label
class label
4 classes
headline
stringlengths
17
80
text
stringlengths
1
16.8k
headline_text
stringlengths
28
16.8k
url
stringlengths
36
49
3politics
ትራምፕን ያስቆጣውና አጋጥሞ አያውቅም የተባለው የኤፍቢአይ እርምጃ
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፍሎሪዳው መኖሪያ ቤታቸው ላይ የኤፍቢአይ አባላት ያደረጉት ብርበራ እሳቸውን ብቻ ሳይሆን ደጋፊዎቻቸውን አስቆጥቷል። ድርጊቱን “የፖለቲካ ሴራ ነው” የሚሉት ትራምፕ፣ ባወጡት መግለጫ ፖሊስ ፍተሻውን ያካሄደው ለዋይት ሐውስ ዳግም እንዳልወዳደር እንቅፋት ለመፍጠር ነው ብለዋል። ፍተሻው ከቀድሞ ፕሬዝዳንት የመንግሥታዊ ሰነዶች አያያዝ ጋር በተገናኘ ነው የተባለ ሲሆን፤ ፍተሻው ከዚህ በፊት በየትኛውም የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ላይ ያላጋጠመ ነው ተብሏል።
ትራምፕን ያስቆጣውና አጋጥሞ አያውቅም የተባለው የኤፍቢአይ እርምጃ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፍሎሪዳው መኖሪያ ቤታቸው ላይ የኤፍቢአይ አባላት ያደረጉት ብርበራ እሳቸውን ብቻ ሳይሆን ደጋፊዎቻቸውን አስቆጥቷል። ድርጊቱን “የፖለቲካ ሴራ ነው” የሚሉት ትራምፕ፣ ባወጡት መግለጫ ፖሊስ ፍተሻውን ያካሄደው ለዋይት ሐውስ ዳግም እንዳልወዳደር እንቅፋት ለመፍጠር ነው ብለዋል። ፍተሻው ከቀድሞ ፕሬዝዳንት የመንግሥታዊ ሰነዶች አያያዝ ጋር በተገናኘ ነው የተባለ ሲሆን፤ ፍተሻው ከዚህ በፊት በየትኛውም የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ላይ ያላጋጠመ ነው ተብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cz9k3nyypvwo
2health
ኮሮናቫይረስ፡ በእንግሊዝ በየቀኑ ወደ 100 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በቫይረሱ ይያዛሉ
በእንግሊዝ ውስጥ ወደ 100 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በየቀኑ በኮሮናቫይረስ እንደሚያዙ አንድ ጥናት ጠቆመ፡፡ እንደለንደን ኢምፔሪያል ኮሌጅ ጥናት ከሆነ ወረርሽኙ በፍጥነት እየጨመረ ሲሆን በየዘጠኝ ቀናትም በበሽታው የሚጠቁ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ ይጨምራል፡፡ አጥኚዎቹ "ወሳኝ ደረጃ ላይ በመሆናችን አንድ ነገር መደረግ አለበት" እያሉ ነው፡፡ ፈረንሳይ እና ጀርመን ቫይረሱን ለመቆጣጠር የተለያየ ደረጃ ያለው ገደብ ጥለዋል፡፡ በፀደይ ወራት ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ ወደ ነበረበት ደረጃ በፍጥነት እየተቃረብን ነው በማለት ባለሙያዎቹ ያስጠነቅቃሉ፡፡ ጥናቱ ወቅታዊ የሆነው የኮቪድ -19 ጥናት በመሆኑ ተጽዕኖ ፈጣሪ ነው ተብሎለታል፤ 86 ሺህ የሚጠጉ በጎ ፈቃደኞች የተሳተፉበት እና የመጨረሻዎቹ ምርመራዎች እሁድ የተካሄደበት ጥናት መሆኑን በመጠቆም፡፡ ጥናቱ እንዳሳየው ቫይረሱ በሁሉም የእድሜ ክልል እና በእያንዳንዱ የእንግሊዝ ግዛት እየጨመረ መሆኑን ያሳያል ፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሰሜናዊ የአገሪቱ ክፍል ስርጭቱ ከፍተኛ ቢሆንም በደቡብ በኩል ቢሆን በፍጥነት እያደገ ነው፡፡ ከአጥኚዎቹ አንዱ የሆኑት ፕሮፌሰር ስቲቨን ሪሌይ መረጃው መገኘት ሲጀምር እንዳዘኑ ገልፀው "አሁን ያሉት እርምጃዎች በቂ አይደሉም" ብለዋል ፡፡ "ለውጥ መኖር አለበት። ፍጥነት በእውነቱ በጣም ፈጣን በመሆኑ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ከገና በፊት ለውጥ ሊኖር ይገባል" ብለዋል ፡፡ ህዝቡ በደንብ ህጎችን ማክበር አለበት ወይም መንግሥት ከባድ ገደቦችን መጣል አለበት ሲሉም ተከራክረዋል ፡፡ "መረጃዎቹ በፍጥነት መወሰንን የሚሹ ናቸው" ብለው ገልጸዋል።
ኮሮናቫይረስ፡ በእንግሊዝ በየቀኑ ወደ 100 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በቫይረሱ ይያዛሉ በእንግሊዝ ውስጥ ወደ 100 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በየቀኑ በኮሮናቫይረስ እንደሚያዙ አንድ ጥናት ጠቆመ፡፡ እንደለንደን ኢምፔሪያል ኮሌጅ ጥናት ከሆነ ወረርሽኙ በፍጥነት እየጨመረ ሲሆን በየዘጠኝ ቀናትም በበሽታው የሚጠቁ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ ይጨምራል፡፡ አጥኚዎቹ "ወሳኝ ደረጃ ላይ በመሆናችን አንድ ነገር መደረግ አለበት" እያሉ ነው፡፡ ፈረንሳይ እና ጀርመን ቫይረሱን ለመቆጣጠር የተለያየ ደረጃ ያለው ገደብ ጥለዋል፡፡ በፀደይ ወራት ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ ወደ ነበረበት ደረጃ በፍጥነት እየተቃረብን ነው በማለት ባለሙያዎቹ ያስጠነቅቃሉ፡፡ ጥናቱ ወቅታዊ የሆነው የኮቪድ -19 ጥናት በመሆኑ ተጽዕኖ ፈጣሪ ነው ተብሎለታል፤ 86 ሺህ የሚጠጉ በጎ ፈቃደኞች የተሳተፉበት እና የመጨረሻዎቹ ምርመራዎች እሁድ የተካሄደበት ጥናት መሆኑን በመጠቆም፡፡ ጥናቱ እንዳሳየው ቫይረሱ በሁሉም የእድሜ ክልል እና በእያንዳንዱ የእንግሊዝ ግዛት እየጨመረ መሆኑን ያሳያል ፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሰሜናዊ የአገሪቱ ክፍል ስርጭቱ ከፍተኛ ቢሆንም በደቡብ በኩል ቢሆን በፍጥነት እያደገ ነው፡፡ ከአጥኚዎቹ አንዱ የሆኑት ፕሮፌሰር ስቲቨን ሪሌይ መረጃው መገኘት ሲጀምር እንዳዘኑ ገልፀው "አሁን ያሉት እርምጃዎች በቂ አይደሉም" ብለዋል ፡፡ "ለውጥ መኖር አለበት። ፍጥነት በእውነቱ በጣም ፈጣን በመሆኑ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ከገና በፊት ለውጥ ሊኖር ይገባል" ብለዋል ፡፡ ህዝቡ በደንብ ህጎችን ማክበር አለበት ወይም መንግሥት ከባድ ገደቦችን መጣል አለበት ሲሉም ተከራክረዋል ፡፡ "መረጃዎቹ በፍጥነት መወሰንን የሚሹ ናቸው" ብለው ገልጸዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-54726762
2health
ኮሮናቫይረስ፡ በኢትዮጵያ ኮቪድ-19 በጽኑ የሚታመሙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር "በአስደንጋጭ ሁኔታ" ጨመረ
በኢትዮጵያ ከጥቂት ሳምንታት ወዲህ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የሚያዙ፣ ወደ ጽኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡና በበሽታው ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር "በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ" መሆኑን የሕብረተሰብ ጤና ኢነስቲቲዩት አስታወቀ። ቀደም ሲል በጽኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ህክምና እያገኙ የነበሩ ሰዎች ቁጥር በአራት መቶዎች ውስጥ የቆየ ሲሆን ይህ አሃዝ ባለፉት ቀናት ውስጥ አምስት መቶን ተሻግሮ ወደ ስድስት መቶ መጠጋቱን በየዕለቱ የሚወጣው የበሽታው የዕለት ሁኔታ ሪፖርት ያመለክታል። ሰኞ ዕለት በጽኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ይገኙ የነበሩት ሰዎች ቁጥር 531 የነበረ ሲሆን ትናንት ማክሰኞ ቁጥሩ በ60 ጨምሮ 591 በመድረሱ በህክምና ተቋማቱ ላይ ጫና መፈጠሩ ተነግሯል። በዚህም ሳቢያ የጽኑ ህሙማን ክትትል ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች በሚውሉት የሰው ሰራሽ መተንፈሻ መርጃ (ቬንትሌተር) እና ኦክስጂን አቅርቦት ላይ እጥረት አጋጥሟል የሕብረተሰብ ጤና ተቋም ትናንት እናደለው የሰውሰራሽ መተንፈሻ ድጋፍ ከሚያስፈልጋቸው ሰዎች መካከል ስምነቱ በመጠባበቅ ላይ ነበሩ። ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በነበሩ ቀናት የተደረጉ የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤቶች እንደሚያመለክቱት በየዕለቱ በአማካይ ከ1300 በላይ ሰዎች ላይ በወረርሽኙ መያዛቸውን ያመለክታል። አጠቃላይ የምርመራው ውጤት በመቶኛ ሲሰላ ከተመረመሩት 100 ሰዎች ውስጥ በአማካኝ 19 ሰዎች ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። በዚህም በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከ32 በመቶ በላይ ጨምሯል። በበሽታው ሰበብ ለህልፈት የሚዳረጉ ሰዎችን ቁጥር ስንመለከትም ከዕለት ዕለት ዕየጨመረ በአማካይ ከ15 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ህይወት እያለፈ ነው። ይህም ቀደም ካሉት ሳምንታት ጋር ሲነጻጸር በ89 በመቶ መጨመሩን ባለሙያዎቹ ተናግረዋል። ወረርሽኙ ከቁጥጥር ውጪ እንዳይሆን ተሰግቷል የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ማክሰኞ ዕለት፣ በሰጡት መግለጫ "ወረርሽኙ ከቁጥጥር ውጭ ከመሆኑ በፊት ሁሉም ኃላፊነቱን መወጣት አለበት" ሲሉ አሳስበዋል። የበሽታው ስርጭት ባለፉት ወራት በተለይም ባለፉት ሳምንታት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ጠቅሰው፤ ቀደም ሲል በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ከ10 በመቶ በታች የነበረው ከፍ ብሎ አዲስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአማካይ 17 በመቶ ማሻቀቡን ተናግረዋል። በዚህም እስካሳለፍነው ቅዳሜ ድረስ በነበሩት 10 ቀናት ውስጥ "ከ12 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ፣ የ149 ሰዎች ህይወትም በወረርሽኙ ሳቢያ አልፏል" ብለዋል። የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን እንዲሁም የጽኑ ህሙማን ህክምና የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥርም በባለፉት ቀናት ለመጀመሪያ ጊዜ ከ450 መብለጡን ተናግረዋል። በዚህም ሳቢያ የጽኑ ህሙማን ክፍሎች መሙላታቸውን፣ ያሉ የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያዎች (ቬንትሌተር) በህሙማን ሙሉ ለሙሉ መያዛቸውን እንዲሁም የኦክስጅን እጥረት ማጋጠሙን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ እስከ መጋቢት 06/2013 ዓ.ም ድረስ በተደረገ የኮሮናቫይረስ ምርመራ 176,618 ሰዎች በወረርሽኙ መያዛቸው የተረጋጠ ሲሆን 2,555 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። በተጨማሪም 531 ግለሰቦች በኮቪድ-19 ምክንያት በጽኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፤ ይህ ቁጥርም በሽታው ኢትዮጵያ ውስጥ ከተገኘ በኋላ ከፍተኛው ነው። የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ተቋም እንዳለው ከእነዚህም ውስጥ 66ቱ ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ (ቬንትሌተር) ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው። የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ተቋም ዛሬ ባወጣው መረጃ መሰረት ያሉት የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያዎች በመያዛቸው በጽኑ የታመሙ 8 ያህል ግለሰቦች የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ። "ክትባት መሰጠቱ ይቀጥላል" የጤና ሚኒስትሯ በአገሪቷ እየተሰጠ ያለውን የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት አስመልክቶ የአስትራዜኒካ ክትባትን መስጠት እንደሚቀጥል ተናግረዋል። አንዳንድ አገራት ከአስትራዜኒካ የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል ባሉት ችግር ምክንያት ክትባቱን መስጠት ቢያቆሙም በኢትዮጵያ ክትባቱ መሰጠት እንደሚቀጥል የጤና ሚኒስቴር ገልጿል። ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያን፣ ዴንማርክ፣ ኖርዌይ እና ስፔንን ጨምሮ ስምንት የአውሮፓ አገራት ክትባቱ ከደም መርጋት ጋር የተያያዘ ችግር ሊኖረው ይችላል በሚል የአስትራዜኔካ ክትባት ለጊዜው እንዲቆም አድርገዋል። የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ዛሬ ማክሰኞ፣ በሰጡት መግለጫ ላይ እንዳሉት በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ውስጥ እየተሰጠ ያለው የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ጋር በተያያዘ እስካሁን ያጋጠመ ችግር እንደሌለ ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ መሰጠት የተጀመረው ወረርሽኙ በአገሪቱ ውስጥ መገኘቱ ይፋ በተደረገ በዓመቱ ባለፈው ቅዳሜ መጋቢት 04/2013 ዓ.ም ነበር። በአገሪቱ እየተሰጠ የሚገኘው የአስትራዜኔካ ምርት የሆነው 2.2 ሚሊየን ብልቃጥ ክትባት ኮቫክስ ከተሰኘው ዓለም አቀፍ የክትባት አቅርቦት ጥምረት የቀረበ ነው። ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ እስካሁን ባለው መረጃ ተከሰተ የተባለው ችግር "ከአስትራዜኒካ ክትባት ጋር ግንኙነት እንደሌለውና ክትባቱ መቀጠል እንዳለበት የዓለም የጤና ድርጅት፣ የአውሮፓና የእንግሊዝ የመድኃኒት ጥናትና ቁጥጥር ባለስልጣን በይፋ አስታውቀዋል" ብለዋል። በአውሮፓ ሕብረት አባላት አገራትና በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ እስካሁን 17 ሚሊዮን ሰዎች የአስትራዜንካ ክትባትን መከተባቸውና ከእነዚህ ውስጥም 40ዎቹ የደም መርጋት ችግር እንዳጋጠማቸው የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። የዓለም ጤና ድርጅት በርካታ የአውሮፓ አገራት የአስትራዜኒካ ክትባት እንዳይሰጥ ማገዳቸውን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ ክትባቱ የደም መርጋት ስለማስከተሉ ምንም አይነት ማስረጃ የለም ብሏል። ዶ/ር ሊያ ታደሰም ክትባቱ በበርካታ አገራት ውስጥ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሰዎች መዳረሱንና በኢትዮጵያም መሰጠቱ እንደሚቀጥል ተናግረው ጉዳዩ "በሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በኩል ጥብቅ ክትትል ይደረግበታል" ብለዋል። በዚህም መሠረት ክትባቱን በተመለከተ አዲስ ነገር የሚኖር ከሆነ ሕብረተሰቡ እንዲያውቀው እንደሚደረግ ገልጸው "ከክትባቱ ጋር ተያይዞ እስካሁን የገጠመ ችግር ባለመኖሩ ክትባቱን መስጠታችንን እንቀጥላለን" ብለዋል። በዚህም መሠረት ክትባቱ ለጤና ባለሙያዎች፣ ተጓዳኝ በሽታ ላለባቸው ሰዎችና ለአረጋዊያን በተከታታይ የሚሰጥ መሆኑን በመግለጽ እስከሚቀጥለው ዓመት ታኅሣስ ድረስ ከአገሪቱ ሕዝብ 20 በመቶውን እንዲከተብ ይደረጋል ብለዋል።
ኮሮናቫይረስ፡ በኢትዮጵያ ኮቪድ-19 በጽኑ የሚታመሙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር "በአስደንጋጭ ሁኔታ" ጨመረ በኢትዮጵያ ከጥቂት ሳምንታት ወዲህ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የሚያዙ፣ ወደ ጽኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡና በበሽታው ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር "በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ" መሆኑን የሕብረተሰብ ጤና ኢነስቲቲዩት አስታወቀ። ቀደም ሲል በጽኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ህክምና እያገኙ የነበሩ ሰዎች ቁጥር በአራት መቶዎች ውስጥ የቆየ ሲሆን ይህ አሃዝ ባለፉት ቀናት ውስጥ አምስት መቶን ተሻግሮ ወደ ስድስት መቶ መጠጋቱን በየዕለቱ የሚወጣው የበሽታው የዕለት ሁኔታ ሪፖርት ያመለክታል። ሰኞ ዕለት በጽኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ይገኙ የነበሩት ሰዎች ቁጥር 531 የነበረ ሲሆን ትናንት ማክሰኞ ቁጥሩ በ60 ጨምሮ 591 በመድረሱ በህክምና ተቋማቱ ላይ ጫና መፈጠሩ ተነግሯል። በዚህም ሳቢያ የጽኑ ህሙማን ክትትል ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች በሚውሉት የሰው ሰራሽ መተንፈሻ መርጃ (ቬንትሌተር) እና ኦክስጂን አቅርቦት ላይ እጥረት አጋጥሟል የሕብረተሰብ ጤና ተቋም ትናንት እናደለው የሰውሰራሽ መተንፈሻ ድጋፍ ከሚያስፈልጋቸው ሰዎች መካከል ስምነቱ በመጠባበቅ ላይ ነበሩ። ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በነበሩ ቀናት የተደረጉ የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤቶች እንደሚያመለክቱት በየዕለቱ በአማካይ ከ1300 በላይ ሰዎች ላይ በወረርሽኙ መያዛቸውን ያመለክታል። አጠቃላይ የምርመራው ውጤት በመቶኛ ሲሰላ ከተመረመሩት 100 ሰዎች ውስጥ በአማካኝ 19 ሰዎች ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። በዚህም በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከ32 በመቶ በላይ ጨምሯል። በበሽታው ሰበብ ለህልፈት የሚዳረጉ ሰዎችን ቁጥር ስንመለከትም ከዕለት ዕለት ዕየጨመረ በአማካይ ከ15 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ህይወት እያለፈ ነው። ይህም ቀደም ካሉት ሳምንታት ጋር ሲነጻጸር በ89 በመቶ መጨመሩን ባለሙያዎቹ ተናግረዋል። ወረርሽኙ ከቁጥጥር ውጪ እንዳይሆን ተሰግቷል የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ማክሰኞ ዕለት፣ በሰጡት መግለጫ "ወረርሽኙ ከቁጥጥር ውጭ ከመሆኑ በፊት ሁሉም ኃላፊነቱን መወጣት አለበት" ሲሉ አሳስበዋል። የበሽታው ስርጭት ባለፉት ወራት በተለይም ባለፉት ሳምንታት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ጠቅሰው፤ ቀደም ሲል በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ከ10 በመቶ በታች የነበረው ከፍ ብሎ አዲስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአማካይ 17 በመቶ ማሻቀቡን ተናግረዋል። በዚህም እስካሳለፍነው ቅዳሜ ድረስ በነበሩት 10 ቀናት ውስጥ "ከ12 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ፣ የ149 ሰዎች ህይወትም በወረርሽኙ ሳቢያ አልፏል" ብለዋል። የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን እንዲሁም የጽኑ ህሙማን ህክምና የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥርም በባለፉት ቀናት ለመጀመሪያ ጊዜ ከ450 መብለጡን ተናግረዋል። በዚህም ሳቢያ የጽኑ ህሙማን ክፍሎች መሙላታቸውን፣ ያሉ የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያዎች (ቬንትሌተር) በህሙማን ሙሉ ለሙሉ መያዛቸውን እንዲሁም የኦክስጅን እጥረት ማጋጠሙን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ እስከ መጋቢት 06/2013 ዓ.ም ድረስ በተደረገ የኮሮናቫይረስ ምርመራ 176,618 ሰዎች በወረርሽኙ መያዛቸው የተረጋጠ ሲሆን 2,555 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። በተጨማሪም 531 ግለሰቦች በኮቪድ-19 ምክንያት በጽኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፤ ይህ ቁጥርም በሽታው ኢትዮጵያ ውስጥ ከተገኘ በኋላ ከፍተኛው ነው። የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ተቋም እንዳለው ከእነዚህም ውስጥ 66ቱ ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ (ቬንትሌተር) ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው። የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ተቋም ዛሬ ባወጣው መረጃ መሰረት ያሉት የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያዎች በመያዛቸው በጽኑ የታመሙ 8 ያህል ግለሰቦች የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ። "ክትባት መሰጠቱ ይቀጥላል" የጤና ሚኒስትሯ በአገሪቷ እየተሰጠ ያለውን የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት አስመልክቶ የአስትራዜኒካ ክትባትን መስጠት እንደሚቀጥል ተናግረዋል። አንዳንድ አገራት ከአስትራዜኒካ የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል ባሉት ችግር ምክንያት ክትባቱን መስጠት ቢያቆሙም በኢትዮጵያ ክትባቱ መሰጠት እንደሚቀጥል የጤና ሚኒስቴር ገልጿል። ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያን፣ ዴንማርክ፣ ኖርዌይ እና ስፔንን ጨምሮ ስምንት የአውሮፓ አገራት ክትባቱ ከደም መርጋት ጋር የተያያዘ ችግር ሊኖረው ይችላል በሚል የአስትራዜኔካ ክትባት ለጊዜው እንዲቆም አድርገዋል። የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ዛሬ ማክሰኞ፣ በሰጡት መግለጫ ላይ እንዳሉት በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ውስጥ እየተሰጠ ያለው የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ጋር በተያያዘ እስካሁን ያጋጠመ ችግር እንደሌለ ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ መሰጠት የተጀመረው ወረርሽኙ በአገሪቱ ውስጥ መገኘቱ ይፋ በተደረገ በዓመቱ ባለፈው ቅዳሜ መጋቢት 04/2013 ዓ.ም ነበር። በአገሪቱ እየተሰጠ የሚገኘው የአስትራዜኔካ ምርት የሆነው 2.2 ሚሊየን ብልቃጥ ክትባት ኮቫክስ ከተሰኘው ዓለም አቀፍ የክትባት አቅርቦት ጥምረት የቀረበ ነው። ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ እስካሁን ባለው መረጃ ተከሰተ የተባለው ችግር "ከአስትራዜኒካ ክትባት ጋር ግንኙነት እንደሌለውና ክትባቱ መቀጠል እንዳለበት የዓለም የጤና ድርጅት፣ የአውሮፓና የእንግሊዝ የመድኃኒት ጥናትና ቁጥጥር ባለስልጣን በይፋ አስታውቀዋል" ብለዋል። በአውሮፓ ሕብረት አባላት አገራትና በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ እስካሁን 17 ሚሊዮን ሰዎች የአስትራዜንካ ክትባትን መከተባቸውና ከእነዚህ ውስጥም 40ዎቹ የደም መርጋት ችግር እንዳጋጠማቸው የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። የዓለም ጤና ድርጅት በርካታ የአውሮፓ አገራት የአስትራዜኒካ ክትባት እንዳይሰጥ ማገዳቸውን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ ክትባቱ የደም መርጋት ስለማስከተሉ ምንም አይነት ማስረጃ የለም ብሏል። ዶ/ር ሊያ ታደሰም ክትባቱ በበርካታ አገራት ውስጥ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሰዎች መዳረሱንና በኢትዮጵያም መሰጠቱ እንደሚቀጥል ተናግረው ጉዳዩ "በሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በኩል ጥብቅ ክትትል ይደረግበታል" ብለዋል። በዚህም መሠረት ክትባቱን በተመለከተ አዲስ ነገር የሚኖር ከሆነ ሕብረተሰቡ እንዲያውቀው እንደሚደረግ ገልጸው "ከክትባቱ ጋር ተያይዞ እስካሁን የገጠመ ችግር ባለመኖሩ ክትባቱን መስጠታችንን እንቀጥላለን" ብለዋል። በዚህም መሠረት ክትባቱ ለጤና ባለሙያዎች፣ ተጓዳኝ በሽታ ላለባቸው ሰዎችና ለአረጋዊያን በተከታታይ የሚሰጥ መሆኑን በመግለጽ እስከሚቀጥለው ዓመት ታኅሣስ ድረስ ከአገሪቱ ሕዝብ 20 በመቶውን እንዲከተብ ይደረጋል ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-56398440
5sports
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ዓይናቸውን ለምን እስያ ላይ ጣሉ?
“ሃይማኖተኛ አደለሁም። የማምነው ነገር የለኝም። ሊቨርፑል እምነቴ ነው። ለእኔ የሕይወቴ መስመር ነው።” ይህን ያለው ቪጃይ ነው። ቪጃይ ውልደቱ ሲንጋፖር ነው። ከሊቨርፑሉ አንፊልድ ስታዲየም 11 ሺህ ኪሎ ሜትር ርቆ ይገኛል። የሚወደው ቡድን ትውልድ ከተማውን እንዲጎበኝ እአአ ከ2011 ጀምሮ ሲጠብቅ ቆይቷል። ይህ ግን የእሱ ብቻ ታሪክ አይደለም። በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በሊቨርፑል እና በክሪስታል ፓላስ መካከል የወዳጅነት ጨዋታ ተደርጓል። ከ50,000 በላይ ደጋፊዎች የሲንጋፖርን ብሔራዊ ስታዲየም ከአፍ እስከ ገደፉ ሞልተውታል። ለሦስት ዓመታት የተጣለው የኮቪድ የጉዞ እገዳ ተነሳ። የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቡድኖችም ለቅድመ-ውድድር ዝግጅት አድማስን እያቋረጡ ነው። ጉዞዎቹ በገንዘብ ረገድ ያላቸው ጠቀሜታ ለመገመት አስቸጋሪ ነው። ማንቸስተር ዩናይትድ እአአ በ2021 ወደ 56 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገቢ እንዳጣ ክለቡ ይፋ አድርጎ ነበር። “ዋነኛው” ምክንያት ኮቪድ መስተጓጎል መሆኑ ተጠቅሷል። ከዚህ መካከል አንዱ በሕንድ ሊደረግ የነበረው የቅድመ ውድድር ዘመን ጉብኝት መሰረዙ ነው። አሁን እገዳው ቀንሷል። ክለቦችም ቁጥር አንድ ወደሚሉት የገበያ ስፍራ እየጎረፉ ነው። የሊቨርፑል ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት ቢሊ ሆጋን “እስያ በደጋፊዎች ብዛት ቀዳሚዋ መዳረሻችን ናት” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። “የትኛውንም አውሮፕላን ተሳፍረህ ወደ ኤስያ ብትሄድ የሊቨርፑል ደጋፊዎችን ማግኘት ትችላለህ፣ ሲል አንድ ሰው የነገረኝን ማስታወስ እፈልጋለሁ። አንድ ሦስተኛው ዓለም አቀፍ ደጋፊያችን መገኛው እዚህ ነው። በእስያ ውስጥ ትልቅ ዕድል እንዳለ ይሰማናል።” በዚህ ክረምት ማንቸስተር ዩናይትድ ፊቱን ወደ ታይላንድን እና አውስትራሊያን አዙሯል። ከሊቨርፑል እና ከክሪስታል ፓላስ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ አከከናውኗል። ቶተንሃም ሆትስፐር ወደ ደቡብ ኮሪያ አቅንቷል። ደቡብ ኮሪያ የክለቡ ከፍተኛ ኮከብ ግብ አግቢው ሶን ሄንግ ሚን አገር ነች። ከስፖርት አንጻር እነዚህ ጉዞዎች ትርጉማቸው እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። በተለያዩ የሰዓት ዞኖች የሚደረጉ ረዥም በረራዎች፣ በከፍተኛ ሙቀት እና እርጥበታማ የአየር ሁኔታ ልምምድ ማድረግን ያካትታል። ይህ ግን እንግሊዝ ለሚኖራቸው የአዲሱ የውድድር ዘመን ዝግጅት ጥሩ  አይደለም። የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ በጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ “የምመርጠው ነገር አይደለም” ብለዋል። “ሲጀምር እኔ አሰልጣኝ ነኝ። ለሁለት ሳምንት ኦስትሪያ ቆይተን በቀን ሁለት ጊዜ ብናሰልጥን ጥሩ ነበር። “የደጋፊዎቻችን ቁጥር እስያ ውስጥ ምን ያህል ትልቅ እንደሆነ እናውቃለን። ወደ እነርሱ ቀረብ ማለት ጥሩ ነገር ነው።” እንደ እውነቱ ከሆነ በእግር ኳስ ውስጥ ለረዥም ጊዜ የከረመ ክርክር ነበር። ክርክሩ ከረጅም ጊዜ በፊት ውሳኔ ያገኘ ይመስላል። ከፋይናንስ ጋር ያለው ወገን የበላይነት ይዟል። በዚህ ዓመት የወጡ አዳዲስ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ፕሪሚየር ሊጉ ለመጀመሪያ ጊዜ ከዓለም አቀፍ ጨዋታ አስተላላፊዎች ከፍተኛ ገቢ ያገኛል። ይህም ለመጀመሪያ ጊዜ ከእንግሊዝ ገበያ ከሚገኘው የበለጠ ገቢ ይሆናል። በሚቀጥለው የውድድር ዓመት እስከ 2025 ባለው ጊዜ ከእስያ ገበያ 1.4 ቢሊዮን ዶላር ይሸፍናል ተብሎ ይጠበቃል። ስፐርስ በደቡብ ኮሪያ የወደጅነት ጨዋታ አድርጓል። ይህም ከሃገሪቱ ክለቦች ከተወጣጡ የኮከቦች ቡድን ጋር ተደረገ ሲሆን፣ የጨዋታው ትኬት በ25 ደቂቃ ውስጥ ተሸጦ ተጠናቋል። በአገሪቱ ታሪክ ከፍተኛ ስርጭት ያገኘ የስፖርት ዝግጅት ሆኗል። ባንኮክ የሚገኙ የውድድሩ አዘጋጆች በማንቸስተር ዩናይትድ እና ሊቨርፑል መካከል ለሚደረገው የወዳጅነት ጨዋታ የትኬት መነሻ ዋጋው 136 ዶላር አድርገዋል። በሲንጋፖር ርካሽ የተባለለት ቲኬት 107 ዶላር ተቸብችቧል። እነዚህ ዋጋዎች ከእንግሊዝ የነጥብ ጨዋታዎች አንጻር እንኳን ውድ የሚባሉ ናቸው። ሆኖም የፕሪሚየር ሊጉን ከፍተኛ ክለቦችን የመሳብ ጠንካራ አቅም አላቸው። የሊቨርፑል ቃል አቀባይ “የእነዚህን የቲኬቶች ዋጋ እኛ አልወሰንም። እኛ የተወሰነልንን ክፍያ እንቀበላለን። እኛ ከትኬት ገቢ ምንም አይነት ድርሻ አንቀበልም" ብለው ለቢቢሲ ገልጸዋል። የእስያ ገቢ ክለቦቹ ከእነዚህ የወዳጅነት ግጥሚያዎች ምን ያህል እንደሚያገኙ አይታወቅም። ምክንያቱም መረጃው በጥብቅ ስለሚያዝ። ተንታኞች እንደሚሉት ግን ክፍያውን ለጉዞዎቹ ብቸኛ ምክንያት አድርጎ አያስቀምጥም።  ለዚህ እንደምክንያት የሚቀመጠው የጉዞ እና የሠራተኞች ወጪዎች መኖራቸው ነው። “በእውነቱ ከሆነ ቡድኖቹ ከቅድመ-ውድድር ጨዋታዎች ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ በቀጥታ አያገኙም። ምናልባትም በአንድ ግጥሚያ ጥቂት ሚሊዮን ዶላር ቢገኝ ነው” ሲል የስፖርት ቢዝነሱ የእስያ-ፓስፊክ አርታኢ ኬቨን ማኩላግ ይገልጻል። “ነገር ግን አንድ ትልቅ ዓላማ አለ። ይህም የስም ግንባታ እና በቀጣይ የቴሌቭዥን ሥርጭት ገበያውን በሚመራውና የስፖንሰርሺፕ ስምምነቶችን በሚያስገኘው ገበያ ውስጥ መሳተፍ ነው። ትክክለኛው ገንዘብ ይህ ነው።” ሊቨርፑል በሲንጋፖር በከተመበት ወቅት ከ240 ሚሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያለው አዲስ የማሊያ ስፖንሰርሺፕ ስምምነት ተፈራርሟል። ስምምነቱ ስታንዳርድር ቻርተርድ ከተባለውና ትኩረቱን እስያ ላይ ካደረገው ባንክ ጋር ተደርሷል። የእግር ኳስ ክለቦች የስፖንሰርን አቅማቸውን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከማሳደግ ባለፈ የደጋፊዎችን መረጃ ሊያቀርቡላቸው ይችላሉ። ለምሳሌ ማንቸስተር ዩናይትድ የደጋፊ ግንኙነት አስተዳደር (ሲአርኤም) ዳታቤዝ 50 ሚሊዮን መዝገቦችን እንደያዘ ይገምታል። ባለፈው ዓመት በማኅበራዊ ሚዲያው 176 ሚሊዮን አስፍሯል። ይህም ለስፖንሰርሺፕ ገንዘብ፣ ስያሜ እና ለግብይት ክፍል የሚረዱ ከክለቡ ጋር የተመዘገቡ ወይም የተሳተፉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደጋፊዎችን ጠቃሚ መረጃ ያስገኛል። “የመጀመሪያው ትልልቅ ስፖንሰሮች የሚጠይቁት በደጋፊዎች ዙሪያ ያለውን መረጃ ነው” ሲል ማኩላግ ተናግሯል። “ገንዘባቸውን ፈሰስ ከማድረጋቸው በፊት አንድ ክለብ ምን ያህል ደጋፊ እንዳለው፣ ዕድሜ፣ ወንድ፣ ሴት፣ የገቢ መጠን እና የመሳሰሉትን ነገሮች ማወቅ ይፈልጋሉ።” የእንግሊዝ እግር ኳስን በገንዘብ በስፋት እንዲሰበሰብ ያስቻለው ግን የቴሌቭዥን ገቢ ነው። ለዓመታት ሌሎች የስፖርት ሊጎች (የአውሮፓ እግር ኳስ ሊጎችን ጨምሮ) ፕሪሚየር ሊጉን በቅናት ሲመለከቱ ኖረዋል። ወደ እስያ በማቅናት እነዚህ ሊጎች ቀዳሚ ናቸው። የፕሪሚየር ሊጉ ፉክክር፣ ልዩ የሆነው የደጋፊዎች ባህል እና ከእንግሊዘኛ ቋንቋ ጋር ያለው ትስስር ሊጉ በዓለም አቀፍ ደረጃ 3.2 ቢሊየን ተመልካቾችን በመሳብ በብዛት የታየ የስፖርት ሊግ እንዲሆን አስተዋጽኦ አድርጓል። ፕሪሚየር ሊግ እንደሚለው ግማሹ የዓለም ደጋፊ እና አንድ አራተኛው የቴሌቭዥን ተመልካቾች በእስያ ፓስፊክ ይገኛል። ይህ ሁሉ የሆነው ብዙ ጨዋታዎች በእኩለ ሌሊት እየተጠናቀቁም ነው። እነዚህን ሁሉ ደጋፊዎች ይዞ ማቆየት ፈታኝ እንደሚሆን ባለሙያዎች ይናገራሉ። በተለይም ለወጣቱ ትውልድ በጣም ሰፊ የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዎች እና የአኗኗር ዘይቤዎች አማራጮች መኖራቸው ዋነኛው ስጋት ነው። የስፔኑ ኃያል ክለብ ሪያል ማድሪድ ፕሬዝዳንት የሆኑት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ባለፈው ዓመት “ወጣቶች በእግር ኳስ ላይ ፍላጎት የላቸውም። ራሳቸውን የሚያዘናጉባቸው ሌሎች መድረኮች አሏቸው” ማለታቸውን ማስታወስ ተገቢ ነው። ይህ አመለካከት የቴሌቭዥን ገቢ ውሎ አድሮ እየቀነሰ እንደሚሄድ ከተገመተው ትንበያ ጋር ተደማምሮ በአውሮፓ ከፍተኛ የእግር ኳስ ክለቦች ውስጥ ያሉ አንዳንድ ኃላፊዎችን ደጋፊዎቻቸውን ለማሳተፍ አዲስ ውድድር መፈጠር እንዳለበት አሳምኗቸዋል። አንደኛው ሃሳብ የአውሮፓ ሱፐር ሊግ ነበር። አምስት የእንግሊዝ ክለቦችን ጨምሮ ሁሌም ተሳታፊ በሚሆኑ ክለቦች የሚደረግ ውድድር ለማድረግ ያቀደ ነበር። ይህም በዓለም ዙሪያ በተለይም በእስያ ውስጥ ያሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አድናቂዎችን ታላሚ ያደረገ ነበር። እነዚህ ሁሌም ኃያል ቡድኖች እርስ በእርስ ሲፎካከሩ ማየት የሚፈልጉ ናቸው፤ ግን በጅምር ቀረ። በዩናይትድ ኪንግደም እና በዓለምአቀፍ ደጋፊዎች ዘንድ ያስነሳው ቁጣ እንዲሰረዝ ምክንያት ሆነ። “የአውሮፓ እግር ኳስ ክለቦች ስለእስያ ግምት መያዝ የለባቸውም። ስለሚያገኙት እያንዳንዱ ዶላር መታገል ግን አለባቸው” ሲሉ በፈረንሳይ በኤምሊዮን ቢዝነስ ትምህርት ቤት የስፖርት ፕሮፌሰር የሆኑት ሲሞን ቻድዊክ ተናግረዋል። “የእስያ ሸማቾች ብልህ፣ የተራቀቁ እና አስተዋይ ናቸው። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአውሮፓ እግር ኳስ በእስያ ደጋፊዎች መካከል መጠነኛ መለያየት እንዳለ ሊከራከሩ ይችላሉ። ስለዚህ ክለቦች እስያን በቀላሉ እንደሚቆጣጠሩት በማሰብ እብሪተኛ ወይም የዋህ እንዳይሆኑ ይመከራሉ።" ቻድዊክ አክለውም የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዎች በውጭ አገራት ሊደረጉ ይችላሉ ተብሎ በ 2008 ለመጀመሪያ ጊዜ የቀረበው ሃሳብ ከአጭር እስከ መካከለኛ ባለው ጊዜ የማይሳካ ነው። ጉዳዩ ግን በድጋሚ ሊታይ ይችላል። ወደ ሲንጋፖር እንመለስ፤ ቪጃይ ሸሚዙን አውልቆ ጀርባውን ያሳያል። በንቅሳት ተዥጎርጉሯል። የሊቨርፑል ስም እና ክለቡ በታሪኩ ዋንጫ ያገኘባቸው ዓመታትን ተነቅሷል። ስለ ወደፊቱም ቢሆን ብሩህ ተስፋ ሰንቋል። “አባቴ የሊቨርፑል ደጋፊ ነበር። ከሴት ልጆቼ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ያደረግኩት ነገር የሊቨርፑል ማሊያን ለእነሱ ማልበስ ነበር። እመኑኝ ይህ በትውልዶችን ቅብብል ይቀጥላል” ሲል ያጠናቅቃል።
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ዓይናቸውን ለምን እስያ ላይ ጣሉ? “ሃይማኖተኛ አደለሁም። የማምነው ነገር የለኝም። ሊቨርፑል እምነቴ ነው። ለእኔ የሕይወቴ መስመር ነው።” ይህን ያለው ቪጃይ ነው። ቪጃይ ውልደቱ ሲንጋፖር ነው። ከሊቨርፑሉ አንፊልድ ስታዲየም 11 ሺህ ኪሎ ሜትር ርቆ ይገኛል። የሚወደው ቡድን ትውልድ ከተማውን እንዲጎበኝ እአአ ከ2011 ጀምሮ ሲጠብቅ ቆይቷል። ይህ ግን የእሱ ብቻ ታሪክ አይደለም። በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በሊቨርፑል እና በክሪስታል ፓላስ መካከል የወዳጅነት ጨዋታ ተደርጓል። ከ50,000 በላይ ደጋፊዎች የሲንጋፖርን ብሔራዊ ስታዲየም ከአፍ እስከ ገደፉ ሞልተውታል። ለሦስት ዓመታት የተጣለው የኮቪድ የጉዞ እገዳ ተነሳ። የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቡድኖችም ለቅድመ-ውድድር ዝግጅት አድማስን እያቋረጡ ነው። ጉዞዎቹ በገንዘብ ረገድ ያላቸው ጠቀሜታ ለመገመት አስቸጋሪ ነው። ማንቸስተር ዩናይትድ እአአ በ2021 ወደ 56 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገቢ እንዳጣ ክለቡ ይፋ አድርጎ ነበር። “ዋነኛው” ምክንያት ኮቪድ መስተጓጎል መሆኑ ተጠቅሷል። ከዚህ መካከል አንዱ በሕንድ ሊደረግ የነበረው የቅድመ ውድድር ዘመን ጉብኝት መሰረዙ ነው። አሁን እገዳው ቀንሷል። ክለቦችም ቁጥር አንድ ወደሚሉት የገበያ ስፍራ እየጎረፉ ነው። የሊቨርፑል ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት ቢሊ ሆጋን “እስያ በደጋፊዎች ብዛት ቀዳሚዋ መዳረሻችን ናት” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። “የትኛውንም አውሮፕላን ተሳፍረህ ወደ ኤስያ ብትሄድ የሊቨርፑል ደጋፊዎችን ማግኘት ትችላለህ፣ ሲል አንድ ሰው የነገረኝን ማስታወስ እፈልጋለሁ። አንድ ሦስተኛው ዓለም አቀፍ ደጋፊያችን መገኛው እዚህ ነው። በእስያ ውስጥ ትልቅ ዕድል እንዳለ ይሰማናል።” በዚህ ክረምት ማንቸስተር ዩናይትድ ፊቱን ወደ ታይላንድን እና አውስትራሊያን አዙሯል። ከሊቨርፑል እና ከክሪስታል ፓላስ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ አከከናውኗል። ቶተንሃም ሆትስፐር ወደ ደቡብ ኮሪያ አቅንቷል። ደቡብ ኮሪያ የክለቡ ከፍተኛ ኮከብ ግብ አግቢው ሶን ሄንግ ሚን አገር ነች። ከስፖርት አንጻር እነዚህ ጉዞዎች ትርጉማቸው እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። በተለያዩ የሰዓት ዞኖች የሚደረጉ ረዥም በረራዎች፣ በከፍተኛ ሙቀት እና እርጥበታማ የአየር ሁኔታ ልምምድ ማድረግን ያካትታል። ይህ ግን እንግሊዝ ለሚኖራቸው የአዲሱ የውድድር ዘመን ዝግጅት ጥሩ  አይደለም። የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ በጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ “የምመርጠው ነገር አይደለም” ብለዋል። “ሲጀምር እኔ አሰልጣኝ ነኝ። ለሁለት ሳምንት ኦስትሪያ ቆይተን በቀን ሁለት ጊዜ ብናሰልጥን ጥሩ ነበር። “የደጋፊዎቻችን ቁጥር እስያ ውስጥ ምን ያህል ትልቅ እንደሆነ እናውቃለን። ወደ እነርሱ ቀረብ ማለት ጥሩ ነገር ነው።” እንደ እውነቱ ከሆነ በእግር ኳስ ውስጥ ለረዥም ጊዜ የከረመ ክርክር ነበር። ክርክሩ ከረጅም ጊዜ በፊት ውሳኔ ያገኘ ይመስላል። ከፋይናንስ ጋር ያለው ወገን የበላይነት ይዟል። በዚህ ዓመት የወጡ አዳዲስ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ፕሪሚየር ሊጉ ለመጀመሪያ ጊዜ ከዓለም አቀፍ ጨዋታ አስተላላፊዎች ከፍተኛ ገቢ ያገኛል። ይህም ለመጀመሪያ ጊዜ ከእንግሊዝ ገበያ ከሚገኘው የበለጠ ገቢ ይሆናል። በሚቀጥለው የውድድር ዓመት እስከ 2025 ባለው ጊዜ ከእስያ ገበያ 1.4 ቢሊዮን ዶላር ይሸፍናል ተብሎ ይጠበቃል። ስፐርስ በደቡብ ኮሪያ የወደጅነት ጨዋታ አድርጓል። ይህም ከሃገሪቱ ክለቦች ከተወጣጡ የኮከቦች ቡድን ጋር ተደረገ ሲሆን፣ የጨዋታው ትኬት በ25 ደቂቃ ውስጥ ተሸጦ ተጠናቋል። በአገሪቱ ታሪክ ከፍተኛ ስርጭት ያገኘ የስፖርት ዝግጅት ሆኗል። ባንኮክ የሚገኙ የውድድሩ አዘጋጆች በማንቸስተር ዩናይትድ እና ሊቨርፑል መካከል ለሚደረገው የወዳጅነት ጨዋታ የትኬት መነሻ ዋጋው 136 ዶላር አድርገዋል። በሲንጋፖር ርካሽ የተባለለት ቲኬት 107 ዶላር ተቸብችቧል። እነዚህ ዋጋዎች ከእንግሊዝ የነጥብ ጨዋታዎች አንጻር እንኳን ውድ የሚባሉ ናቸው። ሆኖም የፕሪሚየር ሊጉን ከፍተኛ ክለቦችን የመሳብ ጠንካራ አቅም አላቸው። የሊቨርፑል ቃል አቀባይ “የእነዚህን የቲኬቶች ዋጋ እኛ አልወሰንም። እኛ የተወሰነልንን ክፍያ እንቀበላለን። እኛ ከትኬት ገቢ ምንም አይነት ድርሻ አንቀበልም" ብለው ለቢቢሲ ገልጸዋል። የእስያ ገቢ ክለቦቹ ከእነዚህ የወዳጅነት ግጥሚያዎች ምን ያህል እንደሚያገኙ አይታወቅም። ምክንያቱም መረጃው በጥብቅ ስለሚያዝ። ተንታኞች እንደሚሉት ግን ክፍያውን ለጉዞዎቹ ብቸኛ ምክንያት አድርጎ አያስቀምጥም።  ለዚህ እንደምክንያት የሚቀመጠው የጉዞ እና የሠራተኞች ወጪዎች መኖራቸው ነው። “በእውነቱ ከሆነ ቡድኖቹ ከቅድመ-ውድድር ጨዋታዎች ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ በቀጥታ አያገኙም። ምናልባትም በአንድ ግጥሚያ ጥቂት ሚሊዮን ዶላር ቢገኝ ነው” ሲል የስፖርት ቢዝነሱ የእስያ-ፓስፊክ አርታኢ ኬቨን ማኩላግ ይገልጻል። “ነገር ግን አንድ ትልቅ ዓላማ አለ። ይህም የስም ግንባታ እና በቀጣይ የቴሌቭዥን ሥርጭት ገበያውን በሚመራውና የስፖንሰርሺፕ ስምምነቶችን በሚያስገኘው ገበያ ውስጥ መሳተፍ ነው። ትክክለኛው ገንዘብ ይህ ነው።” ሊቨርፑል በሲንጋፖር በከተመበት ወቅት ከ240 ሚሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያለው አዲስ የማሊያ ስፖንሰርሺፕ ስምምነት ተፈራርሟል። ስምምነቱ ስታንዳርድር ቻርተርድ ከተባለውና ትኩረቱን እስያ ላይ ካደረገው ባንክ ጋር ተደርሷል። የእግር ኳስ ክለቦች የስፖንሰርን አቅማቸውን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከማሳደግ ባለፈ የደጋፊዎችን መረጃ ሊያቀርቡላቸው ይችላሉ። ለምሳሌ ማንቸስተር ዩናይትድ የደጋፊ ግንኙነት አስተዳደር (ሲአርኤም) ዳታቤዝ 50 ሚሊዮን መዝገቦችን እንደያዘ ይገምታል። ባለፈው ዓመት በማኅበራዊ ሚዲያው 176 ሚሊዮን አስፍሯል። ይህም ለስፖንሰርሺፕ ገንዘብ፣ ስያሜ እና ለግብይት ክፍል የሚረዱ ከክለቡ ጋር የተመዘገቡ ወይም የተሳተፉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደጋፊዎችን ጠቃሚ መረጃ ያስገኛል። “የመጀመሪያው ትልልቅ ስፖንሰሮች የሚጠይቁት በደጋፊዎች ዙሪያ ያለውን መረጃ ነው” ሲል ማኩላግ ተናግሯል። “ገንዘባቸውን ፈሰስ ከማድረጋቸው በፊት አንድ ክለብ ምን ያህል ደጋፊ እንዳለው፣ ዕድሜ፣ ወንድ፣ ሴት፣ የገቢ መጠን እና የመሳሰሉትን ነገሮች ማወቅ ይፈልጋሉ።” የእንግሊዝ እግር ኳስን በገንዘብ በስፋት እንዲሰበሰብ ያስቻለው ግን የቴሌቭዥን ገቢ ነው። ለዓመታት ሌሎች የስፖርት ሊጎች (የአውሮፓ እግር ኳስ ሊጎችን ጨምሮ) ፕሪሚየር ሊጉን በቅናት ሲመለከቱ ኖረዋል። ወደ እስያ በማቅናት እነዚህ ሊጎች ቀዳሚ ናቸው። የፕሪሚየር ሊጉ ፉክክር፣ ልዩ የሆነው የደጋፊዎች ባህል እና ከእንግሊዘኛ ቋንቋ ጋር ያለው ትስስር ሊጉ በዓለም አቀፍ ደረጃ 3.2 ቢሊየን ተመልካቾችን በመሳብ በብዛት የታየ የስፖርት ሊግ እንዲሆን አስተዋጽኦ አድርጓል። ፕሪሚየር ሊግ እንደሚለው ግማሹ የዓለም ደጋፊ እና አንድ አራተኛው የቴሌቭዥን ተመልካቾች በእስያ ፓስፊክ ይገኛል። ይህ ሁሉ የሆነው ብዙ ጨዋታዎች በእኩለ ሌሊት እየተጠናቀቁም ነው። እነዚህን ሁሉ ደጋፊዎች ይዞ ማቆየት ፈታኝ እንደሚሆን ባለሙያዎች ይናገራሉ። በተለይም ለወጣቱ ትውልድ በጣም ሰፊ የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዎች እና የአኗኗር ዘይቤዎች አማራጮች መኖራቸው ዋነኛው ስጋት ነው። የስፔኑ ኃያል ክለብ ሪያል ማድሪድ ፕሬዝዳንት የሆኑት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ባለፈው ዓመት “ወጣቶች በእግር ኳስ ላይ ፍላጎት የላቸውም። ራሳቸውን የሚያዘናጉባቸው ሌሎች መድረኮች አሏቸው” ማለታቸውን ማስታወስ ተገቢ ነው። ይህ አመለካከት የቴሌቭዥን ገቢ ውሎ አድሮ እየቀነሰ እንደሚሄድ ከተገመተው ትንበያ ጋር ተደማምሮ በአውሮፓ ከፍተኛ የእግር ኳስ ክለቦች ውስጥ ያሉ አንዳንድ ኃላፊዎችን ደጋፊዎቻቸውን ለማሳተፍ አዲስ ውድድር መፈጠር እንዳለበት አሳምኗቸዋል። አንደኛው ሃሳብ የአውሮፓ ሱፐር ሊግ ነበር። አምስት የእንግሊዝ ክለቦችን ጨምሮ ሁሌም ተሳታፊ በሚሆኑ ክለቦች የሚደረግ ውድድር ለማድረግ ያቀደ ነበር። ይህም በዓለም ዙሪያ በተለይም በእስያ ውስጥ ያሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አድናቂዎችን ታላሚ ያደረገ ነበር። እነዚህ ሁሌም ኃያል ቡድኖች እርስ በእርስ ሲፎካከሩ ማየት የሚፈልጉ ናቸው፤ ግን በጅምር ቀረ። በዩናይትድ ኪንግደም እና በዓለምአቀፍ ደጋፊዎች ዘንድ ያስነሳው ቁጣ እንዲሰረዝ ምክንያት ሆነ። “የአውሮፓ እግር ኳስ ክለቦች ስለእስያ ግምት መያዝ የለባቸውም። ስለሚያገኙት እያንዳንዱ ዶላር መታገል ግን አለባቸው” ሲሉ በፈረንሳይ በኤምሊዮን ቢዝነስ ትምህርት ቤት የስፖርት ፕሮፌሰር የሆኑት ሲሞን ቻድዊክ ተናግረዋል። “የእስያ ሸማቾች ብልህ፣ የተራቀቁ እና አስተዋይ ናቸው። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአውሮፓ እግር ኳስ በእስያ ደጋፊዎች መካከል መጠነኛ መለያየት እንዳለ ሊከራከሩ ይችላሉ። ስለዚህ ክለቦች እስያን በቀላሉ እንደሚቆጣጠሩት በማሰብ እብሪተኛ ወይም የዋህ እንዳይሆኑ ይመከራሉ።" ቻድዊክ አክለውም የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያዎች በውጭ አገራት ሊደረጉ ይችላሉ ተብሎ በ 2008 ለመጀመሪያ ጊዜ የቀረበው ሃሳብ ከአጭር እስከ መካከለኛ ባለው ጊዜ የማይሳካ ነው። ጉዳዩ ግን በድጋሚ ሊታይ ይችላል። ወደ ሲንጋፖር እንመለስ፤ ቪጃይ ሸሚዙን አውልቆ ጀርባውን ያሳያል። በንቅሳት ተዥጎርጉሯል። የሊቨርፑል ስም እና ክለቡ በታሪኩ ዋንጫ ያገኘባቸው ዓመታትን ተነቅሷል። ስለ ወደፊቱም ቢሆን ብሩህ ተስፋ ሰንቋል። “አባቴ የሊቨርፑል ደጋፊ ነበር። ከሴት ልጆቼ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ያደረግኩት ነገር የሊቨርፑል ማሊያን ለእነሱ ማልበስ ነበር። እመኑኝ ይህ በትውልዶችን ቅብብል ይቀጥላል” ሲል ያጠናቅቃል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/crg7j1m7792o
3politics
ታጣቂዎች የጋምቤላ ከተማን በከፊል ተቆጣጥረው እንደነበረ ክልሉ ገለጸ
ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ ላይ ዛሬ ማክሰኞ ማለዳ ላይ ጥቃት ከፍተው የከተማዋን የተወሰነ ክፍል ተቆጣጥረው እንደነበረ የክልሉ መንግሥት ገለጸ። የክልሉ መስተዳደር ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው በጋምቤላ ከተማ “የሸኔ እና የጋምቤላ ነፃነት ግንባር” በጋራ ጥቃት ከፍተው እንደነበረና ከረፋድ አራት ሰዓት በኋላ መጠነኛ መረጋጋት እንዳለ አመልክቷል። በታጣቂዎች እና በፀጥታ ኃይሎች መካከል ዛሬ ማክሰኞ ከማለዳ ጀምሮ በተካሄደ የተኩስ ልውውጥ በክልሉ የፀጥታ አባላት እና በታጣቂዎቹ ላይ ጉዳት መድረሱንም የቢቢሲ ምንጮች ገልጸዋል። የጋምቤላ ክልል ርዕሰ አቶ ኡሞድ ኡጁሉ መስተዳደር ስለተከሰተው ሁኔታ ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ በሰጡት መግለጫ እናዳሉት፣ በጋምቤላ ከተማ ያጋጠመው የፀጥታ ችግር የፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተናግረዋል። ከተማዋም በአሁኑ ጊዜ በክልሉ የፀጥታ ኃይል ቀጥጥር ስር ሙሉ ለሙሉ መግባቷን አቶ ኡሞድ ገልጸው፣ ታጣቂዎቹ የከፈቱትን ጥቃት ተከትሎ የፀጥታ ኃይሉ በወሰደው እርምጃ “በታጣቂዎቹ ላይ ከፍተኛ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ መድረሱን” አመልክተው በፀጥታ ኃይሉ ላይ መጠነኛ ጉዳት መድረሱን አመልክተዋል። በጋምቤላ ከተማ ማክሰኞ ሰኔ 07/2014 ዓ.ም. ከንጋት 11 ሰዓት ተኩል ገደማ ጀምሮ ለሰዓታት የቆየ ከባድ የተኩስ ልውውጥ ሲካሄድ እንደነበርና ከፊል የከተማዋ ክፍልም በታጣቂዎቹ ቁጥጥር ስር መግባቱን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። አንድ የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣን ክስተቱ በጋምቤላ ከተማ ውስጥ ማጋጠሙን አረጋግጠው፣ በዚህም የሰው ህይወት መጥፋቱንና የተጎዱ መኖራቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የክልሉ ባለሥልጣን ከዕኩለ ቀን በፊት ለቢቢሲ እንደተናገሩት ቢያንስ ሁለት የፀጥታ ኃይሎች እንዲሁም ከታጣቂዎቹ የሦስቱ ህይወት ማለፉን ከሆስፒታል ምንጮቻቸው መረዳታቸውን ተናግረዋል። ክልሉ ማክሰኞ ረፋድ ላይ ባወጣው መግለጫ በጥቃቱ መካከል የደረሰው ጉዳት በውል እንደማይታወቅ አመልክቶ በታጣቂዎችና በፀጥታ ኃይሎች ላይ ጉዳት መድረሱን ገልጾ ነበር። ዛሬ ማለዳ ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው የተኩስ ልውውጥ “ያለማቋረጥ እስከ ረፋዱ 4 ሰዓት ከ20 ድረስ ሲካሄድ ቆይቶ” አሁን በከተማዋ ውስጥ መረጋጋት እንደሚታይና “የመንግሥት የፀጥታ ኃይል ባካሄደው ብርቱ ትግል ከተማውን በከፊል ነፃ ማውጣት እንደተቻለ” ክልሉ ገልጿል። ሁለት የከተማዋ ነዋሪዎች እንዳሉት በዚሁ ክስተት ሳቢያ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ የንግድ ሥራዎች ብሎም ሌሎች መደበኛ እንቅስቃሴዎች የተስተጓጎሉ ሲሆን ነዋሪዎችም በቤታቸው ዘግተው መቀመጣቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። የክልሉ መንግሥት ክስተቱን በሚመለከት ረፋድ ላይ ባወጣው መግለጫ ላይ የከተማው ነዋሪ ኅብረተሰብ ከቤት ባለመውጣት የፀጥታ ኃይሉ እያደረገ ላለው የሕግ ማስከበር ተግባር የበኩሉን እንዲወጣ ተጠይቋል። በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ቢሮ አካባቢም ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ ላለፉት አስከ ረፋድ አራት ሰዓት ድረስ ሲሰማ እንደነበረ አንድ በአቅራቢያው የነበሩ ነዋሪ ጠዋት ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በከተማዋ ስለተከሰተው የተኩስ ልውውጥና አሁን ስላለው ሁኔታ “ምንም የምንሰጠው መረጃ የለም’’ ሲሉ ረፋድ ላይ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ቢቢሲ ተጨማሪ መረጃ ከርዕሰ መስተዳደሩ ለማግኘት ቢጠይቅም ለጊዜው ከዚህ ያለፈ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። በዚህም የከተማዋን የተወሰነ ክፍል ታጣቂዎቹ መቆጣጠራቸውን ብሎም የጥቃቱ ኢላማ የርዕሰ መስተዳደሩን ጽህፈት ቤት ለመቆጣጠር ያለመ ሳይሆን እንደማይቀር የከተማዋ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገልጸዋል። በተኩስ ልውውጡ በርካቶች መቁሰላቸውን ብሎም ታጣቂዎቹ ከርዕሰ መስተዳደሩ ጽህፈት ቤት በተጨማሪ በተለምዶ ቤተ መንግሥት የሚባለውን የርዕሰ መስተዳደሩን መኖሪያ ቤት እንዲሁም የነዳጅ መከማቻ ዴፖ ለመቆጣጠር ጥቃት ከፍተው እንደነበር ነዋሪዎች ተናግረዋል። የክልሉ ባለሥልጣንም ጥቃቱን በሚመለከት “ለፌደራል መንግሥት አሳውቀናል። ከአቅራቢያ ወደ ከተማው ኃይል ለማሰማራት እየሞከሩ እንደሆነ ነግረውናል። እዚህ ያለው ኃይላቸው ግን ትንሽ ነው’’ ሲሉ ማክሰኞ ጠዋት ለቢቢሲ ገልጸው ነበር። ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁት አንድ የከተማው ነዋሪ ከባሮ ወንዝ ተሻግሮ ያለው የከተማው ክፍል በታጣቂዎች ቁጥጥር ስለሆነ ጠዋት ከባሮ ማዶ ተሻግረው እንደሚገኙ ተናግረዋል። “ከአራት ቀን በፊትም ተመሳሳይ ሙከራ ተደርጎ ነበር። ከዚህ በፊት በዚህ መጠን የታጣቂዎች እንቅስቃሴ አይተን አናውቅም ነበር’’ ሲሉም ነዋሪው አክለዋል። መንግሥት በሽብርተኝነት የሰየመውና ኦነግ-ሸኔ የሚለው፣ እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ሲል የሚጠራው ታጣቂ ቡድን የሕዝብ ግንኙነት ኦዳ ተርቢ የተሰኘው ግለሰብ በትዊተር ገጹ ሠራዊቱ ከጋምቤላ ነጻነት ግንባር ጋር በመሆን በጋምቤላ ከተማ ወታደራዊ ዘመቻ እያካሄደ ነው ብሏል። ይኸው ገጽ አክሎም ከጋምቤላ በተጨማሪም በምዕራብ ኦሮሚያ በደምቢ ዶሎ ተመሳሳይ ወታደራዊ ዘመቻ እያደረገ መሆኑን ገልጿል። የጋምቤላ ክልል በምዕራብ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር የሚዋሰን ሲሆን፣ ታጣቂዎች ይንቀሳቀሱባቸዋል ከሚባሉት ከምዕራብ ኦሮሚያ እና ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ጋር ይዋሰናል። በተለያዩ ጊዜያት ከጎረቤት አገር ሱዳን ዘልቀው የሚገቡ ታጣቂዎች በነዋሪዎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት ሲፈጽሙ እንደነበረም አይዘነጋም።
ታጣቂዎች የጋምቤላ ከተማን በከፊል ተቆጣጥረው እንደነበረ ክልሉ ገለጸ ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ ላይ ዛሬ ማክሰኞ ማለዳ ላይ ጥቃት ከፍተው የከተማዋን የተወሰነ ክፍል ተቆጣጥረው እንደነበረ የክልሉ መንግሥት ገለጸ። የክልሉ መስተዳደር ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው በጋምቤላ ከተማ “የሸኔ እና የጋምቤላ ነፃነት ግንባር” በጋራ ጥቃት ከፍተው እንደነበረና ከረፋድ አራት ሰዓት በኋላ መጠነኛ መረጋጋት እንዳለ አመልክቷል። በታጣቂዎች እና በፀጥታ ኃይሎች መካከል ዛሬ ማክሰኞ ከማለዳ ጀምሮ በተካሄደ የተኩስ ልውውጥ በክልሉ የፀጥታ አባላት እና በታጣቂዎቹ ላይ ጉዳት መድረሱንም የቢቢሲ ምንጮች ገልጸዋል። የጋምቤላ ክልል ርዕሰ አቶ ኡሞድ ኡጁሉ መስተዳደር ስለተከሰተው ሁኔታ ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ በሰጡት መግለጫ እናዳሉት፣ በጋምቤላ ከተማ ያጋጠመው የፀጥታ ችግር የፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተናግረዋል። ከተማዋም በአሁኑ ጊዜ በክልሉ የፀጥታ ኃይል ቀጥጥር ስር ሙሉ ለሙሉ መግባቷን አቶ ኡሞድ ገልጸው፣ ታጣቂዎቹ የከፈቱትን ጥቃት ተከትሎ የፀጥታ ኃይሉ በወሰደው እርምጃ “በታጣቂዎቹ ላይ ከፍተኛ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ መድረሱን” አመልክተው በፀጥታ ኃይሉ ላይ መጠነኛ ጉዳት መድረሱን አመልክተዋል። በጋምቤላ ከተማ ማክሰኞ ሰኔ 07/2014 ዓ.ም. ከንጋት 11 ሰዓት ተኩል ገደማ ጀምሮ ለሰዓታት የቆየ ከባድ የተኩስ ልውውጥ ሲካሄድ እንደነበርና ከፊል የከተማዋ ክፍልም በታጣቂዎቹ ቁጥጥር ስር መግባቱን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። አንድ የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣን ክስተቱ በጋምቤላ ከተማ ውስጥ ማጋጠሙን አረጋግጠው፣ በዚህም የሰው ህይወት መጥፋቱንና የተጎዱ መኖራቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የክልሉ ባለሥልጣን ከዕኩለ ቀን በፊት ለቢቢሲ እንደተናገሩት ቢያንስ ሁለት የፀጥታ ኃይሎች እንዲሁም ከታጣቂዎቹ የሦስቱ ህይወት ማለፉን ከሆስፒታል ምንጮቻቸው መረዳታቸውን ተናግረዋል። ክልሉ ማክሰኞ ረፋድ ላይ ባወጣው መግለጫ በጥቃቱ መካከል የደረሰው ጉዳት በውል እንደማይታወቅ አመልክቶ በታጣቂዎችና በፀጥታ ኃይሎች ላይ ጉዳት መድረሱን ገልጾ ነበር። ዛሬ ማለዳ ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው የተኩስ ልውውጥ “ያለማቋረጥ እስከ ረፋዱ 4 ሰዓት ከ20 ድረስ ሲካሄድ ቆይቶ” አሁን በከተማዋ ውስጥ መረጋጋት እንደሚታይና “የመንግሥት የፀጥታ ኃይል ባካሄደው ብርቱ ትግል ከተማውን በከፊል ነፃ ማውጣት እንደተቻለ” ክልሉ ገልጿል። ሁለት የከተማዋ ነዋሪዎች እንዳሉት በዚሁ ክስተት ሳቢያ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ የንግድ ሥራዎች ብሎም ሌሎች መደበኛ እንቅስቃሴዎች የተስተጓጎሉ ሲሆን ነዋሪዎችም በቤታቸው ዘግተው መቀመጣቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። የክልሉ መንግሥት ክስተቱን በሚመለከት ረፋድ ላይ ባወጣው መግለጫ ላይ የከተማው ነዋሪ ኅብረተሰብ ከቤት ባለመውጣት የፀጥታ ኃይሉ እያደረገ ላለው የሕግ ማስከበር ተግባር የበኩሉን እንዲወጣ ተጠይቋል። በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ቢሮ አካባቢም ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ ላለፉት አስከ ረፋድ አራት ሰዓት ድረስ ሲሰማ እንደነበረ አንድ በአቅራቢያው የነበሩ ነዋሪ ጠዋት ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በከተማዋ ስለተከሰተው የተኩስ ልውውጥና አሁን ስላለው ሁኔታ “ምንም የምንሰጠው መረጃ የለም’’ ሲሉ ረፋድ ላይ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ቢቢሲ ተጨማሪ መረጃ ከርዕሰ መስተዳደሩ ለማግኘት ቢጠይቅም ለጊዜው ከዚህ ያለፈ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። በዚህም የከተማዋን የተወሰነ ክፍል ታጣቂዎቹ መቆጣጠራቸውን ብሎም የጥቃቱ ኢላማ የርዕሰ መስተዳደሩን ጽህፈት ቤት ለመቆጣጠር ያለመ ሳይሆን እንደማይቀር የከተማዋ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገልጸዋል። በተኩስ ልውውጡ በርካቶች መቁሰላቸውን ብሎም ታጣቂዎቹ ከርዕሰ መስተዳደሩ ጽህፈት ቤት በተጨማሪ በተለምዶ ቤተ መንግሥት የሚባለውን የርዕሰ መስተዳደሩን መኖሪያ ቤት እንዲሁም የነዳጅ መከማቻ ዴፖ ለመቆጣጠር ጥቃት ከፍተው እንደነበር ነዋሪዎች ተናግረዋል። የክልሉ ባለሥልጣንም ጥቃቱን በሚመለከት “ለፌደራል መንግሥት አሳውቀናል። ከአቅራቢያ ወደ ከተማው ኃይል ለማሰማራት እየሞከሩ እንደሆነ ነግረውናል። እዚህ ያለው ኃይላቸው ግን ትንሽ ነው’’ ሲሉ ማክሰኞ ጠዋት ለቢቢሲ ገልጸው ነበር። ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁት አንድ የከተማው ነዋሪ ከባሮ ወንዝ ተሻግሮ ያለው የከተማው ክፍል በታጣቂዎች ቁጥጥር ስለሆነ ጠዋት ከባሮ ማዶ ተሻግረው እንደሚገኙ ተናግረዋል። “ከአራት ቀን በፊትም ተመሳሳይ ሙከራ ተደርጎ ነበር። ከዚህ በፊት በዚህ መጠን የታጣቂዎች እንቅስቃሴ አይተን አናውቅም ነበር’’ ሲሉም ነዋሪው አክለዋል። መንግሥት በሽብርተኝነት የሰየመውና ኦነግ-ሸኔ የሚለው፣ እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ሲል የሚጠራው ታጣቂ ቡድን የሕዝብ ግንኙነት ኦዳ ተርቢ የተሰኘው ግለሰብ በትዊተር ገጹ ሠራዊቱ ከጋምቤላ ነጻነት ግንባር ጋር በመሆን በጋምቤላ ከተማ ወታደራዊ ዘመቻ እያካሄደ ነው ብሏል። ይኸው ገጽ አክሎም ከጋምቤላ በተጨማሪም በምዕራብ ኦሮሚያ በደምቢ ዶሎ ተመሳሳይ ወታደራዊ ዘመቻ እያደረገ መሆኑን ገልጿል። የጋምቤላ ክልል በምዕራብ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር የሚዋሰን ሲሆን፣ ታጣቂዎች ይንቀሳቀሱባቸዋል ከሚባሉት ከምዕራብ ኦሮሚያ እና ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ጋር ይዋሰናል። በተለያዩ ጊዜያት ከጎረቤት አገር ሱዳን ዘልቀው የሚገቡ ታጣቂዎች በነዋሪዎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት ሲፈጽሙ እንደነበረም አይዘነጋም።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cmje02png3mo
3politics
ስደተኛው የአፍጋኒስታን ፕሬዝዳንት ሚሊዮን ዶላሮችን አሽሽተዋል መባሉን አስተባበሉ
በቅርቡ ከአገራቸው የሸሹት የአፍጋኒስታን ፕሬዝዳንት የነበሩት አሽረፍ ጋኒ ሚሊዮን ዶላሮችን ከካቡል ይዘው ወጥተዋል የሚለው ወሬ ‹መሰረተ ቢስና ሐሰተኛ› ነው ሲሉ ተናገሩ፡፡ አሽረፍ ጋኒ ትናንት በቪዲዮ ከተጠለሉበት የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ በሰጡት መግለጫ ከአገሪቱ በርካታ ገንዘብ መውሰዳቸው በስፋት እንደሚወራ ጠቅሰው ይህ ግን ፍጹም ሐሰት ነው ብለዋል፡፡ የታሊባንን ወደ ካቡል መገስገስ ተከትሎ ከአገራቸው የሸሹት የአፍጋኒሰታን የቀድሞ ፕሬዝዳንት አሽራፍ ጋኒ የት አገር እንደሄዱ እስከ ትናንት ድረስ ሲያነጋግር ነበር፡፡ በመጨረሻ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ አሽረፍ ጋኒ ከእኔ ዘንድ ናቸው ብላለች፡፡ አሽረፍ ጋኒ ካቡልን የለቀቁት ታሊባኖች ካቡል መግባታቸው እስደተሰማ በሰዓታት ውስጥ ባለፈው እሑድ ነበር፡፡ የኢምሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሽረፍ ጋኒን እና ቤተሰባቸውን በእንግድነት የተቀበለው በሰብአዊነት ምክንያት ነው ሲል መግለጫ አውጥቷል፡፡ አገራቸውን በክፉ ጊዜ በዚያ ፍጥነት ጥለው መሄዳቸው አሽረፍ ጋኒን ለከፍተኛ ትችት ዳርጓቸው ቆይቷል፡፡ ትናንት ረቡዕ የቪዲዮ መግለጫ የሰጡት አሽረፍ ጋኒ ግን ‹እኔ ቶሎ አገሪቱን ጥዬ ባልሄድ ኖሮ በካቡል ደም ይፈስ ነበር› ሲሉ ተናግረዋል፡፡ "ለጊዜው ኢምሬትስ ነው ያለሁት፡፡ ደም መፋሰስ እንዲቆም በሚል ነው ወደዚህ የመጣሁት፡፡ አሁን ንግግር ጀምረናል፤ ወደ አፍጋኒስታን የምመለስበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እየተነጋገርኩ ነው" ብለዋል በመግለጫቸው፡፡ የ72 ዓመቱ ስደተኛው ፕሬዝዳንት አሽረፍ ጋኒ አገሪቱን ለታሊባን አስረክበው በዚያ ፍጥነት መሸሻቸው አፍጋኒስታናዊያንን ብቻ ሳይሆን ጆ ባይደንንም ያስገረመ ይመስላል፡፡ ባይደን ባለፈው ሰኞ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አፍጋኒሰታናዊያን ለመዋጋትና ለመሞት የማይፈቅዱለትን ጦርነት የአሜሪካን ወታደሮች የሚሞቱት ምን በወጣቸው ሲሉ አስተያየት ሰጥተው ነበር፡፡ በፌስቡክ በቀጥታ ለሕዝብ በተላለፈው የአሽረፍ ጋኒ የትናንቱ መግለጫ ላይ ከካቡል የወጡበትን ሁኔታ የገለጹት ስደተኛው ፕሬዝዳንት እንዳብራሩት ከቤተ መንግሥት እንዲለቁ የተደረጉበትን ፍጥነት ‹ጠባቂዎቼ ጫማዬን እስካጠልቅ ድረስ እንኳ አልታገሱኝም›› ብለዋል፡፡ ‹ፋታ አልነበረም፡፡ ከታሊባን ጋር የጥምረት መንግሥት እንዲኖር ለመደራደር ፈልጌ ነበር፡፡ ሆኖም ፋታ አልነበረም› ብለዋል አሽረፍ ጋኒ፡፡ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ከአገራቸው ለሚሸሹ መሪዎች ከለላ ስትሰጥ ይህ የመጀመርያዋ አይደለም፡፡ ኢምሬቶች ከዚህ ቀደም የፓኪስታኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ለነበሩት ቤናዘር ቡቶ በ1990ዎቹ በተመሳሳይ ሁኔታ ዱባይ የክፉ ጊዜ ቤታቸው እንድትሆን ፈቅደው ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የተባቡሩት አረብ ኢምሬትስ የሌሎች አገሮች ፖለቲካ በፍጹም ወደ አፈሯ እንዲመጣ አትሻም ብሏል የቢቢሲ የደኅንነት ጉዳዮች ዘጋቢ ፍራንክ ጋርድነር፡፡ በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ በርካታ ፓኪስታናዊያንና አፍጋኒስታናዊያን በሠራተኝነት ይኖራሉ፡፡ አሽረፍ ጋኒ ወደ ሥልጣን የመጡት በ2014 ሲሆን በየካቲት 2020 ደግሞ በድጋሚ ምርጫን አሸንፈው ነበር፡፡ ከዓመት በፊት ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው አንድ ቃለ ምልልስ ታሊባን ወታደራዊ ድሎችን እያገኘ መሆኑ ያሳስባቸው እንደሆነ ተጠይቀው ሲመልሱ ‹ይህ ቬትናም አይደለም፡፡ መንግሥት ሊወድቅ አይችልም› ሲሉ ምላሽ ሰጥተው እንደነበር ይታወሳል፡፡
ስደተኛው የአፍጋኒስታን ፕሬዝዳንት ሚሊዮን ዶላሮችን አሽሽተዋል መባሉን አስተባበሉ በቅርቡ ከአገራቸው የሸሹት የአፍጋኒስታን ፕሬዝዳንት የነበሩት አሽረፍ ጋኒ ሚሊዮን ዶላሮችን ከካቡል ይዘው ወጥተዋል የሚለው ወሬ ‹መሰረተ ቢስና ሐሰተኛ› ነው ሲሉ ተናገሩ፡፡ አሽረፍ ጋኒ ትናንት በቪዲዮ ከተጠለሉበት የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ በሰጡት መግለጫ ከአገሪቱ በርካታ ገንዘብ መውሰዳቸው በስፋት እንደሚወራ ጠቅሰው ይህ ግን ፍጹም ሐሰት ነው ብለዋል፡፡ የታሊባንን ወደ ካቡል መገስገስ ተከትሎ ከአገራቸው የሸሹት የአፍጋኒሰታን የቀድሞ ፕሬዝዳንት አሽራፍ ጋኒ የት አገር እንደሄዱ እስከ ትናንት ድረስ ሲያነጋግር ነበር፡፡ በመጨረሻ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ አሽረፍ ጋኒ ከእኔ ዘንድ ናቸው ብላለች፡፡ አሽረፍ ጋኒ ካቡልን የለቀቁት ታሊባኖች ካቡል መግባታቸው እስደተሰማ በሰዓታት ውስጥ ባለፈው እሑድ ነበር፡፡ የኢምሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሽረፍ ጋኒን እና ቤተሰባቸውን በእንግድነት የተቀበለው በሰብአዊነት ምክንያት ነው ሲል መግለጫ አውጥቷል፡፡ አገራቸውን በክፉ ጊዜ በዚያ ፍጥነት ጥለው መሄዳቸው አሽረፍ ጋኒን ለከፍተኛ ትችት ዳርጓቸው ቆይቷል፡፡ ትናንት ረቡዕ የቪዲዮ መግለጫ የሰጡት አሽረፍ ጋኒ ግን ‹እኔ ቶሎ አገሪቱን ጥዬ ባልሄድ ኖሮ በካቡል ደም ይፈስ ነበር› ሲሉ ተናግረዋል፡፡ "ለጊዜው ኢምሬትስ ነው ያለሁት፡፡ ደም መፋሰስ እንዲቆም በሚል ነው ወደዚህ የመጣሁት፡፡ አሁን ንግግር ጀምረናል፤ ወደ አፍጋኒስታን የምመለስበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እየተነጋገርኩ ነው" ብለዋል በመግለጫቸው፡፡ የ72 ዓመቱ ስደተኛው ፕሬዝዳንት አሽረፍ ጋኒ አገሪቱን ለታሊባን አስረክበው በዚያ ፍጥነት መሸሻቸው አፍጋኒስታናዊያንን ብቻ ሳይሆን ጆ ባይደንንም ያስገረመ ይመስላል፡፡ ባይደን ባለፈው ሰኞ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አፍጋኒሰታናዊያን ለመዋጋትና ለመሞት የማይፈቅዱለትን ጦርነት የአሜሪካን ወታደሮች የሚሞቱት ምን በወጣቸው ሲሉ አስተያየት ሰጥተው ነበር፡፡ በፌስቡክ በቀጥታ ለሕዝብ በተላለፈው የአሽረፍ ጋኒ የትናንቱ መግለጫ ላይ ከካቡል የወጡበትን ሁኔታ የገለጹት ስደተኛው ፕሬዝዳንት እንዳብራሩት ከቤተ መንግሥት እንዲለቁ የተደረጉበትን ፍጥነት ‹ጠባቂዎቼ ጫማዬን እስካጠልቅ ድረስ እንኳ አልታገሱኝም›› ብለዋል፡፡ ‹ፋታ አልነበረም፡፡ ከታሊባን ጋር የጥምረት መንግሥት እንዲኖር ለመደራደር ፈልጌ ነበር፡፡ ሆኖም ፋታ አልነበረም› ብለዋል አሽረፍ ጋኒ፡፡ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ከአገራቸው ለሚሸሹ መሪዎች ከለላ ስትሰጥ ይህ የመጀመርያዋ አይደለም፡፡ ኢምሬቶች ከዚህ ቀደም የፓኪስታኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ለነበሩት ቤናዘር ቡቶ በ1990ዎቹ በተመሳሳይ ሁኔታ ዱባይ የክፉ ጊዜ ቤታቸው እንድትሆን ፈቅደው ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የተባቡሩት አረብ ኢምሬትስ የሌሎች አገሮች ፖለቲካ በፍጹም ወደ አፈሯ እንዲመጣ አትሻም ብሏል የቢቢሲ የደኅንነት ጉዳዮች ዘጋቢ ፍራንክ ጋርድነር፡፡ በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ በርካታ ፓኪስታናዊያንና አፍጋኒስታናዊያን በሠራተኝነት ይኖራሉ፡፡ አሽረፍ ጋኒ ወደ ሥልጣን የመጡት በ2014 ሲሆን በየካቲት 2020 ደግሞ በድጋሚ ምርጫን አሸንፈው ነበር፡፡ ከዓመት በፊት ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው አንድ ቃለ ምልልስ ታሊባን ወታደራዊ ድሎችን እያገኘ መሆኑ ያሳስባቸው እንደሆነ ተጠይቀው ሲመልሱ ‹ይህ ቬትናም አይደለም፡፡ መንግሥት ሊወድቅ አይችልም› ሲሉ ምላሽ ሰጥተው እንደነበር ይታወሳል፡፡
https://www.bbc.com/amharic/news-58243666
0business
የኢትዮጵያ አበባ ላኪዎችን ገቢ ክፉኛ የጎዳው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ
በዓለም አቀፍ ደረጃ ወረርሽኝ በሆነው ኮሮናቫይረስ ምክንያት በጥቂት ቀናት ውስጥ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ማጣታቸውን የአበባ አምራቾች ገለጹ። ኢትዮ አግሪሴፍት በሆለታ እና በባህርዳር ካሉት ሁለት የአበባ እርሻዎች በዓመት እስከ 40 ሚሊዮን አበባ ዘንግ ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ ያቀርብ እንደነበር ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ኢሳያስ ከበደ ለቢቢሲ ገልጸዋል። እንደ አቶ ኢሳያስ ገለጻ በቀጥታ እና በጨረታ ለዓለም ገበያ በሽያጭ ይቀርብ የነበረው አበባ ባለፉት ሶስት ሳምንታት ዋጋው በከፍተኛ ደረጃ ወርዷል። በየቀኑ እስከ 45ሺህ ዘንግ የሚጠጋ አበባ ለዓለም ገበያ ያቀርብ የነበረው አግሪ ሴፍት ከማርች 15 በኋላ በመቋረጡ በየቀኑ 21200 የአሜሪካ ዶላር ወይም 678400 ብር እያጣ መሆኑን ገልፀዋል። • በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ ሦስት ሰዎች ተገኙ • የአሜሪካ እስር ቤቶች በኮሮናቫይረስ ምክንያት እስረኛ መልቀቅ ጀመሩ ድርጅቱ ሠራተኞቹን እረፍት እንዲወጡ እያደረገ ከመሆኑም በላይ በየቀኑ ወደ አንድ መቶ ሺህ የሚጠጋ የአበባ ዘንግ ወደ ኮምፖስተነት ለመቀየር ተገዷል። ከባህርዳር ከተማ ወጣ ብሎ የሚገኘው ጣና ፍሎራም በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተመሳሳይ ችግር ገጥሞታል።ድርጅቱ ባለፉት ስምንት ቀናት ብቻ አንድ ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ዘንግ ገበያ በማጣት ምክንያት ለመጣል መገደዱን የጣና ፍሎራ ሽያጭ መምሪያ ሥራ አስኪያጅ አቶ አብነት በላይነህ ገልጸዋል። ባለፉት ስምንት ቀናት በገጠመው የገበያ ችግር ምክንያት ወደ 10 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ማጣቱን አስታውቀዋል። አክለውም ከ700 በላይ የሚሆኑ ሠራተኞቹም ያለሥራ መቀመጣቸውን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ አበባና አትክልት አምራች ላኪዎች ማህበር ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ ዘውዴ በተለይ ለቢቢሲ እንደገለጹት ማህበሩ ከኮሮና ቫይረስ መከሰት ጀምሮ በሥራቸው ላይ ሊፈጥር የሚችለውን ተጽዕኖ እና በእርሻዎቹ እንዳይሰራጭ ለማድረግ እየተሠራ ቆይቷል። ከየካቲት እስከ ግንቦት ያሉት ወራት በአበባ ሥራ ትልቅ የንግድ እንቅስቃሴ ያለበት መሆኑን ጠቅሰው አሁን ያለው የአበባ ዋጋ ካለፈው አመት አማካይ ጋር ሲነጻጸር በ85 በመቶ መቀነሱን አስታውቀዋል። በቶሎ የሚበላሽ እና የማይከማች ምርት ከመሆኑም በላይ የወጪ ንግዱ 80 በመቶ ቅናሽ በማሳየቱ አምራቾችን በገንዘብ ረገድ እንዲፈተኑ እያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። እንደ አቶ ኢሳያስ ገለጻ ከሆነ በአሁኑ ወቅት አበቦች እንዳይጎዱ በመንከባከብ እና ቀሪ ሠራተኞችን ደግሞ እረፍት እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ከስምንት መቶ በላይ ሠራተኞች ያሉት ድርጅቱ ችግሩ በዚሁ ከቀጠለ ደሞዝ ለመክፈል እንደሚቸገር ተናግረዋል። በዚህ ሃሳብ የሚስማሙት አቶ አብነት በበኩላቸው መንግስት በዘርፉ ለተሰማሩ አካላት ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል። • ሁለት ኢትዮጵያዊያን ጣሊያን ውስጥ በኮሮናቫይረስ መሞታቸው ተረጋገጠ ችግሩ ከመባባሱ በፊት መንግስት ድርጅቶች ብድር የሚከፈሉበትን ጊዜ በማስረዘም፤ ተጨማሪ ብድር የሚያገኙበትና የአበባ ፍላጎት ወዳሉባቸው አገራት ካርጎ እንዲጀመር የኢትዮጵያ አበባና አትክልት አምራች ላኪዎች ማህበር ጠይቋል። መንግስት ችግሩን መገንዘቡንና በሚቀጥለው ሳምንት መጀመሪያ ምላሽ ይሰጣል ብለው እንደሚጠብቁ አቶ ቴዎድሮስ ተናግረዋል። የኮሮና ወረርሽኝ በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተጨባጭ ጉዳት ፈጥኖ በመለየት የሚቻለውን ሁሉ ለማድረግ መንግሥት እንቅስቃሴ መጀመሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መግለፃቸው ይታወሳል።
የኢትዮጵያ አበባ ላኪዎችን ገቢ ክፉኛ የጎዳው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በዓለም አቀፍ ደረጃ ወረርሽኝ በሆነው ኮሮናቫይረስ ምክንያት በጥቂት ቀናት ውስጥ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ማጣታቸውን የአበባ አምራቾች ገለጹ። ኢትዮ አግሪሴፍት በሆለታ እና በባህርዳር ካሉት ሁለት የአበባ እርሻዎች በዓመት እስከ 40 ሚሊዮን አበባ ዘንግ ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ ያቀርብ እንደነበር ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ኢሳያስ ከበደ ለቢቢሲ ገልጸዋል። እንደ አቶ ኢሳያስ ገለጻ በቀጥታ እና በጨረታ ለዓለም ገበያ በሽያጭ ይቀርብ የነበረው አበባ ባለፉት ሶስት ሳምንታት ዋጋው በከፍተኛ ደረጃ ወርዷል። በየቀኑ እስከ 45ሺህ ዘንግ የሚጠጋ አበባ ለዓለም ገበያ ያቀርብ የነበረው አግሪ ሴፍት ከማርች 15 በኋላ በመቋረጡ በየቀኑ 21200 የአሜሪካ ዶላር ወይም 678400 ብር እያጣ መሆኑን ገልፀዋል። • በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ ሦስት ሰዎች ተገኙ • የአሜሪካ እስር ቤቶች በኮሮናቫይረስ ምክንያት እስረኛ መልቀቅ ጀመሩ ድርጅቱ ሠራተኞቹን እረፍት እንዲወጡ እያደረገ ከመሆኑም በላይ በየቀኑ ወደ አንድ መቶ ሺህ የሚጠጋ የአበባ ዘንግ ወደ ኮምፖስተነት ለመቀየር ተገዷል። ከባህርዳር ከተማ ወጣ ብሎ የሚገኘው ጣና ፍሎራም በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተመሳሳይ ችግር ገጥሞታል።ድርጅቱ ባለፉት ስምንት ቀናት ብቻ አንድ ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ዘንግ ገበያ በማጣት ምክንያት ለመጣል መገደዱን የጣና ፍሎራ ሽያጭ መምሪያ ሥራ አስኪያጅ አቶ አብነት በላይነህ ገልጸዋል። ባለፉት ስምንት ቀናት በገጠመው የገበያ ችግር ምክንያት ወደ 10 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ማጣቱን አስታውቀዋል። አክለውም ከ700 በላይ የሚሆኑ ሠራተኞቹም ያለሥራ መቀመጣቸውን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ አበባና አትክልት አምራች ላኪዎች ማህበር ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ ዘውዴ በተለይ ለቢቢሲ እንደገለጹት ማህበሩ ከኮሮና ቫይረስ መከሰት ጀምሮ በሥራቸው ላይ ሊፈጥር የሚችለውን ተጽዕኖ እና በእርሻዎቹ እንዳይሰራጭ ለማድረግ እየተሠራ ቆይቷል። ከየካቲት እስከ ግንቦት ያሉት ወራት በአበባ ሥራ ትልቅ የንግድ እንቅስቃሴ ያለበት መሆኑን ጠቅሰው አሁን ያለው የአበባ ዋጋ ካለፈው አመት አማካይ ጋር ሲነጻጸር በ85 በመቶ መቀነሱን አስታውቀዋል። በቶሎ የሚበላሽ እና የማይከማች ምርት ከመሆኑም በላይ የወጪ ንግዱ 80 በመቶ ቅናሽ በማሳየቱ አምራቾችን በገንዘብ ረገድ እንዲፈተኑ እያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። እንደ አቶ ኢሳያስ ገለጻ ከሆነ በአሁኑ ወቅት አበቦች እንዳይጎዱ በመንከባከብ እና ቀሪ ሠራተኞችን ደግሞ እረፍት እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ከስምንት መቶ በላይ ሠራተኞች ያሉት ድርጅቱ ችግሩ በዚሁ ከቀጠለ ደሞዝ ለመክፈል እንደሚቸገር ተናግረዋል። በዚህ ሃሳብ የሚስማሙት አቶ አብነት በበኩላቸው መንግስት በዘርፉ ለተሰማሩ አካላት ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል። • ሁለት ኢትዮጵያዊያን ጣሊያን ውስጥ በኮሮናቫይረስ መሞታቸው ተረጋገጠ ችግሩ ከመባባሱ በፊት መንግስት ድርጅቶች ብድር የሚከፈሉበትን ጊዜ በማስረዘም፤ ተጨማሪ ብድር የሚያገኙበትና የአበባ ፍላጎት ወዳሉባቸው አገራት ካርጎ እንዲጀመር የኢትዮጵያ አበባና አትክልት አምራች ላኪዎች ማህበር ጠይቋል። መንግስት ችግሩን መገንዘቡንና በሚቀጥለው ሳምንት መጀመሪያ ምላሽ ይሰጣል ብለው እንደሚጠብቁ አቶ ቴዎድሮስ ተናግረዋል። የኮሮና ወረርሽኝ በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተጨባጭ ጉዳት ፈጥኖ በመለየት የሚቻለውን ሁሉ ለማድረግ መንግሥት እንቅስቃሴ መጀመሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መግለፃቸው ይታወሳል።
https://www.bbc.com/amharic/news-51986046
0business
ኢንዶኔዥያ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ላይ ጥላ የነበረውን እገዳ አነሳች
ኢንዶኔዥያ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ላይ ጥላ የነበረውን እገዳ አነሳች። የላየን ኤር አየር መንገድ ከሦስት ዓመታት በፊት 189 ሰዎች የሞቱበት የአውሮፕላን መከስከስ ከገጠመው በኋላ የቦይንግ ማክስ 737 አውሮፕላኖች እንዳይበሩ ተከልክሎ ነበር። በተመሳሳይ የኢትዮጵያ አየር መንገድም ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖችን ከአንድ ወር በኋላ ወደ በረራ ለመመለስ በመጨረሻው የዝግጅት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ መግለጹ ይታወሳል። በመጋቢት 2011 ዓ. ም. የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ተከስክሶ 149 መሞታቸውን ተከትሎ ቦይንግ 737 ማክስ ከበረራ ታግዶ ቆይቷል። አሜሪካ እና የአውሮፓ አገራት 737 ማክስ አውሮፕላን ወደ በረራ እንዲመለስ ከፈቀዱ ወራት ተቆጥረዋል። ዘንድሮ አውስትራሊያ፣ ጃፓን፣ ሕንድ፣ ማሌዥያ እና ሲንጋፖር 737 ማክስ ላይ የጣሉትን እገዳ ያነሱ ሲሆን፤ እስካሁን ባጠቃላይ 180 አገራት ለ737 ማክስ ፈቃድ ሰጥተዋል። የኢንዶኔዥያ የትራንስፖርት ሚኒስቴር እንዳለው፤ በ737 ማክስ የደኅንነት መቆጣጠሪያ ላይ ፍተሻ መካሄዱን ተከትሎ አውሮፕላኑ በቅርቡ ወደ በረራ እንዲመለስ ተወስኗል። አየር መንገዶች 737 ማክስ አውሮፕላኖቻቸውን ከማብረራቸው በፊት መከተል ያለባቸውን የፍተሻ መመሪያ ተደንግጓል። መንግሥትም ፍተሻ የሚያካሂድ ይሆናል። ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኑ የተከሰከሰበት ላየን ኤር 10 ማክስ አውሮፕላኖች ያሉት ሲሆን፤ አውሮፕላኖቹ ወደ በረራ እንዲመለሱ ከተወሰነ በኋላ ከቢቢሲ አስተያየት ቢጠየቅም እስካሁን ምላሽ አልተኘም። በኢንዶኔዥያ መንግሥት የሚተዳደረው ጋሩዳ አየር መንግድ በበኩሉ አሁን ላይ ዋነኛ ትኩረቱ ያለበትን ዕዳ ማቃለል እንደሆነና 737 ማክስ አውሮፕላንን ወደ በረራ የመመለስ ዕቅድ እንደሌለው ገልጿል። እገዳው ከመጣሉ በፊት አየር መንገዱ አንድ 737 ማክስ አውሮፕላኑ ብቻ ነበር እየተንቀሳቀሰ የነበረው። አየር መንገዱ ወጭ ለመቀነስ ሲል የሚያበራቸውን አውሮፕላኖች ከ144 ወደ 66 መቀነሱንም አስታውቋል። እአአ በ2018 የላየን ኤር አየር መንገድ የበበራ ቁጥር 610 አውሮፕላን ከጃካርታ ተነስቶ ጉዞ ማድረግ በጀመረ በ13 ደቂቃ ውስጥ ነበር ወድቆ የተከሰከሰው። ከአምስት ወር በኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ለመብረር ከተነሳ ከደቂቃዎች በኋላ ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ መከስከሱ ይታወሳል። በሁለቱ አደጋዎች በአውሮፕላኖቹ ውስጥ የነበሩ ሁሉም 346 ሰዎች ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን ቦይንግ ለሟቾቹ ቤተሰቦች በቢሊዮን ዶላሮች የሚቆጠር ካሳ እንዲከፍል ተጠይቋል። አደጋዎቹን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ላየን ኤር ብቻ ሳይሆኑ በዓለም ዙሪያ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ካለባቸው የደኅንነት መቆጣጠሪያ ችግር ጋር በተያያዘ በረራ እንዲያቆሙ ተደርገው ቆይተዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ተወልደ ገብረማሪያምን ጠቅሶ ባወጣው መግለጫ፤ አየር መንገዱ ከሁሉም በፊት ቅድሚያ የሚሰጠው ለደኅንነት መሆኑን በመግለጽ አውሮፕላኖቹ ወደ አገልግሎት ሊመለሱ መሆኑን ገልጿል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ 737 ማክስ ወደ በረራ ለመመለስ የወሰነው በዓለም ዙሪያ ያሉ የበረራ ደኅንነት ተቆጣጠሪ አካላት ቦይንግ 737 ማክስ ለበረራ ብቁ ነው ብለው አስፈላጊውን ፈቃድ ከመስጠታቸው በተጨማሪ "በዓለም ዙሪያ ያሉ ሌሎች 34 አየር መንገዶች አውሮፕላኑን ወደ በረራ መመለሳቸውን ተከትሎ ነው" ብሏል።
ኢንዶኔዥያ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ላይ ጥላ የነበረውን እገዳ አነሳች ኢንዶኔዥያ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ላይ ጥላ የነበረውን እገዳ አነሳች። የላየን ኤር አየር መንገድ ከሦስት ዓመታት በፊት 189 ሰዎች የሞቱበት የአውሮፕላን መከስከስ ከገጠመው በኋላ የቦይንግ ማክስ 737 አውሮፕላኖች እንዳይበሩ ተከልክሎ ነበር። በተመሳሳይ የኢትዮጵያ አየር መንገድም ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖችን ከአንድ ወር በኋላ ወደ በረራ ለመመለስ በመጨረሻው የዝግጅት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ መግለጹ ይታወሳል። በመጋቢት 2011 ዓ. ም. የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ተከስክሶ 149 መሞታቸውን ተከትሎ ቦይንግ 737 ማክስ ከበረራ ታግዶ ቆይቷል። አሜሪካ እና የአውሮፓ አገራት 737 ማክስ አውሮፕላን ወደ በረራ እንዲመለስ ከፈቀዱ ወራት ተቆጥረዋል። ዘንድሮ አውስትራሊያ፣ ጃፓን፣ ሕንድ፣ ማሌዥያ እና ሲንጋፖር 737 ማክስ ላይ የጣሉትን እገዳ ያነሱ ሲሆን፤ እስካሁን ባጠቃላይ 180 አገራት ለ737 ማክስ ፈቃድ ሰጥተዋል። የኢንዶኔዥያ የትራንስፖርት ሚኒስቴር እንዳለው፤ በ737 ማክስ የደኅንነት መቆጣጠሪያ ላይ ፍተሻ መካሄዱን ተከትሎ አውሮፕላኑ በቅርቡ ወደ በረራ እንዲመለስ ተወስኗል። አየር መንገዶች 737 ማክስ አውሮፕላኖቻቸውን ከማብረራቸው በፊት መከተል ያለባቸውን የፍተሻ መመሪያ ተደንግጓል። መንግሥትም ፍተሻ የሚያካሂድ ይሆናል። ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኑ የተከሰከሰበት ላየን ኤር 10 ማክስ አውሮፕላኖች ያሉት ሲሆን፤ አውሮፕላኖቹ ወደ በረራ እንዲመለሱ ከተወሰነ በኋላ ከቢቢሲ አስተያየት ቢጠየቅም እስካሁን ምላሽ አልተኘም። በኢንዶኔዥያ መንግሥት የሚተዳደረው ጋሩዳ አየር መንግድ በበኩሉ አሁን ላይ ዋነኛ ትኩረቱ ያለበትን ዕዳ ማቃለል እንደሆነና 737 ማክስ አውሮፕላንን ወደ በረራ የመመለስ ዕቅድ እንደሌለው ገልጿል። እገዳው ከመጣሉ በፊት አየር መንገዱ አንድ 737 ማክስ አውሮፕላኑ ብቻ ነበር እየተንቀሳቀሰ የነበረው። አየር መንገዱ ወጭ ለመቀነስ ሲል የሚያበራቸውን አውሮፕላኖች ከ144 ወደ 66 መቀነሱንም አስታውቋል። እአአ በ2018 የላየን ኤር አየር መንገድ የበበራ ቁጥር 610 አውሮፕላን ከጃካርታ ተነስቶ ጉዞ ማድረግ በጀመረ በ13 ደቂቃ ውስጥ ነበር ወድቆ የተከሰከሰው። ከአምስት ወር በኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ለመብረር ከተነሳ ከደቂቃዎች በኋላ ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ መከስከሱ ይታወሳል። በሁለቱ አደጋዎች በአውሮፕላኖቹ ውስጥ የነበሩ ሁሉም 346 ሰዎች ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን ቦይንግ ለሟቾቹ ቤተሰቦች በቢሊዮን ዶላሮች የሚቆጠር ካሳ እንዲከፍል ተጠይቋል። አደጋዎቹን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ላየን ኤር ብቻ ሳይሆኑ በዓለም ዙሪያ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ካለባቸው የደኅንነት መቆጣጠሪያ ችግር ጋር በተያያዘ በረራ እንዲያቆሙ ተደርገው ቆይተዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ተወልደ ገብረማሪያምን ጠቅሶ ባወጣው መግለጫ፤ አየር መንገዱ ከሁሉም በፊት ቅድሚያ የሚሰጠው ለደኅንነት መሆኑን በመግለጽ አውሮፕላኖቹ ወደ አገልግሎት ሊመለሱ መሆኑን ገልጿል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ 737 ማክስ ወደ በረራ ለመመለስ የወሰነው በዓለም ዙሪያ ያሉ የበረራ ደኅንነት ተቆጣጠሪ አካላት ቦይንግ 737 ማክስ ለበረራ ብቁ ነው ብለው አስፈላጊውን ፈቃድ ከመስጠታቸው በተጨማሪ "በዓለም ዙሪያ ያሉ ሌሎች 34 አየር መንገዶች አውሮፕላኑን ወደ በረራ መመለሳቸውን ተከትሎ ነው" ብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59815429
5sports
በካሜሩን እየተካሄደ ያለው የ2021 የአፍሪካ ዋንጫ የግጥሚያ ፕሮግራምና ውጤቶች
በኮሮናቫይረስ ምክንያት ለአንድ ዓመት የተራዘመው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከእሑድ ጥር 01/2014 ዓ.ም ጀምሮ ካሜሩን ውስጥ እየተካሄደ ነው። እተካሄደ ያለውን የአፍሪካ ዋንጫ የግጥሚያ ፕሮግራሞችንና ውጤቶችን ቀጥሎ ከተቀመጠው ዝርዝር ላይ ይመልከቱ። የውድድሩ አዘጋጅ ካሜሩን በአፍሪካ ዋንጫ በመሳተፍ ከምድቡ ሃገራት የሚያክላት የለም። ቡርኪና ፋሶ ለ12ኛ ጊዜ፤ ኢትዮጵያ ደግሞ በአንድ ዝቅ ብላ ለ11ኛ ጊዜ ትሳተፋለች። ለውድድሩ እንግዳ ያልሆነችው ኬፕ ቨርዴ የዘንድሮ ተሳትፎዋ ለሶስተኛ ጊዜ ነው። ከኢትዮጵያ በቀር ሁሉም የምድቡ ሃገራት በአውሮፓ ሊጎች የሚጫወቱ ተጫዋቾቻቸውን ይዘው ነው ወደ ካሜሩን ያቀኑት። ነገር ግን ከሽመልስ በቀለና ሙጂብ ቃሲም በቀር ሁሉንም ተጫዋቾቿን ከሃገር ውስጥ ክለቦች የመረጠችው ኢትዮጵያ የውድድሩ ክስተት ልትሆን እንደምትችል ብዙዎች ይገምታሉ።
በካሜሩን እየተካሄደ ያለው የ2021 የአፍሪካ ዋንጫ የግጥሚያ ፕሮግራምና ውጤቶች በኮሮናቫይረስ ምክንያት ለአንድ ዓመት የተራዘመው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከእሑድ ጥር 01/2014 ዓ.ም ጀምሮ ካሜሩን ውስጥ እየተካሄደ ነው። እተካሄደ ያለውን የአፍሪካ ዋንጫ የግጥሚያ ፕሮግራሞችንና ውጤቶችን ቀጥሎ ከተቀመጠው ዝርዝር ላይ ይመልከቱ። የውድድሩ አዘጋጅ ካሜሩን በአፍሪካ ዋንጫ በመሳተፍ ከምድቡ ሃገራት የሚያክላት የለም። ቡርኪና ፋሶ ለ12ኛ ጊዜ፤ ኢትዮጵያ ደግሞ በአንድ ዝቅ ብላ ለ11ኛ ጊዜ ትሳተፋለች። ለውድድሩ እንግዳ ያልሆነችው ኬፕ ቨርዴ የዘንድሮ ተሳትፎዋ ለሶስተኛ ጊዜ ነው። ከኢትዮጵያ በቀር ሁሉም የምድቡ ሃገራት በአውሮፓ ሊጎች የሚጫወቱ ተጫዋቾቻቸውን ይዘው ነው ወደ ካሜሩን ያቀኑት። ነገር ግን ከሽመልስ በቀለና ሙጂብ ቃሲም በቀር ሁሉንም ተጫዋቾቿን ከሃገር ውስጥ ክለቦች የመረጠችው ኢትዮጵያ የውድድሩ ክስተት ልትሆን እንደምትችል ብዙዎች ይገምታሉ።
https://www.bbc.com/amharic/news-59928971
0business
የአውሮፓ አቪየሽን ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ዳግም መብረር እንዲችል ፈቀደ
የአውሮፓ የአቪየሽን ደኅንነት ኤጀንሲ (EASA ) የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ከዚህ በኋላ ወደ ሰማይ ለመመለስ ዝግጁ ናቸው ሲል አረጋገጠ። የኤጀንሰው ኃላፊ ለቢቢሲ እንደተናገሩት አውሮፕላኖቹ ከዚህ በኋላ ለመብረር አንዳችም ስጋት እንደሌለባቸው እርግጠኛ ሆነን መናገር እንችላለን ብለዋል። የኤጀንሲው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፓትሪክ፣ ድርጅታቸው ከአውሮፕላኖቹ አምራች ጋር በመሆን ጥብቅ ፍተሻና ምርመራ እንዳደረገና ለበረራ ዝግጁ እንደሆኑም እንዳረጋገጠ ለቢቢሲ አብራርተዋል። አውሮፕላኖቹ ከበረራ የተገለሉት በአወሮፓውያኑ 2019 እንደነበር ይታወሳል። አውሮፕላኖቹ ከበረራ የታገዱት በኢትዯጵያና በኢንዶኔዢያ ሰማይ ላይ ተከስክሰው 346 መንገደኞች ማለቃቸውን ተከትሎ ነበር። አሁን የቦይንግ ማክስ አውሮፕላኖች በአሜሪካ እና በብራዚል፣ ከጥር አጋማሽ ጀምሮ ደግሞ በመላው አውሮፓ በረራ እንደሚጀምሩ ይጠበቃል። የማክስ አውሮፕላኖች የመጀመርያው አደጋ የተመዘገበው በላየን አየር መንገድ ሲሆን ይህም በጥቅምት 2018 በኢንዶኒዢያ ሰማይ ላይ ነበር። ሁለተኛው አደጋ ደግሞ ወደ ናይሮቢ በማቅናት ላይ በነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ እንደነበር ይታወሳል። የሁለቱም አደጋዎች ምንጭ ከአውሮፕላኑ የአደጋ ጊዜ ሶፍት ዌር እንከን ጋር የተያያዘ እንደነበር አይዘነጋም። ሶፍትዌሩ ራሱን በራሱ የሚያዝና፣ በተሳሳተ ጊዜ ራሱን የሚያነቃ ሆኖ የተሰራ ሲሆን፣ አውሮፕላኑን ከአብራሪው ቁጥጥር ውጭ እንዲሆን የሚያደርግ ሆኖ በመነደፉ እክል እንደነበረበረበት በኋላ ላይ ተረጋግጧል። የአውሮፓ አቪየሽን ቁጥጥር ባለሥልጣን ኃላፊ ለቢቢሲ እንደተናገሩት እነዚህ እክል የነበረባቸው አውሮፕላኖች ወደ ሰማይ እንዲመለሱ ለመወሰን የነበረባቸው እክል ብቻ መመርመር በቂ አልነበረም። ስለዚህ መላ ስሪታቸውን እንደ አዲስ ፈትሸን ነው እንዲመለሱ የወሰነው ብለዋል። ለማክስ አውሮፕላን የተገጠመለት አዲስ ሶፍትዌርን በተመለከተ አብራሪዎች አዲስ ስልጠና እንዲወስዱ ይገደዳሉ ተብሏል።
የአውሮፓ አቪየሽን ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ዳግም መብረር እንዲችል ፈቀደ የአውሮፓ የአቪየሽን ደኅንነት ኤጀንሲ (EASA ) የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ከዚህ በኋላ ወደ ሰማይ ለመመለስ ዝግጁ ናቸው ሲል አረጋገጠ። የኤጀንሰው ኃላፊ ለቢቢሲ እንደተናገሩት አውሮፕላኖቹ ከዚህ በኋላ ለመብረር አንዳችም ስጋት እንደሌለባቸው እርግጠኛ ሆነን መናገር እንችላለን ብለዋል። የኤጀንሲው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፓትሪክ፣ ድርጅታቸው ከአውሮፕላኖቹ አምራች ጋር በመሆን ጥብቅ ፍተሻና ምርመራ እንዳደረገና ለበረራ ዝግጁ እንደሆኑም እንዳረጋገጠ ለቢቢሲ አብራርተዋል። አውሮፕላኖቹ ከበረራ የተገለሉት በአወሮፓውያኑ 2019 እንደነበር ይታወሳል። አውሮፕላኖቹ ከበረራ የታገዱት በኢትዯጵያና በኢንዶኔዢያ ሰማይ ላይ ተከስክሰው 346 መንገደኞች ማለቃቸውን ተከትሎ ነበር። አሁን የቦይንግ ማክስ አውሮፕላኖች በአሜሪካ እና በብራዚል፣ ከጥር አጋማሽ ጀምሮ ደግሞ በመላው አውሮፓ በረራ እንደሚጀምሩ ይጠበቃል። የማክስ አውሮፕላኖች የመጀመርያው አደጋ የተመዘገበው በላየን አየር መንገድ ሲሆን ይህም በጥቅምት 2018 በኢንዶኒዢያ ሰማይ ላይ ነበር። ሁለተኛው አደጋ ደግሞ ወደ ናይሮቢ በማቅናት ላይ በነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ እንደነበር ይታወሳል። የሁለቱም አደጋዎች ምንጭ ከአውሮፕላኑ የአደጋ ጊዜ ሶፍት ዌር እንከን ጋር የተያያዘ እንደነበር አይዘነጋም። ሶፍትዌሩ ራሱን በራሱ የሚያዝና፣ በተሳሳተ ጊዜ ራሱን የሚያነቃ ሆኖ የተሰራ ሲሆን፣ አውሮፕላኑን ከአብራሪው ቁጥጥር ውጭ እንዲሆን የሚያደርግ ሆኖ በመነደፉ እክል እንደነበረበረበት በኋላ ላይ ተረጋግጧል። የአውሮፓ አቪየሽን ቁጥጥር ባለሥልጣን ኃላፊ ለቢቢሲ እንደተናገሩት እነዚህ እክል የነበረባቸው አውሮፕላኖች ወደ ሰማይ እንዲመለሱ ለመወሰን የነበረባቸው እክል ብቻ መመርመር በቂ አልነበረም። ስለዚህ መላ ስሪታቸውን እንደ አዲስ ፈትሸን ነው እንዲመለሱ የወሰነው ብለዋል። ለማክስ አውሮፕላን የተገጠመለት አዲስ ሶፍትዌርን በተመለከተ አብራሪዎች አዲስ ስልጠና እንዲወስዱ ይገደዳሉ ተብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/55391882
2health
'መድኃኒት' አግኝቻለሁ ስትል የነበረችው ማደጋስካር ክትባት ለማግኘት ጠየቀች
ፕሬዝዳንቷ ከተለያዩ እጽዋት በተዘጋጀ ውህድ የኮሮናቫይረስን ማከም ይቻላል ሲሉ የነበረችው ማደጋስካር፣ የበሽታውን መከለከያ ክትባት ለማግኘት ከሚያስችላት ዓለም አቀፍ ጥምረት ውስጥ ገባች። የኮሮናቫይረስ ከተከሰተ ከጥቂት ወራት በኋላ በሽታውን ለማከም ያስችላል ያለችውን ባሕላዊ መድኃኒት ያስተዋወቀችው ማደጋስካር ክትባት እንደማያስፈልጋት ገልጻ ነበር። ኮቫክስ የተባለውና ለበርካታ አገራት የኮሮናቫይረስ ክትባትን ለማቅረብ ከሚሰራው ጥምረት የአገራት ዝርዝር ውስጥ ባለመግባቷ ክትባቱን ሳታገኝ ቆይታለች። ማዳጋስካር ኮቪድ-ኦርጋኒክስ የተባለውን ባሕላዊ መድኃኒት በፕሬዝዳንቷ አማካይነት ስታስተዋውቅ የቆየች ሲሆን መድኃኒቱ ወደ ሌሎች አገራትም እንደተላከ ተዘግቦ ነበር። ነገር ግን የመድኃኒቱ ምንነትና ያስገኘውን ውጤት በሚመለከት በጤና ባለሙያዎች የተባለ ነገር የለም። ማዳጋስካር የተለያዩ የአፍሪካ አገራት ተቀብለው ሕዝባቸውን እየከተቡት ያለውን የወረርሽኙን መከላከያ ክትባት በኮቫክስ በኩል ለማግኘት ጥያቄ አቅርባለች። የአገሪቱ የጤና ሚኒስትር ፕሮፌሰር ጃን ልዊስ ራኮቶቮ እንዳሉት ክትባቱን ለማግኘት የተለያዩ ደረጃዎችን ማለፍ አለበት ለዚህ ደግሞ ምዝገባን መፈጸም ዋነኛው እርምጃ ነው ሲሉ የክትባት አቅርቦት ጥምረት ከሆነው ኮቫክስ ውስጥ ለመግባት ማዳጋስካር እያደረገች ያለውን ገልጸዋል። የማደጋስካሩ ፕሬዝደንት አንድሬ ራጆሊን ኮቪድ-19ን ይፈውሳል በማለት ሲያስተዋውቁት የነበረው 'መድኃኒት' በስፋት መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። እስካሁን ባለው የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ መሠረት ኮሮናቫይረስን የሚፈውስ ምንም አይነት መድኃኒት የለም። በማዳጋስካር እስካሁን ከ24 ሺህ 400 በላይ ሰዎች በወረርሽኙ መያዛቸው የታወቀ ሲሆን 418 ሰዎች ደግሞ በበሽታው ሰበብ ለሞት ተዳርገዋል።
'መድኃኒት' አግኝቻለሁ ስትል የነበረችው ማደጋስካር ክትባት ለማግኘት ጠየቀች ፕሬዝዳንቷ ከተለያዩ እጽዋት በተዘጋጀ ውህድ የኮሮናቫይረስን ማከም ይቻላል ሲሉ የነበረችው ማደጋስካር፣ የበሽታውን መከለከያ ክትባት ለማግኘት ከሚያስችላት ዓለም አቀፍ ጥምረት ውስጥ ገባች። የኮሮናቫይረስ ከተከሰተ ከጥቂት ወራት በኋላ በሽታውን ለማከም ያስችላል ያለችውን ባሕላዊ መድኃኒት ያስተዋወቀችው ማደጋስካር ክትባት እንደማያስፈልጋት ገልጻ ነበር። ኮቫክስ የተባለውና ለበርካታ አገራት የኮሮናቫይረስ ክትባትን ለማቅረብ ከሚሰራው ጥምረት የአገራት ዝርዝር ውስጥ ባለመግባቷ ክትባቱን ሳታገኝ ቆይታለች። ማዳጋስካር ኮቪድ-ኦርጋኒክስ የተባለውን ባሕላዊ መድኃኒት በፕሬዝዳንቷ አማካይነት ስታስተዋውቅ የቆየች ሲሆን መድኃኒቱ ወደ ሌሎች አገራትም እንደተላከ ተዘግቦ ነበር። ነገር ግን የመድኃኒቱ ምንነትና ያስገኘውን ውጤት በሚመለከት በጤና ባለሙያዎች የተባለ ነገር የለም። ማዳጋስካር የተለያዩ የአፍሪካ አገራት ተቀብለው ሕዝባቸውን እየከተቡት ያለውን የወረርሽኙን መከላከያ ክትባት በኮቫክስ በኩል ለማግኘት ጥያቄ አቅርባለች። የአገሪቱ የጤና ሚኒስትር ፕሮፌሰር ጃን ልዊስ ራኮቶቮ እንዳሉት ክትባቱን ለማግኘት የተለያዩ ደረጃዎችን ማለፍ አለበት ለዚህ ደግሞ ምዝገባን መፈጸም ዋነኛው እርምጃ ነው ሲሉ የክትባት አቅርቦት ጥምረት ከሆነው ኮቫክስ ውስጥ ለመግባት ማዳጋስካር እያደረገች ያለውን ገልጸዋል። የማደጋስካሩ ፕሬዝደንት አንድሬ ራጆሊን ኮቪድ-19ን ይፈውሳል በማለት ሲያስተዋውቁት የነበረው 'መድኃኒት' በስፋት መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። እስካሁን ባለው የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ መሠረት ኮሮናቫይረስን የሚፈውስ ምንም አይነት መድኃኒት የለም። በማዳጋስካር እስካሁን ከ24 ሺህ 400 በላይ ሰዎች በወረርሽኙ መያዛቸው የታወቀ ሲሆን 418 ሰዎች ደግሞ በበሽታው ሰበብ ለሞት ተዳርገዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-56599700
3politics
የትራምፕ ቤት እንዲበረበር ያዘዙት ዳኛ ዝርዝር መረጃዎች ይፋ እንዲሆኑ አዘዙ
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መኖሪያ ቤት እንዲፈተሽ ትዕዛዝ የሰጡት ዳኛ ብርበራውን እንዲያጸድቁ ያደረጓቸው ሰነዶች ይፋ እንዲሆኑ አዘዙ። በዐቃብያነ-ሕግ የተሰበሰቡትን ማስረጃዎች ብሎም ለችሎቹ ያቀረቡት ቃለ መሃላ ሰነድ ቅጂ ይፋ የሚሆን ከሆነ ስለምርመራው ተጨማሪ መረጃዎችን ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። የአገሪቱ የፍትህ ሚኒስቴርም መረጃው ይፋ የሚወጣ ከሆነ በሂደት ላይ ያለውን ምርመራ ይጎዳል ሲል ወቅሷል። የብርበራ ማዘዣው እንደሚገልጸው ትራምፕ የፕሬዝዳንትነት ግዜያቸው ካበቃ በኋላ ከኋይት ሀውስ ወደ ቤታቸው የመንግሥትን መዛግብት አላግባብ ወስደዋል በሚል ወንጀል በመጠርጠራቸው ነው ኤፍቢአይ ምርመራውን የጀመረው። የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ከሥልጣናቸው ሲለቁ ሰነዶችን እና ኢሜሎችን ወደ ብሔራዊ ቤተ መዛግብት የማስተላለፍ ግዴታ አለባቸው። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ትራምፕ የቀረበባቸውን ውንጀላ ውድቅ ያደረጉ ሲሆን መርማሪዎች በፍሎሪዳ በሚገኘው ቤታቸው ውስጥ አግኝተነዋል ያሏቸውን ሚስጥራዊ ሰነዶች እርሳቸው ቀድመው ያሳወቁ መሆናቸውን አስረድተዋል። ጉዳዩ ላይ የተሰየሙት ዳኛ ብሩስ ራይንሃርት ትላንት በሰጡት ትዕዛዝ ዛሬ ዓርብ ከምሽትቱ አንድ ሰዓት ላይ ዝርዝር መረጃዎችን የያዘው የቃለመሃላ ሰነዱ እንዲለቅ አዘዋል። ዳኛው ዐቃቤ ሕግ የምስክሮችን፣ የሕግ አስከባሪ አካላትን፣ ያልተከሰሱ አካላትን ማንነትእ ንዲሁም የምርመራውን ስልት፣ አቅጣጫ፣ ወሰን፣ ምንጭ እና ዘዴ የሚገልጹ የሰነዱን ክፍሎች ይፋ እንዳይሆኑ አሳማኝ ምክንያት በማቅረቡ እነዚህ ዝርዝሮች ይፋ በሚሆነው ሰነድ ውስጥ እንደማይካተቱ ተናግረዋል። የፍትህ ሚኒስቴር በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መሠረት የቅጣት ውሳኔዎችን የያዘ የቃለ መሃላ ቅጂ ለችሎቱ ማስገባቱን አስታውቋል። የተሻሻለው ሰነድ ትራምፕ ምስጢራዊ ሰነዶችን በፕሬዝዳንትነታቸው የመጨረሻ ቀናት ለምን እንደወሰዱ እና በፓልም ቢች ውስጥ ተከማችተው በነበሩበት ጊዜ ምን እንደፈጸሙ ፍንጭ ሊሰጥ ይችላል ተበሎ ይጠበቃል። የተለያዩ የዜና አውታሮች ጉዳዩ ላይ የሕዝብ ጥቅም ስላለው ብሎም የፍተሻውን ታሪካዊነት ከግምት ውስጥ በመክተት ሰነዱን ለሕዝብ ለማውጣት ችሎቱን ጠይቀዋል። የፍትህ መሥሪያ ቤቱ በበኩሉ ይህ የሚሆን ከሆነ በሂደት ላይ ያለውን ምርመራ ሊጠገን የማይችል ጉዳት ሊያደርስበት ይችላል ሲል እርምጃውን ተቃውሟል። ከውስጡ የሚወጡት መረጃዎች ሲቀነሱም ሰነዱን “ትርጉም የለሽ” ያደርጉታል ብሏል። ትራምፕ እና ጠበቃቸው ፍተሻው ፖለቲካዊ ይዘት ያለው እና ሕገ ወጥ ነው ያሉ ሲሆን ምንም መረጃ ያልተቀነሰበት ሰነድ እንዲለቀቅ ጠይቀዋል። የትራምፕ ቃል አቀባይ ቴይለር ቡዶዊች ይዘቱን "ለመደበቅ" የሚደረገው ጥረት "አስቂኝ" እና "የመንግሥት ሙስናን ለመደበቅ ያለመ ሊሆን ይችላል" ብለዋል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የዶናልድ ትራምፕ የጠበቆች ቡድን ምርመራው እንዲታገድ ብሎም ገለልተኛ የሦስተኛ ወገን ጠበቃ እንዲመጣላቸው እና ኤፍቢአይ በፍተሻው ወቅት የወሰዳቸውን ሰነዶች እንዲከታተል ጠይቋል።
የትራምፕ ቤት እንዲበረበር ያዘዙት ዳኛ ዝርዝር መረጃዎች ይፋ እንዲሆኑ አዘዙ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መኖሪያ ቤት እንዲፈተሽ ትዕዛዝ የሰጡት ዳኛ ብርበራውን እንዲያጸድቁ ያደረጓቸው ሰነዶች ይፋ እንዲሆኑ አዘዙ። በዐቃብያነ-ሕግ የተሰበሰቡትን ማስረጃዎች ብሎም ለችሎቹ ያቀረቡት ቃለ መሃላ ሰነድ ቅጂ ይፋ የሚሆን ከሆነ ስለምርመራው ተጨማሪ መረጃዎችን ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። የአገሪቱ የፍትህ ሚኒስቴርም መረጃው ይፋ የሚወጣ ከሆነ በሂደት ላይ ያለውን ምርመራ ይጎዳል ሲል ወቅሷል። የብርበራ ማዘዣው እንደሚገልጸው ትራምፕ የፕሬዝዳንትነት ግዜያቸው ካበቃ በኋላ ከኋይት ሀውስ ወደ ቤታቸው የመንግሥትን መዛግብት አላግባብ ወስደዋል በሚል ወንጀል በመጠርጠራቸው ነው ኤፍቢአይ ምርመራውን የጀመረው። የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ከሥልጣናቸው ሲለቁ ሰነዶችን እና ኢሜሎችን ወደ ብሔራዊ ቤተ መዛግብት የማስተላለፍ ግዴታ አለባቸው። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ትራምፕ የቀረበባቸውን ውንጀላ ውድቅ ያደረጉ ሲሆን መርማሪዎች በፍሎሪዳ በሚገኘው ቤታቸው ውስጥ አግኝተነዋል ያሏቸውን ሚስጥራዊ ሰነዶች እርሳቸው ቀድመው ያሳወቁ መሆናቸውን አስረድተዋል። ጉዳዩ ላይ የተሰየሙት ዳኛ ብሩስ ራይንሃርት ትላንት በሰጡት ትዕዛዝ ዛሬ ዓርብ ከምሽትቱ አንድ ሰዓት ላይ ዝርዝር መረጃዎችን የያዘው የቃለመሃላ ሰነዱ እንዲለቅ አዘዋል። ዳኛው ዐቃቤ ሕግ የምስክሮችን፣ የሕግ አስከባሪ አካላትን፣ ያልተከሰሱ አካላትን ማንነትእ ንዲሁም የምርመራውን ስልት፣ አቅጣጫ፣ ወሰን፣ ምንጭ እና ዘዴ የሚገልጹ የሰነዱን ክፍሎች ይፋ እንዳይሆኑ አሳማኝ ምክንያት በማቅረቡ እነዚህ ዝርዝሮች ይፋ በሚሆነው ሰነድ ውስጥ እንደማይካተቱ ተናግረዋል። የፍትህ ሚኒስቴር በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መሠረት የቅጣት ውሳኔዎችን የያዘ የቃለ መሃላ ቅጂ ለችሎቱ ማስገባቱን አስታውቋል። የተሻሻለው ሰነድ ትራምፕ ምስጢራዊ ሰነዶችን በፕሬዝዳንትነታቸው የመጨረሻ ቀናት ለምን እንደወሰዱ እና በፓልም ቢች ውስጥ ተከማችተው በነበሩበት ጊዜ ምን እንደፈጸሙ ፍንጭ ሊሰጥ ይችላል ተበሎ ይጠበቃል። የተለያዩ የዜና አውታሮች ጉዳዩ ላይ የሕዝብ ጥቅም ስላለው ብሎም የፍተሻውን ታሪካዊነት ከግምት ውስጥ በመክተት ሰነዱን ለሕዝብ ለማውጣት ችሎቱን ጠይቀዋል። የፍትህ መሥሪያ ቤቱ በበኩሉ ይህ የሚሆን ከሆነ በሂደት ላይ ያለውን ምርመራ ሊጠገን የማይችል ጉዳት ሊያደርስበት ይችላል ሲል እርምጃውን ተቃውሟል። ከውስጡ የሚወጡት መረጃዎች ሲቀነሱም ሰነዱን “ትርጉም የለሽ” ያደርጉታል ብሏል። ትራምፕ እና ጠበቃቸው ፍተሻው ፖለቲካዊ ይዘት ያለው እና ሕገ ወጥ ነው ያሉ ሲሆን ምንም መረጃ ያልተቀነሰበት ሰነድ እንዲለቀቅ ጠይቀዋል። የትራምፕ ቃል አቀባይ ቴይለር ቡዶዊች ይዘቱን "ለመደበቅ" የሚደረገው ጥረት "አስቂኝ" እና "የመንግሥት ሙስናን ለመደበቅ ያለመ ሊሆን ይችላል" ብለዋል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የዶናልድ ትራምፕ የጠበቆች ቡድን ምርመራው እንዲታገድ ብሎም ገለልተኛ የሦስተኛ ወገን ጠበቃ እንዲመጣላቸው እና ኤፍቢአይ በፍተሻው ወቅት የወሰዳቸውን ሰነዶች እንዲከታተል ጠይቋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c72r7klmz8xo
3politics
ኢትዯጵያ፡ አገራዊ ምርጫው በዚህ ዓመት መካሄድ እንደሚችል ተገለጸ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ በጠራው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ስድስተኛው ዙር አገራዊ መርጫ ሊካሄድ እንደሚችል የጤና ጥበቃ ሚኒስትሯ ባቀረቡት ሪፖርት ላይ አስታወቁ። በኮሮናቫይረስ ስጋት ምክንያት አስከ አንድ ዓመት ለሚደርስ ጊዜ እንዲሸጋገር የተወሰነው ምርጫ እንዲካሄድ የወረርሽኙ ሁኔታን በተመለከተ ከጤና ባለስልጣናት የሚሰጡ ምክሮችን መሰረት እንደሚያደርግ ተገልጾ ነበር። በዚህም መሰረት የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ በአገሪቱ ያለውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሁኔታን በተመለከተ የመስሪያ ቤታቸውን ግምገማ ለሕዝብ ተወካዮች ምከክር ቤት ባቀረቡበት ጊዜ ነው አገራዊ ምርጫን ለማካሄድ እንደሚቻል አመልክተዋል። ካለው የወረርሽኝ ስጋት አንጻር የኮሮናቫይረስ መስፋፋትን ለመከላከል የሚያስችሉ እርምጃዎችን ከግምት ውስጥ የሚያስገባ የምርጫ ሥነምግባር፣ ደንብና ማስፈፀሚያ መመሪያዎችን በማዘጋጀት ስድስተኛውን አጠቃላይ ምርጫ ማካሄድ እንደሚቻል ሚኒስትሯ ገልጸዋል። አክለውም ምርጫውን ለማካሄድ በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ ከፍተኛ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት ካጋጠመ "ይህ በተለየ ሁኔታ መታየት ሊያስፈልገው እንደሚችል ታሳቢ በማድረግ መዘጋጀት ያስፈልጋል" ሲሉ ሚኒስትሯ በሪፖርታቸው ላይ ጠቅሰዋል። ሚኒስትሯ እንዳሉት በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ወረርሽኙ በሁሉም ክልሎች የተሰራጨ ሲሆን፤ በዚህም የኮሮናቫይረስ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል 95 በመቶ የሚሆኑት የታወቀ የጉዞ ታሪክ የሌላቸው መሆኑን ጠቅሰዋል። እስካሁንም በተደረገው ምርመራ ከ66 ሺህ 200 ሰዎች በላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን 1 ሺህ 45 ሰዎች በወረርሽኙ ምክንያት መሞታቸውን ገልጸዋል። ነገር ግን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭት እየቀነሰ ባይሆንም የቅድመ መከላከልና ስርጭቱን በመግታት ሂደት ውስጥ በሁሉም ደረጃ አቅም ማሳደግ መቻሉን አመልክተዋል። በዚህም የአገሪቱ የመመርመርም ሆነ የክትትል አቅም በማደጉ በከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ጋር መድረስ እንደተቻለ ተናግረዋል። ከዚህም ባሻገር ከበሽታው መከላከልና ሕክምና አንጻር የተሰሩ ሥራዎችንና የተገኙ ውጤቶችን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለምክር ቤቱ ዝርዝር የሆነ ሪፖርት አቅርበዋል። በአገሪቱ ካለው የወረርሽኝ መስፋፋት ሁኔታ አኳያ አገራዊ ምርጫን ከማካሄድ አንጻር የበርካታ አገራት ተሞክሮዎች ላይ ምልከታ የተደረገባቸው ሲሆን፣ በአንዳንዶቹ በወረርሽኝ ወቅት ምርጫ ተካሂዷል፤ በአብዛኞቹ ደግሞ እንዲተላለፍ ተደርጓል። በኢትዮጵያም በሽታውን የመከላከልም ሆነ የመቆጣጠር ዝግጅነቱ ዝቅተኛ በነበረበት ወቅት ምርጫን ማከናወን ስጋቱ የበለጠ የሚያሳድገው በመሆኑ በተላለፈው ውሳኔ እንዲራዘም መደረጉ ይታወሳል። ስለዚህም ወረርሽኙ የጤና ስጋት መሆኑ እንዳለ ቢሆንም ቀደም ሲል ከነበረው ልምድ እንፃር ከፍተኛ አለመሆኑ፣ በሽታው ከዚህም በኋላ ረዘም ላለ ጊዜ ስጋት ሆኖ ሊቆይ ሰለሚችል፤ ምርጫው ሲራዘም ከነበርንበት ሁኔታ አንጻር ስለስርጭቱ የተሻለ መረጃ መኖሩ ተገልጿል። እንዲሁም አስፈላጊውን የበሽታው ምርመራ፣ ክትትል፣ ሕክምናና ጥንቃቄን በተመለከተ የተሻለ አቅምና ግንዛቤ በመኖሩ፤ በተጨማሪም የተለያዩ አገራትን የምርጫ ተሞክሮን በማየት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት ምርጫውን ለማካሄድ የሚያስችል ሁኔታ እንዳለ ተገልጿል። ይህንንም ተከትሎ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀጣዩን አገራዊ ምርጫን በተመለከተ በቀረበውን የጤና ሚኒስቴር ሪፖር ላይ በመወያየት ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ላይ ይካሄዳል ተብሎ የነበረው ምርጫ በኮሮናቫይረስ ስጋት ሳቢያ እንዲራዘምና በክልሎችና በፌደራል ደረጃ ያሉት ምክር ቤቶች ቀጣዩ ምርጫ እስኪካሄድ ድረስ በሥራቸው ላይ እንዲቀጥሉ መወሰኑ ይታወሳል።
ኢትዯጵያ፡ አገራዊ ምርጫው በዚህ ዓመት መካሄድ እንደሚችል ተገለጸ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ በጠራው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ስድስተኛው ዙር አገራዊ መርጫ ሊካሄድ እንደሚችል የጤና ጥበቃ ሚኒስትሯ ባቀረቡት ሪፖርት ላይ አስታወቁ። በኮሮናቫይረስ ስጋት ምክንያት አስከ አንድ ዓመት ለሚደርስ ጊዜ እንዲሸጋገር የተወሰነው ምርጫ እንዲካሄድ የወረርሽኙ ሁኔታን በተመለከተ ከጤና ባለስልጣናት የሚሰጡ ምክሮችን መሰረት እንደሚያደርግ ተገልጾ ነበር። በዚህም መሰረት የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ በአገሪቱ ያለውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሁኔታን በተመለከተ የመስሪያ ቤታቸውን ግምገማ ለሕዝብ ተወካዮች ምከክር ቤት ባቀረቡበት ጊዜ ነው አገራዊ ምርጫን ለማካሄድ እንደሚቻል አመልክተዋል። ካለው የወረርሽኝ ስጋት አንጻር የኮሮናቫይረስ መስፋፋትን ለመከላከል የሚያስችሉ እርምጃዎችን ከግምት ውስጥ የሚያስገባ የምርጫ ሥነምግባር፣ ደንብና ማስፈፀሚያ መመሪያዎችን በማዘጋጀት ስድስተኛውን አጠቃላይ ምርጫ ማካሄድ እንደሚቻል ሚኒስትሯ ገልጸዋል። አክለውም ምርጫውን ለማካሄድ በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ ከፍተኛ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት ካጋጠመ "ይህ በተለየ ሁኔታ መታየት ሊያስፈልገው እንደሚችል ታሳቢ በማድረግ መዘጋጀት ያስፈልጋል" ሲሉ ሚኒስትሯ በሪፖርታቸው ላይ ጠቅሰዋል። ሚኒስትሯ እንዳሉት በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ወረርሽኙ በሁሉም ክልሎች የተሰራጨ ሲሆን፤ በዚህም የኮሮናቫይረስ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል 95 በመቶ የሚሆኑት የታወቀ የጉዞ ታሪክ የሌላቸው መሆኑን ጠቅሰዋል። እስካሁንም በተደረገው ምርመራ ከ66 ሺህ 200 ሰዎች በላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን 1 ሺህ 45 ሰዎች በወረርሽኙ ምክንያት መሞታቸውን ገልጸዋል። ነገር ግን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭት እየቀነሰ ባይሆንም የቅድመ መከላከልና ስርጭቱን በመግታት ሂደት ውስጥ በሁሉም ደረጃ አቅም ማሳደግ መቻሉን አመልክተዋል። በዚህም የአገሪቱ የመመርመርም ሆነ የክትትል አቅም በማደጉ በከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ጋር መድረስ እንደተቻለ ተናግረዋል። ከዚህም ባሻገር ከበሽታው መከላከልና ሕክምና አንጻር የተሰሩ ሥራዎችንና የተገኙ ውጤቶችን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለምክር ቤቱ ዝርዝር የሆነ ሪፖርት አቅርበዋል። በአገሪቱ ካለው የወረርሽኝ መስፋፋት ሁኔታ አኳያ አገራዊ ምርጫን ከማካሄድ አንጻር የበርካታ አገራት ተሞክሮዎች ላይ ምልከታ የተደረገባቸው ሲሆን፣ በአንዳንዶቹ በወረርሽኝ ወቅት ምርጫ ተካሂዷል፤ በአብዛኞቹ ደግሞ እንዲተላለፍ ተደርጓል። በኢትዮጵያም በሽታውን የመከላከልም ሆነ የመቆጣጠር ዝግጅነቱ ዝቅተኛ በነበረበት ወቅት ምርጫን ማከናወን ስጋቱ የበለጠ የሚያሳድገው በመሆኑ በተላለፈው ውሳኔ እንዲራዘም መደረጉ ይታወሳል። ስለዚህም ወረርሽኙ የጤና ስጋት መሆኑ እንዳለ ቢሆንም ቀደም ሲል ከነበረው ልምድ እንፃር ከፍተኛ አለመሆኑ፣ በሽታው ከዚህም በኋላ ረዘም ላለ ጊዜ ስጋት ሆኖ ሊቆይ ሰለሚችል፤ ምርጫው ሲራዘም ከነበርንበት ሁኔታ አንጻር ስለስርጭቱ የተሻለ መረጃ መኖሩ ተገልጿል። እንዲሁም አስፈላጊውን የበሽታው ምርመራ፣ ክትትል፣ ሕክምናና ጥንቃቄን በተመለከተ የተሻለ አቅምና ግንዛቤ በመኖሩ፤ በተጨማሪም የተለያዩ አገራትን የምርጫ ተሞክሮን በማየት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት ምርጫውን ለማካሄድ የሚያስችል ሁኔታ እንዳለ ተገልጿል። ይህንንም ተከትሎ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀጣዩን አገራዊ ምርጫን በተመለከተ በቀረበውን የጤና ሚኒስቴር ሪፖር ላይ በመወያየት ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ላይ ይካሄዳል ተብሎ የነበረው ምርጫ በኮሮናቫይረስ ስጋት ሳቢያ እንዲራዘምና በክልሎችና በፌደራል ደረጃ ያሉት ምክር ቤቶች ቀጣዩ ምርጫ እስኪካሄድ ድረስ በሥራቸው ላይ እንዲቀጥሉ መወሰኑ ይታወሳል።
https://www.bbc.com/amharic/news-54198845
2health
“ከስኳር ሕመምተኞች አንድ አራተኛው ስለበሽታው ምንም መረጃ አያገኙም” ጥናት
ከስኳር ታማሚዎች አንድ አራተኛው ምንም ዓይነት እርዳታ እንደማያገኙ አንድ ጥናት አረጋገጠ። የዓለም የስኳር ሕመም ፌዴሬሽን እንዳለው ከታማሚዎች 26 ከመቶ የሚሆኑት ስለበሽታው ምንም ዓይነት መረጃ አያገኙም። በዚህ የተነሳ ሕይወታቸው ትልቅ ፈተና ውስጥ ይወድቃል። በቂ መረጃ እና ትምህርት ስለማያገኙ ደግሞ በአጭር ጊዜ ውስጥ ስትሮክ፣ የኩላሊት ሕመም፣ መታወር፣ የእግር እብጠት እና የአእምሮ ጤና መቃወስ ይገጥማቸዋል። ይህ ጥናት እዚህ ድምዳሜ ላይ የደረሰው በበይነ መረብ አማካኝነት 3 ሺህ 208 የሚሆኑ የስኳር ታማሚዎችን እና የጤና ባለሙያዎችን መጠይቅ ካደረገላቸው በኋላ ነው። ተጠያቂዎቹ ከብራዚል፣ ሕንድ እና ናይጄሪያ ናቸው። ይህ የጥናት ውጤት ለሌላው አስደናቂ ቢመስልም በችግሩ ላለፉት ግን ምንም ነው። በሰባት ዓመቴ ‘ዓይነት-1’ የስኳር በሽታ እንዳለብኝ የተነገረኝ ኮስታሪካ እያለሁ ነበር። ያደኩት ስለበሽታው ምንም መረጃ ሳይኖረኝ ነው። ልጅነቴ በብዙ ጭንቅ የተሞላ ነበር። ለአጥንት ሕመም የተሰጠኝ መድኃኒት የጎንዮሽ ጉዳት አድርሶብህ ነው ለስኳር የተዳረከው ተባልኩ። በልጅነቴ የስኳር መጠን (ጉሉኮስ) መለኪያ አልነበረኝም። ድንገተኛ እና ከባድ ድንጋጤ [ፓኒክ አታክ] በየቀኑ ያጋጥመኝ ነበር። ኢንሱሊን መውሰድ አለመውሰዴን እስክዘነጋ ድረስ እሰቃይ ነበር። ምናልባት ሳልወስድ የወሰድኩ መስሎኝ ነው እያልኩ ኢንሱሊን ሁለት ጊዜ ወስጄ አውቃለሁ። 25 ዓመት ሲሆነኝ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ሄድኩ። ያን ጊዜ ነው ስለ በሽታዬ በደንብ ማወቅ የቻልኩት። ዛሬ ግን ከዩናይትድ ኪንግደም ብሔራዊ ጤና አገልግሎት በቂ መረጃ በማግኘቴና ክትትል በማድረጌ በተሻለ የስኳር ሕመሜን መቆጣጠር ችያለሁ። እንደኔው ብዙ መረጃ ሳያገኝ የሚሰቃይ ሰው ይኖር ይሆን ወይ? ብዬ ስጠይቅ አና ሉሺያን አገኘሁ። አና ከሜክሲኮ ናት። እሷ እንደነገረችኝ ከሆነ የስኳር ሕመምተኛ እንደሆነች ባወቀች ጊዜ የእርሷ ብቻ ሳይሆን የቤተሰቧ ሕይወትም ነው አብሮ የተቃወሰው። አና ሉሺያ የዓይነት 1 የስኳር በሽታ ታማሚ ናት። ይህ የሆነው ገና 8 ዓመት ሳይሞላት ነበር። ይህን ያወቀችው ወደ ጽኑ ሕሙማን ክፍል ከተወሰደች በኋላ ነበር። “ገና ልጅ ነበርኩ፤ ጣፋጭ ነገር አትበይም አሉኝ፤ ይህን ተመገቢ፣ ያን አትመገቢ ሲሉኝ ጊዜ ተስፋ ቆረጥኩ” ትላለች። እናቷ ክሌመንቲና ስለልጃቸው አና ሲናገሩ የመጀመሪያዎቹ ቀናት ፈታኝ እንደነበሩ ያሰታውሳሉ። “ሐኪሞቹ መርፌ አወጋግ እንድለማመድ እና እሷን እንድወጋት ነገሩኝ። ቀስ በቀስ አብረን ተማርን” ይላሉ ክሌመንቲና። ነገር ግን አናና እናቷ ስለ ስኳር ሕመም መረጃ ባላገኙባቸው የመጀመርያ ጊዜያት ብዙ ምስቅልቅል እንዳጋጠማቸው አይዘነጉትም። “ትምህርት ቤት ራሱ የተለየ እንክብካቤ ሊኖር ይገባል፤ ስኳር ሕመምተኛ ተማሪዎችን ሲያገኙ ከዚህ በኋላ ሕይወትሽን በዚህ ሁኔታ መምራት ይኖርብሻል ማለት አለባቸው።’’ ስኳር የማይድኑት በሽታ ነው። አንድ ታማሚ ስኳር አለው የሚባለው ሰውነቱ የስኳር መጠንን ማመጣጠን ወይም መቆጣጠር ሲያቅተው ነው። ይህም የሚሆነው ኢንሱሊን በሚባለው ሆርሞን የተነሳ ነው። በአጠቃላይ ሁለት ዓይነት የስኳር ሕመም አለ። ዓይነት-1 እና ዓይነት-2 የሚባል። አሁን አና ሉሺያ ዕድሜዋ 17 ደርሷል። አሁን ሁሉን ነገር በራሷ ነው የምትወጣው። ነገር ግን በስኳር በሽታ መያዝ ቀላል እንዳልሆነ ትናገራለች። “ትንሽ ሰዓት ነው የምተኛው። ምክንያቱም የስኳር መጠኔን መለካት አለብኝ። መርፌ ራሴን ከወጋሁ በኋላ ደግሞ ትንሽ ሰዓት መቆየት አለብኝ።” አሁን ዘመናዊ የሚባል የስኳር መጠን መለኪያ [ጉሉኮስ ሴንሰር] አላት። ‘ፍሪስታይል ሊብሬ’ ይባላል። እጇን በመርፌ ሳትወጋ በቀላሉ የጉሉኮስ መጠኗን ማወቅ ያስችላታል። አሁን አሁን ስታስበው “ምናለ ቀደም ብሎ ይህ መሣሪያ በነበረኝ” ትላለች። ምንም እንኳ አና ሉሺያ የቤተሰብ ድጋፍ ባይለያትም ከትምህርት ቤት፣ የቤት ሥራ እና ፈተና ጋር ስኳርን ማስታመም ቀላል እንዳልሆነ ደጋግማ ትናገራለች። ፕሮፌሰር አንድሩ ቦልተን እንደሚሉት የስኳር በሽተኞች ተገቢው መረጃ ካልተሰጣቸው ለጭንቀት እና ድብታ እንዲሁም በኋላ ላይ ነገሩ ከከፋ ራስን እስከማጥፋት የሚያደርስ ነው። ጥናቱ እንደሚለው ከሆነ ታማሚዎች ብቻም ሳይሆኑ የጤና ድጋፍ ሠራተኞችም በስኳር በሽታ ዙርያ በቂ ሥልጠና ማግኘት አለባቸው። ብዙዎቹ ለምሳሌ ስኳር ሕመም ለከፋ ድብታ እንደሚዳርግ መረጃው የላቸውም። “ብዙ የስኳር ታማሚዎች ከፍተኛ ድብታ ውስጥ ሲገቡ ለራሳቸው አስፈላጊውን እንክብካቤ ማድረግ ያስጠላቸዋል። የስኳር መጠናቸውን መቆጣጠር ይተዋሉ” ይላሉ ፕሮፌሰር ቦልተን። ፕሮፌሰሩ የሚመክሩት የስኳር ታማሚዎች ማንኛውንም መረጃ ማግኘት ከፈለጉ ያን መረጃ ከጤና ባለሙያ ብቻ እንዲቀበሉ ነው። ብዙ ሰዎች ከማኅበራዊ ሚዲያ መረጃ ቃርመው ችግር ውስጥ እየገቡ ነው። ሌላው ችግር ታማሚዎች ሐኪም ለማየት መስጋታቸው ነው። ጥናቱ እንዳሳየው ከሆነ ስኳር ሕመምተኞች 99 ከመቶ የሚሆኑት በዓመት በድምሩ ከሦስት ሰዓት የበለጠ ሐኪም ዘንድ ቀርበው አያወሩም። ይህ ደግሞ አደጋውን የከፋ ያደርገዋል። ስኳር ከሐኪም ጋር በመመካከር የሚገፋ ደዌ ነው። ለብቻ አይወጡትም።
“ከስኳር ሕመምተኞች አንድ አራተኛው ስለበሽታው ምንም መረጃ አያገኙም” ጥናት ከስኳር ታማሚዎች አንድ አራተኛው ምንም ዓይነት እርዳታ እንደማያገኙ አንድ ጥናት አረጋገጠ። የዓለም የስኳር ሕመም ፌዴሬሽን እንዳለው ከታማሚዎች 26 ከመቶ የሚሆኑት ስለበሽታው ምንም ዓይነት መረጃ አያገኙም። በዚህ የተነሳ ሕይወታቸው ትልቅ ፈተና ውስጥ ይወድቃል። በቂ መረጃ እና ትምህርት ስለማያገኙ ደግሞ በአጭር ጊዜ ውስጥ ስትሮክ፣ የኩላሊት ሕመም፣ መታወር፣ የእግር እብጠት እና የአእምሮ ጤና መቃወስ ይገጥማቸዋል። ይህ ጥናት እዚህ ድምዳሜ ላይ የደረሰው በበይነ መረብ አማካኝነት 3 ሺህ 208 የሚሆኑ የስኳር ታማሚዎችን እና የጤና ባለሙያዎችን መጠይቅ ካደረገላቸው በኋላ ነው። ተጠያቂዎቹ ከብራዚል፣ ሕንድ እና ናይጄሪያ ናቸው። ይህ የጥናት ውጤት ለሌላው አስደናቂ ቢመስልም በችግሩ ላለፉት ግን ምንም ነው። በሰባት ዓመቴ ‘ዓይነት-1’ የስኳር በሽታ እንዳለብኝ የተነገረኝ ኮስታሪካ እያለሁ ነበር። ያደኩት ስለበሽታው ምንም መረጃ ሳይኖረኝ ነው። ልጅነቴ በብዙ ጭንቅ የተሞላ ነበር። ለአጥንት ሕመም የተሰጠኝ መድኃኒት የጎንዮሽ ጉዳት አድርሶብህ ነው ለስኳር የተዳረከው ተባልኩ። በልጅነቴ የስኳር መጠን (ጉሉኮስ) መለኪያ አልነበረኝም። ድንገተኛ እና ከባድ ድንጋጤ [ፓኒክ አታክ] በየቀኑ ያጋጥመኝ ነበር። ኢንሱሊን መውሰድ አለመውሰዴን እስክዘነጋ ድረስ እሰቃይ ነበር። ምናልባት ሳልወስድ የወሰድኩ መስሎኝ ነው እያልኩ ኢንሱሊን ሁለት ጊዜ ወስጄ አውቃለሁ። 25 ዓመት ሲሆነኝ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ሄድኩ። ያን ጊዜ ነው ስለ በሽታዬ በደንብ ማወቅ የቻልኩት። ዛሬ ግን ከዩናይትድ ኪንግደም ብሔራዊ ጤና አገልግሎት በቂ መረጃ በማግኘቴና ክትትል በማድረጌ በተሻለ የስኳር ሕመሜን መቆጣጠር ችያለሁ። እንደኔው ብዙ መረጃ ሳያገኝ የሚሰቃይ ሰው ይኖር ይሆን ወይ? ብዬ ስጠይቅ አና ሉሺያን አገኘሁ። አና ከሜክሲኮ ናት። እሷ እንደነገረችኝ ከሆነ የስኳር ሕመምተኛ እንደሆነች ባወቀች ጊዜ የእርሷ ብቻ ሳይሆን የቤተሰቧ ሕይወትም ነው አብሮ የተቃወሰው። አና ሉሺያ የዓይነት 1 የስኳር በሽታ ታማሚ ናት። ይህ የሆነው ገና 8 ዓመት ሳይሞላት ነበር። ይህን ያወቀችው ወደ ጽኑ ሕሙማን ክፍል ከተወሰደች በኋላ ነበር። “ገና ልጅ ነበርኩ፤ ጣፋጭ ነገር አትበይም አሉኝ፤ ይህን ተመገቢ፣ ያን አትመገቢ ሲሉኝ ጊዜ ተስፋ ቆረጥኩ” ትላለች። እናቷ ክሌመንቲና ስለልጃቸው አና ሲናገሩ የመጀመሪያዎቹ ቀናት ፈታኝ እንደነበሩ ያሰታውሳሉ። “ሐኪሞቹ መርፌ አወጋግ እንድለማመድ እና እሷን እንድወጋት ነገሩኝ። ቀስ በቀስ አብረን ተማርን” ይላሉ ክሌመንቲና። ነገር ግን አናና እናቷ ስለ ስኳር ሕመም መረጃ ባላገኙባቸው የመጀመርያ ጊዜያት ብዙ ምስቅልቅል እንዳጋጠማቸው አይዘነጉትም። “ትምህርት ቤት ራሱ የተለየ እንክብካቤ ሊኖር ይገባል፤ ስኳር ሕመምተኛ ተማሪዎችን ሲያገኙ ከዚህ በኋላ ሕይወትሽን በዚህ ሁኔታ መምራት ይኖርብሻል ማለት አለባቸው።’’ ስኳር የማይድኑት በሽታ ነው። አንድ ታማሚ ስኳር አለው የሚባለው ሰውነቱ የስኳር መጠንን ማመጣጠን ወይም መቆጣጠር ሲያቅተው ነው። ይህም የሚሆነው ኢንሱሊን በሚባለው ሆርሞን የተነሳ ነው። በአጠቃላይ ሁለት ዓይነት የስኳር ሕመም አለ። ዓይነት-1 እና ዓይነት-2 የሚባል። አሁን አና ሉሺያ ዕድሜዋ 17 ደርሷል። አሁን ሁሉን ነገር በራሷ ነው የምትወጣው። ነገር ግን በስኳር በሽታ መያዝ ቀላል እንዳልሆነ ትናገራለች። “ትንሽ ሰዓት ነው የምተኛው። ምክንያቱም የስኳር መጠኔን መለካት አለብኝ። መርፌ ራሴን ከወጋሁ በኋላ ደግሞ ትንሽ ሰዓት መቆየት አለብኝ።” አሁን ዘመናዊ የሚባል የስኳር መጠን መለኪያ [ጉሉኮስ ሴንሰር] አላት። ‘ፍሪስታይል ሊብሬ’ ይባላል። እጇን በመርፌ ሳትወጋ በቀላሉ የጉሉኮስ መጠኗን ማወቅ ያስችላታል። አሁን አሁን ስታስበው “ምናለ ቀደም ብሎ ይህ መሣሪያ በነበረኝ” ትላለች። ምንም እንኳ አና ሉሺያ የቤተሰብ ድጋፍ ባይለያትም ከትምህርት ቤት፣ የቤት ሥራ እና ፈተና ጋር ስኳርን ማስታመም ቀላል እንዳልሆነ ደጋግማ ትናገራለች። ፕሮፌሰር አንድሩ ቦልተን እንደሚሉት የስኳር በሽተኞች ተገቢው መረጃ ካልተሰጣቸው ለጭንቀት እና ድብታ እንዲሁም በኋላ ላይ ነገሩ ከከፋ ራስን እስከማጥፋት የሚያደርስ ነው። ጥናቱ እንደሚለው ከሆነ ታማሚዎች ብቻም ሳይሆኑ የጤና ድጋፍ ሠራተኞችም በስኳር በሽታ ዙርያ በቂ ሥልጠና ማግኘት አለባቸው። ብዙዎቹ ለምሳሌ ስኳር ሕመም ለከፋ ድብታ እንደሚዳርግ መረጃው የላቸውም። “ብዙ የስኳር ታማሚዎች ከፍተኛ ድብታ ውስጥ ሲገቡ ለራሳቸው አስፈላጊውን እንክብካቤ ማድረግ ያስጠላቸዋል። የስኳር መጠናቸውን መቆጣጠር ይተዋሉ” ይላሉ ፕሮፌሰር ቦልተን። ፕሮፌሰሩ የሚመክሩት የስኳር ታማሚዎች ማንኛውንም መረጃ ማግኘት ከፈለጉ ያን መረጃ ከጤና ባለሙያ ብቻ እንዲቀበሉ ነው። ብዙ ሰዎች ከማኅበራዊ ሚዲያ መረጃ ቃርመው ችግር ውስጥ እየገቡ ነው። ሌላው ችግር ታማሚዎች ሐኪም ለማየት መስጋታቸው ነው። ጥናቱ እንዳሳየው ከሆነ ስኳር ሕመምተኞች 99 ከመቶ የሚሆኑት በዓመት በድምሩ ከሦስት ሰዓት የበለጠ ሐኪም ዘንድ ቀርበው አያወሩም። ይህ ደግሞ አደጋውን የከፋ ያደርገዋል። ስኳር ከሐኪም ጋር በመመካከር የሚገፋ ደዌ ነው። ለብቻ አይወጡትም።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cyxr563deqyo
5sports
ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ዓለም አቀፍ የግብ ክብረ ወሰንን ሰበረ
የ36 ዓመቱ ክርስቲያኖ ሮናልዶ አሁንም በዓለም እግር ኳስ መድረክ ታሪክ መስራቱን ቀጥሏል። ሮናልዶ ትናንት ምሽት አገሩ ፖርቹጋል በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከአየርላንድ ባደረገችው ጨዋታ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር በወንዶች ዓለም አቀፍ ውድድር ከፍተኛውን ግብ ያስቆጠረ ተጫዋች መሆን ችሏል። ፖርቹጋል አየርላንድን 2 ለ1 ባሸነፈችበት ጨዋታ ሮናልዶ መጀመሪያ ላይ የተገኘውን ፍጹም ቅጣት ምት ወደ ግብ መቀየር አለመቻሉ በርካቶችን ያስቆጨ ቢሆንም በጨዋታው መገባደጃ አካባቢ ባስቆጠራቸው ሁለት ጎሎች በዓለማችን ለብሄራዊ ቡድን ከፍተኛ ግብ ያስቆጠረ ተጫዋች ሆኗል። በዚህም መሰረት ሮናልዶ ለአገሩ 111 ግቦችን በስሙ ያስቆጠረ ሲሆን ከዚህ በፊት ሪከርዱን ይዞት የቆየው ኢራናዊው አሊ ዳኢ ነበር። እሱም ከአውሮፓውያኑ 1993 እስከ 2006 ባሉት ዓመታት ባደረጋቸው ጨዋታዎች 109 ግቦችን አስቆጥሮ ነበር። ሮናልዶ በዘንድሮው የአውሮፓ ዋንጫ ፈረንሳይ ላይ ባስቆጠራቸው ሁለት ግቦች አማካይነት የአሊን ክብረ ወሰን መጋራት ችሎ የነበረ ሲሆን በርካቶችም ይህ ዓመት ሳይጠናቀቅ ተጨማሪ ጎሎችን እንደሚያስቆጥርና ክብረ ወሰኑን የግሉ እንደሚያደርገው ሲገልጹ ነበር። ከዚህ ክብረ ወሰን በተጨማሪ ደግሞ፤ ባሳለፍነው ሳምንት ለማንቸስተር ዩናይትድ በድጋሚ የፈረመው ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ለብሄራዊ ቡድን 180 ጊዜ ጨዋታዎችን በማድረግ በአውሮፓ ለብሄራዊ ቡድን በመጫወት አሁንም ክብረ ወሰኑን ከስፔኑ ሰርጂዮ ራሞስ ጋር መጋራት ችሏል። በዓለማችን እግር ኳስ ታሪክ ለብሄራዊ ቡድን ከፍተኛውን ጨዋታ በማድረግ ክብረ ወሰኑን የያዘው ደግሞ ማሌዢያዊው ሶህ ቺን አን ሲሆን ለአገሩም ከአውሮፓውያኑ 1969 እስከ 1984 ባሉት ዓመታት 195 ጊዜ ተጫውቷል። ከጁቬንቱስ ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ ዝውውሩን የጨረሰው ሮናልዶ ለብሄራዊ ቡድን ከ90 በላይ ግቦችን ማስቆጠር የቻለ ሁለተኛው ተጫዋች ሲሆን አንደኛው ደግሞ ኢራናዊው አሊ ነው። ''በጣም ደስተኛ ነኝ። ክብረ ወሰኑን በመስበሬ ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን በጨዋታው መጨረሻ አካባቢ የተለየ እንቅስቃሴ አድርገናል። ባለቀ ሰአት ለአገሬ ሁለት ግብ ማስቆጠሬም ጥሩ ነው። የብድን አጋሮቼም በጣም የሚደነቁ ነበሩ። እስከመጨረሻው ድረስ ተስፋ አልቆረጥንም ነበር። በጣም ደስ ብሎኛል'' ሲል ደስታውን ገልጿል ሮናልዶ። በበርካታ የእግር ኳስ አፍቃሪያን የዓለማችን የምን ጊዜም ምርጥ ተጫዋች እየተባለ የሚሞካሸው ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ይህን ታሪክ መስራቱ ይበልጥ ይህ ክብር ይገባዋል ለሚሉት ትልቅ ማሳያ ሆኗል። ሮናልዶ ለበርካታ ዓመታት ከፖርቹጋል እስከ እንግሊዝ እንዲሁም ከስፔን እስከ ጣልያን በዘለቀው አስገራሚ የእግር ኳስ ህይወቱ በቻምፒየንስ ሊግ ከፍተኛውን ግብ ማስቆጠር የቻለ ተጫዋች ሲሆን እስካሁንም 5 ጊዜ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ አሸናፊ ነው። በጣም በሚያስገርም ሁኔታ ደግሞ ሮናልዶ ካስቆጠራቸው ግቦች መካከል ግማሽ የሚሆኑትን ያስቆጠረው በጨዋታዎች የመጨረሻ 30 ደቂቃዎች ውስጥ ነው። 33 ግቦችን ደግሞ በመጨረሻዎቹ 15 ደቂቃዎች አስቆጥሯል። ሮናልዶ እስካሁን ባደረጋቸው 180 ጨዋታዎች ለአገሩ 11 ግቦችን ሲያስቆጥር በርካቶች ከሮናልዶ በላይ ነው እያሉ የሚያሞካሹት አርጀንቲናዊው ሊዮኔል ሜሲ ደግሞ በ151 ጨዋታዎች 76 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል። ከዚህ በኋላ ደግሞ የ34 ዓመቱ ሜሲ ይህንን የሮናልዶ ክብረ ወሰን የማሻሻል እድሉ ያለው አይመስልም።
ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ዓለም አቀፍ የግብ ክብረ ወሰንን ሰበረ የ36 ዓመቱ ክርስቲያኖ ሮናልዶ አሁንም በዓለም እግር ኳስ መድረክ ታሪክ መስራቱን ቀጥሏል። ሮናልዶ ትናንት ምሽት አገሩ ፖርቹጋል በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከአየርላንድ ባደረገችው ጨዋታ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር በወንዶች ዓለም አቀፍ ውድድር ከፍተኛውን ግብ ያስቆጠረ ተጫዋች መሆን ችሏል። ፖርቹጋል አየርላንድን 2 ለ1 ባሸነፈችበት ጨዋታ ሮናልዶ መጀመሪያ ላይ የተገኘውን ፍጹም ቅጣት ምት ወደ ግብ መቀየር አለመቻሉ በርካቶችን ያስቆጨ ቢሆንም በጨዋታው መገባደጃ አካባቢ ባስቆጠራቸው ሁለት ጎሎች በዓለማችን ለብሄራዊ ቡድን ከፍተኛ ግብ ያስቆጠረ ተጫዋች ሆኗል። በዚህም መሰረት ሮናልዶ ለአገሩ 111 ግቦችን በስሙ ያስቆጠረ ሲሆን ከዚህ በፊት ሪከርዱን ይዞት የቆየው ኢራናዊው አሊ ዳኢ ነበር። እሱም ከአውሮፓውያኑ 1993 እስከ 2006 ባሉት ዓመታት ባደረጋቸው ጨዋታዎች 109 ግቦችን አስቆጥሮ ነበር። ሮናልዶ በዘንድሮው የአውሮፓ ዋንጫ ፈረንሳይ ላይ ባስቆጠራቸው ሁለት ግቦች አማካይነት የአሊን ክብረ ወሰን መጋራት ችሎ የነበረ ሲሆን በርካቶችም ይህ ዓመት ሳይጠናቀቅ ተጨማሪ ጎሎችን እንደሚያስቆጥርና ክብረ ወሰኑን የግሉ እንደሚያደርገው ሲገልጹ ነበር። ከዚህ ክብረ ወሰን በተጨማሪ ደግሞ፤ ባሳለፍነው ሳምንት ለማንቸስተር ዩናይትድ በድጋሚ የፈረመው ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ለብሄራዊ ቡድን 180 ጊዜ ጨዋታዎችን በማድረግ በአውሮፓ ለብሄራዊ ቡድን በመጫወት አሁንም ክብረ ወሰኑን ከስፔኑ ሰርጂዮ ራሞስ ጋር መጋራት ችሏል። በዓለማችን እግር ኳስ ታሪክ ለብሄራዊ ቡድን ከፍተኛውን ጨዋታ በማድረግ ክብረ ወሰኑን የያዘው ደግሞ ማሌዢያዊው ሶህ ቺን አን ሲሆን ለአገሩም ከአውሮፓውያኑ 1969 እስከ 1984 ባሉት ዓመታት 195 ጊዜ ተጫውቷል። ከጁቬንቱስ ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ ዝውውሩን የጨረሰው ሮናልዶ ለብሄራዊ ቡድን ከ90 በላይ ግቦችን ማስቆጠር የቻለ ሁለተኛው ተጫዋች ሲሆን አንደኛው ደግሞ ኢራናዊው አሊ ነው። ''በጣም ደስተኛ ነኝ። ክብረ ወሰኑን በመስበሬ ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን በጨዋታው መጨረሻ አካባቢ የተለየ እንቅስቃሴ አድርገናል። ባለቀ ሰአት ለአገሬ ሁለት ግብ ማስቆጠሬም ጥሩ ነው። የብድን አጋሮቼም በጣም የሚደነቁ ነበሩ። እስከመጨረሻው ድረስ ተስፋ አልቆረጥንም ነበር። በጣም ደስ ብሎኛል'' ሲል ደስታውን ገልጿል ሮናልዶ። በበርካታ የእግር ኳስ አፍቃሪያን የዓለማችን የምን ጊዜም ምርጥ ተጫዋች እየተባለ የሚሞካሸው ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ይህን ታሪክ መስራቱ ይበልጥ ይህ ክብር ይገባዋል ለሚሉት ትልቅ ማሳያ ሆኗል። ሮናልዶ ለበርካታ ዓመታት ከፖርቹጋል እስከ እንግሊዝ እንዲሁም ከስፔን እስከ ጣልያን በዘለቀው አስገራሚ የእግር ኳስ ህይወቱ በቻምፒየንስ ሊግ ከፍተኛውን ግብ ማስቆጠር የቻለ ተጫዋች ሲሆን እስካሁንም 5 ጊዜ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ አሸናፊ ነው። በጣም በሚያስገርም ሁኔታ ደግሞ ሮናልዶ ካስቆጠራቸው ግቦች መካከል ግማሽ የሚሆኑትን ያስቆጠረው በጨዋታዎች የመጨረሻ 30 ደቂቃዎች ውስጥ ነው። 33 ግቦችን ደግሞ በመጨረሻዎቹ 15 ደቂቃዎች አስቆጥሯል። ሮናልዶ እስካሁን ባደረጋቸው 180 ጨዋታዎች ለአገሩ 11 ግቦችን ሲያስቆጥር በርካቶች ከሮናልዶ በላይ ነው እያሉ የሚያሞካሹት አርጀንቲናዊው ሊዮኔል ሜሲ ደግሞ በ151 ጨዋታዎች 76 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል። ከዚህ በኋላ ደግሞ የ34 ዓመቱ ሜሲ ይህንን የሮናልዶ ክብረ ወሰን የማሻሻል እድሉ ያለው አይመስልም።
https://www.bbc.com/amharic/news-58418103
5sports
ሰንበሬ ክብረ ወሰን ስታሻሽል ማራቶን ያሸነፈው ኢትዮጵያዊ ውጤቱ ተሰረዘበት
እሁድ ዕለት ጀርመን ውስጥ በተካሄደ ውድድር አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ የ5 ኪሎ ሜትር ክብረ ወሰንን ስታሻሽል ኦስትሪያ ቬይና በተደረገው ማራቶን ያሸነፈው ደራራ ሁሪሳ ያልተፈቀደ ጫማ አድርጎ በመሮጡ ውጤቱ ተሰረዘበት። አትሌት ሰንበሬ የ5 ኪሎ ሜትር ውድድሯን ከዚህ ቀደም በኬንያዊቷ አትሌት ቢያትሪስ ቼፕኮኤች በ14፡44 ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን 14፡30 በሆነ ሰዓት ማሻሻል ችላለች። በቶኪዮ ኦሊምፒክ 5ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃ የነበረችው አትሌት ሰንበሬ ከውጤቱ በኋላ "በጣም ደስታ ተሰምቶኛል" ያለች ሲሆን፤ "ከኦሊምፒክ በኋላ ይህን የዓለም ክብረ ወሰን ማሻሻል እንደምችል ገብቶኛል" ማለቷን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። ከዚህ በተጨማሪ ትናንት ኬንያዊቷ አትሌት አግነስ ቲሮፕ ጀርመን ውስጥ በተካሄደው የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር የዓለም ክብረ ወሰንን ማሻሻል ችላለች። አትሌት አግነስ በሞሮኮ አትሌት አሰማኤ ሌግህዛኦዩ ከ19 ዓመት በፊት ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን በ28 ሰከንዶች በማሻሻል 30፡17 በሆነ ሰዓት ውድድሯን አጠናቃለች። ያልተፈቀደ ጫማ እሁድ መስከረም 02/2014 ዓ.ም ኦስትሪያ ዋና ከተማ ቬይና በተካሄደው የወንዶች ማራቶንን አሸንፎ የነበረው ኢትዮጵያዊው አትሌት ደራራ ሁሪሳ ተጫምቶት የነበረው የጫማ ሶል (መርገጫው) ከሚፈቀደው በላይ አንድ ሴንቲ ሜትር ወፍሮ በመገኘቱ ውጤቱ ውድቅ ተደርጎበታል። አትሌት ደራራ ውድድሩን 2፡09፡22 በሆነ ሰዓት ቢያጠናቅቅም ከ45 ደቂቃዎች በኋላ የውድድር ደንብን በመጣሱ ውጤቱ እንደተሰረዘበት ተነግሮታል። የውድድሩ አዘጋጆች አትሌቶች መጫማት የሚችሉት የጫማ ሶል ውፍረት 4 ሳንቲ ሜትር መሆን አለበት ይላሉ። አትሌቱ ግን ተጫምቶት ነበረ የተባለው የጫማ ሶል 5 ሳንቲ ሜትር የሚወፍር መሆኑን ሮይተር የዜና ወኪል የውድድሩን አዘጋጆች ጠቅሶ ዘግቧል። ከዚህ በተጨማሪም አትሌት ደራራ ከውድድሩ መጀመር በፊት በሞላው ቅጽ ላይ የተለየ ጫማ አድርጎ ወደ ውድድሩ ስለመግባቱ ተመልክቷል። "በቴክኒክ ስብሰባ ላይ በጫማ ዙሪያ ያለውን መመሪያ ትኩረት ሰጥተን ተናግረናል። አለመታደል ሆኖ የአትሌቱን ውጤት ከመሰረዝ ውጪ ሌላ አማራጭ አልነበረንም" በማለት የውድድሩ አስተባባሪ ሃነስ ላንገር ተናግረዋል። "እንደዚህ አይነት ነገር ሲከሰት ይህ የመጀመሪው ነው። በውድድሮች ላይ እንደዚህ አይነት ነገር እንዳይከሰት ቀድሞ ማጣራት የሚቻልበት አሰራራ ከአሁን በኋላ ይኖራል ብዬ አስባለሁ" ሲሉ የውድድሩ አዘጋጅ ተናግረዋል። ከአትሌት ደራራ ቀጥሎ በሁለተኛነት ያጠናቀቀው ኬንያዊው ሊኦናርድ ላንጋት የአንደኝነት ደረጃውን በመያዝ የውድድሩ አሸናፊ ተብሏል። "የአትሌቱ ውጤት እንደተሰረዘ አልሰማሁም ነበር። ውድድሩን ለማሸነፍ አቅጄ ነበር። በመጨረሻ በማሸነፌ ፈጣሪን አመሰግናለሁ" ብሏል ኬንያዊው አትሌት ላንጋት። ይህ ውድድር በየዓመቱ ሚያዝያ ወር ላይ ይካሄደ የነበረ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት መካሄዱ በበርካታ አትሌቶች ተቃውሞን አስተናግዶ ነበር። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ከፍተኛ ሙቀት ነው። በተያያዘ ዜና እዚያው ኦስትሪያ ውስጥ በግማሽ ማራቶን ውድድር ላይ ተሳታፊ የነበረ አትሌት ሕይወቱ ስለማለፉም ተሰምቷል። የውድድሩ አዘጋጆች እንዳሉት ከሆነ፤ የ40 ዓመቱ የኦስትሪያ አትሌት ውድድሩን ከጨረሰ በኋላ ራሱ ስቶ ሆስፒታል ከገባ በኋላ ነው ሕይወቱ ያለፈው። የውድድሩ አዘጋጆች በክስተቱ እጅጉን ማዘናቸውን ከመግለጽ ውጪ ስለ አትሌቱ አሟሟት ዝርዝር መረጃ አልሰጡም።
ሰንበሬ ክብረ ወሰን ስታሻሽል ማራቶን ያሸነፈው ኢትዮጵያዊ ውጤቱ ተሰረዘበት እሁድ ዕለት ጀርመን ውስጥ በተካሄደ ውድድር አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ የ5 ኪሎ ሜትር ክብረ ወሰንን ስታሻሽል ኦስትሪያ ቬይና በተደረገው ማራቶን ያሸነፈው ደራራ ሁሪሳ ያልተፈቀደ ጫማ አድርጎ በመሮጡ ውጤቱ ተሰረዘበት። አትሌት ሰንበሬ የ5 ኪሎ ሜትር ውድድሯን ከዚህ ቀደም በኬንያዊቷ አትሌት ቢያትሪስ ቼፕኮኤች በ14፡44 ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን 14፡30 በሆነ ሰዓት ማሻሻል ችላለች። በቶኪዮ ኦሊምፒክ 5ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃ የነበረችው አትሌት ሰንበሬ ከውጤቱ በኋላ "በጣም ደስታ ተሰምቶኛል" ያለች ሲሆን፤ "ከኦሊምፒክ በኋላ ይህን የዓለም ክብረ ወሰን ማሻሻል እንደምችል ገብቶኛል" ማለቷን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። ከዚህ በተጨማሪ ትናንት ኬንያዊቷ አትሌት አግነስ ቲሮፕ ጀርመን ውስጥ በተካሄደው የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር የዓለም ክብረ ወሰንን ማሻሻል ችላለች። አትሌት አግነስ በሞሮኮ አትሌት አሰማኤ ሌግህዛኦዩ ከ19 ዓመት በፊት ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን በ28 ሰከንዶች በማሻሻል 30፡17 በሆነ ሰዓት ውድድሯን አጠናቃለች። ያልተፈቀደ ጫማ እሁድ መስከረም 02/2014 ዓ.ም ኦስትሪያ ዋና ከተማ ቬይና በተካሄደው የወንዶች ማራቶንን አሸንፎ የነበረው ኢትዮጵያዊው አትሌት ደራራ ሁሪሳ ተጫምቶት የነበረው የጫማ ሶል (መርገጫው) ከሚፈቀደው በላይ አንድ ሴንቲ ሜትር ወፍሮ በመገኘቱ ውጤቱ ውድቅ ተደርጎበታል። አትሌት ደራራ ውድድሩን 2፡09፡22 በሆነ ሰዓት ቢያጠናቅቅም ከ45 ደቂቃዎች በኋላ የውድድር ደንብን በመጣሱ ውጤቱ እንደተሰረዘበት ተነግሮታል። የውድድሩ አዘጋጆች አትሌቶች መጫማት የሚችሉት የጫማ ሶል ውፍረት 4 ሳንቲ ሜትር መሆን አለበት ይላሉ። አትሌቱ ግን ተጫምቶት ነበረ የተባለው የጫማ ሶል 5 ሳንቲ ሜትር የሚወፍር መሆኑን ሮይተር የዜና ወኪል የውድድሩን አዘጋጆች ጠቅሶ ዘግቧል። ከዚህ በተጨማሪም አትሌት ደራራ ከውድድሩ መጀመር በፊት በሞላው ቅጽ ላይ የተለየ ጫማ አድርጎ ወደ ውድድሩ ስለመግባቱ ተመልክቷል። "በቴክኒክ ስብሰባ ላይ በጫማ ዙሪያ ያለውን መመሪያ ትኩረት ሰጥተን ተናግረናል። አለመታደል ሆኖ የአትሌቱን ውጤት ከመሰረዝ ውጪ ሌላ አማራጭ አልነበረንም" በማለት የውድድሩ አስተባባሪ ሃነስ ላንገር ተናግረዋል። "እንደዚህ አይነት ነገር ሲከሰት ይህ የመጀመሪው ነው። በውድድሮች ላይ እንደዚህ አይነት ነገር እንዳይከሰት ቀድሞ ማጣራት የሚቻልበት አሰራራ ከአሁን በኋላ ይኖራል ብዬ አስባለሁ" ሲሉ የውድድሩ አዘጋጅ ተናግረዋል። ከአትሌት ደራራ ቀጥሎ በሁለተኛነት ያጠናቀቀው ኬንያዊው ሊኦናርድ ላንጋት የአንደኝነት ደረጃውን በመያዝ የውድድሩ አሸናፊ ተብሏል። "የአትሌቱ ውጤት እንደተሰረዘ አልሰማሁም ነበር። ውድድሩን ለማሸነፍ አቅጄ ነበር። በመጨረሻ በማሸነፌ ፈጣሪን አመሰግናለሁ" ብሏል ኬንያዊው አትሌት ላንጋት። ይህ ውድድር በየዓመቱ ሚያዝያ ወር ላይ ይካሄደ የነበረ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት መካሄዱ በበርካታ አትሌቶች ተቃውሞን አስተናግዶ ነበር። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ከፍተኛ ሙቀት ነው። በተያያዘ ዜና እዚያው ኦስትሪያ ውስጥ በግማሽ ማራቶን ውድድር ላይ ተሳታፊ የነበረ አትሌት ሕይወቱ ስለማለፉም ተሰምቷል። የውድድሩ አዘጋጆች እንዳሉት ከሆነ፤ የ40 ዓመቱ የኦስትሪያ አትሌት ውድድሩን ከጨረሰ በኋላ ራሱ ስቶ ሆስፒታል ከገባ በኋላ ነው ሕይወቱ ያለፈው። የውድድሩ አዘጋጆች በክስተቱ እጅጉን ማዘናቸውን ከመግለጽ ውጪ ስለ አትሌቱ አሟሟት ዝርዝር መረጃ አልሰጡም።
https://www.bbc.com/amharic/news-58541869
2health
ኮቪድ-19 በእንፋሎት ይጠፋል ያሉት ጆን ማጉፉሊ በሽታው ይዟቸው ይሆን?
ለአስራ አንድ ቀናት ያልታዩት የታንዛኒያው ፕሬዝደንት ጆን ማጉፉሊ ጉዳይ ጥያቄ እያስነሳ ነው። ቀንደኛ ተቃዋሚው ቱንዱ ሊሱ 'ምንጮቼ እንደነገሩኝ ከሆነ ፕሬዝደንቱ ኮሮናቫይረስ ይዟቸው ሕክምና ለማግኘት ወደ ኬንያ አምርተዋል' ሲሉ ለቢቢሲ ሹክ ብለዋል። ነገር ግን ቢቢሲ ይህንን ጉዳዩ ማጣራት አልቻለም። የማጉፉሊ አስተዳደር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን የመከተበት መንገድ ብዙ ትችት አስተከትሏል። ምስራቅ አፍሪካዊቷ ሃገር የኮቪድ-19 ክትባት ላለመግዛት መወሰኗም አነጋጋሪ ነበር። የ61 ዓመቱ ማጉፉሊ ኮቪድ-19ን ሲያናንቁት ነው የከረሙት። ለዚህ በሽታ ፀሎትና እንፋሎት መታጠን በቂ ነው ሲሉም ተደምጠዋል። ባለፈው ወር መገባደጃ ገደማ አንድ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣን ቀብር ላይ የተገኙት ማጉፉሊ ታንዛኒያ ኮቪድን ባለፈው ዓመት አሸንፋለች፤ ዘንድሮም ትደግማለች ብለው ነበር። ባለሥልጣኑ የሞቱት በከፊል ራስ ገዝ የሆነችው የዛንዚባር ደሴት ምክትል ፕሬዝደንት በኮቪድ-19 ምክንያት ሕይወታቸውን ካጡ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ነው። ተቃዋሚው ሊሱ እንደሚሉት ፕሬዝደንቱ ሰኞ ምሽት ሕክምና ለማግኘት ወደ ናይሮቢ ሆስፒታል አቅንተዋል። ሊሱ አክለው ፕሬዝደንቱ የልብ ሕመም እንዳጋጠማቸውና አደገኛ ሁኔታ ላእ እንደሚገኙ ይናገራሉ። የታንዛኒያ መንግሥት ጆን ማጉፉሊ ከአደባባይ ስለመጥፋታቸው እስካሁን ትንፍሽ ያለው ነገር የለም። ነገር ግን ለመጨረሻ ጊዜ ከ11 ቀናት በፊት ዳሬ ሳላም ውስጥ ስለታዩት የታንዛኒያው ፕሬዝደንት ያልተረጋገጡ መረጃዎች እንዳይወጡ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። የናይሮቢ ሆስፒታል በበኩሉ በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት መስጠት አልችልም ብሏል። አቶ ሊሱ መንግሥት ስለ ፕሬዝደንቱ ደህንነት መረጃ አለመስጠቱ ከተማውን ሃሜት እንዲሞላው እያደረገው ነው ይላል። አክለው የፕሬዝደንቱ ጤና ጉዳይ ግላዊ ምስጢር ሊሆን አይገባም ሲሉ መንግሥትን ይተቻሉ። የታንዛኒያው ፕሬዝደንት ኮቪድ-19 ቢይዛቸው የሚገርም አይደለም፤ ምክንያቱም ጥንቃቄ ሲያደርጉ አልነበረም ይላሉ ሊሱ። "የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አድርገው አያውቁም፤ ደግሞ ሕዝብ ወደተሰበሰበበት ያለምንም ጥንቃቄ ይሄዳሉ" ይላሉ በስደት ቤልጂየም የሚገኙት ተቃዋሚው ሊሱ። "እሳቸው እኮ ለወራት የበሽታውን መድኃኒት ሲያጣጥሉ የከረሙ ናቸው። ፀሎትና ቅጥል ነው የሚያድነው ሲሉ ነበር።" የ53 ዓመቱ ተቃዋሚ አክለው የፋይንናስ ሚኒስትሩ ፊሊፕ ምፓንጎም በኬንያዋ መዲና ሆስፒታል ውስጥ ሕክምና እያገኙ ነው ይላሉ። ማጉፉሊ እንደተባለው ኮሮናቫይረስ ይዟቸው ከሆነ አንድም በሽታውን ሲክዱ መኖራቸው ያስተቻቸዋል፤ ሁለት ደግሞ ጎረቤት ሃገር ሄደው መታከማቸው የተደራጀ የጤና ሥርዓት እንደሌለ ማሳያ መሆኑ ያስወርፋቸዋል ትላለች የቢቢሲ አፍሪካ ባልደረባ ለይላ ናቱ። የታንዛኒያ መንግሥት ኮሮናቫይረስን በተመለከተ መረጃ ስለማይሰጥ የበሽታውን መስፋፋት መጠን መለየት ከባድ ነው።
ኮቪድ-19 በእንፋሎት ይጠፋል ያሉት ጆን ማጉፉሊ በሽታው ይዟቸው ይሆን? ለአስራ አንድ ቀናት ያልታዩት የታንዛኒያው ፕሬዝደንት ጆን ማጉፉሊ ጉዳይ ጥያቄ እያስነሳ ነው። ቀንደኛ ተቃዋሚው ቱንዱ ሊሱ 'ምንጮቼ እንደነገሩኝ ከሆነ ፕሬዝደንቱ ኮሮናቫይረስ ይዟቸው ሕክምና ለማግኘት ወደ ኬንያ አምርተዋል' ሲሉ ለቢቢሲ ሹክ ብለዋል። ነገር ግን ቢቢሲ ይህንን ጉዳዩ ማጣራት አልቻለም። የማጉፉሊ አስተዳደር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን የመከተበት መንገድ ብዙ ትችት አስተከትሏል። ምስራቅ አፍሪካዊቷ ሃገር የኮቪድ-19 ክትባት ላለመግዛት መወሰኗም አነጋጋሪ ነበር። የ61 ዓመቱ ማጉፉሊ ኮቪድ-19ን ሲያናንቁት ነው የከረሙት። ለዚህ በሽታ ፀሎትና እንፋሎት መታጠን በቂ ነው ሲሉም ተደምጠዋል። ባለፈው ወር መገባደጃ ገደማ አንድ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣን ቀብር ላይ የተገኙት ማጉፉሊ ታንዛኒያ ኮቪድን ባለፈው ዓመት አሸንፋለች፤ ዘንድሮም ትደግማለች ብለው ነበር። ባለሥልጣኑ የሞቱት በከፊል ራስ ገዝ የሆነችው የዛንዚባር ደሴት ምክትል ፕሬዝደንት በኮቪድ-19 ምክንያት ሕይወታቸውን ካጡ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ነው። ተቃዋሚው ሊሱ እንደሚሉት ፕሬዝደንቱ ሰኞ ምሽት ሕክምና ለማግኘት ወደ ናይሮቢ ሆስፒታል አቅንተዋል። ሊሱ አክለው ፕሬዝደንቱ የልብ ሕመም እንዳጋጠማቸውና አደገኛ ሁኔታ ላእ እንደሚገኙ ይናገራሉ። የታንዛኒያ መንግሥት ጆን ማጉፉሊ ከአደባባይ ስለመጥፋታቸው እስካሁን ትንፍሽ ያለው ነገር የለም። ነገር ግን ለመጨረሻ ጊዜ ከ11 ቀናት በፊት ዳሬ ሳላም ውስጥ ስለታዩት የታንዛኒያው ፕሬዝደንት ያልተረጋገጡ መረጃዎች እንዳይወጡ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። የናይሮቢ ሆስፒታል በበኩሉ በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት መስጠት አልችልም ብሏል። አቶ ሊሱ መንግሥት ስለ ፕሬዝደንቱ ደህንነት መረጃ አለመስጠቱ ከተማውን ሃሜት እንዲሞላው እያደረገው ነው ይላል። አክለው የፕሬዝደንቱ ጤና ጉዳይ ግላዊ ምስጢር ሊሆን አይገባም ሲሉ መንግሥትን ይተቻሉ። የታንዛኒያው ፕሬዝደንት ኮቪድ-19 ቢይዛቸው የሚገርም አይደለም፤ ምክንያቱም ጥንቃቄ ሲያደርጉ አልነበረም ይላሉ ሊሱ። "የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አድርገው አያውቁም፤ ደግሞ ሕዝብ ወደተሰበሰበበት ያለምንም ጥንቃቄ ይሄዳሉ" ይላሉ በስደት ቤልጂየም የሚገኙት ተቃዋሚው ሊሱ። "እሳቸው እኮ ለወራት የበሽታውን መድኃኒት ሲያጣጥሉ የከረሙ ናቸው። ፀሎትና ቅጥል ነው የሚያድነው ሲሉ ነበር።" የ53 ዓመቱ ተቃዋሚ አክለው የፋይንናስ ሚኒስትሩ ፊሊፕ ምፓንጎም በኬንያዋ መዲና ሆስፒታል ውስጥ ሕክምና እያገኙ ነው ይላሉ። ማጉፉሊ እንደተባለው ኮሮናቫይረስ ይዟቸው ከሆነ አንድም በሽታውን ሲክዱ መኖራቸው ያስተቻቸዋል፤ ሁለት ደግሞ ጎረቤት ሃገር ሄደው መታከማቸው የተደራጀ የጤና ሥርዓት እንደሌለ ማሳያ መሆኑ ያስወርፋቸዋል ትላለች የቢቢሲ አፍሪካ ባልደረባ ለይላ ናቱ። የታንዛኒያ መንግሥት ኮሮናቫይረስን በተመለከተ መረጃ ስለማይሰጥ የበሽታውን መስፋፋት መጠን መለየት ከባድ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/news-56356719
5sports
ኢትዮጵያ፡ አካል ጉዳተኛው የቴኳንዶ ስፖርት አሰልጣኝ
ከማል ቃሲም የተወለደው ጎንደር ከተማ ነው። በህጻንነቱ ከቤተሰቦቹ ጋር በመሆን ወደ ወረታ አመሩ። "ተጫዋችና ደስተኛ" ነበርኩ የሚለው ከማል በአምስት ዓመቱ የገጠመው አደጋ ህይወቱን እስከወዲያኛው ቀይሮታል። "ጉዳት የደረሰብኝ በ1985 ዓ.ም ነበር። ወረታ ውስጥ ከእኩዮቼ ጋር ስጫወት በመንግሥት ሽግግር ወቅት ከአገልግሎት ውጪ ሆኖ በተተወ ታንክ ነው ጉዳት የደረሰብኝ።" በወቅቱ የአምስት ዓመት ታዳጊ የነበረው ከማል ታንኩ ላይ እየተጫወተ ሳለ "አፈሙዙን በሚያሽከረክረው ክፍተት መሐል አንድ እግሬ ሆኖ ለመሻገር ስሞክር አንደኛው እግሬ አፈሙዝ ስር ገባ። በዚያው ቅጽበት አፈሙዙ በሚዞርበት ጊዜ እግሬ ላይ አደጋው ደረሰ" ሲል ያስታውሳል። ከወረታ ወደ ባሕር ዳር ለህክምና ተወስዶ ለወራት እዚያው ከቆየ በኋላ ወደቀየው ተመለሰ። በድንገተኛው አደጋ ጉዳት የደረሰበት ታዳጊው ከማል ከህክምናው ሲመለስ ቀኝ እግሩ ጉልበቱ ላይ ተቆርጦ በሁለት ምርኩዞች ተደግፎ ነበር። "ህይወት እንደ አዲስ ተጀመረ። ያኛው ሌላ አሁን ደግሞ ሌላ ህይወት" የሚለው ከማል "በአካባቢያችን ሌላ አካል ጉዳተኛ አልነበረም። እንኳን በዚያ ወቅት አሁን እንኳን ማኅረሰቡ ውስጥ ስለአካል ጉዳተኝነት ያለው አመለካከት ፈታኝ ነበር። መውጣት መግባት መጫወት አልችልም ነበር" ይላል። በታዳጊነቱ በደረሰበት አደጋ አካል ጉዳተኛ የሆነው ከማል ተደራራቢ ችግሮችን መጋፈጥ ጀመረ። ሌላ ችግር ቤተሰቡ ውስጥ ተከሰተ፤ አባት እና እናቱ ተለያይተው በተለያየ ቦታ በየፊናቸው ህይወታቸውን ለመምራት ሲወስኑ፤ እሱም ከእናቱ ተለይቶ ከአባቱ ጋር መኖር ጀመረ። አደጋው ከደረሰበት በኋላ ከማል ሰባት ዓመት ሲሆነው ወደ ትምህርት ቤት መሄድ ጀመረ። ነገር ግን "ሙሉ ለሙሉ ህይወቴ ስለተቀየረ ትምህርት ቤት እረብሽ፣ እነጫነጭ ነበር" ሲል በጸባዩ ላይ ለውጥ መከሰቱን ያስታውሳል። ለአካል ጉዳተኞች የሚመች መሠረት ልማት አለመኖር እና ህብረተሰቡ ስለ አካል ጉዳተኝነት ያለው አስተሳሰብም ህይወቱን ከባድ አድርጎት ነበር። "ከባድ ነው። ትምህርት ቤት ነጻ ሆኜ መጫወት አልችልም። ትልልቆቹም ባለፍኩ ባገደምኩ ቁጥር ከንፈር መምጠጥ፤ በዚህ እድሜው እንደዚህ ሆኖ እያሉ ሲናገሩ መስማት ተስፋ ያስቆርጣሉ" ይላል። በሁለት ክራንች መንቀሳቀስም መጫወትም አልመችህ ሲለው አንዱን ክራንች በመተው እንደልቡ ለመሆን ሞከረ። በዚህም ለመንቀሳቀስ በሚያደርገው ሙከራ በተደጋጋሚ በመውደቅ እግሩ መጎዳት እና መድማት ይገጥመው ጀመር። በዚህ መልኩ እስከ ስድስተኛ ክፍል ወረታ ውስጥ ተማረ። በወቅቱ "ጸባዬ አስቸጋሪ እረባሽና አልቃሻ ሆኜ። ከባድ ጊዜ ነበር ያሳለፍኩት። ከልጆች ጋር ጋር መግባባት እየተቸገርኩ እጣላ ነበር። አንዳንድ ጊዜም በክራንች እስከመማታት እደርስ ነበር" የሚለው ከማል 6ኛ ክፍል ሲደርስ ወደ እናቱ ተመልሶ ጎንደር መኖር ጀመረ። ጎንደር ሌሎች የአካል ጉዳተኞችን ተዋወቀ ስለዚህም ከወረታ ብቸኝነቱ በተወሰነ ደረጃ ተላቀቀ። ነገር ግን እናቱ ሥራ ስላልነበራቸው የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ የሚያገኙት አንድ አካል ጉዳተኞችን ከሚረዳ ድርጅት ነበር። "ለአካል ጉዳተኞች የሚሰጠውን ስንዴ እና ዘይት በችግር ላይ ለነበረችው እናቴ አመጣላት ነበር። እዚያ ሌሎች አካል ጉዳተኞችን ባገኝም ጥሩ ስሜት አይሰማኝም ነበር። የዝቅትኝነት ስሜት ይሰማኝ ጀመር" የሚለው ከማል 'ረጂ እንጂ ተረጂ አልሆንም' ብሎ እርዳታውን መቀበል አቆመ። ስምንተኛ ክፍል ደርሶ ለማለፍ የሚያስችለውን ውጤት ባለማምጣቱ ለመድገም ተገደደ። በቀጣዩ ዓመት ደግሞ ሠው ሠራሽ እግር ለማሠራት ወደ ደሴ አምርቶ ለወራት እዚያው በመቆየቱ ስምንተኛ ክፍልን በማታው ክፍለ ጊዜ መማር ጀመረ። የማታ ተማሪ መሆኑ እንዲሁም ቀን ላይ የሚሰራው ነገር ስላልነበረው አጋጣሚው ከቴኳንዶ ስፖርት ጋር እንዲተዋወቅ ዕድል ፈጠረለት። ከጓደኛው ጋር ቴኳንዶ የሚሰራበት ቦታ በመሄድ ስፖርቱን የተመለከተው ከማል፤ ለሰዓታት ከተመለከተ በኋላ አንዳች ነገር ውስጡ ተፈጠረ። ከማልን የተመለከተው የቴኳንዶ አሰልጣኙ ስሜቱን ጠይቆት ፍላጎት ካለው በነጻ እንዲማር ስለፈቀደለት በቴኳንዶ ፍቅር ወደቀ። "እየወደቅኩ እየተነሳሁ ከምንም በላይ በአስተማሪዬ ድጋፍ እና በጓደኞቼ አይዞህ ባይነት ቴኳንዶውን መለማመድ ቀጠልኩ" ነገር ግን በዙሪያው ካሉ ሰዎችና ከቤተሰቡ ጭምር 'ምን ያደረግልሃል?' ይሉት ነበር። ሆኖም እንዳሰበው ቀላል አልነበረም። ከወላጆቹ በስተቀር ሁሉም 'ምን ሊያደርግልህ?' የሚል ጥያቄ እያቀረቡ ተስፋ አስቆራጭ አስተያት ሰጥተውታል። "በአንድ እግር ቴኳንዶ ከባድ ነው። ወድቄ እሰበራለሁ። እጄን ተሰብሬያለሁ። የቀረችውን አንድ እግሬን ተሰብሬ 2 ወር በተኛሁበት ጊዜ የነቀፉኝ ሰዎች ደስ አላቸው። እኔ ግን እስከ ህይወቴ ፍጻሜ ስፖርቱን ከመሥራት ማንም እንደማያግደኝ አወቅኩኝ።" ከማል ቴኳንዶ መጀመሩ ብዙ ነገሮችን እንዲለውጥ ምክንያት ሆኖታል። አንደኛው ደግሞ ክራንቹን የሚጠቀምበትን ዘዴ መቀየሩ እና በሚመቸው መንገድ እንዲያስተካክለው ማድረጉ ነው። "ክራንቹ መጀመሪያ ላይ ብረት ብቻ ነው። ቴኳንዶ ይህንን ምቹ እንዳደርግ ረድቶኛል። ይኸውም እንደጫማ ምቹ አድርጌ እንድሠራ አድርጎኛል። እንደጀመርኩ እግሬን ሳነሳ ክራንቹ ተሰብሮ ወድቄያለሁ። ሳስተምርም ወደቄ አውቃለሁ። የውሃ ቱቦ ነው በየጊዜው ቼክ አደርገዋለሁ። በየጊዜው እቀይረዋለሁ አሁን በምቾት እሠራለሁ።" ቴኳንዶ በተለያዩ የቀበቶ ቀለሞች የሚሰጡ ደጃዎች አሉት። ጀማሪዎች በነጭ ቀበቶ ይጀምራሉ። ቢጫ፣ አረንጓዴ፣ ቀይ እና ጥቁር። እነዚህን ቀበቶዎች አንድ ሰልጣኝ የተለያዩ የስልጠናዎችን ካጠናቀቀ በኋላ ከአሰልጣኙ የሚያገኘው ይሆናል። ከዚያ በኋላ ደግሞ በዲግሪ የሚገለጹና ዳን የሚባሉ ዘጠኝ ደረጃዎች አሉ። ዳን የሚሰጠው በአሰልጣኝ ሳይሆን በቴኳንዶ ማኅበራት የተግባርና የጽሁፍ ፈተና ሲታለፍ ከኮሪያ የሚሰጥ ነው። "ወደ ሦስተኛ ዳን ዲግሪ ደርሻለሁ። የሚሻሻሉ ዲግሪዎች ናቸው። አሁን 3ኛ ዳን አለኝ። በዚህ ዓመት አራተኛውን ላገኝ እችላለሁ። ጊዜው ደርሷል" ይላል ከማል በቴኳንዶ የደረሰበትን ደረጃ ሲገልጽ። "ለእኔ ሲባል ምንም የተለየ የሚደረግልኝ ነገር የለም" የሚለው ከማል በዚህ ሂደት ውስጥ ሁሉ የተለያዩ ጉዳቶች ቢገጥሙትም ወደኋላ አላለም። ሦስተኛ ዳን የፈተኑት የውጭ አገር ሰዎች እንደነበሩ የሚኣስታውሰው ከማል፤ የሚተበቅበትን ካከናወነ በኋላ ፈታኞቹ ቆመው እንዳጨበጨቡለት ይናገራል። "የተፈተንነው 15 ነበርን፤ ስድስቱ ወደቁ። ዘጠኛችን አለፍን። የእኔ ውቴት ጥሩ ነበር። ቴኳንዶ የሚጠይቀውን የሥራ የፓተርን ሙሉ ሠርቼ ነው ያገኘሁት" ነው በማለት ተወዳድሮ ፈተና በማለፍ አሁን ላለበት መብቃቱን ይጠቅሳል። ከማል ቴኳንዶን ለሌሎች ማስተማር በሚያስብበት ጊዜ አካል ጉዳተኛ የቴኳንዶ አስተማሪ ስለሌለ 'ይሳካልኝ ይሆን?' እያለ ጥርጣሬ ቢገባውም የጓደኞቹና የአስተማሪው ማበረታቻ ድጋፍ ሆኖት በ2002 ዓ.ም ወረታ ውስጥ የማስተማሪያ ማዕከል ከፍቶ ማስተማር ጀመረ። ሆኖም እንዳሰበው ቀላል አልነበበረም። ለማስተማር የሚረዳውን ፈቃድ አላገኘም። መንቀሳቀሻ የሚሆን በቂ ገንዘብ እጁ ላይ አልነበረውም። ለመንቀሳቀሻ የሚሆን ገንዘብ ለማግኘትም ፎቶውን አስር አስር ብር ሸጦ ወደ ሁለት ሺህ ብር ገደማ ሲያገኝ ሥራውን ጀመረ። "ማስታወቂያ ስለጥፍ ግራ ገባቸው። 'ማነው የሚያስተመረው አሉኝ?' ሰዉ ለመማር ፈቃደኛ አልሆነም። የማውቃቸውን ጠርቼ በነጻ ማሠራት ጀመርኩኝ። አዳራሽም ዘመድ ፈቀደልኝ። አራት ወይም አምስት ሰው ይዤ ስሠራ ሌላው ሰው አዳራሽ ሞልቶ ያይ ነበር" ይላል። ከዚያም ሰልጣኞች መምጣት ሲጀምሩ ፈቃድ ማውጣት ስለነበረበት ወደ አዲስ አበባ ሄዶ በመፈተን በተግባርና በጽሑፍም አንደኛ በመውጣት ፈቃድ ማግኘቱን ይናገራል። ከስድስት ወር የቴኳንዶ ስልጠና በኋላ 40 ተማሪዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ አስመረቀ። የተለያዩ ፈተናዎችና ውጣ ውረዶች የገጠሙት ከማል ቃሲም ከወራታ ፓዌ ከዚያም ወደ ባሕር ዳር በመሄድ ስልጠና ሰጥቷል። በ2007 ዓ.ም ላይ አዲስ አበባ በተዋወቀው አንድ የውጭ አገር ዜጋ አማካይነት ባገኘው ድጋፍ ወደ ጀርመን በመሄድ ሰው ሠራሽ እግር ሲሰራለት በዚያውም የአንድ ወር ስልጠና አግኝቷል። ከማል ለዓመታት በዘለቀው የቴኳንዶ ስፖርት ህይወቱ የተለየ ደስታ የፈጠረለትን አጋጣሚ "የመጀመሪያዋውን ጥቁር ቀበቶ ስቀበል ነው" ሲል ያስረዳል። ባለትዳር እና የልጅ አባት የሆነው ከማል በቀጣይ ለቤተሰቡ "ጥሩ ነገር መስጠት" እንዲሁም የቴኳንዶ ስልጠና ሥራውን የበለጠ የማጠናከር አላማ አለው። ከዚህ በተጨማሪም በግል ህይወቱ ዙሪያ መጽሐፍና ዘጋቢ ፊልም ማዘጋጀት ይፈልጋል። አሁንም ብዙዎች ቴኳንዶ መሥራቱን እንደሚጠራጠሩ የሚናገረው ከማል "ለሰዎች ፎቶዬን ሳሳያቸው በፎቶ ጥበብ የተዘጋጀ ነው ይሉኛል። እኔም ወስጄ በተግባር እሰራሁ አሳያቸዋልሁ።" በቴኳንዶ ስፖርት ከ15 ዓመት በላይ የቆየው ከማል በወረታ፣ በፓዌ እና በባሕር ዳር በሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶችን አሰልጥኗል። በተጨማሪም በዘርፉ ውድድር ባይኖርም የተለያዩ መድረኮች ላይ ትዕንቶችን በማቅረብ ሽልማቶችን አግኝቷል። በመላው ኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች በሚሳተፉበት የፓራሎምፒክ ውድድር ላይ ደግሞ የአማራ ክልልን በመወከል በጦርና አሎሎ ውርወራ፤ በተሽከርካሪ ወንበር እንዲሁም ክብደት ማንሳት ተሳትፎ ከሃያ በላይ ሜዳሊያዎችን አጥልቋል። በቅርቡ በተመሠረተው የተሸከርካሪ ወንበር የቅርጫት ኳስ ውድድርም ተሳታፊ በመሆን ላይ ይገኛል። ከስፖርቱ ጎን ለጎን ከማል ቃሲም የተሽከርካሪ ወንበር ተጠቃሚዎችና የእግር አካል ጉዳተኞች ማኅበር ሊቀ መንበር በመሆን ያለውን ልምድ በማካፈል ላይ ይገኛል።
ኢትዮጵያ፡ አካል ጉዳተኛው የቴኳንዶ ስፖርት አሰልጣኝ ከማል ቃሲም የተወለደው ጎንደር ከተማ ነው። በህጻንነቱ ከቤተሰቦቹ ጋር በመሆን ወደ ወረታ አመሩ። "ተጫዋችና ደስተኛ" ነበርኩ የሚለው ከማል በአምስት ዓመቱ የገጠመው አደጋ ህይወቱን እስከወዲያኛው ቀይሮታል። "ጉዳት የደረሰብኝ በ1985 ዓ.ም ነበር። ወረታ ውስጥ ከእኩዮቼ ጋር ስጫወት በመንግሥት ሽግግር ወቅት ከአገልግሎት ውጪ ሆኖ በተተወ ታንክ ነው ጉዳት የደረሰብኝ።" በወቅቱ የአምስት ዓመት ታዳጊ የነበረው ከማል ታንኩ ላይ እየተጫወተ ሳለ "አፈሙዙን በሚያሽከረክረው ክፍተት መሐል አንድ እግሬ ሆኖ ለመሻገር ስሞክር አንደኛው እግሬ አፈሙዝ ስር ገባ። በዚያው ቅጽበት አፈሙዙ በሚዞርበት ጊዜ እግሬ ላይ አደጋው ደረሰ" ሲል ያስታውሳል። ከወረታ ወደ ባሕር ዳር ለህክምና ተወስዶ ለወራት እዚያው ከቆየ በኋላ ወደቀየው ተመለሰ። በድንገተኛው አደጋ ጉዳት የደረሰበት ታዳጊው ከማል ከህክምናው ሲመለስ ቀኝ እግሩ ጉልበቱ ላይ ተቆርጦ በሁለት ምርኩዞች ተደግፎ ነበር። "ህይወት እንደ አዲስ ተጀመረ። ያኛው ሌላ አሁን ደግሞ ሌላ ህይወት" የሚለው ከማል "በአካባቢያችን ሌላ አካል ጉዳተኛ አልነበረም። እንኳን በዚያ ወቅት አሁን እንኳን ማኅረሰቡ ውስጥ ስለአካል ጉዳተኝነት ያለው አመለካከት ፈታኝ ነበር። መውጣት መግባት መጫወት አልችልም ነበር" ይላል። በታዳጊነቱ በደረሰበት አደጋ አካል ጉዳተኛ የሆነው ከማል ተደራራቢ ችግሮችን መጋፈጥ ጀመረ። ሌላ ችግር ቤተሰቡ ውስጥ ተከሰተ፤ አባት እና እናቱ ተለያይተው በተለያየ ቦታ በየፊናቸው ህይወታቸውን ለመምራት ሲወስኑ፤ እሱም ከእናቱ ተለይቶ ከአባቱ ጋር መኖር ጀመረ። አደጋው ከደረሰበት በኋላ ከማል ሰባት ዓመት ሲሆነው ወደ ትምህርት ቤት መሄድ ጀመረ። ነገር ግን "ሙሉ ለሙሉ ህይወቴ ስለተቀየረ ትምህርት ቤት እረብሽ፣ እነጫነጭ ነበር" ሲል በጸባዩ ላይ ለውጥ መከሰቱን ያስታውሳል። ለአካል ጉዳተኞች የሚመች መሠረት ልማት አለመኖር እና ህብረተሰቡ ስለ አካል ጉዳተኝነት ያለው አስተሳሰብም ህይወቱን ከባድ አድርጎት ነበር። "ከባድ ነው። ትምህርት ቤት ነጻ ሆኜ መጫወት አልችልም። ትልልቆቹም ባለፍኩ ባገደምኩ ቁጥር ከንፈር መምጠጥ፤ በዚህ እድሜው እንደዚህ ሆኖ እያሉ ሲናገሩ መስማት ተስፋ ያስቆርጣሉ" ይላል። በሁለት ክራንች መንቀሳቀስም መጫወትም አልመችህ ሲለው አንዱን ክራንች በመተው እንደልቡ ለመሆን ሞከረ። በዚህም ለመንቀሳቀስ በሚያደርገው ሙከራ በተደጋጋሚ በመውደቅ እግሩ መጎዳት እና መድማት ይገጥመው ጀመር። በዚህ መልኩ እስከ ስድስተኛ ክፍል ወረታ ውስጥ ተማረ። በወቅቱ "ጸባዬ አስቸጋሪ እረባሽና አልቃሻ ሆኜ። ከባድ ጊዜ ነበር ያሳለፍኩት። ከልጆች ጋር ጋር መግባባት እየተቸገርኩ እጣላ ነበር። አንዳንድ ጊዜም በክራንች እስከመማታት እደርስ ነበር" የሚለው ከማል 6ኛ ክፍል ሲደርስ ወደ እናቱ ተመልሶ ጎንደር መኖር ጀመረ። ጎንደር ሌሎች የአካል ጉዳተኞችን ተዋወቀ ስለዚህም ከወረታ ብቸኝነቱ በተወሰነ ደረጃ ተላቀቀ። ነገር ግን እናቱ ሥራ ስላልነበራቸው የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ የሚያገኙት አንድ አካል ጉዳተኞችን ከሚረዳ ድርጅት ነበር። "ለአካል ጉዳተኞች የሚሰጠውን ስንዴ እና ዘይት በችግር ላይ ለነበረችው እናቴ አመጣላት ነበር። እዚያ ሌሎች አካል ጉዳተኞችን ባገኝም ጥሩ ስሜት አይሰማኝም ነበር። የዝቅትኝነት ስሜት ይሰማኝ ጀመር" የሚለው ከማል 'ረጂ እንጂ ተረጂ አልሆንም' ብሎ እርዳታውን መቀበል አቆመ። ስምንተኛ ክፍል ደርሶ ለማለፍ የሚያስችለውን ውጤት ባለማምጣቱ ለመድገም ተገደደ። በቀጣዩ ዓመት ደግሞ ሠው ሠራሽ እግር ለማሠራት ወደ ደሴ አምርቶ ለወራት እዚያው በመቆየቱ ስምንተኛ ክፍልን በማታው ክፍለ ጊዜ መማር ጀመረ። የማታ ተማሪ መሆኑ እንዲሁም ቀን ላይ የሚሰራው ነገር ስላልነበረው አጋጣሚው ከቴኳንዶ ስፖርት ጋር እንዲተዋወቅ ዕድል ፈጠረለት። ከጓደኛው ጋር ቴኳንዶ የሚሰራበት ቦታ በመሄድ ስፖርቱን የተመለከተው ከማል፤ ለሰዓታት ከተመለከተ በኋላ አንዳች ነገር ውስጡ ተፈጠረ። ከማልን የተመለከተው የቴኳንዶ አሰልጣኙ ስሜቱን ጠይቆት ፍላጎት ካለው በነጻ እንዲማር ስለፈቀደለት በቴኳንዶ ፍቅር ወደቀ። "እየወደቅኩ እየተነሳሁ ከምንም በላይ በአስተማሪዬ ድጋፍ እና በጓደኞቼ አይዞህ ባይነት ቴኳንዶውን መለማመድ ቀጠልኩ" ነገር ግን በዙሪያው ካሉ ሰዎችና ከቤተሰቡ ጭምር 'ምን ያደረግልሃል?' ይሉት ነበር። ሆኖም እንዳሰበው ቀላል አልነበረም። ከወላጆቹ በስተቀር ሁሉም 'ምን ሊያደርግልህ?' የሚል ጥያቄ እያቀረቡ ተስፋ አስቆራጭ አስተያት ሰጥተውታል። "በአንድ እግር ቴኳንዶ ከባድ ነው። ወድቄ እሰበራለሁ። እጄን ተሰብሬያለሁ። የቀረችውን አንድ እግሬን ተሰብሬ 2 ወር በተኛሁበት ጊዜ የነቀፉኝ ሰዎች ደስ አላቸው። እኔ ግን እስከ ህይወቴ ፍጻሜ ስፖርቱን ከመሥራት ማንም እንደማያግደኝ አወቅኩኝ።" ከማል ቴኳንዶ መጀመሩ ብዙ ነገሮችን እንዲለውጥ ምክንያት ሆኖታል። አንደኛው ደግሞ ክራንቹን የሚጠቀምበትን ዘዴ መቀየሩ እና በሚመቸው መንገድ እንዲያስተካክለው ማድረጉ ነው። "ክራንቹ መጀመሪያ ላይ ብረት ብቻ ነው። ቴኳንዶ ይህንን ምቹ እንዳደርግ ረድቶኛል። ይኸውም እንደጫማ ምቹ አድርጌ እንድሠራ አድርጎኛል። እንደጀመርኩ እግሬን ሳነሳ ክራንቹ ተሰብሮ ወድቄያለሁ። ሳስተምርም ወደቄ አውቃለሁ። የውሃ ቱቦ ነው በየጊዜው ቼክ አደርገዋለሁ። በየጊዜው እቀይረዋለሁ አሁን በምቾት እሠራለሁ።" ቴኳንዶ በተለያዩ የቀበቶ ቀለሞች የሚሰጡ ደጃዎች አሉት። ጀማሪዎች በነጭ ቀበቶ ይጀምራሉ። ቢጫ፣ አረንጓዴ፣ ቀይ እና ጥቁር። እነዚህን ቀበቶዎች አንድ ሰልጣኝ የተለያዩ የስልጠናዎችን ካጠናቀቀ በኋላ ከአሰልጣኙ የሚያገኘው ይሆናል። ከዚያ በኋላ ደግሞ በዲግሪ የሚገለጹና ዳን የሚባሉ ዘጠኝ ደረጃዎች አሉ። ዳን የሚሰጠው በአሰልጣኝ ሳይሆን በቴኳንዶ ማኅበራት የተግባርና የጽሁፍ ፈተና ሲታለፍ ከኮሪያ የሚሰጥ ነው። "ወደ ሦስተኛ ዳን ዲግሪ ደርሻለሁ። የሚሻሻሉ ዲግሪዎች ናቸው። አሁን 3ኛ ዳን አለኝ። በዚህ ዓመት አራተኛውን ላገኝ እችላለሁ። ጊዜው ደርሷል" ይላል ከማል በቴኳንዶ የደረሰበትን ደረጃ ሲገልጽ። "ለእኔ ሲባል ምንም የተለየ የሚደረግልኝ ነገር የለም" የሚለው ከማል በዚህ ሂደት ውስጥ ሁሉ የተለያዩ ጉዳቶች ቢገጥሙትም ወደኋላ አላለም። ሦስተኛ ዳን የፈተኑት የውጭ አገር ሰዎች እንደነበሩ የሚኣስታውሰው ከማል፤ የሚተበቅበትን ካከናወነ በኋላ ፈታኞቹ ቆመው እንዳጨበጨቡለት ይናገራል። "የተፈተንነው 15 ነበርን፤ ስድስቱ ወደቁ። ዘጠኛችን አለፍን። የእኔ ውቴት ጥሩ ነበር። ቴኳንዶ የሚጠይቀውን የሥራ የፓተርን ሙሉ ሠርቼ ነው ያገኘሁት" ነው በማለት ተወዳድሮ ፈተና በማለፍ አሁን ላለበት መብቃቱን ይጠቅሳል። ከማል ቴኳንዶን ለሌሎች ማስተማር በሚያስብበት ጊዜ አካል ጉዳተኛ የቴኳንዶ አስተማሪ ስለሌለ 'ይሳካልኝ ይሆን?' እያለ ጥርጣሬ ቢገባውም የጓደኞቹና የአስተማሪው ማበረታቻ ድጋፍ ሆኖት በ2002 ዓ.ም ወረታ ውስጥ የማስተማሪያ ማዕከል ከፍቶ ማስተማር ጀመረ። ሆኖም እንዳሰበው ቀላል አልነበበረም። ለማስተማር የሚረዳውን ፈቃድ አላገኘም። መንቀሳቀሻ የሚሆን በቂ ገንዘብ እጁ ላይ አልነበረውም። ለመንቀሳቀሻ የሚሆን ገንዘብ ለማግኘትም ፎቶውን አስር አስር ብር ሸጦ ወደ ሁለት ሺህ ብር ገደማ ሲያገኝ ሥራውን ጀመረ። "ማስታወቂያ ስለጥፍ ግራ ገባቸው። 'ማነው የሚያስተመረው አሉኝ?' ሰዉ ለመማር ፈቃደኛ አልሆነም። የማውቃቸውን ጠርቼ በነጻ ማሠራት ጀመርኩኝ። አዳራሽም ዘመድ ፈቀደልኝ። አራት ወይም አምስት ሰው ይዤ ስሠራ ሌላው ሰው አዳራሽ ሞልቶ ያይ ነበር" ይላል። ከዚያም ሰልጣኞች መምጣት ሲጀምሩ ፈቃድ ማውጣት ስለነበረበት ወደ አዲስ አበባ ሄዶ በመፈተን በተግባርና በጽሑፍም አንደኛ በመውጣት ፈቃድ ማግኘቱን ይናገራል። ከስድስት ወር የቴኳንዶ ስልጠና በኋላ 40 ተማሪዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ አስመረቀ። የተለያዩ ፈተናዎችና ውጣ ውረዶች የገጠሙት ከማል ቃሲም ከወራታ ፓዌ ከዚያም ወደ ባሕር ዳር በመሄድ ስልጠና ሰጥቷል። በ2007 ዓ.ም ላይ አዲስ አበባ በተዋወቀው አንድ የውጭ አገር ዜጋ አማካይነት ባገኘው ድጋፍ ወደ ጀርመን በመሄድ ሰው ሠራሽ እግር ሲሰራለት በዚያውም የአንድ ወር ስልጠና አግኝቷል። ከማል ለዓመታት በዘለቀው የቴኳንዶ ስፖርት ህይወቱ የተለየ ደስታ የፈጠረለትን አጋጣሚ "የመጀመሪያዋውን ጥቁር ቀበቶ ስቀበል ነው" ሲል ያስረዳል። ባለትዳር እና የልጅ አባት የሆነው ከማል በቀጣይ ለቤተሰቡ "ጥሩ ነገር መስጠት" እንዲሁም የቴኳንዶ ስልጠና ሥራውን የበለጠ የማጠናከር አላማ አለው። ከዚህ በተጨማሪም በግል ህይወቱ ዙሪያ መጽሐፍና ዘጋቢ ፊልም ማዘጋጀት ይፈልጋል። አሁንም ብዙዎች ቴኳንዶ መሥራቱን እንደሚጠራጠሩ የሚናገረው ከማል "ለሰዎች ፎቶዬን ሳሳያቸው በፎቶ ጥበብ የተዘጋጀ ነው ይሉኛል። እኔም ወስጄ በተግባር እሰራሁ አሳያቸዋልሁ።" በቴኳንዶ ስፖርት ከ15 ዓመት በላይ የቆየው ከማል በወረታ፣ በፓዌ እና በባሕር ዳር በሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶችን አሰልጥኗል። በተጨማሪም በዘርፉ ውድድር ባይኖርም የተለያዩ መድረኮች ላይ ትዕንቶችን በማቅረብ ሽልማቶችን አግኝቷል። በመላው ኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች በሚሳተፉበት የፓራሎምፒክ ውድድር ላይ ደግሞ የአማራ ክልልን በመወከል በጦርና አሎሎ ውርወራ፤ በተሽከርካሪ ወንበር እንዲሁም ክብደት ማንሳት ተሳትፎ ከሃያ በላይ ሜዳሊያዎችን አጥልቋል። በቅርቡ በተመሠረተው የተሸከርካሪ ወንበር የቅርጫት ኳስ ውድድርም ተሳታፊ በመሆን ላይ ይገኛል። ከስፖርቱ ጎን ለጎን ከማል ቃሲም የተሽከርካሪ ወንበር ተጠቃሚዎችና የእግር አካል ጉዳተኞች ማኅበር ሊቀ መንበር በመሆን ያለውን ልምድ በማካፈል ላይ ይገኛል።
https://www.bbc.com/amharic/news-54507780
5sports
የለንደን ደርቢ፡ ሁለቱ አሰልጣኞች ለምን ቀይ ካርድ ተመዘዘባቸው?
ስታምፎርድ ብሪጅ ለአሰልጣኞች ፍጥጫ እና የደስታ መፈንጫ ቦታ መሆንን ቀጥሎበታል። የቼልሲው አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል እና የቶተንሃሙ አቻቸው አንቶኒዮ ኮንቴ ቡጢ ቀረሽ ግብግብ ውስጥ በመግባታቸው ሁለቱም ከጨዋታው ፍጻሜ በኋላ ቀይ ካርድ ተመዞባቸዋል። “አየሩም፣ ሜዳውም፣ ጨዋታውና ተቀያሪ ቦታውም ሁሉም ሞቅ ያለ ነበር፥ እንዲህ ዓይነት ጨዋታ በውድድሩ ጅማሬ ላይ መሆኑ ያስደስታል” ሲሉ ቱሄል ከጨዋታ በኋላ ፈገግ ብለው አስተያየት ሰጥተዋል። በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ፍትጊያ የበዛበት ጨዋታ እሰከ 68ኛው ደቂቃ ድረስ የተረጋጋ ይመስል ነበር። ካሊዱ ኩሊባሊ ክለቡ ቼልሲን መሪ ማድረግ ችሎ ነበር። ፒዬር-ኤሚል ሆቢዬር ቶተንሃምን አቻ ያደረገች ጎል ማስቆጠሩ የጨዋታውን መልክ ቀየረች። ከጎሉ ህጋዊነት ጋር ተያይዞ ሁለቱ አሰልጣኞች ተፋጠው በአራተኛው ዳኛ ገላጋይነት ተለያዩ። ሁለቱም የማስጠንቀቂያ ቢጫ ካርድ ተመዘዘባቸው። ጎሉ ከመቆጠሩ በፊት ካይ ሃቨርትዝ ጥፋት ተፈጽሞበታል የሚል ነው የቼልሲ ክስ። የቶተንሃሙ ሪቻርለሰን ጎሉ ሲቆጠር ከጨዋታ ክልል ውጭ ከመሆን ባለፈ የግብ ጠባቂውን እይታ ከልሎታል የሚልም ቅሬታ በቼልሲ ቀርቦ ነበር። ከዘጠኝ ደቂቃ በኋላ ሪስ ጀምስ በድጋሚ ቼልሲን ቀዳሚ አደረገ። ቱሄል በደስታ እየቦረቁ ሲሮጡ ታዩ። በተጨማሪ ስድስት ደቂቃዎች ሃሪ ኬን በጨዋታም በጎልም ተበልጦ የቆየውን ቡድኑን አቻ ለማድረግ በቃ። የመሐል ዳኛው ጨዋታው መጠናቀቁን የሚያበስረውን ፊሽካ አሰሙ። እንደተለመደው አሰልጣኞቹ ተጨባብጠው ሊለያዩ ነው ሲባል ተጨባብጠው የእጃቸውን ጥንካሬ ይፈትሹ ገቡ። ይህ ደግሞ ወደ ግብግብ አምርቶ ሁለቱም ቀይ ካር ለማየት በቁ። ኬን ከማስቆጠሩ በፊት ክርስቲያን ሮሜሮ የቼልሲውን አዲስ ፈራሚ ማርክ ኩኩሬላን ጸጉር ስቧል የሚል ሌላ ቅሬታ በቼልሲ ቀረቧል። “ሁለቱም ጎሎች በቫር ዘመን መጽደቅ አልበረባቸውም። ዳኛው ትልቅ ሚና መጫወት ነበረባቸው” ሲሉ ቱሄል ለቢቢሲ ገልጸዋል። “የመጀመሪያው ጎል እንዴት ከጨዋታ ውጭ እንዳልሆነ እና ሁለተኛው ደግሞ ቀይ ካርድ አለመሆኑ አልገባኝም” ብለዋል። የመሐል ዳኛው ቴይለር ወደፊት የቼልሲን ጨዋታ መምራት የለባቸውም ሲሉም ቅሬታ አሰምተዋል። ሲጨባበጡም የመከባበር ነገር ከኮንቴ በኩል እንዳላዩ የቼልሲው አሰልጣኝ ገልጸዋል። “ሰው ሲጨባበጥ ዓይን ለዓይን መተያየት ያለብን ይመስለኛል። ብቻ ብዙ ነገሮች ትክክል አልነበሩም” ብለዋል። ኮንቴ ግን በጉዳዩ ላይ ብዙም ማውራት የፈለጉ አይመስሉም። “ችግር ካለ በእኔ እና በእሱ መካከል ነው” ብለዋል። “በተፈጠረው ክስተት ተዝናንተናል። በሚቀጥለው ጊዜ ስንጨባበጥ ችግሩን እንፈታዋለን። እኔም በቦታዬ እሱም በቦታው እንቀመጣለን” ሲሉ አክለዋል። ቱሄል ሁለተኛው ጎል ሲቆጠር እየዘለሉ ደስታቸውን በመግለጻቸው ግማሽ ይቅርታ ጠይቀዋል። “መሐል ላይ ማድረግ እንደሌለብኝ ተሰምቶን ነበር። ግን አንዳንድ ጨዋታዎች እንደዚህ ያደርጋሉ” ብለዋል። ፕሪሚየር ሊጉ ከተጀመረ በኋላ ቶተንሃም ስታምፎርድ ብሪጅ አይቀናውም። ወደ ሰማያዊዎቹ ሜዳ አቅንቶ 22 ጊዜ ተሸንፏል። አንድ ጊዜ ብቻ ሲያሸንፍ 12 ጊዜ አቻ ተለያይቷል። “ብዙ ጊዜ በስታፎርድ ብሪጅ አይቀናንም። ስለዚህ ባለቀ ሰዓት ጎል አስቆጥረን አንድ ነጥብ ማግኘታችን አስደስቶናል” ያለው የቶተንሃሙ አምበል ሃሪ ኬን ነው። “ቀይ ካርዶቹን መመልከት ያሳዝናል። በስሜት የተሞላ የለንደን ደርቢ ነበር። ሁለቱም ቡድኖች ለማሸነፍ ተጫውተዋል። አንዳንዴ ተመሳሳይ ነገር ያጋጥማል” ብሏል። ሌላ ውድድር ካላገናኛቸው በስተቀር የትናንቱ ጨዋታ በየካቲት የሚደረገው የሁለቱ ቡድኖች ግጥሚያ ከወዲሁ በጉጉት እንዲጠበቅ በር ከፍቷል።
የለንደን ደርቢ፡ ሁለቱ አሰልጣኞች ለምን ቀይ ካርድ ተመዘዘባቸው? ስታምፎርድ ብሪጅ ለአሰልጣኞች ፍጥጫ እና የደስታ መፈንጫ ቦታ መሆንን ቀጥሎበታል። የቼልሲው አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል እና የቶተንሃሙ አቻቸው አንቶኒዮ ኮንቴ ቡጢ ቀረሽ ግብግብ ውስጥ በመግባታቸው ሁለቱም ከጨዋታው ፍጻሜ በኋላ ቀይ ካርድ ተመዞባቸዋል። “አየሩም፣ ሜዳውም፣ ጨዋታውና ተቀያሪ ቦታውም ሁሉም ሞቅ ያለ ነበር፥ እንዲህ ዓይነት ጨዋታ በውድድሩ ጅማሬ ላይ መሆኑ ያስደስታል” ሲሉ ቱሄል ከጨዋታ በኋላ ፈገግ ብለው አስተያየት ሰጥተዋል። በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ፍትጊያ የበዛበት ጨዋታ እሰከ 68ኛው ደቂቃ ድረስ የተረጋጋ ይመስል ነበር። ካሊዱ ኩሊባሊ ክለቡ ቼልሲን መሪ ማድረግ ችሎ ነበር። ፒዬር-ኤሚል ሆቢዬር ቶተንሃምን አቻ ያደረገች ጎል ማስቆጠሩ የጨዋታውን መልክ ቀየረች። ከጎሉ ህጋዊነት ጋር ተያይዞ ሁለቱ አሰልጣኞች ተፋጠው በአራተኛው ዳኛ ገላጋይነት ተለያዩ። ሁለቱም የማስጠንቀቂያ ቢጫ ካርድ ተመዘዘባቸው። ጎሉ ከመቆጠሩ በፊት ካይ ሃቨርትዝ ጥፋት ተፈጽሞበታል የሚል ነው የቼልሲ ክስ። የቶተንሃሙ ሪቻርለሰን ጎሉ ሲቆጠር ከጨዋታ ክልል ውጭ ከመሆን ባለፈ የግብ ጠባቂውን እይታ ከልሎታል የሚልም ቅሬታ በቼልሲ ቀርቦ ነበር። ከዘጠኝ ደቂቃ በኋላ ሪስ ጀምስ በድጋሚ ቼልሲን ቀዳሚ አደረገ። ቱሄል በደስታ እየቦረቁ ሲሮጡ ታዩ። በተጨማሪ ስድስት ደቂቃዎች ሃሪ ኬን በጨዋታም በጎልም ተበልጦ የቆየውን ቡድኑን አቻ ለማድረግ በቃ። የመሐል ዳኛው ጨዋታው መጠናቀቁን የሚያበስረውን ፊሽካ አሰሙ። እንደተለመደው አሰልጣኞቹ ተጨባብጠው ሊለያዩ ነው ሲባል ተጨባብጠው የእጃቸውን ጥንካሬ ይፈትሹ ገቡ። ይህ ደግሞ ወደ ግብግብ አምርቶ ሁለቱም ቀይ ካር ለማየት በቁ። ኬን ከማስቆጠሩ በፊት ክርስቲያን ሮሜሮ የቼልሲውን አዲስ ፈራሚ ማርክ ኩኩሬላን ጸጉር ስቧል የሚል ሌላ ቅሬታ በቼልሲ ቀረቧል። “ሁለቱም ጎሎች በቫር ዘመን መጽደቅ አልበረባቸውም። ዳኛው ትልቅ ሚና መጫወት ነበረባቸው” ሲሉ ቱሄል ለቢቢሲ ገልጸዋል። “የመጀመሪያው ጎል እንዴት ከጨዋታ ውጭ እንዳልሆነ እና ሁለተኛው ደግሞ ቀይ ካርድ አለመሆኑ አልገባኝም” ብለዋል። የመሐል ዳኛው ቴይለር ወደፊት የቼልሲን ጨዋታ መምራት የለባቸውም ሲሉም ቅሬታ አሰምተዋል። ሲጨባበጡም የመከባበር ነገር ከኮንቴ በኩል እንዳላዩ የቼልሲው አሰልጣኝ ገልጸዋል። “ሰው ሲጨባበጥ ዓይን ለዓይን መተያየት ያለብን ይመስለኛል። ብቻ ብዙ ነገሮች ትክክል አልነበሩም” ብለዋል። ኮንቴ ግን በጉዳዩ ላይ ብዙም ማውራት የፈለጉ አይመስሉም። “ችግር ካለ በእኔ እና በእሱ መካከል ነው” ብለዋል። “በተፈጠረው ክስተት ተዝናንተናል። በሚቀጥለው ጊዜ ስንጨባበጥ ችግሩን እንፈታዋለን። እኔም በቦታዬ እሱም በቦታው እንቀመጣለን” ሲሉ አክለዋል። ቱሄል ሁለተኛው ጎል ሲቆጠር እየዘለሉ ደስታቸውን በመግለጻቸው ግማሽ ይቅርታ ጠይቀዋል። “መሐል ላይ ማድረግ እንደሌለብኝ ተሰምቶን ነበር። ግን አንዳንድ ጨዋታዎች እንደዚህ ያደርጋሉ” ብለዋል። ፕሪሚየር ሊጉ ከተጀመረ በኋላ ቶተንሃም ስታምፎርድ ብሪጅ አይቀናውም። ወደ ሰማያዊዎቹ ሜዳ አቅንቶ 22 ጊዜ ተሸንፏል። አንድ ጊዜ ብቻ ሲያሸንፍ 12 ጊዜ አቻ ተለያይቷል። “ብዙ ጊዜ በስታፎርድ ብሪጅ አይቀናንም። ስለዚህ ባለቀ ሰዓት ጎል አስቆጥረን አንድ ነጥብ ማግኘታችን አስደስቶናል” ያለው የቶተንሃሙ አምበል ሃሪ ኬን ነው። “ቀይ ካርዶቹን መመልከት ያሳዝናል። በስሜት የተሞላ የለንደን ደርቢ ነበር። ሁለቱም ቡድኖች ለማሸነፍ ተጫውተዋል። አንዳንዴ ተመሳሳይ ነገር ያጋጥማል” ብሏል። ሌላ ውድድር ካላገናኛቸው በስተቀር የትናንቱ ጨዋታ በየካቲት የሚደረገው የሁለቱ ቡድኖች ግጥሚያ ከወዲሁ በጉጉት እንዲጠበቅ በር ከፍቷል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cjj4pl2840go
3politics
ለመጀመሪያ ጊዜ ለዋይት ሀውስ ጥቁር ሴት ቃል አቀባይ ተሾመች
ካሪን ጄን-ፒይር የመጀመሪያዋ ጥቁር፣ ሴት፣ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ቃል አቀባይ ሆና በፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ተሰይማለች። የ44 ዓመቷ ካሪን ቦታውን የምትረከበው ከጄን ሳኪ ነው። ከቀጣዩ ሳምንት በኋላ ከዋይት ሀውስ ዘገባ ለሚሠሩ ጋዜጠኞች መረጃ መስጠት ትጀምራለች። ጄን ሳኪ ግራ ዘመሙ ኤምኤስኤንቢሲ ውስጥ በቅርቡ ሥራ እንደምትጀምር ተገልጿል። ቦታዋን የምትረከበውን ቃል አቀባይ "በሥነ ምግባር የታነጸች ድንቅ ሴት" ስትል ገልጻለች። "የራሷ የአሠራር ስልት አላት። ድንቅና የላቀ ችሎታዋን እንደምታሳይ አልጠራጠርም" ስትለም አክላለች። የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ የአሜሪካ መንግሥት ፊት ሆኖ ለአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን እንዲሁም ለመላው ዓለምም ይታያል። ማንኛውም ፖለቲካዊ ቀውስ ወይም ብሔራዊ አደጋ ሲከሰት ቀድመው የሚታዮት እነዚህ ቃል አቀባዮች ናቸው። ቃል አቀባዮች ፖሊሲ ባያረቁም አንድ የአሜሪካ አስተዳደር በሕዝቡ ዘንድ በምን መንገድ እንደሚታይ ይቀርጻሉ። የባይደን አስተዳደር እስከ ዛሬ ድረስ በፖለቲካው መድረክ ገሸሽ የተደረጉ ጥቁር ሴቶችን በማሳተፍ ቀጥሏል። ምክትል ፕሬዝዳንቷ ካሚላ ሐሪስ፣ የአገር ውስጥ ፖሊሲ ካውንስል ቃል አቀባይ ሱዛን ራይስ፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ኬታንጂ ብራውን ጃክሰን፣ በተባበሩት መንግሥታት የአሜሪካ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድን እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል። ካሪን ጄን-ፒይር ከዚህ ቀደም በኤምኤስኤንቢሲ ተንታኝ ነበረች። በፖለቲካው የሁለት አሥርታት ተሞክሮ አዳብራለች። በፍሬንች ካረቢያኗ ማርቲኒኪው ደሴት ተወልዳ ኒው ዮርክ አድጋለች። በኦባማ አስተዳደር ቁልፍ ቦታ ከነበራቸው አንዷ ናት። እአአ በ2016 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሲካሄድ ሙቭኦን የተባለው ብሔራዊ ንቅናቄ ቃል አቀባይ ነበረች። ባይደን ካሚላ ሐሪስን ምክትላቸው አድርገው ከመረጡ በኋላ በቃል አቀባይነት ሠርታለች። የፊታችን ጥቅምት በአሜሪካ የአስተዳደር አጋማሽ ምርጫ ይካሄዳል። ይህም ባይደን ፕሬዝዳንት ሆነው የሚቀጥሉበት ዓመታት በምን አቅጣጫ እንደሚጓዙ ይወስናል።
ለመጀመሪያ ጊዜ ለዋይት ሀውስ ጥቁር ሴት ቃል አቀባይ ተሾመች ካሪን ጄን-ፒይር የመጀመሪያዋ ጥቁር፣ ሴት፣ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ቃል አቀባይ ሆና በፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ተሰይማለች። የ44 ዓመቷ ካሪን ቦታውን የምትረከበው ከጄን ሳኪ ነው። ከቀጣዩ ሳምንት በኋላ ከዋይት ሀውስ ዘገባ ለሚሠሩ ጋዜጠኞች መረጃ መስጠት ትጀምራለች። ጄን ሳኪ ግራ ዘመሙ ኤምኤስኤንቢሲ ውስጥ በቅርቡ ሥራ እንደምትጀምር ተገልጿል። ቦታዋን የምትረከበውን ቃል አቀባይ "በሥነ ምግባር የታነጸች ድንቅ ሴት" ስትል ገልጻለች። "የራሷ የአሠራር ስልት አላት። ድንቅና የላቀ ችሎታዋን እንደምታሳይ አልጠራጠርም" ስትለም አክላለች። የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ የአሜሪካ መንግሥት ፊት ሆኖ ለአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን እንዲሁም ለመላው ዓለምም ይታያል። ማንኛውም ፖለቲካዊ ቀውስ ወይም ብሔራዊ አደጋ ሲከሰት ቀድመው የሚታዮት እነዚህ ቃል አቀባዮች ናቸው። ቃል አቀባዮች ፖሊሲ ባያረቁም አንድ የአሜሪካ አስተዳደር በሕዝቡ ዘንድ በምን መንገድ እንደሚታይ ይቀርጻሉ። የባይደን አስተዳደር እስከ ዛሬ ድረስ በፖለቲካው መድረክ ገሸሽ የተደረጉ ጥቁር ሴቶችን በማሳተፍ ቀጥሏል። ምክትል ፕሬዝዳንቷ ካሚላ ሐሪስ፣ የአገር ውስጥ ፖሊሲ ካውንስል ቃል አቀባይ ሱዛን ራይስ፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ኬታንጂ ብራውን ጃክሰን፣ በተባበሩት መንግሥታት የአሜሪካ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድን እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል። ካሪን ጄን-ፒይር ከዚህ ቀደም በኤምኤስኤንቢሲ ተንታኝ ነበረች። በፖለቲካው የሁለት አሥርታት ተሞክሮ አዳብራለች። በፍሬንች ካረቢያኗ ማርቲኒኪው ደሴት ተወልዳ ኒው ዮርክ አድጋለች። በኦባማ አስተዳደር ቁልፍ ቦታ ከነበራቸው አንዷ ናት። እአአ በ2016 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሲካሄድ ሙቭኦን የተባለው ብሔራዊ ንቅናቄ ቃል አቀባይ ነበረች። ባይደን ካሚላ ሐሪስን ምክትላቸው አድርገው ከመረጡ በኋላ በቃል አቀባይነት ሠርታለች። የፊታችን ጥቅምት በአሜሪካ የአስተዳደር አጋማሽ ምርጫ ይካሄዳል። ይህም ባይደን ፕሬዝዳንት ሆነው የሚቀጥሉበት ዓመታት በምን አቅጣጫ እንደሚጓዙ ይወስናል።
https://www.bbc.com/amharic/news-61343905
0business
ቀጣዩ 8.5 በመቶ የኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት እድገት በባለሙያዎች ዕይታ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እንደሚያደርገው በጠቅላይ ሚኒስቴሩ ፅህፈት ቤት አዳራሽ ሐሙስ ሰኔ አራት ቀን 16ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዶ 476.1 ቢሊዮን ብር ገደማ ይሆናል በተባለው በቀጣዩ የበጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ላይ ተወያይቷል። ከዚሁ ውስጥ በመንግሥት ረቂቅ በጀት መሰረት 176 ቢሊዮን ብር ገደማ የሚሆነው ለክልሎች የሚሰጥ ሲሆን፤ የፌዴራል መንግሥት ደግሞ ለመደበኛ ወጪዎቹ 133 ቢሊዮን ብር፣ ለካፒታል ወጪዎቹ 160 ቢሊዮን ብር ይደርሰዋል መባሉን የአገር ውስጥ የብዙሃን መገናኛ አውታሮች ዘግበዋል። ረቂቅ በጀቱን በሚመለከት ማብራሪያ የሰጡት የፌዴራል መንግሥቱ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ቀጣዩ የበጀት ዓመት በኢትዮጵያ 8.5 በመቶ ዕድገት እንደሚመዘገብ ለሕዝብ እንደራሴዎቹ ተናግረዋል። ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ኢትዮጵያ 9 በመቶ የምጣኔ ሃብት ዕድገትን እጠብቃለሁ ብላ ነበር። ዓለም አቀፉ ወረርሽኝ ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ ላይ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም አገራት ምጣኔ ሃብት ላይ ከባድ የሚባል ጫናን እየፈጠረ ባለበትና የዚህ በሽታ ተጽዕኖ ለዓመታት ባይሆን ለቀጣይ ረዥም ወራት እንሚቀጥል እየተነገረ ባለበት ሁኔታ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በዚህ መጠን ሊያድግ የሚችልበት ዕድል መኖሩ እያነጋገረ ነው። የቀጣዩን የበጀት ዓመት የአገሪቱን በጀትና ተጠባቂ ዕድገትን በተመለከተ ቢቢሲ የምጣኔ ሃብት ባለሞያዎቹን አለማየሁ ገዳን (ዶ/ር) እና አቶ ዋሲሁን በላይ ያላቸውን ዕይታ ጠይቋል። የምጣኔ ሃብት ተንታኙ አቶ ዋሲሁን በላይ ባለፈው የበጀት ዓመት ቀርቦ ከነበረው 386.9 ቢሊዮን ብር ጋር ሲነፃፀር ዘንድሮ የቀረበው በጀት ከፍ ያለ ብልጫ ያለው ቢመስልም፤ በመገባደድ ላይ ያለው የበጀት ዓመት ከመጠናቀቁ በፊት መንግሥት 28 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ተጨማሪ በጀት ማስፀደቁን ጨምረው በማስታወስ አሁንም ጭማሪው የሚታይ መሆኑን ይጠቅሳሉ። ነገር ግን የቀጣይ ዓመት የአገሪቱ በጀት ከመጨመሩ ጎን ለጎን ይመዘገባል ተብሎ በገንዘብ ሚኒስትሩ የቀረበው የተጠባቂ ዕድገት ቁጥር ምጣኔ ሃብታዊ እድገት ላይ ባለሞያዎቹ ጥያቄዎችን ያነሳሉ። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በዓለም ዙርያ ምጣኔ ሃብቶችን በሚገዳደርበት እና "በርካታ አገራት ዕድገታቸው የቁልቁል እንደሚሆን በተነበዩበት ወቅት፤ ከስምንት በመቶ የሚሻገር ዕድገትን መጠበቅ አስቸጋሪ ነው" ይላሉ አለማየሁ (ዶ/ር)። "ምናልባት በገንዘብ ሚኒስትሩ የቀረበው የተጠባቂ ዕድገት መጠን በወረርሽኙ የሚደርሰውን ምጣኔ ሃብታዊ ጡጫ ያላካተተ ይሆን?" ሲሉም ይጠይቃሉ። ወረርሽኙ በ2013 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት (ከቀጣዩ ሐምሌ እስከ መስከረም) ድረስ የኢትዮጵያን ምጣኔ ሃብት ክፉኛ ይደቁሳል፤ ከዚያ ወዲያ ግን ተግ ይላል ብለን ብናስብ እንኳ ይላሉ ባለሞያው አለማየሁ "በእኔ ግምት ምጣኔ ሃብቱ በ5.6 በመቶ ይቀነሳል" ሲሉ የእራሳቸውን እይታ ያስቀምጣሉ። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ግምታቸውን ባደረጉት ጥናት ላይ መሠረት እንዳደረጉ ይገልፁና "ይህ ማለት የ8.5 በመቶ ዕድገት ላይ ለመድረስ ወረርሽኑ ከሚያደርሰው ጉዳት ጋር የሚደመር አጠቃላይ የ14 በመቶ ገደማ ይጠበቃል እንደማለት ነው" ይላሉ። ይህን መሰል ዕድገት ማስመዝገብ ደግሞ የመሆን ዕድሉ የጠበበ ነው ባይ ናቸው። የገንዘብ ሚኒስትሩ የተጠባቂ ዕድገት መግለጫ የወረርሽኙን ጉዳት ያላካተተ ከሆነ ግን ከጉዳቱ ጋር ተወራርዶ የሚኖረው ዕድገት 3 በመቶን የሚጠጋ ይሆናል እንደማለት ነው እንደእርሳቸው ግምት። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አቶ ዋሲሁን እንደሚሉት ምንም እንኳ የወረርሽኙ ዳፋ ለኢትዮጵያ ባይቀርላትም፤ ቢያንስ እስካሁን እጅጉን የተጋነነ ስርጭትን ባለማስተዋሏ ወደሌሎች አገራት የምትልካቸው ቡናን የመሳሰሉ ምርቶች ፍላጎትም ሲቀንስ ባለመታየቱ መልካም ነገር ነው ይላሉ። የኮሮናቫይረስ ጣጣ ለረጅም ጊዜ ሊዘልቅ እንደሚችል የሚሰጉት አለማየሁ (ዶ/ር) እንደሚሉት የወረርሽኙ ምጣኔ ሃብታዊ ጉዳት በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሦስት ወራት ላይ ብቻ ይቀጥላል ማለት "ይህ ጥሩ የሚባለው፥ ከቀናን (ቤስት ኬዝ ሲናርዮ) የሚባለው ግምት ነው" ይላሉ። ወደ እውነታ የሚጠጋው ግምት ግን የወረርሽኙ ምጣኔ ሃብታዊ ጫና "አነሰ ቢባል ለስድስት ወራት ያህል፤ ያ ማለት እስከ ታኅሳስ ወር ድረስ" ይዘልቃል የሚለው ነው እንደ አለማየሁ (ዶ/ር)። ለሁለት ሩብ የበጀት ዓመታት ያ ማለት እስከወርሃ ታህሳስ ድረስ የኮቪድ-19 መዘዝንና ቡጢውን ምጣኔ ሃብቱ ላይ ማሳረፉን ከቀጠለ ደግሞ ባለሙያው እንደሚገምቱት ምጣኔ ሃብቱ በአስራ አንድ በመቶ እንደሚቀንስ ነው። "በታዳጊ አገራት ከፍ ያለ ዕድገትን ማስመዝገብ አስገራሚ ነገር አይደለም" የሚሉት አቶ ዋሲሁን፤ ከዚሁም አንፃር በአዲሱ የበጀት ዓመት 8.5 በመቶ ዕድገት ይመዘገባል መባሉ የሚደንቅ ሊሆን አይገባም ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ከፍተኛ በጀት በጅተህ መሠረተ ልማት ላይ ማፍሰስ ብቻውን እኮ የአገር ውስጥ ጠቅላላ ምርትን (ጂዲፒውን) እንዲያድግ ያደርገዋል" ሲሉ የእድገት ምክንያት ሊሆኑ ከሚችሉት ነገሮች መካከል ይጠቅሳሉ፤ አቶ ዋሲሁን። አለማየሁ ገዳ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ መንግሥት እስካሁን ድረስ ምጣኔ ሃብቱን ለማረጋጋት ብሎም ለማነቃቃት የወሰዳቸውን እርምጃዎች ያደንቃሉ፤ የበለጠ እንዲያደርግም ይመክራሉ። በአንድ በኩል መንግሥት እንደሌሎች በርካታ አገራት ምጣኔ ሃብቱን ሙሉ በሙሉ በመዝጋት በኢትዮጵያ አውድ እንደማያዋጣ አውቆ እርሱን ያለማድረጉ እና ከዚያ ይልቅ ሥራዎች ከሞላ ጎደል እየተሰሩ ጥንቃቄዎች እንዲወሰዱ ማድረግን ዓይነተኛ አቅጣጫ አድርጎ መንቀሳቀሱ ተገቢ ነበር ይላሉ። "ሰዎች የጤናቸው ሁኔታ ባሉበት መስሪያ ቤት አካባቢ እየተጠበቀ፤ ምጣኔ ሃብቱ እንዲንቀሳቀስ ማድረጉ ቆንጆ ነገር ነው።" በሌላ ወገን ወረርሽኙ ለሚጎዱ ዘርፎች የማነቃቂያ ድጋፍ ማዘጋጀቱና ይህንን ለማቅረብ መስራቱም መልካም ነው ባይ ናቸው። ሆኖም "የግል ክፍለ-ኢኮኖሚውን በተለይ ኢንደስትሪው አገልግሎት ላይ ያሉትን ሰዎች እንዴት እንደሚደግፍ ኮስተር ያለ ዕቅድ አውጥቶ መከታተል ያለበት ይመስለኛል። [የእስካሁኑን እንቅስቃሴ] ሳየው ወጥ የሆነ አሰራር አይመስልም" ይላሉ። "በደንብ ታስቦበት፣ በአጭር ጊዜ እንደዚህ [ይሆናል] በረጅም ጊዜ እንደዚህ [ይሆናል] ተብሎ እየተሄደበት አይመስለኝም።" ከዚህም በዘለለ ቁጥራቸው ከሦስት ሚሊዮን ይሻገራል ያሏቸውን ራሳቸውን በራሳቸው (አንዳንዶቹ) ቤተሰባቸውን ጨምሮ የሚያስተዳድሩ ሰዎች "የመንግሥታዊ ድጋፍ ጠበል አልደረሳቸውም" ይላሉ። የእነዚህ ሰዎች ዋነኛ ወጪ የመስሪያ ቦታ ኪራይ ክፍያ በመሆኑ እርሱን በተመለከተ በአከራዮች በጎ ፈቃድ ላይ የማይመሰረት የክፍያ ቅነሳ እርምጃ ያስፈልጋል ባይ ናቸው። መንግሥት የኪራይ ወጪያቸውን በተወሰነ ድርሻ እንዲከፍል ማድረግም ሌላ የማነቃቂያ እርምጃ ሊሆን ይችላል ሲሉ አለማየሁ ገዳ (ዶ/ር) ለቢቢሲ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል። በቀጣይ ዓመት ኢትዮጵያ ሊኖራት የሚችለውን ምጣኔ ሃብታዊ እድገት ትንበያን በተመለከተ አቶ ዋሲሁን ግምታቸውን ሲያስቀምጡ "የተለጠጠ ታቅድና በጥረት የምትደርስበት ያህል ነው የምትሰራው። መንግሥት ይሄን ሲያስቀምጥ የጥረቱን ያስቀመጠ ይመስለኛል።" "ምክንያቱም ምን ያህል በሽተኛ ይዘህ ነው 8.5 በመቶ አድጋለሁ የምትለው? ሰላሳ አርባ ሺህ ነው ወይንስ አሁን እየሆነ እንዳለው በየቀኑ መቶ መቶ እየጨመርን? የሚለውም መታየት አለበት" ሲሉ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በቀጣይ ወራት ሊፈጥር የሚችለው እንቅፋት ከግምት ውስጥ መግባት እንዳለበት ይጠቅሳሉ።
ቀጣዩ 8.5 በመቶ የኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት እድገት በባለሙያዎች ዕይታ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እንደሚያደርገው በጠቅላይ ሚኒስቴሩ ፅህፈት ቤት አዳራሽ ሐሙስ ሰኔ አራት ቀን 16ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዶ 476.1 ቢሊዮን ብር ገደማ ይሆናል በተባለው በቀጣዩ የበጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ላይ ተወያይቷል። ከዚሁ ውስጥ በመንግሥት ረቂቅ በጀት መሰረት 176 ቢሊዮን ብር ገደማ የሚሆነው ለክልሎች የሚሰጥ ሲሆን፤ የፌዴራል መንግሥት ደግሞ ለመደበኛ ወጪዎቹ 133 ቢሊዮን ብር፣ ለካፒታል ወጪዎቹ 160 ቢሊዮን ብር ይደርሰዋል መባሉን የአገር ውስጥ የብዙሃን መገናኛ አውታሮች ዘግበዋል። ረቂቅ በጀቱን በሚመለከት ማብራሪያ የሰጡት የፌዴራል መንግሥቱ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ቀጣዩ የበጀት ዓመት በኢትዮጵያ 8.5 በመቶ ዕድገት እንደሚመዘገብ ለሕዝብ እንደራሴዎቹ ተናግረዋል። ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ኢትዮጵያ 9 በመቶ የምጣኔ ሃብት ዕድገትን እጠብቃለሁ ብላ ነበር። ዓለም አቀፉ ወረርሽኝ ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ ላይ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም አገራት ምጣኔ ሃብት ላይ ከባድ የሚባል ጫናን እየፈጠረ ባለበትና የዚህ በሽታ ተጽዕኖ ለዓመታት ባይሆን ለቀጣይ ረዥም ወራት እንሚቀጥል እየተነገረ ባለበት ሁኔታ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በዚህ መጠን ሊያድግ የሚችልበት ዕድል መኖሩ እያነጋገረ ነው። የቀጣዩን የበጀት ዓመት የአገሪቱን በጀትና ተጠባቂ ዕድገትን በተመለከተ ቢቢሲ የምጣኔ ሃብት ባለሞያዎቹን አለማየሁ ገዳን (ዶ/ር) እና አቶ ዋሲሁን በላይ ያላቸውን ዕይታ ጠይቋል። የምጣኔ ሃብት ተንታኙ አቶ ዋሲሁን በላይ ባለፈው የበጀት ዓመት ቀርቦ ከነበረው 386.9 ቢሊዮን ብር ጋር ሲነፃፀር ዘንድሮ የቀረበው በጀት ከፍ ያለ ብልጫ ያለው ቢመስልም፤ በመገባደድ ላይ ያለው የበጀት ዓመት ከመጠናቀቁ በፊት መንግሥት 28 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ተጨማሪ በጀት ማስፀደቁን ጨምረው በማስታወስ አሁንም ጭማሪው የሚታይ መሆኑን ይጠቅሳሉ። ነገር ግን የቀጣይ ዓመት የአገሪቱ በጀት ከመጨመሩ ጎን ለጎን ይመዘገባል ተብሎ በገንዘብ ሚኒስትሩ የቀረበው የተጠባቂ ዕድገት ቁጥር ምጣኔ ሃብታዊ እድገት ላይ ባለሞያዎቹ ጥያቄዎችን ያነሳሉ። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በዓለም ዙርያ ምጣኔ ሃብቶችን በሚገዳደርበት እና "በርካታ አገራት ዕድገታቸው የቁልቁል እንደሚሆን በተነበዩበት ወቅት፤ ከስምንት በመቶ የሚሻገር ዕድገትን መጠበቅ አስቸጋሪ ነው" ይላሉ አለማየሁ (ዶ/ር)። "ምናልባት በገንዘብ ሚኒስትሩ የቀረበው የተጠባቂ ዕድገት መጠን በወረርሽኙ የሚደርሰውን ምጣኔ ሃብታዊ ጡጫ ያላካተተ ይሆን?" ሲሉም ይጠይቃሉ። ወረርሽኙ በ2013 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት (ከቀጣዩ ሐምሌ እስከ መስከረም) ድረስ የኢትዮጵያን ምጣኔ ሃብት ክፉኛ ይደቁሳል፤ ከዚያ ወዲያ ግን ተግ ይላል ብለን ብናስብ እንኳ ይላሉ ባለሞያው አለማየሁ "በእኔ ግምት ምጣኔ ሃብቱ በ5.6 በመቶ ይቀነሳል" ሲሉ የእራሳቸውን እይታ ያስቀምጣሉ። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ግምታቸውን ባደረጉት ጥናት ላይ መሠረት እንዳደረጉ ይገልፁና "ይህ ማለት የ8.5 በመቶ ዕድገት ላይ ለመድረስ ወረርሽኑ ከሚያደርሰው ጉዳት ጋር የሚደመር አጠቃላይ የ14 በመቶ ገደማ ይጠበቃል እንደማለት ነው" ይላሉ። ይህን መሰል ዕድገት ማስመዝገብ ደግሞ የመሆን ዕድሉ የጠበበ ነው ባይ ናቸው። የገንዘብ ሚኒስትሩ የተጠባቂ ዕድገት መግለጫ የወረርሽኙን ጉዳት ያላካተተ ከሆነ ግን ከጉዳቱ ጋር ተወራርዶ የሚኖረው ዕድገት 3 በመቶን የሚጠጋ ይሆናል እንደማለት ነው እንደእርሳቸው ግምት። የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አቶ ዋሲሁን እንደሚሉት ምንም እንኳ የወረርሽኙ ዳፋ ለኢትዮጵያ ባይቀርላትም፤ ቢያንስ እስካሁን እጅጉን የተጋነነ ስርጭትን ባለማስተዋሏ ወደሌሎች አገራት የምትልካቸው ቡናን የመሳሰሉ ምርቶች ፍላጎትም ሲቀንስ ባለመታየቱ መልካም ነገር ነው ይላሉ። የኮሮናቫይረስ ጣጣ ለረጅም ጊዜ ሊዘልቅ እንደሚችል የሚሰጉት አለማየሁ (ዶ/ር) እንደሚሉት የወረርሽኙ ምጣኔ ሃብታዊ ጉዳት በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሦስት ወራት ላይ ብቻ ይቀጥላል ማለት "ይህ ጥሩ የሚባለው፥ ከቀናን (ቤስት ኬዝ ሲናርዮ) የሚባለው ግምት ነው" ይላሉ። ወደ እውነታ የሚጠጋው ግምት ግን የወረርሽኙ ምጣኔ ሃብታዊ ጫና "አነሰ ቢባል ለስድስት ወራት ያህል፤ ያ ማለት እስከ ታኅሳስ ወር ድረስ" ይዘልቃል የሚለው ነው እንደ አለማየሁ (ዶ/ር)። ለሁለት ሩብ የበጀት ዓመታት ያ ማለት እስከወርሃ ታህሳስ ድረስ የኮቪድ-19 መዘዝንና ቡጢውን ምጣኔ ሃብቱ ላይ ማሳረፉን ከቀጠለ ደግሞ ባለሙያው እንደሚገምቱት ምጣኔ ሃብቱ በአስራ አንድ በመቶ እንደሚቀንስ ነው። "በታዳጊ አገራት ከፍ ያለ ዕድገትን ማስመዝገብ አስገራሚ ነገር አይደለም" የሚሉት አቶ ዋሲሁን፤ ከዚሁም አንፃር በአዲሱ የበጀት ዓመት 8.5 በመቶ ዕድገት ይመዘገባል መባሉ የሚደንቅ ሊሆን አይገባም ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ከፍተኛ በጀት በጅተህ መሠረተ ልማት ላይ ማፍሰስ ብቻውን እኮ የአገር ውስጥ ጠቅላላ ምርትን (ጂዲፒውን) እንዲያድግ ያደርገዋል" ሲሉ የእድገት ምክንያት ሊሆኑ ከሚችሉት ነገሮች መካከል ይጠቅሳሉ፤ አቶ ዋሲሁን። አለማየሁ ገዳ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ መንግሥት እስካሁን ድረስ ምጣኔ ሃብቱን ለማረጋጋት ብሎም ለማነቃቃት የወሰዳቸውን እርምጃዎች ያደንቃሉ፤ የበለጠ እንዲያደርግም ይመክራሉ። በአንድ በኩል መንግሥት እንደሌሎች በርካታ አገራት ምጣኔ ሃብቱን ሙሉ በሙሉ በመዝጋት በኢትዮጵያ አውድ እንደማያዋጣ አውቆ እርሱን ያለማድረጉ እና ከዚያ ይልቅ ሥራዎች ከሞላ ጎደል እየተሰሩ ጥንቃቄዎች እንዲወሰዱ ማድረግን ዓይነተኛ አቅጣጫ አድርጎ መንቀሳቀሱ ተገቢ ነበር ይላሉ። "ሰዎች የጤናቸው ሁኔታ ባሉበት መስሪያ ቤት አካባቢ እየተጠበቀ፤ ምጣኔ ሃብቱ እንዲንቀሳቀስ ማድረጉ ቆንጆ ነገር ነው።" በሌላ ወገን ወረርሽኙ ለሚጎዱ ዘርፎች የማነቃቂያ ድጋፍ ማዘጋጀቱና ይህንን ለማቅረብ መስራቱም መልካም ነው ባይ ናቸው። ሆኖም "የግል ክፍለ-ኢኮኖሚውን በተለይ ኢንደስትሪው አገልግሎት ላይ ያሉትን ሰዎች እንዴት እንደሚደግፍ ኮስተር ያለ ዕቅድ አውጥቶ መከታተል ያለበት ይመስለኛል። [የእስካሁኑን እንቅስቃሴ] ሳየው ወጥ የሆነ አሰራር አይመስልም" ይላሉ። "በደንብ ታስቦበት፣ በአጭር ጊዜ እንደዚህ [ይሆናል] በረጅም ጊዜ እንደዚህ [ይሆናል] ተብሎ እየተሄደበት አይመስለኝም።" ከዚህም በዘለለ ቁጥራቸው ከሦስት ሚሊዮን ይሻገራል ያሏቸውን ራሳቸውን በራሳቸው (አንዳንዶቹ) ቤተሰባቸውን ጨምሮ የሚያስተዳድሩ ሰዎች "የመንግሥታዊ ድጋፍ ጠበል አልደረሳቸውም" ይላሉ። የእነዚህ ሰዎች ዋነኛ ወጪ የመስሪያ ቦታ ኪራይ ክፍያ በመሆኑ እርሱን በተመለከተ በአከራዮች በጎ ፈቃድ ላይ የማይመሰረት የክፍያ ቅነሳ እርምጃ ያስፈልጋል ባይ ናቸው። መንግሥት የኪራይ ወጪያቸውን በተወሰነ ድርሻ እንዲከፍል ማድረግም ሌላ የማነቃቂያ እርምጃ ሊሆን ይችላል ሲሉ አለማየሁ ገዳ (ዶ/ር) ለቢቢሲ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል። በቀጣይ ዓመት ኢትዮጵያ ሊኖራት የሚችለውን ምጣኔ ሃብታዊ እድገት ትንበያን በተመለከተ አቶ ዋሲሁን ግምታቸውን ሲያስቀምጡ "የተለጠጠ ታቅድና በጥረት የምትደርስበት ያህል ነው የምትሰራው። መንግሥት ይሄን ሲያስቀምጥ የጥረቱን ያስቀመጠ ይመስለኛል።" "ምክንያቱም ምን ያህል በሽተኛ ይዘህ ነው 8.5 በመቶ አድጋለሁ የምትለው? ሰላሳ አርባ ሺህ ነው ወይንስ አሁን እየሆነ እንዳለው በየቀኑ መቶ መቶ እየጨመርን? የሚለውም መታየት አለበት" ሲሉ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በቀጣይ ወራት ሊፈጥር የሚችለው እንቅፋት ከግምት ውስጥ መግባት እንዳለበት ይጠቅሳሉ።
https://www.bbc.com/amharic/news-53021260
2health
በደቡብ ኮርያ የሀሎዊን በዓል በአደባባይ ሲከበር በደረሰ አደጋ ቢያንስ 151 ሰዎች ሞቱ
በደቡብ ኮርያ የሀሎዊን በዓል ለማክበር የወጡ ሰዎች በገጠማቸው አደጋ ቢያንስ 151 የሚደርሱት ሕይወታቸው አልፏል። 82 ሰዎች ደግሞ ተጎድተዋል። በመዲናዋ ሴዑል በሚገኝ ጠባብ አደባባይ ላይ በዓሉን ለማክበር የወጡ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ነበር። ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወዲህ ያለ አፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል የተካሄደ የመጀመሪያው የአደባባይ ክብረ በዓል ነበር። የሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ስለነበር መገፋፋትና መረጋገጥ መከሰቱ ተዘግቧል። ከሞቱት መካከል አብዛኞቹ በ20ዎቹ ዕድሜ ክልል የሚገኙ ሲሆን፤ 19ኙ የውጭ አገር ዜጋ ናቸው። አደጋው በምን ምክንያት እንደተከሰተ ምርመራ እየተደረገ እንደሆነ ተገልጿል። አስቸኳይ ስብሰባ ከተካሄደ በኋላ የደቡብ ኮርያ ፕሬዝዳንት ዮን ሱን-ዮል የተጎዱትን የሚያክም ግብረ ኃይል አቋቁመዋል። እአአ ከ2014 ወዲህ በአገሪቱ የተከሰተ የከፋ አደጋ ነው ተብሏል። ያኔ ስዑል የተባለ መርከብ ሰጥማ 300 ሰዎች ሞተዋል። ሀሎዊን የተከበረበት ኢታዎን የተባለው ሰፈር በምሽት ሕይወት ዝነኛ ነው። በተለይ ቅዳሜና እሑድ አገሬውና ጎብኚዎች ያዘወትሩታል። ሀሎዊን በደቡብ ኮርያ ብዙ ሰው ወደ አደባባይ ከሚወጣባቸው ቀኖች መካከል ነው። ትላንትም በዓሉን ለማክበር 100,000 በቦታው ተገኝተው እንደነበር ተገልጿል። በአንድ የተጨናነቀ መንገድ ላይ መገፋፋቱ እንደተጀመረ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የወጡ ቪድዮዎች አሳይተዋል። መንገዱ እጅግ ጠባብ ሲሆን፣ በቦታው የነበሩ ሰዎች በርካታ ነበሩ። አንድ ቪድዮ ሰዎች መተንፈስ ተቸግረው ያሳያል። ሰዎች በሰዎች ላይ ተደራርበውም ይታያል። የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች አስክሬኖች ሲያወጡ የሰዎች ለቅሶና ሲቃም ይሰማ ነበር። የተወሰኑ ሰዎች አስክሬን ወደ አምቡላንስ ሲወሰድ፣ የተቀሩት አስክሬን በፕላስቲክ ተሸፍኖ መንገድ ዳር ተቀምጦ ታይቷል። ራሳቸውን የሳቱ ሰዎችን ሕይወት ለማትረፍ ትንፋሽ በመስጠት ሲሞክሩ የነበሩም አሉ። ከመላው አገሪቱ በመቶች የሚቆጠሩ የአደጋ ሠራተኞች ናቸው በቦታው የተገኙት። የሞቱትን ሰዎች አስክሬን ቤተሰቦቻቸው እንዲወስዱ የሚደረግ ሲሆን፤ የሟቾች ቁጥር በርካታ በመሆኑ ሂደቱ ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል ተገልጿል። አደጋው ሲከሰት የ30 ዓመቷ ጂዎን ጋውል ከጓደኞቿ ጋር እየጠጣች እንደነበር ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል ነግራለች። “ሰዎች መጎዳታቸውን ጓደኛዬ ስትነግረኝ ደንግጬ ከመጠጥ ቤቱ ወጣሁ። መንገድ ላይ ራሳቸውን ለሳቱ ሰዎች ትንፋሽ የሚሰጡ ሰዎች አየሁ” ብላለች። በቦታው የነበረ ዶክተር እንዳለው፣ መጀመሪያ ላይ ለተወሰኑ ሰዎች ትንፋሽ በመስጠት ሕይወታቸውን ለማዳን ሲሞክር ነበር። ቆይቶ ግን ራሳቸውን የሳቱ ሰዎች ቁጥር እየናረ ሄዷል። አካባቢው መጨናነቁን ያዩ ሰዎች አደጋ ሊገጥም እንደሚችል የሚጠቁሙ ጽሑፎች ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሲጽፉ ነበር። ፓርክ የንግ-ሁን የተባለ የዓይን እማኝ ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንዳለው፣ ለገና እና ሌሎች በዓሎች ከሚሰበሰቡ ሰዎች የበለጠ ነበር የወጣው። የአደባባይ በዓሎች እና የሰዎች ደኅንነትን የተመለከቱ ፖሊሲዎች እንዲከለሱ ውሳኔ ተላልፏል። የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ፣ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፣ የአውሮፓ ኅብረት ዲፕሎማት ጆሴፕ ቦሬል እና የአሜሪካ ብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ጄክ ሱልቪን የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል።
በደቡብ ኮርያ የሀሎዊን በዓል በአደባባይ ሲከበር በደረሰ አደጋ ቢያንስ 151 ሰዎች ሞቱ በደቡብ ኮርያ የሀሎዊን በዓል ለማክበር የወጡ ሰዎች በገጠማቸው አደጋ ቢያንስ 151 የሚደርሱት ሕይወታቸው አልፏል። 82 ሰዎች ደግሞ ተጎድተዋል። በመዲናዋ ሴዑል በሚገኝ ጠባብ አደባባይ ላይ በዓሉን ለማክበር የወጡ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ነበር። ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወዲህ ያለ አፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል የተካሄደ የመጀመሪያው የአደባባይ ክብረ በዓል ነበር። የሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ስለነበር መገፋፋትና መረጋገጥ መከሰቱ ተዘግቧል። ከሞቱት መካከል አብዛኞቹ በ20ዎቹ ዕድሜ ክልል የሚገኙ ሲሆን፤ 19ኙ የውጭ አገር ዜጋ ናቸው። አደጋው በምን ምክንያት እንደተከሰተ ምርመራ እየተደረገ እንደሆነ ተገልጿል። አስቸኳይ ስብሰባ ከተካሄደ በኋላ የደቡብ ኮርያ ፕሬዝዳንት ዮን ሱን-ዮል የተጎዱትን የሚያክም ግብረ ኃይል አቋቁመዋል። እአአ ከ2014 ወዲህ በአገሪቱ የተከሰተ የከፋ አደጋ ነው ተብሏል። ያኔ ስዑል የተባለ መርከብ ሰጥማ 300 ሰዎች ሞተዋል። ሀሎዊን የተከበረበት ኢታዎን የተባለው ሰፈር በምሽት ሕይወት ዝነኛ ነው። በተለይ ቅዳሜና እሑድ አገሬውና ጎብኚዎች ያዘወትሩታል። ሀሎዊን በደቡብ ኮርያ ብዙ ሰው ወደ አደባባይ ከሚወጣባቸው ቀኖች መካከል ነው። ትላንትም በዓሉን ለማክበር 100,000 በቦታው ተገኝተው እንደነበር ተገልጿል። በአንድ የተጨናነቀ መንገድ ላይ መገፋፋቱ እንደተጀመረ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የወጡ ቪድዮዎች አሳይተዋል። መንገዱ እጅግ ጠባብ ሲሆን፣ በቦታው የነበሩ ሰዎች በርካታ ነበሩ። አንድ ቪድዮ ሰዎች መተንፈስ ተቸግረው ያሳያል። ሰዎች በሰዎች ላይ ተደራርበውም ይታያል። የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች አስክሬኖች ሲያወጡ የሰዎች ለቅሶና ሲቃም ይሰማ ነበር። የተወሰኑ ሰዎች አስክሬን ወደ አምቡላንስ ሲወሰድ፣ የተቀሩት አስክሬን በፕላስቲክ ተሸፍኖ መንገድ ዳር ተቀምጦ ታይቷል። ራሳቸውን የሳቱ ሰዎችን ሕይወት ለማትረፍ ትንፋሽ በመስጠት ሲሞክሩ የነበሩም አሉ። ከመላው አገሪቱ በመቶች የሚቆጠሩ የአደጋ ሠራተኞች ናቸው በቦታው የተገኙት። የሞቱትን ሰዎች አስክሬን ቤተሰቦቻቸው እንዲወስዱ የሚደረግ ሲሆን፤ የሟቾች ቁጥር በርካታ በመሆኑ ሂደቱ ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል ተገልጿል። አደጋው ሲከሰት የ30 ዓመቷ ጂዎን ጋውል ከጓደኞቿ ጋር እየጠጣች እንደነበር ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል ነግራለች። “ሰዎች መጎዳታቸውን ጓደኛዬ ስትነግረኝ ደንግጬ ከመጠጥ ቤቱ ወጣሁ። መንገድ ላይ ራሳቸውን ለሳቱ ሰዎች ትንፋሽ የሚሰጡ ሰዎች አየሁ” ብላለች። በቦታው የነበረ ዶክተር እንዳለው፣ መጀመሪያ ላይ ለተወሰኑ ሰዎች ትንፋሽ በመስጠት ሕይወታቸውን ለማዳን ሲሞክር ነበር። ቆይቶ ግን ራሳቸውን የሳቱ ሰዎች ቁጥር እየናረ ሄዷል። አካባቢው መጨናነቁን ያዩ ሰዎች አደጋ ሊገጥም እንደሚችል የሚጠቁሙ ጽሑፎች ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሲጽፉ ነበር። ፓርክ የንግ-ሁን የተባለ የዓይን እማኝ ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንዳለው፣ ለገና እና ሌሎች በዓሎች ከሚሰበሰቡ ሰዎች የበለጠ ነበር የወጣው። የአደባባይ በዓሎች እና የሰዎች ደኅንነትን የተመለከቱ ፖሊሲዎች እንዲከለሱ ውሳኔ ተላልፏል። የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ፣ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፣ የአውሮፓ ኅብረት ዲፕሎማት ጆሴፕ ቦሬል እና የአሜሪካ ብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ጄክ ሱልቪን የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cg3lzn6v10wo
3politics
መንግሥት እርዳታ ከማቅረብ ውጪ በሌሎች ተግባራት ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችን ከአገር ላስወጣ እችላለሁ አለ
በትግራይ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ ከማቅረብ ይልቅ በሌሎች ተግባራት ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችን ከአገር እስከማስወጣት የሚደርስ ውሳኔ ሊውስድ እንደሚችል መንግሥት አስታወቀ። የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ድኤታ አምባሳደር ሬድዋን ዛሬ በሰጡት መግለጫ እርዳታ ለመስጠት ወይም ለማስተባበር ከሚፈልጉ አካላት መካከል "ከእርዳታ ይልቅ ፕሮፓጋንዳ የማስተባበር፣ የኢትዮጵያን መንግሥት የማዋከብ፣ የማጠልሸት ዘመቻ ላይ ያሉ" እንዳሉ ጠቅሰዋል። መንግሥት እነዚህ አካሎች እንዳስጠነቀቀ ተናግረው፤ "ጉዳዩ በዚህ ከቀጠለ መንግሥት አገር የማዳን ኃላፊነት ስለሚወጣ ከአንዳንዶቹ ጋር አብሮ የመሥራት ሁኔታውን እንደገና እንደሚቃኝ፣ አንዳንዶቹንም ከአገር ለማስወጣት እንደሚገደድ" ገልጸዋል። ይህንን ማሳሰቢያ የሰጡት ለተባበሩት መንግሥታት እንዲሁም ለሌሎች እርዳታ አቅራቢ እና አስተባባሪ አካሎች ነው። መንግሥት የተኩስ አቁም አውጆ ሳለ፤ "በሌላኛው ወገን የሚደረገው ትንኮሳ በዚህ የሚቀጥል ከሆነ መንግሥት ያሳለፈውን ውሳኔ እንደገና ለማጤን ይገደዳል። በዚህም ምክንያት ሁሉን አቀፍ እርምጃ ለመውሰድ ይገደዳል" ሲሉም አስጠንቅቀዋል። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ "በሌላኛው ወገን የሚደረገውን ትንኮሳ አንዲያጋልጥ፣ እንደዲኮንን" የፌደራል መንግሥቱ ይጠይቃል ሲሉም በመግለጫው አስታውቀዋል። 'ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የተናጠል ተኩስ አቁም ውሳኔውን አልደገፈም' የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ መንግሥት በትግራይ ሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ ሲል የተናጠል የተኩስ አቁም እርምጃ ቢወስድም፤ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ግን "አፍራሽ ዝንባሌ አሳይቷል" ብለዋል። ዓለም አቀፉ ማኅበተሰብ ወደ ትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ መንግሥት ተኩስ እንዲያቆም ሲጠይቅ ቢቆይም፤ የፌደራል መንግሥት የተኩስ አቁም ከወሰነ በኋላ ግን ውሳኔውን በአዎንታዊ መንገድ እንዳላየው ወቅሰዋል። አምባሳደር ሬድዋን፤ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ሲጠይቁ የነበሩ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ወገኖች "አዎንታዊ ውሳኔውን ተከትሎ አዎንታዊ ድጋፍ ለማድረግ ሳይሆን፤ ብዙዎች ሲንቀሳቀሱለት የነበረወን ውሳኔ መንግሥት ወስኖም እያለ ይህንን ከማደነቅ፣ የጎደለውን ከመሙላትና ከማሳሰብ ይልቅ ለዚህ አፍራሽና አሉታዊ ምክንያት በመደርደር የውሳኔውን አነስተኛነት ለማሳየት ተንቀሳቅሰዋል" ሲሉ ወቅሰዋል። መንግሥት የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔው፤ "ተጨማሪ እልቂትን ለማስቀረት ያለመ፣ የምጣኔ ሀብትና ፖለቲካዊ አመክንዮም ያለው" እንደሆነ በተደጋጋሚ ገልጿል። የትግራይ ሀይሎች በበኩላቸው የመከላከያ ሠራዊቱ ላይ ድል እንደተቀዳጁ ገልጸው፤ የፌደራል መንግሥት የተኩስ አቁም ለመቀበል ባለ ሰባት ነጥብ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጠዋል። የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ጉዳይ የተለያዩ የረድኤት ድርጅቶች የፌደራል መንግሥት በትግራይ ክልል እርዳታ እንዲዳረስ ተገቢውን ድጋፍ እያደረገ እንዳልሆነ ወቅሰዋል። አምባሳደር ሬድዋን ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ "የሰብዓዊ እርዳታ እናቀርባለን ወይም እናስተባብራለን ያሉ አካላት ሲጠይቋቸው የነበሩ ነገሮች በአጠቃላይ ተመልሰው እያለም አሁንም መንግሥት በአካባቢው በነበረበትና ግጭት ይካሄድ በነበረበት ወቅት ያሰሟቸው የነበሩ ወቀሳዎችና ስሞታዎች እያሰሙ ነው" ሲሉ ገልጸዋል። ከሳምንታት በፊት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ወደ ትግራይ ክልል የምግብ እርዳታ ጭኖ ሲሄድ መሰናክል ገጥሞት እንደነበረ ከቀናት በኋላ ግን እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎቹን ወደ ክልሉ ማስገባት መቻሉን ገልጿል። በአውሮፓ ሕብረት አቅራቢነት የጸደቀውን የውሳኔ ሐሳብ በተመለከተ በ47ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የአውሮፓ ሕብረት ከትግራዩ ግጭት ጋር በተያያዘ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እንደሚያሳስበውና የኤርትራ ሠራዊት አባላት ከትግራይ በአስቸኳይ እንዲውጡ በመጠየቅ ያቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ተቀባይነት ማግኘቱ ይታወሳል። የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ ይህ የሕብረቱ የውሳኔ ሐሳብ "ጊዜውያን ያልጠበቀ እና በፖለቲካ ፍላጎት የተላለፈ" ነው ሲል ተቃውሟል። አምባሳደር ሬድዋን ይህንኑ ጉዳይ አንስተው የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን "ስሞታ ሳያሰማ፣ መንግሥት አልተባበረንም ሳይል፤ አንዳንድ አገራትን በማስፈራራት፣ አንዳንዶቹን በማባበል የውሳኔ ሐሳብ ቀርቦ ኢትዮጵያ ላያ አቋም እንዲወጣ መደረጉ" የመንግሥትን አዎንታዊ እርምጃ ከግምት ያላስገባ እንደሆነ ተናግረዋል።
መንግሥት እርዳታ ከማቅረብ ውጪ በሌሎች ተግባራት ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችን ከአገር ላስወጣ እችላለሁ አለ በትግራይ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ ከማቅረብ ይልቅ በሌሎች ተግባራት ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችን ከአገር እስከማስወጣት የሚደርስ ውሳኔ ሊውስድ እንደሚችል መንግሥት አስታወቀ። የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ድኤታ አምባሳደር ሬድዋን ዛሬ በሰጡት መግለጫ እርዳታ ለመስጠት ወይም ለማስተባበር ከሚፈልጉ አካላት መካከል "ከእርዳታ ይልቅ ፕሮፓጋንዳ የማስተባበር፣ የኢትዮጵያን መንግሥት የማዋከብ፣ የማጠልሸት ዘመቻ ላይ ያሉ" እንዳሉ ጠቅሰዋል። መንግሥት እነዚህ አካሎች እንዳስጠነቀቀ ተናግረው፤ "ጉዳዩ በዚህ ከቀጠለ መንግሥት አገር የማዳን ኃላፊነት ስለሚወጣ ከአንዳንዶቹ ጋር አብሮ የመሥራት ሁኔታውን እንደገና እንደሚቃኝ፣ አንዳንዶቹንም ከአገር ለማስወጣት እንደሚገደድ" ገልጸዋል። ይህንን ማሳሰቢያ የሰጡት ለተባበሩት መንግሥታት እንዲሁም ለሌሎች እርዳታ አቅራቢ እና አስተባባሪ አካሎች ነው። መንግሥት የተኩስ አቁም አውጆ ሳለ፤ "በሌላኛው ወገን የሚደረገው ትንኮሳ በዚህ የሚቀጥል ከሆነ መንግሥት ያሳለፈውን ውሳኔ እንደገና ለማጤን ይገደዳል። በዚህም ምክንያት ሁሉን አቀፍ እርምጃ ለመውሰድ ይገደዳል" ሲሉም አስጠንቅቀዋል። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ "በሌላኛው ወገን የሚደረገውን ትንኮሳ አንዲያጋልጥ፣ እንደዲኮንን" የፌደራል መንግሥቱ ይጠይቃል ሲሉም በመግለጫው አስታውቀዋል። 'ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የተናጠል ተኩስ አቁም ውሳኔውን አልደገፈም' የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ መንግሥት በትግራይ ሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ ሲል የተናጠል የተኩስ አቁም እርምጃ ቢወስድም፤ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ግን "አፍራሽ ዝንባሌ አሳይቷል" ብለዋል። ዓለም አቀፉ ማኅበተሰብ ወደ ትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ መንግሥት ተኩስ እንዲያቆም ሲጠይቅ ቢቆይም፤ የፌደራል መንግሥት የተኩስ አቁም ከወሰነ በኋላ ግን ውሳኔውን በአዎንታዊ መንገድ እንዳላየው ወቅሰዋል። አምባሳደር ሬድዋን፤ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ሲጠይቁ የነበሩ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ወገኖች "አዎንታዊ ውሳኔውን ተከትሎ አዎንታዊ ድጋፍ ለማድረግ ሳይሆን፤ ብዙዎች ሲንቀሳቀሱለት የነበረወን ውሳኔ መንግሥት ወስኖም እያለ ይህንን ከማደነቅ፣ የጎደለውን ከመሙላትና ከማሳሰብ ይልቅ ለዚህ አፍራሽና አሉታዊ ምክንያት በመደርደር የውሳኔውን አነስተኛነት ለማሳየት ተንቀሳቅሰዋል" ሲሉ ወቅሰዋል። መንግሥት የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔው፤ "ተጨማሪ እልቂትን ለማስቀረት ያለመ፣ የምጣኔ ሀብትና ፖለቲካዊ አመክንዮም ያለው" እንደሆነ በተደጋጋሚ ገልጿል። የትግራይ ሀይሎች በበኩላቸው የመከላከያ ሠራዊቱ ላይ ድል እንደተቀዳጁ ገልጸው፤ የፌደራል መንግሥት የተኩስ አቁም ለመቀበል ባለ ሰባት ነጥብ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጠዋል። የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ጉዳይ የተለያዩ የረድኤት ድርጅቶች የፌደራል መንግሥት በትግራይ ክልል እርዳታ እንዲዳረስ ተገቢውን ድጋፍ እያደረገ እንዳልሆነ ወቅሰዋል። አምባሳደር ሬድዋን ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ "የሰብዓዊ እርዳታ እናቀርባለን ወይም እናስተባብራለን ያሉ አካላት ሲጠይቋቸው የነበሩ ነገሮች በአጠቃላይ ተመልሰው እያለም አሁንም መንግሥት በአካባቢው በነበረበትና ግጭት ይካሄድ በነበረበት ወቅት ያሰሟቸው የነበሩ ወቀሳዎችና ስሞታዎች እያሰሙ ነው" ሲሉ ገልጸዋል። ከሳምንታት በፊት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ወደ ትግራይ ክልል የምግብ እርዳታ ጭኖ ሲሄድ መሰናክል ገጥሞት እንደነበረ ከቀናት በኋላ ግን እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎቹን ወደ ክልሉ ማስገባት መቻሉን ገልጿል። በአውሮፓ ሕብረት አቅራቢነት የጸደቀውን የውሳኔ ሐሳብ በተመለከተ በ47ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የአውሮፓ ሕብረት ከትግራዩ ግጭት ጋር በተያያዘ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እንደሚያሳስበውና የኤርትራ ሠራዊት አባላት ከትግራይ በአስቸኳይ እንዲውጡ በመጠየቅ ያቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ተቀባይነት ማግኘቱ ይታወሳል። የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ ይህ የሕብረቱ የውሳኔ ሐሳብ "ጊዜውያን ያልጠበቀ እና በፖለቲካ ፍላጎት የተላለፈ" ነው ሲል ተቃውሟል። አምባሳደር ሬድዋን ይህንኑ ጉዳይ አንስተው የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን "ስሞታ ሳያሰማ፣ መንግሥት አልተባበረንም ሳይል፤ አንዳንድ አገራትን በማስፈራራት፣ አንዳንዶቹን በማባበል የውሳኔ ሐሳብ ቀርቦ ኢትዮጵያ ላያ አቋም እንዲወጣ መደረጉ" የመንግሥትን አዎንታዊ እርምጃ ከግምት ያላስገባ እንደሆነ ተናግረዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-57853275
3politics
“መንግሥት ውስጥ የተሸሸገ ሸኔ አለ” የሰላም ሚኒስትር ዲኤታ ታዬ ደንደአ
የሰላም ሚኒስትር ዲኤታ እና የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ታዬ ደንደአ የግድያ ማስፈራሪያዎች እንደሚደርሷቸው ለቢቢሲ ተናገሩ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማኅበራዊ ሚዲያዎች እና በተለያዩ መድረኮች በሚያነሷቸው ሃሳቦች አነጋገሪ የሆኑት ሚኒስትር ዲኤታው፤ በብልጽግና ፓርቲ ውስጥ አለ ስለሚሉት ‘የማፊያ ቡድን’ እና በግል ስለሚደርሱባቸው ጫናዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ታዬ በቅርብ በተካሄደው የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት ስብሰባ ላይ አስተያየት “እንዳልሰጥ ድምጼ ታፍኗል” ብለው የፌስቡክ ገጻቸው ላይ ካሰፈሩ በኋላ ጉዳዩ የብዙዎች መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። አቶ ታዬ በጨፌው [በኦሮሚያ ምክር ቤት] የሆነው ሲያስረዱ፤ አፈ ጉባኤዋ የዕለቱን አጀንዳ ካቀረቡ በኋላ ምክር ቤቱ በሁለት ተጨማሪ ጉዳዮች ላይ እንዲነጋገር አጀንዳ ለማስያዝ ያደረጉት ጥረት አለመሳካቱን ይናገራሉ። የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ የሆኑት አቶ ታዬ፤ የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት ከመቼውም ጊዜ በላይ “እየተበላሸ መጥቷል” ስላሉት የክልሉ የደኅንነት ሁኔታ አጀንዳ አድርጎ እንዲወያይበት ማቅረብ ፈልገው እንደነበረ ይገልጻሉ። ሁለተኛው ማንሳት የፈለጉት ጉዳይ ደግሞ “ከሌብነት ጋር በተያያዘ በክልላችን አስተዳደሩ ተዳክሟል” የሚል መሆኑን ጠቅሰዋል። “እጄን ሳወጣ ይዩኝ አይዩኝ [አፈ ጉባኤዋ] አላውቅም ዝም ብለው አጀንዳ ወደማጸደቅ ሄዱ። ከዚያ ‘ክብርት አፈ ጉባኤ የማነሳው ሃሳብ አለኝ’ አልኩ” ይላሉ አቶ ታዬ። “ከዚያ ዕድል እንደመስጠት አሉና እንዳልናገር ደግሞ ማይክሮፎኑን ዘጉብኝ። ትንሽ ቆይተው ‘ዕድሉን መጠቀም አልቻሉም’ አሉ። ‘ዝጉበት፣ ዝጉበት’ የሚል ድምጽ ይሰማ ነበር” በማለት አቶ ታዬ በጨፌው አጋጥሟል ያሉትን ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ታዬ አስተያየቴን እንዳልሰጥ የተከለልኩት፤ ምክር ቤቱ በአጀንዳነት የያዛቸው ሪፖርቶች ችግር እንዳሉባቸው ስለሚታወቅ ነው ይላሉ። ከአንድ ዓመት በፊት የኦሮሚያ የፀጥታ ስጋት በአጭር ወራት ውስጥ ይወገዳል ተብሎ፣ ከአንድ ዓመት በኋላ ስንገናኝ የክልሉ የፀጥታ ችግር ተባብሷል የሚሉት አቶ ታዬ፤ ለዚህ የፀጥታ መደፍረስ ምክንያቱ ምንድን ነው? ተጠያቂውስ ማን ነው? በሚሉ ጉዳዮች ላይ ምክር ቤቱ እንዲወያይ ቢፈልጉም ዕድሉ እንደተነፈጉ ያስረዳሉ። የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ታዬ፤ በፓርቲው ውስጥ “ሌብነት ላይ የተሰማራ የተደራጀ ማፊያ አለ” ሲሉ ይከስሳሉ። አክለውም “ለዜጎች ክብር የለውም” ያሉት ቡድን በአካል እንጂ በሃሳብ ብልጽግና አይደለም ሲሉ ተናግረዋል። “ወረቀት ይዞ ብልጽግና ነኝ ሊል ይችላል እንጂ፣ ይህ ሰው አስፈራርቶ አፍኖ የሚወስድ ቡድን ብልጽግና አይደለም። . . . የታገልንለት ወደ ኋላ እንዲመለስ፤ ማፊያ እጅ እንዲገባ እኛ እንፈልግም” ብለዋል። አቶ ታዬ በንግግራቸው በኦሮሚያ ክልል አስተዳደር ውስጥ አለ ያሉት የማፊያ ቡድን፣ አባላቱ እነማን እንደሆኑ እንዲሁም “ማፊያ” ያሉት ቡድን ፈጽሟል ስላሉት አሉታዊ ተግባር ያቀረቡት ማስረጃ የለም። “እዚህ ቡድን ውስጥ ያሉት እነ እከሌ ናቸው ብሎ ለመዘርዘር ጊዜው አሁን አይደለም። ጊዜው ሲደርስ ስማቸውን እንዘረዝራለን” ሲሉ በደፈናው ማለፍን መርጠዋል። አቶ ታዬ በቅርቡ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ የደኅንነት ስጋት እንዳለባቸው ገልጸው ነበር። “ ‘እንረሽንሃለን...ግንባርህን እንልሃለን’ እያሉ በግልጽ የሚያስፈራሩ አሉ።...ሁሉንም አስፈራርቶ አይሆንም። ሰው መጉዳት፣ ሰው መግደል ይቻላል። ይህ ብዙ ቦታ ሆኗል። ሃጫሉ ሁንዴሳ ላይም ተፈጽሟል” በማለት ጠንከር ያለ አስተያየት ሰጥተዋል። የግል ጠባቂዎቻቸው እንዲነሱ መደረጋቸውን የሚናገሩት ሚኒስትር ዲኤታው፣ ምንም እንኳ የግድያ ዛቻን ጨምሮ ማስፈራሪያ ቢደርስባቸውም፤ “በትግላቸው” እንደሚቀጥሉ ይናገራሉ። ቢቢሲ የሚኒስትር ዲኤታ ጠባቂዎች ስለመነሳታቸው ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ማረጋገጥ አልቻለም። “... እኛ ከቤት የወጣነው ለነጻነት ነው። ለሕዝብ ነጻነት ታግዬ ብታፈን በተቃራኒ ጎራ ስለታገልኩ ነው። ዋስትናችን ትግላችን ነው” ሲሉም አክለዋል። አቶ ታዬ በኦሮሚያ ክልል አስተዳደር ውስጥ አሉ የሚሏቸው ብልሹ አሰራሮችን በንግግር ለመፍታት መንገዶች ዝግ መሆናቸውን ይናገራሉ። “በውይይት ውስጣችንን ማየት አለብን። በኦሮሚያ ሥልጣን ላይ ያለው ቡድን ግን ይህ እንዲደረግ አይፈልግም። ለውይይት በሩ ዝግ ነው። እኔ በጣም ብዙ ጊዜ ሞክሪያለሁ። ለዚህ ማስረጃ ማቅረብ እችላለሁ። የሚሰማኝ ግን አጣሁ” ብለዋል። የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታው አሁን በኦሮሚያ ክልል ያለው የፀጥታ ሁኔታ “...ወንድ ልጅ የሚደፈርበት፣ አባ ገዳዎች የሚገደሉበት፣ ሰው ወጥቶ መግባት የማይችልበት፣ እጅግ በጣም አስቀያሚ ነገሮች ያሉበት” ሲሉ ይገልጹታል። አቶ ታዬ የዜጎች ደኅንነትን ማረጋገጥ ሳይቻል ሰው ወጥቶ መግባት ስጋት ሆኖበት ሳለ፤ “በክልሉ አጠቃላይ ስኬት ማስመዝገብ ተችሏል ሲባል፤ ቀድሞ ምን ታቅዶ ነበር” ያስብላል ይላሉ። “በክልሉ ከተገነቡት ትምህርት ቤቶች ይልቅ የተቃጠሉት ይበልጣሉ። ሕዝባችን መኖሪያ ቤቱ ተቃጥሎ መሄጃ አጥቷል። በሬው ታርዶበት የሚያርስበት የለውም። ያለው ችግር ተቆጥሮ አያልቅም።” አቶ ታዬ ለጠቀሷቸው ዘርፈ ብዙ ችግሮች እርሳቸው አባል የሆኑበትን አስተዳደርን ተጠያቂው ያደርጋሉ። “ከሁሉም በላይ የሕዝብ ደኅንነት የማረጋገጥ ኃላፊነት ያለበት መንግሥት ነው። ...ስለዚህ በአሁኑ ጊዜ በኦሮሚያ ለተከሰተው ችግር ትልቁን ኃላፊነት መውሰድ ያለበት መንግሥት ነው” ብለዋል። አቶ ታዬ “ክልሉ ገብቶበታል” ላሉት ችግር ከመንግሥት በተጨማሪ ሌሎች ኃላፊነት መውሰድ ያለባቸው አካላት እንዳሉ ይናገራሉ። “በሰላማዊ መንገድ ከተማ ተገብቶ ከዚያ በኋላ ወደ ጫካ መሄድ አግባብ አይደለም” በማለት በክልሉ የሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ቡድንም “የሰላም ፀር” መሆኑን አንስተዋል። አቶ ታዬ ከዚህ ቀደም በአሮሚያ ክልል ሁለት ሸኔ ነው ያለው ሲሉ ተደምጠው ነበር። ሚኒስትር ዲኤታው መንግሥት አሸባሪ ሲል የፈረጀው እና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጠራው ቡድን አንዱ መሆኑን ገልጸው፤ “ሌላኛው ሸኔ መንግሥት ውስጥ የተሸሸገው ነው” ሲሉ ጠንከር ያለ አስተያየት ይሰጣሉ። “ጫካ ያለው አለ። ሌላኛው ደግሞ መንግሥት ውስጥ የተሸሸገው አለ። ወንጀል ደግሞ በዚህም በዚያም ይፈጽማሉ። ስለዚህ እኛ ውስጥ ያለ አለ፤ ከውጪም አለ” ብለዋል። በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ካሉ የፀጥታ ችግሮች አንጻር የመስተዳደሩ መዋቅር ላይ ትችቶች ሲሰነዘሩበት የቆየ ሲሆን፣ ባለሥልጣናትም መዋቅራቸውን ለማስተካከል እርምጃ እንደሚወስዱ በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲናገሩ ቆይተዋል። አቶ ታዬ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻቸው እና በተለያዩ መድረኮች አባል የሆኑበትን አስተዳደር አጥብቀው የሚተቹት ‘ሥልጣን ስለሚፈልጉ ነው’ የሚሉ ትችቶች ሲነሱባቸው ይታያል። አቶ ታዬ ግን ይህ “ቀልድ ነው” ይላሉ። “ሥልጣን ብንፈልግ ኖሮ በወያኔ ዘመንም አገኘው ነበር። ወያኔ አይደለም ለእኛ አይነት ሰው በአግባቡ መጻፍ ለማይችሉት ሁሉ ሥልጣን ሲሰጥ ነበር። ሥልጣን ፍለጋ እድሜያችንን አልገበርንም።” አቶ ታዬ አሁን ያሉበት የሚኒስትር ዲኤታ ሥልጣን ከዚህ ቀደም ከነበሩበት ከፍ ያለ መሆኑን ተናግረው፤ “ሰው በየዕለቱ እየተገደለ፣ ኢኮኖሚ እየደቀቀ፣ ወጥቶ መግባት እና በሕይወት መኖር አሳሳቢ በሆነበት ጊዜ ምን አይነት ሥልጣን ያምራል? የማይመስል ነገር ከማስመስል ቢቀር ይሻላል” ብለዋል። **** ማስታወሻ፡ አቶ ታዬ ደንደአ በዚህ ቃለ ምልልስ ላይ ለሰነዘሯቸው ሃሳቦች ከሚመለከታቸው የኦሮሚያ ክልል አካላት ምላሽ ለማግኘት ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ያደረገው ጥረት አልተሳካም። ነገር ግን ከዚህ በኋላም ምላሽ ለመስጠት የሚፈልግ ወገን ካለ ለማስተናገድ ዝግጁ ነን።
“መንግሥት ውስጥ የተሸሸገ ሸኔ አለ” የሰላም ሚኒስትር ዲኤታ ታዬ ደንደአ የሰላም ሚኒስትር ዲኤታ እና የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ታዬ ደንደአ የግድያ ማስፈራሪያዎች እንደሚደርሷቸው ለቢቢሲ ተናገሩ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማኅበራዊ ሚዲያዎች እና በተለያዩ መድረኮች በሚያነሷቸው ሃሳቦች አነጋገሪ የሆኑት ሚኒስትር ዲኤታው፤ በብልጽግና ፓርቲ ውስጥ አለ ስለሚሉት ‘የማፊያ ቡድን’ እና በግል ስለሚደርሱባቸው ጫናዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ታዬ በቅርብ በተካሄደው የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት ስብሰባ ላይ አስተያየት “እንዳልሰጥ ድምጼ ታፍኗል” ብለው የፌስቡክ ገጻቸው ላይ ካሰፈሩ በኋላ ጉዳዩ የብዙዎች መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። አቶ ታዬ በጨፌው [በኦሮሚያ ምክር ቤት] የሆነው ሲያስረዱ፤ አፈ ጉባኤዋ የዕለቱን አጀንዳ ካቀረቡ በኋላ ምክር ቤቱ በሁለት ተጨማሪ ጉዳዮች ላይ እንዲነጋገር አጀንዳ ለማስያዝ ያደረጉት ጥረት አለመሳካቱን ይናገራሉ። የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ የሆኑት አቶ ታዬ፤ የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት ከመቼውም ጊዜ በላይ “እየተበላሸ መጥቷል” ስላሉት የክልሉ የደኅንነት ሁኔታ አጀንዳ አድርጎ እንዲወያይበት ማቅረብ ፈልገው እንደነበረ ይገልጻሉ። ሁለተኛው ማንሳት የፈለጉት ጉዳይ ደግሞ “ከሌብነት ጋር በተያያዘ በክልላችን አስተዳደሩ ተዳክሟል” የሚል መሆኑን ጠቅሰዋል። “እጄን ሳወጣ ይዩኝ አይዩኝ [አፈ ጉባኤዋ] አላውቅም ዝም ብለው አጀንዳ ወደማጸደቅ ሄዱ። ከዚያ ‘ክብርት አፈ ጉባኤ የማነሳው ሃሳብ አለኝ’ አልኩ” ይላሉ አቶ ታዬ። “ከዚያ ዕድል እንደመስጠት አሉና እንዳልናገር ደግሞ ማይክሮፎኑን ዘጉብኝ። ትንሽ ቆይተው ‘ዕድሉን መጠቀም አልቻሉም’ አሉ። ‘ዝጉበት፣ ዝጉበት’ የሚል ድምጽ ይሰማ ነበር” በማለት አቶ ታዬ በጨፌው አጋጥሟል ያሉትን ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ታዬ አስተያየቴን እንዳልሰጥ የተከለልኩት፤ ምክር ቤቱ በአጀንዳነት የያዛቸው ሪፖርቶች ችግር እንዳሉባቸው ስለሚታወቅ ነው ይላሉ። ከአንድ ዓመት በፊት የኦሮሚያ የፀጥታ ስጋት በአጭር ወራት ውስጥ ይወገዳል ተብሎ፣ ከአንድ ዓመት በኋላ ስንገናኝ የክልሉ የፀጥታ ችግር ተባብሷል የሚሉት አቶ ታዬ፤ ለዚህ የፀጥታ መደፍረስ ምክንያቱ ምንድን ነው? ተጠያቂውስ ማን ነው? በሚሉ ጉዳዮች ላይ ምክር ቤቱ እንዲወያይ ቢፈልጉም ዕድሉ እንደተነፈጉ ያስረዳሉ። የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ታዬ፤ በፓርቲው ውስጥ “ሌብነት ላይ የተሰማራ የተደራጀ ማፊያ አለ” ሲሉ ይከስሳሉ። አክለውም “ለዜጎች ክብር የለውም” ያሉት ቡድን በአካል እንጂ በሃሳብ ብልጽግና አይደለም ሲሉ ተናግረዋል። “ወረቀት ይዞ ብልጽግና ነኝ ሊል ይችላል እንጂ፣ ይህ ሰው አስፈራርቶ አፍኖ የሚወስድ ቡድን ብልጽግና አይደለም። . . . የታገልንለት ወደ ኋላ እንዲመለስ፤ ማፊያ እጅ እንዲገባ እኛ እንፈልግም” ብለዋል። አቶ ታዬ በንግግራቸው በኦሮሚያ ክልል አስተዳደር ውስጥ አለ ያሉት የማፊያ ቡድን፣ አባላቱ እነማን እንደሆኑ እንዲሁም “ማፊያ” ያሉት ቡድን ፈጽሟል ስላሉት አሉታዊ ተግባር ያቀረቡት ማስረጃ የለም። “እዚህ ቡድን ውስጥ ያሉት እነ እከሌ ናቸው ብሎ ለመዘርዘር ጊዜው አሁን አይደለም። ጊዜው ሲደርስ ስማቸውን እንዘረዝራለን” ሲሉ በደፈናው ማለፍን መርጠዋል። አቶ ታዬ በቅርቡ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ የደኅንነት ስጋት እንዳለባቸው ገልጸው ነበር። “ ‘እንረሽንሃለን...ግንባርህን እንልሃለን’ እያሉ በግልጽ የሚያስፈራሩ አሉ።...ሁሉንም አስፈራርቶ አይሆንም። ሰው መጉዳት፣ ሰው መግደል ይቻላል። ይህ ብዙ ቦታ ሆኗል። ሃጫሉ ሁንዴሳ ላይም ተፈጽሟል” በማለት ጠንከር ያለ አስተያየት ሰጥተዋል። የግል ጠባቂዎቻቸው እንዲነሱ መደረጋቸውን የሚናገሩት ሚኒስትር ዲኤታው፣ ምንም እንኳ የግድያ ዛቻን ጨምሮ ማስፈራሪያ ቢደርስባቸውም፤ “በትግላቸው” እንደሚቀጥሉ ይናገራሉ። ቢቢሲ የሚኒስትር ዲኤታ ጠባቂዎች ስለመነሳታቸው ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ማረጋገጥ አልቻለም። “... እኛ ከቤት የወጣነው ለነጻነት ነው። ለሕዝብ ነጻነት ታግዬ ብታፈን በተቃራኒ ጎራ ስለታገልኩ ነው። ዋስትናችን ትግላችን ነው” ሲሉም አክለዋል። አቶ ታዬ በኦሮሚያ ክልል አስተዳደር ውስጥ አሉ የሚሏቸው ብልሹ አሰራሮችን በንግግር ለመፍታት መንገዶች ዝግ መሆናቸውን ይናገራሉ። “በውይይት ውስጣችንን ማየት አለብን። በኦሮሚያ ሥልጣን ላይ ያለው ቡድን ግን ይህ እንዲደረግ አይፈልግም። ለውይይት በሩ ዝግ ነው። እኔ በጣም ብዙ ጊዜ ሞክሪያለሁ። ለዚህ ማስረጃ ማቅረብ እችላለሁ። የሚሰማኝ ግን አጣሁ” ብለዋል። የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታው አሁን በኦሮሚያ ክልል ያለው የፀጥታ ሁኔታ “...ወንድ ልጅ የሚደፈርበት፣ አባ ገዳዎች የሚገደሉበት፣ ሰው ወጥቶ መግባት የማይችልበት፣ እጅግ በጣም አስቀያሚ ነገሮች ያሉበት” ሲሉ ይገልጹታል። አቶ ታዬ የዜጎች ደኅንነትን ማረጋገጥ ሳይቻል ሰው ወጥቶ መግባት ስጋት ሆኖበት ሳለ፤ “በክልሉ አጠቃላይ ስኬት ማስመዝገብ ተችሏል ሲባል፤ ቀድሞ ምን ታቅዶ ነበር” ያስብላል ይላሉ። “በክልሉ ከተገነቡት ትምህርት ቤቶች ይልቅ የተቃጠሉት ይበልጣሉ። ሕዝባችን መኖሪያ ቤቱ ተቃጥሎ መሄጃ አጥቷል። በሬው ታርዶበት የሚያርስበት የለውም። ያለው ችግር ተቆጥሮ አያልቅም።” አቶ ታዬ ለጠቀሷቸው ዘርፈ ብዙ ችግሮች እርሳቸው አባል የሆኑበትን አስተዳደርን ተጠያቂው ያደርጋሉ። “ከሁሉም በላይ የሕዝብ ደኅንነት የማረጋገጥ ኃላፊነት ያለበት መንግሥት ነው። ...ስለዚህ በአሁኑ ጊዜ በኦሮሚያ ለተከሰተው ችግር ትልቁን ኃላፊነት መውሰድ ያለበት መንግሥት ነው” ብለዋል። አቶ ታዬ “ክልሉ ገብቶበታል” ላሉት ችግር ከመንግሥት በተጨማሪ ሌሎች ኃላፊነት መውሰድ ያለባቸው አካላት እንዳሉ ይናገራሉ። “በሰላማዊ መንገድ ከተማ ተገብቶ ከዚያ በኋላ ወደ ጫካ መሄድ አግባብ አይደለም” በማለት በክልሉ የሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ቡድንም “የሰላም ፀር” መሆኑን አንስተዋል። አቶ ታዬ ከዚህ ቀደም በአሮሚያ ክልል ሁለት ሸኔ ነው ያለው ሲሉ ተደምጠው ነበር። ሚኒስትር ዲኤታው መንግሥት አሸባሪ ሲል የፈረጀው እና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጠራው ቡድን አንዱ መሆኑን ገልጸው፤ “ሌላኛው ሸኔ መንግሥት ውስጥ የተሸሸገው ነው” ሲሉ ጠንከር ያለ አስተያየት ይሰጣሉ። “ጫካ ያለው አለ። ሌላኛው ደግሞ መንግሥት ውስጥ የተሸሸገው አለ። ወንጀል ደግሞ በዚህም በዚያም ይፈጽማሉ። ስለዚህ እኛ ውስጥ ያለ አለ፤ ከውጪም አለ” ብለዋል። በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ካሉ የፀጥታ ችግሮች አንጻር የመስተዳደሩ መዋቅር ላይ ትችቶች ሲሰነዘሩበት የቆየ ሲሆን፣ ባለሥልጣናትም መዋቅራቸውን ለማስተካከል እርምጃ እንደሚወስዱ በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲናገሩ ቆይተዋል። አቶ ታዬ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻቸው እና በተለያዩ መድረኮች አባል የሆኑበትን አስተዳደር አጥብቀው የሚተቹት ‘ሥልጣን ስለሚፈልጉ ነው’ የሚሉ ትችቶች ሲነሱባቸው ይታያል። አቶ ታዬ ግን ይህ “ቀልድ ነው” ይላሉ። “ሥልጣን ብንፈልግ ኖሮ በወያኔ ዘመንም አገኘው ነበር። ወያኔ አይደለም ለእኛ አይነት ሰው በአግባቡ መጻፍ ለማይችሉት ሁሉ ሥልጣን ሲሰጥ ነበር። ሥልጣን ፍለጋ እድሜያችንን አልገበርንም።” አቶ ታዬ አሁን ያሉበት የሚኒስትር ዲኤታ ሥልጣን ከዚህ ቀደም ከነበሩበት ከፍ ያለ መሆኑን ተናግረው፤ “ሰው በየዕለቱ እየተገደለ፣ ኢኮኖሚ እየደቀቀ፣ ወጥቶ መግባት እና በሕይወት መኖር አሳሳቢ በሆነበት ጊዜ ምን አይነት ሥልጣን ያምራል? የማይመስል ነገር ከማስመስል ቢቀር ይሻላል” ብለዋል። **** ማስታወሻ፡ አቶ ታዬ ደንደአ በዚህ ቃለ ምልልስ ላይ ለሰነዘሯቸው ሃሳቦች ከሚመለከታቸው የኦሮሚያ ክልል አካላት ምላሽ ለማግኘት ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ያደረገው ጥረት አልተሳካም። ነገር ግን ከዚህ በኋላም ምላሽ ለመስጠት የሚፈልግ ወገን ካለ ለማስተናገድ ዝግጁ ነን።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cqlk0392qlko
0business
የቴስላ የገበያ ደርሻ መዳከሙን ተከትሎ ኤለን መስክ ቁጥር አንድ ባለጠጋ መሆኑ ቀረ
ኤለን መስክ የሐብቱ ዋና ምንጭ የሆነው የቴስላ የኤሌክትሪክ መኪና አክሲዮን ዋጋ በመቀነሱ በዓለም የሐብታሞች ደረጃ የቀዳሚነቱን ቦታ አጥቷል። በጥር ወር መጀመሪያ ላይ ከ 880 ዶላር በላይ የደረሰው የቴስላ አክሲዮኖች ዋጋ አሁን ላይ 20 በመቶ በላይ አሽቆልቁሏል። ኩባንያው በቅርቡ በ1.5 ቢሊዮን ዶላር ቢትኮይን ላይ ኢንቨስት በማድረጉ ምከንያት የቴስላ ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል። ይህን ተከትሎም የአማዞኑ አለቃ ጄፍ ቤዞስን በሐብታሞች ዝርዝር ውስጥ ወደ ነበረበት ቀዳሚ ቦታ ተመልሷል። ምንም እንኳን ኩባንያው የገበያ ደርሻው መቀነሱ ችግር ውስጥ ባይከተውም፤ ኩባንያው ከቢትኮይን ጋር መያያዙ አንዳንድ የቴስላ ባለአክሲዮኖች የአክሲዮን ድርሻቸውን እንዲሸጡ አነሳስቷቸዋል ሲሉ የዌድቡሽ ሴኩሪቲሱ ተንታኝ ዳን ኢቭስ ተናግረዋል። ቴስላ በ1.5 ቢሊዮን ዶላር ቢትኮይን መግዛቱ እና ቢትኮይንን እንደ ክፍያም ለመቀበል ማቀዱን ተከትሎ የቢትኮይን ዋጋ በቅርብ ሳምንታት በ50 በመቶ አድጓል። እንደ ማስተርካርድ እና የኒው ዮርክ ባንክ ያሉ ዋና ዋና ኩባንያዎች ቴስላን ተከትለው የዲጂታል ገንዘብን ለመቀበል ማቀዳቸውን አስታውቀዋል። መስክ ለቢትኮይን ትኩረት በሰጠበት ወቅት ቴስላ ሌሎች ተግዳሮቶችም እየገጠሙት ነው ፡፡ ኩባንያው ዝቅተኛ ዋጋ ያላቸውን መኪኖች ለማሻሻል በማሰብ የመኪኖቹን ሽያጭ በቅርቡ አቁሟል። ከዚህ በተጨማሪም፤ በዚህ ወር መጀመሪያ የቻይና ተቆጣጣሪዎች የባትሪ ቃጠሎ እና ያልተለመደ የፍጥነት ሪፖርት ከተደረገ በኋላ በደህንነት እና በጥራት ጉዳዮች ላይ ድርጅቱን አነጋግረዋል። እነዚህም ምክንያቶች የቴስላን ገቢ ከቀነሱ ጉዳይ መካከል ተጠቅሰዋል። እንደ ጄኔራል ሞተርስ እና ቮልስዋገን ያሉ ተፎካካሪ መኪና አምራቾችም በቅርብ ወራት በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ላይ ትኩረታቸውን አጠናክረዋል። እነዚህ ተግዳሮቶች የመጡት የቴስላ የአክሲዮን ዋጋዎች ከ 90 ዶላር ወደ 700 ዶላር በላይ በመመንደግ አስገራሚ ጭማሪን ካስከተሉ በኋላ የመጡ ናቸው። ጭማሪዎች መስክ በጥር ወር ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም የሐብታሞች ዘውርዝር የአማዞኑን ባለቤት ጄፍ ቤዞስን እንዲበልጥ አስችለውት ነበር።
የቴስላ የገበያ ደርሻ መዳከሙን ተከትሎ ኤለን መስክ ቁጥር አንድ ባለጠጋ መሆኑ ቀረ ኤለን መስክ የሐብቱ ዋና ምንጭ የሆነው የቴስላ የኤሌክትሪክ መኪና አክሲዮን ዋጋ በመቀነሱ በዓለም የሐብታሞች ደረጃ የቀዳሚነቱን ቦታ አጥቷል። በጥር ወር መጀመሪያ ላይ ከ 880 ዶላር በላይ የደረሰው የቴስላ አክሲዮኖች ዋጋ አሁን ላይ 20 በመቶ በላይ አሽቆልቁሏል። ኩባንያው በቅርቡ በ1.5 ቢሊዮን ዶላር ቢትኮይን ላይ ኢንቨስት በማድረጉ ምከንያት የቴስላ ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል። ይህን ተከትሎም የአማዞኑ አለቃ ጄፍ ቤዞስን በሐብታሞች ዝርዝር ውስጥ ወደ ነበረበት ቀዳሚ ቦታ ተመልሷል። ምንም እንኳን ኩባንያው የገበያ ደርሻው መቀነሱ ችግር ውስጥ ባይከተውም፤ ኩባንያው ከቢትኮይን ጋር መያያዙ አንዳንድ የቴስላ ባለአክሲዮኖች የአክሲዮን ድርሻቸውን እንዲሸጡ አነሳስቷቸዋል ሲሉ የዌድቡሽ ሴኩሪቲሱ ተንታኝ ዳን ኢቭስ ተናግረዋል። ቴስላ በ1.5 ቢሊዮን ዶላር ቢትኮይን መግዛቱ እና ቢትኮይንን እንደ ክፍያም ለመቀበል ማቀዱን ተከትሎ የቢትኮይን ዋጋ በቅርብ ሳምንታት በ50 በመቶ አድጓል። እንደ ማስተርካርድ እና የኒው ዮርክ ባንክ ያሉ ዋና ዋና ኩባንያዎች ቴስላን ተከትለው የዲጂታል ገንዘብን ለመቀበል ማቀዳቸውን አስታውቀዋል። መስክ ለቢትኮይን ትኩረት በሰጠበት ወቅት ቴስላ ሌሎች ተግዳሮቶችም እየገጠሙት ነው ፡፡ ኩባንያው ዝቅተኛ ዋጋ ያላቸውን መኪኖች ለማሻሻል በማሰብ የመኪኖቹን ሽያጭ በቅርቡ አቁሟል። ከዚህ በተጨማሪም፤ በዚህ ወር መጀመሪያ የቻይና ተቆጣጣሪዎች የባትሪ ቃጠሎ እና ያልተለመደ የፍጥነት ሪፖርት ከተደረገ በኋላ በደህንነት እና በጥራት ጉዳዮች ላይ ድርጅቱን አነጋግረዋል። እነዚህም ምክንያቶች የቴስላን ገቢ ከቀነሱ ጉዳይ መካከል ተጠቅሰዋል። እንደ ጄኔራል ሞተርስ እና ቮልስዋገን ያሉ ተፎካካሪ መኪና አምራቾችም በቅርብ ወራት በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ላይ ትኩረታቸውን አጠናክረዋል። እነዚህ ተግዳሮቶች የመጡት የቴስላ የአክሲዮን ዋጋዎች ከ 90 ዶላር ወደ 700 ዶላር በላይ በመመንደግ አስገራሚ ጭማሪን ካስከተሉ በኋላ የመጡ ናቸው። ጭማሪዎች መስክ በጥር ወር ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም የሐብታሞች ዘውርዝር የአማዞኑን ባለቤት ጄፍ ቤዞስን እንዲበልጥ አስችለውት ነበር።
https://www.bbc.com/amharic/56179063
0business
በኢትዮጵያ የሲሚንቶ ዋጋን አላስቀምስ ያሉት አራት ማነቆዎች
በኢትዮጵያ ውስጥ በሚካሄዱ በርካታ የግንባታ ሥራዎች አማካይነት እውን ከሚሆኑ ጠቃሚ ግንባታዎች በተጨማሪ ዘርፉ በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች የሥር ዕድልን እንደፈጠረ ይነገራል። ይሁን እንጂ ዋነኞቹ የግንባታ ግብዓቶች በሆኑት በሲሚንቶ እና በብረት ላይ የሚታየው የዋጋ ንረት፤ በአገሪቱ እየተከናወኑ ላሉ የግንባታ ሥራዎች ዋነኛ ፈተና ሆኖ ቀጥሏል። በአገሪቱ የሚገኙ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች፤ በስርጭት ችግር፣ በውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ በደኅንነት እጦት እና በጥሬ ዕቃ አቅርቦት መስተጓጎል ምርታቸው እየተፈተነ ነው። እነዚህም ዋጋቸው በከፍተኛ ደረጃ እንዲንር ምክንያት ሆነዋል። ይህም የአገሪቱን የግንባታ ዘርፍ ከፍኛ እየጎዳው እንደሆነ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎችና ተቋማት ይናገራሉ። ስርጭት በኢትዮጵያ የሲሚንቶ ዋጋ ጣራ እንዲነካ ከፍተኛ ድርሻውን ከሚይዙት ምክንያቶች መካከል አንዱ በስርጭት ሥርዓቱ ውስጥ ያለ እንከን ነው። ምርቱ ያለቀለት ሲሚንቶ ከፋብሪካ ወጥቶ የመጨረሻው ተጠቃሚ ጋር እስኪደርስ ድረስ ብዙ ሰንሰለቶችን ያልፋል። ፍቃድ ያላቸው ወኪሎች የሲሚንቶ ምርት ከፋብሪካ ተረክበው ለጅምላ አካፋፋዮች ያስረክባሉ። ጅምላ አከፋፋዮች ደግሞ ለቸርቻሪዎች ያቀርባሉ። የቢቢሲ ሪፖርተር በአዳማ ከተማ ተዘዋውሮ የሲሚንቶ ዋጋ ሁኔታን ተመልክቷል። በዚህም ባለፉት ጥቂት ወራት የሲሚንቶ ዋጋ ከነበረበት 500 ብር ገደማ ጨምሮ ከ1ሺህ ብር በላይ እየተሸጠ መሆኑን ተረድቷል። የኦሮሚያ ክልል ከሲሚንቶ ሰርጭት ጋር ተያይዞ ያለውን ችግር ለመቅረፍ ሲሚንቶ የማከፋፈሉን ሥራ ከወኪሎች እጅ በማውጣት ኃላፊነቱን በማኅበር ተደራጅተው ለሚገኙ ወጣቶች ለመስጠት ስለማቀዱ ገልጿል። አቶ ደረጄ ብርሃኑ ሲሚንቶ አከፋፋይ ወይም ወኪል ናቸው። አቶ ደረጄ ሲሚንቶ ከፋብሪካ ተረክበው 'በተመጣጣኝ ዋጋ' ለጅምላ ሻጮች እንደሚያከፋፍሉ ይናገራሉ የሚናገሩት አቶ ደረጄ፤ ለሲሚንቶ ዋጋ መናር ችግሩ ያለው ወኪሎች ጋር አይደለም ይላሉ። "ፋብሪካዎች ጥሬ ዕቃ በማጣታቸው ዋጋ ጨምረዋል። እንጂ ወኪሎች አይደሉም የጨመሩት። . . .ሌላው ዋጋ እየጨመሩ ያሉት ባለ ሱቆች ናቸው (ቸርቻሪዎች)። ብዙ ፈላጊ ስላለ ባለ ሱቆች ናቸው ዋጋ ጨምረው እየሸጡ ያሉት" ይላሉ። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሲሚንቶ ሸማቶች እንደሚሉት ከሆነ አከፋፋዮች (ወኪሎች) ከፋብሪካ የሚረከቡትን ሲሚንቶ ለነጋዴዎች ከመሸጥ ይልቅ አየር በአየር ለደላሎች የሚሸጡበት አጋጣሚ እንዳለ ያስረዳሉ። "እንደዚህ አይነቱ ለደላሎች አየር በአየር የመሸጥ ሥራ የሚሰሩ ሊኖሩ ይችላሉ" የሚሉት አቶ ብርሃኑ ሁሉም ግን በዚህ ድርጊት ውስጥ አሉበት ማለት እንደማይቻል ይገልጻሉ። ሲሚንቶ በችርቻሮ የሚሸጡበት ሱቅ ያላቸው አቶ ሙሴ እምሩ ደግሞ በሲሚንቶ ስርጭት ውስጥ ፈተና የሆኑት ደላሎች መሆናቸውን በማንሳት፣ "እኛ የምንረከበው ከደላሎች ነው" ይላሉ። ሲሚንቶ የሚያስረክቧቸው ደላሎች ሲሚንቶውን ከሌሎች ደላሎች በመግዛት የሚሸጡበት ሱቅ ሳይኖራቸው የምርት ዝውውሩን በስልክ ብቻ የሚያከናውኑ መሆናቸውን ይጠቅሳሉ። እንደ አቶ ሙሴ ገለጻ ከሆነ ወኪሎች የሲሚንቶ ምርት ከፋብሪካ ከተረከቡ በኋላ ሲሚቶው የመጨረሻው ተጠቃሚ ጋር ከመድረሱ በፊት በአካፋፋዮች እና ከአንድ በላይ በሆኑ ደላሎች በኩል ያልፋል። የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት እና የሲሚንቶ ችግርን ለመቅረፍ የተቋቋመው ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አወሉ አብዲ ከሲሚንቶ ስርጭት ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን ለመቅፍ የክልሉ መንግሥት ወኪሎችን ከንግድ ሰንሰለቱ ሙሉ በሙሉ አስወጥቶ ስርጭቱ በተደራጁ ወጣቶች እንዲከናወን መወሰኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ወጣቶች አደራጅተን ማከማቻ እና የሽያጭ ቦታዎችን በየከተሞቹ እናዘጋጃለን። በፋይናንስ በኩልም ሁኔታዎች ይመቻቻሉ። ከሲሚንቶ ኢንዱስትሪዎች ጋር አብረው እንዲሰሩ ይደረጋል" ብለዋል። የባለሥልጣናት ቤተሰቦች በስርጭቱ ውስጥ መሳተፍ ከሲሚንቶ ስርጭት ጋር ተያይዞ ከሚነሱት ወቀሳዎች መካከል የመንግሥት ባለሥልጣናት የቤተሰብ አባላትን ጨምሮ በጥቅም የተሳሰሩ የአከፋፋዮች ሰንሰለት አንዱ ሊሆን እንደሚችል በዘርፉ ንግድ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ይናገራሉ። በሲሚንቶ አከፋፋይነት ተሰማርተው ከሚገኙት መካከል ቢቢሲ ያናገራቸው ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ግለሰቦች እንደሚሉት ይህ የተወሰኑ ባለሥልጣናት ቤተሰቦች እና ከእነሱ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎች በስርጭቱ ውስጥ እንዳሉበት እንደሚወራ በመግለጽ በተጨባጭ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ አመልክተዋል። ሌሎች ደግሞ በግላጭ ማንነታቸው ወጥቶ አይታወቅ እንጂ በተዘዋዋሪ ብዙም ባይሆኑ የተወሰኑ ግለሰቦች በስርጭቱ ውስጥ እጃቸውን እንዳስገቡ እንደሚያምኑ ገልጸዋል። በተመሳሳይ ከዚህ ቀደም የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ አባላት በሲሚንቶ ንግድ ውስጥ የባለሥልጣናት ቤተሰብ አባላት ተሳትፎ አላቸው በሚል እርስ በእርስ ሲካሰሱ እንደነበር ይታወሳል። አቶ አወሉ አብዲ ግን በሲሚንቶ ንግድ ውስጥ የባለሥልጣናት የቤተሰብ አባላት ተሳታፊ ናቸው የሚባለውን እውነት አይደለም ይላሉ። "የክልሉ ባለሥልጣናት የቤተሰብ አባላት በሲሚንቶ ንግድ ውስጥ ገብተዋል የሚላው በተደረገው ምርመራ ሐሰት መሆኑ ተደርሶበታል። ዘመድ ሳይሆን የዘመድ ዘመድ በሲሚንቶ ንግድ የተሳተፈ አልተገኘም" ይላሉ አቶ አወሉ። "በአገር ደረጃ ዘጠና አካባቢ ወኪሎች ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል አንድም የባለሥልጣን ዘመድ የለም። በባለቤቶቻቸው ስም ሲሚንቶ እየነገዱ ነው የሚለው የሐሰት ወሬ ነው" ብለዋል። የደኅንነት ችግር በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሲሚንቶ የገበያ ድርሻውን ይዘው የሚገኙት በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ናቸው። ዳንጎቴ፣ ደርባ፣ ሙገር፣ ኢትዮ ሴሜነን- በአንድ አካባቢ ይገኛሉ። በምዕራብ ሸዋ ዞን ውስጥ። በእነዚህ ስፍራዎች ደግሞ እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጠራው እና መንግሥት ሸኔ ብሎ አሸባሪ ሲል የፈረጀው ታጣቂ ቡድን ይንቀሳቀሳል። ይህንን በታጣቂዎች የሚፈጠር የደኅንነት ስጋትን ለማስወገድ መንግሥት በግዙፍ ተቋማት አካባቢ ደኅንነትን ለማረጋገጥ የረዥም እና የአጭር ጊዜ እቅድ አውጥቶ እየሰራ እንደሆነ አቶ አወሉ ይናገራሉ። "ወደፊት 'ኢንደስትሪያል ፎርስ' የተባለ ኃይል ተደራጅቶ ይህን የኢንዱስትሪ ደኅንነት እንዲያረጋግጥ አቅጣጫ ተቀምጧል። እስከዚያው ድረስ ደግሞ በቂ ፀጥታ ኃይል በአካባቢዎቹ እንዲሰማራ ከውሳኔ ተደርሷል" ይላሉ። ከጥቂት ሳምንታት በፊት የውጭ አገር ዜጎችን ጨምሮ የሲሚንቶ ፋብሪካ ሠራተኞች በታጣቂዎች ታግተው ማስለቀቂያ ገንዘብ ተጠይቆባቸው ነበር። የአካባቢው ባለሥልጣናት ለዚህ እገታ ታጣቂውን ቡድን 'ሸኔ'ን ተጠያቂ አድርገው ነበር። በቅርቡ ከሲሚንቶ ምርት እና ስርጭት ጋር ተያይዞ ላሉ ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝደንት ሽመልስ አብዲሳ፣ የማዕድን ሚንስትሩ ታከለ ኡማ እና ሲሚንቶ አምራቾች ውይይት አካሂደው ነበር። በዚህ ውይይት ላይ የማዕድን ሚንስትሩ ከደኅንነት እጦት ጋር ተያይዞ ላሉ ቸግሮችን ለመፍታት የአካባቢው ወጣቶች በዘርፉ ላይ ያላቸውን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ አንዱ መፍትሄ መሆኑን መግባባት ላይ እንደተደረሰበት ገልጸዋል። ኢንጅነር ታከለ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ "የአካባቢው ወጣቶች በዘርፉ ላይ ያላቸውን ተጠቃሚነት ማስከበር በአንድ በኩል የወጣቶችን ህይወት የሚያሻሽል ሲሆን በሌላ በኩል ማኅበረሰበቡ በአካባቢው ለሚገኙ ተቋማት የሚኖሮውን የኔነት ስሜት የሚያሳድግ ነው። ይህም ለአካባቢው ሰላም እና ፋብሪካዎቹ የሚገጥማቸውን የፀጥታ ችግር ለማስቀረት የጎላ ሚና እንደሚኖረው ተግባብተናል" ብለዋል። የውጭ ምንዛሬ እጥረት ኢትዮጵያ ባለፉት በርካታ ዓመታት በተለይም የሰሜኑ ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ በውጭ ምንዛሬ እጥረት አዙሪት ውስጥ እንደምተገኝ የተለያዩ አስመጪዎችና ሪፖርቶች ያመለክታሉ። የውጭ ምንዛሬው እጥረት በኮንትራክሽን ዘረፉ ላይ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በአገሪቱ ምጣኔ ሃብት ላይ ትልቁን ፈተና እንደደቀነ ከውጪ በሚመጡ ምርቶች ላይ የሚታየው የዋጋ መናር ቀላሉ ማሳያ ነው። አምራቾች ከውጪ ለሚያስገቧቸው ግብዓቶቻቸው በውጭ ምንዛሬ መክፈል ይጠብቅባቸዋል። ሲሚንቶ ፋብሪካዎች ደግሞ ለምርታቸው የሚያስፈልጓቸውን የድንጋይ ከሰል እና መለዋወጫዎችን ከውጭ ያስገባሉ። አቶ አወሉም በኢትዮጵያ ከየሲሚንቶ ምርት ጋር ተያይዞ ያለው ዋነኛው ችግሩ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ነው ይላሉ። በተደጋጋሚ እንደተጠቀሰው የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ለውጭ ምንዛሬ እጥረት ዘላቂው መፍትሄ አገሪቱ ለውጭ ገበያ የምታቀርበውን ምርት (ወጪ ንግድ) ላይ በርትቶ መስራት ሁነኛ አማራጭ ነው ይላሉ።
በኢትዮጵያ የሲሚንቶ ዋጋን አላስቀምስ ያሉት አራት ማነቆዎች በኢትዮጵያ ውስጥ በሚካሄዱ በርካታ የግንባታ ሥራዎች አማካይነት እውን ከሚሆኑ ጠቃሚ ግንባታዎች በተጨማሪ ዘርፉ በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች የሥር ዕድልን እንደፈጠረ ይነገራል። ይሁን እንጂ ዋነኞቹ የግንባታ ግብዓቶች በሆኑት በሲሚንቶ እና በብረት ላይ የሚታየው የዋጋ ንረት፤ በአገሪቱ እየተከናወኑ ላሉ የግንባታ ሥራዎች ዋነኛ ፈተና ሆኖ ቀጥሏል። በአገሪቱ የሚገኙ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች፤ በስርጭት ችግር፣ በውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ በደኅንነት እጦት እና በጥሬ ዕቃ አቅርቦት መስተጓጎል ምርታቸው እየተፈተነ ነው። እነዚህም ዋጋቸው በከፍተኛ ደረጃ እንዲንር ምክንያት ሆነዋል። ይህም የአገሪቱን የግንባታ ዘርፍ ከፍኛ እየጎዳው እንደሆነ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎችና ተቋማት ይናገራሉ። ስርጭት በኢትዮጵያ የሲሚንቶ ዋጋ ጣራ እንዲነካ ከፍተኛ ድርሻውን ከሚይዙት ምክንያቶች መካከል አንዱ በስርጭት ሥርዓቱ ውስጥ ያለ እንከን ነው። ምርቱ ያለቀለት ሲሚንቶ ከፋብሪካ ወጥቶ የመጨረሻው ተጠቃሚ ጋር እስኪደርስ ድረስ ብዙ ሰንሰለቶችን ያልፋል። ፍቃድ ያላቸው ወኪሎች የሲሚንቶ ምርት ከፋብሪካ ተረክበው ለጅምላ አካፋፋዮች ያስረክባሉ። ጅምላ አከፋፋዮች ደግሞ ለቸርቻሪዎች ያቀርባሉ። የቢቢሲ ሪፖርተር በአዳማ ከተማ ተዘዋውሮ የሲሚንቶ ዋጋ ሁኔታን ተመልክቷል። በዚህም ባለፉት ጥቂት ወራት የሲሚንቶ ዋጋ ከነበረበት 500 ብር ገደማ ጨምሮ ከ1ሺህ ብር በላይ እየተሸጠ መሆኑን ተረድቷል። የኦሮሚያ ክልል ከሲሚንቶ ሰርጭት ጋር ተያይዞ ያለውን ችግር ለመቅረፍ ሲሚንቶ የማከፋፈሉን ሥራ ከወኪሎች እጅ በማውጣት ኃላፊነቱን በማኅበር ተደራጅተው ለሚገኙ ወጣቶች ለመስጠት ስለማቀዱ ገልጿል። አቶ ደረጄ ብርሃኑ ሲሚንቶ አከፋፋይ ወይም ወኪል ናቸው። አቶ ደረጄ ሲሚንቶ ከፋብሪካ ተረክበው 'በተመጣጣኝ ዋጋ' ለጅምላ ሻጮች እንደሚያከፋፍሉ ይናገራሉ የሚናገሩት አቶ ደረጄ፤ ለሲሚንቶ ዋጋ መናር ችግሩ ያለው ወኪሎች ጋር አይደለም ይላሉ። "ፋብሪካዎች ጥሬ ዕቃ በማጣታቸው ዋጋ ጨምረዋል። እንጂ ወኪሎች አይደሉም የጨመሩት። . . .ሌላው ዋጋ እየጨመሩ ያሉት ባለ ሱቆች ናቸው (ቸርቻሪዎች)። ብዙ ፈላጊ ስላለ ባለ ሱቆች ናቸው ዋጋ ጨምረው እየሸጡ ያሉት" ይላሉ። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሲሚንቶ ሸማቶች እንደሚሉት ከሆነ አከፋፋዮች (ወኪሎች) ከፋብሪካ የሚረከቡትን ሲሚንቶ ለነጋዴዎች ከመሸጥ ይልቅ አየር በአየር ለደላሎች የሚሸጡበት አጋጣሚ እንዳለ ያስረዳሉ። "እንደዚህ አይነቱ ለደላሎች አየር በአየር የመሸጥ ሥራ የሚሰሩ ሊኖሩ ይችላሉ" የሚሉት አቶ ብርሃኑ ሁሉም ግን በዚህ ድርጊት ውስጥ አሉበት ማለት እንደማይቻል ይገልጻሉ። ሲሚንቶ በችርቻሮ የሚሸጡበት ሱቅ ያላቸው አቶ ሙሴ እምሩ ደግሞ በሲሚንቶ ስርጭት ውስጥ ፈተና የሆኑት ደላሎች መሆናቸውን በማንሳት፣ "እኛ የምንረከበው ከደላሎች ነው" ይላሉ። ሲሚንቶ የሚያስረክቧቸው ደላሎች ሲሚንቶውን ከሌሎች ደላሎች በመግዛት የሚሸጡበት ሱቅ ሳይኖራቸው የምርት ዝውውሩን በስልክ ብቻ የሚያከናውኑ መሆናቸውን ይጠቅሳሉ። እንደ አቶ ሙሴ ገለጻ ከሆነ ወኪሎች የሲሚንቶ ምርት ከፋብሪካ ከተረከቡ በኋላ ሲሚቶው የመጨረሻው ተጠቃሚ ጋር ከመድረሱ በፊት በአካፋፋዮች እና ከአንድ በላይ በሆኑ ደላሎች በኩል ያልፋል። የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት እና የሲሚንቶ ችግርን ለመቅረፍ የተቋቋመው ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አወሉ አብዲ ከሲሚንቶ ስርጭት ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን ለመቅፍ የክልሉ መንግሥት ወኪሎችን ከንግድ ሰንሰለቱ ሙሉ በሙሉ አስወጥቶ ስርጭቱ በተደራጁ ወጣቶች እንዲከናወን መወሰኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል። "ወጣቶች አደራጅተን ማከማቻ እና የሽያጭ ቦታዎችን በየከተሞቹ እናዘጋጃለን። በፋይናንስ በኩልም ሁኔታዎች ይመቻቻሉ። ከሲሚንቶ ኢንዱስትሪዎች ጋር አብረው እንዲሰሩ ይደረጋል" ብለዋል። የባለሥልጣናት ቤተሰቦች በስርጭቱ ውስጥ መሳተፍ ከሲሚንቶ ስርጭት ጋር ተያይዞ ከሚነሱት ወቀሳዎች መካከል የመንግሥት ባለሥልጣናት የቤተሰብ አባላትን ጨምሮ በጥቅም የተሳሰሩ የአከፋፋዮች ሰንሰለት አንዱ ሊሆን እንደሚችል በዘርፉ ንግድ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ይናገራሉ። በሲሚንቶ አከፋፋይነት ተሰማርተው ከሚገኙት መካከል ቢቢሲ ያናገራቸው ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ግለሰቦች እንደሚሉት ይህ የተወሰኑ ባለሥልጣናት ቤተሰቦች እና ከእነሱ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎች በስርጭቱ ውስጥ እንዳሉበት እንደሚወራ በመግለጽ በተጨባጭ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ አመልክተዋል። ሌሎች ደግሞ በግላጭ ማንነታቸው ወጥቶ አይታወቅ እንጂ በተዘዋዋሪ ብዙም ባይሆኑ የተወሰኑ ግለሰቦች በስርጭቱ ውስጥ እጃቸውን እንዳስገቡ እንደሚያምኑ ገልጸዋል። በተመሳሳይ ከዚህ ቀደም የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ አባላት በሲሚንቶ ንግድ ውስጥ የባለሥልጣናት ቤተሰብ አባላት ተሳትፎ አላቸው በሚል እርስ በእርስ ሲካሰሱ እንደነበር ይታወሳል። አቶ አወሉ አብዲ ግን በሲሚንቶ ንግድ ውስጥ የባለሥልጣናት የቤተሰብ አባላት ተሳታፊ ናቸው የሚባለውን እውነት አይደለም ይላሉ። "የክልሉ ባለሥልጣናት የቤተሰብ አባላት በሲሚንቶ ንግድ ውስጥ ገብተዋል የሚላው በተደረገው ምርመራ ሐሰት መሆኑ ተደርሶበታል። ዘመድ ሳይሆን የዘመድ ዘመድ በሲሚንቶ ንግድ የተሳተፈ አልተገኘም" ይላሉ አቶ አወሉ። "በአገር ደረጃ ዘጠና አካባቢ ወኪሎች ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል አንድም የባለሥልጣን ዘመድ የለም። በባለቤቶቻቸው ስም ሲሚንቶ እየነገዱ ነው የሚለው የሐሰት ወሬ ነው" ብለዋል። የደኅንነት ችግር በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሲሚንቶ የገበያ ድርሻውን ይዘው የሚገኙት በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ናቸው። ዳንጎቴ፣ ደርባ፣ ሙገር፣ ኢትዮ ሴሜነን- በአንድ አካባቢ ይገኛሉ። በምዕራብ ሸዋ ዞን ውስጥ። በእነዚህ ስፍራዎች ደግሞ እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጠራው እና መንግሥት ሸኔ ብሎ አሸባሪ ሲል የፈረጀው ታጣቂ ቡድን ይንቀሳቀሳል። ይህንን በታጣቂዎች የሚፈጠር የደኅንነት ስጋትን ለማስወገድ መንግሥት በግዙፍ ተቋማት አካባቢ ደኅንነትን ለማረጋገጥ የረዥም እና የአጭር ጊዜ እቅድ አውጥቶ እየሰራ እንደሆነ አቶ አወሉ ይናገራሉ። "ወደፊት 'ኢንደስትሪያል ፎርስ' የተባለ ኃይል ተደራጅቶ ይህን የኢንዱስትሪ ደኅንነት እንዲያረጋግጥ አቅጣጫ ተቀምጧል። እስከዚያው ድረስ ደግሞ በቂ ፀጥታ ኃይል በአካባቢዎቹ እንዲሰማራ ከውሳኔ ተደርሷል" ይላሉ። ከጥቂት ሳምንታት በፊት የውጭ አገር ዜጎችን ጨምሮ የሲሚንቶ ፋብሪካ ሠራተኞች በታጣቂዎች ታግተው ማስለቀቂያ ገንዘብ ተጠይቆባቸው ነበር። የአካባቢው ባለሥልጣናት ለዚህ እገታ ታጣቂውን ቡድን 'ሸኔ'ን ተጠያቂ አድርገው ነበር። በቅርቡ ከሲሚንቶ ምርት እና ስርጭት ጋር ተያይዞ ላሉ ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝደንት ሽመልስ አብዲሳ፣ የማዕድን ሚንስትሩ ታከለ ኡማ እና ሲሚንቶ አምራቾች ውይይት አካሂደው ነበር። በዚህ ውይይት ላይ የማዕድን ሚንስትሩ ከደኅንነት እጦት ጋር ተያይዞ ላሉ ቸግሮችን ለመፍታት የአካባቢው ወጣቶች በዘርፉ ላይ ያላቸውን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ አንዱ መፍትሄ መሆኑን መግባባት ላይ እንደተደረሰበት ገልጸዋል። ኢንጅነር ታከለ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ "የአካባቢው ወጣቶች በዘርፉ ላይ ያላቸውን ተጠቃሚነት ማስከበር በአንድ በኩል የወጣቶችን ህይወት የሚያሻሽል ሲሆን በሌላ በኩል ማኅበረሰበቡ በአካባቢው ለሚገኙ ተቋማት የሚኖሮውን የኔነት ስሜት የሚያሳድግ ነው። ይህም ለአካባቢው ሰላም እና ፋብሪካዎቹ የሚገጥማቸውን የፀጥታ ችግር ለማስቀረት የጎላ ሚና እንደሚኖረው ተግባብተናል" ብለዋል። የውጭ ምንዛሬ እጥረት ኢትዮጵያ ባለፉት በርካታ ዓመታት በተለይም የሰሜኑ ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ በውጭ ምንዛሬ እጥረት አዙሪት ውስጥ እንደምተገኝ የተለያዩ አስመጪዎችና ሪፖርቶች ያመለክታሉ። የውጭ ምንዛሬው እጥረት በኮንትራክሽን ዘረፉ ላይ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በአገሪቱ ምጣኔ ሃብት ላይ ትልቁን ፈተና እንደደቀነ ከውጪ በሚመጡ ምርቶች ላይ የሚታየው የዋጋ መናር ቀላሉ ማሳያ ነው። አምራቾች ከውጪ ለሚያስገቧቸው ግብዓቶቻቸው በውጭ ምንዛሬ መክፈል ይጠብቅባቸዋል። ሲሚንቶ ፋብሪካዎች ደግሞ ለምርታቸው የሚያስፈልጓቸውን የድንጋይ ከሰል እና መለዋወጫዎችን ከውጭ ያስገባሉ። አቶ አወሉም በኢትዮጵያ ከየሲሚንቶ ምርት ጋር ተያይዞ ያለው ዋነኛው ችግሩ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ነው ይላሉ። በተደጋጋሚ እንደተጠቀሰው የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ለውጭ ምንዛሬ እጥረት ዘላቂው መፍትሄ አገሪቱ ለውጭ ገበያ የምታቀርበውን ምርት (ወጪ ንግድ) ላይ በርትቶ መስራት ሁነኛ አማራጭ ነው ይላሉ።
https://www.bbc.com/amharic/news-61438921
3politics
የኦሮሚያው ግጭት እርዳታ የሚጠብቁ ሰዎችን ቁጥር እንደጨመረው ተመድ ገለጸ
በኦሮሚያ ክልል እየተባባሰ የመጣው ግጭት የሰብአዊ እርዳታ የሚጠባበቁ ነዋሪዎችን ቁጥር እንደጨመረው የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ዩኤን ኦቻ) አስታወቀ። በክልሉ የሚፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ከመምጣቱ ባሻገር የመሠረታዊ አገልግሎቶች አቅርቦት ላይም ጫና እንደተፈጠረ ኦቻ ባወጣው ሪፖርት ገልጿል። በተባባሰው ግጭት ምክንያት በቅርቡ ምን ያህል ሰዎች እንደተፈናቀሉ ለማወቅ አዳጋች ቢሆንም፣ የክልሉ ባለሥልጣናት እስካሁን ባወጧቸው አሐዞች መሠረት በምዕራብ ወለጋ ዞን 106,000 ነዋሪዎች እንዲሁም በሆሮ ጉዱሩ 116,000 ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ሪፖርቱ ጠቅሷል። “በክልሉ ተደራራቢ ቀውሶች መፈጠራቸው የሰብአዊ እርዳታ ፍላጎት እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል። ግጭቶችን ተከትሎ ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው እየተፈናቀሉም ነው” ሲል ኦቻ ኅዳር 28 ቀን 2015 ዓ. ም. ባወጣው ሪፖርት ገልጿል። ባለፉት ቀናት በምዕራብ ኦሮሚያ ምሥራቅ ወለጋ ዞን ብሔር ተኮር በሆኑ ጥቃቶች ሰላማዊ ሰዎች ሰለባ መሆናቸው ሲገለጽ ቆይቷል። በተለይም በምሥራቅ ወለጋ ዞን ውስጥ በሚገኙት ጊዳ አያና እና ኪራሙ ወረዳዎች ባለፉት ቀናት በነበሩ ጥቃቶች በርካቶች ሲገደሉ በመቶ ሺዎች መፈናቀላቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች በተቀሰቀሱ ግጭቶች እና ጥቃቶች ሳቢያ እየደረሱ ያሉ ግድያዎች፣ የአካል ጉዳቶች እና መፈናቀሎች እጅግ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንደሆኑ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ኅዳር 28/2015 ዓ.ም. ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል። የሰሞነኛው ግጭት ዋነኛ ተሳታፊዎች “ሸኔ እና የአማራ ታጣቂዎች” ናቸው ያለው ኢሰመኮ፤ በክልሉ ዞኖች በታጣቂ ቡድኖቹ በተፈጸሙ ጥቃቶች በመቶዎች የሚገመቱ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን እና ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎች ደግሞ ለአካል ጉዳት መዳረጋቸውን ገልጿል። ኦቻ በበኩሉ፣ ከሰሞኑ በተነሳው ግጭት ምን ያህል ሰዎች እንደተፈናቀሉ ገና ባይታወቅም፣ እስካሁን በእነዚህ አካባቢዎች የተፈናቀሉና እርዳታ የሚጠባበቁ ሰዎችን ቁጥር ከፍ እንደሚያደርገው ጠቅሷል። ክልሉ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ሰዎች ተጨማሪ መጠለያዎችን እያዘጋጀ እንደሆነ በሪፖርቱ ተገልጿል። የእርዳታ አቅርቦት እና እርዳታ የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥር እንደማይመጣጠን የገለጸው ኦቻ፣ በምዕራብ ወለጋ ዞን እርዳታ ከሚፈልጉ 19,000 አባወራዎች መካከል 1,100 ብቻ ድጋፍ እንዳገኙና በምሥራቅ ወለጋ ዞን እርዳታ ከሚፈልጉ 30,000 አባወራዎች 9,337 ብቻ ድጋፍ እንዳገኙ አስታውቋል። በበጀት እጥረት እና እርዳታ ማሳለጫ መንገዶች በማጣት፤ ኦቻ ኦሮሚያን ጨምሮ ሰብአዊ እርዳታ በሚያደርስባቸው አካባቢዎች ድጋፍ ከሚፈልጉ ሰዎች ግማሽ ያህሉን እንኳን ማዳረስ እንዳልቻለ በሪፖርቱ አካቷል። በክልሉ በተለይም በድርቅ በተጠቁ አካባቢዎች የሕጻናት መቀንጨር መከሰቱንም የኦቻ ሪፖርት ያመለክታል።እስካሁን 563,000 ሕጻናት ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን፣ 1.96 በመቶው በከፋ ሁኔታ እንዲሁም 18 በመቶው በተወሰነ መጠን መቀንጨር ገጥሟቸዋል። የኮሌራ እና ኩፍኝ ወረርሽኝ ያለውን ችግር እንዳባባሱት እንዲሁም የተመጣጠ ምግብ እጥረት ላይ የቤተሰቦች አለመኖር ክፉኛ በድርቅ የተጎዱ ወረዳዎች ያሉ ሕጻናትን ለአደጋ ማጋለጡን ኦቻ አክሏል።
የኦሮሚያው ግጭት እርዳታ የሚጠብቁ ሰዎችን ቁጥር እንደጨመረው ተመድ ገለጸ በኦሮሚያ ክልል እየተባባሰ የመጣው ግጭት የሰብአዊ እርዳታ የሚጠባበቁ ነዋሪዎችን ቁጥር እንደጨመረው የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ዩኤን ኦቻ) አስታወቀ። በክልሉ የሚፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ከመምጣቱ ባሻገር የመሠረታዊ አገልግሎቶች አቅርቦት ላይም ጫና እንደተፈጠረ ኦቻ ባወጣው ሪፖርት ገልጿል። በተባባሰው ግጭት ምክንያት በቅርቡ ምን ያህል ሰዎች እንደተፈናቀሉ ለማወቅ አዳጋች ቢሆንም፣ የክልሉ ባለሥልጣናት እስካሁን ባወጧቸው አሐዞች መሠረት በምዕራብ ወለጋ ዞን 106,000 ነዋሪዎች እንዲሁም በሆሮ ጉዱሩ 116,000 ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ሪፖርቱ ጠቅሷል። “በክልሉ ተደራራቢ ቀውሶች መፈጠራቸው የሰብአዊ እርዳታ ፍላጎት እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል። ግጭቶችን ተከትሎ ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው እየተፈናቀሉም ነው” ሲል ኦቻ ኅዳር 28 ቀን 2015 ዓ. ም. ባወጣው ሪፖርት ገልጿል። ባለፉት ቀናት በምዕራብ ኦሮሚያ ምሥራቅ ወለጋ ዞን ብሔር ተኮር በሆኑ ጥቃቶች ሰላማዊ ሰዎች ሰለባ መሆናቸው ሲገለጽ ቆይቷል። በተለይም በምሥራቅ ወለጋ ዞን ውስጥ በሚገኙት ጊዳ አያና እና ኪራሙ ወረዳዎች ባለፉት ቀናት በነበሩ ጥቃቶች በርካቶች ሲገደሉ በመቶ ሺዎች መፈናቀላቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች በተቀሰቀሱ ግጭቶች እና ጥቃቶች ሳቢያ እየደረሱ ያሉ ግድያዎች፣ የአካል ጉዳቶች እና መፈናቀሎች እጅግ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንደሆኑ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ኅዳር 28/2015 ዓ.ም. ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል። የሰሞነኛው ግጭት ዋነኛ ተሳታፊዎች “ሸኔ እና የአማራ ታጣቂዎች” ናቸው ያለው ኢሰመኮ፤ በክልሉ ዞኖች በታጣቂ ቡድኖቹ በተፈጸሙ ጥቃቶች በመቶዎች የሚገመቱ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን እና ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎች ደግሞ ለአካል ጉዳት መዳረጋቸውን ገልጿል። ኦቻ በበኩሉ፣ ከሰሞኑ በተነሳው ግጭት ምን ያህል ሰዎች እንደተፈናቀሉ ገና ባይታወቅም፣ እስካሁን በእነዚህ አካባቢዎች የተፈናቀሉና እርዳታ የሚጠባበቁ ሰዎችን ቁጥር ከፍ እንደሚያደርገው ጠቅሷል። ክልሉ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ሰዎች ተጨማሪ መጠለያዎችን እያዘጋጀ እንደሆነ በሪፖርቱ ተገልጿል። የእርዳታ አቅርቦት እና እርዳታ የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥር እንደማይመጣጠን የገለጸው ኦቻ፣ በምዕራብ ወለጋ ዞን እርዳታ ከሚፈልጉ 19,000 አባወራዎች መካከል 1,100 ብቻ ድጋፍ እንዳገኙና በምሥራቅ ወለጋ ዞን እርዳታ ከሚፈልጉ 30,000 አባወራዎች 9,337 ብቻ ድጋፍ እንዳገኙ አስታውቋል። በበጀት እጥረት እና እርዳታ ማሳለጫ መንገዶች በማጣት፤ ኦቻ ኦሮሚያን ጨምሮ ሰብአዊ እርዳታ በሚያደርስባቸው አካባቢዎች ድጋፍ ከሚፈልጉ ሰዎች ግማሽ ያህሉን እንኳን ማዳረስ እንዳልቻለ በሪፖርቱ አካቷል። በክልሉ በተለይም በድርቅ በተጠቁ አካባቢዎች የሕጻናት መቀንጨር መከሰቱንም የኦቻ ሪፖርት ያመለክታል።እስካሁን 563,000 ሕጻናት ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን፣ 1.96 በመቶው በከፋ ሁኔታ እንዲሁም 18 በመቶው በተወሰነ መጠን መቀንጨር ገጥሟቸዋል። የኮሌራ እና ኩፍኝ ወረርሽኝ ያለውን ችግር እንዳባባሱት እንዲሁም የተመጣጠ ምግብ እጥረት ላይ የቤተሰቦች አለመኖር ክፉኛ በድርቅ የተጎዱ ወረዳዎች ያሉ ሕጻናትን ለአደጋ ማጋለጡን ኦቻ አክሏል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c72n3zyy0gmo
0business
አሳሳቢ የሆነው በባንክ የተቀመጠ ገንዘብ ዝርፊያ እና የባንኮች ኃላፊነት
አቶ እንዳለ ገ/መድኅን ከሚሰሩበት የመንግሥት መሥሪያ ቤት የቁጠባ አገልግሎት በብድር ያገኙትን 200 ሺህ ብር ለጋራ መኖሪያ ቤት ቅድሚያ ክፍያ ለመክፈል በማሰብ በባንክ አስቀምጠው በመጠባበቅ ላይ ነበሩ። ነገር ግን ምንም አይነካብኝም ብለው ያሰቡት ሁለት መቶ ሺህ ሊሞላ 5 ሺህ ብር የጎደለው ገንዘባቸው፣ ባልጠበቁት መንገድ በዘራፊዎች ከአካውንታቸው ተመንትፎ ለዘርፈ ብዙ ቀውስ መዳረጋቸውን ይናገራሉ። አንድ ዕለት “ከባንክ ነው የምንደውለው” ያሉት ግለሰቦች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሚያካሂደው “ይቆጥቡ ይሸለሙ” መርሃ ግብር የሞተር ሳይክል ሽልማት እንደደረሳቸው ተነገራቸው። ቀጥሎም በወቅቱ ሞተር ሳይክሉን ሊሰጧቸው እንደማይችሉ ነገር ግን ገንዘቡን ሊያስገቡ እንደፈለጉ በመናገር የተለያዩ መረጃዎችን ጠየቋቸው። ይህንንም ተከትሎ አቶ እንዳለ የተጠየቁን ቁጥር ሁሉ ተናግረው በመጨረሻም በአቢሲኒያ እና በንግድ ባንክ አካውንቶቻቸው ውስጥ የነበረው 195 ሺህ ብር ተወስዶባቸዋል። ይህ የአቶ እንዳለ ታሪክ ብቻ ሳይሆን በርካታ ሰዎች የገጠማቸው የማጭበርበር ድርጊት ነው። ዝርፊያው በተለይም የሞባይል ባንኪንግ አገልገሎት የሚጠቀሙ ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ሲሆን፣ በርካቶች በተለያየ ማኅበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች ላይ እሮሮ ሲያሰሙ የከረሙበትም ጉዳይ ነው። የፌደራሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በዚህ የማጭበርበር ድርጊት ላይ የወንጀል ምርመራ እንዲሁም ክስ የተጀመረባቸው መዝገቦችን በተመለከተ ባደረገው ጥናት በባንኮች ላይ የሚፈጸሙ ምዝበራዎች መበራከታቸውን አመልክቷል። የሞባይል ባንኪንግን ጨምሮ በመዝገብ የተያዙት ወንጀሎች በአምስት ዓመታት ውስጥ ብቻ 1.9 ቢሊዮን ብር ኪሳራ ማድረሳቸውን ጥናቱ አትቷል። በዝርዝሩም ከፍተኛ ዝርፊያ ያጋጠመው በንግድ ባንክ ሲሆን አቢሲኒያ ባንክ እና ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ይከተላሉ። በቼክ የሚፈጸሙ፣ በቁጠባ ሂሳብ ላይ፣ በሃዋላ በሚላክ ገንዘብ ላይ፣ የይለፍ ቃል ምንተፋ ብሎም በሌሎች መንገዶች ስርቆቱ እንደሚፈጸም ጥናቱ ያሳያል። በሞባይል ባንኪንግ የሚፈጸመው ስርቆት በርካታ ስልቶች ያሉት ሲሆን ከተዋናዮቹ መካከል የባንክ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች እና ሌሎች የባንክ ሠራተኞች ጭምር እንደሚሳተፉበት ይገልጻል። ሠራተኞቹ ከደንበኞች አካውንት ጋር የራሳቸውን ወይም የዘመዶቻቸውን ብሎም የጓደኞቻቸውን ቁጥር በማያያዝ እና ሐሰተኛ ቅጽ በመሙላት ስርቆቱን እንደሚፈጽሙ ጥናቱ አመልክቷል። በማሳያነት የተጠቀሰው መዝገብ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፒኮክ መናፈሻ ቅርንጫፍ ሠራተኛ የሆነ አንድ ግለሰብ በባንኩ ደንበኛ ለረጅም ጊዜ ሳይንቀሳቀስ የቆየውን አካውንት በማንቀሳቀስ ስርቆት መፈጸሙን ያሳያል። ለዚህም ግለሰቡ ካስገቡት የሞባይል ባንኪንግ ቁጥር ውጪ ሌላ በማስገባት በአጠቃላይ 2.5 ሚሊዮን ብር ገደማ ከግለሰቡ ሂሳብ ወስዷል ሲል ጥናቱ ያሳያል። አክሎም የስርቆቱ ዋና ተዋናዮች የባንክ ኃላፊዎች መሆናቸውን ጠቅሶ፣ ነገር ግን መደበኛ የባንኩ ሠራተኞች አይሳተፉበትም ብሎ ለመደምደም ግን አስቸጋሪ እንደሆነ ገልጿል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ለዓመታት በባንክ ሥራ ላይ የቆዩ አንድ ግለሰብ እንደሚሉት በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በርካታ የባንክ ሠራተኞች ለእስር እየተዳረጉ ነው። ነገር ግን ሙሉ በሙሉ በባንኮች ውስጥ ሆነው ወንጀሉን የሚፈጽሙ ሰዎች እንደማይያዙ ያክላሉ። በባንኮች መካከል የቅልጥፍና ውድድር በመኖሩ ምክንያት የባንክ ሠራተኞች ሁልጊዜ የባንኩን የአሰራር ሥነ ሥርዓት እንደማይከተሉ የሚናገሩት እኚሁ ግለሰብ፤ በምሳሌነትም በሥርዓቱ መሰረት ያለ ባንክ ደብተር ገንዘብ መክፈል ባይቻልም በአብዛኛው የባንክ ደንበኞችን ለመያዝ በሚደረገው ፉክክር ያለ ደብተር ክፍያ መፈጸም እጅግ የተለመደ ነው ይላሉ። በዚህም ሳቢያ አንድ ሰው ያለደብተር በመቅረብ አጭበርብሮ ገንዘብ ቢዘርፍ ከፋዩ ባለሙያ በኋላ ላይ ሲጣራ ተጠያቂ ሲሆን ባንኩም “ባስከመጥኩለት ሥርዓት መሰረት አልሰራም” በሚል አሳልፎ ይሰጠዋል ሲሉ ያስረዳል። ይህ ሁኔታ ከፍተኛ የገንዘብ ምዝበራ የሚካሄድበትን የቼክ ማጭበርበር ወንጀልንም ይመለከታል። ዝርፊያው ከተፈጸመ በኋላ ከፋዩ ወይም የቅርብ አለቃው ለእስር ይዳረጉ እንጂ፣ ዋነኛዎቹ አጥፊዎች ሌሎች እንደሚሆኑ ይናገራሉ። “ባንኮች ትልልቅ ደንበኞቻቸውን ለመያዝ ከፍተኛ ፉክክር ያደርጋሉ” የሚሉት ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱት የባንክ ባለሙያ፣ ቼክ ለመክፈል የሚያስፈልጉ ሂደቶችን በሙሉ ማሟላት ካስፈለገ አንድ ቀን ሙሉ ሊወስድ እንደሚችል በመጥቀስ “ይህ ደግሞ ትልልቅ ደንበኞችን ያርቃል” ይላሉ። ታዲያ አንድ ግለሰብ ቼክ ፈርሞ ለተከፋይ ሲልክ ለባንኩ ቀድሞ ደውሎ ገንዘቡ እንዲዘጋጅ ካዘዘ በኋላ ገንዘብ የሚወስደው ግለሰብ ገንዘቡን ተቀብሎ ይሄዳል። ቼኩ ማለፍ ያለበት ሂደትን ግለሰቡ ገንዘቡን ይዞ ከሄደ በኋላ የሚከናወን ይሆናል። በአሰራሩ መሰረት ግን ቼኩን የተቀበለው የመጀመሪያው ሠራተኛ ወደ ደንበኛው በመደወል ካረገገጠ በኋላ በመፈረም ለቀጣይ አለቃው ያስፈርማል። ቀጥሎም መስኮት ላይ ያለው ከፋይ በድጋሚ ፊርማዎቹን አረጋግጦ ይከፍላል። ነገር ግን ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ባለው ፉክክር፣ በቅርብ አለቆቻቸው ዝርዝር ሂደትን እንዳይከተሉ የሚበረታቱት ከፋዮች መጨረሻ ወንጀል መፈጸሙ ሲታወቅ ግን ሂደቱን አልተከተሉም ተብለው ለእስር እንደሚዳረጉ እኚሁ በባንክ ሥራ የበርካታ ዓመታት ልምድ ያላቸው ግለሰብ ይናገራሉ። ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከተ የመጣው የሞባይል ባንኪንግን መሰረት ያደረገ ዘረፋ ግን በርግጥም በባንኮች የአሰራር ግድፈት ጭምር የታገዘ መሆኑን ይናገራሉ። “የስማርት ስልክ የሌለው፣ እንኳን ስልኩን አንብቦ አገልግሎቱን መፈጸም ቀርቶ ፊርማ እንኳን በአሻራ የሚፈርሙ ሰዎች የሞባይል ባንኪንግ አግልገሎት እንዲጠቀሙ እና እንዲመዘገቡ መደረጉ ለከፍተኛ ዝርፊያ ይዳርጋል” ሲሉም ይናገራሉ። ቀጥሎም ገንዘብ ያለው እና የሌለው ሰውን እንዲሁም የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎቱን የሚጠቀመውን እና የማየጠቀመውን በመለየት ለሦስተኛ ሰው አሳልፈው የሚሰጡት ራሳቸው በባንኮች ውስጥ የሚሰሩ አንዳንድ ሰዎች እንደሆኑም ያስረዳሉ። አሁን አሁን ከአካውንት ወደ ቴሌ ብር በማስላክ ዝርፊያውን ቀላል እንዳደረገውም ግለሰቡ ተናግረዋል። በዚህ ሂደት ሐሰተኛ መታወቂያ ከሚያወጡ የቀበሌ ሠራተኞች እስከ የባንክ ኃላፊዎች ተሳታፊ መሆናቸውም አልቀረም። የባንክ ግልጋሎቶች በዘመኑባቸው አገራት እንዲህ አይነት በባንክ አካውንት ላይ ብሎም የሞባይል ክፍያ አገልግሎቶች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመከላከል ባንኮች ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን ይሰራሉ። ከእነዚህም መካከል ከአንድ በላይ የሆነ የደንበኛውን ማንነት የማረጋጥ ሂደት ይጠቀሳል። ከዚያ በመለስ ባንኮች ለደንበኞቻቸው በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን አጭር የጽሁፍ መልዕክት በመላክ ሳይታክቱ ያስተምራሉ። የኢትዮጵያ ባንኮች ምን ማድረግ አለባቸው የሚለውን ኋላ ላይ የምንመለስበት ቢሆንም ለምን ይህንን ማደረግ አይፈልጉም ስንል ግን የባንክ ሠራተኛ የሆኑ ምንጫችንን ጠይቀናቸዋል። “ገበያ ያርቅብናል ብለው ስለሚያስቡ ነው” ይላሉ። ይህም በተለይም እንደ ሞባይል ባንኪንግ ያሉ አገልግሎቶች ገና እየተለመዱ ያሉ ሲሆኑ ደንበኞች እንደዚህ አይነት ችግር ካለው ይቅርብን ብለው እንዳይተዉት በመስጋት መሆኑን ይናገራሉ። ይህ ዘላቂ እና አዋጭ መንገድ ነው ወይ ስንል የባንክ እና የኢኮኖሚ ባለሞያውን አብዱልመናን መሐመድን ጠይቀናቸዋል። ባንኮች ደንበኞቻቸውን ማስተማር እንደሚገባቸው እንዲሁም ይህ የማስተማር ሂደት በተገቢው የመገናኛ ዘዴ ሊሰጥ እንደሚገባ ተናግረዋል። በተለይም በዲጂታል ባንኪንግ ሥርዓት ወቅት ደንበኞችን ሊያጋጥሙ ስለሚችሉ ማጭበርበሮች ማስተማር ከፍተኛ ትርጉም አለው ይላሉ። የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ከአጋሮቹ ጋር በመሆን ያጠናው ጥናት በራሱ የባንኮችን ኃላፊነት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። “እነዚህ በባንኮች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች የሚያመሳስላቸው ነገር በአብዛኛው ከባንክ አሰራር ጋር ግንኙነት ያላቸው “የውስጥ ሠራተኞች’’ ሳይሳተፉባቸው የማይፈጸሙ ናቸው። የትኛውም ወንጀል ከመፈጸሙ በፊት አካውንቱ ላይ ገንዘብ ያለውን ከሌለው መለየት ያስፈልጋል” ሲል በግልጽ የባንኮች ተሳትፎን ያሳያል። እንዲሁም እነዚህን መረጃዎች በዚህ ጥልቀት እና ስፋት ከአንዳንድ የባንክ ሠራተኞች ትብብር ውጪ ማግኘት የማይቻል መሆኑንም ጥናቱ ያትታል። አብዱልመናን እንደሚሉት ባንኮች የደንበኞቻቸውን የግል መረጃዎች የመጠበቅ ከፍተኛ ኃላፊነት ያለባቸው ሲሆን፣ በአብዛኛውም ይህንን እንደሚፈጽሙ ይናገራሉ። ነገር ግን ይህ እምነት የማይጣስበት አጋጣሚ የለም ማለት እንዳልሆነ ያክላሉ። ጨምረውም ይህንን ለመፍታትም ባንኮች በሚጠቀሙባቸው ሥርዓቶች ውስጥ ሠራተኞቻቸው ለመጥፎ አላማ ሊያውሏቸው የሚችሉ ክፍተቶችን የመሙላት አስፈላጊነትን አጽንኦት ይሰጣሉ። እንዲሁም መንግሥት ሕጎቹን በመከለስ በባንኮች ውስጥ ሥልጣን ያላቸው ሰዎች ያለ አግባብ እንዳይመዘብሩ ማድረግ ይገባዋል፤ እንደ ባለሙያው ገለጻ። ይህ ካልሆነ ግን ከደንበኞች ባሻገር እንዲህ ያሉ ተግባራት ባንኮች ላይ የሚጣለውን አመኔታ በመሸርሸር ለበለጠ ችግር ሊዳርጋቸው እንደሚችልም ይናገራሉ። ይህ በጥቅሉ ኢኮኖሚውን በመጉዳት ጉዳቱን የከፋ ያደርገዋል ሲሉም ያስጠነቅቃሉ። ነገር ግን እነዚህ ችግሮች እስከሚፈቱ ድረስ ደንበኞች በአጭበርባሪዎች መበደላቸው ብሎም ክስ ከመመስረት ውጪ ገንዘባቸውን ለማግኘት ሳይችሉ ቀርተዋል። በምሳሌነትም አቶ እንዳለ ለፖሊስ ያላቸውን ማስረጃዎች በሙሉ ይዘው ቢያመለክቱም፣ እስካሁን የተያዘ ተጠርጣሪ ያለመኖሩ ያሳስባቸዋል። ነገር ግን አሁንም በብድር ያገኙትን ገንዘባቸውን የሚያስመልስላቸው ፍትህ እየተጠባበቁ ነው። ከኑሮ ውድነቱ ጋር ተደራርቦ ይህን ያህል ገንዘብ ማጣታቸው ከባድ ቀውስጥ ውስጥ እንደከተታቸው የሚገልጹት አቶ እንዳለ፣ ባዶ እጃቸውን ቢቀሩም “ያው እዳ ስለሆነ ከደመወዜ እየተቆረጠ መክፈል መች ይቀርልኛል?” ሲሉ በተስፋ መቁረጥ ይናገራሉ።
አሳሳቢ የሆነው በባንክ የተቀመጠ ገንዘብ ዝርፊያ እና የባንኮች ኃላፊነት አቶ እንዳለ ገ/መድኅን ከሚሰሩበት የመንግሥት መሥሪያ ቤት የቁጠባ አገልግሎት በብድር ያገኙትን 200 ሺህ ብር ለጋራ መኖሪያ ቤት ቅድሚያ ክፍያ ለመክፈል በማሰብ በባንክ አስቀምጠው በመጠባበቅ ላይ ነበሩ። ነገር ግን ምንም አይነካብኝም ብለው ያሰቡት ሁለት መቶ ሺህ ሊሞላ 5 ሺህ ብር የጎደለው ገንዘባቸው፣ ባልጠበቁት መንገድ በዘራፊዎች ከአካውንታቸው ተመንትፎ ለዘርፈ ብዙ ቀውስ መዳረጋቸውን ይናገራሉ። አንድ ዕለት “ከባንክ ነው የምንደውለው” ያሉት ግለሰቦች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሚያካሂደው “ይቆጥቡ ይሸለሙ” መርሃ ግብር የሞተር ሳይክል ሽልማት እንደደረሳቸው ተነገራቸው። ቀጥሎም በወቅቱ ሞተር ሳይክሉን ሊሰጧቸው እንደማይችሉ ነገር ግን ገንዘቡን ሊያስገቡ እንደፈለጉ በመናገር የተለያዩ መረጃዎችን ጠየቋቸው። ይህንንም ተከትሎ አቶ እንዳለ የተጠየቁን ቁጥር ሁሉ ተናግረው በመጨረሻም በአቢሲኒያ እና በንግድ ባንክ አካውንቶቻቸው ውስጥ የነበረው 195 ሺህ ብር ተወስዶባቸዋል። ይህ የአቶ እንዳለ ታሪክ ብቻ ሳይሆን በርካታ ሰዎች የገጠማቸው የማጭበርበር ድርጊት ነው። ዝርፊያው በተለይም የሞባይል ባንኪንግ አገልገሎት የሚጠቀሙ ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ሲሆን፣ በርካቶች በተለያየ ማኅበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች ላይ እሮሮ ሲያሰሙ የከረሙበትም ጉዳይ ነው። የፌደራሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በዚህ የማጭበርበር ድርጊት ላይ የወንጀል ምርመራ እንዲሁም ክስ የተጀመረባቸው መዝገቦችን በተመለከተ ባደረገው ጥናት በባንኮች ላይ የሚፈጸሙ ምዝበራዎች መበራከታቸውን አመልክቷል። የሞባይል ባንኪንግን ጨምሮ በመዝገብ የተያዙት ወንጀሎች በአምስት ዓመታት ውስጥ ብቻ 1.9 ቢሊዮን ብር ኪሳራ ማድረሳቸውን ጥናቱ አትቷል። በዝርዝሩም ከፍተኛ ዝርፊያ ያጋጠመው በንግድ ባንክ ሲሆን አቢሲኒያ ባንክ እና ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ይከተላሉ። በቼክ የሚፈጸሙ፣ በቁጠባ ሂሳብ ላይ፣ በሃዋላ በሚላክ ገንዘብ ላይ፣ የይለፍ ቃል ምንተፋ ብሎም በሌሎች መንገዶች ስርቆቱ እንደሚፈጸም ጥናቱ ያሳያል። በሞባይል ባንኪንግ የሚፈጸመው ስርቆት በርካታ ስልቶች ያሉት ሲሆን ከተዋናዮቹ መካከል የባንክ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች እና ሌሎች የባንክ ሠራተኞች ጭምር እንደሚሳተፉበት ይገልጻል። ሠራተኞቹ ከደንበኞች አካውንት ጋር የራሳቸውን ወይም የዘመዶቻቸውን ብሎም የጓደኞቻቸውን ቁጥር በማያያዝ እና ሐሰተኛ ቅጽ በመሙላት ስርቆቱን እንደሚፈጽሙ ጥናቱ አመልክቷል። በማሳያነት የተጠቀሰው መዝገብ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፒኮክ መናፈሻ ቅርንጫፍ ሠራተኛ የሆነ አንድ ግለሰብ በባንኩ ደንበኛ ለረጅም ጊዜ ሳይንቀሳቀስ የቆየውን አካውንት በማንቀሳቀስ ስርቆት መፈጸሙን ያሳያል። ለዚህም ግለሰቡ ካስገቡት የሞባይል ባንኪንግ ቁጥር ውጪ ሌላ በማስገባት በአጠቃላይ 2.5 ሚሊዮን ብር ገደማ ከግለሰቡ ሂሳብ ወስዷል ሲል ጥናቱ ያሳያል። አክሎም የስርቆቱ ዋና ተዋናዮች የባንክ ኃላፊዎች መሆናቸውን ጠቅሶ፣ ነገር ግን መደበኛ የባንኩ ሠራተኞች አይሳተፉበትም ብሎ ለመደምደም ግን አስቸጋሪ እንደሆነ ገልጿል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ለዓመታት በባንክ ሥራ ላይ የቆዩ አንድ ግለሰብ እንደሚሉት በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በርካታ የባንክ ሠራተኞች ለእስር እየተዳረጉ ነው። ነገር ግን ሙሉ በሙሉ በባንኮች ውስጥ ሆነው ወንጀሉን የሚፈጽሙ ሰዎች እንደማይያዙ ያክላሉ። በባንኮች መካከል የቅልጥፍና ውድድር በመኖሩ ምክንያት የባንክ ሠራተኞች ሁልጊዜ የባንኩን የአሰራር ሥነ ሥርዓት እንደማይከተሉ የሚናገሩት እኚሁ ግለሰብ፤ በምሳሌነትም በሥርዓቱ መሰረት ያለ ባንክ ደብተር ገንዘብ መክፈል ባይቻልም በአብዛኛው የባንክ ደንበኞችን ለመያዝ በሚደረገው ፉክክር ያለ ደብተር ክፍያ መፈጸም እጅግ የተለመደ ነው ይላሉ። በዚህም ሳቢያ አንድ ሰው ያለደብተር በመቅረብ አጭበርብሮ ገንዘብ ቢዘርፍ ከፋዩ ባለሙያ በኋላ ላይ ሲጣራ ተጠያቂ ሲሆን ባንኩም “ባስከመጥኩለት ሥርዓት መሰረት አልሰራም” በሚል አሳልፎ ይሰጠዋል ሲሉ ያስረዳል። ይህ ሁኔታ ከፍተኛ የገንዘብ ምዝበራ የሚካሄድበትን የቼክ ማጭበርበር ወንጀልንም ይመለከታል። ዝርፊያው ከተፈጸመ በኋላ ከፋዩ ወይም የቅርብ አለቃው ለእስር ይዳረጉ እንጂ፣ ዋነኛዎቹ አጥፊዎች ሌሎች እንደሚሆኑ ይናገራሉ። “ባንኮች ትልልቅ ደንበኞቻቸውን ለመያዝ ከፍተኛ ፉክክር ያደርጋሉ” የሚሉት ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱት የባንክ ባለሙያ፣ ቼክ ለመክፈል የሚያስፈልጉ ሂደቶችን በሙሉ ማሟላት ካስፈለገ አንድ ቀን ሙሉ ሊወስድ እንደሚችል በመጥቀስ “ይህ ደግሞ ትልልቅ ደንበኞችን ያርቃል” ይላሉ። ታዲያ አንድ ግለሰብ ቼክ ፈርሞ ለተከፋይ ሲልክ ለባንኩ ቀድሞ ደውሎ ገንዘቡ እንዲዘጋጅ ካዘዘ በኋላ ገንዘብ የሚወስደው ግለሰብ ገንዘቡን ተቀብሎ ይሄዳል። ቼኩ ማለፍ ያለበት ሂደትን ግለሰቡ ገንዘቡን ይዞ ከሄደ በኋላ የሚከናወን ይሆናል። በአሰራሩ መሰረት ግን ቼኩን የተቀበለው የመጀመሪያው ሠራተኛ ወደ ደንበኛው በመደወል ካረገገጠ በኋላ በመፈረም ለቀጣይ አለቃው ያስፈርማል። ቀጥሎም መስኮት ላይ ያለው ከፋይ በድጋሚ ፊርማዎቹን አረጋግጦ ይከፍላል። ነገር ግን ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ባለው ፉክክር፣ በቅርብ አለቆቻቸው ዝርዝር ሂደትን እንዳይከተሉ የሚበረታቱት ከፋዮች መጨረሻ ወንጀል መፈጸሙ ሲታወቅ ግን ሂደቱን አልተከተሉም ተብለው ለእስር እንደሚዳረጉ እኚሁ በባንክ ሥራ የበርካታ ዓመታት ልምድ ያላቸው ግለሰብ ይናገራሉ። ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከተ የመጣው የሞባይል ባንኪንግን መሰረት ያደረገ ዘረፋ ግን በርግጥም በባንኮች የአሰራር ግድፈት ጭምር የታገዘ መሆኑን ይናገራሉ። “የስማርት ስልክ የሌለው፣ እንኳን ስልኩን አንብቦ አገልግሎቱን መፈጸም ቀርቶ ፊርማ እንኳን በአሻራ የሚፈርሙ ሰዎች የሞባይል ባንኪንግ አግልገሎት እንዲጠቀሙ እና እንዲመዘገቡ መደረጉ ለከፍተኛ ዝርፊያ ይዳርጋል” ሲሉም ይናገራሉ። ቀጥሎም ገንዘብ ያለው እና የሌለው ሰውን እንዲሁም የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎቱን የሚጠቀመውን እና የማየጠቀመውን በመለየት ለሦስተኛ ሰው አሳልፈው የሚሰጡት ራሳቸው በባንኮች ውስጥ የሚሰሩ አንዳንድ ሰዎች እንደሆኑም ያስረዳሉ። አሁን አሁን ከአካውንት ወደ ቴሌ ብር በማስላክ ዝርፊያውን ቀላል እንዳደረገውም ግለሰቡ ተናግረዋል። በዚህ ሂደት ሐሰተኛ መታወቂያ ከሚያወጡ የቀበሌ ሠራተኞች እስከ የባንክ ኃላፊዎች ተሳታፊ መሆናቸውም አልቀረም። የባንክ ግልጋሎቶች በዘመኑባቸው አገራት እንዲህ አይነት በባንክ አካውንት ላይ ብሎም የሞባይል ክፍያ አገልግሎቶች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመከላከል ባንኮች ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን ይሰራሉ። ከእነዚህም መካከል ከአንድ በላይ የሆነ የደንበኛውን ማንነት የማረጋጥ ሂደት ይጠቀሳል። ከዚያ በመለስ ባንኮች ለደንበኞቻቸው በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን አጭር የጽሁፍ መልዕክት በመላክ ሳይታክቱ ያስተምራሉ። የኢትዮጵያ ባንኮች ምን ማድረግ አለባቸው የሚለውን ኋላ ላይ የምንመለስበት ቢሆንም ለምን ይህንን ማደረግ አይፈልጉም ስንል ግን የባንክ ሠራተኛ የሆኑ ምንጫችንን ጠይቀናቸዋል። “ገበያ ያርቅብናል ብለው ስለሚያስቡ ነው” ይላሉ። ይህም በተለይም እንደ ሞባይል ባንኪንግ ያሉ አገልግሎቶች ገና እየተለመዱ ያሉ ሲሆኑ ደንበኞች እንደዚህ አይነት ችግር ካለው ይቅርብን ብለው እንዳይተዉት በመስጋት መሆኑን ይናገራሉ። ይህ ዘላቂ እና አዋጭ መንገድ ነው ወይ ስንል የባንክ እና የኢኮኖሚ ባለሞያውን አብዱልመናን መሐመድን ጠይቀናቸዋል። ባንኮች ደንበኞቻቸውን ማስተማር እንደሚገባቸው እንዲሁም ይህ የማስተማር ሂደት በተገቢው የመገናኛ ዘዴ ሊሰጥ እንደሚገባ ተናግረዋል። በተለይም በዲጂታል ባንኪንግ ሥርዓት ወቅት ደንበኞችን ሊያጋጥሙ ስለሚችሉ ማጭበርበሮች ማስተማር ከፍተኛ ትርጉም አለው ይላሉ። የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ከአጋሮቹ ጋር በመሆን ያጠናው ጥናት በራሱ የባንኮችን ኃላፊነት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። “እነዚህ በባንኮች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች የሚያመሳስላቸው ነገር በአብዛኛው ከባንክ አሰራር ጋር ግንኙነት ያላቸው “የውስጥ ሠራተኞች’’ ሳይሳተፉባቸው የማይፈጸሙ ናቸው። የትኛውም ወንጀል ከመፈጸሙ በፊት አካውንቱ ላይ ገንዘብ ያለውን ከሌለው መለየት ያስፈልጋል” ሲል በግልጽ የባንኮች ተሳትፎን ያሳያል። እንዲሁም እነዚህን መረጃዎች በዚህ ጥልቀት እና ስፋት ከአንዳንድ የባንክ ሠራተኞች ትብብር ውጪ ማግኘት የማይቻል መሆኑንም ጥናቱ ያትታል። አብዱልመናን እንደሚሉት ባንኮች የደንበኞቻቸውን የግል መረጃዎች የመጠበቅ ከፍተኛ ኃላፊነት ያለባቸው ሲሆን፣ በአብዛኛውም ይህንን እንደሚፈጽሙ ይናገራሉ። ነገር ግን ይህ እምነት የማይጣስበት አጋጣሚ የለም ማለት እንዳልሆነ ያክላሉ። ጨምረውም ይህንን ለመፍታትም ባንኮች በሚጠቀሙባቸው ሥርዓቶች ውስጥ ሠራተኞቻቸው ለመጥፎ አላማ ሊያውሏቸው የሚችሉ ክፍተቶችን የመሙላት አስፈላጊነትን አጽንኦት ይሰጣሉ። እንዲሁም መንግሥት ሕጎቹን በመከለስ በባንኮች ውስጥ ሥልጣን ያላቸው ሰዎች ያለ አግባብ እንዳይመዘብሩ ማድረግ ይገባዋል፤ እንደ ባለሙያው ገለጻ። ይህ ካልሆነ ግን ከደንበኞች ባሻገር እንዲህ ያሉ ተግባራት ባንኮች ላይ የሚጣለውን አመኔታ በመሸርሸር ለበለጠ ችግር ሊዳርጋቸው እንደሚችልም ይናገራሉ። ይህ በጥቅሉ ኢኮኖሚውን በመጉዳት ጉዳቱን የከፋ ያደርገዋል ሲሉም ያስጠነቅቃሉ። ነገር ግን እነዚህ ችግሮች እስከሚፈቱ ድረስ ደንበኞች በአጭበርባሪዎች መበደላቸው ብሎም ክስ ከመመስረት ውጪ ገንዘባቸውን ለማግኘት ሳይችሉ ቀርተዋል። በምሳሌነትም አቶ እንዳለ ለፖሊስ ያላቸውን ማስረጃዎች በሙሉ ይዘው ቢያመለክቱም፣ እስካሁን የተያዘ ተጠርጣሪ ያለመኖሩ ያሳስባቸዋል። ነገር ግን አሁንም በብድር ያገኙትን ገንዘባቸውን የሚያስመልስላቸው ፍትህ እየተጠባበቁ ነው። ከኑሮ ውድነቱ ጋር ተደራርቦ ይህን ያህል ገንዘብ ማጣታቸው ከባድ ቀውስጥ ውስጥ እንደከተታቸው የሚገልጹት አቶ እንዳለ፣ ባዶ እጃቸውን ቢቀሩም “ያው እዳ ስለሆነ ከደመወዜ እየተቆረጠ መክፈል መች ይቀርልኛል?” ሲሉ በተስፋ መቁረጥ ይናገራሉ።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c4nxpn797wgo
0business
ከኮሮናቫይረስ በእጅጉ እያተረፉ ያሉት ትልልቅ ድርጅቶች
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የበርካታ አገራት ኢኮኖሚ ላይ ከባድ ጫና እያደረሰ ቢሆንም ትልልቅ የሚባሉት የዓለማችን የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ግን ጥሩ የሚባል ትርፍ እየሰበሰቡ ነው። በበይነ መረብ አማካይነት የተለያዩ አይት መገልገያዎችን የሚሸጠው አማዞን ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ማግስት ባሉት ሶስት ወራት ብቻ ሽያጩ 40 በመቶ ከፍ እንዳለለት ያስታወቀ ሲሆን ታዋቂው የስልክና የላፕቶፕ አምራች አፕል ደግሞ የአይፎንና ሌሎች መቀየሪያ መሳሪያዎች በደንብ እንደተቸበቸቡለት ገልጿል። ፌስቡክ ደግሞ በስሬ በማስተዳድራቸው እንደ ዋትስአፕና ኢንስታግራም ባሉ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተጠቃሚዎች ቁጥር 15 በመቶ ከፍ ብሎልኛል ብሏል። • በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ትርፉ መጨመሩን ሳምሰንግ አስታወቀ • ኮሮናቫይረስ የቀሰቀሳቸው የአና የሚበሉ ሥዕሎች • ከኮሮናቫይረስ የትኞቹ ድርጅቶች አተረፉ? እነማንስ ከሰሩ? የአማዞን የሩብ ዓመት ትርፍ 5.2 ቢሊየን ዶላር ሲሆን ድርጅቱ ከተቋቋመበት ከአውሮፓውያኑ 1994 ጀምሮ ይህ ከፍተኛው ነው ተብሏል። ድርጅቱ እንደውም ከኮሮናቫይረስ መከሰት በኋላ ለሰራተⶉቹ መከላከያ መሳሪያዎችን ለመግዛትና የመከላከያ ጥንቃቄዎችን ለማድረግ ከፍተኛ ወጪ ማውጣቱ ትርፉን ዝቅ ያደርገዋል ተብሎ ተፈርቶ ነበር። በአጠቃላይ በበይነ መረብ የሚካሄዱ ንግዶች የሽያጭ መጠኑ 40 በመቶ ከፍ ብሏል። እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ባሉት ሶስት ወራት ደግሞ በአጠቃላይ 88.9 ቢሊየን ዶላር አንቀሳቅሷል። ትርፍም ቢሆን በአስገራሚ ሁኔታ ባለፈው ዓመት ከነበረበት 2.6 ቢሊየን ዶላር ወደ 5.2 ቢሊየን ዶላር ከፍ ብሏል። በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በወረርሽኙ ምክንያት ቤት ውስጥ ብዙ ጊዜያቸውን ማሳለፋቸውን ተከትሎ የበይነ መረብ ሽያጭ በእጅጉ ተጧጡፏል። አማዞንም ቢሆን የደንበኞቹን ፍላጎት ለማሟላት በሩብ ዓመቱ ብቻ ተጨማሪ 175 ሺ ሰራተኞችን ቀጥሯል። ፍላጎቱ በዚሁ መቀጠሉ ስለማይቀር በርካታ መጋዘኖችንና ሰራተኞችን ለመጨመርም እያሰበ ነው። የአፕል የሩብ ዓመት ትርፍ ደግሞ ባለፈው ዓመት ከነበረበት 11 በመቶ በመጨመር 59.7 ቢሊየን ደርሷል። ሰዎች ስራቸውን ከቤታቸው ሆነው መስራታቸው የተለያዩ መገልገያዎችን እንዲጠቀሙ አድርጓቸዋል። በዚህም ምክንያት የማክ ላፕቶፖችና አይፓዶች በእጅጉ ተፈላጊ ነበሩ። ሁለቱም የአፕል ምርቶች ከወረርሽኙ መከሰት በኋላ ገበያቸው እንደደራ ድርጅቱ አስታውቋል። በዚህም ምክንያት ባለፈው ከነበረው 10 ቢሊየን ዶላር ትርፍ ወደ 11.25 ቢሊየን ዶላር ከፍ ብሏል። ፌስቡክ ደግሞ ከኮሮናቫይረስ በኋላ ትርፉ በእጅጉ እንደሚቀንስ ቢጠበቅም እንደውም የ 11 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። አነስተኛ ድርጅቶች ያሏቸው ሰዎች ለማስታወቂያ ወደ ፌስቡክ ላይሄዱ እንደሚችሉ ባለሙያዎች ተንብየው ነበር። ነገር ግን ወረርሽኙን ተከትሎ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ቁጥር በእጅጉ በመጨመሩ ምክንያት ለማስታወቂያ የሚመጡ ድርጅቶችም ቁጥር አብሮ ከፍ ብሏል። በዚህም ምክንያት የድርጅቱ የሩብ ዓመት ትርፍ 5.2 ቢሊየን ዶላር እንዲደርስ ሆኗል። ፌስቡክ እንደሚለው ባለፈው ሰኔ ወር ብቻ በሁሉም የማህበራዊ ሚዲያዎቸ ላይ 2.4 ቢሊየን ተጠቃሚዎች የነበሩ ሲሆን ይህም የ15 በመቶ ጭማሪ አለው። ከአራቱ ትልልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች አንዱ የሆነው አልፋቤትም ቢሆን እንደ ሌሎቹ ባይሆንም ትርፋማ ሆኗል። ድርጅቱ በስሩ ጉግልና ዩቲዩብን የያዘ ሲሆን እስካሁን ያገኘሁት ትርፍ 38.3 ቢሊየን ዶላር ነው ብሏል። ይህ ደግሞ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የሁለት በመቶ ቅናሽ ያሳያል።
ከኮሮናቫይረስ በእጅጉ እያተረፉ ያሉት ትልልቅ ድርጅቶች የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የበርካታ አገራት ኢኮኖሚ ላይ ከባድ ጫና እያደረሰ ቢሆንም ትልልቅ የሚባሉት የዓለማችን የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ግን ጥሩ የሚባል ትርፍ እየሰበሰቡ ነው። በበይነ መረብ አማካይነት የተለያዩ አይት መገልገያዎችን የሚሸጠው አማዞን ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ማግስት ባሉት ሶስት ወራት ብቻ ሽያጩ 40 በመቶ ከፍ እንዳለለት ያስታወቀ ሲሆን ታዋቂው የስልክና የላፕቶፕ አምራች አፕል ደግሞ የአይፎንና ሌሎች መቀየሪያ መሳሪያዎች በደንብ እንደተቸበቸቡለት ገልጿል። ፌስቡክ ደግሞ በስሬ በማስተዳድራቸው እንደ ዋትስአፕና ኢንስታግራም ባሉ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተጠቃሚዎች ቁጥር 15 በመቶ ከፍ ብሎልኛል ብሏል። • በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ትርፉ መጨመሩን ሳምሰንግ አስታወቀ • ኮሮናቫይረስ የቀሰቀሳቸው የአና የሚበሉ ሥዕሎች • ከኮሮናቫይረስ የትኞቹ ድርጅቶች አተረፉ? እነማንስ ከሰሩ? የአማዞን የሩብ ዓመት ትርፍ 5.2 ቢሊየን ዶላር ሲሆን ድርጅቱ ከተቋቋመበት ከአውሮፓውያኑ 1994 ጀምሮ ይህ ከፍተኛው ነው ተብሏል። ድርጅቱ እንደውም ከኮሮናቫይረስ መከሰት በኋላ ለሰራተⶉቹ መከላከያ መሳሪያዎችን ለመግዛትና የመከላከያ ጥንቃቄዎችን ለማድረግ ከፍተኛ ወጪ ማውጣቱ ትርፉን ዝቅ ያደርገዋል ተብሎ ተፈርቶ ነበር። በአጠቃላይ በበይነ መረብ የሚካሄዱ ንግዶች የሽያጭ መጠኑ 40 በመቶ ከፍ ብሏል። እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ባሉት ሶስት ወራት ደግሞ በአጠቃላይ 88.9 ቢሊየን ዶላር አንቀሳቅሷል። ትርፍም ቢሆን በአስገራሚ ሁኔታ ባለፈው ዓመት ከነበረበት 2.6 ቢሊየን ዶላር ወደ 5.2 ቢሊየን ዶላር ከፍ ብሏል። በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በወረርሽኙ ምክንያት ቤት ውስጥ ብዙ ጊዜያቸውን ማሳለፋቸውን ተከትሎ የበይነ መረብ ሽያጭ በእጅጉ ተጧጡፏል። አማዞንም ቢሆን የደንበኞቹን ፍላጎት ለማሟላት በሩብ ዓመቱ ብቻ ተጨማሪ 175 ሺ ሰራተኞችን ቀጥሯል። ፍላጎቱ በዚሁ መቀጠሉ ስለማይቀር በርካታ መጋዘኖችንና ሰራተኞችን ለመጨመርም እያሰበ ነው። የአፕል የሩብ ዓመት ትርፍ ደግሞ ባለፈው ዓመት ከነበረበት 11 በመቶ በመጨመር 59.7 ቢሊየን ደርሷል። ሰዎች ስራቸውን ከቤታቸው ሆነው መስራታቸው የተለያዩ መገልገያዎችን እንዲጠቀሙ አድርጓቸዋል። በዚህም ምክንያት የማክ ላፕቶፖችና አይፓዶች በእጅጉ ተፈላጊ ነበሩ። ሁለቱም የአፕል ምርቶች ከወረርሽኙ መከሰት በኋላ ገበያቸው እንደደራ ድርጅቱ አስታውቋል። በዚህም ምክንያት ባለፈው ከነበረው 10 ቢሊየን ዶላር ትርፍ ወደ 11.25 ቢሊየን ዶላር ከፍ ብሏል። ፌስቡክ ደግሞ ከኮሮናቫይረስ በኋላ ትርፉ በእጅጉ እንደሚቀንስ ቢጠበቅም እንደውም የ 11 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። አነስተኛ ድርጅቶች ያሏቸው ሰዎች ለማስታወቂያ ወደ ፌስቡክ ላይሄዱ እንደሚችሉ ባለሙያዎች ተንብየው ነበር። ነገር ግን ወረርሽኙን ተከትሎ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ቁጥር በእጅጉ በመጨመሩ ምክንያት ለማስታወቂያ የሚመጡ ድርጅቶችም ቁጥር አብሮ ከፍ ብሏል። በዚህም ምክንያት የድርጅቱ የሩብ ዓመት ትርፍ 5.2 ቢሊየን ዶላር እንዲደርስ ሆኗል። ፌስቡክ እንደሚለው ባለፈው ሰኔ ወር ብቻ በሁሉም የማህበራዊ ሚዲያዎቸ ላይ 2.4 ቢሊየን ተጠቃሚዎች የነበሩ ሲሆን ይህም የ15 በመቶ ጭማሪ አለው። ከአራቱ ትልልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች አንዱ የሆነው አልፋቤትም ቢሆን እንደ ሌሎቹ ባይሆንም ትርፋማ ሆኗል። ድርጅቱ በስሩ ጉግልና ዩቲዩብን የያዘ ሲሆን እስካሁን ያገኘሁት ትርፍ 38.3 ቢሊየን ዶላር ነው ብሏል። ይህ ደግሞ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የሁለት በመቶ ቅናሽ ያሳያል።
https://www.bbc.com/amharic/news-53605349
0business
ስፔን፡ በሙስና እየተወነጀሉ ያሉት ንጉስ ጁዋን ካርሎስ አገር ጥለው አቡዳቢ ገቡ ተባለ
የቀድሞው የስፔን ንጉስ ጁዋን ካርሎስ ከተከፈተባቸው የሙስና ምርመራ ጋር ተያይዞ አገራቸውን ለቀው ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አቅንተዋል ተብሏል። ኤንአይዩኤስ የተባለው የስፔን ሚዲያ ቡድን የቀድሞው ንጉስ አቡዳቢ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የሚያሳይ ፎቶም ይዞ ወጥቷል። ንጉስ ጁዋን ካርሎስ አገራቸው ስፔንን ለቅቄ እሄዳለሁ የማለታቸው ዜና በርካቶችን ከሰሞኑ አስደንግጧል። ንጉሱ ምንም ስህተት እንዳልፈፀሙና አቃቤ ህግም ለጥያቄ ከፈለጋቸው ለመተባበርም ዝግጁ መሆናቸውንም አስታውቀው ነበር። ስፔንን ለቀው መሄዳቸው በዘውዳዊው ስርአት ላይ ከፍተኛ ክርክርና ውዝግብም አስከትሏል፤ ንጉስ ካርሎስም የት ናቸው የሚለው ላይም በርካቶች የተለያየ አስተያየት እየሰጡ ነው። የአገር ውስጥ ሚዲያዎች ወደ ዶሚኒካን ሪፐብሊክ፣ ካሪቢያን ደሴቶችና የስፔን ጎረቤት ወደሆነችው ፖርቹጋል ሄደዋል የሚሉ ዘገባዎችንም አስነብበዋል። ነገር ግን አዲስ የወጡት መረጃዎች እንደሚያሳዩት ንጉስ ጁዋን ካርሎስ በአቡዳቢ ባለ አምስት ኮከቡ ኤምሬትስ ፓላስ ሆቴል ውስጥ እንዳሉ ነው። አንድ ሙሉውን ፎቅ ተቆጣጥረዋልም ተብሏል። ንጉስ ካርሎስ ከአቡዳቢው አልጋ ወራሽ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር የጠበቀ ግንኙነት አላቸው። ነገር ግን አሁንም ቢሆን በርግጠኝነት ያሉበት ቦታ አልታወቀም። የስፔን የልዑላውያን ቤተሰብም ሆነ መንግሥት ንጉስ ካርሎስ ያሉበትን ቦታ አስመልክቶ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል። ንጉሥ ካርሎስ ከጎርጎሳውያኑ 1975 ጀምሮ ለአርባ ዓመታት ስፔንን በንግሥና ከመሩ በኋላ በ2014 ነበር ስልጣነ መንበሩን ለልጃቸው ያስተላለፉት፡፡ ስልጣኑን ለልጃቸው የሰጡት የሴት ልጃቸው ባለቤት ጋር ተያይዞ በተነሳ የሙስና ውንጀላ ነው። ስፔን የምጣኔ ኃብት ቀውስ በነበረችበት ወቅት የዝሆን አደን በማካሄድ ቅንጦታዊ ድርጊት ፈፅመዋል የሚል ውዝግብም ተከትሎ ነው። እነዚህ ውዝግቦች በዚሁ አላቆሙም። ከወራት በፊትም የስፔን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ንጉሱ ከሳዑዲ አረቢያ የፈጣን ባቡር ግንባታ ጋርም ተያይዞ በሙስና ምርመራ ከፍቶባቸዋል። ይህንንም ተከትሎ የቀድሞው ንጉስ ያለመከሰስ መብታቸውን አጥተዋል። ከቀናት በፊትም የ82 አመቱ ንጉስ ካርሎስ ለልጃቸው ፍሊፕ ካርሎስ ስድስተኛ በፃፉትም ደብዳቤ ነው አገር ጥለው እንደሚሄዱ ውሳኔያቸውን ያሳወቁት። የስፔንን ህዝብንም ሆነ ተቋማቱን በበለጠ ለማገልገል አገር ጥለው እንደሄዱ የጠቆመው ደብዳቤው እሳቸው በሌሉበትም መንገድ ልጃቸው በተረጋጋ መንገድ ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበውታል።
ስፔን፡ በሙስና እየተወነጀሉ ያሉት ንጉስ ጁዋን ካርሎስ አገር ጥለው አቡዳቢ ገቡ ተባለ የቀድሞው የስፔን ንጉስ ጁዋን ካርሎስ ከተከፈተባቸው የሙስና ምርመራ ጋር ተያይዞ አገራቸውን ለቀው ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አቅንተዋል ተብሏል። ኤንአይዩኤስ የተባለው የስፔን ሚዲያ ቡድን የቀድሞው ንጉስ አቡዳቢ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የሚያሳይ ፎቶም ይዞ ወጥቷል። ንጉስ ጁዋን ካርሎስ አገራቸው ስፔንን ለቅቄ እሄዳለሁ የማለታቸው ዜና በርካቶችን ከሰሞኑ አስደንግጧል። ንጉሱ ምንም ስህተት እንዳልፈፀሙና አቃቤ ህግም ለጥያቄ ከፈለጋቸው ለመተባበርም ዝግጁ መሆናቸውንም አስታውቀው ነበር። ስፔንን ለቀው መሄዳቸው በዘውዳዊው ስርአት ላይ ከፍተኛ ክርክርና ውዝግብም አስከትሏል፤ ንጉስ ካርሎስም የት ናቸው የሚለው ላይም በርካቶች የተለያየ አስተያየት እየሰጡ ነው። የአገር ውስጥ ሚዲያዎች ወደ ዶሚኒካን ሪፐብሊክ፣ ካሪቢያን ደሴቶችና የስፔን ጎረቤት ወደሆነችው ፖርቹጋል ሄደዋል የሚሉ ዘገባዎችንም አስነብበዋል። ነገር ግን አዲስ የወጡት መረጃዎች እንደሚያሳዩት ንጉስ ጁዋን ካርሎስ በአቡዳቢ ባለ አምስት ኮከቡ ኤምሬትስ ፓላስ ሆቴል ውስጥ እንዳሉ ነው። አንድ ሙሉውን ፎቅ ተቆጣጥረዋልም ተብሏል። ንጉስ ካርሎስ ከአቡዳቢው አልጋ ወራሽ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር የጠበቀ ግንኙነት አላቸው። ነገር ግን አሁንም ቢሆን በርግጠኝነት ያሉበት ቦታ አልታወቀም። የስፔን የልዑላውያን ቤተሰብም ሆነ መንግሥት ንጉስ ካርሎስ ያሉበትን ቦታ አስመልክቶ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል። ንጉሥ ካርሎስ ከጎርጎሳውያኑ 1975 ጀምሮ ለአርባ ዓመታት ስፔንን በንግሥና ከመሩ በኋላ በ2014 ነበር ስልጣነ መንበሩን ለልጃቸው ያስተላለፉት፡፡ ስልጣኑን ለልጃቸው የሰጡት የሴት ልጃቸው ባለቤት ጋር ተያይዞ በተነሳ የሙስና ውንጀላ ነው። ስፔን የምጣኔ ኃብት ቀውስ በነበረችበት ወቅት የዝሆን አደን በማካሄድ ቅንጦታዊ ድርጊት ፈፅመዋል የሚል ውዝግብም ተከትሎ ነው። እነዚህ ውዝግቦች በዚሁ አላቆሙም። ከወራት በፊትም የስፔን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ንጉሱ ከሳዑዲ አረቢያ የፈጣን ባቡር ግንባታ ጋርም ተያይዞ በሙስና ምርመራ ከፍቶባቸዋል። ይህንንም ተከትሎ የቀድሞው ንጉስ ያለመከሰስ መብታቸውን አጥተዋል። ከቀናት በፊትም የ82 አመቱ ንጉስ ካርሎስ ለልጃቸው ፍሊፕ ካርሎስ ስድስተኛ በፃፉትም ደብዳቤ ነው አገር ጥለው እንደሚሄዱ ውሳኔያቸውን ያሳወቁት። የስፔንን ህዝብንም ሆነ ተቋማቱን በበለጠ ለማገልገል አገር ጥለው እንደሄዱ የጠቆመው ደብዳቤው እሳቸው በሌሉበትም መንገድ ልጃቸው በተረጋጋ መንገድ ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበውታል።
https://www.bbc.com/amharic/news-53711892
5sports
አልቀመስ ያለው የዓለም ዋንጫ ተሳታፊ ብሔራዊ ቡድኖች የማሊያ ዋጋ
ኳታር እያስተናገደች ያለው የ2022 የፊፋ የዓለም ዋንጫ እጅግ ውድ የሆነው የዓለም ዋንጫ ብቻ አይደለም። በዓለም ዙሪያ ያሉ ደጋፊዎች የሚወዷቸውን የብሔራዊ ቡድኖቻቸውን ማሊያ ለመግዛት ከፍተኛ  ገንዘብ ማውጣት አለባቸው። በአንዳንድ አገሮች አንድ ሰው በወር ከሚያገኘው ዝቅተኛ ደመወዝ ከአንድ ሦስተኛ በላይ ማውጣት ይጠበቅባቸዋል ማለት ነው። ጃኒን ጋርሺያ የጎዳና ንግድ በሚደራበት የሪዮ ዴ ጄኔሮ ሰሜናዊ ክፍል ሳንስ ፔና አደባባይ ላይ ያለውን ድንኳን ስታይ ሁለት ጊዜ አላሰበችም። ከየአቅጣጫው በተንጠለጠሉ በመቶዎች በሚቆጠሩ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን ማሊያዎች ያጌጠ ቢጫ እና ሰማያዊ መብራት ነበር። የ42 ዓመቷ መምህርት እየሳቀች “ሰማያዊ ወሰድኩ (የብራዚል ሁለተኛ ማሊያ)። በጣም የሚያምር ስለነበር ብዙ የሥራ ባልደረቦቼ እና ጓደኞቼ እንድገዛላቸው ጠይቀውኛል” ብላለች። ጋርሺያ ለማሊያው 14 ዶላር ነው ያወጣችው። ይህም በአሜሪካው ግዙፍ የስፖርት ትጥቅ አምራች ናይኪ ከሚሸጥበት ዋጋ አንድ አምስተኛ (65 ዶላር) ያህል ነው። በ2022 የዓለም ዋንጫ ላይ የብራዚል ተጫዋቾች ከለበሱት ማሊያ  ጋር ተመሳሳይ የሆነ ፕሪሚየም ጥራት ያለው አለ፤ ይህ ግን 130 ዶላር ያስከፍላል። በብራዚል ዝቅተኛው ደመወዝ 225 ዶላር አካባቢ ነው። የርካሹ ማሊያ የዚህን ደሞዝ 30 በመቶ የሚጠጋ ሲሆን ውድ የሆነው ማሊያ ደግሞ 58 በመቶ አካባቢ ነው። “የእግር ኳስ ማሊያዎች ለእኛ የቅንጦት ዕቃ ሆነዋል” ትላለች ጋርሺያ። በመስከረም ወር ላይ የብራዚል የቢዝነስ መጽሔት “ኤግዛሜ” ባወጣው መጣጥፍ፣ ከዓለም ዋንጫው በፊት ይፋ የሆነው አዲሱ የብራዚል ማሊያ ከአራት ዓመታት በፊት ከወጣው ዋጋው 40 በመቶ ጨምሯል ሲል ዘግቧል። ነገር ግን የማሊያ ዋጋ መናር ግርምትን የፈጠረባት፣ ቅሬታ ያስነሳባት አገር ብራዚል ብቻ አይደለችም። ትልቅ የኢኮኖሚ ቀውስ በተጋፈጠችው እንግሊዝም ለ2022 የዓለም ዋንጫ የተዘጋጀው ማሊያ እስካሁን ከተሸጡት ሁሉ እጅግ ውድ የሚባል ነው (መደበኛ የሚባለው ማሊያ 85 ዶላር ይሸጣል)። ቀደም ሲል የነበረው የዋጋ ጭማሪ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮንን ጨምሮ ከበርካታ ፖለቲከኞች ወቀሳ ደርሶበታል። ካሜሮን እአአ በ2014 ለቢቢሲ “በጣም ውድ ነው። ወላጆች አዲሱን ማሊያ ለመግዛት ከፍተኛ ጫና ውስጥ ይገባሉ። እኛ መጠቀሚያ ልንሆን አይገባም” ሲሉ ገልጸው ነበር። ያለፈው ውድድር አሸናፊ ፈረንሳይ ደጋፊዎች ለማሊያ 93 ዶላርአካባቢ ያወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ለሁለቱም ቡድኖች ትጥቅ የሚያቀርበው ናይኪ ነው። ዋጋው በእነዚህ አገራት በደጋፊዎች ኪስ ላይ ያለው ተጽእኖ ከአንዳንድ ቡድኖች ጋር ሲወዳደር አነስተኛ ነው። በእንግሊዝ ዝቅተኛው የአንድ ሰዓት ሥራ ክፍያ 11.50 ዶላር ገደማ ሲሆን፣ ይህም በወር 1,750 ዶላር አካባቢ ይደርሳል። በፈረንሳይ ዝቅተኛው የወር ደሞዝ ወደ 1,400 ዶላር ገደማ ነው። በጋና ያለው የመግዛት አቅም እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። ለዚህም ነው በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ በአገሪቱ ያሉ ደጋፊዎች በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ቅሬታቸውን የገለጹት። ምክንያት ሲባሉ በጀርመኑ ፑማ ኩባንያ የተሰራው የ“ጥቋቁር ከዋክብቱ” የዓለም ዋንጫ ትጥቅ ዋጋ 94 ዶላር ገደማ መሆኑ ነው። “ፎርጂዱ ማልያ እስካሁን ገበያ ላይ አልዋለም?" ሲል አንድ ደጋፊ ጠይቋል። እንደ የሥራ እና የሠራተኛ ግንኙነት ሚኒስቴር ከሆነ በጋና ያለው ሕጋዊ ዝቅተኛ የደመወዝ ጣሪያ በሰዓት 0.95 ዶላር ነው። በወር 145 ዶላር አካባቢ ማለት ነው። የወቅቱ የአፍሪካ ሻምፒዮና በሆነችው ሴኔጋል ሐሰተኛ ማልያዎች የዋና ከተማዋ ዳካርን ጎዳናዎች አጥለቅልቀዋል። የአገሪቱ እግር ኳስ አስተዳዳሪ “ብሔራዊ ቡድኑን ለመደገፍ” ሲባል ደጋፊዎች በፑማ የተሠራውን ዋናውን ማሊያ እንዲገዙ ጠይቋል። እስከ ቅርብ ቀን ድረስ ዋናው ማሊያ በ71 ዶላር እየተሸጠ ነበር። ይህም ከ75 በመቶ በላይ ከሚሆኑ የሴኔጋል ወርሃዊ ዝቅተኛ ደሞዝ ጋር ተመሳሳይ ነው። “ዋናው ማሊያ በጣም ውድ ነው። ጥሩ ማሊያ ነው፣ እዚህ ያሉ ሰዎች ግን ምንም ገንዘብ የላቸውም” ሲል ሴኔጋላዊው የጎዳና ላይ ነጋዴ ማሊክ ለሬዲዮ ፍራንስ ኢንተርናሽናል ተናግሯል። “ብዙ ደንበኞች እያገኘሁ ነው” ካለ በኋላ ሴኔጋል ለጥሎ ማለፍ ብትበቃ ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ እሸጣለሁ ሲል ተስፋ ሰንቋል። የእግር ኳስ ቡድኖችን ማሊያ ለማምረት የሚወጣው ወጪ ውድ አይደለም። በባርሴሎና ዮሃን ክራይፍ የስፖርት ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት መምህር የሆኑት ሪቻርድ ዴንተን እንደሚገምቱት አንድ ማሊያ ለማምረት የሚያስፈልገው ወጪ ከ10 ዶላር በታች ነው። “በእርግጠኝነት የገበያ ዋጋውን ተመጣጣኝ እንዳይሆን ከማድርግ ባለፈ ለዚህ ምንም ማረጋገጫ የለም ብሎ ለመከራከርም በር ሊከፍት ይችላል” ሲሉ ዴንተን ይናገራሉ። “ለአንድ ሰው ምክንያታዊ ያልሆነው ዋጋ ለሌላው ምክንያታዊ ሊሆን ይችላል፤ ምክንያቱም ሌሎች ወጪዎች እና ኢንቨስትመንቶች በመጨረሻው ዋጋ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉና” ብለዋል። በእግር ኳስ ቢዝነስ ላይ የተካኑት የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ሴሳር ግራፊቲ በበኩላቸው የእግር ኳስ ማሊያ ዋጋ በዋናነት በምርቱ ዋጋ ብቻ የሚገለጽ እንዳልሆነ ያስረዳሉ። ታክስ፣ የሎጂስቲክስ ወጪዎች እና ትራንስፖርትን ጨምሮ ከፍተኛ ተጽዕኖ አላቸው። ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወዲህ ባለው የምርቶች ግብአት የአቅርቦት ችግር የእቃ ዋጋ ጨምሯል። በዩክሬን ያለው ጦርነትም ዓለም አቀፍ የነዳጅ ወጪ እንዲንር አድርጓል። ግራፊቲ አክለውም “ለክለቦች እና ለብሔራዊ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ከፍተኛ ገንዘብ መክፈል ስላለባቸው ትጥቅ አምራች ኩባንያዎች ከማልያ ሽያጭ ብዙ ገንዘብ አያገኙም” ይላሉ። እንደ ናይኪ እና የጀርመን ተቀናቃኙ አዲዳስ ያሉ ግዙፍ አምራቾች ስም ያላቸው ቡድኖች ትጥቆቻቸውን እንዲለብሱ ለማድረግ ብዙ ወጪ ያፈሳሉ። በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ናይኪ ከ32ቱ ተሳታፊ ቡድኖች ለ13ቱ ትጥቅ አቅራቢ ነው። አዲዳስ የአራት ጊዜ የዓለም ሻምፒዮናዋን ጀርመንን፣ የሁለት ጊዜ ሻምፒዮን የሆነችውን አርጀንቲናንና ለውድድሩ ትልቅ ግምት የተሰጣትን ስፔንን ጨምሮ ለሰባቱ ትጥቅ ያቀርባል። ሁለቱ አምራቾች በጋራ በመሆን እንደ አርጀንቲና፣ ብራዚል፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣሊያን እና ስፔን ላሉ ቡድኖች ትጥቅ ያቀርባሉ። ለብሔራዊ ፌዴሬሽኖቻቸውም በአጠቃላይ በዓመት 275 ሚሊዮን ዶላር እንደሚከፍሉ የስፖርት ቢዝነስ ላይ የሚሰራው ስፖርትስፕሮ ዘግቧል። “አዲዳስ ወይም ናይኪ ከእግር ኳስ ቡድኖቹ ጋር በሚደረጉ ስምምነቶች ውስጥ ያንን ኢንቨስትመንት ካላስመለሱ የማይደሰቱ ባለአክሲዮኖች አሏቸው” ሲሉ ዴንተን ይገልጻሉ። “ነገር ግን ማሊያው ውድ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን በራሳችን መወሰን አለብን። ለዚህም ነው አንዳንድ ሰዎች ርካሽ ወይን ሲጠጡ ሌሎች ደግሞ ውድ ወይን የሚጠጡት።” ቢቢሲ አስተያየት እንዲሰጡት አዲዳስ፣ ፑማ እና ናይኪን ጠይቋል። ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ምላሽ የሰጠው አዲዳስ ብቻ ነው። ኩባንያው በሰጠው ምላሽም ዋጋው ማሊያዎቹን ለመሥራት ጥቅም ላይ ከሚውለው የጨርቅ ጥራት እና ከዘላቂነቱ ጋር የሚያያዝ መሆኑን ገልጿል። “የእኛ ማሊያዎች በሜዳ ላይ ከሚለበሱት ጋር ተመሳሳይ በሆነ ጨርቅ ያዘጋጃሉ። ደጋፊዎች ለዓመታት በኩራት እንዲለብሷቸውም ነው የተዘጋጁት። ዋጋው ወደ ማሊያነት የሚያመጣውን ዘላቂነት እና የፈጠራ ደረጃን የሚያንፀባርቅ ነው” ብሏል። ጃኒን ጋርሺያ እና ጓደኞቿ ከዋናው ማሊያ እየወጡ ነው። ሁሉም ሰው በዋጋው መወደድ የራቀ አይመስልም። የናይኪ ተወካዮች እንዳሉት ለዘንድሮው የኳታር ውድድር የተዘጋጀው ማሊያ በ26 ዓመታት ውስጥ በኩባንያው እና በብራዚል እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ሲቢኤፍ) መካከል በነበረው ሽርክና በመሸጥ ቀዳሚው ነው። ጋርሺያ ግን በዚህ ሃሳብ አትስማማም። “ማን እንደሚገዛቸው ማወቅ እፈልጋለሁ” ትላለች። “ሁሌም እንደሚለበሱት እንደ ዲዛይነር ቦርሳ ወይም ልብስ አይደሉም።”
አልቀመስ ያለው የዓለም ዋንጫ ተሳታፊ ብሔራዊ ቡድኖች የማሊያ ዋጋ ኳታር እያስተናገደች ያለው የ2022 የፊፋ የዓለም ዋንጫ እጅግ ውድ የሆነው የዓለም ዋንጫ ብቻ አይደለም። በዓለም ዙሪያ ያሉ ደጋፊዎች የሚወዷቸውን የብሔራዊ ቡድኖቻቸውን ማሊያ ለመግዛት ከፍተኛ  ገንዘብ ማውጣት አለባቸው። በአንዳንድ አገሮች አንድ ሰው በወር ከሚያገኘው ዝቅተኛ ደመወዝ ከአንድ ሦስተኛ በላይ ማውጣት ይጠበቅባቸዋል ማለት ነው። ጃኒን ጋርሺያ የጎዳና ንግድ በሚደራበት የሪዮ ዴ ጄኔሮ ሰሜናዊ ክፍል ሳንስ ፔና አደባባይ ላይ ያለውን ድንኳን ስታይ ሁለት ጊዜ አላሰበችም። ከየአቅጣጫው በተንጠለጠሉ በመቶዎች በሚቆጠሩ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን ማሊያዎች ያጌጠ ቢጫ እና ሰማያዊ መብራት ነበር። የ42 ዓመቷ መምህርት እየሳቀች “ሰማያዊ ወሰድኩ (የብራዚል ሁለተኛ ማሊያ)። በጣም የሚያምር ስለነበር ብዙ የሥራ ባልደረቦቼ እና ጓደኞቼ እንድገዛላቸው ጠይቀውኛል” ብላለች። ጋርሺያ ለማሊያው 14 ዶላር ነው ያወጣችው። ይህም በአሜሪካው ግዙፍ የስፖርት ትጥቅ አምራች ናይኪ ከሚሸጥበት ዋጋ አንድ አምስተኛ (65 ዶላር) ያህል ነው። በ2022 የዓለም ዋንጫ ላይ የብራዚል ተጫዋቾች ከለበሱት ማሊያ  ጋር ተመሳሳይ የሆነ ፕሪሚየም ጥራት ያለው አለ፤ ይህ ግን 130 ዶላር ያስከፍላል። በብራዚል ዝቅተኛው ደመወዝ 225 ዶላር አካባቢ ነው። የርካሹ ማሊያ የዚህን ደሞዝ 30 በመቶ የሚጠጋ ሲሆን ውድ የሆነው ማሊያ ደግሞ 58 በመቶ አካባቢ ነው። “የእግር ኳስ ማሊያዎች ለእኛ የቅንጦት ዕቃ ሆነዋል” ትላለች ጋርሺያ። በመስከረም ወር ላይ የብራዚል የቢዝነስ መጽሔት “ኤግዛሜ” ባወጣው መጣጥፍ፣ ከዓለም ዋንጫው በፊት ይፋ የሆነው አዲሱ የብራዚል ማሊያ ከአራት ዓመታት በፊት ከወጣው ዋጋው 40 በመቶ ጨምሯል ሲል ዘግቧል። ነገር ግን የማሊያ ዋጋ መናር ግርምትን የፈጠረባት፣ ቅሬታ ያስነሳባት አገር ብራዚል ብቻ አይደለችም። ትልቅ የኢኮኖሚ ቀውስ በተጋፈጠችው እንግሊዝም ለ2022 የዓለም ዋንጫ የተዘጋጀው ማሊያ እስካሁን ከተሸጡት ሁሉ እጅግ ውድ የሚባል ነው (መደበኛ የሚባለው ማሊያ 85 ዶላር ይሸጣል)። ቀደም ሲል የነበረው የዋጋ ጭማሪ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮንን ጨምሮ ከበርካታ ፖለቲከኞች ወቀሳ ደርሶበታል። ካሜሮን እአአ በ2014 ለቢቢሲ “በጣም ውድ ነው። ወላጆች አዲሱን ማሊያ ለመግዛት ከፍተኛ ጫና ውስጥ ይገባሉ። እኛ መጠቀሚያ ልንሆን አይገባም” ሲሉ ገልጸው ነበር። ያለፈው ውድድር አሸናፊ ፈረንሳይ ደጋፊዎች ለማሊያ 93 ዶላርአካባቢ ያወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ለሁለቱም ቡድኖች ትጥቅ የሚያቀርበው ናይኪ ነው። ዋጋው በእነዚህ አገራት በደጋፊዎች ኪስ ላይ ያለው ተጽእኖ ከአንዳንድ ቡድኖች ጋር ሲወዳደር አነስተኛ ነው። በእንግሊዝ ዝቅተኛው የአንድ ሰዓት ሥራ ክፍያ 11.50 ዶላር ገደማ ሲሆን፣ ይህም በወር 1,750 ዶላር አካባቢ ይደርሳል። በፈረንሳይ ዝቅተኛው የወር ደሞዝ ወደ 1,400 ዶላር ገደማ ነው። በጋና ያለው የመግዛት አቅም እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። ለዚህም ነው በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ በአገሪቱ ያሉ ደጋፊዎች በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ቅሬታቸውን የገለጹት። ምክንያት ሲባሉ በጀርመኑ ፑማ ኩባንያ የተሰራው የ“ጥቋቁር ከዋክብቱ” የዓለም ዋንጫ ትጥቅ ዋጋ 94 ዶላር ገደማ መሆኑ ነው። “ፎርጂዱ ማልያ እስካሁን ገበያ ላይ አልዋለም?" ሲል አንድ ደጋፊ ጠይቋል። እንደ የሥራ እና የሠራተኛ ግንኙነት ሚኒስቴር ከሆነ በጋና ያለው ሕጋዊ ዝቅተኛ የደመወዝ ጣሪያ በሰዓት 0.95 ዶላር ነው። በወር 145 ዶላር አካባቢ ማለት ነው። የወቅቱ የአፍሪካ ሻምፒዮና በሆነችው ሴኔጋል ሐሰተኛ ማልያዎች የዋና ከተማዋ ዳካርን ጎዳናዎች አጥለቅልቀዋል። የአገሪቱ እግር ኳስ አስተዳዳሪ “ብሔራዊ ቡድኑን ለመደገፍ” ሲባል ደጋፊዎች በፑማ የተሠራውን ዋናውን ማሊያ እንዲገዙ ጠይቋል። እስከ ቅርብ ቀን ድረስ ዋናው ማሊያ በ71 ዶላር እየተሸጠ ነበር። ይህም ከ75 በመቶ በላይ ከሚሆኑ የሴኔጋል ወርሃዊ ዝቅተኛ ደሞዝ ጋር ተመሳሳይ ነው። “ዋናው ማሊያ በጣም ውድ ነው። ጥሩ ማሊያ ነው፣ እዚህ ያሉ ሰዎች ግን ምንም ገንዘብ የላቸውም” ሲል ሴኔጋላዊው የጎዳና ላይ ነጋዴ ማሊክ ለሬዲዮ ፍራንስ ኢንተርናሽናል ተናግሯል። “ብዙ ደንበኞች እያገኘሁ ነው” ካለ በኋላ ሴኔጋል ለጥሎ ማለፍ ብትበቃ ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ እሸጣለሁ ሲል ተስፋ ሰንቋል። የእግር ኳስ ቡድኖችን ማሊያ ለማምረት የሚወጣው ወጪ ውድ አይደለም። በባርሴሎና ዮሃን ክራይፍ የስፖርት ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት መምህር የሆኑት ሪቻርድ ዴንተን እንደሚገምቱት አንድ ማሊያ ለማምረት የሚያስፈልገው ወጪ ከ10 ዶላር በታች ነው። “በእርግጠኝነት የገበያ ዋጋውን ተመጣጣኝ እንዳይሆን ከማድርግ ባለፈ ለዚህ ምንም ማረጋገጫ የለም ብሎ ለመከራከርም በር ሊከፍት ይችላል” ሲሉ ዴንተን ይናገራሉ። “ለአንድ ሰው ምክንያታዊ ያልሆነው ዋጋ ለሌላው ምክንያታዊ ሊሆን ይችላል፤ ምክንያቱም ሌሎች ወጪዎች እና ኢንቨስትመንቶች በመጨረሻው ዋጋ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉና” ብለዋል። በእግር ኳስ ቢዝነስ ላይ የተካኑት የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ሴሳር ግራፊቲ በበኩላቸው የእግር ኳስ ማሊያ ዋጋ በዋናነት በምርቱ ዋጋ ብቻ የሚገለጽ እንዳልሆነ ያስረዳሉ። ታክስ፣ የሎጂስቲክስ ወጪዎች እና ትራንስፖርትን ጨምሮ ከፍተኛ ተጽዕኖ አላቸው። ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወዲህ ባለው የምርቶች ግብአት የአቅርቦት ችግር የእቃ ዋጋ ጨምሯል። በዩክሬን ያለው ጦርነትም ዓለም አቀፍ የነዳጅ ወጪ እንዲንር አድርጓል። ግራፊቲ አክለውም “ለክለቦች እና ለብሔራዊ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ከፍተኛ ገንዘብ መክፈል ስላለባቸው ትጥቅ አምራች ኩባንያዎች ከማልያ ሽያጭ ብዙ ገንዘብ አያገኙም” ይላሉ። እንደ ናይኪ እና የጀርመን ተቀናቃኙ አዲዳስ ያሉ ግዙፍ አምራቾች ስም ያላቸው ቡድኖች ትጥቆቻቸውን እንዲለብሱ ለማድረግ ብዙ ወጪ ያፈሳሉ። በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ናይኪ ከ32ቱ ተሳታፊ ቡድኖች ለ13ቱ ትጥቅ አቅራቢ ነው። አዲዳስ የአራት ጊዜ የዓለም ሻምፒዮናዋን ጀርመንን፣ የሁለት ጊዜ ሻምፒዮን የሆነችውን አርጀንቲናንና ለውድድሩ ትልቅ ግምት የተሰጣትን ስፔንን ጨምሮ ለሰባቱ ትጥቅ ያቀርባል። ሁለቱ አምራቾች በጋራ በመሆን እንደ አርጀንቲና፣ ብራዚል፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣሊያን እና ስፔን ላሉ ቡድኖች ትጥቅ ያቀርባሉ። ለብሔራዊ ፌዴሬሽኖቻቸውም በአጠቃላይ በዓመት 275 ሚሊዮን ዶላር እንደሚከፍሉ የስፖርት ቢዝነስ ላይ የሚሰራው ስፖርትስፕሮ ዘግቧል። “አዲዳስ ወይም ናይኪ ከእግር ኳስ ቡድኖቹ ጋር በሚደረጉ ስምምነቶች ውስጥ ያንን ኢንቨስትመንት ካላስመለሱ የማይደሰቱ ባለአክሲዮኖች አሏቸው” ሲሉ ዴንተን ይገልጻሉ። “ነገር ግን ማሊያው ውድ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን በራሳችን መወሰን አለብን። ለዚህም ነው አንዳንድ ሰዎች ርካሽ ወይን ሲጠጡ ሌሎች ደግሞ ውድ ወይን የሚጠጡት።” ቢቢሲ አስተያየት እንዲሰጡት አዲዳስ፣ ፑማ እና ናይኪን ጠይቋል። ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ምላሽ የሰጠው አዲዳስ ብቻ ነው። ኩባንያው በሰጠው ምላሽም ዋጋው ማሊያዎቹን ለመሥራት ጥቅም ላይ ከሚውለው የጨርቅ ጥራት እና ከዘላቂነቱ ጋር የሚያያዝ መሆኑን ገልጿል። “የእኛ ማሊያዎች በሜዳ ላይ ከሚለበሱት ጋር ተመሳሳይ በሆነ ጨርቅ ያዘጋጃሉ። ደጋፊዎች ለዓመታት በኩራት እንዲለብሷቸውም ነው የተዘጋጁት። ዋጋው ወደ ማሊያነት የሚያመጣውን ዘላቂነት እና የፈጠራ ደረጃን የሚያንፀባርቅ ነው” ብሏል። ጃኒን ጋርሺያ እና ጓደኞቿ ከዋናው ማሊያ እየወጡ ነው። ሁሉም ሰው በዋጋው መወደድ የራቀ አይመስልም። የናይኪ ተወካዮች እንዳሉት ለዘንድሮው የኳታር ውድድር የተዘጋጀው ማሊያ በ26 ዓመታት ውስጥ በኩባንያው እና በብራዚል እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ሲቢኤፍ) መካከል በነበረው ሽርክና በመሸጥ ቀዳሚው ነው። ጋርሺያ ግን በዚህ ሃሳብ አትስማማም። “ማን እንደሚገዛቸው ማወቅ እፈልጋለሁ” ትላለች። “ሁሌም እንደሚለበሱት እንደ ዲዛይነር ቦርሳ ወይም ልብስ አይደሉም።”
https://www.bbc.com/amharic/articles/cd1567j3kmko
2health
ኮሮናቫይረስ፡ በሕንድ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር 5 ሚሊየን አለፈ
በሕንድ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አምስት ሚሊየን ማለፉ ተገለፀ። ይህም አገሪቱን በአሜሪካ በመቀጠል በቫይረሱ ክፉኛ የተጎዳች እንድትሆን አድርጓታል። በሕንድ በአንድ ቀን ብቻ እስከ 90 000 ሰዎች በኮቪድ-19 እየተያዙ ሲሆን ቫይረሱም በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ ነው ተብሏል። እስካሁን ድረስ በአገሪቱ ከ80 ሺህ በላይ ሰዎች ሲሞቱ፣ በቫይረሱ ምክንያት በጽኑ ለታመሙ አልጋ እንዲሁም የኦክስጅን አቅርቦት እጥረት ተከስቷል። በሕንድ የቫይረሱ ስርጭት እየተስፋፋ የመጣው በመጋቢት ወር ተጥሎ የነበረውን የእንቅስቃሴ ገደብ የምጣኔ ሃብቱን ለማነቃቃት በሚል ከተነሳ ወዲህ ነው። ቫይረሱ ወደትንንሽ ከተሞች ከመሰራጨቱ በፊት እንደ ሙምባይና ደልሂ ያሉ ግዙፍ ከተሞችን ክፉኛ አጥቅቶ ነበር። ሕንድ ምጣኔ ሃብቷን ክፍት ማድረግ በጀመረችበትና ሰዎች ወደ ስራ በተመለሱበት ወቅት የቫይረሱ ስርጭት እየተስፋፋ መምጣቱ ተስተውሏል። ባለፉት ሳምንት ብቻ 600,000 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው በምርመራ ተረጋግጧል። በሕንድ አሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 5,020,359 የደረሰ ሲሆን፣ ባለፈው 24 ሰዓታት ብቻ 90,123 መያዛቸው መታወቁ ተገልጿል። በአገሪቱ የኦክስጅን ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ኦክስጅን አምራች ኢንደስትሪዎች ገልፀዋል። በዚህ ወር ብቻ ሆስፒታሎችና የእንክብካቤ ማዕከላት 2,700 ቶን ኦክስጅን የተጠቀሙ ሲሆን፣ በሚያዚያ ወር ግን 750 ቶን ብቻ ነበር ፍጆታቸው ተብሏል። የቫይረሱ ስርጭት እየጨመረባቸው ከሚገኙ የህንድ ከተሞች መካከል ማሃራሽትራ፣ ማድያ ፕራዴሽ፣ ጉጅራት፣ ራጃስታን፣ ቴሌንጋና፣ አንድሃራ ፕራዴሽ ናቸው።
ኮሮናቫይረስ፡ በሕንድ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር 5 ሚሊየን አለፈ በሕንድ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አምስት ሚሊየን ማለፉ ተገለፀ። ይህም አገሪቱን በአሜሪካ በመቀጠል በቫይረሱ ክፉኛ የተጎዳች እንድትሆን አድርጓታል። በሕንድ በአንድ ቀን ብቻ እስከ 90 000 ሰዎች በኮቪድ-19 እየተያዙ ሲሆን ቫይረሱም በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ ነው ተብሏል። እስካሁን ድረስ በአገሪቱ ከ80 ሺህ በላይ ሰዎች ሲሞቱ፣ በቫይረሱ ምክንያት በጽኑ ለታመሙ አልጋ እንዲሁም የኦክስጅን አቅርቦት እጥረት ተከስቷል። በሕንድ የቫይረሱ ስርጭት እየተስፋፋ የመጣው በመጋቢት ወር ተጥሎ የነበረውን የእንቅስቃሴ ገደብ የምጣኔ ሃብቱን ለማነቃቃት በሚል ከተነሳ ወዲህ ነው። ቫይረሱ ወደትንንሽ ከተሞች ከመሰራጨቱ በፊት እንደ ሙምባይና ደልሂ ያሉ ግዙፍ ከተሞችን ክፉኛ አጥቅቶ ነበር። ሕንድ ምጣኔ ሃብቷን ክፍት ማድረግ በጀመረችበትና ሰዎች ወደ ስራ በተመለሱበት ወቅት የቫይረሱ ስርጭት እየተስፋፋ መምጣቱ ተስተውሏል። ባለፉት ሳምንት ብቻ 600,000 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው በምርመራ ተረጋግጧል። በሕንድ አሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 5,020,359 የደረሰ ሲሆን፣ ባለፈው 24 ሰዓታት ብቻ 90,123 መያዛቸው መታወቁ ተገልጿል። በአገሪቱ የኦክስጅን ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ኦክስጅን አምራች ኢንደስትሪዎች ገልፀዋል። በዚህ ወር ብቻ ሆስፒታሎችና የእንክብካቤ ማዕከላት 2,700 ቶን ኦክስጅን የተጠቀሙ ሲሆን፣ በሚያዚያ ወር ግን 750 ቶን ብቻ ነበር ፍጆታቸው ተብሏል። የቫይረሱ ስርጭት እየጨመረባቸው ከሚገኙ የህንድ ከተሞች መካከል ማሃራሽትራ፣ ማድያ ፕራዴሽ፣ ጉጅራት፣ ራጃስታን፣ ቴሌንጋና፣ አንድሃራ ፕራዴሽ ናቸው።
https://www.bbc.com/amharic/news-54165435
0business
በሃርጌሳ የገበያ ሥፍራ በደረሰው የእሳት አደጋ በቢሊየን ዶላር የሚገመት ውድመት ደርሷል ተባለ
ባለፈው አርብ ራስ ገዝ አስተዳደር በሆነችው ሶማሊላንድ ዋና ከተማ ሃርጌሳ በገበያ ስፍራ በተከሰተ የእሳት አደጋ በቢሊየን ዶላር የሚገመት ንብረት ሳይወድም እንዳልቀረ ተገለጸ። በአደጋው ለተጎዱት ከአጎራባች አገራት ዕርዳታ መግባት መጀመሩን ተከትሎ በአካባቢው አስተዳደር የተቋቋመው ኮሚሽን፣ የእሳት አደጋው ከአንድ ቢሊየን ዶላር በላይ የሚገመቱ ንብረቶችን ሳያወድም እንዳልቀረ አስታውቋል። በእሳት አደጋው ምክንያት ከደረሰው ከፍተኛ ውድመት በኋላ የተቀረፁ ተንቀሳቃሽ ምስሎች በማኅበራዊ ሚዲያዎች ተጋርተዋል። አርብ አመሻሽ ላይ የተነሳው እሳት በአጠቃላይ የገበያውን ሥፍራ አውድሞታል። በሃርጌሳ የሚገኙ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ቤተሰቦችን ሜዳ ላይ ያስቀረውን ይህንን እሳት ለማጥፋትም ሰዓታት ፈጅቷል። በሶማሊላንድ ፕሬዚደንት ሙሴ ቢሂ የተዋቀረውና በአደጋው የደረሰውን ጉዳት የሚያጣራው ኮሚሽን በአደጋው ከአንድ ቢሊየን ዶላር በላይ ውድመት ሳይደርስ እንዳልቀረ አመልክቷል። "እንደ የመጀመሪያ ደረጃው ሪፖርት ከሆነ በእሳት አደጋው የደረሰው የጉዳት መጠን ከ1.5 እስከ 2 ቢሊየን ዶላር ይደርሳል ተብሎ ይገመታል" ሲሉ የሃርጌሳ ከተማ ከንቲባ አብዲካሪን አሕመድ ሞጌ ተናግረዋል። የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሃመድ ሁሴን ሮብሌ እሁድ ዕለት ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋር ከተወያዩ በኋላ ባደረጉት ንግግር መንግሥታቸው በሃርጌሳ የንግድ ገበያ ዋሂን ለደረሰው ከባድ የእሳት አደጋ ለአደጋ ጊዜ ምላሽ የሚውል 11.7 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል። በሌላ በኩል የእንግሊዙን ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን እና የአሜሪካ የኮንግረንስ አባል ኢልሃን ኦማርን ጨምሮ የዓለም መሪዎች በሃርጌሳ ሕዝቦች ላይ በደረሰው አደጋ የተሰማቸውን ሃዘን የገለፁ ሲሆን በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከጎናቸው እንደሚቆሙ ገልጸዋል። የገበያው ሥፍራ በመቶዎች በሚቆጠሩ ትናንሽ ሱቆች እና ነጋዴዎች የተጨናነቀ ነበር። በዚህ በሃርጌሳ ከተማ የንግድ ማዕከል በሆነውና በሺዎች የሚቆጠሩ ሹቆችና ሸዶች መገኛ ዋሂን የገበያ ሥፍራ ላይ የደረሰው የእሳት አደጋ መንስኤ እስካሁን አልታወቀም። የገበያ ሥፍራው ለኢትዮጵያ፣ ለጂቡቲ እና ለተወሰኑ የሶማሊያ አካባቢዎች አገልግሎት ይሰጥ የነበረ ሲሆን በአፍሪካ ቀንድ ሦስተኛው ትልቁ የገበያ ሥፍራ ነበር። በአደጋው ለተጎዱት ድጋፍ የማሰባሰብ ሥራ እየተሰራ ሲሆን ጎረቤት አገራትም የልዑካን ቡድን ወደ ሶማሊላንድ በመላክ ከሃርጌሳ ሕዝብ ጋር የደረሰውን ጉዳት መጋራት ችለዋል። ሶማሊላንድ እአአ በ1991 የሲያድ ባሬ መንግሥት መውደቅን ተከትሎ ከሶማሊያ ነጻ መውጣቷን ያወጀችው ከ30 ዓመታት በፊት ሲሆን እስካሁን ግን ይፋዊ እውቅና አላገኘችም።
በሃርጌሳ የገበያ ሥፍራ በደረሰው የእሳት አደጋ በቢሊየን ዶላር የሚገመት ውድመት ደርሷል ተባለ ባለፈው አርብ ራስ ገዝ አስተዳደር በሆነችው ሶማሊላንድ ዋና ከተማ ሃርጌሳ በገበያ ስፍራ በተከሰተ የእሳት አደጋ በቢሊየን ዶላር የሚገመት ንብረት ሳይወድም እንዳልቀረ ተገለጸ። በአደጋው ለተጎዱት ከአጎራባች አገራት ዕርዳታ መግባት መጀመሩን ተከትሎ በአካባቢው አስተዳደር የተቋቋመው ኮሚሽን፣ የእሳት አደጋው ከአንድ ቢሊየን ዶላር በላይ የሚገመቱ ንብረቶችን ሳያወድም እንዳልቀረ አስታውቋል። በእሳት አደጋው ምክንያት ከደረሰው ከፍተኛ ውድመት በኋላ የተቀረፁ ተንቀሳቃሽ ምስሎች በማኅበራዊ ሚዲያዎች ተጋርተዋል። አርብ አመሻሽ ላይ የተነሳው እሳት በአጠቃላይ የገበያውን ሥፍራ አውድሞታል። በሃርጌሳ የሚገኙ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ቤተሰቦችን ሜዳ ላይ ያስቀረውን ይህንን እሳት ለማጥፋትም ሰዓታት ፈጅቷል። በሶማሊላንድ ፕሬዚደንት ሙሴ ቢሂ የተዋቀረውና በአደጋው የደረሰውን ጉዳት የሚያጣራው ኮሚሽን በአደጋው ከአንድ ቢሊየን ዶላር በላይ ውድመት ሳይደርስ እንዳልቀረ አመልክቷል። "እንደ የመጀመሪያ ደረጃው ሪፖርት ከሆነ በእሳት አደጋው የደረሰው የጉዳት መጠን ከ1.5 እስከ 2 ቢሊየን ዶላር ይደርሳል ተብሎ ይገመታል" ሲሉ የሃርጌሳ ከተማ ከንቲባ አብዲካሪን አሕመድ ሞጌ ተናግረዋል። የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሃመድ ሁሴን ሮብሌ እሁድ ዕለት ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋር ከተወያዩ በኋላ ባደረጉት ንግግር መንግሥታቸው በሃርጌሳ የንግድ ገበያ ዋሂን ለደረሰው ከባድ የእሳት አደጋ ለአደጋ ጊዜ ምላሽ የሚውል 11.7 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል። በሌላ በኩል የእንግሊዙን ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን እና የአሜሪካ የኮንግረንስ አባል ኢልሃን ኦማርን ጨምሮ የዓለም መሪዎች በሃርጌሳ ሕዝቦች ላይ በደረሰው አደጋ የተሰማቸውን ሃዘን የገለፁ ሲሆን በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከጎናቸው እንደሚቆሙ ገልጸዋል። የገበያው ሥፍራ በመቶዎች በሚቆጠሩ ትናንሽ ሱቆች እና ነጋዴዎች የተጨናነቀ ነበር። በዚህ በሃርጌሳ ከተማ የንግድ ማዕከል በሆነውና በሺዎች የሚቆጠሩ ሹቆችና ሸዶች መገኛ ዋሂን የገበያ ሥፍራ ላይ የደረሰው የእሳት አደጋ መንስኤ እስካሁን አልታወቀም። የገበያ ሥፍራው ለኢትዮጵያ፣ ለጂቡቲ እና ለተወሰኑ የሶማሊያ አካባቢዎች አገልግሎት ይሰጥ የነበረ ሲሆን በአፍሪካ ቀንድ ሦስተኛው ትልቁ የገበያ ሥፍራ ነበር። በአደጋው ለተጎዱት ድጋፍ የማሰባሰብ ሥራ እየተሰራ ሲሆን ጎረቤት አገራትም የልዑካን ቡድን ወደ ሶማሊላንድ በመላክ ከሃርጌሳ ሕዝብ ጋር የደረሰውን ጉዳት መጋራት ችለዋል። ሶማሊላንድ እአአ በ1991 የሲያድ ባሬ መንግሥት መውደቅን ተከትሎ ከሶማሊያ ነጻ መውጣቷን ያወጀችው ከ30 ዓመታት በፊት ሲሆን እስካሁን ግን ይፋዊ እውቅና አላገኘችም።
https://www.bbc.com/amharic/news-60985421
5sports
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ጨዋታዋ በኬፕ ቨርዴ ተረታች
ብርኪና ፋሶ እና አዘጋጇ ካሜሩን ከዳረጉት የመክፈቻ ጨዋታ በኋላ በኦሌምቤ ስታዲየም በተደረገው ሁለተኛ ጨዋታ ኬፕ ቨርዴ ኢትዮጵያን 1 ለ 0 አሸንፋለች። አሰልጣኝ ቡቢስታ ጭምሮ የኬፕ ቨርዴ ዘጠኝ ተጫዋቾች በኮቪድ ምክንያት በስታዲየሙ ያልተገኙ ሲሆን ብሉ ሻርኮች ከዋልያዎቹ ጋር ባደረጉት ጨዋታ 6 ተጨዋቾችን ብቻ በተጠባባዊ ወንበር ላይ ለማስቀመጥ ተገደው ነበር። ይሁን እንጂ የኬፕ ቨርዴ ብሔራዊ ቡድን ዋልያዎቹን በመርታት 3 ነጥብ ይዘው ወጥተዋል። በጨዋታው ጅማሬ ላይ የዋልያዎቹ ያሬድ ባዬህ በተጋጣሚው ጁሊዮ ታቫሬስ ላይ በሰራው ጥፋት በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። ያሬድ መጀመሪያ ላይ በአንጎላዊው ዳኛ ሄልደር ማርቲንስ ዴ ካርቫልሆ ቢጫ ተስጥቶት የነበረው ቢሆንም በረዳት ዳኛው ጥያቄ የማሃል ዳኛው ክስተቱን በቪ ኤ አር ከተመከቱ በኋላ ተጨዋቹ በቀይ ወጥቷል። ተቀይሮ የገባው ምኞት ደበበ በራሱ ላይ ጎል ለማስቆጠር ተቃርቦ የነበረ ቢሆንም የዋልያዎቹ ግብ ጠባቂው ተክለማርያም ሻንቆ ግብ ከመሆን ታድጎታል። በኮሮናቫይረስ ምክንያት ለሌላ ጊዜ ከተላለፈ በኋላ በተጀመረው የዘንድሮ የአፍሪካ ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ ካሜሮን ቡርኪና ፋሶን 2-1 አሸንፋለች። በያውንዴ በተካሄደው በዚህ ጨዋታ ቡርኪና ፋሶ የመጀመሪያ አጋማሽ ጎል አስቆጥረው መምራት ችለው ነበር። ሆኖም የአስተናጋጇ ካሜሮን አምበል አቡባካር ቡድኑ ያገኘውን የቅጣት ምቶች ዕድል ወደ ጎል በመቀየር ከእረፍት በፊት የውጤትን ብልጫ ወደ አስተናጋጆቹ ዞሯል። ምድብ ሀ በድል የጀመሩት የማይበገሩት አናብስት ግብ ጠባቂ አንድሬ ኦናና በሁለተኛው አጋማሽ ሁለት ወሳኝ ሙከራዎችን ግብ እንዳይሆኑ አክሽፏል። ዛሬ በአፍሪካ ዋንጫ ውድድር አራት ጨዋታዎች የሚደረጉ ሲሆን የባለፈው የውድድር ዘመን ሁለተኛ የነበረችው ሴኔጋል እና የአራት ጊዜ ሻምፒዮኗ ምሽት ላይ ይጫወታሉ።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ጨዋታዋ በኬፕ ቨርዴ ተረታች ብርኪና ፋሶ እና አዘጋጇ ካሜሩን ከዳረጉት የመክፈቻ ጨዋታ በኋላ በኦሌምቤ ስታዲየም በተደረገው ሁለተኛ ጨዋታ ኬፕ ቨርዴ ኢትዮጵያን 1 ለ 0 አሸንፋለች። አሰልጣኝ ቡቢስታ ጭምሮ የኬፕ ቨርዴ ዘጠኝ ተጫዋቾች በኮቪድ ምክንያት በስታዲየሙ ያልተገኙ ሲሆን ብሉ ሻርኮች ከዋልያዎቹ ጋር ባደረጉት ጨዋታ 6 ተጨዋቾችን ብቻ በተጠባባዊ ወንበር ላይ ለማስቀመጥ ተገደው ነበር። ይሁን እንጂ የኬፕ ቨርዴ ብሔራዊ ቡድን ዋልያዎቹን በመርታት 3 ነጥብ ይዘው ወጥተዋል። በጨዋታው ጅማሬ ላይ የዋልያዎቹ ያሬድ ባዬህ በተጋጣሚው ጁሊዮ ታቫሬስ ላይ በሰራው ጥፋት በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። ያሬድ መጀመሪያ ላይ በአንጎላዊው ዳኛ ሄልደር ማርቲንስ ዴ ካርቫልሆ ቢጫ ተስጥቶት የነበረው ቢሆንም በረዳት ዳኛው ጥያቄ የማሃል ዳኛው ክስተቱን በቪ ኤ አር ከተመከቱ በኋላ ተጨዋቹ በቀይ ወጥቷል። ተቀይሮ የገባው ምኞት ደበበ በራሱ ላይ ጎል ለማስቆጠር ተቃርቦ የነበረ ቢሆንም የዋልያዎቹ ግብ ጠባቂው ተክለማርያም ሻንቆ ግብ ከመሆን ታድጎታል። በኮሮናቫይረስ ምክንያት ለሌላ ጊዜ ከተላለፈ በኋላ በተጀመረው የዘንድሮ የአፍሪካ ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ ካሜሮን ቡርኪና ፋሶን 2-1 አሸንፋለች። በያውንዴ በተካሄደው በዚህ ጨዋታ ቡርኪና ፋሶ የመጀመሪያ አጋማሽ ጎል አስቆጥረው መምራት ችለው ነበር። ሆኖም የአስተናጋጇ ካሜሮን አምበል አቡባካር ቡድኑ ያገኘውን የቅጣት ምቶች ዕድል ወደ ጎል በመቀየር ከእረፍት በፊት የውጤትን ብልጫ ወደ አስተናጋጆቹ ዞሯል። ምድብ ሀ በድል የጀመሩት የማይበገሩት አናብስት ግብ ጠባቂ አንድሬ ኦናና በሁለተኛው አጋማሽ ሁለት ወሳኝ ሙከራዎችን ግብ እንዳይሆኑ አክሽፏል። ዛሬ በአፍሪካ ዋንጫ ውድድር አራት ጨዋታዎች የሚደረጉ ሲሆን የባለፈው የውድድር ዘመን ሁለተኛ የነበረችው ሴኔጋል እና የአራት ጊዜ ሻምፒዮኗ ምሽት ላይ ይጫወታሉ።
https://www.bbc.com/amharic/59933436
0business
ሩሲያ ወደ አሜሪካ እና አውሮፓ በምትልካቸው ምርቶች ላይ ማዕቀብ ጣለች
ሞስኮ በምዕራባውያን አገራት ለተጣለባት ማዕቀብ አጸፋ ከ200 በላይ የተለያዩ አይነት ምርቶች ከሩሲያ ወደ ውጭ እንዳይላኩ እገዳ ጣለች። በዚህ የሩሲያ የማዕቀብ እርምጃ የቴሌኮም፣ የህክምና፣ የግብርና፣ የኤሌክትሪክ እና የቴክኖሎጆ መሳሪያዎች ማዕቀብ ከተጣለባቸው ምርቶች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው። በተጨማሪም "ሩሲያን የሚጎዳ እርምጃ የወሰዱ" ባለቻቸው አገራት ላይ የእንጨት ምርቶች ሽያጭን አግዳለች። ይህ የሩሲያ እርምጃ የአውሮፓ ሕብረትን እና አሜሪካንን ጨምሮ ሌሎች 48 አገራትን የሚመለከት ነው። የሩሲያ የማዕቀብ ውሳኔ ከአገሪቱ የሚላኩ ምርቶች ላይ አስካለንበት የፈረንጆች ዓመት ማብቂያ ድረስ እገዳ እንዲጣልባቸው አድርጓል። በሩሲያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሚኻይል ሚሹስቲን በተፈረመው በዚህ ትዕዛዝ ላይ እንደተጠቀሰው ከሩሲያ ወደ ውጭ አገራት የሚላኩ ምርቶችን ማቀብ "በሩሲያ ገበያ ውስጥ መረጋጋት ለመፍጠር አስፈላጊ ነው" ተብሏል። ይህ የሩሲያ የአጸፋ እርምጃ በዩክሬን ላይ ወረራ መፈጸሟን ተከትሎ ምዕራባውያን በሩሲያ የገንዘብ እና የኃይል አቅርቦት ላይ ከባድ የሚባሉ ተከታታይ ማዕቀቦችን በመጣላቸው የመጣ ነው። ከዚህ በተጨማሪም በምዕራቡ ዓለም ከፍተኛ ሀብት ካላቸው ሩሲያውያን ከበርቴዎች መካከል ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር ቅርበት አላቸው በተባሉት ላይም ንብረታቸውን እንዳያንቀሳቅሱና ጉዞ እንዳያደርጉ ዕቀባ ተጥሎባቸዋል። ሩሲያ ወደ ውጭ እንዳይላኩ ካገደቻቸው ምርቶቿ መካከል መኪኖች፣ የባቡር ፉርጎዎች፣ የእቃ ማጓጓዣ ኮንቴይነሮች እና የኃይል ማመንጫ ተርባይኖች እንደሚገኙበት ታውቋል። በቅርብ የወጡ መረጃዎች እንደሚያመልክቱት ዩናይትድ ኪንግደም ከሩሲያ ጋር ከፍተኛ የንግድ ልውውጥ ከሚያደርጉ አገራት መካከል ስትሆን በዚህም በሁለቱ አገራት መካከል በአጠቃላይ 15.9 ቢሊዮን ፓወንድ የሚያወጣ የንግድ ልውውጥ ይካሄዳል። ሩሲያ ለአውሮፓ አገራት ነዳጅ እና ጋር በማቅረብ ከፍተኛ ድርሻ ያላት ሲሆን፣ ከጦርነቱ በኋላ አገራት እነዚህን ምርቶች መግዛታቸውን ለማቆም ውይይት እያደረጉ ነው። አሜሪካ ከሩሲያ ትገዛ የነበረው የነዳጅ እና የጋዝ አቅርቦት እንዲቋረጥ በዚህ ሳምንት ወስናለች። ሩሲያ በዩክሬን ላይ በከፈተችው ወረራ ሳቢያ ምዕራባውያን በአገሪቱ ላይ ከባድ ምጣኔ ሀብታዊ እቀባን እየጣሉ ሲሆን፣ ግዙፎቹ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎቻቸውም ሥራቸውን እያቋረጡ ከሩሲያ እየወጡ ነው። በዚህም ምክንያት ሩሲያ በአጸፋው ለእነዚህ አገራት የምታቀርባቸውን ተለያዩ አይነት ምርቶችን ላለመሸጥ የወሰነችው።
ሩሲያ ወደ አሜሪካ እና አውሮፓ በምትልካቸው ምርቶች ላይ ማዕቀብ ጣለች ሞስኮ በምዕራባውያን አገራት ለተጣለባት ማዕቀብ አጸፋ ከ200 በላይ የተለያዩ አይነት ምርቶች ከሩሲያ ወደ ውጭ እንዳይላኩ እገዳ ጣለች። በዚህ የሩሲያ የማዕቀብ እርምጃ የቴሌኮም፣ የህክምና፣ የግብርና፣ የኤሌክትሪክ እና የቴክኖሎጆ መሳሪያዎች ማዕቀብ ከተጣለባቸው ምርቶች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው። በተጨማሪም "ሩሲያን የሚጎዳ እርምጃ የወሰዱ" ባለቻቸው አገራት ላይ የእንጨት ምርቶች ሽያጭን አግዳለች። ይህ የሩሲያ እርምጃ የአውሮፓ ሕብረትን እና አሜሪካንን ጨምሮ ሌሎች 48 አገራትን የሚመለከት ነው። የሩሲያ የማዕቀብ ውሳኔ ከአገሪቱ የሚላኩ ምርቶች ላይ አስካለንበት የፈረንጆች ዓመት ማብቂያ ድረስ እገዳ እንዲጣልባቸው አድርጓል። በሩሲያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሚኻይል ሚሹስቲን በተፈረመው በዚህ ትዕዛዝ ላይ እንደተጠቀሰው ከሩሲያ ወደ ውጭ አገራት የሚላኩ ምርቶችን ማቀብ "በሩሲያ ገበያ ውስጥ መረጋጋት ለመፍጠር አስፈላጊ ነው" ተብሏል። ይህ የሩሲያ የአጸፋ እርምጃ በዩክሬን ላይ ወረራ መፈጸሟን ተከትሎ ምዕራባውያን በሩሲያ የገንዘብ እና የኃይል አቅርቦት ላይ ከባድ የሚባሉ ተከታታይ ማዕቀቦችን በመጣላቸው የመጣ ነው። ከዚህ በተጨማሪም በምዕራቡ ዓለም ከፍተኛ ሀብት ካላቸው ሩሲያውያን ከበርቴዎች መካከል ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር ቅርበት አላቸው በተባሉት ላይም ንብረታቸውን እንዳያንቀሳቅሱና ጉዞ እንዳያደርጉ ዕቀባ ተጥሎባቸዋል። ሩሲያ ወደ ውጭ እንዳይላኩ ካገደቻቸው ምርቶቿ መካከል መኪኖች፣ የባቡር ፉርጎዎች፣ የእቃ ማጓጓዣ ኮንቴይነሮች እና የኃይል ማመንጫ ተርባይኖች እንደሚገኙበት ታውቋል። በቅርብ የወጡ መረጃዎች እንደሚያመልክቱት ዩናይትድ ኪንግደም ከሩሲያ ጋር ከፍተኛ የንግድ ልውውጥ ከሚያደርጉ አገራት መካከል ስትሆን በዚህም በሁለቱ አገራት መካከል በአጠቃላይ 15.9 ቢሊዮን ፓወንድ የሚያወጣ የንግድ ልውውጥ ይካሄዳል። ሩሲያ ለአውሮፓ አገራት ነዳጅ እና ጋር በማቅረብ ከፍተኛ ድርሻ ያላት ሲሆን፣ ከጦርነቱ በኋላ አገራት እነዚህን ምርቶች መግዛታቸውን ለማቆም ውይይት እያደረጉ ነው። አሜሪካ ከሩሲያ ትገዛ የነበረው የነዳጅ እና የጋዝ አቅርቦት እንዲቋረጥ በዚህ ሳምንት ወስናለች። ሩሲያ በዩክሬን ላይ በከፈተችው ወረራ ሳቢያ ምዕራባውያን በአገሪቱ ላይ ከባድ ምጣኔ ሀብታዊ እቀባን እየጣሉ ሲሆን፣ ግዙፎቹ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎቻቸውም ሥራቸውን እያቋረጡ ከሩሲያ እየወጡ ነው። በዚህም ምክንያት ሩሲያ በአጸፋው ለእነዚህ አገራት የምታቀርባቸውን ተለያዩ አይነት ምርቶችን ላለመሸጥ የወሰነችው።
https://www.bbc.com/amharic/news-60696158
5sports
ኢትዮጵያውያን ሴት አትሌቶች ደምቀው የታዩበት ምስጢር ምን ይሆን?
እርግጥ ነው በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ቀድሞ ኢትዮጵያን የወከለው አትሌት ከበደ ባልቻ ነው። ከበደ የፊንላንዷ ሄልሲንኪ በፈረንጆቹ 1983 ባዘጋጀችው ሻምፒዮና ለአገሩ እንዲሁም ለአፍሪካ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ አመጣ። ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያ ወደ ሜዳሊያ የተመለሰችው በኃይሌ ገብረ ሥላሴ አማካይነት ጀርመን ባዘጋጀችው የ1993 ዓለም ሻምፒዮና ነበር። ነገር ግን በ1995 ላይ አዲስ ታሪክ ተፃፈ። አትሌት ደራርቱ ቱሉ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን የወከለች የመጀመሪያዋ ሴት አትሌት ሆና ወደ ስዊዲን አቀናች። ደራርቱ በ10 ሺህ ሜትር ውድድር ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ይዛ ተመለሰች። ደራርቱ የከፈተችውን መንገድ ተከትለው ጌጤ ዋሚ ወርቅ፣ ቁጥሬ ዱለቻ እና አየለች ወርቁ በ1999 ስፔን ሲቪያ ላይ በተደረገው ውድድር የነሐስ ሜዳሊያ ይዘው ተመለሱ። ወደ ካናዳ እናቅና። ኤድመንተን 8ኛውን የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና አሰናዳች። ደራርቱ ቱሉ ወርቅ፣ ብርሃኔ አደሬ ብር፣ ጌጤ ዋሚ እና አየለች ወርቁ ደግሞ ነሐስ ሰበሰቡ። በአውሮፓውያን አቆጣጠር 2003 ዓ.ም. በፈረንሳይ ፓሪስ በተዘጋጀው ዘጠነኛው ሻምፒዮና፣ የ18 ዓመቷ ጥሩነሽ ዲባባ በ5 ሺህ ሜትር ታዋቂዎቹን ስፔናዊቷ ማርታ ዶሚንጌዝን፣ ብርሃኔ አደሬን እንዲሁም ኬንያዊቷ አዲት ማሳይን በአስደናቂ ብቃት በመቅደም ወርቅ አጠለቀች። ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር ከዓለም አራተኛ ሆና አጠናቀቀች። 2005 በፊንላንድ ሄልሲንኪ የተካሄደው ሻምፒዮና ግን ልዩ ነበር። በ5 ሺህ እና በ10 ሺህ ውድድሮች ሴት አትሌቶች ከአንድ እስከ ሦስት ተከታትለው በመግባት “አረንጓዴው ጎርፍን” ለዓለም አስተዋወቁ። ጥሩነሽ ዲባባ በሁለቱም ርቀቶች ወርቅ ደራርባ በማጥለቅ ኢትዮጵያ አሜሪካና ሩሲያን ተከትላ ከዓለም ሦስተኛ እንድትሆን አደረገች። ሴት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ያስመገቡት ድል ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም። ሶፊያ አሰፋ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ ያመጣች አትሌት ናት። ሴቶች አትሌቶቻችን በቻምፒዮናው መድረክ በ5 ሺህ እና በ10 ሺህ ሜትር ከአንድ እስከ ሦስት ተከታትለው በመግባት የሚደርሳቸው የለም። ጥሩነሽ ዲባባ በዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና 5 ጊዜ ወርቅ በማምጣት የአገሯን ሰንድቅ ዓላማ ከፍ ማድረግ ችላለች። ዘንድሮ በአሜሪካዋ ኦሪገን ግዛት በተካሄደው ውድድርም ሴት አትሌቶች ደምቀው ታይተዋል። ኢትዮጵያ ካገኘቻቸው አራት የወርቅ ሜዳሊያዎች ሦስቱ የተገኙት በሴት አትሌቶች ነው። ለመሆኑ ሴት አትሌቶች በዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ከጊዜ ጊዜ እየደመቁ የሄዱበት ምስጢር ምን ይሆን? “ዘንድሮ ያስመዘግበነው ውጤት ያስፈልገን ነበር” ትላለች የስፖርት ጋዜጠኛዋ ሃና ገብረሥላሴ። “ሕዝቡ ለአትሌቶቹ ያደረገውን አቀባበል ስንመለከት፣ የተገኘው ውጤት ትርጉሙ ምን ያህል እንደሆነ የሚያሳይ ነው።” ከአትሌቶች ምርጫና ከዝግጅት ጋር በተያያዘ እንደሌላው ጊዜ ባይሆንም የተወሰነ ስጋት እንደነበረ የምታወሳው ሃና፣ ሌሎች አገራት ካደረጉት ዝግጅት አንፃር ሲታይ ከተጠበቀው በላይ የሆነ ውጤት መጥቷል ትላለች። ጋዜጠኛዋ አክላ ከዚህ በፊት ከነበሩት የቅርብ ጊዜ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናዎች ጋር ሲነፃፀር የዘንድሮው ውጤት ልዩ ነው የሚል ምልከታ አላት። “ሄልሲንኪና ፓሪስ ጥሩ ውጤት ያመጣንባቸው መድረኮች ናቸው። ከቅርብ ጊዜ ትዝታችን ዴጉ ነው አነስ ያለ ውጤት ያመጣንበት። ከዚህ አንፃር የዘንድሮው ውጤት በልዩነት የሚታይ ነው።” ኢትዮጵያ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና እስከ ዛሬ 33 የወርቅ ሜዳሊያዎችን ጨምሮ በጠቅላላው 95 ሜዳሊያዎችን መሰብሰብ ችላለች። በዚህ ውጤት መሠረት ኢትዮጵያ ከዓለም ስድስተኛ፤ ከአፍሪካ ደግሞ ከኬንያ በመቀጠል ሁለተኛ ናት። የዘንድውን የኦሪገን ውጤትን ጨምሮ ሴት አትሌቶች 47 ሜዳሊያ አስገኝተዋል። ወንድ አትሌቶች ደግሞ 48። ሃና “የዚህ ምስጢሩ ፅናት ነው” ትላለች። አትሌቲክስ ፅናት የጠይቃል የምትለው ሃና “ለሴቶች አዳላሽ እንዳልባል እንጂ፣ ሴት አትሌቶቻችን የሚያሳይት ዓይነት ወጥ አቋም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በወንዶች ላይ አታይም። “አትሌቲክስ በጣም ተግቶ የመዘጋጀት፤ በተደጋጋሚ የሚመጡ የውድድሮችን ተጠቅሞ ብቃትን ማሳየት ይጠይቃል።” ሃና፤ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ብቻ ሳይሆን ባለፉት ጥቂት የኦሊምፒክ ውድድሮች ሴት አትሌቶቻችን ደምቀው እንደታዩ ታወሳለች። “በሁለቱም መድረኮች ሴት አትሌቶቻችን በብዛትም፣ በተፎካካሪነትም የበለጠውን ድርሻ ሲወስዱ እየተመለከትን ነው።” ቢሆንም በትክክል ይሄ ነው ምክንያቱ ለማለት ጥናት ማድረግ እንደሚገባ ሃና ትናገራለች። “ሴት አትሌቶች ምክር ይሰማሉ። ታዛዥ ናቸው። የሚሰጣቸውን ሥልጠና በትክክል ይተገብራሉ የሚባሉ ሐሳቦች ሲነገሩ እሰማለሁ” ስትል የስኬታቸውን ምስጢር ታስቀምጣለች። የአገሯን ስም በተለያዩ መድረኮች ያስጠራችው ደራርቱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆና ከተመረጠች በኋላ ለውጥ ማምጣት ችላለች የሚል አስተያየት በተደጋጋሚ ይሰማል። ነገር ግን ለደራርቱ ሁኔታዎች ሁሉ የተመቻቹ ነበሩ ማለት ከባድ ነው። ደራርቱ ፌዴሬሽኑን መምራት ከጀመረች ወዲህ ሁለት ጊዜ በዓለም ሻምፒዮና፤ አንድ ጊዜ በኦሊምፒክ መድረክ፤ አንድ ጊዜ ደግሞ በዓለም የቤት ውስጥ ውድድር ተሳትፋለች። በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ በተሰናደው የ2019 የዓለም ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ሁለት ወርቅ፣ አምስት ብርና አንድ ነሐስ ይዛ ተመልሳለች። በዚህ ውድድር የኢትዮጵያ አትሌቶች በሚታወቁበት የመካከለኛና ረዥም ርቀት ውድድር የተለመደውን ወርቅ ማስመዝገብ ባይችሉም ተስፋ ያላቸው አትሌቶች ታይተዋል። ኢትዮጵያ በመድረኩ በስምንት ሜዳሊያ አምስተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች። ከዚህ በኋላ በደራርቱ የተመራው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ታላቅ ወደ ሚባለው የኦሊምፒክ መድረክ ነው ያቀናው። በ2022 ቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ ያገኘችው ሜዳሊያ ብዛት አራት ነበር። ይህ ውጤት ኢትዮጵያ በኦሊምፒክ መድረክ ካመጣቻቸው ዝቅተኛ ከተባሉት የሚመደብ ነው። ቀጥሎ ኢትዮጵያ የተሳተፈችበት ዓለም አቀፍ መድረክ ባለፈው መጋቢት የተካሄደው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ፍልሚያ ነው። ይህ መድረክ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ደምቀው የታዩበት ነበር። ኢትዮጵያ፤ በአራት ወርቅ፣ በሦስት ብርና በሁለት የነሐስ አሜሪካንን አስከትላ ከዓለም ቁንጮ ሆና አጠናቃለች። በደራርቱ አመራር ወደ ኦሪገን የተጓዘው የአትሌቲክስ ቡድን አራት ወርቅ፣ አራት ብርና ሁለት ነሐስ በመሰብሰብ ከዓለም ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል። ሃና፤ ደራርቱ ቱሉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየመጣ ላለው ውጤት ብቸኛዋ ምክንያት ባትሆንም ትልቅ ሥፍራ እንዳላት ትናገራለች። “በውድድር ዝግጅት ወቅት እየመጣች የምታበረታታ ናት። ከልጅነትህ ጀምሮ የምታደንቃትን ሴት በቅርበት ማግኘት በራሱ ትልቅ ሚና አለው። እንደሷ ጀግና የመሆን ፍላጎት እንዲያድር፤ እንደሷ ከተወዳዳሪነት አልፎ ወደፊት ለሌሎች ምሳሌ የመሆን ምኞት እንዲያድር ያደርጋል። “እንኳን ለአትሌቶች ቀርቶ ለእኛ ራሱ፤ ደራርቱን ማግኘት የሚሰጠው መነቃቃት የተለየ ነው።” ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደሚታየው የዘንድሮውም የአትሌቲክስ ሻምፒዮና አገር ውስጥ ያለው የፖለቲካ ሁኔታ የተንፀባረቀበት ነው። ጉዳፍ ፀጋይ የ5 ሺህ ሜትር ውድድርን ባሸነፈችበት ወቅት አንድ ተመልካች የትግራይ ክልል ባንዲራን ይዞ ወደ መሮጫ ትራክ ሲገባ በቀጥታ ቴሌቪዥን ሥርጭት ታይቷል። ከዚህ በፊትም አትሌቶች ፖለቲካዊ መልዕክት ያዘለ ምልክት በሩጫ መደረኮች ላይ ማሳየታቸው የሚዘነጋ አይደለም። ከአራት የወርቅ ሜዳሊያዎች ሦስቱን ያስገኙት ሴት አትሌቶች ከትግራይ ክልል የመጡ ናቸው። አሁን ባለው የእርስ በርስ ግጭት ምክንያት አትሌቶቹ ከቤተሰቦቻቸው ጋር መገናኘት አለመቻላቸውም ይታወቃል። አትሌቶቹ ይህን ጫና ተቋቁመው ድል መንሳታቸው የሚደነቅ ነው ሲሉ በርካታ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ሃናም ይህ የሚደነቅ ነው ትላለች። “ባለው ፖለቲካ ምክንያት በቤተሰብ፣ በበማኅረሰብ ያለው ጫና፤ በተለይ መጀመሪያ አካባቢ ከአትሌቶች ጋር የጋራ ልምምድ ማድረግ እስኪከብድ ድረስ መድረሱ፤ በተመሳሳይ መጀመሪያ አካባቢ የውድድር ዕድል አለማግኘትን የመሳሰሉ ጫናዎች ተቋቁመው ነው ውጤት ያመጡት።” ሃና አትሌቶች የተሸከሙት ጫና ከምናነገርውም፤ ከምናስበውም በላይ ነው ትላለች። “ጫናው የበለጠ ጠንካራ እንዲሆኑ፤ ለፅናት እንዲቆሙ አድርጓቸዋል ብዬ አስባለሁ። ለዚያም ነው ሦስቱም አትሌቶች ላይ ስሜታዊነት የተመለክተነው። ውድድሩን እንዳገባደዱ የሚታይባቸው ስሜት ደስታና ሃዘን የተደበላለቀበት እንደሆነ ይታያል። ከቤተሰቦቻቸው የተሰሙትን አስተያየቶች ስትመለከት ደስታህን ጎዶሎ ሊያደርገው እንደሚችል እውን ነው።” አትሌቶቹ አገር ቤት ሲገቡ ሞቅ ያለ አቀባበል ጠብቋቸዋል። ሐሙስ ዕለት በቤተ-መንግሥት በተካሄደው የዕውቅና እና ሽልማት መርሃ ግብር ላይ የተገኙት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተለይ ደግሞ ሴት አትሌቶች ያመጡትን ውጤት በማድነቅ ምስጋናቸውን ገልጠዋል። ፕሬዝዳንቷ “ለተጨነቀው፣ ላዘነው፣ ለተከዘው፣ ኑሮ ለከበደው፣ እንደ አገር የት ነን ለሚለው ፈገግታን ያስገኘ ነው። . . . እኔ ላሸነፍ፣ እኔ ልቀደም ብቻ ሳይሆን በመተባበር በቡድን በመስራት ለሌሎች በር የከፈቱ አይተናል፤ ለተሰንበት የሰጠሽን ትልቅ ትምህርት ነው” ብለዋል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን አትሌት ደራርቱ ቱሉ በበኩሏ በትግራይ ያለው ሁኔታ ከክልሉ የመጡ አትሌቶች ቤተሰቦቻቸው ማግኘት አስቸጋሪ እንዳደረገው ተናግራለች። “በትግራይ አትሌቶች አሉን፤ አልመጡም። ስለዚህ ባሉበት ልምምድ እንዲጀምሩ፤ አስፈላጊ አትሌቶች ደግሞ እዚህ እንዲመጡ መንግሥትም ለእነዚህ አትሌቶች መንገድ ከፍቶ ቤተሰቦቻቸው እንዲያገኙ ትብብር እንዲያደርግልን እጠይቃለሁ” ብላለች። ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች ማራቶን ድል የቀናት በማሬ ዲባባ አማካይነት በ2015 የቤይጂንግ ውድድር ላይ ነበር። በዘንድሮው ሻምፒዮና የርቀቱን ክብረ ወሰንን በመስበር ወርቅ ያጠለቀችው አትሌት ጎተይቶም ገብረሥላሴ ከውድድሩ በኋላ በተደበላለቀ ስሜት ውስጥ ሆና ታይታ ነበር። “የቤሰተብ ናፍቆት እንጂ ሌላ የደረሰብኝ ጫና የለም። ምግብ ስበላ ቤተሰቦቼ ትዝ ይሉኛል። ይሄ ተፅዕኖ ይፈጥራል። ሰው ሲደሰት አይቻለሁ። ቤተሰቦቻችን ያሉበት ቦታ ብንሄድ ደግሞ የእኛም ደስታ ሙሉ ይሆን ነበር። የእግር እንጂ የአዕምሮ እረፍት አልነበረንም” ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች። ጎተይቶም ከመንግሥት ዕውቅና እና ሽልማት ከተበረከተላት በኋላ ለቢቢሲ በሰጠችው አስተያየት፤ “ሁሉም አሸንፋለሁ ብሎ እንደሚገባው እኔም አሸንፋለሁ በሚል ተስፋ ነው የገባሁት” ብላለች። “ከተፎካካሪዬ ጋር ስንሄድበት የነበረው ፍጥነት የአስር ሺህ እንጂ የማራቶን አይመስልም ነበር፤ ይህም ውድድሩን ፈታኝ አድርጎታል።” “ከውጤት አንፃር አብዛኛው በሴቶች የመጣ መሆኑን ሳይ ደስተኛ አድርጎኛል፤ ግን ወንዶቹም ጠንክረው ሠርተዋል። ማራቶን ላይ ወንዶች ማሸነፋቸው ደግሞ እኛም እንድናሸንፍ ሞራል ሆኖናል።”
ኢትዮጵያውያን ሴት አትሌቶች ደምቀው የታዩበት ምስጢር ምን ይሆን? እርግጥ ነው በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ቀድሞ ኢትዮጵያን የወከለው አትሌት ከበደ ባልቻ ነው። ከበደ የፊንላንዷ ሄልሲንኪ በፈረንጆቹ 1983 ባዘጋጀችው ሻምፒዮና ለአገሩ እንዲሁም ለአፍሪካ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ አመጣ። ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያ ወደ ሜዳሊያ የተመለሰችው በኃይሌ ገብረ ሥላሴ አማካይነት ጀርመን ባዘጋጀችው የ1993 ዓለም ሻምፒዮና ነበር። ነገር ግን በ1995 ላይ አዲስ ታሪክ ተፃፈ። አትሌት ደራርቱ ቱሉ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን የወከለች የመጀመሪያዋ ሴት አትሌት ሆና ወደ ስዊዲን አቀናች። ደራርቱ በ10 ሺህ ሜትር ውድድር ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ይዛ ተመለሰች። ደራርቱ የከፈተችውን መንገድ ተከትለው ጌጤ ዋሚ ወርቅ፣ ቁጥሬ ዱለቻ እና አየለች ወርቁ በ1999 ስፔን ሲቪያ ላይ በተደረገው ውድድር የነሐስ ሜዳሊያ ይዘው ተመለሱ። ወደ ካናዳ እናቅና። ኤድመንተን 8ኛውን የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና አሰናዳች። ደራርቱ ቱሉ ወርቅ፣ ብርሃኔ አደሬ ብር፣ ጌጤ ዋሚ እና አየለች ወርቁ ደግሞ ነሐስ ሰበሰቡ። በአውሮፓውያን አቆጣጠር 2003 ዓ.ም. በፈረንሳይ ፓሪስ በተዘጋጀው ዘጠነኛው ሻምፒዮና፣ የ18 ዓመቷ ጥሩነሽ ዲባባ በ5 ሺህ ሜትር ታዋቂዎቹን ስፔናዊቷ ማርታ ዶሚንጌዝን፣ ብርሃኔ አደሬን እንዲሁም ኬንያዊቷ አዲት ማሳይን በአስደናቂ ብቃት በመቅደም ወርቅ አጠለቀች። ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር ከዓለም አራተኛ ሆና አጠናቀቀች። 2005 በፊንላንድ ሄልሲንኪ የተካሄደው ሻምፒዮና ግን ልዩ ነበር። በ5 ሺህ እና በ10 ሺህ ውድድሮች ሴት አትሌቶች ከአንድ እስከ ሦስት ተከታትለው በመግባት “አረንጓዴው ጎርፍን” ለዓለም አስተዋወቁ። ጥሩነሽ ዲባባ በሁለቱም ርቀቶች ወርቅ ደራርባ በማጥለቅ ኢትዮጵያ አሜሪካና ሩሲያን ተከትላ ከዓለም ሦስተኛ እንድትሆን አደረገች። ሴት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ያስመገቡት ድል ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም። ሶፊያ አሰፋ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ ያመጣች አትሌት ናት። ሴቶች አትሌቶቻችን በቻምፒዮናው መድረክ በ5 ሺህ እና በ10 ሺህ ሜትር ከአንድ እስከ ሦስት ተከታትለው በመግባት የሚደርሳቸው የለም። ጥሩነሽ ዲባባ በዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና 5 ጊዜ ወርቅ በማምጣት የአገሯን ሰንድቅ ዓላማ ከፍ ማድረግ ችላለች። ዘንድሮ በአሜሪካዋ ኦሪገን ግዛት በተካሄደው ውድድርም ሴት አትሌቶች ደምቀው ታይተዋል። ኢትዮጵያ ካገኘቻቸው አራት የወርቅ ሜዳሊያዎች ሦስቱ የተገኙት በሴት አትሌቶች ነው። ለመሆኑ ሴት አትሌቶች በዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ከጊዜ ጊዜ እየደመቁ የሄዱበት ምስጢር ምን ይሆን? “ዘንድሮ ያስመዘግበነው ውጤት ያስፈልገን ነበር” ትላለች የስፖርት ጋዜጠኛዋ ሃና ገብረሥላሴ። “ሕዝቡ ለአትሌቶቹ ያደረገውን አቀባበል ስንመለከት፣ የተገኘው ውጤት ትርጉሙ ምን ያህል እንደሆነ የሚያሳይ ነው።” ከአትሌቶች ምርጫና ከዝግጅት ጋር በተያያዘ እንደሌላው ጊዜ ባይሆንም የተወሰነ ስጋት እንደነበረ የምታወሳው ሃና፣ ሌሎች አገራት ካደረጉት ዝግጅት አንፃር ሲታይ ከተጠበቀው በላይ የሆነ ውጤት መጥቷል ትላለች። ጋዜጠኛዋ አክላ ከዚህ በፊት ከነበሩት የቅርብ ጊዜ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናዎች ጋር ሲነፃፀር የዘንድሮው ውጤት ልዩ ነው የሚል ምልከታ አላት። “ሄልሲንኪና ፓሪስ ጥሩ ውጤት ያመጣንባቸው መድረኮች ናቸው። ከቅርብ ጊዜ ትዝታችን ዴጉ ነው አነስ ያለ ውጤት ያመጣንበት። ከዚህ አንፃር የዘንድሮው ውጤት በልዩነት የሚታይ ነው።” ኢትዮጵያ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና እስከ ዛሬ 33 የወርቅ ሜዳሊያዎችን ጨምሮ በጠቅላላው 95 ሜዳሊያዎችን መሰብሰብ ችላለች። በዚህ ውጤት መሠረት ኢትዮጵያ ከዓለም ስድስተኛ፤ ከአፍሪካ ደግሞ ከኬንያ በመቀጠል ሁለተኛ ናት። የዘንድውን የኦሪገን ውጤትን ጨምሮ ሴት አትሌቶች 47 ሜዳሊያ አስገኝተዋል። ወንድ አትሌቶች ደግሞ 48። ሃና “የዚህ ምስጢሩ ፅናት ነው” ትላለች። አትሌቲክስ ፅናት የጠይቃል የምትለው ሃና “ለሴቶች አዳላሽ እንዳልባል እንጂ፣ ሴት አትሌቶቻችን የሚያሳይት ዓይነት ወጥ አቋም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በወንዶች ላይ አታይም። “አትሌቲክስ በጣም ተግቶ የመዘጋጀት፤ በተደጋጋሚ የሚመጡ የውድድሮችን ተጠቅሞ ብቃትን ማሳየት ይጠይቃል።” ሃና፤ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ብቻ ሳይሆን ባለፉት ጥቂት የኦሊምፒክ ውድድሮች ሴት አትሌቶቻችን ደምቀው እንደታዩ ታወሳለች። “በሁለቱም መድረኮች ሴት አትሌቶቻችን በብዛትም፣ በተፎካካሪነትም የበለጠውን ድርሻ ሲወስዱ እየተመለከትን ነው።” ቢሆንም በትክክል ይሄ ነው ምክንያቱ ለማለት ጥናት ማድረግ እንደሚገባ ሃና ትናገራለች። “ሴት አትሌቶች ምክር ይሰማሉ። ታዛዥ ናቸው። የሚሰጣቸውን ሥልጠና በትክክል ይተገብራሉ የሚባሉ ሐሳቦች ሲነገሩ እሰማለሁ” ስትል የስኬታቸውን ምስጢር ታስቀምጣለች። የአገሯን ስም በተለያዩ መድረኮች ያስጠራችው ደራርቱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆና ከተመረጠች በኋላ ለውጥ ማምጣት ችላለች የሚል አስተያየት በተደጋጋሚ ይሰማል። ነገር ግን ለደራርቱ ሁኔታዎች ሁሉ የተመቻቹ ነበሩ ማለት ከባድ ነው። ደራርቱ ፌዴሬሽኑን መምራት ከጀመረች ወዲህ ሁለት ጊዜ በዓለም ሻምፒዮና፤ አንድ ጊዜ በኦሊምፒክ መድረክ፤ አንድ ጊዜ ደግሞ በዓለም የቤት ውስጥ ውድድር ተሳትፋለች። በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ በተሰናደው የ2019 የዓለም ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ሁለት ወርቅ፣ አምስት ብርና አንድ ነሐስ ይዛ ተመልሳለች። በዚህ ውድድር የኢትዮጵያ አትሌቶች በሚታወቁበት የመካከለኛና ረዥም ርቀት ውድድር የተለመደውን ወርቅ ማስመዝገብ ባይችሉም ተስፋ ያላቸው አትሌቶች ታይተዋል። ኢትዮጵያ በመድረኩ በስምንት ሜዳሊያ አምስተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች። ከዚህ በኋላ በደራርቱ የተመራው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ታላቅ ወደ ሚባለው የኦሊምፒክ መድረክ ነው ያቀናው። በ2022 ቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ ያገኘችው ሜዳሊያ ብዛት አራት ነበር። ይህ ውጤት ኢትዮጵያ በኦሊምፒክ መድረክ ካመጣቻቸው ዝቅተኛ ከተባሉት የሚመደብ ነው። ቀጥሎ ኢትዮጵያ የተሳተፈችበት ዓለም አቀፍ መድረክ ባለፈው መጋቢት የተካሄደው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ፍልሚያ ነው። ይህ መድረክ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ደምቀው የታዩበት ነበር። ኢትዮጵያ፤ በአራት ወርቅ፣ በሦስት ብርና በሁለት የነሐስ አሜሪካንን አስከትላ ከዓለም ቁንጮ ሆና አጠናቃለች። በደራርቱ አመራር ወደ ኦሪገን የተጓዘው የአትሌቲክስ ቡድን አራት ወርቅ፣ አራት ብርና ሁለት ነሐስ በመሰብሰብ ከዓለም ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል። ሃና፤ ደራርቱ ቱሉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየመጣ ላለው ውጤት ብቸኛዋ ምክንያት ባትሆንም ትልቅ ሥፍራ እንዳላት ትናገራለች። “በውድድር ዝግጅት ወቅት እየመጣች የምታበረታታ ናት። ከልጅነትህ ጀምሮ የምታደንቃትን ሴት በቅርበት ማግኘት በራሱ ትልቅ ሚና አለው። እንደሷ ጀግና የመሆን ፍላጎት እንዲያድር፤ እንደሷ ከተወዳዳሪነት አልፎ ወደፊት ለሌሎች ምሳሌ የመሆን ምኞት እንዲያድር ያደርጋል። “እንኳን ለአትሌቶች ቀርቶ ለእኛ ራሱ፤ ደራርቱን ማግኘት የሚሰጠው መነቃቃት የተለየ ነው።” ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደሚታየው የዘንድሮውም የአትሌቲክስ ሻምፒዮና አገር ውስጥ ያለው የፖለቲካ ሁኔታ የተንፀባረቀበት ነው። ጉዳፍ ፀጋይ የ5 ሺህ ሜትር ውድድርን ባሸነፈችበት ወቅት አንድ ተመልካች የትግራይ ክልል ባንዲራን ይዞ ወደ መሮጫ ትራክ ሲገባ በቀጥታ ቴሌቪዥን ሥርጭት ታይቷል። ከዚህ በፊትም አትሌቶች ፖለቲካዊ መልዕክት ያዘለ ምልክት በሩጫ መደረኮች ላይ ማሳየታቸው የሚዘነጋ አይደለም። ከአራት የወርቅ ሜዳሊያዎች ሦስቱን ያስገኙት ሴት አትሌቶች ከትግራይ ክልል የመጡ ናቸው። አሁን ባለው የእርስ በርስ ግጭት ምክንያት አትሌቶቹ ከቤተሰቦቻቸው ጋር መገናኘት አለመቻላቸውም ይታወቃል። አትሌቶቹ ይህን ጫና ተቋቁመው ድል መንሳታቸው የሚደነቅ ነው ሲሉ በርካታ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ሃናም ይህ የሚደነቅ ነው ትላለች። “ባለው ፖለቲካ ምክንያት በቤተሰብ፣ በበማኅረሰብ ያለው ጫና፤ በተለይ መጀመሪያ አካባቢ ከአትሌቶች ጋር የጋራ ልምምድ ማድረግ እስኪከብድ ድረስ መድረሱ፤ በተመሳሳይ መጀመሪያ አካባቢ የውድድር ዕድል አለማግኘትን የመሳሰሉ ጫናዎች ተቋቁመው ነው ውጤት ያመጡት።” ሃና አትሌቶች የተሸከሙት ጫና ከምናነገርውም፤ ከምናስበውም በላይ ነው ትላለች። “ጫናው የበለጠ ጠንካራ እንዲሆኑ፤ ለፅናት እንዲቆሙ አድርጓቸዋል ብዬ አስባለሁ። ለዚያም ነው ሦስቱም አትሌቶች ላይ ስሜታዊነት የተመለክተነው። ውድድሩን እንዳገባደዱ የሚታይባቸው ስሜት ደስታና ሃዘን የተደበላለቀበት እንደሆነ ይታያል። ከቤተሰቦቻቸው የተሰሙትን አስተያየቶች ስትመለከት ደስታህን ጎዶሎ ሊያደርገው እንደሚችል እውን ነው።” አትሌቶቹ አገር ቤት ሲገቡ ሞቅ ያለ አቀባበል ጠብቋቸዋል። ሐሙስ ዕለት በቤተ-መንግሥት በተካሄደው የዕውቅና እና ሽልማት መርሃ ግብር ላይ የተገኙት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተለይ ደግሞ ሴት አትሌቶች ያመጡትን ውጤት በማድነቅ ምስጋናቸውን ገልጠዋል። ፕሬዝዳንቷ “ለተጨነቀው፣ ላዘነው፣ ለተከዘው፣ ኑሮ ለከበደው፣ እንደ አገር የት ነን ለሚለው ፈገግታን ያስገኘ ነው። . . . እኔ ላሸነፍ፣ እኔ ልቀደም ብቻ ሳይሆን በመተባበር በቡድን በመስራት ለሌሎች በር የከፈቱ አይተናል፤ ለተሰንበት የሰጠሽን ትልቅ ትምህርት ነው” ብለዋል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን አትሌት ደራርቱ ቱሉ በበኩሏ በትግራይ ያለው ሁኔታ ከክልሉ የመጡ አትሌቶች ቤተሰቦቻቸው ማግኘት አስቸጋሪ እንዳደረገው ተናግራለች። “በትግራይ አትሌቶች አሉን፤ አልመጡም። ስለዚህ ባሉበት ልምምድ እንዲጀምሩ፤ አስፈላጊ አትሌቶች ደግሞ እዚህ እንዲመጡ መንግሥትም ለእነዚህ አትሌቶች መንገድ ከፍቶ ቤተሰቦቻቸው እንዲያገኙ ትብብር እንዲያደርግልን እጠይቃለሁ” ብላለች። ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች ማራቶን ድል የቀናት በማሬ ዲባባ አማካይነት በ2015 የቤይጂንግ ውድድር ላይ ነበር። በዘንድሮው ሻምፒዮና የርቀቱን ክብረ ወሰንን በመስበር ወርቅ ያጠለቀችው አትሌት ጎተይቶም ገብረሥላሴ ከውድድሩ በኋላ በተደበላለቀ ስሜት ውስጥ ሆና ታይታ ነበር። “የቤሰተብ ናፍቆት እንጂ ሌላ የደረሰብኝ ጫና የለም። ምግብ ስበላ ቤተሰቦቼ ትዝ ይሉኛል። ይሄ ተፅዕኖ ይፈጥራል። ሰው ሲደሰት አይቻለሁ። ቤተሰቦቻችን ያሉበት ቦታ ብንሄድ ደግሞ የእኛም ደስታ ሙሉ ይሆን ነበር። የእግር እንጂ የአዕምሮ እረፍት አልነበረንም” ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች። ጎተይቶም ከመንግሥት ዕውቅና እና ሽልማት ከተበረከተላት በኋላ ለቢቢሲ በሰጠችው አስተያየት፤ “ሁሉም አሸንፋለሁ ብሎ እንደሚገባው እኔም አሸንፋለሁ በሚል ተስፋ ነው የገባሁት” ብላለች። “ከተፎካካሪዬ ጋር ስንሄድበት የነበረው ፍጥነት የአስር ሺህ እንጂ የማራቶን አይመስልም ነበር፤ ይህም ውድድሩን ፈታኝ አድርጎታል።” “ከውጤት አንፃር አብዛኛው በሴቶች የመጣ መሆኑን ሳይ ደስተኛ አድርጎኛል፤ ግን ወንዶቹም ጠንክረው ሠርተዋል። ማራቶን ላይ ወንዶች ማሸነፋቸው ደግሞ እኛም እንድናሸንፍ ሞራል ሆኖናል።”
https://www.bbc.com/amharic/articles/cjj4v9vp8pzo
0business
ታንዛኒያ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ ተመደበች
ታንዛኒያ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ዝርዝር ውስጥ መግባቷ ተገለፀ ። ይህ የሆነው የዓለም ባንክ የዓለም አገራትን ምጣኔ ሐብት ከተመለከተ በኋላ ነው። ምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ታንዛኒያ ከዚህ ዝርዝር ውስጥ የገባችው፤ በአገሪቷ ያለው የአንድ ሰው ዓመታዊ አማካይ የነፍስ ወከፍ ገቢ በ1006 እና 3955 ዶላር መካከል በመሆኑ ነው። የአንድ ሰው ዓመታዊ አማካይ ነፍስ ወከፍ ገቢ አገሪቷ የምታገኘው ዓመታዊ ገቢ የዶላር ዋጋ ለሕዝብ ብዛቷ በማካፈል የሚገኝ ስሌት ነው። ባለፈው ዓመት የታንዛኒያ ኢኮኖሚ በ6.8 በመቶ ያደገ ሲሆን፤ ከሁለት ዓመታት በፊትም 7 በመቶ እድገት አሳይቶ ነበር። ይህም በዓለማችን ፈጣኑ የኢኮኖሚ እድገት ከሚባሉት ውስጥ የሚመደብ ነው። እንደ አጥኚዎቹ ከሆነ ይህ የምጣኔ ሐብት እድገት ለአስር ዓመታት የቀጠለ ሲሆን ፕሬዚደንት ጆን ማጉፉሊም ሥልጣን ላይ ከወጡ በኋላም እንደቀጠ ይገኛል። አገሪቷ በቀጠናው ከፍተኛ ምጣኔ ሐብት ያላት ሁለተኛዋ አገር ሆናለች። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወደ አፍሪካ መዛመቱን ተከትሎ ሚያዚያ ወር ላይ የዓለም ባንክ ከሰሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገራት ከግማሽ ምዕተ ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮቪድ-19 ምክንያት የኢኮኖሚ ድቀት ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ተንብዮ ነበር። ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም የአህጉሪቱ ምጣኔ ሃብት በዚህ ዓመት ብቻ በ2.1 በመቶ የሚጎዳ ሲሆን ይህ ጉዳት እስከ 5.1 ድረስ ሊደርስ ይችላል ብሏል። የዓለም ባንክና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት አበዳሪ አገራት ለአፍሪካ እዳቸውን ለተወሰነ ጊዜ እንዲያራዝሙ እና አገራት ያላቸውን ገንዘብ ወደ ሕይወት ማዳንና ኑሮን ማሻሻል ላይ ማዋል እንዲችሉ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል። በአፍሪካ በምጣኔ ሃብታቸው ግዙፍ የሆኑት ናይጄሪያና አንጎላ በወረርሽኙ ምክንያት የነዳጅ ዋጋ መውረድ ምጣኔ ሃብታቸው ክፉኛ ከተጎዳ አገራት መካከል ይገኙበታል። ደቡብ አፍሪካም ብትሆን የማዕድን ገቢዋ አሽቆልቁሎባታል።
ታንዛኒያ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ ተመደበች ታንዛኒያ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ዝርዝር ውስጥ መግባቷ ተገለፀ ። ይህ የሆነው የዓለም ባንክ የዓለም አገራትን ምጣኔ ሐብት ከተመለከተ በኋላ ነው። ምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ታንዛኒያ ከዚህ ዝርዝር ውስጥ የገባችው፤ በአገሪቷ ያለው የአንድ ሰው ዓመታዊ አማካይ የነፍስ ወከፍ ገቢ በ1006 እና 3955 ዶላር መካከል በመሆኑ ነው። የአንድ ሰው ዓመታዊ አማካይ ነፍስ ወከፍ ገቢ አገሪቷ የምታገኘው ዓመታዊ ገቢ የዶላር ዋጋ ለሕዝብ ብዛቷ በማካፈል የሚገኝ ስሌት ነው። ባለፈው ዓመት የታንዛኒያ ኢኮኖሚ በ6.8 በመቶ ያደገ ሲሆን፤ ከሁለት ዓመታት በፊትም 7 በመቶ እድገት አሳይቶ ነበር። ይህም በዓለማችን ፈጣኑ የኢኮኖሚ እድገት ከሚባሉት ውስጥ የሚመደብ ነው። እንደ አጥኚዎቹ ከሆነ ይህ የምጣኔ ሐብት እድገት ለአስር ዓመታት የቀጠለ ሲሆን ፕሬዚደንት ጆን ማጉፉሊም ሥልጣን ላይ ከወጡ በኋላም እንደቀጠ ይገኛል። አገሪቷ በቀጠናው ከፍተኛ ምጣኔ ሐብት ያላት ሁለተኛዋ አገር ሆናለች። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወደ አፍሪካ መዛመቱን ተከትሎ ሚያዚያ ወር ላይ የዓለም ባንክ ከሰሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገራት ከግማሽ ምዕተ ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮቪድ-19 ምክንያት የኢኮኖሚ ድቀት ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ተንብዮ ነበር። ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም የአህጉሪቱ ምጣኔ ሃብት በዚህ ዓመት ብቻ በ2.1 በመቶ የሚጎዳ ሲሆን ይህ ጉዳት እስከ 5.1 ድረስ ሊደርስ ይችላል ብሏል። የዓለም ባንክና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት አበዳሪ አገራት ለአፍሪካ እዳቸውን ለተወሰነ ጊዜ እንዲያራዝሙ እና አገራት ያላቸውን ገንዘብ ወደ ሕይወት ማዳንና ኑሮን ማሻሻል ላይ ማዋል እንዲችሉ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል። በአፍሪካ በምጣኔ ሃብታቸው ግዙፍ የሆኑት ናይጄሪያና አንጎላ በወረርሽኙ ምክንያት የነዳጅ ዋጋ መውረድ ምጣኔ ሃብታቸው ክፉኛ ከተጎዳ አገራት መካከል ይገኙበታል። ደቡብ አፍሪካም ብትሆን የማዕድን ገቢዋ አሽቆልቁሎባታል።
https://www.bbc.com/amharic/news-53282427
2health
ኮሮናቫይረስ፡ የደልሂ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተከሰተውን የኦክስጂን እጥረት 'አሳፋሪ' ሲል ተቸ
በሕንድ ደልሂ የሚገኘው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማዕከላዊው መንግሥት በከተማው ያለውን የኦክስጂን እጥረት የያዘበትን መንገድ በይፋ ተችቷል፡፡ አገሪቱ ረቡዕ 2 ሺህ 23 ሰዎች መሞታቸውን በኮቪድ ምክንያት ሪፖርት ሲሆን ይህም በቀን የተመዘገበው ከፍተኛው ቁጥር ሆኗል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ከ 200 በላይ የሚሆኑት የኦክስጂን እጥረት በገጠማቸው በደልሂ ሆስፒታሎች የተመዘገቡ ናቸው፡፡ ፍርድ ቤቱ በስድስት የግል ሆስፒታሎች ባለቤቶች የቀረበለትን አቤቱታ እየሰማ ይገኛል። መንግስት የኦክስጂን አቅርቦት ከፋብሪካዎች ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ወደ ሆስፒታሎች እንዲደርስ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡ "ይህ አሳፋሪ ነው። መንግሥት በመላ ህንድ የኦክስጂን አቅርቦትን አስመልክቶ ምን እየሰራ እንደሆነ ማወቅ እንፈልጋለን። የኦክስጂን አቅርቦቶችን ለማረጋገጥ መለመን፣ መበደር ... መስረቅ ካለበት ይህ የመንግስት ሃላፊነት ነው" ብለዋል ዳኞቹ፡፡ ቁጥራቸው ምን ያህል እንደሆነ ማወቅ ባይቻልም በመላ አገሪቱ በርካታ ሰዎች ኦክስጅን ሲጠብቁ ህይወታቸው አልፏል፡፡ የህንድ ማህበራዊ ድር አምባዎችም እንዲሁ በኦክስጂን ያስፈልገናል ጥሪ ተሞልተዋል፡፡ በዋና ዋና ከተሞች በሚገኙ እና በሞሉ ሆስፒታሎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ይሰባሰባሉ፡፡ የጤና አገልግሎቶች ችግሩን ለመቋቋም በመታገል ላይ ናቸው፡፡ ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው አንዱ የሆነው የምዕራባዊው የማሃራሽትራ ግዛት ባለሥልጣናት የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ መሆኑን ተከትሎ ከሐሙስ ምሽት ጀምሮ ተጨማሪ ገደቦችን ጥለዋል፡፡ ግዛቲቱ ቀድሞውኑም በከፊል እገዳ ስር ነበረች። ማሃራሽትራ በሕንድ የበለፀገች ግዛት ስትሆን የፋይናንስ ማዕከልዋ ሙምባይ የምትገኝበት ነው፡፡ ወረርሽኙ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶም የኮቪድ ስርጭት ማዕከል ሆናለች፡፡ በህንድ በቫይረሱ ከተያዙ ከ 15 ሚሊዮን በላይ ሰዎች መካከል ሩብ ያህሉ በግዛቲቱ የተመዘገቡ ናቸው፡፡ ማሃራሽትራ ከሌሎች ግዛቶች በበለጠ 67 ሲህ 468 በቫይረሱ የሞቱ ሰዎችን ሪፖርት አድርጋለች። በህንድ ከ 180 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ መሞታቸውን አረጋግጣለች፡፡ የሟቾች ቁጥር ቢጨምርም የሞት ምጣኔው በአንፃራዊነት ዝቅተኛ ነው፡፡ ህንድ ባለፈው ወር ጥብቅ ባልነበረው የደህንነት ፕሮቶኮሎች፣ በአዲሱ የቫይረሱ ዓይነት እና ሚሊዮኖች በተሳተፉበት የሂንዱዎች ፌስቲቫል ምክንያት ቁጥሩ በከፍተኛ ፍጥነት መጨመሩ ተገልጿል፡፡ በብሄራዊ የቫይሮሎጂ ተቋም እንዳስታወቀው በማሃራሽትራ ከተመረመሩት መካከል 61 በመቶ የሚሆኑት ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። በየደረጃው ምርጫ በሚደረግበት በምዕራብ ቤንጋል ግዛት ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲን ጨምሮ ግዙፍ የምርጫ ስብሰባዎች መካሄዳቸው አልተቋረጠም፡፡ መራጮች ሐሙስ ለ 6ኛ ዙር ምርጫ ድምጽ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ መንግስት ምርጫው እንዲካሄድ ያሳለፈውን ውሳኔውን ተከላክሏል፡፡ ብዙዎች በሀገሪቱ እየዘገየ የመጣው የክትባት እንቅስቃሴ ስርጭቱን ለመግታት ሲባል በፍጥነት መካሄድ አለበት ብለዋል፡፡ በህንድ ከ 130 ሚሊዮን በላይ ክትባቶችን ብትሰጥ የደረሳቸው የጤና ሠራተኞች፣ ተጋላጭ ሠራተኞች እና ከ 45 አመት በላይ የሆኑ እና ማንኛውም በሽታ ያለባቸው ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡ ከግንቦት 1 ጀምሮ ደግሞ ከ 18 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ለክትባቱ ብቁ ይሆናሉ፡፡ የአቅርቦት መዘግየት ሂደቱን የበለጠ ሊያዘገየው ይችላል ተብሏል።
ኮሮናቫይረስ፡ የደልሂ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተከሰተውን የኦክስጂን እጥረት 'አሳፋሪ' ሲል ተቸ በሕንድ ደልሂ የሚገኘው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማዕከላዊው መንግሥት በከተማው ያለውን የኦክስጂን እጥረት የያዘበትን መንገድ በይፋ ተችቷል፡፡ አገሪቱ ረቡዕ 2 ሺህ 23 ሰዎች መሞታቸውን በኮቪድ ምክንያት ሪፖርት ሲሆን ይህም በቀን የተመዘገበው ከፍተኛው ቁጥር ሆኗል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ከ 200 በላይ የሚሆኑት የኦክስጂን እጥረት በገጠማቸው በደልሂ ሆስፒታሎች የተመዘገቡ ናቸው፡፡ ፍርድ ቤቱ በስድስት የግል ሆስፒታሎች ባለቤቶች የቀረበለትን አቤቱታ እየሰማ ይገኛል። መንግስት የኦክስጂን አቅርቦት ከፋብሪካዎች ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ወደ ሆስፒታሎች እንዲደርስ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡ "ይህ አሳፋሪ ነው። መንግሥት በመላ ህንድ የኦክስጂን አቅርቦትን አስመልክቶ ምን እየሰራ እንደሆነ ማወቅ እንፈልጋለን። የኦክስጂን አቅርቦቶችን ለማረጋገጥ መለመን፣ መበደር ... መስረቅ ካለበት ይህ የመንግስት ሃላፊነት ነው" ብለዋል ዳኞቹ፡፡ ቁጥራቸው ምን ያህል እንደሆነ ማወቅ ባይቻልም በመላ አገሪቱ በርካታ ሰዎች ኦክስጅን ሲጠብቁ ህይወታቸው አልፏል፡፡ የህንድ ማህበራዊ ድር አምባዎችም እንዲሁ በኦክስጂን ያስፈልገናል ጥሪ ተሞልተዋል፡፡ በዋና ዋና ከተሞች በሚገኙ እና በሞሉ ሆስፒታሎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ይሰባሰባሉ፡፡ የጤና አገልግሎቶች ችግሩን ለመቋቋም በመታገል ላይ ናቸው፡፡ ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው አንዱ የሆነው የምዕራባዊው የማሃራሽትራ ግዛት ባለሥልጣናት የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ መሆኑን ተከትሎ ከሐሙስ ምሽት ጀምሮ ተጨማሪ ገደቦችን ጥለዋል፡፡ ግዛቲቱ ቀድሞውኑም በከፊል እገዳ ስር ነበረች። ማሃራሽትራ በሕንድ የበለፀገች ግዛት ስትሆን የፋይናንስ ማዕከልዋ ሙምባይ የምትገኝበት ነው፡፡ ወረርሽኙ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶም የኮቪድ ስርጭት ማዕከል ሆናለች፡፡ በህንድ በቫይረሱ ከተያዙ ከ 15 ሚሊዮን በላይ ሰዎች መካከል ሩብ ያህሉ በግዛቲቱ የተመዘገቡ ናቸው፡፡ ማሃራሽትራ ከሌሎች ግዛቶች በበለጠ 67 ሲህ 468 በቫይረሱ የሞቱ ሰዎችን ሪፖርት አድርጋለች። በህንድ ከ 180 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ መሞታቸውን አረጋግጣለች፡፡ የሟቾች ቁጥር ቢጨምርም የሞት ምጣኔው በአንፃራዊነት ዝቅተኛ ነው፡፡ ህንድ ባለፈው ወር ጥብቅ ባልነበረው የደህንነት ፕሮቶኮሎች፣ በአዲሱ የቫይረሱ ዓይነት እና ሚሊዮኖች በተሳተፉበት የሂንዱዎች ፌስቲቫል ምክንያት ቁጥሩ በከፍተኛ ፍጥነት መጨመሩ ተገልጿል፡፡ በብሄራዊ የቫይሮሎጂ ተቋም እንዳስታወቀው በማሃራሽትራ ከተመረመሩት መካከል 61 በመቶ የሚሆኑት ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። በየደረጃው ምርጫ በሚደረግበት በምዕራብ ቤንጋል ግዛት ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲን ጨምሮ ግዙፍ የምርጫ ስብሰባዎች መካሄዳቸው አልተቋረጠም፡፡ መራጮች ሐሙስ ለ 6ኛ ዙር ምርጫ ድምጽ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ መንግስት ምርጫው እንዲካሄድ ያሳለፈውን ውሳኔውን ተከላክሏል፡፡ ብዙዎች በሀገሪቱ እየዘገየ የመጣው የክትባት እንቅስቃሴ ስርጭቱን ለመግታት ሲባል በፍጥነት መካሄድ አለበት ብለዋል፡፡ በህንድ ከ 130 ሚሊዮን በላይ ክትባቶችን ብትሰጥ የደረሳቸው የጤና ሠራተኞች፣ ተጋላጭ ሠራተኞች እና ከ 45 አመት በላይ የሆኑ እና ማንኛውም በሽታ ያለባቸው ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡ ከግንቦት 1 ጀምሮ ደግሞ ከ 18 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ለክትባቱ ብቁ ይሆናሉ፡፡ የአቅርቦት መዘግየት ሂደቱን የበለጠ ሊያዘገየው ይችላል ተብሏል።
https://www.bbc.com/amharic/news-56841524
0business
የኢትዮጵያን ገበያ ያንኳኳው 'የቻይና በርበሬ' የት ገባ?
ያሳለፍነው የኅዳር ወር ክረምቱን ተሰቅሎ የሚቆየው የበርበሬ ዋጋ የሚረጋጋበት፤ አዲስ ምርት የሚገባበት እና በርካታ ኢትዮጵያዊያን ረዘም ላለ ጊዜ የሚያቆያቸውን የበርበሬ ምርት የሚሸምቱበት ነው። ወቅቱ ገበሬው፣ ሸማቹ፣ ነጋዴው እና ደላላው በጋራ የሚረባረቡበት ነው። ታዲያ አዲስ አበባ በርበሬ አብቅላ ኢትዮጵያን ባትመግብም በመላው አገሪቱ የሚመረተው ሁሉ ተሰብስቦ ወደ የክልሉ ይከፋፈልባታል። በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ የሚዘዋወርበት ተክለሐይማኖት ደግሞ ዋነኛው የበርበሬ ግብይት ማዕከል ይባላል። ታዲያ ካለፈው ሐምሌ ወር ጀምሮ በእነዚህ አከፋፋዮች ዘንድ ያልተለመደ ምርት "የቻይና በርበሬ" በሚል ስያሜ ብቅ ብሎ መስከረም አጋማሽ ላይ መጥፋቱን ነጋዴዎች ይናገራሉ። "በርበሬውን ከተክለ-ሐይማኖት ስናመጣው የታሸገበት ማዳበሪያ 'ሜድ ኢን ቻይና' [ቻይና የተሰራ] ይላል" ሲል ብርሌው አየሁ የተባለ ነጋዴ ይናገራል። መሪ አካባቢ በሚገኘው የበርበሬ ገበያ 30 ገደማ የበርበሬ ነጋዴዎች ቢገኙበትም በጥቅምት ወር አጋማሽ ለዚህ ዘገባ ሲባል "የቻይና በርበሬ ያለህ" ተብሎ ቢፈለግም አለኝ ያለ አልተገኘም። ብርሌው እንደሚለው ከሆነ ነጋዴዎቹ በርበሬውን ይሸጡ እንደነበር እንኳን እንዲታወቅባቸው አይፈልጉም፤ ደንበኛ ላለማጣት። በርግጥ ተክለሐይማኖት አካባቢ የሚገኙት ዋነኛ የበርበሬ አከፋፋዮች ለዚህ ምስክር ናቸው። ቢቢሲ ተዘዋውሮ ያነጋጋራቸው ሦስት አከፋፋዮች "ይዘነውም አይተነውም አናውቅም" ይላሉ። ነገር ግን በተቃራኒው አብዲ የተሰኘ አንድ አከፋፋይ አብዛኛው አከፋፋይ ይይዘው እንደነበር እና በኅዳር ወር አዲስ የበርበሬ ምርት በመድረሱ እና ዋጋውም በመረጋጋቱ 'የቻይና በርበሬ' ከገበያ መውጣቱን ይናገራል። ቢቢሲ ይህንን 'የቻይና በርበሬ' የተባለውን የበርበሬ ምርት ምንጭ በተመለከተ ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር መረጃ ለማግኘት በተደጋጋሚ ያደረገው ጥረት አልተሳካለትም። በአሁኑ ጊዜ የበርበሬ ዋጋ ቢያንስ እስከ መቶ ብር ድረስ ቅናሽ አሳይቷል። የሐረር በርበሬ 220 ብር በመሸጥ ዝቅተኛ ዋጋውን ይዟል። ከፍተኛ ጥራት አለው የሚባለው የማረቆ በርበሬ ደግሞ በኪሎ ቢበዛ 300 ብር ቢሸጥ ነው ሲል አብዲ ይናገራል። እስካለፈው ጥቅምት ወር መጨረሻ ድረስ ዝቅተኛው የበርበሬ ዋጋ 340 ብር ደርሶ እንደነበር ሸማቾች ይናገራሉ። በርበሬ ወይም 'ሬድ ፔፐር' በዓለም ላይ ከቲማቲም ቀጥሎ በከፍተኛ ደረጃ የሰው ልጆች የሚመገበው የምግብ ምርት ነው። በአውሮፓውያኑ 2018 በተደረገ ጥናት ቬትናማውያን በዓለም ከፍተኛው የበርበሬ ወይም 'ሬድ ፔፐር' ተጠቃሚ ተብለዋል። ቀጥሎም ሕንድ እና አሜሪካ የሚከተሉ ሲሆን ሦስቱ አገራት በዓለም ላይ በዓመት ጥቅም ላይ ከሚውለው በርበሬ ውስጥ 41 በመቶውን ያህል ይመገባሉ። ኢትዮጵያዊያን አጥብቀው የሚወዱት በርበሬ ዋጋ ለምን ይዋዥቃል? ኢትዮጵያውያን ገበሬዎች ከሚያመርቱት በርበሬ ውስጥ 92.4 በመቶ የሚሆነውን ለገበያ እንደሚያቀርቡና ይህም በአገሪቱ ውስጥ ካሉ ከፍተኛ የገበያ ሰብሎች ውስጥ እንደሚያስመድበው ከሁለት ዓመት በፊት አራት ምሁራን ባሳተሙት ጥናት ላይ ተጠቅሷል። አምራች ገበሬዎቹ ከ60 በመቶ በላይ ምርታቸውን በአካባቢያቸው ለሚገኙ ጅምላ ነጋዴዎች ይሸጣሉ ሲል በአበበ ቢራ፣ ጥጋቡ ዳኘው፣ አበበ ዳኘው እና አስማማው አለሙ የተጠናው ጥናት ያሳያል። መነሻው ከደቡብ አሜሪካ እንደሆነ የሚነገርለት በርበሬ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በደቡብ ክልሎች በከፍተኛ መጠን ይመረታል። ታዲያ ባለሞያዎቹ ባጠኑት ጥናት መሰረት ከፍተኛው የበርበሬ ምርት ተግዳሮት የግብአት እጥረት ነው። የበርበሬ ምርት ከፍተኛ የሆነ ለበሽታ ተጋላጭነት ደግሞ ሌላኛው ማነቆ ነው። በተጨማሪም በርበሬ ሲተከል፣ ሲታረም እና ደርሶ ሲሰበሰብ ከፍተኛ የሆነ የሰው ኃይል ይፈልጋል። ስለዚህም በርበሬን ለማምረት የሚያስፈልገው ከፍተኛ የሰው ኃይል በምርቱ ላይ እና በዋጋው ላይ የእራሱ ተጽእኖ እንዳለው አጥኚዎቹ አመልክተዋል። ሌላው ዋነኛ የበርበሬ ገበያ ላይ ያለው ማነቆ በግብይት ወቅት ያሉ ችግሮች ሲሆኑ፣ አጥኚዎቹ ያነጋገሯቸው አምራቾች እንደሚሉት ከመንግሥት ድጋፍ ማጣት ዋነኛው የገበያው ችግር አባባሽ ነው። በመቀጠልም በቂ የመጋዘን ስፍራ አለመኖር፣ የብድር አገልግሎት እጥረት፣ በገዢ እና በሻጭ መካከል ያለ የትክክለኛ መረጃ ክፍተት እንዲሁም ከጥራት ጋር የተያያዙ ተግዳሮቶች የበርበሬን ገበያ በመፈተን ይጠቀሳሉ። በኢትዮጵያ የኢኮኖሚስቶች ማኅበር ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት እና የመንግሥት የኢኮኖሚ አማካሪ ሆነው ያገለገሉት ተባባሪ ፕሮፌሰር ሰዒድ ኑሩ (ዶ/ር) አራት ዋና ዋና ማነቆዎች በርበሬን ጨምሮ ሌሎች ወቅትን ጠብቀው የሚመረቱ ምርቶች ላይ ለሚታዩ የዋጋ መናር ምክንያት ናቸው ይላሉ። የመጀመሪያው ምርቱን በበቂ ሁኔታ ያለማምረት ነው። አንድ ምርት በበቂ ሁኔታ በአገር ውስጥ ማምረት ካልተቻለ የቱንም አይነት እርምጃ ቢወሰድ ውጤት ማየት አይታሰብም ይላሉ ሰዒድ (ዶ/ር)። እንደ የተባበሩት አረብ ኤምሬት ያሉ በቂ የውጪ ምንዛሬ ያላቸው አገራት "ከበለገው ይግጣሉ" በማለት፣ በቂ ገንዘብ ያለው አገር በልግ ከሆነበት አገር የፈለገውን ምርት ገዝቶ ከዓመት ዓመት ሕዝቡን በተረጋጋ ገበያ ሊመግብ እንደሚችል ያብራራሉ። ሁለተኛው እንደ በርበሬ ያሉ ምርቶችን ተገቢ የሆነ የማቆያ ዘዴዎችን በመጠቀም ከዓመት ዓመት እንዲቆይ ማድረግ ሌላው እርምጃ ነው። እንደ ቲማቲም ያሉ ከበርበሬ ይልቅ በአጭር ጊዜ የሚበላሹ ምርቶችን እንኳን ከገበያ እንዳይጠፉ የሚያደርግ ዘዴ መኖሩን የሚያስታውሱት ሰዒድ (ዶ/ር) ይህንን በበርበሬ ላይ መተግበር ቀላል ነው ይላሉ። ሌላው መፍትሄ ነጋዴዎች ምርቱ በረከሰ ጊዜ እንዲያከማቹ ማስቻል ነው። "ኢትዮጵያ ውስጥ ነጋዴዎች ምርትን ያከማቻሉ የሚለው በአሉታዊ መልኩ ብቻ መወሰዱ አግባብ አይደለም" ይላሉ የኢኮኖሚ ባለሞያው። "በውጪው አገር ኢንቨርተሪ የሚባል ኢንቨስትመንት አለ። አንድ ምርት ሲረክስ ነጋዴዎች ሰብስበው የሚያቆዩበት እና ምርቱ ገንዘባቸውን ይዞ ለቆየበት እንደ ሽልማት የተወሰነ ጭማሪ አድርገው፣ ምርቱ ሲጠፋ ለገበያ የሚያቀርቡበት ሥርዓት ማለት ነው። ይህ መጥፎ ጊዜ ጠብቀው ምርት የሚያከማቹትን አያጠቃልልም። በሪል ስቴት ወይም መሰል ምርቶች ላይ እንደሚደረግ ኢንቨስትመንት ማለት ነው" ሲሉ ሰዒድ (ዶ/ር) ያብራራሉ። ሌላኛው ማነቆ እንደ በርበሬ ያሉ ምርቶች ላይ እሴት የሚጨምር ኢንዱስትሪ ቁጥር ትንሽ ከመሆኑ ጋር ይያያዛል። በርበሬ ተመጥኖ እና ተዘጋጅቶ ረጅም ጊዜ የሚቆይ ምርት እንደመሆኑ፣ ዋጋው በረከሰ ወቅት በርበሬው ቢዘጋጅ ምርቱ በማይኖርበት ጊዜ የተወሰነ ገንዘብ ጨምሮ መሸጥ ዋነኛ አማራጭ መሆን ይቻላል ሲሉም ሦስተኛውን ችግር እና መፍትሄውን ያመላክታሉ። የምርት እጥረት ባለበት ወቅት ከውጪ ማስገባቱ መፍትሄ ይሆናል? የምርቱ እጥረት ባለበት ወቅት ከውጪ ማስገባት በእርግጥም በቂ የውጪ ምንዛሬ ላለው አገር መፍትሄ ነው የሚሉት ሰዒድ (ዶ/ር)፣ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ አገሮች ግን በርካታ ችግሮችን የሚያስከትል እርምጃ ነው ይላሉ። ነገር ግን አንድ ጊዜ ወይም ሁለት ጊዜ ማስገባት በጥንቃቄ የሚወሰድ እርምጃ ከሆነ በርካታ ጥቅሞች እንዳሉት አጽንኦት ይሰጡታል። ባለሙያው ስለ ጥቅሞቹ ከማብራራታቸው በፊት እጥረትን እንደ ችግር መመልከት ማቆም እንደሚያስፈልግ እና ለአንድ አልሚ እጥረት የገበያ እድል ሆኖ መታየት እንደሚገባው ያብራራሉ። ይህም የማምረት ችግር ለሌለበት አገር በተለይም ለእጥረት መፍትሄ መስጠት ለአምራቾች የገበያ እድል ነው ይላሉ። ለዚህ ምሳሌ ሲጠቅሱ፡ "ከዓመታት በፊት የአገር ባህል ልብስ ከአውሮፓ ከሚመጡ ልብሶች በላይ ውድ መሆኑን ያዩ ቻይናውያን ወስደው በርካሽ ቴክኖሎጂ ሰርተው መልሰው አመጡት። ይህ እንግዲህ በየዕለቱ የማንለብሰው የክት ልብስ ነው። ታዲያ በየዕለቱ የምንጠቀማቸው ምርቶች እጥረት ሲፈጠር ይሄንን ለመሙላት መንቀሳቀስ ነበር የሚገባን" ሲሉ ሰዒድ (ዶ/ር) ያስረዳሉ። ኢትዮጵያ የበርበሬ እጥረትን ለመፍታት ከውጪ አገር ማስገባቷ ዘላቂ እስካልሆነ ድረስ ለጥቅም ማዋል እንደሚያግዝ ያስረዳሉ። አንዱ ቴክኖሎጂውን መቅሰም ነው። የምግብ ምርት እንደመሆኑ አመራረቱን ማየት ቢያስፈልግም አንድን ምርት አንድ ጊዜ ወይም ሁለቴ አስገብቶ ምርቱን መሞከር ችግር እንደሌለውም ይናገራሉ። ነገር ግን ኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች በግብርና ሥራ ለዘመናት የቆዩበት ሙያ ሆኖ ሳለ ልክ እንደ ኢንዱስትሪ ምርቶች የግብርና ምርት ማስገባት ግን አስመጪውን እና ሸማቹን ለስንፍና መንግሥትን ደግሞ ለከባድ የውጪ ምንዛሬ እጥረት ይዳርጋል ይላሉ። ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላቸውን እንደ ማሽኖች ያሉ ግብአቶችን ለማስገባት እንጂ አንድም ኪሎ የግብርና ምርት በቋሚነት ኢትዮጵያ ማስገባቷ አግባብ አይደለም ሲሉም ያክላሉ። "አስመጪዎች በተሻለ ጥራት በቅናሽ የተመረት የግብርና ምርት ማምጣት ከጭቃው ከአፈሩ ጋር መታገልን ያስቀርላቸዋል። ይህ አንዴ ከተለመደ ከባድ ነው። ስንፍናን ያመጣል። ሱፐር ማርኬት ውስጥ ከግብፅ የሚመጣ አራት ፍሬ ብርቱካን በ280 ብር ይሸጣል። የተገነጠለ ዶሮ፣ እንቁላል እንዲሁም ሽንኩርት ከውጪ ይገባል። የአየር ንብረታችን እጅግ የተመቸ ሆኖ ሳለ ይህ እንዴት ሆነ ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል" ይላሉ ሰኢድ ኑሩ (ዶ/ር)። እንደ መውጫ ከመስከረም አስከ ኅዳር ድረስ በግዴታ ነጋዴው ይዞ ሲሸጠው የቆየው 'የቻይና በርበሬን' በተመለከተ ነጋዴዎቹ በእርግጥም ቅሬታ ነበራቸው። በርበሬው ገና ከማዳበሪያው ሲፈታ ጀምሮ "የኬሚካል ሽታ" እንዳለው እና በርበሬውን የገዙ ደንበኞችም ደስተኛ እንዳልሆኑ ብርሌው ተናግሯል። "የቻይናው በርበሬ በ250 ሲመጣ የአገር ውስጥ በርበሬ 350 ነበር የሚሸጠው። ይሄ ከፍተኛ የዋጋ ልዩነት ነበር። የገዙኝ ደንበኞችም ሲፈጭም ዱቄቱ እንደሚያምር ነግረውኝ ነበር። ምግብ ውስጥ ሲገባ ነው ችግሩ" ሲል ብርሌው ለቢቢሲ ተናግሯል። ደንበኞቹ ቅር መሰኘታቸውን እንደነገሩት አልሸሸገም። የኢኮኖሚ ባለሞያው ሰዒድ (ዶ/ር) ከውጪ አገር እንዲህ ያሉ የግብርና ምርቶች ሲገቡ በሽታ ይዘው እንዳይመጡ ጥንቃቄ ተደርጎ መሞከር ይገባዋል ሲሉም ያስጠነቅቅቃሉ። ገበሬዎች የቅንጬ አረም የሚሉት ከፍተኛ ጉዳት ያለው አረም ብሎም በአንድ ወቅት ከሕንድ የገባ ማንጎን ተከትሎ የመጣ የሰብል በሽታን በምሳሌነት ያነሳሉ። "ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የነጋዴ ቁጥር ለቁጥጥር የማይመች ነው" የሚሉት ባለሙያው በሌላው አገር አነስተኛ ቁጥር ያለው ትልልቅ ነጋዴ ስላለ ከመንግሥት ጋር ለመደራደር ቀላል ያደርገዋል። ይህ ለአምራች ገበሬውም እንደሚሰራ ይናገራሉ። ትርፍ የሚገኘው አንድም ብዙ ምርት በአነስተኛ ዋጋ በመሸጥ ወይም አነስተኛ ምርት በከፍተኛ ዋጋ በመሸጥ እንደሆነ የሚናገሩት ባለሙያው፣ አነስተኛ ነጋዴም ሆነ ገበሬ ያለበት አገር የዋጋ መናሩ የሚገመት ነው ይላሉ። "ባደጉ አገራት መንግሥት የሚደራደረው አራት አምስት ከሚሆኑ ሱፐርማርኬቶች ጋር ነው። እኛ ጋር 20 ሺህ ሱቆችን ዘጋን የሚል ዜና እንሰማለን። ይህ የበለጠ እጥረት ይፈጥራል። አንድ አዲስ አበባ በቅርቡ የተከፈተ ሱፐር ማርኬት አለ። ከራሱ ማሳ ብርቱካን 30 ብር በኪሎ አምጥቶ ይሸጣል። ከእርሱ ሱፐርማርኬት ምርቱን የገዙ አጠገቡ ያሉ ትንንሽ ሱቆች ራሱን ብርቱካን በእጥፍ 60 ብር ይሸጣሉ" ሲሉ ሰዒድ (ዶ/ር) በትልልቅ አቅራቢዎች እና አነስተኛ ቸርቻሪዎች መካከል ያለውን ልዩነት ያስረዳሉ። እንዲሁም የኢትዮጵያ የገበያ መዋቅር ደላላ የተጫነው እና ሰዎች በምርት ሥራ ላይ ከመሳተፍ ይልቅ በመሃል በመደለል እያተረፉ መኖርን መምረጣቸው ሌላው ከፍተኛ ችግር ነው ይላሉ ሰኢድ (ዶ/ር)። ልክ እንደ አበባ ሁሉ የምግብ የሚያመርቱ ትልልቅ ኩባንያዎችን በማገዝ ወደ አገር ውስጥ በመጋበዝ ከእነሱ መማር እንደሚያስፈልግም ይናገራሉ። "በአንድ ጊዜ 100 ሻማ ማብራት አይቻልም" የሚሉት ሰኢድ "ከአንድ ሻማ መጀመር ግን ይቻላል" ይላሉ። የአበባ አምራቾች ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ከ10 ዓመት በፊት ኬንያ ውስጥ ምርጫን ተከትሎ የመጣ ቀውስን ሸሽተው ነበር። አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ የአበባ ምርት ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ ምንጭ እንደሆነ እና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአገር ውስጥ ባለሃብቶች የገቡበት ብሎም የቴክኖሎጂ ሽግግሩም በተሳካ ሁኔታ የተሳለጠበት ዘርፍ መሆኑን ያነሳሉ። ይህ በሌላው ዘርፍ መደገም አለበት እንደ ሰኢድ ኑሩ (ዶ/ር) ትንታኔ። "የመጀመሪያውም፣ ሁለተኛውም ሦስተኛውም መፍትሄ አንድ ነው። በግብርና ራሳችንን መቻል ነው" ሲሉ ዘመናዊ ግብርናን ማስፋፋት ብቸኛው መፍትሄ መሆኑን ባለሙያው ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያን ገበያ ያንኳኳው 'የቻይና በርበሬ' የት ገባ? ያሳለፍነው የኅዳር ወር ክረምቱን ተሰቅሎ የሚቆየው የበርበሬ ዋጋ የሚረጋጋበት፤ አዲስ ምርት የሚገባበት እና በርካታ ኢትዮጵያዊያን ረዘም ላለ ጊዜ የሚያቆያቸውን የበርበሬ ምርት የሚሸምቱበት ነው። ወቅቱ ገበሬው፣ ሸማቹ፣ ነጋዴው እና ደላላው በጋራ የሚረባረቡበት ነው። ታዲያ አዲስ አበባ በርበሬ አብቅላ ኢትዮጵያን ባትመግብም በመላው አገሪቱ የሚመረተው ሁሉ ተሰብስቦ ወደ የክልሉ ይከፋፈልባታል። በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ የሚዘዋወርበት ተክለሐይማኖት ደግሞ ዋነኛው የበርበሬ ግብይት ማዕከል ይባላል። ታዲያ ካለፈው ሐምሌ ወር ጀምሮ በእነዚህ አከፋፋዮች ዘንድ ያልተለመደ ምርት "የቻይና በርበሬ" በሚል ስያሜ ብቅ ብሎ መስከረም አጋማሽ ላይ መጥፋቱን ነጋዴዎች ይናገራሉ። "በርበሬውን ከተክለ-ሐይማኖት ስናመጣው የታሸገበት ማዳበሪያ 'ሜድ ኢን ቻይና' [ቻይና የተሰራ] ይላል" ሲል ብርሌው አየሁ የተባለ ነጋዴ ይናገራል። መሪ አካባቢ በሚገኘው የበርበሬ ገበያ 30 ገደማ የበርበሬ ነጋዴዎች ቢገኙበትም በጥቅምት ወር አጋማሽ ለዚህ ዘገባ ሲባል "የቻይና በርበሬ ያለህ" ተብሎ ቢፈለግም አለኝ ያለ አልተገኘም። ብርሌው እንደሚለው ከሆነ ነጋዴዎቹ በርበሬውን ይሸጡ እንደነበር እንኳን እንዲታወቅባቸው አይፈልጉም፤ ደንበኛ ላለማጣት። በርግጥ ተክለሐይማኖት አካባቢ የሚገኙት ዋነኛ የበርበሬ አከፋፋዮች ለዚህ ምስክር ናቸው። ቢቢሲ ተዘዋውሮ ያነጋጋራቸው ሦስት አከፋፋዮች "ይዘነውም አይተነውም አናውቅም" ይላሉ። ነገር ግን በተቃራኒው አብዲ የተሰኘ አንድ አከፋፋይ አብዛኛው አከፋፋይ ይይዘው እንደነበር እና በኅዳር ወር አዲስ የበርበሬ ምርት በመድረሱ እና ዋጋውም በመረጋጋቱ 'የቻይና በርበሬ' ከገበያ መውጣቱን ይናገራል። ቢቢሲ ይህንን 'የቻይና በርበሬ' የተባለውን የበርበሬ ምርት ምንጭ በተመለከተ ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር መረጃ ለማግኘት በተደጋጋሚ ያደረገው ጥረት አልተሳካለትም። በአሁኑ ጊዜ የበርበሬ ዋጋ ቢያንስ እስከ መቶ ብር ድረስ ቅናሽ አሳይቷል። የሐረር በርበሬ 220 ብር በመሸጥ ዝቅተኛ ዋጋውን ይዟል። ከፍተኛ ጥራት አለው የሚባለው የማረቆ በርበሬ ደግሞ በኪሎ ቢበዛ 300 ብር ቢሸጥ ነው ሲል አብዲ ይናገራል። እስካለፈው ጥቅምት ወር መጨረሻ ድረስ ዝቅተኛው የበርበሬ ዋጋ 340 ብር ደርሶ እንደነበር ሸማቾች ይናገራሉ። በርበሬ ወይም 'ሬድ ፔፐር' በዓለም ላይ ከቲማቲም ቀጥሎ በከፍተኛ ደረጃ የሰው ልጆች የሚመገበው የምግብ ምርት ነው። በአውሮፓውያኑ 2018 በተደረገ ጥናት ቬትናማውያን በዓለም ከፍተኛው የበርበሬ ወይም 'ሬድ ፔፐር' ተጠቃሚ ተብለዋል። ቀጥሎም ሕንድ እና አሜሪካ የሚከተሉ ሲሆን ሦስቱ አገራት በዓለም ላይ በዓመት ጥቅም ላይ ከሚውለው በርበሬ ውስጥ 41 በመቶውን ያህል ይመገባሉ። ኢትዮጵያዊያን አጥብቀው የሚወዱት በርበሬ ዋጋ ለምን ይዋዥቃል? ኢትዮጵያውያን ገበሬዎች ከሚያመርቱት በርበሬ ውስጥ 92.4 በመቶ የሚሆነውን ለገበያ እንደሚያቀርቡና ይህም በአገሪቱ ውስጥ ካሉ ከፍተኛ የገበያ ሰብሎች ውስጥ እንደሚያስመድበው ከሁለት ዓመት በፊት አራት ምሁራን ባሳተሙት ጥናት ላይ ተጠቅሷል። አምራች ገበሬዎቹ ከ60 በመቶ በላይ ምርታቸውን በአካባቢያቸው ለሚገኙ ጅምላ ነጋዴዎች ይሸጣሉ ሲል በአበበ ቢራ፣ ጥጋቡ ዳኘው፣ አበበ ዳኘው እና አስማማው አለሙ የተጠናው ጥናት ያሳያል። መነሻው ከደቡብ አሜሪካ እንደሆነ የሚነገርለት በርበሬ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በደቡብ ክልሎች በከፍተኛ መጠን ይመረታል። ታዲያ ባለሞያዎቹ ባጠኑት ጥናት መሰረት ከፍተኛው የበርበሬ ምርት ተግዳሮት የግብአት እጥረት ነው። የበርበሬ ምርት ከፍተኛ የሆነ ለበሽታ ተጋላጭነት ደግሞ ሌላኛው ማነቆ ነው። በተጨማሪም በርበሬ ሲተከል፣ ሲታረም እና ደርሶ ሲሰበሰብ ከፍተኛ የሆነ የሰው ኃይል ይፈልጋል። ስለዚህም በርበሬን ለማምረት የሚያስፈልገው ከፍተኛ የሰው ኃይል በምርቱ ላይ እና በዋጋው ላይ የእራሱ ተጽእኖ እንዳለው አጥኚዎቹ አመልክተዋል። ሌላው ዋነኛ የበርበሬ ገበያ ላይ ያለው ማነቆ በግብይት ወቅት ያሉ ችግሮች ሲሆኑ፣ አጥኚዎቹ ያነጋገሯቸው አምራቾች እንደሚሉት ከመንግሥት ድጋፍ ማጣት ዋነኛው የገበያው ችግር አባባሽ ነው። በመቀጠልም በቂ የመጋዘን ስፍራ አለመኖር፣ የብድር አገልግሎት እጥረት፣ በገዢ እና በሻጭ መካከል ያለ የትክክለኛ መረጃ ክፍተት እንዲሁም ከጥራት ጋር የተያያዙ ተግዳሮቶች የበርበሬን ገበያ በመፈተን ይጠቀሳሉ። በኢትዮጵያ የኢኮኖሚስቶች ማኅበር ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት እና የመንግሥት የኢኮኖሚ አማካሪ ሆነው ያገለገሉት ተባባሪ ፕሮፌሰር ሰዒድ ኑሩ (ዶ/ር) አራት ዋና ዋና ማነቆዎች በርበሬን ጨምሮ ሌሎች ወቅትን ጠብቀው የሚመረቱ ምርቶች ላይ ለሚታዩ የዋጋ መናር ምክንያት ናቸው ይላሉ። የመጀመሪያው ምርቱን በበቂ ሁኔታ ያለማምረት ነው። አንድ ምርት በበቂ ሁኔታ በአገር ውስጥ ማምረት ካልተቻለ የቱንም አይነት እርምጃ ቢወሰድ ውጤት ማየት አይታሰብም ይላሉ ሰዒድ (ዶ/ር)። እንደ የተባበሩት አረብ ኤምሬት ያሉ በቂ የውጪ ምንዛሬ ያላቸው አገራት "ከበለገው ይግጣሉ" በማለት፣ በቂ ገንዘብ ያለው አገር በልግ ከሆነበት አገር የፈለገውን ምርት ገዝቶ ከዓመት ዓመት ሕዝቡን በተረጋጋ ገበያ ሊመግብ እንደሚችል ያብራራሉ። ሁለተኛው እንደ በርበሬ ያሉ ምርቶችን ተገቢ የሆነ የማቆያ ዘዴዎችን በመጠቀም ከዓመት ዓመት እንዲቆይ ማድረግ ሌላው እርምጃ ነው። እንደ ቲማቲም ያሉ ከበርበሬ ይልቅ በአጭር ጊዜ የሚበላሹ ምርቶችን እንኳን ከገበያ እንዳይጠፉ የሚያደርግ ዘዴ መኖሩን የሚያስታውሱት ሰዒድ (ዶ/ር) ይህንን በበርበሬ ላይ መተግበር ቀላል ነው ይላሉ። ሌላው መፍትሄ ነጋዴዎች ምርቱ በረከሰ ጊዜ እንዲያከማቹ ማስቻል ነው። "ኢትዮጵያ ውስጥ ነጋዴዎች ምርትን ያከማቻሉ የሚለው በአሉታዊ መልኩ ብቻ መወሰዱ አግባብ አይደለም" ይላሉ የኢኮኖሚ ባለሞያው። "በውጪው አገር ኢንቨርተሪ የሚባል ኢንቨስትመንት አለ። አንድ ምርት ሲረክስ ነጋዴዎች ሰብስበው የሚያቆዩበት እና ምርቱ ገንዘባቸውን ይዞ ለቆየበት እንደ ሽልማት የተወሰነ ጭማሪ አድርገው፣ ምርቱ ሲጠፋ ለገበያ የሚያቀርቡበት ሥርዓት ማለት ነው። ይህ መጥፎ ጊዜ ጠብቀው ምርት የሚያከማቹትን አያጠቃልልም። በሪል ስቴት ወይም መሰል ምርቶች ላይ እንደሚደረግ ኢንቨስትመንት ማለት ነው" ሲሉ ሰዒድ (ዶ/ር) ያብራራሉ። ሌላኛው ማነቆ እንደ በርበሬ ያሉ ምርቶች ላይ እሴት የሚጨምር ኢንዱስትሪ ቁጥር ትንሽ ከመሆኑ ጋር ይያያዛል። በርበሬ ተመጥኖ እና ተዘጋጅቶ ረጅም ጊዜ የሚቆይ ምርት እንደመሆኑ፣ ዋጋው በረከሰ ወቅት በርበሬው ቢዘጋጅ ምርቱ በማይኖርበት ጊዜ የተወሰነ ገንዘብ ጨምሮ መሸጥ ዋነኛ አማራጭ መሆን ይቻላል ሲሉም ሦስተኛውን ችግር እና መፍትሄውን ያመላክታሉ። የምርት እጥረት ባለበት ወቅት ከውጪ ማስገባቱ መፍትሄ ይሆናል? የምርቱ እጥረት ባለበት ወቅት ከውጪ ማስገባት በእርግጥም በቂ የውጪ ምንዛሬ ላለው አገር መፍትሄ ነው የሚሉት ሰዒድ (ዶ/ር)፣ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ አገሮች ግን በርካታ ችግሮችን የሚያስከትል እርምጃ ነው ይላሉ። ነገር ግን አንድ ጊዜ ወይም ሁለት ጊዜ ማስገባት በጥንቃቄ የሚወሰድ እርምጃ ከሆነ በርካታ ጥቅሞች እንዳሉት አጽንኦት ይሰጡታል። ባለሙያው ስለ ጥቅሞቹ ከማብራራታቸው በፊት እጥረትን እንደ ችግር መመልከት ማቆም እንደሚያስፈልግ እና ለአንድ አልሚ እጥረት የገበያ እድል ሆኖ መታየት እንደሚገባው ያብራራሉ። ይህም የማምረት ችግር ለሌለበት አገር በተለይም ለእጥረት መፍትሄ መስጠት ለአምራቾች የገበያ እድል ነው ይላሉ። ለዚህ ምሳሌ ሲጠቅሱ፡ "ከዓመታት በፊት የአገር ባህል ልብስ ከአውሮፓ ከሚመጡ ልብሶች በላይ ውድ መሆኑን ያዩ ቻይናውያን ወስደው በርካሽ ቴክኖሎጂ ሰርተው መልሰው አመጡት። ይህ እንግዲህ በየዕለቱ የማንለብሰው የክት ልብስ ነው። ታዲያ በየዕለቱ የምንጠቀማቸው ምርቶች እጥረት ሲፈጠር ይሄንን ለመሙላት መንቀሳቀስ ነበር የሚገባን" ሲሉ ሰዒድ (ዶ/ር) ያስረዳሉ። ኢትዮጵያ የበርበሬ እጥረትን ለመፍታት ከውጪ አገር ማስገባቷ ዘላቂ እስካልሆነ ድረስ ለጥቅም ማዋል እንደሚያግዝ ያስረዳሉ። አንዱ ቴክኖሎጂውን መቅሰም ነው። የምግብ ምርት እንደመሆኑ አመራረቱን ማየት ቢያስፈልግም አንድን ምርት አንድ ጊዜ ወይም ሁለቴ አስገብቶ ምርቱን መሞከር ችግር እንደሌለውም ይናገራሉ። ነገር ግን ኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች በግብርና ሥራ ለዘመናት የቆዩበት ሙያ ሆኖ ሳለ ልክ እንደ ኢንዱስትሪ ምርቶች የግብርና ምርት ማስገባት ግን አስመጪውን እና ሸማቹን ለስንፍና መንግሥትን ደግሞ ለከባድ የውጪ ምንዛሬ እጥረት ይዳርጋል ይላሉ። ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላቸውን እንደ ማሽኖች ያሉ ግብአቶችን ለማስገባት እንጂ አንድም ኪሎ የግብርና ምርት በቋሚነት ኢትዮጵያ ማስገባቷ አግባብ አይደለም ሲሉም ያክላሉ። "አስመጪዎች በተሻለ ጥራት በቅናሽ የተመረት የግብርና ምርት ማምጣት ከጭቃው ከአፈሩ ጋር መታገልን ያስቀርላቸዋል። ይህ አንዴ ከተለመደ ከባድ ነው። ስንፍናን ያመጣል። ሱፐር ማርኬት ውስጥ ከግብፅ የሚመጣ አራት ፍሬ ብርቱካን በ280 ብር ይሸጣል። የተገነጠለ ዶሮ፣ እንቁላል እንዲሁም ሽንኩርት ከውጪ ይገባል። የአየር ንብረታችን እጅግ የተመቸ ሆኖ ሳለ ይህ እንዴት ሆነ ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል" ይላሉ ሰኢድ ኑሩ (ዶ/ር)። እንደ መውጫ ከመስከረም አስከ ኅዳር ድረስ በግዴታ ነጋዴው ይዞ ሲሸጠው የቆየው 'የቻይና በርበሬን' በተመለከተ ነጋዴዎቹ በእርግጥም ቅሬታ ነበራቸው። በርበሬው ገና ከማዳበሪያው ሲፈታ ጀምሮ "የኬሚካል ሽታ" እንዳለው እና በርበሬውን የገዙ ደንበኞችም ደስተኛ እንዳልሆኑ ብርሌው ተናግሯል። "የቻይናው በርበሬ በ250 ሲመጣ የአገር ውስጥ በርበሬ 350 ነበር የሚሸጠው። ይሄ ከፍተኛ የዋጋ ልዩነት ነበር። የገዙኝ ደንበኞችም ሲፈጭም ዱቄቱ እንደሚያምር ነግረውኝ ነበር። ምግብ ውስጥ ሲገባ ነው ችግሩ" ሲል ብርሌው ለቢቢሲ ተናግሯል። ደንበኞቹ ቅር መሰኘታቸውን እንደነገሩት አልሸሸገም። የኢኮኖሚ ባለሞያው ሰዒድ (ዶ/ር) ከውጪ አገር እንዲህ ያሉ የግብርና ምርቶች ሲገቡ በሽታ ይዘው እንዳይመጡ ጥንቃቄ ተደርጎ መሞከር ይገባዋል ሲሉም ያስጠነቅቅቃሉ። ገበሬዎች የቅንጬ አረም የሚሉት ከፍተኛ ጉዳት ያለው አረም ብሎም በአንድ ወቅት ከሕንድ የገባ ማንጎን ተከትሎ የመጣ የሰብል በሽታን በምሳሌነት ያነሳሉ። "ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የነጋዴ ቁጥር ለቁጥጥር የማይመች ነው" የሚሉት ባለሙያው በሌላው አገር አነስተኛ ቁጥር ያለው ትልልቅ ነጋዴ ስላለ ከመንግሥት ጋር ለመደራደር ቀላል ያደርገዋል። ይህ ለአምራች ገበሬውም እንደሚሰራ ይናገራሉ። ትርፍ የሚገኘው አንድም ብዙ ምርት በአነስተኛ ዋጋ በመሸጥ ወይም አነስተኛ ምርት በከፍተኛ ዋጋ በመሸጥ እንደሆነ የሚናገሩት ባለሙያው፣ አነስተኛ ነጋዴም ሆነ ገበሬ ያለበት አገር የዋጋ መናሩ የሚገመት ነው ይላሉ። "ባደጉ አገራት መንግሥት የሚደራደረው አራት አምስት ከሚሆኑ ሱፐርማርኬቶች ጋር ነው። እኛ ጋር 20 ሺህ ሱቆችን ዘጋን የሚል ዜና እንሰማለን። ይህ የበለጠ እጥረት ይፈጥራል። አንድ አዲስ አበባ በቅርቡ የተከፈተ ሱፐር ማርኬት አለ። ከራሱ ማሳ ብርቱካን 30 ብር በኪሎ አምጥቶ ይሸጣል። ከእርሱ ሱፐርማርኬት ምርቱን የገዙ አጠገቡ ያሉ ትንንሽ ሱቆች ራሱን ብርቱካን በእጥፍ 60 ብር ይሸጣሉ" ሲሉ ሰዒድ (ዶ/ር) በትልልቅ አቅራቢዎች እና አነስተኛ ቸርቻሪዎች መካከል ያለውን ልዩነት ያስረዳሉ። እንዲሁም የኢትዮጵያ የገበያ መዋቅር ደላላ የተጫነው እና ሰዎች በምርት ሥራ ላይ ከመሳተፍ ይልቅ በመሃል በመደለል እያተረፉ መኖርን መምረጣቸው ሌላው ከፍተኛ ችግር ነው ይላሉ ሰኢድ (ዶ/ር)። ልክ እንደ አበባ ሁሉ የምግብ የሚያመርቱ ትልልቅ ኩባንያዎችን በማገዝ ወደ አገር ውስጥ በመጋበዝ ከእነሱ መማር እንደሚያስፈልግም ይናገራሉ። "በአንድ ጊዜ 100 ሻማ ማብራት አይቻልም" የሚሉት ሰኢድ "ከአንድ ሻማ መጀመር ግን ይቻላል" ይላሉ። የአበባ አምራቾች ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ከ10 ዓመት በፊት ኬንያ ውስጥ ምርጫን ተከትሎ የመጣ ቀውስን ሸሽተው ነበር። አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ የአበባ ምርት ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ ምንጭ እንደሆነ እና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአገር ውስጥ ባለሃብቶች የገቡበት ብሎም የቴክኖሎጂ ሽግግሩም በተሳካ ሁኔታ የተሳለጠበት ዘርፍ መሆኑን ያነሳሉ። ይህ በሌላው ዘርፍ መደገም አለበት እንደ ሰኢድ ኑሩ (ዶ/ር) ትንታኔ። "የመጀመሪያውም፣ ሁለተኛውም ሦስተኛውም መፍትሄ አንድ ነው። በግብርና ራሳችንን መቻል ነው" ሲሉ ዘመናዊ ግብርናን ማስፋፋት ብቸኛው መፍትሄ መሆኑን ባለሙያው ለቢቢሲ ተናግረዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59807834
2health
ኮቪድ-19፡ የዓለማችን ትልቁ የፕላስቲክ ጓንት አምራች ድርጅት ፋብሪካዎቹን ሊዘጋ ነው
የዓለማችን ትልቁ የፕላስቲክ ጓንት አምራቹ 'ቶፕ ግላቭ' ከግማሽ በላይ የሚሆኑትን ፋብሪካዎቹን እንደሚዘጋ አስታወቀ። ድርጅቱ ይህን ያለው 2500 የሚሆኑ ሠራተኞቹ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ተከትሎ ነው። ንብረትነቱ የማሌዥያ የሆነው 'ቶፕ ግላቭ' ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ሲባል 28 ማምረቻዎቹን ተራ በተራ ይዘጋል ተብሏል። ፋብሪካዎቹ መቼ መዘጋት እንደሚጀምሩ የታወቀ ነገር ባይኖርም ደረጃ በደረጃ ለመዝጋት መታቀዱ ተገልጿል። ድርጅቱ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ የበሽታው መከላከያ ግብዓት ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮለት ነበር። ይሁን እንጅ በሚተማመንባቸው ዝቅተኛ ተከፋይ ስደተኛ ሰራተኞቹ የሥራ ሁኔታ ላይ ከፍተኛ ስጋቶች ነበሩ። ሰኞ ዕለት የማሌዥያ የጤና ሚኒስተር የቶፕ ግላቭ ፋብሪካዎች እና የሰራተኞች መኖሪያ በሚገኙበት አካባቢው የኮቪድ -19 ወረርሽኝ ስርጭት መጨመሩን አስታውቋል። ይህንን ተከትሎ 5 ሺህ 800 ሰራተኞች እስካሁን የተመረመሩ ሲሆን ከእነዚህም መካከል 2 ሺህ 453ቱ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ብሏል። ቶፕ ግላቭ በማሌዥያ 41 ፋብሪካዎች ያሉት ሲሆን አብዛኞቹ ሰራተኞቹ ከኔፓል የመጡና በተጨናነቁ የመኖሪያ ህንፃዎች የሚኖሩ ናቸው። "በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው ሆስፒታል ገብተዋል። የቅርብ ንክኪ ያላቸውም ራሳቸውን ለይተዋል" ሲሉ የጤና ሚኒስቴር ዳሬክተር ጀነራል ኑር ሂሻም አብዱላህ ለሮይተርስ የዜና ወኪል ተናግረዋል። ቶፕ ግላቭ በዚህ ዓመት በዓለማችን ከፍተኛ ትርፍ በማስመዝገብ በዓለም ትኩረት ውስጥ ቆይቷል፤ በዚህ ብቻም ሳይሆን በሰራተኞች የጉልበት ብዝበዛ ክሶችም የዓለም ዋነኛ ትኩረትም ሆኗል። ሐምሌ ወር ላይ አሜሪካ የሰራተኞች የጉልበት ብዝበዛን ምከንያት በማድረግ ከሁለት የድርጅቱ ቅርንጫፎች ጓንቶች እንዳይገቡ አግዳለች። የአሜሪካ የሰራተኛ መሥሪያ ቤት በቅርቡ ባወጣው ሪፖርትም ተመሳሳይ ሃሳብ አንስቷል። መስከረም ወር ላይም ስደተኛ ሰራተኞች ለሎስ አንጀለስ ታይምስ በቶፕ ግላቭ ፋብሪካዎች ያለውን የሥራ ሁኔታ አስቸጋሪነት ተናግረዋል። ስደተኞቹ በሳምንት 72 ሰዓታት እንደሚሰሩና ዝቅተኛ ክፍያ እንደሚከፈላቸውና በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚኖሩ ነበር ለሎስ አንጀልስ ታይምስ ያስረዱት። ከጥቂት ሳምንታት በኋላም ድርጅቱ ከገለልተኛ አማካሪው በተሰጠው ምክረ ሃሳብ መሰረት ለሰራተኞቹ የቅጥር የማካካሻ ክፍያ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታውቆ ነበር። የማሌዥያ የፕላስቲክ ጓንት አምራቹ ቶፕ ግላቭ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ፣ ኮንዶም፣ የፕላስቲክ ድድ እንዲሁም ሌሎችን ምርቶችን በማምረት ይታወቃል።
ኮቪድ-19፡ የዓለማችን ትልቁ የፕላስቲክ ጓንት አምራች ድርጅት ፋብሪካዎቹን ሊዘጋ ነው የዓለማችን ትልቁ የፕላስቲክ ጓንት አምራቹ 'ቶፕ ግላቭ' ከግማሽ በላይ የሚሆኑትን ፋብሪካዎቹን እንደሚዘጋ አስታወቀ። ድርጅቱ ይህን ያለው 2500 የሚሆኑ ሠራተኞቹ በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ተከትሎ ነው። ንብረትነቱ የማሌዥያ የሆነው 'ቶፕ ግላቭ' ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ሲባል 28 ማምረቻዎቹን ተራ በተራ ይዘጋል ተብሏል። ፋብሪካዎቹ መቼ መዘጋት እንደሚጀምሩ የታወቀ ነገር ባይኖርም ደረጃ በደረጃ ለመዝጋት መታቀዱ ተገልጿል። ድርጅቱ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ የበሽታው መከላከያ ግብዓት ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮለት ነበር። ይሁን እንጅ በሚተማመንባቸው ዝቅተኛ ተከፋይ ስደተኛ ሰራተኞቹ የሥራ ሁኔታ ላይ ከፍተኛ ስጋቶች ነበሩ። ሰኞ ዕለት የማሌዥያ የጤና ሚኒስተር የቶፕ ግላቭ ፋብሪካዎች እና የሰራተኞች መኖሪያ በሚገኙበት አካባቢው የኮቪድ -19 ወረርሽኝ ስርጭት መጨመሩን አስታውቋል። ይህንን ተከትሎ 5 ሺህ 800 ሰራተኞች እስካሁን የተመረመሩ ሲሆን ከእነዚህም መካከል 2 ሺህ 453ቱ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ብሏል። ቶፕ ግላቭ በማሌዥያ 41 ፋብሪካዎች ያሉት ሲሆን አብዛኞቹ ሰራተኞቹ ከኔፓል የመጡና በተጨናነቁ የመኖሪያ ህንፃዎች የሚኖሩ ናቸው። "በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው ሆስፒታል ገብተዋል። የቅርብ ንክኪ ያላቸውም ራሳቸውን ለይተዋል" ሲሉ የጤና ሚኒስቴር ዳሬክተር ጀነራል ኑር ሂሻም አብዱላህ ለሮይተርስ የዜና ወኪል ተናግረዋል። ቶፕ ግላቭ በዚህ ዓመት በዓለማችን ከፍተኛ ትርፍ በማስመዝገብ በዓለም ትኩረት ውስጥ ቆይቷል፤ በዚህ ብቻም ሳይሆን በሰራተኞች የጉልበት ብዝበዛ ክሶችም የዓለም ዋነኛ ትኩረትም ሆኗል። ሐምሌ ወር ላይ አሜሪካ የሰራተኞች የጉልበት ብዝበዛን ምከንያት በማድረግ ከሁለት የድርጅቱ ቅርንጫፎች ጓንቶች እንዳይገቡ አግዳለች። የአሜሪካ የሰራተኛ መሥሪያ ቤት በቅርቡ ባወጣው ሪፖርትም ተመሳሳይ ሃሳብ አንስቷል። መስከረም ወር ላይም ስደተኛ ሰራተኞች ለሎስ አንጀለስ ታይምስ በቶፕ ግላቭ ፋብሪካዎች ያለውን የሥራ ሁኔታ አስቸጋሪነት ተናግረዋል። ስደተኞቹ በሳምንት 72 ሰዓታት እንደሚሰሩና ዝቅተኛ ክፍያ እንደሚከፈላቸውና በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚኖሩ ነበር ለሎስ አንጀልስ ታይምስ ያስረዱት። ከጥቂት ሳምንታት በኋላም ድርጅቱ ከገለልተኛ አማካሪው በተሰጠው ምክረ ሃሳብ መሰረት ለሰራተኞቹ የቅጥር የማካካሻ ክፍያ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታውቆ ነበር። የማሌዥያ የፕላስቲክ ጓንት አምራቹ ቶፕ ግላቭ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ፣ ኮንዶም፣ የፕላስቲክ ድድ እንዲሁም ሌሎችን ምርቶችን በማምረት ይታወቃል።
https://www.bbc.com/amharic/news-55036274
2health
ኮሮናቫይረስ፡ ኮቪድ-19 ምን እንደሆነ አናውቅም የሚሉት 10 አገራት
ኮቪድ ዓለምን አምሷል፡፡ እኛ ግን አናውቀውም የሚሉ 10 አገሮች አሉ ብንላችሁስ፡፡ ለመሆኑ እነዚህ አገሮች እነማን ናቸው? የማያውቁት ኮቪድ እንዴት እያደረጋቸው ይሆን? 1.ፕላው (Palau) ይቺ አገር የት ያለች ትመስልዎታለች? ሩቅ ምዕራብ ፓስፊክ ነው የምትገኘው፡፡ ማይክሮኒዢያ ሪጂን በሚባለው አካባቢ ከነ ፊሊፒንስ እና ኢንዶኒዢያ ነጠል ብላ በባትሪ ተፈልጋ የምትገኝ ጢኒጥ ደሴት ናት፡፡ እዚያ ፕላው የሚባል ሆቴል አለ፡፡ ድሮ በ1982 ነበር የተከፈተው፡፡ ያኔ የአገሩን ስም የያዘው ይኸው እስከዛሬ አለ፡፡ በአገሩ ሌላ ሆቴል የሌለ ይመስል፡፡ በፓስፊክ ውቅያኖስ ሰማያዊ ቀለም ውሀ ውስጥ ጠብ ያለች ነጥብ የምትመስለው ይቺ አገር የቱሪስት አገር ናት፡፡ ያለፈውን ዓመት ብቻ አሐዝ ብንወስድ፣ ወደ ፕላው ደሴት 90ሺህ ቱሪስት ገብቷል፡፡ ይህ አሐዝ ከፕላው ጠቅላላ ሕዝብ አምስት እጥፍ ይበልጣል ብንላችሁስ? 40 ከመቶ የአገሪቱ ጥቅል አገራዊ ምርት ገቢ በቱሪዝም የሚታለብ ነው፡፡ ይህ ግን ከኮቪድ በፊት ያለ ታሪክ ነው፡፡ ኮቪድ ድንበሯን ሲያዘጋት ፕላው ደሴት ጉሮሮዋ ተዘጋ፡፡ እንኳን ሌላው መዝናኛ ይቅርና የአገሪቱን ስም የያዘው ሆቴል ሳይቀር ተዘጋ፡፡ ‹‹ለውድ ደንበኞቻችን፡- ኮቪድ የሚባል በሽታ በተቀረው ዓለም ስለተከሰተ ፕላው ሆቴል ለጊዜው ዝግ መሆናችንን ለውድ እንገልጻለን›› ብለው በር ላይ ሳይለጥፉ አልቀሩም፡፡ ፕላው አገር አንድም ዜጋ በቫይረሱ ባይያዝባትም ቫይረሱ ግን ቱሪዝማዊ ኢኮኖሚዋን ደም እያስተፋው ነው፡፡ 2. የማርሻል ደሴቶች 4ሺህ ኪሎ ሜትር ርቀው በማዕከላዊ ፓስፊክ ውቅያኖስ መሀል፣ ከምድር ወገብ ሰሜን፣ ብጥስጥስ ብለው ከሚገኙት የእሳተ ገሞራ ደሴቶች ውስጥ የማርሻል ደሴቶች ይገኙበታል፡፡ በሀዋይ እና በፊሊፒንስ መሀል ነው የሚገኙት፡፡ በውስጣቸው 1200 ጥቃቅን ደሴቶችና የጎመራ ፍንጥቅጣቂ የሆኑ የሰመጡ ደቂቀ ደሴቶች (ኮራል አቶልስ) ይገኛሉ፡፡ ሁለተኛውን የዓለም ጦርነት ተከትሎ የአሜሪካ የሩቅ ግዛት ሆነው የቆዩ ቢሆንም ከ1986 ወዲህ ራሳቸውን ችለዋል። ደህንነቱና መከላከያን እንዲሁም ጠቀም ያለ ድጎማን ግን አሁንም ከአሜሪካ ነው የሚያገኙት። የሕዝብ ብዛት 55ሺህ ሲሆን ዋና ከተማቸው ማጁራ ትባላለች፡፡ እነዚህ ደቂቀ ደሴቶችና የቱሪስት መዳረሻ የሆኑ ስብስቦች ማርሻል ደሴቶች ተብለው ይጠራሉ፡፡ ኮቪድ ምን እንደሆነ ባያውቁም ምጣኔ ሀብታዊ ቁንጥጫው ግን ፓሲፊክን አቋርጦ ተሰምቷቸዋል። ታዲያ አንድ ፕላው በቱሪዝም በኩል አይደለም ቁንጥጫው፡፡ በዓሣ ማጥመድና መላክ ጥሩ ገንዘብ ያገኙ ነበር፡፡ ኮቪድ ይህንን አስተጓጎለባቸው፡፡ በኮቪድ ምክንያት 700 ሰዎች ሥራ አጥተዋል፡፡ ይህ ትንሽ ሕዝብ ላላት ማርሻል አይላንድስ ብዙ ቁጥር ነው፡፡ የሕዝብ ብዛቷ 300ሺህ ቢሆን ነው፡፡ ዋና ከተማዋ ፖርትቪላ ይባላል፡፡ በ1ሺህ 300 ኪሎ ሜትር ላይ የተሰፉ የሚመስሉ 80 ደሴቶች የፈጠሯት አገር ናት፡፡ ከፈረንሳይና እንግሊዝ ቅኝ ነጻ የወጣችው ገና በ1980 ነበር፡፡ አብዛኛው ሕዝቧ ገጠር የሚኖር ገበሬ ነው፡፡ የብዙ አገር ህዝቦች ድንበር ክፈቱልን ሥራ እንስራበት እያሉ ነው የሚያስቸግሩት፡፡ ቫኑዋቱ ብትሄዱ ግን በተቃራኒው ነው የምትሰሙት፡፡ ዶ/ር ሌን ታሪቮንዳ የኅብረተሰብ ጤና ዳይሬክተር ናቸው፣ የቫኑዋቱ ደሴት፡፡ ዶ/ር ሌን የመጡባት ደሴት አምባኡ ደሴት ትባላለች፡፡ 10ሺ ሰዎች ይኖሩባታል፡፡ ‹‹እኔ የመጣሁበት ደሴት ሄዳችሁ ድንበሩ ይከፈት ወይ ብትሏቸው አረ እንዳታስጨርሱን ነው የሚሏችሁ›› ይላሉ ለቢቢሲ፡፡ መታመም አንፈልግም ነው የሚሉት፡፡ 80 ከመቶ የታሪቮንዳ አገር ሕዝብ ገጠር ነው የሚኖር፡፡ የኮቪድ ሕመም ብዙም አልተሰማቸውም፡፡ እርሻ እንጂ ቱሪዝም ላይ ስላልተንጠላጠሉ ሊሆን ይችላል፡፡ ዶር ሌን ድንበር ለመክፈት አስበው ነበር፡፡ ነገር ግን ጎረቤት ፓፓዎ ጊኒ ለወራት ከቫይረሱ ነጻ ሆና ቆይታ ሐምሌ ላይ እንዴት ጉድ እንደሆነች ሰምተዋል፡፡ ስለዚህ ድንበር መክፈቱ ይቆየን ብለዋል፡፡ 4. ቶንጋ ቶንጋን የፈጠሩት ደግሞ 170 ደቂቀ ደሴቶች ናቸው፡፡ እዚያው ደቡባዊ ፓስፊክ ነው የሚገኙት፡፡ ቶንጋ ደሴቶቿን ብትሰበስብ በስፋት ከጃፓን አታንስም፡፡ ለ165 አመታት ንጉሣዊ የፊውዳል አስተዳደር ነበራት፡፡ ከዚህ ፊውዳላዊ ሥርዓት የወጣችው በ2010 ዓ. ም ነበር፡፡ ጥብቅ ክርስቲያን አማኞች ያሏት ቶንጋ ከእንግሊዝ ነጻ የሆነችው በ1970 ዓ.ም ነበር፡፡ ቶንጋ ምን አይነት ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ የሌላት አገር ተደርጋ ትታያለች፡፡ ማዕድን አልባም ናት ይባላል፡፡ ይህ ነው የሚባል የተፈጥሮ ማዕድን ሀብት ባይኖራትም በዓሣ ሀብት ራሷን ትደጉማለች፡፡ ሌላው የገቢ ምንጭ እርሻ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ ቶንጋዊያውን ከውጭ አገር የሚልኩት ገንዘብ ነው፡፡ ብዙዎቹ ቶንጋዊያን ያሉት በኒዊዚላንድ ነው፡፡ በአገሪቱ የሥራ አጥ ቁጥር ከፍ ያለ ነው፡፡ ያም ሆኖ የውጭ ምንዛሬዋን የምታገኝበት አንዱ ቀዳዳ ቱሪዝም ስለነበር ኮቪድ ባይደርስባትም ምጣኔ ሀብታዊ ጉዳት አድርሶባታል፡፡ 5. ሰሙዋ በፓስፊክ ውቅያኖስ የምትገኘው ሰሙዋ እስከ 1961 ዓ. ም ድረስ በኒውዚላንድ ሥር ነበር የምትተዳደረው፡፡ 9 የእሳተ ገሞራ ደሴቶች ነው የፈጠሯት ይቺን አገር፡፡ ሆኖም 99 ከመቶ ሕዝቧ የሚኖረው በኡፖሉና ሳቫይ ደሴቶች ነው፡፡ ዋና ከተማዋ አፒያ ይባላል፡፡ ምጣኔ ሀብቷ በእርሻና በዓሣ ሀብት የተንጠለጠለ ነው፡፡ ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቱሪዝም ሞቅ ደመቅ ብሎላት ነበር፡፡ በተለይ ያማሩ የባሕር ዳርቻዎቿ ተወዳጅ ሆነውላታል፡፡ ከቱሪዝም ጋር የባሕር ማዶ ዓለም አቀፍ ኦፍሾር የባንክ አገልግሎት በማሳለጧ ሀብታሞች ሸሸግ ማድረግ የፈለጉትን ገንዘብ ይዘው እዚያ ይሄዳሉ፡፡ አንድም ለመዝናናት፣ አንድም ለባንክ አገልግሎት፡፡ 200ሺህ የማይሞላው ሕዝቧ የወግ አጥባቂ ባህልና የጥብቅ ክርስትና ተከታይ ነው፡፡ አሁንም ቢሆን ዜጎቿ ወደ ኒውዚላንድና ሌሎች አገሮች እየተሰደዱ ገንዘብ ወደ ቤተሰብ ይልካሉ፡፡ ኮሮና በሌሎች አገሮች ያደረሰው ጉዳት ሕመሙ ተሰምቷል፣ ሩቅ በምትገኘው በሰሙዋ ደሴት፡፡ 6.ቱቫሉ ቱቫሉን የፈጠሩት 9 ደሴቶች ናቸው፡፡ ከነዚህ ውስጥ 5ቱ እሳተ ገሞራ ወልዶ፣ አሳብጦ፣ በድጋሚ አስምጦ ዳግም የወለዳቸው (ኮራል አቶልስ) ናቸው፡፡ የተቀሩት አራቱ ደግሞ ሕዝብ በደንብ ይኖርባቸዋል፡፡ ቱቫሉ በማዕከላዊ ፓስፊክ ውቅያኖስ ነው የምትገኘው፡፡ ፉናፉቲ ይባላል ዋና ከተማዋ፡፡ በቱቫሉ ተራራ አይታሰብም፡፡ ከባሕር ጠለል በላይ ከ4.5 ሜትር ከፍ ያለ ቦታ የለም፡፡ የአየር ንብረት በቱቫሉ ትልቁ ጉዳይ ቢሆን የማይገርመውም ለዚሁ ነው፡፡ የባሕር ጠለል ከፍታ ከምድረ ገጽ ከሚያጠፋቸው አገሮች አንዷ ቱቫሉ ነው የምትሆነው፡፡ በቱቫሉ ወንዝም ምንጭም ስለሌለ ኑሮ የዝናብ ጥገኛ ነው፡፡ የኮኮናት ተክል የአገሪቱ ገቢ ምንጭ ነው፡፡ ይህ ገቢ እንዲታወክ ምክንያት በመሆኑ ኮቪድ ቱቫሉ ባይገባም ገብቷል፡፡ 7. ናውሩ በዓለም ትንሽዋ አገር ናውሩ ናት፡፡ ይቺ ደሴት ስሟ በቅርብ ጊዜ ይነሳ የነበረው አውስትራሊያ አገሪቱን እንደ ጓሮ እየተጠቀመቻት ነው በሚል ነው፡፡ ናውሩ ስደተኞች ማጎርያ አለ፤ ንብረትነቱ የአውስትራሊያ የሆነ፡፡ ይሄ ማጎርያ ታዲያ ለናውሩ አንድ የገቢ ምንጭ መሆኑ ይገርማል፡፡ ናውሩዎች አንዱ ሥራ ቀጣሪ ኢንደስትሪያችሁ ምንድነው ቢባሉ የአውስታራሊያ የስደተኛ ካምፕ ብለው ሊመልሱ ይችላሉ፡፡ ከ2013 ጀምሮ አውስትራሊያ በጀልባ ወደ አገሯ ሊገቡ የሚሞክሩ ስደተኞችን በሙሉ ወደ ናውሩ ነው የምትወስዳቸው፡፡ ካልሆነም ፓፓው ኒው ጊኒ፡፡ ከአውስትራሊያ 3ሺህ ኪሎ ሜትር ርቃ በሰሜን ምሥራቅ ፓስፊክ አቅጣጫ የምትገኘው ናውሩ የዜጎቿ ብዛት 10 ሺህ ቢሆን ነው፡፡ ናውሩን የሚያኖራት እርዳታ ነው፡፡ ሌላው ብቸኛ ሀብቷ ፎስፌት ማዕድን ነው፡፡ በናውሩ የውጭ ጋዜጠኛ ሄዶ መዘገብ አይችልም፡፡ ምክንያቱም በካምፖቹ ውስጥ ያለውን ኢሰብአዊ ድርጊት ያጋልጣል፡፡ ይህ ደግሞ ናውሩ የገቢ ምንጬን ሊጎዳብኝ ይችላል ትላለች፡፡ ናውሩን በዓመት የሚጎበኛት ሰው ከ200 አይበልጥም ይባላል፡፡ ቴሌግራፍ በአንድ ዘገባው በናውሩ እስከዛሬ የገባው ቱሪስት ቢደመር ከ15ሺህ አይበልጥም ሲል ጽፏል፡፡ በስፋት ቫቲካን ሲቲና ሞናኮ ብቻ ናቸው የሚበልጧት፤ ለዚህም ነው የዓለም ትንሽዋ ሪፐብሊክ ደሴት የምትባለው፡፡ ቱሪስት የአገሪቱ ገቢ ምንጭ አለመሆኑ በኮቪድ-19 አልተጎዳችም ማለት ግን አይደለም፡፡ ለጊዜው ከ10ሺህ ዜጎቼ አንድም ሰው ኮቪድ-19 አልያዘውም ብትልም ሕመሙ ግን ናውሩም ደርሷል፡፡ 8. ኪሪባቲ ኪሪባቲ የብጥስጣሽ ደሴቶች አገር በመሆኗ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ 4ሺህ ኪሎ ሜትር፣ ከሰሜን ደቡብ ደግሞ 2ሺህ ኪሎ ሜትር ታስኬዳች፡፡ ይህ ማለት ግን ይህ ሁሉ ርቀት ሰው የሚኖርበት ደረቅ መሬት ነው ማለት አይደለም፡፡ ነጻነቷን ያገኘችው ከእንግሊዝ በ1979 ዓ.ም ነው፡፡ በ1960ዎቹ ይቺ አገር አንዳንድ ደሴቶቿ ለእንግሊዝ የኑክሌር መሞከሪያ ሆነው አገልግለዋል፡፡ እንደ ብዙዎቹ የፓስፊክ ደቂቀ ደሴቶች ሁሉ ኪሪባቲም የዓለም ሙቀት መጨመር ከምድረ ገጽ ሊያጠፋት እንደሚችል ይገመታል፡፡ ኪሪባቲ ከፊጂ ደሴት መሬት ተከራይታ ምግብ ታመርታለች፡፡ ኢኮኖሚዋ ደካማ ሲሆን ኮኮናትና ኮፕራ በመላክ ነው የምትታወቀው፡፡ የዓሣ ማጥመድ ፍቃድ ለውጭ ኩባንያዎች እየቸበቸበች ኢኮኖሚዋን በከፊል ትደጉማለች፡፡ 9ኛ የሰለሞን ደሴቶች፤ 10ኛ ማይክሮኒዢያ በዝርዝሩ 9ኛ እና 10ኛ ላይ ያሉት የሰለሞን ደሴቶች እና ማይክሮኒዢያ ናቸው፡፡ ሁለቱም አገራት በዓሣ ምርትና በቱሪዝም ይታወቃሉ፡፡ ሁሉም በኮቪድ-19 የተጠቃ ዜጋ የለባቸውም፡፡ ይህ ዝርዝር ታዲያ ሰሜን ኮሪያና ቱርከሜኒስታን አላካተተም፡፡ ሆኖም እነዚህ ሁለት አገራት በይፋ ከኮቪድ-19 የያዘው ዜጋ አለም የለምም ብለው አያውቁም፡፡ ወይም አይታመኑ ይሆናል፡፡
ኮሮናቫይረስ፡ ኮቪድ-19 ምን እንደሆነ አናውቅም የሚሉት 10 አገራት ኮቪድ ዓለምን አምሷል፡፡ እኛ ግን አናውቀውም የሚሉ 10 አገሮች አሉ ብንላችሁስ፡፡ ለመሆኑ እነዚህ አገሮች እነማን ናቸው? የማያውቁት ኮቪድ እንዴት እያደረጋቸው ይሆን? 1.ፕላው (Palau) ይቺ አገር የት ያለች ትመስልዎታለች? ሩቅ ምዕራብ ፓስፊክ ነው የምትገኘው፡፡ ማይክሮኒዢያ ሪጂን በሚባለው አካባቢ ከነ ፊሊፒንስ እና ኢንዶኒዢያ ነጠል ብላ በባትሪ ተፈልጋ የምትገኝ ጢኒጥ ደሴት ናት፡፡ እዚያ ፕላው የሚባል ሆቴል አለ፡፡ ድሮ በ1982 ነበር የተከፈተው፡፡ ያኔ የአገሩን ስም የያዘው ይኸው እስከዛሬ አለ፡፡ በአገሩ ሌላ ሆቴል የሌለ ይመስል፡፡ በፓስፊክ ውቅያኖስ ሰማያዊ ቀለም ውሀ ውስጥ ጠብ ያለች ነጥብ የምትመስለው ይቺ አገር የቱሪስት አገር ናት፡፡ ያለፈውን ዓመት ብቻ አሐዝ ብንወስድ፣ ወደ ፕላው ደሴት 90ሺህ ቱሪስት ገብቷል፡፡ ይህ አሐዝ ከፕላው ጠቅላላ ሕዝብ አምስት እጥፍ ይበልጣል ብንላችሁስ? 40 ከመቶ የአገሪቱ ጥቅል አገራዊ ምርት ገቢ በቱሪዝም የሚታለብ ነው፡፡ ይህ ግን ከኮቪድ በፊት ያለ ታሪክ ነው፡፡ ኮቪድ ድንበሯን ሲያዘጋት ፕላው ደሴት ጉሮሮዋ ተዘጋ፡፡ እንኳን ሌላው መዝናኛ ይቅርና የአገሪቱን ስም የያዘው ሆቴል ሳይቀር ተዘጋ፡፡ ‹‹ለውድ ደንበኞቻችን፡- ኮቪድ የሚባል በሽታ በተቀረው ዓለም ስለተከሰተ ፕላው ሆቴል ለጊዜው ዝግ መሆናችንን ለውድ እንገልጻለን›› ብለው በር ላይ ሳይለጥፉ አልቀሩም፡፡ ፕላው አገር አንድም ዜጋ በቫይረሱ ባይያዝባትም ቫይረሱ ግን ቱሪዝማዊ ኢኮኖሚዋን ደም እያስተፋው ነው፡፡ 2. የማርሻል ደሴቶች 4ሺህ ኪሎ ሜትር ርቀው በማዕከላዊ ፓስፊክ ውቅያኖስ መሀል፣ ከምድር ወገብ ሰሜን፣ ብጥስጥስ ብለው ከሚገኙት የእሳተ ገሞራ ደሴቶች ውስጥ የማርሻል ደሴቶች ይገኙበታል፡፡ በሀዋይ እና በፊሊፒንስ መሀል ነው የሚገኙት፡፡ በውስጣቸው 1200 ጥቃቅን ደሴቶችና የጎመራ ፍንጥቅጣቂ የሆኑ የሰመጡ ደቂቀ ደሴቶች (ኮራል አቶልስ) ይገኛሉ፡፡ ሁለተኛውን የዓለም ጦርነት ተከትሎ የአሜሪካ የሩቅ ግዛት ሆነው የቆዩ ቢሆንም ከ1986 ወዲህ ራሳቸውን ችለዋል። ደህንነቱና መከላከያን እንዲሁም ጠቀም ያለ ድጎማን ግን አሁንም ከአሜሪካ ነው የሚያገኙት። የሕዝብ ብዛት 55ሺህ ሲሆን ዋና ከተማቸው ማጁራ ትባላለች፡፡ እነዚህ ደቂቀ ደሴቶችና የቱሪስት መዳረሻ የሆኑ ስብስቦች ማርሻል ደሴቶች ተብለው ይጠራሉ፡፡ ኮቪድ ምን እንደሆነ ባያውቁም ምጣኔ ሀብታዊ ቁንጥጫው ግን ፓሲፊክን አቋርጦ ተሰምቷቸዋል። ታዲያ አንድ ፕላው በቱሪዝም በኩል አይደለም ቁንጥጫው፡፡ በዓሣ ማጥመድና መላክ ጥሩ ገንዘብ ያገኙ ነበር፡፡ ኮቪድ ይህንን አስተጓጎለባቸው፡፡ በኮቪድ ምክንያት 700 ሰዎች ሥራ አጥተዋል፡፡ ይህ ትንሽ ሕዝብ ላላት ማርሻል አይላንድስ ብዙ ቁጥር ነው፡፡ የሕዝብ ብዛቷ 300ሺህ ቢሆን ነው፡፡ ዋና ከተማዋ ፖርትቪላ ይባላል፡፡ በ1ሺህ 300 ኪሎ ሜትር ላይ የተሰፉ የሚመስሉ 80 ደሴቶች የፈጠሯት አገር ናት፡፡ ከፈረንሳይና እንግሊዝ ቅኝ ነጻ የወጣችው ገና በ1980 ነበር፡፡ አብዛኛው ሕዝቧ ገጠር የሚኖር ገበሬ ነው፡፡ የብዙ አገር ህዝቦች ድንበር ክፈቱልን ሥራ እንስራበት እያሉ ነው የሚያስቸግሩት፡፡ ቫኑዋቱ ብትሄዱ ግን በተቃራኒው ነው የምትሰሙት፡፡ ዶ/ር ሌን ታሪቮንዳ የኅብረተሰብ ጤና ዳይሬክተር ናቸው፣ የቫኑዋቱ ደሴት፡፡ ዶ/ር ሌን የመጡባት ደሴት አምባኡ ደሴት ትባላለች፡፡ 10ሺ ሰዎች ይኖሩባታል፡፡ ‹‹እኔ የመጣሁበት ደሴት ሄዳችሁ ድንበሩ ይከፈት ወይ ብትሏቸው አረ እንዳታስጨርሱን ነው የሚሏችሁ›› ይላሉ ለቢቢሲ፡፡ መታመም አንፈልግም ነው የሚሉት፡፡ 80 ከመቶ የታሪቮንዳ አገር ሕዝብ ገጠር ነው የሚኖር፡፡ የኮቪድ ሕመም ብዙም አልተሰማቸውም፡፡ እርሻ እንጂ ቱሪዝም ላይ ስላልተንጠላጠሉ ሊሆን ይችላል፡፡ ዶር ሌን ድንበር ለመክፈት አስበው ነበር፡፡ ነገር ግን ጎረቤት ፓፓዎ ጊኒ ለወራት ከቫይረሱ ነጻ ሆና ቆይታ ሐምሌ ላይ እንዴት ጉድ እንደሆነች ሰምተዋል፡፡ ስለዚህ ድንበር መክፈቱ ይቆየን ብለዋል፡፡ 4. ቶንጋ ቶንጋን የፈጠሩት ደግሞ 170 ደቂቀ ደሴቶች ናቸው፡፡ እዚያው ደቡባዊ ፓስፊክ ነው የሚገኙት፡፡ ቶንጋ ደሴቶቿን ብትሰበስብ በስፋት ከጃፓን አታንስም፡፡ ለ165 አመታት ንጉሣዊ የፊውዳል አስተዳደር ነበራት፡፡ ከዚህ ፊውዳላዊ ሥርዓት የወጣችው በ2010 ዓ. ም ነበር፡፡ ጥብቅ ክርስቲያን አማኞች ያሏት ቶንጋ ከእንግሊዝ ነጻ የሆነችው በ1970 ዓ.ም ነበር፡፡ ቶንጋ ምን አይነት ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ የሌላት አገር ተደርጋ ትታያለች፡፡ ማዕድን አልባም ናት ይባላል፡፡ ይህ ነው የሚባል የተፈጥሮ ማዕድን ሀብት ባይኖራትም በዓሣ ሀብት ራሷን ትደጉማለች፡፡ ሌላው የገቢ ምንጭ እርሻ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ ቶንጋዊያውን ከውጭ አገር የሚልኩት ገንዘብ ነው፡፡ ብዙዎቹ ቶንጋዊያን ያሉት በኒዊዚላንድ ነው፡፡ በአገሪቱ የሥራ አጥ ቁጥር ከፍ ያለ ነው፡፡ ያም ሆኖ የውጭ ምንዛሬዋን የምታገኝበት አንዱ ቀዳዳ ቱሪዝም ስለነበር ኮቪድ ባይደርስባትም ምጣኔ ሀብታዊ ጉዳት አድርሶባታል፡፡ 5. ሰሙዋ በፓስፊክ ውቅያኖስ የምትገኘው ሰሙዋ እስከ 1961 ዓ. ም ድረስ በኒውዚላንድ ሥር ነበር የምትተዳደረው፡፡ 9 የእሳተ ገሞራ ደሴቶች ነው የፈጠሯት ይቺን አገር፡፡ ሆኖም 99 ከመቶ ሕዝቧ የሚኖረው በኡፖሉና ሳቫይ ደሴቶች ነው፡፡ ዋና ከተማዋ አፒያ ይባላል፡፡ ምጣኔ ሀብቷ በእርሻና በዓሣ ሀብት የተንጠለጠለ ነው፡፡ ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቱሪዝም ሞቅ ደመቅ ብሎላት ነበር፡፡ በተለይ ያማሩ የባሕር ዳርቻዎቿ ተወዳጅ ሆነውላታል፡፡ ከቱሪዝም ጋር የባሕር ማዶ ዓለም አቀፍ ኦፍሾር የባንክ አገልግሎት በማሳለጧ ሀብታሞች ሸሸግ ማድረግ የፈለጉትን ገንዘብ ይዘው እዚያ ይሄዳሉ፡፡ አንድም ለመዝናናት፣ አንድም ለባንክ አገልግሎት፡፡ 200ሺህ የማይሞላው ሕዝቧ የወግ አጥባቂ ባህልና የጥብቅ ክርስትና ተከታይ ነው፡፡ አሁንም ቢሆን ዜጎቿ ወደ ኒውዚላንድና ሌሎች አገሮች እየተሰደዱ ገንዘብ ወደ ቤተሰብ ይልካሉ፡፡ ኮሮና በሌሎች አገሮች ያደረሰው ጉዳት ሕመሙ ተሰምቷል፣ ሩቅ በምትገኘው በሰሙዋ ደሴት፡፡ 6.ቱቫሉ ቱቫሉን የፈጠሩት 9 ደሴቶች ናቸው፡፡ ከነዚህ ውስጥ 5ቱ እሳተ ገሞራ ወልዶ፣ አሳብጦ፣ በድጋሚ አስምጦ ዳግም የወለዳቸው (ኮራል አቶልስ) ናቸው፡፡ የተቀሩት አራቱ ደግሞ ሕዝብ በደንብ ይኖርባቸዋል፡፡ ቱቫሉ በማዕከላዊ ፓስፊክ ውቅያኖስ ነው የምትገኘው፡፡ ፉናፉቲ ይባላል ዋና ከተማዋ፡፡ በቱቫሉ ተራራ አይታሰብም፡፡ ከባሕር ጠለል በላይ ከ4.5 ሜትር ከፍ ያለ ቦታ የለም፡፡ የአየር ንብረት በቱቫሉ ትልቁ ጉዳይ ቢሆን የማይገርመውም ለዚሁ ነው፡፡ የባሕር ጠለል ከፍታ ከምድረ ገጽ ከሚያጠፋቸው አገሮች አንዷ ቱቫሉ ነው የምትሆነው፡፡ በቱቫሉ ወንዝም ምንጭም ስለሌለ ኑሮ የዝናብ ጥገኛ ነው፡፡ የኮኮናት ተክል የአገሪቱ ገቢ ምንጭ ነው፡፡ ይህ ገቢ እንዲታወክ ምክንያት በመሆኑ ኮቪድ ቱቫሉ ባይገባም ገብቷል፡፡ 7. ናውሩ በዓለም ትንሽዋ አገር ናውሩ ናት፡፡ ይቺ ደሴት ስሟ በቅርብ ጊዜ ይነሳ የነበረው አውስትራሊያ አገሪቱን እንደ ጓሮ እየተጠቀመቻት ነው በሚል ነው፡፡ ናውሩ ስደተኞች ማጎርያ አለ፤ ንብረትነቱ የአውስትራሊያ የሆነ፡፡ ይሄ ማጎርያ ታዲያ ለናውሩ አንድ የገቢ ምንጭ መሆኑ ይገርማል፡፡ ናውሩዎች አንዱ ሥራ ቀጣሪ ኢንደስትሪያችሁ ምንድነው ቢባሉ የአውስታራሊያ የስደተኛ ካምፕ ብለው ሊመልሱ ይችላሉ፡፡ ከ2013 ጀምሮ አውስትራሊያ በጀልባ ወደ አገሯ ሊገቡ የሚሞክሩ ስደተኞችን በሙሉ ወደ ናውሩ ነው የምትወስዳቸው፡፡ ካልሆነም ፓፓው ኒው ጊኒ፡፡ ከአውስትራሊያ 3ሺህ ኪሎ ሜትር ርቃ በሰሜን ምሥራቅ ፓስፊክ አቅጣጫ የምትገኘው ናውሩ የዜጎቿ ብዛት 10 ሺህ ቢሆን ነው፡፡ ናውሩን የሚያኖራት እርዳታ ነው፡፡ ሌላው ብቸኛ ሀብቷ ፎስፌት ማዕድን ነው፡፡ በናውሩ የውጭ ጋዜጠኛ ሄዶ መዘገብ አይችልም፡፡ ምክንያቱም በካምፖቹ ውስጥ ያለውን ኢሰብአዊ ድርጊት ያጋልጣል፡፡ ይህ ደግሞ ናውሩ የገቢ ምንጬን ሊጎዳብኝ ይችላል ትላለች፡፡ ናውሩን በዓመት የሚጎበኛት ሰው ከ200 አይበልጥም ይባላል፡፡ ቴሌግራፍ በአንድ ዘገባው በናውሩ እስከዛሬ የገባው ቱሪስት ቢደመር ከ15ሺህ አይበልጥም ሲል ጽፏል፡፡ በስፋት ቫቲካን ሲቲና ሞናኮ ብቻ ናቸው የሚበልጧት፤ ለዚህም ነው የዓለም ትንሽዋ ሪፐብሊክ ደሴት የምትባለው፡፡ ቱሪስት የአገሪቱ ገቢ ምንጭ አለመሆኑ በኮቪድ-19 አልተጎዳችም ማለት ግን አይደለም፡፡ ለጊዜው ከ10ሺህ ዜጎቼ አንድም ሰው ኮቪድ-19 አልያዘውም ብትልም ሕመሙ ግን ናውሩም ደርሷል፡፡ 8. ኪሪባቲ ኪሪባቲ የብጥስጣሽ ደሴቶች አገር በመሆኗ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ 4ሺህ ኪሎ ሜትር፣ ከሰሜን ደቡብ ደግሞ 2ሺህ ኪሎ ሜትር ታስኬዳች፡፡ ይህ ማለት ግን ይህ ሁሉ ርቀት ሰው የሚኖርበት ደረቅ መሬት ነው ማለት አይደለም፡፡ ነጻነቷን ያገኘችው ከእንግሊዝ በ1979 ዓ.ም ነው፡፡ በ1960ዎቹ ይቺ አገር አንዳንድ ደሴቶቿ ለእንግሊዝ የኑክሌር መሞከሪያ ሆነው አገልግለዋል፡፡ እንደ ብዙዎቹ የፓስፊክ ደቂቀ ደሴቶች ሁሉ ኪሪባቲም የዓለም ሙቀት መጨመር ከምድረ ገጽ ሊያጠፋት እንደሚችል ይገመታል፡፡ ኪሪባቲ ከፊጂ ደሴት መሬት ተከራይታ ምግብ ታመርታለች፡፡ ኢኮኖሚዋ ደካማ ሲሆን ኮኮናትና ኮፕራ በመላክ ነው የምትታወቀው፡፡ የዓሣ ማጥመድ ፍቃድ ለውጭ ኩባንያዎች እየቸበቸበች ኢኮኖሚዋን በከፊል ትደጉማለች፡፡ 9ኛ የሰለሞን ደሴቶች፤ 10ኛ ማይክሮኒዢያ በዝርዝሩ 9ኛ እና 10ኛ ላይ ያሉት የሰለሞን ደሴቶች እና ማይክሮኒዢያ ናቸው፡፡ ሁለቱም አገራት በዓሣ ምርትና በቱሪዝም ይታወቃሉ፡፡ ሁሉም በኮቪድ-19 የተጠቃ ዜጋ የለባቸውም፡፡ ይህ ዝርዝር ታዲያ ሰሜን ኮሪያና ቱርከሜኒስታን አላካተተም፡፡ ሆኖም እነዚህ ሁለት አገራት በይፋ ከኮቪድ-19 የያዘው ዜጋ አለም የለምም ብለው አያውቁም፡፡ ወይም አይታመኑ ይሆናል፡፡
https://www.bbc.com/amharic/news-53864759
5sports
‹‹ባል›› የብዙዎችን ሕይወት ይቀይራል የተባለለት የአፍሪካ አዲሱ የቅርጫት ኳስ ሊግ
‹‹አፍሪካ፤ መጥተናል፤ ጨዋታው ይጀመር›› በሚሉት ቃላት ነበር ለአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን የቅርጫት ኳስ ሊግ ወይም ባል ሴኔጋላዊ ፕሬዘዳንቱ አማዱ ጋሎ ፋል ያስጀመሩት፡፡ የመጀመሪያው የሊጉ ጨዋታ እሁድ በናይጄሪያ እና በሩዋንዳ መካከል ተካሂዶ ናይጄሪያ የመጀመሪያውን ጎል በማስቆጠር ታሪካዊ ብትሆንም ሩዋንዳ ጨዋታውን 83 ለ 60 ረትታለች፡፡ በሜዳዋ እና በደጋፊዎቿ ፊት የተጫወተችው ሩዋንዳ ክፍተኛ ድጋፍ እንደነበራትም ተዘግቧል፡፡ ‹‹ይሄ የብዙዎችን ህይወት ይቀይራል፡፡ በመላው አህጉሩ ላሉ ሰዎች ቤተሰቦቻቸውን ለመመገብ የሚያስችል እና ሌሎች በርካታ እድሎችን የሚፈጥር ነው›› ሲል የቀድሞው የኤን.ቢ.ኤ ተጫዋች እና አሁን ለናይጄሪያ ተሰልፎ የሚጫወተው ቤን ኡዞ ለቢቢሲ ስፖርት ተናግሯል፡፡ ‹‹ይህ የአፍሪካ ኤን ቢኤ ነው፣ እናም በዚህ አህጉር ለሚያድጉ ልጆች ይህ የራሴ ብለው የሚጠሩት እና የመጪውን ግዜ ተጫዋቾች የምናፈራበት ነው›› ሲልም አክሏል፡፡ የሊጉ ጨዋታዎች ከአንድ አመት በፊት እንዲጀመሩ እቅድ ተይዞላቸው የነበረ ቢሆንም በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለ14 ወራት ዘግይቶ ተጀምሯል፡፡ በዚህ የመጀመሪያው የውድድር አመት ከ12 አገራት የሚወጣጡ ቡድኖች የሚወዳደሩ ይሆናል፡፡ አንጎላ፣ ግብጽ፣ ሞሮኮ፣ ናይጄሪያ፣ ሴኔጋል እና ቱኒዚያ እንደሚሳተፉ ታውቋል፡፡ ቀሪ ስድስት ቡድኖች የማጣሪያ ጨዋታዎችን አድርገው ማሸነፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የዚህ አመት የሊጉ ጫዋታዎች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በሩዋንዳዋ ዋና ከተማ በሚገኛው እና 10 ሺህ ሰው በሚይዘው የኪጋሊ አሬና ይካሄዳል፡፡ በእያንዳንዱ ጨዋታም 1ሺህ500 አካባቢ ታዳሚዎች እና ተጋባዥ እንግዳዎች ይከታተሉታል፡፡ በሊጉ 26 ጨዋታዎች የሚደረጉ ሲሆን እስከ ፍፃሜው ጨዋታ ድረስ ሁለት ሳምንታትን የሚፈጅ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
‹‹ባል›› የብዙዎችን ሕይወት ይቀይራል የተባለለት የአፍሪካ አዲሱ የቅርጫት ኳስ ሊግ ‹‹አፍሪካ፤ መጥተናል፤ ጨዋታው ይጀመር›› በሚሉት ቃላት ነበር ለአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን የቅርጫት ኳስ ሊግ ወይም ባል ሴኔጋላዊ ፕሬዘዳንቱ አማዱ ጋሎ ፋል ያስጀመሩት፡፡ የመጀመሪያው የሊጉ ጨዋታ እሁድ በናይጄሪያ እና በሩዋንዳ መካከል ተካሂዶ ናይጄሪያ የመጀመሪያውን ጎል በማስቆጠር ታሪካዊ ብትሆንም ሩዋንዳ ጨዋታውን 83 ለ 60 ረትታለች፡፡ በሜዳዋ እና በደጋፊዎቿ ፊት የተጫወተችው ሩዋንዳ ክፍተኛ ድጋፍ እንደነበራትም ተዘግቧል፡፡ ‹‹ይሄ የብዙዎችን ህይወት ይቀይራል፡፡ በመላው አህጉሩ ላሉ ሰዎች ቤተሰቦቻቸውን ለመመገብ የሚያስችል እና ሌሎች በርካታ እድሎችን የሚፈጥር ነው›› ሲል የቀድሞው የኤን.ቢ.ኤ ተጫዋች እና አሁን ለናይጄሪያ ተሰልፎ የሚጫወተው ቤን ኡዞ ለቢቢሲ ስፖርት ተናግሯል፡፡ ‹‹ይህ የአፍሪካ ኤን ቢኤ ነው፣ እናም በዚህ አህጉር ለሚያድጉ ልጆች ይህ የራሴ ብለው የሚጠሩት እና የመጪውን ግዜ ተጫዋቾች የምናፈራበት ነው›› ሲልም አክሏል፡፡ የሊጉ ጨዋታዎች ከአንድ አመት በፊት እንዲጀመሩ እቅድ ተይዞላቸው የነበረ ቢሆንም በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለ14 ወራት ዘግይቶ ተጀምሯል፡፡ በዚህ የመጀመሪያው የውድድር አመት ከ12 አገራት የሚወጣጡ ቡድኖች የሚወዳደሩ ይሆናል፡፡ አንጎላ፣ ግብጽ፣ ሞሮኮ፣ ናይጄሪያ፣ ሴኔጋል እና ቱኒዚያ እንደሚሳተፉ ታውቋል፡፡ ቀሪ ስድስት ቡድኖች የማጣሪያ ጨዋታዎችን አድርገው ማሸነፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የዚህ አመት የሊጉ ጫዋታዎች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በሩዋንዳዋ ዋና ከተማ በሚገኛው እና 10 ሺህ ሰው በሚይዘው የኪጋሊ አሬና ይካሄዳል፡፡ በእያንዳንዱ ጨዋታም 1ሺህ500 አካባቢ ታዳሚዎች እና ተጋባዥ እንግዳዎች ይከታተሉታል፡፡ በሊጉ 26 ጨዋታዎች የሚደረጉ ሲሆን እስከ ፍፃሜው ጨዋታ ድረስ ሁለት ሳምንታትን የሚፈጅ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
https://www.bbc.com/amharic/news-57127671
5sports
በፕሪሚየር ሊጉ የጥር ወር የዝውውር መስኮት ማን ማንን አስፈረመ?
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የጥር ወር የዝውውር መስኮት በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ትናንት እኩለ ለሊት ላይ ተጠናቋል። ከዚህ በታች የትኞቹ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ማንን አስፈረሙ የሚለውን እንመለከታለን። ኒውካስትል ዩናይትድ ለጥቂት ሳምንታት በቆየው የዝውውር መስኮት በርካታ ተጫዋቾችን ካስፈረሙ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ቀዳሚ ስፍራን የሚይዘው ኒውካስትል ነው። ኒውካስትል ብሩኖ ጉዊማሬዝን ጨምሮ ስመ ጥር እግር ኳሰኞችን በዚህ የጥር ወር የዝውውር መስኮት መያዝ ችሏል። ብሩኖ ጉዊማሬዝን ከፈረንሳዩ ሊዮን በ35 ሚሊዮን ፓዎንድ ወደ ሴንት ጀምስ ፓርክ አምርቷል። ኒው ካስትል የግራ መስመር ተመላላሹን ማት ታርጌት ከአስተን ቪላ በውሰት ወስዷል። የ26 ዓመቱ ታርጌት እስከ የውድድር ዘመኑ መጨረሻ ድረስ በሴንት ጀምስ ፓርክ የሚቆይ ይሆናል። ከዚህ በተጨማሪም ኒውካስትል ዳን በርን ከብራይተን በ13 ሚሊዮን ፓውንድ በማስፈረም የተከላካይ መስመሩን አጠናክሯል። ክሪስ ውድ ከበርንሊ ወደ ኒውካስትል በ25 ሚሊዮን ፓውንድ ተዘዋውሯል። በጥሩ የዝውውር መስኮት ኒውካስትልን ከተቀላቀሉ ተጫዋቾች መካከል ብዙ ልምድ ያለው የ31 ዓመቱ ተከላካይ ኪረን ትሪፒየር ይገኝበታል። ቲሪፒየር እስከ ቀጣይ ዓመት የውድድር ዘመን ማብቂያ ድረስ በ12 ሚሊዮን ፓውንድ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ኒውካስትልን ተቀላቅሏል። ኤቨርተን ፍራንክ ላምፓርድን አሰልጣኙ አድርጎ የቀጠረው የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን በዚህ የዝውውር መስኮት ብዙ ተጫዋቾችን ካስፈረሙ ክለቦች መካከል አንዱ ነው። የኤቨርተን የጥር ወር ትልቁ ፈራሚ የቶተንሃም ተጫዋች የነበረው ዴሊ አሊ ነው። ዴሊ አሊ እስከ 40 ሚሊዮን ፓውንድ ሊደርስ በሚችል ወጪ ከሰሜን ለንደኑ ክለብ ወደ ሊቨርፑል ከተማ መጥቷል። ኤቨርተን ቢሊ ክሬሊን ከፍሊትዉድ ታውን ይፋ ባልተደረገ መጠን አዘዋውሯል። ሌላው የኤቨርተን የጥር ወር ትልቁ ፈራሚ የማንችስተር ዩናይትዱ ዶኒ ቫን ደ ቢክ ነው። በኦልትራፎርድ በቂ የጨዋታ ጊዜን እያሳለፈ ያልነበረው አማካዩ ቫን ደ ቢክ በውሰት ወደ ኤቨርተን አቅንቷል። ኤቨርተን የአስተን ቪላውን አንዋር ኤል ጋዚን በውሰት ሲወስድ ከሬንጀርስ ደግሞ የቀኝ ተመላላሹ ናታን ፒተርሰንን በ12 ሚሊዮን ፓውንድ ለአምስት ዓመታት አስፈርሟል። ሊቨርፑል ሌላኛው የመርሲሳይድ ክለብ ሊቨርፑል ሉዊዝ ዲያዝን ከፖርቶ አስመጥቷል። ክሎፕ ለኮሎምቢያዊው የክንፍ ተጫዋች 37 ሚሊዮን ፓውንድ በመክፈል ለቀጣይ አምስት ዓመታት አስፈርመውታል። ቶተንሃም የሰሜን ለንደኑ ክለብ ንዶምብሌን አሰናብቶ ሁለት የጁቬንቱስ ተጫዋቾችን ወደ ሰሜን ለንደን አምጥቷል። የኡራጋዩ አማካይ ሮድሪጎ ቤንታንኩር ለቀጣይ 4 ዓመታት በሰሜን ለንደኑ ክለብ ለመቆየት ውል ያኖረ ሲሆን፤ የስዊድኑ የክንፍ ተጫዋች ዴጃን ኩሉሴቪስኪ ለ18 ወራት በውሰት ቶተንሃምን ተቀላቅሏል። በሌላ በኩል ቶተንሃም ክብረ ወሰን በሆነ ዋጋ ያስፈረመውን ንዶምብሌን በውሰት ለሊዮን ሰጥቷል። አርጀንቲናዊው ጂኦቫኒ ሎ ሴልሶ ቪላሪያን እንዲሁም የ20 ዓመቱ ታዳጊ ብራያን ጊል ቫሌንሺያን እስከ ውድድሩ ዘመኑ መጠናቀቂያ በውሰት ተቀላቅለዋል። አስተን ቪላ ሉካስ ዲኘ ከኤቨርተን ወደ ቪላ በ25 ሚሊዮን ፓዎንድ ተዘዋውሯል። የፈረንሳዩ የግራ መስመር ተጫዋች በኤቨርተን ቆይታው ተመራጭ ሳይሆን በመቅረቱ ክለቡ እንዲለቀው ጥያቄ አቅርቦ ነበር ተብሏል። የበርካቶችን ቀልብ ስቦ የነበረው የስቲቨን ጄራርድ ፈራሚ ብራዚላዊው ፊሊፔ ኩቲኒዮ ነው። ኩቲንሆ በጥር ወር የዝውውር መስኮት ከባርሴሎና በውሰት ወደ ቪላ መጥቷል። ቪላዎች የአርሰናሉን ተከላካይ ካለም ቻምበርስን በነጻ ወስደዋል። ስዊዲናዊው ግብ ጠባቂ ሮቢን ኦሴን ከጣሊያኑ ሮማ አስንተን ቪላን በውሰት ተቀላቅሏል። ማንችስተር ሲቲ የፕሪሚየር ሊጉን ሰንጠረዥ በሰፊ የነጥብ ልዩነት እየመሩ የሚገኙት ሲቲዎች አርጀንቲናዊውን የፊት መስመር ተጫዋች ለአምስት ዓመታት አስፈርመዋል። ከሪቨር ፕሌት ሲቲን የተቀላቀለው ጁሊያን አልቫሬዝ እስከ ሐምሌ ድረስ በክለቡ ይቆያል። ብሬንትፎርድ የክርስቲያን ኤሪክሰን ወደ ፕሪሚየር ሊጉ መመለስ የበርካቶችን ልብ በደስታ ያሞቀ ይመስላል። የቀድሞ የቶተንሃም ተጫዋች በ2020 የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር አገሩን ዴንማርክን ወክሎ እየተጫወተ ሳለ በልብ ሕመም ተዝለፍልፎ ሜዳ ላይ ወድቆ እንደነበረ ይታወሳል። የ29 ዓመቱ ኤሪክሰን በአውሮፓ ዋንጫ ላይ ካጋጠመው ክስተት በኋላ እግር ኳስ ባይጫወትም፤ ብሬንትፎርድ ለስድስት ወራት አስፈርመውታል በተመሳሳይ አርሰናል በርካታ ተጫዋቾቹን ከኤሜሬትስ አሰናብቶ፤ ለአሁናዊ ችግሩ መፍትሄ ሊሰጥ የሚችል አዲስ ተጫዋች ወደ ኤሜሬትስ ማምጣት ተስኖታል። የሚኬል አርቴታው አርሰናል፤ ጎል አዳኙን ፒዬር ኦባሚያንግ በነጻ ለባርሴሎና አሳልፎ ሰጥቶ ተተኪውን አጥቂ ማስፈረም ሳይችል የውድድር መስኮቱ ተዘግቷል።
በፕሪሚየር ሊጉ የጥር ወር የዝውውር መስኮት ማን ማንን አስፈረመ? የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የጥር ወር የዝውውር መስኮት በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ትናንት እኩለ ለሊት ላይ ተጠናቋል። ከዚህ በታች የትኞቹ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ማንን አስፈረሙ የሚለውን እንመለከታለን። ኒውካስትል ዩናይትድ ለጥቂት ሳምንታት በቆየው የዝውውር መስኮት በርካታ ተጫዋቾችን ካስፈረሙ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ቀዳሚ ስፍራን የሚይዘው ኒውካስትል ነው። ኒውካስትል ብሩኖ ጉዊማሬዝን ጨምሮ ስመ ጥር እግር ኳሰኞችን በዚህ የጥር ወር የዝውውር መስኮት መያዝ ችሏል። ብሩኖ ጉዊማሬዝን ከፈረንሳዩ ሊዮን በ35 ሚሊዮን ፓዎንድ ወደ ሴንት ጀምስ ፓርክ አምርቷል። ኒው ካስትል የግራ መስመር ተመላላሹን ማት ታርጌት ከአስተን ቪላ በውሰት ወስዷል። የ26 ዓመቱ ታርጌት እስከ የውድድር ዘመኑ መጨረሻ ድረስ በሴንት ጀምስ ፓርክ የሚቆይ ይሆናል። ከዚህ በተጨማሪም ኒውካስትል ዳን በርን ከብራይተን በ13 ሚሊዮን ፓውንድ በማስፈረም የተከላካይ መስመሩን አጠናክሯል። ክሪስ ውድ ከበርንሊ ወደ ኒውካስትል በ25 ሚሊዮን ፓውንድ ተዘዋውሯል። በጥሩ የዝውውር መስኮት ኒውካስትልን ከተቀላቀሉ ተጫዋቾች መካከል ብዙ ልምድ ያለው የ31 ዓመቱ ተከላካይ ኪረን ትሪፒየር ይገኝበታል። ቲሪፒየር እስከ ቀጣይ ዓመት የውድድር ዘመን ማብቂያ ድረስ በ12 ሚሊዮን ፓውንድ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ኒውካስትልን ተቀላቅሏል። ኤቨርተን ፍራንክ ላምፓርድን አሰልጣኙ አድርጎ የቀጠረው የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን በዚህ የዝውውር መስኮት ብዙ ተጫዋቾችን ካስፈረሙ ክለቦች መካከል አንዱ ነው። የኤቨርተን የጥር ወር ትልቁ ፈራሚ የቶተንሃም ተጫዋች የነበረው ዴሊ አሊ ነው። ዴሊ አሊ እስከ 40 ሚሊዮን ፓውንድ ሊደርስ በሚችል ወጪ ከሰሜን ለንደኑ ክለብ ወደ ሊቨርፑል ከተማ መጥቷል። ኤቨርተን ቢሊ ክሬሊን ከፍሊትዉድ ታውን ይፋ ባልተደረገ መጠን አዘዋውሯል። ሌላው የኤቨርተን የጥር ወር ትልቁ ፈራሚ የማንችስተር ዩናይትዱ ዶኒ ቫን ደ ቢክ ነው። በኦልትራፎርድ በቂ የጨዋታ ጊዜን እያሳለፈ ያልነበረው አማካዩ ቫን ደ ቢክ በውሰት ወደ ኤቨርተን አቅንቷል። ኤቨርተን የአስተን ቪላውን አንዋር ኤል ጋዚን በውሰት ሲወስድ ከሬንጀርስ ደግሞ የቀኝ ተመላላሹ ናታን ፒተርሰንን በ12 ሚሊዮን ፓውንድ ለአምስት ዓመታት አስፈርሟል። ሊቨርፑል ሌላኛው የመርሲሳይድ ክለብ ሊቨርፑል ሉዊዝ ዲያዝን ከፖርቶ አስመጥቷል። ክሎፕ ለኮሎምቢያዊው የክንፍ ተጫዋች 37 ሚሊዮን ፓውንድ በመክፈል ለቀጣይ አምስት ዓመታት አስፈርመውታል። ቶተንሃም የሰሜን ለንደኑ ክለብ ንዶምብሌን አሰናብቶ ሁለት የጁቬንቱስ ተጫዋቾችን ወደ ሰሜን ለንደን አምጥቷል። የኡራጋዩ አማካይ ሮድሪጎ ቤንታንኩር ለቀጣይ 4 ዓመታት በሰሜን ለንደኑ ክለብ ለመቆየት ውል ያኖረ ሲሆን፤ የስዊድኑ የክንፍ ተጫዋች ዴጃን ኩሉሴቪስኪ ለ18 ወራት በውሰት ቶተንሃምን ተቀላቅሏል። በሌላ በኩል ቶተንሃም ክብረ ወሰን በሆነ ዋጋ ያስፈረመውን ንዶምብሌን በውሰት ለሊዮን ሰጥቷል። አርጀንቲናዊው ጂኦቫኒ ሎ ሴልሶ ቪላሪያን እንዲሁም የ20 ዓመቱ ታዳጊ ብራያን ጊል ቫሌንሺያን እስከ ውድድሩ ዘመኑ መጠናቀቂያ በውሰት ተቀላቅለዋል። አስተን ቪላ ሉካስ ዲኘ ከኤቨርተን ወደ ቪላ በ25 ሚሊዮን ፓዎንድ ተዘዋውሯል። የፈረንሳዩ የግራ መስመር ተጫዋች በኤቨርተን ቆይታው ተመራጭ ሳይሆን በመቅረቱ ክለቡ እንዲለቀው ጥያቄ አቅርቦ ነበር ተብሏል። የበርካቶችን ቀልብ ስቦ የነበረው የስቲቨን ጄራርድ ፈራሚ ብራዚላዊው ፊሊፔ ኩቲኒዮ ነው። ኩቲንሆ በጥር ወር የዝውውር መስኮት ከባርሴሎና በውሰት ወደ ቪላ መጥቷል። ቪላዎች የአርሰናሉን ተከላካይ ካለም ቻምበርስን በነጻ ወስደዋል። ስዊዲናዊው ግብ ጠባቂ ሮቢን ኦሴን ከጣሊያኑ ሮማ አስንተን ቪላን በውሰት ተቀላቅሏል። ማንችስተር ሲቲ የፕሪሚየር ሊጉን ሰንጠረዥ በሰፊ የነጥብ ልዩነት እየመሩ የሚገኙት ሲቲዎች አርጀንቲናዊውን የፊት መስመር ተጫዋች ለአምስት ዓመታት አስፈርመዋል። ከሪቨር ፕሌት ሲቲን የተቀላቀለው ጁሊያን አልቫሬዝ እስከ ሐምሌ ድረስ በክለቡ ይቆያል። ብሬንትፎርድ የክርስቲያን ኤሪክሰን ወደ ፕሪሚየር ሊጉ መመለስ የበርካቶችን ልብ በደስታ ያሞቀ ይመስላል። የቀድሞ የቶተንሃም ተጫዋች በ2020 የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር አገሩን ዴንማርክን ወክሎ እየተጫወተ ሳለ በልብ ሕመም ተዝለፍልፎ ሜዳ ላይ ወድቆ እንደነበረ ይታወሳል። የ29 ዓመቱ ኤሪክሰን በአውሮፓ ዋንጫ ላይ ካጋጠመው ክስተት በኋላ እግር ኳስ ባይጫወትም፤ ብሬንትፎርድ ለስድስት ወራት አስፈርመውታል በተመሳሳይ አርሰናል በርካታ ተጫዋቾቹን ከኤሜሬትስ አሰናብቶ፤ ለአሁናዊ ችግሩ መፍትሄ ሊሰጥ የሚችል አዲስ ተጫዋች ወደ ኤሜሬትስ ማምጣት ተስኖታል። የሚኬል አርቴታው አርሰናል፤ ጎል አዳኙን ፒዬር ኦባሚያንግ በነጻ ለባርሴሎና አሳልፎ ሰጥቶ ተተኪውን አጥቂ ማስፈረም ሳይችል የውድድር መስኮቱ ተዘግቷል።
https://www.bbc.com/amharic/news-60218464
2health
ኮሮናቫይረስ ፡ አውስትራሊያ 85 ሚሊዮን ክትባቶች ለዜጎቿ ልታቀርብ ነው
የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚንስትር አሁን እየበለጸጉ የሚገኙት ሁለቱ ክትባቶች ስኬታማ የሚሆኑ ከሆነ 85 ሚሊዮን ክትባቶችን መንግሥት ለሕዝቡ እንደሚያቀርብ አስታወቁ። ጠቅላይ ሚንስትር ስኮት ሞሪሰን አገራቸው የኮሮናቫይረስ ክትባት ለዜጎቿ በነጻ ለማቅረብ ሁለት የኮሮናቫይረስ ክትባቶችን ለመግዛት ስምምነቶችን ፈርማለች ብለዋል። እንደ ጠቅላይ ሚንስትሩ ከሆነ አውስትራሊያ ክትባቶቹን ለመግዛት 1.24 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ታደርጋለች። "25 ሚሊዮን አውስትራሊያውያን ከየካቲት 2013 ጀምሮ ክትባቱን ማግኘት ይችላሉ ለዚህ ግን ማረጋገጫ የለም" ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ስኮት የካቲት ላይ ለዜጎች ክትባቱን በነጻ ማቅረቡ መቶ በመቶ እርግጠኛ ባይሆንም የአገሪቱ የጤና ባለሙያዎች ክትባቶቹ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ይሁንታቸውን የሚሰጡ ከሆነ፤ አውስትራሊያ ክትባቶቹን ቀድማ እንደምታገኝ ጠቁመዋል። አንደኛው ክትባት በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እና በመድኃኒት አምራቹ ኩባንያ አስትራዜኔካ ጥምረት እየበለጸገ የሚገኝ ሲሆን፤ ሌላኛው ደግሞ በአውስትራሊያው ኩዊንስላንድ ዩኒቨርሲቲ እና ሲኤስኤል የሚመረት ነው። አውስትራሊያ ለመግዛት ውል ከያዘችው መካከል 33.8 ሚሊዮን ክትባት ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን 51 ሚሊዮን የሚሆነው ደግሞ በኩዊንስላንድ ዩኒቨርሲቲ የሚመረተውን ነው። በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እየተዘጋጀ የሚገኘው ክትባት በሦስተኛ ደረጃ ክሊኒካዊ ሙከራ ላይ የደረሰ ሲሆን በ30ሺህ ሰዎች ላይ ክትባቱ ተሞክሯል። በመላው ዓለም የሚገኙ አገራት የኮሮናቫይረስ ክትባት እንዲደርሳቸው የተለያዩ አይነት ጥረቶችን ሲያካሂዱ ቆይተዋል። ሐምሌ ወር ላይ የዓለም ጤና ድርጅት 165 የዓለም አገራት፤ ድሃ አገራት ክትባቱን ለዜጎቻቸው እንዲያደርሱ ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎት ማሳየታቸውን አስታውቆ ነበር። በዓለም ዙሪያ በአሁኑ ወቅት 140 የኮሮናቫይረስ ክትባቶችን ለማበልጸግ ምርምሮች እየተከናወኑ ይገኛሉ። አውስትራሊያ እስካሁን ድረስ ከ26ሺህ በላይ ዜጎቿ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሲሆን 769 ደግሞ ህይወታቸው አልፏል።
ኮሮናቫይረስ ፡ አውስትራሊያ 85 ሚሊዮን ክትባቶች ለዜጎቿ ልታቀርብ ነው የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚንስትር አሁን እየበለጸጉ የሚገኙት ሁለቱ ክትባቶች ስኬታማ የሚሆኑ ከሆነ 85 ሚሊዮን ክትባቶችን መንግሥት ለሕዝቡ እንደሚያቀርብ አስታወቁ። ጠቅላይ ሚንስትር ስኮት ሞሪሰን አገራቸው የኮሮናቫይረስ ክትባት ለዜጎቿ በነጻ ለማቅረብ ሁለት የኮሮናቫይረስ ክትባቶችን ለመግዛት ስምምነቶችን ፈርማለች ብለዋል። እንደ ጠቅላይ ሚንስትሩ ከሆነ አውስትራሊያ ክትባቶቹን ለመግዛት 1.24 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ታደርጋለች። "25 ሚሊዮን አውስትራሊያውያን ከየካቲት 2013 ጀምሮ ክትባቱን ማግኘት ይችላሉ ለዚህ ግን ማረጋገጫ የለም" ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ስኮት የካቲት ላይ ለዜጎች ክትባቱን በነጻ ማቅረቡ መቶ በመቶ እርግጠኛ ባይሆንም የአገሪቱ የጤና ባለሙያዎች ክትባቶቹ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ይሁንታቸውን የሚሰጡ ከሆነ፤ አውስትራሊያ ክትባቶቹን ቀድማ እንደምታገኝ ጠቁመዋል። አንደኛው ክትባት በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እና በመድኃኒት አምራቹ ኩባንያ አስትራዜኔካ ጥምረት እየበለጸገ የሚገኝ ሲሆን፤ ሌላኛው ደግሞ በአውስትራሊያው ኩዊንስላንድ ዩኒቨርሲቲ እና ሲኤስኤል የሚመረት ነው። አውስትራሊያ ለመግዛት ውል ከያዘችው መካከል 33.8 ሚሊዮን ክትባት ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን 51 ሚሊዮን የሚሆነው ደግሞ በኩዊንስላንድ ዩኒቨርሲቲ የሚመረተውን ነው። በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እየተዘጋጀ የሚገኘው ክትባት በሦስተኛ ደረጃ ክሊኒካዊ ሙከራ ላይ የደረሰ ሲሆን በ30ሺህ ሰዎች ላይ ክትባቱ ተሞክሯል። በመላው ዓለም የሚገኙ አገራት የኮሮናቫይረስ ክትባት እንዲደርሳቸው የተለያዩ አይነት ጥረቶችን ሲያካሂዱ ቆይተዋል። ሐምሌ ወር ላይ የዓለም ጤና ድርጅት 165 የዓለም አገራት፤ ድሃ አገራት ክትባቱን ለዜጎቻቸው እንዲያደርሱ ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎት ማሳየታቸውን አስታውቆ ነበር። በዓለም ዙሪያ በአሁኑ ወቅት 140 የኮሮናቫይረስ ክትባቶችን ለማበልጸግ ምርምሮች እየተከናወኑ ይገኛሉ። አውስትራሊያ እስካሁን ድረስ ከ26ሺህ በላይ ዜጎቿ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሲሆን 769 ደግሞ ህይወታቸው አልፏል።
https://www.bbc.com/amharic/news-54053426
2health
የኮቪድ ወረርሽኝ ትልቅ አደጋ ነው - ኪም ጆንግ ኡን
በሰሜን ኮሪያ በፍጥነት እየተዛመተ ያለው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለሀገሪቱ "ትልቅ አደጋ" ነው ሲሉ መሪዋ ኪም ጆንግ ኡን መናገራቸውን የመንግሥት ሚዲያዎች ዘግበዋል። ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሮናቫይረስ ሞት መመዝገቡን ያስታወቀችው ሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም በያዝነው ሳምንት ቅዳሜ ዕለት ባደረጉት አስቸኳይ ስብሰባ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ሁለንተናዊ ትግል እንዲደረግ ጠይቀዋል። ባለስልጣናቱ በያዝነው ሳምንት ሃሙስ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች መገኘታቸው መረጋገጡን አስታውቀዋል። ባለሙያዎች በበኩላቸው አሁን ተያዙ የተባሉት የመጀመሪያ እንዳልሆኑና ለተወሰነ ጊዜ እየተዛመተ ነበር ይላሉ። በሰሜን ኮሪያ ወረርሽኙ ከፍኛ ሊሆን እንደሚችልና አስከፊ መዘዝ ሊያስከትል ይችላል የሚል ስጋትም ጭሯል። 25 ሚሊዮን ነዋሪዎቿ በክትባት መርሃ ግብር እጥረት እና በደካማ የጤና አጠባበቅ ስርአት ምክንያት ለአደጋ የተጋለጡ መሆናቸውም ተገልጿል። ባለፉት ሳምንታት ውስጥ ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ በማይታወቅ ትኩሳት እንደተጠቁ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ቅዳሜ እለት ዘግበዋል። የሃገሪቱ የመመርመር አቅምም የተገደበ በመሆኑ በኮቪድ-19 ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ አልተረጋገጠም። ይህ አኃዝ አርብ እና ሐሙስ ከፍተኛ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን ይህም ሁኔታ በሰሜን ኮሪያ እየተከሰተ ስላለው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ አንዳንድ ፍንጮችን ይሰጣል ተብሏል። "የከፋው ወረርሽኝ በአገራችን ላይ የወደቀ ትልቅ አደጋ ነው" በማለት መሪው መናገራቸውን የኬ ሲ ኤንኤ የዜና ወኪል ዘግቧል። ኪም ለዚህ ችግር መንስኤ ያሉትን የቢሮክራሲ ቀውስ እና የህክምና ብቃት ማነስ እንደሆነ ጠቁመው እንደ ጎረቤት ቻይና ካሉ ሀገራት ምላሽ መማር እንደሚቻልም ጠቁመዋል። ከሚያዝያ ወር ጀምሮ 27 ሰዎች ትኩሳት ካጋጠማቸው በኋላ መሞታቸውን የመንግስት ሚዲያዎች ዘግበዋል። በዋና ከተማዋ ፒዮንግያንግ በኦሚክሮን ልውጥ ከሞተው አንድ ሰው በስተቀር እነዚህ ግለሰቦች ኮቪድ- 19 ተይዘው ነበር ወይ ስለሚለው ጉዳይ ሪፖርቶቹ ያሉት ነገር የለም።
የኮቪድ ወረርሽኝ ትልቅ አደጋ ነው - ኪም ጆንግ ኡን በሰሜን ኮሪያ በፍጥነት እየተዛመተ ያለው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለሀገሪቱ "ትልቅ አደጋ" ነው ሲሉ መሪዋ ኪም ጆንግ ኡን መናገራቸውን የመንግሥት ሚዲያዎች ዘግበዋል። ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሮናቫይረስ ሞት መመዝገቡን ያስታወቀችው ሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም በያዝነው ሳምንት ቅዳሜ ዕለት ባደረጉት አስቸኳይ ስብሰባ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ሁለንተናዊ ትግል እንዲደረግ ጠይቀዋል። ባለስልጣናቱ በያዝነው ሳምንት ሃሙስ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች መገኘታቸው መረጋገጡን አስታውቀዋል። ባለሙያዎች በበኩላቸው አሁን ተያዙ የተባሉት የመጀመሪያ እንዳልሆኑና ለተወሰነ ጊዜ እየተዛመተ ነበር ይላሉ። በሰሜን ኮሪያ ወረርሽኙ ከፍኛ ሊሆን እንደሚችልና አስከፊ መዘዝ ሊያስከትል ይችላል የሚል ስጋትም ጭሯል። 25 ሚሊዮን ነዋሪዎቿ በክትባት መርሃ ግብር እጥረት እና በደካማ የጤና አጠባበቅ ስርአት ምክንያት ለአደጋ የተጋለጡ መሆናቸውም ተገልጿል። ባለፉት ሳምንታት ውስጥ ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ በማይታወቅ ትኩሳት እንደተጠቁ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ቅዳሜ እለት ዘግበዋል። የሃገሪቱ የመመርመር አቅምም የተገደበ በመሆኑ በኮቪድ-19 ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ አልተረጋገጠም። ይህ አኃዝ አርብ እና ሐሙስ ከፍተኛ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን ይህም ሁኔታ በሰሜን ኮሪያ እየተከሰተ ስላለው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ አንዳንድ ፍንጮችን ይሰጣል ተብሏል። "የከፋው ወረርሽኝ በአገራችን ላይ የወደቀ ትልቅ አደጋ ነው" በማለት መሪው መናገራቸውን የኬ ሲ ኤንኤ የዜና ወኪል ዘግቧል። ኪም ለዚህ ችግር መንስኤ ያሉትን የቢሮክራሲ ቀውስ እና የህክምና ብቃት ማነስ እንደሆነ ጠቁመው እንደ ጎረቤት ቻይና ካሉ ሀገራት ምላሽ መማር እንደሚቻልም ጠቁመዋል። ከሚያዝያ ወር ጀምሮ 27 ሰዎች ትኩሳት ካጋጠማቸው በኋላ መሞታቸውን የመንግስት ሚዲያዎች ዘግበዋል። በዋና ከተማዋ ፒዮንግያንግ በኦሚክሮን ልውጥ ከሞተው አንድ ሰው በስተቀር እነዚህ ግለሰቦች ኮቪድ- 19 ተይዘው ነበር ወይ ስለሚለው ጉዳይ ሪፖርቶቹ ያሉት ነገር የለም።
https://www.bbc.com/amharic/news-61454622
5sports
እየተካሄደ ስላለው የአፍሪካ ዋንጫ ሊያውቋቸው የሚገቡ አንኳር ነጥቦች
የፈረንጆቹ 2022 የመጀመሪያውና ትልቁ የእግር ኳስ ድግስ በሚቀጥለው እሑድ በካሜሩን መዲና ያውንዴ ይጀመራል። የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግን ጨምሮ በሌሎች ሊጎች የምናውቃቸው ኮከቦች መናኸሪያቸውን ካሜሩን አድርገዋል። በመክፈቻው ጨዋታ አዘጋጇ ካሜሩን ቡርኪና ፋሶን ታስተናግዳለች። ለጥቆ ደግሞ ኢትዮጵያ ከኬፕ ቨርድ ትገናኘለች። የዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ሊካሄድ የነበረው ባለፈው ዓመት ጥር ነበር። ነገር ግን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በአንድ ዓመት ተራዝሞ ወደ ዘንድሮ ተሸጋግሯል። የአፍሪካ እግር ኳስ አስተዳዳሪ ካፍ ባለፈው ወር ውድድሩን በኦሚክሮን ዝርያ መስፋፋት ምክንያት ያራዝመዋል ተብሎ የተናፈሰው ወሬ ሃሰት ነው ማለቱ ይታወሳል። የቀድሞው የአርሰናልና የእንግሊዝ አጥቂ የነበረው ኢያን ራይት መገናኛ ብዙሃን ስለአፍሪካ ዋንጫ ሲዘግቡ "በንቀትና የዘረኝነት መንፈስ ተላብሰው ነው" ሲል ወቅሶ ነበር። የጨዋታው ሰንጠረዥ ምን ይመስላል? የአፍሪካ ዋንጫ 24 ብሔራዊ ቡድኖችን ያሳትፋል። ይህ በውደድሩ ታሪክ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ይህ ማለት እያንዳንዳቸው አራት ቡድኖችን ያቀፉ ስድስት ምድቦች አሉት ማለት ነው። ከእነዚህ መካከል አንደኛና ሁለተኛ የሚወጡት ወደ ቀጣዩ ዙር በቀጥታ ሲያልፉ፤ አራት ምርጥ ሶስተኛ ቡድኖችም ወደ ዙር 16ን ይቀላቀላሉ። የምድብ ጨዋታዎች ቀን 10 ሰዓት እንዲሁም ምሽት 1 ሰዓትና ማታ 4 ሰዓት ይከናወናሉ። በቀጣዩ የጥሎ ማለፍ ውድድር ጊዜ ደግሞ `ጨዋታዎቹ ማታ 1 እና 4 ሰዓት ይታያሉ። ለዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ጥቅም ላይ የሚውለው ኳስ ቶጉ የሚባል ካሜሩን ውስጥ ታዋቂ ከሆነ ጨርቅ ስሙን ያገኘ ኳስ ነው። ለዋንጫ እነማን ይፎካከራሉ? በማንችስተር ሲቲው የክንፍ ተጫዋች የምትመራው ያለፈው የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ አልጄሪያን ለዋንጫው አለማጨት ከባድ ነው። የሳድዮ ማኔ ሃገር ሴኔጋል በአፍሪካ ብሔራዊ ቡድኖች ሰንጠረዥ አናት ላይ የምትገኝ ሲሆን ባለፈው የአፍሪካ ዋንጫ በአልጄሪያ ተረታ ሁለተኛ መሆኗ አይዘነጋም። ያለፉትን 34 ጨዋታዎች ሽንፈት ካላስተናገደችው አልጄሪያና ከሴኔጋል ቀጥሎ በወቅቱ የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ኮከብ ሞሐመድ ሳላህ የምትመራው ግብፅም ስሟ ለዋንጫ ከሚቀናቀኑ መካከል ይነሳል። ግብፅ የአፍሪካ ዋንጫ ለሰባት ጊዜ በማንሳት የሚገዳደራት የለም። ጋና እና ናይረጄሪያ በአፍሪካ በጣም ውጤታማ ከሚባሉ ብሔራዊ ቡድኖች መካከል ቢሆኑም ለ2022 የዓለም ዋንጫ ያደረጉት ጉዞ ግን ብዙም አሳማኝ አልነበረም። ለስድስተኛ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን ለማንሳት የምትፋለመው ካሜሩን ደግሞ በሕዝቧ ፊት ዋንጫውን ለማስቀረት ትጥራለች። የዓለም ዋንጫ የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ጨዋታዎችን ያለምንም ሽንፈት ያከናወነችው ማሊ የውድድሩ ክስተት ልትሆን ትችላለች። አይቮሪ ኮስት፣ ሞሮኮና ቱኒዚያም ከዚህ በፊት ውድድሩን ያነሱ ቡድኖች ሲሆኑ ኮሞሮስና ጋምቢያ ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሳተፉ ይሆናል። ውድድሩ የሚካሄድበት ወቅት አንዳንድ የአውሮፓ ሊግ ክለቦች ተጫዋቾችን በዚህ ወቅት አንለቅም በማለት ብዙ ግርግር አስነስተው ነበር። ዋትፈርድ የተሰኘው የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ክለብ ለምሳሌ የናይጄሪያውን ኢማኔኤል ዴኒስ አልለቅም በማለት ክርክር አስነስቶ ነበር። ቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ በሚቀጥለው ዓመት ሰኔና ሐምሌ በአይቮሪ ኮስት አዘጋጅነት ይካሄዳል። የፊፋው አለቃ ጂያኒ ኢንፋንቲኖ የብሔራዊ ቡድን ውድድሮች በመስከረምና ኅዳር መካከል ይከናወኑ የሚል ሐሳብ አቅርበዋል። የኮሮናቫይረስ ጉዳይ? ወረርሽኙ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ ጥላውን ማንዣበቡ አልቀረም። ካፍም የታዳሚዎችን ቁጥር 60 በመቶ ቀንሷል። አዘጋጇ ካሜሩን የምታደርጋቸው ፍልሚያዎች 80 በመቶ ታዳሚ እንዲኖራቸውና ሁለት ጊዜ የተከተቡና የኮቪድ ውጤታቸው ኔጌቲቭ የሆኑ ሰዎች ናቸው ወደ ስታድዬም መግባት የሚችሉት። እስካሁን 2 በመቶ ሕዝቧ ብቻ የተከተበው ካሜሩን በሚቀጥሉት 30 ቀናት ሕዝቧ ለጨዋታው በማለት ወደ ክትባት ጣቢያዎች ያመራ ይሆን የሚለው አጓጊ ሆኗል። በኢትዮጵያ ምድብ የምትገኘው ኬፕ ቨርደን ጨምሮ የተወሰኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫቾች እንዲሁም ጋምቢያ ልምምድ እያደረጉ በሚገኙበት ካምፕ ወረርሽኙ አግኝቷቸው ነበር። የ2019 የአፍሪካ ዋንጫን እንድታስተናግድ ተመርጣ የነበረችው ካሜሩን በቂ መሠረተ ልማት የላትም ተብሎ ውድድሩ ወደ ግብፅ መዛወሩ ይታወሳል። ካሜሩን የደህንነት ጉዳይም ያሳስባታል። በደቡብ ምዕራብ የምትገኘው የሊምቤ ከተማ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በታጣቂዎች ጥቃት እየታመሰች ትገኛለች። ውድድሩን እንዴት መከታተል እችላለሁ? ቢቢሲ፤ ሁለት የሩብ ፍፃሜ ፍልሚያዎች፣ ሁለት የግማሽ ፍፃሜ ግጥሚያችና ፍፃሜውን ጨምሮ 10 የተመረጡ ጨዋታዎችን ያስተላልፋል። ስካይ ስፖርት የተሰኘው ጣቢያ ሁሉንም ጨዋታዎች በቴሌቪዥን ሲያስተላልፍ፤ ሱፐርስፖርት፣ ቤይንስፖርትና ካናልፕላስ ካሜሩን ተገኝተው ውድድሩን በቴሌቪዥን መስኮት ከሚያቀርቡ መካከል ናቸው። የቢቢሲ ስፖርት ድረ-ገፅ ደግሞ ከስር ከስር ሁሉንም ክስተቶች እየተከታተለ ይዘግብላችኋል።
እየተካሄደ ስላለው የአፍሪካ ዋንጫ ሊያውቋቸው የሚገቡ አንኳር ነጥቦች የፈረንጆቹ 2022 የመጀመሪያውና ትልቁ የእግር ኳስ ድግስ በሚቀጥለው እሑድ በካሜሩን መዲና ያውንዴ ይጀመራል። የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግን ጨምሮ በሌሎች ሊጎች የምናውቃቸው ኮከቦች መናኸሪያቸውን ካሜሩን አድርገዋል። በመክፈቻው ጨዋታ አዘጋጇ ካሜሩን ቡርኪና ፋሶን ታስተናግዳለች። ለጥቆ ደግሞ ኢትዮጵያ ከኬፕ ቨርድ ትገናኘለች። የዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ሊካሄድ የነበረው ባለፈው ዓመት ጥር ነበር። ነገር ግን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በአንድ ዓመት ተራዝሞ ወደ ዘንድሮ ተሸጋግሯል። የአፍሪካ እግር ኳስ አስተዳዳሪ ካፍ ባለፈው ወር ውድድሩን በኦሚክሮን ዝርያ መስፋፋት ምክንያት ያራዝመዋል ተብሎ የተናፈሰው ወሬ ሃሰት ነው ማለቱ ይታወሳል። የቀድሞው የአርሰናልና የእንግሊዝ አጥቂ የነበረው ኢያን ራይት መገናኛ ብዙሃን ስለአፍሪካ ዋንጫ ሲዘግቡ "በንቀትና የዘረኝነት መንፈስ ተላብሰው ነው" ሲል ወቅሶ ነበር። የጨዋታው ሰንጠረዥ ምን ይመስላል? የአፍሪካ ዋንጫ 24 ብሔራዊ ቡድኖችን ያሳትፋል። ይህ በውደድሩ ታሪክ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ይህ ማለት እያንዳንዳቸው አራት ቡድኖችን ያቀፉ ስድስት ምድቦች አሉት ማለት ነው። ከእነዚህ መካከል አንደኛና ሁለተኛ የሚወጡት ወደ ቀጣዩ ዙር በቀጥታ ሲያልፉ፤ አራት ምርጥ ሶስተኛ ቡድኖችም ወደ ዙር 16ን ይቀላቀላሉ። የምድብ ጨዋታዎች ቀን 10 ሰዓት እንዲሁም ምሽት 1 ሰዓትና ማታ 4 ሰዓት ይከናወናሉ። በቀጣዩ የጥሎ ማለፍ ውድድር ጊዜ ደግሞ `ጨዋታዎቹ ማታ 1 እና 4 ሰዓት ይታያሉ። ለዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ጥቅም ላይ የሚውለው ኳስ ቶጉ የሚባል ካሜሩን ውስጥ ታዋቂ ከሆነ ጨርቅ ስሙን ያገኘ ኳስ ነው። ለዋንጫ እነማን ይፎካከራሉ? በማንችስተር ሲቲው የክንፍ ተጫዋች የምትመራው ያለፈው የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ አልጄሪያን ለዋንጫው አለማጨት ከባድ ነው። የሳድዮ ማኔ ሃገር ሴኔጋል በአፍሪካ ብሔራዊ ቡድኖች ሰንጠረዥ አናት ላይ የምትገኝ ሲሆን ባለፈው የአፍሪካ ዋንጫ በአልጄሪያ ተረታ ሁለተኛ መሆኗ አይዘነጋም። ያለፉትን 34 ጨዋታዎች ሽንፈት ካላስተናገደችው አልጄሪያና ከሴኔጋል ቀጥሎ በወቅቱ የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ኮከብ ሞሐመድ ሳላህ የምትመራው ግብፅም ስሟ ለዋንጫ ከሚቀናቀኑ መካከል ይነሳል። ግብፅ የአፍሪካ ዋንጫ ለሰባት ጊዜ በማንሳት የሚገዳደራት የለም። ጋና እና ናይረጄሪያ በአፍሪካ በጣም ውጤታማ ከሚባሉ ብሔራዊ ቡድኖች መካከል ቢሆኑም ለ2022 የዓለም ዋንጫ ያደረጉት ጉዞ ግን ብዙም አሳማኝ አልነበረም። ለስድስተኛ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን ለማንሳት የምትፋለመው ካሜሩን ደግሞ በሕዝቧ ፊት ዋንጫውን ለማስቀረት ትጥራለች። የዓለም ዋንጫ የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ጨዋታዎችን ያለምንም ሽንፈት ያከናወነችው ማሊ የውድድሩ ክስተት ልትሆን ትችላለች። አይቮሪ ኮስት፣ ሞሮኮና ቱኒዚያም ከዚህ በፊት ውድድሩን ያነሱ ቡድኖች ሲሆኑ ኮሞሮስና ጋምቢያ ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሳተፉ ይሆናል። ውድድሩ የሚካሄድበት ወቅት አንዳንድ የአውሮፓ ሊግ ክለቦች ተጫዋቾችን በዚህ ወቅት አንለቅም በማለት ብዙ ግርግር አስነስተው ነበር። ዋትፈርድ የተሰኘው የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ክለብ ለምሳሌ የናይጄሪያውን ኢማኔኤል ዴኒስ አልለቅም በማለት ክርክር አስነስቶ ነበር። ቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ በሚቀጥለው ዓመት ሰኔና ሐምሌ በአይቮሪ ኮስት አዘጋጅነት ይካሄዳል። የፊፋው አለቃ ጂያኒ ኢንፋንቲኖ የብሔራዊ ቡድን ውድድሮች በመስከረምና ኅዳር መካከል ይከናወኑ የሚል ሐሳብ አቅርበዋል። የኮሮናቫይረስ ጉዳይ? ወረርሽኙ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ ጥላውን ማንዣበቡ አልቀረም። ካፍም የታዳሚዎችን ቁጥር 60 በመቶ ቀንሷል። አዘጋጇ ካሜሩን የምታደርጋቸው ፍልሚያዎች 80 በመቶ ታዳሚ እንዲኖራቸውና ሁለት ጊዜ የተከተቡና የኮቪድ ውጤታቸው ኔጌቲቭ የሆኑ ሰዎች ናቸው ወደ ስታድዬም መግባት የሚችሉት። እስካሁን 2 በመቶ ሕዝቧ ብቻ የተከተበው ካሜሩን በሚቀጥሉት 30 ቀናት ሕዝቧ ለጨዋታው በማለት ወደ ክትባት ጣቢያዎች ያመራ ይሆን የሚለው አጓጊ ሆኗል። በኢትዮጵያ ምድብ የምትገኘው ኬፕ ቨርደን ጨምሮ የተወሰኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫቾች እንዲሁም ጋምቢያ ልምምድ እያደረጉ በሚገኙበት ካምፕ ወረርሽኙ አግኝቷቸው ነበር። የ2019 የአፍሪካ ዋንጫን እንድታስተናግድ ተመርጣ የነበረችው ካሜሩን በቂ መሠረተ ልማት የላትም ተብሎ ውድድሩ ወደ ግብፅ መዛወሩ ይታወሳል። ካሜሩን የደህንነት ጉዳይም ያሳስባታል። በደቡብ ምዕራብ የምትገኘው የሊምቤ ከተማ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በታጣቂዎች ጥቃት እየታመሰች ትገኛለች። ውድድሩን እንዴት መከታተል እችላለሁ? ቢቢሲ፤ ሁለት የሩብ ፍፃሜ ፍልሚያዎች፣ ሁለት የግማሽ ፍፃሜ ግጥሚያችና ፍፃሜውን ጨምሮ 10 የተመረጡ ጨዋታዎችን ያስተላልፋል። ስካይ ስፖርት የተሰኘው ጣቢያ ሁሉንም ጨዋታዎች በቴሌቪዥን ሲያስተላልፍ፤ ሱፐርስፖርት፣ ቤይንስፖርትና ካናልፕላስ ካሜሩን ተገኝተው ውድድሩን በቴሌቪዥን መስኮት ከሚያቀርቡ መካከል ናቸው። የቢቢሲ ስፖርት ድረ-ገፅ ደግሞ ከስር ከስር ሁሉንም ክስተቶች እየተከታተለ ይዘግብላችኋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59904953
0business
3.7 ቢሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸው የብር ኖቶች ምን ይዘዋል?
የወረቀት የብር ኖቶች በኢትዮጵያ የግብይት ሥርዓት ውስጥ ጥቅም ላይ መዋል ከጀመሩ በኋላ አገሪቱ ለ7ኛ ጊዜ የብር ኖቶች ለውጥ ማድረጓን መስከረም 04/2013 ዓ.ም ይፋ ተደርጓል። በብዙዎች ዘንድ የባንክ ኖቶች ለውጥ ሊኖር ይችላል የሚለው ግምት መነገር ከጀመረ ጥቂት ዓመታት ተቆጥረዋል። አሁን ግን አዲሱ ዓመት በገባ በአራተኛው ቀን ምንም ነገር ሳይሰማ ይፋ የተደረገው የብር ለውጥ አገሪቱ እያካሄደችው ካለው የምጣኔ ሀብት ማሻሻያ እርምጃዎች ውስጥ አንዱ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ብር በዘመናት ሂደት ውስጥ በርካታ ለውጦችን ያስተናገደ ሲሆን፤ ከዋጋ አንጻርም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ አሁን ካለበት ደረጃ ላይ ደርሷል። ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርና የሐሰተኛ የብር ኖት በገበያው ውስጥ በተደጋጋሚ መከሰታቸው በተለያዩ ጊዜያት ሲዘገብ ቆይቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የብር ለውጡ ለሕገ ወጥ ተግባራት የሚውለውን ገንዘብ ለማስቀረት፣ ሙስናንና የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴዎችን ለመቆጣጠር ይረዳል ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት በአገሪቱ ያጋጠመውን የማክሮ ኢኮኖሚ ሚዛን መዛባትን ለማስተካከል ባለፉት ሁለት ዓመታት የተለያዩ ጥረቶች በመደረጋቸው ምጣኔ ሀብቱ ከነበረበት ችግር በመውጣት በማንሰራራት ላይ መሆኑን አመልክተዋል። ጨምረውም በአገሪቱ ያለውን የዋጋ ንረት የመቆጣጠሩ ተግባር በሚፈለገው መጠን ማከናወን እንዳልተቻለ ጠቅሰው፤ ለዚህ ደግሞ ከባንክ ውጪ የሚንቀሳቀስ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ መኖሩ ደግሞ ችግሩን በማባባሱ የብር ኖት መቀየር አንድ መፍትሄ መሆኑን ተናግረዋል። ምን ተለወጠ? አዲሶቹ የብር ኖቶች ቀደም ሲል ከነበሩት በተሻለ ለአጠቃቀም ምቹና ረዥም ጊዜ እንዲያገለግሉ ተደርገው መሰራታቸ የተገለጸ ሲሆን፤ ኖቶቹን በመቀየሩ ሥራ ለህትመት ብቻ በአጠቃላይ 3 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ወጪ እንደተደረገ ተነግሯል። ከቀለም አንጻር አዲሱ ባለ 200 ብር ኖት ሐምራዊ፣ ባለ100 ብር ኖት ውሃ ሰማያዊ፣ ባለ50 ብር ኖት ቀይ ብርቱካናማ፣ ባለ10 ብር ኖት ደግሞ አረንጓዴ ቀለም አላቸው። ቀደም ሲል በዝውውር ውስጥ የቆየው የባለ5 ብር ኖት ለውጥ ሳይደረግበት በሥራ ላይ የሚቆይ ሲሆን፤ ነገር ግን የወረቀት ገንዘቡ ቀስ በቀስ በሳንቲም እንደሚተካ ተገልጿል። በአዳዲሶቹ የብር ኖቶች ላይ ቀደም ሲል በነበሩት ላይ ያልነበሩ የአገሪቱን ገጽታ የሚያሳዩ ምስሎች የተካተቱበት ሲሆን፤ በዚህም በባለ አስር ብር ኖት ላይ ግመል፣ በባለ መቶ ብር ኖት ላይ ደግሞ የሶፍ ኡመር ዋሻና የሐረር ግንብ እንዲካተቱባቸው ተደርጓል። ከባንክ ውጪ ያለ ብር የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ እንዳመለከቱት "ከኢትዮጵያ ውጪ በጎረቤት አገራት ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው የኢትዮጵያ ብር ተከማችቶ ይገኛል።" ከብር ለውጡ ጋር ተያይዞም በውጪ አገራት ውስጥ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብር ወደ አገር ውስጥ እንዳይገባ ከፍተኛ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ባለፈው ዓመት ብሔራዊ ባንክ ያወጣው ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ በቤት ውስጥ ማስቀመጥ የሚከለክለው ሕግም ተግባራዊ መሆኑ የሚቀጥል ሲሆን፤ ይህንን ደንብ በመተላለፍ የሚንቀሳቀስ ገንዘብ በቁጥጥር ስር ውሎ ለመንግሥት አገልግሎት ይውላል። ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ በየጊዜው ድንገተኛ ፍተሻ እንደሚኖርም ተገልጿል። የብር ለውጥ ሂደት ላለፉት 23 ዓመታት በዝውውር ላይ የነበሩትን የብር ኖቶች ከገበያ በማስወጣት በአዲሶቹ የመተካቱ ሂደት በሚቀጥሉት ሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ እንደሚከናወን የጊዜ ሰሌዳ ተቀምጧል። ነገር ግን አሮጌዎቹን የብር ኖቶች በአዲስ በመተካቱ ሂደት ውስጥ 100 ሺህ እና ከዚያ በላይ ብር ያላቸው ሰዎች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ መቀየር እንዳለባቸው ተገልጿል። በዚህ ሂደት ውስጥ እስከ 10 ሺህ ብር ድረስ ለሚደረግ የብር ለውጥ ቀጥታ ገንዘቡን በመስጠት የሚከናወን ሲሆን፤ ከአስር ሺህ ብር በላይ የሚቀየር ከሆነ ደግሞ ብሩን ለመለወጥ ባመጣው ግለሰብ ስም የባንክ ደብተር ተከፍቶ እንዲቀመጥ ይደረጋል ተብሏል። የደኅንነት ገጽታዎች ይፋ የተደረጉት አዳዲሶቹ የብር ኖቶች አስመስለው የሚሰሩ ሐሰተኛ የብር ኖቶችን ለመከላከልና ለመለየት በሚያስችል ሁኔታ የተለያዩ የደኅንነት መጠበቂያ ገጽታዎች እንዲኖሯቸው ተደርጓል። በተጨማሪም ለዓይነ ስውራን አጠቃቀም እንዲያመች የመለያ ምልክት ያለው ሲሆን፤ በዚህም ዓይነ ስውራን የብሩን ዋጋ በእጅ ዳሰሳ ማወቅ የሚችሉበት ምልክትና የደኅንነት መጠበቂያ ገጽታ አላቸው። ከዚህ ባሻገርም የብር ኖቱ ወደ ላይ ወይም ወደታች በሚንቀሳቀስበት ጊዜ ደማቅ የቀለም ፍንጣቂ የደኅንነት መጠበቂያ ገጽታ ያለው ሲሆን፤ የብር ኖቶቱ በእጅ ሲዳሰሱ የመጎርበጥ ስሜት እንዲሁም የብሩ ዋጋ ይታያል። አዲሶቹ ኖቶች ተጨማሪ ባለቀለም ኮከብ የደኅንነት ገጽታን ከማካተታቸው ባሻገር አብረቅራቂ የደኅንነት መጠበቂያ ክር፤ በክሩ ላይ ደግሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ስያሜ በምህጻረ ቃላት በአማርኛና በእንግሊዝኛ እንዲሁም የብሩ መጠን ሰፍሮ ይገኛል። በሌላ በኩል ደግሞ አዲሶቹ የብር ኖቶችን ወደ ብርሃን አቅጣጫ በማዞር ሲታዩ ከፊት ከሚታየው ምስል ትይዩ ተመሳሳይ ደብዛዛ መልክ የያዘ ምልክት ይታያል። እንዲሁም የብር ኖቶቹ በብርሃን አቅጣጫ ሲታዮ ኳስ የሚመስሉ ምልክቶች ከኖቶቹ በስተጀርባ ካለው ተመሳሳይ ምልክት ጋር በፍፁም ትይዩ ሆነው በአንድ ቦታ ላይ ያርፋሉ። የብር ለውጥ ታሪክ በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ የሚገኙት የብር ኖቶች ወደ ዝውውር እንዲገቡ የተደረጉት ከ23 ዓመት በፊት በ1990 ዓ.ም ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትን ተከትሎ እንደነበረ ይታወሳል። ከአጼ ኃይለ ሥላሴ አስተዳደር ዘመን ጀምሮ በኢትዮጵያ ሥራ ላይ በነበሩ የገንዘብ የወረቀት ገንዘቦች ላይ በተለያዩ ጊዜያት ለውጥ የተደረገ ሲሆን፤ ወደ አምሳ ዓመታት በሚጠጋው የንጉሡ የሥልጣን ዘመን አራት ጊዜ የብር ኖቶች ለውጥ ተደርጓል። ወታደራዊው መንግሥት ዘውዳዊውን ሥርዓት አስወግዶ አገሪቱን መምራት ከጀመረ ከጥቂት ዓመታት በኋላ በ1969 ዓ.ም የንጉሡ ምስልን የያዙትን የመገበያያ ገንዘቦች ለውጦት ቆይቷል። በተመሳሳይም ኢህአዴግ ደርግን አስወግዶ አገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላም ለሰባት ዓመታት ያህል ቀድሞ የነበረውን ገንዘብ ሲጠቀም ቆይቶ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የድንበር ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ የብር ኖቶቹ እንዲቀየሩ አድርጓል። በኢትዮጵያ ከንጉሡ ዘመን ጀምሮ አገልግሎት ላይ የነበሩት የገንዘብ ኖቶች 1፣ 5፣ 10፣ 50 እና 100 ብር የነበሩ ሲሆን፤ ለረጀም ጊዜ ከፍተኛ ዋጋ ያለው የገንዘብ ኖት 100 ብር ሆኖ ቆይቷል። ቢሆንም ግን በአጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ አገልግሎት ላይ ከዋሉት የብር ኖቶች መካከል የ2 ብር እና የ500 ብር ኖቶች ነበሩበት። ስለዚህም በአገሪቱ የወረቀት ገንዘብ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ዋጋ የነበረው የብር ኖት ባለ 500 ብር ኖት የነበረ ሲሆን በኋላ ላይ ግን ከግብይት እንዲወጣ መደረጉን የብሔራዊ ባንክ መረጃ ያመለክታል። ስለዚህም አሁን ከወረቀት የብር ኖቶች መካከል እንዲገባ የተደረገው የባለ 200 ብር ኖት በታሪክ ሁለተኛው ከፍተኛ ዋጋ ያለው ሲሆን ወደገበያ ሲገባም ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ የብር ኖት ለውጥ እንደሚደረግ በተለያዩ መንገዶች ሲነገር የቆየ ሲሆን፤ ከብር ዋጋ መቀነስ ጋር ተያይዞ 500 ዋጋ ያለው የብር ኖት ወደ ገበያ እንደሚገባ አንዳንድ ሰዎች ሲገልጹ ቆይተው ነበር። በአገሪቱ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጦች መደረግ ከጀመሩባቸው ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር እንደሚካሄድ በጉምሩክና በፖሊስ በኩል በተደጋጋሚ የሚወጡ ሪፖርቶች የሚያመለክቱ ሲሆን፤ ይህም ለውጥ ያስፈለገው ይህንኑ ለመከላከል መሆኑ ተነግሯል።
3.7 ቢሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸው የብር ኖቶች ምን ይዘዋል? የወረቀት የብር ኖቶች በኢትዮጵያ የግብይት ሥርዓት ውስጥ ጥቅም ላይ መዋል ከጀመሩ በኋላ አገሪቱ ለ7ኛ ጊዜ የብር ኖቶች ለውጥ ማድረጓን መስከረም 04/2013 ዓ.ም ይፋ ተደርጓል። በብዙዎች ዘንድ የባንክ ኖቶች ለውጥ ሊኖር ይችላል የሚለው ግምት መነገር ከጀመረ ጥቂት ዓመታት ተቆጥረዋል። አሁን ግን አዲሱ ዓመት በገባ በአራተኛው ቀን ምንም ነገር ሳይሰማ ይፋ የተደረገው የብር ለውጥ አገሪቱ እያካሄደችው ካለው የምጣኔ ሀብት ማሻሻያ እርምጃዎች ውስጥ አንዱ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ብር በዘመናት ሂደት ውስጥ በርካታ ለውጦችን ያስተናገደ ሲሆን፤ ከዋጋ አንጻርም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ አሁን ካለበት ደረጃ ላይ ደርሷል። ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርና የሐሰተኛ የብር ኖት በገበያው ውስጥ በተደጋጋሚ መከሰታቸው በተለያዩ ጊዜያት ሲዘገብ ቆይቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የብር ለውጡ ለሕገ ወጥ ተግባራት የሚውለውን ገንዘብ ለማስቀረት፣ ሙስናንና የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴዎችን ለመቆጣጠር ይረዳል ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት በአገሪቱ ያጋጠመውን የማክሮ ኢኮኖሚ ሚዛን መዛባትን ለማስተካከል ባለፉት ሁለት ዓመታት የተለያዩ ጥረቶች በመደረጋቸው ምጣኔ ሀብቱ ከነበረበት ችግር በመውጣት በማንሰራራት ላይ መሆኑን አመልክተዋል። ጨምረውም በአገሪቱ ያለውን የዋጋ ንረት የመቆጣጠሩ ተግባር በሚፈለገው መጠን ማከናወን እንዳልተቻለ ጠቅሰው፤ ለዚህ ደግሞ ከባንክ ውጪ የሚንቀሳቀስ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ መኖሩ ደግሞ ችግሩን በማባባሱ የብር ኖት መቀየር አንድ መፍትሄ መሆኑን ተናግረዋል። ምን ተለወጠ? አዲሶቹ የብር ኖቶች ቀደም ሲል ከነበሩት በተሻለ ለአጠቃቀም ምቹና ረዥም ጊዜ እንዲያገለግሉ ተደርገው መሰራታቸ የተገለጸ ሲሆን፤ ኖቶቹን በመቀየሩ ሥራ ለህትመት ብቻ በአጠቃላይ 3 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ወጪ እንደተደረገ ተነግሯል። ከቀለም አንጻር አዲሱ ባለ 200 ብር ኖት ሐምራዊ፣ ባለ100 ብር ኖት ውሃ ሰማያዊ፣ ባለ50 ብር ኖት ቀይ ብርቱካናማ፣ ባለ10 ብር ኖት ደግሞ አረንጓዴ ቀለም አላቸው። ቀደም ሲል በዝውውር ውስጥ የቆየው የባለ5 ብር ኖት ለውጥ ሳይደረግበት በሥራ ላይ የሚቆይ ሲሆን፤ ነገር ግን የወረቀት ገንዘቡ ቀስ በቀስ በሳንቲም እንደሚተካ ተገልጿል። በአዳዲሶቹ የብር ኖቶች ላይ ቀደም ሲል በነበሩት ላይ ያልነበሩ የአገሪቱን ገጽታ የሚያሳዩ ምስሎች የተካተቱበት ሲሆን፤ በዚህም በባለ አስር ብር ኖት ላይ ግመል፣ በባለ መቶ ብር ኖት ላይ ደግሞ የሶፍ ኡመር ዋሻና የሐረር ግንብ እንዲካተቱባቸው ተደርጓል። ከባንክ ውጪ ያለ ብር የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ እንዳመለከቱት "ከኢትዮጵያ ውጪ በጎረቤት አገራት ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው የኢትዮጵያ ብር ተከማችቶ ይገኛል።" ከብር ለውጡ ጋር ተያይዞም በውጪ አገራት ውስጥ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብር ወደ አገር ውስጥ እንዳይገባ ከፍተኛ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ባለፈው ዓመት ብሔራዊ ባንክ ያወጣው ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ በቤት ውስጥ ማስቀመጥ የሚከለክለው ሕግም ተግባራዊ መሆኑ የሚቀጥል ሲሆን፤ ይህንን ደንብ በመተላለፍ የሚንቀሳቀስ ገንዘብ በቁጥጥር ስር ውሎ ለመንግሥት አገልግሎት ይውላል። ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ በየጊዜው ድንገተኛ ፍተሻ እንደሚኖርም ተገልጿል። የብር ለውጥ ሂደት ላለፉት 23 ዓመታት በዝውውር ላይ የነበሩትን የብር ኖቶች ከገበያ በማስወጣት በአዲሶቹ የመተካቱ ሂደት በሚቀጥሉት ሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ እንደሚከናወን የጊዜ ሰሌዳ ተቀምጧል። ነገር ግን አሮጌዎቹን የብር ኖቶች በአዲስ በመተካቱ ሂደት ውስጥ 100 ሺህ እና ከዚያ በላይ ብር ያላቸው ሰዎች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ መቀየር እንዳለባቸው ተገልጿል። በዚህ ሂደት ውስጥ እስከ 10 ሺህ ብር ድረስ ለሚደረግ የብር ለውጥ ቀጥታ ገንዘቡን በመስጠት የሚከናወን ሲሆን፤ ከአስር ሺህ ብር በላይ የሚቀየር ከሆነ ደግሞ ብሩን ለመለወጥ ባመጣው ግለሰብ ስም የባንክ ደብተር ተከፍቶ እንዲቀመጥ ይደረጋል ተብሏል። የደኅንነት ገጽታዎች ይፋ የተደረጉት አዳዲሶቹ የብር ኖቶች አስመስለው የሚሰሩ ሐሰተኛ የብር ኖቶችን ለመከላከልና ለመለየት በሚያስችል ሁኔታ የተለያዩ የደኅንነት መጠበቂያ ገጽታዎች እንዲኖሯቸው ተደርጓል። በተጨማሪም ለዓይነ ስውራን አጠቃቀም እንዲያመች የመለያ ምልክት ያለው ሲሆን፤ በዚህም ዓይነ ስውራን የብሩን ዋጋ በእጅ ዳሰሳ ማወቅ የሚችሉበት ምልክትና የደኅንነት መጠበቂያ ገጽታ አላቸው። ከዚህ ባሻገርም የብር ኖቱ ወደ ላይ ወይም ወደታች በሚንቀሳቀስበት ጊዜ ደማቅ የቀለም ፍንጣቂ የደኅንነት መጠበቂያ ገጽታ ያለው ሲሆን፤ የብር ኖቶቱ በእጅ ሲዳሰሱ የመጎርበጥ ስሜት እንዲሁም የብሩ ዋጋ ይታያል። አዲሶቹ ኖቶች ተጨማሪ ባለቀለም ኮከብ የደኅንነት ገጽታን ከማካተታቸው ባሻገር አብረቅራቂ የደኅንነት መጠበቂያ ክር፤ በክሩ ላይ ደግሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ስያሜ በምህጻረ ቃላት በአማርኛና በእንግሊዝኛ እንዲሁም የብሩ መጠን ሰፍሮ ይገኛል። በሌላ በኩል ደግሞ አዲሶቹ የብር ኖቶችን ወደ ብርሃን አቅጣጫ በማዞር ሲታዩ ከፊት ከሚታየው ምስል ትይዩ ተመሳሳይ ደብዛዛ መልክ የያዘ ምልክት ይታያል። እንዲሁም የብር ኖቶቹ በብርሃን አቅጣጫ ሲታዮ ኳስ የሚመስሉ ምልክቶች ከኖቶቹ በስተጀርባ ካለው ተመሳሳይ ምልክት ጋር በፍፁም ትይዩ ሆነው በአንድ ቦታ ላይ ያርፋሉ። የብር ለውጥ ታሪክ በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ የሚገኙት የብር ኖቶች ወደ ዝውውር እንዲገቡ የተደረጉት ከ23 ዓመት በፊት በ1990 ዓ.ም ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትን ተከትሎ እንደነበረ ይታወሳል። ከአጼ ኃይለ ሥላሴ አስተዳደር ዘመን ጀምሮ በኢትዮጵያ ሥራ ላይ በነበሩ የገንዘብ የወረቀት ገንዘቦች ላይ በተለያዩ ጊዜያት ለውጥ የተደረገ ሲሆን፤ ወደ አምሳ ዓመታት በሚጠጋው የንጉሡ የሥልጣን ዘመን አራት ጊዜ የብር ኖቶች ለውጥ ተደርጓል። ወታደራዊው መንግሥት ዘውዳዊውን ሥርዓት አስወግዶ አገሪቱን መምራት ከጀመረ ከጥቂት ዓመታት በኋላ በ1969 ዓ.ም የንጉሡ ምስልን የያዙትን የመገበያያ ገንዘቦች ለውጦት ቆይቷል። በተመሳሳይም ኢህአዴግ ደርግን አስወግዶ አገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላም ለሰባት ዓመታት ያህል ቀድሞ የነበረውን ገንዘብ ሲጠቀም ቆይቶ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የድንበር ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ የብር ኖቶቹ እንዲቀየሩ አድርጓል። በኢትዮጵያ ከንጉሡ ዘመን ጀምሮ አገልግሎት ላይ የነበሩት የገንዘብ ኖቶች 1፣ 5፣ 10፣ 50 እና 100 ብር የነበሩ ሲሆን፤ ለረጀም ጊዜ ከፍተኛ ዋጋ ያለው የገንዘብ ኖት 100 ብር ሆኖ ቆይቷል። ቢሆንም ግን በአጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ አገልግሎት ላይ ከዋሉት የብር ኖቶች መካከል የ2 ብር እና የ500 ብር ኖቶች ነበሩበት። ስለዚህም በአገሪቱ የወረቀት ገንዘብ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ዋጋ የነበረው የብር ኖት ባለ 500 ብር ኖት የነበረ ሲሆን በኋላ ላይ ግን ከግብይት እንዲወጣ መደረጉን የብሔራዊ ባንክ መረጃ ያመለክታል። ስለዚህም አሁን ከወረቀት የብር ኖቶች መካከል እንዲገባ የተደረገው የባለ 200 ብር ኖት በታሪክ ሁለተኛው ከፍተኛ ዋጋ ያለው ሲሆን ወደገበያ ሲገባም ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ የብር ኖት ለውጥ እንደሚደረግ በተለያዩ መንገዶች ሲነገር የቆየ ሲሆን፤ ከብር ዋጋ መቀነስ ጋር ተያይዞ 500 ዋጋ ያለው የብር ኖት ወደ ገበያ እንደሚገባ አንዳንድ ሰዎች ሲገልጹ ቆይተው ነበር። በአገሪቱ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጦች መደረግ ከጀመሩባቸው ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር እንደሚካሄድ በጉምሩክና በፖሊስ በኩል በተደጋጋሚ የሚወጡ ሪፖርቶች የሚያመለክቱ ሲሆን፤ ይህም ለውጥ ያስፈለገው ይህንኑ ለመከላከል መሆኑ ተነግሯል።
https://www.bbc.com/amharic/news-54145137
2health
ሐኪሞች የንግሥት ኤልዛቤት የጤና ሁኔታ አሳሳቢ ነው አሉ
የዩናይትድ ኪንግደም እና የኮመን ዌልዝ አገራት ንግሥት የሆኑት ንግሥት ኤልዛቤት ዳግማዊት ሐኪሞች የንግሥቲቱ ጤና አሳሳቢ ነው አሉ። የንግሥቲቱ ይፋዊ መኖሪያ ቤት ባኪንግሃም ቤተ-መንግሥት እንዳስታወቀው ንግሥት ኤልዛቤት ሁለተኛ በጤና ክትትል ስር እንደሚገኙ ይፋ አድርጓል። የንግሥት ኤልዛቤት ልጅ ልዑል ቻርልስ ንግሥቲቱ ወደሚገኙበት ባልሞራል ቤተ-መንግሥት አቅንተዋል። የ96 ዓመቷ የዩኬ እና የኮመን ዌልዝ አገራት ንግሥት ኤልዛቤት ዳግማዊት በ70 ዓመት የንግሥና ዘመናቸው በርካታ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ለውጦችን ተመልክተዋል። ከቀናት በፊት የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ሊዝ ትረስ በንግሥት ኤልዛቤት የንግሥና ዘመን 15ኛዋ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዋል። የንግሥቲቱን የጤና መቃወስ ዜና መሰማቱን ተከትሎ አዲሷ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዝ ትረስ "መላው አገር" በዜናው "እጅጉን ተረብሿል" ብለዋል። የንግሥቲቱ የጤና ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ተከትሎ በርካርታ የንጉሣውያን ቤተሰብ አባላት ወደ ስኮትላንድ እያቀኑ ነው። ለባልሞር ቤተ-መንግሥት ቅርበት ባለው አበርዲን አየር መንገድ ከወትሮ በተለየ እንቅስቃሴ እየታየ ነው። ንግሥቲቱ ወዳሉበት ስኮትላንድ ከተጓዙት መካከል ልዑል ቻርልስ ይገኙበታል። የሰሴክስ መስፍን እና ሶፋኒት ሄሪ እና ሜጋን ወደ ስኮትላንድ እንደሚሄዱ የጥንዶቹ ቃል አቀባይ ተናግረዋል። የዮርክ መስፍን ልዑል አንድሩ ወደ ስኮትላንድ እያቀኑ ሲሆን፣ ልዕልት አን ቀደም ሲል ስኮትላንድ ደርሰዋል። አዲሷ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዝ ትረስ የእኔ እና የዩናይትድ ኪንግደም ሕዝብ መልካም ምኞት ከንግሥት ኤልዛቤት እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ነው ብለዋል። የንግሥት ኤልዛቤት የጤና ሁኔታ ማሽቆልቆሉ መገለጹን ተከትሎ በርካታ በአገሪቱ ያሉ ተዋቂ ግለሰቦች እና ፖለቲከኞች መልካም ምኞታቸውን እየገለጹ ነው። የካንትበሪ ሊቀጳጳስ ጀስቲን ዌብሊ፤ እኔ፣ የእንግሊዝ ቤተ-ክርስቲያ እና መላዋ አገሪቱ ንግሥቲቷን በጸሎታቸው እያሰቡ ነው ብለዋል። የስኮትላንድ ተቀዳሚ ሚንስትር ኒኮላ ስተርጅን የንግሥቲቱ ጤና እጅጉን አሳስቦኛል ብለዋል። ተቀዳሚ ሚኒስትሯ ለንግሥት ኤልዛቤት እና ለመላው ንጉሣውያን ቤተሰቦች መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ ብለዋል።
ሐኪሞች የንግሥት ኤልዛቤት የጤና ሁኔታ አሳሳቢ ነው አሉ የዩናይትድ ኪንግደም እና የኮመን ዌልዝ አገራት ንግሥት የሆኑት ንግሥት ኤልዛቤት ዳግማዊት ሐኪሞች የንግሥቲቱ ጤና አሳሳቢ ነው አሉ። የንግሥቲቱ ይፋዊ መኖሪያ ቤት ባኪንግሃም ቤተ-መንግሥት እንዳስታወቀው ንግሥት ኤልዛቤት ሁለተኛ በጤና ክትትል ስር እንደሚገኙ ይፋ አድርጓል። የንግሥት ኤልዛቤት ልጅ ልዑል ቻርልስ ንግሥቲቱ ወደሚገኙበት ባልሞራል ቤተ-መንግሥት አቅንተዋል። የ96 ዓመቷ የዩኬ እና የኮመን ዌልዝ አገራት ንግሥት ኤልዛቤት ዳግማዊት በ70 ዓመት የንግሥና ዘመናቸው በርካታ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ለውጦችን ተመልክተዋል። ከቀናት በፊት የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ሊዝ ትረስ በንግሥት ኤልዛቤት የንግሥና ዘመን 15ኛዋ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዋል። የንግሥቲቱን የጤና መቃወስ ዜና መሰማቱን ተከትሎ አዲሷ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዝ ትረስ "መላው አገር" በዜናው "እጅጉን ተረብሿል" ብለዋል። የንግሥቲቱ የጤና ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ተከትሎ በርካርታ የንጉሣውያን ቤተሰብ አባላት ወደ ስኮትላንድ እያቀኑ ነው። ለባልሞር ቤተ-መንግሥት ቅርበት ባለው አበርዲን አየር መንገድ ከወትሮ በተለየ እንቅስቃሴ እየታየ ነው። ንግሥቲቱ ወዳሉበት ስኮትላንድ ከተጓዙት መካከል ልዑል ቻርልስ ይገኙበታል። የሰሴክስ መስፍን እና ሶፋኒት ሄሪ እና ሜጋን ወደ ስኮትላንድ እንደሚሄዱ የጥንዶቹ ቃል አቀባይ ተናግረዋል። የዮርክ መስፍን ልዑል አንድሩ ወደ ስኮትላንድ እያቀኑ ሲሆን፣ ልዕልት አን ቀደም ሲል ስኮትላንድ ደርሰዋል። አዲሷ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዝ ትረስ የእኔ እና የዩናይትድ ኪንግደም ሕዝብ መልካም ምኞት ከንግሥት ኤልዛቤት እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ነው ብለዋል። የንግሥት ኤልዛቤት የጤና ሁኔታ ማሽቆልቆሉ መገለጹን ተከትሎ በርካታ በአገሪቱ ያሉ ተዋቂ ግለሰቦች እና ፖለቲከኞች መልካም ምኞታቸውን እየገለጹ ነው። የካንትበሪ ሊቀጳጳስ ጀስቲን ዌብሊ፤ እኔ፣ የእንግሊዝ ቤተ-ክርስቲያ እና መላዋ አገሪቱ ንግሥቲቷን በጸሎታቸው እያሰቡ ነው ብለዋል። የስኮትላንድ ተቀዳሚ ሚንስትር ኒኮላ ስተርጅን የንግሥቲቱ ጤና እጅጉን አሳስቦኛል ብለዋል። ተቀዳሚ ሚኒስትሯ ለንግሥት ኤልዛቤት እና ለመላው ንጉሣውያን ቤተሰቦች መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c51088xn194o
5sports
ዋሊያዎቹ ከማላዊና ከግብፅ በሚያደርጉት ጨዋታ ምን ውጤት ይጠበቃል?
ቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ በፈረንጆቹ 2023 በአይቮሪኮስት አስተናጋጅነት ሊካሄድ ዕቅድ ተይዞለታል። የአህጉሪቱ እግር ኳስ አስተዳዳሪ ከፍተኛ አካል ካፍ ዕጣ ደልድሎ አገራት የማጣሪያ ጨዋታቸውን ማድረግ ጀምረዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አራት ከግብፅ፣ ከጊኒ እና ከማላዊ ጋር ተደልድላለች። ካፍ የኢትዮጵያ ሜዳዎች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎችን ለማድረግ ብቁ አይደሉም በማለቱ ዋሊያዎቹ በገለልተኛ ሜዳ ይጫወታሉ። ዋሊያዎቹ በሜዳቸው ለመጫወት “ባለመታደላቸው” ከግብፅ የሚያደርጉትን የመጀመሪያ ዙር ፍልሚያ በባዳ ስታዲየም ሊያደርጉ ወስነዋል። ነገር ግን በመጀመሪያ ጨዋታቸው ማላዊን የሚገጥሙ ይሆናል። አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ዋሊያዎቹን እየመሩ ወደ ማላዊ ዋና ከተማ ሊሎንጉዌ ከማቅናቸው በፊት መግለጫ ሰጥተዋል። አሠልጣኙ “ፈርዖኖቹን በገዛ ሜዳችን ብንገጥም ደስ ይለን ነበር” የሚል የቁጭት አስተያየት ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከግንቦት 16 ጀምሮ ለማጣሪያ ጨዋታዎች ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል። አሠልጣኝ ውበቱ መጀመሪያ 28 ተጫዋቾችን መልምለው ከሌሶቶ ብሔራዊ ቡድን ጋር አዲስ አበባ ላይ የወዳጅነት ፍልሚያ አድርገው የመጨረሻ 23 ተጫዋቾችን ለይተዋል። እነማን ወደ ማላዊ ይጓዛሉ? አሠልጣኝ ውበቱ የባሕር ዳሩ ፋሲል ገብረሚካዔልን፣ የኢትዮጵያ ቡናው ታዳጊ በረኛ በረከት አማረንና የሐዋሳ ከተማውን ዳግም ተፈራ በግብ ጠባቂነት ይዘው ወደ ማላዊ ይሄዳሉ። አስራት ቱንጆ፣ ረመዳን የሱፍ፣ ሄኖክ አዱኛ፣ ሱሌይማን ሃሚድ፣ ምኞት ደበበ፣ ያሬድ ባዬ፣ ጊት ጋትኩትና ሚሊዮን ሶሎሞን የተከላካይ መስመሩን እንዲቆጣጠሩ የተመረጡ ናቸው። የአማካይ መስመሩን የሚመራው ጉምቱው ሽመልስ በቀለ ነው። በተጨማሪ አማኑዔል ዮሐንስ፣ ጋቶች ፓኖም፣ ሱራፌል ዳኛቸው፣ በዛብህ መለዮና መስዑድ ሞሐመድ ተመርጠዋል። የኢትዮጵያ ቡናው ፈርጥ አቡበከር ናስር የአጥቂውን መስመር እየመራ ወደ ሊሎንጉዌ ያቀናል። አማኑዔል ገብረመድህን፣ ቸርነት ጉግሳ፣ ዳዋ ሆጤሳ፣ በረከት ደስታና ይገዙ ቦጋለ ሌሎች በአጥቂ መስመር ላይ የሚሰለፉ ናቸው። ውበቱ እንደተለመደው በ4-4-3 አሰላለፍ ተጋጣሚዎቻቸውን እንደሚገጥሙ ይጠበቃል። የፕሪሚዬር ሊጉን ኮከብ ጎል አግቢ ሰንጠረዥ በጥምር የሚመራው ነባሩ አጥቂ ጌታነህ ከበደ ከአሠልጣኙ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ሳይመረጥ እንደቀረ ውበቱ ጠቁመዋል። ጌታነህ በዘጠኝ ቁጥር ቦታ አለመኖሩ አቡበከር ናስር ስኬታማ በሚሆንበት መስመር በደንብ እንዲጫወት ዕድል ሊፈጥር ይችላል። የጌታነህ ከበደን አለመኖር ተከትሎ ሽመልስ በቀለ ቡድኑን በአምበልነት እየመራ ወደ ማላዊ ያቀናል። ሽመልስ በቀለ ሶከር ኢትዯጵያ ከተሰኘው የአገር ውስጥ የስፖርት አውታር ባደረገው ቃለ-ምልልስ ከሁለቱ ጨዋታዎች ቢያንስ አራት ነጥብ ለማግኘት እንደሚጫወቱ ተናግሯል። 'ዘ ፍሌምስ' በተሰኘ ቅጽል ስሙ የሚታወቀው የማላዊ ብሔራዊ ቡድን ባለፈው የአፍሪካ ዋንጫ ከምድቡ ማለፍ ችሎ ነበር። ዘ ፍሌምስ በዙር 16 ጨዋታ በሞሮኮ ተርትተው ወደ አገራቸው ተመልሰዋል። ኢትዮጵያና ማላዊ ከፈረንጆቹ 2003 ጀምሮ በተለያዩ ውድድሮችና በወዳጅነት ስድስት ጊዜ ተገናኝተዋል። ማላዊ ሁለት ጊዜ በማሸነፍ የበላይነቱን ስትይዝ ኢትዮጵያ አንድ ጊዜ ረትታለች። አራት ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥተዋል። የማላዊ ብሔራዊ ቡድን ዘ ፍሌምስ መጋቢት በወጣው የፊፋ የዓለም የብሔራዊ ቡድኖች ሠንጠረዥ 120ኛ ላይ ተቀምጠዋል። ዋሊያዎቹ ደግሞ ከዓለም 140ኛ ከአፍሪካ ደግሞ 44ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። የማላዊ ብሔራዊ ቡድን በአብዛኛው አገር ውስጥ በሚጫወቱ ተጫዋቾች፣ መቀመጫቸውን አውሮፓና በሌሎች የአፍሪካ አገራት ባደረጉ እግር ኳሰኞች የተዋቀረ ነው። አውሮፓ ከሚጫወቱ ተጫዋቾች መካከል ለሞልዶቫው ሽሪፍ የሚጫወተው ቻርልስ ፔትሮ ይጠቀሳል። ኢትዮጵያና ማላዊ እሁድ ግንቦት 26/2014 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ሰዓት በቢንጉ ብሔራዊ ስታድዬም ይጫወታሉ። ሞሐመድ ሳላህ ፈርዖኖቹን ለመቀላቀል ወደ ግብፅ አቅንቷል። ግብፅ በመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ፍልሚያዋ በሜዳዋ እሁድ ምሽት 4፡00 ሰዓት ጊኒን ታስተናግዳለች። ፈርዖኖቹ ከምድብ በቀላሉ የማለፍ ግምት ተሰጥቷዋል። በፕሮፌሽናል እግር ኳሰኞች ማኅበር (ፒኤፍኤ) የዓመቱ ምርጥ ዕጩ ሆኖ የተመረጠው ሳላህ ቡድን እየመራ ወደሜዳ እንደሚገባ ይጠበቃል። ግብ ጠባቂው ሞሐመድ ኤል-ሼናዊን ጨምሮ ሰባት የአል አህሊ ተጫዋች በብሔራዊ ቡድኑ ተካተዋል። የአርሰናሉ ሞሐመድ ኤልኔኒ እንዲሁም የኢስታንቡል ባሼክሽር አማካይ ሞሐመድ ትሬዚጌ ለፈርዖኖቹ ተመርጠዋል። ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ የሚደረገውን ፍልሚያ መርታት የተሳናት ግብፅ አዲስ አሠልጣኝ ቀጥራለች። ተሰናባቹን ፖርቹጋላዊ አሠልጣኝ ካርሎስ ኬሮዥን የተኩት የ54 ዓመቱ ኢሃብ ጋላል ለቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ ማለፍ ቀዳሚው ዕቅዳቸው እንደሆነ ገልጠዋል። ግብፅ ከጊኒ ጨዋታዋ ቀጥሎ ኢትዮጵያን በገልለተኛ ሜዳ ለመግጠም ወደ ማላዊ ታቀናለች። ዋሊያዎቹ ከፈርዖኖቹ ሐሙስ ሰኔ 02/2014 በማላዊ ስታድዬም ምሽት 1፡00 ሰዓት ይፋለማሉ። ከአሠልጣኝ ውበቱ አባተ ጎን ለጎን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሐፊ ባሕሩ ጥላሁን መግለጫ ሰጥተዋል። “ፌዴርሽኑ ዋሊያዎቹን ለመደገፍ የታቸለውን ሁሉ እያደረገ ነው” ብለዋል ዋና ፀሐፊው። ዋሊያዎቹ ከሌሶቶ ብሔራዊ ቡድን ጋር የወዳጅነት ጨዋታ እንዲያደርጉ ፌዴሬሽኑ ሁኔታዎችን ማመቻቸቱን አቶ ባሕሩ ጠቅሰዋል። እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋሊያዎቹ ግብፅ የሚያደርጉትን ጨዋታ ማላዊ ላይ እንዲያከናውኑ የወሰነው “ከወጪ አንፃር” መሆኑን ፀሐፊው ጠቅሰዋል። አልፎም ተጫዋቾቹ ከማላዊ ጨዋታ መልስ እዚያው ሆነው እንዲያገግሙ በማሰብ እንደሆነም አስረድተዋል። አቶ ባሕሩ “በማላዊ ስታድዬም ከግብፅ ጋር ለመፋለም ቢያንስ 50 ሺህ ዶላር ያስፈልገናል” ብለዋል። ዋና ፀሐፊው አክለው “የግብፅ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ወጪያችሁን እንቻልና ጨዋታው ካይሮ ይሁን” ብሎ እንደጠየቃቸው ይፋ አድርገዋል። “ነገር ግን...” ይላሉ ዋና ፀሐፊው “... ነገር ግን ይህ ክብረ ነክ ነው ብለን አንቀበልም ብለናል።” የመጀመሪያው ዙር የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በሚቀጥለው ሳምንት ከተጠናቀቀ በኋላ ሁለተኛው ዙር ጨዋታ በመጪው መስከረም ይካሄዳል። መስከረም ላይ በሚደረጉት ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ከጊኒ ጋር የደርሶ መልስ ጨዋታ ታደርጋለች። ተንታኞ ከምድቡ ለኢትዮጵያ ዝቅተኛ ግምት ቢሰጡም አሠልጣኝ ውበቱና ተጫዋቻቸውን ግን ይህን ለመሻር አቅደዋል።
ዋሊያዎቹ ከማላዊና ከግብፅ በሚያደርጉት ጨዋታ ምን ውጤት ይጠበቃል? ቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ በፈረንጆቹ 2023 በአይቮሪኮስት አስተናጋጅነት ሊካሄድ ዕቅድ ተይዞለታል። የአህጉሪቱ እግር ኳስ አስተዳዳሪ ከፍተኛ አካል ካፍ ዕጣ ደልድሎ አገራት የማጣሪያ ጨዋታቸውን ማድረግ ጀምረዋል። ኢትዮጵያ በምድብ አራት ከግብፅ፣ ከጊኒ እና ከማላዊ ጋር ተደልድላለች። ካፍ የኢትዮጵያ ሜዳዎች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎችን ለማድረግ ብቁ አይደሉም በማለቱ ዋሊያዎቹ በገለልተኛ ሜዳ ይጫወታሉ። ዋሊያዎቹ በሜዳቸው ለመጫወት “ባለመታደላቸው” ከግብፅ የሚያደርጉትን የመጀመሪያ ዙር ፍልሚያ በባዳ ስታዲየም ሊያደርጉ ወስነዋል። ነገር ግን በመጀመሪያ ጨዋታቸው ማላዊን የሚገጥሙ ይሆናል። አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ዋሊያዎቹን እየመሩ ወደ ማላዊ ዋና ከተማ ሊሎንጉዌ ከማቅናቸው በፊት መግለጫ ሰጥተዋል። አሠልጣኙ “ፈርዖኖቹን በገዛ ሜዳችን ብንገጥም ደስ ይለን ነበር” የሚል የቁጭት አስተያየት ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከግንቦት 16 ጀምሮ ለማጣሪያ ጨዋታዎች ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል። አሠልጣኝ ውበቱ መጀመሪያ 28 ተጫዋቾችን መልምለው ከሌሶቶ ብሔራዊ ቡድን ጋር አዲስ አበባ ላይ የወዳጅነት ፍልሚያ አድርገው የመጨረሻ 23 ተጫዋቾችን ለይተዋል። እነማን ወደ ማላዊ ይጓዛሉ? አሠልጣኝ ውበቱ የባሕር ዳሩ ፋሲል ገብረሚካዔልን፣ የኢትዮጵያ ቡናው ታዳጊ በረኛ በረከት አማረንና የሐዋሳ ከተማውን ዳግም ተፈራ በግብ ጠባቂነት ይዘው ወደ ማላዊ ይሄዳሉ። አስራት ቱንጆ፣ ረመዳን የሱፍ፣ ሄኖክ አዱኛ፣ ሱሌይማን ሃሚድ፣ ምኞት ደበበ፣ ያሬድ ባዬ፣ ጊት ጋትኩትና ሚሊዮን ሶሎሞን የተከላካይ መስመሩን እንዲቆጣጠሩ የተመረጡ ናቸው። የአማካይ መስመሩን የሚመራው ጉምቱው ሽመልስ በቀለ ነው። በተጨማሪ አማኑዔል ዮሐንስ፣ ጋቶች ፓኖም፣ ሱራፌል ዳኛቸው፣ በዛብህ መለዮና መስዑድ ሞሐመድ ተመርጠዋል። የኢትዮጵያ ቡናው ፈርጥ አቡበከር ናስር የአጥቂውን መስመር እየመራ ወደ ሊሎንጉዌ ያቀናል። አማኑዔል ገብረመድህን፣ ቸርነት ጉግሳ፣ ዳዋ ሆጤሳ፣ በረከት ደስታና ይገዙ ቦጋለ ሌሎች በአጥቂ መስመር ላይ የሚሰለፉ ናቸው። ውበቱ እንደተለመደው በ4-4-3 አሰላለፍ ተጋጣሚዎቻቸውን እንደሚገጥሙ ይጠበቃል። የፕሪሚዬር ሊጉን ኮከብ ጎል አግቢ ሰንጠረዥ በጥምር የሚመራው ነባሩ አጥቂ ጌታነህ ከበደ ከአሠልጣኙ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ሳይመረጥ እንደቀረ ውበቱ ጠቁመዋል። ጌታነህ በዘጠኝ ቁጥር ቦታ አለመኖሩ አቡበከር ናስር ስኬታማ በሚሆንበት መስመር በደንብ እንዲጫወት ዕድል ሊፈጥር ይችላል። የጌታነህ ከበደን አለመኖር ተከትሎ ሽመልስ በቀለ ቡድኑን በአምበልነት እየመራ ወደ ማላዊ ያቀናል። ሽመልስ በቀለ ሶከር ኢትዯጵያ ከተሰኘው የአገር ውስጥ የስፖርት አውታር ባደረገው ቃለ-ምልልስ ከሁለቱ ጨዋታዎች ቢያንስ አራት ነጥብ ለማግኘት እንደሚጫወቱ ተናግሯል። 'ዘ ፍሌምስ' በተሰኘ ቅጽል ስሙ የሚታወቀው የማላዊ ብሔራዊ ቡድን ባለፈው የአፍሪካ ዋንጫ ከምድቡ ማለፍ ችሎ ነበር። ዘ ፍሌምስ በዙር 16 ጨዋታ በሞሮኮ ተርትተው ወደ አገራቸው ተመልሰዋል። ኢትዮጵያና ማላዊ ከፈረንጆቹ 2003 ጀምሮ በተለያዩ ውድድሮችና በወዳጅነት ስድስት ጊዜ ተገናኝተዋል። ማላዊ ሁለት ጊዜ በማሸነፍ የበላይነቱን ስትይዝ ኢትዮጵያ አንድ ጊዜ ረትታለች። አራት ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥተዋል። የማላዊ ብሔራዊ ቡድን ዘ ፍሌምስ መጋቢት በወጣው የፊፋ የዓለም የብሔራዊ ቡድኖች ሠንጠረዥ 120ኛ ላይ ተቀምጠዋል። ዋሊያዎቹ ደግሞ ከዓለም 140ኛ ከአፍሪካ ደግሞ 44ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። የማላዊ ብሔራዊ ቡድን በአብዛኛው አገር ውስጥ በሚጫወቱ ተጫዋቾች፣ መቀመጫቸውን አውሮፓና በሌሎች የአፍሪካ አገራት ባደረጉ እግር ኳሰኞች የተዋቀረ ነው። አውሮፓ ከሚጫወቱ ተጫዋቾች መካከል ለሞልዶቫው ሽሪፍ የሚጫወተው ቻርልስ ፔትሮ ይጠቀሳል። ኢትዮጵያና ማላዊ እሁድ ግንቦት 26/2014 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ሰዓት በቢንጉ ብሔራዊ ስታድዬም ይጫወታሉ። ሞሐመድ ሳላህ ፈርዖኖቹን ለመቀላቀል ወደ ግብፅ አቅንቷል። ግብፅ በመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ፍልሚያዋ በሜዳዋ እሁድ ምሽት 4፡00 ሰዓት ጊኒን ታስተናግዳለች። ፈርዖኖቹ ከምድብ በቀላሉ የማለፍ ግምት ተሰጥቷዋል። በፕሮፌሽናል እግር ኳሰኞች ማኅበር (ፒኤፍኤ) የዓመቱ ምርጥ ዕጩ ሆኖ የተመረጠው ሳላህ ቡድን እየመራ ወደሜዳ እንደሚገባ ይጠበቃል። ግብ ጠባቂው ሞሐመድ ኤል-ሼናዊን ጨምሮ ሰባት የአል አህሊ ተጫዋች በብሔራዊ ቡድኑ ተካተዋል። የአርሰናሉ ሞሐመድ ኤልኔኒ እንዲሁም የኢስታንቡል ባሼክሽር አማካይ ሞሐመድ ትሬዚጌ ለፈርዖኖቹ ተመርጠዋል። ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ የሚደረገውን ፍልሚያ መርታት የተሳናት ግብፅ አዲስ አሠልጣኝ ቀጥራለች። ተሰናባቹን ፖርቹጋላዊ አሠልጣኝ ካርሎስ ኬሮዥን የተኩት የ54 ዓመቱ ኢሃብ ጋላል ለቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ ማለፍ ቀዳሚው ዕቅዳቸው እንደሆነ ገልጠዋል። ግብፅ ከጊኒ ጨዋታዋ ቀጥሎ ኢትዮጵያን በገልለተኛ ሜዳ ለመግጠም ወደ ማላዊ ታቀናለች። ዋሊያዎቹ ከፈርዖኖቹ ሐሙስ ሰኔ 02/2014 በማላዊ ስታድዬም ምሽት 1፡00 ሰዓት ይፋለማሉ። ከአሠልጣኝ ውበቱ አባተ ጎን ለጎን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሐፊ ባሕሩ ጥላሁን መግለጫ ሰጥተዋል። “ፌዴርሽኑ ዋሊያዎቹን ለመደገፍ የታቸለውን ሁሉ እያደረገ ነው” ብለዋል ዋና ፀሐፊው። ዋሊያዎቹ ከሌሶቶ ብሔራዊ ቡድን ጋር የወዳጅነት ጨዋታ እንዲያደርጉ ፌዴሬሽኑ ሁኔታዎችን ማመቻቸቱን አቶ ባሕሩ ጠቅሰዋል። እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋሊያዎቹ ግብፅ የሚያደርጉትን ጨዋታ ማላዊ ላይ እንዲያከናውኑ የወሰነው “ከወጪ አንፃር” መሆኑን ፀሐፊው ጠቅሰዋል። አልፎም ተጫዋቾቹ ከማላዊ ጨዋታ መልስ እዚያው ሆነው እንዲያገግሙ በማሰብ እንደሆነም አስረድተዋል። አቶ ባሕሩ “በማላዊ ስታድዬም ከግብፅ ጋር ለመፋለም ቢያንስ 50 ሺህ ዶላር ያስፈልገናል” ብለዋል። ዋና ፀሐፊው አክለው “የግብፅ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ወጪያችሁን እንቻልና ጨዋታው ካይሮ ይሁን” ብሎ እንደጠየቃቸው ይፋ አድርገዋል። “ነገር ግን...” ይላሉ ዋና ፀሐፊው “... ነገር ግን ይህ ክብረ ነክ ነው ብለን አንቀበልም ብለናል።” የመጀመሪያው ዙር የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በሚቀጥለው ሳምንት ከተጠናቀቀ በኋላ ሁለተኛው ዙር ጨዋታ በመጪው መስከረም ይካሄዳል። መስከረም ላይ በሚደረጉት ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ከጊኒ ጋር የደርሶ መልስ ጨዋታ ታደርጋለች። ተንታኞ ከምድቡ ለኢትዮጵያ ዝቅተኛ ግምት ቢሰጡም አሠልጣኝ ውበቱና ተጫዋቻቸውን ግን ይህን ለመሻር አቅደዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/crgn6184knno
2health
ኮሮናቫይረስ፡ የፖላንዱ ፕሬዝዳንት በኮቪድ-19 ተያዙ
የፖላንድ ፕሬዝዳንት አንድሬ ዱዳ በኮቪድ-19 መያዛቸው ተገለፀ። የፕሬዝዳንቱ ጤና ሁኔታ "መልካም" መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ራሳቸውን ለይተው ውሸባ ገብተዋል ተብሏል። የ48 ዓመቱ ጉልማሳ ፕሬዝዳንት ዱዳ፣ አርብ እለት የኮሮናቫይረስ ማድረጋቸውንና መያዛቸው መታወቁ ዛሬ፣ ቅዳሜ ይፋ ተደርጓል። ፕሬዝዳንቱ በኮሮናቫይረስ የተያዙ የተለያዩ ርዕሰ ብሄሮችን ያገኙ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ይገኙበታል። 38 ሚሊዮን ዜጎች ያላት ፓላንድ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት እያገረሸ ሲሆን አርብ ዕለት ብቻ ከ13 ሺህ 600 በላይ ሰዎች እንደሚያዙ የሚወጣው ሪፖርት ያሳያል። አገሪቱ በአጠቃላይ " አደገኛ ቀጠና" ውስጥ መግባቷ የተገለፀ ሲሆን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና ሆቴሎች በከፊል ተዘግተዋል። ፕሬዝዳንት ዱዳ በቫይረሱ እንዴት እንደተያዙ የተገለፀ ነገር ባይኖርም፣ ሰኞ ዕለት የቡልጋርያ ፕሬዝዳንት ሩመን ራዴቭ በተገኙበት በታሊን በተዘጋጀ በዓል ላይ ተገኝተው ነበር ተብሏል። የቡልጋርያው ፕሬዝዳንት ከዚህ በዓል በኋላ ራሳቸውን ለይተው መቀመጣቸውን ተሰምቷል። "ፕሬዝዳንቱ ትናንት ተመርምረው በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል" ሲሉ የፕሬዝዳንታዊ ጽሕፈት ቤት ኃላፊው የትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። አክለውም የፕሬዝዳንቱን ጤንነት ለመከታተል ከአስፈላጊ ሕክምና ባለሙያዎች ጋር ግንኙነት እያደረጉ መሆኑን ይናገራሉ። አውሮፓ እስካሁን ድረስ 7.8 ሚሊዮን በቫይረሱ ሲያዙ፣ በዚሁ ምክንያት ደግሞ 247 000 ሰዎች ሞተዋል። በአውሮፓ ጣልያን፣ ኦስትርያ፣ ክሮሺያ፣ ስሎቫንያ እና ቦሲኒያ በቫይረሱ ክፉኛ ከተጎዱ አገራት መካከል ናቸው።
ኮሮናቫይረስ፡ የፖላንዱ ፕሬዝዳንት በኮቪድ-19 ተያዙ የፖላንድ ፕሬዝዳንት አንድሬ ዱዳ በኮቪድ-19 መያዛቸው ተገለፀ። የፕሬዝዳንቱ ጤና ሁኔታ "መልካም" መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ራሳቸውን ለይተው ውሸባ ገብተዋል ተብሏል። የ48 ዓመቱ ጉልማሳ ፕሬዝዳንት ዱዳ፣ አርብ እለት የኮሮናቫይረስ ማድረጋቸውንና መያዛቸው መታወቁ ዛሬ፣ ቅዳሜ ይፋ ተደርጓል። ፕሬዝዳንቱ በኮሮናቫይረስ የተያዙ የተለያዩ ርዕሰ ብሄሮችን ያገኙ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ይገኙበታል። 38 ሚሊዮን ዜጎች ያላት ፓላንድ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት እያገረሸ ሲሆን አርብ ዕለት ብቻ ከ13 ሺህ 600 በላይ ሰዎች እንደሚያዙ የሚወጣው ሪፖርት ያሳያል። አገሪቱ በአጠቃላይ " አደገኛ ቀጠና" ውስጥ መግባቷ የተገለፀ ሲሆን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና ሆቴሎች በከፊል ተዘግተዋል። ፕሬዝዳንት ዱዳ በቫይረሱ እንዴት እንደተያዙ የተገለፀ ነገር ባይኖርም፣ ሰኞ ዕለት የቡልጋርያ ፕሬዝዳንት ሩመን ራዴቭ በተገኙበት በታሊን በተዘጋጀ በዓል ላይ ተገኝተው ነበር ተብሏል። የቡልጋርያው ፕሬዝዳንት ከዚህ በዓል በኋላ ራሳቸውን ለይተው መቀመጣቸውን ተሰምቷል። "ፕሬዝዳንቱ ትናንት ተመርምረው በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል" ሲሉ የፕሬዝዳንታዊ ጽሕፈት ቤት ኃላፊው የትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። አክለውም የፕሬዝዳንቱን ጤንነት ለመከታተል ከአስፈላጊ ሕክምና ባለሙያዎች ጋር ግንኙነት እያደረጉ መሆኑን ይናገራሉ። አውሮፓ እስካሁን ድረስ 7.8 ሚሊዮን በቫይረሱ ሲያዙ፣ በዚሁ ምክንያት ደግሞ 247 000 ሰዎች ሞተዋል። በአውሮፓ ጣልያን፣ ኦስትርያ፣ ክሮሺያ፣ ስሎቫንያ እና ቦሲኒያ በቫይረሱ ክፉኛ ከተጎዱ አገራት መካከል ናቸው።
https://www.bbc.com/amharic/54672465
0business
በምዕራቡ ዓለም የሥራ አስፈጻሚዎች ደመወዝ ለምን በሚሊዮን ዶላሮች ሆነ?
በአውሮፓና አሜሪካ ለምን ለሥራ አስፈጻሚዎች በሚሊዮን ዶላር ይከፈላል? ካፒታሊዝም ነው፡፡ ድሆች ይበልጥ ድሀ፣ ሀብታሞች ይበልጥ ሀብታም እየሆኑ ይሄዳሉ፡፡ ካፒታሊዝም ነው፡፡ ሀብታሞች በጣም ሀብታም፣ ወዝ አደሮች ደግሞ ከድህነት አረንቋ ይወጣሉ፡፡ ቀስ በቀስ፡፡ ሁለቱ አተያዮች ሊያከራክሩ ይችላሉ፡፡ ሁለቱም ግን እውነትነት አላቸው፡፡ የዓለም አዱኛ ከዓለም ሕዝብ 1 እጅ እንኳ በማይሞሉ ጥቂት ሰዎች መያዙ ግን አያከራክርም፡፡ የዚህ ጽሑፍ ማጠንጠኛ ደመወዝ ነው፡፡ የወዝ ደም፤ የላብ ክፍያ፡፡ የሚያልባቸው ሁሉ ለምን ተቀራራቢ ደምወዝ አይከፈላቸውም? የነጭ ባለኮሌታዎች ዋጋ ለምን ይንራል? ዋናዎቹ ባለጉዳዮቻችን የኩባንያ ባለቤቶች ሳይሆኑ ሥራ አስፈጻሚዎቻቸው ናቸው፡፡ እርግጥ ነው አንዳንድ ኩባንያዎች ፈጣሪዎቻቸው ሥራ አስፈጻሚዎቻቸውም ጭምር ናቸው፡፡ እነሱንም እንመለከታለን፡፡ ይቺ ዓለም ፍትሐዊ ናት? ይህ ጥያቄ እንደመላሹ ነው፡፡ በሚሊዮን ዶላር የሚከፈለው አለቃ ለዚህ ጥያቄ የሚሰጠው ምላሽ አዎንታዊ ነው፡፡ ለላብ አደሩ አሉታዊ ነው፡፡ በ2020 ብዙ ኩባንያዎች የገንዘብ ቀውስ ገጥሟቸዋል፡፡ ብዙዎች ሠራተኞቻቸውን በትነዋል፡፡ ያም ሆኖ ለሥራ አስፈጻሚዎቻቸው በሚሊዮን ዶላሮች ከፍለዋል፤ ይከፍላሉ፡፡ ለምሳሌ የአሜሪካኑን ጎልድማን ሳክስ ባንክ ሥራ አስፈጻሚ ዴቪድ ሰሎሞንን ደመወዝ እንውሰድ፡፡ በዓመት 30 ሚሊዮን ዶላር በአማካይ ወደ ባንክ ደብተሩ ሸርተት ብሎ ይገባለታል፡፡ ዘንድሮ ብቻ ነው 10 ሚሊዮን የተቀነሰበት፡፡ እሱም ከማሌዢያ መንግሥት ጋር በተፈጠረ ምዝበራ የተነሳ ነው፡፡ ድሮ ደመወዝ እንደዚህ አልበረም፡፡ በላብ አደሩና በአሰሪ አለቆች መካከል እንዲህ የሰማይና የምድር ያህል የሚራራቅ ክፍያ ልዩነት አልነበረም፡፡ የሎንዶኑ ‹ሃይ ፔይ ሴንተር› የሠራው አንድ ጥናት የፋይናንሻል ታይምስ ስቶክ ኤክሰቼንጅ (ኤፍቲኤስኢ) ኃላፊዎች በአማካይ 5 ሚሊዮን ዶላር ነው ደመወዛቸው ይላል፡፡ ይህ ማለት ሁሉም ቋሚ ሰራተኞች ከሚያገኙት ድምር መቶ እጥፍ ማለት ነው፡፡ ኢካዶ የድረገጽ ሱፐርማርኬትን እንውሰድ፡፡ ሥራ አስፈጻሚው ቲም ስቴይነር በ2019 ዓ/ም ደመወዙ ስንት ነበር? ማመን ይከብዳል፡፡ 59 ሚሊዮን ዶላር፡፡ አዎ አልተሳሳቱም፡፡ 59 ሚሊዮን ዶላር ዓመታዊ ደመወዝ ይከፈለዋል፡፡ ይህ ክፍያ ማለት አማካይ የሱፐርማርኬቱ ሰራተኞች በጠቅላላ ተደምሮ 2ሺ 605 ጊዜ እጥፍ ክፍያ ማለት ነው፡፡ በሌላ ቋንቋ ቲም በቀን የሚከፈለው የሌሎቹ የዓመት ደመወዛቸው ተደምሮ በ7 ቢባዛ የሚያገኙት ነው፡፡ እና ይቺ ዓለም ፍትሐዊ ናት? ለቲም ትሆን ይሆናል፡፡ ካች አፕና የጨው ብልቃጥ ለሚደረድር የኢካዶ ሠራተኛ ግን በፍጹም፡፡ አትላንቲክን እንሻገር፡፡ ዋሺንግተን ዲሲ የሚገኘው የኢኮኖሚክ ፖሊሲ ኢንስቲትዩት በሠራው ጥናት 350 የአሜሪካ ግዙፍ ኩባንያዎች ሥራ አስፈጻሚዎች የሚያገኙት አማካይ ደመወዝ 21 ሚሊዮን ዶላር ነው፡፡ ይህ ጥናት ይፋ የሆነበት ጊዜ ራሱ አስገራሚ ነው፡፡ በሽታ ሰው አይመርጥም ይባላል፡፡ የኮሮና ወረርሽኝ ግን ደሃና ጥቁሩ ላይ ነው የበረታው፡፡ ለምን? ብዙ ምክንያቶች አሉ፡፡ አንዱ ላብ አደሩ የጤና መድኅን የለውም፡፡ ሌላው ላብ አደሩ የሚሠራበት ሁኔታ ለተህዋሲው የሚያጋልጥ ነው፡፡ ሌላው ላብ አደሩ ጥሮ ግሮ ሲሠራ ፋታ የለውም፡፡ ራሱን ለመጠበቅ አይችልም፡፡ ሌላው ላብ አደሩ የሚያድረው ባልተመቻቸ ሁኔታና በተጨናነቀ ጭርንቁስ ሰፈር ነው፡፡ የዚህ ሁሉ ምንጭ የክፍያ ማነስ ነው፡፡ ለምሳሌ ‹ወሳኝ ሠራተኞች› እያለ ሚዲያው የሚጠራቸው ለፍቶ አዳሪዎች የሰውን ነፍስ ለማዳን ራሳቸውን የሚያጋልጡ ናቸው፡፡ የጤና ረዳቶችን ይጨምራል፡፡ ሆኖም ሕዝብ እየወጣ ሻማ አበራላቸው እንጂ ክፍያ አልጨመረላቸውም፡፡ ብዙ ሚስኪን ላብ አደሮች ለፍተው ሲያድሩ በዚያው ፍግም ብለው ያልፋሉ፡፡ አኗኗራቸውም አሟሟታቸውም አላማረም፡፡ የካታሊስት ሥርዓት ግን ሊያደርግ የቻለው ደማቅ የሻማ ማብራት ሥነ ሥርዓት ማሰናዳት ነው፡፡ ሌላም ያደረገው ነገር አለ፡፡ ሚሊዮን ዶላር የሚያገኘው/የምታገኘው ሥራ አስፈጻሚ በሻማ ማብራቱ ሥነ ሥርዓት ላይ የሐዘን ቃል ያሰማሉ፡፡ ይህ ለሥራ አስፈጻሚዎች ቁልል ደመወዝ የመክፈሉ ሐሳብና ፖሊሲው በሬገን መንግሥት ጊዜ ነው ይበልጥ እየተዋወቀ የመጣው ይባላል፡፡ በታላቋ ብሪታኒያ ደግሞ ማርጋሬት ታቸር ናቸው የጀመሩት ይላሉ፡፡ ምናልባት የፖለቲካ ፍልስፍናቸው የነጭ ካፒታሊዝም ስለነበር ይሆናል፡፡ ያን ጊዜ ሁሉም ነገር ወደ ግል ዘርፉ እየሄደ ነበር፡፡ ሁሉም ነገር ለነጻ ገበያ ተላልፎ እየተሰጠ ነበር፡፡ ሬገንም ሆኑ ታቼር የሠራተኛ ማኅበራትን በበጎ አይመለከቱም ነበር፡፡ ለዚህም ይመስላል ሠራተኞች ለክፍያ መሻሻል ሳይታገሉ፣ ቢታገሉም ፍሬ ሳያፈራላቸው እንዲሁ ላብ አደር ሆነው ጉልበታቸው ሲበዘበዝ የኖረው፡፡ "ያንን ዘመን ልብ ብለን ካስተዋልን ክፍያ ሲሻሻል የሁሉም በአንድ ላይ ነበር እንጂ የሥራ አስፈጻሚው ለብቻ ተነጥሎ አይታይም ነበር" ይላሉ ሳንዲ ፔፐር፡፡ ሳንዲ በሎንዶን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ የክፍያ ጉዳዮች ተመራማሪ ናቸው፡፡ ሳንዲ ለምን በየዘመኑ የተራ ሠራተኞችና የሥራ አስፈጻሚዎች ክፍያ እየተንቦረቀቀ መጣ በሚለው ላይ ጥናት አድርገዋል፡፡ ቀድሞ አለቃና ተራው ሠራተኛ በክፍያ ጭማሪ ወቅት በእኩል ይታይ የነበረው አሠራር እየፈረሰ የመጣው የሥራ አስፈጻሚዎች ክፍያ ከሽርክና ዋጋ እና ውጤት ተኮር አበሎች ጋር እየተሳሰረ መምጣቱን ተከትሎ ነው፡ ይላሉ ሚስተር ሳንዲ፡፡ ትርፍን ብቻ የሚያሳድደው ኒዎ ሊበራሊዝም ይህን አሠራር እያበረታታው መጣ፡፡ ከ2000 ዓ/ም ጀምሮ የተወሰደ የኤፍቲኤስኢ100 ዳታ እንደሚያሳያው የሠራተኞች ደመወዝ ጭማሪ በየዓመቱ በአማካይ 3 ከመቶ ሲሆን የሥራ አስፈጻሚዎች ግን በ10 ከመቶ ይመነደጋል፤ በየዓመቱ፡፡ አሁን ባለው አሰራር የሥራ አስፈጻሚዎችን ክፍያ የሚወስነው የኩባንያዎች ዓመታዊ የትርፍ አፈጻጸም እየሆነ መጥቷል፡፡ ምክንያቱም ሥራ አስፈጻሚዎች ለኩባንያዎች ማበብና መክሰም ወሳኞች እየሆኑ መምጣታቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ከመደበኛ የደመወዝ ምጣኔ በተጨማሪ ሥራ አስፈጻሚዎች ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች እንዲንበሸበሹ አድርጓቸዋል፡፡ ከነዚህም መካከል በኩባንያው ውስጥ ድርሻ እንዲኖራቸው በማድረግ የባለቤትነት ስሜት እንዲያድርባቸው ማስቻል፤ ኩባንያው ትርፋማ ሲሆን ደግሞ በተገኘው ትርፍ ልክ አበል መስጠትን ያካትታል፡፡ ለአብነት ቅድም ባነሳነው የኢካዶ የድረ ገጽ ሱፐርማርኬት ምሳሌ ሥራ አስፈጻሚው ስቴይነር በ2019 ከተከፈላቸው ዓመታዊ ደመወዝ ውስጥ 54 ሚሊዮን ፓውንድ ጉርሻ ይገኝበታል፡፡ ይህም የኩባንያውን የ5 ዓመት የእድገትና ትርፍ እቅድ በማሳካታቸው ያገኙት ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ ኩባንያዎች ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም የሚወስንላቸው በዓመት አንድ ጊዜ በሚሰበሰብ ቦርድ ነው፡፡ የቦርድ አባላት ደግሞ ከሌሎች ኩባንያዎች የተውጣጡ ሥራ አስፈጻሚዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ይህ በእንዲህ ሳለ ብዙዎቹ የብሪታኒያ ቢዝነሶች በግለሰቦች ባለቤትነት መሆናቸው በአያሌው ቀንሷል፡፡ የትልልቅ ሼር ባለቤቶች ጡንቻ እየፈረጠመ ነው የመጣው፡፡ እነሱ ደግሞ የስቶክ ዋጋ በፍጥነት እንዲጨምርላቸው ይፈልጋሉ፡፡ ስለዚህ ለሥራ አስፈጻሚዎች ወፍራም ደመወዝ ይከፍላሉ፡፡ የቦርድ አባላት ደግሞ የሼር ባለቤቶችን ለማስደሰት የሥራ አስፈጻሚን ደመወዝ ከፍ ያደርጋሉ፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፡፡ የሥራ አስፈጻሚ ጥቅማ ጥቅም የሚሰላው ከተመሳሳይ ኩባንያዎች ጋር በማወዳደር ነው፡፡ እነሱ በሌላ ኩባንያዎች ሥራ አስፈጻሚ ስለሆኑ የሌላውን ሲያሻሽሉ የነሱም እንደሚሻሳል ይረዳሉ፡፡ ስለዚህ ወፍራሙን ደመወዝና ቁልሉን አበል ያጸድቁታል፡፡ አንዳንድ ጊዜ የቦርድ አባላት ከሠራተኞችም ይወከላል፡፡ ሠራተኞች ትልቁን አለቃ ማስቀየም አይፈልጉም፡፡ ነገ ሊያባርራቸው ይችላል፡፡ ወይም በትርፍ ላይ ያለን ኩባንያ ጥሎ ሄዶ ኮርፖሬሽኑን ለሌላ ኪሳራ ሊያጋልጠው ይችላል፡፡ ኩባንያው ከሰረ ማለት የሥራ ዋስትና ታጣ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የክፍያ ጭማሪን በምንም መልኩ ለመቃወም አይደፍሩም፡፡ ምንም እንኳ ለሥራ አስፈጻሚዎች የሚከፈለው ረብጣ ዶላር ልክ ነው አይደለም በሚለው ላይ ሰፊ ክርክር ቢኖርም የነጻ ገበያ አቀንቃኝ የሆኑ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ግን አስፈጻሚዎች ለኩባንያ የሚያመጡት ገቢ አጥጋቢ እስከሆነ ድረስ የሚያጠግብ ደመወዝ መከፈሉ ምንድነው ችግሩ? ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡ ነገሩ ሁሉ ገበያ መር ነው፡፡ አንድ ኩባንያ በኪሳራ እየሰመጠ ለአለቆች ያን ያህል ሊከፍል አይችልም፡፡ ገበያ መር ስንል የቁስ ዋጋን ብቻ ሳይሆን የወዝአደር ዋጋም ማለታችን ነው ይላሉ፡፡ "ሥራ አስፈጻሚዎች ቁልፍ የስኬት ሞተሮች ናቸው፡፡" ይላሉ በአዳም ስሚዝ ኢንስቲትዩት የኒዮሊበራል ባለሙያዎች ስብስብ (ቲንክታንክ) ፕሮግራም ኃላፊ ዳኒኤል ፕራዮር፡፡ "ግልጽ ነው እኮ፤ አንድን ኩባንያ አትራፊ ማድረግ የሚያስችል የአስተዳደር ጥበብ፣ የዕውቀት ስንቅና ብልሀት ያላቸው ሰዎች ጥቂት ናቸው፡፡ በገበያው እንዲህ ዓይነት ላቅ ያለ የአመራር ክህሎት ሁሉም ሰው የለውም፡፡ ስለዚህ እነዚህ ጥቂት ሰዎች ላይ ገበያው ይራኮታል፡፡ ክፍያቸው ጣሪያ የሚነካውም ለዚሁ ነው" ይላሉ፡፡ ዴቪድ ቦልቾፈር ግን በዚህ አይስማሙም፡፡ "ማነው የአመራር ክህሎት ያላቸው ሰዎች ጥቂት ናቸው ያለው ብለው ይጠይቃሉ፡፡ ይሄ ማጭበርበር ነው፡፡" ሚስተር ዳንኤል ክፍያው ተገቢ ነው የሚሉት የአፕሉን ስቲቭ ጆብስ፣ የአማዞኑን ጄፍ ቤዞስ፣ የተስላና የስፔስኤክስ ፈጣሪን ኤሎን መስክንና የመሳሰሉትን እጅግ የነጠረ ክህሎት በማንሳት ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች አዲስ ነገር ፈጥረው የገበያና የቴክኖሎጂ አብዮት ያመጡ ሰዎች ናቸው፡፡ "መደበኛ ሥራ አስፈጻሚዎች ግን እንደነ ኤሎን መስክ ያሉት አይደሉም" ይላሉ ዴቪድ ቦልቾፈር፡፡ እነዚህ መደበኛ ሥራ አስፈጻሚዎች ሚናቸውም ክፍያቸውም የተጋነነ ነው ብለው የሚከራከሩትም ለዚሁ ነው፡፡ አንድ ኩባንያ በሥራ አስፈጻሚው ብርታትና ምጥቀት ብቻ አይደለም ትርፋማ የሚሆነው የሚሉት ሚስተር ዴቪድ ፔይ ቼክ በሚለው መጽሐፋቸው ላይ ይህን ጉዳይ በዝርዝር ጽፈውታል፡፡ አንዳንድ ዘርፎች በተለያዩ ምክንያቶች አትራፊነታቸው ይቀጥላል፤ የትኛውም ተመሳሳይ አቅም ያለው ሰው ቢመራቸው፡፡ የቴሌኮም ዘርፎችን ምሳሌ ማንሳት ይቻላል፡፡ ወይም ቀድሞውኑም ጥሩ መሠረት ላይ የተገነቡ ቢዝነሶች፡፡ በዚህ ረገድ ሥራ አስፈጻሚዎች ምንም ቦታ ላይኖራቸው ይችላል፡፡ ምናልባት የሠራተኞች ትጋት ይሆናል የትርፍማነቱ ምንጭ፡፡ ሆኖም አለቆች የሚበሉት ደመወዝ የትየሌሌ ነው፡፡ "በኮርፖሬሽኖች የሥራ አስፈጻሚዎች ሚና ብዙውን ጊዜ ይጋነናል፡፡ ይህ ሆን ተብሎ የሚደረግ ማጭበርበሪያ ነው፡፡" ይላሉ ዴቪድ ቦልቸር፡፡ ቦልቸር ሌላም ማስረጃ ያቀርባሉ፡፡ ለምሳሌ የ2008 የፋይናንስ ቀውስ ጊዜ ባንኮች በኪሳራ ሲንኮታኮቱ ሥራ አስፈጻሚዎቻቸው ግን ሚሊዮን ዶላሮችን ታቅፈው ነው የሄዱት፡፡ ይህ ነገር በጊዜው ብዙዎችን አቁስሎ ነገሩ ላይ ጥያቄም መነሳት ጀምሮ ነበር፡፡ "ክፍያ አስፈጻሚዎች ባስገኙት የስኬት መጠን ነው ከተባለ የነዚህ ባንኮች ሥራ አስፈጻሚዎች ለምን ከኪሳ በኋላም ወፍራም ደመወዝ እየተከፈላቸው ቆዩ?" ሲሉም ይጠይቃሉ፡፡ መልሱን ራሳቸው ሲመልሱም የጥቅም ትስስር ስላለ ነው ይላሉ፡፡ የጥቅም ትስስሩ በቦርድ አባላት፣ በሥራ አስፈጻሚዎችና በሽርክና ባለቤቶች መካከል ነው፡፡ ተራው ሠራተኛ ደመወዙ ለምን ያሽቆለቁላል? የሥራ አስፈጻሚዎች ደመወዝ ሲመነደግ የተራ ሠራተኛው ደመወዝ ቁልቁለቱን ተያይዞታል፡፡ ለምሳሌ በዚህ ወረርሽኝ የወሳኝ ሰራተኞች ደመወዝ ማነሱ ብቻ ሳይሆን እሱንም ለማግኘት ሕይወታቸው ላይ ለመቆመር ይገደዳሉ፡፡ ይህ የተራ ሠራተኞች ደመወዝ ማሽቆልቆል ብዙዎችን ደም እያፈላ ነው፡፡ ለምሳሌ በሺህ የሚቆጠሩ የብሪቲሽ ጋስ ኩባንያ ሰራተኞች የ5 ቀን የሥራ ማቆም አድማ አድርገው ነበር፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ የሠራተኛ ቅነሳ መደረጉ ነው፡፡ ብዙ ሠራተኞች በጥቂት መብቶች ብቻ ተወስነው በአስቸጋሪ ሁኔታ እንዲሰሩ መገደዳቸው ነው፡፡ ውጥረቱ ይበልጥ የተካረረው ደግሞ ከ2018 ጀምሮ ብሪቲሽ ጋስን በባለቤትነት የያዘው ሴንትሪካ ኩባንያ ሥራ አስፈጻሚ የ44 ከመቶ ጭማሪ ማግኘታቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ዓመታዊ ደመወዛቸው 2 ሚሊዮን ተኩል ፓውንድ ያልፋል፡፡ "ይህ ስግብግብነት ነው" ይላል የ32 ዓመቱ የብሪቲሽ ጋስ ሰራተኛ ጆን፡፡ ይህ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር እንኳ የማይከፈላቸው ደመወዝ መጠን ነው፡፡ እንዴት ነው ሰራተኛን እየቀነሰ ያለ ኩባንያ ለሥራ አስፈጻሚው ይህን ያህል ፓውንድ የሚከፍለው? በጭራሽ ስሜት አይሰጥም፡፡ አንዳንድ መልካም ሥራ አስፈጻሚዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ የቦይንግ፣ የማሪዮት ኢንተርናሽናል የፒደብሊውሲ ሥራ አስፈጻሚዎች ሰራተኛ እንዳይቀነስ ሲሉ ደመወዛቸውን ጭማሪ ይቅርብን ያሉ ናቸው፡፡ አንዳንዶች ይህን ድርጊታቸውን ለታይታ የተደረገ እንጂ መሰረታዊ ለውጥ የማያመጣ ነው ሲሉ ይተቹታል፡፡ መጪው ጊዜ አስፈሪ ነው፡፡ ለተራ ሰራተኛ፣ ለላብ አደሩ፣ ድምጹ ለማይሰማው፣ ላቡ ለሚንቆረቆረው ብዙኃን በተለይ መጪው ዘመን ቀበቶ ጠበቅ የሚደረግበት ነው፡፡ ምክንያቱም ኩባንያዎች ገቢ ቀንሷል፡፡ ከቴክ ኩባንያዎች ውጭ ያለው ዘርፍ በወረርሽኙ ድባቅ ተመቷል፡፡ የአርተፊሻል ልህቀትና ሌሎች ማሽኖች የጉልበት ሥራን ዋጋ እያሳጡት ነው፡፡ ኢንተርኔት ንግድ የሰራተኛን አስፈላጊነት እምብዛምም አድርጎታል፡፡ ፋይናንስ ኢንዱስትሪዎች በእንብርክክ እየሄዱ ነው፡፡ የሰራተኛ ማኅበራት እየተዳከሙ ሄደዋል፡፡ ስለዚህ መጪው ጊዜ ሚሊየነሮች ቢሊየነሮች የሚሆኑበት፣ ላብ አደሮች ይበልጥ ላባቸው በከንቱ የሚፈስበት እንደሆነ የዓለም ምጣኔ ሀብትን በቅርብ የሚከታተሉ አዋቂዎች ትንቢት ነው፡፡ የዓለም ሀብት በጥቂቶች እጅ ይቀፈደዳል፡፡ ቢሊዮኖች ግን በቃ ቁጥር ናቸው፡፡ ተወልደው፣ ኖረው፣ ጥረው ግረው፣ የሚሞቱ፡፡
በምዕራቡ ዓለም የሥራ አስፈጻሚዎች ደመወዝ ለምን በሚሊዮን ዶላሮች ሆነ? በአውሮፓና አሜሪካ ለምን ለሥራ አስፈጻሚዎች በሚሊዮን ዶላር ይከፈላል? ካፒታሊዝም ነው፡፡ ድሆች ይበልጥ ድሀ፣ ሀብታሞች ይበልጥ ሀብታም እየሆኑ ይሄዳሉ፡፡ ካፒታሊዝም ነው፡፡ ሀብታሞች በጣም ሀብታም፣ ወዝ አደሮች ደግሞ ከድህነት አረንቋ ይወጣሉ፡፡ ቀስ በቀስ፡፡ ሁለቱ አተያዮች ሊያከራክሩ ይችላሉ፡፡ ሁለቱም ግን እውነትነት አላቸው፡፡ የዓለም አዱኛ ከዓለም ሕዝብ 1 እጅ እንኳ በማይሞሉ ጥቂት ሰዎች መያዙ ግን አያከራክርም፡፡ የዚህ ጽሑፍ ማጠንጠኛ ደመወዝ ነው፡፡ የወዝ ደም፤ የላብ ክፍያ፡፡ የሚያልባቸው ሁሉ ለምን ተቀራራቢ ደምወዝ አይከፈላቸውም? የነጭ ባለኮሌታዎች ዋጋ ለምን ይንራል? ዋናዎቹ ባለጉዳዮቻችን የኩባንያ ባለቤቶች ሳይሆኑ ሥራ አስፈጻሚዎቻቸው ናቸው፡፡ እርግጥ ነው አንዳንድ ኩባንያዎች ፈጣሪዎቻቸው ሥራ አስፈጻሚዎቻቸውም ጭምር ናቸው፡፡ እነሱንም እንመለከታለን፡፡ ይቺ ዓለም ፍትሐዊ ናት? ይህ ጥያቄ እንደመላሹ ነው፡፡ በሚሊዮን ዶላር የሚከፈለው አለቃ ለዚህ ጥያቄ የሚሰጠው ምላሽ አዎንታዊ ነው፡፡ ለላብ አደሩ አሉታዊ ነው፡፡ በ2020 ብዙ ኩባንያዎች የገንዘብ ቀውስ ገጥሟቸዋል፡፡ ብዙዎች ሠራተኞቻቸውን በትነዋል፡፡ ያም ሆኖ ለሥራ አስፈጻሚዎቻቸው በሚሊዮን ዶላሮች ከፍለዋል፤ ይከፍላሉ፡፡ ለምሳሌ የአሜሪካኑን ጎልድማን ሳክስ ባንክ ሥራ አስፈጻሚ ዴቪድ ሰሎሞንን ደመወዝ እንውሰድ፡፡ በዓመት 30 ሚሊዮን ዶላር በአማካይ ወደ ባንክ ደብተሩ ሸርተት ብሎ ይገባለታል፡፡ ዘንድሮ ብቻ ነው 10 ሚሊዮን የተቀነሰበት፡፡ እሱም ከማሌዢያ መንግሥት ጋር በተፈጠረ ምዝበራ የተነሳ ነው፡፡ ድሮ ደመወዝ እንደዚህ አልበረም፡፡ በላብ አደሩና በአሰሪ አለቆች መካከል እንዲህ የሰማይና የምድር ያህል የሚራራቅ ክፍያ ልዩነት አልነበረም፡፡ የሎንዶኑ ‹ሃይ ፔይ ሴንተር› የሠራው አንድ ጥናት የፋይናንሻል ታይምስ ስቶክ ኤክሰቼንጅ (ኤፍቲኤስኢ) ኃላፊዎች በአማካይ 5 ሚሊዮን ዶላር ነው ደመወዛቸው ይላል፡፡ ይህ ማለት ሁሉም ቋሚ ሰራተኞች ከሚያገኙት ድምር መቶ እጥፍ ማለት ነው፡፡ ኢካዶ የድረገጽ ሱፐርማርኬትን እንውሰድ፡፡ ሥራ አስፈጻሚው ቲም ስቴይነር በ2019 ዓ/ም ደመወዙ ስንት ነበር? ማመን ይከብዳል፡፡ 59 ሚሊዮን ዶላር፡፡ አዎ አልተሳሳቱም፡፡ 59 ሚሊዮን ዶላር ዓመታዊ ደመወዝ ይከፈለዋል፡፡ ይህ ክፍያ ማለት አማካይ የሱፐርማርኬቱ ሰራተኞች በጠቅላላ ተደምሮ 2ሺ 605 ጊዜ እጥፍ ክፍያ ማለት ነው፡፡ በሌላ ቋንቋ ቲም በቀን የሚከፈለው የሌሎቹ የዓመት ደመወዛቸው ተደምሮ በ7 ቢባዛ የሚያገኙት ነው፡፡ እና ይቺ ዓለም ፍትሐዊ ናት? ለቲም ትሆን ይሆናል፡፡ ካች አፕና የጨው ብልቃጥ ለሚደረድር የኢካዶ ሠራተኛ ግን በፍጹም፡፡ አትላንቲክን እንሻገር፡፡ ዋሺንግተን ዲሲ የሚገኘው የኢኮኖሚክ ፖሊሲ ኢንስቲትዩት በሠራው ጥናት 350 የአሜሪካ ግዙፍ ኩባንያዎች ሥራ አስፈጻሚዎች የሚያገኙት አማካይ ደመወዝ 21 ሚሊዮን ዶላር ነው፡፡ ይህ ጥናት ይፋ የሆነበት ጊዜ ራሱ አስገራሚ ነው፡፡ በሽታ ሰው አይመርጥም ይባላል፡፡ የኮሮና ወረርሽኝ ግን ደሃና ጥቁሩ ላይ ነው የበረታው፡፡ ለምን? ብዙ ምክንያቶች አሉ፡፡ አንዱ ላብ አደሩ የጤና መድኅን የለውም፡፡ ሌላው ላብ አደሩ የሚሠራበት ሁኔታ ለተህዋሲው የሚያጋልጥ ነው፡፡ ሌላው ላብ አደሩ ጥሮ ግሮ ሲሠራ ፋታ የለውም፡፡ ራሱን ለመጠበቅ አይችልም፡፡ ሌላው ላብ አደሩ የሚያድረው ባልተመቻቸ ሁኔታና በተጨናነቀ ጭርንቁስ ሰፈር ነው፡፡ የዚህ ሁሉ ምንጭ የክፍያ ማነስ ነው፡፡ ለምሳሌ ‹ወሳኝ ሠራተኞች› እያለ ሚዲያው የሚጠራቸው ለፍቶ አዳሪዎች የሰውን ነፍስ ለማዳን ራሳቸውን የሚያጋልጡ ናቸው፡፡ የጤና ረዳቶችን ይጨምራል፡፡ ሆኖም ሕዝብ እየወጣ ሻማ አበራላቸው እንጂ ክፍያ አልጨመረላቸውም፡፡ ብዙ ሚስኪን ላብ አደሮች ለፍተው ሲያድሩ በዚያው ፍግም ብለው ያልፋሉ፡፡ አኗኗራቸውም አሟሟታቸውም አላማረም፡፡ የካታሊስት ሥርዓት ግን ሊያደርግ የቻለው ደማቅ የሻማ ማብራት ሥነ ሥርዓት ማሰናዳት ነው፡፡ ሌላም ያደረገው ነገር አለ፡፡ ሚሊዮን ዶላር የሚያገኘው/የምታገኘው ሥራ አስፈጻሚ በሻማ ማብራቱ ሥነ ሥርዓት ላይ የሐዘን ቃል ያሰማሉ፡፡ ይህ ለሥራ አስፈጻሚዎች ቁልል ደመወዝ የመክፈሉ ሐሳብና ፖሊሲው በሬገን መንግሥት ጊዜ ነው ይበልጥ እየተዋወቀ የመጣው ይባላል፡፡ በታላቋ ብሪታኒያ ደግሞ ማርጋሬት ታቸር ናቸው የጀመሩት ይላሉ፡፡ ምናልባት የፖለቲካ ፍልስፍናቸው የነጭ ካፒታሊዝም ስለነበር ይሆናል፡፡ ያን ጊዜ ሁሉም ነገር ወደ ግል ዘርፉ እየሄደ ነበር፡፡ ሁሉም ነገር ለነጻ ገበያ ተላልፎ እየተሰጠ ነበር፡፡ ሬገንም ሆኑ ታቼር የሠራተኛ ማኅበራትን በበጎ አይመለከቱም ነበር፡፡ ለዚህም ይመስላል ሠራተኞች ለክፍያ መሻሻል ሳይታገሉ፣ ቢታገሉም ፍሬ ሳያፈራላቸው እንዲሁ ላብ አደር ሆነው ጉልበታቸው ሲበዘበዝ የኖረው፡፡ "ያንን ዘመን ልብ ብለን ካስተዋልን ክፍያ ሲሻሻል የሁሉም በአንድ ላይ ነበር እንጂ የሥራ አስፈጻሚው ለብቻ ተነጥሎ አይታይም ነበር" ይላሉ ሳንዲ ፔፐር፡፡ ሳንዲ በሎንዶን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ የክፍያ ጉዳዮች ተመራማሪ ናቸው፡፡ ሳንዲ ለምን በየዘመኑ የተራ ሠራተኞችና የሥራ አስፈጻሚዎች ክፍያ እየተንቦረቀቀ መጣ በሚለው ላይ ጥናት አድርገዋል፡፡ ቀድሞ አለቃና ተራው ሠራተኛ በክፍያ ጭማሪ ወቅት በእኩል ይታይ የነበረው አሠራር እየፈረሰ የመጣው የሥራ አስፈጻሚዎች ክፍያ ከሽርክና ዋጋ እና ውጤት ተኮር አበሎች ጋር እየተሳሰረ መምጣቱን ተከትሎ ነው፡ ይላሉ ሚስተር ሳንዲ፡፡ ትርፍን ብቻ የሚያሳድደው ኒዎ ሊበራሊዝም ይህን አሠራር እያበረታታው መጣ፡፡ ከ2000 ዓ/ም ጀምሮ የተወሰደ የኤፍቲኤስኢ100 ዳታ እንደሚያሳያው የሠራተኞች ደመወዝ ጭማሪ በየዓመቱ በአማካይ 3 ከመቶ ሲሆን የሥራ አስፈጻሚዎች ግን በ10 ከመቶ ይመነደጋል፤ በየዓመቱ፡፡ አሁን ባለው አሰራር የሥራ አስፈጻሚዎችን ክፍያ የሚወስነው የኩባንያዎች ዓመታዊ የትርፍ አፈጻጸም እየሆነ መጥቷል፡፡ ምክንያቱም ሥራ አስፈጻሚዎች ለኩባንያዎች ማበብና መክሰም ወሳኞች እየሆኑ መምጣታቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ከመደበኛ የደመወዝ ምጣኔ በተጨማሪ ሥራ አስፈጻሚዎች ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች እንዲንበሸበሹ አድርጓቸዋል፡፡ ከነዚህም መካከል በኩባንያው ውስጥ ድርሻ እንዲኖራቸው በማድረግ የባለቤትነት ስሜት እንዲያድርባቸው ማስቻል፤ ኩባንያው ትርፋማ ሲሆን ደግሞ በተገኘው ትርፍ ልክ አበል መስጠትን ያካትታል፡፡ ለአብነት ቅድም ባነሳነው የኢካዶ የድረ ገጽ ሱፐርማርኬት ምሳሌ ሥራ አስፈጻሚው ስቴይነር በ2019 ከተከፈላቸው ዓመታዊ ደመወዝ ውስጥ 54 ሚሊዮን ፓውንድ ጉርሻ ይገኝበታል፡፡ ይህም የኩባንያውን የ5 ዓመት የእድገትና ትርፍ እቅድ በማሳካታቸው ያገኙት ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ ኩባንያዎች ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም የሚወስንላቸው በዓመት አንድ ጊዜ በሚሰበሰብ ቦርድ ነው፡፡ የቦርድ አባላት ደግሞ ከሌሎች ኩባንያዎች የተውጣጡ ሥራ አስፈጻሚዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ይህ በእንዲህ ሳለ ብዙዎቹ የብሪታኒያ ቢዝነሶች በግለሰቦች ባለቤትነት መሆናቸው በአያሌው ቀንሷል፡፡ የትልልቅ ሼር ባለቤቶች ጡንቻ እየፈረጠመ ነው የመጣው፡፡ እነሱ ደግሞ የስቶክ ዋጋ በፍጥነት እንዲጨምርላቸው ይፈልጋሉ፡፡ ስለዚህ ለሥራ አስፈጻሚዎች ወፍራም ደመወዝ ይከፍላሉ፡፡ የቦርድ አባላት ደግሞ የሼር ባለቤቶችን ለማስደሰት የሥራ አስፈጻሚን ደመወዝ ከፍ ያደርጋሉ፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፡፡ የሥራ አስፈጻሚ ጥቅማ ጥቅም የሚሰላው ከተመሳሳይ ኩባንያዎች ጋር በማወዳደር ነው፡፡ እነሱ በሌላ ኩባንያዎች ሥራ አስፈጻሚ ስለሆኑ የሌላውን ሲያሻሽሉ የነሱም እንደሚሻሳል ይረዳሉ፡፡ ስለዚህ ወፍራሙን ደመወዝና ቁልሉን አበል ያጸድቁታል፡፡ አንዳንድ ጊዜ የቦርድ አባላት ከሠራተኞችም ይወከላል፡፡ ሠራተኞች ትልቁን አለቃ ማስቀየም አይፈልጉም፡፡ ነገ ሊያባርራቸው ይችላል፡፡ ወይም በትርፍ ላይ ያለን ኩባንያ ጥሎ ሄዶ ኮርፖሬሽኑን ለሌላ ኪሳራ ሊያጋልጠው ይችላል፡፡ ኩባንያው ከሰረ ማለት የሥራ ዋስትና ታጣ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የክፍያ ጭማሪን በምንም መልኩ ለመቃወም አይደፍሩም፡፡ ምንም እንኳ ለሥራ አስፈጻሚዎች የሚከፈለው ረብጣ ዶላር ልክ ነው አይደለም በሚለው ላይ ሰፊ ክርክር ቢኖርም የነጻ ገበያ አቀንቃኝ የሆኑ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ግን አስፈጻሚዎች ለኩባንያ የሚያመጡት ገቢ አጥጋቢ እስከሆነ ድረስ የሚያጠግብ ደመወዝ መከፈሉ ምንድነው ችግሩ? ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡ ነገሩ ሁሉ ገበያ መር ነው፡፡ አንድ ኩባንያ በኪሳራ እየሰመጠ ለአለቆች ያን ያህል ሊከፍል አይችልም፡፡ ገበያ መር ስንል የቁስ ዋጋን ብቻ ሳይሆን የወዝአደር ዋጋም ማለታችን ነው ይላሉ፡፡ "ሥራ አስፈጻሚዎች ቁልፍ የስኬት ሞተሮች ናቸው፡፡" ይላሉ በአዳም ስሚዝ ኢንስቲትዩት የኒዮሊበራል ባለሙያዎች ስብስብ (ቲንክታንክ) ፕሮግራም ኃላፊ ዳኒኤል ፕራዮር፡፡ "ግልጽ ነው እኮ፤ አንድን ኩባንያ አትራፊ ማድረግ የሚያስችል የአስተዳደር ጥበብ፣ የዕውቀት ስንቅና ብልሀት ያላቸው ሰዎች ጥቂት ናቸው፡፡ በገበያው እንዲህ ዓይነት ላቅ ያለ የአመራር ክህሎት ሁሉም ሰው የለውም፡፡ ስለዚህ እነዚህ ጥቂት ሰዎች ላይ ገበያው ይራኮታል፡፡ ክፍያቸው ጣሪያ የሚነካውም ለዚሁ ነው" ይላሉ፡፡ ዴቪድ ቦልቾፈር ግን በዚህ አይስማሙም፡፡ "ማነው የአመራር ክህሎት ያላቸው ሰዎች ጥቂት ናቸው ያለው ብለው ይጠይቃሉ፡፡ ይሄ ማጭበርበር ነው፡፡" ሚስተር ዳንኤል ክፍያው ተገቢ ነው የሚሉት የአፕሉን ስቲቭ ጆብስ፣ የአማዞኑን ጄፍ ቤዞስ፣ የተስላና የስፔስኤክስ ፈጣሪን ኤሎን መስክንና የመሳሰሉትን እጅግ የነጠረ ክህሎት በማንሳት ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች አዲስ ነገር ፈጥረው የገበያና የቴክኖሎጂ አብዮት ያመጡ ሰዎች ናቸው፡፡ "መደበኛ ሥራ አስፈጻሚዎች ግን እንደነ ኤሎን መስክ ያሉት አይደሉም" ይላሉ ዴቪድ ቦልቾፈር፡፡ እነዚህ መደበኛ ሥራ አስፈጻሚዎች ሚናቸውም ክፍያቸውም የተጋነነ ነው ብለው የሚከራከሩትም ለዚሁ ነው፡፡ አንድ ኩባንያ በሥራ አስፈጻሚው ብርታትና ምጥቀት ብቻ አይደለም ትርፋማ የሚሆነው የሚሉት ሚስተር ዴቪድ ፔይ ቼክ በሚለው መጽሐፋቸው ላይ ይህን ጉዳይ በዝርዝር ጽፈውታል፡፡ አንዳንድ ዘርፎች በተለያዩ ምክንያቶች አትራፊነታቸው ይቀጥላል፤ የትኛውም ተመሳሳይ አቅም ያለው ሰው ቢመራቸው፡፡ የቴሌኮም ዘርፎችን ምሳሌ ማንሳት ይቻላል፡፡ ወይም ቀድሞውኑም ጥሩ መሠረት ላይ የተገነቡ ቢዝነሶች፡፡ በዚህ ረገድ ሥራ አስፈጻሚዎች ምንም ቦታ ላይኖራቸው ይችላል፡፡ ምናልባት የሠራተኞች ትጋት ይሆናል የትርፍማነቱ ምንጭ፡፡ ሆኖም አለቆች የሚበሉት ደመወዝ የትየሌሌ ነው፡፡ "በኮርፖሬሽኖች የሥራ አስፈጻሚዎች ሚና ብዙውን ጊዜ ይጋነናል፡፡ ይህ ሆን ተብሎ የሚደረግ ማጭበርበሪያ ነው፡፡" ይላሉ ዴቪድ ቦልቸር፡፡ ቦልቸር ሌላም ማስረጃ ያቀርባሉ፡፡ ለምሳሌ የ2008 የፋይናንስ ቀውስ ጊዜ ባንኮች በኪሳራ ሲንኮታኮቱ ሥራ አስፈጻሚዎቻቸው ግን ሚሊዮን ዶላሮችን ታቅፈው ነው የሄዱት፡፡ ይህ ነገር በጊዜው ብዙዎችን አቁስሎ ነገሩ ላይ ጥያቄም መነሳት ጀምሮ ነበር፡፡ "ክፍያ አስፈጻሚዎች ባስገኙት የስኬት መጠን ነው ከተባለ የነዚህ ባንኮች ሥራ አስፈጻሚዎች ለምን ከኪሳ በኋላም ወፍራም ደመወዝ እየተከፈላቸው ቆዩ?" ሲሉም ይጠይቃሉ፡፡ መልሱን ራሳቸው ሲመልሱም የጥቅም ትስስር ስላለ ነው ይላሉ፡፡ የጥቅም ትስስሩ በቦርድ አባላት፣ በሥራ አስፈጻሚዎችና በሽርክና ባለቤቶች መካከል ነው፡፡ ተራው ሠራተኛ ደመወዙ ለምን ያሽቆለቁላል? የሥራ አስፈጻሚዎች ደመወዝ ሲመነደግ የተራ ሠራተኛው ደመወዝ ቁልቁለቱን ተያይዞታል፡፡ ለምሳሌ በዚህ ወረርሽኝ የወሳኝ ሰራተኞች ደመወዝ ማነሱ ብቻ ሳይሆን እሱንም ለማግኘት ሕይወታቸው ላይ ለመቆመር ይገደዳሉ፡፡ ይህ የተራ ሠራተኞች ደመወዝ ማሽቆልቆል ብዙዎችን ደም እያፈላ ነው፡፡ ለምሳሌ በሺህ የሚቆጠሩ የብሪቲሽ ጋስ ኩባንያ ሰራተኞች የ5 ቀን የሥራ ማቆም አድማ አድርገው ነበር፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ የሠራተኛ ቅነሳ መደረጉ ነው፡፡ ብዙ ሠራተኞች በጥቂት መብቶች ብቻ ተወስነው በአስቸጋሪ ሁኔታ እንዲሰሩ መገደዳቸው ነው፡፡ ውጥረቱ ይበልጥ የተካረረው ደግሞ ከ2018 ጀምሮ ብሪቲሽ ጋስን በባለቤትነት የያዘው ሴንትሪካ ኩባንያ ሥራ አስፈጻሚ የ44 ከመቶ ጭማሪ ማግኘታቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ዓመታዊ ደመወዛቸው 2 ሚሊዮን ተኩል ፓውንድ ያልፋል፡፡ "ይህ ስግብግብነት ነው" ይላል የ32 ዓመቱ የብሪቲሽ ጋስ ሰራተኛ ጆን፡፡ ይህ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር እንኳ የማይከፈላቸው ደመወዝ መጠን ነው፡፡ እንዴት ነው ሰራተኛን እየቀነሰ ያለ ኩባንያ ለሥራ አስፈጻሚው ይህን ያህል ፓውንድ የሚከፍለው? በጭራሽ ስሜት አይሰጥም፡፡ አንዳንድ መልካም ሥራ አስፈጻሚዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ የቦይንግ፣ የማሪዮት ኢንተርናሽናል የፒደብሊውሲ ሥራ አስፈጻሚዎች ሰራተኛ እንዳይቀነስ ሲሉ ደመወዛቸውን ጭማሪ ይቅርብን ያሉ ናቸው፡፡ አንዳንዶች ይህን ድርጊታቸውን ለታይታ የተደረገ እንጂ መሰረታዊ ለውጥ የማያመጣ ነው ሲሉ ይተቹታል፡፡ መጪው ጊዜ አስፈሪ ነው፡፡ ለተራ ሰራተኛ፣ ለላብ አደሩ፣ ድምጹ ለማይሰማው፣ ላቡ ለሚንቆረቆረው ብዙኃን በተለይ መጪው ዘመን ቀበቶ ጠበቅ የሚደረግበት ነው፡፡ ምክንያቱም ኩባንያዎች ገቢ ቀንሷል፡፡ ከቴክ ኩባንያዎች ውጭ ያለው ዘርፍ በወረርሽኙ ድባቅ ተመቷል፡፡ የአርተፊሻል ልህቀትና ሌሎች ማሽኖች የጉልበት ሥራን ዋጋ እያሳጡት ነው፡፡ ኢንተርኔት ንግድ የሰራተኛን አስፈላጊነት እምብዛምም አድርጎታል፡፡ ፋይናንስ ኢንዱስትሪዎች በእንብርክክ እየሄዱ ነው፡፡ የሰራተኛ ማኅበራት እየተዳከሙ ሄደዋል፡፡ ስለዚህ መጪው ጊዜ ሚሊየነሮች ቢሊየነሮች የሚሆኑበት፣ ላብ አደሮች ይበልጥ ላባቸው በከንቱ የሚፈስበት እንደሆነ የዓለም ምጣኔ ሀብትን በቅርብ የሚከታተሉ አዋቂዎች ትንቢት ነው፡፡ የዓለም ሀብት በጥቂቶች እጅ ይቀፈደዳል፡፡ ቢሊዮኖች ግን በቃ ቁጥር ናቸው፡፡ ተወልደው፣ ኖረው፣ ጥረው ግረው፣ የሚሞቱ፡፡
https://www.bbc.com/amharic/55854396
5sports
ማርቲን ሉተር ኪንግ ማነው? ለምንስ እስከ ዛሬ ይታወሳል?
'ሕልም አለኝ' የሚለው የማርቲን ሉተር ኪንግ ንግግር አሜሪካ ውስጥ ያለውን የዘር ጭቆና እና የእኩልነት መብት አለመከበር የሚቃወም ነበር። በርካቶችን ለተሻለ አስተሳሰብ አነሳስቷል፤ ታዋቂና ቀንደኛ ሰዎችን አከራክሯል፤ ዘንድሮም ድረስ የሚነገርለት ሐሳብ ሆኗል። ነገር ግን ዛሬም ላይ እነዚህ ጉዳዮች አልባት አላገኙም። ጥቁርና ድሀ ማኅበረሰቦችን ለማግለል ተብለው የሚወጡ የምርጫ እገዳዎችና ሌሎችም ተግባራት ማርቲን ሉተር ኪንግ ሲታገልለት የነበረው ጭቆና አሁንም ድረስ ስለመኖሩ ማሳያ ነው። ማርቲን ሉተር ኪንግ ማነው? ነሐሴ ወር 1963 ላይ እስከ 250 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ዋሽንግተን ዲሲ ወደሚገኘው ታዋቂው ሊንከን ሜሞሪያል ተምመው ነበር። ይሄ ሁሉ ሰው ታዲያ አንድ ሰው ንግግር ሲያደርግ ለማዳመጥ ነበር። ስሙም ዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር ይባላል። ንግግሮቹ ዛሬም ድረስ በመላው ዓለም እንደ ነጻነት ማብሰሪያ ይታያሉ። ማርቲን ሉተር ኪንግ በደቡባዊ ጆርጂያ ግዛት ከአንድ የሃይማኖት አባት ነው የተወለደው። አባቱ እሳቸው ካለፉበት የሕይወት ዓይነት በተለየ መልኩ ልጆቻቸው እንዲሄዱ ከፍተኛ ፍላጎት ነበራቸው። ዘርና ቀለምን መሠረት ያደረገ መድልዎ በመላው ደቡባዊ አሜሪካ ተንሰራፍቶ ነበር። በርካታ ይህንን የሚደግፉ ሕጎችም ተግባራዊ ይደረጉ ነበር። ጥቁር ሰዎች እና ነጭ ሰዎች በተለያየ አካባቢ ነበር የሚኖሩት። እንዲገናኙ አይፈለግም። ጥቁሮች ለጥቁሮች ብቻ ተብለው በተሰሩ ምግብ ቤቶች እና መጠጥ ቤቶች ብቻ ነበር የሚዝናኑት። ሌላው ቀርቶ ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ እንኳን ጥቁሮች ለብቻው እጅግ ባረጁ መኪናዎች እንዲጠቀሙ ተደርጓል። በአጠቃላይ ጥቁሮች ምንም ያህል ጥሩ ሥራ ቢሠሩም ከነጮች ያነሰ ክፍያ እንዲሰጣቸው ሕጎች ነበሩ። የጥቁሮች ትምህርት ቤት፣ የጥቁሮች የጤና ተቋማት እና የጥቁሮች መንደር እየተባለ መከፋፈል በጊዜው የተለመደና ተቀባይነት ያለው ተግባር ነበር። በፖለቲካው ዘርፍ ደግሞ ጥቁሮች እነሱ የፈለጓቸውን መሪዎች እንዳይመርጡ በተጠና እንዲሁም በተዘዋዋሪ መልኩ ሲሠራ ነበር። ነገር ግን አሁን ላይ የማርቲን ሉተር ኪንግ ሕልሞች በሙሉ ተሳክተዋል ብላችሁ ካሰባችሁ ተሳስታችኋል። የእርሱ ቤተሰቦች እንደሚሉት በተለይ በቅርብ ወራት እየተስተዋሉ ያሉ ነገሮች ከማርቲን ሕልም በእጅጉ የራቁና የተቃረኑ ናቸው። በእነማርቲን ሉተር ኪንግ ዘመን ጥቁሮችን በግልጽ ያገልሉ የነበሩ ሕጎች አሁንም መልካቸውን ቀይረው እንዳሉ ናቸው። የሪፐብሊካን ፓርቲ ደጋፊ ፖለቲከኞች አሁንም ድረስ የአናሳ ቡድኖች በተለይም የጥቁር ማኅበረሰቦችን ስም የማጠልሸትና ከሌላው ማኅበረሰብ በመለየት በምርጫ ላይ ያላቸውን ተሳትፎ መቀነስን ተግባራዊ ያደርጋሉ። ለዚህ እንደ ማሳያ የሚጠቀሰው ጥቁሮች ብሔራዊ መታወቂያ የሚያገኙበትን መንገድ ማጥበቃቸው ነው። በተጨማሪ ደግሞ ሰዎች ለምርጫ በሚሰለፉበት ወቅት የሚቀርቡ ምግብና መጠጦችን መከልከልም ይጠቀሳል። ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በምርጫ አሸንፈው ዋይት ሀውስን ከተቆጣጠሩ በኋላ መሰል ሕጎች እንደ ፍሎሪዳ፣ ቴክሳስ እና አሪዞና ባሉ ግዛቶች በስፋት ተግባራዊ ተደርገዋል። አሜሪካ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግን በምታስታውስበት የፈረንጆቹ ጥር 17/2022 የታዋቂው ነጻነት ታጋይ ልጆች፤ ሰዎች ዝም ብለው በደፈናው ስሙን ብቻ አስበው እንዳይውሉ ጠይቀዋል። ቀኑን ማክበር ብቻ ሳይሆን የእሱን ፈለግ በመከተል የጥቁር ሕዝቦችን ነጻነትና እኩልነት የሚያረጋግጡ ሕጎች እንዲወጡ ለማስገደድ የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል። ሴት ልጁ በርኒስ ኪንግ "እኛ የማርቲን ሉተር ኪንግን በዓል እያከበርን ሲሆን እናንተም በተመሳሳይ እንድታከብሩት እጠይቃለው። ነገር ግን የምርጫ መብታችን አደጋ ላይ ከወደቀ ሁላችንም ይህንን ቀን ምክንያት አድርገን እሱ ያደርገው የነበረውን ማስቀጠል አለብን" ብላለች። "አባቴ የሚወዳት አገሩ በፍጹም ዴሞክራሲ እንድትመራ ይናገርና ያደርግ የነበረውን እንቅስቃሴ የአሜሪካ ሴኔት ላይ ጫና በማሳረፍ እንድናስቀጥለው እጠይቃለው።" የጥቁሮች የምርጫ መብት ጥያቄ ከቅርብ ዓመታት ጀምሮ በአሜሪካ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ውዝግብን ያስነሳ ጉዳይ ነው። ታዋቂው የሃይማኖት መሪ ሬቭረንድ አል ሻርፕተን 'የአሜሪካን ዴሞክራሲ የሚፈታተን ወሳኝ ጊዜ' ነው ብለዋል። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በበኩላቸው የምርጫ መብት ጉዳይ የአሜሪካ የልብ ትርታ ነው ብለዋል የማርቲን ሉተር ኪንግ መነሻ በሆነችው አትላንታ ንግግር ሲያደርጉ። "ከማርቲን ሉተር ኪንግ ጎን መሆን ነው የምትፈልጉት ወይስ ከጆርጅ ዋላስ?" ሲሉም ጥያቄ ሰንዝረዋል። ጆርጅ ዋላስ የቀድሞ የአለባማ ገዢ የነበሩና የጥቁሮችን የበታችነት የሚሰብኩ ሰው ናቸው። ማርቲን ሉተር ኪንግ ምንድነው የሠራው? ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ያንን ንግግር ሲያደርግ ክፍፍልን አምርሮ ይተች ነበር። ነገር ግን ከነጭ ወግ አጥባቂዎች በኩል ያገኘው ምላሽ ከበድ ያለ ነበር። ቤተሰቦቹ በየዕለቱ የእንገድላችኋለን ማስፈራሪያዎች ይደርሷቸው የነበረ ሲሆን ቤታቸውም በቦምብ ጋይቷል። ኪንግ ምንም አይነት አመጽ ባልተቀላቀለበት የትግል መንገድ የሚያምን ሲሆን ሁሌም ቢሆን ሰዎች በንግግርና በኅብረት ብቻ ማሸነፍ እንደሚችሉ ያምናል። ፕሮፌሰር ቤንቶ እንደሚሉት በርካቶች የእሱን መንገድ ደካማነትና ሽንፈትን እሺ ብሎ መቀበል ሊመስላቸው ይችላል። ነገር ግን ይህ ትልቅ ስህተት ነው ይላሉ። "ኪንግ ከአመጽ የጸዳችና በመግባባት ላይ የተመሠረተች አሜሪካን ያስብ ነበር። ዘረኝነት የተወገደበት፣ እኩልና ነጻ ማኅበረሰብ ተፈጥሮ ማየት ትልቁ ሕልሙ ነበር።" በአውሮፓውያኑ 1963 ማርቲን ሉተር ኪንግ በዋሺንግተን ያደረገውም ንግግር በነጻነት መብት ትግል ውስጥ ወሳኝ ሚና አለው። በወቅቱ ኪንግ ከአመጽ ነጻ በሆነ መልኩ እንዴት ለውጥን ማምጣት እንደሚቻልና የዘር አኩልነትን ማስፈን እንደሚገባ መርሑን በግልጽ አስቀምጧል። በቀጣዩ ዓመት በሕዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች ላይ ጥቁሮች እንዲሄዱ አልያም በሁሉም ቦታ ተንቀሳቅሰው ሥራ እንዲሠሩ የሚፈቅደው ሕግ ጸደቀ። ነገር ግን ፍልሚያው ገና በጅምር በሚባል ደረጃ ላይ ነበር። የእኩልነት ጠላቶች በወቅቱ ዘረኛ ፖሊሲዎች እንዲወጡ ከፍተኛ ጫና ያሳድሩ ነበር። በደቡባዊ ግዛቶችም ጥቁሮች በተለይ ምርጫ ላይ ያላቸውን ተሳተፎ በእጅጉ የሚቀንሱ ፖሊሲዎች ይጡ ነበር። ኪንግም 1965 ላይ መሰል ሕጎች እንዳይወጡ የሚቃወመውን በአለባማ ሰልማ የተካሄደውን ሞንቶጎመሪ ሰልፍ አካሂዷል። በወቅቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎቹ ተቃውሟቸውን ቢያሰሙም ከፖሊስም ሆነ ከነጮች የጠበቃቸው ጭካኔ የተሞላበት ምላሽ ነበር። ነገር ግን ኪንግ አሁንም ከአመጽ የጸዳ በሚለው መርሑ በመመራት ጥያቄውን ሲያሰማ ነበር። ማርቲን ሉተር ኪንግ እንዴት ነው የሞተው? ኪንግ በተለያዩ ጊዜያት 29 ጊዜ ታስሯል። ሚያዝያ 4/1968 አሪዞና ሜምፊስ በሚገኘው የሆቴል ክፍል በረንዳ ላይ ነው አንድ ነጭ ግለሰብ በጠመንጃ ተኩሶ የገደለው። የኪንግ ግድያ ግን የእሱን ሥራዎች በአሜሪካ አላንኳሰሰውም። የኪንግ ትግልና የትግል መንገድ እንዲሁም ተጽዕኖው አሁንም ድረስ ቀጥሏል። የኪንግን ግድያ ተከትሎ በርካታ የመብት ተሟጋቾች ፈርተዋል። "የእሱ ሥራዎች ሁሌም ሕያው ሆነው ይቆያሉ። ማኅበራዊ ፍትሕን ለማስፈን ምን አይነት ተቃውሞና ኅብረት መታየት እንዳለበት አሳይቶናል" ይላሉ ፕሮፌሰር ቤንቶ። የማርቲን ሉተር ኪንግ ንግግሮች በሰው ልጆች ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ በርካቶችን ካበረታቱ እና ለተሻለ ለውጥ ካነሳሱ ንግግሮች ውስጥ በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ናቸው። ለሰዎች አኩልነት ድምጹን ማሰማት አቁሞ የማያውቀው ማርቲን ሉተር ኪንግ ሁሌም የግል ደኅንነቱን ትልቅ አደጋ ላይ ጥሎ ነው ለዴሞክራሲ የታገለው።
ማርቲን ሉተር ኪንግ ማነው? ለምንስ እስከ ዛሬ ይታወሳል? 'ሕልም አለኝ' የሚለው የማርቲን ሉተር ኪንግ ንግግር አሜሪካ ውስጥ ያለውን የዘር ጭቆና እና የእኩልነት መብት አለመከበር የሚቃወም ነበር። በርካቶችን ለተሻለ አስተሳሰብ አነሳስቷል፤ ታዋቂና ቀንደኛ ሰዎችን አከራክሯል፤ ዘንድሮም ድረስ የሚነገርለት ሐሳብ ሆኗል። ነገር ግን ዛሬም ላይ እነዚህ ጉዳዮች አልባት አላገኙም። ጥቁርና ድሀ ማኅበረሰቦችን ለማግለል ተብለው የሚወጡ የምርጫ እገዳዎችና ሌሎችም ተግባራት ማርቲን ሉተር ኪንግ ሲታገልለት የነበረው ጭቆና አሁንም ድረስ ስለመኖሩ ማሳያ ነው። ማርቲን ሉተር ኪንግ ማነው? ነሐሴ ወር 1963 ላይ እስከ 250 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ዋሽንግተን ዲሲ ወደሚገኘው ታዋቂው ሊንከን ሜሞሪያል ተምመው ነበር። ይሄ ሁሉ ሰው ታዲያ አንድ ሰው ንግግር ሲያደርግ ለማዳመጥ ነበር። ስሙም ዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር ይባላል። ንግግሮቹ ዛሬም ድረስ በመላው ዓለም እንደ ነጻነት ማብሰሪያ ይታያሉ። ማርቲን ሉተር ኪንግ በደቡባዊ ጆርጂያ ግዛት ከአንድ የሃይማኖት አባት ነው የተወለደው። አባቱ እሳቸው ካለፉበት የሕይወት ዓይነት በተለየ መልኩ ልጆቻቸው እንዲሄዱ ከፍተኛ ፍላጎት ነበራቸው። ዘርና ቀለምን መሠረት ያደረገ መድልዎ በመላው ደቡባዊ አሜሪካ ተንሰራፍቶ ነበር። በርካታ ይህንን የሚደግፉ ሕጎችም ተግባራዊ ይደረጉ ነበር። ጥቁር ሰዎች እና ነጭ ሰዎች በተለያየ አካባቢ ነበር የሚኖሩት። እንዲገናኙ አይፈለግም። ጥቁሮች ለጥቁሮች ብቻ ተብለው በተሰሩ ምግብ ቤቶች እና መጠጥ ቤቶች ብቻ ነበር የሚዝናኑት። ሌላው ቀርቶ ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ እንኳን ጥቁሮች ለብቻው እጅግ ባረጁ መኪናዎች እንዲጠቀሙ ተደርጓል። በአጠቃላይ ጥቁሮች ምንም ያህል ጥሩ ሥራ ቢሠሩም ከነጮች ያነሰ ክፍያ እንዲሰጣቸው ሕጎች ነበሩ። የጥቁሮች ትምህርት ቤት፣ የጥቁሮች የጤና ተቋማት እና የጥቁሮች መንደር እየተባለ መከፋፈል በጊዜው የተለመደና ተቀባይነት ያለው ተግባር ነበር። በፖለቲካው ዘርፍ ደግሞ ጥቁሮች እነሱ የፈለጓቸውን መሪዎች እንዳይመርጡ በተጠና እንዲሁም በተዘዋዋሪ መልኩ ሲሠራ ነበር። ነገር ግን አሁን ላይ የማርቲን ሉተር ኪንግ ሕልሞች በሙሉ ተሳክተዋል ብላችሁ ካሰባችሁ ተሳስታችኋል። የእርሱ ቤተሰቦች እንደሚሉት በተለይ በቅርብ ወራት እየተስተዋሉ ያሉ ነገሮች ከማርቲን ሕልም በእጅጉ የራቁና የተቃረኑ ናቸው። በእነማርቲን ሉተር ኪንግ ዘመን ጥቁሮችን በግልጽ ያገልሉ የነበሩ ሕጎች አሁንም መልካቸውን ቀይረው እንዳሉ ናቸው። የሪፐብሊካን ፓርቲ ደጋፊ ፖለቲከኞች አሁንም ድረስ የአናሳ ቡድኖች በተለይም የጥቁር ማኅበረሰቦችን ስም የማጠልሸትና ከሌላው ማኅበረሰብ በመለየት በምርጫ ላይ ያላቸውን ተሳትፎ መቀነስን ተግባራዊ ያደርጋሉ። ለዚህ እንደ ማሳያ የሚጠቀሰው ጥቁሮች ብሔራዊ መታወቂያ የሚያገኙበትን መንገድ ማጥበቃቸው ነው። በተጨማሪ ደግሞ ሰዎች ለምርጫ በሚሰለፉበት ወቅት የሚቀርቡ ምግብና መጠጦችን መከልከልም ይጠቀሳል። ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በምርጫ አሸንፈው ዋይት ሀውስን ከተቆጣጠሩ በኋላ መሰል ሕጎች እንደ ፍሎሪዳ፣ ቴክሳስ እና አሪዞና ባሉ ግዛቶች በስፋት ተግባራዊ ተደርገዋል። አሜሪካ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግን በምታስታውስበት የፈረንጆቹ ጥር 17/2022 የታዋቂው ነጻነት ታጋይ ልጆች፤ ሰዎች ዝም ብለው በደፈናው ስሙን ብቻ አስበው እንዳይውሉ ጠይቀዋል። ቀኑን ማክበር ብቻ ሳይሆን የእሱን ፈለግ በመከተል የጥቁር ሕዝቦችን ነጻነትና እኩልነት የሚያረጋግጡ ሕጎች እንዲወጡ ለማስገደድ የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል። ሴት ልጁ በርኒስ ኪንግ "እኛ የማርቲን ሉተር ኪንግን በዓል እያከበርን ሲሆን እናንተም በተመሳሳይ እንድታከብሩት እጠይቃለው። ነገር ግን የምርጫ መብታችን አደጋ ላይ ከወደቀ ሁላችንም ይህንን ቀን ምክንያት አድርገን እሱ ያደርገው የነበረውን ማስቀጠል አለብን" ብላለች። "አባቴ የሚወዳት አገሩ በፍጹም ዴሞክራሲ እንድትመራ ይናገርና ያደርግ የነበረውን እንቅስቃሴ የአሜሪካ ሴኔት ላይ ጫና በማሳረፍ እንድናስቀጥለው እጠይቃለው።" የጥቁሮች የምርጫ መብት ጥያቄ ከቅርብ ዓመታት ጀምሮ በአሜሪካ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ውዝግብን ያስነሳ ጉዳይ ነው። ታዋቂው የሃይማኖት መሪ ሬቭረንድ አል ሻርፕተን 'የአሜሪካን ዴሞክራሲ የሚፈታተን ወሳኝ ጊዜ' ነው ብለዋል። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በበኩላቸው የምርጫ መብት ጉዳይ የአሜሪካ የልብ ትርታ ነው ብለዋል የማርቲን ሉተር ኪንግ መነሻ በሆነችው አትላንታ ንግግር ሲያደርጉ። "ከማርቲን ሉተር ኪንግ ጎን መሆን ነው የምትፈልጉት ወይስ ከጆርጅ ዋላስ?" ሲሉም ጥያቄ ሰንዝረዋል። ጆርጅ ዋላስ የቀድሞ የአለባማ ገዢ የነበሩና የጥቁሮችን የበታችነት የሚሰብኩ ሰው ናቸው። ማርቲን ሉተር ኪንግ ምንድነው የሠራው? ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ያንን ንግግር ሲያደርግ ክፍፍልን አምርሮ ይተች ነበር። ነገር ግን ከነጭ ወግ አጥባቂዎች በኩል ያገኘው ምላሽ ከበድ ያለ ነበር። ቤተሰቦቹ በየዕለቱ የእንገድላችኋለን ማስፈራሪያዎች ይደርሷቸው የነበረ ሲሆን ቤታቸውም በቦምብ ጋይቷል። ኪንግ ምንም አይነት አመጽ ባልተቀላቀለበት የትግል መንገድ የሚያምን ሲሆን ሁሌም ቢሆን ሰዎች በንግግርና በኅብረት ብቻ ማሸነፍ እንደሚችሉ ያምናል። ፕሮፌሰር ቤንቶ እንደሚሉት በርካቶች የእሱን መንገድ ደካማነትና ሽንፈትን እሺ ብሎ መቀበል ሊመስላቸው ይችላል። ነገር ግን ይህ ትልቅ ስህተት ነው ይላሉ። "ኪንግ ከአመጽ የጸዳችና በመግባባት ላይ የተመሠረተች አሜሪካን ያስብ ነበር። ዘረኝነት የተወገደበት፣ እኩልና ነጻ ማኅበረሰብ ተፈጥሮ ማየት ትልቁ ሕልሙ ነበር።" በአውሮፓውያኑ 1963 ማርቲን ሉተር ኪንግ በዋሺንግተን ያደረገውም ንግግር በነጻነት መብት ትግል ውስጥ ወሳኝ ሚና አለው። በወቅቱ ኪንግ ከአመጽ ነጻ በሆነ መልኩ እንዴት ለውጥን ማምጣት እንደሚቻልና የዘር አኩልነትን ማስፈን እንደሚገባ መርሑን በግልጽ አስቀምጧል። በቀጣዩ ዓመት በሕዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች ላይ ጥቁሮች እንዲሄዱ አልያም በሁሉም ቦታ ተንቀሳቅሰው ሥራ እንዲሠሩ የሚፈቅደው ሕግ ጸደቀ። ነገር ግን ፍልሚያው ገና በጅምር በሚባል ደረጃ ላይ ነበር። የእኩልነት ጠላቶች በወቅቱ ዘረኛ ፖሊሲዎች እንዲወጡ ከፍተኛ ጫና ያሳድሩ ነበር። በደቡባዊ ግዛቶችም ጥቁሮች በተለይ ምርጫ ላይ ያላቸውን ተሳተፎ በእጅጉ የሚቀንሱ ፖሊሲዎች ይጡ ነበር። ኪንግም 1965 ላይ መሰል ሕጎች እንዳይወጡ የሚቃወመውን በአለባማ ሰልማ የተካሄደውን ሞንቶጎመሪ ሰልፍ አካሂዷል። በወቅቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎቹ ተቃውሟቸውን ቢያሰሙም ከፖሊስም ሆነ ከነጮች የጠበቃቸው ጭካኔ የተሞላበት ምላሽ ነበር። ነገር ግን ኪንግ አሁንም ከአመጽ የጸዳ በሚለው መርሑ በመመራት ጥያቄውን ሲያሰማ ነበር። ማርቲን ሉተር ኪንግ እንዴት ነው የሞተው? ኪንግ በተለያዩ ጊዜያት 29 ጊዜ ታስሯል። ሚያዝያ 4/1968 አሪዞና ሜምፊስ በሚገኘው የሆቴል ክፍል በረንዳ ላይ ነው አንድ ነጭ ግለሰብ በጠመንጃ ተኩሶ የገደለው። የኪንግ ግድያ ግን የእሱን ሥራዎች በአሜሪካ አላንኳሰሰውም። የኪንግ ትግልና የትግል መንገድ እንዲሁም ተጽዕኖው አሁንም ድረስ ቀጥሏል። የኪንግን ግድያ ተከትሎ በርካታ የመብት ተሟጋቾች ፈርተዋል። "የእሱ ሥራዎች ሁሌም ሕያው ሆነው ይቆያሉ። ማኅበራዊ ፍትሕን ለማስፈን ምን አይነት ተቃውሞና ኅብረት መታየት እንዳለበት አሳይቶናል" ይላሉ ፕሮፌሰር ቤንቶ። የማርቲን ሉተር ኪንግ ንግግሮች በሰው ልጆች ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ በርካቶችን ካበረታቱ እና ለተሻለ ለውጥ ካነሳሱ ንግግሮች ውስጥ በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ናቸው። ለሰዎች አኩልነት ድምጹን ማሰማት አቁሞ የማያውቀው ማርቲን ሉተር ኪንግ ሁሌም የግል ደኅንነቱን ትልቅ አደጋ ላይ ጥሎ ነው ለዴሞክራሲ የታገለው።
https://www.bbc.com/amharic/news-60028025
3politics
የታገቱ የካማሺ ዞን የማረሚያ ቤት ኃላፊዎችን ለማስለቀቅ እየተሞከረ እንደሆነ ተገለጸ
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የካማሺ ዞን የማረሚያ ቤት አዛዥ ተወካይን ጨምሮ ሦስት የጸጥታ አካላት በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን በታጣቂዎች መታገታቸውን የክልሉ ኮሚሽን ለቢቢሲ ገለጸ። ታጋቾቹን ለማስለቀቅም የኦሮሚያና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ጥረት መጀመራቸውን አስታውቀዋል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ምስጋናው እንጅፋታ ለቢቢሲ እንደገለጹት በማረሚያ ቤት ኃላፊዎቹ ላይ እገታው የተፈጸመው ባለፈው ሳምንት ሐሙስ መጋቢት 22፣ 2014 ዓ.ም ከአሶሳ ከተማ ወደ ካማሺ ዞን እየሄዱ ባሉበት ወቅት መንገድ ላይ ነው። ሦስቱ ታጋቾች የት እንዳሉና በምን ምክንያት እንደታገቱ ሙሉ መረጃ ባይኖርም እስከ ትላንት በስቲያ ድረስ በሕይወት እንዳሉ መረጃ እንዳላቸው ምክትል ኮሚሽነሩ ተናግረዋል። "በሌላ ስልክ አስደውለው በሕይወት እንዳሉና "አታስቡ" የሚል መልዕክትም ለቤተሰብ ማስተላለፋቸውን'" ምክትል ኮሚሽነሩ ለቢቢሲ ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት ከኦሮሚያ ክልል ጋር እየተነጋገሩ እንደሆነና የክልሉም አባ ገዳዎች፣ የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ግለሰቦቹን ለማስለቀቅ ጥረት እያደረጉ ነው ብለዋል። በካማሺ ዞን በኩልም የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ወደ ስፍራው አምርተው ቀጥታ ግንኙነት በማድረግ በውይይት ሰዎቹ እንዲለቀቁ ለማድረግም እቅድ እንዳለ አስታውቀዋል። ከካማሺ ዞን በኩል የሚወከሉት እኚሁ የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ከዛሬ ጀምሮ ወደ ስፍራው እንደሚያመሩም አስታውቀዋል። አጋቾቹ እነማን እንደሆኑ ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምክትል ኮሚሽነር ምስጋናው ሲመልሱ " እስካሁን በግልፅ የደረስንበት ነገር የለም፤ ነገር ግን በመረጃ ደረጃ በአካባቢው ታጣቂው የኦነግ ሸኔ ኃይል በስፋት ይንቀሳቀሳል። የተለያዩ ግድያዎችንም እዛው መንገድ ላይ በተደጋጋሚ ይፈፅሙ ነበር። ጥርጣሬያችንም ኦነግ ሸኔ ነው የሚል ነው" ብለዋል። በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺና መተከል ዞኖችን ጨምሮ በተለያዩ ዞኖች ከዚህ ቀደም በታጣቂዎች በተደጋጋሚ በሚፈጸሙ ጥቃቶች ምክንያት በርካታ ሰዎች ለሞትና ለመፈናቀል ሲዳረጉ መቆየታቸው ይታወሳል። የክልሉ መንግሥት እነዚህንም ጥቃቶች በመፈጸም ታጣቂውን የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄን ተጠያቂ ሲያደርግ ቆይቷል። ከዚህ ቀደም የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥትና ታጣቂው የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞከራሲያዊ ንቅናቄ (ጉሕዴን) ቡድን በክልሉ በተደጋጋሚ በንፁሃን ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለማስቆም የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ይታወሳል።
የታገቱ የካማሺ ዞን የማረሚያ ቤት ኃላፊዎችን ለማስለቀቅ እየተሞከረ እንደሆነ ተገለጸ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የካማሺ ዞን የማረሚያ ቤት አዛዥ ተወካይን ጨምሮ ሦስት የጸጥታ አካላት በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን በታጣቂዎች መታገታቸውን የክልሉ ኮሚሽን ለቢቢሲ ገለጸ። ታጋቾቹን ለማስለቀቅም የኦሮሚያና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ጥረት መጀመራቸውን አስታውቀዋል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ምስጋናው እንጅፋታ ለቢቢሲ እንደገለጹት በማረሚያ ቤት ኃላፊዎቹ ላይ እገታው የተፈጸመው ባለፈው ሳምንት ሐሙስ መጋቢት 22፣ 2014 ዓ.ም ከአሶሳ ከተማ ወደ ካማሺ ዞን እየሄዱ ባሉበት ወቅት መንገድ ላይ ነው። ሦስቱ ታጋቾች የት እንዳሉና በምን ምክንያት እንደታገቱ ሙሉ መረጃ ባይኖርም እስከ ትላንት በስቲያ ድረስ በሕይወት እንዳሉ መረጃ እንዳላቸው ምክትል ኮሚሽነሩ ተናግረዋል። "በሌላ ስልክ አስደውለው በሕይወት እንዳሉና "አታስቡ" የሚል መልዕክትም ለቤተሰብ ማስተላለፋቸውን'" ምክትል ኮሚሽነሩ ለቢቢሲ ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት ከኦሮሚያ ክልል ጋር እየተነጋገሩ እንደሆነና የክልሉም አባ ገዳዎች፣ የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ግለሰቦቹን ለማስለቀቅ ጥረት እያደረጉ ነው ብለዋል። በካማሺ ዞን በኩልም የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ወደ ስፍራው አምርተው ቀጥታ ግንኙነት በማድረግ በውይይት ሰዎቹ እንዲለቀቁ ለማድረግም እቅድ እንዳለ አስታውቀዋል። ከካማሺ ዞን በኩል የሚወከሉት እኚሁ የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ከዛሬ ጀምሮ ወደ ስፍራው እንደሚያመሩም አስታውቀዋል። አጋቾቹ እነማን እንደሆኑ ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምክትል ኮሚሽነር ምስጋናው ሲመልሱ " እስካሁን በግልፅ የደረስንበት ነገር የለም፤ ነገር ግን በመረጃ ደረጃ በአካባቢው ታጣቂው የኦነግ ሸኔ ኃይል በስፋት ይንቀሳቀሳል። የተለያዩ ግድያዎችንም እዛው መንገድ ላይ በተደጋጋሚ ይፈፅሙ ነበር። ጥርጣሬያችንም ኦነግ ሸኔ ነው የሚል ነው" ብለዋል። በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺና መተከል ዞኖችን ጨምሮ በተለያዩ ዞኖች ከዚህ ቀደም በታጣቂዎች በተደጋጋሚ በሚፈጸሙ ጥቃቶች ምክንያት በርካታ ሰዎች ለሞትና ለመፈናቀል ሲዳረጉ መቆየታቸው ይታወሳል። የክልሉ መንግሥት እነዚህንም ጥቃቶች በመፈጸም ታጣቂውን የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄን ተጠያቂ ሲያደርግ ቆይቷል። ከዚህ ቀደም የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥትና ታጣቂው የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞከራሲያዊ ንቅናቄ (ጉሕዴን) ቡድን በክልሉ በተደጋጋሚ በንፁሃን ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለማስቆም የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ይታወሳል።
https://www.bbc.com/amharic/news-60992723
3politics
ትራምፕ እና ኦባማ ስለመጪው የግማሽ አመት ምርጫ ምን አሉ?
ሁለቱ የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዘዳንቶች ባራክ ኦባማ እና ዶናልድ ትራምፕ በፔንሲልቫኒያ ባደረጉት የግማሽ አመት የምርጫ የድጋፍ ቅስቀሳ ምሽት ላይ ሁለቱም ስለ አገራቸው ያላቸውን የተለያየ ስጋት ገልጸዋል። ኦባማ ይህ የግማሽ አመት ምርጫ የአሜሪካን የዴሞክራሲ ጉዞ የሚወስን ነው ሲሉ፤ ትራምፕ ደግሞ የአገሪቷን የደህንነት ጉዳይ ቁርጡን የምናውቅበት ነው ሲሉ ቀስቅሰዋል። የፔንሲልቫኒያ ግዛት ዴሞክራቶችም ሆኑ ሪፐብሊካን የበላይነት የሌላቸው ሲሆን በተለያየ ግዜ ለተለያየ ፓርቲ የሚመረጥበት በተለምዶ ‘’ስዊንግ ስቴት’’ ተብለው ከሚጠሩ ግዛቶች አንዱ ነው። በግዛቲቱ ሪፐብሊካኑም ሆኑ ዴሞክራቱ በሚያሸንፉበት ወቅት የሚኖረው የድምጽ ልዩነት እጅግ ጠባብ ነው። በቅርቡ ለሚካሄደው የግማሽ አመት ምርጫ የግዛቲቱ ድምጽ አጅግ አስፈላጊ በመሆኑ ነው ሁለቱ የቀድሞ ፕሬዘዳንቶች ፓርቲያቸውን ለማገዝ እና ለመቀስቀስ የተገኙት። እ.ኤ.አ. በ 2016 ትራምፕ ዋይት ሃውስን ለማግኘት የዚሁ ግዛት ድል ረድቷቸዋል። በመቀጠልም በ 2020 የጆ ባይደን የትውልድ ግዛት የሆነችውን ፔንሲልቫኒያን ዴሞክራቶች 2 በመቶ በሚሆን የድምጽ ብልጫ አሸንፈው ተረክበዋታል። ጆ ባይደን በፊላደልፊያ ቅዳሜ ዕለት ተገኝተው ቅስቀሳቸውን ባደረጉበት ወቅትም ‘’ወደ ቤቴ በመመለሴ ደስ ብሎኛል’’ ብለዋል። ፓርቲያቸው ላቀረባቸው ዕጩም ድጋፋቸውን ለግሰዋል። ዲሞክራቶች በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አብላጫ ድምጽ የማያገኙ ከሆነ የጤና መድህን ብሎም የጽንስ ማቋረጥ መብቶች ላይ ተጨማሪ እገዳ እንዲጣል ማስቻል እንደሆነም ተናግረዋል። የምርጫው ውጤት ትንበያዎች እንደሚያሳዩት ዴሞክራቶች በኮንግረስ የበላይነትን አያገኙም። ይህንንም ተከትሎ ቢያንስ በሴኔት የበላይነትን ለማግኘት ከፍተኛ ትንቅንቅ እያደረጉ ናቸው። ‘’በዚች የአሜሪካ የልብ ምት በሆነችው ግዛት ውስጥ መስቀለኛ መንገድ ላይ እንገኛለን’’ ሲሉ ጆ ባይደን ተናግረዋል። አክለውም ለዲሞክራቶች ድምጽ መስጠት ማለት ለሴቶች ጤና፣ በጦር መሳሪያ ቁጥጥር ብሎም ለጤና አገልግሎት ድምጽ መስጠት ነው ሲሉም አክለዋል። አንድ የግዛቲቱ ነዋሪ የትኛውንም ፓርቲ ይደግፉ የፕሬዘዳንቶቹ መገኘት ነዋሪው ወጥቶ እንዲመርጥ ያስችላል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ነገር ግን ፕሬዘዳንቶቹን ለመመልከት ከወጡት ነዋሪዎች መካከል የተወሰኑ ኦባማን ለማየት መምጣታቸውን እና ባይደን ለብቻቸው ቢሆኑ ኖሮ ግን እንደማይመጡ ተናግረዋል። በምርጫ ዘመን አጋማሽ ላይ የሚደረገው ይህ ‘የሚድ ተርም’ ምርጫ በስልጣን ላይ ያለው ፕሬዘዳንት ላይ የሚደረግ ሕዝበ ውሳኔ ተደርጎ ይታያል። የጆ ባይደን ተቀባይነት 40 በመቶ ላይ እንዳለ በሚነገርበት በዚህ ወቅት ሪፐብሊካኑ የኑሮ ውድነት እና ስደትን የመሳሰሉ ምክንያቶችን በማንሳት ፕሬዘዳንቱ ላይ ቅስቀሳቸውን እንዲያጧጡፉም ረድቷቸዋል። ትራምፕ በበኩላቸው ዲሞክራቶች በዋሽንግተን የሚቆዩ ከሆነ ለተጨማሪ ወንጀሎች እንዲሁም ላልተገደበ የስደተኞች ፍሰት ያጋልጣሉ ሲሉ ቀስቅሰዋል። ‘’ለቤተሰባችሁ ደህንነት እና ጥበቃ የምትፈልጉ ከሆነ እያንዳንዱን ዴሞክራት በድምጻችሁ ከወንበሩ ማስነሳት አለባችሁ’’ ብለዋል። ‘’ያለው ምርጫ አንድ ብቻ ነው። የአሜሪካን መውደቅ የምትፈልጉ ከሆነ ድምጻችሁን ለአክራሪ ዴሞክራቶች ስጡ። የአገራችንን መውደም የማትፈልጉ ከሆነ ግን ሪፐብሊካንን ምረጡ’’ ሲሉ ትራምፕ ቀስቅሰዋል። እንዲሁም በ 2024 ለሚደረገው ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ሊወዳደሩ እንደሚችሉም ጠቁመዋል። እንዲሁም በድጋሚ የአሜሪካ የምርጫ ስርአት የተጭበረበረ ነው የሚለውን የሃሰት ክሳቸውን ማቅረባቸውን ቀጥለዋል። አንድ የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊ የቀድሞው ፕሬዘዳንት ‘’ህይወትን ያለ ጭቆና እና ምን ማድረግ እንዳለብን ሳይነገረን እንድንኖር ረድተውናል’’ በሚል ለድጋፍ መውጣቱን ተናግሯል። በርካታ መራጮች በፍርሃት እና በሃሰት ቅስቀሳዎች ታጅበው ከሁለት ቀናት በኋላ በሚካሄደው የግማሽ አመት ምርጫ ይሳተፋሉ። ይህም የአሜሪካን የምርጫ ስርአት ታማኝነት የሚፈተሽበት ነውም ብለው ያምናሉ።
ትራምፕ እና ኦባማ ስለመጪው የግማሽ አመት ምርጫ ምን አሉ? ሁለቱ የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዘዳንቶች ባራክ ኦባማ እና ዶናልድ ትራምፕ በፔንሲልቫኒያ ባደረጉት የግማሽ አመት የምርጫ የድጋፍ ቅስቀሳ ምሽት ላይ ሁለቱም ስለ አገራቸው ያላቸውን የተለያየ ስጋት ገልጸዋል። ኦባማ ይህ የግማሽ አመት ምርጫ የአሜሪካን የዴሞክራሲ ጉዞ የሚወስን ነው ሲሉ፤ ትራምፕ ደግሞ የአገሪቷን የደህንነት ጉዳይ ቁርጡን የምናውቅበት ነው ሲሉ ቀስቅሰዋል። የፔንሲልቫኒያ ግዛት ዴሞክራቶችም ሆኑ ሪፐብሊካን የበላይነት የሌላቸው ሲሆን በተለያየ ግዜ ለተለያየ ፓርቲ የሚመረጥበት በተለምዶ ‘’ስዊንግ ስቴት’’ ተብለው ከሚጠሩ ግዛቶች አንዱ ነው። በግዛቲቱ ሪፐብሊካኑም ሆኑ ዴሞክራቱ በሚያሸንፉበት ወቅት የሚኖረው የድምጽ ልዩነት እጅግ ጠባብ ነው። በቅርቡ ለሚካሄደው የግማሽ አመት ምርጫ የግዛቲቱ ድምጽ አጅግ አስፈላጊ በመሆኑ ነው ሁለቱ የቀድሞ ፕሬዘዳንቶች ፓርቲያቸውን ለማገዝ እና ለመቀስቀስ የተገኙት። እ.ኤ.አ. በ 2016 ትራምፕ ዋይት ሃውስን ለማግኘት የዚሁ ግዛት ድል ረድቷቸዋል። በመቀጠልም በ 2020 የጆ ባይደን የትውልድ ግዛት የሆነችውን ፔንሲልቫኒያን ዴሞክራቶች 2 በመቶ በሚሆን የድምጽ ብልጫ አሸንፈው ተረክበዋታል። ጆ ባይደን በፊላደልፊያ ቅዳሜ ዕለት ተገኝተው ቅስቀሳቸውን ባደረጉበት ወቅትም ‘’ወደ ቤቴ በመመለሴ ደስ ብሎኛል’’ ብለዋል። ፓርቲያቸው ላቀረባቸው ዕጩም ድጋፋቸውን ለግሰዋል። ዲሞክራቶች በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አብላጫ ድምጽ የማያገኙ ከሆነ የጤና መድህን ብሎም የጽንስ ማቋረጥ መብቶች ላይ ተጨማሪ እገዳ እንዲጣል ማስቻል እንደሆነም ተናግረዋል። የምርጫው ውጤት ትንበያዎች እንደሚያሳዩት ዴሞክራቶች በኮንግረስ የበላይነትን አያገኙም። ይህንንም ተከትሎ ቢያንስ በሴኔት የበላይነትን ለማግኘት ከፍተኛ ትንቅንቅ እያደረጉ ናቸው። ‘’በዚች የአሜሪካ የልብ ምት በሆነችው ግዛት ውስጥ መስቀለኛ መንገድ ላይ እንገኛለን’’ ሲሉ ጆ ባይደን ተናግረዋል። አክለውም ለዲሞክራቶች ድምጽ መስጠት ማለት ለሴቶች ጤና፣ በጦር መሳሪያ ቁጥጥር ብሎም ለጤና አገልግሎት ድምጽ መስጠት ነው ሲሉም አክለዋል። አንድ የግዛቲቱ ነዋሪ የትኛውንም ፓርቲ ይደግፉ የፕሬዘዳንቶቹ መገኘት ነዋሪው ወጥቶ እንዲመርጥ ያስችላል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ነገር ግን ፕሬዘዳንቶቹን ለመመልከት ከወጡት ነዋሪዎች መካከል የተወሰኑ ኦባማን ለማየት መምጣታቸውን እና ባይደን ለብቻቸው ቢሆኑ ኖሮ ግን እንደማይመጡ ተናግረዋል። በምርጫ ዘመን አጋማሽ ላይ የሚደረገው ይህ ‘የሚድ ተርም’ ምርጫ በስልጣን ላይ ያለው ፕሬዘዳንት ላይ የሚደረግ ሕዝበ ውሳኔ ተደርጎ ይታያል። የጆ ባይደን ተቀባይነት 40 በመቶ ላይ እንዳለ በሚነገርበት በዚህ ወቅት ሪፐብሊካኑ የኑሮ ውድነት እና ስደትን የመሳሰሉ ምክንያቶችን በማንሳት ፕሬዘዳንቱ ላይ ቅስቀሳቸውን እንዲያጧጡፉም ረድቷቸዋል። ትራምፕ በበኩላቸው ዲሞክራቶች በዋሽንግተን የሚቆዩ ከሆነ ለተጨማሪ ወንጀሎች እንዲሁም ላልተገደበ የስደተኞች ፍሰት ያጋልጣሉ ሲሉ ቀስቅሰዋል። ‘’ለቤተሰባችሁ ደህንነት እና ጥበቃ የምትፈልጉ ከሆነ እያንዳንዱን ዴሞክራት በድምጻችሁ ከወንበሩ ማስነሳት አለባችሁ’’ ብለዋል። ‘’ያለው ምርጫ አንድ ብቻ ነው። የአሜሪካን መውደቅ የምትፈልጉ ከሆነ ድምጻችሁን ለአክራሪ ዴሞክራቶች ስጡ። የአገራችንን መውደም የማትፈልጉ ከሆነ ግን ሪፐብሊካንን ምረጡ’’ ሲሉ ትራምፕ ቀስቅሰዋል። እንዲሁም በ 2024 ለሚደረገው ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ሊወዳደሩ እንደሚችሉም ጠቁመዋል። እንዲሁም በድጋሚ የአሜሪካ የምርጫ ስርአት የተጭበረበረ ነው የሚለውን የሃሰት ክሳቸውን ማቅረባቸውን ቀጥለዋል። አንድ የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊ የቀድሞው ፕሬዘዳንት ‘’ህይወትን ያለ ጭቆና እና ምን ማድረግ እንዳለብን ሳይነገረን እንድንኖር ረድተውናል’’ በሚል ለድጋፍ መውጣቱን ተናግሯል። በርካታ መራጮች በፍርሃት እና በሃሰት ቅስቀሳዎች ታጅበው ከሁለት ቀናት በኋላ በሚካሄደው የግማሽ አመት ምርጫ ይሳተፋሉ። ይህም የአሜሪካን የምርጫ ስርአት ታማኝነት የሚፈተሽበት ነውም ብለው ያምናሉ።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c28wl49vp3eo
3politics
ፕሬዝዳንት ፑቲን በዩክሬን ለሩሲያ ታማኝ የሆነ መሪ ለማስቀመጥ እያሴሩ ነው ተባለ
ፕሬዝዳንት ፑቲን በዩክሬን ለሩሲያ ታማኝ የሆነ መሪ ለማስቀመጥ እያሴሩ እንደሆነ ብሪታኒያ ደርሼበታለሁ አለች። ዩናይትድ ኪንግደም ፕሬዝዳንት ፑቲን የሩሲያ ደጋፊ የሆነ ፖለቲከኛ የዩክሬንን መንግስት እንዲመራ ለማድረግ አሲረዋል ስትል ከሳለች። የቀድሞ የዩክሬን ፓርላማ አባል የነበሩት ፖለቲከኛ ኢቭሄን ሙሬዬቭን የሩሲያ ምርጫ እንደሆኑ የዩኬ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ከዚህ በፊት ባልተለመደ ሁኔታ ስም ጠቅሶ ገልጿል። ሩሲያ 100 ሺህ ወታደሮቿን ዩክሬን ድንበር አቅራቢያ ያሰፈረች ቢሆንም ወረራ የማድረግ እቅድ የለኝም ስትል በተደጋጋሚ ገልጻለች። የዩናይትድ ኪንግደም ሚኒስትሮች የሩስያ መንግስት ዩክሬን ላይ ወረራ የሚፈጽም ከሆነ ከባድ መዘዝ ይጠብቀዋል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሊዝ ትረስ በጽሁፍ በሰጡት መግለጫ "በዛሬው የወጣው መረጃ ዩክሬንን ለመናድ ሩስያ እያደረገች ያለችውን እንቅስቃሴ ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ሲሆን የሩሲያ መንግስትንም እሳቤ የሚያንጸባርቅ ነው" ብለዋል። ሩሲያ ጉዳዩን እንድታረግብ፣ የወረራ ዘመቻዋን እንድታቆም ሀሰተኛ መረጃ ከማሰራጨት እንድትቆጠብ እና የዲፕሎማሲ መንገድን እንድትከተል ሲሉም አሳስበዋል። "ዩኬ እና አጋሮቻችን ደጋግመው እንደተናገሩት በዩክሬን ላይ የሚፈጸም ማንኛውም የሩሲያ ወታደራዊ ወረራ ከባድ ኪሳራን የሚያስከትል ትልቅ ስትራቴጂካዊ ስህተት ነው" ሲሉም አክለዋል። እንደ አውሮፓውያኑ በ2014 ሩሲያ የዩክሬንን ግዛት ከመያዟ ቀደም ብሎ በሀገሪቱ ለሩስያ የታመኑ ፕሬዝዳንቷን ከስልጣን ተወግደው ነበር። የምዕራባውያን እና የዩክሬን የስለላ አገልግሎቶች በተያዘው የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት መጀመሪያ በድንበር ላይ የሰፈረው የሩሲያ ጦር ሌላ ወረራ ሊፈጽም እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። ምንም አይነት ጥቃት ዩክሬን ላይ ለማድረስ እቅድ የለኝም የምትለው ሩሲያ ደግሞ ዩክሬን ወደ ኔቶ ወታደራዊ ጥምረት መግባት የለባትም የሚል አቋም ግን አላት። ፕሬዝዳንት ፑቲን በአከባቢው ኔቶ እያደረገ ያለው ወታደራዊ ልምምድን የሚልከው የጦር መሳሪያ መላኩን ለሩሲያ ደህንነት ቀጥተኛ ስጋት እንደሆነ ጠቅሰው ይህ እንዲቆም ጠይቀዋል። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትዊተር ገፁ እንዳስታወቀው የብሪታኒያ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሀሰት መረጃዎችን እያሰራጨ ነው ያለሲሆን "ይህን መሰል ቀስቃሽ ተግባር እንዲያቆም" እና "እርባና ቢስ ወሬውን እንዲተው" አሳስቧል።
ፕሬዝዳንት ፑቲን በዩክሬን ለሩሲያ ታማኝ የሆነ መሪ ለማስቀመጥ እያሴሩ ነው ተባለ ፕሬዝዳንት ፑቲን በዩክሬን ለሩሲያ ታማኝ የሆነ መሪ ለማስቀመጥ እያሴሩ እንደሆነ ብሪታኒያ ደርሼበታለሁ አለች። ዩናይትድ ኪንግደም ፕሬዝዳንት ፑቲን የሩሲያ ደጋፊ የሆነ ፖለቲከኛ የዩክሬንን መንግስት እንዲመራ ለማድረግ አሲረዋል ስትል ከሳለች። የቀድሞ የዩክሬን ፓርላማ አባል የነበሩት ፖለቲከኛ ኢቭሄን ሙሬዬቭን የሩሲያ ምርጫ እንደሆኑ የዩኬ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ከዚህ በፊት ባልተለመደ ሁኔታ ስም ጠቅሶ ገልጿል። ሩሲያ 100 ሺህ ወታደሮቿን ዩክሬን ድንበር አቅራቢያ ያሰፈረች ቢሆንም ወረራ የማድረግ እቅድ የለኝም ስትል በተደጋጋሚ ገልጻለች። የዩናይትድ ኪንግደም ሚኒስትሮች የሩስያ መንግስት ዩክሬን ላይ ወረራ የሚፈጽም ከሆነ ከባድ መዘዝ ይጠብቀዋል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሊዝ ትረስ በጽሁፍ በሰጡት መግለጫ "በዛሬው የወጣው መረጃ ዩክሬንን ለመናድ ሩስያ እያደረገች ያለችውን እንቅስቃሴ ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ሲሆን የሩሲያ መንግስትንም እሳቤ የሚያንጸባርቅ ነው" ብለዋል። ሩሲያ ጉዳዩን እንድታረግብ፣ የወረራ ዘመቻዋን እንድታቆም ሀሰተኛ መረጃ ከማሰራጨት እንድትቆጠብ እና የዲፕሎማሲ መንገድን እንድትከተል ሲሉም አሳስበዋል። "ዩኬ እና አጋሮቻችን ደጋግመው እንደተናገሩት በዩክሬን ላይ የሚፈጸም ማንኛውም የሩሲያ ወታደራዊ ወረራ ከባድ ኪሳራን የሚያስከትል ትልቅ ስትራቴጂካዊ ስህተት ነው" ሲሉም አክለዋል። እንደ አውሮፓውያኑ በ2014 ሩሲያ የዩክሬንን ግዛት ከመያዟ ቀደም ብሎ በሀገሪቱ ለሩስያ የታመኑ ፕሬዝዳንቷን ከስልጣን ተወግደው ነበር። የምዕራባውያን እና የዩክሬን የስለላ አገልግሎቶች በተያዘው የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት መጀመሪያ በድንበር ላይ የሰፈረው የሩሲያ ጦር ሌላ ወረራ ሊፈጽም እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። ምንም አይነት ጥቃት ዩክሬን ላይ ለማድረስ እቅድ የለኝም የምትለው ሩሲያ ደግሞ ዩክሬን ወደ ኔቶ ወታደራዊ ጥምረት መግባት የለባትም የሚል አቋም ግን አላት። ፕሬዝዳንት ፑቲን በአከባቢው ኔቶ እያደረገ ያለው ወታደራዊ ልምምድን የሚልከው የጦር መሳሪያ መላኩን ለሩሲያ ደህንነት ቀጥተኛ ስጋት እንደሆነ ጠቅሰው ይህ እንዲቆም ጠይቀዋል። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትዊተር ገፁ እንዳስታወቀው የብሪታኒያ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሀሰት መረጃዎችን እያሰራጨ ነው ያለሲሆን "ይህን መሰል ቀስቃሽ ተግባር እንዲያቆም" እና "እርባና ቢስ ወሬውን እንዲተው" አሳስቧል።
https://www.bbc.com/amharic/news-60101331
5sports
የቱርካዊው የእግር ኳስ ኮከብ ጉዞ ከታዋቂ ፖለቲከኛነት እስከ ታክሲ ሹፌርነት
ሃካን ሱኩር በቱርክ እግር ኳስ ታሪክ በርካታ ጎሎችን ያስቆጠረ ተጫዋች ነው። እስካሁንም የሚድርስበት አልተገኘም። በአንድ ወቅት በአውሮጳ እግር ኳስ አሉ ከሚባሉ ተጫዋቾችም አንዱ ነበር። አሁን ግን አሜሪካ ውስጥ የታክሲ ሹፌር ሆኗል፤ መፃሕፍትም ይሸጣል። እንዴት? ከአንድ የጀርመን ጋዜጣ ጋር ቆይታ ያደረገው የ48 ዓመቱ ሳኩር ሕይወቱ ባልተጠቀ መንገድ እንዴት እንዲህ ሊሆን እንደቻለ ያስረዳል። ሱኩር፤ ከቱርክ ፕሬዝደንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶዋን ጋር ያለኝ ቅራኔ ነው ለዚህ ያበቃኝ ይላል። ከእንገድልሃለን ማስፈራሪያ ጀምሮ እስከ ገንዘብ ክልከላ ድረስ የዘለቀ እርምጃ እንደተወሰደበት ይዘክራል። «ምንም ነገር የለኝም። ኤርዶዋን ሁሉን ነገር ወስዶብኛል። ነፃነቴን ገፎኛል። ሃሳቤን ነፃ ሆኜ መግለፅ ተሳነኝ፤ ሠርቼ መብላት አልቻልኩም።» በፈረንጆቹ ከ92-2007 ባለው ጊዜ ሳኩር ለቱርክ 112 ጊዜ ተሰልፎ የተጫወተ ሲሆን 51 ጎሎችን አስቆጥሯል። ቱርክ በ2002 የዓለም ዋንጫ ሶስተኛ ስትወጣ የቡድኑ አባል ነበር። ለእንግሊዙ የእግር ኳስ ክለብ ብላክበርን ይጫወት የነበረው ሱኩር፤ የእግር ኳስ ሕይወቱን አብዛኛውን ጊዜ ያሳለፈው ጋላታሳራይ ለተሰኘው የቱርክ ክለብ በመጫወት ነበር። ሱፐር ሊግ በመባል በሚታወቀው የቱርክ እግር ኳስ ሊግ እንደ ሱኩር ብዙ ጎል ያገባ እስካሁን አልተገኘም። ሱኩር ጫማ ሲሰቅል ወደ ፖለቲካ ገባ። በግሪጎሪያን አቆጣጠር 2011 ላይ ምርጫ የኤርዶዋንን ፓርቲ ወክሎ ተዋዳድሮ በማሸነፉ በላይኛው ምክር ቤት የሕዝብ እንደራሴ ለመሆን በቃ። ነገር ግን ፌቱላህ ጉሌን ከተሰኘው የኤርዶዋን ዋነኛ ተቀናቃኝ ድርጅት ጋር ተያይዞ ስሙ ይነሳ ነበር። የቱርክ መንግሥት ደግሞ 2016 ላይ ለተከሰተውና በርካታ ሰዎችን ለቀጠፈው የቱርክ የመፈንቅለ-መንግሥት ሙከራ ድርጅቱን ተጠያቂ ያደርጋል። ሱኩር በወቅቱ አሜሪካ ነበር። የመፈንቅለ-መንግሥት ሙከራውንም አጣጥሏል። ነገር ግን የቱርክ መንግሥት ቴሌቪዥን ጣቢያ ተጨዋቹ የፌቱላህ አባል ነው፤ አሁን በጥገኝነት አሜሪካ ይገኛል ሲል ዘገበ። ዘገባው ሱኩር፤ ሳን ፍራንሲስኮ በተሰኘችው የአሜሪካ የሃብታሞች ከተማ 3 ሚሊዮን ዶላር በሚያወጣ ቤት ውስጥ ይኖራል፤ የራሱ ካፌም አለው ሲል አተተ። «እርግጥ ነው ካሊፎርኒያ ውስጥ ካፌ ነበረኝ። ነገር ግን የማላውቃቸው ሰዎች ካፌዬን መጎብኘት ጀመሩ። አሁን የኡበር ሹፌር ነኝ።» ቱርክ ውስጥ ያሉ ቤቶቹ፣ ቢዝነሶቹም ሆኑ የባንክ አካውንቶቹ በኤርዶዋን መንግሥት እግድ እንደተጣለባቸው ይናገራል። የመንግሥትን ወቀሳም ያጣጥላል። ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት ኒው ዮርክ ታይምስ ከተሰኘው ጋዜጣ ጋር ቆይታ ያደረገው ሱኩር «ሃገሬን እወዳለሁ፣ ሕዝቡን እንዲሁ። ምንም እንኳ ስለኔ ያላቸው አተያይ የተጣመመ ቢሆንም» ብሏል። በወቅቱ ዘገባው የኤርዶዋን መንግሥትን ጨቋኝነት ያሳያል በሚሉ ሰዎች ዘንድ ትኩረት አግኝቷል። 2018 ላይ የአርሴናሉ አማካይ ሜሱት ኦዚል ከፕሬዝደንት ኤርዶዋን ጋር ፎቶ በመነሳቱ ነቀፌታ አስተናግዶ ነበር። ኤርዶዋን፤ ኦዚል ሲሞሸር ሚዜው ሆነው መታየታቸውም አይዘነጋም።
የቱርካዊው የእግር ኳስ ኮከብ ጉዞ ከታዋቂ ፖለቲከኛነት እስከ ታክሲ ሹፌርነት ሃካን ሱኩር በቱርክ እግር ኳስ ታሪክ በርካታ ጎሎችን ያስቆጠረ ተጫዋች ነው። እስካሁንም የሚድርስበት አልተገኘም። በአንድ ወቅት በአውሮጳ እግር ኳስ አሉ ከሚባሉ ተጫዋቾችም አንዱ ነበር። አሁን ግን አሜሪካ ውስጥ የታክሲ ሹፌር ሆኗል፤ መፃሕፍትም ይሸጣል። እንዴት? ከአንድ የጀርመን ጋዜጣ ጋር ቆይታ ያደረገው የ48 ዓመቱ ሳኩር ሕይወቱ ባልተጠቀ መንገድ እንዴት እንዲህ ሊሆን እንደቻለ ያስረዳል። ሱኩር፤ ከቱርክ ፕሬዝደንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶዋን ጋር ያለኝ ቅራኔ ነው ለዚህ ያበቃኝ ይላል። ከእንገድልሃለን ማስፈራሪያ ጀምሮ እስከ ገንዘብ ክልከላ ድረስ የዘለቀ እርምጃ እንደተወሰደበት ይዘክራል። «ምንም ነገር የለኝም። ኤርዶዋን ሁሉን ነገር ወስዶብኛል። ነፃነቴን ገፎኛል። ሃሳቤን ነፃ ሆኜ መግለፅ ተሳነኝ፤ ሠርቼ መብላት አልቻልኩም።» በፈረንጆቹ ከ92-2007 ባለው ጊዜ ሳኩር ለቱርክ 112 ጊዜ ተሰልፎ የተጫወተ ሲሆን 51 ጎሎችን አስቆጥሯል። ቱርክ በ2002 የዓለም ዋንጫ ሶስተኛ ስትወጣ የቡድኑ አባል ነበር። ለእንግሊዙ የእግር ኳስ ክለብ ብላክበርን ይጫወት የነበረው ሱኩር፤ የእግር ኳስ ሕይወቱን አብዛኛውን ጊዜ ያሳለፈው ጋላታሳራይ ለተሰኘው የቱርክ ክለብ በመጫወት ነበር። ሱፐር ሊግ በመባል በሚታወቀው የቱርክ እግር ኳስ ሊግ እንደ ሱኩር ብዙ ጎል ያገባ እስካሁን አልተገኘም። ሱኩር ጫማ ሲሰቅል ወደ ፖለቲካ ገባ። በግሪጎሪያን አቆጣጠር 2011 ላይ ምርጫ የኤርዶዋንን ፓርቲ ወክሎ ተዋዳድሮ በማሸነፉ በላይኛው ምክር ቤት የሕዝብ እንደራሴ ለመሆን በቃ። ነገር ግን ፌቱላህ ጉሌን ከተሰኘው የኤርዶዋን ዋነኛ ተቀናቃኝ ድርጅት ጋር ተያይዞ ስሙ ይነሳ ነበር። የቱርክ መንግሥት ደግሞ 2016 ላይ ለተከሰተውና በርካታ ሰዎችን ለቀጠፈው የቱርክ የመፈንቅለ-መንግሥት ሙከራ ድርጅቱን ተጠያቂ ያደርጋል። ሱኩር በወቅቱ አሜሪካ ነበር። የመፈንቅለ-መንግሥት ሙከራውንም አጣጥሏል። ነገር ግን የቱርክ መንግሥት ቴሌቪዥን ጣቢያ ተጨዋቹ የፌቱላህ አባል ነው፤ አሁን በጥገኝነት አሜሪካ ይገኛል ሲል ዘገበ። ዘገባው ሱኩር፤ ሳን ፍራንሲስኮ በተሰኘችው የአሜሪካ የሃብታሞች ከተማ 3 ሚሊዮን ዶላር በሚያወጣ ቤት ውስጥ ይኖራል፤ የራሱ ካፌም አለው ሲል አተተ። «እርግጥ ነው ካሊፎርኒያ ውስጥ ካፌ ነበረኝ። ነገር ግን የማላውቃቸው ሰዎች ካፌዬን መጎብኘት ጀመሩ። አሁን የኡበር ሹፌር ነኝ።» ቱርክ ውስጥ ያሉ ቤቶቹ፣ ቢዝነሶቹም ሆኑ የባንክ አካውንቶቹ በኤርዶዋን መንግሥት እግድ እንደተጣለባቸው ይናገራል። የመንግሥትን ወቀሳም ያጣጥላል። ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት ኒው ዮርክ ታይምስ ከተሰኘው ጋዜጣ ጋር ቆይታ ያደረገው ሱኩር «ሃገሬን እወዳለሁ፣ ሕዝቡን እንዲሁ። ምንም እንኳ ስለኔ ያላቸው አተያይ የተጣመመ ቢሆንም» ብሏል። በወቅቱ ዘገባው የኤርዶዋን መንግሥትን ጨቋኝነት ያሳያል በሚሉ ሰዎች ዘንድ ትኩረት አግኝቷል። 2018 ላይ የአርሴናሉ አማካይ ሜሱት ኦዚል ከፕሬዝደንት ኤርዶዋን ጋር ፎቶ በመነሳቱ ነቀፌታ አስተናግዶ ነበር። ኤርዶዋን፤ ኦዚል ሲሞሸር ሚዜው ሆነው መታየታቸውም አይዘነጋም።
https://www.bbc.com/amharic/51116646
0business
በኪራይ አህያ ንግድ ጀምረው ቢሊየነር የሆኑት ኢትዮጵያዊ
ቶኩማ ፊጤ እባላለሁ፣ ተወልጄ ያደግኩት በምዕራብ ሸዋ ዞን በባኮ ትቤ ወረዳ፣ ቦኖ በሚባል ገጠር ውስጥ ነው። እዚያም ለቤተሰቦቼ ከብት ስጠብቅ ቆይቼ እድሜዬ ለትምህርት ሲደርስ ወደ ትምህርት ቤት ተላኩኝ። ነፍስ ካወቅኩ ጀምሮ በአእምሮዬ ውስጥ የሚመላለሰው ነገር ቢኖር የንግድ ሥራ ነው። የንግድ ሥራን በደንብ የጀመርኩትም የሰባተኛ እና የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ሆኜ ነው። በዚያን ጊዜ አህያ ተከራይቼ፣ ከገጠር ወደ ከተማ እህል በማመላለስ እሸጥ ነበር። ከከተማ ስመለስ ደግሞ እንደ ጋዝ፣ ዘይት፣ ጨው፣ ቡና የመሳሰሉትን ነገሮች በመግዛት አምጥቼ እሸጥ ነበር። በውስጤ ትልቅ ራዕይ ነበረኝ። ጠንክሬ ከሠራሁ አንደምለወጥ አምን ነበር። ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ወደ ወረዳ ከተማ በመጣሁበት ጊዜ የበለጠውኑ እየተጠናከርኩ ራሴን መቻል ጀመርኩ። የሚያስፈልጉኝን ወጪዎች ከመሸፈን አልፌ ቤተሰቦቼን መደጎም የቻልኩት በዚህ ጊዜ ነው። ከዚህ በፊት ከአንድ ገበያ ወደ ሌላ ገበያ በመሄድ ያገኘሁትን ነገር ሁሉ እሸጥ ነበር። በኋላ ላይ ገን አንድ አዲስ ሃሳብ በአእምሮዬ ሽው አለ። እርሱም የንግድ ፈቃድ አውጥቶ መስራት የሚል ነበር። በዚህም መሰረት ወደ አምቦ ሄጄ የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈባቸውን መጻሕፍት ለመግዛት የሚያስችለኝን የንግድ ፈቃድ አወጣሁ። በዚህም መሠረት ያገለገሉትን ወረቀቶችን ሰብስቦ ለፋብሪካ ማቅረብ የሚያስችለኝን ንግድ የጀመርኩት በዚሁ ነበር። ያገለገሉ መጽሐፍትን በየትምህርት ቤቱ እየዞርኩ መግዛት ጀመርኩ። ይህንን ፈቃድ በማወጣበት ሰዓት በባንክ የቁጠባ ሂሳብ ደብተሬ ላይ የነበረኝ 72 ብር ብቻ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜም እነዚያን መጽሐፍት ገዝቼ የጫንኩት ኖኖ ቁንባ ከሚባል ወረዳ ነበር። የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈባቸው መጽሐፍት ከተጣሉበት እና ከተከማቹበት በማሰባሰብ በመኪና ጭኜ ወሰድኩኝ። በዚያን ቀን ለረዱኝ ሰዎች፣ ለጨረታ ኮሚቴዎች፣ ለመኪና ማስጫኛ የሚሆን የክፍያ ገንዘብ አልነበረኝም። እሁን እንጂ ሸጬ እከፍላችኋለሁ ብዬ ለምኜ አሳመንኳቸው። ከዚያ በኋላ መጽሐፍ የተባለ፣ አልያም ያገለገለ ወረቀት ከያለበት ዞሬ ያላሰባሰብኩበት የኦሮሚያ ዞን የለም ማለት ይቻላል። ይህንን የማሰባስበውን ወረቀት ደግሞ ለወረቀት ፋብሪካዎች አስረክባለሁ። ለእኔ ትልቅ ሥራ ነው ብዬ የጀመርኩት እንግዲህ እርሱን ነበር። ያገለገሉ መጽሐፍትን ሰብስቦ መሸጡ ጥሩ ገቢ ባገኝበትም ቀጣይነት ያለው ሥራ ስላልነበረ ሌላ ንግድ ሃሳብ ማሰላሰል ጀመርኩ። በዚህም መሰረት ቀጥሎ የከጀመርኩት ሥራ ያገለገሉ ብረታ ብረቶችን መሰብሰብ ነው። በገጠር አካባቢዎች በመዞር ከገበሬዎች ላይ አሮጌ በርሜሎችን፣ የተሰባበሩ መጥረብያዎችን እና የመሳሰሉትን ማሰባሰብ ጀመርኩ። እነዚህን የማሰባስባቸውን ብረታ ብረቶች የማቀርበው ደግሞ ለአቢሲኒያ ብረታ ብረት ፋብሪካ ነበር። ይህ የወዳደቁ ብረታ ብረቶችን የማሰባሰብ ሥራ ከሌሎች የተሻለ ስለነበር ጥሩ ገቢ ማግኘት ጀመርኩ። ይሁን እንጂ አንደ እርሱን እየሰራሁ፣ እንደለመደብኝ ቀጥሎ ምን መሥራት እንዳለብኝ ወደ ማሰላሰል ገባሁ። ሦስተኛውን የንግድ ፈቃድ ያወጣሁበት ሥራ የኤጀንሲ ፈቃድ ነበር። ይህንንም ያሰብኩት ሥራ ለሌላቸው ወጣቶች ሥራ ይፈጥራል በሚል አስተሳሰብ ነበር። በመጀመሪያ ስለ ኤጀንሲ ብዙ እውቀት አልነበረኝም። ስለሆነም በደንብ አጥንቼ አንዴት እንደሚሰራ ለማወቅ እና ፈቀድ ለማውጣት ሦስት ዓመታት ወስዶብኛል። እንዲህ ዓይነቱን የኤጀንሲ ሥራ የማውቃቸው ሰዎች እየሰሩ ስላልነበረ ለመልመድ ትንሽ ተቸግሬ ነበር። በመጨረሻ ግን ተሳክቶልኝ በአዲስ አበባ ውስጥ በዚህ የኤጀንሲ ሥራ ፈቃድ አገኘሁ። በዚህን ሰዓት ነበር በሁለት ነገሮች ስኬታማ መሆን እንደምችል የተረዳሁት። አንደኛው የቢዝነስ ሥራዬን ማሳደግ እንደምችል ሁለተኛው ደግሞ ለሌላቸው ዜጎች ሥራ መፍጠር እንደምችል አመንኩ። ይህ የኤጀንሲ ሥራ በወኪልነት ለድርጅቶች ሠራተኛ መቅጠር ነበር። ለምሳሌ እንደ ጥበቃ፣ የጽዳት ሥራ እና የመሳሰሉት ይገኙበታል። በዚህም መሠረት እኛም ከተለያዩ ቦታዎች ሰዎችን ለሥራ እንመለምል ነበር። እነዚህንም ሰዎች አውቶብስ ተራ ድረስ ሄዶ በመቀበል፣ ወዳዘጋጀንላቸው መጠለያ በመውሰድ፣ ሥልጠና በመስጠት ወደ ተቀጠሩበት ስፍራ እናደርሳለን። በመሆኑም ይህ ሥራ ውስብስብ እና ከባድ ነበር። በተለይም ከገጠር ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ ሰዎች አንዳንዶቹ ቋንቋ ስለማይችሉ ይቸገራሉ። ከተማም ለመልመድ የሚቸገሩም ሰዎች ነበሩ። ይሁን እንጂ ባለፉት 12 ዓመታት ውስጥ ከተለያዩ ቦታ ለመጡ ለ32000 ሰዎች የሥራ እድል እንዲያገኙ አድርገናል። ከእነዚህም መካከል 8500 የሚሆኑት በራሴ ድርጅት ውስጥ ተቀጥረው ደመወዝ የምንከደፍላቸው ሠራተኞች ናቸው። ሌሎቹ ደግሞ ሥራቸውን እየሰሩ ትምህርታቸውን በመከታተል የመንግሥት ሥራ ሲቀጠሩ፣ ለትምህርት ወደ ውጪ አገር የሄዱ ጭምር ይገኙበታል። በአሁኑ ጊዜ ድርጅታችን 29 ፈቃዶች አሉት። ከእነዚህ መካከል 18 ፈቃዶች ከውጪ አገር እቃዎችን የምናስገባበት ሲሆን፣ 11 ፈቃዶች ደግሞ በአገር ውስጥ የተለያዩ ሥራዎች የምንሰራበት ነው። በአገራችን ውስጥ በክልሎችም ሆነ በፌደራል ደረጃ እንደ ቴሌ፣ መብራት ኃይል እና ውሃና ፍሳሽ ያሉ ተቋማት የሚያወጧቸው ጨረታዎች የከፍተኛ ብር ነው ጨረታ የሚያወጡት። በእንደዚህ ዓይነት ትልልቅ ፕሮጀክቶች ላይ ስንጫረት ደግሞ ከብዙ ባለሀብቶች እና ከታዋቂ ሰዎች ጋር ነው የምንወዳደረው። እንደዚህ አይነት ትላልቅ ጨረታዎች ላይ ደግሞ እንደኛ ዓይነት ብዙ ሰው አይሳተፍም። ይህ ደግሞ ተጽዕኖም አለ። ይሁን እንጂ እኔ ደግሞ እንዲህ ዓይነት ነገሮችን መሞከር እወዳለሁ። አንዳንዴ ሰባት ጊዜ ወድቀን በስምንተኛው ይሳካልናል። ሌሎቹ ደግሞ አትችሉም ይሉናል። እኛም ሰምተን እንደምንችል አሳይተናቸዋል። እንደ እነዚህ ያሉ ጨረታዎች ደግሞ በቢሊዮኖች በሚተመን ብር የሚካሄድ ጨረታ ነው። በአብዛኛውም ጊዜ ደጋግመን በመሞከር በመጨረሻም ይሳካልናል። በዓመትም እንደዚህ ዓይነት ያሉ እስከ 50 ጨረታዎች ላይ እንሳተፋለን። በአሁኑ ሰዓት ሁለት ትልልቅ ድርጅቶች አሉን። እነርሱም ቲኤፍጂ ጄነራል ትሬዲንግ እና ቶኩማ ጄኔራል ትሬዲንግ ይባላሉ። እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የተለያዩ የሕንጻ ግንባታ በማካሄድ ላይ እንገኛለን። ይህንን ስናደርግ ግን አንዲት ካሬ ሜትር እንኳ ከመንግሥት አልተሰጠንም። ሁሉንም በራሳችን ገንዘብ ገዝተን ነው የምናለማው። በአሁኑ ሰዓት ያለኝ ሀብት ግንባታዎችን እና በባንክ ያለኝ ገንዘብ ተደማምሮ ቢያንስ 5 ቢሊየን 500 ሚሊየን ይጠጋል። በቋሚነት ድርጅቴ ውስጥ የሚሰሩ 8500 ሠራተኞችም ደሞዝ እንከፍላለን። ልዩ የሚያደርገን አንዱ ነገር ከባንክ ተበድሬ አለማወቄ ነው። የምሠራቸውን ማንኛቸውንም ሥራዎች በራሴ አቅጄ ነው የምሰራው። ሰባራ ሳንቲም የባንክ ዕዳ የለብኝም። ይህ ያለኝን ሀብት ደግሞ የራሴ ብቻ አይደለም። የሠራተኞቼ እና የሕዝቡም ነው ብዬ አምናለሁ። በዚህም የተነሳ በዓመት በሚሊየን ብር የሚቆጠር ለተለያዩ ወገኖች ድጋፍ እንዳርጋለን። ለምሳሌ ባለፈው ዓመት በባኮ ወረዳ 26 ኪሎ ሜትር መንገድ በራሳችን ወጪ አሰርተናል። በአሁኑ ጊዜ በባኮ ገጠር የጀመርኩት ሥራ ተስፋፍቶ ዱባይና አሜሪካ ደርሷል። እቅዴም ይህንኑ ሀብት በትሪሊየን እንዲደርስ ማድረግ ነው። በማደግ ላይ ላሉ ወጣቶች የማስተላልፈው ምክር ቢኖር “ሥራ መናቅ የለባችሁም” የሚል ነው። ሥራን ከትንሽ ነገር መጀመር አለባቸው። ሀብት ማፍራት በሂደት የሚመጣ ስለሆነ “በአንዴ ለምን ሀብታም አልሆንኩም” ብሎ ተስፋ መቁረጥ የለባቸውም። በትንሽ በመጀመር እርሱኑ በማሻሻል ወደ ተሻለ ነገር በማሳደግ የሀብት ባለቤት ወደ መሆን ይደረሳል። እኔ ንግድ በጀመርኩበት ሰዓት ከአንቦም ሆነ ከአዲስ አበባ ምንም ዘመድ አልነበረኝም። አዲስ አበባ መጥቼ ለአልጋ ከፍዬ የማድርበት በማጣት መንገድ ላይ አድሬ አውቃለሁ። ይሁን እንጂ ተቸግርያለሁ፣ ከስሬያለሁ ብዬ ተስፋ ቆርጬ አላውቅም። ይኸው እኔ የገጠር ልጅ ዛሬ በአንቦ እና በአዲስ አበባ ብቻም ሳይሆን፣ በተለያዩ የዓለም ከተሞች በመዘዋወር እቃዎችን ገዝቼ ወደ አገሬ አስገባለሁ። ለዚህ ደግሞ ያበቃኝ ትዕግስትና ተስፋ አለመቁረጤ ነው ብዬ አስባለሁ።
በኪራይ አህያ ንግድ ጀምረው ቢሊየነር የሆኑት ኢትዮጵያዊ ቶኩማ ፊጤ እባላለሁ፣ ተወልጄ ያደግኩት በምዕራብ ሸዋ ዞን በባኮ ትቤ ወረዳ፣ ቦኖ በሚባል ገጠር ውስጥ ነው። እዚያም ለቤተሰቦቼ ከብት ስጠብቅ ቆይቼ እድሜዬ ለትምህርት ሲደርስ ወደ ትምህርት ቤት ተላኩኝ። ነፍስ ካወቅኩ ጀምሮ በአእምሮዬ ውስጥ የሚመላለሰው ነገር ቢኖር የንግድ ሥራ ነው። የንግድ ሥራን በደንብ የጀመርኩትም የሰባተኛ እና የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ሆኜ ነው። በዚያን ጊዜ አህያ ተከራይቼ፣ ከገጠር ወደ ከተማ እህል በማመላለስ እሸጥ ነበር። ከከተማ ስመለስ ደግሞ እንደ ጋዝ፣ ዘይት፣ ጨው፣ ቡና የመሳሰሉትን ነገሮች በመግዛት አምጥቼ እሸጥ ነበር። በውስጤ ትልቅ ራዕይ ነበረኝ። ጠንክሬ ከሠራሁ አንደምለወጥ አምን ነበር። ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ወደ ወረዳ ከተማ በመጣሁበት ጊዜ የበለጠውኑ እየተጠናከርኩ ራሴን መቻል ጀመርኩ። የሚያስፈልጉኝን ወጪዎች ከመሸፈን አልፌ ቤተሰቦቼን መደጎም የቻልኩት በዚህ ጊዜ ነው። ከዚህ በፊት ከአንድ ገበያ ወደ ሌላ ገበያ በመሄድ ያገኘሁትን ነገር ሁሉ እሸጥ ነበር። በኋላ ላይ ገን አንድ አዲስ ሃሳብ በአእምሮዬ ሽው አለ። እርሱም የንግድ ፈቃድ አውጥቶ መስራት የሚል ነበር። በዚህም መሰረት ወደ አምቦ ሄጄ የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈባቸውን መጻሕፍት ለመግዛት የሚያስችለኝን የንግድ ፈቃድ አወጣሁ። በዚህም መሠረት ያገለገሉትን ወረቀቶችን ሰብስቦ ለፋብሪካ ማቅረብ የሚያስችለኝን ንግድ የጀመርኩት በዚሁ ነበር። ያገለገሉ መጽሐፍትን በየትምህርት ቤቱ እየዞርኩ መግዛት ጀመርኩ። ይህንን ፈቃድ በማወጣበት ሰዓት በባንክ የቁጠባ ሂሳብ ደብተሬ ላይ የነበረኝ 72 ብር ብቻ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜም እነዚያን መጽሐፍት ገዝቼ የጫንኩት ኖኖ ቁንባ ከሚባል ወረዳ ነበር። የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈባቸው መጽሐፍት ከተጣሉበት እና ከተከማቹበት በማሰባሰብ በመኪና ጭኜ ወሰድኩኝ። በዚያን ቀን ለረዱኝ ሰዎች፣ ለጨረታ ኮሚቴዎች፣ ለመኪና ማስጫኛ የሚሆን የክፍያ ገንዘብ አልነበረኝም። እሁን እንጂ ሸጬ እከፍላችኋለሁ ብዬ ለምኜ አሳመንኳቸው። ከዚያ በኋላ መጽሐፍ የተባለ፣ አልያም ያገለገለ ወረቀት ከያለበት ዞሬ ያላሰባሰብኩበት የኦሮሚያ ዞን የለም ማለት ይቻላል። ይህንን የማሰባስበውን ወረቀት ደግሞ ለወረቀት ፋብሪካዎች አስረክባለሁ። ለእኔ ትልቅ ሥራ ነው ብዬ የጀመርኩት እንግዲህ እርሱን ነበር። ያገለገሉ መጽሐፍትን ሰብስቦ መሸጡ ጥሩ ገቢ ባገኝበትም ቀጣይነት ያለው ሥራ ስላልነበረ ሌላ ንግድ ሃሳብ ማሰላሰል ጀመርኩ። በዚህም መሰረት ቀጥሎ የከጀመርኩት ሥራ ያገለገሉ ብረታ ብረቶችን መሰብሰብ ነው። በገጠር አካባቢዎች በመዞር ከገበሬዎች ላይ አሮጌ በርሜሎችን፣ የተሰባበሩ መጥረብያዎችን እና የመሳሰሉትን ማሰባሰብ ጀመርኩ። እነዚህን የማሰባስባቸውን ብረታ ብረቶች የማቀርበው ደግሞ ለአቢሲኒያ ብረታ ብረት ፋብሪካ ነበር። ይህ የወዳደቁ ብረታ ብረቶችን የማሰባሰብ ሥራ ከሌሎች የተሻለ ስለነበር ጥሩ ገቢ ማግኘት ጀመርኩ። ይሁን እንጂ አንደ እርሱን እየሰራሁ፣ እንደለመደብኝ ቀጥሎ ምን መሥራት እንዳለብኝ ወደ ማሰላሰል ገባሁ። ሦስተኛውን የንግድ ፈቃድ ያወጣሁበት ሥራ የኤጀንሲ ፈቃድ ነበር። ይህንንም ያሰብኩት ሥራ ለሌላቸው ወጣቶች ሥራ ይፈጥራል በሚል አስተሳሰብ ነበር። በመጀመሪያ ስለ ኤጀንሲ ብዙ እውቀት አልነበረኝም። ስለሆነም በደንብ አጥንቼ አንዴት እንደሚሰራ ለማወቅ እና ፈቀድ ለማውጣት ሦስት ዓመታት ወስዶብኛል። እንዲህ ዓይነቱን የኤጀንሲ ሥራ የማውቃቸው ሰዎች እየሰሩ ስላልነበረ ለመልመድ ትንሽ ተቸግሬ ነበር። በመጨረሻ ግን ተሳክቶልኝ በአዲስ አበባ ውስጥ በዚህ የኤጀንሲ ሥራ ፈቃድ አገኘሁ። በዚህን ሰዓት ነበር በሁለት ነገሮች ስኬታማ መሆን እንደምችል የተረዳሁት። አንደኛው የቢዝነስ ሥራዬን ማሳደግ እንደምችል ሁለተኛው ደግሞ ለሌላቸው ዜጎች ሥራ መፍጠር እንደምችል አመንኩ። ይህ የኤጀንሲ ሥራ በወኪልነት ለድርጅቶች ሠራተኛ መቅጠር ነበር። ለምሳሌ እንደ ጥበቃ፣ የጽዳት ሥራ እና የመሳሰሉት ይገኙበታል። በዚህም መሠረት እኛም ከተለያዩ ቦታዎች ሰዎችን ለሥራ እንመለምል ነበር። እነዚህንም ሰዎች አውቶብስ ተራ ድረስ ሄዶ በመቀበል፣ ወዳዘጋጀንላቸው መጠለያ በመውሰድ፣ ሥልጠና በመስጠት ወደ ተቀጠሩበት ስፍራ እናደርሳለን። በመሆኑም ይህ ሥራ ውስብስብ እና ከባድ ነበር። በተለይም ከገጠር ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ ሰዎች አንዳንዶቹ ቋንቋ ስለማይችሉ ይቸገራሉ። ከተማም ለመልመድ የሚቸገሩም ሰዎች ነበሩ። ይሁን እንጂ ባለፉት 12 ዓመታት ውስጥ ከተለያዩ ቦታ ለመጡ ለ32000 ሰዎች የሥራ እድል እንዲያገኙ አድርገናል። ከእነዚህም መካከል 8500 የሚሆኑት በራሴ ድርጅት ውስጥ ተቀጥረው ደመወዝ የምንከደፍላቸው ሠራተኞች ናቸው። ሌሎቹ ደግሞ ሥራቸውን እየሰሩ ትምህርታቸውን በመከታተል የመንግሥት ሥራ ሲቀጠሩ፣ ለትምህርት ወደ ውጪ አገር የሄዱ ጭምር ይገኙበታል። በአሁኑ ጊዜ ድርጅታችን 29 ፈቃዶች አሉት። ከእነዚህ መካከል 18 ፈቃዶች ከውጪ አገር እቃዎችን የምናስገባበት ሲሆን፣ 11 ፈቃዶች ደግሞ በአገር ውስጥ የተለያዩ ሥራዎች የምንሰራበት ነው። በአገራችን ውስጥ በክልሎችም ሆነ በፌደራል ደረጃ እንደ ቴሌ፣ መብራት ኃይል እና ውሃና ፍሳሽ ያሉ ተቋማት የሚያወጧቸው ጨረታዎች የከፍተኛ ብር ነው ጨረታ የሚያወጡት። በእንደዚህ ዓይነት ትልልቅ ፕሮጀክቶች ላይ ስንጫረት ደግሞ ከብዙ ባለሀብቶች እና ከታዋቂ ሰዎች ጋር ነው የምንወዳደረው። እንደዚህ አይነት ትላልቅ ጨረታዎች ላይ ደግሞ እንደኛ ዓይነት ብዙ ሰው አይሳተፍም። ይህ ደግሞ ተጽዕኖም አለ። ይሁን እንጂ እኔ ደግሞ እንዲህ ዓይነት ነገሮችን መሞከር እወዳለሁ። አንዳንዴ ሰባት ጊዜ ወድቀን በስምንተኛው ይሳካልናል። ሌሎቹ ደግሞ አትችሉም ይሉናል። እኛም ሰምተን እንደምንችል አሳይተናቸዋል። እንደ እነዚህ ያሉ ጨረታዎች ደግሞ በቢሊዮኖች በሚተመን ብር የሚካሄድ ጨረታ ነው። በአብዛኛውም ጊዜ ደጋግመን በመሞከር በመጨረሻም ይሳካልናል። በዓመትም እንደዚህ ዓይነት ያሉ እስከ 50 ጨረታዎች ላይ እንሳተፋለን። በአሁኑ ሰዓት ሁለት ትልልቅ ድርጅቶች አሉን። እነርሱም ቲኤፍጂ ጄነራል ትሬዲንግ እና ቶኩማ ጄኔራል ትሬዲንግ ይባላሉ። እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የተለያዩ የሕንጻ ግንባታ በማካሄድ ላይ እንገኛለን። ይህንን ስናደርግ ግን አንዲት ካሬ ሜትር እንኳ ከመንግሥት አልተሰጠንም። ሁሉንም በራሳችን ገንዘብ ገዝተን ነው የምናለማው። በአሁኑ ሰዓት ያለኝ ሀብት ግንባታዎችን እና በባንክ ያለኝ ገንዘብ ተደማምሮ ቢያንስ 5 ቢሊየን 500 ሚሊየን ይጠጋል። በቋሚነት ድርጅቴ ውስጥ የሚሰሩ 8500 ሠራተኞችም ደሞዝ እንከፍላለን። ልዩ የሚያደርገን አንዱ ነገር ከባንክ ተበድሬ አለማወቄ ነው። የምሠራቸውን ማንኛቸውንም ሥራዎች በራሴ አቅጄ ነው የምሰራው። ሰባራ ሳንቲም የባንክ ዕዳ የለብኝም። ይህ ያለኝን ሀብት ደግሞ የራሴ ብቻ አይደለም። የሠራተኞቼ እና የሕዝቡም ነው ብዬ አምናለሁ። በዚህም የተነሳ በዓመት በሚሊየን ብር የሚቆጠር ለተለያዩ ወገኖች ድጋፍ እንዳርጋለን። ለምሳሌ ባለፈው ዓመት በባኮ ወረዳ 26 ኪሎ ሜትር መንገድ በራሳችን ወጪ አሰርተናል። በአሁኑ ጊዜ በባኮ ገጠር የጀመርኩት ሥራ ተስፋፍቶ ዱባይና አሜሪካ ደርሷል። እቅዴም ይህንኑ ሀብት በትሪሊየን እንዲደርስ ማድረግ ነው። በማደግ ላይ ላሉ ወጣቶች የማስተላልፈው ምክር ቢኖር “ሥራ መናቅ የለባችሁም” የሚል ነው። ሥራን ከትንሽ ነገር መጀመር አለባቸው። ሀብት ማፍራት በሂደት የሚመጣ ስለሆነ “በአንዴ ለምን ሀብታም አልሆንኩም” ብሎ ተስፋ መቁረጥ የለባቸውም። በትንሽ በመጀመር እርሱኑ በማሻሻል ወደ ተሻለ ነገር በማሳደግ የሀብት ባለቤት ወደ መሆን ይደረሳል። እኔ ንግድ በጀመርኩበት ሰዓት ከአንቦም ሆነ ከአዲስ አበባ ምንም ዘመድ አልነበረኝም። አዲስ አበባ መጥቼ ለአልጋ ከፍዬ የማድርበት በማጣት መንገድ ላይ አድሬ አውቃለሁ። ይሁን እንጂ ተቸግርያለሁ፣ ከስሬያለሁ ብዬ ተስፋ ቆርጬ አላውቅም። ይኸው እኔ የገጠር ልጅ ዛሬ በአንቦ እና በአዲስ አበባ ብቻም ሳይሆን፣ በተለያዩ የዓለም ከተሞች በመዘዋወር እቃዎችን ገዝቼ ወደ አገሬ አስገባለሁ። ለዚህ ደግሞ ያበቃኝ ትዕግስትና ተስፋ አለመቁረጤ ነው ብዬ አስባለሁ።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cz5negrvzp1o
3politics
"እስካሁን ደቂቃ ድረስ ድርድር አልተደረገም" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
"እስካሁን ደቂቃ ድረስ ከህወሓት ጋር ድርድር አልተደረገም። ድርድር አላደረግንም ማለት ግን እስከናካቴው ድርድር አይኖርም ማለት አይደለም" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ምላሽ ሰጡ። በዛሬው ዕለት የካቲት 15፣ 2014 ዓ. ም. በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እንዲሁም የመንግሥታቸው የስድስት ወራት አፈጻጸም በተመለከተ ማብራሪያ ሲስጡ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የፌደራል መንግሥቱ ከህወሓት ጋር ድርድር እያደረገ ነው? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ነው ይህንን ምላሽ የሰጡት። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሥራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ፤ በኢትዮጵያ መንግሥትና በህወሓት መካከል እየተካሄደ ነው ስለሚባለው ድርድር ጥያቄያቸውን አቅርበዋል። በተለይም ህወሓት በኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሽብርተኛ ተብሎ ከመፈረጁ አንጻር ድርድሩ፣ ከሞራል፣ ከሕጋዊነት እና ቅቡልነት አንፃር እንዴት ይታያል? የሚልም ጥያቄ በማቅረብ ማብራሪያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይስጡኝ ብለዋል። በተጨማሪም በቅርቡ መንግሥት የእነ አቶ ስብሃት ነጋን ክስ ማቋረጡ ከሕግ አግባብ ውጭና ሕገ መንግሥቱን የሚጣረስ ነው በሚል ውሳኔው እንዲቀለበስና ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። በሦስተኛው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤት አባሎች የቀረቡላቸውን ጥያቄዎችና አስተያየቶች በሁለት ከፍለው ምላሽ ሰጥተዋል። ከሰሜኑ ጦርነት ጋር ተያይዘው የሚነሱ ጥያቄዎች፣ በአፋር ክልል እንደ አዲስ ያገረሸው ጦርነት፣ የእስረኞች መፈታት፣ ከህወሓት ጋር እየተደረገ ያለው ድርድር፣ የሻከረው ዲፕሎማሲ፣ የልዩ ኃይሎች መዋቅር እንዲሁም በአምባሳደሮች ሹመት ላይ ምላሽ ሰጥተዋል። ስለ እስረኞች መፈታት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለይም ስለእነ አቶ ስብሃት ነጋ ክስ መቋረጥና እስረኞች የተፈቱበትን ምክንያት እንዲያብራሩ ከብዙ የምክር ቤቱ አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ እስረኞች የተፈቱት "እኛ የሞራል ልዕልና ስላለን ነው" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። "እኛ የሞራል ልዕልና አለን። እናፈርሳቸዋልን፣ እንገድላቸዋለን ላልናቸው ምሕረት መስጠታችን የሞራል ልዕልና ይሰጠናል። ጉዳት የለውም" ሲሉ ውሳኔውን አስረድተዋል። አያይዘውም "ጠላቶቻን በቀየሱልን መንገድ መጓዝ አሸናፊ አያደርገንም። እኛ ለድል የሚያበቃንን መንገድ መቀየስ አለብን" ብለዋል። እስረኞችን ለመፈታት የወሰኑት በሦስት ምክንያቶች እንደሆነ ጠቅሰው "አንደኛው ዘላቂ ሰላም ለማምጣትና የጋራ ቤት ለመሥራት ነው" ብለዋል። ጨምረውም "ሁለተኛውም ምክንያት የታሳሪዎችን ሁለንተናዊ ሁኔታ ያገናዘበ ነው። ሁሉም እስረኛ አይደለም የተፈታው። ሦስተኛው ምክንያታችን ያገኘውን ድል ለማጽናት ነው" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። እስረኞችን ክስ አቋርጦ መፍታት ሕጋዊ ተቃርኖ የሌለው ውሳኔ እንደሆነ ጠቅሰው "በእርስ በእርስ ጦርነት ፍፁም ድል የለም። እኛ የምንመርጠው በቂ ድል ነው። አገርን ለመታደግ ነው" ሲሉ እስረኞች የተፈቱበት ምክያት አስረድተዋል። አያይዘውም "እነዚህ ሰዎች በመፈታታቸው ኢትዮጵያ ተጠቃሚ ናት። የፈታናቸው በጉቦ፣ በዝምድና አይደለም። የመፈታታቸውን ጥቅም አይተነዋል" ብለዋል። ድርድር እየተደረገ ነው? የፌደራል መንግሥቱ ከህወሓት ጋር ድርድር እያደረገ ነው? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ "እስካሁን ደቂቃ ድረስ ድርድር አልተደረገም። ድርድር አላደረግንም ማለት ግን እስከናካቴው ድርድር አይኖርም ማለት አይደለም" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ለሰላም አማራጮች የሆኑ መንገዶች እንደሚወሰዱ ጠቁመው "የሰላም አማራጭ ካለ፣ ህወሓት ቀልብ ከገዛ በደስታ እናየዋለን" ሲሉ ተናግረዋል። ትላንት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአገር ምክክር ኮሚሽነሮች መመረጣቸውን አጣቅሰው "እኔ ድርድር ብዬ የማስበው አገር አቀፍ ውይይቱን ነው" ብለዋል። በምክር ቤቱ የጸደቁት 11 ኮሚሽነሮች ሚናቸው "ሁሉንም ማኅበረሰብ ማወያየት ነው እንጂ በሕዝበ ውሳኔ የሚወስነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው" ሲሉም አክለዋል። ብሔራዊ ውይይት ይህ ብሔራዊ ውይይት በቀላሉ መታየት እንደሌለበትና የተቃዋሚ ፖርቲዎችም ዕድሉን መጠቀም እንዳለባቸው አፅንኦት ሰጥተዋል። "ለህወሓትም ሆነ ለየትኛውም ኃይሎች" ትናንት የጸደቁት ኮሚሽነሮች ዋነኛ ተግባራቸው መድረኮችን ማመቻቸትና አጀንዳዎችን መፍጠር ነው ብለዋል። በአፍሪካ ውስጥ በአብዛኛው የሚደረገው የልሂቃን ውይይት እንደተደረገና ይህ ደግሞ አገራዊ አጀንዳ ሳይሆን ሥልጣን ክፍፍል መሆኑን ጠቅሰው በአሁኑ ወቅት አገሪቷ የምትዘጋጅበት ውይይትም ሆነ ድርድር የሥልጣን ክፍፍል አለመሆኑ ልብ ሊባል ይገባል ብለዋል። የሥልጣን ክፍፍሉ በምርጫ የተጠናቀቀ ጉዳይ ነው ብለው፤ በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ኢትዮጵያን የሚገዛት ብልፅግና ፓርቲ መሆኑን አስታውሰዋል። ብሔራዊ ውይይቱና ምክክሩ የሚደረገው በቆሰሉ ታሪኮችና ነገ በምንገነባት ኢትዮጵያ ላይ ፟እንደሆነ "የምንገነባው አገር ከሥልጣናችን በላይ ስለሆነ ነው፤ ለወደፊቱ ትውልድ ስለሆነ ነው" ሲሉም አስረድተዋል። የውይይቱ ሂደት በዋነኝት ሊያካትታቸው የሚገባ ጉዳዮች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህም ግልፅ፣ የሚገለል ማኅበረሰብ የሌለበትና ሁሉንም ሕዝብ አሳታፊ ሊሆን እንደሚገባም አንስተዋል። እንደ ምሳሌ የጠቀሱት በሕገ መንግሥቱ ላይ ያለውን አንቀፅ 39፣ በርካታ ጥያቄ የሚያነሱ ፓርቲዎችን ጉዳይ እንዲሁም የሰንደቅ አላማ ጉዳይን ሲሆን በአሁኑ ወቅት አገሪቱን የሚያከራክሩና የሚያጣሉ ጉዳዮች መቋጫ ሊያገኙ የሚችሉበት ነው ብለዋል። ውይይት የሚያስፈልገው ሽኩቻ፣ ጦርነትና የፖለቲካ ሽግግር ሲኖር መሆኑን ጠቅሰው አገሪቷ እያተዘጋጀችበት ያለችውም ምክክር አራት ምዕራፎች እንዳሉት ጠቅሰዋል። እስካሁን የተካሄደው ቅድመ ዝግጅት ሲሆን እስካሁን ያለው ብሔርና ፆታን ባሳተፈ መልኩ የተዋቀረ በመሆኑ ጥሩ ጅማሮ ነው ብለዋል። "በውይይትና በድርድር የሚፈታ ችግር ካለ መንግሥት ለማንም በሩ ክፍት ነው። እኛ የምንጠላው የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚነካ ሲሆን ነው" ብለዋል። በጦርነቱ ለተጎዱት አማራና አፋር ክልሎች በጀት በጦርነቱ የተጎዱትን የአማራና የአፋር ክልሎች መልሶ ለማቋቋም የተመደበው በጀት አነስተኛ ነው በሚል ከምክር ቤት አባላት ጥያቄ ቀርቦላቸዋል። የሁለቱን ክልሎች ብቻ ሳይሆን የሌሎችም ሕዝቦች ችግር መጠቀስ አለበት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ "የትግራይ ሕዝብ መብራት የለውም፣ ምግብ እየተቸገረ ነው፣ መድኃኒት እጥረት ላይ ነው" ብለዋል። አክለውም "ትግራይ እንድትገነጠል አንፈልግም፤ ትግራይ ትገንጠል ብትባል 100 ፐርሰንት አይሆንም ትላላችሁ። እንዲገነጠሉ የማንፈልግ ከሆነ እንዳይጎዱም ስለ ሕዝቡ የሚገባውን መብት ማሰብ አለብን። ያንን ማድረግ ከቻልን ነው አብረን ነው መኖር የምንችለው" ብለዋል። በተጨማሪ በሰሞኑ እንደ አዲስ ካገረሸው ጦርነት ጋር ተያይዞ የአፋር ክልል በፌደራሉ ወይም በመከላከያ ተዘንግቷል በሚል ከምክር ቤት አባል ጥያቄ የቀረበላቸው ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩም በምላሹ የፌደራል መንግሥት ከአፋር ክልል ጋር በከፍተኛ ቅርበት እንደሚሠራ ተናግረዋል። "ማንኛውም የአፋር ጥቃት፣ የአማራ ጥቃት የኢትዮጵያ ጥቃት ነው" በማለትም የሰሞኑ ጥቃት አላማ አፋር አይደለም ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ በትግራይና በአፋር ክልል የተነሳውን ጦርነት ህወሓት "የእርዳታ እህል እንዳይገባ በሚል ነው ጥቃት የከፈተው" ብለውታል። የአማራና የአፋር ክልሎች ወደ ትግራይ እርዳታ እንዳይገባ ዘግተዋል የሚባለውም ከእውነት የራቀ እንደሆነም አስረድተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ዘንድ መንግሥታቸው የትግራይን ሕዝብ ሆን ብሎ እንደሚያስርብና እርዳታ እንደሚከለክል እንደሚታሰብም ገልጸዋል። "ስማችን በዓለም ላይ ጠልሽቷል፤ እኛ ሕዝብ እንዲራብ አንፈልግም" ብለዋል። በዚህ ጦርነት እንደ ትግራይ ክልል የተጎዳ የለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአማራና የአፋር ሌላውም ኢትዮጵያ ትግራይን መገንባት እንዳለበትም አስረድተዋል። ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር የሚለውና መንግሥት ኦነግ ሸኔ የሚለውን ቡድን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ "ኃይሉ አላማ የሌለው፣ ዘረፋና ግድያና የሚፈፅም" መሆኑን ጠቅሰው ይህንን ኃይልም ለመግታት መንግሥትና የኦሮሚያ ክልል ለወራት ያህል ከፍተኛ መስዋዕትነት እንደከፈሉ ተናግረዋል። በኦሮሚያ ላይ ከፍተኛ መሠረተ ልማቶችን ቢያወድምና መንግሥትም ኃይሉን ለመግታት ከፍተኛ ሥራ ቢሠራም "በወታደራዊ ሥራዎች ብቻ የሚፈታ አይደለም። ሕዝቡስ ለምን ተሸከመው? ለምን ቀለበው? የሚለው ጥያቄ ከሕዝቡ ጋር ሆኖ መፈታት አለበት" በማለት አስረድተዋል። ሆኖም የትኛውም ታጣቂ ኃይል "ኢትዮጵያን አያሸንፍም" ብለዋል። ልዩ ኃይል የልዩ ኃይል አወቃቀር ላይ የተነሳውን ጥያቄ በተመለከተ በየክልሉ ያለውን ችግር ለመፍታት ልዩ ኃይል አስፈላጊ እንደሆነና የልዩ ኃይል አባላት እንዴት ይሥሩ? የሚለው ላይ ግን ንግግር በማድረግ ለወደፊት አቅጣጫ ማስቀመጥ እንደሚቻል ተናግረዋል። የተቃዋሚዎች ተሳትፎ የምክር ቤቱ አባላት ካነሱት ጥያቄ መካከል መንግሥት ምን ያህል ከተቃዋሚዎች ጋር ይሠራል? የሚለው ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በምላሻቸው የአገር ምክክር ኮሚሽን በሁለቱ ወገኖች መካከል የሚኖረውን መናበብ የተሻለ ያደርጋል ብለው እንደሚያምኑ ጠቁመዋል። እስካሁን ድረስ በነበረው ሂደት "የልሂቃን አክራሪነት እጅግ አደገኛ ነው። ዋልታ ረገጥነት አገርን ይጎዳል" ሲሉ አጠቃላይ የፖለቲካ ልሂቃል ግምገማቸውን አስቀምጠዋል። ድርቅ በሶማሌ፣ ኦሮሚያና ሌሎችም በአገሪቱ በተለያዩ ክልሎች የተስፋፋውን አሳሳቢ ድርቅ በተመለከተ ምላሽ ሲሰጡ "እስካሁን ሰው አልሞተብንም" ብለው እስካሁን 750 ሺህ ኩንታል ምግብን ጨምሮ የልጆች ምግብ፣ የከብት መኖ እና ክትባት እንደተላከ ጠቅሰዋል። ግድቡ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጨትና ከሱዳን እንዲሁም ከግብፅ ጋር ያለውን ውጥረት በተመለከተ "ውሃው ተርባይኑን መትቶ ሄዷል። ከዚህ በኋላም በድርድርና በውይይት አብረን እንሠራለን" በማለት ኢትዮጵያ ሦስቱንም አገራት ያማከለ አካሄድ እንደምታራምድ ተናግረዋል። የዲፕሎማቶች ሹመት በአገሪቱ ውስጥ አነጋጋሪ የተባሉት የሁለቱ ጄኔራሎች ባጫ ደበሌና ሃሰን ኢብራሂም እንዲሁም የኢንጂነር ስለሺ በቀለ በአምባሳደርነት የተሾሙበት መስፈርት ምንድን ነው? የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል። በተለይም በቅርቡ የተሰጡ የአምባሳደር ሹመቶችን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ "ብቃት ያላቸው ሰዎች ናቸው የተሾሙት" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። "በኢትዮጵያም በዓለምም ብዙ ወታደር አምባሳደር አለ። ውጊያ መምራት እና ዲፕሎማሲ ተመጋጋቢ ነው" በማለት ሹመቶቹ በምን ምክንያት እንደተሰጡም ጠቁመዋል። ሳዑዲ ያሉ ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ አረቢያ በተለይም በእስር ቤቶች የሚንገላቱ ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽ፤ ሁሉም ሳዑዲ ያሉት ወደ ኢትዮጵያ እንዳይመለሱ ያደረገው ምክንያት ከመካከላቸው "የሠለጠኑ ገዳዮች" እንዲሁም በሌላ መንገድም የደኅንነት ስጋት የሆኑ ስላሉበት እንደሆነ አስረድተዋል። "ከሳዑዲ ጋር በቅርበት እየሠራን ው። ስንመልሳቸው ጥፋት የሚያስከትሉ እንደሚኖሩ ስጋት ስላለብን ነው። አብረው የሚጎዱ ንጹሀንም ስላሉ ጥናት እያደረግን ነው" ሲሉ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
"እስካሁን ደቂቃ ድረስ ድርድር አልተደረገም" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ "እስካሁን ደቂቃ ድረስ ከህወሓት ጋር ድርድር አልተደረገም። ድርድር አላደረግንም ማለት ግን እስከናካቴው ድርድር አይኖርም ማለት አይደለም" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ምላሽ ሰጡ። በዛሬው ዕለት የካቲት 15፣ 2014 ዓ. ም. በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እንዲሁም የመንግሥታቸው የስድስት ወራት አፈጻጸም በተመለከተ ማብራሪያ ሲስጡ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የፌደራል መንግሥቱ ከህወሓት ጋር ድርድር እያደረገ ነው? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ነው ይህንን ምላሽ የሰጡት። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሥራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ፤ በኢትዮጵያ መንግሥትና በህወሓት መካከል እየተካሄደ ነው ስለሚባለው ድርድር ጥያቄያቸውን አቅርበዋል። በተለይም ህወሓት በኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሽብርተኛ ተብሎ ከመፈረጁ አንጻር ድርድሩ፣ ከሞራል፣ ከሕጋዊነት እና ቅቡልነት አንፃር እንዴት ይታያል? የሚልም ጥያቄ በማቅረብ ማብራሪያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይስጡኝ ብለዋል። በተጨማሪም በቅርቡ መንግሥት የእነ አቶ ስብሃት ነጋን ክስ ማቋረጡ ከሕግ አግባብ ውጭና ሕገ መንግሥቱን የሚጣረስ ነው በሚል ውሳኔው እንዲቀለበስና ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። በሦስተኛው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤት አባሎች የቀረቡላቸውን ጥያቄዎችና አስተያየቶች በሁለት ከፍለው ምላሽ ሰጥተዋል። ከሰሜኑ ጦርነት ጋር ተያይዘው የሚነሱ ጥያቄዎች፣ በአፋር ክልል እንደ አዲስ ያገረሸው ጦርነት፣ የእስረኞች መፈታት፣ ከህወሓት ጋር እየተደረገ ያለው ድርድር፣ የሻከረው ዲፕሎማሲ፣ የልዩ ኃይሎች መዋቅር እንዲሁም በአምባሳደሮች ሹመት ላይ ምላሽ ሰጥተዋል። ስለ እስረኞች መፈታት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለይም ስለእነ አቶ ስብሃት ነጋ ክስ መቋረጥና እስረኞች የተፈቱበትን ምክንያት እንዲያብራሩ ከብዙ የምክር ቤቱ አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ እስረኞች የተፈቱት "እኛ የሞራል ልዕልና ስላለን ነው" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። "እኛ የሞራል ልዕልና አለን። እናፈርሳቸዋልን፣ እንገድላቸዋለን ላልናቸው ምሕረት መስጠታችን የሞራል ልዕልና ይሰጠናል። ጉዳት የለውም" ሲሉ ውሳኔውን አስረድተዋል። አያይዘውም "ጠላቶቻን በቀየሱልን መንገድ መጓዝ አሸናፊ አያደርገንም። እኛ ለድል የሚያበቃንን መንገድ መቀየስ አለብን" ብለዋል። እስረኞችን ለመፈታት የወሰኑት በሦስት ምክንያቶች እንደሆነ ጠቅሰው "አንደኛው ዘላቂ ሰላም ለማምጣትና የጋራ ቤት ለመሥራት ነው" ብለዋል። ጨምረውም "ሁለተኛውም ምክንያት የታሳሪዎችን ሁለንተናዊ ሁኔታ ያገናዘበ ነው። ሁሉም እስረኛ አይደለም የተፈታው። ሦስተኛው ምክንያታችን ያገኘውን ድል ለማጽናት ነው" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። እስረኞችን ክስ አቋርጦ መፍታት ሕጋዊ ተቃርኖ የሌለው ውሳኔ እንደሆነ ጠቅሰው "በእርስ በእርስ ጦርነት ፍፁም ድል የለም። እኛ የምንመርጠው በቂ ድል ነው። አገርን ለመታደግ ነው" ሲሉ እስረኞች የተፈቱበት ምክያት አስረድተዋል። አያይዘውም "እነዚህ ሰዎች በመፈታታቸው ኢትዮጵያ ተጠቃሚ ናት። የፈታናቸው በጉቦ፣ በዝምድና አይደለም። የመፈታታቸውን ጥቅም አይተነዋል" ብለዋል። ድርድር እየተደረገ ነው? የፌደራል መንግሥቱ ከህወሓት ጋር ድርድር እያደረገ ነው? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ "እስካሁን ደቂቃ ድረስ ድርድር አልተደረገም። ድርድር አላደረግንም ማለት ግን እስከናካቴው ድርድር አይኖርም ማለት አይደለም" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ለሰላም አማራጮች የሆኑ መንገዶች እንደሚወሰዱ ጠቁመው "የሰላም አማራጭ ካለ፣ ህወሓት ቀልብ ከገዛ በደስታ እናየዋለን" ሲሉ ተናግረዋል። ትላንት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአገር ምክክር ኮሚሽነሮች መመረጣቸውን አጣቅሰው "እኔ ድርድር ብዬ የማስበው አገር አቀፍ ውይይቱን ነው" ብለዋል። በምክር ቤቱ የጸደቁት 11 ኮሚሽነሮች ሚናቸው "ሁሉንም ማኅበረሰብ ማወያየት ነው እንጂ በሕዝበ ውሳኔ የሚወስነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው" ሲሉም አክለዋል። ብሔራዊ ውይይት ይህ ብሔራዊ ውይይት በቀላሉ መታየት እንደሌለበትና የተቃዋሚ ፖርቲዎችም ዕድሉን መጠቀም እንዳለባቸው አፅንኦት ሰጥተዋል። "ለህወሓትም ሆነ ለየትኛውም ኃይሎች" ትናንት የጸደቁት ኮሚሽነሮች ዋነኛ ተግባራቸው መድረኮችን ማመቻቸትና አጀንዳዎችን መፍጠር ነው ብለዋል። በአፍሪካ ውስጥ በአብዛኛው የሚደረገው የልሂቃን ውይይት እንደተደረገና ይህ ደግሞ አገራዊ አጀንዳ ሳይሆን ሥልጣን ክፍፍል መሆኑን ጠቅሰው በአሁኑ ወቅት አገሪቷ የምትዘጋጅበት ውይይትም ሆነ ድርድር የሥልጣን ክፍፍል አለመሆኑ ልብ ሊባል ይገባል ብለዋል። የሥልጣን ክፍፍሉ በምርጫ የተጠናቀቀ ጉዳይ ነው ብለው፤ በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ኢትዮጵያን የሚገዛት ብልፅግና ፓርቲ መሆኑን አስታውሰዋል። ብሔራዊ ውይይቱና ምክክሩ የሚደረገው በቆሰሉ ታሪኮችና ነገ በምንገነባት ኢትዮጵያ ላይ ፟እንደሆነ "የምንገነባው አገር ከሥልጣናችን በላይ ስለሆነ ነው፤ ለወደፊቱ ትውልድ ስለሆነ ነው" ሲሉም አስረድተዋል። የውይይቱ ሂደት በዋነኝት ሊያካትታቸው የሚገባ ጉዳዮች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህም ግልፅ፣ የሚገለል ማኅበረሰብ የሌለበትና ሁሉንም ሕዝብ አሳታፊ ሊሆን እንደሚገባም አንስተዋል። እንደ ምሳሌ የጠቀሱት በሕገ መንግሥቱ ላይ ያለውን አንቀፅ 39፣ በርካታ ጥያቄ የሚያነሱ ፓርቲዎችን ጉዳይ እንዲሁም የሰንደቅ አላማ ጉዳይን ሲሆን በአሁኑ ወቅት አገሪቱን የሚያከራክሩና የሚያጣሉ ጉዳዮች መቋጫ ሊያገኙ የሚችሉበት ነው ብለዋል። ውይይት የሚያስፈልገው ሽኩቻ፣ ጦርነትና የፖለቲካ ሽግግር ሲኖር መሆኑን ጠቅሰው አገሪቷ እያተዘጋጀችበት ያለችውም ምክክር አራት ምዕራፎች እንዳሉት ጠቅሰዋል። እስካሁን የተካሄደው ቅድመ ዝግጅት ሲሆን እስካሁን ያለው ብሔርና ፆታን ባሳተፈ መልኩ የተዋቀረ በመሆኑ ጥሩ ጅማሮ ነው ብለዋል። "በውይይትና በድርድር የሚፈታ ችግር ካለ መንግሥት ለማንም በሩ ክፍት ነው። እኛ የምንጠላው የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚነካ ሲሆን ነው" ብለዋል። በጦርነቱ ለተጎዱት አማራና አፋር ክልሎች በጀት በጦርነቱ የተጎዱትን የአማራና የአፋር ክልሎች መልሶ ለማቋቋም የተመደበው በጀት አነስተኛ ነው በሚል ከምክር ቤት አባላት ጥያቄ ቀርቦላቸዋል። የሁለቱን ክልሎች ብቻ ሳይሆን የሌሎችም ሕዝቦች ችግር መጠቀስ አለበት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ "የትግራይ ሕዝብ መብራት የለውም፣ ምግብ እየተቸገረ ነው፣ መድኃኒት እጥረት ላይ ነው" ብለዋል። አክለውም "ትግራይ እንድትገነጠል አንፈልግም፤ ትግራይ ትገንጠል ብትባል 100 ፐርሰንት አይሆንም ትላላችሁ። እንዲገነጠሉ የማንፈልግ ከሆነ እንዳይጎዱም ስለ ሕዝቡ የሚገባውን መብት ማሰብ አለብን። ያንን ማድረግ ከቻልን ነው አብረን ነው መኖር የምንችለው" ብለዋል። በተጨማሪ በሰሞኑ እንደ አዲስ ካገረሸው ጦርነት ጋር ተያይዞ የአፋር ክልል በፌደራሉ ወይም በመከላከያ ተዘንግቷል በሚል ከምክር ቤት አባል ጥያቄ የቀረበላቸው ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩም በምላሹ የፌደራል መንግሥት ከአፋር ክልል ጋር በከፍተኛ ቅርበት እንደሚሠራ ተናግረዋል። "ማንኛውም የአፋር ጥቃት፣ የአማራ ጥቃት የኢትዮጵያ ጥቃት ነው" በማለትም የሰሞኑ ጥቃት አላማ አፋር አይደለም ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ በትግራይና በአፋር ክልል የተነሳውን ጦርነት ህወሓት "የእርዳታ እህል እንዳይገባ በሚል ነው ጥቃት የከፈተው" ብለውታል። የአማራና የአፋር ክልሎች ወደ ትግራይ እርዳታ እንዳይገባ ዘግተዋል የሚባለውም ከእውነት የራቀ እንደሆነም አስረድተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ዘንድ መንግሥታቸው የትግራይን ሕዝብ ሆን ብሎ እንደሚያስርብና እርዳታ እንደሚከለክል እንደሚታሰብም ገልጸዋል። "ስማችን በዓለም ላይ ጠልሽቷል፤ እኛ ሕዝብ እንዲራብ አንፈልግም" ብለዋል። በዚህ ጦርነት እንደ ትግራይ ክልል የተጎዳ የለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአማራና የአፋር ሌላውም ኢትዮጵያ ትግራይን መገንባት እንዳለበትም አስረድተዋል። ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር የሚለውና መንግሥት ኦነግ ሸኔ የሚለውን ቡድን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ "ኃይሉ አላማ የሌለው፣ ዘረፋና ግድያና የሚፈፅም" መሆኑን ጠቅሰው ይህንን ኃይልም ለመግታት መንግሥትና የኦሮሚያ ክልል ለወራት ያህል ከፍተኛ መስዋዕትነት እንደከፈሉ ተናግረዋል። በኦሮሚያ ላይ ከፍተኛ መሠረተ ልማቶችን ቢያወድምና መንግሥትም ኃይሉን ለመግታት ከፍተኛ ሥራ ቢሠራም "በወታደራዊ ሥራዎች ብቻ የሚፈታ አይደለም። ሕዝቡስ ለምን ተሸከመው? ለምን ቀለበው? የሚለው ጥያቄ ከሕዝቡ ጋር ሆኖ መፈታት አለበት" በማለት አስረድተዋል። ሆኖም የትኛውም ታጣቂ ኃይል "ኢትዮጵያን አያሸንፍም" ብለዋል። ልዩ ኃይል የልዩ ኃይል አወቃቀር ላይ የተነሳውን ጥያቄ በተመለከተ በየክልሉ ያለውን ችግር ለመፍታት ልዩ ኃይል አስፈላጊ እንደሆነና የልዩ ኃይል አባላት እንዴት ይሥሩ? የሚለው ላይ ግን ንግግር በማድረግ ለወደፊት አቅጣጫ ማስቀመጥ እንደሚቻል ተናግረዋል። የተቃዋሚዎች ተሳትፎ የምክር ቤቱ አባላት ካነሱት ጥያቄ መካከል መንግሥት ምን ያህል ከተቃዋሚዎች ጋር ይሠራል? የሚለው ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በምላሻቸው የአገር ምክክር ኮሚሽን በሁለቱ ወገኖች መካከል የሚኖረውን መናበብ የተሻለ ያደርጋል ብለው እንደሚያምኑ ጠቁመዋል። እስካሁን ድረስ በነበረው ሂደት "የልሂቃን አክራሪነት እጅግ አደገኛ ነው። ዋልታ ረገጥነት አገርን ይጎዳል" ሲሉ አጠቃላይ የፖለቲካ ልሂቃል ግምገማቸውን አስቀምጠዋል። ድርቅ በሶማሌ፣ ኦሮሚያና ሌሎችም በአገሪቱ በተለያዩ ክልሎች የተስፋፋውን አሳሳቢ ድርቅ በተመለከተ ምላሽ ሲሰጡ "እስካሁን ሰው አልሞተብንም" ብለው እስካሁን 750 ሺህ ኩንታል ምግብን ጨምሮ የልጆች ምግብ፣ የከብት መኖ እና ክትባት እንደተላከ ጠቅሰዋል። ግድቡ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጨትና ከሱዳን እንዲሁም ከግብፅ ጋር ያለውን ውጥረት በተመለከተ "ውሃው ተርባይኑን መትቶ ሄዷል። ከዚህ በኋላም በድርድርና በውይይት አብረን እንሠራለን" በማለት ኢትዮጵያ ሦስቱንም አገራት ያማከለ አካሄድ እንደምታራምድ ተናግረዋል። የዲፕሎማቶች ሹመት በአገሪቱ ውስጥ አነጋጋሪ የተባሉት የሁለቱ ጄኔራሎች ባጫ ደበሌና ሃሰን ኢብራሂም እንዲሁም የኢንጂነር ስለሺ በቀለ በአምባሳደርነት የተሾሙበት መስፈርት ምንድን ነው? የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል። በተለይም በቅርቡ የተሰጡ የአምባሳደር ሹመቶችን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ "ብቃት ያላቸው ሰዎች ናቸው የተሾሙት" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። "በኢትዮጵያም በዓለምም ብዙ ወታደር አምባሳደር አለ። ውጊያ መምራት እና ዲፕሎማሲ ተመጋጋቢ ነው" በማለት ሹመቶቹ በምን ምክንያት እንደተሰጡም ጠቁመዋል። ሳዑዲ ያሉ ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ አረቢያ በተለይም በእስር ቤቶች የሚንገላቱ ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽ፤ ሁሉም ሳዑዲ ያሉት ወደ ኢትዮጵያ እንዳይመለሱ ያደረገው ምክንያት ከመካከላቸው "የሠለጠኑ ገዳዮች" እንዲሁም በሌላ መንገድም የደኅንነት ስጋት የሆኑ ስላሉበት እንደሆነ አስረድተዋል። "ከሳዑዲ ጋር በቅርበት እየሠራን ው። ስንመልሳቸው ጥፋት የሚያስከትሉ እንደሚኖሩ ስጋት ስላለብን ነው። አብረው የሚጎዱ ንጹሀንም ስላሉ ጥናት እያደረግን ነው" ሲሉ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
https://www.bbc.com/amharic/60479375
5sports
ዋሊያዎቹ ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ደቡብ አፍሪካን ዛሬ ይገጥማሉ
በኳታር 2022 የዓለም ዋንጫ ለመሳተፍ ከጋና፣ ደቡብ አፍሪካ እና ከዚምባብዌ ጋር የተደለደለው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ሶስተኛ የምድብ ጨዋታውን ቅዳሜ መስከረም 28/2014 ዓ.ም በባህር ዳር ስቴዲየም ከባፋና ባፋናዎች ጋር ያደርጋል። በምድቡ የመጀመሪያ ጨዋታው ወደ ጋና ያቀኑት ዋሊያዎቹ በጨዋታው አንድ ለባዶ በሆነ ውጤት መሸነፋቸው የሚታወስ ነው። ምንም እንኳን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ኳስ ይዞ ለመጫወትና የበላይነት ለመውሰድ ቢሞክርም በጨዋታው ግን ግብ ማስቆጠር ሳይችል ቀርቷል። ጨዋታው በተጀመረ 35ኛው ደቂቃ ላይ የጋናው ሚባራክ ዋክሶ ከርቀት የሞከራት ኳስ ወደ ግብነት ተቀይራ ጨዋታው በጋና አንድ ለባዶ አሸናፊነት ተጠናቋል። በመቀጠል በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በባህር ዳር ስቴዲየም ዚምባቡዌን የገጠመ ሲሆን ጨዋታውን አንድ ለባዶ በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል። ከባድ የተባለው ምድብ ውስጥ የተደለደሉት ዋሊያዎቹ ለድል ያበቃቻቸውን ግብ ማስቆጠር የቻሉት በጨዋታው መጠናቀቂያ ሰዓት ላይ የተገኘውን የፍጹም ቅጣት ምት ተከላካዩ አስቻለው ታመነ ወደ ግብነት በመቀየሩ ነው። ጨዋታውን አንድ ለባዶ በሆነ ውጤት በማሸነፍ ዋሊያዎቹ የመጀመሪያውን ሦስት ነጥብ በባህር ዳር ስታዲየም ማግኘት ችለዋል። እስካሁን በምድቡ በተደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች ደቡብ አፍሪካ ዚምባብዌን ካሸነፈች በኋላ ከጋና ደግሞ አቻ ተለያይታለች። ዚምባብዌ ደግሞ ከደቡብ አፍሪካ አቻ ተለያይታ በኢትዮጵያ አንድ ለባዶ ተሸንፋለች። በዚህም ምድቡን ደቡብ አፍሪካ በአራት ነጥብ ስትመራ፣ ጋናና ኢትዮጵያ በተመሳሳይ በሦስት ነጥብ በመያዝ ሁለተኛና ሦስተኛ ደረጃቸውን አስጠብቀዋል። ዚምባቡዌ ደግሞ በአንድ ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ኳታር በምታስተናግደው የ2022 የዓለም ዋንጫ ለመሳተፍ እድላችን አሁንም ከፍተኛ ነው የሚሉት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ፤ ከደቡብ አፍሪካ አቻቸው ጋር ላለባቸው የምድብ ማጣሪያ በባህር ዳር በመከተም ዝግጅት ጀምረዋል። ለዚህ ጨዋታ ዝግጅት ለማድረግ ደግሞ ለ25 ተጨዋቾች ጥሪ አድርገዋል። በዚህም ግብ ጠባቂዎች ጀማል ጣሰው፣ ተክለማርያም ሻንቆና ፋሲል ገብረሚካኤል ሲሆኑ፤ ተከላካዮች አስቻለው ታመነ፣ አስራት ቱጂ፣ ሱሌማን ሀሚድ፣ ረመዳን የሱፍ፣ ያሬድ ባዬ፣ ደስታ ዮሐንስ፣ ምኞት ደበበና መናፍ አወል ተካተዋል። አማካዮች ደግሞ ሽመልስ በቀለ ፣ ይሁኔ በላይ፣ ጋቶች ፓኖም፣ መሱድ መሐመድ፣ ሱራፌል ዳኛቸው፣ ታፈሰ ሠለሞን፣ ሽመክት ጉግሳና አማኑኤል ዮሐንስ ናቸው። የፊት መስመር ተጫዋቾች ደግሞ አማኑኤል ገብረሚካኤል፣ ጌታነህ ከበደ፣ አቤል ያለው፣ ቸርነት ጉግሳ፣ መስፍን ታፈሰና አቡበክር ናስር መሆናቸው ይፋ ተደርጓል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን በፌስቡክ ገጹ ላይ ባሰፈረው መልዕክት በአለም ዋንጫ ማጣሪያ የፊታችን ቅዳሜ የደቡብ አፍሪካ አቻውን የሚገጥሙት ዋልያዎቹ መደበኛ ልምምዳቸውን ሐሙስ ዕለት መስራታቸውን ገልጿል። ለግብጹ ጎና ኤፍሲ የሚጫወተው የመሀል ክፍል አንቀሳቃሹ ሽምስ በቀለ ከቀናት በፊት ባህር ዳር የሚገኘውን ቡድን የተቀላቀለ ሲሆን ከቡድን አጋሮቹ ጋርም ልምምድ መስራቱን ፌደሬሽኑ አስታውቋል።
ዋሊያዎቹ ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ደቡብ አፍሪካን ዛሬ ይገጥማሉ በኳታር 2022 የዓለም ዋንጫ ለመሳተፍ ከጋና፣ ደቡብ አፍሪካ እና ከዚምባብዌ ጋር የተደለደለው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ሶስተኛ የምድብ ጨዋታውን ቅዳሜ መስከረም 28/2014 ዓ.ም በባህር ዳር ስቴዲየም ከባፋና ባፋናዎች ጋር ያደርጋል። በምድቡ የመጀመሪያ ጨዋታው ወደ ጋና ያቀኑት ዋሊያዎቹ በጨዋታው አንድ ለባዶ በሆነ ውጤት መሸነፋቸው የሚታወስ ነው። ምንም እንኳን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ኳስ ይዞ ለመጫወትና የበላይነት ለመውሰድ ቢሞክርም በጨዋታው ግን ግብ ማስቆጠር ሳይችል ቀርቷል። ጨዋታው በተጀመረ 35ኛው ደቂቃ ላይ የጋናው ሚባራክ ዋክሶ ከርቀት የሞከራት ኳስ ወደ ግብነት ተቀይራ ጨዋታው በጋና አንድ ለባዶ አሸናፊነት ተጠናቋል። በመቀጠል በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በባህር ዳር ስቴዲየም ዚምባቡዌን የገጠመ ሲሆን ጨዋታውን አንድ ለባዶ በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል። ከባድ የተባለው ምድብ ውስጥ የተደለደሉት ዋሊያዎቹ ለድል ያበቃቻቸውን ግብ ማስቆጠር የቻሉት በጨዋታው መጠናቀቂያ ሰዓት ላይ የተገኘውን የፍጹም ቅጣት ምት ተከላካዩ አስቻለው ታመነ ወደ ግብነት በመቀየሩ ነው። ጨዋታውን አንድ ለባዶ በሆነ ውጤት በማሸነፍ ዋሊያዎቹ የመጀመሪያውን ሦስት ነጥብ በባህር ዳር ስታዲየም ማግኘት ችለዋል። እስካሁን በምድቡ በተደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች ደቡብ አፍሪካ ዚምባብዌን ካሸነፈች በኋላ ከጋና ደግሞ አቻ ተለያይታለች። ዚምባብዌ ደግሞ ከደቡብ አፍሪካ አቻ ተለያይታ በኢትዮጵያ አንድ ለባዶ ተሸንፋለች። በዚህም ምድቡን ደቡብ አፍሪካ በአራት ነጥብ ስትመራ፣ ጋናና ኢትዮጵያ በተመሳሳይ በሦስት ነጥብ በመያዝ ሁለተኛና ሦስተኛ ደረጃቸውን አስጠብቀዋል። ዚምባቡዌ ደግሞ በአንድ ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ኳታር በምታስተናግደው የ2022 የዓለም ዋንጫ ለመሳተፍ እድላችን አሁንም ከፍተኛ ነው የሚሉት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ፤ ከደቡብ አፍሪካ አቻቸው ጋር ላለባቸው የምድብ ማጣሪያ በባህር ዳር በመከተም ዝግጅት ጀምረዋል። ለዚህ ጨዋታ ዝግጅት ለማድረግ ደግሞ ለ25 ተጨዋቾች ጥሪ አድርገዋል። በዚህም ግብ ጠባቂዎች ጀማል ጣሰው፣ ተክለማርያም ሻንቆና ፋሲል ገብረሚካኤል ሲሆኑ፤ ተከላካዮች አስቻለው ታመነ፣ አስራት ቱጂ፣ ሱሌማን ሀሚድ፣ ረመዳን የሱፍ፣ ያሬድ ባዬ፣ ደስታ ዮሐንስ፣ ምኞት ደበበና መናፍ አወል ተካተዋል። አማካዮች ደግሞ ሽመልስ በቀለ ፣ ይሁኔ በላይ፣ ጋቶች ፓኖም፣ መሱድ መሐመድ፣ ሱራፌል ዳኛቸው፣ ታፈሰ ሠለሞን፣ ሽመክት ጉግሳና አማኑኤል ዮሐንስ ናቸው። የፊት መስመር ተጫዋቾች ደግሞ አማኑኤል ገብረሚካኤል፣ ጌታነህ ከበደ፣ አቤል ያለው፣ ቸርነት ጉግሳ፣ መስፍን ታፈሰና አቡበክር ናስር መሆናቸው ይፋ ተደርጓል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን በፌስቡክ ገጹ ላይ ባሰፈረው መልዕክት በአለም ዋንጫ ማጣሪያ የፊታችን ቅዳሜ የደቡብ አፍሪካ አቻውን የሚገጥሙት ዋልያዎቹ መደበኛ ልምምዳቸውን ሐሙስ ዕለት መስራታቸውን ገልጿል። ለግብጹ ጎና ኤፍሲ የሚጫወተው የመሀል ክፍል አንቀሳቃሹ ሽምስ በቀለ ከቀናት በፊት ባህር ዳር የሚገኘውን ቡድን የተቀላቀለ ሲሆን ከቡድን አጋሮቹ ጋርም ልምምድ መስራቱን ፌደሬሽኑ አስታውቋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-58839830
2health
የኮቪድ -19 ዝርያዎች በክትባቱ ላይ ‘ስጋት’ ፈጥረዋል ተባለ
በከፍተኛ ተላላፊ የሆኑት የኮሮናቫይረስ ዓይነቶች መስፋፋት በአሜሪካ "ለአራተኛ ጊዜ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎችን ቁጥር ሊያንረው ይችላል" የሚል ስጋት መኖሩን አንድ ከፍተኛ የጤና ባለሥልጣን አስጠንቅቀዋል፡፡ የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከል ማዕከል (ሲ ዲ ሲ) ኃላፊ በቅርቡ የሚወጡት የኮቪድ -19 መረጃዎች እንዳሳሰባቸው ተናግረዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት በቀን ወደ 70 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች መያዛቸው መመዝገቡን "በጣም ከፍተኛ ቁጥር" ነው ብለዋል፡፡ በተመሳሳይ ጊዜ በየቀኑ ወደ 2 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች እንደሚሞቱ ተናግረዋል፡፡ "እባካችሁ በግልፅ አድምጡኝ በዚህ ዝርያ ስርጭት ያገኘነውን ስኬት ልናጣው እንችላለን፡፡ አዳዲሶቹ ዝርያዎች ለህዝባችንም ሆነ ለዕድገታችን እውነተኛ ስጋት ናቸው" ሲሉ የሲዲሲዋ ዳይሬክተር ዶ/ር ሮሼል ዋለንስኪ ሰኞ ዕለት ገልጸዋል። በርካታ የኮቪድ -19 ዝርያዎች ስርጭት ቢኖርም የጤና ባለሙያዎች ለጥቂቶቹ ብቻ ትኩረት ሰጥተዋል፡፡ በዚህም መጀመሪያ በእንግሊዝ፣ በደቡብ አፍሪካ እና በብራዚል ይበልጥ ተላላፊ የሚመስሉ ዓይነቶችን ያካትታሉ፡፡ ሲዲሲ በእንግሊዝ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው በጣም ተላላፊው B.1.1.7 የተሰኘው ዝርያ በዚህ ወር በአሜሪካ ዋነኛው ስጋት እንደሚሆን ተንብይዋል፡፡ ክትባቶች መሰጠት ከጀመሩበት ጥር ወር ጀምሮ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ ዕለታዊ የሰዎች በቫይረሱ የመያዝ እና የሞት ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል፡፡ ሲዲሲ ይህን ለብዙዎች ክትባት እስከሚሰጥ ድረስ አዲሶቹ ዝርያዎች ቀድሞውኑ በችግር ላይ ያሉ የጤና ስርዓቶችን አደጋ ላይ እስከሚጥሉ ድረስ በፍጥነት ሊዛመቱ ይችላሉ ብሏል፡፡ እንደሲዲሲ መረጃ ከሆነ አሳሳቢ የሆኑ ዝርያዎችን የሚያካትቱ ከ 2 ሺህ 463 በላይ ኢንፌክሽኖች ሪፖርት ተደርገዋል፡፡ ቢያንስ 2 ሺህ400 የሚሆኑት በእንግሊዝ የተገኘው ዝርያ ዓይነት ናቸው፡፡ በአሜሪካ ውስጥ በአዳዲሶቹ ዝርያዎች የተያዙ ሰዎች እውነተኛ ቁጥር ከዚህ የበለጠ ነው ተብሎ ይገመታል፡፡ በአዳዲሶቹ ዝርያዎች የሚጠቁ ሰዎች ላይ በጣም ከባድ በሽታ ስለማምጣቱ ምንም ማስረጃ የለም፡፡ የሳይንስ ሊቃውንት በሥራ ላይ የዋሉት ክትባቶች አዳዲሶቹንም ዝርያዎች ጭምር ይከላከላሉ ብለው ያምናሉ፡፡ እስከሰኞ ድረስ አሜሪካ ከ 76 ሚሊዮን በላይ ክትባቶችን እንደሰጠች የሲዲሲ መረጃዎች ያመለክታሉ። አሜሪካ ከዓለም ሀገሮች ከፍተኛውን የክትባት መጠን ሰጥታለች፡፡ ሆኖም ቁጥሮቹ ከሕዝብ ቁጥር ለ100 ሰዎች ከተሰጠው አንጻር ሲወዳደር አሜሪካ ከእንግሊዝ፣ ከአረብ ኤሚሬቶች እና ከእስራኤል ቀጥሎ በአራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ በአሜሪካ ክትባት ከተሰጣቸው መካከል የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ እንደሚገኙበት ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡ ሁለቱም በጥር ወር ኋዋይት ሃውስ ክትባቱ እንደወሰዱ አንድ አማካሪ ለኒው ዮርክ ታይምስ እና ለሌሎች የአሜሪካ የመገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል፡፡ የትኛው ክትባት እንደወሰዱ ግልፅ ባይሆንም በጥር ወር በተቆጣጣሪዎች ፈቃድ ያገኙት የፋይዘር እና ሞደርና ክትባት ብቻ ነበር፡፡ በጆንሰን እና ጆንሰን የተሠራው እና አንድ ጊዜ ብቻ የሚሰጠው ክትባት በአሜሪካ ጥቅም ላይ እንዲውል ቅዳሜ ፈቃድ አግኝቷል፡፡ ዶ/ር ዋለንስኪ በአሜሪካ ግዛቶች ሪፖርቶች "በእውነት ተጨንቄያለሁ። ሰዎችን ከኮቪድ-19 ለመከላከል ወደምንመክረው ትክክለኛ የህዝብ ጤና አጠባበቅ እርምጃዎችን ወደ ኋላ ትመልሳለች" ብለዋል፡፡ "አራተኛ ዙር ከፍተኛ ቫይረሱ ስርጭር በዚህ እንዳይከሰት የማስቆም አቅም አለን፡፡ እባካችሁ በእምነታችን ጠንካራ እንሁን" ብለዋል፡፡ አሜሪካ ከ 28 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙባት እና ከኮቪድ -19 ጋር በተያያዘ 500,000 ሰዎችን ሞት አስመዝግባለች ይላል የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ፡፡
የኮቪድ -19 ዝርያዎች በክትባቱ ላይ ‘ስጋት’ ፈጥረዋል ተባለ በከፍተኛ ተላላፊ የሆኑት የኮሮናቫይረስ ዓይነቶች መስፋፋት በአሜሪካ "ለአራተኛ ጊዜ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎችን ቁጥር ሊያንረው ይችላል" የሚል ስጋት መኖሩን አንድ ከፍተኛ የጤና ባለሥልጣን አስጠንቅቀዋል፡፡ የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከል ማዕከል (ሲ ዲ ሲ) ኃላፊ በቅርቡ የሚወጡት የኮቪድ -19 መረጃዎች እንዳሳሰባቸው ተናግረዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት በቀን ወደ 70 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች መያዛቸው መመዝገቡን "በጣም ከፍተኛ ቁጥር" ነው ብለዋል፡፡ በተመሳሳይ ጊዜ በየቀኑ ወደ 2 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች እንደሚሞቱ ተናግረዋል፡፡ "እባካችሁ በግልፅ አድምጡኝ በዚህ ዝርያ ስርጭት ያገኘነውን ስኬት ልናጣው እንችላለን፡፡ አዳዲሶቹ ዝርያዎች ለህዝባችንም ሆነ ለዕድገታችን እውነተኛ ስጋት ናቸው" ሲሉ የሲዲሲዋ ዳይሬክተር ዶ/ር ሮሼል ዋለንስኪ ሰኞ ዕለት ገልጸዋል። በርካታ የኮቪድ -19 ዝርያዎች ስርጭት ቢኖርም የጤና ባለሙያዎች ለጥቂቶቹ ብቻ ትኩረት ሰጥተዋል፡፡ በዚህም መጀመሪያ በእንግሊዝ፣ በደቡብ አፍሪካ እና በብራዚል ይበልጥ ተላላፊ የሚመስሉ ዓይነቶችን ያካትታሉ፡፡ ሲዲሲ በእንግሊዝ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው በጣም ተላላፊው B.1.1.7 የተሰኘው ዝርያ በዚህ ወር በአሜሪካ ዋነኛው ስጋት እንደሚሆን ተንብይዋል፡፡ ክትባቶች መሰጠት ከጀመሩበት ጥር ወር ጀምሮ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ ዕለታዊ የሰዎች በቫይረሱ የመያዝ እና የሞት ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል፡፡ ሲዲሲ ይህን ለብዙዎች ክትባት እስከሚሰጥ ድረስ አዲሶቹ ዝርያዎች ቀድሞውኑ በችግር ላይ ያሉ የጤና ስርዓቶችን አደጋ ላይ እስከሚጥሉ ድረስ በፍጥነት ሊዛመቱ ይችላሉ ብሏል፡፡ እንደሲዲሲ መረጃ ከሆነ አሳሳቢ የሆኑ ዝርያዎችን የሚያካትቱ ከ 2 ሺህ 463 በላይ ኢንፌክሽኖች ሪፖርት ተደርገዋል፡፡ ቢያንስ 2 ሺህ400 የሚሆኑት በእንግሊዝ የተገኘው ዝርያ ዓይነት ናቸው፡፡ በአሜሪካ ውስጥ በአዳዲሶቹ ዝርያዎች የተያዙ ሰዎች እውነተኛ ቁጥር ከዚህ የበለጠ ነው ተብሎ ይገመታል፡፡ በአዳዲሶቹ ዝርያዎች የሚጠቁ ሰዎች ላይ በጣም ከባድ በሽታ ስለማምጣቱ ምንም ማስረጃ የለም፡፡ የሳይንስ ሊቃውንት በሥራ ላይ የዋሉት ክትባቶች አዳዲሶቹንም ዝርያዎች ጭምር ይከላከላሉ ብለው ያምናሉ፡፡ እስከሰኞ ድረስ አሜሪካ ከ 76 ሚሊዮን በላይ ክትባቶችን እንደሰጠች የሲዲሲ መረጃዎች ያመለክታሉ። አሜሪካ ከዓለም ሀገሮች ከፍተኛውን የክትባት መጠን ሰጥታለች፡፡ ሆኖም ቁጥሮቹ ከሕዝብ ቁጥር ለ100 ሰዎች ከተሰጠው አንጻር ሲወዳደር አሜሪካ ከእንግሊዝ፣ ከአረብ ኤሚሬቶች እና ከእስራኤል ቀጥሎ በአራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ በአሜሪካ ክትባት ከተሰጣቸው መካከል የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ እንደሚገኙበት ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡ ሁለቱም በጥር ወር ኋዋይት ሃውስ ክትባቱ እንደወሰዱ አንድ አማካሪ ለኒው ዮርክ ታይምስ እና ለሌሎች የአሜሪካ የመገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል፡፡ የትኛው ክትባት እንደወሰዱ ግልፅ ባይሆንም በጥር ወር በተቆጣጣሪዎች ፈቃድ ያገኙት የፋይዘር እና ሞደርና ክትባት ብቻ ነበር፡፡ በጆንሰን እና ጆንሰን የተሠራው እና አንድ ጊዜ ብቻ የሚሰጠው ክትባት በአሜሪካ ጥቅም ላይ እንዲውል ቅዳሜ ፈቃድ አግኝቷል፡፡ ዶ/ር ዋለንስኪ በአሜሪካ ግዛቶች ሪፖርቶች "በእውነት ተጨንቄያለሁ። ሰዎችን ከኮቪድ-19 ለመከላከል ወደምንመክረው ትክክለኛ የህዝብ ጤና አጠባበቅ እርምጃዎችን ወደ ኋላ ትመልሳለች" ብለዋል፡፡ "አራተኛ ዙር ከፍተኛ ቫይረሱ ስርጭር በዚህ እንዳይከሰት የማስቆም አቅም አለን፡፡ እባካችሁ በእምነታችን ጠንካራ እንሁን" ብለዋል፡፡ አሜሪካ ከ 28 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙባት እና ከኮቪድ -19 ጋር በተያያዘ 500,000 ሰዎችን ሞት አስመዝግባለች ይላል የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ፡፡
https://www.bbc.com/amharic/news-56249154
2health
ኮሮናቫይረስ፡ የኮሮና ክትባትን በዓለም ለማሰራጨት 8ሺህ ግዙፍ አውሮፕላኖች ያስፈልጋሉ
ይበለውና የኮሮና ክትባት ቢሳካ በነገታው እንወጋዋለን ማለት አይደለም፡፡ በመላው ዓለም ማሰራጨቱ በራሱ ሌላ ትልቅ ፈተና ነው ሲል የአቪየሽን ኢንደስትሪ ማኅበር ተናግሯል፡፡ ምናልባትም በአውሮፕላን የካርጎ ታሪክ እጅግ ከባዱ ፈተና፣ እጅግ ከባዱ ኃላፊነት ይሆናል ተብሏል፡፡ የዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር (IATA) እንደሚለው ምናልባት ክትባቱ ቢሳካ እያንዳንዳቸው የቦይንግ 747 አውሮፕላኖች አይነት ግዝፈትና ፍጥነት ያላቸው 8ሺህ ግዙፍ የካርጎ አውሮፕላኖች ያስፈልጋሉ ብሏል፤ ክትባቱን ለማዳረስ፡፡ ምንም እንኳ ለጊዜው ክትባት ባይፈበረክም፣ መሳካቱ አይቀርም በሚል የአየር ትራንስፖርት ማኅበሩ ነገሮችን ለማቀናጀት ከወዲሁ ተፍ ተፍ እያለ ነው፡፡ ማኅበሩ በጤና ዙርያ ከሚሰሩት በርካታ ድርጅቶች፣ ከዓለም ጤና ድርጅት፣ ከመድኃኒት አምራቾች፣ ከመድኃኒት አቀባባዮች፣ አከፋፋዮች፣ ከአውሮፕላን ካርጎ ሥራ ተሳታፊዎች ጋር በጥምረት መስራት ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ ይህ 8ሺህ ቦይንግ ያስፈልጋል የተባለው ታዲያ አንድ ሰው በሕይወት ዘመኑ አንድ ጊዜ ብቻ፣ አንድ ጠብታ ክትባት ብቻ ነው የሚያስፈልገው በሚል የተሰላ ሲሆን ይህ ግምት ለምሳሌ በእጥፍ ቢጨምር እጥፍ ካርጎ አውሮፕላን ያሻል ማለት ነው፡፡ የአየር ትራንስፖርት ማኅበሩ ሥራ አስፈጻሚ አሌክሳንደር ዴ ጁኒያክ እንዲህ ተናግረዋል፣ ‹‹የኮቪድ 19 ክትባትን በጥንቃቄ ማጓጓዝ የዚህ ክፍለ ዘመን ትልቁ የካርጎ ኢንዱስትሪ ግብ ነው፡፡ ነገር ግን እንዲሁ በዘፈቀደ የሚጓጓዝ አይደለም፤ ከፍተኛ ዝግጅት ይፈልጋል፡፡ ለዝግጅቱ ትክክለኛው ጊዜ ደግሞ አሁን ነው›› በርካታ አየር መንገዶች በወረርሽኙ ጊዜ የሰዎች ከቦታ ቦታ እንቅስቃሴ በመታቀቡ ወደ ካርጎ ሥራ ገብተው ቆይተዋል፡፡ በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድም ይጠቀሳል፡፡ ነገር ግን ማንም እቃ የሚያጓጉዝ አየር መንገድ ክትባትን ማጓጓዝ ይችላል ማለት አይደለም፡፡ ክትባት ለማጓጓዝ ካርጎው ከ2 እስከ 8 ሴንትግሬድ የሙቀት መጠን ሊኖረው ይገባል፡፡ አንዳንድ ክትባቶች ደግሞ እጅግ ቀዝቃዛ (ከዜሮ በታች) የሆነ የሙቀት መጠንን ሊፈልጉ ይችላሉ፡፡ ይህን ማሟላት ለብዙ አየር መንገዶች ፈተና ሊሆን ይችላል፡፡ ዝግጅት ከወዲሁ የተጀመረውም ለዚሁ ነው፡፡ ይህንን ክትባት የማጓጓዙን ፈተና ለመቀነስ አንዱ መንገድ አገራት በየራሳቸው ክትባቱን እንዲያመርቱት ማድረግ ቢሆንም ይህ ለብዙ የዓለም አገራት የሚቻል አይሆንም፡፡ በተለይ በርካታ የካርጎ በረራዎች ወደ ደቡብ ምሥራቅ ኢሲያ ይደረጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በርካታ ሕዝብ ስለሚገኝና ክትባት የማምረት አቅም ያለው አገርም ባለመኖሩ ነው፡፡ ክትባቱን በቀላሉ ወደ አፍሪካ ለማጓጓዝም የሚቻል አይደለም ብሏል ማኅበሩ፡፡ ይህም በቂ የካርጎ አቅም ስለሌለ፣ አፍሪካ ሰፊ አህጉር በመሆኗና የድንበር ውስብስብነት መኖሩ ነው፡፡ የካርጎ ሥራው ልክ ወታደራዊ ጥንቃቄን የሚፈልግ ነው፤ ከተጓጓዘ በኋላም ቢሆን የሚቀመጥበት ቦታ መድኃኒቱን ለማስቀመጥ የሚሆን መሆን አለበት፡፡ ይህ ደግሞ ለበርካታ የአፍሪካ አገሮች ፈተና ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በዓለም ደረጃ 140 ቤተ ሙከራዎች ክትባት ለመሥራት ተፍ ተፍ ማለት ጀምረው ነበር፡፡ አሁን 24 የሚሆኑት በሰዎች ላይ ሙከራ ጀምረዋል፡፡ ከነዚህ ሁሉ ትልቅ ተስፋ የተሰጠው የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲው የክትባት ሙከራ ነው፡፡. ሩሲያ ክትባቱ በእጄ ገብቷል ብትልም ዓለም በአገሪቱ ላይ እምነት በማጣቱ ይመስላል እምብዛምም የራሺያ ክትባት አይወራም፡፡ የጤና ባለሙያዎች የሩሲያ ክትባት ሳይንሳዊ ሂደትን የተከተለ አይደለም፣ ብሔራዊ ኩራተን ከጤና አስበልጧል ሲሉ ይተቹታል፡፡
ኮሮናቫይረስ፡ የኮሮና ክትባትን በዓለም ለማሰራጨት 8ሺህ ግዙፍ አውሮፕላኖች ያስፈልጋሉ ይበለውና የኮሮና ክትባት ቢሳካ በነገታው እንወጋዋለን ማለት አይደለም፡፡ በመላው ዓለም ማሰራጨቱ በራሱ ሌላ ትልቅ ፈተና ነው ሲል የአቪየሽን ኢንደስትሪ ማኅበር ተናግሯል፡፡ ምናልባትም በአውሮፕላን የካርጎ ታሪክ እጅግ ከባዱ ፈተና፣ እጅግ ከባዱ ኃላፊነት ይሆናል ተብሏል፡፡ የዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር (IATA) እንደሚለው ምናልባት ክትባቱ ቢሳካ እያንዳንዳቸው የቦይንግ 747 አውሮፕላኖች አይነት ግዝፈትና ፍጥነት ያላቸው 8ሺህ ግዙፍ የካርጎ አውሮፕላኖች ያስፈልጋሉ ብሏል፤ ክትባቱን ለማዳረስ፡፡ ምንም እንኳ ለጊዜው ክትባት ባይፈበረክም፣ መሳካቱ አይቀርም በሚል የአየር ትራንስፖርት ማኅበሩ ነገሮችን ለማቀናጀት ከወዲሁ ተፍ ተፍ እያለ ነው፡፡ ማኅበሩ በጤና ዙርያ ከሚሰሩት በርካታ ድርጅቶች፣ ከዓለም ጤና ድርጅት፣ ከመድኃኒት አምራቾች፣ ከመድኃኒት አቀባባዮች፣ አከፋፋዮች፣ ከአውሮፕላን ካርጎ ሥራ ተሳታፊዎች ጋር በጥምረት መስራት ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ ይህ 8ሺህ ቦይንግ ያስፈልጋል የተባለው ታዲያ አንድ ሰው በሕይወት ዘመኑ አንድ ጊዜ ብቻ፣ አንድ ጠብታ ክትባት ብቻ ነው የሚያስፈልገው በሚል የተሰላ ሲሆን ይህ ግምት ለምሳሌ በእጥፍ ቢጨምር እጥፍ ካርጎ አውሮፕላን ያሻል ማለት ነው፡፡ የአየር ትራንስፖርት ማኅበሩ ሥራ አስፈጻሚ አሌክሳንደር ዴ ጁኒያክ እንዲህ ተናግረዋል፣ ‹‹የኮቪድ 19 ክትባትን በጥንቃቄ ማጓጓዝ የዚህ ክፍለ ዘመን ትልቁ የካርጎ ኢንዱስትሪ ግብ ነው፡፡ ነገር ግን እንዲሁ በዘፈቀደ የሚጓጓዝ አይደለም፤ ከፍተኛ ዝግጅት ይፈልጋል፡፡ ለዝግጅቱ ትክክለኛው ጊዜ ደግሞ አሁን ነው›› በርካታ አየር መንገዶች በወረርሽኙ ጊዜ የሰዎች ከቦታ ቦታ እንቅስቃሴ በመታቀቡ ወደ ካርጎ ሥራ ገብተው ቆይተዋል፡፡ በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድም ይጠቀሳል፡፡ ነገር ግን ማንም እቃ የሚያጓጉዝ አየር መንገድ ክትባትን ማጓጓዝ ይችላል ማለት አይደለም፡፡ ክትባት ለማጓጓዝ ካርጎው ከ2 እስከ 8 ሴንትግሬድ የሙቀት መጠን ሊኖረው ይገባል፡፡ አንዳንድ ክትባቶች ደግሞ እጅግ ቀዝቃዛ (ከዜሮ በታች) የሆነ የሙቀት መጠንን ሊፈልጉ ይችላሉ፡፡ ይህን ማሟላት ለብዙ አየር መንገዶች ፈተና ሊሆን ይችላል፡፡ ዝግጅት ከወዲሁ የተጀመረውም ለዚሁ ነው፡፡ ይህንን ክትባት የማጓጓዙን ፈተና ለመቀነስ አንዱ መንገድ አገራት በየራሳቸው ክትባቱን እንዲያመርቱት ማድረግ ቢሆንም ይህ ለብዙ የዓለም አገራት የሚቻል አይሆንም፡፡ በተለይ በርካታ የካርጎ በረራዎች ወደ ደቡብ ምሥራቅ ኢሲያ ይደረጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በርካታ ሕዝብ ስለሚገኝና ክትባት የማምረት አቅም ያለው አገርም ባለመኖሩ ነው፡፡ ክትባቱን በቀላሉ ወደ አፍሪካ ለማጓጓዝም የሚቻል አይደለም ብሏል ማኅበሩ፡፡ ይህም በቂ የካርጎ አቅም ስለሌለ፣ አፍሪካ ሰፊ አህጉር በመሆኗና የድንበር ውስብስብነት መኖሩ ነው፡፡ የካርጎ ሥራው ልክ ወታደራዊ ጥንቃቄን የሚፈልግ ነው፤ ከተጓጓዘ በኋላም ቢሆን የሚቀመጥበት ቦታ መድኃኒቱን ለማስቀመጥ የሚሆን መሆን አለበት፡፡ ይህ ደግሞ ለበርካታ የአፍሪካ አገሮች ፈተና ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በዓለም ደረጃ 140 ቤተ ሙከራዎች ክትባት ለመሥራት ተፍ ተፍ ማለት ጀምረው ነበር፡፡ አሁን 24 የሚሆኑት በሰዎች ላይ ሙከራ ጀምረዋል፡፡ ከነዚህ ሁሉ ትልቅ ተስፋ የተሰጠው የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲው የክትባት ሙከራ ነው፡፡. ሩሲያ ክትባቱ በእጄ ገብቷል ብትልም ዓለም በአገሪቱ ላይ እምነት በማጣቱ ይመስላል እምብዛምም የራሺያ ክትባት አይወራም፡፡ የጤና ባለሙያዎች የሩሲያ ክትባት ሳይንሳዊ ሂደትን የተከተለ አይደለም፣ ብሔራዊ ኩራተን ከጤና አስበልጧል ሲሉ ይተቹታል፡፡
https://www.bbc.com/amharic/news-54093179
3politics
ትግራይ ፡ የቀድሞው ርዕሰ መስተዳደርና ምክትል ሚኒስትር በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ
የቀድሞው የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳደር፣ የገንዘብ ምክትል ሚኒስትርና ምክትል ርዕሰ መስተዳደርን ጨምሮ በርካታ የህወሓት ፖለቲካዊና ወታደራዊ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸው እንዲሁም መገደላቸውን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ። የሠራዊቱ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት ብርጋዲየር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው እንደገለጹት በጸጥታ አካላት ከተያዙት ውስጥ ሰባት የህወሓት ፖለቲካዊ አመራሮች እንዲሁም "ከአገር መከላከያ ሠራዊት ከድተው ቡድኑን የተቀላቀሉ" ወታደራዊ መኮንኖች እንደሚገኙበት አመልክተዋል። የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት አቶ አባይ ወልዱ እና ቀደም ሲል የፌደራል የገንዘብ ምክትል ሚኒስትር በኋላ ደግሞ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር የነበሩት አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር) ከተያዙት የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች መካከል ይገኙበታል። በተጨማሪም ብርጋዲየር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ከአገር መከላከያ ሠራዊት ከድተው ከህወሓት ጋር ተሰልፈው ነበር ያሏቸው ጄኔራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ መኮንኖች፣ መስመራዊ መኮንኖች እንዲሁም የግል ጥበቃዎቻቸው ላይ እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል። መገደላቸው ከተነገረው ከፍተኛ መኮንኖች መካከል የቀደሞው የአገር መከላከያ የሎጂስቲክስ ኃላፊ ሜጀር ጄኔራል ኢብራሂም አብዱልጀሊል እና የመከላከያ ሠራዊት የኢንዶክትሪኔሽን የቀድሞ ኃላፊ የነበሩት ብርጋዲየር ጄኔራል ገብረኪዳን ገብረማርያም እንደሚገኙበት ተጠቅሷል። በክልሉ የተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ከነበሩ ውስጥም የትግራይ ኦዲተር ቢሮ ኃላፊ ረዳኢ በርሄ (ዶ/ር)፣ የክልሉ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ኃላፊ ሙሉጌታ ይርጋ (ዶ/ር)፣የኃይማኖት ጉዳይ ክትትል ኃላፊ አቶ ዕቁባይ በርሄ፣ የክልሉ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤትና የሠላምና ደኅንነት ኃሃላፊ አቶ ጌታቸው ተፈሪ እንዲሁም የክልሉ ማኅበራዊ ጉዳይ ኃላፊ ወ/ሮ ኪሮስ ሐጎስ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተገልጿል። የመከላከያ ሠራዊቱ የስምሪት መምሪያ ኃላፊው ብርጋዲየር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ጨምረው እንደተናገሩት እርምጃ እንደተወሰደባቸው ከተገለጹት ሁለት ጄነራል መኮንኖች በተጨማሪ ከፍተኛ መኮንኖች፣ መስመራዊ መኮንኖችና የግል ጥበቃዎቻቸው እንዲሁም አንድ የክልሉ ረዳት ኮሚሽነር የነበረና ከፖሊስ የከዳ ግለሰብ መገደላቸውን አመልክተዋል። በተጨማሪም ከመከላከያ ሠራዊት ከድተው ከህወሓት ጋር ተቀላቅለው ነበር ያሏቸው ኮሎኔል ገብረእግዚአብሔር አምባዬና ኮሎኔል ትርፏ አሰፋ የተባሉ ሁለት ከፍተኛ መኮንኖች በቁጥጥር ስር የዋሉ መሆናቸውን ገልጸዋል። እየተፈለጉ ያሉትን የህወሓት ፖለቲካዊና ወታደራዊ አመራሮችን ለመያዝ የአገር መከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስና የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት በጥምረት አሰሳና ፍተሻ እያደረጉ መሆናቸውን ብርጋዲየር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው አመልክተዋል። ቀደም ሲል የተያዙ ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ በቁጥጥር ስር የዋሉት የቀድሞ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ወደ አዲስ አበባ መወሰዳቸውን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ከእነዚህም መካከል በሰማኒያዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙትና የህወሓት መስራች የሆኑት አቶ ስብሐት ነጋ የሚገኙበት ሲሆን አብረዋቸውም ሌሎች በክልሉና በቡድኑ ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ የነበሩ ግለሰቦች ይገኙበታል። ከዚህ በፊትም በተመሳሳይ የጸጥታ ኃይሉ ባደረገው አሰሳ የተገደሉና በቁጥጥር ስር የዋሉ የህወሓት ወታደራዊ መኮንኖችና ሲቪል አመራሮች የስም ዝርዝር ይፋ መደረጉ ይታወሳል። የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ታኅሳስ 23 ቀን 2013 ዓ. ም. በሰጠው መግለጫ፤ የቀድሞ የትራንስፖርት ሚኒስትር ደኤታ ወ/ሮ ሙሉ ገብረእግዚአብሔርና በርካታ ወታደራዊ መኮንኖች መማረካቸውን እንዲሁም በርካቶች መደምሰሳቸውን አስታወቆ ነበር። እስካሁን መገደላቸው እንዲሁም መያዛቸው ከተገለፁ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ሌላ የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንትና በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት አዲስዓለም ባሌማንና የቀድሞዋን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ ኬርያ ኢብራሂም ጨምሮ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙ የተለያዩ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የቀድሞ ባለሥልጣናት ይገኛሉ። እየተፈለጉ ያሉ አመራሮች እስካሁን ድረስ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር የነበሩት ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤልም ሆኑ ሌሎች ከፍተኛ ሹማምንቶች ያሉበት ሁኔታ በዚህ መግለጫ ላይ አልተጠቀሰም። ከጥቂት ሳምንት በፊት የመከላከያ ሠራዊቱ ከፍተኛ የህወሓት አመራሮች ያሉበትን ለጠቆመ የ10 ሚሊዮን ብር ሽልማት ማዘጋጀቱን መግለጹ ይታወሳል። መንግሥት በቁጥጥር ስር ውለዋል ወይም ተገድለዋል ያላቸውን የህወሓት ወታደራዊ መኮንኖችና ሲቪል አመራሮችን በተመለከተ ከቡድኑም ሆነ ከሌላ ገለልተኛ ወገን የተሰማ ነገር የለም። የክልሉ ዋና ከተማ መቀለ በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ቁጥጥር ስር ስትገባ የህወሓት አመራሮች ውጊያውን እንደሚቀጥሉ ከገለጹ በኋላ ስላሉበት ሁኔታና ወቅታዊ ጉዳዮች በይፋ የሰጡት መግለጫ የለም። ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ምሽት የህወሓት ኃይሎች በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን ተከትሎ በትግራይ ክልል ወታደራዊ ግጭት ተቀስቅሶ ክልሉን ይመራ የነበረው ህወሓት ከሥልጣን መወገዱ ይታወሳል። በትግራይ ክልል ከተከሰተው ቀውስ ጋር በተያያዘ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና የፌደራል ፖሊስ በበርካታ የህወሓት ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራሮች ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣታቸው ይፋ አድርገው ነበር። ለእስር ማዘዣውም ዋነኛ ምክንያቶቹ ህወሓትን በበላይነት በመምራት፣ በትግራይ ክልል በሚገኘው በአገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመፈፀም፣ የአገር ክህደት ወንጀል ፈጽመዋል፣ የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ አባላት እንዲታገቱ አድርገዋል በሚል ተጠርጥረው ነው። በተጨማሪም የቀድሞው የአገሪቱ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም የነበሩት ሜጀር ጄኔራል ጻድቃን ገብረተንሳይን ጨምሮ፣ ከፍተኛ የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ኃይል፣ የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ አመራሮችም በአገር ክደትና በሠራዊት አባላት ላይ በተፈጸመ ወንጀል ተጠርጥረው የመያዣ ትዕዛዝ ወጥቶባቸዋል።
ትግራይ ፡ የቀድሞው ርዕሰ መስተዳደርና ምክትል ሚኒስትር በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ የቀድሞው የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳደር፣ የገንዘብ ምክትል ሚኒስትርና ምክትል ርዕሰ መስተዳደርን ጨምሮ በርካታ የህወሓት ፖለቲካዊና ወታደራዊ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸው እንዲሁም መገደላቸውን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ። የሠራዊቱ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት ብርጋዲየር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው እንደገለጹት በጸጥታ አካላት ከተያዙት ውስጥ ሰባት የህወሓት ፖለቲካዊ አመራሮች እንዲሁም "ከአገር መከላከያ ሠራዊት ከድተው ቡድኑን የተቀላቀሉ" ወታደራዊ መኮንኖች እንደሚገኙበት አመልክተዋል። የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት አቶ አባይ ወልዱ እና ቀደም ሲል የፌደራል የገንዘብ ምክትል ሚኒስትር በኋላ ደግሞ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር የነበሩት አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር) ከተያዙት የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች መካከል ይገኙበታል። በተጨማሪም ብርጋዲየር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ከአገር መከላከያ ሠራዊት ከድተው ከህወሓት ጋር ተሰልፈው ነበር ያሏቸው ጄኔራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ መኮንኖች፣ መስመራዊ መኮንኖች እንዲሁም የግል ጥበቃዎቻቸው ላይ እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል። መገደላቸው ከተነገረው ከፍተኛ መኮንኖች መካከል የቀደሞው የአገር መከላከያ የሎጂስቲክስ ኃላፊ ሜጀር ጄኔራል ኢብራሂም አብዱልጀሊል እና የመከላከያ ሠራዊት የኢንዶክትሪኔሽን የቀድሞ ኃላፊ የነበሩት ብርጋዲየር ጄኔራል ገብረኪዳን ገብረማርያም እንደሚገኙበት ተጠቅሷል። በክልሉ የተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ከነበሩ ውስጥም የትግራይ ኦዲተር ቢሮ ኃላፊ ረዳኢ በርሄ (ዶ/ር)፣ የክልሉ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ኃላፊ ሙሉጌታ ይርጋ (ዶ/ር)፣የኃይማኖት ጉዳይ ክትትል ኃላፊ አቶ ዕቁባይ በርሄ፣ የክልሉ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤትና የሠላምና ደኅንነት ኃሃላፊ አቶ ጌታቸው ተፈሪ እንዲሁም የክልሉ ማኅበራዊ ጉዳይ ኃላፊ ወ/ሮ ኪሮስ ሐጎስ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተገልጿል። የመከላከያ ሠራዊቱ የስምሪት መምሪያ ኃላፊው ብርጋዲየር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ጨምረው እንደተናገሩት እርምጃ እንደተወሰደባቸው ከተገለጹት ሁለት ጄነራል መኮንኖች በተጨማሪ ከፍተኛ መኮንኖች፣ መስመራዊ መኮንኖችና የግል ጥበቃዎቻቸው እንዲሁም አንድ የክልሉ ረዳት ኮሚሽነር የነበረና ከፖሊስ የከዳ ግለሰብ መገደላቸውን አመልክተዋል። በተጨማሪም ከመከላከያ ሠራዊት ከድተው ከህወሓት ጋር ተቀላቅለው ነበር ያሏቸው ኮሎኔል ገብረእግዚአብሔር አምባዬና ኮሎኔል ትርፏ አሰፋ የተባሉ ሁለት ከፍተኛ መኮንኖች በቁጥጥር ስር የዋሉ መሆናቸውን ገልጸዋል። እየተፈለጉ ያሉትን የህወሓት ፖለቲካዊና ወታደራዊ አመራሮችን ለመያዝ የአገር መከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስና የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት በጥምረት አሰሳና ፍተሻ እያደረጉ መሆናቸውን ብርጋዲየር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው አመልክተዋል። ቀደም ሲል የተያዙ ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ በቁጥጥር ስር የዋሉት የቀድሞ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ወደ አዲስ አበባ መወሰዳቸውን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ከእነዚህም መካከል በሰማኒያዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙትና የህወሓት መስራች የሆኑት አቶ ስብሐት ነጋ የሚገኙበት ሲሆን አብረዋቸውም ሌሎች በክልሉና በቡድኑ ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ የነበሩ ግለሰቦች ይገኙበታል። ከዚህ በፊትም በተመሳሳይ የጸጥታ ኃይሉ ባደረገው አሰሳ የተገደሉና በቁጥጥር ስር የዋሉ የህወሓት ወታደራዊ መኮንኖችና ሲቪል አመራሮች የስም ዝርዝር ይፋ መደረጉ ይታወሳል። የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ታኅሳስ 23 ቀን 2013 ዓ. ም. በሰጠው መግለጫ፤ የቀድሞ የትራንስፖርት ሚኒስትር ደኤታ ወ/ሮ ሙሉ ገብረእግዚአብሔርና በርካታ ወታደራዊ መኮንኖች መማረካቸውን እንዲሁም በርካቶች መደምሰሳቸውን አስታወቆ ነበር። እስካሁን መገደላቸው እንዲሁም መያዛቸው ከተገለፁ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ሌላ የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንትና በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት አዲስዓለም ባሌማንና የቀድሞዋን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ ኬርያ ኢብራሂም ጨምሮ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙ የተለያዩ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የቀድሞ ባለሥልጣናት ይገኛሉ። እየተፈለጉ ያሉ አመራሮች እስካሁን ድረስ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር የነበሩት ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤልም ሆኑ ሌሎች ከፍተኛ ሹማምንቶች ያሉበት ሁኔታ በዚህ መግለጫ ላይ አልተጠቀሰም። ከጥቂት ሳምንት በፊት የመከላከያ ሠራዊቱ ከፍተኛ የህወሓት አመራሮች ያሉበትን ለጠቆመ የ10 ሚሊዮን ብር ሽልማት ማዘጋጀቱን መግለጹ ይታወሳል። መንግሥት በቁጥጥር ስር ውለዋል ወይም ተገድለዋል ያላቸውን የህወሓት ወታደራዊ መኮንኖችና ሲቪል አመራሮችን በተመለከተ ከቡድኑም ሆነ ከሌላ ገለልተኛ ወገን የተሰማ ነገር የለም። የክልሉ ዋና ከተማ መቀለ በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ቁጥጥር ስር ስትገባ የህወሓት አመራሮች ውጊያውን እንደሚቀጥሉ ከገለጹ በኋላ ስላሉበት ሁኔታና ወቅታዊ ጉዳዮች በይፋ የሰጡት መግለጫ የለም። ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ምሽት የህወሓት ኃይሎች በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን ተከትሎ በትግራይ ክልል ወታደራዊ ግጭት ተቀስቅሶ ክልሉን ይመራ የነበረው ህወሓት ከሥልጣን መወገዱ ይታወሳል። በትግራይ ክልል ከተከሰተው ቀውስ ጋር በተያያዘ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና የፌደራል ፖሊስ በበርካታ የህወሓት ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራሮች ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣታቸው ይፋ አድርገው ነበር። ለእስር ማዘዣውም ዋነኛ ምክንያቶቹ ህወሓትን በበላይነት በመምራት፣ በትግራይ ክልል በሚገኘው በአገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመፈፀም፣ የአገር ክህደት ወንጀል ፈጽመዋል፣ የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ አባላት እንዲታገቱ አድርገዋል በሚል ተጠርጥረው ነው። በተጨማሪም የቀድሞው የአገሪቱ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም የነበሩት ሜጀር ጄኔራል ጻድቃን ገብረተንሳይን ጨምሮ፣ ከፍተኛ የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ኃይል፣ የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ አመራሮችም በአገር ክደትና በሠራዊት አባላት ላይ በተፈጸመ ወንጀል ተጠርጥረው የመያዣ ትዕዛዝ ወጥቶባቸዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-55610109
5sports
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ማስተናገድ የሚያስችል የተሟላ ስታዲየም የላትም ተባለ
የአፍሪካ እግር ኳስ ማኅበር (ካፍ) የባሕር ዳር ስታዲየም ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እንዳያስተናግድ ማገዱን ተከትሎ አገሪቱ መሰል ውድድሮችን ማስተናገድ እንደማትችል ተረጋግጧል። የብሔራዊ ቡድን ውድድሮችን ላለፉት ዓመታት ሲያስተናግድ የቆየው የባሕር ዳር ስታዲየም የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ እና የአፍሪካ የክለብ ሻምፒዮና ውድድሮች እንዳይካሄድበት ማገዱን ካፍ አስታውቋ። ካፍ ይህን ውሳኔውን ያስታወቀው ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በላከው ደብዳቤ ነው። የባሕር ዳር ስታዲየም የካፍ የስታዲየሞች መመዘኛ መስፈርቶችን ሙሉ በሙሉ ባለማሟላቱ በገደብ ውድድሮችን ሲያስተናግድ መቆየቱ ይታወሳል። ካፍ ከሳምንታት በኋላ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከጋና ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ በየትኛው አገር እና ስታዲየም ለመጫወት እንደምትመርጥ ኢትዮጵያ ከጥቅምት 10 በፊት በአስቸኳይ እንድታሳውቅ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ይህ ማድረግ ካልተቻለ ካፍ ጨዋታውን ወደ ተጋጣሚዋ አገር ጋና እንደሚወስድ አሳውቋል። የባሕር ዳር ስታዲየም የጨዋታ ሜዳው እና ለጨዋታ ሜዳው አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ባለሟሟላቱ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የቡድኖች እና የጨዋታ አመራሮች ማረፊያ ክፍሎች ስለሌሉ እንዲሁም የህክምና ክፍሉ የተሟላ ባለመሆኑ ውድድር እንዳይካሄድበት የታዘዘው። በተጨማሪም የተመልካቾች መሠረተ ልማት ባለመሟላታቸው፣ የክብር እንግዶች መቀመጫ እና የመስተንግዶ አካባቢ በበቂ ደረጃ ባለመዘጋጀቱ፣ በስታዲየሙ ደረጃውን የጠበቀ የመገናኛ ብዙኃን ማዕከል አለመኖር እና የልምምድ ሜዳው ዝቅተኛ ደረጃ በመያዙ ለመታገድ በቅቷል። የካፍ የክለብ ላይሰንሲንግ ኃላፊ መሐመድ ሲዳት በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ አቅንተው የተለያዩ ስታዲየሞችን ገምግመዋል ተብሏል። ኃላፊው በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ከባሕር ዳር ስታዲየም በተጨማሪ የአበበ ቢቂላ እና የጅማ ዩንቨርሲቲ ስታዲየሞችን ተመልክተዋል። የጅማ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በርካታ ማሟላት ያለባቸው ነገሮች እንዳሉት ገልጸው ስታዲየሙ የተጓደሉትን ነገሮች ካሟላ ወደፊት የገምጋሚ ቡድን እንደሚልኩ አስታውቀዋል። ስታዲየሙ አሁን ባለው ሁኔታ ምንም አይነት ዓለም አቀፍ ውድድር ማስተናገድ እንደማይችል አሳውቀዋል። የአበበ ቢቂላ ስታዲየም በታዳጊ ደረጃ የሚዘጋጁ ውድድሮችን እና የሴት የብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎችን በጊዜያዊነት ማስተናገድ እንደሚችል ገልጸዋል። የሐዋሳ ዩንቨርሲቲ ስታዲየምን በተመለከተ መጫወቻ ሳሩ ደረጃውን ያልጠበቀ፣ ሜዳው አጠገብ ያለው መሮጫም መስተካከል እንዳለበት የገለጹ ሲሆን መልበሻ ክፍሎቹ በአዲስ መልክ ሊሻሻሉ እንደሚገባቸው አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ማስተናገድ የሚያስችል የተሟላ ስታዲየም የላትም ተባለ የአፍሪካ እግር ኳስ ማኅበር (ካፍ) የባሕር ዳር ስታዲየም ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እንዳያስተናግድ ማገዱን ተከትሎ አገሪቱ መሰል ውድድሮችን ማስተናገድ እንደማትችል ተረጋግጧል። የብሔራዊ ቡድን ውድድሮችን ላለፉት ዓመታት ሲያስተናግድ የቆየው የባሕር ዳር ስታዲየም የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ እና የአፍሪካ የክለብ ሻምፒዮና ውድድሮች እንዳይካሄድበት ማገዱን ካፍ አስታውቋ። ካፍ ይህን ውሳኔውን ያስታወቀው ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በላከው ደብዳቤ ነው። የባሕር ዳር ስታዲየም የካፍ የስታዲየሞች መመዘኛ መስፈርቶችን ሙሉ በሙሉ ባለማሟላቱ በገደብ ውድድሮችን ሲያስተናግድ መቆየቱ ይታወሳል። ካፍ ከሳምንታት በኋላ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከጋና ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ በየትኛው አገር እና ስታዲየም ለመጫወት እንደምትመርጥ ኢትዮጵያ ከጥቅምት 10 በፊት በአስቸኳይ እንድታሳውቅ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ይህ ማድረግ ካልተቻለ ካፍ ጨዋታውን ወደ ተጋጣሚዋ አገር ጋና እንደሚወስድ አሳውቋል። የባሕር ዳር ስታዲየም የጨዋታ ሜዳው እና ለጨዋታ ሜዳው አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ባለሟሟላቱ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የቡድኖች እና የጨዋታ አመራሮች ማረፊያ ክፍሎች ስለሌሉ እንዲሁም የህክምና ክፍሉ የተሟላ ባለመሆኑ ውድድር እንዳይካሄድበት የታዘዘው። በተጨማሪም የተመልካቾች መሠረተ ልማት ባለመሟላታቸው፣ የክብር እንግዶች መቀመጫ እና የመስተንግዶ አካባቢ በበቂ ደረጃ ባለመዘጋጀቱ፣ በስታዲየሙ ደረጃውን የጠበቀ የመገናኛ ብዙኃን ማዕከል አለመኖር እና የልምምድ ሜዳው ዝቅተኛ ደረጃ በመያዙ ለመታገድ በቅቷል። የካፍ የክለብ ላይሰንሲንግ ኃላፊ መሐመድ ሲዳት በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ አቅንተው የተለያዩ ስታዲየሞችን ገምግመዋል ተብሏል። ኃላፊው በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ከባሕር ዳር ስታዲየም በተጨማሪ የአበበ ቢቂላ እና የጅማ ዩንቨርሲቲ ስታዲየሞችን ተመልክተዋል። የጅማ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በርካታ ማሟላት ያለባቸው ነገሮች እንዳሉት ገልጸው ስታዲየሙ የተጓደሉትን ነገሮች ካሟላ ወደፊት የገምጋሚ ቡድን እንደሚልኩ አስታውቀዋል። ስታዲየሙ አሁን ባለው ሁኔታ ምንም አይነት ዓለም አቀፍ ውድድር ማስተናገድ እንደማይችል አሳውቀዋል። የአበበ ቢቂላ ስታዲየም በታዳጊ ደረጃ የሚዘጋጁ ውድድሮችን እና የሴት የብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎችን በጊዜያዊነት ማስተናገድ እንደሚችል ገልጸዋል። የሐዋሳ ዩንቨርሲቲ ስታዲየምን በተመለከተ መጫወቻ ሳሩ ደረጃውን ያልጠበቀ፣ ሜዳው አጠገብ ያለው መሮጫም መስተካከል እንዳለበት የገለጹ ሲሆን መልበሻ ክፍሎቹ በአዲስ መልክ ሊሻሻሉ እንደሚገባቸው አስታውቀዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-58964342
3politics
በርካታ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በሚኖሩባት የቨርጂኒያ ምርጫ የሪፐብሊካን ዕጩ እየመሩ ነው
በርካታ ትቅልደ ኢትዮጵያውያን በሚኖሩባት የአሜሪካዋ ቨርጂኒያ ግዛት እየተካሄደ ባለው የግዛቲቱ አስተዳዳሪ ምርጫ የሪፐብሊካኑ ዕጩ ግሌን ዮንከን ተቀናቃኛቸውን እየመሩ መሆኑ ተነገረ። አንዳንድ የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ከአሁኑ ግሌን ዮንከን ማሸነፋቸውን ይፋ ማድረግ ጀምረዋል። ከጥቂት ሰዓታት በፊት በነበረ ውጤት ግሌን ዮንከን በ2.7 ነጥብ የዲሞክራቱን ዕጩ ቴሪ መካሌፍ ቀድመዋቸዋል። እስከ አሁን 95 ከመቶ የሚሆው ድምጽ ተቆጥሯል። የዲሞክራቱ ዕጩ ሚስተር መካሌፍ በፈረንጆች 2014 እስከ 2018 ድረስ ለአራት ዓመታት የግዛቷ ገዢ ሆነው ያገለገሉ ናቸው። ይህ ምርጫ ጆ ባይደን ፕሬዝዳንትነት ከተመረጡ በኋላ ዲሞክራቶች በሕዝብ ዘንድ ያላቸው ተቀባይነት መለኪያ ተደርጎ ተወስዷል። በዚህ ግዛት ዲሞክራቶች ከተሸነፉ የጆ ባይደን ቅቡልነት ማጣት አንድ ማሳያ እንደሆነ ተንታኞች ይናገራሉ። ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ጆ ባይደን ቨርጂኒያን በ10 ነጥብ የበላይነት ማሸነፋቸው አይዘነጋም። አሁን የገዥነት ምርጫውን እየመሩ የሚገኙት ግሌን ዮንከን ባደረጉት የድል ንግግር "ይህ ወሳኝ ድል ነው" ብለዋል። የዲሞክራቱ ዕጩ ቴሪ በበኩላቸው ሽንፈቱን ገና ያልተቀበሉ ሲሆን ለደጋፊዎቻቸው "ጊዜው ገና ነው" እያሉ ነው። ከቨርጂኒያ ሌላ በኒው ጀርሲም በዲሞክቶችና በሪፐብሊካን መካከል ጥብቅ ፉክክር እየተደረገ ነው። ጆ ባይደን ወደ ዋይት ሐውስ ከገቡ ወዲህ የዋጋ ግሽበት መባባስ፣ የተቀዛቀዘው የምጣኔ ሀብት ቶሎ አለማንሰራራት እና ዝርክርክ የተባለው የአሜሪካ ከአፍጋኒስታን የወጣችበት መንገድ በሕዝብ ዘንድ ለዲሞክራቶች የነበረው ተስፋና እምነትን ሸርሽሯል እየተባለ ነው። በርካታ ትውልድ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን በሚገኙባት ቨርጂኒያ አሸናፊው ማን እንደሆነ በይፋ ማምሻውን ይለይለታል ቢባልም ፎክስ ኒውስን ጨምሮ በርካታ የአሜሪካ ሚዲያዎች አሸናፈው የሪፐብሊካኑ ግሌን ዮንከን መሆናቸውን ይፋ አድርገዋል።
በርካታ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በሚኖሩባት የቨርጂኒያ ምርጫ የሪፐብሊካን ዕጩ እየመሩ ነው በርካታ ትቅልደ ኢትዮጵያውያን በሚኖሩባት የአሜሪካዋ ቨርጂኒያ ግዛት እየተካሄደ ባለው የግዛቲቱ አስተዳዳሪ ምርጫ የሪፐብሊካኑ ዕጩ ግሌን ዮንከን ተቀናቃኛቸውን እየመሩ መሆኑ ተነገረ። አንዳንድ የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ከአሁኑ ግሌን ዮንከን ማሸነፋቸውን ይፋ ማድረግ ጀምረዋል። ከጥቂት ሰዓታት በፊት በነበረ ውጤት ግሌን ዮንከን በ2.7 ነጥብ የዲሞክራቱን ዕጩ ቴሪ መካሌፍ ቀድመዋቸዋል። እስከ አሁን 95 ከመቶ የሚሆው ድምጽ ተቆጥሯል። የዲሞክራቱ ዕጩ ሚስተር መካሌፍ በፈረንጆች 2014 እስከ 2018 ድረስ ለአራት ዓመታት የግዛቷ ገዢ ሆነው ያገለገሉ ናቸው። ይህ ምርጫ ጆ ባይደን ፕሬዝዳንትነት ከተመረጡ በኋላ ዲሞክራቶች በሕዝብ ዘንድ ያላቸው ተቀባይነት መለኪያ ተደርጎ ተወስዷል። በዚህ ግዛት ዲሞክራቶች ከተሸነፉ የጆ ባይደን ቅቡልነት ማጣት አንድ ማሳያ እንደሆነ ተንታኞች ይናገራሉ። ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ጆ ባይደን ቨርጂኒያን በ10 ነጥብ የበላይነት ማሸነፋቸው አይዘነጋም። አሁን የገዥነት ምርጫውን እየመሩ የሚገኙት ግሌን ዮንከን ባደረጉት የድል ንግግር "ይህ ወሳኝ ድል ነው" ብለዋል። የዲሞክራቱ ዕጩ ቴሪ በበኩላቸው ሽንፈቱን ገና ያልተቀበሉ ሲሆን ለደጋፊዎቻቸው "ጊዜው ገና ነው" እያሉ ነው። ከቨርጂኒያ ሌላ በኒው ጀርሲም በዲሞክቶችና በሪፐብሊካን መካከል ጥብቅ ፉክክር እየተደረገ ነው። ጆ ባይደን ወደ ዋይት ሐውስ ከገቡ ወዲህ የዋጋ ግሽበት መባባስ፣ የተቀዛቀዘው የምጣኔ ሀብት ቶሎ አለማንሰራራት እና ዝርክርክ የተባለው የአሜሪካ ከአፍጋኒስታን የወጣችበት መንገድ በሕዝብ ዘንድ ለዲሞክራቶች የነበረው ተስፋና እምነትን ሸርሽሯል እየተባለ ነው። በርካታ ትውልድ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን በሚገኙባት ቨርጂኒያ አሸናፊው ማን እንደሆነ በይፋ ማምሻውን ይለይለታል ቢባልም ፎክስ ኒውስን ጨምሮ በርካታ የአሜሪካ ሚዲያዎች አሸናፈው የሪፐብሊካኑ ግሌን ዮንከን መሆናቸውን ይፋ አድርገዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59145177
0business
አሜሪካ ከቻይና የተወሰኑ ምርቶች እንዳይገቡ ልታግድ ነው
አሜሪካ ከቻይና ግዛት ዢንጂያንግ የሚገቡ የተወሰኑ ምርቶች ወደ አገሯ እንዳይገቡ ልታግድ መሆኑ ተገለፀ። ለአሜሪካ ይህን ውሳኔ ያስተላለፈችው ምርቶቹ ሰዎች ያለፈቃዳቸው ጉልበታቸውን በመጠቀም የተመረቱ ናቸው የሚል ነው። ምርቶቹን እንዳይገቡ የማድረግ እቅዱ የጥጥ እና ቲማቲም ምርቶችን የሚያካትት ሲሆን፤ እነዚህ ምርቶች ቻይና ወደ አሜሪካ የምትልካቸው ሁለት ዋነኛ ምርቶች ናቸው። የትራምፕ አስተዳደር የዢንጂያንግ የኡገር ሙስሊሞችን አያያዝ ተከትሎ በቻይና ላይ ጫና እያሳደረ ነው። በቅርብ ዓመታትም ቻይና ገንጣዮችና ሽብርትኝነትን እንደ ችግር በመጥቀስም በዢንጂያንግ ያላትን የፀጥታ አካላት ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምራለች። በአንዳንዶች ግምት እስከ ሚሊየን የሚደርሱ ግለሰቦች በቀላል ጥፋቶች ያለ ምንም ክስ በካምፖች ውስጥ ታጉረው ይገኛሉ። ቻይና በበኩሏ ትምህርት የሚሰጥባቸው ካምፖች ናቸው እንጂ እስር ቤቶች አይደሉም ብላለች። የአሜሪካ ጉምሩክና የድንበር ጥበቃ አሁን ላይ በግዳጅ የጉልበት ሥራ የሚመረቱ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ ምርቶች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ ለማገድ የሚያስችል ሕግ እያዘጋጀ ነው። ሕጉ ሕገ-ወጥ የሰዎችን ዝውውርን፣ የህፃናት የጉልበት ብዝበዛን እና የሰብዓዊ መብት ጥሰትን ለመከላከል ያለመ ነው ተብሏል። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ የአሜሪካ ሕግ አውጪዎች በዢንጂያንግ በግዳጅ የጉልበት ሥራ የሚመረቱ ሁሉንም ምርቶች ከግምት በማስገባት፤ በተገቢው መልኩ የተመረቱ መሆናቸውን የሚያሳይ ማረጋገጫ መጠየቅ የሚያስችል ሕግ አርቅቀው ነበር። የጉምሩክና የድንበር ጥበቃ ኮሚሽነር ብሬንዳ ስሚዝ "ከዢንጂያንግ ከሚመጡ የጥጥ እና ቲማቲም ጋር በተያያዘ በምርት አቅርቦት ሂደት የግዳጅ ጉልበት የመጠቀም አጋጣሚዎች እንደሚኖሩ ድምዳሜ ላይ የሚያደርስ ማስረጃ ባይኖረንም፤ ምክንያት ግን አለን " ሲሉ ለሮይተርስ ተናግረዋል። እነዚህን ክፍተቶች ለመሙላትም ምርመራችንን እንቀጥላለን ብለዋል ኮሚሽነሯ። ረቂቅ ሕጉ በአሜሪካ ነጋዴዎች፣ ልብስ አምራቾች እና የምግብ አቅራቢዎች ላይ ተፅዕኖ ሊኖረው ይችላል ተብሏል። ቻይና የዓለማችንን 20 በመቶ ጥጥ ፍላጎት አቅራቢ ስትሆን አብዛኛው የሚመጣው ከዢንጂያንግ ግዛት ነው። ግዛቷ የቻይና ፋብሪካዎች ግብዓት የሆኑ የፔትሮሊየም ኬሚካል እና ሌሎች ጥሬ እቃዎች ምንጭም ናት።
አሜሪካ ከቻይና የተወሰኑ ምርቶች እንዳይገቡ ልታግድ ነው አሜሪካ ከቻይና ግዛት ዢንጂያንግ የሚገቡ የተወሰኑ ምርቶች ወደ አገሯ እንዳይገቡ ልታግድ መሆኑ ተገለፀ። ለአሜሪካ ይህን ውሳኔ ያስተላለፈችው ምርቶቹ ሰዎች ያለፈቃዳቸው ጉልበታቸውን በመጠቀም የተመረቱ ናቸው የሚል ነው። ምርቶቹን እንዳይገቡ የማድረግ እቅዱ የጥጥ እና ቲማቲም ምርቶችን የሚያካትት ሲሆን፤ እነዚህ ምርቶች ቻይና ወደ አሜሪካ የምትልካቸው ሁለት ዋነኛ ምርቶች ናቸው። የትራምፕ አስተዳደር የዢንጂያንግ የኡገር ሙስሊሞችን አያያዝ ተከትሎ በቻይና ላይ ጫና እያሳደረ ነው። በቅርብ ዓመታትም ቻይና ገንጣዮችና ሽብርትኝነትን እንደ ችግር በመጥቀስም በዢንጂያንግ ያላትን የፀጥታ አካላት ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምራለች። በአንዳንዶች ግምት እስከ ሚሊየን የሚደርሱ ግለሰቦች በቀላል ጥፋቶች ያለ ምንም ክስ በካምፖች ውስጥ ታጉረው ይገኛሉ። ቻይና በበኩሏ ትምህርት የሚሰጥባቸው ካምፖች ናቸው እንጂ እስር ቤቶች አይደሉም ብላለች። የአሜሪካ ጉምሩክና የድንበር ጥበቃ አሁን ላይ በግዳጅ የጉልበት ሥራ የሚመረቱ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ ምርቶች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ ለማገድ የሚያስችል ሕግ እያዘጋጀ ነው። ሕጉ ሕገ-ወጥ የሰዎችን ዝውውርን፣ የህፃናት የጉልበት ብዝበዛን እና የሰብዓዊ መብት ጥሰትን ለመከላከል ያለመ ነው ተብሏል። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ የአሜሪካ ሕግ አውጪዎች በዢንጂያንግ በግዳጅ የጉልበት ሥራ የሚመረቱ ሁሉንም ምርቶች ከግምት በማስገባት፤ በተገቢው መልኩ የተመረቱ መሆናቸውን የሚያሳይ ማረጋገጫ መጠየቅ የሚያስችል ሕግ አርቅቀው ነበር። የጉምሩክና የድንበር ጥበቃ ኮሚሽነር ብሬንዳ ስሚዝ "ከዢንጂያንግ ከሚመጡ የጥጥ እና ቲማቲም ጋር በተያያዘ በምርት አቅርቦት ሂደት የግዳጅ ጉልበት የመጠቀም አጋጣሚዎች እንደሚኖሩ ድምዳሜ ላይ የሚያደርስ ማስረጃ ባይኖረንም፤ ምክንያት ግን አለን " ሲሉ ለሮይተርስ ተናግረዋል። እነዚህን ክፍተቶች ለመሙላትም ምርመራችንን እንቀጥላለን ብለዋል ኮሚሽነሯ። ረቂቅ ሕጉ በአሜሪካ ነጋዴዎች፣ ልብስ አምራቾች እና የምግብ አቅራቢዎች ላይ ተፅዕኖ ሊኖረው ይችላል ተብሏል። ቻይና የዓለማችንን 20 በመቶ ጥጥ ፍላጎት አቅራቢ ስትሆን አብዛኛው የሚመጣው ከዢንጂያንግ ግዛት ነው። ግዛቷ የቻይና ፋብሪካዎች ግብዓት የሆኑ የፔትሮሊየም ኬሚካል እና ሌሎች ጥሬ እቃዎች ምንጭም ናት።
https://www.bbc.com/amharic/54078493
5sports
ከፍተኛ ገንዘብ የተከፈለባቸው አፍሪካዊያን ተጫዋቾች እነማን ናቸው?
በከፍተኛ የዝውውር ክፍያ ለአርሰናል የፈረመው የፊት መስመር ተጫዋቹ ኒኮላስ ፔፔ ውድ ዋጋ የወጣበት አፍሪካዊ የእግር ኳስ ተጫዋች ሆኗል። በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የእግር ኳስ ውድድር ቀዳሚ ተጠቃሽ ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው የለንደኑ አርሰናል ኮትዲቯራዊውን ኒኮላስ ፔፔን በ89 ሚሊዮን ዶላር ክፍያ ካዘዋወረ በኋላ የመነጋገሪያ ርዕስ ሆኗል። በዚህም ነሐሴ 3 2011ዓ.ም በሚጀመረው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ላይ ቡድናቸው የተጠማውን ዋንጫ ያስገኝልናል በሚል የአርሰናል ደጋፊዎች የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ እየገለጹ ነው። • አወዛጋቢው የእግር ኳስ ዳኞች ማስመሪያ • ቢጫና ቀይ ካርዶች እንዴት ወደ እግር ኳስ ሜዳ መጡ? • የአውሮፓን እግር ኳስ የሚዘውረው ሃብታሙ 'ደላላ' የተለያዩ አፍሪካዊያን እግር ኳስ ተጫዋቾች በተለያየ የገንዘብ መጠን ከአንድ ቡድን ወደ ሌላ ቡድን ሲዘዋወሩ ቆይተዋል። እስከ ዛሬ ከፍተኛ ክፍያ የተፈጸመባቸው አፍሪካዊያን ተጫዋቾች እነማን ናቸው። • ኒኮላስ ፔፔ - 89 ሚሊዮን ዶላር (72ሚሊዮን ፓወንድ) • ሴድሪክ ባካምቡ - 79 ሚሊዮን ዶላር (65 ሚሊዮን ፓወንድ) • ሪያድ ማህሬዝ - 72 ሚሊዮን ዶላር (60 ሚሊዮን ፓወንድ) • ፒየር ኤምሪክ ኦባሚያንግ - 68 ሚሊዮን ዶላር (56.1 ሚሊዮን ፓወንድ) • ናቢ ኬዬታ - 64 ሚሊዮን ዶላር (52.75 ሚሊዮን ፓወንድ) በከፍተኛ ወጪ በመዘዋወር ክብረ ወሰኑን የጨበጠው ኒኮላስ ፔፔ በፈረንሳይ ሊግ አንድ፣ ውስጥ ለሚገኘው ሊል ለተባለው ቡድን ሲጫወት በ74 ጨዋታዎች 35 ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን፤ ከሁለት ዓመት በፊት ደግሞ እዚያው ፈረንሳይ ውስጥ አንገርስ ለተሰኘ ቡድን ይጫወት ነበር። ፔፔ ለአርሰናል በፈረመበት ወቅት እንደተናገረው "እዚህ በመምጣቴ የተለየ ስሜት ተሰምቶኛል" ብሏል። ጨምሮም "ከከፍተኛ ትግልና ከረጀም ጉዞ በኋላ ለዚህ ታላቅ ቡድን ስፈርም ለእኔ ትልቅ ሽልማት ነው" በማለት ለአርሰናል በመፈረሙ የተሰማውን ደስታ ገልጿል።
ከፍተኛ ገንዘብ የተከፈለባቸው አፍሪካዊያን ተጫዋቾች እነማን ናቸው? በከፍተኛ የዝውውር ክፍያ ለአርሰናል የፈረመው የፊት መስመር ተጫዋቹ ኒኮላስ ፔፔ ውድ ዋጋ የወጣበት አፍሪካዊ የእግር ኳስ ተጫዋች ሆኗል። በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የእግር ኳስ ውድድር ቀዳሚ ተጠቃሽ ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው የለንደኑ አርሰናል ኮትዲቯራዊውን ኒኮላስ ፔፔን በ89 ሚሊዮን ዶላር ክፍያ ካዘዋወረ በኋላ የመነጋገሪያ ርዕስ ሆኗል። በዚህም ነሐሴ 3 2011ዓ.ም በሚጀመረው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ላይ ቡድናቸው የተጠማውን ዋንጫ ያስገኝልናል በሚል የአርሰናል ደጋፊዎች የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ እየገለጹ ነው። • አወዛጋቢው የእግር ኳስ ዳኞች ማስመሪያ • ቢጫና ቀይ ካርዶች እንዴት ወደ እግር ኳስ ሜዳ መጡ? • የአውሮፓን እግር ኳስ የሚዘውረው ሃብታሙ 'ደላላ' የተለያዩ አፍሪካዊያን እግር ኳስ ተጫዋቾች በተለያየ የገንዘብ መጠን ከአንድ ቡድን ወደ ሌላ ቡድን ሲዘዋወሩ ቆይተዋል። እስከ ዛሬ ከፍተኛ ክፍያ የተፈጸመባቸው አፍሪካዊያን ተጫዋቾች እነማን ናቸው። • ኒኮላስ ፔፔ - 89 ሚሊዮን ዶላር (72ሚሊዮን ፓወንድ) • ሴድሪክ ባካምቡ - 79 ሚሊዮን ዶላር (65 ሚሊዮን ፓወንድ) • ሪያድ ማህሬዝ - 72 ሚሊዮን ዶላር (60 ሚሊዮን ፓወንድ) • ፒየር ኤምሪክ ኦባሚያንግ - 68 ሚሊዮን ዶላር (56.1 ሚሊዮን ፓወንድ) • ናቢ ኬዬታ - 64 ሚሊዮን ዶላር (52.75 ሚሊዮን ፓወንድ) በከፍተኛ ወጪ በመዘዋወር ክብረ ወሰኑን የጨበጠው ኒኮላስ ፔፔ በፈረንሳይ ሊግ አንድ፣ ውስጥ ለሚገኘው ሊል ለተባለው ቡድን ሲጫወት በ74 ጨዋታዎች 35 ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን፤ ከሁለት ዓመት በፊት ደግሞ እዚያው ፈረንሳይ ውስጥ አንገርስ ለተሰኘ ቡድን ይጫወት ነበር። ፔፔ ለአርሰናል በፈረመበት ወቅት እንደተናገረው "እዚህ በመምጣቴ የተለየ ስሜት ተሰምቶኛል" ብሏል። ጨምሮም "ከከፍተኛ ትግልና ከረጀም ጉዞ በኋላ ለዚህ ታላቅ ቡድን ስፈርም ለእኔ ትልቅ ሽልማት ነው" በማለት ለአርሰናል በመፈረሙ የተሰማውን ደስታ ገልጿል።
https://www.bbc.com/amharic/news-49204222
2health
‘ሲጨንቀን ከሐኪም የማይጠበቅ ምክር እንሰጣለን' - በዓይደር ሆስፒታል የካንሰር ሕክምና ባለሙያ
ተክለመድኅን ተክለሃይማኖት የ14 ዓመት ልጅ ነው፤ ከስድስት ወር በፊት ሆዱ አብጦ፣ ከባድ ሙቀት፣ የክብደት መቀነስ እና የአፍንጫ መድማት ምልክቶች ሲያሳይ ወላጆቹ ከተንቤን ወደ መቀለ ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ይዘውት ሄዱ። የሕክምና ባለሙያዎቹ ምርመራቸውን አደረጉ፤ የደም ካንሰር (lukimea) እንዳለበትም ለቤተሰብ አሳወቁ። በወቅቱ የመጀመርያው ደረጃ የኬሞቴራፒ (የጨረር) ህክምና ተደርጎለት መጠነኛ የጤና መሻሻል ማሳየቱን የጤና ባለሞያዎቹ ይናገራሉ። ሁለተኛው የኬሞቴራፒ ህክምና እንዲደረግለትም ከሁለት ሳምንታት በኋላ እንዲመለስ ተነግሮት ከሆስፒታሉ ቢወጡም፣ ወላጆቹ ግን ለስድስት ወራት በዚያው ጠፉ። በዚህ ሁኔታ መቆየት ከሚገባበት በላይ ዘግይቶ እንደገና ወደ ሆስፒታሉ ሲመለስ ግን ከዚህ ቀደም የታዩት ምልክቶች ተባባሱ። "ለደም ምርመራ እና መድኃኒት መግዣ የሚሆን ገንዘብ ስለሌለን ነው የጠፋነው" ይላሉ ወላጆቹ። በዚህ ምክንያት፣ ልጁ የሚያሳያቸው ምልክቶች ከቀን ወደ ቀን መሻሻል ያሳዩ ይሆናል በሚል ተስፋ ቤት ይዘውት መቀመጣቸውን ይናገራሉ። ሆኖም ግን በዚህ ወቅት በሽታው በመባባሱ ሆስፒታል ተኝቶ ህክምና ማግኘት እንዳለበት ተነገራቸው። የዓይደር ሆስፒታል ሠራተኞች ግን፣ ሆስፒታሉ ባጋጠመው የመድኃኒት እና ሌሎች ቁሳቁሶች እጥረት ምክንያት፣ ህጻናት እና አዋቂዎች የካንሰር ህሙማን የሚያክሙበት አቅም እየተሟጠጠ መምጣቱን ይናገራሉ። አክለውም 'ተስፋ መቁረጥ ደረጃ ላይ ነን' ብለዋል። አብዛኛው በክልሉ ህጻናት ላይ የሚታየው ካንሰር የደም ካንሰር መሆኑን የሚገልጸው የካንሰር ሐኪም እና ጥናት [ኦንኮሎጂ] ትምህርት ክፍል ኃላፊ ዶክተር ክብሮም ሕሉፍ፣ ህጻናት ላይ የሚታዩ የካንሰር አይነቶች በቀላሉ መታከም የሚችሉ ናቸው ይላል። ሆኖም "አሁን ህክምና የለም፤ በህይወት እንዲቆዩ ብቻ የመጠቀሚያ ቀን ያለፈባቸው መድኃኒቶች እየሰጠናቸው ነው። ምናልባት እድለኞች ከሆኑ፤ ከጊዜ በኋላ ምን ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ግን ማወቅ አንችልም" ሲል ለቢቢሲ ገልጿል። በክልሉ የካንሰር ህሙማን ልጆች ያሉዋቸው ቤተሰቦች ገንዘብ የሚያገኙበት አማራጭ በመቋረጡ ምክንያት ልጆቻቸውን ከክልሉ ውጪም ቢሆን ለማሳከም ለትራንስፖርት እና ሌሎች ወጪዎች ገንዘብ ለማግኘት መቸገራቸው ይናገራሉ። የካንሰር ህክምና ከባድ ወጪ እና ረጅም ጊዜ የሚፈልግ ነው። በዚህ ምክንያት፣ እንደ ኬሞቴራፒ ያሉ ለካንሰር ህሙማን የሚሰጡ የህክምና አይነቶች ባለማግኘታቸው በርካታ ህጻናት ቤት ውስጥ እየሞቱ ነው የሚል ስጋት ከሕክምና ባለሙያዎቹ ይሰማል። ከአምስት ዓመት በፊት በ1999 ዓ.ም በዓይደር ሆስፒታል የህጻናት የካንሰር ህክምና ክፍል ሲከፍት መሰል ችግሮችን ለማቃለል እና ሰዎች በአቅራቢያቸው አገልግሎት እንዲያገኙ ለማገዝ በሚል መንግሥት የኬሞቴራፒ ወጪውን ግማሽ ክፍያ ሲሸፍን፣ ቀሪውን ክፍያ ደግሞ ቤተሰቦች በብድር መልክ እንዲከፍሉ በማድረግ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል። ባለፉት ሦስት ዓመታትም ከተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች፣ የተወሰኑ የአማራ ክልል አካባቢዎች፣ ከአፋር እንዲሁም ከኤርትራ የሚመጡ የካንሰር ሕሙማን በሆስፒታሉ አገልግሎት ሲያገኙ እንደነበረ እና የአዲስ ተካሚዎች ቁጥር ከ72 ወደ 110 ከፍ ብሎ እንደነበር ከሆስፒታሉ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። በጦርነቱ ምክንያት እና ከዚያ በኋላ በቀጠለው የማኅበራዊ አገልግሎቶች መቋረጥ ምክንያት ግን ይሄንን ቁጥር በግማሽ መቀነሱ ይጠቀሳል። ለ17 ወራት በቀጠለው ጦርነት ምክንያት በክልሉ የሚገኙ የካንሰር ህሙማን በከባድ ችግር ላይ ወድቀው ከሚገኙ ታካሚዎች መካከል ይጠቀሳሉ። ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ ባሉ ጊዜያት 1643 አዋቂዎች እና 126 ህጻናት የካንሰር ታካሚዎች ወደ ሆስፒታሉ መምጣታቸው የሚያሳየው የሆስፒታሉ ሪፖርት፣ አብዛኛዎቹ ግን በትራንስፖርት ችግር፣ በገንዘብ ማጣት እና የስልክ አገልግሎት ባለመኖሩ ምክንያት መጥተው ህክምና ማግኘት አልቻሉም ሲል የሆስፒታሉ አስተዳደር ያስረዳል። "70 በመቶ የካንሰር ታካሚዎቻችን ሴቶች ናቸው። ከእነዚህ 30 በመቶ የጡት ካንሰር አለባቸው። የማህጸን በር ካንሰር ያለባቸው 126 ሴቶች ሲኖሩ ከእነዚህ 15 ብቻ ናቸው የመጀመሪያው ደረጃ ቀዶ ጥገና የተደረገላቸው። ቀሪዎቹ 111 ግን የኬሞቴራፒ ህክምና ባለመኖሩ ምንም አማራጭ ስለሌለ ወደ ቤታቸው ልከናቸዋል" ይላል ሆስፒታሉ። ባለፈው ወር የሆስፒታሉ ባለሙያዎች፣ ከላባራቶሪ እስከ የኬሞቴራፒ መድኃኒት ድረስ እጥረት በማጋጠሙ ምክንያት ከ1700 በላይ የካንሰር ህሙማን ለሞት አደጋ ተጋልጠዋል ሲሉ ለቢቢሲ ገልጸው ነበር። ከጦርነቱ በፊት፣ ሆስፒታሉ ከ60 እስከ 70 በመቶ የኬሞቴራፒ አገልግሎት በመስጠት ከ45 በላይ የካንሰር መድኃኒቶች በሆስፒታሉ እንደነበሩት ይገለጻል። በአሁኑ ወቅት ያለው የኬሞቴራፒ አገልግሎት ከ10 በመቶ በታች ሲሆን፣ ሦስት የመድኃኒት አይነቶች ብቻ እንዳሉትም የካንሰር ሕክምና ክፍል መጋቢት ወር ላይ ያወጣው ሪፖርት ያመለክታል። በዚህ ምክንያት የአገልግሎት ጊዜ ያለፈባቸው መድኃኒቶችም እያለቁ ናቸው ሲል ዶክተር ክብሮም ያስረዳል። "አሁን ላይ ኬሞቴራፒ ሙሉ ለሙሉ ተቋርጧል። የካንሰር መድኃኒቶች እጅግ ከባድ ናቸው። ለምሳሌ ኬሞቴራፒ የሚወስድ ታካሚ ወደ ላይ የማለት ችግር ሊኖረው ስለሚችል ለዚህ የሚሰጥ መድኃኒት ነበር፤ አሁን እሱም ነው የሌለን። በግሉኮስ መልክ የሚሰጡ መድኃኒቶች የሉም። አብዛኛዎቹ ታካሚዎች ህክምና የለም እያልን ነው የምንመልሳቸው፤ የማጽናናት ሥራ እንጂ የህክምና ሥራም እየሰራን አይደለም" ይላል። የአንጀት ካንሰር ታካሚዎች ህክምናቸው ሙሉ ለሙሉ ተቋርጧል የሚለው ኃላፊው፣ ሁሉም የካንሰር ታካሚዎች ከባድ ችግር ላይ ናቸው ሲል ይናገራል። "የተለያዩ መድኃኒቶችን ነበር የሚወስዱት፤ ካጋጠመን እጥረት አንጻር አራት ለሚወስዱት አንድ ስንሰጣቸው ነበር፤ የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው ጭምር። አሁን ግን እሱም ተቋረጠ" ሲል ለቢቢሲ ገልጿል። 'ሲጨንቀን ከሐኪም የማይጠበቀውን እንላለን' የካቲት ወር አጋማሽ ላይ የዓለም የጤና ድርጅት በስድስት ወራት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ አንቲባዮቲክስ፣ የወባ እና የስኳር እንዲሁም የከባድ የምግብ እጥረት መድኃኒቶች የያዙ የተለያዩ የህክምና ቁሳቁሶችን ወደ ትግራይ እንዲያስገባ ፈቃድ አግኝቶ ነበር። ሆኖም ክልሉ ውስጥ ባለው የነዳጅ እጥረት ምክንያት ወደ ሚፈለገው ቦታ ማድረስ አልተቻለም ሲል የገጠመውን ተግዳሮት ገልጾ ነበር። ባለፈው መጋቢት ወር፣ የፌደራል መንግሥት እና የትግራይ ኃይሎች ለሰብዓዊነት በሚል ግጭት ለማቆም ከወሰኑ በኋላ፣ በተለያዩ ጊዜያት ሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ የዓለም ምግብ ፕሮግራም እና የቀይ መስቀል መኪኖች መቀለ መድረሳቸው ተነግሯል። አብዛኛው ወደ ክልሉ የገባው መድኃኒት አጣዳፊ ለሆኑ ወይም በኢንፌክሽን ለሚመጡ በሽታዎች መከላከያ የሚሆን እንጂ፣ እንደ ካንሰር ያሉ በሽታዎችን ከግምት ውስጥ ያስገቡ አይደሉም የሚለው ዶክተር ክብሮም፣ "በዚህ ሳቢያ በቅርቡ በርካታ ታካሚዎቻችን አጥተናል፤ ልናጣቸው ጫፍ የደረሱም አሉ" በማለት ስጋቱን ይገልጻል። "500 ተከታታይ ኬሞቴራፒ ማግኘት ያለባቸው፣ 300 የሚጠጉ ደግሞ ፈጣን የጨረር ህክምና የሚያስፈልጋቸው ሰዎች አሉ። ችግሩ በዚህ ከቀጠለ እነዚህንም እናጣቸዋለን ማለት ነው። ስልክም ስለሌለ መድኃኒት የለም ብለን ወደ ቤታቸው የመለስናቸው ታካሚዎች ምን እንደገጠማቸው አናውቅም" ብሏል። በተለይ ከመቀለ ውጪ የሚኖሩ የካንሰር ህሙማን በገንዘብ እጥረት እና በትራንስፖርት ችግር ምክንያት ወደ ሆስፒታሉ መምጣት ማቆማቸውን ባለሙያው ይናገራል። "ካንሰር ከባድ በሽታ ነው፤ ሞት ደረጃ የሚያደርስ እና ህክምናውም ከባድ የሆነ በሽታ ነው። ከአሁን በፊት ህክምና እየሰጠን ተስፋ አላችሁ እንላቸው ነበር። አሁን ግን 'በሽታህ ይህ ነው፣ መድኃኒት ግን የለም፤ ምንም ማድረግ አልችልም' ማለት ለእኔ የሞት ፍርድ መንገር ነው። ሲጨንቀን ከሐኪም የማይጠበቀውን እንላለን፤ እስቲ ፀበል ሞክሩ ብለን ነው የምንሸኛቸው" ሲል ያስረዳል። ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል አሁን ያጋጠሙት ችግሮች መፍትሄ ካላገኙ ሆስፒታሉ ለህጻናት እና ለአዋቂዎች የካንሰር ህሙማን ህክምና መስጠት የማይችልበት ደረጃ ደርሶ "መፍረስ" ላይ ነው የሚገኘው በማለት የጤና ሚኒቴር እና ሌሎች ተቋማት ትኩረት እንዲሰጡት የሆስፒታሉ ሠራተኞች ይማጸናሉ። "ማስታገሻ ሳይቀር እኮ ነው ያጣነው፤ አንድ ሰው እባክህ ወደ ላይ እያለኝ ነው ብሎን መድኃኒት መስጠት አልቻልንም። ሆስፒታሉ የሚዘጋበት ደረጃ ላይ ደርሷል፤ ይህ ማለት ህክምና በማጣት ምክንያት ትውልድ ማጣት ነው። የእኔ ትልቅ ስጋት ይህ ነው" ይላል ዶክተር ክብሮም።
‘ሲጨንቀን ከሐኪም የማይጠበቅ ምክር እንሰጣለን' - በዓይደር ሆስፒታል የካንሰር ሕክምና ባለሙያ ተክለመድኅን ተክለሃይማኖት የ14 ዓመት ልጅ ነው፤ ከስድስት ወር በፊት ሆዱ አብጦ፣ ከባድ ሙቀት፣ የክብደት መቀነስ እና የአፍንጫ መድማት ምልክቶች ሲያሳይ ወላጆቹ ከተንቤን ወደ መቀለ ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ይዘውት ሄዱ። የሕክምና ባለሙያዎቹ ምርመራቸውን አደረጉ፤ የደም ካንሰር (lukimea) እንዳለበትም ለቤተሰብ አሳወቁ። በወቅቱ የመጀመርያው ደረጃ የኬሞቴራፒ (የጨረር) ህክምና ተደርጎለት መጠነኛ የጤና መሻሻል ማሳየቱን የጤና ባለሞያዎቹ ይናገራሉ። ሁለተኛው የኬሞቴራፒ ህክምና እንዲደረግለትም ከሁለት ሳምንታት በኋላ እንዲመለስ ተነግሮት ከሆስፒታሉ ቢወጡም፣ ወላጆቹ ግን ለስድስት ወራት በዚያው ጠፉ። በዚህ ሁኔታ መቆየት ከሚገባበት በላይ ዘግይቶ እንደገና ወደ ሆስፒታሉ ሲመለስ ግን ከዚህ ቀደም የታዩት ምልክቶች ተባባሱ። "ለደም ምርመራ እና መድኃኒት መግዣ የሚሆን ገንዘብ ስለሌለን ነው የጠፋነው" ይላሉ ወላጆቹ። በዚህ ምክንያት፣ ልጁ የሚያሳያቸው ምልክቶች ከቀን ወደ ቀን መሻሻል ያሳዩ ይሆናል በሚል ተስፋ ቤት ይዘውት መቀመጣቸውን ይናገራሉ። ሆኖም ግን በዚህ ወቅት በሽታው በመባባሱ ሆስፒታል ተኝቶ ህክምና ማግኘት እንዳለበት ተነገራቸው። የዓይደር ሆስፒታል ሠራተኞች ግን፣ ሆስፒታሉ ባጋጠመው የመድኃኒት እና ሌሎች ቁሳቁሶች እጥረት ምክንያት፣ ህጻናት እና አዋቂዎች የካንሰር ህሙማን የሚያክሙበት አቅም እየተሟጠጠ መምጣቱን ይናገራሉ። አክለውም 'ተስፋ መቁረጥ ደረጃ ላይ ነን' ብለዋል። አብዛኛው በክልሉ ህጻናት ላይ የሚታየው ካንሰር የደም ካንሰር መሆኑን የሚገልጸው የካንሰር ሐኪም እና ጥናት [ኦንኮሎጂ] ትምህርት ክፍል ኃላፊ ዶክተር ክብሮም ሕሉፍ፣ ህጻናት ላይ የሚታዩ የካንሰር አይነቶች በቀላሉ መታከም የሚችሉ ናቸው ይላል። ሆኖም "አሁን ህክምና የለም፤ በህይወት እንዲቆዩ ብቻ የመጠቀሚያ ቀን ያለፈባቸው መድኃኒቶች እየሰጠናቸው ነው። ምናልባት እድለኞች ከሆኑ፤ ከጊዜ በኋላ ምን ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ግን ማወቅ አንችልም" ሲል ለቢቢሲ ገልጿል። በክልሉ የካንሰር ህሙማን ልጆች ያሉዋቸው ቤተሰቦች ገንዘብ የሚያገኙበት አማራጭ በመቋረጡ ምክንያት ልጆቻቸውን ከክልሉ ውጪም ቢሆን ለማሳከም ለትራንስፖርት እና ሌሎች ወጪዎች ገንዘብ ለማግኘት መቸገራቸው ይናገራሉ። የካንሰር ህክምና ከባድ ወጪ እና ረጅም ጊዜ የሚፈልግ ነው። በዚህ ምክንያት፣ እንደ ኬሞቴራፒ ያሉ ለካንሰር ህሙማን የሚሰጡ የህክምና አይነቶች ባለማግኘታቸው በርካታ ህጻናት ቤት ውስጥ እየሞቱ ነው የሚል ስጋት ከሕክምና ባለሙያዎቹ ይሰማል። ከአምስት ዓመት በፊት በ1999 ዓ.ም በዓይደር ሆስፒታል የህጻናት የካንሰር ህክምና ክፍል ሲከፍት መሰል ችግሮችን ለማቃለል እና ሰዎች በአቅራቢያቸው አገልግሎት እንዲያገኙ ለማገዝ በሚል መንግሥት የኬሞቴራፒ ወጪውን ግማሽ ክፍያ ሲሸፍን፣ ቀሪውን ክፍያ ደግሞ ቤተሰቦች በብድር መልክ እንዲከፍሉ በማድረግ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል። ባለፉት ሦስት ዓመታትም ከተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች፣ የተወሰኑ የአማራ ክልል አካባቢዎች፣ ከአፋር እንዲሁም ከኤርትራ የሚመጡ የካንሰር ሕሙማን በሆስፒታሉ አገልግሎት ሲያገኙ እንደነበረ እና የአዲስ ተካሚዎች ቁጥር ከ72 ወደ 110 ከፍ ብሎ እንደነበር ከሆስፒታሉ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። በጦርነቱ ምክንያት እና ከዚያ በኋላ በቀጠለው የማኅበራዊ አገልግሎቶች መቋረጥ ምክንያት ግን ይሄንን ቁጥር በግማሽ መቀነሱ ይጠቀሳል። ለ17 ወራት በቀጠለው ጦርነት ምክንያት በክልሉ የሚገኙ የካንሰር ህሙማን በከባድ ችግር ላይ ወድቀው ከሚገኙ ታካሚዎች መካከል ይጠቀሳሉ። ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ ባሉ ጊዜያት 1643 አዋቂዎች እና 126 ህጻናት የካንሰር ታካሚዎች ወደ ሆስፒታሉ መምጣታቸው የሚያሳየው የሆስፒታሉ ሪፖርት፣ አብዛኛዎቹ ግን በትራንስፖርት ችግር፣ በገንዘብ ማጣት እና የስልክ አገልግሎት ባለመኖሩ ምክንያት መጥተው ህክምና ማግኘት አልቻሉም ሲል የሆስፒታሉ አስተዳደር ያስረዳል። "70 በመቶ የካንሰር ታካሚዎቻችን ሴቶች ናቸው። ከእነዚህ 30 በመቶ የጡት ካንሰር አለባቸው። የማህጸን በር ካንሰር ያለባቸው 126 ሴቶች ሲኖሩ ከእነዚህ 15 ብቻ ናቸው የመጀመሪያው ደረጃ ቀዶ ጥገና የተደረገላቸው። ቀሪዎቹ 111 ግን የኬሞቴራፒ ህክምና ባለመኖሩ ምንም አማራጭ ስለሌለ ወደ ቤታቸው ልከናቸዋል" ይላል ሆስፒታሉ። ባለፈው ወር የሆስፒታሉ ባለሙያዎች፣ ከላባራቶሪ እስከ የኬሞቴራፒ መድኃኒት ድረስ እጥረት በማጋጠሙ ምክንያት ከ1700 በላይ የካንሰር ህሙማን ለሞት አደጋ ተጋልጠዋል ሲሉ ለቢቢሲ ገልጸው ነበር። ከጦርነቱ በፊት፣ ሆስፒታሉ ከ60 እስከ 70 በመቶ የኬሞቴራፒ አገልግሎት በመስጠት ከ45 በላይ የካንሰር መድኃኒቶች በሆስፒታሉ እንደነበሩት ይገለጻል። በአሁኑ ወቅት ያለው የኬሞቴራፒ አገልግሎት ከ10 በመቶ በታች ሲሆን፣ ሦስት የመድኃኒት አይነቶች ብቻ እንዳሉትም የካንሰር ሕክምና ክፍል መጋቢት ወር ላይ ያወጣው ሪፖርት ያመለክታል። በዚህ ምክንያት የአገልግሎት ጊዜ ያለፈባቸው መድኃኒቶችም እያለቁ ናቸው ሲል ዶክተር ክብሮም ያስረዳል። "አሁን ላይ ኬሞቴራፒ ሙሉ ለሙሉ ተቋርጧል። የካንሰር መድኃኒቶች እጅግ ከባድ ናቸው። ለምሳሌ ኬሞቴራፒ የሚወስድ ታካሚ ወደ ላይ የማለት ችግር ሊኖረው ስለሚችል ለዚህ የሚሰጥ መድኃኒት ነበር፤ አሁን እሱም ነው የሌለን። በግሉኮስ መልክ የሚሰጡ መድኃኒቶች የሉም። አብዛኛዎቹ ታካሚዎች ህክምና የለም እያልን ነው የምንመልሳቸው፤ የማጽናናት ሥራ እንጂ የህክምና ሥራም እየሰራን አይደለም" ይላል። የአንጀት ካንሰር ታካሚዎች ህክምናቸው ሙሉ ለሙሉ ተቋርጧል የሚለው ኃላፊው፣ ሁሉም የካንሰር ታካሚዎች ከባድ ችግር ላይ ናቸው ሲል ይናገራል። "የተለያዩ መድኃኒቶችን ነበር የሚወስዱት፤ ካጋጠመን እጥረት አንጻር አራት ለሚወስዱት አንድ ስንሰጣቸው ነበር፤ የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው ጭምር። አሁን ግን እሱም ተቋረጠ" ሲል ለቢቢሲ ገልጿል። 'ሲጨንቀን ከሐኪም የማይጠበቀውን እንላለን' የካቲት ወር አጋማሽ ላይ የዓለም የጤና ድርጅት በስድስት ወራት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ አንቲባዮቲክስ፣ የወባ እና የስኳር እንዲሁም የከባድ የምግብ እጥረት መድኃኒቶች የያዙ የተለያዩ የህክምና ቁሳቁሶችን ወደ ትግራይ እንዲያስገባ ፈቃድ አግኝቶ ነበር። ሆኖም ክልሉ ውስጥ ባለው የነዳጅ እጥረት ምክንያት ወደ ሚፈለገው ቦታ ማድረስ አልተቻለም ሲል የገጠመውን ተግዳሮት ገልጾ ነበር። ባለፈው መጋቢት ወር፣ የፌደራል መንግሥት እና የትግራይ ኃይሎች ለሰብዓዊነት በሚል ግጭት ለማቆም ከወሰኑ በኋላ፣ በተለያዩ ጊዜያት ሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ የዓለም ምግብ ፕሮግራም እና የቀይ መስቀል መኪኖች መቀለ መድረሳቸው ተነግሯል። አብዛኛው ወደ ክልሉ የገባው መድኃኒት አጣዳፊ ለሆኑ ወይም በኢንፌክሽን ለሚመጡ በሽታዎች መከላከያ የሚሆን እንጂ፣ እንደ ካንሰር ያሉ በሽታዎችን ከግምት ውስጥ ያስገቡ አይደሉም የሚለው ዶክተር ክብሮም፣ "በዚህ ሳቢያ በቅርቡ በርካታ ታካሚዎቻችን አጥተናል፤ ልናጣቸው ጫፍ የደረሱም አሉ" በማለት ስጋቱን ይገልጻል። "500 ተከታታይ ኬሞቴራፒ ማግኘት ያለባቸው፣ 300 የሚጠጉ ደግሞ ፈጣን የጨረር ህክምና የሚያስፈልጋቸው ሰዎች አሉ። ችግሩ በዚህ ከቀጠለ እነዚህንም እናጣቸዋለን ማለት ነው። ስልክም ስለሌለ መድኃኒት የለም ብለን ወደ ቤታቸው የመለስናቸው ታካሚዎች ምን እንደገጠማቸው አናውቅም" ብሏል። በተለይ ከመቀለ ውጪ የሚኖሩ የካንሰር ህሙማን በገንዘብ እጥረት እና በትራንስፖርት ችግር ምክንያት ወደ ሆስፒታሉ መምጣት ማቆማቸውን ባለሙያው ይናገራል። "ካንሰር ከባድ በሽታ ነው፤ ሞት ደረጃ የሚያደርስ እና ህክምናውም ከባድ የሆነ በሽታ ነው። ከአሁን በፊት ህክምና እየሰጠን ተስፋ አላችሁ እንላቸው ነበር። አሁን ግን 'በሽታህ ይህ ነው፣ መድኃኒት ግን የለም፤ ምንም ማድረግ አልችልም' ማለት ለእኔ የሞት ፍርድ መንገር ነው። ሲጨንቀን ከሐኪም የማይጠበቀውን እንላለን፤ እስቲ ፀበል ሞክሩ ብለን ነው የምንሸኛቸው" ሲል ያስረዳል። ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል አሁን ያጋጠሙት ችግሮች መፍትሄ ካላገኙ ሆስፒታሉ ለህጻናት እና ለአዋቂዎች የካንሰር ህሙማን ህክምና መስጠት የማይችልበት ደረጃ ደርሶ "መፍረስ" ላይ ነው የሚገኘው በማለት የጤና ሚኒቴር እና ሌሎች ተቋማት ትኩረት እንዲሰጡት የሆስፒታሉ ሠራተኞች ይማጸናሉ። "ማስታገሻ ሳይቀር እኮ ነው ያጣነው፤ አንድ ሰው እባክህ ወደ ላይ እያለኝ ነው ብሎን መድኃኒት መስጠት አልቻልንም። ሆስፒታሉ የሚዘጋበት ደረጃ ላይ ደርሷል፤ ይህ ማለት ህክምና በማጣት ምክንያት ትውልድ ማጣት ነው። የእኔ ትልቅ ስጋት ይህ ነው" ይላል ዶክተር ክብሮም።
https://www.bbc.com/amharic/news-61369295
3politics
በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣናቸውን ያጡት የኖቤል ሎውሬት አን ሳን ሱ ቺ ማን ናቸው?
በአንድ ወቅት የሰብአዊ መብትና የዲሞክራሲ ባንዲራ ሆነው ይታዩ ነበር፡፡ አሁን ግን በብዙ ተቋማት ዓይንዎትን ላፈር ተብለዋል፤ አን ሳን ሱ ቺ፡፡ ከሳምንት በፊት በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣናቸውን አጥተዋል፡፡ አሁን በቁም እስር ላይ ናቸው፡፡ ከስማቸው አወዛጋቢነት እስከ አገሪቱ ትክክለኛ የስም አጠራር ድረስ የቀድሞዋ በርማ የአሁኗ ሚየንማር፣ የቀድሞዋ የሰብአዊ መብት እመቤት፣ የአሁኗ እስረኛ የሰሞኑ የሚዲያ ዐቢይ ጉዳይ ሆነዋል፡፡ በእርግጥ የሴትዮዋ ‹ሌጋሲ› በትክክል ምንድነው? በሚለው ጉዳይ ሚዲያዎችና ተቋማት ተስማምተው አያውቁም፡፡ ለመሆኑ ኦን ሳን ሱ ቺ ማን ናቸው? አን ሳን ሱ ቺ አባታቸው የበርማ የነጻነት አባት የሚባሉት የጄኔራል ኦን ሳን ሴት ልጅ ናቸው፡፡ ታላቋ ብሪታኒያ በርማን (በአዲሱ ስሟ ሚየንማር) ለአንድ ክፍለ ዘመን ያህል ጊዜ በቅኝ ገዝታታለች፡፡ ጄኔራል ኦን ሰን ለበርማ ነጻነት ተዋድቀዋል፡፡ የተገደሉትም በ1947 በተቀናቃኞቻቸው ነበር፡፡ ያን ጊዜ ሳን ሱ ቺ ገና 2 ዓመቷ ነበር፡፡ አን ሳን ሱ ቺ በሰኔ 19፣ 1945 ነበር የተወለዱት፡፡ ኦን ሳን ሱ ቺ በ1960ዎቹ መጀመርያ ከእናታቸው ዳው ኪን ኬዪ ጋር ወደ ሕንድ ሄዱ፡፡ እናታቸው በደልሂ የበርማ አምባሳደር ተደርገው በመሾማቸው ነበር ወደዚያ ያቀኑት፡፡ ሕንድ አራት ዓመት ከኖሩ በኋላ ወደ ታላቋ ብሪታኒያ በማቅናት በሥመጥሩ ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ፍልስፍናን፣ ፖለቲካንና ምጣኔ ሀብትን አጥንተዋል፡፡ አን ሳን ሱ ቺ በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ሳሉ የወደፊት ባለቤታቸው ጋር ተገናኙ፡፡ እንግሊዛዊው ባለቤታቸው ማይክል አሪስ የታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ነበሩ፡፡ አሁን በሕይወት የሉም፡፡ ኦን ሳን ሱ ቺ ከትምህርት በኋላ በቡታን እና በጃፓን በተለያዩ ሥራዎች ላይ ተሳትፈዋል፡፡ ከዚያ በኋላ ወደ ታላቋ ብሪታኒያ በመሄድ ጎጆ መሥርተው አሌክሳንደርና ኪም የሚባሉ ልጆችን አፍርተዋል፡፡ በ1988 ከታላቋ ብሪታኒያ ወደ ሚየንማር ዋና ከተማ ያንጎን ሲመለሱ በጠና ታመው የነበሩትን እናታቸውን ለማስታመም ነበር፡፡ የአጋጣሚ ነገር ሆኖ በበዚያ ወቅት በሚየንማር በርካታ የዲሞክራሲ ጥያቄዎችን ያነሱ ወጣቶች አደባባይ ወጥተው ተቃውሞ ያስነሱበት ጊዜ ነበር፡፡ ተቃዋሚዎቹ ወጣቶች ብቻ ሳይሆኑ የቡድሀ መነኮሳት፣ የቢሮ ሰራተኞችና ተማሪዎችም ይገኙበት ነበር፡፡ ይህን ተቃውሞ ተከትሎ አን ሳን ሱ ቺ ጠቅልለው በሚየንማር መኖር ጀመሩ፡፡ ከ2 ዓመት በኋላ በ1990 አዲስ በተመሠረተው የናሽናል ሊግ ፓርቲ ውስጥ ገብተው ተቃውሞ ውስጥ በቀጥታ መሳተፍ ጀመሩ፡፡ በአካባቢ ምርጫ ተወዳድረውም አሸነፉ፡፡ በከፍተኛ ድምጽ የኦን ሳን ሱ ቺ በምርጫ ማሸነፍ ያስቆጣው ወታደራዊው መንግሥት ሴትዮዋን ለሚቀጥሉት 20 ዓመታት በቁም እስር አስቀመጣቸው፡፡ በ1991 ኦን ሳን ሱ ቺ በቁም እስር ላይ ሳሉ የኖቤል ሽልማትን አሸነፉ፡፡ ይህም ወታደራዊውን መንግሥት በይበልጥ አስቆጣ፡፡ በ2010 ኦን ሳን ሱ ቺ ከቁም እስር ነጻ ተባሉ፡፡ በ2012 አን ሳን ሱ ቺና ፓርቲያቸው በአካባቢ ምርጫ እንዲሳተፉ ወታደራዊው መንግሥት ፈቀደ፡፡ በ2015 የብሔራዊ ሊግ ለዲሞክራሲ (NLD) ፓርቲያቸው ለመጀመርያ ጊዜ በተደረገ ከፍተኛ ፉክክር በታየበት ምርጫ አሸነፈ፡፡ አን ሳን ሱ ቺ በሚየንማር የሮሒንጋ ሙስሊሞች ላይ ወታደሩ ያደረሰውን ግፍና ጭፍጨፋ ለማውገዝ አለመፍቀዳቸው በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ዘንድ ቁጣን ቀሰቀሰ፡፡ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ የሮሒንጋ ሙስሊሞች ከሚየንማር ሞትን ሽሽት ወደ ባንግላዴሽ ተሰደዋል፡፡ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ ክብራቸው ዝቅ ይበል እንጂ አን ሳን ሱ ቺ በአገራቸው ቡድሀዎች ዘንድ እጅግ ተወዳጅ ናቸው፡፡ አን ሳን ሱ ቺ በ2015 የተደረገውን ምርጫ አሸንፈው መንግሥት ቢመሠርቱም የአገሪቱ ፕሬዝዳንት መሆን ግን አልተፈቀደላቸውም፡፡ ይፋዊ ሥልጣናቸው ‹የመንግሥት የበላይ ጠባቂ› ወይም ስቴት ካውንስለርነት ነው፡፡ ይህም የሆነው ያፈሯቸው ልጆች የውጭ ዜግነት ስላላቸው ነው፡፡ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሚስተር ዊ ቢሆኑም አን ሳን ሱ ቺ ግን በውስጥ ታዋቂነት (de facto) የአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ሆነው ይወሰዳሉ፡፡ ስቴት ካውንስል የሚባለው ሹመት የተፈጠረው አን ሳን ሱ ቺ ሕጋዊ ፕሬዝዳንት መሆን ስለማይችሉ ነው፡፡ ሆኖም በፖለቲካ ሥልጣን ረገድ የጠቅላይ ሚኒስትር ያህል ቁልፍ ቦታ ነው፡፡ አን ሳን ሱ ቺ ይህን ሥልጣን ከመቆናጠጣቸው በፊት ለአጫጭር ጊዜም ቢሆን የኢነርጂ ሚኒስትር፣ የትምህርት ሚኒስትር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል፡፡ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ማለትም 2020 አን ሳን ሱ ቺ እና ፓርቲያቸው ምርጫ ማሸነፍ ችሎ ነበር፡፡ በቁጥጥር ሥር የዋሉትም አዲሱን መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና በሚሉበት ሰዓት ነው፡፡ በ2021 የዛሬ ሳምንት አካባቢ የተወካዮች ምክር ቤት ሸንጎ አዲስ የሥራ ዘመን ስብሰባ በሚጀምርበት ቀን አን ሳን ሱ ቺ በድጋሚ በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡ አን ሳን ሱ ቺ አሁን የ76 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ ናቸው፡፡
በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣናቸውን ያጡት የኖቤል ሎውሬት አን ሳን ሱ ቺ ማን ናቸው? በአንድ ወቅት የሰብአዊ መብትና የዲሞክራሲ ባንዲራ ሆነው ይታዩ ነበር፡፡ አሁን ግን በብዙ ተቋማት ዓይንዎትን ላፈር ተብለዋል፤ አን ሳን ሱ ቺ፡፡ ከሳምንት በፊት በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣናቸውን አጥተዋል፡፡ አሁን በቁም እስር ላይ ናቸው፡፡ ከስማቸው አወዛጋቢነት እስከ አገሪቱ ትክክለኛ የስም አጠራር ድረስ የቀድሞዋ በርማ የአሁኗ ሚየንማር፣ የቀድሞዋ የሰብአዊ መብት እመቤት፣ የአሁኗ እስረኛ የሰሞኑ የሚዲያ ዐቢይ ጉዳይ ሆነዋል፡፡ በእርግጥ የሴትዮዋ ‹ሌጋሲ› በትክክል ምንድነው? በሚለው ጉዳይ ሚዲያዎችና ተቋማት ተስማምተው አያውቁም፡፡ ለመሆኑ ኦን ሳን ሱ ቺ ማን ናቸው? አን ሳን ሱ ቺ አባታቸው የበርማ የነጻነት አባት የሚባሉት የጄኔራል ኦን ሳን ሴት ልጅ ናቸው፡፡ ታላቋ ብሪታኒያ በርማን (በአዲሱ ስሟ ሚየንማር) ለአንድ ክፍለ ዘመን ያህል ጊዜ በቅኝ ገዝታታለች፡፡ ጄኔራል ኦን ሰን ለበርማ ነጻነት ተዋድቀዋል፡፡ የተገደሉትም በ1947 በተቀናቃኞቻቸው ነበር፡፡ ያን ጊዜ ሳን ሱ ቺ ገና 2 ዓመቷ ነበር፡፡ አን ሳን ሱ ቺ በሰኔ 19፣ 1945 ነበር የተወለዱት፡፡ ኦን ሳን ሱ ቺ በ1960ዎቹ መጀመርያ ከእናታቸው ዳው ኪን ኬዪ ጋር ወደ ሕንድ ሄዱ፡፡ እናታቸው በደልሂ የበርማ አምባሳደር ተደርገው በመሾማቸው ነበር ወደዚያ ያቀኑት፡፡ ሕንድ አራት ዓመት ከኖሩ በኋላ ወደ ታላቋ ብሪታኒያ በማቅናት በሥመጥሩ ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ፍልስፍናን፣ ፖለቲካንና ምጣኔ ሀብትን አጥንተዋል፡፡ አን ሳን ሱ ቺ በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ሳሉ የወደፊት ባለቤታቸው ጋር ተገናኙ፡፡ እንግሊዛዊው ባለቤታቸው ማይክል አሪስ የታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ነበሩ፡፡ አሁን በሕይወት የሉም፡፡ ኦን ሳን ሱ ቺ ከትምህርት በኋላ በቡታን እና በጃፓን በተለያዩ ሥራዎች ላይ ተሳትፈዋል፡፡ ከዚያ በኋላ ወደ ታላቋ ብሪታኒያ በመሄድ ጎጆ መሥርተው አሌክሳንደርና ኪም የሚባሉ ልጆችን አፍርተዋል፡፡ በ1988 ከታላቋ ብሪታኒያ ወደ ሚየንማር ዋና ከተማ ያንጎን ሲመለሱ በጠና ታመው የነበሩትን እናታቸውን ለማስታመም ነበር፡፡ የአጋጣሚ ነገር ሆኖ በበዚያ ወቅት በሚየንማር በርካታ የዲሞክራሲ ጥያቄዎችን ያነሱ ወጣቶች አደባባይ ወጥተው ተቃውሞ ያስነሱበት ጊዜ ነበር፡፡ ተቃዋሚዎቹ ወጣቶች ብቻ ሳይሆኑ የቡድሀ መነኮሳት፣ የቢሮ ሰራተኞችና ተማሪዎችም ይገኙበት ነበር፡፡ ይህን ተቃውሞ ተከትሎ አን ሳን ሱ ቺ ጠቅልለው በሚየንማር መኖር ጀመሩ፡፡ ከ2 ዓመት በኋላ በ1990 አዲስ በተመሠረተው የናሽናል ሊግ ፓርቲ ውስጥ ገብተው ተቃውሞ ውስጥ በቀጥታ መሳተፍ ጀመሩ፡፡ በአካባቢ ምርጫ ተወዳድረውም አሸነፉ፡፡ በከፍተኛ ድምጽ የኦን ሳን ሱ ቺ በምርጫ ማሸነፍ ያስቆጣው ወታደራዊው መንግሥት ሴትዮዋን ለሚቀጥሉት 20 ዓመታት በቁም እስር አስቀመጣቸው፡፡ በ1991 ኦን ሳን ሱ ቺ በቁም እስር ላይ ሳሉ የኖቤል ሽልማትን አሸነፉ፡፡ ይህም ወታደራዊውን መንግሥት በይበልጥ አስቆጣ፡፡ በ2010 ኦን ሳን ሱ ቺ ከቁም እስር ነጻ ተባሉ፡፡ በ2012 አን ሳን ሱ ቺና ፓርቲያቸው በአካባቢ ምርጫ እንዲሳተፉ ወታደራዊው መንግሥት ፈቀደ፡፡ በ2015 የብሔራዊ ሊግ ለዲሞክራሲ (NLD) ፓርቲያቸው ለመጀመርያ ጊዜ በተደረገ ከፍተኛ ፉክክር በታየበት ምርጫ አሸነፈ፡፡ አን ሳን ሱ ቺ በሚየንማር የሮሒንጋ ሙስሊሞች ላይ ወታደሩ ያደረሰውን ግፍና ጭፍጨፋ ለማውገዝ አለመፍቀዳቸው በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ዘንድ ቁጣን ቀሰቀሰ፡፡ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ የሮሒንጋ ሙስሊሞች ከሚየንማር ሞትን ሽሽት ወደ ባንግላዴሽ ተሰደዋል፡፡ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ ክብራቸው ዝቅ ይበል እንጂ አን ሳን ሱ ቺ በአገራቸው ቡድሀዎች ዘንድ እጅግ ተወዳጅ ናቸው፡፡ አን ሳን ሱ ቺ በ2015 የተደረገውን ምርጫ አሸንፈው መንግሥት ቢመሠርቱም የአገሪቱ ፕሬዝዳንት መሆን ግን አልተፈቀደላቸውም፡፡ ይፋዊ ሥልጣናቸው ‹የመንግሥት የበላይ ጠባቂ› ወይም ስቴት ካውንስለርነት ነው፡፡ ይህም የሆነው ያፈሯቸው ልጆች የውጭ ዜግነት ስላላቸው ነው፡፡ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሚስተር ዊ ቢሆኑም አን ሳን ሱ ቺ ግን በውስጥ ታዋቂነት (de facto) የአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ሆነው ይወሰዳሉ፡፡ ስቴት ካውንስል የሚባለው ሹመት የተፈጠረው አን ሳን ሱ ቺ ሕጋዊ ፕሬዝዳንት መሆን ስለማይችሉ ነው፡፡ ሆኖም በፖለቲካ ሥልጣን ረገድ የጠቅላይ ሚኒስትር ያህል ቁልፍ ቦታ ነው፡፡ አን ሳን ሱ ቺ ይህን ሥልጣን ከመቆናጠጣቸው በፊት ለአጫጭር ጊዜም ቢሆን የኢነርጂ ሚኒስትር፣ የትምህርት ሚኒስትር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል፡፡ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ማለትም 2020 አን ሳን ሱ ቺ እና ፓርቲያቸው ምርጫ ማሸነፍ ችሎ ነበር፡፡ በቁጥጥር ሥር የዋሉትም አዲሱን መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና በሚሉበት ሰዓት ነው፡፡ በ2021 የዛሬ ሳምንት አካባቢ የተወካዮች ምክር ቤት ሸንጎ አዲስ የሥራ ዘመን ስብሰባ በሚጀምርበት ቀን አን ሳን ሱ ቺ በድጋሚ በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡ አን ሳን ሱ ቺ አሁን የ76 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ ናቸው፡፡
https://www.bbc.com/amharic/news-55975691
5sports
ኦሊምፒክ ፡ "ኮሮናቫይረስ ጠፋም አልጠፋ" በሚቀጥለው ዓመት ኦሊምፒክ ይካሄዳል
በኮሮናቫይረስ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሞ የነበረው የቶኪዮ ኦሊምፒክ በሚቀጥለው ዓመት በማንኛውም ሁኔታ እንደሚካሄድ ተገለጸ። የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ምክትል ፕሬዝዳንት "ኮቪድ-19 ጠፋም አልጠፋ በሚቀጥለው ዓመት ኦሊምፒክ ይካሄዳል" ብለዋል። ጆን ኮትስ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንዳረጋገጡት በሚቀጥለው ዓመት ኦሊምፒክ የሚጀምረው በሐምሌ 23 ይሆናል። ኦሊምፒክ መካሄድ የነበረበት ዘንድሮ በሐምሌ ወር ነበር። ሆኖም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ተከትሎ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሞ ነበር። ሆኖም ውድድሩን ከፈረንጆቹ 2021 ወዲያ መግፋት ስሜት የሚሰጥ ነገር አይደለም ብለዋል። በሐምሌ ወር የቶክዮ 2020 ኦሊምፒክ ሊቀመንበር ቶሺሮ ሙቶ "ውድድሮቹን በዝግ ስታዲየም ማካሄድ ይቻል ነበር። ያንን ስላልፈለግን ነው ያዘገየነው" ብለው ነበር። ምናልባት ከየአገሩ የሚመጡ ወኪሎችን ቁጥር በመቀነስ፣ በየውድድሩ የሚታደሙ ተመልካቾችን በማሳነስ፣ እንዲሁም የመክፈቻና መዝጊያ ሥነ ሥርዓቱን ቀለል በማድረግ የሚካሄድበት መንገድ ሊቀየስ ይችላል። ከመላው ዓለም 11 ሺህ አትሌቶች ከ200 አገራት እንደሚገኙ ይጠበቅ ነበር። በሚቀጥለው ዓመት ሐምሌ ላይ ውድድሩ ሲታሰብ የጉዞ ገደቦችን በተመለከተ የተባለ ነገር የለም። ሚስተር ሙቶ የኦሊምፒክ ውድድሩን ለማድረግ የኮቪድ-19 ክትባትን መጠበቅ አይኖርብንም ብለዋል። የጤና ባለሙያዎች በበኩላቸው በወረርሽኝ መሀል ክትባት ሳይኖር እንዲህ ዓይነት ውድድር ሊካሄድ አይችልም ይላሉ። "ክትባት ከተገኘ መልካም፤ ካልተገኘ ግን እሱ እስኪገኝ ኦሊምፒክ አይቆምም" ብለዋል ሊቀመንበሩ። የውድድሩ አስተባባሪ ዮሺሮ ሞሪ በሚያዝያ ወር ኦሊምፒክ በ2021 ካልተደረገ እስከናካቴው መሰረዝ ነው ያለበት ብለው ነበር። ከዚህ ቀደም የኦሎምፒክ ውድድር በጦርነት ምክንያት ሳይካሄድ ቀርቶ ያውቃል እንጂ የሚካሄድበት ጊዜ ሲገፋ ይህ በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ነው።
ኦሊምፒክ ፡ "ኮሮናቫይረስ ጠፋም አልጠፋ" በሚቀጥለው ዓመት ኦሊምፒክ ይካሄዳል በኮሮናቫይረስ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሞ የነበረው የቶኪዮ ኦሊምፒክ በሚቀጥለው ዓመት በማንኛውም ሁኔታ እንደሚካሄድ ተገለጸ። የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ምክትል ፕሬዝዳንት "ኮቪድ-19 ጠፋም አልጠፋ በሚቀጥለው ዓመት ኦሊምፒክ ይካሄዳል" ብለዋል። ጆን ኮትስ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንዳረጋገጡት በሚቀጥለው ዓመት ኦሊምፒክ የሚጀምረው በሐምሌ 23 ይሆናል። ኦሊምፒክ መካሄድ የነበረበት ዘንድሮ በሐምሌ ወር ነበር። ሆኖም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ተከትሎ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሞ ነበር። ሆኖም ውድድሩን ከፈረንጆቹ 2021 ወዲያ መግፋት ስሜት የሚሰጥ ነገር አይደለም ብለዋል። በሐምሌ ወር የቶክዮ 2020 ኦሊምፒክ ሊቀመንበር ቶሺሮ ሙቶ "ውድድሮቹን በዝግ ስታዲየም ማካሄድ ይቻል ነበር። ያንን ስላልፈለግን ነው ያዘገየነው" ብለው ነበር። ምናልባት ከየአገሩ የሚመጡ ወኪሎችን ቁጥር በመቀነስ፣ በየውድድሩ የሚታደሙ ተመልካቾችን በማሳነስ፣ እንዲሁም የመክፈቻና መዝጊያ ሥነ ሥርዓቱን ቀለል በማድረግ የሚካሄድበት መንገድ ሊቀየስ ይችላል። ከመላው ዓለም 11 ሺህ አትሌቶች ከ200 አገራት እንደሚገኙ ይጠበቅ ነበር። በሚቀጥለው ዓመት ሐምሌ ላይ ውድድሩ ሲታሰብ የጉዞ ገደቦችን በተመለከተ የተባለ ነገር የለም። ሚስተር ሙቶ የኦሊምፒክ ውድድሩን ለማድረግ የኮቪድ-19 ክትባትን መጠበቅ አይኖርብንም ብለዋል። የጤና ባለሙያዎች በበኩላቸው በወረርሽኝ መሀል ክትባት ሳይኖር እንዲህ ዓይነት ውድድር ሊካሄድ አይችልም ይላሉ። "ክትባት ከተገኘ መልካም፤ ካልተገኘ ግን እሱ እስኪገኝ ኦሊምፒክ አይቆምም" ብለዋል ሊቀመንበሩ። የውድድሩ አስተባባሪ ዮሺሮ ሞሪ በሚያዝያ ወር ኦሊምፒክ በ2021 ካልተደረገ እስከናካቴው መሰረዝ ነው ያለበት ብለው ነበር። ከዚህ ቀደም የኦሎምፒክ ውድድር በጦርነት ምክንያት ሳይካሄድ ቀርቶ ያውቃል እንጂ የሚካሄድበት ጊዜ ሲገፋ ይህ በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/54053429
5sports
አሜሪካ ከኦሊምፒክ መቅረቷ ዋጋ ያስከፍላታል ስትል ቻይና አስጠነቀቀች
አሜሪካ በአውሮፓውያኑ 2022 ቤጂንግ በሚካሄደው የክረምት ኦሎምፒክ ዲፕሎማቶቿ እንደማትልክ ማስታወቋን ተከትሎ ይህ ውሳኔዋ ዋጋ ያስከፍላታል ስትል ቻይና ዛተች። የቻይና የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ዛሆ ሊጂያን ዝርዝር መረጃ ሳይሰጡ ቻይና ለአሜሪካ ውሳኔ የአጸፋ ምላሽ ትሰጣለች ሲሉ ተናግረዋል። ትናንት ሰኞ አሜሪካ ከቻይና የሰብአዊ መብት አያያዝ ጋር በተያያዘ ነው ዲፕሎማቶቿን ለኦሊምፒክ ውድድሩ እንደማትልክ ያስታወቀችው። ይህንንም ስጋቷን ለመግለፅ ምንም ዓይነት ኦፊሴላዊ ልዑካን ወደ ውድድሩ እንደማትልክ ኋይት ሃውስ አስታውቋል። ሆኖም የአሜሪካ ስፖርተኞች መወዳደር እንደሚችሉ እና የመንግሥትን ሙሉ ድጋፍ እንደሚያገኙ ተነግሯል። ከዚህ ቀደም አሜሪካ ያለመሳተፍ ውሳኔ ካስተላለፈች፣ ቻይና "ተመሳሳይ እርምጃዎችን" እንደምትወስድ ተናግራለች። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ባለፈው ወር የዲፕሎማቶች ልዑካን ላለመላክ እያሰቡ መሆኑን ተናግረዋል። የኋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ ሰኞ ክልከላውን መደረጉን አረጋግጠው አስተዳደሩ የዚህ አካል አይሆንም ብለዋል። "የአሜሪካ ዲፕሎማቶች ውድድሩ በዢንጂያንግ አስከፊ የሰብአዊ መብት ረገጣ እና ጭካኔ እየተካሄደ ባለበት ወቅት መሆኑ የተለመደው የቻይና መደበኛ እንቅስቃሴ አድርገው ይመለከቱታል። እኛ ያንን ማድረግ አንችልም" ሲሉ ገልጸዋል። ሳኪ አክለውም የአሜሪካ መንግሥት እንዳሉት "ለውድድሩ ሲዘጋጁ የነበሩ ስፖርተኞች መቅጣት ትክክለኛው እርምጃ ነው" ብሎ አያስብም። ሆኖም በውድድሩ ላይ የአሜሪካ ልዑካንን አለመላክ "ግልጽ መልዕክት ሊያስተላልፍ ይችላል" ብለዋል። "የፖለቲካ መድረክ" በዋሽንግተን ቻይና ኤምባሲ በበኩሉ የአሜሪካን ውሳኔ አስመልክቶ በሰጠው ምላሽ ድርጊቱ "የኦሊምፒክ መንፈስን በእጅጉ የሚጻረር ነው" ብሏል። "እነዚህ ሰዎች መጡ ቀሩ አይመጡ ማንንም አያሳስብም። በቤጂንግ 2022 የክረምት ኦሊምፒክ ላይም ምንም ዓይነት ተጽእኖ የለውም" ሲሉ ቃል አቀባዩ ሊዩ ፔንግዩ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። ሊዩ አክለውም ለአሜሪካ ፖለቲከኞች ምንም ግብዣ እንዳልቀረበላቸው ገልጸው "ስለዚህ ይህ 'የዲፕሎማቶች አለመሳተፍ' ከየት እንደመጣ አይታወቅም" ብለዋል። የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዣኦ ሊጂያን ከውሳኔው ቀደም ብሎ እንደተናገሩት "አሜሪካ የራሷን መንገድ ለመያዝ ካሰበች ቻይናም ተመሳሳይ እርምጃዎችን ትወስዳለች" ብለዋል ። "የክረምት ኦሊምፒክ ጨዋታዎች የፖለቲካዊ ፍላጎት መጠቀሚያ መድረክ አለመሆኑን አፅንኦት መስጠት እፈልጋለሁ" ሲሉ ዣኦ በመደበኛ ጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ ተናግረዋል ። በቻይና ማህበራዊ ድር አምባ ዌይቦ ላይ "የአሜሪካ ዲፕሎማቶች በቤጂንግ የክረምት ኦሊምፒክ ያለመሳተፍ ውሳኔ" የሚለው የፍለጋ ርዕስ ከማክሰኞ ማለዳ ጀምሮ ሳንሱር ተደርጓል። ግሎባል ታይምስ በተባለው የመንግሥት ሚዲያ ላይ ከወጣው ጽሁፍ በታች ያሉት አብዛኛዎቹ አስተያየቶች ተሰርዘዋል። ከ1 ሺህ 500 የሚጠጉ አስተያየቶች ውስጥ ስምንቱ ብቻ ናቸው ያልተነኩት። "ኦሊምፒክ የስፖርተኞች ነው። ከፖለቲከኞች ጋር ምን አገናኘው? ላለመሳተፍ ብትወስኑ የሚጎዱት የራሳችሁ ሃገር ሰዎች (ስፖርተኞችን ጨምሮ) ነው" ይላል አንዱ አስተያየት። ከአሜሪካ እና ከሌሎች ሀገራት የተወከሉ ከፍተኛ የመንግሥት ተወካዮች ብዙውን ጊዜ በኦሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ ይገኛሉ። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ቀዳማዊት እመቤት ጂል ባይደን በቶኪዮ በተካሄደው የበጋ ኦሎምፒክ የአሜሪካን ልዑካን መርተው ተገኝተዋል። አሜሪካ ውስጥ የዲፕሎማቶች አለመሳተፍ ውሳኔው በዲሞክራቲክ እና ሪፐብሊካን ህግ አውጭዎች ድጋፍ አግኝቷል። የሪፐብሊካኑ የዩታ ሴናተር ሚት ሮምኒ በትዊተር ገፃቸው እንዳስታወቁት የባይደን አስተዳደር በኦሊምፒክ የዲፕሎማቶች ተሳትፎን እንዳይኖር "መከልከሉ ማለቱ ትክክል ነው" ብለዋል። ዲሞክራቷ የምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲም ውሳኔውን አድንቀዋል። "ስፖርተኞቻችንን መደገፍ እና ማክበር ቢኖርብንም አሜሪካ እና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለእነዚህ ጨዋታዎች የእኛን ይፋዊ ድጋፍ መስጠት አንችልም። ወይም ኦሊምፒክ የዘር ማጥፋት እና ጅምላ የሰብአዊ መብት ረገጣ በሚፈጽምባት ሃገር ውስጥ መካሄዱ ምንም ችግር እንደሌለው አድርገን መቀጠል አንችልም" በማለት ፔሎሲ ተናግረዋል። አንዳንድ የዩናይትድ ስቴትስ ፖለቲከኞች ግን የዲፕሎማቶች አለመሳተፍ በቂ አይደለም ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል። ሴናተር ቶም ኮተን ውሳኔውን "ግማሽ እርምጃ" ሲሉ የገለጹ ሲሆን አስተዳደሩ በውድድሩ ላይ "ሙሉ በሙሉ አለመሳተፍ ነበረበት" ብለዋል። ቻይና በዚንጂያንግ ራስ ገዝ አስተዳደር ውስጥ በኡይግሮች እና ሌሎች አናሳ የሙስሊም ዜጎች ላይ ጭቆና እየፈጸመች ነው ስትል አሜሪካ ትከሳለች። ዩናይትድ ኪንግደም እና አውስትራሊያን ጨምሮ ሌሎች ሃገራት ተመሳሳይ እርመጃ ለመውሰድ እያሰቡ ነው ተብሏል። አሜሪካ ከዚህ ቀደም ሶቪየት አፍጋኒስታንን በመውረሯ ምክያት በአውሮፓውያኑ 1980 ውድድር ስፖርተኞቿ እንዳይሳተፉ አድርጋለች። ሶቪየት ህብረት እና አጋሮቿ በበኩላቸው በሎስ አንጀለስ የተካሄደውን ቀጣዩን የ1984ቱን የበጋ ኦሊምፒክን ሳይሳተፉ ቀሩ። አሜሪካ በአውሮፓውያኑ 2028 ኦሊምፒክን በሎስ አንጀለስ ልታዘጋጅ ሽር ጉድ እያለች ነው።
አሜሪካ ከኦሊምፒክ መቅረቷ ዋጋ ያስከፍላታል ስትል ቻይና አስጠነቀቀች አሜሪካ በአውሮፓውያኑ 2022 ቤጂንግ በሚካሄደው የክረምት ኦሎምፒክ ዲፕሎማቶቿ እንደማትልክ ማስታወቋን ተከትሎ ይህ ውሳኔዋ ዋጋ ያስከፍላታል ስትል ቻይና ዛተች። የቻይና የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ዛሆ ሊጂያን ዝርዝር መረጃ ሳይሰጡ ቻይና ለአሜሪካ ውሳኔ የአጸፋ ምላሽ ትሰጣለች ሲሉ ተናግረዋል። ትናንት ሰኞ አሜሪካ ከቻይና የሰብአዊ መብት አያያዝ ጋር በተያያዘ ነው ዲፕሎማቶቿን ለኦሊምፒክ ውድድሩ እንደማትልክ ያስታወቀችው። ይህንንም ስጋቷን ለመግለፅ ምንም ዓይነት ኦፊሴላዊ ልዑካን ወደ ውድድሩ እንደማትልክ ኋይት ሃውስ አስታውቋል። ሆኖም የአሜሪካ ስፖርተኞች መወዳደር እንደሚችሉ እና የመንግሥትን ሙሉ ድጋፍ እንደሚያገኙ ተነግሯል። ከዚህ ቀደም አሜሪካ ያለመሳተፍ ውሳኔ ካስተላለፈች፣ ቻይና "ተመሳሳይ እርምጃዎችን" እንደምትወስድ ተናግራለች። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ባለፈው ወር የዲፕሎማቶች ልዑካን ላለመላክ እያሰቡ መሆኑን ተናግረዋል። የኋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ ሰኞ ክልከላውን መደረጉን አረጋግጠው አስተዳደሩ የዚህ አካል አይሆንም ብለዋል። "የአሜሪካ ዲፕሎማቶች ውድድሩ በዢንጂያንግ አስከፊ የሰብአዊ መብት ረገጣ እና ጭካኔ እየተካሄደ ባለበት ወቅት መሆኑ የተለመደው የቻይና መደበኛ እንቅስቃሴ አድርገው ይመለከቱታል። እኛ ያንን ማድረግ አንችልም" ሲሉ ገልጸዋል። ሳኪ አክለውም የአሜሪካ መንግሥት እንዳሉት "ለውድድሩ ሲዘጋጁ የነበሩ ስፖርተኞች መቅጣት ትክክለኛው እርምጃ ነው" ብሎ አያስብም። ሆኖም በውድድሩ ላይ የአሜሪካ ልዑካንን አለመላክ "ግልጽ መልዕክት ሊያስተላልፍ ይችላል" ብለዋል። "የፖለቲካ መድረክ" በዋሽንግተን ቻይና ኤምባሲ በበኩሉ የአሜሪካን ውሳኔ አስመልክቶ በሰጠው ምላሽ ድርጊቱ "የኦሊምፒክ መንፈስን በእጅጉ የሚጻረር ነው" ብሏል። "እነዚህ ሰዎች መጡ ቀሩ አይመጡ ማንንም አያሳስብም። በቤጂንግ 2022 የክረምት ኦሊምፒክ ላይም ምንም ዓይነት ተጽእኖ የለውም" ሲሉ ቃል አቀባዩ ሊዩ ፔንግዩ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። ሊዩ አክለውም ለአሜሪካ ፖለቲከኞች ምንም ግብዣ እንዳልቀረበላቸው ገልጸው "ስለዚህ ይህ 'የዲፕሎማቶች አለመሳተፍ' ከየት እንደመጣ አይታወቅም" ብለዋል። የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዣኦ ሊጂያን ከውሳኔው ቀደም ብሎ እንደተናገሩት "አሜሪካ የራሷን መንገድ ለመያዝ ካሰበች ቻይናም ተመሳሳይ እርምጃዎችን ትወስዳለች" ብለዋል ። "የክረምት ኦሊምፒክ ጨዋታዎች የፖለቲካዊ ፍላጎት መጠቀሚያ መድረክ አለመሆኑን አፅንኦት መስጠት እፈልጋለሁ" ሲሉ ዣኦ በመደበኛ ጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ ተናግረዋል ። በቻይና ማህበራዊ ድር አምባ ዌይቦ ላይ "የአሜሪካ ዲፕሎማቶች በቤጂንግ የክረምት ኦሊምፒክ ያለመሳተፍ ውሳኔ" የሚለው የፍለጋ ርዕስ ከማክሰኞ ማለዳ ጀምሮ ሳንሱር ተደርጓል። ግሎባል ታይምስ በተባለው የመንግሥት ሚዲያ ላይ ከወጣው ጽሁፍ በታች ያሉት አብዛኛዎቹ አስተያየቶች ተሰርዘዋል። ከ1 ሺህ 500 የሚጠጉ አስተያየቶች ውስጥ ስምንቱ ብቻ ናቸው ያልተነኩት። "ኦሊምፒክ የስፖርተኞች ነው። ከፖለቲከኞች ጋር ምን አገናኘው? ላለመሳተፍ ብትወስኑ የሚጎዱት የራሳችሁ ሃገር ሰዎች (ስፖርተኞችን ጨምሮ) ነው" ይላል አንዱ አስተያየት። ከአሜሪካ እና ከሌሎች ሀገራት የተወከሉ ከፍተኛ የመንግሥት ተወካዮች ብዙውን ጊዜ በኦሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ ይገኛሉ። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ቀዳማዊት እመቤት ጂል ባይደን በቶኪዮ በተካሄደው የበጋ ኦሎምፒክ የአሜሪካን ልዑካን መርተው ተገኝተዋል። አሜሪካ ውስጥ የዲፕሎማቶች አለመሳተፍ ውሳኔው በዲሞክራቲክ እና ሪፐብሊካን ህግ አውጭዎች ድጋፍ አግኝቷል። የሪፐብሊካኑ የዩታ ሴናተር ሚት ሮምኒ በትዊተር ገፃቸው እንዳስታወቁት የባይደን አስተዳደር በኦሊምፒክ የዲፕሎማቶች ተሳትፎን እንዳይኖር "መከልከሉ ማለቱ ትክክል ነው" ብለዋል። ዲሞክራቷ የምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲም ውሳኔውን አድንቀዋል። "ስፖርተኞቻችንን መደገፍ እና ማክበር ቢኖርብንም አሜሪካ እና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለእነዚህ ጨዋታዎች የእኛን ይፋዊ ድጋፍ መስጠት አንችልም። ወይም ኦሊምፒክ የዘር ማጥፋት እና ጅምላ የሰብአዊ መብት ረገጣ በሚፈጽምባት ሃገር ውስጥ መካሄዱ ምንም ችግር እንደሌለው አድርገን መቀጠል አንችልም" በማለት ፔሎሲ ተናግረዋል። አንዳንድ የዩናይትድ ስቴትስ ፖለቲከኞች ግን የዲፕሎማቶች አለመሳተፍ በቂ አይደለም ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል። ሴናተር ቶም ኮተን ውሳኔውን "ግማሽ እርምጃ" ሲሉ የገለጹ ሲሆን አስተዳደሩ በውድድሩ ላይ "ሙሉ በሙሉ አለመሳተፍ ነበረበት" ብለዋል። ቻይና በዚንጂያንግ ራስ ገዝ አስተዳደር ውስጥ በኡይግሮች እና ሌሎች አናሳ የሙስሊም ዜጎች ላይ ጭቆና እየፈጸመች ነው ስትል አሜሪካ ትከሳለች። ዩናይትድ ኪንግደም እና አውስትራሊያን ጨምሮ ሌሎች ሃገራት ተመሳሳይ እርመጃ ለመውሰድ እያሰቡ ነው ተብሏል። አሜሪካ ከዚህ ቀደም ሶቪየት አፍጋኒስታንን በመውረሯ ምክያት በአውሮፓውያኑ 1980 ውድድር ስፖርተኞቿ እንዳይሳተፉ አድርጋለች። ሶቪየት ህብረት እና አጋሮቿ በበኩላቸው በሎስ አንጀለስ የተካሄደውን ቀጣዩን የ1984ቱን የበጋ ኦሊምፒክን ሳይሳተፉ ቀሩ። አሜሪካ በአውሮፓውያኑ 2028 ኦሊምፒክን በሎስ አንጀለስ ልታዘጋጅ ሽር ጉድ እያለች ነው።
https://www.bbc.com/amharic/news-59559003
2health
ኮሮናቫይረስ፡ እስራኤል 5ሺ የኮቪድ ክትባት ጠብታዎችን ፍልስጤማዊያን ልትሰጥ ነው
9 ሚሊዮን ሕዝቧን በሙሉ ለመከተብ በከፍተኛ ዘመቻ ላይ የሆነችው እስራኤል 5ሺ ጠብታ ክትባቶችን ለፍልስጤማዊያን አበረክታለሁ ብላለች። ሆኖም እነዚህ ክትባቶች የሚሰጡት በፍልስጤም የጤና መኮንን ለሆኑ ተጋላጭ የኅብረተሰብ ክፍሎች ብቻ ነው። እስራኤል በአሁን ሰዓት በጣም የተቀላጠፈ የክትባት ዘመቻ በማካሄድ ላይ ካሉ የዓለም አገራት ቁንጮዋ ናት። ሆኖም በዌስት ባንክና ጋዛ የሚገኙ ፍልስጤማዊያን ይህ ወግ አልደረሳቸውም። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እስራኤል በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚኖሩ ፍልስጤሞችን የመከተብ ግዴታ አለባት ሲል አሳስቧል። ሆኖም እስራኤል በመጀመርያ ይህ ግዴታ የለብኝም፤ በሁለተኛ ደረጃ ከፍልስጤም አስተዳደርም ቢሆን ጥያቄው አልቀረበልኝም ብላለች። እስራኤል 640ሺህ ዜጎች በተህዋሲው ተይዘውባት 5ሺ የሚጠጉት ሞተውባታል። ይበልጥ የተጠቁት ደግሞ በዌስት ባንክና በጋዛ 160ሺ ፍልስጤማዊያን በተህዋሲው እንደተያዙና ወደ 2ሺ የሚጠጉት እንደሞቱ ጥናቶች ያሳያሉ። እስራኤል ክትባት እያቀረበላት ካለው ፋይዘር ጋር ያላት አንዱ ስምምነት በዜጎች ጤና ላይ መረጃን ለመድኃኒት አምራቹ በየጊዜው ማቅረብ ነው። እስራኤል እስከአሁን የሕዝቧን 20 እጅ የኮቪድ ክትባት ከትባለች። ይህም በድምሩ ወደ 2 ሚሊዮን እየተጠጋ ያለ ቁጥር ነው። እነዚህ ሕዝቦቿ ታዲያ የፋይዘርን በሳምንታት ልዩነት የሚሰጠውን 2 ጠብታ ክትባት ሙሉ በሙሉ ያገኙ ዜጎች ናቸው። ከነዚህ ሌላ ደግሞ 3 ሚሊዮን ዜጎቿ የመጀመርያውን ዙር ጠብታ ማግኘት ችለዋል። አገሪቱ በክትባት ደረጃ ብዙ ርቀት ብትሄድም የእንቅስቃሴ ገደቦች አሁንም እንዳሉ ነው ያሉት። የእሰራኤል መከላከያ ሚኒስትር የሆኑት ቤኒ ጋንዝ ቢሮ እንዳረጋገጠው እስራኤል የተወሰኑ ጠብታዎቹን ወደ ፍልሥጤም አስተዳደር ታስተላልፋለች። ጠብታዎቹን ግን ፍልስጤሞች እሺ ብለው ስለመቀበል አለመቀበላቸው ያሉት ነገር የለም። በፍልስጤም ከፊል አስተዳደር ሥር የሚገኘው ዌስት ባንክም ሆነ በሐማስ አስተዳደር ሥር ያለው ጋዛ ምንም ዓይነት የክትባት ዘመቻን አልጀመሩም። የፍልስጤም ባለሥልጣናት ከመድኃኒት አቅራቢዎች ጋር ንግግር መጀመራቸው ይግለጹ እንጂ መቼ ክትባት እንደሚደርስና ለሕዝባቸው በምን መንገድ እንደሚያቀርቡ እስከአሁን ያሉት ነገር የለም። የፍልስጤም ባለሥልጣናት ተስፋ ያደረጉት የዓለም ጤና ድርጅት የሚደግፈውን ኮቫክስ የተሰኘ ፕሮጀክት ጥላ ሥር መታቀፍና ድጋፍ ማግኘትን ነው። ይህ ፕሮጀክት ድህ አገራት ክትባት እንዲያገኙ የሚያግዝ ነው። እስከአሁን ጥቂት ሩሲያ ሰራሹ ክትባት ፍልስጤም መድረሱ ቢነገርም ለማን እንደታደለ ግን የሚታወቅ ነገር የለም። በዌስት ባንክ ወደ 3 ሚሊዮን፣ በጋዛ ደግሞ ወደ 2 ሚሊዮን የሚጠጉ ፍልስጠማዊያን ይኖራሉ። ለፍልስጤሞች ክትባት የመስጠቱ ኃላፊነት የማን ነው የሚለው ጉዳይ ግን አሁንም እያነጋገረ ነው። እስራኤል በዚህ ጉዳይ ላይ ምላሽ ለመስጠት የኦስሎ ስምምነትን ትጠቅሳለች። የኦስሎ ስምምነት ዌስት ባንክና ጋዛ የፍልሥጤም አስተዳደር ሙሉ ዘላቂ ሰላም ስምምነት እስኪፈረም በጊዜያዊነት እንዲያስተዳድሩ ስለሚል የጤና ጉዳዮችንም የሚመለከተው ይህን አስተዳደር ነው ስትል ትከራከራለች። ፍልስጤሞች በበኩላቸው ይህ የኦስሎ ስምምነት አንዳች ወረርሽኝ በመጣ ጊዜ እስራኤል ለጋዛና ዌስት ባንክ ትብብር ትሰጣለች የሚል አንቀጽ እንዳለውም ይጠቅሳሉ። የተባበሩት መንግሥታት ባልደረባ ግን በግድ በተያዙ ግዛቶች ሁሉ የጄኔቫ ስምምነት ተግባራዊ እንደሚሆንና ፍልስጤሞችን የመከተቡ ኃላፊነት ሙሉ በሙሉ የእስራኤል እንደሆነ ያሰምሩበታል። የአለም አቀፍ ጉዳዮች አዋቂ የሆኑ ሰዎች በዚህ ረገድ የተለያየ አቋምን ያንጸባርቃሉ። እስራኤል አሁን የጀመረችው ሰፊ የክትባት ዘመቻ የአረብ እስራኤል ዜጎችን እንዲሁም እስራኤል በጉልበት በያዘቻቸው የምሥራቅ ኢየሩሳሌም አካባቢዎች የሚገኙ ፍልስጠማዊያንን የሚያካትት ነው።
ኮሮናቫይረስ፡ እስራኤል 5ሺ የኮቪድ ክትባት ጠብታዎችን ፍልስጤማዊያን ልትሰጥ ነው 9 ሚሊዮን ሕዝቧን በሙሉ ለመከተብ በከፍተኛ ዘመቻ ላይ የሆነችው እስራኤል 5ሺ ጠብታ ክትባቶችን ለፍልስጤማዊያን አበረክታለሁ ብላለች። ሆኖም እነዚህ ክትባቶች የሚሰጡት በፍልስጤም የጤና መኮንን ለሆኑ ተጋላጭ የኅብረተሰብ ክፍሎች ብቻ ነው። እስራኤል በአሁን ሰዓት በጣም የተቀላጠፈ የክትባት ዘመቻ በማካሄድ ላይ ካሉ የዓለም አገራት ቁንጮዋ ናት። ሆኖም በዌስት ባንክና ጋዛ የሚገኙ ፍልስጤማዊያን ይህ ወግ አልደረሳቸውም። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እስራኤል በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚኖሩ ፍልስጤሞችን የመከተብ ግዴታ አለባት ሲል አሳስቧል። ሆኖም እስራኤል በመጀመርያ ይህ ግዴታ የለብኝም፤ በሁለተኛ ደረጃ ከፍልስጤም አስተዳደርም ቢሆን ጥያቄው አልቀረበልኝም ብላለች። እስራኤል 640ሺህ ዜጎች በተህዋሲው ተይዘውባት 5ሺ የሚጠጉት ሞተውባታል። ይበልጥ የተጠቁት ደግሞ በዌስት ባንክና በጋዛ 160ሺ ፍልስጤማዊያን በተህዋሲው እንደተያዙና ወደ 2ሺ የሚጠጉት እንደሞቱ ጥናቶች ያሳያሉ። እስራኤል ክትባት እያቀረበላት ካለው ፋይዘር ጋር ያላት አንዱ ስምምነት በዜጎች ጤና ላይ መረጃን ለመድኃኒት አምራቹ በየጊዜው ማቅረብ ነው። እስራኤል እስከአሁን የሕዝቧን 20 እጅ የኮቪድ ክትባት ከትባለች። ይህም በድምሩ ወደ 2 ሚሊዮን እየተጠጋ ያለ ቁጥር ነው። እነዚህ ሕዝቦቿ ታዲያ የፋይዘርን በሳምንታት ልዩነት የሚሰጠውን 2 ጠብታ ክትባት ሙሉ በሙሉ ያገኙ ዜጎች ናቸው። ከነዚህ ሌላ ደግሞ 3 ሚሊዮን ዜጎቿ የመጀመርያውን ዙር ጠብታ ማግኘት ችለዋል። አገሪቱ በክትባት ደረጃ ብዙ ርቀት ብትሄድም የእንቅስቃሴ ገደቦች አሁንም እንዳሉ ነው ያሉት። የእሰራኤል መከላከያ ሚኒስትር የሆኑት ቤኒ ጋንዝ ቢሮ እንዳረጋገጠው እስራኤል የተወሰኑ ጠብታዎቹን ወደ ፍልሥጤም አስተዳደር ታስተላልፋለች። ጠብታዎቹን ግን ፍልስጤሞች እሺ ብለው ስለመቀበል አለመቀበላቸው ያሉት ነገር የለም። በፍልስጤም ከፊል አስተዳደር ሥር የሚገኘው ዌስት ባንክም ሆነ በሐማስ አስተዳደር ሥር ያለው ጋዛ ምንም ዓይነት የክትባት ዘመቻን አልጀመሩም። የፍልስጤም ባለሥልጣናት ከመድኃኒት አቅራቢዎች ጋር ንግግር መጀመራቸው ይግለጹ እንጂ መቼ ክትባት እንደሚደርስና ለሕዝባቸው በምን መንገድ እንደሚያቀርቡ እስከአሁን ያሉት ነገር የለም። የፍልስጤም ባለሥልጣናት ተስፋ ያደረጉት የዓለም ጤና ድርጅት የሚደግፈውን ኮቫክስ የተሰኘ ፕሮጀክት ጥላ ሥር መታቀፍና ድጋፍ ማግኘትን ነው። ይህ ፕሮጀክት ድህ አገራት ክትባት እንዲያገኙ የሚያግዝ ነው። እስከአሁን ጥቂት ሩሲያ ሰራሹ ክትባት ፍልስጤም መድረሱ ቢነገርም ለማን እንደታደለ ግን የሚታወቅ ነገር የለም። በዌስት ባንክ ወደ 3 ሚሊዮን፣ በጋዛ ደግሞ ወደ 2 ሚሊዮን የሚጠጉ ፍልስጠማዊያን ይኖራሉ። ለፍልስጤሞች ክትባት የመስጠቱ ኃላፊነት የማን ነው የሚለው ጉዳይ ግን አሁንም እያነጋገረ ነው። እስራኤል በዚህ ጉዳይ ላይ ምላሽ ለመስጠት የኦስሎ ስምምነትን ትጠቅሳለች። የኦስሎ ስምምነት ዌስት ባንክና ጋዛ የፍልሥጤም አስተዳደር ሙሉ ዘላቂ ሰላም ስምምነት እስኪፈረም በጊዜያዊነት እንዲያስተዳድሩ ስለሚል የጤና ጉዳዮችንም የሚመለከተው ይህን አስተዳደር ነው ስትል ትከራከራለች። ፍልስጤሞች በበኩላቸው ይህ የኦስሎ ስምምነት አንዳች ወረርሽኝ በመጣ ጊዜ እስራኤል ለጋዛና ዌስት ባንክ ትብብር ትሰጣለች የሚል አንቀጽ እንዳለውም ይጠቅሳሉ። የተባበሩት መንግሥታት ባልደረባ ግን በግድ በተያዙ ግዛቶች ሁሉ የጄኔቫ ስምምነት ተግባራዊ እንደሚሆንና ፍልስጤሞችን የመከተቡ ኃላፊነት ሙሉ በሙሉ የእስራኤል እንደሆነ ያሰምሩበታል። የአለም አቀፍ ጉዳዮች አዋቂ የሆኑ ሰዎች በዚህ ረገድ የተለያየ አቋምን ያንጸባርቃሉ። እስራኤል አሁን የጀመረችው ሰፊ የክትባት ዘመቻ የአረብ እስራኤል ዜጎችን እንዲሁም እስራኤል በጉልበት በያዘቻቸው የምሥራቅ ኢየሩሳሌም አካባቢዎች የሚገኙ ፍልስጠማዊያንን የሚያካትት ነው።
https://www.bbc.com/amharic/news-55883434
5sports
የኳስ ሃሜት፡ 'ምባፔ ከፈረንሳይ ለመውጣት የቤተሰብ ፈቃድ ያስፈልገዋል'
እሁድ እንደመሆኑ የእግር ኳስ ዓለም ምን እያለ ነው የሚለውን እናስቃኛችሁ። የፈረንሳዩ የ21 ዓመት እግር ኳሰኛ ኪሊያን ምባፔ በአንጋፋ የአውሮፓ ክለቦች እየተፈለገ ነው። ለፓሪስ ሰይንት ዠርሜይን የሚጫወተው ወጣቱ ምባፔ ግን ክለቡን ሊለቅ የሚችለው ከቤተሰብ ፈቃድ ካገኘ ነው ሲል ሰን የተሰኘው ጋዜጣ በእሁድ ዕትሙ አስነብቧል። ዩቬንቱስ፡ ወደ ጣልያን ስናቀና አሮጊቶቹ ዩቬንቱሶች የማንቸስተር ዩናይትዱን አማካይ ፖል ፖግባ በሚቀጥለው ጥር በውል ለማስፈረም አቅደዋል ያለው ሚረር ነው። ዩናይትድ ፖግባን ለዩቬንቱስ ሰጥቶ በምትኩ ብራዚላዊው የክንፍ ተጫዋች ዳግላስ ኮስታና ከባርሴሎና በውሰት ዩቬንቱስ የሚገኘው ሚራለም ፒያንቺን እንዲወሰድ የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል ብሎ ያተመው ደግሞ ካልቺዮ መርካቶ ነው። ዶርትመንድ፡ የቦሩሲያ ዶርትመንድ ቀንደኛ አጥቂ የሆነው የ20 ዓመቱ ኧርሊንግ አላንድ አባት አልፍ-ኢንግ ልጃቸው አሁን በዶርትመንድ ደስተኛ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ነገር ግን ወደፊት ክለብ ሊቀይር ይችላል ይላሉ። አልፍ-ኢንግ ለእንግሊዙ ሊድስ ተከላካይ ሆነው ተጫውተዋል። ይህ ወሬ የተገኘው ከጣልያኑ ቱቶስፖርት ጋዜጣ ነው። አርሴናል፡ የአርሴናሉ አሠልጣኝ ማይክል አርቴታ የ32 ዓመቱ ጀርመናዊ አማካይ ሜሱት ኦዚል የኮንትራት ውሉ ከመገባደዱ በፊት ለክለቡ ሊጫወት ይችላል ብሏል ያለው ስታር ነው። ኦዚል ከአርቴታ ጋር ባለመጣጣሙ ምክንያት ከቡድኑ መቀነሱ ይታወሳል። ኮንትራቱ ሳይጠናቀቅ ወደ ሌላ ክለብ ሊዘዋወር ይችላል የሚሉ ወሬዎች እየተሰሙ ነው። ዎልቭስ፡ ዎልቨርሃምፕተን ዎንደረርስ የ23 ዓመቱን የማንቸስተር ሲቲ ተጫዋች ኦልክሳንደር በ19 ሚሊዮን ዩሮ ለማስፈረም የነበራቸው ተስፋ ጨልሟል። ነገር ግን በሚቀጥለው ጥር ሌላ ጥያቄ ያቀርባሉ ሲል ስታር ጋዜጣ በእሁድ ዕትሙ አስነብቧል። ቶተንሃም፡ የቶተንሃም ሆትስፐርስ ሊቀ መንበር ዳኒኤል ሌቪ እንግሊዛዊው ዴሊ አሊ ክለቡን ለቆ እንዳይወጣ የ18 ወራት ገደብ ሊጥሉበት ነው ብሏል 90ሚን የተሰኘው የስፖርት ጋዜጣ። አሊ ከቶተንሃም ጋር ያለው ኮንትራት ከመጠናቀቁ በፊት ወደ ፓሪስ ሴይንት ዠርሜይን ሊያመራ ይችላል የሚሉ ወሬዎች አሉ። ዩናይትድ፡ የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ አሠልጣኝ ሉዊስ ቫን ሃል የኔዘርላንዱ አማካይ ቫን ደ ቢክ ዩናይትድን መቀላቀሉ ትክክለኛ ውሳኔ አልነበረም ብለዋል ያለው ደግሞ በደች ቋንቋ የሚታተመው ዚጎ ስፖርት ነው። ቼልሲ፡ ሰማያዊዎቹ ግብ ጠባቂያቸው ኬፓ አሪዛባላጋን የሚገዛ አጥተዋል እየተባለ ነው። ወሬው የሰንደይ ኤክስፕረስ ነው። ቼልሲ ኬፓን ለመሸጥ ቢያቅዱም ገዥ አልተገኘም። ከኬፓ ሌላ የ29 ዓመቱ ስፔናዊ ማርኮስ አሎንሶን የሚፈልገው ክለብ ጠፍቷል ተብሏል። ኬፓ በእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ታሪክ ውዱ በረኛ ቢሆንም ከቼልሲዎች ልብ ወጥቷል። በሌሎች ወሬዎች ዌስትብሮም የኒውካስትሉን ድዋይት ጌይል ለመግዛት ዕቅድ ላይ መሆናቸው፤ አርሴናል ደግሞ ዊሊያም ሳሊባን ከገዛ ዓመት ሳይሆን ለሽያጭ ሊያቀርብ መሆኑ ተሰምቷል። ሊቨርፑል ደግሞ ለገና በዓል ለወትሮው የሚደረገውን የምሳ ግብዣ ዘንድሮ በኮቪድ-19 ምክንያት እንደማይኖር ዩርገን ክሎፕ አሳውቀዋል።
የኳስ ሃሜት፡ 'ምባፔ ከፈረንሳይ ለመውጣት የቤተሰብ ፈቃድ ያስፈልገዋል' እሁድ እንደመሆኑ የእግር ኳስ ዓለም ምን እያለ ነው የሚለውን እናስቃኛችሁ። የፈረንሳዩ የ21 ዓመት እግር ኳሰኛ ኪሊያን ምባፔ በአንጋፋ የአውሮፓ ክለቦች እየተፈለገ ነው። ለፓሪስ ሰይንት ዠርሜይን የሚጫወተው ወጣቱ ምባፔ ግን ክለቡን ሊለቅ የሚችለው ከቤተሰብ ፈቃድ ካገኘ ነው ሲል ሰን የተሰኘው ጋዜጣ በእሁድ ዕትሙ አስነብቧል። ዩቬንቱስ፡ ወደ ጣልያን ስናቀና አሮጊቶቹ ዩቬንቱሶች የማንቸስተር ዩናይትዱን አማካይ ፖል ፖግባ በሚቀጥለው ጥር በውል ለማስፈረም አቅደዋል ያለው ሚረር ነው። ዩናይትድ ፖግባን ለዩቬንቱስ ሰጥቶ በምትኩ ብራዚላዊው የክንፍ ተጫዋች ዳግላስ ኮስታና ከባርሴሎና በውሰት ዩቬንቱስ የሚገኘው ሚራለም ፒያንቺን እንዲወሰድ የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል ብሎ ያተመው ደግሞ ካልቺዮ መርካቶ ነው። ዶርትመንድ፡ የቦሩሲያ ዶርትመንድ ቀንደኛ አጥቂ የሆነው የ20 ዓመቱ ኧርሊንግ አላንድ አባት አልፍ-ኢንግ ልጃቸው አሁን በዶርትመንድ ደስተኛ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ነገር ግን ወደፊት ክለብ ሊቀይር ይችላል ይላሉ። አልፍ-ኢንግ ለእንግሊዙ ሊድስ ተከላካይ ሆነው ተጫውተዋል። ይህ ወሬ የተገኘው ከጣልያኑ ቱቶስፖርት ጋዜጣ ነው። አርሴናል፡ የአርሴናሉ አሠልጣኝ ማይክል አርቴታ የ32 ዓመቱ ጀርመናዊ አማካይ ሜሱት ኦዚል የኮንትራት ውሉ ከመገባደዱ በፊት ለክለቡ ሊጫወት ይችላል ብሏል ያለው ስታር ነው። ኦዚል ከአርቴታ ጋር ባለመጣጣሙ ምክንያት ከቡድኑ መቀነሱ ይታወሳል። ኮንትራቱ ሳይጠናቀቅ ወደ ሌላ ክለብ ሊዘዋወር ይችላል የሚሉ ወሬዎች እየተሰሙ ነው። ዎልቭስ፡ ዎልቨርሃምፕተን ዎንደረርስ የ23 ዓመቱን የማንቸስተር ሲቲ ተጫዋች ኦልክሳንደር በ19 ሚሊዮን ዩሮ ለማስፈረም የነበራቸው ተስፋ ጨልሟል። ነገር ግን በሚቀጥለው ጥር ሌላ ጥያቄ ያቀርባሉ ሲል ስታር ጋዜጣ በእሁድ ዕትሙ አስነብቧል። ቶተንሃም፡ የቶተንሃም ሆትስፐርስ ሊቀ መንበር ዳኒኤል ሌቪ እንግሊዛዊው ዴሊ አሊ ክለቡን ለቆ እንዳይወጣ የ18 ወራት ገደብ ሊጥሉበት ነው ብሏል 90ሚን የተሰኘው የስፖርት ጋዜጣ። አሊ ከቶተንሃም ጋር ያለው ኮንትራት ከመጠናቀቁ በፊት ወደ ፓሪስ ሴይንት ዠርሜይን ሊያመራ ይችላል የሚሉ ወሬዎች አሉ። ዩናይትድ፡ የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ አሠልጣኝ ሉዊስ ቫን ሃል የኔዘርላንዱ አማካይ ቫን ደ ቢክ ዩናይትድን መቀላቀሉ ትክክለኛ ውሳኔ አልነበረም ብለዋል ያለው ደግሞ በደች ቋንቋ የሚታተመው ዚጎ ስፖርት ነው። ቼልሲ፡ ሰማያዊዎቹ ግብ ጠባቂያቸው ኬፓ አሪዛባላጋን የሚገዛ አጥተዋል እየተባለ ነው። ወሬው የሰንደይ ኤክስፕረስ ነው። ቼልሲ ኬፓን ለመሸጥ ቢያቅዱም ገዥ አልተገኘም። ከኬፓ ሌላ የ29 ዓመቱ ስፔናዊ ማርኮስ አሎንሶን የሚፈልገው ክለብ ጠፍቷል ተብሏል። ኬፓ በእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ታሪክ ውዱ በረኛ ቢሆንም ከቼልሲዎች ልብ ወጥቷል። በሌሎች ወሬዎች ዌስትብሮም የኒውካስትሉን ድዋይት ጌይል ለመግዛት ዕቅድ ላይ መሆናቸው፤ አርሴናል ደግሞ ዊሊያም ሳሊባን ከገዛ ዓመት ሳይሆን ለሽያጭ ሊያቀርብ መሆኑ ተሰምቷል። ሊቨርፑል ደግሞ ለገና በዓል ለወትሮው የሚደረገውን የምሳ ግብዣ ዘንድሮ በኮቪድ-19 ምክንያት እንደማይኖር ዩርገን ክሎፕ አሳውቀዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-55292812
3politics
በጋምቤላ በተፈጸመው ጥቃት ቢያንስ 40 ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች ቆሰሉ
በጋምቤላ ከተማ ታጣቂ ቡድኖች የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ ከ40 በላይ ሰዎች መገደላቸውን በክልሉ የተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ የሚገኙ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለቢቢሲ ተናገሩ። የክልሉ መስተዳደር የኦነግ-ሸኔ እና የጋምቤላ ነጻነት ግንባር ታጣቂዎች ናቸው ያላቸው ኃይሎች ማክሰኞ ሰኔ 07/2014 ዓ.ም. ማለዳ ላይ በዋና ከተማዋ ውስጥ ጥቃት ከፍተው ለሰዓታት የቆየ የተኩስ ልውውጥ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር መካሄዱን ነዋሪዎች ገልጸዋል። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ አንድ የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣን ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት ጥቃቱን ተከትሎ ከ40 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ገልጸው፤ ከዚህ ውስጥ 10ሩ የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ የታጣቂው ኃይሉ አባላት ናቸው ብለዋል። ሌላ ባለሥልጣን በተመሳሳይ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከአርባ እንደሚልቅ ገልጸው ከመካከላቸውም ሁለት ሰላማዊ ሰዎች እንዲሁም 11 የፀጥታ ኃይል አባላት መሞታቸውንና ቀሪዎቹ ጥቃቱን የፈጸሙት ታጠቂዎች ናቸው ብለዋል። ጨምረውም የፀጥታ ኃይሉ በጫካ ውስጥና በተለያዩ ስፍራዎች አሰሳ እያካሄደ በመሆኑ፣ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ሊጨምር ስለሚችል ትክክለኛውን አሃዝ አሁን ማወቅ አስቸጋሪ ነው ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በጥቃቱ ሕይወታቸው ከጠፋው ሰዎች በተጨማሪ 36 ሰዎች ደግሞ የመቁሰል ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና እያገኙ መሆናቸውን ባለሥልጣኑ አመልከተዋል። ትናንት በከተማዋ ላይ የተከፈተው ጥቃት በተለይ በክልሉ ምክር ቤት እና በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ጽህፈት ቤት አካባቢ ላይ አትኩሮ የነበረ በመሆኑ፣ ቁልፍ የክልሉን ተቋማት ለመቆጣጠር ያለመ ይመስል እንደነበር ቢቢሲ ያነጋገራቸው የክልሉ ባለሥልጣንና ነዋሪ ተናግረው ነበር። ታጣቂዎቹ የጋምቤላ ከተማን ከፊል ተቆጣጥረው እንደነበረና እስከ እኩለ ቀን ድረስ በዘለቀው የተኩስ ልውውጥ በርካታ የታጣቂው ቡድን አባላት መገደላቸው ተነግሯል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ማክሰኞ አመሻሽ ላይ በሰጡት መግለጫ ላይም የፀጥታ ኃይሉ በወሰደው እርምጃ በታጣቂዎቹ ላይ “ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ መድረሱን፣ በወገን ጦር ላይም መጠነኛ ጉዳት መድረሱን” ተናግረዋል። የከተማው ነዋሪዎች ለቢቢሲ እንደተናገሩትና በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተሰራጩ ምስሎች እንዳሳዩት በርካታ የታጠቂው ቡድን አባላት ናቸው የተባሉ አስከሬኖች በጋምቤላ ከተማ መንገዶች ላይ ታይተዋል። ዛሬ ረቡዕ ረፋድ ላይ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪ እንደሚሉትም፣ ከተማዋ ሰላም መሆኗንና ከጠዋት ጀምሮ በመንገዶች ላይ ወድቀው የነበሩ አሰከሬኖች እየተሰበሰቡ ናቸው። ነገር ግን ከጥቃቱ ጋር ተያይዞ ማክሰኞ ዕለት ተዘግተው የዋሉት የመንግሥት ተቋማት እና የግል የሥራ እንቅስቃሴዎች መልሰው እንዳልተጀመሩ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገልጸዋል። ከማክሰኞ ዕኩለ ቀን በኋላ በከተማዋ ውስጥ የተኩስ ድምጾች መቆሙን፣ ነገር ግን ከከተማው ወጣ ባሉ አካባቢዎች አሁንም የተኩስ ድምጽ አልፎ አልፎ እንደሚሰማ ተናግረዋል። ማለዳ ላይ በድንገት ጥቃት ከፍተው የነበሩት ታጣቂዎቹ በርከት ያለውን የጋምቤላ ከተማን ክፍሎች ለመቆጣጠር ችለው የነበረ ሲሆን፣ የክልሉ የፀጥታ ኃይል በወሰደው እርምጃ ረፋድ ላይ ታጣቂዎቹን ከአብዛኛው የከተማዋ ክፍሎች ለማስወጣት መቻሉን ነዋሪዎች ለቢበሲ ተናግረው ነበር። የክልሉ መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ማክሰኞ አመሻሽ ላይ በሰጡት መግለጫ “የክልሉ የፀጥታ ኃይሎች ባካሄዱት ቅንጅታዊ ማጥቃት ከተማዋን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር እንደቻሉ” ገልጸዋል። መንግሥት በሽብርተኛ ቡድንነት የፈረጀው እና ሸኔ በሚል የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ ዓለም አቀፍ የሕዝብ ግንኙነት እንደሆነ የሚነገረው ኦዳ ተርቢ፣ በትዊተር ገጹ ላይ የቡድኑ ታጣቂዎች ከጋምቤላ ነጻነት ግንባር ጋር ተቀናጅተው ጥቃት መፈጸማቸውን አረጋግጧል። ማክሰኞ ዕለት በጋምቤላ ከተማ ውስጥ የተከሰተውን ጥቃት በተመለከተ የፌደራል መንግሥት አስካሁን በይፋ ያለው ነገር የለም። ከደቡብ ሱዳን ጋር በሚዋሰነው የምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሆነው የጋምቤላ ክልል ታጣቂዎች ከሚንቀሳቀሱባቸው የምዕራብ ኦሮሚያ እና የከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ጋር ይዋሰናል።
በጋምቤላ በተፈጸመው ጥቃት ቢያንስ 40 ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች ቆሰሉ በጋምቤላ ከተማ ታጣቂ ቡድኖች የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ ከ40 በላይ ሰዎች መገደላቸውን በክልሉ የተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ የሚገኙ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለቢቢሲ ተናገሩ። የክልሉ መስተዳደር የኦነግ-ሸኔ እና የጋምቤላ ነጻነት ግንባር ታጣቂዎች ናቸው ያላቸው ኃይሎች ማክሰኞ ሰኔ 07/2014 ዓ.ም. ማለዳ ላይ በዋና ከተማዋ ውስጥ ጥቃት ከፍተው ለሰዓታት የቆየ የተኩስ ልውውጥ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር መካሄዱን ነዋሪዎች ገልጸዋል። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ አንድ የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣን ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት ጥቃቱን ተከትሎ ከ40 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ገልጸው፤ ከዚህ ውስጥ 10ሩ የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ የታጣቂው ኃይሉ አባላት ናቸው ብለዋል። ሌላ ባለሥልጣን በተመሳሳይ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከአርባ እንደሚልቅ ገልጸው ከመካከላቸውም ሁለት ሰላማዊ ሰዎች እንዲሁም 11 የፀጥታ ኃይል አባላት መሞታቸውንና ቀሪዎቹ ጥቃቱን የፈጸሙት ታጠቂዎች ናቸው ብለዋል። ጨምረውም የፀጥታ ኃይሉ በጫካ ውስጥና በተለያዩ ስፍራዎች አሰሳ እያካሄደ በመሆኑ፣ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ሊጨምር ስለሚችል ትክክለኛውን አሃዝ አሁን ማወቅ አስቸጋሪ ነው ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በጥቃቱ ሕይወታቸው ከጠፋው ሰዎች በተጨማሪ 36 ሰዎች ደግሞ የመቁሰል ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና እያገኙ መሆናቸውን ባለሥልጣኑ አመልከተዋል። ትናንት በከተማዋ ላይ የተከፈተው ጥቃት በተለይ በክልሉ ምክር ቤት እና በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ጽህፈት ቤት አካባቢ ላይ አትኩሮ የነበረ በመሆኑ፣ ቁልፍ የክልሉን ተቋማት ለመቆጣጠር ያለመ ይመስል እንደነበር ቢቢሲ ያነጋገራቸው የክልሉ ባለሥልጣንና ነዋሪ ተናግረው ነበር። ታጣቂዎቹ የጋምቤላ ከተማን ከፊል ተቆጣጥረው እንደነበረና እስከ እኩለ ቀን ድረስ በዘለቀው የተኩስ ልውውጥ በርካታ የታጣቂው ቡድን አባላት መገደላቸው ተነግሯል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ማክሰኞ አመሻሽ ላይ በሰጡት መግለጫ ላይም የፀጥታ ኃይሉ በወሰደው እርምጃ በታጣቂዎቹ ላይ “ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ መድረሱን፣ በወገን ጦር ላይም መጠነኛ ጉዳት መድረሱን” ተናግረዋል። የከተማው ነዋሪዎች ለቢቢሲ እንደተናገሩትና በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተሰራጩ ምስሎች እንዳሳዩት በርካታ የታጠቂው ቡድን አባላት ናቸው የተባሉ አስከሬኖች በጋምቤላ ከተማ መንገዶች ላይ ታይተዋል። ዛሬ ረቡዕ ረፋድ ላይ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪ እንደሚሉትም፣ ከተማዋ ሰላም መሆኗንና ከጠዋት ጀምሮ በመንገዶች ላይ ወድቀው የነበሩ አሰከሬኖች እየተሰበሰቡ ናቸው። ነገር ግን ከጥቃቱ ጋር ተያይዞ ማክሰኞ ዕለት ተዘግተው የዋሉት የመንግሥት ተቋማት እና የግል የሥራ እንቅስቃሴዎች መልሰው እንዳልተጀመሩ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገልጸዋል። ከማክሰኞ ዕኩለ ቀን በኋላ በከተማዋ ውስጥ የተኩስ ድምጾች መቆሙን፣ ነገር ግን ከከተማው ወጣ ባሉ አካባቢዎች አሁንም የተኩስ ድምጽ አልፎ አልፎ እንደሚሰማ ተናግረዋል። ማለዳ ላይ በድንገት ጥቃት ከፍተው የነበሩት ታጣቂዎቹ በርከት ያለውን የጋምቤላ ከተማን ክፍሎች ለመቆጣጠር ችለው የነበረ ሲሆን፣ የክልሉ የፀጥታ ኃይል በወሰደው እርምጃ ረፋድ ላይ ታጣቂዎቹን ከአብዛኛው የከተማዋ ክፍሎች ለማስወጣት መቻሉን ነዋሪዎች ለቢበሲ ተናግረው ነበር። የክልሉ መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ማክሰኞ አመሻሽ ላይ በሰጡት መግለጫ “የክልሉ የፀጥታ ኃይሎች ባካሄዱት ቅንጅታዊ ማጥቃት ከተማዋን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር እንደቻሉ” ገልጸዋል። መንግሥት በሽብርተኛ ቡድንነት የፈረጀው እና ሸኔ በሚል የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ ዓለም አቀፍ የሕዝብ ግንኙነት እንደሆነ የሚነገረው ኦዳ ተርቢ፣ በትዊተር ገጹ ላይ የቡድኑ ታጣቂዎች ከጋምቤላ ነጻነት ግንባር ጋር ተቀናጅተው ጥቃት መፈጸማቸውን አረጋግጧል። ማክሰኞ ዕለት በጋምቤላ ከተማ ውስጥ የተከሰተውን ጥቃት በተመለከተ የፌደራል መንግሥት አስካሁን በይፋ ያለው ነገር የለም። ከደቡብ ሱዳን ጋር በሚዋሰነው የምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሆነው የጋምቤላ ክልል ታጣቂዎች ከሚንቀሳቀሱባቸው የምዕራብ ኦሮሚያ እና የከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ጋር ይዋሰናል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cpe11842gy7o
3politics
ትራምፕ 'ትሩዝ ሶሻል' የተባለ አዲስ ማኅበራዊ ሚዲያ ሊመሠርቱ ነው
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ 'ትሩዝ ሶሻል' የተባለ አዲስ ማኅበራዊ ሚዲያ ሊመሠርቱ መሆኑን አስታወቁ። ትራምፕ ማኅበራዊ ሚዲያው በአሜሪካ የተቃዋሚ ድምጾችን ዝም በማሰኘት የሚታወቁ "ታላላቅ የቴክኖሎጂ ጭቆና ያስቆማል" ብለዋል። ትራምፕ የሚመሩት ትራምፕ ሚዲያ እና ቴክኖሎጂ ቡድን (ቲኤምቲጂ) በደንበኝነት ምዝገባ ቪዲዮ-በፍላጎት የሚሰጥ አገልግሎት ለማስጀመር አስቧል። በጥር ወር ደጋፊዎቻቸው የአሜሪካን ምክር ቤት ህንጻን ካፒቶል ሂልን በመውረራቸው ምክንያት ትራምፕ እንደ ትዊተር እና ፌስቡክ ካሉ ታዋቂ የማኅበራዊ ሚዲያ ትስስር መድረኮች በጊዜያዊነት ወይም በቋሚነት ታግደዋል። እሳቸው እና አማካሪዎቻቸው ከዚያ በኋላ ተፎካካሪ የማኅበራዊ ሚዲያ ለመፍጠር ስለማቀዳቸው ፍንጭ ሰጥተዋል። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ 'ከዶናልድ ጄ ትራምፕ ዴስክ' የሚባል ድረ-ገጽ ጀምረው ነበር። ድረ-ገጹ ከተጀመረ ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ እስከወዲያኛው ተዘግቷል። በቲኤምቲጂ መግለጫ መሠረት 'ትሩዝ ሶሻል' በሚቀጥለው ወር ለተመረጡ ሰዎች ብቻ ክፍት ሆኖ በአውሮፓውያኑ 2022 የመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት ደግሞ በአገር አቀፍ ደረጃ ይለቀቃል ተብሏል። ትራምፕ "ታሊባን በትዊተር ላይ ትልቅ ቦታ ኖሮት ተወዳጁ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዝም እንዲል በተደረገበት ዓለም ውስጥ እየኖርን ነው" ሲሉ ጽፈዋል። "ሁሉም ሰው ለምን ትልልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን አትገዳደሩም ብሎ ይጠይቀኛል? ደህና፣ በቅርቡ ይሆናለን!" በማለት አክለዋል። አዲሱ ኩባንያ የሚሠራ ገጽ እንዳለው የሚጠቁም ነገር የለም። ትራምፕ ትዊተር ወይም ፌስቡክን የሚገዳደር መድረክ መፍጠር ቢፈልጉም ያ ግን በቀላሉ የሚሳካ አይመስልም። ቲኤምቲጂ በፍላጎት መሠረት የሚሠራው የቪዲዮ አገልግሎት የመዝናኛ ፕሮግራምን፣ ዜናዎችን፣ ፖድካስቶችን እና ሌሎችንም ያሳያል ተብሏል። ኩባንያው በናስዳክ የአክሲዮን ላይ ከተዘረዘረው ከስፔክ ጋር ለመዋሃድ አስቧል። ትራምፕ አዲስ ማኅበራዊ ሚዲያ ይፋ የተደረገው የቀድሞው ረዳታቸው ጄሰን ሚለር 'ጌትር' የተባለ ሌላ የማኅበራዊ ሚዲያ ከጀመረ ከወራት በኋላ ነው።
ትራምፕ 'ትሩዝ ሶሻል' የተባለ አዲስ ማኅበራዊ ሚዲያ ሊመሠርቱ ነው የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ 'ትሩዝ ሶሻል' የተባለ አዲስ ማኅበራዊ ሚዲያ ሊመሠርቱ መሆኑን አስታወቁ። ትራምፕ ማኅበራዊ ሚዲያው በአሜሪካ የተቃዋሚ ድምጾችን ዝም በማሰኘት የሚታወቁ "ታላላቅ የቴክኖሎጂ ጭቆና ያስቆማል" ብለዋል። ትራምፕ የሚመሩት ትራምፕ ሚዲያ እና ቴክኖሎጂ ቡድን (ቲኤምቲጂ) በደንበኝነት ምዝገባ ቪዲዮ-በፍላጎት የሚሰጥ አገልግሎት ለማስጀመር አስቧል። በጥር ወር ደጋፊዎቻቸው የአሜሪካን ምክር ቤት ህንጻን ካፒቶል ሂልን በመውረራቸው ምክንያት ትራምፕ እንደ ትዊተር እና ፌስቡክ ካሉ ታዋቂ የማኅበራዊ ሚዲያ ትስስር መድረኮች በጊዜያዊነት ወይም በቋሚነት ታግደዋል። እሳቸው እና አማካሪዎቻቸው ከዚያ በኋላ ተፎካካሪ የማኅበራዊ ሚዲያ ለመፍጠር ስለማቀዳቸው ፍንጭ ሰጥተዋል። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ 'ከዶናልድ ጄ ትራምፕ ዴስክ' የሚባል ድረ-ገጽ ጀምረው ነበር። ድረ-ገጹ ከተጀመረ ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ እስከወዲያኛው ተዘግቷል። በቲኤምቲጂ መግለጫ መሠረት 'ትሩዝ ሶሻል' በሚቀጥለው ወር ለተመረጡ ሰዎች ብቻ ክፍት ሆኖ በአውሮፓውያኑ 2022 የመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት ደግሞ በአገር አቀፍ ደረጃ ይለቀቃል ተብሏል። ትራምፕ "ታሊባን በትዊተር ላይ ትልቅ ቦታ ኖሮት ተወዳጁ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዝም እንዲል በተደረገበት ዓለም ውስጥ እየኖርን ነው" ሲሉ ጽፈዋል። "ሁሉም ሰው ለምን ትልልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን አትገዳደሩም ብሎ ይጠይቀኛል? ደህና፣ በቅርቡ ይሆናለን!" በማለት አክለዋል። አዲሱ ኩባንያ የሚሠራ ገጽ እንዳለው የሚጠቁም ነገር የለም። ትራምፕ ትዊተር ወይም ፌስቡክን የሚገዳደር መድረክ መፍጠር ቢፈልጉም ያ ግን በቀላሉ የሚሳካ አይመስልም። ቲኤምቲጂ በፍላጎት መሠረት የሚሠራው የቪዲዮ አገልግሎት የመዝናኛ ፕሮግራምን፣ ዜናዎችን፣ ፖድካስቶችን እና ሌሎችንም ያሳያል ተብሏል። ኩባንያው በናስዳክ የአክሲዮን ላይ ከተዘረዘረው ከስፔክ ጋር ለመዋሃድ አስቧል። ትራምፕ አዲስ ማኅበራዊ ሚዲያ ይፋ የተደረገው የቀድሞው ረዳታቸው ጄሰን ሚለር 'ጌትር' የተባለ ሌላ የማኅበራዊ ሚዲያ ከጀመረ ከወራት በኋላ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/news-58964348
5sports
ሴሬና ዊሊያምስ ከሜዳ ቴኒስ ከመገለሏ በፊት የምታደርገውን ውድድር በድል ጀመረች
ሴሬና ዊልያምስ በኒውዮርክ በተስፋ እና በፈንጠዝያ በተሞላው አዝናኝ ምሽት መሰናበቻዋ የሆነውን የየዩኤስ ኦፕን ውድድርን በድል ጀመረች። ከውድድሩ በኋላ ከሜዳ ቴኒስ የምትርቀው ዊሊያምስ የሞንቴኔግሮዋን ዳንካ ኮቪኒችብ 6-3 እና 6-3 አሸንፋለች። በአርተር አሼ ስታዲየም የተገኙት 25 ሺህ ተመልካቾች ለኮከቧ ያላቸውን ከብር የገለጹ ሲሆን እና እሷም በተለመደው መንገድ ምላሽ ሰጥታለች። የ40 ዓመቷ ዊሊያምስ ረቡዕ ዕለት በሚደረገው የሁለተኛው ዙር ጨዋታ ከኢስቶኒያዋ አኔት ኮንታቬይት ጋር ትጫወታለች። የ23 ጊዜ የግራንድ ስላም አሸናፊዋ ሴሬና በአውስትራሊያዋ ማርጋሬት ኮርት የተያዘውን ክብረወሰን ለመጋራት አንድ ድል ብቻ ይቀራታል። ከታላቅ እህቷ ቬኑስ ጋር በጥንዶች ውድድር እየተሳተፈች ትገኛለች። በዚህም ስንብት ውድድሯን ለማራዘም ያለመች ይመስላል። ጉዞዋንም 80ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችውን ኮቪኒችን በማሸነፍ ጀምራለች። ከተመልካቾች ከፍተኛ ድጋፍ ያገኘችው ሴሬና የደጋፊዎች ሁኔታ ውሳኔዋ ላይ ተጽዕኖ እንዳለቸው “አሁንም በጣም ከባድ ነው ምክንያቱም እዚያ መገኘትን በጣም እወደዋለሁ” ስትል ትገልጻለች። "ብዙ ውድድሮችን በተጫወትኩ ቁጥር ብዙ መሳተፍ እንደምችል ይሰማኛል።  የበለጠ በተጫወትኩት ቁጥር የበለጠ ማንጸባረቅ እንደምችል ማሰብ በጣም ከባድ ነው።“ "ነገር ግን ወደ ቀጣዩ ነገር ለመሸጋገር ጊዜው አሁን ነው። ማድረግ የምፈልጋቸው ሌሎች ብዙ ነገሮች ስላሉ አስፈላጊ ይመስለኛል" ብላለች። ዊሊያምስ ከቴኒስ ተጫዋችነት በላይ ሆና ቆይታለች። አሜሪካዊት ተምሳሌት እና በዓለም ላይ በጣም ታዋቂ ከሆኑ የስፖርት ኮከቦች አንዷ ለመሆን በቅታለች። ከስፖርቱ እንደምትለይ ታዋቂ በሆነው የፋሽን መጽሔት ቮግ ላይ ማስታወቋ ይታወሳል። የቀድሞዋ የዓለም ቁጥር አንድ ከስፖርቱ መገለል የሚለውን ቃል ባትጠቀምም ከስፖርቱ “ጋር መለወጥ ፈልጌ ነው” ማለትን መርጣለች። ዓላማዋ አንጸባራቂ የስፖርት ህይወቷን በሀገሯ ውድድር ለማጠናቀቅ ነው። የሚስማማው፣ የመጨረሻ ግጥሚያዋ ሊሆን ለሚችለው፣ የታዋቂነት እና የአድናቆት ምሽት ነበር። ዊልያምስ ወደ ሜዳ ስትግባ ከፍተተኛ አቀባበል ተደርጎላታል። “ሜዳ ስገባ አቀባበሉ በጣም አስደናቂ ነበር:: በጣም ጥሩ ስሜት ነበር" ብላለች። "የማልረሳው ስሜት ነው። ለእኔ ትልቅ ትርጉም ነበረው።" ዊልያምስን "ታናሽ እህቴ” ብሎ የጠራው የፊልም ዳይሬክተሩኡ ስፓይክ ሊ በሜዳ ተገኝቷል። ሌላዋ ቅርብ ጓደኛዋ የቮግ መጽሔት አርታኢ አና ዊንቱር ከተጫዋቹቿ ቤተሰብ ጀርባ ባለው ሳጥን ውስጥ ተቀምጣ ነበር። በስታዲየም ከተገኙ እና ምስላቸው ከታዩት ታዋቂ ሰዎች መካከል የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ቢል ክሊንተን፣ ሙዚቀኛዋ ግላዲስ ናይት፣ ቦክሰኛው ማይክ ታይሰን እና ሞዴል ቤላ ሃዲድ ይገኙበታል። ልጇ ኦሎምፒያ ከአባቷ አሌክሲስ እና ከአያቷ ጋር በሜዳ ተገኝታለች። ደጋፊዎችም ለእሷ አድናቆታቸውን በተለያዩ መንገዶች ገልጸዋል።
ሴሬና ዊሊያምስ ከሜዳ ቴኒስ ከመገለሏ በፊት የምታደርገውን ውድድር በድል ጀመረች ሴሬና ዊልያምስ በኒውዮርክ በተስፋ እና በፈንጠዝያ በተሞላው አዝናኝ ምሽት መሰናበቻዋ የሆነውን የየዩኤስ ኦፕን ውድድርን በድል ጀመረች። ከውድድሩ በኋላ ከሜዳ ቴኒስ የምትርቀው ዊሊያምስ የሞንቴኔግሮዋን ዳንካ ኮቪኒችብ 6-3 እና 6-3 አሸንፋለች። በአርተር አሼ ስታዲየም የተገኙት 25 ሺህ ተመልካቾች ለኮከቧ ያላቸውን ከብር የገለጹ ሲሆን እና እሷም በተለመደው መንገድ ምላሽ ሰጥታለች። የ40 ዓመቷ ዊሊያምስ ረቡዕ ዕለት በሚደረገው የሁለተኛው ዙር ጨዋታ ከኢስቶኒያዋ አኔት ኮንታቬይት ጋር ትጫወታለች። የ23 ጊዜ የግራንድ ስላም አሸናፊዋ ሴሬና በአውስትራሊያዋ ማርጋሬት ኮርት የተያዘውን ክብረወሰን ለመጋራት አንድ ድል ብቻ ይቀራታል። ከታላቅ እህቷ ቬኑስ ጋር በጥንዶች ውድድር እየተሳተፈች ትገኛለች። በዚህም ስንብት ውድድሯን ለማራዘም ያለመች ይመስላል። ጉዞዋንም 80ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችውን ኮቪኒችን በማሸነፍ ጀምራለች። ከተመልካቾች ከፍተኛ ድጋፍ ያገኘችው ሴሬና የደጋፊዎች ሁኔታ ውሳኔዋ ላይ ተጽዕኖ እንዳለቸው “አሁንም በጣም ከባድ ነው ምክንያቱም እዚያ መገኘትን በጣም እወደዋለሁ” ስትል ትገልጻለች። "ብዙ ውድድሮችን በተጫወትኩ ቁጥር ብዙ መሳተፍ እንደምችል ይሰማኛል።  የበለጠ በተጫወትኩት ቁጥር የበለጠ ማንጸባረቅ እንደምችል ማሰብ በጣም ከባድ ነው።“ "ነገር ግን ወደ ቀጣዩ ነገር ለመሸጋገር ጊዜው አሁን ነው። ማድረግ የምፈልጋቸው ሌሎች ብዙ ነገሮች ስላሉ አስፈላጊ ይመስለኛል" ብላለች። ዊሊያምስ ከቴኒስ ተጫዋችነት በላይ ሆና ቆይታለች። አሜሪካዊት ተምሳሌት እና በዓለም ላይ በጣም ታዋቂ ከሆኑ የስፖርት ኮከቦች አንዷ ለመሆን በቅታለች። ከስፖርቱ እንደምትለይ ታዋቂ በሆነው የፋሽን መጽሔት ቮግ ላይ ማስታወቋ ይታወሳል። የቀድሞዋ የዓለም ቁጥር አንድ ከስፖርቱ መገለል የሚለውን ቃል ባትጠቀምም ከስፖርቱ “ጋር መለወጥ ፈልጌ ነው” ማለትን መርጣለች። ዓላማዋ አንጸባራቂ የስፖርት ህይወቷን በሀገሯ ውድድር ለማጠናቀቅ ነው። የሚስማማው፣ የመጨረሻ ግጥሚያዋ ሊሆን ለሚችለው፣ የታዋቂነት እና የአድናቆት ምሽት ነበር። ዊልያምስ ወደ ሜዳ ስትግባ ከፍተተኛ አቀባበል ተደርጎላታል። “ሜዳ ስገባ አቀባበሉ በጣም አስደናቂ ነበር:: በጣም ጥሩ ስሜት ነበር" ብላለች። "የማልረሳው ስሜት ነው። ለእኔ ትልቅ ትርጉም ነበረው።" ዊልያምስን "ታናሽ እህቴ” ብሎ የጠራው የፊልም ዳይሬክተሩኡ ስፓይክ ሊ በሜዳ ተገኝቷል። ሌላዋ ቅርብ ጓደኛዋ የቮግ መጽሔት አርታኢ አና ዊንቱር ከተጫዋቹቿ ቤተሰብ ጀርባ ባለው ሳጥን ውስጥ ተቀምጣ ነበር። በስታዲየም ከተገኙ እና ምስላቸው ከታዩት ታዋቂ ሰዎች መካከል የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ቢል ክሊንተን፣ ሙዚቀኛዋ ግላዲስ ናይት፣ ቦክሰኛው ማይክ ታይሰን እና ሞዴል ቤላ ሃዲድ ይገኙበታል። ልጇ ኦሎምፒያ ከአባቷ አሌክሲስ እና ከአያቷ ጋር በሜዳ ተገኝታለች። ደጋፊዎችም ለእሷ አድናቆታቸውን በተለያዩ መንገዶች ገልጸዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/czvngj5rdkko
2health
ኮሮናቫይረስ፡ በኦክስፎርዱ የክትባት ሙከራ ላይ አንድ ሰው ቢሞትም የደህንነት ስጋት የለበትም ተባለ
በአስትራዜኔካ እና ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ በጥምረት እየበለጸገ የሚገኘው የኮሮናቫይረስ ክትባት ላይ ሙከራ በሚደረግባት ብራዚል የአንድ በጎ ፈቃደኛ ሕይወቱ ማለፏን ተከትሎ ክትባቱ ምንም አይነት የድህንነት ስጋት እንደሌለበት ተገለጸ። የብራዚል ጤና ባለስልጣን ከሙከራው ጋር በተያያዘ ሕይወቱ ስላለፈው በጎ ፈቃደኛ ምንም አይነት መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል። የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ቡድን በበኩሉ በጉዳዩ ላይ ጥንቃቄ የተሞላበት ምርመራ እንደሚደረግና ክትባቱ ግን ምንም አይነት የደህንነት ስጋት እንደሌለበት አስታውቋል። ቢቢሲ ባገኘው መረጃ መሰረት ደግሞ በጎ ፈቃደኘው ክትባቱን አልወሰደም። በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እየተሰራ የሚገኘው ክትባት ላይ ከሚሳተፉት በጎ ፈቃደኞች መካከል ግማሽ የሚሆኑት ብቻ ሲሆን ክትባቱን እንዲወስዱ የተደረገው ቀሪዎቹ ደግሞ ማረጋገጫ የተሰጠው የማጅራት ገትር ክትባት ነው የተሰጣቸው። የሙከራው ተሳታፊ በጎ ፈቃደኞችም እራሳቸው የሚሰጣቸው የኮሮረናቫይረስ ክትባት ይሁን የማጅራት ገትር የሚያውቁት ነገር የለም። ይህ የሚደረገውም በገዛ ፈቃዳቸው ነው ተብሏል። ግዙፉ የመድሀኒት አምራች አስትራዜኔካ በበኩሉ በእያንዳንዱ የግለሰብ የሙከራ ሂደት ላይ አስተያየት እንደማይሰጥና ሙከራው ሲካሄድ ግን አስፈላጊው ጥንቃቄና የደህንነት እርምጃዎች መወሰዳቸውን አስታውቋል። ''ሁሉም ወሳኝ የጤና ሁኔታዎች በጥንቃቄ ተመርምረዋል፤ ከግምት ውስጥም ገብተዋል። ሙከራውም ሆነ የምርምር ሂደቱ ምንም አይነት አሳሳቢ ነገር አልተገኘባቸውም፤ የሚመለከታቸው ኃላፊዎችም ሂደቱን እንዲከታተሉት አድርገናል'' ብሏል። በአሁኑ ሰአት ከፍተኛ ተስፋ ከተጣለባቸው የክትባት ሙከራዎች መካከል ይሄኛው በቀዳሚነት የሚጠቀስ ሲሆን በቅርቡ ለገበያ እንደሚበቃም ይጠበቃል። እስካሁን ደረጃ አንድና ደረጃ ሁለት የሙከራ ሂደቶችን በስኬታማነት ያጠናቀቀው ይኸው ክትባት ደረጃ ሶስትን ለማጠናቀቅ ደግሞ በዩኬ፣ ብራዚልና ሕንድ በበጎ ፈቃደኞች ላይ ሙከራውን እያካሄደ ይገኛል። ባሳለፍነው ወር በዩኬ ይካሄድ የነበረው ሙከራ የጎንዮሽ ጉዳት ሊኖረው ይችላል በሚል ተቋርጦ የነበረ ሲሆን ከቀናት በኋላ ግን ሙከራውን ለማከናወን ምንም ስጋት እንደሌለ በመገለጹ ሂደቱ በድጋሚ እንዲጀመር ሆኗል። የብራዚል ጤና ባለስልጣን በጎ ፈቃደኛው ሕይወቱ ስለማለፉ ከትናንት በስትያ መስማቱን አስታውቋል። የብራዚል መገናኛ ብዙኃን በበኩላቸው ሕይወቱ ያላፈችው ግለሰብ የ28 ዓመት የህክምና ባለሙያ እንደሆነና ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ሕይወቱ እንዳለፈች ዘግበዋል። ይህ ክትባት ሙሉ ፈቃድ የሚያገኝ ከሆነ ብራዚል በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ብልቃጦችን ለመግዛት ወስናለች። በአገሪቱ እስካሁን 5.3 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ከአሜሪካና ሕንድ በመቀጠል በዓለማችን ሶስተኛው ከፍተኛ ቁጥር ነው። የሟቾች ቁጥር ደግሞ እስካሁን 155 ሺ መድረሱ ተረጋግጧል።
ኮሮናቫይረስ፡ በኦክስፎርዱ የክትባት ሙከራ ላይ አንድ ሰው ቢሞትም የደህንነት ስጋት የለበትም ተባለ በአስትራዜኔካ እና ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ በጥምረት እየበለጸገ የሚገኘው የኮሮናቫይረስ ክትባት ላይ ሙከራ በሚደረግባት ብራዚል የአንድ በጎ ፈቃደኛ ሕይወቱ ማለፏን ተከትሎ ክትባቱ ምንም አይነት የድህንነት ስጋት እንደሌለበት ተገለጸ። የብራዚል ጤና ባለስልጣን ከሙከራው ጋር በተያያዘ ሕይወቱ ስላለፈው በጎ ፈቃደኛ ምንም አይነት መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል። የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ቡድን በበኩሉ በጉዳዩ ላይ ጥንቃቄ የተሞላበት ምርመራ እንደሚደረግና ክትባቱ ግን ምንም አይነት የደህንነት ስጋት እንደሌለበት አስታውቋል። ቢቢሲ ባገኘው መረጃ መሰረት ደግሞ በጎ ፈቃደኘው ክትባቱን አልወሰደም። በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እየተሰራ የሚገኘው ክትባት ላይ ከሚሳተፉት በጎ ፈቃደኞች መካከል ግማሽ የሚሆኑት ብቻ ሲሆን ክትባቱን እንዲወስዱ የተደረገው ቀሪዎቹ ደግሞ ማረጋገጫ የተሰጠው የማጅራት ገትር ክትባት ነው የተሰጣቸው። የሙከራው ተሳታፊ በጎ ፈቃደኞችም እራሳቸው የሚሰጣቸው የኮሮረናቫይረስ ክትባት ይሁን የማጅራት ገትር የሚያውቁት ነገር የለም። ይህ የሚደረገውም በገዛ ፈቃዳቸው ነው ተብሏል። ግዙፉ የመድሀኒት አምራች አስትራዜኔካ በበኩሉ በእያንዳንዱ የግለሰብ የሙከራ ሂደት ላይ አስተያየት እንደማይሰጥና ሙከራው ሲካሄድ ግን አስፈላጊው ጥንቃቄና የደህንነት እርምጃዎች መወሰዳቸውን አስታውቋል። ''ሁሉም ወሳኝ የጤና ሁኔታዎች በጥንቃቄ ተመርምረዋል፤ ከግምት ውስጥም ገብተዋል። ሙከራውም ሆነ የምርምር ሂደቱ ምንም አይነት አሳሳቢ ነገር አልተገኘባቸውም፤ የሚመለከታቸው ኃላፊዎችም ሂደቱን እንዲከታተሉት አድርገናል'' ብሏል። በአሁኑ ሰአት ከፍተኛ ተስፋ ከተጣለባቸው የክትባት ሙከራዎች መካከል ይሄኛው በቀዳሚነት የሚጠቀስ ሲሆን በቅርቡ ለገበያ እንደሚበቃም ይጠበቃል። እስካሁን ደረጃ አንድና ደረጃ ሁለት የሙከራ ሂደቶችን በስኬታማነት ያጠናቀቀው ይኸው ክትባት ደረጃ ሶስትን ለማጠናቀቅ ደግሞ በዩኬ፣ ብራዚልና ሕንድ በበጎ ፈቃደኞች ላይ ሙከራውን እያካሄደ ይገኛል። ባሳለፍነው ወር በዩኬ ይካሄድ የነበረው ሙከራ የጎንዮሽ ጉዳት ሊኖረው ይችላል በሚል ተቋርጦ የነበረ ሲሆን ከቀናት በኋላ ግን ሙከራውን ለማከናወን ምንም ስጋት እንደሌለ በመገለጹ ሂደቱ በድጋሚ እንዲጀመር ሆኗል። የብራዚል ጤና ባለስልጣን በጎ ፈቃደኛው ሕይወቱ ስለማለፉ ከትናንት በስትያ መስማቱን አስታውቋል። የብራዚል መገናኛ ብዙኃን በበኩላቸው ሕይወቱ ያላፈችው ግለሰብ የ28 ዓመት የህክምና ባለሙያ እንደሆነና ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ሕይወቱ እንዳለፈች ዘግበዋል። ይህ ክትባት ሙሉ ፈቃድ የሚያገኝ ከሆነ ብራዚል በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ብልቃጦችን ለመግዛት ወስናለች። በአገሪቱ እስካሁን 5.3 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ከአሜሪካና ሕንድ በመቀጠል በዓለማችን ሶስተኛው ከፍተኛ ቁጥር ነው። የሟቾች ቁጥር ደግሞ እስካሁን 155 ሺ መድረሱ ተረጋግጧል።
https://www.bbc.com/amharic/news-54641714
2health
ቀይ መስቀል በሰሜን ኢትዮጵያ የመድኃኒት እና የሕክምና መገልገያ እጥረት አሳስቦኛል አለ
በሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነት ተከትሎ በአካባቢው የመድኃኒት እና የሕክምና መገልገያ መሳሪያዎች አቅርቦት አለመኖር በእጅጉ እንዳሳሰበው ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታወቀ። አንድ ዓመት ካለፈው ጦርነት ጋር ተያይዞ በትግራይ፣ በአማራ እና በአፋር ክልሎች የሚገኙ የሕክምና ተቋማት ውድመት የገጠማቸው ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በአሁኑ ወቅት የአስፈላጊ አቅርቦቶችን ችግር እንደገጠማቸው ተነግሯል። "የሕክምና አገልግሎት አቅራቢዎች መሠረታዊ ግብዓቶችን እያገኙ አይደለም፤ እንዲሁም በአንዳንድ መሠረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል" ብሏል ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (አይሲአርሲ) ጥር 09/2014 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ። ቀይ መስቀል የመድኃኒት እና ሕክምና መስጫ መሳሪዎች እጥረት ከጤና መሠረተ ልማት ውድመቶች ጋር ተደማምሮ የጤና አገልግሎት አቅርቦትን እጅግ አስቸጋሪ አድርጎታል ይላል። ቀይ መስቀል በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ፤ "ሰዎች ለመኖር የሚያስፈልጋቸውን መሠረታዊ ነገር ከመከልከል" ጋር የሚስተካከል ነው ብሏል። አይሲአርሲ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦቱን የበለጠ ተጎጂ በሆኑት ላይ ትኩረት እያደረኩ ነው በሏል። "የሕክምና አቅርቦቶች በመቀነሳቸው ምላሽ የመስጠት አቅማችንን ተገድቧል" ያለው ቀይ መስቀል፤ ጦርነት፣ የደኅንነት እጦት እና ገደቦች የሰብዓዊ እርዳታውን ፈተና ውስጥ ከከተቱት ምክንያቶች መካከል ቀዳሚ መሆናቸውን በትናንቱ መግለጫው አስታውቋል። "በአማራ ክልል አንዳንድ ሆስፒታሎች በመድኃኒት እጥረት ምክንያት ተዘግተዋል" ሲሉ በአማራ እና አፋር ክልሎች የቀይ መስቀል ተወካይ ሚቻ ዌዲኪንደ ተናግረዋል። "ሥር የሰደዱ በሽታዎች ያለባቸው ሰዎች በየዕለቱ እየሞቱ ነው። የጤና ተቋማት አገልግሎት እየሰጡ ባለመሆናቸው፤ ውሃ ወይም መብራት ስለማይኖራቸው እናቶች በቤት ውስጥ እየወለዱ ነው" ብለዋል የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ የአማራ እና አፋር ክልል ተወካይ። ከአማራ እና አፋር በተጨማሪ በትግራይ ክልልም ከፍተኛ የሆነ መድኃኒት እና የሕክምና ቁሳቁሶች እጥረት መኖሩ ቀይ መስቀል በመግለጫ ተመልክቷል። "በትግራይ ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውሉ እንደ ጓንት፣ የቀዶ ሕክምና ቁሳቁሶች እና ሰውነት ውስጥ የሚገቡ የሕክምና ቱቦዎች ሳይቀሩ እየታጠቡ ዳግም ጥቅም ላይ እንዲውሉ እየተደረገ ነው" ሲሉ በኢትዮጵያ የቀይ መስቀል የጤና አስተባባሪ አፖሎ ባራሳ። ከላይ የተጠቀሱት አይነት ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ መዋል ያለባቸውን የጤና መሳሪያዎችን ዳግም መጠቀም፤ ለኢንፌክሽን የመጋለጥ እድልን ያሰፋል ይላሉ ተወካይዋ። በአንዳንድ አካባቢዎች ታካሚዎች የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድኃኒቶችን ከመውሰዳቸውም በተጨማሪ ሐኪሞች የሰዎችን ቁስል ለማጽዳት ጨው ለመጠቀም መገደዳቸውን ጭምር አፖሎ ባራሳ ይገልጻሉ። ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በጦርነቱ ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም አካላት በፍጥነት የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ የበኩላቸውን እንዲወጡ በመግለጫው ጠይቋል። ኮሚቴው ከኢትዮጵያ የቀይ መስቀል ማኅበር ጋር በመሆን እአአ 2021 ላይ በአማራ፣ በአፋር፣ በትግራይ፣ በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች ለሚገኙ 130 የጤና ተቋማት ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል። በዚህም ወደ 120 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ድጋፉን ማግኘታቸውን በመግለጫው አመልክቷል። የቀይ መስቀል ኮሚቴ እያደረገ ካለው የሕክምና ድጋፍ በተጨማሪ በሰሜን ኢትዮጵያ ባሉ አካባቢዎች ያለው የምግብ እና የኑሮ ሁኔታ ያሳስበኛልም ብሏል። ኮሚቴው በስድስት ወራት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በአማራ ክልል ላልይበላ ከተማ እንዲሁም በመቀለ ከተማ ከ3 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል። በመጨረሻም ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ጨምሮም በቅርቡ ንጹሃን ዜጎችን ለጉዳት የዳረገ ግጭት መኖሩ አሳስቦኛል ብሏል። ኮሚቴው የግጭቱ ተሳታፊዎች ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ እርዳታ ሕግጋቶችን እንዲያከብሩ ጠይቋል። ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ በሰሜን ኢትዮጵያ ባሉ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ የሕዝብ መገልገያ መሠረተ ልማቶች ላይ በተለይም የሕክምና ተቋማት ላይ ዘረፋና ውድመት መፈጸሙ የተለያዩ መንግሥታዊና የተራድኦ ድርጅቶች ያወጧቸው ሪፖርቶች አመልክተዋል። የጤና ተቋማት በገጠማቸው ችግርና በመድኃኒትና በሕክምና መገልገያዎች አለመኖር ምክንያት በአካባቢዎቹ ያሉ ነዋሪዎች ከባድ የጤና ችግር ያለባቸው ሰዎች ለአደጋ መጋለጣቸው እተነገረ ነው።
ቀይ መስቀል በሰሜን ኢትዮጵያ የመድኃኒት እና የሕክምና መገልገያ እጥረት አሳስቦኛል አለ በሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነት ተከትሎ በአካባቢው የመድኃኒት እና የሕክምና መገልገያ መሳሪያዎች አቅርቦት አለመኖር በእጅጉ እንዳሳሰበው ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታወቀ። አንድ ዓመት ካለፈው ጦርነት ጋር ተያይዞ በትግራይ፣ በአማራ እና በአፋር ክልሎች የሚገኙ የሕክምና ተቋማት ውድመት የገጠማቸው ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በአሁኑ ወቅት የአስፈላጊ አቅርቦቶችን ችግር እንደገጠማቸው ተነግሯል። "የሕክምና አገልግሎት አቅራቢዎች መሠረታዊ ግብዓቶችን እያገኙ አይደለም፤ እንዲሁም በአንዳንድ መሠረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል" ብሏል ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (አይሲአርሲ) ጥር 09/2014 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ። ቀይ መስቀል የመድኃኒት እና ሕክምና መስጫ መሳሪዎች እጥረት ከጤና መሠረተ ልማት ውድመቶች ጋር ተደማምሮ የጤና አገልግሎት አቅርቦትን እጅግ አስቸጋሪ አድርጎታል ይላል። ቀይ መስቀል በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ፤ "ሰዎች ለመኖር የሚያስፈልጋቸውን መሠረታዊ ነገር ከመከልከል" ጋር የሚስተካከል ነው ብሏል። አይሲአርሲ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦቱን የበለጠ ተጎጂ በሆኑት ላይ ትኩረት እያደረኩ ነው በሏል። "የሕክምና አቅርቦቶች በመቀነሳቸው ምላሽ የመስጠት አቅማችንን ተገድቧል" ያለው ቀይ መስቀል፤ ጦርነት፣ የደኅንነት እጦት እና ገደቦች የሰብዓዊ እርዳታውን ፈተና ውስጥ ከከተቱት ምክንያቶች መካከል ቀዳሚ መሆናቸውን በትናንቱ መግለጫው አስታውቋል። "በአማራ ክልል አንዳንድ ሆስፒታሎች በመድኃኒት እጥረት ምክንያት ተዘግተዋል" ሲሉ በአማራ እና አፋር ክልሎች የቀይ መስቀል ተወካይ ሚቻ ዌዲኪንደ ተናግረዋል። "ሥር የሰደዱ በሽታዎች ያለባቸው ሰዎች በየዕለቱ እየሞቱ ነው። የጤና ተቋማት አገልግሎት እየሰጡ ባለመሆናቸው፤ ውሃ ወይም መብራት ስለማይኖራቸው እናቶች በቤት ውስጥ እየወለዱ ነው" ብለዋል የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ የአማራ እና አፋር ክልል ተወካይ። ከአማራ እና አፋር በተጨማሪ በትግራይ ክልልም ከፍተኛ የሆነ መድኃኒት እና የሕክምና ቁሳቁሶች እጥረት መኖሩ ቀይ መስቀል በመግለጫ ተመልክቷል። "በትግራይ ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውሉ እንደ ጓንት፣ የቀዶ ሕክምና ቁሳቁሶች እና ሰውነት ውስጥ የሚገቡ የሕክምና ቱቦዎች ሳይቀሩ እየታጠቡ ዳግም ጥቅም ላይ እንዲውሉ እየተደረገ ነው" ሲሉ በኢትዮጵያ የቀይ መስቀል የጤና አስተባባሪ አፖሎ ባራሳ። ከላይ የተጠቀሱት አይነት ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ መዋል ያለባቸውን የጤና መሳሪያዎችን ዳግም መጠቀም፤ ለኢንፌክሽን የመጋለጥ እድልን ያሰፋል ይላሉ ተወካይዋ። በአንዳንድ አካባቢዎች ታካሚዎች የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድኃኒቶችን ከመውሰዳቸውም በተጨማሪ ሐኪሞች የሰዎችን ቁስል ለማጽዳት ጨው ለመጠቀም መገደዳቸውን ጭምር አፖሎ ባራሳ ይገልጻሉ። ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በጦርነቱ ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም አካላት በፍጥነት የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ የበኩላቸውን እንዲወጡ በመግለጫው ጠይቋል። ኮሚቴው ከኢትዮጵያ የቀይ መስቀል ማኅበር ጋር በመሆን እአአ 2021 ላይ በአማራ፣ በአፋር፣ በትግራይ፣ በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች ለሚገኙ 130 የጤና ተቋማት ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል። በዚህም ወደ 120 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ድጋፉን ማግኘታቸውን በመግለጫው አመልክቷል። የቀይ መስቀል ኮሚቴ እያደረገ ካለው የሕክምና ድጋፍ በተጨማሪ በሰሜን ኢትዮጵያ ባሉ አካባቢዎች ያለው የምግብ እና የኑሮ ሁኔታ ያሳስበኛልም ብሏል። ኮሚቴው በስድስት ወራት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በአማራ ክልል ላልይበላ ከተማ እንዲሁም በመቀለ ከተማ ከ3 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል። በመጨረሻም ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ጨምሮም በቅርቡ ንጹሃን ዜጎችን ለጉዳት የዳረገ ግጭት መኖሩ አሳስቦኛል ብሏል። ኮሚቴው የግጭቱ ተሳታፊዎች ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ እርዳታ ሕግጋቶችን እንዲያከብሩ ጠይቋል። ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ በሰሜን ኢትዮጵያ ባሉ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ የሕዝብ መገልገያ መሠረተ ልማቶች ላይ በተለይም የሕክምና ተቋማት ላይ ዘረፋና ውድመት መፈጸሙ የተለያዩ መንግሥታዊና የተራድኦ ድርጅቶች ያወጧቸው ሪፖርቶች አመልክተዋል። የጤና ተቋማት በገጠማቸው ችግርና በመድኃኒትና በሕክምና መገልገያዎች አለመኖር ምክንያት በአካባቢዎቹ ያሉ ነዋሪዎች ከባድ የጤና ችግር ያለባቸው ሰዎች ለአደጋ መጋለጣቸው እተነገረ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/news-60041869
5sports
እግር ኳስ: ካፍ የኢትዮጵያ ስታድየሞች "ይታረሱ" ያለው ለምን ይሆን?
ዋሊያዎቹ በሜዳቸው ማድረግ ያለባቸውን ጨዋታ 'በባዕድ ሜዳ' ማድረግ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ የካፍን መመዘኛ የሚያሟሉ ስታድየሞች የላችሁም መባሉ ነው። ኢትዮጵያ የሜዳ እጥረት የለባትም ቢባል ማጋነን አይሆንም። በየክልሉ ቢያንስ አንድ 50 ሺህ ሰው የሚያስተናግድ ስታድየም ተገንብቷል። እና ካፍ ኢትዮጵያ "ደህና" ስታድየም የላትም የሚለው ለምንድነው? ከቅርብ ጊዜ ክስተት እንነሳ። ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ዓመት በሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ ማጣሪያዋን ለማድረግ እየተሰናዳች ነው። ግብፅ፣ ማላዊና ጊኒ ኢትዮጵያ ባለችበት ምድብ ይገኛሉ። ዋሊያዎቹ በሕጉ መሠረት የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ከሜዳቸው ውጪ ከማላዊ ጋር ያደርጋሉ። ነገር ግን ቀጣዩ ጨዋታቸው ከግብፅ ጋር በገዛ ሜዳቸው እንደሆነ የካፍ የጨዋታ መረሃ ግብር ያሳያል። ቢሆንም ይህ ጨዋታ እዚያው ማላዊ እንዲደረግ የአፍሪካ እግር ኳስ አስተዳዳሪው አካል ካፍ ወስኗል። የማላዊ እግር ኳስ ማኅበር ፕሬዝደንት ዋልተር ኒያሚላንዱ "በአገሬ ያላችሁ የሊቨርፑል ደጋፊዎች ሞ ሳላህ ሊመጣላችሁ ነው፤ እንኳን ደስ አላችሁ" የሚል መልዕክት በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል። ብዙዎች ይህ "የግብፅ ሤራ ነው" ይላሉ። ለዚህም የሞሐመድ ሳላህ አገር የኢትዮጵያ ሜዳ አይመጥነኝም ብላ ቅሬታ በማቅረቧ ነው ይህ የሆነው የሚል አመክንዮ ያስደምጣሉ። ነገሩ ግን ወዲህ ነው ይላል የኢትዮጵያን እግር ኳስ በቅርበት የሚከታተለው ፍሬው አሥራት። "የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽንና ስፖርት ኮሚሽኑ ካፍ 'ሜዳዬን አሻሽያለሁ፤ ምርመራ ይደረገልኝ' ብለው በጠየቁት መሠረት ነው ምርመራ የተደረገው" ይላል ፍሬው። በዚህ ጥያቄ መሠረት የካፍ መርማሪ የሆኑት ግለሰብ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ወደ ባሕር ዳር ስታድየም አቅንተው የሜዳውን ጥራት ተመልክተው ተመልሰዋል። "ይህ ማለት ግብፅ ሜዳው ይመርመርልኝ አላለችም ማለት አይደለም" ይላል ፍሬው። "በተመሳሳይ ሰዓት የግብፅ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለካፍ ደብዳቤ አስገብቶ ነበር። ነገር ግን ካፍ መልዕክተኛ የላከው በኢትዮጵያ ጥያቄ መሠረት ነው።" ፍሬው የግብፅ ደብዳቤ አዲስ አበባ ያለችበትን ከፍታ ወይም "አልቲቲዩድ" በመፍራት የተፃፈ እንጂ የሜዳ ጉዳይን በዋነኛነት የሚዳስስ አይደለም ይላል። "ሜዳው ይታረስ" የካፍ መልዕክተኛ የባሕር ዳር ስታድየምን ከእግር እስከ ራሱ ከመረመሩ በኋላ ውጤቱን በጉጉት ሲጠባበቁ ለነበሩት ባለሥልጣናት የሰጡት ምላሽ አዎንታዊ አልነበረም። መርማሪው "ምን አጎደልን?" በሚል ስሜት ውስጥ ለነበሩት የፌዴራልና የክልል ስፖርት ቢሮ ኃላፊዎች ይህን ትዕዛዝ አስተላለፉ፡ "ሜዳው ይታረስ።" መርማሪው የባሕር ስታድየም የካፍን ዝቅተኛ መመዘኛዎች እንኳ አያሟላም የሚል መርዶ ተናገሩ። "እርግጥ ስታድየም የመገንባት ችግር የለብንም" ይላል ፍሬው። ነገር ግን. . . ሲል ያክላል "ነገር ግን ስታድየሞቹ ካፍ የሚጠይቀውን ደረጃ ይዘው አይጠናቀቁም። ውጫዊ ቁመናቸው ያምርና አጨራረሳቸው ግን የሚያስከፋ ይሆናል።" ካፍ "ሚኒመም ስታንዳርድ" ይላቸዋል። አማርኛው ቢያንስ ይህን እንኳን አሟሉልኝ መሆኑ ነው። ፍሬው ካፍ ከሚጠይቃቸው በርካታ መመዘኛዎች ጥቂቱን እንዲህ ይጠቅሳል። "አንደኛው የመጫወቻ ሜዳ ነው። አብዛኛዎቹ ስታድየሞች የመጫወቻ ሜዳቸው ዝናብ ሲዘንብ ውሃ ያቁራሉ። ብዙዎቹ ስታድየሞቻችን ይህን ለማስወግድ የሚያስችል የፍሳሽ ሥርዓት (ድሬይኔጅ ሲስተም) የላቸውም።" "ከዚያ ውጪ ደግሞ መልበሻ ክፍሎቻችን መቀመጫ አልባ ናቸው። ይህ ደግሞ የካፍን መመዘኛ እንድንወድቅ ከሚያደርገን መካከል ነው።" ፍሬው ይቀጥላል. . . "አብዛኞቹን ሜዳዎች ተመልክተህ ከሆነ ለደጋፊዎች የተሠራ መቀመጫ የላቸውም። ይህ ደግሞ ለአደጋ የሚያጋልጥ ነው። ካፍ ውድድሮቹ በመሰል ስታድየሞች እንዲደረጉ በፍፁም አይፈልግም።" ፍሬው ጨምሮም አብዛኞቹ ሜዳዎቻችን በምሽት ጨዋታ እንዲደረግ የሚያስችል መብራት እንደሌላቸው ያወሳል። "በተጨማሪ ካፍ ስታደየሞቹ ቢቻል ጣራ እንዲኖራቸው ይጠይቃል። የእኛ ስታድየሞች ደግሞ ጣራ አልባ ናቸው። ሌላው ደግሞ የተሟላ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት "ሚድያ ሩም" [የመገናኛ ብዙኃን ክፍል] ጉዳይ ነው። ይህንንም አላሟላንም።" "አልፎም ደረጃውን የጠበቀ የሕክምና ክፍል እንዲኖረን ካፍ ያስገድዳል።" ፍሬው እንደሚለው ከላይ ከተጠቀሱት መመዘኛዎቹ የተወሰኑት እንኳ ቢሟሉ ጨዋታዎች እየተደረገ ማሻሻያ እንዲከናወን ይፈልጋል፤ ነገር ግን ባሕር ዳርን ጨምሮ ሁሉም ስታድየሞች ዝቅተኛውን መመዘኛ አላሟሉም። "ካፍ ባሕር ዳር ስታድየምን ከተመለከተ በኋላ ሜዳው ድጋሚ ታርሶ ሣር ይተከልበት ነው ያለው። የፈሳሽ ውሃ ማሳለጫው [ድሬይኔጅ ሲስተም] እንዲስተካከልም ማሳሰቢያ ሰጥቷል። ጥራት አለው ብለን የምንለው የባሕር ዳር ስታድየም መልበሻ ክፍልም ፈርሶ እንደ አዲስ መሠራት አለበት የሚል ግብረ መልስ ሰጥቷል።" በቅርብ ጊዜ ከተሠሩና የተሻለ የምንለው የባሕር ዳር ስታድየም ይህን ካላሟላ ሌሎቹስ የሚል ጥያቄ ያነሳል ፍሬው። የኢትዮጵያ ስታድየሞች የማን ናቸው? የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስታድየሞችን የመገንባትም ሆነ የማስተዳደር ኃላፊነት የለብኝም ይላል። የፌዴሬሽኑ ዋና ፀሐፊ ባሕሩ ጥላሁን በየትኛውም አገር የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ስታድየም የመገንባትም ሆነ የማስተዳደር ሥልጣን የለውም ይላሉ። "የእኛ ሥልጣን እግር ኳስን ማስፋፋት እንጂ መሠረተ ልማት መገንባት አይደለም። ይህ ጉዳይ የሚመለከታቸው የፌዴራል መንግሥቱና የክልል መንግሥታት ናቸው።" ዋና ፀሐፊው "ይህ ማለት ግን ፌዴሬሽኑ 'ቴክኒካል' ድጋፍ አይሰጥም ማለት አይደለም" ይላሉ። "በዚህ ሥራ የተካኑ ባለሙያዎችን ከመንግሥት ጋር ማገናኘት፤ ኤክስፐርቶችን የማቅረብ ሥራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሊሆን ይችላል።" አቶ ባሕሩ "እንደውም በፌዴሬሽኑ ፕሬዝደንት ጥረት ነው ለበርካታ ጊዜያት ስታድየሞቻችን ሳይታገዱ የሰነበቱት" ይላሉ። "ለበርካታ ጊዜያት ጨዋታዎችን በባሕር ዳር ስናደርግ የነበረው በገደብ ነበር። ይህ የእግር ኳስ ዲፕሎማሲው ውጤት ነው። አቶ ኢሳያሳ ጅራ [የፌዴሬሽኑ ፕሬዝደንት] ያለንበትን ሁኔታ ለካፍ እያስረዱ ነው ይህ ሲሆን የቆየው፤ እንጂ ሙሉ በሙሉ ስታድየሞቻችንን ለማገድ ያሰቡት የዛሬ ሁለት ዓመት ነበር።" ዋና ፀሐፊው ካፍ በየጊዜው የሚልክላቸውን ደብዳቤዎች ለአማራ ክልልና ለስፖርት ኮሚሽን በማቅረብ መፍትሔ ለማበጀት ይሠሩ እንደነበር ያወሳሉ። "ምንም እንኳ የተወሰነ መሻሻል ብናሳይም ካፍ በሚፈልገው መልኩ ግን አልነበረም። ካፍም መሻሻል እንዳለ አምኗል፣ ነገር ግን በዚህ ደረጃ ጨዋታን ማካሄድ እንደማይችል ነው የነገረን።" አቶ ባሕሩ ጨምረውም በሂደቱ ውስጥ መሻሻሎችን ማሳወቅና ባለሙያ ማቅረብ ነው ሲሉ የፌዴሬሽኑን ኃላፊነት ያብራራሉ። "ለምሳሌ ግሪጎሪ ኢንተርናሽናል የተባለ አፍሪካ ውስጥ ከ20 በላይ ስታድየሞችን የገነባ ድርጅት አምጥተን ከባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር አገናኝተን፤ የአዲስ አበባ ስታድየም እድሳትን ተመልክቶ፤ የሚሠራበትን ዋጋ አቅርቦ ነው የሄደው።" አቶ ባሕሩ ኢትዮጵያ ከሜዳዋ ውጪ በመጫወቷ ዋጋ እየከፈለ ያለው ፌዴሬሽኑ ነው ይላሉ። "ፌዴሬሽኑ ፊፋና ካፍ በሚመድቡለትና ከስፖንሰር በሚያገኘው ገቢ ነው የሚተዳደረው። ለብሔራዊ ቡድኑ ተብሎ ከመንግሥት የሚመደብለት ገንዘብ የለም።" ዋና ፀሐፊው ብሐራዊ ቡድኑ ከማላዊ ቀጥሎ ከግብፅ ጋር ያለውን ጨዋታ በማላዊ ስታድዬም ለማድረግ የወሰነው ከወጪ አኳያ እንደሆነ ይገልጣሉ። "ባለፈው በጋና ጨዋታ ተመልክተናል። አሁንም ደግሞ ማላዊ ላይ ግብፅን ለመግጠም አስበናል። ማላዊን የመረጥነው ወጪ ለመቀነስ በማሰብ ነው። ሁለተኛ ደግሞ ተጫዋቾቻችን ከአገር አገር በመመላለስ እንዳይዳከሙ በማሰብ ነው። ታድያ ይህ የሚያሳፍር እንጂ ደረት የሚያስነፋ አይለም።" "አሁን የምንቀሳቀስበት ገንዘብ ስላገኘን እየተሳተፍን ሊሆን ይችላል። ነገሩ እየከበደን ሲሄድ ግን ውድድር እስከማቋረጥ ልንደርስ እንችላለን። ይህ ደግሞ እንደአገር ብዙ ጥያቄ የሚያስነሳ ነው። ነገር ግን ይህን ለማስወገድ ከባሕልና ስፖርት ጋር እየሠራን ነው።" ያለው ተስፋ ምንድነው? ፍሬውም ከዋና ፀሐፊው ሐሳብ ጋር ይስማማል። ስታድየም ገንብቶ ማጠናቀቅና ማስተዳደር ያለበት የፌዴራል መንግሥት አሊያም የክልል የስፖርት ቢሮዎች እንጂ የፌዴሬሽኑ አይደለም ይላል። ለምሳሌ የአዲስ አበባ ስታድየም የፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን ንብረት ነው። የሚቆጣጠረውም ኮሚሽኑ ነው ይላል። "ቢሆንም ግን የሚጠቀምበት ስታድዬም እስከሆነ ድረስ ስታድየሞቻችን ጥራታቸውን ጠብቀው እንዲገነቡ ጫና የማድረግ ኃላፊነት እንዳለበት አምናለሁ።" ምንም እንኳን ስታዲየሞቻችን ከካፍ ዝቅተኛው መመዘኛ በታች ቢሆኑም አሁን እድሳት ላይ ያለው የአዲስ አበባ ስታድየምና የአደይ አበባ ስታድየም ግንባት የተስፋ ስንቅ እንደሚሆኑ ፍሬው ይናገራል። የድሬዳዋና የባሕር ዳር ስታድየሞችም የካፍ መመዘኛን ባሟላ መልኩ ቢያንስ በዚህ ዓመት ሊጠናቀቁ እንደሚችሉ ፍሬው ይጠቁማል። "ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ሆ ብሎ ስታድየሞችን በአንድ ጊዜ መጨረስ የሚከብድ ይመስለኛል" የሚለው ፍሬው አሁን የስፖርት ሚኒስቴር እያደረገ ያለው የተጀመሩ ስታድየሞችን በደረጃ የማጠናቀቅ እርምጃ አዋጭ እንደሆነ ያብራራል። "እንደውም ቢርቅ በሚቀጥለው ዓመት አጋማሽ ዋሊያዎቹ በሜዳቸው ሲጫወቱ ልናይ እንችል ይሆናል።"
እግር ኳስ: ካፍ የኢትዮጵያ ስታድየሞች "ይታረሱ" ያለው ለምን ይሆን? ዋሊያዎቹ በሜዳቸው ማድረግ ያለባቸውን ጨዋታ 'በባዕድ ሜዳ' ማድረግ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ የካፍን መመዘኛ የሚያሟሉ ስታድየሞች የላችሁም መባሉ ነው። ኢትዮጵያ የሜዳ እጥረት የለባትም ቢባል ማጋነን አይሆንም። በየክልሉ ቢያንስ አንድ 50 ሺህ ሰው የሚያስተናግድ ስታድየም ተገንብቷል። እና ካፍ ኢትዮጵያ "ደህና" ስታድየም የላትም የሚለው ለምንድነው? ከቅርብ ጊዜ ክስተት እንነሳ። ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ዓመት በሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ ማጣሪያዋን ለማድረግ እየተሰናዳች ነው። ግብፅ፣ ማላዊና ጊኒ ኢትዮጵያ ባለችበት ምድብ ይገኛሉ። ዋሊያዎቹ በሕጉ መሠረት የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ከሜዳቸው ውጪ ከማላዊ ጋር ያደርጋሉ። ነገር ግን ቀጣዩ ጨዋታቸው ከግብፅ ጋር በገዛ ሜዳቸው እንደሆነ የካፍ የጨዋታ መረሃ ግብር ያሳያል። ቢሆንም ይህ ጨዋታ እዚያው ማላዊ እንዲደረግ የአፍሪካ እግር ኳስ አስተዳዳሪው አካል ካፍ ወስኗል። የማላዊ እግር ኳስ ማኅበር ፕሬዝደንት ዋልተር ኒያሚላንዱ "በአገሬ ያላችሁ የሊቨርፑል ደጋፊዎች ሞ ሳላህ ሊመጣላችሁ ነው፤ እንኳን ደስ አላችሁ" የሚል መልዕክት በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል። ብዙዎች ይህ "የግብፅ ሤራ ነው" ይላሉ። ለዚህም የሞሐመድ ሳላህ አገር የኢትዮጵያ ሜዳ አይመጥነኝም ብላ ቅሬታ በማቅረቧ ነው ይህ የሆነው የሚል አመክንዮ ያስደምጣሉ። ነገሩ ግን ወዲህ ነው ይላል የኢትዮጵያን እግር ኳስ በቅርበት የሚከታተለው ፍሬው አሥራት። "የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽንና ስፖርት ኮሚሽኑ ካፍ 'ሜዳዬን አሻሽያለሁ፤ ምርመራ ይደረገልኝ' ብለው በጠየቁት መሠረት ነው ምርመራ የተደረገው" ይላል ፍሬው። በዚህ ጥያቄ መሠረት የካፍ መርማሪ የሆኑት ግለሰብ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ወደ ባሕር ዳር ስታድየም አቅንተው የሜዳውን ጥራት ተመልክተው ተመልሰዋል። "ይህ ማለት ግብፅ ሜዳው ይመርመርልኝ አላለችም ማለት አይደለም" ይላል ፍሬው። "በተመሳሳይ ሰዓት የግብፅ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለካፍ ደብዳቤ አስገብቶ ነበር። ነገር ግን ካፍ መልዕክተኛ የላከው በኢትዮጵያ ጥያቄ መሠረት ነው።" ፍሬው የግብፅ ደብዳቤ አዲስ አበባ ያለችበትን ከፍታ ወይም "አልቲቲዩድ" በመፍራት የተፃፈ እንጂ የሜዳ ጉዳይን በዋነኛነት የሚዳስስ አይደለም ይላል። "ሜዳው ይታረስ" የካፍ መልዕክተኛ የባሕር ዳር ስታድየምን ከእግር እስከ ራሱ ከመረመሩ በኋላ ውጤቱን በጉጉት ሲጠባበቁ ለነበሩት ባለሥልጣናት የሰጡት ምላሽ አዎንታዊ አልነበረም። መርማሪው "ምን አጎደልን?" በሚል ስሜት ውስጥ ለነበሩት የፌዴራልና የክልል ስፖርት ቢሮ ኃላፊዎች ይህን ትዕዛዝ አስተላለፉ፡ "ሜዳው ይታረስ።" መርማሪው የባሕር ስታድየም የካፍን ዝቅተኛ መመዘኛዎች እንኳ አያሟላም የሚል መርዶ ተናገሩ። "እርግጥ ስታድየም የመገንባት ችግር የለብንም" ይላል ፍሬው። ነገር ግን. . . ሲል ያክላል "ነገር ግን ስታድየሞቹ ካፍ የሚጠይቀውን ደረጃ ይዘው አይጠናቀቁም። ውጫዊ ቁመናቸው ያምርና አጨራረሳቸው ግን የሚያስከፋ ይሆናል።" ካፍ "ሚኒመም ስታንዳርድ" ይላቸዋል። አማርኛው ቢያንስ ይህን እንኳን አሟሉልኝ መሆኑ ነው። ፍሬው ካፍ ከሚጠይቃቸው በርካታ መመዘኛዎች ጥቂቱን እንዲህ ይጠቅሳል። "አንደኛው የመጫወቻ ሜዳ ነው። አብዛኛዎቹ ስታድየሞች የመጫወቻ ሜዳቸው ዝናብ ሲዘንብ ውሃ ያቁራሉ። ብዙዎቹ ስታድየሞቻችን ይህን ለማስወግድ የሚያስችል የፍሳሽ ሥርዓት (ድሬይኔጅ ሲስተም) የላቸውም።" "ከዚያ ውጪ ደግሞ መልበሻ ክፍሎቻችን መቀመጫ አልባ ናቸው። ይህ ደግሞ የካፍን መመዘኛ እንድንወድቅ ከሚያደርገን መካከል ነው።" ፍሬው ይቀጥላል. . . "አብዛኞቹን ሜዳዎች ተመልክተህ ከሆነ ለደጋፊዎች የተሠራ መቀመጫ የላቸውም። ይህ ደግሞ ለአደጋ የሚያጋልጥ ነው። ካፍ ውድድሮቹ በመሰል ስታድየሞች እንዲደረጉ በፍፁም አይፈልግም።" ፍሬው ጨምሮም አብዛኞቹ ሜዳዎቻችን በምሽት ጨዋታ እንዲደረግ የሚያስችል መብራት እንደሌላቸው ያወሳል። "በተጨማሪ ካፍ ስታደየሞቹ ቢቻል ጣራ እንዲኖራቸው ይጠይቃል። የእኛ ስታድየሞች ደግሞ ጣራ አልባ ናቸው። ሌላው ደግሞ የተሟላ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት "ሚድያ ሩም" [የመገናኛ ብዙኃን ክፍል] ጉዳይ ነው። ይህንንም አላሟላንም።" "አልፎም ደረጃውን የጠበቀ የሕክምና ክፍል እንዲኖረን ካፍ ያስገድዳል።" ፍሬው እንደሚለው ከላይ ከተጠቀሱት መመዘኛዎቹ የተወሰኑት እንኳ ቢሟሉ ጨዋታዎች እየተደረገ ማሻሻያ እንዲከናወን ይፈልጋል፤ ነገር ግን ባሕር ዳርን ጨምሮ ሁሉም ስታድየሞች ዝቅተኛውን መመዘኛ አላሟሉም። "ካፍ ባሕር ዳር ስታድየምን ከተመለከተ በኋላ ሜዳው ድጋሚ ታርሶ ሣር ይተከልበት ነው ያለው። የፈሳሽ ውሃ ማሳለጫው [ድሬይኔጅ ሲስተም] እንዲስተካከልም ማሳሰቢያ ሰጥቷል። ጥራት አለው ብለን የምንለው የባሕር ዳር ስታድየም መልበሻ ክፍልም ፈርሶ እንደ አዲስ መሠራት አለበት የሚል ግብረ መልስ ሰጥቷል።" በቅርብ ጊዜ ከተሠሩና የተሻለ የምንለው የባሕር ዳር ስታድየም ይህን ካላሟላ ሌሎቹስ የሚል ጥያቄ ያነሳል ፍሬው። የኢትዮጵያ ስታድየሞች የማን ናቸው? የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስታድየሞችን የመገንባትም ሆነ የማስተዳደር ኃላፊነት የለብኝም ይላል። የፌዴሬሽኑ ዋና ፀሐፊ ባሕሩ ጥላሁን በየትኛውም አገር የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ስታድየም የመገንባትም ሆነ የማስተዳደር ሥልጣን የለውም ይላሉ። "የእኛ ሥልጣን እግር ኳስን ማስፋፋት እንጂ መሠረተ ልማት መገንባት አይደለም። ይህ ጉዳይ የሚመለከታቸው የፌዴራል መንግሥቱና የክልል መንግሥታት ናቸው።" ዋና ፀሐፊው "ይህ ማለት ግን ፌዴሬሽኑ 'ቴክኒካል' ድጋፍ አይሰጥም ማለት አይደለም" ይላሉ። "በዚህ ሥራ የተካኑ ባለሙያዎችን ከመንግሥት ጋር ማገናኘት፤ ኤክስፐርቶችን የማቅረብ ሥራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሊሆን ይችላል።" አቶ ባሕሩ "እንደውም በፌዴሬሽኑ ፕሬዝደንት ጥረት ነው ለበርካታ ጊዜያት ስታድየሞቻችን ሳይታገዱ የሰነበቱት" ይላሉ። "ለበርካታ ጊዜያት ጨዋታዎችን በባሕር ዳር ስናደርግ የነበረው በገደብ ነበር። ይህ የእግር ኳስ ዲፕሎማሲው ውጤት ነው። አቶ ኢሳያሳ ጅራ [የፌዴሬሽኑ ፕሬዝደንት] ያለንበትን ሁኔታ ለካፍ እያስረዱ ነው ይህ ሲሆን የቆየው፤ እንጂ ሙሉ በሙሉ ስታድየሞቻችንን ለማገድ ያሰቡት የዛሬ ሁለት ዓመት ነበር።" ዋና ፀሐፊው ካፍ በየጊዜው የሚልክላቸውን ደብዳቤዎች ለአማራ ክልልና ለስፖርት ኮሚሽን በማቅረብ መፍትሔ ለማበጀት ይሠሩ እንደነበር ያወሳሉ። "ምንም እንኳ የተወሰነ መሻሻል ብናሳይም ካፍ በሚፈልገው መልኩ ግን አልነበረም። ካፍም መሻሻል እንዳለ አምኗል፣ ነገር ግን በዚህ ደረጃ ጨዋታን ማካሄድ እንደማይችል ነው የነገረን።" አቶ ባሕሩ ጨምረውም በሂደቱ ውስጥ መሻሻሎችን ማሳወቅና ባለሙያ ማቅረብ ነው ሲሉ የፌዴሬሽኑን ኃላፊነት ያብራራሉ። "ለምሳሌ ግሪጎሪ ኢንተርናሽናል የተባለ አፍሪካ ውስጥ ከ20 በላይ ስታድየሞችን የገነባ ድርጅት አምጥተን ከባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር አገናኝተን፤ የአዲስ አበባ ስታድየም እድሳትን ተመልክቶ፤ የሚሠራበትን ዋጋ አቅርቦ ነው የሄደው።" አቶ ባሕሩ ኢትዮጵያ ከሜዳዋ ውጪ በመጫወቷ ዋጋ እየከፈለ ያለው ፌዴሬሽኑ ነው ይላሉ። "ፌዴሬሽኑ ፊፋና ካፍ በሚመድቡለትና ከስፖንሰር በሚያገኘው ገቢ ነው የሚተዳደረው። ለብሔራዊ ቡድኑ ተብሎ ከመንግሥት የሚመደብለት ገንዘብ የለም።" ዋና ፀሐፊው ብሐራዊ ቡድኑ ከማላዊ ቀጥሎ ከግብፅ ጋር ያለውን ጨዋታ በማላዊ ስታድዬም ለማድረግ የወሰነው ከወጪ አኳያ እንደሆነ ይገልጣሉ። "ባለፈው በጋና ጨዋታ ተመልክተናል። አሁንም ደግሞ ማላዊ ላይ ግብፅን ለመግጠም አስበናል። ማላዊን የመረጥነው ወጪ ለመቀነስ በማሰብ ነው። ሁለተኛ ደግሞ ተጫዋቾቻችን ከአገር አገር በመመላለስ እንዳይዳከሙ በማሰብ ነው። ታድያ ይህ የሚያሳፍር እንጂ ደረት የሚያስነፋ አይለም።" "አሁን የምንቀሳቀስበት ገንዘብ ስላገኘን እየተሳተፍን ሊሆን ይችላል። ነገሩ እየከበደን ሲሄድ ግን ውድድር እስከማቋረጥ ልንደርስ እንችላለን። ይህ ደግሞ እንደአገር ብዙ ጥያቄ የሚያስነሳ ነው። ነገር ግን ይህን ለማስወገድ ከባሕልና ስፖርት ጋር እየሠራን ነው።" ያለው ተስፋ ምንድነው? ፍሬውም ከዋና ፀሐፊው ሐሳብ ጋር ይስማማል። ስታድየም ገንብቶ ማጠናቀቅና ማስተዳደር ያለበት የፌዴራል መንግሥት አሊያም የክልል የስፖርት ቢሮዎች እንጂ የፌዴሬሽኑ አይደለም ይላል። ለምሳሌ የአዲስ አበባ ስታድየም የፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን ንብረት ነው። የሚቆጣጠረውም ኮሚሽኑ ነው ይላል። "ቢሆንም ግን የሚጠቀምበት ስታድዬም እስከሆነ ድረስ ስታድየሞቻችን ጥራታቸውን ጠብቀው እንዲገነቡ ጫና የማድረግ ኃላፊነት እንዳለበት አምናለሁ።" ምንም እንኳን ስታዲየሞቻችን ከካፍ ዝቅተኛው መመዘኛ በታች ቢሆኑም አሁን እድሳት ላይ ያለው የአዲስ አበባ ስታድየምና የአደይ አበባ ስታድየም ግንባት የተስፋ ስንቅ እንደሚሆኑ ፍሬው ይናገራል። የድሬዳዋና የባሕር ዳር ስታድየሞችም የካፍ መመዘኛን ባሟላ መልኩ ቢያንስ በዚህ ዓመት ሊጠናቀቁ እንደሚችሉ ፍሬው ይጠቁማል። "ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ሆ ብሎ ስታድየሞችን በአንድ ጊዜ መጨረስ የሚከብድ ይመስለኛል" የሚለው ፍሬው አሁን የስፖርት ሚኒስቴር እያደረገ ያለው የተጀመሩ ስታድየሞችን በደረጃ የማጠናቀቅ እርምጃ አዋጭ እንደሆነ ያብራራል። "እንደውም ቢርቅ በሚቀጥለው ዓመት አጋማሽ ዋሊያዎቹ በሜዳቸው ሲጫወቱ ልናይ እንችል ይሆናል።"
https://www.bbc.com/amharic/news-61507185
0business
በዓለም ግዙፉ የፀሐይ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ሊገነባ ነው
በዓለም ከፀሐይ ብርሃን ከሚመነጩ ግዙፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ምንጮች አንዱ ይሆናል የተባለለትን ፕሮጀክት ዩናይትድ ኪንግደም ልትገነባ ነው። 880 ሺህ ፓናል የፀሐይ ብርሃን ተቀባይ ሰሌዳዎች የሚዘረጉበት ሜዳ የተዘጋጀ ሲሆን ይህም 890 ሄክታር ስፋት ይኖረዋል። የፀሐይ ብርሃን ሰሌዳዎች ይዘረጉበታል የተባለው ቦታ በሰሜን ኬንት ጠረፍ ሲሆን የአካባቢው ነዋሪዎች ግን የገጠሩን ውበት ያጠፋል በሚል ፕሮጀክቱን ክፉኛ ተቃውመውታል። ፕሮጀክቱ ከ2017 ጀምሮ ሲያጨቃጭቅ ቆይቶ ከሦስት ዓመታት ክርክርና ንትርክ በኋላ መጽደቁ ተዘግቧል። ይህ የፀሐይ ብርሃን ኤሌክትሪክ ኃይል ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ ለ91 ሺህ መኖርያ ቤቶች ኤሌክትሪክ ማቅረብ ይችላል። ከ350 ሜጋ ዋት በላይ ኃይል ያመነጫል። የፕሮጀክቱ ወጪ 450 ሚሊዮን ፓውንድ ሲሆን እንደ ፈረንጆቹ በ2022 ሥራ ይጀምራል ተብሏል። ፕሮጀክቱ በዓለም ካሉ ግዙፍ የኃይል ማጠራቀሚያ ቋቶች አንዱ እንደሚሆን ይጠበቃል። የኃይል ማጠራቀሚያ ቋቱ 20 የእግር ኳስ ሜዳዎች ቢዘረጉ የሚኖራቸው ስፋት ይኖረዋል። ግንባታውን በጥምረት የሚያካሄዱት ሃይቭ ኢነርጂና ዊርሶል ኢንርጂ የተባሉ የሶላር ኃይል ተቋራጭ ኩባንያዎች ናቸው። የአረንጓዴ መብት ተቆርቋሪዎች በዚህ ፕሮጀክት ላይ የተለያየ አቋም የወሰዱ ሲሆን የዱር አራዊቶችን ሕይወትና ብዝሃነት ያዛባል የሚሉ አልጠፉም። ውብ የገጠር ሕይወትን ወደ ተራ ኢንዱስትሪ አውራጃ ገጽታ ይቀይረዋል ብለው የተቃወሙትም በርካታ ናቸው። ፍሬንድስ ኦፍ ኧርዝ የተባለ የአረንጓዴና ልምላሜ ተቆርቋሪ ድርጅት ግን ፕሮጀክቱን ደግፎታል። ምክንያቱ ደግሞ የፀሐይ ብርሃን ተቀባይ ሰሌዳዎች የሚዘረጉበት ቦታ ለዘመናት የታረሰና በአረንጓዴ ቢሸፈንም ለሰደድ እሳት የሚጋለጥ በመሆኑ ነው። "ይህን ለዘመናት የታረሰ መሬት ለምርት ለማብቃት በርካታ ማዳበሪያ ያስፈልጋል፤ ይህ ራሱን የቻለ ጉዳት ነው። ለኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ መጠቀም ብልህነት ነው" ብሏል ድርጅቱ። ፕሮጀክቱ ዩናይትድ ኪንግደም ታዳሽ ኃይልን ለመገንባትና ከበካይ የኃይል አቅርቦት ለመታቀብ የገባችው ቃል አንድ አካል ነው።
በዓለም ግዙፉ የፀሐይ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ሊገነባ ነው በዓለም ከፀሐይ ብርሃን ከሚመነጩ ግዙፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ምንጮች አንዱ ይሆናል የተባለለትን ፕሮጀክት ዩናይትድ ኪንግደም ልትገነባ ነው። 880 ሺህ ፓናል የፀሐይ ብርሃን ተቀባይ ሰሌዳዎች የሚዘረጉበት ሜዳ የተዘጋጀ ሲሆን ይህም 890 ሄክታር ስፋት ይኖረዋል። የፀሐይ ብርሃን ሰሌዳዎች ይዘረጉበታል የተባለው ቦታ በሰሜን ኬንት ጠረፍ ሲሆን የአካባቢው ነዋሪዎች ግን የገጠሩን ውበት ያጠፋል በሚል ፕሮጀክቱን ክፉኛ ተቃውመውታል። ፕሮጀክቱ ከ2017 ጀምሮ ሲያጨቃጭቅ ቆይቶ ከሦስት ዓመታት ክርክርና ንትርክ በኋላ መጽደቁ ተዘግቧል። ይህ የፀሐይ ብርሃን ኤሌክትሪክ ኃይል ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ ለ91 ሺህ መኖርያ ቤቶች ኤሌክትሪክ ማቅረብ ይችላል። ከ350 ሜጋ ዋት በላይ ኃይል ያመነጫል። የፕሮጀክቱ ወጪ 450 ሚሊዮን ፓውንድ ሲሆን እንደ ፈረንጆቹ በ2022 ሥራ ይጀምራል ተብሏል። ፕሮጀክቱ በዓለም ካሉ ግዙፍ የኃይል ማጠራቀሚያ ቋቶች አንዱ እንደሚሆን ይጠበቃል። የኃይል ማጠራቀሚያ ቋቱ 20 የእግር ኳስ ሜዳዎች ቢዘረጉ የሚኖራቸው ስፋት ይኖረዋል። ግንባታውን በጥምረት የሚያካሄዱት ሃይቭ ኢነርጂና ዊርሶል ኢንርጂ የተባሉ የሶላር ኃይል ተቋራጭ ኩባንያዎች ናቸው። የአረንጓዴ መብት ተቆርቋሪዎች በዚህ ፕሮጀክት ላይ የተለያየ አቋም የወሰዱ ሲሆን የዱር አራዊቶችን ሕይወትና ብዝሃነት ያዛባል የሚሉ አልጠፉም። ውብ የገጠር ሕይወትን ወደ ተራ ኢንዱስትሪ አውራጃ ገጽታ ይቀይረዋል ብለው የተቃወሙትም በርካታ ናቸው። ፍሬንድስ ኦፍ ኧርዝ የተባለ የአረንጓዴና ልምላሜ ተቆርቋሪ ድርጅት ግን ፕሮጀክቱን ደግፎታል። ምክንያቱ ደግሞ የፀሐይ ብርሃን ተቀባይ ሰሌዳዎች የሚዘረጉበት ቦታ ለዘመናት የታረሰና በአረንጓዴ ቢሸፈንም ለሰደድ እሳት የሚጋለጥ በመሆኑ ነው። "ይህን ለዘመናት የታረሰ መሬት ለምርት ለማብቃት በርካታ ማዳበሪያ ያስፈልጋል፤ ይህ ራሱን የቻለ ጉዳት ነው። ለኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ መጠቀም ብልህነት ነው" ብሏል ድርጅቱ። ፕሮጀክቱ ዩናይትድ ኪንግደም ታዳሽ ኃይልን ለመገንባትና ከበካይ የኃይል አቅርቦት ለመታቀብ የገባችው ቃል አንድ አካል ነው።
https://www.bbc.com/amharic/news-52845065
3politics
ከቤተሰቦቻቸው ጋር መሣሪያ ደግነው ፎቶ የተነሱት የአሜሪካ ምክር ቤት አባል እየተተቹ ነው
የአሜሪካ ኮንግረስ አባል የሆኑት ግለሰብ ከቤተሰቦቻቸው ጋር መሣሪያ ደግነው ለገና የተነሱት ፎቶ ከሁሉም አቅጣጫ ትችት እንዲያስተናግዱ አድርጓቸዋል። የኬንታኪ የሪፐብሊካን ፓርቲ ተወካይ የሆኑት ቶማስ ማሲ በትዊተር ገፃቸው የለጠፉት ይህ ፎቶ "መልካም ገና። ሳንታ እባክህ አሞን ይዘህ ና" የሚል ፅሑፍ የታከለበት ነው። ይህ የኮንግረስ አባሉ ፎቶ ሰውዬው ከሁለቱም የአሜሪካ አውራ ፓርቲዎች ትችት እንዲዘንብባቸው አድርጓቸዋል። ቢቢሲ የኮንግረስ አባሉን አስተያየት ለማካተት ጥረት እያደረገ ይገኛል። ሰውዬው ፎቶውን ትዊተር ላይ ከሰቀሉ በኋላ ድጋፍ የሰጧቸውን ሰዎች 'ሪትዊት' በማድረግ ድምፃቸውን ሲያስተጋቡ የተቃወሟቸው ሰዎች ደግሞ ምላሽ ሲሲጡ ተስተውለዋል። ቶማስ ፎቶውን የለጠፉት ሚሺጋን ውስጥ አንድ የ15 ዓመት ተማሪ የአባቱን ሽጉጥ ተጠቅሞ ትምህርት ቤት ውስጥ በከፈተው ተኩስ አራት ሕፃናት ሞተው ሰባት መቁሰላቸው ከተሰማ ከቀናት በኋላ ነው። የተጠርጣሪው ወላጆች በሰው ልጅ ሞት እጃቸው አለበት፤ አደጋው ከመድረሱ በፊት ማስጠንቀቂያ አልሰጡም በሚል ቢከሰሱም ጥፋተኛ አይደለንም ብለዋል። በጦር መሣሪያ ጉዳይ ለሁለት በተከፈለችው አሜሪካ መሰል አደጋዎች በየጊዜው ይከሰታሉ። ከዚህ በፊት በነበሩ የትምህርት ቤት ተኩሶች ምክንያት ልጆቻቸውን ያጡ ወላጆች የኮንግረስ አባሉን ድርጊት በፅኑ ተቃውመውታል። የፍሬድ ጋተንበርግ ሴት ልጅ ሃይሜ ከሶስት ዓመት በፊት ፓርክላንድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ውስጥ በተከፈተ ተኩስ ነው ሕይወቷን ያጣችው። ፍሬድ ከኮንግረስ አባሉ ፎቶ ሥር የልጁን ጉርድ ፎቶ እና የመቃብሯን ፎቶ ለጥፎ፤ "የቤተሰቦቻችንን ፎቶ እየለጠፍንም አይደል፤ ይሄ የኔ ቤተሰብ ፎቶ ነው። አንደኛው የልጄ ፎቶ ነው፤ ሌላኛው ደግሞ የመቃብሯ። ልጄን ያጣሁት በመሣሪያ ምክንያት ነው። በቅርቡ ተማሪዎችን የገደለው ተማሪም እንዲሁም እንዳንተ ቤተሰብ ከወላጆቹ ጋር መሣሪያ ይዞ ፎቶ ይነሳ ነበር" ሲል ፅፏል። ሌላኛው ዮዋኪን የተሰኘው ልጁን በፓርክላንድ ትምህርት ቤት ተኩስ ሳቢያ ያጣው ማኔኤል ኦሊቨር የሰውየው ደርጊ ፍፁም ተቀባይነት የለውም ሲል ለሲኤንኤን ተናግሯል። የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላትም ይህን የቶማስ ድርጊት በፅኑ አውግዘውታል። የኢሊኖይ ግዛት የኮንግረሱ ሪፐብሊካን ፓርቲ ተወካይ የሆኑት አዳም ኪንዚንገር የፓርቲ አጋራቸውን ወቅሰዋል። ይሁን እንጂ ሌሎች ትላልቅ ስም ያላቸው ወግ አጥባቂ የአሜሪካ ፖለቲከኞች ደግሞ ለሰውዬው ድጋፋቸውን አሳይተዋል። የኮሎራዶ ተወካይ የሆኑትና የጦር መሣሪያ መብት ባለቤትነት መብት ተሟጋች የሆኑት ሎረን ቦበርት እንዲሁም ሌላኛው ሪፐብሊካን ሆዜ ካስቲሎ ለቶማስ ድጋፋቸውን ችረዋል። ቶማስ ማሴ የኬንታኪ ተወካይ ሆነው ለመጀመሪያ ጊዜ የተመረጡት በፈረንጆቹ 2012 ነበር። ሰውዬው 'ሰከንድ አሜንድመንት' በመባል የሚታወቀው የጦር መሣሪያ የመታጠቅ መብት ሕግ ቀንደኛ አቀንቃኝ ናቸው። የጦር መሣሪያ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ በትምህርት ቤቶች የሚከሰተውን ግድያ አያቆመውም ብለውም ተከራክረዋል። ባለፈው ሚያዚያ የጦር መሣሪያ የሚገዙ ሰዎች ዕድሜ ከ21 ወደ 18 ዝቅ ሊል ይገባል ብለውም ሞግተዋል። በአሜሪካው ባለፈው ዓመት ብቻ 20 ሺህ ሰዎች በጦር መሣሪያ አመፅ ምክንያት ሞተዋል። ይህም ባለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት ከታየው የላቀ ነው።
ከቤተሰቦቻቸው ጋር መሣሪያ ደግነው ፎቶ የተነሱት የአሜሪካ ምክር ቤት አባል እየተተቹ ነው የአሜሪካ ኮንግረስ አባል የሆኑት ግለሰብ ከቤተሰቦቻቸው ጋር መሣሪያ ደግነው ለገና የተነሱት ፎቶ ከሁሉም አቅጣጫ ትችት እንዲያስተናግዱ አድርጓቸዋል። የኬንታኪ የሪፐብሊካን ፓርቲ ተወካይ የሆኑት ቶማስ ማሲ በትዊተር ገፃቸው የለጠፉት ይህ ፎቶ "መልካም ገና። ሳንታ እባክህ አሞን ይዘህ ና" የሚል ፅሑፍ የታከለበት ነው። ይህ የኮንግረስ አባሉ ፎቶ ሰውዬው ከሁለቱም የአሜሪካ አውራ ፓርቲዎች ትችት እንዲዘንብባቸው አድርጓቸዋል። ቢቢሲ የኮንግረስ አባሉን አስተያየት ለማካተት ጥረት እያደረገ ይገኛል። ሰውዬው ፎቶውን ትዊተር ላይ ከሰቀሉ በኋላ ድጋፍ የሰጧቸውን ሰዎች 'ሪትዊት' በማድረግ ድምፃቸውን ሲያስተጋቡ የተቃወሟቸው ሰዎች ደግሞ ምላሽ ሲሲጡ ተስተውለዋል። ቶማስ ፎቶውን የለጠፉት ሚሺጋን ውስጥ አንድ የ15 ዓመት ተማሪ የአባቱን ሽጉጥ ተጠቅሞ ትምህርት ቤት ውስጥ በከፈተው ተኩስ አራት ሕፃናት ሞተው ሰባት መቁሰላቸው ከተሰማ ከቀናት በኋላ ነው። የተጠርጣሪው ወላጆች በሰው ልጅ ሞት እጃቸው አለበት፤ አደጋው ከመድረሱ በፊት ማስጠንቀቂያ አልሰጡም በሚል ቢከሰሱም ጥፋተኛ አይደለንም ብለዋል። በጦር መሣሪያ ጉዳይ ለሁለት በተከፈለችው አሜሪካ መሰል አደጋዎች በየጊዜው ይከሰታሉ። ከዚህ በፊት በነበሩ የትምህርት ቤት ተኩሶች ምክንያት ልጆቻቸውን ያጡ ወላጆች የኮንግረስ አባሉን ድርጊት በፅኑ ተቃውመውታል። የፍሬድ ጋተንበርግ ሴት ልጅ ሃይሜ ከሶስት ዓመት በፊት ፓርክላንድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ውስጥ በተከፈተ ተኩስ ነው ሕይወቷን ያጣችው። ፍሬድ ከኮንግረስ አባሉ ፎቶ ሥር የልጁን ጉርድ ፎቶ እና የመቃብሯን ፎቶ ለጥፎ፤ "የቤተሰቦቻችንን ፎቶ እየለጠፍንም አይደል፤ ይሄ የኔ ቤተሰብ ፎቶ ነው። አንደኛው የልጄ ፎቶ ነው፤ ሌላኛው ደግሞ የመቃብሯ። ልጄን ያጣሁት በመሣሪያ ምክንያት ነው። በቅርቡ ተማሪዎችን የገደለው ተማሪም እንዲሁም እንዳንተ ቤተሰብ ከወላጆቹ ጋር መሣሪያ ይዞ ፎቶ ይነሳ ነበር" ሲል ፅፏል። ሌላኛው ዮዋኪን የተሰኘው ልጁን በፓርክላንድ ትምህርት ቤት ተኩስ ሳቢያ ያጣው ማኔኤል ኦሊቨር የሰውየው ደርጊ ፍፁም ተቀባይነት የለውም ሲል ለሲኤንኤን ተናግሯል። የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላትም ይህን የቶማስ ድርጊት በፅኑ አውግዘውታል። የኢሊኖይ ግዛት የኮንግረሱ ሪፐብሊካን ፓርቲ ተወካይ የሆኑት አዳም ኪንዚንገር የፓርቲ አጋራቸውን ወቅሰዋል። ይሁን እንጂ ሌሎች ትላልቅ ስም ያላቸው ወግ አጥባቂ የአሜሪካ ፖለቲከኞች ደግሞ ለሰውዬው ድጋፋቸውን አሳይተዋል። የኮሎራዶ ተወካይ የሆኑትና የጦር መሣሪያ መብት ባለቤትነት መብት ተሟጋች የሆኑት ሎረን ቦበርት እንዲሁም ሌላኛው ሪፐብሊካን ሆዜ ካስቲሎ ለቶማስ ድጋፋቸውን ችረዋል። ቶማስ ማሴ የኬንታኪ ተወካይ ሆነው ለመጀመሪያ ጊዜ የተመረጡት በፈረንጆቹ 2012 ነበር። ሰውዬው 'ሰከንድ አሜንድመንት' በመባል የሚታወቀው የጦር መሣሪያ የመታጠቅ መብት ሕግ ቀንደኛ አቀንቃኝ ናቸው። የጦር መሣሪያ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ በትምህርት ቤቶች የሚከሰተውን ግድያ አያቆመውም ብለውም ተከራክረዋል። ባለፈው ሚያዚያ የጦር መሣሪያ የሚገዙ ሰዎች ዕድሜ ከ21 ወደ 18 ዝቅ ሊል ይገባል ብለውም ሞግተዋል። በአሜሪካው ባለፈው ዓመት ብቻ 20 ሺህ ሰዎች በጦር መሣሪያ አመፅ ምክንያት ሞተዋል። ይህም ባለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት ከታየው የላቀ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/news-59545032
0business
የኢትዮጵያ የምግብ ዘይት እጥረት አዙሪት እና ምክንያቱ
ከሰሞኑ የምግብ ዘይት ዋጋ መናር የኢትዮጵያውያን ዋነኛ መነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ ሰንብቷል። ትልቁን የገበያ ድርሻ በሚይዘው የፓልም ዘይትም ሆነ በሱፍ (ሰንፍላወር) ዘይት ላይ ድንገተኛ የሆነ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ታይቷል። ይህም በተጠቃሚው ላይ ከፍተኛ ጫናን ፈጥሯል። በ6500 ወርሃዊ ደሞዝ 7 የቤተሰብ አባላት የሚያስተዳድሩት አንድ የመንግሥት ሠራተኛ፤ 5 ሊትር የፓልም ዘይት ከ1000 አስከ 1200 ብር እየገዙ መሆኑን በመናገር፤ " . . . አንድ ፍሬ ሳሙና ከ26-30 ብር እየተገዛ፤ ለተለያዩ ጉዳዮች ከደሞዝ እየተቆረጠ መኖር በጣም ከባድ ነዉ" በማለት ምሬታቸውን ይገልጻሉ። አቶ ነጌሳ ቱካና ደግሞ በጉጂ ዞን ኦዶ ሻኪሶ ወረዳ የአንድ አነስተኛ ምግብ ቤት ባለቤት ናቸው። በቀን ከ80 እስከ 100 ለሚሆኑ ተጠቃሚዎችም ምግብ ይሸጣሉ። "ሦስት ሊትር ዘይት 550 ብር ገብቷል። እሱ ራሱ አይገኝም። ለምግብ ቤቶች ሥራ በጣም አስቸጋሪ ሆኗል" ይላሉ። በዘይት የችርቻሮ ንግድ ላይ የተሰማሩት የመንዲ ከተማ ነጋዴው በምርት እጥረት እና ዋጋ ንረት የንግድ ሥራቸው መቀዛቀዙን ይናገራሉ። የዘይት ዋጋ በኢትዮጵያ በድንገት ከፍተኛ ጭማሪ ሲያሳይ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። እንደው በድንገት የዘይት ዋጋ ለምን ጣራ ይነካል? ስንል አምራቾችን፣ ጅምላ አካፋፋዮችን፣ ቸርቻሪዎችን እና የሚመለከተውን የመንግሥት አካል ጠይቀናል። የኢትዮጵያ የዘይት ምርት እና ፍጆታ ከጥቂት ዓመታት በፊት ፉድ፣ ቤቨሬጅ ኤንድ ፋርማሱቲካል ዲቨሎፕመንት ኢንስቲትዩት ኦፍ ኢትዮጵያ እና ግሎባል አሊያንስ ፎር ኢምፕሩቭድ ኒዩትሪሸን የሰሩት ጥናት በአገሪቱ የዘይት ገበያ ላይ የፓልም፣ የሱፍ፣ የአትክልት፣ የወይራ (ኦሊቭ ኦይል) እና የሶያ ዘይት አይነቶች ጥቅም ላይ እንደሚውሉ አሳይቷል። ይህ ጥናት እንደሚያመለክተው ከሆነ ኢትዮጵያ እስከ 90 በመቶ የሚሆነውን የዘይት ፍላጎቷን በፓልም ዘይት የምታሟላበት ዓመታት አሉ። ኢትዮጵያ በፓልም ዘይት ምርታቸው ከሚታወቁት ኢንዶኔዢያ እና ማሌዢያ ከፍተኛ መጠን ያለው የፓልም ዘይት ታስገባለች። ታዲያ የፓልም ዘይትን ወደ አገር ውስጥ እንዲያስገቡ ተፈቅዶላቸው የነበሩት መንግሥታዊዎቹ አለ በጅምላ እና ጅንአድ ናቸው። በእነዚህ የመንግሥት ተቋማት በኩል የሚገባው ፓልም ዘይት ለተጠቃሚዎች የሚደርሰው በሸማቾች ማኅበራት በኩል ነው። እንደ ፌቤላ እና ሸሙ ያሉት የግል የዘይት ፋብሪካዎችም የፓልም ደፍድፍ ወደ አገር ውስጥ በማስገባት በአገር ውስጥ የፓልም ዘይት ያመርታሉ። የተቀሩትን የዘይት አይነቶች ደግሞ የግል ተቋማት በኢትዮጵያ እንዲያመርቱ እና ከውጪ እንዲያስገቡ ይፈቀድላቸዋል። የሰሞኑ የዘይት ዋጋ ጭማሪ በቅርቡ ላገጠመው የዘይት ዋጋ ጭማሪ፤ ከሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት እስከ 'የተጋነነ ትርፍ ፈላጊ ነጋዴዎች' በምክንያትነት ቀርበዋል። ዘይት አምራቾች ምን ይላሉ? የዛሬ አንድ ዓመት ፌቤላ የተባለው ግዙፉ የዘይት ፋብሪካ ተመርቆ ወደ ሥራ ሲገባ፤ የኢትዮጵያን የዘይት እጥረት ይቀርፋል ተብሎ ተስፋ ተደርጎ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቡሬ ከተማ ተገኝተው ፋብሪካውን መርቀው ከፍተዋል። በወቅቱም 60 በመቶ የኢትዮጵያን የዘይት ፍላጎትን ያሟላልም ተብሎለት ነበር - ፌቤላ ኢንደስትሪያል ኮምፕሌክስ። ነገር ግን ዛሬም የዘይት ዋጋ መናር ብዙዎችን እንዳማረረ ቀጥሏል። ፋብሪካው በበኩሉ ከጥሬ ዕቃ አቅርቦት ጋር የተያያዙ ብዙ ፈተኛ ሁኔታዎች ቢገጥሙኝም የተቻለኝን ሁሉ እያደረኩ ነው ይላል። ፌቤላ ኢንደስትሪያል ኮምፕሌክስ የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ አካል ሲሆን የኩባንያው ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰጠኝ እንግዳው፣ ፋብሪካው ባለፈው አንድ ዓመት 166 ሚሊዮን ሊትር የፓልም ዘይት አምርቶ ማከፋፈሉን ይናገራሉ። አቶ ሰጠኝ ፋብሪካቸው በአምስት ዙሮች 105 ሺህ ሜትሪክ ቶን የፓልም ድፍድፍ ዘይት ከውጪ ማስመጣቱንም አመልክተዋል። በሊትር ከ40 ወደ 82 ብር ከአንድ ዓመት በፊት ፋብሪካው 1 ሊትር ዘይት በ40 ብር ለገበያ ሲያቀርብ እንደነበረ የሚያስታውሱት አቶ ሰጠኝ፤ ዛሬ ላይ ግን የ1 ሊትር የፓልም ዘይት ዋጋ 82 ብር መሆኑን ይናገራሉ። ፋብሪካው ዋጋውን በእጥፍ እንዲጨምር ያስገደዱት በርካታ ምክንያቶች ናቸው በማለት፣ የመጀመሪያው የፓልም ድፍድፍ ዘይት ዋጋ መጨመርን ይጠቅሳሉ። "አንድ ሜትሪክ ቶን የፓልም ድፍድፍ ዘይት 762 ዶላር ነበር የምንገዛው። 4ኛው ዙር ላይ ለአንድ ሜትሪ ቶን 1361 ዶላር ከፍለናል። አሁን እያሰራጨን ያለነው ዘይት ደግሞ በ5ኛው ዙር በ1407 ዶላር ተገዝቶ በገባ ድፍድፍ ፓልም የተመረተ ነው" በማለት የዋጋውን ጭማሪውን ያስረዳሉ። ከፓልም ድፍድፍ ዘይት መወደድ በተጨማሪ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ የደኅንነት ስጋት፣ የአገር ውስጥ ግብዓት ዋጋ ጭማሪ እና የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሌሎች ለፋብሪካው ፈተኛ ሁኔታዎችን የፈጠሩ ናቸው ይላሉ። አቶ ሰጠኝ ፌቤላ ባሉት ግዙፍ 5 ማሽኖች አማካይነት በቀን እስከ 1.5 ሚሊዮን ሊትር ዘይት የማምረት አቅም ቢኖረውም አሁን ላይ የምርት አቅማቸው በግማሽ መገደቡን ይጠቅሳሉ። "በኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ምክንያት በቀን 750 ሺህ ሊትር ብቻ ነው የምናመርተው። ይህን ችግር ለመቅረፍ ከፍተኛ የነዳጅ መጠን የሚጠቀሙ ጀነሬተሮችን ገዝተን እየተጠቀምን ነው።" በአሁኑ ወቅት ፋብሪካው ከቅባት እህሎች ዘይት ለማምረት የሚያስፈልገውን ግብዓት ማቅረብ የሚችል የአገር ውስጥ አቅራቢ ባለመኖሩ፣ ለዘይት ምርቱ የሚያስፈልገውን ግብዓት ለማግኘት የራሱ እርሻ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ አለው። ይሁን እንጂ በክልሉ ያለው የፀጥታ ችግር የእርሻ ሥራቸው ውጤታማ እንዳይሆን እንዳደረገው አቶ ሰጠኝ ይገልጻሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ፌቤላ ፋብሪካ አንድ ሊትር በ82 ብር ለአካፋፋዮች ያቅርብ እንጂ ቢቢሲ ባደረገው ቅኝት በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ባለ 1 ሊትር ፓልም ዘይት እስከ 150 ብር፣ ባለ 3 ሊትር 550 ብር እና ባለ5 ሊትር ደግሞ በትንሹ 900 ብር ይጠየቅበታል። ለባለ 1 ሊትሩ ሰንፍላወር ዘይት ደግሞ ከ180 አስከ 190 ብር ይጠየቃል። አቶ ሰጠኝ ግን "አከፋፋዮች አሁን (ማክሰኞ የካቲት 29) ፋብሪካ በር ላይ 1 ሊትር ፓልም ዘይት በ82 ብር ነው እየጫኑ ያሉት" ይላሉ። ይህ ሰፊ የዋጋ ልዩነት ከየት መጣ? "ጭማሪው እኛን አይመለከትም" ይላሉ አቶ ሰጠኝ፤ ፋብሪካው ከመንግሥት በተሰጠው ኮታ መሠረት ለ7 ክልሎች እና ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከላይ በተጠቀሰው የፋብሪካ ዋጋ የፓልም ዘይት እያከፋፈለ እንደሆነ በመጥቀስ። ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈገ ለጉዳዩ ቅርበት ያለው የሽያጭ ባለሙያ፤ ከፍተኛ ፍላጎት ባለባቸው የመሠረታዊ ሸቀጦች ዋጋ የሚተመነው በግለሰቦች ፍላጎት እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግሯል። ይህ ዘይትን ጨምሮ መሠረታዊ ሸቀጦችን ወደ አገር ውስጥ በማስገባት እና በማከፋፈል ሂደት ውስጥ የበርካታ ዓመታት ልምድ ያለው የሽያጭ ባለሙያ እንደሚለው፤ በመሠረታዊ ሸቀጦች አስመጪዎች ከ30 በመቶ ያላነሰ ትርፍ መያዛቸው የተለመደ ነው። የሽያጭ ባለሙያው እንደሚለው ከሆነ የዘይትም ሆነ የሌሎች መሠረታዊ ፍጆታዎች የሽያጭ ዋጋ የሚተመነው ምክንያታዊ በሆኑ ምጣኔ ሃብታዊ ስሌት ላይ ተመስርቶ ሳይሆን በግለሰቦች ፍላጎት ነው። አስመጪዎች ምርቶችን ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት የውጭ ምንዛሬ ከባንኮች ማግኘት ስለማይችሉ ሌሎች አማራጮችን ለመጠቀም ይገደዳሉ። እናም በተለያየ መንገድ ያገኙትም የውጭ ምንዛሪ የሚያካክሱት በሚያስገቡት ምርት ላይ ዋጋ ያስፈልገናል የሚሉትን በመጨመር ነው ይላል የሽያጭ ባለሙያው። 'የውጭ ምንዛሬ ታጣ ይሉናል' ዘይት ከአስመጪዎች በመግዛት በጅምላ እና በችርቻሮ ለተጠቃሚዎች የሚያደርሱት የመንዲ ከተማ ነጋዴ በአካባቢያቸው የምርት እጥረት መኖሩን ይናገራሉ። "ዘይት ከእዲስ አበባና ከአዳማ ነበር የምናመጣዉ። አሁን ግን አጥተናል፤ ማምጣት ልቻልንም" ይላሉ። "አስመጪዎችን ስንጠይቅ 'የውጭ ምንዛሬ ታጣ' ይሉናል" በማለት የሚሰጣቸውን ምላሽ ይናገራሉ። የንግድ ሰንሰለት ርዝመት የሽያጭ ባለሙያ ዘይትን ጨምሮ በሌሎች መሠረታዊ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ጭማሪ እንዲከሰት የሚያደርገው ሌላኛው ትልቁ ምክንያት የንግድ ሰንሰለቱ መርዘም ነው ይላል። "የንግድ ሰንሰለቱ በጣም ረዥም ነው። አስመጪዎች ምርቱን ከሞጆ ደረቅ ወደብ አንስተው መርካቶ ያስገባሉ። አስመጪዎች ዋጋ ተምነው ለጅምላ አካፋፋዮች ያደርሳሉ" በማለት የገበያ ሰንሰለቱን ሂደት ያብራራል። "ከዚያም ጅምላ አፋፋዮች ደግሞ የራሳቸውን ትርፍ ይዘው ክፍለ አገር ላለ ሌላ ጀምላ አከፋፋይ ያደርሳሉ። እነዚህ ጀምላ አካፋፋዮች ደግሞ ለቸርቻሪ ይሸጣሉ። ቸርቻሪ በነጠላ እቃ ላይ ብዙ ትርፍ ይይዛል። በመጨረሻ ዘይቱ ተጠቃሚው ጋር ሲደርስ ዋጋው ይከመራል።" ከዚህ በተጨማሪም አቅም ያለው ተጠቃሚ ደግሞ "ገና ለገና 'ዘይት ጠፋ ሲባል' ከሚያስፈልገው በላይ ካርቶን ሙሉ ገዝቶ ስለሚያስቀምጥም ፍላጎት እንዲጨመር ያደርጋል" በማለት ተጨማሪ ምክንያት ያስቀምጣል። የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት በንግድ እና የቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ አበባ ታመነ ከሰሞኑ ለተከሰተው የዘይት ዋጋ ጭማሪ ዋነኛ ምክንያቱ የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ነው ይላሉ። ወ/ሮ አበባ እንደሚሉት በአዲስ አበባ ከተማ ያጋጠመው የሰንፍላወር (የሱፍ) ዘይት እጥረት እንጂ የፓልም ዘይት አይደለም። ዩክሬን ከፍተኛ የሱፍ ዘይት አምራች አገር መሆኗን በማስታወስ፤ በጦርነቱ ምክንያት አስመጪዎች ምርት ማግኘት ባለመቻላቸው እጥረት አጋጥሟል ይላሉ። "በራሳቸው ዶላር ምርት ያገኙት እንኳ 'ዋጋ እየጨመረ ስለሚሄድ ነገ እና ከነገ ወዲያ የተሻለ ትርፍ አገኛለሁ' በሚል አስተሳሳብ ጂቡቲ ወደብ ላይ ምርት የሚያቆዩ ነጋዴዎች ስላሉ እጥረቱ ሊያጋጥም ችሏል" ይላሉ። የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተሯ ሰኞ የካቲት 28/2014 ዓ.ም ለቢቢሲ በተናገሩበት ቀን፤ መንግሥት ገበያውን ለማረጋጋት 40 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ከሳዑዲ አረቢያ ለማስገባት ስምምነት መጨረሱን ተናግረው ነበር። "በአካል ተገናኝተው ከስምምነት ተደርሷል። 20 ሚሊዮን ሊትሩ የሰን ፍላወር ነው ቀሪው ፓልም ነው። ይህ ዘይት በቅርብ ቀን ይገባል ገበያውንም ያረጋጋል" ሲሉ ለቢቢሲ ገልጸው ነበር። ወ/ሮ አበባ ይህን ይበሉ እንጂ የገንዘብ ሚኒስቴር 40 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ለመግዛት ከስምምነት አለመድረሱን እና ጉዳዩ ገና በጥናት ላይ እንደሚገኝ ስለመናገሩ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
የኢትዮጵያ የምግብ ዘይት እጥረት አዙሪት እና ምክንያቱ ከሰሞኑ የምግብ ዘይት ዋጋ መናር የኢትዮጵያውያን ዋነኛ መነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ ሰንብቷል። ትልቁን የገበያ ድርሻ በሚይዘው የፓልም ዘይትም ሆነ በሱፍ (ሰንፍላወር) ዘይት ላይ ድንገተኛ የሆነ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ታይቷል። ይህም በተጠቃሚው ላይ ከፍተኛ ጫናን ፈጥሯል። በ6500 ወርሃዊ ደሞዝ 7 የቤተሰብ አባላት የሚያስተዳድሩት አንድ የመንግሥት ሠራተኛ፤ 5 ሊትር የፓልም ዘይት ከ1000 አስከ 1200 ብር እየገዙ መሆኑን በመናገር፤ " . . . አንድ ፍሬ ሳሙና ከ26-30 ብር እየተገዛ፤ ለተለያዩ ጉዳዮች ከደሞዝ እየተቆረጠ መኖር በጣም ከባድ ነዉ" በማለት ምሬታቸውን ይገልጻሉ። አቶ ነጌሳ ቱካና ደግሞ በጉጂ ዞን ኦዶ ሻኪሶ ወረዳ የአንድ አነስተኛ ምግብ ቤት ባለቤት ናቸው። በቀን ከ80 እስከ 100 ለሚሆኑ ተጠቃሚዎችም ምግብ ይሸጣሉ። "ሦስት ሊትር ዘይት 550 ብር ገብቷል። እሱ ራሱ አይገኝም። ለምግብ ቤቶች ሥራ በጣም አስቸጋሪ ሆኗል" ይላሉ። በዘይት የችርቻሮ ንግድ ላይ የተሰማሩት የመንዲ ከተማ ነጋዴው በምርት እጥረት እና ዋጋ ንረት የንግድ ሥራቸው መቀዛቀዙን ይናገራሉ። የዘይት ዋጋ በኢትዮጵያ በድንገት ከፍተኛ ጭማሪ ሲያሳይ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። እንደው በድንገት የዘይት ዋጋ ለምን ጣራ ይነካል? ስንል አምራቾችን፣ ጅምላ አካፋፋዮችን፣ ቸርቻሪዎችን እና የሚመለከተውን የመንግሥት አካል ጠይቀናል። የኢትዮጵያ የዘይት ምርት እና ፍጆታ ከጥቂት ዓመታት በፊት ፉድ፣ ቤቨሬጅ ኤንድ ፋርማሱቲካል ዲቨሎፕመንት ኢንስቲትዩት ኦፍ ኢትዮጵያ እና ግሎባል አሊያንስ ፎር ኢምፕሩቭድ ኒዩትሪሸን የሰሩት ጥናት በአገሪቱ የዘይት ገበያ ላይ የፓልም፣ የሱፍ፣ የአትክልት፣ የወይራ (ኦሊቭ ኦይል) እና የሶያ ዘይት አይነቶች ጥቅም ላይ እንደሚውሉ አሳይቷል። ይህ ጥናት እንደሚያመለክተው ከሆነ ኢትዮጵያ እስከ 90 በመቶ የሚሆነውን የዘይት ፍላጎቷን በፓልም ዘይት የምታሟላበት ዓመታት አሉ። ኢትዮጵያ በፓልም ዘይት ምርታቸው ከሚታወቁት ኢንዶኔዢያ እና ማሌዢያ ከፍተኛ መጠን ያለው የፓልም ዘይት ታስገባለች። ታዲያ የፓልም ዘይትን ወደ አገር ውስጥ እንዲያስገቡ ተፈቅዶላቸው የነበሩት መንግሥታዊዎቹ አለ በጅምላ እና ጅንአድ ናቸው። በእነዚህ የመንግሥት ተቋማት በኩል የሚገባው ፓልም ዘይት ለተጠቃሚዎች የሚደርሰው በሸማቾች ማኅበራት በኩል ነው። እንደ ፌቤላ እና ሸሙ ያሉት የግል የዘይት ፋብሪካዎችም የፓልም ደፍድፍ ወደ አገር ውስጥ በማስገባት በአገር ውስጥ የፓልም ዘይት ያመርታሉ። የተቀሩትን የዘይት አይነቶች ደግሞ የግል ተቋማት በኢትዮጵያ እንዲያመርቱ እና ከውጪ እንዲያስገቡ ይፈቀድላቸዋል። የሰሞኑ የዘይት ዋጋ ጭማሪ በቅርቡ ላገጠመው የዘይት ዋጋ ጭማሪ፤ ከሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት እስከ 'የተጋነነ ትርፍ ፈላጊ ነጋዴዎች' በምክንያትነት ቀርበዋል። ዘይት አምራቾች ምን ይላሉ? የዛሬ አንድ ዓመት ፌቤላ የተባለው ግዙፉ የዘይት ፋብሪካ ተመርቆ ወደ ሥራ ሲገባ፤ የኢትዮጵያን የዘይት እጥረት ይቀርፋል ተብሎ ተስፋ ተደርጎ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቡሬ ከተማ ተገኝተው ፋብሪካውን መርቀው ከፍተዋል። በወቅቱም 60 በመቶ የኢትዮጵያን የዘይት ፍላጎትን ያሟላልም ተብሎለት ነበር - ፌቤላ ኢንደስትሪያል ኮምፕሌክስ። ነገር ግን ዛሬም የዘይት ዋጋ መናር ብዙዎችን እንዳማረረ ቀጥሏል። ፋብሪካው በበኩሉ ከጥሬ ዕቃ አቅርቦት ጋር የተያያዙ ብዙ ፈተኛ ሁኔታዎች ቢገጥሙኝም የተቻለኝን ሁሉ እያደረኩ ነው ይላል። ፌቤላ ኢንደስትሪያል ኮምፕሌክስ የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ አካል ሲሆን የኩባንያው ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰጠኝ እንግዳው፣ ፋብሪካው ባለፈው አንድ ዓመት 166 ሚሊዮን ሊትር የፓልም ዘይት አምርቶ ማከፋፈሉን ይናገራሉ። አቶ ሰጠኝ ፋብሪካቸው በአምስት ዙሮች 105 ሺህ ሜትሪክ ቶን የፓልም ድፍድፍ ዘይት ከውጪ ማስመጣቱንም አመልክተዋል። በሊትር ከ40 ወደ 82 ብር ከአንድ ዓመት በፊት ፋብሪካው 1 ሊትር ዘይት በ40 ብር ለገበያ ሲያቀርብ እንደነበረ የሚያስታውሱት አቶ ሰጠኝ፤ ዛሬ ላይ ግን የ1 ሊትር የፓልም ዘይት ዋጋ 82 ብር መሆኑን ይናገራሉ። ፋብሪካው ዋጋውን በእጥፍ እንዲጨምር ያስገደዱት በርካታ ምክንያቶች ናቸው በማለት፣ የመጀመሪያው የፓልም ድፍድፍ ዘይት ዋጋ መጨመርን ይጠቅሳሉ። "አንድ ሜትሪክ ቶን የፓልም ድፍድፍ ዘይት 762 ዶላር ነበር የምንገዛው። 4ኛው ዙር ላይ ለአንድ ሜትሪ ቶን 1361 ዶላር ከፍለናል። አሁን እያሰራጨን ያለነው ዘይት ደግሞ በ5ኛው ዙር በ1407 ዶላር ተገዝቶ በገባ ድፍድፍ ፓልም የተመረተ ነው" በማለት የዋጋውን ጭማሪውን ያስረዳሉ። ከፓልም ድፍድፍ ዘይት መወደድ በተጨማሪ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ የደኅንነት ስጋት፣ የአገር ውስጥ ግብዓት ዋጋ ጭማሪ እና የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሌሎች ለፋብሪካው ፈተኛ ሁኔታዎችን የፈጠሩ ናቸው ይላሉ። አቶ ሰጠኝ ፌቤላ ባሉት ግዙፍ 5 ማሽኖች አማካይነት በቀን እስከ 1.5 ሚሊዮን ሊትር ዘይት የማምረት አቅም ቢኖረውም አሁን ላይ የምርት አቅማቸው በግማሽ መገደቡን ይጠቅሳሉ። "በኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ምክንያት በቀን 750 ሺህ ሊትር ብቻ ነው የምናመርተው። ይህን ችግር ለመቅረፍ ከፍተኛ የነዳጅ መጠን የሚጠቀሙ ጀነሬተሮችን ገዝተን እየተጠቀምን ነው።" በአሁኑ ወቅት ፋብሪካው ከቅባት እህሎች ዘይት ለማምረት የሚያስፈልገውን ግብዓት ማቅረብ የሚችል የአገር ውስጥ አቅራቢ ባለመኖሩ፣ ለዘይት ምርቱ የሚያስፈልገውን ግብዓት ለማግኘት የራሱ እርሻ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ አለው። ይሁን እንጂ በክልሉ ያለው የፀጥታ ችግር የእርሻ ሥራቸው ውጤታማ እንዳይሆን እንዳደረገው አቶ ሰጠኝ ይገልጻሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ፌቤላ ፋብሪካ አንድ ሊትር በ82 ብር ለአካፋፋዮች ያቅርብ እንጂ ቢቢሲ ባደረገው ቅኝት በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ባለ 1 ሊትር ፓልም ዘይት እስከ 150 ብር፣ ባለ 3 ሊትር 550 ብር እና ባለ5 ሊትር ደግሞ በትንሹ 900 ብር ይጠየቅበታል። ለባለ 1 ሊትሩ ሰንፍላወር ዘይት ደግሞ ከ180 አስከ 190 ብር ይጠየቃል። አቶ ሰጠኝ ግን "አከፋፋዮች አሁን (ማክሰኞ የካቲት 29) ፋብሪካ በር ላይ 1 ሊትር ፓልም ዘይት በ82 ብር ነው እየጫኑ ያሉት" ይላሉ። ይህ ሰፊ የዋጋ ልዩነት ከየት መጣ? "ጭማሪው እኛን አይመለከትም" ይላሉ አቶ ሰጠኝ፤ ፋብሪካው ከመንግሥት በተሰጠው ኮታ መሠረት ለ7 ክልሎች እና ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከላይ በተጠቀሰው የፋብሪካ ዋጋ የፓልም ዘይት እያከፋፈለ እንደሆነ በመጥቀስ። ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈገ ለጉዳዩ ቅርበት ያለው የሽያጭ ባለሙያ፤ ከፍተኛ ፍላጎት ባለባቸው የመሠረታዊ ሸቀጦች ዋጋ የሚተመነው በግለሰቦች ፍላጎት እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግሯል። ይህ ዘይትን ጨምሮ መሠረታዊ ሸቀጦችን ወደ አገር ውስጥ በማስገባት እና በማከፋፈል ሂደት ውስጥ የበርካታ ዓመታት ልምድ ያለው የሽያጭ ባለሙያ እንደሚለው፤ በመሠረታዊ ሸቀጦች አስመጪዎች ከ30 በመቶ ያላነሰ ትርፍ መያዛቸው የተለመደ ነው። የሽያጭ ባለሙያው እንደሚለው ከሆነ የዘይትም ሆነ የሌሎች መሠረታዊ ፍጆታዎች የሽያጭ ዋጋ የሚተመነው ምክንያታዊ በሆኑ ምጣኔ ሃብታዊ ስሌት ላይ ተመስርቶ ሳይሆን በግለሰቦች ፍላጎት ነው። አስመጪዎች ምርቶችን ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት የውጭ ምንዛሬ ከባንኮች ማግኘት ስለማይችሉ ሌሎች አማራጮችን ለመጠቀም ይገደዳሉ። እናም በተለያየ መንገድ ያገኙትም የውጭ ምንዛሪ የሚያካክሱት በሚያስገቡት ምርት ላይ ዋጋ ያስፈልገናል የሚሉትን በመጨመር ነው ይላል የሽያጭ ባለሙያው። 'የውጭ ምንዛሬ ታጣ ይሉናል' ዘይት ከአስመጪዎች በመግዛት በጅምላ እና በችርቻሮ ለተጠቃሚዎች የሚያደርሱት የመንዲ ከተማ ነጋዴ በአካባቢያቸው የምርት እጥረት መኖሩን ይናገራሉ። "ዘይት ከእዲስ አበባና ከአዳማ ነበር የምናመጣዉ። አሁን ግን አጥተናል፤ ማምጣት ልቻልንም" ይላሉ። "አስመጪዎችን ስንጠይቅ 'የውጭ ምንዛሬ ታጣ' ይሉናል" በማለት የሚሰጣቸውን ምላሽ ይናገራሉ። የንግድ ሰንሰለት ርዝመት የሽያጭ ባለሙያ ዘይትን ጨምሮ በሌሎች መሠረታዊ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ጭማሪ እንዲከሰት የሚያደርገው ሌላኛው ትልቁ ምክንያት የንግድ ሰንሰለቱ መርዘም ነው ይላል። "የንግድ ሰንሰለቱ በጣም ረዥም ነው። አስመጪዎች ምርቱን ከሞጆ ደረቅ ወደብ አንስተው መርካቶ ያስገባሉ። አስመጪዎች ዋጋ ተምነው ለጅምላ አካፋፋዮች ያደርሳሉ" በማለት የገበያ ሰንሰለቱን ሂደት ያብራራል። "ከዚያም ጅምላ አፋፋዮች ደግሞ የራሳቸውን ትርፍ ይዘው ክፍለ አገር ላለ ሌላ ጀምላ አከፋፋይ ያደርሳሉ። እነዚህ ጀምላ አካፋፋዮች ደግሞ ለቸርቻሪ ይሸጣሉ። ቸርቻሪ በነጠላ እቃ ላይ ብዙ ትርፍ ይይዛል። በመጨረሻ ዘይቱ ተጠቃሚው ጋር ሲደርስ ዋጋው ይከመራል።" ከዚህ በተጨማሪም አቅም ያለው ተጠቃሚ ደግሞ "ገና ለገና 'ዘይት ጠፋ ሲባል' ከሚያስፈልገው በላይ ካርቶን ሙሉ ገዝቶ ስለሚያስቀምጥም ፍላጎት እንዲጨመር ያደርጋል" በማለት ተጨማሪ ምክንያት ያስቀምጣል። የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት በንግድ እና የቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ አበባ ታመነ ከሰሞኑ ለተከሰተው የዘይት ዋጋ ጭማሪ ዋነኛ ምክንያቱ የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ነው ይላሉ። ወ/ሮ አበባ እንደሚሉት በአዲስ አበባ ከተማ ያጋጠመው የሰንፍላወር (የሱፍ) ዘይት እጥረት እንጂ የፓልም ዘይት አይደለም። ዩክሬን ከፍተኛ የሱፍ ዘይት አምራች አገር መሆኗን በማስታወስ፤ በጦርነቱ ምክንያት አስመጪዎች ምርት ማግኘት ባለመቻላቸው እጥረት አጋጥሟል ይላሉ። "በራሳቸው ዶላር ምርት ያገኙት እንኳ 'ዋጋ እየጨመረ ስለሚሄድ ነገ እና ከነገ ወዲያ የተሻለ ትርፍ አገኛለሁ' በሚል አስተሳሳብ ጂቡቲ ወደብ ላይ ምርት የሚያቆዩ ነጋዴዎች ስላሉ እጥረቱ ሊያጋጥም ችሏል" ይላሉ። የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተሯ ሰኞ የካቲት 28/2014 ዓ.ም ለቢቢሲ በተናገሩበት ቀን፤ መንግሥት ገበያውን ለማረጋጋት 40 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ከሳዑዲ አረቢያ ለማስገባት ስምምነት መጨረሱን ተናግረው ነበር። "በአካል ተገናኝተው ከስምምነት ተደርሷል። 20 ሚሊዮን ሊትሩ የሰን ፍላወር ነው ቀሪው ፓልም ነው። ይህ ዘይት በቅርብ ቀን ይገባል ገበያውንም ያረጋጋል" ሲሉ ለቢቢሲ ገልጸው ነበር። ወ/ሮ አበባ ይህን ይበሉ እንጂ የገንዘብ ሚኒስቴር 40 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ለመግዛት ከስምምነት አለመድረሱን እና ጉዳዩ ገና በጥናት ላይ እንደሚገኝ ስለመናገሩ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-60658208
5sports
በ2020 በስፖርት ሜዳዎች ላይ የተስተዋሉ የተቃውሞ ምልክቶች
በፈረንጆቹ 2000 የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝደንት ኔልሰን ማንዴላ "ስፖርት ዓለምን የመቀየር ኃይል አለው" ሲሉ ተናግረው ነበር። ከሁለት አሥርት ዓመታት በኋላ በ2020 ይህ እውን ሆኖ ታይቷል። ያለፈው የፈረንጆቹ ዓመት [2020] በሁሉም የስፖርት ዘርፎች ያሉ የዓለማችን ስፖርተኛ ዓለምን ለመቀየር ቆርጠው የተነሱበት ነበር። ዘረኝነት ይብቃ ሲሉ ጮኸዋል። ለውጥ ይምጣ ሲሉም ጠይቀዋል። ሴራሊዮናዊው አጥቂ ኬይ ካማራ በአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከር ነው የሚጫወተው። የቀድሞ ክለቡ ከኮሎራዶ ራፒድስ ሚኒሶታ ዩናይትድን ተቀላቅሏል። ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ በፖሊስ እጅ በግፍ መገደሉን ተከትሎ ተቃውሟቸውን ካሰሙ ተጫዋቾች መካከል ነው ካማራ። "የልጆቼ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ነው አቋሜን በይፋ እንድገልፅ ያደረገኝ" ይላል ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ። ከአሜሪካ አልፎ በእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ የሚጫወቱ እግር ኳሰኞች ዘረኝነትን በመቃወም መንበርከክ የጀመሩት በ2020 ነው። አሜሪካዊቷ የዝላይ ውድድር ክብረ-ወሰን ባለቤት ቶሪ ፍራንክሊን እንደምትለው ስፖርት በሰዎች አስተሳሰብ ላይ ተፅዕኖ ማሳደር ይችላል። አልፎም ዘረኝነት ለመዋጋት በሚደረገው ፍልሚያ የስፖርት ሚና የሚናቅ አይደለም ትላለች። "እኔ ስፖርት ትልቅ ተፅዕኖ ማምጣት እንደሚችል ነው የማስበው" ትላለች ፍራንክሊን። "በአሜሪካ ባህል ስፖርት ትልቅ ቦታ አለው። በቴሌቪዥን ሰፊ ሽፋን ይሰጠዋል። መገናኛ ብዙሃን ይዘግቡታል። ለዚህ ነው ዘረኝነትን በመቃወም እጃችንን ስናነሳ ለውጥ ልናመጣ እንችላለን የምለው።" ባለፈው ነሐሴ የአሜሪካ ቅርጫት ኳስ ክለብ ሚልዋውኪ ባክስ ተጫዋቾች ከኦርላንዶ ማጂክ ጋር የነበራቸውን ጨዋታ ጃኮብ ብሌክ የተሰኘው ጥቁር አሜሪካዊ በፖሊስ ጥይት መመታቱን ተከትሎ አንጫወትም ብለው ነበር። ብሌክ በፖሊስ ጥይት በተደጋጋሚ የተመታው በቅርጫት ኳስ ክለቡ ስታድየም አቅራቢያ ነበር። ይህንን ተከትሎ ኤንቢኤ የተባለው የቅርጫት ኳስ አስተዳደር ሌሎችም ጨዋታዎች እንዲሰረዙ ትዕዛዝ አስተላልፎ ነበር። በወቅቱ በአሜሪካ ቅርጫት ኳስ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ስፖርታዊ ውድድሮች እንዲሰረዙ ተደርጎ ነበር። የሚያነሳሳ ለውጥ በአትሌቲክስ ዓለም ትልቁ ውድድር የኦሊምፒክ ጨዋታ ነው። ይህ ውድድር በ2020 ሊካሄድ ዕቅድ ተይዞለት የነበረ ቢሆንም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ይህ ሳይሆን ቀርቷል። ከዚህ ቀደም በነበሩ የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በርካታ አትሌቶች ለውጥ ለማምጣት እጃቸውን ወደላይ አንስተው ነበር። አትሌቶቹ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ለውጦችን የሚጠይቁ ርዕሶችን አንስተዋል። ነገር ግን ባፈለው ዓመት ጥር የኦሊምፒክ ኮሚቴ አዲስ ሕግጋትን አውጥቷል። ሕጉ አትሌቶቹ በኦሊምፒክ መድረክ ላይ ፖለቲካዊ፣ ሐይማኖታዊ፣ አሊያም ከዘር ጋር የተገናኘ መልዕክት ማስተላለፍ አይችሉም ይላል። ኮሚቴው በተለይ ደግሞ በእጅ ምልክት ማሳየትና መንበርከክ ክልክል ነው ብሏል። የኦሊምፒክ ሕጎችን አልቀበልም ማለት እንደማይቻልም ኮሚቴው አዲስ ባወጣው መመሪያ ላይ አስቀምጧል። በ2019 በተካሄደው የፓን አሜሪካን ጨዋታዎች ላይ ተቃውሟቸውን እጃቸውን ከፍ በማድረግ ያሳዩ ሁለት አትሌቶች የ12 ወራት ቅጣት ተላልፎባቸው ነበር። በኦሊምፒክ ሜዳ ከታዩ ታሪካዊ ተቃውሞዎች መካከል አንዱ አሜሪካዊያኒ ቶኒ ስሚዝና ጆን ካርሎስ በ1968 የሜክሲኮ ኦሊምፒክ ያለ ጫማ፣ በጥቁር ካልሲና ጥቁር ጓንት ሆነው እጃቸውን በማንሳት ተቃውሟቸውን የገለፁበት መንገድ ነው። አትሌቶቹ በዚህ ድርጊታቸው ዕግድ ተጥሎባቸው ነበር። ሌላኛው ክስተት የታየው በ2016ቱ የሪዮ ኦሊምፒክ ነው። በወቅቱ በማራቶን ውድድር የነሐስ ሜዳሊያ ባለቤት የነበረው ኢትዮጵያዊው ፈይሳ ሌሊሳ ሁለት እጆቹን ወዳላይ በማንሳት በማጣመር የኦሮሞ ተቃውሞን ያጎላበት መንገድ ነው። ፈይሳ ይህን ምልክት የተቃውሞ ምልክት ያሳየው በውድድሩ መጠናቀቂያ መስመር ላይና በጋዜጣዊ መግለጫ ቦታ ላይ ነበር። ይህ ከሆነ ከሁለት ዓመት በኋላ የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከስልጣን ወርደው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተተኩ። ምንም እንኳ ፈይሳ ብቻውን ለውጥ አምጥቷል ባይቻልም በወቅቱ በአገር ቤት የነበረውን ተቃውሞ ለዓለም ሕዝብ በማንፀባረቅ ሚና እንደተጫወተ የሚካድ አይደለም። ነገር ግን የኮሚቴው መመሪያ መሰል ተቃውሞዎች በምንም ዓይነት መንገድ በኦሊምፒክ መድረክ ላይ እንዲታይ አይፈቅድም። አሁን ሁሉም ስፖርተኞች ጥያቄያቸው አንድ ነው - ቀጣይ ምን ማድረግ እንችላለን? የሚል። አብዛኛዎቹ ገና ብዙ መንገድ ይቀረናል ይላሉ። ለውጥ ለማምጣት ስፖርት የበኩሉን መወጣት ይቻል እንጂ ብቸኛው መንገድ እንዳልሆነ በርካቶች ይስማማሉ። ነገር ግን ታሪክ ስፖርት ተፅዕኖ ፈጣሪ መሆኑን መዝግቦ አሳይቶናል።
በ2020 በስፖርት ሜዳዎች ላይ የተስተዋሉ የተቃውሞ ምልክቶች በፈረንጆቹ 2000 የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝደንት ኔልሰን ማንዴላ "ስፖርት ዓለምን የመቀየር ኃይል አለው" ሲሉ ተናግረው ነበር። ከሁለት አሥርት ዓመታት በኋላ በ2020 ይህ እውን ሆኖ ታይቷል። ያለፈው የፈረንጆቹ ዓመት [2020] በሁሉም የስፖርት ዘርፎች ያሉ የዓለማችን ስፖርተኛ ዓለምን ለመቀየር ቆርጠው የተነሱበት ነበር። ዘረኝነት ይብቃ ሲሉ ጮኸዋል። ለውጥ ይምጣ ሲሉም ጠይቀዋል። ሴራሊዮናዊው አጥቂ ኬይ ካማራ በአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከር ነው የሚጫወተው። የቀድሞ ክለቡ ከኮሎራዶ ራፒድስ ሚኒሶታ ዩናይትድን ተቀላቅሏል። ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ በፖሊስ እጅ በግፍ መገደሉን ተከትሎ ተቃውሟቸውን ካሰሙ ተጫዋቾች መካከል ነው ካማራ። "የልጆቼ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ነው አቋሜን በይፋ እንድገልፅ ያደረገኝ" ይላል ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ። ከአሜሪካ አልፎ በእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ የሚጫወቱ እግር ኳሰኞች ዘረኝነትን በመቃወም መንበርከክ የጀመሩት በ2020 ነው። አሜሪካዊቷ የዝላይ ውድድር ክብረ-ወሰን ባለቤት ቶሪ ፍራንክሊን እንደምትለው ስፖርት በሰዎች አስተሳሰብ ላይ ተፅዕኖ ማሳደር ይችላል። አልፎም ዘረኝነት ለመዋጋት በሚደረገው ፍልሚያ የስፖርት ሚና የሚናቅ አይደለም ትላለች። "እኔ ስፖርት ትልቅ ተፅዕኖ ማምጣት እንደሚችል ነው የማስበው" ትላለች ፍራንክሊን። "በአሜሪካ ባህል ስፖርት ትልቅ ቦታ አለው። በቴሌቪዥን ሰፊ ሽፋን ይሰጠዋል። መገናኛ ብዙሃን ይዘግቡታል። ለዚህ ነው ዘረኝነትን በመቃወም እጃችንን ስናነሳ ለውጥ ልናመጣ እንችላለን የምለው።" ባለፈው ነሐሴ የአሜሪካ ቅርጫት ኳስ ክለብ ሚልዋውኪ ባክስ ተጫዋቾች ከኦርላንዶ ማጂክ ጋር የነበራቸውን ጨዋታ ጃኮብ ብሌክ የተሰኘው ጥቁር አሜሪካዊ በፖሊስ ጥይት መመታቱን ተከትሎ አንጫወትም ብለው ነበር። ብሌክ በፖሊስ ጥይት በተደጋጋሚ የተመታው በቅርጫት ኳስ ክለቡ ስታድየም አቅራቢያ ነበር። ይህንን ተከትሎ ኤንቢኤ የተባለው የቅርጫት ኳስ አስተዳደር ሌሎችም ጨዋታዎች እንዲሰረዙ ትዕዛዝ አስተላልፎ ነበር። በወቅቱ በአሜሪካ ቅርጫት ኳስ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ስፖርታዊ ውድድሮች እንዲሰረዙ ተደርጎ ነበር። የሚያነሳሳ ለውጥ በአትሌቲክስ ዓለም ትልቁ ውድድር የኦሊምፒክ ጨዋታ ነው። ይህ ውድድር በ2020 ሊካሄድ ዕቅድ ተይዞለት የነበረ ቢሆንም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ይህ ሳይሆን ቀርቷል። ከዚህ ቀደም በነበሩ የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በርካታ አትሌቶች ለውጥ ለማምጣት እጃቸውን ወደላይ አንስተው ነበር። አትሌቶቹ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ለውጦችን የሚጠይቁ ርዕሶችን አንስተዋል። ነገር ግን ባፈለው ዓመት ጥር የኦሊምፒክ ኮሚቴ አዲስ ሕግጋትን አውጥቷል። ሕጉ አትሌቶቹ በኦሊምፒክ መድረክ ላይ ፖለቲካዊ፣ ሐይማኖታዊ፣ አሊያም ከዘር ጋር የተገናኘ መልዕክት ማስተላለፍ አይችሉም ይላል። ኮሚቴው በተለይ ደግሞ በእጅ ምልክት ማሳየትና መንበርከክ ክልክል ነው ብሏል። የኦሊምፒክ ሕጎችን አልቀበልም ማለት እንደማይቻልም ኮሚቴው አዲስ ባወጣው መመሪያ ላይ አስቀምጧል። በ2019 በተካሄደው የፓን አሜሪካን ጨዋታዎች ላይ ተቃውሟቸውን እጃቸውን ከፍ በማድረግ ያሳዩ ሁለት አትሌቶች የ12 ወራት ቅጣት ተላልፎባቸው ነበር። በኦሊምፒክ ሜዳ ከታዩ ታሪካዊ ተቃውሞዎች መካከል አንዱ አሜሪካዊያኒ ቶኒ ስሚዝና ጆን ካርሎስ በ1968 የሜክሲኮ ኦሊምፒክ ያለ ጫማ፣ በጥቁር ካልሲና ጥቁር ጓንት ሆነው እጃቸውን በማንሳት ተቃውሟቸውን የገለፁበት መንገድ ነው። አትሌቶቹ በዚህ ድርጊታቸው ዕግድ ተጥሎባቸው ነበር። ሌላኛው ክስተት የታየው በ2016ቱ የሪዮ ኦሊምፒክ ነው። በወቅቱ በማራቶን ውድድር የነሐስ ሜዳሊያ ባለቤት የነበረው ኢትዮጵያዊው ፈይሳ ሌሊሳ ሁለት እጆቹን ወዳላይ በማንሳት በማጣመር የኦሮሞ ተቃውሞን ያጎላበት መንገድ ነው። ፈይሳ ይህን ምልክት የተቃውሞ ምልክት ያሳየው በውድድሩ መጠናቀቂያ መስመር ላይና በጋዜጣዊ መግለጫ ቦታ ላይ ነበር። ይህ ከሆነ ከሁለት ዓመት በኋላ የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከስልጣን ወርደው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተተኩ። ምንም እንኳ ፈይሳ ብቻውን ለውጥ አምጥቷል ባይቻልም በወቅቱ በአገር ቤት የነበረውን ተቃውሞ ለዓለም ሕዝብ በማንፀባረቅ ሚና እንደተጫወተ የሚካድ አይደለም። ነገር ግን የኮሚቴው መመሪያ መሰል ተቃውሞዎች በምንም ዓይነት መንገድ በኦሊምፒክ መድረክ ላይ እንዲታይ አይፈቅድም። አሁን ሁሉም ስፖርተኞች ጥያቄያቸው አንድ ነው - ቀጣይ ምን ማድረግ እንችላለን? የሚል። አብዛኛዎቹ ገና ብዙ መንገድ ይቀረናል ይላሉ። ለውጥ ለማምጣት ስፖርት የበኩሉን መወጣት ይቻል እንጂ ብቸኛው መንገድ እንዳልሆነ በርካቶች ይስማማሉ። ነገር ግን ታሪክ ስፖርት ተፅዕኖ ፈጣሪ መሆኑን መዝግቦ አሳይቶናል።
https://www.bbc.com/amharic/news-55505986
0business
የዓለማችን 10 ቱጃሮች ከወረርሽኙ በኋላ ሃብታቸው እጥፍ ማደጉ ተሰማ
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ቱጃሮችን የበለጥ ባለጸጋ፤ በድህነት አረንቋ ውስጥ የነበሩትን ደግሞ የበለጠ ደሃ እንዳደረጋቸው ኦክስፋም የተሰኘው የእርዳታ ድርጅት አስታወቀ። ድርጅቱ እንዳለው የዓለማችን ደሃ ሃገራት የገቢ ምንጫቸው በመድረቁ ምክንያት በቀን 21 ሺህ ሰው እየሞተባቸው ነው። ነገር ግን የምድራችን 10 ባለሃብቶች በፈረንጆቹ ከመጋቢት 2020 ጀምሮ ሃብታቸው እጥፍ ማደጉን ኦክስፋም ገልጧል። ድርጅቱ ለወትሮው ዳቮስ ከሚከናወነው የዓለም ምጣኔ ሃብት ስብሰባ በፊት ነበር የምድራችን የሃብት ክፍፍልን የሚያሳይ መረጃ የሚለቀው። ዳቮስ፤ በየዓመቱ ፖለቲከኞች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የመብት ተሟጋቾች፣ የምጣኔ ሃብት ሰዎች እንዲሁም ጋዜጠኞች በስዊዝ ስኪ ሪዞርት ተሰባስበው ውይይት የሚያደርጉበት፣ የሚከራከሩበት እንዲሁም ዘና የሚሉበት ስፍራ ነው። ነገር ግን ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የዳቮስ ምጣኔ ሃብት ጉባዔ በኦሚክሮን ምክንያት በበይነ መረብ የሚከናወን ይሆናል። በዚህ ሳምንት የሚከናወነው ጉባዔ የወረርሽኙ ጉዳይ፣ የክትባት ክፍፍልና ኃይል ማመንጨት ሐሳብ ይነሳበታል ተብሎ ይገመታል። የኦክስፋም የታላቋ ብሪታኒያ ቅርንጫፍ ኃላፊ ዳኒ ስሪስካንዳራጃህ እንዳሉት ድርጅታቸው ሪፖርቱን የስብሰባው ሰሞን የሚለቀው የምጣኔ ሃብት፣ የንግድና ፖለቲካ ሰዎችን ቀልብ ለመግዛት ነው። "በዚህ ወረርሽኝ ወቅት ቢያንስ በየቀኑ አንድ ሰው ቢሊየነር ይሆናል። በሌላ በኩል 99 በመቶ የሚሆነው የዓለማችን ሕዝብ በእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት ታፍኖ ነበር። የዓለም አቀፍ ንግድና ቱሪዝም ተቀዛቅዞም ነበር። በዚህ ምክንያት 160 ሚሊየን የዓለማችን ሰዎች ወደ ድህነት ዓለም ተገፍትረዋል።" "አንዳች ነገር የዓለማችንን ምጣኔ ሃብት ሸንቁሮ ይዞታል" ሲሉ አክለዋል ኃላፊው። ኦክስፋም የፎርብስ መፅሔት መረጃን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው የዓለማችን አስር ሃብታሞች እኚህ ናቸው፤ ኢላን መስክ፣ ጄፍ ቤዞስ፣ በርናርድ አርኖልት፣ ቢል ጌትስ፣ ላሪ ኤሊሰን፣ ላሪ ፔጅ፣ ሰርጌ ብሪን፣ ማርክ ዛከርበርግ፣ ስቲቭ ባልመር እና ዋረን ባፌት። አስሩ ስማቸው የከበደ ቱጃሮች ጠቅላላ ሃብታቸው ከ700 ቢሊየን ወደ 1.5 ትሪሊየን ሲያድግ በግል ደግሞ የኢላን መስክ ገቢ በአንድ ሺህ እጥፍ ሲወንጨፍ ቢል ጌትስ በበኩሉ 30 በመቶ ጭማሪ አምጥቷል። ፎርብስ መፅሔት የዓለማችን ቱጃሮችን የሚለካው ባለቸው ተቀማጭ ሃብት ለምሳሌ መሬትና ሌሎች ሲቀነስ ዕዳ በማድረግ ነው። ኦክስፋም ከዓለም ባንክ ወስዶ በሪፖርቱ ባካተተው መረጃ መሠረት በጤና አገልግሎት እጦት፣ በረሃብ፣ ፆታዊ ጥቃት እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ በየአራት ሰከንዱ አንድ ሰው ይሞታል። ድርጅቱ እንዳለው በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት 160 ሚሊየን የዓለማችን ሰዎች በቀን ከ5.50 ዶላር በታች ገቢ ነበራቸው። የዓለም ባንክ መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሃገራት በቀን 5.50 ዶላር የደህነት መለኪያ ነው ይላል። የኦክስፋም ዘገባ አክሎ ደሃ ሃገራት ዕዳቸው እየበዛ ስለመጣ ከማሕበረሰባዊ ወጪያቸው ላይ እየቀነሱ ለሌላ እያዋሉት ነው ብሏል። የፆታ እኩልነትን በተለመከተ ደግሞ በፈንጆቹ 2019 ጋር ሲነፃፀር 13 ሚሊዮን ሴቶች ከሥራ ገበታቸው ተፈናቅለዋል። በተለይ ደግሞ በዩናይትድ ኪንግደም፣ ባንግላዴሽና ዩናይትድ ስቴትስ ጥቁሮች በኮቪድ ምክንያት እጅግ ተጎድተዋል። ዳኒ ስሪስካንዳራጃህ የዓለም መንግሥታት አሁን እየሄድንበት ያለውን የከፋ መንገድ ለመቀልበስ አንድ መላ መምታት አለባቸው ይላሉ። ይህ ቱጃሮችን መቅረጥን ሊያካትት ይገባል፤ ከፍተኛ ገቢ ካላቸው የሚገኘው ቀረጥ ጥራት ላለው የጤና አገልግሎትና ለማሕበረሰባዊ ግልጋሎቶች ሊውል ይጋል ይላሉ ኃላፊው።
የዓለማችን 10 ቱጃሮች ከወረርሽኙ በኋላ ሃብታቸው እጥፍ ማደጉ ተሰማ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ቱጃሮችን የበለጥ ባለጸጋ፤ በድህነት አረንቋ ውስጥ የነበሩትን ደግሞ የበለጠ ደሃ እንዳደረጋቸው ኦክስፋም የተሰኘው የእርዳታ ድርጅት አስታወቀ። ድርጅቱ እንዳለው የዓለማችን ደሃ ሃገራት የገቢ ምንጫቸው በመድረቁ ምክንያት በቀን 21 ሺህ ሰው እየሞተባቸው ነው። ነገር ግን የምድራችን 10 ባለሃብቶች በፈረንጆቹ ከመጋቢት 2020 ጀምሮ ሃብታቸው እጥፍ ማደጉን ኦክስፋም ገልጧል። ድርጅቱ ለወትሮው ዳቮስ ከሚከናወነው የዓለም ምጣኔ ሃብት ስብሰባ በፊት ነበር የምድራችን የሃብት ክፍፍልን የሚያሳይ መረጃ የሚለቀው። ዳቮስ፤ በየዓመቱ ፖለቲከኞች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የመብት ተሟጋቾች፣ የምጣኔ ሃብት ሰዎች እንዲሁም ጋዜጠኞች በስዊዝ ስኪ ሪዞርት ተሰባስበው ውይይት የሚያደርጉበት፣ የሚከራከሩበት እንዲሁም ዘና የሚሉበት ስፍራ ነው። ነገር ግን ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የዳቮስ ምጣኔ ሃብት ጉባዔ በኦሚክሮን ምክንያት በበይነ መረብ የሚከናወን ይሆናል። በዚህ ሳምንት የሚከናወነው ጉባዔ የወረርሽኙ ጉዳይ፣ የክትባት ክፍፍልና ኃይል ማመንጨት ሐሳብ ይነሳበታል ተብሎ ይገመታል። የኦክስፋም የታላቋ ብሪታኒያ ቅርንጫፍ ኃላፊ ዳኒ ስሪስካንዳራጃህ እንዳሉት ድርጅታቸው ሪፖርቱን የስብሰባው ሰሞን የሚለቀው የምጣኔ ሃብት፣ የንግድና ፖለቲካ ሰዎችን ቀልብ ለመግዛት ነው። "በዚህ ወረርሽኝ ወቅት ቢያንስ በየቀኑ አንድ ሰው ቢሊየነር ይሆናል። በሌላ በኩል 99 በመቶ የሚሆነው የዓለማችን ሕዝብ በእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት ታፍኖ ነበር። የዓለም አቀፍ ንግድና ቱሪዝም ተቀዛቅዞም ነበር። በዚህ ምክንያት 160 ሚሊየን የዓለማችን ሰዎች ወደ ድህነት ዓለም ተገፍትረዋል።" "አንዳች ነገር የዓለማችንን ምጣኔ ሃብት ሸንቁሮ ይዞታል" ሲሉ አክለዋል ኃላፊው። ኦክስፋም የፎርብስ መፅሔት መረጃን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው የዓለማችን አስር ሃብታሞች እኚህ ናቸው፤ ኢላን መስክ፣ ጄፍ ቤዞስ፣ በርናርድ አርኖልት፣ ቢል ጌትስ፣ ላሪ ኤሊሰን፣ ላሪ ፔጅ፣ ሰርጌ ብሪን፣ ማርክ ዛከርበርግ፣ ስቲቭ ባልመር እና ዋረን ባፌት። አስሩ ስማቸው የከበደ ቱጃሮች ጠቅላላ ሃብታቸው ከ700 ቢሊየን ወደ 1.5 ትሪሊየን ሲያድግ በግል ደግሞ የኢላን መስክ ገቢ በአንድ ሺህ እጥፍ ሲወንጨፍ ቢል ጌትስ በበኩሉ 30 በመቶ ጭማሪ አምጥቷል። ፎርብስ መፅሔት የዓለማችን ቱጃሮችን የሚለካው ባለቸው ተቀማጭ ሃብት ለምሳሌ መሬትና ሌሎች ሲቀነስ ዕዳ በማድረግ ነው። ኦክስፋም ከዓለም ባንክ ወስዶ በሪፖርቱ ባካተተው መረጃ መሠረት በጤና አገልግሎት እጦት፣ በረሃብ፣ ፆታዊ ጥቃት እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ በየአራት ሰከንዱ አንድ ሰው ይሞታል። ድርጅቱ እንዳለው በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት 160 ሚሊየን የዓለማችን ሰዎች በቀን ከ5.50 ዶላር በታች ገቢ ነበራቸው። የዓለም ባንክ መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሃገራት በቀን 5.50 ዶላር የደህነት መለኪያ ነው ይላል። የኦክስፋም ዘገባ አክሎ ደሃ ሃገራት ዕዳቸው እየበዛ ስለመጣ ከማሕበረሰባዊ ወጪያቸው ላይ እየቀነሱ ለሌላ እያዋሉት ነው ብሏል። የፆታ እኩልነትን በተለመከተ ደግሞ በፈንጆቹ 2019 ጋር ሲነፃፀር 13 ሚሊዮን ሴቶች ከሥራ ገበታቸው ተፈናቅለዋል። በተለይ ደግሞ በዩናይትድ ኪንግደም፣ ባንግላዴሽና ዩናይትድ ስቴትስ ጥቁሮች በኮቪድ ምክንያት እጅግ ተጎድተዋል። ዳኒ ስሪስካንዳራጃህ የዓለም መንግሥታት አሁን እየሄድንበት ያለውን የከፋ መንገድ ለመቀልበስ አንድ መላ መምታት አለባቸው ይላሉ። ይህ ቱጃሮችን መቅረጥን ሊያካትት ይገባል፤ ከፍተኛ ገቢ ካላቸው የሚገኘው ቀረጥ ጥራት ላለው የጤና አገልግሎትና ለማሕበረሰባዊ ግልጋሎቶች ሊውል ይጋል ይላሉ ኃላፊው።
https://www.bbc.com/amharic/news-60020490
0business
ሪሃና የፌንቲ የውበት መጠበቂያ ምርቶቿን በአፍሪካ ልታቀርብ ነው
ሪሃና ፌንቲ ቢውቲ እና ፌንቲ ስኪን የተባሉ የውበት መጠበቂያ ምርቶቿን ከዚህ ወር መጨረሻ ጀምሮ በስምንት የአፍሪካ ሃገራት ገበያዎች እንደሚቀርቡ አስታውቃለች። ሪሃና በማህበራዊ ድረ-ገጿ ላይ እንዳሰፈረችው ምርቶቿን ወደ አህጉሪቷ የማምጣቱን ሁኔታ በጉጉት እየጠበቀች እንደነበር እና ይህም ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሆነ ተናግራለች። የውበት ምርቶቹ በቦትስዋና፣ ጋና፣ ኬንያ፣ ናሚቢያ፣ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ዛምቢያ እና ዚምባብዌ እንደሚገኙም ተጠቅሷል። ሮቢን ሪሃና ፌንቲ ወይም ሪሃና ፌንቲ የተሰኘውን የውበት መጠበቂያ ምርቶቿን ከቅንጦት እቃዎች አምራቹ ሞየት ሄነሲ ሉዊ ቩቶን ጋር በመጣመር በአውሮፓውያኑ 2017 ጀመረች። አርቲስቷ 1.7 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሃብት ያላት ሲሆን 1.4 ቢሊዮን ዶላር የሚገመተው ከፌንቲ ቢውቲ የተገኘ ነው። ኩባንያው በመጀመሪያዎቹ 40 ቀናት ውስጥ 100 ሚሊዮን ዶላር እንዳገኘ ተዘግቧል። እንደ ፎርብስ ዘገባ ከሆነ እንደ ካይሊ ጄነር የውበት መጠበቂያ አምራች የሆነው ካይሊ ኮስሜቲክስ፣ የኪም ካርዳሺያን ኬኬደብልዩ ቢውቲና የጀሲካ አልባ ኦነስት ካምፓሊ በበለጠ የሪሃና የውበት ማስጠበቂያ ምርቶች ኩባንያ የበለጠ ገንዘብ ያገኛል።
ሪሃና የፌንቲ የውበት መጠበቂያ ምርቶቿን በአፍሪካ ልታቀርብ ነው ሪሃና ፌንቲ ቢውቲ እና ፌንቲ ስኪን የተባሉ የውበት መጠበቂያ ምርቶቿን ከዚህ ወር መጨረሻ ጀምሮ በስምንት የአፍሪካ ሃገራት ገበያዎች እንደሚቀርቡ አስታውቃለች። ሪሃና በማህበራዊ ድረ-ገጿ ላይ እንዳሰፈረችው ምርቶቿን ወደ አህጉሪቷ የማምጣቱን ሁኔታ በጉጉት እየጠበቀች እንደነበር እና ይህም ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሆነ ተናግራለች። የውበት ምርቶቹ በቦትስዋና፣ ጋና፣ ኬንያ፣ ናሚቢያ፣ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ዛምቢያ እና ዚምባብዌ እንደሚገኙም ተጠቅሷል። ሮቢን ሪሃና ፌንቲ ወይም ሪሃና ፌንቲ የተሰኘውን የውበት መጠበቂያ ምርቶቿን ከቅንጦት እቃዎች አምራቹ ሞየት ሄነሲ ሉዊ ቩቶን ጋር በመጣመር በአውሮፓውያኑ 2017 ጀመረች። አርቲስቷ 1.7 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሃብት ያላት ሲሆን 1.4 ቢሊዮን ዶላር የሚገመተው ከፌንቲ ቢውቲ የተገኘ ነው። ኩባንያው በመጀመሪያዎቹ 40 ቀናት ውስጥ 100 ሚሊዮን ዶላር እንዳገኘ ተዘግቧል። እንደ ፎርብስ ዘገባ ከሆነ እንደ ካይሊ ጄነር የውበት መጠበቂያ አምራች የሆነው ካይሊ ኮስሜቲክስ፣ የኪም ካርዳሺያን ኬኬደብልዩ ቢውቲና የጀሲካ አልባ ኦነስት ካምፓሊ በበለጠ የሪሃና የውበት ማስጠበቂያ ምርቶች ኩባንያ የበለጠ ገንዘብ ያገኛል።
https://www.bbc.com/amharic/61392235
0business
የዓለም የምግብ ዋጋ ለተከታታይ አምስት ወራት መቀነሱን የፋኦ መረጃ አመለከተ
የተባበሩት መንግሥታት በዓለም ዙሪያ ባደረገው ጥናት ለተከታታይ አምስት ወራት የምግብ ዋጋ ቅናሽ መታየቱን አመለከተ። ይህም በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም ያለው የኑሮ ውድነት ላይ ጫና ከሚያሳድሩ ችግሮች አንዱ ሊቀንስ እንደሚችል ማሳያ ነው ተብሏል። መረጃው እንዳለው በነሐሴ ወር የዋጋ ጠቋሚው ወደ 138 የቀነሰ ሲሆን፣ አሁን ላይ ደግሞ ሩሲያ ዩክሬንን ከመውረሯ በፊት ከነበረው ጊዜ ዝቅ ማለቱን አሳይቷል። ሩሲያ እና ዩክሬን የሱፍ ዘይት፣ በቆሎ እና ስንዴን ጨምሮ ሌሎች የምግብ ምርቶችን ወደ ውጭ የሚልኩ ዋነኛ አገራት ናቸው። የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) እንዳለው ሐምሌ ወር ላይ በድርጅቱ የተደገፈውና የዩክሬን ወደቦች እንዲከፈቱ የተደረሰው ስምምነት የጥራጥሬ እና የአትክልት ዘይት ዋጋን ቀንሷል። ይህም ማለት ተጨማሪ ምርቶች ወደ ዓለም አቀፍ ገበያው ገብተዋል ማለት ነው። የፋኦው ኢሪን ኮሌር፣ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የምግብ ዋጋ መቀነስ ምክንያቶች የተለያዩ ናቸው። “የጥራጥሬ ምርት አቅርቦት ችግር በዚህ ዓመት ለተከሰተው የምግብ ዋጋ መናር ዋነኛው መንስዔ ሆኖ ነበር። ነገር ግን አሁን ላይ አቅርቦቶች እየጨመሩ ነው” ብለዋል ኮሌር። ለዚህም ምክንያቱ በተለይ በካናዳ፣ በአሜሪካ እና በሩሲያ ያለው ምርት የተሻለ በመሆኑ እንደሆነ ተናግረዋል። እነዚህ ሦስት አገራት ዋነኛ የስንዴ ላኪዎች ናቸው። በሌሎች ምግቦች ላይም ምግቦችን ወደ ውጪ ለመላክ የነበረው ገደብ በመቅለሉ የስኳር እና የዘይት ዋጋ እንዲቀንስ የረዳ ሲሆን፣ በሌሎች ምርቶች ላይ ያለው ፍላጎት መቀነስም የሥጋ እና የወተት ተዋፅኦ ውጤቶች ዋጋ እንዲቀንስ አድርጓል ብለዋል። ኢንዶኔዥያ የፓልም ዘይት የውጪ ንግድ ቀረጥን በጊዜያዊነት በመቀነሷም የምግብ አምራቾች በብዛት ለሚጠቀሙት የአትክልት ዘይት ተጨማሪ አማራጭ እንዲያገኙ አስችሏቸዋል። የምግብ ዋጋ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚከሰት የዋጋ ግሽበት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከሚያደርጉ ምክንያቶች አንዱ ነው። በዚህ ሳምንት ዩሮዞን በነሐሴ ወር ዓመታዊ የዋጋ ግሽበቱ 9.1 በመቶ መድረሱን አስታውቋል። ለዚህ የዋጋ ግሽበት ምክንያቱ አንዱ ኢነርጅ (ኃይል) ሲሆን አሃዙም 38.3 በመቶ ነበር። ነገር ግን ያልተቀነባበሩ ምግቦች በ10.9 በመቶ ግሽበት ተመዝግቦባቸው ከኃይል በሁለተኛ ደረጃ ላይ ነበር የተቀመጡት። በቅርቡ በዩናይትድ ኪንግደም እና በአሜሪካ የታየው የዋጋ ግሽበት መረጃ ተመሳሳይነት ታይቶበታል። የፋኦ መረጃ፣ በወተት ተዋፅኦ፣ ሥጋ እና ስኳር ምርቶች ላይ የዋጋ ቅናሽ መታየቱን አመልክቷል። የከብት እና ሌሎች የእንስሳት ምርቶች ዋጋ በግንባር ቀደምትነት ወደ ውጪ በሚላኩባቸው አገራት ውስጥ ባለው ደካማ ፍላጎት ምክንያት ቀንሷል። ለዚህ ምን አልባት ሸማቾች ወደ ርካሽ አማራጮች ፊታቸውን እያዞሩ መሆኑን እንደሚያመላክት ፋኦ ጠቁሟል። የኢዲ ኤንድ ኤፍ ማን የግብርና ምርቶች ድርጅት የምርምር ኃላፊ ኮና ሃቅ እንዳሉት፣ የምጣኔ ሐብት ውድቀቱ አሳሳቢነት እያደገ በመምጣቱ እንደ በቆሎ፣ የአትክልት ዘይት እና ሌሎች ምርቶች ፍላጎት ይወድቃል የሚል ስጋት ተፈጥሯል። ሆኖም ኮሌር፣ አሁን ባለው የአቅርቦት ሰንሰለት ችግር እና ለውጡ እንዲመጣ በሚወስደው ጊዜ ምክንያት ሁሉም አገራት የዋጋ መቀነሱን ወዲያውኑ ሊመለከቱት አይችሉም ብለዋል። የፋኦ መረጃ እንደሚያሳየው መጋቢት ወር ላይ ከፍተኛ ሆኖ ከተመዘገበው 159.7 በመቶ የምግብ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰ ቢሆንም ባለፈው ዓመት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር ግን አሁንም በ10 ነጥብ ከፍ ያለ ነው። በአውሮፓ የተከሰተውን የሙቀት ማዕበል እና በፓኪስታን የተከሰተው የጎርፍ መጥለቅለቅን በመጥቀስም የአየር ሁኔታ በምግብ ሰብል ዋጋ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ መጨመሩን ኮሌር አስረድተዋል። በዚህ ሳምንት የዩክሬን የግብርና ሚኒስትር ማይኮላ ሶልስኪ፣ በጦርነቱ ምክንያት በመጪዎቹ ምርቶች ላይ ጉዳት እንደሚደርስ አስጠንቅቀዋል። ለሚቀጥለው ዓመት ምርት ስንዴ እና ገብስ የሚዘራባቸው ቦታዎች በሩሲያ ወረራ ምክንያት 20 በመቶው እንዲቀንስ ሆኗል። የዩክሬን ግብርና ምክር ቤት በበኩሉ ድጋፎች በመጥፋታቸው ምርት እንደሚቀንስ አሳውቋል። ኮሌር በበኩላቸው አሁን ላይ በዓለም አቀፍ የምግብ ዋጋ መቀነስ ከታየ በኋላም ቢሆን በ2011 ከታየው በላይ ሊጨምር እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። “ለዚህም በርካታ ምክንያቶች አሉ። አንዱ የኢነርጂ ዋጋ መጨመር ሲሆን ይህም የማዳበሪያ ዋጋ መናርን  እንዲሁም የአቅርቦት አለመረጋጋትን ያስከትላል” ብለዋል። “ምንም እንኳን የተወሰኑት የዩክሬን ወደቦች ቢከፈቱም ጊዜያዊ ነው የሚሆነው፣መጠኑም ቢሆን አነስተኛ ነው ። በመሆኑም የምግብ ዋጋን ይበልጥ ለመቀነስ እንዲረዳ ይህንን መጠን መጨመር ያስፈልጋል” ሲሉ ተናግረዋል።
የዓለም የምግብ ዋጋ ለተከታታይ አምስት ወራት መቀነሱን የፋኦ መረጃ አመለከተ የተባበሩት መንግሥታት በዓለም ዙሪያ ባደረገው ጥናት ለተከታታይ አምስት ወራት የምግብ ዋጋ ቅናሽ መታየቱን አመለከተ። ይህም በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም ያለው የኑሮ ውድነት ላይ ጫና ከሚያሳድሩ ችግሮች አንዱ ሊቀንስ እንደሚችል ማሳያ ነው ተብሏል። መረጃው እንዳለው በነሐሴ ወር የዋጋ ጠቋሚው ወደ 138 የቀነሰ ሲሆን፣ አሁን ላይ ደግሞ ሩሲያ ዩክሬንን ከመውረሯ በፊት ከነበረው ጊዜ ዝቅ ማለቱን አሳይቷል። ሩሲያ እና ዩክሬን የሱፍ ዘይት፣ በቆሎ እና ስንዴን ጨምሮ ሌሎች የምግብ ምርቶችን ወደ ውጭ የሚልኩ ዋነኛ አገራት ናቸው። የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) እንዳለው ሐምሌ ወር ላይ በድርጅቱ የተደገፈውና የዩክሬን ወደቦች እንዲከፈቱ የተደረሰው ስምምነት የጥራጥሬ እና የአትክልት ዘይት ዋጋን ቀንሷል። ይህም ማለት ተጨማሪ ምርቶች ወደ ዓለም አቀፍ ገበያው ገብተዋል ማለት ነው። የፋኦው ኢሪን ኮሌር፣ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የምግብ ዋጋ መቀነስ ምክንያቶች የተለያዩ ናቸው። “የጥራጥሬ ምርት አቅርቦት ችግር በዚህ ዓመት ለተከሰተው የምግብ ዋጋ መናር ዋነኛው መንስዔ ሆኖ ነበር። ነገር ግን አሁን ላይ አቅርቦቶች እየጨመሩ ነው” ብለዋል ኮሌር። ለዚህም ምክንያቱ በተለይ በካናዳ፣ በአሜሪካ እና በሩሲያ ያለው ምርት የተሻለ በመሆኑ እንደሆነ ተናግረዋል። እነዚህ ሦስት አገራት ዋነኛ የስንዴ ላኪዎች ናቸው። በሌሎች ምግቦች ላይም ምግቦችን ወደ ውጪ ለመላክ የነበረው ገደብ በመቅለሉ የስኳር እና የዘይት ዋጋ እንዲቀንስ የረዳ ሲሆን፣ በሌሎች ምርቶች ላይ ያለው ፍላጎት መቀነስም የሥጋ እና የወተት ተዋፅኦ ውጤቶች ዋጋ እንዲቀንስ አድርጓል ብለዋል። ኢንዶኔዥያ የፓልም ዘይት የውጪ ንግድ ቀረጥን በጊዜያዊነት በመቀነሷም የምግብ አምራቾች በብዛት ለሚጠቀሙት የአትክልት ዘይት ተጨማሪ አማራጭ እንዲያገኙ አስችሏቸዋል። የምግብ ዋጋ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚከሰት የዋጋ ግሽበት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከሚያደርጉ ምክንያቶች አንዱ ነው። በዚህ ሳምንት ዩሮዞን በነሐሴ ወር ዓመታዊ የዋጋ ግሽበቱ 9.1 በመቶ መድረሱን አስታውቋል። ለዚህ የዋጋ ግሽበት ምክንያቱ አንዱ ኢነርጅ (ኃይል) ሲሆን አሃዙም 38.3 በመቶ ነበር። ነገር ግን ያልተቀነባበሩ ምግቦች በ10.9 በመቶ ግሽበት ተመዝግቦባቸው ከኃይል በሁለተኛ ደረጃ ላይ ነበር የተቀመጡት። በቅርቡ በዩናይትድ ኪንግደም እና በአሜሪካ የታየው የዋጋ ግሽበት መረጃ ተመሳሳይነት ታይቶበታል። የፋኦ መረጃ፣ በወተት ተዋፅኦ፣ ሥጋ እና ስኳር ምርቶች ላይ የዋጋ ቅናሽ መታየቱን አመልክቷል። የከብት እና ሌሎች የእንስሳት ምርቶች ዋጋ በግንባር ቀደምትነት ወደ ውጪ በሚላኩባቸው አገራት ውስጥ ባለው ደካማ ፍላጎት ምክንያት ቀንሷል። ለዚህ ምን አልባት ሸማቾች ወደ ርካሽ አማራጮች ፊታቸውን እያዞሩ መሆኑን እንደሚያመላክት ፋኦ ጠቁሟል። የኢዲ ኤንድ ኤፍ ማን የግብርና ምርቶች ድርጅት የምርምር ኃላፊ ኮና ሃቅ እንዳሉት፣ የምጣኔ ሐብት ውድቀቱ አሳሳቢነት እያደገ በመምጣቱ እንደ በቆሎ፣ የአትክልት ዘይት እና ሌሎች ምርቶች ፍላጎት ይወድቃል የሚል ስጋት ተፈጥሯል። ሆኖም ኮሌር፣ አሁን ባለው የአቅርቦት ሰንሰለት ችግር እና ለውጡ እንዲመጣ በሚወስደው ጊዜ ምክንያት ሁሉም አገራት የዋጋ መቀነሱን ወዲያውኑ ሊመለከቱት አይችሉም ብለዋል። የፋኦ መረጃ እንደሚያሳየው መጋቢት ወር ላይ ከፍተኛ ሆኖ ከተመዘገበው 159.7 በመቶ የምግብ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰ ቢሆንም ባለፈው ዓመት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር ግን አሁንም በ10 ነጥብ ከፍ ያለ ነው። በአውሮፓ የተከሰተውን የሙቀት ማዕበል እና በፓኪስታን የተከሰተው የጎርፍ መጥለቅለቅን በመጥቀስም የአየር ሁኔታ በምግብ ሰብል ዋጋ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ መጨመሩን ኮሌር አስረድተዋል። በዚህ ሳምንት የዩክሬን የግብርና ሚኒስትር ማይኮላ ሶልስኪ፣ በጦርነቱ ምክንያት በመጪዎቹ ምርቶች ላይ ጉዳት እንደሚደርስ አስጠንቅቀዋል። ለሚቀጥለው ዓመት ምርት ስንዴ እና ገብስ የሚዘራባቸው ቦታዎች በሩሲያ ወረራ ምክንያት 20 በመቶው እንዲቀንስ ሆኗል። የዩክሬን ግብርና ምክር ቤት በበኩሉ ድጋፎች በመጥፋታቸው ምርት እንደሚቀንስ አሳውቋል። ኮሌር በበኩላቸው አሁን ላይ በዓለም አቀፍ የምግብ ዋጋ መቀነስ ከታየ በኋላም ቢሆን በ2011 ከታየው በላይ ሊጨምር እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። “ለዚህም በርካታ ምክንያቶች አሉ። አንዱ የኢነርጂ ዋጋ መጨመር ሲሆን ይህም የማዳበሪያ ዋጋ መናርን  እንዲሁም የአቅርቦት አለመረጋጋትን ያስከትላል” ብለዋል። “ምንም እንኳን የተወሰኑት የዩክሬን ወደቦች ቢከፈቱም ጊዜያዊ ነው የሚሆነው፣መጠኑም ቢሆን አነስተኛ ነው ። በመሆኑም የምግብ ዋጋን ይበልጥ ለመቀነስ እንዲረዳ ይህንን መጠን መጨመር ያስፈልጋል” ሲሉ ተናግረዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c2lg5qzp2dxo
5sports
ሲም ካርድ ከመቀየር እስከ ጽንስ ማቋረጥ የደረሰው የአውስትራሊያ እግር ኳስ ዘረኝነት
የአውስትራሊያ እግር ኳስ ሊግ በአገሪቱ በጣም ውጤታማ ከሆኑት ክለቦች የአንዱ ከአገሪቱ ቀደምት ነዋሪዎች ከሆነው ማኅበረሰብ የመጡ ተጫዋቾች ላይ ከፍተኛ ጥቃት በአሰልጣኞች ደርሶባቸዋል በሚል ምርመራ ጀመረ። እንደ አውስትራሊያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኤቢሲ) ዘገባ ከሆነ ተጫዋቾቹ ከቤተሰባቸው እንዲገለሉ እና ከፍቅር አጋሮቻቸው ጋር እንዲለያዩ ተነግሯቸዋል። በሌላ አጋጣሚ ደግሞ እርግዝና እንዲያቋርጡ ታዘዋል ሲል አመልክቷል። ሃውቶን የተባለው እግር ኳስ ክለብ "አሳዛኝ" ያለውን ጉዳይ ለመመርመር ቃል ገብቷል። ይህ የታወቀው ቡድኑ በነባር የአገሪቱ ተወላጆች [አቦርጂንስ] ዙሪያ ስላለው አያያዝ በተገመገመበት ወቅት ነው። የሪፖርቱን ይዘት ጠንቅቆ የሚያውቀው ኤቢሲ ከ2005 እስከ 2021 ባለው ጊዜ ውስጥ መቀመጫውን ሜልበርን ባደረገው ክለብ ላሳለፉ ሦስት ተጫዋቾችን ቃለ መጠይቅ አድርጓል። ሃውቶን ሃውክስ በመባልም ይታወቃል። ከስፖርቱና በቤተሰቦቻቸው አንዱን እንዲመርጡ መገደዳቸውን ለመገናኛ ብዙኃኑ ተናግረዋል። ሌላው ደግሞ አንድ አሰልጣኝ "ያልተወለደ ልጄን እንዳስወርድ እና የትዳር ጓደኛዬን መተው እንዳለብኝ ጠይቆኛል" ብለዋል። "ሲም ካርዴን ከስልኬ እንዳወጣ እና በእኔ እና በቤተሰቤ መካከል ምንም ተጨማሪ ግንኙነት እንዳይኖር ተደርጌያለሁ። ከዚያ ምሽት ጀምሮ ከአንዱ አሰልጣኝ ጋር እንደምኖርም ተነገረኝ" ብሏል። የትዳር ጓደኛው ፅንሱን ያላቋረጠች ሲሆን ጥንዶቹ ከወራት በኋላ ታርቀዋል። የመጀመሪያ ልጃቸውን ከወለዱ በኋላ እንደገና በድጋሚ ያረገዘችው ሚስት ተመሳሳይ መከራ እንዳያጋጥማቸው እርግዝናውን ማቋረጥ እንደሚገባት ተሰምቷት እንደነበር ለኤቢሲ ተናገራለች። ሌላ ተጫዋችም ለኤቢሲ እንዳስታወቀው ሃውቶን ጓደኛው ማርገዟን ሲያውቅ ተመሳሳይ ምላሽ እንደሰጠው ተናግሯል። በኋላም ከእርሷ ጋር ለመለያየት እና ግንኙነቱን ለማቋረጥ ተገደደ። እሷም በኋላ ላይ ፅንስ አቋረጠች። ከሌላ ግዛት የመጣው ሦስተኛው ተጫዋች በበኩሉ ቤተሰቡ ከእሱ ጋር ለመኖር ወደ ሜልበርን እንዳይዛወር ለማድረግ ክለቡ መሞከሩን ተናግሯል። ሦስቱም ጥንዶች ከክስተቶቹ በኋላ የነበራቸውን የአዕምሯዊ ጤንነት ውጣ ውረድን ተናግረዋል። ውንጀላውን የሚገልጸው ዘገባ ከሁለት ሳምንት በፊት በሃውቶን እንደደረሰው ኤቢሲ ዘግቧል። ለአውስትራሊያ እግር ኳስ ሊግ (ኤኤፍኤል) ባለሥልጣናትም ተላልፏል። ዛሬ ረቡዕ ዕለት መገናኛ ብዙኃን ጋር ቆይታ ያደረጉት የኤኤፍኤል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጊለን ማክላክላን የኤቢሲን ዘገባ "ፈታኝ እና የሚረብሽ" ብለውታል። "ከዚህ በላይ ከባድ ውንጀላዎችን ማግኘት ከባድ ነው" ብለዋል። በስም ጥር ጠበቃ የሚመራ ገለልተኛ ቡድን ጉዳዩን ለመመርመር እንደሚመደብም ጠቁመዋል። ምርመራው በሚከናወንበት ወቅት አሰልጣኞች ከኃላፊነታቸው ይነሱ አይነሱ በሚለው ላይ ክለቦች ዛሬ ይወሰናሉ። የሃውቶን ቃል አቀባይ ግኝቱ "አስጨናቂ ታሪካዊ ውንጀላዎችን" ቢያነሳም በክለቡ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ "ካለው ባህል አኳያ ደኅንነቱ የተጠበቀ" መሆኑንም አመልክቷል። "ክለቡ በዚህ ሂደት ለተሳተፉት ሁሉ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል። ደኅንነታቸውም ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው" ሲል አክሏል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በርካታ የኤኤፍኤል ተጫዋቾች በስታዲየም ከሚገኙ ተመልካቾች የሚደርስባቸውን የዘረኝነት ጥቃት እና የክለብ ባለሥልጣናትን ደካማ ድጋፍ በማንሳት ቅሬታ አቅርበዋል። ቀደምት የአገሬው ተወላጅ እና  የኤኤፍኤል ኮከብ የነበረው አዳም ጉደስ እንደተናገረው በተቀናቃኝ ደጋፊዎች ለዓመታት ሲደርስበት የነበረው ግፍ "ልቡ ተሰበሮ" በ2015 ጫማውን እንዲሰቅል አስገድዶታል። ሌላው መቀመጫውን ሜልበርን ያደረገው ኮሊንግዉድ የተባለው ክለብ ባለፈው ዓመት በተደረገ ግምገማ "ከዘረኝነት" ጋር በተያያዘ ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል።
ሲም ካርድ ከመቀየር እስከ ጽንስ ማቋረጥ የደረሰው የአውስትራሊያ እግር ኳስ ዘረኝነት የአውስትራሊያ እግር ኳስ ሊግ በአገሪቱ በጣም ውጤታማ ከሆኑት ክለቦች የአንዱ ከአገሪቱ ቀደምት ነዋሪዎች ከሆነው ማኅበረሰብ የመጡ ተጫዋቾች ላይ ከፍተኛ ጥቃት በአሰልጣኞች ደርሶባቸዋል በሚል ምርመራ ጀመረ። እንደ አውስትራሊያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኤቢሲ) ዘገባ ከሆነ ተጫዋቾቹ ከቤተሰባቸው እንዲገለሉ እና ከፍቅር አጋሮቻቸው ጋር እንዲለያዩ ተነግሯቸዋል። በሌላ አጋጣሚ ደግሞ እርግዝና እንዲያቋርጡ ታዘዋል ሲል አመልክቷል። ሃውቶን የተባለው እግር ኳስ ክለብ "አሳዛኝ" ያለውን ጉዳይ ለመመርመር ቃል ገብቷል። ይህ የታወቀው ቡድኑ በነባር የአገሪቱ ተወላጆች [አቦርጂንስ] ዙሪያ ስላለው አያያዝ በተገመገመበት ወቅት ነው። የሪፖርቱን ይዘት ጠንቅቆ የሚያውቀው ኤቢሲ ከ2005 እስከ 2021 ባለው ጊዜ ውስጥ መቀመጫውን ሜልበርን ባደረገው ክለብ ላሳለፉ ሦስት ተጫዋቾችን ቃለ መጠይቅ አድርጓል። ሃውቶን ሃውክስ በመባልም ይታወቃል። ከስፖርቱና በቤተሰቦቻቸው አንዱን እንዲመርጡ መገደዳቸውን ለመገናኛ ብዙኃኑ ተናግረዋል። ሌላው ደግሞ አንድ አሰልጣኝ "ያልተወለደ ልጄን እንዳስወርድ እና የትዳር ጓደኛዬን መተው እንዳለብኝ ጠይቆኛል" ብለዋል። "ሲም ካርዴን ከስልኬ እንዳወጣ እና በእኔ እና በቤተሰቤ መካከል ምንም ተጨማሪ ግንኙነት እንዳይኖር ተደርጌያለሁ። ከዚያ ምሽት ጀምሮ ከአንዱ አሰልጣኝ ጋር እንደምኖርም ተነገረኝ" ብሏል። የትዳር ጓደኛው ፅንሱን ያላቋረጠች ሲሆን ጥንዶቹ ከወራት በኋላ ታርቀዋል። የመጀመሪያ ልጃቸውን ከወለዱ በኋላ እንደገና በድጋሚ ያረገዘችው ሚስት ተመሳሳይ መከራ እንዳያጋጥማቸው እርግዝናውን ማቋረጥ እንደሚገባት ተሰምቷት እንደነበር ለኤቢሲ ተናገራለች። ሌላ ተጫዋችም ለኤቢሲ እንዳስታወቀው ሃውቶን ጓደኛው ማርገዟን ሲያውቅ ተመሳሳይ ምላሽ እንደሰጠው ተናግሯል። በኋላም ከእርሷ ጋር ለመለያየት እና ግንኙነቱን ለማቋረጥ ተገደደ። እሷም በኋላ ላይ ፅንስ አቋረጠች። ከሌላ ግዛት የመጣው ሦስተኛው ተጫዋች በበኩሉ ቤተሰቡ ከእሱ ጋር ለመኖር ወደ ሜልበርን እንዳይዛወር ለማድረግ ክለቡ መሞከሩን ተናግሯል። ሦስቱም ጥንዶች ከክስተቶቹ በኋላ የነበራቸውን የአዕምሯዊ ጤንነት ውጣ ውረድን ተናግረዋል። ውንጀላውን የሚገልጸው ዘገባ ከሁለት ሳምንት በፊት በሃውቶን እንደደረሰው ኤቢሲ ዘግቧል። ለአውስትራሊያ እግር ኳስ ሊግ (ኤኤፍኤል) ባለሥልጣናትም ተላልፏል። ዛሬ ረቡዕ ዕለት መገናኛ ብዙኃን ጋር ቆይታ ያደረጉት የኤኤፍኤል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጊለን ማክላክላን የኤቢሲን ዘገባ "ፈታኝ እና የሚረብሽ" ብለውታል። "ከዚህ በላይ ከባድ ውንጀላዎችን ማግኘት ከባድ ነው" ብለዋል። በስም ጥር ጠበቃ የሚመራ ገለልተኛ ቡድን ጉዳዩን ለመመርመር እንደሚመደብም ጠቁመዋል። ምርመራው በሚከናወንበት ወቅት አሰልጣኞች ከኃላፊነታቸው ይነሱ አይነሱ በሚለው ላይ ክለቦች ዛሬ ይወሰናሉ። የሃውቶን ቃል አቀባይ ግኝቱ "አስጨናቂ ታሪካዊ ውንጀላዎችን" ቢያነሳም በክለቡ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ "ካለው ባህል አኳያ ደኅንነቱ የተጠበቀ" መሆኑንም አመልክቷል። "ክለቡ በዚህ ሂደት ለተሳተፉት ሁሉ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል። ደኅንነታቸውም ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው" ሲል አክሏል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በርካታ የኤኤፍኤል ተጫዋቾች በስታዲየም ከሚገኙ ተመልካቾች የሚደርስባቸውን የዘረኝነት ጥቃት እና የክለብ ባለሥልጣናትን ደካማ ድጋፍ በማንሳት ቅሬታ አቅርበዋል። ቀደምት የአገሬው ተወላጅ እና  የኤኤፍኤል ኮከብ የነበረው አዳም ጉደስ እንደተናገረው በተቀናቃኝ ደጋፊዎች ለዓመታት ሲደርስበት የነበረው ግፍ "ልቡ ተሰበሮ" በ2015 ጫማውን እንዲሰቅል አስገድዶታል። ሌላው መቀመጫውን ሜልበርን ያደረገው ኮሊንግዉድ የተባለው ክለብ ባለፈው ዓመት በተደረገ ግምገማ "ከዘረኝነት" ጋር በተያያዘ ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c974qrz47nro
3politics
የዚምባብዌ ምክትል ፕሬዚዳንት ባለቤት በባለቤታቸው ግድያ ሙከራ ተከሰሱ
የዚምባብዌ ምክትል ፕሬዚዳንት ባለቤት ሜሪ ሙባይዋ በባለቤታቸው ግድያ ሙከራ ተከስሰዋል። የሙስና ክስ ያለባቸው ሜሪ ሙባይዋ ሰኞ እለት ፍርድ ቤት ቀርበው የነበረ ሲሆን፤ ክሱንም ውንጀላ ነው በማለት ክደውታል። አቃቤ ህግጋት በበኩላቸው ባለቤታቸውን ጄኔራል ኮንስታንቲኖ ቺዌንጋን ደቡብ አፍሪካ ህክምና እያደረጉ በነበረበት ወቅት ሊገድሏቸው ሞክረዋል ብለዋል። •ከኮርኔል በኮምፒውተር ሳይንስ ፒኤችዲ በማግኘት የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት የሆነችው ረድኤት አበበ •መንግሥት አደገኛ የሆነውን የትግራይን መገለል መለስ ብሎ ሊያጤነው ይገባል- ክራይስስ ግሩፕ •የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን ክፍፍልና ጠብ ጄኔራል ኮንስታንቲኖ ቺዌንጋ ሮበርት ሙጋቤ ከሁለት አመት በፊት ከስልጣናቸው ሲገረሰሱም ቁልፍ ሚናን ተጫውተዋል። ጄኔራሉም ቢሆኑ ከስድስት ወራት በፊት በደቡብ አፍሪካ ህክምና እንዳያገኙ "ከፍተኛ ጫና አድርጋብኛለች" በማለት ወንጅለዋታል። ከዚህም በተጨማሪ በፕሪቶሪያ ሆስፒታል ውስጥ እየታከሙ በነበረበት ወቅትም ግሉኮሱን ነቅላዋለች ብለዋል። ጄኔራሉ ለተጨማሪ ህክምና ቻይና ሄደውም ከአራት ወራት ቆይታ በኋላ ተመልሰዋል። ሜሪ ሙባይዋ በቁጥጥር ስር የዋሉት በባለፈው ሳምንት ቅዳሜ እለት ሲሆን ዋስም ተከልክለዋል። ከግድያ ሙከራ በተጨማሪ 750ሺ ዶላር ገንዘብ ከማጭበርበርና በህገወጥ መንገድ በማዘዋወርም ተከሰዋል። የቢቢሲ አፍሪካ ዘጋቢ አንድሪው ሃርዲንግ እንደሚለው ከበርቴዎቹ በግድያ ሙከራና በመመራረዝ ውንጀላዎች ፍርድ ቤት በተደጋጋሚ ከመምጣታቸው አንፃር ይህ ሁኔታ አዲስ ነገር አይደለም።
የዚምባብዌ ምክትል ፕሬዚዳንት ባለቤት በባለቤታቸው ግድያ ሙከራ ተከሰሱ የዚምባብዌ ምክትል ፕሬዚዳንት ባለቤት ሜሪ ሙባይዋ በባለቤታቸው ግድያ ሙከራ ተከስሰዋል። የሙስና ክስ ያለባቸው ሜሪ ሙባይዋ ሰኞ እለት ፍርድ ቤት ቀርበው የነበረ ሲሆን፤ ክሱንም ውንጀላ ነው በማለት ክደውታል። አቃቤ ህግጋት በበኩላቸው ባለቤታቸውን ጄኔራል ኮንስታንቲኖ ቺዌንጋን ደቡብ አፍሪካ ህክምና እያደረጉ በነበረበት ወቅት ሊገድሏቸው ሞክረዋል ብለዋል። •ከኮርኔል በኮምፒውተር ሳይንስ ፒኤችዲ በማግኘት የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት የሆነችው ረድኤት አበበ •መንግሥት አደገኛ የሆነውን የትግራይን መገለል መለስ ብሎ ሊያጤነው ይገባል- ክራይስስ ግሩፕ •የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን ክፍፍልና ጠብ ጄኔራል ኮንስታንቲኖ ቺዌንጋ ሮበርት ሙጋቤ ከሁለት አመት በፊት ከስልጣናቸው ሲገረሰሱም ቁልፍ ሚናን ተጫውተዋል። ጄኔራሉም ቢሆኑ ከስድስት ወራት በፊት በደቡብ አፍሪካ ህክምና እንዳያገኙ "ከፍተኛ ጫና አድርጋብኛለች" በማለት ወንጅለዋታል። ከዚህም በተጨማሪ በፕሪቶሪያ ሆስፒታል ውስጥ እየታከሙ በነበረበት ወቅትም ግሉኮሱን ነቅላዋለች ብለዋል። ጄኔራሉ ለተጨማሪ ህክምና ቻይና ሄደውም ከአራት ወራት ቆይታ በኋላ ተመልሰዋል። ሜሪ ሙባይዋ በቁጥጥር ስር የዋሉት በባለፈው ሳምንት ቅዳሜ እለት ሲሆን ዋስም ተከልክለዋል። ከግድያ ሙከራ በተጨማሪ 750ሺ ዶላር ገንዘብ ከማጭበርበርና በህገወጥ መንገድ በማዘዋወርም ተከሰዋል። የቢቢሲ አፍሪካ ዘጋቢ አንድሪው ሃርዲንግ እንደሚለው ከበርቴዎቹ በግድያ ሙከራና በመመራረዝ ውንጀላዎች ፍርድ ቤት በተደጋጋሚ ከመምጣታቸው አንፃር ይህ ሁኔታ አዲስ ነገር አይደለም።
https://www.bbc.com/amharic/50818834
5sports
ግዙፉ የአውስትራሊያው የስፖርት ክለብ “ዘረኛ” ነው ተባለ
በአውስራሊያ ሊግ ተሳታፊ ከሆኑት ክለቦች መካከል አንዱ እና ግዙፉ ኮሊምግዉድ “ዘረኛ የሆነ ስርዓትን ዘርግቷል” ሲል አንድ ገለልተኛ አጣሪ ቡድን አጋለጠ። ይህ ገለልተኛ አጣሪ ቡድን ይፋ ባደረገው ሪፖርት እንዳተተው ይህ ግዙፍ የራግቢ ቡድን ዘረኝነትን በተመለከተ ለሚነሱ ቅሬታዎች ምላሽ ለመስጠት ፍላጎት የለውም ከፍ ሲልም ቅሬታ በሚያነሱት ላይ ቅጣት ያስተላልፋል ብሏል። ሪፖርቱን ተከትሎ ግዙፉ ክለብ “የተሻለ ለመሆን እጥራለሁ” ብሏል። የክለቡ ፕሬዝደንት ክለቡ ጥፋተኛ መሆኑን አምነው ጸረ-ዘረኛ የሆኑ ፖሊሲዎችን በማርቀቅ የተሻለ ስፍራ ለመሆን እሰራለሁ ብሏል። ጥናቱ ይፋ እንዳደረገው ከሆነ የዘር መድሎ ደርሶብኛል ከሚል ስፖርተኛ ይልቅ ዘረኝነትን በተመለከተ በመገናኛ ብዙሃን ለሚነሱ ጥያቄዎች ክለቡ ምላሽ ይሰጣል፣ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ዘረኝነትን ለመከላከል ክለቡ ምንም አይነት ስትራቴጂ አልነበረውም፤ እንዲሁም ዘረኝነትን በተመለከተ በክለቡ ሲወሰዱ የነበሩ እርምጃዎች ተጎጂውን ሳይሆን የክለቡን ስምእና ዝና ለመጠበቅ ያለመ ነው። ይህ የጥናት ውጤት ይፋ የተደረገው ገለልተኛ ጥንት አድራጊ ቡድኑ ተጫዋቾችን፣ የክለቡ ሰራተኞችን እና ደጋፊዎችን ካነጋገረ በኋላ ነው። በዚህ ጥናት ላይ የቀድሞ የክለቡ ተጫዋች ሄሪቲኤር ሉሙምባ በክላቡ አጋጥሞኛል ስላለው ጉዳይ ተሞክሮውን አጋርቷል። የዘር ሃረጉ ከብራዚል እና አንጎላ የሚመዘዘው ተጫዋች የቡድን አባላቶቹ ‘ቺምፕ’ (ቺምፓዚ) በሚል ስም ይጠሩት እንደነበረ ተናግሯል። የቀድሞ የክለቡ ተጫዋች ሉሙምባ ክለቡን ኮሊንግውድ እና የአውስትራሊያ ሊግን ለመክሰስ በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቋል። የአውስትራሊያው ራግቢ ሊግ በርካታ ተመልካቾች ያሉት ሊግ ሲሆን በሊጉ ውስጥ ዘረኝነትን ለመከላከል የተለያዩ ጠንካራ እርምጃዎችችን እንደሚወስድ አስታውቋል።
ግዙፉ የአውስትራሊያው የስፖርት ክለብ “ዘረኛ” ነው ተባለ በአውስራሊያ ሊግ ተሳታፊ ከሆኑት ክለቦች መካከል አንዱ እና ግዙፉ ኮሊምግዉድ “ዘረኛ የሆነ ስርዓትን ዘርግቷል” ሲል አንድ ገለልተኛ አጣሪ ቡድን አጋለጠ። ይህ ገለልተኛ አጣሪ ቡድን ይፋ ባደረገው ሪፖርት እንዳተተው ይህ ግዙፍ የራግቢ ቡድን ዘረኝነትን በተመለከተ ለሚነሱ ቅሬታዎች ምላሽ ለመስጠት ፍላጎት የለውም ከፍ ሲልም ቅሬታ በሚያነሱት ላይ ቅጣት ያስተላልፋል ብሏል። ሪፖርቱን ተከትሎ ግዙፉ ክለብ “የተሻለ ለመሆን እጥራለሁ” ብሏል። የክለቡ ፕሬዝደንት ክለቡ ጥፋተኛ መሆኑን አምነው ጸረ-ዘረኛ የሆኑ ፖሊሲዎችን በማርቀቅ የተሻለ ስፍራ ለመሆን እሰራለሁ ብሏል። ጥናቱ ይፋ እንዳደረገው ከሆነ የዘር መድሎ ደርሶብኛል ከሚል ስፖርተኛ ይልቅ ዘረኝነትን በተመለከተ በመገናኛ ብዙሃን ለሚነሱ ጥያቄዎች ክለቡ ምላሽ ይሰጣል፣ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ዘረኝነትን ለመከላከል ክለቡ ምንም አይነት ስትራቴጂ አልነበረውም፤ እንዲሁም ዘረኝነትን በተመለከተ በክለቡ ሲወሰዱ የነበሩ እርምጃዎች ተጎጂውን ሳይሆን የክለቡን ስምእና ዝና ለመጠበቅ ያለመ ነው። ይህ የጥናት ውጤት ይፋ የተደረገው ገለልተኛ ጥንት አድራጊ ቡድኑ ተጫዋቾችን፣ የክለቡ ሰራተኞችን እና ደጋፊዎችን ካነጋገረ በኋላ ነው። በዚህ ጥናት ላይ የቀድሞ የክለቡ ተጫዋች ሄሪቲኤር ሉሙምባ በክላቡ አጋጥሞኛል ስላለው ጉዳይ ተሞክሮውን አጋርቷል። የዘር ሃረጉ ከብራዚል እና አንጎላ የሚመዘዘው ተጫዋች የቡድን አባላቶቹ ‘ቺምፕ’ (ቺምፓዚ) በሚል ስም ይጠሩት እንደነበረ ተናግሯል። የቀድሞ የክለቡ ተጫዋች ሉሙምባ ክለቡን ኮሊንግውድ እና የአውስትራሊያ ሊግን ለመክሰስ በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቋል። የአውስትራሊያው ራግቢ ሊግ በርካታ ተመልካቾች ያሉት ሊግ ሲሆን በሊጉ ውስጥ ዘረኝነትን ለመከላከል የተለያዩ ጠንካራ እርምጃዎችችን እንደሚወስድ አስታውቋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-55893665
3politics
ለረጅም ዓመታት ጃፓንን በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩት ሺንዞ አቤ ሲታወሱ
ለጃፓን የላይኛው ምክር ቤት የሚወዳደር ዕጩን ወክለው ቅስቀሳ በሚያደርጉበት ወቅት በተተኮሰባቸው ጥይት ሕይወታቸው ያለፈው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ በብዙ መልኩ ይታወሳሉ። “ጠብ አጫሪ” በሆነው የውጭ ፖሊሲያቸው እንዲሁም 'አቤኖሚክስ' ተብሎ በሚጠራው ለየት ያለ የምጣኔ ሀብት ስትራቴጂያቸው በጃፓን ስም አትርፈዋል። ህያው ሥራ ከመቃብር በላይ ነው እንዲሉ፣ በርካቶች ሲገልጿቸው “ወግ አጥባቂ ብሔረተኛ ይሏቸዋል” የ67 ዓመቱን ፖለቲከኛ። አቤ ፓርቲያቸውን ሊበራል ዲሞክራቲክ ፓርቲን (ኤልዲፒ) ሁለት ጊዜ አሸናፊ እንዲሆን አድርገውታል። የመጀመሪያው የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቆይታቸው አጭር ነበር። በአውሮፓውያኑ 2006 ወደ ሥልጣን መጥተው አንድ ዓመት አካባቢ አገሪቱን የመሩት አቤ የሥልጣን ቆይታቸውም አወዛጋቢ ነበር። ነገር ግን ከስድስት ዓመታት በኋላ በአውሮፓውያኑ 2012 በአስገራሚ ሁኔታ ተመልሰው በጤና ምክንያት ከሥልጣን እስከለቀቁበት 2020 ድረስ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ነበሩ። አቤ ለሁለተኛ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲሆኑ አገራቸው የምጣኔ ሀብት ድቀት ላይ ነበረች። የገንዘብ ፖሊሲውን በማላላት፣ ማነቃቂያዎች እንዲሁም መዋቅራዊ የሆኑ ማሻሻዎችን በማድረግ እያሽቆለቆለ የነበረውን ምጣኔ ሀብት ወደ ተረጋጋ ሁኔታ እንደሚመጣ አድርገዋል ተብለው ይወደሳሉ። ጃፓን በአውሮፓውያኑ 2011 በቶሁኩ ከደረሰው ከባድ ርዕደ መሬት እንዲሁም ሱናሚ እንድታገግም ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። በዚህ የመሬት መንቀጥቀጥ እና ሱናሚ ወደ 20 ሺህ የሚደርሱ ጃፓናውያን ሕይወት ከመቅጠፍ በተጨማሪ የፉኩሺማ የኒውክሌር ማመንጫዎችን አቅልጦ ከፍተኛ ቀውስ አድርሷል። ከሁለት ዓመት በፊት በአውሮፓውያኑ 2020 አቤ በፈቃዳቸው ከሥልጣናቸው ወረዱ። ለሳምንታት ያህል የጤናቸው ሁኔታ መወያያ ከሆነም በኋላ ነበር ከሥልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ ያቀረቡት። መጀመሪያም ከስድስት ዓመት በፊት ሥልጣን በለቀቁበት ወቅት በአንጀት አልሰር (ቁስለት) ህመም ሲሰቃዩ የነበረ ሲሆን፣ በዚህም ወቅት ይህ ቁስለት ማገርሸቱን አስታውቀው ነበር። እሳቸውንም በመተካት የፓርቲያቸው አባልና የቅርብ አጋር የሆኑት ዮሺሃዴ ሱጋ ወደ ሥልጣን መጡ። ሆኖም አቤ በጃፓን ፖለቲካ ውስጥ ከፍተኛ ስፍራ ያላቸው ሰው ተደርገው መታየታቸው አላከተመም። አቤ ከፖለቲከኛ ቤተሰብ ነው የመጡት። አባታቸው የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲሁም አያታቸው ደግሞ ጃፓንን በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩት ኖቡሱኬ ኪሺ ናቸው ። ለፓርላማ አባልነት የተመረጡት በአውሮፓውያኑ 1993 ሲሆን በአውሮፓውያኑ 2005 የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁኒቺሮ ኮይዙሚ ከፍተኛ የካቢኔ ፀሐፊ አድርገው ሾሟቸው። ከዚያም በአውሮፓውያኑ 2006 ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ በዕድሜ የጃፓን ትንሹ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን ቻሉ። ነገር ግን አስተዳደራቸው በተከታታይ ቅሌቶች የተሞላ ነበር። ወደ 50 ሚሊዮን የሚጠጉ ጉዳዮችን የያዘው የመንግሥት የጡረታ መዝገብ መጥፋት አስደዳደራቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ጎድቶታል። በአውሮፓውያኑ 2007 ለተደረገው የላይኛው ምክር ቤት ምርጫም ፓርቲያቸው ኤልዲፒ ከባድ ኪሳራን አስተናገደ። በዚያው ዓመትም በአንጀት አልሰር (ቁስለት) ምክንያት አቤ ከሥልጣናቸው ለቀቁ። ከስድስት ዓመት በኋላም በህክምና በሽታውን አሸንፌያለሁ በማለት ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት መንበር ተመለሱ። በመቀጠልም በነበሩት ምርጫዎች በአውሮፓውያኑ 2014 እና 2017 በድጋሚ ተመርጠዋል። ይህም ለረጅም ዓመታት ጃፓንን የመሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ያደርጋቸዋል። ተወዳጅነታቸውም በዓመታት ውስጥ ቢለዋወጥም በፖርቲያቸው ኤልዲፒ ውስጥ በነበራቸው ከባድ ተፅእኖ ምክንያት የተገዳደራቸው አልነበረም። የፓርቲያቸውንም ደንብና ሕግ በማሻሻል ለሦስተኛ ጊዜ የፓርቲው መሪ ለመሆን ችለዋል። አቤ በመከላከያ እና በውጭ ጉዳይ ፖሊሲያቸው ቁርጠኛና 'ጠብ አጫሪ' የሚባል አቋም ነበራቸው። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቃት በኋላ ሰላማዊ የሚባለውንም የጃፓን ሕገ መንግሥት ለማሻሻል ሲጥሩ ቆይተዋል። በአሜሪካ የተረቀቀውን የጃፓን ሕገ መንግሥት ወግ አጥባቂዎች፣ የጃፓን ወታደሮች በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የደረሰባቸውን አሳፋሪ ሽንፈት ማስታወሻ ነው ሲሉ ይተቹታል። ጭፍን ብሔረተኛነታቸውም ከቻይና እና ከደቡብ ኮሪያ ጋር ውጥረት ውስጥ እንዲገቡ ምክንያት ሆኗል። በተለይም በሁለተኛው ከዓለም ጦርነት በፊትና በዚያው ወቅት ጃፓን ነበራት ከሚባለው የጦረኝነት አቋም ጋር ተያይዞ አወዛጋቢ የሆነውን በቶኪዮ የሚገኘውን ያሱኩኒ ቤተ መቅደስ በአውሮፓውያኑ 2013 መጎብኘታቸውን ተከትሎ ከሁለቱ አገራት ጋር ነገሮች ተጋግለው ነበር። አቤ ያሱኩኒን በተደጋጋሚ መጎብኘታቸውም በጃፓን የሚገኙ የግራ ዘመም ፖለቲከኞችን ያስቆጣ ነበር። አቤ በጦርነቱ ወቅት ጃፓን ያደረሰችውን የመብት ጥሰቶችና ጭካኔዎች ለማንፃት እየሞከሩ ነው ብለዋቸዋል። የጋራ የራስ መከላከል መብት የሚል ፅንሰ ሃሳብ በማስተዋወቅ ሰነዱ ተቀባይነት እንዲያገኝ በአውሮፓውያኑ 2015 ይከራከሩ ነበር። ይህም ጃፓን እንዲሁም ጥቃት የደረሰባቸውን አጋሮቿን ለመካላከል በውጭ አገራት ወታደሮችን እንድታሰማራ የሚል ነው። ይህ ሰነድ ከጃፓን ጎረቤት አገራት እንዲሁም ከጃፓን ሕዝብ እንኳን ሳይቀር ተቃውሞ ቢገጥም የአገሪቱ ፓርላማ ይህንን አወዛጋቢ ዕቅድ አጸደቀው። ሆኖም የጃፓንን ጦር እንደገና ለማወቀር ሕገ መንግሥቱን የመከለስ ትልቁ አላማቸው አልተሳካም ነበር። እናም በአሁኑ ወቅትም ይህ ዕቅዳቸው በአገሪቱ ውስጥ ከፋፋይ ርዕሰ ጉዳይ ሆኖ ቀጥሏል። በተጨማሪም ጃፓን ሰሜናዊ ግዛቶቼ ብላ የምትጠራቸውን ቦታዎችን ማስመለስ አልቻሉም። ይህ ቦታ ጃፓን እና ሩሲያ ይገባኛል ብለው የሚወዛገቡባበቸውና በሰሜናዊ የሆካይዶ ግዛት ውስጥ ያሉ የደሴቶች ሰንሰለትን ይሸፍናል። አቤ ከቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ጥብቅ ግንኙነት የነበራቸው ሲሆን፣ አሜሪካ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች ላይ የጣለችውን አስከፊ  የንግድ ታሪፍ በጃፓን ላይ ተግባራዊ እንዳይሆን ተከላክለዋል በሚልም በበጎ ይነሳሉ። 'አቤኖምክስ' በመባል የሚታወቀው የአቤ ለየት ያለ የምጣኔ ሀብት ፖሊሲ በመጀመሪያ የሥልጣን ዘመናቸው እድገት እንዲታይ እንደረዳቸው ታይቷል። ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ነጌቲቭ (አሉታዊ) የወለድ ተመን በማስተዋወቅ ሸማቾች እና ኩባንያዎች ገንዘብ እንዲበደሩና እንዲያወጡ ረድቷቸዋል። የመንግሥት ወጪን በመሰረተ ልማት ላይ ማሳደግ፣ የግብር እፎይታን የመሳሰሉ ማበረታቻዎችንም አመጡ። በተጨማሪም በርካታ ሴቶች ወደ ሥራው ዓለም እንዲመጡና የጉልበት ጫናን ለማቃለል ስደተኞች ወደ ሥራ እንዲገቡ የመሳሳሉ በርካታ ስር ነቀል ማሻሻያዎችን አመጡ። ነገር ግን ጥረታቸው ፈተና ገጠመው። በተለይም በአውሮፓውያኑ 2020 ጃፓን እንደገና ምጣኔ ሀብቷ ማሽቆልቆሉን ተከትሎ ዘላቂነቱና ውጤታማነቱ ላይ ጥያቄ ተነሳባቸው። በምጣኔ ሀብት ፖሊሲያቸው ዘላቂነት ላይ ጥያቄ ሲነሳባቸው የነበረው አቤ፣ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ አያያዛቸው ጋርም ተያይዞ ስጋቶች መነሳት ጀመሩ። ተቺዎቻቸው እንደሚሏቸው የአገር ውስጥ ቱሪዝምን ለማሳደግ በሚል ያደረጓቸው ዘመቻዎች ወረርሽኙ እንዲባባስ አስተዋፅኦ አድርገዋል ብለው ያምናሉ። ሌሎች በአቤኖሚክስ ፖሊሲ የተገቡ ቃሎች ለምሳሌ ተጨማሪ ሴቶችን በሥራ ኃይል ማብቃት፣ ወገንተኝነትን መዋጋት እና ጤናማ ያልሆኑ የሥራ ባህሎችን መለወጥ ሳይፈጸሙ ቀርተዋል ይላሉ። በዓለም አቀፍ ደረጃ በ11 አገራት መካከል የተካሄደውን ግዙፍ የንግድ ስምምነት፣ ትራንስ ፓስፊክ ፓርትነር ሺፕ፣ በተለይም በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአገዛዝ ዘመን አሜሪካ በድንገት መውጣቷን ተከትሎ አጋርነቱን በማስጠበቅ ዕውቅና ተችሯቸዋል። አቤ ከሥልጣን የለቀቁት ከሁለት ዓመት በፊት ነሐሴ መጨረሻ ገደማ በአውሮፓውያኑ 2020 ነበር። ተተኪ ባለመምረጣቸውም በፓርቲያቸው ኤልዲፒ ውስጥ ባሉ አንጃዎች መካከል የውስጥ ትግል አስከተለ። በመጨረሻም በአንጋፋው ፖለቲከኛ እና የረዥም ጊዜ የካቢኔ አባል በሆኑት ዮሺሂዴ ሱጋ ተተኩ። ነገር ግን አቤ በጃፓን የውስጥ ፖለቲካ ላይ ከፍተኛ ቦታ ነበራቸው። ሱጋ በአሁኑ ወቅት በጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ ቢተኩም የአቤ በፖለቲካው ላይ የቁንጮነት ቦታ አልተነካም። በዛሬው ዕለት አርብ ሐምሌ 01/2014 ዓ.ም አቤ በደቡባዊ ናራ ከተማ ለጃፓን የላይኛው ምክር ቤት የሚወዳደር ዕጩን ወክለው ቅስቀሳ ሲያደርጉ ነበር። ንግግር እያደረጉ ባለበት ወቅት በአንድ ታጣቂ በጥይት ተመቱ። የተኮሰባቸው የ41 ዓመቱ ግለሰብ በጃፓን እንደ ባሕር ኃይል የሚታየው የራስ መከላከያ ኃይል የቀድሞ አባል እንደሆነም ይታመናል። አቤ በጥይት ተመትተው ሲወድቁና ወደ ሆስፒታል ሲወሰዱም ራሳቸውን ያውቁ ነበር። ነገር ግን ከደረሰባቸው ጉዳት አላገገሙም፤ ላይመለሱ አሸለቡ።
ለረጅም ዓመታት ጃፓንን በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩት ሺንዞ አቤ ሲታወሱ ለጃፓን የላይኛው ምክር ቤት የሚወዳደር ዕጩን ወክለው ቅስቀሳ በሚያደርጉበት ወቅት በተተኮሰባቸው ጥይት ሕይወታቸው ያለፈው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ በብዙ መልኩ ይታወሳሉ። “ጠብ አጫሪ” በሆነው የውጭ ፖሊሲያቸው እንዲሁም 'አቤኖሚክስ' ተብሎ በሚጠራው ለየት ያለ የምጣኔ ሀብት ስትራቴጂያቸው በጃፓን ስም አትርፈዋል። ህያው ሥራ ከመቃብር በላይ ነው እንዲሉ፣ በርካቶች ሲገልጿቸው “ወግ አጥባቂ ብሔረተኛ ይሏቸዋል” የ67 ዓመቱን ፖለቲከኛ። አቤ ፓርቲያቸውን ሊበራል ዲሞክራቲክ ፓርቲን (ኤልዲፒ) ሁለት ጊዜ አሸናፊ እንዲሆን አድርገውታል። የመጀመሪያው የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቆይታቸው አጭር ነበር። በአውሮፓውያኑ 2006 ወደ ሥልጣን መጥተው አንድ ዓመት አካባቢ አገሪቱን የመሩት አቤ የሥልጣን ቆይታቸውም አወዛጋቢ ነበር። ነገር ግን ከስድስት ዓመታት በኋላ በአውሮፓውያኑ 2012 በአስገራሚ ሁኔታ ተመልሰው በጤና ምክንያት ከሥልጣን እስከለቀቁበት 2020 ድረስ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ነበሩ። አቤ ለሁለተኛ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲሆኑ አገራቸው የምጣኔ ሀብት ድቀት ላይ ነበረች። የገንዘብ ፖሊሲውን በማላላት፣ ማነቃቂያዎች እንዲሁም መዋቅራዊ የሆኑ ማሻሻዎችን በማድረግ እያሽቆለቆለ የነበረውን ምጣኔ ሀብት ወደ ተረጋጋ ሁኔታ እንደሚመጣ አድርገዋል ተብለው ይወደሳሉ። ጃፓን በአውሮፓውያኑ 2011 በቶሁኩ ከደረሰው ከባድ ርዕደ መሬት እንዲሁም ሱናሚ እንድታገግም ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። በዚህ የመሬት መንቀጥቀጥ እና ሱናሚ ወደ 20 ሺህ የሚደርሱ ጃፓናውያን ሕይወት ከመቅጠፍ በተጨማሪ የፉኩሺማ የኒውክሌር ማመንጫዎችን አቅልጦ ከፍተኛ ቀውስ አድርሷል። ከሁለት ዓመት በፊት በአውሮፓውያኑ 2020 አቤ በፈቃዳቸው ከሥልጣናቸው ወረዱ። ለሳምንታት ያህል የጤናቸው ሁኔታ መወያያ ከሆነም በኋላ ነበር ከሥልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ ያቀረቡት። መጀመሪያም ከስድስት ዓመት በፊት ሥልጣን በለቀቁበት ወቅት በአንጀት አልሰር (ቁስለት) ህመም ሲሰቃዩ የነበረ ሲሆን፣ በዚህም ወቅት ይህ ቁስለት ማገርሸቱን አስታውቀው ነበር። እሳቸውንም በመተካት የፓርቲያቸው አባልና የቅርብ አጋር የሆኑት ዮሺሃዴ ሱጋ ወደ ሥልጣን መጡ። ሆኖም አቤ በጃፓን ፖለቲካ ውስጥ ከፍተኛ ስፍራ ያላቸው ሰው ተደርገው መታየታቸው አላከተመም። አቤ ከፖለቲከኛ ቤተሰብ ነው የመጡት። አባታቸው የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲሁም አያታቸው ደግሞ ጃፓንን በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩት ኖቡሱኬ ኪሺ ናቸው ። ለፓርላማ አባልነት የተመረጡት በአውሮፓውያኑ 1993 ሲሆን በአውሮፓውያኑ 2005 የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁኒቺሮ ኮይዙሚ ከፍተኛ የካቢኔ ፀሐፊ አድርገው ሾሟቸው። ከዚያም በአውሮፓውያኑ 2006 ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ በዕድሜ የጃፓን ትንሹ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን ቻሉ። ነገር ግን አስተዳደራቸው በተከታታይ ቅሌቶች የተሞላ ነበር። ወደ 50 ሚሊዮን የሚጠጉ ጉዳዮችን የያዘው የመንግሥት የጡረታ መዝገብ መጥፋት አስደዳደራቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ጎድቶታል። በአውሮፓውያኑ 2007 ለተደረገው የላይኛው ምክር ቤት ምርጫም ፓርቲያቸው ኤልዲፒ ከባድ ኪሳራን አስተናገደ። በዚያው ዓመትም በአንጀት አልሰር (ቁስለት) ምክንያት አቤ ከሥልጣናቸው ለቀቁ። ከስድስት ዓመት በኋላም በህክምና በሽታውን አሸንፌያለሁ በማለት ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት መንበር ተመለሱ። በመቀጠልም በነበሩት ምርጫዎች በአውሮፓውያኑ 2014 እና 2017 በድጋሚ ተመርጠዋል። ይህም ለረጅም ዓመታት ጃፓንን የመሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ያደርጋቸዋል። ተወዳጅነታቸውም በዓመታት ውስጥ ቢለዋወጥም በፖርቲያቸው ኤልዲፒ ውስጥ በነበራቸው ከባድ ተፅእኖ ምክንያት የተገዳደራቸው አልነበረም። የፓርቲያቸውንም ደንብና ሕግ በማሻሻል ለሦስተኛ ጊዜ የፓርቲው መሪ ለመሆን ችለዋል። አቤ በመከላከያ እና በውጭ ጉዳይ ፖሊሲያቸው ቁርጠኛና 'ጠብ አጫሪ' የሚባል አቋም ነበራቸው። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቃት በኋላ ሰላማዊ የሚባለውንም የጃፓን ሕገ መንግሥት ለማሻሻል ሲጥሩ ቆይተዋል። በአሜሪካ የተረቀቀውን የጃፓን ሕገ መንግሥት ወግ አጥባቂዎች፣ የጃፓን ወታደሮች በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የደረሰባቸውን አሳፋሪ ሽንፈት ማስታወሻ ነው ሲሉ ይተቹታል። ጭፍን ብሔረተኛነታቸውም ከቻይና እና ከደቡብ ኮሪያ ጋር ውጥረት ውስጥ እንዲገቡ ምክንያት ሆኗል። በተለይም በሁለተኛው ከዓለም ጦርነት በፊትና በዚያው ወቅት ጃፓን ነበራት ከሚባለው የጦረኝነት አቋም ጋር ተያይዞ አወዛጋቢ የሆነውን በቶኪዮ የሚገኘውን ያሱኩኒ ቤተ መቅደስ በአውሮፓውያኑ 2013 መጎብኘታቸውን ተከትሎ ከሁለቱ አገራት ጋር ነገሮች ተጋግለው ነበር። አቤ ያሱኩኒን በተደጋጋሚ መጎብኘታቸውም በጃፓን የሚገኙ የግራ ዘመም ፖለቲከኞችን ያስቆጣ ነበር። አቤ በጦርነቱ ወቅት ጃፓን ያደረሰችውን የመብት ጥሰቶችና ጭካኔዎች ለማንፃት እየሞከሩ ነው ብለዋቸዋል። የጋራ የራስ መከላከል መብት የሚል ፅንሰ ሃሳብ በማስተዋወቅ ሰነዱ ተቀባይነት እንዲያገኝ በአውሮፓውያኑ 2015 ይከራከሩ ነበር። ይህም ጃፓን እንዲሁም ጥቃት የደረሰባቸውን አጋሮቿን ለመካላከል በውጭ አገራት ወታደሮችን እንድታሰማራ የሚል ነው። ይህ ሰነድ ከጃፓን ጎረቤት አገራት እንዲሁም ከጃፓን ሕዝብ እንኳን ሳይቀር ተቃውሞ ቢገጥም የአገሪቱ ፓርላማ ይህንን አወዛጋቢ ዕቅድ አጸደቀው። ሆኖም የጃፓንን ጦር እንደገና ለማወቀር ሕገ መንግሥቱን የመከለስ ትልቁ አላማቸው አልተሳካም ነበር። እናም በአሁኑ ወቅትም ይህ ዕቅዳቸው በአገሪቱ ውስጥ ከፋፋይ ርዕሰ ጉዳይ ሆኖ ቀጥሏል። በተጨማሪም ጃፓን ሰሜናዊ ግዛቶቼ ብላ የምትጠራቸውን ቦታዎችን ማስመለስ አልቻሉም። ይህ ቦታ ጃፓን እና ሩሲያ ይገባኛል ብለው የሚወዛገቡባበቸውና በሰሜናዊ የሆካይዶ ግዛት ውስጥ ያሉ የደሴቶች ሰንሰለትን ይሸፍናል። አቤ ከቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ጥብቅ ግንኙነት የነበራቸው ሲሆን፣ አሜሪካ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች ላይ የጣለችውን አስከፊ  የንግድ ታሪፍ በጃፓን ላይ ተግባራዊ እንዳይሆን ተከላክለዋል በሚልም በበጎ ይነሳሉ። 'አቤኖምክስ' በመባል የሚታወቀው የአቤ ለየት ያለ የምጣኔ ሀብት ፖሊሲ በመጀመሪያ የሥልጣን ዘመናቸው እድገት እንዲታይ እንደረዳቸው ታይቷል። ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ነጌቲቭ (አሉታዊ) የወለድ ተመን በማስተዋወቅ ሸማቾች እና ኩባንያዎች ገንዘብ እንዲበደሩና እንዲያወጡ ረድቷቸዋል። የመንግሥት ወጪን በመሰረተ ልማት ላይ ማሳደግ፣ የግብር እፎይታን የመሳሰሉ ማበረታቻዎችንም አመጡ። በተጨማሪም በርካታ ሴቶች ወደ ሥራው ዓለም እንዲመጡና የጉልበት ጫናን ለማቃለል ስደተኞች ወደ ሥራ እንዲገቡ የመሳሳሉ በርካታ ስር ነቀል ማሻሻያዎችን አመጡ። ነገር ግን ጥረታቸው ፈተና ገጠመው። በተለይም በአውሮፓውያኑ 2020 ጃፓን እንደገና ምጣኔ ሀብቷ ማሽቆልቆሉን ተከትሎ ዘላቂነቱና ውጤታማነቱ ላይ ጥያቄ ተነሳባቸው። በምጣኔ ሀብት ፖሊሲያቸው ዘላቂነት ላይ ጥያቄ ሲነሳባቸው የነበረው አቤ፣ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ አያያዛቸው ጋርም ተያይዞ ስጋቶች መነሳት ጀመሩ። ተቺዎቻቸው እንደሚሏቸው የአገር ውስጥ ቱሪዝምን ለማሳደግ በሚል ያደረጓቸው ዘመቻዎች ወረርሽኙ እንዲባባስ አስተዋፅኦ አድርገዋል ብለው ያምናሉ። ሌሎች በአቤኖሚክስ ፖሊሲ የተገቡ ቃሎች ለምሳሌ ተጨማሪ ሴቶችን በሥራ ኃይል ማብቃት፣ ወገንተኝነትን መዋጋት እና ጤናማ ያልሆኑ የሥራ ባህሎችን መለወጥ ሳይፈጸሙ ቀርተዋል ይላሉ። በዓለም አቀፍ ደረጃ በ11 አገራት መካከል የተካሄደውን ግዙፍ የንግድ ስምምነት፣ ትራንስ ፓስፊክ ፓርትነር ሺፕ፣ በተለይም በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአገዛዝ ዘመን አሜሪካ በድንገት መውጣቷን ተከትሎ አጋርነቱን በማስጠበቅ ዕውቅና ተችሯቸዋል። አቤ ከሥልጣን የለቀቁት ከሁለት ዓመት በፊት ነሐሴ መጨረሻ ገደማ በአውሮፓውያኑ 2020 ነበር። ተተኪ ባለመምረጣቸውም በፓርቲያቸው ኤልዲፒ ውስጥ ባሉ አንጃዎች መካከል የውስጥ ትግል አስከተለ። በመጨረሻም በአንጋፋው ፖለቲከኛ እና የረዥም ጊዜ የካቢኔ አባል በሆኑት ዮሺሂዴ ሱጋ ተተኩ። ነገር ግን አቤ በጃፓን የውስጥ ፖለቲካ ላይ ከፍተኛ ቦታ ነበራቸው። ሱጋ በአሁኑ ወቅት በጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ ቢተኩም የአቤ በፖለቲካው ላይ የቁንጮነት ቦታ አልተነካም። በዛሬው ዕለት አርብ ሐምሌ 01/2014 ዓ.ም አቤ በደቡባዊ ናራ ከተማ ለጃፓን የላይኛው ምክር ቤት የሚወዳደር ዕጩን ወክለው ቅስቀሳ ሲያደርጉ ነበር። ንግግር እያደረጉ ባለበት ወቅት በአንድ ታጣቂ በጥይት ተመቱ። የተኮሰባቸው የ41 ዓመቱ ግለሰብ በጃፓን እንደ ባሕር ኃይል የሚታየው የራስ መከላከያ ኃይል የቀድሞ አባል እንደሆነም ይታመናል። አቤ በጥይት ተመትተው ሲወድቁና ወደ ሆስፒታል ሲወሰዱም ራሳቸውን ያውቁ ነበር። ነገር ግን ከደረሰባቸው ጉዳት አላገገሙም፤ ላይመለሱ አሸለቡ።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cy0ydy4p0m5o
3politics
በአማኑዔል ወንድሙ ግድያ ላይ የኦሮሚያ ክልል ምላሽ
በያዝነው ሳምንት ግንቦት 3፣ 2013 ዓ.ም በቄለም ወለጋ ዞን ደምቢ ዶሎ ከተማ አማኑኤል ወንድሙ የተባለ ወጣት በአደባባይ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች መገደሉን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። የአካባቢው የመንግሥት ኃላፊዎች ወጣቱ ባለስልጣናትን በመግደል የሚታወቀው 'አባ ቶርቤ' የተባለ ህቡዕ አባል ቡድን ነው በማለት መገደሉን ቢያረጋግጡም ለሕዝብ እንዲታይ ተደረገ እንጂ በአደባባይ አልተገደለም ሲሉ አስተባብለዋል። የደምቢ ዶሎ ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት እንዲሁ ሰዎችን ሲገድል በነበረው እና 'የአባ ቶርቤ' ቡድን አባል በሆነው ግለሰብ ላይ እርምጃ ተወሰደ ሲልም በፌስቡክ ገጹ ላይ ጽፏል። የአማኑኤል ወንድሙን ግድያ በተመለከተ ቢቢሲ የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻን የጠየቀ ሲሆን ኃላፊው በክልሉ ህዝብን እያሸበሩ ነው የሚሏቸው አካላት ላይ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ በአፅንኦት ተናግረዋል። "በከተሞች ሰውን እየገደሉ ህዝብን ማሸበር የነሱ የእለት ተእለት ተግባር ነው። እነሱ የሚያደርጉት መግደል ነው። ሰላምን ለማስከበር የሚሄደው ኃይል እነዚህ አካላትን አጋልጦ እርምጃ ወስዶ ሊቆጣጠር ይገባል የሚል እምነት አለኝ። ስለዚህ የተወሰደው እርምጃ የትኛውም አይነት ይሁን ህዝብን አሸብሮ፣ አስፈራርቶ እቆጣጠራለሁ የሚለው ኃይል ላይ እርምጃ መወሰድ አለበት።" ብለዋል። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ይህንን በተመለከተም አቅጣጫ ሰጥቶ እየሰራበት መሆኑንም በተጨማሪ ገልፀዋል። "ሰው በቤቱ፣ በቀዬው ነው እየተገደለ ያለው፤ በማያውቀው ነገር ነው እየሞተ ያለው፤ እንዲህ አይነት ተግባር በሚፈፅሙ አካላት ላይ የሚወሰደው እርምጃ እነሱ በሚፈፅሙት ልክ ተመጣጣኝ መሆን አለበት።" በማለትም ይናገራሉ። ነገር ግን አማኑኤል በአደባባይ ነው የተገደለው ስለሚባለው ጉዳይ ""ወጣቱ የደምቢ ዶሎ ነዋሪ አደባባይ ላይ ነው የተገደለው ስለሚባለው ነገር ግን መረጃ የለኝም" ብለዋል። የቄለም ወለጋ ዞን የደህንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተሰማ ዋሪዮ በበኩላቸው ወጣቱ ቆስሎ ከተያዘ በኋላ ለሕዝብ እንዲታይ ተደረገ እንጂ በአደባባይ አልተገደለም ይላሉ። "ተጠርጣሪ አይደለም" የሚሉት አቶ ተሰማ፤ ይህ ወጣት ሁለት ሰዎች በጥይት መትቶ እያመለጠ ሳለ በፀጥታ ኃይሎች በጥይት ተመትቶ መያዙን ይናገራሉ። የደምቢዶሎ ከተማ ነዋሪ የሆኑት እና ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸውን እንዳይጠቀስ የጠየቁ ግለሰብ ወጣቱ በአደባባይ ሲገደል ማየታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። "አማኑኤል ሕዝብ የሚወደው ልጅ ነበር" ካሉ በኋላ፤ በጥይት ተመትቶ ከተያዘ በኋላ "ሲገደል በዓይናችን አይተናል" ብለዋል። እኚህ ነዋሪ እንደሚሉት ከሆነ የመንግሥት ጸጥታ አስከባሪ አካላት ወጣቱ ለመያዝ ሲንቀሳቀሱ ወጣቱ ከአንድ ሱቅ እቃ እየገዛ ነበር ይላሉ። የአማኑኤል ወንድሙ ግድያን በተመለከተ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከፍርድ ውጭ የተፈፀመበት ግድያና (extrajudicial killing) በአደባባይ ለህዝብ እንዲታይ የተደረገበት መንገድ እንዳሳሰበው ትናንትና ግንቦት 4/2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ኮሚሽኑ ማንኛውንም ከፍርድ ውጭ የሚካሄዱ ግድያዎችን የሚያወግዝ መሆኑን አስታውቆ ሁሉም የሕግ አስፈፃሚ አካላት ሕጋዊ መንገዶች ብቻ አንዲተገብሩ መልዕክቱን አስተላልፏል። እናንተ ክልሉን እያስተዳደራችሁ እንዴት የወጣቱን የአደባባይ ግድያ አናውቅም ትላላችሁ? ተብለው ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ የ ክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ በበኩላቸው የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን ወንጅለዋል። "የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሁልጊዜ የክልሉን ስም ለማጥፋት ስለሚሰራ እነሱ ያላቸው መረጃ እኔ የለኝም። እነሱ ሄደው አይተው ነው ወይስ ከማህበራዊ ሚዲያ ያገኙትን ይዘው ነው ይህንን መግለጫ ያወጡት?" በማለት የሚጠይቁት አቶ ጌታቸው አክለውም "ይህ መጣራት አለበት። በማስረጃ ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት። ማን ምን አደረገ የሚለውን ነገር ሳይቀበሉ እንዲሁ ሆነ ብሎ ከአንድ ወገን ብቻ መረጃ ይዞ ማውራት ተቀባይነት የለውም። ለሰብዓዊ መብት ነው የምሰራው የሚል ተቋም ጉዳዩን መዘገብ ያለበት በአካል ተገኝቶ ነው። የሚጠየቅም አካል ካለ እርምጃ ሊወሰድ የሚችለው መረጃው ሙሉ ሲሆን ነው።" ይላሉ ኮሚሽኑ በበኩሉ "ከፍርድ ውጭ የሚካሄዱ ግድያዎች ህዝቦች በሕግ የበላይነት ላይ ዕምነት እንዲያጡ እና በዚህ ረገድ የተገኙ ስኬቶች እንዲቀለበሱ ያደርጋሉ" ከማለት በተጨማሪ ባለሥልጣናት ጉዳዩን በአፋጣኝ እንዲመረምሩ እና ተገቢ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ጠይቋል። ከዚህ ቀደምም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኦሮሚያ ክልል ያለው የእስረኞች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ እንዳሳሰበው መግለፁ ይታወሳል። ከዚህ በተጨማሪ ተጠርጣሪዎችን በሕግ ከመዳኘት ይልቅ የፖለቲካ (የአስተዳደራዊ) ውሳኔዎች ሰለባ እንዲሆኑ ተድርጓል ብሎ ነበር። ከሰሞኑ የወጣው ቪዲዮ ምንን ያሳያል? በዚህ የፌስቡክ ገጽ ላይ ወጣቱ ከመገደሉ በፊት ለቀረቡለት ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጥ ይታያል። ቪዲዮን እየቀረጸ የሚገኘው ሰው የወጣቱን ስም እና የትውልድ ስፍራውን ይጠይቀዋል። እጁ ወደ ኋላ የታሰረው ወጣት አንገቱ ላይ ሽጉጥ ተንጠልጥሎ ይታያል። በወጣቱ እግር ላይ እና በዙሪያው ደም የሚታይ ሲሆን ልብሱም በጭቃ ተለውሷል። አደባባይ ፊትለፊት የቆመው ወጣት ስሙ አማኑኤል ወንድሙ ከበደ እንደሚባል እና ትውልዱ ደምቢ ዶሎ ከተማ 07 ተብሎ በሚጠራ ስፍራ እንደሆነ ይናገራል። በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ የደንብ ልብስ በለበሱ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎ ተከቦ ይታያል። ስለ ግድያው የአካባቢው ባለስልጣናት ምን አሉ? የከተማው ኮሚውኒኬሽን ጽ/ቤት እንደሚለው ከሆነ ይህ ወጣት የመንግሥት ባለስልጣናትን በመግደል የሚታወቀው "አባ ቶርቤ' የተሰኘው ህቡዕ ቡድን አባል ነበር። ወጣቱ ትናንት በቁጥጥር ሥር ከመዋሉ በፊትም ንጋት ላይ ገመቹ መንገሻ የተባለ ግለሰብ በጥይት መትቶ ለማምለጥ ሲሞክር "በጸጥታ ኃይሎች ጠንካራ ትስስር እግሩን ተመትቶ ተይዟል" ብሏል። ከዚህ በተጨማሪም ከቀናት በፊት በደምቢዶሎ ከተማ የኦሮሚያ ብሮድካስቲን ኔትዎርክ ጋዜጠኛ የነበረውን ሲሳይ ፊዳ የገደለው የአባ ቶርቤ ቡድን ነው ሲል አክሏል። አቶ ተሰማ በደምቢዶሎ አካባቢ ከሰሞኑ በኦነግ ሸኔ እና በመንግሥት ኃይሎች መካከል የተኩስ ልውውጥ እንደነበረ ተናግረው፤ ወጣቱ አንገት ላይ የተንጠለጠለው ሽጉጥ ንጹሃን ዜጎችን እና የመንግሥት ኃይሎችን ሲገድልበት የነበረ ነው ብለዋል። ቢቢሲ የዞኑ ፖሊስ ባልደረቦችን አነጋግሮ ያገኘው ምላሽ አቶ ተሰማ ከሰጡት አስተያየት ጋር ተመሳሳይ ነው።
በአማኑዔል ወንድሙ ግድያ ላይ የኦሮሚያ ክልል ምላሽ በያዝነው ሳምንት ግንቦት 3፣ 2013 ዓ.ም በቄለም ወለጋ ዞን ደምቢ ዶሎ ከተማ አማኑኤል ወንድሙ የተባለ ወጣት በአደባባይ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች መገደሉን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። የአካባቢው የመንግሥት ኃላፊዎች ወጣቱ ባለስልጣናትን በመግደል የሚታወቀው 'አባ ቶርቤ' የተባለ ህቡዕ አባል ቡድን ነው በማለት መገደሉን ቢያረጋግጡም ለሕዝብ እንዲታይ ተደረገ እንጂ በአደባባይ አልተገደለም ሲሉ አስተባብለዋል። የደምቢ ዶሎ ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት እንዲሁ ሰዎችን ሲገድል በነበረው እና 'የአባ ቶርቤ' ቡድን አባል በሆነው ግለሰብ ላይ እርምጃ ተወሰደ ሲልም በፌስቡክ ገጹ ላይ ጽፏል። የአማኑኤል ወንድሙን ግድያ በተመለከተ ቢቢሲ የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻን የጠየቀ ሲሆን ኃላፊው በክልሉ ህዝብን እያሸበሩ ነው የሚሏቸው አካላት ላይ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ በአፅንኦት ተናግረዋል። "በከተሞች ሰውን እየገደሉ ህዝብን ማሸበር የነሱ የእለት ተእለት ተግባር ነው። እነሱ የሚያደርጉት መግደል ነው። ሰላምን ለማስከበር የሚሄደው ኃይል እነዚህ አካላትን አጋልጦ እርምጃ ወስዶ ሊቆጣጠር ይገባል የሚል እምነት አለኝ። ስለዚህ የተወሰደው እርምጃ የትኛውም አይነት ይሁን ህዝብን አሸብሮ፣ አስፈራርቶ እቆጣጠራለሁ የሚለው ኃይል ላይ እርምጃ መወሰድ አለበት።" ብለዋል። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ይህንን በተመለከተም አቅጣጫ ሰጥቶ እየሰራበት መሆኑንም በተጨማሪ ገልፀዋል። "ሰው በቤቱ፣ በቀዬው ነው እየተገደለ ያለው፤ በማያውቀው ነገር ነው እየሞተ ያለው፤ እንዲህ አይነት ተግባር በሚፈፅሙ አካላት ላይ የሚወሰደው እርምጃ እነሱ በሚፈፅሙት ልክ ተመጣጣኝ መሆን አለበት።" በማለትም ይናገራሉ። ነገር ግን አማኑኤል በአደባባይ ነው የተገደለው ስለሚባለው ጉዳይ ""ወጣቱ የደምቢ ዶሎ ነዋሪ አደባባይ ላይ ነው የተገደለው ስለሚባለው ነገር ግን መረጃ የለኝም" ብለዋል። የቄለም ወለጋ ዞን የደህንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተሰማ ዋሪዮ በበኩላቸው ወጣቱ ቆስሎ ከተያዘ በኋላ ለሕዝብ እንዲታይ ተደረገ እንጂ በአደባባይ አልተገደለም ይላሉ። "ተጠርጣሪ አይደለም" የሚሉት አቶ ተሰማ፤ ይህ ወጣት ሁለት ሰዎች በጥይት መትቶ እያመለጠ ሳለ በፀጥታ ኃይሎች በጥይት ተመትቶ መያዙን ይናገራሉ። የደምቢዶሎ ከተማ ነዋሪ የሆኑት እና ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸውን እንዳይጠቀስ የጠየቁ ግለሰብ ወጣቱ በአደባባይ ሲገደል ማየታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። "አማኑኤል ሕዝብ የሚወደው ልጅ ነበር" ካሉ በኋላ፤ በጥይት ተመትቶ ከተያዘ በኋላ "ሲገደል በዓይናችን አይተናል" ብለዋል። እኚህ ነዋሪ እንደሚሉት ከሆነ የመንግሥት ጸጥታ አስከባሪ አካላት ወጣቱ ለመያዝ ሲንቀሳቀሱ ወጣቱ ከአንድ ሱቅ እቃ እየገዛ ነበር ይላሉ። የአማኑኤል ወንድሙ ግድያን በተመለከተ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከፍርድ ውጭ የተፈፀመበት ግድያና (extrajudicial killing) በአደባባይ ለህዝብ እንዲታይ የተደረገበት መንገድ እንዳሳሰበው ትናንትና ግንቦት 4/2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ኮሚሽኑ ማንኛውንም ከፍርድ ውጭ የሚካሄዱ ግድያዎችን የሚያወግዝ መሆኑን አስታውቆ ሁሉም የሕግ አስፈፃሚ አካላት ሕጋዊ መንገዶች ብቻ አንዲተገብሩ መልዕክቱን አስተላልፏል። እናንተ ክልሉን እያስተዳደራችሁ እንዴት የወጣቱን የአደባባይ ግድያ አናውቅም ትላላችሁ? ተብለው ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ የ ክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ በበኩላቸው የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን ወንጅለዋል። "የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሁልጊዜ የክልሉን ስም ለማጥፋት ስለሚሰራ እነሱ ያላቸው መረጃ እኔ የለኝም። እነሱ ሄደው አይተው ነው ወይስ ከማህበራዊ ሚዲያ ያገኙትን ይዘው ነው ይህንን መግለጫ ያወጡት?" በማለት የሚጠይቁት አቶ ጌታቸው አክለውም "ይህ መጣራት አለበት። በማስረጃ ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት። ማን ምን አደረገ የሚለውን ነገር ሳይቀበሉ እንዲሁ ሆነ ብሎ ከአንድ ወገን ብቻ መረጃ ይዞ ማውራት ተቀባይነት የለውም። ለሰብዓዊ መብት ነው የምሰራው የሚል ተቋም ጉዳዩን መዘገብ ያለበት በአካል ተገኝቶ ነው። የሚጠየቅም አካል ካለ እርምጃ ሊወሰድ የሚችለው መረጃው ሙሉ ሲሆን ነው።" ይላሉ ኮሚሽኑ በበኩሉ "ከፍርድ ውጭ የሚካሄዱ ግድያዎች ህዝቦች በሕግ የበላይነት ላይ ዕምነት እንዲያጡ እና በዚህ ረገድ የተገኙ ስኬቶች እንዲቀለበሱ ያደርጋሉ" ከማለት በተጨማሪ ባለሥልጣናት ጉዳዩን በአፋጣኝ እንዲመረምሩ እና ተገቢ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ጠይቋል። ከዚህ ቀደምም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኦሮሚያ ክልል ያለው የእስረኞች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ እንዳሳሰበው መግለፁ ይታወሳል። ከዚህ በተጨማሪ ተጠርጣሪዎችን በሕግ ከመዳኘት ይልቅ የፖለቲካ (የአስተዳደራዊ) ውሳኔዎች ሰለባ እንዲሆኑ ተድርጓል ብሎ ነበር። ከሰሞኑ የወጣው ቪዲዮ ምንን ያሳያል? በዚህ የፌስቡክ ገጽ ላይ ወጣቱ ከመገደሉ በፊት ለቀረቡለት ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጥ ይታያል። ቪዲዮን እየቀረጸ የሚገኘው ሰው የወጣቱን ስም እና የትውልድ ስፍራውን ይጠይቀዋል። እጁ ወደ ኋላ የታሰረው ወጣት አንገቱ ላይ ሽጉጥ ተንጠልጥሎ ይታያል። በወጣቱ እግር ላይ እና በዙሪያው ደም የሚታይ ሲሆን ልብሱም በጭቃ ተለውሷል። አደባባይ ፊትለፊት የቆመው ወጣት ስሙ አማኑኤል ወንድሙ ከበደ እንደሚባል እና ትውልዱ ደምቢ ዶሎ ከተማ 07 ተብሎ በሚጠራ ስፍራ እንደሆነ ይናገራል። በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ የደንብ ልብስ በለበሱ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎ ተከቦ ይታያል። ስለ ግድያው የአካባቢው ባለስልጣናት ምን አሉ? የከተማው ኮሚውኒኬሽን ጽ/ቤት እንደሚለው ከሆነ ይህ ወጣት የመንግሥት ባለስልጣናትን በመግደል የሚታወቀው "አባ ቶርቤ' የተሰኘው ህቡዕ ቡድን አባል ነበር። ወጣቱ ትናንት በቁጥጥር ሥር ከመዋሉ በፊትም ንጋት ላይ ገመቹ መንገሻ የተባለ ግለሰብ በጥይት መትቶ ለማምለጥ ሲሞክር "በጸጥታ ኃይሎች ጠንካራ ትስስር እግሩን ተመትቶ ተይዟል" ብሏል። ከዚህ በተጨማሪም ከቀናት በፊት በደምቢዶሎ ከተማ የኦሮሚያ ብሮድካስቲን ኔትዎርክ ጋዜጠኛ የነበረውን ሲሳይ ፊዳ የገደለው የአባ ቶርቤ ቡድን ነው ሲል አክሏል። አቶ ተሰማ በደምቢዶሎ አካባቢ ከሰሞኑ በኦነግ ሸኔ እና በመንግሥት ኃይሎች መካከል የተኩስ ልውውጥ እንደነበረ ተናግረው፤ ወጣቱ አንገት ላይ የተንጠለጠለው ሽጉጥ ንጹሃን ዜጎችን እና የመንግሥት ኃይሎችን ሲገድልበት የነበረ ነው ብለዋል። ቢቢሲ የዞኑ ፖሊስ ባልደረቦችን አነጋግሮ ያገኘው ምላሽ አቶ ተሰማ ከሰጡት አስተያየት ጋር ተመሳሳይ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/news-57097406
0business
ሮናልዶ፣ ኬን፣ ምባፔ፣ ግሪዝማን. . . የተሳኩትና ያልተሳኩት ዝውውሮች የትኞቹ ናቸው?
ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ ያደረገውን ዝውውር ጨምሮ የፕሪሚየር ሊጉን ክለቦች ከአንድ ቢሊየን ፓውንድ በላይ በዝውውር መስኮቱ አውጥተዋል። አጠቃላይ ወጪው ግን ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት ቀንሷል። ትልቁ ስምምነት ኒኮላ ቭላሲክ ከሲኤስኬኤ ሞስኮ ወደ ዌስትሃም በ26.8 ሚሊዮን ፓውንድ ያደረገው ሆኗል። በአጠቃላይ የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች በዝውውር መስኮቱ 1.1 ቢሊዮን ፓውንድ ወጪ አድረገዋል። ከቀዳሚው ዓመት የ1.3 ቢሊዮን ፓውንድ ዝውውር በ11 በመቶ ዝቅ ብሏል። እንደ ፋይናንስ ድርጅቱ ዴይሎት ዘገባ ከሆነ ይህ ከ2015 ጀምሮ በፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ዝቅተኛ ጠቅላላ ወጪ ሆኖ ተመዝግቧል። የመጨረሻው ቀን የፕሪሚየር ሊጉ ዝውውሮች የትኞቹ ናቸው? ቶተንሃም ለባርሴሎናው ተከላካይ ኤመርሰን ሮያል 25.8 ሚሊዮን ፓውንድ ያወጣ ሲሆን የመስመር ተጫዋቹ ዳንኤል ጄምስ ከማንችስተር ዩናይትድ በ25 ሚሊዮን ፓውንድ ሊድስን ተቀላቅሏል። ብራይተን የስፔኑን ተከላካይ ማርክ ኩኩሬላን ከጌታፌ በ15.4 ሚሊዮን ፓውንድ አስፈርሟል። ሴኔጋላዊው አጥቂ አብደላህ ሲማ ወደ ስቶክ በውሰት ከመዛወሩ በፊት ከሲላቪያ ፕራግ በተመሳሳይ ብራይተንን ተቀላቅሏል። ከቭላሲክ በተጨማሪ ዌስትሃም የአማካዩን አሌክስ ክራልን ከስፓርታክ ሞስኮ በውሰት አምጥቷል። ሌስተር በበኩሉ ከአርቢ ሌፕዢንግ የክንፍ ተጫዋቹን አዴሞላ ሉክማንን በአንድ ዓመት የውሰት ውል አስፈርሟል። በርንሌይ ዌልሳዊውን ኮነር ሮበርትስን ከስዋንሲ በማምጣት በጥቂት ቀናት ውስጥ ሁለተኛውን ተከላካይ አስፈርሟል። ክሪስታል ፓላስ በበኩሉ አጥቂውን አድሰን ኢዶዋርድን ከሴልቲክ በ15 ሚሊዮን ፓውንድ አዘዋውረዋል። አርሴናል የጃፓኑን ተከላካይ ታሂሮ ቶሚያሱን ከቦሎኛ አስፈርሟል። በውሰት ደግሞ አርሰናል ሄክቶር ቤለሪን ወደ ሪያል ቤቲስና ሬይስ ኔልሰን ወደ ፌይኖርድ እንዲዛወሩ ፈቅደዋል። ሰሎሞን ሮንዶን በነጻ ዝውውር ለኤቨርተን ፊርማውን አኑሯል። ሜክሲኳዊው አጥቂ ሳንቲያጎ ሙኖዝ ደግሞ ወደ ኒውካስል አቅንቷል። የአውሮፓ ዋና ዋና ዝውውሮችስ ምን ይመስላሉ? ዋና ዋናዎቹ የአውሮፓ ክለቦች በዝውውሩ መጠናቀቂያ ዕለት ንቁ ተሳትፎ ቢኖራቸውም ሪያል ማድሪድ ምባፔን ለማስፈረም ያደረገው ሙከራ አልተሳካም። የስፔኑ ግዙፍ ክለብ የፈረንሳዩን አማካይ ኤድዋርዶ ካማቪንጋን ከሬንስ አስፈርሟል። ሮናልዶን በማንችስተር ዩናይትድ የተነጠቁት ጁቬንቱሶች አጥቂው ሞይስ ኬንን ከኤቨርተን በሁለት ዓመት የውሰት ውል እንደገና ማስፈረም ችለዋል። ባርሴሎና ያሉበትን የፋይናንስ ስጋቶችን ለማቃለል ተጫዋቾችን የለቀቀ ሲሆን ኢላይክስ ሞሪባን ለአርቢ ሌፕዢንግ አሳልፎ ሲሰጥ አንቶኒ ግሪዝማን ደግሞ በውሰት ወደ አትሌቲኮ ማድሪድ ተመልሷል። ትልልቆቹ ዝውውሮች የትኞቹ ናቸው? አርሰናል፣ ማንችስተር ዩናይትድ፣ ማንቸስተር ሲቲ እና ቼልሲ አራቱ ከፍተኛ ገንዘብ ያወጡ የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ሆነዋል። ማንቸስተር ሲቲ ትልቁን የዝውውር መስኮቱን ስምምነት የእንግሊዝን የዝውውር ክብረ ወሰንን በመስበር ጃክ ግሪሊሽ ከአስቶን ቪላ በ 100 ሚሊዮን ፓውንድ የግሉ አድርጓል። የአውሮፓ ሻምፒዮኑ ቼልሲ ደግሞ አጥቂውን ሮሜሎ ሉካኩን ከኢንተር ሚላን በ97.5 ሚሊዮን ፓውንድ መልሶ አስፈርሟል። ማንችስተር ዩናይትድ ጄደን ሳንቾን ከዶርትመንድ በ 73 ሚሊዮን ፓውንድ እና ራፋኤል ቫራንን ከሪያል ማድሪድ በ34 ሚሊዮን ፓውንድ ኦልድ ትራፎርድ አድርሷል። አርሰናል በዝውውር መስኮቱ ከፍተኛ ገንዘብ ካወጡ ክለቦች አንዱ ነበር። ቤን ዋይት ከብራይተን (50 ሚሊዮን ፓውንድ)፣ ማርቲን ኦዴጋርድ ከሪያል ማድሪድ (30 ሚሊዮን ፓውንድ) እና አሮን ራምስዴል ከሸፊልድ ዩናይትድ (24 ሚሊዮን ፓውንድ) ጨምሮ ሌሎችንም ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ ቀላቅሏል። ሊቨርፑል በአንጻራዊ ሁኔታ የተቀዛቀዘ የዝውውር መስኮት አሳልፏል። ተከላካዩን ኢብራሂማ ኮናቴን ከአርቢ ሌፕዢንግ ለማስፈረም 36 ሚሊዮን ፓውንድ አውጥቷል። በመጨረሻው የዝውውር ቀን የአራት ዓመት ውል የፈረመውን አምበሉን ጆርዳን ሄንደርሰን ጨምሮ ለበርካታ ቁልፍ ተጫዋቾቹን ውል አራዝሟል። በጣም ትኩረት የሳበው ዝውውር ሊዮኔል ሜሲ ለ21 ዓመታት ከቆየበት ባርሴሎና በነጻ ዝውውር ወደ ፓሪስ ሴንት ዠርሜን ያቀናበት ሆኗል። ያልተሳኩት ዝውውሮችስ? የ2021 የክረምት የዝውውር መስኮት ባልተሳኩ ስምምነቶችም ይታወሳል። ማንችስተር ሲቲ አብዛኛውን የዝውውር መስኮት የእንግሊዙን አምበል ሃሪ ኬንን ለማዘዋወር ጥረት ቢያደርግም አጥቂው በስፐርስ ለመቆየት ተስማምቷል። ሪያል ማድሪድ ምባፔን ለማስፈረም ሁለት ጊዜ ሞክሯል። ማድሪዶች ሁለት ጊዜ ከ100 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ ያቀረቡት ዋጋ በፓሪስ ሴንት ዠርሜን ውድቅ ተደርጓል። ቼልሲ ፈረንሳዊውን ተከላካይ ጁልስ ኩንዴን ለማስፈረም ቢፈልግም ሲቪያ ከመሸጫ ዋጋው 80 ሚሊዮን ዩሮ በታች ለመቀበል ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። አይንስሊ ማይትላንድ-ኒልስ ማህበራዊ ድር አምባውን ተጠቅሞ ከአርሰናል ለመልቀቅ ያደረገው ሙከራ አልተሳካም። የጄሴ ሊንጋርድ ወደ ዌስትሃም የታቀደው ዝውውር ባለመሳካቱ በማንችስተር ዩናይትድ ይቆያል። ዎልቭስም የሊሉን አማካይ ሬናቶ ሳንቼዝን ዘግይቶ ለማዘዋወር ያደረገውን ጥረት አቋርጧል።
ሮናልዶ፣ ኬን፣ ምባፔ፣ ግሪዝማን. . . የተሳኩትና ያልተሳኩት ዝውውሮች የትኞቹ ናቸው? ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ ያደረገውን ዝውውር ጨምሮ የፕሪሚየር ሊጉን ክለቦች ከአንድ ቢሊየን ፓውንድ በላይ በዝውውር መስኮቱ አውጥተዋል። አጠቃላይ ወጪው ግን ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት ቀንሷል። ትልቁ ስምምነት ኒኮላ ቭላሲክ ከሲኤስኬኤ ሞስኮ ወደ ዌስትሃም በ26.8 ሚሊዮን ፓውንድ ያደረገው ሆኗል። በአጠቃላይ የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች በዝውውር መስኮቱ 1.1 ቢሊዮን ፓውንድ ወጪ አድረገዋል። ከቀዳሚው ዓመት የ1.3 ቢሊዮን ፓውንድ ዝውውር በ11 በመቶ ዝቅ ብሏል። እንደ ፋይናንስ ድርጅቱ ዴይሎት ዘገባ ከሆነ ይህ ከ2015 ጀምሮ በፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ዝቅተኛ ጠቅላላ ወጪ ሆኖ ተመዝግቧል። የመጨረሻው ቀን የፕሪሚየር ሊጉ ዝውውሮች የትኞቹ ናቸው? ቶተንሃም ለባርሴሎናው ተከላካይ ኤመርሰን ሮያል 25.8 ሚሊዮን ፓውንድ ያወጣ ሲሆን የመስመር ተጫዋቹ ዳንኤል ጄምስ ከማንችስተር ዩናይትድ በ25 ሚሊዮን ፓውንድ ሊድስን ተቀላቅሏል። ብራይተን የስፔኑን ተከላካይ ማርክ ኩኩሬላን ከጌታፌ በ15.4 ሚሊዮን ፓውንድ አስፈርሟል። ሴኔጋላዊው አጥቂ አብደላህ ሲማ ወደ ስቶክ በውሰት ከመዛወሩ በፊት ከሲላቪያ ፕራግ በተመሳሳይ ብራይተንን ተቀላቅሏል። ከቭላሲክ በተጨማሪ ዌስትሃም የአማካዩን አሌክስ ክራልን ከስፓርታክ ሞስኮ በውሰት አምጥቷል። ሌስተር በበኩሉ ከአርቢ ሌፕዢንግ የክንፍ ተጫዋቹን አዴሞላ ሉክማንን በአንድ ዓመት የውሰት ውል አስፈርሟል። በርንሌይ ዌልሳዊውን ኮነር ሮበርትስን ከስዋንሲ በማምጣት በጥቂት ቀናት ውስጥ ሁለተኛውን ተከላካይ አስፈርሟል። ክሪስታል ፓላስ በበኩሉ አጥቂውን አድሰን ኢዶዋርድን ከሴልቲክ በ15 ሚሊዮን ፓውንድ አዘዋውረዋል። አርሴናል የጃፓኑን ተከላካይ ታሂሮ ቶሚያሱን ከቦሎኛ አስፈርሟል። በውሰት ደግሞ አርሰናል ሄክቶር ቤለሪን ወደ ሪያል ቤቲስና ሬይስ ኔልሰን ወደ ፌይኖርድ እንዲዛወሩ ፈቅደዋል። ሰሎሞን ሮንዶን በነጻ ዝውውር ለኤቨርተን ፊርማውን አኑሯል። ሜክሲኳዊው አጥቂ ሳንቲያጎ ሙኖዝ ደግሞ ወደ ኒውካስል አቅንቷል። የአውሮፓ ዋና ዋና ዝውውሮችስ ምን ይመስላሉ? ዋና ዋናዎቹ የአውሮፓ ክለቦች በዝውውሩ መጠናቀቂያ ዕለት ንቁ ተሳትፎ ቢኖራቸውም ሪያል ማድሪድ ምባፔን ለማስፈረም ያደረገው ሙከራ አልተሳካም። የስፔኑ ግዙፍ ክለብ የፈረንሳዩን አማካይ ኤድዋርዶ ካማቪንጋን ከሬንስ አስፈርሟል። ሮናልዶን በማንችስተር ዩናይትድ የተነጠቁት ጁቬንቱሶች አጥቂው ሞይስ ኬንን ከኤቨርተን በሁለት ዓመት የውሰት ውል እንደገና ማስፈረም ችለዋል። ባርሴሎና ያሉበትን የፋይናንስ ስጋቶችን ለማቃለል ተጫዋቾችን የለቀቀ ሲሆን ኢላይክስ ሞሪባን ለአርቢ ሌፕዢንግ አሳልፎ ሲሰጥ አንቶኒ ግሪዝማን ደግሞ በውሰት ወደ አትሌቲኮ ማድሪድ ተመልሷል። ትልልቆቹ ዝውውሮች የትኞቹ ናቸው? አርሰናል፣ ማንችስተር ዩናይትድ፣ ማንቸስተር ሲቲ እና ቼልሲ አራቱ ከፍተኛ ገንዘብ ያወጡ የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ሆነዋል። ማንቸስተር ሲቲ ትልቁን የዝውውር መስኮቱን ስምምነት የእንግሊዝን የዝውውር ክብረ ወሰንን በመስበር ጃክ ግሪሊሽ ከአስቶን ቪላ በ 100 ሚሊዮን ፓውንድ የግሉ አድርጓል። የአውሮፓ ሻምፒዮኑ ቼልሲ ደግሞ አጥቂውን ሮሜሎ ሉካኩን ከኢንተር ሚላን በ97.5 ሚሊዮን ፓውንድ መልሶ አስፈርሟል። ማንችስተር ዩናይትድ ጄደን ሳንቾን ከዶርትመንድ በ 73 ሚሊዮን ፓውንድ እና ራፋኤል ቫራንን ከሪያል ማድሪድ በ34 ሚሊዮን ፓውንድ ኦልድ ትራፎርድ አድርሷል። አርሰናል በዝውውር መስኮቱ ከፍተኛ ገንዘብ ካወጡ ክለቦች አንዱ ነበር። ቤን ዋይት ከብራይተን (50 ሚሊዮን ፓውንድ)፣ ማርቲን ኦዴጋርድ ከሪያል ማድሪድ (30 ሚሊዮን ፓውንድ) እና አሮን ራምስዴል ከሸፊልድ ዩናይትድ (24 ሚሊዮን ፓውንድ) ጨምሮ ሌሎችንም ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ ቀላቅሏል። ሊቨርፑል በአንጻራዊ ሁኔታ የተቀዛቀዘ የዝውውር መስኮት አሳልፏል። ተከላካዩን ኢብራሂማ ኮናቴን ከአርቢ ሌፕዢንግ ለማስፈረም 36 ሚሊዮን ፓውንድ አውጥቷል። በመጨረሻው የዝውውር ቀን የአራት ዓመት ውል የፈረመውን አምበሉን ጆርዳን ሄንደርሰን ጨምሮ ለበርካታ ቁልፍ ተጫዋቾቹን ውል አራዝሟል። በጣም ትኩረት የሳበው ዝውውር ሊዮኔል ሜሲ ለ21 ዓመታት ከቆየበት ባርሴሎና በነጻ ዝውውር ወደ ፓሪስ ሴንት ዠርሜን ያቀናበት ሆኗል። ያልተሳኩት ዝውውሮችስ? የ2021 የክረምት የዝውውር መስኮት ባልተሳኩ ስምምነቶችም ይታወሳል። ማንችስተር ሲቲ አብዛኛውን የዝውውር መስኮት የእንግሊዙን አምበል ሃሪ ኬንን ለማዘዋወር ጥረት ቢያደርግም አጥቂው በስፐርስ ለመቆየት ተስማምቷል። ሪያል ማድሪድ ምባፔን ለማስፈረም ሁለት ጊዜ ሞክሯል። ማድሪዶች ሁለት ጊዜ ከ100 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ ያቀረቡት ዋጋ በፓሪስ ሴንት ዠርሜን ውድቅ ተደርጓል። ቼልሲ ፈረንሳዊውን ተከላካይ ጁልስ ኩንዴን ለማስፈረም ቢፈልግም ሲቪያ ከመሸጫ ዋጋው 80 ሚሊዮን ዩሮ በታች ለመቀበል ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። አይንስሊ ማይትላንድ-ኒልስ ማህበራዊ ድር አምባውን ተጠቅሞ ከአርሰናል ለመልቀቅ ያደረገው ሙከራ አልተሳካም። የጄሴ ሊንጋርድ ወደ ዌስትሃም የታቀደው ዝውውር ባለመሳካቱ በማንችስተር ዩናይትድ ይቆያል። ዎልቭስም የሊሉን አማካይ ሬናቶ ሳንቼዝን ዘግይቶ ለማዘዋወር ያደረገውን ጥረት አቋርጧል።
https://www.bbc.com/amharic/news-58386455
3politics
ጀርመን ውስጥ መፈንቅለ መንግሥት ለመፈጸም አሲረዋል የተባሉ 25 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
ፖሊስ በመላዋ ጀርመን ባካሄደው ዘመቻ መፈንቅለ መንግሥት ለማካሄድ እያሴሩ ነበሩ የተባሉ 25 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ። የጀርመን መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት ከሆነ ቀኝ ዘመም ፖለቲከኞች እና የቀድሞ የጦር አባላት ሪችስታግ የተባለውን የአገሪቱን ምክር ቤት ሕንጻ በኃይል በመያዝ የመንግሥትን ሥልጣን ለመቆጣጠር አሲረው ነበር ተብሏል። የዚህ ያልተጠበቀ ሴራን በማቀናበር ሄንሪች 8ኛ የተባለው የ71 ዓመት ግለሰብ ዋነኛ ተዋናይ መሆኑም በስፋት ተዘግቧል። እንደ የጀርመን ዐቃቤ ሕግ ከሆነ ይህ ግለሰብ መፈንቅለ መንግሥት ሲያሴሩ ከነበሩ ሁለት ዋነኛ ግለሰቦች መካከል አንዱ መሆኑን ገልጿል። 23ቱ ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉት ጀርመን ካሏት 16 ግዛቶች በ11ዱ ውስጥ ነው። ሁለት ተጨማሪ ሰዎች ደግሞ በኦስትሪያ እና ጣሊያን ከሴራው ጋር በተገናኘ በቁጥጥር ስር ውለዋል። በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል የጽንፈኛው ሪችስበርገር ንቅናቄ አባላት ይገኙበታል። የዚህ ንቅናቄ አባላት ኃይል በተቀላቀለባቸው ጥቃቶች እና ከዘረኝነት ጋር በተያያዘ ድርጊቶች በጀርምን ፖሊስ ጥብቅ ክትትል ሲደረግባቸው የቆዩ ናቸው። በግምት 50 የሚሆኑ ሰዎች የዚህ ንቅናቄ አካል የነበሩ ሲሆን፤ አሁን ላይ ያለችውን የጀርመን አስተዳደርን አይቀበሉም። ዓላማቸውም ያለውን የጀርመን ሪፐብሊክ ሥርዓትን በማስወገድ እአአ 1871 ላይ የነበረውን የጀርመን አስተዳደርን መመለስን ይፈልጋሉ። “ለዚህ ቡድን እስካሁን መጠሪያ የለንም” ሲሉ የፌደራል መንግሥቱ ዐቃቤ ሕግ ቃል አቀባይ ተናግረዋል። የጀርመን የፍትሕ ሚኒስትር ማርኮ በሽማን ግዙፍ ፀረ-ሽብር ዘመቻ በመላው አገሪቱ እየተካሄደ እንደሆነ እና “ሕገ-መንግሥታዊ አካላት ላይ ጥቃት” ታቅዶ እንደነበረ በትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል። የአገሪቱ ዐቃቤ ሕግ እንደሚለው ከሆነ ቡድኑ ከእአአ 2021 ጀምሮ ባለፉት 12 ወራት መፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ ሲያሴር ቆይቷል። በጀርመን ጦር ውስጥ ልዩ የኮማንዶ አባላት የነበሩ ግለሰቦችም የመፈንቅለ መንግሥቱ ቁልፍ አካል መሆናቸው ተመላክቷል። መፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ ሲያሴሩ የነበሩት ግለሰቦች ዕቅዳቸውን ከተገበሩ በኋላ፣ ጀርመንን እንዴት ማስተዳደር እንዳለባቸው ዝርዝር ዕቅድ አውጥተው ጨርሰው እንደነበረ ተገልጿል። የቡድኑ አባላት ዓላማቸውን እውን ማድረግ የሚችሉት “ሰዎችን መግደልን ጨምሮ፣ ኃይል በተቀላቀለበት መንገድ ብቻ ነው” ብሏል የአገሪቱ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ።
ጀርመን ውስጥ መፈንቅለ መንግሥት ለመፈጸም አሲረዋል የተባሉ 25 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ ፖሊስ በመላዋ ጀርመን ባካሄደው ዘመቻ መፈንቅለ መንግሥት ለማካሄድ እያሴሩ ነበሩ የተባሉ 25 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ። የጀርመን መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት ከሆነ ቀኝ ዘመም ፖለቲከኞች እና የቀድሞ የጦር አባላት ሪችስታግ የተባለውን የአገሪቱን ምክር ቤት ሕንጻ በኃይል በመያዝ የመንግሥትን ሥልጣን ለመቆጣጠር አሲረው ነበር ተብሏል። የዚህ ያልተጠበቀ ሴራን በማቀናበር ሄንሪች 8ኛ የተባለው የ71 ዓመት ግለሰብ ዋነኛ ተዋናይ መሆኑም በስፋት ተዘግቧል። እንደ የጀርመን ዐቃቤ ሕግ ከሆነ ይህ ግለሰብ መፈንቅለ መንግሥት ሲያሴሩ ከነበሩ ሁለት ዋነኛ ግለሰቦች መካከል አንዱ መሆኑን ገልጿል። 23ቱ ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉት ጀርመን ካሏት 16 ግዛቶች በ11ዱ ውስጥ ነው። ሁለት ተጨማሪ ሰዎች ደግሞ በኦስትሪያ እና ጣሊያን ከሴራው ጋር በተገናኘ በቁጥጥር ስር ውለዋል። በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል የጽንፈኛው ሪችስበርገር ንቅናቄ አባላት ይገኙበታል። የዚህ ንቅናቄ አባላት ኃይል በተቀላቀለባቸው ጥቃቶች እና ከዘረኝነት ጋር በተያያዘ ድርጊቶች በጀርምን ፖሊስ ጥብቅ ክትትል ሲደረግባቸው የቆዩ ናቸው። በግምት 50 የሚሆኑ ሰዎች የዚህ ንቅናቄ አካል የነበሩ ሲሆን፤ አሁን ላይ ያለችውን የጀርመን አስተዳደርን አይቀበሉም። ዓላማቸውም ያለውን የጀርመን ሪፐብሊክ ሥርዓትን በማስወገድ እአአ 1871 ላይ የነበረውን የጀርመን አስተዳደርን መመለስን ይፈልጋሉ። “ለዚህ ቡድን እስካሁን መጠሪያ የለንም” ሲሉ የፌደራል መንግሥቱ ዐቃቤ ሕግ ቃል አቀባይ ተናግረዋል። የጀርመን የፍትሕ ሚኒስትር ማርኮ በሽማን ግዙፍ ፀረ-ሽብር ዘመቻ በመላው አገሪቱ እየተካሄደ እንደሆነ እና “ሕገ-መንግሥታዊ አካላት ላይ ጥቃት” ታቅዶ እንደነበረ በትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል። የአገሪቱ ዐቃቤ ሕግ እንደሚለው ከሆነ ቡድኑ ከእአአ 2021 ጀምሮ ባለፉት 12 ወራት መፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ ሲያሴር ቆይቷል። በጀርመን ጦር ውስጥ ልዩ የኮማንዶ አባላት የነበሩ ግለሰቦችም የመፈንቅለ መንግሥቱ ቁልፍ አካል መሆናቸው ተመላክቷል። መፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ ሲያሴሩ የነበሩት ግለሰቦች ዕቅዳቸውን ከተገበሩ በኋላ፣ ጀርመንን እንዴት ማስተዳደር እንዳለባቸው ዝርዝር ዕቅድ አውጥተው ጨርሰው እንደነበረ ተገልጿል። የቡድኑ አባላት ዓላማቸውን እውን ማድረግ የሚችሉት “ሰዎችን መግደልን ጨምሮ፣ ኃይል በተቀላቀለበት መንገድ ብቻ ነው” ብሏል የአገሪቱ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c87em2n78gpo
2health
ኮቪድ-19 ፡ የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚደንት ማይክ ፔንስ የኮቪድ-19 ክትባት ተከተቡ
የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚደንት ማይክ ፔንስ በቴሌቪዥን የቀጥታ ሥርጭት እየታዩ የኮሮናቫይረስ ክትባት ተከተቡ። ምክትል ፕሬዚደንቱ ለተመልካቾችና ለዶክተሮች "ምንም ነገር አልተሰማኝም" ብለዋል። ማይክ ፔንስ በቀጥታ ሥርጭት እየታዩ የመከተባቸው ዓላማ የክትባቱን ደህንነትና ውጤታማነት ለማስተዋወቅና በአሜሪካ ሕዝቦች ዘንድ መተማመንን ለመፍጠር እንደሆነ ዋይት ሃውስ አስታውቋል። በዚህ በዋይት ሃውስ በተሰናዳው ዝግጅት የምክትል ፕሬዚደንቱ ባለቤት እና የጤና ጥበቃ ጠቅላይ ኃላፊ [ሰርጅን ጀነራል] ጀሮሜ አዳምስም ክትባቱን ወስደዋል። የ61 ዓመቱ ማይክ ፔንስ ከባለቤታቸው ካረን እና አዳምስ ጋር የመጀመሪያዎቹን ሁለት ዶዝ የፋይዘር/ ባዮንቴክ ክትባት የወሰዱት ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ነው። አሜሪካ 95 በመቶ በሽታውን ይከላከላል የተባለውን የፋይዘር/ ባዮንቴክ ክትባት መከተብ የጀመረችው ባሳለፍነው ሰኞ ነበር። የመጀመሪያ ሦስት ሚሊየን ዶዝ [መጠን] ክትባቶችም በ50 የአገሪቷ ግዛቶች ተሰራጭተዋል። ጥቅምት ወር ላይ በኮሮናቫይረስ ተይዘው በሆስፒታል ሕክምና ከተደረገላቸው በኋላ ያገገሙት ማይክ ፔንስ፤ ክትባቱን ለመውሰድ ጊዜ አስቀምጠው እንዳልነበርና በተገቢው ጊዜ ግን ለመከተብ በጉጉት ሲጠባበቁ እንደነበር ተናግረዋል። ዘጋቢዎች እንደሚሉት በርካታ ደጋፊዎቻቸው ስለክትባቱ ደህንነትና ውጤታማነት ጥርጣሬ አላቸው። ለኮቪድ-19 ተጋላጭ ከሆኑት የሚመደቡት የ78 ዓመቱ ተመራጩ ፕሬዚደንት ጆ ባይደንም በሚቀጥለው ሳምንት ይከተባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ጆ ባይደን በመጭው በፈረንጆቹ ጥር 20 ወር በዋይት ሃውስ ሥራቸውን ሲጀምሩ በመጀመሪያዎቹ 100 ቀናት፤ 100 ሚሊየን የአሜሪካ ሕዝቦችን ለመከተብ ግብ አስቀምጠዋል። ይህ ቁጥር የአሜሪካ ሕዝብ አንድ ሦስተኛ እንደሆነ ይገመታል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በሞደርና የሚመረተው ሁለተኛው ክትባት በባለሙያዎች ተቀባይነት ካገኘ በኋላ ለድንገተኛ ጊዜ እንዲውል ፈቃድ ለማግኘት እየተቃረበ ነው። በአሜሪካ ከ310 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን፤ በዓለማችን ከፍተኛ በቫይረሱ የተያዙ እና የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከተመዘገበባቸው አገራት ግንባር ቀደሟ ናት።
ኮቪድ-19 ፡ የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚደንት ማይክ ፔንስ የኮቪድ-19 ክትባት ተከተቡ የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚደንት ማይክ ፔንስ በቴሌቪዥን የቀጥታ ሥርጭት እየታዩ የኮሮናቫይረስ ክትባት ተከተቡ። ምክትል ፕሬዚደንቱ ለተመልካቾችና ለዶክተሮች "ምንም ነገር አልተሰማኝም" ብለዋል። ማይክ ፔንስ በቀጥታ ሥርጭት እየታዩ የመከተባቸው ዓላማ የክትባቱን ደህንነትና ውጤታማነት ለማስተዋወቅና በአሜሪካ ሕዝቦች ዘንድ መተማመንን ለመፍጠር እንደሆነ ዋይት ሃውስ አስታውቋል። በዚህ በዋይት ሃውስ በተሰናዳው ዝግጅት የምክትል ፕሬዚደንቱ ባለቤት እና የጤና ጥበቃ ጠቅላይ ኃላፊ [ሰርጅን ጀነራል] ጀሮሜ አዳምስም ክትባቱን ወስደዋል። የ61 ዓመቱ ማይክ ፔንስ ከባለቤታቸው ካረን እና አዳምስ ጋር የመጀመሪያዎቹን ሁለት ዶዝ የፋይዘር/ ባዮንቴክ ክትባት የወሰዱት ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ነው። አሜሪካ 95 በመቶ በሽታውን ይከላከላል የተባለውን የፋይዘር/ ባዮንቴክ ክትባት መከተብ የጀመረችው ባሳለፍነው ሰኞ ነበር። የመጀመሪያ ሦስት ሚሊየን ዶዝ [መጠን] ክትባቶችም በ50 የአገሪቷ ግዛቶች ተሰራጭተዋል። ጥቅምት ወር ላይ በኮሮናቫይረስ ተይዘው በሆስፒታል ሕክምና ከተደረገላቸው በኋላ ያገገሙት ማይክ ፔንስ፤ ክትባቱን ለመውሰድ ጊዜ አስቀምጠው እንዳልነበርና በተገቢው ጊዜ ግን ለመከተብ በጉጉት ሲጠባበቁ እንደነበር ተናግረዋል። ዘጋቢዎች እንደሚሉት በርካታ ደጋፊዎቻቸው ስለክትባቱ ደህንነትና ውጤታማነት ጥርጣሬ አላቸው። ለኮቪድ-19 ተጋላጭ ከሆኑት የሚመደቡት የ78 ዓመቱ ተመራጩ ፕሬዚደንት ጆ ባይደንም በሚቀጥለው ሳምንት ይከተባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ጆ ባይደን በመጭው በፈረንጆቹ ጥር 20 ወር በዋይት ሃውስ ሥራቸውን ሲጀምሩ በመጀመሪያዎቹ 100 ቀናት፤ 100 ሚሊየን የአሜሪካ ሕዝቦችን ለመከተብ ግብ አስቀምጠዋል። ይህ ቁጥር የአሜሪካ ሕዝብ አንድ ሦስተኛ እንደሆነ ይገመታል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በሞደርና የሚመረተው ሁለተኛው ክትባት በባለሙያዎች ተቀባይነት ካገኘ በኋላ ለድንገተኛ ጊዜ እንዲውል ፈቃድ ለማግኘት እየተቃረበ ነው። በአሜሪካ ከ310 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን፤ በዓለማችን ከፍተኛ በቫይረሱ የተያዙ እና የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከተመዘገበባቸው አገራት ግንባር ቀደሟ ናት።
https://www.bbc.com/amharic/news-55365780
5sports
ሊዮኔል ሜሲ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ ዋንጫ አነሳ
ሊዮኔል ሜሲ በኮፓ አሜሪካ የፍፃሜ ፍልሚያ ሃገሩ አርጀንቲና ብራዚልን መርታቷን ተከትሎ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ ዋንጫ ማንሳት ችሏል። ሁለቱ ሃገራት በግዙፉ ሪዮ ማራካኛ ስታዲዬም የፍፃሜውን ጨዋታ አድርገው አርጀንቲና በዲ ማሪያ ጎል አንድ ለባዳ ረትታለች። የ34 ዓመቱ ሜሲ የጨዋታውን ፍፃሜ የሚያበስረው ፊሽካ ሲነፋ በደስታ መሬታ ላይ ከመውደቁ የቡድን አጋሮቹ እየሮጡ ሲከቡት ይታያል። ሜሲ ሃገሩ አርጀንቲና ዋንጫ እንድታገኝ 10 ጊዜ ትላልቅ ውድድሮች ላይ ተሳትፎ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳካለት ዘንድሮ ነው። የስድስት ጊዜ የዓለም ኮከብ ሽልማት ባለቤቱ ሜሲ ሃገሩ አርጀንቲያ ከ28 ዓመታት በኋላ ዋንጫ እንድታነሳም አስችሏል። አንሄል ዲ ማሪያ የማሸነፈያ ጎል በማስቆጠር የጨዋታው ኮከብ ሆኖ ተመርጧል። ሜሲ በፍፃሜው ጨዋታ ጎልና መረብ የሚያገናኝበት አንድ ወርቃማ ዕድል አግኝቶ ሳይጠቀምበት ቀርቷል። የውድድሩ አዘጋጅ የሆነችው የባለፈው ኮፓ አሜሪካ ዋንጫ ባለድል ብራዚል በሜዳዋ ዋንጫ የማንሳት ሕልሟ ሳያሳካላት ቀርቷል። በሜሲ ተቃራኒ 10 ቁጥር ለብሶ የሚጫወተው ኔይማር በጨዋታው ፍፃሜ በሐዘን አንገቱን ሲደፋ ታይቷል። ኔይማር፤ ብራዚል ያለፈውን የኮፓ አሜሪካ ዋንጫ ስታነሳ በጉዳት ምክንያት የቡድኑ አባል መሆን አልቻለም ነበር። ባርሴሎና እያሉ ለአራት ዓመት አብረው የተጫወቱት ኔይማርና ሜሲ ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ ረዘም ላለ ደቂቃ ተቃቅፈው ታይተዋል። በኮቪድ-19 ምክንያት ጨዋታውን መታደም የቻሉት 7 ሺህ ሰዎች ብቻ ቢሆንም በውድድሩ ለጀመሪያ ጊዜ ነው ተመልካቾች ገብተው መታደም የቻሉት። በወረርሽኙ ምክንያት በአንድ ዓመት የዘገየው የኮፓ አሜሪካ ፍልሚያ አርጀንቲናና ኮሎምቢያ እንዲያዘጋጁት ነበር የታሰበው። ነገር ግን ከሁለት ዓመት በፊት አዘጋጇ ብራዚል ትሁን ተብሎ ቢወሰንም በኮሮናቫይረስ ምክንያት ውሳኔው ትክክል አይደለም የሚሉ ቅሬታዎች ቀርበውበት ነበር። ሜሲ በአራት ዓለም ዋንጫዎችና በስድስት ኮፓ አሜሪካ ውድድሮች ሃገሩ አርጀንቲናን ወክሎ ተጫውቷል። 10 የላሊ ጋ ዋንጫ፣ 4 ጊዜ የቻምፒየንስ ሊግ ባለድል እና የስድስት ባለንደኦር ባለቤት የሆነው ሜሲ በዓለም አቀፍ መድረክ ምንም ድል አላገኘም የሚል ትችት ይቀርብበት ነበር። ከአርጀንቲና ጋር ድል ማጣጣም ያልቻለው ሜሲ በአንድ ወቅት ራሱን ከቡድኑ ማግለሉን አስታውቆ መልሶ መጫወት መጀመሩ ይታወሳል። ከባርሴሎና ጋር ያለውን ውል ያጠናቀቀው ሜሲ ቀጣይ መዳረሻው የት ነው የሚሆነው የሚለው አሁንም አነጋጋሪ ሆኗል። ኳታር በምታዘጋጀው የ2022 ዓለም ዋንጫ ላይ ይሳተፋል አይሳተፍም የሚለውም ሌላኛው አነጋጋሪ ጉዳይ ነው።
ሊዮኔል ሜሲ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ ዋንጫ አነሳ ሊዮኔል ሜሲ በኮፓ አሜሪካ የፍፃሜ ፍልሚያ ሃገሩ አርጀንቲና ብራዚልን መርታቷን ተከትሎ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ ዋንጫ ማንሳት ችሏል። ሁለቱ ሃገራት በግዙፉ ሪዮ ማራካኛ ስታዲዬም የፍፃሜውን ጨዋታ አድርገው አርጀንቲና በዲ ማሪያ ጎል አንድ ለባዳ ረትታለች። የ34 ዓመቱ ሜሲ የጨዋታውን ፍፃሜ የሚያበስረው ፊሽካ ሲነፋ በደስታ መሬታ ላይ ከመውደቁ የቡድን አጋሮቹ እየሮጡ ሲከቡት ይታያል። ሜሲ ሃገሩ አርጀንቲና ዋንጫ እንድታገኝ 10 ጊዜ ትላልቅ ውድድሮች ላይ ተሳትፎ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳካለት ዘንድሮ ነው። የስድስት ጊዜ የዓለም ኮከብ ሽልማት ባለቤቱ ሜሲ ሃገሩ አርጀንቲያ ከ28 ዓመታት በኋላ ዋንጫ እንድታነሳም አስችሏል። አንሄል ዲ ማሪያ የማሸነፈያ ጎል በማስቆጠር የጨዋታው ኮከብ ሆኖ ተመርጧል። ሜሲ በፍፃሜው ጨዋታ ጎልና መረብ የሚያገናኝበት አንድ ወርቃማ ዕድል አግኝቶ ሳይጠቀምበት ቀርቷል። የውድድሩ አዘጋጅ የሆነችው የባለፈው ኮፓ አሜሪካ ዋንጫ ባለድል ብራዚል በሜዳዋ ዋንጫ የማንሳት ሕልሟ ሳያሳካላት ቀርቷል። በሜሲ ተቃራኒ 10 ቁጥር ለብሶ የሚጫወተው ኔይማር በጨዋታው ፍፃሜ በሐዘን አንገቱን ሲደፋ ታይቷል። ኔይማር፤ ብራዚል ያለፈውን የኮፓ አሜሪካ ዋንጫ ስታነሳ በጉዳት ምክንያት የቡድኑ አባል መሆን አልቻለም ነበር። ባርሴሎና እያሉ ለአራት ዓመት አብረው የተጫወቱት ኔይማርና ሜሲ ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ ረዘም ላለ ደቂቃ ተቃቅፈው ታይተዋል። በኮቪድ-19 ምክንያት ጨዋታውን መታደም የቻሉት 7 ሺህ ሰዎች ብቻ ቢሆንም በውድድሩ ለጀመሪያ ጊዜ ነው ተመልካቾች ገብተው መታደም የቻሉት። በወረርሽኙ ምክንያት በአንድ ዓመት የዘገየው የኮፓ አሜሪካ ፍልሚያ አርጀንቲናና ኮሎምቢያ እንዲያዘጋጁት ነበር የታሰበው። ነገር ግን ከሁለት ዓመት በፊት አዘጋጇ ብራዚል ትሁን ተብሎ ቢወሰንም በኮሮናቫይረስ ምክንያት ውሳኔው ትክክል አይደለም የሚሉ ቅሬታዎች ቀርበውበት ነበር። ሜሲ በአራት ዓለም ዋንጫዎችና በስድስት ኮፓ አሜሪካ ውድድሮች ሃገሩ አርጀንቲናን ወክሎ ተጫውቷል። 10 የላሊ ጋ ዋንጫ፣ 4 ጊዜ የቻምፒየንስ ሊግ ባለድል እና የስድስት ባለንደኦር ባለቤት የሆነው ሜሲ በዓለም አቀፍ መድረክ ምንም ድል አላገኘም የሚል ትችት ይቀርብበት ነበር። ከአርጀንቲና ጋር ድል ማጣጣም ያልቻለው ሜሲ በአንድ ወቅት ራሱን ከቡድኑ ማግለሉን አስታውቆ መልሶ መጫወት መጀመሩ ይታወሳል። ከባርሴሎና ጋር ያለውን ውል ያጠናቀቀው ሜሲ ቀጣይ መዳረሻው የት ነው የሚሆነው የሚለው አሁንም አነጋጋሪ ሆኗል። ኳታር በምታዘጋጀው የ2022 ዓለም ዋንጫ ላይ ይሳተፋል አይሳተፍም የሚለውም ሌላኛው አነጋጋሪ ጉዳይ ነው።
https://www.bbc.com/amharic/news-57794201
2health
ኮቪድ-19፡ የኮሮናቫይረስ ክትባቶች ቅይጥ ቫይረሱን በጥሩ መንገድ መከላከል እንደሚችል ጥናት አመለከተ
ለመጀመሪያውም ይሁን ለሁለተኛው ዙር የኮሮናቫይረስ ክትባት የተለያዩ ምርቶችን ቀላቅሎ መጠቀም ቫይረሱን በሚገባ መከላከል እንደሚችል በዩናይትድ ኪንግደም የተደረገ አንድ ጥናት አመለከተ፡፡ የፋይዘርና የአስትራዜኒካ ክትባቶችን በተለያየ ቅደም ተከተል በመስጠት የተደረገው ሙከራ ውጤታማ ነው ተብሏል። በሁለቱም ቅደም ተከተል የተደረገው ሙከራ በጥሩ ሁኔታ ሰርቷል የተባለ ሲሆን በሽታ የመከላከል ሥርዓትን ማሻሻላቸውም ተጠቅሷል፡፡ ታዲያ ይህ ግኝት አዳዲስ የክትባት አይነቶች እንዲመረቱ በር የሚከፍት መሆኑን ባለሙያዎች አስረድተዋል። የሙከራ ውጤቱም ቀደም ሲል ሁለት ዙር የአስትራዜኒካ ክትባት በክረምት ወቅት የወሰዱ ሰዎች ተጨማሪ ክትባት ቢወስዱ ጠንካራ የመከላከል አቅማቸውን ሊያዳብሩ እንደሚችሉ ፍንጭ ተሰጥቷል፡፡ በዩናይትድ ኪንግደም የታወቁት የሕክምና ባለሙያ ፕሮፌሰር ጆናታን ቫንታም በዩኬ ውስጥ አሁን እየተሰጠ ያለውንና ውጤታማ የሆነውን ተመሳሳይ [ያልተቀላቀለ] ክትባትን የማዳረስ መርሃ ግብርን ለመለወጥ ምንም ምክንያት የለም ያሉ ሲሆን፤ ክትባቶቹ በጥሩ አቅርቦት ላይ ያሉ እና ሕይወትን የሚያድኑ ናቸው ሲሉ ገልጸዋል። ሆኖም ለወደፊቱ አንዳች ነገር ለሆን ይችላል የሚሉት ፕሮፌሰሩ "ክትባቶቹን ቀይጦ መጠቀም መርሃ ግብሩን የበለጠ እንደጊዜው ለማስኬድ እንዲሁም የክትባት ምርት ሂደት ላይ ያሉ አገራትን ለመደገፍ እና የክትባት አቅርቦት ችግር ያጋጠማቸው አገራትን ለመርዳት ይግዛል" ብለዋል። የተለያዩ አገራት ክትባቶችን ቀላቅለው መጠቀም ጀምረዋል። ስፔን እና ጀርመን የአስትራዜኔካ የመጀመሪያ ዙር ክትባት ለወሰዱ ታዳጊዎች ፋይዘር ወይም ሞዴርና የተሰኙ ክትባቶችን ለሁለተኛ ዙር እየሰጡ ነው። ይሁን እንጅ ክትባቶችን ቀላቅለው የወሰዱ ሰዎች አልፎ አልፎ የደም መርጋት ችግርን እንዳጋጠማቸው ተገልጿል።
ኮቪድ-19፡ የኮሮናቫይረስ ክትባቶች ቅይጥ ቫይረሱን በጥሩ መንገድ መከላከል እንደሚችል ጥናት አመለከተ ለመጀመሪያውም ይሁን ለሁለተኛው ዙር የኮሮናቫይረስ ክትባት የተለያዩ ምርቶችን ቀላቅሎ መጠቀም ቫይረሱን በሚገባ መከላከል እንደሚችል በዩናይትድ ኪንግደም የተደረገ አንድ ጥናት አመለከተ፡፡ የፋይዘርና የአስትራዜኒካ ክትባቶችን በተለያየ ቅደም ተከተል በመስጠት የተደረገው ሙከራ ውጤታማ ነው ተብሏል። በሁለቱም ቅደም ተከተል የተደረገው ሙከራ በጥሩ ሁኔታ ሰርቷል የተባለ ሲሆን በሽታ የመከላከል ሥርዓትን ማሻሻላቸውም ተጠቅሷል፡፡ ታዲያ ይህ ግኝት አዳዲስ የክትባት አይነቶች እንዲመረቱ በር የሚከፍት መሆኑን ባለሙያዎች አስረድተዋል። የሙከራ ውጤቱም ቀደም ሲል ሁለት ዙር የአስትራዜኒካ ክትባት በክረምት ወቅት የወሰዱ ሰዎች ተጨማሪ ክትባት ቢወስዱ ጠንካራ የመከላከል አቅማቸውን ሊያዳብሩ እንደሚችሉ ፍንጭ ተሰጥቷል፡፡ በዩናይትድ ኪንግደም የታወቁት የሕክምና ባለሙያ ፕሮፌሰር ጆናታን ቫንታም በዩኬ ውስጥ አሁን እየተሰጠ ያለውንና ውጤታማ የሆነውን ተመሳሳይ [ያልተቀላቀለ] ክትባትን የማዳረስ መርሃ ግብርን ለመለወጥ ምንም ምክንያት የለም ያሉ ሲሆን፤ ክትባቶቹ በጥሩ አቅርቦት ላይ ያሉ እና ሕይወትን የሚያድኑ ናቸው ሲሉ ገልጸዋል። ሆኖም ለወደፊቱ አንዳች ነገር ለሆን ይችላል የሚሉት ፕሮፌሰሩ "ክትባቶቹን ቀይጦ መጠቀም መርሃ ግብሩን የበለጠ እንደጊዜው ለማስኬድ እንዲሁም የክትባት ምርት ሂደት ላይ ያሉ አገራትን ለመደገፍ እና የክትባት አቅርቦት ችግር ያጋጠማቸው አገራትን ለመርዳት ይግዛል" ብለዋል። የተለያዩ አገራት ክትባቶችን ቀላቅለው መጠቀም ጀምረዋል። ስፔን እና ጀርመን የአስትራዜኔካ የመጀመሪያ ዙር ክትባት ለወሰዱ ታዳጊዎች ፋይዘር ወይም ሞዴርና የተሰኙ ክትባቶችን ለሁለተኛ ዙር እየሰጡ ነው። ይሁን እንጅ ክትባቶችን ቀላቅለው የወሰዱ ሰዎች አልፎ አልፎ የደም መርጋት ችግርን እንዳጋጠማቸው ተገልጿል።
https://www.bbc.com/amharic/news-57648418
5sports
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የቀጣይ ቀናት ጨዋታዎች ግምት
በምንም ነገር ላይ እርግጠኛ መሆን አይቻልም ይባላል። ማንቸስተር ዩናይትድስ በሊቨርፑል መሸነፉ እርግጥ ነው? “ከአስሩ የሊጉ ጨዋታዎች ብቸኛው በእርግጠኝነት የምገምተው ጨዋታ ነው” ይላል የቢቢሲው ክሪስ ሱቶን። “ማንቸስትር ስንት ጎል ያስተናግዳል? የሚለው ነው ጥያቄው። ከድጡ ወደ ማጡ እንደሚሆንባቸው እርግጠኛ ነኝ” ይላል። ሱቶን ከሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ ውጪም የሌሎችንም ጨዋታዎች ግምት አስቀምጧል። ቶተንሃም ከ ዎልቭስ ባለፈው ሳምንት ቶተንሃም ከቼልሲ ጋር በነበረው ጨዋታ ባሳየው አቋም ተበሳጭቻለሁ። ዎልቭሶች ፖርቹጋላዊውን ጎንካሎ ጉዋዴዝን በማስፈርም የፊት መስመራቸውን አጠናክረዋል። ዎልቭሶች ባለፈው ዓመት የማጥቃት መስመራቸው ስስ መሆኑ ታይቷል። ቶተንሃም ተመሳሳይ ችግር የለበትም። ግምት፡ 3 - 1 ክሪስታል ፓላስ ከ አስቶን ቪላ ክሪስታል ፓላስ ሰኞ ዕለት ከሊቨርፑል ጋር ድንቅ ፉክክር አድርጓል። ከውጤቱም ጥሩ መነሳሳት ያገኛሉ ብዬ አስባለሁ። ቪላም ከኤቨርተን ጋር ከነበረው ጨዋታ ጥሩ መነቃቃት ያገኛል ብዬ አስባለሁ። ይህ ለመገመት ከባድ የሆነ ጨዋታ ነው። ግምት፡ 1 - 1 ኤቨርተን ከ ኖቲንግሃም ፎረስት ኖቲንግሃም ፎረስት ባለፈው ሳምንት ዌስት ሃምን በማሸነፍ ትልቅ ውጤት አስመዘግቧል። ኤቨርተንም የውድድር ዓመቱን በጥሩ መልኩ ለማስኬድ ተመሳሳይ ድል ይፈልጋል። ቡድኑ ይህ ነው የሚባል ጥሩ አጥቂ የለውም። በዚህ ጨዋታ ግን ውጤቱ ይቀናቸዋል ብዬ እገምታለሁ። ግምት፡ 2 - 0 ፉልሃም ከ ብሬንትፎርድ የብሬንትፎርድ ጉዞ ተመችቶኛል። ባለፈው ሳምንት 3 ለ 0 ማንቸስተር ዩናይትድን ያሸንፋሉ ብዩ 4 ለ 0 አሸንፈዋል። ፉልሃም ደግሞ ከሊቨርፑል ነጥብ በተጋራበት መንገድ ይጫወታል ብዬ አስባለሁ። ከፍተኛ ፉክክር ያለው ጨዋታ ይሆናል። ፉልሃም ሁለቱንም የመክፈቻ ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል። የዚህ ሳምንቱም ተመሳሳይ ይሆናል። ግምት፡ 1 - 1 ሌስተር ከ ሳውዝሃምፕተን የሳውዝሃምፕተኑ አለቃ ራልፍ ሃሰንሃልት ጫና ውስጥ ወደቁ ይመስላል። በቅድመ ውድድር ወቅት በሦስት ተከላካይ ቢጫወቱም ሊጉ ሲጀመር ወደ አራት ተከላካይ ተመልሰዋል። ሌስተሮች በተከላካይ መስመር ላይ ክፍተት ቢኖርባቸውም ወደ ፊት ሲሄዱ ግን ጥሩ ናቸው። በዚህ ጨዋታ ጎል የሚቆጠር ሲሆን የብሬንዳን ሮጀርስ ቡድን እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ። ግምት፡ 2 - 1 በርንማውዝ ከ አርሴናል አርሴናል ድንቅ አጀማመር ያደረገ ሲሆን፣ ጋብርኤል ጂሰስም ልዩነት ፈጣሪ መሆን ችሏል። ስለዝውውሩ ብዙ የተባለ ሲሆን እሱም ማስመከር ችሏል። በዚህ ጨዋታ ግን ጎል አያስቆጥርም። በመድፈኞቹ አጀማመር ተደንቀን ለዋንጫ ልንገምታቸው ይገባል የሚል ግምት የለኝም። በርንማውዝ ባለፈው ሳምንት በማንቸስትር ሲተቲ ተሸንፏል። ግምት፡ 0 - 2 ሊድስ ከ ቼልሲ ሊድስ ከሳውዛሃምፕተን ጋር በነበረው ጨዋታ ከ2 ለ 0 ከመምራት አቻ መለያየታቸው የሚያስቆጭ ነው። የቼልሲ የፊት መስመር አሁንም ያልተመለሰ ጥያቄ አለበት። ከቶትንሃም ጋር በነበረው ጨዋታ ግን ድንቅ ነበሩ። ኤላንድ ሮድ ላይ በተተመሳሳይ መንገድ ከተጫወቱ ሦስት ነጥቡን ያሳካሉ። ግምት፡ 0 - 3 ዌስት ሃም ከ ብራይተን ዌስት ሃሞች የመጀመሪያዎቹን ሁለት ጨዋታዎች ቢሸነፉም በቅድመ ውድድር ዘመን ከደረሰባቸው የጉዳት መጠን አንጻር ስጋት ሊኖር አይገባም። ውጤቱን በቅርቡ እንደሚያሻሽሉ ጥርጥር የለኝም። ብራይተንን ባለፉት አስር ጨዋታዎች ማሸነፍ አለመቻላቸውን ግን አሁንም አይቀይሩትም። የግረሃም ፖተር ቡድን በደንብ የተቀናጀ ሲሆን ነጥብ እንደሚያገኝም እገምታለሁ። ግምት፡ 1 - 1 ኒውካስል ከ ማንቸስትር ሲቲ በኒውካስል ሜዳ ድንቅ ድባብ እንደሚፈጠር እና አንድ ወይም ሁለት ዕድል እንደሚፈጥሩ አስባለሁ። ጨዋታው በማንቸስተር ሲቲ የበላይነት እንደሚጠናቀቅ እገምታለሁ። ኤርሊንግ ሃላንድ በበርንማውዝ ጨዋታ ተሳትፎው ዝቅ ያለ ነው ቢባልም ለኢካይ ጉዶዋን ጎል ማስቆጠር ዕድል አመቻችቷል። ኒውካስሎች አጥቂውን ላይ በማተኮር ለመቆጣጠር ካሰቡ ለሌሎች ክፍተት ሊፈጥርላቸው ይችላል። ግምት፡ 1 - 3 ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ሊቨርፑል ማንቸስተሮች ይህንን ጨዋታ ካሸነፉ ከሊቨርፑል በላይ ይቀመጣሉ። ግን አይሳካላቸውም። ኤሪክ ቴን ሃግ ያላቸውን ቡድን እንዴት እንደሚቀይሩ አላውቅም። ሊቨርፑል ካደረገው ደካማ አጀማመር ሌላ የዳርዊን ኑኔዝ ቅጣት እና ጉዳቶች እንቅፋት ይሆኑባቸዋል። ምንም ቢሆን ግን የየርገን ክሎፕ ቡድን የበላይነቱን ይይዛል። ግምት፡ 1 - 5
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የቀጣይ ቀናት ጨዋታዎች ግምት በምንም ነገር ላይ እርግጠኛ መሆን አይቻልም ይባላል። ማንቸስተር ዩናይትድስ በሊቨርፑል መሸነፉ እርግጥ ነው? “ከአስሩ የሊጉ ጨዋታዎች ብቸኛው በእርግጠኝነት የምገምተው ጨዋታ ነው” ይላል የቢቢሲው ክሪስ ሱቶን። “ማንቸስትር ስንት ጎል ያስተናግዳል? የሚለው ነው ጥያቄው። ከድጡ ወደ ማጡ እንደሚሆንባቸው እርግጠኛ ነኝ” ይላል። ሱቶን ከሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ ውጪም የሌሎችንም ጨዋታዎች ግምት አስቀምጧል። ቶተንሃም ከ ዎልቭስ ባለፈው ሳምንት ቶተንሃም ከቼልሲ ጋር በነበረው ጨዋታ ባሳየው አቋም ተበሳጭቻለሁ። ዎልቭሶች ፖርቹጋላዊውን ጎንካሎ ጉዋዴዝን በማስፈርም የፊት መስመራቸውን አጠናክረዋል። ዎልቭሶች ባለፈው ዓመት የማጥቃት መስመራቸው ስስ መሆኑ ታይቷል። ቶተንሃም ተመሳሳይ ችግር የለበትም። ግምት፡ 3 - 1 ክሪስታል ፓላስ ከ አስቶን ቪላ ክሪስታል ፓላስ ሰኞ ዕለት ከሊቨርፑል ጋር ድንቅ ፉክክር አድርጓል። ከውጤቱም ጥሩ መነሳሳት ያገኛሉ ብዬ አስባለሁ። ቪላም ከኤቨርተን ጋር ከነበረው ጨዋታ ጥሩ መነቃቃት ያገኛል ብዬ አስባለሁ። ይህ ለመገመት ከባድ የሆነ ጨዋታ ነው። ግምት፡ 1 - 1 ኤቨርተን ከ ኖቲንግሃም ፎረስት ኖቲንግሃም ፎረስት ባለፈው ሳምንት ዌስት ሃምን በማሸነፍ ትልቅ ውጤት አስመዘግቧል። ኤቨርተንም የውድድር ዓመቱን በጥሩ መልኩ ለማስኬድ ተመሳሳይ ድል ይፈልጋል። ቡድኑ ይህ ነው የሚባል ጥሩ አጥቂ የለውም። በዚህ ጨዋታ ግን ውጤቱ ይቀናቸዋል ብዬ እገምታለሁ። ግምት፡ 2 - 0 ፉልሃም ከ ብሬንትፎርድ የብሬንትፎርድ ጉዞ ተመችቶኛል። ባለፈው ሳምንት 3 ለ 0 ማንቸስተር ዩናይትድን ያሸንፋሉ ብዩ 4 ለ 0 አሸንፈዋል። ፉልሃም ደግሞ ከሊቨርፑል ነጥብ በተጋራበት መንገድ ይጫወታል ብዬ አስባለሁ። ከፍተኛ ፉክክር ያለው ጨዋታ ይሆናል። ፉልሃም ሁለቱንም የመክፈቻ ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል። የዚህ ሳምንቱም ተመሳሳይ ይሆናል። ግምት፡ 1 - 1 ሌስተር ከ ሳውዝሃምፕተን የሳውዝሃምፕተኑ አለቃ ራልፍ ሃሰንሃልት ጫና ውስጥ ወደቁ ይመስላል። በቅድመ ውድድር ወቅት በሦስት ተከላካይ ቢጫወቱም ሊጉ ሲጀመር ወደ አራት ተከላካይ ተመልሰዋል። ሌስተሮች በተከላካይ መስመር ላይ ክፍተት ቢኖርባቸውም ወደ ፊት ሲሄዱ ግን ጥሩ ናቸው። በዚህ ጨዋታ ጎል የሚቆጠር ሲሆን የብሬንዳን ሮጀርስ ቡድን እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ። ግምት፡ 2 - 1 በርንማውዝ ከ አርሴናል አርሴናል ድንቅ አጀማመር ያደረገ ሲሆን፣ ጋብርኤል ጂሰስም ልዩነት ፈጣሪ መሆን ችሏል። ስለዝውውሩ ብዙ የተባለ ሲሆን እሱም ማስመከር ችሏል። በዚህ ጨዋታ ግን ጎል አያስቆጥርም። በመድፈኞቹ አጀማመር ተደንቀን ለዋንጫ ልንገምታቸው ይገባል የሚል ግምት የለኝም። በርንማውዝ ባለፈው ሳምንት በማንቸስትር ሲተቲ ተሸንፏል። ግምት፡ 0 - 2 ሊድስ ከ ቼልሲ ሊድስ ከሳውዛሃምፕተን ጋር በነበረው ጨዋታ ከ2 ለ 0 ከመምራት አቻ መለያየታቸው የሚያስቆጭ ነው። የቼልሲ የፊት መስመር አሁንም ያልተመለሰ ጥያቄ አለበት። ከቶትንሃም ጋር በነበረው ጨዋታ ግን ድንቅ ነበሩ። ኤላንድ ሮድ ላይ በተተመሳሳይ መንገድ ከተጫወቱ ሦስት ነጥቡን ያሳካሉ። ግምት፡ 0 - 3 ዌስት ሃም ከ ብራይተን ዌስት ሃሞች የመጀመሪያዎቹን ሁለት ጨዋታዎች ቢሸነፉም በቅድመ ውድድር ዘመን ከደረሰባቸው የጉዳት መጠን አንጻር ስጋት ሊኖር አይገባም። ውጤቱን በቅርቡ እንደሚያሻሽሉ ጥርጥር የለኝም። ብራይተንን ባለፉት አስር ጨዋታዎች ማሸነፍ አለመቻላቸውን ግን አሁንም አይቀይሩትም። የግረሃም ፖተር ቡድን በደንብ የተቀናጀ ሲሆን ነጥብ እንደሚያገኝም እገምታለሁ። ግምት፡ 1 - 1 ኒውካስል ከ ማንቸስትር ሲቲ በኒውካስል ሜዳ ድንቅ ድባብ እንደሚፈጠር እና አንድ ወይም ሁለት ዕድል እንደሚፈጥሩ አስባለሁ። ጨዋታው በማንቸስተር ሲቲ የበላይነት እንደሚጠናቀቅ እገምታለሁ። ኤርሊንግ ሃላንድ በበርንማውዝ ጨዋታ ተሳትፎው ዝቅ ያለ ነው ቢባልም ለኢካይ ጉዶዋን ጎል ማስቆጠር ዕድል አመቻችቷል። ኒውካስሎች አጥቂውን ላይ በማተኮር ለመቆጣጠር ካሰቡ ለሌሎች ክፍተት ሊፈጥርላቸው ይችላል። ግምት፡ 1 - 3 ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ሊቨርፑል ማንቸስተሮች ይህንን ጨዋታ ካሸነፉ ከሊቨርፑል በላይ ይቀመጣሉ። ግን አይሳካላቸውም። ኤሪክ ቴን ሃግ ያላቸውን ቡድን እንዴት እንደሚቀይሩ አላውቅም። ሊቨርፑል ካደረገው ደካማ አጀማመር ሌላ የዳርዊን ኑኔዝ ቅጣት እና ጉዳቶች እንቅፋት ይሆኑባቸዋል። ምንም ቢሆን ግን የየርገን ክሎፕ ቡድን የበላይነቱን ይይዛል። ግምት፡ 1 - 5
https://www.bbc.com/amharic/articles/c51dr554ny4o
2health
ሕክምና ፡ ቁመት ለመጨመር ምን አይነት ቀዶ ሕክምና ነው የሚደረገው?
ሳም ቤከር የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪ ሳለ የክፍሉ ረዥም ልጅ ነበር። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሆነው ጓደኞቹ ሁሉ ዘለግ ዘለግ ያሉ ሲሆኑ የእሱ ቁመት ግን አልጨመረም። "ኮሌጅ ስገባ ከሌሎች ወንዶችና ሴቶች ያጠርኩ መሆኔን አስተዋልኩ። ሴቶች ከእነሱ ከሚያጥር ሰው ጋር ፍቅር አይጀምሩም። እናም ሚስት አላገኝም ብዬ እሰጋ ነበር" ይላል። የ30 ዓመቱ የኒው ዮርክ ነዋሪ ሳም እረዝማለሁ ብሎ ቢጠብቅም ቁመቱ አልጨምር አለው። "ቁመትና ስኬትን አስተሳስሬ ነው የማየው" የሚለው ሳም ቁመት ለመጨመር አማራጮች ያስስ ጀመር። ከፍ ያለ ጫማ ማድረግ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ወዘተ. . . የሚሉት አማራጮች አላሳመኑትም። እግር ስለሚያረዝም ቀዶ ሕክምና ሲያነብ ግን ትኩረቱን ሳበው። "ጥቂት ኢንቾች ከጨመርኩ በኋላ መራመድና መሮጥ እችል ይሆን? ብዬ አሰብኩ" በየዓመቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቁመታቸውን ለመጨመር ቀዶ ሕክምና ያደርጋሉ። ቀዶ ሕክምናው ብዙ የጎንዮሽ ጉዳቶች እንደሚያስከትል ባለሙያዎች ይናገራሉ። ሳም ስለ ቀዶ ሕክምናው ከእናቱ ጋር ከተወያየ በኋላ የጎንዮሽ ጉዳት ቢኖርም እንኳን ለማካሄድ ወሰነ። ቀዶ ሕክምናውን ያደረገው ከዛሬ አምስት ዓመት በፊት ሲሆን፤ ይህም ከ162 ሴንቲ ሜትር ወደ 170 ሴንቲ ሜትር ከፍ እንዲል አስችሎታል። "ሐኪሙ መጀመሪያ ሲያገኘኝ ቀዶ ሕክምናው ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ነግሮኛል። ጥቂት ኢንቾች ከጨመርኩ በኋላ መራመድና መሮጥ እችል ይሆን? ብዬ አሰብኩ።" ከቀዶ ሕክምናው በኋላ ሆስፒታል ውስጥ የማገገሚያ ሕክምና ተደርጎለታል። ለስድስት ወራት፣ በሳምንት ለአራት ቀን ሕክምና ይሰጠው እንደነበር ያስታውሳል። "እንደ አዲስ መራመድ መማር ነበረብኝ" ይላል። ብዙ አገሮች እግር ለማርዘም ቀዶ ሕክምና ይሰጣሉ። እስከ አምስት ኢንች ወይም 13 ሴንቲ ሜትር ድረስ ቁመት መጨመርም ይቻላል። አሜሪካ፣ ጀርመን እና ደቡብ ኮርያ የሚገኙ ሆስፒታሎች በዓመት ከ100 እስከ 200 ቀዶ ሕክምናዎችን ያደርጋሉ። ስፔን፣ ሕንድ፣ ቱርክ እና ጣልያን ውስጥ በዓመት ከ20 እስከ 40 የሚደርሱ ቀዶ ሕክምናዎች ይካሄዳሉ። ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ደግሞ በዓመት 15 ጊዜ ቀዶ ሕክምናው ይደረጋል። ቀዶ ሕክምናውን የሚያደርጉ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል። ቀዶ ሕክምናው እንዴት ይካሄዳል? ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ቀዶ ሕክምናው እስከ 50 ሺህ ፓውንድ ያስከፍላል። አሜሪካ ውስጥ ደግሞ ከ75 ሺህ እስከ 280 ሺህ ዶላር ያስወጣል። ቀዶ ሕክምናው ውድ ነው። ረዥም ሰዓታት ይወስዳል። ያማልም። በሕክምናው ፈር ቀዳጅ የሆኑት የሶቪየቱ ጋቪል ሊዝሮቭ ናቸው። ሕክምናውን የጀመሩት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተረፉ ወታደሮችን ለማከም ነበር። ቀዶ ሕክምናው ባለፉት 70 ዓመታት ከፍተኛ መሻሻል አሳይቷል። ሕክምናው የሚካሄደው የእግር አጥንትን ቦርቡሮ ለሁለት ከከፈሉ በኋላ አነስተኛ ብረት በክፍተቱ በመክተት ነው። ግለሰቡ የሚፈለገው ርዝመት ላይ እስኪደርስ ብረቱ በየቀኑ አንድ ሚሊ ሜትር ከፍ እንዲል ይደረጋል። ታካሚው ከቀዶ ሕክምናው በኋላ ለወራት የማገገሚያ ሕክምና ይሰጠዋል። ቀዶ ሕክምናው ነርቭ ሊጎዳ፣ የደም ዝውውር ሊገታም ይችላል። የእግር አጥንትን መልሶ ለመግጠም የሚያስቸግርበትም ጊዜ አለ። "ቀዶ ሕክምናውን ያደረግኩት በ46 ዓመቴ ነበር" ባርኒ ቀዶ ሕክምናውን ያደረገው ከአምስት ዓመት በፊት ጣልያን ሲሆን፤ 3 ኢንች ጨምሯል። የእግር ቀዶ ሕክምና እንዲያደርግ የታዘዘው በሐኪሞች ምክር ነበር። "ቀዶ ሕክምናውን ያደረግኩት በ46 ዓመቴ ነበር። የእግሬ አጥንት መልሶ ሊገጥም አልቻለም። የሦስት ኢንች ክፍተት ተፈጥሮ ነበር" ይላል። ቀዶ ሕክምናው ምቾት ነስቶት እንደነበር ይናገራል። "እያንዳንዱ የእግሬ ነርቭ እንደተወጠረ ይሰማኝ ነበር። ህመሙ ቀላል አልነበረም።" የብሪትሽ የአጥንት ሕክምና [ኦርቶፒዲክ] ማኅበሩ ፕሮፌሰር ሀሚሽ ሲምሰን እንደሚሉት፤ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ሕክምናው እየተሻሻለ መጥቷል። "ሂደቱ አስተማማኝ እየሆነ ቢመጣም ከአጥንት በተጨማሪ ጡንቻ፣ ነርቭ፣ የደም መዘዋወሪያ እና ቆዳን ማሳደግም ስለሚያስፈልግ ሂደቱ ውስስብ ነው" ይላሉ። በዩናይትድ ኪንግደም የሚሠሩት ዶ/ር ዴቪድ ጎደር፤ አንዳንድ ሰዎች ገንዘብ ለማዳን ብለው ደኅንነቱ በማያስተማምን ቦታ ቀዶ ሕክምናውን እንደሚያገኙ ይናገራሉ። ባርኒ ቀዶ ሕክምናውን ካካሄደ ከአምስት ዓመታት በኋላ ነው የመጨረሻውን የሕክምና ደረጃ ያጠናቀቀው። በስተመጨረሻ እግሩ ውስጥ የቀረው ብረት እንዲወጣ ተደርጓል። "የአንዳንዶች ቀዶ ሕክምና በስኬት ይጠናቀቃል። እኔ ግን ለማገገም ገና ጊዜ ይወስድብኛል። ሆኖም ቀዶ ሕክምናውን ማድረጌ አይጸጽተኝም። አጭር ሰዎች ከሚገጥማቸው መድልዎ ነጻ ሆኜ ሕይወቴን እንድገፋ እድል ሰጥቶኛል" ይላል።
ሕክምና ፡ ቁመት ለመጨመር ምን አይነት ቀዶ ሕክምና ነው የሚደረገው? ሳም ቤከር የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪ ሳለ የክፍሉ ረዥም ልጅ ነበር። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሆነው ጓደኞቹ ሁሉ ዘለግ ዘለግ ያሉ ሲሆኑ የእሱ ቁመት ግን አልጨመረም። "ኮሌጅ ስገባ ከሌሎች ወንዶችና ሴቶች ያጠርኩ መሆኔን አስተዋልኩ። ሴቶች ከእነሱ ከሚያጥር ሰው ጋር ፍቅር አይጀምሩም። እናም ሚስት አላገኝም ብዬ እሰጋ ነበር" ይላል። የ30 ዓመቱ የኒው ዮርክ ነዋሪ ሳም እረዝማለሁ ብሎ ቢጠብቅም ቁመቱ አልጨምር አለው። "ቁመትና ስኬትን አስተሳስሬ ነው የማየው" የሚለው ሳም ቁመት ለመጨመር አማራጮች ያስስ ጀመር። ከፍ ያለ ጫማ ማድረግ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ወዘተ. . . የሚሉት አማራጮች አላሳመኑትም። እግር ስለሚያረዝም ቀዶ ሕክምና ሲያነብ ግን ትኩረቱን ሳበው። "ጥቂት ኢንቾች ከጨመርኩ በኋላ መራመድና መሮጥ እችል ይሆን? ብዬ አሰብኩ" በየዓመቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቁመታቸውን ለመጨመር ቀዶ ሕክምና ያደርጋሉ። ቀዶ ሕክምናው ብዙ የጎንዮሽ ጉዳቶች እንደሚያስከትል ባለሙያዎች ይናገራሉ። ሳም ስለ ቀዶ ሕክምናው ከእናቱ ጋር ከተወያየ በኋላ የጎንዮሽ ጉዳት ቢኖርም እንኳን ለማካሄድ ወሰነ። ቀዶ ሕክምናውን ያደረገው ከዛሬ አምስት ዓመት በፊት ሲሆን፤ ይህም ከ162 ሴንቲ ሜትር ወደ 170 ሴንቲ ሜትር ከፍ እንዲል አስችሎታል። "ሐኪሙ መጀመሪያ ሲያገኘኝ ቀዶ ሕክምናው ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ነግሮኛል። ጥቂት ኢንቾች ከጨመርኩ በኋላ መራመድና መሮጥ እችል ይሆን? ብዬ አሰብኩ።" ከቀዶ ሕክምናው በኋላ ሆስፒታል ውስጥ የማገገሚያ ሕክምና ተደርጎለታል። ለስድስት ወራት፣ በሳምንት ለአራት ቀን ሕክምና ይሰጠው እንደነበር ያስታውሳል። "እንደ አዲስ መራመድ መማር ነበረብኝ" ይላል። ብዙ አገሮች እግር ለማርዘም ቀዶ ሕክምና ይሰጣሉ። እስከ አምስት ኢንች ወይም 13 ሴንቲ ሜትር ድረስ ቁመት መጨመርም ይቻላል። አሜሪካ፣ ጀርመን እና ደቡብ ኮርያ የሚገኙ ሆስፒታሎች በዓመት ከ100 እስከ 200 ቀዶ ሕክምናዎችን ያደርጋሉ። ስፔን፣ ሕንድ፣ ቱርክ እና ጣልያን ውስጥ በዓመት ከ20 እስከ 40 የሚደርሱ ቀዶ ሕክምናዎች ይካሄዳሉ። ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ደግሞ በዓመት 15 ጊዜ ቀዶ ሕክምናው ይደረጋል። ቀዶ ሕክምናውን የሚያደርጉ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል። ቀዶ ሕክምናው እንዴት ይካሄዳል? ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ቀዶ ሕክምናው እስከ 50 ሺህ ፓውንድ ያስከፍላል። አሜሪካ ውስጥ ደግሞ ከ75 ሺህ እስከ 280 ሺህ ዶላር ያስወጣል። ቀዶ ሕክምናው ውድ ነው። ረዥም ሰዓታት ይወስዳል። ያማልም። በሕክምናው ፈር ቀዳጅ የሆኑት የሶቪየቱ ጋቪል ሊዝሮቭ ናቸው። ሕክምናውን የጀመሩት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተረፉ ወታደሮችን ለማከም ነበር። ቀዶ ሕክምናው ባለፉት 70 ዓመታት ከፍተኛ መሻሻል አሳይቷል። ሕክምናው የሚካሄደው የእግር አጥንትን ቦርቡሮ ለሁለት ከከፈሉ በኋላ አነስተኛ ብረት በክፍተቱ በመክተት ነው። ግለሰቡ የሚፈለገው ርዝመት ላይ እስኪደርስ ብረቱ በየቀኑ አንድ ሚሊ ሜትር ከፍ እንዲል ይደረጋል። ታካሚው ከቀዶ ሕክምናው በኋላ ለወራት የማገገሚያ ሕክምና ይሰጠዋል። ቀዶ ሕክምናው ነርቭ ሊጎዳ፣ የደም ዝውውር ሊገታም ይችላል። የእግር አጥንትን መልሶ ለመግጠም የሚያስቸግርበትም ጊዜ አለ። "ቀዶ ሕክምናውን ያደረግኩት በ46 ዓመቴ ነበር" ባርኒ ቀዶ ሕክምናውን ያደረገው ከአምስት ዓመት በፊት ጣልያን ሲሆን፤ 3 ኢንች ጨምሯል። የእግር ቀዶ ሕክምና እንዲያደርግ የታዘዘው በሐኪሞች ምክር ነበር። "ቀዶ ሕክምናውን ያደረግኩት በ46 ዓመቴ ነበር። የእግሬ አጥንት መልሶ ሊገጥም አልቻለም። የሦስት ኢንች ክፍተት ተፈጥሮ ነበር" ይላል። ቀዶ ሕክምናው ምቾት ነስቶት እንደነበር ይናገራል። "እያንዳንዱ የእግሬ ነርቭ እንደተወጠረ ይሰማኝ ነበር። ህመሙ ቀላል አልነበረም።" የብሪትሽ የአጥንት ሕክምና [ኦርቶፒዲክ] ማኅበሩ ፕሮፌሰር ሀሚሽ ሲምሰን እንደሚሉት፤ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ሕክምናው እየተሻሻለ መጥቷል። "ሂደቱ አስተማማኝ እየሆነ ቢመጣም ከአጥንት በተጨማሪ ጡንቻ፣ ነርቭ፣ የደም መዘዋወሪያ እና ቆዳን ማሳደግም ስለሚያስፈልግ ሂደቱ ውስስብ ነው" ይላሉ። በዩናይትድ ኪንግደም የሚሠሩት ዶ/ር ዴቪድ ጎደር፤ አንዳንድ ሰዎች ገንዘብ ለማዳን ብለው ደኅንነቱ በማያስተማምን ቦታ ቀዶ ሕክምናውን እንደሚያገኙ ይናገራሉ። ባርኒ ቀዶ ሕክምናውን ካካሄደ ከአምስት ዓመታት በኋላ ነው የመጨረሻውን የሕክምና ደረጃ ያጠናቀቀው። በስተመጨረሻ እግሩ ውስጥ የቀረው ብረት እንዲወጣ ተደርጓል። "የአንዳንዶች ቀዶ ሕክምና በስኬት ይጠናቀቃል። እኔ ግን ለማገገም ገና ጊዜ ይወስድብኛል። ሆኖም ቀዶ ሕክምናውን ማድረጌ አይጸጽተኝም። አጭር ሰዎች ከሚገጥማቸው መድልዎ ነጻ ሆኜ ሕይወቴን እንድገፋ እድል ሰጥቶኛል" ይላል።
https://www.bbc.com/amharic/news-55198053
3politics
መንግሥት ከህወሓት ጋር "የተደራደሩ" ጥያቄን በፍጹም እንደማይቀበል በድጋሚ አስታወቀ
የኢትዮጵያ መንግሥት ከአጋር አገራት እየቀረበለት ያለውን 'ከህወሓት ጋር ተደራደሩ' የሚሉ ምክረ ሐሳቦች በፍጹም እንደማይቀበል በድጋሚ አስታወቀ። ይህ የተገለጸው የኢፌድሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት አመሻሽ ላይ ባወጣው መግለጫ ነው። ሚኒስቴሩ ከአጋር አገራት ጋር በቅርብ መሥራቱን እንደሚቀጥል በመግለጫው አረጋግጦ ሆኖም ግን፤ እጅ ለመጠምዘዝ የሚሞክሩ ያላቸውን መንግሥታትን ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና የአገሪቱን ሉዓላዊነት እንዲያከብሩ አስጠንቅቋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዚህ ጠንከር ያለ መግለጫው በኢትዮጵያ ላይ እጃቸውን የሚያስገቡ የውጭ መንግሥታትን የኮነነው የሚነሱበትን ክሶች በአምስት ፈርጅ በመክፈል አንድ በአንድ ከዳሰሰ በኋላ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት በርካታ ጊዜ ከእነዚህ መንግሥታት ጋር በበጎ ስሜት ለመነጋገር መሞከሩን ያስታወሰው መግለጫው፤ ነገር ግን ከአጋር አገራት ተመሳሳይ ስሜት ባለማየቱ አጋር የሚባሉ አገራትን እውነተኛ ፍላጎት ለመጠራጠር እየተገደደ መምጣቱን ያወሳል። አጋር አገራት ኢትዮጵያ በተጨባጭ ያለችበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ለመረዳት አለመሞከራቸውን እና ከዚያ ይልቅ ችግሩን የሚያባብሱ ሆነው መገኘታቸውንም ይዘረዝራል። እነዚህ በስም ያልተገለጹት አጋር አገራቱ በሐሰተኛ ሚዲያዎችና ዜናዎች እየተመሩ ወደተሳሳተ አቅጣጫና ድምዳሜ እየሄዱ እንደሆነም ይጠቅሳል። ይህም በመሆኑ መንግሥት በ5 ጉዳዮች ላይ የማያሻማና ግልጽ መልእክት ማስተላለፍ አስፈልጎታል ሲል እነዚህን አንኳር የተባሉ ጉዳዮችን ይዘረዝራል። እነዚህ አንኳር የተባሉት ጉዳዮች በዋናነት በትግራይ ስላለው ሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት፣ በአገሪቱ የለተያዩ አካባቢዎች እየተፈፀሙ ነው ስለሚባሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ ከህወሓት ጋር የተኩስ አቁም ስለማድረግና በጠረጴዛ ዙርያ ንግግር እንዲጀመር የሚቀርቡ ውትወታዎች እና የመብት አራማጆችን ድምጽ ስለማፈን በተነሱ ጉዳዮች ዙርያ ዘርዘር ያሉ ማብራሪያዎች በመግለጫው ተካተውበታል። የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት መንግሥት ሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ላይ ያለውን ዝግጁነት ብቻም ሳይሆን ቆራጥነቱን በሥራ አሳይቷል የሚለው መግለጫው፤ በትግራይ ለሚዳረሱ ሰብአዊ ድጋፎች ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሙሉ አጋርነት መስጠት ብቻም ሳይሆን በመላው ትግራይ ገብተው እንዲሰሩም ፈቅዷል ይላል። መግለጫው እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ አሁንም ሰብአዊ ድጋፍ የሚያቀርቡ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች መድረስ አልቻልንም ብለው መናገራቸው ከእውነት የራቀ ነው ብሏል። በደኅንነት ስጋት የተነሳ አንዳንድ አካባቢዎች ለሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት ምቹ እንዳልሆኑና ይህንንም ድርጅቶቹ እንደሚረዱ አብራርቷል። ሀቁ ይህ ሆኖም ዓለም አቀፍ ሰብአዊ ድጋፍ ሰጪዎች ተመሳሳይ ቅሬታ ማቅረባቸው እንዳሳዘነው ገልጧል፡፡ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተም የሚደርሱትን ቅሬታዎች ለማጣራት በፌዴራል ዐቃቤ ሕግ እና በፌዴራል ፖሊስ የሚመራ ቡድን መቋቋሙን፣ ምርመራ ለማድረግም ወደ ትግራይ ማቅናቱን አስታውሶ፤ የምርመራ ውጤታቸውን ባለፈው ሳምንት ይፋ ማድረጋቸውን ገልጧል። በዚህም ጥፋተኞች ተጠያቂነት እንደሚኖርባቸው ማረጋገጡን አስምሮበታል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የማይካድራ ጭፍጨፋን ጨምሮ በርካታ ምርመራዎችን አድርጎ መግለጫ ያወጣ መሆኑን አውስቷል። ከዚህም ባሻገርም መግለጫው ኢሰመኮ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጀት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር በቅንጅት ምርመራ ለማድረግ መስማማቱንም አስታውሷል። በኢትዮጵያ መንግሥት ግብዣ የአፍሪካ ኅብረት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ራሱን የቻለ ምርመራ እያደረገ እንደሆነም ጠቅሶ፤ ይህ ሁሉ እየሆነ ባለበት ሁኔታ ኢትዮጵያን ቸልተኛ እንደሆነች አድርጎ መክሰስ ፖለቲካዊ ጫና ለማሳደር ከመሻት የመነጨ እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም ብሏል የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ። ግጭት ይቁም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ በተለይ ግጭት እንዲቆም ከስምምነት እንዲደረስ እና ብሔራዊ ምክክርን በተመለከተ የውጭ መንግሥታት እየሰነዘሩ ያሉትን ሐሳብ ክፉኛ ተችቷል። ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር ከሲቪል ማኅበረሰቡና ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ምሁራንና የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተከታታይ ንግግሮችን እያደረገ ያለበት ሁኔታን በዝርዝር ጠቅሶ፤ ነገር ግን አጋር አገራት መንግሥት ከህወሓት ጋር ንግግር እንዲጀምር ግፊት ማድረጋቸው በጭራሽ ተቀባይነት እንደሌለው አትቷል። ፓርላማው ድርጅቱን በአሸባሪነት በፈረጀበት ሁኔታ ከህወሓት ጋር በጠላትነት መተያየቱ እንዲቀርና ድርድር እንዲጀመር የሚጠይቁ አጋር መንግሥታትን ተደጋጋሚ ጥያቄዎቻቸውን በፍጹም እንደማይቀበል የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። "ህወሓት ሕገ-ወጥ ቡድን ነው። የአገሪቱን ሉዓላዊነት አደጋ ውስጥ የከተተና ሕገ-መንግሥቱን የጣሰ ቡድን ነው። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ቡድን ተርታ ውስጥ እንዲገባ ወስኗል። ለዚህም ነው የኢትዮጽያ መንግሥት የአጋር አገራትን ግጭት ቆሞ ከህወሓት ጋር የተደራደሩ ጥሪ በፍጹም ሊቀበለው የማይችለው" ይላል መግለጫው። መግለጫው አንዳንድ አጋር መንግሥታት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ መግባታቸውን እንዲያቆሙም ጠይቋል። በተለይም የአማራ ክልል ልዩ ኃይልን በተመለከተ የሚሰነዘሩ ሐሳቦችን እንደማይቀበል የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ገልጧል። "ኢትዮጵያ ሉዓላዊት አገር ናት። የራሷን የጸጥታ ኃይልና ሠራዊት በግዛቷ በፈለገችው ሁኔታና መልክ ማሰማራት ትችላለች። የአማራ ልዩ ኃይል በትግራይ መሰማራትም በዚህ አግባብ የተፈጸመ ነው" ብሏል። የኢትዮጵያ መንግሥት በጋራ ጉዳዮች ላይ አሁንም ቢሆን ከአጋር መንግሥታት ጋር ለመነጋገር ዝግጁ ቢሆንም እጅን ለመጠምዘዝ የሚሞከሩ ሁኔታዎች የሚቀጥሉ ከሆነ ግን ይህን ግንኙነት በድጋሚ ለማጤን ይገደዳል ብሏል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ።
መንግሥት ከህወሓት ጋር "የተደራደሩ" ጥያቄን በፍጹም እንደማይቀበል በድጋሚ አስታወቀ የኢትዮጵያ መንግሥት ከአጋር አገራት እየቀረበለት ያለውን 'ከህወሓት ጋር ተደራደሩ' የሚሉ ምክረ ሐሳቦች በፍጹም እንደማይቀበል በድጋሚ አስታወቀ። ይህ የተገለጸው የኢፌድሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት አመሻሽ ላይ ባወጣው መግለጫ ነው። ሚኒስቴሩ ከአጋር አገራት ጋር በቅርብ መሥራቱን እንደሚቀጥል በመግለጫው አረጋግጦ ሆኖም ግን፤ እጅ ለመጠምዘዝ የሚሞክሩ ያላቸውን መንግሥታትን ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና የአገሪቱን ሉዓላዊነት እንዲያከብሩ አስጠንቅቋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዚህ ጠንከር ያለ መግለጫው በኢትዮጵያ ላይ እጃቸውን የሚያስገቡ የውጭ መንግሥታትን የኮነነው የሚነሱበትን ክሶች በአምስት ፈርጅ በመክፈል አንድ በአንድ ከዳሰሰ በኋላ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት በርካታ ጊዜ ከእነዚህ መንግሥታት ጋር በበጎ ስሜት ለመነጋገር መሞከሩን ያስታወሰው መግለጫው፤ ነገር ግን ከአጋር አገራት ተመሳሳይ ስሜት ባለማየቱ አጋር የሚባሉ አገራትን እውነተኛ ፍላጎት ለመጠራጠር እየተገደደ መምጣቱን ያወሳል። አጋር አገራት ኢትዮጵያ በተጨባጭ ያለችበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ለመረዳት አለመሞከራቸውን እና ከዚያ ይልቅ ችግሩን የሚያባብሱ ሆነው መገኘታቸውንም ይዘረዝራል። እነዚህ በስም ያልተገለጹት አጋር አገራቱ በሐሰተኛ ሚዲያዎችና ዜናዎች እየተመሩ ወደተሳሳተ አቅጣጫና ድምዳሜ እየሄዱ እንደሆነም ይጠቅሳል። ይህም በመሆኑ መንግሥት በ5 ጉዳዮች ላይ የማያሻማና ግልጽ መልእክት ማስተላለፍ አስፈልጎታል ሲል እነዚህን አንኳር የተባሉ ጉዳዮችን ይዘረዝራል። እነዚህ አንኳር የተባሉት ጉዳዮች በዋናነት በትግራይ ስላለው ሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት፣ በአገሪቱ የለተያዩ አካባቢዎች እየተፈፀሙ ነው ስለሚባሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ ከህወሓት ጋር የተኩስ አቁም ስለማድረግና በጠረጴዛ ዙርያ ንግግር እንዲጀመር የሚቀርቡ ውትወታዎች እና የመብት አራማጆችን ድምጽ ስለማፈን በተነሱ ጉዳዮች ዙርያ ዘርዘር ያሉ ማብራሪያዎች በመግለጫው ተካተውበታል። የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት መንግሥት ሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ላይ ያለውን ዝግጁነት ብቻም ሳይሆን ቆራጥነቱን በሥራ አሳይቷል የሚለው መግለጫው፤ በትግራይ ለሚዳረሱ ሰብአዊ ድጋፎች ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሙሉ አጋርነት መስጠት ብቻም ሳይሆን በመላው ትግራይ ገብተው እንዲሰሩም ፈቅዷል ይላል። መግለጫው እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ አሁንም ሰብአዊ ድጋፍ የሚያቀርቡ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች መድረስ አልቻልንም ብለው መናገራቸው ከእውነት የራቀ ነው ብሏል። በደኅንነት ስጋት የተነሳ አንዳንድ አካባቢዎች ለሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት ምቹ እንዳልሆኑና ይህንንም ድርጅቶቹ እንደሚረዱ አብራርቷል። ሀቁ ይህ ሆኖም ዓለም አቀፍ ሰብአዊ ድጋፍ ሰጪዎች ተመሳሳይ ቅሬታ ማቅረባቸው እንዳሳዘነው ገልጧል፡፡ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተም የሚደርሱትን ቅሬታዎች ለማጣራት በፌዴራል ዐቃቤ ሕግ እና በፌዴራል ፖሊስ የሚመራ ቡድን መቋቋሙን፣ ምርመራ ለማድረግም ወደ ትግራይ ማቅናቱን አስታውሶ፤ የምርመራ ውጤታቸውን ባለፈው ሳምንት ይፋ ማድረጋቸውን ገልጧል። በዚህም ጥፋተኞች ተጠያቂነት እንደሚኖርባቸው ማረጋገጡን አስምሮበታል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የማይካድራ ጭፍጨፋን ጨምሮ በርካታ ምርመራዎችን አድርጎ መግለጫ ያወጣ መሆኑን አውስቷል። ከዚህም ባሻገርም መግለጫው ኢሰመኮ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጀት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር በቅንጅት ምርመራ ለማድረግ መስማማቱንም አስታውሷል። በኢትዮጵያ መንግሥት ግብዣ የአፍሪካ ኅብረት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ራሱን የቻለ ምርመራ እያደረገ እንደሆነም ጠቅሶ፤ ይህ ሁሉ እየሆነ ባለበት ሁኔታ ኢትዮጵያን ቸልተኛ እንደሆነች አድርጎ መክሰስ ፖለቲካዊ ጫና ለማሳደር ከመሻት የመነጨ እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም ብሏል የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ። ግጭት ይቁም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ በተለይ ግጭት እንዲቆም ከስምምነት እንዲደረስ እና ብሔራዊ ምክክርን በተመለከተ የውጭ መንግሥታት እየሰነዘሩ ያሉትን ሐሳብ ክፉኛ ተችቷል። ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር ከሲቪል ማኅበረሰቡና ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ምሁራንና የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተከታታይ ንግግሮችን እያደረገ ያለበት ሁኔታን በዝርዝር ጠቅሶ፤ ነገር ግን አጋር አገራት መንግሥት ከህወሓት ጋር ንግግር እንዲጀምር ግፊት ማድረጋቸው በጭራሽ ተቀባይነት እንደሌለው አትቷል። ፓርላማው ድርጅቱን በአሸባሪነት በፈረጀበት ሁኔታ ከህወሓት ጋር በጠላትነት መተያየቱ እንዲቀርና ድርድር እንዲጀመር የሚጠይቁ አጋር መንግሥታትን ተደጋጋሚ ጥያቄዎቻቸውን በፍጹም እንደማይቀበል የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። "ህወሓት ሕገ-ወጥ ቡድን ነው። የአገሪቱን ሉዓላዊነት አደጋ ውስጥ የከተተና ሕገ-መንግሥቱን የጣሰ ቡድን ነው። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ቡድን ተርታ ውስጥ እንዲገባ ወስኗል። ለዚህም ነው የኢትዮጽያ መንግሥት የአጋር አገራትን ግጭት ቆሞ ከህወሓት ጋር የተደራደሩ ጥሪ በፍጹም ሊቀበለው የማይችለው" ይላል መግለጫው። መግለጫው አንዳንድ አጋር መንግሥታት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ መግባታቸውን እንዲያቆሙም ጠይቋል። በተለይም የአማራ ክልል ልዩ ኃይልን በተመለከተ የሚሰነዘሩ ሐሳቦችን እንደማይቀበል የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ገልጧል። "ኢትዮጵያ ሉዓላዊት አገር ናት። የራሷን የጸጥታ ኃይልና ሠራዊት በግዛቷ በፈለገችው ሁኔታና መልክ ማሰማራት ትችላለች። የአማራ ልዩ ኃይል በትግራይ መሰማራትም በዚህ አግባብ የተፈጸመ ነው" ብሏል። የኢትዮጵያ መንግሥት በጋራ ጉዳዮች ላይ አሁንም ቢሆን ከአጋር መንግሥታት ጋር ለመነጋገር ዝግጁ ቢሆንም እጅን ለመጠምዘዝ የሚሞከሩ ሁኔታዎች የሚቀጥሉ ከሆነ ግን ይህን ግንኙነት በድጋሚ ለማጤን ይገደዳል ብሏል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ።
https://www.bbc.com/amharic/57155325
2health
አስትራዜኒካ ከሚያመርተው የኮሮናቫይረስ ክትባት ትርፍ መሰብሰብ ሊጀምር ነው
አስትራዜኒካ የሚያመርተውን የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ያለትርፍ ለአገራት የሚሰራጭበትን አሠራር ሊቀይር እንደሆነ ተሰምቷል። ግዙፉ መድኃኒት አምራች ኩባንያ ከቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆኑ ተከታታይ የንግድ ስምምነቶች የተፈራረመ ሲሆን ከክትባቱ ሽያጭ መጠነኛ ገቢ እንደሚያስገባ አስታውቋል። ሆኖም ኩባንያው ለድሃ አገራት ክትባቱን ያለትርፍ ማቅረቡን እንደሚቀጥል ገልጿል። ኩባንያው ከዚህ ቀደም ከክትባቱ ገንዘብ ለማግኘት አቅዶ የነበረው ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስጋት መሆኑ ካበቃ በኋላ ነው። የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፓስካል ሶሪዮት፤ ወረርሽኙ ወደተወሰኑ አከባቢዎች እየጠበበ መምጣቱን ተናግረዋል። "ቀደም ሲል ያለምንም ትርፍ ክትባቱን ለማቅረብ የወሰነው ዋናው ዓላማችን የዓለምን ጤና መጠበቅ ስለነበር ነው" ብለዋል። "ምንም እንኳን በተለያዩ አገራት የፖለቲካ ትችቶችን ብናስተናግድም ከተፎካካሪዎች በተቃራኒ ትርፍ ለማግኘት አለመሥራታችን ምንም አይነት ፀፀት አላስከተለብንም" ሲሉ ሥራ አስፈጻሚው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ጋር በተደረገ ትብር የበለጸገው ክትባቱ በዓለም ዙሪያ የአንድ ሚሊዮን ሰዎችን ሕይወት መታደግ መቻሉንም ጠቅሰዋል። "በፍፁም አልፀፀትምም። እንደ ኩባንያ እኛ በሠራነው ሥራ ኩራት ይሰማናል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን አድነናል። የአስተራዜኒካ ቡድን ጥሩ ሥራ መሥራቱን ቀጥሎበታል" ሲሉም አክለዋል። ከክትባቱ ሽያጭ ከፍተኛ ገቢ እንደማይጠበቅ የገለጹ ኃላፊው፤ ክትባቱ በተመጣጣኝ ዋጋ መቅረቡን ለማረጋገጥ ለአገራት በየደረጃው የዋጋ ተመን እንደሚወጣ ተናግረዋል። እስከዚህ የፈረንጆቹ ዓመት መገባደጃ ድረስ አስትራዜኒካ 250 ሚሊዮን ክትባቶችን በኮቫክስ መርሐ ግብር አማካይነት ለታዳጊ አገራት እንደሚያቀርብ ይጠበቃል። ፋይዘር እና ሞደርናን ጨምሮ ሌሎች የክትባት አምራቾች ከምርቶቻቸው ትርፍ እያገኙ ያገኛሉ። በመድኃኒት ኢንዱስትሪ ውስጥ ያለው መደበኛ የትርፍ ጣሪያ 20 በመቶ መሆኑን የሚገልጹት ሶሪዮት፤ የኮቪድ-19 ክትባት ግን አንድ ብልቃጥ 5 ዶላር የሚሸጥ በመሆኑ አስተራዜኒካ አነስተኛ ትርፍ እንደሚያገኝ ጠቁመዋል። 'ግሎባል ጀስቲስ ናው' የተሰኘ እንቅስቃሴ ዳይሬክተር ኒክ ዴርደን በበኩላቸው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በቀጠለበት በዚህ ወቅት አስትራዜኒካ ከክትባቱ ትርፍ ለማግኘት መወሰኑ ተገቢ አለመሆኑን በመጥቀስ ውሳኔውን ተቃውመዋል።
አስትራዜኒካ ከሚያመርተው የኮሮናቫይረስ ክትባት ትርፍ መሰብሰብ ሊጀምር ነው አስትራዜኒካ የሚያመርተውን የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ያለትርፍ ለአገራት የሚሰራጭበትን አሠራር ሊቀይር እንደሆነ ተሰምቷል። ግዙፉ መድኃኒት አምራች ኩባንያ ከቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆኑ ተከታታይ የንግድ ስምምነቶች የተፈራረመ ሲሆን ከክትባቱ ሽያጭ መጠነኛ ገቢ እንደሚያስገባ አስታውቋል። ሆኖም ኩባንያው ለድሃ አገራት ክትባቱን ያለትርፍ ማቅረቡን እንደሚቀጥል ገልጿል። ኩባንያው ከዚህ ቀደም ከክትባቱ ገንዘብ ለማግኘት አቅዶ የነበረው ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስጋት መሆኑ ካበቃ በኋላ ነው። የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፓስካል ሶሪዮት፤ ወረርሽኙ ወደተወሰኑ አከባቢዎች እየጠበበ መምጣቱን ተናግረዋል። "ቀደም ሲል ያለምንም ትርፍ ክትባቱን ለማቅረብ የወሰነው ዋናው ዓላማችን የዓለምን ጤና መጠበቅ ስለነበር ነው" ብለዋል። "ምንም እንኳን በተለያዩ አገራት የፖለቲካ ትችቶችን ብናስተናግድም ከተፎካካሪዎች በተቃራኒ ትርፍ ለማግኘት አለመሥራታችን ምንም አይነት ፀፀት አላስከተለብንም" ሲሉ ሥራ አስፈጻሚው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ጋር በተደረገ ትብር የበለጸገው ክትባቱ በዓለም ዙሪያ የአንድ ሚሊዮን ሰዎችን ሕይወት መታደግ መቻሉንም ጠቅሰዋል። "በፍፁም አልፀፀትምም። እንደ ኩባንያ እኛ በሠራነው ሥራ ኩራት ይሰማናል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን አድነናል። የአስተራዜኒካ ቡድን ጥሩ ሥራ መሥራቱን ቀጥሎበታል" ሲሉም አክለዋል። ከክትባቱ ሽያጭ ከፍተኛ ገቢ እንደማይጠበቅ የገለጹ ኃላፊው፤ ክትባቱ በተመጣጣኝ ዋጋ መቅረቡን ለማረጋገጥ ለአገራት በየደረጃው የዋጋ ተመን እንደሚወጣ ተናግረዋል። እስከዚህ የፈረንጆቹ ዓመት መገባደጃ ድረስ አስትራዜኒካ 250 ሚሊዮን ክትባቶችን በኮቫክስ መርሐ ግብር አማካይነት ለታዳጊ አገራት እንደሚያቀርብ ይጠበቃል። ፋይዘር እና ሞደርናን ጨምሮ ሌሎች የክትባት አምራቾች ከምርቶቻቸው ትርፍ እያገኙ ያገኛሉ። በመድኃኒት ኢንዱስትሪ ውስጥ ያለው መደበኛ የትርፍ ጣሪያ 20 በመቶ መሆኑን የሚገልጹት ሶሪዮት፤ የኮቪድ-19 ክትባት ግን አንድ ብልቃጥ 5 ዶላር የሚሸጥ በመሆኑ አስተራዜኒካ አነስተኛ ትርፍ እንደሚያገኝ ጠቁመዋል። 'ግሎባል ጀስቲስ ናው' የተሰኘ እንቅስቃሴ ዳይሬክተር ኒክ ዴርደን በበኩላቸው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በቀጠለበት በዚህ ወቅት አስትራዜኒካ ከክትባቱ ትርፍ ለማግኘት መወሰኑ ተገቢ አለመሆኑን በመጥቀስ ውሳኔውን ተቃውመዋል።
https://www.bbc.com/amharic/news-59272481
2health
በኮሮናቫይረስ የሚሞቱ ሰዎች መጨመሩን ተከትሎ ኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መመሪያዋን አሻሻለች
በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የሚሞቱ፣ ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ መጨመሩን ተከትሎ ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያግዝ የተሻሻለ መመሪያ መውጣቱ ተገልጿል። በተሻሻለው መመሪያ መሰረት ከስድስት አመት በላይ የሆኑ ህፃናት ማስክ እንዲያደርጉ፣ በሰርግ፣ በቀብር እንዲሁም በስብሰባዎች ላይ የሚገኙ ሰዎች ብዛት ከአምሳ እንዳይበልጥ፣ በካፌዎችና በሬስቶራንቶች በአንድ ጠረጴዛ ከሶስት ተገልጋዮች በላይ እንዳይቀመጡ የሚሉና ሌሎች ዝርዝሮች ተካትተውበታል። የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ያወጡት ይህ መመሪያ ከነሐሴ 13 ፣ 2013 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል። በተሻሻለው መመሪያ መሰረት ማንኛውም ሰው ማስክ ሳያደርግ እንዳይንቀሳቀስ የሚያግድ ሲሆን ይህም ከስድስት አመት በላይ የሆኑ ህፃናትን እንደሚጨምር የጤና ሚኒስቴር በትናንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ አስፍሯል። የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አስገዳጅ የማይሆነው ከስድስት አመት በታች ለሆኑ ህፃናት እንዲሁም በማስረጃ የተረጋገጠ የመተንፈሻ አካላት ወይም መሰል ችግር ካለባቸው በስተቀር ሁሉም ዜጎች ሲንቀሳቀሱ ማስክ ማድረግ አለባቸው። የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛዎች በክፍት ገበያዎች፣ በትራንስፖርት መሳፈሪያ ቦታዎች፣ ህዝባዊ አገልግሎት በሚሰጥባቸው ቦታዎችና ሌሎች ህዝብ በሚበዛባቸው መሰል አካባቢዎች ከመደረግ በተጨማሪ ሁለት የአዋቂ እርምጃ (አካላዊ ርቀት) መጠበቅ አስገዳጅ ነው ተብሏል። በማንኛውም መንግስታዊ እና የግል ተቋም አገልግሎት መስጫ ስፍራዎች ላይ ሰራተኞችና ደንበኞች ከሁለት የአዋቂ እርምጃ ወይም አካላዊ ርቀታቸውን ጠብቀው እንዲገለገሉና ማስክ እንዲያደርጉ ያስገድዳል። በእነዚህ የአገልግሎት ስፍራዎች በአንድ ጠረጴዛ ከሶስት ተገልጋዮች በላይ እንዲቀመጡ ማድረግም ተከልክሏል። ማንኛውም የመንግሥታዊ እና የግል ተቋማት በመግቢያና መውጫ በሮች የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚረዱ የጥንቃቄ ቁሳቁሶችን ማቅረብና አስፈላጊ ጥንቃቄዎችን መተግበራቸውን የማረጋገጥ ግዴታ አለባቸው ብሏል። በአስከሬን ማስተካከል፣ ግነዛና ማጓጓዝ ወቅትም ሊደረጉ ስለሚገባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎችም መመሪያው አስቀምጧል። ከቀብር በኋላ ሀዘን ለማስተዛዘን በድንኳን፣ በቤት ውስጥ ወይም ለዚሁ በተዘጋጀው ቦታ ላይ ለቅሶ የሚደርሰው ሰው ከ50 እንዳይበልጥ ያዛል። አካላዊ ርቀት መጠበቅ እንዲሁም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ አለባቸው ይላል። በስብሰባም ወቅት በተመሳሳይ የኮቪድ-19 ጥንቃቄዎችን በተከተለ መልኩ እስከ 50 ሰው መሰብሰብ ይቻላል። ከ50 ሰዎች በላይ መሰብሰብ ግዴታ ሆኖ ከተገኘ ስብሰባው ሊደረግበት የታሰበበት ስፍራ ጠቅላላ ስፋት ከግምት ውስጥ ሊገባ እንደሚገባ ጠቁሞ በዚህም መሰረት ቦታው ሊይዝ ከሚችለው ሰው ብዛት አንድ አራተኛ በማይበልጥ መሆን አለበት። እንዲሁም ልዩ ፈቃድ ከሰላም ሚኒስቴር እንዲሁም ከክልሉ፣ ዞን እና ወረዳ የሰላም እና ፀጥታ መዋቅሮች መገኘት አለበት። ስብሰባውንም የጠራው አካል የመከላከያ ዘዴዎቹ መተግበራቸውን ማረጋገጥ ይገባዋል ይላል። የሃይማኖት ስነ ስርዓትን በተመለከተ ሃይማኖታዊ አገልግልቶች አካላዊ ርቀትን በጠበቀ መልኩ ሊፈፀሙ እንደሚገባ መመሪያው አስቀምጧል። የሃይማኖት ስርዓት የሚከናወንባቸው ስፍራዎችም እንዲሁ መያዝ ከሚችሉት አንድ አራተኛ በማይበልጥ ስርዓቱን እንዲያካሂዱ ተቀምጧል። በእነዚህ የእምነት ተቋማት ቅጥር ግቢ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ ግዴታ ነው። የቤት ውስጥ ማህበራዊ ዝግጅቶችን በተመለከተም ለልደት፣ ምረቃ፣ ማህበር እና ቀብር እና ከቀብር መልስ ያሉ ስነ ስርዓቶች ውጭ እና መሰል በቤት ውስጥ የሚዘጋጁ ማህበራዊ በዓላት ከቤተሰብ አባላት ከሆኑ ውጭ ተጠራርቶ ማክበር የተከለከለም ነው። ሰርግን በተመለከተም አካላዊ ርቀትን በጠበቀ መልኩ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ በማድረግ እና ተገቢውን የኮቪድ-19 መከላከያ የንፅህና እርምጃዎች በተገበረ መልኩ ከ50 በማይበልጡ ሰዎች ማካሄድ እንደሚቻል ተቀምጧል። የአደባባይ በዓላትን አከባበር ጋር ተያይዞ ህዝብን በብዛት የሚያሳትፉ የአደባባይ ላይ በዓላት የወረርሽኙ ስርጭት እስኪረጋጋ ድረስ ባይደረጉ በማለትም ምክረ-ኃሳብ አስቀምጧል። በዓላቱ የሚደረጉ ከሆነ ግን የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ መደረጉን እንዲሁም አካላዊ ርቀትን በጠበቀ መልኩ መሆን አለበት ብሏል። ስፍራዎቹም ከሚይዙት ቦታ ከአንድ አራተኛ ቦታ በማይበልጥ ሰው ስርዓቱ ሊካሄድ እንደሚገባም ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል ብሏል። ስፖርታዊ ውድድሮችም በተመለከተ በተመሳሳይ ስፍራው ከሚይዘው የታዳሚ ብዛት ከአንድ አራተኛ በማይበልጥ እንዲሆን ተቀምጧል። አገልግሎት የሚሰጡ እንደ ካፌዎች፣ ባር፣ ሬስቶራንቶች፣ መጠጥ ቤቶች፣ የመዝናኛ እና መጫዎቻ አገልግሎቶች በአንድ ጠረጴዛ ከሶስት ሰው በላይ ማስተናገድ አይችሉም። በእያንዳንዱ ጠረጴዛ የሁለት ሜትር ርቀት መጠበቅ አለበት። አገልግሎትን የሚሰጡም ሆነ ደንበኞች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛን የማድረግ ግዴታ አለባቸው። ከዚህም በተጨማሪ የወረርሽኙ ስርጭት ያለበት ሁኔታ በየጊዜው እየታየ በሌላ መመሪያ እስኪወሰን ድረስ የአረጋዊያን መጦሪያዎች ስፍራዎች እና የማገገሚያ ማዕከላት ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን በአካል መጠየቅ የተከለከለ መሆኑን አስፍሮ ነገር ግን እርዳታ ማቅረብ የሚፈልጉ ከተቋሙ አስተዳደር ድረስ በመቅረብ ድጋፍ ማድረግ እንደሚችሉም ጠቁሟል። በማረሚያ ቤቶች ላይ ታራሚን ለመጠየቅ አካላዊ ርቀትን ጨምሮ ሌሎች አስገዳጅ የኮቪድ- 19 መከላከያን በጠበቀ መልኩ መሆን አለበት ተብሏል። በቤት ውስጥ ማቆያ እና እንክብካቤን በተመለከተ ቀለል ባለ በኮቪድ-19 የተያዘ ታማሚ በቤት ውስጥ የኮቪድ-19 ህክምና አገልግሎት እንዲያገኝ ይደረጋል። ህመምተኞቹ ከሌላው የቤተሰብ አባላት ራሳቸውን መለየት፣ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ መጠቀም፣ ቢያንስ ለ10 ተከታታይ ቀናት መለየትና ከቤት አለመውጣት ይጠበቅባቸዋል። ኮቪድ-19 ያለበት ሰው ቫይረሱ እንዳለበት እያወቀ ወደ ሃገር ውስጥ መግባት፣ ከማህበረሰቡ ጋር መቀላቀል ወይም ከሌሎች ሰዎች ጋር መገናኘት የተከለከለ ነው። ከትራንዚት መንገደኛ በስተቀር በአገሪቱ አለም አቀፍ ማረፊያ በኩል የሚገባ ከአስር አመት ዕድሜ በላይ የሆነ ማንኛውም ተጓዥ ከ120 ሰዓት ወይም አምስት ቀን በላይ ያልሆነው የተረጋጋጠ ምርመራ ኔጌቲቭ ውጤት ይዞ መምጣትና ለሰባት ቀናት መንገደኞች ራሳቸውን ለይተው ማቆየት አለባቸው። ነገር ሰባት ቀናት ራሳቸውን ለመለየት የማይገደዱት በ90 ቀናት ውስጥ ኮቪድ-19 ታመው ያገገሙ፣ ዲፕሎማቶች፣ የኮቪድ-19 ክትባትን በተሟላ ሁኔታ ወስደው ያጠናቀቁ ከሆነ ለተለያዩ ስብሰባዎች የሚመጡ ቱሪስቶች ወይም ለድንገተኛ ጉዳይ የሚመጡ መንገደኞች ናቸው። ለተለያዩ ጉባዔ የሚመጡ ሰዎች የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረግና ውጤታቸው ኔጌቲቭ መሆን አለበት። ማንኛውም ፖዘቲቭ ሰው ወደ ሃገር ውስጥ መግባት የተከለከለ ነው።. በአገሪቱ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በኩል የሚያልፉ የትራንዚት መንገደኞችን በተመለከተም በረራቸው እስኪደርስ ድረስ አየር መንገዱን ለቆ መሄድ ወይም አየር መንገዱ ከለያቸው ሆቴሎች ውጪ ወደ ከተማ መግባት አይችሉም። የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከሳምንታት በፊት ሶስተኛው ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እየጀመረ መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶች እየታዩ እንደሆነ አስታውቋል። በተለያዩ የዓለም ሀገራት መረጃዎች እና ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሦስተኛው ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰቱ ታውቋል። ለዚህም እንደ ምክንያት የሚጠቀሰው የኮቪድ-19 ዴልታ ቫይረስ ሲሆን በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 የዴልታ ቫይረስ መኖሩ ባይረጋገጥም የሶስተኛ ዙር ወረርሽኝ መከሰቱን የሚያሳዩ ምልክቶች መታየት መጀመራቸውም ተገልጿል። በኢትዮጵያ ሁለተኛው ዙር ካበቃ በኋላ በተወሰነ መልኩ በማህበረሰቡ መዘናጋቶች እንዲሁም የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶች በአግባቡ ባለመተግበራቸው ሶስተኛው ዙር ሊከሰት የሚችልበት ምልክቶች እየታዩ ነው። ተቋሙ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የወጡ መመሪያዎቹ እንዲከበሩና ማስክ ማድረግ፣የእጅን ንፅህና በአግባቡ መጠበቅ እና ርቀትን በመጠበቅ በተጨማሪም የኮቪድ-19 ክትባት በመከተብ የኮቪድ-19 መከላከከልና መቆጣጠር እንደሚቻልም አሳሳስቧል። የጤና ሚኒስትሯ ዶክተርር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው "ከፊታችን የተጋረጠብንን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ እንዲያልፍ፣ የጥንቃቄ መንገዶችን፣ ክልከላዎችና ግዴታዎች እያንዳንዱ ዜጋ፣ ተቋም፣ አመራር፣ የህግ አስከባሪ አካላት በከፍተኛ የሃላፊነት መንፈስ በመተግበርና በማስፈፀም ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ" ማለታቸውም በመግለጫው ላይ ሰፍሯል። በኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ 295 ሺህ 19 ግለሰቦች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 268 ሺህ 252 ግለሰቦች ከኮቪድ-19 ቫይረስ አገግመዋል እንዲሁም 4ሺህ 553 ግለሰቦች በኮቪድ-19 ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል። አጠቃላይ ክትባት የተከተቡ ሰዎች ቁጥርም 2,335 ሺህ 71 ሲሆን አገሪቷ በአጠቃላይ 3,134 ሺህ 967 ምርመራዎችን አካሂዳለች።
በኮሮናቫይረስ የሚሞቱ ሰዎች መጨመሩን ተከትሎ ኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መመሪያዋን አሻሻለች በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የሚሞቱ፣ ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ መጨመሩን ተከትሎ ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያግዝ የተሻሻለ መመሪያ መውጣቱ ተገልጿል። በተሻሻለው መመሪያ መሰረት ከስድስት አመት በላይ የሆኑ ህፃናት ማስክ እንዲያደርጉ፣ በሰርግ፣ በቀብር እንዲሁም በስብሰባዎች ላይ የሚገኙ ሰዎች ብዛት ከአምሳ እንዳይበልጥ፣ በካፌዎችና በሬስቶራንቶች በአንድ ጠረጴዛ ከሶስት ተገልጋዮች በላይ እንዳይቀመጡ የሚሉና ሌሎች ዝርዝሮች ተካትተውበታል። የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ያወጡት ይህ መመሪያ ከነሐሴ 13 ፣ 2013 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል። በተሻሻለው መመሪያ መሰረት ማንኛውም ሰው ማስክ ሳያደርግ እንዳይንቀሳቀስ የሚያግድ ሲሆን ይህም ከስድስት አመት በላይ የሆኑ ህፃናትን እንደሚጨምር የጤና ሚኒስቴር በትናንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ አስፍሯል። የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አስገዳጅ የማይሆነው ከስድስት አመት በታች ለሆኑ ህፃናት እንዲሁም በማስረጃ የተረጋገጠ የመተንፈሻ አካላት ወይም መሰል ችግር ካለባቸው በስተቀር ሁሉም ዜጎች ሲንቀሳቀሱ ማስክ ማድረግ አለባቸው። የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛዎች በክፍት ገበያዎች፣ በትራንስፖርት መሳፈሪያ ቦታዎች፣ ህዝባዊ አገልግሎት በሚሰጥባቸው ቦታዎችና ሌሎች ህዝብ በሚበዛባቸው መሰል አካባቢዎች ከመደረግ በተጨማሪ ሁለት የአዋቂ እርምጃ (አካላዊ ርቀት) መጠበቅ አስገዳጅ ነው ተብሏል። በማንኛውም መንግስታዊ እና የግል ተቋም አገልግሎት መስጫ ስፍራዎች ላይ ሰራተኞችና ደንበኞች ከሁለት የአዋቂ እርምጃ ወይም አካላዊ ርቀታቸውን ጠብቀው እንዲገለገሉና ማስክ እንዲያደርጉ ያስገድዳል። በእነዚህ የአገልግሎት ስፍራዎች በአንድ ጠረጴዛ ከሶስት ተገልጋዮች በላይ እንዲቀመጡ ማድረግም ተከልክሏል። ማንኛውም የመንግሥታዊ እና የግል ተቋማት በመግቢያና መውጫ በሮች የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚረዱ የጥንቃቄ ቁሳቁሶችን ማቅረብና አስፈላጊ ጥንቃቄዎችን መተግበራቸውን የማረጋገጥ ግዴታ አለባቸው ብሏል። በአስከሬን ማስተካከል፣ ግነዛና ማጓጓዝ ወቅትም ሊደረጉ ስለሚገባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎችም መመሪያው አስቀምጧል። ከቀብር በኋላ ሀዘን ለማስተዛዘን በድንኳን፣ በቤት ውስጥ ወይም ለዚሁ በተዘጋጀው ቦታ ላይ ለቅሶ የሚደርሰው ሰው ከ50 እንዳይበልጥ ያዛል። አካላዊ ርቀት መጠበቅ እንዲሁም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ አለባቸው ይላል። በስብሰባም ወቅት በተመሳሳይ የኮቪድ-19 ጥንቃቄዎችን በተከተለ መልኩ እስከ 50 ሰው መሰብሰብ ይቻላል። ከ50 ሰዎች በላይ መሰብሰብ ግዴታ ሆኖ ከተገኘ ስብሰባው ሊደረግበት የታሰበበት ስፍራ ጠቅላላ ስፋት ከግምት ውስጥ ሊገባ እንደሚገባ ጠቁሞ በዚህም መሰረት ቦታው ሊይዝ ከሚችለው ሰው ብዛት አንድ አራተኛ በማይበልጥ መሆን አለበት። እንዲሁም ልዩ ፈቃድ ከሰላም ሚኒስቴር እንዲሁም ከክልሉ፣ ዞን እና ወረዳ የሰላም እና ፀጥታ መዋቅሮች መገኘት አለበት። ስብሰባውንም የጠራው አካል የመከላከያ ዘዴዎቹ መተግበራቸውን ማረጋገጥ ይገባዋል ይላል። የሃይማኖት ስነ ስርዓትን በተመለከተ ሃይማኖታዊ አገልግልቶች አካላዊ ርቀትን በጠበቀ መልኩ ሊፈፀሙ እንደሚገባ መመሪያው አስቀምጧል። የሃይማኖት ስርዓት የሚከናወንባቸው ስፍራዎችም እንዲሁ መያዝ ከሚችሉት አንድ አራተኛ በማይበልጥ ስርዓቱን እንዲያካሂዱ ተቀምጧል። በእነዚህ የእምነት ተቋማት ቅጥር ግቢ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ ግዴታ ነው። የቤት ውስጥ ማህበራዊ ዝግጅቶችን በተመለከተም ለልደት፣ ምረቃ፣ ማህበር እና ቀብር እና ከቀብር መልስ ያሉ ስነ ስርዓቶች ውጭ እና መሰል በቤት ውስጥ የሚዘጋጁ ማህበራዊ በዓላት ከቤተሰብ አባላት ከሆኑ ውጭ ተጠራርቶ ማክበር የተከለከለም ነው። ሰርግን በተመለከተም አካላዊ ርቀትን በጠበቀ መልኩ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ በማድረግ እና ተገቢውን የኮቪድ-19 መከላከያ የንፅህና እርምጃዎች በተገበረ መልኩ ከ50 በማይበልጡ ሰዎች ማካሄድ እንደሚቻል ተቀምጧል። የአደባባይ በዓላትን አከባበር ጋር ተያይዞ ህዝብን በብዛት የሚያሳትፉ የአደባባይ ላይ በዓላት የወረርሽኙ ስርጭት እስኪረጋጋ ድረስ ባይደረጉ በማለትም ምክረ-ኃሳብ አስቀምጧል። በዓላቱ የሚደረጉ ከሆነ ግን የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ መደረጉን እንዲሁም አካላዊ ርቀትን በጠበቀ መልኩ መሆን አለበት ብሏል። ስፍራዎቹም ከሚይዙት ቦታ ከአንድ አራተኛ ቦታ በማይበልጥ ሰው ስርዓቱ ሊካሄድ እንደሚገባም ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል ብሏል። ስፖርታዊ ውድድሮችም በተመለከተ በተመሳሳይ ስፍራው ከሚይዘው የታዳሚ ብዛት ከአንድ አራተኛ በማይበልጥ እንዲሆን ተቀምጧል። አገልግሎት የሚሰጡ እንደ ካፌዎች፣ ባር፣ ሬስቶራንቶች፣ መጠጥ ቤቶች፣ የመዝናኛ እና መጫዎቻ አገልግሎቶች በአንድ ጠረጴዛ ከሶስት ሰው በላይ ማስተናገድ አይችሉም። በእያንዳንዱ ጠረጴዛ የሁለት ሜትር ርቀት መጠበቅ አለበት። አገልግሎትን የሚሰጡም ሆነ ደንበኞች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛን የማድረግ ግዴታ አለባቸው። ከዚህም በተጨማሪ የወረርሽኙ ስርጭት ያለበት ሁኔታ በየጊዜው እየታየ በሌላ መመሪያ እስኪወሰን ድረስ የአረጋዊያን መጦሪያዎች ስፍራዎች እና የማገገሚያ ማዕከላት ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን በአካል መጠየቅ የተከለከለ መሆኑን አስፍሮ ነገር ግን እርዳታ ማቅረብ የሚፈልጉ ከተቋሙ አስተዳደር ድረስ በመቅረብ ድጋፍ ማድረግ እንደሚችሉም ጠቁሟል። በማረሚያ ቤቶች ላይ ታራሚን ለመጠየቅ አካላዊ ርቀትን ጨምሮ ሌሎች አስገዳጅ የኮቪድ- 19 መከላከያን በጠበቀ መልኩ መሆን አለበት ተብሏል። በቤት ውስጥ ማቆያ እና እንክብካቤን በተመለከተ ቀለል ባለ በኮቪድ-19 የተያዘ ታማሚ በቤት ውስጥ የኮቪድ-19 ህክምና አገልግሎት እንዲያገኝ ይደረጋል። ህመምተኞቹ ከሌላው የቤተሰብ አባላት ራሳቸውን መለየት፣ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ መጠቀም፣ ቢያንስ ለ10 ተከታታይ ቀናት መለየትና ከቤት አለመውጣት ይጠበቅባቸዋል። ኮቪድ-19 ያለበት ሰው ቫይረሱ እንዳለበት እያወቀ ወደ ሃገር ውስጥ መግባት፣ ከማህበረሰቡ ጋር መቀላቀል ወይም ከሌሎች ሰዎች ጋር መገናኘት የተከለከለ ነው። ከትራንዚት መንገደኛ በስተቀር በአገሪቱ አለም አቀፍ ማረፊያ በኩል የሚገባ ከአስር አመት ዕድሜ በላይ የሆነ ማንኛውም ተጓዥ ከ120 ሰዓት ወይም አምስት ቀን በላይ ያልሆነው የተረጋጋጠ ምርመራ ኔጌቲቭ ውጤት ይዞ መምጣትና ለሰባት ቀናት መንገደኞች ራሳቸውን ለይተው ማቆየት አለባቸው። ነገር ሰባት ቀናት ራሳቸውን ለመለየት የማይገደዱት በ90 ቀናት ውስጥ ኮቪድ-19 ታመው ያገገሙ፣ ዲፕሎማቶች፣ የኮቪድ-19 ክትባትን በተሟላ ሁኔታ ወስደው ያጠናቀቁ ከሆነ ለተለያዩ ስብሰባዎች የሚመጡ ቱሪስቶች ወይም ለድንገተኛ ጉዳይ የሚመጡ መንገደኞች ናቸው። ለተለያዩ ጉባዔ የሚመጡ ሰዎች የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረግና ውጤታቸው ኔጌቲቭ መሆን አለበት። ማንኛውም ፖዘቲቭ ሰው ወደ ሃገር ውስጥ መግባት የተከለከለ ነው።. በአገሪቱ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በኩል የሚያልፉ የትራንዚት መንገደኞችን በተመለከተም በረራቸው እስኪደርስ ድረስ አየር መንገዱን ለቆ መሄድ ወይም አየር መንገዱ ከለያቸው ሆቴሎች ውጪ ወደ ከተማ መግባት አይችሉም። የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከሳምንታት በፊት ሶስተኛው ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እየጀመረ መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶች እየታዩ እንደሆነ አስታውቋል። በተለያዩ የዓለም ሀገራት መረጃዎች እና ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሦስተኛው ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰቱ ታውቋል። ለዚህም እንደ ምክንያት የሚጠቀሰው የኮቪድ-19 ዴልታ ቫይረስ ሲሆን በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 የዴልታ ቫይረስ መኖሩ ባይረጋገጥም የሶስተኛ ዙር ወረርሽኝ መከሰቱን የሚያሳዩ ምልክቶች መታየት መጀመራቸውም ተገልጿል። በኢትዮጵያ ሁለተኛው ዙር ካበቃ በኋላ በተወሰነ መልኩ በማህበረሰቡ መዘናጋቶች እንዲሁም የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶች በአግባቡ ባለመተግበራቸው ሶስተኛው ዙር ሊከሰት የሚችልበት ምልክቶች እየታዩ ነው። ተቋሙ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የወጡ መመሪያዎቹ እንዲከበሩና ማስክ ማድረግ፣የእጅን ንፅህና በአግባቡ መጠበቅ እና ርቀትን በመጠበቅ በተጨማሪም የኮቪድ-19 ክትባት በመከተብ የኮቪድ-19 መከላከከልና መቆጣጠር እንደሚቻልም አሳሳስቧል። የጤና ሚኒስትሯ ዶክተርር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው "ከፊታችን የተጋረጠብንን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ እንዲያልፍ፣ የጥንቃቄ መንገዶችን፣ ክልከላዎችና ግዴታዎች እያንዳንዱ ዜጋ፣ ተቋም፣ አመራር፣ የህግ አስከባሪ አካላት በከፍተኛ የሃላፊነት መንፈስ በመተግበርና በማስፈፀም ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ" ማለታቸውም በመግለጫው ላይ ሰፍሯል። በኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ 295 ሺህ 19 ግለሰቦች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 268 ሺህ 252 ግለሰቦች ከኮቪድ-19 ቫይረስ አገግመዋል እንዲሁም 4ሺህ 553 ግለሰቦች በኮቪድ-19 ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል። አጠቃላይ ክትባት የተከተቡ ሰዎች ቁጥርም 2,335 ሺህ 71 ሲሆን አገሪቷ በአጠቃላይ 3,134 ሺህ 967 ምርመራዎችን አካሂዳለች።
https://www.bbc.com/amharic/58297000