዲስ አውሮፕላን ማረፊያ ፣ በርካታ መንገዶችን የሚያገናኝ መስመር እና 100 ያህል አዳዲስ ሆቴሎችን ገንብታለች። የፍጻሜዎቹን ጨዋታ በሚያስተናግደው ስታዲየም ዙሪያ አንድ ሙሉ ከተማ ተገንብቷ። የኳታር መንግሥት ስታዲየሞቹን ለመገንባት ብቻ 30 ሺህ የውጭ አገር ሠራተኞች መቀጠራቸውን አስታውቋል። አብዛኛዎቹ ከባንግላዴሽ፣ ከሕንድ፣ ከኔፓል እና ከፊሊፒንስ የመጡ ናቸው። በኳታር ስንት የውጭ አገር ሠራተኞች ሞተዋል? ኳታር የዓለም ዋንጫ አዘጋጅነት ካሸነፈች በኋላ ከሕንድ፣ ከፓኪስታን፣ ከኔፓል፣ ከባንግላዲሽ እና ከስሪላንካ የመጡ 6 ሺህ 500 ስደተኛ ሠራተኞች መሞታቸውን ዘጋርዲያን በዘገባው አስነብቧል። ይህ አሃዝ በኳታር የሚገኙ የየአገራቱ ኤምባሲዎች ያወጡትን መረጃ የተመሠረት ያደረገ ነው። ይሁን እንጂ የኳታር መንግሥት የሞቱት ግለሰቦች በሙሉ ከዓለም ዋንጫ ጋር በተያያዙ ፕሮጄክቶች ላይ የሚሰሩ ስላልሆኑ መረጃው የተሳሳተ ነው ብሏል። ከሟቾቹ መካከል ብዙዎቹ በኳታር ውስጥ ለበርካታ ዓመታት ሲሰሩ እንደቆዩ እና በእርጅና ወይም በሌሎች የተፈጥሮ ምክንያቶች ሊሞቱ እንደሚችሉ ተናግሯል። ከ2014 እስከ 2020 ባለው ወቅት ውስጥ በዓለም ዋንጫ ስታዲየሞች ግንባታ ላይ የነበሩ 37 የጉልበት ሠራተኞች መሞታቸውን የገለጸው የኳታር መንግሥት፣ ከእነዚህ ውስጥ ሦስቱ ሞቶች ብቻ “ከሥራ ጋር የተገናኙ” መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ ብሏል። ይሁን እንጂ ዓለም አቀፉ የሠራተኞች ድርጅት በዚህ አይስማማም፣ በማለት በመንግሥት የቀረበው አሃዝ በጣም ዝቅተኛ ግምት ነው ይላል። ኳታር በሥራ ላይ እያሉ በልብ ድካም እና በተንፈስ ችግር የሚሞቱትን ከሥራ ጋር በተገናኘ አድርጎ አድርጋ አትቆጥርም። ሆኖም እነዚህ የህመም ምልክቶች ከፍተኛ በሆነ ሙቀት እና በከባድ የጉልበት ሥራ ምክንያት በሙቀት ወላፈን ሲመቱ የሚመጣ ነው። ተቋሙ ከዓለም ዋንጫ ጋር የተያያዙ አደጋዎችን በተመለከተ በኳታር ውስጥ በመንግሥት ከሚተዳደሩ ሆስፒታሎች እና የአምቡላንስ አገልግሎቶች የተሰበሰቡ መረጃዎች ላይ በመመስረት የራሱን አሃዝ አዘጋጅቷል። በአውሮፓውያኑ 2021 ብቻ 50 የውጭ አገር ሠራተኞች መሞታቸውን እና ከ500 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት፣ 37 ሺህ 600 ደግሞ ቀላል እና መካከለኛ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ብሏል። ቢቢሲ አረብኛም የኳታር መንግሥት የውጭ አገር ሠራተኞችን ሞት አሃዝ መቀነሱን የሚጠቁሙ መረጃዎችን ሰብስቧል። በአውሮፓውያኑ 2010 ኳታር ዓለም ዋንጫን ለማዘጋጀት ውድድሩን ካሸነፈች በኋላ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በውጭ አገር ሠራተኞች አያያዟ ላይ ከፍተኛ ወቀሳ አሰምተዋል። በአውሮፓውያኑ 2016 ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ የኳታር ኩባንያዎችን የግዳጅ የጉልበት ሥራን ይጠቀማሉ ሲል ከሷል። በርካታ ሠራተኞች በማያፈናፍንና በተጨናነቀ መጠለያ ውስጥ እንደሚኖሩ፣ ከፍተኛ የቅጥር ክፍያ እንዲከፍሉ መደረጋቸውን፣ ደመወዝ እንደተከለከሉ እና ፓስፖርታቸውም እንደተቀማ አስታውቋል። ከአውሮፓውያኑ 2017 ጀምሮ መንግሥት የውጭ አገር ሠራተኞችን በጣም በሞቃታማ የአየር ሁኔታ ውስጥ እንዳይሰሩ ለመከላከል፣ የሥራ ሰዓታቸውን ለመቀነስ እና በሠራተኞች ካምፖች ውስጥ ያለውን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል አንዳንድ እርምጃዎችን እንደሚወስድ አሳውቆ ነበር። ሆኖም ባለፈው ዓመት ሌላኛው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድን ሂውማን ራይትስ ዎች የውጭ አገር ሠራተኞች አሁንም “በቅጣት እና ሕገወጥ በሆነ የደመወዝ ቅነሳ” እየተሰቃዩ መሆናቸውን ገልጿል። ለረጅም ሰዓታት አድካሚና የሚያንገላታ ሥራ ሰርተው ለወራት ደመወዝ እንዳልተከፈላቸውም አስታውቋል። የኳታር ኩባንያዎች ከባርነት አይተናነስም በሚባልለት ካፋላ በተሰኘው የዓረብ አገራት ሕግን ተከትለው ይሰሩ ነበር። በዚህም አሰራር መሰረት ሠራተኞች ስፖንሰር ቢደረጉም ሥራቸውን መልቀቅ አይችሉም፤ ፖስፖርታቸውንም ይነጠቃሉ። እንደ ዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት (አይኤልኦ) ባሉ ተቋማት ጫና ምከንያት የኳታር መንግሥት ካፋላን ቢያስቀርም፤ ነገር ግን አምነስቲ አሁንም ኩባንያዎች የጉልበት ሠራተኞች ቀጣሪዎች እንዳይቀይሩ ጫና ያደርጋሉ ብሏል። በሠራተኛ ሕጉ ላይ ያለው ማሻሻያ የዓለም ዋንጫ ካለቀ በኋላም መቆም እንደሌለበት አስጠንቅቋል። ከዓለም አቀፉ ሠራተኞች ተቋም ጋር በመተባበር የኳታር መንግሥት በርካታ ማሻሻያዎችን አድርጓል። ከእነዚህም መካከል አሠሪዎች ለሠራተኞቻቸው በወቅቱ ክፍያ እንዲከፍሉ ለማድረግ የተነደፈ የደመወዝ ጥበቃ ዘዴን ያጠቃልላል። የኳታር መንግሥት ቃል አቀባይ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ማሻሻያው በኳታር የሚገኙ አብዛኞቹን የውጭ አገር ሠራተኞችን የሥራ ሁኔታ የለወጠ ነው። “ማሻሻያዎቹ ተግባራዊ መሆናቸውንም ለማረጋገጥ እርምጃዎች ተወስደዋል” ብለዋል ቃል አቀባዩ ። “እነዚህ እርምጃዎች በቀጠሉ ቁጥር ሕግን የሚጥሱ ኩባንያዎች ቁጥር ማሽቆልቆሉን ይቀጥላል” ሲሉም አስረድተዋል። ይህ ጉዳይ እስከ ፍጻሜዎቹ ጨዋታዎች ድረስ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚችል አመላካች ነው። ዓለም አቀፉን እግር ኳስ የሚመራው ፊፋ ለዓለም ዋንጫ ተሳታፊ 32 ቡድኖች “ትኩረት ሰጥተው በእግር ኳስ ላይ እንዲያተኩሩ” የሚጠይቅ ደብዳቤ ጽፏል። ስፖርቱን ወደ ርዕዮተ ዓለም ወይም ፖለቲካዊ “ጦርነት” መወሰድ ወይም “የሞራል ትምህርቶችን ለመስጠት መጠቀሚያ” መሆን የለበትም ብሏል። ለፊፋ ደብዳቤም በምላሹ አሥር የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበራት “ሰብአዊ መብቶች ሁሉን አቀፍ እና በሁሉም ቦታ የሚተገበሩ ናቸው” ብለዋል። የአውስትራሊያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ኳታር በስደተኛ ሠራተኞች ላይ በደል እየፈፀመች ነው በሚል ነቅፎ ቪዲዮ አውጥቷል። የዴንማርክ ተጫዋቾች የኳታርን የሰብአዊ መብት አያያዝ ለመቃወም ሙሉ ለሙሉ ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ። | ለዓለም ዋንጫ ዝግጅት በርካታ የውጭ አገር ሠራተኞች የሞቱባት ኳታር የሠራተኞች አያያዝ በጉጉት የሚጠበቀው የዓለም ዋንጫ ውድድሮች እሁድ ኅዳር 11/2015 ዓ.ም. ይጀመራል። ከተለያየ የዓለማችን ክፍሎች የሚተሙ የእግር ኳስ ደጋፊዎችም በአስር ሺዎች በሚቆጠሩ ስደተኛ ሠራተኞች አማካኝነት በተገነቡ ስታዲየሞች ጨዋታዎችን ይመለከታሉ። በሠራተኞች ላይ ሞትን ጨምሮ በርካታ የመብት ጥሰቶች ደርሰዋል በሚልም ኳታር ተደራራቢ ውግዘቶችን እያስተናገደች ትገኛለች። ኳታር ለዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ውድድር ሰባት ስታዲየሞችን እንዲሁም አዲስ አውሮፕላን ማረፊያ ፣ በርካታ መንገዶችን የሚያገናኝ መስመር እና 100 ያህል አዳዲስ ሆቴሎችን ገንብታለች። የፍጻሜዎቹን ጨዋታ በሚያስተናግደው ስታዲየም ዙሪያ አንድ ሙሉ ከተማ ተገንብቷ። የኳታር መንግሥት ስታዲየሞቹን ለመገንባት ብቻ 30 ሺህ የውጭ አገር ሠራተኞች መቀጠራቸውን አስታውቋል። አብዛኛዎቹ ከባንግላዴሽ፣ ከሕንድ፣ ከኔፓል እና ከፊሊፒንስ የመጡ ናቸው። በኳታር ስንት የውጭ አገር ሠራተኞች ሞተዋል? ኳታር የዓለም ዋንጫ አዘጋጅነት ካሸነፈች በኋላ ከሕንድ፣ ከፓኪስታን፣ ከኔፓል፣ ከባንግላዲሽ እና ከስሪላንካ የመጡ 6 ሺህ 500 ስደተኛ ሠራተኞች መሞታቸውን ዘጋርዲያን በዘገባው አስነብቧል። ይህ አሃዝ በኳታር የሚገኙ የየአገራቱ ኤምባሲዎች ያወጡትን መረጃ የተመሠረት ያደረገ ነው። ይሁን እንጂ የኳታር መንግሥት የሞቱት ግለሰቦች በሙሉ ከዓለም ዋንጫ ጋር በተያያዙ ፕሮጄክቶች ላይ የሚሰሩ ስላልሆኑ መረጃው የተሳሳተ ነው ብሏል። ከሟቾቹ መካከል ብዙዎቹ በኳታር ውስጥ ለበርካታ ዓመታት ሲሰሩ እንደቆዩ እና በእርጅና ወይም በሌሎች የተፈጥሮ ምክንያቶች ሊሞቱ እንደሚችሉ ተናግሯል። ከ2014 እስከ 2020 ባለው ወቅት ውስጥ በዓለም ዋንጫ ስታዲየሞች ግንባታ ላይ የነበሩ 37 የጉልበት ሠራተኞች መሞታቸውን የገለጸው የኳታር መንግሥት፣ ከእነዚህ ውስጥ ሦስቱ ሞቶች ብቻ “ከሥራ ጋር የተገናኙ” መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ ብሏል። ይሁን እንጂ ዓለም አቀፉ የሠራተኞች ድርጅት በዚህ አይስማማም፣ በማለት በመንግሥት የቀረበው አሃዝ በጣም ዝቅተኛ ግምት ነው ይላል። ኳታር በሥራ ላይ እያሉ በልብ ድካም እና በተንፈስ ችግር የሚሞቱትን ከሥራ ጋር በተገናኘ አድርጎ አድርጋ አትቆጥርም። ሆኖም እነዚህ የህመም ምልክቶች ከፍተኛ በሆነ ሙቀት እና በከባድ የጉልበት ሥራ ምክንያት በሙቀት ወላፈን ሲመቱ የሚመጣ ነው። ተቋሙ ከዓለም ዋንጫ ጋር የተያያዙ አደጋዎችን በተመለከተ በኳታር ውስጥ በመንግሥት ከሚተዳደሩ ሆስፒታሎች እና የአምቡላንስ አገልግሎቶች የተሰበሰቡ መረጃዎች ላይ በመመስረት የራሱን አሃዝ አዘጋጅቷል። በአውሮፓውያኑ 2021 ብቻ 50 የውጭ አገር ሠራተኞች መሞታቸውን እና ከ500 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት፣ 37 ሺህ 600 ደግሞ ቀላል እና መካከለኛ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ብሏል። ቢቢሲ አረብኛም የኳታር መንግሥት የውጭ አገር ሠራተኞችን ሞት አሃዝ መቀነሱን የሚጠቁሙ መረጃዎችን ሰብስቧል። በአውሮፓውያኑ 2010 ኳታር ዓለም ዋንጫን ለማዘጋጀት ውድድሩን ካሸነፈች በኋላ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በውጭ አገር ሠራተኞች አያያዟ ላይ ከፍተኛ ወቀሳ አሰምተዋል። በአውሮፓውያኑ 2016 ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ የኳታር ኩባንያዎችን የግዳጅ የጉልበት ሥራን ይጠቀማሉ ሲል ከሷል። በርካታ ሠራተኞች በማያፈናፍንና በተጨናነቀ መጠለያ ውስጥ እንደሚኖሩ፣ ከፍተኛ የቅጥር ክፍያ እንዲከፍሉ መደረጋቸውን፣ ደመወዝ እንደተከለከሉ እና ፓስፖርታቸውም እንደተቀማ አስታውቋል። ከአውሮፓውያኑ 2017 ጀምሮ መንግሥት የውጭ አገር ሠራተኞችን በጣም በሞቃታማ የአየር ሁኔታ ውስጥ እንዳይሰሩ ለመከላከል፣ የሥራ ሰዓታቸውን ለመቀነስ እና በሠራተኞች ካምፖች ውስጥ ያለውን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል አንዳንድ እርምጃዎችን እንደሚወስድ አሳውቆ ነበር። ሆኖም ባለፈው ዓመት ሌላኛው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድን ሂውማን ራይትስ ዎች የውጭ አገር ሠራተኞች አሁንም “በቅጣት እና ሕገወጥ በሆነ የደመወዝ ቅነሳ” እየተሰቃዩ መሆናቸውን ገልጿል። ለረጅም ሰዓታት አድካሚና የሚያንገላታ ሥራ ሰርተው ለወራት ደመወዝ እንዳልተከፈላቸውም አስታውቋል። የኳታር ኩባንያዎች ከባርነት አይተናነስም በሚባልለት ካፋላ በተሰኘው የዓረብ አገራት ሕግን ተከትለው ይሰሩ ነበር። በዚህም አሰራር መሰረት ሠራተኞች ስፖንሰር ቢደረጉም ሥራቸውን መልቀቅ አይችሉም፤ ፖስፖርታቸውንም ይነጠቃሉ። እንደ ዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት (አይኤልኦ) ባሉ ተቋማት ጫና ምከንያት የኳታር መንግሥት ካፋላን ቢያስቀርም፤ ነገር ግን አምነስቲ አሁንም ኩባንያዎች የጉልበት ሠራተኞች ቀጣሪዎች እንዳይቀይሩ ጫና ያደርጋሉ ብሏል። በሠራተኛ ሕጉ ላይ ያለው ማሻሻያ የዓለም ዋንጫ ካለቀ በኋላም መቆም እንደሌለበት አስጠንቅቋል። ከዓለም አቀፉ ሠራተኞች ተቋም ጋር በመተባበር የኳታር መንግሥት በርካታ ማሻሻያዎችን አድርጓል። ከእነዚህም መካከል አሠሪዎች ለሠራተኞቻቸው በወቅቱ ክፍያ እንዲከፍሉ ለማድረግ የተነደፈ የደመወዝ ጥበቃ ዘዴን ያጠቃልላል። የኳታር መንግሥት ቃል አቀባይ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ማሻሻያው በኳታር የሚገኙ አብዛኞቹን የውጭ አገር ሠራተኞችን የሥራ ሁኔታ የለወጠ ነው። “ማሻሻያዎቹ ተግባራዊ መሆናቸውንም ለማረጋገጥ እርምጃዎች ተወስደዋል” ብለዋል ቃል አቀባዩ ። “እነዚህ እርምጃዎች በቀጠሉ ቁጥር ሕግን የሚጥሱ ኩባንያዎች ቁጥር ማሽቆልቆሉን ይቀጥላል” ሲሉም አስረድተዋል። ይህ ጉዳይ እስከ ፍጻሜዎቹ ጨዋታዎች ድረስ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚችል አመላካች ነው። ዓለም አቀፉን እግር ኳስ የሚመራው ፊፋ ለዓለም ዋንጫ ተሳታፊ 32 ቡድኖች “ትኩረት ሰጥተው በእግር ኳስ ላይ እንዲያተኩሩ” የሚጠይቅ ደብዳቤ ጽፏል። ስፖርቱን ወደ ርዕዮተ ዓለም ወይም ፖለቲካዊ “ጦርነት” መወሰድ ወይም “የሞራል ትምህርቶችን ለመስጠት መጠቀሚያ” መሆን የለበትም ብሏል። ለፊፋ ደብዳቤም በምላሹ አሥር የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበራት “ሰብአዊ መብቶች ሁሉን አቀፍ እና በሁሉም ቦታ የሚተገበሩ ናቸው” ብለዋል። የአውስትራሊያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ኳታር በስደተኛ ሠራተኞች ላይ በደል እየፈፀመች ነው በሚል ነቅፎ ቪዲዮ አውጥቷል። የዴንማርክ ተጫዋቾች የኳታርን የሰብአዊ መብት አያያዝ ለመቃወም ሙሉ ለሙሉ ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cj594vzzzj5o |
5sports
| ሊቨርፑል ከሪያል ማድሪድ በነበረው ጨዋታ የተፈጠሩ ክስተቶች እንዲመረመሩ ጠየቀ | ሊቨርፑል ከሪያል ማድሪድ ጋር ያደረጉትን የቻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታን እንዲዘገይ ያደረገውና ደጋፊዎች ያጋጠሟቸው "ተቀባይነት የሌላቸው ጉዳዮች" ላይ ምርመራ እንዲደረግ ጠየቀ። የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበራት ኅብረት የደህንንት ምክንያቶችን ጠቅሶ ጨዋታውን እንዲዘገይ ያደረገው ሲሆን በዚህም ጨዋታው ከ30 ደቂቃ በላይ መዘግየት አጋጥሞታል። በፈረንሳይዋ መዲና ፓሪስ ስታድ ዴ ፍራንስ ስታዲየም የተደረገው የቻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ እስከ ምሽቱ አራት ተኩል ድረስ ያልተጀመረ ሲሆን በዚህ ጨዋታም ሪያል ማድሪድ ሊቨርፑልን 1 ለ0 ረትቷል። ጥቂት ደጋፊዎችም በግንብ አጥሮች ላይ ለመውጣት ሲሞክሩ ፖሊሶች አስለቃሽ ጭስ ተኩሰዋል። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ደጋፊዎች በተጨናነቁ ሰልፎች ወደ ስታዲየሙ ለመግባት ሲሞክሩ የሚያሳዩ ምስሎችም መውጣት ጀምረዋል። በርካቶች ጨዋታው ከመጀመሩ ከሰዓታት በፊት ወደ ስታዲየሙ እንደደረሱ ቢናገሩም ወደ ስታዲየሙ ግቢ እንዳይገቡ መከልከላቸውን ተናግረዋል። "የሊቨርፑል ደጋፊዎች ወደ ስታድ ዴ ፍራንስ ስታዲየም ለመግባት ሲሞክሩ ባጋጠሟቸው ጉዳዮች እንዲሁም የጸጥታው ብልሽት በደጋፊዎቻችን ላይ የፈጠረው እክል በጣም አሳዝኖናል" ሲል የአንፊልድ ክለብ መግለጫ አውጥቷል። "ይህ በአውሮፓ እግር ኳስ ታላቅ ውድድር ነው እና ደጋፊዎች ዛሬ ማምሻውን ያየናቸው ትዕይንቶች ሊያጋጥማቸው አይገባም። የእነዚህ ተቀባይነት የሌላቸው ጉዳዮች መንስኤዎች ላይ መደበኛ ምርመራ እንዲደረግ በይፋ ጠይቀናል" ብሏል። የአውሮፓ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ዩኤፋ በበኩሉ "በእነዚህ በተፈጠሩት ክስተቶች ለተጎዱት እናዝናለን። የተፈጠሩትንም ጉዳዮች ከፈረንሳይ ፖሊስ እና ባለስልጣናት እንዲሁም ከፈረንሳይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በጋራ እንመረምራለን" ብሏል። ሆኖም ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት በሊቨርፑል ደጋፊዎች መግቢያ በኩል ሃሰተኛ ትኬቶችን የያዙ በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎች ለማለፍ ሲሞክሩ ቲኬቱ ባለመስራቱ መታገዳቸውንም ገልጿል። በዚህም ወደ ስታዲየሙ ለመግባት የሚሞክሩ በርካታ ደጋፊዎች ላይ መጨናነቅ መፍጠሩንና እውነተኛ ቲኬት የያዙ ደጋፊዎች ወደ ስታዲየሙ እንዲገቡ ለማድረግ በነበረውም ሙከራ ጨዋታው በ35 ደቂቃ መዘግየቱን አስታውቋል። ጨዋታው ከተጀመረም በኋላ ከስታዲየም ውጭ የነበሩ ደጋፊዎች ቁጥር መበራከቱ የቀጠለ ሲሆን ፖሊሶች አስለቃሽ ጭስ በመጠቀም ከስታዲየሙ እንዲርቁም አድርገዋቸዋል ብሏል። የፈረንሳይ ፖሊስ በበኩሉ ሃሰተኛ ትኬቶችን የያዙ ደጋፊዎች በግድ ወደ ስታዲየሙ ለመግባት እንደሞከሩና "ፖሊስ በሰጠው ፈጣን ምላሽ ሁኔታው እንደተረጋጋ" ገልጿል። | ሊቨርፑል ከሪያል ማድሪድ በነበረው ጨዋታ የተፈጠሩ ክስተቶች እንዲመረመሩ ጠየቀ ሊቨርፑል ከሪያል ማድሪድ ጋር ያደረጉትን የቻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታን እንዲዘገይ ያደረገውና ደጋፊዎች ያጋጠሟቸው "ተቀባይነት የሌላቸው ጉዳዮች" ላይ ምርመራ እንዲደረግ ጠየቀ። የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበራት ኅብረት የደህንንት ምክንያቶችን ጠቅሶ ጨዋታውን እንዲዘገይ ያደረገው ሲሆን በዚህም ጨዋታው ከ30 ደቂቃ በላይ መዘግየት አጋጥሞታል። በፈረንሳይዋ መዲና ፓሪስ ስታድ ዴ ፍራንስ ስታዲየም የተደረገው የቻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ እስከ ምሽቱ አራት ተኩል ድረስ ያልተጀመረ ሲሆን በዚህ ጨዋታም ሪያል ማድሪድ ሊቨርፑልን 1 ለ0 ረትቷል። ጥቂት ደጋፊዎችም በግንብ አጥሮች ላይ ለመውጣት ሲሞክሩ ፖሊሶች አስለቃሽ ጭስ ተኩሰዋል። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ደጋፊዎች በተጨናነቁ ሰልፎች ወደ ስታዲየሙ ለመግባት ሲሞክሩ የሚያሳዩ ምስሎችም መውጣት ጀምረዋል። በርካቶች ጨዋታው ከመጀመሩ ከሰዓታት በፊት ወደ ስታዲየሙ እንደደረሱ ቢናገሩም ወደ ስታዲየሙ ግቢ እንዳይገቡ መከልከላቸውን ተናግረዋል። "የሊቨርፑል ደጋፊዎች ወደ ስታድ ዴ ፍራንስ ስታዲየም ለመግባት ሲሞክሩ ባጋጠሟቸው ጉዳዮች እንዲሁም የጸጥታው ብልሽት በደጋፊዎቻችን ላይ የፈጠረው እክል በጣም አሳዝኖናል" ሲል የአንፊልድ ክለብ መግለጫ አውጥቷል። "ይህ በአውሮፓ እግር ኳስ ታላቅ ውድድር ነው እና ደጋፊዎች ዛሬ ማምሻውን ያየናቸው ትዕይንቶች ሊያጋጥማቸው አይገባም። የእነዚህ ተቀባይነት የሌላቸው ጉዳዮች መንስኤዎች ላይ መደበኛ ምርመራ እንዲደረግ በይፋ ጠይቀናል" ብሏል። የአውሮፓ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ዩኤፋ በበኩሉ "በእነዚህ በተፈጠሩት ክስተቶች ለተጎዱት እናዝናለን። የተፈጠሩትንም ጉዳዮች ከፈረንሳይ ፖሊስ እና ባለስልጣናት እንዲሁም ከፈረንሳይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በጋራ እንመረምራለን" ብሏል። ሆኖም ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት በሊቨርፑል ደጋፊዎች መግቢያ በኩል ሃሰተኛ ትኬቶችን የያዙ በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎች ለማለፍ ሲሞክሩ ቲኬቱ ባለመስራቱ መታገዳቸውንም ገልጿል። በዚህም ወደ ስታዲየሙ ለመግባት የሚሞክሩ በርካታ ደጋፊዎች ላይ መጨናነቅ መፍጠሩንና እውነተኛ ቲኬት የያዙ ደጋፊዎች ወደ ስታዲየሙ እንዲገቡ ለማድረግ በነበረውም ሙከራ ጨዋታው በ35 ደቂቃ መዘግየቱን አስታውቋል። ጨዋታው ከተጀመረም በኋላ ከስታዲየም ውጭ የነበሩ ደጋፊዎች ቁጥር መበራከቱ የቀጠለ ሲሆን ፖሊሶች አስለቃሽ ጭስ በመጠቀም ከስታዲየሙ እንዲርቁም አድርገዋቸዋል ብሏል። የፈረንሳይ ፖሊስ በበኩሉ ሃሰተኛ ትኬቶችን የያዙ ደጋፊዎች በግድ ወደ ስታዲየሙ ለመግባት እንደሞከሩና "ፖሊስ በሰጠው ፈጣን ምላሽ ሁኔታው እንደተረጋጋ" ገልጿል። | https://www.bbc.com/amharic/news-61612597 |
3politics
| በሶማሊያ ለሁለተኛ ጊዜ ፕሬዝዳንት የሆኑት ሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ ማን ናቸው? | የመሪነት ሥልጣንን ሲጨብጡ የመጀመሪያቸው አይደለም። እአአ ከ2012 እስከ 2017 የሶማሊያ ስምንተኛው ፕሬዝዳንት ነበሩ። በ2017 በድጋሚ ሲወዳደሩ ግን የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ረቷቸው። በቀውስ በምትናጠው የአፍሪካ ቀንድ አገር ሶማሊያ በድጋሚ በመመረጥ ሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ ታሪክ ሠርተዋል። የትላንቱ ምርጫ በአገሪቷ ታሪክ ፉክክር የበዛበት ነበር። የምርጫ ሂደቱ በሦስት ዙር ተካሂዷል። አዲሱ ፕሬዝዳንት በትምህርት ዘርፍ ይታወቃሉ። የምረጡኝ ቅስቀሳቸው ማጠንጠኛ ሶማሊያን ከተቀረው ዓለም ማስታረቅና የሕዝቡን አንድነት ማረጋገጥ ነው። በበዓለ ሲመታቸው የተናገሩትም ይህን ሕልማቸውን ነው። "ከቀጠናውና ከዓለም አቀፍ አካላት ጋር በቅርበት እንደምንሠራ ቃል እገባለሁ" ብለዋል። ከድምጻቸው እርቅ ይስተጋባል። ለእያንዳንዱ የሶማሊያ ዜጋ እንደሚሠሩም ተናግረዋል። በሦስተኛው የድምጽ መስጫ ደረጃ በ214 አብላጫ ድምጽ፣ 110 ድምጽ ያገኙትን ፋርማጆ አሸንፈዋል። 2017 ላይ ያሸነፏቸው ፋርማጆን በ2022 መልሰው አሸንፈዋቸዋል። ያለፉትን ሁለት ዓመታት ያሳለፉት በሞቃዲሾ የምርጫ ቅስቀሳ በማድረግ ነው። ፋርማጆ ሥልጣናቸውን ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ለማራዘም ሲሞክሩ ከተቃወሙ መካከል ሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ አንዱ ናቸው። አምና የፀጥታ ኃይል አባላት ቤታቸውን ከፈተሹ በኋላ መነጋገሪያ ሆነዋል። ፍተሻው የተካሄደው ተቃዋሚዎች ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ በወጠኑበት ወቅት ነበር። ሶማሊያ ለ30 ዓመታት በእርስ በእርስ ጦርነት ስትናጥ አገሪቱን ጥለው ካልሄዱ ጥቂት መሪዎች መካከልም አንዱ ናቸው። ሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ ከፍተኛ ድርቅን ጨምሮ በበርካታ ችግሮች የተሸበበች አገር ነው ከፋርማጆ የሚረከቡት። የተባበሩት መንግሥታት እንደሚለው፣ ድርቁ ካልተገታ ወደ ረሃብ ከፍ ሊል ይችላል። ከ3.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በሩሃብ አፋፍ ላይ ሆነው አፋጣኝ የምግብ እርዳታ ይጠብቃሉ። ሶማሊያን የኑሮ ውድነትና የዩክሬን ጦርነት ያባባሰው የዋጋ ግሽበትም ይፈትናታል። በፌደራል መንግሥቱና በክልሎች መካከል እየሰፋ ያለው ልዩነትም ሌላው የሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ የቤት ሥራ ይሆናል። ሙስና ሌላው የሶማሊያ ማነቆ ነው። ተንታኞች እንደሚሉት አዲሱ ፕሬዝዳንት አገራቸው ከኬንያ፣ ጂቡቲ እና ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጋር ያላትን ግንኙነት የማደስ ኃላፊነትም ተጥሎባቸዋል። የቀድሞው ፕሬዝዳንት የሶማሊያ እና ኬንያን ግንኙነት ቆርጠዋል። አገራቱ በባሕር ወሰንም ይወዛገባሉ። ሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ 2012 ላይ ሲመረጡ አገራቸው ከምዕራባውያን እና ከአፍሪካ አገራት ጋር መደበኛ የዲፕሎማሲ ትስስተሯን እንድታድስ አስችለዋል። በሌላ በኩል በአስተዳደራቸው ስር ያለውን ሙስና ማስወገድ አልቻሉም ተብለው ይታማሉ። የተወለዱት እአአ በ1955 ሂራን ግዛት ነው። በሞቃዲሾ በመካከለኛው መደብ ሰፈር አድገው ከሶማሊያ ብሔራዊ ዩኒቨርስቲ በምህንድስና በ1981 ተመርቀዋል። በቅርብ የሚያውቋቸው ዝምተኛና የማይታበዩ ሰው ናቸው ይሏቸዋል። ሁለተኛ ዲግሪ ከመሥራታቸው በፊት በሕንድ ቦሆፓል ዩኒቨርስቲ አስተማሪ ነበሩ። ወደ ሶማሊያ ሲመለሱ በተባበሩት መንግሥታት የተዘረጋውን የመምህራን ሥልጠና ለመምራት በትምህርት ሚኒስቴር ተቀጠሩ። በ1991 ማዕከላዊው መንግሥት ሲንኮታኮት፣ በዩኒሴፍ የትምህር ኃላፊ ሆነው ተቀጠሩ። በደቡብና ማዕከላዊ ሶማሊያ ይዘዋወሩ ነበር። ወቅቱ በትምህርት ዘርፍ ያለውን ውድቀት በቅርበት ያስተዋሉበት ነበር። ከሦስት ዓመታት በኋላ፣ በሞቃዲሾ ጦርነቱ ከተነሳ ወዲህ ግንባር ቀደም ከሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አንዱን ከፈቱ። የሙስሊም ወንድማማችነት (Muslim Brotherhood) የሶማሊያ ቅርንጫፍ የሆነው አል-ኢላህ ጋር ግንኙነት አላቸው። የጎሳ ግጭት በተነሳበት ወቅት ለማኅበረሰቡ የትምህርት ሥርዓት በመዘርጋት ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። ቡድኑ በግብፅና ሱዳን ጋር በተመሳሳይ በሆነ የእስልምና አስተምህሮት የሚተዳደር ትምህርት ቤቶች ከፍቷል። እንደ አል-ሸባብ እና አል-ቃይዳ ያሉ አክራሪዎችንም ያወግዛል። ሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ "ለዘብተኛ ሙስሊም" ተብለው ይታወቃሉ። በጦርነት የደቀቀችውን ሶማሊያ ለመደገፍ በንግድ ሰዎች የተቋቋመው 'ዩኒየን ኦፍ ኢስላሚክ ኮርትስ' ከተባለው ፍርድ ቤት ጋርም ትስስር አላቸው። ፍርድ ቤቱ በ2006 ለአገሪቱ አንጻራዊ ሰላም አምጥቷል። አል-ሸባብ በፍርድ ቤቱ ያለው ጫና እየጨመረ መሄድ ያሰጋት ኢትዮጵያ ፍርድ ቤቱን የሚቀለብስ እርምጃ መውሰዷ ይታወሳል። የአዲሱ ፕሬዝዳንት ደጋፊዎች እንደሚሉት፣ ሰላምና መረጋጋትን ለመመለስ የሚሠሩ መሪ ናቸው። በ1990ዎቹ የሲቪል ማኅበራት ውስጥ ከፍተኛ ንቅናቄ ያደርጉ ነበር። የጎሳ ግጭትን በማርገብም ይታወቃሉ። ሞቃዲሾን ለሁለት ሰንጥቆ በሁለት ተፎካካሪ ጎሳዎች እንድትመራ ያደረጋት "ግሪን ላየን" የተባለውን አካሄድ ለማፍረስ በተደረገው ድርድር ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። ይህ አካሄድ "የሞቃዲሾ ካንሰር" ተብሎ ይጠራ ነበር። ለነዋሪዎችና ለፖለቲከኞችም ሕይወትን ፈታኝ አድርጓ ቆይቷል። በሽግግር አስተዳደር ወቅት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አማካሪ ነበሩ። በ2001 ከግጭት በኋላ እርቅ ለማውረድ የሚጥረው የ'ሴንተር ፎር ሪሰርች ኤንድ ዳያሎግ' አጥኚ ሆነው ተቀጥረዋል። ይህ ማዕከል ከምዕራቡ ዓለም ጋር ባለው ቅርርብ ይተቻል። ሆኖም ጥናቶቻቸው ሶማሊያን ከ30 ዓመታት የእርስ በእርስ ጦርነት ለማውጣት ያግዛሉ ተብሎ ይታመናል። | በሶማሊያ ለሁለተኛ ጊዜ ፕሬዝዳንት የሆኑት ሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ ማን ናቸው? የመሪነት ሥልጣንን ሲጨብጡ የመጀመሪያቸው አይደለም። እአአ ከ2012 እስከ 2017 የሶማሊያ ስምንተኛው ፕሬዝዳንት ነበሩ። በ2017 በድጋሚ ሲወዳደሩ ግን የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ረቷቸው። በቀውስ በምትናጠው የአፍሪካ ቀንድ አገር ሶማሊያ በድጋሚ በመመረጥ ሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ ታሪክ ሠርተዋል። የትላንቱ ምርጫ በአገሪቷ ታሪክ ፉክክር የበዛበት ነበር። የምርጫ ሂደቱ በሦስት ዙር ተካሂዷል። አዲሱ ፕሬዝዳንት በትምህርት ዘርፍ ይታወቃሉ። የምረጡኝ ቅስቀሳቸው ማጠንጠኛ ሶማሊያን ከተቀረው ዓለም ማስታረቅና የሕዝቡን አንድነት ማረጋገጥ ነው። በበዓለ ሲመታቸው የተናገሩትም ይህን ሕልማቸውን ነው። "ከቀጠናውና ከዓለም አቀፍ አካላት ጋር በቅርበት እንደምንሠራ ቃል እገባለሁ" ብለዋል። ከድምጻቸው እርቅ ይስተጋባል። ለእያንዳንዱ የሶማሊያ ዜጋ እንደሚሠሩም ተናግረዋል። በሦስተኛው የድምጽ መስጫ ደረጃ በ214 አብላጫ ድምጽ፣ 110 ድምጽ ያገኙትን ፋርማጆ አሸንፈዋል። 2017 ላይ ያሸነፏቸው ፋርማጆን በ2022 መልሰው አሸንፈዋቸዋል። ያለፉትን ሁለት ዓመታት ያሳለፉት በሞቃዲሾ የምርጫ ቅስቀሳ በማድረግ ነው። ፋርማጆ ሥልጣናቸውን ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ለማራዘም ሲሞክሩ ከተቃወሙ መካከል ሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ አንዱ ናቸው። አምና የፀጥታ ኃይል አባላት ቤታቸውን ከፈተሹ በኋላ መነጋገሪያ ሆነዋል። ፍተሻው የተካሄደው ተቃዋሚዎች ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ በወጠኑበት ወቅት ነበር። ሶማሊያ ለ30 ዓመታት በእርስ በእርስ ጦርነት ስትናጥ አገሪቱን ጥለው ካልሄዱ ጥቂት መሪዎች መካከልም አንዱ ናቸው። ሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ ከፍተኛ ድርቅን ጨምሮ በበርካታ ችግሮች የተሸበበች አገር ነው ከፋርማጆ የሚረከቡት። የተባበሩት መንግሥታት እንደሚለው፣ ድርቁ ካልተገታ ወደ ረሃብ ከፍ ሊል ይችላል። ከ3.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በሩሃብ አፋፍ ላይ ሆነው አፋጣኝ የምግብ እርዳታ ይጠብቃሉ። ሶማሊያን የኑሮ ውድነትና የዩክሬን ጦርነት ያባባሰው የዋጋ ግሽበትም ይፈትናታል። በፌደራል መንግሥቱና በክልሎች መካከል እየሰፋ ያለው ልዩነትም ሌላው የሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ የቤት ሥራ ይሆናል። ሙስና ሌላው የሶማሊያ ማነቆ ነው። ተንታኞች እንደሚሉት አዲሱ ፕሬዝዳንት አገራቸው ከኬንያ፣ ጂቡቲ እና ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጋር ያላትን ግንኙነት የማደስ ኃላፊነትም ተጥሎባቸዋል። የቀድሞው ፕሬዝዳንት የሶማሊያ እና ኬንያን ግንኙነት ቆርጠዋል። አገራቱ በባሕር ወሰንም ይወዛገባሉ። ሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ 2012 ላይ ሲመረጡ አገራቸው ከምዕራባውያን እና ከአፍሪካ አገራት ጋር መደበኛ የዲፕሎማሲ ትስስተሯን እንድታድስ አስችለዋል። በሌላ በኩል በአስተዳደራቸው ስር ያለውን ሙስና ማስወገድ አልቻሉም ተብለው ይታማሉ። የተወለዱት እአአ በ1955 ሂራን ግዛት ነው። በሞቃዲሾ በመካከለኛው መደብ ሰፈር አድገው ከሶማሊያ ብሔራዊ ዩኒቨርስቲ በምህንድስና በ1981 ተመርቀዋል። በቅርብ የሚያውቋቸው ዝምተኛና የማይታበዩ ሰው ናቸው ይሏቸዋል። ሁለተኛ ዲግሪ ከመሥራታቸው በፊት በሕንድ ቦሆፓል ዩኒቨርስቲ አስተማሪ ነበሩ። ወደ ሶማሊያ ሲመለሱ በተባበሩት መንግሥታት የተዘረጋውን የመምህራን ሥልጠና ለመምራት በትምህርት ሚኒስቴር ተቀጠሩ። በ1991 ማዕከላዊው መንግሥት ሲንኮታኮት፣ በዩኒሴፍ የትምህር ኃላፊ ሆነው ተቀጠሩ። በደቡብና ማዕከላዊ ሶማሊያ ይዘዋወሩ ነበር። ወቅቱ በትምህርት ዘርፍ ያለውን ውድቀት በቅርበት ያስተዋሉበት ነበር። ከሦስት ዓመታት በኋላ፣ በሞቃዲሾ ጦርነቱ ከተነሳ ወዲህ ግንባር ቀደም ከሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አንዱን ከፈቱ። የሙስሊም ወንድማማችነት (Muslim Brotherhood) የሶማሊያ ቅርንጫፍ የሆነው አል-ኢላህ ጋር ግንኙነት አላቸው። የጎሳ ግጭት በተነሳበት ወቅት ለማኅበረሰቡ የትምህርት ሥርዓት በመዘርጋት ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። ቡድኑ በግብፅና ሱዳን ጋር በተመሳሳይ በሆነ የእስልምና አስተምህሮት የሚተዳደር ትምህርት ቤቶች ከፍቷል። እንደ አል-ሸባብ እና አል-ቃይዳ ያሉ አክራሪዎችንም ያወግዛል። ሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ "ለዘብተኛ ሙስሊም" ተብለው ይታወቃሉ። በጦርነት የደቀቀችውን ሶማሊያ ለመደገፍ በንግድ ሰዎች የተቋቋመው 'ዩኒየን ኦፍ ኢስላሚክ ኮርትስ' ከተባለው ፍርድ ቤት ጋርም ትስስር አላቸው። ፍርድ ቤቱ በ2006 ለአገሪቱ አንጻራዊ ሰላም አምጥቷል። አል-ሸባብ በፍርድ ቤቱ ያለው ጫና እየጨመረ መሄድ ያሰጋት ኢትዮጵያ ፍርድ ቤቱን የሚቀለብስ እርምጃ መውሰዷ ይታወሳል። የአዲሱ ፕሬዝዳንት ደጋፊዎች እንደሚሉት፣ ሰላምና መረጋጋትን ለመመለስ የሚሠሩ መሪ ናቸው። በ1990ዎቹ የሲቪል ማኅበራት ውስጥ ከፍተኛ ንቅናቄ ያደርጉ ነበር። የጎሳ ግጭትን በማርገብም ይታወቃሉ። ሞቃዲሾን ለሁለት ሰንጥቆ በሁለት ተፎካካሪ ጎሳዎች እንድትመራ ያደረጋት "ግሪን ላየን" የተባለውን አካሄድ ለማፍረስ በተደረገው ድርድር ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። ይህ አካሄድ "የሞቃዲሾ ካንሰር" ተብሎ ይጠራ ነበር። ለነዋሪዎችና ለፖለቲከኞችም ሕይወትን ፈታኝ አድርጓ ቆይቷል። በሽግግር አስተዳደር ወቅት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አማካሪ ነበሩ። በ2001 ከግጭት በኋላ እርቅ ለማውረድ የሚጥረው የ'ሴንተር ፎር ሪሰርች ኤንድ ዳያሎግ' አጥኚ ሆነው ተቀጥረዋል። ይህ ማዕከል ከምዕራቡ ዓለም ጋር ባለው ቅርርብ ይተቻል። ሆኖም ጥናቶቻቸው ሶማሊያን ከ30 ዓመታት የእርስ በእርስ ጦርነት ለማውጣት ያግዛሉ ተብሎ ይታመናል። | https://www.bbc.com/amharic/news-61468546 |
2health
| በአውስትራሊያ በአፍንጫ የሚወሰድ የኮቪድ-19 መከላከያ ላይ ሙከራ እየተደረገ ነው | የደም መርጋት ሲያጋጥም ጥቅም ላይ የሚውለው መድኃኒት (blood thinner) ኮሮናቫይረስን ለመከላከል እንዲውል የአውስትራሊያ አጥኚዎች ምርምር እያደረጉበት ይገኛሉ። ሙከራ የተደረገበት መድኃኒት በአፍንጫ የሚሳብ (nasal spray) ነው። አጥኚዎቹ እንዳሉት፤ መድኃኒቱ የኮሮናቫይረስ የፕሮቲን መጠን እንዳይጨምር በማድረግ የበሽታውን ስርጭት ይከላከላል ተብሎ ይታመናል። በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች በአፍንጫቸው መድኃኒቱን ሲወስዱ በሽታውን ማስተላለፍ ማቆማቸውን ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል። ሙከራው እአአ በ2022 አጋማሽ ነው የሚጠናቀቀው። ውጤታማ ከሆነ ለክትባት አጋዥ ይሆናል። ይህ ዘዴ በቫይረሱ የተያዘን ሰው ለማከም እንዲሁም በአፍንጫ ከተወሰደ በኋላ ቫይረሱን ለመከላከለም እንደሚውል ተጠቁሟል። የምርምሩ መሪ ፕ/ር ዶን ካምቤል "መድኃኒቱ ሰው በሚበዛበት አካባቢ ለሚሆኑ ሰዎች ይረዳል" ብለዋል። ሰዎች ወደ መደብር ወይም ሌላ ቦታ ከመሄዳቸው በፊት መድኃኒቱን አፍንጫቸው ላይ ነፍተው ከቤታቸው መውጣት እንደሚችሉ ፕሮፌሰሩ ያስረዳሉ። በሌሎች አገሮችም በአፍንጫ የሚወሰዱ መድኃኒቶች ላይ ምርምር እየተደረገ ሲሆን፤ የአውስትራሊያውን ልዩ የሚያደርገው ኸፕሪን ከተባለው የደም መርጋት መድኃኒት መሠራቱ ነው። ኸፕሪን በአፍንጫ ሲወሰድ ወደ ደም ሳይገባ አፍንጫ ላይ ይቆያል። ስለዚህም ቫይረሱ ወደ ሰውነት እንዳይገባ ይከላከላል። ሙከራው ከመንግሥት 3 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ተደርጎለት በ400 ኮሮናቫይረስ የያዛቸው ሰዎች ያሉባቸው ቤቶች ይተገበራል ተብሎ ይጠበቃል። እያንዳንዱ ሰው በቀን ሦስት ጊዜ መድኃኒቱን በአፍንጫው ይስባል። ሙከራ በሚደረግባቸው ቤቶች መድኃኒቱ የቫይረሱን ስርጭት መግታት አለመግታቱ ይፈተሻል። በሙከራው ከሚሳተፉት መካከል ሜልበርን ዩኒቨርስቲ፣ ሞናሽ ዩኒቨርስቲ፣ ሜልበርነስ ኖርዘን ኸልዝ፣ ፒተር ዶርቲ ኢንስትቲትዩት፣ መርዶክ ችልድረንስ ሪሰርች እና ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ይገኙበታል። የምርምሩ ተሳታፊ ፕሮፌሰር ሚቼል መክቶስ እንዳሉት፤ ኸፕሪን ለታካሚዎች እንዲሰጥ ፈቃድ ተሰጥቶት በስፋት ገበያ ላይ የሚገኝ መድኃኒት መሆኑ ጥናቱን ያፋጥነዋል። ፕሮፌሰር ዶን በበኩላቸው በአፍንጫ የሚወሰደውን መድኃኒት ላለፉት 20 ወራት እንደተጠቀሙትና ምንም ዓይነት የጎንዮሽ ጉዳት እንዳላስከተለባቸው ገልጸዋል። ጨምረውም "መድኃኒቱ ውጤታማ ይሆናል ብለን እናምናለን" ብለዋል። | በአውስትራሊያ በአፍንጫ የሚወሰድ የኮቪድ-19 መከላከያ ላይ ሙከራ እየተደረገ ነው የደም መርጋት ሲያጋጥም ጥቅም ላይ የሚውለው መድኃኒት (blood thinner) ኮሮናቫይረስን ለመከላከል እንዲውል የአውስትራሊያ አጥኚዎች ምርምር እያደረጉበት ይገኛሉ። ሙከራ የተደረገበት መድኃኒት በአፍንጫ የሚሳብ (nasal spray) ነው። አጥኚዎቹ እንዳሉት፤ መድኃኒቱ የኮሮናቫይረስ የፕሮቲን መጠን እንዳይጨምር በማድረግ የበሽታውን ስርጭት ይከላከላል ተብሎ ይታመናል። በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች በአፍንጫቸው መድኃኒቱን ሲወስዱ በሽታውን ማስተላለፍ ማቆማቸውን ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል። ሙከራው እአአ በ2022 አጋማሽ ነው የሚጠናቀቀው። ውጤታማ ከሆነ ለክትባት አጋዥ ይሆናል። ይህ ዘዴ በቫይረሱ የተያዘን ሰው ለማከም እንዲሁም በአፍንጫ ከተወሰደ በኋላ ቫይረሱን ለመከላከለም እንደሚውል ተጠቁሟል። የምርምሩ መሪ ፕ/ር ዶን ካምቤል "መድኃኒቱ ሰው በሚበዛበት አካባቢ ለሚሆኑ ሰዎች ይረዳል" ብለዋል። ሰዎች ወደ መደብር ወይም ሌላ ቦታ ከመሄዳቸው በፊት መድኃኒቱን አፍንጫቸው ላይ ነፍተው ከቤታቸው መውጣት እንደሚችሉ ፕሮፌሰሩ ያስረዳሉ። በሌሎች አገሮችም በአፍንጫ የሚወሰዱ መድኃኒቶች ላይ ምርምር እየተደረገ ሲሆን፤ የአውስትራሊያውን ልዩ የሚያደርገው ኸፕሪን ከተባለው የደም መርጋት መድኃኒት መሠራቱ ነው። ኸፕሪን በአፍንጫ ሲወሰድ ወደ ደም ሳይገባ አፍንጫ ላይ ይቆያል። ስለዚህም ቫይረሱ ወደ ሰውነት እንዳይገባ ይከላከላል። ሙከራው ከመንግሥት 3 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ተደርጎለት በ400 ኮሮናቫይረስ የያዛቸው ሰዎች ያሉባቸው ቤቶች ይተገበራል ተብሎ ይጠበቃል። እያንዳንዱ ሰው በቀን ሦስት ጊዜ መድኃኒቱን በአፍንጫው ይስባል። ሙከራ በሚደረግባቸው ቤቶች መድኃኒቱ የቫይረሱን ስርጭት መግታት አለመግታቱ ይፈተሻል። በሙከራው ከሚሳተፉት መካከል ሜልበርን ዩኒቨርስቲ፣ ሞናሽ ዩኒቨርስቲ፣ ሜልበርነስ ኖርዘን ኸልዝ፣ ፒተር ዶርቲ ኢንስትቲትዩት፣ መርዶክ ችልድረንስ ሪሰርች እና ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ይገኙበታል። የምርምሩ ተሳታፊ ፕሮፌሰር ሚቼል መክቶስ እንዳሉት፤ ኸፕሪን ለታካሚዎች እንዲሰጥ ፈቃድ ተሰጥቶት በስፋት ገበያ ላይ የሚገኝ መድኃኒት መሆኑ ጥናቱን ያፋጥነዋል። ፕሮፌሰር ዶን በበኩላቸው በአፍንጫ የሚወሰደውን መድኃኒት ላለፉት 20 ወራት እንደተጠቀሙትና ምንም ዓይነት የጎንዮሽ ጉዳት እንዳላስከተለባቸው ገልጸዋል። ጨምረውም "መድኃኒቱ ውጤታማ ይሆናል ብለን እናምናለን" ብለዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59770888 |
5sports
| የአውስትራሊያ ሴት እግር ኳስ ተጫዋቾች በስፖርቱ ውስጥ ጾታዊ ጥቃት መኖሩን ተናገሩ | የቀድሞዋ የአውስትራሊያ ሴት የእግር ኳስ ተጫዋች ሊሳ ዴ ቫና በስፖርቱ ውስጥ ስላለው የጾታዊ ጥቃት ባህል ለአንድ ጋዜጣ የሰጠችው ቃለ ምልልስ አነጋጋሪ ሆኗል። የ36 ዓመቷ የቀድሞ የማቲልዳስ የእግር ኳስ ቡድን አጥቂ በይፋ መናገሯን ተከትሎም ሌሎች የሃገሪቱ ሴት ተጫዋቾች ተመሳሳይ ሃሳቦችን ማንጸባረቅ ጀምረዋል። የአውስትራሊያ የእግር ኳስ ባለስልጣን እንዲህ ያሉ ቅሬታዎች ቀርበውለት እንደማያውቁ በመግለጽ እነዚህን ክሶች ተከትሎ ግን ሊሳን ጨምሮ ሌሎች ተጫዋቾች የሚያሰሙትን አቤቱታ ተቀብሎ ገለልተኛ አጣሪ ቡድን ለመመስረት ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል። "በእግር ኳስ ጨዋታ ከሚሳተፉ ሰዎች የሚጠበቁ ስነምግባሮችን ለሚጥስ ማንኛውም ዓይነት ተግባርም ሆነ ጾታዊ ጥቃት ምንም አይነት ትዕግስት የለንም" ሲል ባለስልጣኑ ተናግሯል። ሊሳ ባለፈው ወር ጫማዋን እስከምትሰቅል ድረስ ለሃገሯ 150 ጊዜ ተሰልፋ ተጫውታለች። ለማቲልዳስ በምትጫወትበት ወቅት በአንድ የቡድን አጋሯ ወሲባዊ ጥቃት እንደተፈጸመባት በአውስትራሊያ ለሚታተመው ሲድኒ ቴሌግራፍ ተናግራለች። "ወሲባዊ ጥቃት ደርሶብኝ ነበር ወይ? አዎ። የማሸማቀቅ ድርጊቶች ተፈጽመውብኝ ነበር ወይ? አዎ። ተገልያለሁ? አዎ። ምቾት የሚነሱ ነገሮችን ተመልክቼ ነበር ወይ? አዎ" ስትል ተናግራለች። በየትኛውም ስፖርታዊ ጨዋታዎች ውስጥ ያሉ ስነምግባር የጎደላቸው ተግባራት በሙሉ እንደሚረብሿትም አክላለች። ሊሳን የሚደግፉ ምስክርነቶች በቀድሞ የቡድን አጋሯ ኤሊሲያ ካርናቫስ እና በቀድሞ ማናጀሯ ሮዝ ጋሮፋኖ መሰጠታቸውን ጋዜጣው ዘግቧል። ራሄል ዶብሶን የተሰኘች የቀድሞ የቡድን አጋሯም መጀመሪያ ቡድኑን ስትቀላቀል ጥቃት ለመፈጸም የታሰቡ ግንኙነቶች ውስጥ ማለፏን ተናግራለች። "ይህ አሁንም በከፍተኛዎቹ ሰዎች ደረጃም የቀጠለ ነገር ነው። ይህንን ለመግታት አንዳች ነገር ካልተደረገ ምንም የሚቀየር ነገር የለም" ስትል ለጋዜጣው ተናግራለች። የአሜሪካ ሴት የእግር ኳስ ተጫዋቾች ተመሳሳይ መልዕክቶችን ካስተላለፉ በኋላ ነው የአውስትራሊያ ተጫዋቾችም ጥቃቶቹን ማጋለጥ የጀመሩት። ይህ በጂምናስቲክ ብሎም በዋና ስፖርት ውስጥ ያሉ ሴት ስፖርተኞችም በተለያየ ወቅት ይፋ እያወጡት ያለ ክስተት ሆኗል። | የአውስትራሊያ ሴት እግር ኳስ ተጫዋቾች በስፖርቱ ውስጥ ጾታዊ ጥቃት መኖሩን ተናገሩ የቀድሞዋ የአውስትራሊያ ሴት የእግር ኳስ ተጫዋች ሊሳ ዴ ቫና በስፖርቱ ውስጥ ስላለው የጾታዊ ጥቃት ባህል ለአንድ ጋዜጣ የሰጠችው ቃለ ምልልስ አነጋጋሪ ሆኗል። የ36 ዓመቷ የቀድሞ የማቲልዳስ የእግር ኳስ ቡድን አጥቂ በይፋ መናገሯን ተከትሎም ሌሎች የሃገሪቱ ሴት ተጫዋቾች ተመሳሳይ ሃሳቦችን ማንጸባረቅ ጀምረዋል። የአውስትራሊያ የእግር ኳስ ባለስልጣን እንዲህ ያሉ ቅሬታዎች ቀርበውለት እንደማያውቁ በመግለጽ እነዚህን ክሶች ተከትሎ ግን ሊሳን ጨምሮ ሌሎች ተጫዋቾች የሚያሰሙትን አቤቱታ ተቀብሎ ገለልተኛ አጣሪ ቡድን ለመመስረት ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል። "በእግር ኳስ ጨዋታ ከሚሳተፉ ሰዎች የሚጠበቁ ስነምግባሮችን ለሚጥስ ማንኛውም ዓይነት ተግባርም ሆነ ጾታዊ ጥቃት ምንም አይነት ትዕግስት የለንም" ሲል ባለስልጣኑ ተናግሯል። ሊሳ ባለፈው ወር ጫማዋን እስከምትሰቅል ድረስ ለሃገሯ 150 ጊዜ ተሰልፋ ተጫውታለች። ለማቲልዳስ በምትጫወትበት ወቅት በአንድ የቡድን አጋሯ ወሲባዊ ጥቃት እንደተፈጸመባት በአውስትራሊያ ለሚታተመው ሲድኒ ቴሌግራፍ ተናግራለች። "ወሲባዊ ጥቃት ደርሶብኝ ነበር ወይ? አዎ። የማሸማቀቅ ድርጊቶች ተፈጽመውብኝ ነበር ወይ? አዎ። ተገልያለሁ? አዎ። ምቾት የሚነሱ ነገሮችን ተመልክቼ ነበር ወይ? አዎ" ስትል ተናግራለች። በየትኛውም ስፖርታዊ ጨዋታዎች ውስጥ ያሉ ስነምግባር የጎደላቸው ተግባራት በሙሉ እንደሚረብሿትም አክላለች። ሊሳን የሚደግፉ ምስክርነቶች በቀድሞ የቡድን አጋሯ ኤሊሲያ ካርናቫስ እና በቀድሞ ማናጀሯ ሮዝ ጋሮፋኖ መሰጠታቸውን ጋዜጣው ዘግቧል። ራሄል ዶብሶን የተሰኘች የቀድሞ የቡድን አጋሯም መጀመሪያ ቡድኑን ስትቀላቀል ጥቃት ለመፈጸም የታሰቡ ግንኙነቶች ውስጥ ማለፏን ተናግራለች። "ይህ አሁንም በከፍተኛዎቹ ሰዎች ደረጃም የቀጠለ ነገር ነው። ይህንን ለመግታት አንዳች ነገር ካልተደረገ ምንም የሚቀየር ነገር የለም" ስትል ለጋዜጣው ተናግራለች። የአሜሪካ ሴት የእግር ኳስ ተጫዋቾች ተመሳሳይ መልዕክቶችን ካስተላለፉ በኋላ ነው የአውስትራሊያ ተጫዋቾችም ጥቃቶቹን ማጋለጥ የጀመሩት። ይህ በጂምናስቲክ ብሎም በዋና ስፖርት ውስጥ ያሉ ሴት ስፖርተኞችም በተለያየ ወቅት ይፋ እያወጡት ያለ ክስተት ሆኗል። | https://www.bbc.com/amharic/58814088 |
0business
| ኮሮና ቫይረስ፡ የዓለም ባንክ ከሰሃራ በታች የሚገኙ አገራት ኢኮኖሚያዊ ድቀት እንደሚያጋጥማቸው ተነበየ | የዓለም ባንክ ከሰሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገራት ከግማሽ ምዕተዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮቪድ-19 ምክንያት የኢኮኖሚ ድቀት ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ተነበየ። ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም የአህጉሪቱ ምጣኔ ሃብት በዚህ ዓመት ብቻ በ2.1 በመቶ የሚጎዳ ሲሆን ይህ ጉዳት እስከ 5.1 ድረስ ሊደርስ ይችላል ብሏል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በ52 የአፍሪካ አገሮች የተከሰተ ሲሆን እስካሁን ድረስ በመላ አህጉሪቱ 10,250 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎችም ቁጥርም 492 ደርሷል። የዓለም ባንክና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ፈንድ አበዳሪ አገራት ለአፍሪካ እዳቸውን ለተወሰነ ጊዜ እንዲያራዝሙ እና አገራት ያላቸው ገንዘብ ወደ ሕይወት ማዳንና ኑሮን ማሻሻል ላይ ማዋል እንዲችሉ ጥሪ አቅርበዋል። አፍሪካ በኮቪድ-19 ከተጠቁ አህጉራት የመጨረሻዋ ስትሆን፣ አገራት ድንበራቸውን መዝጋት፣ ዜጎቻቸው ከቤት ውጪ እንዳይንቀሳቀሱ ማድረግ፣ መንገደኞችን በለይቶ ማቆያ ማስቀመጥ ርምጃዎችን የወሰዱት በፍጥነት ነበር። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የመጀመሪያው ጉዳት ንግድን ማስተጓጎል ነበር። የዓለም ባንክ እንደሚለው ከሆነ የግብርና ምርቶች አቅርቦት መቀነስ፣ የአቅርቦት መስተጓጎል፣ እና የሕይወት መጥፋት ወደ ምግብ እጥረት ሊመራ ይችላል። በአፍሪካ በምጣኔ ሃብታቸው ግዙፍ የሆኑት ናይጄሪያና አንጎላ በወረርሽኙ ምክንያት የነዳጅ ዋጋ መውረድ ምጣኔ ሃብታቸው ክፉኛ ከተጎዳ አገራት መካከል ይገኙበታል። ደቡብ አፍሪካም ብትሆን የማዕድን ገቢዋ አሽቆልቁሏል። • በኮሮናቫይረስ ከተያዙት ኢትዮጵያዊያን ሦስቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት ናቸው ከኢትዮጵያና ኬንያ የሚላኩ የግብርና ምርቶች ሁሉም ተዘግተዋል። ከባህርማዶ ወደ አገር ውስጥ ይደረግ የነበረው የጎብኚዎች ፍሰት፣ የሚላክ የውጪ ምንዛሪ፣ እንዲሁም የቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ቆሟል። በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የበረሃ አንበጣ ወረርሽኝ፣ የእርስ በእርስ ግጭት፣ እንዲሁም በደቡባዊ አፍሪካ ያለው ድርቅ በአፍሪካ ያለውን ችግር ተደራራቢ አድርጎታል። የዓለም ባንክ ብድር መክፈል ለተወሰነ ጊዜ እንዲቆም የሚል ምክረ ሃሳብ ያቀረበ ሲሆን፣ ይህም በዓመት ለብድር ክፍያ የሚውለውን ወደ 35 ቢሊየን ዶላር እንዲሁም ለወለድ ክፍያ የሚውለውን 44 ቢሊየን ዶላር ነፃ ያደርጋል ተብሏል። ድርጅቱ አክሎም የአፍሪካ አገራት ለድሃ ዜጎቻቸው ምግብ እንዲያከፋፍሉ፣ መሰረታዊ ግልጋሎቶች ላይ የተጣሉ ክፍያዎችን እንዲያነሱ መክሯል። | ኮሮና ቫይረስ፡ የዓለም ባንክ ከሰሃራ በታች የሚገኙ አገራት ኢኮኖሚያዊ ድቀት እንደሚያጋጥማቸው ተነበየ የዓለም ባንክ ከሰሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገራት ከግማሽ ምዕተዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮቪድ-19 ምክንያት የኢኮኖሚ ድቀት ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ተነበየ። ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም የአህጉሪቱ ምጣኔ ሃብት በዚህ ዓመት ብቻ በ2.1 በመቶ የሚጎዳ ሲሆን ይህ ጉዳት እስከ 5.1 ድረስ ሊደርስ ይችላል ብሏል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በ52 የአፍሪካ አገሮች የተከሰተ ሲሆን እስካሁን ድረስ በመላ አህጉሪቱ 10,250 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎችም ቁጥርም 492 ደርሷል። የዓለም ባንክና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ፈንድ አበዳሪ አገራት ለአፍሪካ እዳቸውን ለተወሰነ ጊዜ እንዲያራዝሙ እና አገራት ያላቸው ገንዘብ ወደ ሕይወት ማዳንና ኑሮን ማሻሻል ላይ ማዋል እንዲችሉ ጥሪ አቅርበዋል። አፍሪካ በኮቪድ-19 ከተጠቁ አህጉራት የመጨረሻዋ ስትሆን፣ አገራት ድንበራቸውን መዝጋት፣ ዜጎቻቸው ከቤት ውጪ እንዳይንቀሳቀሱ ማድረግ፣ መንገደኞችን በለይቶ ማቆያ ማስቀመጥ ርምጃዎችን የወሰዱት በፍጥነት ነበር። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የመጀመሪያው ጉዳት ንግድን ማስተጓጎል ነበር። የዓለም ባንክ እንደሚለው ከሆነ የግብርና ምርቶች አቅርቦት መቀነስ፣ የአቅርቦት መስተጓጎል፣ እና የሕይወት መጥፋት ወደ ምግብ እጥረት ሊመራ ይችላል። በአፍሪካ በምጣኔ ሃብታቸው ግዙፍ የሆኑት ናይጄሪያና አንጎላ በወረርሽኙ ምክንያት የነዳጅ ዋጋ መውረድ ምጣኔ ሃብታቸው ክፉኛ ከተጎዳ አገራት መካከል ይገኙበታል። ደቡብ አፍሪካም ብትሆን የማዕድን ገቢዋ አሽቆልቁሏል። • በኮሮናቫይረስ ከተያዙት ኢትዮጵያዊያን ሦስቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት ናቸው ከኢትዮጵያና ኬንያ የሚላኩ የግብርና ምርቶች ሁሉም ተዘግተዋል። ከባህርማዶ ወደ አገር ውስጥ ይደረግ የነበረው የጎብኚዎች ፍሰት፣ የሚላክ የውጪ ምንዛሪ፣ እንዲሁም የቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ቆሟል። በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የበረሃ አንበጣ ወረርሽኝ፣ የእርስ በእርስ ግጭት፣ እንዲሁም በደቡባዊ አፍሪካ ያለው ድርቅ በአፍሪካ ያለውን ችግር ተደራራቢ አድርጎታል። የዓለም ባንክ ብድር መክፈል ለተወሰነ ጊዜ እንዲቆም የሚል ምክረ ሃሳብ ያቀረበ ሲሆን፣ ይህም በዓመት ለብድር ክፍያ የሚውለውን ወደ 35 ቢሊየን ዶላር እንዲሁም ለወለድ ክፍያ የሚውለውን 44 ቢሊየን ዶላር ነፃ ያደርጋል ተብሏል። ድርጅቱ አክሎም የአፍሪካ አገራት ለድሃ ዜጎቻቸው ምግብ እንዲያከፋፍሉ፣ መሰረታዊ ግልጋሎቶች ላይ የተጣሉ ክፍያዎችን እንዲያነሱ መክሯል። | https://www.bbc.com/amharic/news-52230764 |
2health
| ኦሚክሮን፡ በፍጥነት በሚዛመተው አዲሱ የኮቪድ ዝርያ የሚያዙ ሰዎች ምን ይሆናሉ? | እንሆ ሁለት ትላልቅ ጥያቄዎች፡ ኦሚክሮን በምን ያህል ፍጥነት ሊዛመት ይችላል? በኦሚክሮን ዝርያ የሚያዙ ሰዎች ምን ይሆናሉ? እኒህን ሁለት ጥያቄዎች መልስ አገኘንላቸው ማለት ኦሚክሮን የተሰኘው አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ምን ያህል አደገኛ ነው የሚለውን መለስን ማለት ነው። የምድራችን ሳይንቲስቶች እኒህን ጥያቄዎች ለመመለስ ደፋ ቀና እያሉ ነው። ትንሽ ፍንጭ የሚሰጥ ነገር ያገኙም ይመስላል። የመከላከል አቅም በጣም አስፈላጊ ነው። ኦሚክሮን ሁሉን ነገር ወደኋላ መልሶ እንደአዲስ እንድንድህ ሊያደርገን ነው ባይባልም አዲሱ የኮቪድ ዝርያ ምን ያህል አስጊ ነው የሚለውን መመልስ ጥቂት ሳምንታትን ሊጠይቅ ይችላል። ኦሚክሮን በምን ያህል ፍጥነት እየተዛመተ ይሆን? መልሱ "በፍጥነት" የሚል ነው። ይህ ዝርያ በክትባትም ይሁን በርካታ ሰዎች በመያዛቸው ምክንያት የተሻለ የመከላከል አቅም አዳብረዋል በሚባሉ ሥፍራዎችም በፍጥነት እየተስፋፋ ይገኛል። ለምሳሌ ደቡብ አፍሪካ ከአንድ ወር በፊት ዴልታ ከተሰኘው የኮቪድ ዝርያ ጋር ተላምዳ በቀን የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 300 ወርዶ ነበር። አሁን ግን አራተኛው የኮቪድ ማዕበል ከ10 ሺህ በላይ ሰዎችን አዳርሷል። ዩናይትድ ኪንግደምም ብትሆንም ኦሚክሮን እንደሰደድ እሣት እየተዛመተባት ይገኛል። ሳይንቲስቶች የኦሚክሮንን ዱካ እያገኙ ያሉት ዝርያው የኮቪድ ምርመራ በሚደረግበት ወቅት ትቶ በሚያልፋቸው አሻራዎች አማካይነት ነው። ይህ አሻራ ኤስ-ጂን ይሰኛል። ይህ ከኮቪድ ምርምራ ላይ የሚገኝ ቅንጣት ባለፈው ወር መጨረሻ ወደ 0.1 በመቶ ወርዶ ነበር። አሁን ግን ወደ 5 በመቶ አድጓል። ይህ በቁጥር ሲገለጥ በቀን 2500 ሰዎች በአዲሱ ዝርያ ይያዛሉ ማለት ነው። ይህ ስሌት ሙሉ በሙሉ ትክክል ነው ማለት ባይቻልም በአራተኛው የኮቪድ ማዕበል የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ማሻቀቡ የማይታበይ ሐቅ ነው። ለምሳሌ በዩናይትድ ኪንግደም የኦሚክሮን ቁጥር በየሦስት ቀኑ እጥፍ እየሆነ እንደሚሄድ መረጃዎች ጠቋሚ ናቸው። ኦሚክሮን የሚዛመትበት ፍጥነት ዴልታ ከተሰኘው ዝርያ በላይ ሲሆን ኮሮናቫይረስ ባለፈው ዓመት መባቻ ሲጀምር ሲስፋፋ የነበረውን ዓይነት ፍጥነት እንዳለው ተደርሶበታል። በዚህ ፍጥነቱ መዛመቱን ከቀጠለ በቀን 2500 የነበረው ቁጥር ከአንድ ወር በኋላ በቀን 100 ሺህ ይሆናል ማለት ነው። እኔን ይይዘኝ ይሆን? በሽታው ምን ያህል ከባድ ነው? ሳይንቲስቶች እስካሁን ድረስ ባደረጉት ጥናት ጭንቀት ውስጥ የከተተታቸው የኦሚክሮን ዝርያ የኮቨድ ክትባትን የመቋቋም አቅሙ ነው። ኦሚክሮን አሠራሩ ክትባቱ እንዲከላከል ከተሠራለት የመጀመሪያው የኮቪድ ዝርያ ለየት ያለ ነው። ጥናቶች እንደሚጠቁሙት የኮቪድ ክትባት ሁለት ጊዜ የወሰዱ ሰዎች አዲሱን ዝርያ የመከላከል አቅማቸው ከ20 እስከ 40 እጥፍ ሊቀንስ ይችላል። እርግጥ ነው እስካሁን በአዲሱ ዝርያ ዙሪያ አጠንጥነው የተሠሩ ጥናቶች ቁጥር ትንሽ ነው። ነገር ግን እኒህ ጥናቶች የአዲሱን ዝርያ የመዛመት ኃይል የሚያሳዩ ናቸው። ቢሆንም ስለ አዲሱ ዝርያ መልካም ዜናም አልጠፋም። ፋይዘር-ባዮንቴክ የሠራው ሙከራ እንደሚያመለክተው ማጠናከሪያ ክትባት [ሦስተኛ ክትባት] የወሰዱ ሰዎች ኦሚክሮንን የመከላከል አቅማቸው ከፍ ይላል። ለኦሚክሮን ሦስት ዙር መከተብ ማለት ለዋናውና የቀደመው ቫይረስ ሁለት ዙር እንደመከተብ ማለት ነው። የኤደንብራ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ኤሌኖር ራይሊ ይህን ሙከራ "አበረታች" ሲሉ ይገልፁትና "ማጠናከሪያው ክትባት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ የሚያሳይ ነው" ይላሉ። ኦሚክሮን ምን ያህል ከባድ የኮሮናቫይረስ ዝርያ እንደሆነ ግን እስካሁን የምናውቀው ጥቂት ነው። በዝርያው ተይዘው ሆስፒታል የገቡ ሰዎች ጥናት እስኪደርግባቸው ድረስ ስለበሽታው ኃያልነት ያለው እውቀት እፍኝ አይሞላም። እርስዎ ሁለት ጊዜ ክትባት ወሰዱ ማለት አሊያም ከዚህ በፊት ኮቪድ ይዞዎት ነበር ማለት ኦሚክሮንን የመከላከል አቅምዎ የተሻለ ነው ይላሉ ሳይንቲስቶች። እና ወደፊት ምን ሊሆን ይችላል? ኮሮናቫይረስን እንዲከላከሉ ተብለው የተዘጋጁት ክትባቶች ኦሚክሮንን ሊከላከሉ እንደሚችሉ ግምት አለ። ነገር ግን አብዛኛዎቻችን ጤና ብንሆን እንኳ ሁላችንም ደህና ላንሆን እንችላለን። አንዳንድ ሰዎች የመከላከል አቅማቸው እጅግ የደከመ ነው። አንዳንዶች ቢከተቡም ላይከላከሉ ይችላሉ። አንዳንዶች ክትባት መውሰድ አይችሉ ይሆናል። አንዳንዶች ደግሞ በውዴታ ክትባት አንወስድም እያሉ ነው። በዴልታ ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ሆስፒታል እስከመግባት ደርሰዋል። አዲሱ ዝርያ ብዙ ሰዎች በአንድ ጊዜ ወደ ሆስፒታል እንዲገቡ ካደረገ ችግር ሊፈጠር ይችላል። የዋርዊክ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ማይክል ቲልደስሊ "ማዕበል ትልቅ ከሆነ ባለፈው ጥር እንደተመለከትነው ዓይነት ሊሆን ይችላል። ሆስፒታሎችም ሊጨናነቁ ይችላሉ" ባይ ናቸው። ነገር ግን አሁን ያለን መረጃ ጥቂት ስለሆነ ይህ ነው ብሎ መናገር እንደሚከብድ ያስረዳሉ። የዓለም ሳይንቲስቶች የተስማሙበት ይህ ነው የሚባል ኦሚክሮን እየተዛመተበት ያለ ፍጥነት የለም። በሽታው ምን ያህል ከባድ ሊሆን እንደሚችልም በውል አይታወቅም። ክትባቱን ሊፈታተነው ይችላል ወይ የሚለውም ምላሽ አላገኘም። ማድረግ የሚቻለው ራስን ከበሽታው እየጠበቁ በቀጣይ ሳምንታት የሚሆነውን በቅርበት መከታተል ነው። | ኦሚክሮን፡ በፍጥነት በሚዛመተው አዲሱ የኮቪድ ዝርያ የሚያዙ ሰዎች ምን ይሆናሉ? እንሆ ሁለት ትላልቅ ጥያቄዎች፡ ኦሚክሮን በምን ያህል ፍጥነት ሊዛመት ይችላል? በኦሚክሮን ዝርያ የሚያዙ ሰዎች ምን ይሆናሉ? እኒህን ሁለት ጥያቄዎች መልስ አገኘንላቸው ማለት ኦሚክሮን የተሰኘው አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ምን ያህል አደገኛ ነው የሚለውን መለስን ማለት ነው። የምድራችን ሳይንቲስቶች እኒህን ጥያቄዎች ለመመለስ ደፋ ቀና እያሉ ነው። ትንሽ ፍንጭ የሚሰጥ ነገር ያገኙም ይመስላል። የመከላከል አቅም በጣም አስፈላጊ ነው። ኦሚክሮን ሁሉን ነገር ወደኋላ መልሶ እንደአዲስ እንድንድህ ሊያደርገን ነው ባይባልም አዲሱ የኮቪድ ዝርያ ምን ያህል አስጊ ነው የሚለውን መመልስ ጥቂት ሳምንታትን ሊጠይቅ ይችላል። ኦሚክሮን በምን ያህል ፍጥነት እየተዛመተ ይሆን? መልሱ "በፍጥነት" የሚል ነው። ይህ ዝርያ በክትባትም ይሁን በርካታ ሰዎች በመያዛቸው ምክንያት የተሻለ የመከላከል አቅም አዳብረዋል በሚባሉ ሥፍራዎችም በፍጥነት እየተስፋፋ ይገኛል። ለምሳሌ ደቡብ አፍሪካ ከአንድ ወር በፊት ዴልታ ከተሰኘው የኮቪድ ዝርያ ጋር ተላምዳ በቀን የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 300 ወርዶ ነበር። አሁን ግን አራተኛው የኮቪድ ማዕበል ከ10 ሺህ በላይ ሰዎችን አዳርሷል። ዩናይትድ ኪንግደምም ብትሆንም ኦሚክሮን እንደሰደድ እሣት እየተዛመተባት ይገኛል። ሳይንቲስቶች የኦሚክሮንን ዱካ እያገኙ ያሉት ዝርያው የኮቪድ ምርመራ በሚደረግበት ወቅት ትቶ በሚያልፋቸው አሻራዎች አማካይነት ነው። ይህ አሻራ ኤስ-ጂን ይሰኛል። ይህ ከኮቪድ ምርምራ ላይ የሚገኝ ቅንጣት ባለፈው ወር መጨረሻ ወደ 0.1 በመቶ ወርዶ ነበር። አሁን ግን ወደ 5 በመቶ አድጓል። ይህ በቁጥር ሲገለጥ በቀን 2500 ሰዎች በአዲሱ ዝርያ ይያዛሉ ማለት ነው። ይህ ስሌት ሙሉ በሙሉ ትክክል ነው ማለት ባይቻልም በአራተኛው የኮቪድ ማዕበል የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ማሻቀቡ የማይታበይ ሐቅ ነው። ለምሳሌ በዩናይትድ ኪንግደም የኦሚክሮን ቁጥር በየሦስት ቀኑ እጥፍ እየሆነ እንደሚሄድ መረጃዎች ጠቋሚ ናቸው። ኦሚክሮን የሚዛመትበት ፍጥነት ዴልታ ከተሰኘው ዝርያ በላይ ሲሆን ኮሮናቫይረስ ባለፈው ዓመት መባቻ ሲጀምር ሲስፋፋ የነበረውን ዓይነት ፍጥነት እንዳለው ተደርሶበታል። በዚህ ፍጥነቱ መዛመቱን ከቀጠለ በቀን 2500 የነበረው ቁጥር ከአንድ ወር በኋላ በቀን 100 ሺህ ይሆናል ማለት ነው። እኔን ይይዘኝ ይሆን? በሽታው ምን ያህል ከባድ ነው? ሳይንቲስቶች እስካሁን ድረስ ባደረጉት ጥናት ጭንቀት ውስጥ የከተተታቸው የኦሚክሮን ዝርያ የኮቨድ ክትባትን የመቋቋም አቅሙ ነው። ኦሚክሮን አሠራሩ ክትባቱ እንዲከላከል ከተሠራለት የመጀመሪያው የኮቪድ ዝርያ ለየት ያለ ነው። ጥናቶች እንደሚጠቁሙት የኮቪድ ክትባት ሁለት ጊዜ የወሰዱ ሰዎች አዲሱን ዝርያ የመከላከል አቅማቸው ከ20 እስከ 40 እጥፍ ሊቀንስ ይችላል። እርግጥ ነው እስካሁን በአዲሱ ዝርያ ዙሪያ አጠንጥነው የተሠሩ ጥናቶች ቁጥር ትንሽ ነው። ነገር ግን እኒህ ጥናቶች የአዲሱን ዝርያ የመዛመት ኃይል የሚያሳዩ ናቸው። ቢሆንም ስለ አዲሱ ዝርያ መልካም ዜናም አልጠፋም። ፋይዘር-ባዮንቴክ የሠራው ሙከራ እንደሚያመለክተው ማጠናከሪያ ክትባት [ሦስተኛ ክትባት] የወሰዱ ሰዎች ኦሚክሮንን የመከላከል አቅማቸው ከፍ ይላል። ለኦሚክሮን ሦስት ዙር መከተብ ማለት ለዋናውና የቀደመው ቫይረስ ሁለት ዙር እንደመከተብ ማለት ነው። የኤደንብራ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ኤሌኖር ራይሊ ይህን ሙከራ "አበረታች" ሲሉ ይገልፁትና "ማጠናከሪያው ክትባት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ የሚያሳይ ነው" ይላሉ። ኦሚክሮን ምን ያህል ከባድ የኮሮናቫይረስ ዝርያ እንደሆነ ግን እስካሁን የምናውቀው ጥቂት ነው። በዝርያው ተይዘው ሆስፒታል የገቡ ሰዎች ጥናት እስኪደርግባቸው ድረስ ስለበሽታው ኃያልነት ያለው እውቀት እፍኝ አይሞላም። እርስዎ ሁለት ጊዜ ክትባት ወሰዱ ማለት አሊያም ከዚህ በፊት ኮቪድ ይዞዎት ነበር ማለት ኦሚክሮንን የመከላከል አቅምዎ የተሻለ ነው ይላሉ ሳይንቲስቶች። እና ወደፊት ምን ሊሆን ይችላል? ኮሮናቫይረስን እንዲከላከሉ ተብለው የተዘጋጁት ክትባቶች ኦሚክሮንን ሊከላከሉ እንደሚችሉ ግምት አለ። ነገር ግን አብዛኛዎቻችን ጤና ብንሆን እንኳ ሁላችንም ደህና ላንሆን እንችላለን። አንዳንድ ሰዎች የመከላከል አቅማቸው እጅግ የደከመ ነው። አንዳንዶች ቢከተቡም ላይከላከሉ ይችላሉ። አንዳንዶች ክትባት መውሰድ አይችሉ ይሆናል። አንዳንዶች ደግሞ በውዴታ ክትባት አንወስድም እያሉ ነው። በዴልታ ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ሆስፒታል እስከመግባት ደርሰዋል። አዲሱ ዝርያ ብዙ ሰዎች በአንድ ጊዜ ወደ ሆስፒታል እንዲገቡ ካደረገ ችግር ሊፈጠር ይችላል። የዋርዊክ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ማይክል ቲልደስሊ "ማዕበል ትልቅ ከሆነ ባለፈው ጥር እንደተመለከትነው ዓይነት ሊሆን ይችላል። ሆስፒታሎችም ሊጨናነቁ ይችላሉ" ባይ ናቸው። ነገር ግን አሁን ያለን መረጃ ጥቂት ስለሆነ ይህ ነው ብሎ መናገር እንደሚከብድ ያስረዳሉ። የዓለም ሳይንቲስቶች የተስማሙበት ይህ ነው የሚባል ኦሚክሮን እየተዛመተበት ያለ ፍጥነት የለም። በሽታው ምን ያህል ከባድ ሊሆን እንደሚችልም በውል አይታወቅም። ክትባቱን ሊፈታተነው ይችላል ወይ የሚለውም ምላሽ አላገኘም። ማድረግ የሚቻለው ራስን ከበሽታው እየጠበቁ በቀጣይ ሳምንታት የሚሆነውን በቅርበት መከታተል ነው። | https://www.bbc.com/amharic/news-59596054 |
3politics
| የሚየንማር ዜጎች ሥራ አቁመው ተቃውሞውን ተቀላቀሉ | በሚየንማር በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን የተወገዱት አን ሳን ሱ ቺ እንዲለቀቁ የሚጠይቀው አገራዊ ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው። ሠራተኞችም የሥራ ማቆም አድማ በመምታት ተቃውሞውን ተቀላቅለዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በመዲናዋ ፒ ታው በሚገኙት ያንጎን እና ማንዳሊ አደባባዮች ተቃውሞ እያካሄዱ ነው። ሚየንማር እንደዚህ ያለ ተቃውሞ ካየች ከአስር ዓመት በላይ ይሆኗታል። ወታደራዊ ሃይሉ የሚየንማርን መሪ በመፈንቅለ መንግሥት አስወግዶ ለአንድ ዓመት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደንግጓል። መሪዋ፣ ፕሬዘዳንት ዊን ሚንት እንዲሁም ሌሎችም የገዢው ፓርቲ ኤንኤልዲ አባላት የቁም እስር ላይ ይገኛሉ። "አንሠራም" በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በኔይ ፒ ታው የተቃውሞ ሰልፍ እያካሄዱ ነው። በሌሎች ከተሞችም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ነዋሪዎች ተቃውሞውን ተቀላቅለዋል። መምህራን፣ ጠበቃዎች፣ የባንክ ሠራተኞችና የመንግሥት ተቀጣሪዎች ከተቃዋሚዎቹ መካከል ይገኙበታል። በሺዎች የሚቆጠሩ መምህራን ያንጎን ከተባለ ከተማ ሱሌ ፓጎንዳ ወደተባለው ማዕከላዊ ሚየንማር አቅንተዋል። ሠራተኞች የተቃውሞው አካል እንዲሆኑ ሥራ እንዲያቆሙም በበይነ መረብ ንቅናቄ እየተደረገ ነው። የ28 ዓመቱ የፋብሪካ ሠራተኛ ሂኒን ታዚን "ዛሬ የሥራ ቀን ነው። እኛ ግን አንሠራም። ደሞዛችን ቢቆረጥም አንሠራም" ሲል ለኤኤፍፒ ተናግሯል። በኔይ ፒይ ታው ፓሊስ ሰልፈኞችን ለመበተን ውሃ እንደተጠቀመና ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች እንዳሉም ተዘግቧል። ተቃዋሚዎች እርስ በእርስ ሲረዳዱና አይናቸውን ሲያሹ አንድ ተንቀሳቃሽ ምስል ያሳያል። በየጎዳናው መፈክር ይዘው ድምጻቸውን የሚያሰሙ ተቃዋሚዎችም ታይተዋል። የሚየንማሩ ኤንኤልዲ ፓርቲ ብሔራዊ ምርጫ አሸንፏል መባሉን ተከትሎ መከላከለያው መፈንቅለ መንግሥት አካሂዷል። ወታደራዊ ሀይሉ ምርጫው ተጭበርብሯል በማለት ተቃዋሚዎችን ደግፏል። ሆኖም ግን የአገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ምርጫው ስለመጭበርበሩ ምንም ማስረጃ የለም ብሏል። መከላከያው የገንዘብ፣ የጤና፣ የአገር ውስጥ እና የውጪ ጉዳይ ሚንስትሮችን አንስቶ ሌሎች ባለሥልጣኖች ሾሟል። ፌስቡክ፣ ትዊተር እና ኢንስታግራም የመሳሰሉትን ወታደራዊ ሀይሉ አግዷል። ከቅዳሜ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ተቃውሞ እየተካሄደ ይገኛል። ሚየንማር ውስጥ እንዲህ ያለ ተቃውሞ የተካሄደው እአአ በ2007 ነበር። በያኔው የሻፍሮን አብዮት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ወታደራዊ አገዛዙን ለመቃወም አደባባይ ወጥተው ነበር። | የሚየንማር ዜጎች ሥራ አቁመው ተቃውሞውን ተቀላቀሉ በሚየንማር በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን የተወገዱት አን ሳን ሱ ቺ እንዲለቀቁ የሚጠይቀው አገራዊ ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው። ሠራተኞችም የሥራ ማቆም አድማ በመምታት ተቃውሞውን ተቀላቅለዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በመዲናዋ ፒ ታው በሚገኙት ያንጎን እና ማንዳሊ አደባባዮች ተቃውሞ እያካሄዱ ነው። ሚየንማር እንደዚህ ያለ ተቃውሞ ካየች ከአስር ዓመት በላይ ይሆኗታል። ወታደራዊ ሃይሉ የሚየንማርን መሪ በመፈንቅለ መንግሥት አስወግዶ ለአንድ ዓመት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደንግጓል። መሪዋ፣ ፕሬዘዳንት ዊን ሚንት እንዲሁም ሌሎችም የገዢው ፓርቲ ኤንኤልዲ አባላት የቁም እስር ላይ ይገኛሉ። "አንሠራም" በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በኔይ ፒ ታው የተቃውሞ ሰልፍ እያካሄዱ ነው። በሌሎች ከተሞችም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ነዋሪዎች ተቃውሞውን ተቀላቅለዋል። መምህራን፣ ጠበቃዎች፣ የባንክ ሠራተኞችና የመንግሥት ተቀጣሪዎች ከተቃዋሚዎቹ መካከል ይገኙበታል። በሺዎች የሚቆጠሩ መምህራን ያንጎን ከተባለ ከተማ ሱሌ ፓጎንዳ ወደተባለው ማዕከላዊ ሚየንማር አቅንተዋል። ሠራተኞች የተቃውሞው አካል እንዲሆኑ ሥራ እንዲያቆሙም በበይነ መረብ ንቅናቄ እየተደረገ ነው። የ28 ዓመቱ የፋብሪካ ሠራተኛ ሂኒን ታዚን "ዛሬ የሥራ ቀን ነው። እኛ ግን አንሠራም። ደሞዛችን ቢቆረጥም አንሠራም" ሲል ለኤኤፍፒ ተናግሯል። በኔይ ፒይ ታው ፓሊስ ሰልፈኞችን ለመበተን ውሃ እንደተጠቀመና ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች እንዳሉም ተዘግቧል። ተቃዋሚዎች እርስ በእርስ ሲረዳዱና አይናቸውን ሲያሹ አንድ ተንቀሳቃሽ ምስል ያሳያል። በየጎዳናው መፈክር ይዘው ድምጻቸውን የሚያሰሙ ተቃዋሚዎችም ታይተዋል። የሚየንማሩ ኤንኤልዲ ፓርቲ ብሔራዊ ምርጫ አሸንፏል መባሉን ተከትሎ መከላከለያው መፈንቅለ መንግሥት አካሂዷል። ወታደራዊ ሀይሉ ምርጫው ተጭበርብሯል በማለት ተቃዋሚዎችን ደግፏል። ሆኖም ግን የአገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ምርጫው ስለመጭበርበሩ ምንም ማስረጃ የለም ብሏል። መከላከያው የገንዘብ፣ የጤና፣ የአገር ውስጥ እና የውጪ ጉዳይ ሚንስትሮችን አንስቶ ሌሎች ባለሥልጣኖች ሾሟል። ፌስቡክ፣ ትዊተር እና ኢንስታግራም የመሳሰሉትን ወታደራዊ ሀይሉ አግዷል። ከቅዳሜ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ተቃውሞ እየተካሄደ ይገኛል። ሚየንማር ውስጥ እንዲህ ያለ ተቃውሞ የተካሄደው እአአ በ2007 ነበር። በያኔው የሻፍሮን አብዮት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ወታደራዊ አገዛዙን ለመቃወም አደባባይ ወጥተው ነበር። | https://www.bbc.com/amharic/55976538 |
2health
| በአፍሪካ በሕይወት መቆያ ዕድሜ በ10 ዓመት ጨመረ | በአፍሪካ በሕይወት የመቆያ ዕድሜ በ10 ዓመት መጨመሩን የዓለም ጤና ድርጅት ገለጸ። አፍሪካ ውስጥ ሰዎች በሕይወት ይቆዩበት የነበረው አማካይ ዕድሜ ከዚህ ቀደም 46 የነበረ ሲሆን፣ አሁን ወደ 56 ከፍ ብሏል። ሰዎች ዘለግ ያሉ ዓመታት መኖር የጀመሩት የተሻለ የሕክምና አቅርቦት በመዘርጋቱ እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። ነገር ግን የዕድሜ ልኬቱ ከተቀረው ዓለም ጋር ሲነጻጸር አሁንም ከአማካዩ ያነሰ እንደሆነ አክሏል። ሰዎች በሕይወት የሚቆዩበት ዕድሜ የሚሰላው ዕድሜያቸውን፣ ጾታቸውን እና የሚኖሩበትን አገር ከግምት በማስገባት ነው። የዓለም ጤና ድርጅት አሁን ያወጣው መረጃ ላይ ለመድረስ እአአ ከ2000 እስከ 2019 ከ47 የአፍሪካ አገራት የሰበሰበውን መረጃ ገምግሟል። “በሌሎች አካባቢዎች ካለው መሻሻል የአፍሪካ ይበልጣል። ግን ኮሮናቫይረስ ያሳደረው ተጽዕኖ ለውጡን ሊቀለብስ ይችላል” ብሏል የዓለም ጤና ድርጅት። የተባበሩት መንግሥታት፣ የዓለም ጤና ድርጅትም መረጃ ጠቅሶ በድረ ገጹ እንዳሰፈረው፣ በአፍሪካ ለታየው በሕይወት መቆያ ዕድሜ መሻሻል የጤና ሚኒስትሮች ምስጋና ይገባቸዋል። እአአ በ2000 የሕክምና ሽፋን 24 በመቶ የነበረ ሲሆን በ2019 ወደ 46 በመቶ አድጓል። በአፍሪካ በሕይወት መቆያ ዕድሜ ከጨመረባቸው ምክንያቶች አንዱ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት መሻሻሉ ነው። እንደ ኤችአይቪ፣ ቲቢ እና ወባ ያሉ በሽታዎችን ለመቆጣጠር ከ2005 ወዲህ ከፍተኛ ጥረት እየተደረ መሆኑ ይጠቀሳል። ተመድ እንደሚለው፣ ተላላፊ በሽታዎችን ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት አበረታች ቢሆንም በተቃራኒው እንደ ስኳርና ደም ግፊት ያሉ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በቁጥር እየጨመሩ ነው። የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ዶ/ር ማትሺዲሶ ሞይቲ “ሰዎች ጤናማ ሆነው ለረዥም ዓመታት እየኖሩ ነው። በሽታን ለመከላከልም አበረታች ጥረት ተጀምሯል። ነገር ግን የታየው ለውጥ መገታት የለበትም። አገራት እንደ ካንሰር ያሉ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመቅረፍ ጥረት ካላደረጉ የታየው ለውጥ ይከስማል” ብለዋል። ኮሮናቫይስ በሕክምና መስጫ ተቋማት ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ በሕይወት መቆያ ዕድሜ ላይ ጫና ሊያሳድር እንደሚችል አያይዘው አንስተዋል። የዓለም ጤና ድርጅት የዳሰሳ ጥናት ሲሠራ ምላሽ ከሰጡ 36 የአፍሪካ አገራት መካል ወደ 90 በመቶው የሕክምና አገልግሎት መስተጓጎል እንደገጠማቸው ተናግረዋል። መንግሥታት ለዜጎች ጤና ጥበቃ የሚመድቡት በጀት ከፍ ማለት እንዳለበት የዓለም ጤና ድርጅት መክሯል። በአብዛኛው የአፍሪካ አገራት ከብሔራዊ የጤና በጀት 50 በመተo ብቻ ነው የሚያቀርቡት። ይህም ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት ፈጥሯል። ከግማሽ በላይ በጀት የሚመድቡ አገራት አልጄሪያ፣ ቦትስዋና፣ ኬፕ ቨርዴ፣ ኢስዋቲኒ፣ ጋቦን፣ ሲሸልስ እና ደቡብ አፍሪካ ናቸው። ዜጎች ከኪሳቸው ከፍተኛ ገንዘብ አውጥተው ለሕክምና መክፈል እንደሌለባቸው የጠቀሰው የዓለም ጤና ድርጅት፣ የመንግሥት በጀት የግድ መሻሻል እንዳለበት ምክረ ሐሳቡን አስቀምጧል። ከደመወዛቸው ከ10 በመቶ በላዩን ለሕክምና የሚያውሉ ሰዎች አስጊ ደረጃ የደረሱ ይባላሉ። ባለፉት 20 ዓመታት በ15 የአፍሪካ አገራት ዜጎች በከፍተኛ ሁኔታ የራሳቸውን የሕክምና ወጪ ሲሸፍኑ ተስተውሏል። | በአፍሪካ በሕይወት መቆያ ዕድሜ በ10 ዓመት ጨመረ በአፍሪካ በሕይወት የመቆያ ዕድሜ በ10 ዓመት መጨመሩን የዓለም ጤና ድርጅት ገለጸ። አፍሪካ ውስጥ ሰዎች በሕይወት ይቆዩበት የነበረው አማካይ ዕድሜ ከዚህ ቀደም 46 የነበረ ሲሆን፣ አሁን ወደ 56 ከፍ ብሏል። ሰዎች ዘለግ ያሉ ዓመታት መኖር የጀመሩት የተሻለ የሕክምና አቅርቦት በመዘርጋቱ እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። ነገር ግን የዕድሜ ልኬቱ ከተቀረው ዓለም ጋር ሲነጻጸር አሁንም ከአማካዩ ያነሰ እንደሆነ አክሏል። ሰዎች በሕይወት የሚቆዩበት ዕድሜ የሚሰላው ዕድሜያቸውን፣ ጾታቸውን እና የሚኖሩበትን አገር ከግምት በማስገባት ነው። የዓለም ጤና ድርጅት አሁን ያወጣው መረጃ ላይ ለመድረስ እአአ ከ2000 እስከ 2019 ከ47 የአፍሪካ አገራት የሰበሰበውን መረጃ ገምግሟል። “በሌሎች አካባቢዎች ካለው መሻሻል የአፍሪካ ይበልጣል። ግን ኮሮናቫይረስ ያሳደረው ተጽዕኖ ለውጡን ሊቀለብስ ይችላል” ብሏል የዓለም ጤና ድርጅት። የተባበሩት መንግሥታት፣ የዓለም ጤና ድርጅትም መረጃ ጠቅሶ በድረ ገጹ እንዳሰፈረው፣ በአፍሪካ ለታየው በሕይወት መቆያ ዕድሜ መሻሻል የጤና ሚኒስትሮች ምስጋና ይገባቸዋል። እአአ በ2000 የሕክምና ሽፋን 24 በመቶ የነበረ ሲሆን በ2019 ወደ 46 በመቶ አድጓል። በአፍሪካ በሕይወት መቆያ ዕድሜ ከጨመረባቸው ምክንያቶች አንዱ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት መሻሻሉ ነው። እንደ ኤችአይቪ፣ ቲቢ እና ወባ ያሉ በሽታዎችን ለመቆጣጠር ከ2005 ወዲህ ከፍተኛ ጥረት እየተደረ መሆኑ ይጠቀሳል። ተመድ እንደሚለው፣ ተላላፊ በሽታዎችን ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት አበረታች ቢሆንም በተቃራኒው እንደ ስኳርና ደም ግፊት ያሉ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በቁጥር እየጨመሩ ነው። የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ዶ/ር ማትሺዲሶ ሞይቲ “ሰዎች ጤናማ ሆነው ለረዥም ዓመታት እየኖሩ ነው። በሽታን ለመከላከልም አበረታች ጥረት ተጀምሯል። ነገር ግን የታየው ለውጥ መገታት የለበትም። አገራት እንደ ካንሰር ያሉ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመቅረፍ ጥረት ካላደረጉ የታየው ለውጥ ይከስማል” ብለዋል። ኮሮናቫይስ በሕክምና መስጫ ተቋማት ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ በሕይወት መቆያ ዕድሜ ላይ ጫና ሊያሳድር እንደሚችል አያይዘው አንስተዋል። የዓለም ጤና ድርጅት የዳሰሳ ጥናት ሲሠራ ምላሽ ከሰጡ 36 የአፍሪካ አገራት መካል ወደ 90 በመቶው የሕክምና አገልግሎት መስተጓጎል እንደገጠማቸው ተናግረዋል። መንግሥታት ለዜጎች ጤና ጥበቃ የሚመድቡት በጀት ከፍ ማለት እንዳለበት የዓለም ጤና ድርጅት መክሯል። በአብዛኛው የአፍሪካ አገራት ከብሔራዊ የጤና በጀት 50 በመተo ብቻ ነው የሚያቀርቡት። ይህም ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት ፈጥሯል። ከግማሽ በላይ በጀት የሚመድቡ አገራት አልጄሪያ፣ ቦትስዋና፣ ኬፕ ቨርዴ፣ ኢስዋቲኒ፣ ጋቦን፣ ሲሸልስ እና ደቡብ አፍሪካ ናቸው። ዜጎች ከኪሳቸው ከፍተኛ ገንዘብ አውጥተው ለሕክምና መክፈል እንደሌለባቸው የጠቀሰው የዓለም ጤና ድርጅት፣ የመንግሥት በጀት የግድ መሻሻል እንዳለበት ምክረ ሐሳቡን አስቀምጧል። ከደመወዛቸው ከ10 በመቶ በላዩን ለሕክምና የሚያውሉ ሰዎች አስጊ ደረጃ የደረሱ ይባላሉ። ባለፉት 20 ዓመታት በ15 የአፍሪካ አገራት ዜጎች በከፍተኛ ሁኔታ የራሳቸውን የሕክምና ወጪ ሲሸፍኑ ተስተውሏል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cml9zd8vngmo |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ ሙሉ ሕዝቧን እየከተበች ያለችው እስራኤል በክትባቱ ፍቱንነት ጥርጣሬ የገባት ለምንድነው? | ሕዝቧን በብዙ ቁጥር እየከተበች ያለችው እስራኤል የክትባቱን ፈዋሽነት የሚጠራጠሩ ዜጎቿ አሳስበዋታል። ተራ ዜጎች ብቻም ሳይሆኑ የጤና ባለሙያዎቿም ስለ ክትባቱ ፈዋሽነት መጠነኛ ጥርጣሬ የገባቸው ይመስላል። እስራኤል የኮቪድ ክትባትን በብዛት በመግዛት አገሯ አከማችታለች። በርካታ ሕዝቧን ክትባቱን ለመክተብ በከፍተኛ ዝግጅት ላይ ትገኛለች። ዝጅግት ላይ ብቻም ሳይሆን ግማሽ ሚሊዮን ሕዝቧን ክትባት እንዲደርሰው አድርጋለች። የእስራኤል ግብ ሙሉ በሙሉ ሕዝቧን መከተብና ተህዋሲውን ታሪክ ማድረግ ነው። እንዲያው አንዳንዶች ይቺ አገር እስራኤል ሕዝቧን "የቤተሙከራ አይጥ" ልታደርገው ነው ወይ? እስከማለት ደርሰዋል። ይህን ስታደርግ ታዲያ ብዙ የጤና አዋቂ ሳይንቲስቶች ዐይናቸውን በዚያች አገር ላይ ጥለዋል። ለምን? ዋናው ምክንያት በእስራኤል የሚታየው የክትባት ውጤት ለተቀረው ዓለም ብዙ ተስፋ ስለሚኖረው ነው። ሳይንቲስቶች እስራኤል ላይ ዓይናቸውን የጣሉበት አንዱ ምክንያትም ይኸው ነው። አንድ ሕዝብ ሙሉ በሙሉ ክትባት ሲከተብ በዚያች አገር ተህዋሲው ምን ሊሆን ይችላል የሚለው አጓጉቷቸዋል። ይህንን የክትባቱን ዘመቻ እያስተባበሩ ከሚገኙት ዋናው ሰው የፋይዘር ክትባት እንደተባለው ፍቱን ስለመሆኑ እርግጠኛ አይደለሁም በሚል ጥርጣሬ እንደገባቸው በይፋ ተናግረዋል። ይህን እንዲሉ ያደረጋቸው ታዲያ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች የፋይዘር ክትባትን ከወሰዱ በኋላም ተህዋሲው ስለተገኘባቸው ነው። ጥርጣሬው መፈጠር የጀመረውም አንድም በዚህ የተነሳ ነው። ሌሎች ሳይንቲስቶች ግን በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለመስጠት ጊዜው ገና ነው ይላሉ። እኚህ በክትባቱ ላይ ጥርጣሬን ያነሱት ፕሮፌሰር ናችማን አሽ በጤና ጥበቃ ሚኒስትር ጥርጣሪያቸው ውድቅ ተደርጎባቸዋል። "የፕሮፌሰሩ አስተያየት ከአውድ ውጭ የተነገረና ትክክል ያልሆነ ነው" ብሏል የእስራኤል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ። "በጽኑ የሚታመሙ ዜጎቻችን ቁጥር መቀነስ አለበት ብለዋል ፕሮፌሰሩ፣ ገና 2ኛው ዙር ብልቃጥ በመሰጠት ላይ ያለው አሁን ስለሆነ ይህ ውጤቱ በቀጣይነት የሚታይ እንጂ አሁን ምንም ማለት የሚቻልበት ደረጃ ላይ አይደለንም" ብሏል ይኸው መግለጫው። እርግጥ ነው ክትባቱ የራሱ ባህሪ አለው። አንድ ሰው ክትባት ከወሰደ በኋላ ሰውነቱ የተህዋሲውን ጄኔቲክ አውቆ ወራሪ ኃይል እንደመጣ ተገንዝቦ ለዚህ የሚሆን መከላከያ ለማዘጋጀት ጊዜ ይፈልጋል። አንቲቦዲና ቲ'ሴል አምርቶ ተህዋሲውን ለመጋፈጥ ጊዜ ይፈልጋል። ይህ እስኪሆን የተከተበ ሰውም ቢሆን ሊታመም ይችላል። ቢመረመር ተህዋሲው ሊገኝበት ይችላል። ይህ ሂደት ታዲያ እስከ 2 ሳምንት ሊወስድ እንደሚችል ፕሮፌሰር ዳኔ አልትማን፣ የኢምፔሪያል ኮሌጅ ለንደን ኢሚኑሎጂስት ይናገራሉ። ክላት በእስራኤል ትልቁ የጤና ሽፋን ሰጪ ድርጅት ነው። ይህ ድርጅት በቅርቡ ባወጣው መረጃ መሰረት ከተከተቡ 200 ሺህ፣ እድሜያቸው ከ60 በላይ የሆኑት ውስጥ በዚሁ እድሜ ላይ ያሉ ክትባቱን ግን ካልወሰዱ ሰዎች ጋር በማወዳደር በሰራው ጥናት በሁለት ሳምንት ውስጥ የተከተቡትም ያልተከተቡትም ላይ ተመጣጣኝ ቁጥር ያለው ሰው በተህዋሲው መያዙን ይፋ አድርጓል። ይህ ነው በፋይዘር ክትባት ላይ ጥርጣሬ እንዲነግስ ምክንያት የሆነው። ከዚያ በኋላ ቆይቶ ግን የተከተቡት ካልተከተቡት በ33 ከመቶ ባነሰ በተህዋሲው መያዛቸው እየተስተዋለ መምጣቱ ተነግሯል። "ይህ ገና ጅምር ላይ ያለ የጥናት ውጤት ነው፤ በዚህ ደረጃ ራሱ በ33 በመቶ የተህዋሲው መዛመት ቀንሷል። ስለዚህ የሚያሳስብ ነገር የለም" ብለዋል የክላት ድርጅት የጤና መኮንን ራን ባሊቸር። በፋይዘር የክሊኒክ የሙከራ ጊዜም ቢሆን ተመሳሳይ ነገር ታይቷል። ክትባቱን በወሰዱና ባልወሰዱት መሀል በተደረገ ጥናት ግልጽ ልዩነት ለማየትና የመዛመት ፍጥነት ሲቀንስ ለመታዘብ 100 ቀናት ያስፈልጋሉ ነው የሚለው መድኃኒት አምራቹ ፋይዘር። እስራኤል ዜጎቿን መከተብ የጀመረችው በታህሣሥ 19 ነበር። አሁን የሕዝቧን 10 ከመቶ ከከተበች 2 ሳምንት አልፏታል። ዛሬ ላይ ደግሞ ከ9 ሚሊዮን ሕዝቧ ውስጥ ግማሽ ሚሊዮኑ ክትባት ደርሶታል። ነገር ግን በአገሪቱ ውስጥ በተህዋሲው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መቀነስ በጉልህ አልታየም። ለምን? ክትባት የወሰደ ሰው የመከላከል አቅም ለማዳበር ከሚወስድበት ጊዜ አንጻር ቢያንስ ለአንድ ወራት ያህል ክትባቱ ያመጣውን ለውጥ ለማወቅ ከባድ ይሆናል ተብሏል። ፕሮፌሰር ባሊቸር ግን በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ ወደ ጽኑ ሕሙማን የሚሄዱ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣት አለበት ይላሉ። ፋይዘር መድኃኒት አምራች ሁለት ጠብታ ክትባቱን የወሰደ ሰው 95% በተህዋሲው ያለመያዝ እድሉ የሰፋ ነው ይላል። ነገር ግን በብዙ ክትባቶች እንደታየው ከዚህ ያነሰ መቶኛ እንኳ የፈውስ እድል ብዙ ለውጥ ያመጣል። አመታዊው የፍሉ ክትባት ለምሳሌ ፈዋሽነቱ ከ40-60% ብቻ ነው። ሆኖም በየዓመቱ በሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን ከሞት ይታደጋል። አንዱ አሁን እያነጋገረ ያለው አንድ ጠብታ የወሰዱ ዜጎችን ሁለተኛውን ጠብታ እየሰጡ ቀስ በቀስ ሕዝቡን ማዳረስ ነው ወይስ አንዱን ጠብታ ለሰፊው ሕዝብ ካዳረሱ በኋላ ለ2ኛው ዙር እንደገና መጀመር ይሻላል የሚለው ነው። ታላቋ ብሪታኒያ እንዳመነችው ብዙ ሰዎችን የመጀመርያውን ጠብታ ካዳረሱ በኋላ ለ2ኛው መመለስ ይሻላል የሚል ነው። በዚህ ዘዴ በተህዋሲው የሚጋለጡ ሰዎችን ቁጥር መቀነስ ይቻላል ብላ አምናለች። ትንሽ ቁጥር ያለውን ሕዝብ 2 ጠብታ ሰጥቶ ትንሽ ቁጥር ያለውን ሕዝብ ከተህዋሲው በደንብ መከላከል የተሻለ ነው የሚሉም አሉ። ጠብታው መሰጠት ያለበት በ2 ሳምንት ልዩነት መሆኑም ሌላው ፈተና ነው። ምክንያቱም አንድ ሰው አንድ ጠብታ ከወሰደ በኋላ ሌላ ሁለት ሳምንት መጠበቅ ተህዋሲው ከጋረጠው ፈተና አንጻር ትእግስትን የሚፈታተን በመሆኑ ነው። ፕሮፌሰር ኢቫንስ ማጠቃለያ ሐሳብ ሲሰጡ ይህን ይላሉ፡ "ከእስራኤል አሁን የሚመጡ ሪፖርቶች ያልተሟሉ ብቻ ሳይሆን መረጃን የሚሰጡ፥ እንዲሁም አጥጋቢ ሆነው አላገኘናቸውም። በታላቋ ብሪታኒያ ሁለተኛውን ጠብታ አዘግይቶ የመጀመርያውን ጠብታ ማዳረስ የሚለውን አሰራር ሊያስቀይር የሚችል ነገርም አላገኘንባቸውም" ዞሮ ዞሮ በቀጣይ ወራት በእስራኤል ተህዋሲው ድራሹ እየጠፋ ካልመጣ ዓለም መደንገጡ አይቀርም። | ኮሮናቫይረስ፡ ሙሉ ሕዝቧን እየከተበች ያለችው እስራኤል በክትባቱ ፍቱንነት ጥርጣሬ የገባት ለምንድነው? ሕዝቧን በብዙ ቁጥር እየከተበች ያለችው እስራኤል የክትባቱን ፈዋሽነት የሚጠራጠሩ ዜጎቿ አሳስበዋታል። ተራ ዜጎች ብቻም ሳይሆኑ የጤና ባለሙያዎቿም ስለ ክትባቱ ፈዋሽነት መጠነኛ ጥርጣሬ የገባቸው ይመስላል። እስራኤል የኮቪድ ክትባትን በብዛት በመግዛት አገሯ አከማችታለች። በርካታ ሕዝቧን ክትባቱን ለመክተብ በከፍተኛ ዝግጅት ላይ ትገኛለች። ዝጅግት ላይ ብቻም ሳይሆን ግማሽ ሚሊዮን ሕዝቧን ክትባት እንዲደርሰው አድርጋለች። የእስራኤል ግብ ሙሉ በሙሉ ሕዝቧን መከተብና ተህዋሲውን ታሪክ ማድረግ ነው። እንዲያው አንዳንዶች ይቺ አገር እስራኤል ሕዝቧን "የቤተሙከራ አይጥ" ልታደርገው ነው ወይ? እስከማለት ደርሰዋል። ይህን ስታደርግ ታዲያ ብዙ የጤና አዋቂ ሳይንቲስቶች ዐይናቸውን በዚያች አገር ላይ ጥለዋል። ለምን? ዋናው ምክንያት በእስራኤል የሚታየው የክትባት ውጤት ለተቀረው ዓለም ብዙ ተስፋ ስለሚኖረው ነው። ሳይንቲስቶች እስራኤል ላይ ዓይናቸውን የጣሉበት አንዱ ምክንያትም ይኸው ነው። አንድ ሕዝብ ሙሉ በሙሉ ክትባት ሲከተብ በዚያች አገር ተህዋሲው ምን ሊሆን ይችላል የሚለው አጓጉቷቸዋል። ይህንን የክትባቱን ዘመቻ እያስተባበሩ ከሚገኙት ዋናው ሰው የፋይዘር ክትባት እንደተባለው ፍቱን ስለመሆኑ እርግጠኛ አይደለሁም በሚል ጥርጣሬ እንደገባቸው በይፋ ተናግረዋል። ይህን እንዲሉ ያደረጋቸው ታዲያ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች የፋይዘር ክትባትን ከወሰዱ በኋላም ተህዋሲው ስለተገኘባቸው ነው። ጥርጣሬው መፈጠር የጀመረውም አንድም በዚህ የተነሳ ነው። ሌሎች ሳይንቲስቶች ግን በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለመስጠት ጊዜው ገና ነው ይላሉ። እኚህ በክትባቱ ላይ ጥርጣሬን ያነሱት ፕሮፌሰር ናችማን አሽ በጤና ጥበቃ ሚኒስትር ጥርጣሪያቸው ውድቅ ተደርጎባቸዋል። "የፕሮፌሰሩ አስተያየት ከአውድ ውጭ የተነገረና ትክክል ያልሆነ ነው" ብሏል የእስራኤል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ። "በጽኑ የሚታመሙ ዜጎቻችን ቁጥር መቀነስ አለበት ብለዋል ፕሮፌሰሩ፣ ገና 2ኛው ዙር ብልቃጥ በመሰጠት ላይ ያለው አሁን ስለሆነ ይህ ውጤቱ በቀጣይነት የሚታይ እንጂ አሁን ምንም ማለት የሚቻልበት ደረጃ ላይ አይደለንም" ብሏል ይኸው መግለጫው። እርግጥ ነው ክትባቱ የራሱ ባህሪ አለው። አንድ ሰው ክትባት ከወሰደ በኋላ ሰውነቱ የተህዋሲውን ጄኔቲክ አውቆ ወራሪ ኃይል እንደመጣ ተገንዝቦ ለዚህ የሚሆን መከላከያ ለማዘጋጀት ጊዜ ይፈልጋል። አንቲቦዲና ቲ'ሴል አምርቶ ተህዋሲውን ለመጋፈጥ ጊዜ ይፈልጋል። ይህ እስኪሆን የተከተበ ሰውም ቢሆን ሊታመም ይችላል። ቢመረመር ተህዋሲው ሊገኝበት ይችላል። ይህ ሂደት ታዲያ እስከ 2 ሳምንት ሊወስድ እንደሚችል ፕሮፌሰር ዳኔ አልትማን፣ የኢምፔሪያል ኮሌጅ ለንደን ኢሚኑሎጂስት ይናገራሉ። ክላት በእስራኤል ትልቁ የጤና ሽፋን ሰጪ ድርጅት ነው። ይህ ድርጅት በቅርቡ ባወጣው መረጃ መሰረት ከተከተቡ 200 ሺህ፣ እድሜያቸው ከ60 በላይ የሆኑት ውስጥ በዚሁ እድሜ ላይ ያሉ ክትባቱን ግን ካልወሰዱ ሰዎች ጋር በማወዳደር በሰራው ጥናት በሁለት ሳምንት ውስጥ የተከተቡትም ያልተከተቡትም ላይ ተመጣጣኝ ቁጥር ያለው ሰው በተህዋሲው መያዙን ይፋ አድርጓል። ይህ ነው በፋይዘር ክትባት ላይ ጥርጣሬ እንዲነግስ ምክንያት የሆነው። ከዚያ በኋላ ቆይቶ ግን የተከተቡት ካልተከተቡት በ33 ከመቶ ባነሰ በተህዋሲው መያዛቸው እየተስተዋለ መምጣቱ ተነግሯል። "ይህ ገና ጅምር ላይ ያለ የጥናት ውጤት ነው፤ በዚህ ደረጃ ራሱ በ33 በመቶ የተህዋሲው መዛመት ቀንሷል። ስለዚህ የሚያሳስብ ነገር የለም" ብለዋል የክላት ድርጅት የጤና መኮንን ራን ባሊቸር። በፋይዘር የክሊኒክ የሙከራ ጊዜም ቢሆን ተመሳሳይ ነገር ታይቷል። ክትባቱን በወሰዱና ባልወሰዱት መሀል በተደረገ ጥናት ግልጽ ልዩነት ለማየትና የመዛመት ፍጥነት ሲቀንስ ለመታዘብ 100 ቀናት ያስፈልጋሉ ነው የሚለው መድኃኒት አምራቹ ፋይዘር። እስራኤል ዜጎቿን መከተብ የጀመረችው በታህሣሥ 19 ነበር። አሁን የሕዝቧን 10 ከመቶ ከከተበች 2 ሳምንት አልፏታል። ዛሬ ላይ ደግሞ ከ9 ሚሊዮን ሕዝቧ ውስጥ ግማሽ ሚሊዮኑ ክትባት ደርሶታል። ነገር ግን በአገሪቱ ውስጥ በተህዋሲው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መቀነስ በጉልህ አልታየም። ለምን? ክትባት የወሰደ ሰው የመከላከል አቅም ለማዳበር ከሚወስድበት ጊዜ አንጻር ቢያንስ ለአንድ ወራት ያህል ክትባቱ ያመጣውን ለውጥ ለማወቅ ከባድ ይሆናል ተብሏል። ፕሮፌሰር ባሊቸር ግን በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ ወደ ጽኑ ሕሙማን የሚሄዱ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣት አለበት ይላሉ። ፋይዘር መድኃኒት አምራች ሁለት ጠብታ ክትባቱን የወሰደ ሰው 95% በተህዋሲው ያለመያዝ እድሉ የሰፋ ነው ይላል። ነገር ግን በብዙ ክትባቶች እንደታየው ከዚህ ያነሰ መቶኛ እንኳ የፈውስ እድል ብዙ ለውጥ ያመጣል። አመታዊው የፍሉ ክትባት ለምሳሌ ፈዋሽነቱ ከ40-60% ብቻ ነው። ሆኖም በየዓመቱ በሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን ከሞት ይታደጋል። አንዱ አሁን እያነጋገረ ያለው አንድ ጠብታ የወሰዱ ዜጎችን ሁለተኛውን ጠብታ እየሰጡ ቀስ በቀስ ሕዝቡን ማዳረስ ነው ወይስ አንዱን ጠብታ ለሰፊው ሕዝብ ካዳረሱ በኋላ ለ2ኛው ዙር እንደገና መጀመር ይሻላል የሚለው ነው። ታላቋ ብሪታኒያ እንዳመነችው ብዙ ሰዎችን የመጀመርያውን ጠብታ ካዳረሱ በኋላ ለ2ኛው መመለስ ይሻላል የሚል ነው። በዚህ ዘዴ በተህዋሲው የሚጋለጡ ሰዎችን ቁጥር መቀነስ ይቻላል ብላ አምናለች። ትንሽ ቁጥር ያለውን ሕዝብ 2 ጠብታ ሰጥቶ ትንሽ ቁጥር ያለውን ሕዝብ ከተህዋሲው በደንብ መከላከል የተሻለ ነው የሚሉም አሉ። ጠብታው መሰጠት ያለበት በ2 ሳምንት ልዩነት መሆኑም ሌላው ፈተና ነው። ምክንያቱም አንድ ሰው አንድ ጠብታ ከወሰደ በኋላ ሌላ ሁለት ሳምንት መጠበቅ ተህዋሲው ከጋረጠው ፈተና አንጻር ትእግስትን የሚፈታተን በመሆኑ ነው። ፕሮፌሰር ኢቫንስ ማጠቃለያ ሐሳብ ሲሰጡ ይህን ይላሉ፡ "ከእስራኤል አሁን የሚመጡ ሪፖርቶች ያልተሟሉ ብቻ ሳይሆን መረጃን የሚሰጡ፥ እንዲሁም አጥጋቢ ሆነው አላገኘናቸውም። በታላቋ ብሪታኒያ ሁለተኛውን ጠብታ አዘግይቶ የመጀመርያውን ጠብታ ማዳረስ የሚለውን አሰራር ሊያስቀይር የሚችል ነገርም አላገኘንባቸውም" ዞሮ ዞሮ በቀጣይ ወራት በእስራኤል ተህዋሲው ድራሹ እየጠፋ ካልመጣ ዓለም መደንገጡ አይቀርም። | https://www.bbc.com/amharic/news-55745103 |
2health
| የሜክሲኮ ፕሬዝዳንት በኮቪድ ተያዙ | የሜክሲኮ ፕሬዝዳንት አንድሬ ማኑኤል ሎፔዝ ኦብራዶር ኮቪድ ተመርምረው ተህዋሲው እንደተገኘባቸው ይፋ አደረጉ። የ67 ዓመቱ ፕሬዝዳንት በትዊተር ሰሌዳቸው እንደጻፉት አሁን የበሽታውን ቀላል ምልክቶችን ማሳየት ጀምረዋል። የፕሬዝዳንቱ በተህዋሲው የመያዝ ዜና የመጣው ሜክሲኮ በወረርሽኝ እየታመሰች ባለችበት ወቅት ነው። ሜክሲኮ እስከዛሬ ከ150ሺህ ባላይ ዜጎቿን በተህዋሲው አጥታለች። ሎፔዝ ኦብራዶር አገሪቱን ከቤቴ ሆኜ መምራቴን እቀጥላለሁ ብለዋል። ሩሲያ ሰራሹን ክትባት ለማግኘትም ከፑቲን ጋር እነጋገራለሁ ብለዋል። ትናንት ሁለቱ መሪዎች ዛሬ ሰኞ በስልክ በሁለትዮሽ ግንኙነቶች ዙርያ ይነጋገራሉ የሚሉ ዘገባዎች ወጥተው ነበር። ዋናው አጀንዳ የሚሆነውም ሰፑትኒክ የተሰኘውን ሩሲያ ሰራሽ ክትባት ሜክሲኮ የምታገኝበትን ዘዴ መቀየስ ነው። ባለፈው ዓመት ፕሬዝደንት ሎፔዝ ሩሲያ ሰራሹን የኮቪድ ክትባት ፈዋሽነቱ እንደተረጋገጠ 12 ሚሊዮን ጠብታ ወደ አገሬ አስገባለሁ ብለው ተናግረው ነበር። ሜክሲኮ ሩሲያ ሰራሹን ክትባት ፈዋሽነት ለጊዜው አላረጋገጠችም። ሆኖም ግን 128 ሚሊዮን ለሚሆነው ሕዝቧ ክትባቱን ለማዳረስ የፋይዘር ባዮንቴክ መዘግየት ታክሎበት ወደ ሩሲያ ለማማተር ተገዳለች። አሁን ለሩሲያው ስፑትኪን ክትባት አውቅና የሰጡ ዋና ዋና አገራት ብራዚል፣ አርጀንቲናና ሀንጋሪ ናቸው። ጆስ ሉዊስ አሎሚያ ዛጋራ የተባለ አንድ የጤና ረዳት የፕሬዝዳንቱን ጤንነት ከገመገመ በኋላ በመልካም ሁኔታ ላይ ይገኛሉ፤ የሚያሳስብ ነገር የለም ብሏል። የጤና ባለሙያዎች ቡድን ለፕሬዝዳንቱ የቅርብ ክትትል እያደረጉላቸው ይገኛሉ። ሜክሲኮ በተህዋሲው የተያዙባት ዜጎች ቁጥር ወደ 2 ሚሊዮን እየተጠጋ ይገኛል። በ150ሺ ሟቾች ቁጥርም ግማሽ ሚሊዮን እየተጠጋ ያለ ሕዝብ ከሞተባት አሜሪካ፣ እንዲሁም ከብራዚልና ሕንድ ቀጥሎ ከዓለም በ4ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። | የሜክሲኮ ፕሬዝዳንት በኮቪድ ተያዙ የሜክሲኮ ፕሬዝዳንት አንድሬ ማኑኤል ሎፔዝ ኦብራዶር ኮቪድ ተመርምረው ተህዋሲው እንደተገኘባቸው ይፋ አደረጉ። የ67 ዓመቱ ፕሬዝዳንት በትዊተር ሰሌዳቸው እንደጻፉት አሁን የበሽታውን ቀላል ምልክቶችን ማሳየት ጀምረዋል። የፕሬዝዳንቱ በተህዋሲው የመያዝ ዜና የመጣው ሜክሲኮ በወረርሽኝ እየታመሰች ባለችበት ወቅት ነው። ሜክሲኮ እስከዛሬ ከ150ሺህ ባላይ ዜጎቿን በተህዋሲው አጥታለች። ሎፔዝ ኦብራዶር አገሪቱን ከቤቴ ሆኜ መምራቴን እቀጥላለሁ ብለዋል። ሩሲያ ሰራሹን ክትባት ለማግኘትም ከፑቲን ጋር እነጋገራለሁ ብለዋል። ትናንት ሁለቱ መሪዎች ዛሬ ሰኞ በስልክ በሁለትዮሽ ግንኙነቶች ዙርያ ይነጋገራሉ የሚሉ ዘገባዎች ወጥተው ነበር። ዋናው አጀንዳ የሚሆነውም ሰፑትኒክ የተሰኘውን ሩሲያ ሰራሽ ክትባት ሜክሲኮ የምታገኝበትን ዘዴ መቀየስ ነው። ባለፈው ዓመት ፕሬዝደንት ሎፔዝ ሩሲያ ሰራሹን የኮቪድ ክትባት ፈዋሽነቱ እንደተረጋገጠ 12 ሚሊዮን ጠብታ ወደ አገሬ አስገባለሁ ብለው ተናግረው ነበር። ሜክሲኮ ሩሲያ ሰራሹን ክትባት ፈዋሽነት ለጊዜው አላረጋገጠችም። ሆኖም ግን 128 ሚሊዮን ለሚሆነው ሕዝቧ ክትባቱን ለማዳረስ የፋይዘር ባዮንቴክ መዘግየት ታክሎበት ወደ ሩሲያ ለማማተር ተገዳለች። አሁን ለሩሲያው ስፑትኪን ክትባት አውቅና የሰጡ ዋና ዋና አገራት ብራዚል፣ አርጀንቲናና ሀንጋሪ ናቸው። ጆስ ሉዊስ አሎሚያ ዛጋራ የተባለ አንድ የጤና ረዳት የፕሬዝዳንቱን ጤንነት ከገመገመ በኋላ በመልካም ሁኔታ ላይ ይገኛሉ፤ የሚያሳስብ ነገር የለም ብሏል። የጤና ባለሙያዎች ቡድን ለፕሬዝዳንቱ የቅርብ ክትትል እያደረጉላቸው ይገኛሉ። ሜክሲኮ በተህዋሲው የተያዙባት ዜጎች ቁጥር ወደ 2 ሚሊዮን እየተጠጋ ይገኛል። በ150ሺ ሟቾች ቁጥርም ግማሽ ሚሊዮን እየተጠጋ ያለ ሕዝብ ከሞተባት አሜሪካ፣ እንዲሁም ከብራዚልና ሕንድ ቀጥሎ ከዓለም በ4ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። | https://www.bbc.com/amharic/55792459 |
2health
| በፈረንሳይ የፌስቡክ ተጽእኖ ፈጣሪዎች የኮቪድ-19 ክትባትን እንዲያጥላሉ ገንዘብ ቀረበላቸው | በፈረንሳይ ማንነቱ ያልታወቀ አንድ አካል በማኅበራዊ ትስስር መድረኮች ተጽእኖ ፈጣሪ የሆኑ ግለሰቦችን እያደነ የኮቪድ-19 ክትባትን ካጥላላችሁልኝ ከፍተኛ ገንዘብ እሰጣችኋለሁ እያለ በማባበል ላይ ነው፡፡ ደለብ ያለ ገንዘብ እንደቀረበላቸው ያመኑ በርካታ የፌስቡክ፣ የዩትዩብና የኢኒስታግራም ዝነኞች ጉዳዩን አደባባይ አውጥተውታል፡፡ ማንነቱ ያልታወቀው ይህ ገንዘብ ከፋይ አካል/ድርጅት መቀመጫውን በዩኬ እንዳደረገ ቢገመትም ሊደረስበት ግን አልቻለም፡፡ ዝነኞቹን በገንዘብ የሚያማልለው ኢሜይል እየላከ ሲሆን በተለይም ፋይዘር የተባለውን የክትባት ዓይነት ዘዴኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ እንዲከፍቱበት ዝነኞችን ያባብላል፡፡ ለምሳሌ በዩትዩብ ወደ 2 ሚሊዮን የሚጠጉ ተከታዮች ያሉት ሊዮ ግራሴት እጅግ የሚያማልል ገንዘብ እንደቀረበለት በትዊተር ሰሌዳው አጋልጧል፡፡ ገንዘብ ያቀረበለት ድርጅት በሊክንድኢን ገጹ ሠራተኞቹ በሩሲያ እንደሚገኙ እንደሚያመላክትም አስረድቷል፡፡ ሊዮ ጨምሮ እንዳጋለጠው ድርጅቱ ክትባቱን ሲያጥላላ በፍጹም ገንዘብ እንደተከፈለው እንዳይናገር እና ቪዲዮም ስፖንሰር እንደተደረገ እንዳይገልጽ በዚህ ድርጅት ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶታል፡፡ ‹‹የስም ማጥፋት ማስታወቂያ ሲሰራ ቪዲዮውን በራሴ እንደሰራሁት እንድናገር ገፋፍተውኛል›› ብሏል ሊዮ፡፡ ሊዮ ይኸው ድርጅት ፋይዘር የተባለውን ክትባት የሚወስዱ ሰዎች አስትራዜኒካ ከወሰዱት ጋር ሲነጻጸሩ በሦስት እጥፍ ሞታቸው እንደተፋጠነ እንዲናገር ጠይቆታል፡፡ ከሊዮ በተጨማሪ በርካታ የፈረንሳይ የማኅበራዊ ትስስር መድረክ ዝነኞች በተመሳሳይና ለተመሳሳይ እኩይ ተግባር ከፍ ያለ ገንዘብ እንደቀረበላቸው መናገር ጀምረዋል፡፡ በኢናስታግራም 85 ሺህ ተከታዮች ያሉት ሌላ ዝነኛ ለፈረንሳይ ቲቪ እንደተናገረው ለ30 ሰከንድ የስም ማጥፋት ቪዲዮ 2 ሺህ ዩሮ ቀርቦልኛል ብሏል፡፡ የፈረንሳይ የጤና ሚኒስትር ኦሊቪየር ቬራን ይህ ገንዘብ ለዝነኞች የሚረጨው ድርጅት የት እንደሆነ የምናውቀው ነገር የለም፡፡ ድርጊቱ ግን አሳፋሪ ነው ብለዋል፡፡ በሁለት ዙር የሚሰጠው ፋይዘር ክትባት ሙሉ ስሙ ፋይዘር እና ባዮንቴክ ሲሆን በፈረንሳይ ለሕዝብ በብዛት እየተሰጠ ያለ የክትባት ዓይነት ነው፡፡ ክትባቱን የፈጠሩት የአሜሪካው ፋይዘርና የጀርመኑ ባዮንቴክ በሽርክና ነው፡፡ ሌላው በሁለት ዙር የሚሰጠው አስትራዜኒካ በፈረንሳይ በ2ኛ ደረጃ እየተሰጠ ሲሆን የሚያመርተው ደግሞ የዩኬና ስዊድሽ ጥምረት የሆነ ፋርማሱቲካል ኩባንያ ነው፡፡ ባለፈው መጋቢት የአውሮጳ ኅብረት አንድ ሪፖርት የሩሲያና የቻይና ሚዲያዎች በምዕራቡ ዓለም እየተሰጡ ያሉ የኮቪድ-19 ክትባቶችን ኅብረተሰቡ በጥርጣሬ እንዲያያቸው ለማድረግ ውስጥ ውስጡን ይሰራሉ ሲል ከሶ ነበር፡፡ ሞስኮ ይህንን ክስ አጣጥላዋለች፡፡ | በፈረንሳይ የፌስቡክ ተጽእኖ ፈጣሪዎች የኮቪድ-19 ክትባትን እንዲያጥላሉ ገንዘብ ቀረበላቸው በፈረንሳይ ማንነቱ ያልታወቀ አንድ አካል በማኅበራዊ ትስስር መድረኮች ተጽእኖ ፈጣሪ የሆኑ ግለሰቦችን እያደነ የኮቪድ-19 ክትባትን ካጥላላችሁልኝ ከፍተኛ ገንዘብ እሰጣችኋለሁ እያለ በማባበል ላይ ነው፡፡ ደለብ ያለ ገንዘብ እንደቀረበላቸው ያመኑ በርካታ የፌስቡክ፣ የዩትዩብና የኢኒስታግራም ዝነኞች ጉዳዩን አደባባይ አውጥተውታል፡፡ ማንነቱ ያልታወቀው ይህ ገንዘብ ከፋይ አካል/ድርጅት መቀመጫውን በዩኬ እንዳደረገ ቢገመትም ሊደረስበት ግን አልቻለም፡፡ ዝነኞቹን በገንዘብ የሚያማልለው ኢሜይል እየላከ ሲሆን በተለይም ፋይዘር የተባለውን የክትባት ዓይነት ዘዴኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ እንዲከፍቱበት ዝነኞችን ያባብላል፡፡ ለምሳሌ በዩትዩብ ወደ 2 ሚሊዮን የሚጠጉ ተከታዮች ያሉት ሊዮ ግራሴት እጅግ የሚያማልል ገንዘብ እንደቀረበለት በትዊተር ሰሌዳው አጋልጧል፡፡ ገንዘብ ያቀረበለት ድርጅት በሊክንድኢን ገጹ ሠራተኞቹ በሩሲያ እንደሚገኙ እንደሚያመላክትም አስረድቷል፡፡ ሊዮ ጨምሮ እንዳጋለጠው ድርጅቱ ክትባቱን ሲያጥላላ በፍጹም ገንዘብ እንደተከፈለው እንዳይናገር እና ቪዲዮም ስፖንሰር እንደተደረገ እንዳይገልጽ በዚህ ድርጅት ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶታል፡፡ ‹‹የስም ማጥፋት ማስታወቂያ ሲሰራ ቪዲዮውን በራሴ እንደሰራሁት እንድናገር ገፋፍተውኛል›› ብሏል ሊዮ፡፡ ሊዮ ይኸው ድርጅት ፋይዘር የተባለውን ክትባት የሚወስዱ ሰዎች አስትራዜኒካ ከወሰዱት ጋር ሲነጻጸሩ በሦስት እጥፍ ሞታቸው እንደተፋጠነ እንዲናገር ጠይቆታል፡፡ ከሊዮ በተጨማሪ በርካታ የፈረንሳይ የማኅበራዊ ትስስር መድረክ ዝነኞች በተመሳሳይና ለተመሳሳይ እኩይ ተግባር ከፍ ያለ ገንዘብ እንደቀረበላቸው መናገር ጀምረዋል፡፡ በኢናስታግራም 85 ሺህ ተከታዮች ያሉት ሌላ ዝነኛ ለፈረንሳይ ቲቪ እንደተናገረው ለ30 ሰከንድ የስም ማጥፋት ቪዲዮ 2 ሺህ ዩሮ ቀርቦልኛል ብሏል፡፡ የፈረንሳይ የጤና ሚኒስትር ኦሊቪየር ቬራን ይህ ገንዘብ ለዝነኞች የሚረጨው ድርጅት የት እንደሆነ የምናውቀው ነገር የለም፡፡ ድርጊቱ ግን አሳፋሪ ነው ብለዋል፡፡ በሁለት ዙር የሚሰጠው ፋይዘር ክትባት ሙሉ ስሙ ፋይዘር እና ባዮንቴክ ሲሆን በፈረንሳይ ለሕዝብ በብዛት እየተሰጠ ያለ የክትባት ዓይነት ነው፡፡ ክትባቱን የፈጠሩት የአሜሪካው ፋይዘርና የጀርመኑ ባዮንቴክ በሽርክና ነው፡፡ ሌላው በሁለት ዙር የሚሰጠው አስትራዜኒካ በፈረንሳይ በ2ኛ ደረጃ እየተሰጠ ሲሆን የሚያመርተው ደግሞ የዩኬና ስዊድሽ ጥምረት የሆነ ፋርማሱቲካል ኩባንያ ነው፡፡ ባለፈው መጋቢት የአውሮጳ ኅብረት አንድ ሪፖርት የሩሲያና የቻይና ሚዲያዎች በምዕራቡ ዓለም እየተሰጡ ያሉ የኮቪድ-19 ክትባቶችን ኅብረተሰቡ በጥርጣሬ እንዲያያቸው ለማድረግ ውስጥ ውስጡን ይሰራሉ ሲል ከሶ ነበር፡፡ ሞስኮ ይህንን ክስ አጣጥላዋለች፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/57251178 |
2health
| ወረርሽኙ መቀጠሉ የዙምን ሽያጭ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ተገለፀ | የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በርካታ የአለማችን ህዝብ በቤት መገደቡ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት ለስብሰባዎችና ለሌሎች ዝግጅቶች መገልገያ የሆነው የድምፅና የቪዲዮው መተግበሪያው ዙም ከፍተኛ ሽያጭ እንዳስመዘገበና ትርፉም በዚሁም ሊቀጥልም እንደሚችል ኩባንያው አስታውቋል። በካሊፎርኒያ መቀመጫውን ያደረገው የዙም ኩባንያ 2.5 ቢሊዮን ዶላርም ትርፍ አገኛለሁ ብሎ የተነበየ ሲሆን ይህም በመጋቢት ወር አገኘዋለሁ ብሎ ካሰበው እጥፍ ነው ተብሏል። ወረርሽኙን ተከትሎም ስሙ የገነነው ዙም አገራት ሁለተኛ ዙር ወረርሽኝን በማስተናገዳቸውም በርካታ ሰዎች ለየእለት ግንኙነታቸው ተመራጭ መተግበሪያ አድርጎታል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የአለማችን ህዝቦችም መተግበሪያውን ከቤተሰብና ከጓደኞች ጋር ለመጫወት፣ በመማር ማስተማር ሂደት፣ ጉባኤዎችና የተለያዩ ዝግጅቶችን ለማካሄድና፣ ለስብሰባዎችም ተመራጭ አድርገውታል። የዙም መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ ኤሪክ ዩዋን እንደሚሉት "ሰራተኞች ከየትኛውም ቦታ መስራትን በቀጠሉበት ወቅት" የከፋይ ኩባንያ ደንበኞች ቁጥር እየጨመረ ነው ብሏል። በጥቅምት ወር አጋማሽ ላይ ዙም 434 ሺህ ከአስር ሰራተኞች በላይ ያሉት ከፋይ ኩባንያ ደንበኞች እንዳሉት የተዘገበ ሲሆን ይህም ከባለፈው አመት ጋር 485 በመቶ ጭማሪ ያሳየ ነው ተብሏል። በዚህም ምክንያት ኩባንያው ከጠበቀው በላይ ሽያጭና ትርፍም እየተንበሸበሸ እንደሆነም ተነግሯል፥ ዙም ከባለፈው አመት ነሐሴ እስከ ጥቅምት ባለው የሩብ አመት ሽያጭ 777 ሚሊዮን ዶላር የመዘገበ ሲሆን ይህም ከሁለት አመት በፊት በዚህ ወቅት ከነበረው ጋር ሲነፃፀር 367 በመቶ ጭማሬ አሳይቷል። ትርፉም በዚሁ ሩብ አመት 198.4 ሚሊዮን ዶላር ሲሆን ከሁለት አመት በፊት የነበረው የሩብ አመት ትርፍ 2.2 ሚሊዮን ዶላር ነበር። በዚህ ሳምንት ሰኞ ሽያጩንና ትርፉን እንደገና በመገምገም ለሶስተኛ ጊዜ አዲስ ትንበያን ያወጣ ሲሆን በመጪው አውሮፖውያኑ አዲስ አመትም 2.5 ቢሊዮን ዶላር እንደሚሆንም ለኢንቨስተሮች አሳውቋል። በነሐሴ ወር ላይ ኩባንያው ተንብዮት የነበረው 2.37 ቢሊዮን ዶላር ነበር። ወረርሽኙ ከመከሰቱ በፊት የነበረው ሽያጭ 622̌.7 ሚሊዮን ዶላርም ነበር ተብሏል። | ወረርሽኙ መቀጠሉ የዙምን ሽያጭ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ተገለፀ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በርካታ የአለማችን ህዝብ በቤት መገደቡ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት ለስብሰባዎችና ለሌሎች ዝግጅቶች መገልገያ የሆነው የድምፅና የቪዲዮው መተግበሪያው ዙም ከፍተኛ ሽያጭ እንዳስመዘገበና ትርፉም በዚሁም ሊቀጥልም እንደሚችል ኩባንያው አስታውቋል። በካሊፎርኒያ መቀመጫውን ያደረገው የዙም ኩባንያ 2.5 ቢሊዮን ዶላርም ትርፍ አገኛለሁ ብሎ የተነበየ ሲሆን ይህም በመጋቢት ወር አገኘዋለሁ ብሎ ካሰበው እጥፍ ነው ተብሏል። ወረርሽኙን ተከትሎም ስሙ የገነነው ዙም አገራት ሁለተኛ ዙር ወረርሽኝን በማስተናገዳቸውም በርካታ ሰዎች ለየእለት ግንኙነታቸው ተመራጭ መተግበሪያ አድርጎታል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የአለማችን ህዝቦችም መተግበሪያውን ከቤተሰብና ከጓደኞች ጋር ለመጫወት፣ በመማር ማስተማር ሂደት፣ ጉባኤዎችና የተለያዩ ዝግጅቶችን ለማካሄድና፣ ለስብሰባዎችም ተመራጭ አድርገውታል። የዙም መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ ኤሪክ ዩዋን እንደሚሉት "ሰራተኞች ከየትኛውም ቦታ መስራትን በቀጠሉበት ወቅት" የከፋይ ኩባንያ ደንበኞች ቁጥር እየጨመረ ነው ብሏል። በጥቅምት ወር አጋማሽ ላይ ዙም 434 ሺህ ከአስር ሰራተኞች በላይ ያሉት ከፋይ ኩባንያ ደንበኞች እንዳሉት የተዘገበ ሲሆን ይህም ከባለፈው አመት ጋር 485 በመቶ ጭማሪ ያሳየ ነው ተብሏል። በዚህም ምክንያት ኩባንያው ከጠበቀው በላይ ሽያጭና ትርፍም እየተንበሸበሸ እንደሆነም ተነግሯል፥ ዙም ከባለፈው አመት ነሐሴ እስከ ጥቅምት ባለው የሩብ አመት ሽያጭ 777 ሚሊዮን ዶላር የመዘገበ ሲሆን ይህም ከሁለት አመት በፊት በዚህ ወቅት ከነበረው ጋር ሲነፃፀር 367 በመቶ ጭማሬ አሳይቷል። ትርፉም በዚሁ ሩብ አመት 198.4 ሚሊዮን ዶላር ሲሆን ከሁለት አመት በፊት የነበረው የሩብ አመት ትርፍ 2.2 ሚሊዮን ዶላር ነበር። በዚህ ሳምንት ሰኞ ሽያጩንና ትርፉን እንደገና በመገምገም ለሶስተኛ ጊዜ አዲስ ትንበያን ያወጣ ሲሆን በመጪው አውሮፖውያኑ አዲስ አመትም 2.5 ቢሊዮን ዶላር እንደሚሆንም ለኢንቨስተሮች አሳውቋል። በነሐሴ ወር ላይ ኩባንያው ተንብዮት የነበረው 2.37 ቢሊዮን ዶላር ነበር። ወረርሽኙ ከመከሰቱ በፊት የነበረው ሽያጭ 622̌.7 ሚሊዮን ዶላርም ነበር ተብሏል። | https://www.bbc.com/amharic/news-55141283 |
5sports
| ኢትዮጵያውያን ሴት አትሌቶች ደምቀውበት ያለፈው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን | በአሜሪካዋ ግዛት ኦሪገን፣ ዩጂን ከተማ ውስጥ ሲካሄድ በሰነበተው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ላይ ሴት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ታሪክ በማስመዝገብ ደምቀው ታይተዋል። ኢትዮጵያ በውድድሩ ካስመዘገበቻቸው 10 ሜዳሊያዎች 7ቱ የተመዘገቡት በተለያዩ ርቀቶች በተሳተፉ ሴት አትሌቶች አማካይነት የተገኙ ናቸው። ኢትዮጵያ በ4 የወርቅ፣ በ4 የብር እና በ2 የነሐስ ሜዳሊያዎች ከአፍሪካ አንደኛ ከዓለም ደግሞ ከአሜሪካ በመቀጠል ሁለተኛ ሆና ውድድሩን አጠናቃለች። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በዓለም የአትሌቲክስ ሻምፒዮን በርካታ ሜዳሊያዎች ሲያስመዘግቡ ይህ የመጀመሪያው ነው። ጉዳፍ ፀጋይ በ5 ሺህ ሜትር፣ ለተሰንበር ግደይ በ10 ሺህ ሜትር እንዲሁም ጎተይቶም ገ/ሥላሴ በማራቶን ኢትዮጵያ ካስመዘገበቻቸው 4 የወርቅ ሜዳሊያዎች ሦስቱን ማስገኘት ችለዋል። ቀሪ አንድ የወርቅ ሜዳሊያ የተገኘው በወንዶች የማራቶን ውድድር በታምራት ቶላ አማካይነት ነው። ከ4ቱ የብር ሜዳሊያዎች ሁለቱን ያጠለቁት ጉዳፍ ፀጋይ እና ወርቅውሃ ጌታቸው ናቸው። ይህም ጉዳፍ በ1 ሺህ 500 ሜትር፤ ወርቅውሃ ደግሞ በ3 ሺህ ሜትር መስናክል። የተቀሩትን ሁለት የብር ሜዳሊያዎች ለሜቻ ግርማ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል እንዲሁም ሞሰነት ገረመው በማራቶን ለአገራቸው አስመዝግበዋል። ሁለቱ የነሐስ ሜዳሊያዎች የተመዘገቡት በሁለት ሴት አትሌቶች ነው። ዳዊት ስዩም በ5 ሺህ ሜትር እንዲሁም መቅደስ አበበ በ3 ሺህ ሜትር። ወርቅ ያስመዘገቡት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በውድድሩ ከፍተኛ ብቃታቸውን ከማሳየታቸው ባሻገር የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናንም ክብረ ወሰን ለማሻሻል በቅተዋል። ደራርቱ ቱሉ ያለፉትን ጥቂት ዓመታት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሽንን በበላይነት ስትመራ ቆይታለች። በተለያዩ የአትሌቲክስ መድረኮች ላይ የአገሯን ስም ያስጠራችው ደራርቱ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆና ከተመረጠች በኋላ፣ ይህ የኦሪገኑ ሻምፒዮና ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበበት ዓለም አቀፍ ውድድር ነው። ደራርቱ ፌዴሬሽኑን መምራት ከጀመረች ወዲህ ሁለት ጊዜ በዓለም ሻምፒዮና፤ አንድ ጊዜ በኦሊምፒክ መድረክ፤ አንድ ጊዜ ደግሞ በዓለም የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያ ተሳታፊ ሆናለች። በኳታር ዶሃ በተሰናደው የ2019 የዓለም ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ሁለት ወርቅ፣ አምስት ብርና አንድ ነሐስ ይዛ ተመልሳለች። በዚህ ውድድር የኢትዮጵያ አትሌቶች በሚታወቁበት የመካከለኛና ረዥም ርቀት ውድድር ተለመደውን ወርቅ ማስመዝገብ ባይችሉም ተስፋ ያላቸው አትሌቶች ታይተው ነበር። ኢትዮጵያ በመድረኩ በስምንት ሜዳሊያ አምስተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቀቀች። ከዚህ በኋላ በደራርቱ የተመራው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ታላቅ ወደ ሚባለው የኦሊምፒክ መድረክ ነው ያቀናው። በ2022 ቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ ያገኘችው ሜዳሊያ ብዛት አራት ነው። ይህ ውጤት ኢትዮጵያ በኦሊምፒክ መድረክ ካመጣቻቸው ዝቅተኛ ከተባሉት የሚመደብ ነው። ቀጥሎ ኢትዮጵያ የተሳተፈችበት ዓለም አቀፍ መድረክ ባለፈው መጋቢት የተካሄደው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ፍልሚያ ነው። ይህ መድረክ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ደምቀው የታዩበት ነበር። ኢትዮጵያ፤ በአራት ወርቅ፣ በሦስት ብርና በሁለት የነሐስ አሜሪካን አስከትላ ከዓለም ሁለተኛ ሆና አጠናቃለች። | ኢትዮጵያውያን ሴት አትሌቶች ደምቀውበት ያለፈው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን በአሜሪካዋ ግዛት ኦሪገን፣ ዩጂን ከተማ ውስጥ ሲካሄድ በሰነበተው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ላይ ሴት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ታሪክ በማስመዝገብ ደምቀው ታይተዋል። ኢትዮጵያ በውድድሩ ካስመዘገበቻቸው 10 ሜዳሊያዎች 7ቱ የተመዘገቡት በተለያዩ ርቀቶች በተሳተፉ ሴት አትሌቶች አማካይነት የተገኙ ናቸው። ኢትዮጵያ በ4 የወርቅ፣ በ4 የብር እና በ2 የነሐስ ሜዳሊያዎች ከአፍሪካ አንደኛ ከዓለም ደግሞ ከአሜሪካ በመቀጠል ሁለተኛ ሆና ውድድሩን አጠናቃለች። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በዓለም የአትሌቲክስ ሻምፒዮን በርካታ ሜዳሊያዎች ሲያስመዘግቡ ይህ የመጀመሪያው ነው። ጉዳፍ ፀጋይ በ5 ሺህ ሜትር፣ ለተሰንበር ግደይ በ10 ሺህ ሜትር እንዲሁም ጎተይቶም ገ/ሥላሴ በማራቶን ኢትዮጵያ ካስመዘገበቻቸው 4 የወርቅ ሜዳሊያዎች ሦስቱን ማስገኘት ችለዋል። ቀሪ አንድ የወርቅ ሜዳሊያ የተገኘው በወንዶች የማራቶን ውድድር በታምራት ቶላ አማካይነት ነው። ከ4ቱ የብር ሜዳሊያዎች ሁለቱን ያጠለቁት ጉዳፍ ፀጋይ እና ወርቅውሃ ጌታቸው ናቸው። ይህም ጉዳፍ በ1 ሺህ 500 ሜትር፤ ወርቅውሃ ደግሞ በ3 ሺህ ሜትር መስናክል። የተቀሩትን ሁለት የብር ሜዳሊያዎች ለሜቻ ግርማ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል እንዲሁም ሞሰነት ገረመው በማራቶን ለአገራቸው አስመዝግበዋል። ሁለቱ የነሐስ ሜዳሊያዎች የተመዘገቡት በሁለት ሴት አትሌቶች ነው። ዳዊት ስዩም በ5 ሺህ ሜትር እንዲሁም መቅደስ አበበ በ3 ሺህ ሜትር። ወርቅ ያስመዘገቡት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በውድድሩ ከፍተኛ ብቃታቸውን ከማሳየታቸው ባሻገር የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናንም ክብረ ወሰን ለማሻሻል በቅተዋል። ደራርቱ ቱሉ ያለፉትን ጥቂት ዓመታት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሽንን በበላይነት ስትመራ ቆይታለች። በተለያዩ የአትሌቲክስ መድረኮች ላይ የአገሯን ስም ያስጠራችው ደራርቱ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆና ከተመረጠች በኋላ፣ ይህ የኦሪገኑ ሻምፒዮና ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበበት ዓለም አቀፍ ውድድር ነው። ደራርቱ ፌዴሬሽኑን መምራት ከጀመረች ወዲህ ሁለት ጊዜ በዓለም ሻምፒዮና፤ አንድ ጊዜ በኦሊምፒክ መድረክ፤ አንድ ጊዜ ደግሞ በዓለም የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያ ተሳታፊ ሆናለች። በኳታር ዶሃ በተሰናደው የ2019 የዓለም ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ሁለት ወርቅ፣ አምስት ብርና አንድ ነሐስ ይዛ ተመልሳለች። በዚህ ውድድር የኢትዮጵያ አትሌቶች በሚታወቁበት የመካከለኛና ረዥም ርቀት ውድድር ተለመደውን ወርቅ ማስመዝገብ ባይችሉም ተስፋ ያላቸው አትሌቶች ታይተው ነበር። ኢትዮጵያ በመድረኩ በስምንት ሜዳሊያ አምስተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቀቀች። ከዚህ በኋላ በደራርቱ የተመራው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ታላቅ ወደ ሚባለው የኦሊምፒክ መድረክ ነው ያቀናው። በ2022 ቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ ያገኘችው ሜዳሊያ ብዛት አራት ነው። ይህ ውጤት ኢትዮጵያ በኦሊምፒክ መድረክ ካመጣቻቸው ዝቅተኛ ከተባሉት የሚመደብ ነው። ቀጥሎ ኢትዮጵያ የተሳተፈችበት ዓለም አቀፍ መድረክ ባለፈው መጋቢት የተካሄደው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ፍልሚያ ነው። ይህ መድረክ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ደምቀው የታዩበት ነበር። ኢትዮጵያ፤ በአራት ወርቅ፣ በሦስት ብርና በሁለት የነሐስ አሜሪካን አስከትላ ከዓለም ሁለተኛ ሆና አጠናቃለች። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cyep9eld3deo |
5sports
| በአንድ ቀን የተወለዱ ልጆች በስሟ እንዲጠሩ ስለተደረገላት አትሌት ያውቃሉ? | ናዋል ኤል ሞውታዋኬል ሞሮኳዊት አትሌት ናት። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ነሐሴ 8፣ 1984 በሎስ አንጀለስ ኦሎምፒክ ድል ተቀዳጅታለች። ማሸነፏ እጅግ ያስደሰታቸው ሞሮኳዊው ንጉሥ ሐሰን በእለቱ የተወለዱ ሴቶች ባጠቃላይ ናዋል ተብለው እንዲጠሩ ውሳኔ አስተላልፈዋል። ሰሞኑን 36ኛ ዓመት ልደታቸውን የሚያከብሩ የሞሮኮ ሴቶች ስማቸው ናዋል የመሆን እድሉ ሰፊ ነው። ናዋል በኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳልያ ያገኘች የመጀመሪያዋ ሞሮኳዊት ናት። በ400 ሜትር የመሰናክል ዝላይ ያሸነፈች የመጀመሪያዋ ሴትም ናት። በሎስ አንጀለሱ ኦሎምፒክ ላይ የተገኘች ብቸኛዋ ሞሮኳዊት ሴት ናዋል ነበረች። በኦሎምፒክ ታሪክ ድል የተቀዳጀች የመጀመሪያዋ ሴት አረብ አፍሪካዊትም ናት። የውድድሩ ተካፋይ የነበረው ሰዒድ አዊታ በ500 ሜትር ሩጫ ያሸነፈው ምናልባትም በናዋል ድል ተነሳስቶ ይሆናል። “ስለውድድሩ ሳስብ ሌሊቱን በሙሉ እንቅልፍ አልወሰደኝም” ናዋል ከውድድሩ አንድ ቀን በፊት ሲያቃዣት ነበር። መሰናክል ዘላ አንዳች ጉድጓድ ውስጥ እንደምትገባ ይሰማት እንደነበር ታስታውሳለች። “በጣም ፈርቼ ነበር። ብቸኛዋ ሞሮኳዊት ሴት ስለነበርኩ ሁሉም የቡድኑ አባላት ተስፋ ጥለውብኝ ነበር።” ውድድሩን ከማሸነፏ በፊት የነበረውን ምሽት እንዲህ ታስታውሰዋለች። “ስለ ውድድሩ ሳስብ ሌሊቱን በሙሉ እንቅልፍ አልወሰደኝም ነበር። ሲያቃዠኝ፣ ሲያልበኝ ስለነበር መተኛት አልቻልኩም። ዝግ ብዬ ስሮጥ ይታየኝ ነበር።” በችሎታዋ አምና በውድድሩ ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ ትፈልግ ነበር። “ያሰብኩት ከመጨረሻዎቹ ስምንት ተወዳዳሪዎች አንዷ እንደምሆን ነበር። አሰልጣኞቼ እንደማሸንፍ ስላሰቡ በራሴ እንድተማመን ደጋግመው ይነግሩኝ ነበር።” ናዋል እና አሰልጣኞቿ ከመጨረሻው ውድድር በፊት የሷና የተፎካካሪዎቿን ያለፉ ውድድሮች ቪድዮ ይመለከቱ እንደነበር ታስታውሳለች። የሷን ደካማና ጠንካራ ጎኖች ከተፎካካሪዎቿ ጋር ያነጻጽሩም ነበር። “ላሸንፍ ስለምችል ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ጠንካራ መሆን እንዳለብኝ ይነግሩኝ ነበር” ትላለች። ናዋል እንደምታሸንፍ ማመኗ የስኬቷ ሚስጥር ነበር። እራሷን “ያንቺ ጊዜ ነው። ድል ሊያመልጥሽ አይገባም” እያለችም ነበር። የናዋል አሜሪካዊት ጓደና ጁዲ ብራውንም የውድድሩ ተሳታፊ ነበረች። በእርግጥ የውድድሩ ተመልካቾች የ22 ዓመቷ ናዋል ደጋፊ አልነበሩም። ጋዜጠኞች ውድድሩን በአንክሮ ይከታተላሉ ነበር። ውድድሩ በይፋ ከመከፈቱ በፊት ናዋል በስህተት የጀመረች መስሏት ተደናግጣ ነበር። ኋላ ላይ ግን ተረጋጋች። “የመጀሪያውን፣ ሁለተኛውንና ሦስተኛውን መሰናክል በግራ እግሬ ዘለልኩ። ከዛ እስከ መጨረሻው ድረስ ቀኝና ግራ እግሬን መለዋወጥ ጀመርኩ።” ተፎካካሪዎቿን በቅርብ ርቀት ማየት ስላልቻለች ግራ ተጋብታ እንደነበር ታስታውሳለች። “ሌሎቹ ሯጮች የት ገቡ? ብዬ አሰብኩ። ለካ በጣም ቀድሜያቸዋለሁ። የመጨረሻውን ነጥብ ከማለፌ በፊት እኔ ብቻ እያለፍኩ መሆኑን ለማረጋገጥ ወደ ግራና ቀኝ ተመለከትኩ።” “አባቴ በቦታው ባለመኖሩ ከፍቶኝ ነበር” ናዋል ወርቅ ስታገኝ ጓደኛዋ ጁዲ ብራውን ብር አግኝታለች። “ሳሸንፍ በጣም ነው ደስ ያለኝ። ግን አባቴ በቦታው ባለመኖሩ ከፍቶኝ ነበር። ሁሌም ይደግፈኝ የነበረው አባቴ ከውድድሩ ከወራት በፊት ሕይወቱ አልፏል።” የናዋል ቤተሰቦች ስፖርት ወዳጅ ናቸው። አባቷ የጁዶካ ተጫዋች (እንደ ማርሻል አርት አይነት ውድድር) እናቷ ደግሞ መረብ ኳስ ተጫዋች ነበሩ። ናዋል ህልሟን እንድታሳካ ቤተሰቦቿ ይደግፏት ነበር። “ማሸነፌ ለአገሬ ትልቅ ዜና ነበር። ማንም ያልጠበቀው ድል ነው። አንዲት ታዳጊ ሞሮኳዊት ከምርጥ አትሌቶች ጋር ተፎካክራ አሸንፋ ወርቅ ታገኛለች ብሎ ማንም አላሰበም። በልቤና በአዕምሮዬ እስከወዲያኛው የሚኖር ታሪካዊ ቅጽበት ነው።” የናዋል ድል በወግ አጥባቂ አረብና ሙስሊም አገሮች ለሚኖሩ ብዙ ሴቶች በር ከፍቷል። “ከዛ በኋላ ብዙ ሞሮኳዊ ሴቶች አሸንፈዋል። በአልጄሪያ፣ ቱኒዚያ፣ ግብፅ እና ባህሬን የሚኖሩ ሴቶችም እንዲሁ። በኦሎምፒክስ ላይ ሴቶች አሳትፈው የማያውቁ አገሮች፤ ሴቶችን ለተሳትፎ ብቻ በቡድናቸው ከማካተት አልፈዋል። ሴቶች የሚካተቱት ለተሳትፎ ሳይሆን ለማሸነፍ ሆኗል” ትላለች አትሌቷ። | በአንድ ቀን የተወለዱ ልጆች በስሟ እንዲጠሩ ስለተደረገላት አትሌት ያውቃሉ? ናዋል ኤል ሞውታዋኬል ሞሮኳዊት አትሌት ናት። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ነሐሴ 8፣ 1984 በሎስ አንጀለስ ኦሎምፒክ ድል ተቀዳጅታለች። ማሸነፏ እጅግ ያስደሰታቸው ሞሮኳዊው ንጉሥ ሐሰን በእለቱ የተወለዱ ሴቶች ባጠቃላይ ናዋል ተብለው እንዲጠሩ ውሳኔ አስተላልፈዋል። ሰሞኑን 36ኛ ዓመት ልደታቸውን የሚያከብሩ የሞሮኮ ሴቶች ስማቸው ናዋል የመሆን እድሉ ሰፊ ነው። ናዋል በኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳልያ ያገኘች የመጀመሪያዋ ሞሮኳዊት ናት። በ400 ሜትር የመሰናክል ዝላይ ያሸነፈች የመጀመሪያዋ ሴትም ናት። በሎስ አንጀለሱ ኦሎምፒክ ላይ የተገኘች ብቸኛዋ ሞሮኳዊት ሴት ናዋል ነበረች። በኦሎምፒክ ታሪክ ድል የተቀዳጀች የመጀመሪያዋ ሴት አረብ አፍሪካዊትም ናት። የውድድሩ ተካፋይ የነበረው ሰዒድ አዊታ በ500 ሜትር ሩጫ ያሸነፈው ምናልባትም በናዋል ድል ተነሳስቶ ይሆናል። “ስለውድድሩ ሳስብ ሌሊቱን በሙሉ እንቅልፍ አልወሰደኝም” ናዋል ከውድድሩ አንድ ቀን በፊት ሲያቃዣት ነበር። መሰናክል ዘላ አንዳች ጉድጓድ ውስጥ እንደምትገባ ይሰማት እንደነበር ታስታውሳለች። “በጣም ፈርቼ ነበር። ብቸኛዋ ሞሮኳዊት ሴት ስለነበርኩ ሁሉም የቡድኑ አባላት ተስፋ ጥለውብኝ ነበር።” ውድድሩን ከማሸነፏ በፊት የነበረውን ምሽት እንዲህ ታስታውሰዋለች። “ስለ ውድድሩ ሳስብ ሌሊቱን በሙሉ እንቅልፍ አልወሰደኝም ነበር። ሲያቃዠኝ፣ ሲያልበኝ ስለነበር መተኛት አልቻልኩም። ዝግ ብዬ ስሮጥ ይታየኝ ነበር።” በችሎታዋ አምና በውድድሩ ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ ትፈልግ ነበር። “ያሰብኩት ከመጨረሻዎቹ ስምንት ተወዳዳሪዎች አንዷ እንደምሆን ነበር። አሰልጣኞቼ እንደማሸንፍ ስላሰቡ በራሴ እንድተማመን ደጋግመው ይነግሩኝ ነበር።” ናዋል እና አሰልጣኞቿ ከመጨረሻው ውድድር በፊት የሷና የተፎካካሪዎቿን ያለፉ ውድድሮች ቪድዮ ይመለከቱ እንደነበር ታስታውሳለች። የሷን ደካማና ጠንካራ ጎኖች ከተፎካካሪዎቿ ጋር ያነጻጽሩም ነበር። “ላሸንፍ ስለምችል ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ጠንካራ መሆን እንዳለብኝ ይነግሩኝ ነበር” ትላለች። ናዋል እንደምታሸንፍ ማመኗ የስኬቷ ሚስጥር ነበር። እራሷን “ያንቺ ጊዜ ነው። ድል ሊያመልጥሽ አይገባም” እያለችም ነበር። የናዋል አሜሪካዊት ጓደና ጁዲ ብራውንም የውድድሩ ተሳታፊ ነበረች። በእርግጥ የውድድሩ ተመልካቾች የ22 ዓመቷ ናዋል ደጋፊ አልነበሩም። ጋዜጠኞች ውድድሩን በአንክሮ ይከታተላሉ ነበር። ውድድሩ በይፋ ከመከፈቱ በፊት ናዋል በስህተት የጀመረች መስሏት ተደናግጣ ነበር። ኋላ ላይ ግን ተረጋጋች። “የመጀሪያውን፣ ሁለተኛውንና ሦስተኛውን መሰናክል በግራ እግሬ ዘለልኩ። ከዛ እስከ መጨረሻው ድረስ ቀኝና ግራ እግሬን መለዋወጥ ጀመርኩ።” ተፎካካሪዎቿን በቅርብ ርቀት ማየት ስላልቻለች ግራ ተጋብታ እንደነበር ታስታውሳለች። “ሌሎቹ ሯጮች የት ገቡ? ብዬ አሰብኩ። ለካ በጣም ቀድሜያቸዋለሁ። የመጨረሻውን ነጥብ ከማለፌ በፊት እኔ ብቻ እያለፍኩ መሆኑን ለማረጋገጥ ወደ ግራና ቀኝ ተመለከትኩ።” “አባቴ በቦታው ባለመኖሩ ከፍቶኝ ነበር” ናዋል ወርቅ ስታገኝ ጓደኛዋ ጁዲ ብራውን ብር አግኝታለች። “ሳሸንፍ በጣም ነው ደስ ያለኝ። ግን አባቴ በቦታው ባለመኖሩ ከፍቶኝ ነበር። ሁሌም ይደግፈኝ የነበረው አባቴ ከውድድሩ ከወራት በፊት ሕይወቱ አልፏል።” የናዋል ቤተሰቦች ስፖርት ወዳጅ ናቸው። አባቷ የጁዶካ ተጫዋች (እንደ ማርሻል አርት አይነት ውድድር) እናቷ ደግሞ መረብ ኳስ ተጫዋች ነበሩ። ናዋል ህልሟን እንድታሳካ ቤተሰቦቿ ይደግፏት ነበር። “ማሸነፌ ለአገሬ ትልቅ ዜና ነበር። ማንም ያልጠበቀው ድል ነው። አንዲት ታዳጊ ሞሮኳዊት ከምርጥ አትሌቶች ጋር ተፎካክራ አሸንፋ ወርቅ ታገኛለች ብሎ ማንም አላሰበም። በልቤና በአዕምሮዬ እስከወዲያኛው የሚኖር ታሪካዊ ቅጽበት ነው።” የናዋል ድል በወግ አጥባቂ አረብና ሙስሊም አገሮች ለሚኖሩ ብዙ ሴቶች በር ከፍቷል። “ከዛ በኋላ ብዙ ሞሮኳዊ ሴቶች አሸንፈዋል። በአልጄሪያ፣ ቱኒዚያ፣ ግብፅ እና ባህሬን የሚኖሩ ሴቶችም እንዲሁ። በኦሎምፒክስ ላይ ሴቶች አሳትፈው የማያውቁ አገሮች፤ ሴቶችን ለተሳትፎ ብቻ በቡድናቸው ከማካተት አልፈዋል። ሴቶች የሚካተቱት ለተሳትፎ ሳይሆን ለማሸነፍ ሆኗል” ትላለች አትሌቷ። | https://www.bbc.com/amharic/news-53740809 |
3politics
| በጣሊያን ኤምባሲ የሚገኙ የቀድሞ ባለስልጣናት በቀናት ውስጥ ምህረት ሊደረግላቸው ይችላል ተባለ | ሠላሳ ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ አዲስ አበባ በሚገኘው የጣሊያን ኤምባሲ ውስጥ በጥገኝነት የሚገኙት ሁለት የደርግ ከፍተኛ ባለስልጣናት በቀጣይ ቀናት ይቅርታ ሊደረግላቸው ይችላል ተባለ። እነዚህ ከፍተኛ ባለስልጣናት ኮሎኔል ብርሃኑ ባይህ እና ሌፍተናንት ጄነራል አዲስ ተድላ ከደርግ መንግሥት መውደቅ በኋላ በጣሊያን ኤምባሲ ውስጥ ላለፉት ሦሰት አስርት ዓመታት ቆይተዋል። የኢህአዴግ ሠራዊት አዲስ አበባን ከመያዙ አንድ ቀን ቀደም ብለው በጣሊያን ኤምባሲ ውስጥ ከተጠለሉት አራት የወቅቱ ከፍተኛ ባለስልጣንት መካከል የነበሩት ብርሃኑ ባይህ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲሁም ሌፍተናንት ጀነራል አዲስ ተድላ የሠራዊቱ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ነበሩ። ይህንን ጉዳይ በተመለከተ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ አቶ አወል ሱልጣን ለቢቢሲ እንደገለጹት የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው የነበሩት ሁለቱ የቀድሞ ባለስልጣናት፤ የሞት ፍርዳቸው ወደ እድሜ ልክ እስራት በርዕሰ ብሔሯ ተቀንሶላቸዋል። ሁለቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት በደርግ መንግሥት ውስጥ በነበራቸው ተሳትፎ ወቅት ተፈጽመዋል በተባሉ የተለያዩ ወንጀሎች ተከሰው ነው የሞት ቅጣት የተበየነባቸው። አቶ አወል እንዳሉት የጣሊያን ኤምባሲ ሁለቱ ግለሰቦች እንቅስቃሴያቸው ተገድቦ ለበርካታ ዓመታት በመቆየታቸው እና እድሜያቸው መግፋቱን ተከትሎ ከእድሜ ጋር ተያይዘው በሚመጡ ሕመሞችም ችግር ላያ ያሉ መሆኑን በመጥቀስ ግለሰቦቹ ነጻ እንዲወጡ ሃሳብ መቅረቡን ለቢቢሲ ተናግረዋል። "እኛ ያሉበትን ሁኔታ አናውቅም። የሚታመሙ ሰዎች መሆናቸውን ከኤምባሲው ተገልጾልናል። ኤምባሲው ግለሰቦቹ ቢወጡ የሚል ምክረ ሃሳብ አቅርቧል" ብለዋል። ዐቃቤ ሕግም በተመሳሳይ የተላለፈባቸው የሞት ፍርድ ወደ የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲቀነስ በይቅርታ እና የምህርት ቦርድ በኩል ለርዕሰ ብሔሯ ጥያቄ ማቅረቡን ተናግረዋል። "ግለሰቦቹ ጥፋተኛ የተባሉበት ወንጀል በይቅርታ የሚያስለቅቅ ባይሆንም፤ ግለሰቦቹ ባለፉት 30 ዓመታት በጣሊያን ኤምባሲ ውስጥ እንቅስቃሴያቸው ተገድቦ እስር በሚመስል ሁኔታ ነጻነታቸውን አጥተው ቆይተዋል" ብለዋል። የጣሊያን ኤምባሲ ለዐቃቤ ሕግ ባስታወቀው መሠረት ግለሰቦቹ ከኤምባሲው ምንም አይነት ድጋፍ ሲደረግላቸው አልነበረም። ከቤተሰባቸው ይቀርብላቸው የነበረውን ቀለብ እየተጠቀሙ ነው እስካሁን የቆዩት ብለዋል አቶ አወል። በዐቃቤ ሕግ ጥያቄ መሠረት ፕሬዝደንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ የሞት ቅጣቱን ወደ እድሜ ልክ እስራት እንዲቀነስ ካደረጉ በኋላ በቀጣይም ዐቃቤ ሕግ ግለሰቦቹ በአመክሮ እንዲለቀቁ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ጥያቄ እንደሚያቀርቡ አቶ አወል አስታውቀዋል። "ፕሬዝደንቷ የሞት ቅጣቱን ወደ የእድሜ ልክ ቅጣት ቀይረውታል። በቀጣይ ግለሰቦቹ እስካሁን የቆዩበት ሁኔታ ከጥፋታቸው እንዲማሩ ስላደረጋቸው እና ከዚህ በኋላ ባሉበት ሁኔታ እንዲቆዩ ማደረግ የፍትሕ ዓላማ ስላማይሆን ሊወጡ የሚችሉበትን ሁኔታ ከሕግ አግባብ ነገሮችን ለማየት ጥረት አድርገናል። በዚህ መሠረትም ሰዎቹ በአመክሮ እንዲላቀቁ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ዛሬ ወይም ሰኞ እንልካለን" ብለዋል። ፍርድ ቤቱ ደግሞ ይህን ከመረመረ በኋላ ግለሰቦቹ በቀጣይ ቀናት በአመክሮን እንዲለቀቁ ያጸድቃል ብለን እናስባለን ሲሉ አቶ አወል ለቢቢሲ ተናግረዋል። የግለሰቦቹን ጉዳይ የሚመለከተው በተከሰሱበት ወንጀል ከዚህ ቀደም ጥፋተኛ ብሎ በፈረደባቸው ከፍተኛ ፍርድ ቤት መሆኑንም ተናግረዋል። የኤርትራ ነጻነት ግንባር አሥመራን ሲቆጣጠርና የኢህአዴግ ኃይሎች ድል እየቀናቸው ወደ አዲስ አበባ ለመግባት አንድ ሳምንት ሲቀራቸው የወቀቱ ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኃይለማሪያም ስልጣናቸውንና አገራቸውን ለቀው አስካሁን ድረስ በጥገኝነት ወደሚገኙባት ዚምባብዌ ካቀኑ ከሳምንት በኋላ ነበር ባለስልጣናቱ ወደ ጣሊያን ኤምባሲ የገቡት። ኮሎኔል ብርሃኑ ባይህ እንዲሁም ሌፍተናንት ጄነራል አዲስ ተድላ በውቅቱ ተይዘው ከነበሩ ከሌሎች ባልደረቦቻቸው ጋር በስልጣን ዘመናቸው ወቅት ተፈጽመዋል በተባሉ ወንጀሎች ክስ ተመስርቶባቸው በሌሉበት የሞት ቅጣት ተወስኖባቸው ነበር። መንግሥትም የጣሊያን መንግሥት ተፈላጊዎቹን አሳልፎ እንዲሰጠው በተደጋጋሚ ቢጠይቅም ጣሊያን ጥያቄውን ሳትቀበለው ግለሰቦቹን አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው ኤምባሲዋ ውስጥ አስጠግታ 30 ዓመት ሊሞላው ጥቂት ወራት ለቀሩት ጊዜ ጠብቃ አቆይታቸዋለች። በወቅቱ በኤምባሲው ውስጥ ጥገኝነት በመጠየቅ ገብተው የነበሩት ከፍተኛ ባለስልጣናት ስምንት የነበሩ ሲሆን አራቱ በእራሳቸው ፈቃድ ኤምባሲውን ለቀው መውጣታቸው ይነገራል። አሁን ኤምባሲው ውስጥ ከሚገኙት ከኮሎኔል ብርሃኑ ባይህ እና ሌፍተናንት ጀነራል አዲስ ተድላ በተጨማሪ ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኃይለማሪያም አገር ለቀው ሲሄዱ ለቀናት የመሪነት ቦታውን ይዘው የነበሩት ሌ/ጀኔራል ተስፋዬ ገብረኪዳን እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ኃይሉ ይመኑ ይገኙ ነበር። እነዚህ ከፍተኛ የቀድሞ ባለስልጣናት በኤምባሲው ውስጥ ጥገኝነት አግኝተው ለተለያዩ ጊዜያት ከቆዩ በኋላ እዚያው እንዳሉ በተለያዩ ምክንያቶች ህይወታቸው እንዳለፈ ይታወቃል። ዚምባብዌ የሚገኙትንና በጣሊያን ኤምባሲ ውስጥ ያሉትን ጨምሮ በወቅቱ እጃቸውን ሰጥተው በነበሩ የቀድሞው መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ በስልጣን ዘመናቸው ተፈጽመዋል በተባሉ ጥፋቶች የከባድ ክስ ተመስርቶባቸው የፍርድ ሂደቱ ለዓመታት ከተካሄደ በኋላ አብዛኞቹ የሞትና የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸዋል። ነገር ግን በእስር ላይ ሳሉ ህይወታቸው ካለፈው ውጪ ያሉት ባለስልጣናት ከ20 ዓመታት እስር በኋላ በምህረት ነጻ መውጣታቸው ይታወቃል። | በጣሊያን ኤምባሲ የሚገኙ የቀድሞ ባለስልጣናት በቀናት ውስጥ ምህረት ሊደረግላቸው ይችላል ተባለ ሠላሳ ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ አዲስ አበባ በሚገኘው የጣሊያን ኤምባሲ ውስጥ በጥገኝነት የሚገኙት ሁለት የደርግ ከፍተኛ ባለስልጣናት በቀጣይ ቀናት ይቅርታ ሊደረግላቸው ይችላል ተባለ። እነዚህ ከፍተኛ ባለስልጣናት ኮሎኔል ብርሃኑ ባይህ እና ሌፍተናንት ጄነራል አዲስ ተድላ ከደርግ መንግሥት መውደቅ በኋላ በጣሊያን ኤምባሲ ውስጥ ላለፉት ሦሰት አስርት ዓመታት ቆይተዋል። የኢህአዴግ ሠራዊት አዲስ አበባን ከመያዙ አንድ ቀን ቀደም ብለው በጣሊያን ኤምባሲ ውስጥ ከተጠለሉት አራት የወቅቱ ከፍተኛ ባለስልጣንት መካከል የነበሩት ብርሃኑ ባይህ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲሁም ሌፍተናንት ጀነራል አዲስ ተድላ የሠራዊቱ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ነበሩ። ይህንን ጉዳይ በተመለከተ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ አቶ አወል ሱልጣን ለቢቢሲ እንደገለጹት የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው የነበሩት ሁለቱ የቀድሞ ባለስልጣናት፤ የሞት ፍርዳቸው ወደ እድሜ ልክ እስራት በርዕሰ ብሔሯ ተቀንሶላቸዋል። ሁለቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት በደርግ መንግሥት ውስጥ በነበራቸው ተሳትፎ ወቅት ተፈጽመዋል በተባሉ የተለያዩ ወንጀሎች ተከሰው ነው የሞት ቅጣት የተበየነባቸው። አቶ አወል እንዳሉት የጣሊያን ኤምባሲ ሁለቱ ግለሰቦች እንቅስቃሴያቸው ተገድቦ ለበርካታ ዓመታት በመቆየታቸው እና እድሜያቸው መግፋቱን ተከትሎ ከእድሜ ጋር ተያይዘው በሚመጡ ሕመሞችም ችግር ላያ ያሉ መሆኑን በመጥቀስ ግለሰቦቹ ነጻ እንዲወጡ ሃሳብ መቅረቡን ለቢቢሲ ተናግረዋል። "እኛ ያሉበትን ሁኔታ አናውቅም። የሚታመሙ ሰዎች መሆናቸውን ከኤምባሲው ተገልጾልናል። ኤምባሲው ግለሰቦቹ ቢወጡ የሚል ምክረ ሃሳብ አቅርቧል" ብለዋል። ዐቃቤ ሕግም በተመሳሳይ የተላለፈባቸው የሞት ፍርድ ወደ የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲቀነስ በይቅርታ እና የምህርት ቦርድ በኩል ለርዕሰ ብሔሯ ጥያቄ ማቅረቡን ተናግረዋል። "ግለሰቦቹ ጥፋተኛ የተባሉበት ወንጀል በይቅርታ የሚያስለቅቅ ባይሆንም፤ ግለሰቦቹ ባለፉት 30 ዓመታት በጣሊያን ኤምባሲ ውስጥ እንቅስቃሴያቸው ተገድቦ እስር በሚመስል ሁኔታ ነጻነታቸውን አጥተው ቆይተዋል" ብለዋል። የጣሊያን ኤምባሲ ለዐቃቤ ሕግ ባስታወቀው መሠረት ግለሰቦቹ ከኤምባሲው ምንም አይነት ድጋፍ ሲደረግላቸው አልነበረም። ከቤተሰባቸው ይቀርብላቸው የነበረውን ቀለብ እየተጠቀሙ ነው እስካሁን የቆዩት ብለዋል አቶ አወል። በዐቃቤ ሕግ ጥያቄ መሠረት ፕሬዝደንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ የሞት ቅጣቱን ወደ እድሜ ልክ እስራት እንዲቀነስ ካደረጉ በኋላ በቀጣይም ዐቃቤ ሕግ ግለሰቦቹ በአመክሮ እንዲለቀቁ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ጥያቄ እንደሚያቀርቡ አቶ አወል አስታውቀዋል። "ፕሬዝደንቷ የሞት ቅጣቱን ወደ የእድሜ ልክ ቅጣት ቀይረውታል። በቀጣይ ግለሰቦቹ እስካሁን የቆዩበት ሁኔታ ከጥፋታቸው እንዲማሩ ስላደረጋቸው እና ከዚህ በኋላ ባሉበት ሁኔታ እንዲቆዩ ማደረግ የፍትሕ ዓላማ ስላማይሆን ሊወጡ የሚችሉበትን ሁኔታ ከሕግ አግባብ ነገሮችን ለማየት ጥረት አድርገናል። በዚህ መሠረትም ሰዎቹ በአመክሮ እንዲላቀቁ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ዛሬ ወይም ሰኞ እንልካለን" ብለዋል። ፍርድ ቤቱ ደግሞ ይህን ከመረመረ በኋላ ግለሰቦቹ በቀጣይ ቀናት በአመክሮን እንዲለቀቁ ያጸድቃል ብለን እናስባለን ሲሉ አቶ አወል ለቢቢሲ ተናግረዋል። የግለሰቦቹን ጉዳይ የሚመለከተው በተከሰሱበት ወንጀል ከዚህ ቀደም ጥፋተኛ ብሎ በፈረደባቸው ከፍተኛ ፍርድ ቤት መሆኑንም ተናግረዋል። የኤርትራ ነጻነት ግንባር አሥመራን ሲቆጣጠርና የኢህአዴግ ኃይሎች ድል እየቀናቸው ወደ አዲስ አበባ ለመግባት አንድ ሳምንት ሲቀራቸው የወቀቱ ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኃይለማሪያም ስልጣናቸውንና አገራቸውን ለቀው አስካሁን ድረስ በጥገኝነት ወደሚገኙባት ዚምባብዌ ካቀኑ ከሳምንት በኋላ ነበር ባለስልጣናቱ ወደ ጣሊያን ኤምባሲ የገቡት። ኮሎኔል ብርሃኑ ባይህ እንዲሁም ሌፍተናንት ጄነራል አዲስ ተድላ በውቅቱ ተይዘው ከነበሩ ከሌሎች ባልደረቦቻቸው ጋር በስልጣን ዘመናቸው ወቅት ተፈጽመዋል በተባሉ ወንጀሎች ክስ ተመስርቶባቸው በሌሉበት የሞት ቅጣት ተወስኖባቸው ነበር። መንግሥትም የጣሊያን መንግሥት ተፈላጊዎቹን አሳልፎ እንዲሰጠው በተደጋጋሚ ቢጠይቅም ጣሊያን ጥያቄውን ሳትቀበለው ግለሰቦቹን አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው ኤምባሲዋ ውስጥ አስጠግታ 30 ዓመት ሊሞላው ጥቂት ወራት ለቀሩት ጊዜ ጠብቃ አቆይታቸዋለች። በወቅቱ በኤምባሲው ውስጥ ጥገኝነት በመጠየቅ ገብተው የነበሩት ከፍተኛ ባለስልጣናት ስምንት የነበሩ ሲሆን አራቱ በእራሳቸው ፈቃድ ኤምባሲውን ለቀው መውጣታቸው ይነገራል። አሁን ኤምባሲው ውስጥ ከሚገኙት ከኮሎኔል ብርሃኑ ባይህ እና ሌፍተናንት ጀነራል አዲስ ተድላ በተጨማሪ ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኃይለማሪያም አገር ለቀው ሲሄዱ ለቀናት የመሪነት ቦታውን ይዘው የነበሩት ሌ/ጀኔራል ተስፋዬ ገብረኪዳን እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ኃይሉ ይመኑ ይገኙ ነበር። እነዚህ ከፍተኛ የቀድሞ ባለስልጣናት በኤምባሲው ውስጥ ጥገኝነት አግኝተው ለተለያዩ ጊዜያት ከቆዩ በኋላ እዚያው እንዳሉ በተለያዩ ምክንያቶች ህይወታቸው እንዳለፈ ይታወቃል። ዚምባብዌ የሚገኙትንና በጣሊያን ኤምባሲ ውስጥ ያሉትን ጨምሮ በወቅቱ እጃቸውን ሰጥተው በነበሩ የቀድሞው መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ በስልጣን ዘመናቸው ተፈጽመዋል በተባሉ ጥፋቶች የከባድ ክስ ተመስርቶባቸው የፍርድ ሂደቱ ለዓመታት ከተካሄደ በኋላ አብዛኞቹ የሞትና የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸዋል። ነገር ግን በእስር ላይ ሳሉ ህይወታቸው ካለፈው ውጪ ያሉት ባለስልጣናት ከ20 ዓመታት እስር በኋላ በምህረት ነጻ መውጣታቸው ይታወቃል። | https://www.bbc.com/amharic/55314978 |
0business
| በፈረንሳይ በአዲስ ዓመት ዋዜማ 874 መኪናዎች ተቃጠሉ | ፈረንሳይ ውስጥ በአዲስ ዓመት ዋዜማ በአጠቃላይ 874 መኪናዎች ዶግ አመድ መሆናቸውን ፖሊስ አስታወቀ። ቢሆንም የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳለው ይህ ቁጥር ከ2019 ጋር ሲነፃፀር የወረደ ነው። ባለሥልጣናቱ ጨምረው እንደጠቆሙት በዘንድሮው የአዲስ ዓመት በርካታ ሰዎች ለጥቂት ሰዓታት በሕግ ጥላ ሥር እንዲቆዩ ተደርገዋል። ባለፈው ዓመት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመከላከል ሲባል የተጣለውን ሰዓት እላፊ ተከትሎ ፈረንሳይ ምንም ዓይነት ረብሻ አላስተናገደችም። ከፈረንጆቹ 2005 ጀምሮ መኪና ማቃጠል ፈረንሳይ እየተለመደ የመጣ የከተሜዎች ባሕል መሆን ጀምሯል። በቅርብ ዓመታት ይህንን ድርጊት ለመከላከል ሲባል ቢያንስ 95 ሺህ ፖሊሶች ወደ መንገድ ወጥተው ሲያስሱ ነበር። የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት በየዓመቱ ቢያንስ 32 ሺህ የእሣት አደጋ ሠራተኞች በተጠንቀቅ ቆመው ይጠብቃሉ። በዋና ከተማዋ ፓሪስ የአፍና አፍንጫ መከላከያ ማድረግ የዜጎችና ጎብኚዎች ግዴታ ነው። ነገር ግን ይህንን ተላልፈው ተገኝተዋል የተባሉ 779 ሰዎች በከተማዋ ባለሥልጣናት ቅጣት ተላልፎባቸዋል። ምንም እንኳ ፈረንሳይ የተወሰኑ የኮቪድ-19 ገደቦችን ብታነሳም ከሰሞኑ በተቀሰቀሰው የኦሚክሮን ዝርያ ምክንያት ሕግጋቱ ተመልሰው ተግባራዊ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከሰኞ ጀምሮ ከ2 ሺህ በላይ ሰዎች ዝግ በሆነ አዳራሾች መሰባሰብ አይችሉም። ከዚህም አልፎ ከቤታቸው ሆነው መሥራት የሚችሉ ሰዎች ወደ ቢሮ እንዳይገቡ እግድ ይጣልባቸዋል። ፈረንሳይ በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት የመጀመሪያዋ ቅዳሜ መቶ ሺህ ሰዎች በኮሮናቫይረስ እንደተያዙባት ይፋ ማድረጓ ይታወሳል። | በፈረንሳይ በአዲስ ዓመት ዋዜማ 874 መኪናዎች ተቃጠሉ ፈረንሳይ ውስጥ በአዲስ ዓመት ዋዜማ በአጠቃላይ 874 መኪናዎች ዶግ አመድ መሆናቸውን ፖሊስ አስታወቀ። ቢሆንም የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳለው ይህ ቁጥር ከ2019 ጋር ሲነፃፀር የወረደ ነው። ባለሥልጣናቱ ጨምረው እንደጠቆሙት በዘንድሮው የአዲስ ዓመት በርካታ ሰዎች ለጥቂት ሰዓታት በሕግ ጥላ ሥር እንዲቆዩ ተደርገዋል። ባለፈው ዓመት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመከላከል ሲባል የተጣለውን ሰዓት እላፊ ተከትሎ ፈረንሳይ ምንም ዓይነት ረብሻ አላስተናገደችም። ከፈረንጆቹ 2005 ጀምሮ መኪና ማቃጠል ፈረንሳይ እየተለመደ የመጣ የከተሜዎች ባሕል መሆን ጀምሯል። በቅርብ ዓመታት ይህንን ድርጊት ለመከላከል ሲባል ቢያንስ 95 ሺህ ፖሊሶች ወደ መንገድ ወጥተው ሲያስሱ ነበር። የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት በየዓመቱ ቢያንስ 32 ሺህ የእሣት አደጋ ሠራተኞች በተጠንቀቅ ቆመው ይጠብቃሉ። በዋና ከተማዋ ፓሪስ የአፍና አፍንጫ መከላከያ ማድረግ የዜጎችና ጎብኚዎች ግዴታ ነው። ነገር ግን ይህንን ተላልፈው ተገኝተዋል የተባሉ 779 ሰዎች በከተማዋ ባለሥልጣናት ቅጣት ተላልፎባቸዋል። ምንም እንኳ ፈረንሳይ የተወሰኑ የኮቪድ-19 ገደቦችን ብታነሳም ከሰሞኑ በተቀሰቀሰው የኦሚክሮን ዝርያ ምክንያት ሕግጋቱ ተመልሰው ተግባራዊ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከሰኞ ጀምሮ ከ2 ሺህ በላይ ሰዎች ዝግ በሆነ አዳራሾች መሰባሰብ አይችሉም። ከዚህም አልፎ ከቤታቸው ሆነው መሥራት የሚችሉ ሰዎች ወደ ቢሮ እንዳይገቡ እግድ ይጣልባቸዋል። ፈረንሳይ በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት የመጀመሪያዋ ቅዳሜ መቶ ሺህ ሰዎች በኮሮናቫይረስ እንደተያዙባት ይፋ ማድረጓ ይታወሳል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59850637 |
0business
| የዋጋ ግሽበትን ለመቀነስ ያለሙት የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች | በተለያዩ ምክንያቶች በኢትዮጵያ በሚገኙ ከተሞች የመሠረታዊ ምርቶች ዋጋ ያለማቋረጥ እያሻቀበ ዜጎች ላይ ጫና እየፈጠረ ነው። ለዋጋ ግሽበቱ ምክንያት በመሆን ከሚጠቀሱት መካከል በአገሪቱ ያለው ጦርነት እና ያስከተላቸው ጊዜያዊ ችግሮች እንዲሁም በወጪ ንግድ ያለው መዛነፍ ይጠቀሳሉ። በሌላ በኩል በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ እና በሌሎች ዓለም አቀፋዊ የምጣኔ ሀብት ምክንያቶች በኢትዮጵያ ኑሮ 'የማይቀመሰ' ሆኗል የሚለውን ብዙዎች የሚጋሩት ነው። ከኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው የኅዳር ወር 2014 ዓ.ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ከአምናው ጋር ሲነጻጸር የ33 በመቶ ጭማሪ አለው። ከዚህ ውስጥ የምግብ ነክ ምርቶች የኅዳር ወር በ38.9 በመቶ የጨመረ ሲሆን አምና በተመሳሳይ ወቅት ተንከባላይ የምግብ ነክ ዋጋ ግሽበት 23.2 ሆኖ ተመዝግቦ ነበር። ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የኅብረተብ ክፍሎች ደግሞ በዋጋ ግሽበቱ በቀዳሚነት ተጎጂ ሆነዋል። እነዚህን የኅብረተብ ክፍሎች ተደራሽ ለማድረግ በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ የቅዳሜ እሁድ ገበያዎች ከሳምንታት በፊት ሥራ ጀምረዋል። ገበያዎቹ ለምን ተቋቋሙ? ገበያዎቹ በአንድ በኩል ለሸማቾች ምክንያታዊ በሆነ ዋጋ ምርት የማቅረብ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ለአምራቾች ገበያ የመፍጠር ዓላማ ያላቸው ናቸው። የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መስፍን አሰፋ ላለፉት ዘጠኝ ሳምንታት በአዲስ አበባ የተለያዩ አከባቢዎች የተከናወኑት የእሁድ ገበያዎች ቀዳሚ ዓላማ በከተማው የሚስተዋለውን የዋጋ ንረት "ለመከላከል እና ለመቆጣጠር" እንዲሁም ሸማቾችን እና አምራቾችን በቀጥታ ለማገናኘት ያለመ እንደሆነ ይናገራሉ። "በተለይም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የኅብረተብ ክፍሎች በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶችን ማግኘት እንዲችሉ እና ከዚያ ጎን ለጎን ደግሞ ለአምራች፣ አርሶ አደሮችም፣ ፋብሪካዎችም የገበያ ችግሮቻቸውን ለመፍታት ያለመ ነው።...ከተማችን ላይ ያለውን የምርት አቅርቦት መጠን ማሳደግም" ዓላማው ነው ሲሉ ለቢቢሲ አብራርተዋል። በአዲስ አበባ ይህ ገበያ በየሳምንቱ እሁድ የሚደረግ ሲሆን በድሬዳዋ ደግሞ ቅዳሜንም ያካትታል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የድሬዳዋ ከተማ የንግድ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሚኑ ጠሃ፣ የገበያዎቹ "ዋና ዓላማ የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስ ነው። በተለይ መካከለኛ እና ዝቅተኛ ገቢ ያለው የኅብረተሰብ ክፍል ዋጋ ሳይጨመርበት የግብር ምርቶችን እና የፋብሪካ ምርቶችን በቀላሉ በተመጣጣኝ ዋጋ አግኝቶ ከኑሮ ጫናው እንዲላቀቅ የተጀመረ ነው" ሲሉ ገልጸዋል። ገበያዎቹ ምርትን በተመጣጣኝ ዋጋ ያቀርባሉ የሚሉት አቶ አሚኑ፣ የሽንኩርትን ገበያ ለአብነት በማንሳት "በመደበኛው ገበያ እስከ አርባ ብር የሚሸጠው ሽንኩርት እኛ ባዘጋጀነው የቅዳሜ እና የእሁድ ገበያ እስከ 28 ብር የሚሽጥ ነው" ብለዋል። በገበያዎቹ ምን እና ማን ያቀርባል? በአዲስ አበባ በአስራ አንድ፣ በድሬዳዋ ደግሞ በአራት ቦታዎች የተዘረጉት እነዚህ የእረፍት ቀናት ገበያዎች የግብርና እና የፋብሪካ ምርቶች የሚቀርቡበት ነው። በሁለቱም ከተሞች ያሉ የከተማ ግብርና ውጤቶች እንዲሁም በከተሞቹ ዙሪያ ያሉ አርሶ አድሮች የሚያመርቷቸው የእህል ምርቶች በገበያዎቹ አማካኝነት ለነዋሪዎች ይቀርባል። በድሬዳዋ ከተማ እነዚህ ገበያዎች በአብዛኛው ጤፍን ጨምሮ አትክልት እና ፍራፍሬ፤ ከቃሪያ እስከ ሽንኩርት ያሉ የጓሮ አትክልቶችን እንዲሁም በከተማ ውስጥ ያሉ ፋብሪካዎች የሚያመርቷቸው ዘይት፣ ዱቄት፣ መኮሮኒ፣ ፓስታ፣ ብስኩትን እና ሳሙናን የመሰሉ ምርቶች ይቀርቡበታል። የፋብሪካ ምርቶቹ "በተመጣጣኝ ዋጋ ኅብረተሰቡ ማግኘት እንዲችል ነው፤ አከፋፋይ እና ቸርቻሪ እጅ ሳይገባ ማለት ነው። በፋብሪካ ዋጋ ኅብረተሰብ እንዲያገኝ የተደረገ ነው" ሲሉ አቶ አሚኑ ተናግረዋል። እንደ ድሬዳዋ ሁሉ በአዲስ አበባም በገበያዎቹ መሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ይቀርቡበታል። ገበያዎቹ እንደ ቲማቲም፣ ሽንኩርት፣ ድንች፣ ጎመን ያሉ አትክልቶች፤ ሙዝ እና ብርቱካንን የመሳሰሉ ፍራፍሬዎች፤ ጤፍ እና ስንዴን ጨምሮ የሰብል ምርቶች፤ ዘይት፣ ፓስታ፣ የዳቦ ዱቄት አይነት የኢንዱስትሪ ውጤቶችንም የሚያካትት ነው። "በዋናነት ምርቶቹ ትኩረት ያደረጉት ኅብረተሰቡ በየዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ ለምግብነት የሚያውላቸው እና የሚጠቀምባቸውን ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ በአቅራቢያው እንዲያገኝ ያለመ" እንደሆነ አቶ መስፍን ጠቅሰዋል። ለገበያዎቹ ምርት የሚያቀርቡት በከተማ ግብርና የተሰማሩ በግልም ይሁን ተደራጅተው የሚሰሩ አምራቾች ናቸው። በተጨማሪም በከተሞቹ ዙሪያ ያሉ አርሶ አደሮች እና ፋብሪካዎች ናቸው። ከተሞቹ ከኦሮሚያ፣ ከአማራ፣ ከደቡብ ክልል የሚገኙ ምርቶችን በቅዳሜና እሁድ ገበያዎች አማካኝነት ያቀርባሉ። ገበያዎቹ እስከመቼ ይቀጥላሉ? በድሬዳዋ የቅዳሜ እና እሁድ ገበያ በተጀመረ በአንድ ወር ከአስራ አምስት ቀን ውስጥ ወይም እስከ 6ኛው ሳምንት አርባ ሚሊዮን ብር የሚያህል ግብይት መፈጸሙን አቶ አሚኑ ተናግረዋል። "በዚህ ስድስት ሳምንት ውስጥ አርባ ሚሊዮን ግብይት ቢካሄድም ግን በመደበኛ የገበያ ዋጋ ሊያወጣ ይችል የነበረው ከአስር ሚሊዮን ብር በላይ ኅብረተሰቡን አድነነዋል" ብለዋል ኃላፊው። የገበያ ልውውጡን ትክክለኛው አሀዝ መረጃ ለጊዜው የለኝም ያሉት አቶ መስፍን ደግሞ ልውውጡ "ሰፊ ቁጥር ያለው እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ" መምጣቱን ጠቅሰው በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል። "ዘመናዊ የንግድ ሥርዓት እየገነባን እስክንሄድ፣ የቁጥጥር ሥርዓታችን ውጤታማ እየሆነ ሲሄድ፣ ምርታማነታችንን በምንፈልገው ደረጃ እስኪደርስ ... ገበያዎቹ ተጠናክረው ይቀጥላሉ" የሚሉት አቶ መስፍን እነዚህ የመገበያያ አማራጮች የሚይዟቸው ምርቶች እያደጉ ቦታዎቹም እየጨመሩ እንደሚሄዱም አመላክተዋል። በድሬዳዋ ደግሞ በስሩ ያሉ ሁሉም ቀበሌዎች ለእነዚህ የገበያ አማራጮች ስፍራዎችን እንዲያዘጋጁ እየተደረገ መሆኑን አቶ አሚኑ ተናግረዋል። ገበያዎቹ አሁን በያዙት ቅርጽ ወይም ተጨማሪ አማራጮችን በማካተት በዘላቂነት እንሚቀጥሉም አንስተዋል። ኃላፊዎቹ እነዚህ ገበያዎች የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር የቀረቡ አማራጮች መሆኑን ጠቅሰው፣ ሰፊው ገበያ ላይ የሚስተዋሉ እና ዜጎች ላይ ጫና እንዲፈጠር ምክንያት የሆኑ የንግድ ሥርዓቱ ችግሮችን ለመቅረፍ የተጀመሩ ቁጥጥሮች እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። | የዋጋ ግሽበትን ለመቀነስ ያለሙት የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች በተለያዩ ምክንያቶች በኢትዮጵያ በሚገኙ ከተሞች የመሠረታዊ ምርቶች ዋጋ ያለማቋረጥ እያሻቀበ ዜጎች ላይ ጫና እየፈጠረ ነው። ለዋጋ ግሽበቱ ምክንያት በመሆን ከሚጠቀሱት መካከል በአገሪቱ ያለው ጦርነት እና ያስከተላቸው ጊዜያዊ ችግሮች እንዲሁም በወጪ ንግድ ያለው መዛነፍ ይጠቀሳሉ። በሌላ በኩል በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ እና በሌሎች ዓለም አቀፋዊ የምጣኔ ሀብት ምክንያቶች በኢትዮጵያ ኑሮ 'የማይቀመሰ' ሆኗል የሚለውን ብዙዎች የሚጋሩት ነው። ከኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው የኅዳር ወር 2014 ዓ.ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ከአምናው ጋር ሲነጻጸር የ33 በመቶ ጭማሪ አለው። ከዚህ ውስጥ የምግብ ነክ ምርቶች የኅዳር ወር በ38.9 በመቶ የጨመረ ሲሆን አምና በተመሳሳይ ወቅት ተንከባላይ የምግብ ነክ ዋጋ ግሽበት 23.2 ሆኖ ተመዝግቦ ነበር። ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የኅብረተብ ክፍሎች ደግሞ በዋጋ ግሽበቱ በቀዳሚነት ተጎጂ ሆነዋል። እነዚህን የኅብረተብ ክፍሎች ተደራሽ ለማድረግ በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ የቅዳሜ እሁድ ገበያዎች ከሳምንታት በፊት ሥራ ጀምረዋል። ገበያዎቹ ለምን ተቋቋሙ? ገበያዎቹ በአንድ በኩል ለሸማቾች ምክንያታዊ በሆነ ዋጋ ምርት የማቅረብ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ለአምራቾች ገበያ የመፍጠር ዓላማ ያላቸው ናቸው። የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መስፍን አሰፋ ላለፉት ዘጠኝ ሳምንታት በአዲስ አበባ የተለያዩ አከባቢዎች የተከናወኑት የእሁድ ገበያዎች ቀዳሚ ዓላማ በከተማው የሚስተዋለውን የዋጋ ንረት "ለመከላከል እና ለመቆጣጠር" እንዲሁም ሸማቾችን እና አምራቾችን በቀጥታ ለማገናኘት ያለመ እንደሆነ ይናገራሉ። "በተለይም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የኅብረተብ ክፍሎች በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶችን ማግኘት እንዲችሉ እና ከዚያ ጎን ለጎን ደግሞ ለአምራች፣ አርሶ አደሮችም፣ ፋብሪካዎችም የገበያ ችግሮቻቸውን ለመፍታት ያለመ ነው።...ከተማችን ላይ ያለውን የምርት አቅርቦት መጠን ማሳደግም" ዓላማው ነው ሲሉ ለቢቢሲ አብራርተዋል። በአዲስ አበባ ይህ ገበያ በየሳምንቱ እሁድ የሚደረግ ሲሆን በድሬዳዋ ደግሞ ቅዳሜንም ያካትታል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የድሬዳዋ ከተማ የንግድ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሚኑ ጠሃ፣ የገበያዎቹ "ዋና ዓላማ የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስ ነው። በተለይ መካከለኛ እና ዝቅተኛ ገቢ ያለው የኅብረተሰብ ክፍል ዋጋ ሳይጨመርበት የግብር ምርቶችን እና የፋብሪካ ምርቶችን በቀላሉ በተመጣጣኝ ዋጋ አግኝቶ ከኑሮ ጫናው እንዲላቀቅ የተጀመረ ነው" ሲሉ ገልጸዋል። ገበያዎቹ ምርትን በተመጣጣኝ ዋጋ ያቀርባሉ የሚሉት አቶ አሚኑ፣ የሽንኩርትን ገበያ ለአብነት በማንሳት "በመደበኛው ገበያ እስከ አርባ ብር የሚሸጠው ሽንኩርት እኛ ባዘጋጀነው የቅዳሜ እና የእሁድ ገበያ እስከ 28 ብር የሚሽጥ ነው" ብለዋል። በገበያዎቹ ምን እና ማን ያቀርባል? በአዲስ አበባ በአስራ አንድ፣ በድሬዳዋ ደግሞ በአራት ቦታዎች የተዘረጉት እነዚህ የእረፍት ቀናት ገበያዎች የግብርና እና የፋብሪካ ምርቶች የሚቀርቡበት ነው። በሁለቱም ከተሞች ያሉ የከተማ ግብርና ውጤቶች እንዲሁም በከተሞቹ ዙሪያ ያሉ አርሶ አድሮች የሚያመርቷቸው የእህል ምርቶች በገበያዎቹ አማካኝነት ለነዋሪዎች ይቀርባል። በድሬዳዋ ከተማ እነዚህ ገበያዎች በአብዛኛው ጤፍን ጨምሮ አትክልት እና ፍራፍሬ፤ ከቃሪያ እስከ ሽንኩርት ያሉ የጓሮ አትክልቶችን እንዲሁም በከተማ ውስጥ ያሉ ፋብሪካዎች የሚያመርቷቸው ዘይት፣ ዱቄት፣ መኮሮኒ፣ ፓስታ፣ ብስኩትን እና ሳሙናን የመሰሉ ምርቶች ይቀርቡበታል። የፋብሪካ ምርቶቹ "በተመጣጣኝ ዋጋ ኅብረተሰቡ ማግኘት እንዲችል ነው፤ አከፋፋይ እና ቸርቻሪ እጅ ሳይገባ ማለት ነው። በፋብሪካ ዋጋ ኅብረተሰብ እንዲያገኝ የተደረገ ነው" ሲሉ አቶ አሚኑ ተናግረዋል። እንደ ድሬዳዋ ሁሉ በአዲስ አበባም በገበያዎቹ መሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ይቀርቡበታል። ገበያዎቹ እንደ ቲማቲም፣ ሽንኩርት፣ ድንች፣ ጎመን ያሉ አትክልቶች፤ ሙዝ እና ብርቱካንን የመሳሰሉ ፍራፍሬዎች፤ ጤፍ እና ስንዴን ጨምሮ የሰብል ምርቶች፤ ዘይት፣ ፓስታ፣ የዳቦ ዱቄት አይነት የኢንዱስትሪ ውጤቶችንም የሚያካትት ነው። "በዋናነት ምርቶቹ ትኩረት ያደረጉት ኅብረተሰቡ በየዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ ለምግብነት የሚያውላቸው እና የሚጠቀምባቸውን ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ በአቅራቢያው እንዲያገኝ ያለመ" እንደሆነ አቶ መስፍን ጠቅሰዋል። ለገበያዎቹ ምርት የሚያቀርቡት በከተማ ግብርና የተሰማሩ በግልም ይሁን ተደራጅተው የሚሰሩ አምራቾች ናቸው። በተጨማሪም በከተሞቹ ዙሪያ ያሉ አርሶ አደሮች እና ፋብሪካዎች ናቸው። ከተሞቹ ከኦሮሚያ፣ ከአማራ፣ ከደቡብ ክልል የሚገኙ ምርቶችን በቅዳሜና እሁድ ገበያዎች አማካኝነት ያቀርባሉ። ገበያዎቹ እስከመቼ ይቀጥላሉ? በድሬዳዋ የቅዳሜ እና እሁድ ገበያ በተጀመረ በአንድ ወር ከአስራ አምስት ቀን ውስጥ ወይም እስከ 6ኛው ሳምንት አርባ ሚሊዮን ብር የሚያህል ግብይት መፈጸሙን አቶ አሚኑ ተናግረዋል። "በዚህ ስድስት ሳምንት ውስጥ አርባ ሚሊዮን ግብይት ቢካሄድም ግን በመደበኛ የገበያ ዋጋ ሊያወጣ ይችል የነበረው ከአስር ሚሊዮን ብር በላይ ኅብረተሰቡን አድነነዋል" ብለዋል ኃላፊው። የገበያ ልውውጡን ትክክለኛው አሀዝ መረጃ ለጊዜው የለኝም ያሉት አቶ መስፍን ደግሞ ልውውጡ "ሰፊ ቁጥር ያለው እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ" መምጣቱን ጠቅሰው በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል። "ዘመናዊ የንግድ ሥርዓት እየገነባን እስክንሄድ፣ የቁጥጥር ሥርዓታችን ውጤታማ እየሆነ ሲሄድ፣ ምርታማነታችንን በምንፈልገው ደረጃ እስኪደርስ ... ገበያዎቹ ተጠናክረው ይቀጥላሉ" የሚሉት አቶ መስፍን እነዚህ የመገበያያ አማራጮች የሚይዟቸው ምርቶች እያደጉ ቦታዎቹም እየጨመሩ እንደሚሄዱም አመላክተዋል። በድሬዳዋ ደግሞ በስሩ ያሉ ሁሉም ቀበሌዎች ለእነዚህ የገበያ አማራጮች ስፍራዎችን እንዲያዘጋጁ እየተደረገ መሆኑን አቶ አሚኑ ተናግረዋል። ገበያዎቹ አሁን በያዙት ቅርጽ ወይም ተጨማሪ አማራጮችን በማካተት በዘላቂነት እንሚቀጥሉም አንስተዋል። ኃላፊዎቹ እነዚህ ገበያዎች የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር የቀረቡ አማራጮች መሆኑን ጠቅሰው፣ ሰፊው ገበያ ላይ የሚስተዋሉ እና ዜጎች ላይ ጫና እንዲፈጠር ምክንያት የሆኑ የንግድ ሥርዓቱ ችግሮችን ለመቅረፍ የተጀመሩ ቁጥጥሮች እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59839436 |
2health
| ኮቪድ-19፡ በስህተት የ16 ሺህ ሰዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራ ውጤት ሳይገለጽ ቀረ | ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ በገጠመ የቴክኒክ ስህተት ወደ 16 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ሳይገለጽ ቀረ። ይህም በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች ለመለየት የሚደረገውን ጥረት አጓቷል። የአገሪቱ የሕብረተሰብ ጤና ተቋም እንዳለው ከመስከረም 25 እስከ ጥቅምት 2 ድረስ 15,841 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው በእለታዊ ሪፖርት ሳይካተት ቀርቷል። ሪፖርት ያልተደረጉት ሰዎች ባሳለፍነው ቅዳሜ እና እሁድ በወጡት እለታዊ ሪፖርቶች ተካተዋል። • የኮቪድ-19 ፀር ሳሙና ወይስ ፀረ-ቫይረስ ፈሳሽ? • ትራምፕ ደጋፊዎቻቸውን ለማየት ሆስፒታል ጥለው ወጡ • ልብስ ሳያረጥብ በፀረ ተህዋስ የሚያፀዳው የኢትዮጵያዊው ፈጠራ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ውጤታቸው ቢነገራቸውም ከእነሱ ጋር ንክኪ ያላቸው ሰዎች መረጃው እንዳልደረሳቸው ተቋሙ አስታውቋል። በገጠመው የቴክኒክ ስህተት ምክንያት ባለፈው ሳምንት የወጡ ሪፖርቶች በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርን አሳንሰዋል። በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በቫይረሱ እንደተያዙ የተገለጸው 7,000 ሰዎች ቢሆንም፤ ትክክለኛው ቁጥር ወደ 11,000 ይጠጋል። ሪፖርት ካልተደረጉት ሰዎች አብላጫውን ቁጥር የሚይዙት የሰሜን ምዕራብ ኢንግላንድ ነዋሪዎች ናቸው። በርካታ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የሚኖሩት በሊቨርፑል እና በማንችስተር ነው። ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች በአጠቃላይ እንደተነገራቸው ገልጸዋል። የክትባት ምርምር ግብረ ኃይል ኃላፊ ኬት ቢንግሀም ለፋይናንሽያል ታይምስ እንደተናገሩት፤ ከዩኬ ዜጎች ከፊሉ ይከተባሉ። “ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ሰዎች ክትባት አይሰጥም። ክትባቱ ከ50 ዓመት በላይ ለሆኑና በዋናነትም ለጤና ባለሙያዎችና አረጋውያንን ለሚንከባከቡ ሰዎች ይሰጣል” ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ወረርሽኙን የማሸነፍ ተስፋ እንዳለ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ማኅበረሰቡ “ጥንቃቄ ማድረግ እንጂ መፍራት የለበትም” ሲሉም አክለዋል። በአገሪቱ የምርመራ ውጤት መዘግየቱ መንግሥትን እያስተቸ ባለበት ወቅት፤ በስህተት ውጤታቸው ያልተገለጸ ሰዎች የመኖራቸው ዜና ነገሮችን አባብሷል። በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸው ሰዎች መረጃውን አለማግኘታቸው ሌላው አሳሳቢ ነገር ነው። ባለሙያዎች እንደሚሉት፤ ቫይረሱ ከተገኘበት ሰው ጋር ንክኪ የነበራቸው ግለሰቦች በ48 ሰዓታት ውስጥ ሊነገራቸው ይገባል። ስህተቱ የኮምፒውተር እንደሆነና አሁን መስተካከሉ ተገልጿል። መንግሥት ትላንት ባወጣው ሪፖርት ተጨማሪ 22,961 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸውና አጠቃላይ በበሽታው የተያዙ ቁጥር 502,978 መድረሱን ገልጿል። የሕብረተሰብ ጤና ተቋም ኃላፊው ማይክል ብሮይድ እንዳሉት፤ አብዛኞቹ ሪፖርት ያልተደረጉ ቁጥሮች የቅርብ ጊዜ የምርመራ ውጤት ናቸው። “ችግሩን በአፋጣኝ ለመቅረፍና የምርመራ ውጤቶቹን ለመግለጽ ሞክረናል። ስህተቱ ሊፈጥር የሚችለውን ስጋት እንረዳለን። በቀጣይ ተመሳሳይ ነገር እንዳይፈጠር ጥብቅ እርምጃ ወስደናል” ብለዋል። | ኮቪድ-19፡ በስህተት የ16 ሺህ ሰዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራ ውጤት ሳይገለጽ ቀረ ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ በገጠመ የቴክኒክ ስህተት ወደ 16 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ሳይገለጽ ቀረ። ይህም በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች ለመለየት የሚደረገውን ጥረት አጓቷል። የአገሪቱ የሕብረተሰብ ጤና ተቋም እንዳለው ከመስከረም 25 እስከ ጥቅምት 2 ድረስ 15,841 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው በእለታዊ ሪፖርት ሳይካተት ቀርቷል። ሪፖርት ያልተደረጉት ሰዎች ባሳለፍነው ቅዳሜ እና እሁድ በወጡት እለታዊ ሪፖርቶች ተካተዋል። • የኮቪድ-19 ፀር ሳሙና ወይስ ፀረ-ቫይረስ ፈሳሽ? • ትራምፕ ደጋፊዎቻቸውን ለማየት ሆስፒታል ጥለው ወጡ • ልብስ ሳያረጥብ በፀረ ተህዋስ የሚያፀዳው የኢትዮጵያዊው ፈጠራ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ውጤታቸው ቢነገራቸውም ከእነሱ ጋር ንክኪ ያላቸው ሰዎች መረጃው እንዳልደረሳቸው ተቋሙ አስታውቋል። በገጠመው የቴክኒክ ስህተት ምክንያት ባለፈው ሳምንት የወጡ ሪፖርቶች በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርን አሳንሰዋል። በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በቫይረሱ እንደተያዙ የተገለጸው 7,000 ሰዎች ቢሆንም፤ ትክክለኛው ቁጥር ወደ 11,000 ይጠጋል። ሪፖርት ካልተደረጉት ሰዎች አብላጫውን ቁጥር የሚይዙት የሰሜን ምዕራብ ኢንግላንድ ነዋሪዎች ናቸው። በርካታ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የሚኖሩት በሊቨርፑል እና በማንችስተር ነው። ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች በአጠቃላይ እንደተነገራቸው ገልጸዋል። የክትባት ምርምር ግብረ ኃይል ኃላፊ ኬት ቢንግሀም ለፋይናንሽያል ታይምስ እንደተናገሩት፤ ከዩኬ ዜጎች ከፊሉ ይከተባሉ። “ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ሰዎች ክትባት አይሰጥም። ክትባቱ ከ50 ዓመት በላይ ለሆኑና በዋናነትም ለጤና ባለሙያዎችና አረጋውያንን ለሚንከባከቡ ሰዎች ይሰጣል” ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ወረርሽኙን የማሸነፍ ተስፋ እንዳለ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ማኅበረሰቡ “ጥንቃቄ ማድረግ እንጂ መፍራት የለበትም” ሲሉም አክለዋል። በአገሪቱ የምርመራ ውጤት መዘግየቱ መንግሥትን እያስተቸ ባለበት ወቅት፤ በስህተት ውጤታቸው ያልተገለጸ ሰዎች የመኖራቸው ዜና ነገሮችን አባብሷል። በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸው ሰዎች መረጃውን አለማግኘታቸው ሌላው አሳሳቢ ነገር ነው። ባለሙያዎች እንደሚሉት፤ ቫይረሱ ከተገኘበት ሰው ጋር ንክኪ የነበራቸው ግለሰቦች በ48 ሰዓታት ውስጥ ሊነገራቸው ይገባል። ስህተቱ የኮምፒውተር እንደሆነና አሁን መስተካከሉ ተገልጿል። መንግሥት ትላንት ባወጣው ሪፖርት ተጨማሪ 22,961 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸውና አጠቃላይ በበሽታው የተያዙ ቁጥር 502,978 መድረሱን ገልጿል። የሕብረተሰብ ጤና ተቋም ኃላፊው ማይክል ብሮይድ እንዳሉት፤ አብዛኞቹ ሪፖርት ያልተደረጉ ቁጥሮች የቅርብ ጊዜ የምርመራ ውጤት ናቸው። “ችግሩን በአፋጣኝ ለመቅረፍና የምርመራ ውጤቶቹን ለመግለጽ ሞክረናል። ስህተቱ ሊፈጥር የሚችለውን ስጋት እንረዳለን። በቀጣይ ተመሳሳይ ነገር እንዳይፈጠር ጥብቅ እርምጃ ወስደናል” ብለዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54423275 |
2health
| ለሁለተኛ ጊዜ በኮቪድ-19 የተያዘው ከመጀመሪያው በባሰ በጠና ታመመ | አሜሪካ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በኮሮናቫይረስ የተያዘው ሰው፤ ከመጀመሪያው በባሰ ሁኔታ በጠና መታመሙን ሐኪሞች ተናገሩ። የ25 ዓመቱ ግለሰብ ከሳምባው በቂ ኦክስጅን ወደ ሰውነቱ መዘዋወር ስላልቻለ ሆስፒታል ገብቷል። በድጋሚ በቫይረሱ የመያዝ እድል አነስተኛ ሲሆን፤ ግለሰቡም እያገገመ ይገኛል። የኔቫዳ ነዋሪ የሆነው ግለሰብ በተለየ ሁኔታ ለኮቪድ-19 ተጋላጭ የሚያደርገው ህመም ወይም በሽታ የመቋቋም ኃይል ውስንንነት የለበትም። ግለሰቡ ከመጋቢት እስከ ሰኔ ድረስ ያሳየው የበሽታው ምልክቶች ቀጣዮቹ ናቸው፦ ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ግለሰቡ ሁለት ጊዜ በቫይረሱ ተይዟል። መጀመሪያ የያዘው ቫይረስ ተደብቆ በድጋሚ አላገረሸበትም። የሁለቱ ቫይረሶች የዘረ መል ቅንጣት የተለያየ ነው። በኔቫዳ ዩኒቨርስቲ መመህር የሆኑት ዶ/ር ማርክ ፓንዶሪ “ቀደም ያለ ኢንፌክሽን ለሁለተኛ ጊዜ በበሽታው ከመያዝ እንደማያድን ግኝታችን ይጠቁማል። ለሁለተኛ ጊዜ በቫይረሱ የመያዝ እድል መኖሩ በሽታን ስለመከላከል አቅም ያለንን አመለካከት ይለውጣል” ብለዋል። ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ፣ እጃቸውን አዘውትረው መታጠብ እና አካላዊ ርቀት መጠበቅ እንዳለባቸውም ዶክተሩ መክረዋል። ሁሉም ሰው በሽታውን የመከላከል አቅም ያዳብራል? መጠነኛ ምልክት ያሳዩ ሰዎች በሽታውን መከላከል ይችላሉ? በሽታውን የመከላከል አቅም ለምን ያህል ጊዜ ይቆያል? የሚሉት ገና መልስ ያልተገኘላቸው ጥያቄዎች ናቸው። በሽታው በጊዜ ሂደት የሚያሳድርብንን ተጽዕኖ ለመረዳት እንዲሁም ክትባት ለማግኘትም እነዚህን ጥያቄዎች መመለስ ያሻል። እስካሁን በቫይረሱ ከተያዙ ከ37 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ዳግመኛ በሽታው የያዛቸው እጅግ ጥቂቶቹ ናቸው። ከሆንግ ኮንግ፣ ቤልጄም እና ኔዘርላንድ የተገኘ መረጃ እንደሚያሳየው፤ ለሁለተኛ ጊዜ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ከመጀመሪያው በበለጠ አልታመሙም። ኢኳዶር ውስጥ ግን ከመጀሪያው በላቀ የታመመ ሰው ነበር። ሰውነት ቫይረሱን የመቋቋም አቅም ስለሚያዳብር ለሁለተኛ ጊዜ በሽታው ሲከሰት ቀለል ይላል የሚል መላ ምት ነበር። አሜሪካ ያለው ግለሰብ በሁለተኛው ዙር ለምን በሽታው እንደጠናበት አልታወቀም። ምናልባትም ከመጀመሪያው በላቀ ከፍተኛ መጠን ላለው ቫይረስ ተጋልጦ ሊሆን ይችላል። ለመጀመሪያው ቫይረስ የዳበረው በሽታ የመከላከል አቅም ሁለተኛውን ዙር ከባድ አድርጎት እንደሆነም ይገመታል። የኢስት አንጅሊያው ፕ/ር ፖል ሀንተር “በሁለቱ ህመም መካከል ያለው ጊዜ አጭር መሆኑና ሁለተኛው ዙር ከመጀመሪያው መባሱ አሳሳቢ ነው” ይላሉ። የአሜሪካውን ግልሰብ የተመለከተው ጥናት ምን ይጠቁማል? ለሚለው ምላሽ ለመስጠት ገና ነው ብለዋል ፕ/ር ፖል። | ለሁለተኛ ጊዜ በኮቪድ-19 የተያዘው ከመጀመሪያው በባሰ በጠና ታመመ አሜሪካ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በኮሮናቫይረስ የተያዘው ሰው፤ ከመጀመሪያው በባሰ ሁኔታ በጠና መታመሙን ሐኪሞች ተናገሩ። የ25 ዓመቱ ግለሰብ ከሳምባው በቂ ኦክስጅን ወደ ሰውነቱ መዘዋወር ስላልቻለ ሆስፒታል ገብቷል። በድጋሚ በቫይረሱ የመያዝ እድል አነስተኛ ሲሆን፤ ግለሰቡም እያገገመ ይገኛል። የኔቫዳ ነዋሪ የሆነው ግለሰብ በተለየ ሁኔታ ለኮቪድ-19 ተጋላጭ የሚያደርገው ህመም ወይም በሽታ የመቋቋም ኃይል ውስንንነት የለበትም። ግለሰቡ ከመጋቢት እስከ ሰኔ ድረስ ያሳየው የበሽታው ምልክቶች ቀጣዮቹ ናቸው፦ ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ግለሰቡ ሁለት ጊዜ በቫይረሱ ተይዟል። መጀመሪያ የያዘው ቫይረስ ተደብቆ በድጋሚ አላገረሸበትም። የሁለቱ ቫይረሶች የዘረ መል ቅንጣት የተለያየ ነው። በኔቫዳ ዩኒቨርስቲ መመህር የሆኑት ዶ/ር ማርክ ፓንዶሪ “ቀደም ያለ ኢንፌክሽን ለሁለተኛ ጊዜ በበሽታው ከመያዝ እንደማያድን ግኝታችን ይጠቁማል። ለሁለተኛ ጊዜ በቫይረሱ የመያዝ እድል መኖሩ በሽታን ስለመከላከል አቅም ያለንን አመለካከት ይለውጣል” ብለዋል። ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ፣ እጃቸውን አዘውትረው መታጠብ እና አካላዊ ርቀት መጠበቅ እንዳለባቸውም ዶክተሩ መክረዋል። ሁሉም ሰው በሽታውን የመከላከል አቅም ያዳብራል? መጠነኛ ምልክት ያሳዩ ሰዎች በሽታውን መከላከል ይችላሉ? በሽታውን የመከላከል አቅም ለምን ያህል ጊዜ ይቆያል? የሚሉት ገና መልስ ያልተገኘላቸው ጥያቄዎች ናቸው። በሽታው በጊዜ ሂደት የሚያሳድርብንን ተጽዕኖ ለመረዳት እንዲሁም ክትባት ለማግኘትም እነዚህን ጥያቄዎች መመለስ ያሻል። እስካሁን በቫይረሱ ከተያዙ ከ37 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ዳግመኛ በሽታው የያዛቸው እጅግ ጥቂቶቹ ናቸው። ከሆንግ ኮንግ፣ ቤልጄም እና ኔዘርላንድ የተገኘ መረጃ እንደሚያሳየው፤ ለሁለተኛ ጊዜ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ከመጀመሪያው በበለጠ አልታመሙም። ኢኳዶር ውስጥ ግን ከመጀሪያው በላቀ የታመመ ሰው ነበር። ሰውነት ቫይረሱን የመቋቋም አቅም ስለሚያዳብር ለሁለተኛ ጊዜ በሽታው ሲከሰት ቀለል ይላል የሚል መላ ምት ነበር። አሜሪካ ያለው ግለሰብ በሁለተኛው ዙር ለምን በሽታው እንደጠናበት አልታወቀም። ምናልባትም ከመጀመሪያው በላቀ ከፍተኛ መጠን ላለው ቫይረስ ተጋልጦ ሊሆን ይችላል። ለመጀመሪያው ቫይረስ የዳበረው በሽታ የመከላከል አቅም ሁለተኛውን ዙር ከባድ አድርጎት እንደሆነም ይገመታል። የኢስት አንጅሊያው ፕ/ር ፖል ሀንተር “በሁለቱ ህመም መካከል ያለው ጊዜ አጭር መሆኑና ሁለተኛው ዙር ከመጀመሪያው መባሱ አሳሳቢ ነው” ይላሉ። የአሜሪካውን ግልሰብ የተመለከተው ጥናት ምን ይጠቁማል? ለሚለው ምላሽ ለመስጠት ገና ነው ብለዋል ፕ/ር ፖል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54527534 |
5sports
| ሮማን አብራሞቪች ቼልሲን ለመሸጥ ወሰኑ | የቼልሲው ባለቤት ሮማን አብራሞቪች ክለቡን ለመሸጥ ማቀዳቸውን ገለጹ። ባለሃብቱ አብራሞቪች በፕሪሚየር ሊጉ ክለብ ድረ-ገጽ ላይ ባወጡት መግለጫ "በጣም ከባዱን እና የሚያመውን ውሳኔ" መወሰናቸውን ተናግረዋል። ሩሲያዊው "ምንም ዓይነት ብድር እንዲመለስ" ያልጠየቁ ሲሆን የሽያጩ ገቢም ለጦርነት ተጎጂዎች ይውላል ብለዋል። ሩሲያ በዩክሬን ላይ ከፈጸመችው ወረራ በኋላ አብራሞቪች ቅዳሜ ዕለት እንዳስታወቁት የቼልሲን "ኃላፊነት እና ተጠሪነት" ለፋውንዴሽኑ እንደሚሰጡ ተናግረው ነበር። ይህም ክለቡን ከ 1.5 ቢሊየን ፓውንድ በላይ ብድር ውስጥ የዘፈቁት አብራሞቪች ቼልሲን ለሽያጭ ያቀርባሉ የሚል ግምት ፈጠረ። ይህንን ተከትሎም ቢሊየነሩ ሃንስ ጆርጅ ዊስ ክለቡን የመግዛት ዕድል እንደቀረበላቸው ረቡዕ ዕለት ለስዊዘርላንዱ ብሊክ ጋዜጣ ተናግረዋል። ዊስ እንዳስታወቁት አብራሞቪች በፓርላማው የማዕቀብ ስጋት "ቼልሲን በፍጥነት ለመሸጥ" እንደፈለጉ ተናግረዋል። የ55 ዓመቱ አብራሞቪች ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ጠንካራ ግንኙነት እንዳላቸው ቢነገርም እሳቸው ግን አስተባብለዋል። "ከሽያጩ የሚገኘው የተጣራ ገንዘብ በሙሉ ለዩክሬን ጦርነት ተገጎጂዎች" እንደሚሰጥ ተናግረዋል። ቼልሲን ለመግዛት ለአብራሞቪች ጥያቄ እንደቀረበላቸው ቢቢሲ ስፖርት የተረዳ ሲሆን ክለቡም እስከ ሦስት ቢሊዮን ፓውንድ ይገመታል። አብራሞቪች በመግለጫቸው "ሁሌም ውሳኔዎችን የምወስነው የክለቡን ፍላጎት ከግምት በማስገባት ነው" ብለዋል። "አሁን ባለው ሁኔታ ለክለቡ፣ ለደጋፊው፣ ለሠራተኞቹ እንዲሁም ለክለቡ ስፖንሰሮች እና አጋር አካላት ይጠቅማል ብዬ ስለማምን ክለቡን ለመሸጥ ወስኛለሁ።" በማለት ገልጸዋል። "የክለቡ ሽያጭ ፈጣን ሳይሆን ተገቢውን ሂደት የሚከተል ነው። ምንም ዓይነት ብድር እንዲከፈልም አልጠይቅም።" "ከሽያጩ የተገኘው ገንዘብ በሙሉ የሚለግስበት የበጎ አድራጎት ድርጅት እንዲያቋቁም ለቡድኔ መመሪያ ሰጥቻለሁ። ፋውንዴሽኑ በዩክሬን በጦርነት ተጎጂ ለሆኑ ጥቅም ላይ ይውላል።" ቢቢሲ ስፖርት እንደተረዳው ከሆነ የቼልሲ ፋውንዴሽን ክለቡን ለመቆጣጠር እስካሁን አልተስማማም። አብራሞቪች ቅዳሜ ዕለት ባወጡት መግለጫ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የፈፀመችውን ወረራ ባለመጥቀሳቸው ተወቅሰዋል። የቡድኑ ተጫዋቾች ዜናው ቀደም ብሎ እንዲደርሳቸው አልተደረገም ተብሏል። ተጫዋቾች ዜናውን የሰሙት ከሉተን ታውን ከሚያደርጉት የአምስተኛው ዙር የኤፍኤ ካፕ ጨዋታ ጥቂት ደቂቃዎች ቀደም ብሎ ነው። በጨዋታው ቡድኑ ከመመራት ተነስቶ 3 ለ 2 በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍጻሜው ተቀላቅሏል። አብራሞቪች ቼልሲን እአአ በ2003 በ140 ሚሊዮን ፓውንድ መግዛታቸው ይታወሳል። ባለሃብቱ በመግለጫቸው ግዢው "ለንግድም ሆነ ለገንዘብ ሲባል የተደረገ አልነበረም። ለስፖርቱ እና ለክለቡ ንጹህ ፍቅር ሲባል የተደረገ ነው" ብለዋል። አብራሞቪች በክለቡ ውጤታማ ነበሩ? ክለቡን ከገዙበት ጊዜ ጀምሮ ቼልሲ ከመለወጥ ባለፈ በፕሪሚየር ሊጉ በትልቅ ደረጃ ለመወዳደር ገንዘብ ምን ያህል እንደሚያስፈልግ ምሳሌ ሆኗል። አብራሞቪች ለክለቡ ከ 1.5 ቢሊዮን ፓውንድ በላይ ብድር የወሰዱ ሲሆን ይህም ትልቅ ስኬት አስመዝግቧል። በእርሳቸው የባለቤትነት ክለቡ የሚቻለውን ሁሉ ትልልቅ ዋንጫ ማንሳት ችሏል። የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግን ሁለት ጊዜ፣ ፕሪሚየር ሊግ እና ኤፍኤ ካፕ አምስት አምስት ጊዜ፣ ዩሮፓ ሊግ ሁለት ጊዜ እና የሊግ ዋንጫን ሦስት ጊዜ ማንሳት ችሏል። ባለፈው ነሐሴ የዩኤፋ ሱፐር ካፕን ያሸነፉ ሲሆን በየካቲት ደግሞ የመጀመሪያውን የዓለም የክለቦች ዋንጫን አንስተዋል። 13 የተለያዩ አሰልጣኞችን የሾመ ሲሆን ክለቡ በዝውውር ገበያው ሁለት ቢሊዮን ፓውንድ በላይ ወጪ አድርጓል። የቼልሲ ሴቶች ቡድንም በአብራሞቪች ስር ውጤማ መሆን ችሏል። የሴቶችን ሱፐር ሊግ አራት ጊዜ ሲያነሳ የሴቶችን ኤፍ ኤ ካፕ ሦስት ጊዜ ማሸነፍ ችሏል። ባለለፈው ዓመትም ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ ደርሷል። የክለቡ ስም በመግነኑ እንደ አውስትራሊያዊቷ ሳም ኬር እና ዴንማርካዊው አጥቂ ፔርኒል ሃርደር ያሉ የዓለም ኮከቦች ወደ ክለቡ ሊዘዋወሩ ችለዋል። አብራሞቪች ለምን መሸጥ መረጡ? ሌሎች የሩሲያ ቢሊየነሮች ንብረታቸው ከመታገድ ባለፈ የአውሮፓ ህብረት ማዕቀብ ዒላማ ሆነዋል። ይህ ደግሞ ከኤቨርተን ጋር ግንኙነት ያላቸውን ሩሲያዊው ቢሊየነር አሊሸር ኡስማኖቭንም ያጠቃልላል። የዩናይትድ ኪንግደም መንግስት በአብራሞቪች ወይም በኡስማኖቭ ላይ እስካሁን እገዳ አልጣለም። የሌበር ፓርቲ ተወካይ የሆኑት ክሪስ ብራያንት ማክሰኞ ዕለት ለህዝብ እንደራሴዎች አራርሞቪች "ማዕቀብ በጣም በመፍራቱ ቤቱን ነገ ሊሸጥ ነው። ሌላውም የመኖሪያ አፓርታማው ይቀጥላል" ብለዋል። ረቡዕ ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ጥያቄዎችን ባስተናገዱበት ወቅት የሌበር ፓርቲ መሪው ኬይር ስታርመር አብራሞቪች ለምን ማዕቀብ እንዳልተጣለባቸው ጠይቀው ነበር። "አሁን ባለው ደረጃ በማንኛውም ግለሰብ ጉዳዮች ላይ አስተያየት መስጠት ተገቢ አይደለም" ሲሉ ጆንሰን ምላሽ ሰጥተዋል። የሩሲያዊው ቃል አቀባይ ግን የሌበር ፓርቲ መሪውን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ አብራሞቪች ምንም ማእቀብ የሚያስጥል ነገር አላደረጉም ብለዋል። ዊስ አክለውም "አብራሞቪች በእንግሊዝ ያሏቸውን ቪላዎቻቸውን በሙሉ ለመሸጥ እየሞከሩ ነው። ቼልሲንም በፍጥነት መሸት ይፈልጋሉ" ብለዋል። "እኔ እና ሌሎች ሶስት ሰዎች ቼልሲን ከአብራሞቪች ለመግዛት ማክሰኞ ቀርቦልን ነበር።" የአብራሞቪች ቃል አቀባይ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም። | ሮማን አብራሞቪች ቼልሲን ለመሸጥ ወሰኑ የቼልሲው ባለቤት ሮማን አብራሞቪች ክለቡን ለመሸጥ ማቀዳቸውን ገለጹ። ባለሃብቱ አብራሞቪች በፕሪሚየር ሊጉ ክለብ ድረ-ገጽ ላይ ባወጡት መግለጫ "በጣም ከባዱን እና የሚያመውን ውሳኔ" መወሰናቸውን ተናግረዋል። ሩሲያዊው "ምንም ዓይነት ብድር እንዲመለስ" ያልጠየቁ ሲሆን የሽያጩ ገቢም ለጦርነት ተጎጂዎች ይውላል ብለዋል። ሩሲያ በዩክሬን ላይ ከፈጸመችው ወረራ በኋላ አብራሞቪች ቅዳሜ ዕለት እንዳስታወቁት የቼልሲን "ኃላፊነት እና ተጠሪነት" ለፋውንዴሽኑ እንደሚሰጡ ተናግረው ነበር። ይህም ክለቡን ከ 1.5 ቢሊየን ፓውንድ በላይ ብድር ውስጥ የዘፈቁት አብራሞቪች ቼልሲን ለሽያጭ ያቀርባሉ የሚል ግምት ፈጠረ። ይህንን ተከትሎም ቢሊየነሩ ሃንስ ጆርጅ ዊስ ክለቡን የመግዛት ዕድል እንደቀረበላቸው ረቡዕ ዕለት ለስዊዘርላንዱ ብሊክ ጋዜጣ ተናግረዋል። ዊስ እንዳስታወቁት አብራሞቪች በፓርላማው የማዕቀብ ስጋት "ቼልሲን በፍጥነት ለመሸጥ" እንደፈለጉ ተናግረዋል። የ55 ዓመቱ አብራሞቪች ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ጠንካራ ግንኙነት እንዳላቸው ቢነገርም እሳቸው ግን አስተባብለዋል። "ከሽያጩ የሚገኘው የተጣራ ገንዘብ በሙሉ ለዩክሬን ጦርነት ተገጎጂዎች" እንደሚሰጥ ተናግረዋል። ቼልሲን ለመግዛት ለአብራሞቪች ጥያቄ እንደቀረበላቸው ቢቢሲ ስፖርት የተረዳ ሲሆን ክለቡም እስከ ሦስት ቢሊዮን ፓውንድ ይገመታል። አብራሞቪች በመግለጫቸው "ሁሌም ውሳኔዎችን የምወስነው የክለቡን ፍላጎት ከግምት በማስገባት ነው" ብለዋል። "አሁን ባለው ሁኔታ ለክለቡ፣ ለደጋፊው፣ ለሠራተኞቹ እንዲሁም ለክለቡ ስፖንሰሮች እና አጋር አካላት ይጠቅማል ብዬ ስለማምን ክለቡን ለመሸጥ ወስኛለሁ።" በማለት ገልጸዋል። "የክለቡ ሽያጭ ፈጣን ሳይሆን ተገቢውን ሂደት የሚከተል ነው። ምንም ዓይነት ብድር እንዲከፈልም አልጠይቅም።" "ከሽያጩ የተገኘው ገንዘብ በሙሉ የሚለግስበት የበጎ አድራጎት ድርጅት እንዲያቋቁም ለቡድኔ መመሪያ ሰጥቻለሁ። ፋውንዴሽኑ በዩክሬን በጦርነት ተጎጂ ለሆኑ ጥቅም ላይ ይውላል።" ቢቢሲ ስፖርት እንደተረዳው ከሆነ የቼልሲ ፋውንዴሽን ክለቡን ለመቆጣጠር እስካሁን አልተስማማም። አብራሞቪች ቅዳሜ ዕለት ባወጡት መግለጫ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የፈፀመችውን ወረራ ባለመጥቀሳቸው ተወቅሰዋል። የቡድኑ ተጫዋቾች ዜናው ቀደም ብሎ እንዲደርሳቸው አልተደረገም ተብሏል። ተጫዋቾች ዜናውን የሰሙት ከሉተን ታውን ከሚያደርጉት የአምስተኛው ዙር የኤፍኤ ካፕ ጨዋታ ጥቂት ደቂቃዎች ቀደም ብሎ ነው። በጨዋታው ቡድኑ ከመመራት ተነስቶ 3 ለ 2 በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍጻሜው ተቀላቅሏል። አብራሞቪች ቼልሲን እአአ በ2003 በ140 ሚሊዮን ፓውንድ መግዛታቸው ይታወሳል። ባለሃብቱ በመግለጫቸው ግዢው "ለንግድም ሆነ ለገንዘብ ሲባል የተደረገ አልነበረም። ለስፖርቱ እና ለክለቡ ንጹህ ፍቅር ሲባል የተደረገ ነው" ብለዋል። አብራሞቪች በክለቡ ውጤታማ ነበሩ? ክለቡን ከገዙበት ጊዜ ጀምሮ ቼልሲ ከመለወጥ ባለፈ በፕሪሚየር ሊጉ በትልቅ ደረጃ ለመወዳደር ገንዘብ ምን ያህል እንደሚያስፈልግ ምሳሌ ሆኗል። አብራሞቪች ለክለቡ ከ 1.5 ቢሊዮን ፓውንድ በላይ ብድር የወሰዱ ሲሆን ይህም ትልቅ ስኬት አስመዝግቧል። በእርሳቸው የባለቤትነት ክለቡ የሚቻለውን ሁሉ ትልልቅ ዋንጫ ማንሳት ችሏል። የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግን ሁለት ጊዜ፣ ፕሪሚየር ሊግ እና ኤፍኤ ካፕ አምስት አምስት ጊዜ፣ ዩሮፓ ሊግ ሁለት ጊዜ እና የሊግ ዋንጫን ሦስት ጊዜ ማንሳት ችሏል። ባለፈው ነሐሴ የዩኤፋ ሱፐር ካፕን ያሸነፉ ሲሆን በየካቲት ደግሞ የመጀመሪያውን የዓለም የክለቦች ዋንጫን አንስተዋል። 13 የተለያዩ አሰልጣኞችን የሾመ ሲሆን ክለቡ በዝውውር ገበያው ሁለት ቢሊዮን ፓውንድ በላይ ወጪ አድርጓል። የቼልሲ ሴቶች ቡድንም በአብራሞቪች ስር ውጤማ መሆን ችሏል። የሴቶችን ሱፐር ሊግ አራት ጊዜ ሲያነሳ የሴቶችን ኤፍ ኤ ካፕ ሦስት ጊዜ ማሸነፍ ችሏል። ባለለፈው ዓመትም ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ ደርሷል። የክለቡ ስም በመግነኑ እንደ አውስትራሊያዊቷ ሳም ኬር እና ዴንማርካዊው አጥቂ ፔርኒል ሃርደር ያሉ የዓለም ኮከቦች ወደ ክለቡ ሊዘዋወሩ ችለዋል። አብራሞቪች ለምን መሸጥ መረጡ? ሌሎች የሩሲያ ቢሊየነሮች ንብረታቸው ከመታገድ ባለፈ የአውሮፓ ህብረት ማዕቀብ ዒላማ ሆነዋል። ይህ ደግሞ ከኤቨርተን ጋር ግንኙነት ያላቸውን ሩሲያዊው ቢሊየነር አሊሸር ኡስማኖቭንም ያጠቃልላል። የዩናይትድ ኪንግደም መንግስት በአብራሞቪች ወይም በኡስማኖቭ ላይ እስካሁን እገዳ አልጣለም። የሌበር ፓርቲ ተወካይ የሆኑት ክሪስ ብራያንት ማክሰኞ ዕለት ለህዝብ እንደራሴዎች አራርሞቪች "ማዕቀብ በጣም በመፍራቱ ቤቱን ነገ ሊሸጥ ነው። ሌላውም የመኖሪያ አፓርታማው ይቀጥላል" ብለዋል። ረቡዕ ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ጥያቄዎችን ባስተናገዱበት ወቅት የሌበር ፓርቲ መሪው ኬይር ስታርመር አብራሞቪች ለምን ማዕቀብ እንዳልተጣለባቸው ጠይቀው ነበር። "አሁን ባለው ደረጃ በማንኛውም ግለሰብ ጉዳዮች ላይ አስተያየት መስጠት ተገቢ አይደለም" ሲሉ ጆንሰን ምላሽ ሰጥተዋል። የሩሲያዊው ቃል አቀባይ ግን የሌበር ፓርቲ መሪውን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ አብራሞቪች ምንም ማእቀብ የሚያስጥል ነገር አላደረጉም ብለዋል። ዊስ አክለውም "አብራሞቪች በእንግሊዝ ያሏቸውን ቪላዎቻቸውን በሙሉ ለመሸጥ እየሞከሩ ነው። ቼልሲንም በፍጥነት መሸት ይፈልጋሉ" ብለዋል። "እኔ እና ሌሎች ሶስት ሰዎች ቼልሲን ከአብራሞቪች ለመግዛት ማክሰኞ ቀርቦልን ነበር።" የአብራሞቪች ቃል አቀባይ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም። | https://www.bbc.com/amharic/news-60596117 |
5sports
| እግር ኳስ፡ ህይወቱ በሱስ ምክንያት የተመሳቀለው የፕሪምየር ሊግ ቡድን አምበል | "በጣም ብዙ እርዳታ አስፈልጎኝ ነበር። ወደ ሌላ አይነት ሕይወት ለመሸጋገር ከብዶኝ ነበር፤ ምክንያቱም ህይወቴን በሙሉ እግር ኳስን ብቻ ነበር የማውቀው። ከእንደዚያ አይነት ቦታ መውደቅ ከባድ ነው።" ክላውስ ሉንደክቫም ቁርጭምጭሚቱ ላይ ባጋጠመው ተደጋጋሚ ጉዳት ምክንያት በአውሮፓውያኑ 2008 ከእግር ኳስ እራሱን እንዲያገል መገደዱን በተመለከተ የተናገረው ነው። ጫማውን ከሰቀለ በኋላ ደግሞ የአልኮልና የአደንዛኝ እጽ ሱሰኛ ሆነ። ክላውስ በወቅቱ የ35 ዓመት እግር ኳስ ተጫዋች የነበረ ሲሆን በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በሚጫወተው ሳውዝሃምፕተን ውስጥ እጅግ የላቀ ብቃት አላቸው ከሚባሉት ተጫዋቾች መካከል ነበር። ለቡድኑ ከ400 በላይ ጨዋታዎች ላይ የተሰለፈ ሲሆን በአውሮፓውያኑ 1996 ነበር ከኤስኬ በርገን ሳውዝህምፕተንን የተቀላቀለው። በሳውዝህምፕተን ደጋፊዎች ዘንድ ከፍተኛ ክብርና መወደድን ማግኘት ችሏል። ክልጅነቱ ጀምሮ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ መጫወት ህልሙ እንደነበር በተደጋጋሚ ይገልጻል። "የመጀመሪያም የመጨረሻም ፍላጎቴ በእንግሊዝ እግር ኳስ መጫወት ነበር" ይላል። "የልጅነት ህልሜ ነው እውን የሆነው። እውነቱን ለመናገር ያንን ያክል ጊዜ ተፎካካሪ ሆኜ እቆያለሁ ብዬ አላስብኩም ነበር" ይላል የኖርዌይ ዜግነት ያለው ክላውስ። ከኖርዌይ ብሔራዊ ቡድን ጋር በመሆንም 40 ጨዋታዎችን ማሸነፍ ችሏል። ''ለእኔ ከሌላ አገር መጥቶ ለሳውዝህምፕተን ለ12 ዓመታት መጫወትና የቡድኑ አምበል ለመሆን መቻል ልዩ እና ትልቅ ቦታ ያለው ነገር ነው" ይላል። በ2008 (እአአ) 18 ሺህ የሳውዝሀምፕተን ደጋፊዎች በተገኙበት ቡድኑ ሴልቲክን ገጥሞ ነበር። በወቅቱ ክላውስ ከነጉዳቱ ነበር ወደ ሜዳ ገባው። ነገር ግን የመጀመሪያዎቹን ጥቂት ደቂቃዎች ከተጫወተ በኋላ ተቀይሮ ሲወጣ በከፍተኛ ጭብጨባ ነበር የተሸኘው። ያቺ ዕለት ለክላውስ የእግር ኳስ ሕይወቱ ማብቂያ የመጀመሪያዋ ነበረች። ከመጨረሻው ጨዋታ አንድ ዓመት በኋላ ደግሞ ክላውስ ሉንደክቫም ሙሉ በሙሉ ሌላ ዓለም ውስጥ ገብቶ በሱስ የተጠመደ ሰው ሆኖ ነበር። የቀን ተቀን ሕይወቱን ይመራበት የነበረው የታቀደና በስልጠና የታገዘ የኑሮ ዘይቤው ሲቀየር እግር ኳስ ከህይወቱ ወጣ። ለበርካታ ዓመታት የሚያውቀው ስልጠና ማድረግ፣ ለጨዋታ መጓዝ፣ እግር ኳስ መጫወት፣ ከጉዳት ማገገም የሚባሉት ነገሮች ታሪክ ሆነው ቀሩ። ከእግር ኳስ በኋላ በሳውዝሃምፕተን የነበረው ቆይታ በተስፋ መቁረጥና በጭንቀት የተሞላ ነበር። ይህንን አስጨናቂ ጊዜ ለማለፍም ፊቱን ወደ አልኮልና ወደ አደንዛዥ እጽ አዞረ። "በሕይወቴ በርካታ ስህተቶችን ሰርቻለሁ። አሁን መለስ ብዬ ሳስበው በጣም ከባድ ጊዜ ነበር። በተለይ እግር ኳስ ተጫዋቾች ጠዋት ከእንቅልፋቸው ሲነሱ ተስፋና ትርጉም የሚሰጣቸው ነገር ሊኖር ይገባል። ከእግር ኳስ በኋላም ቢሆን የሚሰሩት ነገር መኖር አለበት።" ''እኔ በወቅቱ ሁሉም ነገር ነበረኝ። በጣም ብዙ ገንዘብ ነበረኝ፣ በጣም ምርጥ ቤተሰብ እና መኖሪያ ቤት ነበረኝ። ኖርዌይ ውስጥም የራሴ መኖሪያ ቤት ነበረኝ። ጀልባዎች፣ መኪናዎች፤ ሁሉም ነገር ነበረኝ። ነገር ግን በደግንገት ድብርት ውስጥ ገባሁና ብቸኝነት ተሰማኝ። የሚፈልገኝ ሰው እንደሌለ ተሰማኝ።" "የእግር ኳስ መልበሻ ክፍሉን ናፈቅኩት። በየሳምንቱ ከቡድን ጓደኞቼ ጋር መሰልጠንና መጫወት አማረኝ። ይሄ ሁሉ ነገር በድንገት ከህይወቴ ሲጠፋ በጣም ከባድ ጊዜን እንዳሳልፍ አደረገኝ።" በርካታ እግር ኳስ ተጫዋቾች ጫማቸውን ከሰቀሉ በኋላ በተመሳሳይ የህይወት መስመር ውስጥ ሲገቡ ይታያሉ። እጅግ በተራቀቀውና ትንሿ ስህተት እንኳን ትልቅ ዋጋ በምታስከፍልበት የእግር ኳስ ዘርፍ ውጤታማ ለመሆን በየቀኑ መጣርና መልፋት ግድ ይላል። ይሄ ሁሉ ልፋትና የዕለት ተዕለት ስልጠና በአንድ ጊዜ ሲቋረጥ ተጨዋቾች ከፍተኛ ድብርትና የህይወት መመሰቃቀልና ትርጉም ማጣት ውስጥ ይገባሉ። ምንም እንኳን ልክ እንደ ክላውስ አብዛኛዎቹ ተጫዋቾች የሚፈልጉት ነገር በሙሉ የተሟላላቸው ቢሆንም ከድብርት ግን ማምለጥ አይችሉም። "በየቀኑ ስኬታማ ለመሆን መጣር፣ የውስጥ አቅምን አሟጥጦ መጠቀም፣ በየቀኑ እና በየሳምንቱ ምርጥ ሆኖ ለመገኘትና በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎችን ለማስደስት የሚደረገው ትግል በጣም አስደሳችና ሰውነትን የሚያነቃቃ ነው" ይላል ክላውስ። ክላውስ ሉንደክቫም ከኖርዌዩ ኤስኬ ብራን ወደ ሳውዝሃምፕተን የተቀላቀለው በ350 ሺህ ፓውንድ ነበር። በነበረው የእግር ኳስ ህይወትም ሁሉም ተጫዋት ሊተማመንበት የሚችል አይነት ሰው ነበር። ምርጥና ቀጣይነት ያለው አቋም የሚያሳይ ተጫዋች ነበር። ነገር ግን ከእግር በኋላ የነበረው ማንነት ከመጀመሪያው በፍጹም የተለየ ነበር። በአንድ ወቅት እንደውም በፖሊስ ቁጥጥር ስር እስከመዋልና በሱሱ ምክንያት ሆስፒታል እስከመግባት ደርሶ ነበር። "እግር ኳስ ካቆምኩኝ በኋላ ምናልባት ለትንሽ ዓመታት ቀለል ያለ ሕይወት መኖር አለብኝ ብዬ ለእራሴ ነገርኩት። በወቅቱ በርካታ የበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ እሳተፍ ነበር። በሄድኩበት ቦታ ሁሉ መጠጥ ነበር። በዚያውም ለመዝናናት እየተባለ መጠጥ ቤት መሄድ ተጀመረ።" "ወዲያው እራሴን መቆጣጠር አቃተኝ። ከባድ ድብርት ውስጥም ገባሁ። ሳላስበው ከዚህ በፊት አይቼው በማላውቀው ሁኔታ እራሴን ተስፋ ቆርጬ አገኘሁት። ፊቴንም ወደ መጠጥና ኮኬይን አዞርኩኝ። ነገር ግን የአልኮልና የኮኬይን ጥገኛ ስሆን ነገሮች እንደውም እየከፉ መጡ።" "በየቀኑ መጠጣትና አደንዛዥ እጽ መጠቀም ጀመርኩ። ባለቤቴ እና ሁለት ሴት ልጆቼ ወደ ኖርዌይ ተመለሱ።" "ከአንዴም ሁለት ጊዜ እራሴን ለማጥፋት ሞክሬያለው። በጣም ከባድ ጭንቀት ውስጥ ገባሁና ሁሉም ነገር ትርጉም አጣብኝ። ድሮ የማውቀው ማንነቴ ጠፋብኝ። በወቅቱ የመረጥኩት ሁሉንም ለመርሳት አልኮል መጠጣት ነበር። ጥፋተኝነቴንና ሃፍረቴን ለመደበቅ ሁሌም መስከር ነበረብኝ።" ምንም እንኳን ክላውስ ሉንደክቫም በጣም አስቸጋሪ የህይወት ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ለመረዳት ብዙ ጊዜ ቢፈጅበትም እርዳታ ለመጠየቅ ግን አልቦዘነም ነበር። የቀድሞው የአርሰናል እግር ኳስ ክለብ ተጫዋች ፒተር ኬይ ወዳቋቋመው የስፖርተኞች ክሊኒክ ገባ። "የቀድሞው ሳውዝሀምፕተን አምበል እና በርካቶች እንደ ጀግናቸው የሚቆጥሩት የነበረው ሰው እንደዚህ ተሰብሮ ማየት ከባድ ነው። በወቅቱ በጣም ከባድ ቢሆንም አብረውኝ ለነበሩ ሰዎች ስሜንና ያለብኝን ችግር ስናገር ብዙዎቹ ይደነግጡ ነበር።" ረጅም ጊዜ የፈጀው የማገገም ሂደት ቀላል አልነበረም። ተመልሶ አልኮል መጠጣትና ኮኬይን መጠቀምን ጨምሮ ሌሎች አስቸጋሪ ፈተናዎች ነበሩ በመሀል ላይ። ነገር ግን ቆራጥ መሆንና ሕይወትን ለመቀየር እራስን ማሳመን ወሳኝ መሆኑን ክላውስ ይናራል። "በጣም ብዙ ውጣ ውረዶች ነበሩ። ሁለት ጊዜ ወደ ሱሴ ተመልሼ ነበር። አሁን ጥቂት ዓመታት አልፎታል ግን ሱሰኛ መሆኔን አምኜ ለመቀበል ትንሽ ጊዜ ፈጅቶብኝ ነበር።" "በነበረኛ ቆይታ ያለ አልኮልና አደንዛኝ እጽ ጥሩ ሕይወት መኖር እንደሚቻል እየገባኝ መጣ። በጣም ደስተኛ ሆንኩኝ፤ በእራሴም ኮራሁ። ምንም እንኳን ያሳለፍኩት ጊዜ ቀላል ባይሆንም አሁን ካለሁበት ሁኔታ ላይ በመገኘቴ በጣም እድለኛ ነኝ።" ምንም እንኳን ክላውስ ሉንደክቫም እና ባለቤቱ በአውሮፓውያኑ 2014 ላይ ትዳራቸውን አፍርሰው ፍቺ ቢፈጽሙም አሁን ጥሩ የሚባል ግንኙነት ያላቸው። ከሁለቱ ሴት ልጆቹ ጋር ያለውም ግንኙነት ከምን ጊዜውም በበለጠ ጥሩ የሚባል ነው። ክላውስ ለሳውዝሀምፕተን በሚጫወትበት ወቅት ስለ አእምሮ ጤና እና ጭንቀት ማውራት ብዙም የተለመደ ነገር አልነበረም። ነገር ግን አሁን ነገሮች በፍጥነት እየተቀየሩ ይመስላል። ሰዎች በህይወታቸው የሚገጥማቸውን ጭንቀትና አስቸጋሪ ነገር ማጋራት ጀምረዋል። ክላውስ በአሁኑ ጊዜ አደንዛዥ እጽ የሚጠቀሙና ሱሰኛ የሆኑ ሰዎችን በመርዳት ላይ ተሰማርቶ ይገኛል። ከቀድሞ ክለቡ ሳውዝሀምፕተን ጋር በተመሳሳይ ጉዳዮች ዙሪያ ለመስራትም ፍላጎት አለው። ከቀድሞ ቡድኑም ጋር ግንኙነት የፈጠረ ሲሆን በቡድኑ ታሪክ ስማቸው ከሚጠቀስ ተጫዋቾች መካከል አንዱ እንደመሆኑ፤ ተጫዋቾች ሊያጋጥሟችው ስለሚችሉ ፈተናዎች ግንዛቤ ማስጨጥ ደግሞ ህልሙ ነው። | እግር ኳስ፡ ህይወቱ በሱስ ምክንያት የተመሳቀለው የፕሪምየር ሊግ ቡድን አምበል "በጣም ብዙ እርዳታ አስፈልጎኝ ነበር። ወደ ሌላ አይነት ሕይወት ለመሸጋገር ከብዶኝ ነበር፤ ምክንያቱም ህይወቴን በሙሉ እግር ኳስን ብቻ ነበር የማውቀው። ከእንደዚያ አይነት ቦታ መውደቅ ከባድ ነው።" ክላውስ ሉንደክቫም ቁርጭምጭሚቱ ላይ ባጋጠመው ተደጋጋሚ ጉዳት ምክንያት በአውሮፓውያኑ 2008 ከእግር ኳስ እራሱን እንዲያገል መገደዱን በተመለከተ የተናገረው ነው። ጫማውን ከሰቀለ በኋላ ደግሞ የአልኮልና የአደንዛኝ እጽ ሱሰኛ ሆነ። ክላውስ በወቅቱ የ35 ዓመት እግር ኳስ ተጫዋች የነበረ ሲሆን በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በሚጫወተው ሳውዝሃምፕተን ውስጥ እጅግ የላቀ ብቃት አላቸው ከሚባሉት ተጫዋቾች መካከል ነበር። ለቡድኑ ከ400 በላይ ጨዋታዎች ላይ የተሰለፈ ሲሆን በአውሮፓውያኑ 1996 ነበር ከኤስኬ በርገን ሳውዝህምፕተንን የተቀላቀለው። በሳውዝህምፕተን ደጋፊዎች ዘንድ ከፍተኛ ክብርና መወደድን ማግኘት ችሏል። ክልጅነቱ ጀምሮ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ መጫወት ህልሙ እንደነበር በተደጋጋሚ ይገልጻል። "የመጀመሪያም የመጨረሻም ፍላጎቴ በእንግሊዝ እግር ኳስ መጫወት ነበር" ይላል። "የልጅነት ህልሜ ነው እውን የሆነው። እውነቱን ለመናገር ያንን ያክል ጊዜ ተፎካካሪ ሆኜ እቆያለሁ ብዬ አላስብኩም ነበር" ይላል የኖርዌይ ዜግነት ያለው ክላውስ። ከኖርዌይ ብሔራዊ ቡድን ጋር በመሆንም 40 ጨዋታዎችን ማሸነፍ ችሏል። ''ለእኔ ከሌላ አገር መጥቶ ለሳውዝህምፕተን ለ12 ዓመታት መጫወትና የቡድኑ አምበል ለመሆን መቻል ልዩ እና ትልቅ ቦታ ያለው ነገር ነው" ይላል። በ2008 (እአአ) 18 ሺህ የሳውዝሀምፕተን ደጋፊዎች በተገኙበት ቡድኑ ሴልቲክን ገጥሞ ነበር። በወቅቱ ክላውስ ከነጉዳቱ ነበር ወደ ሜዳ ገባው። ነገር ግን የመጀመሪያዎቹን ጥቂት ደቂቃዎች ከተጫወተ በኋላ ተቀይሮ ሲወጣ በከፍተኛ ጭብጨባ ነበር የተሸኘው። ያቺ ዕለት ለክላውስ የእግር ኳስ ሕይወቱ ማብቂያ የመጀመሪያዋ ነበረች። ከመጨረሻው ጨዋታ አንድ ዓመት በኋላ ደግሞ ክላውስ ሉንደክቫም ሙሉ በሙሉ ሌላ ዓለም ውስጥ ገብቶ በሱስ የተጠመደ ሰው ሆኖ ነበር። የቀን ተቀን ሕይወቱን ይመራበት የነበረው የታቀደና በስልጠና የታገዘ የኑሮ ዘይቤው ሲቀየር እግር ኳስ ከህይወቱ ወጣ። ለበርካታ ዓመታት የሚያውቀው ስልጠና ማድረግ፣ ለጨዋታ መጓዝ፣ እግር ኳስ መጫወት፣ ከጉዳት ማገገም የሚባሉት ነገሮች ታሪክ ሆነው ቀሩ። ከእግር ኳስ በኋላ በሳውዝሃምፕተን የነበረው ቆይታ በተስፋ መቁረጥና በጭንቀት የተሞላ ነበር። ይህንን አስጨናቂ ጊዜ ለማለፍም ፊቱን ወደ አልኮልና ወደ አደንዛዥ እጽ አዞረ። "በሕይወቴ በርካታ ስህተቶችን ሰርቻለሁ። አሁን መለስ ብዬ ሳስበው በጣም ከባድ ጊዜ ነበር። በተለይ እግር ኳስ ተጫዋቾች ጠዋት ከእንቅልፋቸው ሲነሱ ተስፋና ትርጉም የሚሰጣቸው ነገር ሊኖር ይገባል። ከእግር ኳስ በኋላም ቢሆን የሚሰሩት ነገር መኖር አለበት።" ''እኔ በወቅቱ ሁሉም ነገር ነበረኝ። በጣም ብዙ ገንዘብ ነበረኝ፣ በጣም ምርጥ ቤተሰብ እና መኖሪያ ቤት ነበረኝ። ኖርዌይ ውስጥም የራሴ መኖሪያ ቤት ነበረኝ። ጀልባዎች፣ መኪናዎች፤ ሁሉም ነገር ነበረኝ። ነገር ግን በደግንገት ድብርት ውስጥ ገባሁና ብቸኝነት ተሰማኝ። የሚፈልገኝ ሰው እንደሌለ ተሰማኝ።" "የእግር ኳስ መልበሻ ክፍሉን ናፈቅኩት። በየሳምንቱ ከቡድን ጓደኞቼ ጋር መሰልጠንና መጫወት አማረኝ። ይሄ ሁሉ ነገር በድንገት ከህይወቴ ሲጠፋ በጣም ከባድ ጊዜን እንዳሳልፍ አደረገኝ።" በርካታ እግር ኳስ ተጫዋቾች ጫማቸውን ከሰቀሉ በኋላ በተመሳሳይ የህይወት መስመር ውስጥ ሲገቡ ይታያሉ። እጅግ በተራቀቀውና ትንሿ ስህተት እንኳን ትልቅ ዋጋ በምታስከፍልበት የእግር ኳስ ዘርፍ ውጤታማ ለመሆን በየቀኑ መጣርና መልፋት ግድ ይላል። ይሄ ሁሉ ልፋትና የዕለት ተዕለት ስልጠና በአንድ ጊዜ ሲቋረጥ ተጨዋቾች ከፍተኛ ድብርትና የህይወት መመሰቃቀልና ትርጉም ማጣት ውስጥ ይገባሉ። ምንም እንኳን ልክ እንደ ክላውስ አብዛኛዎቹ ተጫዋቾች የሚፈልጉት ነገር በሙሉ የተሟላላቸው ቢሆንም ከድብርት ግን ማምለጥ አይችሉም። "በየቀኑ ስኬታማ ለመሆን መጣር፣ የውስጥ አቅምን አሟጥጦ መጠቀም፣ በየቀኑ እና በየሳምንቱ ምርጥ ሆኖ ለመገኘትና በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎችን ለማስደስት የሚደረገው ትግል በጣም አስደሳችና ሰውነትን የሚያነቃቃ ነው" ይላል ክላውስ። ክላውስ ሉንደክቫም ከኖርዌዩ ኤስኬ ብራን ወደ ሳውዝሃምፕተን የተቀላቀለው በ350 ሺህ ፓውንድ ነበር። በነበረው የእግር ኳስ ህይወትም ሁሉም ተጫዋት ሊተማመንበት የሚችል አይነት ሰው ነበር። ምርጥና ቀጣይነት ያለው አቋም የሚያሳይ ተጫዋች ነበር። ነገር ግን ከእግር በኋላ የነበረው ማንነት ከመጀመሪያው በፍጹም የተለየ ነበር። በአንድ ወቅት እንደውም በፖሊስ ቁጥጥር ስር እስከመዋልና በሱሱ ምክንያት ሆስፒታል እስከመግባት ደርሶ ነበር። "እግር ኳስ ካቆምኩኝ በኋላ ምናልባት ለትንሽ ዓመታት ቀለል ያለ ሕይወት መኖር አለብኝ ብዬ ለእራሴ ነገርኩት። በወቅቱ በርካታ የበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ እሳተፍ ነበር። በሄድኩበት ቦታ ሁሉ መጠጥ ነበር። በዚያውም ለመዝናናት እየተባለ መጠጥ ቤት መሄድ ተጀመረ።" "ወዲያው እራሴን መቆጣጠር አቃተኝ። ከባድ ድብርት ውስጥም ገባሁ። ሳላስበው ከዚህ በፊት አይቼው በማላውቀው ሁኔታ እራሴን ተስፋ ቆርጬ አገኘሁት። ፊቴንም ወደ መጠጥና ኮኬይን አዞርኩኝ። ነገር ግን የአልኮልና የኮኬይን ጥገኛ ስሆን ነገሮች እንደውም እየከፉ መጡ።" "በየቀኑ መጠጣትና አደንዛዥ እጽ መጠቀም ጀመርኩ። ባለቤቴ እና ሁለት ሴት ልጆቼ ወደ ኖርዌይ ተመለሱ።" "ከአንዴም ሁለት ጊዜ እራሴን ለማጥፋት ሞክሬያለው። በጣም ከባድ ጭንቀት ውስጥ ገባሁና ሁሉም ነገር ትርጉም አጣብኝ። ድሮ የማውቀው ማንነቴ ጠፋብኝ። በወቅቱ የመረጥኩት ሁሉንም ለመርሳት አልኮል መጠጣት ነበር። ጥፋተኝነቴንና ሃፍረቴን ለመደበቅ ሁሌም መስከር ነበረብኝ።" ምንም እንኳን ክላውስ ሉንደክቫም በጣም አስቸጋሪ የህይወት ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ለመረዳት ብዙ ጊዜ ቢፈጅበትም እርዳታ ለመጠየቅ ግን አልቦዘነም ነበር። የቀድሞው የአርሰናል እግር ኳስ ክለብ ተጫዋች ፒተር ኬይ ወዳቋቋመው የስፖርተኞች ክሊኒክ ገባ። "የቀድሞው ሳውዝሀምፕተን አምበል እና በርካቶች እንደ ጀግናቸው የሚቆጥሩት የነበረው ሰው እንደዚህ ተሰብሮ ማየት ከባድ ነው። በወቅቱ በጣም ከባድ ቢሆንም አብረውኝ ለነበሩ ሰዎች ስሜንና ያለብኝን ችግር ስናገር ብዙዎቹ ይደነግጡ ነበር።" ረጅም ጊዜ የፈጀው የማገገም ሂደት ቀላል አልነበረም። ተመልሶ አልኮል መጠጣትና ኮኬይን መጠቀምን ጨምሮ ሌሎች አስቸጋሪ ፈተናዎች ነበሩ በመሀል ላይ። ነገር ግን ቆራጥ መሆንና ሕይወትን ለመቀየር እራስን ማሳመን ወሳኝ መሆኑን ክላውስ ይናራል። "በጣም ብዙ ውጣ ውረዶች ነበሩ። ሁለት ጊዜ ወደ ሱሴ ተመልሼ ነበር። አሁን ጥቂት ዓመታት አልፎታል ግን ሱሰኛ መሆኔን አምኜ ለመቀበል ትንሽ ጊዜ ፈጅቶብኝ ነበር።" "በነበረኛ ቆይታ ያለ አልኮልና አደንዛኝ እጽ ጥሩ ሕይወት መኖር እንደሚቻል እየገባኝ መጣ። በጣም ደስተኛ ሆንኩኝ፤ በእራሴም ኮራሁ። ምንም እንኳን ያሳለፍኩት ጊዜ ቀላል ባይሆንም አሁን ካለሁበት ሁኔታ ላይ በመገኘቴ በጣም እድለኛ ነኝ።" ምንም እንኳን ክላውስ ሉንደክቫም እና ባለቤቱ በአውሮፓውያኑ 2014 ላይ ትዳራቸውን አፍርሰው ፍቺ ቢፈጽሙም አሁን ጥሩ የሚባል ግንኙነት ያላቸው። ከሁለቱ ሴት ልጆቹ ጋር ያለውም ግንኙነት ከምን ጊዜውም በበለጠ ጥሩ የሚባል ነው። ክላውስ ለሳውዝሀምፕተን በሚጫወትበት ወቅት ስለ አእምሮ ጤና እና ጭንቀት ማውራት ብዙም የተለመደ ነገር አልነበረም። ነገር ግን አሁን ነገሮች በፍጥነት እየተቀየሩ ይመስላል። ሰዎች በህይወታቸው የሚገጥማቸውን ጭንቀትና አስቸጋሪ ነገር ማጋራት ጀምረዋል። ክላውስ በአሁኑ ጊዜ አደንዛዥ እጽ የሚጠቀሙና ሱሰኛ የሆኑ ሰዎችን በመርዳት ላይ ተሰማርቶ ይገኛል። ከቀድሞ ክለቡ ሳውዝሀምፕተን ጋር በተመሳሳይ ጉዳዮች ዙሪያ ለመስራትም ፍላጎት አለው። ከቀድሞ ቡድኑም ጋር ግንኙነት የፈጠረ ሲሆን በቡድኑ ታሪክ ስማቸው ከሚጠቀስ ተጫዋቾች መካከል አንዱ እንደመሆኑ፤ ተጫዋቾች ሊያጋጥሟችው ስለሚችሉ ፈተናዎች ግንዛቤ ማስጨጥ ደግሞ ህልሙ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/news-55287481 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ በኖርዌይ የአንዲት መርከብ ተሳፋሪዎችና ሠራተኞች በቫይረሱ ተያዙ | በኖርዌይ የመዝናኛ መርከብ ላይ ተሳፍረው የነበሩ ቢያንስ 40 መንገደኞችና ሠራተኞች በኮቪድ-19 መያዛቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ። ኤምኤስ ሮልስ አሙንድሰን በተባለችው መርከብ ላይ ተሳፍረው የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሌሎች መንገደኞች ደግሞ ለይቶ ማቆያ ገብተው የምርመራ ውጤታቸውን እየተጠባበቁ እንደሆነ የመርከቧ ባለንብረት ተናግረዋል። ሁርቲግሩትን የተባለ የኖርዌይ ድርጅት ንብረት የሆነችው መርከብ በትሮምሶ ወደብ ያረፈችው ባሳለፍነው አርብ ነበር። በዚህም ሳቢያ ድርጅቱ ሁሉንም የመዝናኛ መርከቦቹን እንዳይንቀሳቀሱ አግዷል። የድርጅቱ ኃላፊ ዳንኤል ስካይልዳም "አሁን ትኩረት ያደረግነው ባልደረቦቻችንና እንግዶቻችንን ለመንከባከብ የምንችለውን ሁሉ በማድረግ ላይ ነው" ሲሉ በመግለጫቸው ተናግረዋል። አራት የመርከቡ ሠራተኞች የኮሮናቫይረስ ምልክት ታይቶባቸው አርብ ዕለት መርከቧ ወደብ ላይ ካረፈች በኋላ ሆስፒታል የገቡ ሲሆን በኋላ ላይ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ከ158 ሠራተኞች መካከልም ሌሎች 32ቱ በቫይረሱ መያዛቸው የምርመራ ውጤታቸው አመላክቷል። ይሁን እንጂ 180 የሚሆኑ መንገደኞች ከመርከቧ እንዲወጡ የተፈቀደላቸው ሲሆን በባለሥልጣናት ቁጥጥር እንዲመረመሩ ተደርጓል። ሁሉም መንገደኞች ራሳቸውን እንዲለዩ መደረጉንም የጤና ባለሥልጣናት ተናግረዋል። ከሐምሌ አጋማሽ ጀምሮ በመርከቧ ጉዞ ላይ ከነበሩ 387 ተሳፋሪዎች መካካልም እስካሁን በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠው አምስት እንደሆኑ ተገልጿል። የጤና ባለሥልጣን የሆኑት ሊን ቮልድ ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንደተናገሩት አሁን ከተከሰተው የቫይረስ ሥርጭት ጋር ተያይዞ በርካታ ሰዎች ቫይረሱ ሊገኝባቸው እንደሚችል ገልፀዋል። መርከቧ በአርክቲክ በሚገኘው ስቫልባርድ ለአንድ ሳምንት የቆየች ሲሆን በኢንግላንድና ስኮትላንድ የሚገኙ ወደቦችን ደግሞ መስከረም ላይ ለመጎብኘት እቅድ ይዛ ነበር ተብሏል። ይሁን እንጂ ኢንዱስትሪው በወረርሽኙ በመመታቱ ሁሉም የወደፊት ጉዞዎች ስለመኖራቸው የታወቀ ነገር እንደሌለ ተገልጿል። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ወረርሽኙ በመርከቦች ላይ በመዛመቱ በሺህዎች የሚቆጠሩ መንገደኞች በባሕር ላይ እንቅስቃሴያቸው ተገድቦ መቆየታቸው ይታወሳል። | ኮሮናቫይረስ፡ በኖርዌይ የአንዲት መርከብ ተሳፋሪዎችና ሠራተኞች በቫይረሱ ተያዙ በኖርዌይ የመዝናኛ መርከብ ላይ ተሳፍረው የነበሩ ቢያንስ 40 መንገደኞችና ሠራተኞች በኮቪድ-19 መያዛቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ። ኤምኤስ ሮልስ አሙንድሰን በተባለችው መርከብ ላይ ተሳፍረው የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሌሎች መንገደኞች ደግሞ ለይቶ ማቆያ ገብተው የምርመራ ውጤታቸውን እየተጠባበቁ እንደሆነ የመርከቧ ባለንብረት ተናግረዋል። ሁርቲግሩትን የተባለ የኖርዌይ ድርጅት ንብረት የሆነችው መርከብ በትሮምሶ ወደብ ያረፈችው ባሳለፍነው አርብ ነበር። በዚህም ሳቢያ ድርጅቱ ሁሉንም የመዝናኛ መርከቦቹን እንዳይንቀሳቀሱ አግዷል። የድርጅቱ ኃላፊ ዳንኤል ስካይልዳም "አሁን ትኩረት ያደረግነው ባልደረቦቻችንና እንግዶቻችንን ለመንከባከብ የምንችለውን ሁሉ በማድረግ ላይ ነው" ሲሉ በመግለጫቸው ተናግረዋል። አራት የመርከቡ ሠራተኞች የኮሮናቫይረስ ምልክት ታይቶባቸው አርብ ዕለት መርከቧ ወደብ ላይ ካረፈች በኋላ ሆስፒታል የገቡ ሲሆን በኋላ ላይ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ከ158 ሠራተኞች መካከልም ሌሎች 32ቱ በቫይረሱ መያዛቸው የምርመራ ውጤታቸው አመላክቷል። ይሁን እንጂ 180 የሚሆኑ መንገደኞች ከመርከቧ እንዲወጡ የተፈቀደላቸው ሲሆን በባለሥልጣናት ቁጥጥር እንዲመረመሩ ተደርጓል። ሁሉም መንገደኞች ራሳቸውን እንዲለዩ መደረጉንም የጤና ባለሥልጣናት ተናግረዋል። ከሐምሌ አጋማሽ ጀምሮ በመርከቧ ጉዞ ላይ ከነበሩ 387 ተሳፋሪዎች መካካልም እስካሁን በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠው አምስት እንደሆኑ ተገልጿል። የጤና ባለሥልጣን የሆኑት ሊን ቮልድ ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንደተናገሩት አሁን ከተከሰተው የቫይረስ ሥርጭት ጋር ተያይዞ በርካታ ሰዎች ቫይረሱ ሊገኝባቸው እንደሚችል ገልፀዋል። መርከቧ በአርክቲክ በሚገኘው ስቫልባርድ ለአንድ ሳምንት የቆየች ሲሆን በኢንግላንድና ስኮትላንድ የሚገኙ ወደቦችን ደግሞ መስከረም ላይ ለመጎብኘት እቅድ ይዛ ነበር ተብሏል። ይሁን እንጂ ኢንዱስትሪው በወረርሽኙ በመመታቱ ሁሉም የወደፊት ጉዞዎች ስለመኖራቸው የታወቀ ነገር እንደሌለ ተገልጿል። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ወረርሽኙ በመርከቦች ላይ በመዛመቱ በሺህዎች የሚቆጠሩ መንገደኞች በባሕር ላይ እንቅስቃሴያቸው ተገድቦ መቆየታቸው ይታወሳል። | https://www.bbc.com/amharic/53640749 |
5sports
| በካሜሮን ዕድሜያቸውን ያጭበረበሩ እግር ኳስ ተጫዋቾች ሊቀጡ ነው | በካሜሮን ዕድሜያቸውን አጭበርብረዋል ተብለው የተጠረጠሩ አርባ አራት የእግር ኳስ ተጫዋቾች ምርመራ ተከፍቶባቸዋል። ተጫዋቾቹ ከዕድሜያቸው በተጨማሪ ማንነታቸውንም አጭበርብረዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል። አብዛኛዎቹ ተጫዋቾች ከአማተር ክለቦች የተውጣጡ ሲሆን ጥቂቶቹ ደግሞ የብሄራዊ ሊጎች ተጫዋቾች መሆናቸውን የካሜሮን እግር ኳስ አስተዳዳሪ ፌካፉት አስታውቋል። ተጫዋቾቹ በማጭበርበር ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ ለስድስት ወር ያህል ከየትኛውም ጨዋታ የመታገድ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው የፌካፉት ባለስልጣን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ተጫዋቾቹ እድሜያቸውንና ማንነታቸውን ሲያጭበረብሩ ተባባሪ ናቸው ተብለው የተከሰሱ በርካታ የክለብ ፕሬዚዳንቶች ፌካፉት በሚያደርገው ማጣራት እንዲገኙ ተጠርተዋል። ፌዴሬሽኑ ምርምሩንና መረጃዎችን የሚሰማው በዝግ ነው ተብሏል። በካሜሮን የዕድሜ ማጭበርበር ክስ የተለመደ ነው። በአውሮፓውያኑ 2016፣ 14 የካሜሮን ተጫዋቾች በአመት ሁለት ጊዜ በሚደረገው የዩ 17 የአፍሪካ ዋንጫ ከመካሄዱ ጥቂት ቀናት በፊት ታግደዋል። | በካሜሮን ዕድሜያቸውን ያጭበረበሩ እግር ኳስ ተጫዋቾች ሊቀጡ ነው በካሜሮን ዕድሜያቸውን አጭበርብረዋል ተብለው የተጠረጠሩ አርባ አራት የእግር ኳስ ተጫዋቾች ምርመራ ተከፍቶባቸዋል። ተጫዋቾቹ ከዕድሜያቸው በተጨማሪ ማንነታቸውንም አጭበርብረዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል። አብዛኛዎቹ ተጫዋቾች ከአማተር ክለቦች የተውጣጡ ሲሆን ጥቂቶቹ ደግሞ የብሄራዊ ሊጎች ተጫዋቾች መሆናቸውን የካሜሮን እግር ኳስ አስተዳዳሪ ፌካፉት አስታውቋል። ተጫዋቾቹ በማጭበርበር ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ ለስድስት ወር ያህል ከየትኛውም ጨዋታ የመታገድ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው የፌካፉት ባለስልጣን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ተጫዋቾቹ እድሜያቸውንና ማንነታቸውን ሲያጭበረብሩ ተባባሪ ናቸው ተብለው የተከሰሱ በርካታ የክለብ ፕሬዚዳንቶች ፌካፉት በሚያደርገው ማጣራት እንዲገኙ ተጠርተዋል። ፌዴሬሽኑ ምርምሩንና መረጃዎችን የሚሰማው በዝግ ነው ተብሏል። በካሜሮን የዕድሜ ማጭበርበር ክስ የተለመደ ነው። በአውሮፓውያኑ 2016፣ 14 የካሜሮን ተጫዋቾች በአመት ሁለት ጊዜ በሚደረገው የዩ 17 የአፍሪካ ዋንጫ ከመካሄዱ ጥቂት ቀናት በፊት ታግደዋል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cl7gxeyvdggo |
2health
| አስትራዜኒካ የደም መርጋት ያስከትላል? የዓለም ጤና ድርጅት ክትባቱን ሊገመግም ነው | የዓለም ጤና ድርጅት ብዙ እየተወራበት ያለውን የኦክስፎርድ አስትራዜኒካን ውጤታማነትን በተለይም ከደም መርጋት ጋር ያለውን ተያያዥነት በክትባት ሊቃውንት ሊያስገመግም ነው፡፡ ክትባቱ ውጤታማ ነው ከተባለ በኋላ ብዙ አገራት ለሕዝባቸው ማደል ጀምረው ነበር፡፡ ሆኖም ደም እንዲረጋ ያደርጋል የሚል መረጃ መውጣቱን ተከትሎ ብዙ የአውሮፓ አገራት ለጊዜው የክትባት እደላው እንዲቆም ወስነዋል፡፡ አንዳንድ ክትባቱን የወሰዱ ሰዎች ደማቸው የመርጋት ምልክት በማሳየቱ ነው ስጋት የተፈጠረው፡፡ እነዚህ የክትባት ሊቃውንት ለግምገማ የሚቀመጡት ዛሬ ማክሰኞ ነው፡፡ በተመሳሳይ የአውሮጳ መድኃኒት ኤጀንሲ ኃላፊዎችም ዛሬ በጉዳዩ ላይ ለመምከር ይሰበሰባሉ ተብሏል፡፡ የክትባት ሊቃውንት ቡድን ሁኔታዎችን ከገመገመ በኋላ ኦክስፎርድ አስትራዜኒካ ክትባት ለሰዎች ቢሰጥ የከፋ ጉዳት እንደሌለው የሚያትት መግለጫ ሐሙስ ያወጣል ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡ በአውሮፓ ኅብረትና በታላቋ ብሪታኒያ በድምሩ 17 ሚሊዮን ዜጎች አስትራዜኒካ ክትባትን የወሰዱ ሲሆን ከዚህ ሁሉ ተከታቢ መሀል የደም መርጋት አጋጠማቸው የተባሉትን ሰዎች ቁጥር ከ40 አይበልጥም፡፡ አሁን ይህ ክትባት በእርግጥ የደም መርጋትን ያመጣል ወይ የሚለው በተጨባጭ የታወቀ ባይሆንም ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያን እና ስፔንን ጨምሮ በርካታ አገራት ክትባቱን ለጊዜው ይቆየን ብለዋል፡፡ ቤልጂየም፣ ፖላንድ፣ ቼክ ሪፐብሊክና ዩክሬን ግን ክትባቱን ለሕዝባቸው ማደላቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት በበኩሉ ክትባቱ በእርግጥ የደም መርጋት ያስከትላል በሚለው ላይ አዲስ ምርመራ መጀመሩን ይፋ አድርጓል፡፡ ባለፈው ማክሰኞ የዓለም ጤና ድርጅት ቃል አቀባይ ክትባቱ ደም እንደሚያረጋ የተገኘ አንዳችም ተጨባጭ መረጃ የለም ብለው ነበር፡፡ በርከት ያሉ የጤና ባለሙያዎች እንደሚሉት ክትባቱን መውሰድ የጎንዮሽ ጉዳቱን በመፍራት ካለመውሰድ የተሻለ ነው፡፡ ክትባቱ ደም እንዲረጋ ያደርጋል የሚሉት አጋጣሚዎችም ከጠቅላላው ተከታቢ ቁጥር ጋር ሲነጻጸር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም ይላሉ፡፡ | አስትራዜኒካ የደም መርጋት ያስከትላል? የዓለም ጤና ድርጅት ክትባቱን ሊገመግም ነው የዓለም ጤና ድርጅት ብዙ እየተወራበት ያለውን የኦክስፎርድ አስትራዜኒካን ውጤታማነትን በተለይም ከደም መርጋት ጋር ያለውን ተያያዥነት በክትባት ሊቃውንት ሊያስገመግም ነው፡፡ ክትባቱ ውጤታማ ነው ከተባለ በኋላ ብዙ አገራት ለሕዝባቸው ማደል ጀምረው ነበር፡፡ ሆኖም ደም እንዲረጋ ያደርጋል የሚል መረጃ መውጣቱን ተከትሎ ብዙ የአውሮፓ አገራት ለጊዜው የክትባት እደላው እንዲቆም ወስነዋል፡፡ አንዳንድ ክትባቱን የወሰዱ ሰዎች ደማቸው የመርጋት ምልክት በማሳየቱ ነው ስጋት የተፈጠረው፡፡ እነዚህ የክትባት ሊቃውንት ለግምገማ የሚቀመጡት ዛሬ ማክሰኞ ነው፡፡ በተመሳሳይ የአውሮጳ መድኃኒት ኤጀንሲ ኃላፊዎችም ዛሬ በጉዳዩ ላይ ለመምከር ይሰበሰባሉ ተብሏል፡፡ የክትባት ሊቃውንት ቡድን ሁኔታዎችን ከገመገመ በኋላ ኦክስፎርድ አስትራዜኒካ ክትባት ለሰዎች ቢሰጥ የከፋ ጉዳት እንደሌለው የሚያትት መግለጫ ሐሙስ ያወጣል ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡ በአውሮፓ ኅብረትና በታላቋ ብሪታኒያ በድምሩ 17 ሚሊዮን ዜጎች አስትራዜኒካ ክትባትን የወሰዱ ሲሆን ከዚህ ሁሉ ተከታቢ መሀል የደም መርጋት አጋጠማቸው የተባሉትን ሰዎች ቁጥር ከ40 አይበልጥም፡፡ አሁን ይህ ክትባት በእርግጥ የደም መርጋትን ያመጣል ወይ የሚለው በተጨባጭ የታወቀ ባይሆንም ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያን እና ስፔንን ጨምሮ በርካታ አገራት ክትባቱን ለጊዜው ይቆየን ብለዋል፡፡ ቤልጂየም፣ ፖላንድ፣ ቼክ ሪፐብሊክና ዩክሬን ግን ክትባቱን ለሕዝባቸው ማደላቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት በበኩሉ ክትባቱ በእርግጥ የደም መርጋት ያስከትላል በሚለው ላይ አዲስ ምርመራ መጀመሩን ይፋ አድርጓል፡፡ ባለፈው ማክሰኞ የዓለም ጤና ድርጅት ቃል አቀባይ ክትባቱ ደም እንደሚያረጋ የተገኘ አንዳችም ተጨባጭ መረጃ የለም ብለው ነበር፡፡ በርከት ያሉ የጤና ባለሙያዎች እንደሚሉት ክትባቱን መውሰድ የጎንዮሽ ጉዳቱን በመፍራት ካለመውሰድ የተሻለ ነው፡፡ ክትባቱ ደም እንዲረጋ ያደርጋል የሚሉት አጋጣሚዎችም ከጠቅላላው ተከታቢ ቁጥር ጋር ሲነጻጸር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም ይላሉ፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/news-56411449 |
0business
| የጓቲማላ ተቃዋሚዎች ምክር ቤቱን በእሳት አቃጠሉ | በመቶዎች የሚቆጠሩ ጓቲማላውያን ተቃዋሚዎች የአገሪቱን ምክር ቤት ህንፃ መዝብረው እሳት ለቀውበታል ተብሏል። ፖሊስም ተቃዋሚዎችን ለመበተን አስለቃሽ ጋዝ ተጠቅሟል። የተወሰነው የህንፃው ክፍልም በቃጠሎው ጉዳት ደርሶበታል። የእሳት አደጋ አገልግሎት ሰራተኞች እሳቱን ማጥፋት ቢችሉም በርካታ ሰዎችም በጭሱ ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ህክምናም እየተደረገላቸውይገኛሉ። ከሰሞኑ ምክር ቤቱ ያፀደቀውን በጀት በመቃወምም ነው ተቃውሟቸውን እየገለፁ ያሉት። በጀቱ ትልልቅ የልማት ፕሮጀክቶች ከመንግሥት ጋር ግንኙነት ያላቸው ኩባንያዎች እንዲሰሯቸው በማድረግ ቅድሚያ ሰጥቷል። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከፍተኛ የማህበራዊና ምጣኔ ኃብታዊ ጫና የደረሰባቸውን የማህበረሰቡ አካላትን ችላ ብሏልም በማለት እየወቀሱ ይገኛሉ። ከዚህም በተጨማሪ በትምህርትና በጤና ላይ ከፍተኛ የሆነ የበጀት ቅነሳ መደረጉም ተቃዋሚዎችን ያበሳጨ ጉዳይ ሆኗል። ሌላው ተቃዋሚዎቹ ዋነኛ ቁልፍ ጉዳይ ብለው የሚያነሱት ጓቲማላ በኤታና ኢዮታ በተባሉት አውሎ ንፋስ መመታቷን ተከትሎ ህዝቧ እንዲህ አይነት ውርጅብኝ ባለበት ወቅት ፓርላማው ሆን ብሎ የወሰነው ውሳኔ ነው ይላሉ። ፓርላማው ህዝቡ በተደናገረበት ወቅት ይህንን ውሳኔ መወሰኑም አስተችቶታል። የአገሪቱ ፕሬዚዳንት አሌሃንድሮ ጊማቴይ ከስልጣናቸው እንዲለቁ ተቃዋሚዎች በመጠየቅ ላይ ናቸው። በትናንትናውም እለት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ የተሳተፈበት የተቃውሞ ሰልፍ የተደረገ ሲሆን በአንፃራዊነትም ሰላማዊ ነው ተብሏል። ምክትል ፕሬዚዳንቱ ጉይሌርሞ ካስቲሎ በበኩላቸው በጀቱ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ የገለፁ ሲሆን እሳቸውም ሆነ ፕሬዚዳንቱ "ለአገሪቱ ደህንነት ሲባል ከስልጣን መውረድ አለብን" ብለዋል። | የጓቲማላ ተቃዋሚዎች ምክር ቤቱን በእሳት አቃጠሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ጓቲማላውያን ተቃዋሚዎች የአገሪቱን ምክር ቤት ህንፃ መዝብረው እሳት ለቀውበታል ተብሏል። ፖሊስም ተቃዋሚዎችን ለመበተን አስለቃሽ ጋዝ ተጠቅሟል። የተወሰነው የህንፃው ክፍልም በቃጠሎው ጉዳት ደርሶበታል። የእሳት አደጋ አገልግሎት ሰራተኞች እሳቱን ማጥፋት ቢችሉም በርካታ ሰዎችም በጭሱ ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ህክምናም እየተደረገላቸውይገኛሉ። ከሰሞኑ ምክር ቤቱ ያፀደቀውን በጀት በመቃወምም ነው ተቃውሟቸውን እየገለፁ ያሉት። በጀቱ ትልልቅ የልማት ፕሮጀክቶች ከመንግሥት ጋር ግንኙነት ያላቸው ኩባንያዎች እንዲሰሯቸው በማድረግ ቅድሚያ ሰጥቷል። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከፍተኛ የማህበራዊና ምጣኔ ኃብታዊ ጫና የደረሰባቸውን የማህበረሰቡ አካላትን ችላ ብሏልም በማለት እየወቀሱ ይገኛሉ። ከዚህም በተጨማሪ በትምህርትና በጤና ላይ ከፍተኛ የሆነ የበጀት ቅነሳ መደረጉም ተቃዋሚዎችን ያበሳጨ ጉዳይ ሆኗል። ሌላው ተቃዋሚዎቹ ዋነኛ ቁልፍ ጉዳይ ብለው የሚያነሱት ጓቲማላ በኤታና ኢዮታ በተባሉት አውሎ ንፋስ መመታቷን ተከትሎ ህዝቧ እንዲህ አይነት ውርጅብኝ ባለበት ወቅት ፓርላማው ሆን ብሎ የወሰነው ውሳኔ ነው ይላሉ። ፓርላማው ህዝቡ በተደናገረበት ወቅት ይህንን ውሳኔ መወሰኑም አስተችቶታል። የአገሪቱ ፕሬዚዳንት አሌሃንድሮ ጊማቴይ ከስልጣናቸው እንዲለቁ ተቃዋሚዎች በመጠየቅ ላይ ናቸው። በትናንትናውም እለት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ የተሳተፈበት የተቃውሞ ሰልፍ የተደረገ ሲሆን በአንፃራዊነትም ሰላማዊ ነው ተብሏል። ምክትል ፕሬዚዳንቱ ጉይሌርሞ ካስቲሎ በበኩላቸው በጀቱ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ የገለፁ ሲሆን እሳቸውም ሆነ ፕሬዚዳንቱ "ለአገሪቱ ደህንነት ሲባል ከስልጣን መውረድ አለብን" ብለዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-55033851 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ ብዙ ያልተነገረለት ኮቪድ-19 በአንጎላችን ላይ ሊያደርስ የሚችለው ጉዳት ምንድን ነው? | ስትሮክ፣ ቅዠት፣ ጭንቀት፣ ግራ መጋባት፣ ድካም ፣ እያለ ይቀጥላል። ኮቪድ-19 የመተንፈሻ አካላት ላይ ብቻ ጉዳት የሚያደርስ ከመሰላችሁ ተሳስታችኋል። እያንዳንዱ ሳምንት ባለፈ ቁጥር ኮሮናቫይረስ ዘርፈ ብዙ አእምሯዊና አካላዊ ጉዳቶችን ማስከተል ይጀምራል። ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የተረጋገጡ በርካታ ሰዎች በመጀመሪያ አካባቢ ብዙም የሚሰጋ ህመም የማይሰማቸው ሲሆን፤ ቀስ በቀስ ግን ማስታወስ አለመቻልና ድካምን የመሳሰሉ ጠንከር ያሉ ምልክቶች ማሳየት ይጀምራሉ። ፖል ማይልሪያ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሁለት ከባድ የሚባሉ ስትሮኮች [የአንጎል ውስጥ ደም መፍሰስ] አጋጥመውታል። የ64 ዓመቱ ፖል በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ የኮምዩኒኬሽንስ ኃላፊ ሲሆን እምብዛም ስጋት ውስጥ ሊከተው ሚችል የጤና እክል አልነበረበትም። በለንደኑ የአንጎልና የአንጎል ቀዶ ህክምና ብሔራዊ ሆስፒታል ውስጥ እጅግ ከፍተኛ የጤና መሻሻል ያሳየ የኮሮረናቫይረስ ታማሚ ሆኗል። ካጋጠመው ስትሮክ በኋላም ፖል ጥሩ የሚባል መሻሻል ታይቶበታል። የመጀመሪያው ስትሮክ ያጋጠመው በሆስፒታል የጽኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ እያለ ነበር። በዚህ ምክንያት ሕይወቱ ልታልፍበት የምትችለበት እድልም ከፍተኛ ነበር። ለዚህም ሲባል ደም የሚያቀጥን መድኃኒት እንዲወስድ ተደርጎ ነበር። ከጥቂት ቀናት በኋላ ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ ስትሮክ አጋጠመው። ሁለተኛው ግን በጣም የከፋና ሕይወቱን ትልቅ አደጋ ውስጥ የከተተ ነበር። አማካሪ የአንጎል ሐኪም ሆኑት ዶክተር አርቪንድ ቻንድራቴቫ፤ ፖል በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታሉ ሲመጣ ሥራቸውን ጨርሰው እየወጡ ነበር። ''ፖል ፊቱ ላይ ግራ መጋባት ይስተዋልበት ነበር። መመልከት የሚችለው በአንድ አቅጣጫ በኩል ብቻ ነበር፤ ተንቀሳቃሽ ስልኩን ለመጠቀምም ሲቸገርና የይለፍ ቃሉን ማስታወስ አቅቶት ግራ ሲጋባ ነበር'' ብለዋል ዶክተሩ። ዶክተር አርቪንድ እንደሚሉት በፖል ጭንቅላት ውስጥ አጋጥሞ የነበረው የደም መርጋት ከዚህ በፊት አይተውት የማያውቁት አይነት እንደሆነ ይናገራሉ። ፖል በተደረገለት ምርመራ የደም መርጋት ምልክቶች ታይተውበታል። በምርመራው የተገኘው ውጤትም አጋትሟቸው በማያውቁት ሁኔታ እጅግ የተለየና አሳሳቢ ነበር። "በሕይወቴ እንዲህ ያለ ውስብስብና ከፍተኛ ከፍተኛ ደም መርጋት ሁኔታ ተመልክቼ አላውቅም" የሚሉት ዶክተር አርቪንድ ኮሮረናቫይረስ የፖል ደም በእጅጉ የተጣበቀ እንዲሆን እንዳደረግ ይገልጻሉ። በእንቅስቃሴ ገደቡ ጊዜ ስትሮክ አጋጥሟቸው ድንገተኛ ክፍል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር ቀንሶ ነበር። ነገር ግን በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ የአንጎል ህክምና ባለሙያዎች በኮቪድ-19 ምክንያት ስትሮክ ያጋጠማቸው ስድስት ሕመምተኞችን አክመዋል። ለአደጋው መንስኤ የነበረው በሰውነት እና በአንጎል ውስጥ እብጠት የሚያስከትሉ የሰውነት በሽታ ተከላካይ ሕዋሳት በጣም ከመጠን በላይ መበራከት ነው። ዶክተር አርቪንድ የፖልን አንጎል የውስጥ ክፍልን የሚያሳዩ ምስሎችን ሲመለከቱ በቫይረሱ ምክንያት የማየት አቅሙ መዳከሙን፣ ማስታወስ እንደሚቸግረው፣ መናገር እንደሚከብደውና ነገሮችን ማስተዋል ከባድ እንደሚሆንበት አስተውለዋል። ያጋጠመው ስትሮክ በጣም ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ ሐኪሞች በሕይወት አይተርፍም ወይም የአካል ጉዳተኛ ይሆናል ብለዋ ገምተው ነበር። ፖልም ቢሆን "ከሁለተኛው ስትሮክ በኋላ ባለቤቴ እና ሴት ልጆቼ አበቃለት ብለው እንደገና ደግመው እንደማያዩኝም ገምተው ነበር'' ሲል ተናግሯል። ''ዶክተሮቹ ምንም ማድረግ የሚችሉት ነገር እንደሌለና ያለው አማራጭ መጠበቅ ብቻ እንደሆነ ነገሯቸው። ነገር ግን እኔ በሆነ መንገድ ተረፍኩኝ፤ ጤናዬም ቀስ በቀስ መስተካከል ጀመረ።'' ፖል እየተሻለው መሆኑን ካሳዩ ነገሮች መካከል ከነርሶቹ ጋር በእንግሊዝኛ የጀመረውን ንግግር በፖርቹጊዝ መጨረስ መጀመሩ ነበር። ፖል ስድስት ቋንቋዎችን የሚናገር ሲሆን ከስትሮኩ በኋላ ጭንቅላቱ ቀድሞ የተማራቸውን ነገሮችና በዚህ ሁኔታ ውስጥ ቋንቋዎችን ማስታወስ መጀመሩ ለዶክተሩ አበረታች ውጤት ነበር። ፖል እንደሚለው ከስትሮኩ በኋላ እንደቀድሞው በፍጥነት ማንበብ ያቃተው ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ነገሮችን ይዘነጋል። ነገር ግን ካጋጠሙት ሁለት ስትሮኮች አንጻር በጭንቅላቱ ላይ የደረሰው ጉዳት ከታሰበው በታች ትንሽ ነው። አካላዊ የማገገም ሂደቱም ቢሆን ተስፋ ሰጪ ነበር። ዶክተሮች ለዚህ በምክንያትነት ያስቀመጡት ደግሞ ከዚህ በፊት የነበረው አካላዊ ብቃት ጥሩ መሆኑን ነው። "በየቀኑ ለአንድ ሰዓት ያህል ብስክሌት እነዳለሁ፣ በሳምንት ውስጥ የስፖርት ማዘውተሪያ እሄዳለሁ፣ በአቅራቢያ ባለ ወንዝ ውስጥም እዋኛለሁ። ከዚህ በኋላ ግን ሳይክል መንዳት የምችል አይመስለኝም። ነገር ግን መዋኘት መቀጠል የምችል ይመስለኛል'' ብሏል ፖል። በላንሴት የሥነ አእምሮ ክፍል ባደረገው ጥናት መሰረት በዩናይትድ ኪንግደም ሆስፒታሎች ውስጥ 125 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ምክንያት የአንጎል ውስጥ ችግር አጋጥሟቸዋል። ግማሽ የሚሆኑት ደግሞ ስትሮክ ያጋጠማቸው ሲሆን የደም መርጋት ችግርና የአንጎል እብጠት እንዲሁም እብደት መሰል ሁኔታ ተስተውሎባቸዋል። ካናዳዊው የአንጎል ህክምና ተመራማሪው ፕሮፌሰር አድሪያን ኦዊን እንደሚሉት በኮሮረናቫይረስ ምክንያት ከባድ የጤና እክል ካጋጠማቸው በኋላ ሲሻላቸው ወደቤታቸው የሚላኩ ሰዎች ድነዋል ማለት አይደለም። ታማሚዎቹ ወደቤታቸው ከተመለሱ በኋላ ለበርካታ ሳምንታት ሊቆይ የሚችል የማገገም ሂደት ይጠብቃቸዋል ብለዋል። በዚህም ምክንያት የኮቪድ-19 ታማሚዎች የሚያሳዩት ምልክቶችና አንጎላቸው ላይ የሚስተዋለውን የአጭርና የረጅም ጊዜ ጉዳት በአግባቡ መመርመር ወደፊት ለሚያጋጥሙ ችግሮች መፍትሄ ሊሆን እንደሚችል ፕሮፌሰር አድሪያን ያሳስባሉ። | ኮሮናቫይረስ፡ ብዙ ያልተነገረለት ኮቪድ-19 በአንጎላችን ላይ ሊያደርስ የሚችለው ጉዳት ምንድን ነው? ስትሮክ፣ ቅዠት፣ ጭንቀት፣ ግራ መጋባት፣ ድካም ፣ እያለ ይቀጥላል። ኮቪድ-19 የመተንፈሻ አካላት ላይ ብቻ ጉዳት የሚያደርስ ከመሰላችሁ ተሳስታችኋል። እያንዳንዱ ሳምንት ባለፈ ቁጥር ኮሮናቫይረስ ዘርፈ ብዙ አእምሯዊና አካላዊ ጉዳቶችን ማስከተል ይጀምራል። ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የተረጋገጡ በርካታ ሰዎች በመጀመሪያ አካባቢ ብዙም የሚሰጋ ህመም የማይሰማቸው ሲሆን፤ ቀስ በቀስ ግን ማስታወስ አለመቻልና ድካምን የመሳሰሉ ጠንከር ያሉ ምልክቶች ማሳየት ይጀምራሉ። ፖል ማይልሪያ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሁለት ከባድ የሚባሉ ስትሮኮች [የአንጎል ውስጥ ደም መፍሰስ] አጋጥመውታል። የ64 ዓመቱ ፖል በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ የኮምዩኒኬሽንስ ኃላፊ ሲሆን እምብዛም ስጋት ውስጥ ሊከተው ሚችል የጤና እክል አልነበረበትም። በለንደኑ የአንጎልና የአንጎል ቀዶ ህክምና ብሔራዊ ሆስፒታል ውስጥ እጅግ ከፍተኛ የጤና መሻሻል ያሳየ የኮሮረናቫይረስ ታማሚ ሆኗል። ካጋጠመው ስትሮክ በኋላም ፖል ጥሩ የሚባል መሻሻል ታይቶበታል። የመጀመሪያው ስትሮክ ያጋጠመው በሆስፒታል የጽኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ እያለ ነበር። በዚህ ምክንያት ሕይወቱ ልታልፍበት የምትችለበት እድልም ከፍተኛ ነበር። ለዚህም ሲባል ደም የሚያቀጥን መድኃኒት እንዲወስድ ተደርጎ ነበር። ከጥቂት ቀናት በኋላ ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ ስትሮክ አጋጠመው። ሁለተኛው ግን በጣም የከፋና ሕይወቱን ትልቅ አደጋ ውስጥ የከተተ ነበር። አማካሪ የአንጎል ሐኪም ሆኑት ዶክተር አርቪንድ ቻንድራቴቫ፤ ፖል በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታሉ ሲመጣ ሥራቸውን ጨርሰው እየወጡ ነበር። ''ፖል ፊቱ ላይ ግራ መጋባት ይስተዋልበት ነበር። መመልከት የሚችለው በአንድ አቅጣጫ በኩል ብቻ ነበር፤ ተንቀሳቃሽ ስልኩን ለመጠቀምም ሲቸገርና የይለፍ ቃሉን ማስታወስ አቅቶት ግራ ሲጋባ ነበር'' ብለዋል ዶክተሩ። ዶክተር አርቪንድ እንደሚሉት በፖል ጭንቅላት ውስጥ አጋጥሞ የነበረው የደም መርጋት ከዚህ በፊት አይተውት የማያውቁት አይነት እንደሆነ ይናገራሉ። ፖል በተደረገለት ምርመራ የደም መርጋት ምልክቶች ታይተውበታል። በምርመራው የተገኘው ውጤትም አጋትሟቸው በማያውቁት ሁኔታ እጅግ የተለየና አሳሳቢ ነበር። "በሕይወቴ እንዲህ ያለ ውስብስብና ከፍተኛ ከፍተኛ ደም መርጋት ሁኔታ ተመልክቼ አላውቅም" የሚሉት ዶክተር አርቪንድ ኮሮረናቫይረስ የፖል ደም በእጅጉ የተጣበቀ እንዲሆን እንዳደረግ ይገልጻሉ። በእንቅስቃሴ ገደቡ ጊዜ ስትሮክ አጋጥሟቸው ድንገተኛ ክፍል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር ቀንሶ ነበር። ነገር ግን በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ የአንጎል ህክምና ባለሙያዎች በኮቪድ-19 ምክንያት ስትሮክ ያጋጠማቸው ስድስት ሕመምተኞችን አክመዋል። ለአደጋው መንስኤ የነበረው በሰውነት እና በአንጎል ውስጥ እብጠት የሚያስከትሉ የሰውነት በሽታ ተከላካይ ሕዋሳት በጣም ከመጠን በላይ መበራከት ነው። ዶክተር አርቪንድ የፖልን አንጎል የውስጥ ክፍልን የሚያሳዩ ምስሎችን ሲመለከቱ በቫይረሱ ምክንያት የማየት አቅሙ መዳከሙን፣ ማስታወስ እንደሚቸግረው፣ መናገር እንደሚከብደውና ነገሮችን ማስተዋል ከባድ እንደሚሆንበት አስተውለዋል። ያጋጠመው ስትሮክ በጣም ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ ሐኪሞች በሕይወት አይተርፍም ወይም የአካል ጉዳተኛ ይሆናል ብለዋ ገምተው ነበር። ፖልም ቢሆን "ከሁለተኛው ስትሮክ በኋላ ባለቤቴ እና ሴት ልጆቼ አበቃለት ብለው እንደገና ደግመው እንደማያዩኝም ገምተው ነበር'' ሲል ተናግሯል። ''ዶክተሮቹ ምንም ማድረግ የሚችሉት ነገር እንደሌለና ያለው አማራጭ መጠበቅ ብቻ እንደሆነ ነገሯቸው። ነገር ግን እኔ በሆነ መንገድ ተረፍኩኝ፤ ጤናዬም ቀስ በቀስ መስተካከል ጀመረ።'' ፖል እየተሻለው መሆኑን ካሳዩ ነገሮች መካከል ከነርሶቹ ጋር በእንግሊዝኛ የጀመረውን ንግግር በፖርቹጊዝ መጨረስ መጀመሩ ነበር። ፖል ስድስት ቋንቋዎችን የሚናገር ሲሆን ከስትሮኩ በኋላ ጭንቅላቱ ቀድሞ የተማራቸውን ነገሮችና በዚህ ሁኔታ ውስጥ ቋንቋዎችን ማስታወስ መጀመሩ ለዶክተሩ አበረታች ውጤት ነበር። ፖል እንደሚለው ከስትሮኩ በኋላ እንደቀድሞው በፍጥነት ማንበብ ያቃተው ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ነገሮችን ይዘነጋል። ነገር ግን ካጋጠሙት ሁለት ስትሮኮች አንጻር በጭንቅላቱ ላይ የደረሰው ጉዳት ከታሰበው በታች ትንሽ ነው። አካላዊ የማገገም ሂደቱም ቢሆን ተስፋ ሰጪ ነበር። ዶክተሮች ለዚህ በምክንያትነት ያስቀመጡት ደግሞ ከዚህ በፊት የነበረው አካላዊ ብቃት ጥሩ መሆኑን ነው። "በየቀኑ ለአንድ ሰዓት ያህል ብስክሌት እነዳለሁ፣ በሳምንት ውስጥ የስፖርት ማዘውተሪያ እሄዳለሁ፣ በአቅራቢያ ባለ ወንዝ ውስጥም እዋኛለሁ። ከዚህ በኋላ ግን ሳይክል መንዳት የምችል አይመስለኝም። ነገር ግን መዋኘት መቀጠል የምችል ይመስለኛል'' ብሏል ፖል። በላንሴት የሥነ አእምሮ ክፍል ባደረገው ጥናት መሰረት በዩናይትድ ኪንግደም ሆስፒታሎች ውስጥ 125 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ምክንያት የአንጎል ውስጥ ችግር አጋጥሟቸዋል። ግማሽ የሚሆኑት ደግሞ ስትሮክ ያጋጠማቸው ሲሆን የደም መርጋት ችግርና የአንጎል እብጠት እንዲሁም እብደት መሰል ሁኔታ ተስተውሎባቸዋል። ካናዳዊው የአንጎል ህክምና ተመራማሪው ፕሮፌሰር አድሪያን ኦዊን እንደሚሉት በኮሮረናቫይረስ ምክንያት ከባድ የጤና እክል ካጋጠማቸው በኋላ ሲሻላቸው ወደቤታቸው የሚላኩ ሰዎች ድነዋል ማለት አይደለም። ታማሚዎቹ ወደቤታቸው ከተመለሱ በኋላ ለበርካታ ሳምንታት ሊቆይ የሚችል የማገገም ሂደት ይጠብቃቸዋል ብለዋል። በዚህም ምክንያት የኮቪድ-19 ታማሚዎች የሚያሳዩት ምልክቶችና አንጎላቸው ላይ የሚስተዋለውን የአጭርና የረጅም ጊዜ ጉዳት በአግባቡ መመርመር ወደፊት ለሚያጋጥሙ ችግሮች መፍትሄ ሊሆን እንደሚችል ፕሮፌሰር አድሪያን ያሳስባሉ። | https://www.bbc.com/amharic/news-53282426 |
5sports
| ፊፋ በእንግሊዝ ተጫዋቾች ላይ የተሰነዘረውን ጥቃት መመርመር ጀመረ | እንግሊዝ ሃንጋሪን 4 ለ 0 ባሸነፈችበት ጨዋታ ላይ በተጫዋቾች ላይ የተሰነዘረውን የዘረኝነት ጥቃት ለመመርመር ፊፋ ሥራ መጀመሩ ተነገረ። ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ በሃንጋሪ ዋና ከተማ ቡዳፔስት ውስጥ በተካሄደው የእግር ኳስ ግጥሚያ ላይ የእንግሊዝ ተጫዋቾቹ ራሂም ስተርሊንግ እና ጁድ ቤሊንግሃም የዘረኝነት ጥቃት ኢላማ ሆነው ነበር። ቡዳፔስት ውስጥ በሚገኘው ፑስካስ አሬና ስታዲየም በተደረገውና እንግሊዝ በሰፊ የግብ ልዩነት ባሸነፈችበት ጨዋታ ወቅት ተጨዋቾቹ ላይ የተለያዩ ነገሮች ከተመልካቾቹ ተወርውሮባቸዋል። ይህም የተከሰተው በጨዋታው ሁለተኛ አጋማሽ ላይ ነበር። ከክስተቱ በኋላ ተጫዋቾቿ ላይ ጥቃት የተሰነዘረባት እንግሊዝ ድርጊቱን "ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው" ስትል አውግዛዋለች። ለጀርመኑ ቡድን ቦሪሲያ ዶርትሙንድ የመሃል መስመር ተጫዋች የሆነው የ18 ዓመቱ ቤሊንግሃም ከጥቃቱ በኋላ የዘረኝነት ጥቃቱን በተመለከተ ትዊተር ላይ እንዳሰፈረው "የሚመለከታቸው ባለሥልጣናት ተገቢውን የቅጣት እርምጃ ካልወሰዱ ድርጊቱ የጨዋታው አካል ሆኖ ይቀጥላል። ጥላቻ እንዲሰፍን ማድረግ የለብንም።" ብሏል። የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንም "እንዲህ አይነቱ አሳፋሪ ድርጊት እስከ መጨረሻው ከእግር ኳስ ሜዳዎች እንዲወገዱ በአጥፊዎች ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ መወሰድ አለበት" ሲሉ የዓለም እግር ኳስ የበላይ አካል የሆነውን ፊፋን ጠይቀዋል። አርብ ከሰዓት በኋላ ፊፋ እንዳስታወቀው በእግሊዝና በሃንጋሪ ግጥሚያ ወቅት የነበረውን የጨዋታውን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ በድርጊቱ ላይ የሥነ ሥርዓት እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል ሂደት መጀመሩን አስታውቋል። ጨምሮም ፊፋ የትኛውንም አይነት ዘረኝነት፣ መድልዎና ጥቃትን አጥብቆ የሚቃወምበት አቋሙ አሁንም ጽኑ እንደሆነ ገልጿል። "በእግር ኳስ ውስጥ የሚከሰቱ እንዲህ አይነት ተቀባይነት የሌላቸው ተግባራትን ፈጽሞ አይታገስም" ሲል አቋሙን አሳውቋል። የአውሮፓ የእግር ኳስ ማኅበር (ዩኤፋ) የሃንጋሪ ደጋፊዎች ቀደም ሲል አሳይተውት በነበረው የዘረኝነት ድርጊት ምክንያት ብሔራዊ ቡድኑ ሦስት ጨዋታዎችን በዝግ ስታዲየም እንዲያደርግ ወስኖ ነበር። ነገር ግን የሐሙስ ዕለቱ ጨዋታ በፊፋ አማካይነት የሚደረግ በመሆኑ የዩኤፋ ውሳኔ ተግባራዊ ሳይደረግ ደጋፊዎች በስታዲየም ተገኝተው ጨዋታውን ለመከታተል ችለው ነበር። የአውሮፓ የእግር ኳስ ማኅበር በሃንጋሪ ላይ ቅጣት ጥሎ የነበረው ባለፈው ሰኔ ወር ላይ በነበረ ጨዋታ ወቅት ካጋጠሙ የዘረኝነትና የመድልዎ ተግባራት ጋር በተያያዘ ነበር። | ፊፋ በእንግሊዝ ተጫዋቾች ላይ የተሰነዘረውን ጥቃት መመርመር ጀመረ እንግሊዝ ሃንጋሪን 4 ለ 0 ባሸነፈችበት ጨዋታ ላይ በተጫዋቾች ላይ የተሰነዘረውን የዘረኝነት ጥቃት ለመመርመር ፊፋ ሥራ መጀመሩ ተነገረ። ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ በሃንጋሪ ዋና ከተማ ቡዳፔስት ውስጥ በተካሄደው የእግር ኳስ ግጥሚያ ላይ የእንግሊዝ ተጫዋቾቹ ራሂም ስተርሊንግ እና ጁድ ቤሊንግሃም የዘረኝነት ጥቃት ኢላማ ሆነው ነበር። ቡዳፔስት ውስጥ በሚገኘው ፑስካስ አሬና ስታዲየም በተደረገውና እንግሊዝ በሰፊ የግብ ልዩነት ባሸነፈችበት ጨዋታ ወቅት ተጨዋቾቹ ላይ የተለያዩ ነገሮች ከተመልካቾቹ ተወርውሮባቸዋል። ይህም የተከሰተው በጨዋታው ሁለተኛ አጋማሽ ላይ ነበር። ከክስተቱ በኋላ ተጫዋቾቿ ላይ ጥቃት የተሰነዘረባት እንግሊዝ ድርጊቱን "ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው" ስትል አውግዛዋለች። ለጀርመኑ ቡድን ቦሪሲያ ዶርትሙንድ የመሃል መስመር ተጫዋች የሆነው የ18 ዓመቱ ቤሊንግሃም ከጥቃቱ በኋላ የዘረኝነት ጥቃቱን በተመለከተ ትዊተር ላይ እንዳሰፈረው "የሚመለከታቸው ባለሥልጣናት ተገቢውን የቅጣት እርምጃ ካልወሰዱ ድርጊቱ የጨዋታው አካል ሆኖ ይቀጥላል። ጥላቻ እንዲሰፍን ማድረግ የለብንም።" ብሏል። የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንም "እንዲህ አይነቱ አሳፋሪ ድርጊት እስከ መጨረሻው ከእግር ኳስ ሜዳዎች እንዲወገዱ በአጥፊዎች ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ መወሰድ አለበት" ሲሉ የዓለም እግር ኳስ የበላይ አካል የሆነውን ፊፋን ጠይቀዋል። አርብ ከሰዓት በኋላ ፊፋ እንዳስታወቀው በእግሊዝና በሃንጋሪ ግጥሚያ ወቅት የነበረውን የጨዋታውን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ በድርጊቱ ላይ የሥነ ሥርዓት እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል ሂደት መጀመሩን አስታውቋል። ጨምሮም ፊፋ የትኛውንም አይነት ዘረኝነት፣ መድልዎና ጥቃትን አጥብቆ የሚቃወምበት አቋሙ አሁንም ጽኑ እንደሆነ ገልጿል። "በእግር ኳስ ውስጥ የሚከሰቱ እንዲህ አይነት ተቀባይነት የሌላቸው ተግባራትን ፈጽሞ አይታገስም" ሲል አቋሙን አሳውቋል። የአውሮፓ የእግር ኳስ ማኅበር (ዩኤፋ) የሃንጋሪ ደጋፊዎች ቀደም ሲል አሳይተውት በነበረው የዘረኝነት ድርጊት ምክንያት ብሔራዊ ቡድኑ ሦስት ጨዋታዎችን በዝግ ስታዲየም እንዲያደርግ ወስኖ ነበር። ነገር ግን የሐሙስ ዕለቱ ጨዋታ በፊፋ አማካይነት የሚደረግ በመሆኑ የዩኤፋ ውሳኔ ተግባራዊ ሳይደረግ ደጋፊዎች በስታዲየም ተገኝተው ጨዋታውን ለመከታተል ችለው ነበር። የአውሮፓ የእግር ኳስ ማኅበር በሃንጋሪ ላይ ቅጣት ጥሎ የነበረው ባለፈው ሰኔ ወር ላይ በነበረ ጨዋታ ወቅት ካጋጠሙ የዘረኝነትና የመድልዎ ተግባራት ጋር በተያያዘ ነበር። | https://www.bbc.com/amharic/news-58386459 |
3politics
| ክልልነት በጠየቁ የደቡብ አካባቢዎች ላይ ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ | በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ስር ያሉ 6 ዞኖችና የአምስት ልዩ ወረዳ ብሔሮች እና ብሔረሰቦች ክልል እንሁን ጥያቄ ላይ ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ አሳለፈ። የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ 12/2014 ዓ.ም. ባካሄደው 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 1ኛ ዓመት፣ በ1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ በአንድ ክልል እንጠቃለል ጥያቄ ተቀብሎ ከመረመረ በኋላ ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ውሳኔ ተላልፏል። በዚህም የወላይታ፣ የጋሞ፣ የጎፋ፣ የደቡብ ኦሞ፣ የጌዴኦ፣ የኮንሶ ዞኖች፣ እንዲሁም የደራሼ፣ የአማሮ፣ የቡርጂ፣ የአሌ እና የባስኬቶ ልዩ ወረዳ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በጋራ ''የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል''ን የመመስረት ጥያቄ ላይ ውሳኔ ለመስጠትም የህዝብ ይሁንታ መገኘት ስላለበትም ነው ሕዝብ ውሳኔ የሚካሄደው። በዚህም መሠረት ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ አማካኝነት በሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ ሕዝበ ውሳኔ እንዲያደራጅ እና የሕዝበ ውሳኔው ውጤትም ሪፖርት ለፌዴሬሽን ምክር ቤት እንዲቀርብም ጠይቋል። በተጨማሪም የሕዝበ ውሳኔው ሂደት ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና የሕዝብን ተሳትፎ ባረጋገጠ መልኩ እንዲጠናቀቅ አመራሮችና የፀጥታ አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ምክር ቤቱ በአብላጫ ድምጽ ውሳኔ አስተላልፏል። ሌሎቹ የሃድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታና ጠምባሮ፣ ስልጤ፣ ጉራጌ ዞኖች እና የም ልዩ ወረዳ በነባሩ የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል አንድ ላይ እንደሚቀጥሉም ተገልጿል። የስድስት ዞኖች እና የአምስት ልዩ ወረዳዎች በአንድ ክልል የመሆን ጥያቄ በየደረጃው ባሉ ዞኖችና ልዩ ወረዳ በየብሔረሰብ ምክር ቤቶች ውይይት ተደርጎበትና ጸድቆ የመጣ ሲሆን፣ ይህንንም ጥያቄ አስመልክቶ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የማንነት፣ የአስተዳደር ወሰን እና የሰላም ግንባታ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሲመክርና ሲመረምር ቆይቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል። በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 46/2 ክልሎች የሚዋቀሩት በሕዝበ አሰፋፈር፣ ቋንቋ፣ ማንነትና ፈቃድ ላይ የተመሰረተ መሆኑን የሚጠቅስ ሲሆን ኮሚቴው ዞኖቹና ወረዳዎቹ ያቀረቡት ጥያቄ ሕገ መንግሥቱን የተከተለ መሆኑንም መርምሯል። በተጨማሪም ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በማንኛውም ጊዜ ክልል የመመስረት መብት እንዳላቸው የተደነገገ በመሆኑ የቀረበው ጥያቄ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት አካል እንደሆነ ሕገ መንግሥቱን በመጥቀስ ውሳኔው መተላለፉ ተጠቅሷል። በርካታ የሕዝብ ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ ባለማግኘታቸው ለግጭት ለሰዎች ሕይወት መጥፋት ለንብረት መውደም መንስኤ ሆኖ የቆየ መሆኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር መናገራቸው ተገልጿል። "ሰላምን ለማስፈን፣ አንድ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ማኅበረሰብ ለመገንባትና በፍትሃዊነት ላይ የተመሠረተ ልማት ለማፋጠን የሕዝቦች ጥያቄዎች በአፋጣኝ ሊመለሱ ይገባል" ማለታቸውም ተጠቅሷል። በቅርብ ዓመታት በደቡብ ክልል በተናጠል ክልል የመመስረት ጥያቄ በክልሉ ካሉ ዞኖች እየቀረበ ይገኛል። አለመረጋጋት እና ለሰው ሕይወት መጥፋት ምክንያት ከሆኑት መካከል በሲዳማ እና በወላይታ መከሰቱ ይታወሳል። ሲዳማ በክልልነት በመደራጀት ከደቡብ ክልል የወጣ የመጀመሪያው ዞን በመሆን 10ኛው የአገሪቱ ክልል ለመሆን ችሏል። በማስከተልም የምዕራብ ኦሞ፣ የቤንች ሸኮ፣ የከፋ፣ የዳውሮ፣ የሸካ ዞኖች እና የኮንታ ልዩ ወረዳ በአንድ ላይ ተጣምረው በሕዝበ ውሳኔ 11ኛው፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ተመስርቷል። ከዚህም በኋላ ቢሆን በቀሩት የክልሉ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ውስጥ በጥምረት አልያም በተናጠል ክልል የመሆን ጥያቄዎች የደቡብ ክልል ዋነኛው ጉዳይ ሆኖ ቆይቷል። በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ስር የሆኑ እና ራሳቸውን የቻሉ ክልሎች ሆነው ለመደራጀት የተለያዩ ጥያቄዎች ሲያቀርቡ የነበሩ ዞኖችን እና ልዩ ወረዳዎች በተለያዩ ክልሎች ስር ለመደራጀት የሚያስችላቸውን ውሳኔ በምክር ቤቶቻቸው አማካኝነት እያሳለፉ ነው። ከ50 በላይ ብሔር ብሔረሰቦችን የያዘው የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ከአገሪቱ ትልቅ ከሚባሉት ክልሎች መካከል አንዱ ሆኖ ቆይቷል። | ክልልነት በጠየቁ የደቡብ አካባቢዎች ላይ ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ስር ያሉ 6 ዞኖችና የአምስት ልዩ ወረዳ ብሔሮች እና ብሔረሰቦች ክልል እንሁን ጥያቄ ላይ ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ አሳለፈ። የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ 12/2014 ዓ.ም. ባካሄደው 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 1ኛ ዓመት፣ በ1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ በአንድ ክልል እንጠቃለል ጥያቄ ተቀብሎ ከመረመረ በኋላ ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ውሳኔ ተላልፏል። በዚህም የወላይታ፣ የጋሞ፣ የጎፋ፣ የደቡብ ኦሞ፣ የጌዴኦ፣ የኮንሶ ዞኖች፣ እንዲሁም የደራሼ፣ የአማሮ፣ የቡርጂ፣ የአሌ እና የባስኬቶ ልዩ ወረዳ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በጋራ ''የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል''ን የመመስረት ጥያቄ ላይ ውሳኔ ለመስጠትም የህዝብ ይሁንታ መገኘት ስላለበትም ነው ሕዝብ ውሳኔ የሚካሄደው። በዚህም መሠረት ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ አማካኝነት በሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ ሕዝበ ውሳኔ እንዲያደራጅ እና የሕዝበ ውሳኔው ውጤትም ሪፖርት ለፌዴሬሽን ምክር ቤት እንዲቀርብም ጠይቋል። በተጨማሪም የሕዝበ ውሳኔው ሂደት ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና የሕዝብን ተሳትፎ ባረጋገጠ መልኩ እንዲጠናቀቅ አመራሮችና የፀጥታ አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ምክር ቤቱ በአብላጫ ድምጽ ውሳኔ አስተላልፏል። ሌሎቹ የሃድያ፣ ሀላባ፣ ከምባታና ጠምባሮ፣ ስልጤ፣ ጉራጌ ዞኖች እና የም ልዩ ወረዳ በነባሩ የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል አንድ ላይ እንደሚቀጥሉም ተገልጿል። የስድስት ዞኖች እና የአምስት ልዩ ወረዳዎች በአንድ ክልል የመሆን ጥያቄ በየደረጃው ባሉ ዞኖችና ልዩ ወረዳ በየብሔረሰብ ምክር ቤቶች ውይይት ተደርጎበትና ጸድቆ የመጣ ሲሆን፣ ይህንንም ጥያቄ አስመልክቶ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የማንነት፣ የአስተዳደር ወሰን እና የሰላም ግንባታ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሲመክርና ሲመረምር ቆይቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል። በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 46/2 ክልሎች የሚዋቀሩት በሕዝበ አሰፋፈር፣ ቋንቋ፣ ማንነትና ፈቃድ ላይ የተመሰረተ መሆኑን የሚጠቅስ ሲሆን ኮሚቴው ዞኖቹና ወረዳዎቹ ያቀረቡት ጥያቄ ሕገ መንግሥቱን የተከተለ መሆኑንም መርምሯል። በተጨማሪም ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በማንኛውም ጊዜ ክልል የመመስረት መብት እንዳላቸው የተደነገገ በመሆኑ የቀረበው ጥያቄ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት አካል እንደሆነ ሕገ መንግሥቱን በመጥቀስ ውሳኔው መተላለፉ ተጠቅሷል። በርካታ የሕዝብ ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ ባለማግኘታቸው ለግጭት ለሰዎች ሕይወት መጥፋት ለንብረት መውደም መንስኤ ሆኖ የቆየ መሆኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር መናገራቸው ተገልጿል። "ሰላምን ለማስፈን፣ አንድ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ማኅበረሰብ ለመገንባትና በፍትሃዊነት ላይ የተመሠረተ ልማት ለማፋጠን የሕዝቦች ጥያቄዎች በአፋጣኝ ሊመለሱ ይገባል" ማለታቸውም ተጠቅሷል። በቅርብ ዓመታት በደቡብ ክልል በተናጠል ክልል የመመስረት ጥያቄ በክልሉ ካሉ ዞኖች እየቀረበ ይገኛል። አለመረጋጋት እና ለሰው ሕይወት መጥፋት ምክንያት ከሆኑት መካከል በሲዳማ እና በወላይታ መከሰቱ ይታወሳል። ሲዳማ በክልልነት በመደራጀት ከደቡብ ክልል የወጣ የመጀመሪያው ዞን በመሆን 10ኛው የአገሪቱ ክልል ለመሆን ችሏል። በማስከተልም የምዕራብ ኦሞ፣ የቤንች ሸኮ፣ የከፋ፣ የዳውሮ፣ የሸካ ዞኖች እና የኮንታ ልዩ ወረዳ በአንድ ላይ ተጣምረው በሕዝበ ውሳኔ 11ኛው፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ተመስርቷል። ከዚህም በኋላ ቢሆን በቀሩት የክልሉ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ውስጥ በጥምረት አልያም በተናጠል ክልል የመሆን ጥያቄዎች የደቡብ ክልል ዋነኛው ጉዳይ ሆኖ ቆይቷል። በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ስር የሆኑ እና ራሳቸውን የቻሉ ክልሎች ሆነው ለመደራጀት የተለያዩ ጥያቄዎች ሲያቀርቡ የነበሩ ዞኖችን እና ልዩ ወረዳዎች በተለያዩ ክልሎች ስር ለመደራጀት የሚያስችላቸውን ውሳኔ በምክር ቤቶቻቸው አማካኝነት እያሳለፉ ነው። ከ50 በላይ ብሔር ብሔረሰቦችን የያዘው የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ከአገሪቱ ትልቅ ከሚባሉት ክልሎች መካከል አንዱ ሆኖ ቆይቷል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c0v4j8l3yqyo |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ በቱርክ የኦክስጅን ቬንትሌተር ፈንድቶ የኮሮና ህሙማንን ገደለ | በቱርክ በሚገኝ የኮሮናቫይረስ ህሙማን ማዕከል የኦክስጅን ቬንትሌተር ፈንድቶ ዘጠኝ የኮሮና ህሙማንን ገድሏል። አደጋው ያጋጠመው ጋዚንቴፕ በምትባለው ግዛት የሚገኘው የሳንኮ ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል ነው። የቬንትሌተሩም መፈንዳትም በፅኑ ህሙማኑ ክፍል ውስጥ እሳት ማስነሳቱንም የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል። አንደኛው ህመምተኛም ወደ ሌላ ሆስፒታል ሊዛወር ሲል ነው የሞተው ተብሏል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀምሮ 2 ሚሊዮን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የተመዘገቡ ሲሆን 17 ሺህ 610 ሰዎችም ህይወታቸውን ማጣታቸውን ከጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የተገኘው መረጃ ያስረዳል። ፍንዳታው ባስከተለው እሳት የደረሰ ጉዳት እንደሌለም ሪፖርት የተደረገ ሲሆን ወዲያውም እሳቱን ለማጥፋት ርብርብ ተደርጓል። ሟቾቹ ከ56-85 እድሜ የሚገመቱ መሆኑንም ከሆስፒታሉ የወጣው መግለጫ ያሳያል። የኦክስጅን ቬንትሌተር ፍንዳታው እንዴት ተከሰተ ለሚለውም ምርመራ ተከፍቷል። በፅኑ ህሙማን የሚገኙ በርካታ ሌሎች ህመምተኞችም አቅራቢያው ወደሚገኝ ሆስፒታልም ህክምና እንዲያገኙ መወሰዳቸውንም የጋዚያንቴፕ አስተዳደር ቢሮ በመግለጫው ጠቅሷል። "ባለስልጣናቱ የሚያስፈልገውን እርምጃም እየወሰዱ ነው" ብሏል መግለጫው። አክሎም በሞቱ ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ፣ ዘመዶች መፅናናትን ተመኝቷል። የቱርክ ፕሬዚዳንት ኢብራሒም ካሊን ቃለ አቀባይም በትዊተር ገፃቸው "ለቆሰሉት በቶሎ እንዲያገግሙ እንመኛለን" በማለት ምኞታቸውን አስተላልፈዋል። በባለፈው ወር እንዲሁ በሮማንያ በተነሳ እሳት 10 የኮሮናቫይረስ ህሙማን ህይወታቸው አልፏል። ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ለእሳቱ መነሻ የሆነው አንድ የህክምና ቁሳቁስ በእሳት ተያይዞ አቅራቢያ የነበረውን የኦክስጅን ሲሊንደር በማቀጣጠሉ ነው። በጥር ወርም እንዲሁ በሩሲያዋ ቼልያቢንስክ ግዛት በሚገኝ ጊዜያው የኮሮናቫይረስ ሆስፒታል ውስጥ የኦክስጅን ክፍሉ ውስጥ ፍንዳታ በመነሳቱ እሳት አስከትሏል። በቦታው የነበሩ 150 የኮሮናቫይረስ ህመምተኞችም በአስቸኳይ እንዲወጡ መደረጋቸውንም የሩሲያ ድንገተኛና አስከቸኳይ ሚኒስቴር ገልጿል። | ኮሮናቫይረስ፡ በቱርክ የኦክስጅን ቬንትሌተር ፈንድቶ የኮሮና ህሙማንን ገደለ በቱርክ በሚገኝ የኮሮናቫይረስ ህሙማን ማዕከል የኦክስጅን ቬንትሌተር ፈንድቶ ዘጠኝ የኮሮና ህሙማንን ገድሏል። አደጋው ያጋጠመው ጋዚንቴፕ በምትባለው ግዛት የሚገኘው የሳንኮ ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል ነው። የቬንትሌተሩም መፈንዳትም በፅኑ ህሙማኑ ክፍል ውስጥ እሳት ማስነሳቱንም የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል። አንደኛው ህመምተኛም ወደ ሌላ ሆስፒታል ሊዛወር ሲል ነው የሞተው ተብሏል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀምሮ 2 ሚሊዮን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የተመዘገቡ ሲሆን 17 ሺህ 610 ሰዎችም ህይወታቸውን ማጣታቸውን ከጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የተገኘው መረጃ ያስረዳል። ፍንዳታው ባስከተለው እሳት የደረሰ ጉዳት እንደሌለም ሪፖርት የተደረገ ሲሆን ወዲያውም እሳቱን ለማጥፋት ርብርብ ተደርጓል። ሟቾቹ ከ56-85 እድሜ የሚገመቱ መሆኑንም ከሆስፒታሉ የወጣው መግለጫ ያሳያል። የኦክስጅን ቬንትሌተር ፍንዳታው እንዴት ተከሰተ ለሚለውም ምርመራ ተከፍቷል። በፅኑ ህሙማን የሚገኙ በርካታ ሌሎች ህመምተኞችም አቅራቢያው ወደሚገኝ ሆስፒታልም ህክምና እንዲያገኙ መወሰዳቸውንም የጋዚያንቴፕ አስተዳደር ቢሮ በመግለጫው ጠቅሷል። "ባለስልጣናቱ የሚያስፈልገውን እርምጃም እየወሰዱ ነው" ብሏል መግለጫው። አክሎም በሞቱ ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ፣ ዘመዶች መፅናናትን ተመኝቷል። የቱርክ ፕሬዚዳንት ኢብራሒም ካሊን ቃለ አቀባይም በትዊተር ገፃቸው "ለቆሰሉት በቶሎ እንዲያገግሙ እንመኛለን" በማለት ምኞታቸውን አስተላልፈዋል። በባለፈው ወር እንዲሁ በሮማንያ በተነሳ እሳት 10 የኮሮናቫይረስ ህሙማን ህይወታቸው አልፏል። ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ለእሳቱ መነሻ የሆነው አንድ የህክምና ቁሳቁስ በእሳት ተያይዞ አቅራቢያ የነበረውን የኦክስጅን ሲሊንደር በማቀጣጠሉ ነው። በጥር ወርም እንዲሁ በሩሲያዋ ቼልያቢንስክ ግዛት በሚገኝ ጊዜያው የኮሮናቫይረስ ሆስፒታል ውስጥ የኦክስጅን ክፍሉ ውስጥ ፍንዳታ በመነሳቱ እሳት አስከትሏል። በቦታው የነበሩ 150 የኮሮናቫይረስ ህመምተኞችም በአስቸኳይ እንዲወጡ መደረጋቸውንም የሩሲያ ድንገተኛና አስከቸኳይ ሚኒስቴር ገልጿል። | https://www.bbc.com/amharic/news-55383518 |
2health
| ኮሮናቫይረስ: እስራኤል የፋይዘር ክትባት ውጤታማ ሆኖ ማግኘቷን ገለፀች | ከእስራኤል የክትባት መርሃ ግብር የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የፋይዘር ክትባት የኮሮናቫይረስ ምልክቶችን 94 በመቶ የመከላከል አቅም አለው። ይህም ክትባቱ በክሊኒክ ውስጥ በተደረጉለት ሙከራዎች ወቅት የነበረውን ያህል ከፍተኛ ቁጥር ባለው ህዝብ ውስጥም ውጤታማ መሆኑን ያሳያል፡፡ በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች ከፍተኛ ውጤታማነት እያስገኘ መሆኑን የማህበረሰብ ጤና ሐኪሙ ፕሮፌሰር ሀጋይ ሌቪን ተናግረዋል። "በጣም ተጋላጭ ለሆኑት ቡድኖች ከፍተኛ የክትባት ሽፋን መስጠት ወሳኝ" ነበር ብለዋል፡፡ የእስራኤል ትልቁ የጤና ፈንድ ክላሊት በተመሳሰይ ዕድሜ እና የጤና ሁኔታ በሚገኙ 600,000 ክትባት በወሰዱ ሰዎች ላይ መልካም የሚባል ውጤት መገኘቱን፣ ክትባት ካልወሰዱ ሰዎች አንጻር እንደታየባቸው አመልክቷል፡፡ ክትባቱን በወሰዱት ዘንድ 94% ያነሰ ኢንፌክሽኖችን አግኝቷል፡፡ በተጨማሪም ክትባቱ ሁሉንም ማለት በሚቻል ሁኔታ ከባድ ህመሞችን ተከላክሏል፡፡ ውጤቱ ከ70 ዎቹ በላይ የሆኑትን ጨምሮ በሁሉም የዕድሜ ቡድኖች ውስጥ ተመሳሳይ ነበር፡፡ ይህ "እንደ እንግሊዝ ላሉት ሌሎች ሀገሮች" ስለ ክትባቱ ጠቃሚ መልዕክት ከማስተላለፉም በተጨማሪ፣ በቫይረሱ በጣም ሊታመሙ የሚችሉትን የህብረተሰብ ክፍሎች "በከፍተኛ" ሁኔታ ክትባቱን እንዲያገኙ ያግዛል ብለዋል ፕሮፌሰር ሌቪን፡፡ ፕሮፌሰሩ አክለውም የእንቅስቃሴ ገደቦችን ከማላላት በፊት ምን ያህል ቁጥር መከተብ እንደሚያስፈልግ መናገር አልችልም ብለዋል፡፡ "በመተላለፍ ላይ ያለው ተጽዕኖ ምን እንደሆነ እስካሁን አናውቅም" ብለዋል፡፡ ሆኖም ቢያንስ "ክትባቱ ግለሰብን ለመጠበቅ ጠቃሚ ነው" ሲሉም አክለዋል፡፡ የእስራኤል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መረጃን በመተንተን ላይ የሚገኙት ፕሮፌሰር ኤራን ሴጋል በበኩላቸው ክትባቱ በኮቪድ -19 ጉዳዮች ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ለመረዳት ሃገሪቱ ዕድሜያቸው ከ60ዎቹ በላይ ከሆኑት መካከል 80 በመቶውን መከተብ እንዳለባት ጠቁመዋል፡፡ እስራኤል የክትባት መርሃግብሩ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ለመመልከት በዓለም ላይ የመጀመሪያዋ ሀገር ብትሆንም፣ ወደዚህ ደረጃ ለመድረስ ከፍተኛ የሆነ ህዝብን ማዳረስ እና በርካታ ሳምንታትን ሊፈጅባት ይችላል፡፡ በመጀመሪያ ክትባት በተወሰዱ እና ዕድሜያቸው ከ60ዎቹ በላይ በሆናቸው እና ከዚያ ቀደም ነዋሪዎቻቸውን ባስከተቡ ከተሞች ውስጥ የቫይረሱ ስርጭት ሲቀንስ ታይቷል። ይህም ቀደም ባሉት የእንቅስቃሴ ገደቦች ወቅት ያልታየ ነው ተብሏል፡፡ ይህም ከእገዳው ይልቅ ክትባቱ ለቁጥሩ መቀነስ ትልቅ ሚና እንዳለው ጠንካራ ማስረጃ ይሰጣል፡፡ ፕሮፌሰር ሴጋል እንደሚያስጠነቀቁት ከሆነ ቁጥሩ ከሚጠበቀው በላይ በዝግታ የቀነሰ ሲሆን ምናልባትም በእስራኤል ውስጥ ዋነኛው የቫይረሱ ዝርያ በሆነው እና በብሪታንያ በተገኘው የኮሮናቫይረስ ዝርያ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ "በጣም ፈጣን" በሆነው በእስራኤል የክትባት መርሃ ግብር እንኳን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሊከላከሉት የማይችሉ ሲሆን በበሽታው ከተያዙም በጠና ሊታመሙ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ "አሁንም ቢሆን ከእንቅስቃሴ እገዳው ለመውጣት በጥንቃቄ መውጣት አለብን" ወይም ብዙ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ሆስፒታል መተኛት ሊገደዱ ይችላሉ ይላሉ፡ እስራኤል ከፍተኛ የሆነ የኢንፌክሽን ማዕበል እያጋጠማት እና በጥብቅ እገዳዎች ውስጥ ብትቆይም ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በላይ የሆኑ ሁሉ የመከተብ መብት ስላላቸው ትምህርት ቤቶች የመከፈት ተስፋ አላቸው ተብሏል፡፡ በፍልስጤም ግዛቶች ክትባቱን ማን መስጠት አለበት በሚለው ጥያቄ ሃገሪቱ ትችት ደርሶባታል፡፡ ለጤና ሠራተኞች እንዲደርስ እስራኤል በዌስት ባንክ እና በጋዛ ላሉት ፍልስጤሞች የተወሰነ መጠን ያለው ክትባት ማሳለፍ የጀመረችው ገና አሁን ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ከነዋሪዎቿ ለሩብ ያህሉ ሁለቱንም ዙር ክትባት ሰጥታለች፡፡ | ኮሮናቫይረስ: እስራኤል የፋይዘር ክትባት ውጤታማ ሆኖ ማግኘቷን ገለፀች ከእስራኤል የክትባት መርሃ ግብር የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የፋይዘር ክትባት የኮሮናቫይረስ ምልክቶችን 94 በመቶ የመከላከል አቅም አለው። ይህም ክትባቱ በክሊኒክ ውስጥ በተደረጉለት ሙከራዎች ወቅት የነበረውን ያህል ከፍተኛ ቁጥር ባለው ህዝብ ውስጥም ውጤታማ መሆኑን ያሳያል፡፡ በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች ከፍተኛ ውጤታማነት እያስገኘ መሆኑን የማህበረሰብ ጤና ሐኪሙ ፕሮፌሰር ሀጋይ ሌቪን ተናግረዋል። "በጣም ተጋላጭ ለሆኑት ቡድኖች ከፍተኛ የክትባት ሽፋን መስጠት ወሳኝ" ነበር ብለዋል፡፡ የእስራኤል ትልቁ የጤና ፈንድ ክላሊት በተመሳሰይ ዕድሜ እና የጤና ሁኔታ በሚገኙ 600,000 ክትባት በወሰዱ ሰዎች ላይ መልካም የሚባል ውጤት መገኘቱን፣ ክትባት ካልወሰዱ ሰዎች አንጻር እንደታየባቸው አመልክቷል፡፡ ክትባቱን በወሰዱት ዘንድ 94% ያነሰ ኢንፌክሽኖችን አግኝቷል፡፡ በተጨማሪም ክትባቱ ሁሉንም ማለት በሚቻል ሁኔታ ከባድ ህመሞችን ተከላክሏል፡፡ ውጤቱ ከ70 ዎቹ በላይ የሆኑትን ጨምሮ በሁሉም የዕድሜ ቡድኖች ውስጥ ተመሳሳይ ነበር፡፡ ይህ "እንደ እንግሊዝ ላሉት ሌሎች ሀገሮች" ስለ ክትባቱ ጠቃሚ መልዕክት ከማስተላለፉም በተጨማሪ፣ በቫይረሱ በጣም ሊታመሙ የሚችሉትን የህብረተሰብ ክፍሎች "በከፍተኛ" ሁኔታ ክትባቱን እንዲያገኙ ያግዛል ብለዋል ፕሮፌሰር ሌቪን፡፡ ፕሮፌሰሩ አክለውም የእንቅስቃሴ ገደቦችን ከማላላት በፊት ምን ያህል ቁጥር መከተብ እንደሚያስፈልግ መናገር አልችልም ብለዋል፡፡ "በመተላለፍ ላይ ያለው ተጽዕኖ ምን እንደሆነ እስካሁን አናውቅም" ብለዋል፡፡ ሆኖም ቢያንስ "ክትባቱ ግለሰብን ለመጠበቅ ጠቃሚ ነው" ሲሉም አክለዋል፡፡ የእስራኤል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መረጃን በመተንተን ላይ የሚገኙት ፕሮፌሰር ኤራን ሴጋል በበኩላቸው ክትባቱ በኮቪድ -19 ጉዳዮች ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ለመረዳት ሃገሪቱ ዕድሜያቸው ከ60ዎቹ በላይ ከሆኑት መካከል 80 በመቶውን መከተብ እንዳለባት ጠቁመዋል፡፡ እስራኤል የክትባት መርሃግብሩ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ለመመልከት በዓለም ላይ የመጀመሪያዋ ሀገር ብትሆንም፣ ወደዚህ ደረጃ ለመድረስ ከፍተኛ የሆነ ህዝብን ማዳረስ እና በርካታ ሳምንታትን ሊፈጅባት ይችላል፡፡ በመጀመሪያ ክትባት በተወሰዱ እና ዕድሜያቸው ከ60ዎቹ በላይ በሆናቸው እና ከዚያ ቀደም ነዋሪዎቻቸውን ባስከተቡ ከተሞች ውስጥ የቫይረሱ ስርጭት ሲቀንስ ታይቷል። ይህም ቀደም ባሉት የእንቅስቃሴ ገደቦች ወቅት ያልታየ ነው ተብሏል፡፡ ይህም ከእገዳው ይልቅ ክትባቱ ለቁጥሩ መቀነስ ትልቅ ሚና እንዳለው ጠንካራ ማስረጃ ይሰጣል፡፡ ፕሮፌሰር ሴጋል እንደሚያስጠነቀቁት ከሆነ ቁጥሩ ከሚጠበቀው በላይ በዝግታ የቀነሰ ሲሆን ምናልባትም በእስራኤል ውስጥ ዋነኛው የቫይረሱ ዝርያ በሆነው እና በብሪታንያ በተገኘው የኮሮናቫይረስ ዝርያ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ "በጣም ፈጣን" በሆነው በእስራኤል የክትባት መርሃ ግብር እንኳን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሊከላከሉት የማይችሉ ሲሆን በበሽታው ከተያዙም በጠና ሊታመሙ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ "አሁንም ቢሆን ከእንቅስቃሴ እገዳው ለመውጣት በጥንቃቄ መውጣት አለብን" ወይም ብዙ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ሆስፒታል መተኛት ሊገደዱ ይችላሉ ይላሉ፡ እስራኤል ከፍተኛ የሆነ የኢንፌክሽን ማዕበል እያጋጠማት እና በጥብቅ እገዳዎች ውስጥ ብትቆይም ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በላይ የሆኑ ሁሉ የመከተብ መብት ስላላቸው ትምህርት ቤቶች የመከፈት ተስፋ አላቸው ተብሏል፡፡ በፍልስጤም ግዛቶች ክትባቱን ማን መስጠት አለበት በሚለው ጥያቄ ሃገሪቱ ትችት ደርሶባታል፡፡ ለጤና ሠራተኞች እንዲደርስ እስራኤል በዌስት ባንክ እና በጋዛ ላሉት ፍልስጤሞች የተወሰነ መጠን ያለው ክትባት ማሳለፍ የጀመረችው ገና አሁን ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ከነዋሪዎቿ ለሩብ ያህሉ ሁለቱንም ዙር ክትባት ሰጥታለች፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/news-56073530 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ሪፐብሊካኖች በሚያደርጉት እጩ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሚዲያዎች እንዳይሳተፉ ተወሰነ | የአሜሪካ የሪፐብሊካን ፓርቲ በዚህ ወር እጩ ፕሬዚዳንቱን በይፋ ለመምረጥ እቅድ ይዟል። ይህ ምርጫም ሚዲያዎች እንዳይሳተፉበትና በዝግም እንደሚካሄድ ተገልጿል። የሪፐብሊካን ቃለ አቀባይ እንደተናገሩት ሚዲያ እንዳይሳተፍ የተወሰነው ከኮሮናቫይረስ መመሪያዎች ጋር በተያያዘ መሆኑንም አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል። በሰሜን ካሮላይና የሪፐብሊካን ልዑካን ተሰባስበውም እጩ ፕሬዚዳንቱን ዶናልድ ትራምፕን በይፋ እንደገና ይመርጣሉ። 336 የሚሆኑ ልዑካን በሰሜን ካሮላይና ግዛት፣ ቻርሎቴ ከተማ በዚህ ወር ይሰባሰባሉ። እነዚህ ልዑካን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ቁጥሩ በመገደቡ መገኘት ያልቻሉትን በሺዎች የሚቆጠሩ አባላትን ወክለው ይገኛሉ። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፓርቲያቸው ብቸኛ እጩ ተወዳዳሪ ሲሆኑ፤ እንደገና በይፋ መመረጣቸውም የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻቸውንም እንዲሁ በይፋ መጀመሩን የሚያበስር ነው ተብሏል። "ፓርቲያችን በፌደራል እንዲሁም በተለያዩ ግዛቶች የወጡ የኮሮናቫይረስ መመሪያዎችን በመከተልም ነው ስብሰባውን የሚሳተፉ ሰዎች ቁጥርን የወሰንነው" በማለት ቃለ አቀባይዋ ተናግረዋል። ይህ ውሳኔ ከዚህ በፊት ይደረጉ የነበሩ ስብሰባዎቸን አካሄድ የቀየረ ነው ተብሏል። ከዚህ ቀደም እንዲህ አይነቱ ስብሰባ የበርካታ ሚዲያዎችን ቀልብ የሚስብና ለህዝቡም መልዕክቶች ይፋ የሚሆኑበት ነበር። የሰሜን ካሮላይና አስተዳዳሪ በሚገኙት ሰዎች ብዛትና አካላዊ ርቀት ጋር ተያይዞ ስብሰባውን ወደ ሌላ ቦታ እንዲያደርጉት መጠየቀቻውን ተከትሎ ግንቦት ወር ላይ ወደ ጃክሰን፣ ፎሎሪዳ እንደሚደረግ ትራምፕ ተናግረው ነበር። ነገር ግን ወደ በኋላ ፍሎሪዳ ሊደረግ የነበረውን ስብሰባ በመሰረዝ ወደቀደመው እቅድ በመመለስ ሰሜን ካሮላይና እንዲካሄድ ተወስኗል።ግዛቲቷ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ያለምክንያት እያቀጣጠሉ ነው በማለት ወንጅለዋል። | ኮሮናቫይረስ፡ሪፐብሊካኖች በሚያደርጉት እጩ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሚዲያዎች እንዳይሳተፉ ተወሰነ የአሜሪካ የሪፐብሊካን ፓርቲ በዚህ ወር እጩ ፕሬዚዳንቱን በይፋ ለመምረጥ እቅድ ይዟል። ይህ ምርጫም ሚዲያዎች እንዳይሳተፉበትና በዝግም እንደሚካሄድ ተገልጿል። የሪፐብሊካን ቃለ አቀባይ እንደተናገሩት ሚዲያ እንዳይሳተፍ የተወሰነው ከኮሮናቫይረስ መመሪያዎች ጋር በተያያዘ መሆኑንም አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል። በሰሜን ካሮላይና የሪፐብሊካን ልዑካን ተሰባስበውም እጩ ፕሬዚዳንቱን ዶናልድ ትራምፕን በይፋ እንደገና ይመርጣሉ። 336 የሚሆኑ ልዑካን በሰሜን ካሮላይና ግዛት፣ ቻርሎቴ ከተማ በዚህ ወር ይሰባሰባሉ። እነዚህ ልዑካን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ቁጥሩ በመገደቡ መገኘት ያልቻሉትን በሺዎች የሚቆጠሩ አባላትን ወክለው ይገኛሉ። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፓርቲያቸው ብቸኛ እጩ ተወዳዳሪ ሲሆኑ፤ እንደገና በይፋ መመረጣቸውም የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻቸውንም እንዲሁ በይፋ መጀመሩን የሚያበስር ነው ተብሏል። "ፓርቲያችን በፌደራል እንዲሁም በተለያዩ ግዛቶች የወጡ የኮሮናቫይረስ መመሪያዎችን በመከተልም ነው ስብሰባውን የሚሳተፉ ሰዎች ቁጥርን የወሰንነው" በማለት ቃለ አቀባይዋ ተናግረዋል። ይህ ውሳኔ ከዚህ በፊት ይደረጉ የነበሩ ስብሰባዎቸን አካሄድ የቀየረ ነው ተብሏል። ከዚህ ቀደም እንዲህ አይነቱ ስብሰባ የበርካታ ሚዲያዎችን ቀልብ የሚስብና ለህዝቡም መልዕክቶች ይፋ የሚሆኑበት ነበር። የሰሜን ካሮላይና አስተዳዳሪ በሚገኙት ሰዎች ብዛትና አካላዊ ርቀት ጋር ተያይዞ ስብሰባውን ወደ ሌላ ቦታ እንዲያደርጉት መጠየቀቻውን ተከትሎ ግንቦት ወር ላይ ወደ ጃክሰን፣ ፎሎሪዳ እንደሚደረግ ትራምፕ ተናግረው ነበር። ነገር ግን ወደ በኋላ ፍሎሪዳ ሊደረግ የነበረውን ስብሰባ በመሰረዝ ወደቀደመው እቅድ በመመለስ ሰሜን ካሮላይና እንዲካሄድ ተወስኗል።ግዛቲቷ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ያለምክንያት እያቀጣጠሉ ነው በማለት ወንጅለዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-53627157 |
5sports
| ዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች፡ ፈረንሳይ ድል ሲቀናት አርጀንቲና እጅ ሰጥታለች | የአምናዋ የዓለም ሻምፒዮና ፈረንሳይ ከመመራት ተነስታ 4 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት አውስትራሊያን በማሸነፍ አጀማመሯን አሳምራለች። ፈረንሳይ እንደካሪም ቤንዜማ፣ ንጎሎ ካንቴ እና ፖል ፖግባ ያሉ ኮከቦቿን በጉዳት አጥታ ነው ወደ ዓለም ዋንጫው ያቀናችው። ትላንት በመጀመሪያው የምድብ ጨዋታዋ በአውስትራሊያ ቀድሞ ጎል ተቆጥሮባታል። ክሬግ ጉድዊን ነው ጎሏን ለቢጫ ለባሾቹ ያስቆጠረው። አድሪዬ ራቢዮ ሰማያዊዎቹን በ27ኛው ደቂቃ አቻ አደረገ። ኦሊቨር ዥሩ ሁለተኛዋን ጎል አስቆጥሮ ፈረንሳይ 2 ለ 0 በምምራት ወደ መልበሻ ክፍ አመሩ። ምሽቱን ድንቅ ሆኖ ያመሸው ክሊያን ምባፔ ሦስተኛዋን ጎል አስቆጥሯል። ዥሩ አራተኛዋን ጎል አስቆጥሮ ጨዋታው 4 ለ 1 ተጠናቋል። ዥሩ ለብሔራዊ ቡድኑ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ቁጥር 51 አድርሷል። በዚህም ከቲዬሪ ሄነሪ እኩል ለመሆን በቅቷል። በዚሁ ምድብ አራት የሚገኙት ቱኒዝያ እና ዴንማርክ ያለምንም ጎል አቻ ተለያይተዋል። በርካታ የእንግሊዝ ፕሪሚር ሊግ ተጫዋቾችን ያሰለፉት ዴንማርኮች በኤጁኬሽን ስታዲየም ጠንካራ ፉክክር ገጥሟቸዋል። ሁለቱም ቡድኖች ያስቆጠሯቸው ጎሎች ከጨዋታ ውጪ በሚል ተሽረዋል። በ95 ደቂቃ ኳስ ፍጹም ቅጣት ክልል ውስጥ በእጅ ተነክቷል በሚል ዳኛው ሜዳ ዳር የሚገኘውን ቴሌቪዥን ደጋግመው ቢመለከቱም ፍጹም ቅጣት ምቱን ለዴንማርክ ሳይሰጡ ቀርተዋል። የምድብ ሦስት ጨዋታዎችም ትላንት ነው የተከናወኑት። በእግር ኳስ ታሪክ የጎላ ስም የሌላት ሳዑዲ አረቢያ ለዋንጫው የምትገመተውን አርጀንቲናን ማሸነፍ ችላለች። ሳዑዲዎች በሉሳይል ስታዲየም ባደረጉት የመጀመሪያ ጨዋታቸው አንድ ለባዶ ከመመራት በመነሳት ሁለት ግቦችን አስቆጥረው ምድብ ሦስትን መምራት ጀምረዋል። አርጀንቲና ያገኘችውን ፍጹም ቅጣት ምት ሊዮኔል ሜሲ አስቆጥሮ አገሩን ቀዳሚ ማድረግ ችሎ ነበር። በአርጀንቲና በኩል በርካታ ግቦችን ለማስቆጠር ባደረጓቸው ተደጋጋሚ ጥረቶች ሦስት ግቦችን ማስቆጠር ቢችሉም ከጨዋታ ውጪ በመሆናቸው ተሰርዘዋል። ሁለተኛው አጋማሽ ተጀምሮ በ10 ደቂቃ ውስጥ ሳዑዲ ውጤት ቀያሪውን ግብ አስቆጠረች። ሳሌህ አል-ሼህሪ የመጀመሪያዋን ጎል ሲያስቆጥር ሳሌም አል ዳወሳሪ ያስቆጠራት ግብ ቡድኑን አሸናፊ አድርጋለች። የምድቡ ደካማ ቡድን በሆነችው ሳዑዲ የተሸነፈችው አርጀንቲና ቀጣይ ሁለት የምድብ ጨዋታዎች በውድድሩ የሚኖራትን ዕጣ ፈንታ ይወስናሉ። ሳዑዲ በታሪኳ ለዓለም ዋንጫ ጥሎ ማለፍ የበቃችው በ1994 ነበር። ሪያድ ደስታዋን ለመግለጽ አንድ ቀን አይበቃኝም ብላለች። ልዑል ሳልማን ረቡዕም ብሔራዊ በዓል ነው ሲሉ ደስታው እንዲራዘም ፈቃዳቸው ሆኗል። ሜሲ እና አርጀንቲና ቀጣይ ጨዋታቸውን በሐዘን ለመጠበቅ ተገደዋል። በምድቡ ሌላ ጨዋታ ሜክሲኮ እና ፖላንድ ያለ ጎል አቻ ተለያይተዋል። የፖላንዱ አምበል እና የጎል ቀበኛ ሮበርት ሌዋንዶውስኪ አገሩን ለድል ልታበቃ የምትችል ፍጹም ቅጣት ምት አግኝቶ ሳይጠቀምባት ቀርቷል። በስታዲየም 974 በተደረገው ጨዋታ የሜክሲኮው ግብ ዘብ ጉሌርሞ ኦቾአ ፍጹም ቅጣት ምቱን አድኗል። በርካታ የሜክሲኮ ደጋፊዎች የታደሙበት ጨዋታ ይህ ነው የሚባል ፉክክር ሳይታይበት ተጠናቋል። ምድቡን ሳዑዲ ስትመራ ፖላንድ እና ሜክሲኮ ይከተላሉ። ምድቡ ግርጌ ላይ የምትገኘው አርጀንቲና በቀጣይ ከሜክሲኮ ትጫወታለች። የዓለም ዋንጫው ዛሬም ቀጥሎ ይካሄዳል። የምድብ አምስት እና ስድስት ጨዋታዎች ዛሬ ይከናወናሉ። ምድብ አምስት ላይ ጀርመን እና ጃፓን ይገናኛሉ። ሁለቱ ቡድኖች በኻሊፋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም 10 ሰዓት ጨዋታቸውን ይጀምራሉ። በዚሁ ምድብ የሚገኙት ስፔን እና ኮስታሪካም ጨዋታቸውን ያከናውናሉ። የአል ቱማማ ስታዲየም የሁለቱን ቡድኖች ጨዋታ አንድ ሰዓት ላይ ያስተናግዳል። በምድብ ስድስት አፍሪካዊቷ ሞሮኮ ከክሮሽያ ትጫወታለች። ጨዋታው ቀን ሰባት ሰዓት በአል ባይት ስታዲየም ይከናወናል። ቤልጂየም ደግሞ ካናዳን ትገጥማለች። ምሽት አራት ሰዓት የሚከናወነው ጨዋታ በአህማድ ቢን አሊ ስታዲየም ይደረጋል። | ዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች፡ ፈረንሳይ ድል ሲቀናት አርጀንቲና እጅ ሰጥታለች የአምናዋ የዓለም ሻምፒዮና ፈረንሳይ ከመመራት ተነስታ 4 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት አውስትራሊያን በማሸነፍ አጀማመሯን አሳምራለች። ፈረንሳይ እንደካሪም ቤንዜማ፣ ንጎሎ ካንቴ እና ፖል ፖግባ ያሉ ኮከቦቿን በጉዳት አጥታ ነው ወደ ዓለም ዋንጫው ያቀናችው። ትላንት በመጀመሪያው የምድብ ጨዋታዋ በአውስትራሊያ ቀድሞ ጎል ተቆጥሮባታል። ክሬግ ጉድዊን ነው ጎሏን ለቢጫ ለባሾቹ ያስቆጠረው። አድሪዬ ራቢዮ ሰማያዊዎቹን በ27ኛው ደቂቃ አቻ አደረገ። ኦሊቨር ዥሩ ሁለተኛዋን ጎል አስቆጥሮ ፈረንሳይ 2 ለ 0 በምምራት ወደ መልበሻ ክፍ አመሩ። ምሽቱን ድንቅ ሆኖ ያመሸው ክሊያን ምባፔ ሦስተኛዋን ጎል አስቆጥሯል። ዥሩ አራተኛዋን ጎል አስቆጥሮ ጨዋታው 4 ለ 1 ተጠናቋል። ዥሩ ለብሔራዊ ቡድኑ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ቁጥር 51 አድርሷል። በዚህም ከቲዬሪ ሄነሪ እኩል ለመሆን በቅቷል። በዚሁ ምድብ አራት የሚገኙት ቱኒዝያ እና ዴንማርክ ያለምንም ጎል አቻ ተለያይተዋል። በርካታ የእንግሊዝ ፕሪሚር ሊግ ተጫዋቾችን ያሰለፉት ዴንማርኮች በኤጁኬሽን ስታዲየም ጠንካራ ፉክክር ገጥሟቸዋል። ሁለቱም ቡድኖች ያስቆጠሯቸው ጎሎች ከጨዋታ ውጪ በሚል ተሽረዋል። በ95 ደቂቃ ኳስ ፍጹም ቅጣት ክልል ውስጥ በእጅ ተነክቷል በሚል ዳኛው ሜዳ ዳር የሚገኘውን ቴሌቪዥን ደጋግመው ቢመለከቱም ፍጹም ቅጣት ምቱን ለዴንማርክ ሳይሰጡ ቀርተዋል። የምድብ ሦስት ጨዋታዎችም ትላንት ነው የተከናወኑት። በእግር ኳስ ታሪክ የጎላ ስም የሌላት ሳዑዲ አረቢያ ለዋንጫው የምትገመተውን አርጀንቲናን ማሸነፍ ችላለች። ሳዑዲዎች በሉሳይል ስታዲየም ባደረጉት የመጀመሪያ ጨዋታቸው አንድ ለባዶ ከመመራት በመነሳት ሁለት ግቦችን አስቆጥረው ምድብ ሦስትን መምራት ጀምረዋል። አርጀንቲና ያገኘችውን ፍጹም ቅጣት ምት ሊዮኔል ሜሲ አስቆጥሮ አገሩን ቀዳሚ ማድረግ ችሎ ነበር። በአርጀንቲና በኩል በርካታ ግቦችን ለማስቆጠር ባደረጓቸው ተደጋጋሚ ጥረቶች ሦስት ግቦችን ማስቆጠር ቢችሉም ከጨዋታ ውጪ በመሆናቸው ተሰርዘዋል። ሁለተኛው አጋማሽ ተጀምሮ በ10 ደቂቃ ውስጥ ሳዑዲ ውጤት ቀያሪውን ግብ አስቆጠረች። ሳሌህ አል-ሼህሪ የመጀመሪያዋን ጎል ሲያስቆጥር ሳሌም አል ዳወሳሪ ያስቆጠራት ግብ ቡድኑን አሸናፊ አድርጋለች። የምድቡ ደካማ ቡድን በሆነችው ሳዑዲ የተሸነፈችው አርጀንቲና ቀጣይ ሁለት የምድብ ጨዋታዎች በውድድሩ የሚኖራትን ዕጣ ፈንታ ይወስናሉ። ሳዑዲ በታሪኳ ለዓለም ዋንጫ ጥሎ ማለፍ የበቃችው በ1994 ነበር። ሪያድ ደስታዋን ለመግለጽ አንድ ቀን አይበቃኝም ብላለች። ልዑል ሳልማን ረቡዕም ብሔራዊ በዓል ነው ሲሉ ደስታው እንዲራዘም ፈቃዳቸው ሆኗል። ሜሲ እና አርጀንቲና ቀጣይ ጨዋታቸውን በሐዘን ለመጠበቅ ተገደዋል። በምድቡ ሌላ ጨዋታ ሜክሲኮ እና ፖላንድ ያለ ጎል አቻ ተለያይተዋል። የፖላንዱ አምበል እና የጎል ቀበኛ ሮበርት ሌዋንዶውስኪ አገሩን ለድል ልታበቃ የምትችል ፍጹም ቅጣት ምት አግኝቶ ሳይጠቀምባት ቀርቷል። በስታዲየም 974 በተደረገው ጨዋታ የሜክሲኮው ግብ ዘብ ጉሌርሞ ኦቾአ ፍጹም ቅጣት ምቱን አድኗል። በርካታ የሜክሲኮ ደጋፊዎች የታደሙበት ጨዋታ ይህ ነው የሚባል ፉክክር ሳይታይበት ተጠናቋል። ምድቡን ሳዑዲ ስትመራ ፖላንድ እና ሜክሲኮ ይከተላሉ። ምድቡ ግርጌ ላይ የምትገኘው አርጀንቲና በቀጣይ ከሜክሲኮ ትጫወታለች። የዓለም ዋንጫው ዛሬም ቀጥሎ ይካሄዳል። የምድብ አምስት እና ስድስት ጨዋታዎች ዛሬ ይከናወናሉ። ምድብ አምስት ላይ ጀርመን እና ጃፓን ይገናኛሉ። ሁለቱ ቡድኖች በኻሊፋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም 10 ሰዓት ጨዋታቸውን ይጀምራሉ። በዚሁ ምድብ የሚገኙት ስፔን እና ኮስታሪካም ጨዋታቸውን ያከናውናሉ። የአል ቱማማ ስታዲየም የሁለቱን ቡድኖች ጨዋታ አንድ ሰዓት ላይ ያስተናግዳል። በምድብ ስድስት አፍሪካዊቷ ሞሮኮ ከክሮሽያ ትጫወታለች። ጨዋታው ቀን ሰባት ሰዓት በአል ባይት ስታዲየም ይከናወናል። ቤልጂየም ደግሞ ካናዳን ትገጥማለች። ምሽት አራት ሰዓት የሚከናወነው ጨዋታ በአህማድ ቢን አሊ ስታዲየም ይደረጋል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cn0491jyxz8o |
5sports
| አሠልጣኝ ኤሪክሰንን ጨምሮ ታዋቂ ተጫዋቾችን ያጭበረበረው ደላላ | ለእግር ኳስ ደጋፊዎች እንደ መጀመሪያዋ የውድድር ዘመን ጨዋታ ጣፋጭ የለም። በጉጉት የጠበቁት ሊግ አሊያም የዋንጫ ፍልሚያ ሲጀምር የምትታየው የመጀመሪያዋ ጨዋታ እንደ ጨቅላ የሚያስቦርቅ ነገር አላት። ጊዜው 2009 በፈረንጆቹ። በእንግሊዝ ሊግ ሁለት የሚጫወተው ኖትስ ካውንቲ የ09/10 የውድድር ዘመን የመጀመሪያ ጨዋታውን እያካሄደ ነው። ኖትስ ካውንቲ ከዚህ ጨዋታ አንድ ወር ቀድሞ ሙንቶ ፋይናንስ በሚባል ጥምር ተቋም ተገዝቷል። ሙንቶ፤ በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ኖትስ ካውንቲን ከፕሪሚዬር ሊጉ ዝቅ ብሎ ለሚደረው የቻምፒዮንሺፕ ውድድር ለማድረስ ቃል ገብቷል። እኔን ጨምሮ የዕድሜ መሰሎቼ ወጣት የኖትስ ደጋፊዎች የከተማ ተቀናቃኛችን ኖቲንግሃም ፎረስትን ጥለን ወደላይኛው ሊግ ስናል እያለምን ነው። ነገር ግን ነባር የቡድኑ ደጋፊዎች ይህ የአዲሱ የክለቡ ባለቤት ቃል ብዙም የተዋጠላቸው አይመስልም። ከጥቂት ቀናት በኋላ እውቁ አሠልጣኝ ስቬን-ጎራን ኤሪክሰን የክለቡ ዳይሬክተር ሆነው ተቀጠሩ። እንግሊዝን ለዓለምና አውሮፓ ዋንጫ ያደረሱት አሠልጣኝ ካሜራው መብራቱን እየለቀቀባቸው ለዓለም ሕዝብ ስለክለቡ መግለጫ ሰጡ። ይሄኔ የክለቡ ጥንታዊ ደጋፊዎች ሳይቀሩ ሕልማቸው ለመለመ። ኖትስ ካውንቲ አይደለም ለቻምፒዮን ሺፕ ለፕሪሚዬር ሊግ የመወዳደር አቅም አለው ሲሉ ይፎክሩ ጀመር። አዎ፤ የምናወራው ከሊግ 2 ላለመውረድ ስለሚታገለው፤ የደረጃ ሠንጠረዡ አጋማሽ ለመድረስ ስለሚንጠራራው ኖትስ ካውንቲ ነው። እነሆ ኖትስ ካውንቲ በኤሪክሰን እየተመራ ወደ ፕሪሚዬር ሊግ ሊገሰግስ ነው። 9 ሺህ ሰው የሚያስተናግደው ሜዶው ሌን ጠጠር ቢወረወር መሬት እንዳያደርፍ ሆኖ ሞልቷል። ኤሪክሰን በተዘጋጀለቻው የክብር መንበር ተሰይመው ቡድናቸውን ይመለከታሉ። አዲሱ ፈራሚ ሊ ሂዩስ ብቃቱን ለማሳየት ቋምጧል። ኖትስ ካውንቲ ከብራድፈርድ ሲቲ። ጨዋታው ተጀመረ። የመጀመሪያው ጎል - ኖትስ ካውንቲ። ስታድየሙ በአንድ እግሩ ቆመ። ሊ ሂዩስ ጎል አገባ። ደገመ። ደጋገመ። በመጀመሪያ ጨዋታ ሶስታ [ሃትሪክ] ሠራ። ፍልሚያው በኖትስ ካውንቲ 5 ለምንም አሸናፊነት ተጠቀቀ። በኖትስ ካውንቲ ደጋፊነቴ ከተደስትኩባቸው ቀናት መካከል ይህ ከቤተሰቦቼ ጋር ያየሁት ፍልሚያ በፍፁም ከአእምሮዬ አይጠፋም። ነገር ግን ሁሉም ነገር ሕልም ነበር። ምንም እንኳ የዛኔ ነገሩ ባይገባኝም ከመካከለኛው ምስራቅ ናቸው የተባሉት ቱጃር የክለቡ ባለቤቶች ሐሰት ነበሩ። ባለቤቶቹ ካዝና ውስጥ አሉ የተባሉት ሚሊዮኖች ረብጣዎች የውሃ ሽታ ሆኑ። የደጋፊዎች ሕልም መክኖ ቀረ። ክለቡ፣ ደጋፊዎቹ እንዲሁም ኤሪክሰን የአጭበርባሪው ረስል ኪንግ የቅጥፈት ስልት ሰለባ ሆኑ። እነሆ ይህ ከሆነ ከአስር ዓመት በኋላ እኔና ሌሎቹ የሙያ አጋሮቼ ምንድነው የተፈጠረው የሚለውን ለመመርመር ተነሳን። ያገኘነውን ነገር ግን ካሰብነውም በላይ ውስብስብ ነው። ዓመታት የወሰደ፤ ከኖቲንግሃም በጀርዚ አድርወጎ ባህሬይንን ተሻግሮ በዱባይ በኩል ሰሜን ኮሪያ የዘለቀ የሐሰት፣ ስግብግብነት ታሪክ። ደጋፊዎቹ ክለቡ ሲሸጥ ባለቤቱ ማነው ከየትስ ነው የመጣው፤ ሚሊዮን ዶላሮቹስ የማናቸው፤ ብለው አልጠየቁም። ይባስ ብሎ ኤሪክሰን የክለቡ የእግር ኳስ ዳይሬክተር ሆነው ሲፈርሙ ሁሉም ጮቤ ረገጠ። ስዊድናዊው አሠልጣኝ ቀጥታ ወደ ሥራ ነው የገቡት። ጊዜ ሳይፈጁ ተጫዋቾች ማስፈረም ጀመሩ። አንድ ካስፐር ሽማይክል የሚባል ወጣትና ተስፈኛ ግብ ጠባቂ ለማምጣት እንዳቀዱም ተናገሩ። ሽማይክል ሊድስ ዩናይትድን ከመቀላቀሉ በፊት ለኖትስ ካውንቲ አንድ ዓመት ተጫውቷል። ኤሪክሰን ወደ ኖትስ ካውንቲ ከመምጣታቸው በፊት ማንቸስተር ሲቲን አሠልጥነዋል። ይሄኔ ነው የዝነኛው ማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ ፒተር ሽማይክል ልጅ ካስፐር ሽማይክልን የተመለከቱት። ካስፐር በወቅቱ እንደአሞራ ተወርውሮ ኳስ የሚቀልበው ጆ ሃርትን ረትቶ ቋሚ ተሰላፊ መሆን ባለመቻሉ ወደሌላ ክለብ መዛወርን ያልማል። ኤሪክሰን ካስፐርና አባቱን ፒተር ሽማይክልን ካሳመኑ በኋላ ዓመታዊ ደሞዝ 1.5 ሚሊዮን ዩሮ እንዲባለ አስማምተው ለአምስት ዓመት አስፈረሙት። ምን ሽማይክል ብቻ ኖትስ ካውንቲ ማስፈረም የማይችለው እግር ኳሰኛ እንደሌለ ይወራ ጀመር። ብራዚላዊው ተከላካይ ሮቤርቶ ካርሎስ፤ ፖርቹጋላዊው ኮከብ ሉዊዝ ፊጎ የጡረታ ዘመናቸውን በኖትስ ካውንቲ ሊያሳልፉ ይችላሉ የሚሉ ወሬዎች ይናፈሱ ጀመር። ነገር ግን የብዙዎችን ቀልብ ገዝቶ የነበረው የ34 ዓመቱ እንግሊዛዊ ዴቪድ ቤካም ኤልኤ ጋላክሲን ጥሎ ሊመጣ ነው የሚለው የከተማው ወሬ ነበር። በዚህ ሁሉ ወሬ መሃል የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ካያቸው ድንቅ ተከላካዮች መካከል አንዱ ሆነው የ34 ዓመቱ ሶል ካምፕቤል ወደ ሜዶው ሌን ዘለቀ። ካምፕቤል ከአንድ ወር በኋላ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከሞርካምቤ ጋር በነበረው ፍልሚያ አደረገ። ከቤተሰቦቼ ጋር ወደ ተፋላሚዎቻችን ሜዳ ሄደን ጨዋታውን ተመለከትን። ውጤቱ ግን አስካፊ ነበር። ኖትስ ካውንቲ 2-1 ተረታ። ደጋፊዎች መቸም ሽንፈት ያለ ነው፤ ካምፕቤልን ወደ አቋሙ መመለሱ አይቀሬ ነው ብለው ተስፋ ሰንቀው ወደ ቤታቸው ገቡ። ቢሆንም ከጥቂት ቀናት በኋላ ሶል ካምፕቤል ከኖትስ ጋር ያለውን ስምምነት አፍርሶ መልቀቁ ተሰማ። ይህ ዜና ከመሰማቱ ከጥቂት ቀናት በኋላ ደግሞ ዘ ሰን የተባለው ጋዜጣ ኖትስ ካውንቲን የደለለው ረስል ኪንግ የተባለው ግለሰብ በ1990ዎቹ በማጭበርበር ወንጀል ተከሶ ሁለት ዓመት ከርቸሌ ከርሞ እንደወጣ አስነበበ። ክለቡ፤ ኪንግ "ስትራቴጂያዊ አማካሪ" ነው እንጂ ከዚያ ዘለለ ሚና የለውም ሲል ዘገባውን አጣጣለ። ነገር ግን እውነታው ይህ አልነበረም። ኪንግ፤ የባህሬይን ንጉሣዊ ቤተሰብ የውጭ ሃብት ተቆጣጣሪ ነኝ በማለት ከለንደን ኢንቨስትመን ባንክን ያታልል ኖሯል። ረስል ኪንግ ከዚሁ ባንክ ማረጋገጫ አስፅፎ ነው የኖትስ ካውንቲ ባለቤትነቱን ያረጋገጠው። በተመሳሳይ ሰዓት የአንድ ግዙፍ የማዕድን አውጭ ኩባንያ ባለቤት ነኝ በማለት ከሰሜን ኮሪያ መንግሥት ጋር የድንጋይ ከሰልና ወርቅ ለማውጣት ስምምነት ይገባል። ይሄን የምርመራ ዘገባ ስናዋቅር ያገኘናቸው ኤሪክሰን ግለሰቡ አግባብቶ ወደ ሰሜን ኮሪያ እንደወሰዳቸውና የሃገሪቱ ባለሥልጣናት ለ2010 ዓለም ዋንጫ እንድናልፍ ደካማ ምድብ ውስጥ መድቡን ብለው እንደጠየቋቸው ነግረውናል። ኤሪክሰን ይህን በፍፁም ማድረግ እንደማይችሉ ለሰሜን ኮሪያ ባለሥልጣናት እንደነገራቸው ያክላሉ። ከሰሜን ኮሪያ ጋር የማዕድን ማውጣት ስምምነት የገባው ኪንግ ይህን ተጠቅሞ ኩባንያው በአክሲዮን ገበያ እንደሚዘገብ መጣር ይጀምራል። ነገር ግን ይህ አልተሳካለትም። ይሄኔ ኪንግ ወደ ባሕሬይን ይበርና በመካከለኛው ምስራቅ እንደ ፋይናንሻል ታይምስ ያለ ጋዜጣ ለመመሥረት ያቅዳል። ኪንግ የኋላ ኋላ የማጭበርበር ሂደቱ አልሳካ ብሎት በፖሊስ ይፈለግ ጀመረ። በስተመጨረሻም የካቴና ሲሳይ ሆኖ በአሜሪካዋ ከተማ ጀርዚ በፈፀመው ወንጀል ምክንያት ወደ ከርቸሌ ይላካል። ሰውየው ባለፈው ዓመት ከእሥር ተለቋል። ስለሰራነው የምርመራ ዘገባ ምላሽ ካለው በሚል ጥያቄ ብናቀርብለትም ፈቃደኛ ሊሆን አልቻለም። በኪንግ ተጭበርብሮ ብሩን ሲዘራ የነበረው ኖትስ ካውንቲ ሁለት ጊዜ ሙሉ በሙሉ ተዘግቶ ታሪክ ሆኖ ከመቅረት ተርፎ አሁን በአዲስ ባለቤት እጅ ወድቋል። እኔን ጨምሮ በርካታ ደጋፊዎች ክለባችን ባለመሸጡ ደስተኛ ብንሆንም ያንን የስድስት ወር የደስታ የሃዘን ጊዜ መቼም አንረሳውም። ምንድነው የሆነው? ሕልም ነው? ወይስ እውነት? ኖትስ አሁን በናሽናል ሊግ ውድድር ስድስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። | አሠልጣኝ ኤሪክሰንን ጨምሮ ታዋቂ ተጫዋቾችን ያጭበረበረው ደላላ ለእግር ኳስ ደጋፊዎች እንደ መጀመሪያዋ የውድድር ዘመን ጨዋታ ጣፋጭ የለም። በጉጉት የጠበቁት ሊግ አሊያም የዋንጫ ፍልሚያ ሲጀምር የምትታየው የመጀመሪያዋ ጨዋታ እንደ ጨቅላ የሚያስቦርቅ ነገር አላት። ጊዜው 2009 በፈረንጆቹ። በእንግሊዝ ሊግ ሁለት የሚጫወተው ኖትስ ካውንቲ የ09/10 የውድድር ዘመን የመጀመሪያ ጨዋታውን እያካሄደ ነው። ኖትስ ካውንቲ ከዚህ ጨዋታ አንድ ወር ቀድሞ ሙንቶ ፋይናንስ በሚባል ጥምር ተቋም ተገዝቷል። ሙንቶ፤ በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ኖትስ ካውንቲን ከፕሪሚዬር ሊጉ ዝቅ ብሎ ለሚደረው የቻምፒዮንሺፕ ውድድር ለማድረስ ቃል ገብቷል። እኔን ጨምሮ የዕድሜ መሰሎቼ ወጣት የኖትስ ደጋፊዎች የከተማ ተቀናቃኛችን ኖቲንግሃም ፎረስትን ጥለን ወደላይኛው ሊግ ስናል እያለምን ነው። ነገር ግን ነባር የቡድኑ ደጋፊዎች ይህ የአዲሱ የክለቡ ባለቤት ቃል ብዙም የተዋጠላቸው አይመስልም። ከጥቂት ቀናት በኋላ እውቁ አሠልጣኝ ስቬን-ጎራን ኤሪክሰን የክለቡ ዳይሬክተር ሆነው ተቀጠሩ። እንግሊዝን ለዓለምና አውሮፓ ዋንጫ ያደረሱት አሠልጣኝ ካሜራው መብራቱን እየለቀቀባቸው ለዓለም ሕዝብ ስለክለቡ መግለጫ ሰጡ። ይሄኔ የክለቡ ጥንታዊ ደጋፊዎች ሳይቀሩ ሕልማቸው ለመለመ። ኖትስ ካውንቲ አይደለም ለቻምፒዮን ሺፕ ለፕሪሚዬር ሊግ የመወዳደር አቅም አለው ሲሉ ይፎክሩ ጀመር። አዎ፤ የምናወራው ከሊግ 2 ላለመውረድ ስለሚታገለው፤ የደረጃ ሠንጠረዡ አጋማሽ ለመድረስ ስለሚንጠራራው ኖትስ ካውንቲ ነው። እነሆ ኖትስ ካውንቲ በኤሪክሰን እየተመራ ወደ ፕሪሚዬር ሊግ ሊገሰግስ ነው። 9 ሺህ ሰው የሚያስተናግደው ሜዶው ሌን ጠጠር ቢወረወር መሬት እንዳያደርፍ ሆኖ ሞልቷል። ኤሪክሰን በተዘጋጀለቻው የክብር መንበር ተሰይመው ቡድናቸውን ይመለከታሉ። አዲሱ ፈራሚ ሊ ሂዩስ ብቃቱን ለማሳየት ቋምጧል። ኖትስ ካውንቲ ከብራድፈርድ ሲቲ። ጨዋታው ተጀመረ። የመጀመሪያው ጎል - ኖትስ ካውንቲ። ስታድየሙ በአንድ እግሩ ቆመ። ሊ ሂዩስ ጎል አገባ። ደገመ። ደጋገመ። በመጀመሪያ ጨዋታ ሶስታ [ሃትሪክ] ሠራ። ፍልሚያው በኖትስ ካውንቲ 5 ለምንም አሸናፊነት ተጠቀቀ። በኖትስ ካውንቲ ደጋፊነቴ ከተደስትኩባቸው ቀናት መካከል ይህ ከቤተሰቦቼ ጋር ያየሁት ፍልሚያ በፍፁም ከአእምሮዬ አይጠፋም። ነገር ግን ሁሉም ነገር ሕልም ነበር። ምንም እንኳ የዛኔ ነገሩ ባይገባኝም ከመካከለኛው ምስራቅ ናቸው የተባሉት ቱጃር የክለቡ ባለቤቶች ሐሰት ነበሩ። ባለቤቶቹ ካዝና ውስጥ አሉ የተባሉት ሚሊዮኖች ረብጣዎች የውሃ ሽታ ሆኑ። የደጋፊዎች ሕልም መክኖ ቀረ። ክለቡ፣ ደጋፊዎቹ እንዲሁም ኤሪክሰን የአጭበርባሪው ረስል ኪንግ የቅጥፈት ስልት ሰለባ ሆኑ። እነሆ ይህ ከሆነ ከአስር ዓመት በኋላ እኔና ሌሎቹ የሙያ አጋሮቼ ምንድነው የተፈጠረው የሚለውን ለመመርመር ተነሳን። ያገኘነውን ነገር ግን ካሰብነውም በላይ ውስብስብ ነው። ዓመታት የወሰደ፤ ከኖቲንግሃም በጀርዚ አድርወጎ ባህሬይንን ተሻግሮ በዱባይ በኩል ሰሜን ኮሪያ የዘለቀ የሐሰት፣ ስግብግብነት ታሪክ። ደጋፊዎቹ ክለቡ ሲሸጥ ባለቤቱ ማነው ከየትስ ነው የመጣው፤ ሚሊዮን ዶላሮቹስ የማናቸው፤ ብለው አልጠየቁም። ይባስ ብሎ ኤሪክሰን የክለቡ የእግር ኳስ ዳይሬክተር ሆነው ሲፈርሙ ሁሉም ጮቤ ረገጠ። ስዊድናዊው አሠልጣኝ ቀጥታ ወደ ሥራ ነው የገቡት። ጊዜ ሳይፈጁ ተጫዋቾች ማስፈረም ጀመሩ። አንድ ካስፐር ሽማይክል የሚባል ወጣትና ተስፈኛ ግብ ጠባቂ ለማምጣት እንዳቀዱም ተናገሩ። ሽማይክል ሊድስ ዩናይትድን ከመቀላቀሉ በፊት ለኖትስ ካውንቲ አንድ ዓመት ተጫውቷል። ኤሪክሰን ወደ ኖትስ ካውንቲ ከመምጣታቸው በፊት ማንቸስተር ሲቲን አሠልጥነዋል። ይሄኔ ነው የዝነኛው ማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ ፒተር ሽማይክል ልጅ ካስፐር ሽማይክልን የተመለከቱት። ካስፐር በወቅቱ እንደአሞራ ተወርውሮ ኳስ የሚቀልበው ጆ ሃርትን ረትቶ ቋሚ ተሰላፊ መሆን ባለመቻሉ ወደሌላ ክለብ መዛወርን ያልማል። ኤሪክሰን ካስፐርና አባቱን ፒተር ሽማይክልን ካሳመኑ በኋላ ዓመታዊ ደሞዝ 1.5 ሚሊዮን ዩሮ እንዲባለ አስማምተው ለአምስት ዓመት አስፈረሙት። ምን ሽማይክል ብቻ ኖትስ ካውንቲ ማስፈረም የማይችለው እግር ኳሰኛ እንደሌለ ይወራ ጀመር። ብራዚላዊው ተከላካይ ሮቤርቶ ካርሎስ፤ ፖርቹጋላዊው ኮከብ ሉዊዝ ፊጎ የጡረታ ዘመናቸውን በኖትስ ካውንቲ ሊያሳልፉ ይችላሉ የሚሉ ወሬዎች ይናፈሱ ጀመር። ነገር ግን የብዙዎችን ቀልብ ገዝቶ የነበረው የ34 ዓመቱ እንግሊዛዊ ዴቪድ ቤካም ኤልኤ ጋላክሲን ጥሎ ሊመጣ ነው የሚለው የከተማው ወሬ ነበር። በዚህ ሁሉ ወሬ መሃል የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ካያቸው ድንቅ ተከላካዮች መካከል አንዱ ሆነው የ34 ዓመቱ ሶል ካምፕቤል ወደ ሜዶው ሌን ዘለቀ። ካምፕቤል ከአንድ ወር በኋላ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከሞርካምቤ ጋር በነበረው ፍልሚያ አደረገ። ከቤተሰቦቼ ጋር ወደ ተፋላሚዎቻችን ሜዳ ሄደን ጨዋታውን ተመለከትን። ውጤቱ ግን አስካፊ ነበር። ኖትስ ካውንቲ 2-1 ተረታ። ደጋፊዎች መቸም ሽንፈት ያለ ነው፤ ካምፕቤልን ወደ አቋሙ መመለሱ አይቀሬ ነው ብለው ተስፋ ሰንቀው ወደ ቤታቸው ገቡ። ቢሆንም ከጥቂት ቀናት በኋላ ሶል ካምፕቤል ከኖትስ ጋር ያለውን ስምምነት አፍርሶ መልቀቁ ተሰማ። ይህ ዜና ከመሰማቱ ከጥቂት ቀናት በኋላ ደግሞ ዘ ሰን የተባለው ጋዜጣ ኖትስ ካውንቲን የደለለው ረስል ኪንግ የተባለው ግለሰብ በ1990ዎቹ በማጭበርበር ወንጀል ተከሶ ሁለት ዓመት ከርቸሌ ከርሞ እንደወጣ አስነበበ። ክለቡ፤ ኪንግ "ስትራቴጂያዊ አማካሪ" ነው እንጂ ከዚያ ዘለለ ሚና የለውም ሲል ዘገባውን አጣጣለ። ነገር ግን እውነታው ይህ አልነበረም። ኪንግ፤ የባህሬይን ንጉሣዊ ቤተሰብ የውጭ ሃብት ተቆጣጣሪ ነኝ በማለት ከለንደን ኢንቨስትመን ባንክን ያታልል ኖሯል። ረስል ኪንግ ከዚሁ ባንክ ማረጋገጫ አስፅፎ ነው የኖትስ ካውንቲ ባለቤትነቱን ያረጋገጠው። በተመሳሳይ ሰዓት የአንድ ግዙፍ የማዕድን አውጭ ኩባንያ ባለቤት ነኝ በማለት ከሰሜን ኮሪያ መንግሥት ጋር የድንጋይ ከሰልና ወርቅ ለማውጣት ስምምነት ይገባል። ይሄን የምርመራ ዘገባ ስናዋቅር ያገኘናቸው ኤሪክሰን ግለሰቡ አግባብቶ ወደ ሰሜን ኮሪያ እንደወሰዳቸውና የሃገሪቱ ባለሥልጣናት ለ2010 ዓለም ዋንጫ እንድናልፍ ደካማ ምድብ ውስጥ መድቡን ብለው እንደጠየቋቸው ነግረውናል። ኤሪክሰን ይህን በፍፁም ማድረግ እንደማይችሉ ለሰሜን ኮሪያ ባለሥልጣናት እንደነገራቸው ያክላሉ። ከሰሜን ኮሪያ ጋር የማዕድን ማውጣት ስምምነት የገባው ኪንግ ይህን ተጠቅሞ ኩባንያው በአክሲዮን ገበያ እንደሚዘገብ መጣር ይጀምራል። ነገር ግን ይህ አልተሳካለትም። ይሄኔ ኪንግ ወደ ባሕሬይን ይበርና በመካከለኛው ምስራቅ እንደ ፋይናንሻል ታይምስ ያለ ጋዜጣ ለመመሥረት ያቅዳል። ኪንግ የኋላ ኋላ የማጭበርበር ሂደቱ አልሳካ ብሎት በፖሊስ ይፈለግ ጀመረ። በስተመጨረሻም የካቴና ሲሳይ ሆኖ በአሜሪካዋ ከተማ ጀርዚ በፈፀመው ወንጀል ምክንያት ወደ ከርቸሌ ይላካል። ሰውየው ባለፈው ዓመት ከእሥር ተለቋል። ስለሰራነው የምርመራ ዘገባ ምላሽ ካለው በሚል ጥያቄ ብናቀርብለትም ፈቃደኛ ሊሆን አልቻለም። በኪንግ ተጭበርብሮ ብሩን ሲዘራ የነበረው ኖትስ ካውንቲ ሁለት ጊዜ ሙሉ በሙሉ ተዘግቶ ታሪክ ሆኖ ከመቅረት ተርፎ አሁን በአዲስ ባለቤት እጅ ወድቋል። እኔን ጨምሮ በርካታ ደጋፊዎች ክለባችን ባለመሸጡ ደስተኛ ብንሆንም ያንን የስድስት ወር የደስታ የሃዘን ጊዜ መቼም አንረሳውም። ምንድነው የሆነው? ሕልም ነው? ወይስ እውነት? ኖትስ አሁን በናሽናል ሊግ ውድድር ስድስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። | https://www.bbc.com/amharic/news-61037984 |
3politics
| በምሥራቅ ወለጋ ታጣቂዎች ጥቃት ሰንዝረው እስረኞችን ማስመለጣቸው ተነገረ | በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ሳሲጋ ወረዳ ታጣቂዎች በአንድ ፖሊስ ጣቢያ ላይ በፈጸሙት ጥቃት እስረኞችን አስመልጠው በርካታ የፖሊስ አባላትን ማቁሰላቸው ተነገረ። ቢቢሲ ከአካባቢው ነዋሪዎች እና ከሆስፒታል ምንጮች ማረጋገጥ እንደቻለው ጥቃቱ የተፈጸመው ማክሰኞ ዕለት ነሐሴ 25/2013 ዓ.ም ነው። የአካባቢው ባለስልጣናት ጥቃቱን በተመለከተ ምላሽና ማብራሪያ እንዲሰጡ ከቢቢሲ ጥያቄያ ቢቀርብላቸውም አስካሁን ያሉት ነገር የለም። ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር እያለ የሚጠራውና ከወራት በፊት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪ ድርጅትነት የተፈረጀው መንግሥት ሸኔ እያለ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን ጥቃቱን ስለመፈጸሙ አስታውቋል። በሳሲጋ ወረዳ የጋሎ ከተማ ነዋሪ የሆኑ አንድ ግለሰብ ጥቃቱን በተመለከተ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ማከሰኞ ረፋድ 3፡30 አካባቢ በከተማዋ የተኩስ ድምጽ መሰማት እንደጀመረ ገልጸዋል። የተኩስ ልውውጡም በአካባቢው በነበሩ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና ታጣቂዎቹ መካከል መሆኑን እና ይህም እስከ እኩለ ቀን መቀጠሉን ይናገራሉ። ታጣቂ ቡድኑ ጥቃት የፈጸመው በሳሲጋ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ሲሆን በዚህም ጥቃት እስረኞችን ማስመለጡን ነዋሪው ይናገራሉ። "ከእስር ቤቱ ያመለጡ ስድስት ሰዎች እኔ ወደ ምሠራበት ቦታ ሸሽተው ገብተው ነበር። ክፍት በር ሲያገኙ ነው ዘልቀው የገቡት። ከዚያ በኋላ ወጥተው ሄዱ። እኔም የሥራ ቦታዬን ዘግቼ ከአካባቢው ሄድኩ" በማለት የገጠማቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል። የታጣቂ ቡድኑ ቃል አቀባይ በተረጋገጠው የትዊተር ገጽ ላይ ቡድኑ በሳሲጋ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት ስለመፈጸሙ አስፈሯል። በዚህም ጥቃት "ከ100 በላይ የፖለቲካ እስረኞች ተለቀዋል" ብሏል። ቢቢሲ ከእስር ያመለጡ እስረኞችን ትክክለኛ ቁጥር ከገለልተኛ ወገን ማጣራት አልቻለም። ጥቃቱን ተከትሎ በቁጥር ከ40 በላይ የሚሆኑ የአካባቢው የፖሊስ አባላት ላይ የተለያየ ጉዳት ደርሶባቸው ለሕክምና ወደ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል መምጣታቸውን ከሆስፒታሉ ማረጋገጥ ተችሏል። ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የሆስፒታሉ ሠራተኛ "ከሳሲጋ ጉዳት የደረሰባቸው የፖሊስ አባላት ይመጣሉ ተብለን ስንጠባበቅ ነበር" ብለዋል። በተጨማሪም፤ "በጥይት እንደተመቱ ነው የሚናገሩት (ጉዳት የደረሰባቸው የፖሊስ አባላት)፤ እኛም ጉዳት የደረሰባቸው በጥይት ተመትተው መሆኑን አረጋግጠናል" ይላሉ። ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ስድስት የፖሊስ አባላት ቀዶ ሕክምና እንደተደረገላቸው እና ሌሎች ስምንት የፖሊስ አባላትም የቀዶ ሕክምና እንደሚደረግላቸው መሆኑን የሆስፒታሉ ሠራተኛ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በተጨማሪም "ስድስት ሰዎች ደግሞ ወደ አዲስ አበባ ሪፈር ተብለዋል" በማለት ለተጨማሪ ሕክምና ወደ ሌላ የጤና ተቋም የተላኩ የፖሊስ አባላት መኖራቸውንም ጨምረው ተናግረዋል። በዚህ ጥቃት ሕይወቱ ያለፈ የፖሊስ አባል ስለመኖሩ እስካሁን ማወቅ አልተቻለም። የኦሮሚያ ክልል ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ባልቻ ስለጉዳዩ ተጠይቀው "እኔ አላውቅም። በዚህ ጉዳይ ላይ መረጃ የለኝም" በማለት ዛሬ ለቢቢሲ ምላሽ ሰጥተዋል። ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር እያለ የሚጠራው እና መንግሥት "ሸኔ" የሚለው ታጣቂ ቡድን በምዕራብ ኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች በመንግሥት ባለሥልጣናት እና የጸጥታ አካላት ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን ሲሰነዝር ቆይቷል። ከጥቂት ወራት በፊት የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በዚህ ታጣቂ ቡድን 112 የፖሊስ አባላት፣ 57 የሚሊሻ አባላት እና በተለያየ ደረጃ የሚገኙ 18 ባለሥልጣናት መገደላቸውን አስታውቆ ነበር። በተጨማሪም በአካባቢዎቹ በተለያዩ ጊዜያት በንጹሃን ነዋሪዎች ላይ በተደጋጋሚ ከተፈጸሙ የጅምላ ግድያዎች ጋር በተለያያዘ ክስ ሲቀርብበት ቆይቷል። ከሳምንት በፊት በምስራቅ ወለጋ ኪራሙ ወረዳ ከ100 በላይ ንጹሃን ሰዎች የቡድኑ ታጣቂዎች ናቸው በተባሉ ጥቃት ፈጻሚዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣት መግለጫ አስታውቆ ነበር። እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጣራውና መንግሥት ሸኔ የሚለው ይህ ታጣቂ ቡድን ከፌደራል መንግሥቱ ጋር በሰሜን ኢትዮጵያ ከባድ ጦርነት ውስጥ ከሚገኘው ከህወሓት ጋር በጋር ጸረ መንግሥት እንቅስቃሴ ለማድረግ መስማማቱን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። | በምሥራቅ ወለጋ ታጣቂዎች ጥቃት ሰንዝረው እስረኞችን ማስመለጣቸው ተነገረ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ሳሲጋ ወረዳ ታጣቂዎች በአንድ ፖሊስ ጣቢያ ላይ በፈጸሙት ጥቃት እስረኞችን አስመልጠው በርካታ የፖሊስ አባላትን ማቁሰላቸው ተነገረ። ቢቢሲ ከአካባቢው ነዋሪዎች እና ከሆስፒታል ምንጮች ማረጋገጥ እንደቻለው ጥቃቱ የተፈጸመው ማክሰኞ ዕለት ነሐሴ 25/2013 ዓ.ም ነው። የአካባቢው ባለስልጣናት ጥቃቱን በተመለከተ ምላሽና ማብራሪያ እንዲሰጡ ከቢቢሲ ጥያቄያ ቢቀርብላቸውም አስካሁን ያሉት ነገር የለም። ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር እያለ የሚጠራውና ከወራት በፊት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪ ድርጅትነት የተፈረጀው መንግሥት ሸኔ እያለ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን ጥቃቱን ስለመፈጸሙ አስታውቋል። በሳሲጋ ወረዳ የጋሎ ከተማ ነዋሪ የሆኑ አንድ ግለሰብ ጥቃቱን በተመለከተ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ማከሰኞ ረፋድ 3፡30 አካባቢ በከተማዋ የተኩስ ድምጽ መሰማት እንደጀመረ ገልጸዋል። የተኩስ ልውውጡም በአካባቢው በነበሩ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና ታጣቂዎቹ መካከል መሆኑን እና ይህም እስከ እኩለ ቀን መቀጠሉን ይናገራሉ። ታጣቂ ቡድኑ ጥቃት የፈጸመው በሳሲጋ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ሲሆን በዚህም ጥቃት እስረኞችን ማስመለጡን ነዋሪው ይናገራሉ። "ከእስር ቤቱ ያመለጡ ስድስት ሰዎች እኔ ወደ ምሠራበት ቦታ ሸሽተው ገብተው ነበር። ክፍት በር ሲያገኙ ነው ዘልቀው የገቡት። ከዚያ በኋላ ወጥተው ሄዱ። እኔም የሥራ ቦታዬን ዘግቼ ከአካባቢው ሄድኩ" በማለት የገጠማቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል። የታጣቂ ቡድኑ ቃል አቀባይ በተረጋገጠው የትዊተር ገጽ ላይ ቡድኑ በሳሲጋ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት ስለመፈጸሙ አስፈሯል። በዚህም ጥቃት "ከ100 በላይ የፖለቲካ እስረኞች ተለቀዋል" ብሏል። ቢቢሲ ከእስር ያመለጡ እስረኞችን ትክክለኛ ቁጥር ከገለልተኛ ወገን ማጣራት አልቻለም። ጥቃቱን ተከትሎ በቁጥር ከ40 በላይ የሚሆኑ የአካባቢው የፖሊስ አባላት ላይ የተለያየ ጉዳት ደርሶባቸው ለሕክምና ወደ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል መምጣታቸውን ከሆስፒታሉ ማረጋገጥ ተችሏል። ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የሆስፒታሉ ሠራተኛ "ከሳሲጋ ጉዳት የደረሰባቸው የፖሊስ አባላት ይመጣሉ ተብለን ስንጠባበቅ ነበር" ብለዋል። በተጨማሪም፤ "በጥይት እንደተመቱ ነው የሚናገሩት (ጉዳት የደረሰባቸው የፖሊስ አባላት)፤ እኛም ጉዳት የደረሰባቸው በጥይት ተመትተው መሆኑን አረጋግጠናል" ይላሉ። ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ስድስት የፖሊስ አባላት ቀዶ ሕክምና እንደተደረገላቸው እና ሌሎች ስምንት የፖሊስ አባላትም የቀዶ ሕክምና እንደሚደረግላቸው መሆኑን የሆስፒታሉ ሠራተኛ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በተጨማሪም "ስድስት ሰዎች ደግሞ ወደ አዲስ አበባ ሪፈር ተብለዋል" በማለት ለተጨማሪ ሕክምና ወደ ሌላ የጤና ተቋም የተላኩ የፖሊስ አባላት መኖራቸውንም ጨምረው ተናግረዋል። በዚህ ጥቃት ሕይወቱ ያለፈ የፖሊስ አባል ስለመኖሩ እስካሁን ማወቅ አልተቻለም። የኦሮሚያ ክልል ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ባልቻ ስለጉዳዩ ተጠይቀው "እኔ አላውቅም። በዚህ ጉዳይ ላይ መረጃ የለኝም" በማለት ዛሬ ለቢቢሲ ምላሽ ሰጥተዋል። ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር እያለ የሚጠራው እና መንግሥት "ሸኔ" የሚለው ታጣቂ ቡድን በምዕራብ ኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች በመንግሥት ባለሥልጣናት እና የጸጥታ አካላት ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን ሲሰነዝር ቆይቷል። ከጥቂት ወራት በፊት የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በዚህ ታጣቂ ቡድን 112 የፖሊስ አባላት፣ 57 የሚሊሻ አባላት እና በተለያየ ደረጃ የሚገኙ 18 ባለሥልጣናት መገደላቸውን አስታውቆ ነበር። በተጨማሪም በአካባቢዎቹ በተለያዩ ጊዜያት በንጹሃን ነዋሪዎች ላይ በተደጋጋሚ ከተፈጸሙ የጅምላ ግድያዎች ጋር በተለያያዘ ክስ ሲቀርብበት ቆይቷል። ከሳምንት በፊት በምስራቅ ወለጋ ኪራሙ ወረዳ ከ100 በላይ ንጹሃን ሰዎች የቡድኑ ታጣቂዎች ናቸው በተባሉ ጥቃት ፈጻሚዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣት መግለጫ አስታውቆ ነበር። እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጣራውና መንግሥት ሸኔ የሚለው ይህ ታጣቂ ቡድን ከፌደራል መንግሥቱ ጋር በሰሜን ኢትዮጵያ ከባድ ጦርነት ውስጥ ከሚገኘው ከህወሓት ጋር በጋር ጸረ መንግሥት እንቅስቃሴ ለማድረግ መስማማቱን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። | https://www.bbc.com/amharic/news-58424823 |
5sports
| 95 ለ 0 እና 91 ለ 1 የተጠናቀቁ የእግር ኳስ ጨዋታዎች ላይ ምርመራ ተጀመረ | የሴራ ሊዮን እግር ኳስ ፌዴሬሽን 95 ለ 0 እና 91 ለ 1 በተጠናቀቁ ሁለት የእግር ኳስ ጨዋታዎች ላይ ምርመራ መጀመሩን አስታወቀ። የአገሪቱ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን በሁለት ጨዋታዎች ሊታመን የማይችል 187 ጎሎች መቆጠራቸውን ‘አሳፋሪ’ ብሎታል። በሴራ ሊዮን በሁለተኛ ደረጃ የእግር ኳስ ሊግ በተደረጉት ግጥሚያዎች ካሁንላ ሬንጀርስ እና ገልፍ ኮኖ ክለቦች ተጋጣሚዎቻቸውን በከፍተኛ የጎል ብልጫ አሸንፈዋል። ካሁንላ ክለብ ሉምቤቡ ዩናይትድ የተሰኘውን ቡድን 95 ለ 0 ያሸነፈ ሲሆን፤ ገልፍ ኮኖ ደግሞ ኮኪየም ሌበናን 91 ለ 1 አሸንፏል። በእነዚህ ጨዋታዎች የተመዘገቡት የጎል ብዛቶች በሴራ ሊዮን ታሪክ ታይተው የማይታወቁ ሲሆን፣ የአገሪቱ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም ውጤቱን ሰርዞታል። ሁለቱ ቡድኖች ከፍተኛ ወደሆነው የአገሪቱ ፕሪሚየር ሊግ ለማለፍ ተጋጣሚዎቻቸውን ማመን በማይቻል ውጤት ቢያሸንፉም የሁለቱም ጨዋታ ውጤቶች ተሰርዘዋል። በመጀመሪያው አጋማሽ አሸናፊዎቹ ተጋጣሚዎቻቸውን 2 ለ 0 እና 7 ለ 1 ብቻ እየመሩ ነበር። ከእረፍት መልስ ግን በሁለቱም ጨዋታዎች ከፍተኛ ጎሎች መቆጠራቸው ሆነ ተብሎ ጎሎች እንዲቆጠሩ ሳይደረግ አይቀርም የሚል ጥርጣሬን ፈጥሯል። “ይህን መሰል አሳፋሪ ተግባር ሲፈጸም ዝም ብለን አንመለከትም፤ ተገቢው ቅጣት ይተላለፋል” ሲሉ የአገሪቱ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ቶማስ ብሪማ ለቢቢሲ ስፖርት ተናግረዋል። “አስቸኳይ የሆነ ምርመራ በመክፈት ለዚህ ተጠያቂ የሆኑትን እንለያለን። . . .ጥፋተኛ ሆነው የሚገኙት በሴራ ሊዮን እግር ኳስ ፌዴሬሽን መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ይቀጣሉ፤ ለአገሪቱ ፀረ-ሙስና ኮሚሸንም ተላልፈው ይሰጣሉ” ብለዋል የአገሪቱ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት። ተጋጣሚያቸውን በሰፊ የጎል ልዩነት ያሸነፉት የሁንላ ሬንጀርስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ “ስፖርታዊ ጨዋነትን ያልጠበቀ” ያሉትን ባህሪ አጥብቀው እንደሚያወግዙ ተናግረዋል። በዚሁ ክለብ በከፍተኛ ውጤት የተሸነፈው ሉምቤቡ ዩናይትድ ክለብ አሰልጣኝ በበኩላቸው ሆነ ተብሎ የጨዋታ ውጤት ለማስቀየር የተደረገ ጥረት ስለመኖሩ የማውቀው ነገር የለም ብለዋል። አሰልጣኝ ሞሐመድ ጃን ጃሎህ የሚያሰለጥኑት ቡድን 95 ለ 0 ከመሸነፉም በላይ ሦስት ተጫዋቾቻቸው ከሜዳ ተወግደዋል። “የጨዋታ ውጤት ለማስቀየር ሆነ ተብሎ የተደረገ ነገር ስለመኖሩ የማውቀው ነገር የለም። ስለ ሌሎች ግን መናገር አልችልም” ሲሉ እራሳቸውን ተከላክለዋል። “በሁለተኛው አጋማሽ በርካታ ጎሎች ተቆጥረውብናል። በጣም ተበሳጭቼ ነበር. . . ምን ያክል ጎሎች እንደተቆጠሩብን እንኳ ማወቅ አልቻልኩም ነበር” ብለዋል። የሴራ ሊዮን እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአራቱንም ክለቦች ተጫዋቾች እና አስተዳዳሪዎች፣ ጨዋታውን የመሩ ዳኞችን እና የአካባቢውን እግር ኳስ ማኅበር አባላት ላይ ምርመራ አደርጋለሁ ብሏል። | 95 ለ 0 እና 91 ለ 1 የተጠናቀቁ የእግር ኳስ ጨዋታዎች ላይ ምርመራ ተጀመረ የሴራ ሊዮን እግር ኳስ ፌዴሬሽን 95 ለ 0 እና 91 ለ 1 በተጠናቀቁ ሁለት የእግር ኳስ ጨዋታዎች ላይ ምርመራ መጀመሩን አስታወቀ። የአገሪቱ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን በሁለት ጨዋታዎች ሊታመን የማይችል 187 ጎሎች መቆጠራቸውን ‘አሳፋሪ’ ብሎታል። በሴራ ሊዮን በሁለተኛ ደረጃ የእግር ኳስ ሊግ በተደረጉት ግጥሚያዎች ካሁንላ ሬንጀርስ እና ገልፍ ኮኖ ክለቦች ተጋጣሚዎቻቸውን በከፍተኛ የጎል ብልጫ አሸንፈዋል። ካሁንላ ክለብ ሉምቤቡ ዩናይትድ የተሰኘውን ቡድን 95 ለ 0 ያሸነፈ ሲሆን፤ ገልፍ ኮኖ ደግሞ ኮኪየም ሌበናን 91 ለ 1 አሸንፏል። በእነዚህ ጨዋታዎች የተመዘገቡት የጎል ብዛቶች በሴራ ሊዮን ታሪክ ታይተው የማይታወቁ ሲሆን፣ የአገሪቱ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም ውጤቱን ሰርዞታል። ሁለቱ ቡድኖች ከፍተኛ ወደሆነው የአገሪቱ ፕሪሚየር ሊግ ለማለፍ ተጋጣሚዎቻቸውን ማመን በማይቻል ውጤት ቢያሸንፉም የሁለቱም ጨዋታ ውጤቶች ተሰርዘዋል። በመጀመሪያው አጋማሽ አሸናፊዎቹ ተጋጣሚዎቻቸውን 2 ለ 0 እና 7 ለ 1 ብቻ እየመሩ ነበር። ከእረፍት መልስ ግን በሁለቱም ጨዋታዎች ከፍተኛ ጎሎች መቆጠራቸው ሆነ ተብሎ ጎሎች እንዲቆጠሩ ሳይደረግ አይቀርም የሚል ጥርጣሬን ፈጥሯል። “ይህን መሰል አሳፋሪ ተግባር ሲፈጸም ዝም ብለን አንመለከትም፤ ተገቢው ቅጣት ይተላለፋል” ሲሉ የአገሪቱ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ቶማስ ብሪማ ለቢቢሲ ስፖርት ተናግረዋል። “አስቸኳይ የሆነ ምርመራ በመክፈት ለዚህ ተጠያቂ የሆኑትን እንለያለን። . . .ጥፋተኛ ሆነው የሚገኙት በሴራ ሊዮን እግር ኳስ ፌዴሬሽን መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ይቀጣሉ፤ ለአገሪቱ ፀረ-ሙስና ኮሚሸንም ተላልፈው ይሰጣሉ” ብለዋል የአገሪቱ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት። ተጋጣሚያቸውን በሰፊ የጎል ልዩነት ያሸነፉት የሁንላ ሬንጀርስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ “ስፖርታዊ ጨዋነትን ያልጠበቀ” ያሉትን ባህሪ አጥብቀው እንደሚያወግዙ ተናግረዋል። በዚሁ ክለብ በከፍተኛ ውጤት የተሸነፈው ሉምቤቡ ዩናይትድ ክለብ አሰልጣኝ በበኩላቸው ሆነ ተብሎ የጨዋታ ውጤት ለማስቀየር የተደረገ ጥረት ስለመኖሩ የማውቀው ነገር የለም ብለዋል። አሰልጣኝ ሞሐመድ ጃን ጃሎህ የሚያሰለጥኑት ቡድን 95 ለ 0 ከመሸነፉም በላይ ሦስት ተጫዋቾቻቸው ከሜዳ ተወግደዋል። “የጨዋታ ውጤት ለማስቀየር ሆነ ተብሎ የተደረገ ነገር ስለመኖሩ የማውቀው ነገር የለም። ስለ ሌሎች ግን መናገር አልችልም” ሲሉ እራሳቸውን ተከላክለዋል። “በሁለተኛው አጋማሽ በርካታ ጎሎች ተቆጥረውብናል። በጣም ተበሳጭቼ ነበር. . . ምን ያክል ጎሎች እንደተቆጠሩብን እንኳ ማወቅ አልቻልኩም ነበር” ብለዋል። የሴራ ሊዮን እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአራቱንም ክለቦች ተጫዋቾች እና አስተዳዳሪዎች፣ ጨዋታውን የመሩ ዳኞችን እና የአካባቢውን እግር ኳስ ማኅበር አባላት ላይ ምርመራ አደርጋለሁ ብሏል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cw4pjl34k13o |
0business
| ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ይፋ አደረገ | የኬንያው ግዙፍ የቴሌኮም ኩባንያ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት መስከረም 26/2015 ዓ.ም. በአገሪቱ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ይፋ አደረገ። ኩባንያው በነሐሴ ወር ከአዲስ አበባ በ500 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የድሬዳዋ ከተማ ነበር የሙከራ አገልግሎቱን የጀመረው። በቀጣይ በነበሩ ሳምንታት ደግሞ በአስር ከተሞች ማለትም በሐረር፣ በሐረማያ፣ በአዳማ፣ በባሕር ዳር፣ በቢሾፍቱ፣ በደብረ ብርሃን፣ በጎንደር እና በሌሎች ከተሞች የሙከራ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል። ከእነዚህ ሙከራዎች በኋላ ዛሬ በይፋ አገልግሎቱን በአዲስ አበባ መጀመሩን ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ያስታወቀ ሲሆን፣ በዚህ ሥነ ሥርዓትም ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ ተገኝተዋል። በቅርቡ የነበረውን የኬንያ ምርጫ ያሸነፉት ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ለመጀመሪያ ጉብኝታቸው አዲስ አበባ ገብተዋል። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዛሬ በመላው አገሪቱ የኔትወርክ አገልግሎት ከጀመረም በኋላ ለተጨማሪ 14 ከተሞች አገልግሎቱን እንደሚያዳርስም ተገልጿል። “በሁለገብ የቴሌኮም አገልግሎት ፈቃዳችን ግዴታዎች መሰረት በከተማ የደንበኞቻችን ሙከራዎቻችን የምንቀጥል ሲሆን፣ ለተጨማሪ ከተሞች እና የተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች ኔትወርካችንን እና አገልግሎታችንን ማቅረብ እንቀጥላለን” ሲሉ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዋር ሱሳ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለ125 ዓመታት በላይ በመንግሥት የልማት ድርጅት በብቸኝነት ተይዞ የነበረውን የቴሌኮም ዘርፍ ክፍት በማድረግ የቴሌኮም ፈቃድ የሰጠችው ከሁለት ዓመት በፊት ነበር። በኢትዮጵያ የቴሌኮም ገበያ ለመሰማራት በተደረገው ዓለም አቀፍ ጨረታ በኬንያው ሳፋሪኮም የሚመራው ጥምረት በ850 ሚሊዮን ዶላር ማሸነፉ ይታወሳል። ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያ የተሰኘው ይህ ጥምረት በዘርፉ አሉ የሚባሉ ስመ ጥር የቴሌኮም ኩባንያዎችን እና ተቋማትን በቅንጅት የያዘ ሲሆን፣ እነዚህም ሳፋሪኮም፣ ቮዳኮም ግሩፕ፣ ቮዳፎን ግሩፕና ሱሚቶሞ ኮርፖሬሽን እንዲሁም ሲዲሲ ግሩፕ የተካተቱበት ነው። ዋነኛው የአገሪቱ የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ ኢትዮ ቴሌኮም 40 በመቶ ድርሻውን ለውጭ ባለሀብቶች፣ 5 በመቶውን ለኢትዮጵያውያን እና 55 በመቶውን በመንግሥት ይዞታ ይቀጥላል ተብሎ ነበር። ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች አንዱ የሆነው ኢትዮቴሌኮም ገቢው ትርፋማ ከሚባሉ ድርጅቶች አንዱ ቢሆንም ከሌሎች የቀጠናው ኩባንያዎች ጋር ሲወዳዳር ዝቅተኛ ነበር ይላሉ በዘርፉ ያሉ ተንታኞች። ኢትዮጵያ ኢትዮቴሌኮምን ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት ልማት ድርጅቶችን ድርሻ ለመሸጥ የወሰነችው በዋነኝነት ያላትን ከፍተኛ ዕዳ ለመክፈል እንደሆነ ተንታኞች የሚናገሩ ሲሆን፤ በተጨማሪነት የቴሌኮምን ተደራሽነት ለመጨመርና አገልግሎቱን ለማቀላጠፍ እንደሆነም ይጠቀሳል። ከሳፋሪኮም ከሚመራው ጥምረት በተጨማሪ በአፍሪካ በሕዝብ ብዛት ሁለተኛ ወደ ሆነችው ኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፍ ለመግባት የሚያስችል ሁለተኛ ፈቃድ እንደሚሰጥ መንግሥት መግለጹ ይታወሳል። | ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ይፋ አደረገ የኬንያው ግዙፍ የቴሌኮም ኩባንያ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት መስከረም 26/2015 ዓ.ም. በአገሪቱ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ይፋ አደረገ። ኩባንያው በነሐሴ ወር ከአዲስ አበባ በ500 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የድሬዳዋ ከተማ ነበር የሙከራ አገልግሎቱን የጀመረው። በቀጣይ በነበሩ ሳምንታት ደግሞ በአስር ከተሞች ማለትም በሐረር፣ በሐረማያ፣ በአዳማ፣ በባሕር ዳር፣ በቢሾፍቱ፣ በደብረ ብርሃን፣ በጎንደር እና በሌሎች ከተሞች የሙከራ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል። ከእነዚህ ሙከራዎች በኋላ ዛሬ በይፋ አገልግሎቱን በአዲስ አበባ መጀመሩን ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ያስታወቀ ሲሆን፣ በዚህ ሥነ ሥርዓትም ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ ተገኝተዋል። በቅርቡ የነበረውን የኬንያ ምርጫ ያሸነፉት ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ለመጀመሪያ ጉብኝታቸው አዲስ አበባ ገብተዋል። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዛሬ በመላው አገሪቱ የኔትወርክ አገልግሎት ከጀመረም በኋላ ለተጨማሪ 14 ከተሞች አገልግሎቱን እንደሚያዳርስም ተገልጿል። “በሁለገብ የቴሌኮም አገልግሎት ፈቃዳችን ግዴታዎች መሰረት በከተማ የደንበኞቻችን ሙከራዎቻችን የምንቀጥል ሲሆን፣ ለተጨማሪ ከተሞች እና የተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች ኔትወርካችንን እና አገልግሎታችንን ማቅረብ እንቀጥላለን” ሲሉ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዋር ሱሳ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለ125 ዓመታት በላይ በመንግሥት የልማት ድርጅት በብቸኝነት ተይዞ የነበረውን የቴሌኮም ዘርፍ ክፍት በማድረግ የቴሌኮም ፈቃድ የሰጠችው ከሁለት ዓመት በፊት ነበር። በኢትዮጵያ የቴሌኮም ገበያ ለመሰማራት በተደረገው ዓለም አቀፍ ጨረታ በኬንያው ሳፋሪኮም የሚመራው ጥምረት በ850 ሚሊዮን ዶላር ማሸነፉ ይታወሳል። ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያ የተሰኘው ይህ ጥምረት በዘርፉ አሉ የሚባሉ ስመ ጥር የቴሌኮም ኩባንያዎችን እና ተቋማትን በቅንጅት የያዘ ሲሆን፣ እነዚህም ሳፋሪኮም፣ ቮዳኮም ግሩፕ፣ ቮዳፎን ግሩፕና ሱሚቶሞ ኮርፖሬሽን እንዲሁም ሲዲሲ ግሩፕ የተካተቱበት ነው። ዋነኛው የአገሪቱ የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ ኢትዮ ቴሌኮም 40 በመቶ ድርሻውን ለውጭ ባለሀብቶች፣ 5 በመቶውን ለኢትዮጵያውያን እና 55 በመቶውን በመንግሥት ይዞታ ይቀጥላል ተብሎ ነበር። ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች አንዱ የሆነው ኢትዮቴሌኮም ገቢው ትርፋማ ከሚባሉ ድርጅቶች አንዱ ቢሆንም ከሌሎች የቀጠናው ኩባንያዎች ጋር ሲወዳዳር ዝቅተኛ ነበር ይላሉ በዘርፉ ያሉ ተንታኞች። ኢትዮጵያ ኢትዮቴሌኮምን ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት ልማት ድርጅቶችን ድርሻ ለመሸጥ የወሰነችው በዋነኝነት ያላትን ከፍተኛ ዕዳ ለመክፈል እንደሆነ ተንታኞች የሚናገሩ ሲሆን፤ በተጨማሪነት የቴሌኮምን ተደራሽነት ለመጨመርና አገልግሎቱን ለማቀላጠፍ እንደሆነም ይጠቀሳል። ከሳፋሪኮም ከሚመራው ጥምረት በተጨማሪ በአፍሪካ በሕዝብ ብዛት ሁለተኛ ወደ ሆነችው ኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፍ ለመግባት የሚያስችል ሁለተኛ ፈቃድ እንደሚሰጥ መንግሥት መግለጹ ይታወሳል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cv2p31gzlryo |
2health
| ኮሮናቫይረስ ፡ ወደ ታይዋን ኮቪድ-19 ቫይረስ አስገብቷል የተባለው አብራሪ ከሥራ ተባረረ | የኮሮናቫይረስን ወደ ታይዋን ይዞ ገብቷል የባለ ኒው ዚላንዳዊው የአውሮፕላን አብራሪ ከሥራ ተሰናብቷል። ሰውዬው ታይዋን ውስጥ ከወራት በኋላ ለተከሰተው የኮሮናቫይረስ የማኅበረሰብ ሥርጭት ተጠያቂ ነው ተብሎ ነው ከሥራው የተባረረው። አብራሪው ኢቫ ኤይር ለተሰኘው የታይዋን አየር መንገድ ይሰራ የነበረ ሲሆን፤ ባለፈው ማክሰኞ ከአብራሪው ጋር ግንኙነት የነበረው ግለሰብ የኮሮናቫይረስ እንደተገኘበት ተገልጿል። ታይዋን ለ253 ቀናት አንድም በአገር ውስጥ ያለ ሰው በኮቪድ-19 አልተያዘባትም ነበር። ይህ ዜና ከተሰማ ወዲህ መንግሥት ሕዝቡ የገና በዓል ግርግሩን ገታ እንዲያደርገው አሳስቧል። ከገና ተከትሎ የሚከበረው የአዲስ ዓመት ዋዜማ ቀንም ሰዎች ከቤታቸው ንቅንቅ እንዳይሉ ተነግሯቸዋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዓለምን ማናወጥ ከጀመረ ወዲህ ታይዋን 777 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙባት ሲሆን ሰባት ሰዎች ደግሞ መሞታቸውን አሳውቃለች። የአውሮፕላን አብራሪው በቫይረሱ የተያዘው በያዝነው የታኅሣሥ ወር መግቢያ ላይ ቢሆንም ምንም የበሽታው ምልክት ግን አልነበረውም ተብሏል። አብራሪዎች ወደ ታይዋን ሲመጡ ለሦስት ቀናት ራሳቸውን አግልለው እንዲቆዩ የሚገደዱ ቢሆንም ምልክት ካላሳዩ ምርመራ እንዲያደርጉ አይመከሩም። ሰውዬው ምልክት ባይኖረውም ከዩናይትስ ስቴትስ አውሮፕላኑን እያበረረ ሲመጣ ግን ሲያስል ነበር ተብሏል። ይህንንም ተከትሎ አብራሪው መሬት እንዳረፈ ምርመራ ተደርጎለት ቫይረሱ እንዳለበት ተደርሶበታል። የታይዋን ባለሥልጣናት አንድ ሰው ቫይረሱ እንደተገኘበት ካረጋገጡ በኋላ ከየት ነው የመጣውን የሚለውን ሲያጣሩ ነበር አብራሪው ላይ የደረሱበት። ኒው ዚላንዳዊው አብራሪ ከመመርመሩ በፊት ከማን ጋር ግንኙነት እንደነበረው ባለማሳወቁ ነው ሥራውን ያጣው። ሰውዬው በዚህ ጥፋቱ 300 ሺህ የታይዋን ዶላር [415 ሺህ ብር ገደማ] እንዲቀጣ ተወስኖበታል። ኢቫ ኤይር አብራሪው ከሥራው የተሰናበተው የአየር መንገዱን ደንብ ባለማክበሩና የአውሮፕላኑ ጋቢና [ኮክፒት] ውስጥ ሳለ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ባለማድረጉ ነው ብሏል። ሰውዬው ከአንዲት ሴት በተጨማሪ ሁሉት የሥራ አጋሮቹንም በበሽታው እንዲያዙ አድርጓል ተብሎ ተወቅሷል። ስሙ ያልተጠቀሰው ይህ አብራሪ "ወረርሽኙን ለመግታት የሚደረገውን ጥረት" ችላ ብሏል የሚል ትችት ገጥሞታል። ታይዋን ኮሮናቫይረስ በአውሮፕላን ተሳፍሮ ወደ አገሯ መግባቱን ከሰማች ወዲህ ጥብቅ የመከላከያ መንገዶች እንደ አዲስ ለመዘርጋት አቅዳለች። ቫይረሱን ከአብራሪው ተላልፎባታል ከተባለችው ሴት ጋር በአንድም ሆነ በሌላም መንገድ ግንኙት አላቸው የተባሉ 170 ሰዎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው ነው። የቻይና ጎረቤት የሆነችው ታይዋን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ጥብቅ እርምጃ ከወሰዱና ከተሳካላቸው ጥቂት የዓለማችን ግዛቶች መካከል ናት። የታይዋን 23 ሚሊዮን ነዋሪዎችም በሽታውን ለመከላከል ከባለሥልጣናት የሚሰጡ መመሪያዎችን በማክበር አስተዋፅዖ አበርክተዋል ተብለው ይመሰገናሉ። | ኮሮናቫይረስ ፡ ወደ ታይዋን ኮቪድ-19 ቫይረስ አስገብቷል የተባለው አብራሪ ከሥራ ተባረረ የኮሮናቫይረስን ወደ ታይዋን ይዞ ገብቷል የባለ ኒው ዚላንዳዊው የአውሮፕላን አብራሪ ከሥራ ተሰናብቷል። ሰውዬው ታይዋን ውስጥ ከወራት በኋላ ለተከሰተው የኮሮናቫይረስ የማኅበረሰብ ሥርጭት ተጠያቂ ነው ተብሎ ነው ከሥራው የተባረረው። አብራሪው ኢቫ ኤይር ለተሰኘው የታይዋን አየር መንገድ ይሰራ የነበረ ሲሆን፤ ባለፈው ማክሰኞ ከአብራሪው ጋር ግንኙነት የነበረው ግለሰብ የኮሮናቫይረስ እንደተገኘበት ተገልጿል። ታይዋን ለ253 ቀናት አንድም በአገር ውስጥ ያለ ሰው በኮቪድ-19 አልተያዘባትም ነበር። ይህ ዜና ከተሰማ ወዲህ መንግሥት ሕዝቡ የገና በዓል ግርግሩን ገታ እንዲያደርገው አሳስቧል። ከገና ተከትሎ የሚከበረው የአዲስ ዓመት ዋዜማ ቀንም ሰዎች ከቤታቸው ንቅንቅ እንዳይሉ ተነግሯቸዋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዓለምን ማናወጥ ከጀመረ ወዲህ ታይዋን 777 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙባት ሲሆን ሰባት ሰዎች ደግሞ መሞታቸውን አሳውቃለች። የአውሮፕላን አብራሪው በቫይረሱ የተያዘው በያዝነው የታኅሣሥ ወር መግቢያ ላይ ቢሆንም ምንም የበሽታው ምልክት ግን አልነበረውም ተብሏል። አብራሪዎች ወደ ታይዋን ሲመጡ ለሦስት ቀናት ራሳቸውን አግልለው እንዲቆዩ የሚገደዱ ቢሆንም ምልክት ካላሳዩ ምርመራ እንዲያደርጉ አይመከሩም። ሰውዬው ምልክት ባይኖረውም ከዩናይትስ ስቴትስ አውሮፕላኑን እያበረረ ሲመጣ ግን ሲያስል ነበር ተብሏል። ይህንንም ተከትሎ አብራሪው መሬት እንዳረፈ ምርመራ ተደርጎለት ቫይረሱ እንዳለበት ተደርሶበታል። የታይዋን ባለሥልጣናት አንድ ሰው ቫይረሱ እንደተገኘበት ካረጋገጡ በኋላ ከየት ነው የመጣውን የሚለውን ሲያጣሩ ነበር አብራሪው ላይ የደረሱበት። ኒው ዚላንዳዊው አብራሪ ከመመርመሩ በፊት ከማን ጋር ግንኙነት እንደነበረው ባለማሳወቁ ነው ሥራውን ያጣው። ሰውዬው በዚህ ጥፋቱ 300 ሺህ የታይዋን ዶላር [415 ሺህ ብር ገደማ] እንዲቀጣ ተወስኖበታል። ኢቫ ኤይር አብራሪው ከሥራው የተሰናበተው የአየር መንገዱን ደንብ ባለማክበሩና የአውሮፕላኑ ጋቢና [ኮክፒት] ውስጥ ሳለ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ባለማድረጉ ነው ብሏል። ሰውዬው ከአንዲት ሴት በተጨማሪ ሁሉት የሥራ አጋሮቹንም በበሽታው እንዲያዙ አድርጓል ተብሎ ተወቅሷል። ስሙ ያልተጠቀሰው ይህ አብራሪ "ወረርሽኙን ለመግታት የሚደረገውን ጥረት" ችላ ብሏል የሚል ትችት ገጥሞታል። ታይዋን ኮሮናቫይረስ በአውሮፕላን ተሳፍሮ ወደ አገሯ መግባቱን ከሰማች ወዲህ ጥብቅ የመከላከያ መንገዶች እንደ አዲስ ለመዘርጋት አቅዳለች። ቫይረሱን ከአብራሪው ተላልፎባታል ከተባለችው ሴት ጋር በአንድም ሆነ በሌላም መንገድ ግንኙት አላቸው የተባሉ 170 ሰዎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው ነው። የቻይና ጎረቤት የሆነችው ታይዋን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ጥብቅ እርምጃ ከወሰዱና ከተሳካላቸው ጥቂት የዓለማችን ግዛቶች መካከል ናት። የታይዋን 23 ሚሊዮን ነዋሪዎችም በሽታውን ለመከላከል ከባለሥልጣናት የሚሰጡ መመሪያዎችን በማክበር አስተዋፅዖ አበርክተዋል ተብለው ይመሰገናሉ። | https://www.bbc.com/amharic/news-55435035 |
3politics
| "ባሌን በብርሃን ፍጥነት ነው የገደሉት" የሃይቲ ፕሬዝደንት ባለቤት | በቅርቡ የተገደሉት የሃይቲ ፕሬዝደንት ባለቤት ገዳዮች ወደቤታቸው መጥተው ባላቸውን በእኩለ ለሊት ሲገድሉባቸው የነበረውን ሁኔታ ተናግረዋል። ማርቲን ሞይዝ እንዳሉት ጥቃቱ በጣም በፍጥነት የተፈፀመ ከመሆኑ የተነሳ ባላቸው ጆቨኔል "አንድም ቃል መተንፈስ" አልቻሉም። ፕሬዝደንት ሞይዝ ባፈለው ረቡዕ ነው የተገደሉት። ገዳዮች ተብለው የተጠረጠሩት ደግሞ 28 የውጭ ሃገር ዜጎች ናቸው። ሚስታቸው ማርቲን ሞይዝ ተጎድተው በአሜሪካዋ ከተማ ማያሚ ሕክምና ሲያገኙ ቆይተው አሁን አገግመዋል። ቅዳሜ ዕለት በትዊተር ገፃቸው ባስተላለፉት የድምፅ መልዕክት የባላቸውን ሥራ ለመጨረስ ቃል ገብተዋል። "ከብርሃን በፈጠነ ጊዜ ሰርጎ ገቦች ወደ ቤታቸውን ዘልቀው ባሌን በጥይት ገድለውታል" ብለዋል በድምፅ መልዕክታቸው። "ይህ ድርጊት ስም የለውም። ምክንያቱም ጆቨኔል ሞይዝን የመሰለ ፕሬዝደንትን አንድም ቃል ሳይተነፍስ ለመግደል አጥር አልባ ወንጀለኛ መሆን አለብህ።" ማርቲን ባላቸው የተገደለው በፓለቲካዊ ምክንያት እንደሆነ ይገምታሉ። በተለይ ደግሞ ለፕሬዝደንቱ የተሻለ ሥልጣን የሚሰጣቸው የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ ለማድረግ ማሰባቸውን ተከትሎ ነው። እኒህ ስም የሌላቸው ገዳዮች "የፕሬዝደንቱን ሕልም መግደል ነው የሻቱት" ይላሉ። "አዎ እያለቀስኩ ነው። ነገር ግን ሃገራችን መንገዷን እንድትስት መፍቀድ የለብንም። የፕሬዝደንት ጆቨኔል ሞይዝ፣ ባሌ፣ የምንወደው ፕሬዝደንታችን ደም በከንቱ እንዲፈስ መፍቀድ የለብንም።" የ53 ዓመቱ ሞይዝ በደቡብ፣ ሰሜንና መካከለኛው አሜሪካ ካሉ ሃገራት ድህንት አቆራምዷታል የምትባለውን ሃይቲን ለአራት ዓመታት መርተዋል። የሥልጣን ዘመናቸው ወጣ ገባ ነበር። በሙስናና ብልሹ አስተዳደር ምክንያት በርካታ ተቃውሞ ተነስቶባቸው ያውቃል። ከሁለት ዓመት በፊት የሕዝብ ተወካዮች ምርጫ ማከናወን የነበረባት ሃይቲ ባለመግባባት ምክንያት አራዝማዋለች። በሚቀጥለው መስከረም የሕገ መንግሥት ማሻሻያ እንዲደረግ ሕዝበ ውሳኔ ለማካሄድ አቅደው ነበር የተገደሉት ፕሬዝደንት። ባለፈው የካቲት ፕሬዝደንቱ እሳቸውን ሊገሏቸው ያሰቡ ሰዎች ሐሳብ መክሸፉን ተናግረው ነበር። የገዳዮቹ ዓላማ ምንድነው? እንዴትስ የፕሬዝደንቱን ጥበቃዎች ዘልቀው ገቡ የሚሉት ጥያቄዎች እስካሁን አልተመለሱም። የሃይቲ ፖሊስ አብዛኛዎቹ የገዳዩ ቡድን አባላት ኮሎምቢያዊያን ሲሆኑ ሁለቱ ደግሞ አሜሪካዊያን ናቸው ብሏል። 17 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ሲውሉ፤ ሶስት ሰዎች ከፖሊስ ጋር በነበረ የተኩስ ልውውጥ ተገድለዋል፤ ስምንት ተጠርጣሪዎች ደግሞ እየታሰሱ ነው። | "ባሌን በብርሃን ፍጥነት ነው የገደሉት" የሃይቲ ፕሬዝደንት ባለቤት በቅርቡ የተገደሉት የሃይቲ ፕሬዝደንት ባለቤት ገዳዮች ወደቤታቸው መጥተው ባላቸውን በእኩለ ለሊት ሲገድሉባቸው የነበረውን ሁኔታ ተናግረዋል። ማርቲን ሞይዝ እንዳሉት ጥቃቱ በጣም በፍጥነት የተፈፀመ ከመሆኑ የተነሳ ባላቸው ጆቨኔል "አንድም ቃል መተንፈስ" አልቻሉም። ፕሬዝደንት ሞይዝ ባፈለው ረቡዕ ነው የተገደሉት። ገዳዮች ተብለው የተጠረጠሩት ደግሞ 28 የውጭ ሃገር ዜጎች ናቸው። ሚስታቸው ማርቲን ሞይዝ ተጎድተው በአሜሪካዋ ከተማ ማያሚ ሕክምና ሲያገኙ ቆይተው አሁን አገግመዋል። ቅዳሜ ዕለት በትዊተር ገፃቸው ባስተላለፉት የድምፅ መልዕክት የባላቸውን ሥራ ለመጨረስ ቃል ገብተዋል። "ከብርሃን በፈጠነ ጊዜ ሰርጎ ገቦች ወደ ቤታቸውን ዘልቀው ባሌን በጥይት ገድለውታል" ብለዋል በድምፅ መልዕክታቸው። "ይህ ድርጊት ስም የለውም። ምክንያቱም ጆቨኔል ሞይዝን የመሰለ ፕሬዝደንትን አንድም ቃል ሳይተነፍስ ለመግደል አጥር አልባ ወንጀለኛ መሆን አለብህ።" ማርቲን ባላቸው የተገደለው በፓለቲካዊ ምክንያት እንደሆነ ይገምታሉ። በተለይ ደግሞ ለፕሬዝደንቱ የተሻለ ሥልጣን የሚሰጣቸው የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ ለማድረግ ማሰባቸውን ተከትሎ ነው። እኒህ ስም የሌላቸው ገዳዮች "የፕሬዝደንቱን ሕልም መግደል ነው የሻቱት" ይላሉ። "አዎ እያለቀስኩ ነው። ነገር ግን ሃገራችን መንገዷን እንድትስት መፍቀድ የለብንም። የፕሬዝደንት ጆቨኔል ሞይዝ፣ ባሌ፣ የምንወደው ፕሬዝደንታችን ደም በከንቱ እንዲፈስ መፍቀድ የለብንም።" የ53 ዓመቱ ሞይዝ በደቡብ፣ ሰሜንና መካከለኛው አሜሪካ ካሉ ሃገራት ድህንት አቆራምዷታል የምትባለውን ሃይቲን ለአራት ዓመታት መርተዋል። የሥልጣን ዘመናቸው ወጣ ገባ ነበር። በሙስናና ብልሹ አስተዳደር ምክንያት በርካታ ተቃውሞ ተነስቶባቸው ያውቃል። ከሁለት ዓመት በፊት የሕዝብ ተወካዮች ምርጫ ማከናወን የነበረባት ሃይቲ ባለመግባባት ምክንያት አራዝማዋለች። በሚቀጥለው መስከረም የሕገ መንግሥት ማሻሻያ እንዲደረግ ሕዝበ ውሳኔ ለማካሄድ አቅደው ነበር የተገደሉት ፕሬዝደንት። ባለፈው የካቲት ፕሬዝደንቱ እሳቸውን ሊገሏቸው ያሰቡ ሰዎች ሐሳብ መክሸፉን ተናግረው ነበር። የገዳዮቹ ዓላማ ምንድነው? እንዴትስ የፕሬዝደንቱን ጥበቃዎች ዘልቀው ገቡ የሚሉት ጥያቄዎች እስካሁን አልተመለሱም። የሃይቲ ፖሊስ አብዛኛዎቹ የገዳዩ ቡድን አባላት ኮሎምቢያዊያን ሲሆኑ ሁለቱ ደግሞ አሜሪካዊያን ናቸው ብሏል። 17 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ሲውሉ፤ ሶስት ሰዎች ከፖሊስ ጋር በነበረ የተኩስ ልውውጥ ተገድለዋል፤ ስምንት ተጠርጣሪዎች ደግሞ እየታሰሱ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/news-57794473 |
0business
| ከግማሽ ቢሊዮን ዶላር በላይ በክሪፕቶከረንሲ ያጭበረበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች ተያዙ | በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በክሪፕቶከረንሲ አማካይነት 575 ሚሊዮን ዶላር አጭበርብረዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦች መያዙን የኢስቶኒያ ፖሊስ አስታወቀ። የኢስቶኒያ ፖሊስ ከአሜሪካው የፌደራል መርምራ ቢሮ (ኤፍቢይ) ጋር በመተባበር ሁለቱን ተጠርጣሪዎች ሲከታተል ቆይቶ ነው በቁጥጥር ስር የዋላቸው። የኢስቶኒያ ዜግነት ያላቸው የ37 ዓመት ጎልማሶቹ ሰርጌይ ፓታፔንኮ እና ኢቫን ቱሮጊን ተላለፈው እንዲሰጧቸው የአሜሪካ ባለሥልጣናት እንደሚፈልጉ ተነግሯል። ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ፖሊቢየስ በተባለ የበይነ መረብ ሐሰተኛ ባንክ እና ሃሽፍሌር በተሰኘ የክሪፕቶከረንሲ ግብይት አገልግሎት አማካይነት ነው በመቶዎቹ ሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ያጭበረበሩት። ከዚሁ ጋር በተያያዘም አሜሪካ በግለሰቦቹ ላይ መደበኛ ክስ ከፍታለች። ከአሜሪካ የፍትሕ መሥሪያ ቤት የወጣ መግለጫ፣ ሁለቱ ሰዎች አስከ 20 ዓመት ሊያሳስሩ በሚችሉት የገንዘብ ዝውውር ማጭበርበር እና ሕገ ወጥ ገንዘብን ሕጋዊ ለማድረግ በማሴር ክስ ተመስርቶባቸዋል ብሏል። ተጠርጣሪዎቹ ኢስቶኒያ ዋና ከተማ ታሊን ውስጥ በሚገኝ ፍርድ ቤት ቀርበው እንደነበርና፣ ለአሜሪካ ተላልፈው አስኪሰጡ ድረስ በእስር ላይ እንደሚቆዩ መግለጫው አመልክቷል። እስካሁን ሁለቱ ግለሰቦች ከጠበቆች ስለጉዳዩ የተሰጠ አስተያየት የለም። የአሜሪካ ፍትሕ መሥሪያ ቤት እንዳለው ሁለቱ ተጠርጣሪዎች፣ ማጭበርበር መሆኑን ያላወቁ ሰዎችን በሃሽፍሌር ክሪፕቶከረንሲ ማውጣት ሥራ ውስጥ እንዲሳተፉ እንደሚያደርጉ በመግለጽ ገንዘብ ሰብስበዋል። ክሪፕቶ ማውጣት ማለት ኮምፒውተሮችን በመጠቀም ትርፍ የሚያስገኝ ተጨባጭ ያልሆነ ገንዘብ ማምረት ነው። ይህ ሂደትም በጣም ከፍተኛ መጠን ያለው የኮምፒውተር ኃይልን ይጠቀማል። በዓለም ዙሪያ ያሉ በርካታ ሰዎች ከግማሽ ቢሊዮን ዶላር በላይ ዋጋን የሚያወጣ የሃሽፍሌር ክሪፕቶከረንሲ ኮንትራቶችን በአራት ዓመታት ውስጥ ገዝተዋል። ነገር ግን ግለሰቦቹ የተስማሙትን ሥራ እውን ለማድረግ ሳይችሉ ቀርተዋል። የአሜሪካ የፍትሕ መሥሪያ ቤት እንዳለው በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች ከክሪፕቶው በተጨማሪ ሰዎች ፖሊቢየስ በተባለው የበይነ መረብ ባንክ ላይ መዋዕለ ነዋያቸውን ካፈሰሱ ትርፍ እንደሚያገኙ ቃል ገብተውላቸው ነበር። በዚህም አማካይነትም 25 ሚሊዮን ዶላር ቢሰበስቡም የተባለው ባንክ ግን የት እንዳለ አይታወቅም። ተከሳሾቹ በተጨባጭ የሌሉ ኩባንያዎችን በመጠቀም በወንጀል የተገኘ ገንዘብን ሕጋዊ አድርገዋል። በዚህም ቢያንስ 75 ንብረቶችን እና የቅንጦት መኪኖችን መግዛታቸውን የአሜሪካ መንግሥት ገልጿል። በኢስቶኒያ ፖሊስ የበይነ መረብ ወንጀል ቡድን እና በአሜሪካው ኤፍቢአይ አማካይነት በተካሄደው በዚህ ምርመራ 15 አሜሪካውያንን ጨምሮ 100 ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል። በግለሰቦቹ ተፈጽሟል የተባለው ወንጀል በኢስቶያ ውስጥ ካጋጠሙ ግዙፍ የማጭበርበር ድርጊቶች መካከል አንዱ መሆኑን ፖሊስ የገለጸ ሲሆን፣ የአገሪቱ ባለሥልጣናትም ሕዝቡ እየሰፋ ከመጣው በቴክኖሎጂ የታገዘ ማጭበርበር እራሱን እንዲጠብቅ አስጠንቅቋል። በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላሮችን ማጭበርበር የተጠረጠሩት ሁለቱ ግለሰቦች የተየዙት ኤፍቲኤክስ የተባለው የዓለም ሁለተኛው የክሪፕቶ ግብይት መድረክ ከስሮ የክሪፕቶከረንሲው ገበያ ቀውስ ውስጥ በወደቀበት ጊዜ ነው። ኤፍቲኤክስ ባለፈው ሳምንት ኪሳራ እንደገጠመው አሜሪካ ውስጥ ያሳወቀ ሲሆን፣ በዚህም 50 የሚደርሱ የዋነኛ አበዳሪዎቹ 3.1 ቢሊዮን ዶላር እዳ እንዳለበት የፍርድ ቤት ሰነዶች አመልክተዋል። | ከግማሽ ቢሊዮን ዶላር በላይ በክሪፕቶከረንሲ ያጭበረበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች ተያዙ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በክሪፕቶከረንሲ አማካይነት 575 ሚሊዮን ዶላር አጭበርብረዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦች መያዙን የኢስቶኒያ ፖሊስ አስታወቀ። የኢስቶኒያ ፖሊስ ከአሜሪካው የፌደራል መርምራ ቢሮ (ኤፍቢይ) ጋር በመተባበር ሁለቱን ተጠርጣሪዎች ሲከታተል ቆይቶ ነው በቁጥጥር ስር የዋላቸው። የኢስቶኒያ ዜግነት ያላቸው የ37 ዓመት ጎልማሶቹ ሰርጌይ ፓታፔንኮ እና ኢቫን ቱሮጊን ተላለፈው እንዲሰጧቸው የአሜሪካ ባለሥልጣናት እንደሚፈልጉ ተነግሯል። ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ፖሊቢየስ በተባለ የበይነ መረብ ሐሰተኛ ባንክ እና ሃሽፍሌር በተሰኘ የክሪፕቶከረንሲ ግብይት አገልግሎት አማካይነት ነው በመቶዎቹ ሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ያጭበረበሩት። ከዚሁ ጋር በተያያዘም አሜሪካ በግለሰቦቹ ላይ መደበኛ ክስ ከፍታለች። ከአሜሪካ የፍትሕ መሥሪያ ቤት የወጣ መግለጫ፣ ሁለቱ ሰዎች አስከ 20 ዓመት ሊያሳስሩ በሚችሉት የገንዘብ ዝውውር ማጭበርበር እና ሕገ ወጥ ገንዘብን ሕጋዊ ለማድረግ በማሴር ክስ ተመስርቶባቸዋል ብሏል። ተጠርጣሪዎቹ ኢስቶኒያ ዋና ከተማ ታሊን ውስጥ በሚገኝ ፍርድ ቤት ቀርበው እንደነበርና፣ ለአሜሪካ ተላልፈው አስኪሰጡ ድረስ በእስር ላይ እንደሚቆዩ መግለጫው አመልክቷል። እስካሁን ሁለቱ ግለሰቦች ከጠበቆች ስለጉዳዩ የተሰጠ አስተያየት የለም። የአሜሪካ ፍትሕ መሥሪያ ቤት እንዳለው ሁለቱ ተጠርጣሪዎች፣ ማጭበርበር መሆኑን ያላወቁ ሰዎችን በሃሽፍሌር ክሪፕቶከረንሲ ማውጣት ሥራ ውስጥ እንዲሳተፉ እንደሚያደርጉ በመግለጽ ገንዘብ ሰብስበዋል። ክሪፕቶ ማውጣት ማለት ኮምፒውተሮችን በመጠቀም ትርፍ የሚያስገኝ ተጨባጭ ያልሆነ ገንዘብ ማምረት ነው። ይህ ሂደትም በጣም ከፍተኛ መጠን ያለው የኮምፒውተር ኃይልን ይጠቀማል። በዓለም ዙሪያ ያሉ በርካታ ሰዎች ከግማሽ ቢሊዮን ዶላር በላይ ዋጋን የሚያወጣ የሃሽፍሌር ክሪፕቶከረንሲ ኮንትራቶችን በአራት ዓመታት ውስጥ ገዝተዋል። ነገር ግን ግለሰቦቹ የተስማሙትን ሥራ እውን ለማድረግ ሳይችሉ ቀርተዋል። የአሜሪካ የፍትሕ መሥሪያ ቤት እንዳለው በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች ከክሪፕቶው በተጨማሪ ሰዎች ፖሊቢየስ በተባለው የበይነ መረብ ባንክ ላይ መዋዕለ ነዋያቸውን ካፈሰሱ ትርፍ እንደሚያገኙ ቃል ገብተውላቸው ነበር። በዚህም አማካይነትም 25 ሚሊዮን ዶላር ቢሰበስቡም የተባለው ባንክ ግን የት እንዳለ አይታወቅም። ተከሳሾቹ በተጨባጭ የሌሉ ኩባንያዎችን በመጠቀም በወንጀል የተገኘ ገንዘብን ሕጋዊ አድርገዋል። በዚህም ቢያንስ 75 ንብረቶችን እና የቅንጦት መኪኖችን መግዛታቸውን የአሜሪካ መንግሥት ገልጿል። በኢስቶኒያ ፖሊስ የበይነ መረብ ወንጀል ቡድን እና በአሜሪካው ኤፍቢአይ አማካይነት በተካሄደው በዚህ ምርመራ 15 አሜሪካውያንን ጨምሮ 100 ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል። በግለሰቦቹ ተፈጽሟል የተባለው ወንጀል በኢስቶያ ውስጥ ካጋጠሙ ግዙፍ የማጭበርበር ድርጊቶች መካከል አንዱ መሆኑን ፖሊስ የገለጸ ሲሆን፣ የአገሪቱ ባለሥልጣናትም ሕዝቡ እየሰፋ ከመጣው በቴክኖሎጂ የታገዘ ማጭበርበር እራሱን እንዲጠብቅ አስጠንቅቋል። በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላሮችን ማጭበርበር የተጠረጠሩት ሁለቱ ግለሰቦች የተየዙት ኤፍቲኤክስ የተባለው የዓለም ሁለተኛው የክሪፕቶ ግብይት መድረክ ከስሮ የክሪፕቶከረንሲው ገበያ ቀውስ ውስጥ በወደቀበት ጊዜ ነው። ኤፍቲኤክስ ባለፈው ሳምንት ኪሳራ እንደገጠመው አሜሪካ ውስጥ ያሳወቀ ሲሆን፣ በዚህም 50 የሚደርሱ የዋነኛ አበዳሪዎቹ 3.1 ቢሊዮን ዶላር እዳ እንዳለበት የፍርድ ቤት ሰነዶች አመልክተዋል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c9e1nv2lv8zo |
2health
| በጊኒ ኢቦላ ተቀስቅሶ ሦስት ሰዎች ሞቱ | በጊኒ ኢቦላ ተቀስቅሶ 3 ሰዎች ሞቱ። ሌሎች አራት ሰዎች ደግሞ ተቅማጥ፣ ማስመለስና የመድማት ምልክቶችን እያሳዩ እንደሆነ ተነግሯል። አራቱ ሰዎች እነዚህን ምልክቶች ማሳየት የጀመሩት የአንድ በኢቦላ የሞተችን ነርስ ቀብር ከታደሙ በኋላ ነበር። ባለሥልጣናት አዲስ የተሰራ ክትባት በዓለም ጤና ድርጅት በኩል እንደሚገኝ እየተናገሩ ነው። በፈረንጆቹ ከ2013 እስከ 2016 ብቻ በምዕራፍ አፍሪካ ኢቦላ ወረርሽኝ የ11ሺ ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል። ወረርሽኙ ጊኒን ጨምሮ ጎረቤቶቿን ላይቤሪያንና ሴራሊዮንን በከፍተኛ ሁኔታ አጥቅቶ ነበር። ይህን ተከትሎም በርካታ ክትባቶች ተሞክረዋል። ክትባቶቹ ወረርሽኞቹን ለማቆም በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ አገልግሎት ላይ ሲውሉ ነበር። የዓለም ጤና ድርጅት የጊኒ ተወካይ አልፍሬድ ጆርጅ ኪ ዜርቦ "አስፈላጊውን ክትባት ለማቅረብ የዓለም ጤና ድርጅት ከመድኃኒት አምራቾች ጋር እየተነጋገረ ነው ብለዋል። የኢቦላ ክትባት ለመጀመርያ ጊዜ በ2015 በጊኒ ሙከራ ተደርጎ ውጤት ማስገኘቱ ይታወሳል። ከክትባቱ ሌላ ታማሚው የመዳን እድሉን የሚጨምሩ መድኃኒቶች መፈብረካቸውም ይታወቃል። አሁን በጊኒ የተቀሰቀሰው ኢቦላ በአንድ ጤና ጣቢያ ትሰራ የነበረች ነርስ ታማ ከሞተች በኋላ በቀብሯ ላይ የተገኙ ሰዎች በተህዋሲው መጠቃታቸው ነው የተነገረው። ነርሷ ከሞተች ከ4 ቀናት በኋላ ነበር የተቀበረችው። ምናልባት አስክሬን በማጠብ ላይ የነበሩ ሰዎች ተህዋሲውን እንዳዛመቱ ይገመታል። ብዙውን ጊዜ በኢቦላ የሞቱ ሰዎች አስክሬን አደገኛና መርዛማ የኢቦላ ተህዋሲን የመሸከም አቅም አለው። የተህዋሲው እድሜም ከ2 ቀን እስከ 3 ሳምንት ይቆያል። ኢቦላ ቺምፓዚን ከመሰሉ እንሰሳት ወደ ሰው የሚተላለፍ ተህዋሲ ነው። ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈውም በደም፣ በሰውነት ፈሳሽ ወይም ተህዋሲው ከነካው አካባቢ ሊሆን ይችላል። አሁን ሁሉም በተህዋሲው የተለከፉት እድሜያቸው ከ25 ዓመት በላይ የሆኑና የነርሷን ቀብር የታደሙት ናቸው። የወረርሽኙን መቀስቀስ ተከትሎ ሴራሊዯንና ላይቤሪያ በተጠንቀቅ ላይ ይገኛሉ። የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሃ ለጤና ሚኒስትሮቻቸው ጉዳዩን በንቃት እንዲከታተሉ አዘዋል። የቢቢሲ ዘጋቢ ከሴራሊዯን እንደጻፈችው በአገሪቱ ከኮቪድ ተህዋሲ በላይ ሕዝቡ ስጋት ያለበት ለኢቦላ ወረርሽኝ ነው። ኢቦላ ተህዋሲ ድንገቴ ትኩሳት በመፍጠር በአጭር ሰዓት ታማሚውን በማዳከም የጡንቻ ከባድ ሕመም ፈጥሮ ጉሮሮን አቁሱሎ የሚገድል በሽታ ነው። ከዚህም ባሻገር ማስመለስ፣ ማስቀመጥ እና የውስጥና የውጭ መድማትን ያስከትላል። ታማሚዎች የሚሞቱት ብዙውን ጊዜ ፈሳሽ ከሰውነታቸው ተሟጦ ስለሚያልቅ ነው። ይህም የአንዳች ሰውነት አካል ሥራ ማቆምን ያስከትልና ለሞት ይዳርጋል። | በጊኒ ኢቦላ ተቀስቅሶ ሦስት ሰዎች ሞቱ በጊኒ ኢቦላ ተቀስቅሶ 3 ሰዎች ሞቱ። ሌሎች አራት ሰዎች ደግሞ ተቅማጥ፣ ማስመለስና የመድማት ምልክቶችን እያሳዩ እንደሆነ ተነግሯል። አራቱ ሰዎች እነዚህን ምልክቶች ማሳየት የጀመሩት የአንድ በኢቦላ የሞተችን ነርስ ቀብር ከታደሙ በኋላ ነበር። ባለሥልጣናት አዲስ የተሰራ ክትባት በዓለም ጤና ድርጅት በኩል እንደሚገኝ እየተናገሩ ነው። በፈረንጆቹ ከ2013 እስከ 2016 ብቻ በምዕራፍ አፍሪካ ኢቦላ ወረርሽኝ የ11ሺ ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል። ወረርሽኙ ጊኒን ጨምሮ ጎረቤቶቿን ላይቤሪያንና ሴራሊዮንን በከፍተኛ ሁኔታ አጥቅቶ ነበር። ይህን ተከትሎም በርካታ ክትባቶች ተሞክረዋል። ክትባቶቹ ወረርሽኞቹን ለማቆም በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ አገልግሎት ላይ ሲውሉ ነበር። የዓለም ጤና ድርጅት የጊኒ ተወካይ አልፍሬድ ጆርጅ ኪ ዜርቦ "አስፈላጊውን ክትባት ለማቅረብ የዓለም ጤና ድርጅት ከመድኃኒት አምራቾች ጋር እየተነጋገረ ነው ብለዋል። የኢቦላ ክትባት ለመጀመርያ ጊዜ በ2015 በጊኒ ሙከራ ተደርጎ ውጤት ማስገኘቱ ይታወሳል። ከክትባቱ ሌላ ታማሚው የመዳን እድሉን የሚጨምሩ መድኃኒቶች መፈብረካቸውም ይታወቃል። አሁን በጊኒ የተቀሰቀሰው ኢቦላ በአንድ ጤና ጣቢያ ትሰራ የነበረች ነርስ ታማ ከሞተች በኋላ በቀብሯ ላይ የተገኙ ሰዎች በተህዋሲው መጠቃታቸው ነው የተነገረው። ነርሷ ከሞተች ከ4 ቀናት በኋላ ነበር የተቀበረችው። ምናልባት አስክሬን በማጠብ ላይ የነበሩ ሰዎች ተህዋሲውን እንዳዛመቱ ይገመታል። ብዙውን ጊዜ በኢቦላ የሞቱ ሰዎች አስክሬን አደገኛና መርዛማ የኢቦላ ተህዋሲን የመሸከም አቅም አለው። የተህዋሲው እድሜም ከ2 ቀን እስከ 3 ሳምንት ይቆያል። ኢቦላ ቺምፓዚን ከመሰሉ እንሰሳት ወደ ሰው የሚተላለፍ ተህዋሲ ነው። ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈውም በደም፣ በሰውነት ፈሳሽ ወይም ተህዋሲው ከነካው አካባቢ ሊሆን ይችላል። አሁን ሁሉም በተህዋሲው የተለከፉት እድሜያቸው ከ25 ዓመት በላይ የሆኑና የነርሷን ቀብር የታደሙት ናቸው። የወረርሽኙን መቀስቀስ ተከትሎ ሴራሊዯንና ላይቤሪያ በተጠንቀቅ ላይ ይገኛሉ። የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊሃ ለጤና ሚኒስትሮቻቸው ጉዳዩን በንቃት እንዲከታተሉ አዘዋል። የቢቢሲ ዘጋቢ ከሴራሊዯን እንደጻፈችው በአገሪቱ ከኮቪድ ተህዋሲ በላይ ሕዝቡ ስጋት ያለበት ለኢቦላ ወረርሽኝ ነው። ኢቦላ ተህዋሲ ድንገቴ ትኩሳት በመፍጠር በአጭር ሰዓት ታማሚውን በማዳከም የጡንቻ ከባድ ሕመም ፈጥሮ ጉሮሮን አቁሱሎ የሚገድል በሽታ ነው። ከዚህም ባሻገር ማስመለስ፣ ማስቀመጥ እና የውስጥና የውጭ መድማትን ያስከትላል። ታማሚዎች የሚሞቱት ብዙውን ጊዜ ፈሳሽ ከሰውነታቸው ተሟጦ ስለሚያልቅ ነው። ይህም የአንዳች ሰውነት አካል ሥራ ማቆምን ያስከትልና ለሞት ይዳርጋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-56066789 |
2health
| “ክትባት ቢገኝም ሁለት ሚሊዮን ሰዎች ሊሞቱ ይችላሉ” | የዓለም ጤና ድርጅት ክትባት በስፋት ከመሰራጨቱ በፊት በቫይረሱ የሚሞቱ ሰዎች ሁለት ሚሊዮን ሊደርሱ ይችላሉ አለ። የድርጅቱ የድንገተኛ ቡድን መሪ ዶ/ር ማይክ ራየን እንዳሉት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ካልተባበረ የሟቾች ቁጥር ሊጨምርም ይችላል። ወረርሽኙ መሰራጨት ከጀመረ ወዲህ ወደ አንድ ሚሊዮን ሰዎች ሞተዋል። 32 ሚሊዮን ሰዎች ደግሞ በበሽታው ተይዘዋል። በአንዳንድ አገራት በሽታው እያገረሸ ሲሆን፤ አሜሪካ፣ ሕንድ እና ብራዚል ውስጥ በአጠቃላይ ከ15 ሚሊዮን በላይ ሰው ታሟል። በሽታው ባገረሸባቸው የአውሮፓ አገራት ዳግመኛ የእንቅስቃሴ ገደብ የመጣል እቅድ አለ። አውሮፓ ውስጥ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ አሳሳቢ መሆኑን የተናገሩት ዶ/ር ማይክ፤ የእንቅስቃሴ ገደብ ከመጣል በፊት ምርመራ በማካሄድና በሽታው ካለባቸው ጋር ንክኪ ያላቸውን በመለየት የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት መሞከር ያዋጣል ብለዋል። ስለ ሟቾች ቁጥር ምን ተባለ? ክትባት መሰራጨት ከመጀመሩ በፊት ሁለት ሚሊዮን ሰዎች ሊሞቱ ይችላሉ? የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው ዶ/ር ማይክ “ሊሆን ይችላል” ብለዋል። ለበሽታው የሚሰጠው ህክምና እየተሻሻለ መምጣቱ የሚሞቱ ሰዎችን ቁጥር መቀነሱን ቢናገሩም፤ ውጤታማ ክትባት ቢገኝም እንኳን የሟቾች ቁጥር ከሁለት ሚሊዮን እንደሚያልፍ አስረድተዋል። መንግሥታት ኃላፊነታቸውን በመወጣት የሰዎችን ሕይወት እንዲታደጉም አሳስበዋል። በተለያዩ አገራች ጥብቅ የጥንቃቄ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው። ለምሳሌ በስፔን በሽታው በበረታበት ማድሪድ በከፊል እንቅስቃሴ የመግታት እቅድ ነበር። ተቃውሞ ስለገጠመው ተግባራዊ አልሆነም። ፈረንሳይ ውስጥም የባርና ሬስቶራንት ተቀጣሪዎች ንግዳቸው እንዳይዘጋ ተቃውመዋል። ዩናይትድ ኪንግደም አዳዲስ የጥንቃቄ እርምጃዎች ወስዳለች። እስራኤልም ንግድና በረራ ላይ ጥብቅ ገደብ ጥላለች። በሌላ በኩል በሽታው የከፋባት አሜሪካ ንግድ ተቋሞች ላይ ተጥሎ የነበረውን ገደብ አንስታለች። የተላላፊ በሽታዎች ባለሙያው ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ እንደሚሉት፤ አሜሪካ የወረርሽኙን የመጀመሪያ ዙር ስርጭት ገና አላለፈችም። | “ክትባት ቢገኝም ሁለት ሚሊዮን ሰዎች ሊሞቱ ይችላሉ” የዓለም ጤና ድርጅት ክትባት በስፋት ከመሰራጨቱ በፊት በቫይረሱ የሚሞቱ ሰዎች ሁለት ሚሊዮን ሊደርሱ ይችላሉ አለ። የድርጅቱ የድንገተኛ ቡድን መሪ ዶ/ር ማይክ ራየን እንዳሉት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ካልተባበረ የሟቾች ቁጥር ሊጨምርም ይችላል። ወረርሽኙ መሰራጨት ከጀመረ ወዲህ ወደ አንድ ሚሊዮን ሰዎች ሞተዋል። 32 ሚሊዮን ሰዎች ደግሞ በበሽታው ተይዘዋል። በአንዳንድ አገራት በሽታው እያገረሸ ሲሆን፤ አሜሪካ፣ ሕንድ እና ብራዚል ውስጥ በአጠቃላይ ከ15 ሚሊዮን በላይ ሰው ታሟል። በሽታው ባገረሸባቸው የአውሮፓ አገራት ዳግመኛ የእንቅስቃሴ ገደብ የመጣል እቅድ አለ። አውሮፓ ውስጥ በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ አሳሳቢ መሆኑን የተናገሩት ዶ/ር ማይክ፤ የእንቅስቃሴ ገደብ ከመጣል በፊት ምርመራ በማካሄድና በሽታው ካለባቸው ጋር ንክኪ ያላቸውን በመለየት የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት መሞከር ያዋጣል ብለዋል። ስለ ሟቾች ቁጥር ምን ተባለ? ክትባት መሰራጨት ከመጀመሩ በፊት ሁለት ሚሊዮን ሰዎች ሊሞቱ ይችላሉ? የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው ዶ/ር ማይክ “ሊሆን ይችላል” ብለዋል። ለበሽታው የሚሰጠው ህክምና እየተሻሻለ መምጣቱ የሚሞቱ ሰዎችን ቁጥር መቀነሱን ቢናገሩም፤ ውጤታማ ክትባት ቢገኝም እንኳን የሟቾች ቁጥር ከሁለት ሚሊዮን እንደሚያልፍ አስረድተዋል። መንግሥታት ኃላፊነታቸውን በመወጣት የሰዎችን ሕይወት እንዲታደጉም አሳስበዋል። በተለያዩ አገራች ጥብቅ የጥንቃቄ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው። ለምሳሌ በስፔን በሽታው በበረታበት ማድሪድ በከፊል እንቅስቃሴ የመግታት እቅድ ነበር። ተቃውሞ ስለገጠመው ተግባራዊ አልሆነም። ፈረንሳይ ውስጥም የባርና ሬስቶራንት ተቀጣሪዎች ንግዳቸው እንዳይዘጋ ተቃውመዋል። ዩናይትድ ኪንግደም አዳዲስ የጥንቃቄ እርምጃዎች ወስዳለች። እስራኤልም ንግድና በረራ ላይ ጥብቅ ገደብ ጥላለች። በሌላ በኩል በሽታው የከፋባት አሜሪካ ንግድ ተቋሞች ላይ ተጥሎ የነበረውን ገደብ አንስታለች። የተላላፊ በሽታዎች ባለሙያው ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ እንደሚሉት፤ አሜሪካ የወረርሽኙን የመጀመሪያ ዙር ስርጭት ገና አላለፈችም። | https://www.bbc.com/amharic/news-54306899 |
0business
| የጥቁር ገበያው ምንዛሪ መናር በኢኮኖሚው ላይ ምን ጫና ይዞ ይመጣል? | በአዲስ አበባ መደበኛ ባልሆነው የውጭ ምንዛሬ መስመር በሕገወጥ መንዛሪዎች የሚመራው የጥቁር ገበያ ባለፉት ጥቂት ቀናት ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል። ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ አንድ ዶላር በጥቁር ገበያው ከ64 እስከ 68 ብር ድረስ በመመንዘር ላይ እንደሚገኝ እና በተለያዩ ሁኔታዎች ይህ ዋጋ እስከ 72 ብር ድረስ ከፍ እንደሚል በዚሁ ሥራ ላይ ያለ ግለሰብ ለቢቢሲ ተናግሯል። በመደበኛው የምንዛሪ ገበያ አንድ ዶላር በ45 ብር እየተመነዘረ ይገኛል። በአሁኑ ጊዜ በጥቁር እና መደበኛ ገበያው መካከል ያለው ልዩነት ከ20 ብር በላይ ሆኗል። ይህም ከዛሬ ሦስት ዓመት ሐምሌ 2010 ከነበረበት ጋር ሲነጻጸር የእጥፍ ልዩነት አለው። በወቅቱ አንድ ዶላር በጥቁር ገበያው በ31 ብር ይመነዘር ነበር። በመደበኛ ገበያውም ላይም ቢሆን ቀላል የማይባል ከፍተኛ ማሻቀብ ታይቶበታል። ከሰባት ወራት በፊት ከ40 ብር ያልተሻገረው የመደበኛው ገበያ ምንዛሪ አሁን የአምስት ብር ጭማሪ አሳይቷል። እንዲሁም በ13 ዓመታት ውስጥ የአምስት እጥፍ ጭማሪ ታይቷል። "የጥቁር ገበያው ምንዛሪ መናር እየተባባሰ እንጂ እየተቃለለ ይሄዳል የሚል እምነት የለኝም" የሚሉት ለዓመታት የኢትዯጵያን የምጣኔ ሀብት ጉዳዮች ሲተነትኑ የቆዩ ባለሞያ ናቸው። በሥራቸው ጠባይ ምክኒያት ስማቸው እንዳይጠቀስ የመረጡት እኚሁ የምታኔ ሀብት ባለሞያ መንግሥት የብርን ምንዛሪ ለማዳከም የሚከተለውን ፖሊሲ ለክርክራቸው እንደማስረጃነት ያቀርባሉ። "ይህ ሰዎች ቁጠባቸውን በዶላር እንዲያደርጉ ስለሚያበረታታ የጥቁር ገበያውን ዋጋ ይጨምረዋል። እንደተለመደው ወደ ውጪ ከምንልከው ከውጭ የምናስገባው ጋር ሲነጻጸር እጅግ ያነሰ ስለሆነ በአገሪቱ ያለው የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት እጅግ የተጋነነ ሆኖ ይቀጥላል" ሲሉ አክለዋል። "ግጭቶች እና ተዛማጅ ብቅ ብቅ እያሉ ያሉ ፍላጎቶች የመንግሥትን የውጭ ምንዛሪ ፍላጎት ይጨምሩታል። ይህ ማለት መንግሥት የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት ከግሉ ዘርፍ ጋር ይወዳደራል ማለት ነው። ስለዚህ የግሉ ዘርፍ ብቸኛ አማራጩ ወደሆነው የትይዩ ገበያ ይሸጋገራል" ሲሉ የምጣኔ ሀብት ተንታኙ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም ኢኮኖሚው ላይ የሚጣሉ ማዕቀቦች መንግሥት ከውጭ አገራት በሚያገኛቸውን የምንዛሪ ፈሰሶች ላይ ጫና ይኖራቸዋል ያሉት ባለሙያው፤ ግጭቶች ሲኖሩ ወደ አገር ውስጥ የሚገባው የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት እና ይዞት የሚመጣው ጥሬ ምንዛሬም አብሮ ቀሪ ነው ሲሉ ያስረዳሉ። በባንክ ኢንዱስትሪው ዘርፍ ትንታኔዎችን በመስጠት የሚታወቁት እና መቀመጫቸውን በእንግሊዝ ለንደን ያደረጉት አብዱልመናን መሐመድ በመደበኛ እና በጥቁር ገበያው መካከል ያለው ልዩነት ለዓመታት በ20 እና 30 በመቶ መካከል መቆየቱን ያስታውሳሉ። አሁን ይህ ልዩነት ወደ 50 በመቶ አሻቅቧል ይላሉ። የዚህ ቀጥተኛ ውጤትም አሁንም በከፍተኛ መጠን እየጨመረ በመጣው የዋጋ ግሽበት ላይ እንደሚበረታ አብዱልመናን ይናገራሉ። ለዚህም ምክኒያቱ አስመጪዎች የውጭ ምንዛሪ ከባንኮች ስለማያገኙ ከዚሁ የጥቁር ገበያ በሚያገኙት ምንዛሪ እቃዎችን በማስመጣታቸው ነው ሲሉም ይከራከራሉ። በተጨማሪም መንግሥት ይህንን በጥቁር እና በመደበኛው ገበያ መካከል ያለውን ልዩነት ለመሙላት ሲል በፍጥነት የብርን ዋጋ ማዳከሙ አይቀሬ ነው ሲሉ አብዱልመናን ለቢቢሲ ተናግረዋል። በተጨማሪም የኢኮኖሚው አይገመቴነት ባለሀብቶች ሀብታቸውን እንዳያፈሱ ያግዳል ብለዋል። "የብር በፍጥነት ዋጋ ማጣት ከውጭ የሚገኙ ብድሮችን የመክፈል አቅምን ያዳክማል። ይህ የመንግሥትም ሆነ የግል ተበዳሪዎችን ኪሳራ ውስጥ ሊከት ይችላል። ብድሩንም ሆነ ወለዱን በውጭ ምንዛሪ የመቀየር ኃላፊነት የሚወድቅበት መንግሥትም ከፍተኛ ጫና ውስጥ ይወድቃልል" ሲሉም አክለዋል። ትሬዲንግ ኢኮኖሚክስ ከተሰኘ ድረ-ገጽ የተገኘ መረጃ እንደሚያመላክተው ባለፉት 10 ዓመታት በባንኮች የዶላር ዋጋ በ28 ብር ገዳማ ጭምሯል። 2003 ዓ.ም. ላይ በባንክ 1 የአሜሪካ ዶላር በ16 የኢትዮጵያ ብር ይመነዘር ነበር። ይህ አሳሳቢ ጉዞ ወዴት ያመራል ለሚለው ምላሽ የሰጡት የምጣኔ ሀብት ተንታኙ "ትንበያዎች የሚያሳዩት እኤአ 2022 መደበኛው ምንዛሪ ወደ 47̂ ነጥብ 7 ብር እንደሚያመራ ብሎም በ 2023 ወደ 54 ነጥብ 1 ብር ከፍ እንደሚል ነው። ቁጥሮቹን ብንተዋቸው እንኳን አሁን ያለው አካሄድ የሚያሳየን በእርግጠኝነት የብር ምንዛሪ እየተዳከመ እንደሚሄድ ነው" ሲሉ አስረድተዋል። የኑሮ ውድነት፣ የአገር ውስጥ ኢኮኖሚው በዶላር መንቀሳቀስ (dollarization of domestic economy) እንዲሁም የድህነት መባባስ፣ የብር ዋጋ መውደቅ የአጭር ጊዜ ጫናዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ተንታኙ ገልጸዋል። እንዲሁም ይህ በጊዜ ካልተገታ ወደ ሕዝባዊ አመጽ የሚያመራበት እድል እንዳለም አሳስበዋል። በረጅም ጊዜ ኢኮኖሚው ሙሉ በሙሉ የመውደቅ ቀውስ (Full blown economic crisis) ሊጋረጥበት እንደሚችል ጠቅሰው ይህም ኢኮኖሚው ከተለያዩ አቅጣጫ ቀውሶች ሲገጥሙት የሚከሰት መሆኑን ያስረዳሉ። "የውጭ ንግድ፣ የገንዘብ ፖሊሲው፣ ምርት፣ የብድር አስተዳደር ብሎም በኢንቨስትመንት ላይ የሚያሳድረው ጫና የኢኮኖሚ ውድቀት (Full blown economic crisis) ሊያጋጥም የሚችልበት እድል አለ" ሲሉም ገልጸዋል። የባንክ ዘርፍና እና የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አብዱልመናን በበኩላቸው መንግሥት ይህንን ችግር ለመፍታት ወይም ለማቃለል የብርን በፍጥነት መዳከምን ጨምሮ በርካታ የአስተዳደር እርምጃዎችን መውሰድ አለበት ብለው ያምናሉ። በተጨማሪም ጥብቅ የሆነ የሞኒተሪ ፖሊሲን መተግበር ከመፍትሄዎቹ መካከል እንደሆኑም ገልጸዋል። | የጥቁር ገበያው ምንዛሪ መናር በኢኮኖሚው ላይ ምን ጫና ይዞ ይመጣል? በአዲስ አበባ መደበኛ ባልሆነው የውጭ ምንዛሬ መስመር በሕገወጥ መንዛሪዎች የሚመራው የጥቁር ገበያ ባለፉት ጥቂት ቀናት ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል። ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ አንድ ዶላር በጥቁር ገበያው ከ64 እስከ 68 ብር ድረስ በመመንዘር ላይ እንደሚገኝ እና በተለያዩ ሁኔታዎች ይህ ዋጋ እስከ 72 ብር ድረስ ከፍ እንደሚል በዚሁ ሥራ ላይ ያለ ግለሰብ ለቢቢሲ ተናግሯል። በመደበኛው የምንዛሪ ገበያ አንድ ዶላር በ45 ብር እየተመነዘረ ይገኛል። በአሁኑ ጊዜ በጥቁር እና መደበኛ ገበያው መካከል ያለው ልዩነት ከ20 ብር በላይ ሆኗል። ይህም ከዛሬ ሦስት ዓመት ሐምሌ 2010 ከነበረበት ጋር ሲነጻጸር የእጥፍ ልዩነት አለው። በወቅቱ አንድ ዶላር በጥቁር ገበያው በ31 ብር ይመነዘር ነበር። በመደበኛ ገበያውም ላይም ቢሆን ቀላል የማይባል ከፍተኛ ማሻቀብ ታይቶበታል። ከሰባት ወራት በፊት ከ40 ብር ያልተሻገረው የመደበኛው ገበያ ምንዛሪ አሁን የአምስት ብር ጭማሪ አሳይቷል። እንዲሁም በ13 ዓመታት ውስጥ የአምስት እጥፍ ጭማሪ ታይቷል። "የጥቁር ገበያው ምንዛሪ መናር እየተባባሰ እንጂ እየተቃለለ ይሄዳል የሚል እምነት የለኝም" የሚሉት ለዓመታት የኢትዯጵያን የምጣኔ ሀብት ጉዳዮች ሲተነትኑ የቆዩ ባለሞያ ናቸው። በሥራቸው ጠባይ ምክኒያት ስማቸው እንዳይጠቀስ የመረጡት እኚሁ የምታኔ ሀብት ባለሞያ መንግሥት የብርን ምንዛሪ ለማዳከም የሚከተለውን ፖሊሲ ለክርክራቸው እንደማስረጃነት ያቀርባሉ። "ይህ ሰዎች ቁጠባቸውን በዶላር እንዲያደርጉ ስለሚያበረታታ የጥቁር ገበያውን ዋጋ ይጨምረዋል። እንደተለመደው ወደ ውጪ ከምንልከው ከውጭ የምናስገባው ጋር ሲነጻጸር እጅግ ያነሰ ስለሆነ በአገሪቱ ያለው የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት እጅግ የተጋነነ ሆኖ ይቀጥላል" ሲሉ አክለዋል። "ግጭቶች እና ተዛማጅ ብቅ ብቅ እያሉ ያሉ ፍላጎቶች የመንግሥትን የውጭ ምንዛሪ ፍላጎት ይጨምሩታል። ይህ ማለት መንግሥት የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት ከግሉ ዘርፍ ጋር ይወዳደራል ማለት ነው። ስለዚህ የግሉ ዘርፍ ብቸኛ አማራጩ ወደሆነው የትይዩ ገበያ ይሸጋገራል" ሲሉ የምጣኔ ሀብት ተንታኙ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም ኢኮኖሚው ላይ የሚጣሉ ማዕቀቦች መንግሥት ከውጭ አገራት በሚያገኛቸውን የምንዛሪ ፈሰሶች ላይ ጫና ይኖራቸዋል ያሉት ባለሙያው፤ ግጭቶች ሲኖሩ ወደ አገር ውስጥ የሚገባው የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት እና ይዞት የሚመጣው ጥሬ ምንዛሬም አብሮ ቀሪ ነው ሲሉ ያስረዳሉ። በባንክ ኢንዱስትሪው ዘርፍ ትንታኔዎችን በመስጠት የሚታወቁት እና መቀመጫቸውን በእንግሊዝ ለንደን ያደረጉት አብዱልመናን መሐመድ በመደበኛ እና በጥቁር ገበያው መካከል ያለው ልዩነት ለዓመታት በ20 እና 30 በመቶ መካከል መቆየቱን ያስታውሳሉ። አሁን ይህ ልዩነት ወደ 50 በመቶ አሻቅቧል ይላሉ። የዚህ ቀጥተኛ ውጤትም አሁንም በከፍተኛ መጠን እየጨመረ በመጣው የዋጋ ግሽበት ላይ እንደሚበረታ አብዱልመናን ይናገራሉ። ለዚህም ምክኒያቱ አስመጪዎች የውጭ ምንዛሪ ከባንኮች ስለማያገኙ ከዚሁ የጥቁር ገበያ በሚያገኙት ምንዛሪ እቃዎችን በማስመጣታቸው ነው ሲሉም ይከራከራሉ። በተጨማሪም መንግሥት ይህንን በጥቁር እና በመደበኛው ገበያ መካከል ያለውን ልዩነት ለመሙላት ሲል በፍጥነት የብርን ዋጋ ማዳከሙ አይቀሬ ነው ሲሉ አብዱልመናን ለቢቢሲ ተናግረዋል። በተጨማሪም የኢኮኖሚው አይገመቴነት ባለሀብቶች ሀብታቸውን እንዳያፈሱ ያግዳል ብለዋል። "የብር በፍጥነት ዋጋ ማጣት ከውጭ የሚገኙ ብድሮችን የመክፈል አቅምን ያዳክማል። ይህ የመንግሥትም ሆነ የግል ተበዳሪዎችን ኪሳራ ውስጥ ሊከት ይችላል። ብድሩንም ሆነ ወለዱን በውጭ ምንዛሪ የመቀየር ኃላፊነት የሚወድቅበት መንግሥትም ከፍተኛ ጫና ውስጥ ይወድቃልል" ሲሉም አክለዋል። ትሬዲንግ ኢኮኖሚክስ ከተሰኘ ድረ-ገጽ የተገኘ መረጃ እንደሚያመላክተው ባለፉት 10 ዓመታት በባንኮች የዶላር ዋጋ በ28 ብር ገዳማ ጭምሯል። 2003 ዓ.ም. ላይ በባንክ 1 የአሜሪካ ዶላር በ16 የኢትዮጵያ ብር ይመነዘር ነበር። ይህ አሳሳቢ ጉዞ ወዴት ያመራል ለሚለው ምላሽ የሰጡት የምጣኔ ሀብት ተንታኙ "ትንበያዎች የሚያሳዩት እኤአ 2022 መደበኛው ምንዛሪ ወደ 47̂ ነጥብ 7 ብር እንደሚያመራ ብሎም በ 2023 ወደ 54 ነጥብ 1 ብር ከፍ እንደሚል ነው። ቁጥሮቹን ብንተዋቸው እንኳን አሁን ያለው አካሄድ የሚያሳየን በእርግጠኝነት የብር ምንዛሪ እየተዳከመ እንደሚሄድ ነው" ሲሉ አስረድተዋል። የኑሮ ውድነት፣ የአገር ውስጥ ኢኮኖሚው በዶላር መንቀሳቀስ (dollarization of domestic economy) እንዲሁም የድህነት መባባስ፣ የብር ዋጋ መውደቅ የአጭር ጊዜ ጫናዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ተንታኙ ገልጸዋል። እንዲሁም ይህ በጊዜ ካልተገታ ወደ ሕዝባዊ አመጽ የሚያመራበት እድል እንዳለም አሳስበዋል። በረጅም ጊዜ ኢኮኖሚው ሙሉ በሙሉ የመውደቅ ቀውስ (Full blown economic crisis) ሊጋረጥበት እንደሚችል ጠቅሰው ይህም ኢኮኖሚው ከተለያዩ አቅጣጫ ቀውሶች ሲገጥሙት የሚከሰት መሆኑን ያስረዳሉ። "የውጭ ንግድ፣ የገንዘብ ፖሊሲው፣ ምርት፣ የብድር አስተዳደር ብሎም በኢንቨስትመንት ላይ የሚያሳድረው ጫና የኢኮኖሚ ውድቀት (Full blown economic crisis) ሊያጋጥም የሚችልበት እድል አለ" ሲሉም ገልጸዋል። የባንክ ዘርፍና እና የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አብዱልመናን በበኩላቸው መንግሥት ይህንን ችግር ለመፍታት ወይም ለማቃለል የብርን በፍጥነት መዳከምን ጨምሮ በርካታ የአስተዳደር እርምጃዎችን መውሰድ አለበት ብለው ያምናሉ። በተጨማሪም ጥብቅ የሆነ የሞኒተሪ ፖሊሲን መተግበር ከመፍትሄዎቹ መካከል እንደሆኑም ገልጸዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-58089453 |
3politics
| ሳይፍ ጋዳፊ - የቀድሞው የሊቢያ መሪ ልጅ 'ፕሬዝደንታችሁ አርጋችሁ ምረጡኝ' እያሉ ነው | የቀድሞው የሊቢያ መሪ ሙአማር አል-ጋዳፊ ልጅ በሚቀጥለው ወር በአገሪቱ በሚካሄደው ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ለመሳተፍ መመዝገቡ ተሰምቷል። ሳይፍ አል-ኢስላም ጋዳፊ በአንድ ወቅት ከአባቱ ሥልጣን ለመረከብ ጫፍ የደረሰ ሰው ነበር። ነገር ግን ከ10 ዓመት በፊት ተቃዋሚዎች ላይ የደረሰውን በደል መደገፉ ስሙ እንዲጠለሽ አድርጎታል። ከዚህ ተቃውሞ በኋላ ሊቢያ ወደ ቀድሞ ሰላምና መረጋጋቷ መመለስ ፈጽሙ አልቻለችም። የመብት ተሟጋች ቡድኖች በሚወጥለው ወር የሚካሄደው ምርጫ ነፃና ፍትሐዊ ላይሆን ይችላል የሚል ስጋት አላቸው። ኃያላን የሚባሉ አገራትና የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ ምርጫውን ለማደናቀፍ የሚሞክር አሊያም ውጤት የሚያዛባ አካል ከባድ እርምጃ ይወሰድበታል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። በይነ መረብ ላይ የተሰቀሉ ፎቶዎችና ተንቀሳቃሽ ምስሎች፤ ሳይፍ ጋዳፊ ከአንድ የማስታወቂያ 'ፖስተር' ፊት ቆሞ በምርጫው ለመሳተፍ ሲመዘገብ አሳይተዋል። ፊቱ በፂም የተወረረውና በሊቢያ ባሕላዊ ልብስ ያሸበረቀው ሳይፍ ከቁርዐን ላይ ምዕራፎችን እየመዘዘ ለከበቡት ካሜራዎች ተናግሯል። ሳይፍ አሁን ያለው አቋምና አባቱ ጋዳፊ ሥልጣን ላይ እያሉ ያሳይ የነበረው አቋም ፍፁም የተለያዩ ሆነው ተስተውለዋል። አባቱ በፈረንጆቹ 2011 ከሥልጣን ሲወገዱ ሳይፍ አል-ኢስላም ጋዳፊ በሚሊሻዎች ቁጥጥር ሥር ውሎ ነበር። በሚሊሻዎች ቁጥጥር ስድስት ዓመታትን ካስቆጠረ በኋላ ሞት ተፈርዶበት ነገር ግን ይህ ፍርድ የኋላ ኋላ ሊቀለበስ ችሏል። የጋዳፊ ልጅ ሳይፍ አሁንም በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት [አይሲሲ] በጦር ወንጀሎች ይፈለጋል። ሳይፍ ብቅ ብቅ ማለት የጀመረው ቀስ በቀስ ሲሆን በተለይ ዚንታን ከሚገኘው ቪላ ቤቱ ሆኖ ከኒው ዮርክ ታይምስ ጋር ያደረገው ቃል ምልልስ ብዙ ተመልካች አግኝቷል። እንደ ቢቢሲ ሞኒተሪንግ ባልደረባ አሚራ ፋታላ ዘገባ ከሆነ የጋዳፊ ልጅ በምርጫው ለመሳተፍ መመዝገብ ሊቢያዊያንን ለሁለት ከፍሏል። ነገር ግን ለዓመታት አባቱን ይተካል እየተባለ ሲጠበቅ ስለነበር ወደ ሥልጣን ለመምጣት ማሰቡ ብዙም አስገራሚ አልሆነም። ቢሆንም የቀጣዩን ወር ምርጫ ለማሸነፍ ቀላል እንደማይሆንለት የቢቢሲ መካከለኛው ምሥራቅ አርታኢ ሴባስቲያን አሸር ይናገራል። አርታኢው ወትሮውንም በቋፍ ላይ የሚገኘው የሊቢያ ምርጫ በጋዳፊ ልጅ ወደፊት መምጣት ምክንያት እንዳይናወጥ ስጋት አለው። ለዓመታት በእርስ በርስ ጦርነት ስትታመስ የቆየችው ሊቢያ አሁን በጊዜያዊ መንግሥት አስተዳደር ሥር ብትሆንም አሁንም አለመረጋጋት አለ። በሊቢያ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል በምርጫው ሕግና ቀነ ቀጠሮ ምክንያት የተነሳው አለመግባባት ፕሬዝደንታዊውን ምርጫ እንዳያመክነው ስጋት ጭሯል። በምርጫው ለመሳተፍ ከተመዘገቡት መካከል የአገሪቱን ምሥራቃዊ ክፍል የተቆጣጠረውን አማፂ ቡድን ይመሩ የነበሩት ኻሊፋ ሐፍጣርና በተባበሩት መንግሥታት የሚደገፈውን መንግሥት የሚያስተዳድሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልሃሚድ አል-ድቤባህ ይገኙበታል። | ሳይፍ ጋዳፊ - የቀድሞው የሊቢያ መሪ ልጅ 'ፕሬዝደንታችሁ አርጋችሁ ምረጡኝ' እያሉ ነው የቀድሞው የሊቢያ መሪ ሙአማር አል-ጋዳፊ ልጅ በሚቀጥለው ወር በአገሪቱ በሚካሄደው ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ለመሳተፍ መመዝገቡ ተሰምቷል። ሳይፍ አል-ኢስላም ጋዳፊ በአንድ ወቅት ከአባቱ ሥልጣን ለመረከብ ጫፍ የደረሰ ሰው ነበር። ነገር ግን ከ10 ዓመት በፊት ተቃዋሚዎች ላይ የደረሰውን በደል መደገፉ ስሙ እንዲጠለሽ አድርጎታል። ከዚህ ተቃውሞ በኋላ ሊቢያ ወደ ቀድሞ ሰላምና መረጋጋቷ መመለስ ፈጽሙ አልቻለችም። የመብት ተሟጋች ቡድኖች በሚወጥለው ወር የሚካሄደው ምርጫ ነፃና ፍትሐዊ ላይሆን ይችላል የሚል ስጋት አላቸው። ኃያላን የሚባሉ አገራትና የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ ምርጫውን ለማደናቀፍ የሚሞክር አሊያም ውጤት የሚያዛባ አካል ከባድ እርምጃ ይወሰድበታል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። በይነ መረብ ላይ የተሰቀሉ ፎቶዎችና ተንቀሳቃሽ ምስሎች፤ ሳይፍ ጋዳፊ ከአንድ የማስታወቂያ 'ፖስተር' ፊት ቆሞ በምርጫው ለመሳተፍ ሲመዘገብ አሳይተዋል። ፊቱ በፂም የተወረረውና በሊቢያ ባሕላዊ ልብስ ያሸበረቀው ሳይፍ ከቁርዐን ላይ ምዕራፎችን እየመዘዘ ለከበቡት ካሜራዎች ተናግሯል። ሳይፍ አሁን ያለው አቋምና አባቱ ጋዳፊ ሥልጣን ላይ እያሉ ያሳይ የነበረው አቋም ፍፁም የተለያዩ ሆነው ተስተውለዋል። አባቱ በፈረንጆቹ 2011 ከሥልጣን ሲወገዱ ሳይፍ አል-ኢስላም ጋዳፊ በሚሊሻዎች ቁጥጥር ሥር ውሎ ነበር። በሚሊሻዎች ቁጥጥር ስድስት ዓመታትን ካስቆጠረ በኋላ ሞት ተፈርዶበት ነገር ግን ይህ ፍርድ የኋላ ኋላ ሊቀለበስ ችሏል። የጋዳፊ ልጅ ሳይፍ አሁንም በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት [አይሲሲ] በጦር ወንጀሎች ይፈለጋል። ሳይፍ ብቅ ብቅ ማለት የጀመረው ቀስ በቀስ ሲሆን በተለይ ዚንታን ከሚገኘው ቪላ ቤቱ ሆኖ ከኒው ዮርክ ታይምስ ጋር ያደረገው ቃል ምልልስ ብዙ ተመልካች አግኝቷል። እንደ ቢቢሲ ሞኒተሪንግ ባልደረባ አሚራ ፋታላ ዘገባ ከሆነ የጋዳፊ ልጅ በምርጫው ለመሳተፍ መመዝገብ ሊቢያዊያንን ለሁለት ከፍሏል። ነገር ግን ለዓመታት አባቱን ይተካል እየተባለ ሲጠበቅ ስለነበር ወደ ሥልጣን ለመምጣት ማሰቡ ብዙም አስገራሚ አልሆነም። ቢሆንም የቀጣዩን ወር ምርጫ ለማሸነፍ ቀላል እንደማይሆንለት የቢቢሲ መካከለኛው ምሥራቅ አርታኢ ሴባስቲያን አሸር ይናገራል። አርታኢው ወትሮውንም በቋፍ ላይ የሚገኘው የሊቢያ ምርጫ በጋዳፊ ልጅ ወደፊት መምጣት ምክንያት እንዳይናወጥ ስጋት አለው። ለዓመታት በእርስ በርስ ጦርነት ስትታመስ የቆየችው ሊቢያ አሁን በጊዜያዊ መንግሥት አስተዳደር ሥር ብትሆንም አሁንም አለመረጋጋት አለ። በሊቢያ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል በምርጫው ሕግና ቀነ ቀጠሮ ምክንያት የተነሳው አለመግባባት ፕሬዝደንታዊውን ምርጫ እንዳያመክነው ስጋት ጭሯል። በምርጫው ለመሳተፍ ከተመዘገቡት መካከል የአገሪቱን ምሥራቃዊ ክፍል የተቆጣጠረውን አማፂ ቡድን ይመሩ የነበሩት ኻሊፋ ሐፍጣርና በተባበሩት መንግሥታት የሚደገፈውን መንግሥት የሚያስተዳድሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልሃሚድ አል-ድቤባህ ይገኙበታል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59284872 |
0business
| በኢትዮጵያ ለወራት የቆየው የብድር እቀባ በምጣኔ ሀብቱ ላይ ምን ውጤት ነበረው? | ላለፉት አራት ወራት ተግባራዊ ተደርጎ የነበረው የብድር ክልከላ ሙሉ በሙሉ መነሳቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በዚህ ሳምንት አስታውቋል። ብሔራዊ ባንክ ኅዳር 20/2014 ዓ.ም ባንኮች የብድር አገልግሎት ለሁሉም ደንበኞቻቸው እንዲሰጡ ትዕዛዝ ማስተላለፉን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። የብድር ክልከላው 'የምጣኔ ሀብትን አሻጥር' ለመከላከል በማለምና በጥቁር ገበያና በመደበኛ የባንኮች የውጭ ምንዛሪ ዋጋ መካከል ያለው ልዩነት መስፋቱን ተከትሎ የተጣለው ባለፈው ነሐሴ ወር ነበር። ለመሆኑ ይህ ለወራት የቆየ የብድር እቀባ ምጣኔ ሀብቱን እንዴት ጎድቶታል? "ብድር የምጣኔ ሀብት ሞተር ነው" የሚሉት በኩዌት የሳይንስና ምርምር ተቋም የምጣኔ ሀብት ተመራማሪ ዶ/ር አየለ ገላን እቀባው ቀድሞውኑም መጣል አልነበረበትም ይላሉ። ተመራማሪው እንደሚሉት "ከአገር ደኅንነትና ሕገ ወጥ ገንዘብን ለመቆጣጠር ጭራሽኑ ገንዘብ ምጣኔ ሀብቱ ውስጥ አይግባ፤ ከምንጩ እናድርቀው ማለት አግባብ አይደለም" ብለዋል። ሌሎች የዘርፉ ባለሙያዎችም ብሔራዊ ባንክ በአብዛኛው የሚያሳልፋቸው ውሳኔዎች ምንን መሠረት እንደሚያደርጉ ግልጽ አለመሆኑን በማንሳት ውሳኔዎቹ ውጤት አስገኝተዋል፤ አላስገኙም ለማለት እንደሚያስቸግር ይናገራሉ። ይሁን እንጂ ዘመናዊ የኢኮኖሚ ሥርዓት ባለበት አገር ባንኮች መሠረታዊ ሥራቸውን እንዳይሠሩ ማገድ ምጣኔ ሀብቱን እንዲቆም ማድረግ ነው ይላሉ። ባለሙያዎቹ እያንዳንዱ የሚዘዋወረው ገንዘብ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በብድር መልክ ከባንክ የሚመጣ ነው በማለትም እቀባው በተጣለባቸው ጊዜያት "ብዙ ነገር ጠፍቷል" ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል። ይህንን ሃሳብ የሚጋሩት ዶ/ር አየለም በምጣኔ ሀብቱ ላይ ጠቅላላ ጉዳት የሚያመጣ እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ቁጥጥሩን ማጥበቅ ይቻል ነበር ብለዋል። "ብድር አይነኬ መሆን አለበት፤ ብድር ማቆም ማለት የአንድን ሰው የደም ዝውውርን እንደማቆም ነው" ብለዋል ተመራማሪው። የብድር ክልከላው በምጣኔ ሀብቱ ላይ ያደረሰው ጉዳት እንዴት ይገለጻል? በሚል ለቀረበለቸው ጥያቄም ዶ/ር አየለ "ምጣኔ ሀብቱን ካለበት ወደ ኋላ የመለሰ፣ በምንም መለኪያ የማይገለጽ አጠቃላይ ውድቀት ነው" ሲሉ ገልጸውታል። የብድር አገልግሎት ሳይከለከልም የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት ችግር እንደነበረበት ያስታወሱት ተመራማሪው፤ እቀባው መጣሉ በእሳት ላይ ቤንዚን እንደመጨመር መሆኑን አስረድተዋል። ተጥሎ የነበረው የብድር እቀባ ምን የሚል ነበር? ነሐሴ ወር ላይ በብሔራዊ ባንክ ተላልፎ የነበረው የብድር ክልከላ ባንኮች ሕንጻ፣ መሬትና ቤቶችን መያዣ በማድረግ የሚሰጡ ብድሮችን በጊዜያዊነት እንዲያቆሙ ያዛል። ከማስያዣ ውጭ የሚሰጡና ከወጪ ንግድ ጋር የተያያዙ የብድር ዓይነቶችም ተቋርጠው ነበር። ይሁን እንጂ እቀባው በሌሎች ተንቀሳቃሽ ንብረቶች የሚሰጥን ብድር የሚከለክል አልነበረም። በወቅቱ የገንዘብ ሚኒስቴር ውሳኔው የተላለፈው "በምጣኔ ሀብቱ ውስጥ እየታየ ያለውን አሻጥር" ለመቆጣጠር በማሰብ መሆኑን ገልጾ ነበር። ብሔራዊ ባንኩ ባለፍነው መስከረም ወር ላይ ባስተላለፈው የብድር ክልከላ ላይ ማሻሻያ በማድረግ ባንኮች አምስት የብድር ዓይነቶችን መፍቀድ እንደሚችሉ አስታውቆ ነበር። ከእነዚህም መካከል ባንኮች የሰጡትን ብድር ለማስመለስ በሐራጅ ያወጧቸውን ንብረቶች ለመግዛት ለሚጠይቁ ገዥዎች፣ ባንኩ ብድር መውሰድ ያስችላሉ ያላቸው በሁለተኛ እና ሦስተኛ ወገኖች መካከል የሚደረግ ግብይትና ለባንክ ሠራተኞች የሚሰጥ አስቸኳይ ብድር ይገኙበታል። ከዚህም ባሻገር በጎንደር አካባቢ ለሚገኙ ሰሊጥ አምራቾች የፀደቀ የብድር ዓይነት እንዲለቀቅም ባንኩ ባወጣው ማሻሻያ መገለፁ ተዘግቧል። የብድር ክልከላው መነሳቱ ምን ፋይዳ ይኖረው ይሆን? ብዙ ጊዜ ብሔራዊ ባንክ መሠል ውሳኔዎችን ሲያሳልፍ መነሻው እንደማይታወቅና ለውይይትም ክፍት አለመሆኑን የሚያስታውሱት የዘርፉ ባለሙያዎች፤ እቀባው መነሳቱ ምን አስገኘ የሚለውን ለመናገር መጀመሪያ የተፈለገው ምን እንደሆነ መታወቅ እንዳለበት ይናገራሉ። "በመሆኑም በውሳኔው ምን እንደተገኘ ሊያብራራ የሚችለው ብሔራዊ ባንክ ነው" ይላሉ። ብሔራዊ ባንክ የብድር ክልከላው መነሳቱን ከመግለፅ ያለፈ በጉዳዩ ላይ የሰጠው ማብራሪያ የለም። ቢቢሲ በጉዳዩ ላይ ከብሔራዊ ባንክ ማብራሪያ ለመጠየቅ ያደረገው ሙከራም አልተሳካም። በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ለበርካቶች መተዳደሪያ ነው። ባንኮችም ብድር በመስጠት ከፍተኛ ገቢ ያገኛሉ። ሌሎችም ብድርን የተንተራሱ በርካታ ዘርፎች አሉ። በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዘርፉ የበርካቶች መተዳደሪያ እንደሆነ እንደ አብነት በመጥቀስ፤ እቀባው መነሳቱ ይህን ዘርፍ እንዲያንሰራራ ያደርገው ይሆን? ተብለው የተጠየቁት የምጣኔ ሀብት ተመራማሪው ዶ/ር አየለ፤ የኮንስትራክሽን ዘርፉም ሆነ ሌላው ከባንክ ከሚገኝ ብድርና ራሱ ካለው ጋር አዋህዶ ነው የሚንቀሳቀሰው ይላሉ። ነገር ግን የኮንስትራክሽን ዘርፉ ብዙ ሰዎችን ቢቀጥርም፤ እርሱን "እንደ ኢኮኖሚ ሞተር" አድርጎ መውሰድ ስህተት መሆኑን ተናግረዋል። "ትልቁ የኢኮኖሚ በሽታ ኮንስትራክሽንን እንደ ኢኮኖሚ ሞተር ማሰብ ነው" ይላሉ ዶ/ር አየለ። ላለፉት 30 ዓመታት በርካታ የኮንስትራክሽን ሥራዎች መሠራታቸውን ያስታወሱት ተመራማሪው፤ ይህ ግን የኢኮኖሚ መረጋጋትን እንዳላመጣና የኑሮ ውድነትን እንዳልቀነሰም ያስረዳሉ። በመሆኑም ብሔራዊ ባንክ ለኮንስትራክሽን የሚሰጠውን ብድር ቀንሶ ወደ ግብርና ወይም ጥቃቅን ኢንደስትሪዎች እንዲዞር ማድረግ አለበት ሲሉም ይመክራሉ። "ብድር ለእንስሳት እርባታ፣ ለፍራፍሬ ምርት፣ ለወተት፣ ለአልባሳት ምርት እና ምርት ለሚገኝባቸው ዘርፎች ቢዛወር፤ ከባንክ የተሰጠው ብድር ወደ ዋጋ ግሽበት (ኢንፍሌሽን) ሳይሆን የተረጋጋ ገበያ እንዲኖር ያደርግ ነበር" ብለዋል ዶ/ር አየለ። የኢትዮጵያ አጠቃላይ የኢኮኖሚ ዕድገት ባለፈው ዓመት በ2020 ከነበረበት 6 በመቶ በዚህ የአውሮፓውያን ዓመት በ2021 ሁለት በመቶ ብቻ እንደሚያድግ ተገምቷል። ይህም በሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ ከታየው በጣም ዝቅተኛ እንደሆነ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርክት (አይኤምኤፍ) መረጃ አሳይቷል። አገሪቱ በዓመት ወደ 14 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ እቃዎችን ከውጭ የምታስገባ ሲሆን ወደ ውጪ የምትልከው 3.4 ቢሊዮን ዶላር ብቻ የሚያወጡ ምርቶችን ነው። ከዚህም በተጨማሪ የአገሪቱ ብሔራዊ ዕዳ በዚህ ዓመት 60 ቢሊዮን ዶላር ወይም ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) 70 በመቶ ይደርሳል ተብሏል። በርካታ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎችም "ይህ የሚያሳስብ ነው" ብለዋል። በኢትዮጵያ የሰሜኑ ክፍል እየተካሄደ ካለው ጦርነት ጋር ተያይዞ አሜሪካ ኢትዮጵያን ከአጎዋ የቀረጥ ነፃ ንግድ ተጠቃሚነት እድል ማገዷ፣ የአበዳሪዎች ብድር ለመስጠት ማቅማማት እንዲሁም በጦርነቱ ሳቢያ የአገር ውስጥ የንግድ እንቅስቃሴዎች መስተጓጎል በምጣኔ ሀብቱ ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሯል። | በኢትዮጵያ ለወራት የቆየው የብድር እቀባ በምጣኔ ሀብቱ ላይ ምን ውጤት ነበረው? ላለፉት አራት ወራት ተግባራዊ ተደርጎ የነበረው የብድር ክልከላ ሙሉ በሙሉ መነሳቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በዚህ ሳምንት አስታውቋል። ብሔራዊ ባንክ ኅዳር 20/2014 ዓ.ም ባንኮች የብድር አገልግሎት ለሁሉም ደንበኞቻቸው እንዲሰጡ ትዕዛዝ ማስተላለፉን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። የብድር ክልከላው 'የምጣኔ ሀብትን አሻጥር' ለመከላከል በማለምና በጥቁር ገበያና በመደበኛ የባንኮች የውጭ ምንዛሪ ዋጋ መካከል ያለው ልዩነት መስፋቱን ተከትሎ የተጣለው ባለፈው ነሐሴ ወር ነበር። ለመሆኑ ይህ ለወራት የቆየ የብድር እቀባ ምጣኔ ሀብቱን እንዴት ጎድቶታል? "ብድር የምጣኔ ሀብት ሞተር ነው" የሚሉት በኩዌት የሳይንስና ምርምር ተቋም የምጣኔ ሀብት ተመራማሪ ዶ/ር አየለ ገላን እቀባው ቀድሞውኑም መጣል አልነበረበትም ይላሉ። ተመራማሪው እንደሚሉት "ከአገር ደኅንነትና ሕገ ወጥ ገንዘብን ለመቆጣጠር ጭራሽኑ ገንዘብ ምጣኔ ሀብቱ ውስጥ አይግባ፤ ከምንጩ እናድርቀው ማለት አግባብ አይደለም" ብለዋል። ሌሎች የዘርፉ ባለሙያዎችም ብሔራዊ ባንክ በአብዛኛው የሚያሳልፋቸው ውሳኔዎች ምንን መሠረት እንደሚያደርጉ ግልጽ አለመሆኑን በማንሳት ውሳኔዎቹ ውጤት አስገኝተዋል፤ አላስገኙም ለማለት እንደሚያስቸግር ይናገራሉ። ይሁን እንጂ ዘመናዊ የኢኮኖሚ ሥርዓት ባለበት አገር ባንኮች መሠረታዊ ሥራቸውን እንዳይሠሩ ማገድ ምጣኔ ሀብቱን እንዲቆም ማድረግ ነው ይላሉ። ባለሙያዎቹ እያንዳንዱ የሚዘዋወረው ገንዘብ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በብድር መልክ ከባንክ የሚመጣ ነው በማለትም እቀባው በተጣለባቸው ጊዜያት "ብዙ ነገር ጠፍቷል" ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል። ይህንን ሃሳብ የሚጋሩት ዶ/ር አየለም በምጣኔ ሀብቱ ላይ ጠቅላላ ጉዳት የሚያመጣ እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ቁጥጥሩን ማጥበቅ ይቻል ነበር ብለዋል። "ብድር አይነኬ መሆን አለበት፤ ብድር ማቆም ማለት የአንድን ሰው የደም ዝውውርን እንደማቆም ነው" ብለዋል ተመራማሪው። የብድር ክልከላው በምጣኔ ሀብቱ ላይ ያደረሰው ጉዳት እንዴት ይገለጻል? በሚል ለቀረበለቸው ጥያቄም ዶ/ር አየለ "ምጣኔ ሀብቱን ካለበት ወደ ኋላ የመለሰ፣ በምንም መለኪያ የማይገለጽ አጠቃላይ ውድቀት ነው" ሲሉ ገልጸውታል። የብድር አገልግሎት ሳይከለከልም የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት ችግር እንደነበረበት ያስታወሱት ተመራማሪው፤ እቀባው መጣሉ በእሳት ላይ ቤንዚን እንደመጨመር መሆኑን አስረድተዋል። ተጥሎ የነበረው የብድር እቀባ ምን የሚል ነበር? ነሐሴ ወር ላይ በብሔራዊ ባንክ ተላልፎ የነበረው የብድር ክልከላ ባንኮች ሕንጻ፣ መሬትና ቤቶችን መያዣ በማድረግ የሚሰጡ ብድሮችን በጊዜያዊነት እንዲያቆሙ ያዛል። ከማስያዣ ውጭ የሚሰጡና ከወጪ ንግድ ጋር የተያያዙ የብድር ዓይነቶችም ተቋርጠው ነበር። ይሁን እንጂ እቀባው በሌሎች ተንቀሳቃሽ ንብረቶች የሚሰጥን ብድር የሚከለክል አልነበረም። በወቅቱ የገንዘብ ሚኒስቴር ውሳኔው የተላለፈው "በምጣኔ ሀብቱ ውስጥ እየታየ ያለውን አሻጥር" ለመቆጣጠር በማሰብ መሆኑን ገልጾ ነበር። ብሔራዊ ባንኩ ባለፍነው መስከረም ወር ላይ ባስተላለፈው የብድር ክልከላ ላይ ማሻሻያ በማድረግ ባንኮች አምስት የብድር ዓይነቶችን መፍቀድ እንደሚችሉ አስታውቆ ነበር። ከእነዚህም መካከል ባንኮች የሰጡትን ብድር ለማስመለስ በሐራጅ ያወጧቸውን ንብረቶች ለመግዛት ለሚጠይቁ ገዥዎች፣ ባንኩ ብድር መውሰድ ያስችላሉ ያላቸው በሁለተኛ እና ሦስተኛ ወገኖች መካከል የሚደረግ ግብይትና ለባንክ ሠራተኞች የሚሰጥ አስቸኳይ ብድር ይገኙበታል። ከዚህም ባሻገር በጎንደር አካባቢ ለሚገኙ ሰሊጥ አምራቾች የፀደቀ የብድር ዓይነት እንዲለቀቅም ባንኩ ባወጣው ማሻሻያ መገለፁ ተዘግቧል። የብድር ክልከላው መነሳቱ ምን ፋይዳ ይኖረው ይሆን? ብዙ ጊዜ ብሔራዊ ባንክ መሠል ውሳኔዎችን ሲያሳልፍ መነሻው እንደማይታወቅና ለውይይትም ክፍት አለመሆኑን የሚያስታውሱት የዘርፉ ባለሙያዎች፤ እቀባው መነሳቱ ምን አስገኘ የሚለውን ለመናገር መጀመሪያ የተፈለገው ምን እንደሆነ መታወቅ እንዳለበት ይናገራሉ። "በመሆኑም በውሳኔው ምን እንደተገኘ ሊያብራራ የሚችለው ብሔራዊ ባንክ ነው" ይላሉ። ብሔራዊ ባንክ የብድር ክልከላው መነሳቱን ከመግለፅ ያለፈ በጉዳዩ ላይ የሰጠው ማብራሪያ የለም። ቢቢሲ በጉዳዩ ላይ ከብሔራዊ ባንክ ማብራሪያ ለመጠየቅ ያደረገው ሙከራም አልተሳካም። በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ለበርካቶች መተዳደሪያ ነው። ባንኮችም ብድር በመስጠት ከፍተኛ ገቢ ያገኛሉ። ሌሎችም ብድርን የተንተራሱ በርካታ ዘርፎች አሉ። በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዘርፉ የበርካቶች መተዳደሪያ እንደሆነ እንደ አብነት በመጥቀስ፤ እቀባው መነሳቱ ይህን ዘርፍ እንዲያንሰራራ ያደርገው ይሆን? ተብለው የተጠየቁት የምጣኔ ሀብት ተመራማሪው ዶ/ር አየለ፤ የኮንስትራክሽን ዘርፉም ሆነ ሌላው ከባንክ ከሚገኝ ብድርና ራሱ ካለው ጋር አዋህዶ ነው የሚንቀሳቀሰው ይላሉ። ነገር ግን የኮንስትራክሽን ዘርፉ ብዙ ሰዎችን ቢቀጥርም፤ እርሱን "እንደ ኢኮኖሚ ሞተር" አድርጎ መውሰድ ስህተት መሆኑን ተናግረዋል። "ትልቁ የኢኮኖሚ በሽታ ኮንስትራክሽንን እንደ ኢኮኖሚ ሞተር ማሰብ ነው" ይላሉ ዶ/ር አየለ። ላለፉት 30 ዓመታት በርካታ የኮንስትራክሽን ሥራዎች መሠራታቸውን ያስታወሱት ተመራማሪው፤ ይህ ግን የኢኮኖሚ መረጋጋትን እንዳላመጣና የኑሮ ውድነትን እንዳልቀነሰም ያስረዳሉ። በመሆኑም ብሔራዊ ባንክ ለኮንስትራክሽን የሚሰጠውን ብድር ቀንሶ ወደ ግብርና ወይም ጥቃቅን ኢንደስትሪዎች እንዲዞር ማድረግ አለበት ሲሉም ይመክራሉ። "ብድር ለእንስሳት እርባታ፣ ለፍራፍሬ ምርት፣ ለወተት፣ ለአልባሳት ምርት እና ምርት ለሚገኝባቸው ዘርፎች ቢዛወር፤ ከባንክ የተሰጠው ብድር ወደ ዋጋ ግሽበት (ኢንፍሌሽን) ሳይሆን የተረጋጋ ገበያ እንዲኖር ያደርግ ነበር" ብለዋል ዶ/ር አየለ። የኢትዮጵያ አጠቃላይ የኢኮኖሚ ዕድገት ባለፈው ዓመት በ2020 ከነበረበት 6 በመቶ በዚህ የአውሮፓውያን ዓመት በ2021 ሁለት በመቶ ብቻ እንደሚያድግ ተገምቷል። ይህም በሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ ከታየው በጣም ዝቅተኛ እንደሆነ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርክት (አይኤምኤፍ) መረጃ አሳይቷል። አገሪቱ በዓመት ወደ 14 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ እቃዎችን ከውጭ የምታስገባ ሲሆን ወደ ውጪ የምትልከው 3.4 ቢሊዮን ዶላር ብቻ የሚያወጡ ምርቶችን ነው። ከዚህም በተጨማሪ የአገሪቱ ብሔራዊ ዕዳ በዚህ ዓመት 60 ቢሊዮን ዶላር ወይም ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ) 70 በመቶ ይደርሳል ተብሏል። በርካታ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎችም "ይህ የሚያሳስብ ነው" ብለዋል። በኢትዮጵያ የሰሜኑ ክፍል እየተካሄደ ካለው ጦርነት ጋር ተያይዞ አሜሪካ ኢትዮጵያን ከአጎዋ የቀረጥ ነፃ ንግድ ተጠቃሚነት እድል ማገዷ፣ የአበዳሪዎች ብድር ለመስጠት ማቅማማት እንዲሁም በጦርነቱ ሳቢያ የአገር ውስጥ የንግድ እንቅስቃሴዎች መስተጓጎል በምጣኔ ሀብቱ ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሯል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59463389 |
5sports
| የዱባይ ማራቶን በኢትዮጵያውያን አትሌቶች የበላይነት ተጠናቀቀ | ትናንት ሌሊት በተከናወነው የዱባይ ማራቶን በሁለቱም ጾታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በበላይነት አጠናቀዋል። በወንዶች አትሌት ኦሊቃ አዱኛ ቢቂላ ሲያሸንፍ በሴቶች ደግሞ ወርቅነሽ ደገፋ የመጀመሪያ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። አትሌት ኦሊቃ ውድድሩን በአንደኝነት ለማጠናቀቅ 02፡06፡15 የፈጀበት ሲሆን፤ ሌሎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከሦስተኛ እስከ 10 ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል። ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ኬኒያዊው ኤሪክ ኪፕታኑ ነው። በሴቶች በተካሄደው ውድድር አትሌት ወርቅነሽ ደገፋ 02፡19፡37 በመግባት በአንደኝነት ስትጨርስ፤ ሌሎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከሁለተኛ እስከ ዘጠነኛ ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል። አትሌት ጉተኒ ሾኔ ሁለተኛ ስትሆን አትሌት በዳቱ ሂርጳ ደግሞ ሦስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። አትሌት ወርቅነሽ ትናንት ከውድድሩ በፊት ለቢቢሲ ለዚህ ውድድር ከፍተኛ ዝግጅት ማድረጓን ተናግራለች። አትሌት ወርቅነሽ "የዱባይ አቀማመጥ ለኔ በጣም ምቹ ነው አሸንፋሁ" ብላ ነበር። አትሌት ወርቅነሽ ደገፋ የ2017ቱን የዱባይ ማራቶን ማሸነፏ ይታወሳል። ሁለተኛ ደረጃን የያዘችው አትሌት ጉተኒ ሾሜ 02፡20፡11 የገባች ሲሆን አትሌት በዳቱ ደግሞ 02፡21፡54 በሆነ ሰዓት አጠናቃለች። የዱባይ ማራቶን መዘጋጀት ከጀመረ ወዲህ ኢትዮጵያውያን ሴት አትሌቶች 15 ጊዜ በወንዶች ደግሞ 14 ጊዜ አሸንፈዋል። | የዱባይ ማራቶን በኢትዮጵያውያን አትሌቶች የበላይነት ተጠናቀቀ ትናንት ሌሊት በተከናወነው የዱባይ ማራቶን በሁለቱም ጾታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በበላይነት አጠናቀዋል። በወንዶች አትሌት ኦሊቃ አዱኛ ቢቂላ ሲያሸንፍ በሴቶች ደግሞ ወርቅነሽ ደገፋ የመጀመሪያ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። አትሌት ኦሊቃ ውድድሩን በአንደኝነት ለማጠናቀቅ 02፡06፡15 የፈጀበት ሲሆን፤ ሌሎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከሦስተኛ እስከ 10 ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል። ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ኬኒያዊው ኤሪክ ኪፕታኑ ነው። በሴቶች በተካሄደው ውድድር አትሌት ወርቅነሽ ደገፋ 02፡19፡37 በመግባት በአንደኝነት ስትጨርስ፤ ሌሎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከሁለተኛ እስከ ዘጠነኛ ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል። አትሌት ጉተኒ ሾኔ ሁለተኛ ስትሆን አትሌት በዳቱ ሂርጳ ደግሞ ሦስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። አትሌት ወርቅነሽ ትናንት ከውድድሩ በፊት ለቢቢሲ ለዚህ ውድድር ከፍተኛ ዝግጅት ማድረጓን ተናግራለች። አትሌት ወርቅነሽ "የዱባይ አቀማመጥ ለኔ በጣም ምቹ ነው አሸንፋሁ" ብላ ነበር። አትሌት ወርቅነሽ ደገፋ የ2017ቱን የዱባይ ማራቶን ማሸነፏ ይታወሳል። ሁለተኛ ደረጃን የያዘችው አትሌት ጉተኒ ሾሜ 02፡20፡11 የገባች ሲሆን አትሌት በዳቱ ደግሞ 02፡21፡54 በሆነ ሰዓት አጠናቃለች። የዱባይ ማራቶን መዘጋጀት ከጀመረ ወዲህ ኢትዮጵያውያን ሴት አትሌቶች 15 ጊዜ በወንዶች ደግሞ 14 ጊዜ አሸንፈዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-51232629 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ ደቡብ ኮርያ ለድመት እና ውሾች የኮቪድ-19 ምርመራ ልታደርግ ነው | ደቡብ ኮሪያ በዋና ከተማዋ ሶል የሚገኙ ውሾች እና ድመቶች የኮቪድ-19 ምልክት ካሳዩ ምርመራ እንደሚደረግላቸው የሶል ሜትሮፖሊታን አስተዳደር አስታወቀ። የከተማዋ አስተዳደር እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከጥቂት ሳምንታት በፊት በኮቪድ-19 የተያዘች ድመት መገኘቷን ተከትሎ ነው። ምልክቱን የሚያሳዩ የቤት እንሰሳት ብቻ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ይደረግላቸዋል ተብሏል። በተጨማሪም ቫይረሱ ለያዘው ሰው የተጋለጡና ትኩሳት ወይንም ደግሞ የመተንፈስ ችግር የገጠማቸው ድመትና ውሾች ምርመራ እንደሚደረግላቸው ተገልጿል። እነዚህ የቤት እንስሳት ተመርምረው ተህዋሲው እንዳለባቸው ከተረጋገጠ በቤት ውስጥ ራሳቸውን አግልለው እንዲቀመጡ ይደረጋል። እንደ ዩንሃፕ የተሰኘ መገናኛ ብዙኀን ዘገባ ከሆነ የደቡብ ኮሪያ በሽታ መቆጣጣር ኃላፊ የሆኑት ፓርክ ዮ ሚ እነዚህ የቤት እንስሳት መንግሥት ወዳዘጋጃቸው ለይቶ ማቆያ ውስጥ መግባት አይጠበቅባቸውም። ነገር ግን የእነዚህ እንስሳት ባለቤት በኮቪድ-19 ታምሞ ሆስፒታል ከገባ፣ በጠና ከታመመ ወይንም ደግሞ በእድሜ መግፋት ምክንያት ለመንከባከብ ካልቻለ የከተማ አስተዳደሩ ወደሚያስተዳድረው የለይቶ ማቆያ ይወሰዳሉ ተብሏል። እስካሁን ድረስ የኮሮናቫይረስ ከቤት እንስሳት ወደ ሰው ስለመተላለፉ የተገኘ ማረጋገጫ የለም። ኃላፊዋ አክለውም ነዋሪዎች "የቤት እንስሳቶቻቸውን በሚያንሸራሽሩበት ወቅት ከሰዎችም ሆነ ከሌሎች እንስሳት ቢያንስ ሁለት ሜትር እንዲያርቋቸው" አደራ ብለዋል። ባለፈው ወር በአንድ የሃይማኖት ተቋም ውስጥ የተገኘች ድመት በኮሮናቫይረስ መያዟ በምርመራ መረጋገጡን ዮንሃብ የዜና ወኪል ዘግቧል። የጤና ባለሙያዎች በሃይማኖት ተቋሙ ውስጥ የነበሩ እናትና ልጅ ቫይረሱን ወደ ድመቷ ማስተላለፋቸውን ጠርጥረዋል። እናትና ልጅ በኮቪድ 19 መያዛቸው ተረጋግጧል። ባለሙያዎች ድመትም ሆነ ውሻ ቫይረሱን ወደ ሰው የማስተላለፍ እድላቸው በጣም የጠበበ ነው ያሉ ሲሆን ድመቶች ግን እርስ በእርስ ቫይረሱን ሊያስተላልፉ ይችላሉ ብለዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ በተደጋጋሚ የቤት አንስሳት በቫይረሱ መያዛቸው በምርመራ ተረጋግጦ ያውቃል። ባለፈው ወር በሳንዲያጎ መካነ አንስሳት ሁለት ጎሬላዎች ይንከባከባቸው ከነበረ ግለሰብ የኮሮናቫይረስ ተይዘው ተገኝተዋል። በኒውዮርክ ብሮንክስ መካነ አንስሳት ደግሞ ዝሆን እና ታይገር፣ በስፔን ባርሴሎና መካነ እንስሳት አንበሳ በኮሮና ተህዋሲ ተይዘዋል። | ኮሮናቫይረስ፡ ደቡብ ኮርያ ለድመት እና ውሾች የኮቪድ-19 ምርመራ ልታደርግ ነው ደቡብ ኮሪያ በዋና ከተማዋ ሶል የሚገኙ ውሾች እና ድመቶች የኮቪድ-19 ምልክት ካሳዩ ምርመራ እንደሚደረግላቸው የሶል ሜትሮፖሊታን አስተዳደር አስታወቀ። የከተማዋ አስተዳደር እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከጥቂት ሳምንታት በፊት በኮቪድ-19 የተያዘች ድመት መገኘቷን ተከትሎ ነው። ምልክቱን የሚያሳዩ የቤት እንሰሳት ብቻ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ይደረግላቸዋል ተብሏል። በተጨማሪም ቫይረሱ ለያዘው ሰው የተጋለጡና ትኩሳት ወይንም ደግሞ የመተንፈስ ችግር የገጠማቸው ድመትና ውሾች ምርመራ እንደሚደረግላቸው ተገልጿል። እነዚህ የቤት እንስሳት ተመርምረው ተህዋሲው እንዳለባቸው ከተረጋገጠ በቤት ውስጥ ራሳቸውን አግልለው እንዲቀመጡ ይደረጋል። እንደ ዩንሃፕ የተሰኘ መገናኛ ብዙኀን ዘገባ ከሆነ የደቡብ ኮሪያ በሽታ መቆጣጣር ኃላፊ የሆኑት ፓርክ ዮ ሚ እነዚህ የቤት እንስሳት መንግሥት ወዳዘጋጃቸው ለይቶ ማቆያ ውስጥ መግባት አይጠበቅባቸውም። ነገር ግን የእነዚህ እንስሳት ባለቤት በኮቪድ-19 ታምሞ ሆስፒታል ከገባ፣ በጠና ከታመመ ወይንም ደግሞ በእድሜ መግፋት ምክንያት ለመንከባከብ ካልቻለ የከተማ አስተዳደሩ ወደሚያስተዳድረው የለይቶ ማቆያ ይወሰዳሉ ተብሏል። እስካሁን ድረስ የኮሮናቫይረስ ከቤት እንስሳት ወደ ሰው ስለመተላለፉ የተገኘ ማረጋገጫ የለም። ኃላፊዋ አክለውም ነዋሪዎች "የቤት እንስሳቶቻቸውን በሚያንሸራሽሩበት ወቅት ከሰዎችም ሆነ ከሌሎች እንስሳት ቢያንስ ሁለት ሜትር እንዲያርቋቸው" አደራ ብለዋል። ባለፈው ወር በአንድ የሃይማኖት ተቋም ውስጥ የተገኘች ድመት በኮሮናቫይረስ መያዟ በምርመራ መረጋገጡን ዮንሃብ የዜና ወኪል ዘግቧል። የጤና ባለሙያዎች በሃይማኖት ተቋሙ ውስጥ የነበሩ እናትና ልጅ ቫይረሱን ወደ ድመቷ ማስተላለፋቸውን ጠርጥረዋል። እናትና ልጅ በኮቪድ 19 መያዛቸው ተረጋግጧል። ባለሙያዎች ድመትም ሆነ ውሻ ቫይረሱን ወደ ሰው የማስተላለፍ እድላቸው በጣም የጠበበ ነው ያሉ ሲሆን ድመቶች ግን እርስ በእርስ ቫይረሱን ሊያስተላልፉ ይችላሉ ብለዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ በተደጋጋሚ የቤት አንስሳት በቫይረሱ መያዛቸው በምርመራ ተረጋግጦ ያውቃል። ባለፈው ወር በሳንዲያጎ መካነ አንስሳት ሁለት ጎሬላዎች ይንከባከባቸው ከነበረ ግለሰብ የኮሮናቫይረስ ተይዘው ተገኝተዋል። በኒውዮርክ ብሮንክስ መካነ አንስሳት ደግሞ ዝሆን እና ታይገር፣ በስፔን ባርሴሎና መካነ እንስሳት አንበሳ በኮሮና ተህዋሲ ተይዘዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-55984271 |
2health
| ልጅን አቅፎ መተኛት ወይስ ለብቻ በተዘጋጀ አልጋ ላይ ማስተኛት? | ወላጆች ስለ ልጆቻቸው የሚያሳስቧቸው ጉዳዮች በርካታ ናቸው። ይህ ግን ከአገር አገር፣ ከባህል ባህል፣ ከኑሮ ደረጃ ወይም በሌሎች ምክንያቶች ሊለያይ ይችላል። "ልጄ ክፍሉ ውስጥ ይሆን?" የሚለው ጥያቄ በበርካታ የምዕራቡ ዓለም ወላጆች ጭንቅላት ውስጥ የሚመላለስ ሃሳብ ነው። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን ይህ እየተለወጠ የመጣ ይመስላል። የህጻናት አስተዳደግና ሁኔታም እየተቀያየረ ነው። ይህ ደግሞ በምዕራባውያኑ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የዓለማችን ከፍል እየሆነ ያለ ነው። በአንዳንድ ባህሎች ከልጆች ጋር አንድ ክፍል መጋራት አንዳንዴም አንድ አልጋ ላይ መተኛት የተለመደ ቢሆንም የምዕራቡ ዓለም ወላጆች ግን ልጆቻቸውን የሚያሳድጉበት የራሳቸው የሆነ መንገድ አላቸው። በእቅድ የሚመራ የእንቅልፍ ሥርዓትና የእንቅልፍ ልምምድ ስልጠና እስከመስጠትም ተደርሷል። ምናልባት እነዚህ ነገሮች ዘመናዊና አዲስ ዓይነት ልጆችን የማሳደጊያ መንገዶች መስለው ሊታዩ ይችላሉ። በአሜሪካና ዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ ወላጆች ልጆቻቸው ከተወለዱ በኋላ ቢያንስ ለመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት አብረዋቸው አንድ ክፍል ውስጥ እንዲያስተኟቸው ይመከራሉ። በመላው ዓለም በሚገኙ በርካታ ማሕበረሰቦች፤ ልጆች ከዚህ ረዘም ላለ ጊዜ ከወላጆቻቸው ጋር ያሳልፋሉ። በአውሮፓውያኑ 2016 ላይ በተሰራ አንድ ጥናት መሰረት በተለይ የእስያ አገራት የሚገኙ ወላጆች ረዘም ላለ ጊዜ ከልጆቻቸው ጋር አንድ ክፍል ውስጥ አልያም በአንድ አልጋ ላይ ይተኛሉ። ለምሳሌ እንደ ሕንድ እና ኢንዶኔዢያ ባሉ አገራት 70 በመቶ የሚሆኑት ወላጆች እንዲሁም በስሪላንካ እና ቪዬትናም 80 በመቶ የሚሆኑት ወላጆች ረዘም ላለ ጊዜ ከልጆቻቸው ጋር በአንድ አልጋ ላይ ይተኛሉ። በአፍሪካ ደግሞ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ረዘም ላለ ጊዜ በአንድ ክፍል ውስጥ አልያም በተመሳሳይ አልጋ መተኛት ብዙም የተለመደ አይደለም ይላል ጥናቱ። ከዚህ መረዳት የሚቻለው ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ቢያንስ በመጀመሪያዎቹ ወራት በአንድ አልጋ ላይ መተኛት የተለመደ ነገር መሆኑን ነው። ዴብሚታ ዱታ በሕንዷ ባንጋሎር ዶክተር እና የልጆች አስተዳደግ አማካሪ ሲሆኑ ምንም እንኳን የምዕራባውያን ተጽዕኖዎች ቢኖሩም የአልጋ መጋራት አሁንም ሕንድ ውስጥ ጠንካራ ባህል ነው ይላሉ። ሌላው ቀርቶ በርካታ ልጆች ያሉበት ቤት ቢሆንም አልያም ልጆቹ ሲያድጉ የራሳቸው ክፍል የሚሰጣቸው ቢሆንም በመጀመሪያዎቹ ወራት (እስከ 12 ወራት) ግን ከወላጆቻቸው ጋር በአንድ አልጋ ላይ እንዲተኙ ይደረጋሉ። ''በአንድ አልጋ ላይ መተኛት ዋነኛው ጥቅሙ ልጆች ሌሊት ላይ ከእንቅልፋቸው እንዳይነሱ እና ወላጆቻቸውን እንዳይረብሹ ነው'' ይላሉ ዶክተር ዴብሚታ። አክለውም ''ሴት ልጄ ሰባት ዓመት እስከሚሞላት ድረስ ከእኛ ጋር ነበር አልጋ የምትጋራው። ጡት መጥባት ካቆመች በኋላ እንኳን ከእኛ ጋር መተኛት ትወድ ነበር'' ይላሉ። ልጆች ከልጅነታቸው ጀምሮ ነጻነታቸውን አውጀው እንዲያድጉ ማድረግ የምዕራቡ ዓለም ፍልስፍና ተደርጎ ይቆጠራል። በዚህ ምክንያት ከወላጆች ጋር አልጋ መጋራት ልጆች በራሳቸው ነገሮችን ማድረግ የማይችሉ እንዲሆኑ እንደሚያደርጋቸው ይታመናል። በተጨማሪም ልጆች ከወላጆች ጋር አብረው የሚተኙ ከሆነ ሁሉም ፍላጎታቸው ያለገደብ ይሟላል ተብሎ ይታሰባል። ይህ ደግሞ የልጆች አስተዳደግ ላይ ተጽእኖ ይፈጥራል ይላሉ ምዕራባውያኑ። እንደ ዶክተር ዴብሚታ ያሉ ወላጆች ግን በዚህ ሀሳብ አይስማሙም። '' ትንሽ በራስ መተማመን እንዲኖራቸውና መጠኑን ያላለፈ ነጻነት ከሰጠናቸው ልጆች በራሳቸው ጊዜ ከወላጆቻቸው መለየት ይጀምራሉ። ለዘለአለም ከወላጆቻቸው ጋር መቆየት አይፈልጉም'' ይላሉ ዶክተር ዴብሚታ። በምዕራቡ ዓለም የሚገኙ በርካታ ወላጆች ግን ልጆችን እንቅልፍ ማለማመድ ላይ ተጠምደዋል። ልጆች ቢያለቅሱ እንኳን እዚያው ትንሿ አልጋቸው ላይ ሆነው ለቅሷቸውን እስኪጨርሱ እስከመጠበቅ ደርሰዋል። በዚህ ሂደት ውስጥ ልጆች ለረጅም ጊዜ እንቅልፋቸውን መተኛት እንደሚማሩ ይታሰባል። በዚህ መካከልም ወላጆች በቂ የሆነ እረፈት ያገኛሉ ማለት ነው። በአውስትራሊያ በመንግሥት ድጋፍ የሚደረግላቸው እንቅልፍ ማስተማሪያ ማዕከላት ጭምር አሉ። ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ እነዚህ ማዕከላት ይዘው በመሄድ ልጆቻቸው ረዘም ላለ ጊዜ እንቅልፍ መተኛት እንዲማሩ ማድረግ ይችላሉ። በመሆኑም በተለያዩ አገራት ያለው የባህል ልዩነት ልጆች የት መተኛት አለባቸው የሚለውን ብቻ ሳይሆን መቼ እና እንዴት መተኛት አለባቸው የሚለውን ይወስናል ማለት ነው። በቶክዮ ቤይ ኡራያሱ ኢቺካዋ ሜዲካል ማዕከል ውስጥ በተሰራ ጥናት መሰረት፤ ጃፓን ውስጥ የሚገኙ ህጻናት ሦስተኛ ወራቸው ላይ ሲደርሱ ከሌሎች የእስያ አገራት ያነሰ እንቅልፍ እንደሚተኙ ተገልጿል። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ጃፓን ውስጥ እንቅልፍ የስንፍና ምልክት ተደርጎ ስለሚቆጠር ሊሆን እንደሚችል ይነገራል። በእስያ አገራት የሚገኙ ህጻናት ለምሳሌ ከምዕራቡ ዓለም ህጻናት ጋር ሲነጻጸር እንቅልፍ ሳይተኙ ረዘም ላለ ጊዜ ይቆያሉ። ይህ ደግሞ የሚሆነው ወላጆች ከሥራ ሲመለሱም ይሁን በየትኛውም አጋጣሚ ከልጆቻቸው ጋር እንደ ልብ መጫወትና ጊዜ ማሳለፍ ስለሚፈልጉ ነው ይላል ጥናቱ። በዩናይትድ ኪንግደም ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር በአንድ ክፍል ውስጥ እንዲተኙ ይመከራል። ልክ እንደ ዩናይትድ ኪንግደም በአሜሪካም የዘርፉ ባለሙያዎች ተመሳሳይ ምክር ይሰጣሉ። ምክንያቱ ደግሞ ልጆች ብቻቸውን ሆነው የሆነ እክል ቢያጋጥማቸው ሊከሰት የሚችለውን የሞት ቁጥር ለመቀነስ ብቻ ነው። ይሁን እንጅ ባለሙያዎቹ ከልጆች ጋር አንድ ላይ መተኛትን አጥብቀው ይቃወማሉ። ለዚህ በምክንያትነት የተቀመጠው ደግሞ ልጆች ታፍነው ሊሞቱ ይችላሉ የሚል ነው። ነገር ግን በጉዳዩ ላይ በቂና ጥልቅ የሆነ ምርምር ባለመካሄዱ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር አልጋ መጋራታቸው ጠቃሚ ነው ወይስ ጎጂ የሚለው ላይ ጥርት ያለ አቋም መያዝ ከባድ ነው ይላሉ- የህጻናት ህክምና ባለሙያው ዶክተር ራሽሚ ዲያዝ። በዚህ ጉዳይ የተሰሩት ጥናቶችም ቢሆኑ አብዛኛዎቹ ካደጉት አገራት በተሰበሰበ መረጃ ላይ የተመሰረቱ ናቸው። በእነዚህ አገራት ደግሞ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር አልጋ የመጋራት ባህላቸው ዝቅተኛ ነው። በሌላ በኩል ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው አገራት ከልጆች ጋር አልጋ መጋራት የተለመደ ባህል ሲሆን በእነዚህ አገራት በእንቅልፍ ላይ እያሉ የሚሞቱ ህጻናት ቁጥር በእጅጉ ዝቅተኛ ነው። ልክ ከልጆች ጋር አልጋ መጋራት ሌሊት ላይ ቅርብ ለመሆን እንደሚያስችለው ሁሉ፤ ልጆች ቀን ላይ እንዳይተኙ ማድረግ ደግሞ ወላጆች ሥራቸውን እየሰሩ ከልጆቻቸው ጋር ጥሩ ጊዜ እንዲያሳልፉ ሊረዳቸው ይችላል። ሌላኛው ከልጆች አስተዳደግ ጋር የሚነሳው ነጥብ ልጆችን አቅፎ መንቀሳቀስ ብዙ እንዳያለቅሱ ያደርጋቸዋል ወይ የሚለው ነው። በዚሁ ጉዳይ ላይ ምርምር የሰራችው ኩሮዳ እንደምትለው ወላጆች ልጆቻቸውን አቀፏቸው፣ አዘሏቸው ወይም አላዘሏቸው ማልቀሳቸው አይቀርም። ''ልጆችን ማቀፍ እና እንዳያለቅሱ ማድረግ ምንም አይነት ግንኙነት የላቸውም። በዚህ ላይ ልስማማ አልችልም'' ትላለች። በኩሮዳ ጥናት መሰረት ልጆችን ማቀፍ የልብ ምታቸውና እንቅስቃሴያቸው እንዲቀንስ እንደሚያደረግ የተስተዋለ ሲሆን ከለቅሷቸው ጋር ግን የሚገናኘው ነገር የለም። ነገር ግን ልጆችን አቅፎ ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሱ ትኩረታቸው በሌላ ነገር ላይ እንዲሆን ሲደረግ የማልቀሳቸው መጠን የሚቀንስ ሲሆን እያለቀሱም ከሆነ የማቆም እድላቸው ከፍተኛ ነው። ከልጆች ጋር ዐይን ለዐይን መተያየት ሁሌም ቢሆን ከህጻናቱ በኩል የሚጠበቅ ነገር ነው። ከዚህ በተጨማሪ ለመጀመሪያዎቹ ወራት ህጻናት ያለማቋረጥ ምግብ መመገብ አለባቸው። ሌላው ቀርቶ ከአዋቂዎች የእንቅልፍ ሥርዓት ጋር መላመድ በሚጀምሩበት ወቅት እንኳን እስከ አንድ ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ሌሊት ላይ ከእንቅልፋቸው ሊነቁ ይችላሉ። ይህ ደግሞ የተለመደ ነገር ነው። ነገር ግን ምዕራባውያን ወላጆች ከጓደኞቻቸውና ቤተሰቦቻቸው የሚነገራቸው ነገር ለየት ያለ ነው። ልጆች ሌሊት ላይ የሚነቁ ከሆነ ችግር ውስጥ እንደሆኑ ነው የሚነገራቸው። ይህ ደግሞ ከባህል ጋር የሚገናኝ ነገር ነው። ልጆች ሌሊት መነሳታቸው የተለመደና ጤናማ ነገር ቢሆንም፤ ቀን ላይ ረዥም ሰዓት የማይተኙ ከሆነ ግን ሌሊት ላይ ሳይነቁ ሊተኙ ይችላሉ። ልጆች ሌሊት ላይ ለጥ ብለው መተኛት አለባቸው የሚለው ብሂል የመጣው በአውሮፓውያኑ 1950ዎቹ አካባቢ በተሰራ አንድ ጥናት ላይ ተመስርቶ ነው። በጥናቱ መሰረት ከእንግሊዟ ለንደን ከተማ ከተውጣጡ ከ160 ህጻናት መካከል 70 በመቶ የሚሆኑት ህጻናት በሦስተኛ ወራቸው ላይ ሌሊቱን ሙሉ ነበር የሚተኙት። ነገር ግን ተመራማሪዎቹ ሌሊቱን ሙሉ መተኛት ብለው የገለጹት ህጻናቱ ሌሊት ላይ ወላጆቻቸውን አለመረበሻቸውንና ድምጻቸው አለመሰማቱን ብቻ ነው። ምናልባት ህጻናቱ ወላጆቻቸውን አይረብሹ እንጂ ቢያንስ አንድ ጊዜ እንኳን መንቃታቸው አይቀርም። አሁንም ቢሆን ከህጻናት እንቅልፍና አስተዳደግ ጋር በተያያዘ የሚሰሩት ጥናቶች በጣም ጥቂት የሚባል የዓለማችንን ማህበረሰብ ከግምት ውስጥ ያስገባ ነው። አብዛኛዎቹ ጥናቶች የተሰሩት 'ባደጉት' በሚባሉት ምዕራባውያን አገራት ውስጥ በሚገኙ ህጻናት ላይ ብቻ ነው። ምንም እንኳን በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ያለው የልጆች አስተዳደግ በተለያዩ ባህሎች ላይ የተመሰረተ ቢሆንም፤ ልጆች ሁልጊዜም ከወላጆቻቸው ተገቢውን ጊዜና እንክብካቤ ማግኘት አለባቸው የሚለው ግን አጠያያቂ ጉዳይ አይደለም። | ልጅን አቅፎ መተኛት ወይስ ለብቻ በተዘጋጀ አልጋ ላይ ማስተኛት? ወላጆች ስለ ልጆቻቸው የሚያሳስቧቸው ጉዳዮች በርካታ ናቸው። ይህ ግን ከአገር አገር፣ ከባህል ባህል፣ ከኑሮ ደረጃ ወይም በሌሎች ምክንያቶች ሊለያይ ይችላል። "ልጄ ክፍሉ ውስጥ ይሆን?" የሚለው ጥያቄ በበርካታ የምዕራቡ ዓለም ወላጆች ጭንቅላት ውስጥ የሚመላለስ ሃሳብ ነው። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን ይህ እየተለወጠ የመጣ ይመስላል። የህጻናት አስተዳደግና ሁኔታም እየተቀያየረ ነው። ይህ ደግሞ በምዕራባውያኑ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የዓለማችን ከፍል እየሆነ ያለ ነው። በአንዳንድ ባህሎች ከልጆች ጋር አንድ ክፍል መጋራት አንዳንዴም አንድ አልጋ ላይ መተኛት የተለመደ ቢሆንም የምዕራቡ ዓለም ወላጆች ግን ልጆቻቸውን የሚያሳድጉበት የራሳቸው የሆነ መንገድ አላቸው። በእቅድ የሚመራ የእንቅልፍ ሥርዓትና የእንቅልፍ ልምምድ ስልጠና እስከመስጠትም ተደርሷል። ምናልባት እነዚህ ነገሮች ዘመናዊና አዲስ ዓይነት ልጆችን የማሳደጊያ መንገዶች መስለው ሊታዩ ይችላሉ። በአሜሪካና ዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ ወላጆች ልጆቻቸው ከተወለዱ በኋላ ቢያንስ ለመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት አብረዋቸው አንድ ክፍል ውስጥ እንዲያስተኟቸው ይመከራሉ። በመላው ዓለም በሚገኙ በርካታ ማሕበረሰቦች፤ ልጆች ከዚህ ረዘም ላለ ጊዜ ከወላጆቻቸው ጋር ያሳልፋሉ። በአውሮፓውያኑ 2016 ላይ በተሰራ አንድ ጥናት መሰረት በተለይ የእስያ አገራት የሚገኙ ወላጆች ረዘም ላለ ጊዜ ከልጆቻቸው ጋር አንድ ክፍል ውስጥ አልያም በአንድ አልጋ ላይ ይተኛሉ። ለምሳሌ እንደ ሕንድ እና ኢንዶኔዢያ ባሉ አገራት 70 በመቶ የሚሆኑት ወላጆች እንዲሁም በስሪላንካ እና ቪዬትናም 80 በመቶ የሚሆኑት ወላጆች ረዘም ላለ ጊዜ ከልጆቻቸው ጋር በአንድ አልጋ ላይ ይተኛሉ። በአፍሪካ ደግሞ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ረዘም ላለ ጊዜ በአንድ ክፍል ውስጥ አልያም በተመሳሳይ አልጋ መተኛት ብዙም የተለመደ አይደለም ይላል ጥናቱ። ከዚህ መረዳት የሚቻለው ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ቢያንስ በመጀመሪያዎቹ ወራት በአንድ አልጋ ላይ መተኛት የተለመደ ነገር መሆኑን ነው። ዴብሚታ ዱታ በሕንዷ ባንጋሎር ዶክተር እና የልጆች አስተዳደግ አማካሪ ሲሆኑ ምንም እንኳን የምዕራባውያን ተጽዕኖዎች ቢኖሩም የአልጋ መጋራት አሁንም ሕንድ ውስጥ ጠንካራ ባህል ነው ይላሉ። ሌላው ቀርቶ በርካታ ልጆች ያሉበት ቤት ቢሆንም አልያም ልጆቹ ሲያድጉ የራሳቸው ክፍል የሚሰጣቸው ቢሆንም በመጀመሪያዎቹ ወራት (እስከ 12 ወራት) ግን ከወላጆቻቸው ጋር በአንድ አልጋ ላይ እንዲተኙ ይደረጋሉ። ''በአንድ አልጋ ላይ መተኛት ዋነኛው ጥቅሙ ልጆች ሌሊት ላይ ከእንቅልፋቸው እንዳይነሱ እና ወላጆቻቸውን እንዳይረብሹ ነው'' ይላሉ ዶክተር ዴብሚታ። አክለውም ''ሴት ልጄ ሰባት ዓመት እስከሚሞላት ድረስ ከእኛ ጋር ነበር አልጋ የምትጋራው። ጡት መጥባት ካቆመች በኋላ እንኳን ከእኛ ጋር መተኛት ትወድ ነበር'' ይላሉ። ልጆች ከልጅነታቸው ጀምሮ ነጻነታቸውን አውጀው እንዲያድጉ ማድረግ የምዕራቡ ዓለም ፍልስፍና ተደርጎ ይቆጠራል። በዚህ ምክንያት ከወላጆች ጋር አልጋ መጋራት ልጆች በራሳቸው ነገሮችን ማድረግ የማይችሉ እንዲሆኑ እንደሚያደርጋቸው ይታመናል። በተጨማሪም ልጆች ከወላጆች ጋር አብረው የሚተኙ ከሆነ ሁሉም ፍላጎታቸው ያለገደብ ይሟላል ተብሎ ይታሰባል። ይህ ደግሞ የልጆች አስተዳደግ ላይ ተጽእኖ ይፈጥራል ይላሉ ምዕራባውያኑ። እንደ ዶክተር ዴብሚታ ያሉ ወላጆች ግን በዚህ ሀሳብ አይስማሙም። '' ትንሽ በራስ መተማመን እንዲኖራቸውና መጠኑን ያላለፈ ነጻነት ከሰጠናቸው ልጆች በራሳቸው ጊዜ ከወላጆቻቸው መለየት ይጀምራሉ። ለዘለአለም ከወላጆቻቸው ጋር መቆየት አይፈልጉም'' ይላሉ ዶክተር ዴብሚታ። በምዕራቡ ዓለም የሚገኙ በርካታ ወላጆች ግን ልጆችን እንቅልፍ ማለማመድ ላይ ተጠምደዋል። ልጆች ቢያለቅሱ እንኳን እዚያው ትንሿ አልጋቸው ላይ ሆነው ለቅሷቸውን እስኪጨርሱ እስከመጠበቅ ደርሰዋል። በዚህ ሂደት ውስጥ ልጆች ለረጅም ጊዜ እንቅልፋቸውን መተኛት እንደሚማሩ ይታሰባል። በዚህ መካከልም ወላጆች በቂ የሆነ እረፈት ያገኛሉ ማለት ነው። በአውስትራሊያ በመንግሥት ድጋፍ የሚደረግላቸው እንቅልፍ ማስተማሪያ ማዕከላት ጭምር አሉ። ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ እነዚህ ማዕከላት ይዘው በመሄድ ልጆቻቸው ረዘም ላለ ጊዜ እንቅልፍ መተኛት እንዲማሩ ማድረግ ይችላሉ። በመሆኑም በተለያዩ አገራት ያለው የባህል ልዩነት ልጆች የት መተኛት አለባቸው የሚለውን ብቻ ሳይሆን መቼ እና እንዴት መተኛት አለባቸው የሚለውን ይወስናል ማለት ነው። በቶክዮ ቤይ ኡራያሱ ኢቺካዋ ሜዲካል ማዕከል ውስጥ በተሰራ ጥናት መሰረት፤ ጃፓን ውስጥ የሚገኙ ህጻናት ሦስተኛ ወራቸው ላይ ሲደርሱ ከሌሎች የእስያ አገራት ያነሰ እንቅልፍ እንደሚተኙ ተገልጿል። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ጃፓን ውስጥ እንቅልፍ የስንፍና ምልክት ተደርጎ ስለሚቆጠር ሊሆን እንደሚችል ይነገራል። በእስያ አገራት የሚገኙ ህጻናት ለምሳሌ ከምዕራቡ ዓለም ህጻናት ጋር ሲነጻጸር እንቅልፍ ሳይተኙ ረዘም ላለ ጊዜ ይቆያሉ። ይህ ደግሞ የሚሆነው ወላጆች ከሥራ ሲመለሱም ይሁን በየትኛውም አጋጣሚ ከልጆቻቸው ጋር እንደ ልብ መጫወትና ጊዜ ማሳለፍ ስለሚፈልጉ ነው ይላል ጥናቱ። በዩናይትድ ኪንግደም ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር በአንድ ክፍል ውስጥ እንዲተኙ ይመከራል። ልክ እንደ ዩናይትድ ኪንግደም በአሜሪካም የዘርፉ ባለሙያዎች ተመሳሳይ ምክር ይሰጣሉ። ምክንያቱ ደግሞ ልጆች ብቻቸውን ሆነው የሆነ እክል ቢያጋጥማቸው ሊከሰት የሚችለውን የሞት ቁጥር ለመቀነስ ብቻ ነው። ይሁን እንጅ ባለሙያዎቹ ከልጆች ጋር አንድ ላይ መተኛትን አጥብቀው ይቃወማሉ። ለዚህ በምክንያትነት የተቀመጠው ደግሞ ልጆች ታፍነው ሊሞቱ ይችላሉ የሚል ነው። ነገር ግን በጉዳዩ ላይ በቂና ጥልቅ የሆነ ምርምር ባለመካሄዱ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር አልጋ መጋራታቸው ጠቃሚ ነው ወይስ ጎጂ የሚለው ላይ ጥርት ያለ አቋም መያዝ ከባድ ነው ይላሉ- የህጻናት ህክምና ባለሙያው ዶክተር ራሽሚ ዲያዝ። በዚህ ጉዳይ የተሰሩት ጥናቶችም ቢሆኑ አብዛኛዎቹ ካደጉት አገራት በተሰበሰበ መረጃ ላይ የተመሰረቱ ናቸው። በእነዚህ አገራት ደግሞ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር አልጋ የመጋራት ባህላቸው ዝቅተኛ ነው። በሌላ በኩል ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው አገራት ከልጆች ጋር አልጋ መጋራት የተለመደ ባህል ሲሆን በእነዚህ አገራት በእንቅልፍ ላይ እያሉ የሚሞቱ ህጻናት ቁጥር በእጅጉ ዝቅተኛ ነው። ልክ ከልጆች ጋር አልጋ መጋራት ሌሊት ላይ ቅርብ ለመሆን እንደሚያስችለው ሁሉ፤ ልጆች ቀን ላይ እንዳይተኙ ማድረግ ደግሞ ወላጆች ሥራቸውን እየሰሩ ከልጆቻቸው ጋር ጥሩ ጊዜ እንዲያሳልፉ ሊረዳቸው ይችላል። ሌላኛው ከልጆች አስተዳደግ ጋር የሚነሳው ነጥብ ልጆችን አቅፎ መንቀሳቀስ ብዙ እንዳያለቅሱ ያደርጋቸዋል ወይ የሚለው ነው። በዚሁ ጉዳይ ላይ ምርምር የሰራችው ኩሮዳ እንደምትለው ወላጆች ልጆቻቸውን አቀፏቸው፣ አዘሏቸው ወይም አላዘሏቸው ማልቀሳቸው አይቀርም። ''ልጆችን ማቀፍ እና እንዳያለቅሱ ማድረግ ምንም አይነት ግንኙነት የላቸውም። በዚህ ላይ ልስማማ አልችልም'' ትላለች። በኩሮዳ ጥናት መሰረት ልጆችን ማቀፍ የልብ ምታቸውና እንቅስቃሴያቸው እንዲቀንስ እንደሚያደረግ የተስተዋለ ሲሆን ከለቅሷቸው ጋር ግን የሚገናኘው ነገር የለም። ነገር ግን ልጆችን አቅፎ ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሱ ትኩረታቸው በሌላ ነገር ላይ እንዲሆን ሲደረግ የማልቀሳቸው መጠን የሚቀንስ ሲሆን እያለቀሱም ከሆነ የማቆም እድላቸው ከፍተኛ ነው። ከልጆች ጋር ዐይን ለዐይን መተያየት ሁሌም ቢሆን ከህጻናቱ በኩል የሚጠበቅ ነገር ነው። ከዚህ በተጨማሪ ለመጀመሪያዎቹ ወራት ህጻናት ያለማቋረጥ ምግብ መመገብ አለባቸው። ሌላው ቀርቶ ከአዋቂዎች የእንቅልፍ ሥርዓት ጋር መላመድ በሚጀምሩበት ወቅት እንኳን እስከ አንድ ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ሌሊት ላይ ከእንቅልፋቸው ሊነቁ ይችላሉ። ይህ ደግሞ የተለመደ ነገር ነው። ነገር ግን ምዕራባውያን ወላጆች ከጓደኞቻቸውና ቤተሰቦቻቸው የሚነገራቸው ነገር ለየት ያለ ነው። ልጆች ሌሊት ላይ የሚነቁ ከሆነ ችግር ውስጥ እንደሆኑ ነው የሚነገራቸው። ይህ ደግሞ ከባህል ጋር የሚገናኝ ነገር ነው። ልጆች ሌሊት መነሳታቸው የተለመደና ጤናማ ነገር ቢሆንም፤ ቀን ላይ ረዥም ሰዓት የማይተኙ ከሆነ ግን ሌሊት ላይ ሳይነቁ ሊተኙ ይችላሉ። ልጆች ሌሊት ላይ ለጥ ብለው መተኛት አለባቸው የሚለው ብሂል የመጣው በአውሮፓውያኑ 1950ዎቹ አካባቢ በተሰራ አንድ ጥናት ላይ ተመስርቶ ነው። በጥናቱ መሰረት ከእንግሊዟ ለንደን ከተማ ከተውጣጡ ከ160 ህጻናት መካከል 70 በመቶ የሚሆኑት ህጻናት በሦስተኛ ወራቸው ላይ ሌሊቱን ሙሉ ነበር የሚተኙት። ነገር ግን ተመራማሪዎቹ ሌሊቱን ሙሉ መተኛት ብለው የገለጹት ህጻናቱ ሌሊት ላይ ወላጆቻቸውን አለመረበሻቸውንና ድምጻቸው አለመሰማቱን ብቻ ነው። ምናልባት ህጻናቱ ወላጆቻቸውን አይረብሹ እንጂ ቢያንስ አንድ ጊዜ እንኳን መንቃታቸው አይቀርም። አሁንም ቢሆን ከህጻናት እንቅልፍና አስተዳደግ ጋር በተያያዘ የሚሰሩት ጥናቶች በጣም ጥቂት የሚባል የዓለማችንን ማህበረሰብ ከግምት ውስጥ ያስገባ ነው። አብዛኛዎቹ ጥናቶች የተሰሩት 'ባደጉት' በሚባሉት ምዕራባውያን አገራት ውስጥ በሚገኙ ህጻናት ላይ ብቻ ነው። ምንም እንኳን በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ያለው የልጆች አስተዳደግ በተለያዩ ባህሎች ላይ የተመሰረተ ቢሆንም፤ ልጆች ሁልጊዜም ከወላጆቻቸው ተገቢውን ጊዜና እንክብካቤ ማግኘት አለባቸው የሚለው ግን አጠያያቂ ጉዳይ አይደለም። | https://www.bbc.com/amharic/news-56549405 |
2health
| በአፍሪካ የተፈራውን ያክል ድህነት ሰዎችን ለኮሮናቫይረስ አጋልጧል? | ከአፍሪካ በኮሮናቫይረስ በተያዙ ሰዎች ቁጥር ቀዳሚዋ ደቡብ አፍሪካ ናት። አሁን ላይ ግን በአገሪቱ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ነው። በሌሎች የአፍሪካ አገራት ያለው ስርጭት መጠንም በአንጻራዊነት ዝግ ያለ ነው። አፍሪካ ውስጥ በርካታ የተጨናነቁ መንደሮች አሉ። በእነዚህ መንደሮች ንጽህናና አካላዊ ርቀት መጠበቅ ከባድ ነው። በአንጻራዊነት ደህና በሚባሉ ከተማ ቀመስ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች ቫይረሱን በፍጥነት ሊያሰራጩት እንደሚችሉ የጤና ባለሙያዎች ሲያስጠነቅቁ ተደምጠዋል። በደቡብ አፍሪካ የኮቪድ-19 አማካሪ ቡድን ኃላፊ ሳሊም አብዱል ካሪም እንደሚሉት፤ ሰዎች በብዛት፣ ተጨናንቀው በሚኖሩባቸው አካባቢዎች ቫይረሱ በፍጥነት ይሰራጫል። እውነታው ከዚህ የባለሙያዎች መላ ምት ተቃራኒ ቢሆንስ? የተጨናነቁ መንደሮች እንደተገመተው ለበሽታው መሰራጨት ምክንያት ሳይሆኑ እንዲያውም ቫይረሱ በስፋት እንዳይስፋፋ አድርገው ቢሆንስ? የአህጉሪቱ ድህነት እንደተፈራው ለወረርሽኙ ተጋላጭ ሳያደርጋት ቀርቶ ቢሆንስ? ሚሥጥሩ ምንድን ነው? ኮሮናቫይረስ መሰራጨት ሲጀምር ሁሉም ባለሙያዎች አፍሪካ አደጋ ውስጥ ትወድቃለች ብለዋል። የደቡብ አፍሪካው ቫይሮሎጂስት ሻቢር ማህዲ “ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደምንገባ አስቤ ነበር። አበቃልን ብዬም ነበር” ይላሉ። በጣም ተስፋ ሰጪ ናቸው የተባሉ መላ ምቶች ሳይቀሩ ለህሙማን አልጋ እንደሚጠፋ፣ የጤና ሥርዓቱ እንደሚቃወስ ሲጠቁሙ ነበር። ሆኖም ግን በደቡብ አፍሪካ በቫይረሱ ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከዩናይትድ ኪንግደም በሰባት እጥፍ ያንሳል። ደቡብ አፍሪካ ብቻ ሳትሆን ሌሎች አገራትም የተፈራው ያህል ቫይረሱ ጉዳት እያደረሰባቸው አይደለም። ሆስፒታሎች እንደተሰጋው አልተጨናነቁም። በተቀረው ዓለም እንደተከሰተው የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ ጫፍ ላይ ደርሶም አልታየም። ፕ/ር ሻቢር፤ “በአብዛኞቹ የአፍሪካ አገራት የቫይረሱ ስርጭት ጫፍ አልታየም። ለምን እንደሆነ አልገባኝም። ግልጽ ያልሆነና ለማመን የሚያስቸግር ነው” ይላሉ። አፍሪካ ውስጥ ኮሮናቫይረስ በአስጊ ሁኔታ ያልተሰራጨው አብዛኛው የአህጉሪቱ ነዋሪ ወጣት ስለሆነ ነው የሚሉ ባለሙያዎች አሉ። የአፍሪካውያን አማካይ እድሜ ከአውሮፓውያኑ በግማሽ ያንሳል። የቶኒ ብሌር ተቋም የአፍሪካ ዳይሬክተር ቲም ብሮምፊልድ እንደሚሉት፤ አፍሪካ የወጣቶች አህጉር መሆኗ ከበሽታው ተከላክሏታል። ነገር ግን በበሽታው የተያዙ ሰዎችን እድሜ ከግምት ያስገቡ የስታትስቲክስ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፤ እድሜ ከበሽታው የሚከላከል ብቸኛ ነገር አይደለም። ፕ/ር ሳሊም “ትልቁ ነጥብ እድሜ አይደለም” የሚሉትም ለዚህ ነው። በደቡብ አፍሪካ እና በሌሎችም አገራት ወረርሽኙ መሰራጨት እንደጀመረ የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሉ ሚናው ቀላል አይደለም። ሰዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንዲያደርጉም ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ተላልፏል። በሌላ በኩል የአህጉሪቱ ከፍታ እና ሙቀት የበሽታውን ስርጭት ይቀንሳል የሚለው መላ ምት እንደማይሠራ ተገልጿል። በቂ የመሠረተ ልማት ዝርጋት ባለመኖሩ ለወደፊት በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ሊጨምር ይችላል የሚል ስጋት ያላቸው አሉ። “አፍሪካ ክፉውን ጊዜ አልፋለች ማለት አልችልም። አንድ ቀን ወረርሽኙ በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምር ይሆናል” ሲሉ ፕ/ር ሳሊም ያስረዳሉ። ሌሎቹ ኮሮናቫይረሶች በሶዌቶ የክትባት ቤተ ሙከራ ውስጥ ሳይንቲስቶች ምርምር እያደረጉ ይገኛሉ። በቤተ ሙከራው ለአምስት ዓመታት የቆየ የሰው ደም ናሙና አለ። ይህም የኢንፍሉዌንዛ ክትባት ላይ ምርምር ሲካሄድ የተገኘ ናሙና ነው። ተመራማሪዎቹ፤ ሰዎች በሌሎች አይነት ኮሮናቫይረሶች መያዛቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ እየፈለጉ ነው። ይህ ማለት ሰውነት ራሱን ከኮቪድ-19 የሚከላከልበት አቅም አዳብሯል ማለት ነው። “ከዚህ ቀደም በሽታን የመከላከል አቅም ማዳበር ተችሎ ሊሆን ይችላል። ቫይረሱ በሌሎች የዓለም ክፍሎች የተስፋፋው ያህል በአፍሪካ ያልተሰራጨውም ለዚህ ይሆናል” ይላሉ ፕ/ር ሻቢር። በተጨናነቀ መንደር የሚኖሩ ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ስለሆኑ ምናልባትም በጊዜ ሂደት ኮቪድ-19ን መከላከል የሚያስችል አቅም አዳብረው ሊሆን እንደሚችል የደቡብ አፍሪካ ሳይንቲስቶች ይገምታሉ። “በከፍተኛ ሁኔታ በተጨናነቁ አካባቢዎች በሽታውን የመከላከል አቅም ሊፈጠር ይችላል። ብዙ ሰዎች ምንም የበሽታው ምልክት የማይታይባቸው ወይም መጠነኛ ምልክት የሚያሳዩት ለዚህ ይሆናል” ሲሉ ፕሮፌሰሩ ያስረዳሉ። የአፍሪካ ድህነት የኮሮናቫይረስ ተጋላጭነትን ቀንሶት ሊሆን እንደሚችልም ያምናሉ። በሌላ በኩል እንደ ብራዚል ባሉ ዜጎች ተጨናንቀው የሚኖሩባቸው አገሮች በርካቶች በቫይረሱ እየተያዙ ነው። | በአፍሪካ የተፈራውን ያክል ድህነት ሰዎችን ለኮሮናቫይረስ አጋልጧል? ከአፍሪካ በኮሮናቫይረስ በተያዙ ሰዎች ቁጥር ቀዳሚዋ ደቡብ አፍሪካ ናት። አሁን ላይ ግን በአገሪቱ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ነው። በሌሎች የአፍሪካ አገራት ያለው ስርጭት መጠንም በአንጻራዊነት ዝግ ያለ ነው። አፍሪካ ውስጥ በርካታ የተጨናነቁ መንደሮች አሉ። በእነዚህ መንደሮች ንጽህናና አካላዊ ርቀት መጠበቅ ከባድ ነው። በአንጻራዊነት ደህና በሚባሉ ከተማ ቀመስ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች ቫይረሱን በፍጥነት ሊያሰራጩት እንደሚችሉ የጤና ባለሙያዎች ሲያስጠነቅቁ ተደምጠዋል። በደቡብ አፍሪካ የኮቪድ-19 አማካሪ ቡድን ኃላፊ ሳሊም አብዱል ካሪም እንደሚሉት፤ ሰዎች በብዛት፣ ተጨናንቀው በሚኖሩባቸው አካባቢዎች ቫይረሱ በፍጥነት ይሰራጫል። እውነታው ከዚህ የባለሙያዎች መላ ምት ተቃራኒ ቢሆንስ? የተጨናነቁ መንደሮች እንደተገመተው ለበሽታው መሰራጨት ምክንያት ሳይሆኑ እንዲያውም ቫይረሱ በስፋት እንዳይስፋፋ አድርገው ቢሆንስ? የአህጉሪቱ ድህነት እንደተፈራው ለወረርሽኙ ተጋላጭ ሳያደርጋት ቀርቶ ቢሆንስ? ሚሥጥሩ ምንድን ነው? ኮሮናቫይረስ መሰራጨት ሲጀምር ሁሉም ባለሙያዎች አፍሪካ አደጋ ውስጥ ትወድቃለች ብለዋል። የደቡብ አፍሪካው ቫይሮሎጂስት ሻቢር ማህዲ “ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደምንገባ አስቤ ነበር። አበቃልን ብዬም ነበር” ይላሉ። በጣም ተስፋ ሰጪ ናቸው የተባሉ መላ ምቶች ሳይቀሩ ለህሙማን አልጋ እንደሚጠፋ፣ የጤና ሥርዓቱ እንደሚቃወስ ሲጠቁሙ ነበር። ሆኖም ግን በደቡብ አፍሪካ በቫይረሱ ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከዩናይትድ ኪንግደም በሰባት እጥፍ ያንሳል። ደቡብ አፍሪካ ብቻ ሳትሆን ሌሎች አገራትም የተፈራው ያህል ቫይረሱ ጉዳት እያደረሰባቸው አይደለም። ሆስፒታሎች እንደተሰጋው አልተጨናነቁም። በተቀረው ዓለም እንደተከሰተው የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ ጫፍ ላይ ደርሶም አልታየም። ፕ/ር ሻቢር፤ “በአብዛኞቹ የአፍሪካ አገራት የቫይረሱ ስርጭት ጫፍ አልታየም። ለምን እንደሆነ አልገባኝም። ግልጽ ያልሆነና ለማመን የሚያስቸግር ነው” ይላሉ። አፍሪካ ውስጥ ኮሮናቫይረስ በአስጊ ሁኔታ ያልተሰራጨው አብዛኛው የአህጉሪቱ ነዋሪ ወጣት ስለሆነ ነው የሚሉ ባለሙያዎች አሉ። የአፍሪካውያን አማካይ እድሜ ከአውሮፓውያኑ በግማሽ ያንሳል። የቶኒ ብሌር ተቋም የአፍሪካ ዳይሬክተር ቲም ብሮምፊልድ እንደሚሉት፤ አፍሪካ የወጣቶች አህጉር መሆኗ ከበሽታው ተከላክሏታል። ነገር ግን በበሽታው የተያዙ ሰዎችን እድሜ ከግምት ያስገቡ የስታትስቲክስ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፤ እድሜ ከበሽታው የሚከላከል ብቸኛ ነገር አይደለም። ፕ/ር ሳሊም “ትልቁ ነጥብ እድሜ አይደለም” የሚሉትም ለዚህ ነው። በደቡብ አፍሪካ እና በሌሎችም አገራት ወረርሽኙ መሰራጨት እንደጀመረ የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሉ ሚናው ቀላል አይደለም። ሰዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እንዲያደርጉም ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ተላልፏል። በሌላ በኩል የአህጉሪቱ ከፍታ እና ሙቀት የበሽታውን ስርጭት ይቀንሳል የሚለው መላ ምት እንደማይሠራ ተገልጿል። በቂ የመሠረተ ልማት ዝርጋት ባለመኖሩ ለወደፊት በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ሊጨምር ይችላል የሚል ስጋት ያላቸው አሉ። “አፍሪካ ክፉውን ጊዜ አልፋለች ማለት አልችልም። አንድ ቀን ወረርሽኙ በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምር ይሆናል” ሲሉ ፕ/ር ሳሊም ያስረዳሉ። ሌሎቹ ኮሮናቫይረሶች በሶዌቶ የክትባት ቤተ ሙከራ ውስጥ ሳይንቲስቶች ምርምር እያደረጉ ይገኛሉ። በቤተ ሙከራው ለአምስት ዓመታት የቆየ የሰው ደም ናሙና አለ። ይህም የኢንፍሉዌንዛ ክትባት ላይ ምርምር ሲካሄድ የተገኘ ናሙና ነው። ተመራማሪዎቹ፤ ሰዎች በሌሎች አይነት ኮሮናቫይረሶች መያዛቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ እየፈለጉ ነው። ይህ ማለት ሰውነት ራሱን ከኮቪድ-19 የሚከላከልበት አቅም አዳብሯል ማለት ነው። “ከዚህ ቀደም በሽታን የመከላከል አቅም ማዳበር ተችሎ ሊሆን ይችላል። ቫይረሱ በሌሎች የዓለም ክፍሎች የተስፋፋው ያህል በአፍሪካ ያልተሰራጨውም ለዚህ ይሆናል” ይላሉ ፕ/ር ሻቢር። በተጨናነቀ መንደር የሚኖሩ ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ስለሆኑ ምናልባትም በጊዜ ሂደት ኮቪድ-19ን መከላከል የሚያስችል አቅም አዳብረው ሊሆን እንደሚችል የደቡብ አፍሪካ ሳይንቲስቶች ይገምታሉ። “በከፍተኛ ሁኔታ በተጨናነቁ አካባቢዎች በሽታውን የመከላከል አቅም ሊፈጠር ይችላል። ብዙ ሰዎች ምንም የበሽታው ምልክት የማይታይባቸው ወይም መጠነኛ ምልክት የሚያሳዩት ለዚህ ይሆናል” ሲሉ ፕሮፌሰሩ ያስረዳሉ። የአፍሪካ ድህነት የኮሮናቫይረስ ተጋላጭነትን ቀንሶት ሊሆን እንደሚችልም ያምናሉ። በሌላ በኩል እንደ ብራዚል ባሉ ዜጎች ተጨናንቀው የሚኖሩባቸው አገሮች በርካቶች በቫይረሱ እየተያዙ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/news-54009884 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ 'የኮቪድ-19 የመጀመሪያውን ዙር ክትባት መውሰድ ቫይረሱ እንዳይስፋፋ ያደርጋል' | የመጀመሪያውን ዙር የኮሮናቫይረስ ክትባት መወጋት የበሽታውን ሥርጭት በግማሽ እንደሚቀንስ አንድ ጥናት አመለከተ። የፋይዘርና የአስትራዜኔካ የመጀመሪያው ዙር ክትባት የተሰጣቸውና ከሦስት ሳምንታት በኋላ በቫይረሱ እንዲያዙ የተደረጉ ሰዎች ቫይረሱን ወደ ሌላ ሰው የማስተላለፍ ዕድላቸው ዝቅ ያለ ነው ብሏ ጥናቱ። የዩናይትድ ኪንግድ ጤና ሚኒስትር ማት ሃንኮክ የጥናቱን ውጤት "አስደናቂ ዜና" ሲሉ ገልፀውታል። ሚኒስትሩ ሰዎች የክትባት ተራቸው ከደረሰ ሳያመነቱ ሄደው እንዲከተቡም አሳስበዋል። በጥናቱ ላይ የተሳተፉ ሰዎች ክትባቱ ከተሰጣቸው ከ14 ቀናት በኋላ በቫይረሱ ቢጋለጡም ብዙም ምልክት አላሳዩም። ምንም እንኳ የጥናቱ ውጤት "የሚበረታታ" ቢሆን ሰዎች ልክ ቫይረሱ እንዳለባቸው እያሰቡ መንቀሳቀስ አለባቸው ይላሉ ዶክተር ሜሪ ራምሴ። ክትባቱ በተለይ በጋራ የሚኖሩ ሰዎች ክትባቱን ከአንድ ወደ ሌላ እንዳያስተላልፉ ፍቱን ነው ይላሉ የጤና ሙያተኞች። የዋርዊክ ዩኒቨርሲቲ ምሁሩ ማይክ ቲልደስሊ ጥናቱ ክትባቶች ምን ያክል ውጤታማ እንደሆኑ ያሳያል፤ ሰዎች ክትባት መውሰድ እንዳለባቸውም ይጠቁማል ይላሉ። ይህ ጥናት የኮሮናቫይረስ ክትባት ምን ያክል የወረርሽኙን ሥርጭት እየገታው እንዳለ ማሳያ ነው ተብሏል። ጥናቱን ያሠራው 'ፐብሊክ ሄልዝ ኢንግላንድ' የተሰኘው የመንግሥት ድርጅት እንደሚለው ክትባቶች ሰዎች ተሰባስበው ለሚኖሩባቸው እንደ ማረሚያ ቤት ላሉ ቦታዎች ፍቱን ነው ይላል። አሁን ምናልባት አስጊ የሚሆነው ነገር አዲስ ዓይነት የኮሮናቫይረስ ዝርያ ቢመጣ ክትባቱ መከላከል ይችላል ወይ የሚለው ነው። ነገር ግን የዘርፉ ሰዎች ክትባቶቹ አዲስ ዓይነት የኮቪድ-19 ዝርያ ቢመጣ እንኳ መከላከል ያስችላሉ ይላሉ። ክትባት ምንድነው? ክትባት ማለት ለአንድ ኢንፌክሽን፣ በሽታ ወይም ተህዋሲ ሰውነታችን እንዲከላከል የሚዘጋጅ ጠብታ ነው። ክትባት በይዘቱ የተዳከመ የተህዋሲ ቅንጣትን የያዘ ሊሆን ይችላል። ይህም ማለት በሽታውን፣ ቫይረሱን አሊያም ክትባቱን ነው ሰዎች የሚወጉት ማለት ነው። ወይም ደግሞ በሽታው በሽታ እንዳያስከትል በሚያስችል ደረጃ ራሱን ለሰውነታችን ብቻ እንዲያጋልጥ አድርጎ ማንነቱን ማሳጣት ማለት ነው። በዚህ ሂደት የሰውነታችን በሽታ ተከላካይ ሠራዊት ለጠላት ኃይል እንዳይሸነፍ፣ እጅ እንዳይሰጥ፣ እንዲነቃ፣ የማንቃት ትጥቅና ስንቅን የማቀበል ያህል ነው የክትባቱ ሁነኛ ተግባር። ክትባት ለሕመም አያጋልጥም። ነገር ግን አንዳንድ ሰዎችን ሊያዳክማቸው፣ ወይም መጠነኛ የጎንዮሽ ጉዳት ሊያደርስባቸው ይችላል። ከእነዚህም ምልክቶች መካከል ክንድ ላይ ቁስለት ወይም ደግሞ ጊዜያዊ ትኩሳት የተለመዱ ናቸው። | ኮሮናቫይረስ፡ 'የኮቪድ-19 የመጀመሪያውን ዙር ክትባት መውሰድ ቫይረሱ እንዳይስፋፋ ያደርጋል' የመጀመሪያውን ዙር የኮሮናቫይረስ ክትባት መወጋት የበሽታውን ሥርጭት በግማሽ እንደሚቀንስ አንድ ጥናት አመለከተ። የፋይዘርና የአስትራዜኔካ የመጀመሪያው ዙር ክትባት የተሰጣቸውና ከሦስት ሳምንታት በኋላ በቫይረሱ እንዲያዙ የተደረጉ ሰዎች ቫይረሱን ወደ ሌላ ሰው የማስተላለፍ ዕድላቸው ዝቅ ያለ ነው ብሏ ጥናቱ። የዩናይትድ ኪንግድ ጤና ሚኒስትር ማት ሃንኮክ የጥናቱን ውጤት "አስደናቂ ዜና" ሲሉ ገልፀውታል። ሚኒስትሩ ሰዎች የክትባት ተራቸው ከደረሰ ሳያመነቱ ሄደው እንዲከተቡም አሳስበዋል። በጥናቱ ላይ የተሳተፉ ሰዎች ክትባቱ ከተሰጣቸው ከ14 ቀናት በኋላ በቫይረሱ ቢጋለጡም ብዙም ምልክት አላሳዩም። ምንም እንኳ የጥናቱ ውጤት "የሚበረታታ" ቢሆን ሰዎች ልክ ቫይረሱ እንዳለባቸው እያሰቡ መንቀሳቀስ አለባቸው ይላሉ ዶክተር ሜሪ ራምሴ። ክትባቱ በተለይ በጋራ የሚኖሩ ሰዎች ክትባቱን ከአንድ ወደ ሌላ እንዳያስተላልፉ ፍቱን ነው ይላሉ የጤና ሙያተኞች። የዋርዊክ ዩኒቨርሲቲ ምሁሩ ማይክ ቲልደስሊ ጥናቱ ክትባቶች ምን ያክል ውጤታማ እንደሆኑ ያሳያል፤ ሰዎች ክትባት መውሰድ እንዳለባቸውም ይጠቁማል ይላሉ። ይህ ጥናት የኮሮናቫይረስ ክትባት ምን ያክል የወረርሽኙን ሥርጭት እየገታው እንዳለ ማሳያ ነው ተብሏል። ጥናቱን ያሠራው 'ፐብሊክ ሄልዝ ኢንግላንድ' የተሰኘው የመንግሥት ድርጅት እንደሚለው ክትባቶች ሰዎች ተሰባስበው ለሚኖሩባቸው እንደ ማረሚያ ቤት ላሉ ቦታዎች ፍቱን ነው ይላል። አሁን ምናልባት አስጊ የሚሆነው ነገር አዲስ ዓይነት የኮሮናቫይረስ ዝርያ ቢመጣ ክትባቱ መከላከል ይችላል ወይ የሚለው ነው። ነገር ግን የዘርፉ ሰዎች ክትባቶቹ አዲስ ዓይነት የኮቪድ-19 ዝርያ ቢመጣ እንኳ መከላከል ያስችላሉ ይላሉ። ክትባት ምንድነው? ክትባት ማለት ለአንድ ኢንፌክሽን፣ በሽታ ወይም ተህዋሲ ሰውነታችን እንዲከላከል የሚዘጋጅ ጠብታ ነው። ክትባት በይዘቱ የተዳከመ የተህዋሲ ቅንጣትን የያዘ ሊሆን ይችላል። ይህም ማለት በሽታውን፣ ቫይረሱን አሊያም ክትባቱን ነው ሰዎች የሚወጉት ማለት ነው። ወይም ደግሞ በሽታው በሽታ እንዳያስከትል በሚያስችል ደረጃ ራሱን ለሰውነታችን ብቻ እንዲያጋልጥ አድርጎ ማንነቱን ማሳጣት ማለት ነው። በዚህ ሂደት የሰውነታችን በሽታ ተከላካይ ሠራዊት ለጠላት ኃይል እንዳይሸነፍ፣ እጅ እንዳይሰጥ፣ እንዲነቃ፣ የማንቃት ትጥቅና ስንቅን የማቀበል ያህል ነው የክትባቱ ሁነኛ ተግባር። ክትባት ለሕመም አያጋልጥም። ነገር ግን አንዳንድ ሰዎችን ሊያዳክማቸው፣ ወይም መጠነኛ የጎንዮሽ ጉዳት ሊያደርስባቸው ይችላል። ከእነዚህም ምልክቶች መካከል ክንድ ላይ ቁስለት ወይም ደግሞ ጊዜያዊ ትኩሳት የተለመዱ ናቸው። | https://www.bbc.com/amharic/news-56926149 |
5sports
| አርሰናል ቼልሲን አሸንፎ መሪነቱን ሲያስቀጥል ኒውካስል በግስጋሴው ቀጥሏል | ትናንት እና ከትናንት በሰቲያ የተከናወኑት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ባማረ ጨዋታ ታጅበው አስደናቂ ውጤቶች ተዘምግቦባቸው ተጠናቀዋል። አርሰናል፣ ኒውካስትል ዩናይትትድ እና ሊቨርፑል ከሜዳቸው ውጪ ተጉዘው ወሳኝ ሦስት ነጥቦችን ይዘው ተመልሰዋል። ማንችስተር ዩናይትድ ደግሞ በቪላ ፓርክ የበላይነት ተይዞበት 3 ለ 1 ሲሸነፍ ዌስትሃም ዩናይትድ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት በተጨማሪ ሰዓት በተቆጠረበት ጎል በክርስታል ፓላስ 2 ለ 1 ተሸንፏል። አርሰናል ትናንት በስታንፎርድ ብሪጅ ሄዶ ያገኘው ሦስት ነጥብ በትክክልም የሊጉ የዋንጫ ተፎካካሪ መሆኑን ያስመሰከረበት ነበር። ቀደም ሲል ቶተንሃምን፣ ቀጥሎ ሊቨርፑልን ከዚያም ቼልሲ በመርታት የዋንጫ ተፎካካሪ መሆኑን አሳይቷል። በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ላይም ማንችስተር ሲቲን በሁለት ነጥብ በመብለጥ መሪነቱን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህ ድል በኋላ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድኑ “ወደ አዲስ ደረጃ ከፍ ብሏል” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል። ወደ ሴንቲ ሜሪ ያቀነው ኒውካስል ደግሞ በተጋጣሚው ላይ አራት ጎሎችን በማስቆጠር በአስደናቂ ግስጋሴው ቀጥሏል። ኒውካስል የትናንት ድሉን ተከትሎ ከቶተነሃም በላይ ከሲቲ በታች ሆኖ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ፓራጓዊው የፊት መስመር ተጫዋቹ ሚጉኤል አልሚሮን በትናንቱ ጨዋታው ጎል በማስቆጠር ቡድኑን ቀዳሚ ማድረግ ችሏል። ለኒውካስል የተቀሩትን ጎሎች ክሪስ ውድ፣ ጆ ዊልሎክ እና ብሩኖ ጉሜሬሽ አስቆጥረዋል። ሳውዝሃምፕተን በሜዳው እና በደጋፊው ፊት በሰፊ የጎል ልዩነት በመሸነፉ አሰልጣኝ ራልፍ ሃሳንሃትል ከሰራቸው ሊነሱ ይችላሉ የሚሉ መረጃዎች በስፋት እየወጡ ይገኛሉ። ሳውዝሃምፕተን ከባለፉት 8 ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው አንዱን ብቻ ነው። አሰልጣኙ ግን ከኒውካስል ጨዋታ በኋላ በሰጡት አስተያየት ትኩረታቸው የወደፊት ጨዋታዎች ላይ እንጂ ስለ ሥራቸው እንዳልሆነ ተናግረዋል። ክርስቲያኖ ሮናልዶን በቋሚ አሰላልፍ ይዘው የገቡት አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ በቪላ ፓርክ ሽንፈትን ተከናንበው ተመልሰዋል። ስፔናዊው አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሪ በመጀመሪያ ጨዋታቸው ቪላን መርተው በሜዳቸው ቀያይ ሴጣኞቹን ከ23 ዓመታት በኋላ ማሸነፍ ችለዋል። ቴን ሃግ ተጫዋቾቻው ያሳዩት አቋም “መጥፎ” ነበር ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል። አሰልጣኙ ለፊት መስመር ተጫዋቹ ሮናልዶ ኳስ ለማድረስ ሲባል በረዥሙ ሲሻሙ የነበሩት ኳሶች ውጤታማ እንዳልነበሩ ተናግረዋል። 15ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ የተጠናቀቀው በቶተነሃም እና ሊቨርፑል ጨዋታ ነበር። ሞ ሳላህ በመጀመሪያው አጋማሽ ያስቆጠራቸው ሁለት ጎሎች ቡድኑ ወሳኝ ሦስት ነጥብ ይዞ እንዲወጣ ረድቶታል። በሁለተኛው አጋማሽ ቶተነሃም አጥቅቶ በመጫወት ወደ ጨዋታው ለመመለስ ጥረት ያደረገ ቢሆንም ከአንድ ጎል የዘለለ ማስቆጠር አልቻለም። ሊቨርፑል ቶተነሃምን ያሸነፈው በኖቲንግሃም ፎረስት እና በሊድስ ዩናይትድ ተከታታይ ሽንፈቶች ከደረሰበት በኋላ ነው። ሊጉን አርሰናል፤ ማንችስተር ሲቲ፣ ኒውካስል እና ቶተነሃምን አስከትሎ እየመራ ሲሆን ማንችስተር ዩናትድ እና ብራይተን 5ኛ እና 6ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ቼልሲ እና ሊቨርፑል ደግሞ 7ኛ እና 8ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። በወራጅ ቀጠናው ላይ ደግሞ ሳውዝሃምፕተን፣ ዎልቭስ እና ኖቲንግሃም ፎረስት ይገኛሉ። | አርሰናል ቼልሲን አሸንፎ መሪነቱን ሲያስቀጥል ኒውካስል በግስጋሴው ቀጥሏል ትናንት እና ከትናንት በሰቲያ የተከናወኑት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ባማረ ጨዋታ ታጅበው አስደናቂ ውጤቶች ተዘምግቦባቸው ተጠናቀዋል። አርሰናል፣ ኒውካስትል ዩናይትትድ እና ሊቨርፑል ከሜዳቸው ውጪ ተጉዘው ወሳኝ ሦስት ነጥቦችን ይዘው ተመልሰዋል። ማንችስተር ዩናይትድ ደግሞ በቪላ ፓርክ የበላይነት ተይዞበት 3 ለ 1 ሲሸነፍ ዌስትሃም ዩናይትድ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት በተጨማሪ ሰዓት በተቆጠረበት ጎል በክርስታል ፓላስ 2 ለ 1 ተሸንፏል። አርሰናል ትናንት በስታንፎርድ ብሪጅ ሄዶ ያገኘው ሦስት ነጥብ በትክክልም የሊጉ የዋንጫ ተፎካካሪ መሆኑን ያስመሰከረበት ነበር። ቀደም ሲል ቶተንሃምን፣ ቀጥሎ ሊቨርፑልን ከዚያም ቼልሲ በመርታት የዋንጫ ተፎካካሪ መሆኑን አሳይቷል። በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ላይም ማንችስተር ሲቲን በሁለት ነጥብ በመብለጥ መሪነቱን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህ ድል በኋላ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድኑ “ወደ አዲስ ደረጃ ከፍ ብሏል” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል። ወደ ሴንቲ ሜሪ ያቀነው ኒውካስል ደግሞ በተጋጣሚው ላይ አራት ጎሎችን በማስቆጠር በአስደናቂ ግስጋሴው ቀጥሏል። ኒውካስል የትናንት ድሉን ተከትሎ ከቶተነሃም በላይ ከሲቲ በታች ሆኖ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ፓራጓዊው የፊት መስመር ተጫዋቹ ሚጉኤል አልሚሮን በትናንቱ ጨዋታው ጎል በማስቆጠር ቡድኑን ቀዳሚ ማድረግ ችሏል። ለኒውካስል የተቀሩትን ጎሎች ክሪስ ውድ፣ ጆ ዊልሎክ እና ብሩኖ ጉሜሬሽ አስቆጥረዋል። ሳውዝሃምፕተን በሜዳው እና በደጋፊው ፊት በሰፊ የጎል ልዩነት በመሸነፉ አሰልጣኝ ራልፍ ሃሳንሃትል ከሰራቸው ሊነሱ ይችላሉ የሚሉ መረጃዎች በስፋት እየወጡ ይገኛሉ። ሳውዝሃምፕተን ከባለፉት 8 ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው አንዱን ብቻ ነው። አሰልጣኙ ግን ከኒውካስል ጨዋታ በኋላ በሰጡት አስተያየት ትኩረታቸው የወደፊት ጨዋታዎች ላይ እንጂ ስለ ሥራቸው እንዳልሆነ ተናግረዋል። ክርስቲያኖ ሮናልዶን በቋሚ አሰላልፍ ይዘው የገቡት አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ በቪላ ፓርክ ሽንፈትን ተከናንበው ተመልሰዋል። ስፔናዊው አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሪ በመጀመሪያ ጨዋታቸው ቪላን መርተው በሜዳቸው ቀያይ ሴጣኞቹን ከ23 ዓመታት በኋላ ማሸነፍ ችለዋል። ቴን ሃግ ተጫዋቾቻው ያሳዩት አቋም “መጥፎ” ነበር ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል። አሰልጣኙ ለፊት መስመር ተጫዋቹ ሮናልዶ ኳስ ለማድረስ ሲባል በረዥሙ ሲሻሙ የነበሩት ኳሶች ውጤታማ እንዳልነበሩ ተናግረዋል። 15ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ የተጠናቀቀው በቶተነሃም እና ሊቨርፑል ጨዋታ ነበር። ሞ ሳላህ በመጀመሪያው አጋማሽ ያስቆጠራቸው ሁለት ጎሎች ቡድኑ ወሳኝ ሦስት ነጥብ ይዞ እንዲወጣ ረድቶታል። በሁለተኛው አጋማሽ ቶተነሃም አጥቅቶ በመጫወት ወደ ጨዋታው ለመመለስ ጥረት ያደረገ ቢሆንም ከአንድ ጎል የዘለለ ማስቆጠር አልቻለም። ሊቨርፑል ቶተነሃምን ያሸነፈው በኖቲንግሃም ፎረስት እና በሊድስ ዩናይትድ ተከታታይ ሽንፈቶች ከደረሰበት በኋላ ነው። ሊጉን አርሰናል፤ ማንችስተር ሲቲ፣ ኒውካስል እና ቶተነሃምን አስከትሎ እየመራ ሲሆን ማንችስተር ዩናትድ እና ብራይተን 5ኛ እና 6ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ቼልሲ እና ሊቨርፑል ደግሞ 7ኛ እና 8ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። በወራጅ ቀጠናው ላይ ደግሞ ሳውዝሃምፕተን፣ ዎልቭስ እና ኖቲንግሃም ፎረስት ይገኛሉ። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c723012gr2go |
2health
| 'በስምምነት' እግሩ በመጋዝ የተቆረጠው አውስትራሊያዊ ሕይወቱ አለፈ | በሰሜን ምሥራቅ አውስትራሊያ 'በስምምነት' እግሩ በመጋዝ የተቆረጠው አውስትራሊያዊ አዛውንት ሕይወቱ ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ። እንደፖሊስ መረጃ ከሆነ ሟች እና የ36 ዓመቱ ተጠርጣሪ እግር የሚቆርጥበት ሁኔታን በተመለከተ አንዳች አይነት ስምምነትና 'ቅድመ ዝግጅት' ነበራቸው። የ66 ዓመቱን አዛውንት እግር በባትሪ ኃይል በሚሰራ መጋዝ ቆርጧል የተባለው ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ በግድያ ወንጀል ክስ ተመስርቶበታል። እንደ ፖሊስ ከሆነ ሁለቱ ግለሰቦች ቀድሞ የሚተዋወቁ ሲሆን፤ ሟቹ እግሩ በመጋዝ ሲቆረጥ እራሱን ለመከላከል ያደረገው ጥረት የለም። መርማሪ ፖሊስ ጋሪ ሃንተር "ፖሊስ ሆኜ በሠራሁባቸው 34 ዓመታት ውስጥ እንዲህ አይነት ሁኔታ አጋጥሞኝ አያውቅም" ሲሉ ለአውስትራሊያ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል። መርማሪው ፖሊስ ድርጊቱን "አሳዛኝ" በማለት ገልጸው የሟች እግር ለምን እንደተቆረጠ እስካሁን ግልጽ አይደለም ብለዋል። ፖሊስ ክስተቱን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል። የ66 ዓመቱ ግለሰብ እና በግድያ ወንጀል ክስ የተመሰረተበት የ36 ዓመት ተጠርጣሪ ቅዳሜ ማለዳ በሰሜን ኩዊንስላንድ በምትገኘው በኢንስፌይል መናፈሻ ስፍራ ተገኝተው ነበር። ቀድሞውኑ ይተዋወቁ የነበሩት ሁለቱ ሰዎች፤ አብረው በመኪና ወደ ፓርኩ አቅንተው ለ20 ደቂቃዎች ያክል ዛፍ ስር ተቀምጠው ከቆዩ በኋላ የ36 ዓመቱ ግለሰብ የሌላኛውን እግር በመጋዝ ከጉልበቱ በታች ቆርጦታል ብሏል ፖሊስ። ተጠርጣሪው እግሩ የተቆረጠውን ግለሰብ መኪና ውስጥ ተመልሶ እንዲገባ ከረዳው በኋላ ከአካባቢው በእግሯ ተሰውሯል። መንገደኛ የተጎዳውን ሰው ተመልክቶ ለድንገተኛ አደጋ አገልግሎት ቢደውልም የ66 ዓመቱ አዛውንት ብዙም ሳይቆዩ ሕይወታቸው አልፏል። ተጠርጣሪው ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርባል። | 'በስምምነት' እግሩ በመጋዝ የተቆረጠው አውስትራሊያዊ ሕይወቱ አለፈ በሰሜን ምሥራቅ አውስትራሊያ 'በስምምነት' እግሩ በመጋዝ የተቆረጠው አውስትራሊያዊ አዛውንት ሕይወቱ ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ። እንደፖሊስ መረጃ ከሆነ ሟች እና የ36 ዓመቱ ተጠርጣሪ እግር የሚቆርጥበት ሁኔታን በተመለከተ አንዳች አይነት ስምምነትና 'ቅድመ ዝግጅት' ነበራቸው። የ66 ዓመቱን አዛውንት እግር በባትሪ ኃይል በሚሰራ መጋዝ ቆርጧል የተባለው ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ በግድያ ወንጀል ክስ ተመስርቶበታል። እንደ ፖሊስ ከሆነ ሁለቱ ግለሰቦች ቀድሞ የሚተዋወቁ ሲሆን፤ ሟቹ እግሩ በመጋዝ ሲቆረጥ እራሱን ለመከላከል ያደረገው ጥረት የለም። መርማሪ ፖሊስ ጋሪ ሃንተር "ፖሊስ ሆኜ በሠራሁባቸው 34 ዓመታት ውስጥ እንዲህ አይነት ሁኔታ አጋጥሞኝ አያውቅም" ሲሉ ለአውስትራሊያ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል። መርማሪው ፖሊስ ድርጊቱን "አሳዛኝ" በማለት ገልጸው የሟች እግር ለምን እንደተቆረጠ እስካሁን ግልጽ አይደለም ብለዋል። ፖሊስ ክስተቱን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል። የ66 ዓመቱ ግለሰብ እና በግድያ ወንጀል ክስ የተመሰረተበት የ36 ዓመት ተጠርጣሪ ቅዳሜ ማለዳ በሰሜን ኩዊንስላንድ በምትገኘው በኢንስፌይል መናፈሻ ስፍራ ተገኝተው ነበር። ቀድሞውኑ ይተዋወቁ የነበሩት ሁለቱ ሰዎች፤ አብረው በመኪና ወደ ፓርኩ አቅንተው ለ20 ደቂቃዎች ያክል ዛፍ ስር ተቀምጠው ከቆዩ በኋላ የ36 ዓመቱ ግለሰብ የሌላኛውን እግር በመጋዝ ከጉልበቱ በታች ቆርጦታል ብሏል ፖሊስ። ተጠርጣሪው እግሩ የተቆረጠውን ግለሰብ መኪና ውስጥ ተመልሶ እንዲገባ ከረዳው በኋላ ከአካባቢው በእግሯ ተሰውሯል። መንገደኛ የተጎዳውን ሰው ተመልክቶ ለድንገተኛ አደጋ አገልግሎት ቢደውልም የ66 ዓመቱ አዛውንት ብዙም ሳይቆዩ ሕይወታቸው አልፏል። ተጠርጣሪው ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርባል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60459117 |
5sports
| የአውሮፓ ታላላቅ አሰልጣኞች መልቀቅ እና ቀጣይ እጣ ፈንታቸው | አንቶኒዮ ኮንቴ ሴሪ አን ካሸነፈ በኋላ ኢንተር ሚላንን በቃኝ ብሏል። ዚኔዲን ዚዳን ከሪያል ማድሪድ ኃላፊነቱን ሲለቅ ቶተንሃም የፓሪስ ሴንት ዠርሜኑን አለቃ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖን ለማስኮበልል እየሞከረ ነው። የሊግ 1 አሸናፊነት ክሪስቶፍ ጋልቲየርን በሊል ማቆየት አልቻለም። ጁቬንቱሶች አንድሪያ ፒርሎን በማሰናበት በማሲሚሊያኖ አሌግሪ ሊተኩት እየሠሩ ነው። በጀርመን ዮሃንስ ፍሊክ ከባየር ሙኒክ መነሳት ተመሳሳይ ውሳኔ በሌሎች ክለቦችም ዘንድ እንዲተገበር መንገድ ከፍቷል። የ2020 - 21 የውድድር ዘመን አቧራ ገና አልሰከነም። ከዚህ በፊት ታይቶ በማያውቅ ሁኔታ ብዛት ያላቸው ታላላቅ አሰልጣኞች ከሥራቸው ሲለቁ ተመልክተናል። ከገንዘብ ነክ ጉዳዮች እስከ አድካሚው ዓመት ያለውን ዝርዝር ሁኔታ የቢቢሲ ሬዲዮ 5 ባለሙያዎች ለምን እንደሆነ ይተነትኑታል። "በከፍተኛ ሁኔታ የተፈጠሩ አለመግባባቶች" የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የእግር ኳስ ክለቦችን ፋይናንስ አሽመድምዷል። ኬፒኤምጂ እንደተባለው የገበያ ኩባንያ ከሆነ በአውሮፓ ኃያላኑ 32 ክለቦች ከየካቲት 2020 ጀምሮ 6.1 ቢሊዮን ዩሮ አጥተዋል። በጀርመን ፍሊክ ባየርን ለቀቀ። ጁሊያን ናጌልስማን በቦታው ተተካ። ጄሲ ማርች ደግሞ አር ቢ ላይፕዚግን በመረከቡ በርካታ ለውጦች ተከታትለው መጡ። ከዚያን ጊዜ ወዲህ በጣሊያን፣ በስፔን፣ በእንግሊዝ እና በፈረንሳይ ያለው ተመሳሳይ ታሪክ ነው። ጀርመናዊው የእግር ኳስ ጋዜጠኛ ራፋኤል ሆኒግስቴይን በቢቢሲ ራዲዮ 5 ቀጥታ ስርጭት ላይ "መልቀቂያዎቹ የሚያመሳስላቸው በኮቪድ-19 ወቅት ስለ ገንዘብ ብዙ ውስጣዊ ክርክሮችን በመመልከታችን ነው" ብሏል። "ከእነዚህ አሰልጣኞች ብዙዎቹ ለቀዋል። ምክንያቱም ለሌላ ሥራ ለመሰለፍ ሳይሆን ስለበቃቸው ነው" ሲል ተናግሯል። አክሎም "ከዚህ ቀደሙ በተለየ በእነዚህ ትላልቅ ክለቦች ትላልቅ አሰልጣኞች በዚህ ቁጥሮች ሲለቁ አላየንም" ብሏል። "ፍሊክ በተጫዋቾች ዝውውር ላይ ከፍተኛ አለመግባባት ከተፈጠረ በኋላ ነው የለቀቀው። ምክንያቱ ደግሞ ኮቪድ-19 ነው። ፍሊክ የሚፈልገውን ያህል ገንዘብ ሙኒክ ማውጣት አልቻለም። በዚህም አለመግባባቱ ተጀመረ" ሲል አስረድቷል። በላሊጋው 2ኛ ሆኖ ያጠናቀቀው ሪያል ማድሪድ በኬፒኤምጂ ጥናት የአውሮፓ ውዱ ክለብ በመሆን አጠናቋል። ዚዳን ግን በቦርዱ እና በፕሬዚዳንት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ስለመደገፉ አልተሰማውም ሲል የስፔን እግር ኳስ ባለሙያው ጊየም ባላጌ አስታውቋል። ኮንቴ በ11 ዓመታት የመጀመሪያውን የጣሊያን ዋንጫ ለክለቡ ቢያሳካም በኢንተርም ተመሳሳይ ታሪክ ነው ያለው። ምክንያቱም በክለቡ የፋይናንስ ችግር የተነሳ በዚህ ክረምት የደመወዝ ክፍያን በ 20 በመቶ ለመቀነስ ተዘጋጅቷል። ጣሊያናዊው ጋዜጠኛ ጋብሪኤል ማርኮቲ "ኮንቴ ገንዘብ ፈለገ፤ ጥያቄዎችንም አቀረበ። ነገር ግን አንድ ወይም ሁለት ታላላቅ ተጫዋቾችን ከማግኘት ይልቅ አንድ ወይም ሁለት ታላላቅ ተጫዋቾችን መሸጥ ሊኖርበት ነው" ብሏል። "ስሜቱ ተለውጧል፡፡ ፔፕ ጋርዲዮላ ወይም የርገን ክሎፕን ካልሆንክ እነዚያን ጥያቄዎች ማንሳት በጣም ከባድ ነው" ይላል፡፡ ማርኮቲ አክሎም "አዳዲስ ተጨዋቾችን ከመግዛት ይልቅ አዲስ አሰልጣኝ ማምጣት ይረክሳል። በግልጽ እንደሚታየው ተያያዥ ምላሽ ስለመኖሩ አይካድም። አብዛኛው ከድህረ ኮሮናቫይረስ ገንዘብ፣ ኢንቨስትመንት እና ኢኮኖሚ ጋር የተያያዘ ነው" ብሏል፡፡ "ለዚህም ነው ዚዳን ከማድሪድ የለቀቀው፣ ኮንቴ ኢንተርን የተሰናበተው። ይህ የዝውውር መስኮት ለአሰልጣኞች እና ለተጫዋቾች በጣም የተለየ መሆኑ የማይካድ ሃቅ ነው" ሲል ያስረዳል፡፡ አንዳንዶቹ ደክመዋል፣ ሌሎች ደግሞ አዲስ ፈተናዎች አስፈልጓቸዋል ያለፈው ዓመት በወረርሽኙ ከተስተጓጎለ በኋላ በመላው አውሮፓ ያሉ ክለቦች በተጨናነቀ የጊዜ ሰሌዳዎች እንዲጫወቱ ማስገደዱን ተከትሎ ውስጣዊ ውጥረቶች መኖራቸው የተጠበቀ ሊሆን ይችላል፡፡ እንደ ኮንቴ ያሉት አንዳንዶቹም ችግሮች ቢኖሩም፣ በዝውውር ገንዘብ ላይ አለመግባባት ቢፈጠርም ስኬት አስመዝግበዋል። ዚዳን ዋንጫ ማንሳት ቢሳነውም በዕድሜ የገፋውን የሪያል ቡድን ይዞ የላሊጋው ሻምፒዮንነትን ለጥቂት ሲያጣ በቻምፒየንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ ደርሶ በቼልሲ ተሸንፏል። የፈረንሣዊው የእግር ኳስ ጋዜጠኛ ጁሊየን ሎረን እንደተናገረው "በተፈጠረው ነገር በሙሉ ይህ ለዚዳን ልዩ ዓመት ነበር። በኮሮናቫይረስ ተያዘ፡፡ ቡድኑን እስከደረሰበት ደረጃም ለማብቃት ችሏል።" "ምናልባትም ከዚህ የተሻለ ማድረግ ከባድ እንደሚሆን ተሰምቶት ሊሆን ይችላል፡፡ ምናልባትም ብዙዎች አሰልጣኞች ሲለቁ በልባቸው ውስጥ ያለው ይህ ነው - 'በዚህ ዓመት ካደረግነው የበለጠ ልንሠራ እንችላለን?' የሚል፡፡ "ጋልቲየ በሚቀጥለው ዓመት ሊል የሊግ 1 ን በድጋሚ የሚያሸንፍበት ዕድል እንደሌለ አስቦ ይሆናል። ሌሎች አማራጮች እያሉ ለምን ይቆያሉ? ለኮንቴም ምናልባት ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል፡፡" ባላጌ አክሎም "ትላልቅ ክለቦች አሰልጣኞቻቸውን እየቀያየሩ ነው። ትላልቅ ሥራዎች ክፍት ስለሆኑ ለመመረጥ ዝግጁ የሆኑ ሁለት ወይም ሦስት አሰልጣኞች አሉ" ብሏል፡፡ "በእርግጥ ዚዳን ወደ ሌላ ሥራ እንደሚሄድ ቢጠበቅም፤ ዝሎና ተዳክሞ ነበር፡፡ ብዙ አሰልጣኞችንም ነክቷል።" ማን ወዴት እያመራ ነው? በጣም ስመ ገናና የሆኑ አሰልጣኞች ከአንዱ ወደ ሌላው ክለብ በመንቀሳቀስ ላይ በመሆናቸው ማን ወዴት ያመራል የሚሉ ግምቶች እጥረት የለም፡፡ ኮንቴ ከሪያል ማድሪድ እና በፕሪሚየር ሊጉ ደግሞ ክፍት ከሆነው የቶተንሃም ሥራ ጋር ስሙ ተገናኝቷል፡፡ የቀድሞው አሰልጣኙ ፖቸቲኖን በተመለከተ ስፐርስ ከፓሪስ ሴንት ጀርሜን ጋር ግንኙነት አድርገዋል። ማርኮቲ በበኩሉ ለቢቢሲ ራዲዮ 5 እንደገለጸው ፖቸቲኖ የማድሪድ ዋነኛ ዒላማ ነው፡፡ ሲሞኔ ኢንዛጊ ሐሙስ ዕለት ከሌላው የሴሪ ኤ ቡድን ላዚዮ መሰናበቱን ተከትሎ በኢንተር የኮንቴ ተተኪ ሆኖ የተሰለፈ ይመስላል፡፡ የቀድሞው አለቃቸውን አሌግሪን እንደሚተኩ የሚነገርላቸው ጁቬንቱሶች የሚያሰናበቱት አንድሪያ ፒርሎ መጨረሻ ምን እንደሚሆን ለመገመት ይከብዳል፡፡ ሊልን ለመልቀቅ "ጊዜዬ አሁን ደርሷል" የሚል ጥልቅ እምነት ያለው ጋልቲየ በቀጣይ ከኒስ እና ሊዮን አሰልጣኝት ጋር ስሙ ተያይዟል። የቀድሞው የዎልቭሶች አለቃ ኑኖ ኤስፒሪቶ ሳንቶም እንዲሁ አዲስ ክለብ እየፈለገ ነው፡፡ | የአውሮፓ ታላላቅ አሰልጣኞች መልቀቅ እና ቀጣይ እጣ ፈንታቸው አንቶኒዮ ኮንቴ ሴሪ አን ካሸነፈ በኋላ ኢንተር ሚላንን በቃኝ ብሏል። ዚኔዲን ዚዳን ከሪያል ማድሪድ ኃላፊነቱን ሲለቅ ቶተንሃም የፓሪስ ሴንት ዠርሜኑን አለቃ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖን ለማስኮበልል እየሞከረ ነው። የሊግ 1 አሸናፊነት ክሪስቶፍ ጋልቲየርን በሊል ማቆየት አልቻለም። ጁቬንቱሶች አንድሪያ ፒርሎን በማሰናበት በማሲሚሊያኖ አሌግሪ ሊተኩት እየሠሩ ነው። በጀርመን ዮሃንስ ፍሊክ ከባየር ሙኒክ መነሳት ተመሳሳይ ውሳኔ በሌሎች ክለቦችም ዘንድ እንዲተገበር መንገድ ከፍቷል። የ2020 - 21 የውድድር ዘመን አቧራ ገና አልሰከነም። ከዚህ በፊት ታይቶ በማያውቅ ሁኔታ ብዛት ያላቸው ታላላቅ አሰልጣኞች ከሥራቸው ሲለቁ ተመልክተናል። ከገንዘብ ነክ ጉዳዮች እስከ አድካሚው ዓመት ያለውን ዝርዝር ሁኔታ የቢቢሲ ሬዲዮ 5 ባለሙያዎች ለምን እንደሆነ ይተነትኑታል። "በከፍተኛ ሁኔታ የተፈጠሩ አለመግባባቶች" የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የእግር ኳስ ክለቦችን ፋይናንስ አሽመድምዷል። ኬፒኤምጂ እንደተባለው የገበያ ኩባንያ ከሆነ በአውሮፓ ኃያላኑ 32 ክለቦች ከየካቲት 2020 ጀምሮ 6.1 ቢሊዮን ዩሮ አጥተዋል። በጀርመን ፍሊክ ባየርን ለቀቀ። ጁሊያን ናጌልስማን በቦታው ተተካ። ጄሲ ማርች ደግሞ አር ቢ ላይፕዚግን በመረከቡ በርካታ ለውጦች ተከታትለው መጡ። ከዚያን ጊዜ ወዲህ በጣሊያን፣ በስፔን፣ በእንግሊዝ እና በፈረንሳይ ያለው ተመሳሳይ ታሪክ ነው። ጀርመናዊው የእግር ኳስ ጋዜጠኛ ራፋኤል ሆኒግስቴይን በቢቢሲ ራዲዮ 5 ቀጥታ ስርጭት ላይ "መልቀቂያዎቹ የሚያመሳስላቸው በኮቪድ-19 ወቅት ስለ ገንዘብ ብዙ ውስጣዊ ክርክሮችን በመመልከታችን ነው" ብሏል። "ከእነዚህ አሰልጣኞች ብዙዎቹ ለቀዋል። ምክንያቱም ለሌላ ሥራ ለመሰለፍ ሳይሆን ስለበቃቸው ነው" ሲል ተናግሯል። አክሎም "ከዚህ ቀደሙ በተለየ በእነዚህ ትላልቅ ክለቦች ትላልቅ አሰልጣኞች በዚህ ቁጥሮች ሲለቁ አላየንም" ብሏል። "ፍሊክ በተጫዋቾች ዝውውር ላይ ከፍተኛ አለመግባባት ከተፈጠረ በኋላ ነው የለቀቀው። ምክንያቱ ደግሞ ኮቪድ-19 ነው። ፍሊክ የሚፈልገውን ያህል ገንዘብ ሙኒክ ማውጣት አልቻለም። በዚህም አለመግባባቱ ተጀመረ" ሲል አስረድቷል። በላሊጋው 2ኛ ሆኖ ያጠናቀቀው ሪያል ማድሪድ በኬፒኤምጂ ጥናት የአውሮፓ ውዱ ክለብ በመሆን አጠናቋል። ዚዳን ግን በቦርዱ እና በፕሬዚዳንት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ስለመደገፉ አልተሰማውም ሲል የስፔን እግር ኳስ ባለሙያው ጊየም ባላጌ አስታውቋል። ኮንቴ በ11 ዓመታት የመጀመሪያውን የጣሊያን ዋንጫ ለክለቡ ቢያሳካም በኢንተርም ተመሳሳይ ታሪክ ነው ያለው። ምክንያቱም በክለቡ የፋይናንስ ችግር የተነሳ በዚህ ክረምት የደመወዝ ክፍያን በ 20 በመቶ ለመቀነስ ተዘጋጅቷል። ጣሊያናዊው ጋዜጠኛ ጋብሪኤል ማርኮቲ "ኮንቴ ገንዘብ ፈለገ፤ ጥያቄዎችንም አቀረበ። ነገር ግን አንድ ወይም ሁለት ታላላቅ ተጫዋቾችን ከማግኘት ይልቅ አንድ ወይም ሁለት ታላላቅ ተጫዋቾችን መሸጥ ሊኖርበት ነው" ብሏል። "ስሜቱ ተለውጧል፡፡ ፔፕ ጋርዲዮላ ወይም የርገን ክሎፕን ካልሆንክ እነዚያን ጥያቄዎች ማንሳት በጣም ከባድ ነው" ይላል፡፡ ማርኮቲ አክሎም "አዳዲስ ተጨዋቾችን ከመግዛት ይልቅ አዲስ አሰልጣኝ ማምጣት ይረክሳል። በግልጽ እንደሚታየው ተያያዥ ምላሽ ስለመኖሩ አይካድም። አብዛኛው ከድህረ ኮሮናቫይረስ ገንዘብ፣ ኢንቨስትመንት እና ኢኮኖሚ ጋር የተያያዘ ነው" ብሏል፡፡ "ለዚህም ነው ዚዳን ከማድሪድ የለቀቀው፣ ኮንቴ ኢንተርን የተሰናበተው። ይህ የዝውውር መስኮት ለአሰልጣኞች እና ለተጫዋቾች በጣም የተለየ መሆኑ የማይካድ ሃቅ ነው" ሲል ያስረዳል፡፡ አንዳንዶቹ ደክመዋል፣ ሌሎች ደግሞ አዲስ ፈተናዎች አስፈልጓቸዋል ያለፈው ዓመት በወረርሽኙ ከተስተጓጎለ በኋላ በመላው አውሮፓ ያሉ ክለቦች በተጨናነቀ የጊዜ ሰሌዳዎች እንዲጫወቱ ማስገደዱን ተከትሎ ውስጣዊ ውጥረቶች መኖራቸው የተጠበቀ ሊሆን ይችላል፡፡ እንደ ኮንቴ ያሉት አንዳንዶቹም ችግሮች ቢኖሩም፣ በዝውውር ገንዘብ ላይ አለመግባባት ቢፈጠርም ስኬት አስመዝግበዋል። ዚዳን ዋንጫ ማንሳት ቢሳነውም በዕድሜ የገፋውን የሪያል ቡድን ይዞ የላሊጋው ሻምፒዮንነትን ለጥቂት ሲያጣ በቻምፒየንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ ደርሶ በቼልሲ ተሸንፏል። የፈረንሣዊው የእግር ኳስ ጋዜጠኛ ጁሊየን ሎረን እንደተናገረው "በተፈጠረው ነገር በሙሉ ይህ ለዚዳን ልዩ ዓመት ነበር። በኮሮናቫይረስ ተያዘ፡፡ ቡድኑን እስከደረሰበት ደረጃም ለማብቃት ችሏል።" "ምናልባትም ከዚህ የተሻለ ማድረግ ከባድ እንደሚሆን ተሰምቶት ሊሆን ይችላል፡፡ ምናልባትም ብዙዎች አሰልጣኞች ሲለቁ በልባቸው ውስጥ ያለው ይህ ነው - 'በዚህ ዓመት ካደረግነው የበለጠ ልንሠራ እንችላለን?' የሚል፡፡ "ጋልቲየ በሚቀጥለው ዓመት ሊል የሊግ 1 ን በድጋሚ የሚያሸንፍበት ዕድል እንደሌለ አስቦ ይሆናል። ሌሎች አማራጮች እያሉ ለምን ይቆያሉ? ለኮንቴም ምናልባት ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል፡፡" ባላጌ አክሎም "ትላልቅ ክለቦች አሰልጣኞቻቸውን እየቀያየሩ ነው። ትላልቅ ሥራዎች ክፍት ስለሆኑ ለመመረጥ ዝግጁ የሆኑ ሁለት ወይም ሦስት አሰልጣኞች አሉ" ብሏል፡፡ "በእርግጥ ዚዳን ወደ ሌላ ሥራ እንደሚሄድ ቢጠበቅም፤ ዝሎና ተዳክሞ ነበር፡፡ ብዙ አሰልጣኞችንም ነክቷል።" ማን ወዴት እያመራ ነው? በጣም ስመ ገናና የሆኑ አሰልጣኞች ከአንዱ ወደ ሌላው ክለብ በመንቀሳቀስ ላይ በመሆናቸው ማን ወዴት ያመራል የሚሉ ግምቶች እጥረት የለም፡፡ ኮንቴ ከሪያል ማድሪድ እና በፕሪሚየር ሊጉ ደግሞ ክፍት ከሆነው የቶተንሃም ሥራ ጋር ስሙ ተገናኝቷል፡፡ የቀድሞው አሰልጣኙ ፖቸቲኖን በተመለከተ ስፐርስ ከፓሪስ ሴንት ጀርሜን ጋር ግንኙነት አድርገዋል። ማርኮቲ በበኩሉ ለቢቢሲ ራዲዮ 5 እንደገለጸው ፖቸቲኖ የማድሪድ ዋነኛ ዒላማ ነው፡፡ ሲሞኔ ኢንዛጊ ሐሙስ ዕለት ከሌላው የሴሪ ኤ ቡድን ላዚዮ መሰናበቱን ተከትሎ በኢንተር የኮንቴ ተተኪ ሆኖ የተሰለፈ ይመስላል፡፡ የቀድሞው አለቃቸውን አሌግሪን እንደሚተኩ የሚነገርላቸው ጁቬንቱሶች የሚያሰናበቱት አንድሪያ ፒርሎ መጨረሻ ምን እንደሚሆን ለመገመት ይከብዳል፡፡ ሊልን ለመልቀቅ "ጊዜዬ አሁን ደርሷል" የሚል ጥልቅ እምነት ያለው ጋልቲየ በቀጣይ ከኒስ እና ሊዮን አሰልጣኝት ጋር ስሙ ተያይዟል። የቀድሞው የዎልቭሶች አለቃ ኑኖ ኤስፒሪቶ ሳንቶም እንዲሁ አዲስ ክለብ እየፈለገ ነው፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/news-57278702 |
3politics
| የአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የጦር መሣሪያ ቁጥጥር ረቂቅ ሕግን አጸደቀ | የአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት በጦር መሣሪያ ቁጥጥር ላይ አዲስ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ። ይህ ሲሆን ከ30 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ወትሮም የዲሞክራቶችና የሪፐብሊካንን ጎራ የሚለየው የጦር መሣሪያ ቁጥጥር ጉዳይ ከረዥም ዘመን ትግል በኋላ ነው ለዚህ የበቃው። 15 የሪፐብሊካን ፓርቲ እንደራሴዎች ረቂቁን ደግፈው ድምጽ ሰጥተዋል። ረቂቁ በ65 ድጋፍና በ33 ተቃውሞ አልፏል። ይህ የሆነው ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የተኩስ እሩምታን የከፈቱ ግለሰቦችን ተከትሎ በርካቶች ሕይወታቸውን ካጡ በኋላ ነው። በኒውዮርክ፣ ቡፋሎ ባለፈው ወር በአንድ ሱፐርማርኬት ውስጥ ጥቁሮችን እየነጠለ ተኩስ የከፈተው ወጣት እንዲሁም በቴክሳስ፣ ዩቫልዲ ከተማ፣ በአንድ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በርካታ ሕጻናትን ጨምሮ በድምሩ 31 ሰዎች መገደላቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። ይህ ረቂቅ በሚቀጥለው ሳምንት የታችኛው ምክር ቤት ከመከረበት በኋላ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ፈርመውበት ሕግ ይሆናል። ይህም በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ የሚፈጸም ተግባር ነው። ምንም እንኳ ይህ ረቂቅ እዚህ ለመድረሱ ብዙ ውጣ ውረድ ቢያይም የታሰበውን ያህል አንጀት አርስ እንዳልሆነ በጉዳዩ ላይ ብዙ ሕዝባዊ ንቅናቄን ሲመሩ የነበሩ ተሟጋቾች እየተናገሩ ነው። ረቂቁ አያሌ ውስንነቶች አሉበት የሚሉ የሕግ አዋቂዎችም ጥቂት አይደሉም። ይህ ረቂቅ ሕግ ሆኖ በቅርቡ ሲጸድቅ የጦር መሣሪያ ገዝቼ ማንገት እፈልጋለሁ የሚል ሰው በተለይ ዕድሜው ከ21 በታች ከሆነ የጀርባ ታሪኩ በብርቱ እንዲጠና ይደረጋል። ከዚህ ሌላ 15 ቢሊዮን ዶላር ከፌዴራል መንግሥት ለግዛቶች ይመደባል። ይህም ከጦር መሣሪያ ቁጥጥር ጋር በተያያዘ ለሚከናወኑ ሥራዎች በሚል ፈሰስ የሚደረግ ነው። በተለይም በትምህርት ቤቶች አካባቢ የጥበቃ ቁጥጥርን ለማጠናከር እና ለአእምሮ ጤና ማጎልበቻ መርሐ ግብር ማስፈጸሚያ የሚውል ይሆናል። ከዚህ ሌላ ግዛቶች የደኅንነት ስጋት ናቸው ብለው ለሚያምኗቸው ግለሰቦች አስቀድመው ትጥቅ ማስፈታትን ያበረታታል። ይህ “ሬድ ፍላግ” ተብሎ የሚጠራው የሕግ ሐሳብ ፖሊስ፥ ቤተሰብ ወይም የሥራ ባልደቦችም ሊሆኑ ይችላሉ አንድ ግለሰብ ለደኅንነት ስጋት ነው ብለው በጽኑ ካሰቡ፣ የታጠቀውን መሣሪያ እንዲፈታ ጥያቄ የሚያቀርቡበት ዘዴ ነው። ሌላው በዚህ ረቂቅ የተካተተው “ቦይፍሬንድ ሉፕሆል” በሚል በይበልጥ የሚታወቀው ሐሳብ ሲሆን ይህም ያልተጋቡ ፍቅረኛሞች፣ በመጠናናት ዘመናቸው ምናልባትም ከሁለቱ አንዱ ቀደም ብሎ የጾታ ጥቃት ታሪክ ያለው ሰው ከሆነ ከዚያ ወዲህ መሣሪያ እንዳይታጠቅ የሚከለክል ነው። ከዚህ በፊት የፌዴራል ሕግ ያገቡ፣ ወይም ልጅ ያላቸው ወይም በእጮኛነት ደረጃ ያሉ እና በጾታ ጥቃት ታሪክ ያላቸው ሰዎችን ብቻ መሣሪያ እንዳይታጠቁ ክልከላ ያደርግ ነበር። አሁን በአዲሱ ረቂቅ ግን ይህ ሕግ አዲስ እየተጠናኑ ያሉ አፍላ ፍቅረኛሞች ጭምር እንዲያካትቱ ተደርጓል። አሁን በሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የመሣሪያ ቁጥጥር ረቂቁ በሰፊ ድጋፍ ማለፉ ልዩ ያደረገው። በርካታ ሪፐብሊካን እንደራሴዎች ለመሣሪያ ቁጥጥር ረቂቅ ይህን ያህል ድጋፍ ሲሰጡ ለመጀመርያ ጊዜ ነው። በታሪክ ለዘመናት በዲሞክራቶች ይቀርብ የነበሩ የመሣሪያ ቁጥጥር ረቂቅ የሕግ ሐሳቦች ወዲያውኑ በሪፐብሊካን ተወካዮች ውድቅ ሲደረጉ ኖረዋል። የዲሞክራት እንደራሴዎች ተጠሪ ቸክ ሹመር “ይህ ረቂቅ ሕግ ማለፉ ሁሉን ችግር ይቀርፋል ባንልም ሐቀኛውን መንገድ መያዛችንን አመላካች ነው” ብለዋል። የብሔራዊ ጠመንጃ ማኅበር (NRA) ረቂቅ ሕጉን በጽኑ ተቃውሞታል። ጆ ባይደን ውሳኔው የሚበረታታ ነው ቢሉም እሩምታ ተኩስ መክፈት የሚያስችሉ ዘመናዊ ጠመንጃዎች ላይ ዕቀባ እንዲደረግ የነበራቸውን ፍላጎት አለማሟላቱ ግን ቅር አሰኝቷቸዋል። በቡፋሎም ሆነ በቴክሳሱ ጥቃት 31 ሰዎች የተገደሉት አከታትለው ጥይት በሚተፉ አውቶማቲክና ከፊል አውቶማቲክ መሣሪያዎችን ገዝተው በታጠቁ ወጣቶች ነበር። በአሜሪካ አሁን በአማካይ በግለሰቦች እጅ 390 ሚሊዮን ጠመንጃና ሽጉጦች ይገኛሉ። በ2020 ብቻ 45 ሺህ አሜሪካዊያን በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ በጦር መሣሪያ ተገድለዋል። | የአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የጦር መሣሪያ ቁጥጥር ረቂቅ ሕግን አጸደቀ የአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት በጦር መሣሪያ ቁጥጥር ላይ አዲስ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ። ይህ ሲሆን ከ30 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ወትሮም የዲሞክራቶችና የሪፐብሊካንን ጎራ የሚለየው የጦር መሣሪያ ቁጥጥር ጉዳይ ከረዥም ዘመን ትግል በኋላ ነው ለዚህ የበቃው። 15 የሪፐብሊካን ፓርቲ እንደራሴዎች ረቂቁን ደግፈው ድምጽ ሰጥተዋል። ረቂቁ በ65 ድጋፍና በ33 ተቃውሞ አልፏል። ይህ የሆነው ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የተኩስ እሩምታን የከፈቱ ግለሰቦችን ተከትሎ በርካቶች ሕይወታቸውን ካጡ በኋላ ነው። በኒውዮርክ፣ ቡፋሎ ባለፈው ወር በአንድ ሱፐርማርኬት ውስጥ ጥቁሮችን እየነጠለ ተኩስ የከፈተው ወጣት እንዲሁም በቴክሳስ፣ ዩቫልዲ ከተማ፣ በአንድ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በርካታ ሕጻናትን ጨምሮ በድምሩ 31 ሰዎች መገደላቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። ይህ ረቂቅ በሚቀጥለው ሳምንት የታችኛው ምክር ቤት ከመከረበት በኋላ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ፈርመውበት ሕግ ይሆናል። ይህም በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ የሚፈጸም ተግባር ነው። ምንም እንኳ ይህ ረቂቅ እዚህ ለመድረሱ ብዙ ውጣ ውረድ ቢያይም የታሰበውን ያህል አንጀት አርስ እንዳልሆነ በጉዳዩ ላይ ብዙ ሕዝባዊ ንቅናቄን ሲመሩ የነበሩ ተሟጋቾች እየተናገሩ ነው። ረቂቁ አያሌ ውስንነቶች አሉበት የሚሉ የሕግ አዋቂዎችም ጥቂት አይደሉም። ይህ ረቂቅ ሕግ ሆኖ በቅርቡ ሲጸድቅ የጦር መሣሪያ ገዝቼ ማንገት እፈልጋለሁ የሚል ሰው በተለይ ዕድሜው ከ21 በታች ከሆነ የጀርባ ታሪኩ በብርቱ እንዲጠና ይደረጋል። ከዚህ ሌላ 15 ቢሊዮን ዶላር ከፌዴራል መንግሥት ለግዛቶች ይመደባል። ይህም ከጦር መሣሪያ ቁጥጥር ጋር በተያያዘ ለሚከናወኑ ሥራዎች በሚል ፈሰስ የሚደረግ ነው። በተለይም በትምህርት ቤቶች አካባቢ የጥበቃ ቁጥጥርን ለማጠናከር እና ለአእምሮ ጤና ማጎልበቻ መርሐ ግብር ማስፈጸሚያ የሚውል ይሆናል። ከዚህ ሌላ ግዛቶች የደኅንነት ስጋት ናቸው ብለው ለሚያምኗቸው ግለሰቦች አስቀድመው ትጥቅ ማስፈታትን ያበረታታል። ይህ “ሬድ ፍላግ” ተብሎ የሚጠራው የሕግ ሐሳብ ፖሊስ፥ ቤተሰብ ወይም የሥራ ባልደቦችም ሊሆኑ ይችላሉ አንድ ግለሰብ ለደኅንነት ስጋት ነው ብለው በጽኑ ካሰቡ፣ የታጠቀውን መሣሪያ እንዲፈታ ጥያቄ የሚያቀርቡበት ዘዴ ነው። ሌላው በዚህ ረቂቅ የተካተተው “ቦይፍሬንድ ሉፕሆል” በሚል በይበልጥ የሚታወቀው ሐሳብ ሲሆን ይህም ያልተጋቡ ፍቅረኛሞች፣ በመጠናናት ዘመናቸው ምናልባትም ከሁለቱ አንዱ ቀደም ብሎ የጾታ ጥቃት ታሪክ ያለው ሰው ከሆነ ከዚያ ወዲህ መሣሪያ እንዳይታጠቅ የሚከለክል ነው። ከዚህ በፊት የፌዴራል ሕግ ያገቡ፣ ወይም ልጅ ያላቸው ወይም በእጮኛነት ደረጃ ያሉ እና በጾታ ጥቃት ታሪክ ያላቸው ሰዎችን ብቻ መሣሪያ እንዳይታጠቁ ክልከላ ያደርግ ነበር። አሁን በአዲሱ ረቂቅ ግን ይህ ሕግ አዲስ እየተጠናኑ ያሉ አፍላ ፍቅረኛሞች ጭምር እንዲያካትቱ ተደርጓል። አሁን በሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የመሣሪያ ቁጥጥር ረቂቁ በሰፊ ድጋፍ ማለፉ ልዩ ያደረገው። በርካታ ሪፐብሊካን እንደራሴዎች ለመሣሪያ ቁጥጥር ረቂቅ ይህን ያህል ድጋፍ ሲሰጡ ለመጀመርያ ጊዜ ነው። በታሪክ ለዘመናት በዲሞክራቶች ይቀርብ የነበሩ የመሣሪያ ቁጥጥር ረቂቅ የሕግ ሐሳቦች ወዲያውኑ በሪፐብሊካን ተወካዮች ውድቅ ሲደረጉ ኖረዋል። የዲሞክራት እንደራሴዎች ተጠሪ ቸክ ሹመር “ይህ ረቂቅ ሕግ ማለፉ ሁሉን ችግር ይቀርፋል ባንልም ሐቀኛውን መንገድ መያዛችንን አመላካች ነው” ብለዋል። የብሔራዊ ጠመንጃ ማኅበር (NRA) ረቂቅ ሕጉን በጽኑ ተቃውሞታል። ጆ ባይደን ውሳኔው የሚበረታታ ነው ቢሉም እሩምታ ተኩስ መክፈት የሚያስችሉ ዘመናዊ ጠመንጃዎች ላይ ዕቀባ እንዲደረግ የነበራቸውን ፍላጎት አለማሟላቱ ግን ቅር አሰኝቷቸዋል። በቡፋሎም ሆነ በቴክሳሱ ጥቃት 31 ሰዎች የተገደሉት አከታትለው ጥይት በሚተፉ አውቶማቲክና ከፊል አውቶማቲክ መሣሪያዎችን ገዝተው በታጠቁ ወጣቶች ነበር። በአሜሪካ አሁን በአማካይ በግለሰቦች እጅ 390 ሚሊዮን ጠመንጃና ሽጉጦች ይገኛሉ። በ2020 ብቻ 45 ሺህ አሜሪካዊያን በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ በጦር መሣሪያ ተገድለዋል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c728rg65jkgo |
0business
| የዋጋ ግሽበት እጅግ የሚያሰጋቸው አገራት የትኞቹ ናቸው? | የዋጋ ግሽበት ዓለምን ከጥግ ጥግ አስግቷል። ከኢትዮጵያ እስከ ሲሪ ላንካ ከብራዚል እስከ ደቡብ አፍሪካ። ምግብ ተወዷል። ነዳጅ ተወዷል። ምን ያልተወደደ አለ? የተለይ የመሠረታዊ አቅርቦቶች ዋጋ መናር ዓለምን አስጨንቋል። በእርግጥ የዋጋ ግሽበት ከሌላው የዓለም ክፍል በላይ የሚያንገዳግዳቸው አገሮች አሉ። ለዚህ ምክንያቱ ሰብል አለመሰብሰቡ፣ ወረርሽኙ መክፋቱ እና የተፈጥሮ ጋዝ መጥፋቱ ነው። በዚህ ደግሞ በአፍሪካ ከሰሀራ በታች ያሉ አገራት ዋነኛ ተጎጂ ናቸው። ቱርክ፣ ብራዚል እና ሲሪ ላንካም ይጠቀሳሉ። ከሰሀራ በታች ያሉ አገራት አብዛኞቹ ከሰሀራ በታች ያሉ አገራት ምግብ ለማብሰል የተጣራ ፈሳሽ ጋዝ (በሲሊንደር የሚታሸግ ቡታ ጋዝ) ይጠቀማሉ። የጋዝ ዋጋ ደግሞ እያሻቀበ ይገኛል። ባለፈው ዓመት በአንዳንድ የናይጄሪያ ግዛቶች ጋዝ በእጥፍ ጨምሯል። ብዙዎች ወደ ማገዶ እንጨት፣ ከሰል እና ኬሮሲን ፊታቸውን ለማዞር ተገደዋል። እነዚህ አማራጭ ኃይል ምንጮች ደግሞ አካባቢን ይበክላሉ። የተጠቃሚዎቹን ሳምባም ይጎዳሉ። የነዳጅ ዋጋ መጨመር፤ የማዳበሪያ ዋጋ እንዲሁም ምግብ ከእርሻ ወደ መደብር የሚጓጓዝበት ዋጋም እንዲንር ምክንያት ሆኗል። የናሳ የመሬት ምልከታ እንደሚጠቁመው በበርካታ የአፍሪካ አገሮች ዝናብ ከጠፋ ሰነባብቷል። ይህም የዋጋ ግሽበት አስከትሏል። በአንጎላ ባለፈው ዓመት የምግብ ዋጋ 36.4 በመቶ መጨመሩን የአገሪቱ የስታትስቲክስ ተቋም ይፋ አድርጓል። በማላዊ የኑሮ ውድነት ፀረ መንግሥት ሰልፎችን አስከትሏል። በአፍሪካ 282 ሚሊዮን ሰዎች ተመጣጣኝ ምግብ እንደማያገኙ የተባበሩት መንግሥታት ገልጿል። ቱርክ ጥቅምት ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በኢስታንቡል እና ዲያርባሪክ ከተሞች ሰልፍ መውጣታቸው ይታወሳል። አምና የዋጋ ግሽበት በ36 በመቶ ከፍ ብሏል። የአገሪቱ የስታትስቲክስ ተቋም እንዳለው የምግብ ዋጋ በዓመት 44 በመቶ ጨምሯል። በኢስታንቡል በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በመንግሥት ሱቆች ለዳቦ ሰልፍ ይዘው ማየት ተለምዷል። የግል ዳቦ ቤቶች ዋጋ ስለማይቀመስ ከእነሱ መግዛት አይታሰብም። ነዳጅና ማዳበሪያ ከመወደዱ ባሻገር የቱርክ መንግሥት የስንዴ ዋጋን መጨመሩ ዳቦ እንዲወደድ አድርጓል። የአውቶብስና ባቡር ክፍያም በእጥፍ ጨምሯል። የመብራት ክፍያ 50 በመቶ፣ የጋዝ ክፍያ 25 በመቶ ከፍ ብሏል። መንግሥታት የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር የወለድ መጠንን የሚጨምሩበት አሠራር አለ። ይህም ገንዘብን ለማግኘት አስቸጋሪ ያደርጋል። ፕሬዘዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን "ወለድን መጨመር ሀብታምን የበለጠ ሀብታም የሚያደርግ፣ ድሃን የባሰ የሚያደኸይ ሰይጣናዊ አካሄድ ነው" ብለዋል። የአገሪቱ ብሔራዊ ባንክ የወለድ መጠንን እንዲቀንስም አዘዋል። ይህ ውሳኔ የቱርክ መገበያያ ሊራ ከዶላር አንጻር ዋጋው በ45 በመቶ እንዲያሽቆለቁል አድርጓል። መንግሥት ለዋጋ ግሽበት መፍትሔ ያለው የደመወዝ መጠንን በ50 በመቶ ማሳደግ ነው። የምጣኔ ሀብት ተንታኞች የቱርክ የዋጋ ግሽበት በመጪው ፀደይ 50 በመቶ ይደርሳል ብለው ተንብየዋል። ብራዚል የብራዚል የስታትስቲክስ ተቋም እንደሚለው የሸቀጥ ዋጋ በ10 በመቶ፣ የነዳጅ ዋጋ በ50 በመቶ ጨምሯል። አምና በድርቅ ሳቢያ መሠረታዊ ሰብል የሆኑት ሩዝ እና ባቄላ ጠፍተው ነበር። የምግብ ዋጋም በ14 በመቶ አሻቅቧል። ብራዚል በቀንድ ከብት ከዓለም አንደኛ ብትሆንም የሥጋ ዋጋ እጅግ ከፍ ብሏል። ሥጋ የሚገዙ ዜጎች ቁጥርም በ67 በመቶ አሽቆልቁሏል። በድርቁ ሳቢያ ኃይል አመንጪዎችም እየተንገዳገዱ ነው። ለምሳሌ የአገሪቱ ከውሃ ኤሌክትሪክ ኃይል አመንጪ ተቋም ተዘግቷል። በዚህ ምክንያት የመብራት ክፍያ በአንድ አምስተኛ ጭማሪ አሳይቷል። ከ213 ሚሊዮን ብራዚላውያን 27 ሚሊዮኑ ከድህነት ወለል በታች እንደሚኖሩ ጉቴሮ ቫርጋስ የተባለ ድርጅት ገልጿል። እነዚህ ሰዎች በወር በ49 ዶላር ይኖራሉ። ሲሪ ላንካ አምና ከነበረው የምግብ ዋጋ አንጻር የዘንድሮው 20 በመቶ ንሯል። ደሴቷ ሲሪ ላንካ አምና መሠረታዊ የምግብ አቅርቦትን ከውጭ ለማስገባት ስትሞክር የምግብ ዋጋ በጣም ተወዶባታል። ዋነኛ ገቢዋን ከቱሪዝም ታገኝ ነበር። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ግን ለሁለት ዓመታት የአገሪቱን የእንጀራ ገመድ በጥሷል። በአገሪቱ ያለው የውጭ ምንዛሬ ክምችት ተመናምኗል። ባንኮች የውጭ ምንዛሬ ስለሌላቸው መንግሥት ምግብ ጫኝ መርከቦች እንዳይገቡ አግዷል። ይህም በመደብሮች የምግብ አቅርቦት ውስን እንዲሆን፣ የሸቀጥ ዋጋም እንዲንር አድርጓል። በተለይም ሩዝ፣ ስንዴ እና የዱቄት ወተት ዋጋቸው አይቀመስም። ነዳጅም በ85 በመቶ ጨምሯል። የተቆጣውን ሕዝብ ለማረጋጋት መንግሥት 1 ቢሊዮን ዶላር መድቦ፤ በሠራተኞችን ደመወዝ እና ጡረታ ላይ ማሻሻያ አድርጓል። ከአንዳንድ የምግብ ዓይነቶች እና መድኃኒት ላይም ቀረጥ ተነስቷል። | የዋጋ ግሽበት እጅግ የሚያሰጋቸው አገራት የትኞቹ ናቸው? የዋጋ ግሽበት ዓለምን ከጥግ ጥግ አስግቷል። ከኢትዮጵያ እስከ ሲሪ ላንካ ከብራዚል እስከ ደቡብ አፍሪካ። ምግብ ተወዷል። ነዳጅ ተወዷል። ምን ያልተወደደ አለ? የተለይ የመሠረታዊ አቅርቦቶች ዋጋ መናር ዓለምን አስጨንቋል። በእርግጥ የዋጋ ግሽበት ከሌላው የዓለም ክፍል በላይ የሚያንገዳግዳቸው አገሮች አሉ። ለዚህ ምክንያቱ ሰብል አለመሰብሰቡ፣ ወረርሽኙ መክፋቱ እና የተፈጥሮ ጋዝ መጥፋቱ ነው። በዚህ ደግሞ በአፍሪካ ከሰሀራ በታች ያሉ አገራት ዋነኛ ተጎጂ ናቸው። ቱርክ፣ ብራዚል እና ሲሪ ላንካም ይጠቀሳሉ። ከሰሀራ በታች ያሉ አገራት አብዛኞቹ ከሰሀራ በታች ያሉ አገራት ምግብ ለማብሰል የተጣራ ፈሳሽ ጋዝ (በሲሊንደር የሚታሸግ ቡታ ጋዝ) ይጠቀማሉ። የጋዝ ዋጋ ደግሞ እያሻቀበ ይገኛል። ባለፈው ዓመት በአንዳንድ የናይጄሪያ ግዛቶች ጋዝ በእጥፍ ጨምሯል። ብዙዎች ወደ ማገዶ እንጨት፣ ከሰል እና ኬሮሲን ፊታቸውን ለማዞር ተገደዋል። እነዚህ አማራጭ ኃይል ምንጮች ደግሞ አካባቢን ይበክላሉ። የተጠቃሚዎቹን ሳምባም ይጎዳሉ። የነዳጅ ዋጋ መጨመር፤ የማዳበሪያ ዋጋ እንዲሁም ምግብ ከእርሻ ወደ መደብር የሚጓጓዝበት ዋጋም እንዲንር ምክንያት ሆኗል። የናሳ የመሬት ምልከታ እንደሚጠቁመው በበርካታ የአፍሪካ አገሮች ዝናብ ከጠፋ ሰነባብቷል። ይህም የዋጋ ግሽበት አስከትሏል። በአንጎላ ባለፈው ዓመት የምግብ ዋጋ 36.4 በመቶ መጨመሩን የአገሪቱ የስታትስቲክስ ተቋም ይፋ አድርጓል። በማላዊ የኑሮ ውድነት ፀረ መንግሥት ሰልፎችን አስከትሏል። በአፍሪካ 282 ሚሊዮን ሰዎች ተመጣጣኝ ምግብ እንደማያገኙ የተባበሩት መንግሥታት ገልጿል። ቱርክ ጥቅምት ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በኢስታንቡል እና ዲያርባሪክ ከተሞች ሰልፍ መውጣታቸው ይታወሳል። አምና የዋጋ ግሽበት በ36 በመቶ ከፍ ብሏል። የአገሪቱ የስታትስቲክስ ተቋም እንዳለው የምግብ ዋጋ በዓመት 44 በመቶ ጨምሯል። በኢስታንቡል በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በመንግሥት ሱቆች ለዳቦ ሰልፍ ይዘው ማየት ተለምዷል። የግል ዳቦ ቤቶች ዋጋ ስለማይቀመስ ከእነሱ መግዛት አይታሰብም። ነዳጅና ማዳበሪያ ከመወደዱ ባሻገር የቱርክ መንግሥት የስንዴ ዋጋን መጨመሩ ዳቦ እንዲወደድ አድርጓል። የአውቶብስና ባቡር ክፍያም በእጥፍ ጨምሯል። የመብራት ክፍያ 50 በመቶ፣ የጋዝ ክፍያ 25 በመቶ ከፍ ብሏል። መንግሥታት የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር የወለድ መጠንን የሚጨምሩበት አሠራር አለ። ይህም ገንዘብን ለማግኘት አስቸጋሪ ያደርጋል። ፕሬዘዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን "ወለድን መጨመር ሀብታምን የበለጠ ሀብታም የሚያደርግ፣ ድሃን የባሰ የሚያደኸይ ሰይጣናዊ አካሄድ ነው" ብለዋል። የአገሪቱ ብሔራዊ ባንክ የወለድ መጠንን እንዲቀንስም አዘዋል። ይህ ውሳኔ የቱርክ መገበያያ ሊራ ከዶላር አንጻር ዋጋው በ45 በመቶ እንዲያሽቆለቁል አድርጓል። መንግሥት ለዋጋ ግሽበት መፍትሔ ያለው የደመወዝ መጠንን በ50 በመቶ ማሳደግ ነው። የምጣኔ ሀብት ተንታኞች የቱርክ የዋጋ ግሽበት በመጪው ፀደይ 50 በመቶ ይደርሳል ብለው ተንብየዋል። ብራዚል የብራዚል የስታትስቲክስ ተቋም እንደሚለው የሸቀጥ ዋጋ በ10 በመቶ፣ የነዳጅ ዋጋ በ50 በመቶ ጨምሯል። አምና በድርቅ ሳቢያ መሠረታዊ ሰብል የሆኑት ሩዝ እና ባቄላ ጠፍተው ነበር። የምግብ ዋጋም በ14 በመቶ አሻቅቧል። ብራዚል በቀንድ ከብት ከዓለም አንደኛ ብትሆንም የሥጋ ዋጋ እጅግ ከፍ ብሏል። ሥጋ የሚገዙ ዜጎች ቁጥርም በ67 በመቶ አሽቆልቁሏል። በድርቁ ሳቢያ ኃይል አመንጪዎችም እየተንገዳገዱ ነው። ለምሳሌ የአገሪቱ ከውሃ ኤሌክትሪክ ኃይል አመንጪ ተቋም ተዘግቷል። በዚህ ምክንያት የመብራት ክፍያ በአንድ አምስተኛ ጭማሪ አሳይቷል። ከ213 ሚሊዮን ብራዚላውያን 27 ሚሊዮኑ ከድህነት ወለል በታች እንደሚኖሩ ጉቴሮ ቫርጋስ የተባለ ድርጅት ገልጿል። እነዚህ ሰዎች በወር በ49 ዶላር ይኖራሉ። ሲሪ ላንካ አምና ከነበረው የምግብ ዋጋ አንጻር የዘንድሮው 20 በመቶ ንሯል። ደሴቷ ሲሪ ላንካ አምና መሠረታዊ የምግብ አቅርቦትን ከውጭ ለማስገባት ስትሞክር የምግብ ዋጋ በጣም ተወዶባታል። ዋነኛ ገቢዋን ከቱሪዝም ታገኝ ነበር። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ግን ለሁለት ዓመታት የአገሪቱን የእንጀራ ገመድ በጥሷል። በአገሪቱ ያለው የውጭ ምንዛሬ ክምችት ተመናምኗል። ባንኮች የውጭ ምንዛሬ ስለሌላቸው መንግሥት ምግብ ጫኝ መርከቦች እንዳይገቡ አግዷል። ይህም በመደብሮች የምግብ አቅርቦት ውስን እንዲሆን፣ የሸቀጥ ዋጋም እንዲንር አድርጓል። በተለይም ሩዝ፣ ስንዴ እና የዱቄት ወተት ዋጋቸው አይቀመስም። ነዳጅም በ85 በመቶ ጨምሯል። የተቆጣውን ሕዝብ ለማረጋጋት መንግሥት 1 ቢሊዮን ዶላር መድቦ፤ በሠራተኞችን ደመወዝ እና ጡረታ ላይ ማሻሻያ አድርጓል። ከአንዳንድ የምግብ ዓይነቶች እና መድኃኒት ላይም ቀረጥ ተነስቷል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60165449 |
0business
| ምጣኔ ሃብት ፡ አዲሶቹ የብር ኖቶች እና የያዟቸው የደኅንነት ገጽታዎች | ኢትዮጵያ ከሁለት አስር ዓመታት በላይ ስትገለገልባቸው የነበሩ የ10፣ የ50፣ እናየ100 የገንዘብ ዓይነቶችን ሙሉ ለሙሉ በመተካት አዲስ የገንዘብ ኖቶች ይፋ አድርጋለች። በቅርቡ ይፋ የተደረጉት የብር ኖቶች ቀደም ሲል ከነበሩት በተሻለ አጠቃቀም ምቹና ረዥም ጊዜ እንዲያገለግሉ ተደርገው መሰራታቸው የተገለጸ ቢሆንም ተጠቃሚዎች አንዳንድ ቅሬታዎች ሲያሰሙ ተደምጧል። በአዲሱ የ100 እና የ10 ብር ኖቶች ላይ ከላይ ወደ ታች የተዘረጋው መስመር ብሔራዊ ባንክ አስቀድሞ እንደገለፀው በአንበሳው መካከል አያልፍም። አንዳንዱ ላይ በአንበሳው ጆሮ፣ አንዳንዶቹ ላይ ደግሞ በአንበሳው ላይ ተሰምሮ ይታያል። ነጠብጣቡም የሚጀምረው አንዳንዱ ላይ ከብሩ ጫፍ ሌሎቹ ላይ ደግሞ ትንሽ ወረድ ብሎ እንደሆነ ማስተዋል ይቻላል። ይህንን ተከትሎ እነዚህ የገንዘብ ኖቶች የተጭበረበሩ ናቸው የሚል አሉባልታ በማህበራዊ መገናኛ ብዙኃን ተጠቃሚዎች ዘንድ ሲሰራጭም እየተሰማ ነው። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የብሔራዊ ባንክ የከረንሲ አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ አበበ ሰንበቴ ግን አዲሶቹ የብር ኖቶች ላይ የሚታየው ልዩነት ተራ የሕትመት ችግር እንጂ ተመሳስሎ የተሠራ እንዳልሆነ ገልፀዋል። አክለውም ይህ በገንዘቡ አጠቃቀም ላይ የሚያመጣው ለውጥ እንደሌለ አስረግጠው ይናገራሉ። ይህንን በኅብረተሰቡ ውስጥ እየተነገሩ ያሉ ሁኔታዎችን ሲያብራሩም በአዲስ የገንዘብ ኖቶች ላይ ለደኅንነት የተቀመጡ ምልክቶች ላይ የተወሰነ ልዩነት ሊኖር እንደሚችልም ምክንያቱን አስቀምጠዋል። በተቻለ መጠን መስመሮች መኖር ካለባቸው ስፍራ ፈቀቅ ሊሉ እንደሚችሉ ጠቅሰው፣ "የሕትመት ችግሩ ባይኖር ይመከራል፤ አይኖርም ግን ተብሎ አይጠበቅም" ብለዋል። እነዚያ ምልክቶች በትክክል በአዲሱ የገንዘብ ኖት ላይ እስከተገለፀ ድረስ ያን ያህል ችግር ነው ተብሎ ሊወሰድ እንደማይችል አብራርተዋል። ብሔራዊ ባንክ ገንዘቡ ሲታተም በቅድሚያ ያየው መኖሩን የገለፁት አቶ አበበ፣ ሕትመቱን ለሚሰሩት አካላት ያንን በተቻለ መጠን እንዲያጠቡትም ገለፃ እንደተደረገላቸው ያስታውሳሉ። ነገር ግን ባለው ሁኔታ ማሽኑ ላይ ለህትመት ሲገባ መዛነፉ እንደተፈጠረ ይናገራሉ። አቶ አበበ አዲሶቹን ብሮች ከቀደመው ጋር በማነጻጸርም ኀብረተሰቡ እነዚህን የደኅንነት መለያ ምልክቶች የሆኑ መስመሮች የተሰሩት ወረቀቱ ላይ በመታተም ሳይሆን ወረቀቱ ውስጥ ተሰርተው ነው ብለዋል። ከዚህ ቀደም በባለ 50 ብር እና በባለ 100 ብር ኖቶች ላይ ያለው መስመር የታተመው በገንዘቡ ላይ መሆኑን አስታውሰው የአሁኑ ግን በወረቀቱ ውስጥ መሰራቱን ይናገራሉ። የሚጠራጠር ተገልጋይ ካለ ብሩን በብርሃን ላይ ወስዶ በሚመለከትበት ወቅት ቀጥታ ከላይ ወደ ታች የሚወርድ መስመር እንደሚመለከት ያስረዳሉ። አቶ አበበ እንደሚሉት ይህም ሁኔታ ብርን አስመስለው የሚሰሩ ግለሰቦች በጭራሽ ሊሰሩት በማይችሉበት ሁኔታ ዲዛይን ተደርጓል። ሆኖም እንዲህ ዓይነት የመስመር መዛነፍ በሁሉም ኖቶች ላይ ሳይሆን ባበለ መቶ በተወሰኑ ቅጠሎች ላይ የተከሰተ መሆኑን ተናግረዋል። ሌላው ለአቶ አበበ ቢቢሲ ኣቀረበላቸው ጥያቄ በሁለት መቶ ብር ኖቶች ላይ የታየውን የእንግሊዝኛ ፊደላት ግድፈት ነው። በብሩ ላይ መቶ ወይም በእንግሊዝኛው hundred ተብሎ ከተፃፉ ፊደላት መካከል ዲ(d) ኦ (0) እንደሚመስል ማስተዋል ይቻላል። አቶ አበበ ሲመልሱም የተመረጠው ፎንት መሆኑን በማንሳት ይህ ተጠቃሚዎችን በሚያሳስት ደረጃ አለመቀመጡን አብራርተዋል። ከዚህ ቀደም የነበረው ባለ መቶ ብሮች ላይ ካለው ጋር ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ነው ያሉት አቶ አበበ ፊደላቶቹ 'ፎንት' ሲመረጡ የተከሰተ መሆኑን ይናገራሉ። እነዚህ የፊደል አጣጣሎች የተመረጠው መሆኑ ጠቅሰው የሚያመጣው ምንም አይነት ችግር እንደማይኖርም ይገልፃሉ። ሁለት መቶ የሚለው የአማርኛ ፊደልና ቁጥሩ በአግባቡ መቀመጡን ገልፀው፣ ይህ የብር ተጠቃሚው ላይ የሚፈጥረው ችገር አለመኖሩን አረጋግጠዋል። የአይነ ስውራን ብሔራዊ ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ወሰን አለሙ በቀድሞው ብር ላይም ሆነ በአሁኑ የብር ኖቶች ላይ የሚዳሰሱ ምልክቶች መኖራቸውን በማንሳት የአሁኑ ከቀድሞው የተሻለ መሆኑን ያነሳሉ። ምልክቶቹ በቀኝና በግራ ጫፍ ላይ እንዳሉ የሚገልፁት አቶ ወሰን፣ ብሔራዊ ባንኩ እንዳለው ነጥቦቹ ከአስር ብር ጀምሮ እስከ ሁለት መቶ ብር ድረስ ብዛታቸው እየተለያየ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል። የአይነስውር ማህበሩ ፕሬዝዳንት ለቢቢሲ እንደተናገሩት የተቀመጡት ምልክቶች በጣም የተጠጋጉ በመሆናቸው በእጅ ለመለየት አስቸጋሪ ናቸው። ብሮቹን ለመለየት ከዚህ ቀደም ስፋቱና ቁመታቸውን ይጠቀሙ እንደነበር ገልፀው፣ የአሁኖቹ መቶ እና ሁለት መቶ ብሮች ያላቸው የመጠን ልዩነት በጣም አነስተኛ መሆኑን ይናገራሉ። አቶ አበበ በበኩላቸው ለብሔራዊ ባንኩ የመጣ እንዲህ አይነት አስተያየት እስካሁን ድረስ አለመኖሩን ገልፀው ፤ የተቀመጡት ምልክቶች ሌሎች አገራትም የሚጠቀሙባቸው መሆናቸውን አስረድተዋል። ቴክኖሎጂው በትክክል ማየት የተሳናቸው ሰዎች ሊጠቀሙበት ይችላሉ ተብሎ መቀመጡን በመግለጽ በባለመቶው ላይ ስድስት፣ በባለ ሁለት መቶው ላይ ደግሞ ስምንት ምልከቶች መኖራቸውን ገልፀዋል። አቶ ወሰን እነዚህ ምልክቶች ብሩ የወረቀት በመሆኑ ሊፈገፈጉ ይችላል የሚል ስጋት አላቸው። አቶ አበበ ግን የገንዘቡ ጥራትም ቢሆን ሌሎች አገራት የሚጠቀሙባቸው ጥራቱን የጠበቀ ወረቀት መሆኑን ያስረዳሉ። በርግጥ በሌሎች አገራት ላይ የፕላስቲክ ገንዘቦች ያሉ ቢሆኑም ኢትዮጵያ ግን በአሁኑ ሰዓት እነዚያን ለመጠቀም የማትችልባቸው የተለያዩ ምክንያቶች መኖራቸውን አንስተዋል። የገንዘብ ሕትመት ሚስጥራዊነቱን በጠበቀ መልኩ እንደሚካሄድ ተናግረው የሚኖሩ ጉድለቶች በሚመጡ አስተያየቶች በሂደት እንደሚስተካከሉ ገልፀዋል። ሕትመት የአንድ ጊዜ ክንውን አይደለም በማለትም ባንኩ የሚቀርቡ አስተያየቶችን ካመነባቸው በሂደት ማስተካከያ እንደሚደርግ ተናግረዋል። ገንዘቡ ላይ የሚታዩ የደኅንነት መጠበቂያ ምልክቶች ምንድን ናቸው? አዳዲሶቹ የገንዘብ ኖቶች አስመስለው የሚሰሩ ሐሰተኛ የብር ኖቶችን ለመከላከልና ለመለየት በሚያስችል ሁኔታ የተለያዩ የደኅንነት መጠበቂያ ገጽታዎች እንዲኖሯቸው ተደርጓል። ለአይነ ስውራንም የእውቅና ምልክት ያላቸው ሲሆን የብሩን ዋጋ በእጅ ዳሰሳ ማወቅ የሚችሉበት የደኅንነት መጠበቂያ ያለው ነው። በተመሳሳይ ገንዘቡ ወደ ላይ ወይንም ወደታች ሲዞር የሚንቀሳቀስ ደማቅ የቀለም ፍንጣቂ የደኅንነት መጠበቂያ ምልክት እንዳለውም ተነግሯል። እንደ ብሔራዊ ባንክ ገለፃ ከሆነ አዳዲሶቹ ገንዘቦች የሚሽከረከር ደማቅ ቀለም ኮኮብ አዲስ የደህንነት መጠበቂያ ክር፤ በክሩ ውስጥም NBET፣ ኢብባ እና ገንዘቡ አይኖቶች ተፅፈው ይገኙበታል ነው የተባለው። ገንዘቡ ወደ ብርሃን አቅጣጫ ተደርጎ ሲታይ በላይ ላይ ከሚገኘው ምስል ፊት ለፊት ተመሳሳይ ደብዛዛ ውሃ መልክ ያለው ምልክት እንደሚታይ ተጠቁሟል። የብር ኖቶቹ በብርሃን አቅጣጫ ሲታይ ኳስ መሳይ ምልክት ከኖቶቹ በስተኋላ ካለው ተመሳሳይ ምልክት ጋር በፍፁም ትይዩ ሆነው በአንድ ቦታ ላይ ያርፋሉ። እንዲሁም አንበሳው ምስል ራስ ላይ 'አልትራቫዮሌት ጨረር' ሲበራበት ወደ ቢጫነት የሚለወጥ' ፍሎረሰንት' ምልክት አለው ተብሏል። ኖቶቹን በመቀየሩ ሥራ ለህትመት ብቻ በአጠቃላይ 3 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ወጪ እንደተደረገ ተነግሯል። ከቀለም አንጻር አዲሱ ባለ 200 ብር ኖት ሐምራዊ፣ ባለ100 ብር ኖት ውሃ ሰማያዊ፣ ባለ50 ብር ኖት ቀይ ብርቱካናማ፣ ባለ10 ብር ኖት ደግሞ አረንጓዴ ቀለም አላቸው። | ምጣኔ ሃብት ፡ አዲሶቹ የብር ኖቶች እና የያዟቸው የደኅንነት ገጽታዎች ኢትዮጵያ ከሁለት አስር ዓመታት በላይ ስትገለገልባቸው የነበሩ የ10፣ የ50፣ እናየ100 የገንዘብ ዓይነቶችን ሙሉ ለሙሉ በመተካት አዲስ የገንዘብ ኖቶች ይፋ አድርጋለች። በቅርቡ ይፋ የተደረጉት የብር ኖቶች ቀደም ሲል ከነበሩት በተሻለ አጠቃቀም ምቹና ረዥም ጊዜ እንዲያገለግሉ ተደርገው መሰራታቸው የተገለጸ ቢሆንም ተጠቃሚዎች አንዳንድ ቅሬታዎች ሲያሰሙ ተደምጧል። በአዲሱ የ100 እና የ10 ብር ኖቶች ላይ ከላይ ወደ ታች የተዘረጋው መስመር ብሔራዊ ባንክ አስቀድሞ እንደገለፀው በአንበሳው መካከል አያልፍም። አንዳንዱ ላይ በአንበሳው ጆሮ፣ አንዳንዶቹ ላይ ደግሞ በአንበሳው ላይ ተሰምሮ ይታያል። ነጠብጣቡም የሚጀምረው አንዳንዱ ላይ ከብሩ ጫፍ ሌሎቹ ላይ ደግሞ ትንሽ ወረድ ብሎ እንደሆነ ማስተዋል ይቻላል። ይህንን ተከትሎ እነዚህ የገንዘብ ኖቶች የተጭበረበሩ ናቸው የሚል አሉባልታ በማህበራዊ መገናኛ ብዙኃን ተጠቃሚዎች ዘንድ ሲሰራጭም እየተሰማ ነው። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የብሔራዊ ባንክ የከረንሲ አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ አበበ ሰንበቴ ግን አዲሶቹ የብር ኖቶች ላይ የሚታየው ልዩነት ተራ የሕትመት ችግር እንጂ ተመሳስሎ የተሠራ እንዳልሆነ ገልፀዋል። አክለውም ይህ በገንዘቡ አጠቃቀም ላይ የሚያመጣው ለውጥ እንደሌለ አስረግጠው ይናገራሉ። ይህንን በኅብረተሰቡ ውስጥ እየተነገሩ ያሉ ሁኔታዎችን ሲያብራሩም በአዲስ የገንዘብ ኖቶች ላይ ለደኅንነት የተቀመጡ ምልክቶች ላይ የተወሰነ ልዩነት ሊኖር እንደሚችልም ምክንያቱን አስቀምጠዋል። በተቻለ መጠን መስመሮች መኖር ካለባቸው ስፍራ ፈቀቅ ሊሉ እንደሚችሉ ጠቅሰው፣ "የሕትመት ችግሩ ባይኖር ይመከራል፤ አይኖርም ግን ተብሎ አይጠበቅም" ብለዋል። እነዚያ ምልክቶች በትክክል በአዲሱ የገንዘብ ኖት ላይ እስከተገለፀ ድረስ ያን ያህል ችግር ነው ተብሎ ሊወሰድ እንደማይችል አብራርተዋል። ብሔራዊ ባንክ ገንዘቡ ሲታተም በቅድሚያ ያየው መኖሩን የገለፁት አቶ አበበ፣ ሕትመቱን ለሚሰሩት አካላት ያንን በተቻለ መጠን እንዲያጠቡትም ገለፃ እንደተደረገላቸው ያስታውሳሉ። ነገር ግን ባለው ሁኔታ ማሽኑ ላይ ለህትመት ሲገባ መዛነፉ እንደተፈጠረ ይናገራሉ። አቶ አበበ አዲሶቹን ብሮች ከቀደመው ጋር በማነጻጸርም ኀብረተሰቡ እነዚህን የደኅንነት መለያ ምልክቶች የሆኑ መስመሮች የተሰሩት ወረቀቱ ላይ በመታተም ሳይሆን ወረቀቱ ውስጥ ተሰርተው ነው ብለዋል። ከዚህ ቀደም በባለ 50 ብር እና በባለ 100 ብር ኖቶች ላይ ያለው መስመር የታተመው በገንዘቡ ላይ መሆኑን አስታውሰው የአሁኑ ግን በወረቀቱ ውስጥ መሰራቱን ይናገራሉ። የሚጠራጠር ተገልጋይ ካለ ብሩን በብርሃን ላይ ወስዶ በሚመለከትበት ወቅት ቀጥታ ከላይ ወደ ታች የሚወርድ መስመር እንደሚመለከት ያስረዳሉ። አቶ አበበ እንደሚሉት ይህም ሁኔታ ብርን አስመስለው የሚሰሩ ግለሰቦች በጭራሽ ሊሰሩት በማይችሉበት ሁኔታ ዲዛይን ተደርጓል። ሆኖም እንዲህ ዓይነት የመስመር መዛነፍ በሁሉም ኖቶች ላይ ሳይሆን ባበለ መቶ በተወሰኑ ቅጠሎች ላይ የተከሰተ መሆኑን ተናግረዋል። ሌላው ለአቶ አበበ ቢቢሲ ኣቀረበላቸው ጥያቄ በሁለት መቶ ብር ኖቶች ላይ የታየውን የእንግሊዝኛ ፊደላት ግድፈት ነው። በብሩ ላይ መቶ ወይም በእንግሊዝኛው hundred ተብሎ ከተፃፉ ፊደላት መካከል ዲ(d) ኦ (0) እንደሚመስል ማስተዋል ይቻላል። አቶ አበበ ሲመልሱም የተመረጠው ፎንት መሆኑን በማንሳት ይህ ተጠቃሚዎችን በሚያሳስት ደረጃ አለመቀመጡን አብራርተዋል። ከዚህ ቀደም የነበረው ባለ መቶ ብሮች ላይ ካለው ጋር ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ነው ያሉት አቶ አበበ ፊደላቶቹ 'ፎንት' ሲመረጡ የተከሰተ መሆኑን ይናገራሉ። እነዚህ የፊደል አጣጣሎች የተመረጠው መሆኑ ጠቅሰው የሚያመጣው ምንም አይነት ችግር እንደማይኖርም ይገልፃሉ። ሁለት መቶ የሚለው የአማርኛ ፊደልና ቁጥሩ በአግባቡ መቀመጡን ገልፀው፣ ይህ የብር ተጠቃሚው ላይ የሚፈጥረው ችገር አለመኖሩን አረጋግጠዋል። የአይነ ስውራን ብሔራዊ ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ወሰን አለሙ በቀድሞው ብር ላይም ሆነ በአሁኑ የብር ኖቶች ላይ የሚዳሰሱ ምልክቶች መኖራቸውን በማንሳት የአሁኑ ከቀድሞው የተሻለ መሆኑን ያነሳሉ። ምልክቶቹ በቀኝና በግራ ጫፍ ላይ እንዳሉ የሚገልፁት አቶ ወሰን፣ ብሔራዊ ባንኩ እንዳለው ነጥቦቹ ከአስር ብር ጀምሮ እስከ ሁለት መቶ ብር ድረስ ብዛታቸው እየተለያየ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል። የአይነስውር ማህበሩ ፕሬዝዳንት ለቢቢሲ እንደተናገሩት የተቀመጡት ምልክቶች በጣም የተጠጋጉ በመሆናቸው በእጅ ለመለየት አስቸጋሪ ናቸው። ብሮቹን ለመለየት ከዚህ ቀደም ስፋቱና ቁመታቸውን ይጠቀሙ እንደነበር ገልፀው፣ የአሁኖቹ መቶ እና ሁለት መቶ ብሮች ያላቸው የመጠን ልዩነት በጣም አነስተኛ መሆኑን ይናገራሉ። አቶ አበበ በበኩላቸው ለብሔራዊ ባንኩ የመጣ እንዲህ አይነት አስተያየት እስካሁን ድረስ አለመኖሩን ገልፀው ፤ የተቀመጡት ምልክቶች ሌሎች አገራትም የሚጠቀሙባቸው መሆናቸውን አስረድተዋል። ቴክኖሎጂው በትክክል ማየት የተሳናቸው ሰዎች ሊጠቀሙበት ይችላሉ ተብሎ መቀመጡን በመግለጽ በባለመቶው ላይ ስድስት፣ በባለ ሁለት መቶው ላይ ደግሞ ስምንት ምልከቶች መኖራቸውን ገልፀዋል። አቶ ወሰን እነዚህ ምልክቶች ብሩ የወረቀት በመሆኑ ሊፈገፈጉ ይችላል የሚል ስጋት አላቸው። አቶ አበበ ግን የገንዘቡ ጥራትም ቢሆን ሌሎች አገራት የሚጠቀሙባቸው ጥራቱን የጠበቀ ወረቀት መሆኑን ያስረዳሉ። በርግጥ በሌሎች አገራት ላይ የፕላስቲክ ገንዘቦች ያሉ ቢሆኑም ኢትዮጵያ ግን በአሁኑ ሰዓት እነዚያን ለመጠቀም የማትችልባቸው የተለያዩ ምክንያቶች መኖራቸውን አንስተዋል። የገንዘብ ሕትመት ሚስጥራዊነቱን በጠበቀ መልኩ እንደሚካሄድ ተናግረው የሚኖሩ ጉድለቶች በሚመጡ አስተያየቶች በሂደት እንደሚስተካከሉ ገልፀዋል። ሕትመት የአንድ ጊዜ ክንውን አይደለም በማለትም ባንኩ የሚቀርቡ አስተያየቶችን ካመነባቸው በሂደት ማስተካከያ እንደሚደርግ ተናግረዋል። ገንዘቡ ላይ የሚታዩ የደኅንነት መጠበቂያ ምልክቶች ምንድን ናቸው? አዳዲሶቹ የገንዘብ ኖቶች አስመስለው የሚሰሩ ሐሰተኛ የብር ኖቶችን ለመከላከልና ለመለየት በሚያስችል ሁኔታ የተለያዩ የደኅንነት መጠበቂያ ገጽታዎች እንዲኖሯቸው ተደርጓል። ለአይነ ስውራንም የእውቅና ምልክት ያላቸው ሲሆን የብሩን ዋጋ በእጅ ዳሰሳ ማወቅ የሚችሉበት የደኅንነት መጠበቂያ ያለው ነው። በተመሳሳይ ገንዘቡ ወደ ላይ ወይንም ወደታች ሲዞር የሚንቀሳቀስ ደማቅ የቀለም ፍንጣቂ የደኅንነት መጠበቂያ ምልክት እንዳለውም ተነግሯል። እንደ ብሔራዊ ባንክ ገለፃ ከሆነ አዳዲሶቹ ገንዘቦች የሚሽከረከር ደማቅ ቀለም ኮኮብ አዲስ የደህንነት መጠበቂያ ክር፤ በክሩ ውስጥም NBET፣ ኢብባ እና ገንዘቡ አይኖቶች ተፅፈው ይገኙበታል ነው የተባለው። ገንዘቡ ወደ ብርሃን አቅጣጫ ተደርጎ ሲታይ በላይ ላይ ከሚገኘው ምስል ፊት ለፊት ተመሳሳይ ደብዛዛ ውሃ መልክ ያለው ምልክት እንደሚታይ ተጠቁሟል። የብር ኖቶቹ በብርሃን አቅጣጫ ሲታይ ኳስ መሳይ ምልክት ከኖቶቹ በስተኋላ ካለው ተመሳሳይ ምልክት ጋር በፍፁም ትይዩ ሆነው በአንድ ቦታ ላይ ያርፋሉ። እንዲሁም አንበሳው ምስል ራስ ላይ 'አልትራቫዮሌት ጨረር' ሲበራበት ወደ ቢጫነት የሚለወጥ' ፍሎረሰንት' ምልክት አለው ተብሏል። ኖቶቹን በመቀየሩ ሥራ ለህትመት ብቻ በአጠቃላይ 3 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ወጪ እንደተደረገ ተነግሯል። ከቀለም አንጻር አዲሱ ባለ 200 ብር ኖት ሐምራዊ፣ ባለ100 ብር ኖት ውሃ ሰማያዊ፣ ባለ50 ብር ኖት ቀይ ብርቱካናማ፣ ባለ10 ብር ኖት ደግሞ አረንጓዴ ቀለም አላቸው። | https://www.bbc.com/amharic/54297291 |
0business
| ከባንክ አገልግሎት ወደ ተቆራረጠችው ትግራይ ገንዘብ ለመላክ የሚከፈለው ከባድ ዋጋ | ላለፉት ሁለት ዓመታት በጦርነት ውስጥ በቆየችው ትግራይ መሠረታዊ አገልግሎቶች በመቋረጣቸው ሕይወት ከባድ ሆኗል። በርካቶች ከጦርነቱ በፊት የነበራቸውን ሕይወት እና ጓደኝነት፣ ትምህርት እና ሥራ፣ ከምንም በላይ ሰላምን ይናፍቃሉ። የታመሙ ሮጥ ብለው የሚታከሙበት የሕክምና ተቋም ህንጻው ብቻ ቀርቷል። ሮጥ ብለው ያገኙትን የሚሸምቱበት ሱቅ ባዶውን ያዛጋል። ያለቻቸውን በውድ ዋጋ የሚሸጡ ነጋዴዎች ጋር ለመሄድ ደግሞ ገንዘብ ወሳኝ፤ ግን ከየት ይምጣ። የሁለት ልጆች አባት የሆነው አቶ አብርሃ ይሕደጎ፣ በአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ውስጥ የመዝገብ ቤት ሠራተኛ ነበር። አሁን ላይ ግን የሚከፈለው ገንዘብ እንደሌለና ሥራውን እንዳቆመ ገልጿል። “ጦርነቱ ያስጨንቀናል፤ የምንኖረው ሕይወትን እንኳ ምን ብዬ እንደምገልጸው አላውቅም - እየባሰበት ነው። እኔ፤ አልፎ አልፎ የሚላክልኝን ገንዘብ ጠብቄ ልጆቼን ለመቀለብ እየጣርኩ ነው። እዚህ ሁሉንም ነገር ስለተወደደ ገንዘቡ ጥቅም የለውም፤ ምንም ነገር መግዛት አይቻልም” ይላል። በባሕር ማዶ ወዳጅ ዘመድ ያላቸው ችግራቸውን ጠቅሰው የድጋፍ ተማጽኖ ድምጽ ያሰማሉ። ገንዘብ ግን ወደ ትግራይ ለማስገባት ውጣ ውረዱ ከባድ ነው። ለዚህም ነው የትግራይ ተወላጅ የሆኑት የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር፣ ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም ሳይቀር ለቤተሰቦቻቸው ገንዘብ ለመላክ መቸገራቸውን የተናገሩት። ጦርነቱ ባንክን ጨምሮ የተለያዩ ማኅበራዊ አገልግሎቶች እንዲቋረጡ ምክንያት በመሆኑ በሚሊዮን የሚቆጠር የክልሉ ሕዝብ የባንክ አገልግሎት አያገኝም። የፋይናንስ አገልግሎቶች መቋረጥ ደግሞ ወደ ክልሉ ገንዘብ መላክን እጅግ አስቸጋሪ እና ብዙ ወጪ የሚጠይቅ እንዲሆን አድርጎታል። ይሄንን ተከትሎ አንዳንድ ቤተሰቦች ገንዘብ ለማግኘት ንብረታቸውንና ሌላ አለኝ የሚሉትን ነገር ሸጠዋል። አንዳንዶች ደግሞ በውጭ አገራት የሚገኙ ቤተሰቦቻቸው እና ጓደኞቻቸው እጅ ይጠባበቃሉ። ሰላም ባለኸኝ በመቀለ ዩኒቨርሲቲ የሥርዓተ-ጾታ ባለሞያ ስትሆን፣ በትግራይ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት በነበሩት ጥቂት ወራት ነጻ የትምህርት ዕድል አግኝታ ነው ወደ ቤልጅም የሄደችው። አሁን ግን በጦርነቱ ምክንያት ወደ ትግራይ መመለስ እንዳልቻለች ትናገራለች። እንደ ሰላም ያሉ በውጭ አገር ሆነው ቤተሰቦቻቸውንና ጓደኞቻቸውን በገንዘብ እያገዙ የሚገኙ ሰዎች፣ ወደ ትግራይ ገንዘብ ለመላክ እጅግ የተወሳሰበና ዋስትና የሌላቸው መንገዶችን ይጠቀማሉ። ሰላም “በሕይወት ለመቆየት፣ እንባ እየተናነቃቸው ገንዘብ ላኩልን ስለሚሉን፣ የምንልከው ገንዘብ ከግማሽ በላይ እየተወሰደብንም ቢሆን ሕጋዊ ያልሆነ መንገድ እንድንጠቀም ተገደናል” ትላለች። እሷ፣ ከአንድ ዓመት በላይ ገንዘብ ለመላክ የተለያዩ መንገዶችን ስትጠቀም መቆየቷን ትናገራለች። የመጀመሪያው አዲስ አበባ ያሉ ሰዎችን መጠቀም ነው። አዲስ አበባ ያሉ አቀባባዮች መቀለ ከሚኖሩ ገንዘብ ካላቸው ሰዎች ጋር ግንኙነት አላቸው። አዲስ አበባ ለሚገኙት ሰዎች በስማቸው በባንክ አካውንታቸው ውስጥ ገንዘብ ካስገቡ በኋላ፣ ለማን እንደሚሰጥ እና የላኪ ስም በስልክ ይነገራቸዋል። ከባንክ አገልግሎት ከራቀች ረዥም ወራትን ባስቆጠረችው መቀለ የሚኖሩ ባለሀብቶች ጋር ደውለው ምን ያህል ገንዘብ እንደተላከ፣ መቼ መውሰድ እንደሚቻል ይነጋገራሉ። ከዚያም መልሰው ለገንዘቡ ላኪ መረጃውን በማስተላለፍ ኮሚሽናቸውን ተቀብለው ሥራቸውን ይጨርሳሉ። እዚህ ላይ ገንዘብ ላኪ እና ተቀባይ መረጃ የመለዋወጥ ድርሻውን ራሳቸው ይወጣሉ። ሌላኛው ገንዘብ መቀባበያ መንገድ ደግሞ በአፋር እና በአማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ እና ገንዘብ በማዘዋወር ተግባር ላይ የተሰማሩ ሰዎችን መጠቀም ነው። ይህ የገንዘብ ዝውውር ግን አንድ ስምምነት ይፈልጋል። መጀመሪያ ላኪው ከገንዘብ አዘዋዋሪዎቹ ጋር በሚያደርገው ስምምነት መሰረት ከ30 እስከ 50 በመቶ የድለላ ዋጋ [ኮሚሽን] እንዲከፍል ይስማማል። ሁለቱም የሚያስማማቸው መጠን ላይ ከደረሱ በኋላ ተቀባዩ ቀሪው ገንዘብ ይደርሰዋል። በአፋር ክልል ያለው እንቅስቃሴ የሚከፈለው ገንዘብ አዲስ አበባ ካለው ዝቅ ያለ ቢሆንም፣ ገንዘቡ ተቀባዩ ጋር እስኪ ደርስ እስከ ሦስት ወር ሊወስድ እንደሚችል ተጠቃሚዎች ይናገራሉ። ተራ በቃል የሚፈጸም ንግግር ብቸኛው ገንዘብ ላኪው ያለው መተማመኛ ሲሆን፣ አንዳንድ የገንዘብ አዘዋዋሪዎች ገንዘቡን ካደረሱ በኋላ የተቀባዩን ድምጽ ወይም ምስል ቀርጸው ላኪው ጋር በመላክ ድርሻቸውን እንደተወጡ ያረጋግጣሉ። ሰላም እነዚህ ሁሉንም አማራጮች ተጠቅማባቸዋለች። አንድ ጊዜ “ወንድሜ ታሞ ስለነበረ፣ የሚታከምበት ገንዘብ ቶሎ ብላችሁ ላኩ ስለተባልን 67 ሺህ ብር ላኩኝ። ቤተሰቦቼ የደረሳቸው ግን 30 ሺህ ብር ብቻ ነበር። በዚህ በጣም ተበሳጭቻለሁ” ትላለች። የዚህ ምክንያት የገንዘብ አዘዋዋሪዎቹ መስመር ከአዲስ አበባ ጀምሮ እስከ ትግራይ የተዘረጋ ስለሆነ፣ የሚላከው ገንዘብ ተቀባዩ እጅ እስኪደርስ በርካታ የጥቅም ተካፋይ ሰዎች ስላሉ እንደሆነ ይነገራል። ከዚህ ቀደም ቢቢሲ ያነጋገረው በዚህ ሥራ ላይ ተሰማርቶ የሚገኝ አንድ ግለሰብ “የምንወስደው ኮሚሽን ሁሉ ወደ ኪሳችን አይገባም። አንድ ገንዘብ ከባንክ ስናወጣ ለበርካታ ሰዎች የሚሆን ስለምናወጣ እነሱም የሻይ ይፈልጋሉ። በተጨማሪም ወደ ትግራይ ብዙ ገንዘብ ይዞ መግባት ከባድ እና መሰናክሎች የበዛበት ነው። እነዚህን በገንዘብ እየሸፈንን ነው የምንሄደው” ብሎ ነበር። ትግራይ ውስጥ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ 616 የባንክ ቅርንጫፎች በመዘጋታቸው ምክንያት ወደ ባንኮቹ ገንዘብ መላክም ሆነ፣ በትግራይ ክልል ከተከፈቱ የሂሳብ ቁጥሮች ገንዘብ ማንቀሳቀስ አይቻልም። አሁን ያለው የገንዘብ ዝውውር ሰንሰለት እጅግ አደገኛ እና የከተማ አስተዳደሮች እና የፀጥታ አካላት ቁጥጥር የሚያደርጉበት ስለሆነ፣ በርካታ ሰዎች ገንዘባቸው በተለያየ መንገድ ጠፍቶ መቅረቱን ይናገራሉ። ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ የቆቦ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ በኩል ሲያልፍ የነበረ ሦስት ሚሊዮን ብር በፀጥታ አካላት ቁጥጥር ላይ መዋሉን አስታውቆ ነበር። በዚህ መሠረት የገንዘብ አዘዋዋሪዎቹ መንገድ ላይ ፍተሻ ሲኖር የያዙት ገንዘብ እንደሚወረስባቸው ይናገራሉ። ሰላም ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር በአፋር ክልል በኩል ያለውን የገንዘብ ዝውውር ተጠቅማ ወደ ትግራይ የላከቸው ስድስት ሺህ ዩሮ፣ ገንዘቡን እንዲያደርስ የተቀበለው ግለሰብ እጅ ላይ መቅረቱን ትናገራለች። ይህ የበርካታ ሰዎች ላይ ደርሷል። “ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ላይ አስተማሪ ነው፤ አንዱ ጓደኛችን በእሱ በኩል የላከው አንድ ሺህ ዩሮ በሦስት ቀን መቀለ ደረሰ። የሚያስከፍለው ኮሚሽን 22 በመቶ ስለነበረ፣ የሚቀንስልን በማግኘታችን ደስ አለን። ‘በርከት አድርጋችሁ የምትልኩ ከሆነ ለእናንተም የምትከፍሉት ይቀንስላችኋል፣ እኔም አልመላለስም’ ስላለን የተለያዩ ሰዎች ጠይቄ 6 ሺህ ዩሮ ላኩለት” ትላለች። ከዚህ ገንዘብ ውስጥ 3 ሺህ ዩሮ የራሷ ሲሆን ቀሪውን የጓደኞቿ ነበር። ገንዘቡ በወቅቱ በነበረው የባንክ ምንዛሪ ከ327 ሺህ ብር በላይ ይገመታል። “ባንኮች ቢሰሩ እንዲህ ላለ ችግር አንዳረግም ነበር፤ ግን ደግሞ ቤተሰቦቻችን በሕይወት እንዲቆዩልን ስለምንፈልግ የጭንቅ አማራጮች እንድንወስድ ተገደናል” ስትል ትናገራለች። ሁለት ዓመት ሊሞላው ጥቂት ቀናት የቀሩት ጦርነት እንዲያበቃ በተለያዩ ወገኖች ከሚደረገው ጥረት ጎን ለጎን በክልሉ ተቋርጠው የሚገኙት ባንክን ጨምሮ ሌሎች መሠረታዊ አገልግሎቶች ወደ ሥራ እንዲመለሱ የሚደረገው ግፊት ይጠቀሳል። በትግራይ ክልል መቀለ ከተማ እንደ ሳተላይት ስልክ ያሉ መሣሪያዎች በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የእርዳታ ተቋማት የሚጠቀሙባቸው መሳሪያዎች ሆነው ቆይተዋል። ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማኅበር እነዚህ የሳተላይት ስልኮችን ተጠቅሞ ነዋሪዎች ከክልሉ ውጪ ከሚገኙ ቤተሰቦቻቸው እና ጓደኞቻቸው ጋር ለማገናኘት ሲሰራ ቆይቷል። እስከ አሁን ማኅበሩ “በጦርነት እና ግጭት የተለያዩ” ሰዎች 115 ሺህ የሚጠጉ የስልክ ጥሪዎች እና መልዕክቶች እንዲያስተላልፉ ማድረጉን ይገልጻል። ወደ ክልሉ እርዳታ የጫነ መኪና ሲያመላልስ የነበረ ለደኅንነቱ ሲል ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈቀደ አሽከርካሪ የፌደራል ኃይሎች በትግራይ ከነበሩበት ጊዜ አንስቶ ሦስተኛው ዙር ጦርነት እስከተነሳበት ወቅት በነበሩ የተለያዩ ግዜያት እርዳታ ሲያደርስ ነበር። “መንገድ ላይ ብዙ ነገሮች አሉ፤ በጦርነቱ ምክንያት የደረሰው ውድመት በየቦታ ይታያል። የተቃጠሉ መኪኖች፣ የወደሙ መኖሪያ ቤቶች በርካታ ናቸው። ጦርነቱ መንገድ ላይ የሚታይ ነው የሚመስለው” ይላል። በክልሉ በተንቀሳቀሰባቸው አካባቢዎች ያጋጠመ ሰፊ ማኅበራዊ ቀውስ መኖሩን የሚናገረው አሽከርካሪው፣ አንዳንድ አሽከርካሪዎች ከአዲስ አበባ ሲነሱ ገንዘብ አድርሱልን ከሚሉ ሰዎች ገንዘብ ተቀብለው እንደሚሄዱ ይገልጻል። “በትግራይ ሁለንታዊ ችግር አለ፤ መንገድ ላይ ‘እባክህን ገንዘብ ወይ መድኃኒት አምጣልን’ ብሎ የሚጠይቅ ሰው ብዙ ነው፤ በተለይ የካንሰር ህሙማን። ከእዚያው ለመግዛትም አቅም የላቸውም፤ ሁሉም ሰው ግን ገንዘብ ይጠይቃል።” የጦርነቱን ዳግም ማገርሸት ተከትሎ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ ወደ ትግራይ ሲያደርሰው የነበረው ሰብአዊ እርዳታን እንዳቆመ ባለፈው የነሐሴ ወር አስታውቆ ነበር። በዚህ ወቅት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የዓለም የምግብ ፕሮግራም ይገልጻል። “እንዲህ አይነት ጦርነት ይኖራል ብዬ አስቤ አላውቅም፤ በዚህ ዘመን እናትህ በሕይወት እያለች ለአንድ ቀንም ቢሆን ድምጿ በስልክ አለመስማት ከባድ ነው። በየቀኑ ሰዎች ሞቱ፣ የአየር ጥቃት ተፈጸመ፣ ህጻናት በረሃብ እየሞቱ ነው የሚሉ ዜናዎች ስሰማ ይጨንቀኛል” የምትለው ሰላም ጦርነቱ የሚቆምበትን ጊዜ በጉጉት እየጠበቀች መሆኗን ትናገራለች። | ከባንክ አገልግሎት ወደ ተቆራረጠችው ትግራይ ገንዘብ ለመላክ የሚከፈለው ከባድ ዋጋ ላለፉት ሁለት ዓመታት በጦርነት ውስጥ በቆየችው ትግራይ መሠረታዊ አገልግሎቶች በመቋረጣቸው ሕይወት ከባድ ሆኗል። በርካቶች ከጦርነቱ በፊት የነበራቸውን ሕይወት እና ጓደኝነት፣ ትምህርት እና ሥራ፣ ከምንም በላይ ሰላምን ይናፍቃሉ። የታመሙ ሮጥ ብለው የሚታከሙበት የሕክምና ተቋም ህንጻው ብቻ ቀርቷል። ሮጥ ብለው ያገኙትን የሚሸምቱበት ሱቅ ባዶውን ያዛጋል። ያለቻቸውን በውድ ዋጋ የሚሸጡ ነጋዴዎች ጋር ለመሄድ ደግሞ ገንዘብ ወሳኝ፤ ግን ከየት ይምጣ። የሁለት ልጆች አባት የሆነው አቶ አብርሃ ይሕደጎ፣ በአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ውስጥ የመዝገብ ቤት ሠራተኛ ነበር። አሁን ላይ ግን የሚከፈለው ገንዘብ እንደሌለና ሥራውን እንዳቆመ ገልጿል። “ጦርነቱ ያስጨንቀናል፤ የምንኖረው ሕይወትን እንኳ ምን ብዬ እንደምገልጸው አላውቅም - እየባሰበት ነው። እኔ፤ አልፎ አልፎ የሚላክልኝን ገንዘብ ጠብቄ ልጆቼን ለመቀለብ እየጣርኩ ነው። እዚህ ሁሉንም ነገር ስለተወደደ ገንዘቡ ጥቅም የለውም፤ ምንም ነገር መግዛት አይቻልም” ይላል። በባሕር ማዶ ወዳጅ ዘመድ ያላቸው ችግራቸውን ጠቅሰው የድጋፍ ተማጽኖ ድምጽ ያሰማሉ። ገንዘብ ግን ወደ ትግራይ ለማስገባት ውጣ ውረዱ ከባድ ነው። ለዚህም ነው የትግራይ ተወላጅ የሆኑት የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር፣ ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም ሳይቀር ለቤተሰቦቻቸው ገንዘብ ለመላክ መቸገራቸውን የተናገሩት። ጦርነቱ ባንክን ጨምሮ የተለያዩ ማኅበራዊ አገልግሎቶች እንዲቋረጡ ምክንያት በመሆኑ በሚሊዮን የሚቆጠር የክልሉ ሕዝብ የባንክ አገልግሎት አያገኝም። የፋይናንስ አገልግሎቶች መቋረጥ ደግሞ ወደ ክልሉ ገንዘብ መላክን እጅግ አስቸጋሪ እና ብዙ ወጪ የሚጠይቅ እንዲሆን አድርጎታል። ይሄንን ተከትሎ አንዳንድ ቤተሰቦች ገንዘብ ለማግኘት ንብረታቸውንና ሌላ አለኝ የሚሉትን ነገር ሸጠዋል። አንዳንዶች ደግሞ በውጭ አገራት የሚገኙ ቤተሰቦቻቸው እና ጓደኞቻቸው እጅ ይጠባበቃሉ። ሰላም ባለኸኝ በመቀለ ዩኒቨርሲቲ የሥርዓተ-ጾታ ባለሞያ ስትሆን፣ በትግራይ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት በነበሩት ጥቂት ወራት ነጻ የትምህርት ዕድል አግኝታ ነው ወደ ቤልጅም የሄደችው። አሁን ግን በጦርነቱ ምክንያት ወደ ትግራይ መመለስ እንዳልቻለች ትናገራለች። እንደ ሰላም ያሉ በውጭ አገር ሆነው ቤተሰቦቻቸውንና ጓደኞቻቸውን በገንዘብ እያገዙ የሚገኙ ሰዎች፣ ወደ ትግራይ ገንዘብ ለመላክ እጅግ የተወሳሰበና ዋስትና የሌላቸው መንገዶችን ይጠቀማሉ። ሰላም “በሕይወት ለመቆየት፣ እንባ እየተናነቃቸው ገንዘብ ላኩልን ስለሚሉን፣ የምንልከው ገንዘብ ከግማሽ በላይ እየተወሰደብንም ቢሆን ሕጋዊ ያልሆነ መንገድ እንድንጠቀም ተገደናል” ትላለች። እሷ፣ ከአንድ ዓመት በላይ ገንዘብ ለመላክ የተለያዩ መንገዶችን ስትጠቀም መቆየቷን ትናገራለች። የመጀመሪያው አዲስ አበባ ያሉ ሰዎችን መጠቀም ነው። አዲስ አበባ ያሉ አቀባባዮች መቀለ ከሚኖሩ ገንዘብ ካላቸው ሰዎች ጋር ግንኙነት አላቸው። አዲስ አበባ ለሚገኙት ሰዎች በስማቸው በባንክ አካውንታቸው ውስጥ ገንዘብ ካስገቡ በኋላ፣ ለማን እንደሚሰጥ እና የላኪ ስም በስልክ ይነገራቸዋል። ከባንክ አገልግሎት ከራቀች ረዥም ወራትን ባስቆጠረችው መቀለ የሚኖሩ ባለሀብቶች ጋር ደውለው ምን ያህል ገንዘብ እንደተላከ፣ መቼ መውሰድ እንደሚቻል ይነጋገራሉ። ከዚያም መልሰው ለገንዘቡ ላኪ መረጃውን በማስተላለፍ ኮሚሽናቸውን ተቀብለው ሥራቸውን ይጨርሳሉ። እዚህ ላይ ገንዘብ ላኪ እና ተቀባይ መረጃ የመለዋወጥ ድርሻውን ራሳቸው ይወጣሉ። ሌላኛው ገንዘብ መቀባበያ መንገድ ደግሞ በአፋር እና በአማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ እና ገንዘብ በማዘዋወር ተግባር ላይ የተሰማሩ ሰዎችን መጠቀም ነው። ይህ የገንዘብ ዝውውር ግን አንድ ስምምነት ይፈልጋል። መጀመሪያ ላኪው ከገንዘብ አዘዋዋሪዎቹ ጋር በሚያደርገው ስምምነት መሰረት ከ30 እስከ 50 በመቶ የድለላ ዋጋ [ኮሚሽን] እንዲከፍል ይስማማል። ሁለቱም የሚያስማማቸው መጠን ላይ ከደረሱ በኋላ ተቀባዩ ቀሪው ገንዘብ ይደርሰዋል። በአፋር ክልል ያለው እንቅስቃሴ የሚከፈለው ገንዘብ አዲስ አበባ ካለው ዝቅ ያለ ቢሆንም፣ ገንዘቡ ተቀባዩ ጋር እስኪ ደርስ እስከ ሦስት ወር ሊወስድ እንደሚችል ተጠቃሚዎች ይናገራሉ። ተራ በቃል የሚፈጸም ንግግር ብቸኛው ገንዘብ ላኪው ያለው መተማመኛ ሲሆን፣ አንዳንድ የገንዘብ አዘዋዋሪዎች ገንዘቡን ካደረሱ በኋላ የተቀባዩን ድምጽ ወይም ምስል ቀርጸው ላኪው ጋር በመላክ ድርሻቸውን እንደተወጡ ያረጋግጣሉ። ሰላም እነዚህ ሁሉንም አማራጮች ተጠቅማባቸዋለች። አንድ ጊዜ “ወንድሜ ታሞ ስለነበረ፣ የሚታከምበት ገንዘብ ቶሎ ብላችሁ ላኩ ስለተባልን 67 ሺህ ብር ላኩኝ። ቤተሰቦቼ የደረሳቸው ግን 30 ሺህ ብር ብቻ ነበር። በዚህ በጣም ተበሳጭቻለሁ” ትላለች። የዚህ ምክንያት የገንዘብ አዘዋዋሪዎቹ መስመር ከአዲስ አበባ ጀምሮ እስከ ትግራይ የተዘረጋ ስለሆነ፣ የሚላከው ገንዘብ ተቀባዩ እጅ እስኪደርስ በርካታ የጥቅም ተካፋይ ሰዎች ስላሉ እንደሆነ ይነገራል። ከዚህ ቀደም ቢቢሲ ያነጋገረው በዚህ ሥራ ላይ ተሰማርቶ የሚገኝ አንድ ግለሰብ “የምንወስደው ኮሚሽን ሁሉ ወደ ኪሳችን አይገባም። አንድ ገንዘብ ከባንክ ስናወጣ ለበርካታ ሰዎች የሚሆን ስለምናወጣ እነሱም የሻይ ይፈልጋሉ። በተጨማሪም ወደ ትግራይ ብዙ ገንዘብ ይዞ መግባት ከባድ እና መሰናክሎች የበዛበት ነው። እነዚህን በገንዘብ እየሸፈንን ነው የምንሄደው” ብሎ ነበር። ትግራይ ውስጥ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ 616 የባንክ ቅርንጫፎች በመዘጋታቸው ምክንያት ወደ ባንኮቹ ገንዘብ መላክም ሆነ፣ በትግራይ ክልል ከተከፈቱ የሂሳብ ቁጥሮች ገንዘብ ማንቀሳቀስ አይቻልም። አሁን ያለው የገንዘብ ዝውውር ሰንሰለት እጅግ አደገኛ እና የከተማ አስተዳደሮች እና የፀጥታ አካላት ቁጥጥር የሚያደርጉበት ስለሆነ፣ በርካታ ሰዎች ገንዘባቸው በተለያየ መንገድ ጠፍቶ መቅረቱን ይናገራሉ። ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ የቆቦ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ በኩል ሲያልፍ የነበረ ሦስት ሚሊዮን ብር በፀጥታ አካላት ቁጥጥር ላይ መዋሉን አስታውቆ ነበር። በዚህ መሠረት የገንዘብ አዘዋዋሪዎቹ መንገድ ላይ ፍተሻ ሲኖር የያዙት ገንዘብ እንደሚወረስባቸው ይናገራሉ። ሰላም ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር በአፋር ክልል በኩል ያለውን የገንዘብ ዝውውር ተጠቅማ ወደ ትግራይ የላከቸው ስድስት ሺህ ዩሮ፣ ገንዘቡን እንዲያደርስ የተቀበለው ግለሰብ እጅ ላይ መቅረቱን ትናገራለች። ይህ የበርካታ ሰዎች ላይ ደርሷል። “ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ላይ አስተማሪ ነው፤ አንዱ ጓደኛችን በእሱ በኩል የላከው አንድ ሺህ ዩሮ በሦስት ቀን መቀለ ደረሰ። የሚያስከፍለው ኮሚሽን 22 በመቶ ስለነበረ፣ የሚቀንስልን በማግኘታችን ደስ አለን። ‘በርከት አድርጋችሁ የምትልኩ ከሆነ ለእናንተም የምትከፍሉት ይቀንስላችኋል፣ እኔም አልመላለስም’ ስላለን የተለያዩ ሰዎች ጠይቄ 6 ሺህ ዩሮ ላኩለት” ትላለች። ከዚህ ገንዘብ ውስጥ 3 ሺህ ዩሮ የራሷ ሲሆን ቀሪውን የጓደኞቿ ነበር። ገንዘቡ በወቅቱ በነበረው የባንክ ምንዛሪ ከ327 ሺህ ብር በላይ ይገመታል። “ባንኮች ቢሰሩ እንዲህ ላለ ችግር አንዳረግም ነበር፤ ግን ደግሞ ቤተሰቦቻችን በሕይወት እንዲቆዩልን ስለምንፈልግ የጭንቅ አማራጮች እንድንወስድ ተገደናል” ስትል ትናገራለች። ሁለት ዓመት ሊሞላው ጥቂት ቀናት የቀሩት ጦርነት እንዲያበቃ በተለያዩ ወገኖች ከሚደረገው ጥረት ጎን ለጎን በክልሉ ተቋርጠው የሚገኙት ባንክን ጨምሮ ሌሎች መሠረታዊ አገልግሎቶች ወደ ሥራ እንዲመለሱ የሚደረገው ግፊት ይጠቀሳል። በትግራይ ክልል መቀለ ከተማ እንደ ሳተላይት ስልክ ያሉ መሣሪያዎች በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የእርዳታ ተቋማት የሚጠቀሙባቸው መሳሪያዎች ሆነው ቆይተዋል። ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማኅበር እነዚህ የሳተላይት ስልኮችን ተጠቅሞ ነዋሪዎች ከክልሉ ውጪ ከሚገኙ ቤተሰቦቻቸው እና ጓደኞቻቸው ጋር ለማገናኘት ሲሰራ ቆይቷል። እስከ አሁን ማኅበሩ “በጦርነት እና ግጭት የተለያዩ” ሰዎች 115 ሺህ የሚጠጉ የስልክ ጥሪዎች እና መልዕክቶች እንዲያስተላልፉ ማድረጉን ይገልጻል። ወደ ክልሉ እርዳታ የጫነ መኪና ሲያመላልስ የነበረ ለደኅንነቱ ሲል ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈቀደ አሽከርካሪ የፌደራል ኃይሎች በትግራይ ከነበሩበት ጊዜ አንስቶ ሦስተኛው ዙር ጦርነት እስከተነሳበት ወቅት በነበሩ የተለያዩ ግዜያት እርዳታ ሲያደርስ ነበር። “መንገድ ላይ ብዙ ነገሮች አሉ፤ በጦርነቱ ምክንያት የደረሰው ውድመት በየቦታ ይታያል። የተቃጠሉ መኪኖች፣ የወደሙ መኖሪያ ቤቶች በርካታ ናቸው። ጦርነቱ መንገድ ላይ የሚታይ ነው የሚመስለው” ይላል። በክልሉ በተንቀሳቀሰባቸው አካባቢዎች ያጋጠመ ሰፊ ማኅበራዊ ቀውስ መኖሩን የሚናገረው አሽከርካሪው፣ አንዳንድ አሽከርካሪዎች ከአዲስ አበባ ሲነሱ ገንዘብ አድርሱልን ከሚሉ ሰዎች ገንዘብ ተቀብለው እንደሚሄዱ ይገልጻል። “በትግራይ ሁለንታዊ ችግር አለ፤ መንገድ ላይ ‘እባክህን ገንዘብ ወይ መድኃኒት አምጣልን’ ብሎ የሚጠይቅ ሰው ብዙ ነው፤ በተለይ የካንሰር ህሙማን። ከእዚያው ለመግዛትም አቅም የላቸውም፤ ሁሉም ሰው ግን ገንዘብ ይጠይቃል።” የጦርነቱን ዳግም ማገርሸት ተከትሎ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ ወደ ትግራይ ሲያደርሰው የነበረው ሰብአዊ እርዳታን እንዳቆመ ባለፈው የነሐሴ ወር አስታውቆ ነበር። በዚህ ወቅት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የዓለም የምግብ ፕሮግራም ይገልጻል። “እንዲህ አይነት ጦርነት ይኖራል ብዬ አስቤ አላውቅም፤ በዚህ ዘመን እናትህ በሕይወት እያለች ለአንድ ቀንም ቢሆን ድምጿ በስልክ አለመስማት ከባድ ነው። በየቀኑ ሰዎች ሞቱ፣ የአየር ጥቃት ተፈጸመ፣ ህጻናት በረሃብ እየሞቱ ነው የሚሉ ዜናዎች ስሰማ ይጨንቀኛል” የምትለው ሰላም ጦርነቱ የሚቆምበትን ጊዜ በጉጉት እየጠበቀች መሆኗን ትናገራለች። | https://www.bbc.com/amharic/articles/ce5g410x6j0o |
3politics
| በምንጃር እና ፈንታሌ አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰተው ምንድን ነው? | ከአዲስ አበባ ሰሜን ምሥራቅ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው የአማራ እና የኦሮሚያ ክልል በሚዋሰኑበት አካባቢ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት ነዋሪዎችና የፀጥታ ኃይሎች ላይ ጉዳት መድረሱን የአካባቢዎቹ ባለሥልጣናት ገለጹ። የአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እና የኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞኖች በሚዋሰኑበት አካባቢ ጥቃት መፈጸሙንም የሁለቱም ዞኖች አስተዳዳሪዎች ገልጸው በጥቃቱ የፌደራል ፖሊስ አባላት፣ የአካባቢ ሚሊሻዎችና በነዋሪዎች ላይ ሞትና ጉዳት መድረሱን አመልክተዋል። ጥቃቱ በማን እንደተፈጸመ በግልጽ ባይነገርም በሁለቱም አካባቢዎች ያሉ አስተዳዳሪዎች ግን አንዳቸው ከአንዳቸው ተጎራባች ወረዳ የመጡ ታጣቂዎች እንደሆኑ ገልጸዋል። የኦሮሚያ እና የአማራ ክልሎች ይህንን ከስተት በተመለከተ ባወጡት መግለጫ ላይ ጥቃቱን የፈጸሙት "ጽንፈኛ ኃይሎች" መሆናቸውን ገልጸው፣ ይህም በማኅበረሰቦች መካከል ግጭትን ለመፍጠር የታቀደ ነው ብለዋል። ከዚህ በፊትም በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች በይዞታ ይገባኛል ምክንያት አልፎ አልፎ ግጭቶች ያጋጥሙ የነበረ ሲሆን፣ የአሁኑ ጥቃት ግን የፀጥታ ኃይሎች ላይ ያነጣጠረ ነው። የኦሮሚያ እና የአማራ ክልሎች ጥቃት ፈጻሚዎቹን ተከታትሎ በመያዝ ለሕግ ለማቅረብ በጋራ እየሰሩ መሆናቸውን ባወጡት መግለጫ አመልክተዋል። የተከሰተው ምነድን ነው? ማከሰኞ መጋቢት 20/2014 ዓ.ም በተከሰተው ጥቃት የሰሜን ሸዋ የምንጃር ሸንኮራ እና በምሥራቅ ሸዋ የፈንታሌ ኃላፊዎች እንደሚሉት ታጣቂዎቹ ከሌላኛው አካባቢ እንደመጡና ጉዳት እንዳደረሱ ይናገራሉ። በአማራ ክልል ባለው የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ቦሰት እንዳሉት ከኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ በሆነዉ አሞራቤት ቀበሌ አውራ ጎዳና መንደር ላይ ታጣቂዎቹ ከቀኑ ሰባት ሰዓት ጀምሮ ጥቃት መፈጸማቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም ዋና አስተዳዳሪው ከአጎራባቹ የኦሮሚያ ክልል ፈንታሌ ወረዳ መጡ ያሏቸው ጥቃት ፈጻሚዎቹ "የተደራጁ እና የቡድንና በከባድ መሳሪያ የታጠቁ" መሆናቸውን አመልክተው፣ በጥቃቱ የሰው ሕይወት መጥፋቱንና ንብረት መጎዳቱን በወረዳው የማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ አመልክተዋል። በአካባቢው ከዚህ ቀደምም የተለያዩ ጥቃቶች ያጋጥሙ እንደነበር የገለጹት አቶ ታደሰ ከቀናት በፊት የተፈጸመው ጥቃት መነሻ በግልጽ እንደማይታወቅ ገልጸው "ምናልባትም ማንነታቸው ያልታወቁ ፀረ ሰላም ኃይሎች አቅደው አካባቢውን በማውደም ነዋሪዎችን ለማፈናቀል አልመው" የፈጸሙት ሊሆን እንደሚችሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል። በኦሮሚያ ክልል የምሥራቅ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አባቡ ዋቆ በበኩላቸው ከአጎራባቹ የአማራ ክልል አካባቢ የመጣ ታጣቂ ቡድን በዞኑ የፀጥታ ኃይሎች ላይ ጥቃት ፈጽሞ ጉዳት አድርሷል ብለዋል። ነገር ግን በቀጣይ ቀናት ጥቃቱን የፈጸመው አካል ማነው? ከየት የመጣነው? የሚለው ይጠራል ያሉት አቶ አባቡ "የብሔር ግጭት መፍጠር የሚፈልጉ በኦሮሚያ እና አማራ ድንበር ላይ የሚንቀሳቀስ የተደራጀ ጽንፈኛ ኃይል ሊሆን ይችላል" የሚል ግምት እንዳላቸው ተናግረዋል። አስተዳዳሪው ጥቃት ፈጻሚው ቡድን ማንነቱ የማይታወቅ መሆኑን አመልክተው፣ ታጥቆ የሚንቀሳቀስ እንደሆነና ባለፈው ማክሰኞ በአካባቢው የሚሊሻ አባላት ላይ በፈጸመው ጥቃትም ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል። በጥቃቱ ጉዳት ደርሶባቸዋል ያሏቸው የፀጥታ አባላት ለሥራ ተሰማርተው በቡድን እየተመለሱ ሳለ በተፈጸመባቸው ድንገተኛ ጥቃት ከመካከላቸው 18ቱ መገደላቸውንና 15 ደግሞ መቁሰላቸውን ረቡዕ ከሰዓት በኋላ ገልጸዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የምሥራቅ ሸዋ ፖሊስ አዛዥ ኤቢሳ አሰፋ ለክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ኦቢኤን እንደተናገሩት በጥቃቱ የተገደሉት 26 ሰዎች ናቸው ብለዋል። የፖሊስ አዛዡ ጥቃቱ ያደረሰው ቡድንን ማንነት ያልገለጹ ሲሆን፣ ነገር ግን "የተደራጀ እና ዘመናዊ ጦር መሳሪያ የታጠቀ ነው" ሲሉ ከተፈጸመው ጥቃት ተነስተው ግምታቸውን አስቀምጠዋል። የኦሮሚያ ክልል ጥቃቱን ተከትሎ የኦሮሚያ ክልል መስተዳደር ባወጣው መግለጫ ጥቃቱን የፈጸሙት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ በሚገኘው ምንጃር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች መሆናቸውን አመልክቷል። ክልሉ እንዳለው በምሥራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ ቆርኬ/አውራ ጎዳና በሚባለው ልዩ ሥፍራ "በምንጃር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ ኃይሎች በጉዞ ላይ በነበሩት የሕዝብ ሚሊሻና የፌዴራል ፖሊስ ላይ" ጥቃት ማድረሳቸውን አስታውቆ ሐዘኑን ገልጿል። ጥቃቱ "የአማራና የኦሮሞ ሕዝቦች ዘላቂ አብሮነትና ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞን ለማደናቀፍ በጽንፈኛ ኃይሎች የተወጠነ የጥፋት ዕቅድ አካል" ነው በማለት፣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ጥቃት ፈጻሚዎቹን ለሕግ ለማቅረብ እንደሚሰራ የኦሮሚያ ክልል አመልክቷል። ጨምሮም የኦሮሚያ ክልል ከአማራ ክልል ጋር በመሆን ጥቃቱ በደረሰበት ቦታ ላይ ተገቢውን ክትትል በማድረግ ወንጀለኞችን ህግ ፊት ለማቅረብ በጋራ እየሠራ መሆኑን አመልክቷል። የአማራ ክልል ይህንን ጥቃት ተከትሎ የአማራ ክልል ባወጣው መግለጫ ተመሳሳይ ጥቃቶች በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ውስጥ መፈጸማቸውን አስታውሶ፣ የክልሉ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በሰውና በንብረት ላይ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ሐዘን ገልጿል። ጨምሮም "ተስፈኛ ጽንፈኞችና አሸባሪዎች" ያለቸው ኃይሎች በአማራ ክልል ሕዝብ እና በአጎራባች ክልል ሕዝብ መካከል ግጭት ለመፍጠር እንዲሁም የክልሉን ሕዝብ "ማኅበራዊ እረፍት ለመንሳት በክልላችን አንዳንድ አካባቢዎች ግጭት ለማጫር ተንቀሳቅሰዋል፤ እየተንቀሳቀሱም ይገኛሉ" ይገኛሉ ብሏል። መግለጫው "ከጽንፈኛና ፀረ ሰላም ኃይሎች ጋር ቀጥተኛም ሆነ ተዘዋዋሪ የጥፋት ትስስር በመፍጠር የአማራ ክልልን የቀውስ ሜዳ ለማድረግ" የጠላት እቅድ በመፈጸምም ሆነ በማስፈጸም ተግባር ላይ ተሳታፊ ናቸው ያላቸው አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አስጠንቅቋል። የክልሉን ሕዝብ ሰላምና ደኅንነት አደጋ ላይ ለመጣል በግልፅም ሆነ በህቡዕ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ከዚህ ድርጊታቸው የማይታቀቡ ከሆነም በማንኛውም አይነት ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጿል። የመንገድ መዘጋት ጥቃቱን ተከትሎ መሃል ኢትዮጵያን ከጂቡቲ ወደብ ጋር በሚያገናኘው መስመር ላይ የሚገኘው ከመተሐራ ወደ ወለንጪቲ ከተማ የሚወስደው ዋነኛ መንገድ ለረጅም ሰዓታት ተዘግቶ እንደነበር የአካባቢው ኃላፊዎች ተናግረዋል። በዚህም ሳቢያ በሁለቱም በኩል የሚያልፉ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች ባሉበት ለመቆም ተገደው የነበረ ሲሆን የመከላከያ ሠራዊት እና የፌዴራል ፖሊስ አባላት ተሰማርተው አካባቢውን ካረጋጉ በኋላ መንገዱ ለተሽከርካሪ ክፍት ሆኗል። | በምንጃር እና ፈንታሌ አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰተው ምንድን ነው? ከአዲስ አበባ ሰሜን ምሥራቅ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው የአማራ እና የኦሮሚያ ክልል በሚዋሰኑበት አካባቢ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት ነዋሪዎችና የፀጥታ ኃይሎች ላይ ጉዳት መድረሱን የአካባቢዎቹ ባለሥልጣናት ገለጹ። የአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እና የኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞኖች በሚዋሰኑበት አካባቢ ጥቃት መፈጸሙንም የሁለቱም ዞኖች አስተዳዳሪዎች ገልጸው በጥቃቱ የፌደራል ፖሊስ አባላት፣ የአካባቢ ሚሊሻዎችና በነዋሪዎች ላይ ሞትና ጉዳት መድረሱን አመልክተዋል። ጥቃቱ በማን እንደተፈጸመ በግልጽ ባይነገርም በሁለቱም አካባቢዎች ያሉ አስተዳዳሪዎች ግን አንዳቸው ከአንዳቸው ተጎራባች ወረዳ የመጡ ታጣቂዎች እንደሆኑ ገልጸዋል። የኦሮሚያ እና የአማራ ክልሎች ይህንን ከስተት በተመለከተ ባወጡት መግለጫ ላይ ጥቃቱን የፈጸሙት "ጽንፈኛ ኃይሎች" መሆናቸውን ገልጸው፣ ይህም በማኅበረሰቦች መካከል ግጭትን ለመፍጠር የታቀደ ነው ብለዋል። ከዚህ በፊትም በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች በይዞታ ይገባኛል ምክንያት አልፎ አልፎ ግጭቶች ያጋጥሙ የነበረ ሲሆን፣ የአሁኑ ጥቃት ግን የፀጥታ ኃይሎች ላይ ያነጣጠረ ነው። የኦሮሚያ እና የአማራ ክልሎች ጥቃት ፈጻሚዎቹን ተከታትሎ በመያዝ ለሕግ ለማቅረብ በጋራ እየሰሩ መሆናቸውን ባወጡት መግለጫ አመልክተዋል። የተከሰተው ምነድን ነው? ማከሰኞ መጋቢት 20/2014 ዓ.ም በተከሰተው ጥቃት የሰሜን ሸዋ የምንጃር ሸንኮራ እና በምሥራቅ ሸዋ የፈንታሌ ኃላፊዎች እንደሚሉት ታጣቂዎቹ ከሌላኛው አካባቢ እንደመጡና ጉዳት እንዳደረሱ ይናገራሉ። በአማራ ክልል ባለው የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ቦሰት እንዳሉት ከኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ በሆነዉ አሞራቤት ቀበሌ አውራ ጎዳና መንደር ላይ ታጣቂዎቹ ከቀኑ ሰባት ሰዓት ጀምሮ ጥቃት መፈጸማቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም ዋና አስተዳዳሪው ከአጎራባቹ የኦሮሚያ ክልል ፈንታሌ ወረዳ መጡ ያሏቸው ጥቃት ፈጻሚዎቹ "የተደራጁ እና የቡድንና በከባድ መሳሪያ የታጠቁ" መሆናቸውን አመልክተው፣ በጥቃቱ የሰው ሕይወት መጥፋቱንና ንብረት መጎዳቱን በወረዳው የማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ አመልክተዋል። በአካባቢው ከዚህ ቀደምም የተለያዩ ጥቃቶች ያጋጥሙ እንደነበር የገለጹት አቶ ታደሰ ከቀናት በፊት የተፈጸመው ጥቃት መነሻ በግልጽ እንደማይታወቅ ገልጸው "ምናልባትም ማንነታቸው ያልታወቁ ፀረ ሰላም ኃይሎች አቅደው አካባቢውን በማውደም ነዋሪዎችን ለማፈናቀል አልመው" የፈጸሙት ሊሆን እንደሚችሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል። በኦሮሚያ ክልል የምሥራቅ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አባቡ ዋቆ በበኩላቸው ከአጎራባቹ የአማራ ክልል አካባቢ የመጣ ታጣቂ ቡድን በዞኑ የፀጥታ ኃይሎች ላይ ጥቃት ፈጽሞ ጉዳት አድርሷል ብለዋል። ነገር ግን በቀጣይ ቀናት ጥቃቱን የፈጸመው አካል ማነው? ከየት የመጣነው? የሚለው ይጠራል ያሉት አቶ አባቡ "የብሔር ግጭት መፍጠር የሚፈልጉ በኦሮሚያ እና አማራ ድንበር ላይ የሚንቀሳቀስ የተደራጀ ጽንፈኛ ኃይል ሊሆን ይችላል" የሚል ግምት እንዳላቸው ተናግረዋል። አስተዳዳሪው ጥቃት ፈጻሚው ቡድን ማንነቱ የማይታወቅ መሆኑን አመልክተው፣ ታጥቆ የሚንቀሳቀስ እንደሆነና ባለፈው ማክሰኞ በአካባቢው የሚሊሻ አባላት ላይ በፈጸመው ጥቃትም ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል። በጥቃቱ ጉዳት ደርሶባቸዋል ያሏቸው የፀጥታ አባላት ለሥራ ተሰማርተው በቡድን እየተመለሱ ሳለ በተፈጸመባቸው ድንገተኛ ጥቃት ከመካከላቸው 18ቱ መገደላቸውንና 15 ደግሞ መቁሰላቸውን ረቡዕ ከሰዓት በኋላ ገልጸዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የምሥራቅ ሸዋ ፖሊስ አዛዥ ኤቢሳ አሰፋ ለክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ኦቢኤን እንደተናገሩት በጥቃቱ የተገደሉት 26 ሰዎች ናቸው ብለዋል። የፖሊስ አዛዡ ጥቃቱ ያደረሰው ቡድንን ማንነት ያልገለጹ ሲሆን፣ ነገር ግን "የተደራጀ እና ዘመናዊ ጦር መሳሪያ የታጠቀ ነው" ሲሉ ከተፈጸመው ጥቃት ተነስተው ግምታቸውን አስቀምጠዋል። የኦሮሚያ ክልል ጥቃቱን ተከትሎ የኦሮሚያ ክልል መስተዳደር ባወጣው መግለጫ ጥቃቱን የፈጸሙት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ በሚገኘው ምንጃር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች መሆናቸውን አመልክቷል። ክልሉ እንዳለው በምሥራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ ቆርኬ/አውራ ጎዳና በሚባለው ልዩ ሥፍራ "በምንጃር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ ኃይሎች በጉዞ ላይ በነበሩት የሕዝብ ሚሊሻና የፌዴራል ፖሊስ ላይ" ጥቃት ማድረሳቸውን አስታውቆ ሐዘኑን ገልጿል። ጥቃቱ "የአማራና የኦሮሞ ሕዝቦች ዘላቂ አብሮነትና ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞን ለማደናቀፍ በጽንፈኛ ኃይሎች የተወጠነ የጥፋት ዕቅድ አካል" ነው በማለት፣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ጥቃት ፈጻሚዎቹን ለሕግ ለማቅረብ እንደሚሰራ የኦሮሚያ ክልል አመልክቷል። ጨምሮም የኦሮሚያ ክልል ከአማራ ክልል ጋር በመሆን ጥቃቱ በደረሰበት ቦታ ላይ ተገቢውን ክትትል በማድረግ ወንጀለኞችን ህግ ፊት ለማቅረብ በጋራ እየሠራ መሆኑን አመልክቷል። የአማራ ክልል ይህንን ጥቃት ተከትሎ የአማራ ክልል ባወጣው መግለጫ ተመሳሳይ ጥቃቶች በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ውስጥ መፈጸማቸውን አስታውሶ፣ የክልሉ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በሰውና በንብረት ላይ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ሐዘን ገልጿል። ጨምሮም "ተስፈኛ ጽንፈኞችና አሸባሪዎች" ያለቸው ኃይሎች በአማራ ክልል ሕዝብ እና በአጎራባች ክልል ሕዝብ መካከል ግጭት ለመፍጠር እንዲሁም የክልሉን ሕዝብ "ማኅበራዊ እረፍት ለመንሳት በክልላችን አንዳንድ አካባቢዎች ግጭት ለማጫር ተንቀሳቅሰዋል፤ እየተንቀሳቀሱም ይገኛሉ" ይገኛሉ ብሏል። መግለጫው "ከጽንፈኛና ፀረ ሰላም ኃይሎች ጋር ቀጥተኛም ሆነ ተዘዋዋሪ የጥፋት ትስስር በመፍጠር የአማራ ክልልን የቀውስ ሜዳ ለማድረግ" የጠላት እቅድ በመፈጸምም ሆነ በማስፈጸም ተግባር ላይ ተሳታፊ ናቸው ያላቸው አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አስጠንቅቋል። የክልሉን ሕዝብ ሰላምና ደኅንነት አደጋ ላይ ለመጣል በግልፅም ሆነ በህቡዕ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ከዚህ ድርጊታቸው የማይታቀቡ ከሆነም በማንኛውም አይነት ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጿል። የመንገድ መዘጋት ጥቃቱን ተከትሎ መሃል ኢትዮጵያን ከጂቡቲ ወደብ ጋር በሚያገናኘው መስመር ላይ የሚገኘው ከመተሐራ ወደ ወለንጪቲ ከተማ የሚወስደው ዋነኛ መንገድ ለረጅም ሰዓታት ተዘግቶ እንደነበር የአካባቢው ኃላፊዎች ተናግረዋል። በዚህም ሳቢያ በሁለቱም በኩል የሚያልፉ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች ባሉበት ለመቆም ተገደው የነበረ ሲሆን የመከላከያ ሠራዊት እና የፌዴራል ፖሊስ አባላት ተሰማርተው አካባቢውን ካረጋጉ በኋላ መንገዱ ለተሽከርካሪ ክፍት ሆኗል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60930010 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ ድመትና ውሾች ኮቪድ እንደሚይዛቸው ተደረሰበት | የኮቪድ ቫይረስ በለማዳ የቤት ውስጥ እንሰሳት በተለይም በውሾችና በድመቶች ላይ በስፋት እንደሚገኝ አንድ ጥናት አመለከተ። ጥናቱ እዚህ ድምዳሜ ላይ የደረሰው 196 የኮቪድ ተህዋሲ የጎበኘው ቤተሰብ ላይ ባደረገው ምርምር ነው። በ196 አባወራዎች ላይ በተደረገው ይህ ምርምር 310 ድመቶችና ውሾች የተካተቱበት ነው። ከነዚህ ውስጥ ስድስት ድመቶችና ሰባት ውሾች ተህዋሲውን ተሸክመው ተገኝተዋል። 54ቱ ደግሞ ከዚህ ቀደም ተህዋሲው ይዞ እንደለቀቃቸው የሚያሳይ የበሽታ ተከላካይ ቅንጣት ተገኝቶባቸዋል። ዶ/ር ኤልስ ብሮንስ በኡትሬች ዩኒቨርስቲ ተመራማሪና መምህር ናቸው። እሳቸው እንደሚሉት ኮቪድ ያለባቸው ሰዎች ከድመትና ውሾቻቸው ጋር ምንም ዓይነት ንክኪ ባያደርጉ ይመረጣል። "እዚህ ጋ ዋናው ነጥብ የእንሰሳቱ ጤና አይደለም" ይላሉ ዶ/ር ኤልስ። ዋናው ነጥብ የቤት እንሰሳቱ "ቫይረሱን ተሸካሚና አዘዋዋሪ ከመሆናቸው ላይ ነው።" አጥኚዎቹ ከቤት እንሰሳቱ ወደ ሰው ቫይረሱ ስለመተላለፉ በእርግጥ ያሉት ነገር ባይኖርም በውሻና በድመት ላይ ግን ተህዋሲው ጎልቶ የማይታይና እነሱም ቢሆን ምንም ዓይነት የበሽታ ምልክቶችን እንደማያሳዩ ደርሰውበታል። ካሳዩም እጅግ ዝቅተኛ የሆኑ ምልክቶቹን ብቻ ነው የሚሆነው። በጥናቱ የተሳተፉ ተመራማሪዎች በርካታ የቤት እንሰሳት ቫይረሱን ያገኙት ከሰው ልጆች እንደሆነና ነገር ግን በተቃራኒው እንዳልሆነ ገምተዋል። የቤት እንሰሳቱ ባለቤቶች ተህዋሲውን ከድመትና ከውሻ የማግኘታቸው ዕድል ዜሮ ነው ልንል አንችልም፤ ነገር ግን ይህ የመሆን ዕድሉ አነስተኛ ነው ብለዋል የእንሰሳት ሐኪምና የማይክሮባዮሎጂካል ዳያግኖስቲክ ሴንተር ባልደረባ ዶ/ር ብራውንስ። በሩሲያ የእንሰሳት ሐኪሞች ለቤት እንሰሳት የተህዋሲውን ክትባት መውጋት መጀመራቸው መዘገቡ ይታወሳል። ዶ/ር ብራውን ግን ይህን ማድረጉ ጥቅሙ አልታይ ብሏቸዋል። "ለጊዜው እንሰሳቱ ተህዋሲውን ወደ ሰው ስለማስተላለፋቸው አስተማማኝ የሆነ ሳይንሳዊ መረጃ አላገኘንም" ይላሉ። | ኮሮናቫይረስ፡ ድመትና ውሾች ኮቪድ እንደሚይዛቸው ተደረሰበት የኮቪድ ቫይረስ በለማዳ የቤት ውስጥ እንሰሳት በተለይም በውሾችና በድመቶች ላይ በስፋት እንደሚገኝ አንድ ጥናት አመለከተ። ጥናቱ እዚህ ድምዳሜ ላይ የደረሰው 196 የኮቪድ ተህዋሲ የጎበኘው ቤተሰብ ላይ ባደረገው ምርምር ነው። በ196 አባወራዎች ላይ በተደረገው ይህ ምርምር 310 ድመቶችና ውሾች የተካተቱበት ነው። ከነዚህ ውስጥ ስድስት ድመቶችና ሰባት ውሾች ተህዋሲውን ተሸክመው ተገኝተዋል። 54ቱ ደግሞ ከዚህ ቀደም ተህዋሲው ይዞ እንደለቀቃቸው የሚያሳይ የበሽታ ተከላካይ ቅንጣት ተገኝቶባቸዋል። ዶ/ር ኤልስ ብሮንስ በኡትሬች ዩኒቨርስቲ ተመራማሪና መምህር ናቸው። እሳቸው እንደሚሉት ኮቪድ ያለባቸው ሰዎች ከድመትና ውሾቻቸው ጋር ምንም ዓይነት ንክኪ ባያደርጉ ይመረጣል። "እዚህ ጋ ዋናው ነጥብ የእንሰሳቱ ጤና አይደለም" ይላሉ ዶ/ር ኤልስ። ዋናው ነጥብ የቤት እንሰሳቱ "ቫይረሱን ተሸካሚና አዘዋዋሪ ከመሆናቸው ላይ ነው።" አጥኚዎቹ ከቤት እንሰሳቱ ወደ ሰው ቫይረሱ ስለመተላለፉ በእርግጥ ያሉት ነገር ባይኖርም በውሻና በድመት ላይ ግን ተህዋሲው ጎልቶ የማይታይና እነሱም ቢሆን ምንም ዓይነት የበሽታ ምልክቶችን እንደማያሳዩ ደርሰውበታል። ካሳዩም እጅግ ዝቅተኛ የሆኑ ምልክቶቹን ብቻ ነው የሚሆነው። በጥናቱ የተሳተፉ ተመራማሪዎች በርካታ የቤት እንሰሳት ቫይረሱን ያገኙት ከሰው ልጆች እንደሆነና ነገር ግን በተቃራኒው እንዳልሆነ ገምተዋል። የቤት እንሰሳቱ ባለቤቶች ተህዋሲውን ከድመትና ከውሻ የማግኘታቸው ዕድል ዜሮ ነው ልንል አንችልም፤ ነገር ግን ይህ የመሆን ዕድሉ አነስተኛ ነው ብለዋል የእንሰሳት ሐኪምና የማይክሮባዮሎጂካል ዳያግኖስቲክ ሴንተር ባልደረባ ዶ/ር ብራውንስ። በሩሲያ የእንሰሳት ሐኪሞች ለቤት እንሰሳት የተህዋሲውን ክትባት መውጋት መጀመራቸው መዘገቡ ይታወሳል። ዶ/ር ብራውን ግን ይህን ማድረጉ ጥቅሙ አልታይ ብሏቸዋል። "ለጊዜው እንሰሳቱ ተህዋሲውን ወደ ሰው ስለማስተላለፋቸው አስተማማኝ የሆነ ሳይንሳዊ መረጃ አላገኘንም" ይላሉ። | https://www.bbc.com/amharic/57662274 |
0business
| ጠ/ሚንስትር ዐብይ አህመድ ግንባታውን ከጎበኙት የላሙ ወደብ ምን ይጠበቃል? | ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ እና የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የላሙ ወደብ ግንባታን ጎበኙ። መሪዎቹ በተጨማሪም ዛሬ ሐሙስ በሞምባሳ የተገኝተው ሊኮኒ የእግረኞች መሻገሪያ ድልድይን በይፋ ይመርቃሉ። 1.2 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው የሞምባሳው ሊኮኒ ድልድይ ለቀጠናው የመጀመሪያው ሲሆን፤ ድልድዩ በ1.9 ቢሊዮን የኬንያ ሽልንግ ወጪ የተገነባ ነው። ሁለቱ መሪዎች ትላንት በመርሳቤት ግዛት የተገነባውን የድንበር መተላለፊያ መርቀዋል። ከዚያም ወደ ላሙ ግዛት አቅንተው የወደብ ግንባታ ሂደቱን ቃኝተዋል። በጉብኝታቸው ወቅት፤ ኢትዮጵያ እና ኬንያ በድንበር ተሻጋሪ የመሠረተ ልማት ግንባታ ዘርፍ እንደሚተባበሩ መሪዎቹ ተናግረዋል። በግንባታ ላይ የሚገኘውን ባለ 32 ክፍል የላሙ ወደብ በጎበኙበት ወቅት፤ ከሞምባሳ በናይሮቢ አድርጎ አዲስ አበባ የሚገባውን አውራ ጎዳና ለማፋጠን ተስማምተዋል። ይህ አውራ ጎዳና የቀጠናውን ንግድ ያሳልጣል ተብሎ ይጠበቃል። ፕሬዝደንት ኡሁሩ "የሞምባሳ-ናይሮቢ-አዲስ አበባ አውራ ጎዳና አካል የሆነውን የላሙ ወደብ ግንባታ ቃኝተናል። በዚህ የላፕሴት ፕሮጀክት አማካይነት ኢትዮጵያ አስተማማኝ እና ቀጥተኛ የሆነ መንገድ ታገኛለች። ሞያሌን፣ ኢሲኦሎን እና የላሙ ወደብን የሚያገናኝ ነው" ብለዋል። ላፕሴት (LAPSSET) የተባለው ፕሮጀክት የላሙ ወደብን፣ ደቡብ ሱዳንን እና የኢትዮጵያ የትራንስፖርት መተላለፊያን የሚወክል ነው። ይህ ፕሮጀክት የኬንያ፣ የኢትዮጵያ እና የደቡብ ሱዳን ነው። ፕሮጅክቱ ሦስቱን አገራት እርስ በእርስ የሚያስተሳስር ሲሆን፤ ከሌሎች የምሥራቅ አፍሪካ አገራት ጋርም እንደሚያገናኛቸው ተገልጿል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የላሙ ወደብ ለኢትዮጵያ እና ለደቡብ ሱዳን እንደሚጠቅም ተናግረዋል። የሁለቱ አገሮች ትብብር መላው አፍሪካን ለማስተሳሰር የሚደረገው ጥረት አካል እንደሆነም ገልጸዋል። "የላሙ ወደብ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለደቡብ ሱዳንም ይጠቅማል። በቀጠናችን የምጣኔ ሀብት ትስስር ለመፍጠርና የሕዝባችንን ሕይወት ለመለወጥ ያለን ራዕይ እውነት እንዲሆን ያግዛል" ብለዋል። ኢትዮጵያ ወደብ አልባ መሆኗና የአውራ ጎዳና መሠረተ ልማት ውስንነት አገሪቱ ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ ጠቅላይ ሚንስትሩ ተናግረዋል። "በ21ኛው ክፍለ ዘመን ያለ መሠረተ ልማት እና የምጣኔ ሀብት ትስስር መኖር አይቻልም። ምሥራቅ አፍሪካን መቀየር የምንችለው ወንድሜ [ኡሁሩ ኬንያታ] ኬንያ ውስጥ እንዳደረጉት ሁሉ እያንዳንዱ መንግሥት ጊዜና አቅሙን መሠረተ ልማት ላይ ለማፍሰስ ቁርጠኛ ሲሆን ነው" ብለዋል። ፕሬዝዳንት ኡሁሩ በበኩላቸው፤ ኬንያ እና ኢትዮጵያ የትራንስፖርት ትስስር ለመፍጠር ከተስማሙ በኋላ የላሙ ወደብ ግንባታ በአመርቂ ሁኔታ እየተገነባ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የመጀመሪያው ክፍል እንደተጠናቀቀና የሁለት ተጨማሪ ክፍሎች ግንባታ 86 በመቶ ማለቁን ተናግረዋል። "በቀጣዩ ዓመት ጥቅምት ላይ እርስዎን እና የደቡብ ሱዳኑን ፕሬዝዳንት ጋብዤ የወደቡን ሦስት ክፍሎች እንደምናስጀምር ተስፋ አደርጋለሁ" ሲሉ ኡሁሩ፤ ለጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ተናግረዋል። ላሙ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ወደብ ሆኖ የምሥራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የንግድ መዳረሻ እንደሚሆንም ኡሁሩ አመልክተዋል። ኢትዮጵያ እና ኬንያ በምን መንገድ በቀጠናው የትራንስፖርት ቢዝነስ እንደሚጣመሩ የሚጠቁም ዝርዝር እቅድ ይፋ እንደሚያደርጉም አክለዋል። ይህም ምሥራቅ አፍሪካን በቀጠናው እንዲሁም በአፍሪካም የሎጅስቲክስ ዘርፍ ግንባር ቀደም የሚያደርግ ነው ብለዋል። ፕሬዘዳንት ኡሁሩ አያይዘውም የላሙ-ዊቱ-ጋሪሰን አውራ ጎዳና 80 በመቶ ተጠናቋል ብለዋል። ይህ አውራ ጎዳና በጋሪሳ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት አመቺ መሆኑ ተጠቁሟል። ከዚህ ቀደም የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን የጎበኙት ፕሬዝዳንቱ፤ ሁለቱ አገሮች ልዩ የምጣኔ ሀብት ማዕከል ሞያሌ ውስጥ ለመገንባት መወሰናቸውን ተናግረዋል። ይህም ድንበር ተሻጋሪ ንግድን ከማሳደጉ ባሻገር የአካባቢውን ነዋሪዎች እንደሚጠቅም ተገልጿል። የላሙ ወደብ ይህ ወደብ የሚገነባው በኬንያዋ ላሙ ግዛት ውስጥ ሲሆን 32 መርከቦች በተመሳሳይ ሰዓት መልህቃቸውን እንዲጥሉ የሚያስችል ነው። የዚህ ወደብ ግንባታ አጠቃላይ ወጪ ወደ 5 ቢሊዮን ዶላር ይገመታል። የመጀመሪያዎቹ ሦስት መርከብ ማረፊያዎች ግንባታ ወጪ በኬንያ መንግሥት የሚሸፍን ይሆናል ተብሏል። የመጀመሪያው መርከብ ማቆሚያ ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን ሁለተኛው እና ሦስተኛዎቹ የመርከብ ማቆሚያዎች ግንባታ ደግሞ በቀጣይ ወራት ይጠናቀቃሉ ተብሎ ይገመታል። ይህንንም ተከትሎ የላሙ ወደብን ወደ ሥራ ለማስገባ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል። | ጠ/ሚንስትር ዐብይ አህመድ ግንባታውን ከጎበኙት የላሙ ወደብ ምን ይጠበቃል? ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ እና የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የላሙ ወደብ ግንባታን ጎበኙ። መሪዎቹ በተጨማሪም ዛሬ ሐሙስ በሞምባሳ የተገኝተው ሊኮኒ የእግረኞች መሻገሪያ ድልድይን በይፋ ይመርቃሉ። 1.2 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው የሞምባሳው ሊኮኒ ድልድይ ለቀጠናው የመጀመሪያው ሲሆን፤ ድልድዩ በ1.9 ቢሊዮን የኬንያ ሽልንግ ወጪ የተገነባ ነው። ሁለቱ መሪዎች ትላንት በመርሳቤት ግዛት የተገነባውን የድንበር መተላለፊያ መርቀዋል። ከዚያም ወደ ላሙ ግዛት አቅንተው የወደብ ግንባታ ሂደቱን ቃኝተዋል። በጉብኝታቸው ወቅት፤ ኢትዮጵያ እና ኬንያ በድንበር ተሻጋሪ የመሠረተ ልማት ግንባታ ዘርፍ እንደሚተባበሩ መሪዎቹ ተናግረዋል። በግንባታ ላይ የሚገኘውን ባለ 32 ክፍል የላሙ ወደብ በጎበኙበት ወቅት፤ ከሞምባሳ በናይሮቢ አድርጎ አዲስ አበባ የሚገባውን አውራ ጎዳና ለማፋጠን ተስማምተዋል። ይህ አውራ ጎዳና የቀጠናውን ንግድ ያሳልጣል ተብሎ ይጠበቃል። ፕሬዝደንት ኡሁሩ "የሞምባሳ-ናይሮቢ-አዲስ አበባ አውራ ጎዳና አካል የሆነውን የላሙ ወደብ ግንባታ ቃኝተናል። በዚህ የላፕሴት ፕሮጀክት አማካይነት ኢትዮጵያ አስተማማኝ እና ቀጥተኛ የሆነ መንገድ ታገኛለች። ሞያሌን፣ ኢሲኦሎን እና የላሙ ወደብን የሚያገናኝ ነው" ብለዋል። ላፕሴት (LAPSSET) የተባለው ፕሮጀክት የላሙ ወደብን፣ ደቡብ ሱዳንን እና የኢትዮጵያ የትራንስፖርት መተላለፊያን የሚወክል ነው። ይህ ፕሮጀክት የኬንያ፣ የኢትዮጵያ እና የደቡብ ሱዳን ነው። ፕሮጅክቱ ሦስቱን አገራት እርስ በእርስ የሚያስተሳስር ሲሆን፤ ከሌሎች የምሥራቅ አፍሪካ አገራት ጋርም እንደሚያገናኛቸው ተገልጿል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የላሙ ወደብ ለኢትዮጵያ እና ለደቡብ ሱዳን እንደሚጠቅም ተናግረዋል። የሁለቱ አገሮች ትብብር መላው አፍሪካን ለማስተሳሰር የሚደረገው ጥረት አካል እንደሆነም ገልጸዋል። "የላሙ ወደብ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለደቡብ ሱዳንም ይጠቅማል። በቀጠናችን የምጣኔ ሀብት ትስስር ለመፍጠርና የሕዝባችንን ሕይወት ለመለወጥ ያለን ራዕይ እውነት እንዲሆን ያግዛል" ብለዋል። ኢትዮጵያ ወደብ አልባ መሆኗና የአውራ ጎዳና መሠረተ ልማት ውስንነት አገሪቱ ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ ጠቅላይ ሚንስትሩ ተናግረዋል። "በ21ኛው ክፍለ ዘመን ያለ መሠረተ ልማት እና የምጣኔ ሀብት ትስስር መኖር አይቻልም። ምሥራቅ አፍሪካን መቀየር የምንችለው ወንድሜ [ኡሁሩ ኬንያታ] ኬንያ ውስጥ እንዳደረጉት ሁሉ እያንዳንዱ መንግሥት ጊዜና አቅሙን መሠረተ ልማት ላይ ለማፍሰስ ቁርጠኛ ሲሆን ነው" ብለዋል። ፕሬዝዳንት ኡሁሩ በበኩላቸው፤ ኬንያ እና ኢትዮጵያ የትራንስፖርት ትስስር ለመፍጠር ከተስማሙ በኋላ የላሙ ወደብ ግንባታ በአመርቂ ሁኔታ እየተገነባ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የመጀመሪያው ክፍል እንደተጠናቀቀና የሁለት ተጨማሪ ክፍሎች ግንባታ 86 በመቶ ማለቁን ተናግረዋል። "በቀጣዩ ዓመት ጥቅምት ላይ እርስዎን እና የደቡብ ሱዳኑን ፕሬዝዳንት ጋብዤ የወደቡን ሦስት ክፍሎች እንደምናስጀምር ተስፋ አደርጋለሁ" ሲሉ ኡሁሩ፤ ለጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ተናግረዋል። ላሙ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ወደብ ሆኖ የምሥራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የንግድ መዳረሻ እንደሚሆንም ኡሁሩ አመልክተዋል። ኢትዮጵያ እና ኬንያ በምን መንገድ በቀጠናው የትራንስፖርት ቢዝነስ እንደሚጣመሩ የሚጠቁም ዝርዝር እቅድ ይፋ እንደሚያደርጉም አክለዋል። ይህም ምሥራቅ አፍሪካን በቀጠናው እንዲሁም በአፍሪካም የሎጅስቲክስ ዘርፍ ግንባር ቀደም የሚያደርግ ነው ብለዋል። ፕሬዘዳንት ኡሁሩ አያይዘውም የላሙ-ዊቱ-ጋሪሰን አውራ ጎዳና 80 በመቶ ተጠናቋል ብለዋል። ይህ አውራ ጎዳና በጋሪሳ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት አመቺ መሆኑ ተጠቁሟል። ከዚህ ቀደም የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን የጎበኙት ፕሬዝዳንቱ፤ ሁለቱ አገሮች ልዩ የምጣኔ ሀብት ማዕከል ሞያሌ ውስጥ ለመገንባት መወሰናቸውን ተናግረዋል። ይህም ድንበር ተሻጋሪ ንግድን ከማሳደጉ ባሻገር የአካባቢውን ነዋሪዎች እንደሚጠቅም ተገልጿል። የላሙ ወደብ ይህ ወደብ የሚገነባው በኬንያዋ ላሙ ግዛት ውስጥ ሲሆን 32 መርከቦች በተመሳሳይ ሰዓት መልህቃቸውን እንዲጥሉ የሚያስችል ነው። የዚህ ወደብ ግንባታ አጠቃላይ ወጪ ወደ 5 ቢሊዮን ዶላር ይገመታል። የመጀመሪያዎቹ ሦስት መርከብ ማረፊያዎች ግንባታ ወጪ በኬንያ መንግሥት የሚሸፍን ይሆናል ተብሏል። የመጀመሪያው መርከብ ማቆሚያ ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን ሁለተኛው እና ሦስተኛዎቹ የመርከብ ማቆሚያዎች ግንባታ ደግሞ በቀጣይ ወራት ይጠናቀቃሉ ተብሎ ይገመታል። ይህንንም ተከትሎ የላሙ ወደብን ወደ ሥራ ለማስገባ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-55255792 |
5sports
| 'ሴቶች ብዙ ያወራሉ' ያሉት የቶክዮ ኦሊምፒክ ኃላፊ ሥራ ሊለቁ ነው | የቶክዮ ኦሊምፒክስ አዘጋጅ ኮሚቴ ኃላፊ የሆኑት ግለሰብ ሴቶችን አስመልክተው የሰጡትን ፆተኛ አስተያየት ተከትሎ በደረሰባቸው ከፍተኛ ወቀሳ ሥልጣናቸውን በገዛ ፍቃዳቸው ሊለቁ ነው። የኮሚቴው ኃላፊው የ83 ዓመቱ ዮሺሮ ሞሪ ሴቶች በስብሰባዎች ላይ "በጣም ብዙ ያወራሉ፤ ሴት የቦርድ ኃላፊዎች ያሉበት ስብሰባ በጣም ብዙ ጊዜ ይወስዳል" ሲሉ ተናግረዋል ተብሏል። ዮሺሮ ሞሪ ለሰጡት አስተያየት ይቅርታ ጠይቀው በሰጠሁት አስተያየት ግን ስልጣኔን አለቅም ብለው ነበር። ይሁን እንጂ ሞሪ ጫናው በርትቶባቸው ሥልጣናቸውን ሊለቁ ከጫፍ ተቃርበዋል። . ጭንቅላቱን ከአዞ አፍ ፈልቅቆ በማውጣት ራሱን ያተረፈው አውስትራሊያዊ . "ለምን ስሜን ለ20 ዓመታት ደበቅኩ?"የቀድሞ የጃፓን ጠቅላይ ሚንስትር ነገ አርብ በይፋ ከቶኪዮ ኦሊምፒክ አዘጋጅ ኮሚቴ ኃላፊነት እንደሚነሱ ይጠበቃል ሲሉ የጃፓን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ሞሪ ሴቶችን በማስመልከት ብዙ ያስወቀሳቸውን ፆተኛ አስተያየት የሰጡት ከአንድ ሳምንት በፊት በተካሄደው የጃፓን ኦሊምፒክ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ነበር።በስበሰባው ላይ "ሴት የቦርድ አባላትን ቁጥር ለመጨመር ካሰብን ለሚያደርጉት ንግግር የሚሰጣቸው ሰዓት የተወሰነ ሊሆን ይገባል። እነሱ እንደሆነ ቶሎ ተናግሮ የመጨረስ ችግር አለባቸው። በጣም ያናድዳል" ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል በማለት የጃፓኑ አሳሂ ሺምቡን ጋዜጣ ዘግቧል።የኦሊምፒክ ኮሚቴ በአሁኑ ወቅት 24 አባላት ያሉት ሲሆን አምስቱ ሴቶች ናቸው።ከትናንት በስቲያ የሴቶች የሕግ ባለሙያዎች ስብስብ የሞሪን አስተያየት ለመቃወም ባለ ነጭ ቀለም ልብስ ለብሰው ታይተዋል። የሴት የሕግ ባለሙያዎቹን ሃሳብ በመደገፈም በርካቶች ነጭ የመልበስ ዘመቻውን ተቀላቅለዋል። በርካቶችም በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሞሪ ስልጣናቸው እንዲለቁ እየጠየቁ እና ፊርማ እያሰበሰቡ ነው። በቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይ በነጻ አገልግሎት ለመስጠት ከተመዘገቡ ከ400 በላይ ሰዎች የሰውዬውን ንግግር ተከትሎ ፍቃደኝነታቸውን ስርዘዋል ተብሏል። በፈረንጆቹ ከ2000 እስከ 2001 ለአንድ ዓመት ብቻ ጃፓን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ያስተዳደሩት ዮሪ ዲፕሎማሲ በራቃቸው አስተያየቶቻቸው ይታወቃሉ። | 'ሴቶች ብዙ ያወራሉ' ያሉት የቶክዮ ኦሊምፒክ ኃላፊ ሥራ ሊለቁ ነው የቶክዮ ኦሊምፒክስ አዘጋጅ ኮሚቴ ኃላፊ የሆኑት ግለሰብ ሴቶችን አስመልክተው የሰጡትን ፆተኛ አስተያየት ተከትሎ በደረሰባቸው ከፍተኛ ወቀሳ ሥልጣናቸውን በገዛ ፍቃዳቸው ሊለቁ ነው። የኮሚቴው ኃላፊው የ83 ዓመቱ ዮሺሮ ሞሪ ሴቶች በስብሰባዎች ላይ "በጣም ብዙ ያወራሉ፤ ሴት የቦርድ ኃላፊዎች ያሉበት ስብሰባ በጣም ብዙ ጊዜ ይወስዳል" ሲሉ ተናግረዋል ተብሏል። ዮሺሮ ሞሪ ለሰጡት አስተያየት ይቅርታ ጠይቀው በሰጠሁት አስተያየት ግን ስልጣኔን አለቅም ብለው ነበር። ይሁን እንጂ ሞሪ ጫናው በርትቶባቸው ሥልጣናቸውን ሊለቁ ከጫፍ ተቃርበዋል። . ጭንቅላቱን ከአዞ አፍ ፈልቅቆ በማውጣት ራሱን ያተረፈው አውስትራሊያዊ . "ለምን ስሜን ለ20 ዓመታት ደበቅኩ?"የቀድሞ የጃፓን ጠቅላይ ሚንስትር ነገ አርብ በይፋ ከቶኪዮ ኦሊምፒክ አዘጋጅ ኮሚቴ ኃላፊነት እንደሚነሱ ይጠበቃል ሲሉ የጃፓን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ሞሪ ሴቶችን በማስመልከት ብዙ ያስወቀሳቸውን ፆተኛ አስተያየት የሰጡት ከአንድ ሳምንት በፊት በተካሄደው የጃፓን ኦሊምፒክ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ነበር።በስበሰባው ላይ "ሴት የቦርድ አባላትን ቁጥር ለመጨመር ካሰብን ለሚያደርጉት ንግግር የሚሰጣቸው ሰዓት የተወሰነ ሊሆን ይገባል። እነሱ እንደሆነ ቶሎ ተናግሮ የመጨረስ ችግር አለባቸው። በጣም ያናድዳል" ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል በማለት የጃፓኑ አሳሂ ሺምቡን ጋዜጣ ዘግቧል።የኦሊምፒክ ኮሚቴ በአሁኑ ወቅት 24 አባላት ያሉት ሲሆን አምስቱ ሴቶች ናቸው።ከትናንት በስቲያ የሴቶች የሕግ ባለሙያዎች ስብስብ የሞሪን አስተያየት ለመቃወም ባለ ነጭ ቀለም ልብስ ለብሰው ታይተዋል። የሴት የሕግ ባለሙያዎቹን ሃሳብ በመደገፈም በርካቶች ነጭ የመልበስ ዘመቻውን ተቀላቅለዋል። በርካቶችም በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሞሪ ስልጣናቸው እንዲለቁ እየጠየቁ እና ፊርማ እያሰበሰቡ ነው። በቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይ በነጻ አገልግሎት ለመስጠት ከተመዘገቡ ከ400 በላይ ሰዎች የሰውዬውን ንግግር ተከትሎ ፍቃደኝነታቸውን ስርዘዋል ተብሏል። በፈረንጆቹ ከ2000 እስከ 2001 ለአንድ ዓመት ብቻ ጃፓን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ያስተዳደሩት ዮሪ ዲፕሎማሲ በራቃቸው አስተያየቶቻቸው ይታወቃሉ። | https://www.bbc.com/amharic/56027725 |
2health
| በአውስትራሊያ አረጋውያን እንክብካቤ ማዕከላት በየሳምንቱ 50 ወሲባዊ ጥቃቶች ይደርሳሉ ተባለ | በአውስትራሊያ የሚገኙ የአረጋውያን እንክብካቤ ማዕከላት ውስጥ በየሳምንቱ አምሳ ያህል ወሲባዊ ጥቃቶች እንደሚደርሱ ከሰሞኑ ብሔራዊ አጣሪ ኮሚቴ ይፋ አድርጓል። ለሁለት አመታት ያህልም በአረጋውያን እንክብካቤ ማዕከላት የሚደርሱ የተለያዩ ጥቃቶችንና መንገላቶችን ይፋ ባደረገበት መረጃ ነው ሮያል ኮሚሽን ይህንንም ያካተተው። መርማሪዎቹ እንዳሉት በጎሮጎሳውያኑ 2018-2019 ጊዜ 2 ሺህ 520 አረጋውያን ወሲባዊ ጥቃት ደርሶባቸዋል። "ይህ ሁኔታ ብሔራዊ እፍረት ነው" ብለውታል የምክር ቤት አባሉ ፒተር ሮዝን ኪው ሲ ለአጣሪው ኮሚቴ "ቁጥሮቹ የሚረብሹትን ያህል እነዚህን መረጃዎች ያገኘው የመንግሥት አካል ክትትትልና ቁጥጥር አለማድረጉ የበለጠ የከፋ ነው" ብለዋል። በአረጋውያኑ የእንክብካቤ ማዕከል ላይ የሚታየው ቸልተኝነት ከፍተኛ ውዝግብና ጥያቄ ያስነሳ ሲሆን ከዚህ ቀደምም በአውስትራሊያ በኮሮናቫይረስ ከሞቱት አብዛኛዎቹ በአረጋውያን ማዕከል የሚገኙ ናቸው። አውስትራሊያ በኮሮናቫይረስ ሞተዋል ብላ ከመዘገበችው 903 ሰዎች መካከል 75 በመቶ በነዚህ ማዕከላት የሚገኙ ናቸው። በእነዚህ ማዕከላት ላይ የሚደርሱ ወሲባዊ ጥቃቶች የቀደመ ስጋት ሆነው የቆዩ መሆናቸውን ያመኑት ፒተር ሮዝን ቁጥሩም በአገሪቱ ያሉትን 13-18 በመቶ ጥቃት እንደደረሰባቸው ያሳያል። በርካቶች በዕድሜያቸው የበለፀጉ ወይም ተጋላጭ የሆኑ ቤተሰቦቻቸውን በአረጋውያኑ ማዕከል የሚያስገቡት ደህንነታቸው ይጠበቃል በሚል ዕምነትም እንደሆነም የምክር ቤት አባሉ አስረድተዋል። "በአረጋውያን ማዕከላት የሚገኙ ሰዎች ከማህበረሰቡ በበለጠ ለወሲባዊ ጥቃት ተጋላጭ መሆናቸው ተቀባይነት የለውም" ብለዋል ፒተር ሮዝን በአጠቃላይ መርማሪዎች እንደሚገምቱት 32 ሺህ ያህል ወሲባዊ፣ አካላዊና የስነልቦናዊ ጥቃቶች መድረሳቸውን ነው። ይህም ቁጥር በአንድ አመት ያህል እንደደረሰ መረጃው ጠቁሟል። ወሲባዊ ጥቃቱ እንክብካቤ በሚሰጡ ግለሰቦች እንዲሁም እዛው ባሉ ነዋሪዎች እንደሚፈፀምም መረጃው ይፋ አድርጓል። | በአውስትራሊያ አረጋውያን እንክብካቤ ማዕከላት በየሳምንቱ 50 ወሲባዊ ጥቃቶች ይደርሳሉ ተባለ በአውስትራሊያ የሚገኙ የአረጋውያን እንክብካቤ ማዕከላት ውስጥ በየሳምንቱ አምሳ ያህል ወሲባዊ ጥቃቶች እንደሚደርሱ ከሰሞኑ ብሔራዊ አጣሪ ኮሚቴ ይፋ አድርጓል። ለሁለት አመታት ያህልም በአረጋውያን እንክብካቤ ማዕከላት የሚደርሱ የተለያዩ ጥቃቶችንና መንገላቶችን ይፋ ባደረገበት መረጃ ነው ሮያል ኮሚሽን ይህንንም ያካተተው። መርማሪዎቹ እንዳሉት በጎሮጎሳውያኑ 2018-2019 ጊዜ 2 ሺህ 520 አረጋውያን ወሲባዊ ጥቃት ደርሶባቸዋል። "ይህ ሁኔታ ብሔራዊ እፍረት ነው" ብለውታል የምክር ቤት አባሉ ፒተር ሮዝን ኪው ሲ ለአጣሪው ኮሚቴ "ቁጥሮቹ የሚረብሹትን ያህል እነዚህን መረጃዎች ያገኘው የመንግሥት አካል ክትትትልና ቁጥጥር አለማድረጉ የበለጠ የከፋ ነው" ብለዋል። በአረጋውያኑ የእንክብካቤ ማዕከል ላይ የሚታየው ቸልተኝነት ከፍተኛ ውዝግብና ጥያቄ ያስነሳ ሲሆን ከዚህ ቀደምም በአውስትራሊያ በኮሮናቫይረስ ከሞቱት አብዛኛዎቹ በአረጋውያን ማዕከል የሚገኙ ናቸው። አውስትራሊያ በኮሮናቫይረስ ሞተዋል ብላ ከመዘገበችው 903 ሰዎች መካከል 75 በመቶ በነዚህ ማዕከላት የሚገኙ ናቸው። በእነዚህ ማዕከላት ላይ የሚደርሱ ወሲባዊ ጥቃቶች የቀደመ ስጋት ሆነው የቆዩ መሆናቸውን ያመኑት ፒተር ሮዝን ቁጥሩም በአገሪቱ ያሉትን 13-18 በመቶ ጥቃት እንደደረሰባቸው ያሳያል። በርካቶች በዕድሜያቸው የበለፀጉ ወይም ተጋላጭ የሆኑ ቤተሰቦቻቸውን በአረጋውያኑ ማዕከል የሚያስገቡት ደህንነታቸው ይጠበቃል በሚል ዕምነትም እንደሆነም የምክር ቤት አባሉ አስረድተዋል። "በአረጋውያን ማዕከላት የሚገኙ ሰዎች ከማህበረሰቡ በበለጠ ለወሲባዊ ጥቃት ተጋላጭ መሆናቸው ተቀባይነት የለውም" ብለዋል ፒተር ሮዝን በአጠቃላይ መርማሪዎች እንደሚገምቱት 32 ሺህ ያህል ወሲባዊ፣ አካላዊና የስነልቦናዊ ጥቃቶች መድረሳቸውን ነው። ይህም ቁጥር በአንድ አመት ያህል እንደደረሰ መረጃው ጠቁሟል። ወሲባዊ ጥቃቱ እንክብካቤ በሚሰጡ ግለሰቦች እንዲሁም እዛው ባሉ ነዋሪዎች እንደሚፈፀምም መረጃው ይፋ አድርጓል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54637492 |
2health
| የእሲያ-ፓሲፊክ አገራት በኮቪድ ምክንያት የተጣሉ ዓለም አቀፍ የጉዞ ገደቦችን ማንሳት ጀመሩ | ሲንጋፖር፣ አውስትራሊያ እና ጃፓንን ጨምሮ የእሲያ-ፓሲፊክ አገራት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ዓለም አቀፍ ጎዞዎች ላይ ተጥለው የነበሩትን ክልካላዎች ማንሳት መጀመራቸውን ሬውተርስ ዘገበ። አገራቱ የዓለም አቀፍ በረራዎች መጀመር በቫይረሱ ስርጭት የተጎዳውን ምጣኔ ሃብታቸውን እንደሚያነቃቃው ታምኖበታል። እንደ እሲያ ፓሲፊክ አየር መንገደኞች ማህበር አሃዝ ከሆነ በእሲያ ብቻ በኮቪድ-19 ምክንያት ሰኔ ወር ላይ የዓለም አቀፍ ተጓዦች ቁጥር 97 በመቶ ቀንሶ ነበር። አሁንም ቢሆን በርካታ የእሲያ አገራት ተጓዦች ከኮቪድ ነጻ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት፣ የህክምና መድህን እና አንዳንዶች ደግሞ ወደ ለይቶ መቆያ መግባትን ግዴታ ስለሚያደርጉ የተጓዦች ቁጥር በቅርቡ ላያንሰራራ ይችላል። ይህም ለአየር መንገዶች እና ለቱሪዝም ዘረፉ ሌላ ፈተና ሆኖ ይቀጥላል። ሲንጋፖር እና ኢንዶኔዢያ በአገራቱ መካከል የኮሮናቫይረስ ምርመራ በማድረግ ለይፋዊ የመንግሥት ሥራ ጉዞ እንዲደረግ ከስምምነት ደርሰዋል። ሲንጋፖር ከዚህ ቀደም ከቻይና፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ጃፓን እና ማሌዢያ ጋር ተመሳሳይ ስምምነትን የደረሰች ሲሆን ከኒው ዚላንድ እና ቪዬትናም ግን ማንኛው ተጓዥ ወደ ሲንጋፖር መግባት ይችላል ተብሏል። የኒው ዚላንድ ዜጎች ደግሞ ወደተወሰኑት የአውስትራሊያ ግዛቶች ከአርብ ጀምሮ ወደ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ መግባት ሳይጠበቅባቸው መጓዝ ይችላሉ። ይሁን እንጂ የኒው ዚላንድ ዜጎች ከአውስትራሊያ ሲመለሱ እራሳቸውን ለሁለት ሳምንት ለይተው የመቆየት ግዴታ ይኖርባቸዋል። ከአምስት ቀናት በኋላ አጠቃላይ ምርጫ የምታከናውነው ኒው ዚላንድ ድንበሮቿን ለአውስትራሊያ ክፍት ለማድረግ እቅድ እንደሌላት ተጠቁሟል። አውስትራሊያ በበኩሏ ዓለም አቀፍ በረራዎችን ለመጀመር ከጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያ እና ሲንጋፖር ጋር ምክክር እያካሄደች ትገኛለች። ጃፓን እና ቪዬትናም ደግሞ ለንግድ የሚደረጉ ጉዞዎች እንዲከናወኑ ተስማምተዋል። | የእሲያ-ፓሲፊክ አገራት በኮቪድ ምክንያት የተጣሉ ዓለም አቀፍ የጉዞ ገደቦችን ማንሳት ጀመሩ ሲንጋፖር፣ አውስትራሊያ እና ጃፓንን ጨምሮ የእሲያ-ፓሲፊክ አገራት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ዓለም አቀፍ ጎዞዎች ላይ ተጥለው የነበሩትን ክልካላዎች ማንሳት መጀመራቸውን ሬውተርስ ዘገበ። አገራቱ የዓለም አቀፍ በረራዎች መጀመር በቫይረሱ ስርጭት የተጎዳውን ምጣኔ ሃብታቸውን እንደሚያነቃቃው ታምኖበታል። እንደ እሲያ ፓሲፊክ አየር መንገደኞች ማህበር አሃዝ ከሆነ በእሲያ ብቻ በኮቪድ-19 ምክንያት ሰኔ ወር ላይ የዓለም አቀፍ ተጓዦች ቁጥር 97 በመቶ ቀንሶ ነበር። አሁንም ቢሆን በርካታ የእሲያ አገራት ተጓዦች ከኮቪድ ነጻ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት፣ የህክምና መድህን እና አንዳንዶች ደግሞ ወደ ለይቶ መቆያ መግባትን ግዴታ ስለሚያደርጉ የተጓዦች ቁጥር በቅርቡ ላያንሰራራ ይችላል። ይህም ለአየር መንገዶች እና ለቱሪዝም ዘረፉ ሌላ ፈተና ሆኖ ይቀጥላል። ሲንጋፖር እና ኢንዶኔዢያ በአገራቱ መካከል የኮሮናቫይረስ ምርመራ በማድረግ ለይፋዊ የመንግሥት ሥራ ጉዞ እንዲደረግ ከስምምነት ደርሰዋል። ሲንጋፖር ከዚህ ቀደም ከቻይና፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ጃፓን እና ማሌዢያ ጋር ተመሳሳይ ስምምነትን የደረሰች ሲሆን ከኒው ዚላንድ እና ቪዬትናም ግን ማንኛው ተጓዥ ወደ ሲንጋፖር መግባት ይችላል ተብሏል። የኒው ዚላንድ ዜጎች ደግሞ ወደተወሰኑት የአውስትራሊያ ግዛቶች ከአርብ ጀምሮ ወደ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ መግባት ሳይጠበቅባቸው መጓዝ ይችላሉ። ይሁን እንጂ የኒው ዚላንድ ዜጎች ከአውስትራሊያ ሲመለሱ እራሳቸውን ለሁለት ሳምንት ለይተው የመቆየት ግዴታ ይኖርባቸዋል። ከአምስት ቀናት በኋላ አጠቃላይ ምርጫ የምታከናውነው ኒው ዚላንድ ድንበሮቿን ለአውስትራሊያ ክፍት ለማድረግ እቅድ እንደሌላት ተጠቁሟል። አውስትራሊያ በበኩሏ ዓለም አቀፍ በረራዎችን ለመጀመር ከጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያ እና ሲንጋፖር ጋር ምክክር እያካሄደች ትገኛለች። ጃፓን እና ቪዬትናም ደግሞ ለንግድ የሚደረጉ ጉዞዎች እንዲከናወኑ ተስማምተዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54506852 |
5sports
| ሴቶች 'ብዙ ያወራሉ' ያሉት የቶክዮ ኦሊምፒክ ኃላፊ ሥራቸውን ለቀቁ | የቶክዮ ኦሊምፒክ አዘጋጅ ኮሚቴ ኃላፊ የሆኑት ግለሰብ ሴቶችን አስመልክተው የሰጡትን አስተያየት ተከትሎ በደረሰባቸው ከፍተኛ ወቀሳ ሥልጣናቸውን በገዛ ፍቃዳቸው ለቀዋል። የኮሚቴው ኃላፊው የ83 ዓመቱ ዮሺሮ ሞሪ ሴቶች በስብሰባዎች ላይ “በጣም ብዙ ያወራሉ፤ ሴት የቦርድ ኃላፊዎች ያሉበት ስብሰባ በጣም ብዙ ጊዜ ይወስዳል' ሲሉ ተናግረዋል ተብሏል። ዮሺሮ ሞሪ ለሰጡት አስተያየት ይቅርታ ጠይቀው በሰጠሁት አስተያየት ግን ስልጣኔን አለቅም ብለው ነበር። ነገር ግን ዛሬ አርብ ዕለት ለሰነዘርኩት ያልተገባ አስተያየት ይቅርታ እጠይቃለው በማለት ከስራቸው በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ይፋ አድርገዋል። ''በአሁኑ ሰአት ዋናው ነገር ሐምሌ ወር ላይ ኦሎምፒክ መካሄዱ ነው። የእኔ በእዚህ አካባቢ መገኘት የዝግጅቱን ስራ ከባድ እንዲያደርገው አልፈልግም'' ብለዋል ዛሬ በተካሄደው የኮሚቴው ልዩ ስብሰባ ላይ። የቀድሞ የጃፓን ጠቅላይ ሚንስትር ነገ አርብ በይፋ ከቶኪዮ ኦሊምፒክ አዘጋጅ ኮሚቴ ኃላፊነት እንደሚነሱ ይጠበቃል ሲሉ የጃፓን መገናኛ ብዙሃን ዘግበው ነበር። ሞሪ ሴቶችን በማስመልከት ብዙ ያስወቀሳቸውን አስተያየት የሰጡት ከአንድ ሳምንት በፊት በተካሄደው የጃፓን ኦሊምፒክ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ነበር። በስበሰባው ላይ "ሴት የቦርድ አባላትን ቁጥር ለመጨመር ካሰብን ለሚያደርጉት ንግግር የሚሰጣቸው ሰዓት የተወሰነ ሊሆን ይገባል። እነሱ እንደሆነ ቶሎ ተናግሮ የመጨረስ ችግር አለባቸው። በጣም ያናድዳል" ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል በማለት የጃፓኑ አሳሂ ሺምቡን ጋዜጣ ዘግቧል። የኦሊምፒክ ኮሚቴ በአሁኑ ወቅት 24 አባላት ያሉት ሲሆን አምስቱ ሴቶች ናቸው።ከትናንት በስቲያ የሴቶች የሕግ ባለሙያዎች ስብስብ የሞሪን አስተያየት ለመቃወም ባለ ነጭ ቀለም ልብስ ለብሰው ታይተዋል። የሴት የሕግ ባለሙያዎቹን ሃሳብ በመደገፈም በርካቶች ነጭ የመልበስ ዘመቻውን ተቀላቅለዋል። በርካቶችም በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሞሪ ስልጣናቸው እንዲለቁ እየጠየቁ እና ፊርማ አሰባስበው ነበር። በቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይ በነጻ አገልግሎት ለመስጠት ከተመዘገቡ ከ400 በላይ ሰዎች የሰውዬውን ንግግር ተከትሎ ፍቃደኝነታቸውን ስርዘዋል ተብሏል። በፈረንጆቹ ከ2000 እስከ 2001 ለአንድ ዓመት ብቻ ጃፓን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ያስተዳደሩት ዮሪ ዲፕሎማሲ በራቃቸው አስተያየቶቻቸው ይታወቃሉ። | ሴቶች 'ብዙ ያወራሉ' ያሉት የቶክዮ ኦሊምፒክ ኃላፊ ሥራቸውን ለቀቁ የቶክዮ ኦሊምፒክ አዘጋጅ ኮሚቴ ኃላፊ የሆኑት ግለሰብ ሴቶችን አስመልክተው የሰጡትን አስተያየት ተከትሎ በደረሰባቸው ከፍተኛ ወቀሳ ሥልጣናቸውን በገዛ ፍቃዳቸው ለቀዋል። የኮሚቴው ኃላፊው የ83 ዓመቱ ዮሺሮ ሞሪ ሴቶች በስብሰባዎች ላይ “በጣም ብዙ ያወራሉ፤ ሴት የቦርድ ኃላፊዎች ያሉበት ስብሰባ በጣም ብዙ ጊዜ ይወስዳል' ሲሉ ተናግረዋል ተብሏል። ዮሺሮ ሞሪ ለሰጡት አስተያየት ይቅርታ ጠይቀው በሰጠሁት አስተያየት ግን ስልጣኔን አለቅም ብለው ነበር። ነገር ግን ዛሬ አርብ ዕለት ለሰነዘርኩት ያልተገባ አስተያየት ይቅርታ እጠይቃለው በማለት ከስራቸው በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ይፋ አድርገዋል። ''በአሁኑ ሰአት ዋናው ነገር ሐምሌ ወር ላይ ኦሎምፒክ መካሄዱ ነው። የእኔ በእዚህ አካባቢ መገኘት የዝግጅቱን ስራ ከባድ እንዲያደርገው አልፈልግም'' ብለዋል ዛሬ በተካሄደው የኮሚቴው ልዩ ስብሰባ ላይ። የቀድሞ የጃፓን ጠቅላይ ሚንስትር ነገ አርብ በይፋ ከቶኪዮ ኦሊምፒክ አዘጋጅ ኮሚቴ ኃላፊነት እንደሚነሱ ይጠበቃል ሲሉ የጃፓን መገናኛ ብዙሃን ዘግበው ነበር። ሞሪ ሴቶችን በማስመልከት ብዙ ያስወቀሳቸውን አስተያየት የሰጡት ከአንድ ሳምንት በፊት በተካሄደው የጃፓን ኦሊምፒክ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ነበር። በስበሰባው ላይ "ሴት የቦርድ አባላትን ቁጥር ለመጨመር ካሰብን ለሚያደርጉት ንግግር የሚሰጣቸው ሰዓት የተወሰነ ሊሆን ይገባል። እነሱ እንደሆነ ቶሎ ተናግሮ የመጨረስ ችግር አለባቸው። በጣም ያናድዳል" ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል በማለት የጃፓኑ አሳሂ ሺምቡን ጋዜጣ ዘግቧል። የኦሊምፒክ ኮሚቴ በአሁኑ ወቅት 24 አባላት ያሉት ሲሆን አምስቱ ሴቶች ናቸው።ከትናንት በስቲያ የሴቶች የሕግ ባለሙያዎች ስብስብ የሞሪን አስተያየት ለመቃወም ባለ ነጭ ቀለም ልብስ ለብሰው ታይተዋል። የሴት የሕግ ባለሙያዎቹን ሃሳብ በመደገፈም በርካቶች ነጭ የመልበስ ዘመቻውን ተቀላቅለዋል። በርካቶችም በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሞሪ ስልጣናቸው እንዲለቁ እየጠየቁ እና ፊርማ አሰባስበው ነበር። በቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይ በነጻ አገልግሎት ለመስጠት ከተመዘገቡ ከ400 በላይ ሰዎች የሰውዬውን ንግግር ተከትሎ ፍቃደኝነታቸውን ስርዘዋል ተብሏል። በፈረንጆቹ ከ2000 እስከ 2001 ለአንድ ዓመት ብቻ ጃፓን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ያስተዳደሩት ዮሪ ዲፕሎማሲ በራቃቸው አስተያየቶቻቸው ይታወቃሉ። | https://www.bbc.com/amharic/news-56038533 |
2health
| የዓለም ጤና ድርጅት አውሮፓን በድጋሚ የወረርሽኙ ማዕከል ናት ሲል አስጠነቀቀ | በአውሮፓ እየተባባሰ በመጣው ስርጭት ምክንያት አህጉሪቱ በድጋሚ የኮቪድ ወረርሽኝ "ማዕከል" ሆናለች ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስጠንቅቋል። የዓለም ጤና ድርጅት የአውሮፓ ኃላፊ ሃንስ ክሉጅ በጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት እንዳሉት አህጉሪቱ በየካቲት ወር ግማሽ ሚሊዮን ተጨማሪ ሞት ልታስመዘግብ ትችላለች። ለስርጭቱ መጨመር በበቂ ሁኔታ ክትባት አለመሰጠቱን በማንሳት ትችቱን ሰንዝሯል። "ለኮቪድ-19 መስፋፋት ምላሽ ከመስጠት ቀድሞውኑ እንዳይከሰት ወደሚያግዙ ስልቶች መለወጥ አለብን" ብለዋል። ከቅርብ ወራት ወዲህ በመላው አህጉሪቱ ክትባቱን የመስጠት ምጣኔው ቀንሷል። በስፔን ውስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች ሁለቱን ዙር ክትባት ወስደዋል። ይህ ቁጥር በፈረንሳይ እና በጀርመን ዝቅተኛ በሚባል ደረጃ፣ 68 በመቶ እና 66 በመቶ ላይ ይገኛል። የአንዳንድ የመካከለኛው እና የምስራቅ አውሮፓ ሃገሮች አሃዝ ደግሞ ከዚህም ዝቅተኛ ነው። እአአ ጥቅምት 2021 ሙሉ ለሙሉ ክትባቱን የወሰዱ ሩሲያውያን 32 በመቶ ብቻ ናቸው። ክሉጅ የማዕከላዊ እስያ ክፍልን ጨምሮ 53 ሃገሮችን በሚሸፍነው የዓለም ጤና ድርጅት የአውሮፓ ዞን የህዝብ ጤና እርምጃዎችን መላላትን ለበሽታው መባባስ እንደተጨማሪ ምክንያት አንስተዋል። የዓለም ጤና ድርጅት በአካባቢው እስካሁን 1.4 ሚሊዮን ሰዎች መሞታቸውን መዝግቧል። የዓለም ጤና ድርጅት የኮቪድ-19 ቴክኒካል ኃላፊ ማሪያ ቫን ኬርክሆቭ ምንም እንኳን "በቂ የክትባት እና የመሳሪያ አቅርቦት" ቢኖርም ወረርሽኙ ባለፉት አራት ሳምንታት በመላው አውሮፓ ከ 55 በመቶ በላይ ከፍ ብሏል ብለዋል። ባልደረባቸው ዶክተር ማይክ ሪያን የአውሮፓ ተሞክሮ "ለዓለም የማስጠንቀቂያ ደወል ነው" ሲሉ ገልጸውታል። በጀርመን ስርጭቱ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቶ ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ ወደ 34000 የሚጠጉ በኮቪድ የተያዙ ሰዎች ተመዝግበዋል። በጀርመን ያለው የኮቪድ ስርጭት በዕለት ከ 37000 የሚበልጡ ሰዎች በቫይረሱ ከሚያዙባት የዩኬ የቅርብ ጊዜ ቁጥሮች በታች ነው። የህብረተሰብ ጤና ባለሥልጣናት ግን አራተኛው ማዕበል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሞት ሊያስከትል እና በጤና ስርዓቱ ላይ ጫና ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት አላቸው። ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 165 ሰዎች መሞታቸው የተመዘገበ ሲሆን ይህም ከአንድ ሳምንት በፊት ከነበረው 126 ሞት ጨማሪ አሳይቷል። የጀርመን አርኬአይ ኢንስቲትዩቱ ሎተር ዊለር ስለ አስፈሪ ቁጥሮች ተናግረዋል። "አሁን የመከላከያ እርምጃዎችን ካልወሰድን አራተኛው ማዕበል የበለጠ አደጋ ያመጣል" ብለዋል። ክትባቱን ካልወሰዱት ጀርመናውያን መካከል ከ60 በላይ ዕድሜ ያላቸው ከሦስት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሲሆን እነዚሀም ለበለጠ አደጋ የተጋለጡ ናቸው። ሃንስ ክሉጅ እንደሚሉት የቫይረሱ መጨመር በጀርመን ብቻ የተገደበ አይደለም። ባለፈው ሳምንት የሟቾች ቁጥር በጣም በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረው በሩሲያ ሲሆን ከ 8,100 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። በዩክሬን ደግሞ 3800 ሰዎች ሞተዋል። ሁለቱም ሀገራት በጣም ዝቅተኛ ክትባት የሰጡ ሲሆን ዩክሬን ባለፉት 24 ሰዓታት 27377 አዳዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን አስመዝግባለች። ሮማኒያ በ 24 ሰዓታት ውስጥ ከፍተኛ የሆነውን የ591 ሰዎችን ሞት አስመዝግባለች። በሃንጋሪ በየዕለቱ በኮቪድ የሚያዙ ሰዎች ከእጥፍ በላይ አድጎ ባለፈው ሳምንት 6268 ደርሷል። ጭንብል መልበስ አስገዳጅ የሆነው በሕዝብ ማመላለሻዎች እና በሆስፒታሎች ብቻ ነው። ዶክተር ሪያን "በአሁን ተጨማሪ ጥቂት ሰዎችን ከከተብን ወረርሽኙ አብቅቷል የሚል ሃሳብ ላይ ነን። ጉዳዩ እንደዚያ አይደለም" ብለው ሃገራት ቀዳዳቸውን እንዲደፍኑ ሃሳባቸውን ሰንዝረዋል። የደች መንግሥት ጭንብል መልበስ እና አካላዊ መራራቅን ህዝብ በሚሰባሰብበት ቦታዎች ላይ እንደሚጀምር በዚህ ሳምንት ተናግሯል። ምክንያቱ ያለው ደግሞ በሳምንት ውስጥ የሆስፒታል አልጋዎች የመያዝ ምጣኔ በ 31 በመቶ ከፍ በማለቱ ነው ። የኮቪድ ስርጭት ከፍተኛ ደረጃ ላይ በመድረሱ ላትቪያ ከሰኞ ጀምሮ ለሦስት ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጥታለች። ክሮሺያ ሐሙስ ዕለት 6310 አዳዲስ በቫእረሱ የተያዙ ሰዎችን መዝግባለች። ይህ ቁጥር እስካሁን ድረስ ከታየው ከፍተኛው ቁጥር ነው። ስሎቫኪያ ሁለተኛውን ከፍተኛ ቁጥር መዝግባለች። የቼክ ስርጭት በፀደይ ወቅት ወደ ነበረበት ደረጃ ተመልሷል። የእንግሊዝ ምክትል ዋና የህክምና መኮንን ፕሮፌሰር ጆናታን ቫን ታም በበኩላቸው በጣም ብዙ ሰዎች ወረርሽኙ እንዳበቃ ያምናሉ ብለዋል። ከፍተኛ የክትባት መጠን በደረሰባቸው ሃገሮች የስርጭት መጠኑ አሁንም በአንጻራዊነት ሁኔታ ዝቅተኛ ነው። ጣሊያን ከ12 አመት በላይ ለሆኑት ዜጎቿ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ክትባት ብትሰጥም ባለፈው ሳምንት ውስጥ አዳዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች በ16.6 በመቶ ጨምሯል። ከመስከረም በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የፖርቹጋል የስርጭት መጠን ከ 1000 በላይ ሆኗል። ረቡዕ 2287 ሰዎች በቫይረሱ የታዩዛበት ስፔን የስርጭት መጨመር ካላዩት ጥቂት ሃገሮች አንዷ ሆናለች። | የዓለም ጤና ድርጅት አውሮፓን በድጋሚ የወረርሽኙ ማዕከል ናት ሲል አስጠነቀቀ በአውሮፓ እየተባባሰ በመጣው ስርጭት ምክንያት አህጉሪቱ በድጋሚ የኮቪድ ወረርሽኝ "ማዕከል" ሆናለች ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስጠንቅቋል። የዓለም ጤና ድርጅት የአውሮፓ ኃላፊ ሃንስ ክሉጅ በጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት እንዳሉት አህጉሪቱ በየካቲት ወር ግማሽ ሚሊዮን ተጨማሪ ሞት ልታስመዘግብ ትችላለች። ለስርጭቱ መጨመር በበቂ ሁኔታ ክትባት አለመሰጠቱን በማንሳት ትችቱን ሰንዝሯል። "ለኮቪድ-19 መስፋፋት ምላሽ ከመስጠት ቀድሞውኑ እንዳይከሰት ወደሚያግዙ ስልቶች መለወጥ አለብን" ብለዋል። ከቅርብ ወራት ወዲህ በመላው አህጉሪቱ ክትባቱን የመስጠት ምጣኔው ቀንሷል። በስፔን ውስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች ሁለቱን ዙር ክትባት ወስደዋል። ይህ ቁጥር በፈረንሳይ እና በጀርመን ዝቅተኛ በሚባል ደረጃ፣ 68 በመቶ እና 66 በመቶ ላይ ይገኛል። የአንዳንድ የመካከለኛው እና የምስራቅ አውሮፓ ሃገሮች አሃዝ ደግሞ ከዚህም ዝቅተኛ ነው። እአአ ጥቅምት 2021 ሙሉ ለሙሉ ክትባቱን የወሰዱ ሩሲያውያን 32 በመቶ ብቻ ናቸው። ክሉጅ የማዕከላዊ እስያ ክፍልን ጨምሮ 53 ሃገሮችን በሚሸፍነው የዓለም ጤና ድርጅት የአውሮፓ ዞን የህዝብ ጤና እርምጃዎችን መላላትን ለበሽታው መባባስ እንደተጨማሪ ምክንያት አንስተዋል። የዓለም ጤና ድርጅት በአካባቢው እስካሁን 1.4 ሚሊዮን ሰዎች መሞታቸውን መዝግቧል። የዓለም ጤና ድርጅት የኮቪድ-19 ቴክኒካል ኃላፊ ማሪያ ቫን ኬርክሆቭ ምንም እንኳን "በቂ የክትባት እና የመሳሪያ አቅርቦት" ቢኖርም ወረርሽኙ ባለፉት አራት ሳምንታት በመላው አውሮፓ ከ 55 በመቶ በላይ ከፍ ብሏል ብለዋል። ባልደረባቸው ዶክተር ማይክ ሪያን የአውሮፓ ተሞክሮ "ለዓለም የማስጠንቀቂያ ደወል ነው" ሲሉ ገልጸውታል። በጀርመን ስርጭቱ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቶ ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ ወደ 34000 የሚጠጉ በኮቪድ የተያዙ ሰዎች ተመዝግበዋል። በጀርመን ያለው የኮቪድ ስርጭት በዕለት ከ 37000 የሚበልጡ ሰዎች በቫይረሱ ከሚያዙባት የዩኬ የቅርብ ጊዜ ቁጥሮች በታች ነው። የህብረተሰብ ጤና ባለሥልጣናት ግን አራተኛው ማዕበል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሞት ሊያስከትል እና በጤና ስርዓቱ ላይ ጫና ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት አላቸው። ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 165 ሰዎች መሞታቸው የተመዘገበ ሲሆን ይህም ከአንድ ሳምንት በፊት ከነበረው 126 ሞት ጨማሪ አሳይቷል። የጀርመን አርኬአይ ኢንስቲትዩቱ ሎተር ዊለር ስለ አስፈሪ ቁጥሮች ተናግረዋል። "አሁን የመከላከያ እርምጃዎችን ካልወሰድን አራተኛው ማዕበል የበለጠ አደጋ ያመጣል" ብለዋል። ክትባቱን ካልወሰዱት ጀርመናውያን መካከል ከ60 በላይ ዕድሜ ያላቸው ከሦስት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሲሆን እነዚሀም ለበለጠ አደጋ የተጋለጡ ናቸው። ሃንስ ክሉጅ እንደሚሉት የቫይረሱ መጨመር በጀርመን ብቻ የተገደበ አይደለም። ባለፈው ሳምንት የሟቾች ቁጥር በጣም በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረው በሩሲያ ሲሆን ከ 8,100 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። በዩክሬን ደግሞ 3800 ሰዎች ሞተዋል። ሁለቱም ሀገራት በጣም ዝቅተኛ ክትባት የሰጡ ሲሆን ዩክሬን ባለፉት 24 ሰዓታት 27377 አዳዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን አስመዝግባለች። ሮማኒያ በ 24 ሰዓታት ውስጥ ከፍተኛ የሆነውን የ591 ሰዎችን ሞት አስመዝግባለች። በሃንጋሪ በየዕለቱ በኮቪድ የሚያዙ ሰዎች ከእጥፍ በላይ አድጎ ባለፈው ሳምንት 6268 ደርሷል። ጭንብል መልበስ አስገዳጅ የሆነው በሕዝብ ማመላለሻዎች እና በሆስፒታሎች ብቻ ነው። ዶክተር ሪያን "በአሁን ተጨማሪ ጥቂት ሰዎችን ከከተብን ወረርሽኙ አብቅቷል የሚል ሃሳብ ላይ ነን። ጉዳዩ እንደዚያ አይደለም" ብለው ሃገራት ቀዳዳቸውን እንዲደፍኑ ሃሳባቸውን ሰንዝረዋል። የደች መንግሥት ጭንብል መልበስ እና አካላዊ መራራቅን ህዝብ በሚሰባሰብበት ቦታዎች ላይ እንደሚጀምር በዚህ ሳምንት ተናግሯል። ምክንያቱ ያለው ደግሞ በሳምንት ውስጥ የሆስፒታል አልጋዎች የመያዝ ምጣኔ በ 31 በመቶ ከፍ በማለቱ ነው ። የኮቪድ ስርጭት ከፍተኛ ደረጃ ላይ በመድረሱ ላትቪያ ከሰኞ ጀምሮ ለሦስት ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጥታለች። ክሮሺያ ሐሙስ ዕለት 6310 አዳዲስ በቫእረሱ የተያዙ ሰዎችን መዝግባለች። ይህ ቁጥር እስካሁን ድረስ ከታየው ከፍተኛው ቁጥር ነው። ስሎቫኪያ ሁለተኛውን ከፍተኛ ቁጥር መዝግባለች። የቼክ ስርጭት በፀደይ ወቅት ወደ ነበረበት ደረጃ ተመልሷል። የእንግሊዝ ምክትል ዋና የህክምና መኮንን ፕሮፌሰር ጆናታን ቫን ታም በበኩላቸው በጣም ብዙ ሰዎች ወረርሽኙ እንዳበቃ ያምናሉ ብለዋል። ከፍተኛ የክትባት መጠን በደረሰባቸው ሃገሮች የስርጭት መጠኑ አሁንም በአንጻራዊነት ሁኔታ ዝቅተኛ ነው። ጣሊያን ከ12 አመት በላይ ለሆኑት ዜጎቿ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ክትባት ብትሰጥም ባለፈው ሳምንት ውስጥ አዳዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች በ16.6 በመቶ ጨምሯል። ከመስከረም በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የፖርቹጋል የስርጭት መጠን ከ 1000 በላይ ሆኗል። ረቡዕ 2287 ሰዎች በቫይረሱ የታዩዛበት ስፔን የስርጭት መጨመር ካላዩት ጥቂት ሃገሮች አንዷ ሆናለች። | https://www.bbc.com/amharic/news-59165910 |
5sports
| አሜሪካ፡ ፖሊሶች ጄኮብ ብሌክ ላይ መተኮሳቸውን በመቃወም ቴኒስ ተጫዋቿ ኦሳካ ራሷን ከውድድር አገለለች | ጃፓናዊቷ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ናዮሚ ኦሳካ ፖሊሶች ጄኮብ ብሌክ ላይ መተኮሳቸውን በመቃወም ከታላቁ የኒው ዮርክ ቴኒስ ውድድር ራሷን አገለለች። “ጥቁር ሴት እንደመሆኔ እኔ ቴኒስ ስጫወት ከማየት በበለጠ ቅድሚያ የሚሰጣቸው አንገብጋቢ ጉዳዮች እንዳሉ አምናለሁ” ብላለች በትዊተር ገጿ። ምንም መሣሪያ ያልታጠቀው ጥቁር አሜሪካዊው ጄኮብ ላይ ፖሊሶች ከጀርባው ተኩሰውበታል። እሁድ በኪኖሻ ግዛት ከተተኮሰበት በኋላ በመላው ዊስኮንሰን ተቃውሞ ተቀጣጥሏል። በፖርትላንድ፣ ሚኒሶታና ሌሎችም ግዛቶች ተቃውሞው ቀጥሏል። ከወራት በፊት ጆርጅ ፍሎይድ በፖሊስ መገደሉን በመቃወም በመላው አገሪቱ የ ‘ብላክ ላይቭስ ማተር’ [የጥቁሮች ሕይወት ዋጋ አላት] ሰልፎች መካሄዳቸው አይዘነጋም። ደብሊውቲኤ የተባለው የሜዳ ቴኒስ ውድድር አዘጋጆች እስከ አርብ ድረስ ጨዋታው እንደተሰረዘ አስታውቀዋል። “የዘር መድልዎና ኢፍትሐዊነትን የቴኒስ ስፓርት እንደሚቃወም ማሳየት እንፈልጋለን” የሚል መግለጫም አውጥተዋል። ናዮሚ ኦሳካ ከግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ መውጣቷን መግለጿን ተከትሎ ነበር ይህ መግለጫ የወጣው። በጃፓንኛና በእንግሊዘኛ በጻፈችው ትዊት “ቴኒስ ስላልተጫወትኩ ትልቅ ነገር ይፈጠራል ብዬ አልጠብቅም። ነገር ግን ነጭ ተጫዋቾች በሚበዙበት ስፖርት ውስጥ አንዳች ውይይት እንዲጀመር ምክንያት ከሆንኩኝ ወደ ትክክለኛ አቅጣጫ እየተራመድን ነው” ብላለች። ናዮሚ አያይዛም “ጥቁሮች በፖሊሶች እየተገደሉ መሆኑን ሳይ ያመኛል” ስትል ሀዘኗን ገልጻለች። ጃፓናዊና የሄይቲ ውህድ የሆነችው ናዮሚ፤ ጃፓን ውስጥ የዘረኝነት ሰለባ ናት። ማስታወቂያዎች ላይ የቆዳ ቀለሟን ሲያነጡ፤ ቆዳዋን ነጭ ማድርግ አለባት እያሉ የሚሳለቁ ኮሜዲያኖችም አሉ። በስፓርቱ ዓለም ጄኮብ ብሌክ ላይ መተኮሱን የተቃወሙ ሌሎችም አሉ። የቅርጫት ኳስ ቡድኑ ሚልዋኪ ባክስ ከውድድር መውጣታቸውን ተከትሎ ኤንቢኤ ሦስት ግጥሚያዎች ሰርዟል። ሁለት የቤዝቦል ጨዋታዎችም ተሰርዘዋል። ፖሊሶች ጄኮብ ላይ የተኮሱት ያሳለፍነው እሁድ ሦስት ልጆቹ ወደ ነበሩበት መኪና ሲገባ ነው። አሁን ሆስፒታል ውስጥ እያገገመ ሲሆን፤ ጠበቃው ከዚህ በኋላ መራመድ ከቻለ ተዓምር ነው ብለዋል። ፖሊሶች ጄኮብ ላይ ሰባት ጊዜ መተኮሳቸውን ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞ ሁለት ሰዎች ተገድለዋል። | አሜሪካ፡ ፖሊሶች ጄኮብ ብሌክ ላይ መተኮሳቸውን በመቃወም ቴኒስ ተጫዋቿ ኦሳካ ራሷን ከውድድር አገለለች ጃፓናዊቷ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ናዮሚ ኦሳካ ፖሊሶች ጄኮብ ብሌክ ላይ መተኮሳቸውን በመቃወም ከታላቁ የኒው ዮርክ ቴኒስ ውድድር ራሷን አገለለች። “ጥቁር ሴት እንደመሆኔ እኔ ቴኒስ ስጫወት ከማየት በበለጠ ቅድሚያ የሚሰጣቸው አንገብጋቢ ጉዳዮች እንዳሉ አምናለሁ” ብላለች በትዊተር ገጿ። ምንም መሣሪያ ያልታጠቀው ጥቁር አሜሪካዊው ጄኮብ ላይ ፖሊሶች ከጀርባው ተኩሰውበታል። እሁድ በኪኖሻ ግዛት ከተተኮሰበት በኋላ በመላው ዊስኮንሰን ተቃውሞ ተቀጣጥሏል። በፖርትላንድ፣ ሚኒሶታና ሌሎችም ግዛቶች ተቃውሞው ቀጥሏል። ከወራት በፊት ጆርጅ ፍሎይድ በፖሊስ መገደሉን በመቃወም በመላው አገሪቱ የ ‘ብላክ ላይቭስ ማተር’ [የጥቁሮች ሕይወት ዋጋ አላት] ሰልፎች መካሄዳቸው አይዘነጋም። ደብሊውቲኤ የተባለው የሜዳ ቴኒስ ውድድር አዘጋጆች እስከ አርብ ድረስ ጨዋታው እንደተሰረዘ አስታውቀዋል። “የዘር መድልዎና ኢፍትሐዊነትን የቴኒስ ስፓርት እንደሚቃወም ማሳየት እንፈልጋለን” የሚል መግለጫም አውጥተዋል። ናዮሚ ኦሳካ ከግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ መውጣቷን መግለጿን ተከትሎ ነበር ይህ መግለጫ የወጣው። በጃፓንኛና በእንግሊዘኛ በጻፈችው ትዊት “ቴኒስ ስላልተጫወትኩ ትልቅ ነገር ይፈጠራል ብዬ አልጠብቅም። ነገር ግን ነጭ ተጫዋቾች በሚበዙበት ስፖርት ውስጥ አንዳች ውይይት እንዲጀመር ምክንያት ከሆንኩኝ ወደ ትክክለኛ አቅጣጫ እየተራመድን ነው” ብላለች። ናዮሚ አያይዛም “ጥቁሮች በፖሊሶች እየተገደሉ መሆኑን ሳይ ያመኛል” ስትል ሀዘኗን ገልጻለች። ጃፓናዊና የሄይቲ ውህድ የሆነችው ናዮሚ፤ ጃፓን ውስጥ የዘረኝነት ሰለባ ናት። ማስታወቂያዎች ላይ የቆዳ ቀለሟን ሲያነጡ፤ ቆዳዋን ነጭ ማድርግ አለባት እያሉ የሚሳለቁ ኮሜዲያኖችም አሉ። በስፓርቱ ዓለም ጄኮብ ብሌክ ላይ መተኮሱን የተቃወሙ ሌሎችም አሉ። የቅርጫት ኳስ ቡድኑ ሚልዋኪ ባክስ ከውድድር መውጣታቸውን ተከትሎ ኤንቢኤ ሦስት ግጥሚያዎች ሰርዟል። ሁለት የቤዝቦል ጨዋታዎችም ተሰርዘዋል። ፖሊሶች ጄኮብ ላይ የተኮሱት ያሳለፍነው እሁድ ሦስት ልጆቹ ወደ ነበሩበት መኪና ሲገባ ነው። አሁን ሆስፒታል ውስጥ እያገገመ ሲሆን፤ ጠበቃው ከዚህ በኋላ መራመድ ከቻለ ተዓምር ነው ብለዋል። ፖሊሶች ጄኮብ ላይ ሰባት ጊዜ መተኮሳቸውን ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞ ሁለት ሰዎች ተገድለዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-53929600 |
2health
| ረመዳን፡ ጾም በሰውነታችን ውስጥ የሚያስከትለው ለውጥና የሚሰጠው ጥቅም | ታላቁ የረመዳን ጾም ወቅት እነሆ ተጀምሯል። በመላው ዓለም በሚገኙ ሙስሊሞች ዘንድ በጉጉት የሚተበቀው ይህ ወቅት ቀኑ በጾም ምሽት ላይ ደግሞ ከቤተሰብና ከዘመድ ጋር ተሰብስቦ በአንድነት ማፍጠር የተለመደ ነው። ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ዓለማችን በገጠማት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በአንድ ላይ ተሰብስቦ ሐይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶችን መካፈልና ከተለያዩ ሰዎች ጋር መሰባሰብ እንዲቀር ይመከራል። ስለዚህም በሐይማኖት አባቶች የሚሰጠውን ምክር ተግባራዊ በማድረግ ይህንን ቅዱስ የጾም ወቅት እራሳችንንና ሌሎችን በመጠበቅ ልናሳልፈው ይገባል። በወረርሽኙ ምክንያት ምዕመናን ቀደም ሲል ሲያከናውኗቸው የነበሩ የጋር ሥርዓቶችን ማድረግ ባይችሉም፤ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ከቅርብ የቤተሰብ አባላቸው ጋር የተለመደውን ሥርዓት መፈጸም ይችላሉ ተብሏል። መጾም ታላቅ መንፈሳዊ ጸጋ እንደሚያስገኝ የሐይማኖት አባቶች ይናገራሉ። ከዚህ ባሻገር ደግሞ የጤና ባለሙያዎች ጾም ከሚያስገኘው መንፈሳዊ በረከት በተጨማሪ ለአካላዊ ጤንነት የሚሰጠው ጠቀሜታ አለው ይላሉ። ዝርዝሩን እነሆ. . . በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ረመዳንን በጾም ያሳልፋሉ። ጀንበር ወጥታ እስክትጠልቅ ድረስ። ሰውነታችን ከጾም ጋር የሚተዋወቀው ለመጨረሻ ጊዜ ምግብ ከቀመስን ከስምንት ሰዓታት በኋላ ነው። ይህም ማለት አንጀታችን ከተመገብነው ምግብ የሚያገኛቸውን ንጥረ ነገሮች በሙሉ አሟጦ ከጨረሰ በኋላ ነው የሚሆነው። ከዚህ በኋላ ሰውነታችን ተስፋ ይቆርጥና ፊቱን ጡንቻችንና ጉበታችን ውስጥ ወደተከማቸ ጉሉኮስ ያዞራል። የተቀረው የሰውነታችን አካል ጉልበት የሚያገኘውም ከዚህ የመጠባበቂያ 'ግምጃ ቤት' ከሚያገኘው ኃይል ይሆናል ማለት ነው። ከጡንቻና ከጉበት የጉሉኮስ ክምችት ሲያልቅ ሰውነታችን ሌላ አማራጭ ስለማይኖረው ስብን (Fat) ማቃጠል ይጀምራል። ከዚህ በኋላ ሙቀትና ጉልበትን የሚያገኘውም ከሌላ ሳይሆን ስብን በማቃጠል ነው። በዚህ ሂደት ውስጥ ታዲያ መልካም ነገሮች ይከሰታሉ። የሚቃጠለው ስብ በመሆኑ ክብደት መቀነስ፣ የኮሌስትሮል መጠን መውረድ ይኖራል። የስኳር መጠናችን በዚህ ወቅት ዝቅ ማለቱ አይቀርም። ሆኖም በደማችን ውስጥ የሚገኘው የስኳር መጠን ስለሚቀንስ ድካምና መዛልን ያስከትልብናል። ይህን ተከትሎ መጠነኛ ራስ ምታት፣ ማቅለሽለሽና መልካም ያልሆነ የአፍ ጠረን ሊከተል ይችላል። ይህ የሚሆነው በረሀብ ምክንያት ሆዳችንን ሲሞረሙረንና ያለ ምግብ መቆየቱ ለሰውነታችን እየከበደው ሲመጣ ነው። ከ3-7ኛ ቀን፤ ሰውነታችን በፈሳሽ እጥረት የሚጎዳበት ጊዜ ሰውነታችሁ ጾሙን እየተለማመደ ሲመጣ በውስጣችን የሚገኘው የስብ ክምችት እየተሰባበረ ራሱን ወደ የደም ስኳርነት (Blood sugar) ይለውጣል። የምንወስደው ፈሳሽ መጠን እየቀነሰ መምጣቱ በሰውነታችን ውስጥ ያለው ፈሳሽ ወደመሟጠጥ (ዲሃይድሬሽን) ስለሚያመራ በ"ማፍጠሪያ" ሰዓትና ከዚያም በኋላ ባለው የሌሊቱ ክፍለ ጊዜ በርከት ያሉ ፈሳሾችን መውሰድ ይመከራል። በጾም መግደፊያ ሰዓት የምትወስዱት የምግብ መጠን ጉልበት ሰጪ የሆኑ ተመጣጣኝ ምግቦችን ማግኘት ይኖርበታል። በፕሮቲን ከበለጸጉ ምግቦች ባሻገር ጨው እና በርከት ያለ ውኃ ከሌሎች የተመጣጠኑ ምግቦች ጋር ማግኘት ለሰውነታችን መልካም ሁኔታን ይፈጥራል። ከ8ኛ-15ኛ ቀናት በዚህ ጊዜ ሰውነታችን ጾሙን ተላምዶታል። በዚህም የተነሳ ድካምና መዛሉ እንደመጀመሪያዎቹ ጊዜያት ይሆናል ተብሎ አይጠበቅም። ዶክተር ራዚን ማህሩፍ የአኔስቴሺያና የጽኑ ሕሙማን ሕክምና አማካሪ ናቸው። በኬምብሪጅ አዴንብሩክ ሆስፒታል ውስጥ ነው የሚሠሩት። እርሳቸው እንደሚሉት በዚህ ጊዜ ጾሙ ለሰውነታችን ሌላም በጎ ጎን ይዞ ይመጣል። ለምሳሌ በሌላው ጊዜ በርከታ ያለ ካሎሪ ያላቸው ምግቦችን የምንወስድ ከነበረ ሰውነታችን ሥራዎችን በአግባቡ ለመፈፀም ፈተና ውስጥ ይወድቅ ነበር። ወይም ደግሞ እክል ይገጥመዋል። በጾም ጊዜ ግን ይህ ሁኔታ ይስተካከላል። "ምክንያቱም የካሎሪ ክምችት ስለማይበዛበት ሰውነታችን ወደ ሌሎች ሥራዎች ትኩረቱን ያደርጋል" ይላሉ ሐኪሙ። ለዚህም ነው "ጾም ኢንፌክሽን በመዋጋትና ጤናን በመመለስ አስተዋጽኦ የሚኖረው።" ከ16ኛ- 30ኛ ያሉ ቀናት በረመዳን ሁለተኛው ምዕራፍ (ከ15ኛው ቀን ጀምሮ) ሰውነት ሙሉ በሙሉ ጾሙን ይላመዳል። በዚህ ጊዜ እነ ደንዳኔ፣ ጉበት፣ ኩላሊት እንዲሁም ቆዳ ሁሉም ራሳቸውን በማጽዳት ሂደት (ዲቶክሲፊኬሽን) ውስጥ ነው የሚሆኑት። ዶክተር ማህሩፍ እንደሚሉት በዚህ ወቅት ጤና ተመልሶ፣ ሰውነታችን የቀድሞውን ጉልበቱን የሚያገኝበትና የማስታወስ አቅምና ትኩረት የማድረግ ብቃት ወደ ቀድሞው ሁኔታ የሚመለስበት ጊዜ ነው። በዚህ ጊዜ ሰውነታችን ጉልበት ለማግኘት ወደ ፕሮቲን መሄድ አይኖርበትም። ይህ የሚሆነው ብዙውን ጊዜ ረሀብ ሲሰማንና ሰውነታችን ከጡንቻዎቻችን እየቀሰመ የሚወስደውን ምግብ ማደን ሲጀምር ነው። በዚህ መንገድ የሚቀጥለው ግን ለቀናትና ለሳምንታት በተከታታይ ስንጾም ነው። የረመዳን ጾም የሚጸናው የየዕለቱ ጀምበር ወጥታ እስክትጠልቅ ብቻ ስለሆነ ሰውነታችን ጉልበት ከምግብ እንዲያገኝ የ"ኢፍጣር" ሰዓት ዕድል ይሰጠዋል። ፈሳሽም እንደልብ ያገኛል። ይህ ጡንቻዎቻችን ውስጥ ያለን ክምችት ለመጠባበቂያነት ያቆይልናል። የተወሰነ ኪሎ እንድንቀንስም ይረዳናል። ይህም ለሰውነት መልካም ነገር ነው። ጾም ጤናን ይጎዳል? የካምብሪጁ አዲንብሩክ ሆስፒታል ሐኪም ዶክተር ማሕሩፍ ምላሻቸው "እንደሁኔታው" የሚል ነው። እንደርሳቸው አመለካከት በርከት ያሉ ሁኔታዎች ጾምን ለሰውነታችን ጎጂም ጠቃሚም ሊያደርጉት ይችላሉ። ጾም ለሰውነታችን መልካም የሚሆንበት አንዱ ምክንያት መቼ ምን መብላት እንዳለብን ትኩረት እንድናደርግ ስለሚያስችለን ነው። ሁለተኛው ክብደታችንን መቆጣጠርና፣ የካሎሪ መጠን መወሰን ስለሚያስችል ነው። ለወር ያህል መጾም እምብዛምም የሚያመጣው የጤና እክል ባይኖርም ከዚያ በኋላ ግን ለተከታታይ ጊዜ ያለማቋረጥ መጾም ግን አስቸጋሪ ሊሆን እንደሚችል ሐኪሙ ሳይጠቁሙ አያልፉም። እንደ ሐኪሙ ማብራሪያ ያለማቋረጥ መጾም በቋሚነት ኪሎ ለመቀነስ አይረዳም። ምክንያቱም ከሆነ ጊዜ በኋላ ሰውነታችን ስብን ወደ ጉልበት መቀየር ያቆምል። ከዚያ ይልቅ ፊቱን ወደ ጡንቻዎቻችን ነው የሚያዞረው። ይህ ደግሞ ጤናማ አይደለም። ምክንያቱም ሰውነታችን ከሆነ ወቅት በኋላ "በመራብ ስሜት" ላይ ስለሚቆይ ነው። ሐኪሙ እንደሚሉት ከረመዳን ውጭ መጾም ቢያስፈልግ እንኳ በሳምንት ሁለት ቀን ብቻ እያፈራረቁ መጾም በመደዳ ለተከታታይ ቀናት ከመጾም እጅግ የተሻለ ጤናማ ተግባር ነው። "ረመዳን በአግባቡ ከተጾመና በቂ ፈሳሽ በቀን ውስጥ ማግኘት ከተቻለ፣ ጠቃሚ የጡንቻ ክምችቶች ሳይቃጠል ኪሎ መቀነስ ስለሚያስችል የጤና በረከትም ያስገኛል" ይላሉ እኚሁ ሐኪም። | ረመዳን፡ ጾም በሰውነታችን ውስጥ የሚያስከትለው ለውጥና የሚሰጠው ጥቅም ታላቁ የረመዳን ጾም ወቅት እነሆ ተጀምሯል። በመላው ዓለም በሚገኙ ሙስሊሞች ዘንድ በጉጉት የሚተበቀው ይህ ወቅት ቀኑ በጾም ምሽት ላይ ደግሞ ከቤተሰብና ከዘመድ ጋር ተሰብስቦ በአንድነት ማፍጠር የተለመደ ነው። ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ዓለማችን በገጠማት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በአንድ ላይ ተሰብስቦ ሐይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶችን መካፈልና ከተለያዩ ሰዎች ጋር መሰባሰብ እንዲቀር ይመከራል። ስለዚህም በሐይማኖት አባቶች የሚሰጠውን ምክር ተግባራዊ በማድረግ ይህንን ቅዱስ የጾም ወቅት እራሳችንንና ሌሎችን በመጠበቅ ልናሳልፈው ይገባል። በወረርሽኙ ምክንያት ምዕመናን ቀደም ሲል ሲያከናውኗቸው የነበሩ የጋር ሥርዓቶችን ማድረግ ባይችሉም፤ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ከቅርብ የቤተሰብ አባላቸው ጋር የተለመደውን ሥርዓት መፈጸም ይችላሉ ተብሏል። መጾም ታላቅ መንፈሳዊ ጸጋ እንደሚያስገኝ የሐይማኖት አባቶች ይናገራሉ። ከዚህ ባሻገር ደግሞ የጤና ባለሙያዎች ጾም ከሚያስገኘው መንፈሳዊ በረከት በተጨማሪ ለአካላዊ ጤንነት የሚሰጠው ጠቀሜታ አለው ይላሉ። ዝርዝሩን እነሆ. . . በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ረመዳንን በጾም ያሳልፋሉ። ጀንበር ወጥታ እስክትጠልቅ ድረስ። ሰውነታችን ከጾም ጋር የሚተዋወቀው ለመጨረሻ ጊዜ ምግብ ከቀመስን ከስምንት ሰዓታት በኋላ ነው። ይህም ማለት አንጀታችን ከተመገብነው ምግብ የሚያገኛቸውን ንጥረ ነገሮች በሙሉ አሟጦ ከጨረሰ በኋላ ነው የሚሆነው። ከዚህ በኋላ ሰውነታችን ተስፋ ይቆርጥና ፊቱን ጡንቻችንና ጉበታችን ውስጥ ወደተከማቸ ጉሉኮስ ያዞራል። የተቀረው የሰውነታችን አካል ጉልበት የሚያገኘውም ከዚህ የመጠባበቂያ 'ግምጃ ቤት' ከሚያገኘው ኃይል ይሆናል ማለት ነው። ከጡንቻና ከጉበት የጉሉኮስ ክምችት ሲያልቅ ሰውነታችን ሌላ አማራጭ ስለማይኖረው ስብን (Fat) ማቃጠል ይጀምራል። ከዚህ በኋላ ሙቀትና ጉልበትን የሚያገኘውም ከሌላ ሳይሆን ስብን በማቃጠል ነው። በዚህ ሂደት ውስጥ ታዲያ መልካም ነገሮች ይከሰታሉ። የሚቃጠለው ስብ በመሆኑ ክብደት መቀነስ፣ የኮሌስትሮል መጠን መውረድ ይኖራል። የስኳር መጠናችን በዚህ ወቅት ዝቅ ማለቱ አይቀርም። ሆኖም በደማችን ውስጥ የሚገኘው የስኳር መጠን ስለሚቀንስ ድካምና መዛልን ያስከትልብናል። ይህን ተከትሎ መጠነኛ ራስ ምታት፣ ማቅለሽለሽና መልካም ያልሆነ የአፍ ጠረን ሊከተል ይችላል። ይህ የሚሆነው በረሀብ ምክንያት ሆዳችንን ሲሞረሙረንና ያለ ምግብ መቆየቱ ለሰውነታችን እየከበደው ሲመጣ ነው። ከ3-7ኛ ቀን፤ ሰውነታችን በፈሳሽ እጥረት የሚጎዳበት ጊዜ ሰውነታችሁ ጾሙን እየተለማመደ ሲመጣ በውስጣችን የሚገኘው የስብ ክምችት እየተሰባበረ ራሱን ወደ የደም ስኳርነት (Blood sugar) ይለውጣል። የምንወስደው ፈሳሽ መጠን እየቀነሰ መምጣቱ በሰውነታችን ውስጥ ያለው ፈሳሽ ወደመሟጠጥ (ዲሃይድሬሽን) ስለሚያመራ በ"ማፍጠሪያ" ሰዓትና ከዚያም በኋላ ባለው የሌሊቱ ክፍለ ጊዜ በርከት ያሉ ፈሳሾችን መውሰድ ይመከራል። በጾም መግደፊያ ሰዓት የምትወስዱት የምግብ መጠን ጉልበት ሰጪ የሆኑ ተመጣጣኝ ምግቦችን ማግኘት ይኖርበታል። በፕሮቲን ከበለጸጉ ምግቦች ባሻገር ጨው እና በርከት ያለ ውኃ ከሌሎች የተመጣጠኑ ምግቦች ጋር ማግኘት ለሰውነታችን መልካም ሁኔታን ይፈጥራል። ከ8ኛ-15ኛ ቀናት በዚህ ጊዜ ሰውነታችን ጾሙን ተላምዶታል። በዚህም የተነሳ ድካምና መዛሉ እንደመጀመሪያዎቹ ጊዜያት ይሆናል ተብሎ አይጠበቅም። ዶክተር ራዚን ማህሩፍ የአኔስቴሺያና የጽኑ ሕሙማን ሕክምና አማካሪ ናቸው። በኬምብሪጅ አዴንብሩክ ሆስፒታል ውስጥ ነው የሚሠሩት። እርሳቸው እንደሚሉት በዚህ ጊዜ ጾሙ ለሰውነታችን ሌላም በጎ ጎን ይዞ ይመጣል። ለምሳሌ በሌላው ጊዜ በርከታ ያለ ካሎሪ ያላቸው ምግቦችን የምንወስድ ከነበረ ሰውነታችን ሥራዎችን በአግባቡ ለመፈፀም ፈተና ውስጥ ይወድቅ ነበር። ወይም ደግሞ እክል ይገጥመዋል። በጾም ጊዜ ግን ይህ ሁኔታ ይስተካከላል። "ምክንያቱም የካሎሪ ክምችት ስለማይበዛበት ሰውነታችን ወደ ሌሎች ሥራዎች ትኩረቱን ያደርጋል" ይላሉ ሐኪሙ። ለዚህም ነው "ጾም ኢንፌክሽን በመዋጋትና ጤናን በመመለስ አስተዋጽኦ የሚኖረው።" ከ16ኛ- 30ኛ ያሉ ቀናት በረመዳን ሁለተኛው ምዕራፍ (ከ15ኛው ቀን ጀምሮ) ሰውነት ሙሉ በሙሉ ጾሙን ይላመዳል። በዚህ ጊዜ እነ ደንዳኔ፣ ጉበት፣ ኩላሊት እንዲሁም ቆዳ ሁሉም ራሳቸውን በማጽዳት ሂደት (ዲቶክሲፊኬሽን) ውስጥ ነው የሚሆኑት። ዶክተር ማህሩፍ እንደሚሉት በዚህ ወቅት ጤና ተመልሶ፣ ሰውነታችን የቀድሞውን ጉልበቱን የሚያገኝበትና የማስታወስ አቅምና ትኩረት የማድረግ ብቃት ወደ ቀድሞው ሁኔታ የሚመለስበት ጊዜ ነው። በዚህ ጊዜ ሰውነታችን ጉልበት ለማግኘት ወደ ፕሮቲን መሄድ አይኖርበትም። ይህ የሚሆነው ብዙውን ጊዜ ረሀብ ሲሰማንና ሰውነታችን ከጡንቻዎቻችን እየቀሰመ የሚወስደውን ምግብ ማደን ሲጀምር ነው። በዚህ መንገድ የሚቀጥለው ግን ለቀናትና ለሳምንታት በተከታታይ ስንጾም ነው። የረመዳን ጾም የሚጸናው የየዕለቱ ጀምበር ወጥታ እስክትጠልቅ ብቻ ስለሆነ ሰውነታችን ጉልበት ከምግብ እንዲያገኝ የ"ኢፍጣር" ሰዓት ዕድል ይሰጠዋል። ፈሳሽም እንደልብ ያገኛል። ይህ ጡንቻዎቻችን ውስጥ ያለን ክምችት ለመጠባበቂያነት ያቆይልናል። የተወሰነ ኪሎ እንድንቀንስም ይረዳናል። ይህም ለሰውነት መልካም ነገር ነው። ጾም ጤናን ይጎዳል? የካምብሪጁ አዲንብሩክ ሆስፒታል ሐኪም ዶክተር ማሕሩፍ ምላሻቸው "እንደሁኔታው" የሚል ነው። እንደርሳቸው አመለካከት በርከት ያሉ ሁኔታዎች ጾምን ለሰውነታችን ጎጂም ጠቃሚም ሊያደርጉት ይችላሉ። ጾም ለሰውነታችን መልካም የሚሆንበት አንዱ ምክንያት መቼ ምን መብላት እንዳለብን ትኩረት እንድናደርግ ስለሚያስችለን ነው። ሁለተኛው ክብደታችንን መቆጣጠርና፣ የካሎሪ መጠን መወሰን ስለሚያስችል ነው። ለወር ያህል መጾም እምብዛምም የሚያመጣው የጤና እክል ባይኖርም ከዚያ በኋላ ግን ለተከታታይ ጊዜ ያለማቋረጥ መጾም ግን አስቸጋሪ ሊሆን እንደሚችል ሐኪሙ ሳይጠቁሙ አያልፉም። እንደ ሐኪሙ ማብራሪያ ያለማቋረጥ መጾም በቋሚነት ኪሎ ለመቀነስ አይረዳም። ምክንያቱም ከሆነ ጊዜ በኋላ ሰውነታችን ስብን ወደ ጉልበት መቀየር ያቆምል። ከዚያ ይልቅ ፊቱን ወደ ጡንቻዎቻችን ነው የሚያዞረው። ይህ ደግሞ ጤናማ አይደለም። ምክንያቱም ሰውነታችን ከሆነ ወቅት በኋላ "በመራብ ስሜት" ላይ ስለሚቆይ ነው። ሐኪሙ እንደሚሉት ከረመዳን ውጭ መጾም ቢያስፈልግ እንኳ በሳምንት ሁለት ቀን ብቻ እያፈራረቁ መጾም በመደዳ ለተከታታይ ቀናት ከመጾም እጅግ የተሻለ ጤናማ ተግባር ነው። "ረመዳን በአግባቡ ከተጾመና በቂ ፈሳሽ በቀን ውስጥ ማግኘት ከተቻለ፣ ጠቃሚ የጡንቻ ክምችቶች ሳይቃጠል ኪሎ መቀነስ ስለሚያስችል የጤና በረከትም ያስገኛል" ይላሉ እኚሁ ሐኪም። | https://www.bbc.com/amharic/news-44128047 |
0business
| የኤሎን መስክ ኩባንያ የነበረውን አብዛኛውን ቢትኮይን መልሶ ሸጠ | ከአንድ ዓመት በፊት በክሪፕቶከረንሲ ላይ ብዙ ኢንቨስት አድርጎ የነበረው የኤሎም መስክ ተቋም ቴስላ፤ ገዝቶት የነበረውን አብዛኛውን ቢትኮይን መልሶ ሸጠ። የኤሌክትሪክ መኪና አምራቹ ቴስላ ከነበረው ቢትኮይን 75 በመቶ የሚሆነውን መሸጡ ተገልጿል። ቴስላ የሸጠው ቢትኮይን እአአ 2021 መጨረሻ ላይ 2 ቢሊዮን ዶላር ያወጣ ነበር። ኩባንያው ዋጋው እየወደቀ ካለው የክሪፕቶካረንሲ ኢንቨስትመንት እራሱን እያራቀ ነው ተብሏል። የቢትኮይን ዋጋ በጥቂት ወራት ውስጥ 50 በመቶ በላይ ዋጋውን አጥቷል። ትልቅ ስም ካላቸው የክሪፕቶከረንሲ ወዳጆች መካከል የቴስላ ኩባንያ ባለቤት ኤሎን መስክ ተጠቃሽ ነው። ቴስላ እአአ 2021 መጀመሪያ ላይ 1.5 ቢሊዮን ዶላር አውጥቶ ቢትኮይን ላይ ኢንቨስት ማድረጉ የክሪፕቶከረንሲ ዋጋን ከፍ አድርጎት ነበር። ቴስላ ለሚሸጣቸው የኤሌክትሪክ መኪኖች ቢትኮይንን በክፍያ መልክ እቀባላለሁ ብሎ የነበረ ቢሆንም፤ የቢትኮይን ግብይት የሚሳለጥበት ሥርዓት ከፍተኛ ኃይል እንደሚፈልግ በማስታወስ ቴስላ የከባቢ አየርን ለመጠበቅ ሲባል ቢትኮይንን እንደ ክፍያ አማራጭ ማቅረቤን ትቼዋለሁ ብሏል። ቢትኮይን ከስምንት ወራት ገደማ በፊት ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቶ አንድ ቢትኮይን 70 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ጋር ተጠግቶ ነበር። ዛሬ ላይ ግን የአንድ የቢትኮይን ዋጋ ከ25 ሺህ ዶላር በታች እየተሸጠ ነው። ቴስላ ከፍተኛ ገንዘብ አውጥቶ የሸመተውን ክሪፕቶከረንሲ መልሶ እንደማይሸጥ የኩባንያው ዋና ሥራ አስኪያጅ ኤሎን መስክ በወቅቱ በትዊተር ጉጹ ላይ ጽፎ ነበር። ኩባንያው ገዝቶት የነበረውን ቢትኮይን መልሶ እንደሸጠ ያሳወቀው የሩብ ዓመት ሪፖርቱን ይፋ ባደረገበት ጊዜ ነው። ቴስላ ትርፋማነቴን ከጎዱት ምክንያቶች መካከል አንዱ ቢትኮይን ነው ብሏል። በአውሮፓውያኑ 2022 የኤሌክትሪክ መኪና አምራቹ ኩባንያ የገበያ ድርሻ በ40 በመቶ ወርዷል። | የኤሎን መስክ ኩባንያ የነበረውን አብዛኛውን ቢትኮይን መልሶ ሸጠ ከአንድ ዓመት በፊት በክሪፕቶከረንሲ ላይ ብዙ ኢንቨስት አድርጎ የነበረው የኤሎም መስክ ተቋም ቴስላ፤ ገዝቶት የነበረውን አብዛኛውን ቢትኮይን መልሶ ሸጠ። የኤሌክትሪክ መኪና አምራቹ ቴስላ ከነበረው ቢትኮይን 75 በመቶ የሚሆነውን መሸጡ ተገልጿል። ቴስላ የሸጠው ቢትኮይን እአአ 2021 መጨረሻ ላይ 2 ቢሊዮን ዶላር ያወጣ ነበር። ኩባንያው ዋጋው እየወደቀ ካለው የክሪፕቶካረንሲ ኢንቨስትመንት እራሱን እያራቀ ነው ተብሏል። የቢትኮይን ዋጋ በጥቂት ወራት ውስጥ 50 በመቶ በላይ ዋጋውን አጥቷል። ትልቅ ስም ካላቸው የክሪፕቶከረንሲ ወዳጆች መካከል የቴስላ ኩባንያ ባለቤት ኤሎን መስክ ተጠቃሽ ነው። ቴስላ እአአ 2021 መጀመሪያ ላይ 1.5 ቢሊዮን ዶላር አውጥቶ ቢትኮይን ላይ ኢንቨስት ማድረጉ የክሪፕቶከረንሲ ዋጋን ከፍ አድርጎት ነበር። ቴስላ ለሚሸጣቸው የኤሌክትሪክ መኪኖች ቢትኮይንን በክፍያ መልክ እቀባላለሁ ብሎ የነበረ ቢሆንም፤ የቢትኮይን ግብይት የሚሳለጥበት ሥርዓት ከፍተኛ ኃይል እንደሚፈልግ በማስታወስ ቴስላ የከባቢ አየርን ለመጠበቅ ሲባል ቢትኮይንን እንደ ክፍያ አማራጭ ማቅረቤን ትቼዋለሁ ብሏል። ቢትኮይን ከስምንት ወራት ገደማ በፊት ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቶ አንድ ቢትኮይን 70 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ጋር ተጠግቶ ነበር። ዛሬ ላይ ግን የአንድ የቢትኮይን ዋጋ ከ25 ሺህ ዶላር በታች እየተሸጠ ነው። ቴስላ ከፍተኛ ገንዘብ አውጥቶ የሸመተውን ክሪፕቶከረንሲ መልሶ እንደማይሸጥ የኩባንያው ዋና ሥራ አስኪያጅ ኤሎን መስክ በወቅቱ በትዊተር ጉጹ ላይ ጽፎ ነበር። ኩባንያው ገዝቶት የነበረውን ቢትኮይን መልሶ እንደሸጠ ያሳወቀው የሩብ ዓመት ሪፖርቱን ይፋ ባደረገበት ጊዜ ነው። ቴስላ ትርፋማነቴን ከጎዱት ምክንያቶች መካከል አንዱ ቢትኮይን ነው ብሏል። በአውሮፓውያኑ 2022 የኤሌክትሪክ መኪና አምራቹ ኩባንያ የገበያ ድርሻ በ40 በመቶ ወርዷል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cev51ryzz9xo |
5sports
| የ2020 ቶኪዮ ኦሊምፒክ፡ በቶኪዮ ኦሊምፒክ የሚጠበቁ ኢትዮጵያውያንና አፍሪካውያን ተወዳዳሪዎች እነማን ናቸው? | አፍሪካውያን ሯጮች በተለይም ኢትዮጵያውያንና ኬንያውያን አትሌቶች በመካከለኛ እና በረጅም ርቀት የሩጫ መስኮች በኦሊምፒክ ውድድሮች ላይ የበላይ ናቸው። ባለፈው ዓመት ሊካሄድ ታቅዶ በኮሮናቫይረስ ወረርሽን ምክንያት ወደዚህ ዓመት የተሸጋገረው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ከዚህ በፊት በውድድሩ ውስጥ ያልነበሩ ስፖርቶችን በማካተት በዚህ ሳምንት መካሄድ ይጀምራል። በዚህም መሰረት አምስት የስፖርት አይነቶች በውድድሩ ውስጥ እንደተካተቱ ታውቋል፤ እነሱም የውሃ ላይ ሸርተቴ (ሰርፊንግ)፣ ተራራ መውጣት (ክላይምቢንግ)፣ ቤዝቦል፣ ስኬት ቦርዲንግ እና ካራቴ ሲሆኑ የተወሰኑ አፍሪካውያን በእነዚህ ዘርፎቹ ይወዳደራሉ። አርብ ሐምሌ 16/2013 ዓ.ም የቶኪዮው ኦሊምፒክ ሲጀምር በተለያዩ ስፖርት ውድድሮች የሚሳተፉ በርካታ አፍሪካውያን ሲኖሩ ኢትዮጵያም በኦሊምፒክ ስሟ በሚጠራባቸው ዘርፎች የሚሳተፉ ስፖርተኞችን ልካለች። ከኢትዮጵያውያን በተጨማሪ በርካታ አገራት በተለያዩ ዘርፎች በውድድሩ ይሳተፋሉ ከእነዚህ መካከል በቶኪዮው ኦሊምፒክ ላይ ትኩረት ከተደረገባቸው መካከል ከስኬታማዎቹ እና ከአዲሶቹ መካከል የተወሰኑትን ወድድር ዘርፎቹ እንዲህ አቅርበናል። ሥነ ዘዴ እነዚህ የአፍሪካ ስፖርተኞች የተለያዩ የአህጉሪቱን ክልሎች ይወክላሉ ተብለው ነው የቀረቡት። የተመረጡትም በኦሊምፒክ ተሳትፏቸው፣ ባገኙት ሜዳሊያ ብዛት እና ከሚወዳደሩበት የተለየ የስፖርት አይነት አንጻር ነው። ተሳታፊዎች የአርትኦት ዝግጅት፡ ንኬቺ ኦግቦና፣ ፕሪንሰስ አቡሜሬ እና ሙቶኒ ሙቺሪ። ዲዛይን፡ ኦላኒዬ አዴቢምፔ እና ሚሊሰንት ዋቺራ። የድረ ገጽ ዝግጅት፡ ፒዩሪቲ ቢሪር። ተጨማሪ፡ ሳሊ ሞራሌስ እና ሴሌስቲን ካሮኔይ ምስሎች፡ ጌቲ ኢሜጅስ፣ የዓለም ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን፣ ኤኤፍፒ፣ ናይጄሪያን ኒውስ፣ የናይጄሪያ የውሃ ስፖርቶች ፌዴሬሽን፣ መክሰብ ደበሳይ፣ የሞዛምቢክ የውሃ ቀዘፋ ቡድን፣ ጊያና ፋሩክ፣ ኢፒኤ፣ ፕሬስፎከስ/ኒውስ ፒክስ እና ፒኤ፣ ኤርዊዘርየት ትዊተር፣ ብሩስ ቫይን እና ኦሊምፒክ፣ ክላይምብ ዛምቢያ፣ ዲደብሊው እና የሞዛምቢክ ቡድን። | የ2020 ቶኪዮ ኦሊምፒክ፡ በቶኪዮ ኦሊምፒክ የሚጠበቁ ኢትዮጵያውያንና አፍሪካውያን ተወዳዳሪዎች እነማን ናቸው? አፍሪካውያን ሯጮች በተለይም ኢትዮጵያውያንና ኬንያውያን አትሌቶች በመካከለኛ እና በረጅም ርቀት የሩጫ መስኮች በኦሊምፒክ ውድድሮች ላይ የበላይ ናቸው። ባለፈው ዓመት ሊካሄድ ታቅዶ በኮሮናቫይረስ ወረርሽን ምክንያት ወደዚህ ዓመት የተሸጋገረው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ከዚህ በፊት በውድድሩ ውስጥ ያልነበሩ ስፖርቶችን በማካተት በዚህ ሳምንት መካሄድ ይጀምራል። በዚህም መሰረት አምስት የስፖርት አይነቶች በውድድሩ ውስጥ እንደተካተቱ ታውቋል፤ እነሱም የውሃ ላይ ሸርተቴ (ሰርፊንግ)፣ ተራራ መውጣት (ክላይምቢንግ)፣ ቤዝቦል፣ ስኬት ቦርዲንግ እና ካራቴ ሲሆኑ የተወሰኑ አፍሪካውያን በእነዚህ ዘርፎቹ ይወዳደራሉ። አርብ ሐምሌ 16/2013 ዓ.ም የቶኪዮው ኦሊምፒክ ሲጀምር በተለያዩ ስፖርት ውድድሮች የሚሳተፉ በርካታ አፍሪካውያን ሲኖሩ ኢትዮጵያም በኦሊምፒክ ስሟ በሚጠራባቸው ዘርፎች የሚሳተፉ ስፖርተኞችን ልካለች። ከኢትዮጵያውያን በተጨማሪ በርካታ አገራት በተለያዩ ዘርፎች በውድድሩ ይሳተፋሉ ከእነዚህ መካከል በቶኪዮው ኦሊምፒክ ላይ ትኩረት ከተደረገባቸው መካከል ከስኬታማዎቹ እና ከአዲሶቹ መካከል የተወሰኑትን ወድድር ዘርፎቹ እንዲህ አቅርበናል። ሥነ ዘዴ እነዚህ የአፍሪካ ስፖርተኞች የተለያዩ የአህጉሪቱን ክልሎች ይወክላሉ ተብለው ነው የቀረቡት። የተመረጡትም በኦሊምፒክ ተሳትፏቸው፣ ባገኙት ሜዳሊያ ብዛት እና ከሚወዳደሩበት የተለየ የስፖርት አይነት አንጻር ነው። ተሳታፊዎች የአርትኦት ዝግጅት፡ ንኬቺ ኦግቦና፣ ፕሪንሰስ አቡሜሬ እና ሙቶኒ ሙቺሪ። ዲዛይን፡ ኦላኒዬ አዴቢምፔ እና ሚሊሰንት ዋቺራ። የድረ ገጽ ዝግጅት፡ ፒዩሪቲ ቢሪር። ተጨማሪ፡ ሳሊ ሞራሌስ እና ሴሌስቲን ካሮኔይ ምስሎች፡ ጌቲ ኢሜጅስ፣ የዓለም ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን፣ ኤኤፍፒ፣ ናይጄሪያን ኒውስ፣ የናይጄሪያ የውሃ ስፖርቶች ፌዴሬሽን፣ መክሰብ ደበሳይ፣ የሞዛምቢክ የውሃ ቀዘፋ ቡድን፣ ጊያና ፋሩክ፣ ኢፒኤ፣ ፕሬስፎከስ/ኒውስ ፒክስ እና ፒኤ፣ ኤርዊዘርየት ትዊተር፣ ብሩስ ቫይን እና ኦሊምፒክ፣ ክላይምብ ዛምቢያ፣ ዲደብሊው እና የሞዛምቢክ ቡድን። | https://www.bbc.com/amharic/news-57911750 |
0business
| የኬንያና የሶማሊያ እሰጥ አገባ የጫት ንግድን እየጎዳው ነው ተባለ | ኬንያ እና ሶማሊያ የገቡበት ዲፕሊማሲያዊ እስጥ አገባ በጫት ንግድ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ማሳደሩ ተነገረ። የሶማሊያ መንግሥት ከኬንያ በሚገባ የጫት ምርት ላይ እግድ መጣሉን ተከትሎ ጫት አምራች ኬንያውያን ገበሬዎች ከፍተኛ ኪሰራ እየገጠማቸው መሆኑ ተግልጿል። ሶማሊያ ከወራት በፊት ከኬንያ በሚገባው የጫት ምርት ላይ እግድ የጣለችው የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ምክንያት በማድረግ ነበር። ይሁን እንጂ አሁንም ቢሆን የኬንያ የጫት ምርት ወደ ሶማሊያ ከመግባቱ በፊት ኬንያ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ይኖርባታል ትላለች ሶማሊያ። ሶማሊያ የኬንያን የጫት ምርት ወደ አገሬ ከማስገባቴ በፊት ኬንያ በውስጣዊ ጉዳዬ ጣልቃ ከመግባት መቆጠብ ይኖርባታል፣ የሶማሊያን አየር ክልል ማክበር ይኖርባታል፤ እንዲሁም እንደ ስኳር፣ ወተት እና ማር ያሉ የሶማሊያ ምርቶችን እንድትቀበል ጠይቃለች። ኬንያ በበኩሏ በሶማሊያ ውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ አለመግባቷን እና ፍትሃዊ ከሆነ የንግድ ስምምነት ለመድረስ ዝግጁ መሆኑኗን ትገልጻለች። ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ሶማሊያ ከኢትዮጵያ የጫት ምርት ማስገባቷን ቀጥላለች። ሶማሊያ በአብዛኛው የጫት ምርትን የምታገኘው ከኢትዮጵያና ከኬንያ ነው። በምስሥቃዊ ኬንያ የምትገኘው ሜሩ ጫት በማብቀል ትታወቃለች። ወደ ሶማሊያ ይላክ የነበረው የጫት ምርት ላይ እግድ መጣሉን ተከትሎ ጫት አምራች ገበሬዎች ለችግር ተጋልጠናል እያሉ ነው። የዘጠኝ ልጆች እናት የሆነችው ሜሪ ናቶንጃ “አረንጓዴው ወርቅ” የምትለውን ጫት ለበርካታ ዓመታት ስታመርት ቆይታለች። የጫት ምርት ወደ ዩናይትድ ኪንግደም እና ሶማሊያ በሚላክበት ወቅት ጥሩ ገቢ ታገኝ እንደነበረም ሜሪ ታስታውሳለች። ከስድስት ዓመታት በፊት ዩናይትድ ኪንግደም ጫት ወደ አገሬ አይገባም ስትል ወሰነች። ባሳለፍነው ዓመት ሕዳር ወር ላይም ሶማሊያ ከኬንያ በሚገባ የጫት ምርት ላይ ገደብ ጣለች። ይህን ጊዜ ሜሪ እሷ እና መሰል በሺዎች የሚቆጠሩ ጫት አምራች ገበሬዎች ሕይወታቸው መፈተኑን ትናገራለች። “ሕይወት ፈተና ሆኖብናል። ገንዘብ በእጃችን የለም። መልበስ እና መብላት ከባድ ሆኖብናል። ልጆቻችን ጾማቸውን እያደሩ ነው። በየሦስት ወሩ ምርት እየሰበሰብን ከአንድ እስከ አምስት ሺህ ዶላር እናገኝ ነበር። አሁን ግን አንድ ዶላር እንኳን ማግኘት አንችልም።” የኬንያ የጫት ነጋዴዎች ማኅበር እንደሚለው ከሆነ የኬንያ ጫት አምራች ገበሬዎች ከዚህ ቀደም እስከ 50 ቶን የሚመዝን ጫት ወደ ሶማሊያ በመላክ እስከ 140 ሺህ ዶላር ድረስ ገቢ ያስገኙ ነበር። አሁን ላይ ገበሬዎች ከምርታቸው እጅግ አነስተኛ የሚሆነውን ለኬንያ ገበያ ካቀረቡ በኋላ ሌላው ፈላጊ ስለሌለው ምርቱ እየተጣለ ነው ይላል ማኅበሩ። ባሳለፍነው ወር በሶማሊያ እና በኬንያ መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ አለመግባባት ተካሮ ሶማሊያ የኬንያን አምባሳደር አባራ በናይሮቢ የሚገኘውን አምባሳደሯን መጥራቷ ይታወሳል። | የኬንያና የሶማሊያ እሰጥ አገባ የጫት ንግድን እየጎዳው ነው ተባለ ኬንያ እና ሶማሊያ የገቡበት ዲፕሊማሲያዊ እስጥ አገባ በጫት ንግድ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ማሳደሩ ተነገረ። የሶማሊያ መንግሥት ከኬንያ በሚገባ የጫት ምርት ላይ እግድ መጣሉን ተከትሎ ጫት አምራች ኬንያውያን ገበሬዎች ከፍተኛ ኪሰራ እየገጠማቸው መሆኑ ተግልጿል። ሶማሊያ ከወራት በፊት ከኬንያ በሚገባው የጫት ምርት ላይ እግድ የጣለችው የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ምክንያት በማድረግ ነበር። ይሁን እንጂ አሁንም ቢሆን የኬንያ የጫት ምርት ወደ ሶማሊያ ከመግባቱ በፊት ኬንያ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ይኖርባታል ትላለች ሶማሊያ። ሶማሊያ የኬንያን የጫት ምርት ወደ አገሬ ከማስገባቴ በፊት ኬንያ በውስጣዊ ጉዳዬ ጣልቃ ከመግባት መቆጠብ ይኖርባታል፣ የሶማሊያን አየር ክልል ማክበር ይኖርባታል፤ እንዲሁም እንደ ስኳር፣ ወተት እና ማር ያሉ የሶማሊያ ምርቶችን እንድትቀበል ጠይቃለች። ኬንያ በበኩሏ በሶማሊያ ውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ አለመግባቷን እና ፍትሃዊ ከሆነ የንግድ ስምምነት ለመድረስ ዝግጁ መሆኑኗን ትገልጻለች። ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ሶማሊያ ከኢትዮጵያ የጫት ምርት ማስገባቷን ቀጥላለች። ሶማሊያ በአብዛኛው የጫት ምርትን የምታገኘው ከኢትዮጵያና ከኬንያ ነው። በምስሥቃዊ ኬንያ የምትገኘው ሜሩ ጫት በማብቀል ትታወቃለች። ወደ ሶማሊያ ይላክ የነበረው የጫት ምርት ላይ እግድ መጣሉን ተከትሎ ጫት አምራች ገበሬዎች ለችግር ተጋልጠናል እያሉ ነው። የዘጠኝ ልጆች እናት የሆነችው ሜሪ ናቶንጃ “አረንጓዴው ወርቅ” የምትለውን ጫት ለበርካታ ዓመታት ስታመርት ቆይታለች። የጫት ምርት ወደ ዩናይትድ ኪንግደም እና ሶማሊያ በሚላክበት ወቅት ጥሩ ገቢ ታገኝ እንደነበረም ሜሪ ታስታውሳለች። ከስድስት ዓመታት በፊት ዩናይትድ ኪንግደም ጫት ወደ አገሬ አይገባም ስትል ወሰነች። ባሳለፍነው ዓመት ሕዳር ወር ላይም ሶማሊያ ከኬንያ በሚገባ የጫት ምርት ላይ ገደብ ጣለች። ይህን ጊዜ ሜሪ እሷ እና መሰል በሺዎች የሚቆጠሩ ጫት አምራች ገበሬዎች ሕይወታቸው መፈተኑን ትናገራለች። “ሕይወት ፈተና ሆኖብናል። ገንዘብ በእጃችን የለም። መልበስ እና መብላት ከባድ ሆኖብናል። ልጆቻችን ጾማቸውን እያደሩ ነው። በየሦስት ወሩ ምርት እየሰበሰብን ከአንድ እስከ አምስት ሺህ ዶላር እናገኝ ነበር። አሁን ግን አንድ ዶላር እንኳን ማግኘት አንችልም።” የኬንያ የጫት ነጋዴዎች ማኅበር እንደሚለው ከሆነ የኬንያ ጫት አምራች ገበሬዎች ከዚህ ቀደም እስከ 50 ቶን የሚመዝን ጫት ወደ ሶማሊያ በመላክ እስከ 140 ሺህ ዶላር ድረስ ገቢ ያስገኙ ነበር። አሁን ላይ ገበሬዎች ከምርታቸው እጅግ አነስተኛ የሚሆነውን ለኬንያ ገበያ ካቀረቡ በኋላ ሌላው ፈላጊ ስለሌለው ምርቱ እየተጣለ ነው ይላል ማኅበሩ። ባሳለፍነው ወር በሶማሊያ እና በኬንያ መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ አለመግባባት ተካሮ ሶማሊያ የኬንያን አምባሳደር አባራ በናይሮቢ የሚገኘውን አምባሳደሯን መጥራቷ ይታወሳል። | https://www.bbc.com/amharic/news-55212239 |
3politics
| በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን የያዙት የቡርኪናፋሶ መሪ መፈንቅለ መንግሥት ተደረገባቸው | የቡርኪናፋሶ የጦር መኮንኖች በብሔራዊው ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው የአገሪቱ ወታደራዊ መሪ ሌተናል ኮሎኔል ፖል ሄንሪ ዳምቢባ ከሥልጣን መወገዳቸውን አስታወቁ። የቡድኑ መሪ ሻምበል ኢብራሂም ትራኦሬ እንደተናገሩት የወታደራዊ መሪው ሌትናል ኮሎኔል ዳምቢባ ከመሪነት የተወገዱት፣ በአገሪቱ የሚንቀሳቀሱትን እስላማዊ አማጺያንን በአግባቡ መቆጣጠር አልቻሉም በሚል ነው። መኮንኑ ጨምረውም ላልተወሰነ ጊዜ ሁሉም የአገሪቱ ድንበሮች ዝግ እንደሚሆኑ እና የትኛውም አይነት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ መከልከሉን አሳውቀዋል። አሁን ከሥልጣን መወገዳቸው የተገለጸው ዳምቢባ የሚመሩት ቡድን፣ ባለፈው ዓመት ጥር ላይ ነበር በሕዝብ የተመረጠውን አስተዳደር በመፈንቅለ መንግሥት ገልብጦ ወደ ሥልጣን የመጣው። በወቅቱም ወታደራዊ ቡድኑ መንግሥት የእስላማዊ ቡድኖችን ጥቃት ማስቆም አልቻለም በሚል ነበር መፈንቅለ መንግሥት ማድረጉን ያሳወቀው። ትናንት አርብ ጠዋት ላይ በዋና ከተማዋ ዋጋዱጉ ውስጥ ከባድ ተኩስ ከተሰማ በኋላ ሕዝቡ እንዲረጋጋ ሌተናል ኮሎኔል ዳምቢባ ጠይቀው ነበር። ትናንት ምሽት ላይ ከ20 በላይ የሚሆኑ አብዛኞቹ ፊታቸው የተሸፈነ የታጠቁ ወታደሮች በብሔራዊው ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው የቡድኑ መሪ ናቸው በተባሉት ትራኦሬ የተፈረመ መግለጫ አቅርበዋል። “እየተባባሰ የሚሄድ ችግር በገጠመን ጊዜ ዳምቢባ በደኅንነት ጉዳዮች ላይ እንዲያተኩሩ ለማድረግ በተደጋጋሚ ሞክረናል፤ ነገር ግን የዳምቢባ ተግባር ለማድረግ ካቀድነው ውጪ በመሆኑ አሁን ከሥልጣን እንዲወገድ ወስነናል” ብሏል መግለጫው። ከዚህ በኋላም በመላዋ አገሪቱ ከምሽት 3 ሰዓት እስከ ንጋት 11 የሚቆይ የሰዓት እላፊ ገደብ የተጣለ ሲሆን፣ ሌተናል ኮሎኔል ዳምቢባ የት እንዳሉ የታወቀ ነገር የለም። አሜሪካ ቡርኪናፋሶ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ነገር “በእጅጉ እንዳሳሰባት” በመግለጽ በአገሪቱ ውስጥ ያሉ ዜጎቿ እንቅስቃሴያቸውን እንዲቆጥቡ መክራለች። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ “መረጋጋት እንዲሰፍንና ሁሉም ወገኖች ከየትኛውም ድርጊት እንዲቆጠቡ” ጥሪ አቅርበዋል። የምዕራብ አፍሪካ አገራት የኢኮኖሚ ማኅበር የሆነው ኤኮዋስ “ሥልጣንን ሕገ መንግሥታዊ ከሆነ መንገድ ውጪ መያዝና በሥልጣን ላይ መቆየትን አጥብቄ እቃወማለሁ” በማለት በቡርኪናፋሶ የተካሄደውን የመንግሥት ግልበጣውን አውግዞታል። አርብ ዕለት አጥቢያ በፕሬዝዳንቱ ቤተ መንግሥት እና በዋና ከተማዋ ዋጋዱጉ ውስጥ ባለ ጦር ሰፈር አቅራቢያ የተኩስ ድምጽና ፍንዳታ መጀመሪያ ላይ ተሰምቶ ነበር። ይህንንም ተከትሎ ጠዋት ላይ ወታደሮች አንዳንድ መንገዶችን በመዝጋት ቁልፍ የከተማ ክፍሎች ላይ በመሰማራታቸው ለወትሮ ግርግር የሚበዛበት ከተማ ጭር ብሎ ነበረ። ቀን ላይ የተኩስ ድምጽ የተሰማ ሲሆን የአገሪቱ ቴሌቪዥን ጣቢያም ስርጭቱን ለሰዓታት አቋርጦ ቆይቶ ነበር። የመፈንቅለ መንግሥት ወሬ በስፋት በተናፈሰበት አርብ ከሰዓት በኋላ ፕሬዝዳንቱ ሌ/ኮሎኔል ዳምቢባ፣ በአንዳንድ ወታደሮች ዘንድ የተፈጠረ ስሜታዊነት “ግራ መጋባትን” መፍጠሩን በመግለጽ “ሰላምና መረጋጋት እንዲፈጠር ድርድር እየተካሄደ ነው” በማለት ሕዝቡ እንዲረጋጋ ጠይቀው ነበር። አሁን ከሥልጣን መባረራቸው የተነገረው ዳምቢባ ባለፈው ዓመት ጥር ፕሬዝዳንት ሮች ካቦሬን እየጨረ የመጣውን የእስላማዊ ታጣቂዎች ጥቃትን መቆጣጠር አልቻሉም በሚል ነበር በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ያስወገዱት። ነገር ግን ዳምቢባ ወደ ሥልጣን ከመጡም በኋላ በርካታ ዜጎች ደኅንነት እንደማይሰማቸው በመግለጽ በዚህ ሳምንት በተለያዩ የቡርኪናፋሶ ክፍሎች የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደዋል። አርብ ከሰዓት በኋላ አንዳንዶች በዋና ከተማዋ ዋጋዱጉ ውስጥ ሌተናል ኮሎኔል ዳምቢባ ከሥልጣን እንዲወርዱ የሚጠይቅ ተቃውሞ ሲያሰሙ ነበር። በቡርኪናፋሶ የእስላማዊ ታጣቂዎች እንቅስቃሴ ከሰባት ዓመት በፊት የጀመረ ሲሆን፣ በዚህም ሳቢያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲገደሉ፣ ሁለት ሚሊዮን የሚገመቱ ሰዎች ደግሞ ከቤታቸው ለመፈናቀል ተገደዋል። ቡርኪናፋሶ በአውሮፓውያኑ 1960 ነጻ አገር ከሆነች በኋላ እስካሁን ድረስ ስምንት የተሳኩ መፈንቅለ መንግሥቶች ተካሂዶባታል። | በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን የያዙት የቡርኪናፋሶ መሪ መፈንቅለ መንግሥት ተደረገባቸው የቡርኪናፋሶ የጦር መኮንኖች በብሔራዊው ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው የአገሪቱ ወታደራዊ መሪ ሌተናል ኮሎኔል ፖል ሄንሪ ዳምቢባ ከሥልጣን መወገዳቸውን አስታወቁ። የቡድኑ መሪ ሻምበል ኢብራሂም ትራኦሬ እንደተናገሩት የወታደራዊ መሪው ሌትናል ኮሎኔል ዳምቢባ ከመሪነት የተወገዱት፣ በአገሪቱ የሚንቀሳቀሱትን እስላማዊ አማጺያንን በአግባቡ መቆጣጠር አልቻሉም በሚል ነው። መኮንኑ ጨምረውም ላልተወሰነ ጊዜ ሁሉም የአገሪቱ ድንበሮች ዝግ እንደሚሆኑ እና የትኛውም አይነት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ መከልከሉን አሳውቀዋል። አሁን ከሥልጣን መወገዳቸው የተገለጸው ዳምቢባ የሚመሩት ቡድን፣ ባለፈው ዓመት ጥር ላይ ነበር በሕዝብ የተመረጠውን አስተዳደር በመፈንቅለ መንግሥት ገልብጦ ወደ ሥልጣን የመጣው። በወቅቱም ወታደራዊ ቡድኑ መንግሥት የእስላማዊ ቡድኖችን ጥቃት ማስቆም አልቻለም በሚል ነበር መፈንቅለ መንግሥት ማድረጉን ያሳወቀው። ትናንት አርብ ጠዋት ላይ በዋና ከተማዋ ዋጋዱጉ ውስጥ ከባድ ተኩስ ከተሰማ በኋላ ሕዝቡ እንዲረጋጋ ሌተናል ኮሎኔል ዳምቢባ ጠይቀው ነበር። ትናንት ምሽት ላይ ከ20 በላይ የሚሆኑ አብዛኞቹ ፊታቸው የተሸፈነ የታጠቁ ወታደሮች በብሔራዊው ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው የቡድኑ መሪ ናቸው በተባሉት ትራኦሬ የተፈረመ መግለጫ አቅርበዋል። “እየተባባሰ የሚሄድ ችግር በገጠመን ጊዜ ዳምቢባ በደኅንነት ጉዳዮች ላይ እንዲያተኩሩ ለማድረግ በተደጋጋሚ ሞክረናል፤ ነገር ግን የዳምቢባ ተግባር ለማድረግ ካቀድነው ውጪ በመሆኑ አሁን ከሥልጣን እንዲወገድ ወስነናል” ብሏል መግለጫው። ከዚህ በኋላም በመላዋ አገሪቱ ከምሽት 3 ሰዓት እስከ ንጋት 11 የሚቆይ የሰዓት እላፊ ገደብ የተጣለ ሲሆን፣ ሌተናል ኮሎኔል ዳምቢባ የት እንዳሉ የታወቀ ነገር የለም። አሜሪካ ቡርኪናፋሶ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ነገር “በእጅጉ እንዳሳሰባት” በመግለጽ በአገሪቱ ውስጥ ያሉ ዜጎቿ እንቅስቃሴያቸውን እንዲቆጥቡ መክራለች። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ “መረጋጋት እንዲሰፍንና ሁሉም ወገኖች ከየትኛውም ድርጊት እንዲቆጠቡ” ጥሪ አቅርበዋል። የምዕራብ አፍሪካ አገራት የኢኮኖሚ ማኅበር የሆነው ኤኮዋስ “ሥልጣንን ሕገ መንግሥታዊ ከሆነ መንገድ ውጪ መያዝና በሥልጣን ላይ መቆየትን አጥብቄ እቃወማለሁ” በማለት በቡርኪናፋሶ የተካሄደውን የመንግሥት ግልበጣውን አውግዞታል። አርብ ዕለት አጥቢያ በፕሬዝዳንቱ ቤተ መንግሥት እና በዋና ከተማዋ ዋጋዱጉ ውስጥ ባለ ጦር ሰፈር አቅራቢያ የተኩስ ድምጽና ፍንዳታ መጀመሪያ ላይ ተሰምቶ ነበር። ይህንንም ተከትሎ ጠዋት ላይ ወታደሮች አንዳንድ መንገዶችን በመዝጋት ቁልፍ የከተማ ክፍሎች ላይ በመሰማራታቸው ለወትሮ ግርግር የሚበዛበት ከተማ ጭር ብሎ ነበረ። ቀን ላይ የተኩስ ድምጽ የተሰማ ሲሆን የአገሪቱ ቴሌቪዥን ጣቢያም ስርጭቱን ለሰዓታት አቋርጦ ቆይቶ ነበር። የመፈንቅለ መንግሥት ወሬ በስፋት በተናፈሰበት አርብ ከሰዓት በኋላ ፕሬዝዳንቱ ሌ/ኮሎኔል ዳምቢባ፣ በአንዳንድ ወታደሮች ዘንድ የተፈጠረ ስሜታዊነት “ግራ መጋባትን” መፍጠሩን በመግለጽ “ሰላምና መረጋጋት እንዲፈጠር ድርድር እየተካሄደ ነው” በማለት ሕዝቡ እንዲረጋጋ ጠይቀው ነበር። አሁን ከሥልጣን መባረራቸው የተነገረው ዳምቢባ ባለፈው ዓመት ጥር ፕሬዝዳንት ሮች ካቦሬን እየጨረ የመጣውን የእስላማዊ ታጣቂዎች ጥቃትን መቆጣጠር አልቻሉም በሚል ነበር በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ያስወገዱት። ነገር ግን ዳምቢባ ወደ ሥልጣን ከመጡም በኋላ በርካታ ዜጎች ደኅንነት እንደማይሰማቸው በመግለጽ በዚህ ሳምንት በተለያዩ የቡርኪናፋሶ ክፍሎች የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደዋል። አርብ ከሰዓት በኋላ አንዳንዶች በዋና ከተማዋ ዋጋዱጉ ውስጥ ሌተናል ኮሎኔል ዳምቢባ ከሥልጣን እንዲወርዱ የሚጠይቅ ተቃውሞ ሲያሰሙ ነበር። በቡርኪናፋሶ የእስላማዊ ታጣቂዎች እንቅስቃሴ ከሰባት ዓመት በፊት የጀመረ ሲሆን፣ በዚህም ሳቢያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲገደሉ፣ ሁለት ሚሊዮን የሚገመቱ ሰዎች ደግሞ ከቤታቸው ለመፈናቀል ተገደዋል። ቡርኪናፋሶ በአውሮፓውያኑ 1960 ነጻ አገር ከሆነች በኋላ እስካሁን ድረስ ስምንት የተሳኩ መፈንቅለ መንግሥቶች ተካሂዶባታል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c9enzkkp0k8o |
0business
| ቻይና የከፋ ድህነትን ከግዛቷ ማስወገዷን አወጀች | የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ አገራቸውን "በተዓምርዊ" ሁኔታ ከከፋ ድህነት መውጣቷን ተናገሩ። ፕሬዝዳንቱ መንግሥታቸው ባለፉት ስምንት ዓመታት ከ100 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ከድህነት ማውጣት መቻሉን ገልፀዋል። ዢ ጂንፒንግ ቤይጂንግ ውስጥ በተዘጋጀ ሥነ ሥርዓት ላይ እንደተናገሩት "የተሟላ ድል" በማለት ስኬቱን አንቆለጳጵሰው "በታሪክ ውስጥ የሚመዘገብ" ብለውታል። ነገር ግን ይህ የፕሬዝዳንቱ ንግግር ያልተዋጠላቸው ባለሙያዎች ድህነት በቻይና እንዴት እንደተለካ ጠይቀዋል። በቻይና የከፋ ድህነት ተብሎ የሚገለፀው በዓመት ገቢው ከ620 ዶላር በታች የሆነ ግለሰብ ነው። ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው "የከፋ ድህነትን የማስወገድ ተግባሩ ተጠናቅቋል" ብለዋል። አሁን ባለው መስፈርት በገጠራማ የአገሪቱ ክፍሎች የሚኖሩ 98.99 ሚሊዮን ድሆች በሙሉ ከድህነት ወጥተዋል፤ 832 በድህነት የተጎዱ አካባቢዎች እና 128 ሺህ መንደሮች ደግሞ ከድህነት ዝርዝር ውስጥ ስማቸው ተፍቋል" ሲሉ አክለዋል። ዢ ጂንፒንግ ወደ ስልጣን ከመጡበት 2012 (እኤአ) ጀምሮ በገጠር ያለን ድህነትን ማስወገድ ቁልፍ ተግባራቸው አድርገው ሲሰሩ ነበር። ቻይና ባለፈው ዓመት የመጨረሻዎቹን ድሃ የተሰኙ አካባቢዎችን ከድህነት ዝርዝር ውስጥ ስማቸውን አንስታለች። በዚህም የተነሳ ቻይና በ2020 የከፋ ድህነትን ማስወገድ ችላለች። ዛሬ፣ ሐሙስ በተካሄደ ክብረ በዓል ላይ ዢ ጂንፒንግ ድህነትን በመዋጋት ተግባር ውስጥ ለተሳተፉ አካላት ሜዳሊያ ሸልመዋል። ነገር ግን ባለሙያዎች ቻይና ድህነትን የምትበይንበትን መስፈርት ዝቅ አድርጋ አስቀምጣለች፤ አሁንም በድሃ አካባቢዎች ተጨማሪ ሃብት ማፍሰስ ያስፈልጋል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። በቻይና አንድ ሰው የከፋ ድህነት ውስጥ ይኖራል ለመባል የቀን ገቢው 1.69 ዶላር መሆን አለበት። እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከሆነ የዓለም ባንክ ግን 1.90 ዶላር የሚያገኝን ሰው የከፋ ድህነት ውስጥ ይገኛል ሲል ይበይናል። በቻይና አሁንም በዜጎች መካከል የሰፋ የሃብት ልዩነት ይታያል። | ቻይና የከፋ ድህነትን ከግዛቷ ማስወገዷን አወጀች የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ አገራቸውን "በተዓምርዊ" ሁኔታ ከከፋ ድህነት መውጣቷን ተናገሩ። ፕሬዝዳንቱ መንግሥታቸው ባለፉት ስምንት ዓመታት ከ100 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ከድህነት ማውጣት መቻሉን ገልፀዋል። ዢ ጂንፒንግ ቤይጂንግ ውስጥ በተዘጋጀ ሥነ ሥርዓት ላይ እንደተናገሩት "የተሟላ ድል" በማለት ስኬቱን አንቆለጳጵሰው "በታሪክ ውስጥ የሚመዘገብ" ብለውታል። ነገር ግን ይህ የፕሬዝዳንቱ ንግግር ያልተዋጠላቸው ባለሙያዎች ድህነት በቻይና እንዴት እንደተለካ ጠይቀዋል። በቻይና የከፋ ድህነት ተብሎ የሚገለፀው በዓመት ገቢው ከ620 ዶላር በታች የሆነ ግለሰብ ነው። ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው "የከፋ ድህነትን የማስወገድ ተግባሩ ተጠናቅቋል" ብለዋል። አሁን ባለው መስፈርት በገጠራማ የአገሪቱ ክፍሎች የሚኖሩ 98.99 ሚሊዮን ድሆች በሙሉ ከድህነት ወጥተዋል፤ 832 በድህነት የተጎዱ አካባቢዎች እና 128 ሺህ መንደሮች ደግሞ ከድህነት ዝርዝር ውስጥ ስማቸው ተፍቋል" ሲሉ አክለዋል። ዢ ጂንፒንግ ወደ ስልጣን ከመጡበት 2012 (እኤአ) ጀምሮ በገጠር ያለን ድህነትን ማስወገድ ቁልፍ ተግባራቸው አድርገው ሲሰሩ ነበር። ቻይና ባለፈው ዓመት የመጨረሻዎቹን ድሃ የተሰኙ አካባቢዎችን ከድህነት ዝርዝር ውስጥ ስማቸውን አንስታለች። በዚህም የተነሳ ቻይና በ2020 የከፋ ድህነትን ማስወገድ ችላለች። ዛሬ፣ ሐሙስ በተካሄደ ክብረ በዓል ላይ ዢ ጂንፒንግ ድህነትን በመዋጋት ተግባር ውስጥ ለተሳተፉ አካላት ሜዳሊያ ሸልመዋል። ነገር ግን ባለሙያዎች ቻይና ድህነትን የምትበይንበትን መስፈርት ዝቅ አድርጋ አስቀምጣለች፤ አሁንም በድሃ አካባቢዎች ተጨማሪ ሃብት ማፍሰስ ያስፈልጋል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። በቻይና አንድ ሰው የከፋ ድህነት ውስጥ ይኖራል ለመባል የቀን ገቢው 1.69 ዶላር መሆን አለበት። እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከሆነ የዓለም ባንክ ግን 1.90 ዶላር የሚያገኝን ሰው የከፋ ድህነት ውስጥ ይገኛል ሲል ይበይናል። በቻይና አሁንም በዜጎች መካከል የሰፋ የሃብት ልዩነት ይታያል። | https://www.bbc.com/amharic/56201582 |
5sports
| የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ባለድሎች ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው | በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን አመርቂ ድል ያስመዘገቡት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አባላት በአዲስ አበባ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው። በውድድሩ ላይ ኢትዮጵያ ከአዘጋጇ አሜሪካ በመከተል የሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። በዓለም የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በአጠቃላይ 10 ሜዳሊያዎችን አግኝተዋል። እነዚህም አራት ወርቅ፣ አራት ብር እና ሁለት የነሐስ ሜዳሊያዎች ናቸው። በአሜሪካዋ ኦሪጎን ግዛት በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተገኘው የሜዳሊያ ብዛት በታሪክ የላቀ ውጤት የተመዘገበበት ነው ተብሏል። ረቡዕ ምሽት አዲስ አበባ የገቡት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አባላት ሐሙስ ጠዋት አዲስ አበባ ውስጥ ደማቅ የጀግና አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ደስተቻቸውን ለመግለጽ ወደ ዋና ዋና መንገዶች የወጡ ሲሆን፣ አትሌቶቹም በከፍት መኪናዎች ላይ ሆነው ታይተዋል። ቡድኑ ወደ ታላቁ ቤተ-መንግሥት በማቅናት በአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ እና በሌሎችም ታዋቂ ግለሰቦች አቀባበል ተደርጎላቸዋል። የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ታላቅ ድልን ያስመዘገበውን ቡድን አባል የነበረችው እና የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የሆነችው አትሌት ደራርቱ ቱሉ ለሰጠችው አመራርም አድናቆት ተችሯታል። ደራርቱ በአትሌቶቹ ውጤት እንደኮራች በመግለጽ፤ በቀጣዩ ውድድር ከባድ ፉክክር እንደሚጠብቃቸው አውቀው እንዲዘጋጁ አትሌቶቹን አሳስባለች። ጨምራም ጦርነት ከተካሄደበት የትግራይ ክልል የመጡ አትሌቶች ቤተሰቦቻቸውን ማግኘት እንዲችሉ የፌደራል መንግሥት ሁኔታዎችን እንዲያመቻች ጠይቃለች። “ከትግራይ የመጡት አትሌቶች አስካሁን ቤተሰቦቻቸውን የማግኘት ዕድል አላገኙም” ስትል በቤተ-መንግሥት ውስጥ በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ላይ ተናግራለች። በውድድሩ ላይ ሦስት ወርቅ ሜዳሊያ ያመጡት ለተሰንበት ግደይ፣ ጎተይቶም ገብረሥላሴ እና ጉዳፍ ፀጋይ ከትግራይ ክልል የመጡ አትሌቶች ናቸው። በጦርነቱ ምክንያት በትግራይ ክልል የግንኙነት መስመሮች ከተቋረጡ ከአንድ ዓመት በላይ እንደሆነው ይታወቃል። በሥነ ሥርዓቱ ላይ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሜዳሊያ ላስገኙ አትሌቶች ከ700ሺህ እስከ 2.5 ሚሊዮን ብር ድረስ የገንዘብ ሽልማት ተበርክቷል። በ5 ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ እና በ1 ሺህ 500 ሜትር የብር ሜዳሊያ ያስገኘቸው አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ የ2.5 ሚሊየን ብር ተሸላሚ ሆናለች። አትሌት ለተሰንበት ግደይ በ10 ሺህ ሜትር ወርቅ በማስገኘቷ 1.5 ሚሊየን ብር እንዲሁም በ5 ሺህ ሜትር ላበረከተችው ውጤታማ የቡድን ሥራ 500 ሺህ ብር በድምሩ የ2 ሚሊየን ብር ተሸላሚ ሆናለች። በማራቶን ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ ላመጡት አትሌት ጎተይቶም ገብረ ሥላሴ እና ታምራት ቶላ እያንዳንዳቸው የ1 ሚሊዮን 750 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆነዋል። በወንዶች ማራቶን የብር ሜዳሊያ ያስገኘው ሞስነት ገረመው፣ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል የብር ሜዳሊያ ላስገኘቸው ወርቅውሃ ጌታቸው እንዲሁም በወንዶች 3 ሺህ መሰናክል የብር ሜዳሊያ ላስገኘው ለሜቻ ግርማ ለእያንዳንዳቸው የ1 ሚሊየን ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። በ5ሺህ ሜትር እና በ3ሺህ ሜትር መሰናክል የነሐስ ሜዳሊያ ያስገኙት አትሌት ዳዊት ስዩም እና መቅደስ አበበ የ700 ሺህ ብር ሽልማት ተሰጥቷል። | የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ባለድሎች ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን አመርቂ ድል ያስመዘገቡት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አባላት በአዲስ አበባ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው። በውድድሩ ላይ ኢትዮጵያ ከአዘጋጇ አሜሪካ በመከተል የሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። በዓለም የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በአጠቃላይ 10 ሜዳሊያዎችን አግኝተዋል። እነዚህም አራት ወርቅ፣ አራት ብር እና ሁለት የነሐስ ሜዳሊያዎች ናቸው። በአሜሪካዋ ኦሪጎን ግዛት በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተገኘው የሜዳሊያ ብዛት በታሪክ የላቀ ውጤት የተመዘገበበት ነው ተብሏል። ረቡዕ ምሽት አዲስ አበባ የገቡት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አባላት ሐሙስ ጠዋት አዲስ አበባ ውስጥ ደማቅ የጀግና አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ደስተቻቸውን ለመግለጽ ወደ ዋና ዋና መንገዶች የወጡ ሲሆን፣ አትሌቶቹም በከፍት መኪናዎች ላይ ሆነው ታይተዋል። ቡድኑ ወደ ታላቁ ቤተ-መንግሥት በማቅናት በአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ እና በሌሎችም ታዋቂ ግለሰቦች አቀባበል ተደርጎላቸዋል። የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ታላቅ ድልን ያስመዘገበውን ቡድን አባል የነበረችው እና የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የሆነችው አትሌት ደራርቱ ቱሉ ለሰጠችው አመራርም አድናቆት ተችሯታል። ደራርቱ በአትሌቶቹ ውጤት እንደኮራች በመግለጽ፤ በቀጣዩ ውድድር ከባድ ፉክክር እንደሚጠብቃቸው አውቀው እንዲዘጋጁ አትሌቶቹን አሳስባለች። ጨምራም ጦርነት ከተካሄደበት የትግራይ ክልል የመጡ አትሌቶች ቤተሰቦቻቸውን ማግኘት እንዲችሉ የፌደራል መንግሥት ሁኔታዎችን እንዲያመቻች ጠይቃለች። “ከትግራይ የመጡት አትሌቶች አስካሁን ቤተሰቦቻቸውን የማግኘት ዕድል አላገኙም” ስትል በቤተ-መንግሥት ውስጥ በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ላይ ተናግራለች። በውድድሩ ላይ ሦስት ወርቅ ሜዳሊያ ያመጡት ለተሰንበት ግደይ፣ ጎተይቶም ገብረሥላሴ እና ጉዳፍ ፀጋይ ከትግራይ ክልል የመጡ አትሌቶች ናቸው። በጦርነቱ ምክንያት በትግራይ ክልል የግንኙነት መስመሮች ከተቋረጡ ከአንድ ዓመት በላይ እንደሆነው ይታወቃል። በሥነ ሥርዓቱ ላይ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሜዳሊያ ላስገኙ አትሌቶች ከ700ሺህ እስከ 2.5 ሚሊዮን ብር ድረስ የገንዘብ ሽልማት ተበርክቷል። በ5 ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ እና በ1 ሺህ 500 ሜትር የብር ሜዳሊያ ያስገኘቸው አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ የ2.5 ሚሊየን ብር ተሸላሚ ሆናለች። አትሌት ለተሰንበት ግደይ በ10 ሺህ ሜትር ወርቅ በማስገኘቷ 1.5 ሚሊየን ብር እንዲሁም በ5 ሺህ ሜትር ላበረከተችው ውጤታማ የቡድን ሥራ 500 ሺህ ብር በድምሩ የ2 ሚሊየን ብር ተሸላሚ ሆናለች። በማራቶን ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ ላመጡት አትሌት ጎተይቶም ገብረ ሥላሴ እና ታምራት ቶላ እያንዳንዳቸው የ1 ሚሊዮን 750 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆነዋል። በወንዶች ማራቶን የብር ሜዳሊያ ያስገኘው ሞስነት ገረመው፣ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል የብር ሜዳሊያ ላስገኘቸው ወርቅውሃ ጌታቸው እንዲሁም በወንዶች 3 ሺህ መሰናክል የብር ሜዳሊያ ላስገኘው ለሜቻ ግርማ ለእያንዳንዳቸው የ1 ሚሊየን ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። በ5ሺህ ሜትር እና በ3ሺህ ሜትር መሰናክል የነሐስ ሜዳሊያ ያስገኙት አትሌት ዳዊት ስዩም እና መቅደስ አበበ የ700 ሺህ ብር ሽልማት ተሰጥቷል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c2934kd1kw7o |
5sports
| በሙስና ተፈርዶባቸው የነበሩት የቀድሞው የዓለም አትሌቲክስ ኃላፊ አረፉ | የቀድሞ የዓለም አትሌቲክስ ኃላፊ ላሚን ዲያክ በ88 ዓመታቸው ሴኔጋል ውስጥ ማረፋቸው ተሰማ። ባለፈው ዓመት በሙስና ወንጀል ተከሰው የነበሩት ዲያክ ከአውሮፓውያኑ 1999 እስከ 2015 የዓለም አትሌቲክስ (የቀድሞው የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር-አይኤኤፍ) ፕሬዝዳንት ነበሩ። በአውሮፓውያኑ 2020 ከሩሲያ አበረታች መድኃኒት ቅሌት ጋር ተያይዞ በሙስና እና በሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል። የፈረንሳይ ፍርድ ቤት በአራት ዓመት እስራት እንዲቀጡ የበየነባቸው ሲሆን ሁለት ዓመቱ ተቀንሶላቸዋል። ነገር ግን ሳይታሰሩ ወደ ሴኔጋል ተመልሰው እንዲሄዱ ተፈቅዶላቸው በቁም እስረኛነት ቆይተዋል። በኋላም በዋስ ተለቀዋል። ልጃቸው ፓፓ ማሳታ ዲያክ "በተፈጥሯዊ ምክንያት ቤት ውስጥ ህይወቱ አልፏል" በማለት ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል። የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው በዛሬው ዕለት እንደሚፈጸም ተነግሯል። ቀደም ሲል ዲያክ ጠበቆች በጤና እጦት ላይ እንዳሉ እና ከታሰሩ እንደሚሞቱ ተናግረው ነበር። የቀድሞው ኃላፊ ጥፋተኛ ቢባሉም በሴኔጋል ድጋፍ አላቸው። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ዲያክ ወደ አገር ቤት እንዲመለሱ ያስቻለውን 565 ሺህ ዶላር ዋስትና የከፈሉት ጃራፍ የተባለው የሴኔጋሉ እግር ኳስ ክለብ ባለቤት ቼክ ሴክ ናቸው። ሴክ የቀድሞ የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ሲሆኑ አሁን በንግድ ሥራ ይተዳደራሉ። "ጥሩ ሰውና ታላቅ መሪ ነበር። ወደ አገሩ እንዲመለስ እንፈልጋለን። 565 ሺህ ዶላር ለመሰብሰብ አንድ ወር ፈጅቶብናል" ሲሉ ከዲያክ ህልፈት በኋላ ተናግረዋል። "ህይወቱ ሌላ ቦታ እንዲያልፍ አስበን አለማወቃችን በጣም አስፈላጊ ነበር።" "ተወዳጅ የአገሩ ልጅ፣ ሁለንተናዊ አስደናቂ ዜጋ" ሲሉ ሴክ ቀደም ሲል ዲያክን ገልጸዋቸው ነበር። | በሙስና ተፈርዶባቸው የነበሩት የቀድሞው የዓለም አትሌቲክስ ኃላፊ አረፉ የቀድሞ የዓለም አትሌቲክስ ኃላፊ ላሚን ዲያክ በ88 ዓመታቸው ሴኔጋል ውስጥ ማረፋቸው ተሰማ። ባለፈው ዓመት በሙስና ወንጀል ተከሰው የነበሩት ዲያክ ከአውሮፓውያኑ 1999 እስከ 2015 የዓለም አትሌቲክስ (የቀድሞው የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር-አይኤኤፍ) ፕሬዝዳንት ነበሩ። በአውሮፓውያኑ 2020 ከሩሲያ አበረታች መድኃኒት ቅሌት ጋር ተያይዞ በሙስና እና በሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል። የፈረንሳይ ፍርድ ቤት በአራት ዓመት እስራት እንዲቀጡ የበየነባቸው ሲሆን ሁለት ዓመቱ ተቀንሶላቸዋል። ነገር ግን ሳይታሰሩ ወደ ሴኔጋል ተመልሰው እንዲሄዱ ተፈቅዶላቸው በቁም እስረኛነት ቆይተዋል። በኋላም በዋስ ተለቀዋል። ልጃቸው ፓፓ ማሳታ ዲያክ "በተፈጥሯዊ ምክንያት ቤት ውስጥ ህይወቱ አልፏል" በማለት ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል። የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው በዛሬው ዕለት እንደሚፈጸም ተነግሯል። ቀደም ሲል ዲያክ ጠበቆች በጤና እጦት ላይ እንዳሉ እና ከታሰሩ እንደሚሞቱ ተናግረው ነበር። የቀድሞው ኃላፊ ጥፋተኛ ቢባሉም በሴኔጋል ድጋፍ አላቸው። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ዲያክ ወደ አገር ቤት እንዲመለሱ ያስቻለውን 565 ሺህ ዶላር ዋስትና የከፈሉት ጃራፍ የተባለው የሴኔጋሉ እግር ኳስ ክለብ ባለቤት ቼክ ሴክ ናቸው። ሴክ የቀድሞ የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ሲሆኑ አሁን በንግድ ሥራ ይተዳደራሉ። "ጥሩ ሰውና ታላቅ መሪ ነበር። ወደ አገሩ እንዲመለስ እንፈልጋለን። 565 ሺህ ዶላር ለመሰብሰብ አንድ ወር ፈጅቶብናል" ሲሉ ከዲያክ ህልፈት በኋላ ተናግረዋል። "ህይወቱ ሌላ ቦታ እንዲያልፍ አስበን አለማወቃችን በጣም አስፈላጊ ነበር።" "ተወዳጅ የአገሩ ልጅ፣ ሁለንተናዊ አስደናቂ ዜጋ" ሲሉ ሴክ ቀደም ሲል ዲያክን ገልጸዋቸው ነበር። | https://www.bbc.com/amharic/news-59521751 |
3politics
| የትራምፕን የዋይት ሐውስ ሰነዶች መርማሪዎች እንዲመለከቱ ፍርድ ቤት ፈቀደ | አንድ የአሜሪካ ዳኛ የካፒቶል አመጽን ከትትሎ ምርመራ የሚያደርገው የኮንግረስ ኮሚቴ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዋይት ሐውስ ሰነዶችን እንዲመለከት ፈቃድ ሰጡ። ትራምፕ ሰዶቹን መርማሪ ኮሚቴው እንዳይመለከተው ያስችለኛል ያሉትን ሕጋዊ መብት አንስተው ተከራክረው ነበር። ምርመራውን የሚያካሂደው ኮሚቴ ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ መንግሥት ምክር ቤት ህንጻ (ካፒቶል ሂል) ላይ ባለፈው ዓመት ጥር ወር የተካሄደውን አመጽ ቀደመው ያውቁ ነበር የሚለውን ለመለየት ለሚያደርገው ጥረት መልስ ለማግኘት ነው። የአሜሪካ ኮንግረስ በምርጫ ያሸነፉትን የጆ ባይደንን ፕሬዝደንትነት ለማጽደቅ በተቀመጠበት ወቅት የትራምፕ ደጋፊዎች ካፒቶል ሂል ላይ ወረራ መፈጸማቸው ይታወሳል። ትራምፕ ምንም አይነት ማስረጃ ሳያቀርቡ ምርጫው ተጭበርብሯል የሚል መከራከሪያ ሲያቀርቡ ቆይተዋል። ምርመራ እያካሄደ የሚገኘው ኮሚቴ በኮንግረሱ ላይ በትራምፕ ደጋፊዎች ጥቃት ከመሰንዘሩ በፊት የዋይት ሐውስ የስልክ ልውውጦች እና ትራምፕ ከማን ጋር ተገናኝተዋል ነበር የሚለውን ለማወቅ ነው ስነዶቹን የሚመለከተው። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ደግሞ ሰነዶቹ ለማንም ይፋ እንዳይሆኑ ሲቃወሙ ነበር። ነገር ግን ጉዳዩን የተመለከቱት ዳኛ ታንያ ቹትካን ማክሰኞ ዕለት የዋይት ሐውስ ሰነዶችን የሚጠብቀው ብሔራዊ የማህደር መስሪያ ቤት ትብበር እንዲያደርግና ሰነዶቹን ለመርማሪ ኮሚቴው እንዲሰጥ አዝዘዋል። ዳኛ ታንያ በቀድሞው ፕሬዝዳነት ባራክ ኦባማ የተሾሙ ሲሆን የዶናልድ ትራምፕን ጥያቄም ውድቅ አድርገዋል። "ፕሬዝዳንቶች እኮ ንጉሥ አይደሉም። ቅሬታ ያቀረቡት ግለሰብም አሁን ላይ ፕሬዝዳንት አይደሉም" ብለዋል ዳኛዋ ታንያ ባስተላለፉት ባለ 39 ገጽ የውሳኔ ሀሳብ። ነገር ግን ይህ ውሳኔ ወደ ፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት እንደሚሄድ ይጠበቃል። እስካሁን ድረስ 16 የዶናልድ ትራምፕ የቅርብ ረዳቶች ባለፉት ሁለት ቀናት ውስጥ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ታዘዋል። ከእነዚህም መካከል የቀድሞ የዋይት ሐውስ ፕሬስ ሴክሬታሪ ኬይሊ ማክናኒ፣ የትራምፕ ከፍተኛ አማካሪ የነበሩት ስቴፈን ሚለር፣ የቀድሞ የቅስቀሳ ኃላፊው ቢል ስቴፈን፣ የቀድሞ የዋይት ሐውስ ከፍተኛ ኃላፊ ማርክ ሚዶውስ እና የቀድሞ የፕሬዝዳንቱ የደኅንነት አማካሪ ማይክል ፍሊን ይገኙበታል። ከካፒቶል ሂል ጥቃት ጋር ተያይዞ እስካሁን ድረስ 670 ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን በወቅቱም አንድ የካፒቶል ሒል የፖሊስ አባልን ጨምሮ አምስት ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል። | የትራምፕን የዋይት ሐውስ ሰነዶች መርማሪዎች እንዲመለከቱ ፍርድ ቤት ፈቀደ አንድ የአሜሪካ ዳኛ የካፒቶል አመጽን ከትትሎ ምርመራ የሚያደርገው የኮንግረስ ኮሚቴ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዋይት ሐውስ ሰነዶችን እንዲመለከት ፈቃድ ሰጡ። ትራምፕ ሰዶቹን መርማሪ ኮሚቴው እንዳይመለከተው ያስችለኛል ያሉትን ሕጋዊ መብት አንስተው ተከራክረው ነበር። ምርመራውን የሚያካሂደው ኮሚቴ ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ መንግሥት ምክር ቤት ህንጻ (ካፒቶል ሂል) ላይ ባለፈው ዓመት ጥር ወር የተካሄደውን አመጽ ቀደመው ያውቁ ነበር የሚለውን ለመለየት ለሚያደርገው ጥረት መልስ ለማግኘት ነው። የአሜሪካ ኮንግረስ በምርጫ ያሸነፉትን የጆ ባይደንን ፕሬዝደንትነት ለማጽደቅ በተቀመጠበት ወቅት የትራምፕ ደጋፊዎች ካፒቶል ሂል ላይ ወረራ መፈጸማቸው ይታወሳል። ትራምፕ ምንም አይነት ማስረጃ ሳያቀርቡ ምርጫው ተጭበርብሯል የሚል መከራከሪያ ሲያቀርቡ ቆይተዋል። ምርመራ እያካሄደ የሚገኘው ኮሚቴ በኮንግረሱ ላይ በትራምፕ ደጋፊዎች ጥቃት ከመሰንዘሩ በፊት የዋይት ሐውስ የስልክ ልውውጦች እና ትራምፕ ከማን ጋር ተገናኝተዋል ነበር የሚለውን ለማወቅ ነው ስነዶቹን የሚመለከተው። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ደግሞ ሰነዶቹ ለማንም ይፋ እንዳይሆኑ ሲቃወሙ ነበር። ነገር ግን ጉዳዩን የተመለከቱት ዳኛ ታንያ ቹትካን ማክሰኞ ዕለት የዋይት ሐውስ ሰነዶችን የሚጠብቀው ብሔራዊ የማህደር መስሪያ ቤት ትብበር እንዲያደርግና ሰነዶቹን ለመርማሪ ኮሚቴው እንዲሰጥ አዝዘዋል። ዳኛ ታንያ በቀድሞው ፕሬዝዳነት ባራክ ኦባማ የተሾሙ ሲሆን የዶናልድ ትራምፕን ጥያቄም ውድቅ አድርገዋል። "ፕሬዝዳንቶች እኮ ንጉሥ አይደሉም። ቅሬታ ያቀረቡት ግለሰብም አሁን ላይ ፕሬዝዳንት አይደሉም" ብለዋል ዳኛዋ ታንያ ባስተላለፉት ባለ 39 ገጽ የውሳኔ ሀሳብ። ነገር ግን ይህ ውሳኔ ወደ ፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት እንደሚሄድ ይጠበቃል። እስካሁን ድረስ 16 የዶናልድ ትራምፕ የቅርብ ረዳቶች ባለፉት ሁለት ቀናት ውስጥ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ታዘዋል። ከእነዚህም መካከል የቀድሞ የዋይት ሐውስ ፕሬስ ሴክሬታሪ ኬይሊ ማክናኒ፣ የትራምፕ ከፍተኛ አማካሪ የነበሩት ስቴፈን ሚለር፣ የቀድሞ የቅስቀሳ ኃላፊው ቢል ስቴፈን፣ የቀድሞ የዋይት ሐውስ ከፍተኛ ኃላፊ ማርክ ሚዶውስ እና የቀድሞ የፕሬዝዳንቱ የደኅንነት አማካሪ ማይክል ፍሊን ይገኙበታል። ከካፒቶል ሂል ጥቃት ጋር ተያይዞ እስካሁን ድረስ 670 ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን በወቅቱም አንድ የካፒቶል ሒል የፖሊስ አባልን ጨምሮ አምስት ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59230353 |
5sports
| ጉዳፍ ጸጋይ በ5ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ሆነች | በአሜሪካዋ ኦሪገን እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 5 ሺህ ሜትር የፍፃሜ ውድድር ጉዳፍ ፀጋይ ወርቅ ባለቤት ሆናለች። ጉዳፍ በዚህ ድሏ ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ያገኘቻቸውን የወርቅ ቁጥሮች አራት ማድረስ ችላለች። ከፍተኛ ፉክክር በነበረበት ውድድር ጉዳፍ 14፡46: 29 በመግባት ነው ባለክብር የሆነችው። ኬንያዊቷ ቢትሪስ ቺቤት ሁለተኛ በመሆን የብር ሜዳሊያ ባለቤት ለመሆን በቅታለች። ሌላኛው ኢትዮጵያዊት ዳዊት ስዩም ሦስተኛ በመውጣት የነሃስ ሜዳሊያ አስገኝታለች። ለድሉ መሳካት ትልቅ ድርሻ የነበራት ለተሰንበት ግደይ አምስተኛ በመውጣት አጠናቃለች። ለተሰንበት በዚሁ የኦሪገን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ10 ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ማግኘቷ ይታወሳል። ከእኩለ ሌሊት በኋላ በተካሄደው የ5ሺህ ሜትር ውድድር የመጨረሻዎቹ 100 ሜትሮች ድረስ አሸናፊዋን መለየት አስቸጋሪ የሆነበት ነበር። በ1500 ሜትር ልምድ ያላት ጉዳፍ ትንቅንቁን የኋላ ኋላ በበላይነት አጠናቃለች። ጉዳፍ ከወራት በፊት በ1500 ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር ክብረ ወሰኑን መስበሯ ይታወሳል። በኦሪገኑ ውድድርም ከቀናት በፊት በዚሁ ዘርፍ ሁለተኛ ሆና በማጠናቀቅ የብር ሜዳሊያ ባለቤት ለመሆን በቅታለች። ጉዳፍ ከውድድሩ በኋላ “በመጎዳቴ ምክንያት የቶክዮው ኦሎምፒክ በጣም ከባዱ ጊዜ ነበር” ማለቷን ወርልድ አትሌቲክስ አስነብቧል። “ለ1500 ሜትር በደንብ ስዘጋጅ ቆይቻለሁ። ይህም በጨረሻዎቹ ሜትሮች ላይ በፍጥነት እንድሄድ ጠቅሞኛል። ሲፋን ትልቅ እና እሷም የ1500 ሜትር አትሌት መሆኗን አውቃለሁ። ስለዚህ እሷም ፍጥነቱ አላት። እሷ ስትቀደም እኔ ፍጥነቴን በመጨመር ሜዳሊያውን ለማግኘት በቅቻለሁ” ብላለች። ዳዊት በበኩሏ ከዓመታት የጉዳት ቆይታ በኋላ ነው ወደ ድል የተመሰለችው። “የሜዳሊያ አሸናፊ ሆኜ መድረክ ላይ ለመውጣት ተስፋ አድርጌያለሁ” ትላለች ዳዊት። “በዚህ ዘርፍ የሜዳሊያ ባለቤት ለመሆን አልሜያለሁ። ለአምስት ዓመታት ከጉዳት ጋር ስታገል ቆይቻለሁ። ስለዚህ ይህ ድል ለእኔ ልዩ ነው” ብላለቸ። ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው በእስካሁን ቆይታ አራት የወርቅ፣ አራት የብር እና ሁለት የነሃስ ሜዳሊያዎችን አግኝታለች። በኦሪጎን እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ይጠናቀቃል። ኢትዮጵያ ሜዳሊያ የምትጠበቅብትን የወንዶች 5000 ሜትርን ጨምሮ በሌሎች ዘርፎችም ቀሪ ውድድሮችን ታከናውናለች። | ጉዳፍ ጸጋይ በ5ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ሆነች በአሜሪካዋ ኦሪገን እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 5 ሺህ ሜትር የፍፃሜ ውድድር ጉዳፍ ፀጋይ ወርቅ ባለቤት ሆናለች። ጉዳፍ በዚህ ድሏ ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ያገኘቻቸውን የወርቅ ቁጥሮች አራት ማድረስ ችላለች። ከፍተኛ ፉክክር በነበረበት ውድድር ጉዳፍ 14፡46: 29 በመግባት ነው ባለክብር የሆነችው። ኬንያዊቷ ቢትሪስ ቺቤት ሁለተኛ በመሆን የብር ሜዳሊያ ባለቤት ለመሆን በቅታለች። ሌላኛው ኢትዮጵያዊት ዳዊት ስዩም ሦስተኛ በመውጣት የነሃስ ሜዳሊያ አስገኝታለች። ለድሉ መሳካት ትልቅ ድርሻ የነበራት ለተሰንበት ግደይ አምስተኛ በመውጣት አጠናቃለች። ለተሰንበት በዚሁ የኦሪገን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ10 ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ማግኘቷ ይታወሳል። ከእኩለ ሌሊት በኋላ በተካሄደው የ5ሺህ ሜትር ውድድር የመጨረሻዎቹ 100 ሜትሮች ድረስ አሸናፊዋን መለየት አስቸጋሪ የሆነበት ነበር። በ1500 ሜትር ልምድ ያላት ጉዳፍ ትንቅንቁን የኋላ ኋላ በበላይነት አጠናቃለች። ጉዳፍ ከወራት በፊት በ1500 ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር ክብረ ወሰኑን መስበሯ ይታወሳል። በኦሪገኑ ውድድርም ከቀናት በፊት በዚሁ ዘርፍ ሁለተኛ ሆና በማጠናቀቅ የብር ሜዳሊያ ባለቤት ለመሆን በቅታለች። ጉዳፍ ከውድድሩ በኋላ “በመጎዳቴ ምክንያት የቶክዮው ኦሎምፒክ በጣም ከባዱ ጊዜ ነበር” ማለቷን ወርልድ አትሌቲክስ አስነብቧል። “ለ1500 ሜትር በደንብ ስዘጋጅ ቆይቻለሁ። ይህም በጨረሻዎቹ ሜትሮች ላይ በፍጥነት እንድሄድ ጠቅሞኛል። ሲፋን ትልቅ እና እሷም የ1500 ሜትር አትሌት መሆኗን አውቃለሁ። ስለዚህ እሷም ፍጥነቱ አላት። እሷ ስትቀደም እኔ ፍጥነቴን በመጨመር ሜዳሊያውን ለማግኘት በቅቻለሁ” ብላለች። ዳዊት በበኩሏ ከዓመታት የጉዳት ቆይታ በኋላ ነው ወደ ድል የተመሰለችው። “የሜዳሊያ አሸናፊ ሆኜ መድረክ ላይ ለመውጣት ተስፋ አድርጌያለሁ” ትላለች ዳዊት። “በዚህ ዘርፍ የሜዳሊያ ባለቤት ለመሆን አልሜያለሁ። ለአምስት ዓመታት ከጉዳት ጋር ስታገል ቆይቻለሁ። ስለዚህ ይህ ድል ለእኔ ልዩ ነው” ብላለቸ። ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው በእስካሁን ቆይታ አራት የወርቅ፣ አራት የብር እና ሁለት የነሃስ ሜዳሊያዎችን አግኝታለች። በኦሪጎን እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ይጠናቀቃል። ኢትዮጵያ ሜዳሊያ የምትጠበቅብትን የወንዶች 5000 ሜትርን ጨምሮ በሌሎች ዘርፎችም ቀሪ ውድድሮችን ታከናውናለች። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c1vg3ew6y76o |
5sports
| ኬንያዊው አትሌት ኪፕቾጌ የዓመቱ የዓለም የስፖርት ኮከብ ሆኖ ተመረጠ | የማራቶኑ ጀግና ኤሉድ ኪፕቾጌ ቢቢሲ በሚያደርገው ምርጫ የአመቱ የዓለም የስፖርት ኮከብ ሆኖ ተመርጧል። ኪፕቾጌ ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች በማጠናቀቅ ታሪክ የሰራ የመጀመሪያው ሯጭ መሆን ችሏል። የ35 አመቱ ኬንያዊ በኦስትሪያዋ መዲና ቪየና በተደረገው የማራቶን ወይም የ42.2 ኪሎሜትር ርቀትን በ1 ሰዓት ከ 59 ደቂቃ ከ 40 ሰኮንዶች በመግባት አለምን አስደምሟል። • ኪፕቾጌ ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች አጠናቀቀ • ኬኒያዊው አትሌት የዓለምን የማራቶን ክብረ ወሰን ሰበረ • ኪፕቾጌ ማራቶንን ከ2 ሰዓት በታች ለመሮጥ ዝግጅቱን አጠናቀቀ ይህንንም ውድድር ከማሸነፉ ከስድስት ወራት በፊት የለንደንን ማራቶን ለአራተኛ ጊዜ አሸንፏል። ከሶስት ዓመት በፊት ሪዮ በተደረገው የኦሎምፒክ ውድድር አሸንፎ የነበረው ኪፕቾጌ፤ ለንደን ላይ ባደረገው ውድድርም በሃያ ስምንት ሰኮንዶች የሪዮ ሰአቱን አሻሽሎታል። ለህዝብ ክፍት በነበረው በዚህ የኮከብነት ምርጫም አሜሪካዊቷን የጂምናዝየም ስፖርተኛ ሲሞን ቢሌስ፣ የደቡብ አፍሪካ የራግቢ ተጫዋቹን ሲያ ኮሊሲ፣ የክሪኬት ተጫዋቹን ስቲቭ ስሚዝ፣ አሜሪካዊው ጎልፍ ተጫዋች ታይገር ውድስና አሜሪካዊቷ እግር ኳሰኛ ሜጋን ራፒኖን በመርታት ኪፕቾጌ አሸንፏል። በባለፈው አመት ጣልያናዊው የጎልፍ ተጫዋች ፍራንቸስኮ ሞሊናሪ ማሸነፉ ይታወሳል። | ኬንያዊው አትሌት ኪፕቾጌ የዓመቱ የዓለም የስፖርት ኮከብ ሆኖ ተመረጠ የማራቶኑ ጀግና ኤሉድ ኪፕቾጌ ቢቢሲ በሚያደርገው ምርጫ የአመቱ የዓለም የስፖርት ኮከብ ሆኖ ተመርጧል። ኪፕቾጌ ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች በማጠናቀቅ ታሪክ የሰራ የመጀመሪያው ሯጭ መሆን ችሏል። የ35 አመቱ ኬንያዊ በኦስትሪያዋ መዲና ቪየና በተደረገው የማራቶን ወይም የ42.2 ኪሎሜትር ርቀትን በ1 ሰዓት ከ 59 ደቂቃ ከ 40 ሰኮንዶች በመግባት አለምን አስደምሟል። • ኪፕቾጌ ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች አጠናቀቀ • ኬኒያዊው አትሌት የዓለምን የማራቶን ክብረ ወሰን ሰበረ • ኪፕቾጌ ማራቶንን ከ2 ሰዓት በታች ለመሮጥ ዝግጅቱን አጠናቀቀ ይህንንም ውድድር ከማሸነፉ ከስድስት ወራት በፊት የለንደንን ማራቶን ለአራተኛ ጊዜ አሸንፏል። ከሶስት ዓመት በፊት ሪዮ በተደረገው የኦሎምፒክ ውድድር አሸንፎ የነበረው ኪፕቾጌ፤ ለንደን ላይ ባደረገው ውድድርም በሃያ ስምንት ሰኮንዶች የሪዮ ሰአቱን አሻሽሎታል። ለህዝብ ክፍት በነበረው በዚህ የኮከብነት ምርጫም አሜሪካዊቷን የጂምናዝየም ስፖርተኛ ሲሞን ቢሌስ፣ የደቡብ አፍሪካ የራግቢ ተጫዋቹን ሲያ ኮሊሲ፣ የክሪኬት ተጫዋቹን ስቲቭ ስሚዝ፣ አሜሪካዊው ጎልፍ ተጫዋች ታይገር ውድስና አሜሪካዊቷ እግር ኳሰኛ ሜጋን ራፒኖን በመርታት ኪፕቾጌ አሸንፏል። በባለፈው አመት ጣልያናዊው የጎልፍ ተጫዋች ፍራንቸስኮ ሞሊናሪ ማሸነፉ ይታወሳል። | https://www.bbc.com/amharic/news-50798738 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ ሳይታወቅ ለዓመታት በሌሊት ወፎች ውስጥ ነበር | የሰው ልጆች ላይ ጉዳት እያስከተለ ያለው ኮሮናቫይረስ ለበርካታ ዓመታት ሳይታወቅ በሌሊት ወፎች ሰውነት ውስጥ እንደነበር ጥናቶች ያሳያሉ። ኮቪድ-19ን የሚያስከትለው ቫይረስ በሌሊት ወፎች ላይ ከታየ ከ40 እስከ 70 ዓመታት አልፈዋል። ወደ ሰው ልጆች ከተሻረገ ጥቂት ጊዜው መሆኑን ሳይንቲስቶች ይናገራሉ። መረጃው፤ ኮቪድ-19 በሰው የተሠራና ከቤተ ሙከራ አምልጦ የወጣ ነው የሚለው የሴራ ትንተና ላይ እውነትን የተመረኮዘ ስለመሆኑ ጥያቄ ያጭራል። ፕ/ር ዴቪድ ሮበርትሰን በግላስጎው ዩኒቨርስቲ ነው የሚሠሩት። የሳቸው ጥናት ‘ኔቸር ማይክሮባዮሎጂ’ በተባለ መጽሔት ላይ ታትሟል። ፕ/ር ዴቪድ እንደሚናገሩት፤ ሳርስ-ኮቭ-2 ከሌሊት ወፎች ቫይረስ ጋር የዘረ መል ተመሳሳይነት ቢኖረውም፤ አንዳቸው ከሌላቸው የበርካታ ዓሠርታት ልዩነት አላቸው። “እነዚህ ሰውን ሊይዙ የሚችሉ ቫይረሶች ዘለግ ላለ ጊዜ እንደኖሩ ጥናቱ ያሳያል” ይላሉ። ቫይረሱ መቼ እና እንዴት ወደ ሰው ልጆች እንደተሸጋገረ መታወቅ እንዳለበት ተመራማሪው ያስረዳሉ። “በሌሊት ወፎች ላይ ቫይረሱ እንዳለ ካወቅን ለመቆጣጠር መሞከር አለብን።” ለወደፊቱ ወረርሽኞች እንዳይቀሰቀሱ፤ ሰዎች የሚገጥሟቸው ህመሞች የቅርብ ክትትል እንደሚያሻቸው ጥናቱ ያሳያል። ከዱር የሌሊት ወፎች ላይ ናሙና ተወስዶ ምርመራ መካሄድም አለበት። ፕሮፌሰሩ እንደሚሉት፤ “እነዚህ ቫይረሶች ዓመታት አስቆጥረዋል ማለት ሰዎችን ጨምሮ ሌላም መኖሪያቸው የሚያደርጉት አካል አግኝተዋል ማለት ነው።” በጥናቱ፤ የሳርስ-ኮቭ-2 ዘረ መል ተቀራራቢው ከሆኑ የሌሊት ወፍ ላይ ያሉ ቫይረሶች ማለትም አርኤቲጂ13 እንዲሁም ከሌሎች ጋር ንጽጽር ተደርጓል። ሁለቱ አይነቶች በምን ወቅት ላይ ተመሳሳይ የዘር ግንድ እንደነበራቸውም ተጠንቷል። በዚህ መሠረትም ሁሉቱ ዓይነቶች ከአስርታት በፊት በተለያየ የእድገት ሁኔታ ማለፋቸው ተደርሶበታል። በሪዲንግ ዩኒቨርስቲ የሚሠሩት ፕ/ር ማርክ ፓጌል በጥናቱ ባይሳተፉም፤ ሰዎችን ሊጎዱ የሚችሉ ኮሮናቫይረሶች ሳይታወቁ በሌሊት ወፎች ላይ ከ40 እስከ 70 ዓመታት መኖራቸውን ምርምሩ እንደሚያሳይ ይስማማሉ። “ከእንስሳት ወደ ሰዎች የሚተላለፉ በሽታዎች ምን ያህል አደገኛ እንደሆኑ ጥናቱ ያሳያል። እንስሳት ውስጥ በጥገኝነት የሚኖሩና ለሰው ልጅ ጎጂ የሆኑ፤ እስካሁን ድረስ ግን ያልታወቁ ሌሎች ቫይረሶችም ሊኖሩ ይችላሉ።” ቫይረሶቹ ወደ ሌሎች የዱር እንስሳት ተላልፈው ሊሆን ይችላል። በተለይም በሕገ ወጥ የእንስሳት ዝውውር ሳቢያ እርስ በእርስ የተቀራረቡ እንስሳት የበለጠ ተጋላጭ ናቸው። እስካሁን ድረስ ያለው መረጃ እንደሚያሳየው ግን የቫይረስ ዋነኛ ተሸካሚ የሆኑት የሌሊት ወፎች ናቸው። ከዚህ ቀደም የሰሠሩ ጥናቶች ፓንጎሎኖች ለሳርስ-ኮቭ-2 ዝግመተ ለውጥ አስተዋጽኦ እንዳበረከቱ ያሳያል። አሁን ግን ይህ ትክክል እንዳልሆነ ተደርሶበታል። ቻይናን መዳረሻው ባደረገ ሕገ ወጥ የዱር እንስሳት ንግድ ወቅት ፓንጎሊኖች ከሌሎች እንስሳት ጋር ንክኪ ነበራቸው። ስለዚህም ፓንጎሊኖች ለቫይረሱ የተጋለጡት በቅርቡ ነው። | ኮሮናቫይረስ፡ ሳይታወቅ ለዓመታት በሌሊት ወፎች ውስጥ ነበር የሰው ልጆች ላይ ጉዳት እያስከተለ ያለው ኮሮናቫይረስ ለበርካታ ዓመታት ሳይታወቅ በሌሊት ወፎች ሰውነት ውስጥ እንደነበር ጥናቶች ያሳያሉ። ኮቪድ-19ን የሚያስከትለው ቫይረስ በሌሊት ወፎች ላይ ከታየ ከ40 እስከ 70 ዓመታት አልፈዋል። ወደ ሰው ልጆች ከተሻረገ ጥቂት ጊዜው መሆኑን ሳይንቲስቶች ይናገራሉ። መረጃው፤ ኮቪድ-19 በሰው የተሠራና ከቤተ ሙከራ አምልጦ የወጣ ነው የሚለው የሴራ ትንተና ላይ እውነትን የተመረኮዘ ስለመሆኑ ጥያቄ ያጭራል። ፕ/ር ዴቪድ ሮበርትሰን በግላስጎው ዩኒቨርስቲ ነው የሚሠሩት። የሳቸው ጥናት ‘ኔቸር ማይክሮባዮሎጂ’ በተባለ መጽሔት ላይ ታትሟል። ፕ/ር ዴቪድ እንደሚናገሩት፤ ሳርስ-ኮቭ-2 ከሌሊት ወፎች ቫይረስ ጋር የዘረ መል ተመሳሳይነት ቢኖረውም፤ አንዳቸው ከሌላቸው የበርካታ ዓሠርታት ልዩነት አላቸው። “እነዚህ ሰውን ሊይዙ የሚችሉ ቫይረሶች ዘለግ ላለ ጊዜ እንደኖሩ ጥናቱ ያሳያል” ይላሉ። ቫይረሱ መቼ እና እንዴት ወደ ሰው ልጆች እንደተሸጋገረ መታወቅ እንዳለበት ተመራማሪው ያስረዳሉ። “በሌሊት ወፎች ላይ ቫይረሱ እንዳለ ካወቅን ለመቆጣጠር መሞከር አለብን።” ለወደፊቱ ወረርሽኞች እንዳይቀሰቀሱ፤ ሰዎች የሚገጥሟቸው ህመሞች የቅርብ ክትትል እንደሚያሻቸው ጥናቱ ያሳያል። ከዱር የሌሊት ወፎች ላይ ናሙና ተወስዶ ምርመራ መካሄድም አለበት። ፕሮፌሰሩ እንደሚሉት፤ “እነዚህ ቫይረሶች ዓመታት አስቆጥረዋል ማለት ሰዎችን ጨምሮ ሌላም መኖሪያቸው የሚያደርጉት አካል አግኝተዋል ማለት ነው።” በጥናቱ፤ የሳርስ-ኮቭ-2 ዘረ መል ተቀራራቢው ከሆኑ የሌሊት ወፍ ላይ ያሉ ቫይረሶች ማለትም አርኤቲጂ13 እንዲሁም ከሌሎች ጋር ንጽጽር ተደርጓል። ሁለቱ አይነቶች በምን ወቅት ላይ ተመሳሳይ የዘር ግንድ እንደነበራቸውም ተጠንቷል። በዚህ መሠረትም ሁሉቱ ዓይነቶች ከአስርታት በፊት በተለያየ የእድገት ሁኔታ ማለፋቸው ተደርሶበታል። በሪዲንግ ዩኒቨርስቲ የሚሠሩት ፕ/ር ማርክ ፓጌል በጥናቱ ባይሳተፉም፤ ሰዎችን ሊጎዱ የሚችሉ ኮሮናቫይረሶች ሳይታወቁ በሌሊት ወፎች ላይ ከ40 እስከ 70 ዓመታት መኖራቸውን ምርምሩ እንደሚያሳይ ይስማማሉ። “ከእንስሳት ወደ ሰዎች የሚተላለፉ በሽታዎች ምን ያህል አደገኛ እንደሆኑ ጥናቱ ያሳያል። እንስሳት ውስጥ በጥገኝነት የሚኖሩና ለሰው ልጅ ጎጂ የሆኑ፤ እስካሁን ድረስ ግን ያልታወቁ ሌሎች ቫይረሶችም ሊኖሩ ይችላሉ።” ቫይረሶቹ ወደ ሌሎች የዱር እንስሳት ተላልፈው ሊሆን ይችላል። በተለይም በሕገ ወጥ የእንስሳት ዝውውር ሳቢያ እርስ በእርስ የተቀራረቡ እንስሳት የበለጠ ተጋላጭ ናቸው። እስካሁን ድረስ ያለው መረጃ እንደሚያሳየው ግን የቫይረስ ዋነኛ ተሸካሚ የሆኑት የሌሊት ወፎች ናቸው። ከዚህ ቀደም የሰሠሩ ጥናቶች ፓንጎሎኖች ለሳርስ-ኮቭ-2 ዝግመተ ለውጥ አስተዋጽኦ እንዳበረከቱ ያሳያል። አሁን ግን ይህ ትክክል እንዳልሆነ ተደርሶበታል። ቻይናን መዳረሻው ባደረገ ሕገ ወጥ የዱር እንስሳት ንግድ ወቅት ፓንጎሊኖች ከሌሎች እንስሳት ጋር ንክኪ ነበራቸው። ስለዚህም ፓንጎሊኖች ለቫይረሱ የተጋለጡት በቅርቡ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/news-53600806 |
0business
| የአውሮፕላን ትኬት ዋጋ ‘የማይቀመስ’ የሆነው ለምንድን ነው? ወደፊትስ ይቀንስ ይሆን? | በቅርቡ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ኬንያ መዲና፣ ናይሮቢ የበረሩ ሦስት ተሳፋሪዎች በነፍስ ወከፍ 28 ሺህ ብር ከፍለናል ይላሉ። ሦስቱ ጓደኛሞች በአማካኝ 1፡45 ሰዓት ለሚወስደው የኢኮኖሚ ክፍል በረራ ደርሶ መልስ በድምሩ 84 ሺህ ብር ከፍለዋል። እርግጥ ነው የአውሮፕላን በረራ ዋጋ በተሳፋሪ የበረራ ቀን እና ሰዓት እንዲሁም ‘በኢኮኖሚ እና በቢዝነስ ክፍሎች’ ምርጫ ይለያያል። ቢሆንም በተለይ ከኮቪድ ወረርሽኝ በኋላ በአህጉረ አፍሪካ የአውሮፕላን በረራ አቅሙ ያላቸው የሚጓዙበት እየሆነ ነው። ስሙን እንድንጠቅስ ያልፈለገ አንድ ኢትዮጵያዊ፣ ከናይሮቢ ወደ አዲስ አበባ የበረራ ዋጋ የማይቀመስ በመሆኑ “በሞያሌ በኩል በባስ አገር ቤት ደርሼ መጥቻለሁ” ይላል። የኬንያ አየር መንገድ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት ለበረራ ብዙ በማስከፈል ከአፍሪካ ቁንጮው ሆኖ ብቅ ብሏል። አየር መንገዱ አፍሪካ ውስጥ አሉ ከሚባሉት የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ከደቡብ አፍሪካ አየር መንገድ እንዲሁም ከፈረንሳዩ ኤር ፍራንስ የላቀ ገንዘብ ለቲኬት ያስከፍላል ተብሏል። ኬኪው (KQ) በተሰኘ ምሕፃረ ቃል የሚታወቀው የጎረቤት አገር ኬንያ አየር መንገድ ውድ ነው የተባለው ወደ 24 የአፍሪካ አገራት ሲበር የሚያስከፍለው ዋጋ ተጠንቶ ነው። አፍሪካን ኮምፒቲሽን ፎረም የተሰኘው ድረ ገጽ የኬንያ አየር መንገድ ለአገር ውስጥ እና ለዓለም አቀፍ በረራ ከፍተኛ ገንዘብ ይጠይቃል ሲል ፅፏል። ነገር ግን የደቡብ አፍሪካው እና የኢትዮጵያ አየር መንገድም እንዲሁ እጅግ ብዙ ለቲኬት ከሚያስከፍሉ የአፍሪካ አየር መንገዶች መካከል ናቸው። የኮቪድ ወረርሽኝ እና የዩክሬንን ጦርነት ተከትሎ የአውሮፕላን በረራ ዋጋ ጭማሪ ቢያሳይም በተለይ የአፍሪካ በረራዎች እጅግ መወደዳቸው ብዙዎችን ያነጋገረ ጉዳይ ሆኗል። በቅርቡ በዩናይትድ ኪንግደሙ ብሪቲሽ ኤርዌይስ ወደ ናይሮቢ ደርሶ መልስ የቆረጠው ዙሪች 800 ፓውንድ ገደማ እንደከፈለ ይናገራል። በተቃራኒው በቅርቡ የሚካሄደውን የኢትዮጵያ ታላቁ ሩጫን ለመታደም ወደ ኢትዮጵያ ለማቅናት ያቀደችው ሚሼል የቲኬት ዋጋው ከ800 ዶላር በላይ እንደሆነባት በትዊተር ገጿ ፅፋለች። ይህ አሁን ባለው የምንዛሪ ዋጋ 97 ሺህ ሽልንግ ገደማ ነው። ከኮቪድ ወረርሽኝ በፊት ከናይሮቢ አዲስ አበባ ደርሶ መልስ በኢትዮጵያ አየር መንገድም ይሁን በኬንያ ኤርዌይስ ለመብረር ከ19 ሺህ እስከ 25 ሺህ ሽልንግ ይጠይቅ ነበር። አሁን ግን ከ80 ሺህ ሽልንግ በላይ ይጠይቃል። ይህ የሆነበት ምክንያት ምንድን ነው? የነዳጅ ዋጋ ወይስ ሌላ ተጨማሪ ምክንያት? የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና የኦፕሬሽን ኦፊሰር [ሲኦኦ] ለማ ያደቻ፣ ለዚህ አንዱ ምክንያት የሌሎች አገራት መንግሥታት የሚጡልብን “ግብር” ነው ይላሉ። አቶ ለማ እንደሚሉት የአየር በረራ ዋጋ የሚተመነው በሚያስወጣው ወጪ ላይ ተመርኩዞ ነው። ለዚህም አየር መንገዳቸው ወደ ተለያዩ አገራት ሲጓዝ የሚያወጣውን ወጪ አስልቶ እንዲሁም አየር መንገዱ የሚያቀርበውን አገልግሎት ከግምት አስገብቶ ዋጋ ይተምናል። ይህንን በምሳሌ ሲያብራሩ አንድ ሰው በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀጥታ ከደቡብ አፍሪካ ሲመጣና ከደቡብ አፍሪካ ተነስቶ ናይሮቢ አርፎ ወደ አዲስ አበባ ሲመጣ ምቾቱ አንድ አይደለም ይላሉ። “አውሮፕላኑ ቀጥታ ከመምጣት ይልቅ ከአንድ ከተማ ወደ ሌላ እያቆራረጠ የሚጓዝ ከሆነ ይህ አንድን መንገደኛ ምቾት ይነሳል። ስለዚህ ቀጥታ ሲመጣ ዋጋው ይጨምራል፤ እያቆራረጠ ሲመጣ ደግሞ ዋጋው ሊቀንስ ይችላል” ይላሉ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ አብዛኛውን ጊዜ ከአፍሪካ፣ አውሮፓ፣ እስያና የአሜሪካ አገራት ቀጥታ በረራ እንደሚያደርግ የሚናገሩት ኃላፊው፣ ይህ ማለት ደንበኞች ሳይጉላሉ በምቾት ይመጣሉ ማለት ነው። ስለዚህ በገበያው መሠረት ላቅ ያለ ክፍያ ሊከፍሉ ይችላሉ ሲሉ ያስረዳሉ። ኦፕሬሽን ኦፊሰሩ ሌላው ለበረራ ቲኬት ዋጋ መወደድ እንደ ምክንያት የሚያነሱት በዓለም አቀፍ ገበያ የነዳጅ ዋጋ መናሩን ነው። አልፎም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ የአየር ማረፊያ የአገልግሎት ክፍያ ከፍ ማለቱን ኃላፊው ይጠቅሳሉ። አቶ ለማ፤ በአየር መንገዶች አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች መንገደኛ ከመመዝገብ ጀምሮ ለማሳፈር፣ ምግብ ለማቅረብ፣ ነዳጅ ለመሙላት፣ ለፅዳት ሥራ እና ለሌሎችም አገልግሎቶች የሚያስከፍሉት ዋጋ መጨመሩ ለቲኬት ዋጋ መናር ምክንያት ነው ይላሉ። “እነዚህ ወጪዎች እየጨመሩ በሚመጡበት ጊዜ እኛ ደግሞ የሚያካክስ ክፍያ እንጠይቃለን።” የኢትዮጵያ አየር መንገድ ራሱን የሚያስተዳድረው ራሱ በሚያገኘው ገንዘብ እንደሆነ የሚናገሩት አቶ ለማ፤ “ሠርቶ ከሚያገኘው ገቢ ደግሞ ወጪውን መሸፈን ይኖርበታል” ይላሉ። በፈረንጆቹ 2022 የአቪዬሽን ኢንዱስትሪው የቲኬት ዋጋ ጭማሪ ያሳየው በተለያዩ ምክንያቶች ነው ሲሉ የኬንያ ኤርዌይስ ኃላፊ ለቢቢሲ ይናገራሉ። በኢትዮጵያ የኬንያ ኤርዌይስ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ፌሊክስ ምዋንጋንጊ የቲኬት ዋጋ ገበያ ላይ ባለው ፍላጎትና አቅርቦት ላይ የተወሰነ ነው ይላሉ። ፌሊክስ እንደሚሉት ከኮቪድ በፊት ኢንዱስትሪው ድጎማ ያገኝ ነበር። ነገር ግን በድኅረ-ኮቪድ ይህ ድጎማ እምብዛም አይደለም። ኃላፊው እንደሚገልጹት በተለይ በአህጉረ አፍሪካ ያለው አቅርቦት በተወሰኑ አየር መንገዶች ላይ የተመረኮዘ በመሆኑ የቲኬት ዋጋው ላይ ለውጥ ታይቷል። “አፍሪካ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ አየር መንገዶች ጥቂት ናቸው። ይህ ማለት አቅርቦቱ የተወሰነ ነው ማለት ነው። ይህ በተዘዋዋሪ የበረራ ዋጋ እንዲወደድ ያደርጋል።” ኃላፊው ከኮቪድ በኋላ የፍላጎት ጭማሪ መታየቱን ጠቅሰው፣ ይህን ተከትሎ የቲኬት ዋጋ ከፍ ማለቱን ይናገራሉ። አክለው ደንበኞች አፍሪካ ውስጥ ለሚደረግ በረራ ከየትኛው የዓለም ክፍል ሆነው ቲኬት ቢቆርጡ ዋጋው ተመሳሳይ ነው ይላሉ። የኢትዮጵያ አየር መንገዱ ኃላፊ አንደኛው የድርጅቱ ዓላማ “ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ደንበኞችንና ኢትዮጵያውያንን ማገልገል ነው” ካሉ በኋላ “በአጠቃላይ ኦፕሬሽኑ ትርፋማ ሲሆን በአንዳንድ የበረራ መስመሮች በኪሳራም ይሁን ከሌሎች መስመሮች በሚገኘው ትርፍ እንሠራለን” ይላሉ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተወዳዳሪዎች አንዳንድ ጊዜ ዝቅተኛ ዋጋ ሊያቀርቡ እንደሚችሉ የሚያምኑት ኃላፊው “ብሔራዊ አየር መንገድ ከሆነ በአገሩ መንግሥት ሊደገፍ ይችላል።” “እንደምታውቁት በኮቪድ ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድና አንድ ሌላ ድርጅት ናቸው ከኪሳራ ማገገሚያ ገንዘብ [bailout] ያልተቀበሉት። እኛ ወጨያችንና ገቢያችንን በደንብ አመዛዝነን ነው የምንሠራው።” ኃላፊው፤ የቲኬት ዋጋ ቲኬቱ በሚቆርጥበት ወቅት ላይ የተመሠረት ሊሆን እንደሚችልም ይገልጣሉ። ለምሳሌ አንድ ደንበኛ ቲኬቱን የገዛው በረራው ከሚደረግበት ጊዜ ከስድስት ወራት በፊት ከሆነ ዋጋው የሚቀንሰው አየር መንገዱ ብሩን ተቀብሎ ስለሚሠራበት ይህ ታሳቢ ተደርጎ ቅናሽ እንደሚኖረው ያብራራሉ። በተቃራኒው ቲኬቱ የተቆረጠው ለበረራው ቅርብ በሆነ ጊዜ ከሆነ ‘ቢድ ፕራይሲንግ’ በተባለው መንገድ እንደሚሸጥ ይጠቅሳሉ። ‘ቢድ ፕራይሲንግ’ ምን እንደሆነ የሚያብራሩት አቶ ለማ፤ ይህ ማለት ደንበኞች በቀሩት ወንበሮች ይወዳደሩ እና የተሻለ ዋጋ የከፈለ ያገኘዋል ማለት ነው። ፌሊክስ፤ ልክ እንደ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቺፍ ኦፕሬቲንግ ኦፊሰር ለማ ያደቻ ሁሉ ደንበኞች የጉዞ ቀን ሲቃረብ ቲኬት የሚቆርጡ ከሆነ ዋጋው ከፍ ሊልባቸው እንደሚችል ይገልጻሉ። ማኔጀሩ አክለው ‘አይታክስ’ [አይ ገቨርንመንት] ታክስ ተብሎ የሚታወቀው የግብር ዓይነት ለቲኬት ዋጋ መወደድ አስተዋፅዖ እንዳለው ለቢቢሲ ይናገራሉ። ይህ ማለት አየር መንገዶች ለሚያርፉበት አገር መንግሥት የሚከፍሉት የአገልግሎት ክፍያ ነው። “ለምሳሌ ከናይሮቢ ወደ ኢንቴቤ [ኡጋንዳ] ሲኬድ ለመንግሥት የሚከፈል የመነሻ ክፍያ አለ። ይህ የበረራ ዋጋ ላይ ለውጥ ያመጣል። አንዳንድ ጊዜ የመንግሥት ግብር ከቲኬቱ ዋጋ አስከ 30 በመቶ ይደርሳል።” እየተገባደደ ያለው የፈረንጆቹ 2022 በአየር ትራንስፖርቱ ዘርፍ በጉዞ መሠረዝ፣ በዕቃዎች መጥፋት እና በበረራዎች መዘግየት ምክንያት ደንበኞች እጅግ የተጉላሉበት ዓመት ሆኖ ተመዝግቧል። በርካታ አየር መንገዶች ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በፊት የነበራቸውን ገቢ እና የበረራ ቁጥር ለማሳደግ በሚል በወሰዱት እርምጃ ኢንዱስትሪው ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ አሳይቷል። ዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ማኅበር [IATA] ዋና ሥራ አስኪያጅ ዊሊ ዌልሽ የነዳጅ ዋጋ በመጨሩ ምክንያት የበረራ ቲኬት ዋጋ “ያለጥርጥር ይጨምራል” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ማኅበሩ እንደሚለው በፈረንጆቹ 2021 የአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ከ15 ቢሊዮን ዶላር በላይ ከስሯል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቺፍ ኦፕሬቲንግ ኦፊሰር እንደጠቀሱት ድጎማ ካለገኙ ጥቂት አየር መንገዶች መካከል የሆነ አየር መንገደዱ [ኢቲ]፣ በወረርሽኙ ወቅት በጭነት አውሮፕላኖች ምክንያት ትርፋማ መሆኑን አውጆ ነበር። ነገር ግን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የአፍሪካ ቁንጮ የሚባለው የኢትዮጵያ አየር መንገድም ሆነ ሌሎች ዋና ዋና አየር መንገዶች የቲኬት ዋጋቸው የማይቀመስ ሆኗል። የበርካታ ደንበኞች ቅሬታ የሆነው የቅርብ ርቀት በረራዎች ዋጋ እጅግ መናር ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለዚህ ማብራሪያ ይኖረው ይሆን? ቺፍ ኦፕሬቲንግ ኦፊሰሩ አቶ ለማ ለዚህ ምክንያቱ ‘ፌቬኒው ማኔጅመንት’ ነው ይላሉ። “ለምሳሌ ከአዲስ አበባ ወደ አሥመራ ስንበር፣ አሥመራ ላይ የምንከፍላቸው ክፍያዎች አሉ። መንግሥት የሚጥለው ግብር ማለት ነው።” እንግሊዝ ውስጥ የአየር ማረፊያ ታክስ በጣም ከፍተኛ ነው የሚሉት ኃላፊው ውሃ መቀየር፣ ነዳጅ መሙላት እና ሌሎች መሬት ላይ የሚከናወኑ ሥራዎችን የሚሠሩ ድርጅቶች ክፍያቸው ላቅ ያለ እንደሆነ ይናገራሉ። አብዛኛውን ጊዜ አየር መንዱ ራቅ ወዳሉ፣ እንደ አውሮፓ እና አሜሪካ ሲጓዝ አማራጮች ስላሉት ዋጋቸው ተመጣጣኝ ከሆኑ ድርጅቶች ጋር እንደሚሠራ የሚናገሩት ኃላፊው፣ በአፍሪካ አገራት ግን ‘በሞኖፖሊ’ ስለተያዘ የዋጋ ልዩነት ያመጣል ይላሉ። “እንዳለመታደል ሆኖ አየር መንገዱ በቀዳሚነት በሚሠራባቸው የአፍሪካ አገራት ወጪው (ኮስት ኦፍ ቢዝነስ) በጣም ከፍተኛ ነው የሚሉት ኃላፊው፣ በዚህ ምክንያት የቲኬት ዋጋ እንደተወደደ ያስረዳሉ። በተለያዩ አገራት ያሉ የታክስ ሕጎች ለቲኬት ዋጋ መጨመር ሚና እንዳላቸው በማንሳት፣ አንዳንድ አገራት የገቢ ግብር ጭምር እንደሚያስከፍሉ ይናገራሉ። “በኢትዮጵያ መንግሥት እና በረራው በሚደረግበት አገር መንግሥት መካከል ታክስ አለመጠየቅ ስምምነት ካለ ታክሱ ኢትዮጵያ ውስጥ እንጂ ውጪ አገር አንከፍልም።” ነገር ግን ይህ ስምምነት ከሌለ የቲኬት ዋጋው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊኖረው እንደሚችል ኃላፊው ያብራራሉ። በኢትዮጵያ የኬንያ ኤርዌይስ ኃላፊ የሆኑት ፌሊክስም፣ አንዳንድ ጊዜ አጭር ርቀት የሚጓዝ በረራ ከረዥሙ የሚወደድበትን ምክንያት ያስረዳሉ። ለምሳሌ ይላሉ ኃላፊው፤ “ወደ ዱባይ የሚደረግ በረራ ረዥም ሰዓት ይወስዳል። ስለዚህ አንድ አሊያም ሁለት ሰዓት ከሚወስድ በረራ የላቀ ዋጋ ሊኖረው ይገባል ማለት አይደለም።” የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከናይሮቢ ዱባይ የሚያደርገው በረራ፤ ከናይሮቢ አዲስ አበባ ከሚያደርገው ያነሰ የቲኬት ዋጋ ነው ያለው። ከናይሮቢ አዲስ አበባ በአማካኝ ከአንድ ሰዓት ተኩል እስከ ሁለት ሰዓት ሲወስድ፣ ከናይሮቢ ዱባይ የሚደረግ በረራ 6 ሰዓታት ሊፈጅ ይችላል። የኬንያ ኤርዌይስ በረራም በተመሳሳይ ለአጭር ርቀት በረራ የሚያስከፍለው ክፍያ ላቅ ያለው ነው የሚል ወቀሳ ይደርስበታል። ፌሊክስ፤ ይህ የሚሆነው ‘ቫሊዩ ቤዝድ ፕራይሲንግ’ ስለምንጠቀም ነው ሲሉ ያስረዳሉ። “እኔ የማቀርበው አገልግሎት ዋጋ እና ገበያው ላይ ያለው ዋጋ ምን ያህል ነው? የሚለው ይታያል። ይህ ዋጋ ገበያ ላይ ባለው ውድድር የሚወሰን ይሆናል። ስለዚህ ረዥም ርቀት ያላቸው በረራዎች ከአጭር ርቀቱ በተነፃፃሪ ዝቅተኛ ዋጋ እንዲኖራቸው የሚያደርገው ያለው የአቅርቦት አቅም ነው።” ኃላፊው ሌላው ለአጭር ርቀት በረራዎች መወደድ ምክንያት ነው የሚሉት አገልግሎቱን የሚሰጡት ድርጅቶች ቁጥር ውሱን መሆኑ ነው። ከአዲስ አበባ-ናይሮቢ፤ ከናይሮቢ-አዲስ አበባ፤ የሚደረገውን በረራ በምሳሌነት የሚያነሱት ፌሊክስ ይህን አገልግሎት የሚሰጡት ‘ኬኪው’ እና ‘ኢቲ’ ብቻ ናቸው ይላሉ። ከሌሎች አገራት የሚነሱ አየር መንገዶች ይህ አገልግሎት ሊሰጡ ቢችሉም የሚወስዱት ሰዓት ግን ረዥም ሊሆን እንደሚችል ይጠቅሳሉ። አጭር ርቀት በረራ የሚሰጡ አየር መንገዶች ጥቂት መሆናቸው ውድድር ስለማይኖር ዋጋ ከፍ እንዲል እንደሚያደርገው ነው የሚገልጹት። ደንበኞች ወደ መዳረሻቸው ቀጥታ ሳይሆን አቆራርጠው ሲሄዱ ዋጋ የሚቀንሰው የሚወስድባቸው ሰዓት ከቀጥታ በረራ ከፍ ያለ ስለሆነ ነው የሚል ትንታኔ ይሰጣሉ። አሁን ባለው ሁኔታ የአውሮፕላን ቲኬት ዋጋ የመቀነሱ ነገር ከባድ እንደሆነ የአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ተንታኞች ይናገራሉ። ኤሜሬትስ፣ የጃፓን አየር መንገድ፣ ኤር ኤዥያ. . . በቲኬቶቻቸው ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ካሳዩ አየር መንገዶች መካከል ይጠቀሳሉ። በኮሮናቫይረስ ወረረሽኝ፣ በነዳጅ ዋጋ መናር እና በተለያዩ ክፍለ ዓለማት ባሉ ግጭቶች ምክንያት የተሰቀለው የበረራ ዋጋ በቅርቡ ይወርዳል ተብሎ አይገመትም። ፌሊክስ ግን ምናልባት “ከአንድ ዓመት በኋላ” የሚል ግምታቸውን ያስቀምጣሉ። “አየር መንገዶች አሁን ያለው ዋጋ ባለበት ይቀጥል ወይስ ገበያው ላይ ሌሎች አየር መንገዶች ይጨመሩ የሚል ጫና አለባቸው።” ፌሊክስ፤ ገበያው ላይ ተጨማሪ አየር መንገዶች እንዲመጡ ማድረጉ ዋጋውን ያረጋጋዋል የሚል እምነት አላቸው። “ይህ በዓመት ሁለት ጊዜ ይጓዝ የነበረ መንገደኛ በእጥፍ እንዲጓዝ ያስችለዋል ማለት ነው። ነገር ግን የበረራ ዋጋ ምናልባት ለአንድ ዓመት ባለበት የሚቀጥል ይመስለኛል። ምክንያቱም አየር መንገዶች ኪሳራታቸውን መመለስ ይፈልጋሉ።” ነገር ግን ደንበኞች ሁለት አማራጮችን ተጠቅመው የተሻለ የበረራ ዋጋ ሊያገኙ እንደሚችሉ ኃላፊው ይጠቁማሉ። አንደኛው ‘ፕሮሞሽናል ፌር’ [የማስታወቂያ ቅናሽ] መጠቀም ሲሆን፣ ሌላኛው ደግሞ ጉዞን አስቀድሞ በማቀድ በቅናሽ ቲኬት መቁረጥ ነው። | የአውሮፕላን ትኬት ዋጋ ‘የማይቀመስ’ የሆነው ለምንድን ነው? ወደፊትስ ይቀንስ ይሆን? በቅርቡ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ኬንያ መዲና፣ ናይሮቢ የበረሩ ሦስት ተሳፋሪዎች በነፍስ ወከፍ 28 ሺህ ብር ከፍለናል ይላሉ። ሦስቱ ጓደኛሞች በአማካኝ 1፡45 ሰዓት ለሚወስደው የኢኮኖሚ ክፍል በረራ ደርሶ መልስ በድምሩ 84 ሺህ ብር ከፍለዋል። እርግጥ ነው የአውሮፕላን በረራ ዋጋ በተሳፋሪ የበረራ ቀን እና ሰዓት እንዲሁም ‘በኢኮኖሚ እና በቢዝነስ ክፍሎች’ ምርጫ ይለያያል። ቢሆንም በተለይ ከኮቪድ ወረርሽኝ በኋላ በአህጉረ አፍሪካ የአውሮፕላን በረራ አቅሙ ያላቸው የሚጓዙበት እየሆነ ነው። ስሙን እንድንጠቅስ ያልፈለገ አንድ ኢትዮጵያዊ፣ ከናይሮቢ ወደ አዲስ አበባ የበረራ ዋጋ የማይቀመስ በመሆኑ “በሞያሌ በኩል በባስ አገር ቤት ደርሼ መጥቻለሁ” ይላል። የኬንያ አየር መንገድ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት ለበረራ ብዙ በማስከፈል ከአፍሪካ ቁንጮው ሆኖ ብቅ ብሏል። አየር መንገዱ አፍሪካ ውስጥ አሉ ከሚባሉት የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ከደቡብ አፍሪካ አየር መንገድ እንዲሁም ከፈረንሳዩ ኤር ፍራንስ የላቀ ገንዘብ ለቲኬት ያስከፍላል ተብሏል። ኬኪው (KQ) በተሰኘ ምሕፃረ ቃል የሚታወቀው የጎረቤት አገር ኬንያ አየር መንገድ ውድ ነው የተባለው ወደ 24 የአፍሪካ አገራት ሲበር የሚያስከፍለው ዋጋ ተጠንቶ ነው። አፍሪካን ኮምፒቲሽን ፎረም የተሰኘው ድረ ገጽ የኬንያ አየር መንገድ ለአገር ውስጥ እና ለዓለም አቀፍ በረራ ከፍተኛ ገንዘብ ይጠይቃል ሲል ፅፏል። ነገር ግን የደቡብ አፍሪካው እና የኢትዮጵያ አየር መንገድም እንዲሁ እጅግ ብዙ ለቲኬት ከሚያስከፍሉ የአፍሪካ አየር መንገዶች መካከል ናቸው። የኮቪድ ወረርሽኝ እና የዩክሬንን ጦርነት ተከትሎ የአውሮፕላን በረራ ዋጋ ጭማሪ ቢያሳይም በተለይ የአፍሪካ በረራዎች እጅግ መወደዳቸው ብዙዎችን ያነጋገረ ጉዳይ ሆኗል። በቅርቡ በዩናይትድ ኪንግደሙ ብሪቲሽ ኤርዌይስ ወደ ናይሮቢ ደርሶ መልስ የቆረጠው ዙሪች 800 ፓውንድ ገደማ እንደከፈለ ይናገራል። በተቃራኒው በቅርቡ የሚካሄደውን የኢትዮጵያ ታላቁ ሩጫን ለመታደም ወደ ኢትዮጵያ ለማቅናት ያቀደችው ሚሼል የቲኬት ዋጋው ከ800 ዶላር በላይ እንደሆነባት በትዊተር ገጿ ፅፋለች። ይህ አሁን ባለው የምንዛሪ ዋጋ 97 ሺህ ሽልንግ ገደማ ነው። ከኮቪድ ወረርሽኝ በፊት ከናይሮቢ አዲስ አበባ ደርሶ መልስ በኢትዮጵያ አየር መንገድም ይሁን በኬንያ ኤርዌይስ ለመብረር ከ19 ሺህ እስከ 25 ሺህ ሽልንግ ይጠይቅ ነበር። አሁን ግን ከ80 ሺህ ሽልንግ በላይ ይጠይቃል። ይህ የሆነበት ምክንያት ምንድን ነው? የነዳጅ ዋጋ ወይስ ሌላ ተጨማሪ ምክንያት? የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና የኦፕሬሽን ኦፊሰር [ሲኦኦ] ለማ ያደቻ፣ ለዚህ አንዱ ምክንያት የሌሎች አገራት መንግሥታት የሚጡልብን “ግብር” ነው ይላሉ። አቶ ለማ እንደሚሉት የአየር በረራ ዋጋ የሚተመነው በሚያስወጣው ወጪ ላይ ተመርኩዞ ነው። ለዚህም አየር መንገዳቸው ወደ ተለያዩ አገራት ሲጓዝ የሚያወጣውን ወጪ አስልቶ እንዲሁም አየር መንገዱ የሚያቀርበውን አገልግሎት ከግምት አስገብቶ ዋጋ ይተምናል። ይህንን በምሳሌ ሲያብራሩ አንድ ሰው በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀጥታ ከደቡብ አፍሪካ ሲመጣና ከደቡብ አፍሪካ ተነስቶ ናይሮቢ አርፎ ወደ አዲስ አበባ ሲመጣ ምቾቱ አንድ አይደለም ይላሉ። “አውሮፕላኑ ቀጥታ ከመምጣት ይልቅ ከአንድ ከተማ ወደ ሌላ እያቆራረጠ የሚጓዝ ከሆነ ይህ አንድን መንገደኛ ምቾት ይነሳል። ስለዚህ ቀጥታ ሲመጣ ዋጋው ይጨምራል፤ እያቆራረጠ ሲመጣ ደግሞ ዋጋው ሊቀንስ ይችላል” ይላሉ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ አብዛኛውን ጊዜ ከአፍሪካ፣ አውሮፓ፣ እስያና የአሜሪካ አገራት ቀጥታ በረራ እንደሚያደርግ የሚናገሩት ኃላፊው፣ ይህ ማለት ደንበኞች ሳይጉላሉ በምቾት ይመጣሉ ማለት ነው። ስለዚህ በገበያው መሠረት ላቅ ያለ ክፍያ ሊከፍሉ ይችላሉ ሲሉ ያስረዳሉ። ኦፕሬሽን ኦፊሰሩ ሌላው ለበረራ ቲኬት ዋጋ መወደድ እንደ ምክንያት የሚያነሱት በዓለም አቀፍ ገበያ የነዳጅ ዋጋ መናሩን ነው። አልፎም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ የአየር ማረፊያ የአገልግሎት ክፍያ ከፍ ማለቱን ኃላፊው ይጠቅሳሉ። አቶ ለማ፤ በአየር መንገዶች አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች መንገደኛ ከመመዝገብ ጀምሮ ለማሳፈር፣ ምግብ ለማቅረብ፣ ነዳጅ ለመሙላት፣ ለፅዳት ሥራ እና ለሌሎችም አገልግሎቶች የሚያስከፍሉት ዋጋ መጨመሩ ለቲኬት ዋጋ መናር ምክንያት ነው ይላሉ። “እነዚህ ወጪዎች እየጨመሩ በሚመጡበት ጊዜ እኛ ደግሞ የሚያካክስ ክፍያ እንጠይቃለን።” የኢትዮጵያ አየር መንገድ ራሱን የሚያስተዳድረው ራሱ በሚያገኘው ገንዘብ እንደሆነ የሚናገሩት አቶ ለማ፤ “ሠርቶ ከሚያገኘው ገቢ ደግሞ ወጪውን መሸፈን ይኖርበታል” ይላሉ። በፈረንጆቹ 2022 የአቪዬሽን ኢንዱስትሪው የቲኬት ዋጋ ጭማሪ ያሳየው በተለያዩ ምክንያቶች ነው ሲሉ የኬንያ ኤርዌይስ ኃላፊ ለቢቢሲ ይናገራሉ። በኢትዮጵያ የኬንያ ኤርዌይስ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ፌሊክስ ምዋንጋንጊ የቲኬት ዋጋ ገበያ ላይ ባለው ፍላጎትና አቅርቦት ላይ የተወሰነ ነው ይላሉ። ፌሊክስ እንደሚሉት ከኮቪድ በፊት ኢንዱስትሪው ድጎማ ያገኝ ነበር። ነገር ግን በድኅረ-ኮቪድ ይህ ድጎማ እምብዛም አይደለም። ኃላፊው እንደሚገልጹት በተለይ በአህጉረ አፍሪካ ያለው አቅርቦት በተወሰኑ አየር መንገዶች ላይ የተመረኮዘ በመሆኑ የቲኬት ዋጋው ላይ ለውጥ ታይቷል። “አፍሪካ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ አየር መንገዶች ጥቂት ናቸው። ይህ ማለት አቅርቦቱ የተወሰነ ነው ማለት ነው። ይህ በተዘዋዋሪ የበረራ ዋጋ እንዲወደድ ያደርጋል።” ኃላፊው ከኮቪድ በኋላ የፍላጎት ጭማሪ መታየቱን ጠቅሰው፣ ይህን ተከትሎ የቲኬት ዋጋ ከፍ ማለቱን ይናገራሉ። አክለው ደንበኞች አፍሪካ ውስጥ ለሚደረግ በረራ ከየትኛው የዓለም ክፍል ሆነው ቲኬት ቢቆርጡ ዋጋው ተመሳሳይ ነው ይላሉ። የኢትዮጵያ አየር መንገዱ ኃላፊ አንደኛው የድርጅቱ ዓላማ “ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ደንበኞችንና ኢትዮጵያውያንን ማገልገል ነው” ካሉ በኋላ “በአጠቃላይ ኦፕሬሽኑ ትርፋማ ሲሆን በአንዳንድ የበረራ መስመሮች በኪሳራም ይሁን ከሌሎች መስመሮች በሚገኘው ትርፍ እንሠራለን” ይላሉ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተወዳዳሪዎች አንዳንድ ጊዜ ዝቅተኛ ዋጋ ሊያቀርቡ እንደሚችሉ የሚያምኑት ኃላፊው “ብሔራዊ አየር መንገድ ከሆነ በአገሩ መንግሥት ሊደገፍ ይችላል።” “እንደምታውቁት በኮቪድ ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድና አንድ ሌላ ድርጅት ናቸው ከኪሳራ ማገገሚያ ገንዘብ [bailout] ያልተቀበሉት። እኛ ወጨያችንና ገቢያችንን በደንብ አመዛዝነን ነው የምንሠራው።” ኃላፊው፤ የቲኬት ዋጋ ቲኬቱ በሚቆርጥበት ወቅት ላይ የተመሠረት ሊሆን እንደሚችልም ይገልጣሉ። ለምሳሌ አንድ ደንበኛ ቲኬቱን የገዛው በረራው ከሚደረግበት ጊዜ ከስድስት ወራት በፊት ከሆነ ዋጋው የሚቀንሰው አየር መንገዱ ብሩን ተቀብሎ ስለሚሠራበት ይህ ታሳቢ ተደርጎ ቅናሽ እንደሚኖረው ያብራራሉ። በተቃራኒው ቲኬቱ የተቆረጠው ለበረራው ቅርብ በሆነ ጊዜ ከሆነ ‘ቢድ ፕራይሲንግ’ በተባለው መንገድ እንደሚሸጥ ይጠቅሳሉ። ‘ቢድ ፕራይሲንግ’ ምን እንደሆነ የሚያብራሩት አቶ ለማ፤ ይህ ማለት ደንበኞች በቀሩት ወንበሮች ይወዳደሩ እና የተሻለ ዋጋ የከፈለ ያገኘዋል ማለት ነው። ፌሊክስ፤ ልክ እንደ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቺፍ ኦፕሬቲንግ ኦፊሰር ለማ ያደቻ ሁሉ ደንበኞች የጉዞ ቀን ሲቃረብ ቲኬት የሚቆርጡ ከሆነ ዋጋው ከፍ ሊልባቸው እንደሚችል ይገልጻሉ። ማኔጀሩ አክለው ‘አይታክስ’ [አይ ገቨርንመንት] ታክስ ተብሎ የሚታወቀው የግብር ዓይነት ለቲኬት ዋጋ መወደድ አስተዋፅዖ እንዳለው ለቢቢሲ ይናገራሉ። ይህ ማለት አየር መንገዶች ለሚያርፉበት አገር መንግሥት የሚከፍሉት የአገልግሎት ክፍያ ነው። “ለምሳሌ ከናይሮቢ ወደ ኢንቴቤ [ኡጋንዳ] ሲኬድ ለመንግሥት የሚከፈል የመነሻ ክፍያ አለ። ይህ የበረራ ዋጋ ላይ ለውጥ ያመጣል። አንዳንድ ጊዜ የመንግሥት ግብር ከቲኬቱ ዋጋ አስከ 30 በመቶ ይደርሳል።” እየተገባደደ ያለው የፈረንጆቹ 2022 በአየር ትራንስፖርቱ ዘርፍ በጉዞ መሠረዝ፣ በዕቃዎች መጥፋት እና በበረራዎች መዘግየት ምክንያት ደንበኞች እጅግ የተጉላሉበት ዓመት ሆኖ ተመዝግቧል። በርካታ አየር መንገዶች ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በፊት የነበራቸውን ገቢ እና የበረራ ቁጥር ለማሳደግ በሚል በወሰዱት እርምጃ ኢንዱስትሪው ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ አሳይቷል። ዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ማኅበር [IATA] ዋና ሥራ አስኪያጅ ዊሊ ዌልሽ የነዳጅ ዋጋ በመጨሩ ምክንያት የበረራ ቲኬት ዋጋ “ያለጥርጥር ይጨምራል” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ማኅበሩ እንደሚለው በፈረንጆቹ 2021 የአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ከ15 ቢሊዮን ዶላር በላይ ከስሯል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቺፍ ኦፕሬቲንግ ኦፊሰር እንደጠቀሱት ድጎማ ካለገኙ ጥቂት አየር መንገዶች መካከል የሆነ አየር መንገደዱ [ኢቲ]፣ በወረርሽኙ ወቅት በጭነት አውሮፕላኖች ምክንያት ትርፋማ መሆኑን አውጆ ነበር። ነገር ግን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የአፍሪካ ቁንጮ የሚባለው የኢትዮጵያ አየር መንገድም ሆነ ሌሎች ዋና ዋና አየር መንገዶች የቲኬት ዋጋቸው የማይቀመስ ሆኗል። የበርካታ ደንበኞች ቅሬታ የሆነው የቅርብ ርቀት በረራዎች ዋጋ እጅግ መናር ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለዚህ ማብራሪያ ይኖረው ይሆን? ቺፍ ኦፕሬቲንግ ኦፊሰሩ አቶ ለማ ለዚህ ምክንያቱ ‘ፌቬኒው ማኔጅመንት’ ነው ይላሉ። “ለምሳሌ ከአዲስ አበባ ወደ አሥመራ ስንበር፣ አሥመራ ላይ የምንከፍላቸው ክፍያዎች አሉ። መንግሥት የሚጥለው ግብር ማለት ነው።” እንግሊዝ ውስጥ የአየር ማረፊያ ታክስ በጣም ከፍተኛ ነው የሚሉት ኃላፊው ውሃ መቀየር፣ ነዳጅ መሙላት እና ሌሎች መሬት ላይ የሚከናወኑ ሥራዎችን የሚሠሩ ድርጅቶች ክፍያቸው ላቅ ያለ እንደሆነ ይናገራሉ። አብዛኛውን ጊዜ አየር መንዱ ራቅ ወዳሉ፣ እንደ አውሮፓ እና አሜሪካ ሲጓዝ አማራጮች ስላሉት ዋጋቸው ተመጣጣኝ ከሆኑ ድርጅቶች ጋር እንደሚሠራ የሚናገሩት ኃላፊው፣ በአፍሪካ አገራት ግን ‘በሞኖፖሊ’ ስለተያዘ የዋጋ ልዩነት ያመጣል ይላሉ። “እንዳለመታደል ሆኖ አየር መንገዱ በቀዳሚነት በሚሠራባቸው የአፍሪካ አገራት ወጪው (ኮስት ኦፍ ቢዝነስ) በጣም ከፍተኛ ነው የሚሉት ኃላፊው፣ በዚህ ምክንያት የቲኬት ዋጋ እንደተወደደ ያስረዳሉ። በተለያዩ አገራት ያሉ የታክስ ሕጎች ለቲኬት ዋጋ መጨመር ሚና እንዳላቸው በማንሳት፣ አንዳንድ አገራት የገቢ ግብር ጭምር እንደሚያስከፍሉ ይናገራሉ። “በኢትዮጵያ መንግሥት እና በረራው በሚደረግበት አገር መንግሥት መካከል ታክስ አለመጠየቅ ስምምነት ካለ ታክሱ ኢትዮጵያ ውስጥ እንጂ ውጪ አገር አንከፍልም።” ነገር ግን ይህ ስምምነት ከሌለ የቲኬት ዋጋው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊኖረው እንደሚችል ኃላፊው ያብራራሉ። በኢትዮጵያ የኬንያ ኤርዌይስ ኃላፊ የሆኑት ፌሊክስም፣ አንዳንድ ጊዜ አጭር ርቀት የሚጓዝ በረራ ከረዥሙ የሚወደድበትን ምክንያት ያስረዳሉ። ለምሳሌ ይላሉ ኃላፊው፤ “ወደ ዱባይ የሚደረግ በረራ ረዥም ሰዓት ይወስዳል። ስለዚህ አንድ አሊያም ሁለት ሰዓት ከሚወስድ በረራ የላቀ ዋጋ ሊኖረው ይገባል ማለት አይደለም።” የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከናይሮቢ ዱባይ የሚያደርገው በረራ፤ ከናይሮቢ አዲስ አበባ ከሚያደርገው ያነሰ የቲኬት ዋጋ ነው ያለው። ከናይሮቢ አዲስ አበባ በአማካኝ ከአንድ ሰዓት ተኩል እስከ ሁለት ሰዓት ሲወስድ፣ ከናይሮቢ ዱባይ የሚደረግ በረራ 6 ሰዓታት ሊፈጅ ይችላል። የኬንያ ኤርዌይስ በረራም በተመሳሳይ ለአጭር ርቀት በረራ የሚያስከፍለው ክፍያ ላቅ ያለው ነው የሚል ወቀሳ ይደርስበታል። ፌሊክስ፤ ይህ የሚሆነው ‘ቫሊዩ ቤዝድ ፕራይሲንግ’ ስለምንጠቀም ነው ሲሉ ያስረዳሉ። “እኔ የማቀርበው አገልግሎት ዋጋ እና ገበያው ላይ ያለው ዋጋ ምን ያህል ነው? የሚለው ይታያል። ይህ ዋጋ ገበያ ላይ ባለው ውድድር የሚወሰን ይሆናል። ስለዚህ ረዥም ርቀት ያላቸው በረራዎች ከአጭር ርቀቱ በተነፃፃሪ ዝቅተኛ ዋጋ እንዲኖራቸው የሚያደርገው ያለው የአቅርቦት አቅም ነው።” ኃላፊው ሌላው ለአጭር ርቀት በረራዎች መወደድ ምክንያት ነው የሚሉት አገልግሎቱን የሚሰጡት ድርጅቶች ቁጥር ውሱን መሆኑ ነው። ከአዲስ አበባ-ናይሮቢ፤ ከናይሮቢ-አዲስ አበባ፤ የሚደረገውን በረራ በምሳሌነት የሚያነሱት ፌሊክስ ይህን አገልግሎት የሚሰጡት ‘ኬኪው’ እና ‘ኢቲ’ ብቻ ናቸው ይላሉ። ከሌሎች አገራት የሚነሱ አየር መንገዶች ይህ አገልግሎት ሊሰጡ ቢችሉም የሚወስዱት ሰዓት ግን ረዥም ሊሆን እንደሚችል ይጠቅሳሉ። አጭር ርቀት በረራ የሚሰጡ አየር መንገዶች ጥቂት መሆናቸው ውድድር ስለማይኖር ዋጋ ከፍ እንዲል እንደሚያደርገው ነው የሚገልጹት። ደንበኞች ወደ መዳረሻቸው ቀጥታ ሳይሆን አቆራርጠው ሲሄዱ ዋጋ የሚቀንሰው የሚወስድባቸው ሰዓት ከቀጥታ በረራ ከፍ ያለ ስለሆነ ነው የሚል ትንታኔ ይሰጣሉ። አሁን ባለው ሁኔታ የአውሮፕላን ቲኬት ዋጋ የመቀነሱ ነገር ከባድ እንደሆነ የአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ተንታኞች ይናገራሉ። ኤሜሬትስ፣ የጃፓን አየር መንገድ፣ ኤር ኤዥያ. . . በቲኬቶቻቸው ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ካሳዩ አየር መንገዶች መካከል ይጠቀሳሉ። በኮሮናቫይረስ ወረረሽኝ፣ በነዳጅ ዋጋ መናር እና በተለያዩ ክፍለ ዓለማት ባሉ ግጭቶች ምክንያት የተሰቀለው የበረራ ዋጋ በቅርቡ ይወርዳል ተብሎ አይገመትም። ፌሊክስ ግን ምናልባት “ከአንድ ዓመት በኋላ” የሚል ግምታቸውን ያስቀምጣሉ። “አየር መንገዶች አሁን ያለው ዋጋ ባለበት ይቀጥል ወይስ ገበያው ላይ ሌሎች አየር መንገዶች ይጨመሩ የሚል ጫና አለባቸው።” ፌሊክስ፤ ገበያው ላይ ተጨማሪ አየር መንገዶች እንዲመጡ ማድረጉ ዋጋውን ያረጋጋዋል የሚል እምነት አላቸው። “ይህ በዓመት ሁለት ጊዜ ይጓዝ የነበረ መንገደኛ በእጥፍ እንዲጓዝ ያስችለዋል ማለት ነው። ነገር ግን የበረራ ዋጋ ምናልባት ለአንድ ዓመት ባለበት የሚቀጥል ይመስለኛል። ምክንያቱም አየር መንገዶች ኪሳራታቸውን መመለስ ይፈልጋሉ።” ነገር ግን ደንበኞች ሁለት አማራጮችን ተጠቅመው የተሻለ የበረራ ዋጋ ሊያገኙ እንደሚችሉ ኃላፊው ይጠቁማሉ። አንደኛው ‘ፕሮሞሽናል ፌር’ [የማስታወቂያ ቅናሽ] መጠቀም ሲሆን፣ ሌላኛው ደግሞ ጉዞን አስቀድሞ በማቀድ በቅናሽ ቲኬት መቁረጥ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cn41y4nn9jdo |
3politics
| ተመድ በወታደሮች ቁጥጥር ስር የሚገኙት የማሊ ፐሬዚዳንት ባስቸኳይ እንዲለቀቁ ጥሪ አቀረበ | የማሊ መከላከያ ሰራዊት የሀገሪቱን ፕሬዝደንት ባህ ንዳዋና ጠቅላይ ሚኒስተር ሞክታር ኦዋኔ በቁጥጥር ስር አዋለ መባሉን ተከትሎ በሀገሪቱ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጀት ተልዕኮ መሪዎቹ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቋል። ተልዕኮው በፈረንሳኛ ቋንቋ በትዊተር አማካኝነት ባቀረበው ጥሪ የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ማሊ ነገሮችን "እንድታረጋጋ"ም ጠይቋል። ይህ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጥሪ የሀገሪቱ የሽግግር መንግስት ጊዜያዊ ፕሬዝዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር በዋና ከተማዋ አቅራቢያ በሚኝ ወታደራዊ ካምፕ መወሰዳቸውን ተከትሎ የመጣ ነው። የመከላከያ ሚንስትሩም በወታደሩ ቁጥጥር ስር እንደዋሉም ተዘግቧል። ታዲያ ይህ ድርጊት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በሀገሪቱ ሁለተኛ መፈንቅለ መንግስት እንዳያስከትል ስጋት ጭሯል። ትላንት - ሰኞ የጊዜያዊ መንግስቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለኤ ኤፍ ፒ የዜና ተቋም በስልክ ወታደሮች "ሊይዟቸው መምጣታቸውን" ተናግረው ነበር ታዲያ ሀሳባቸውን ሳይቆጩ ስልኩ መቋረጡንም ነው ኤ ኤፍ ፒ የዘገበው። የአፍሪካ ህብረት፣ የሰሜን አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ፣ የአውሮፓ ህብረትና አሜሪካም ድርጊቱን አውግዘው ፖለቲከኞቹ ያለቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱም ጠይቀዋል። የመሪዎቹ እስር የተሰማው የሀገሪቱ መንግስት በባለፈው መፈንቅለ መንግስት የተሳተፉ ሁለት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ላይ የስልጣን ሽግሽግ ማድረጉ ከታወቀ ከአንድ ሰዓት በኋላ ነው። ከ ዘጠኝ ወራት በፊትም በተደረገ መፈንቅለ መንግስት በስልጣን የነበሩት ፕሬዝዳንት ከተነሱ በኋላ ማሊ መረጋጋት ርቋት ነበር። | ተመድ በወታደሮች ቁጥጥር ስር የሚገኙት የማሊ ፐሬዚዳንት ባስቸኳይ እንዲለቀቁ ጥሪ አቀረበ የማሊ መከላከያ ሰራዊት የሀገሪቱን ፕሬዝደንት ባህ ንዳዋና ጠቅላይ ሚኒስተር ሞክታር ኦዋኔ በቁጥጥር ስር አዋለ መባሉን ተከትሎ በሀገሪቱ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጀት ተልዕኮ መሪዎቹ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቋል። ተልዕኮው በፈረንሳኛ ቋንቋ በትዊተር አማካኝነት ባቀረበው ጥሪ የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ማሊ ነገሮችን "እንድታረጋጋ"ም ጠይቋል። ይህ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጥሪ የሀገሪቱ የሽግግር መንግስት ጊዜያዊ ፕሬዝዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር በዋና ከተማዋ አቅራቢያ በሚኝ ወታደራዊ ካምፕ መወሰዳቸውን ተከትሎ የመጣ ነው። የመከላከያ ሚንስትሩም በወታደሩ ቁጥጥር ስር እንደዋሉም ተዘግቧል። ታዲያ ይህ ድርጊት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በሀገሪቱ ሁለተኛ መፈንቅለ መንግስት እንዳያስከትል ስጋት ጭሯል። ትላንት - ሰኞ የጊዜያዊ መንግስቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለኤ ኤፍ ፒ የዜና ተቋም በስልክ ወታደሮች "ሊይዟቸው መምጣታቸውን" ተናግረው ነበር ታዲያ ሀሳባቸውን ሳይቆጩ ስልኩ መቋረጡንም ነው ኤ ኤፍ ፒ የዘገበው። የአፍሪካ ህብረት፣ የሰሜን አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ፣ የአውሮፓ ህብረትና አሜሪካም ድርጊቱን አውግዘው ፖለቲከኞቹ ያለቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱም ጠይቀዋል። የመሪዎቹ እስር የተሰማው የሀገሪቱ መንግስት በባለፈው መፈንቅለ መንግስት የተሳተፉ ሁለት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ላይ የስልጣን ሽግሽግ ማድረጉ ከታወቀ ከአንድ ሰዓት በኋላ ነው። ከ ዘጠኝ ወራት በፊትም በተደረገ መፈንቅለ መንግስት በስልጣን የነበሩት ፕሬዝዳንት ከተነሱ በኋላ ማሊ መረጋጋት ርቋት ነበር። | https://www.bbc.com/amharic/news-57237154 |
3politics
| የኢራንን የኑክሊየር ሳይንቲስቶች እያደነ የሚገድላቸው ማን ነው? | ባለፈው ሳምንት የእስራኤል ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚሆኑት ሰው ድንገት ተነስተው ወደ ቱርክ በረሩ። አንድ የኢራን ህቡዕ ቡድን የእስራኤል ቱሪስቶችን ለመግደል ተንቀሳቅሷል የሚል መረጃ ስለደረሳቸው ነው ፈጥነው ቱርክ የገቡት። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በእስራኤልና ኢራን መካከል የጦፈ ግን ደግሞ ድብቅ ውጊያ እየተደረገ ነው፤ ከመጋረጃ በስተጀርባ። ይህ ነገር ወደለየለት ጦርነት እንዳያመራ መፈራቱ አልቀረም። ለበርካታ ዓመታት ሁለቱ አገራት በምሥጢራዊ ጥቃት ተጠምደው ነው የኖሩት። እስራኤል በምድር ላይ የኢራንን ያህል ጠላት የለኝም ትላለች። ኢራን በበኩሏ በይፋ እስራኤል ከመካከለኛው ምሥራቅ መጥፋት ያለባት አገር ናት እስከማለት ደፍራ ተናግራለች። በዋናነት ደግሞ ከአሜሪካ ጋር በማበር በአካባቢው ገናና አገር ሆኜ እንዳልወጣ፣ ዕድገቴን እንዳላፋጥን አንቃ ይዛኛለች በማለት ትከሳታለች። አንዳቸው በአንዳቸው ላይ ጣት ሲጠቋቆሙ ቆይተው ነገሮች ከፈረንጆች 2020 ወዲህ ጀምሮ መልካቸውን እየቀየሩ መጡ። ኢራን የእስራኤል ምሥጢራዊ ቡድን ታላቁን የኑክሊየር ሳይንቲስቴን ገደለብኝ ስትል ከሰሰች። ሳይንቲስቱ ሞህሲን ፋኽሪዛድ ናቸው። የተገደሉት በቴህራን ጎዳና ላይ መኪናቸውን እያሽከረከሩ ሳለ በርቀት መቆጣጠሪያ በሚታዘዝ መትረየስ ተደብድበው ነበር። እስራኤል ድርጊቱን ስለመፈጸሟ አላመነችም፣ አላስተባበለችም። ሁልጊዜም እንደምታደርገው ዝምታን መርጣለች። ሞህሲን ፋኽሪዛድ እንዲህ በህቡዕ ቡድን ሲገደሉ የመጀመሪያው የኢራን ሳይንቲስት አይደሉም። ከፈረንጆቹ 2007 ወዲህ ብቻ አምስት የኢራን ቁንጮ ሳይንቲስቶች ተገድለዋል። ኒውዮርክ ታይምስ እኚህ ባለሥልጣን በምን ዝግጅትና ሁኔታ እንደተገደሉ ምንጮቹን ሳይጠቅስ በዝርዝር ዘግቦ ነበር። የቀድሞው የሞሳድ አለቃ በኋላ ላይ እንደተናገሩት እኚህ የኑክሊየር ሳይንቲስት ለዓመታት የእሰራኤል ራስ ምታት ሆነው ቆይተዋል። በኑክሊየር ሳይንስ ዘርፍ ያላቸው ዕውቀት እስራኤልን ሲያሳስባት ነው የኖረው። “በክትትላችን ውስጥ ነው የኖሩት” ብለዋል እኚህ የሞሳድ የቀድሞ ባለሥልጣን። የምዕራብ አገራት የደኅንነት መሥሪያ ቤቶች እንደሚሉት ከሆነ ሞህሲን ፋኽሪዛድ ኢራን በምሥጢር ልትገነባው ለምትሞክረው የኒክሊየር ኃይል ዋናው አዛዥ ነበሩ። ከዚህ ወዲያ ኢራንና እስራኤል ከመጋረጃ ጀርባ በተለያዩ ኦፕሬሽኖች ተጠምደው ነው የቆዩት። ጆ ባይደን በቀዳሚያቸው ዶናልድ ትራምፕ እንደ መናኛ ተቀዳዶ የተጣለውን ሰላማዊ የኑክሊየር ስምምነት ለመመለስ እየጣሩ ነው። ስምምነቱን ለመመለስ አንድ ዋና ማነቆ ሆኖ የያዛቸው ጉዳይ በሽብር ቡድን ዝርዝር የገባውን የኢራን አብዮታዊ ዘብ ስሙ ከሽብርተኞች መዝገብ ይፋቅ የሚለው ሐሳብ አሜሪካንን ስላላስማማት ነው። እስራኤል በቅርብ ጊዜ በኢራን ተደግሶልኝ ነበር ያለችውን የግድያ ሙከራ ማክሸፏን ተናግራለች። ኢራን በበኩሏ በእስራኤል ውስጥ የድሮን ጥቃት ኦፕሬሽን ማድረጓን በኩራት ገልጻለች። ሆኖም ዝርዝር ሁኔታው አልተብራራም። ሁለቱ አገራት አንዱ የሌላውን የመርከብ ጭነት በማጥቃት ይወነጃጀላሉ። ኢራን ከምድር በታች ባለት የኑክሊየር ማብሊያ ማዕከል ላይ ለተፈጸመባት አሻጥር እስራኤልን ተጠያቂ አድርጋለች። ከቀናት በፊት ኢራን ሦስት ከሞሳድ ጋር ግንኙነት ነበራቸው ያለቻቸውን፣ ሌላ ተጨማሪ የኢራን ኒክሊየር ሳይንቲስት ሊገድሉ እንደሆነ እንደደረሰችባቸው የከሰሰቻቸውን ሰዎች ፍርድ ቤት ልታቀርብ እንደሆነ ተናግራለች። ኢራን ከዚህ ሌላ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገሯ በማይታወቅ ሁኔታ እየሞቱ ያሉ ቁልፍ ሰዎች እያጋጠሟት እንደሆነ አምናለች። ከእነዚህ መካከልም ሁለት የኤሮስፔስ ኃላፊዎች በሥራ ላይ ሳሉ “ተሰውተዋል” ብላለች። አሟሟታቸው ግን ምሥጢራዊ ነው። ሌላ በመከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ ይሠራ የነበረ መሐንዲስም እንዲሁ በአሻጥር ተገድሎብኛል ብላለች። ይሁንና ለእነዚህ ግድያዎች እስራኤልን በቀጥታ ተጠያቂ እስከማድረግ አልሄደችም። ከመጋረጃው ጀርባ በሁለቱ አገራት መካከል እየተደረገ ባለው ጦርነት እስራኤል እና ኢራን ይበልጥ ወደ መድረክ እየወጡ ይመስላል። ይህ ነገር ወደ ሆሊውድም ዘልቆ በአፕል የቴሌቪዥን የቲቪ ትዕይንት ላይ አንድ የሞሳድ ሰላይ የኢራንን አብዮታዊ ጥበቃን በጣጥሶ ሲገባ ያሳያል። የሆሊውድ ፊልም ግን በመሬት ላይ የማይታይ ነገር አይደለም። ለምሳሌ ከቅርብ ቀናት በፊት እስራኤል ዜጎቼ ሆይ! እባካችሁ ወደ ቱርክ አትሂዱ፤ በቱርክ አገር ያላችሁም ከሆነ ቶሎ ውጡ ስትል አስታውቃለች። ይህም አንድ የኢራን ህቡዕ ቡድን በአንዳች ስፍራ የእስራኤል ዜጎችን ኢላማ ለማድረግ እየተሰናዳ መሆኑን ስለደረሰችበት ነው። መሐመድ ሙራንዲ የቴህራን ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር ናቸው። የኢራን የኑክሊየር ድርድር የሚዲያ ጉዳዮች አማካሪም ናቸው። በምዕራባዊያን ከለላ ሰላማዊ ዜጎችን እያደኑ መግደል ማስገደል ለእስራኤል የተለመደ ተግባር ነው ይላሉ። “ይሁንና እስራኤል እንደምትለው ያህል በኢራን ውስጥ ኦፕሬሽን አታስፈጽምም። በድንገት የሞቱ የኢራን ዜጎችም የእስራኤል ልዩ ኦፕሬሽን የሥራ ውጤት አድርጎ የማቅረብ አዝማሚያ አለ” ባይ ናቸው። ፕሮፌሰሩ ጨምረውም “አትጠራጠሩ፣ ኢራን እያንዳንዱን ጥቃት ትበቀላለች” ብለዋል። ኢራን ልዩ ኃይሏ 'ቁዱስ' ይባላል። ቁዱስ የአብዮታዊ ዘብ አንድ ክንፍ ነው። ዓላማና ተግባሩ ደግሞ ከኢራን ውጪ ምሥጢራዊ ግዳጆችን መወጣት ነው። የቁዱስ ብርጌድ ዋና አለቃ ጄኔራል ኢስማኢል ቃኒ፣ ኢራን ማንኛውንም የአሜሪካና የእስራኤል ጠላት የሆነ ቡድንን መደገፏን ትቀጥልበታለች ብለዋል። ጄኔራል ኢስማኢል ማናቸው? ከተባለ ቃሲም ሱለይማኒን የተኩ ሰው ናቸው። ቃሲም ሱለይማኒ ደግሞ ከሁለት ዓመት በፊት በኢራቅ ዋና ከተማ ባግዳድ፣ በጥር ወር፣ አሜሪካ በድሮን ጥቃት እንደገደለቻቸው ይታወሳል። ሱለይማኒ አሜሪካ በዐይነ ቁራኛ ስትከታተላቸው የነበሩ ሰው ናቸው። ዶናልድ ትራምፕ እርምጃ ይወሰደብት እስኪሉ ድረስ በአሜሪካ የስለላ ቡድን መነጽር ሥር ነበር። ትራምፕ እርምጃው ከተወሰደ በኋላ “ሱለይማኒ የዓለማችን ቁጥር አንድ አሸባሪ ነበር” ሲሉ ተናግረዋል። ትራምፕ ሱለይማኒ እንዲገደሉ የወሰኑት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ማይክ ፓምፔዎ ግፊት ነው ተብሏል። ዶናልድ ትራምፕ በመካከለኛው ምሥራቅ የኢራን ሚና እንዲኮሰምን ትልቁን ሚና የተጫወቱ የእስራኤል ባለውለታ ተደርገው ይወስዳሉ። በተለይ አስራኤል ከመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻል የቀየሰችወን ‘አብረሃም አኮርድ’ የተባለውን ዕቅዷን በማስተዋወቅ እስራኤልን ከአረብ አገራት ጋር አወዳጅተው ነው የሄዱት። የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ እና ባህሬይን ከእስራኤል ጋር ግንኙነታቸውን እንዲያድሱ በማገዝ ‘አብረሃም አኮርድ’ ስምምነትን በማፈጣጠም ይበልጥ ኢራንን የመነጠል ሥራም ሠርተዋል። “ኢራን የአብረሃም አኮርድ ስምምነቶችን እጅግ ትጸየፋለች” ይላሉ አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ የአረብ ዲፕሎማት። አንድ የኢራን የቀድሞ ባለሥልጣን ግን ይህን ያሰተባብላሉ። “ስምምነቱን ባንወደውም ዘላቂ እንደማይሆን እናውቃለን፤ ጊዜያዊ እፍ እፍ ነው፤ የትም አያደርስም” ብለዋል ለቢቢሲ። የጆ ባይደን የሰሞኑ የሳዑዲ አረቢያና የእስራኤል ጉብኝት እንዳለ ሆኖ፣ አንድ በባይደን አስተዳደር ውስጥ ያሉ ባለሥልጣን የእስራኤልና ኢራን ፍጥጫ ወደከፋ ደረጃ እንደማይሸጋገር እናውቃለን፤ ቢያንስ በአጭር ጊዜ ያ እንደማይሆን እንረዳለን ይላሉ። ሪች ጎልድበርግ ደግሞ መቀመጫውን ዋሺንግተን ያደረገ የመከላከያ ጉዳዮች የጥናትና ምርምር ቡድን ባልደረባ ናቸው። እሳቸው እንደሚያምኑት እስራኤል የምታደርጋቸው ምሥጢራዊ ኦፕሬሽኖች ከመበርከታቸው የተነሳ አሁን አሁን ተራ ዕለታዊ ጉዳዮች እንዲመስሉ እያደረገች ነው። “...አንድ ቀን ግን ዓለም ከመንቃቱ በፊት እስራኤል በኢራን ኑክሊየር ማበልጸጊያ ማዕከል ላይ ድንገተኛ የአየር ጥቃት ማድረሷ አይቀርም፤ ዓለም ጥቃቱን እናስቁመው ከማለቱ በፊት ጥቃቱ ተገባዶ እናገኘው ይሆናል” ብለዋል። | የኢራንን የኑክሊየር ሳይንቲስቶች እያደነ የሚገድላቸው ማን ነው? ባለፈው ሳምንት የእስራኤል ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚሆኑት ሰው ድንገት ተነስተው ወደ ቱርክ በረሩ። አንድ የኢራን ህቡዕ ቡድን የእስራኤል ቱሪስቶችን ለመግደል ተንቀሳቅሷል የሚል መረጃ ስለደረሳቸው ነው ፈጥነው ቱርክ የገቡት። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በእስራኤልና ኢራን መካከል የጦፈ ግን ደግሞ ድብቅ ውጊያ እየተደረገ ነው፤ ከመጋረጃ በስተጀርባ። ይህ ነገር ወደለየለት ጦርነት እንዳያመራ መፈራቱ አልቀረም። ለበርካታ ዓመታት ሁለቱ አገራት በምሥጢራዊ ጥቃት ተጠምደው ነው የኖሩት። እስራኤል በምድር ላይ የኢራንን ያህል ጠላት የለኝም ትላለች። ኢራን በበኩሏ በይፋ እስራኤል ከመካከለኛው ምሥራቅ መጥፋት ያለባት አገር ናት እስከማለት ደፍራ ተናግራለች። በዋናነት ደግሞ ከአሜሪካ ጋር በማበር በአካባቢው ገናና አገር ሆኜ እንዳልወጣ፣ ዕድገቴን እንዳላፋጥን አንቃ ይዛኛለች በማለት ትከሳታለች። አንዳቸው በአንዳቸው ላይ ጣት ሲጠቋቆሙ ቆይተው ነገሮች ከፈረንጆች 2020 ወዲህ ጀምሮ መልካቸውን እየቀየሩ መጡ። ኢራን የእስራኤል ምሥጢራዊ ቡድን ታላቁን የኑክሊየር ሳይንቲስቴን ገደለብኝ ስትል ከሰሰች። ሳይንቲስቱ ሞህሲን ፋኽሪዛድ ናቸው። የተገደሉት በቴህራን ጎዳና ላይ መኪናቸውን እያሽከረከሩ ሳለ በርቀት መቆጣጠሪያ በሚታዘዝ መትረየስ ተደብድበው ነበር። እስራኤል ድርጊቱን ስለመፈጸሟ አላመነችም፣ አላስተባበለችም። ሁልጊዜም እንደምታደርገው ዝምታን መርጣለች። ሞህሲን ፋኽሪዛድ እንዲህ በህቡዕ ቡድን ሲገደሉ የመጀመሪያው የኢራን ሳይንቲስት አይደሉም። ከፈረንጆቹ 2007 ወዲህ ብቻ አምስት የኢራን ቁንጮ ሳይንቲስቶች ተገድለዋል። ኒውዮርክ ታይምስ እኚህ ባለሥልጣን በምን ዝግጅትና ሁኔታ እንደተገደሉ ምንጮቹን ሳይጠቅስ በዝርዝር ዘግቦ ነበር። የቀድሞው የሞሳድ አለቃ በኋላ ላይ እንደተናገሩት እኚህ የኑክሊየር ሳይንቲስት ለዓመታት የእሰራኤል ራስ ምታት ሆነው ቆይተዋል። በኑክሊየር ሳይንስ ዘርፍ ያላቸው ዕውቀት እስራኤልን ሲያሳስባት ነው የኖረው። “በክትትላችን ውስጥ ነው የኖሩት” ብለዋል እኚህ የሞሳድ የቀድሞ ባለሥልጣን። የምዕራብ አገራት የደኅንነት መሥሪያ ቤቶች እንደሚሉት ከሆነ ሞህሲን ፋኽሪዛድ ኢራን በምሥጢር ልትገነባው ለምትሞክረው የኒክሊየር ኃይል ዋናው አዛዥ ነበሩ። ከዚህ ወዲያ ኢራንና እስራኤል ከመጋረጃ ጀርባ በተለያዩ ኦፕሬሽኖች ተጠምደው ነው የቆዩት። ጆ ባይደን በቀዳሚያቸው ዶናልድ ትራምፕ እንደ መናኛ ተቀዳዶ የተጣለውን ሰላማዊ የኑክሊየር ስምምነት ለመመለስ እየጣሩ ነው። ስምምነቱን ለመመለስ አንድ ዋና ማነቆ ሆኖ የያዛቸው ጉዳይ በሽብር ቡድን ዝርዝር የገባውን የኢራን አብዮታዊ ዘብ ስሙ ከሽብርተኞች መዝገብ ይፋቅ የሚለው ሐሳብ አሜሪካንን ስላላስማማት ነው። እስራኤል በቅርብ ጊዜ በኢራን ተደግሶልኝ ነበር ያለችውን የግድያ ሙከራ ማክሸፏን ተናግራለች። ኢራን በበኩሏ በእስራኤል ውስጥ የድሮን ጥቃት ኦፕሬሽን ማድረጓን በኩራት ገልጻለች። ሆኖም ዝርዝር ሁኔታው አልተብራራም። ሁለቱ አገራት አንዱ የሌላውን የመርከብ ጭነት በማጥቃት ይወነጃጀላሉ። ኢራን ከምድር በታች ባለት የኑክሊየር ማብሊያ ማዕከል ላይ ለተፈጸመባት አሻጥር እስራኤልን ተጠያቂ አድርጋለች። ከቀናት በፊት ኢራን ሦስት ከሞሳድ ጋር ግንኙነት ነበራቸው ያለቻቸውን፣ ሌላ ተጨማሪ የኢራን ኒክሊየር ሳይንቲስት ሊገድሉ እንደሆነ እንደደረሰችባቸው የከሰሰቻቸውን ሰዎች ፍርድ ቤት ልታቀርብ እንደሆነ ተናግራለች። ኢራን ከዚህ ሌላ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገሯ በማይታወቅ ሁኔታ እየሞቱ ያሉ ቁልፍ ሰዎች እያጋጠሟት እንደሆነ አምናለች። ከእነዚህ መካከልም ሁለት የኤሮስፔስ ኃላፊዎች በሥራ ላይ ሳሉ “ተሰውተዋል” ብላለች። አሟሟታቸው ግን ምሥጢራዊ ነው። ሌላ በመከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ ይሠራ የነበረ መሐንዲስም እንዲሁ በአሻጥር ተገድሎብኛል ብላለች። ይሁንና ለእነዚህ ግድያዎች እስራኤልን በቀጥታ ተጠያቂ እስከማድረግ አልሄደችም። ከመጋረጃው ጀርባ በሁለቱ አገራት መካከል እየተደረገ ባለው ጦርነት እስራኤል እና ኢራን ይበልጥ ወደ መድረክ እየወጡ ይመስላል። ይህ ነገር ወደ ሆሊውድም ዘልቆ በአፕል የቴሌቪዥን የቲቪ ትዕይንት ላይ አንድ የሞሳድ ሰላይ የኢራንን አብዮታዊ ጥበቃን በጣጥሶ ሲገባ ያሳያል። የሆሊውድ ፊልም ግን በመሬት ላይ የማይታይ ነገር አይደለም። ለምሳሌ ከቅርብ ቀናት በፊት እስራኤል ዜጎቼ ሆይ! እባካችሁ ወደ ቱርክ አትሂዱ፤ በቱርክ አገር ያላችሁም ከሆነ ቶሎ ውጡ ስትል አስታውቃለች። ይህም አንድ የኢራን ህቡዕ ቡድን በአንዳች ስፍራ የእስራኤል ዜጎችን ኢላማ ለማድረግ እየተሰናዳ መሆኑን ስለደረሰችበት ነው። መሐመድ ሙራንዲ የቴህራን ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር ናቸው። የኢራን የኑክሊየር ድርድር የሚዲያ ጉዳዮች አማካሪም ናቸው። በምዕራባዊያን ከለላ ሰላማዊ ዜጎችን እያደኑ መግደል ማስገደል ለእስራኤል የተለመደ ተግባር ነው ይላሉ። “ይሁንና እስራኤል እንደምትለው ያህል በኢራን ውስጥ ኦፕሬሽን አታስፈጽምም። በድንገት የሞቱ የኢራን ዜጎችም የእስራኤል ልዩ ኦፕሬሽን የሥራ ውጤት አድርጎ የማቅረብ አዝማሚያ አለ” ባይ ናቸው። ፕሮፌሰሩ ጨምረውም “አትጠራጠሩ፣ ኢራን እያንዳንዱን ጥቃት ትበቀላለች” ብለዋል። ኢራን ልዩ ኃይሏ 'ቁዱስ' ይባላል። ቁዱስ የአብዮታዊ ዘብ አንድ ክንፍ ነው። ዓላማና ተግባሩ ደግሞ ከኢራን ውጪ ምሥጢራዊ ግዳጆችን መወጣት ነው። የቁዱስ ብርጌድ ዋና አለቃ ጄኔራል ኢስማኢል ቃኒ፣ ኢራን ማንኛውንም የአሜሪካና የእስራኤል ጠላት የሆነ ቡድንን መደገፏን ትቀጥልበታለች ብለዋል። ጄኔራል ኢስማኢል ማናቸው? ከተባለ ቃሲም ሱለይማኒን የተኩ ሰው ናቸው። ቃሲም ሱለይማኒ ደግሞ ከሁለት ዓመት በፊት በኢራቅ ዋና ከተማ ባግዳድ፣ በጥር ወር፣ አሜሪካ በድሮን ጥቃት እንደገደለቻቸው ይታወሳል። ሱለይማኒ አሜሪካ በዐይነ ቁራኛ ስትከታተላቸው የነበሩ ሰው ናቸው። ዶናልድ ትራምፕ እርምጃ ይወሰደብት እስኪሉ ድረስ በአሜሪካ የስለላ ቡድን መነጽር ሥር ነበር። ትራምፕ እርምጃው ከተወሰደ በኋላ “ሱለይማኒ የዓለማችን ቁጥር አንድ አሸባሪ ነበር” ሲሉ ተናግረዋል። ትራምፕ ሱለይማኒ እንዲገደሉ የወሰኑት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ማይክ ፓምፔዎ ግፊት ነው ተብሏል። ዶናልድ ትራምፕ በመካከለኛው ምሥራቅ የኢራን ሚና እንዲኮሰምን ትልቁን ሚና የተጫወቱ የእስራኤል ባለውለታ ተደርገው ይወስዳሉ። በተለይ አስራኤል ከመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻል የቀየሰችወን ‘አብረሃም አኮርድ’ የተባለውን ዕቅዷን በማስተዋወቅ እስራኤልን ከአረብ አገራት ጋር አወዳጅተው ነው የሄዱት። የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ እና ባህሬይን ከእስራኤል ጋር ግንኙነታቸውን እንዲያድሱ በማገዝ ‘አብረሃም አኮርድ’ ስምምነትን በማፈጣጠም ይበልጥ ኢራንን የመነጠል ሥራም ሠርተዋል። “ኢራን የአብረሃም አኮርድ ስምምነቶችን እጅግ ትጸየፋለች” ይላሉ አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ የአረብ ዲፕሎማት። አንድ የኢራን የቀድሞ ባለሥልጣን ግን ይህን ያሰተባብላሉ። “ስምምነቱን ባንወደውም ዘላቂ እንደማይሆን እናውቃለን፤ ጊዜያዊ እፍ እፍ ነው፤ የትም አያደርስም” ብለዋል ለቢቢሲ። የጆ ባይደን የሰሞኑ የሳዑዲ አረቢያና የእስራኤል ጉብኝት እንዳለ ሆኖ፣ አንድ በባይደን አስተዳደር ውስጥ ያሉ ባለሥልጣን የእስራኤልና ኢራን ፍጥጫ ወደከፋ ደረጃ እንደማይሸጋገር እናውቃለን፤ ቢያንስ በአጭር ጊዜ ያ እንደማይሆን እንረዳለን ይላሉ። ሪች ጎልድበርግ ደግሞ መቀመጫውን ዋሺንግተን ያደረገ የመከላከያ ጉዳዮች የጥናትና ምርምር ቡድን ባልደረባ ናቸው። እሳቸው እንደሚያምኑት እስራኤል የምታደርጋቸው ምሥጢራዊ ኦፕሬሽኖች ከመበርከታቸው የተነሳ አሁን አሁን ተራ ዕለታዊ ጉዳዮች እንዲመስሉ እያደረገች ነው። “...አንድ ቀን ግን ዓለም ከመንቃቱ በፊት እስራኤል በኢራን ኑክሊየር ማበልጸጊያ ማዕከል ላይ ድንገተኛ የአየር ጥቃት ማድረሷ አይቀርም፤ ዓለም ጥቃቱን እናስቁመው ከማለቱ በፊት ጥቃቱ ተገባዶ እናገኘው ይሆናል” ብለዋል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c29xn1dj09zo |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ የላቲን አሜሪካው ቁጥር-1 ቢሊዮነር በኮቪድ ተያዙ | በመላው ላቲን አሜሪካ የናጠጡ ሀብታም የሚባሉት ካርሎስ ስሊም በኮቪድ ተህዋሲ መያዛቸው ታወቀ፡፡ የ80 ዓመቱ ቢሊዮነር ካርሎስ ሜክሲኳዊ ሲሆኑ በቴሌኮሚኒኬሽን ቢዝነስ እውቅ ናቸው፡፡ ለጊዜው መጠነኛ የኮቪድ ምልክቶችን ብቻ እያሳዩ ነው ተብሏል፡፡ ልጃቸው በትዊተር ሰሌዳው እንደጻፈው ‹አባቴ ደህና ነው አታስቡ› ብሏል፡፡ የቢሊየነሩ በኮቪድ መያዝ ዜና የተሰማው የሜክሲኮ ፕሬዝዳንት የ67 ዓመቱ አንድሬስ ማኑል ሎፔዝ ኦብራዶር በኮቪድ መያዛቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ሜክሲኮ ከዓለም አገራት ክፉኛ በኮቪድ ከተጎዱ አገራት ተርታ የምትመደብ ናት፡፡ ወደ 2 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች በተህዋሲው የተያዙ ሲሆን 150ሺህ ዜጎች ደግሞ ሕይወታቸው በዋዛ አልፏል፡፡ ዛሬ ሰኞ የካርሎስ ስሊም ልጅ ዶሚት ካርሎስ ስሊም እንደጻፈው ‹አባቴ ለአንድ ሳምንት መጠነኛ ምልክቶችን ካሳየ በኋላ አሁን ሻል እያለው ነው፤ ለውጥ አለው›› ብሏል፡፡ ቢሊየነሩ ካርሎስ ስሊም ዋንኛውን የሜክሲኮ የቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሰጪ፣ ሞቪል ኩባንያን በባለቤትነት ያስተዳድራሉ፡፡ ፎርብስ መጽሔት የዚህ ቴሌኮም ኩባንያቸው ግምት 52 ቢሊዮን ዶላር ይሆናል ሲል ገምቶታል፡፡ ሜክሲኮ አሁን ወረርሽኙ በከፍተኛ ሁኔታ በመስፋፋቱ በዋና ከተማዋ ሜክሲኮ ሲቲ ሆስፒታሎች እየሞሉ ነው ብሏል በሜክሲኮ የቢቢሲ ዘጋቢ ዊል ግራንት፡፡ የኮቪድ ተህዋሲ ያገኛቸውና አሁን ከቤታቸው ሆነው ሥራ እየሠሩ ያሉት የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሎፔዝ ኦብራዶር የሩሲያ ሠራሹን ስፑትኪን ክትባትን ወደ አገራቸው ለማስገባት ከፑቲን ጋር እንደተነጋገሩ ተዘግቧል፡፡ በዚህም መሠረት 24 ሚሊዮን ጠብታዎች በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ሜክሲኮ ይደርሳሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡ | ኮሮናቫይረስ፡ የላቲን አሜሪካው ቁጥር-1 ቢሊዮነር በኮቪድ ተያዙ በመላው ላቲን አሜሪካ የናጠጡ ሀብታም የሚባሉት ካርሎስ ስሊም በኮቪድ ተህዋሲ መያዛቸው ታወቀ፡፡ የ80 ዓመቱ ቢሊዮነር ካርሎስ ሜክሲኳዊ ሲሆኑ በቴሌኮሚኒኬሽን ቢዝነስ እውቅ ናቸው፡፡ ለጊዜው መጠነኛ የኮቪድ ምልክቶችን ብቻ እያሳዩ ነው ተብሏል፡፡ ልጃቸው በትዊተር ሰሌዳው እንደጻፈው ‹አባቴ ደህና ነው አታስቡ› ብሏል፡፡ የቢሊየነሩ በኮቪድ መያዝ ዜና የተሰማው የሜክሲኮ ፕሬዝዳንት የ67 ዓመቱ አንድሬስ ማኑል ሎፔዝ ኦብራዶር በኮቪድ መያዛቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ሜክሲኮ ከዓለም አገራት ክፉኛ በኮቪድ ከተጎዱ አገራት ተርታ የምትመደብ ናት፡፡ ወደ 2 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች በተህዋሲው የተያዙ ሲሆን 150ሺህ ዜጎች ደግሞ ሕይወታቸው በዋዛ አልፏል፡፡ ዛሬ ሰኞ የካርሎስ ስሊም ልጅ ዶሚት ካርሎስ ስሊም እንደጻፈው ‹አባቴ ለአንድ ሳምንት መጠነኛ ምልክቶችን ካሳየ በኋላ አሁን ሻል እያለው ነው፤ ለውጥ አለው›› ብሏል፡፡ ቢሊየነሩ ካርሎስ ስሊም ዋንኛውን የሜክሲኮ የቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሰጪ፣ ሞቪል ኩባንያን በባለቤትነት ያስተዳድራሉ፡፡ ፎርብስ መጽሔት የዚህ ቴሌኮም ኩባንያቸው ግምት 52 ቢሊዮን ዶላር ይሆናል ሲል ገምቶታል፡፡ ሜክሲኮ አሁን ወረርሽኙ በከፍተኛ ሁኔታ በመስፋፋቱ በዋና ከተማዋ ሜክሲኮ ሲቲ ሆስፒታሎች እየሞሉ ነው ብሏል በሜክሲኮ የቢቢሲ ዘጋቢ ዊል ግራንት፡፡ የኮቪድ ተህዋሲ ያገኛቸውና አሁን ከቤታቸው ሆነው ሥራ እየሠሩ ያሉት የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሎፔዝ ኦብራዶር የሩሲያ ሠራሹን ስፑትኪን ክትባትን ወደ አገራቸው ለማስገባት ከፑቲን ጋር እንደተነጋገሩ ተዘግቧል፡፡ በዚህም መሠረት 24 ሚሊዮን ጠብታዎች በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ሜክሲኮ ይደርሳሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/news-55807195 |