label
class label 4
classes | headline
stringlengths 17
80
| text
stringlengths 1
16.8k
| headline_text
stringlengths 28
16.8k
| url
stringlengths 36
49
|
---|---|---|---|---|
5sports
| ዚነዲን ዚዳን ከሪያል ማድሪድ አሰልጣኝነት ለሁለተኛ ጊዜ ለቀቀ | የሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን ከቡድኑ አሰልጣኝነት ለሁለተኛ ጊዜ መልቀቁ ተነገረ። በዘንድሮው የውድድር ዘመን ያልተሳካለት ሪያል ማድሪድ የዚዳንን ከቡድኑ መልቀቅ በተመለከተ ባወጣው መግለጫ የአሰልጣኙን ውሳኔ "አሁን ማክበር አለብን" ብሏል። ቡድኑ የ48 ዓመቱን አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን ለዓመታት በነበረው ቆይታው ለሪያል ማድሪድ ላበረከተው "የሙያ ብቃትና ከፍተኛ ፍቅር" ምስጋና አቅርቧል። የቀድሞው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አጥቂ ዚዳን እአአ ከ2001 አስከ 2006 ለሪያል ማድሪድ የተጫወተ ሲሆን፤ በአሰልጣኝነት ቡድኑን በመራባቸው ከ2016 አስከ 2018 ባሉት ዓመታት ውስጥ በተከታታይ ሦስት የቻይምፒየንስ ሊግና የላ ሊጋ ዋንጫዎችን ማስገኘት ችሏል። ቀደም ሲል ቡድኑን ከለቀቀ ከ10 ወራት በኋላ ተመልሶ ኃላፊነቱን በመረከብ ለሁለተኛ ጊዜ የላ ሊጋን ዋንጫ ለማንሳት አስችሏል። "ዚዳን ከሪያል ማድሪድ ታላላቅ ከዋክብት መካከል አንዱ ሲሆን በቡድኑ ላይ በተጫዋችነትና በአሰልጣኝነት ያሳረፈው አሻራ ለዘመናት አብሮን ይኖራል" ሲል የቡድኑ መግለጫ ዚዳንን አሞግሶታል። "እሱም በሪያል ማድሪድ ደጋፊዎች ልብ ውስጥ ቦታ እንዳለው ያውቃል፤ ቡድኑ ምንጊዜም ቤቱ ነው" ብሏል። ቀጣይ የዚነዲን ዚዳን መድረሻ የት እንደሚሆን ለወራት የስፔን ጋዜጦች መነጋገሪያ ሆኖ ከርሟል። ዚዳን በሪያል ማድሪድ ውስጥ የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ሦስት ጊዜ በማንሳት ብቸኛው አስልጣኝ ሆኗል። በተጨማሪም ሁለት የዓለም ክለቦች ዋንጫን፣ ሁለት ጊዜ የአውሮፓ ሱፐር ካፕ አሸናፊ እንዲሁም ሁለት የስፔን ሱፐር ካፕ ዋንጫን በማሸነፍ ታሪክ ሰርቷል። | ዚነዲን ዚዳን ከሪያል ማድሪድ አሰልጣኝነት ለሁለተኛ ጊዜ ለቀቀ የሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን ከቡድኑ አሰልጣኝነት ለሁለተኛ ጊዜ መልቀቁ ተነገረ። በዘንድሮው የውድድር ዘመን ያልተሳካለት ሪያል ማድሪድ የዚዳንን ከቡድኑ መልቀቅ በተመለከተ ባወጣው መግለጫ የአሰልጣኙን ውሳኔ "አሁን ማክበር አለብን" ብሏል። ቡድኑ የ48 ዓመቱን አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን ለዓመታት በነበረው ቆይታው ለሪያል ማድሪድ ላበረከተው "የሙያ ብቃትና ከፍተኛ ፍቅር" ምስጋና አቅርቧል። የቀድሞው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አጥቂ ዚዳን እአአ ከ2001 አስከ 2006 ለሪያል ማድሪድ የተጫወተ ሲሆን፤ በአሰልጣኝነት ቡድኑን በመራባቸው ከ2016 አስከ 2018 ባሉት ዓመታት ውስጥ በተከታታይ ሦስት የቻይምፒየንስ ሊግና የላ ሊጋ ዋንጫዎችን ማስገኘት ችሏል። ቀደም ሲል ቡድኑን ከለቀቀ ከ10 ወራት በኋላ ተመልሶ ኃላፊነቱን በመረከብ ለሁለተኛ ጊዜ የላ ሊጋን ዋንጫ ለማንሳት አስችሏል። "ዚዳን ከሪያል ማድሪድ ታላላቅ ከዋክብት መካከል አንዱ ሲሆን በቡድኑ ላይ በተጫዋችነትና በአሰልጣኝነት ያሳረፈው አሻራ ለዘመናት አብሮን ይኖራል" ሲል የቡድኑ መግለጫ ዚዳንን አሞግሶታል። "እሱም በሪያል ማድሪድ ደጋፊዎች ልብ ውስጥ ቦታ እንዳለው ያውቃል፤ ቡድኑ ምንጊዜም ቤቱ ነው" ብሏል። ቀጣይ የዚነዲን ዚዳን መድረሻ የት እንደሚሆን ለወራት የስፔን ጋዜጦች መነጋገሪያ ሆኖ ከርሟል። ዚዳን በሪያል ማድሪድ ውስጥ የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ሦስት ጊዜ በማንሳት ብቸኛው አስልጣኝ ሆኗል። በተጨማሪም ሁለት የዓለም ክለቦች ዋንጫን፣ ሁለት ጊዜ የአውሮፓ ሱፐር ካፕ አሸናፊ እንዲሁም ሁለት የስፔን ሱፐር ካፕ ዋንጫን በማሸነፍ ታሪክ ሰርቷል። | https://www.bbc.com/amharic/news-57251124 |
5sports
| በቶክዮ ኦሎምፒክስ ታዳሚዎች ሊገኙ ይችላሉ ተባለ | የዓለም አቀፉ ኦሎምፒክስ ኮሚቴ ኃላፊ ቶማስ ባህ፤ በቶክዮ ኦሎምፒክስ ላይ ታዳሚዎች እንደሚገኙ "በጣም እርግጠኛ ነኝ" አሉ። ታዳሚዎች ወደ ቶክዮ ከመሄዳቸው በፊት እንዲከተቡ ለማስቻል ኮሚቴው ጥረት እንደሚያደርግም አስታውቀዋል። አሁን ጃፓን ሄደው ስለ ኦሎምፒክስ ውድድር ውይይት እያደረጉ ነው። ዘንድሮ ሐምሌ ላይ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው ኦሎምፒክስ በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ተራዝሟል። በጎርጎሮሳውያኑ 2021 ሐምሌ ላይ ከ200 አገሮች የተውጣጡ 11,000 ተወዳዳሪዎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከጃፓኑ ጠቅላይ ሚንስትር ዮሺሂንዴ ሱጋ ጋር የተነጋገሩት የኦሎምፒክስ ኮሚቴ ኃላፊው ለኤኤፍፒ "በኦሎምፒክስ ስቴድየም ታዳሚዎች እንደምናስተናግድ በጣም እርግጠኛ ነን" ብለዋል። ከዓለም አቀፉ የኦሎምፒክስ ኮሚቴ ባሻገር ጃፓንም ውድድሩ እንደሚካሄድ ማረጋገጫ ሰጥታለች። የጃፓን ቶክዮ ኦሎምፒክስ 2020 ዋና ኃላፊ ቶሺሮ ሙቶ፤ ዓመቱ መባቻ ላይ አንዳንድ ውድድሮች በአነስተኛ ታዳሚዎች እንደሚካሄዱና አገራት የሚመድቧቸው የቡድን አባላት ሊቀነሱ እንደሚችሉም ተናግረው ነበር። የዓለም አቀፉ ኦሎምፒክስ ኮሚቴ ኃላፊ ቶማስ ባህ ባለፈው ሳምንት አንዳንድ ተወዳዳሪዎች ውድድሩን ሰርዘው እንደሆነ ተጠይቀው፤ ማንም ውድድሩን እንዳልሰረዘ አስረግጠው ምላሽ ሰጥተዋል። ምክትላቸው ደግሞ "ኮቪድ-19 ቢኖርም ባይኖርም ውድድሮቹ ይካሄዳሉ" ብለዋል። የኦሎምፒክስ ሚንስትር ሴኮ ሃሺማቶ ውድድሩ "በዚህም አለ በዛ ይካሄዳል" ሲሉ ተናግረዋል። እስከ ቀጣዩ ዓመት ድረስ ለወረርሽኙ ክትባት ሊመረት እንደሚችል የሚጠቁሙ ዜናዎች እየተሰሙ ነው። | በቶክዮ ኦሎምፒክስ ታዳሚዎች ሊገኙ ይችላሉ ተባለ የዓለም አቀፉ ኦሎምፒክስ ኮሚቴ ኃላፊ ቶማስ ባህ፤ በቶክዮ ኦሎምፒክስ ላይ ታዳሚዎች እንደሚገኙ "በጣም እርግጠኛ ነኝ" አሉ። ታዳሚዎች ወደ ቶክዮ ከመሄዳቸው በፊት እንዲከተቡ ለማስቻል ኮሚቴው ጥረት እንደሚያደርግም አስታውቀዋል። አሁን ጃፓን ሄደው ስለ ኦሎምፒክስ ውድድር ውይይት እያደረጉ ነው። ዘንድሮ ሐምሌ ላይ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው ኦሎምፒክስ በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ተራዝሟል። በጎርጎሮሳውያኑ 2021 ሐምሌ ላይ ከ200 አገሮች የተውጣጡ 11,000 ተወዳዳሪዎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከጃፓኑ ጠቅላይ ሚንስትር ዮሺሂንዴ ሱጋ ጋር የተነጋገሩት የኦሎምፒክስ ኮሚቴ ኃላፊው ለኤኤፍፒ "በኦሎምፒክስ ስቴድየም ታዳሚዎች እንደምናስተናግድ በጣም እርግጠኛ ነን" ብለዋል። ከዓለም አቀፉ የኦሎምፒክስ ኮሚቴ ባሻገር ጃፓንም ውድድሩ እንደሚካሄድ ማረጋገጫ ሰጥታለች። የጃፓን ቶክዮ ኦሎምፒክስ 2020 ዋና ኃላፊ ቶሺሮ ሙቶ፤ ዓመቱ መባቻ ላይ አንዳንድ ውድድሮች በአነስተኛ ታዳሚዎች እንደሚካሄዱና አገራት የሚመድቧቸው የቡድን አባላት ሊቀነሱ እንደሚችሉም ተናግረው ነበር። የዓለም አቀፉ ኦሎምፒክስ ኮሚቴ ኃላፊ ቶማስ ባህ ባለፈው ሳምንት አንዳንድ ተወዳዳሪዎች ውድድሩን ሰርዘው እንደሆነ ተጠይቀው፤ ማንም ውድድሩን እንዳልሰረዘ አስረግጠው ምላሽ ሰጥተዋል። ምክትላቸው ደግሞ "ኮቪድ-19 ቢኖርም ባይኖርም ውድድሮቹ ይካሄዳሉ" ብለዋል። የኦሎምፒክስ ሚንስትር ሴኮ ሃሺማቶ ውድድሩ "በዚህም አለ በዛ ይካሄዳል" ሲሉ ተናግረዋል። እስከ ቀጣዩ ዓመት ድረስ ለወረርሽኙ ክትባት ሊመረት እንደሚችል የሚጠቁሙ ዜናዎች እየተሰሙ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/54958645 |
0business
| የዓለማችን ምርጥ 10 አየር መንገዶች የትኞቹ ናቸው? | ስካይትራክስ ዎርልድ ኤይርላይን አዋርድስ በአሁኑ ወቅት የዓለማችን ምርጥ ናቸው ያላቸውን አየር መንገዶች ይፋ አድርጓል። በኢቪዬሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ ትልቅ ግምት ከሚሰጣቸው ሽልማቶች መካከል አንዱ የሆነው ስካይትራክስ ዎርልድ ኤይርላይን አዋርድስ፤ በ2021 የዓለማችን ምርጡ አየር መንገድ የኳታሩ፤ ኳታር ኤይርዌይስ ነው ብሏል። ስካይትራክስ ባለፉት 23 ወራት ከ13 ሚሊዮን በላይ ተጓዦች ባሰባስብኩት ባለው መረጃ መሠረት ከኳታር ኤየርዌይስ በመቀጠል፤ ትናንት በይፋ በተገለጸው የስካይትራክስ ዎርልድ ኤይርላይን አዋርድስ ከላይ ከተጠቀሱት በመቀጠል እንደ ቅድመ ተከተላቸው ምርጥ 10 የዓለማችን አየር መንዶች ውስጥ የተካተቱት አየር መንገዶች፤ ካቲ ፓሲፊክ አየር መንገድ፣ ኢቫ ኤይር፣ ካንታስ አየር መንገድ፣ ሃይናን አየር መንድ እና የፈንሳይ አየር መንድ ናቸው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚህ ዓመት ቀድሞ ከነበረበት ደረጃ 7 ደረጃዎችን በማሻሻል ከዓለም 37ኛ ደረጃን ይዟል። በአፍሪካ ከሚገኙ አየር መንዶች መካከል የኬንያ አየር መንድ 79ኛ፣ የሞሮኮው ሮያል ኤይር ማሮክ 81ኛ እንዲሁም ኤይር ሞሪሺየስ 82 ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። የአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ ተብሎ በስካይትራክስ ዎርልድ ኤይርላይን አዋርድስ ተሸልሟል። ከዚህ በተጨማሪም አየር መንገዱ በተጨማሪ ሦስት ዘርፎች አህጉራዊ ምርጥ አየር መንገድ ተብሏል። አየር መንገዱ በአፍሪካ ምርጡ ቢዝነስ እና ኢኮኖሚ ክላስ ተብሎ ተሸልሟል። በአፍሪካ ምርጡ ካቢን ክሩ (የበረራ ሠራተኞች) የያዘ አየር መንገድ ተብሎ ስካይትሬክስ ዎርልድ ኤየርላይን ሽልማትን ወስዷል። ሽልማቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተወልደ ገ/ማርያም፤ ኩባንያቸው የስካይትራክስ ሽልማት ማግኘቱ፤ አየር መንገዱ ለመንገደኞቹ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት እያቀረበ መሆኑን ያረጋገጠ ነው ብለዋል። ዋና ሥራ አስፈጻሚው ". . . የስካይትራክስ ሽልማት አየር መንገዱ በትክክለኛው አቅጣጫ እያመራ እንደሆነ ያሳያል በዚህም ጥልቅ በሆነ ኩራት እነዚህን ሽልማቶች እንቀበላለን" ብለዋል። ሌሎች ምርጥ አህጉራዊ አየር መንገዶች ስካይትራክስ የፈረንሳዩ ኤየር ፍራንስ የአውሮፓ ምርጡ አየር መንገድ ሲል መርጦታል። የእንግሊዙ ብሪቲሽ ኤይርዌየስ እና የጀርመኑ ሉፍታንዛ ደግሞ ከኤይር ፍራንስ ቀጥሎ የአውሮፓ ምርጦቹ አየር መንዶች ተብለው ተመርጠዋል። በሰሜን አሜሪካ ካሉ አየር መንገዶች ደግሞ የአሜሪካው ዴልታ አየር መንገድ ቀዳሚውን ደረጃ ሲይዝ ጄትብሉ አየር መንገድ እና ኤይር ካናዳ ደግሞ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል። ኳታር አየር መንገድ በመካከለኛው ምሥራቅ ከሚገኙ አየር መንዶች መካከል ምርጡ የተባለ ሲሆን፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ፤ ኢሚሬትስ እና ኢትሃድ አየር መንገድ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል። የዳሰሳ ጥናቱን እንዴት ተከናወነ? ስካይትሬክስ ዎርልድ ኤይርላይን አዋርድስ በተለያዩ ዘርፎች ይሰጣል። ከእነዚህም መካከል የዓለማችን ምርጡ ንጹህ አየር መንገድ፣ ምርጥ ካቢን ክሩ (የበረራ ሠራተኞች) እና ምርጥ ቢዝነስ ክላስ የሚሰኙ ዘርፎች ይገኙበታል። ስካይትሬክስ ከመስከረም 2019 እስከ ሐምሌ 2021 ባሉት 23 ወራት 13.42 ሚሊዮን ተጓዦች ላይ የዳሰሳ ጥናት አድርጎ ባገኘው ውጤት መሠረት ምርጥ የሚላቸውን አየር መንዶች በተለያዩ ዘርፎች ይፋ ያደርጋል። ድርጅቱ እንደሚለው ከ100 በላይ ዜግነት ያላቸው ሰዎች በዳሰሳ ጥናቱ ተሳትፈዋል። ስካይትሬክ በዳሰሳ ጥናቱ ስለታሳተፉ ሰዎች ገንዘብ አይከፍልም። በዚህ የዳሰሳ ጥናት ላይ ከ350 በላይ አየር መንገዶች መሳተፋቸውንም ስካይትሬክ ገልጿል። | የዓለማችን ምርጥ 10 አየር መንገዶች የትኞቹ ናቸው? ስካይትራክስ ዎርልድ ኤይርላይን አዋርድስ በአሁኑ ወቅት የዓለማችን ምርጥ ናቸው ያላቸውን አየር መንገዶች ይፋ አድርጓል። በኢቪዬሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ ትልቅ ግምት ከሚሰጣቸው ሽልማቶች መካከል አንዱ የሆነው ስካይትራክስ ዎርልድ ኤይርላይን አዋርድስ፤ በ2021 የዓለማችን ምርጡ አየር መንገድ የኳታሩ፤ ኳታር ኤይርዌይስ ነው ብሏል። ስካይትራክስ ባለፉት 23 ወራት ከ13 ሚሊዮን በላይ ተጓዦች ባሰባስብኩት ባለው መረጃ መሠረት ከኳታር ኤየርዌይስ በመቀጠል፤ ትናንት በይፋ በተገለጸው የስካይትራክስ ዎርልድ ኤይርላይን አዋርድስ ከላይ ከተጠቀሱት በመቀጠል እንደ ቅድመ ተከተላቸው ምርጥ 10 የዓለማችን አየር መንዶች ውስጥ የተካተቱት አየር መንገዶች፤ ካቲ ፓሲፊክ አየር መንገድ፣ ኢቫ ኤይር፣ ካንታስ አየር መንገድ፣ ሃይናን አየር መንድ እና የፈንሳይ አየር መንድ ናቸው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚህ ዓመት ቀድሞ ከነበረበት ደረጃ 7 ደረጃዎችን በማሻሻል ከዓለም 37ኛ ደረጃን ይዟል። በአፍሪካ ከሚገኙ አየር መንዶች መካከል የኬንያ አየር መንድ 79ኛ፣ የሞሮኮው ሮያል ኤይር ማሮክ 81ኛ እንዲሁም ኤይር ሞሪሺየስ 82 ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። የአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ ተብሎ በስካይትራክስ ዎርልድ ኤይርላይን አዋርድስ ተሸልሟል። ከዚህ በተጨማሪም አየር መንገዱ በተጨማሪ ሦስት ዘርፎች አህጉራዊ ምርጥ አየር መንገድ ተብሏል። አየር መንገዱ በአፍሪካ ምርጡ ቢዝነስ እና ኢኮኖሚ ክላስ ተብሎ ተሸልሟል። በአፍሪካ ምርጡ ካቢን ክሩ (የበረራ ሠራተኞች) የያዘ አየር መንገድ ተብሎ ስካይትሬክስ ዎርልድ ኤየርላይን ሽልማትን ወስዷል። ሽልማቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተወልደ ገ/ማርያም፤ ኩባንያቸው የስካይትራክስ ሽልማት ማግኘቱ፤ አየር መንገዱ ለመንገደኞቹ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት እያቀረበ መሆኑን ያረጋገጠ ነው ብለዋል። ዋና ሥራ አስፈጻሚው ". . . የስካይትራክስ ሽልማት አየር መንገዱ በትክክለኛው አቅጣጫ እያመራ እንደሆነ ያሳያል በዚህም ጥልቅ በሆነ ኩራት እነዚህን ሽልማቶች እንቀበላለን" ብለዋል። ሌሎች ምርጥ አህጉራዊ አየር መንገዶች ስካይትራክስ የፈረንሳዩ ኤየር ፍራንስ የአውሮፓ ምርጡ አየር መንገድ ሲል መርጦታል። የእንግሊዙ ብሪቲሽ ኤይርዌየስ እና የጀርመኑ ሉፍታንዛ ደግሞ ከኤይር ፍራንስ ቀጥሎ የአውሮፓ ምርጦቹ አየር መንዶች ተብለው ተመርጠዋል። በሰሜን አሜሪካ ካሉ አየር መንገዶች ደግሞ የአሜሪካው ዴልታ አየር መንገድ ቀዳሚውን ደረጃ ሲይዝ ጄትብሉ አየር መንገድ እና ኤይር ካናዳ ደግሞ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል። ኳታር አየር መንገድ በመካከለኛው ምሥራቅ ከሚገኙ አየር መንዶች መካከል ምርጡ የተባለ ሲሆን፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ፤ ኢሚሬትስ እና ኢትሃድ አየር መንገድ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል። የዳሰሳ ጥናቱን እንዴት ተከናወነ? ስካይትሬክስ ዎርልድ ኤይርላይን አዋርድስ በተለያዩ ዘርፎች ይሰጣል። ከእነዚህም መካከል የዓለማችን ምርጡ ንጹህ አየር መንገድ፣ ምርጥ ካቢን ክሩ (የበረራ ሠራተኞች) እና ምርጥ ቢዝነስ ክላስ የሚሰኙ ዘርፎች ይገኙበታል። ስካይትሬክስ ከመስከረም 2019 እስከ ሐምሌ 2021 ባሉት 23 ወራት 13.42 ሚሊዮን ተጓዦች ላይ የዳሰሳ ጥናት አድርጎ ባገኘው ውጤት መሠረት ምርጥ የሚላቸውን አየር መንዶች በተለያዩ ዘርፎች ይፋ ያደርጋል። ድርጅቱ እንደሚለው ከ100 በላይ ዜግነት ያላቸው ሰዎች በዳሰሳ ጥናቱ ተሳትፈዋል። ስካይትሬክ በዳሰሳ ጥናቱ ስለታሳተፉ ሰዎች ገንዘብ አይከፍልም። በዚህ የዳሰሳ ጥናት ላይ ከ350 በላይ አየር መንገዶች መሳተፋቸውንም ስካይትሬክ ገልጿል። | https://www.bbc.com/amharic/news-58867140 |
5sports
| 2019 የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር | . | 2019 የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር . | https://www.bbc.com/amharic/news-48640190 |
3politics
| ምርጫ ቦርድ ብልፅግናን ጨምሮ በርካታ ፓርቲዎችን አሳሰበ | የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ገዢው ፓርቲ ብልፅግናን ጨምሮ በርካታ ፓርቲዎች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ጠቅላላ ጉባዔያቸውን እንዲያደርጉ አሳስቧል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዳር 23/ 2014 ዓ.ም ከፓርቲዎች ጋር ባደረገው ውይይት ከስድስተኛው አገራዊ ምርጫ መጠናቀቅ በኋላ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሂዱ ገልጦላቸው ነበር። ነገር ግን ፓርቲዎቹ የሚጠበቅባቸውን አጠናቀው ባለማቅረባቸው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተነሳ በአንድ ወር ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤያቸውን እንዲያከናውኑ እና ለቦርዱ እንዲያስገቡ መወሰኑ ይታወሳል ሲል ቦርዱ ያወጣው መግለጫ ያትታል። አሁን የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በማንሳቱ ፓርቲዎቹ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ጠቅላላ ጉባዔያቸውን እንዲያደርጉ እንዲሁም የሰነድ ማሻሻያ እንዲከውኑ አሳስቧል። ካለፈው ሃገራዊ ምርጫ በኋላ ጠቅላላ ጉባዔ አላደረጉም፤ አልፎም የሰነድ ማሻሻያ አላከናወኑም ተብሎ በቦርዱ የተጠቀሱት 26 ፓርቲዎች ናቸው። ገዢው ብልፅግናን ጨምሮ 13 ሃገራዊና 13 ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቦርዱ ባወጣው መግለጫ ላይ ስማቸው ተጠቅሷል። ቦርዱ በማሕበራዊ ድር አምባ ገፆቹ በለጠፈው መግለጫ ስማቸው ከተጠቀሰ ፓርቲዎች መካከል የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ይገኙበታል። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተራዝሞ የነበረው ሃገራዊው ምርጫ ባለፈው ዓመት ተካሂዶ ገዢው ፓርቲ አብዛኛውን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ማግኘቱ ይታወሳል። | ምርጫ ቦርድ ብልፅግናን ጨምሮ በርካታ ፓርቲዎችን አሳሰበ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ገዢው ፓርቲ ብልፅግናን ጨምሮ በርካታ ፓርቲዎች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ጠቅላላ ጉባዔያቸውን እንዲያደርጉ አሳስቧል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዳር 23/ 2014 ዓ.ም ከፓርቲዎች ጋር ባደረገው ውይይት ከስድስተኛው አገራዊ ምርጫ መጠናቀቅ በኋላ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሂዱ ገልጦላቸው ነበር። ነገር ግን ፓርቲዎቹ የሚጠበቅባቸውን አጠናቀው ባለማቅረባቸው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተነሳ በአንድ ወር ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤያቸውን እንዲያከናውኑ እና ለቦርዱ እንዲያስገቡ መወሰኑ ይታወሳል ሲል ቦርዱ ያወጣው መግለጫ ያትታል። አሁን የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በማንሳቱ ፓርቲዎቹ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ጠቅላላ ጉባዔያቸውን እንዲያደርጉ እንዲሁም የሰነድ ማሻሻያ እንዲከውኑ አሳስቧል። ካለፈው ሃገራዊ ምርጫ በኋላ ጠቅላላ ጉባዔ አላደረጉም፤ አልፎም የሰነድ ማሻሻያ አላከናወኑም ተብሎ በቦርዱ የተጠቀሱት 26 ፓርቲዎች ናቸው። ገዢው ብልፅግናን ጨምሮ 13 ሃገራዊና 13 ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቦርዱ ባወጣው መግለጫ ላይ ስማቸው ተጠቅሷል። ቦርዱ በማሕበራዊ ድር አምባ ገፆቹ በለጠፈው መግለጫ ስማቸው ከተጠቀሰ ፓርቲዎች መካከል የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ይገኙበታል። በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተራዝሞ የነበረው ሃገራዊው ምርጫ ባለፈው ዓመት ተካሂዶ ገዢው ፓርቲ አብዛኛውን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ ማግኘቱ ይታወሳል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60413352 |
2health
| ’ኮሮናቫይረስ፡ ካልተከተቡ አይቀጠሩም’ የሚል ህግ ለአዳዲስ ሠራተኞች ተግባራዊ ሊሆን ይችላል | ኩባንያዎች አዳዲስ ሠራተኞቻቸው፣ ከመቀጠራቸው በፊት እንዲከተቡ ቢጠይቁ ህጋዊ ሊሆን ይችላል ሲሉ የእንግሊዝ የፍትህ ሚንስትር አስታወቁ። እንደሮበርት ባክላንድ ከሆነ ነባር ሠራተኞች ባላቸው ውል መሠረት ክትባቶችን እንዲወስዱ የመጠየቅ ነገር ላይኖር ይችላል። የአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ቢሮ ሰዎች በሥራቸው እንዲቀጥሉ ክትባት እንዲወስዱ ማዘዙ "አድሎአዊ" ነው ብሏል። ነገር ግን አንዳንድ ድርጅቶች ክትባቱን ለመውሰድ ፈቃደኛ ያልሆኑ አዳዲስ ሠራተኞችን እንደማይቀጥሩ ይናገራሉ፡፡ ባክላንድ ረቡዕ ዕለት ከአይቲቪ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ አዳዲስ በሥራ ውል ላይ በጽሑፍ እስከቀረበ ድረስ ሠራተኞችን እንዲከተቡ ማስገደድ ይቻል ይሆናል ብለዋል፡፡ ሆኖም አሠሪዎች ምናልባት ነባር ሠራተኞች እንዲህ ዓይነቱን ትዕዛዝ እምቢ ካሉ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ ሊያስፈልጋቸው ይችላል ተብሏል። አክለውም "ያለ ክትባት ሥራ የለም" የሚሉት መስፈርት ሕጋዊነት "በቅጥርና በልዩ ውል ላይ የተንጠለጠለ ነው" ብለዋል፡፡ "በአጠቃላይ አካሄዱን ሕጋዊ ያደረጉት አሁን ያሉት የሥራ ኮንትራቶች ቢኖሩ እደነቃለሁ፡፡ እውነቱን ለመናገር ጉዳዩ መፈተሽ ያለበት ይመስለኛል" ብለዋል፡፡ መቀመጫውን ለንደን ያደረገው የፒምሊኮ ፕለምበርስ ከህክምና ጋር በተያያዘ ካልሆነ በስተቀር ክትባቱን አልፈልግም የሚሉ አዳዲስ ሠራተኞችን አልቀጥርም ካሉት ኩባንያዎች አንዱ ነው፡፡ ከቅጥር ጋር በተያያዘ የሚሠሩ የህግ ባለሙያዎች በመጀመሪያ እርምጃው ላይ ጥያቄ ቢያነሱም መስራቹ ቻርሊ ሙሊንስ ህጋዊ እንደሆነ ምክር እንደተሰጣቸው ተናግረዋል፡፡ "እኛ በግልጽ ከጠበቆች ጋር የተነጋገርን ሲሆን ክትባቱ ሙሉ በሙሉ ከወጣ በኋላ ከእኛ ጋር ለሚጀምሩ ማናቸውም አዳዲስ ሠራተኞች የክትባቱ ጉዳይ በውሉ ውስጥ በመካተቱ ባለሙያዎቹ በጣም ደስተኞች ናቸው" ብለዋል ለቢቢሲ፡፡ "አዲሶቹን ኮንትራቶች ከሁለት እስከ ሶስት ወራቶች ውስጥ እንጠቀማቸዋለን፡፡ ሰዎች ከእኛ ጋር ሥራ ለመሥራት ሲመጡ ያንን በመፈረም ደስተኛ ካልሆኑ የእነሱ ምርጫ ነው። በእርግጠኝነትም ሥራው ከፒምሊኮ ፕላምበርስ አይሰጣቸውም" ሲሉ ገልጸዋል፡፡ የቤት እንክብካቤ ላይ የተሠማራው ባርቸስተር ሄልዝኬርም ሁሉም አዲስ ቅጥር ሠራተኞችየመከተብ ግዴታ አለባቸው ብሏል፡፡ "ከሠራተኞቻችን ጋር በተያያዘ ፍላጎት ያላቸውን ክትባቱን እንዲያገኙ ለማበረታታት የተቻለንን ሁሉ እያደረግን ነው። በተጨማሪም ሁሉም አዲስ ሠራተኞች ክትባቱን መውሰዳቸውን ሥራ ከመጀመራቸው በፊት ማረጋገጥ አለብን" ያለው ድርጅቱ ደንበኞቹን እና ሠራተኞቹን ጤንነት መጠበቅን ደግሞ በምክንያትነት አስቀምጧል። 'የህግ ክፍተት' ሌዊስ ሲልኪን በሚባለው የሕግ ኩባንያ የሕግ ዳይሬክተር የሆኑት ዴቪድ ሳሙኤል እንዳሉት ድርጅቶች በአዳዲስ ቅጥር ሠራተኞቻቸው ኮንትራቶች ውስጥ "ያለ ክትባት ሥራ የለም" የሚል አንቀጽን ከማስገባት የሚያግዳቸው ሕጋዊ ማዕቀፍ የለም፡፡ አሠሪዎች እያንዳንዱን የሥራ ሚና መተንተን እና እንዲህ ዓይነቱን ሐረግ ከማስተዋወቅ በፊት የጤና እና የደህንነትን አደጋዎችን መገምገም አለባቸው ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ ይህ ባለማድረጉና አንድ ሠራተኛ ያልተከተበት ምክንያት ቢኖረው ውሉ ኢ-ፍትሃዊ ወይም አድሎአዊ ነው ብሎ ለመከራከር ያስችለዋል፡፡ ሌሎች ስጋቶችም አሉ። ለምሳሌ ፣ "ካልተከተቡ ሥራ የለም" የሚለው ፖሊሲ ክትባቱን ለመውሰድ የመጨረሻ መስመር ላይ ባሉ ወጣቶች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ የሚል ስጋት አለ፡፡ "ይህን ለማጽደቅ ከባድ ይሆናል። በተለይም በዚያ ሂደት ውስጥ ካልገቡ እና ካልሰነዱት በሕጋዊ ጥያቄ የመፈታተናቸው ዕድላቸው ሰፊ ነው" ሲሉ ሳሙኤል ለቢቢሲ ገልጸዋል፡፡ የአንዳንድ ሠራተኞች የሥራ ሁኔታ በቢሮ ወይም በፋብሪካ እንዲሠሩ የሚያስገድድ ከሆነ ድርጅታቸው እንደዚህ ዓይነት አንቀፅ ሊቀመጥ ይችላል ወይ የሚል ጥያቄ እንደደረሳቸው አክለው ገልጸዋል፡፡ "ክትባት መውሰድ ግዴታ አይደለም፤ እናም አንድ ሰው እንዲወስድ ማስገደድ አድልአዊ ነው" ብለዋል የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል አቀባይ፡ | ’ኮሮናቫይረስ፡ ካልተከተቡ አይቀጠሩም’ የሚል ህግ ለአዳዲስ ሠራተኞች ተግባራዊ ሊሆን ይችላል ኩባንያዎች አዳዲስ ሠራተኞቻቸው፣ ከመቀጠራቸው በፊት እንዲከተቡ ቢጠይቁ ህጋዊ ሊሆን ይችላል ሲሉ የእንግሊዝ የፍትህ ሚንስትር አስታወቁ። እንደሮበርት ባክላንድ ከሆነ ነባር ሠራተኞች ባላቸው ውል መሠረት ክትባቶችን እንዲወስዱ የመጠየቅ ነገር ላይኖር ይችላል። የአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ቢሮ ሰዎች በሥራቸው እንዲቀጥሉ ክትባት እንዲወስዱ ማዘዙ "አድሎአዊ" ነው ብሏል። ነገር ግን አንዳንድ ድርጅቶች ክትባቱን ለመውሰድ ፈቃደኛ ያልሆኑ አዳዲስ ሠራተኞችን እንደማይቀጥሩ ይናገራሉ፡፡ ባክላንድ ረቡዕ ዕለት ከአይቲቪ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ አዳዲስ በሥራ ውል ላይ በጽሑፍ እስከቀረበ ድረስ ሠራተኞችን እንዲከተቡ ማስገደድ ይቻል ይሆናል ብለዋል፡፡ ሆኖም አሠሪዎች ምናልባት ነባር ሠራተኞች እንዲህ ዓይነቱን ትዕዛዝ እምቢ ካሉ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ ሊያስፈልጋቸው ይችላል ተብሏል። አክለውም "ያለ ክትባት ሥራ የለም" የሚሉት መስፈርት ሕጋዊነት "በቅጥርና በልዩ ውል ላይ የተንጠለጠለ ነው" ብለዋል፡፡ "በአጠቃላይ አካሄዱን ሕጋዊ ያደረጉት አሁን ያሉት የሥራ ኮንትራቶች ቢኖሩ እደነቃለሁ፡፡ እውነቱን ለመናገር ጉዳዩ መፈተሽ ያለበት ይመስለኛል" ብለዋል፡፡ መቀመጫውን ለንደን ያደረገው የፒምሊኮ ፕለምበርስ ከህክምና ጋር በተያያዘ ካልሆነ በስተቀር ክትባቱን አልፈልግም የሚሉ አዳዲስ ሠራተኞችን አልቀጥርም ካሉት ኩባንያዎች አንዱ ነው፡፡ ከቅጥር ጋር በተያያዘ የሚሠሩ የህግ ባለሙያዎች በመጀመሪያ እርምጃው ላይ ጥያቄ ቢያነሱም መስራቹ ቻርሊ ሙሊንስ ህጋዊ እንደሆነ ምክር እንደተሰጣቸው ተናግረዋል፡፡ "እኛ በግልጽ ከጠበቆች ጋር የተነጋገርን ሲሆን ክትባቱ ሙሉ በሙሉ ከወጣ በኋላ ከእኛ ጋር ለሚጀምሩ ማናቸውም አዳዲስ ሠራተኞች የክትባቱ ጉዳይ በውሉ ውስጥ በመካተቱ ባለሙያዎቹ በጣም ደስተኞች ናቸው" ብለዋል ለቢቢሲ፡፡ "አዲሶቹን ኮንትራቶች ከሁለት እስከ ሶስት ወራቶች ውስጥ እንጠቀማቸዋለን፡፡ ሰዎች ከእኛ ጋር ሥራ ለመሥራት ሲመጡ ያንን በመፈረም ደስተኛ ካልሆኑ የእነሱ ምርጫ ነው። በእርግጠኝነትም ሥራው ከፒምሊኮ ፕላምበርስ አይሰጣቸውም" ሲሉ ገልጸዋል፡፡ የቤት እንክብካቤ ላይ የተሠማራው ባርቸስተር ሄልዝኬርም ሁሉም አዲስ ቅጥር ሠራተኞችየመከተብ ግዴታ አለባቸው ብሏል፡፡ "ከሠራተኞቻችን ጋር በተያያዘ ፍላጎት ያላቸውን ክትባቱን እንዲያገኙ ለማበረታታት የተቻለንን ሁሉ እያደረግን ነው። በተጨማሪም ሁሉም አዲስ ሠራተኞች ክትባቱን መውሰዳቸውን ሥራ ከመጀመራቸው በፊት ማረጋገጥ አለብን" ያለው ድርጅቱ ደንበኞቹን እና ሠራተኞቹን ጤንነት መጠበቅን ደግሞ በምክንያትነት አስቀምጧል። 'የህግ ክፍተት' ሌዊስ ሲልኪን በሚባለው የሕግ ኩባንያ የሕግ ዳይሬክተር የሆኑት ዴቪድ ሳሙኤል እንዳሉት ድርጅቶች በአዳዲስ ቅጥር ሠራተኞቻቸው ኮንትራቶች ውስጥ "ያለ ክትባት ሥራ የለም" የሚል አንቀጽን ከማስገባት የሚያግዳቸው ሕጋዊ ማዕቀፍ የለም፡፡ አሠሪዎች እያንዳንዱን የሥራ ሚና መተንተን እና እንዲህ ዓይነቱን ሐረግ ከማስተዋወቅ በፊት የጤና እና የደህንነትን አደጋዎችን መገምገም አለባቸው ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ ይህ ባለማድረጉና አንድ ሠራተኛ ያልተከተበት ምክንያት ቢኖረው ውሉ ኢ-ፍትሃዊ ወይም አድሎአዊ ነው ብሎ ለመከራከር ያስችለዋል፡፡ ሌሎች ስጋቶችም አሉ። ለምሳሌ ፣ "ካልተከተቡ ሥራ የለም" የሚለው ፖሊሲ ክትባቱን ለመውሰድ የመጨረሻ መስመር ላይ ባሉ ወጣቶች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ የሚል ስጋት አለ፡፡ "ይህን ለማጽደቅ ከባድ ይሆናል። በተለይም በዚያ ሂደት ውስጥ ካልገቡ እና ካልሰነዱት በሕጋዊ ጥያቄ የመፈታተናቸው ዕድላቸው ሰፊ ነው" ሲሉ ሳሙኤል ለቢቢሲ ገልጸዋል፡፡ የአንዳንድ ሠራተኞች የሥራ ሁኔታ በቢሮ ወይም በፋብሪካ እንዲሠሩ የሚያስገድድ ከሆነ ድርጅታቸው እንደዚህ ዓይነት አንቀፅ ሊቀመጥ ይችላል ወይ የሚል ጥያቄ እንደደረሳቸው አክለው ገልጸዋል፡፡ "ክትባት መውሰድ ግዴታ አይደለም፤ እናም አንድ ሰው እንዲወስድ ማስገደድ አድልአዊ ነው" ብለዋል የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል አቀባይ፡ | https://www.bbc.com/amharic/news-56121979 |
5sports
| እውቁ ተጫዋች እግር ኳሰኞች ዘረኝነትን በመጠየፍ ማሕበራዊ ሚድያን መተው አለባቸው ይላል | የእንግሊዝ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝና የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋች ፊል ኔቪል እግር ኳስ ተጫዋቾች እራሳቸውን ከማሕበራዊ ሚድያ በማግለል ዘረኝነትን እንደሚጠየፉ ማሳየት አለባቸው ሲል አሳስቧል። ሰኞ ምሽት ማንችስተር ዩናይትድ ከዎልቭስ ጋር በነበረው ጨዋታ ፖል ፖግባ ፍፁም ቅጣት መሳቱን ተከትሎ ማሕበራዊ ድር አምባዎች ላይ ዘረኝነት የተጠናወታቸው ትችቶች ቀርበውበት ነበር። «እስከመቼ ነው እንዲህ የምንዘልቀው? ተጫዋቾቼ ያጋጥማቸዋል፤ ፕሪሚዬር ሊግ ላይ አለ፤ እንዲሁም ቻምፒዮንስ ሊግ ላይ። ትዊተርም ሆነ ኢንስታግራም ግድ ከሌላቸው እኛ የሆነ ነገር ማድግ አለብን» ብሏል ኔቪል። በሁኔታው እግጅ የበገነው ኔቪል «እኔ ማሕበራዊ ድር አምባን በሚዘውሩ ሰዎች ተስፋ ቆርጫለሁ» ይላል። «ሁኔታውን እየተከታተልን ነው ብለው ኢሜይል ይልኩልሃ። ነገር ግን ምን ሲፈጠር አታይም።» ለዚያም ነው ማሕበራዊ ሚድያን ማግለል ያዋጣል የሚለው ኔቪል። «ቢያንስ ለ6 ወራት ማቋረጥ። እስቲ ምን እንደሚፈጠር እንይ» ብሏል። ፖል ፖግባ ላይ ዘረኛ አስተያየቶች ከተሰጡ በኋላ ትዊተር ሁኔታውን 'አምርሮ እንደሚቃወም' አሳውቆ 'የተወሰኑ ገፆችን ዘግቻለሁ' ብሏል። ድርጅቱ 'በተለይ እንግሊዝ ውስጥ በሚጫወቱ ተጫዋቾች ላይ የበይነ-መረብ ዘረኝነት ጥቃት እየተሰነዘረ መሆኑን ተረድናል' ሲል አትቷል። • ማንቸስተር ሲቲ፡ የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ አደጋ? ፌስቡክም እንዲሁ ለዘረኛ አስተያየቶች 'ቦት እንደሌለው' አሳውቆ ኢንስታግራምን ጨምሮ በሌሎች መድረኮች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን ለመመከት እየሠራን ነው ሲል ገልጿል። የፈረንሳዊው እግር ኳሰኞ ፖግባ የሥራ ባልደረቦች በይነ-መረብ ላይ ያስተዋሏቸውን ፀያፍ እና ዘረኛ ጥቃቶች አምርረው አውግዘዋል። ሃሪ ማክጓዬር፣ ማርከስ ራሽፎርድ እና ዴቪድ ዲ ሂያ ጥቂቶቹ ናቸው። የዩናይትድ አመራሮችም ጥቃቱን እንደሚቃወሙ ለማሳወቅ ጊዜ አልወሰደባቸውም። | እውቁ ተጫዋች እግር ኳሰኞች ዘረኝነትን በመጠየፍ ማሕበራዊ ሚድያን መተው አለባቸው ይላል የእንግሊዝ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝና የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋች ፊል ኔቪል እግር ኳስ ተጫዋቾች እራሳቸውን ከማሕበራዊ ሚድያ በማግለል ዘረኝነትን እንደሚጠየፉ ማሳየት አለባቸው ሲል አሳስቧል። ሰኞ ምሽት ማንችስተር ዩናይትድ ከዎልቭስ ጋር በነበረው ጨዋታ ፖል ፖግባ ፍፁም ቅጣት መሳቱን ተከትሎ ማሕበራዊ ድር አምባዎች ላይ ዘረኝነት የተጠናወታቸው ትችቶች ቀርበውበት ነበር። «እስከመቼ ነው እንዲህ የምንዘልቀው? ተጫዋቾቼ ያጋጥማቸዋል፤ ፕሪሚዬር ሊግ ላይ አለ፤ እንዲሁም ቻምፒዮንስ ሊግ ላይ። ትዊተርም ሆነ ኢንስታግራም ግድ ከሌላቸው እኛ የሆነ ነገር ማድግ አለብን» ብሏል ኔቪል። በሁኔታው እግጅ የበገነው ኔቪል «እኔ ማሕበራዊ ድር አምባን በሚዘውሩ ሰዎች ተስፋ ቆርጫለሁ» ይላል። «ሁኔታውን እየተከታተልን ነው ብለው ኢሜይል ይልኩልሃ። ነገር ግን ምን ሲፈጠር አታይም።» ለዚያም ነው ማሕበራዊ ሚድያን ማግለል ያዋጣል የሚለው ኔቪል። «ቢያንስ ለ6 ወራት ማቋረጥ። እስቲ ምን እንደሚፈጠር እንይ» ብሏል። ፖል ፖግባ ላይ ዘረኛ አስተያየቶች ከተሰጡ በኋላ ትዊተር ሁኔታውን 'አምርሮ እንደሚቃወም' አሳውቆ 'የተወሰኑ ገፆችን ዘግቻለሁ' ብሏል። ድርጅቱ 'በተለይ እንግሊዝ ውስጥ በሚጫወቱ ተጫዋቾች ላይ የበይነ-መረብ ዘረኝነት ጥቃት እየተሰነዘረ መሆኑን ተረድናል' ሲል አትቷል። • ማንቸስተር ሲቲ፡ የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ አደጋ? ፌስቡክም እንዲሁ ለዘረኛ አስተያየቶች 'ቦት እንደሌለው' አሳውቆ ኢንስታግራምን ጨምሮ በሌሎች መድረኮች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን ለመመከት እየሠራን ነው ሲል ገልጿል። የፈረንሳዊው እግር ኳሰኞ ፖግባ የሥራ ባልደረቦች በይነ-መረብ ላይ ያስተዋሏቸውን ፀያፍ እና ዘረኛ ጥቃቶች አምርረው አውግዘዋል። ሃሪ ማክጓዬር፣ ማርከስ ራሽፎርድ እና ዴቪድ ዲ ሂያ ጥቂቶቹ ናቸው። የዩናይትድ አመራሮችም ጥቃቱን እንደሚቃወሙ ለማሳወቅ ጊዜ አልወሰደባቸውም። | https://www.bbc.com/amharic/news-49417562 |
0business
| ኮሮናቫይረስ፡ ኢትዮጵያ የሞባይል ባንኪንግን ዘርፍ ለአገር በቀል ኩባንያዎች ክፍት አደረገች | በባንኮችና በጥቃቅን የገንዘብ ድርጅቶች ተይዞ የነበረውን የሞባይል ባንኪንግ ዘርፍ ለሌሎችም ድርጅቶችም ክፍት እንዲሆን ብሔራዊ ባንክ ባወጣው አዲስ መመሪያ ወሰነ። ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የጥሬ ገንዘብን በመጠቀም የሚፈጠረው ግንኙነት ለመቀነስ ኢትዮጵያ በሞባይል ባንኪንግ ያላትን ህግ በማላላት የአገር ውስጥ ባለኃብቶች እንዲሰማሩበት ክፍት አድርጋለች። ይህም ንክኪን ለመቀነስና ህዝቡ ሙሉ በሙሉ ጥሬ ገንዘብ መጠቀምን ያቆማል ተብሏል። •ኢትዮጵያ፡ ሁለት ሰዎች ከኮቪድ-19 መዳናቸው ተገለፀ •በአማራ ክልል ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የትምህርት ተቋማት ለመጠለያነት ተዘጋጁ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው አዲስ መመሪያ መሰረትም ፈቃድ ለማውጣት የሚፈልጉ አምሳ ሚሊዮን ብር፣ ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆን እንዲሁም 10 ባለድርሻ ያሉት አክሲዮን መሆን እንዳለባቸው አስታውቋል። መመሪያውም ከትናንትና መጋቢት 24፣2012 ዓ.ም ጀምሮ በተግባር ላይ የዋለ ሲሆን በቀን ስምንት ሺ ብር ያህል እንዲሁም በወር 60ሺ ብር ማውጣት ይቻላል። የሞባይል ባንኪንግ ፈቃድ ያላቸው ኩባንያዎችም ገንዘብ የማስቀመጥ፣ ብድር፣ ኢንሹራንስ እንዲሁም ሌሎች አገልግሎት መስጠት ያስችላቸዋል። በመንግሥት ይዞታ ስር ያሉ ተቋማትም የሞባይል ባንኪንግ ፈቃድ መጠየቅ እንደሚችሉም ባንኩ በመመሪያው አስቀምጧል፥ ይህ ውሳኔም እንደ ኢትዮ ቴሌኮምም ሆነ ሌሎች ድርጅቶች እንዲወዳደሩ በር ይከፍትላቸዋል። •"ከቤት አትውጡ የሚሉን ልጆቼን ምን እንዳበላቸው ነው?" •በኮሮናቫይረስ የወረርሽኝ 'ዘመን' ተስፋ የሚሰጡ 5 ነገሮች በርካታ ኢትዮጵያውያን ግብይይት የሚፈፅሙት በጥሬ ገንዘብ ሲሆን የሞባይል ባንኪንግ እንደ ሌሎች አገራት የተለመደ አይደለም። በተለያየ ደረጃ የሚገኙ ባለስልጣናት ብዙዎች ቤታቸው እንዲቀመጡና በተጨናነቁ ስፍራዎች መገኘት እንዲቆጠቡ ምክርም ቢለግሱም ብዙዎች ወደ ባንኮች የሚያደርጉትን ጉዞ አልቀነሱም፤ በጥሬ ገንዘብ የሚደረጉ ንክኪዎችም አልቀነሱም። አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ከትራንስፖርት ጀምሮ የተለያዩ ክፍያዎችን የሚፈፅመው በጥሬ ገንዘብ ነው። | ኮሮናቫይረስ፡ ኢትዮጵያ የሞባይል ባንኪንግን ዘርፍ ለአገር በቀል ኩባንያዎች ክፍት አደረገች በባንኮችና በጥቃቅን የገንዘብ ድርጅቶች ተይዞ የነበረውን የሞባይል ባንኪንግ ዘርፍ ለሌሎችም ድርጅቶችም ክፍት እንዲሆን ብሔራዊ ባንክ ባወጣው አዲስ መመሪያ ወሰነ። ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የጥሬ ገንዘብን በመጠቀም የሚፈጠረው ግንኙነት ለመቀነስ ኢትዮጵያ በሞባይል ባንኪንግ ያላትን ህግ በማላላት የአገር ውስጥ ባለኃብቶች እንዲሰማሩበት ክፍት አድርጋለች። ይህም ንክኪን ለመቀነስና ህዝቡ ሙሉ በሙሉ ጥሬ ገንዘብ መጠቀምን ያቆማል ተብሏል። •ኢትዮጵያ፡ ሁለት ሰዎች ከኮቪድ-19 መዳናቸው ተገለፀ •በአማራ ክልል ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የትምህርት ተቋማት ለመጠለያነት ተዘጋጁ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው አዲስ መመሪያ መሰረትም ፈቃድ ለማውጣት የሚፈልጉ አምሳ ሚሊዮን ብር፣ ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆን እንዲሁም 10 ባለድርሻ ያሉት አክሲዮን መሆን እንዳለባቸው አስታውቋል። መመሪያውም ከትናንትና መጋቢት 24፣2012 ዓ.ም ጀምሮ በተግባር ላይ የዋለ ሲሆን በቀን ስምንት ሺ ብር ያህል እንዲሁም በወር 60ሺ ብር ማውጣት ይቻላል። የሞባይል ባንኪንግ ፈቃድ ያላቸው ኩባንያዎችም ገንዘብ የማስቀመጥ፣ ብድር፣ ኢንሹራንስ እንዲሁም ሌሎች አገልግሎት መስጠት ያስችላቸዋል። በመንግሥት ይዞታ ስር ያሉ ተቋማትም የሞባይል ባንኪንግ ፈቃድ መጠየቅ እንደሚችሉም ባንኩ በመመሪያው አስቀምጧል፥ ይህ ውሳኔም እንደ ኢትዮ ቴሌኮምም ሆነ ሌሎች ድርጅቶች እንዲወዳደሩ በር ይከፍትላቸዋል። •"ከቤት አትውጡ የሚሉን ልጆቼን ምን እንዳበላቸው ነው?" •በኮሮናቫይረስ የወረርሽኝ 'ዘመን' ተስፋ የሚሰጡ 5 ነገሮች በርካታ ኢትዮጵያውያን ግብይይት የሚፈፅሙት በጥሬ ገንዘብ ሲሆን የሞባይል ባንኪንግ እንደ ሌሎች አገራት የተለመደ አይደለም። በተለያየ ደረጃ የሚገኙ ባለስልጣናት ብዙዎች ቤታቸው እንዲቀመጡና በተጨናነቁ ስፍራዎች መገኘት እንዲቆጠቡ ምክርም ቢለግሱም ብዙዎች ወደ ባንኮች የሚያደርጉትን ጉዞ አልቀነሱም፤ በጥሬ ገንዘብ የሚደረጉ ንክኪዎችም አልቀነሱም። አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ከትራንስፖርት ጀምሮ የተለያዩ ክፍያዎችን የሚፈፅመው በጥሬ ገንዘብ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/52138509 |
3politics
| የሶሪያው ፕሬዝዳንት አሳድ ታሪካዊ የታባለ ጉብኝት በአረብ ኤምሬትስ አደረጉ | የሶሪያው የእርስ በእርስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ከ11 ዓመታት በኋላ ፕሬዝዳንት ባሻር አሳድ የመጀመሪያቸውን የአረብ አገር ጉብኝት በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ አድርገዋል። ጉብኝቱ በጦርነቱ ምክንያት አሳድን አግልለው የነበሩ የአረብ አገራት ዳግም ግንኙነታቸውን ሊያድሱ እንደሚችሉ አመላካች ነው ተብሏል። ሆኖም አሜሪካ ጉዞው "በጣም ቅር አሰኝቶኛል" ብላለች። ፕሬዝዳንት አሳድ በጉብኝታቸው ኤምሬትስ ውስጥ ካገኟቸው ሰዎች መካከል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ ውዝግቦች ስማቸው የሚናሳው የዱባዩ ቢልየነር ሼክ መሐመድ አል ማክቱም አንዱ ናቸው። ባለሐብቱ ካሏቸው 25 ልጆች መካከል አንዷ የሆነችው ላቲፋ እንደ አውሮፓውያኑ በ2018 ከዱባይ ለማምለጥ ያደረገችው ሙከራ ከከሸፈ በኋላ አሁን ታግታ እንደምትገኝ ተናግራ ነበር። እናም አሳድ ያገኟቸው እኚህ ባለሐብት በዚህ እና በሌሎች ጉዳዮች ስማቸው ይብጠለጣላል። በተጨማሪም አሳድ ወደ ተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ዋና ከተማ አቡዳቢ በመጓዝ ከልዑል አልጋ ወራሽ ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ለመገናኘት ችለዋል። "ሶሪያ ለአረብ አገራት ደኅንነት ቁልፍ እንደሆነች እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከአገሪቱ ጋር ያላትን ትብብር ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት አጽንኦት ሰጥተው መናገራቸውን" የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። መሪዎቹ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ለሶሪያ ፖለቲካዊ እና ሰብአዊ ድጋፍ ማድረግ በምትችልበት መንገድ እንዲሁም በአገራቱ ሕዝቦች መካከል ያለውን የኢኮኖሚና ንግድ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸው ተዘግቧል። ፕሬዝዳንት አሳድ ከማንቸስተር ሲቲ እግር ኳስ ክለብ ባለቤት ሼክ መንሱር ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ፎቶ ሲነሱም ታይተዋል። የሶሪያ ፕሬዝደንት በአገራቸው ከአስር ዓመት በፊት በተቀሰቀሰው ደም አፋሳሽ የእርስ በእርስ ጦርነት ሳቢያ 350,000 ሰዎችን መገደላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያመለከተ ሲሆን፣ ባሻር አል አሳድ ከጦርነት መጀመር ወዲህ በጣም ጥቂት ዓለም አቀፍ ጉዞዎችን ብቻ ነው ያደረጉት። ከዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ በተጨማሪ እስካሁን ድረስ ፕሬዝዳንት አሳድ በጦርነት የምትታመሰውን አገራቸውን ለቀው ወታደራዊ ድጋፍ ወደ ሚያደርጉላቸው ሩሲያ እና ኢራንን ተጉዘዋል። የፕሬዝዳንቱን ጉብኝት ተከትሎም የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ አሳድን ለመቀበል መወሰኗ በጣም አሳዛኝ እና ቅር የሚያሰኝ ነው ስትል አሜሪካ ገልጻለች። አሜሪካ በሶሪያ ያለውን የእርስ በርስ ጦርነትን መፍትሄ ለመስጠት መሻሻል እስኪታይ ድረስ ከሶሪያ መሪ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማደስ የሚደረጉ ጥረቶችን እንደምትቃወም ትገልጻለች። እንደ አብዛኞቹ የአረብ አገራት የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የበሶሪያ የእርስ በርስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ ከአገሪቱ ጋር ግንኙነቷን አቋርጣ የነበረ ሲሆን፣ የአማፅያኑ ተዋጊዎች የአሳድን መንግሥት ለመጣል ያደረጉትን ሙከራ የደገፈችበት ወቅትም ነበር። ሆኖም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሁለቱ አገራት ግንኙነት ቀስ በቀስ እየተሻሻለ ሲሆን ከአሜሪካ ተቃውሞ ቢያጋጥማትም የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ሶሪያን ከአረቡ ዓለም ጋር የነበራትን የቀድሞ ግንኙነት ለማደስ ጥረት እያደረገች ነው። እንደ አውሮፓውያኑ በ2018 የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ በሶሪያ ዋና ከተማ ደማስቆ የሚገኘውን ኤምባሲዋን ዳግም የከፈተች ሲሆን፣ ባለፈው ዓመት ዲፕሎማቶች ፕሬዚዳንት አሳድን እንዲያገኙ ልካ ነበር። | የሶሪያው ፕሬዝዳንት አሳድ ታሪካዊ የታባለ ጉብኝት በአረብ ኤምሬትስ አደረጉ የሶሪያው የእርስ በእርስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ከ11 ዓመታት በኋላ ፕሬዝዳንት ባሻር አሳድ የመጀመሪያቸውን የአረብ አገር ጉብኝት በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ አድርገዋል። ጉብኝቱ በጦርነቱ ምክንያት አሳድን አግልለው የነበሩ የአረብ አገራት ዳግም ግንኙነታቸውን ሊያድሱ እንደሚችሉ አመላካች ነው ተብሏል። ሆኖም አሜሪካ ጉዞው "በጣም ቅር አሰኝቶኛል" ብላለች። ፕሬዝዳንት አሳድ በጉብኝታቸው ኤምሬትስ ውስጥ ካገኟቸው ሰዎች መካከል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ ውዝግቦች ስማቸው የሚናሳው የዱባዩ ቢልየነር ሼክ መሐመድ አል ማክቱም አንዱ ናቸው። ባለሐብቱ ካሏቸው 25 ልጆች መካከል አንዷ የሆነችው ላቲፋ እንደ አውሮፓውያኑ በ2018 ከዱባይ ለማምለጥ ያደረገችው ሙከራ ከከሸፈ በኋላ አሁን ታግታ እንደምትገኝ ተናግራ ነበር። እናም አሳድ ያገኟቸው እኚህ ባለሐብት በዚህ እና በሌሎች ጉዳዮች ስማቸው ይብጠለጣላል። በተጨማሪም አሳድ ወደ ተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ዋና ከተማ አቡዳቢ በመጓዝ ከልዑል አልጋ ወራሽ ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ለመገናኘት ችለዋል። "ሶሪያ ለአረብ አገራት ደኅንነት ቁልፍ እንደሆነች እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከአገሪቱ ጋር ያላትን ትብብር ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት አጽንኦት ሰጥተው መናገራቸውን" የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። መሪዎቹ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ለሶሪያ ፖለቲካዊ እና ሰብአዊ ድጋፍ ማድረግ በምትችልበት መንገድ እንዲሁም በአገራቱ ሕዝቦች መካከል ያለውን የኢኮኖሚና ንግድ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸው ተዘግቧል። ፕሬዝዳንት አሳድ ከማንቸስተር ሲቲ እግር ኳስ ክለብ ባለቤት ሼክ መንሱር ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ፎቶ ሲነሱም ታይተዋል። የሶሪያ ፕሬዝደንት በአገራቸው ከአስር ዓመት በፊት በተቀሰቀሰው ደም አፋሳሽ የእርስ በእርስ ጦርነት ሳቢያ 350,000 ሰዎችን መገደላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያመለከተ ሲሆን፣ ባሻር አል አሳድ ከጦርነት መጀመር ወዲህ በጣም ጥቂት ዓለም አቀፍ ጉዞዎችን ብቻ ነው ያደረጉት። ከዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ በተጨማሪ እስካሁን ድረስ ፕሬዝዳንት አሳድ በጦርነት የምትታመሰውን አገራቸውን ለቀው ወታደራዊ ድጋፍ ወደ ሚያደርጉላቸው ሩሲያ እና ኢራንን ተጉዘዋል። የፕሬዝዳንቱን ጉብኝት ተከትሎም የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ አሳድን ለመቀበል መወሰኗ በጣም አሳዛኝ እና ቅር የሚያሰኝ ነው ስትል አሜሪካ ገልጻለች። አሜሪካ በሶሪያ ያለውን የእርስ በርስ ጦርነትን መፍትሄ ለመስጠት መሻሻል እስኪታይ ድረስ ከሶሪያ መሪ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማደስ የሚደረጉ ጥረቶችን እንደምትቃወም ትገልጻለች። እንደ አብዛኞቹ የአረብ አገራት የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የበሶሪያ የእርስ በርስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ ከአገሪቱ ጋር ግንኙነቷን አቋርጣ የነበረ ሲሆን፣ የአማፅያኑ ተዋጊዎች የአሳድን መንግሥት ለመጣል ያደረጉትን ሙከራ የደገፈችበት ወቅትም ነበር። ሆኖም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሁለቱ አገራት ግንኙነት ቀስ በቀስ እየተሻሻለ ሲሆን ከአሜሪካ ተቃውሞ ቢያጋጥማትም የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ሶሪያን ከአረቡ ዓለም ጋር የነበራትን የቀድሞ ግንኙነት ለማደስ ጥረት እያደረገች ነው። እንደ አውሮፓውያኑ በ2018 የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ በሶሪያ ዋና ከተማ ደማስቆ የሚገኘውን ኤምባሲዋን ዳግም የከፈተች ሲሆን፣ ባለፈው ዓመት ዲፕሎማቶች ፕሬዚዳንት አሳድን እንዲያገኙ ልካ ነበር። | https://www.bbc.com/amharic/news-60804731 |
5sports
| የማይክል ጆርዳን ማሊያ በ10.1 ሚሊዮን ዶላር ተሸጠ | የቅርጫት ኳስ ኮከቡ ማይክል ጆርዳን እአአ በ1998 የውድድር ዘመን የለበሰው ማሊያ ክብረ ወሰን በሆነ 10.1 ሚሊዮን ዶላር ተሽጧል። ይህም ከፍተኛ ዋጋ ያወጣ ስፖርት ቁሳቁስ ለመሆን በቅቷል። አጫራች ድርጅቱ ሰዘቢስ እንዳለው ሽያጩ ለስፖርት አድናቂዎች እና ለማስታወሻ ሰብሳቢዎች “ትልቅ ደስታን” የፈጠረ መሆኑን ተናግሯል። ጆርዳን ስድስተኛውን እና የመጨረሻውን የናሽናል ባስኬት ቦል አሶሴሽን (ኤንቢኤ) ዋንጫ ማሸነፉን የሚያስታውስ ማሊያ ነው ተብሏል። በውድድር ዓመቱ ዙሪያ ‘ዘ ላስት ዳንስ’ በሚል ኔትፍሊክስ የተዘጋጀ ዘጋቢ ፊልም አለ። ሰዘቢስ አጫራች ድርጅ ሐሙስ ዕለት እንዳስታወቀው ጆርዳን ለቺካጎ ቡልስ ሲጫወት የለበሰው ማሊያ 20 ተጫራቾችን ትኩረት ስቧል። የሰዘቢስ ኃላፊ ብራህም ዋቸር ተጫራቾች "ብርቅዬውን ታሪካዊ ልብስ ለመውሰድ ጓጉተዋል" ብለዋል። "የዛሬው ክብረወሰን የሰበረ ሽያጭ '... ማይክል ጆርዳን በማያሻማ መልኩ የምንግዜም ኮከብ መሆኑን የሚያጠናክር ነው። ዛሬም ስሙ እና ወደር የለሽ ትሩፋቱ ከዛሬ 25 ዓመት በፊት እንደነበረው ነው" ሲሉ ተናግረዋል። ዋጋው በ1986 የዓለም ዋንጫ ወቅት በእግር ኳስ ኮከቡ ዲዬጎ ማራዶና ለተለበሰውና 9.28 ሚሊዮን ዶላር ከተሸጠው ማሊያ በልጦ ክበረ ወሰኑን ይዟል። ጀርዳን የፊት ገጽ ሽፋን ከያዘበት እና እአአ ሰኔ 1998 ከታተመው ስፖርት ኢላስትሬትድ መጽሔት ጋር ነው ለጨረታ የቀረበው። ጆርዳን በቅርጫት ኳስ ታሪክ ምርጡ ተጫዋች እንደሆነ በብዙዎች ዘንድ ይታመናል። አብዛኛውን የጨዋታ ዘመኑን ቺካጎ ቡልስ ጋር አሳልፏል። በዚህም ዓለም አቀፋዊ ተምሳሌት ከመሆን ባለፈ የኤንቢኤን ስም በዓለም ዙሪያ ከፍ ለማድረግ አግዟል። ቺካጎ ቡልስ በኤንቢኤ የፍጻሜ ጨዋታ የመጀመሪያ ጨዋታን በዩታህ ጃዝ ተሸነፈ። የሚቀጥሉትን ሦስት ጨዋታዎች ቡልስ አሸነፈ። አምስተኛውን ጨዋታ ዩታህ ጃዝ በሁለት ነጥብ በልጦ ማሸነፍ ቻለ። በስድስተኛው ጨዋታ አንገት ለአንገት የተናነቁበት ነበር። ጆርዳን ጨዋታው 5.2 ሰከንዶች ሲቀሩት ቡልሶች 87-86 በሆነ ውጤት እንዲያሸንፉ ያስቻላቸውን ነጥቦች አስቆጠረ። ኮከቡ የመጨረሻውን የኤንቢኤ ዋንጫውን ከፍ ለማድረግ በቃ። ጆርዳን በሰሜን ካሮላይና የአባቱን መገደል ተከትሎ በ1993 ከቅርጫት ኳስ ራሱን አገለለ። ኮከቡ ቺካጎ ቡልስ ለሦስት ተከታታይ ዓመታት ሻምፒዮን እንዲሆን አስችሏል። ጆርዳን "ሁሌም አፅንዖት መስጠት እፈልጋለሁ... የመነሳሳት እና እንደ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች አንድ ነገር የማረጋገጥ ስሜት ሲጠፋብኝ ለማቆም ጊዜው አሁን ነው እላለሁ" ብሏል። 59 ዓመቱ ጆርዳን በ2003 ነበር ጫማውን ለመጨረሻ ጊዜ የሰቀለው። | የማይክል ጆርዳን ማሊያ በ10.1 ሚሊዮን ዶላር ተሸጠ የቅርጫት ኳስ ኮከቡ ማይክል ጆርዳን እአአ በ1998 የውድድር ዘመን የለበሰው ማሊያ ክብረ ወሰን በሆነ 10.1 ሚሊዮን ዶላር ተሽጧል። ይህም ከፍተኛ ዋጋ ያወጣ ስፖርት ቁሳቁስ ለመሆን በቅቷል። አጫራች ድርጅቱ ሰዘቢስ እንዳለው ሽያጩ ለስፖርት አድናቂዎች እና ለማስታወሻ ሰብሳቢዎች “ትልቅ ደስታን” የፈጠረ መሆኑን ተናግሯል። ጆርዳን ስድስተኛውን እና የመጨረሻውን የናሽናል ባስኬት ቦል አሶሴሽን (ኤንቢኤ) ዋንጫ ማሸነፉን የሚያስታውስ ማሊያ ነው ተብሏል። በውድድር ዓመቱ ዙሪያ ‘ዘ ላስት ዳንስ’ በሚል ኔትፍሊክስ የተዘጋጀ ዘጋቢ ፊልም አለ። ሰዘቢስ አጫራች ድርጅ ሐሙስ ዕለት እንዳስታወቀው ጆርዳን ለቺካጎ ቡልስ ሲጫወት የለበሰው ማሊያ 20 ተጫራቾችን ትኩረት ስቧል። የሰዘቢስ ኃላፊ ብራህም ዋቸር ተጫራቾች "ብርቅዬውን ታሪካዊ ልብስ ለመውሰድ ጓጉተዋል" ብለዋል። "የዛሬው ክብረወሰን የሰበረ ሽያጭ '... ማይክል ጆርዳን በማያሻማ መልኩ የምንግዜም ኮከብ መሆኑን የሚያጠናክር ነው። ዛሬም ስሙ እና ወደር የለሽ ትሩፋቱ ከዛሬ 25 ዓመት በፊት እንደነበረው ነው" ሲሉ ተናግረዋል። ዋጋው በ1986 የዓለም ዋንጫ ወቅት በእግር ኳስ ኮከቡ ዲዬጎ ማራዶና ለተለበሰውና 9.28 ሚሊዮን ዶላር ከተሸጠው ማሊያ በልጦ ክበረ ወሰኑን ይዟል። ጀርዳን የፊት ገጽ ሽፋን ከያዘበት እና እአአ ሰኔ 1998 ከታተመው ስፖርት ኢላስትሬትድ መጽሔት ጋር ነው ለጨረታ የቀረበው። ጆርዳን በቅርጫት ኳስ ታሪክ ምርጡ ተጫዋች እንደሆነ በብዙዎች ዘንድ ይታመናል። አብዛኛውን የጨዋታ ዘመኑን ቺካጎ ቡልስ ጋር አሳልፏል። በዚህም ዓለም አቀፋዊ ተምሳሌት ከመሆን ባለፈ የኤንቢኤን ስም በዓለም ዙሪያ ከፍ ለማድረግ አግዟል። ቺካጎ ቡልስ በኤንቢኤ የፍጻሜ ጨዋታ የመጀመሪያ ጨዋታን በዩታህ ጃዝ ተሸነፈ። የሚቀጥሉትን ሦስት ጨዋታዎች ቡልስ አሸነፈ። አምስተኛውን ጨዋታ ዩታህ ጃዝ በሁለት ነጥብ በልጦ ማሸነፍ ቻለ። በስድስተኛው ጨዋታ አንገት ለአንገት የተናነቁበት ነበር። ጆርዳን ጨዋታው 5.2 ሰከንዶች ሲቀሩት ቡልሶች 87-86 በሆነ ውጤት እንዲያሸንፉ ያስቻላቸውን ነጥቦች አስቆጠረ። ኮከቡ የመጨረሻውን የኤንቢኤ ዋንጫውን ከፍ ለማድረግ በቃ። ጆርዳን በሰሜን ካሮላይና የአባቱን መገደል ተከትሎ በ1993 ከቅርጫት ኳስ ራሱን አገለለ። ኮከቡ ቺካጎ ቡልስ ለሦስት ተከታታይ ዓመታት ሻምፒዮን እንዲሆን አስችሏል። ጆርዳን "ሁሌም አፅንዖት መስጠት እፈልጋለሁ... የመነሳሳት እና እንደ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች አንድ ነገር የማረጋገጥ ስሜት ሲጠፋብኝ ለማቆም ጊዜው አሁን ነው እላለሁ" ብሏል። 59 ዓመቱ ጆርዳን በ2003 ነበር ጫማውን ለመጨረሻ ጊዜ የሰቀለው። | https://www.bbc.com/amharic/articles/clj4g99l113o |
3politics
| ዩክሬን ግጭት፡ ጆ ባይደን ፑቲን ዩክሬንን ለመውረር መወሰናቸው "እርግጥ ነው" አሉ | የሩሲያው ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ላይ ወረራ ለመክፈት መወሰናቸው "እርግጥ መሆኑን" የአሜሪካው ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ተናገሩ። ጆ ባይደን ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምትፈፅመው ወረራ "በሚቀጥሉት ቀናት" ሊከሰት ይችላል ብለዋል። ፕሬዚደንቱ ይህን ያሉት የአሜሪካ የስለላ ድርጅት የዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ የወረራው ኢላማ እንደምትሆን ባወጣው መረጃ ላይ ተመስርተው እንደሆነ ተናግረዋል። ሩሲያ በበኩሏ ዩክሬንን ለመውረር አቅዳለች መባሏን በተደጋጋሚ አስተባብላለች። ምዕራባውያን አገራት ሩሲያ ጥቃት ለመሰንዘር ምክንያት ለመፍጠር በዩክሬን ተገንጣይ ምሥራቃዊ ክልሎች የሐሰት ቀውስ ለመፍጠር እየሞከረች ነው ሲሉ ይከሳሉ። በዩክሬን ውስጥ እና በድንበር አካባቢ ከ169 ሺህ እስከ 190 ሺህ የሩሲያ ሠራዊት አባላት እንደሚገኙ አሜሪካ ግምቷን አስቀምጣለች። ይህ አሃዝ ራስ ገዝ በሆኑትና በምሥራቅ ዩክሬን በሚገኙት ተገንጣዮቹ ዶኔትስክ እና ሉሃንስክ ሪፐብሊክ የሚገኙትን በሩሲያ የሚደገፉ ተዋጊዎችን የሚያካትት ነው። እነዚህ ክልሎች እአአ በ1922 ወደ ዩክሬን የተጠቃለሉ ሲሆን አብዛኞቹ ነዋሪዎች የመጀመሪያ ቋንቋቸው ሩሲያኛ ነው። ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ከዋይት ሐውስ በቴሌቪዥን በተላለፈው መግለጫቸው አሜሪካ የሩሲያ ኃይሎች በሚቀጥለው ሳምንት ዩክሬንን ለማጥቃት እቅድና ፍላጎት እንዳላቸው ለማመን የሚያስችል "በቂ ምክንያት" አላት ብለዋል። ባይደን አክለውም "ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ፑቲን ውሳኔውን መወሰኑን አምኛለሁ" ሲሉ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም ፐሬዚደንቱ እና ከፍተኛ ባለሥልጣኖቻቸው ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልትወስድ ስለምትችለው እርምጃ በእርግጠኝነት እንደማያውቁ ተናግረው ነበር። ሆኖም ፕሬዚደንት ባይደን ሩሲያ አሁንም ዲፕሎማሲያዊ መንገድን ልትመርጥ ትችላለች በማለት ውጥረቱን ለማርገብ እና ወደ ድርድር ጠረጴዛ ለመመለስ አሁንም አለመርፈዱን ገልጸዋል። አርብ ዕለት ውጥረቱ እየጨመረ በመምጣቱ የሁለቱ ተገንጣይ አካባቢ መሪዎች ዩክሬን ድብደባ ለመፈፀምና ጥቃት ለማድረስ አቅዳለች በማለት ነዋሪዎች ለቀው እንዲወጡ አስታውቀው ነበር። ይሁን እንጂ ዩክሬን ጥቃት የማድረስ እቅድ እንደሌላት በተደጋጋሚ ገልጻለች። የአገሪቷ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲሚይትሮ ኩሌባ "ይህ የሩሲያ የሐሰት መረጃ ነው" ሲሉም ክሱን አጣጥለውታል። የዶኔትስክ ሕዝቦች ሪፐብሊክ መሪ የሆኑት ዴኒስ ፐሺሊን፣ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ያሳሰቡት አርብ ዕለት በወጣ ተንቀሳቃሽ ምሥል አማካይነት ነው። ይሁን እንጂ ቢቢሲ ባደረገው የመረጃ ማጣራት ተንቀሳቃሽ ምሥሉ የተቀረጸው ከውጥረቱ መባባስ ከሁለት ቀናት በፊት መሆኑን ለማወቅ ችሏል። ዩክሬን፤ ፕሬዚደንት ፑቲን ከተገንጣይ አካባቢዎች ለሚፈልሱ ሰዎች የአደጋ ጊዜ እርዳታ ለማቅረብ በድንበር አቅራቢያ የስደተኞች መጠለያ እንዲቋቋሙ ማዘዛቸውን ገልጻለች። በርካታ የአካባቢዎቹን ነዋሪዎች የጫኑ አውቶብሶችም ወደ ሩሲያ ማምራታቸውን የሩሲያ መንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ መነገሩ ሩሲያ ጥቃቱን ለመሰንዘር ኃይሏን እያጠናከረች ላለው ዝግጅት ዓለምን ለማዘናጋት የተደረገ " የሞስኮ አሳፋሪ እርምጃ " ነው ብሎታል። ዋይት ሐውስ ነዋሪዎችን እንዲወጡ ማድረግ ሞስኮ ሐሰተኛ መረጃን ለጦርነት ሰበብ መጠቀሟን የሚያሳይ ምሳሌ ነው ብሏል። | ዩክሬን ግጭት፡ ጆ ባይደን ፑቲን ዩክሬንን ለመውረር መወሰናቸው "እርግጥ ነው" አሉ የሩሲያው ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ላይ ወረራ ለመክፈት መወሰናቸው "እርግጥ መሆኑን" የአሜሪካው ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ተናገሩ። ጆ ባይደን ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምትፈፅመው ወረራ "በሚቀጥሉት ቀናት" ሊከሰት ይችላል ብለዋል። ፕሬዚደንቱ ይህን ያሉት የአሜሪካ የስለላ ድርጅት የዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ የወረራው ኢላማ እንደምትሆን ባወጣው መረጃ ላይ ተመስርተው እንደሆነ ተናግረዋል። ሩሲያ በበኩሏ ዩክሬንን ለመውረር አቅዳለች መባሏን በተደጋጋሚ አስተባብላለች። ምዕራባውያን አገራት ሩሲያ ጥቃት ለመሰንዘር ምክንያት ለመፍጠር በዩክሬን ተገንጣይ ምሥራቃዊ ክልሎች የሐሰት ቀውስ ለመፍጠር እየሞከረች ነው ሲሉ ይከሳሉ። በዩክሬን ውስጥ እና በድንበር አካባቢ ከ169 ሺህ እስከ 190 ሺህ የሩሲያ ሠራዊት አባላት እንደሚገኙ አሜሪካ ግምቷን አስቀምጣለች። ይህ አሃዝ ራስ ገዝ በሆኑትና በምሥራቅ ዩክሬን በሚገኙት ተገንጣዮቹ ዶኔትስክ እና ሉሃንስክ ሪፐብሊክ የሚገኙትን በሩሲያ የሚደገፉ ተዋጊዎችን የሚያካትት ነው። እነዚህ ክልሎች እአአ በ1922 ወደ ዩክሬን የተጠቃለሉ ሲሆን አብዛኞቹ ነዋሪዎች የመጀመሪያ ቋንቋቸው ሩሲያኛ ነው። ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ከዋይት ሐውስ በቴሌቪዥን በተላለፈው መግለጫቸው አሜሪካ የሩሲያ ኃይሎች በሚቀጥለው ሳምንት ዩክሬንን ለማጥቃት እቅድና ፍላጎት እንዳላቸው ለማመን የሚያስችል "በቂ ምክንያት" አላት ብለዋል። ባይደን አክለውም "ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ፑቲን ውሳኔውን መወሰኑን አምኛለሁ" ሲሉ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም ፐሬዚደንቱ እና ከፍተኛ ባለሥልጣኖቻቸው ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልትወስድ ስለምትችለው እርምጃ በእርግጠኝነት እንደማያውቁ ተናግረው ነበር። ሆኖም ፕሬዚደንት ባይደን ሩሲያ አሁንም ዲፕሎማሲያዊ መንገድን ልትመርጥ ትችላለች በማለት ውጥረቱን ለማርገብ እና ወደ ድርድር ጠረጴዛ ለመመለስ አሁንም አለመርፈዱን ገልጸዋል። አርብ ዕለት ውጥረቱ እየጨመረ በመምጣቱ የሁለቱ ተገንጣይ አካባቢ መሪዎች ዩክሬን ድብደባ ለመፈፀምና ጥቃት ለማድረስ አቅዳለች በማለት ነዋሪዎች ለቀው እንዲወጡ አስታውቀው ነበር። ይሁን እንጂ ዩክሬን ጥቃት የማድረስ እቅድ እንደሌላት በተደጋጋሚ ገልጻለች። የአገሪቷ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲሚይትሮ ኩሌባ "ይህ የሩሲያ የሐሰት መረጃ ነው" ሲሉም ክሱን አጣጥለውታል። የዶኔትስክ ሕዝቦች ሪፐብሊክ መሪ የሆኑት ዴኒስ ፐሺሊን፣ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ያሳሰቡት አርብ ዕለት በወጣ ተንቀሳቃሽ ምሥል አማካይነት ነው። ይሁን እንጂ ቢቢሲ ባደረገው የመረጃ ማጣራት ተንቀሳቃሽ ምሥሉ የተቀረጸው ከውጥረቱ መባባስ ከሁለት ቀናት በፊት መሆኑን ለማወቅ ችሏል። ዩክሬን፤ ፕሬዚደንት ፑቲን ከተገንጣይ አካባቢዎች ለሚፈልሱ ሰዎች የአደጋ ጊዜ እርዳታ ለማቅረብ በድንበር አቅራቢያ የስደተኞች መጠለያ እንዲቋቋሙ ማዘዛቸውን ገልጻለች። በርካታ የአካባቢዎቹን ነዋሪዎች የጫኑ አውቶብሶችም ወደ ሩሲያ ማምራታቸውን የሩሲያ መንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ መነገሩ ሩሲያ ጥቃቱን ለመሰንዘር ኃይሏን እያጠናከረች ላለው ዝግጅት ዓለምን ለማዘናጋት የተደረገ " የሞስኮ አሳፋሪ እርምጃ " ነው ብሎታል። ዋይት ሐውስ ነዋሪዎችን እንዲወጡ ማድረግ ሞስኮ ሐሰተኛ መረጃን ለጦርነት ሰበብ መጠቀሟን የሚያሳይ ምሳሌ ነው ብሏል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60427362 |
3politics
| ምርጫ 2013፡ በአንድ ዓመት ውስጥ ሁሉን አቀፍ ምርጫ እንዲካሄድ ኦፌኮ ጠየቀ | ከቀናት በፊት ሰኔ 14/2013 ዓ.ም በተደረገው ስድስተኛ ብሔራዊ ምርጫ ያልተሳተፈው የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ በአንድ ዓመት ውስጥ ሁሉን አቀፍ ምርጫ እንዲደረግ ባወጣው መግለጫ ጠየቀ። ፓርቲው ለአገሪቱ የፖለቲካ ኃይሎች በሙሉ የመፍትሔ ሃሳብ ብሎ የሰነዘራቸውን ሦስት ነጥቦችንም ዘርዝሯል። በመጀመሪያ ደረጃ ሁሉን አካታች የጋራ መንግሥት እንዲቋቋምና "ያልተሳካ" ብሎ የጠራውን የመንግሥት ተሃድሶ እንዲቀጥል፣ "ሁሉን አካታች ብሔራዊ የመግባባት ድርድር እንዲጀመር" የሚሉ ሃሳቦችን አስፍሯል። በሦስተኛነትም የጋራ መንግሥቱ በጋራ የሚፈጥር ፍኖተ ካርታ እንዲመቻችና በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ሁሉን አቀፍ ነፃ ፍትሃዊና ተቀባይነት ያለው ምርጫ እንዲካሄድም የሚሉ ሃሳቦችን አቅርቧል። በብሔራዊ መግባባት ያልታጀበ ምርጫ አገሪቷን ከገባችበት ችግር ውስጥ እንደማያወጣት ደጋግሞ ሲናገር እንደነበር ፓርቲው አስታውሶ ከመንግሥት በኩልም ሰሚ ባለመገኘቱ "የአገራችን ቀውስ ወደ ሌላ ቀውስ እየተሸጋገረ ነው" ብሏል። ኦፌኮና ኦነግ አመራሮቻው በመታሰራቸው፣ በርካታ ቢሮዎቻቸው በመዘጋታቸው ምክንያት ከምርጫው ራሳቸውን ማግለላቸውን ማስታወቃቸው ይታወሳል። በዚህ ምርጫ ኦፌኮ ተገፍቶ መውጣቱንና "የመላውን ኢትዮጵያ ሕዝቦችን የማይወክል ምርጫ ስጋታቸውንም ከሌሎች ፓርቲዎች ማረጋገጥ" እንደቻሉም አስፍረዋል። በምርጫ ሂደቱም ውስጥ የታዩ ችግሮችንም ጠቅሶ በተለያዩ ምክንያቶች "ሕዝቡን ያላካተተ ምርጫ" እንደሆነም ኦፌኮ በመግለጫው አካቷል። ምርጫው እንደታሰበው "የገዥውን ፓርቲ ቀልብ መሳብ ባለመቻሉ" የመራጮች ምዝገባ ሦስት ጊዜ ተራዝሟል ብሏል። ከዚህም በተጨማሪ ቦርዱ የማያውቃቸው ሰባ ዘጠኝ የምርጫ ጣቢያዎች ተቋቁመው መገኘታቸው፣ በመቶዎች በሚቆጠሩ የምርጫ ክልሎች ላይ ምርጫ አለመካሄዱ የምርጫውን ጉድለት የሚያሳዩ ናቸው ብሏል። በተጨማሪም "በኦሮሚያ ክልል በመቶዎች በሚቆጠሩ ወረዳዎች ውስጥ ገዥው ፓርቲ ብልጽግና በብቸኝነት መወዳደሩን" አስፍሯል። በትግራይ ውስጥ ባለው ጦርነት ምርጫ ባለመካሄዱና ሌሎች ምክንያቶችንም በመጥቀስ "ሃምሳ በመቶው ሕዝብ ከምርጫ ውጪ ነው" ብሎታል። "በምንም ተአምር የአገራችንን ፍላጎቶችን የማያሟላ ምርጫ ማለትም ዘላቂ ሰላም፣ መረጋጋትንና ሁሉንም በእኩልነት የምታስተናግድ ዲሞክራቲክ ኢትዮጵያን የማይፈጥር ከሆነ ለሚሊዮኖች የሚሆን ልማትና ብልጽግናን አያመጣም" ብሏል። ከ37 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ በመራጭነት የተመዘገበበት እና 47 ፓርቲዎች ዕጩዎቻቸውን ያቀረቡበት ብሔራዊ ምርጫ ሰኔ 14/2013 የተካሄደ ሲሆን፤ ምርጫው በፀጥታና በሌሎች ምክንያቶች መካሄድ ባልተቻለባቸውም አካቢዎች ደግሞ ጳጉሜ 1 እንደሚካሄድ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። ከነዚህም መካከል በሶማሌ ክልልና ሐረሪ ክልል እንዲሁም በፀጥታ ችግር ምክንያት ምርጫው በተራዘመባቸው ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ደቡብ ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልሎች በተወሰኑ የምርጫ ክልሎች ምርጫው እንዲራዘም መወሰኑ ይታወሳል። | ምርጫ 2013፡ በአንድ ዓመት ውስጥ ሁሉን አቀፍ ምርጫ እንዲካሄድ ኦፌኮ ጠየቀ ከቀናት በፊት ሰኔ 14/2013 ዓ.ም በተደረገው ስድስተኛ ብሔራዊ ምርጫ ያልተሳተፈው የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ በአንድ ዓመት ውስጥ ሁሉን አቀፍ ምርጫ እንዲደረግ ባወጣው መግለጫ ጠየቀ። ፓርቲው ለአገሪቱ የፖለቲካ ኃይሎች በሙሉ የመፍትሔ ሃሳብ ብሎ የሰነዘራቸውን ሦስት ነጥቦችንም ዘርዝሯል። በመጀመሪያ ደረጃ ሁሉን አካታች የጋራ መንግሥት እንዲቋቋምና "ያልተሳካ" ብሎ የጠራውን የመንግሥት ተሃድሶ እንዲቀጥል፣ "ሁሉን አካታች ብሔራዊ የመግባባት ድርድር እንዲጀመር" የሚሉ ሃሳቦችን አስፍሯል። በሦስተኛነትም የጋራ መንግሥቱ በጋራ የሚፈጥር ፍኖተ ካርታ እንዲመቻችና በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ሁሉን አቀፍ ነፃ ፍትሃዊና ተቀባይነት ያለው ምርጫ እንዲካሄድም የሚሉ ሃሳቦችን አቅርቧል። በብሔራዊ መግባባት ያልታጀበ ምርጫ አገሪቷን ከገባችበት ችግር ውስጥ እንደማያወጣት ደጋግሞ ሲናገር እንደነበር ፓርቲው አስታውሶ ከመንግሥት በኩልም ሰሚ ባለመገኘቱ "የአገራችን ቀውስ ወደ ሌላ ቀውስ እየተሸጋገረ ነው" ብሏል። ኦፌኮና ኦነግ አመራሮቻው በመታሰራቸው፣ በርካታ ቢሮዎቻቸው በመዘጋታቸው ምክንያት ከምርጫው ራሳቸውን ማግለላቸውን ማስታወቃቸው ይታወሳል። በዚህ ምርጫ ኦፌኮ ተገፍቶ መውጣቱንና "የመላውን ኢትዮጵያ ሕዝቦችን የማይወክል ምርጫ ስጋታቸውንም ከሌሎች ፓርቲዎች ማረጋገጥ" እንደቻሉም አስፍረዋል። በምርጫ ሂደቱም ውስጥ የታዩ ችግሮችንም ጠቅሶ በተለያዩ ምክንያቶች "ሕዝቡን ያላካተተ ምርጫ" እንደሆነም ኦፌኮ በመግለጫው አካቷል። ምርጫው እንደታሰበው "የገዥውን ፓርቲ ቀልብ መሳብ ባለመቻሉ" የመራጮች ምዝገባ ሦስት ጊዜ ተራዝሟል ብሏል። ከዚህም በተጨማሪ ቦርዱ የማያውቃቸው ሰባ ዘጠኝ የምርጫ ጣቢያዎች ተቋቁመው መገኘታቸው፣ በመቶዎች በሚቆጠሩ የምርጫ ክልሎች ላይ ምርጫ አለመካሄዱ የምርጫውን ጉድለት የሚያሳዩ ናቸው ብሏል። በተጨማሪም "በኦሮሚያ ክልል በመቶዎች በሚቆጠሩ ወረዳዎች ውስጥ ገዥው ፓርቲ ብልጽግና በብቸኝነት መወዳደሩን" አስፍሯል። በትግራይ ውስጥ ባለው ጦርነት ምርጫ ባለመካሄዱና ሌሎች ምክንያቶችንም በመጥቀስ "ሃምሳ በመቶው ሕዝብ ከምርጫ ውጪ ነው" ብሎታል። "በምንም ተአምር የአገራችንን ፍላጎቶችን የማያሟላ ምርጫ ማለትም ዘላቂ ሰላም፣ መረጋጋትንና ሁሉንም በእኩልነት የምታስተናግድ ዲሞክራቲክ ኢትዮጵያን የማይፈጥር ከሆነ ለሚሊዮኖች የሚሆን ልማትና ብልጽግናን አያመጣም" ብሏል። ከ37 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ በመራጭነት የተመዘገበበት እና 47 ፓርቲዎች ዕጩዎቻቸውን ያቀረቡበት ብሔራዊ ምርጫ ሰኔ 14/2013 የተካሄደ ሲሆን፤ ምርጫው በፀጥታና በሌሎች ምክንያቶች መካሄድ ባልተቻለባቸውም አካቢዎች ደግሞ ጳጉሜ 1 እንደሚካሄድ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። ከነዚህም መካከል በሶማሌ ክልልና ሐረሪ ክልል እንዲሁም በፀጥታ ችግር ምክንያት ምርጫው በተራዘመባቸው ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ደቡብ ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልሎች በተወሰኑ የምርጫ ክልሎች ምርጫው እንዲራዘም መወሰኑ ይታወሳል። | https://www.bbc.com/amharic/57596729 |
3politics
| ፕሬዝዳንት ፑቲን እና ኤርዶሃን ለንግግር ኢራን ገቡ | የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከቱርኩ ፕሬዝደንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶዋን ጋር ለመነጋገር ኢራን ገቡ። ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ባለፈው የካቲት ወር በዩክሬን ላይ ሠራዊታቸውን ካዘመቱ በኋላ ወደ ኢራን ሲጓዙ ይህ ሁለተኛው የውጭ ጉዟቸው ሆኗል። ፑቲን እና ኤርዶሃን በኢራን ቆይታቸው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እንደሚነጋገሩ እና የአገሪቱን የበላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሚኒን ያገኛሉ ተብሏል። የእህል ምርት ገበያ፣ ሶሪያ እና ዩክሬን ፑቲን በቴህራን በሚያደርጉት ጉብኝት ላይ መነጋገሪያ ጉዳዮች እንደሚሆኑ አንድ የቱርክ ባለሥልጣን ተናግረዋል። ፕሬዝዳንት ፑቲን ከጦርነቱ በኋላ ከአገር ውጪ የሚያደርጉት ጉብኝት በቀድሞ የሶቪየት ኅብረት አገራት ተወስኖ ቆይቷል። ከአንድ ወር በፊት ፑቲን የቀድሞ የሶቪየት ኅብረት አካል ወደነበሩት እና በአሁኑ ወቅት የሩሲያ አጋር በሆኑት በታጃኪስታን እና በቱርክሜንስታን ጉብኝት አድርገው ነበር። የዛሬው የፑቲን ጉብኝት ልክ እንደ ሩሲያ ሁሉ በምዕራባውያን ማዕቀብ ስር ከምትገኘው ኢራን ጋር ያላቸውን ወዳጅነት የሚያጠናክሩበት ይሆናል ተብሏል። ይህ የፑቲን የኢራን ጉብኝት የተሰማው የአሜሪካ ባለሥልጣናት ቴህራን ለሞስኮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰው አልባ የጦር አውሮፕላኖችን [ድሮኖች] ለማቅረብ በዕቅድ ላይ ናት ማለታቸው ከተሰማ በኋላ ነው። ዛሬ የሩሲያው ግዙፍ የኃይል ተቋም ጋዝፕሮም ከእስራኤል መንግሥት የነዳጅ ኩባንያ ጋር 40 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ ስምምነት ተፈራርሟል። የፑቲንን የኢራን ጉብኝት በማስመልከት የፕሬዝዳንቱ የውጭ ጉዳይ ፖሊስ አማካሪ ዩሪ ኡሻኮቭ በሰጡት መግለጫ ጉብኝቱ ጠቀሜታው ከፍተኛ ነው ብለዋል። ፑቲን ከአያቶላህ አሊ ኻሚኒ ጋር መገናኘታቸው “በጣም ጠቃሚ ነው” ያሉት አማካሪው፤ ሁለቱ መሪዎች በሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መተማመን ላይ የተመሠረተ ንግግራቸው ዳብሯል ብለዋል። ምንም እንኳ ቱርክ እና ሩሲያ በሶሪያ የእርስ በእርስ ጦርነት በተቃራኒ ጎራ የተሰለፉ ቡድኖችን በየፊናቸው እየደገፉ የቆዩ ቢሆንም፤ በቅርብ ወራት ግን በአገሪቱ ሰላም ለማስፈን ጥረት እያደረጉ ነው። የሩሲያን ወረራ ተከትሎ ምዕራባውያን በሞስኮ ላይ መጠነ ሰፊ ማዕቀቦችን ሲጥሉ፤ አንካራ ግን የሩሲያ እና ዩክሬን አሸማጋይ ለመሆን ስትጥር እንጂ ሞስኮ ላይ ማዕቀብ ስትጥል አልታየችም። ይሁን እንጂ ቱርክ በቅርቡ በሰሜን ሶሪያ የሚንቀሳቀሱትን እና በአሜሪካ የሚደገፉትን የኩርድ ታጣቂዎች ላይ አዲስ ጥቃት ለመክፈት ዝታለች። ይህን የቱርክ ዛቻ ሞስኮ እና ቴህራን በበጎ አልተመለከቱትም። ኤርዶሃን ይህን ኦፕሬሽን ለማካሄድ ያቀዱት ከሶሪያ በሚያዋስናቸው የድንበር አካባቢ 30 ኪሎ ሜትር ስፋት ያለው ደኅንነቱ የተረጋገጠ አካባቢን የመፍጠር እቅዳቸውን እውን ለማድረግ ነው። ከፑቲን እና ኤርዶሃን ንግግር በኋላ በዩክሬን ወደብ ላይ የሚገኘው 22 ሚሊዮን ቶን እህል ወደ ሌላ አገር እንዲሄድ ጦርነት ውስጥ የገቡት የሩሲያ እና ዩክሬን መሪዎች ከስምምነት እንዲደርሱ ያስችላል ተብሎ ይጠበቃል። ሩሲያ በጥቁር ባሕር ላይ ያሰማራቻቸው መርከቦች ምንም አይነት ጭነቶች ከዩክሬን እንዳይወጡ እና ወደ ዩክሬን እንዳይገቡ እያደረጉ ይገኛሉ። | ፕሬዝዳንት ፑቲን እና ኤርዶሃን ለንግግር ኢራን ገቡ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከቱርኩ ፕሬዝደንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶዋን ጋር ለመነጋገር ኢራን ገቡ። ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ባለፈው የካቲት ወር በዩክሬን ላይ ሠራዊታቸውን ካዘመቱ በኋላ ወደ ኢራን ሲጓዙ ይህ ሁለተኛው የውጭ ጉዟቸው ሆኗል። ፑቲን እና ኤርዶሃን በኢራን ቆይታቸው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እንደሚነጋገሩ እና የአገሪቱን የበላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሚኒን ያገኛሉ ተብሏል። የእህል ምርት ገበያ፣ ሶሪያ እና ዩክሬን ፑቲን በቴህራን በሚያደርጉት ጉብኝት ላይ መነጋገሪያ ጉዳዮች እንደሚሆኑ አንድ የቱርክ ባለሥልጣን ተናግረዋል። ፕሬዝዳንት ፑቲን ከጦርነቱ በኋላ ከአገር ውጪ የሚያደርጉት ጉብኝት በቀድሞ የሶቪየት ኅብረት አገራት ተወስኖ ቆይቷል። ከአንድ ወር በፊት ፑቲን የቀድሞ የሶቪየት ኅብረት አካል ወደነበሩት እና በአሁኑ ወቅት የሩሲያ አጋር በሆኑት በታጃኪስታን እና በቱርክሜንስታን ጉብኝት አድርገው ነበር። የዛሬው የፑቲን ጉብኝት ልክ እንደ ሩሲያ ሁሉ በምዕራባውያን ማዕቀብ ስር ከምትገኘው ኢራን ጋር ያላቸውን ወዳጅነት የሚያጠናክሩበት ይሆናል ተብሏል። ይህ የፑቲን የኢራን ጉብኝት የተሰማው የአሜሪካ ባለሥልጣናት ቴህራን ለሞስኮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰው አልባ የጦር አውሮፕላኖችን [ድሮኖች] ለማቅረብ በዕቅድ ላይ ናት ማለታቸው ከተሰማ በኋላ ነው። ዛሬ የሩሲያው ግዙፍ የኃይል ተቋም ጋዝፕሮም ከእስራኤል መንግሥት የነዳጅ ኩባንያ ጋር 40 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ ስምምነት ተፈራርሟል። የፑቲንን የኢራን ጉብኝት በማስመልከት የፕሬዝዳንቱ የውጭ ጉዳይ ፖሊስ አማካሪ ዩሪ ኡሻኮቭ በሰጡት መግለጫ ጉብኝቱ ጠቀሜታው ከፍተኛ ነው ብለዋል። ፑቲን ከአያቶላህ አሊ ኻሚኒ ጋር መገናኘታቸው “በጣም ጠቃሚ ነው” ያሉት አማካሪው፤ ሁለቱ መሪዎች በሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መተማመን ላይ የተመሠረተ ንግግራቸው ዳብሯል ብለዋል። ምንም እንኳ ቱርክ እና ሩሲያ በሶሪያ የእርስ በእርስ ጦርነት በተቃራኒ ጎራ የተሰለፉ ቡድኖችን በየፊናቸው እየደገፉ የቆዩ ቢሆንም፤ በቅርብ ወራት ግን በአገሪቱ ሰላም ለማስፈን ጥረት እያደረጉ ነው። የሩሲያን ወረራ ተከትሎ ምዕራባውያን በሞስኮ ላይ መጠነ ሰፊ ማዕቀቦችን ሲጥሉ፤ አንካራ ግን የሩሲያ እና ዩክሬን አሸማጋይ ለመሆን ስትጥር እንጂ ሞስኮ ላይ ማዕቀብ ስትጥል አልታየችም። ይሁን እንጂ ቱርክ በቅርቡ በሰሜን ሶሪያ የሚንቀሳቀሱትን እና በአሜሪካ የሚደገፉትን የኩርድ ታጣቂዎች ላይ አዲስ ጥቃት ለመክፈት ዝታለች። ይህን የቱርክ ዛቻ ሞስኮ እና ቴህራን በበጎ አልተመለከቱትም። ኤርዶሃን ይህን ኦፕሬሽን ለማካሄድ ያቀዱት ከሶሪያ በሚያዋስናቸው የድንበር አካባቢ 30 ኪሎ ሜትር ስፋት ያለው ደኅንነቱ የተረጋገጠ አካባቢን የመፍጠር እቅዳቸውን እውን ለማድረግ ነው። ከፑቲን እና ኤርዶሃን ንግግር በኋላ በዩክሬን ወደብ ላይ የሚገኘው 22 ሚሊዮን ቶን እህል ወደ ሌላ አገር እንዲሄድ ጦርነት ውስጥ የገቡት የሩሲያ እና ዩክሬን መሪዎች ከስምምነት እንዲደርሱ ያስችላል ተብሎ ይጠበቃል። ሩሲያ በጥቁር ባሕር ላይ ያሰማራቻቸው መርከቦች ምንም አይነት ጭነቶች ከዩክሬን እንዳይወጡ እና ወደ ዩክሬን እንዳይገቡ እያደረጉ ይገኛሉ። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cnkz929yeklo |
2health
| በ20 ቀናት ሁለት ጊዜ ኮሮና የተገኘባት ስፔናዊት በአጭር ጊዜ ዳግም በቫይረሱ የተያዘች ሳትሆን አትቀርም ተባለ | የ31 ዓመቷ የጤና ባለሙያ በ20 ቀናት ውስጥ ሁለት ጊዜ በኮሮና ቫይረስ እንደታያዘች ተገልጿል። ይህንንም ተከትሎ በቫይረሱ ሁለት ጊዜ በመያዝ የታወቀ አጭሩ ጊዜ ነው ሲሉ የስፔን ተመራማሪዎች ገልጸዋል። ባለሙያዋ በሃያ ቀናት ውስጥ ዴልታ እና ኦሚክሮን በተባሉ ሁለት የኮቪድ ዝርያዎች መያዟ ነው የተረጋገጠው። ታዲያ ይህ ሁኔታ አንድ ሰው በቫይረሱ ቀደም ብሎ ቢያዝም ሆነ ሙሉ በሙሉ ክትባቱን ቢወስድ ዳግም በቫይረሱ ሊያዝ እንደሚችል ያመላከተ ነው ሲሉ ተመራማሪዎች ገልጸዋል። በዩኬ ሰዎች በቫይረሱ ከተያዙ በኋላ ዳግም ለመያዝ ቢያንስ 90 ቀን እንደሚፈጅ ታውቋል። በዚህ እሳቤ መሰረት በሀገሪቱ 900 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች በዚህ ወር መግቢያ በቫይረሱ ዳግም የመያዝ እድላቸው ከፍተኛ እንደሆነ የጤና ዘርፉ ባለስልጣናት አሳውቀዋል። በላብራቶሪ ባለው ሂደት እና የሚወሰደው ናሙና ጥቂት በመሆኑ በቫይረሱ ዳግም የተያዙ ሰዎችን ትክክለኛ ቁጥር ለመያዝ አዳጋች ነው። በሃያ ቀናት ልዩነት በቫይረሱ የተያዘችው ስፔናዊት በቫይረሱ እንደተያዘች ካረጋገጠች በኋላ ምንም ዓይነት የኮሮና ምልክቶች አልታዩባትም ነበር። ሆኖም ግን ከሶስት ሳምንታት በነሳ ጊዜ ውስጥ የቫይረሱን ምልክቶች በማየቷ ድጋሚ ለመመርመር ምክንያት ሆኗታል። በውጤቱም ቫይረሱ እንደያዛት የተረጋገጠ ሲሆን ከመጀመሪያው የተለየ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ሁለተኛው ምርመራ ላይ ተገኝቷል። በአውሮፓ ውስጥ በሚገኝ አንድ የህክምና ምርምር ተቋም ጉዳዩን አስመልክቶ ገለጻ ያደረጉት ዶክተር ጄማ ሪሶ ይህ ሁኔታ ኦሚክሮን ሰዎች በቫይረሱ ከተያዙ በኋላ በተፈጥሮ የሚያዳብሩትን ወይም በክትባት የሚያገኙትን በሽታ የመከላከል አቅም እንደሚበግር የሚያሳይ ነው ብለዋል። "በሌላ አገላለጽ በኮቪድ 19 ተይዘው የነበሩ ሰዎች ክትባቱን ሙሉ በሙሉ ቢወስዱ እንኳን ለቫይረሱ አንጋለጠም ብለው ማስብ አይችሉም" ሲሉ አስረድተዋል። ሆኖም ግን በቫይረሱ ቀድሞ መያዝ እና ክትባቱን መውስድ ከከፍ ህመም እና ሆስፒታል ከመግባት ሳይታደግ አይቀርም ሲሉ አክለዋል። ተመራማሪዋ ክትባት ሙሉ በሙሉ ወስደው በቫይረሱ ዳግም የሚያዙ ሰዎች ላይ የሚደረገው ምርመራ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው የኮቪድ ዝርያዎች ለክትባት ያላቸውን አይበገሬነት ለማጥናት ይረዳል ብለዋል። በዓለም ዙሪያ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ዳግም እንደተያዙ የሚያመላክቱ ቁጥሮች ከፍ ያሉት ኦሚክሮን የተባለው ዝርያ መገኘቱ ከታወቀ በኋላ ነው። በሌላ በኩል ባለፈው ወር ቢኤ 2 የተባለው የኮሮና ዝርያ መገኘቱን ተከትሎ በቫይረሱ ዳግም የሚያዙ ሰዎች ተበራክተዋል። ይህ ዝርያ ከመገኘቱ በፊት በዩኬ ለሁለተኛ ጊዜ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር 1 በመቶ ሲሆን ከዚያ በኋላ ግን ወደ 11 በመቶ አሻቅቧል። አብዛኞቹ ሰዎች ቀደም ብሎ አልፋ ወይም ዴልታ በተሰኘው ቫይረስ ተይዘው የነበረ ሲሆን ለሁለለተኛ ጊዜ ሲያዙ የተገኘው ኦሚክሮን ዝርያ ነው። በዚህም መነሻ ማንኛውም ሰው በቫይረሱ ሁለት ጊዜ ሊያዝ እንደሚችል እና በህይወት ዘመን ውስጥ ከሁለት ጊዜም በላይ የመያዝ እድል እንዳል ሳይንቲስቶች ግምታቸውን አስቀምጠዋል። | በ20 ቀናት ሁለት ጊዜ ኮሮና የተገኘባት ስፔናዊት በአጭር ጊዜ ዳግም በቫይረሱ የተያዘች ሳትሆን አትቀርም ተባለ የ31 ዓመቷ የጤና ባለሙያ በ20 ቀናት ውስጥ ሁለት ጊዜ በኮሮና ቫይረስ እንደታያዘች ተገልጿል። ይህንንም ተከትሎ በቫይረሱ ሁለት ጊዜ በመያዝ የታወቀ አጭሩ ጊዜ ነው ሲሉ የስፔን ተመራማሪዎች ገልጸዋል። ባለሙያዋ በሃያ ቀናት ውስጥ ዴልታ እና ኦሚክሮን በተባሉ ሁለት የኮቪድ ዝርያዎች መያዟ ነው የተረጋገጠው። ታዲያ ይህ ሁኔታ አንድ ሰው በቫይረሱ ቀደም ብሎ ቢያዝም ሆነ ሙሉ በሙሉ ክትባቱን ቢወስድ ዳግም በቫይረሱ ሊያዝ እንደሚችል ያመላከተ ነው ሲሉ ተመራማሪዎች ገልጸዋል። በዩኬ ሰዎች በቫይረሱ ከተያዙ በኋላ ዳግም ለመያዝ ቢያንስ 90 ቀን እንደሚፈጅ ታውቋል። በዚህ እሳቤ መሰረት በሀገሪቱ 900 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች በዚህ ወር መግቢያ በቫይረሱ ዳግም የመያዝ እድላቸው ከፍተኛ እንደሆነ የጤና ዘርፉ ባለስልጣናት አሳውቀዋል። በላብራቶሪ ባለው ሂደት እና የሚወሰደው ናሙና ጥቂት በመሆኑ በቫይረሱ ዳግም የተያዙ ሰዎችን ትክክለኛ ቁጥር ለመያዝ አዳጋች ነው። በሃያ ቀናት ልዩነት በቫይረሱ የተያዘችው ስፔናዊት በቫይረሱ እንደተያዘች ካረጋገጠች በኋላ ምንም ዓይነት የኮሮና ምልክቶች አልታዩባትም ነበር። ሆኖም ግን ከሶስት ሳምንታት በነሳ ጊዜ ውስጥ የቫይረሱን ምልክቶች በማየቷ ድጋሚ ለመመርመር ምክንያት ሆኗታል። በውጤቱም ቫይረሱ እንደያዛት የተረጋገጠ ሲሆን ከመጀመሪያው የተለየ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ሁለተኛው ምርመራ ላይ ተገኝቷል። በአውሮፓ ውስጥ በሚገኝ አንድ የህክምና ምርምር ተቋም ጉዳዩን አስመልክቶ ገለጻ ያደረጉት ዶክተር ጄማ ሪሶ ይህ ሁኔታ ኦሚክሮን ሰዎች በቫይረሱ ከተያዙ በኋላ በተፈጥሮ የሚያዳብሩትን ወይም በክትባት የሚያገኙትን በሽታ የመከላከል አቅም እንደሚበግር የሚያሳይ ነው ብለዋል። "በሌላ አገላለጽ በኮቪድ 19 ተይዘው የነበሩ ሰዎች ክትባቱን ሙሉ በሙሉ ቢወስዱ እንኳን ለቫይረሱ አንጋለጠም ብለው ማስብ አይችሉም" ሲሉ አስረድተዋል። ሆኖም ግን በቫይረሱ ቀድሞ መያዝ እና ክትባቱን መውስድ ከከፍ ህመም እና ሆስፒታል ከመግባት ሳይታደግ አይቀርም ሲሉ አክለዋል። ተመራማሪዋ ክትባት ሙሉ በሙሉ ወስደው በቫይረሱ ዳግም የሚያዙ ሰዎች ላይ የሚደረገው ምርመራ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው የኮቪድ ዝርያዎች ለክትባት ያላቸውን አይበገሬነት ለማጥናት ይረዳል ብለዋል። በዓለም ዙሪያ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ዳግም እንደተያዙ የሚያመላክቱ ቁጥሮች ከፍ ያሉት ኦሚክሮን የተባለው ዝርያ መገኘቱ ከታወቀ በኋላ ነው። በሌላ በኩል ባለፈው ወር ቢኤ 2 የተባለው የኮሮና ዝርያ መገኘቱን ተከትሎ በቫይረሱ ዳግም የሚያዙ ሰዎች ተበራክተዋል። ይህ ዝርያ ከመገኘቱ በፊት በዩኬ ለሁለተኛ ጊዜ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር 1 በመቶ ሲሆን ከዚያ በኋላ ግን ወደ 11 በመቶ አሻቅቧል። አብዛኞቹ ሰዎች ቀደም ብሎ አልፋ ወይም ዴልታ በተሰኘው ቫይረስ ተይዘው የነበረ ሲሆን ለሁለለተኛ ጊዜ ሲያዙ የተገኘው ኦሚክሮን ዝርያ ነው። በዚህም መነሻ ማንኛውም ሰው በቫይረሱ ሁለት ጊዜ ሊያዝ እንደሚችል እና በህይወት ዘመን ውስጥ ከሁለት ጊዜም በላይ የመያዝ እድል እንዳል ሳይንቲስቶች ግምታቸውን አስቀምጠዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-61172476 |
5sports
| የ53 ዓመቱ ጃፓናዊ የእግር ኳስ ኮከብ በተጫዋችነት እንዲቀጥል ኮንትራቱ ተራዘመ | አንጋፋው ጃፓናዊ ፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ተጫዋች ካዙዮሺ ሚዩራ እስከ 54 ዓመቱ ድረስ ለመጫወት የሚያስችለውን ውል በመፈራራም በዮኮሃማ ክለብ ለተጨማሪ አንድ ዓመት ለመቆየት ተስማማ። የ2021 የጃፓን ሊግ ውድድር ከመጀመሩ ከአንድ ቀን በፊት ሚዩራ የካቲት 26 ቀን 54 ዓመት ይሆነዋል። የቀድሞው የጃፓን ብሔራዊ ቡድን አጥቂ ዮኮሃማን ከ15 ዓመት በፊት የተቀላቀለ ሲሆን ለ17ኛ የውድድር ዘመን ለክለቡ ይጫወታል። "ለእግር ኳስ ያለኝ ፍላጎትና ፍቅር እየጨመረ ነው" ብሏል። ሚዩራ የእግር ኳስ ህይወቱን የጀመረው በብራዚሉ ሳንቶስ ክለብ ውስጥ 1986 (እአአ) ነበር። በ2017 ደግሞ በ50 ዓመት ከ14 ቀናት ዕድሜው ቴስፓኩሳትሱ ጉንማ ላይ ግብ በማስቆጠር በጃፓን ፕሮፌሽናል ሊግ ጨዋታ ግብ ያስቆጠረ የአንጋፋው ተጫዋችነት ክብረ ወሰንን ይዟል። በጃፓን 'ኪንግ ካዙ' [ንጉሥ ካዙ] ተብሎ የሚጠራው ሚዩራ በአገሪቱ ውስጥ በጣም ተወዳጅ ከሆኑ ስፖርተኞች መካከል አንዱ ሲሆን፤ በ1993 (እአአ) ጄ ሊግ ሲጀመር የውድድሩ ምልክት ተደርጎ ተወስዷል። ለጃፓን በ89 ጨዋታዎች 55 ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን በክሮሽያና በአውስትራሊያ ከመጫወቱ በፊት በጣሊያን ሴሪ አ ለጄኖዋ ተጫውቷል። ሚዩራ ክለቡን በአምበልነት አገለግሏል። ከእግር ኳስ ቤተሰብ የተገኘው ተጫዋቹ ሺዙካ ውስጥ ነው ያደገው። አባታቸው የእግር ኳስ ደጋፊ ሲሆኑ ታላቅ ወንድሙ ያሱቶሺም ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋች ነበር። "አባቴ በሜክሲኮው የ1970 የዓለም ዋንጫ ተገኝቶ ከመመልከት ባለፈ እነፔሌ ያሉበት ጨዋታን ቀርጾ ስለነበር እሱን እያየሁ ነው ያደግኩት" ብሏል በአንድ ወቅት በሰጠው ቃለመጠይቅ። በሦስት ዓመቱ የተቀረጸውን ቪዲዮ መመልከት ብቻ ሳይሆን "የብራዚል ደጋፊ ሆንኩኝ። ከልጅነቴ ጀምሮ ፕሮፌሽናል ተጫዋች ለመሆን እፈልግ ነበር" ብሏል። ወደ ብራዚል በማቅናትም ጁቬንቱስ ለተባለው የአገሪቱ እግር ኳስ ክለብ ፈረመ። ውጣ ውረዶች ቢኖሩበትም በስኬት አለፋቸው። ከእግር ኳስ ሌላ የሚያስበው መስክ ይኖር እንደሆን ሲጠየቅም "ምንም ሃሳብ አልነበረኝም። ሁሌም የምፈልገው ፕሮፌሽናል ተጫዋች መሆን ነበር። ከባድ ጥያቄ ነው" ሲል መልሷል። ብራዚል ውስጥ ፔሌ የተጫወተበንትን ሳንቶስን ጨምሮ በተለያዩ የብራዚል ክለቦች በመዘዋወርም መጫወት ችለወል። ከዚያም ወደ ጃፓን ታዋቂ ተጫዋች ሆኖ ተመለሰ። ጄ ሊግ ሲጀመርም እንደ ጋሪ ሊነክር ያሉ ተጫዋቾችን በመቅደም ኮከብ ሆኖ የውድድር ዓመቱን አጠናቀቀ። በ1994 ወደ ጄኖዋ በውሰት ሄዶ የተጫወተ ሲሆን በዚህም በሴሪ አው የተጫወተ የመጀመሪያው ጃፓናዊ ለመሆን በቃ። በ2005 (እአአ) አሁን ለሚጫወትበት ዮኮሃማ የፈረመ ሲሆን ክለቡ በሁለተኛው ዲቪዚዮን ይጫወት ነበር። ቡድኑ በቀጣዩ ዓመት ወደ ዋናው ሊግ ለማደግ ቻለ። ሚዩራ በተደጋጋሚ ካለመጎዳቱም በላይ ባለው አካላዊ ብቃት አጠባበቅ ይታወቃል። ካለው ጠንካራ አካላዊ ብቃት ባሻገር ታዋቂነቱም እየተጫወተ እንዲቀጥል አድርጎታል። እሱ የሚጫወት ከሆነ እስከ 4000 የሚደርሱ ተጨማሪ ተመልካቾች ወደ ሜዳ ይገባሉ ተብሏል። እና የ53 ዓመቱ ካዙ አሁንም እንደ ታዳጊዎች በየዕለቱ በፍቅር ልምምዶችን ያከናወናል? ተብሎ ሲጠየቅ "አዎ። አሁንም እግር ኳስ መጫወት ያስደስተኛል። ብራዚል ከነበርኩበት ጊዜ በበለጠ እግር ኳስ መጫወት ያስደስተኛል" ሲል ምላሽ ይሰጣል። | የ53 ዓመቱ ጃፓናዊ የእግር ኳስ ኮከብ በተጫዋችነት እንዲቀጥል ኮንትራቱ ተራዘመ አንጋፋው ጃፓናዊ ፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ተጫዋች ካዙዮሺ ሚዩራ እስከ 54 ዓመቱ ድረስ ለመጫወት የሚያስችለውን ውል በመፈራራም በዮኮሃማ ክለብ ለተጨማሪ አንድ ዓመት ለመቆየት ተስማማ። የ2021 የጃፓን ሊግ ውድድር ከመጀመሩ ከአንድ ቀን በፊት ሚዩራ የካቲት 26 ቀን 54 ዓመት ይሆነዋል። የቀድሞው የጃፓን ብሔራዊ ቡድን አጥቂ ዮኮሃማን ከ15 ዓመት በፊት የተቀላቀለ ሲሆን ለ17ኛ የውድድር ዘመን ለክለቡ ይጫወታል። "ለእግር ኳስ ያለኝ ፍላጎትና ፍቅር እየጨመረ ነው" ብሏል። ሚዩራ የእግር ኳስ ህይወቱን የጀመረው በብራዚሉ ሳንቶስ ክለብ ውስጥ 1986 (እአአ) ነበር። በ2017 ደግሞ በ50 ዓመት ከ14 ቀናት ዕድሜው ቴስፓኩሳትሱ ጉንማ ላይ ግብ በማስቆጠር በጃፓን ፕሮፌሽናል ሊግ ጨዋታ ግብ ያስቆጠረ የአንጋፋው ተጫዋችነት ክብረ ወሰንን ይዟል። በጃፓን 'ኪንግ ካዙ' [ንጉሥ ካዙ] ተብሎ የሚጠራው ሚዩራ በአገሪቱ ውስጥ በጣም ተወዳጅ ከሆኑ ስፖርተኞች መካከል አንዱ ሲሆን፤ በ1993 (እአአ) ጄ ሊግ ሲጀመር የውድድሩ ምልክት ተደርጎ ተወስዷል። ለጃፓን በ89 ጨዋታዎች 55 ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን በክሮሽያና በአውስትራሊያ ከመጫወቱ በፊት በጣሊያን ሴሪ አ ለጄኖዋ ተጫውቷል። ሚዩራ ክለቡን በአምበልነት አገለግሏል። ከእግር ኳስ ቤተሰብ የተገኘው ተጫዋቹ ሺዙካ ውስጥ ነው ያደገው። አባታቸው የእግር ኳስ ደጋፊ ሲሆኑ ታላቅ ወንድሙ ያሱቶሺም ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋች ነበር። "አባቴ በሜክሲኮው የ1970 የዓለም ዋንጫ ተገኝቶ ከመመልከት ባለፈ እነፔሌ ያሉበት ጨዋታን ቀርጾ ስለነበር እሱን እያየሁ ነው ያደግኩት" ብሏል በአንድ ወቅት በሰጠው ቃለመጠይቅ። በሦስት ዓመቱ የተቀረጸውን ቪዲዮ መመልከት ብቻ ሳይሆን "የብራዚል ደጋፊ ሆንኩኝ። ከልጅነቴ ጀምሮ ፕሮፌሽናል ተጫዋች ለመሆን እፈልግ ነበር" ብሏል። ወደ ብራዚል በማቅናትም ጁቬንቱስ ለተባለው የአገሪቱ እግር ኳስ ክለብ ፈረመ። ውጣ ውረዶች ቢኖሩበትም በስኬት አለፋቸው። ከእግር ኳስ ሌላ የሚያስበው መስክ ይኖር እንደሆን ሲጠየቅም "ምንም ሃሳብ አልነበረኝም። ሁሌም የምፈልገው ፕሮፌሽናል ተጫዋች መሆን ነበር። ከባድ ጥያቄ ነው" ሲል መልሷል። ብራዚል ውስጥ ፔሌ የተጫወተበንትን ሳንቶስን ጨምሮ በተለያዩ የብራዚል ክለቦች በመዘዋወርም መጫወት ችለወል። ከዚያም ወደ ጃፓን ታዋቂ ተጫዋች ሆኖ ተመለሰ። ጄ ሊግ ሲጀመርም እንደ ጋሪ ሊነክር ያሉ ተጫዋቾችን በመቅደም ኮከብ ሆኖ የውድድር ዓመቱን አጠናቀቀ። በ1994 ወደ ጄኖዋ በውሰት ሄዶ የተጫወተ ሲሆን በዚህም በሴሪ አው የተጫወተ የመጀመሪያው ጃፓናዊ ለመሆን በቃ። በ2005 (እአአ) አሁን ለሚጫወትበት ዮኮሃማ የፈረመ ሲሆን ክለቡ በሁለተኛው ዲቪዚዮን ይጫወት ነበር። ቡድኑ በቀጣዩ ዓመት ወደ ዋናው ሊግ ለማደግ ቻለ። ሚዩራ በተደጋጋሚ ካለመጎዳቱም በላይ ባለው አካላዊ ብቃት አጠባበቅ ይታወቃል። ካለው ጠንካራ አካላዊ ብቃት ባሻገር ታዋቂነቱም እየተጫወተ እንዲቀጥል አድርጎታል። እሱ የሚጫወት ከሆነ እስከ 4000 የሚደርሱ ተጨማሪ ተመልካቾች ወደ ሜዳ ይገባሉ ተብሏል። እና የ53 ዓመቱ ካዙ አሁንም እንደ ታዳጊዎች በየዕለቱ በፍቅር ልምምዶችን ያከናወናል? ተብሎ ሲጠየቅ "አዎ። አሁንም እግር ኳስ መጫወት ያስደስተኛል። ብራዚል ከነበርኩበት ጊዜ በበለጠ እግር ኳስ መጫወት ያስደስተኛል" ሲል ምላሽ ይሰጣል። | https://www.bbc.com/amharic/news-55621028 |
3politics
| ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንን ለመተካት ይፋዊ ያልሆነ ውድድር ተጀመረ | የዩይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን፣ ከካቢኔ ሚኒስትሮቻቸውና ከምክር ቤት አባላት ድጋፍ ሳያገኙ በመቅረታቸው ከወግ አጥባቂው ፓርቲያቸው መሪነት መልቀቃቸውን ተከትሎ እርሳቸውን ለመተካት ፉክክር ተጀምሯል። የፓርላማ አባሉ ቶም ቱጌንዳት ይህንን ውድድር ተቀላቅለው፣ የቦሪስን ቦታ ለመተካት ፍላጎት ያሳዩትን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሱዌላ ብሬቨርማን እና ስቴቭ ቤከርን ተቀላቅለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ፣ እርሳቸውን የሚተካ ሰው እስከሚገኝ እስከ መስከረም ድረስ በጠቅላይ ሚንስትርነት በሥልጣናቸው ላይ ለመቆየት አቅደዋል። ሆኖም በርካታ ባልደረቦቻቸው እና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች አሁኑኑ ሥልጣን እንዲለቁ ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ክፍት የነበሩትን የካቢኔ ቦታዎችን በሌሎች ተክተዋል። በርካታ የካቢኔ አባላሎቻቸው አስተዳደራቸውን በመቃወም ሥራ ከለቀቁ በኋላ ቦሪስ ጆንሰን ሥልጣናቸውን ይዘው ለመቆየት ለሁለት ቀናት እልህ አስጨራሽ ተጋድሎ ካደረጉ በኋላ ሐሙስ ዕለት ከፓርቲ መሪነት እንደሚነሱ ገልጸዋል። ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በከፍተኛ እና በዝቅተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊነት ላይ የነበሩ ወደ 60 የሚጠጉ የወግ አጥባቂ ፓርቲ የምክር ቤት አባላት ከመንግሥት ኃፊነት መልቀቃቸው መንግሥት ኃላፊነቱን ለመወጣት ያለውን አቅም ጥራጣሬ ውስጥ ከቶታል። ቦሪስ ጆንሰን አዲስ ለተሾሙት ካቢኔ አባሎቻቸው ሐሙስ ዕለት ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ ቀሪ ጊዜያቸውን ዋና ዋና የፖሊሲ ለውጦችን ለማድረግ እንደማይጠቀሙበት ቃል ገብተዋል። የኮንሰርቫቲቭ ፓርቲ አመራር ውድድር የጊዜ ሰሌዳ በሚቀጥለው ሳምንት የሚታወቅ ሲሆን፣ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር እስከ መስከረም ወር ማብቂያ ድረስ ይሾማሉ ተብሎ ይጠበቃል። ይሁን እንጂ ይፋዊ ባልሆነ መንገድ ውድድሩ በመካሄድ ላይ ነው። የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ቱገንዳት፣ አርብ ዕለት ለዴይሊ ቴሌግራፍ በጻፉት ጽሁፍ የአመራርነት ወድድራቸውን የጀመሩ ሲሆን “የግብር ቅነሳ እና አዲስ ጉልበትና ሃሳብ” ይዘው እንደሚመጡ ቃል ገብተዋል። የቦሪስ ጆንሰን ቀንደኛ ተቺ የነበሩት የቀድሞ ወታደር ቱገንዳት “ከዚህ ቀደም በጦሩ ውስጥ አገልግያለሁ፣ አሁን ደግሞ በፓርላማ ውስጥ እየሰራሁ ነው። አሁን ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን የቀረበልኝን ጥሪ ለመመለስ ተስፋ አደርጋለሁ” ብለዋል። ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ብራቨርማን በበኩላቸው ለጠቅላይ ሚኒስትርነት እንደሚወዳደሩ አረጋግጠዋል። የብሬግዚት ሚኒስትሩ ቤከርም ሰዎች ለጠቅላይ ሚኒስትርነት እንዲወዳደሩ ከጠየቋቸው በኋላ ለመወዳደር እንዳሰቡ ተናግረዋል። የቦሪስ ጆንሰን ተቃዋሚ የነበሩት የቀድሞው የጤና ኃላፊ ሳጂድ ጃቪድ እና የትራንስፖርት ኃላፊ ግራንት ሻፕስም ውድድሩን ለመቀላቀል እንዳሰቡ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ሊዝ ትረስ፣ የቀድሞ ቻንስለር ሪሺ ሱናክ እና የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ጀረሚ ሃንትም በውድድሩ ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ ይገመታል። በሚቀጥሉት ቀናት በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ገለጻ እንደሚሰጥ ይጠበቃል። ሆኖም ማይክል ጎቭ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶሚኒክ ራብ እና የቀድሞ የጤና ኃላፊ ማት ሃንኩክን ጨምሮ የቀድሞ የፓርቲው አመራር አባላት እንደማይወዳደሩ ተናግረዋል። | ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንን ለመተካት ይፋዊ ያልሆነ ውድድር ተጀመረ የዩይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን፣ ከካቢኔ ሚኒስትሮቻቸውና ከምክር ቤት አባላት ድጋፍ ሳያገኙ በመቅረታቸው ከወግ አጥባቂው ፓርቲያቸው መሪነት መልቀቃቸውን ተከትሎ እርሳቸውን ለመተካት ፉክክር ተጀምሯል። የፓርላማ አባሉ ቶም ቱጌንዳት ይህንን ውድድር ተቀላቅለው፣ የቦሪስን ቦታ ለመተካት ፍላጎት ያሳዩትን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሱዌላ ብሬቨርማን እና ስቴቭ ቤከርን ተቀላቅለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ፣ እርሳቸውን የሚተካ ሰው እስከሚገኝ እስከ መስከረም ድረስ በጠቅላይ ሚንስትርነት በሥልጣናቸው ላይ ለመቆየት አቅደዋል። ሆኖም በርካታ ባልደረቦቻቸው እና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች አሁኑኑ ሥልጣን እንዲለቁ ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ክፍት የነበሩትን የካቢኔ ቦታዎችን በሌሎች ተክተዋል። በርካታ የካቢኔ አባላሎቻቸው አስተዳደራቸውን በመቃወም ሥራ ከለቀቁ በኋላ ቦሪስ ጆንሰን ሥልጣናቸውን ይዘው ለመቆየት ለሁለት ቀናት እልህ አስጨራሽ ተጋድሎ ካደረጉ በኋላ ሐሙስ ዕለት ከፓርቲ መሪነት እንደሚነሱ ገልጸዋል። ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በከፍተኛ እና በዝቅተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊነት ላይ የነበሩ ወደ 60 የሚጠጉ የወግ አጥባቂ ፓርቲ የምክር ቤት አባላት ከመንግሥት ኃፊነት መልቀቃቸው መንግሥት ኃላፊነቱን ለመወጣት ያለውን አቅም ጥራጣሬ ውስጥ ከቶታል። ቦሪስ ጆንሰን አዲስ ለተሾሙት ካቢኔ አባሎቻቸው ሐሙስ ዕለት ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ ቀሪ ጊዜያቸውን ዋና ዋና የፖሊሲ ለውጦችን ለማድረግ እንደማይጠቀሙበት ቃል ገብተዋል። የኮንሰርቫቲቭ ፓርቲ አመራር ውድድር የጊዜ ሰሌዳ በሚቀጥለው ሳምንት የሚታወቅ ሲሆን፣ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር እስከ መስከረም ወር ማብቂያ ድረስ ይሾማሉ ተብሎ ይጠበቃል። ይሁን እንጂ ይፋዊ ባልሆነ መንገድ ውድድሩ በመካሄድ ላይ ነው። የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ቱገንዳት፣ አርብ ዕለት ለዴይሊ ቴሌግራፍ በጻፉት ጽሁፍ የአመራርነት ወድድራቸውን የጀመሩ ሲሆን “የግብር ቅነሳ እና አዲስ ጉልበትና ሃሳብ” ይዘው እንደሚመጡ ቃል ገብተዋል። የቦሪስ ጆንሰን ቀንደኛ ተቺ የነበሩት የቀድሞ ወታደር ቱገንዳት “ከዚህ ቀደም በጦሩ ውስጥ አገልግያለሁ፣ አሁን ደግሞ በፓርላማ ውስጥ እየሰራሁ ነው። አሁን ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን የቀረበልኝን ጥሪ ለመመለስ ተስፋ አደርጋለሁ” ብለዋል። ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ብራቨርማን በበኩላቸው ለጠቅላይ ሚኒስትርነት እንደሚወዳደሩ አረጋግጠዋል። የብሬግዚት ሚኒስትሩ ቤከርም ሰዎች ለጠቅላይ ሚኒስትርነት እንዲወዳደሩ ከጠየቋቸው በኋላ ለመወዳደር እንዳሰቡ ተናግረዋል። የቦሪስ ጆንሰን ተቃዋሚ የነበሩት የቀድሞው የጤና ኃላፊ ሳጂድ ጃቪድ እና የትራንስፖርት ኃላፊ ግራንት ሻፕስም ውድድሩን ለመቀላቀል እንዳሰቡ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ሊዝ ትረስ፣ የቀድሞ ቻንስለር ሪሺ ሱናክ እና የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ጀረሚ ሃንትም በውድድሩ ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ ይገመታል። በሚቀጥሉት ቀናት በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ገለጻ እንደሚሰጥ ይጠበቃል። ሆኖም ማይክል ጎቭ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶሚኒክ ራብ እና የቀድሞ የጤና ኃላፊ ማት ሃንኩክን ጨምሮ የቀድሞ የፓርቲው አመራር አባላት እንደማይወዳደሩ ተናግረዋል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c9873qy97g9o |
3politics
| አገር ጥለው የሸሹት የቀድሞው የአፍጋኒስታን ፕሬዚዳንት ህዝቡን ይቅርታ ጠየቁ | ታሊባን የአፍጋኒስታንን መዲና ካቡልን መክበቡን ተከትሎ አገር ጥለው ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የተሰደዱት የቀድሞው የአፍጋኒስታን ፕሬዚዳንት አሽራፍ ጋኒ ህዝቡን ይቅርታ ጠየቁ። "ካቡልን ለቅቆ መውጣት በሕይወቴ ውስጥ በጣም ከባድ ውሳኔ ነበር።" በማለት የተናገሩት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ከዚህ በተለየ መልኩ ባለማድረጋቸውም ሃዘናቸውን ገልጸዋል። የታሊባን ታጣቂዎች ነሐሴ መጀመሪያ ላይ መዲናዋን ካቡልን መክበባቸውን ተከትሎ ነው አሽራፍ ጋኒ በድንገት ሃገር ጥለው የሸሹት። ህዝቡን ለመተው ሃሳባቸው እንዳልነበር የተናገሩት የቀድሞው ፕሬዚዳንት "ብቸኛው መንገድ ነው" ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም 169 ሚሊዮን ዶላር ይዘው ነው ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የተጓዙት የሚለውን "መሠረተ ቢስ" ውንጀላ በሚል በድጋሚ አስተባለዋል። ረቡዕ ዕለት በትዊተር ላይ በተጋራ መግለጫ እንደተጠቀሰው የቀድሞው ፕሬዚዳንት በአገሪቱ ሁከት እንዳይፈጠር አገሪቱን ለቅቆ ከመውጣት ውጭ ሌላ አማራጭ እንደሌለ ተናግረዋል። "በ 1990ዎቹ የእርስ በእርስ ጦርነትና የከተማ ላይ ውጊያ ካቡል ከደረሰባት ተመሳሳይ አደጋ ላይ እንዳትወድቅ በቤተ መንግሥቴ ደህንነት የተሰጠኝን ምክር በመስማት ነው የወጣሁት። ካቡልን እና ስድስት ሚሊዮን ዜጎቿን ለማዳን" በማለትም አስፍረዋል። አፍጋኒስታንን "ዲሞክራሲያዊ ፣ የበለፀገች እና ሉዓላዊ መንግሥት" እንድትሆን ለመርዳት ለ20 ዓመታት መስራታቸውንም ጠቅሰዋል። አክለውም "የኔ የስልጣን ምዕራፍ ከቀዳሚዎቼ ጋር ተመሳሳይ በሆነ በአሳዛኝ ሁኔታ መቋጨቱ ጥልቅ ጸጸት አሳድሮብኛል" ብለዋል። አገሪቱን ለቀው በመውጣታቸው ከአፍጋኒስታን ፖለቲከኞች ከፍተኛ ትችትን ያስተናገዱት የ 72 ዓመቱ የቀድሞ ፕሬዝዳንት "እኔ ከመውጣቴ በፊት የነበሩትን ክስተቶች" በተመለከተ በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርጉም ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም በፌስ ቡክ በቀጥታ በተላለፈ መልዕክታቸው አሽራፍ በደህንነት ቡድናቸው ከአገር ለመውጣት እንደተገደዱ ተናግረዋል። ምክንያቱንም ሲያስረዱ "ተይዤ የመገደሌ ሁኔታ ከፍተኛ ነበር" ብለዋል። የታሊባን ታጣቂዎች በካቡል ወደሚገኘው የፕሬዚዳንቱ ቤተ መንግሥት ካቀኑ በኋላ "ከክፍል ወደ ክፍል እየተዟዟሩ እኔን መፈለግ ጀመሩ" በማለትም አስረድተዋል። አገሪቱን ለቅቀው ሲወጡ ከፍተኛ ገንዘብ ወስደዋል የሚለውን ክስ በተመለከተም "ሸበጥ ጫማዬን እንኳ አውልቄ ደህና ጫማ እንዳደርግ አልተፈቀደልኝም" ብለዋል። | አገር ጥለው የሸሹት የቀድሞው የአፍጋኒስታን ፕሬዚዳንት ህዝቡን ይቅርታ ጠየቁ ታሊባን የአፍጋኒስታንን መዲና ካቡልን መክበቡን ተከትሎ አገር ጥለው ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የተሰደዱት የቀድሞው የአፍጋኒስታን ፕሬዚዳንት አሽራፍ ጋኒ ህዝቡን ይቅርታ ጠየቁ። "ካቡልን ለቅቆ መውጣት በሕይወቴ ውስጥ በጣም ከባድ ውሳኔ ነበር።" በማለት የተናገሩት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ከዚህ በተለየ መልኩ ባለማድረጋቸውም ሃዘናቸውን ገልጸዋል። የታሊባን ታጣቂዎች ነሐሴ መጀመሪያ ላይ መዲናዋን ካቡልን መክበባቸውን ተከትሎ ነው አሽራፍ ጋኒ በድንገት ሃገር ጥለው የሸሹት። ህዝቡን ለመተው ሃሳባቸው እንዳልነበር የተናገሩት የቀድሞው ፕሬዚዳንት "ብቸኛው መንገድ ነው" ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም 169 ሚሊዮን ዶላር ይዘው ነው ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የተጓዙት የሚለውን "መሠረተ ቢስ" ውንጀላ በሚል በድጋሚ አስተባለዋል። ረቡዕ ዕለት በትዊተር ላይ በተጋራ መግለጫ እንደተጠቀሰው የቀድሞው ፕሬዚዳንት በአገሪቱ ሁከት እንዳይፈጠር አገሪቱን ለቅቆ ከመውጣት ውጭ ሌላ አማራጭ እንደሌለ ተናግረዋል። "በ 1990ዎቹ የእርስ በእርስ ጦርነትና የከተማ ላይ ውጊያ ካቡል ከደረሰባት ተመሳሳይ አደጋ ላይ እንዳትወድቅ በቤተ መንግሥቴ ደህንነት የተሰጠኝን ምክር በመስማት ነው የወጣሁት። ካቡልን እና ስድስት ሚሊዮን ዜጎቿን ለማዳን" በማለትም አስፍረዋል። አፍጋኒስታንን "ዲሞክራሲያዊ ፣ የበለፀገች እና ሉዓላዊ መንግሥት" እንድትሆን ለመርዳት ለ20 ዓመታት መስራታቸውንም ጠቅሰዋል። አክለውም "የኔ የስልጣን ምዕራፍ ከቀዳሚዎቼ ጋር ተመሳሳይ በሆነ በአሳዛኝ ሁኔታ መቋጨቱ ጥልቅ ጸጸት አሳድሮብኛል" ብለዋል። አገሪቱን ለቀው በመውጣታቸው ከአፍጋኒስታን ፖለቲከኞች ከፍተኛ ትችትን ያስተናገዱት የ 72 ዓመቱ የቀድሞ ፕሬዝዳንት "እኔ ከመውጣቴ በፊት የነበሩትን ክስተቶች" በተመለከተ በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርጉም ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም በፌስ ቡክ በቀጥታ በተላለፈ መልዕክታቸው አሽራፍ በደህንነት ቡድናቸው ከአገር ለመውጣት እንደተገደዱ ተናግረዋል። ምክንያቱንም ሲያስረዱ "ተይዤ የመገደሌ ሁኔታ ከፍተኛ ነበር" ብለዋል። የታሊባን ታጣቂዎች በካቡል ወደሚገኘው የፕሬዚዳንቱ ቤተ መንግሥት ካቀኑ በኋላ "ከክፍል ወደ ክፍል እየተዟዟሩ እኔን መፈለግ ጀመሩ" በማለትም አስረድተዋል። አገሪቱን ለቅቀው ሲወጡ ከፍተኛ ገንዘብ ወስደዋል የሚለውን ክስ በተመለከተም "ሸበጥ ጫማዬን እንኳ አውልቄ ደህና ጫማ እንዳደርግ አልተፈቀደልኝም" ብለዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-58500497 |
0business
| ጋናዊው ባለሀብት ቼልሲን በ3.1 ቢሊዮን ዶላር ሊገዙ እንደሆነ ተዘገበ | ጋናዊው የንግድ ሰው የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ኃያል ክለብ የሆነውን ቼልሲ የእግር ኳስ ቡድንን በ3.1 ቢሊዮን ዶላር ለመግዛት ፍላጎታቸውን መግለጻቸው ተዘገበ። በስፋት ዉንቱሚ በሚለው ቅጽል ስማቸው የሚታወቁት ጋናዊው ባለሀብት ቤርናርድ አንትዊ ቦሲያኮ የቼልሲ ቡድንን የመግዛት ፍላጎታቸው የሚሳካ ከሆነ የፕሪሚዬር ሊግ ኃያል ቡድን ባለቤት በመሆን የመጀመሪያው አፍሪካዊ ይሆናሉ። ጋናዊው ባለሀብት ቡድኑን በእጃቸው ካስገቡ የማንችስተር ዩናይትዱን ክሪስቲያኖ ሮናልዶን እና የፓሪ ሴንጄርሜኑን ሊዮኔል ሜሲን የመሳሳሉ የእግር ኳስ ከዋክብትን ወደ ቡድኑ የማምጣት ፍላጉት እንዳላቸው ተነግሯል። ጋናዊው ባለሀብት ቤርናርድ በአገሪቱ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ባለቤት እና ፖለቲከኛ ሲሆኑ፣ በስፖርቱ ዘርፍ ብዙም የሚታወቅ ታሪክ ስለሌላቸው ቼልሲን የመግዛት ፍላጎታቸው ይፋ ሲሆን በርካታ ጋናውያንን አስደንቋል። የግለሰቡ የሀብት ምንጭ የወርቅ ማዕድን ሲሆን በተጨማሪም የሬዲዮ እና የቴሌቪዥን ጣቢያዎች አሏቸው። ነገር ግን አስካሁን ያላቸውን የሀብት መጠን በይፋ ገልጸው ስለማያውቁ ምን ያህል እንደሆነ መረጃ የለም። ባለሀብቱ ቤርናርድ ከማዕድን ማውጣቱ በተጨማሪ በጋና ፖለቲካ ውስጥ ተሳታፊ ሲሆኑ፣ በዚህም የአገሪቱ ገዢ ፓርቲ የአሻንቲ ክልል ሊቀመንበር ናቸው። የወቅቱ የቼልሲ እግር ኳስ ቡድን ባለቤት ሩሲያዊው ሮማን አብራሞቪች ሩሲያ ዩክሬንን መውረሯን ተከተሎ ባጋጠማቸው ጫና ቡድኑን እንደሚሸጡ ከሳምንት በፊት ማሳወቃቸው ይታወሳል። አብራሞቪች የሩሲያው መሪ ቭላድሚር ፑቲን ጋር የቀረበ ግንኙነት አላቸው ከተባሉ ሩሲያውያን ከበርቴዎች መካከል አንዱ በመሆናቸው ከዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት በኩል እቀባዎች ተጥሎባቸዋል። አብራሞቪች ቼልሲን ለመሸጥ ያላቸውን ፍላጎት ይፋ ካደረጉ በኋላ የጋናዊው ባለሀብት ጠበቆች እና የንግድ አማካሪዎች ከቼልሲ ባለቤት ጋር ድርድር ለማድረግ ለንደን እንደነበሩ ተገልጿል። ከበርቴው ንብረታቸው በመታገዱ እና የጉዞ እቀባ ስለተጣለባቸው የእግር ኳስ ቡድናቸውን የመሸጥ ፍላጎታቸው ለጊዜው ተግባራዊ እንዳያደርጉ መገደዳቸው አይቀርም ተብሏል። | ጋናዊው ባለሀብት ቼልሲን በ3.1 ቢሊዮን ዶላር ሊገዙ እንደሆነ ተዘገበ ጋናዊው የንግድ ሰው የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ኃያል ክለብ የሆነውን ቼልሲ የእግር ኳስ ቡድንን በ3.1 ቢሊዮን ዶላር ለመግዛት ፍላጎታቸውን መግለጻቸው ተዘገበ። በስፋት ዉንቱሚ በሚለው ቅጽል ስማቸው የሚታወቁት ጋናዊው ባለሀብት ቤርናርድ አንትዊ ቦሲያኮ የቼልሲ ቡድንን የመግዛት ፍላጎታቸው የሚሳካ ከሆነ የፕሪሚዬር ሊግ ኃያል ቡድን ባለቤት በመሆን የመጀመሪያው አፍሪካዊ ይሆናሉ። ጋናዊው ባለሀብት ቡድኑን በእጃቸው ካስገቡ የማንችስተር ዩናይትዱን ክሪስቲያኖ ሮናልዶን እና የፓሪ ሴንጄርሜኑን ሊዮኔል ሜሲን የመሳሳሉ የእግር ኳስ ከዋክብትን ወደ ቡድኑ የማምጣት ፍላጉት እንዳላቸው ተነግሯል። ጋናዊው ባለሀብት ቤርናርድ በአገሪቱ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ባለቤት እና ፖለቲከኛ ሲሆኑ፣ በስፖርቱ ዘርፍ ብዙም የሚታወቅ ታሪክ ስለሌላቸው ቼልሲን የመግዛት ፍላጎታቸው ይፋ ሲሆን በርካታ ጋናውያንን አስደንቋል። የግለሰቡ የሀብት ምንጭ የወርቅ ማዕድን ሲሆን በተጨማሪም የሬዲዮ እና የቴሌቪዥን ጣቢያዎች አሏቸው። ነገር ግን አስካሁን ያላቸውን የሀብት መጠን በይፋ ገልጸው ስለማያውቁ ምን ያህል እንደሆነ መረጃ የለም። ባለሀብቱ ቤርናርድ ከማዕድን ማውጣቱ በተጨማሪ በጋና ፖለቲካ ውስጥ ተሳታፊ ሲሆኑ፣ በዚህም የአገሪቱ ገዢ ፓርቲ የአሻንቲ ክልል ሊቀመንበር ናቸው። የወቅቱ የቼልሲ እግር ኳስ ቡድን ባለቤት ሩሲያዊው ሮማን አብራሞቪች ሩሲያ ዩክሬንን መውረሯን ተከተሎ ባጋጠማቸው ጫና ቡድኑን እንደሚሸጡ ከሳምንት በፊት ማሳወቃቸው ይታወሳል። አብራሞቪች የሩሲያው መሪ ቭላድሚር ፑቲን ጋር የቀረበ ግንኙነት አላቸው ከተባሉ ሩሲያውያን ከበርቴዎች መካከል አንዱ በመሆናቸው ከዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት በኩል እቀባዎች ተጥሎባቸዋል። አብራሞቪች ቼልሲን ለመሸጥ ያላቸውን ፍላጎት ይፋ ካደረጉ በኋላ የጋናዊው ባለሀብት ጠበቆች እና የንግድ አማካሪዎች ከቼልሲ ባለቤት ጋር ድርድር ለማድረግ ለንደን እንደነበሩ ተገልጿል። ከበርቴው ንብረታቸው በመታገዱ እና የጉዞ እቀባ ስለተጣለባቸው የእግር ኳስ ቡድናቸውን የመሸጥ ፍላጎታቸው ለጊዜው ተግባራዊ እንዳያደርጉ መገደዳቸው አይቀርም ተብሏል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60696157 |
2health
| ክብደትዎን መቀነስ ይፈልጋሉ? ቁርስ እንዴት መመገብ እንዳለብዎ እንንገርዎ | ቁርስዎን በደንብ መመገብ እና ቀለል ያለ እራት መብላት የረሃብ ስሜት እንዳይኖር በማድረግ ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል ይላሉ ተመራማሪዎች። ሳይንቲስቶች ከበድ ያለ ቁርስ ወይም ከበድ ያለ እራት በሰዎች ክብደት ላይ የሚያመጣውን ተፅእኖ ለማነፃፀር ሞክረዋል። የቀኑን ዋነኛ ምግብ በየትኛው ሰዓት ቢመገቡ ሰዎች የሚያቃጥሉት ካሎሪ ተመሳሳይ ሆኖ እንደሚሆን የአበርዲን ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች ደርሰውበታል። ነገር ግን በደንብ ቁርሳቸውን የተመገቡ ሰዎች በቀን ውስጥ ያላቸው የምግብ ፍላጎት አነስተኛ ሆኖ ታይቷል፤ ይህም ማለት የሚፈልጉትን አመጋገብ ለመከተል ቀላል ያደርገዋል። አጥኚዎቹ በዚህ ምርምራቸው ‘ክሮኖ ኒውትሪሽን’ የተሰኘው ፅንሰ ሃሳብን በጥልቀት ለማየት ሞክረዋል። [ክሮኖ ኒውትሪሽን በየትኛው ሰዓት ምግብ መመገብ የበለጠ ውጤታማ ያደርገናል የሚለውን የሚመረምር ሳይንስ ነው። የሰውነትዎን አካላዊ፣ አዕምሯዊ እና ስሜታዊ ዑደቶችን የሚቆጣጠረው ክፍል ምግብ ጋር ያለውንም ዝምድና ይገመግማል። ] ከመሸ በኋላ መመገብ ለሰውነታችን መጥፎ ጊዜ ነው፣ ምክንያቱም የሰውነታችን ሰዓት ምግብን ወደ ኃይል የሚለውጠውን (ሜታቦሊዝም) ወደ እንቅልፍ ስለሚቀይረው ነው። ተመራማሪዎቹ ያሳተፏቸው 30 በጎ ፈቃደኞች ከሁለት ወራት በላይ ቁርስ፣ ምሳ እና እራት በቀን በአጠቃላይ እስከ 1 ሺህ 700 ካሎሪ የሚሆን ምግብ ተዘጋጅቶላቸው ነበር። በአንደኛው ወር ለቀን የሚያስፈልገውን የካሎሪ መጠን ግማሹን ለቁርስ እንዲበሉ እና ምሳ እና እራት ደግሞ አነስ ያለ ምግብ እንዲመገቡ ተደርገዋል። በሁለተኛው ወር እነዚህ በጎ ፈቃደኞች ከቁርስ ይልቅ እራት ላይ ከበድ ያለ ምግብ እንዲበሉ ተደረጉ። ሴል ሜታቦሊዝም በተሰኘው ጆርናል ላይ በታተመው ውጤት መሰረት የቀኑን ከባድ ምግብ በየትኛውም ሰዓት መመገብ ሰውነታችን በቀን ምን ያህል ካሎሪ ያቃጥላል የሚለው ላይ ምንም ልዩነት የለውም። ዋነኛው ልዩነት ግን የታየው በምግብ ፍላጎት ወይም የረሃብ ስሜት ላይ ነው። ከፍተኛ ቁርስ የሚመገቡ ሰዎች በቀን ውስጥ አነስተኛ የምግብ ፍላጎት እንዲኖራቸው ማድረግና የረሃብ ስሜትንም እንዲቆጣጠሩ ያደርጋል። ፕሮፌሰር አሌክሳንድራ ጆንስተን እንደሚሉት በርካቶች የሚመገቡትን የምግብ መጠን በማይቆጣጠሩበት ሁኔታ ውስጥ ጥናቱ ወሳኝ ሊሆን ይችላል። “ጥናቶቹ እንደሚጠቁሙት የምግብ ፍላጎትን ለመቆጣጠር በደንብ ቁርስ መመገብ መሠረታዊ ነው” ይላሉ። “ቀንዎን በጤናማ እና በትልቅ ቁርስ መጀመር ከቻሉ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማድረግ እንዲሁም በተቀሩት ሰዓታት ያለውን የምግብ ፋላጎትን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ዕድል ይሰጣል” በማለት ያስረዳሉ። በጥናቱ ውስጥ የተካተቱት የቁርስ ዓይነቶች የፍራፍሬ ጭማቂ፣ እርጎ፣ እንቁላል፣ ቋሊማ (ሶሴጅ) እና እንጉዳይ የያዘ ሲሆን፣ ይህም ሁሉም ሰዎች ጥጋብ እንዲሰማቸው የሚያደርግ ከፍተኛ የፕሮቲን ይዘት ያለው ነው። ከፍተኛ ቁርስ መመገብ ለምን የምግብ ፍላጎትን እንደሚቀንስ ግልፅ አይደለም። ነገር ግን ፕሮፌሰር ጆንስተን እንደሚሉት ይህ ሁኔታ ከአዕምሯችን የምግብ ፍላጎት ጋር የተያያዘ እንደሆነ ሃሳቦች አሉ ይላሉ። “የአዕምሯችን የምግብ ፍላጎት የሌሊቱን ጾም የምንፈታበትና የመጀመሪያ ምግብ ጋር የበለጠ የተጣጠመ ነው” ይላሉ። ነገር ግን ይህ ውጤት ከበርካቶች የአመጋገብ ልምድ ጋር ተቃራኒ ነው። “በርካቶች የሚተኙበትን ሰዓታት ለመጨመር እየሞከሩ ባለበት ወቅት በማለዳ ተነስተው ምግብ ለማዘጋጀትም ሆነ ተቀምጠው በደንብ ለመብላት ጊዜ አይኖራቸውም። ይህ ማለት በርካቶች በደንብ የሚበሉት እራት ነው” ይላሉ ፕሮፌሰር ጆንስተን። በአሁኑ ወቅት ሳይንቲስቶች በፈረቃ የሚሰሩ ሠራተኞች እኩለ ሌሊት ላይ ሲመገቡ ምን እንደሚፈጠር እየመረመሩ ነው። በተጨማሪም ግለሰቦች እንደ ባህርያቸው የጠዋት ሰዎች ከሆኑ ጠዋት፣ ወይም ደግሞ የማታ ሰዎች ከሆኑ ማታ መብላት ይኖርባቸው ይሆን? የሚለውን ለማየት እየሞከሩ ነው። “አመጋገብዎን ለመለወጥ እያሰቡ ከሆነና የሚራቡበትን ወይም ተጨማሪ መክሰስ ሰውነትዎት የሚፈልግበትን ወቅት ያስቡ” በማለት የሚናገሩት የአስተን ዩኒቨርስቲ የአመጋገብ ባለሙያ ዶክተር ዱዋን ሜሎር ናቸው። “ረሃብ የሚሰማዎት ጠዋት ከሆነ በደንብ ቁርስ መመገብ ሊረዳዎት ይችላል። በተመሳሳይም የምሽት ተመጋቢ ከሆኑም በቀን ውስጥ አነስተኛ ምግቦችን ተመግበው እራት ላይ በደንብ መመገብ ሊጠቅምዎ ይችላል” ይላሉ። | ክብደትዎን መቀነስ ይፈልጋሉ? ቁርስ እንዴት መመገብ እንዳለብዎ እንንገርዎ ቁርስዎን በደንብ መመገብ እና ቀለል ያለ እራት መብላት የረሃብ ስሜት እንዳይኖር በማድረግ ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል ይላሉ ተመራማሪዎች። ሳይንቲስቶች ከበድ ያለ ቁርስ ወይም ከበድ ያለ እራት በሰዎች ክብደት ላይ የሚያመጣውን ተፅእኖ ለማነፃፀር ሞክረዋል። የቀኑን ዋነኛ ምግብ በየትኛው ሰዓት ቢመገቡ ሰዎች የሚያቃጥሉት ካሎሪ ተመሳሳይ ሆኖ እንደሚሆን የአበርዲን ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች ደርሰውበታል። ነገር ግን በደንብ ቁርሳቸውን የተመገቡ ሰዎች በቀን ውስጥ ያላቸው የምግብ ፍላጎት አነስተኛ ሆኖ ታይቷል፤ ይህም ማለት የሚፈልጉትን አመጋገብ ለመከተል ቀላል ያደርገዋል። አጥኚዎቹ በዚህ ምርምራቸው ‘ክሮኖ ኒውትሪሽን’ የተሰኘው ፅንሰ ሃሳብን በጥልቀት ለማየት ሞክረዋል። [ክሮኖ ኒውትሪሽን በየትኛው ሰዓት ምግብ መመገብ የበለጠ ውጤታማ ያደርገናል የሚለውን የሚመረምር ሳይንስ ነው። የሰውነትዎን አካላዊ፣ አዕምሯዊ እና ስሜታዊ ዑደቶችን የሚቆጣጠረው ክፍል ምግብ ጋር ያለውንም ዝምድና ይገመግማል። ] ከመሸ በኋላ መመገብ ለሰውነታችን መጥፎ ጊዜ ነው፣ ምክንያቱም የሰውነታችን ሰዓት ምግብን ወደ ኃይል የሚለውጠውን (ሜታቦሊዝም) ወደ እንቅልፍ ስለሚቀይረው ነው። ተመራማሪዎቹ ያሳተፏቸው 30 በጎ ፈቃደኞች ከሁለት ወራት በላይ ቁርስ፣ ምሳ እና እራት በቀን በአጠቃላይ እስከ 1 ሺህ 700 ካሎሪ የሚሆን ምግብ ተዘጋጅቶላቸው ነበር። በአንደኛው ወር ለቀን የሚያስፈልገውን የካሎሪ መጠን ግማሹን ለቁርስ እንዲበሉ እና ምሳ እና እራት ደግሞ አነስ ያለ ምግብ እንዲመገቡ ተደርገዋል። በሁለተኛው ወር እነዚህ በጎ ፈቃደኞች ከቁርስ ይልቅ እራት ላይ ከበድ ያለ ምግብ እንዲበሉ ተደረጉ። ሴል ሜታቦሊዝም በተሰኘው ጆርናል ላይ በታተመው ውጤት መሰረት የቀኑን ከባድ ምግብ በየትኛውም ሰዓት መመገብ ሰውነታችን በቀን ምን ያህል ካሎሪ ያቃጥላል የሚለው ላይ ምንም ልዩነት የለውም። ዋነኛው ልዩነት ግን የታየው በምግብ ፍላጎት ወይም የረሃብ ስሜት ላይ ነው። ከፍተኛ ቁርስ የሚመገቡ ሰዎች በቀን ውስጥ አነስተኛ የምግብ ፍላጎት እንዲኖራቸው ማድረግና የረሃብ ስሜትንም እንዲቆጣጠሩ ያደርጋል። ፕሮፌሰር አሌክሳንድራ ጆንስተን እንደሚሉት በርካቶች የሚመገቡትን የምግብ መጠን በማይቆጣጠሩበት ሁኔታ ውስጥ ጥናቱ ወሳኝ ሊሆን ይችላል። “ጥናቶቹ እንደሚጠቁሙት የምግብ ፍላጎትን ለመቆጣጠር በደንብ ቁርስ መመገብ መሠረታዊ ነው” ይላሉ። “ቀንዎን በጤናማ እና በትልቅ ቁርስ መጀመር ከቻሉ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማድረግ እንዲሁም በተቀሩት ሰዓታት ያለውን የምግብ ፋላጎትን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ዕድል ይሰጣል” በማለት ያስረዳሉ። በጥናቱ ውስጥ የተካተቱት የቁርስ ዓይነቶች የፍራፍሬ ጭማቂ፣ እርጎ፣ እንቁላል፣ ቋሊማ (ሶሴጅ) እና እንጉዳይ የያዘ ሲሆን፣ ይህም ሁሉም ሰዎች ጥጋብ እንዲሰማቸው የሚያደርግ ከፍተኛ የፕሮቲን ይዘት ያለው ነው። ከፍተኛ ቁርስ መመገብ ለምን የምግብ ፍላጎትን እንደሚቀንስ ግልፅ አይደለም። ነገር ግን ፕሮፌሰር ጆንስተን እንደሚሉት ይህ ሁኔታ ከአዕምሯችን የምግብ ፍላጎት ጋር የተያያዘ እንደሆነ ሃሳቦች አሉ ይላሉ። “የአዕምሯችን የምግብ ፍላጎት የሌሊቱን ጾም የምንፈታበትና የመጀመሪያ ምግብ ጋር የበለጠ የተጣጠመ ነው” ይላሉ። ነገር ግን ይህ ውጤት ከበርካቶች የአመጋገብ ልምድ ጋር ተቃራኒ ነው። “በርካቶች የሚተኙበትን ሰዓታት ለመጨመር እየሞከሩ ባለበት ወቅት በማለዳ ተነስተው ምግብ ለማዘጋጀትም ሆነ ተቀምጠው በደንብ ለመብላት ጊዜ አይኖራቸውም። ይህ ማለት በርካቶች በደንብ የሚበሉት እራት ነው” ይላሉ ፕሮፌሰር ጆንስተን። በአሁኑ ወቅት ሳይንቲስቶች በፈረቃ የሚሰሩ ሠራተኞች እኩለ ሌሊት ላይ ሲመገቡ ምን እንደሚፈጠር እየመረመሩ ነው። በተጨማሪም ግለሰቦች እንደ ባህርያቸው የጠዋት ሰዎች ከሆኑ ጠዋት፣ ወይም ደግሞ የማታ ሰዎች ከሆኑ ማታ መብላት ይኖርባቸው ይሆን? የሚለውን ለማየት እየሞከሩ ነው። “አመጋገብዎን ለመለወጥ እያሰቡ ከሆነና የሚራቡበትን ወይም ተጨማሪ መክሰስ ሰውነትዎት የሚፈልግበትን ወቅት ያስቡ” በማለት የሚናገሩት የአስተን ዩኒቨርስቲ የአመጋገብ ባለሙያ ዶክተር ዱዋን ሜሎር ናቸው። “ረሃብ የሚሰማዎት ጠዋት ከሆነ በደንብ ቁርስ መመገብ ሊረዳዎት ይችላል። በተመሳሳይም የምሽት ተመጋቢ ከሆኑም በቀን ውስጥ አነስተኛ ምግቦችን ተመግበው እራት ላይ በደንብ መመገብ ሊጠቅምዎ ይችላል” ይላሉ። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c4n0dgyddg8o |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ አውስትራሊያ የኮሮና ክትባት በነጻ እሰጣለሁ አለች | አውስትራሊያ ኮቪድ-19 ክትባትን ለአገሬ ሕዝብ ሽራፊ ሳንቲም ሳልቀበል አድላለሁ ብላለች፡፡ አውትራሊያ 25 ሚሊዮን ለሚሆነው ሕዝቧ የምታድለውን ክትባት የምታገኘው ከእንግሊዝ ነው፡፡ አሁን በሙከራ ላይ ካሉ የክትባት ዜናዎች ሁሉ ላቅ ያለ ተስፋ የተጣለበት የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲው ክትባት ነው፡፡ ኦክስፎርድ ክትባቱን ከታዋቂው የመድኃኒት አምራች አስትራዜኔካ ጋር በመቀናጀት እያዳበረው ይገኛል፡፡ ይህ ክትባት በቀጣይ የሚደረጉ የመጨረሻ ምዕራፍ የክሊኒካል ሙከራዎች ስኬታማ ሆነው ከተጠናቀቁ አውስራሊያ ክትባቱን ለመግዛት ቀዳሚ አገር ሆና ተሰልፋለች ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን፡፡ ሞሪሰን እንደሚሉት ክትባቱን እያንዳንዱ ዜጋ እንዲወስድ ግዴታ ይጣልበታል፡፡ በአውስትራሊያ የሟቾች ቁጥር 450 አልፏል፡፡ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰውም በቪክቶሪያ ግዛት ነው፡፡ በዚህ ወር መጀመርያ አካባቢ ቪክቶሪያ የአስቸኳይ ጊዜ በመደንገግ ሰዎች ቤታቸው እንዲቀመጡ አስገድዳ ነበር፡፡ ይህም በሽታው ሥርጭት ከፍ ብሎ በመታየቱ ነው፡፡ አሁን በአውስራሊያ 7ሺ የሚሆኑ ሰዎች በቫይረሱ እንደተነኩ ይገመታል፡፡ ሆኖም አሁን በየቀኑ አዳዲስ ታማሚዎቸ ቁጥር እየጨመረ ሳይሆን እየቀነሰ ነው ያለው፡፡ የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲና የአስትራዜኔካ ጥምረት እየተሞከረ ያለው ክትባት በዓለም ላይ አሁን ተስፋ ከተጣለባቸው አምስት ሙከራዎች በዋነኛነት የሚጠቀስ ነው፡፡ አገራት ይህን ክትባት ወደ ገበያ ሲወጣ ቅድሚያ አግኝተው ለሕዝባቸው ለማድረስ ከፍተኛ ፉክክር ላይ ናቸው፡፡ የመጨረሻው የሙከራ ምዕራፍ ስኬታማ ሲሆን አውስራሊያ መድኃኒቱን በአገሯ ለማምረት ተዘጋጅታ ከወዲሁ ስምምነት ፈጽማለች፡፡ ሞሪስ እንደሚሉት ‹‹ወዲያው አምርተን ወዲያው 25 ሚሊዮን ሕዝባችንን እንከትባለን፡፡›› አንድ አገር ሙሉ ሕዝቧን ለመክተብ ምን ያህል ወጪ ያስወጣታል የሚለው ገና አልተሰላም፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ አውስትራሊያ ሌላ ስምምነት አድርጋለች፡፡ ይህ ስምምነት 25 ሚሊዮን ዶላር አስከፍሏታል፡፡ ስምምነቱ ከአሜሪካ የመድኃኒት ቁሳቁስ አምራች ቤክተን ዲኪንሰን ጋር ሲሆን 100 ሚሊዮን መርፌና ስሪንጆችን ለማቅረብ የተደረገ ስምምነት ነው፡፡ አውስትራሊያ ከአስትራዜኔካ ጋር ያደረገቸው የክትባት ስምምነት በታሪኳ የመጀመርያው ነው፡፡ የአውስትራሊያ ሕዝብ መቼ ይከተባል ለሚለው ሚስተር ሞሪሰን ‹‹ክትባቱ የመጨረሻው ሙከራ ከተሳካ በመጪው ዓመት የመጀመርያዎቹ ወራት አውስትራሊያዊያን ይከተቡታል›› ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሁሉም ዜጋ የመከተብ ግዴታ ይጣልበታል ቢሉም ይህ አከራካሪ ጉዳይ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ ሞሪሰን መንግስታቸው በዚህ ረገድ ገና ፖሊሲ እየቀረጸ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ለአንድ የአገሬው ራዲዮ ጣቢያ በሰጡት ቃለ ምልልስ ሚስተር ሞሪሰን ‹‹በተለየ የጤና ምክንያት መድኃኒቱን ለመከተብ የማይገደዱ›› እንደሚኖሩ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡ ‹‹እያወራን ያለነው የዓለምን ምጣኔ ሀብት ስላንኮታኮተ ወረርሽኝ ነው፡፡ ሺዎችን ሕይወት ስለቀጠፈ ወረርሽኝ ነው፤ ክትባቱ አማራጭ ተደርጎ የሚወሰድ ይሆናል ብዬ አልጠብቅም›› ብለዋል አስገዳጅነቱ አይቀሬ መሆኑን ሲያስገነዝቡ፡፡ ሚስተር ሞሪሰን በትንሹ 95 ከመቶ አውስትራሊያዊያንን ለመከተብ እንደታሰበ አልሸሸጉም፡፡ | ኮሮናቫይረስ፡ አውስትራሊያ የኮሮና ክትባት በነጻ እሰጣለሁ አለች አውስትራሊያ ኮቪድ-19 ክትባትን ለአገሬ ሕዝብ ሽራፊ ሳንቲም ሳልቀበል አድላለሁ ብላለች፡፡ አውትራሊያ 25 ሚሊዮን ለሚሆነው ሕዝቧ የምታድለውን ክትባት የምታገኘው ከእንግሊዝ ነው፡፡ አሁን በሙከራ ላይ ካሉ የክትባት ዜናዎች ሁሉ ላቅ ያለ ተስፋ የተጣለበት የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲው ክትባት ነው፡፡ ኦክስፎርድ ክትባቱን ከታዋቂው የመድኃኒት አምራች አስትራዜኔካ ጋር በመቀናጀት እያዳበረው ይገኛል፡፡ ይህ ክትባት በቀጣይ የሚደረጉ የመጨረሻ ምዕራፍ የክሊኒካል ሙከራዎች ስኬታማ ሆነው ከተጠናቀቁ አውስራሊያ ክትባቱን ለመግዛት ቀዳሚ አገር ሆና ተሰልፋለች ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን፡፡ ሞሪሰን እንደሚሉት ክትባቱን እያንዳንዱ ዜጋ እንዲወስድ ግዴታ ይጣልበታል፡፡ በአውስትራሊያ የሟቾች ቁጥር 450 አልፏል፡፡ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰውም በቪክቶሪያ ግዛት ነው፡፡ በዚህ ወር መጀመርያ አካባቢ ቪክቶሪያ የአስቸኳይ ጊዜ በመደንገግ ሰዎች ቤታቸው እንዲቀመጡ አስገድዳ ነበር፡፡ ይህም በሽታው ሥርጭት ከፍ ብሎ በመታየቱ ነው፡፡ አሁን በአውስራሊያ 7ሺ የሚሆኑ ሰዎች በቫይረሱ እንደተነኩ ይገመታል፡፡ ሆኖም አሁን በየቀኑ አዳዲስ ታማሚዎቸ ቁጥር እየጨመረ ሳይሆን እየቀነሰ ነው ያለው፡፡ የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲና የአስትራዜኔካ ጥምረት እየተሞከረ ያለው ክትባት በዓለም ላይ አሁን ተስፋ ከተጣለባቸው አምስት ሙከራዎች በዋነኛነት የሚጠቀስ ነው፡፡ አገራት ይህን ክትባት ወደ ገበያ ሲወጣ ቅድሚያ አግኝተው ለሕዝባቸው ለማድረስ ከፍተኛ ፉክክር ላይ ናቸው፡፡ የመጨረሻው የሙከራ ምዕራፍ ስኬታማ ሲሆን አውስራሊያ መድኃኒቱን በአገሯ ለማምረት ተዘጋጅታ ከወዲሁ ስምምነት ፈጽማለች፡፡ ሞሪስ እንደሚሉት ‹‹ወዲያው አምርተን ወዲያው 25 ሚሊዮን ሕዝባችንን እንከትባለን፡፡›› አንድ አገር ሙሉ ሕዝቧን ለመክተብ ምን ያህል ወጪ ያስወጣታል የሚለው ገና አልተሰላም፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ አውስትራሊያ ሌላ ስምምነት አድርጋለች፡፡ ይህ ስምምነት 25 ሚሊዮን ዶላር አስከፍሏታል፡፡ ስምምነቱ ከአሜሪካ የመድኃኒት ቁሳቁስ አምራች ቤክተን ዲኪንሰን ጋር ሲሆን 100 ሚሊዮን መርፌና ስሪንጆችን ለማቅረብ የተደረገ ስምምነት ነው፡፡ አውስትራሊያ ከአስትራዜኔካ ጋር ያደረገቸው የክትባት ስምምነት በታሪኳ የመጀመርያው ነው፡፡ የአውስትራሊያ ሕዝብ መቼ ይከተባል ለሚለው ሚስተር ሞሪሰን ‹‹ክትባቱ የመጨረሻው ሙከራ ከተሳካ በመጪው ዓመት የመጀመርያዎቹ ወራት አውስትራሊያዊያን ይከተቡታል›› ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሁሉም ዜጋ የመከተብ ግዴታ ይጣልበታል ቢሉም ይህ አከራካሪ ጉዳይ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ ሞሪሰን መንግስታቸው በዚህ ረገድ ገና ፖሊሲ እየቀረጸ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ለአንድ የአገሬው ራዲዮ ጣቢያ በሰጡት ቃለ ምልልስ ሚስተር ሞሪሰን ‹‹በተለየ የጤና ምክንያት መድኃኒቱን ለመከተብ የማይገደዱ›› እንደሚኖሩ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡ ‹‹እያወራን ያለነው የዓለምን ምጣኔ ሀብት ስላንኮታኮተ ወረርሽኝ ነው፡፡ ሺዎችን ሕይወት ስለቀጠፈ ወረርሽኝ ነው፤ ክትባቱ አማራጭ ተደርጎ የሚወሰድ ይሆናል ብዬ አልጠብቅም›› ብለዋል አስገዳጅነቱ አይቀሬ መሆኑን ሲያስገነዝቡ፡፡ ሚስተር ሞሪሰን በትንሹ 95 ከመቶ አውስትራሊያዊያንን ለመከተብ እንደታሰበ አልሸሸጉም፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/news-53831242 |
3politics
| ኢዜማ በ28 ምርጫ ወረዳዎች ምርጫ እንዲደገም ያቀረበው አቤቱታ ላይ ቦርዱ ምላሽ እንዲሰጥ ፍርድ ቤት ወሰነ | የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ሰኔ 14 በተካሄደው ብሔራዊ ምርጫ በሃያ ስምንት የምርጫ ወረዳዎች ምርጫው እንዲደደገም ያቀረበው አቤቱታ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምላሽ እንዲሰጥ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ አሳልፏል። ይህንን ውሳኔ ያሳለፈው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 2ኛ የምርጫ ጉዳይ ችሎት በዛሬው ዕለት መሆኑንም ኢዜማ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አሳውቋል። ፍርድ ቤቱ ፓርቲው በ28 ምርጫ ወረዳዎች ምርጫ እንዲደገም ያቀረበውን አቤቱታ ሲመረምር ቆይቶም ፓርቲው ያቀረበውን የይግባኝ አቤቱታ ተቀብሎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በጉዳዩ ላይ ምላሽ ይዞ እንዲቀርብ ተወስኗል። ምርጫ ቦርድ ለሐምሌ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ምላሹን ይዞ መቅረብ እንዳለበትም ፍርድ ቤቱ በዛሬው እለት መበየኑ ተገልጿል። ከዚህም በተጨማሪ ኢዜማ ከዚህ ቀደም ለምርጫ ቦርድ ያስገባቸውን የቅሬታ ማስገቢያ ቅፆች ቅጂም ከሐምሌ 30 በፊት ቦርዱ ለፍርድ ቤቱ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ተላልፏል። ኢዜማ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ያስገባው የይግባኝ አቤቱታ ጥሰት ተፈጽሞባቸዋል ባላቸው 28 የምርጫ ወረዳዎች ምርጫው በድጋሚ እንዲካሄድ ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲያስተላልፍለት በመጠየቅ ነው፡፡ ኢዜማ በነዚህ ምርጫ ወረዳዎች የተፈጸሙ ግድፈቶች አሉ በሚል ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት መውሰዱ የሚታወስ ነው። ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤቱታ ያስገባው ኢዜማ፤ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት የወሰድኩት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያቀርብኩለትን ቅሬታዎች እንዲሁም ማስረጃዎችን ሳይገመግም ውሳኔ ስላስተላለፈብኝ ነው ብሏል፡፡ ኢዜማ ሰኔ 14 በተደረገው አገራዊ ምርጫ ከድምጽ አሰጣጥ ጋር ተያይዞ ከቀበሌ እስከ ክልል ባሉ የገዢው ፓርቲ አመራሮች፣ ከቀበሌ ሚሊሻ እስከ ክልል ልዩ ኃይል ድረስ ባሉ የጸጥታ አስከባሪዎች፣ ምርጫ አስፈጻሚዎችና ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች አማካኝነት ምርጫው ሲስተጓጎል ነበር ሲል ከሷል፡፡ ይህም በምርጫው ውጤት ላይ ተጽእኖ አሳድሯል ብሏል፡፡ ለዚህም በቂ የሆነ የሰው፣ የሰነድ የቪዲዮና የምሥል ማስረጃዎችን ማጠናቁሩንም ገልፆ ነበር፡፡ | ኢዜማ በ28 ምርጫ ወረዳዎች ምርጫ እንዲደገም ያቀረበው አቤቱታ ላይ ቦርዱ ምላሽ እንዲሰጥ ፍርድ ቤት ወሰነ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ሰኔ 14 በተካሄደው ብሔራዊ ምርጫ በሃያ ስምንት የምርጫ ወረዳዎች ምርጫው እንዲደደገም ያቀረበው አቤቱታ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምላሽ እንዲሰጥ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ አሳልፏል። ይህንን ውሳኔ ያሳለፈው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 2ኛ የምርጫ ጉዳይ ችሎት በዛሬው ዕለት መሆኑንም ኢዜማ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አሳውቋል። ፍርድ ቤቱ ፓርቲው በ28 ምርጫ ወረዳዎች ምርጫ እንዲደገም ያቀረበውን አቤቱታ ሲመረምር ቆይቶም ፓርቲው ያቀረበውን የይግባኝ አቤቱታ ተቀብሎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በጉዳዩ ላይ ምላሽ ይዞ እንዲቀርብ ተወስኗል። ምርጫ ቦርድ ለሐምሌ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ምላሹን ይዞ መቅረብ እንዳለበትም ፍርድ ቤቱ በዛሬው እለት መበየኑ ተገልጿል። ከዚህም በተጨማሪ ኢዜማ ከዚህ ቀደም ለምርጫ ቦርድ ያስገባቸውን የቅሬታ ማስገቢያ ቅፆች ቅጂም ከሐምሌ 30 በፊት ቦርዱ ለፍርድ ቤቱ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ተላልፏል። ኢዜማ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ያስገባው የይግባኝ አቤቱታ ጥሰት ተፈጽሞባቸዋል ባላቸው 28 የምርጫ ወረዳዎች ምርጫው በድጋሚ እንዲካሄድ ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲያስተላልፍለት በመጠየቅ ነው፡፡ ኢዜማ በነዚህ ምርጫ ወረዳዎች የተፈጸሙ ግድፈቶች አሉ በሚል ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት መውሰዱ የሚታወስ ነው። ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤቱታ ያስገባው ኢዜማ፤ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት የወሰድኩት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያቀርብኩለትን ቅሬታዎች እንዲሁም ማስረጃዎችን ሳይገመግም ውሳኔ ስላስተላለፈብኝ ነው ብሏል፡፡ ኢዜማ ሰኔ 14 በተደረገው አገራዊ ምርጫ ከድምጽ አሰጣጥ ጋር ተያይዞ ከቀበሌ እስከ ክልል ባሉ የገዢው ፓርቲ አመራሮች፣ ከቀበሌ ሚሊሻ እስከ ክልል ልዩ ኃይል ድረስ ባሉ የጸጥታ አስከባሪዎች፣ ምርጫ አስፈጻሚዎችና ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች አማካኝነት ምርጫው ሲስተጓጎል ነበር ሲል ከሷል፡፡ ይህም በምርጫው ውጤት ላይ ተጽእኖ አሳድሯል ብሏል፡፡ ለዚህም በቂ የሆነ የሰው፣ የሰነድ የቪዲዮና የምሥል ማስረጃዎችን ማጠናቁሩንም ገልፆ ነበር፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/news-58008367 |
3politics
| የዩኬው ጠቅላይ ሚኒስትር በመጠጥ ድግስ ተገኝተዋል በሚል ቁጣ በረታባቸው | በመላው ዩናይትድ ኪንግደም የኮቪድ እንቅስቃሴ ገደብ ተጥሎ በነበረበት ወቅት ቦሪስ ጆንሰን በአንድ የመጠጥ ድግስ ላይ ተገኝተዋል በሚል ክፉኛ እየተብጠለጠሉ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ወቀሳ እያዘነቡ ያሉት የሌበርና በገዛ ፓርቲያቸው በኮንሰርቫቲቭ እንደራሴዎች ጭምር ነው። ቦሪስ ወይ ፈጣን ምላሽ ይስጡ ወይም ሥልጣን በአስቸኳይ ይልቀቁ ሲሉ በርካታ የፓርቲ ተወካዮች ድምጻቸውን አሰምተዋል። ይህ የመጠጥ ድግስ ተደርጓል የተባለው ደግሞ በጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት ዳውኒንግ ጎዳና በሚገኘው መናፈሻ ነው። ዳውኒንግ ስትሪት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋዊ መኖርያ እና ጽ/ቤት የሚገኝበት መንገድ ነው። ወትሮም የጋለ ክርክርና ሙግት የማይጠፋበት የዩኬ ተወካዮች ምክር ቤት በዚህ ድግስና የቦሪስ ጆንሰን በድግሱ ተገኝተዋል በሚለው ነጥብ ዙርያ ለቀናት ሲናጥ ነው ቆይቷል። የሌበር ፓርቲ ምክትል አንጌላ ራይነር፣ 'የቦሪስ ጉድ ለጊዜው ተሸሽጎ ሊሆን ይችላል፣ ተደብቆ ግን አይዘልቅም፣ እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል' ሲሉ ተናግረዋል። ይህ የመጠጥ ፌሽታ ድግስ ተደረገ የሚባለው እንደነርሱ አቆጣጠር በግንቦት፣ 2020 ዓ/ም ሲሆን ይህ ጊዜ ደግሞ ዩኬ በጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብ ውስጥ የነበረችበት ወቅት ነው። የስኮቲሽ ወግ አጥባቂው ፓርቲ መሪ ዳግላስ ሮስ በበኩላቸው ቦሪስ ጆንሰን እንደሚባለው በወቅቱ የኮቪድ እንቅስቃሴ ገደብ ጥሰው ከነበረ ያለምንም ማወላወል ሥልጣን እንዲለቁ ጠይቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን እስከአሁን በዚህ ድግስ ስለመገኘት አለመገኘታቸው ትንፍሽ አላሉም። ሆኖም የዚህን ዜና ሾልኮ መውጣት ተከትሎ የተቆጡት እንደራሴዎች ዛሬ ረቡዕ በጥያቄና መልስ ሸንጎ ላይ የሚገኙትን ቦሪስ ጆንሰንን ፊት ለፊት ያፋጠጧቸዋል፣ መፈናፈኛም ያሳጧቸዋል ተብሎ ይጠበቃል። ሰኞ ዕለት አይቲቪ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዋና የግል ጸሐፊያቸውን ማርቲን ሬይኖልድስ 100 የሚሆኑ ሰዎችን በቦሪስ መኖርያ በሚገኝ መናፈሻ ለመጠጥ ድግስ ጥሪ ያደረጉበትን ኢሜይል አሾልኮ በማውጣት ለሕዝብ ይፋ አድርጎታል። ይህን ተከትሎ ነው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የሥልጣን ይልቀቁ ጥያቄ የበረታው። የዓይን እማኞች ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት በወቅቱ በዚህ የመጠጥ ድግስ ላይ ቦሪስ ጆንሰን እና ባለቤታቸው ኬሪ ጆንሰን ተገኝተውም ተዝናንተውም ነበር። የወግ አጥባቂው ፓርቲ የቀድሞ ሚኒስትር ጆኒ ሜርሰር በትዊተር ሰሌዳቸው፤ "ይህ እጅግ አሳፋሪ ነገር ነው፤ የቦሪስ ድርጊት የፓርቲያችንን አገርንና ሕዝብን ምሳሌ ሆኖ በመምራት ላይ የተመሠረተ ባሕል አይወክልም።" ሲሉ ጽፈዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዝምታ ብቻ ሳይሆን የእርሳቸው ቃል አቀባይም ምላሽ አለመስጠት በዩኬ ነገሩን አነጋጋሪ አድርጎታል። | የዩኬው ጠቅላይ ሚኒስትር በመጠጥ ድግስ ተገኝተዋል በሚል ቁጣ በረታባቸው በመላው ዩናይትድ ኪንግደም የኮቪድ እንቅስቃሴ ገደብ ተጥሎ በነበረበት ወቅት ቦሪስ ጆንሰን በአንድ የመጠጥ ድግስ ላይ ተገኝተዋል በሚል ክፉኛ እየተብጠለጠሉ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ወቀሳ እያዘነቡ ያሉት የሌበርና በገዛ ፓርቲያቸው በኮንሰርቫቲቭ እንደራሴዎች ጭምር ነው። ቦሪስ ወይ ፈጣን ምላሽ ይስጡ ወይም ሥልጣን በአስቸኳይ ይልቀቁ ሲሉ በርካታ የፓርቲ ተወካዮች ድምጻቸውን አሰምተዋል። ይህ የመጠጥ ድግስ ተደርጓል የተባለው ደግሞ በጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት ዳውኒንግ ጎዳና በሚገኘው መናፈሻ ነው። ዳውኒንግ ስትሪት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋዊ መኖርያ እና ጽ/ቤት የሚገኝበት መንገድ ነው። ወትሮም የጋለ ክርክርና ሙግት የማይጠፋበት የዩኬ ተወካዮች ምክር ቤት በዚህ ድግስና የቦሪስ ጆንሰን በድግሱ ተገኝተዋል በሚለው ነጥብ ዙርያ ለቀናት ሲናጥ ነው ቆይቷል። የሌበር ፓርቲ ምክትል አንጌላ ራይነር፣ 'የቦሪስ ጉድ ለጊዜው ተሸሽጎ ሊሆን ይችላል፣ ተደብቆ ግን አይዘልቅም፣ እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል' ሲሉ ተናግረዋል። ይህ የመጠጥ ፌሽታ ድግስ ተደረገ የሚባለው እንደነርሱ አቆጣጠር በግንቦት፣ 2020 ዓ/ም ሲሆን ይህ ጊዜ ደግሞ ዩኬ በጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብ ውስጥ የነበረችበት ወቅት ነው። የስኮቲሽ ወግ አጥባቂው ፓርቲ መሪ ዳግላስ ሮስ በበኩላቸው ቦሪስ ጆንሰን እንደሚባለው በወቅቱ የኮቪድ እንቅስቃሴ ገደብ ጥሰው ከነበረ ያለምንም ማወላወል ሥልጣን እንዲለቁ ጠይቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን እስከአሁን በዚህ ድግስ ስለመገኘት አለመገኘታቸው ትንፍሽ አላሉም። ሆኖም የዚህን ዜና ሾልኮ መውጣት ተከትሎ የተቆጡት እንደራሴዎች ዛሬ ረቡዕ በጥያቄና መልስ ሸንጎ ላይ የሚገኙትን ቦሪስ ጆንሰንን ፊት ለፊት ያፋጠጧቸዋል፣ መፈናፈኛም ያሳጧቸዋል ተብሎ ይጠበቃል። ሰኞ ዕለት አይቲቪ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዋና የግል ጸሐፊያቸውን ማርቲን ሬይኖልድስ 100 የሚሆኑ ሰዎችን በቦሪስ መኖርያ በሚገኝ መናፈሻ ለመጠጥ ድግስ ጥሪ ያደረጉበትን ኢሜይል አሾልኮ በማውጣት ለሕዝብ ይፋ አድርጎታል። ይህን ተከትሎ ነው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የሥልጣን ይልቀቁ ጥያቄ የበረታው። የዓይን እማኞች ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት በወቅቱ በዚህ የመጠጥ ድግስ ላይ ቦሪስ ጆንሰን እና ባለቤታቸው ኬሪ ጆንሰን ተገኝተውም ተዝናንተውም ነበር። የወግ አጥባቂው ፓርቲ የቀድሞ ሚኒስትር ጆኒ ሜርሰር በትዊተር ሰሌዳቸው፤ "ይህ እጅግ አሳፋሪ ነገር ነው፤ የቦሪስ ድርጊት የፓርቲያችንን አገርንና ሕዝብን ምሳሌ ሆኖ በመምራት ላይ የተመሠረተ ባሕል አይወክልም።" ሲሉ ጽፈዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዝምታ ብቻ ሳይሆን የእርሳቸው ቃል አቀባይም ምላሽ አለመስጠት በዩኬ ነገሩን አነጋጋሪ አድርጎታል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59954382 |
5sports
| አትሌት ሹራ ቂጣታ የአበበ ቢቂላን የቶኪዮ ኦሊምፒክ ታሪክ ለመድገም እቅድ አለኝ አለ | በቶኪዮ ኦሊምፒክ የወንዶች የማራቶን ውድድር ትልቅ ግምት ከተሰጣቸው አትሌቶች መካከል አንዱ የሆነው ሹራ ቂጣታ የአበባ ቢቂላን የቶኪዮ ኦሊምፒክ ታሪክ ለመድገም እቅድ አለኝ አለ። "አበበ ቢቂላ ባስገኘው ድል ለአገር ትቶ ያለፈውን ታሪክ ለማስመለስ ጥረት እያደረግን ነው። ይህን ውድድር አሸንፌ የአበበ ቢቂላን ታሪክ ወደ አገር ቤት ለመመለስ ሐሳብ አለኝ" ሲል አትሌት ሹራ ቂጣታ ለቢቢሲ ተናግሯል። አበበ ቢቂላ አእአ በ1964 በቶኪዮ ተካሂዶ በነበረው የኦሊምፒክ መድረክ በማራቶን ውድድር ተወዳዳሪዎቹን ከ4 ደቂቃዎች በላይ ጥሎ በመግባት ማሸነፉ ይታወቃል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድንም በዘንድሮው የቶኪዮ ኦሊምፒክ በማራቶችን ወርቅ በማምጣት የአበበ ቢቂላ የማራቶን ድል ለመድገም ከፍተኛ መነሳሳት ውስጥ እንዳለ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ደራርቱ ቱሉ ትናገራለች። በኦሊምፒክ መድረክ ወርቅ የወሰደችው የመጀመሪያዋ ጥቁር አፍሪካዊት ደራርቱ ቱሉ፤ "አበበ ቢቂላ ያስመዘገበው ድል ዛሬ የሆነ ይመስለኛል" ትላለች። በዘንድሮው የቶኪዮ ኦሊምፒክ የማራቶን ውድድር ለማሸነፍ ጠንካራ ዝግጅት መደረጉንም ጠቁማለች። "እኛም አገርም የወርቅ ሜዳሊያ እንጠብቃለን" ያለው ደግሞ በማራቶን ውድድሩ ተስፋ የተጣለበት አትሌት ሹራ ቂጣታ ነው። "እኛ የወርቅ ሜዳሊያ እየጠበቅን ነው። አገርም እንዲሁ የወርቅ ሜዳሊያ ያመጠሉ ብሎ ይጠብቀናል" በማለት አትሌት ሹራ ቂጣታ ለቢቢሲ ተናግሯል። በኦሊምፒክ መድረክ አገሩን ሲወክል የመጀመሪያ ጊዜ የሆነው ሹራ፤ "በራስ በመተማመን የሚሮጥ ሰው ሊያሸንፍ ይችላል" በማለት ይናገራል። ኢትዮጵያ በኦሊምፒክ መድረክ በወንዶች ማራቶችን አራት የወርቅ ሜዳሊያዎችን አግኝታለች። በሮም እና በቶኪዮ ኦሊምፒክ አበበ ቢቂላ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ለአገሩ አስገኝቷል። እአአ በ1968 በተካሄደው የሜክሲኮ ኦሊምፒክ ደግሞ ማሞ ወልዴ ወርቅ ሲያስገኝ ገዛኸኝ አበራ በሲድኒ ኦሊምፒክ ወርቁን ወስዷል። ኢትዮጵያን በወንዶች ማራቶን የሚወክሉት አትሌቶች ሹራ ቂጣታ፣ ለሊሳ ዴሲሳ እና ሲሳይ ለማ ናቸው። በወንዶች ማራቶን የአሸናፊነት ግምቱ የተሰጠው ኬኒያዊው ኢሊዩዲ ኪፕቼጌ ነው። ኪፕቾጌ የርቀቱ ክብረ ወሰን ባለቤት ከመሆኑም በላይ በሪዮ ኦሊምፒክም የወቅት ሜዳሊያ አሸንፏል። ከአንድ ዓመት በፊት በተደረገው የለንደን ኦሊምፒክ ግን ሹራ ኬንያዊውን ኪፕቾጌን ማሸነፍ ችሎ ነበር። ኪፕቾጌ፤ "በኦሊምፒክ አሁንም ወርቅ ማግኘት እፈልጋለሁ። ይህን ማድረግ ከቻልኩ ለእኔ ትልቅ ስኬት ነው" በማለት ለሮይተርስ ተናግሯል። ኪፕቾጌ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ድል ከቀናው በተከታታይ የማራቶን ውድድር በማሸነፍ የአበበ ቢቂላን ታሪክ ይጋራል። ኢትዮጵያ ከኪፕቾጌ ቀጥሎ በማራቶን ፈጣን ሰዓት ያለውን አትሌቷ ቀነኒሳ በቀለን ትታ ነው ወደ ቶኪዮ ያቀናችው። ቀነኒሳ የኦሊምፒክ ማጣሪያ ላይ ለመወዳደር ፍቃደኛ ሳይሆን በመቅረቱ በዚህ ውድድር አይሳተፍም ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ እንደነ ሹራ ባሉት ጠንካራ አትሌቶች ተስፋ ሰንቃለች። ሌላኛው ተጠባቂ አትሌት ሌሊሳ ዴሲሳ ነው። አትሌት ሌሊሳ ከሁለት ዓመት በፊት በኳታር፣ ዶሃ በተደረገው የዓለም የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በማራቶን የወርቅ አሸናፊ ነበር። አትሌት ሲሳይ ለማ ደግሞ በ2020 ሎንዶን ማራቶን ሦስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቅቋል። በቶኪዮ ከፍተኛ ሙቀት ስላለ የማራቶን ውድድሩ ከቶኪዮ ከተማ በ800 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሳፖራ ከተማ ይከናወናል። ውድድሩ የፊታችን እሁድ ይካሄዳል። | አትሌት ሹራ ቂጣታ የአበበ ቢቂላን የቶኪዮ ኦሊምፒክ ታሪክ ለመድገም እቅድ አለኝ አለ በቶኪዮ ኦሊምፒክ የወንዶች የማራቶን ውድድር ትልቅ ግምት ከተሰጣቸው አትሌቶች መካከል አንዱ የሆነው ሹራ ቂጣታ የአበባ ቢቂላን የቶኪዮ ኦሊምፒክ ታሪክ ለመድገም እቅድ አለኝ አለ። "አበበ ቢቂላ ባስገኘው ድል ለአገር ትቶ ያለፈውን ታሪክ ለማስመለስ ጥረት እያደረግን ነው። ይህን ውድድር አሸንፌ የአበበ ቢቂላን ታሪክ ወደ አገር ቤት ለመመለስ ሐሳብ አለኝ" ሲል አትሌት ሹራ ቂጣታ ለቢቢሲ ተናግሯል። አበበ ቢቂላ አእአ በ1964 በቶኪዮ ተካሂዶ በነበረው የኦሊምፒክ መድረክ በማራቶን ውድድር ተወዳዳሪዎቹን ከ4 ደቂቃዎች በላይ ጥሎ በመግባት ማሸነፉ ይታወቃል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድንም በዘንድሮው የቶኪዮ ኦሊምፒክ በማራቶችን ወርቅ በማምጣት የአበበ ቢቂላ የማራቶን ድል ለመድገም ከፍተኛ መነሳሳት ውስጥ እንዳለ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ደራርቱ ቱሉ ትናገራለች። በኦሊምፒክ መድረክ ወርቅ የወሰደችው የመጀመሪያዋ ጥቁር አፍሪካዊት ደራርቱ ቱሉ፤ "አበበ ቢቂላ ያስመዘገበው ድል ዛሬ የሆነ ይመስለኛል" ትላለች። በዘንድሮው የቶኪዮ ኦሊምፒክ የማራቶን ውድድር ለማሸነፍ ጠንካራ ዝግጅት መደረጉንም ጠቁማለች። "እኛም አገርም የወርቅ ሜዳሊያ እንጠብቃለን" ያለው ደግሞ በማራቶን ውድድሩ ተስፋ የተጣለበት አትሌት ሹራ ቂጣታ ነው። "እኛ የወርቅ ሜዳሊያ እየጠበቅን ነው። አገርም እንዲሁ የወርቅ ሜዳሊያ ያመጠሉ ብሎ ይጠብቀናል" በማለት አትሌት ሹራ ቂጣታ ለቢቢሲ ተናግሯል። በኦሊምፒክ መድረክ አገሩን ሲወክል የመጀመሪያ ጊዜ የሆነው ሹራ፤ "በራስ በመተማመን የሚሮጥ ሰው ሊያሸንፍ ይችላል" በማለት ይናገራል። ኢትዮጵያ በኦሊምፒክ መድረክ በወንዶች ማራቶችን አራት የወርቅ ሜዳሊያዎችን አግኝታለች። በሮም እና በቶኪዮ ኦሊምፒክ አበበ ቢቂላ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ለአገሩ አስገኝቷል። እአአ በ1968 በተካሄደው የሜክሲኮ ኦሊምፒክ ደግሞ ማሞ ወልዴ ወርቅ ሲያስገኝ ገዛኸኝ አበራ በሲድኒ ኦሊምፒክ ወርቁን ወስዷል። ኢትዮጵያን በወንዶች ማራቶን የሚወክሉት አትሌቶች ሹራ ቂጣታ፣ ለሊሳ ዴሲሳ እና ሲሳይ ለማ ናቸው። በወንዶች ማራቶን የአሸናፊነት ግምቱ የተሰጠው ኬኒያዊው ኢሊዩዲ ኪፕቼጌ ነው። ኪፕቾጌ የርቀቱ ክብረ ወሰን ባለቤት ከመሆኑም በላይ በሪዮ ኦሊምፒክም የወቅት ሜዳሊያ አሸንፏል። ከአንድ ዓመት በፊት በተደረገው የለንደን ኦሊምፒክ ግን ሹራ ኬንያዊውን ኪፕቾጌን ማሸነፍ ችሎ ነበር። ኪፕቾጌ፤ "በኦሊምፒክ አሁንም ወርቅ ማግኘት እፈልጋለሁ። ይህን ማድረግ ከቻልኩ ለእኔ ትልቅ ስኬት ነው" በማለት ለሮይተርስ ተናግሯል። ኪፕቾጌ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ድል ከቀናው በተከታታይ የማራቶን ውድድር በማሸነፍ የአበበ ቢቂላን ታሪክ ይጋራል። ኢትዮጵያ ከኪፕቾጌ ቀጥሎ በማራቶን ፈጣን ሰዓት ያለውን አትሌቷ ቀነኒሳ በቀለን ትታ ነው ወደ ቶኪዮ ያቀናችው። ቀነኒሳ የኦሊምፒክ ማጣሪያ ላይ ለመወዳደር ፍቃደኛ ሳይሆን በመቅረቱ በዚህ ውድድር አይሳተፍም ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ እንደነ ሹራ ባሉት ጠንካራ አትሌቶች ተስፋ ሰንቃለች። ሌላኛው ተጠባቂ አትሌት ሌሊሳ ዴሲሳ ነው። አትሌት ሌሊሳ ከሁለት ዓመት በፊት በኳታር፣ ዶሃ በተደረገው የዓለም የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በማራቶን የወርቅ አሸናፊ ነበር። አትሌት ሲሳይ ለማ ደግሞ በ2020 ሎንዶን ማራቶን ሦስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቅቋል። በቶኪዮ ከፍተኛ ሙቀት ስላለ የማራቶን ውድድሩ ከቶኪዮ ከተማ በ800 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሳፖራ ከተማ ይከናወናል። ውድድሩ የፊታችን እሁድ ይካሄዳል። | https://www.bbc.com/amharic/news-58079205 |
3politics
| የቡድን ሰባት አገራት የቻይናን አለምአቀፋዊ ተፅዕኖ የሚገዳደር እቅድ አቀረቡ | የቡድን ሰባት (ጂ 7) አመራሮች ቻይና በመካከለኛና ዝቅተኛ አገራት የምታደርገውን የመሰረተ ልማት ግንባታ ሊገዳደር የሚችል እቅድ አቅርበዋል። የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይን ከቻይና ፕሮግራም በከፍተኛ ጥራት ደረጃ አማራጭ ነው ያሉትን በአሜሪካ የተደገፈ የተሻለ አለም መገንባት እቅዳቸውንም አስረድተዋል። በአለም ላይ ያለውን የቻይና ተፅእኖን ለመቀልበስ በሚል የቡድን ሰባት አገራት የራሳቸው አማራጭ ያሉትን ሃሳብ አቅርበዋል። የቻይና ቤልት ኤንድ ሮድ ኢንሺየቲቭ (ቢአርአይ) በበርካታ አገራት ባቡሮችን፣ መንገዶችንንና ወደቦችን ለመገንባት በቢሊዮኖች ዶላር የሚገመት የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል። ነገር ግን አገራት ከማይወጡበት የብድር አዘቅት በመክተትም ከፍተኛ ትችቶች ይቀርቡበታል። በእንግሊዟ ኮርንዌል በነበረው የቡድን ሰባት ጉባኤ የወጣው መግለጫ "በጥራት ከፍተኛ ደረጃ ያለውን ግልፅነት በተሞላ መልኩ አጋርነትን የሚያሳይ ግንኙነትን" ከነዚህ አገራት ጋር መመስረት እንደሚፈልጉ አትቷል። ነገር ግን ቡድን ሰባት ያቀረቡት ይህ እቅድ ፈንዱ ከየት እንደሚመጣ አልተነገረም። የጀርመን መራሒተ መንግሥት አንጌላ መርኬል ለዚህ ጅማሮ ገንዘብ ከየትም ሆነ እንዴት እንደሚመደብ ለመወሰን ጊዜው ገና ነው ብለዋል። አሜሪካ ለአመታት ያህል ቻይና በአገራቱ ላይ የምታካሂደው "የብድር ዲፕሎማሲ" ነው በማለት በከፍተኛ ሁኔታ ታወግዛታለች። ቡድን ሰባት የተባሉት የአለም ሃብታምና በዲሞክራሲ የዳበሩ አገራት የቻይናን ተፅእኖ ከመቀልበስ በተጨማሪ አለም የሚያጋጥማትን የወደፊቱ ወረርሽኝ ለመከላከልም አዲስ እቅድ ነድፈዋል። አገራቱ ለኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት የሚያስፈልገው ፈቃድ ከመቶ ቀናት ባነሰ ጊዜ ውስጥ መስጠት የሚያስችል እርምጃ ለመውሰድ መክረዋል። ይህ እቅድ ከጉባኤው ይፋዊ መግለጫ ጋር እሁድ ይወጣል ተብሏል። በካብሪስ ቤይ ሪዞርት የሚደረገውን የሶስት ቀን ጉባኤ በጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ አዘጋጅነት እየተካሄደ ነው። | የቡድን ሰባት አገራት የቻይናን አለምአቀፋዊ ተፅዕኖ የሚገዳደር እቅድ አቀረቡ የቡድን ሰባት (ጂ 7) አመራሮች ቻይና በመካከለኛና ዝቅተኛ አገራት የምታደርገውን የመሰረተ ልማት ግንባታ ሊገዳደር የሚችል እቅድ አቅርበዋል። የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይን ከቻይና ፕሮግራም በከፍተኛ ጥራት ደረጃ አማራጭ ነው ያሉትን በአሜሪካ የተደገፈ የተሻለ አለም መገንባት እቅዳቸውንም አስረድተዋል። በአለም ላይ ያለውን የቻይና ተፅእኖን ለመቀልበስ በሚል የቡድን ሰባት አገራት የራሳቸው አማራጭ ያሉትን ሃሳብ አቅርበዋል። የቻይና ቤልት ኤንድ ሮድ ኢንሺየቲቭ (ቢአርአይ) በበርካታ አገራት ባቡሮችን፣ መንገዶችንንና ወደቦችን ለመገንባት በቢሊዮኖች ዶላር የሚገመት የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል። ነገር ግን አገራት ከማይወጡበት የብድር አዘቅት በመክተትም ከፍተኛ ትችቶች ይቀርቡበታል። በእንግሊዟ ኮርንዌል በነበረው የቡድን ሰባት ጉባኤ የወጣው መግለጫ "በጥራት ከፍተኛ ደረጃ ያለውን ግልፅነት በተሞላ መልኩ አጋርነትን የሚያሳይ ግንኙነትን" ከነዚህ አገራት ጋር መመስረት እንደሚፈልጉ አትቷል። ነገር ግን ቡድን ሰባት ያቀረቡት ይህ እቅድ ፈንዱ ከየት እንደሚመጣ አልተነገረም። የጀርመን መራሒተ መንግሥት አንጌላ መርኬል ለዚህ ጅማሮ ገንዘብ ከየትም ሆነ እንዴት እንደሚመደብ ለመወሰን ጊዜው ገና ነው ብለዋል። አሜሪካ ለአመታት ያህል ቻይና በአገራቱ ላይ የምታካሂደው "የብድር ዲፕሎማሲ" ነው በማለት በከፍተኛ ሁኔታ ታወግዛታለች። ቡድን ሰባት የተባሉት የአለም ሃብታምና በዲሞክራሲ የዳበሩ አገራት የቻይናን ተፅእኖ ከመቀልበስ በተጨማሪ አለም የሚያጋጥማትን የወደፊቱ ወረርሽኝ ለመከላከልም አዲስ እቅድ ነድፈዋል። አገራቱ ለኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት የሚያስፈልገው ፈቃድ ከመቶ ቀናት ባነሰ ጊዜ ውስጥ መስጠት የሚያስችል እርምጃ ለመውሰድ መክረዋል። ይህ እቅድ ከጉባኤው ይፋዊ መግለጫ ጋር እሁድ ይወጣል ተብሏል። በካብሪስ ቤይ ሪዞርት የሚደረገውን የሶስት ቀን ጉባኤ በጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ አዘጋጅነት እየተካሄደ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/news-57458940 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ ኢትዮጵያ ነፃ የኮቪድ-19 ምርመራ መስጠት መጀመሯን አስታወቀች | የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረግ ለሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ነፃ ምርመራ ማድረግ እንደሚችሉ የጤና ሚኒስቴር እና የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቀዋል። በአዲስ አበባ በሚገኙ በተመረጡ 34 የጤና ጣቢያዎች እና ሆስፒታሎች ከክፍያ ነፃ ናሙና በመስጠትም ምርመራ ማድረግ ይችላሉም ተብሏል። የጤና ማዕከላቱንም ዝርዝር የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በማህበራዊ ሚዲያዎቻቸው አውጥተዋል። ነፃ የኮቪድ-19 ምርመራ ይሰጥባቸዋል ተብለው ከተጠቀሱትም መካከል ሚኒልክ ሆስፒታል፣ አቤት ሆስፒታል፣እንጦጦ ፋና የጤና ማዕከል፣ ህዳሴ የጤና ማዕከል፣ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል፣ የካቲት 12 ሆስፒታል፣የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ይገኙበታል። ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ የጤና ማዕከላት የነፃ ምርመራን በተመለከተ የተባለ ነገር የለም። በአዲስ አበባ በሚገኙ የጤና ማዕከላት ውስጥ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ለማድረግ 1 ሺህ 250 ብር ክፍያ የሚጠየቅ ሲሆን፤ አንዳንድ የጤና ተቋማትም 1 ሺህ 500 ብር ያስከፍላሉ። አገሪቷ ከዚህ ቀደም የኮሮናቫይረስ ምልክት የሚያሳዩና፣ከህመምተኞች ጋር ንክኪ ያላቸውን ብቻ ነበር በነፃ የምትመረምረው። በአሁኑ ወቅት አገሪቷ አስገዳጅ አድርጋው የነበረው የጭምብል ማጥለቅ መመሪያ ላላ ብሏል። የአፍሪካ በሽታዎች መከላከልና ቁጥጥር ማዕከል፣ ሲዲሲ ባወጣው መረጃ መሰረት በአፍሪካ ከፍተኛ የህሙማን ቁጥር ከተመዘገባቸው አገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗን ነው። ኢትዮጵያ እስካሁን ባለው ወደ 1.7 ሚሊዮን የላብራቶሪ ምርመራ ያከናወነች ሲሆን፣ 114 ሺህ 834 ህሙማንንም መዝግባለች። ከነዚህም ውስጥ 1 ሺህ 769 ዜጎቿንም በኮሮናቫይረስ እንዳጣች የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። የጤና ሚኒስትሯ ሊያ ታደሰ በዛሬው ዕለት እንደተናገሩት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌንየም ሜዲካል ኮሌጅ ሲኒየር አንስቴቲስት የሆኑት አቶ ገብረሥላሴ አባዲ በኮቪድ-19 መሞታቸውንም ገልፀዋል። | ኮሮናቫይረስ፡ ኢትዮጵያ ነፃ የኮቪድ-19 ምርመራ መስጠት መጀመሯን አስታወቀች የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረግ ለሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ነፃ ምርመራ ማድረግ እንደሚችሉ የጤና ሚኒስቴር እና የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቀዋል። በአዲስ አበባ በሚገኙ በተመረጡ 34 የጤና ጣቢያዎች እና ሆስፒታሎች ከክፍያ ነፃ ናሙና በመስጠትም ምርመራ ማድረግ ይችላሉም ተብሏል። የጤና ማዕከላቱንም ዝርዝር የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በማህበራዊ ሚዲያዎቻቸው አውጥተዋል። ነፃ የኮቪድ-19 ምርመራ ይሰጥባቸዋል ተብለው ከተጠቀሱትም መካከል ሚኒልክ ሆስፒታል፣ አቤት ሆስፒታል፣እንጦጦ ፋና የጤና ማዕከል፣ ህዳሴ የጤና ማዕከል፣ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል፣ የካቲት 12 ሆስፒታል፣የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ይገኙበታል። ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ የጤና ማዕከላት የነፃ ምርመራን በተመለከተ የተባለ ነገር የለም። በአዲስ አበባ በሚገኙ የጤና ማዕከላት ውስጥ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ለማድረግ 1 ሺህ 250 ብር ክፍያ የሚጠየቅ ሲሆን፤ አንዳንድ የጤና ተቋማትም 1 ሺህ 500 ብር ያስከፍላሉ። አገሪቷ ከዚህ ቀደም የኮሮናቫይረስ ምልክት የሚያሳዩና፣ከህመምተኞች ጋር ንክኪ ያላቸውን ብቻ ነበር በነፃ የምትመረምረው። በአሁኑ ወቅት አገሪቷ አስገዳጅ አድርጋው የነበረው የጭምብል ማጥለቅ መመሪያ ላላ ብሏል። የአፍሪካ በሽታዎች መከላከልና ቁጥጥር ማዕከል፣ ሲዲሲ ባወጣው መረጃ መሰረት በአፍሪካ ከፍተኛ የህሙማን ቁጥር ከተመዘገባቸው አገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗን ነው። ኢትዮጵያ እስካሁን ባለው ወደ 1.7 ሚሊዮን የላብራቶሪ ምርመራ ያከናወነች ሲሆን፣ 114 ሺህ 834 ህሙማንንም መዝግባለች። ከነዚህም ውስጥ 1 ሺህ 769 ዜጎቿንም በኮሮናቫይረስ እንዳጣች የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። የጤና ሚኒስትሯ ሊያ ታደሰ በዛሬው ዕለት እንደተናገሩት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌንየም ሜዲካል ኮሌጅ ሲኒየር አንስቴቲስት የሆኑት አቶ ገብረሥላሴ አባዲ በኮቪድ-19 መሞታቸውንም ገልፀዋል። | https://www.bbc.com/amharic/55260304 |
2health
| ኬንያ ያልተከተቡ ሰዎች መሠረታዊ አገልግሎቶችን እንዳያገኙ ልታግድ ነው | ኬንያውያን የኮቪድ-19 ክትባት ካልወሰዱ ከታኅሣሥ 21 ጀምሮ የሕዝብ ማመላለሻን ጨምሮ የመንግሥት አገልግሎቶችን አያገኙም ሲሉ የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ሙታሂ ካግዌ ተናግሩ። እገዳው አውቶቡሶችን፣ ታክሲዎችን፣ ባቡሮችን እና የአገር ውስጥ በረራዎችን እንደሚያጠቃልል ገልጸዋል። በተጨማሪም እገዳው የሆስፒታል እና የእስር ቤት ጉብኝትን ጨምሮ በትምህርት፣ በኢሚግሬሽን እና በግብር ቢሮዎች ተፈጻሚ ይሆናል ብለዋል። እስካሁን ከአገሪቱ ሕዝብ ከ10 ከመቶ ያነሱ ኬንያውያን ብቻ ናቸው የወረርሽኙን መከላከያ የተከተቡት። ኦፊሴላዊው መረጃ እንደሚያሳየው ኬንያ ከተቀበለችው 10.7 ሚሊዮን ክትባት ውስጥ 6.4 ሚሊዮኑን ብቻ ነው የከተበችው። ሆኖም በአገሪቱ በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአንጻራዊነት ዝቅተኛ ነው። ሮይተርስ የዜና ወኪል ባጠናቀረው መረጃ መሠረት በየቀኑ በአማካይ 59 አዳዲስ ሰዎች በቫይረሱ ይያዛሉ። የካግዌ መግለጫ በቅርቡ ከሚከበሩት የአዲስ ዓመት እና የገና በዓላት በፊት የክትባት ዘመቻውን ለማጠናከር ያለመ ይመስላል። በበዓላት ሰሞን ጉዞ እና ማኅበራዊ ግንኙነት ስለሚጨምር ሰዎች በበሽታው የመጠቃት ዕድላቸው ይጨምራል። መንግሥት በታኅሣሥ ወር መጨረሻ ለ10 ሚሊዮን ሰዎች ክትባት ለመስጠት አቅዷል። ይህም ከጠቅላላው ሕዝብ 20 በመቶውን ብቻ ስለሚይዝ አብዛኛው ሕዝብ የመንግሥት አገልግሎቶች ላያገኝ ይችላል። እገዳዎቹ ሁሌም በጥብቅ ተፈጻሚ ላይሆኑ ይችላሉም ሲሉ ካግዌ ጠቅሰዋል። ካግዌ "ኬንያውያን እስከ ታኅሣሥ 21 ድረስ ክትባቱን እንዲወስዱ ጊዜ ሰጥተናል። እነዚህን እርምጃዎች እስከምንተገብር ድረስ ያለው ተጠያቂነት የግለሰቦች ነው" ማለታቸውን ጠቅሶ የኬንያው ስታንዳርድ ጋዜጣ ዘግቧል። ከማክሰኞ ጀምሮ ከ15 ዓመት በላይ የሆናቸው ሰዎች የፋይዘር ክትባት ሊያገኙ ይችላሉ። | ኬንያ ያልተከተቡ ሰዎች መሠረታዊ አገልግሎቶችን እንዳያገኙ ልታግድ ነው ኬንያውያን የኮቪድ-19 ክትባት ካልወሰዱ ከታኅሣሥ 21 ጀምሮ የሕዝብ ማመላለሻን ጨምሮ የመንግሥት አገልግሎቶችን አያገኙም ሲሉ የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ሙታሂ ካግዌ ተናግሩ። እገዳው አውቶቡሶችን፣ ታክሲዎችን፣ ባቡሮችን እና የአገር ውስጥ በረራዎችን እንደሚያጠቃልል ገልጸዋል። በተጨማሪም እገዳው የሆስፒታል እና የእስር ቤት ጉብኝትን ጨምሮ በትምህርት፣ በኢሚግሬሽን እና በግብር ቢሮዎች ተፈጻሚ ይሆናል ብለዋል። እስካሁን ከአገሪቱ ሕዝብ ከ10 ከመቶ ያነሱ ኬንያውያን ብቻ ናቸው የወረርሽኙን መከላከያ የተከተቡት። ኦፊሴላዊው መረጃ እንደሚያሳየው ኬንያ ከተቀበለችው 10.7 ሚሊዮን ክትባት ውስጥ 6.4 ሚሊዮኑን ብቻ ነው የከተበችው። ሆኖም በአገሪቱ በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአንጻራዊነት ዝቅተኛ ነው። ሮይተርስ የዜና ወኪል ባጠናቀረው መረጃ መሠረት በየቀኑ በአማካይ 59 አዳዲስ ሰዎች በቫይረሱ ይያዛሉ። የካግዌ መግለጫ በቅርቡ ከሚከበሩት የአዲስ ዓመት እና የገና በዓላት በፊት የክትባት ዘመቻውን ለማጠናከር ያለመ ይመስላል። በበዓላት ሰሞን ጉዞ እና ማኅበራዊ ግንኙነት ስለሚጨምር ሰዎች በበሽታው የመጠቃት ዕድላቸው ይጨምራል። መንግሥት በታኅሣሥ ወር መጨረሻ ለ10 ሚሊዮን ሰዎች ክትባት ለመስጠት አቅዷል። ይህም ከጠቅላላው ሕዝብ 20 በመቶውን ብቻ ስለሚይዝ አብዛኛው ሕዝብ የመንግሥት አገልግሎቶች ላያገኝ ይችላል። እገዳዎቹ ሁሌም በጥብቅ ተፈጻሚ ላይሆኑ ይችላሉም ሲሉ ካግዌ ጠቅሰዋል። ካግዌ "ኬንያውያን እስከ ታኅሣሥ 21 ድረስ ክትባቱን እንዲወስዱ ጊዜ ሰጥተናል። እነዚህን እርምጃዎች እስከምንተገብር ድረስ ያለው ተጠያቂነት የግለሰቦች ነው" ማለታቸውን ጠቅሶ የኬንያው ስታንዳርድ ጋዜጣ ዘግቧል። ከማክሰኞ ጀምሮ ከ15 ዓመት በላይ የሆናቸው ሰዎች የፋይዘር ክትባት ሊያገኙ ይችላሉ። | https://www.bbc.com/amharic/news-59108453 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ ሳኡዲ አረቢያ የኡምራ ጉⶋን በመስከረም ወር መጨረሻ ልትጀምር ነው | በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለሰባት ወራት ያህል ተቋርጦ የነበረው የኡምራ ሃይማኖታዊ ጉዞ በዚህ ወር እንደሚጀመር ሳዑዲ አረቢያ አስታወቀች። ከመስከረም 24፣ 2012 ዓ.ም ጀምሮም ስድስት ሺህ የሳዑዲ ዜጎች በየቀኑ የኡምራ ጉዞ እንዲያደርጉ ተፈቅዶላቸዋል። ከሌላ አገር የሚመጡ የኡምራ ፀሎተኞችም ከጥቅምት 22፣ 2013 ዓ.ም ጀምሮ መምጣት ይችላሉ ተብሏል። የየቀኑም ተጓዦች ቁጥር ወደ 20 ሺህ ያድጋል እንደሚያድገም ሳዑዲ አስታውቃለች። ከእስልምና እምነት መሰረቶች አንዱ የሆነው የኡምራ ጉዞ በየትኛውም ወቅት ማከናወን ቢቻልም የሃጂ ጉዞ ግን የእስልምና እምነት ተከታዮች በህይወት ዘመናቸው አንዱ ሊያደርጉት የሚገባ የተቀደሰ ተግባር ነው። በመላው ሙስሊም ማህበረሰብ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የሃጅ ጉዞ በዘንድሮው እክል ገጥሞታል። ከዚህ ቀደም ከሁለት ሚሊዮን በላይ የእስልምና እምነት ተከታዮች ከየአገሩ ተሰባስበው ቢመጡም በዚህ አመት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ሳዑዲ አረቢያ የፈቀደችው ጥቂት ሺዎች እንዲታደሙ ነው። ከሃጅ ጉዞ በተለየ መልኩ በየዓመቱ የትኛውም ጊዜ ላይ መደረግ ለሚችለው ለኡምራ ጉዞ ቢያንስ በዓመት ስምንት ሚሊዮን የሚሆኑ ወደ መካ ያቀኑ ነበር። በየቀኑ 20 ሺህ ተጓዦችን ለመቀበል ያቀደችው ሳዑዲ አረቢያ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ሙሉ በሙሉ ተቀርፏል የሚለው በይፋ እስኪነገር የምትቀበለው ተጓዦች ቁጥር ተወስኖ እንደሚቆይም የሳኡዲ ዜና ወኪል የአገር ውስጥ ሚኒስትሩን ዋቢ አድርገው ዘግበዋል። "ከሌላ አገራት የሚመጡ የኡምራ ፀሎተኞችና ተጓዦችን የምንቀበለው ቀስ በቀስ ሲሆን፤ ከወረርሽኙ ነፃ የሆኑ አገሮችንም ቅድሚያ እንሰጣለን" ማለታቸውም ተዘግቧል። ተጓዦች የኮሮናቫይረስ ወርርሽኝን ለመከላከል የወጡ መመሪያዎች እንደ የፊት ጭምብል፣ አካላዊ ርቀትን መጠበቅን ፅዳትን መጠበቅ እንደሚኖርባቸውም የዜና ወኪሉ አስነብቧል። በሳዑዲ አረቢያ ውስጥ እስካሁን ባለው 330 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 4 ሺህ 452 ሰዎችም ህይወታቸው አልፏል። | ኮሮናቫይረስ፡ ሳኡዲ አረቢያ የኡምራ ጉⶋን በመስከረም ወር መጨረሻ ልትጀምር ነው በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለሰባት ወራት ያህል ተቋርጦ የነበረው የኡምራ ሃይማኖታዊ ጉዞ በዚህ ወር እንደሚጀመር ሳዑዲ አረቢያ አስታወቀች። ከመስከረም 24፣ 2012 ዓ.ም ጀምሮም ስድስት ሺህ የሳዑዲ ዜጎች በየቀኑ የኡምራ ጉዞ እንዲያደርጉ ተፈቅዶላቸዋል። ከሌላ አገር የሚመጡ የኡምራ ፀሎተኞችም ከጥቅምት 22፣ 2013 ዓ.ም ጀምሮ መምጣት ይችላሉ ተብሏል። የየቀኑም ተጓዦች ቁጥር ወደ 20 ሺህ ያድጋል እንደሚያድገም ሳዑዲ አስታውቃለች። ከእስልምና እምነት መሰረቶች አንዱ የሆነው የኡምራ ጉዞ በየትኛውም ወቅት ማከናወን ቢቻልም የሃጂ ጉዞ ግን የእስልምና እምነት ተከታዮች በህይወት ዘመናቸው አንዱ ሊያደርጉት የሚገባ የተቀደሰ ተግባር ነው። በመላው ሙስሊም ማህበረሰብ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የሃጅ ጉዞ በዘንድሮው እክል ገጥሞታል። ከዚህ ቀደም ከሁለት ሚሊዮን በላይ የእስልምና እምነት ተከታዮች ከየአገሩ ተሰባስበው ቢመጡም በዚህ አመት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ሳዑዲ አረቢያ የፈቀደችው ጥቂት ሺዎች እንዲታደሙ ነው። ከሃጅ ጉዞ በተለየ መልኩ በየዓመቱ የትኛውም ጊዜ ላይ መደረግ ለሚችለው ለኡምራ ጉዞ ቢያንስ በዓመት ስምንት ሚሊዮን የሚሆኑ ወደ መካ ያቀኑ ነበር። በየቀኑ 20 ሺህ ተጓዦችን ለመቀበል ያቀደችው ሳዑዲ አረቢያ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ሙሉ በሙሉ ተቀርፏል የሚለው በይፋ እስኪነገር የምትቀበለው ተጓዦች ቁጥር ተወስኖ እንደሚቆይም የሳኡዲ ዜና ወኪል የአገር ውስጥ ሚኒስትሩን ዋቢ አድርገው ዘግበዋል። "ከሌላ አገራት የሚመጡ የኡምራ ፀሎተኞችና ተጓዦችን የምንቀበለው ቀስ በቀስ ሲሆን፤ ከወረርሽኙ ነፃ የሆኑ አገሮችንም ቅድሚያ እንሰጣለን" ማለታቸውም ተዘግቧል። ተጓዦች የኮሮናቫይረስ ወርርሽኝን ለመከላከል የወጡ መመሪያዎች እንደ የፊት ጭምብል፣ አካላዊ ርቀትን መጠበቅን ፅዳትን መጠበቅ እንደሚኖርባቸውም የዜና ወኪሉ አስነብቧል። በሳዑዲ አረቢያ ውስጥ እስካሁን ባለው 330 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 4 ሺህ 452 ሰዎችም ህይወታቸው አልፏል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54276747 |
0business
| በኢንተርኔት አማካኝነት እጽ ይሸጡ የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተያዙ | የአውሮፓ እና የአሜሪካ ፖሊስ በጥምረት ባካሄዱት ኦፐሬሽን ማንነታቸውን በመደበቅ በኢንተርኔት አማካኝነት አደንዛዥ እጽ ሲሸጡ የነበሩ 179 ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋላቸው ተገለጸ። ከግለሰቦቹ በተጨማሪ ፖሊስ ከ6.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ግምት ያለው ጥሬ ገንዘብ እና ዲጂታል ገንዘብ የያዘ ሲሆን እጽ እና የጦር መሳሪያ ከግለሰቦቹ ጋር መያዙም ተነግሯል። እነዚህ ሰዎች በቁጥጥር ሥር የዋሉት ከበርካታ የአውሮፓ አገራት እና አሜሪካ ሲሆን የተደራጁ ወንጀሎች ተከላካይ ኃይል ዩሮፖል፤ “ማንነትን በመደበቅ የሚደረገው ሕገ-ወጥ ግብይነት ጊዜው አብቅቷል” ሲል መግለጫ አውጥቷል። የዩሮፖል የኢንተርኔት ወንጀል ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት ኤድቫራዳስ ሲሌሪስ “ድብቁ ኢንተርኔት ከአሁን በኋላ ሚስጥር አይሆንብንም” ብለዋል። “ዲስራፕትቶር” የሚል ስያሜ የተሰጠው ኦፕሬሽንን የአሜሪካው የፍትሕ ቢሮ እና ዩሮፖል በቅንጅት ያስፈጸሙት ሲሆን በኦፕሬሽኑ እንደ ፌንታኒ፣ ሄሮይን፣ ኮኬን እና ኤክስቴሲ የተሰኙ እጾች ተይዘዋል። በቁጥጥር ሥር ከዋሉት 179 ሰዎች መካከል 119 በአሜሪካ፣ 2 በካናዳ፣ 42 በጀርመን፣ 8 በኔዘርላንድ፣ 4 በዩኬ፣ 3 በኦስትሪያ እና 1 ግለሰብ ደግሞ ስዊድን ውስጥ መያዛቸው ተገልጿል። ሰዎች ማንነታቸው እና መገኛቸው ሳይታወቅ ልዩ መተግበሪያዎችን በመጠቀም “ዳርክ ዌብ” ተብሎ በሚጠራው የኢንተርኔት ክፍል ላይ በርካታ ሕገ-ወጥ ተግባራትን ያከናወናሉ። “በዳርክ ዌብ” ላይ ሰዎች ማንነታቸውን መደበቅ ስለሚችሉ እንደ ኩላሊት ካሉ የሰው ልጆች አካላት እስከ አደንዛዥ እጽ መገበያየት ይቻላል ይላሉ የኢንፎሜሽን መረብ ደህንነት ባለሙያዎች። ፖሊስ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መሰል ወንጀለኞችን በቁጥጥር ሥር እያዋለ ይገኛል። ኤድቫራዳስ ሲሌሪስ ሕግ አስከባሪ አካላት በቅንጅት መስራት ከቻሉ ወንጀለኞችን መቆጣጠር የማይቻልበት ምክንያት የለም ብለዋል። እነዚህ ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውም “የዳርክ ዌብ ወርቃማ ዓመታት” እያለፉ መምጣታቸውን ያሳያል ተብሏል። | በኢንተርኔት አማካኝነት እጽ ይሸጡ የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተያዙ የአውሮፓ እና የአሜሪካ ፖሊስ በጥምረት ባካሄዱት ኦፐሬሽን ማንነታቸውን በመደበቅ በኢንተርኔት አማካኝነት አደንዛዥ እጽ ሲሸጡ የነበሩ 179 ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋላቸው ተገለጸ። ከግለሰቦቹ በተጨማሪ ፖሊስ ከ6.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ግምት ያለው ጥሬ ገንዘብ እና ዲጂታል ገንዘብ የያዘ ሲሆን እጽ እና የጦር መሳሪያ ከግለሰቦቹ ጋር መያዙም ተነግሯል። እነዚህ ሰዎች በቁጥጥር ሥር የዋሉት ከበርካታ የአውሮፓ አገራት እና አሜሪካ ሲሆን የተደራጁ ወንጀሎች ተከላካይ ኃይል ዩሮፖል፤ “ማንነትን በመደበቅ የሚደረገው ሕገ-ወጥ ግብይነት ጊዜው አብቅቷል” ሲል መግለጫ አውጥቷል። የዩሮፖል የኢንተርኔት ወንጀል ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት ኤድቫራዳስ ሲሌሪስ “ድብቁ ኢንተርኔት ከአሁን በኋላ ሚስጥር አይሆንብንም” ብለዋል። “ዲስራፕትቶር” የሚል ስያሜ የተሰጠው ኦፕሬሽንን የአሜሪካው የፍትሕ ቢሮ እና ዩሮፖል በቅንጅት ያስፈጸሙት ሲሆን በኦፕሬሽኑ እንደ ፌንታኒ፣ ሄሮይን፣ ኮኬን እና ኤክስቴሲ የተሰኙ እጾች ተይዘዋል። በቁጥጥር ሥር ከዋሉት 179 ሰዎች መካከል 119 በአሜሪካ፣ 2 በካናዳ፣ 42 በጀርመን፣ 8 በኔዘርላንድ፣ 4 በዩኬ፣ 3 በኦስትሪያ እና 1 ግለሰብ ደግሞ ስዊድን ውስጥ መያዛቸው ተገልጿል። ሰዎች ማንነታቸው እና መገኛቸው ሳይታወቅ ልዩ መተግበሪያዎችን በመጠቀም “ዳርክ ዌብ” ተብሎ በሚጠራው የኢንተርኔት ክፍል ላይ በርካታ ሕገ-ወጥ ተግባራትን ያከናወናሉ። “በዳርክ ዌብ” ላይ ሰዎች ማንነታቸውን መደበቅ ስለሚችሉ እንደ ኩላሊት ካሉ የሰው ልጆች አካላት እስከ አደንዛዥ እጽ መገበያየት ይቻላል ይላሉ የኢንፎሜሽን መረብ ደህንነት ባለሙያዎች። ፖሊስ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መሰል ወንጀለኞችን በቁጥጥር ሥር እያዋለ ይገኛል። ኤድቫራዳስ ሲሌሪስ ሕግ አስከባሪ አካላት በቅንጅት መስራት ከቻሉ ወንጀለኞችን መቆጣጠር የማይቻልበት ምክንያት የለም ብለዋል። እነዚህ ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውም “የዳርክ ዌብ ወርቃማ ዓመታት” እያለፉ መምጣታቸውን ያሳያል ተብሏል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54261909 |
5sports
| እግር ኳስ ፡ የልምምድ ቦታ ክስተቶች ማፈትለካቸው አሰልጣኝ ማይክል አርቴታን አስቆጣ | የአርሰናሉ አሰልጣኝ ማይክል አርቴታ በዳኒ ሴባዮስ እና በዴቪድ ሉዊዝ መካከል የተፈጠረውን ችግር ይፋ ያደረጉ አካላት የእጃቸውን ያገኛሉ ሲሉ ገለጹ። በልምምድ ወቅት ሴባዮስ አደገኛ አጨዋወት መምረጡን ተከትሎ ሁለቱ ተጫዋቾች ተጋጭተው ሉዊዝ በሰነዘረው ቡጢ የቡድን አጋሩ መድማቱን ሪፖርቶች ገልጸዋል፡፡ አርቴታ ድርጊቱን "ምንም አይደለም" ሲሉ የገለጹ ሲሆን ከዚያ ይልቅ ጉዳዩ ይፋ መሆኑ ይበልጥ እንዳሳሰባቸው አስታውቀዋል፡፡ "እኔ ክስተቱ መውጣቱን በጭራሽ አልወደድኩትም" ብለዋል፡፡ ስፔናዊው አሰልጣኝ አክለውም "ከየት እንደመጣ ማወቅ እፈልጋለሁ። እንደዚያ ከሆነ ደግሞ ከሌላው የምጠብቀውን ግላዊ እና ሚስጥራዊ ነገሮችን መያዝን ሙሉ በሙሉ የሚፃረር ስለሆነ መዘዞች ይኖራሉ" ብለዋል፡፡ ክስተቱን እንዲያብራሩ የተጠየቁት አርቴታ ፣ "ልምምዶች በጣም ፉክክር ያለባቸው ናቸው። እነዚህ ጉዳዮች ብዙ ጊዜ የሚከሰቱ ናቸው። ሲከሰቱም በቡድኑ ወዲያውኑ መፍትሄ ያገኛሉ። ስለዚህ ብዙም የምለው ነገር የለም" ሲሉ ገልጸዋል፡፡ "በጭራሽ ምንም ችግር የለም " ሲሉም አክለዋል፡፡ ከሪያል ማድሪድ በውሰት ለአርሴናል በመጫወት ላይ ሚገኘው የስፔኑ አማካይ ሴባዮስ መረጃው ሐሙስ ይፋ ከሆነ በኋላ በማህበራዊ ሚዲያው ዘገባውን ውድቅ አድርጎታል፡፡ የ 24 አመቱ ተጫዋች ከመድፈኞቹ ተጫዋቾች ጋር በአደባባይ አለመግባባት ሲፈጠር የመጀመሪያው አይደለም፡፡ አርሰናል ፉልሃምን 3-0 ባሸነፈበት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ተቀይረው ለመግባት ሲያሟሙቁ ከኤዲ ንኬቲያ ጋር መጋጨታቸው ይታወሳል፡፡ የ 33 ዓመቱ ብራዚላዊው ሉዊዝ በ2019 ነበር ቼልሲን ለቅቆ አርሰናልን የተቀላቀለው፡፡ | እግር ኳስ ፡ የልምምድ ቦታ ክስተቶች ማፈትለካቸው አሰልጣኝ ማይክል አርቴታን አስቆጣ የአርሰናሉ አሰልጣኝ ማይክል አርቴታ በዳኒ ሴባዮስ እና በዴቪድ ሉዊዝ መካከል የተፈጠረውን ችግር ይፋ ያደረጉ አካላት የእጃቸውን ያገኛሉ ሲሉ ገለጹ። በልምምድ ወቅት ሴባዮስ አደገኛ አጨዋወት መምረጡን ተከትሎ ሁለቱ ተጫዋቾች ተጋጭተው ሉዊዝ በሰነዘረው ቡጢ የቡድን አጋሩ መድማቱን ሪፖርቶች ገልጸዋል፡፡ አርቴታ ድርጊቱን "ምንም አይደለም" ሲሉ የገለጹ ሲሆን ከዚያ ይልቅ ጉዳዩ ይፋ መሆኑ ይበልጥ እንዳሳሰባቸው አስታውቀዋል፡፡ "እኔ ክስተቱ መውጣቱን በጭራሽ አልወደድኩትም" ብለዋል፡፡ ስፔናዊው አሰልጣኝ አክለውም "ከየት እንደመጣ ማወቅ እፈልጋለሁ። እንደዚያ ከሆነ ደግሞ ከሌላው የምጠብቀውን ግላዊ እና ሚስጥራዊ ነገሮችን መያዝን ሙሉ በሙሉ የሚፃረር ስለሆነ መዘዞች ይኖራሉ" ብለዋል፡፡ ክስተቱን እንዲያብራሩ የተጠየቁት አርቴታ ፣ "ልምምዶች በጣም ፉክክር ያለባቸው ናቸው። እነዚህ ጉዳዮች ብዙ ጊዜ የሚከሰቱ ናቸው። ሲከሰቱም በቡድኑ ወዲያውኑ መፍትሄ ያገኛሉ። ስለዚህ ብዙም የምለው ነገር የለም" ሲሉ ገልጸዋል፡፡ "በጭራሽ ምንም ችግር የለም " ሲሉም አክለዋል፡፡ ከሪያል ማድሪድ በውሰት ለአርሴናል በመጫወት ላይ ሚገኘው የስፔኑ አማካይ ሴባዮስ መረጃው ሐሙስ ይፋ ከሆነ በኋላ በማህበራዊ ሚዲያው ዘገባውን ውድቅ አድርጎታል፡፡ የ 24 አመቱ ተጫዋች ከመድፈኞቹ ተጫዋቾች ጋር በአደባባይ አለመግባባት ሲፈጠር የመጀመሪያው አይደለም፡፡ አርሰናል ፉልሃምን 3-0 ባሸነፈበት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ተቀይረው ለመግባት ሲያሟሙቁ ከኤዲ ንኬቲያ ጋር መጋጨታቸው ይታወሳል፡፡ የ 33 ዓመቱ ብራዚላዊው ሉዊዝ በ2019 ነበር ቼልሲን ለቅቆ አርሰናልን የተቀላቀለው፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/55026782 |
5sports
| በመጪው ጥቅምት ስታዲየሞች ለተመልካቾች ክፍት ሊደረጉ ይችላል ተባለ | የፕሪሚየር ሊግ የእግር ኳስ ጨዋታዎችንና ሌሎች ስፖርታዊ ውድድሮችን ለመመልከት ከመጪው ጥቅምት ጀምሮ ወደ ስታዲየም መግባት ሊፈቀድላቸው እንደሚችል ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ተናገሩ። ከሦስት ወር በኋላ ስታዲየሞችን ለተመልካች ክፍት ለማድረግ በነሐሴ ወር መጀመሪያ ላይ ሙከራዎች ማድረግ የሚጀመር ሲሆን ነገር ግን የትኛውም ስታዲየም የሚከፈተው የኮሮናቫይረስ መከላከያ መመሪያዎችን ተግባራዊ ማድረግ ከቻሉ ብቻ ነው። እግር ኳስን ጨምሮ አንዳንድ የስፖርት ውድድሮች በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ ለወራት ከተቋረጡ በኋላ በዝግ ስታዲየሞች መካሄድ ጀምረዋል። "የስፖርት ውድድሮች የሚካሄዱባቸውን ስታዲየሞችን በመሰሳሉ በርካታ ሕዝብ የሚታደምባቸው ስፍራዎችን ለመክፈት የሚያስችል ሙከራዎችን እናደርጋለን" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆንሰን ዛሬ ተናግረዋል። ከጥቅምት ወር ጀምሮም ስታዲየሞች ውስጥ ተመልካቾች እንዲገቡ ለማድረግ ወረርሽኙ የማይተላለፍባቸው ሁኔታዎችን ለማረጋገጥ አሁን የሚደረገው ፍተሻ የተሳካ መሆን እንዳለበት አመልክተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጨምረውም "ይህ ለውጥ ሲደረግ ከኮሮናቫይረስ ነጻ በሆነና በአስተማማኝ ሁኔታ መሆን ያለበት ሲሆን ለዚህም ነሐሴ ላይ የሚደረገው ሙከራ ውጤታማ መሆን ይኖርበታል" ብለዋል። ከመጋቢት በኋላ ተቋርጠው የነበሩት የአገር ውስጥ የውድድር ስፖርቶች በሰኔ ወር የተጀመሩ ሲሆን፤ የፕሪሚየር ሊግና የእንግሊዝ እግር ኳስ ሊግ ጨዋታዎች በሰኔ ወር አጋማሽ ላይ በተከታታይ ተጀምረዋል። ዓለም አቀፍ የክሪኬት፣ የጎልፍ፣ የፈረስ ግልቢያ ውድድሮችና ሌሎችም በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ መካሄድ ጀምረዋል። በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተቀሰቀሰ በኋላ በአምስት ወራት ውስጥ 45 ሺህ ሰዎች ከበሽታው ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን ከ292 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ በበሽታው መያዛቸው በምርመራ ተረጋግጧል። | በመጪው ጥቅምት ስታዲየሞች ለተመልካቾች ክፍት ሊደረጉ ይችላል ተባለ የፕሪሚየር ሊግ የእግር ኳስ ጨዋታዎችንና ሌሎች ስፖርታዊ ውድድሮችን ለመመልከት ከመጪው ጥቅምት ጀምሮ ወደ ስታዲየም መግባት ሊፈቀድላቸው እንደሚችል ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ተናገሩ። ከሦስት ወር በኋላ ስታዲየሞችን ለተመልካች ክፍት ለማድረግ በነሐሴ ወር መጀመሪያ ላይ ሙከራዎች ማድረግ የሚጀመር ሲሆን ነገር ግን የትኛውም ስታዲየም የሚከፈተው የኮሮናቫይረስ መከላከያ መመሪያዎችን ተግባራዊ ማድረግ ከቻሉ ብቻ ነው። እግር ኳስን ጨምሮ አንዳንድ የስፖርት ውድድሮች በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ ለወራት ከተቋረጡ በኋላ በዝግ ስታዲየሞች መካሄድ ጀምረዋል። "የስፖርት ውድድሮች የሚካሄዱባቸውን ስታዲየሞችን በመሰሳሉ በርካታ ሕዝብ የሚታደምባቸው ስፍራዎችን ለመክፈት የሚያስችል ሙከራዎችን እናደርጋለን" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆንሰን ዛሬ ተናግረዋል። ከጥቅምት ወር ጀምሮም ስታዲየሞች ውስጥ ተመልካቾች እንዲገቡ ለማድረግ ወረርሽኙ የማይተላለፍባቸው ሁኔታዎችን ለማረጋገጥ አሁን የሚደረገው ፍተሻ የተሳካ መሆን እንዳለበት አመልክተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጨምረውም "ይህ ለውጥ ሲደረግ ከኮሮናቫይረስ ነጻ በሆነና በአስተማማኝ ሁኔታ መሆን ያለበት ሲሆን ለዚህም ነሐሴ ላይ የሚደረገው ሙከራ ውጤታማ መሆን ይኖርበታል" ብለዋል። ከመጋቢት በኋላ ተቋርጠው የነበሩት የአገር ውስጥ የውድድር ስፖርቶች በሰኔ ወር የተጀመሩ ሲሆን፤ የፕሪሚየር ሊግና የእንግሊዝ እግር ኳስ ሊግ ጨዋታዎች በሰኔ ወር አጋማሽ ላይ በተከታታይ ተጀምረዋል። ዓለም አቀፍ የክሪኬት፣ የጎልፍ፣ የፈረስ ግልቢያ ውድድሮችና ሌሎችም በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ መካሄድ ጀምረዋል። በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተቀሰቀሰ በኋላ በአምስት ወራት ውስጥ 45 ሺህ ሰዎች ከበሽታው ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን ከ292 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ በበሽታው መያዛቸው በምርመራ ተረጋግጧል። | https://www.bbc.com/amharic/news-53447238 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ ድሃ ሃገራት ክትባት እያለቀባቸው ነው- የዓለም ጤና ድርጅት | በዓለም አቀፍ የክትባት የመጋራት መርሃግብር አማካይነት የኮቪድ -19 ክትባቶችን የሚያገኙ ብዙ ድሃ ሃገሮች ለመከተብ የሚያስችል በቂ መጠን የላቸውም ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት ከፍተኛ አማካሪው ዶ/ር ብሩስ አይልወርድ በኮቫክስ መርሃ ግብር 90 ሚሊዮን ዶዝ ክትባት ለ 131 ሃገራት መድረሱን ተናግረዋል፡፡ ይህ ግን በዓለም ዙሪያ እየተዛመተ ከሚገኘው ቫይረስ ህዝቦችን ለመከላከል በቂ አለመሆኑን አስታውቀዋል። እጥረቶቹ የተከሰቱት በአንዳንድ የአፍሪካ ሃገሮች ሦስተኛ ዙር ማዕበል መከሰቱን ተከትሎ ነው፡፡ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በሃገራቸውን እየጨመረ የመጣውን ቫይረስ ለመከላከል እየሠራች ባለችበት ወቅት ሃብታም ሃገራት ክትባት ማከማቸታቸውን እንዲያቆሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በአህጉር ደረጃ አፍሪካ ውስጥ 40 ሚሊዮን ዶዞች (መጠን) ብቻ መሰጠቱ ከአጠቃላዩ ህዝብ ከ2 በመቶ በታች እንዲደርሰው ምክንያት መሆኑን ራማፎሳ ገልጸዋል፡፡ ይህንን ለመቅረፍ በደቡብ አፍሪካ ተጨማሪ ክትባቶችን ለማምረት የሚያስችል ማዕከል ለመክፈት መንግስታቸው ከኮቫክስ ጋር እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ኮቫክስ ባለፈው ዓመት የኮቪድ-19 ክትባት በዓለም ዙሪያ እንዲቀርብ ለማድረግ የበለጸጉ አገራት ለድሃ አገራት ወጪዎችን ድጎማ በማድረግ የተቋቋመ ነው፡፡ በዓለም ጤና ድርጅት እና በሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የሚመራው ኮቫክስ እአአ በ 2021 መጨረሻ በዓለም ዙሪያ ሁለት ቢሊዮን ክትባቶችን ለማቅረብ ግብ አንግቦ ነበር፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ ለድሃ አገራት በመስጠት ቢያንስ 20 በመቶ የሚሆነውን ህዝብ ለመከላከል የሚረዳ በቂ ክትባቶችን ለማሰራጨት ተስፋ አቅዶ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የክትባቶቹ ስርጭት በምርት መዘግየት እና በአቅርቦት መቆራረጥ ተስተጓጉሏል። በዚህም በኮቫክስ ላይ ሙሉ በሙሉ ተስፋ ባደረጉ ሀገሮች እጥረት አስከትሏል፡፡ በቅርቡ ክትባቶች እንዳለቀባቸው ሪፖርት ካደረጉ ሃገራት መካከል ኡጋንዳ፣ ዚምባብዌ፣ ባንግላዲሽ እና ትሪኒዳድ እና ቶባጎ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ሰኞ በጄኔቫ የዓለም ጤና ድርጅት መግለጫ ላይ ዶ/ር አይልወርድ መጠነ ሰፊ እጥረቶች መኖራቸውን አምነዋል፡፡ በኮቫክስ ከተሳተፉት 80 ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ሃገራት ውስጥ "ቢያንስ ግማሾቹ ፕሮግራማቸውን ለማስቀጠል የሚያስችል በቂ ክትባት የላቸውም" ብለዋል ዶ/ር አይልወርድ፡፡ "በየቀኑ ከሃገራት የምንሰማውን ከተመለከትን ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ሃገሮች እጥረት አለባቸው። ተጨማሪ ክትባት ለማግኘትም ጥሪ እያቀረቡ ነው፡፡ እውነታው ግን ምናልባትም ከዚህ የበለጠ ሊሆን ይችላል፡፡" . አንዳንድ አገራት እጥረቶችን ለመቋቋም አማራጭ መንገዶችን እንደሞከሩ ገልጸው ለክትባቶች ከገበያ ዋጋ በላይ መክፈላቸውን በምሳሌነት አንስተዋል፡፡ የክትባት አቅርቦቶች ጫና ውስጥ በመግባታቸው ትርፍ ክትባት ያላቸው አንዳንድ ሃብታም ሀገሮች በኮቫክስ እና በሌሎችም መንገዶች ልገሳን ለማሳደግ ጥረቶችን እያደረጉ ናቸው፡፡ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ሰኞ ዕለት 55 ሚሊዮን ክትባቶችን ለተቸገሩ ሃገሮች ለመስጠት እንዴት እንዳቀደ አስታወቋል፡፡ 41 ሚሊዮን የሚሆኑትን በኮቫክስ በኩል ሲያሰራጭ 14 ሚሊዮኑ ደግሞ ቅድሚያ ያስፈልጋቸው ተብለው ለሚታመኑ ሃገራት ይከፋፈላል፡፡ እነዚህ ክትባቶች አሜሪካ በኮቫክስ በኩል 500 ሚሊዮን ዶዝ ለመለገስ ያቀደችው ውስጥ አይካተቱም፡፡ ፕሬዝዳንት ባይደን ይህን ቃል የገቡት በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በቡድን ሰባት ስብሰባ ላይ ነው፡፡ በስብሰባው የቡድን ሰባት ሃገራት በዚህ የፈረንጆች ዓመት አንድ ቢሊዮን ክትባቶችን ለድሃ አገራት ለመስጠት ቃል ገብተዋል፡፡ ህልም የሌለው፣ በጣም ቀርፋፋ እና ምዕራባዊያኑ መሪዎች የምዕተ ዓመቱን የከፋ የህብረተሰብ ጤና ቀውስ ለመቋቋም ቁርጠኛ አይደሉም ሲሉ ተሟጋቾች ዕቅዱን ተችተዋል። አንዳንድ የጤና ባለሙያዎች በዓለም ዙሪያ ወረርሽኙን ለማስቆም በቂ ሰዎች እስኪከተቡ ወራትን ሊጠይቅ ይችላል ብለው ያምናሉ፡፡ የኋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ ሰኞ ዕለት ስለ ዓለም አቀፍ ክትባት ፍላጎት ተጠይቀው "ከዓለም ጋር የምንጋራው ብዙ ክትባት አለን። ትልቁ ተግዳሮት ሆኖ ያገኘነው አቅርቦቱ ሳይሆን የሎጂስቲክስ ፈተናው ነው" ብለዋል። | ኮሮናቫይረስ፡ ድሃ ሃገራት ክትባት እያለቀባቸው ነው- የዓለም ጤና ድርጅት በዓለም አቀፍ የክትባት የመጋራት መርሃግብር አማካይነት የኮቪድ -19 ክትባቶችን የሚያገኙ ብዙ ድሃ ሃገሮች ለመከተብ የሚያስችል በቂ መጠን የላቸውም ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት ከፍተኛ አማካሪው ዶ/ር ብሩስ አይልወርድ በኮቫክስ መርሃ ግብር 90 ሚሊዮን ዶዝ ክትባት ለ 131 ሃገራት መድረሱን ተናግረዋል፡፡ ይህ ግን በዓለም ዙሪያ እየተዛመተ ከሚገኘው ቫይረስ ህዝቦችን ለመከላከል በቂ አለመሆኑን አስታውቀዋል። እጥረቶቹ የተከሰቱት በአንዳንድ የአፍሪካ ሃገሮች ሦስተኛ ዙር ማዕበል መከሰቱን ተከትሎ ነው፡፡ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በሃገራቸውን እየጨመረ የመጣውን ቫይረስ ለመከላከል እየሠራች ባለችበት ወቅት ሃብታም ሃገራት ክትባት ማከማቸታቸውን እንዲያቆሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በአህጉር ደረጃ አፍሪካ ውስጥ 40 ሚሊዮን ዶዞች (መጠን) ብቻ መሰጠቱ ከአጠቃላዩ ህዝብ ከ2 በመቶ በታች እንዲደርሰው ምክንያት መሆኑን ራማፎሳ ገልጸዋል፡፡ ይህንን ለመቅረፍ በደቡብ አፍሪካ ተጨማሪ ክትባቶችን ለማምረት የሚያስችል ማዕከል ለመክፈት መንግስታቸው ከኮቫክስ ጋር እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ኮቫክስ ባለፈው ዓመት የኮቪድ-19 ክትባት በዓለም ዙሪያ እንዲቀርብ ለማድረግ የበለጸጉ አገራት ለድሃ አገራት ወጪዎችን ድጎማ በማድረግ የተቋቋመ ነው፡፡ በዓለም ጤና ድርጅት እና በሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የሚመራው ኮቫክስ እአአ በ 2021 መጨረሻ በዓለም ዙሪያ ሁለት ቢሊዮን ክትባቶችን ለማቅረብ ግብ አንግቦ ነበር፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ ለድሃ አገራት በመስጠት ቢያንስ 20 በመቶ የሚሆነውን ህዝብ ለመከላከል የሚረዳ በቂ ክትባቶችን ለማሰራጨት ተስፋ አቅዶ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የክትባቶቹ ስርጭት በምርት መዘግየት እና በአቅርቦት መቆራረጥ ተስተጓጉሏል። በዚህም በኮቫክስ ላይ ሙሉ በሙሉ ተስፋ ባደረጉ ሀገሮች እጥረት አስከትሏል፡፡ በቅርቡ ክትባቶች እንዳለቀባቸው ሪፖርት ካደረጉ ሃገራት መካከል ኡጋንዳ፣ ዚምባብዌ፣ ባንግላዲሽ እና ትሪኒዳድ እና ቶባጎ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ሰኞ በጄኔቫ የዓለም ጤና ድርጅት መግለጫ ላይ ዶ/ር አይልወርድ መጠነ ሰፊ እጥረቶች መኖራቸውን አምነዋል፡፡ በኮቫክስ ከተሳተፉት 80 ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ሃገራት ውስጥ "ቢያንስ ግማሾቹ ፕሮግራማቸውን ለማስቀጠል የሚያስችል በቂ ክትባት የላቸውም" ብለዋል ዶ/ር አይልወርድ፡፡ "በየቀኑ ከሃገራት የምንሰማውን ከተመለከትን ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ሃገሮች እጥረት አለባቸው። ተጨማሪ ክትባት ለማግኘትም ጥሪ እያቀረቡ ነው፡፡ እውነታው ግን ምናልባትም ከዚህ የበለጠ ሊሆን ይችላል፡፡" . አንዳንድ አገራት እጥረቶችን ለመቋቋም አማራጭ መንገዶችን እንደሞከሩ ገልጸው ለክትባቶች ከገበያ ዋጋ በላይ መክፈላቸውን በምሳሌነት አንስተዋል፡፡ የክትባት አቅርቦቶች ጫና ውስጥ በመግባታቸው ትርፍ ክትባት ያላቸው አንዳንድ ሃብታም ሀገሮች በኮቫክስ እና በሌሎችም መንገዶች ልገሳን ለማሳደግ ጥረቶችን እያደረጉ ናቸው፡፡ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ሰኞ ዕለት 55 ሚሊዮን ክትባቶችን ለተቸገሩ ሃገሮች ለመስጠት እንዴት እንዳቀደ አስታወቋል፡፡ 41 ሚሊዮን የሚሆኑትን በኮቫክስ በኩል ሲያሰራጭ 14 ሚሊዮኑ ደግሞ ቅድሚያ ያስፈልጋቸው ተብለው ለሚታመኑ ሃገራት ይከፋፈላል፡፡ እነዚህ ክትባቶች አሜሪካ በኮቫክስ በኩል 500 ሚሊዮን ዶዝ ለመለገስ ያቀደችው ውስጥ አይካተቱም፡፡ ፕሬዝዳንት ባይደን ይህን ቃል የገቡት በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በቡድን ሰባት ስብሰባ ላይ ነው፡፡ በስብሰባው የቡድን ሰባት ሃገራት በዚህ የፈረንጆች ዓመት አንድ ቢሊዮን ክትባቶችን ለድሃ አገራት ለመስጠት ቃል ገብተዋል፡፡ ህልም የሌለው፣ በጣም ቀርፋፋ እና ምዕራባዊያኑ መሪዎች የምዕተ ዓመቱን የከፋ የህብረተሰብ ጤና ቀውስ ለመቋቋም ቁርጠኛ አይደሉም ሲሉ ተሟጋቾች ዕቅዱን ተችተዋል። አንዳንድ የጤና ባለሙያዎች በዓለም ዙሪያ ወረርሽኙን ለማስቆም በቂ ሰዎች እስኪከተቡ ወራትን ሊጠይቅ ይችላል ብለው ያምናሉ፡፡ የኋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ ሰኞ ዕለት ስለ ዓለም አቀፍ ክትባት ፍላጎት ተጠይቀው "ከዓለም ጋር የምንጋራው ብዙ ክትባት አለን። ትልቁ ተግዳሮት ሆኖ ያገኘነው አቅርቦቱ ሳይሆን የሎጂስቲክስ ፈተናው ነው" ብለዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-57563812 |
3politics
| የኡጋንዳ ምርጫ 2021፡ ዩዌሪ ሙሴቪኒና ቦቢ ዋይን ለፕሬዚደንታዊ ምርጫ ተፋጠዋል | በኡጋንዳ አነጋጋሪ በሆነው ምርጫ የ38 ዓመቱ ኡጋንዳዊው የሙዚቃ ኮከብ ቦቢ ዋይን በአፍሪካ ካስተዳደሩ መሪዎች አንዱ የሆኑትን ዩዌሪ ሙሴቬኒ እየተገዳደራቸው ነው። ሮበርት ክያጉላይ በመድረክ ስሙ ደግሞ ቦቢ ዋይን በመባል የሚታወቀው የሙዚቃ ኮከብ የአገሪቷን ወጣት ትውልድ እንደወከለ የተናገረ ሲሆን፤ የ76 ዓመቱ ዩዌሪ ሙሴቪኒ በበኩላቸው ለአገሪቷ መረጋጋት መቆማቸውን ተናግረዋል። በምርጫ ቅሰቀሳ ዘመቻ ወቅት ከፍተኛ ተቃውሞ የነበረ ሲሆን በርካታ ሰዎችም ተገድለዋል። መንግሥት ማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲዘጉ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ፕሬዚደንት ሙሴቪኒ ይህ የሆነው ፌስቡክ የፓርቲያቸውን በርካታ ደጋፊዎች ገጽ በማገዱ ነው ብለዋል። የኡጋንዳ ፖሊስ በምርጫው ዕለት በዋና መዲናዋ ካምፓላ የሕንጻ ጣሪያዎች ላይ ፖሊስ እንደሚያሰማራ ገልጿል። ሆኖም መሳሪያ የታጠቁ ተሽከርካሪዎች ግን በጎዳናዎች ላይ ቁጥጥር ማድረጋቸውን ጀምረዋል። ምርጫው አንድ ሰዓት ላይ የተከፈተ ሲሆን የምርጫው ውጤት ከቅዳሜ በፊት ይወጣል ተብሎ አይጠበቅም። ፕሬዚደንት ሙሴቪኒ 35 ዓመታትን በሥልጣን ካሳለፉ በኋላ ለስድስተኛ ጊዜ ለመመረጥ ይወዳደራሉ። በዋና መዲናዋ ካምፓላ እና በሌሎች በርካታ አካባቢዎች ዘመቻዎችን ማካሄድ ተከልክሏል። ተቃዋሚ ፓርቲዎች ይህ የተደረገው ዘመቻ ማካሄድ በተከለከለባቸው ቦታዎች በርካታ ደጋፊዎች ስላላቸው እንደሆነ ተናግረዋል። መንግሥት ግን ምክንያቱን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሥርጭትን ለመከላከል ነው ብሏል። ቦቢ ዋይንን ጨምሮ የተቃዋሚ ተወዳዳሪዎች፣ ደጋፊዎችና የዘመቻ ባልደረቦቻቸው በተለያዩ ጊዜያት ታስረዋል። ፖሊስ በገበያ ማዕከላትና ሌሎች ትላልቅ ሕንፃዎች ላይ ኃይሉን ለማሰማራት ያሰበው ባለፈው ሕዳር ወር የተቃዋሚ ፓርቲ አንቂዎች ከሕንጻ ጣሪያዎች ላይ ተቃውሞ መጥራታቸውን ተከትሎ ነው። በዚህ ወቅትም ቦቢ ዋይን ከታሰረ በኋላም ከ50 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። የምርጫ ታዛቢዎች የምርጫ ታዛቢዎች ከአሜሪካ ሳይሆን ከአፍሪካ መሆናቸው ተገልጿል። አሜሪካ ረቡዕ ዕለት አብዛኛው ምርጫውን ለመታዘብ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ታዛቢዎቿን ማስወጣቷን ገልጻለች። በኡጋንዳ የአሜሪካ አምባሳደር ናታሌ ብራውን በመግለጫቸው "ያለ ታዛቢ ፕሬዚደንታዊውም ሆነ የፓርላማ ምርጫው ተጠያቂነት ፣ ግልፅነትና አመኔታ አይኖረውም" ብለዋል። አምባሳደሯ በርካታ ኡጋንዳዊያንም ምርጫውን ለመታዘብ ፈቃድ እንዳላገኙ አክለዋል። የአውሮፓ ሕብረት የምርጫ ባለሙያዎችን ለመላክ ያቀረበው ሃሳብም ተቀባይነት አላገኘም። በምላሹ የፕሬዚደንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ቃል ቃባይ ዶን ዋንያማ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ ከአፍሪካ ሕብረትና ከምስራቅ አፍሪካ ማሕበረሰብ ታዛቢዎች እንዳሉ ገልጸዋል። አክለውም "ኡጋንዳ ለመጨረሻ ጊዜ የምርጫ ታዛቢዎችን ወደ አሜሪካ መቼ እንደላከች አላስታውስም" ብለዋል። የአገሪቷ መንግሥት ቀደም ብሎ ምርጫው ነጻና ፍትሐዊ እንደሚሆን ተናግሮ ነበር። በሌላ በኩል ቦቢ ዋይን መራጮች ሐሙስ ዕለት በምርጫ ጣቢያዎቹ እንዲቆዩና የምርጫ ማጭበርበርን ለመከላከል በስልኮቻቸው ካሜራ እያንዳንዱን ሂደት እንዲቀርጹ ጥሪ አቅርቧል። የአገሪቷ የቴሌኮም ድርጅቶች የኡጋንዳ ኮሚዩኒኬሽን ኮሚሽን ትዕዛዝን ተከትሎ ሁሉም ማህበራዊ ሚዲያ ዎችንና የጽሁፍ መልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያዎችን መዝጋቱን ለደንበኞቹ ያስታወቀው ረቡዕ ዕለት ነበር። | የኡጋንዳ ምርጫ 2021፡ ዩዌሪ ሙሴቪኒና ቦቢ ዋይን ለፕሬዚደንታዊ ምርጫ ተፋጠዋል በኡጋንዳ አነጋጋሪ በሆነው ምርጫ የ38 ዓመቱ ኡጋንዳዊው የሙዚቃ ኮከብ ቦቢ ዋይን በአፍሪካ ካስተዳደሩ መሪዎች አንዱ የሆኑትን ዩዌሪ ሙሴቬኒ እየተገዳደራቸው ነው። ሮበርት ክያጉላይ በመድረክ ስሙ ደግሞ ቦቢ ዋይን በመባል የሚታወቀው የሙዚቃ ኮከብ የአገሪቷን ወጣት ትውልድ እንደወከለ የተናገረ ሲሆን፤ የ76 ዓመቱ ዩዌሪ ሙሴቪኒ በበኩላቸው ለአገሪቷ መረጋጋት መቆማቸውን ተናግረዋል። በምርጫ ቅሰቀሳ ዘመቻ ወቅት ከፍተኛ ተቃውሞ የነበረ ሲሆን በርካታ ሰዎችም ተገድለዋል። መንግሥት ማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲዘጉ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ፕሬዚደንት ሙሴቪኒ ይህ የሆነው ፌስቡክ የፓርቲያቸውን በርካታ ደጋፊዎች ገጽ በማገዱ ነው ብለዋል። የኡጋንዳ ፖሊስ በምርጫው ዕለት በዋና መዲናዋ ካምፓላ የሕንጻ ጣሪያዎች ላይ ፖሊስ እንደሚያሰማራ ገልጿል። ሆኖም መሳሪያ የታጠቁ ተሽከርካሪዎች ግን በጎዳናዎች ላይ ቁጥጥር ማድረጋቸውን ጀምረዋል። ምርጫው አንድ ሰዓት ላይ የተከፈተ ሲሆን የምርጫው ውጤት ከቅዳሜ በፊት ይወጣል ተብሎ አይጠበቅም። ፕሬዚደንት ሙሴቪኒ 35 ዓመታትን በሥልጣን ካሳለፉ በኋላ ለስድስተኛ ጊዜ ለመመረጥ ይወዳደራሉ። በዋና መዲናዋ ካምፓላ እና በሌሎች በርካታ አካባቢዎች ዘመቻዎችን ማካሄድ ተከልክሏል። ተቃዋሚ ፓርቲዎች ይህ የተደረገው ዘመቻ ማካሄድ በተከለከለባቸው ቦታዎች በርካታ ደጋፊዎች ስላላቸው እንደሆነ ተናግረዋል። መንግሥት ግን ምክንያቱን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሥርጭትን ለመከላከል ነው ብሏል። ቦቢ ዋይንን ጨምሮ የተቃዋሚ ተወዳዳሪዎች፣ ደጋፊዎችና የዘመቻ ባልደረቦቻቸው በተለያዩ ጊዜያት ታስረዋል። ፖሊስ በገበያ ማዕከላትና ሌሎች ትላልቅ ሕንፃዎች ላይ ኃይሉን ለማሰማራት ያሰበው ባለፈው ሕዳር ወር የተቃዋሚ ፓርቲ አንቂዎች ከሕንጻ ጣሪያዎች ላይ ተቃውሞ መጥራታቸውን ተከትሎ ነው። በዚህ ወቅትም ቦቢ ዋይን ከታሰረ በኋላም ከ50 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። የምርጫ ታዛቢዎች የምርጫ ታዛቢዎች ከአሜሪካ ሳይሆን ከአፍሪካ መሆናቸው ተገልጿል። አሜሪካ ረቡዕ ዕለት አብዛኛው ምርጫውን ለመታዘብ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ታዛቢዎቿን ማስወጣቷን ገልጻለች። በኡጋንዳ የአሜሪካ አምባሳደር ናታሌ ብራውን በመግለጫቸው "ያለ ታዛቢ ፕሬዚደንታዊውም ሆነ የፓርላማ ምርጫው ተጠያቂነት ፣ ግልፅነትና አመኔታ አይኖረውም" ብለዋል። አምባሳደሯ በርካታ ኡጋንዳዊያንም ምርጫውን ለመታዘብ ፈቃድ እንዳላገኙ አክለዋል። የአውሮፓ ሕብረት የምርጫ ባለሙያዎችን ለመላክ ያቀረበው ሃሳብም ተቀባይነት አላገኘም። በምላሹ የፕሬዚደንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ቃል ቃባይ ዶን ዋንያማ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ ከአፍሪካ ሕብረትና ከምስራቅ አፍሪካ ማሕበረሰብ ታዛቢዎች እንዳሉ ገልጸዋል። አክለውም "ኡጋንዳ ለመጨረሻ ጊዜ የምርጫ ታዛቢዎችን ወደ አሜሪካ መቼ እንደላከች አላስታውስም" ብለዋል። የአገሪቷ መንግሥት ቀደም ብሎ ምርጫው ነጻና ፍትሐዊ እንደሚሆን ተናግሮ ነበር። በሌላ በኩል ቦቢ ዋይን መራጮች ሐሙስ ዕለት በምርጫ ጣቢያዎቹ እንዲቆዩና የምርጫ ማጭበርበርን ለመከላከል በስልኮቻቸው ካሜራ እያንዳንዱን ሂደት እንዲቀርጹ ጥሪ አቅርቧል። የአገሪቷ የቴሌኮም ድርጅቶች የኡጋንዳ ኮሚዩኒኬሽን ኮሚሽን ትዕዛዝን ተከትሎ ሁሉም ማህበራዊ ሚዲያ ዎችንና የጽሁፍ መልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያዎችን መዝጋቱን ለደንበኞቹ ያስታወቀው ረቡዕ ዕለት ነበር። | https://www.bbc.com/amharic/news-55657979 |
3politics
| በስዊድን የመጀመርያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር በተመረጡ በሰዓታት ውስጥ ሥልጣን ለቀቁ | በስዊድን ታሪክ የመጀመርያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ሥልጣን ለቀቁ፡፡ ማግዳሊና አንደርሰን ሥልጣን የለቀቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በተሾሙ በሰዓታት ውስጥ ነው፡፡ ትናንትና ረቡዕ መሪ ሆነው መመረጣቸው ይፋ ከሆነ ከሰዓት በኋላ ነው አንደርሰን የለቀቁት፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ከርሳቸው ፓርቲ ጋር ጥምረት የፈጠረው የፖለቲካ ድርጅት ከጥምረቱ በመልቀቁና የሳቸው ፓርቲ ሶሻል ዲሞክራት ያቀረበው የበጀት ጥያቄ በምክር ቤቱ ሊያልፍ ባለመቻሉ ነው፡፡ ከዚያ ይልቅ ምክር ቤቱ፣ የቀኝ አክራሪ ጸረ- ስደተኛ አቋም ያለው ፓርቲ ያቀረበው በጀት ላይ ድምጽ ሰጥቷል፡፡ ‹‹በዚህ ጊዜ ለአፈጉባኤው ሥልጣን ብለቅ እመኛለሁ ብዬ ነገርኩት›› ብለዋል አንደርሰን ለጋዜጠኞች፡፡ ከርሳቸው ፓርቲ ጋር ጥምረት የፈጠረው ግሪንስ ፓርቲ ‹‹በቀኝ አክራሪዎች የቀረበን በጀት አልቀበልም ሲል ነበር ከጥምረቱ የለቀቀው፡፡ አንደርሰን በዚህ ሁኔታ ለመቀጠል እንደማይፈልጉና የገዛ ፓርቲያቸው በአብላጫ ድምጽ አግኝቶ መንግሥት ሲመሰርት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መመረጥ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡ ‹‹በሕገ መንግሥቱ አካሄድ የጥምር መንግሥት ከተመሠረተና አንድ ፓርቲ ከጥምረቱ ከወጣ መንግሥት ሥልጣን ይለቃል፤ በእንዲህ ሁኔታ ቅቡልነቱ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ መንግሥትን መምራት ደግሞ አልፈልግም›› ብለዋል አንደርሰን፡፡ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አንደርሰን ሥልጣን መልቀቃቸውን ተከትሎ የፓርቲ መሪዎችን እንደሚያነጋግሩ ይጠበቃል፡፡ አንደርሰን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ስዊድንን እንዲመሩ ድምጽ ያገኙት ትናንትና ነበር፡፡ በስዊድን ሕግ አብዛኛዎቹ የተወካዮች ምክር ቤት እንደራሴዎች በተቃውሞ ድምጽ ካልሰጡ ተመራጭ ጠቅላይ ሚኒስትር ያደርጋል፡፡ ሪክስዳግ የሚባለው የስዊድን ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 349 አባላት አሉት፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንደርሰንን የተቃወሙት 174ቱ ናቸው፡፡ ይሁንና 117ቱ ድምጽ ሰጥተዋቸዋል፡፡ ከዚህ አንጻር እንዴት ተመረጡ ሊያስብል ቢችልም 57ቱ ድምጽ ተአቅቦ ማድረጋቸው በስዊድን ሕገ መንግሥት ከምክር ቤት አባላት በድምሩ ብዙ ተወካይ ባይመርጣቸውም ስላልተቃወማቸው ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ ያስችላቸዋል፡፡ አንደርሰን በዚህ የተነሳ አንድ ተጨማሪ ድምጽ አግኝተው ነበር ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት፡፡ በስዊድን ሴቶች ድምጽ መስጠት ከጀመሩ ከመቶ ዓመታት በኋላ የ54 ዓመት ሴት አንደርሰን ሶሻል ዲሞክራትን በመምራት ጠቅላይ ሚኒስትር መሆናቸው ሲበሰር የምክር ቤቱ አባላት ቆመው ነበር ያጨበጨቡላቸው፡፡ በዩኒቨርስቲ ሲቲ ኡፕሳላ የአዳጊዎች የውሃ ዋና ሻምፒዮን የነበሩት አንደርሰን ፖለቲካ ውስጥ የገቡት በ1996 የጠቅላይ ሚኒስትር ጎራን ፐርሰን አማካሪ በመሆን ነበር፡፡ ላለፉት ሰባት ዓመታት ደግሞ በገንዘብ ሚኒስትርነት አገልግለዋል፡፡ ማግደሊና አንደርሰን በሕዝብ እንደራሴዎች ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ ድምጽ ከማግኘታቸው በፊት ስዊድን ከኖርዲክ አገሮች ሁሉ ብቸኛዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ኖሯት የማያውቅ አገር ሆና ቆይታለች፡፡ ስዊድን የጾታ እኩልነት ከፍ ባለ ደረጃ የምታከብር ብልጹግ አገር ናት፡፡ | በስዊድን የመጀመርያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር በተመረጡ በሰዓታት ውስጥ ሥልጣን ለቀቁ በስዊድን ታሪክ የመጀመርያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ሥልጣን ለቀቁ፡፡ ማግዳሊና አንደርሰን ሥልጣን የለቀቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በተሾሙ በሰዓታት ውስጥ ነው፡፡ ትናንትና ረቡዕ መሪ ሆነው መመረጣቸው ይፋ ከሆነ ከሰዓት በኋላ ነው አንደርሰን የለቀቁት፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ከርሳቸው ፓርቲ ጋር ጥምረት የፈጠረው የፖለቲካ ድርጅት ከጥምረቱ በመልቀቁና የሳቸው ፓርቲ ሶሻል ዲሞክራት ያቀረበው የበጀት ጥያቄ በምክር ቤቱ ሊያልፍ ባለመቻሉ ነው፡፡ ከዚያ ይልቅ ምክር ቤቱ፣ የቀኝ አክራሪ ጸረ- ስደተኛ አቋም ያለው ፓርቲ ያቀረበው በጀት ላይ ድምጽ ሰጥቷል፡፡ ‹‹በዚህ ጊዜ ለአፈጉባኤው ሥልጣን ብለቅ እመኛለሁ ብዬ ነገርኩት›› ብለዋል አንደርሰን ለጋዜጠኞች፡፡ ከርሳቸው ፓርቲ ጋር ጥምረት የፈጠረው ግሪንስ ፓርቲ ‹‹በቀኝ አክራሪዎች የቀረበን በጀት አልቀበልም ሲል ነበር ከጥምረቱ የለቀቀው፡፡ አንደርሰን በዚህ ሁኔታ ለመቀጠል እንደማይፈልጉና የገዛ ፓርቲያቸው በአብላጫ ድምጽ አግኝቶ መንግሥት ሲመሰርት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መመረጥ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡ ‹‹በሕገ መንግሥቱ አካሄድ የጥምር መንግሥት ከተመሠረተና አንድ ፓርቲ ከጥምረቱ ከወጣ መንግሥት ሥልጣን ይለቃል፤ በእንዲህ ሁኔታ ቅቡልነቱ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ መንግሥትን መምራት ደግሞ አልፈልግም›› ብለዋል አንደርሰን፡፡ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አንደርሰን ሥልጣን መልቀቃቸውን ተከትሎ የፓርቲ መሪዎችን እንደሚያነጋግሩ ይጠበቃል፡፡ አንደርሰን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ስዊድንን እንዲመሩ ድምጽ ያገኙት ትናንትና ነበር፡፡ በስዊድን ሕግ አብዛኛዎቹ የተወካዮች ምክር ቤት እንደራሴዎች በተቃውሞ ድምጽ ካልሰጡ ተመራጭ ጠቅላይ ሚኒስትር ያደርጋል፡፡ ሪክስዳግ የሚባለው የስዊድን ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 349 አባላት አሉት፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንደርሰንን የተቃወሙት 174ቱ ናቸው፡፡ ይሁንና 117ቱ ድምጽ ሰጥተዋቸዋል፡፡ ከዚህ አንጻር እንዴት ተመረጡ ሊያስብል ቢችልም 57ቱ ድምጽ ተአቅቦ ማድረጋቸው በስዊድን ሕገ መንግሥት ከምክር ቤት አባላት በድምሩ ብዙ ተወካይ ባይመርጣቸውም ስላልተቃወማቸው ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ ያስችላቸዋል፡፡ አንደርሰን በዚህ የተነሳ አንድ ተጨማሪ ድምጽ አግኝተው ነበር ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት፡፡ በስዊድን ሴቶች ድምጽ መስጠት ከጀመሩ ከመቶ ዓመታት በኋላ የ54 ዓመት ሴት አንደርሰን ሶሻል ዲሞክራትን በመምራት ጠቅላይ ሚኒስትር መሆናቸው ሲበሰር የምክር ቤቱ አባላት ቆመው ነበር ያጨበጨቡላቸው፡፡ በዩኒቨርስቲ ሲቲ ኡፕሳላ የአዳጊዎች የውሃ ዋና ሻምፒዮን የነበሩት አንደርሰን ፖለቲካ ውስጥ የገቡት በ1996 የጠቅላይ ሚኒስትር ጎራን ፐርሰን አማካሪ በመሆን ነበር፡፡ ላለፉት ሰባት ዓመታት ደግሞ በገንዘብ ሚኒስትርነት አገልግለዋል፡፡ ማግደሊና አንደርሰን በሕዝብ እንደራሴዎች ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ ድምጽ ከማግኘታቸው በፊት ስዊድን ከኖርዲክ አገሮች ሁሉ ብቸኛዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ኖሯት የማያውቅ አገር ሆና ቆይታለች፡፡ ስዊድን የጾታ እኩልነት ከፍ ባለ ደረጃ የምታከብር ብልጹግ አገር ናት፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/news-59406243 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ በድሬዳዋ ከሃያ በላይ የጤና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በኮቪድ-19 ተያዙ | በድሬዳዋ 21 የሕክምና ባለሙያዎችና በጤና ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች በኮቪድ-19 መያዛቸውን የከተማዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ለቢቢሲ አረጋገጠ። የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪ ስንታየሁ ደበሳ እንደተናገሩት በሕክምና ዘርፍ ላይ ያሉ ባለሙያዎች በቫይረሱ መያዛቸው እተደረገ ያለውን ወረርሽኙን የመከላከል ሥራን ያዳክመዋል የሚል ስጋት አለ ብለዋል። የከተማ አስተዳደሩ የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪዋ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የጤና ባለሙያዎቹና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞቹ ለኮሮናቫይረስ የተጋለጡት በሥራ ቦታቸው ላይ እያሉ ነው። ወይዘሮ ስንታየሁ ለጤና ባለሙያዎቹ በሽታውን ለመከላከል አስፈጊ የሆኑ አቅርቦቶችን በተመለከተም አስተዳደሩ በበቂ ሁኔታ ማቅቡንና ገልጸው "እስካሁን ድረስ እጥረት የለብንም" ብለዋል። ነገር ግን በሕክምና ተቋማቱ የሚኖሩ ንክኪዎች ባለሙያዎቹን ለቫይረሱ ማጋለጡን የሚናገሩት አስተባባሪዋ፤ ከባለሙያዎቹ ጋር በተደረገ ውይይት ለቫይረሱ የተጋለጡት በየትኛው ጊዜ እንደሆነ ለማለየት እንደሚቸገሩ ገልፀዋል። በህክምና ተቋማቱ ያሉ ሁኔታዎች እንደሚያሳዩት ግን ይላሉ ባለሙያዋ "በሕክምና ሥራ ላይ እያሉ ተጋላጭ መሆናቸውን ነው" በማለት ባለሙያዎቹ እየወሰዱ ያሉትን የጥንቃቄ እርምጃዎችን መፈተሽ እንደሚያስፈልግም ለቢቢሲ ተናግረዋል። "የጤና ባለሙያዎቻችን በቫይረሱ እየተያዙ መምጣት ወረርሽኙን ለመከላከል የምናደርገውን ጥረት ያዳክማል" ሲሉም በአስተዳደሩ በኩል ያለውን ስጋት ለቢቢሲ ተናግረዋል። በቫይረሱ ከተያዙት የሕክምና ባለሙያዎች መካከል በድንገተኛ እና በጽኑ ሕሙማን ክፍል የሚሰሩ ነርሶችና ዶክተሮች እንደሚገኙበት በመጥቀስ፤ በዚህ ክፍል የሚሰሩት ባለሙያዎች በሥራ ባህሪያቸው ምክንያት ተጋላጭ መሆናቸውን አብራርተዋል። በድሬዳዋ እስካሁን ድረስ ስምንት ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ናሙናዎች ላይ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ሲደረገላቸው፤ ከእነዚህ መካከል ደግሞ ከ500 በላይ ግለሰቦች በቫይረሱ መያዛቸውንና 17 ሰዎች ደግሞ በዚሁ ምክንያት መሞታቸው ታውቋል። በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከ400 በላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ማገገማቸውን የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪዋ ስንታየሁ ደበሳ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በተያያዘ ዜና በምሥራቅ ባሌ ዞን ጊኒር ከተማ በሚገኙ ሁለት ፖሊስ ጣቢያዎች የሚገኙ 66 ታራሚዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን የዞኑ ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ተካ ለቢቢሲ ገልፀዋል። በጊኒር ከተማ እና በወረዳው በሚገኙ ሁለት ፖሊስ ጣቢያዎች ውስጥ በተደረገው የኮቪድ-19 ምርመራ እነዚህ ታራሚዎች ኮሮናቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን ኃላፊው ተናግረዋል። እነዚህ ቫይረሱ የተገኘባቸው ታራሚዎች ለህክምና ወደ ሮቤ ሆስፒታል መላካቸውንም ቢቢሲ ከኃላፊው መረዳት ችሏል። ኃላፊው በእነዚህ ፖሊስ ጣቢያዎች ታራሚዎች አካላዊ ርቀታቸውን መጠበቅ በማያስችላቸው እና ያለ ምንም ጥንቃቄ መልኩ መታሰራቸው በሽታው እንዲስፋፋ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል። በአሁኑ ሰዓት ኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ፖሊስ ጣቢያዎች የፀረ ተህዋሲ ርጭት ተደርጓል። በቀላል ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችም የዋስ መብታቸው ተጠብቆ እንዲወጡ ሁኔታዎች እየተመቻቹ መሆኑንም ተናግረዋል። ታራሚዎቹን ለመጠየቅ የሚመጡ ቤተሰቦችም በሽታውን ወደ ኅብረተሰቡ ይዘው በመሄድ ስርጭቱ ይስፋፋል የሚል ስጋት ቢኖርም እስካሁን ድረስ ከተጠረጠሩት ሰዎች ላይ በተወሰደ ናሙና ላይ በተደረገ ምርመራ የተያዘ ሰው አለመገኘቱን አብራርተዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ እስካሁን 470 ሺህ የሚጠጋ ምርመራ ተደርጎ ወደ 21 ሺህ 452 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል። ከእነዚህም መካከል በወረርሽኙ ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 380 ደርሷል። | ኮሮናቫይረስ፡ በድሬዳዋ ከሃያ በላይ የጤና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በኮቪድ-19 ተያዙ በድሬዳዋ 21 የሕክምና ባለሙያዎችና በጤና ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች በኮቪድ-19 መያዛቸውን የከተማዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ለቢቢሲ አረጋገጠ። የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪ ስንታየሁ ደበሳ እንደተናገሩት በሕክምና ዘርፍ ላይ ያሉ ባለሙያዎች በቫይረሱ መያዛቸው እተደረገ ያለውን ወረርሽኙን የመከላከል ሥራን ያዳክመዋል የሚል ስጋት አለ ብለዋል። የከተማ አስተዳደሩ የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪዋ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የጤና ባለሙያዎቹና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞቹ ለኮሮናቫይረስ የተጋለጡት በሥራ ቦታቸው ላይ እያሉ ነው። ወይዘሮ ስንታየሁ ለጤና ባለሙያዎቹ በሽታውን ለመከላከል አስፈጊ የሆኑ አቅርቦቶችን በተመለከተም አስተዳደሩ በበቂ ሁኔታ ማቅቡንና ገልጸው "እስካሁን ድረስ እጥረት የለብንም" ብለዋል። ነገር ግን በሕክምና ተቋማቱ የሚኖሩ ንክኪዎች ባለሙያዎቹን ለቫይረሱ ማጋለጡን የሚናገሩት አስተባባሪዋ፤ ከባለሙያዎቹ ጋር በተደረገ ውይይት ለቫይረሱ የተጋለጡት በየትኛው ጊዜ እንደሆነ ለማለየት እንደሚቸገሩ ገልፀዋል። በህክምና ተቋማቱ ያሉ ሁኔታዎች እንደሚያሳዩት ግን ይላሉ ባለሙያዋ "በሕክምና ሥራ ላይ እያሉ ተጋላጭ መሆናቸውን ነው" በማለት ባለሙያዎቹ እየወሰዱ ያሉትን የጥንቃቄ እርምጃዎችን መፈተሽ እንደሚያስፈልግም ለቢቢሲ ተናግረዋል። "የጤና ባለሙያዎቻችን በቫይረሱ እየተያዙ መምጣት ወረርሽኙን ለመከላከል የምናደርገውን ጥረት ያዳክማል" ሲሉም በአስተዳደሩ በኩል ያለውን ስጋት ለቢቢሲ ተናግረዋል። በቫይረሱ ከተያዙት የሕክምና ባለሙያዎች መካከል በድንገተኛ እና በጽኑ ሕሙማን ክፍል የሚሰሩ ነርሶችና ዶክተሮች እንደሚገኙበት በመጥቀስ፤ በዚህ ክፍል የሚሰሩት ባለሙያዎች በሥራ ባህሪያቸው ምክንያት ተጋላጭ መሆናቸውን አብራርተዋል። በድሬዳዋ እስካሁን ድረስ ስምንት ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ናሙናዎች ላይ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ሲደረገላቸው፤ ከእነዚህ መካከል ደግሞ ከ500 በላይ ግለሰቦች በቫይረሱ መያዛቸውንና 17 ሰዎች ደግሞ በዚሁ ምክንያት መሞታቸው ታውቋል። በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከ400 በላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ማገገማቸውን የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪዋ ስንታየሁ ደበሳ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በተያያዘ ዜና በምሥራቅ ባሌ ዞን ጊኒር ከተማ በሚገኙ ሁለት ፖሊስ ጣቢያዎች የሚገኙ 66 ታራሚዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን የዞኑ ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ተካ ለቢቢሲ ገልፀዋል። በጊኒር ከተማ እና በወረዳው በሚገኙ ሁለት ፖሊስ ጣቢያዎች ውስጥ በተደረገው የኮቪድ-19 ምርመራ እነዚህ ታራሚዎች ኮሮናቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን ኃላፊው ተናግረዋል። እነዚህ ቫይረሱ የተገኘባቸው ታራሚዎች ለህክምና ወደ ሮቤ ሆስፒታል መላካቸውንም ቢቢሲ ከኃላፊው መረዳት ችሏል። ኃላፊው በእነዚህ ፖሊስ ጣቢያዎች ታራሚዎች አካላዊ ርቀታቸውን መጠበቅ በማያስችላቸው እና ያለ ምንም ጥንቃቄ መልኩ መታሰራቸው በሽታው እንዲስፋፋ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል። በአሁኑ ሰዓት ኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ፖሊስ ጣቢያዎች የፀረ ተህዋሲ ርጭት ተደርጓል። በቀላል ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችም የዋስ መብታቸው ተጠብቆ እንዲወጡ ሁኔታዎች እየተመቻቹ መሆኑንም ተናግረዋል። ታራሚዎቹን ለመጠየቅ የሚመጡ ቤተሰቦችም በሽታውን ወደ ኅብረተሰቡ ይዘው በመሄድ ስርጭቱ ይስፋፋል የሚል ስጋት ቢኖርም እስካሁን ድረስ ከተጠረጠሩት ሰዎች ላይ በተወሰደ ናሙና ላይ በተደረገ ምርመራ የተያዘ ሰው አለመገኘቱን አብራርተዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ እስካሁን 470 ሺህ የሚጠጋ ምርመራ ተደርጎ ወደ 21 ሺህ 452 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል። ከእነዚህም መካከል በወረርሽኙ ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 380 ደርሷል። | https://www.bbc.com/amharic/news-53696685 |
0business
| ኤቨር ጊቭን፡ የሱዩዝ ቦይን ዘግታ ለቀናት የቆየችው መርከብ ከወራት በኋላ ወደ አገሯ ተመለሰች | በመጋቢት ወር የሱዩዝ ቦይን ዘግታ ለቀናት የቆየችው ኤቨር ጊቭን የዕቃ መጫኛ መርከብ ባለፍነው ሳምንት ያለምንም ችግር ዘግታው በቆየችው የሱዩዝ ቦይ በኩል ወደ አገሯ ተመለሰች። መርከቧ ከሜድትራኒያን ወደ ቀይ ባሕር ከሚጓዙ መርከቦች መካከል እንደነበረች እና በአውሮፓ ጭነቷን በማራገፍ አሁን በድጋሚ ወደ እስያ እያመራች መሆኗን የሱዩዝ ካናል ባለሥልጣን አስታውቋል። ኤቨር ጊቭን በቦዩ ውስጥ መንቀሳቀስ አቅቷት በቆየችባቸው ቀናት አንድ ሰው ለሞት የዳረገ ከፍተኛ ርብርብ ከተደረገ በኋላ ነበር ከቦዩ የተላቀቀችው። የግብፅ ባለሥልጣናት ቦዩ በመዘጋቱ የደረሰባቸው ካሳ እንዲከፈላቸው መጠየቃቸውን ተከትሎ ኤቨር ጊቭን ለተጨማሪ ሦስት ወራት በኢስማሊያ ቦይ አካባቢ ቆይታለች። መርከቧ ለሦስት ተጨማሪ ወራት በኢስማሊያ ቦይ እንድትቆይ የተደረገችው በግብፅ እና ኤቨር ጊቭን ባለቤቶች መካከል የካሳ ስምምነት እስከሚደረግ ነበር። የሱዩዝ ቦይ ባለሥልጣን በትዊተር ገጹ እንዳስታወቀው ኤቨር ጊቭን በሁለት ጀልባዎች እና በተቋሙ ከፍተኛ መሪዎች ታጅባ ቦዩን በማቋረጥ ወደ አገሯ ተመልሳለች። መርከቧ ትናንት አርብ ከሰሜን ወደ ደቡብ ከተጓዙት 26 መርከቦች መካከል አንዷ ስትሆን ሌሎች 36 መርከቦች በተቃራኒ አቅጣጫ ሲጓዙ ነበር። የስዊዝ ካናል ባለሥልጣንም "ምሥራቁን ከምዕራብ ጋር የሚያገናኘው በጣም አጭር እና ፈጣን መንገድ" በማለት መተላለፊያውን አሞግሰዋል። በዓለማችን ካሉ ግዙፍ የጭነት መርካቦች አንዷ የሆነችው ኤቨር ጊቭን 18,300 ኮንቴይነሮችን በሮተርዳም፣ በፊሊክስቶዌ እና በሀምቡርግ በማራገፍ አሁን ወደ ቻይና እየተጓዘች ትገኛለች። የካሳው መጠን ባይታወቅም በቦዩ ላይ ለደረሰው ጉዳት ብሎም መርከቡን ለማስለቀቅ ለተደረጉ ሥራዎች የግብፅ ባለሥልጣናት የጠየቁት 550 ሚሊዮን ዶላር በሂደት እንደተከፈለ ታውቋል። | ኤቨር ጊቭን፡ የሱዩዝ ቦይን ዘግታ ለቀናት የቆየችው መርከብ ከወራት በኋላ ወደ አገሯ ተመለሰች በመጋቢት ወር የሱዩዝ ቦይን ዘግታ ለቀናት የቆየችው ኤቨር ጊቭን የዕቃ መጫኛ መርከብ ባለፍነው ሳምንት ያለምንም ችግር ዘግታው በቆየችው የሱዩዝ ቦይ በኩል ወደ አገሯ ተመለሰች። መርከቧ ከሜድትራኒያን ወደ ቀይ ባሕር ከሚጓዙ መርከቦች መካከል እንደነበረች እና በአውሮፓ ጭነቷን በማራገፍ አሁን በድጋሚ ወደ እስያ እያመራች መሆኗን የሱዩዝ ካናል ባለሥልጣን አስታውቋል። ኤቨር ጊቭን በቦዩ ውስጥ መንቀሳቀስ አቅቷት በቆየችባቸው ቀናት አንድ ሰው ለሞት የዳረገ ከፍተኛ ርብርብ ከተደረገ በኋላ ነበር ከቦዩ የተላቀቀችው። የግብፅ ባለሥልጣናት ቦዩ በመዘጋቱ የደረሰባቸው ካሳ እንዲከፈላቸው መጠየቃቸውን ተከትሎ ኤቨር ጊቭን ለተጨማሪ ሦስት ወራት በኢስማሊያ ቦይ አካባቢ ቆይታለች። መርከቧ ለሦስት ተጨማሪ ወራት በኢስማሊያ ቦይ እንድትቆይ የተደረገችው በግብፅ እና ኤቨር ጊቭን ባለቤቶች መካከል የካሳ ስምምነት እስከሚደረግ ነበር። የሱዩዝ ቦይ ባለሥልጣን በትዊተር ገጹ እንዳስታወቀው ኤቨር ጊቭን በሁለት ጀልባዎች እና በተቋሙ ከፍተኛ መሪዎች ታጅባ ቦዩን በማቋረጥ ወደ አገሯ ተመልሳለች። መርከቧ ትናንት አርብ ከሰሜን ወደ ደቡብ ከተጓዙት 26 መርከቦች መካከል አንዷ ስትሆን ሌሎች 36 መርከቦች በተቃራኒ አቅጣጫ ሲጓዙ ነበር። የስዊዝ ካናል ባለሥልጣንም "ምሥራቁን ከምዕራብ ጋር የሚያገናኘው በጣም አጭር እና ፈጣን መንገድ" በማለት መተላለፊያውን አሞግሰዋል። በዓለማችን ካሉ ግዙፍ የጭነት መርካቦች አንዷ የሆነችው ኤቨር ጊቭን 18,300 ኮንቴይነሮችን በሮተርዳም፣ በፊሊክስቶዌ እና በሀምቡርግ በማራገፍ አሁን ወደ ቻይና እየተጓዘች ትገኛለች። የካሳው መጠን ባይታወቅም በቦዩ ላይ ለደረሰው ጉዳት ብሎም መርከቡን ለማስለቀቅ ለተደረጉ ሥራዎች የግብፅ ባለሥልጣናት የጠየቁት 550 ሚሊዮን ዶላር በሂደት እንደተከፈለ ታውቋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-58290762 |
2health
| በሙቀት ወቅት እንዴት ጥሩ እንቅልፍ መተኛት እንችላለን? | ምንም እንኳን ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን የዝናብ ወቅት ቢሆንም፣ በመካከለኛው ምሥራቅ፣ በአውሮፓ እና በአሜሪካ ሙቀቱ የሚበረታበት ጊዜ ነው። በተጨማሪም ምድራችን በገጠማት የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በየትኛውም ወቅት የሚያጋጥመው ሙቀት በእጅጉ ከፍ ብሏል። በዚህም ሳቢያ ዝናብ ወቅቱን ጠብቆ መዝነብ ትቷል። ሙቀትም እየበረታ ነው። ተመራማሪዎችም የዓለም ሙቀት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እንደሚጨምር ባለፈው ዓመት ተንብየዋል። ይህ ሙቀት የተያዘውን ዓመት ጨምሮ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት እንደሚበረታ ነው ተመራማሪዎቹ የተናገሩት። ለዚህም ዋነኛው ምክንያት የአየር ንብረት ለውጥ ነው ይላሉ። ሙቀት ጨምሯል። አውሮፓ በሙቀት እየተለበለበች ነው። የሙቀት መጨመርን ተከትሎ የጤና ባለሥልጣናት ሕዝባቸውን እያስጠነቀቁ ነው። ኢትዮጵያም በአንዳንድ አካባቢዎች ከፍተኛ ሙቀትን እያስተናገደች ነው። ከሳምንታት በፊት የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የሙቀት መጠን በመጨመሩ ነዋሪዎች የሰውነታቸውን ሙቀት ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ እንዲቆጣጠሩ አሳስቦ ነበር። ሙቀት ቀልድ አይደለም። እንዲህ ዓይነት ሙቀት ሲያጋጥም በርካቶች ከሚቸገሩበት አንዱ ሌሊቱን በጥሩ እንቅልፍ ማሳለፍ ነው። ከቀኑ ይልቅ ሌሊቱ ይረዝማል። እንቅልፍ ይታወካል። ይህ ብቻም ሳይሆን ለእንቅልፍ ጋደም ከማለትዎ በፊት የሰውነትዎን ሙቀት በንቃት ካልተከታተሉ ሰላም ብለው በተኙበት በዚያው ማሸለብን ሊያስከትል ይችላል። ለመሆኑ በሙቀት ወቅት እንዴት ጥሩ እንቅልፍ መተኛት እንችላለን? የተወሰኑ ዘዴዎችን እንጠቁማችሁ። የሙቀት የአየር ጠባይ ቀን ላይ ድካም እንዲሰማን ያደርጋል። ምክንያቱም የሰውነታችንን ሙቀት ለመቆጣጠር ብዙ ኃይል የምንጠቀመው ቀን ላይ ስለሆነ ነው። በመሆኑም ሌሊት ላይ ለመተኛት የሚቸገሩ ከሆነ ቀን ላይ ድካም ቢሰማዎትም ለአፍታም ቢሆን ባያሸልቡ ይመከራል። በሙቀት ወቅት እንቅልፍ ከሌላው ጊዜ በበለጠ ውድ ነው። በመሆኑም እንቅልፍዎን ለሌሊት መቆጠብ ያስፈልጋል። የሙቀት የአየር ጠባይ የወትሮውን ልምዳችንን ሊለውጠው ይችላል። ግን አትለውጡት። ከቀየራችሁት እንቅልፋችሁን ሊረብሸው ይችላል። ወደ አልጋዎ ከመሄድዎ በፊት የሚያደርጓቸውን የተለመዱ ተግባራትዎን ያከናውኑ። የሚሰሩት ሥራም ካለ እንዲሁ። መኝታ ክፍልዎ ቀዝቃዛ መሆኑን ያረጋግጡ። ቀን ላይ የሞቀው አየር እንዳይገባ በቤትዎ በፀሐይ አቅጣጫ ያሉትን መስኮቶች መዝጋትዎን ያረጋግጡ። ከዚያም ወደ መኝታዎ ከመሄድዎ በፊት ነፋሻ አየር እንዲገባ ሁሉንም መስኮቶች ይክፈቷቸው። በቀዝቃዛ ወቅት የሚደራርቧቸውን አንሶላና ብርድ ልብሶች ይቀንሱ። ነገር ግን ስስ አንሶላ ማንጠፍዎን አይዘንጉ። ስስ እና ከጥጥ የተሰራ አንሶላ ላብን የመምጠጥ ኃይል አለው። ከጥጥ የተሰሩ አልባሳት ምንም እንኳን ሙቀት የሚሰጡ ቢሆንም ሌሊት ላይ የሰውነታችን ሙቀት ስለሚቀንስ ብዙም አያሳስብም። አንዳንዴ ብርድ ተሰምቶን ከእንቅልፋችን የምንነቃው በምሽት የሰውነታችን ሙቀት ስለሚቀንስ ነው። በሞቃታማ የአየር ጠባይ በተለይም ወበቅ በሚኖርበት ጊዜ ትንንሽ የቤት ማቀዝቀሻዎች (ፋን) መጠቀም አስፈላጊ ነው። ምክንያቱም ላብ እንዲተን በማድረግ የሰውነት ውስጣዊ የሙቀት መጠንን ለመቆጣጠር ቀላል ያደርገዋል። ማቀዝቀዣ ግን ሁሉም ሰው ጋር ላይኖር ይችላል። ከሌለ በምትኩ የሙቅ ውሃ መያዣ ኮዳ ውስጥ ቀዝቀዛ ፈሳሽ በመሙላት ለመያዝ ይሞክሩ። ከዚህም ሌላ ካልሲዎን አቀዝቅዘው ያድርጉት። እግርዎን ማቀዝቀዝ የቆዳዎንና የሰውነትዎን አጠቃላይ የሙቀት መጠን ለመቀነስ ይረዳል። በሙቀት ወቅት ቀን ላይ በቂ ውሃ መጠጣት የሚመከር ሲሆን ወደ መኝታዎ ከመሄድዎ በፊት ግን ብዙ ውሃ መጠጣትን ያስወግዱ። ምን አልባት ሌሊት የውሃ ጥም እንዲቀሰቅስዎ ላይፈልጉ ይችላሉ። ነገር ግን ከመኝታዎ እየተነሱ ወደ መጸዳጃ ቤት መመላለስ ደግሞ አይፈልጉም። በመሆኑም እንቅልፍዎ እንዳይረበሽ ይህንን ልማድ ያስወግዱ። እዚህ ላይ ግን ችላ ልንለው የማይገባው ጉዳይ የምንጠጣውን ነገር ነው። ለስላሳ መጠጦች አይጎንጩ። አብዛኞቹ ለስላሳ መጠጦች በውስጣቸው ኅብለ ሰረሰር የተባለውን የነርቭ ሥርዓታችንን የሚያነቃቃ 'ካፌን' የተባለ ንጥረ ነገር ስላላቸው ንቁ እንድንሆን ያደርጉናል። ብዙ የአልኮል መጠጦች መውሰድም አይመከርም። በርካታ ሰዎች የአየር ጠባዩ ሞቃታማ ሲሆን ብዙ የአልኮል መጠጦችን ይወስዳሉ። ምንም እንኳን የአልኮል መጠጦች ለመተኛት ሊረዱ ቢችሉም ቀድመን እንድንነቃና የማያረካ እንቅልፍ እንድንተኛ ያደርጉናል። ሙቀት ሰውነታችን ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድረው እንዴት ነው? የመጀመሪያው ድርቀት ወይም በሰውነት ውስጥ ያለ ፈሳሽ ማነስ እንዲፈጠር በማድረግ ነው። ይህ እንዳይሆን በሽንት፣ በላብና በትንፋሽ የሚወጣውን ፈሳሽ ለመተካት በቂ ውሃ መጠጣት ያስፈልጋል። ሌላኛው ተፅዕኖው ከመጠን በላይ የሆነ ሙቀት ማስከተል ነው። ይህ በተለይ የልብ ወይም የአተነፋፈስ ችግር ላለባቸው የተለየ ችግር ሊሆን ይችላል። ምልክቶቹ ራስ ምታት፣ የቆዳ መደንዘዝ እና ማቅለሽለሽ ናቸው። ከፍተኛ የሆነ ድካምም በሙቀት ወቅት የሚያጋጥመን ሌላኛው ችግር ነው። ይህ የሚከሰተው ሰውነታችን በቂ ውሃ ወይም ጨው ማጣት ሲጀምር ነው። ራስን የመሳት ስሜት፣ አቅም ማጣት ወይም የጡንቻ መሸማቀቅ የተወሰኑ ምልክቶቹ ናቸው። የሙቀት ስትሮክ (ሂት ስትሮክ) በሙቀት ወቅት ሰውነታችን የሚያጋጥመው እክል ነው። ሂት ስትሮክ አጋጥሟል የሚባለው የሰውነታችን ሙቀት 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ወይም ከዚያ በላይ ሲሆን ነው። ምልክቶቹ በሙቀት ሳቢያ ከሚከሰት ድካም ጋር ይመሳሰላሉ። ነገር ግን ይህ ያጋጠመው ሰው ራሱን ላያውቅ ይችላል፣ ደረቅ ቆዳ ይኖረዋል እና ላብ ከሰውነቱ መውጣትም ይቆማል። ለመተኛት እየታገሉ ከሆነ ይነሱና የሚያረጋጋዎትን ነገር ያድርጉ ። ለማንበብ፣ ለመጻፍ አሊያም ልብስዎን ለማጠፍ ይሞክሩ። ስልክዎን እያዩ አሊያም የቪዲዮ ጌሞችን እየተጫወቱ አለመሆኑን ግን ያረጋግጡ። ምክንያቱም በስልካችን የምናየው ብርሃን የእንቅልፍ ስሜት እንዲቀንስ ያደርጋል። ጨዋታውም ቢሆን ጭራሽኑ እንድንነቃቃ ነው የሚያደርገን። ከዚያም ሥራዎትን ጨርሰው እንቅልፍዎ ሲመጣ ወደ አልጋዎ ይመለሱ። ልጆች ብዙውን ጊዜ ጥሩ እንቅልፍ ይወስዳቸዋል፤ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ በቤተሰብ ስሜትና በዕለተ ተዕለት ለውጦች ምክንያት ስሜታቸው ሊቀየር ይችላል። በመሆኑም የተለመደውን የመኝታና የመታጠቢያ ጊዜያቸውን አያሳልፉ። ሙቀት ነው ብለው ይዘዋቸው ለመውጣት አይሞክሩ። ወደ መኝታቸው ከመሄዳቸው በፊትም ለብ ባለ ውሃ ማጠብ ይመከራል። ውሃው ግን ቀዝቃዛ መሆን የለበትም። ምክንያቱም ሰውነት ራሱን የሚያሞቀው የደም ዝውውርን በመጨመር ስለሆነ ቀዝቃዛ ውሃ የደም ዝውውር እንዲጨምር ያደርጋል። ሕጻናት እየታጠቡበት ያለው ውሃ ቀዝቃዛ አሊያም ሙቅ መሆኑን አይነግሯችሁም። በመሆኑም የሙቀት መጠኑን መቆጣጠር አስፈላጊ ነው። ሕጻናት ጥሩ እንቅልፍ የሚወስዳቸው የክፍላቸው የሙቀት መጠን ከ16 እስከ 20 ዲግሪ ሴልሺየስ ሲሆን በመሆኑ ከተቻለ ሕጻናት የሚተኙበት ቦታ የሙቀት መለኪያ (ቴርሞሜትር) መግጠም መልካም ነው። አብዛኞቻችን ሥራችንን በአግባቡ ለመስራት በእያንዳንዱ ምሽት ለሰባት ወይም ለስምንት ሰዓታት ጥሩ እንቅልፍ መተኛት እንፈልጋለን። ቢሆንም ግን ጥቂት ሰዓት ብቻ ነው የተኛሁት ብለው አይጨነቁ። በርካታ ሰዎች አንድ ሌሊት ሳይተኙ አሊያም የተረበሸ ሌሊት አሳልፈው ሥራቸውን በሚገባ ይከውናሉ። ምንም እንኳን ከወትሮው በተለየ ደጋግሞ ማዛጋት ቢኖርም ካልተደጋገመ ምንም አትሆኑምና አትጨነቁ። እነዚህ የጤና ምክሮች በሎውቦሮው ዩኒቨርሲቲ የክሊኒካል እንቅልፍ ምርምር ክፍል የቀድሞ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ኬቨን ሞርጋን እና የእንቅልፍ የምክር አገልግሎት ባልደረባ ሊዛ አርቲስ በሰጡት ገለጻ የተመሠረቱ ናቸው። ጽሑፉ ለመጀመሪያ የታተመው ሐምሌ 2019 ነው። | በሙቀት ወቅት እንዴት ጥሩ እንቅልፍ መተኛት እንችላለን? ምንም እንኳን ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን የዝናብ ወቅት ቢሆንም፣ በመካከለኛው ምሥራቅ፣ በአውሮፓ እና በአሜሪካ ሙቀቱ የሚበረታበት ጊዜ ነው። በተጨማሪም ምድራችን በገጠማት የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በየትኛውም ወቅት የሚያጋጥመው ሙቀት በእጅጉ ከፍ ብሏል። በዚህም ሳቢያ ዝናብ ወቅቱን ጠብቆ መዝነብ ትቷል። ሙቀትም እየበረታ ነው። ተመራማሪዎችም የዓለም ሙቀት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እንደሚጨምር ባለፈው ዓመት ተንብየዋል። ይህ ሙቀት የተያዘውን ዓመት ጨምሮ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት እንደሚበረታ ነው ተመራማሪዎቹ የተናገሩት። ለዚህም ዋነኛው ምክንያት የአየር ንብረት ለውጥ ነው ይላሉ። ሙቀት ጨምሯል። አውሮፓ በሙቀት እየተለበለበች ነው። የሙቀት መጨመርን ተከትሎ የጤና ባለሥልጣናት ሕዝባቸውን እያስጠነቀቁ ነው። ኢትዮጵያም በአንዳንድ አካባቢዎች ከፍተኛ ሙቀትን እያስተናገደች ነው። ከሳምንታት በፊት የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የሙቀት መጠን በመጨመሩ ነዋሪዎች የሰውነታቸውን ሙቀት ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ እንዲቆጣጠሩ አሳስቦ ነበር። ሙቀት ቀልድ አይደለም። እንዲህ ዓይነት ሙቀት ሲያጋጥም በርካቶች ከሚቸገሩበት አንዱ ሌሊቱን በጥሩ እንቅልፍ ማሳለፍ ነው። ከቀኑ ይልቅ ሌሊቱ ይረዝማል። እንቅልፍ ይታወካል። ይህ ብቻም ሳይሆን ለእንቅልፍ ጋደም ከማለትዎ በፊት የሰውነትዎን ሙቀት በንቃት ካልተከታተሉ ሰላም ብለው በተኙበት በዚያው ማሸለብን ሊያስከትል ይችላል። ለመሆኑ በሙቀት ወቅት እንዴት ጥሩ እንቅልፍ መተኛት እንችላለን? የተወሰኑ ዘዴዎችን እንጠቁማችሁ። የሙቀት የአየር ጠባይ ቀን ላይ ድካም እንዲሰማን ያደርጋል። ምክንያቱም የሰውነታችንን ሙቀት ለመቆጣጠር ብዙ ኃይል የምንጠቀመው ቀን ላይ ስለሆነ ነው። በመሆኑም ሌሊት ላይ ለመተኛት የሚቸገሩ ከሆነ ቀን ላይ ድካም ቢሰማዎትም ለአፍታም ቢሆን ባያሸልቡ ይመከራል። በሙቀት ወቅት እንቅልፍ ከሌላው ጊዜ በበለጠ ውድ ነው። በመሆኑም እንቅልፍዎን ለሌሊት መቆጠብ ያስፈልጋል። የሙቀት የአየር ጠባይ የወትሮውን ልምዳችንን ሊለውጠው ይችላል። ግን አትለውጡት። ከቀየራችሁት እንቅልፋችሁን ሊረብሸው ይችላል። ወደ አልጋዎ ከመሄድዎ በፊት የሚያደርጓቸውን የተለመዱ ተግባራትዎን ያከናውኑ። የሚሰሩት ሥራም ካለ እንዲሁ። መኝታ ክፍልዎ ቀዝቃዛ መሆኑን ያረጋግጡ። ቀን ላይ የሞቀው አየር እንዳይገባ በቤትዎ በፀሐይ አቅጣጫ ያሉትን መስኮቶች መዝጋትዎን ያረጋግጡ። ከዚያም ወደ መኝታዎ ከመሄድዎ በፊት ነፋሻ አየር እንዲገባ ሁሉንም መስኮቶች ይክፈቷቸው። በቀዝቃዛ ወቅት የሚደራርቧቸውን አንሶላና ብርድ ልብሶች ይቀንሱ። ነገር ግን ስስ አንሶላ ማንጠፍዎን አይዘንጉ። ስስ እና ከጥጥ የተሰራ አንሶላ ላብን የመምጠጥ ኃይል አለው። ከጥጥ የተሰሩ አልባሳት ምንም እንኳን ሙቀት የሚሰጡ ቢሆንም ሌሊት ላይ የሰውነታችን ሙቀት ስለሚቀንስ ብዙም አያሳስብም። አንዳንዴ ብርድ ተሰምቶን ከእንቅልፋችን የምንነቃው በምሽት የሰውነታችን ሙቀት ስለሚቀንስ ነው። በሞቃታማ የአየር ጠባይ በተለይም ወበቅ በሚኖርበት ጊዜ ትንንሽ የቤት ማቀዝቀሻዎች (ፋን) መጠቀም አስፈላጊ ነው። ምክንያቱም ላብ እንዲተን በማድረግ የሰውነት ውስጣዊ የሙቀት መጠንን ለመቆጣጠር ቀላል ያደርገዋል። ማቀዝቀዣ ግን ሁሉም ሰው ጋር ላይኖር ይችላል። ከሌለ በምትኩ የሙቅ ውሃ መያዣ ኮዳ ውስጥ ቀዝቀዛ ፈሳሽ በመሙላት ለመያዝ ይሞክሩ። ከዚህም ሌላ ካልሲዎን አቀዝቅዘው ያድርጉት። እግርዎን ማቀዝቀዝ የቆዳዎንና የሰውነትዎን አጠቃላይ የሙቀት መጠን ለመቀነስ ይረዳል። በሙቀት ወቅት ቀን ላይ በቂ ውሃ መጠጣት የሚመከር ሲሆን ወደ መኝታዎ ከመሄድዎ በፊት ግን ብዙ ውሃ መጠጣትን ያስወግዱ። ምን አልባት ሌሊት የውሃ ጥም እንዲቀሰቅስዎ ላይፈልጉ ይችላሉ። ነገር ግን ከመኝታዎ እየተነሱ ወደ መጸዳጃ ቤት መመላለስ ደግሞ አይፈልጉም። በመሆኑም እንቅልፍዎ እንዳይረበሽ ይህንን ልማድ ያስወግዱ። እዚህ ላይ ግን ችላ ልንለው የማይገባው ጉዳይ የምንጠጣውን ነገር ነው። ለስላሳ መጠጦች አይጎንጩ። አብዛኞቹ ለስላሳ መጠጦች በውስጣቸው ኅብለ ሰረሰር የተባለውን የነርቭ ሥርዓታችንን የሚያነቃቃ 'ካፌን' የተባለ ንጥረ ነገር ስላላቸው ንቁ እንድንሆን ያደርጉናል። ብዙ የአልኮል መጠጦች መውሰድም አይመከርም። በርካታ ሰዎች የአየር ጠባዩ ሞቃታማ ሲሆን ብዙ የአልኮል መጠጦችን ይወስዳሉ። ምንም እንኳን የአልኮል መጠጦች ለመተኛት ሊረዱ ቢችሉም ቀድመን እንድንነቃና የማያረካ እንቅልፍ እንድንተኛ ያደርጉናል። ሙቀት ሰውነታችን ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድረው እንዴት ነው? የመጀመሪያው ድርቀት ወይም በሰውነት ውስጥ ያለ ፈሳሽ ማነስ እንዲፈጠር በማድረግ ነው። ይህ እንዳይሆን በሽንት፣ በላብና በትንፋሽ የሚወጣውን ፈሳሽ ለመተካት በቂ ውሃ መጠጣት ያስፈልጋል። ሌላኛው ተፅዕኖው ከመጠን በላይ የሆነ ሙቀት ማስከተል ነው። ይህ በተለይ የልብ ወይም የአተነፋፈስ ችግር ላለባቸው የተለየ ችግር ሊሆን ይችላል። ምልክቶቹ ራስ ምታት፣ የቆዳ መደንዘዝ እና ማቅለሽለሽ ናቸው። ከፍተኛ የሆነ ድካምም በሙቀት ወቅት የሚያጋጥመን ሌላኛው ችግር ነው። ይህ የሚከሰተው ሰውነታችን በቂ ውሃ ወይም ጨው ማጣት ሲጀምር ነው። ራስን የመሳት ስሜት፣ አቅም ማጣት ወይም የጡንቻ መሸማቀቅ የተወሰኑ ምልክቶቹ ናቸው። የሙቀት ስትሮክ (ሂት ስትሮክ) በሙቀት ወቅት ሰውነታችን የሚያጋጥመው እክል ነው። ሂት ስትሮክ አጋጥሟል የሚባለው የሰውነታችን ሙቀት 40 ዲግሪ ሴልሽየስ ወይም ከዚያ በላይ ሲሆን ነው። ምልክቶቹ በሙቀት ሳቢያ ከሚከሰት ድካም ጋር ይመሳሰላሉ። ነገር ግን ይህ ያጋጠመው ሰው ራሱን ላያውቅ ይችላል፣ ደረቅ ቆዳ ይኖረዋል እና ላብ ከሰውነቱ መውጣትም ይቆማል። ለመተኛት እየታገሉ ከሆነ ይነሱና የሚያረጋጋዎትን ነገር ያድርጉ ። ለማንበብ፣ ለመጻፍ አሊያም ልብስዎን ለማጠፍ ይሞክሩ። ስልክዎን እያዩ አሊያም የቪዲዮ ጌሞችን እየተጫወቱ አለመሆኑን ግን ያረጋግጡ። ምክንያቱም በስልካችን የምናየው ብርሃን የእንቅልፍ ስሜት እንዲቀንስ ያደርጋል። ጨዋታውም ቢሆን ጭራሽኑ እንድንነቃቃ ነው የሚያደርገን። ከዚያም ሥራዎትን ጨርሰው እንቅልፍዎ ሲመጣ ወደ አልጋዎ ይመለሱ። ልጆች ብዙውን ጊዜ ጥሩ እንቅልፍ ይወስዳቸዋል፤ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ በቤተሰብ ስሜትና በዕለተ ተዕለት ለውጦች ምክንያት ስሜታቸው ሊቀየር ይችላል። በመሆኑም የተለመደውን የመኝታና የመታጠቢያ ጊዜያቸውን አያሳልፉ። ሙቀት ነው ብለው ይዘዋቸው ለመውጣት አይሞክሩ። ወደ መኝታቸው ከመሄዳቸው በፊትም ለብ ባለ ውሃ ማጠብ ይመከራል። ውሃው ግን ቀዝቃዛ መሆን የለበትም። ምክንያቱም ሰውነት ራሱን የሚያሞቀው የደም ዝውውርን በመጨመር ስለሆነ ቀዝቃዛ ውሃ የደም ዝውውር እንዲጨምር ያደርጋል። ሕጻናት እየታጠቡበት ያለው ውሃ ቀዝቃዛ አሊያም ሙቅ መሆኑን አይነግሯችሁም። በመሆኑም የሙቀት መጠኑን መቆጣጠር አስፈላጊ ነው። ሕጻናት ጥሩ እንቅልፍ የሚወስዳቸው የክፍላቸው የሙቀት መጠን ከ16 እስከ 20 ዲግሪ ሴልሺየስ ሲሆን በመሆኑ ከተቻለ ሕጻናት የሚተኙበት ቦታ የሙቀት መለኪያ (ቴርሞሜትር) መግጠም መልካም ነው። አብዛኞቻችን ሥራችንን በአግባቡ ለመስራት በእያንዳንዱ ምሽት ለሰባት ወይም ለስምንት ሰዓታት ጥሩ እንቅልፍ መተኛት እንፈልጋለን። ቢሆንም ግን ጥቂት ሰዓት ብቻ ነው የተኛሁት ብለው አይጨነቁ። በርካታ ሰዎች አንድ ሌሊት ሳይተኙ አሊያም የተረበሸ ሌሊት አሳልፈው ሥራቸውን በሚገባ ይከውናሉ። ምንም እንኳን ከወትሮው በተለየ ደጋግሞ ማዛጋት ቢኖርም ካልተደጋገመ ምንም አትሆኑምና አትጨነቁ። እነዚህ የጤና ምክሮች በሎውቦሮው ዩኒቨርሲቲ የክሊኒካል እንቅልፍ ምርምር ክፍል የቀድሞ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ኬቨን ሞርጋን እና የእንቅልፍ የምክር አገልግሎት ባልደረባ ሊዛ አርቲስ በሰጡት ገለጻ የተመሠረቱ ናቸው። ጽሑፉ ለመጀመሪያ የታተመው ሐምሌ 2019 ነው። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cv2r4pxlk29o |
2health
| ስዊድናዊቷ ነርስ ደሴት ለብቻዋ ተለቆላት 60 ፊልሞችን ልትመለከት ነው | ስዊድናዊቷ ነርስ ደሴት ለብቻዋ ተለቆላት 60 ፊልሞችን ልትመለከት ነው፡፡ ነርሷ ይህን ዕድል ያሸነፈችው በስዊድኗ 2ኛ ከተማ በጎተቦሬ (ጉተንበርግ) የሚደረገውን የፊልም ፌስቲቫል በማሸነፏ ነው፡፡ ሊዛ ኤርኖት ይህንን ውድድር ያሸነፈችው ከ12ሺህ የፊልም አፍቃሪዎች መሀል ተወዳድራ ነው፡፡ ተወዳዳሪዎቹ ይህን ዕድል ያመለከቱት ከስዊድን ብቻ ሳይሆን ከመላው ዓለም አመልክተው ነው፡፡ በፌስቲቫሉ የሚቀርቡት 60 ፊልሞች ናቸው፡፡ ነርሲቱ ፊልሞቹን የምትመለከተው ከስዊድን ጠረፍ በምትገኝ ደሴት ቁጭ ብላ ላይትሐውስ ውስጥ በመቀመጥ ነው፡፡ በኮቪድ ወረርሽኝ ወቅት ነርሷ በሆስፒታል ውስጥ የኮቪድ ታማሚዎችን ስትንከባከብ የነበረች ጀግኒት እንደነበረች ተነግሯል፡፡ "አሁን ብቻዬን ከሰዎች ገለል ብዬ መዝናናት እፈልጋለሁ፡፡ የተለየ ሁኔታ ውስጥ መሆን ነው የምሻው" ስትል ተናግራለች፡፡ የፌስቲቫሉ አሰናጆች ወትሮ ብዙ ሺህ ሕዝብ የሚገኝበትን ይህን የፊልም ትእይንት በወረርሽኙ ምክንያት ሊያካሄዱት አልቻሉም፡፡ በሲኒማ ቤቶች የሚታዩ ፊልሞችም አይኖሩም፡፡ ከዚያ ይልቅ ሁሉም የፊልም ፌስቲቫሉ ኩነቶች በቀጥታ በበይነ መረብ ይተላለፋሉ ብለዋል፡፡ የዚህ ፌስቲቫል አሰናጆች ላለፉት ወራት አንድ እውነተኛ የፊልም ወዳጅ ሰው ሲያፈላልጉ ነበር፡፡ አሸናፊው ሰው ብቻውን አንድ ደሴት ላይ ቁጭ ብሎ 60 ፊልሞችን ለመመልከት በሥነ ልቡና እና በስሜት ዝግጁ የሆነ መሆን ይኖርበታል ብለው ነበር፡፡ ነርስ ሊዛ ኤንሮት የኮቪድ ታማሚዎችን በመንከባከብ ጉልበቷ እንደተሟጠጠና አሁን ግን ለአንድ ሳምንት እፎይ ማለት እንደምትሻ ለቢቢሲ የስቶክሆልም ዘጋቢያችን ማዲ ሳቪጅ ነግራታለች፡፡ ነርሲቱ ፓተር ኖስተር ላይትሐውስ ሐምነስካር በምትባል ደሴት የምትቆየው ያለምንም ቴክኖሎጂያዊ ቁሳቁሶች ነው፡፡ ስልክ፣ ኮምፒውተር፣ መጻሕፍትንም ሆነ ሌላ ጊዜ ለማሳለፍያ የሚሆን ነገር መያዝ አይፈቀድላትም፡፡ ‹‹ንፋሱ፣ ባሕሩ እና በደሴት ብቻዬን መሆን ይህ ሁሉ እጅግ ልዩ ስሜት ውስጥ የሚከተኝ ነው የሚሆነው›› ብላለች ነርስ ሊዛ፡፡ ሊዛ በብዛት የኖረችው ስኮቭዴ በምትባል የጎተቦርግ ምሥራቅ የምትገኝ ትንሽዬ ከተማ ውስጥ ነው፡፡ በዚች ትንሽ ከተማ ውስጥ የአንድ የፊልም ወዳጆች ማኅበርም አባል ናት፡፡ ትናንት ቅዳሜ ሊዛ ወደ ደሴቲቱ በታንኳ የተወሰደች ሲሆን ይቺ ደሴት በስዊድን ጠረፍ ከማርስትራንድ ቅርብ የምትገኝ ናት፡፡ ሊዛ በደሴቲቱ የምታሳልፈው ጊዜ በቪዲዮ ለዓለም ይተላለፋል፡፡ የዚህ ታላቅ የፊልም ፌስቲቫል ዋና አሰናጅ ሚሪያ ዌስተርን ይህን ልዩ ዕድል ለአንዲት የኮቪድ ጀግና መስጠታችን የሚገባ ብቻም ሳይሆን ለኛም ትልቅ ደስታን ይፈጥርልናል ብለዋል፡፡ | ስዊድናዊቷ ነርስ ደሴት ለብቻዋ ተለቆላት 60 ፊልሞችን ልትመለከት ነው ስዊድናዊቷ ነርስ ደሴት ለብቻዋ ተለቆላት 60 ፊልሞችን ልትመለከት ነው፡፡ ነርሷ ይህን ዕድል ያሸነፈችው በስዊድኗ 2ኛ ከተማ በጎተቦሬ (ጉተንበርግ) የሚደረገውን የፊልም ፌስቲቫል በማሸነፏ ነው፡፡ ሊዛ ኤርኖት ይህንን ውድድር ያሸነፈችው ከ12ሺህ የፊልም አፍቃሪዎች መሀል ተወዳድራ ነው፡፡ ተወዳዳሪዎቹ ይህን ዕድል ያመለከቱት ከስዊድን ብቻ ሳይሆን ከመላው ዓለም አመልክተው ነው፡፡ በፌስቲቫሉ የሚቀርቡት 60 ፊልሞች ናቸው፡፡ ነርሲቱ ፊልሞቹን የምትመለከተው ከስዊድን ጠረፍ በምትገኝ ደሴት ቁጭ ብላ ላይትሐውስ ውስጥ በመቀመጥ ነው፡፡ በኮቪድ ወረርሽኝ ወቅት ነርሷ በሆስፒታል ውስጥ የኮቪድ ታማሚዎችን ስትንከባከብ የነበረች ጀግኒት እንደነበረች ተነግሯል፡፡ "አሁን ብቻዬን ከሰዎች ገለል ብዬ መዝናናት እፈልጋለሁ፡፡ የተለየ ሁኔታ ውስጥ መሆን ነው የምሻው" ስትል ተናግራለች፡፡ የፌስቲቫሉ አሰናጆች ወትሮ ብዙ ሺህ ሕዝብ የሚገኝበትን ይህን የፊልም ትእይንት በወረርሽኙ ምክንያት ሊያካሄዱት አልቻሉም፡፡ በሲኒማ ቤቶች የሚታዩ ፊልሞችም አይኖሩም፡፡ ከዚያ ይልቅ ሁሉም የፊልም ፌስቲቫሉ ኩነቶች በቀጥታ በበይነ መረብ ይተላለፋሉ ብለዋል፡፡ የዚህ ፌስቲቫል አሰናጆች ላለፉት ወራት አንድ እውነተኛ የፊልም ወዳጅ ሰው ሲያፈላልጉ ነበር፡፡ አሸናፊው ሰው ብቻውን አንድ ደሴት ላይ ቁጭ ብሎ 60 ፊልሞችን ለመመልከት በሥነ ልቡና እና በስሜት ዝግጁ የሆነ መሆን ይኖርበታል ብለው ነበር፡፡ ነርስ ሊዛ ኤንሮት የኮቪድ ታማሚዎችን በመንከባከብ ጉልበቷ እንደተሟጠጠና አሁን ግን ለአንድ ሳምንት እፎይ ማለት እንደምትሻ ለቢቢሲ የስቶክሆልም ዘጋቢያችን ማዲ ሳቪጅ ነግራታለች፡፡ ነርሲቱ ፓተር ኖስተር ላይትሐውስ ሐምነስካር በምትባል ደሴት የምትቆየው ያለምንም ቴክኖሎጂያዊ ቁሳቁሶች ነው፡፡ ስልክ፣ ኮምፒውተር፣ መጻሕፍትንም ሆነ ሌላ ጊዜ ለማሳለፍያ የሚሆን ነገር መያዝ አይፈቀድላትም፡፡ ‹‹ንፋሱ፣ ባሕሩ እና በደሴት ብቻዬን መሆን ይህ ሁሉ እጅግ ልዩ ስሜት ውስጥ የሚከተኝ ነው የሚሆነው›› ብላለች ነርስ ሊዛ፡፡ ሊዛ በብዛት የኖረችው ስኮቭዴ በምትባል የጎተቦርግ ምሥራቅ የምትገኝ ትንሽዬ ከተማ ውስጥ ነው፡፡ በዚች ትንሽ ከተማ ውስጥ የአንድ የፊልም ወዳጆች ማኅበርም አባል ናት፡፡ ትናንት ቅዳሜ ሊዛ ወደ ደሴቲቱ በታንኳ የተወሰደች ሲሆን ይቺ ደሴት በስዊድን ጠረፍ ከማርስትራንድ ቅርብ የምትገኝ ናት፡፡ ሊዛ በደሴቲቱ የምታሳልፈው ጊዜ በቪዲዮ ለዓለም ይተላለፋል፡፡ የዚህ ታላቅ የፊልም ፌስቲቫል ዋና አሰናጅ ሚሪያ ዌስተርን ይህን ልዩ ዕድል ለአንዲት የኮቪድ ጀግና መስጠታችን የሚገባ ብቻም ሳይሆን ለኛም ትልቅ ደስታን ይፈጥርልናል ብለዋል፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/news-55876982 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ በቫይረሱ የተያዘ ሰው ያልተገኘባት የሰሜን አሜሪካ ክፍል | በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአንዳንድ የካናዳ አካባቢዎች እየጨመረ ቢሆንም አንዲት በሰሜናዊ በኩል የምትገኝ አካባቢ ግን ቫይረሱ በማህበረሰቡ ውስጥ እስካሁን አልገባም። ቦታዋም 'ኑናቩት' ትባላች። ባለፈው መጋቢት ወር በርካታ የዓለማችን አገራት ድንበራቸውን እየዘጉ በነበረበት ወቅት የኑናቩት ኃላፊዎችም ቢሆኑ የሚመጣውን አደጋ በማሰብ የጥንቃቄ እርምጃ ለመውሰድ ወስነው ነበር። በዚህም ከካናዳ የሚመጡ ሰዎችን በተመለከተ ጠበቅ ያለ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን ከነዋሪዎች በስተቀር ማንም ሰው ከካናዳ በኩል ወደ ኑናቩት መግባት አይችልም ነበር። ነዋሪዎችም ቢሆኑ ከሌላ ቦታ ሲመጡ ለሁለት ሳምንታት እራሳቸውን ለይተው መቀመጥ ግዴታቸው ሲሆን መንግሥት ባዘጋጃቸው ለይቶ ማቆያዎች አልያም እንደ ዊኒፔግ፣ የሎውናይፍ፣ ኦታዋ እና ኤድመንተን ባሉ ከተሞች ውስጥ በሚገኘኑ ሆቴሎች እንዲቆዩ ይደረጋሉ። የመንግሥት ጥበቃ ኃይሎችም ቢሆኑ በለይቶ ማቆያዎቹ እና ሆቴሎቹ አካባቢ ከፍተኛ ጥበቃ ያደርጋሉ። እስካሁንም 7 ሺ የሚሆኑ የኑናቩት ነዋሪዎች ወደቤታቸው ሲመለሱ በነዚህ ማዕከላት ሁለት ሳምንታትትን አሳልፈዋል። ነገር ግን ይህ ሁሉ ስራ አልጋ በአልጋ አልነበረም። አንዳንድ ሰዎች ሕጉን በመጣሳቸው ምክንያት ለተጨማሪ ቀናት በለይቶ ማቆያ ማዕከላቱ እንዲቆዩ ተደርገዋል። በማዕከላቱ ውስጥ የነበሩ ሰዎችም የምግብ ጥራት ችግር እንዳለ ገልጸዋል። ነገር ግን በመላው ካናዳ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ሲመጣና በጎረቤት አካባቢዎች ከፍተኛ የጥንቃቄ እርምጃዎች መወሰድ ሲጀምሩ ኑናቩት ግን እንድም በቫይረሱ የተያዘ ሰው አላገኘችም። በኑናቩት ወደ 36 ሺ የሚጠጉ ሰዎች የሚኖሩ ሲሆን 25 ማህበረሰቦች ሁለት ሚሊዮን ስኩዌር ኪሎሜትር የሚሸፍን ቦታ ላይ ተበታትነው ኑሯቸውን ይገፋሉ። በሰዎቹ ተፈጥሮአዊ የአኗኗር ዘይቤ ምክንያት አካላዊ ርቀትን መጠበቅ በጣም ቀላል ነው። ነዋሪዎቹ ያን ያክል ስፋት ባለው ቦታ ላይ ሲኖሩ ከሰዎች ጋር የመገናኘት ዕድላቸው በጣም ዝቅተኛ ነው። መንግሥትም ቢሆን ነዋሪዎቹን በዓመት አንዴም ይሁን ሁለቴ የሚያገኛቸው በአውሮፕላን በመታገዝ ነው። በመስከረም ወር መጨረሻ አካባቢ ግን ማዕድን ማውጣት ላይ የተሰማሩ ሰራተኞች ከኑናቩት 160 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ አካባቢ በኮሮረናቫይረስ መያዛቸው ተዘግቦ ነበር። ነገር ግን እነዚህ ሰራተⶉች ወደ ክልሉ ባለመግባታቸው አሁንም ነዋሪዎቹ ከኮሮረናቫይረስ ነጻ ናቸው ተብሏል። ነዋሪዎቹ ወደ ማዕድን አውጪዎቹ አልያም ማዕድን አውጪዎቹ ወደ ነዋሪዎቹ ምንም አይነት ጉዞ ባለማድረጋቸው ቫይረሱ ባለበት ሊቀር ችሏል። ነገር ግን በዚህ አካባቢ እንደ ፈተና የሚቆጠረው በተገቢው መልኩ የኮሮረናቫይረስ ምርመራ ማድረግ አለመቻሉ ነው። መመርመሪያ መሳሪያዎች በአውሮፕላን በመታገዝ ተበታትነው ወደሚኖሩት ማህበረሰቦች መድረስ አለበት። በሆነ አጋጣሚ የሆነ ሰው ቫይረሱ ቢገኝበት ከሌሎች ሰዎች ጋር ንክኪ ከማድረጉ በፊት መረጃውን ለማድረስ አልያም ንክኪ ያላቸውን ሰዎች ለመለየት በጣም ከባድ ያደርገዋል። በተጨማሪም የጤና አገልግሎት መስጫዎች በአካባቢው በበቂ ሁኔታ የሉም። 'ኪኪታኒ' በመባል የሚታወቀው ሆስፒታል ለጽኑ ህሙማን የሚሆኑ 35 አልጋዎች ያሉት ሲሆን በኮቪድ-19 የተያዙ 20 ታማሚዎችን ብቻ ነው ማስተናገድ የሚችለው። ምናልባት ወረርሽኙ በዚህ አካባቢ ቢከሰት ሕክምና የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች ተገቢውን ክትትል ለማድረግና ለይቶ ማቆያዎችን ለማቋቋም አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። ይህ በንዲህ እንዳለ በኑናቩት የሚኖሩት 'ኢኑይት' በመባል የሚታወቁት ቀደምት ማህበረሰቦች ለኮሮረናቫይረስ ተጋላጭ ከሚባሉት መካከል ናቸው። በቂ ያልሆኑና ደህንነታቸው ያልተጠበቁ ቤቶች፣ በአንድ ቦታ ላይ በርካታ ሰዎች ተሰብስበው መኖር እንዲሁም የቲቢ በሽታ ስርጭት ተጋላጭ ያደርጋቸዋል። 80 በመቶ የሚሆነውን የኑናቩት ነዋሪ የሚሸፍኑት ኢኑይቶች ከሌሎች ነዋሪዎች አንጻር በቲቢ የመያዝ ዕድላቸው 300 በመቶ ከፍ ያለ ነው። ካናዳ በአጠቃላይ እንደ ሙሉ የእንቅስቃሴ ገደብ ያሉ የጥንቃቄ እርምጃዎች በመውሰዷ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ሞክራለች።ነገር ግን አሁንም ቢሆን ለመቆጣጠር አልቻለችም። እስካሁንም ድረስ 191 ሺ 732 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 9 ሺ 699 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል። ነገር ግን እንደ ኪቤክና ኦንታሪዮ ባሉ በርካታ ሰዎች በሚኖሩባቸው ግዛቶች በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ መጥቷል። በአሁኑ ሰአት 77 ሺ የሚሆኑ ካናዳውያን በየቀኑ የኮሮረናቫይረስ ምርመራ የሚደረግላቸው ሲሆን የአገሪቱ ግብ ግን በየቀኑ 200 ሺ ሰዎችን ለመመርመር ነው። | ኮሮናቫይረስ፡ በቫይረሱ የተያዘ ሰው ያልተገኘባት የሰሜን አሜሪካ ክፍል በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአንዳንድ የካናዳ አካባቢዎች እየጨመረ ቢሆንም አንዲት በሰሜናዊ በኩል የምትገኝ አካባቢ ግን ቫይረሱ በማህበረሰቡ ውስጥ እስካሁን አልገባም። ቦታዋም 'ኑናቩት' ትባላች። ባለፈው መጋቢት ወር በርካታ የዓለማችን አገራት ድንበራቸውን እየዘጉ በነበረበት ወቅት የኑናቩት ኃላፊዎችም ቢሆኑ የሚመጣውን አደጋ በማሰብ የጥንቃቄ እርምጃ ለመውሰድ ወስነው ነበር። በዚህም ከካናዳ የሚመጡ ሰዎችን በተመለከተ ጠበቅ ያለ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን ከነዋሪዎች በስተቀር ማንም ሰው ከካናዳ በኩል ወደ ኑናቩት መግባት አይችልም ነበር። ነዋሪዎችም ቢሆኑ ከሌላ ቦታ ሲመጡ ለሁለት ሳምንታት እራሳቸውን ለይተው መቀመጥ ግዴታቸው ሲሆን መንግሥት ባዘጋጃቸው ለይቶ ማቆያዎች አልያም እንደ ዊኒፔግ፣ የሎውናይፍ፣ ኦታዋ እና ኤድመንተን ባሉ ከተሞች ውስጥ በሚገኘኑ ሆቴሎች እንዲቆዩ ይደረጋሉ። የመንግሥት ጥበቃ ኃይሎችም ቢሆኑ በለይቶ ማቆያዎቹ እና ሆቴሎቹ አካባቢ ከፍተኛ ጥበቃ ያደርጋሉ። እስካሁንም 7 ሺ የሚሆኑ የኑናቩት ነዋሪዎች ወደቤታቸው ሲመለሱ በነዚህ ማዕከላት ሁለት ሳምንታትትን አሳልፈዋል። ነገር ግን ይህ ሁሉ ስራ አልጋ በአልጋ አልነበረም። አንዳንድ ሰዎች ሕጉን በመጣሳቸው ምክንያት ለተጨማሪ ቀናት በለይቶ ማቆያ ማዕከላቱ እንዲቆዩ ተደርገዋል። በማዕከላቱ ውስጥ የነበሩ ሰዎችም የምግብ ጥራት ችግር እንዳለ ገልጸዋል። ነገር ግን በመላው ካናዳ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ሲመጣና በጎረቤት አካባቢዎች ከፍተኛ የጥንቃቄ እርምጃዎች መወሰድ ሲጀምሩ ኑናቩት ግን እንድም በቫይረሱ የተያዘ ሰው አላገኘችም። በኑናቩት ወደ 36 ሺ የሚጠጉ ሰዎች የሚኖሩ ሲሆን 25 ማህበረሰቦች ሁለት ሚሊዮን ስኩዌር ኪሎሜትር የሚሸፍን ቦታ ላይ ተበታትነው ኑሯቸውን ይገፋሉ። በሰዎቹ ተፈጥሮአዊ የአኗኗር ዘይቤ ምክንያት አካላዊ ርቀትን መጠበቅ በጣም ቀላል ነው። ነዋሪዎቹ ያን ያክል ስፋት ባለው ቦታ ላይ ሲኖሩ ከሰዎች ጋር የመገናኘት ዕድላቸው በጣም ዝቅተኛ ነው። መንግሥትም ቢሆን ነዋሪዎቹን በዓመት አንዴም ይሁን ሁለቴ የሚያገኛቸው በአውሮፕላን በመታገዝ ነው። በመስከረም ወር መጨረሻ አካባቢ ግን ማዕድን ማውጣት ላይ የተሰማሩ ሰራተኞች ከኑናቩት 160 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ አካባቢ በኮሮረናቫይረስ መያዛቸው ተዘግቦ ነበር። ነገር ግን እነዚህ ሰራተⶉች ወደ ክልሉ ባለመግባታቸው አሁንም ነዋሪዎቹ ከኮሮረናቫይረስ ነጻ ናቸው ተብሏል። ነዋሪዎቹ ወደ ማዕድን አውጪዎቹ አልያም ማዕድን አውጪዎቹ ወደ ነዋሪዎቹ ምንም አይነት ጉዞ ባለማድረጋቸው ቫይረሱ ባለበት ሊቀር ችሏል። ነገር ግን በዚህ አካባቢ እንደ ፈተና የሚቆጠረው በተገቢው መልኩ የኮሮረናቫይረስ ምርመራ ማድረግ አለመቻሉ ነው። መመርመሪያ መሳሪያዎች በአውሮፕላን በመታገዝ ተበታትነው ወደሚኖሩት ማህበረሰቦች መድረስ አለበት። በሆነ አጋጣሚ የሆነ ሰው ቫይረሱ ቢገኝበት ከሌሎች ሰዎች ጋር ንክኪ ከማድረጉ በፊት መረጃውን ለማድረስ አልያም ንክኪ ያላቸውን ሰዎች ለመለየት በጣም ከባድ ያደርገዋል። በተጨማሪም የጤና አገልግሎት መስጫዎች በአካባቢው በበቂ ሁኔታ የሉም። 'ኪኪታኒ' በመባል የሚታወቀው ሆስፒታል ለጽኑ ህሙማን የሚሆኑ 35 አልጋዎች ያሉት ሲሆን በኮቪድ-19 የተያዙ 20 ታማሚዎችን ብቻ ነው ማስተናገድ የሚችለው። ምናልባት ወረርሽኙ በዚህ አካባቢ ቢከሰት ሕክምና የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች ተገቢውን ክትትል ለማድረግና ለይቶ ማቆያዎችን ለማቋቋም አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። ይህ በንዲህ እንዳለ በኑናቩት የሚኖሩት 'ኢኑይት' በመባል የሚታወቁት ቀደምት ማህበረሰቦች ለኮሮረናቫይረስ ተጋላጭ ከሚባሉት መካከል ናቸው። በቂ ያልሆኑና ደህንነታቸው ያልተጠበቁ ቤቶች፣ በአንድ ቦታ ላይ በርካታ ሰዎች ተሰብስበው መኖር እንዲሁም የቲቢ በሽታ ስርጭት ተጋላጭ ያደርጋቸዋል። 80 በመቶ የሚሆነውን የኑናቩት ነዋሪ የሚሸፍኑት ኢኑይቶች ከሌሎች ነዋሪዎች አንጻር በቲቢ የመያዝ ዕድላቸው 300 በመቶ ከፍ ያለ ነው። ካናዳ በአጠቃላይ እንደ ሙሉ የእንቅስቃሴ ገደብ ያሉ የጥንቃቄ እርምጃዎች በመውሰዷ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ሞክራለች።ነገር ግን አሁንም ቢሆን ለመቆጣጠር አልቻለችም። እስካሁንም ድረስ 191 ሺ 732 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 9 ሺ 699 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል። ነገር ግን እንደ ኪቤክና ኦንታሪዮ ባሉ በርካታ ሰዎች በሚኖሩባቸው ግዛቶች በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ መጥቷል። በአሁኑ ሰአት 77 ሺ የሚሆኑ ካናዳውያን በየቀኑ የኮሮረናቫይረስ ምርመራ የሚደረግላቸው ሲሆን የአገሪቱ ግብ ግን በየቀኑ 200 ሺ ሰዎችን ለመመርመር ነው። | https://www.bbc.com/amharic/news-54596957 |
5sports
| ማንችስተር ሲቲ ላይ የተጣለው ቅጣት በአሰልጣኙና በተጫዋቾቹ ላይ ምን ውጤት ይኖረዋል? | ማንችስተር ሲቲ የአውሮፓ እግር ኳስ የበላይ አስተዳዳሪ የሆነውን አካል የፈቃድና የገንዘብ አጠቃቀም ደንብን በመጣሱ ለቀጣይ ሁለት የውድድር ዘመኖች በሚደረጉ የአውሮፓ ክለቦች ውድድር ላይ እንዳይሳተፍ እገዳ ተጣለበት። ከዕገዳው በተጨማሪ ቡድኑ የሰላሳ ሚሊዮን ዩሮ የገንዘብ ቅጣት የተጣለበት ሲሆን በፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች ካገኘው ነጥብ ላይ ሊቀነስበት እንደሚችልም ተጠቅሷል። ይህ የዕገዳና የቅጣት ውሳኔ የስፖርት ጉዳዮች ግልግል ፍርድ ቤት ላይ ይግባኝ ሊባልበት የሚችል እንደሆነም ተነግሯል። ቡድኑም በቅጣት ውሳኔው መሳዘኑንና ሕግን ያልተከተለ መሆኑን ገልጾ ይግባኝ እንደሚጠይቅ ገልጿል። የቡድኖችን የገንዘብ ሁኔታ የሚቆጣጠረው አካል እንዳለው ማንችስተር ሲቲ ለአራት ዓመታት ከስፖንሰር ያገኘውን ገቢ ደንብ ተላልፎ፣ አንሮ በማሳወቅና ሌሎች ጥሰቶች፣ በተጨማሪ በምርመራው ሂደት ለመተባበር ፈቃደኛ አልነበረም ብሏል። የቅጣቱ ውሳኔ በይግባኝ እስካልተቀለበሰ ድረስ ቡድኑ ከሁለት የታላቁ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ውጪ የሚሆን ሲሆን ይህም ለቡድኑም ሆነ ለአሰልጣኙ ትልቅ ጉዳትን ያስከትላል። በአውሮፓ የሻምፒዮን ሊግ ውድድር ላይ መታየት ለተጫዋቾችና ለአሰልጣኞች እንደአንድ ስኬት ስለሚቆጠር ቅጣቱ ቡድኑ ውስጥ ያሉትን አሰልጣኞችና ተጫዋቾችን ሊያሸሽ እንዲሁም ሌሎችን ለመቅጠር እንቅፋት ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት አለ። እኤአ እስከ 2021 በማንችስተር ሲቲ ውስጥ ለመቆየት ኮንትራት የፈረመው ፔፕ ጋርዲዮላና ሌሎች እሱን ተከትለው ክለቡን የተቀላቀሉት ተጫዋቾች፣ ቡድኑ በታላቁ የአውሮፓ ክለቦች የውድድር መድረክ ላይ ለሁለት ተከታታይ ወቅቶች የማይሳተፍ ከሆነ ሲቲ ውስጥ የመቆየታቸው ነገር አጠያያቂ ነው። ይህ ደግሞ በዓመታት ውስጥ አሉ ከተባሉ የእንግሊዝ እግር ኳስ ቡድኖች መካከል ለመሰለፍ ከፍተኛ ገንዘብን በማፍሰስ ስሙን የገነባውን ቡድን አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሊጥለው ይችላል። የሲቲ ባለስልጣናት ግን የተባለው አይነት ቅጣት እንዲጣልባቸው የሚያደርግ አንዳችም ጥፋት አለመስራታቸውን ለአሰልጣኙ ጋርዲዮላ ያረጋገጡላቸው ሲሆን፣ ይህ ተጫወቾችንም እንዲረጋጉና ቡድኑ ውስጥ እንዲቆዩ ያግዛል። ይህ ሁሉ የሚሆነው ግን የስፖርት ጉዳዮች የግልግል ፍርድ ቤት በማንችስተር ሲቲ ላይ የተጣለውን ቅጣት ተገቢ አይደለም ብሎ ካነሳው ነው። ቡድኑም ጉዳዩን በቀላሉ እንደማይተወው አሳውቋል። | ማንችስተር ሲቲ ላይ የተጣለው ቅጣት በአሰልጣኙና በተጫዋቾቹ ላይ ምን ውጤት ይኖረዋል? ማንችስተር ሲቲ የአውሮፓ እግር ኳስ የበላይ አስተዳዳሪ የሆነውን አካል የፈቃድና የገንዘብ አጠቃቀም ደንብን በመጣሱ ለቀጣይ ሁለት የውድድር ዘመኖች በሚደረጉ የአውሮፓ ክለቦች ውድድር ላይ እንዳይሳተፍ እገዳ ተጣለበት። ከዕገዳው በተጨማሪ ቡድኑ የሰላሳ ሚሊዮን ዩሮ የገንዘብ ቅጣት የተጣለበት ሲሆን በፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች ካገኘው ነጥብ ላይ ሊቀነስበት እንደሚችልም ተጠቅሷል። ይህ የዕገዳና የቅጣት ውሳኔ የስፖርት ጉዳዮች ግልግል ፍርድ ቤት ላይ ይግባኝ ሊባልበት የሚችል እንደሆነም ተነግሯል። ቡድኑም በቅጣት ውሳኔው መሳዘኑንና ሕግን ያልተከተለ መሆኑን ገልጾ ይግባኝ እንደሚጠይቅ ገልጿል። የቡድኖችን የገንዘብ ሁኔታ የሚቆጣጠረው አካል እንዳለው ማንችስተር ሲቲ ለአራት ዓመታት ከስፖንሰር ያገኘውን ገቢ ደንብ ተላልፎ፣ አንሮ በማሳወቅና ሌሎች ጥሰቶች፣ በተጨማሪ በምርመራው ሂደት ለመተባበር ፈቃደኛ አልነበረም ብሏል። የቅጣቱ ውሳኔ በይግባኝ እስካልተቀለበሰ ድረስ ቡድኑ ከሁለት የታላቁ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ውጪ የሚሆን ሲሆን ይህም ለቡድኑም ሆነ ለአሰልጣኙ ትልቅ ጉዳትን ያስከትላል። በአውሮፓ የሻምፒዮን ሊግ ውድድር ላይ መታየት ለተጫዋቾችና ለአሰልጣኞች እንደአንድ ስኬት ስለሚቆጠር ቅጣቱ ቡድኑ ውስጥ ያሉትን አሰልጣኞችና ተጫዋቾችን ሊያሸሽ እንዲሁም ሌሎችን ለመቅጠር እንቅፋት ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት አለ። እኤአ እስከ 2021 በማንችስተር ሲቲ ውስጥ ለመቆየት ኮንትራት የፈረመው ፔፕ ጋርዲዮላና ሌሎች እሱን ተከትለው ክለቡን የተቀላቀሉት ተጫዋቾች፣ ቡድኑ በታላቁ የአውሮፓ ክለቦች የውድድር መድረክ ላይ ለሁለት ተከታታይ ወቅቶች የማይሳተፍ ከሆነ ሲቲ ውስጥ የመቆየታቸው ነገር አጠያያቂ ነው። ይህ ደግሞ በዓመታት ውስጥ አሉ ከተባሉ የእንግሊዝ እግር ኳስ ቡድኖች መካከል ለመሰለፍ ከፍተኛ ገንዘብን በማፍሰስ ስሙን የገነባውን ቡድን አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሊጥለው ይችላል። የሲቲ ባለስልጣናት ግን የተባለው አይነት ቅጣት እንዲጣልባቸው የሚያደርግ አንዳችም ጥፋት አለመስራታቸውን ለአሰልጣኙ ጋርዲዮላ ያረጋገጡላቸው ሲሆን፣ ይህ ተጫወቾችንም እንዲረጋጉና ቡድኑ ውስጥ እንዲቆዩ ያግዛል። ይህ ሁሉ የሚሆነው ግን የስፖርት ጉዳዮች የግልግል ፍርድ ቤት በማንችስተር ሲቲ ላይ የተጣለውን ቅጣት ተገቢ አይደለም ብሎ ካነሳው ነው። ቡድኑም ጉዳዩን በቀላሉ እንደማይተወው አሳውቋል። | https://www.bbc.com/amharic/sport-51513602 |
0business
| ወደ ኢትዮጵያ ለሚገቡ ለተወሰኑ እቃዎች እና ሸቀጦች የውጭ ምንዛሪ እንዳይሰጥ ተወሰነ | የኢትዮጵያ መንግሥት ከተለያዩ አገራት ለሚገቡ በተወሰኑ እቃዎች እና ሸቀጦች ላይ ላልተወሰነ ጊዜ የውጭ ምንዛሬ እንደማይፈቅድ አስታወቀ። ከእነዚህም መካከል ከረሜላዎች፣ ብስኩቶች፣ ለስላሳ መጠጦች፣ ዊስኪ፣ ወይን፣ ቢራ፣ የተገጣጠሙ የቤት አውቶሞቢሎች እና ባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎች፣ ሰው ሰራሽ ፀጉር፣ የውበት ወይም መኳኳያ እቃዎች ተካትተውበታል። የገንዘብ ሚኒስቴር በቁጥር 38 የሚሆኑ ሸቀጦች እና እቃዎችን ዝርዝር በማውጣት የውጭ ምንዛሬ እንዳይፈቅድላቸው ያሳለፈውን ውሳኔ ብሔራዊ ባንክ ተግባራዊ እንዲያደርግ በደብዳቤ አዟል። በገንዘብ ሚኒስቴር ዲኤታው ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤ እንደሚያትተው የዓለም አቀፉ ምጣኔ ሀብት ቀውስ በአገሪቱ ላይ እየፈጠረ ያለው ጫና እንዲሁም የዋጋ ግሽበት በሕዝቡ ላይ እያደረሰ ያለውንም ችግር ለመፍታት የተለያዩ እርምጃዎችን መውሰዱንም አስታውሷል። እነዚህንም እርምጃዎች ውጤታማ ለማድረግም የውጭ ምንዛሬ ለመሠረታዊ የምግብ ሸቀጦች፣ ለመድኃኒቶች እና የህክምና መሳሪያዎች እንዲውል ተወስኗል። በተጨማሪም ከውጭ ገብተው በአገር ውስጥ እሴት ለሚጨመርባቸው ምርቶች የሚውሉ ግብዓቶችና የካፒታል ዕቃዎችን ለማስገባት የውጭ ምንዛሬ ጥቅም ላይ እንዲውል ውሳኔ መተላለፉም ተገልጿል። ከሰኞ ጥቅምት 07/2015 ዓ.ም. ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ እንዳይሰጡ ክልከላ የተጣለባቸው ከውጭ ወደ አገሪቱ የሚገቡ ሸቀጦች እና ምርቶች የሚከተሉት ናቸው። ከረሜላዎች፣ ማስቲካዎችና ሌሎች ጣፋጭ ምርቶች፣ ቼኮሌት፣ ብስኩቶች እና ዋፈሮች፣ የፍራፍሬ ጭማቂዎች እና የታሸጉ ፍራፍሬዎች፣ ከፍራፍሬ የተዘጋጁ ጃሞች፣ የድንች ጥብሶች፣ የአሳማ ሥጋ፣ የዶሮ ሥጋ፣ የተለያዩ የአሳ ምርቶች፣ የገበታ ጨው፣ የታሸጉ ውሃዎች፣ ለስላሳ መጠጦች እና አልኮል የሌላቸው መጠጦች ለምግብነት ከሚውሉ ውስጥ ይጠቀሳሉ። እንዲሁም ዊሰኪ፣ ወይን፣ ቢራ እና ለሎች አልኮል መጠጦች በሙሉ፣ ሲጋራ፣ ከብርጭቆ የተዘጋጁ የመጠጥ መጠጫዎች፣ የሲጋራ መተርኮሻዎች የተካተቱ ሲሆን፣ ሽቶዎች፣ የውበት ወይም የመኳኳያ ምርቶች፣ የሰው እና አርቴፊሻል ፀጉሮች፣ አርቴፊሻል ጌጣጌጦች፣ የተለያዩ የፀጉር ጌጣጌጦች፣ ባርኔጣዎች እና ኮፍያዎች፣ ሳሙናዎች፣ ርችቶች፣ ቦርሳ እና ዋሌቶች፣ አንዳንድ የቤት እና የቢሮ ዕቃዎች ተካተዋል። ብስክሌቶች፣የተለያዩ መጫወቻ እቃዎች፣ የእጅ፣ የጠረጴዛ እና የግድግዳ ሰዓቶች፣ ዣንጥላዎች፣ ምንጣፎች፣ ከሴራሚክስ እና ፖርስሊን የተዘጋጁ የቤት እቃዎች፣ ጋዝ ላይተር፣ ልብስ ማሳያ አሻንጉሊቶች፣ የአበባ መያዣና ተመሳሳይ እቃዎች፣ የታተመ ስዕላዊ መግለጫ ያላቸው ካርዶች፣ የቀን መቁጠሪያ ካሌንደሮች፣ ሥዕሎች፣ አርቲፊሻል አበባዎች። በተጨማሪም በኤሌክትሪክ ከሚሰሩት ውጪ የተገጣጠሙ የቤት አውቶሞቢል እና ባለሦስት እግር ተሸከርካሪዎች እና ሞተር ሳይክሎችን ለማስገባት የውጭ ምንዛሬ ተከልክሏል። ነገር ግን ይህ ክልከላ በአገር ውስጥ ለሚገጣጠሙ መኪኖች እና ተሽከርካሪዎች እንዲሁም በኤሌክትሪክ የሚሰሩትን አይመለከትም። መንግሥት በአገሪቱ ያለውን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለመቅረፍ ባለፈው ሳምንት ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር እና የውጭ ምንዛሪ ግብይትን ለመቆጣጠር የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን አሳውቆ ነበር። በዚህም በአገሪቱ እየተባባሰ ያለውን የዋጋ ንረት እና የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት በሕገወጥ መንገድ የሚካሄዱ የተለያዩ የገንዘብ ዝውውሮችን ለመቆጣጠር ያስችላሉ ያላቸውን እርምጃዎችን አሳውቋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በአገሪቱ የሚካሄዱ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውሮችን ለመቆጣጠር በጥቆማ ለሚተባበሩ ግለሰቦች የተለያየ መጠን ያለው ወሮታ እንደሚከፍል አስታወቆ ነበር። በዚህም በባንክ ከተፈቀደው በላይ የገንዘብ መጠን ይዘው የሚገኙ ግለሰቦችን ለጠቆሙ ከተያዘው ገንዘብ 15 በመቶ፣ የውጭ አገር ገንዘብ ዝውውር ለሚጠቁሙ 15 በመቶ፣ ሕገወጥ ሐዋላን ለሚጠቁሙ 25 ሺህ ብር ወሮታ ብሔራዊ ባንክ እንደሚከፍል ገዢው አሳውቀዋል። ከዚህ በተጨማሪም የወርቅ ኮንትሮባንድ ለሚጠቁሙ 15 በመቶ የወርቁን ዋጋ፣ የሐሰተኛ የገንዘብ ኖት ህትመትን ለሚጠቁሙ ከ20 ሺህ እስከ 200 ሺህ ብር የሚደርስ ወሮታ እንደሚከፈልም ተገልጿል። በተጨማሪም ከአገር ውስጥ ጥቁር ገበያ የውጭ ምንዛሪን በመግዛት ከውጭ እቃ እያስገቡ ያሉትን ለመቆጣጠር፣ በፍራንኮ ቫሉታ ከውጭ እቃ የሚያስመጡ ግለሰቦችና ተቋማት በውጭ አገር ያላቸውን የዶላር መጠን የሚያሳውቅ የባንክ ስቴትመንት ለብሔራዊ ባንክ የማቅረብ ግዴታ ተጥሎባቸዋል። ባለፉት ሁለት ዓመታት በአገሪቱ ውስጥ ያለው የውጭ ምንዛሪ ዋጋ እየጨመረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ያለው የምንዛሪ ዋጋ ከዚህ በፊት ከነበሩት ሁሉ ከፍተኛው ነው። በዚህም በይፋዊው የባንኮች ግብይት የዶላር የምንዛሪ ዋጋ የአንድ የአሜሪካ ዶላር ዋጋ 52 ብር አካባቢ ሲሆን፣ በጥቁር ገበያ በእጥፍ እንደሚመነዘር ይነገራል። | ወደ ኢትዮጵያ ለሚገቡ ለተወሰኑ እቃዎች እና ሸቀጦች የውጭ ምንዛሪ እንዳይሰጥ ተወሰነ የኢትዮጵያ መንግሥት ከተለያዩ አገራት ለሚገቡ በተወሰኑ እቃዎች እና ሸቀጦች ላይ ላልተወሰነ ጊዜ የውጭ ምንዛሬ እንደማይፈቅድ አስታወቀ። ከእነዚህም መካከል ከረሜላዎች፣ ብስኩቶች፣ ለስላሳ መጠጦች፣ ዊስኪ፣ ወይን፣ ቢራ፣ የተገጣጠሙ የቤት አውቶሞቢሎች እና ባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎች፣ ሰው ሰራሽ ፀጉር፣ የውበት ወይም መኳኳያ እቃዎች ተካትተውበታል። የገንዘብ ሚኒስቴር በቁጥር 38 የሚሆኑ ሸቀጦች እና እቃዎችን ዝርዝር በማውጣት የውጭ ምንዛሬ እንዳይፈቅድላቸው ያሳለፈውን ውሳኔ ብሔራዊ ባንክ ተግባራዊ እንዲያደርግ በደብዳቤ አዟል። በገንዘብ ሚኒስቴር ዲኤታው ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤ እንደሚያትተው የዓለም አቀፉ ምጣኔ ሀብት ቀውስ በአገሪቱ ላይ እየፈጠረ ያለው ጫና እንዲሁም የዋጋ ግሽበት በሕዝቡ ላይ እያደረሰ ያለውንም ችግር ለመፍታት የተለያዩ እርምጃዎችን መውሰዱንም አስታውሷል። እነዚህንም እርምጃዎች ውጤታማ ለማድረግም የውጭ ምንዛሬ ለመሠረታዊ የምግብ ሸቀጦች፣ ለመድኃኒቶች እና የህክምና መሳሪያዎች እንዲውል ተወስኗል። በተጨማሪም ከውጭ ገብተው በአገር ውስጥ እሴት ለሚጨመርባቸው ምርቶች የሚውሉ ግብዓቶችና የካፒታል ዕቃዎችን ለማስገባት የውጭ ምንዛሬ ጥቅም ላይ እንዲውል ውሳኔ መተላለፉም ተገልጿል። ከሰኞ ጥቅምት 07/2015 ዓ.ም. ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ እንዳይሰጡ ክልከላ የተጣለባቸው ከውጭ ወደ አገሪቱ የሚገቡ ሸቀጦች እና ምርቶች የሚከተሉት ናቸው። ከረሜላዎች፣ ማስቲካዎችና ሌሎች ጣፋጭ ምርቶች፣ ቼኮሌት፣ ብስኩቶች እና ዋፈሮች፣ የፍራፍሬ ጭማቂዎች እና የታሸጉ ፍራፍሬዎች፣ ከፍራፍሬ የተዘጋጁ ጃሞች፣ የድንች ጥብሶች፣ የአሳማ ሥጋ፣ የዶሮ ሥጋ፣ የተለያዩ የአሳ ምርቶች፣ የገበታ ጨው፣ የታሸጉ ውሃዎች፣ ለስላሳ መጠጦች እና አልኮል የሌላቸው መጠጦች ለምግብነት ከሚውሉ ውስጥ ይጠቀሳሉ። እንዲሁም ዊሰኪ፣ ወይን፣ ቢራ እና ለሎች አልኮል መጠጦች በሙሉ፣ ሲጋራ፣ ከብርጭቆ የተዘጋጁ የመጠጥ መጠጫዎች፣ የሲጋራ መተርኮሻዎች የተካተቱ ሲሆን፣ ሽቶዎች፣ የውበት ወይም የመኳኳያ ምርቶች፣ የሰው እና አርቴፊሻል ፀጉሮች፣ አርቴፊሻል ጌጣጌጦች፣ የተለያዩ የፀጉር ጌጣጌጦች፣ ባርኔጣዎች እና ኮፍያዎች፣ ሳሙናዎች፣ ርችቶች፣ ቦርሳ እና ዋሌቶች፣ አንዳንድ የቤት እና የቢሮ ዕቃዎች ተካተዋል። ብስክሌቶች፣የተለያዩ መጫወቻ እቃዎች፣ የእጅ፣ የጠረጴዛ እና የግድግዳ ሰዓቶች፣ ዣንጥላዎች፣ ምንጣፎች፣ ከሴራሚክስ እና ፖርስሊን የተዘጋጁ የቤት እቃዎች፣ ጋዝ ላይተር፣ ልብስ ማሳያ አሻንጉሊቶች፣ የአበባ መያዣና ተመሳሳይ እቃዎች፣ የታተመ ስዕላዊ መግለጫ ያላቸው ካርዶች፣ የቀን መቁጠሪያ ካሌንደሮች፣ ሥዕሎች፣ አርቲፊሻል አበባዎች። በተጨማሪም በኤሌክትሪክ ከሚሰሩት ውጪ የተገጣጠሙ የቤት አውቶሞቢል እና ባለሦስት እግር ተሸከርካሪዎች እና ሞተር ሳይክሎችን ለማስገባት የውጭ ምንዛሬ ተከልክሏል። ነገር ግን ይህ ክልከላ በአገር ውስጥ ለሚገጣጠሙ መኪኖች እና ተሽከርካሪዎች እንዲሁም በኤሌክትሪክ የሚሰሩትን አይመለከትም። መንግሥት በአገሪቱ ያለውን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለመቅረፍ ባለፈው ሳምንት ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር እና የውጭ ምንዛሪ ግብይትን ለመቆጣጠር የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን አሳውቆ ነበር። በዚህም በአገሪቱ እየተባባሰ ያለውን የዋጋ ንረት እና የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት በሕገወጥ መንገድ የሚካሄዱ የተለያዩ የገንዘብ ዝውውሮችን ለመቆጣጠር ያስችላሉ ያላቸውን እርምጃዎችን አሳውቋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በአገሪቱ የሚካሄዱ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውሮችን ለመቆጣጠር በጥቆማ ለሚተባበሩ ግለሰቦች የተለያየ መጠን ያለው ወሮታ እንደሚከፍል አስታወቆ ነበር። በዚህም በባንክ ከተፈቀደው በላይ የገንዘብ መጠን ይዘው የሚገኙ ግለሰቦችን ለጠቆሙ ከተያዘው ገንዘብ 15 በመቶ፣ የውጭ አገር ገንዘብ ዝውውር ለሚጠቁሙ 15 በመቶ፣ ሕገወጥ ሐዋላን ለሚጠቁሙ 25 ሺህ ብር ወሮታ ብሔራዊ ባንክ እንደሚከፍል ገዢው አሳውቀዋል። ከዚህ በተጨማሪም የወርቅ ኮንትሮባንድ ለሚጠቁሙ 15 በመቶ የወርቁን ዋጋ፣ የሐሰተኛ የገንዘብ ኖት ህትመትን ለሚጠቁሙ ከ20 ሺህ እስከ 200 ሺህ ብር የሚደርስ ወሮታ እንደሚከፈልም ተገልጿል። በተጨማሪም ከአገር ውስጥ ጥቁር ገበያ የውጭ ምንዛሪን በመግዛት ከውጭ እቃ እያስገቡ ያሉትን ለመቆጣጠር፣ በፍራንኮ ቫሉታ ከውጭ እቃ የሚያስመጡ ግለሰቦችና ተቋማት በውጭ አገር ያላቸውን የዶላር መጠን የሚያሳውቅ የባንክ ስቴትመንት ለብሔራዊ ባንክ የማቅረብ ግዴታ ተጥሎባቸዋል። ባለፉት ሁለት ዓመታት በአገሪቱ ውስጥ ያለው የውጭ ምንዛሪ ዋጋ እየጨመረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ያለው የምንዛሪ ዋጋ ከዚህ በፊት ከነበሩት ሁሉ ከፍተኛው ነው። በዚህም በይፋዊው የባንኮች ግብይት የዶላር የምንዛሪ ዋጋ የአንድ የአሜሪካ ዶላር ዋጋ 52 ብር አካባቢ ሲሆን፣ በጥቁር ገበያ በእጥፍ እንደሚመነዘር ይነገራል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cd1nq0n7v1zo |
5sports
| ከሰመመን ሲነቃ ፈረንሳይኛን አቀላጥፎ መናገር የቻለው የማንችስተር ተጫዋች | የሮሪ ከርትስ ጉዳይ ትንግርት ካልተባለ ምን ሊባል ይችላል? ታሪኩን በአንድ አንቀጽ የሚከተለውን ይመስላል። ሮሪ በ22 ዓመቱ ዘግናኝ የመኪና አደጋ ደረሰበት። ከሳምንታት በኋላ ከሰመመን ነቃ። በቅጡ ተናግሮት የማያውቀውን ፈረንሳይኛ እንደ ልሳን ያንበለብለው ጀመር። ሰው የማያውቀውን ቋንቋ እንዴት ሊናገር ይችላል? ሮሪ ለማንችስተር ታዳጊ ቡድን ተጫዋች ነበር። በሕይወቱ ከኳስ ሌላ ሕልም አልነበረውም። በአንድ ክፉ አጋጣሚ መኪናውን በእንግሊዝ አውራ ጎዳና በፍጥነት ሲያሽከረክር ተገለበጠ። ያን ቀትር ዶፍ እየዘነበ ነበር። መንገዱ ያንሸራትት ነበር። እሱ ከከባድ መኪና ጋር ሲጋጭ ከኋላው በፍጥነት እየተነዱ የነበሩ ስድስት ሌሎች የቤት መኪናዎች ተገጫጭተው እላዩ ላይ ወጡበት። የእርሱ መኪና ጭምድድድ. . . አለች፤ እንደ ካርቶን። እንኳን ሰው ዝንብ ከዚያ አደጋ ይተርፋል ያለ ማንም አልነበረም። ሮሪ ግን ሲፈጥረው በቀላሉ አትሙት ተብሏል መሰለኝ. . .፡፡ ራሱን ሳተ እንጂ ነፍሱ አልወጣችም ነበር። አምቡላንስ መጣ፤ ሆስፒታል ተወሰደ። ለሳምንታት አልነቃም። ሐኪሞቹ የዚህ ወጣት ነፍስ የመትረፍ ዕድሏ የተመናመነ እንደሆነ ለቤተሰቦቹ በይፋ ተናገሩ። ኾኖም ግን አንድ በሙከራ ላይ ያለ መድኃኒት እንዳለና ፍቃዳቸው ከሆነ እሱን መድኃኒት ሊወጉት እንደሚችሉ ጠየቁ። ቤተሰቡ ምን አማራጭ ነበረው? እሺ ከማለት ሌላ። የሮሪ ወላጆች ተስማሙ። አዲሱን መድኃኒት ተወጋ። ሆኖም ከሰመመኑ አልተመለሰም። በግማሽ ሞት፣ በግማሽ ሕይወት መሀል ሆኖ ለሳምንታት ራሱን እንደሳተ ቆየ። እውነት ለመናገር ቤተሰቦቹ እርም ለማውጣት በዝግጅት ላይ ነበሩ። ሁሉም ነገር ተስፋ አስቆራጭ በሚመስልበት በዚያ ሰዓት አንድ ማለዳ ሮሪ ዓይኑን ገለጠ። እሱ ሲነቃ አጠገቡ አንዲት ጥቁር ነርስ ነበረች። አንዳች ነገር ማጉረምረም ጀመረ። ቀጥሎ የሆነው ግን ለሳይንስም ግራ ነው የሆነው። ፈረንሳይኛ ቋንቋን ያንበለብለው ነበር። በአጋጣሚ አጠገቡ የነበረችው ጥቁር ነርስ ፈረንሳያዊት ስለነበረች ልጁ የፈረንሳይ ዜጋ እንደሆነ እርግጠኛ ነበረች። ኋላ ላይ አባትየውን ፈረንሳይ የት አካባቢ እንደሚኖሩ የጠየቀቻቸውም ለዚሁ ነበር። እርሳቸው ግን "ኧረ እኛ ከእግሊዝ ነን፤ የምን ፈረንሳይ አመጣሽብኝ?" አሉ። "ታዲያ እንዴት ልጆዎ ፈረንሳያዊ ሊሆን ቻለ? በእናቱ ወገን ይሆን?" ነርሷ ጠየቀች። በፍጹም ጥርጣሬ አልገባትም ነበር። ሆኖም ሮሪ አይሪሽ እንጂ ፍሬንች አልነበረም። እርግጥ ልጅ እያለ ድሮ በትምህርት ቤት መጠነኛ ፈረንሳይኛ ተምሯል። አለ አይደል? ለመግባባት ያህል የምትሆን ፈረንሳይኛ። ያን ከመማሩ ውጪ በዚህ ደረጃ ቋንቋውን አቀላጥፎ ተናግሮት አያውቅም። አይችልምም። እንዲያውም ልጅ እያለ ከተማረው በኋላ ቋንቋውን ተናግሮ ስለማያውቅ ጭራሽ ፈረንሳይኛን እንደማያስታውሰው ነበር የሚታወቀው። ነገር ግን ከሰመመን ሲነቃ ፈረንሳይኛውን አንበለበለው። ይህ ትንግርት ነበር፤ ለሐኪሞቹም፣ ለወላጆቹም፣ ለሳይንስም። ሮሪ ከሳምንታት ሰመመን ሲነቃ ፈረንሳይኛ ይናገር እንጂ ማን እንደነበረ በጭራሽ አያውቅም ነበር። ለማንችስተር ታዳጊ ቡድን ይጫወት እንደነበረ ቢነገረው ሊገባው አልቻለም። ኳስ ይወድ እንደነበረ እንኳ ረስቷል። ስላለፈ ሕይወቱ በጭራሽ የሚያስታውሰው ነገር የለም። አንዳችም ነገር! ለምሳሌ ምን ሆኖ ወደ ሆስፒታል እደገባ፣ ጭኑ አካባቢ እንደተሰነጠቀ፣ ክርኑ እንደተሰበረ፣ ጭንቅላቱ እንደተፈለጠ ሁሉ አያውቅም። ፈረንሳይኛ ብቻ ያውቃል። ፈረንሳይኛው እንደ ልሳን. . . እንደ ማር. . . ከአፉ ጠብ ይል ነበር። ሆኖም ብዙ አልዘለቀም። በድንገት ዝም አለ። ፈረንሳይኛው በድንገት እንደ ጉም በነነ። በቃ አቃተው። ተናገር ሲባል ኧረ እኔ ፈረንሳይኛ አልችልም ነበር ያለው። እንዴት ይህ ሊሆን ቻለ? ቅደም አያቶቹ ከፈረንሳይ መሆናቸው ይሆን? "አባቴ ነገሩ አስገርሞት መመራመር ያዘ። የደረሰበት ነገር ቢኖር የእርሱ ቅድመ አያቶች ከሰሜን ምዕራብ ፈረንሳይ ኖርማንዲ ግዛት የሚመዘዙ መሆናቸው ነበር" ይላል ሮሪ። ይህ ዘመን ግን በ1800 አካባቢ መሆኑ ነው። ይህ ታዲያ እንዴት ከሮሪ ፈረንሳይኛ መናገር ጋር ሊገናኝ ይችላል? ቋንቋ እንደ ስኳርና ደም ግፊት በደም አይተላለፍ ነገር! ይተላለፍ ይሆን እንዴ? ሮሪ በእርሱ ላይ የደረሰው ትንግርት እንዴት ዓለምን ሲያነጋግር እንደቆየ ለቢቢሲ ሲናገር "ዩቲዩብ ላይ ስሜን ጉግል ብታደርገው ከእኔ መላምቶች ጋር በተያያዘ ብዙ ቪደዮዎችን ታገኛለህ። አንዳንዱ ቋንቋ በትምህርት ብቻ ሳይሆን በዘር የሚተላለፍና አእምሯችን ጓዳ ሊቀበር እንደሚችል የሚገልጽ ነው" ይላል። ሮሪ ላይ ይህ አደጋ የደረሰው በ2012 ላይ ነበር። ያን ጊዜ ሮሪ 22 ዓመቱ ነበር። ዛሬ 30 ዓመት ደፍኗል። ሮሪ ያን ጊዜ ለማንችስተር ዩናይትድ ታዳጊ ቡደን እየተጫወተ በትርፍ ሰዓቱ ለአንድ ተቋራጭ ኩባንያ በተላላኪነት ይሰራ ነበር። የሚገርመው ከዚህ ሁሉ ዓመት በኋላ ዛሬም ድረስ ያ አደጋ እንዴት እንደተፈጠረ ምንም ትዝ አይለውም። ያ አሰቃቂ የመኪና አደጋ ከትዝታ ቋቱ የተፋቀ ጉዳይ ነው። ሆኖም የዓይን እማኞች እንደተናገሩት ሮሪ በዚያ ዝናብ በከፍተኛ ፍጥነት እየነዳ በፍጥነት መስመር ሲቀይር ነበር ከፊት ለፊቱ ከሚገኝ ከባድ ተሸከርካሪ ጋር ሄዶ የተላተመው። ከዚያም ከኋላው የነበሩ መኪናዎች እላዩ ላይ ወጡበት። የእሳት አደጋ መከላከያ ሠራተኞች ሮሪን ከተጫኑት ስድስት መኪናዎች ውስጥ ፈልፍለው ለማውጣት ከግማሽ ሰዓት በላይ ወስዶባቸዋል። ያን ጊዜ ትንፋሽ አልነበረውም። ሆኖም አምቡላንስ ውስጥ የመተንፈሻ መሣሪያዎች ተገጥመውለት በርሚንግሀም ወደሚገኘው ቅድስት ኤልዛቤጥ ሆስፒታል ተወሰደ። ሮሪ የኋላ ታሪኩ ሲጠና 7 ዓመቱ ላይ ሳለ የማጅራት ገትር የመሰለ ሕመም ታሞ እንደነበር ታውቋል። ያን ጊዜም ቢሆን የመትረፍ እድሉ 50 በመቶ ብቻ ነበር። ለ6 ሳምንት በበርሚንግሀም የሕጻናት ሆስፒታል ውስጥ ክትትል ተደረገለት። ከዚያ በኋላ በተወነ ደረጃ ዕይታው ስለተጋረደ መነጽር ማድረግ ጀምሮ ነበር። "ያን ጊዜ ሆስፒታል ከነበርነው ሕጻናት እኔ ብቻ ነኝ የልጅነት ልምሻ ያልያዘኝ። ያለምንም ጉዳት ድኜ ስወጣ ሰው ሁሉ ገርሞት ነበር" ይላል። ይኸው ነው ቅድመ ታሪኩ። ሮሪ ከዚህ በኋላ ምንም የጤና እክል አላጋጠመውም። እንዲያውም ንቁና ቀልጣፋ በመሆኑ እግር ኳስ አካዳሚ ተመዘገበ። ቤተሰቡ የለየለት የበርሚንግሀም ቀንደኛ ደጋፊዎች ናቸው። በ11 ዓመቱ ለበርሚንግሀም የታዳጊ ቡድን እንዲጫወት ተፈቅዶለት ነበር። በ13 ዓመቱ ለሴንትራል አያክስ ቡድን አጥቂ ቦታ ሲጫወት የማንችስተር ዩናይትድ መልማዮች አይተውት ወደዱት፤ ወሰዱት። ከዚህ በኋላ ነበር አሰቃቂው አደጋ የደረሰበት። ከሰመመን ሲነቃ ፈረንሳይኛ መናገሩ ብቻ አይደለም የሮሪ አስገራሚው ነገር። እድሜውንም ረስቶ ነበር። ያኔ 22 ዓመቱ የነበረ ቢሆንም እርሱ ግን የ10 ዓመት ልጅ እንደሆነ ነበር የሚያውቀው። "ውሻዬ የት ሄዳ ነው?" ይላል። "እማዬ ውሻዬን አምጪልኝ" ይለኝ ነበር ትላለች እናቱ። ውሻዋ እኮ ድሮ እሱ ልጅ እያለ ነው እኮ የሞተችው። እርሱ ግን ረስቶታል። ሮሪ በበኩሉ "ቀስ እያልኩ እድሜዬ 10 ሳይሆን 12 እንደነበር ትዝ አለኝ" ይላል። የሚደንቀው ይህ አይደለም። ከሰመመን ከነቃ ከጊዜ በኋላ ደግሞ ሮሪ ራሱን የሆሊውድ ዝነኛ ተዋናይ ማቲው መካነሄይ እንደሆነ ነበር የሚያስበው። ቅዠት ሳይሆን በእውን እርሱ የሆሊውዱ ማቲው ማካነሄይ እንደሆነ በትክክል ያምን ነበር። መጀመርያ እንዲያ ያስብ የነበረው ሆስፒታል አልጋ ላይ ሳለ ነበር። ያስጨንቀው የነበረውም ቶሎ ተነስቶ ቀጣዩን ዝነኛ ፊልሙን መቅረጽ ነበር። እርሱ የኦስካር አሸናፊ ማቲው መካነሄይ እንደነበረ እቺን ታህል ጥርጣሬ አልበረውም። "ክንዴና ጭኔ አካባቢ ተሰብሬ ስለነበር እናቴ ነበረች ሽንት ቤት የምታደርሰኝ። የመጀመሪያ ከሰመመን ነቅቼ ሽንት ቤት ሳለሁ በመስታወት የማየው ልጅ ማን ነው? ስል ግራ ተጋባሁ። አላውቀውም ነበር። ራሴን አላውቀውም። የራሴን መልክ አላውቀውም። እኔ የማውቀው ማቲው መካነሄይን መሆኔን ነበር" ይላል ሮሪ። ምናልባት ሮሪ ያን ጊዜ መስታወቱ የዋሸው ያህል ሳይሰማው አልቀረም። እሱ ቆሞ እንዴት የሌላ ሰው ፊት ያሳየዋል? ሮሪ በኅዳር 2012 ከሆስፒታል ሲወጣ አብዛኛውን ነገር ዘንግቶ ነበር። እንኳንስ የድሮውን ይቅርና ከ15 ደቂቃዎች በፊት ያደረገውን ይረሳል። ስለዚህ ማስታወሻ ደብተር ተገዛለት። ምሳ ሲበላ ምሳ በልቻለሁ ብሎ ይጽፋል። ገላውን ታጥቦ እንደወጣ ገላዬን ታጥቢያለሁ ብሎ ይጽፋል። "በዚህ መንገድ የጨረስኩት የማስታወሻ ደብተር ብዛቱ!" ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል። ሮሪ በዚህ መንገድ ማንነቱን መልሶ ለማግኘት ብርቱ ጥረት አደረገ። በመጨረሻም አንድ ዓመት ካገገመ በኋላ ራሱ ልብሱን መቀየር ቻለ። ከዚያ ሙሉ በሙሉ ድኖ ወደሚወደው እግር ኳስ ለመመለስ ሞከረ። ከስድስት ዓመት በፊት ለስቶርፖርት ክለብ መጫወት ጀመረ። ሐኪሞች ማመን አቃታቸው። እንዴት በዚያ ደረጃ የተጎዳ ልጅ ድኖ ኳስ ሊጫወት እንደሚችል ትንግርት ሆነባቸው። "በእርግጥ መገረም ብቻ ሳይሆን እንዳልጫወት መክረውኛል። ምክንያቱም በጭንቅላቴ ኳስ መግጨት ስለማይኖርብኝ ነው። ጭንቅላቴ በአደጋው ተጎድቶ ነበር" ይላል። ምናልባት ሮሪ ቋንቋ ማስታወስ የቻለው የጭንቅላቱ የቋንቋ ቋት በድንገት በሩ ተከፍቶ ይሆን? አንዳንዶች ጭንቅላታችን ከተወለድን ጀምሮ የሚሰማውንና የሚያየውን ነገር ሁሉ ይመዘግባል። እኛ ማስታወስ ስላቃተን ባዶ ይመስለናል እንጂ አእምሮ እጅግ ውስብስብ ተፈጥሮ ነው ይላሉ። ምናልባት ሮሪ ፈረንሳይኛው ከጭንቅላቱ የቋንቋ ቋት ተዘርግፎበት ቢሆንስ? ሮሪ የመኪና አደጋው ከደረሰበት በኋላ በሙከራ ላይ የነበረ የሆርሞን መድኃኒት ወስዷል። ያ መድኃኒት የሰው ልጅ ላይ ሲሞከር ሮሪ በዓለም ሁለተኛው ሰው ነበር። መድኃኒቱ ጭንቅላታቸው አካባቢ ከፍተኛ አደጋ ደርሶባቸው ለተጎዱ ሰዎች እንዲያገግሙ የሚረዳ ነበር። በአሜሪካ ሐኪሞች የተመራው ይህ የመድኃኒት ሙከራ ሲናፕሴ (Synapse) ይባላል። በከፊል ፕሮግሬስትሮን የተሰኘ የሴቶችን ሆርሞን ነበር የተወጋው። ሐኪሞቹ በየሦስት ወራት ሮሪን ይመለከቱት ነበር። ቤተሰቡ ለእሱ በተአምር መትረፍ ይህ መድኃኒት ዋናው እንደሆነ ያስባል። እሱን ይከታተሉት ከነበሩት ሀኪሞች አንዱ የሆኑት ኒውሮሎጂስቱ ዶ/ር አንቶኒ ቤሊ ግን መድኃኒቱ ለእርሱ እንዳልሰራለት ነው የሚናገሩት። ከዚያ ይልቅ የልጁ ጥንካሬና ዘረመሉ ሊሆን ይችላል ለተአምሩ መፈጠር ምክንያት የሆነው። ሮሪ ሙሉ በሙሉ ይዳን እንጂ አሁንም ድረስ ራሱን አግንኖ የማየት ነገር አለበት። "ፍጹም ነኝ ብዬ የማመን ስሜት ይሰማኛል" ይላል። ሮሪ በእግር ኳሱ ብዙ ተስፋ እንደሌለው ሲያስብ ወደ አስተማሪነት ከዚያም ወደ ጸጉር አስተካካይነት ገባ። "እናቴ 6 እህቶች አሏት። ሁሉም አስተማሪዎች ናቸው። እኔም ለምን በጸጉር ሙያ አስተማሪነት አልሞክርም ብዬ ተነሳሁ። አባቴ ዘርማንዘሮቹ ሁሉ ጸጉር አስተካካዮች ነበሩ። ለምን እሱን አልሞክረውም አልኩኝ" ይላል። የአባቱ ድርጅት ቻርሊ ፓርከር ጸጉር ቤት ይባላል። ከ1980ዎቹ ጀምሮ ቤተሰቤ በጸጉር ሥራ ነው ሲተዳደር የኖረው። "ስለዚህ ከእናቴ ቤተሰቦች አስተማሪነትን ከአባቴ ደግሞ ጸጉር አስተካካይነትን ወሰድኩ።" ሮሪ በኋላ ላይ ተምሮ ከተመረቀ በኋላ በበርሚንግሀም ሳውዝ ኤንድ ሲቲ ኮሌጅ ሌክቸረር ሆኖ ተቀጠረ። ጥቂት እንደሰራ ግን የልቡ አልደርስ አለ። ስለዚህ ለምን የራሴን ጸጉር ቤት አልከፍትም ብሎ "ቻርሊ ፓርከርስ ከት ትሮት ኤንድ ኮፊ" የሚባል የውበት ሳሎን ባለፈው ዓመት ከፈተ። መጀመርያ በ11 ዓመቱ፣ በኋላ ደግሞ በ22 ዓመቱ ሞትን በቆረጣ ጎብኝቶ የመጣው ሮሪ ጭንቅላቱ ላይ በደረሰው አደጋ የዓለም መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል። እሱ ደግሞ ከጭንቅላት በላይ በሚበቅል ጸጉር መተዳደር ጀምሯል። ስለመጪው እሱም፣ ሐኪሞቹም የሚያውቁት ነገር የለም። እንኳን ስለመጪው ስላለፈውስ መቼ በቅጡ አወቁና. . . | ከሰመመን ሲነቃ ፈረንሳይኛን አቀላጥፎ መናገር የቻለው የማንችስተር ተጫዋች የሮሪ ከርትስ ጉዳይ ትንግርት ካልተባለ ምን ሊባል ይችላል? ታሪኩን በአንድ አንቀጽ የሚከተለውን ይመስላል። ሮሪ በ22 ዓመቱ ዘግናኝ የመኪና አደጋ ደረሰበት። ከሳምንታት በኋላ ከሰመመን ነቃ። በቅጡ ተናግሮት የማያውቀውን ፈረንሳይኛ እንደ ልሳን ያንበለብለው ጀመር። ሰው የማያውቀውን ቋንቋ እንዴት ሊናገር ይችላል? ሮሪ ለማንችስተር ታዳጊ ቡድን ተጫዋች ነበር። በሕይወቱ ከኳስ ሌላ ሕልም አልነበረውም። በአንድ ክፉ አጋጣሚ መኪናውን በእንግሊዝ አውራ ጎዳና በፍጥነት ሲያሽከረክር ተገለበጠ። ያን ቀትር ዶፍ እየዘነበ ነበር። መንገዱ ያንሸራትት ነበር። እሱ ከከባድ መኪና ጋር ሲጋጭ ከኋላው በፍጥነት እየተነዱ የነበሩ ስድስት ሌሎች የቤት መኪናዎች ተገጫጭተው እላዩ ላይ ወጡበት። የእርሱ መኪና ጭምድድድ. . . አለች፤ እንደ ካርቶን። እንኳን ሰው ዝንብ ከዚያ አደጋ ይተርፋል ያለ ማንም አልነበረም። ሮሪ ግን ሲፈጥረው በቀላሉ አትሙት ተብሏል መሰለኝ. . .፡፡ ራሱን ሳተ እንጂ ነፍሱ አልወጣችም ነበር። አምቡላንስ መጣ፤ ሆስፒታል ተወሰደ። ለሳምንታት አልነቃም። ሐኪሞቹ የዚህ ወጣት ነፍስ የመትረፍ ዕድሏ የተመናመነ እንደሆነ ለቤተሰቦቹ በይፋ ተናገሩ። ኾኖም ግን አንድ በሙከራ ላይ ያለ መድኃኒት እንዳለና ፍቃዳቸው ከሆነ እሱን መድኃኒት ሊወጉት እንደሚችሉ ጠየቁ። ቤተሰቡ ምን አማራጭ ነበረው? እሺ ከማለት ሌላ። የሮሪ ወላጆች ተስማሙ። አዲሱን መድኃኒት ተወጋ። ሆኖም ከሰመመኑ አልተመለሰም። በግማሽ ሞት፣ በግማሽ ሕይወት መሀል ሆኖ ለሳምንታት ራሱን እንደሳተ ቆየ። እውነት ለመናገር ቤተሰቦቹ እርም ለማውጣት በዝግጅት ላይ ነበሩ። ሁሉም ነገር ተስፋ አስቆራጭ በሚመስልበት በዚያ ሰዓት አንድ ማለዳ ሮሪ ዓይኑን ገለጠ። እሱ ሲነቃ አጠገቡ አንዲት ጥቁር ነርስ ነበረች። አንዳች ነገር ማጉረምረም ጀመረ። ቀጥሎ የሆነው ግን ለሳይንስም ግራ ነው የሆነው። ፈረንሳይኛ ቋንቋን ያንበለብለው ነበር። በአጋጣሚ አጠገቡ የነበረችው ጥቁር ነርስ ፈረንሳያዊት ስለነበረች ልጁ የፈረንሳይ ዜጋ እንደሆነ እርግጠኛ ነበረች። ኋላ ላይ አባትየውን ፈረንሳይ የት አካባቢ እንደሚኖሩ የጠየቀቻቸውም ለዚሁ ነበር። እርሳቸው ግን "ኧረ እኛ ከእግሊዝ ነን፤ የምን ፈረንሳይ አመጣሽብኝ?" አሉ። "ታዲያ እንዴት ልጆዎ ፈረንሳያዊ ሊሆን ቻለ? በእናቱ ወገን ይሆን?" ነርሷ ጠየቀች። በፍጹም ጥርጣሬ አልገባትም ነበር። ሆኖም ሮሪ አይሪሽ እንጂ ፍሬንች አልነበረም። እርግጥ ልጅ እያለ ድሮ በትምህርት ቤት መጠነኛ ፈረንሳይኛ ተምሯል። አለ አይደል? ለመግባባት ያህል የምትሆን ፈረንሳይኛ። ያን ከመማሩ ውጪ በዚህ ደረጃ ቋንቋውን አቀላጥፎ ተናግሮት አያውቅም። አይችልምም። እንዲያውም ልጅ እያለ ከተማረው በኋላ ቋንቋውን ተናግሮ ስለማያውቅ ጭራሽ ፈረንሳይኛን እንደማያስታውሰው ነበር የሚታወቀው። ነገር ግን ከሰመመን ሲነቃ ፈረንሳይኛውን አንበለበለው። ይህ ትንግርት ነበር፤ ለሐኪሞቹም፣ ለወላጆቹም፣ ለሳይንስም። ሮሪ ከሳምንታት ሰመመን ሲነቃ ፈረንሳይኛ ይናገር እንጂ ማን እንደነበረ በጭራሽ አያውቅም ነበር። ለማንችስተር ታዳጊ ቡድን ይጫወት እንደነበረ ቢነገረው ሊገባው አልቻለም። ኳስ ይወድ እንደነበረ እንኳ ረስቷል። ስላለፈ ሕይወቱ በጭራሽ የሚያስታውሰው ነገር የለም። አንዳችም ነገር! ለምሳሌ ምን ሆኖ ወደ ሆስፒታል እደገባ፣ ጭኑ አካባቢ እንደተሰነጠቀ፣ ክርኑ እንደተሰበረ፣ ጭንቅላቱ እንደተፈለጠ ሁሉ አያውቅም። ፈረንሳይኛ ብቻ ያውቃል። ፈረንሳይኛው እንደ ልሳን. . . እንደ ማር. . . ከአፉ ጠብ ይል ነበር። ሆኖም ብዙ አልዘለቀም። በድንገት ዝም አለ። ፈረንሳይኛው በድንገት እንደ ጉም በነነ። በቃ አቃተው። ተናገር ሲባል ኧረ እኔ ፈረንሳይኛ አልችልም ነበር ያለው። እንዴት ይህ ሊሆን ቻለ? ቅደም አያቶቹ ከፈረንሳይ መሆናቸው ይሆን? "አባቴ ነገሩ አስገርሞት መመራመር ያዘ። የደረሰበት ነገር ቢኖር የእርሱ ቅድመ አያቶች ከሰሜን ምዕራብ ፈረንሳይ ኖርማንዲ ግዛት የሚመዘዙ መሆናቸው ነበር" ይላል ሮሪ። ይህ ዘመን ግን በ1800 አካባቢ መሆኑ ነው። ይህ ታዲያ እንዴት ከሮሪ ፈረንሳይኛ መናገር ጋር ሊገናኝ ይችላል? ቋንቋ እንደ ስኳርና ደም ግፊት በደም አይተላለፍ ነገር! ይተላለፍ ይሆን እንዴ? ሮሪ በእርሱ ላይ የደረሰው ትንግርት እንዴት ዓለምን ሲያነጋግር እንደቆየ ለቢቢሲ ሲናገር "ዩቲዩብ ላይ ስሜን ጉግል ብታደርገው ከእኔ መላምቶች ጋር በተያያዘ ብዙ ቪደዮዎችን ታገኛለህ። አንዳንዱ ቋንቋ በትምህርት ብቻ ሳይሆን በዘር የሚተላለፍና አእምሯችን ጓዳ ሊቀበር እንደሚችል የሚገልጽ ነው" ይላል። ሮሪ ላይ ይህ አደጋ የደረሰው በ2012 ላይ ነበር። ያን ጊዜ ሮሪ 22 ዓመቱ ነበር። ዛሬ 30 ዓመት ደፍኗል። ሮሪ ያን ጊዜ ለማንችስተር ዩናይትድ ታዳጊ ቡደን እየተጫወተ በትርፍ ሰዓቱ ለአንድ ተቋራጭ ኩባንያ በተላላኪነት ይሰራ ነበር። የሚገርመው ከዚህ ሁሉ ዓመት በኋላ ዛሬም ድረስ ያ አደጋ እንዴት እንደተፈጠረ ምንም ትዝ አይለውም። ያ አሰቃቂ የመኪና አደጋ ከትዝታ ቋቱ የተፋቀ ጉዳይ ነው። ሆኖም የዓይን እማኞች እንደተናገሩት ሮሪ በዚያ ዝናብ በከፍተኛ ፍጥነት እየነዳ በፍጥነት መስመር ሲቀይር ነበር ከፊት ለፊቱ ከሚገኝ ከባድ ተሸከርካሪ ጋር ሄዶ የተላተመው። ከዚያም ከኋላው የነበሩ መኪናዎች እላዩ ላይ ወጡበት። የእሳት አደጋ መከላከያ ሠራተኞች ሮሪን ከተጫኑት ስድስት መኪናዎች ውስጥ ፈልፍለው ለማውጣት ከግማሽ ሰዓት በላይ ወስዶባቸዋል። ያን ጊዜ ትንፋሽ አልነበረውም። ሆኖም አምቡላንስ ውስጥ የመተንፈሻ መሣሪያዎች ተገጥመውለት በርሚንግሀም ወደሚገኘው ቅድስት ኤልዛቤጥ ሆስፒታል ተወሰደ። ሮሪ የኋላ ታሪኩ ሲጠና 7 ዓመቱ ላይ ሳለ የማጅራት ገትር የመሰለ ሕመም ታሞ እንደነበር ታውቋል። ያን ጊዜም ቢሆን የመትረፍ እድሉ 50 በመቶ ብቻ ነበር። ለ6 ሳምንት በበርሚንግሀም የሕጻናት ሆስፒታል ውስጥ ክትትል ተደረገለት። ከዚያ በኋላ በተወነ ደረጃ ዕይታው ስለተጋረደ መነጽር ማድረግ ጀምሮ ነበር። "ያን ጊዜ ሆስፒታል ከነበርነው ሕጻናት እኔ ብቻ ነኝ የልጅነት ልምሻ ያልያዘኝ። ያለምንም ጉዳት ድኜ ስወጣ ሰው ሁሉ ገርሞት ነበር" ይላል። ይኸው ነው ቅድመ ታሪኩ። ሮሪ ከዚህ በኋላ ምንም የጤና እክል አላጋጠመውም። እንዲያውም ንቁና ቀልጣፋ በመሆኑ እግር ኳስ አካዳሚ ተመዘገበ። ቤተሰቡ የለየለት የበርሚንግሀም ቀንደኛ ደጋፊዎች ናቸው። በ11 ዓመቱ ለበርሚንግሀም የታዳጊ ቡድን እንዲጫወት ተፈቅዶለት ነበር። በ13 ዓመቱ ለሴንትራል አያክስ ቡድን አጥቂ ቦታ ሲጫወት የማንችስተር ዩናይትድ መልማዮች አይተውት ወደዱት፤ ወሰዱት። ከዚህ በኋላ ነበር አሰቃቂው አደጋ የደረሰበት። ከሰመመን ሲነቃ ፈረንሳይኛ መናገሩ ብቻ አይደለም የሮሪ አስገራሚው ነገር። እድሜውንም ረስቶ ነበር። ያኔ 22 ዓመቱ የነበረ ቢሆንም እርሱ ግን የ10 ዓመት ልጅ እንደሆነ ነበር የሚያውቀው። "ውሻዬ የት ሄዳ ነው?" ይላል። "እማዬ ውሻዬን አምጪልኝ" ይለኝ ነበር ትላለች እናቱ። ውሻዋ እኮ ድሮ እሱ ልጅ እያለ ነው እኮ የሞተችው። እርሱ ግን ረስቶታል። ሮሪ በበኩሉ "ቀስ እያልኩ እድሜዬ 10 ሳይሆን 12 እንደነበር ትዝ አለኝ" ይላል። የሚደንቀው ይህ አይደለም። ከሰመመን ከነቃ ከጊዜ በኋላ ደግሞ ሮሪ ራሱን የሆሊውድ ዝነኛ ተዋናይ ማቲው መካነሄይ እንደሆነ ነበር የሚያስበው። ቅዠት ሳይሆን በእውን እርሱ የሆሊውዱ ማቲው ማካነሄይ እንደሆነ በትክክል ያምን ነበር። መጀመርያ እንዲያ ያስብ የነበረው ሆስፒታል አልጋ ላይ ሳለ ነበር። ያስጨንቀው የነበረውም ቶሎ ተነስቶ ቀጣዩን ዝነኛ ፊልሙን መቅረጽ ነበር። እርሱ የኦስካር አሸናፊ ማቲው መካነሄይ እንደነበረ እቺን ታህል ጥርጣሬ አልበረውም። "ክንዴና ጭኔ አካባቢ ተሰብሬ ስለነበር እናቴ ነበረች ሽንት ቤት የምታደርሰኝ። የመጀመሪያ ከሰመመን ነቅቼ ሽንት ቤት ሳለሁ በመስታወት የማየው ልጅ ማን ነው? ስል ግራ ተጋባሁ። አላውቀውም ነበር። ራሴን አላውቀውም። የራሴን መልክ አላውቀውም። እኔ የማውቀው ማቲው መካነሄይን መሆኔን ነበር" ይላል ሮሪ። ምናልባት ሮሪ ያን ጊዜ መስታወቱ የዋሸው ያህል ሳይሰማው አልቀረም። እሱ ቆሞ እንዴት የሌላ ሰው ፊት ያሳየዋል? ሮሪ በኅዳር 2012 ከሆስፒታል ሲወጣ አብዛኛውን ነገር ዘንግቶ ነበር። እንኳንስ የድሮውን ይቅርና ከ15 ደቂቃዎች በፊት ያደረገውን ይረሳል። ስለዚህ ማስታወሻ ደብተር ተገዛለት። ምሳ ሲበላ ምሳ በልቻለሁ ብሎ ይጽፋል። ገላውን ታጥቦ እንደወጣ ገላዬን ታጥቢያለሁ ብሎ ይጽፋል። "በዚህ መንገድ የጨረስኩት የማስታወሻ ደብተር ብዛቱ!" ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል። ሮሪ በዚህ መንገድ ማንነቱን መልሶ ለማግኘት ብርቱ ጥረት አደረገ። በመጨረሻም አንድ ዓመት ካገገመ በኋላ ራሱ ልብሱን መቀየር ቻለ። ከዚያ ሙሉ በሙሉ ድኖ ወደሚወደው እግር ኳስ ለመመለስ ሞከረ። ከስድስት ዓመት በፊት ለስቶርፖርት ክለብ መጫወት ጀመረ። ሐኪሞች ማመን አቃታቸው። እንዴት በዚያ ደረጃ የተጎዳ ልጅ ድኖ ኳስ ሊጫወት እንደሚችል ትንግርት ሆነባቸው። "በእርግጥ መገረም ብቻ ሳይሆን እንዳልጫወት መክረውኛል። ምክንያቱም በጭንቅላቴ ኳስ መግጨት ስለማይኖርብኝ ነው። ጭንቅላቴ በአደጋው ተጎድቶ ነበር" ይላል። ምናልባት ሮሪ ቋንቋ ማስታወስ የቻለው የጭንቅላቱ የቋንቋ ቋት በድንገት በሩ ተከፍቶ ይሆን? አንዳንዶች ጭንቅላታችን ከተወለድን ጀምሮ የሚሰማውንና የሚያየውን ነገር ሁሉ ይመዘግባል። እኛ ማስታወስ ስላቃተን ባዶ ይመስለናል እንጂ አእምሮ እጅግ ውስብስብ ተፈጥሮ ነው ይላሉ። ምናልባት ሮሪ ፈረንሳይኛው ከጭንቅላቱ የቋንቋ ቋት ተዘርግፎበት ቢሆንስ? ሮሪ የመኪና አደጋው ከደረሰበት በኋላ በሙከራ ላይ የነበረ የሆርሞን መድኃኒት ወስዷል። ያ መድኃኒት የሰው ልጅ ላይ ሲሞከር ሮሪ በዓለም ሁለተኛው ሰው ነበር። መድኃኒቱ ጭንቅላታቸው አካባቢ ከፍተኛ አደጋ ደርሶባቸው ለተጎዱ ሰዎች እንዲያገግሙ የሚረዳ ነበር። በአሜሪካ ሐኪሞች የተመራው ይህ የመድኃኒት ሙከራ ሲናፕሴ (Synapse) ይባላል። በከፊል ፕሮግሬስትሮን የተሰኘ የሴቶችን ሆርሞን ነበር የተወጋው። ሐኪሞቹ በየሦስት ወራት ሮሪን ይመለከቱት ነበር። ቤተሰቡ ለእሱ በተአምር መትረፍ ይህ መድኃኒት ዋናው እንደሆነ ያስባል። እሱን ይከታተሉት ከነበሩት ሀኪሞች አንዱ የሆኑት ኒውሮሎጂስቱ ዶ/ር አንቶኒ ቤሊ ግን መድኃኒቱ ለእርሱ እንዳልሰራለት ነው የሚናገሩት። ከዚያ ይልቅ የልጁ ጥንካሬና ዘረመሉ ሊሆን ይችላል ለተአምሩ መፈጠር ምክንያት የሆነው። ሮሪ ሙሉ በሙሉ ይዳን እንጂ አሁንም ድረስ ራሱን አግንኖ የማየት ነገር አለበት። "ፍጹም ነኝ ብዬ የማመን ስሜት ይሰማኛል" ይላል። ሮሪ በእግር ኳሱ ብዙ ተስፋ እንደሌለው ሲያስብ ወደ አስተማሪነት ከዚያም ወደ ጸጉር አስተካካይነት ገባ። "እናቴ 6 እህቶች አሏት። ሁሉም አስተማሪዎች ናቸው። እኔም ለምን በጸጉር ሙያ አስተማሪነት አልሞክርም ብዬ ተነሳሁ። አባቴ ዘርማንዘሮቹ ሁሉ ጸጉር አስተካካዮች ነበሩ። ለምን እሱን አልሞክረውም አልኩኝ" ይላል። የአባቱ ድርጅት ቻርሊ ፓርከር ጸጉር ቤት ይባላል። ከ1980ዎቹ ጀምሮ ቤተሰቤ በጸጉር ሥራ ነው ሲተዳደር የኖረው። "ስለዚህ ከእናቴ ቤተሰቦች አስተማሪነትን ከአባቴ ደግሞ ጸጉር አስተካካይነትን ወሰድኩ።" ሮሪ በኋላ ላይ ተምሮ ከተመረቀ በኋላ በበርሚንግሀም ሳውዝ ኤንድ ሲቲ ኮሌጅ ሌክቸረር ሆኖ ተቀጠረ። ጥቂት እንደሰራ ግን የልቡ አልደርስ አለ። ስለዚህ ለምን የራሴን ጸጉር ቤት አልከፍትም ብሎ "ቻርሊ ፓርከርስ ከት ትሮት ኤንድ ኮፊ" የሚባል የውበት ሳሎን ባለፈው ዓመት ከፈተ። መጀመርያ በ11 ዓመቱ፣ በኋላ ደግሞ በ22 ዓመቱ ሞትን በቆረጣ ጎብኝቶ የመጣው ሮሪ ጭንቅላቱ ላይ በደረሰው አደጋ የዓለም መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል። እሱ ደግሞ ከጭንቅላት በላይ በሚበቅል ጸጉር መተዳደር ጀምሯል። ስለመጪው እሱም፣ ሐኪሞቹም የሚያውቁት ነገር የለም። እንኳን ስለመጪው ስላለፈውስ መቼ በቅጡ አወቁና. . . | https://www.bbc.com/amharic/news-52913458 |
5sports
| ባርሴሎና አሰልጣኝ ሮናልድ ኩማንን አሰናበተ | ሮናልድ ኩማን በኑካምፕ ለ14 ወራት ከዘለቀው የባርሴሎና ዋና አሰልጣኝ ሥራቸው ተባረዋል። ባርሳ በላሊጋው ካደረጋቸው 10 ጨዋታዎች 15 ነጥቦችን ብቻ ሰብስቧል። በዘንድሮው የቻምፒየንስ ሊግ የምድብ ጨዋታዎችም ሁለት ጊዜ ተሸንፏል። ረቡዕ በራዮ ቫሌካኖ ከተሸነፉ በኋላ ከመሪዎቹ በስድስት ነጥብ ርቀው በደረጃ ሰንጠረዡ ላይ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ለባርሳ ሽንፈቱ ባለፉት አራት ጨዋታዎች ሦስተኛው ነው። ባለፈው እሁድ በኤል ክላሲኮ በሪያል ማድሪድ መሸነፋቸው ይታወሳል። የስፔኑ ክለብ ባወጣው መግለጫ "የክለቡ ፕሬዝዳንት ጆአን ላፖርታ ከራዮ ቫሌካኖ ሽንፈት በኋላ ስለ ውሳኔው ለኩማን አሳውቀውታል" ብሏል። "ሮናልድ ኩማን ሐሙስ ዕለት ቡድኑን ይሰናበታሉ።" የ58 አመቱ የቀድሞ የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን፣ የኤቨርተን እና የሳውዝሃምፕተን አሰልጣኝ የአምስት ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒዮናዎቹን ባለፈው የውድድር ዓመት በሊጉ ሦስተኛ ደረጃ ይዘው እንዲጨርሱ አድረጓል። ክለቡ ያጋጠመው ከፍተኛ የገንዘብ ችግር ሆላንዳዊውን አልረዳውም። በዚህ ምክንያት ሊዮኔል ሜሲ ወደ ፓሪስ ሴንት ዠርሜይን እንዲዘዋወር ሆኗል። በክረምቱ ባርሴሎና ለአዳዲስ ፈራሚዎች ምንም ገንዘብ ማውጣትም አልቻለም። ሜምፊስ ዴፓይ፣ ሰርጂዮ አጉዌሮ እና ኤሪክ ጋርሲያ በነጻ ዝውውር ኑ ካመፕ ደርሰዋል። አጥቂው ሉክ ዴ ዮንግ ከሲቪያ በውሰት ተቀላቅሏል። ከረቡዕ ሽንፈት በኋላ ኩማን "[የባርሴሎና ሊግ አቋም] ደህና አለመሆኑን ያሳያል" ብሏል። "ይህ የሚያሳየው ቡድኑ ሚዛኑን አጥቷል፣ በጣም ውጤታማ የሆኑ ተጫዋቾችን አጥቷል። ሌላው የሚያሳየው ደግሞ በቅርብ ዓመታት ሌሎች ክለቦች ሲጠናከሩ እኛ ይህን አላደረግንም።" የኳታሩ ክለብ አል ሳድ አሰልጣኝ የሆነው የቀድሞ የባርሳ አማካይ ዣቪ ኩማንን ለመተካት ከተመረጡት አንዱ ነው። ከእአአ 1987 ወዲህ ባርሳ በተከታታይ ሦስት ጨዋታዎች ከሜዳው ውጪ ጎል ሳያስቆጥር ሲሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ኩማን በመጀመሪያው የውድድር ዘመን የኮፓ ዴልሬይ ዋንጫን ቢያሸንፍም ባርሳ በአትሌቲኮ ማድሪድ እና ሪያል ማድሪድ በላሊጋው ከመበለጡም በላይ ከ2008 በኋላ ዝቅተኛውን ነጥብ ሰብስቦ አጠናቋል። የቀድሞው የኔዘርላንድ የመሃል ተከላካይ እአአ ከ1989 እስ 1995 ለስፔኑ ክለብ ተጫውቶ አራት የሊግ ዋንጫዎችን አንስቷል። በቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆሴፕ ማሪያ ባርቶሜው ዋና አሰልጣኝ ሆኖ ወደ ክለቡ እአአ ነሐሴ 2020 ተመልሷል። አዲሱ ፕሬዝዳንት ላፖርታ ግን የሆላንዳዊው ሹመቱ የሳቸው ውሳኔ አለመሆኑን ደጋግሞ ተናግረዋል። ግንኙነታቸው መሰናክል የበዛበት ሲሆን ኩማን ሜሲ እና አንቶንዮ ግሪዝማን ካጣ በኋላ እንደገና ቡድኑን ለመገንባት ጊዜ እንዲሰጠው በመጠየቅ መስከረም ላይ መግለጫ አውጥቷል። ከእሁዱ የማድሪድ ሽንፈት በኋላ የኩማን መኪና በአንዳንድ የባርሴሎና ደጋፊዎች ተከቦ የነበረ ሲሆን አሰልጣኙ በኋላም "ያልተማሩ ሰዎች" ሲል አጣጥሏቸዋል። ወደ ራዮ ቫሌካኖ ከማቅናታቸው በፊትም "ማህበራዊ ችግር ነው። ደንቦችን እና እሴቶችን ያልተረዱ ያልተማሩ ሰዎች" ሲል ተናግሯል። | ባርሴሎና አሰልጣኝ ሮናልድ ኩማንን አሰናበተ ሮናልድ ኩማን በኑካምፕ ለ14 ወራት ከዘለቀው የባርሴሎና ዋና አሰልጣኝ ሥራቸው ተባረዋል። ባርሳ በላሊጋው ካደረጋቸው 10 ጨዋታዎች 15 ነጥቦችን ብቻ ሰብስቧል። በዘንድሮው የቻምፒየንስ ሊግ የምድብ ጨዋታዎችም ሁለት ጊዜ ተሸንፏል። ረቡዕ በራዮ ቫሌካኖ ከተሸነፉ በኋላ ከመሪዎቹ በስድስት ነጥብ ርቀው በደረጃ ሰንጠረዡ ላይ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ለባርሳ ሽንፈቱ ባለፉት አራት ጨዋታዎች ሦስተኛው ነው። ባለፈው እሁድ በኤል ክላሲኮ በሪያል ማድሪድ መሸነፋቸው ይታወሳል። የስፔኑ ክለብ ባወጣው መግለጫ "የክለቡ ፕሬዝዳንት ጆአን ላፖርታ ከራዮ ቫሌካኖ ሽንፈት በኋላ ስለ ውሳኔው ለኩማን አሳውቀውታል" ብሏል። "ሮናልድ ኩማን ሐሙስ ዕለት ቡድኑን ይሰናበታሉ።" የ58 አመቱ የቀድሞ የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን፣ የኤቨርተን እና የሳውዝሃምፕተን አሰልጣኝ የአምስት ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒዮናዎቹን ባለፈው የውድድር ዓመት በሊጉ ሦስተኛ ደረጃ ይዘው እንዲጨርሱ አድረጓል። ክለቡ ያጋጠመው ከፍተኛ የገንዘብ ችግር ሆላንዳዊውን አልረዳውም። በዚህ ምክንያት ሊዮኔል ሜሲ ወደ ፓሪስ ሴንት ዠርሜይን እንዲዘዋወር ሆኗል። በክረምቱ ባርሴሎና ለአዳዲስ ፈራሚዎች ምንም ገንዘብ ማውጣትም አልቻለም። ሜምፊስ ዴፓይ፣ ሰርጂዮ አጉዌሮ እና ኤሪክ ጋርሲያ በነጻ ዝውውር ኑ ካመፕ ደርሰዋል። አጥቂው ሉክ ዴ ዮንግ ከሲቪያ በውሰት ተቀላቅሏል። ከረቡዕ ሽንፈት በኋላ ኩማን "[የባርሴሎና ሊግ አቋም] ደህና አለመሆኑን ያሳያል" ብሏል። "ይህ የሚያሳየው ቡድኑ ሚዛኑን አጥቷል፣ በጣም ውጤታማ የሆኑ ተጫዋቾችን አጥቷል። ሌላው የሚያሳየው ደግሞ በቅርብ ዓመታት ሌሎች ክለቦች ሲጠናከሩ እኛ ይህን አላደረግንም።" የኳታሩ ክለብ አል ሳድ አሰልጣኝ የሆነው የቀድሞ የባርሳ አማካይ ዣቪ ኩማንን ለመተካት ከተመረጡት አንዱ ነው። ከእአአ 1987 ወዲህ ባርሳ በተከታታይ ሦስት ጨዋታዎች ከሜዳው ውጪ ጎል ሳያስቆጥር ሲሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ኩማን በመጀመሪያው የውድድር ዘመን የኮፓ ዴልሬይ ዋንጫን ቢያሸንፍም ባርሳ በአትሌቲኮ ማድሪድ እና ሪያል ማድሪድ በላሊጋው ከመበለጡም በላይ ከ2008 በኋላ ዝቅተኛውን ነጥብ ሰብስቦ አጠናቋል። የቀድሞው የኔዘርላንድ የመሃል ተከላካይ እአአ ከ1989 እስ 1995 ለስፔኑ ክለብ ተጫውቶ አራት የሊግ ዋንጫዎችን አንስቷል። በቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆሴፕ ማሪያ ባርቶሜው ዋና አሰልጣኝ ሆኖ ወደ ክለቡ እአአ ነሐሴ 2020 ተመልሷል። አዲሱ ፕሬዝዳንት ላፖርታ ግን የሆላንዳዊው ሹመቱ የሳቸው ውሳኔ አለመሆኑን ደጋግሞ ተናግረዋል። ግንኙነታቸው መሰናክል የበዛበት ሲሆን ኩማን ሜሲ እና አንቶንዮ ግሪዝማን ካጣ በኋላ እንደገና ቡድኑን ለመገንባት ጊዜ እንዲሰጠው በመጠየቅ መስከረም ላይ መግለጫ አውጥቷል። ከእሁዱ የማድሪድ ሽንፈት በኋላ የኩማን መኪና በአንዳንድ የባርሴሎና ደጋፊዎች ተከቦ የነበረ ሲሆን አሰልጣኙ በኋላም "ያልተማሩ ሰዎች" ሲል አጣጥሏቸዋል። ወደ ራዮ ቫሌካኖ ከማቅናታቸው በፊትም "ማህበራዊ ችግር ነው። ደንቦችን እና እሴቶችን ያልተረዱ ያልተማሩ ሰዎች" ሲል ተናግሯል። | https://www.bbc.com/amharic/59074458 |
3politics
| ጠ/ሚንስትሯ በመኖሪያ ቤታቸው ሁለት ሴቶች ከፊል እርቃናቸውን ፎቶ ከተነሱ በኋላ ይቅርታ ጠየቁ | የፊንላንዷ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳና ማሪን በመኖሪያ ቤታቸው ሁለት ሴቶች ከወገባቸው በላይ እርቃናቸውን ሆነው ፎቶግራፍ ከተነሱ በኋላ ይቅርታ ጠየቁ። በጠቅላይ ሚኒስትሯ ቤት ካናቴራ ሳይለብሱ እየተሳሳሙ ፎቶ የተነሱት ሁለት ሴቶች ተዋቂ ሰዎች ናቸው ተብሏል። ሁለቱ ሴቶች ፎቶውን የተነሱት ባለፈው ሐምሌ በጠቅላይ ሚኒስትሯ ቤት በእንግድነት ተጋብዘው ሳለ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሯ ባለፈው ሳምንት ሲደንሱ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምሥል መውጣቱን ተከትሎ ወቀሳ በዝቶባቸው እንደነበር ይታወሳል። የአደንዛዥ እፅ ምርመራ እንዲያደርጉ ተጠይቆ፣ እጽ አለመውሰዳቸው ተረጋግጧል። የሁለቱ ዕውቅ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ሴቶች ፎቶ በስፋት በማኅበራዊ ሚዲያ ተዘዋውሯል። ጠቅላይ ሚኒስትሯ “ፎቶዎቹ አግባብ አይደሉም” ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሯ እንዳሉት ሐምሌ ላይ ከሩስሮክ የሙዚቃ ፌስቲቫል በኋላ ሄልሲንኪ በሚገኘው ቤታቸው ድግስ አዘጋጅተው እንደነበረና ፎቶውም ድግሱ ላይ እንደተነሳ ተናግረዋል። ፎቶው የተነሳው ለእንግዶች በተዘጋጀ መጸዳጃ ቤት እንደሆነ የፊንላንድ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። አንድ ሌላ ፓርቲ ላይ ሲጨፍሩ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምሥል ከወጣ በኋላ የፓርቲያቸው አባሎች እንዲሁም ተቀናቃኞቻቸውም ትችት እየሰነዘሩ ነው። በፓርቲው ላይ አደንዛዥ እፅ ወስደው ሊሆን ይችላል ያሉ አንድ ተቀናቃኝ ፖለቲከኛ ጠቅላይ ሚኒስትሯ እንዲመረመሩ ጠይቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሯ የተወሰነ አልኮል ከመጠጣታቸው ውጪ ድግሱ ላይ አደንዛዥ እፅ እንዳልወሰዱና ወስደውም እንደማያውቁ ተከራክረዋል። ምርመራ ከተደረገላቸውም በኋላ ከአደንዛዥ እፅ ነጻ ሆነው ተገኝተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አኒካ ሳሪኮ፣ በጠቅላይ ሚኒስትሯ ቤት የተነሳው ፎቶ በኑሮ ውድነት የሚንገላቱ የፊንላንድ ዜጎችን ሕይወት እንደማይወክል ገልጸዋል። ሆኖም ግን የሰዎችን የሞራል ዝቅታም ይሁን ከፍታ መተንተን “ቦታዬ አይደለም” ብለዋል። ፊንላንድ ከሩሲያ የሚጓዙ ቱሪስቶች ላይ እንደ አብዛኞቹ የአውሮፓ አገራት ገደብ ጥላለች። ጠቅላይ ሚኒስትሯን ዝነኛ እያደረጋቸው የመጣው ግን ከፖሊሲያቸው በላቀ የአኗኗር ዘያቸው ሆኗል። ፊንላንዳውያን ስለ መሪያቸው የተደበላለቀ ስሜት አላቸው። ተራው የፊንላንድ ዜጋ፣ ጠቅላይ ሚኒስሯ እንደ ማንኛውም በእሳቸው የዕድሜ ክልል ያለ ሰው ዘና ማለታቸውን ይደግፋል። ጫና ከሚበዛበት ሥራቸው ውጪ መደነስና መዝናናት መውደዳቸው የተለመ ነው የሚሉም አሉ። እንዲያውም አብዛኛው ወጣት ከጠቅላይ ሚኒስሯ ጋር የሚያመሳስለኝ ነገር አለ ብሎ እንዲያምን ያደርጋል ሲሉ ይከራከራሉ። እነዚህ ሰዎች ጠቅላይ ሚኒስትሯን ለመደገፍም እየደነሱ ቪድዮ ለጥፈዋል። | ጠ/ሚንስትሯ በመኖሪያ ቤታቸው ሁለት ሴቶች ከፊል እርቃናቸውን ፎቶ ከተነሱ በኋላ ይቅርታ ጠየቁ የፊንላንዷ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳና ማሪን በመኖሪያ ቤታቸው ሁለት ሴቶች ከወገባቸው በላይ እርቃናቸውን ሆነው ፎቶግራፍ ከተነሱ በኋላ ይቅርታ ጠየቁ። በጠቅላይ ሚኒስትሯ ቤት ካናቴራ ሳይለብሱ እየተሳሳሙ ፎቶ የተነሱት ሁለት ሴቶች ተዋቂ ሰዎች ናቸው ተብሏል። ሁለቱ ሴቶች ፎቶውን የተነሱት ባለፈው ሐምሌ በጠቅላይ ሚኒስትሯ ቤት በእንግድነት ተጋብዘው ሳለ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሯ ባለፈው ሳምንት ሲደንሱ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምሥል መውጣቱን ተከትሎ ወቀሳ በዝቶባቸው እንደነበር ይታወሳል። የአደንዛዥ እፅ ምርመራ እንዲያደርጉ ተጠይቆ፣ እጽ አለመውሰዳቸው ተረጋግጧል። የሁለቱ ዕውቅ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ሴቶች ፎቶ በስፋት በማኅበራዊ ሚዲያ ተዘዋውሯል። ጠቅላይ ሚኒስትሯ “ፎቶዎቹ አግባብ አይደሉም” ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሯ እንዳሉት ሐምሌ ላይ ከሩስሮክ የሙዚቃ ፌስቲቫል በኋላ ሄልሲንኪ በሚገኘው ቤታቸው ድግስ አዘጋጅተው እንደነበረና ፎቶውም ድግሱ ላይ እንደተነሳ ተናግረዋል። ፎቶው የተነሳው ለእንግዶች በተዘጋጀ መጸዳጃ ቤት እንደሆነ የፊንላንድ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። አንድ ሌላ ፓርቲ ላይ ሲጨፍሩ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምሥል ከወጣ በኋላ የፓርቲያቸው አባሎች እንዲሁም ተቀናቃኞቻቸውም ትችት እየሰነዘሩ ነው። በፓርቲው ላይ አደንዛዥ እፅ ወስደው ሊሆን ይችላል ያሉ አንድ ተቀናቃኝ ፖለቲከኛ ጠቅላይ ሚኒስትሯ እንዲመረመሩ ጠይቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሯ የተወሰነ አልኮል ከመጠጣታቸው ውጪ ድግሱ ላይ አደንዛዥ እፅ እንዳልወሰዱና ወስደውም እንደማያውቁ ተከራክረዋል። ምርመራ ከተደረገላቸውም በኋላ ከአደንዛዥ እፅ ነጻ ሆነው ተገኝተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አኒካ ሳሪኮ፣ በጠቅላይ ሚኒስትሯ ቤት የተነሳው ፎቶ በኑሮ ውድነት የሚንገላቱ የፊንላንድ ዜጎችን ሕይወት እንደማይወክል ገልጸዋል። ሆኖም ግን የሰዎችን የሞራል ዝቅታም ይሁን ከፍታ መተንተን “ቦታዬ አይደለም” ብለዋል። ፊንላንድ ከሩሲያ የሚጓዙ ቱሪስቶች ላይ እንደ አብዛኞቹ የአውሮፓ አገራት ገደብ ጥላለች። ጠቅላይ ሚኒስትሯን ዝነኛ እያደረጋቸው የመጣው ግን ከፖሊሲያቸው በላቀ የአኗኗር ዘያቸው ሆኗል። ፊንላንዳውያን ስለ መሪያቸው የተደበላለቀ ስሜት አላቸው። ተራው የፊንላንድ ዜጋ፣ ጠቅላይ ሚኒስሯ እንደ ማንኛውም በእሳቸው የዕድሜ ክልል ያለ ሰው ዘና ማለታቸውን ይደግፋል። ጫና ከሚበዛበት ሥራቸው ውጪ መደነስና መዝናናት መውደዳቸው የተለመ ነው የሚሉም አሉ። እንዲያውም አብዛኛው ወጣት ከጠቅላይ ሚኒስሯ ጋር የሚያመሳስለኝ ነገር አለ ብሎ እንዲያምን ያደርጋል ሲሉ ይከራከራሉ። እነዚህ ሰዎች ጠቅላይ ሚኒስትሯን ለመደገፍም እየደነሱ ቪድዮ ለጥፈዋል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cyx8xw7rrj4o |
2health
| የኮሮናቫይረስ በአንዳንድ ምግቦች ላይ ለቀናት እንደሚቆይ ጥናት አረጋገጠ | የኮሮናቫይረስ በተለይም ታሽገው በሚሸጡ ምግቦች ላይ እንደሚቆይ የዩናትድ ኪንግደም ተመራማሪዎች ገለጹ። የአገሪቱ የምግብ ጥራት ኤጀንሲ ባሰራው ጥናት ሳይንቲስቶች ቫይረሱን ሆነ ብለው በተወሰኑ የምግብ ማሸጊያዎች ላይ በማድረግ ሙከራውን አድረገዋል። ይህም በአትክልት እና ፍራፍሬ፣ ኬክ እና ዳቦ እንዲሁም የታሸጉ መጠጦች ሙከራው ተደርጎባቸዋል። ሳይንቲስቶቹ ሳይታጠቡ ወይም ሳይበስሉ ሊበሉ የሚችሉ ምግቦችን በመምረጥ ነው ጥናቱን ያካሄዱት። ነገር ግን ይህ ሸማቾች ላይ የሚያመጣው አደጋ ያነሰ መሆኑን ገልጸዋል። በአብዛኛው የምግብ ምርቶች ላይ ሳይንቲስቶቹ ያስቀመጡት የቫይረስ መጠን በ24 ሰአት ውስጥ ከፍተኛ ማሽቆልቆል ታይቶበታል። ነገር ግን በአንዳንድ ማሸጊያዎች ላይ ቫይረሱ ለአንድ ሳምንት ያህል እንደሚቆይ የሳውዝ ሃምፕተን ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ተናግረዋል። ሳርስ ኮቭ 2 የተሰኘውን የቫይረስ አይነት ወስደው ምርምሩን ያደረጉት አጥኚዎች እንደሚሉት ''እንደዚህ ያለ በንክኪ ብቻ በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰራጭ የቫይረስ አይነትን በተመለከተ ያገኘነው ግኝት ትኩረት የሚገባው ነው'' ሲሉ ተናግረዋል። ሳይንቲስቶች ሸማቾች በተለይም ምግብ በሚያዘጋጁበት ወቅት እጃቸውን እንዲታጠቡ እና በጥሬው የሚበሉ ምግቦችን አጥበው እንዲመገቡ አሳስበዋል። ተመራማሪዎች በጥናታቸው የኮሮናቫይረስ በንክኪ ከሚተላለፈው ይልቅ በምራቅ ፍንጣቂዎች በአየር አማካይነት የበለጥ እንደሚተላለፍ አረጋግጠዋል። ጥናቱ እንዳረጋገጠው ቫይረሱ በተለይም ሸካራ ገጽ ባላቸው እንደ ብሮኮሊ ባሉ አትክልቶች ላይ እንደ ፖም ባሉ ልሙጥ ከሆኑት በበለጠ እንደሚቆዩም አረጋግጧል። ጥናቱ አክሎም ፖም በቅርፊቱ ላይ በያዘው ኬሚካል አማካኝነት በቂቃዎች ወይም በሰዓታት ውስጥ በላዩ ላይ ያረፈውን ቫይረስ መግደል እንደሚጀምርም አረጋግጧል። በኬክ እና ዳቦ ላይ በተደረጉ ሙከራዎችም በአንዳንድ ደረቅ ገጽ በላቸው ኬኮች ላይ ቫይረሱ በሰአታት ውስጥ ቁጥሩ መቀነሱን ተናግረዋል። ለዚህም ምናልባት ኬኮቹ በሚበስሉበት ወቅት እንቁላል ስለሚቀቡ እና ይህም እንቁላል ውስጥ ካለ አሲድ አማካኝነት ሊሆን እንደሚችልም ገልጸዋል። በቺዝ እና ቀዝቃዛ ስጋ ቫይረሱን ለቀናት አንዳንዴም ለሳምንት ሊያቆዩ እንደሚችሉ ተመላክቷል። ኮቪድ በፕላስቲካ እቃዎች ላይ እስከ አንድ ሳምንት ድረስ ሊቆይ ይችላል። በካርቶን ላይ ለተወሰኑ ቀናት ብሎም በአልሙኒየም ማሸጊያዎች ላይ የተወሰኑ ሰአታትን ሊቆይ እንደሚችል ሳይንቲስቶቹ ተናግረዋል። | የኮሮናቫይረስ በአንዳንድ ምግቦች ላይ ለቀናት እንደሚቆይ ጥናት አረጋገጠ የኮሮናቫይረስ በተለይም ታሽገው በሚሸጡ ምግቦች ላይ እንደሚቆይ የዩናትድ ኪንግደም ተመራማሪዎች ገለጹ። የአገሪቱ የምግብ ጥራት ኤጀንሲ ባሰራው ጥናት ሳይንቲስቶች ቫይረሱን ሆነ ብለው በተወሰኑ የምግብ ማሸጊያዎች ላይ በማድረግ ሙከራውን አድረገዋል። ይህም በአትክልት እና ፍራፍሬ፣ ኬክ እና ዳቦ እንዲሁም የታሸጉ መጠጦች ሙከራው ተደርጎባቸዋል። ሳይንቲስቶቹ ሳይታጠቡ ወይም ሳይበስሉ ሊበሉ የሚችሉ ምግቦችን በመምረጥ ነው ጥናቱን ያካሄዱት። ነገር ግን ይህ ሸማቾች ላይ የሚያመጣው አደጋ ያነሰ መሆኑን ገልጸዋል። በአብዛኛው የምግብ ምርቶች ላይ ሳይንቲስቶቹ ያስቀመጡት የቫይረስ መጠን በ24 ሰአት ውስጥ ከፍተኛ ማሽቆልቆል ታይቶበታል። ነገር ግን በአንዳንድ ማሸጊያዎች ላይ ቫይረሱ ለአንድ ሳምንት ያህል እንደሚቆይ የሳውዝ ሃምፕተን ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ተናግረዋል። ሳርስ ኮቭ 2 የተሰኘውን የቫይረስ አይነት ወስደው ምርምሩን ያደረጉት አጥኚዎች እንደሚሉት ''እንደዚህ ያለ በንክኪ ብቻ በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰራጭ የቫይረስ አይነትን በተመለከተ ያገኘነው ግኝት ትኩረት የሚገባው ነው'' ሲሉ ተናግረዋል። ሳይንቲስቶች ሸማቾች በተለይም ምግብ በሚያዘጋጁበት ወቅት እጃቸውን እንዲታጠቡ እና በጥሬው የሚበሉ ምግቦችን አጥበው እንዲመገቡ አሳስበዋል። ተመራማሪዎች በጥናታቸው የኮሮናቫይረስ በንክኪ ከሚተላለፈው ይልቅ በምራቅ ፍንጣቂዎች በአየር አማካይነት የበለጥ እንደሚተላለፍ አረጋግጠዋል። ጥናቱ እንዳረጋገጠው ቫይረሱ በተለይም ሸካራ ገጽ ባላቸው እንደ ብሮኮሊ ባሉ አትክልቶች ላይ እንደ ፖም ባሉ ልሙጥ ከሆኑት በበለጠ እንደሚቆዩም አረጋግጧል። ጥናቱ አክሎም ፖም በቅርፊቱ ላይ በያዘው ኬሚካል አማካኝነት በቂቃዎች ወይም በሰዓታት ውስጥ በላዩ ላይ ያረፈውን ቫይረስ መግደል እንደሚጀምርም አረጋግጧል። በኬክ እና ዳቦ ላይ በተደረጉ ሙከራዎችም በአንዳንድ ደረቅ ገጽ በላቸው ኬኮች ላይ ቫይረሱ በሰአታት ውስጥ ቁጥሩ መቀነሱን ተናግረዋል። ለዚህም ምናልባት ኬኮቹ በሚበስሉበት ወቅት እንቁላል ስለሚቀቡ እና ይህም እንቁላል ውስጥ ካለ አሲድ አማካኝነት ሊሆን እንደሚችልም ገልጸዋል። በቺዝ እና ቀዝቃዛ ስጋ ቫይረሱን ለቀናት አንዳንዴም ለሳምንት ሊያቆዩ እንደሚችሉ ተመላክቷል። ኮቪድ በፕላስቲካ እቃዎች ላይ እስከ አንድ ሳምንት ድረስ ሊቆይ ይችላል። በካርቶን ላይ ለተወሰኑ ቀናት ብሎም በአልሙኒየም ማሸጊያዎች ላይ የተወሰኑ ሰአታትን ሊቆይ እንደሚችል ሳይንቲስቶቹ ተናግረዋል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cn0j54rpdryo |
5sports
| የዓለም ዋንጫ፡ አፍሪካን ስለሚወክሉ አገራት ስድስት ወሳኝ ነጥቦች | በኳታር የዓለም ዋንጫ የሚካፈሉ የአፍሪካ አፍሪካ አገራት አዲስ ታሪክ ጽፈዋል። አምስቱም አገራት በራሳቸው ዜጎች ነው የሚሰለጥኑት። አራቱ አሰልጣኞች በዚህ ውድድር ሲካፈሉ የመጀመሪያቸው ነው። የሴኔጋሉ አሉ ሲሴ ብሔራዊ ቡድኑን ሩሲያ ላይም መምራት ችለዋል። በ2018 አምስቱም የአፍሪካ ተወካዮች ከምድባቸው ማለፍ አልቻሉም። ቢቢሲ ስፖርት አፍሪካ ከእነዚህ ቡድኖች ጋር በተያያዘ የሚነሱ ወሳኝ ጥያቄዎችን ይመልሳል። የአፍሪካ ተወካዮች ፈተና ከየምድባቸው ይጀምራል። ሞሮኮ፣ ሴኔጋል፣ ቱኒዝያ፣ ግብጽ እና ናይጄሪያ ከ2018 የዓለም ዋንጫ ምድብ ጨዋታዎች አልዘለሉም። ካሜሮን እና ጋና ርዕስ ከነበሩበት የ2014 የዓለም ዋንጫ በኋላ ለዘንድሮው ውድድር በቅተዋል። የካሜሮን ተጫዋቾች ሜዳ ላይ ቡጢ ተሰናዘሩ። ጋናዎች ከቦነስ ክፍያ ጋር በተያያዘ ተጋጩ። ሴኔጋሎች ለመጀመሪያ ጊዜ አፍሪካ ሻምፒዮን ከሆኑ በኋላ የሚሳተፉበት የዓለም ዋንጫ ነው። የዓለም ኮከብነትን በሁለተኛነት ያጠናቀቀው ሳዲዮ ማኔ በጉዳት ከቡድኑ ርቋል። ሞሮኮ አዲስ አስልጣኝ ከሾመች ሁለት ወር ብቻ ሆናት። ቤልጂየም፣ ክሮሽያ እና ካናዳ በምድቧ ይገኛሉ። ካሜሮን ፍጥነት እና ጉልበት የቀላቀለ አጨዋወት ስትመርጥ ይስተዋላል። የቀድሞ ኮከቧ እና የአገሪቱ የእግር ኳስ ፌደሬሽን ኃላፊ ሳሙኤል ኤቶ ዋንጫውን ማን ያነሳል ተብሎ ተጠይቆ ሞሮኮ እና ካሜሮን ለፍጻሜ ይደርሳሉ ብሏል። ዋንጫው በሪጎበርት ሶንግ የሚመሩት የማይበገሩት አንበሶች ይሆናል ማለቱ ቡድኑ ላይ ጫና እንዳይፈጠር ተሰግቷል። ሦስት የአፍሪካ አገራት የዓለም ዋንጫው የሩብ ፍጻሜ ደርሰዋል። አሁን ቀዳሚው ዓላማ ግማሽ ፍጻሜ ነው። ሴኔጋል ኮከቧን እና በ34 ጎሎች የብሔራዊ ቡድኑ ጎል አግቢነትን የሚመራውን አጥቂዋን ሳዲዮ ማኔን በጉዳት አጥታለች። ጆርጅ ዊሃ የዓለም ኮከብ የተባለው እአአ በ1995 ነው። ከዚያ ወዲህ በዓለም ኮከብነት ምርጫ ከሦስተኛ በላይ ያለውን ደረጃ ይዞ ማጠናቀቅ የቻለው ማኔ ብቻ ነው። ሴኔጋል አሁን ተስፋ ያደረገችው በዋትፎርዱ ኢስማሊያ ሳር እና በአላንያስፖሩ አጥቂ ፋማራ ዲድሁ ላይ ነው። ቡላዬ ዲያም ሌላው ተስፋዋ ነው። ሲሴ ከሴኔጋል ወርቃማ ትውልድ አባላት አንዱ ናቸው። ቡድኑ በጃፓን እና ኮሪያው የ2002 የዓለም ዋንጫ ስምንት ውስጥ መግባት ችሏል። አሰልጣኙ ለዓመታት ያካበቱትን ልምድ ተጠቅመው አዲስ ዕቅድ እንደሚነድፉ ይጠበቃል። ሞሐመድ ሳላህ እና ሪያድ ማህሬዝ ለትልቁ ውድድር ለመብቃት አልቻሉም። አሁን አዲስ አፍሪካ ኮከብ ፍለጋ መውጣት ግድ ይላል። ከአያክስ ጋር በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ እየፈካ የሚገኘው ጋናዊው አማካኝ ሞሐመድ ኩዱስ ከዕጩዎቹ አንዱ ነው። ካሜሮን ምርጥ የአጥቂ ስብስብ አላት። ኤሪካ ማክሲም ቹፖ-ሞቲንግ፣ ካርል ቶኮ ኤካምቢ እና ቪንሰንት አቡበከር ይጠቀሳሉ። ቱኒዚያውያን ድንቅ በአማካኛቸው አይሳ ላይዱኒ ይተማመናሉ። ሞሮኮ በበኩሏ ሃኪም ዛይችን ይዛለች። ዛይች ከቀድሞ አሰልጣኙ ጋር ባለመግባባቱ ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ ቢያገልም አዲስ አስልጣኝ ሲሾም ሃሳቡን ቀይሮ ለቡድኑ መከታ ለመሆን ተዘጋጅቷል። ይህ ዓለም ዋንጫ እንደ ቀደሞዎቹ ሁሉ ሰኔ ላይ አይካሄድም። ይህም በሞቃታማ ወቅት የሚከናወን የዓለም ዋንጫ ያደርገዋል። የኳታር የአየር ሁኔታ ለአውሮፓዊያን የሚቻል አይመስልም። ምሽት ላይ አየሩ ቀዝቀዝ ይላል። የስታዲየሞች አየር ተመጣጣኝ እንዲሆን ኳታር ተዘጋጅታለች። አፍሪካ ቡድኖች ለማጣሪያው በሚያደርጓቸው ጨዋታዎች እጅግ ሞቃታማ የሆኑ ስታዲየሞችን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር ለመጫወት ይገደዳሉ። ታዲያ ይህ ለኳታሩ ውድድር ይጠቅማቸው ይሆን? ኳታር አረብ ዋንጫን ባለፈው ዓመት አዘጋጅታ ነበር። ለፍጻሜ ቱኒዝያ እና አልጄሪያ ደረሱ። ዋንጫው ወደ አልጀርስ አቀና። ቱኒዝያ ብዙ ደጋፊ ኳታር ላይ እንዳላት ያወቀችበት ውድድር ነው። ከዴንማርክ፣ አውስትራሊያ እና ፈረንሳይ ጋር ስትጫወት በሜዳዋ የመጫወት ያህል ስሜት ትጠብቃለች። ሰሜን አፍሪካ አገራት ወደ ጥሎ ማለፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ለማለፍ ይህን ድጋፍ ይሻሉ። “የአፍሪካ በተለይም የአረብ አገራት በኳታር መጫወት ይጠቅመናል” ያለው የቱኒዝያው አምበል ዋህቢ ካዚር ነው። “በተመሳሳይ ድባብ ውስጥ ነው የምንጫወተው። ብዙ ቱኒዝያውያን ዲያስፖራዎች ኳታር ይኖራሉ። በአረብ ዋንጫ ወቅት ቀዩን ማልያ በለበሱ ደጋፊዎች ስታዲየሞች መሞላታቸውን አስተውለናል። ይህም ይረዳናል” ብሏል። ይህ ለሞሮኮም ይሠራል። አፍሪካ በራሷ ልጆች አሰልጣኝነት በዓለም ዋንጫ የተወከለችው ከ40 ዓመት በፊት አንድ የአህጉሪቱ ተወካይ ብቻ በነበረበት፣ በስፔኑ የዓለም ዋንጫ ወቅት ነበር። ረዥም ጊዜ ያገለገሉት የሴኔጋሉ ሲሴ ሲሆኑ የተሾሙት እአአ በ2015 ነው። ሌሎቹ ዓመትም አልደፈኑም። ቱኒዝያ (ጃሌል ካድሪ)፣ ጋና (ኦቶ አዶ) እና ካሜሩን (ሶንግ) ከአፍሪካ ዋንጫ መልስ ሹመቱን ያገኙ ናቸው። ሞሮኮ ደግሞ ነሐሴ ላይ ነው ኃላፊነቱን ለዋሊድ ሬግራጉይን ሰጠችው። | የዓለም ዋንጫ፡ አፍሪካን ስለሚወክሉ አገራት ስድስት ወሳኝ ነጥቦች በኳታር የዓለም ዋንጫ የሚካፈሉ የአፍሪካ አፍሪካ አገራት አዲስ ታሪክ ጽፈዋል። አምስቱም አገራት በራሳቸው ዜጎች ነው የሚሰለጥኑት። አራቱ አሰልጣኞች በዚህ ውድድር ሲካፈሉ የመጀመሪያቸው ነው። የሴኔጋሉ አሉ ሲሴ ብሔራዊ ቡድኑን ሩሲያ ላይም መምራት ችለዋል። በ2018 አምስቱም የአፍሪካ ተወካዮች ከምድባቸው ማለፍ አልቻሉም። ቢቢሲ ስፖርት አፍሪካ ከእነዚህ ቡድኖች ጋር በተያያዘ የሚነሱ ወሳኝ ጥያቄዎችን ይመልሳል። የአፍሪካ ተወካዮች ፈተና ከየምድባቸው ይጀምራል። ሞሮኮ፣ ሴኔጋል፣ ቱኒዝያ፣ ግብጽ እና ናይጄሪያ ከ2018 የዓለም ዋንጫ ምድብ ጨዋታዎች አልዘለሉም። ካሜሮን እና ጋና ርዕስ ከነበሩበት የ2014 የዓለም ዋንጫ በኋላ ለዘንድሮው ውድድር በቅተዋል። የካሜሮን ተጫዋቾች ሜዳ ላይ ቡጢ ተሰናዘሩ። ጋናዎች ከቦነስ ክፍያ ጋር በተያያዘ ተጋጩ። ሴኔጋሎች ለመጀመሪያ ጊዜ አፍሪካ ሻምፒዮን ከሆኑ በኋላ የሚሳተፉበት የዓለም ዋንጫ ነው። የዓለም ኮከብነትን በሁለተኛነት ያጠናቀቀው ሳዲዮ ማኔ በጉዳት ከቡድኑ ርቋል። ሞሮኮ አዲስ አስልጣኝ ከሾመች ሁለት ወር ብቻ ሆናት። ቤልጂየም፣ ክሮሽያ እና ካናዳ በምድቧ ይገኛሉ። ካሜሮን ፍጥነት እና ጉልበት የቀላቀለ አጨዋወት ስትመርጥ ይስተዋላል። የቀድሞ ኮከቧ እና የአገሪቱ የእግር ኳስ ፌደሬሽን ኃላፊ ሳሙኤል ኤቶ ዋንጫውን ማን ያነሳል ተብሎ ተጠይቆ ሞሮኮ እና ካሜሮን ለፍጻሜ ይደርሳሉ ብሏል። ዋንጫው በሪጎበርት ሶንግ የሚመሩት የማይበገሩት አንበሶች ይሆናል ማለቱ ቡድኑ ላይ ጫና እንዳይፈጠር ተሰግቷል። ሦስት የአፍሪካ አገራት የዓለም ዋንጫው የሩብ ፍጻሜ ደርሰዋል። አሁን ቀዳሚው ዓላማ ግማሽ ፍጻሜ ነው። ሴኔጋል ኮከቧን እና በ34 ጎሎች የብሔራዊ ቡድኑ ጎል አግቢነትን የሚመራውን አጥቂዋን ሳዲዮ ማኔን በጉዳት አጥታለች። ጆርጅ ዊሃ የዓለም ኮከብ የተባለው እአአ በ1995 ነው። ከዚያ ወዲህ በዓለም ኮከብነት ምርጫ ከሦስተኛ በላይ ያለውን ደረጃ ይዞ ማጠናቀቅ የቻለው ማኔ ብቻ ነው። ሴኔጋል አሁን ተስፋ ያደረገችው በዋትፎርዱ ኢስማሊያ ሳር እና በአላንያስፖሩ አጥቂ ፋማራ ዲድሁ ላይ ነው። ቡላዬ ዲያም ሌላው ተስፋዋ ነው። ሲሴ ከሴኔጋል ወርቃማ ትውልድ አባላት አንዱ ናቸው። ቡድኑ በጃፓን እና ኮሪያው የ2002 የዓለም ዋንጫ ስምንት ውስጥ መግባት ችሏል። አሰልጣኙ ለዓመታት ያካበቱትን ልምድ ተጠቅመው አዲስ ዕቅድ እንደሚነድፉ ይጠበቃል። ሞሐመድ ሳላህ እና ሪያድ ማህሬዝ ለትልቁ ውድድር ለመብቃት አልቻሉም። አሁን አዲስ አፍሪካ ኮከብ ፍለጋ መውጣት ግድ ይላል። ከአያክስ ጋር በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ እየፈካ የሚገኘው ጋናዊው አማካኝ ሞሐመድ ኩዱስ ከዕጩዎቹ አንዱ ነው። ካሜሮን ምርጥ የአጥቂ ስብስብ አላት። ኤሪካ ማክሲም ቹፖ-ሞቲንግ፣ ካርል ቶኮ ኤካምቢ እና ቪንሰንት አቡበከር ይጠቀሳሉ። ቱኒዚያውያን ድንቅ በአማካኛቸው አይሳ ላይዱኒ ይተማመናሉ። ሞሮኮ በበኩሏ ሃኪም ዛይችን ይዛለች። ዛይች ከቀድሞ አሰልጣኙ ጋር ባለመግባባቱ ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ ቢያገልም አዲስ አስልጣኝ ሲሾም ሃሳቡን ቀይሮ ለቡድኑ መከታ ለመሆን ተዘጋጅቷል። ይህ ዓለም ዋንጫ እንደ ቀደሞዎቹ ሁሉ ሰኔ ላይ አይካሄድም። ይህም በሞቃታማ ወቅት የሚከናወን የዓለም ዋንጫ ያደርገዋል። የኳታር የአየር ሁኔታ ለአውሮፓዊያን የሚቻል አይመስልም። ምሽት ላይ አየሩ ቀዝቀዝ ይላል። የስታዲየሞች አየር ተመጣጣኝ እንዲሆን ኳታር ተዘጋጅታለች። አፍሪካ ቡድኖች ለማጣሪያው በሚያደርጓቸው ጨዋታዎች እጅግ ሞቃታማ የሆኑ ስታዲየሞችን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር ለመጫወት ይገደዳሉ። ታዲያ ይህ ለኳታሩ ውድድር ይጠቅማቸው ይሆን? ኳታር አረብ ዋንጫን ባለፈው ዓመት አዘጋጅታ ነበር። ለፍጻሜ ቱኒዝያ እና አልጄሪያ ደረሱ። ዋንጫው ወደ አልጀርስ አቀና። ቱኒዝያ ብዙ ደጋፊ ኳታር ላይ እንዳላት ያወቀችበት ውድድር ነው። ከዴንማርክ፣ አውስትራሊያ እና ፈረንሳይ ጋር ስትጫወት በሜዳዋ የመጫወት ያህል ስሜት ትጠብቃለች። ሰሜን አፍሪካ አገራት ወደ ጥሎ ማለፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ለማለፍ ይህን ድጋፍ ይሻሉ። “የአፍሪካ በተለይም የአረብ አገራት በኳታር መጫወት ይጠቅመናል” ያለው የቱኒዝያው አምበል ዋህቢ ካዚር ነው። “በተመሳሳይ ድባብ ውስጥ ነው የምንጫወተው። ብዙ ቱኒዝያውያን ዲያስፖራዎች ኳታር ይኖራሉ። በአረብ ዋንጫ ወቅት ቀዩን ማልያ በለበሱ ደጋፊዎች ስታዲየሞች መሞላታቸውን አስተውለናል። ይህም ይረዳናል” ብሏል። ይህ ለሞሮኮም ይሠራል። አፍሪካ በራሷ ልጆች አሰልጣኝነት በዓለም ዋንጫ የተወከለችው ከ40 ዓመት በፊት አንድ የአህጉሪቱ ተወካይ ብቻ በነበረበት፣ በስፔኑ የዓለም ዋንጫ ወቅት ነበር። ረዥም ጊዜ ያገለገሉት የሴኔጋሉ ሲሴ ሲሆኑ የተሾሙት እአአ በ2015 ነው። ሌሎቹ ዓመትም አልደፈኑም። ቱኒዝያ (ጃሌል ካድሪ)፣ ጋና (ኦቶ አዶ) እና ካሜሩን (ሶንግ) ከአፍሪካ ዋንጫ መልስ ሹመቱን ያገኙ ናቸው። ሞሮኮ ደግሞ ነሐሴ ላይ ነው ኃላፊነቱን ለዋሊድ ሬግራጉይን ሰጠችው። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c03nz6g2rndo |
5sports
| ብራዚል ለሴት የብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ከወንዶች እኩል መክፈል ጀመረች | የብራዚል ሴት ብሔራዊ ቡድን እግር ኳስ ተጫዋቾች ከእንግዲህ ከወንድ እግር ኳስ ተጨዋቾች እኩል እንደሚከፈላቸው የብራዚል እግር ኳስ ማኅበር አስታወቀ። ይህ ብቻም ሳይሆን ሁሉም ተጨዋቾች፣ ጉርሻ እና የሽልማት ገንዘብ እንዲሁም በልምምድ ላይ ሳሉ የሚሰጣቸው የኪስ ገንዘብ በሙሉ ከወንዶች ጋር እኩል እንዲሆን ተወስኗል። የማኅበሩ ፕሬዝዳንት ሮጄሪዮ ካቦክሎ እንዳሉት ይህ ውሳኔ የተላለፈው ባለፈው መጋቢት ወር ነው። ብራዚል የወሰችውን ዓይነት እርምጃ እንግሊዝም ከባለፈው ጥር ጀምሮ ተግባራዊ አድርጋለች። የእንግሊዝ እግር ኳስ ማኅበር ቃል አቀባይ እንዳሉት ሴቶች ከወንዶች እኩል ደመወዝም ሆነ ጥቅማ ጥቅም ያገኛሉ። ብራዚል ለዓለም ዋንጫም ሆነ ለኦሎምፒክ ተወዳዳሪዎቿ በክፍያ ረገድ የጾታ መድልዎን አስቀርታለች። እስካሁን አውስትራሊያ፣ ኖርዌይ እና ኒውዚላንድ ለሴት ተጨዋቾች ከወንዶች እኩል እንዲከፈላቸው ቀድመው የወሰኑት አገራት ናቸው። የብራዚል የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከባለፈው መጋቢት ጀምሮ ምንም ዓይነት ውድድር አላደረገም። ምክንያቱ ደግሞ የኮሮና ወረርሽኝ እየተስፋፋ በመሄዱ ነው። ብራዚል በተህዋሲው የተያዙ ዜጎቿ ቁጥር ከአሜሪካና ከሕንድ ቀጥሎ ከዓለም 3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። | ብራዚል ለሴት የብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ከወንዶች እኩል መክፈል ጀመረች የብራዚል ሴት ብሔራዊ ቡድን እግር ኳስ ተጫዋቾች ከእንግዲህ ከወንድ እግር ኳስ ተጨዋቾች እኩል እንደሚከፈላቸው የብራዚል እግር ኳስ ማኅበር አስታወቀ። ይህ ብቻም ሳይሆን ሁሉም ተጨዋቾች፣ ጉርሻ እና የሽልማት ገንዘብ እንዲሁም በልምምድ ላይ ሳሉ የሚሰጣቸው የኪስ ገንዘብ በሙሉ ከወንዶች ጋር እኩል እንዲሆን ተወስኗል። የማኅበሩ ፕሬዝዳንት ሮጄሪዮ ካቦክሎ እንዳሉት ይህ ውሳኔ የተላለፈው ባለፈው መጋቢት ወር ነው። ብራዚል የወሰችውን ዓይነት እርምጃ እንግሊዝም ከባለፈው ጥር ጀምሮ ተግባራዊ አድርጋለች። የእንግሊዝ እግር ኳስ ማኅበር ቃል አቀባይ እንዳሉት ሴቶች ከወንዶች እኩል ደመወዝም ሆነ ጥቅማ ጥቅም ያገኛሉ። ብራዚል ለዓለም ዋንጫም ሆነ ለኦሎምፒክ ተወዳዳሪዎቿ በክፍያ ረገድ የጾታ መድልዎን አስቀርታለች። እስካሁን አውስትራሊያ፣ ኖርዌይ እና ኒውዚላንድ ለሴት ተጨዋቾች ከወንዶች እኩል እንዲከፈላቸው ቀድመው የወሰኑት አገራት ናቸው። የብራዚል የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከባለፈው መጋቢት ጀምሮ ምንም ዓይነት ውድድር አላደረገም። ምክንያቱ ደግሞ የኮሮና ወረርሽኝ እየተስፋፋ በመሄዱ ነው። ብራዚል በተህዋሲው የተያዙ ዜጎቿ ቁጥር ከአሜሪካና ከሕንድ ቀጥሎ ከዓለም 3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። | https://www.bbc.com/amharic/54054552 |
5sports
| ሹራ ቂጣታ፡ “የለንደን ማራቶንን ያሸነፍኩት በቀነኒሳ ምክር ነው” | ከትናንት በስቲያ እሁድ ዕለት በተካሄደው የለንደን ማራቶንን በማሸነፍ ዓለምን ያስደነቀው አትሌት ሹራ ቂጣታ የድሉ ምክንያት የአትሌት ቀነኒሳ በቀለ ምክር መሆኑን ለቢቢሲ ተናገረ። ሹራ ከውድድሩ በፊት ከአትሌት ቀነኒሳ በቀለ ጋር ልምምድ ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውሶ፤ ቀነኒሳ እግሩ ላይ ባጋጠመው ጉዳት በውድድሩ ሳይሳተፍ መቅረቱን ያስታውሳል። "ከውድድሩ በፊት ቀነኒሳ ብዙ ምክር ለግሶኛል። ቀድመህ ወጥተህ እንዳትመራ፣ እራስህን እየጠበክ እሩጥ፣ ከፊት ሆነህ ከንፋስ ጋር አትጋፈጥ፣ ውሃም በደንብ ውሰድ፣ ውሃ ልታነሳ ስትል ደግሞ ከሌሎች ሯጮች ጋር እንዳትጋጭ ተጠንቀቅ ብሎ መክሮኛል" በማለት ከአትሌት ቀነኒሳ ያገኘውን ምክር ያስረዳል። • ቀነኒሳ በቀለ በጉዳት ምክንያት ከለንደን ማራቶን ራሱን አገለለ • ኢትዮጵያዊው ሹራ ቂጣታ በለንደን ማራቶን ማሸነፍ ዓለምን አስደመመ • ''ምን እንደተፈጠረ አልገባኝም" አትሌት ሃጎስ ገ/ሕይወት "እኔም እሱ እንዳለኝ ነበር ያደረኩት። ወደፊትም የወጣሁት እሱ በነገረኝ ኪሎ ሜትር ላይ ነው። በዚህ ምክንያት ነው ውድድሩን ማሸነፍ የቻልኩት" በማለት አትሌት ሹራ ውድድሩን በድል ለማጠናቀቅ የአትሌት ቀነኒሳን ምክር ወሳኝ እንደነበር ለቢቢሲ ተናግሯል። የዚህ ዓመቱ የለንደን ማራቶን ላይ በኢትዮጵያዊው ቀነኒሳ በቀለና በበኬንያዊው ኢሉድ ኪፕቾጌ መካከል የሚደረገውን ፉክክር ዓለም በጉጉት እየተጠባበቀ በነበረበት በመጨረሻው ሰዓት ላይ ቀነኒሳ ባቱ ላይ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት በውድድሩ ዋዜማ ከውድድሩ መውጣቱ ይታወሳል። ከውድድሩ በፊት የለንደን ማራቶንን ያሸንፋል ተብሎ በስፋት ተጠብቆ የነበረው የርቀቱ የክብረ ወሰን ባለቤት ኬኒያዊው ኤሊዩድ ኪፕቼጌ ነበር። ይሁን እንጂ የተጠበቀው ሳይሆን ቀርቶ ኪፕቼጎ 8ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል። "ሚዲያው ሲያወራና ሲያስተላልፍ የነበረው ስለ እነኪፕቾጌ ነበር" ያለው ሹራ፤ ይህን ውድድር ለማሸነፍ እልህ አስጨራሽ ዝግጅት ሲያደርግ እንደነበረ ለቢቢሲ ገልጿል። "ወድድሩ ከባድ ነበር። የአየር ሁኔታውም ዝናባማ ነበር። ጠንካራ አትሌቶችም ነበሩበት፤ ይሁን እንጂ 80 በመቶ ውድድሩን እንዳሸንፍ የሚያስችለኝን ጠንካራ ዝግጅት አድርጌ ስለነበረ ለድል በቅቻለሁ" ሲል አትሌት ሹራ ቂጣታ ያደረገውን ዝግጅት ተናግሯል። ኬኒያዊው አትሌት ኪፕቾጌ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ በውድድሩ ለመሸነፉ ዋነኛ ምክንያት በውድድሩ ላይ እያለ በጆሮው ላይ ባጋጠመው እክል ምክንያት መሆኑን አስፍሮ ነበር። "ከ25ኛው ኪሎ ሜትር በኋላ ጆሮዬ ተደፍኖ አልከፈት አለኝ። ስፖርት እንዲህ ነው። ሽንፈትን ተቀብለን በቀጣይ ለማሸነፍ ማተኮር አለብን" ያለው አትሌት ኪፕቾጌ ለተደረገለት ድጋፍ ምስጋናውን አቅርቧል። አትሌት ኪፕቾጌ በውድድሩ ለመሸነፉ ዋነኛው ምክንያት ጆሮው መደፈኑ መሆኑን በገለፀበት ጽሁፉ አስተያየት መስጫ ሥር በአትሌት ሹራ ስም በተከፈተ ገጽ ምክንያቱን የሚያጣጥል ምላሽ ተሰጥቶ በርካቶች ሲጋሩት ነበር። ይህንን በተመለከተ በቢቢሲ የተጠየቀው አትሌት ሹራ፤ ውድድሩ ከተጠናቀቀ በኋላም ከኪፕቾጌ ጋር እንዳልተገናኙ እንዲሁም ከኪፕቾጌ የፌስቡክ ጽሑፍ ሥር በስሙ የተሰጠው አስተያየት የእርሱ አለመሆኑን ተናግሯል። የ2018 ለንደን ማራቶን በ2ኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው አትሌት ሹራ ቂጣታ የዚህ ዓመቱ የማራቶን ድል "ትልቅ ደስታ እና መነሳሳትን ፈጥሮልኛል" ብሏል። "በሽልማት በኩል ለውድድሩ አሸናፊው የተሰጠው ከነበረው የሽልማት መጠን የዘንድሮ በ50 በመቶ ቀንሷል። 30 ሺህ ዶላር አካባቢ ነው የተሸለምኩት። ሌሎች ሽልማቶችም ይኖራሉ" ሲል አትሌት ሹራ ቂጣታ ለቢቢሲ ተናግሯል። በሹራ ቂጣታ አሸናፊነት የተጠናቀቀው የለንደኑ የወንዶች ማራቶን ውድድር ላይ ኢትዮጵያውያን ሯጮች በበላይነት አጠናቀዋል። በዚህም መሰረት በውድድሩ ሁለተኛ ከወጣው ኬንያዊው ቪንሰንት ኪፕቹምባ ውጪ ከአንድ አስከ ስድስተኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ ያጠናቀቁት ኢትዮጵያውያን ናቸው። አሸናፊው ሹራ ቂጣታ፣ ሦስተኛ ሲሳይ ለማ፣ አራተኛ ሞሰነት ገረመው፣ አምስተኛ ሙሌ ዋሲሁን እና ስድስተኛ ታምራት ቶላ ተከታትለው በመግባት አሸናፊ መሆናቸው ይታወቃል። | ሹራ ቂጣታ፡ “የለንደን ማራቶንን ያሸነፍኩት በቀነኒሳ ምክር ነው” ከትናንት በስቲያ እሁድ ዕለት በተካሄደው የለንደን ማራቶንን በማሸነፍ ዓለምን ያስደነቀው አትሌት ሹራ ቂጣታ የድሉ ምክንያት የአትሌት ቀነኒሳ በቀለ ምክር መሆኑን ለቢቢሲ ተናገረ። ሹራ ከውድድሩ በፊት ከአትሌት ቀነኒሳ በቀለ ጋር ልምምድ ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውሶ፤ ቀነኒሳ እግሩ ላይ ባጋጠመው ጉዳት በውድድሩ ሳይሳተፍ መቅረቱን ያስታውሳል። "ከውድድሩ በፊት ቀነኒሳ ብዙ ምክር ለግሶኛል። ቀድመህ ወጥተህ እንዳትመራ፣ እራስህን እየጠበክ እሩጥ፣ ከፊት ሆነህ ከንፋስ ጋር አትጋፈጥ፣ ውሃም በደንብ ውሰድ፣ ውሃ ልታነሳ ስትል ደግሞ ከሌሎች ሯጮች ጋር እንዳትጋጭ ተጠንቀቅ ብሎ መክሮኛል" በማለት ከአትሌት ቀነኒሳ ያገኘውን ምክር ያስረዳል። • ቀነኒሳ በቀለ በጉዳት ምክንያት ከለንደን ማራቶን ራሱን አገለለ • ኢትዮጵያዊው ሹራ ቂጣታ በለንደን ማራቶን ማሸነፍ ዓለምን አስደመመ • ''ምን እንደተፈጠረ አልገባኝም" አትሌት ሃጎስ ገ/ሕይወት "እኔም እሱ እንዳለኝ ነበር ያደረኩት። ወደፊትም የወጣሁት እሱ በነገረኝ ኪሎ ሜትር ላይ ነው። በዚህ ምክንያት ነው ውድድሩን ማሸነፍ የቻልኩት" በማለት አትሌት ሹራ ውድድሩን በድል ለማጠናቀቅ የአትሌት ቀነኒሳን ምክር ወሳኝ እንደነበር ለቢቢሲ ተናግሯል። የዚህ ዓመቱ የለንደን ማራቶን ላይ በኢትዮጵያዊው ቀነኒሳ በቀለና በበኬንያዊው ኢሉድ ኪፕቾጌ መካከል የሚደረገውን ፉክክር ዓለም በጉጉት እየተጠባበቀ በነበረበት በመጨረሻው ሰዓት ላይ ቀነኒሳ ባቱ ላይ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት በውድድሩ ዋዜማ ከውድድሩ መውጣቱ ይታወሳል። ከውድድሩ በፊት የለንደን ማራቶንን ያሸንፋል ተብሎ በስፋት ተጠብቆ የነበረው የርቀቱ የክብረ ወሰን ባለቤት ኬኒያዊው ኤሊዩድ ኪፕቼጌ ነበር። ይሁን እንጂ የተጠበቀው ሳይሆን ቀርቶ ኪፕቼጎ 8ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል። "ሚዲያው ሲያወራና ሲያስተላልፍ የነበረው ስለ እነኪፕቾጌ ነበር" ያለው ሹራ፤ ይህን ውድድር ለማሸነፍ እልህ አስጨራሽ ዝግጅት ሲያደርግ እንደነበረ ለቢቢሲ ገልጿል። "ወድድሩ ከባድ ነበር። የአየር ሁኔታውም ዝናባማ ነበር። ጠንካራ አትሌቶችም ነበሩበት፤ ይሁን እንጂ 80 በመቶ ውድድሩን እንዳሸንፍ የሚያስችለኝን ጠንካራ ዝግጅት አድርጌ ስለነበረ ለድል በቅቻለሁ" ሲል አትሌት ሹራ ቂጣታ ያደረገውን ዝግጅት ተናግሯል። ኬኒያዊው አትሌት ኪፕቾጌ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ በውድድሩ ለመሸነፉ ዋነኛ ምክንያት በውድድሩ ላይ እያለ በጆሮው ላይ ባጋጠመው እክል ምክንያት መሆኑን አስፍሮ ነበር። "ከ25ኛው ኪሎ ሜትር በኋላ ጆሮዬ ተደፍኖ አልከፈት አለኝ። ስፖርት እንዲህ ነው። ሽንፈትን ተቀብለን በቀጣይ ለማሸነፍ ማተኮር አለብን" ያለው አትሌት ኪፕቾጌ ለተደረገለት ድጋፍ ምስጋናውን አቅርቧል። አትሌት ኪፕቾጌ በውድድሩ ለመሸነፉ ዋነኛው ምክንያት ጆሮው መደፈኑ መሆኑን በገለፀበት ጽሁፉ አስተያየት መስጫ ሥር በአትሌት ሹራ ስም በተከፈተ ገጽ ምክንያቱን የሚያጣጥል ምላሽ ተሰጥቶ በርካቶች ሲጋሩት ነበር። ይህንን በተመለከተ በቢቢሲ የተጠየቀው አትሌት ሹራ፤ ውድድሩ ከተጠናቀቀ በኋላም ከኪፕቾጌ ጋር እንዳልተገናኙ እንዲሁም ከኪፕቾጌ የፌስቡክ ጽሑፍ ሥር በስሙ የተሰጠው አስተያየት የእርሱ አለመሆኑን ተናግሯል። የ2018 ለንደን ማራቶን በ2ኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው አትሌት ሹራ ቂጣታ የዚህ ዓመቱ የማራቶን ድል "ትልቅ ደስታ እና መነሳሳትን ፈጥሮልኛል" ብሏል። "በሽልማት በኩል ለውድድሩ አሸናፊው የተሰጠው ከነበረው የሽልማት መጠን የዘንድሮ በ50 በመቶ ቀንሷል። 30 ሺህ ዶላር አካባቢ ነው የተሸለምኩት። ሌሎች ሽልማቶችም ይኖራሉ" ሲል አትሌት ሹራ ቂጣታ ለቢቢሲ ተናግሯል። በሹራ ቂጣታ አሸናፊነት የተጠናቀቀው የለንደኑ የወንዶች ማራቶን ውድድር ላይ ኢትዮጵያውያን ሯጮች በበላይነት አጠናቀዋል። በዚህም መሰረት በውድድሩ ሁለተኛ ከወጣው ኬንያዊው ቪንሰንት ኪፕቹምባ ውጪ ከአንድ አስከ ስድስተኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ ያጠናቀቁት ኢትዮጵያውያን ናቸው። አሸናፊው ሹራ ቂጣታ፣ ሦስተኛ ሲሳይ ለማ፣ አራተኛ ሞሰነት ገረመው፣ አምስተኛ ሙሌ ዋሲሁን እና ስድስተኛ ታምራት ቶላ ተከታትለው በመግባት አሸናፊ መሆናቸው ይታወቃል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54424934 |
0business
| አበባ ምርት፡ በዘንድሮው የፍቅረኞች ቀን ከአበባ ምርት ከፍተኛ ገቢ መገኘቱ ተገለጸ | በዘንድሮው የፍቅረኞች ቀን ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከላከችው የአበባ ምርት ከፍተኛ ገቢ ማግኘቷ ተገለጸ። የኢትዮጵያ አበባ፣ አትክልት እና ፍራፍሬ አምራችና ላኪዎች ማኅበር ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ዘውዴ ኢትዮጵያ በዘንድሮው የፍቅረኞች ቀን 3 ሺህ ቶን አበባ ወደ ውጭ መላኳንና ከዚህም 55 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይህ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በዋጋም በመጠንም ጭማሬ ማሳየቱን የገለጹት ዳይሬክተሩ በዘንድሮው ገበያ የአበባ ዋጋ የ20 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ብለዋል። ለዚህ የተለያዩ ምክንያቶች መኖራቸውን ዳይሬክተሩ ጠቅሰዋል። በአውሮፓ ባጋጠመው የነዳጅ ዋጋ መጨመር ብዙ አበባ አምራቾች የሚጠበቀውን ያህል ማምረት አለመቻላቸው እንዲሁም ከአፍሪካ በተለይ ከኬንያ የሚላከው አበባ ከኮቪድ ጋር በተያያዘ በገጠመው የካርጎ ችግር ምክንያት ብዙ አበባ አለመላኩ የኢትዮጵያ አበባ ተጠቃሚ እንዲሆን ካስቻሉ ምክንያቶች ዋና ዋና ዋናዎቹ መሆናቸውን ዳይሬክተሩ አስረድተዋል። ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ወደ ውጭ ከላከችው የአበባ ምርት 530 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ያገኘች ሲሆን ይህም አገሪቷ ወደ ውጭ ከምትልከው አጠቃላይ ገቢ 15 በመቶ የሚሆነውን እንደሚይዝ አቶ ቴዎድሮስ አስታውሰዋል። በየዓመቱ በአውሮፓውያኑ ፌብሩዋሪ 14 የሚከበረው የቫላንታይንስ ቀን (የፍቅረኞች ቀን) ሰዎች ለፍቅረኛቸው፣ ለትዳር አጋራቸው፣ ለእጮኛቸው አበባ እና ሌሎች ስጦታዎችን በማበርከት ፍቅራቸውን የሚገልጹበት ዕለት ነው። ይህንን ዕለት ጨምሮ እስከ ሰኔ ያሉት ጊዜያት የእናቶች፣ የሴቶች እና የአባቶች ቀን የሚከበሩበት በመሆኑ ከፍተኛ የአበባ ሽያጭ የሚከናወንበት ወቅት ነው። በመሆኑም ከፍቅረኞች ቀን በኋላ ባሉት ጊዜያት ከፍተኛ የአበባ ሽያጭ እንደሚከናወን ይጠበቃል ብለዋል ዳይሬክተሩ። የኢትዮጵያ አበባዎች የሚላኩት ወደየትኞቹ አገራት ነው? የኢትዮጵያ የአበባ ምርቶች በአጠቃላይ ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ መዳረሻ አገራት ይላካሉ። በአሁኑ የፍቅረኞች ቀን በብዛት የተላኩት ወደ አውሮፓ ነው። ኔዘርላንድስ፣ እንግሊዝ፣ ጀርመን ፣ ጣሊያን እና ሌሎችም አገራት። ወደ ሰሜን አሜሪካ እና ካናዳ ፣ ወደ ሩቅ ምሥራቅ ደግሞ ጃፓንና ኮሪያ እንዲሁም አውስትራሊያም ተልከዋል። በዋናነት የኢትዮጵያ የአበባ ምርት ትልቁ መዳረሻ ግን የዓለም የአበባ ንግድ ማዕከል የምትባለው ኔዘርላንድስ እና ጀርመን መሆናቸውን አቶ ቴዎድሮስ ገልጸዋል። ኔዘርላንድስ በዓለም አቀፍ ደረጃ አበባ ከሚያመርቱ እና ከሚልኩ አገራት ግንባር ቀደም ናት። ኔዘርላንድስ ብዙ አበባ ባታመርትም ወደ ውጭ በመላክና ወደ አገር ውስጥ በማስገባት ቀዳሚውን ሥፍራ ትይዛለች። ከዚያም ኮሎምቢያ፣ ኢኳዶር፣ ኬንያ እና ኢትዮጵያ ይከተላሉ። ኢትዮጵያ ከአምስቱ የአበባ አምራችና ላኪ አገራት ተርታ የገባችው ባለፉት ጥቂት ዓመታት ነው የሚሉት ዳይሬክተሩ ምቹ የግብርና አካባቢ፣ በቂ አምራች ኃይል እና የውሃ ኃብት መኖሩ እንዲሁም ለመካከለኛው ምሥራቅ እና ለአውሮፓ ገበያ ምቹ ቦታ ላይ መገኘቷ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድም በማጓጓዙ በኩል ትልቅ ሥራ መስራቱ እዚህ ደረጃ ውስጥ እንድትካተት ያስቻሏት ምክንያቶች ናቸው ብለዋል። አሁን ላይ ያለው የመሬት አቅርቦት ችግር ከተፈታ ከዚህም በላይ የአበባ ምርት ንግዱን ማሻሻል እንደሚቻል ጠቁመዋል። በዚህ ዘርፍ የሚገኘው የውጭ ምንዛሬም በአገሪቷ ውስጥ ያለውን የወጪ እና የገቢ ንግድ ጉድለት ለመሙላት እንደሚያግዝም አክለዋል። ለፍቅረኞች ቀን የሚፈለጉት አበባዎች ምን ዓይነት ናቸው? ለፍቅረኞች ቀን በዋናነት የሚላከው ቀይ አበባ [ ጽጌሬዳ አበባ] ነው። ተፈላጊነቱም ሆነ ዋጋው ከሌሎች የበለጠ ነው። ዘንድሮ 20 በመቶ የዋጋ ጭማሬ አለው። ካርኔሽን እና የበጋ አበባም በዚህ ወቅት ተፈላጊ ሲሆኑ የእነርሱ ግን ጭማሬያቸው 10 በመቶ ነው። አሁን አሁን የፍቅረኞች ቀን በኢትዮጵያ በተለይ በከተሞች አካባቢ በድምቀት እየተከበረ ቢሆንም በአገር ውስጥ ያለው የአበባ ገበያ ግን በዋጋም በመጠንም እዚህ ግባ የሚባል አለመሆኑን አቶ ቴዎድሮስ ገልጸዋል። ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ተቀዛቅዞ የነበረው የኢትዮጵያ የአበባ ንግድ ከግንቦት 2020 ወዲህ ገበያው ተነቃቅቶ ተፈላጊነቱ እየጨመረ መምጣቱን አቶ ቴዎድሮስ አክለዋል። | አበባ ምርት፡ በዘንድሮው የፍቅረኞች ቀን ከአበባ ምርት ከፍተኛ ገቢ መገኘቱ ተገለጸ በዘንድሮው የፍቅረኞች ቀን ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከላከችው የአበባ ምርት ከፍተኛ ገቢ ማግኘቷ ተገለጸ። የኢትዮጵያ አበባ፣ አትክልት እና ፍራፍሬ አምራችና ላኪዎች ማኅበር ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ዘውዴ ኢትዮጵያ በዘንድሮው የፍቅረኞች ቀን 3 ሺህ ቶን አበባ ወደ ውጭ መላኳንና ከዚህም 55 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይህ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በዋጋም በመጠንም ጭማሬ ማሳየቱን የገለጹት ዳይሬክተሩ በዘንድሮው ገበያ የአበባ ዋጋ የ20 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ብለዋል። ለዚህ የተለያዩ ምክንያቶች መኖራቸውን ዳይሬክተሩ ጠቅሰዋል። በአውሮፓ ባጋጠመው የነዳጅ ዋጋ መጨመር ብዙ አበባ አምራቾች የሚጠበቀውን ያህል ማምረት አለመቻላቸው እንዲሁም ከአፍሪካ በተለይ ከኬንያ የሚላከው አበባ ከኮቪድ ጋር በተያያዘ በገጠመው የካርጎ ችግር ምክንያት ብዙ አበባ አለመላኩ የኢትዮጵያ አበባ ተጠቃሚ እንዲሆን ካስቻሉ ምክንያቶች ዋና ዋና ዋናዎቹ መሆናቸውን ዳይሬክተሩ አስረድተዋል። ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ወደ ውጭ ከላከችው የአበባ ምርት 530 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ያገኘች ሲሆን ይህም አገሪቷ ወደ ውጭ ከምትልከው አጠቃላይ ገቢ 15 በመቶ የሚሆነውን እንደሚይዝ አቶ ቴዎድሮስ አስታውሰዋል። በየዓመቱ በአውሮፓውያኑ ፌብሩዋሪ 14 የሚከበረው የቫላንታይንስ ቀን (የፍቅረኞች ቀን) ሰዎች ለፍቅረኛቸው፣ ለትዳር አጋራቸው፣ ለእጮኛቸው አበባ እና ሌሎች ስጦታዎችን በማበርከት ፍቅራቸውን የሚገልጹበት ዕለት ነው። ይህንን ዕለት ጨምሮ እስከ ሰኔ ያሉት ጊዜያት የእናቶች፣ የሴቶች እና የአባቶች ቀን የሚከበሩበት በመሆኑ ከፍተኛ የአበባ ሽያጭ የሚከናወንበት ወቅት ነው። በመሆኑም ከፍቅረኞች ቀን በኋላ ባሉት ጊዜያት ከፍተኛ የአበባ ሽያጭ እንደሚከናወን ይጠበቃል ብለዋል ዳይሬክተሩ። የኢትዮጵያ አበባዎች የሚላኩት ወደየትኞቹ አገራት ነው? የኢትዮጵያ የአበባ ምርቶች በአጠቃላይ ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ መዳረሻ አገራት ይላካሉ። በአሁኑ የፍቅረኞች ቀን በብዛት የተላኩት ወደ አውሮፓ ነው። ኔዘርላንድስ፣ እንግሊዝ፣ ጀርመን ፣ ጣሊያን እና ሌሎችም አገራት። ወደ ሰሜን አሜሪካ እና ካናዳ ፣ ወደ ሩቅ ምሥራቅ ደግሞ ጃፓንና ኮሪያ እንዲሁም አውስትራሊያም ተልከዋል። በዋናነት የኢትዮጵያ የአበባ ምርት ትልቁ መዳረሻ ግን የዓለም የአበባ ንግድ ማዕከል የምትባለው ኔዘርላንድስ እና ጀርመን መሆናቸውን አቶ ቴዎድሮስ ገልጸዋል። ኔዘርላንድስ በዓለም አቀፍ ደረጃ አበባ ከሚያመርቱ እና ከሚልኩ አገራት ግንባር ቀደም ናት። ኔዘርላንድስ ብዙ አበባ ባታመርትም ወደ ውጭ በመላክና ወደ አገር ውስጥ በማስገባት ቀዳሚውን ሥፍራ ትይዛለች። ከዚያም ኮሎምቢያ፣ ኢኳዶር፣ ኬንያ እና ኢትዮጵያ ይከተላሉ። ኢትዮጵያ ከአምስቱ የአበባ አምራችና ላኪ አገራት ተርታ የገባችው ባለፉት ጥቂት ዓመታት ነው የሚሉት ዳይሬክተሩ ምቹ የግብርና አካባቢ፣ በቂ አምራች ኃይል እና የውሃ ኃብት መኖሩ እንዲሁም ለመካከለኛው ምሥራቅ እና ለአውሮፓ ገበያ ምቹ ቦታ ላይ መገኘቷ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድም በማጓጓዙ በኩል ትልቅ ሥራ መስራቱ እዚህ ደረጃ ውስጥ እንድትካተት ያስቻሏት ምክንያቶች ናቸው ብለዋል። አሁን ላይ ያለው የመሬት አቅርቦት ችግር ከተፈታ ከዚህም በላይ የአበባ ምርት ንግዱን ማሻሻል እንደሚቻል ጠቁመዋል። በዚህ ዘርፍ የሚገኘው የውጭ ምንዛሬም በአገሪቷ ውስጥ ያለውን የወጪ እና የገቢ ንግድ ጉድለት ለመሙላት እንደሚያግዝም አክለዋል። ለፍቅረኞች ቀን የሚፈለጉት አበባዎች ምን ዓይነት ናቸው? ለፍቅረኞች ቀን በዋናነት የሚላከው ቀይ አበባ [ ጽጌሬዳ አበባ] ነው። ተፈላጊነቱም ሆነ ዋጋው ከሌሎች የበለጠ ነው። ዘንድሮ 20 በመቶ የዋጋ ጭማሬ አለው። ካርኔሽን እና የበጋ አበባም በዚህ ወቅት ተፈላጊ ሲሆኑ የእነርሱ ግን ጭማሬያቸው 10 በመቶ ነው። አሁን አሁን የፍቅረኞች ቀን በኢትዮጵያ በተለይ በከተሞች አካባቢ በድምቀት እየተከበረ ቢሆንም በአገር ውስጥ ያለው የአበባ ገበያ ግን በዋጋም በመጠንም እዚህ ግባ የሚባል አለመሆኑን አቶ ቴዎድሮስ ገልጸዋል። ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ተቀዛቅዞ የነበረው የኢትዮጵያ የአበባ ንግድ ከግንቦት 2020 ወዲህ ገበያው ተነቃቅቶ ተፈላጊነቱ እየጨመረ መምጣቱን አቶ ቴዎድሮስ አክለዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60377982 |
2health
| ኮቪድ ያሰራጨው የቬትናም ዜጋ አምስት ዓመት ተፈረደበት | አንድ ቬትናማዊ ግለሰብ የኮቪድ-19 መመሪያዎችን በመጣስ እና ቫይረሱን በማሰራጨት ወንጀል ተከስሶ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ የአምስት ዓመት እስር ተፈረደበት። ሊ ቫን ትሪ አደገኛ እና ከሰው ወደ ሰው በቀላሉ የሚተላለፍ በሽታን በስምንት ሰዎች ላይ በማሰራጨት ወንጀል ጥፋተኛ መሆኑን ተከትሎ ነው ፍርድ ቤቱ ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈበት። ግለሰቡ ኮቪድ ካስያዛቸው ሰዎች መካከል አንድ ግለሰብ ህይወቱ አልፏል ተብሏል። እስከ ቅርብ ጊዜያወት ድረስ ቬትናም የኮሮናቫይረስ ስርጭትን በመቆጣጠርና ጥብቅ መሪያዎችን ተግባራዊ በማድረግ ስኬታማ አገር ነበረች። ነገር ግን ከባለፈው ሰኔ ወር ጀምሮ አዲሱ ዴልታ የተሰኘው የቫይረሱ ዝርያ በአገሪቱ መከሰቱን ተከትሎ በርካቶች በቫይረሱ እየተያዙ ነው። እስካሁን ድረስም በቬትናም ከ530 በላይ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 13ሺህ 300 ሰዎቸው ደግሞ ሕይወታቸው አልፏል። ነገር ግን ከዚህ ቁጥር አብዛኛው የተመዘበው ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ መሆኑ ነገሮች ምን ያክል አሳሳቢ ስለመሆናቸው ማሳያ ነው ተብሏል። በስርጭት ደረጃ ደግሞ ሆ ቺ ሚኒ ከተማ ውስጥ በርካቶች በቫይረሱ ተይዘዋል። በሰኔ ወር መጀመሪያ አካባቢ ጥፋተኛ የተባለው የ28 ዓመቱ ሊ ከሆ ቺ ሚኒ ከተማ ተነስቶ ወደ ትውልድ አካባቢው ካ ማው ግዛት በሞተር ሳይክል ተጉዟል። ካ ማው ከደረሰ በኋላ ደግሞ ስለ ጉዞ ታሪኩ እና ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ለተጠየቀው ጥያቄ ሀሰተኛ መረጃ ሰጥቷል፤ በተጨማሪም እራሱን መለየት ሲገባው ይህንን መመሪያ ተግባራዊ አላደረገም። የአካባቢው ባለስልጣናት ከወራት በፊት እንዳስታወቁት ማንኛውም ተጓዥ ወደ ካ ማው ግዛት ሲገባ እራሱን ለ21 ቀናት ላይቶ ማቆየት ግዴታ ነው። ከትንሽ ቆይታ በኋላ ሊ የኮቪድ19 ምርመራ ሲደረግለት በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠ ሲሆን በወቅቱም ቫይረሱን ለቤተሰቡ አባላት እንዲሁም ለህክምና የሄደበት የጤና ማዕከል ውስጥ የሚሰሩ ባለሙያዎችን አስይዟል። ጉዳዩን የተከታተለው ፍርድ ቤትም ግራ ቀኙን ከሰማ በኋላ ሊ አምስት ዓመት እስራት እና 880 ዶላር መቀጮ ፈርዶበታል። | ኮቪድ ያሰራጨው የቬትናም ዜጋ አምስት ዓመት ተፈረደበት አንድ ቬትናማዊ ግለሰብ የኮቪድ-19 መመሪያዎችን በመጣስ እና ቫይረሱን በማሰራጨት ወንጀል ተከስሶ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ የአምስት ዓመት እስር ተፈረደበት። ሊ ቫን ትሪ አደገኛ እና ከሰው ወደ ሰው በቀላሉ የሚተላለፍ በሽታን በስምንት ሰዎች ላይ በማሰራጨት ወንጀል ጥፋተኛ መሆኑን ተከትሎ ነው ፍርድ ቤቱ ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈበት። ግለሰቡ ኮቪድ ካስያዛቸው ሰዎች መካከል አንድ ግለሰብ ህይወቱ አልፏል ተብሏል። እስከ ቅርብ ጊዜያወት ድረስ ቬትናም የኮሮናቫይረስ ስርጭትን በመቆጣጠርና ጥብቅ መሪያዎችን ተግባራዊ በማድረግ ስኬታማ አገር ነበረች። ነገር ግን ከባለፈው ሰኔ ወር ጀምሮ አዲሱ ዴልታ የተሰኘው የቫይረሱ ዝርያ በአገሪቱ መከሰቱን ተከትሎ በርካቶች በቫይረሱ እየተያዙ ነው። እስካሁን ድረስም በቬትናም ከ530 በላይ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 13ሺህ 300 ሰዎቸው ደግሞ ሕይወታቸው አልፏል። ነገር ግን ከዚህ ቁጥር አብዛኛው የተመዘበው ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ መሆኑ ነገሮች ምን ያክል አሳሳቢ ስለመሆናቸው ማሳያ ነው ተብሏል። በስርጭት ደረጃ ደግሞ ሆ ቺ ሚኒ ከተማ ውስጥ በርካቶች በቫይረሱ ተይዘዋል። በሰኔ ወር መጀመሪያ አካባቢ ጥፋተኛ የተባለው የ28 ዓመቱ ሊ ከሆ ቺ ሚኒ ከተማ ተነስቶ ወደ ትውልድ አካባቢው ካ ማው ግዛት በሞተር ሳይክል ተጉዟል። ካ ማው ከደረሰ በኋላ ደግሞ ስለ ጉዞ ታሪኩ እና ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ለተጠየቀው ጥያቄ ሀሰተኛ መረጃ ሰጥቷል፤ በተጨማሪም እራሱን መለየት ሲገባው ይህንን መመሪያ ተግባራዊ አላደረገም። የአካባቢው ባለስልጣናት ከወራት በፊት እንዳስታወቁት ማንኛውም ተጓዥ ወደ ካ ማው ግዛት ሲገባ እራሱን ለ21 ቀናት ላይቶ ማቆየት ግዴታ ነው። ከትንሽ ቆይታ በኋላ ሊ የኮቪድ19 ምርመራ ሲደረግለት በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠ ሲሆን በወቅቱም ቫይረሱን ለቤተሰቡ አባላት እንዲሁም ለህክምና የሄደበት የጤና ማዕከል ውስጥ የሚሰሩ ባለሙያዎችን አስይዟል። ጉዳዩን የተከታተለው ፍርድ ቤትም ግራ ቀኙን ከሰማ በኋላ ሊ አምስት ዓመት እስራት እና 880 ዶላር መቀጮ ፈርዶበታል። | https://www.bbc.com/amharic/58463475 |
3politics
| የአሜሪካ ምክር ቤት አባሉ ከአንድ አፍሪካዊ ባለሀብት ገንዘብ መቀበላቸው ተረጋገጠ | ከአንድ አፍሪካዊ ቢሊየነር የገንዘብ ድጋፍ ስለማግኘታቸው ዋሽተዋል የተባሉ የአሜሪካ ምክር ቤት አባል ከእንደራሴነታቸው ሊባረሩ እንደሚችሉ ተነገረ። ጄፍ ፎርተንቤሪ የተባሉት የኔብራስከካ ግዛት የሪፐብሊካን ፓርቲ ተወካይ፣ ከስኬታማው ናይጄሪያዊ የንግድ ሰው ጊልበርት ቻጉሪ ሕገወጥ የገንዘብ ድጋፍ ስለመቀበላቸው ለአገር ውስጥ የምርመራ ተቋም ኤፍቢአይ መዋሸታቸውን የፌደራል ዳኞች ደርሰውበታል። ከዚህ ጋር ተያይዞ በሦስት ጥፋቶች አስከ 15 ዓመት የሚደርስ የእስር ቅጣት ለፈረድባቸው ይችላል። ይህ ጉዳይም የውጭ ተጽእኖ ፈጣሪዎች በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ ሊያሳድሩ የሚችሉትን ጫና በተመለከተ ከዚህ በፊት የነበረውን ክርክር መልሶ ቀስቅሶታል። ምንም እንኳን የውጭ ዜጎች ለፖለቲካ ጉዳዮች የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ባይፈቀድላቸውም የ75 ዓመቱ ናይጄሪያዊ ቢሊየነር በርካታ የገንዘብ ስጦታዎችን ማበርከታቸው ይነገራል። በዚህም ከአራት ዓመት በፊት ጊልበርት ቻጉሪ የ1.8 ሚሊዮን ዶላር ቅጣት በአሜሪካ መንግሥት የተጣለባቸው ሲሆን፣ የገንዘብ ስጦታውን የተቀበሉ አንዳንድ ሰዎች ላይም ምርመራ ተደርጎባቸዋል። ግለሰቡ እንደ አውሮፓውያኑ በ2016 አሁን ጥፋተኛ ሆነው ለተገኙት የምክር ቤት አባል ጄፍ ፎርተንቤሪ በአንድ ዝግጅት ላይ በሌሎች ለጋሾች በኩል በሕገወጥ መንገድ የ30,000 ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ሰጥተዋል ተብሏል። መቀመጫቸውን ፈረንሳይ ፓሪስ ያደረጉት የኢንደስትሪዎች ባለቤት የሆኑት ናይጄሪያዊው ባለሀብት ከፍ ያለ ዝና አላቸው። በአንድ ወቅት ከእስላማዊው ታጣቂ ቡድን ሔዝቦላህ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው አሜሪካ እንዳይገቡ ቪዛ ተከልክለው ነበር። ባለሀብቱ በ1990ዎቹ የናይጄሪያ ወታደራዊ መሪ የነበሩትና በኋላም በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ከአገሪቱ ካዝና ዘርፈዋል የሚባሉት የጄነራል ሳኒ አባቻ ዋነኛ አማካሪ ነበሩ። ጊልበርት ቻጉሪ ለምን እንደራሴ ጄፍ ፎርተንቤሪን ኢላማ እንዳደረጉ የታወቀ ነገር ባይኖርም የምርመራ ሰነዱ ባለሀብቱ "ብዙም ትኩረት ከማያገኙ ግዛቶች ለሚመጡ ፖለቲከኞች የገንዘብ ድጋፍ እንዲሰጡ" መመከራቸውን ያመለከተ ሲሆን ምክንያቱም ድጋፉ "ትኩረት ያገኛል" የሚል ነው። እንደራሴው 30,000 ዶላር የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያገኙ የሚገልጽ የተቀረጸ የስልክ ውይይት የተገኘ ቢሆንም፣ ለኤፍቢአይ መርማሪዎች ግን ስለገንዘቡ ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ክደዋል። ዐቃቤ ሕግ ክሱን ባስረዳበት ጊዜ የምክር ቤት አባሉ "ሥራቸውን፣ ዝናቸውንና የቅርብ አጋሮቻቸውን ለመከላከል ሲሉ በተደጋጋሚ" ስለገንዘብ ስጦታው ደብቀዋል ብሏል። ሐሙስ እለት ሎስ አንጀለስ ውስጥ ለሁለት ሰዓታት ጉዳዩን የተመለከቱት ዳኞች፣ ጄፍ ፎርተንቤሪን ሐሰተኛ ቃል በመስጠትና እውነትን ከፌደራል መርማሪዎች በመደበቅ ጥፋተኛ ብለዋቸዋል። የምክር ቤት አባሉ ላይ የቅጣት ውሳኔ የሚሰጠው ከወራት በኋላ ሰኔ ላይ ሲሆን፣ አስከዚው ድረስ ግን እንደራሴው በውሳኔው ላይ ይግባኝ እንደሚጠይቁ ተናግረዋል። ይህንን ተከትሎ በአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራቲክና የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት እንደራሴው በፈቃዳቸው ሥራቸውን እንዲለቁ ጥሪ አቅርበዋል። ነገር ግን ጄፍ ፎርተንቤሪን በፈቃዳቸው ከምክር ቤቱ አባልነታቸው የማይለቁ ከሆነ ከእሳቸው በፊት ጥፋተኛ ሆነው የተገኙ የምክር ቤቱ አባላት እንዳጋጠማቸው ከኮንግረሱ ሊባረሩ ይችላሉ። | የአሜሪካ ምክር ቤት አባሉ ከአንድ አፍሪካዊ ባለሀብት ገንዘብ መቀበላቸው ተረጋገጠ ከአንድ አፍሪካዊ ቢሊየነር የገንዘብ ድጋፍ ስለማግኘታቸው ዋሽተዋል የተባሉ የአሜሪካ ምክር ቤት አባል ከእንደራሴነታቸው ሊባረሩ እንደሚችሉ ተነገረ። ጄፍ ፎርተንቤሪ የተባሉት የኔብራስከካ ግዛት የሪፐብሊካን ፓርቲ ተወካይ፣ ከስኬታማው ናይጄሪያዊ የንግድ ሰው ጊልበርት ቻጉሪ ሕገወጥ የገንዘብ ድጋፍ ስለመቀበላቸው ለአገር ውስጥ የምርመራ ተቋም ኤፍቢአይ መዋሸታቸውን የፌደራል ዳኞች ደርሰውበታል። ከዚህ ጋር ተያይዞ በሦስት ጥፋቶች አስከ 15 ዓመት የሚደርስ የእስር ቅጣት ለፈረድባቸው ይችላል። ይህ ጉዳይም የውጭ ተጽእኖ ፈጣሪዎች በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ ሊያሳድሩ የሚችሉትን ጫና በተመለከተ ከዚህ በፊት የነበረውን ክርክር መልሶ ቀስቅሶታል። ምንም እንኳን የውጭ ዜጎች ለፖለቲካ ጉዳዮች የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ባይፈቀድላቸውም የ75 ዓመቱ ናይጄሪያዊ ቢሊየነር በርካታ የገንዘብ ስጦታዎችን ማበርከታቸው ይነገራል። በዚህም ከአራት ዓመት በፊት ጊልበርት ቻጉሪ የ1.8 ሚሊዮን ዶላር ቅጣት በአሜሪካ መንግሥት የተጣለባቸው ሲሆን፣ የገንዘብ ስጦታውን የተቀበሉ አንዳንድ ሰዎች ላይም ምርመራ ተደርጎባቸዋል። ግለሰቡ እንደ አውሮፓውያኑ በ2016 አሁን ጥፋተኛ ሆነው ለተገኙት የምክር ቤት አባል ጄፍ ፎርተንቤሪ በአንድ ዝግጅት ላይ በሌሎች ለጋሾች በኩል በሕገወጥ መንገድ የ30,000 ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ሰጥተዋል ተብሏል። መቀመጫቸውን ፈረንሳይ ፓሪስ ያደረጉት የኢንደስትሪዎች ባለቤት የሆኑት ናይጄሪያዊው ባለሀብት ከፍ ያለ ዝና አላቸው። በአንድ ወቅት ከእስላማዊው ታጣቂ ቡድን ሔዝቦላህ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው አሜሪካ እንዳይገቡ ቪዛ ተከልክለው ነበር። ባለሀብቱ በ1990ዎቹ የናይጄሪያ ወታደራዊ መሪ የነበሩትና በኋላም በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ከአገሪቱ ካዝና ዘርፈዋል የሚባሉት የጄነራል ሳኒ አባቻ ዋነኛ አማካሪ ነበሩ። ጊልበርት ቻጉሪ ለምን እንደራሴ ጄፍ ፎርተንቤሪን ኢላማ እንዳደረጉ የታወቀ ነገር ባይኖርም የምርመራ ሰነዱ ባለሀብቱ "ብዙም ትኩረት ከማያገኙ ግዛቶች ለሚመጡ ፖለቲከኞች የገንዘብ ድጋፍ እንዲሰጡ" መመከራቸውን ያመለከተ ሲሆን ምክንያቱም ድጋፉ "ትኩረት ያገኛል" የሚል ነው። እንደራሴው 30,000 ዶላር የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያገኙ የሚገልጽ የተቀረጸ የስልክ ውይይት የተገኘ ቢሆንም፣ ለኤፍቢአይ መርማሪዎች ግን ስለገንዘቡ ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ክደዋል። ዐቃቤ ሕግ ክሱን ባስረዳበት ጊዜ የምክር ቤት አባሉ "ሥራቸውን፣ ዝናቸውንና የቅርብ አጋሮቻቸውን ለመከላከል ሲሉ በተደጋጋሚ" ስለገንዘብ ስጦታው ደብቀዋል ብሏል። ሐሙስ እለት ሎስ አንጀለስ ውስጥ ለሁለት ሰዓታት ጉዳዩን የተመለከቱት ዳኞች፣ ጄፍ ፎርተንቤሪን ሐሰተኛ ቃል በመስጠትና እውነትን ከፌደራል መርማሪዎች በመደበቅ ጥፋተኛ ብለዋቸዋል። የምክር ቤት አባሉ ላይ የቅጣት ውሳኔ የሚሰጠው ከወራት በኋላ ሰኔ ላይ ሲሆን፣ አስከዚው ድረስ ግን እንደራሴው በውሳኔው ላይ ይግባኝ እንደሚጠይቁ ተናግረዋል። ይህንን ተከትሎ በአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራቲክና የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት እንደራሴው በፈቃዳቸው ሥራቸውን እንዲለቁ ጥሪ አቅርበዋል። ነገር ግን ጄፍ ፎርተንቤሪን በፈቃዳቸው ከምክር ቤቱ አባልነታቸው የማይለቁ ከሆነ ከእሳቸው በፊት ጥፋተኛ ሆነው የተገኙ የምክር ቤቱ አባላት እንዳጋጠማቸው ከኮንግረሱ ሊባረሩ ይችላሉ። | https://www.bbc.com/amharic/news-60881984 |
2health
| 'በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ህሙማን መጨመርን ተክትሎ ኦሚክሮን መግባቱን ለማረጋገጥ የናሙና ምርመራ እየተደረገ ነው' ጤና ሚኒስቴር | በኢትዮጵያ በያዝነው ሳምንት በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ፤ አዲሱ የቫይረሱ ዝርያ ኦሚክሮን ገብቶ ከሆነ ለማረጋገጥ የናሙና ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝ የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ ለቢቢሲ ገለጹ። ባለፈው ሳምንት ከተመረመሩ 53 ሺህ ሰዎች መካከል 8500 በቫይረሱ ሲያዙ፣ 34 ሰዎች ሞተዋል። በተጨማሪም 440 ሰዎች የጽኑ ሕሙማን ክፍል ገብተዋል። ካለፉት ሳምንታት በተለየ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ፤ ኦሚክሮን ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ መሆኑን ለማወቅ የናሙና ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝና ውጤቱ በቀጣይ ሁለት ሳምንታት ውስጥ ይፋ እንደሚደረግ ዶ/ር ደረጄ ተናግረዋል። "እስካሁን የነበረው አካሄድ ጥሩ ነበር። ነገር ግን ከታኅሳስ 7/2014 ዓ. ም. ወዲህ ባሉት ቀናት በየቀኑ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው" ብለዋል። የዛሬ ሳምንት ገደማ ከሚመረመሩ ሰዎች 3% ብቻ ቫይረሱ ይገኝባቸው የነበረ ሲሆን፤ በዚህ ሳምንት ግን ቁጥሩ ወደ 28% እንዳደገ ገልጸዋል። "በሌሎች አገሮች የሚታየው ኦሚክሮን ዝርያ በኢትዮጵያም ምልክቶቹ ታይተዋል። በአስጊ ሁኔታ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል። አሁን ናሙና እየመረመርን ነው። በናሙና እስክናረጋግጥ ድረስ ኦሚክሮን መግባቱን በይፋ ለመናገር ያስቸግራል" ሲሉ ዶ/ር ደረጄ አብራርተዋል። በኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ ከ4 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተመርምረው 382 ሺህ ቫይረሱ ሲገኝባቸው፤ 6880 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል። ኢትዮጵያ ከአጠቃላይ ሕዝቧ ወደ 10 ሚሊዮን ገደማ ዜጎችን ከትባለች። ዶ/ር ደረጄ እንዳሉት፤ የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታት ዜጎች ክትባት እንዲወስዱ ከማበረታታት ባሻገር ከዚህ ቀደም የተከተቡ ሰዎች ማጎልበቻ (ቡስተር) እንዲወስዱ እንደሚደረግም ጠቁመዋል። ከ100 በላይ አገሮች ውስጥ የተገኘው የኦሚክሮን ዝርያ በፍጥነት በመሰራጨት ላይ ነው። በኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ባልታየ ሁኔታ ትናንት ከተመረመሩ 13147 ሰዎች መካከል 3793 ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ጤና ሚኒስትር ገልጿል። "በቫይረሱ በድጋሚ የመያዝ ዕድል አለ። ማኅበረሰቡ ወረርሽኙ 'ውሸት ነው' ወይም 'ለፖለቲካ ነው' ሳይል ክትባት ይውሰድ። ስለ ክትባት ሐሰተኛ ወሬ ማሰራጨት ያቁም። ከዚህ ቀደም እንደነበረው ለሕሙማን አልጋ የጠፋበት ደረጃ እንዳንደርስ ተጠንቀቁ" ሲሉ አሳስበዋል። የጤና ሚኒስቴር የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ከሚወስዳቸው እርምጃዎች መካከል፤ የጤና ባለሙያዎች በአስገዳጅ ሁኔታ ክትባት እንዲወስዱ ማድረግ እንዲሁም ያልተከተቡ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ የመንግሥት የነጻ ሕክምና ተጠቃሚ እንይሆኑ ማድረግ መሆኑን ዶ/ር ደረጄ ጠቅሰዋል። "አሁን ላይ ከሚመረመሩት ሰዎች አንድ ሦስተኛው ቫይረሱ እየተገኘባቸው ስለሆነ የጥንቃቄ እርምጃ መወሰድ አለበት። ማኅበረሰቡ ማስክ ማድረግ፣ ክትባት መከተብም ይገባዋል" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። የጤና ሚኒስቴር የወረርሽኙን ስረጭት ለመከላከል የሚያወጣቸውን ሕጎች በማስተግበር ረገድ ሕግ አስፈጻሚው አካል ኃላፊነቱን እንዲወጣም አሳስበዋል። በተጨማሪም የጥንቃቄ እርምጃዎችን ማኅበረሰቡ እንዲተገብር ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት እስከ ቀበሌ የሚወርድ ንቅናቄ እንደሚደረግ ጠቁመዋል። ለገና በዓል ከሚመጡ ዳያስፖራዎች ጋር በተያያዘ የምርመራ ውጤት እና የክትባት ሰርተፍኬት ከማረጋገጥ አንስቶ ክትባቱን አገር ውስጥ እስከማቅረብ ድረስ እንደሚዘጋጁ ዶ/ር ደረጄ ተናግረዋል። | 'በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ህሙማን መጨመርን ተክትሎ ኦሚክሮን መግባቱን ለማረጋገጥ የናሙና ምርመራ እየተደረገ ነው' ጤና ሚኒስቴር በኢትዮጵያ በያዝነው ሳምንት በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ፤ አዲሱ የቫይረሱ ዝርያ ኦሚክሮን ገብቶ ከሆነ ለማረጋገጥ የናሙና ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝ የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ ለቢቢሲ ገለጹ። ባለፈው ሳምንት ከተመረመሩ 53 ሺህ ሰዎች መካከል 8500 በቫይረሱ ሲያዙ፣ 34 ሰዎች ሞተዋል። በተጨማሪም 440 ሰዎች የጽኑ ሕሙማን ክፍል ገብተዋል። ካለፉት ሳምንታት በተለየ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ፤ ኦሚክሮን ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ መሆኑን ለማወቅ የናሙና ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝና ውጤቱ በቀጣይ ሁለት ሳምንታት ውስጥ ይፋ እንደሚደረግ ዶ/ር ደረጄ ተናግረዋል። "እስካሁን የነበረው አካሄድ ጥሩ ነበር። ነገር ግን ከታኅሳስ 7/2014 ዓ. ም. ወዲህ ባሉት ቀናት በየቀኑ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው" ብለዋል። የዛሬ ሳምንት ገደማ ከሚመረመሩ ሰዎች 3% ብቻ ቫይረሱ ይገኝባቸው የነበረ ሲሆን፤ በዚህ ሳምንት ግን ቁጥሩ ወደ 28% እንዳደገ ገልጸዋል። "በሌሎች አገሮች የሚታየው ኦሚክሮን ዝርያ በኢትዮጵያም ምልክቶቹ ታይተዋል። በአስጊ ሁኔታ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል። አሁን ናሙና እየመረመርን ነው። በናሙና እስክናረጋግጥ ድረስ ኦሚክሮን መግባቱን በይፋ ለመናገር ያስቸግራል" ሲሉ ዶ/ር ደረጄ አብራርተዋል። በኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ ከ4 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተመርምረው 382 ሺህ ቫይረሱ ሲገኝባቸው፤ 6880 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል። ኢትዮጵያ ከአጠቃላይ ሕዝቧ ወደ 10 ሚሊዮን ገደማ ዜጎችን ከትባለች። ዶ/ር ደረጄ እንዳሉት፤ የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታት ዜጎች ክትባት እንዲወስዱ ከማበረታታት ባሻገር ከዚህ ቀደም የተከተቡ ሰዎች ማጎልበቻ (ቡስተር) እንዲወስዱ እንደሚደረግም ጠቁመዋል። ከ100 በላይ አገሮች ውስጥ የተገኘው የኦሚክሮን ዝርያ በፍጥነት በመሰራጨት ላይ ነው። በኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ባልታየ ሁኔታ ትናንት ከተመረመሩ 13147 ሰዎች መካከል 3793 ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ጤና ሚኒስትር ገልጿል። "በቫይረሱ በድጋሚ የመያዝ ዕድል አለ። ማኅበረሰቡ ወረርሽኙ 'ውሸት ነው' ወይም 'ለፖለቲካ ነው' ሳይል ክትባት ይውሰድ። ስለ ክትባት ሐሰተኛ ወሬ ማሰራጨት ያቁም። ከዚህ ቀደም እንደነበረው ለሕሙማን አልጋ የጠፋበት ደረጃ እንዳንደርስ ተጠንቀቁ" ሲሉ አሳስበዋል። የጤና ሚኒስቴር የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ከሚወስዳቸው እርምጃዎች መካከል፤ የጤና ባለሙያዎች በአስገዳጅ ሁኔታ ክትባት እንዲወስዱ ማድረግ እንዲሁም ያልተከተቡ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ የመንግሥት የነጻ ሕክምና ተጠቃሚ እንይሆኑ ማድረግ መሆኑን ዶ/ር ደረጄ ጠቅሰዋል። "አሁን ላይ ከሚመረመሩት ሰዎች አንድ ሦስተኛው ቫይረሱ እየተገኘባቸው ስለሆነ የጥንቃቄ እርምጃ መወሰድ አለበት። ማኅበረሰቡ ማስክ ማድረግ፣ ክትባት መከተብም ይገባዋል" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። የጤና ሚኒስቴር የወረርሽኙን ስረጭት ለመከላከል የሚያወጣቸውን ሕጎች በማስተግበር ረገድ ሕግ አስፈጻሚው አካል ኃላፊነቱን እንዲወጣም አሳስበዋል። በተጨማሪም የጥንቃቄ እርምጃዎችን ማኅበረሰቡ እንዲተገብር ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት እስከ ቀበሌ የሚወርድ ንቅናቄ እንደሚደረግ ጠቁመዋል። ለገና በዓል ከሚመጡ ዳያስፖራዎች ጋር በተያያዘ የምርመራ ውጤት እና የክትባት ሰርተፍኬት ከማረጋገጥ አንስቶ ክትባቱን አገር ውስጥ እስከማቅረብ ድረስ እንደሚዘጋጁ ዶ/ር ደረጄ ተናግረዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59778547 |
0business
| በፈረንሳይ ሲኒማዎች ላይ የሲጃራ ጭስ ለምን ያለቅጥ ይንቦለቦላል? | ሰፊ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው የፈረንሳይ ፊልም ኢንዱስትሪ በሲጃራ ጭስ የታፈነ ይመስላል። የጸረ ትምባሆ አቀንቃኞች ይህ ሁኔታ ይከነክናቸዋል። አንዳንድ ጊዜም ያስቆጣቸዋል። እውነት አላቸው። በምድራችን ላይ ሲጃራ በፈረንሳይ ሲኒማ የሚታየውን ያህል በየትኛውም ዓለም አይታይም። ሆሊውድንም ቦሊውድንም ጨምሮ። በቁጥር እናስደግፈው? በአማካይ በማንኛውም የፈረንሳይ ሲኒማ ውስጥ የማጨስ ትዕይንት 2 ደቂቃ ከ6 ሰኮንዶች ይይዛል። ይህ አማካይ አሐዝ ነው። ይህ ማለት ስድስት ራሳቸውን የቻሉ ማስታወቂያዎች የሚሄድበት ሰዓት ማለት ነው። በሌላ አነጋገር የፈረንሳይ ሲኒማ በጭስ ተደብቆ ያለ ነው የሚመስለው። የፈረንሳይ ጸረ ካንሰር ማኅበር ነው እዚህ ስሌት ላይ ደምሮና ቀንሶ የደረሰበት። ብቻ ምን አለፋችሁ ትምባሆ ለፈረንሳይ ሲኒማ ደምና አጥንት ሆኗል ይላሉ አንድ የማኅበሩ ባልደረባ። ይህ የሲጃራ ትዕይንቶች ድግግሞሽ በተለያየ መልኩ የሚገለጽ ነው። ለምሳሌ በቀጥታ ተዋንያን ሲያጨሱ መታየት፣ ወይም በሲጃራ ዙርያ ሲወያዩ መስማት፣ ወይም በሌላ። አደጋው ሥነ ልቦናዊ ነው። በሁሉም ሲኒማዎች ቅንጡና ዘናጭ አጫሽ ተዋንያን በቄንጥ ትምባሆ ሲያንበለብሉ የሚያዩ ሰዎች ቀስ በቀስ ነገሩን የዝመና መገለጫ አድርገው ሊወስዱት ይችላሉ። የቀድሞ የፈረንሳይ ሲኒማ ሴት ከዋክብት የነበሩት ጂን ሞሪ እና ብሪጊት ባርዶት ሲጃራቸውን በቄንጥ ሲያጨሱ ማየት ለዓመታት የቀጠለ ከትዝታ የማይጠፋ ምሥል ነው። ከ2015 እስከ 2019 ብቻ በተሠሩ ፊልሞች ላይ በተሠራ አንድ መደበኛ ጥናት 150 ፊልሞች ላይ በቄንጥ የማጤስ ትዕይንት ይታያል። ይህ ታዲያ ማጨስን ብቻ ሳይሆን ትንባሆን የሚያጅቡ ቁሳቁሶች ለምሳሌ እንደ አሽትሬይና መለኮሻ ላይተርን ሊያካትት ይችላል። ለምሳሌ ተዋናዮች ስለ ሲጃራ በአንድም ሆነ በሌላ አመጻድቀው ሲያወሩ የሚያሳዩ ትዕይንቶችን የሚጨምር ነው። ለመሆኑ ተመልካቾች የሲጃራ ትዕይንቶችን ሲመለከቱ ምን ይሰማቸዋል? አንድ የቅርብ ጊዜ ጥናት እንዳመለከተው በነዚህ ፊልሞች ላይ 60 ከመቶ የሚሆኑ ተመልካቾች በትዕይንቱ እንደተማረኩ አምነዋል። በፈረንሳይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአንጻራዊ ሁኔታ ሲጃራ አጫሽ ቀንሷል። ያም ሆኖ ሲጃራና ሲጃራ ማጨስ በሲኒማዎች ውስጥ አሁንም እንደ ትኩስ ፋሽን እየተንሰራፋ ነው። በፈረንሳይ በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ ከአንድ ሚሊዮን ዜጎች በላይ ማጨስ እንዳቆሙ በቅርብ ጊዜ ተዘግቦ ነበር። ሲኒማው ግን ይህን አያንጸባርቅም። አንዳንድ ጊዜ ፊልሞች መሬት ላይ ካለው እውነታም በላይ ሲጃራና ማጨስን በልዩ ሁኔታ ሲያዳንቁት መታየቱ አስገራሚ የሆነውም ለዚሁ ነው። "ይህ ሁኔታ ማጨስን ጤናማ አድርገው ሰዎች እንዲረዱት የሚያደርግ ነው" ይላሉ የማኅበሩ ባልደረባ። አሁን የጸረ ትንባሆና የጸረ ካንሰር ማኅበራት እየጠየቁ ያሉት የፈረንሳይ መንግሥት የሲጃራ ትዕይንት ያለቅጥ የሚያሳዩ ሲኒማዎችን በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ አደብ እንዲያሲዛቸው ነው። አንዱ አደብ ማስያዣ መንገድ በርካታ የሲጃራ ማጨስና ከዚያ ጋር ተያያዥ የሆኑ ትዕይንቶች ላሉባቸው ፊልሞች ለሲኒማ የሚሰጠውን ድጎማ እየቆረጡ መቅጣት ሊሆን ይችላል። ማቲው ካዞቪትዝ በፈረንሳይ ሥመ ጥር የፊልም ዳይሬክተር ናቸው። ይህን ሐሳብ ፈጽሞ አይቀበሉትም። "ፊልሞች የኅብረተሰብ ተምሳሌት ለመሆን አይደለም የሚሠሩት። ፊልሞች የሚሠሩት የኅብረተሰቡን ኑሮ ለማንጸባረቅ ነው" ይላሉ። የሲጃራ ትዕይንት በሲኒማ ላይ ይቀነስ የሚለው ሐሳብ ከንቱና ጸረ ኪናዊ እንደሆነ ተሟግተዋል። በተለያዩ ጊዜ የተጠኑ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከየትኛውም አገር በላይ በፈረንሳይ ሲኒማዎች የትምባሆ ትዕይንቶች ይስተዋላሉ። በአሜሪካ ከ2010 እስከ 2018 ብቻ በወጡ ሲኒማዎች 46 ከመቶ የሚሆኑት አንድ ገጸ ባህሪ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ሲያጨስ ወይም ከሲጃራ ጋር የተያያዘ ተግባር ሲከውን ይታያል። የፈረንሳይ የፊልም ፕሮዲውሰሮች ማኅበር ምክትል ፕሬዝዳንት ዣቪየር ሪጎልት የሲጃራ ትዕይንት በሚያሳዩ ፊልሞች ላይ መንግሥት ቁጥጥር ያድርግ የሚለው ዘመቻ መስመር ያለፈ ነው ብለዋል። "መስመር ያለፈ ብቻ ሳይሆን የፈጠራ ነጻነትንም የሚጋፋ ነው" ይላሉ። ዣቪየር ጨምረው ሲኒማ ስለ ኅብረተሰቡ ምናገባው፤ ኅብረተሰብ ለማስተማር አይደለም ፊልም የምንሠራው ብለዋል። በ60ዎቹ የገነነው የፈንሳይ ሲኒማ በጭስ ተደብቆም ተወዳጅነቱ ቀጥሏል። በሲጃራም ያለ ሲጃራም። | በፈረንሳይ ሲኒማዎች ላይ የሲጃራ ጭስ ለምን ያለቅጥ ይንቦለቦላል? ሰፊ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው የፈረንሳይ ፊልም ኢንዱስትሪ በሲጃራ ጭስ የታፈነ ይመስላል። የጸረ ትምባሆ አቀንቃኞች ይህ ሁኔታ ይከነክናቸዋል። አንዳንድ ጊዜም ያስቆጣቸዋል። እውነት አላቸው። በምድራችን ላይ ሲጃራ በፈረንሳይ ሲኒማ የሚታየውን ያህል በየትኛውም ዓለም አይታይም። ሆሊውድንም ቦሊውድንም ጨምሮ። በቁጥር እናስደግፈው? በአማካይ በማንኛውም የፈረንሳይ ሲኒማ ውስጥ የማጨስ ትዕይንት 2 ደቂቃ ከ6 ሰኮንዶች ይይዛል። ይህ አማካይ አሐዝ ነው። ይህ ማለት ስድስት ራሳቸውን የቻሉ ማስታወቂያዎች የሚሄድበት ሰዓት ማለት ነው። በሌላ አነጋገር የፈረንሳይ ሲኒማ በጭስ ተደብቆ ያለ ነው የሚመስለው። የፈረንሳይ ጸረ ካንሰር ማኅበር ነው እዚህ ስሌት ላይ ደምሮና ቀንሶ የደረሰበት። ብቻ ምን አለፋችሁ ትምባሆ ለፈረንሳይ ሲኒማ ደምና አጥንት ሆኗል ይላሉ አንድ የማኅበሩ ባልደረባ። ይህ የሲጃራ ትዕይንቶች ድግግሞሽ በተለያየ መልኩ የሚገለጽ ነው። ለምሳሌ በቀጥታ ተዋንያን ሲያጨሱ መታየት፣ ወይም በሲጃራ ዙርያ ሲወያዩ መስማት፣ ወይም በሌላ። አደጋው ሥነ ልቦናዊ ነው። በሁሉም ሲኒማዎች ቅንጡና ዘናጭ አጫሽ ተዋንያን በቄንጥ ትምባሆ ሲያንበለብሉ የሚያዩ ሰዎች ቀስ በቀስ ነገሩን የዝመና መገለጫ አድርገው ሊወስዱት ይችላሉ። የቀድሞ የፈረንሳይ ሲኒማ ሴት ከዋክብት የነበሩት ጂን ሞሪ እና ብሪጊት ባርዶት ሲጃራቸውን በቄንጥ ሲያጨሱ ማየት ለዓመታት የቀጠለ ከትዝታ የማይጠፋ ምሥል ነው። ከ2015 እስከ 2019 ብቻ በተሠሩ ፊልሞች ላይ በተሠራ አንድ መደበኛ ጥናት 150 ፊልሞች ላይ በቄንጥ የማጤስ ትዕይንት ይታያል። ይህ ታዲያ ማጨስን ብቻ ሳይሆን ትንባሆን የሚያጅቡ ቁሳቁሶች ለምሳሌ እንደ አሽትሬይና መለኮሻ ላይተርን ሊያካትት ይችላል። ለምሳሌ ተዋናዮች ስለ ሲጃራ በአንድም ሆነ በሌላ አመጻድቀው ሲያወሩ የሚያሳዩ ትዕይንቶችን የሚጨምር ነው። ለመሆኑ ተመልካቾች የሲጃራ ትዕይንቶችን ሲመለከቱ ምን ይሰማቸዋል? አንድ የቅርብ ጊዜ ጥናት እንዳመለከተው በነዚህ ፊልሞች ላይ 60 ከመቶ የሚሆኑ ተመልካቾች በትዕይንቱ እንደተማረኩ አምነዋል። በፈረንሳይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአንጻራዊ ሁኔታ ሲጃራ አጫሽ ቀንሷል። ያም ሆኖ ሲጃራና ሲጃራ ማጨስ በሲኒማዎች ውስጥ አሁንም እንደ ትኩስ ፋሽን እየተንሰራፋ ነው። በፈረንሳይ በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ ከአንድ ሚሊዮን ዜጎች በላይ ማጨስ እንዳቆሙ በቅርብ ጊዜ ተዘግቦ ነበር። ሲኒማው ግን ይህን አያንጸባርቅም። አንዳንድ ጊዜ ፊልሞች መሬት ላይ ካለው እውነታም በላይ ሲጃራና ማጨስን በልዩ ሁኔታ ሲያዳንቁት መታየቱ አስገራሚ የሆነውም ለዚሁ ነው። "ይህ ሁኔታ ማጨስን ጤናማ አድርገው ሰዎች እንዲረዱት የሚያደርግ ነው" ይላሉ የማኅበሩ ባልደረባ። አሁን የጸረ ትንባሆና የጸረ ካንሰር ማኅበራት እየጠየቁ ያሉት የፈረንሳይ መንግሥት የሲጃራ ትዕይንት ያለቅጥ የሚያሳዩ ሲኒማዎችን በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ አደብ እንዲያሲዛቸው ነው። አንዱ አደብ ማስያዣ መንገድ በርካታ የሲጃራ ማጨስና ከዚያ ጋር ተያያዥ የሆኑ ትዕይንቶች ላሉባቸው ፊልሞች ለሲኒማ የሚሰጠውን ድጎማ እየቆረጡ መቅጣት ሊሆን ይችላል። ማቲው ካዞቪትዝ በፈረንሳይ ሥመ ጥር የፊልም ዳይሬክተር ናቸው። ይህን ሐሳብ ፈጽሞ አይቀበሉትም። "ፊልሞች የኅብረተሰብ ተምሳሌት ለመሆን አይደለም የሚሠሩት። ፊልሞች የሚሠሩት የኅብረተሰቡን ኑሮ ለማንጸባረቅ ነው" ይላሉ። የሲጃራ ትዕይንት በሲኒማ ላይ ይቀነስ የሚለው ሐሳብ ከንቱና ጸረ ኪናዊ እንደሆነ ተሟግተዋል። በተለያዩ ጊዜ የተጠኑ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከየትኛውም አገር በላይ በፈረንሳይ ሲኒማዎች የትምባሆ ትዕይንቶች ይስተዋላሉ። በአሜሪካ ከ2010 እስከ 2018 ብቻ በወጡ ሲኒማዎች 46 ከመቶ የሚሆኑት አንድ ገጸ ባህሪ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ሲያጨስ ወይም ከሲጃራ ጋር የተያያዘ ተግባር ሲከውን ይታያል። የፈረንሳይ የፊልም ፕሮዲውሰሮች ማኅበር ምክትል ፕሬዝዳንት ዣቪየር ሪጎልት የሲጃራ ትዕይንት በሚያሳዩ ፊልሞች ላይ መንግሥት ቁጥጥር ያድርግ የሚለው ዘመቻ መስመር ያለፈ ነው ብለዋል። "መስመር ያለፈ ብቻ ሳይሆን የፈጠራ ነጻነትንም የሚጋፋ ነው" ይላሉ። ዣቪየር ጨምረው ሲኒማ ስለ ኅብረተሰቡ ምናገባው፤ ኅብረተሰብ ለማስተማር አይደለም ፊልም የምንሠራው ብለዋል። በ60ዎቹ የገነነው የፈንሳይ ሲኒማ በጭስ ተደብቆም ተወዳጅነቱ ቀጥሏል። በሲጃራም ያለ ሲጃራም። | https://www.bbc.com/amharic/news-57271010 |
3politics
| ኢራናውያን አዲስ ፕሬዝዳንት ለመምረጥ ድምጽ እየሰጡ ነው | ሐሰን ሩሃኒን የሚተኩ ፕሬዝዳንት ለመምረጥ ኢራናውያን ዛሬ አርብ ድምጽ እሰጡ ነው። ከሕዝብ በተሰበሰበ አስተያየት መሠረት የፍትህ ሥርዓቱን በበላይነት የሚመሩት ወግ አጥባቂ የሺአ መሪ ኢብራሂም ራይሲ ያሸንፋሉ ተብሎ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷቸዋል። የቀድሞው ማዕከላዊ ባንክ ገዥ አብዶልናስር ሄማቲ ተቀናቃኛቸው ናቸው። በርካታ ተፎካካሪዎች እንዳይወዳደሩ መታገዳቸው ራይስን ያለ ከባድ ተፎካካሪ እንዳስቀራቸው በመጥቀስ ተቃዋሚዎች እና አንዳንድ የለውጥ አራማጆች ሕዝቡ እንዳእመርጥ ጥሪ አቅርበዋል። ሐይማኖታዊው መሪ አያቶላህ አሊ ካሜኒ አርብ ማለዳ ዋና ከተማዋ ቴህራን ውስጥ ድምጻቸውን ከሰጡ በኋላ ሰዎች እንዲመርጡ አበረታተዋል። "እያንዳንዱ ድምጽ ዋጋ አለው። ይምጡና ፕሬዝዳንትዎን ይምረጡ። ይህ ለአገርዎ የወደፊት ዕጣ ፈንታ አስፈላጊ ነው" ብለዋል። አሜሪካ ከሦስት ዓመት በፊት ከኢራን ጋር የደረሰችውን የኒኩሌር ስምምነትን ወደ ጎን አድርጋ ማዕቀቦችን ወደነበሩበት ከመለሰችበት ጊዜ ጀምሮ በደረሰው የኢኮኖሚ ችግር ምክንያት በኢራናውያን ዘንድ ሰፊ ቅሬታ አለ። ከተፎካካሪዎቹ አንዱ ቢያሸንፉ በኢራን እና በዓለም ኃያላን መካከል ስምምነቱን እንደገና ለማደስ ዓላማ ያደረገው ድርድር ያደናቅፋል ተብሎ አይታሰብም። ለዘብተኛው ሩሃኒ ከምዕራባውያን ጋር ለመግባባት ይፈልጉ የነበረ ቢሆንም ለሁለት ተከታታይ አራት ዓመታት የሥልጣን ጊዜያቸውን በማጠናቀቃቸውን በድጋሚ መወዳደር አይችሉም። ዕጩዎቹን ማን አፀደቀ? 40 የሚሆኑ ሴቶችን ጨምሮ ወደ 600 የሚጠጉ ለፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር ዕጩ ሆነው ተመዝግበዋል። የዕጩ ተወዳዳሪዎችን ብቃት በተመለከተ የመጨረሻ ውሳኔ ያለው ያልተመረጠ አካል ሲሆን 12 የሕግ ባለሙያዎች እና የሐይማኖት ምሁራንን የያዘ ነው። በዚህ አካል ሰባት ዕጩዎች ለፕሬዝዳንትነት እንዲወዳደሩ ፈቃድ ሰጠቷል። እንዲወዳደሩ ካልተፈቀደላቸው ታዋቂ ዕጩዎች መካከል የሩሃኒ የመጀመሪያው ምክትል ፕሬዝዳንት ኢሻቅ ጃሃንጊሪ እና ወግ አጥባቂውና የፓርላማ አፈ ጉባኤ የነበሩት አሊ ላሪጃኒ ይገኙበታል። ሐሙስ ድረስ እንዲወዳደሩ ከተፈቀደላቸው ዕጩዎች መካከል ሦስቱ (የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ጸሐፊው ሰዒድ ጃሊሊ፣ የፓርላማ አባሉ አሊሬዛ ዛካኒ እና የለውጥ አራማጁና የቀድሞ ምክትል ፕሬዝዳንት ሞህሰን መህላራሊዛዴህ) ራሳቸውን አግልለዋል። ጠንካራ አቋም ያላቸው ጃሊሊ እና ዛካኒ ሁለቱም ራይስን ደግፈው የቆሙ ሲሆን መህላራሊዛዴህ ደግሞ የውጥ ኃይሉን "አንድ ለማድረግ" እንደሚፈልጉ ተናግረዋል። ይህም ለሔማቲ ግልጽ ድጋፍ መስጠት ነው ተብሏል። አንድ ተወዳዳሪ በአንደኛው ዙር ከ50 በመቶ በላይ ድምጽ ካላገኘ ሁለተኛ ዙር ምርጫ ይካሄዳል። በውድድሩ እነማን ይሳተፋሉ? ኢብራሂም ራይሲ የ60 ዓመቱ ሐይማኖታዊ መሪ አብዛኛውን የሥራ ዘመናቸውን በዐቃቤ ሕግነት አገልግለዋል። ባለፈው ምርጫ በሩሃኒ ከተሸነፉ ከሁለት ዓመታት በኋላ እአአ በ2019 የፍትህ ዋና ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል። ራይስ ሙስናን ለመዋጋት እና የኢራንን ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት የተሻሉት ሰው እንደሆኑ እያስረዱ ነው። ብዙ ኢራናውያን እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በ1980 ዎቹ በፖለቲካ እስረኞች የጅምላ ግድያ ላይ ሚና አለቸው በማለት ስጋታቸውን ገልጸዋል። አብዶልናሰር ሔማቲ የ64 ዓመቱ ባለሙያ እአአ በ2018 የኢራን ማዕከላዊ ባንክ ገዢ የነበሩ ሲሆን ዕጩ ከሆኑ በኋላ ግን ከኃላፊነት ተነስተዋል። በሩሃኒ እና በቀድሞው ፕሬዝዳንት መሐሙድ አህመዲነጃድ ስር መሾማቸው በኢራን ያሉትን ሁሉንም አንጃዎች በጋራ የማሠራት ብቃት እንዳለቸው ማስረጃ ተደርጎ ታይቷል። የአሜሪካ ማዕቀብ የኢራን ገንዘብ ምንዛሬ ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ለማቃለል ባለመቻላቸው ከሌሎቹ ዕጩዎች ትችት እንዲደርስባቸው ምክንያት ሆኗል። ሞህሲን ረዛይ የ66 ዓመቱ ረዛይ መንፈሳዊውን መሪ በበላይነት የሚያማክሩና በሕግ ጉዳዮች ላይ በሚነሱ አለመግባባቶች የመጨረሻ የመዳኘት ስልጣን ያላቸው የምክር ቤት ጸሐፊ ናቸው። እአአ ከ1988-88 በኢራን እና ኢራቅ ጦርነት ወቅት የእስላማዊው አብዮታዊ ዘብ ቡድን አዛዥ ነበሩ። መከላከያ ኃይሉን ከለቀቁ በኋላ ለሦስት ጊዜያት ለፕሬዝዳንትነት ዕጩ ሆነው ተወዳድረዋል። አሚርሆሴን ቀዚዛዴህ ሃሸሚ አሚርሆሴን ቃዚዛዴህ ሃሸሚ የአንገት በላይ የቀዶ ጥገና ሐኪም ናቸው። ከ2008 ጀምሮ የፓርላማ አባል የነበሩ ሲሆን ከግንቦት ወዲህ ደግሞ ተቀዳሚ አፈ-ጉባኤ ናቸው። የ50 ዓመቱ ዕጩ ከተወዳዳሪዎቹ መካከል በዕድሜ ትንሹ ናቸው። የሕዝብ ተሳትፎ ለምን አስፈላጊ ሆነ? 80 ሚሊዮን ሕዝብ ባላት ኢራን 59 ሚሊዮን ያህል ሰዎች ድምጽ ለመስጠት ብቁ ናቸው። በ2017ቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተሳታፊዎች 73 በመቶ ቢሆንም በመንግሥት በሚደገፈው የኢራን ሰቱደንትስ ፖሊንግ ኤጀንሲ ባደረገው ጥናት ግን በአርቡ ምርጫ 42 በመቶዎቹ ብቻ ሊሳተፉ እንደሚችሉ ጠቁሟል። ይህ እአአ ከ1979ቱ እስላማዊ አብዮት በኋላ በኢራን ከተደረጉት ምርጫዎች ይህ ዝቅተኛ ተሳትፎ የሚኖረው ሲሆን ተመራጩም የመራጮች ቁጥርን እንደ ድጋፍ ስለሚያየው ችግር ሊደቅን ይችላል። ሩሃኒ ሐሙስ ለኢራናውያንን "የተቋም ወይም የቡድን ጉድለቶች" ድምጽ ከመስጠት እንዳያስቆሟቸው ነግረዋቸዋል። "ለጊዜው ስለነገ ለቅሬታዎች አናስብ" ብለዋል። | ኢራናውያን አዲስ ፕሬዝዳንት ለመምረጥ ድምጽ እየሰጡ ነው ሐሰን ሩሃኒን የሚተኩ ፕሬዝዳንት ለመምረጥ ኢራናውያን ዛሬ አርብ ድምጽ እሰጡ ነው። ከሕዝብ በተሰበሰበ አስተያየት መሠረት የፍትህ ሥርዓቱን በበላይነት የሚመሩት ወግ አጥባቂ የሺአ መሪ ኢብራሂም ራይሲ ያሸንፋሉ ተብሎ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷቸዋል። የቀድሞው ማዕከላዊ ባንክ ገዥ አብዶልናስር ሄማቲ ተቀናቃኛቸው ናቸው። በርካታ ተፎካካሪዎች እንዳይወዳደሩ መታገዳቸው ራይስን ያለ ከባድ ተፎካካሪ እንዳስቀራቸው በመጥቀስ ተቃዋሚዎች እና አንዳንድ የለውጥ አራማጆች ሕዝቡ እንዳእመርጥ ጥሪ አቅርበዋል። ሐይማኖታዊው መሪ አያቶላህ አሊ ካሜኒ አርብ ማለዳ ዋና ከተማዋ ቴህራን ውስጥ ድምጻቸውን ከሰጡ በኋላ ሰዎች እንዲመርጡ አበረታተዋል። "እያንዳንዱ ድምጽ ዋጋ አለው። ይምጡና ፕሬዝዳንትዎን ይምረጡ። ይህ ለአገርዎ የወደፊት ዕጣ ፈንታ አስፈላጊ ነው" ብለዋል። አሜሪካ ከሦስት ዓመት በፊት ከኢራን ጋር የደረሰችውን የኒኩሌር ስምምነትን ወደ ጎን አድርጋ ማዕቀቦችን ወደነበሩበት ከመለሰችበት ጊዜ ጀምሮ በደረሰው የኢኮኖሚ ችግር ምክንያት በኢራናውያን ዘንድ ሰፊ ቅሬታ አለ። ከተፎካካሪዎቹ አንዱ ቢያሸንፉ በኢራን እና በዓለም ኃያላን መካከል ስምምነቱን እንደገና ለማደስ ዓላማ ያደረገው ድርድር ያደናቅፋል ተብሎ አይታሰብም። ለዘብተኛው ሩሃኒ ከምዕራባውያን ጋር ለመግባባት ይፈልጉ የነበረ ቢሆንም ለሁለት ተከታታይ አራት ዓመታት የሥልጣን ጊዜያቸውን በማጠናቀቃቸውን በድጋሚ መወዳደር አይችሉም። ዕጩዎቹን ማን አፀደቀ? 40 የሚሆኑ ሴቶችን ጨምሮ ወደ 600 የሚጠጉ ለፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር ዕጩ ሆነው ተመዝግበዋል። የዕጩ ተወዳዳሪዎችን ብቃት በተመለከተ የመጨረሻ ውሳኔ ያለው ያልተመረጠ አካል ሲሆን 12 የሕግ ባለሙያዎች እና የሐይማኖት ምሁራንን የያዘ ነው። በዚህ አካል ሰባት ዕጩዎች ለፕሬዝዳንትነት እንዲወዳደሩ ፈቃድ ሰጠቷል። እንዲወዳደሩ ካልተፈቀደላቸው ታዋቂ ዕጩዎች መካከል የሩሃኒ የመጀመሪያው ምክትል ፕሬዝዳንት ኢሻቅ ጃሃንጊሪ እና ወግ አጥባቂውና የፓርላማ አፈ ጉባኤ የነበሩት አሊ ላሪጃኒ ይገኙበታል። ሐሙስ ድረስ እንዲወዳደሩ ከተፈቀደላቸው ዕጩዎች መካከል ሦስቱ (የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ጸሐፊው ሰዒድ ጃሊሊ፣ የፓርላማ አባሉ አሊሬዛ ዛካኒ እና የለውጥ አራማጁና የቀድሞ ምክትል ፕሬዝዳንት ሞህሰን መህላራሊዛዴህ) ራሳቸውን አግልለዋል። ጠንካራ አቋም ያላቸው ጃሊሊ እና ዛካኒ ሁለቱም ራይስን ደግፈው የቆሙ ሲሆን መህላራሊዛዴህ ደግሞ የውጥ ኃይሉን "አንድ ለማድረግ" እንደሚፈልጉ ተናግረዋል። ይህም ለሔማቲ ግልጽ ድጋፍ መስጠት ነው ተብሏል። አንድ ተወዳዳሪ በአንደኛው ዙር ከ50 በመቶ በላይ ድምጽ ካላገኘ ሁለተኛ ዙር ምርጫ ይካሄዳል። በውድድሩ እነማን ይሳተፋሉ? ኢብራሂም ራይሲ የ60 ዓመቱ ሐይማኖታዊ መሪ አብዛኛውን የሥራ ዘመናቸውን በዐቃቤ ሕግነት አገልግለዋል። ባለፈው ምርጫ በሩሃኒ ከተሸነፉ ከሁለት ዓመታት በኋላ እአአ በ2019 የፍትህ ዋና ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል። ራይስ ሙስናን ለመዋጋት እና የኢራንን ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት የተሻሉት ሰው እንደሆኑ እያስረዱ ነው። ብዙ ኢራናውያን እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በ1980 ዎቹ በፖለቲካ እስረኞች የጅምላ ግድያ ላይ ሚና አለቸው በማለት ስጋታቸውን ገልጸዋል። አብዶልናሰር ሔማቲ የ64 ዓመቱ ባለሙያ እአአ በ2018 የኢራን ማዕከላዊ ባንክ ገዢ የነበሩ ሲሆን ዕጩ ከሆኑ በኋላ ግን ከኃላፊነት ተነስተዋል። በሩሃኒ እና በቀድሞው ፕሬዝዳንት መሐሙድ አህመዲነጃድ ስር መሾማቸው በኢራን ያሉትን ሁሉንም አንጃዎች በጋራ የማሠራት ብቃት እንዳለቸው ማስረጃ ተደርጎ ታይቷል። የአሜሪካ ማዕቀብ የኢራን ገንዘብ ምንዛሬ ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ለማቃለል ባለመቻላቸው ከሌሎቹ ዕጩዎች ትችት እንዲደርስባቸው ምክንያት ሆኗል። ሞህሲን ረዛይ የ66 ዓመቱ ረዛይ መንፈሳዊውን መሪ በበላይነት የሚያማክሩና በሕግ ጉዳዮች ላይ በሚነሱ አለመግባባቶች የመጨረሻ የመዳኘት ስልጣን ያላቸው የምክር ቤት ጸሐፊ ናቸው። እአአ ከ1988-88 በኢራን እና ኢራቅ ጦርነት ወቅት የእስላማዊው አብዮታዊ ዘብ ቡድን አዛዥ ነበሩ። መከላከያ ኃይሉን ከለቀቁ በኋላ ለሦስት ጊዜያት ለፕሬዝዳንትነት ዕጩ ሆነው ተወዳድረዋል። አሚርሆሴን ቀዚዛዴህ ሃሸሚ አሚርሆሴን ቃዚዛዴህ ሃሸሚ የአንገት በላይ የቀዶ ጥገና ሐኪም ናቸው። ከ2008 ጀምሮ የፓርላማ አባል የነበሩ ሲሆን ከግንቦት ወዲህ ደግሞ ተቀዳሚ አፈ-ጉባኤ ናቸው። የ50 ዓመቱ ዕጩ ከተወዳዳሪዎቹ መካከል በዕድሜ ትንሹ ናቸው። የሕዝብ ተሳትፎ ለምን አስፈላጊ ሆነ? 80 ሚሊዮን ሕዝብ ባላት ኢራን 59 ሚሊዮን ያህል ሰዎች ድምጽ ለመስጠት ብቁ ናቸው። በ2017ቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተሳታፊዎች 73 በመቶ ቢሆንም በመንግሥት በሚደገፈው የኢራን ሰቱደንትስ ፖሊንግ ኤጀንሲ ባደረገው ጥናት ግን በአርቡ ምርጫ 42 በመቶዎቹ ብቻ ሊሳተፉ እንደሚችሉ ጠቁሟል። ይህ እአአ ከ1979ቱ እስላማዊ አብዮት በኋላ በኢራን ከተደረጉት ምርጫዎች ይህ ዝቅተኛ ተሳትፎ የሚኖረው ሲሆን ተመራጩም የመራጮች ቁጥርን እንደ ድጋፍ ስለሚያየው ችግር ሊደቅን ይችላል። ሩሃኒ ሐሙስ ለኢራናውያንን "የተቋም ወይም የቡድን ጉድለቶች" ድምጽ ከመስጠት እንዳያስቆሟቸው ነግረዋቸዋል። "ለጊዜው ስለነገ ለቅሬታዎች አናስብ" ብለዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-57519045 |
0business
| ለላይቤሪያው ፕሬዚዳንት ልደት ትልልቅ ሰሌዳዎች መሰቀላቸው አነጋጋሪ ሆኗል | የላይቤሪያው ፕሬዘዳንት ጆርጅ ዊሃ 55ኛ ልደት በአል መቃረብን ተከትሎ ዋና ከተማዋ ሞኖሮቪያ በትልልቅ የመልካም ልደት መግለጫ ቢልቦርዶች ተሞልታለች። ከሁለት ቀናት በኋላ ልደታቸው የሚያከብሩት ፕሬዘዳንቱ እነዚህ ሰሌዳዎች እየቆሙላቸው የሚገኘው በሞኖሮቪያ ከተማ ምክርቤት ሲሆን በተለይም በማዕከላዊ ሞኖሮቪያ በብዛት ተሰቅለው ታይተዋል። አሁንም በርካታ ቢልቦርዶች በመሰቀል ላይ ሲሆኑ ሁሉም ሰሌዳዎቹ ተመሳሳይ መልክት ይዘዋል። «ሁሉም መሪዎች እርስዎን መሆን አለባቸው። ምክኒያቱም እርስዎ የብቃት ፍጹም ምሳሌ ስለሆኑ። መልካም ልደት አለቃ። በልቦት ውስጥ የተሸሸጉት ህልሞችዎ እውን ይሁንልዎት» ሲል በቢልቦርዶቹ ላይ የተከተበው መልዕክት ይነበባል። የገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች ፕሬዚዳንቱ ይህ ይገባቸዋል የሚሉ አስተያየቶችን ሰጥተዋል። የመሪያቸውን ፎቶ በመላው ከተማዋ በመመልከታቸው ደስተኞች ናቸው። ነገር ግን የፕሬዘዳንቱ ተቺዎች ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው። በኢኮኖሚ ቀውሶች ውስጥ የምትገኘው ላይቤሪያ አብዛኛው ህዝቧ ድሀ ሆኖ እያለ ቢልቦርዶቹ ይዘውት የወጡት መልዕክት ግን ግዴለሽነትን ያንጸባርቃል ሲሉም ተችተዋል። የሞኖሮቪያ ከንቲባ ጄፈርሰን ኮጄም ቢሆኑ በቅርቡ ከፍተኛ ወጪ በማውጣት ልደታቸውን ድል አድርገው አክብረዋል። ደጋፊዎቻቸው የአደባባይ ትርኢት ጭምር አቅርበዋል። የእርሳቸውም ምስሎች በትልልቅ ሰሌዳዎች በሞኖረቪያ ጎዳናዎች ላይ ተሰቅለው ታይተው ነበር። | ለላይቤሪያው ፕሬዚዳንት ልደት ትልልቅ ሰሌዳዎች መሰቀላቸው አነጋጋሪ ሆኗል የላይቤሪያው ፕሬዘዳንት ጆርጅ ዊሃ 55ኛ ልደት በአል መቃረብን ተከትሎ ዋና ከተማዋ ሞኖሮቪያ በትልልቅ የመልካም ልደት መግለጫ ቢልቦርዶች ተሞልታለች። ከሁለት ቀናት በኋላ ልደታቸው የሚያከብሩት ፕሬዘዳንቱ እነዚህ ሰሌዳዎች እየቆሙላቸው የሚገኘው በሞኖሮቪያ ከተማ ምክርቤት ሲሆን በተለይም በማዕከላዊ ሞኖሮቪያ በብዛት ተሰቅለው ታይተዋል። አሁንም በርካታ ቢልቦርዶች በመሰቀል ላይ ሲሆኑ ሁሉም ሰሌዳዎቹ ተመሳሳይ መልክት ይዘዋል። «ሁሉም መሪዎች እርስዎን መሆን አለባቸው። ምክኒያቱም እርስዎ የብቃት ፍጹም ምሳሌ ስለሆኑ። መልካም ልደት አለቃ። በልቦት ውስጥ የተሸሸጉት ህልሞችዎ እውን ይሁንልዎት» ሲል በቢልቦርዶቹ ላይ የተከተበው መልዕክት ይነበባል። የገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች ፕሬዚዳንቱ ይህ ይገባቸዋል የሚሉ አስተያየቶችን ሰጥተዋል። የመሪያቸውን ፎቶ በመላው ከተማዋ በመመልከታቸው ደስተኞች ናቸው። ነገር ግን የፕሬዘዳንቱ ተቺዎች ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው። በኢኮኖሚ ቀውሶች ውስጥ የምትገኘው ላይቤሪያ አብዛኛው ህዝቧ ድሀ ሆኖ እያለ ቢልቦርዶቹ ይዘውት የወጡት መልዕክት ግን ግዴለሽነትን ያንጸባርቃል ሲሉም ተችተዋል። የሞኖሮቪያ ከንቲባ ጄፈርሰን ኮጄም ቢሆኑ በቅርቡ ከፍተኛ ወጪ በማውጣት ልደታቸውን ድል አድርገው አክብረዋል። ደጋፊዎቻቸው የአደባባይ ትርኢት ጭምር አቅርበዋል። የእርሳቸውም ምስሎች በትልልቅ ሰሌዳዎች በሞኖረቪያ ጎዳናዎች ላይ ተሰቅለው ታይተው ነበር። | https://www.bbc.com/amharic/news-58716167 |
2health
| በዩናይትድ ኪንግደም በኦሚክሮን የተያዙ ሰዎች ከ10 ሺህ በላይ ሆነ | አዲሱ የኮሮናቫይረስ ልውጥ ኦሚክሮን ወረርሽኝ ከቀን ወደ ቀን በጨመረባት ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) እስካሁን ባለው ከ10 ሺህ ሰዎች በላይ በኦሚክሮን መያዛቸው ተገልጿል። ይህንንም ተከትሎ በለንደን 'ትልቅ ክስተተት' የተሰኘ አዋጅ ተደንግገጓል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በከፍተኛ ሁኔታ ባገረሸባት ዩናይትድ ኪንግደም ከቀናት ከፍተኛ የቁጥር ጭማሪ በኋላ ቅዳሜ ዕለት ብቻ 90 ሺህ 418 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን አረጋግጣለች። የጤና ዘርፉ አማካሪዎች ሁኔታዎች በዚህ ከቀጠሉና አዳዲስ እርምጃዎች ካልተወሰዱ በየቀኑ ሆስፒታሎች የሚተኙ ሰዎች ቁጥር 3 ሺህ ሊደርስ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። የለንደኑ ከንቲባ ሳዲቅ ካን በመዲናይቱ የታወጀው ትልቅ ክስተት "ነገሮች ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆኑ" ያሳያል ብለዋል። ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ሚኒስትሮች ስለ አዲሱ የኮቪድ መረጃ አጭር መግለጫ ተሰጥቷቸዋል። ከዚህ ቀደም ከነበረው ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብ ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ገደቦች እስካልተጣሉ ድረስ በሆስፒታሎች የሚተኙ ሰዎችን ቁጥር መቀነስ እንደማይቻልና እንደ ከዚህ ቀደሙም ሊያሻቅብ እንደሚችልም የመንግሥት አማካሪዎች ተናግረዋል። በእንግሊዝ ካለው የ'ፕላን ቢ' ሕግ ውጪ ጣልቃ መግባት ካልተቻለ በሆስፒታል የሚተኙ ሰዎች ቁጥር ወደ 3 ሺህ ሊያሻቅብ ይችላል ሲሉ የድንገተኛ አደጋ ሳይንሳዊ አማካሪ ቡድን (ሴጅ) አባላት ገልጸዋል። የቅርብ ጊዜ ዕለታዊ መረጃ እንደሚያሳየው 900 የኮቪድ-19 ህሙማን በእንግሊዝ ሆስፒታል ተኝተዋል። የሴጅ አማካሪዎች የኦሚክሮንን ስርጭትን ለመግታት "በአንድ ላይ የሚሰበሰቡ ሰዎችን ቁጥር መቀነስ፣ አካላዊ ርቀትን መጨመር፣ አካላዊ ግንኙነቶችን ማስወገድና ከፍተኛ ስጋት ያላቸውን ቦታዎች መዝጋት" እንደ አማራጮች አቅርበዋል። አዲሱ የኮሮናቫይረስ ልውጥ አሚክሮን በዓለም ላይ ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት እየተሰራጨ ነው ሲል የዓለም ጤና ድርጅት ከሰሞኑ አስጠንቅቋል። ይህ ልውጥ ዝርያ በ77 አገራት ውስጥ መኖሩ ተረጋግጧል። ኦሚክሮን የተሰኘው ልውጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው በደቡብ አፍሪካ በኅዳር ወር ላይ ሲሆን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በአገሪቱ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር አሳይቷል። | በዩናይትድ ኪንግደም በኦሚክሮን የተያዙ ሰዎች ከ10 ሺህ በላይ ሆነ አዲሱ የኮሮናቫይረስ ልውጥ ኦሚክሮን ወረርሽኝ ከቀን ወደ ቀን በጨመረባት ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) እስካሁን ባለው ከ10 ሺህ ሰዎች በላይ በኦሚክሮን መያዛቸው ተገልጿል። ይህንንም ተከትሎ በለንደን 'ትልቅ ክስተተት' የተሰኘ አዋጅ ተደንግገጓል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በከፍተኛ ሁኔታ ባገረሸባት ዩናይትድ ኪንግደም ከቀናት ከፍተኛ የቁጥር ጭማሪ በኋላ ቅዳሜ ዕለት ብቻ 90 ሺህ 418 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን አረጋግጣለች። የጤና ዘርፉ አማካሪዎች ሁኔታዎች በዚህ ከቀጠሉና አዳዲስ እርምጃዎች ካልተወሰዱ በየቀኑ ሆስፒታሎች የሚተኙ ሰዎች ቁጥር 3 ሺህ ሊደርስ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። የለንደኑ ከንቲባ ሳዲቅ ካን በመዲናይቱ የታወጀው ትልቅ ክስተት "ነገሮች ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆኑ" ያሳያል ብለዋል። ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ሚኒስትሮች ስለ አዲሱ የኮቪድ መረጃ አጭር መግለጫ ተሰጥቷቸዋል። ከዚህ ቀደም ከነበረው ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብ ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ገደቦች እስካልተጣሉ ድረስ በሆስፒታሎች የሚተኙ ሰዎችን ቁጥር መቀነስ እንደማይቻልና እንደ ከዚህ ቀደሙም ሊያሻቅብ እንደሚችልም የመንግሥት አማካሪዎች ተናግረዋል። በእንግሊዝ ካለው የ'ፕላን ቢ' ሕግ ውጪ ጣልቃ መግባት ካልተቻለ በሆስፒታል የሚተኙ ሰዎች ቁጥር ወደ 3 ሺህ ሊያሻቅብ ይችላል ሲሉ የድንገተኛ አደጋ ሳይንሳዊ አማካሪ ቡድን (ሴጅ) አባላት ገልጸዋል። የቅርብ ጊዜ ዕለታዊ መረጃ እንደሚያሳየው 900 የኮቪድ-19 ህሙማን በእንግሊዝ ሆስፒታል ተኝተዋል። የሴጅ አማካሪዎች የኦሚክሮንን ስርጭትን ለመግታት "በአንድ ላይ የሚሰበሰቡ ሰዎችን ቁጥር መቀነስ፣ አካላዊ ርቀትን መጨመር፣ አካላዊ ግንኙነቶችን ማስወገድና ከፍተኛ ስጋት ያላቸውን ቦታዎች መዝጋት" እንደ አማራጮች አቅርበዋል። አዲሱ የኮሮናቫይረስ ልውጥ አሚክሮን በዓለም ላይ ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት እየተሰራጨ ነው ሲል የዓለም ጤና ድርጅት ከሰሞኑ አስጠንቅቋል። ይህ ልውጥ ዝርያ በ77 አገራት ውስጥ መኖሩ ተረጋግጧል። ኦሚክሮን የተሰኘው ልውጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው በደቡብ አፍሪካ በኅዳር ወር ላይ ሲሆን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በአገሪቱ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር አሳይቷል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59716727 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ በአባቱ ቀብር ላይ እናቱን በአካላዊ ርቀት ምክንያት ለማፅናናት ያልቻለው ግለሰብ | በአባቱ ቀብር ላይ እናቱን ለማፅናናት አቅፏት የነበረው እንግሊዛዊ አካላዊ ርቀትህን ጠብቅ መባሉ በከፍተኛ ሁኔታ እንዳበሳጨው ገልጿል። ክሬይግ ቢክኔል ይህ የተነገረው ክራውንሂል በተባለው የቀብር ስነ ስርአት አስፈፃሚ ሰራተኛ ነው። ክሬይግም ሆነ ወንድሙ ወንበራቸውን ራቅ አድርገው እንዲቀመጡ ከመንገር በተጨማሪም የኃዘን ስነ ስርአቱም እንዲቋረጥ ተደርጓል። በኃዘን ልቧ ተሰብራ ከነበረው እናቱ ጎን ተቀምጦም በማፅናናትም ላይ እንደነበረ ተናግሯል። የሚልተን ኬይንስ ምክር ቤት በበኩሉ በተፈጠረው ሁኔታ ማዘኑንና ለወደፊቱም የተሻለ አማራጭ እንጠቀማለንም በማለት ምላሽ ሰጥቷል። የ43 አመቱ ክሬይግ በበኩሉ "እናቴን ማፅናናት እንደምፈልግ ለሁሉም ተናግሬ ነበር። በከፍተኛ ሁኔታ ሃዘኗም ጨምሮ ስብርብር ስትል አቀፍኳት" ብሏል። በአባቱ የኃዘን ስርአት ላይ ወንበሮቹ አካላዊ ርቀትን በሚያስጠብቅ መልኩ ተራርቀው የነበረ ሲሆን የናቱንም የበረታ ኃዘንም ተመልክቶ ወደናቱ የተጠጋ ሲሆን ወንድሙም ተከትሎት እናታቸውን ማፅናናት ጀመሩ። የቀብር አስፈፃሚ ሰራተኞቹም ወንበሮቹን በየቦታቸው እንዲመልሱና ማንቀሳቀስ አትችሉም ተብለዋል። በዚህ ሃዘን ላይ እያሉ እንዲህ መባላቸው ከፍተኛ ንዴትና ሃዘን እንደፈጠረበትም ገልጿል። "በከፍተኛ ሁኔታ የባዶነት ስሜት እንዲሰማኝ አድርጓል" ያለው ክሬይግ የኃዘን ስርአቱ እንዲቀጥልና በሰላም እንዲጠናቀቅም ከራሱ ጋር ትግል ማድረግ ነበረበት። "ፈታኝ ነበር። የአባቴ የኃዘን ስርአቱ እንዲቀጥልም ውሳኔ ላይ መድረስ ነበረብኝ" ያለው ክሬይግ አክሎም "በጣም ያዘንኩበትና የፈራሁበትም ወቅት ነው፤ እንዲህ አይነት ስሜት ተሰምቶኝ አያውቅም" ብሏል። የሚልተን ኬይነስ ምክር ቤት በበኩሉ ከዚህ ቀደም እንዲህ አይነት ሁኔታ ተፈፅሞ እንደማያውቅና ቤተሰቡንም በማሳዘናቸው ይቅርታ ጠይቀዋል። የኃዘንም ሆነ የቀብር አስፈፃሚዎች የአንድ ቤተሰብ አባላት ሰብሰብ ብለው ቢቀመጡም ችግር እንደሌለው ትዕዛዝ ተላልፎላቸዋል ብለዋል። የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በኃዘንም ሆነ በቀብር ስርአት ላይ መገኘት ያለባቸው 30 ሰዎች መሆናቸው በመመሪያው ላይ የተቀመጠ ሲሆን እነሱም አካላዊ ርቀትን በጠበቀ መልኩ መሆኑንም አስፍሯል። | ኮሮናቫይረስ፡ በአባቱ ቀብር ላይ እናቱን በአካላዊ ርቀት ምክንያት ለማፅናናት ያልቻለው ግለሰብ በአባቱ ቀብር ላይ እናቱን ለማፅናናት አቅፏት የነበረው እንግሊዛዊ አካላዊ ርቀትህን ጠብቅ መባሉ በከፍተኛ ሁኔታ እንዳበሳጨው ገልጿል። ክሬይግ ቢክኔል ይህ የተነገረው ክራውንሂል በተባለው የቀብር ስነ ስርአት አስፈፃሚ ሰራተኛ ነው። ክሬይግም ሆነ ወንድሙ ወንበራቸውን ራቅ አድርገው እንዲቀመጡ ከመንገር በተጨማሪም የኃዘን ስነ ስርአቱም እንዲቋረጥ ተደርጓል። በኃዘን ልቧ ተሰብራ ከነበረው እናቱ ጎን ተቀምጦም በማፅናናትም ላይ እንደነበረ ተናግሯል። የሚልተን ኬይንስ ምክር ቤት በበኩሉ በተፈጠረው ሁኔታ ማዘኑንና ለወደፊቱም የተሻለ አማራጭ እንጠቀማለንም በማለት ምላሽ ሰጥቷል። የ43 አመቱ ክሬይግ በበኩሉ "እናቴን ማፅናናት እንደምፈልግ ለሁሉም ተናግሬ ነበር። በከፍተኛ ሁኔታ ሃዘኗም ጨምሮ ስብርብር ስትል አቀፍኳት" ብሏል። በአባቱ የኃዘን ስርአት ላይ ወንበሮቹ አካላዊ ርቀትን በሚያስጠብቅ መልኩ ተራርቀው የነበረ ሲሆን የናቱንም የበረታ ኃዘንም ተመልክቶ ወደናቱ የተጠጋ ሲሆን ወንድሙም ተከትሎት እናታቸውን ማፅናናት ጀመሩ። የቀብር አስፈፃሚ ሰራተኞቹም ወንበሮቹን በየቦታቸው እንዲመልሱና ማንቀሳቀስ አትችሉም ተብለዋል። በዚህ ሃዘን ላይ እያሉ እንዲህ መባላቸው ከፍተኛ ንዴትና ሃዘን እንደፈጠረበትም ገልጿል። "በከፍተኛ ሁኔታ የባዶነት ስሜት እንዲሰማኝ አድርጓል" ያለው ክሬይግ የኃዘን ስርአቱ እንዲቀጥልና በሰላም እንዲጠናቀቅም ከራሱ ጋር ትግል ማድረግ ነበረበት። "ፈታኝ ነበር። የአባቴ የኃዘን ስርአቱ እንዲቀጥልም ውሳኔ ላይ መድረስ ነበረብኝ" ያለው ክሬይግ አክሎም "በጣም ያዘንኩበትና የፈራሁበትም ወቅት ነው፤ እንዲህ አይነት ስሜት ተሰምቶኝ አያውቅም" ብሏል። የሚልተን ኬይነስ ምክር ቤት በበኩሉ ከዚህ ቀደም እንዲህ አይነት ሁኔታ ተፈፅሞ እንደማያውቅና ቤተሰቡንም በማሳዘናቸው ይቅርታ ጠይቀዋል። የኃዘንም ሆነ የቀብር አስፈፃሚዎች የአንድ ቤተሰብ አባላት ሰብሰብ ብለው ቢቀመጡም ችግር እንደሌለው ትዕዛዝ ተላልፎላቸዋል ብለዋል። የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በኃዘንም ሆነ በቀብር ስርአት ላይ መገኘት ያለባቸው 30 ሰዎች መሆናቸው በመመሪያው ላይ የተቀመጠ ሲሆን እነሱም አካላዊ ርቀትን በጠበቀ መልኩ መሆኑንም አስፍሯል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54460664 |
3politics
| መፈንቅለ መንግሥት በተሞከረባት ሱዳን ሲቪል መሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ | መፈንቅለ መንግሥት መካሄዱ እየተነገረ ባለበት ጊዜ የሱዳን ሽግግር መንግሥት እና ሌሎች የሲቪል መሪዎች በቁጥጥርስ ስር መዋላቸው ተነገረ። ማንነታቸው ባልተገለጸ ወታደሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል ከተባሉት መካከል ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ እንደሚገኙበት ከካርቱም የሚወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ። የአገሪቱ ጦር ሠራዊት ምን እየተካሄደ እንደሆነ ምንም አይነት አስተያየት ያልሰጠ ሲሆን፣ የዴሞክራሲ እንቅስቃሴ ደጋፊ ቡድኖች ግን ሕዝቡ አደባባይ ወጥቶ እንዲቃወም ጥሪ አቅርበዋል። በፖለቲካ ቀውስ ውስጥ በምትገኘው ሱዳን በሁለት ወር ውስጥ ሁለተኛው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ እየተካሄደ መሆኑ የተነገረው ዛሬ ሰኞ ማለዳ ነው። በዚህም የታጠቁ ወታደሮች በርካታ የአገሪቱ የሽግግር መንግሥት አባላትን በቁጥጥር ስር እንዳዋሏቸው እና የጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክን መኖሪያ ቤትን በወታደሮች መከበቡ ተዘግቧል። ባለሥልጣናቱን በቁጥጥር ስር ያዋለው ወታደራዊ አካል ማን እንደሆነ አስካሁን በይፋ የታወቀ ነገር የለም። በአገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስቴር የፌስቡክ ገጽ ላይ የወጣ መግለጫ እንዳለው ባለሥልጣናቱን በቁጥጥር ስር የማዋል ድርጊት የተፈጸመው "በጥምር ወታደራዊ ኃይሎች" መሆኑንና የተያዙት ሰዎች ያሉት "በማይታወቅ ስፍራ" መሆኑን አመልክቷል። ጨምሮም ጠቅላይ ሚኒስትር ሐምዶክ መፈንቅለ መንግሥቱን እንዲደግፉ ግፊት ቢደረግባቸውም መቃወማቸውንና ሕዝቡ በሰላማዊ ተቃውሞ "አብዮቱን እንዲከላከል" ጥሪ አቅርበዋል ብሏል። ከዋና ከተማዋ ካርቱም አቅራቢያ በምትገኘው ኦምዱርማን ከተማ ውስጥ ያለውን የአገሪቱን የሬዲዮና የቴሌቪዥን ጣቢያ ዋና መሥሪያ ቤትን ወታደሮች ጥሰው እንደገቡ የሱዳን ማስታወቂያ ሚኒስቴር አስታውቋል። በተጨማሪም ወታደራዊ ኃይሎቹ በርካታ ቁጥር ያላቸው የተቋሙን ሠራተኞች በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አመልከቷል። በከባድ ሁኔታ የታጠቁ ወታደሮች እና የፀጥታ ኃይሎች በካርቱም ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ የተሰማሩ ሲሆን የነዋሪዎችን እንቅስቃሴ ገድበዋል። ኤኤፍፒ እንደዘገበው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ እየተካሄደ መሆኑ ከተሰማ በኋላ የሲቪል አስተዳደሩን የሚደግፉ ሰዎች ተቃውሟቸውን ለመግለጽ ወደ አደባባይ ለመውጣት መሞከራቸውን ተከትሎ ወደ ዋና ከተማዋ የሚያስገቡ ዋና መንገዶችን ወታደሮች ዘግተዋል። የሱዳን መገናኛ ብዙኀን እንደዘገቡት በዋና ከተማዋ ካርቱም ውስጥ የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል። ልዩ መልዕክተኛዋን ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ወደ ሱዳን ልካ የነበረችው አሜሪካ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥትን በተመለከተ የሚወጡ ዘገባዎች "በጽኑ እንዳሳሰባት" ገልጻለች። በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ መንግሥት መልዕክተኛ ሆኑት ጄፍሪ ፌልትማን በሱዳን ውስጥ የሚካሄድ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት "ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው እና አሜሪካን የምትሰጠውን ድጋፍ አደጋ ላይ የሚጥል ነው" ሲሉ ትዊተር ላይ ጽፈዋል። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኦማር ሐሰን አልበሽር ከሥልጣን እንዲወርዱ ያደረገውን ሕዝባዊ ተቃውሞ የመራው የሱዳን የሠራተኞች ማኅበር፣ ሕዝቡ አደባባይ ወጥቶ ወታደራዊ መፈንቀለ መንግሥትን እንዲቃወም ጥሪ አቅርቧል። የሱዳንን የሽግግር መንግሥትን በጋራ በሚመሩት ወታደራዊ እና የሲቪል ባለሥልጣናት መካከል አለመግባባት ከተፈጠረ ወራት ተቆጥረዋል። ባለፉት ሳምንታት ወታደራዊ መሪዎቹንና የሲቪል አስተዳደሮቹን የሚደግፉ ሰልፎች በአገሪቱ ውስጥ ሲካሄዱ ነበር። ወታደራዊውን መሪዎች የሚደግፉት ሰልፈኞች ጦር ሠራዊቱ መፈንቅለ መንግሥት አካሂዶ የሲቪል አስተዳደሪዎችን ከሥልጣን እንዲያስወግድ ጥሪ አቅርበዋል። በተመሳሳይ ባለፈው ሐሙስ ዕለት የሲቪል አስተዳደሩን የሚደግፉ ሱዳናውያን አደባባይ ወጥተው አገሪቱ ወደ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር እንድተሸጋገር ለሲቪል መሪዎቹ ድጋፋቸውን ገልጸው ነበር። ዛሬም ሰልፈኞች ሠራዊቱ ሥልጣን ለመያዝ የሚያደርገውን ሙከራ በመቃወም እና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን በመደገፍ ወደ ጎዳናዎች ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ትናንት እሁድ በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት ጄፍሪ ፌልትማን ከጦር ኃይሉ እና ከሲቪል መሪዎቹ ጋር ተገናኝተው አገሪቱን ወደ ሲቪል አስተዳደር አንዲያሸጋግሩ ጥሪ አቅርበዋል። ባለፈው መስከረም ወር በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ላይ መፈንቅለ መንግሥት ተሞክሮ መክሸፉ የሚታወስ፣ ይህንንም ተከትሎ የሽግግር አስተዳደሩን በሚመራው ሉአላዊ ምክር ቤት አባላት መካከል ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል። አገሪቱን ለረጅም ዓመታት በበላይነት የመሩት ኦማር ሐሰን አል ባሽር ከሥልጣን መወገዳቸውን ተከትሎ ከሁለት ዓመት በፊት በአገሪቱ ሠራዊት፣ በሲቪሎች እና ተቃውሞውን በመሩት ቡድኖች መካከል የሥልጣን ክፍፍል መደረጉ ይታወሳል። በዚህም ሲቪሉን በመወከል የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታውን አብደላ ሐምዶክ የያዙ ሲሆን ከሠራዊቱ በኩል ደግሞ የአገሪቱ ሉአላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር በመሆን ሜጀር ጄነራል አብዱል ፋታህ አልቡርሐን ከፍተኛውን ቦታ ይዘዋል። ነገር ግን የሱዳንን የሽግግር አስተዳደር በሚመሩት ወታደራዊና የሲቪል ባለሥልጣናት መካከል ያለው ግንኙነት የሰከነ ሳይሆን ቆይቷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገሪቱ ውስጥ ያለው የደኅንነት ሁኔታ እየተዳከመ የመጣ ሲሆን፣ ምክንያቱም ወታደራዊ መሪዎቹ ሥልጣን የሚያስረክቡበት ወቅትን ለማስተጓጎል ነው ሲሉ ተቺዎች ይናገራሉ። በሜጀር ጄነራል አብዱል ፋታህ አል ቡርሐን የሚመራው ኃያሉ የሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት ለሲቪሎች ሥልጣኑን በመጪው ኅዳር እንዲያስተላልፍ የጊዜ ሰሌዳ ወጥቶለታል። | መፈንቅለ መንግሥት በተሞከረባት ሱዳን ሲቪል መሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ መፈንቅለ መንግሥት መካሄዱ እየተነገረ ባለበት ጊዜ የሱዳን ሽግግር መንግሥት እና ሌሎች የሲቪል መሪዎች በቁጥጥርስ ስር መዋላቸው ተነገረ። ማንነታቸው ባልተገለጸ ወታደሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል ከተባሉት መካከል ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ እንደሚገኙበት ከካርቱም የሚወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ። የአገሪቱ ጦር ሠራዊት ምን እየተካሄደ እንደሆነ ምንም አይነት አስተያየት ያልሰጠ ሲሆን፣ የዴሞክራሲ እንቅስቃሴ ደጋፊ ቡድኖች ግን ሕዝቡ አደባባይ ወጥቶ እንዲቃወም ጥሪ አቅርበዋል። በፖለቲካ ቀውስ ውስጥ በምትገኘው ሱዳን በሁለት ወር ውስጥ ሁለተኛው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ እየተካሄደ መሆኑ የተነገረው ዛሬ ሰኞ ማለዳ ነው። በዚህም የታጠቁ ወታደሮች በርካታ የአገሪቱ የሽግግር መንግሥት አባላትን በቁጥጥር ስር እንዳዋሏቸው እና የጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክን መኖሪያ ቤትን በወታደሮች መከበቡ ተዘግቧል። ባለሥልጣናቱን በቁጥጥር ስር ያዋለው ወታደራዊ አካል ማን እንደሆነ አስካሁን በይፋ የታወቀ ነገር የለም። በአገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስቴር የፌስቡክ ገጽ ላይ የወጣ መግለጫ እንዳለው ባለሥልጣናቱን በቁጥጥር ስር የማዋል ድርጊት የተፈጸመው "በጥምር ወታደራዊ ኃይሎች" መሆኑንና የተያዙት ሰዎች ያሉት "በማይታወቅ ስፍራ" መሆኑን አመልክቷል። ጨምሮም ጠቅላይ ሚኒስትር ሐምዶክ መፈንቅለ መንግሥቱን እንዲደግፉ ግፊት ቢደረግባቸውም መቃወማቸውንና ሕዝቡ በሰላማዊ ተቃውሞ "አብዮቱን እንዲከላከል" ጥሪ አቅርበዋል ብሏል። ከዋና ከተማዋ ካርቱም አቅራቢያ በምትገኘው ኦምዱርማን ከተማ ውስጥ ያለውን የአገሪቱን የሬዲዮና የቴሌቪዥን ጣቢያ ዋና መሥሪያ ቤትን ወታደሮች ጥሰው እንደገቡ የሱዳን ማስታወቂያ ሚኒስቴር አስታውቋል። በተጨማሪም ወታደራዊ ኃይሎቹ በርካታ ቁጥር ያላቸው የተቋሙን ሠራተኞች በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አመልከቷል። በከባድ ሁኔታ የታጠቁ ወታደሮች እና የፀጥታ ኃይሎች በካርቱም ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ የተሰማሩ ሲሆን የነዋሪዎችን እንቅስቃሴ ገድበዋል። ኤኤፍፒ እንደዘገበው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ እየተካሄደ መሆኑ ከተሰማ በኋላ የሲቪል አስተዳደሩን የሚደግፉ ሰዎች ተቃውሟቸውን ለመግለጽ ወደ አደባባይ ለመውጣት መሞከራቸውን ተከትሎ ወደ ዋና ከተማዋ የሚያስገቡ ዋና መንገዶችን ወታደሮች ዘግተዋል። የሱዳን መገናኛ ብዙኀን እንደዘገቡት በዋና ከተማዋ ካርቱም ውስጥ የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል። ልዩ መልዕክተኛዋን ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ወደ ሱዳን ልካ የነበረችው አሜሪካ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥትን በተመለከተ የሚወጡ ዘገባዎች "በጽኑ እንዳሳሰባት" ገልጻለች። በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ መንግሥት መልዕክተኛ ሆኑት ጄፍሪ ፌልትማን በሱዳን ውስጥ የሚካሄድ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት "ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው እና አሜሪካን የምትሰጠውን ድጋፍ አደጋ ላይ የሚጥል ነው" ሲሉ ትዊተር ላይ ጽፈዋል። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኦማር ሐሰን አልበሽር ከሥልጣን እንዲወርዱ ያደረገውን ሕዝባዊ ተቃውሞ የመራው የሱዳን የሠራተኞች ማኅበር፣ ሕዝቡ አደባባይ ወጥቶ ወታደራዊ መፈንቀለ መንግሥትን እንዲቃወም ጥሪ አቅርቧል። የሱዳንን የሽግግር መንግሥትን በጋራ በሚመሩት ወታደራዊ እና የሲቪል ባለሥልጣናት መካከል አለመግባባት ከተፈጠረ ወራት ተቆጥረዋል። ባለፉት ሳምንታት ወታደራዊ መሪዎቹንና የሲቪል አስተዳደሮቹን የሚደግፉ ሰልፎች በአገሪቱ ውስጥ ሲካሄዱ ነበር። ወታደራዊውን መሪዎች የሚደግፉት ሰልፈኞች ጦር ሠራዊቱ መፈንቅለ መንግሥት አካሂዶ የሲቪል አስተዳደሪዎችን ከሥልጣን እንዲያስወግድ ጥሪ አቅርበዋል። በተመሳሳይ ባለፈው ሐሙስ ዕለት የሲቪል አስተዳደሩን የሚደግፉ ሱዳናውያን አደባባይ ወጥተው አገሪቱ ወደ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር እንድተሸጋገር ለሲቪል መሪዎቹ ድጋፋቸውን ገልጸው ነበር። ዛሬም ሰልፈኞች ሠራዊቱ ሥልጣን ለመያዝ የሚያደርገውን ሙከራ በመቃወም እና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን በመደገፍ ወደ ጎዳናዎች ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ትናንት እሁድ በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት ጄፍሪ ፌልትማን ከጦር ኃይሉ እና ከሲቪል መሪዎቹ ጋር ተገናኝተው አገሪቱን ወደ ሲቪል አስተዳደር አንዲያሸጋግሩ ጥሪ አቅርበዋል። ባለፈው መስከረም ወር በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ላይ መፈንቅለ መንግሥት ተሞክሮ መክሸፉ የሚታወስ፣ ይህንንም ተከትሎ የሽግግር አስተዳደሩን በሚመራው ሉአላዊ ምክር ቤት አባላት መካከል ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል። አገሪቱን ለረጅም ዓመታት በበላይነት የመሩት ኦማር ሐሰን አል ባሽር ከሥልጣን መወገዳቸውን ተከትሎ ከሁለት ዓመት በፊት በአገሪቱ ሠራዊት፣ በሲቪሎች እና ተቃውሞውን በመሩት ቡድኖች መካከል የሥልጣን ክፍፍል መደረጉ ይታወሳል። በዚህም ሲቪሉን በመወከል የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታውን አብደላ ሐምዶክ የያዙ ሲሆን ከሠራዊቱ በኩል ደግሞ የአገሪቱ ሉአላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር በመሆን ሜጀር ጄነራል አብዱል ፋታህ አልቡርሐን ከፍተኛውን ቦታ ይዘዋል። ነገር ግን የሱዳንን የሽግግር አስተዳደር በሚመሩት ወታደራዊና የሲቪል ባለሥልጣናት መካከል ያለው ግንኙነት የሰከነ ሳይሆን ቆይቷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገሪቱ ውስጥ ያለው የደኅንነት ሁኔታ እየተዳከመ የመጣ ሲሆን፣ ምክንያቱም ወታደራዊ መሪዎቹ ሥልጣን የሚያስረክቡበት ወቅትን ለማስተጓጎል ነው ሲሉ ተቺዎች ይናገራሉ። በሜጀር ጄነራል አብዱል ፋታህ አል ቡርሐን የሚመራው ኃያሉ የሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት ለሲቪሎች ሥልጣኑን በመጪው ኅዳር እንዲያስተላልፍ የጊዜ ሰሌዳ ወጥቶለታል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59027282 |
0business
| እስያ፡ የሲንጋፖር አየር መንገድ የቆሙ አውሮፕላኖቹን ምግብ ቤት አደረገ | ሲንጋፖራውያን ምሳቸውን ለመመገብ ወደ አየር መንገድ ጎራ ብለው አንድ ጥግ የቆመ A380 ኤርባስ አውሮፕላን ውስጥ መሰየም ብቻ ይጠበቅባቸዋል። በአውሮፕላኑ ውስጥ ምሳቸውን ለመመገብ የቋመጡ ሰዎች ለሁለት ቀን የተዘጋጀውን ወንበር ሙሉ በሙሉ ይዘውታል። በዚህ አውሮፕላን ውስጥ ገብቶ ለመመገብ 496 የአሜሪካ ዶላር መክፈል ይጠበቃል። አየር መንገዱ አገልግሎቱን ፈላጊዎች ስለበዙበት ሁለት ተጨማሪ ቀናትን ምሳና እናት ለማስተናገድ በማሰብ መጨመሩን አስታውቋል። የሲንጋፖር አየር መንገድ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ገበያ አጥተው ፈተና ውስጥ ከወደቁ እና ሌሎች አማራጭ ከሚፈልጉ አየር መንገዶች መካከል አንዱ ነው። አየር መንገዱ በአሁን ሰዓት ሁለት A380 ኤር ባስ አውሮፕላኖችን ለሶስት ሰዓት የምግብ መስተንግዶ እንዲሰጡ ለመጠቀም አቅዷል። ሁለቱም አውሮፕላኖች አካላዊ ርቀትን ለመጠበቅ በሚያስችል መልኩ ተደራጅተው በግማሽ አቅማቸው ብቻ ደንበኞችን ያስተናግዳሉ። ተመጋቢዎች እየተመገቡ ፊልም መመልከት ቢፈልጉ ወይንም ደግሞ በምቾት በተንቆጠቆተው ክፍል ውስጥ መስተናገድ ከፈለጉ መምረጥ ይችላሉ ተብሏል። አውሮፕላኑ ግን ተመጋቢዎቹን ጭኖ መሬት ለቅቆ አይበርም ተብሏል። የሲንጋፖር አየር መንገድ ምግቦቹን ፍላጎት ላላቸው ቤታቸው ድረስ እንደሚያቀርብ አስታውቋል። ይህ ደግሞ የአየር መንገዱ የጥንቃቄ ኪቶችንና የጠረጴዛ ሽፋኖች ያካትታል። የሲንጋፖር አየር መንገድ በኮቪድ-19 ከተጎዱ የአየር መንገዶች መካከል አንዱ ነው ባለፈው ወር አየር መንገዱ 4300 ሰራተኞቹን እንደሚያሰናብት ገልጾ ነበር። ዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበርም በሺዎች የሚቆጠሩ የአቪየሽኑ ስራዎች በኮቪድ-19 ምከንያት እንደሚጎዱ አስጠንቅቆ ነበር። 290 አየር መንገዶችን የሚወክለው ይህ ተቋም በረራዎችን ከባለፈው አመት ጋር በማነጻጸር በ 66 በመቶ ቀንሷል ብሏል። | እስያ፡ የሲንጋፖር አየር መንገድ የቆሙ አውሮፕላኖቹን ምግብ ቤት አደረገ ሲንጋፖራውያን ምሳቸውን ለመመገብ ወደ አየር መንገድ ጎራ ብለው አንድ ጥግ የቆመ A380 ኤርባስ አውሮፕላን ውስጥ መሰየም ብቻ ይጠበቅባቸዋል። በአውሮፕላኑ ውስጥ ምሳቸውን ለመመገብ የቋመጡ ሰዎች ለሁለት ቀን የተዘጋጀውን ወንበር ሙሉ በሙሉ ይዘውታል። በዚህ አውሮፕላን ውስጥ ገብቶ ለመመገብ 496 የአሜሪካ ዶላር መክፈል ይጠበቃል። አየር መንገዱ አገልግሎቱን ፈላጊዎች ስለበዙበት ሁለት ተጨማሪ ቀናትን ምሳና እናት ለማስተናገድ በማሰብ መጨመሩን አስታውቋል። የሲንጋፖር አየር መንገድ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ገበያ አጥተው ፈተና ውስጥ ከወደቁ እና ሌሎች አማራጭ ከሚፈልጉ አየር መንገዶች መካከል አንዱ ነው። አየር መንገዱ በአሁን ሰዓት ሁለት A380 ኤር ባስ አውሮፕላኖችን ለሶስት ሰዓት የምግብ መስተንግዶ እንዲሰጡ ለመጠቀም አቅዷል። ሁለቱም አውሮፕላኖች አካላዊ ርቀትን ለመጠበቅ በሚያስችል መልኩ ተደራጅተው በግማሽ አቅማቸው ብቻ ደንበኞችን ያስተናግዳሉ። ተመጋቢዎች እየተመገቡ ፊልም መመልከት ቢፈልጉ ወይንም ደግሞ በምቾት በተንቆጠቆተው ክፍል ውስጥ መስተናገድ ከፈለጉ መምረጥ ይችላሉ ተብሏል። አውሮፕላኑ ግን ተመጋቢዎቹን ጭኖ መሬት ለቅቆ አይበርም ተብሏል። የሲንጋፖር አየር መንገድ ምግቦቹን ፍላጎት ላላቸው ቤታቸው ድረስ እንደሚያቀርብ አስታውቋል። ይህ ደግሞ የአየር መንገዱ የጥንቃቄ ኪቶችንና የጠረጴዛ ሽፋኖች ያካትታል። የሲንጋፖር አየር መንገድ በኮቪድ-19 ከተጎዱ የአየር መንገዶች መካከል አንዱ ነው ባለፈው ወር አየር መንገዱ 4300 ሰራተኞቹን እንደሚያሰናብት ገልጾ ነበር። ዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበርም በሺዎች የሚቆጠሩ የአቪየሽኑ ስራዎች በኮቪድ-19 ምከንያት እንደሚጎዱ አስጠንቅቆ ነበር። 290 አየር መንገዶችን የሚወክለው ይህ ተቋም በረራዎችን ከባለፈው አመት ጋር በማነጻጸር በ 66 በመቶ ቀንሷል ብሏል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54520081 |
3politics
| በመርዓዊ ከተማ ሐሙስ ዕለት ተከሰተ ስለተባለው ሁኔታ | በምዕራብ ጎጃም ዞን መርዓዊ ከተማ በትናንትናው ዕለት ሐሙስ ግንቦት 12/2013 ዓ.ም በተካሄደ ሰልፍ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ። የብልጽግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በቅርቡ ለሚደረገው ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳ በስፍራው ሰልፍ እንደነበረ ቢቢሲ ካገኘው መረጃ መረዳት ተችሏል። በሰልፉ ላይ የህይወት መጥፋትና የአካል ጉዳት እንደደረሰ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። "ድምፃቸውን በሰላማዊ መንገድ ባሰሙ ተማሪዎች ላይ የጸጥታ አካላት በወሰዱት እርምጃ የሕይወት መጥፋትና የአካል ጉዳት ደርሷል" በማለት አስፍሯል። አብን ዛሬው በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ በተማሪዎቹ ላይ የተፈፀመውን ጥቃት በጥብቅ አወግዛለሁ ብሏል። በተጨማሪም ለጥቃቱ ትዕዛዝ የሰጡና የፈፀሙ አካላት ላይም መንግሥት አስቸኳይ ምርመራ እንዲያደርግና ሕጋዊ እርምጃ እንዲወስድ እንዲሁም ውጤቱ ለሕዝብ ይፋ እንዲደረግም ጠይቋል። ፓርቲው አክሎም "ገዥው የብልጽግና መንግሥት ሕዝቡ የሚሰጠውን ፖለቲካዊ ድጋፍ ብቻ ሳይሆን ተቃውሞንም በአግባቡ ለማዳመጥ መዘጋጀት አለበት" ብሏል። የመርዓዊ ከተማ ኮምዩኒኬሽን ስለጉዳዩ የሰሜን ሜጫ ወረዳ ሰላምና ደኅንነት ጽህፈት ቤትን ጠቅሶ እንዳለው ፖሊስ በንጹሃን ዜጎች ላይ ተኩሶ ገድሏል እየተባለ በሚዲያ የሚናፈሰው ወሬ ፍጹም ሐሰት ነው ብሏል። የሰሜን ሜጫ ወረዳ ሰላምና ደኅንነት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተመስገን ተስፋ፤ "በብልጽግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ ወቅት ሰልፉ በሰላም እንዳይጠናቀቅ ፍላጎት ያላቸው አካላት ሁከት ለመፍጠር ሙከራ አድርገዋል" ብለዋል። የመርዓዊ ከተማ ኮምዩኒኬሽን ኃላፊውን ዋቢ አድርጎ እንዳሰፈረው "ሰልፉን ለማደናቀፍ የተጠቀሙባቸው ምንም የማያውቁ የአገር ተረካቢ ተማሪዎችን ነው" ብሏል። ኃላፊው ሰልፉን ለማደናቀፍ ተማሪዎችን በሽፋንነት ተጠቅመዋል ያሏቸውን አካላት አልጠቀሱም። ነገር ግን "የችግሩ ፈጣሪዎች አላማ በተለያየ ወንጀል ተጠርጥረው ፖሊስ ጣቢያ ማረፊያ ቤት ያሉ ሰዎችን የማስለቀቅ ነበር" ሲሉ ገልፀዋል። አቶ ተመስገን ፖሊስ "ሰላማዊ ሰልፉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍሏል" ያሉ ሲሆን በዚህም የድብደባ እና የአካል ማጉደል ደርሶባቸዋል ብለዋል። በፖሊስ ደረሰ ስለተባለውም ጉዳት ሲያስረዱ አንድ የፖሊስ አባል ላይ የአካል ድብደባ ሲደርስ የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ሽጉጥ ተወስዷል ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ ሰልፉን ለመደገፍ የመጡ አርሶ አደሮች ላይ ደብደባ ማጋጠሙንና በንብረት ላይ ጉዳትና ዘረፋ መፈጸሙን አስረድተዋል። በአሁኑ ወቅት የችግሩን ፈጣሪዎች በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ እየሰራ ነው ያሉ ሲሆን ምርመራው ከተጠናቀቀ በኋላ መረጃው እንደሚሰጥም ኃላፊው ተናግረዋል። ቢቢሲ ያናገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ከድጋፍ ሰልፉ ጋር ተያይዞ ተኩስና አለመረጋጋት እንደነበር አረጋግጠው ደረሰ ስለተባለው ጉዳት የተለያየ መረጃ ሰጥተዋል። ቢሆንም ግን በሰዎች ላይ ስለደረሰ ጉዳት ከጸጥታ ኃላፊዎችና ከህክምና ተቋማት ቢቢሲ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም። | በመርዓዊ ከተማ ሐሙስ ዕለት ተከሰተ ስለተባለው ሁኔታ በምዕራብ ጎጃም ዞን መርዓዊ ከተማ በትናንትናው ዕለት ሐሙስ ግንቦት 12/2013 ዓ.ም በተካሄደ ሰልፍ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ። የብልጽግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በቅርቡ ለሚደረገው ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳ በስፍራው ሰልፍ እንደነበረ ቢቢሲ ካገኘው መረጃ መረዳት ተችሏል። በሰልፉ ላይ የህይወት መጥፋትና የአካል ጉዳት እንደደረሰ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። "ድምፃቸውን በሰላማዊ መንገድ ባሰሙ ተማሪዎች ላይ የጸጥታ አካላት በወሰዱት እርምጃ የሕይወት መጥፋትና የአካል ጉዳት ደርሷል" በማለት አስፍሯል። አብን ዛሬው በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ በተማሪዎቹ ላይ የተፈፀመውን ጥቃት በጥብቅ አወግዛለሁ ብሏል። በተጨማሪም ለጥቃቱ ትዕዛዝ የሰጡና የፈፀሙ አካላት ላይም መንግሥት አስቸኳይ ምርመራ እንዲያደርግና ሕጋዊ እርምጃ እንዲወስድ እንዲሁም ውጤቱ ለሕዝብ ይፋ እንዲደረግም ጠይቋል። ፓርቲው አክሎም "ገዥው የብልጽግና መንግሥት ሕዝቡ የሚሰጠውን ፖለቲካዊ ድጋፍ ብቻ ሳይሆን ተቃውሞንም በአግባቡ ለማዳመጥ መዘጋጀት አለበት" ብሏል። የመርዓዊ ከተማ ኮምዩኒኬሽን ስለጉዳዩ የሰሜን ሜጫ ወረዳ ሰላምና ደኅንነት ጽህፈት ቤትን ጠቅሶ እንዳለው ፖሊስ በንጹሃን ዜጎች ላይ ተኩሶ ገድሏል እየተባለ በሚዲያ የሚናፈሰው ወሬ ፍጹም ሐሰት ነው ብሏል። የሰሜን ሜጫ ወረዳ ሰላምና ደኅንነት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተመስገን ተስፋ፤ "በብልጽግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ ወቅት ሰልፉ በሰላም እንዳይጠናቀቅ ፍላጎት ያላቸው አካላት ሁከት ለመፍጠር ሙከራ አድርገዋል" ብለዋል። የመርዓዊ ከተማ ኮምዩኒኬሽን ኃላፊውን ዋቢ አድርጎ እንዳሰፈረው "ሰልፉን ለማደናቀፍ የተጠቀሙባቸው ምንም የማያውቁ የአገር ተረካቢ ተማሪዎችን ነው" ብሏል። ኃላፊው ሰልፉን ለማደናቀፍ ተማሪዎችን በሽፋንነት ተጠቅመዋል ያሏቸውን አካላት አልጠቀሱም። ነገር ግን "የችግሩ ፈጣሪዎች አላማ በተለያየ ወንጀል ተጠርጥረው ፖሊስ ጣቢያ ማረፊያ ቤት ያሉ ሰዎችን የማስለቀቅ ነበር" ሲሉ ገልፀዋል። አቶ ተመስገን ፖሊስ "ሰላማዊ ሰልፉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍሏል" ያሉ ሲሆን በዚህም የድብደባ እና የአካል ማጉደል ደርሶባቸዋል ብለዋል። በፖሊስ ደረሰ ስለተባለውም ጉዳት ሲያስረዱ አንድ የፖሊስ አባል ላይ የአካል ድብደባ ሲደርስ የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ሽጉጥ ተወስዷል ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ ሰልፉን ለመደገፍ የመጡ አርሶ አደሮች ላይ ደብደባ ማጋጠሙንና በንብረት ላይ ጉዳትና ዘረፋ መፈጸሙን አስረድተዋል። በአሁኑ ወቅት የችግሩን ፈጣሪዎች በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ እየሰራ ነው ያሉ ሲሆን ምርመራው ከተጠናቀቀ በኋላ መረጃው እንደሚሰጥም ኃላፊው ተናግረዋል። ቢቢሲ ያናገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ከድጋፍ ሰልፉ ጋር ተያይዞ ተኩስና አለመረጋጋት እንደነበር አረጋግጠው ደረሰ ስለተባለው ጉዳት የተለያየ መረጃ ሰጥተዋል። ቢሆንም ግን በሰዎች ላይ ስለደረሰ ጉዳት ከጸጥታ ኃላፊዎችና ከህክምና ተቋማት ቢቢሲ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም። | https://www.bbc.com/amharic/news-57198405 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ የውጭ አገር ተጓዦች የኮቪድ-19 ምርመራ ለማድረግ ፈተና ሆኖባቸዋል | አገራት ድንበሮቻቸውን በጥንቃቄ እየከፈቱ ባሉበት በአሁኑ ወቅት የአየር በረራ መጀመርን ተከትሎ በወጡ አዳዲስ ደንቦች ምክንያት ተጓዦች ከኮቪድ-19 ተህዋሲ ነጻ መሆናቸውን በምርመራ እንዲያረጋግጡ ይገደዳሉ። በኢትዮጵያ ይህንን ምርመራ በማድረግ ውጤት ከሚሰጡ ተቋማት መካከል የሆነውና አብዛኞቹ የውጭ አገር ተጓዦችን የሚያስተናግደው ተቋም የምርመራ ፈላጊዎች ቁጥርና አገልግሎቱ ተመጣጣኝ እንዳልሆነ ተገልጋዮች እየተናገሩ ነው። የአየር በረራ አገልግሎት ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ በመቆየቱ ለወራት ሲጠባበቁ የነበሩ ተጓዦች ይህንን ምርመራ ለማድረግ ከባድ ፈተና ሆኖብናል ይላሉ። ምክንያቱ ደግሞ ምርመራውን የሚያከናውነው ተቋም የወሰደውን ናሙና ውጤት ለማሳወቅ ቢያንስ 48 ሰዓታትን ይፈልጋል። አገራት ደግሞ ተጓዦች ከመሳፈራቸው በፊት ምርመራ እንዲያደርጉ የሚፈልጉበት የሰዓት ገደብ ከ48 ሰዓት እስከ 96 ሰዓት እንደየአገሩ ይለያያል። ምርመራውን ከብዙ ጥበቃ በኋላ ባለፈው አርብ ዕለት ማድረግ የቻሉ ተጓዦች ውጤት አልደረሰም በመባላቸው በረራቸውን ለመሰረዝ እንደተገደዱ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ክሊኒኩ ለተመርማሪዎች ውጤት የሚሰጠው የጉዞው ዕለት ወይም ከአንድ ቀን ቀደም ብሎ በ10 ሰዓት ብቻ ነው። በዚህም ምክንያት የጉዞ ቀን፣ የሚጓዙበት አገር የምርመራ ደንብና የክሊኒኩ ውጤት መስጫ ዕለት ለማጣጣም ፈታኝ እንደሆነ ተጓዦቹ ጠቅሰዋል። ቢቢሲ ሰኞ ማለዳ ከንጋቱ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ ምርመራ በሚሰጠው ተቋም ደጃፍ ላይ ተሰልፈው ያገኛቸው ተጓዦች ተቋሙ ስለምርመራው በቂ መረጃ እንዳልሰጣቸው፣ በረራቸውን በተደጋጋሚ ለመሰረዝ እንደተገደዱና ላልተጠበቀ ወጪና መጉላላት እንደተዳረጉ ገልጸዋል። አገልግሎቱን ፈልገው ወደተቋሙ የሄዱ ሰዎች ለቢቢሲ እንደገለጹት ምርመራውን የሚያደርገው ላቦራቶሪ ሥራውን የሚያስኬድበት ግልጽ አሰራር እንዳልዘረጋም ተናግረዋል። አገልግሎት ፈላጊዎች የሚስተናገዱት በቅድሚያ በኢሜይልና በስልክ ከተመዘገቡና የጉዞ ትኬታትና የፓስፖርታቸውን ቅጂ ከሰጡ በኋላ ነው የሚል ማስታወቂያ በክሊኒኩ ደጃፍ ላይ የተለጠፈ ቢሆንም፤ በክሊኒኩ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ የተጠቀሱት የስልክ መስመሮች ከአገልግሎት ወጪ ናቸው አልያም ተዘግተዋል። የኢሜይል ምላሽም ከክሊኒኩ ማግኘት አልተቻለም። የቢቢሲ ዘጋቢዎችም ይህንኑ ማረጋገጥ ችለዋል። የክሊኒኩ ሠራተኞች በበኩላቸው ሰዎች ከተመዘገቡ በኋላ በራሳቸው ምክንያት ሊቀሩ ስለሚችሉ ይህንን የቅድመ ምዝገባ አሰራር ትተን ሰዎች እንደ አመጣጣቸው ማስተናገድ ጀምረናል ይላሉ። ሰኞ ማለዳ በስፍራው ተሰልፈው ከነበሩ ተጓዦች ቢቢሲ እንደተረዳው አንዳንዶቹ ተገልጋዮች እሑድ ከቀትር ጀምሮ ለረዥም ሰዓት አገልግሎቱን ለማግኘት በዝናብ ተሰልፈው የጠበቁ ቢሆንም "አሁን ደክሞናል ከዚህ በላይ አናስተናግድም" በሚል እንዲበተኑ ተደርገዋል። ሌሎች ደግሞ ነገ በአዲስ መልክ አንሰለፍም በሚል ቅሬታ በማንሳታቸውና የክሊኒኩን በር አናዘጋም በማለታቸው ስም ዝርዝራቸው ተጽፎ በቀጣይ ቀን ቅድሚያ ተሰጥቷቸው እንደሚስተናገዱ ቃል እንደተገባላቸው ተናግረዋል። ክሊኒኩ በዚህ መንገድ ተገልጋዮቹን ካሰናበተ በኋላ የተወሰኑ ሰዎችን "አሾልኮ እንዳስገባና አገልግሎት እንደሰጣቸው" በቦታው ነበርኩ ያሉ እማኝ ተናግረዋል። በአካባቢው የሚገኙ የመኪና አስተናባሪዎችና የጎዳና ተዳዳሪዎች የችግሩን ስፋት በመረዳት በጠዋት ወረፋ በመያዝ ሰልፋቸውን እስከ 200 ብር እየሸጡ እንደሚገኙ ተገልጋዮች ይናገራሉ። የምርመራ አገልግሎት ሰጪው ተቋም በርካታ ለምርመራ የሚመጡ ሰዎች በሚስተናገዱበት በአንደኛው ቅርንጫፉ በሁለት ነርሶችና በሁለት ናሙና ሰብሳቢዎች ብቻ አገልግሎቱን እየሰጠ እንደሆነና የሚሰጠው ምርመራው አገልግሎቱን ከሚፈልገው ሰው ጋር ተመጣጣኝ እንዳልሆነ ቢቢሲ ለመታዘብ ችሏል። የቢቢሲ ዘጋቢ ሰኞ ማለዳ በስፍራው እንደተመለከተ የአገልግሎት ደረሰኝ ወረቀት ማተሚያ ማሽን ብልሽት ገጥሟል በሚልም ክሊኒኩ ለግማሽ ሰዓት ያህል ሥራውን አቁሞ ነበር። ክሊኒኩ ምንሊክ ሆስፒታል አካባቢና ቡልጋሪያ ባሉት ቅርንጫፎቹ የምርመራ አገልግሎት ይሰጣል ቢባልም የሌሎች ቅርንጫፎቹ ተገልጋዮች ከሌሎች ቅርንጫፎች ይልቅ ወደ አንደኛው ክሊኒክ በብዛት ሄደው ምርመራ ለማግኘት እየጣሩ ነው። "ወደ ሌላ ቅርንጫፍ ሄደን እድላችንን እንሞክር ስንላቸውም መልስ አይሰጡንም፣ መረጃ እንኳን ማግኘት ብርቅ ነው" ይላሉ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ተገልጋይ። ሰኞ በዚህ ቅርንጫፍ ረዣዥም ሰልፎች የነበሩ ሲሆን በምንሊክ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው የክሊኒኩ ቅርንጫፍ ግን የተገልጋዩ ቁጥር አነስተኛ ሆኖ ታይቷል። ክሊኒኩ ተመርማሪዎችን አንድ ሺህ ሦስት መቶ ሃያ ብር ለአገልግሎቱ ካስከፈለ በኋላ ውጤቱን የሚሰጠው ከ48 ሰዓታት በኋላ እንቁላል ፋብሪካ አካባቢ በሚገኘው ቅርንጫፉ ብቻ ነው። ጠዋት በረራ ያላቸው ሰዎች ውጤት ስለማይደርስላቸው በብዛት ለድጋሚ የትኬት ማስቀየሪያ ወጪ፣ እንዲሁም ለሌላ አዲስ ምርመራ ወጪ እየተዳረጉ መሆናቸውን ቢቢሲ ካናገራቸው ሰዎች ለመረዳት ችሏል። ቢቢሲ ምርመራውን ከሚሰጠው የኢንተርናሽናል ክሊኒካል ላቦራቶሪስ ምላሽ ለማግኘት በማስታወቂያ ሰሌዳቸው ላይ ባሰፈሩት የስልክ አድራሻ በተደጋጋሚ ቢደውልም ቁጥሩ ስለማይሰራ መልስ ማግኘት አልቻለም። | ኮሮናቫይረስ፡ የውጭ አገር ተጓዦች የኮቪድ-19 ምርመራ ለማድረግ ፈተና ሆኖባቸዋል አገራት ድንበሮቻቸውን በጥንቃቄ እየከፈቱ ባሉበት በአሁኑ ወቅት የአየር በረራ መጀመርን ተከትሎ በወጡ አዳዲስ ደንቦች ምክንያት ተጓዦች ከኮቪድ-19 ተህዋሲ ነጻ መሆናቸውን በምርመራ እንዲያረጋግጡ ይገደዳሉ። በኢትዮጵያ ይህንን ምርመራ በማድረግ ውጤት ከሚሰጡ ተቋማት መካከል የሆነውና አብዛኞቹ የውጭ አገር ተጓዦችን የሚያስተናግደው ተቋም የምርመራ ፈላጊዎች ቁጥርና አገልግሎቱ ተመጣጣኝ እንዳልሆነ ተገልጋዮች እየተናገሩ ነው። የአየር በረራ አገልግሎት ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ በመቆየቱ ለወራት ሲጠባበቁ የነበሩ ተጓዦች ይህንን ምርመራ ለማድረግ ከባድ ፈተና ሆኖብናል ይላሉ። ምክንያቱ ደግሞ ምርመራውን የሚያከናውነው ተቋም የወሰደውን ናሙና ውጤት ለማሳወቅ ቢያንስ 48 ሰዓታትን ይፈልጋል። አገራት ደግሞ ተጓዦች ከመሳፈራቸው በፊት ምርመራ እንዲያደርጉ የሚፈልጉበት የሰዓት ገደብ ከ48 ሰዓት እስከ 96 ሰዓት እንደየአገሩ ይለያያል። ምርመራውን ከብዙ ጥበቃ በኋላ ባለፈው አርብ ዕለት ማድረግ የቻሉ ተጓዦች ውጤት አልደረሰም በመባላቸው በረራቸውን ለመሰረዝ እንደተገደዱ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ክሊኒኩ ለተመርማሪዎች ውጤት የሚሰጠው የጉዞው ዕለት ወይም ከአንድ ቀን ቀደም ብሎ በ10 ሰዓት ብቻ ነው። በዚህም ምክንያት የጉዞ ቀን፣ የሚጓዙበት አገር የምርመራ ደንብና የክሊኒኩ ውጤት መስጫ ዕለት ለማጣጣም ፈታኝ እንደሆነ ተጓዦቹ ጠቅሰዋል። ቢቢሲ ሰኞ ማለዳ ከንጋቱ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ ምርመራ በሚሰጠው ተቋም ደጃፍ ላይ ተሰልፈው ያገኛቸው ተጓዦች ተቋሙ ስለምርመራው በቂ መረጃ እንዳልሰጣቸው፣ በረራቸውን በተደጋጋሚ ለመሰረዝ እንደተገደዱና ላልተጠበቀ ወጪና መጉላላት እንደተዳረጉ ገልጸዋል። አገልግሎቱን ፈልገው ወደተቋሙ የሄዱ ሰዎች ለቢቢሲ እንደገለጹት ምርመራውን የሚያደርገው ላቦራቶሪ ሥራውን የሚያስኬድበት ግልጽ አሰራር እንዳልዘረጋም ተናግረዋል። አገልግሎት ፈላጊዎች የሚስተናገዱት በቅድሚያ በኢሜይልና በስልክ ከተመዘገቡና የጉዞ ትኬታትና የፓስፖርታቸውን ቅጂ ከሰጡ በኋላ ነው የሚል ማስታወቂያ በክሊኒኩ ደጃፍ ላይ የተለጠፈ ቢሆንም፤ በክሊኒኩ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ የተጠቀሱት የስልክ መስመሮች ከአገልግሎት ወጪ ናቸው አልያም ተዘግተዋል። የኢሜይል ምላሽም ከክሊኒኩ ማግኘት አልተቻለም። የቢቢሲ ዘጋቢዎችም ይህንኑ ማረጋገጥ ችለዋል። የክሊኒኩ ሠራተኞች በበኩላቸው ሰዎች ከተመዘገቡ በኋላ በራሳቸው ምክንያት ሊቀሩ ስለሚችሉ ይህንን የቅድመ ምዝገባ አሰራር ትተን ሰዎች እንደ አመጣጣቸው ማስተናገድ ጀምረናል ይላሉ። ሰኞ ማለዳ በስፍራው ተሰልፈው ከነበሩ ተጓዦች ቢቢሲ እንደተረዳው አንዳንዶቹ ተገልጋዮች እሑድ ከቀትር ጀምሮ ለረዥም ሰዓት አገልግሎቱን ለማግኘት በዝናብ ተሰልፈው የጠበቁ ቢሆንም "አሁን ደክሞናል ከዚህ በላይ አናስተናግድም" በሚል እንዲበተኑ ተደርገዋል። ሌሎች ደግሞ ነገ በአዲስ መልክ አንሰለፍም በሚል ቅሬታ በማንሳታቸውና የክሊኒኩን በር አናዘጋም በማለታቸው ስም ዝርዝራቸው ተጽፎ በቀጣይ ቀን ቅድሚያ ተሰጥቷቸው እንደሚስተናገዱ ቃል እንደተገባላቸው ተናግረዋል። ክሊኒኩ በዚህ መንገድ ተገልጋዮቹን ካሰናበተ በኋላ የተወሰኑ ሰዎችን "አሾልኮ እንዳስገባና አገልግሎት እንደሰጣቸው" በቦታው ነበርኩ ያሉ እማኝ ተናግረዋል። በአካባቢው የሚገኙ የመኪና አስተናባሪዎችና የጎዳና ተዳዳሪዎች የችግሩን ስፋት በመረዳት በጠዋት ወረፋ በመያዝ ሰልፋቸውን እስከ 200 ብር እየሸጡ እንደሚገኙ ተገልጋዮች ይናገራሉ። የምርመራ አገልግሎት ሰጪው ተቋም በርካታ ለምርመራ የሚመጡ ሰዎች በሚስተናገዱበት በአንደኛው ቅርንጫፉ በሁለት ነርሶችና በሁለት ናሙና ሰብሳቢዎች ብቻ አገልግሎቱን እየሰጠ እንደሆነና የሚሰጠው ምርመራው አገልግሎቱን ከሚፈልገው ሰው ጋር ተመጣጣኝ እንዳልሆነ ቢቢሲ ለመታዘብ ችሏል። የቢቢሲ ዘጋቢ ሰኞ ማለዳ በስፍራው እንደተመለከተ የአገልግሎት ደረሰኝ ወረቀት ማተሚያ ማሽን ብልሽት ገጥሟል በሚልም ክሊኒኩ ለግማሽ ሰዓት ያህል ሥራውን አቁሞ ነበር። ክሊኒኩ ምንሊክ ሆስፒታል አካባቢና ቡልጋሪያ ባሉት ቅርንጫፎቹ የምርመራ አገልግሎት ይሰጣል ቢባልም የሌሎች ቅርንጫፎቹ ተገልጋዮች ከሌሎች ቅርንጫፎች ይልቅ ወደ አንደኛው ክሊኒክ በብዛት ሄደው ምርመራ ለማግኘት እየጣሩ ነው። "ወደ ሌላ ቅርንጫፍ ሄደን እድላችንን እንሞክር ስንላቸውም መልስ አይሰጡንም፣ መረጃ እንኳን ማግኘት ብርቅ ነው" ይላሉ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ተገልጋይ። ሰኞ በዚህ ቅርንጫፍ ረዣዥም ሰልፎች የነበሩ ሲሆን በምንሊክ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው የክሊኒኩ ቅርንጫፍ ግን የተገልጋዩ ቁጥር አነስተኛ ሆኖ ታይቷል። ክሊኒኩ ተመርማሪዎችን አንድ ሺህ ሦስት መቶ ሃያ ብር ለአገልግሎቱ ካስከፈለ በኋላ ውጤቱን የሚሰጠው ከ48 ሰዓታት በኋላ እንቁላል ፋብሪካ አካባቢ በሚገኘው ቅርንጫፉ ብቻ ነው። ጠዋት በረራ ያላቸው ሰዎች ውጤት ስለማይደርስላቸው በብዛት ለድጋሚ የትኬት ማስቀየሪያ ወጪ፣ እንዲሁም ለሌላ አዲስ ምርመራ ወጪ እየተዳረጉ መሆናቸውን ቢቢሲ ካናገራቸው ሰዎች ለመረዳት ችሏል። ቢቢሲ ምርመራውን ከሚሰጠው የኢንተርናሽናል ክሊኒካል ላቦራቶሪስ ምላሽ ለማግኘት በማስታወቂያ ሰሌዳቸው ላይ ባሰፈሩት የስልክ አድራሻ በተደጋጋሚ ቢደውልም ቁጥሩ ስለማይሰራ መልስ ማግኘት አልቻለም። | https://www.bbc.com/amharic/news-53638908 |
3politics
| የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ያስከተለው ጥርጣሬ እና መስዋዕትነት | ባለፈው ሳምንት አንድ ምሽት ላይ በመዲናዋ አዲስ አበባ ብዙ በጎ ፈቃደኛ ዜጎች ተሰባስበው አካባቢያቸውን እየጠበቁ ነበር። መኪኖችን አስቁመው ይፈትሻሉ። አስፈላጊ ሰነዶችንም ይመለከታሉ። ፍተሻውን እያስተባበሩ የነበሩት የዕድሜ ባለ ፀጋ "ሰፈራችን ውስጥ ያቋቋምነው ኮሚቴ 180 አባላት አሉት። ብዙ ሰዎችን ይዘናል። ሽጉጥ እና ፈንጂን ጨምሮ ሌሎችም በርካታ አጠራጣሪ ቁሳቁሶችን አግኝተናል" ብለዋል። በጎ ፈቃደኞቹ በአገር አቀፉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሠረት የትግራይ አማጺያን እና ደጋፊዎቻቸውን ነው የሚፈልጉት። ተቺዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገቢ ባልሆነ መንገድ መታሰራቸውን ቢናገሩም፤ በመዲናዋ ግን እስሩ ሰፊ ድጋፍ ያለው ይመስላል። ምሽት ላይ ሰፈራቸውን ይጠብቁ ከነበሩት አንዱ "ሊያመልጥ እየሞከረ ነው፤ ፍጠኑ" እያለ በስልኩ ሲነጋገር ይደመጣል። ከእሱ በቅርብ ርቀት በብዛት አረጋውያን በጎ ፈቃደኞች ለሥልጠና ተሰብስበዋል። የሚሰጣቸውን ትዕዛት ተከትለው ይለማመዳሉ። በመዲናዋ ያለው አጠቃላይ ድባብ ሰላማዊ ይመስላል። ሆኖም ግን ዩናይትድ ኪንግደምን ጨምሮ በርካታ አገራት በኢትዮጵያ ያለው ደኅንነት ሁኔታ "እያሽቆለቆለ" ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ማስጠንቀቂያው የተሰጠው የትግራይ ኃይሎች ወደ አዲስ አበባ የመዝመት ፍላጎት እንዳላቸው ማሳወቃቸውን ተከትሎ ነው። የሩሲያ ኤምባሲ በበኩሉ "የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በኢትዮጵያ መዲና የዕለት ተዕት ሕይወት ላይ ያመጣው ለውጥ የለም" ሲል በማኅበራዊ ገጹ አስፍሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ጦር ሜዳ ዘምተው ሠራዊቱን እንደሚመሩ ካሳወቁ በኋላ አፋር ግንባር ላይ ሆነውን የሚያሳይ ቪድዮ ተላልፏል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወታደራዊ ልብስ ለብሰው፣ በወታደሮች ተከበው ይታያሉ። "አሁን አካባቢውን መቆጣጠር ችለናል። የሠራዊቱ ሞራል በጣም የሚያስደስት ነው። የኢትዮጵያ ነጻነት እስከሚረጋገጥ ወደ ኋላ አንልም" ብለዋል። በህወሓት ተይዘው የነበሩ ብዙ ከተሞችን መከላከያ እየተቆጣጠረ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። በእነዚህ ውጊያ እየተካሄደባቸው ባሉ አካባቢዎች የስልክ መስመሮች ስለማይሠሩ የተባለውን ለማረጋገጥ ከባድ ነው። በተጨማሪም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የወጣው አዲስ መመሪያ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እና የጦር ሜዳ ውጤቶችን ከተፈቀደለት አካል ውጪ ማንም እንዳይገልጽ ይከለክላል። የህወሓት አመራሮች በቅርቡ በድሮን በተቀረጸ ቪድዮ በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት ናቸው ያሏቸውን ምርኮኞች አሳይተዋል። በተለያዩ ግንባሮች ወደ ፊት እየገፉ እንደሆነም ተናግረዋል። አሁን ላይ ዋነኛ ትኩረት የሆነችው የደብረ ብርሃን ከተማ ናት። ከተማዋ ከአዲስ አበባ ውጭ መከላከያ በከፍተኛ ተጠንቀቅ የሚገኝባት እንደሆነች ይታመናል። አንዳንድ ተንታኞች፤ የትግራይ ኃይሎች ለመልሶ ማጥቃት እንደሚጋለጡ፣ ኤርትራም ጥቃት ልትፈጽም እንደምትችልና ሠራዊቱ ከአቅሙ በላይ ውጥረት ሊገትመው እንደሚችል ያስጠነቅቃሉ። ሰዎች በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ የትኛውም ወገን እያሸነፈ ቢሆን የውጊያው መስፋፋት ሰብዓዊ ቀውሱን አባብሶታል። የተባበሩት መንግሥታት የዓለም ምግብ ፕሮግራም በሰሜን ኢትዮጵያ 9.4 ሚሊዮን ሰዎች እርዳታ እንደሚፈልጉ ገልጿል። የድርጅቱ የአዲስ አበባ ኃላፊ ክሌር ነቪሊ "ግጭቱ በሰሜን ኢትዮጵያ መስፋፋቱን ተከትሎ በርካታ ሰዎች ለአስከፊ ችግር እየተጋለጡ ነው" ብለዋል። በትግራይ አማጽያን የሚደርሰው ጥቃት፣ የፌደራል መንግሥቱ ቢሮክራሲ እንዲሁም አለመረጋጋቱ ሰብዓዊ እርዳታን እያደናቀፈ እንደሚገኝም ተናግረዋል። የዓለም ምግብ ፕሮግራም በትግራይ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር ባሉ ሁለት የአማራ ክልል ከተሞች በቅርቡ እርዳታ ማድረስ ችሏል። ጦርነት ከ'ካህዲዎች' ጋር መሪው ብልጽግና ፓርቲ በጎ ፈቃደኛ ዘማቾችን ለማመስገን ሕዝባዊ ክንውኖች አዲስ አበባ ውስጥ ማካሄዱን ቀጥሏል። የከተማ ምክር ቤት አባሉ ኢቲሳ ደሜ "ከአገር ውስጥ አሸባሪዎች እና ከውጭ ደጋፊዎቻቸው ጋር ጦርነት ውስጥ ነን" ይላል። የ22 ዓመቱ ባቡሽ ስጦታው "ለአገሬ ክብር እንድዋጋ ተጠርቻለሁ። ቤተሰብ ቢሞት በአገር ይለቀሳል፤ አገር ከሌለ ግን ወዴት ይደረሳል? ሕይወቴን ለመስጠት ዝግጁ ነኝ። ገና ሥልጠና አለመውሰዳችን አያሰጋኝም" ይላል። አዛውንቷ ድንቅነሽ ንጋቱም ለተሰበሰበው ሕዝብ መልዕክት አስተላልፈዋል። "አገሬን እወዳታለሁ። መዝመት እፈልግ ነበር። ግን ባለቤቴ እና ልጄ አንቺ አትዝመቺ እኛ እንዘምትልሻለን አሉኝ።" አዛውንቷ አክለውም "በበጎ ፈቃደኛነት ሰልጥኛለሁ። ልጄና ባለቤቴ ጦር ግንባር ሲዋጉ እኔ አካባቢዬን እጠብቃለሁ። መንገድ ላይ የማየውን ሰው ሁሉ ዝመቱ እላለሁ። ጠላት መጥቶ እስከሚገድለን መጠበቅ የለብንም" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከብልጽግና ፓርቲ አመራሮች አንዷ አይዳ አወል "ጀግና ናቸው። ለሁላችሁም ተስፋ ይሆናሉ" ስትል ድንቅነሽን አቅፋ ተናግራለች። "በርካታ ወጣቶች የእሳቸውን አርአያ እንደሚከተሉ እንጠብቃለን። የኢትዮጵያ መንፈስ ከመቼውም በላይ አሁን ጠንክሯል። ከአራዳ ክፍለ ከተማ ከሰባት ሺህ በላይ ሰዎች አገራቸውን ለመርዳት ለመዝመት ወስነዋል" ብላለች አይዳ። የ 'ኒዮ-ኮሎኒያሊዝም' ክስ የኢትዮጵያ መንግሥት የምዕራቡ ዓለም መንግሥታት እና መገናኛ ብዙኃን የግጭቱን እውነተኛ ገጽታ የሚያዛባ መረጃ የማሰራጨት ዘመቻ ሆነ ብለው ከፍተዋል ሲል ይከሳል። በርካታ ኢትዮጵያውያን በዚህ አስተያየት የሚስማሙ ይመስላል። አገሪቱን ለማጣጣል እና የህወሓትን ድል ለማጋነን "ቅኝ ግዛታዊ" ሙከራ ተደርጓል ሲሉ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ አስተያየት ይሰጣሉ። የፖለቲካ ተንታኙ አቻምየለህ እውነቱ "በሁለት ግንባሮች ጥቃት ተከፍቶብናል። አንደኛው ቢቢሲን ጨምሮ ሌሎችም ምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን የከፈቱብን ኒዮ ኮሎኒያል የሆነ የተሳሳተ መረጃ ስርጭት ነው። ሌላው ህወሓት የከፈተው የዘር ጭፍጨፋ ጦርነት ነው" ይላል። የኢትዮጵያ መንግሥትን እንደሚተች የሚናገረው አቻምየለህ፤ ቢሆንም ግን የአገሩን ሉዓላዊነት ከመከላከል ወደኋላ እንደማይል ይገልጻል። የኢትዮጵያ መንግሥት ለቃለ መጠይቅ ከቢቢሲ በተደጋጋሚ የቀረበለትን ጥያቄ አልተቀበለም። ሆኖም ግን የኢትዮጵያ መንግሥት በአገር ውስጥና በውጭ መገናኛ ብዙኃን ላይ ጫና በማሳደር በስፋት ይተቻል። መገናኛ ብዙኃንን የተመለከተ አደገኛ ትርክት በማስነገር እና መረጃ እንዳይገኝ በመገደብም ይኮነናል። ከጦርነቱ በፊት የፖለቲካ እስረኞችንና ጋዜጠኞችን ከእስር በመፍታት ሲሞገሱ የበሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ዳግመኛ መገናኛ ብዙኃንን የሚያፍን እና የሚያስፈራራ ሁኔታ በመፍጠር እየተተቹ ነው። ቢቢሲ በበኩሉ ስለ ኢትዮጵያ እና የተቀረው ዓለም ገለልተኛ፣ ትክክለኛ እና ወገንተኝነት የሌለው ዘገባ በማቅረብ እንደሚቀጥል ይገልጻል። | የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ያስከተለው ጥርጣሬ እና መስዋዕትነት ባለፈው ሳምንት አንድ ምሽት ላይ በመዲናዋ አዲስ አበባ ብዙ በጎ ፈቃደኛ ዜጎች ተሰባስበው አካባቢያቸውን እየጠበቁ ነበር። መኪኖችን አስቁመው ይፈትሻሉ። አስፈላጊ ሰነዶችንም ይመለከታሉ። ፍተሻውን እያስተባበሩ የነበሩት የዕድሜ ባለ ፀጋ "ሰፈራችን ውስጥ ያቋቋምነው ኮሚቴ 180 አባላት አሉት። ብዙ ሰዎችን ይዘናል። ሽጉጥ እና ፈንጂን ጨምሮ ሌሎችም በርካታ አጠራጣሪ ቁሳቁሶችን አግኝተናል" ብለዋል። በጎ ፈቃደኞቹ በአገር አቀፉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሠረት የትግራይ አማጺያን እና ደጋፊዎቻቸውን ነው የሚፈልጉት። ተቺዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገቢ ባልሆነ መንገድ መታሰራቸውን ቢናገሩም፤ በመዲናዋ ግን እስሩ ሰፊ ድጋፍ ያለው ይመስላል። ምሽት ላይ ሰፈራቸውን ይጠብቁ ከነበሩት አንዱ "ሊያመልጥ እየሞከረ ነው፤ ፍጠኑ" እያለ በስልኩ ሲነጋገር ይደመጣል። ከእሱ በቅርብ ርቀት በብዛት አረጋውያን በጎ ፈቃደኞች ለሥልጠና ተሰብስበዋል። የሚሰጣቸውን ትዕዛት ተከትለው ይለማመዳሉ። በመዲናዋ ያለው አጠቃላይ ድባብ ሰላማዊ ይመስላል። ሆኖም ግን ዩናይትድ ኪንግደምን ጨምሮ በርካታ አገራት በኢትዮጵያ ያለው ደኅንነት ሁኔታ "እያሽቆለቆለ" ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ማስጠንቀቂያው የተሰጠው የትግራይ ኃይሎች ወደ አዲስ አበባ የመዝመት ፍላጎት እንዳላቸው ማሳወቃቸውን ተከትሎ ነው። የሩሲያ ኤምባሲ በበኩሉ "የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በኢትዮጵያ መዲና የዕለት ተዕት ሕይወት ላይ ያመጣው ለውጥ የለም" ሲል በማኅበራዊ ገጹ አስፍሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ጦር ሜዳ ዘምተው ሠራዊቱን እንደሚመሩ ካሳወቁ በኋላ አፋር ግንባር ላይ ሆነውን የሚያሳይ ቪድዮ ተላልፏል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወታደራዊ ልብስ ለብሰው፣ በወታደሮች ተከበው ይታያሉ። "አሁን አካባቢውን መቆጣጠር ችለናል። የሠራዊቱ ሞራል በጣም የሚያስደስት ነው። የኢትዮጵያ ነጻነት እስከሚረጋገጥ ወደ ኋላ አንልም" ብለዋል። በህወሓት ተይዘው የነበሩ ብዙ ከተሞችን መከላከያ እየተቆጣጠረ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። በእነዚህ ውጊያ እየተካሄደባቸው ባሉ አካባቢዎች የስልክ መስመሮች ስለማይሠሩ የተባለውን ለማረጋገጥ ከባድ ነው። በተጨማሪም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የወጣው አዲስ መመሪያ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እና የጦር ሜዳ ውጤቶችን ከተፈቀደለት አካል ውጪ ማንም እንዳይገልጽ ይከለክላል። የህወሓት አመራሮች በቅርቡ በድሮን በተቀረጸ ቪድዮ በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት ናቸው ያሏቸውን ምርኮኞች አሳይተዋል። በተለያዩ ግንባሮች ወደ ፊት እየገፉ እንደሆነም ተናግረዋል። አሁን ላይ ዋነኛ ትኩረት የሆነችው የደብረ ብርሃን ከተማ ናት። ከተማዋ ከአዲስ አበባ ውጭ መከላከያ በከፍተኛ ተጠንቀቅ የሚገኝባት እንደሆነች ይታመናል። አንዳንድ ተንታኞች፤ የትግራይ ኃይሎች ለመልሶ ማጥቃት እንደሚጋለጡ፣ ኤርትራም ጥቃት ልትፈጽም እንደምትችልና ሠራዊቱ ከአቅሙ በላይ ውጥረት ሊገትመው እንደሚችል ያስጠነቅቃሉ። ሰዎች በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ የትኛውም ወገን እያሸነፈ ቢሆን የውጊያው መስፋፋት ሰብዓዊ ቀውሱን አባብሶታል። የተባበሩት መንግሥታት የዓለም ምግብ ፕሮግራም በሰሜን ኢትዮጵያ 9.4 ሚሊዮን ሰዎች እርዳታ እንደሚፈልጉ ገልጿል። የድርጅቱ የአዲስ አበባ ኃላፊ ክሌር ነቪሊ "ግጭቱ በሰሜን ኢትዮጵያ መስፋፋቱን ተከትሎ በርካታ ሰዎች ለአስከፊ ችግር እየተጋለጡ ነው" ብለዋል። በትግራይ አማጽያን የሚደርሰው ጥቃት፣ የፌደራል መንግሥቱ ቢሮክራሲ እንዲሁም አለመረጋጋቱ ሰብዓዊ እርዳታን እያደናቀፈ እንደሚገኝም ተናግረዋል። የዓለም ምግብ ፕሮግራም በትግራይ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር ባሉ ሁለት የአማራ ክልል ከተሞች በቅርቡ እርዳታ ማድረስ ችሏል። ጦርነት ከ'ካህዲዎች' ጋር መሪው ብልጽግና ፓርቲ በጎ ፈቃደኛ ዘማቾችን ለማመስገን ሕዝባዊ ክንውኖች አዲስ አበባ ውስጥ ማካሄዱን ቀጥሏል። የከተማ ምክር ቤት አባሉ ኢቲሳ ደሜ "ከአገር ውስጥ አሸባሪዎች እና ከውጭ ደጋፊዎቻቸው ጋር ጦርነት ውስጥ ነን" ይላል። የ22 ዓመቱ ባቡሽ ስጦታው "ለአገሬ ክብር እንድዋጋ ተጠርቻለሁ። ቤተሰብ ቢሞት በአገር ይለቀሳል፤ አገር ከሌለ ግን ወዴት ይደረሳል? ሕይወቴን ለመስጠት ዝግጁ ነኝ። ገና ሥልጠና አለመውሰዳችን አያሰጋኝም" ይላል። አዛውንቷ ድንቅነሽ ንጋቱም ለተሰበሰበው ሕዝብ መልዕክት አስተላልፈዋል። "አገሬን እወዳታለሁ። መዝመት እፈልግ ነበር። ግን ባለቤቴ እና ልጄ አንቺ አትዝመቺ እኛ እንዘምትልሻለን አሉኝ።" አዛውንቷ አክለውም "በበጎ ፈቃደኛነት ሰልጥኛለሁ። ልጄና ባለቤቴ ጦር ግንባር ሲዋጉ እኔ አካባቢዬን እጠብቃለሁ። መንገድ ላይ የማየውን ሰው ሁሉ ዝመቱ እላለሁ። ጠላት መጥቶ እስከሚገድለን መጠበቅ የለብንም" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ከብልጽግና ፓርቲ አመራሮች አንዷ አይዳ አወል "ጀግና ናቸው። ለሁላችሁም ተስፋ ይሆናሉ" ስትል ድንቅነሽን አቅፋ ተናግራለች። "በርካታ ወጣቶች የእሳቸውን አርአያ እንደሚከተሉ እንጠብቃለን። የኢትዮጵያ መንፈስ ከመቼውም በላይ አሁን ጠንክሯል። ከአራዳ ክፍለ ከተማ ከሰባት ሺህ በላይ ሰዎች አገራቸውን ለመርዳት ለመዝመት ወስነዋል" ብላለች አይዳ። የ 'ኒዮ-ኮሎኒያሊዝም' ክስ የኢትዮጵያ መንግሥት የምዕራቡ ዓለም መንግሥታት እና መገናኛ ብዙኃን የግጭቱን እውነተኛ ገጽታ የሚያዛባ መረጃ የማሰራጨት ዘመቻ ሆነ ብለው ከፍተዋል ሲል ይከሳል። በርካታ ኢትዮጵያውያን በዚህ አስተያየት የሚስማሙ ይመስላል። አገሪቱን ለማጣጣል እና የህወሓትን ድል ለማጋነን "ቅኝ ግዛታዊ" ሙከራ ተደርጓል ሲሉ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ አስተያየት ይሰጣሉ። የፖለቲካ ተንታኙ አቻምየለህ እውነቱ "በሁለት ግንባሮች ጥቃት ተከፍቶብናል። አንደኛው ቢቢሲን ጨምሮ ሌሎችም ምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን የከፈቱብን ኒዮ ኮሎኒያል የሆነ የተሳሳተ መረጃ ስርጭት ነው። ሌላው ህወሓት የከፈተው የዘር ጭፍጨፋ ጦርነት ነው" ይላል። የኢትዮጵያ መንግሥትን እንደሚተች የሚናገረው አቻምየለህ፤ ቢሆንም ግን የአገሩን ሉዓላዊነት ከመከላከል ወደኋላ እንደማይል ይገልጻል። የኢትዮጵያ መንግሥት ለቃለ መጠይቅ ከቢቢሲ በተደጋጋሚ የቀረበለትን ጥያቄ አልተቀበለም። ሆኖም ግን የኢትዮጵያ መንግሥት በአገር ውስጥና በውጭ መገናኛ ብዙኃን ላይ ጫና በማሳደር በስፋት ይተቻል። መገናኛ ብዙኃንን የተመለከተ አደገኛ ትርክት በማስነገር እና መረጃ እንዳይገኝ በመገደብም ይኮነናል። ከጦርነቱ በፊት የፖለቲካ እስረኞችንና ጋዜጠኞችን ከእስር በመፍታት ሲሞገሱ የበሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ዳግመኛ መገናኛ ብዙኃንን የሚያፍን እና የሚያስፈራራ ሁኔታ በመፍጠር እየተተቹ ነው። ቢቢሲ በበኩሉ ስለ ኢትዮጵያ እና የተቀረው ዓለም ገለልተኛ፣ ትክክለኛ እና ወገንተኝነት የሌለው ዘገባ በማቅረብ እንደሚቀጥል ይገልጻል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59456795 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ የአፍሪካ አገራት የኮቪድ-19 አንቲቦዲ ምርመራ ሊጀምሩ ነው | ሰባት የአፍሪካ አገራት የኮሮናቫይረስ አንቲቦዲ ምርመራ ሊጀምሩ መሆኑን የአፍሪካ በሽታ መቆጣጣርና መከላከል ማዕከል አስታወቀ። ምርመራው ወረርሽኙ በአፍሪካ ውስጥ ምን ያህል እንደተሰራጨ ለማወቅ የሚደረግ ጥረት አካል ነው ተብሏል። ድርጅቱ በሰተው ዕለታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ "ላይቤሪያ፣ ሴራሊዮን፣ ዛምቢያ፣ ዚምባብዌ፣ ካሜሮን፣ ናይጄሪያ፣ ሞሮኮ ምርመራውን ቀድመው ለማድረግ የተዘጋጁ አገራት ናቸው" ያሉት የአፍሪካ በሽታ መቆጣጣርና መከላከል የበላይ ኃላፊ ጆን ኬንጋሶንግ ናቸው። ኃላፊው አህጉሪቱ እስካሁን ድረስ 9.4 ሚሊዮን የኮሮናቫይረስ ምርመራ ማድረጓን ገልፀው፤ 10 ሚሊዮን ምርመራዎችን ለማከናወን የታቀደውን ዕቅድ ለማሳካት ከአገራት ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል። ዶ/ር ንኬንጋሶንግ አፍሪካ በክትባት ምርመር ረገድም ጥሩ መንገድ ላይ መሆኗን ተናግረዋል። አክለውም በአህጉር ደረጃ ለሚደረግ ክሊኒካል ሙከራ ጥምረት ለማቋቋም ስትራቴጂ መቀረፁን ገልፀው፣ ለክትባቱ የሚያስፈልጉ አቅርቦቶችን ለመግዛት እና የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ይጀመራል ብለዋል። እንደ ጆንስ ሆፕኪንስ መረጃ ከሆነ በአፍሪካ እስካሁን ድረስ 1,084,904 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። በአፍሪካ በብዛት የኮሮናቫይረስ ምርመራ ካደረጉ አገራት መካከል ከፍተኛውን ቁጥር የምትይዘው ደቡብ አፍሪካ ነች። ደቡብ አፍሪካ አህጉሪቱ ከመረመረቻቸው አጠቃላይ የኮሮናቫይረስ ምርመራዎች መካከል 80 በመቶውን መርምራለች ሲል የአፍሪካ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል አስታውቋል። ከደቡብ አፍሪካ በመቀጠል ሞሮኮ፣ ጋና፣ ግብጽ፣ ኢትዮጵያ፣ ኡጋንዳ፣ ሞሪሺየስ፣ ኬንያ፣ ናይጄርያ እና ሩዋንዳ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎችን መርምረዋል። ደቡብ አፍሪካ በኮሮናቫይረስ በተያዙ ሰዎች ቁጥርም ከአፍሪካ ቀዳሚዋ ስትሆን ከዓለም ደግሞ አምስተኛዋ ነች። ነገር ግን በኮሮናቫይረስ ክፉኛ ከተጠቁ አገራት አንጻር ሲታይ በቫይረሱ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር በደቡብ አፍሪካ በጣም ትንሽ ነው። በርግጥ በአገሪቱ የሚገኝ አንድ በሕክምና ምርምር ላይ የተሰማራ ተቋም በአገሪቱ የተመዘገበው የሟቾች ቁጥር ከዚህም ሊልቅ እንደደሚችል አስታውቋል። የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠር እና መከላከል ማዕከል የቫይረሱ ስርጭትን በቅርበት ከሚከታተልባቸው አገራት መካከል ኬንያ፣ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ዛምቢያ፣ ካሜሮን፣ ጋቦን፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ ጋና፣ አይቮሪ ኮስት፣ ሴኔጋል ፣ ግብጽ፣ ሞሮኮ እና አልጄሪያ ይገኙበታል። በመካከለኛው እና ምሥራቅ አፍሪካ ባሉ የአህጉሪቱ አገራት በጣም ዝቅተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተመዘገበ ሲሆን በሌሎች አገራት ደግሞ በአንጻራዊነት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎ መያዛቸው ተመዝግቧል። እንደ አፍሪካ በሽታ መቆጣጠርና መከላከል ማዕከል መረጃ ከሆነ በአህጉሪቱ የሚገኙ አምስት አገራት በአጠቃላይ በአህጉሪቱ በቫይረሱ መያዛቸው ከተገለፀው 75 እጁን ያህል መዝግበዋል። ይህም በመላ አህጉሪቱ የቫይረሱ ስርጭት ምን እንደሚመስል ለማወቅ ያለውን ሁኔታ አዳጋች ማድረጉን የማዕከሉ ኃላፊዎች ይገልፃሉ። | ኮሮናቫይረስ፡ የአፍሪካ አገራት የኮቪድ-19 አንቲቦዲ ምርመራ ሊጀምሩ ነው ሰባት የአፍሪካ አገራት የኮሮናቫይረስ አንቲቦዲ ምርመራ ሊጀምሩ መሆኑን የአፍሪካ በሽታ መቆጣጣርና መከላከል ማዕከል አስታወቀ። ምርመራው ወረርሽኙ በአፍሪካ ውስጥ ምን ያህል እንደተሰራጨ ለማወቅ የሚደረግ ጥረት አካል ነው ተብሏል። ድርጅቱ በሰተው ዕለታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ "ላይቤሪያ፣ ሴራሊዮን፣ ዛምቢያ፣ ዚምባብዌ፣ ካሜሮን፣ ናይጄሪያ፣ ሞሮኮ ምርመራውን ቀድመው ለማድረግ የተዘጋጁ አገራት ናቸው" ያሉት የአፍሪካ በሽታ መቆጣጣርና መከላከል የበላይ ኃላፊ ጆን ኬንጋሶንግ ናቸው። ኃላፊው አህጉሪቱ እስካሁን ድረስ 9.4 ሚሊዮን የኮሮናቫይረስ ምርመራ ማድረጓን ገልፀው፤ 10 ሚሊዮን ምርመራዎችን ለማከናወን የታቀደውን ዕቅድ ለማሳካት ከአገራት ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል። ዶ/ር ንኬንጋሶንግ አፍሪካ በክትባት ምርመር ረገድም ጥሩ መንገድ ላይ መሆኗን ተናግረዋል። አክለውም በአህጉር ደረጃ ለሚደረግ ክሊኒካል ሙከራ ጥምረት ለማቋቋም ስትራቴጂ መቀረፁን ገልፀው፣ ለክትባቱ የሚያስፈልጉ አቅርቦቶችን ለመግዛት እና የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ይጀመራል ብለዋል። እንደ ጆንስ ሆፕኪንስ መረጃ ከሆነ በአፍሪካ እስካሁን ድረስ 1,084,904 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። በአፍሪካ በብዛት የኮሮናቫይረስ ምርመራ ካደረጉ አገራት መካከል ከፍተኛውን ቁጥር የምትይዘው ደቡብ አፍሪካ ነች። ደቡብ አፍሪካ አህጉሪቱ ከመረመረቻቸው አጠቃላይ የኮሮናቫይረስ ምርመራዎች መካከል 80 በመቶውን መርምራለች ሲል የአፍሪካ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል አስታውቋል። ከደቡብ አፍሪካ በመቀጠል ሞሮኮ፣ ጋና፣ ግብጽ፣ ኢትዮጵያ፣ ኡጋንዳ፣ ሞሪሺየስ፣ ኬንያ፣ ናይጄርያ እና ሩዋንዳ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎችን መርምረዋል። ደቡብ አፍሪካ በኮሮናቫይረስ በተያዙ ሰዎች ቁጥርም ከአፍሪካ ቀዳሚዋ ስትሆን ከዓለም ደግሞ አምስተኛዋ ነች። ነገር ግን በኮሮናቫይረስ ክፉኛ ከተጠቁ አገራት አንጻር ሲታይ በቫይረሱ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር በደቡብ አፍሪካ በጣም ትንሽ ነው። በርግጥ በአገሪቱ የሚገኝ አንድ በሕክምና ምርምር ላይ የተሰማራ ተቋም በአገሪቱ የተመዘገበው የሟቾች ቁጥር ከዚህም ሊልቅ እንደደሚችል አስታውቋል። የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠር እና መከላከል ማዕከል የቫይረሱ ስርጭትን በቅርበት ከሚከታተልባቸው አገራት መካከል ኬንያ፣ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ዛምቢያ፣ ካሜሮን፣ ጋቦን፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ ጋና፣ አይቮሪ ኮስት፣ ሴኔጋል ፣ ግብጽ፣ ሞሮኮ እና አልጄሪያ ይገኙበታል። በመካከለኛው እና ምሥራቅ አፍሪካ ባሉ የአህጉሪቱ አገራት በጣም ዝቅተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተመዘገበ ሲሆን በሌሎች አገራት ደግሞ በአንጻራዊነት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎ መያዛቸው ተመዝግቧል። እንደ አፍሪካ በሽታ መቆጣጠርና መከላከል ማዕከል መረጃ ከሆነ በአህጉሪቱ የሚገኙ አምስት አገራት በአጠቃላይ በአህጉሪቱ በቫይረሱ መያዛቸው ከተገለፀው 75 እጁን ያህል መዝግበዋል። ይህም በመላ አህጉሪቱ የቫይረሱ ስርጭት ምን እንደሚመስል ለማወቅ ያለውን ሁኔታ አዳጋች ማድረጉን የማዕከሉ ኃላፊዎች ይገልፃሉ። | https://www.bbc.com/amharic/53775413 |
5sports
| ዛሬ በሚካሄደው የ5ሺህ ሜትር ፍጻሜ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተጠባቂ ናቸው | ዛሬ ከሰዓት በሚካሄዱ ሁለት የፍጻሜ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከሰዓት 9፡40 ላይ የሚጀምረው የሴቶች 5ሺ ሜትር የፍጻሜ ውድድር በጉጉት የሚጠበቅ ነው። በዚህ የፍጻሜ ውድድር ጉዳፍ ጸጋይ፣ እጅጋየሁ ታዬ እና ሰንበሬ ተፈሪ ተጠባቂ ናቸው። ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፋን ሐሰን ደግሞ ዋነኛ ተፎካካሪ ነች። ጉዳፍ ፀጋይ በዚህ ዓመት የካቲት ወር ላይ በፈረንሳይ በተካሄደ የ1ሺህ 500 ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር ክብረ ወሰን ማሻሻል ችላለች። ሰንበሬ ተፈሪ ደግሞ በአውሮፓውያኑ 2015 ላይ ቻይና ቤጂንግ በተካሄደው የ5ሺ ሜትር ውድድር ሁለተኛ ሆና መጨረስ ችላለች። ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት እጅጋየሁ ታዬ በበኩሏ ከዚህ በፊት በኦሎምፒክ ተሳትፋ የማታውቅ ሲሆን በ2018ቱ የታዳጊዎች የዓለም ሻምፒዮና ሁለተኛ ሆና አጠናቃለች። በዚህ ምድብ ኬንያውያኑ ሄለን ኦቢሪ እና አግነስ ቲሮፕ እንዲሁም ለኔዘርላንድስ የምትሮጠው ሲፋን ሐሰን ቀንደኛ ተፎካካሪዎች እንደሚሆኑ ይጠበቃል። ከሴቶች የፍጻሜ ውድድር ቀደም ብሎ ደግሞ የወንዶች 3ሺህ ሜትር መሰናክል የፍጻሜ ውድድር ከቀኑ 9፡15 ላይ ይጀምራል። ከቀናት በፊት በተካሄደው ማጣሪያ ግርማ ላሜቻ እና ዋለ ጌትነት ለፍጻሜ ማለፋቸውን ያረጋገጡ ሲሆን የሜዳሊያ ዝርዝር ውስጥ እንደሚገቡ ይጠበቃል። ዋሌ ጌትነት በዳይመንድ ሊግ ውድድር በ3 ሺ ሜትር መሰናክል ማሸነፍ የቻለ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ሲሆን በኦሎምፒክ ሲሳተፍም የመጀመሪያው ነው። እሁድ ሌሊት ከ9፡35 ጀምሮ በተካሄደ የሴቶች 1500 ሜትር ማጣሪያ ደግሞ ከሶስቱ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች መካከል ሁለቱ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። አትሌቶቹም ፍሬወይኒ ኃይሉ እና ለምለም ኃይሉ ናቸው። ሌላኛዋ አትሌት ድርቤ ወልተጂ ደግሞ 12ኛ ሆኗ በማጠናቀቋ ማጣሪያውን ሳታልፍ ቀርታለች። በ3ሺ ሜትር የሴቶች መሰናክል ውድድር በተለያየ ምደብ ተደልድለው ውድድራቸውን ካደረጉት ሶስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች መካከል ሁለቱ ማጣሪያውን ማለፍ ችለዋል። አትሌቶቹም መቅደስ አበበ እና ዘርፌ ወንድማገኝ ሲሆኑ አትሌት ሎሚ ሙለታ ደግሞ 10ኛ ሆና በማጠናቀቋ ማጣሪያውን ሳታልፍ ቀርታለች። ማጣሪያውን ያለፉት ሁለቱ አትሌቶችም የፊታችን ረቡዕ በሚካሄደው የፍፃሜ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ወክለው ይወዳደራሉ። | ዛሬ በሚካሄደው የ5ሺህ ሜትር ፍጻሜ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተጠባቂ ናቸው ዛሬ ከሰዓት በሚካሄዱ ሁለት የፍጻሜ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከሰዓት 9፡40 ላይ የሚጀምረው የሴቶች 5ሺ ሜትር የፍጻሜ ውድድር በጉጉት የሚጠበቅ ነው። በዚህ የፍጻሜ ውድድር ጉዳፍ ጸጋይ፣ እጅጋየሁ ታዬ እና ሰንበሬ ተፈሪ ተጠባቂ ናቸው። ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፋን ሐሰን ደግሞ ዋነኛ ተፎካካሪ ነች። ጉዳፍ ፀጋይ በዚህ ዓመት የካቲት ወር ላይ በፈረንሳይ በተካሄደ የ1ሺህ 500 ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር ክብረ ወሰን ማሻሻል ችላለች። ሰንበሬ ተፈሪ ደግሞ በአውሮፓውያኑ 2015 ላይ ቻይና ቤጂንግ በተካሄደው የ5ሺ ሜትር ውድድር ሁለተኛ ሆና መጨረስ ችላለች። ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት እጅጋየሁ ታዬ በበኩሏ ከዚህ በፊት በኦሎምፒክ ተሳትፋ የማታውቅ ሲሆን በ2018ቱ የታዳጊዎች የዓለም ሻምፒዮና ሁለተኛ ሆና አጠናቃለች። በዚህ ምድብ ኬንያውያኑ ሄለን ኦቢሪ እና አግነስ ቲሮፕ እንዲሁም ለኔዘርላንድስ የምትሮጠው ሲፋን ሐሰን ቀንደኛ ተፎካካሪዎች እንደሚሆኑ ይጠበቃል። ከሴቶች የፍጻሜ ውድድር ቀደም ብሎ ደግሞ የወንዶች 3ሺህ ሜትር መሰናክል የፍጻሜ ውድድር ከቀኑ 9፡15 ላይ ይጀምራል። ከቀናት በፊት በተካሄደው ማጣሪያ ግርማ ላሜቻ እና ዋለ ጌትነት ለፍጻሜ ማለፋቸውን ያረጋገጡ ሲሆን የሜዳሊያ ዝርዝር ውስጥ እንደሚገቡ ይጠበቃል። ዋሌ ጌትነት በዳይመንድ ሊግ ውድድር በ3 ሺ ሜትር መሰናክል ማሸነፍ የቻለ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ሲሆን በኦሎምፒክ ሲሳተፍም የመጀመሪያው ነው። እሁድ ሌሊት ከ9፡35 ጀምሮ በተካሄደ የሴቶች 1500 ሜትር ማጣሪያ ደግሞ ከሶስቱ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች መካከል ሁለቱ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። አትሌቶቹም ፍሬወይኒ ኃይሉ እና ለምለም ኃይሉ ናቸው። ሌላኛዋ አትሌት ድርቤ ወልተጂ ደግሞ 12ኛ ሆኗ በማጠናቀቋ ማጣሪያውን ሳታልፍ ቀርታለች። በ3ሺ ሜትር የሴቶች መሰናክል ውድድር በተለያየ ምደብ ተደልድለው ውድድራቸውን ካደረጉት ሶስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች መካከል ሁለቱ ማጣሪያውን ማለፍ ችለዋል። አትሌቶቹም መቅደስ አበበ እና ዘርፌ ወንድማገኝ ሲሆኑ አትሌት ሎሚ ሙለታ ደግሞ 10ኛ ሆና በማጠናቀቋ ማጣሪያውን ሳታልፍ ቀርታለች። ማጣሪያውን ያለፉት ሁለቱ አትሌቶችም የፊታችን ረቡዕ በሚካሄደው የፍፃሜ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ወክለው ይወዳደራሉ። | https://www.bbc.com/amharic/58022665 |
3politics
| የክልል እንሁን ጥያቄ፡ በጉራጌ ከተሞች የሥራ ማቆም አድማ ተደረገ | በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ የተካተተው የጉራጌ ሕዝብ እራሱን በቻለ ክልል እንዲዋቀር ጥያቄ ሲቀርብ ቆይቷል። ይህን ጥያቄ በተለይ ከአራት ዓመት በፊት የዞኑ ምክር ቤት ጭምር ለፌደራል መንግሥቱ ማቅረቡ ይታወሳል። ነገር ግን ይህ በክልል የመደራጀት ጥያቄ ዓመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ለጥያቄው ምላሽ ማግኘት እንዳልቻሉ የዞኑ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። የጉራጌ ዞን በክልል የመደራጀት ጥያቄን ተከትሎ ማክሰኞ ዕለት በዞኑ መዲና ወልቂጤ እና በሐዋርያት ከተማ የሥራ ማቆም አድማ ተደርጓል። ይህን ነሐሴ 03/2014 ዓ.ም. የተካሄደውን የሥራ ማቆም አድማ ማን እንደጠራው በትክክል ባይታወቅም ሰኞ ነሐሴ 02/2014 ወረቀት ከተበተነ በኋላ ወልቂጤ ከተማ ከሥራ እንቅስቃሴ ውጪ ሆና መዋሏን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በጉራጌ ጉዳዮች ላይ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሐሳቦችን የሚያቀርበው አቶ ተስፋ ነዳም የሁለቱ ከተሞች ነዋሪዎች ከቤቱ መዋላቸውን “ከዳቦ ቤት እና ከሕክምና ተቋማት ውጪ ሙሉ በሙሉ የንግድ እንቅስቃሴ ቆሞ ውሏል” ሲሉ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። እንደ አቶ ተስፋ ከሆነ በዞኑ ባሉ አንዳንድ አካባቢዎች የመንግሥት አስተዳዳሪዎች ነዋሪዎችን ለውይይት ቢጠሩም ነዋሪዎች ለመሰብሰብ ፍቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረታቸው የታቀዱት ስብሰባዎች ሳይካሄዱ ቀርተዋል ብለዋል። የሥራ ማቆም አድማ የተደረገው የጉራጌ ዞን ከሌሎች ማኅበረሰቦች ጋር በመሆን በክላስተር መደራጀት ሳይሆን በክልልነት እንዲዋቀወር የቀረበው ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ጫና ለማሳደር መሆኑን አቶ ተስፋ ያስረዳሉ። ጨምረውም ከሦስት ዓመታት በፊት የጉራጌ ዞን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት ጥያቄውን ለክልሉ በይፋ አቅርቦ እንደነበረ በማስታወስ፣ የዞኑ አስተዳደርም በአሁን የቀረበውን የአወቃቀር አማራጭን አይቀበልም ሲሉ ይናገራሉ። የጉራጌ ሕዝብ እራሱን በክልልነት የማደረጀት ሙሉ ሕገ-መንግሥታዊ መብት እንዳለው የሚናገሩት አቶ ተስፋ፤ “መንግሥትም ቢሆን በዚህ አደረጃጀት ተደራጁ ወይም የምፈቅደው ይህ ነው የማለት መብት የለውም” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የጉራጌ ዞን ራሱን ችሎ በክልልነት የመደራጀት ጥያቄ ማቅረብ ከጀመረ ዓመታት መቆጠራቸውን የሚናገሩት ደግሞ የጉራጌ ባህላዊ ሸንጎ መሥራችና ሰብሳቢ ወ/ሮ ዛይዳ ግዛው ናቸው። “ለውጡ ከመምጣቱ በፊት ህወሓት አገር ሲመራ ከሌሎች ጋር በክልል አልዋቀርም ብሎ ለመጀመሪያ ጊዜ ተቃውሞ ያሰማው የጉራጌ ማኅብረሰብ ነው” በማለት ይናራሉ። ለዘመናት የዘለቀው ጥያቄ ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ምላሽ አላገኘም የሚሉት ወ/ሮ ዛይዳ፤ “ሕዝቡ ቁጭት ውስጥ ገብቷል። የፖለቲካ አሻጥርም በዝቶበታል” በማለት ወ/ሮ ዛይዳ ያስረዳሉ። ጉራጌ አሁን ተደራጅቶ የሚገኝበት ሁኔታ “የራሱን ቋንቋ፣ ማንነቱን፣ ባህሉን ማሳደግ እናመጠበቅ አልቻለም። የጉራጊኛ ቋንቋ ሊጠፋ ከጫፍ ድርሷል። ቋንቋው ለመማሪያነት አልበቃም እነዚህ ሁሉ መስተካከል ስላለባቸው ነው የክልል ጥያቄ የተነሳው” ይላሉ አቶ ተስፋ። ጉራጌ በክላስተር የሚደራጅ ከሆነ ሕዝቡ ከሁለት በላይ ወደ ሆኑ ዞኖች ተከፋፍሎ ስለሚገባ የጉራጌ ማንነትን ሊያሳጣ ይችላል በማለት ስጋታቸውንም ጨምረው ይናገራሉ። ወ/ሮ ዛይዳ በበኩላቸው፤ ክላስተሩ የሕገ-መንግሥት መሠረት የሌለው እና ሕብረተሰቡ ሳይቀበለው በግድ የሚጫንበት ሃሳብ በመሆኑ አንቀበለውም ይላሉ። “የጉራጌ ማኅብረሰብን ቋንቋ፣ ባህል የሚያጠፋ ነው። እስከ ዛሬ ድረስ በቋንቋው ማስተማር እና አካባቢውን ማልማት ያልቻለ፣ የፖለቲከኖች አሻጥር አድክሞት የኖረ ማኅብረሰብ ከአሁን በኋላ በክላስተር ይደራጅ ቢባል በፍጹም ሊያንሰራራ የማይችልበት ደረጃ ላይ ይገባል” ሲሉ ወ/ሮ ዛይዳም ስጋታቸውን ይገልጻሉ። “በትግል የማይለወጥ ነገር የለም” የሚሉት ደግሞ አቶ ተስፋ፤ “የተቀረውን ሕዝብ የሚጎዳ ነገር ሳይኖር አሁንም ቢሆን ሕጋዊ መስመሩን በመከተል የዞኑ ምክር ቤት ጥያቄ እንዲከበረ ጥረታችንን እንቀጥላለን” ሲሉ አቶ ተስፋ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል። | የክልል እንሁን ጥያቄ፡ በጉራጌ ከተሞች የሥራ ማቆም አድማ ተደረገ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ የተካተተው የጉራጌ ሕዝብ እራሱን በቻለ ክልል እንዲዋቀር ጥያቄ ሲቀርብ ቆይቷል። ይህን ጥያቄ በተለይ ከአራት ዓመት በፊት የዞኑ ምክር ቤት ጭምር ለፌደራል መንግሥቱ ማቅረቡ ይታወሳል። ነገር ግን ይህ በክልል የመደራጀት ጥያቄ ዓመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ለጥያቄው ምላሽ ማግኘት እንዳልቻሉ የዞኑ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። የጉራጌ ዞን በክልል የመደራጀት ጥያቄን ተከትሎ ማክሰኞ ዕለት በዞኑ መዲና ወልቂጤ እና በሐዋርያት ከተማ የሥራ ማቆም አድማ ተደርጓል። ይህን ነሐሴ 03/2014 ዓ.ም. የተካሄደውን የሥራ ማቆም አድማ ማን እንደጠራው በትክክል ባይታወቅም ሰኞ ነሐሴ 02/2014 ወረቀት ከተበተነ በኋላ ወልቂጤ ከተማ ከሥራ እንቅስቃሴ ውጪ ሆና መዋሏን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በጉራጌ ጉዳዮች ላይ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሐሳቦችን የሚያቀርበው አቶ ተስፋ ነዳም የሁለቱ ከተሞች ነዋሪዎች ከቤቱ መዋላቸውን “ከዳቦ ቤት እና ከሕክምና ተቋማት ውጪ ሙሉ በሙሉ የንግድ እንቅስቃሴ ቆሞ ውሏል” ሲሉ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። እንደ አቶ ተስፋ ከሆነ በዞኑ ባሉ አንዳንድ አካባቢዎች የመንግሥት አስተዳዳሪዎች ነዋሪዎችን ለውይይት ቢጠሩም ነዋሪዎች ለመሰብሰብ ፍቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረታቸው የታቀዱት ስብሰባዎች ሳይካሄዱ ቀርተዋል ብለዋል። የሥራ ማቆም አድማ የተደረገው የጉራጌ ዞን ከሌሎች ማኅበረሰቦች ጋር በመሆን በክላስተር መደራጀት ሳይሆን በክልልነት እንዲዋቀወር የቀረበው ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ጫና ለማሳደር መሆኑን አቶ ተስፋ ያስረዳሉ። ጨምረውም ከሦስት ዓመታት በፊት የጉራጌ ዞን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት ጥያቄውን ለክልሉ በይፋ አቅርቦ እንደነበረ በማስታወስ፣ የዞኑ አስተዳደርም በአሁን የቀረበውን የአወቃቀር አማራጭን አይቀበልም ሲሉ ይናገራሉ። የጉራጌ ሕዝብ እራሱን በክልልነት የማደረጀት ሙሉ ሕገ-መንግሥታዊ መብት እንዳለው የሚናገሩት አቶ ተስፋ፤ “መንግሥትም ቢሆን በዚህ አደረጃጀት ተደራጁ ወይም የምፈቅደው ይህ ነው የማለት መብት የለውም” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የጉራጌ ዞን ራሱን ችሎ በክልልነት የመደራጀት ጥያቄ ማቅረብ ከጀመረ ዓመታት መቆጠራቸውን የሚናገሩት ደግሞ የጉራጌ ባህላዊ ሸንጎ መሥራችና ሰብሳቢ ወ/ሮ ዛይዳ ግዛው ናቸው። “ለውጡ ከመምጣቱ በፊት ህወሓት አገር ሲመራ ከሌሎች ጋር በክልል አልዋቀርም ብሎ ለመጀመሪያ ጊዜ ተቃውሞ ያሰማው የጉራጌ ማኅብረሰብ ነው” በማለት ይናራሉ። ለዘመናት የዘለቀው ጥያቄ ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ምላሽ አላገኘም የሚሉት ወ/ሮ ዛይዳ፤ “ሕዝቡ ቁጭት ውስጥ ገብቷል። የፖለቲካ አሻጥርም በዝቶበታል” በማለት ወ/ሮ ዛይዳ ያስረዳሉ። ጉራጌ አሁን ተደራጅቶ የሚገኝበት ሁኔታ “የራሱን ቋንቋ፣ ማንነቱን፣ ባህሉን ማሳደግ እናመጠበቅ አልቻለም። የጉራጊኛ ቋንቋ ሊጠፋ ከጫፍ ድርሷል። ቋንቋው ለመማሪያነት አልበቃም እነዚህ ሁሉ መስተካከል ስላለባቸው ነው የክልል ጥያቄ የተነሳው” ይላሉ አቶ ተስፋ። ጉራጌ በክላስተር የሚደራጅ ከሆነ ሕዝቡ ከሁለት በላይ ወደ ሆኑ ዞኖች ተከፋፍሎ ስለሚገባ የጉራጌ ማንነትን ሊያሳጣ ይችላል በማለት ስጋታቸውንም ጨምረው ይናገራሉ። ወ/ሮ ዛይዳ በበኩላቸው፤ ክላስተሩ የሕገ-መንግሥት መሠረት የሌለው እና ሕብረተሰቡ ሳይቀበለው በግድ የሚጫንበት ሃሳብ በመሆኑ አንቀበለውም ይላሉ። “የጉራጌ ማኅብረሰብን ቋንቋ፣ ባህል የሚያጠፋ ነው። እስከ ዛሬ ድረስ በቋንቋው ማስተማር እና አካባቢውን ማልማት ያልቻለ፣ የፖለቲከኖች አሻጥር አድክሞት የኖረ ማኅብረሰብ ከአሁን በኋላ በክላስተር ይደራጅ ቢባል በፍጹም ሊያንሰራራ የማይችልበት ደረጃ ላይ ይገባል” ሲሉ ወ/ሮ ዛይዳም ስጋታቸውን ይገልጻሉ። “በትግል የማይለወጥ ነገር የለም” የሚሉት ደግሞ አቶ ተስፋ፤ “የተቀረውን ሕዝብ የሚጎዳ ነገር ሳይኖር አሁንም ቢሆን ሕጋዊ መስመሩን በመከተል የዞኑ ምክር ቤት ጥያቄ እንዲከበረ ጥረታችንን እንቀጥላለን” ሲሉ አቶ ተስፋ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/czv81ngnk08o |
3politics
| "ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሱዳን ወታደሮቿን ከኢትዮጵያ ግዛት እንድታስወጣ ያሳስብ" የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር | የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፤ ሱዳን ወታደሮቿን ከኢትዮጵያ ግዛት እንድታስወጣ ዓለም አቀፉ ማሳሰብ እንዳለበት ተናገሩ። አምባሳደር ዲና ሳምንታዊ የመገናኛ ብዙኃን መግለጫቸውን ዛሬ ሲሰጡ፤ ሱዳን እአአ በ1972 በሁለቱ አገሮች መካከል የተደረገውን ስምምነት እንድትከተል አሳስበዋል። የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ድልድዮችን እና ወታደራዊ ሰፈሮችን ለመገንባት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ገልጸው፤ ይህንንም ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እያሳወቁ መሆኑን አክለዋል። ሱዳን ከዚህ እንቅስቃሴ መታቀብ እንዳለባት ገልጸው፤ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው አለመግባባት መፈታት ያለበት በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንደሆነም ተናግረዋል። ሱዳን እና ኢትዮጵያ በድንበር ጉዳይ ውዝግብ ውስጥ ከገቡ ወራት ተቆጥረዋል። አምባሳደር ዲና በዛሬው መግለጫቸው ካነሷቸው ነጥቦች መካከል ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጉዳይ ይጠቀሳል። ኢትዮጵያ፤ ከግብጽ እና ከሱዳን ጋር 2015 ላይ በደረሰችው የሦስትዮሽ ስምምነት መሠረት የግድቡን ግንባታ መቀጠሏን አንስተዋል። በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ጦርነት በተመለከተ፤ የፌደራል መንግሥቱ የተኩስ አቁም ቢያደርግም የህወሓት ኃይሎች "በአማራ እና በአፋር ክልሎች ጥቃት መሰንዘራቸው የተኩስ አቁሙን ውሳኔ የሚፈትን" መሆኑን ጠቁመዋል። "ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ህወሓት የተኩስ አቁሙን እንዲያከብር ጫና ማሳደር አለበት" ብለዋል። የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ካነሷቸው ነጥቦች መካከል በግጭት ሳቢያ ጉዳት የደረሰባቸው አካባቢዎች ጉዳይ ይጠቀሳል። የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በግጭት ከተጎዱ አካባቢዎች መካከል ለጂሌ ጢሙጋ እና ኤፍራታ ግድም ወረዳዎች መልሶ ግንባታ እንዲውል ለእያንዳዳቸው 200,000 ብር መስጠቱም ተጠቁሟል። የሳዑዲ ተመላሾች ጉዳይ ኢትዮጵያ በአንድ ወር ውስጥ 42,000 ዜጎችን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አገር ቤት መመለሷ ተገልጿል። ይህም 84 በመቶ ወንዶች እና 16 በመቶ ሴቶችን ያካተተ ነው ተብሏል። ከስደት ተመላሾች ወደ ትውልድ ቀያቸው እንዲመለሱ የሚደረግ ሲሆን፤ አሁን ላይ በትግራይ ባለው ቀውስ ሳቢያ የትግራይ ተወላጆች የሆኑ ከስደት ተመላሾችን ወደ አካባቢው ለመመለስ አዳጋች እንደሆነ ተገልጿል። አዲስ አበባ ውስጥ ስምንት የስደተኞች መቀበያ ማዕከሎች እንደተቋቋሙና፤ የሳዑዲ ተመላሾች ወደ መዳረሻቸው እስኪሄዱ ድረስ በማዕከሎቹ እንደሚቆዩ ተነግሯል። ከስደት የተመለሱ ዜጎች የአካላዊ ጤናና የሥነ ልቦና ክትትል እንደሚደረግላቸው ተጠቁሟል። ከዚህ በተጨማሪ ከቤተሰቦቻቸው የተለያዩ ልጆች፣ ልጆች ያላቸው እናቶች፣ የሕገ ወጥ የሰው ዝውውር ሰለባ የሆኑ ሰዎች ልዩ ክትትል የሚያገኙባቸው ማዕከሎች እንዳሉ ተገልጿል። ኢትዮጵያ እአአ ከ2017 ወዲህ ከሳዑዲ ያስመለሰቻቸው ዜጎች ባጠቃላይ 415,000 ይደርሳሉ። | "ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሱዳን ወታደሮቿን ከኢትዮጵያ ግዛት እንድታስወጣ ያሳስብ" የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፤ ሱዳን ወታደሮቿን ከኢትዮጵያ ግዛት እንድታስወጣ ዓለም አቀፉ ማሳሰብ እንዳለበት ተናገሩ። አምባሳደር ዲና ሳምንታዊ የመገናኛ ብዙኃን መግለጫቸውን ዛሬ ሲሰጡ፤ ሱዳን እአአ በ1972 በሁለቱ አገሮች መካከል የተደረገውን ስምምነት እንድትከተል አሳስበዋል። የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ድልድዮችን እና ወታደራዊ ሰፈሮችን ለመገንባት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ገልጸው፤ ይህንንም ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እያሳወቁ መሆኑን አክለዋል። ሱዳን ከዚህ እንቅስቃሴ መታቀብ እንዳለባት ገልጸው፤ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው አለመግባባት መፈታት ያለበት በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንደሆነም ተናግረዋል። ሱዳን እና ኢትዮጵያ በድንበር ጉዳይ ውዝግብ ውስጥ ከገቡ ወራት ተቆጥረዋል። አምባሳደር ዲና በዛሬው መግለጫቸው ካነሷቸው ነጥቦች መካከል ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጉዳይ ይጠቀሳል። ኢትዮጵያ፤ ከግብጽ እና ከሱዳን ጋር 2015 ላይ በደረሰችው የሦስትዮሽ ስምምነት መሠረት የግድቡን ግንባታ መቀጠሏን አንስተዋል። በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ጦርነት በተመለከተ፤ የፌደራል መንግሥቱ የተኩስ አቁም ቢያደርግም የህወሓት ኃይሎች "በአማራ እና በአፋር ክልሎች ጥቃት መሰንዘራቸው የተኩስ አቁሙን ውሳኔ የሚፈትን" መሆኑን ጠቁመዋል። "ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ህወሓት የተኩስ አቁሙን እንዲያከብር ጫና ማሳደር አለበት" ብለዋል። የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ካነሷቸው ነጥቦች መካከል በግጭት ሳቢያ ጉዳት የደረሰባቸው አካባቢዎች ጉዳይ ይጠቀሳል። የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በግጭት ከተጎዱ አካባቢዎች መካከል ለጂሌ ጢሙጋ እና ኤፍራታ ግድም ወረዳዎች መልሶ ግንባታ እንዲውል ለእያንዳዳቸው 200,000 ብር መስጠቱም ተጠቁሟል። የሳዑዲ ተመላሾች ጉዳይ ኢትዮጵያ በአንድ ወር ውስጥ 42,000 ዜጎችን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አገር ቤት መመለሷ ተገልጿል። ይህም 84 በመቶ ወንዶች እና 16 በመቶ ሴቶችን ያካተተ ነው ተብሏል። ከስደት ተመላሾች ወደ ትውልድ ቀያቸው እንዲመለሱ የሚደረግ ሲሆን፤ አሁን ላይ በትግራይ ባለው ቀውስ ሳቢያ የትግራይ ተወላጆች የሆኑ ከስደት ተመላሾችን ወደ አካባቢው ለመመለስ አዳጋች እንደሆነ ተገልጿል። አዲስ አበባ ውስጥ ስምንት የስደተኞች መቀበያ ማዕከሎች እንደተቋቋሙና፤ የሳዑዲ ተመላሾች ወደ መዳረሻቸው እስኪሄዱ ድረስ በማዕከሎቹ እንደሚቆዩ ተነግሯል። ከስደት የተመለሱ ዜጎች የአካላዊ ጤናና የሥነ ልቦና ክትትል እንደሚደረግላቸው ተጠቁሟል። ከዚህ በተጨማሪ ከቤተሰቦቻቸው የተለያዩ ልጆች፣ ልጆች ያላቸው እናቶች፣ የሕገ ወጥ የሰው ዝውውር ሰለባ የሆኑ ሰዎች ልዩ ክትትል የሚያገኙባቸው ማዕከሎች እንዳሉ ተገልጿል። ኢትዮጵያ እአአ ከ2017 ወዲህ ከሳዑዲ ያስመለሰቻቸው ዜጎች ባጠቃላይ 415,000 ይደርሳሉ። | https://www.bbc.com/amharic/news-58014959 |
5sports
| የእግር ኳሱ ዓለም ሐዘን በአርጀንቲናዊው ኮከብ ዲያጎ ማራዶና ሞት | የእግር ኳሱ ዓለም በአርጀንቲናዊው ኮከብ ድንገተኛ ሞት ሐዘን ውስጥ ገብቷል። ማራዶናን በተጫጨችነትም ሆነ በአሰልጣኝነት ዘመኑ የሚያውቁት ሰዎች ለቢቢሲ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። የሊቨፑሉ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ "እንኳን ጨዋታው ሲያሟሙቅ የሚያደርገው እንቅስቃሴም ልዩ ነው" ብለውታል። የሪያል ማድሪዱ አሰልጣኝ ፈረንሳያዊው ዚነዲን ዚዳን ደግሞ "በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ የዓለማችን ወጣቶች አርዓያ መሆኑን የመንገር ዕድሉ ገጥሞኝ ነበር" ይላል። | የእግር ኳሱ ዓለም ሐዘን በአርጀንቲናዊው ኮከብ ዲያጎ ማራዶና ሞት የእግር ኳሱ ዓለም በአርጀንቲናዊው ኮከብ ድንገተኛ ሞት ሐዘን ውስጥ ገብቷል። ማራዶናን በተጫጨችነትም ሆነ በአሰልጣኝነት ዘመኑ የሚያውቁት ሰዎች ለቢቢሲ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። የሊቨፑሉ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ "እንኳን ጨዋታው ሲያሟሙቅ የሚያደርገው እንቅስቃሴም ልዩ ነው" ብለውታል። የሪያል ማድሪዱ አሰልጣኝ ፈረንሳያዊው ዚነዲን ዚዳን ደግሞ "በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ የዓለማችን ወጣቶች አርዓያ መሆኑን የመንገር ዕድሉ ገጥሞኝ ነበር" ይላል። | https://www.bbc.com/amharic/news-55145183 |
3politics
| ፖላንድ የተመታችው በዩክሬን ሚሳኤል እንደሚሆን ኔቶ ገለጸ | ፖላንድ ውስጥ ሁለት ሰዎችን የገደለው ሚሳኤል የዩክሬን ሊሆን እንደሚችል የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን (ኔቶ) ዋና ጸሐፊ የሆኑት ጀነራል ጄን ስቶልንበርግ ለቢቢሲ ገለጹ። በዩክሬን ድንበር አቅራቢያ ስለተተኮሰው ሚሳኤል ምርመራ እየተደረገ ሲሆን፣ ዋና ጸሐፊው “ሚሳኤሉ የዩክሬን የአየር መከላከያ የመሆን ዕድሉ ሰፊ ነው” ብለዋል። ሚሳኤሉ የዩክሬን ቢሆንም፣ ለአጠቃላይ ሁኔታው ተጠያቂ ወረራ ያካሄደችው ሩስያ እንደሆነች ተናግረዋል። ሚሳኤሉ የተተኮሰው በሩሲያ እንደሆነ ዩክሬን ገልጻለች። “ይሄ የኛ ሚሳኤል እንዳልሆነ ቅንጣት አልጠራጠርም። ወታደራዊ ሪፖርቶቻችን እንደሚያሳዩት ሚሳኤሉ የሩሲያ ነው” ሲሉ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ተናግረዋል። ከዩክሬን ድንበር በስድስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ፣ በፖላንድ፣ ፕርዝዎዶ በተባለ የእርሻ ቦታ የወደቀው ሚሳኤልን በተመለከተ በሚደረገው ምርመራ ለመሳተፍ ዩክሬን ጠይቃለች። ሩሲያ ባለፈው ማክሰኞ ከዘጠኝ ወራት በፊት የዩክሬን ወረራ ከተጀመረ ወዲህ ትልቁ የተባለ ተከታታይ የሚሳኤል ድብደባ ዩክሬን ላይ ፈጽማለች። ይህንን ተከትሎም ማክሰኞ የዩክሬን የአየር መከላከያዎች አልግሎት እየሰጡ ነበር። ሩሲያ በርካታ ሚሳኤሎችን ብትተኩስም ዩክሬን መታ እንደጣለቻቸው አስታውቃለች። የቡድን 20 አገራት ጉባዔ በኢንዶኔዥያ እየተካሄደ ባለበት ወቅት ነው ሩሲያ ጥቃቱን የፈጸመችው። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ጥቃቱን አውግዟል። የኔቶ አባል በሆነችው ፖላንድ ውስጥ ሚሳኤል መተኮሱ ጦርነቱ በአስጊ ሁኔታ እየተባባሰ መምጣቱን ይጠቁማል ተብሎም ተፈርቷል። የኔቶ ዋና ጸሐፊ እንዳሉት፣ ኔቶ ዘመነኛ የአየር መከላከያዎችን ለዩክሬን ለመስጠት ቃል ገብቷል። “ዩክሬንን ከሚደግፉ የኔቶ አጋሮች ጋር ባደረግነው ውይይት ዘመናዊ የአየር መከላከያ መሣሪያዎችን ለመስጠት ተስማምተናል። መሣሪያዎቹ የሩሲያን ሚሳኤል መተው ይጥላሉ” ብለዋል። ዘላቂ መፍትሄ የሚሆነው ግን ጦርነቱን ማቆም እንደሆነ ዋና ጸሐፊው አስምረውበታል። የፖላንድ ፕሬዝዳንት አንድርዜጅ ዱዳ፣ ከጥቃቱ ጀርባ ያለው S-300 የተባለው የሩሲያ ሚሳኤል እንደሆነ ተናግረዋል። ሆኖም ግን የተሰነዘረው ከሩሲያ እንደሆነ ማስረጃ አልተገኘም። ዩክሬን እና ሩሲያን ለማስታረቅ ስለሚደረገው ጥረት የተጠየቁት የኔቶ ዋና ጸሐፊ “ፑቲን ለመደራደር ፈቃደኛ አልሆኑም። ፑቲን ጦርነቱን ለማቆም ከፈቀዱ ሰላም ይሰፍናል። ዩክሬን ራሷን መከላከል ካቆመች ግን ውድመት ይጠብቃታል” ብለዋል። ሩሲያ ከዩክሬን መውጣቷ ለጦርነቱ ፖለቲካዊ መፍትሄ ወደመስጠት ሊያመራ እንደሚችል አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ጄነራል ተናግረዋል። ሆኖም ግን ሌላኛው ወታደራዊ ጀነራል ማርክ ሚሊ እንዳሉት፣ ዩክሬን አጠቃላይ ግዛቶቿን አስመልሳ ድል የምትቀዳጅበት ጊዜ ሩቅ ሊሆን ይችላል። | ፖላንድ የተመታችው በዩክሬን ሚሳኤል እንደሚሆን ኔቶ ገለጸ ፖላንድ ውስጥ ሁለት ሰዎችን የገደለው ሚሳኤል የዩክሬን ሊሆን እንደሚችል የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን (ኔቶ) ዋና ጸሐፊ የሆኑት ጀነራል ጄን ስቶልንበርግ ለቢቢሲ ገለጹ። በዩክሬን ድንበር አቅራቢያ ስለተተኮሰው ሚሳኤል ምርመራ እየተደረገ ሲሆን፣ ዋና ጸሐፊው “ሚሳኤሉ የዩክሬን የአየር መከላከያ የመሆን ዕድሉ ሰፊ ነው” ብለዋል። ሚሳኤሉ የዩክሬን ቢሆንም፣ ለአጠቃላይ ሁኔታው ተጠያቂ ወረራ ያካሄደችው ሩስያ እንደሆነች ተናግረዋል። ሚሳኤሉ የተተኮሰው በሩሲያ እንደሆነ ዩክሬን ገልጻለች። “ይሄ የኛ ሚሳኤል እንዳልሆነ ቅንጣት አልጠራጠርም። ወታደራዊ ሪፖርቶቻችን እንደሚያሳዩት ሚሳኤሉ የሩሲያ ነው” ሲሉ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ተናግረዋል። ከዩክሬን ድንበር በስድስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ፣ በፖላንድ፣ ፕርዝዎዶ በተባለ የእርሻ ቦታ የወደቀው ሚሳኤልን በተመለከተ በሚደረገው ምርመራ ለመሳተፍ ዩክሬን ጠይቃለች። ሩሲያ ባለፈው ማክሰኞ ከዘጠኝ ወራት በፊት የዩክሬን ወረራ ከተጀመረ ወዲህ ትልቁ የተባለ ተከታታይ የሚሳኤል ድብደባ ዩክሬን ላይ ፈጽማለች። ይህንን ተከትሎም ማክሰኞ የዩክሬን የአየር መከላከያዎች አልግሎት እየሰጡ ነበር። ሩሲያ በርካታ ሚሳኤሎችን ብትተኩስም ዩክሬን መታ እንደጣለቻቸው አስታውቃለች። የቡድን 20 አገራት ጉባዔ በኢንዶኔዥያ እየተካሄደ ባለበት ወቅት ነው ሩሲያ ጥቃቱን የፈጸመችው። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ጥቃቱን አውግዟል። የኔቶ አባል በሆነችው ፖላንድ ውስጥ ሚሳኤል መተኮሱ ጦርነቱ በአስጊ ሁኔታ እየተባባሰ መምጣቱን ይጠቁማል ተብሎም ተፈርቷል። የኔቶ ዋና ጸሐፊ እንዳሉት፣ ኔቶ ዘመነኛ የአየር መከላከያዎችን ለዩክሬን ለመስጠት ቃል ገብቷል። “ዩክሬንን ከሚደግፉ የኔቶ አጋሮች ጋር ባደረግነው ውይይት ዘመናዊ የአየር መከላከያ መሣሪያዎችን ለመስጠት ተስማምተናል። መሣሪያዎቹ የሩሲያን ሚሳኤል መተው ይጥላሉ” ብለዋል። ዘላቂ መፍትሄ የሚሆነው ግን ጦርነቱን ማቆም እንደሆነ ዋና ጸሐፊው አስምረውበታል። የፖላንድ ፕሬዝዳንት አንድርዜጅ ዱዳ፣ ከጥቃቱ ጀርባ ያለው S-300 የተባለው የሩሲያ ሚሳኤል እንደሆነ ተናግረዋል። ሆኖም ግን የተሰነዘረው ከሩሲያ እንደሆነ ማስረጃ አልተገኘም። ዩክሬን እና ሩሲያን ለማስታረቅ ስለሚደረገው ጥረት የተጠየቁት የኔቶ ዋና ጸሐፊ “ፑቲን ለመደራደር ፈቃደኛ አልሆኑም። ፑቲን ጦርነቱን ለማቆም ከፈቀዱ ሰላም ይሰፍናል። ዩክሬን ራሷን መከላከል ካቆመች ግን ውድመት ይጠብቃታል” ብለዋል። ሩሲያ ከዩክሬን መውጣቷ ለጦርነቱ ፖለቲካዊ መፍትሄ ወደመስጠት ሊያመራ እንደሚችል አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ጄነራል ተናግረዋል። ሆኖም ግን ሌላኛው ወታደራዊ ጀነራል ማርክ ሚሊ እንዳሉት፣ ዩክሬን አጠቃላይ ግዛቶቿን አስመልሳ ድል የምትቀዳጅበት ጊዜ ሩቅ ሊሆን ይችላል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c03nwl2w295o |
5sports
| ተሰናባቹ ኡናይ ኤምሪን ሊተኳቸው የሚችሉ 7 አሰልጣኞች | አርሰናል ክለቡን ለ18 ወራት ያሰለጠኑት ስፔናዊው ኡናይ ኤምሪን ከስራቸው አሰናብቷል። ፓሪሴንት-ጀርሜይን ጋር የፈረንሳይ ሊግ ዋንጫ እና ከሲቪያ ጋር ሶስት የዩሮፓ ሊግ ዋንጫዎችን ማንሳት የቻሉት ኡናይ ኤምሪ በአርሰናል አመርቂ ውጤት ማምጣት ባለመቻላቸው ዛሬ የክለቡ አስተዳደር እንዳሰናበታቸው ገልጿል። • የስኮትላንድ እግር ኳስ ማህበር ታዳጊዎች ኳስ በቴስታ እንዳይመቱ ሊያግድ ነው • ከመኪኖች ይልቅ ብስክሌቶች የሚበዙባት ከተማ ክለቡ ቋሚ አሰልጣኝ እስኪያገኝ ድረስ፤ በረዳት አሰልጣኝ እና በቀድሞ የአርሰናል አማካይ ፍሬዲ ሉንበርግ በግዜያዊነት ይሰለጥናል ተብሏል። መድፈኞቹ ባለፉት 7 ጨዋታዎች ማሸነፍ ሳይችሉ የቀሩ ሲሆን፤ ትናንት ምሽት የዩሮፓ ሊግ የምድብ ጨዋታ በሺዎች በሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው ፊትና በሜዳቸው በጀርመኑ ክለብ ኢንትራ ፍራክፈርት 2 ለ 1 ተሸንፈዋል። ለመሆኑ ተሰናባቹ ኡናይ ኤምሪን ማን ሊተካቸው ይችላል? 1. ኑኖ ኤስፒሪቶ ሳንቶስ ኡናይን ይተካሉ ተብለው ከተገመቱ አሠልጣኖች መካከል በዋነኛነት ስማቸው እየተነሳ ያለው የወቅቱ የዎልቨርሃምፕተን አሠልጣኝ ኑኖ ኤስፔሪቶ ሳንቶስ ናቸው። ኑኖ ኤስፒሪቶ ሳንቶስ ዎልቭስን ይዘው በፕሪሚየር ሊጉ ሰንተረዥ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠው ይገኛሉ። 2. ማሲሚላኖ አሌግሪ ስካይ ስፖርት እንደዘገበው ኡናይ ኤምሪ ከአርሰናል ከተለያዩ በኋላ በማሲሚላኖ አሌግሪ እና በአርሰናል ክለብ መካከል ግንኙነቶች ተጀምሯል። በቅርቡ ከጁቬንቱስ የተለያዩት አሌግሪ ከአሮጊቷ ጋር ውጤታማ የሚባል ጊዜን አሳልፈዋል። አሌግሪ ከጁቬንቱስ ጋር አምስት የሴሪያአ እና አራት ኮፓ ኢታሊያ ዋንጫዎችን ከማንሳታቸውም በተጨማሪ ሁለት ጊዜ ለቻምፒያንስ ሊግ ፍጻሜ መድረስ ችለዋል። 3. ካርሎ አንቾሎቲ ናፖሊን እያሰለጠኑ የሚገኙት ካርሎ አንቾሎቲ ሌላው ኡናይ ኤምረን ይተካሉ ተብለው ከተገመቱት አሰልጣኞች መካከል ይገኙበታል። • «የኔ ትውልድ ታሪክ እንደሚሠራ እምነት አለኝ» ሎዛ አበራ ጣሊያናዊው አንቾሎቲ የውድድሩ ዘመን እስኪናቀቅ ድረስ ከናፖሊ ጋር ኮንትራት ቢኖርባቸውም፤ አሰልጣኙ ወደ ኤምሬትስ ሊያቀኑ እንደሚችል በስፋት እየተዘገበ ነው። 4. ብሬንዳን ሮጀርስ ሌስተር ሲቲዎች ዘንድሮ ደንቅ የሚባል የውድድር ዘመን እያሳለፉ ይገኛሉ። በብሬንዳን ሮጀርስ የሚመሩት ቀበሮዎቹ ካለፉት 10 ጨዋታዎች አርሰናልን ጨምሮ በድንቅ ጨዋታ 9 ግጥሚያዎችን በድል ማጠናቀቅ ችለዋል። ብሬንዳን ሮጀርስ ወደ ኢሚሬትስ እንዲያቀኑ የበርካታ የአርሰናል ደጋፊዎች ምኞት ነው። ኡናይ ኤምሪ አርሰናልን እንዲያሰለጥኑ ከመሾማቸው በፊት፤ ክለቡን ለማሰልጠን ስሙ በስፋት ሲነሳ የነበረው ማይክል አርቴታ ነበር። የቀድሞ የአርሰናል ተጫዋች ባለፉት ሶስት ዓመታት ከከማንችሰተር ሲቲው ፔፕ ጋርዲዎላ ሥር ሆኖ የአሰልጠኝነትን ክህሎት ሲማር ቆይቷል። ረዳት አሰልጣኙ አርቴታ፤ ማንችሰተር ሲቲ ሁለት የፕሪሚር ሊግ ዋንጫ፣ ሁለት የሊግ ዋንጫዎችን እና ኤፍ ኤ ዋንጫዎች እንዲያነሳ የበኩሉን አስተዋጽኦ አበርክቷል። ሌላው የቀድሞ የአርሰናል ባለታሪክ አማካይ ፓትሪክ ቪዬራ ቀጣዩ የአርሰናል አሰልጣኝ ሊሆን እንደሚችል እየተጠቀሰ ነው። • የሆንግ ኮንግን የዘር መድልዎ የሚፋለሙ አፍሪካዊያን እግር ኳስ ተጫዋቾች ቪዬራ የማይረሳውን የአርሰናል ወርቃማ የ2003/4 የድል የውድድር ዘመን አንበል በመሆን ክለቡን መርቷል። የፈረንሳዩን ኒስ እግር ኳስ ክለብ እያሰለጠነ የሚገኘው ቪዬራ የሚፈለገውን ውጤት እያስመዘገበ ባይሆንም፤ መድፈኞቹ የቼልሲን አርዓያ የሚከተሉ ከሆነ፤ ቪዬራ የአርሰናል አሰልጣኝ ሆኖ ሊሾም እንደሚችል እየተጠቆመ ነው። 7. ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ በቅርቡ ከፖተንሃም አሰልጣኝነት የተነሱት ፖቸቲኖ፤ ሌላው ቀጣዩ የአርሰናል አሰልጣኝ ይሆናሉ ተብለው ከተገመቱ አሰልጣኖች መካከል ይገኙበታል። የቶተነሃም ባላንጣ የሆነው አርሰናልን ለማሰልጠን ፍላጎት ይኖራቸው ይሆን? ሲሉ የሚጠይቁም አልጠፉም። ፖቸቲኖ ከአርሰናል ውጪ፤ የባየር ሚዩኒክ፣ ሪያል ማድሪድ ወይም ባርሴሎና አሰልጣኝ ለሆኑ እንደሚችሉ በስፋት እየተገመተ ይገኛል። | ተሰናባቹ ኡናይ ኤምሪን ሊተኳቸው የሚችሉ 7 አሰልጣኞች አርሰናል ክለቡን ለ18 ወራት ያሰለጠኑት ስፔናዊው ኡናይ ኤምሪን ከስራቸው አሰናብቷል። ፓሪሴንት-ጀርሜይን ጋር የፈረንሳይ ሊግ ዋንጫ እና ከሲቪያ ጋር ሶስት የዩሮፓ ሊግ ዋንጫዎችን ማንሳት የቻሉት ኡናይ ኤምሪ በአርሰናል አመርቂ ውጤት ማምጣት ባለመቻላቸው ዛሬ የክለቡ አስተዳደር እንዳሰናበታቸው ገልጿል። • የስኮትላንድ እግር ኳስ ማህበር ታዳጊዎች ኳስ በቴስታ እንዳይመቱ ሊያግድ ነው • ከመኪኖች ይልቅ ብስክሌቶች የሚበዙባት ከተማ ክለቡ ቋሚ አሰልጣኝ እስኪያገኝ ድረስ፤ በረዳት አሰልጣኝ እና በቀድሞ የአርሰናል አማካይ ፍሬዲ ሉንበርግ በግዜያዊነት ይሰለጥናል ተብሏል። መድፈኞቹ ባለፉት 7 ጨዋታዎች ማሸነፍ ሳይችሉ የቀሩ ሲሆን፤ ትናንት ምሽት የዩሮፓ ሊግ የምድብ ጨዋታ በሺዎች በሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው ፊትና በሜዳቸው በጀርመኑ ክለብ ኢንትራ ፍራክፈርት 2 ለ 1 ተሸንፈዋል። ለመሆኑ ተሰናባቹ ኡናይ ኤምሪን ማን ሊተካቸው ይችላል? 1. ኑኖ ኤስፒሪቶ ሳንቶስ ኡናይን ይተካሉ ተብለው ከተገመቱ አሠልጣኖች መካከል በዋነኛነት ስማቸው እየተነሳ ያለው የወቅቱ የዎልቨርሃምፕተን አሠልጣኝ ኑኖ ኤስፔሪቶ ሳንቶስ ናቸው። ኑኖ ኤስፒሪቶ ሳንቶስ ዎልቭስን ይዘው በፕሪሚየር ሊጉ ሰንተረዥ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠው ይገኛሉ። 2. ማሲሚላኖ አሌግሪ ስካይ ስፖርት እንደዘገበው ኡናይ ኤምሪ ከአርሰናል ከተለያዩ በኋላ በማሲሚላኖ አሌግሪ እና በአርሰናል ክለብ መካከል ግንኙነቶች ተጀምሯል። በቅርቡ ከጁቬንቱስ የተለያዩት አሌግሪ ከአሮጊቷ ጋር ውጤታማ የሚባል ጊዜን አሳልፈዋል። አሌግሪ ከጁቬንቱስ ጋር አምስት የሴሪያአ እና አራት ኮፓ ኢታሊያ ዋንጫዎችን ከማንሳታቸውም በተጨማሪ ሁለት ጊዜ ለቻምፒያንስ ሊግ ፍጻሜ መድረስ ችለዋል። 3. ካርሎ አንቾሎቲ ናፖሊን እያሰለጠኑ የሚገኙት ካርሎ አንቾሎቲ ሌላው ኡናይ ኤምረን ይተካሉ ተብለው ከተገመቱት አሰልጣኞች መካከል ይገኙበታል። • «የኔ ትውልድ ታሪክ እንደሚሠራ እምነት አለኝ» ሎዛ አበራ ጣሊያናዊው አንቾሎቲ የውድድሩ ዘመን እስኪናቀቅ ድረስ ከናፖሊ ጋር ኮንትራት ቢኖርባቸውም፤ አሰልጣኙ ወደ ኤምሬትስ ሊያቀኑ እንደሚችል በስፋት እየተዘገበ ነው። 4. ብሬንዳን ሮጀርስ ሌስተር ሲቲዎች ዘንድሮ ደንቅ የሚባል የውድድር ዘመን እያሳለፉ ይገኛሉ። በብሬንዳን ሮጀርስ የሚመሩት ቀበሮዎቹ ካለፉት 10 ጨዋታዎች አርሰናልን ጨምሮ በድንቅ ጨዋታ 9 ግጥሚያዎችን በድል ማጠናቀቅ ችለዋል። ብሬንዳን ሮጀርስ ወደ ኢሚሬትስ እንዲያቀኑ የበርካታ የአርሰናል ደጋፊዎች ምኞት ነው። ኡናይ ኤምሪ አርሰናልን እንዲያሰለጥኑ ከመሾማቸው በፊት፤ ክለቡን ለማሰልጠን ስሙ በስፋት ሲነሳ የነበረው ማይክል አርቴታ ነበር። የቀድሞ የአርሰናል ተጫዋች ባለፉት ሶስት ዓመታት ከከማንችሰተር ሲቲው ፔፕ ጋርዲዎላ ሥር ሆኖ የአሰልጠኝነትን ክህሎት ሲማር ቆይቷል። ረዳት አሰልጣኙ አርቴታ፤ ማንችሰተር ሲቲ ሁለት የፕሪሚር ሊግ ዋንጫ፣ ሁለት የሊግ ዋንጫዎችን እና ኤፍ ኤ ዋንጫዎች እንዲያነሳ የበኩሉን አስተዋጽኦ አበርክቷል። ሌላው የቀድሞ የአርሰናል ባለታሪክ አማካይ ፓትሪክ ቪዬራ ቀጣዩ የአርሰናል አሰልጣኝ ሊሆን እንደሚችል እየተጠቀሰ ነው። • የሆንግ ኮንግን የዘር መድልዎ የሚፋለሙ አፍሪካዊያን እግር ኳስ ተጫዋቾች ቪዬራ የማይረሳውን የአርሰናል ወርቃማ የ2003/4 የድል የውድድር ዘመን አንበል በመሆን ክለቡን መርቷል። የፈረንሳዩን ኒስ እግር ኳስ ክለብ እያሰለጠነ የሚገኘው ቪዬራ የሚፈለገውን ውጤት እያስመዘገበ ባይሆንም፤ መድፈኞቹ የቼልሲን አርዓያ የሚከተሉ ከሆነ፤ ቪዬራ የአርሰናል አሰልጣኝ ሆኖ ሊሾም እንደሚችል እየተጠቆመ ነው። 7. ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ በቅርቡ ከፖተንሃም አሰልጣኝነት የተነሱት ፖቸቲኖ፤ ሌላው ቀጣዩ የአርሰናል አሰልጣኝ ይሆናሉ ተብለው ከተገመቱ አሰልጣኖች መካከል ይገኙበታል። የቶተነሃም ባላንጣ የሆነው አርሰናልን ለማሰልጠን ፍላጎት ይኖራቸው ይሆን? ሲሉ የሚጠይቁም አልጠፉም። ፖቸቲኖ ከአርሰናል ውጪ፤ የባየር ሚዩኒክ፣ ሪያል ማድሪድ ወይም ባርሴሎና አሰልጣኝ ለሆኑ እንደሚችሉ በስፋት እየተገመተ ይገኛል። | https://www.bbc.com/amharic/news-50597494 |
0business
| 'በርሜል ሙሉ ገንዘብ ተገኘ የተባለው ሐሰት ነው' - አ/አ ፖሊስ | የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በአራዳ ክፍለ ከተማ በልመና በሚተዳደሩ አንዲት ግለሰብ ቤት ውስጥ ከ45 ሺህ በላይ ብር ማግኘቱን ሲያረጋግጥ፤ በርሜል ሙሉ ገንዘብ ተገኘ የሚለውን ዘገባ ሐሰት ሲል አስተባብሏል። በክፍል ከተማው በተለምዶ አትክልት ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በልመና የሚተዳደሩት ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ነው ገንዘቡ የተገኘው። ኮሚሽኑ ግለሰቧ ረዳትም ሆነ ልጅ በአጠገባቸው የሌላቸው የአእምሮ ህመም ያለባቸው ናቸው ያለ ሲሆን፤ ገንዘቡ የተገኘው በተለያዩ ፌስታሎች ነው ይላል ኮሚሽኑ በፌስቡክ ገፁ ያሰፈረው ዜና። የአካባቢው ነዋሪዎች ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ መሰረት ፖሊስ ሁኔታውን ለማረጋገጥ ወደ ስፍራው በማምራት ገንዘቡን እንዳገኘ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል። "በቦታው ላይ በተደረገው የማረጋገጥ ሥራ በግለሰቧ መኖሪያ ቤት ውስጥ በርካታ የተቋጠሩ ፌስታሎች እና ሌሎች ቆሻሻ ዕቃዎች ተከማችተው የተቀመጡ ሲሆን ከተቋጠሩት ፌስታሎች መካከል ገንዘብ ያለባቸው" ይላል የኮሚሽኑ ገለፃ። በልብስ መዘፍዘፊያ ፕላስቲክ የተወሰነ ብር እንደተገኘ የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከአካባቢው ነዋሪዎች ታዛቢዎችን በመጨመር ፖሊስ እና የወረዳው አስተዳደር ባደረጉት ቆጠራ የተገኘው ገንዘብ 45 ሺህ 858 ብር መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል። ፖሊስ ኮሚሽኑ ጨምሮ እንደገለጸው ከተገኘው ገንዘብ ውስጥ አንድ ሺህ ብር ግለሰቧ ለዕለት ወጪያቸው እንዲጠቀሙበት የተሰጣቸው ሲሆን፤ ቀሪው ብር ደግሞ በግለሰቧ ስም የባንክ የሂሳብ ተከፍቶ ገቢ ተደርጎላቸዋል። በሌላ በኩል ደግሞ በርሜል ሙሉ ገንዘብ ተከማችቶ ተገኘ በሚል በተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች እየተላለፈ ያለው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታዉቋል። ማክሰኞ ረፋዱ ላይ አራዳ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ኢንፎኔት ኮሌጅ አካባቢ አንድ በርሜል ገንዘብ ወድቆ ተገኝቷል ሲሉ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበው ነበር። የተገኘው ገንዘብ የኢትዮጵያ ብር እና ዶላር እንደሆነና ገንዘቡን ማን እንደጣለው ያልተተረጋገጠ መሆኑን በመግለጽ የአካባቢው ፖሊስ በመኪና ጭኖ እንደወሰደውም ተዘግቦ ነበር። ኮሚሽኑ ግን ይህ ዘገባ የተሳሳተ ነው ሲል አስተባብሏል። | 'በርሜል ሙሉ ገንዘብ ተገኘ የተባለው ሐሰት ነው' - አ/አ ፖሊስ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በአራዳ ክፍለ ከተማ በልመና በሚተዳደሩ አንዲት ግለሰብ ቤት ውስጥ ከ45 ሺህ በላይ ብር ማግኘቱን ሲያረጋግጥ፤ በርሜል ሙሉ ገንዘብ ተገኘ የሚለውን ዘገባ ሐሰት ሲል አስተባብሏል። በክፍል ከተማው በተለምዶ አትክልት ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በልመና የሚተዳደሩት ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ነው ገንዘቡ የተገኘው። ኮሚሽኑ ግለሰቧ ረዳትም ሆነ ልጅ በአጠገባቸው የሌላቸው የአእምሮ ህመም ያለባቸው ናቸው ያለ ሲሆን፤ ገንዘቡ የተገኘው በተለያዩ ፌስታሎች ነው ይላል ኮሚሽኑ በፌስቡክ ገፁ ያሰፈረው ዜና። የአካባቢው ነዋሪዎች ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ መሰረት ፖሊስ ሁኔታውን ለማረጋገጥ ወደ ስፍራው በማምራት ገንዘቡን እንዳገኘ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል። "በቦታው ላይ በተደረገው የማረጋገጥ ሥራ በግለሰቧ መኖሪያ ቤት ውስጥ በርካታ የተቋጠሩ ፌስታሎች እና ሌሎች ቆሻሻ ዕቃዎች ተከማችተው የተቀመጡ ሲሆን ከተቋጠሩት ፌስታሎች መካከል ገንዘብ ያለባቸው" ይላል የኮሚሽኑ ገለፃ። በልብስ መዘፍዘፊያ ፕላስቲክ የተወሰነ ብር እንደተገኘ የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከአካባቢው ነዋሪዎች ታዛቢዎችን በመጨመር ፖሊስ እና የወረዳው አስተዳደር ባደረጉት ቆጠራ የተገኘው ገንዘብ 45 ሺህ 858 ብር መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል። ፖሊስ ኮሚሽኑ ጨምሮ እንደገለጸው ከተገኘው ገንዘብ ውስጥ አንድ ሺህ ብር ግለሰቧ ለዕለት ወጪያቸው እንዲጠቀሙበት የተሰጣቸው ሲሆን፤ ቀሪው ብር ደግሞ በግለሰቧ ስም የባንክ የሂሳብ ተከፍቶ ገቢ ተደርጎላቸዋል። በሌላ በኩል ደግሞ በርሜል ሙሉ ገንዘብ ተከማችቶ ተገኘ በሚል በተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች እየተላለፈ ያለው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታዉቋል። ማክሰኞ ረፋዱ ላይ አራዳ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ኢንፎኔት ኮሌጅ አካባቢ አንድ በርሜል ገንዘብ ወድቆ ተገኝቷል ሲሉ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበው ነበር። የተገኘው ገንዘብ የኢትዮጵያ ብር እና ዶላር እንደሆነና ገንዘቡን ማን እንደጣለው ያልተተረጋገጠ መሆኑን በመግለጽ የአካባቢው ፖሊስ በመኪና ጭኖ እንደወሰደውም ተዘግቦ ነበር። ኮሚሽኑ ግን ይህ ዘገባ የተሳሳተ ነው ሲል አስተባብሏል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54977501 |
5sports
| እግር ኳስ፡ ቲየሪ ኦንሪ በዘረኝነት ምክንያት ራሱን ከማኅበራዊ ሚዲያ አገለለ | የቀድሞው የአርሰልና የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጫዋች ቲዬሪ ኦንሪ በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚሰነዘሩ የዘረኝነትና ሌሎች መሰል የበይነ መረብ ጥቃቶችን በመቃወም ራሱን ከማኅበራዊ ሚዲያዎች እንዳገለለ አስታውቋል። የ43 ዓመቱ ኦንሪ 2.3 ለሚሆኑት የትዊተር ተከታዮቹ አርብ ዕለት ባስተላለፈው መልዕክት ችግሩ በጣም አሳሳቢ እንደሆነና ችላ ለማለት እንኳን ከባድ እንደሆነ ገልጿል። ወደ ማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚመለሰው የማኅበራዊ ሚዲያዎች ባለቤቶች ኮፒራይት (የባለቤትነት መብት) ላይ የሚከተሉትን አይነት ጠበቅ ያለ ክትትልና እርምጃ በዘረኝነት ላይም ሲያደርጉት ብቻ እንደሆነ ገልጿል። በጉዳዩ ላይ የተሻለ እርምጃ መወሰድ እንዲጀመርም ጠይቋል። ''በማኅበራዊ ሚዲያዎች በቀላሉ ገጽ መክፈት ይቻላል፤ ሌሎችን ማስፈራራትና የዘረኝነት መልዕክቶችን ማስተላለፍም እንዲሁ። የሚያስገርመውና የሚያሳዝነው ነገር ደግሞ እኚህ ሰዎች ማንነታቸው እንኳን በትክክል አይታወቅም'' ብሏል ፈረንሳያዊው እግረ ኳሰኛ። ''በማኅበራዊ ሚዲያዎቹ የሚታዩት ጥቃቶችና የዘረኝነት መልዕክቶቸ ችላ ለማለት እንኳን ጊዜ የሚሰጡ አይደሉም'' ብሏል። ቲዬሪ ኦንሪ ከእንግሊዙ ክለብ አርሰናል ጋር በመሆን በፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ1999 እስከ 2007 ባሉት ዓመታት ሁለት ጊዜ የፕሪምየር ሊጉ አሸናፊ መሆን የቻለ ተጫዋች ነው። ለአርሰናልና ለፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን በሚጫወትበት ወቅት አንዳንድ የዘረኝነት ጥቃቶች አጋጥመውት እንደነበር ባሳለፍነው መስከረም መግለጹ የሚታወስ ነው። ''እኛ ጥቃት የሚደርስብን ሰዎች ህመም ላይ እንደሆንን ሌሎች እንዲረዱ እንፈልጋለን። ሲበቃ ይበቃል'' ብሏል ኦንሪ። አርብ ዕለት በትዊተር ገጹ ላይ ባስተላለፈው መልዕክት አክሎም ''ከነገ ጠዋት ጀምሮ እራሴን ከማኅበራዊ ሚዲያዎች አግልያለው። ከዚህ በኋላ ወደ ማኅበራዊ ሚዲያዎች የምመለሰው የነዚህ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ባለቤቶች ልክ የኮፒራይት መብት ላይ የሚከተሉትን አይነት ጠበቅ ያለ ክትትልና እርምጃ በዘረኝነት ላይም ሲያደርጉት ብቻ ነው'' ብሏል። ''ይህ ሁኔታ እስከሚቀየር ድረስ ሁሉንም የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቼን አጠፋቸዋለው። ለውጡ ቶሎ እንደሚመጣም ተስፋ አደርጋለው።" ብሏል። ማኅበራዊ ሚዲያን የሚያስተዳድሩት ድርጅቶች ችግሩን ለመቆጣጠር በርካታ ሥራዎችን እያከናወኑ እንደሆነ በተደጋጋሚ ሲገልጹ ነበር። ትዊተር በቅርቡ መሰል የማኅበራዊ ሚዲያ ጥቃቶችን ለመቆጣጠር 'ኪክ ኢት አውት' (Kick It Out) የተሰኘ አሰራር መጀመሩን አስታውቋል። በፌስቡክ ስር የሚገኘው ኢንስታግራም በበኩሉ ባለፈው ዓመት ብቻ 6.6 ሚሊየን የጥላቻ ንግግሮችን እንዳስወገደ ገልጿል። | እግር ኳስ፡ ቲየሪ ኦንሪ በዘረኝነት ምክንያት ራሱን ከማኅበራዊ ሚዲያ አገለለ የቀድሞው የአርሰልና የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጫዋች ቲዬሪ ኦንሪ በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚሰነዘሩ የዘረኝነትና ሌሎች መሰል የበይነ መረብ ጥቃቶችን በመቃወም ራሱን ከማኅበራዊ ሚዲያዎች እንዳገለለ አስታውቋል። የ43 ዓመቱ ኦንሪ 2.3 ለሚሆኑት የትዊተር ተከታዮቹ አርብ ዕለት ባስተላለፈው መልዕክት ችግሩ በጣም አሳሳቢ እንደሆነና ችላ ለማለት እንኳን ከባድ እንደሆነ ገልጿል። ወደ ማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚመለሰው የማኅበራዊ ሚዲያዎች ባለቤቶች ኮፒራይት (የባለቤትነት መብት) ላይ የሚከተሉትን አይነት ጠበቅ ያለ ክትትልና እርምጃ በዘረኝነት ላይም ሲያደርጉት ብቻ እንደሆነ ገልጿል። በጉዳዩ ላይ የተሻለ እርምጃ መወሰድ እንዲጀመርም ጠይቋል። ''በማኅበራዊ ሚዲያዎች በቀላሉ ገጽ መክፈት ይቻላል፤ ሌሎችን ማስፈራራትና የዘረኝነት መልዕክቶችን ማስተላለፍም እንዲሁ። የሚያስገርመውና የሚያሳዝነው ነገር ደግሞ እኚህ ሰዎች ማንነታቸው እንኳን በትክክል አይታወቅም'' ብሏል ፈረንሳያዊው እግረ ኳሰኛ። ''በማኅበራዊ ሚዲያዎቹ የሚታዩት ጥቃቶችና የዘረኝነት መልዕክቶቸ ችላ ለማለት እንኳን ጊዜ የሚሰጡ አይደሉም'' ብሏል። ቲዬሪ ኦንሪ ከእንግሊዙ ክለብ አርሰናል ጋር በመሆን በፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ1999 እስከ 2007 ባሉት ዓመታት ሁለት ጊዜ የፕሪምየር ሊጉ አሸናፊ መሆን የቻለ ተጫዋች ነው። ለአርሰናልና ለፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን በሚጫወትበት ወቅት አንዳንድ የዘረኝነት ጥቃቶች አጋጥመውት እንደነበር ባሳለፍነው መስከረም መግለጹ የሚታወስ ነው። ''እኛ ጥቃት የሚደርስብን ሰዎች ህመም ላይ እንደሆንን ሌሎች እንዲረዱ እንፈልጋለን። ሲበቃ ይበቃል'' ብሏል ኦንሪ። አርብ ዕለት በትዊተር ገጹ ላይ ባስተላለፈው መልዕክት አክሎም ''ከነገ ጠዋት ጀምሮ እራሴን ከማኅበራዊ ሚዲያዎች አግልያለው። ከዚህ በኋላ ወደ ማኅበራዊ ሚዲያዎች የምመለሰው የነዚህ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ባለቤቶች ልክ የኮፒራይት መብት ላይ የሚከተሉትን አይነት ጠበቅ ያለ ክትትልና እርምጃ በዘረኝነት ላይም ሲያደርጉት ብቻ ነው'' ብሏል። ''ይህ ሁኔታ እስከሚቀየር ድረስ ሁሉንም የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቼን አጠፋቸዋለው። ለውጡ ቶሎ እንደሚመጣም ተስፋ አደርጋለው።" ብሏል። ማኅበራዊ ሚዲያን የሚያስተዳድሩት ድርጅቶች ችግሩን ለመቆጣጠር በርካታ ሥራዎችን እያከናወኑ እንደሆነ በተደጋጋሚ ሲገልጹ ነበር። ትዊተር በቅርቡ መሰል የማኅበራዊ ሚዲያ ጥቃቶችን ለመቆጣጠር 'ኪክ ኢት አውት' (Kick It Out) የተሰኘ አሰራር መጀመሩን አስታውቋል። በፌስቡክ ስር የሚገኘው ኢንስታግራም በበኩሉ ባለፈው ዓመት ብቻ 6.6 ሚሊየን የጥላቻ ንግግሮችን እንዳስወገደ ገልጿል። | https://www.bbc.com/amharic/news-56547572 |
0business
| የአሜሪካው አየር መንገድ ያልተከተቡ ሰራተኞቹን 200 ዶላር በየወሩ ሊቀጣ ነው | ዴልታ አየር መንገድ የአሜሪካ ሦስተኛው ትልቁ አየር መንገድ ሲሆን የኮቪድ-19 ላይ ክትባት ባልወሰዱ ሠራተኞች ላይ በየወሩ 200 ዶላር እንዲከፍሉ ሊያደርግ ነው። ሁለቱንም ክትባቶች ወስደው በበሽታው ለተያዙ ለኮቪድ ህመምተኞች ብቻ የሕመም ክፍያ እከፍላለሁ ብሏል። የቫይረሱ ስርጭት በመላው አሜሪካ እየጨመረ ባለበት ሁኔታ ውሳኔው የኮሮናቫይረስን "በከፍተኛ ሁኔታ መስፋፋት" ለመግታት ይረዳል ብለዋል ኃላፊው ኢድ ባስቲያን። እርምጃው አንድ ትልቅ ኩባንያ ሠራተኞቹ እንዲከተቡ ለማድረግ የተወሰደ ሙከራ ነው። ባስቲያን ለሠራተኞች በላኩት በማስታወሻ ላይ የዴልታ ተጨማሪ ክፍያ ከታህሳስ ጀምሮ በጤና እንክብካቤ መድን ዕቅዱ በተመዘገቡ ሠራተኞቹ ላይ እንደሚተገበር ገልጸዋል። ይህም አብዛኛዎቹን 75 ሺህ ሠራተኞቹን የሚመለከት ይሆናል። ዴልታ ለኮቪድ-19 የሆስፒታል ቆይታ በአንድ ሰው በአማካይ 50 ሺህ ዶላር ዋጋ ይከፍላል ብለዋል። "ክትባቱን ያለመውሰድ ውሳኔው ለኩባንያችን እየፈጠረ ያለውን የገንዘብ አደጋን ለመቅረፍ ይህ ተጨማሪ ክፍያ አስፈላጊ ይሆናል" ብለዋል። "B.1.617.2 የተባለው አዲስ ዝርያ ከተስፋፋ ወዲህ ከኮቪድ ጋር በተያያዘ ሆስፒታል የገቡ የዴልታ ሠራተኞች ሙሉ በሙሉ ያልተከተቡ ናቸው።" ከመስከረም 30 ጀምሮ ደግሞ ያልተከተቡ የዴልታ ሠራተኞች በየሳምንቱ የኮቪድ ምርመራዎችን ማድረግ እና በዴልታ የቢሮ ውስጥ ጭምብል ማድረግ አለባቸው። ሁሉም የአሜሪካ አየር መንገድ ሠራተኞች በአውሮፕላን ውስጥ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል መልበስ ቢኖርባቸውም በቢሮዎች ውስጥ ግን አይተገበርም። ዴልታ የተሰኘው የኮሮናቫይረስ ዝርያ በአሜሪካ መስፋፋቱን ተከትሎ የሃገሪቱ ኩባንያዎች ሠራተኞቻቸው ክትባት እንዲወስዱ ለማበረታታት የተለያዩ ዘዴዎች እየሞከሩ ነው። እንደ ዩናይትድ አየር መንገድ፣ ጎልድማን ሳክስ፣ ማይክሮሶፍት እና ጉግል ያሉ ኩባንያዎች ወደ ሥራ ለመግባት ሙሉ በሙሉ መከተብ እንዳለባቸው ለሠራተኞቻቸው ነግረዋል። የኢንቨስትመንት ኩባንያው ቫንጋርድ ለክትቡ ሠራተኞቹ የ 1 ሺህ ዶላር ጉርሻ ሰጥቷል። አማዞን እና አፕል ግን በዚህ ረገድ ምንም ፖሊሲ አላወጡም። የኢንቨስትመንት ባንኩ ክሬዲት ሱይስ ሁሉም ክትባት ያልሰጣቸው ሠራተኞች ከመስከረም 7 ጀምሮ ከቤት እንዲሠሩ እንደሚጠይቅ ረቡዕ ዕለት አስታውቋል። እንደ ሌሎቹ ኩባንያዎች ሁሉ ወደ ቢሮ ሙሉ ለሙሉ መመለሻ ጊዜን እስከ ጥቅምት ድረስ አዘግይቷል። በወረርሽኙ ወቅት ከፍተኛ የፍላጎት መቀዛቀዝ ተከሰቶ የአሜሪካ አየር መንገዶች በራስ መተማመንን ለመመለስ በሚታገሉበት ጊዜ ነው ዴልታ አየር መንገድ በአዲስ እርምጃ የመጣው። የአየር መንገዱ የመንገደኞች እስከ ሰኔ 30 ድረስ ያለው የሦስት ወራት ገቢ 5.3 ቢሊዮን ዶላር ነበር። ቀውሱ ከመጀመሩ በፊት በ 2019 ከነበረው ተመሳሳይ ጊዜ ከ 50 በመቶ በላይ ቀንሷል። | የአሜሪካው አየር መንገድ ያልተከተቡ ሰራተኞቹን 200 ዶላር በየወሩ ሊቀጣ ነው ዴልታ አየር መንገድ የአሜሪካ ሦስተኛው ትልቁ አየር መንገድ ሲሆን የኮቪድ-19 ላይ ክትባት ባልወሰዱ ሠራተኞች ላይ በየወሩ 200 ዶላር እንዲከፍሉ ሊያደርግ ነው። ሁለቱንም ክትባቶች ወስደው በበሽታው ለተያዙ ለኮቪድ ህመምተኞች ብቻ የሕመም ክፍያ እከፍላለሁ ብሏል። የቫይረሱ ስርጭት በመላው አሜሪካ እየጨመረ ባለበት ሁኔታ ውሳኔው የኮሮናቫይረስን "በከፍተኛ ሁኔታ መስፋፋት" ለመግታት ይረዳል ብለዋል ኃላፊው ኢድ ባስቲያን። እርምጃው አንድ ትልቅ ኩባንያ ሠራተኞቹ እንዲከተቡ ለማድረግ የተወሰደ ሙከራ ነው። ባስቲያን ለሠራተኞች በላኩት በማስታወሻ ላይ የዴልታ ተጨማሪ ክፍያ ከታህሳስ ጀምሮ በጤና እንክብካቤ መድን ዕቅዱ በተመዘገቡ ሠራተኞቹ ላይ እንደሚተገበር ገልጸዋል። ይህም አብዛኛዎቹን 75 ሺህ ሠራተኞቹን የሚመለከት ይሆናል። ዴልታ ለኮቪድ-19 የሆስፒታል ቆይታ በአንድ ሰው በአማካይ 50 ሺህ ዶላር ዋጋ ይከፍላል ብለዋል። "ክትባቱን ያለመውሰድ ውሳኔው ለኩባንያችን እየፈጠረ ያለውን የገንዘብ አደጋን ለመቅረፍ ይህ ተጨማሪ ክፍያ አስፈላጊ ይሆናል" ብለዋል። "B.1.617.2 የተባለው አዲስ ዝርያ ከተስፋፋ ወዲህ ከኮቪድ ጋር በተያያዘ ሆስፒታል የገቡ የዴልታ ሠራተኞች ሙሉ በሙሉ ያልተከተቡ ናቸው።" ከመስከረም 30 ጀምሮ ደግሞ ያልተከተቡ የዴልታ ሠራተኞች በየሳምንቱ የኮቪድ ምርመራዎችን ማድረግ እና በዴልታ የቢሮ ውስጥ ጭምብል ማድረግ አለባቸው። ሁሉም የአሜሪካ አየር መንገድ ሠራተኞች በአውሮፕላን ውስጥ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል መልበስ ቢኖርባቸውም በቢሮዎች ውስጥ ግን አይተገበርም። ዴልታ የተሰኘው የኮሮናቫይረስ ዝርያ በአሜሪካ መስፋፋቱን ተከትሎ የሃገሪቱ ኩባንያዎች ሠራተኞቻቸው ክትባት እንዲወስዱ ለማበረታታት የተለያዩ ዘዴዎች እየሞከሩ ነው። እንደ ዩናይትድ አየር መንገድ፣ ጎልድማን ሳክስ፣ ማይክሮሶፍት እና ጉግል ያሉ ኩባንያዎች ወደ ሥራ ለመግባት ሙሉ በሙሉ መከተብ እንዳለባቸው ለሠራተኞቻቸው ነግረዋል። የኢንቨስትመንት ኩባንያው ቫንጋርድ ለክትቡ ሠራተኞቹ የ 1 ሺህ ዶላር ጉርሻ ሰጥቷል። አማዞን እና አፕል ግን በዚህ ረገድ ምንም ፖሊሲ አላወጡም። የኢንቨስትመንት ባንኩ ክሬዲት ሱይስ ሁሉም ክትባት ያልሰጣቸው ሠራተኞች ከመስከረም 7 ጀምሮ ከቤት እንዲሠሩ እንደሚጠይቅ ረቡዕ ዕለት አስታውቋል። እንደ ሌሎቹ ኩባንያዎች ሁሉ ወደ ቢሮ ሙሉ ለሙሉ መመለሻ ጊዜን እስከ ጥቅምት ድረስ አዘግይቷል። በወረርሽኙ ወቅት ከፍተኛ የፍላጎት መቀዛቀዝ ተከሰቶ የአሜሪካ አየር መንገዶች በራስ መተማመንን ለመመለስ በሚታገሉበት ጊዜ ነው ዴልታ አየር መንገድ በአዲስ እርምጃ የመጣው። የአየር መንገዱ የመንገደኞች እስከ ሰኔ 30 ድረስ ያለው የሦስት ወራት ገቢ 5.3 ቢሊዮን ዶላር ነበር። ቀውሱ ከመጀመሩ በፊት በ 2019 ከነበረው ተመሳሳይ ጊዜ ከ 50 በመቶ በላይ ቀንሷል። | https://www.bbc.com/amharic/news-58333315 |
5sports
| የተለያዩ አገራት አትሌቶች ከቶኪዮ ወደ አገራቸው ሲመለሱ የሚጠብቋቸው አስደናቂ ሽልማቶች | በኦሊምፒክ መድረክ አገርን ወክሎ አሸናፊ መሆን ከሚያስገኘው ትልቅ ሐሴት፣ ክብርና ታዋቂነት በተጨማሪ በርካታ አይነት ሽልማቶችም ይዞ ይመጣል። የተለያዩ አገራትም በኦሊምፒክ ተሳትፎ ያደረጉ ተወዳዳሪዎችን የተለያዩ አይነት ሽልማት ይሰጣሉ። ነገር ግን አንዳንድ አገራት ለስፖርተኞቹ ከሚሰጡት ማበረታቻዎች መካከል ከገንዘብ እስከ መኖሪያ ቤት፤ አንዳንዴ ደግሞ ከብት ጭምር ይበረከታል። በኢትዮጵያም ቢሆን መጠኑ ይለያይ እንጂ በዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች ውጤት ላስመዘገቡ ስፖርተኞች ሽልማት ሲበረከት ቆይቷል። በኦሊምፒክ ውድድሮች ላይ አትሌቶች በመሳተፋቸው ብቻ ዓለማ አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ የሚሰጣቸው ገንዘብ ባይኖርም በርካታ አገራት ግን ባንዲራቸውን ላውለበለቡላቸው ስፖርተኞች ጠቀም ያለ ገንዘብና ማበረታቻ ይሰጣሉ። በዚህም መሠረት በቶክዮ ኦሊምፒክ ያሸነፉ ተወዳዳሪዎች በአገራቸው የሚያገኙትን ሽልማትና ማበረታቻ እናስቃኛችሁ። ሁለት ድንቅ መኖሪያ ቤቶች የፊሊፒንሷ ስፖርተኛ ዲያዝ በሴቶች 55 ኪሎግራም ክብደት ማንሳት ማሸነፏን ተከትሎ በአገሪቱ እንደ ጀግና እየተሞካሸች ነው። መሞካሸት ብቻ አይደለም ሕይወቷን የሚቀይሩ ሽልማቶችና ማበረታቻዎች እየጎረፉላት ይገኛሉ። የፊሊፒንስ ስፖርት ኮሚሽን እና የአገሪቱ ፕሬዝዳንት በጥምረት ገንዘብ በማዋጣት ለዚህች ስፖርተኛ 600ሺህ የአሜሪካ ዶላር (27 ሚሊየን ብር አካባቢ ማለት ነው) እንደሚሰጧት ቃል ግበተውላታል። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ሁለት እጅግ ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶች ተሰጥተዋታል። የፊሊፒንስ አየር ኃይል ውስጥ በወር 500 ዶላር እየተከፈላት ታገለግል የነበረችው ዲያዝ እነዚህ ሽልማቶች ሕይወቷን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀይሩትና ብርታት እንደሚሰጣት መገመት ከባድ አይሆንም። ይህች ስፖርተኛ በሚያስገርም ሁኔታ ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ስትዘጋጅ የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከል ውስጥ እንኳን የመሰልጠን እድል አላገኘችም ነበር። እንደውም በአካባቢዋ ያገኘቻቸውን ብረቶች እንዲመቻት አድርጋ ነበር ክብደት ማንሳት ስትለማመድ የቆየችው። የገንዘብ ሽልማት የገንዘብ ሽልማት መጠን ከአገር አገር ይለያያል። በርካታ ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ የሚታወቁትና አትሌቶቻቸውን እጅግ ዘመናዊ በሆኑ ማዕከላት የሚያሰለጥኑ አገራት ለስፖርተኞቹ የሚሰጡት ቀጥተኛ ሽልማት ብዙ ጊዜ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። አንዳንዴም አትሌቶች ምንም ሽልማት ላያገኙ ይችላሉ። ነገር ግን በስንት ጊዜ አንዴ በሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ የሚገቡ አገራት አልያም በውስን የውድድር አይነቶች ብቻ ሜዳሊያ የሚያሰገኙ አገራት ስፖርተኞቻቸውን ለማበረታታት ጠቀም ያለ ገንዘብ በሽልማትነት ያቀርቡላቸዋል። ለምሳሌ ማሌዢያ በ13 የኦሊምፒክ ተሳትፎዋ ማግኘት የቻለችው 11 ሜዳሊያዎችን ብቻ ሲሆን በቶክዮ ኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ለሚያመጣ ስፖርተኛ 241 ሺህ ዶላር፣ ነሐስ ለሚያመጣ ደግሞ 150 ሺህ ዶላር እንዲሁም ብር ለሚያመጣ ስፖርተኛ ደግሞ 24 ሺህ ዶላር እንደምትሸልም አስታውቃለች። በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ደግሞ ማሌዢያ በወንዶች የጥንድ ባድሜንተን ውድድር የብር ሜዳሊያ አግኝታለች። የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ ለሚገቡ አትሌቶቻቸውን ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት ከሚሰጡ አገራት መካከል የተወሰኑት። ሽልማቱ በአሜሪካን ዶላር ነው። አንጸባራቂ፣ ውድ እና አዲስ መኪናዎች ቻይና እና ሩሲያ ደግሞ በሜዳሊያ ከሚጥለቀለቁት አገራት መካከል ተጠቃሽ ናቸው። አገራቱ ለስፖርተኞቻቸውን ጠቀም ካለ የገንዘብ ሽልማት በተጨማሪ በአዳዲስ መኪኖች ያንበሸብሿቸዋል። ለምሳሌ ሩሲያ በኦሊምፒክ መድረክ የአገራቸውን ባንዲራ ማውለብለብ ለቻሉ ስፖርተኞች በጣም ውድ የሚባሉ መኪናዎችን እና ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶችን ታበረክታለች። አንዳንድ ሽልማቶች ደግሞ ለየት ያሉና አስገራሚም ናቸው። ደቡብ አፍሪካውያኑ ሲዝዌ ንዶቩ፣ ማቲው ብሪቴይን፣ ጆን ስሚዝ እና ጄምስ ቶምሰን በወንዶች ቀላል ክብደት በአውሮፓውያኑ 2012 ለንደን ኦሊምፒክ ላይ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ምርጥ ላሞች በሽልማት መልክ ተበርክቶላቸው ነበር። የተሻለ ሥራ እና ከአስገዳጅ ወታደራዊ አገልግሎት ነጻ መሆን በአንዳንድ አገራት ደግሞ በኦሊምፒክ አሸናፊ መሆን የተሻለ ሥራና የተሻለ ክፍያ የሚያስገኝ ሲሆን አንዳንዴ ደግሞ ከአስገዳጅ ወታደራዊ አገልግሎት እስከመቅረትም ያደርሳል። የሕንዷ ክብደት ማንሳት ተወዳዳሪ ሚራቢ ቻኑ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባቷን ተከትሎ 350 ሺህ ዶላር ሽልማት የተበረከተላት ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ የምትሰራበት መስሪያ ቤት የሆነው 'ኢንዲያን ሬልዌይ ሰርቪስ' የደረጃ እድገትና የደሞዝ ጭማሪ ቃል ገብቶላታል። በደቡብ ኮሪያ ደግሞ ሜዳሊያ ማምጣት የቻሉ ስፖርተኞች ጠቀም ያለ የገንዘብ ሽልማት የሚሰጣቸው ሲሆን ዋነኛው ሽልማታቸው ግን ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ የአገሬው ዜጎች መቅረት የማይችሉበት የ18 ወራት ወታደራዊ አገልግሎት እንዲቀርላቸው መደረጉ ነው። ነገር ግን ለበርካታ አትሌቶች በመንግሥታቸው የሚሰጣቸው ገንዘብና ማበረታቻ በቀላሉ የሚታይ አይደለም። ምክንያቱም አብዛኛዎቹ ስፖርተኞች በቂ የሆነ ስልጠና ለማግኘት እንኳን የሚያስችላቸው የገንዘብ አቅም የላቸውም። ለምሳሌ ሳትጠበቅ በኦሊምፒክ መድረክ በሴቶች ጂምናስቲክስ ሁለት ሜዳሊያዎችን ማሸነፍ የቻለችው ብራዚላዊት ሬቤካ አርናልዴ በብራዚል መንግሥት ድጎማ ነበር የምትኖረው። ባለፈው ኅዳር ወር አንድ ዓለመ አቀፍ የጥናት ተቋም ከ48 አገራት የተወጣጡ 500 የሚሆኑ ትልልቅ አትሌቶችን በማነጋገር በሰበሰበው መረጃ መሠረት 60 በመቶ የሚሆኑት በገንዘብ እራሳቸውን መደገፍ እንደማይችሉ ገልጸዋል። አንዳንድ አትሌቶች እንደውም በቶኪዮ ኦሊምፒክ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ገንዘብ ለማግኘት 'ጎ ፈንድ ሚ' ላይ ጭምር በመሄድ እርዳታ ሲያሰባስቡ ነበር። ታዲያ እንዲህ ባሉ አስቸጋሪ ጊዜያት አገራት ለስፖርተኞቻቸው መሰል የገንዘብ፣ መኖሪያ ቤት፣ መኪና አንዳንዴም ከብቶች መሸለማቸው በርካታ ታዳጊዎች ለወደፊት መነሳሳትን እንደሚፈጥርባቸው ይታመናል። | የተለያዩ አገራት አትሌቶች ከቶኪዮ ወደ አገራቸው ሲመለሱ የሚጠብቋቸው አስደናቂ ሽልማቶች በኦሊምፒክ መድረክ አገርን ወክሎ አሸናፊ መሆን ከሚያስገኘው ትልቅ ሐሴት፣ ክብርና ታዋቂነት በተጨማሪ በርካታ አይነት ሽልማቶችም ይዞ ይመጣል። የተለያዩ አገራትም በኦሊምፒክ ተሳትፎ ያደረጉ ተወዳዳሪዎችን የተለያዩ አይነት ሽልማት ይሰጣሉ። ነገር ግን አንዳንድ አገራት ለስፖርተኞቹ ከሚሰጡት ማበረታቻዎች መካከል ከገንዘብ እስከ መኖሪያ ቤት፤ አንዳንዴ ደግሞ ከብት ጭምር ይበረከታል። በኢትዮጵያም ቢሆን መጠኑ ይለያይ እንጂ በዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች ውጤት ላስመዘገቡ ስፖርተኞች ሽልማት ሲበረከት ቆይቷል። በኦሊምፒክ ውድድሮች ላይ አትሌቶች በመሳተፋቸው ብቻ ዓለማ አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ የሚሰጣቸው ገንዘብ ባይኖርም በርካታ አገራት ግን ባንዲራቸውን ላውለበለቡላቸው ስፖርተኞች ጠቀም ያለ ገንዘብና ማበረታቻ ይሰጣሉ። በዚህም መሠረት በቶክዮ ኦሊምፒክ ያሸነፉ ተወዳዳሪዎች በአገራቸው የሚያገኙትን ሽልማትና ማበረታቻ እናስቃኛችሁ። ሁለት ድንቅ መኖሪያ ቤቶች የፊሊፒንሷ ስፖርተኛ ዲያዝ በሴቶች 55 ኪሎግራም ክብደት ማንሳት ማሸነፏን ተከትሎ በአገሪቱ እንደ ጀግና እየተሞካሸች ነው። መሞካሸት ብቻ አይደለም ሕይወቷን የሚቀይሩ ሽልማቶችና ማበረታቻዎች እየጎረፉላት ይገኛሉ። የፊሊፒንስ ስፖርት ኮሚሽን እና የአገሪቱ ፕሬዝዳንት በጥምረት ገንዘብ በማዋጣት ለዚህች ስፖርተኛ 600ሺህ የአሜሪካ ዶላር (27 ሚሊየን ብር አካባቢ ማለት ነው) እንደሚሰጧት ቃል ግበተውላታል። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ሁለት እጅግ ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶች ተሰጥተዋታል። የፊሊፒንስ አየር ኃይል ውስጥ በወር 500 ዶላር እየተከፈላት ታገለግል የነበረችው ዲያዝ እነዚህ ሽልማቶች ሕይወቷን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀይሩትና ብርታት እንደሚሰጣት መገመት ከባድ አይሆንም። ይህች ስፖርተኛ በሚያስገርም ሁኔታ ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ስትዘጋጅ የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከል ውስጥ እንኳን የመሰልጠን እድል አላገኘችም ነበር። እንደውም በአካባቢዋ ያገኘቻቸውን ብረቶች እንዲመቻት አድርጋ ነበር ክብደት ማንሳት ስትለማመድ የቆየችው። የገንዘብ ሽልማት የገንዘብ ሽልማት መጠን ከአገር አገር ይለያያል። በርካታ ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ የሚታወቁትና አትሌቶቻቸውን እጅግ ዘመናዊ በሆኑ ማዕከላት የሚያሰለጥኑ አገራት ለስፖርተኞቹ የሚሰጡት ቀጥተኛ ሽልማት ብዙ ጊዜ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። አንዳንዴም አትሌቶች ምንም ሽልማት ላያገኙ ይችላሉ። ነገር ግን በስንት ጊዜ አንዴ በሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ የሚገቡ አገራት አልያም በውስን የውድድር አይነቶች ብቻ ሜዳሊያ የሚያሰገኙ አገራት ስፖርተኞቻቸውን ለማበረታታት ጠቀም ያለ ገንዘብ በሽልማትነት ያቀርቡላቸዋል። ለምሳሌ ማሌዢያ በ13 የኦሊምፒክ ተሳትፎዋ ማግኘት የቻለችው 11 ሜዳሊያዎችን ብቻ ሲሆን በቶክዮ ኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ለሚያመጣ ስፖርተኛ 241 ሺህ ዶላር፣ ነሐስ ለሚያመጣ ደግሞ 150 ሺህ ዶላር እንዲሁም ብር ለሚያመጣ ስፖርተኛ ደግሞ 24 ሺህ ዶላር እንደምትሸልም አስታውቃለች። በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ደግሞ ማሌዢያ በወንዶች የጥንድ ባድሜንተን ውድድር የብር ሜዳሊያ አግኝታለች። የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ ለሚገቡ አትሌቶቻቸውን ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት ከሚሰጡ አገራት መካከል የተወሰኑት። ሽልማቱ በአሜሪካን ዶላር ነው። አንጸባራቂ፣ ውድ እና አዲስ መኪናዎች ቻይና እና ሩሲያ ደግሞ በሜዳሊያ ከሚጥለቀለቁት አገራት መካከል ተጠቃሽ ናቸው። አገራቱ ለስፖርተኞቻቸውን ጠቀም ካለ የገንዘብ ሽልማት በተጨማሪ በአዳዲስ መኪኖች ያንበሸብሿቸዋል። ለምሳሌ ሩሲያ በኦሊምፒክ መድረክ የአገራቸውን ባንዲራ ማውለብለብ ለቻሉ ስፖርተኞች በጣም ውድ የሚባሉ መኪናዎችን እና ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶችን ታበረክታለች። አንዳንድ ሽልማቶች ደግሞ ለየት ያሉና አስገራሚም ናቸው። ደቡብ አፍሪካውያኑ ሲዝዌ ንዶቩ፣ ማቲው ብሪቴይን፣ ጆን ስሚዝ እና ጄምስ ቶምሰን በወንዶች ቀላል ክብደት በአውሮፓውያኑ 2012 ለንደን ኦሊምፒክ ላይ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ምርጥ ላሞች በሽልማት መልክ ተበርክቶላቸው ነበር። የተሻለ ሥራ እና ከአስገዳጅ ወታደራዊ አገልግሎት ነጻ መሆን በአንዳንድ አገራት ደግሞ በኦሊምፒክ አሸናፊ መሆን የተሻለ ሥራና የተሻለ ክፍያ የሚያስገኝ ሲሆን አንዳንዴ ደግሞ ከአስገዳጅ ወታደራዊ አገልግሎት እስከመቅረትም ያደርሳል። የሕንዷ ክብደት ማንሳት ተወዳዳሪ ሚራቢ ቻኑ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባቷን ተከትሎ 350 ሺህ ዶላር ሽልማት የተበረከተላት ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ የምትሰራበት መስሪያ ቤት የሆነው 'ኢንዲያን ሬልዌይ ሰርቪስ' የደረጃ እድገትና የደሞዝ ጭማሪ ቃል ገብቶላታል። በደቡብ ኮሪያ ደግሞ ሜዳሊያ ማምጣት የቻሉ ስፖርተኞች ጠቀም ያለ የገንዘብ ሽልማት የሚሰጣቸው ሲሆን ዋነኛው ሽልማታቸው ግን ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ የአገሬው ዜጎች መቅረት የማይችሉበት የ18 ወራት ወታደራዊ አገልግሎት እንዲቀርላቸው መደረጉ ነው። ነገር ግን ለበርካታ አትሌቶች በመንግሥታቸው የሚሰጣቸው ገንዘብና ማበረታቻ በቀላሉ የሚታይ አይደለም። ምክንያቱም አብዛኛዎቹ ስፖርተኞች በቂ የሆነ ስልጠና ለማግኘት እንኳን የሚያስችላቸው የገንዘብ አቅም የላቸውም። ለምሳሌ ሳትጠበቅ በኦሊምፒክ መድረክ በሴቶች ጂምናስቲክስ ሁለት ሜዳሊያዎችን ማሸነፍ የቻለችው ብራዚላዊት ሬቤካ አርናልዴ በብራዚል መንግሥት ድጎማ ነበር የምትኖረው። ባለፈው ኅዳር ወር አንድ ዓለመ አቀፍ የጥናት ተቋም ከ48 አገራት የተወጣጡ 500 የሚሆኑ ትልልቅ አትሌቶችን በማነጋገር በሰበሰበው መረጃ መሠረት 60 በመቶ የሚሆኑት በገንዘብ እራሳቸውን መደገፍ እንደማይችሉ ገልጸዋል። አንዳንድ አትሌቶች እንደውም በቶኪዮ ኦሊምፒክ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ገንዘብ ለማግኘት 'ጎ ፈንድ ሚ' ላይ ጭምር በመሄድ እርዳታ ሲያሰባስቡ ነበር። ታዲያ እንዲህ ባሉ አስቸጋሪ ጊዜያት አገራት ለስፖርተኞቻቸው መሰል የገንዘብ፣ መኖሪያ ቤት፣ መኪና አንዳንዴም ከብቶች መሸለማቸው በርካታ ታዳጊዎች ለወደፊት መነሳሳትን እንደሚፈጥርባቸው ይታመናል። | https://www.bbc.com/amharic/news-58142401 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ በርካታ የአውሮፓ አገራት በታላቋ ብሪታኒያ ላይ የጉዞ እቀባ እያደረጉ ነው | በርካታ የአውሮፓ አገራት በታላቋ ብሪታኒያ ላይ የጉዞ እቀባ እያደረጉ ነው። ምክንያቱ ደግሞ በዚያች አገር አዲስ ዓይነት የኮቪድ ዝርያ መገኘቱ ነው። አዲሱ ዝርያ ገና በስፋት ያልተጠና ቢሆንም ከቁጥጥር ውጭ በሆነ መንገድ ከሰው ወደ ሰው ይዛመታል የሚለው ፍርሃት በርካታ አገራትን ድንጋጤ ውስጥ ከቷቸዋል። እስከ አሁን ባለው ብቻ ጀርመን፣ አየርላንድ፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያንና ኔዘርላንድስ እንዲሁም ቤልጂየም ሁሉም ወደ ታላቋ ብሪታኒያ የአየር በረራን አቋርጠዋል። ዛሬ ሰኞ የአውሮፓ ኅብረት መሪዎች ስብሰባ ስለሚቀመጡ ከዚህ የባሰ የእቀባ ውሳኔ ሊኖር እንደሚችል እየተጠበቀ ነው። አዲሱ ኮቪድ-19 ዝርያ በለንደንና በደቡብ ምሥራቅ ኢንግላንድ በአጭር ጊዜ ውስጥ ነው በስፋት የተሰራጨው። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ቅዳሜ በሰጡት አስቸኳይ ትእዛዝ ደረጃ 4 የጥንቃቄ ደንቦች እንዲከበሩ አዘዋል። ለፈረንጆች ገናና አዲስ ዓመት የእንቅስቃሴ ገደቦች ይላላሉ ተብሎ ታስቦ የነበረውን ሐሳብ ሰርዘዋል። የጤና ባለሙያዎች አዲሱ የተህዋሲው ዝርያ ይበልጥ ገዳይ ስለመሆኑም ሆነ ለክትባት እጅ የማይሰጥ ስለመሆኑ ገና እርግጠኛ አልሆኑም። ሆኖም ግን ከለመድነው የኮሮናቫይረስ በ70 በመቶ በይበልጥ የመሰራጨት አቅም አለው መባሉ ማን ይተርፋል እንዲባል አድርጓል። የታላቋ ብሪታኒያ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ይህ አዲስ ዝርያ ቫይረስ ከቁጥጥር ውጭ ሆኖብናል፤ በቁጥጥራችን ልናውለው ይገባል ብለዋል። ታላቋ ብሪታኒያ አዲሱን የቫይረስ ዝርያ ይፋ ባደረገች በሰዓታት ውስጥ ኔዘርላንድ ማንኛውም በረራ ከታላቋ ብሪታኒያ እንዳይመጣብኝ ብላለች። ፈረንሳይ በተመሳሳይ ከባድ መኪና ተሽከርካሪ፣ መርከብ፣ ጀልባዎች፣ እግረኛና በበራዎችን ከእንግሊዝ በኩል ወደ አገሯ እንዳይገቡብኝ ብላለች። አየርላንድና ጀርመንም ተመሳሳይ ውሳኔን አሳልፈዋል። ጣሊያን እስከ ጃንዋሪ 6 ማንም ከታላቋ ብሪታኒያ አይምጣብኝ ብላለች። በአዲሱ የቫይረስ ዝርያ የተጠቃ አንድ ሰው በጣሊያን መገኘቱም ድንጋጤን ፈጥሯል። ቱርክ፣ ቡልጋሪያና ኦስትሪያም ከታላቋ ብሪታኒያ ጉዞ እቀባ አድርገዋል። የዓለም ጤና ድርጅት አዲሱን የኮሮናቫይረስ ዝርያ በተመለከተ ከዩናይትድ ኪንግደም ባለሥልጣናት ጋር በቅርበት እየተነጋገረ እንደሆነ በትዊተር ገጹ አስታውቋል። ድርጅቱ እንዳለው ዩናይትድ ኪንግደም አዲሱን የቫይረስ ዝርያ በተመለከተ እየተካሄዱ ስላሉ ጥናቶች መረጃዎችን ስታጋራ እንደነበር ጠቅሶ፤ ድርጅቱ ስለአዲሱ ቫይረስ ባሕርይ እና አደጋው የደረሰበትን ለአባል አገራቱ እና ለሕዝብ እንደሚያሳውቅ ገልጿል። ምንም እንኳን የተረጋገጠ ነገር ባይኖርም፤ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን አዲሱ የቫይረስ ዝርያ ከቀድሞው እስከ 70 በመቶ ያህል የመዛመት እድሉ ከፍተኛ ነው ብለዋል። ይሁን እንጂ ባለሥልጣናት አዲሱ የቫይረስ ዝርያ ከፍተኛ ሞት ስለማስከተሉ አሊያም እስካሁን በተዘጋጁት የኮሮናቫይረስ ክትባቶች እና ሕክምናዎች ሊበገር ስለመቻሉ የሚያሳይ መረጃ እንደሌለ ተናግረዋል። ዩናይትድ ኪንግደም እና አሜሪካ ፋይዘርና በባዮንቴክ የበለጸገውን የኮሮናቫይረስ ክትባት ለዜጎቻቸው መስጠት መጀመራቸው ይታወሳል። 95 በመቶ ኮሮናቫይረስን ይከላከላል የተባለለት ይህንን ክትባት ለዜጎች በመስጠት ዩናይትድ ኪንግደም ቀዳሚዋ አገር ሆና ነበር። | ኮሮናቫይረስ፡ በርካታ የአውሮፓ አገራት በታላቋ ብሪታኒያ ላይ የጉዞ እቀባ እያደረጉ ነው በርካታ የአውሮፓ አገራት በታላቋ ብሪታኒያ ላይ የጉዞ እቀባ እያደረጉ ነው። ምክንያቱ ደግሞ በዚያች አገር አዲስ ዓይነት የኮቪድ ዝርያ መገኘቱ ነው። አዲሱ ዝርያ ገና በስፋት ያልተጠና ቢሆንም ከቁጥጥር ውጭ በሆነ መንገድ ከሰው ወደ ሰው ይዛመታል የሚለው ፍርሃት በርካታ አገራትን ድንጋጤ ውስጥ ከቷቸዋል። እስከ አሁን ባለው ብቻ ጀርመን፣ አየርላንድ፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያንና ኔዘርላንድስ እንዲሁም ቤልጂየም ሁሉም ወደ ታላቋ ብሪታኒያ የአየር በረራን አቋርጠዋል። ዛሬ ሰኞ የአውሮፓ ኅብረት መሪዎች ስብሰባ ስለሚቀመጡ ከዚህ የባሰ የእቀባ ውሳኔ ሊኖር እንደሚችል እየተጠበቀ ነው። አዲሱ ኮቪድ-19 ዝርያ በለንደንና በደቡብ ምሥራቅ ኢንግላንድ በአጭር ጊዜ ውስጥ ነው በስፋት የተሰራጨው። ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ቅዳሜ በሰጡት አስቸኳይ ትእዛዝ ደረጃ 4 የጥንቃቄ ደንቦች እንዲከበሩ አዘዋል። ለፈረንጆች ገናና አዲስ ዓመት የእንቅስቃሴ ገደቦች ይላላሉ ተብሎ ታስቦ የነበረውን ሐሳብ ሰርዘዋል። የጤና ባለሙያዎች አዲሱ የተህዋሲው ዝርያ ይበልጥ ገዳይ ስለመሆኑም ሆነ ለክትባት እጅ የማይሰጥ ስለመሆኑ ገና እርግጠኛ አልሆኑም። ሆኖም ግን ከለመድነው የኮሮናቫይረስ በ70 በመቶ በይበልጥ የመሰራጨት አቅም አለው መባሉ ማን ይተርፋል እንዲባል አድርጓል። የታላቋ ብሪታኒያ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ይህ አዲስ ዝርያ ቫይረስ ከቁጥጥር ውጭ ሆኖብናል፤ በቁጥጥራችን ልናውለው ይገባል ብለዋል። ታላቋ ብሪታኒያ አዲሱን የቫይረስ ዝርያ ይፋ ባደረገች በሰዓታት ውስጥ ኔዘርላንድ ማንኛውም በረራ ከታላቋ ብሪታኒያ እንዳይመጣብኝ ብላለች። ፈረንሳይ በተመሳሳይ ከባድ መኪና ተሽከርካሪ፣ መርከብ፣ ጀልባዎች፣ እግረኛና በበራዎችን ከእንግሊዝ በኩል ወደ አገሯ እንዳይገቡብኝ ብላለች። አየርላንድና ጀርመንም ተመሳሳይ ውሳኔን አሳልፈዋል። ጣሊያን እስከ ጃንዋሪ 6 ማንም ከታላቋ ብሪታኒያ አይምጣብኝ ብላለች። በአዲሱ የቫይረስ ዝርያ የተጠቃ አንድ ሰው በጣሊያን መገኘቱም ድንጋጤን ፈጥሯል። ቱርክ፣ ቡልጋሪያና ኦስትሪያም ከታላቋ ብሪታኒያ ጉዞ እቀባ አድርገዋል። የዓለም ጤና ድርጅት አዲሱን የኮሮናቫይረስ ዝርያ በተመለከተ ከዩናይትድ ኪንግደም ባለሥልጣናት ጋር በቅርበት እየተነጋገረ እንደሆነ በትዊተር ገጹ አስታውቋል። ድርጅቱ እንዳለው ዩናይትድ ኪንግደም አዲሱን የቫይረስ ዝርያ በተመለከተ እየተካሄዱ ስላሉ ጥናቶች መረጃዎችን ስታጋራ እንደነበር ጠቅሶ፤ ድርጅቱ ስለአዲሱ ቫይረስ ባሕርይ እና አደጋው የደረሰበትን ለአባል አገራቱ እና ለሕዝብ እንደሚያሳውቅ ገልጿል። ምንም እንኳን የተረጋገጠ ነገር ባይኖርም፤ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን አዲሱ የቫይረስ ዝርያ ከቀድሞው እስከ 70 በመቶ ያህል የመዛመት እድሉ ከፍተኛ ነው ብለዋል። ይሁን እንጂ ባለሥልጣናት አዲሱ የቫይረስ ዝርያ ከፍተኛ ሞት ስለማስከተሉ አሊያም እስካሁን በተዘጋጁት የኮሮናቫይረስ ክትባቶች እና ሕክምናዎች ሊበገር ስለመቻሉ የሚያሳይ መረጃ እንደሌለ ተናግረዋል። ዩናይትድ ኪንግደም እና አሜሪካ ፋይዘርና በባዮንቴክ የበለጸገውን የኮሮናቫይረስ ክትባት ለዜጎቻቸው መስጠት መጀመራቸው ይታወሳል። 95 በመቶ ኮሮናቫይረስን ይከላከላል የተባለለት ይህንን ክትባት ለዜጎች በመስጠት ዩናይትድ ኪንግደም ቀዳሚዋ አገር ሆና ነበር። | https://www.bbc.com/amharic/news-55391881 |
5sports
| ጋና ወደ ድል ስትመለስ ሮናልዶ አስቆጠርኩት ያለው ጎል ለፈርናንዴዝ ተቆጥሯል | ደቡብ ኮሪያ ከጋና ያደረጉት ጨዋታ በጎሎች የተንበሸበሸ፣ የስሜት መለዋወጥ እና ካርድ ያስመዘዘ ሆኖ አልፏል። በመጀመሪያው ጨዋታ በፖርቹጋል የተሸነፈችው ጋና በ24ኛው ደቂቃ በሞሐመድ ሳሊሱ ጎል ቀዳሚ ሆነች። ሞሐመድ ኩዱስ ያስቆጠራት ሁለተኛ ጎል ጋናዊያን በቀላሉ አሸነፉ አስብሎ ነበር። የደቡብ ኮሪያ ሊግ ኮከብ ጎል አስቆጣሪው ቾ ጉ-ሱንግ በተከታታይ ያስቆጠራቸው ጎሎች ጨዋታውን ቀየሩት። ደበብ ኮሪያ 2-2 ጋና። ጋናዎች በፍጥነት በኩዱስ ባስቆጠሩት ጎል ምላሽ ሰጡ። ደበብ ኮሪያ 2-3 ጋና። ደቡብ ኮሪያ አቻ ለመሆን ያደረገችውን ተደጋጋሚ ጥረት ግብ ጠባቂው አቲ ዚጊ አክሽፎታል። ጨዋታው በዚሁ ውጤት ተጠናቀቀ። ጋናዎች ሲጨፍሩ የደቡብ ኮሪያው አምበል ሰን ሁንግ-ሚን ሲያለቅስ ታይቷል። የኮሪያው አሰልጣኝ ፓውሎ ቤንቶ ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ ከዳኛው ጋር በነበራቸው እሰጥ አገባ ቀይ ካርድ ተመልክተዋል። በምድቡ ሌላኛ ጨዋታ ፖርቹጋል ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋግጣለች። የጨዋታው መልክ የተቀየረው 54ኛው ደቂቃ ላይ ነው። ቡርኖ ፈርናንዴዝ ያሻማው ኳስ ከመረብ ላይ ያርፋል። ክርስቲያኖ ሮናልዶ ኳሱን ማስቆጠሩን በመተማመን ከቡድን አጋሮቹ ጋር ደስታውን ገልጿል። ጎሏ ሮናልዶን በዓለም ዋንጫ ታሪክ ለፖርቹጋል በርካታ ጎል ካስቆጠረው ኡሴቢዮ የምታስተካክለው ነበረች። በኋላም ሮናልዶ ኳሷን አልነካትም በሚል ጎሏ በፈርናንዴዝ ስም እንድትመዘገብ ተደርጓል። ውሳኔው ሲገለጽ አጥቂው በምጸት ፈገግ ሲል ታይቷል። ጨዋታው መገባደጃ ላይ የተገኘችውን ፍጹም ቅጣት ምትም ፈርናንዴዝ አስቆጥሯል። ምድቡን በስድስት ነጥብ የምትመራው ፖርቹጋል ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋግጣለች። ጋና በሦስት ነትብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ደቡብ ኮሪያ እና ኡራጓይ አንድ አንድ ነጥብ አላቸው። በምድብ ሰባት ጨዋታ ካሜሮን እና ሰርቢያ 3 ለ 3 በሆነ ውጤት አቻ ተለያይተዋል። ጂን-ቻርለስ ካስቴሌቶ በ29ኛው ደቂቃ ካሜሮንን ቀዳሚ ያደረገች ጎል አስቆጠረ። ስታርሂንጃ ፓቭሎቪች እና ሰርጌይ ሚሊንኮቪች-ሳቪች በተከታታይ ባስቆጠሯቸው ጎሎች ሰርቢያ 2 ለ 1 እየመራች እረፍት ወጡ። አሌክሳንደር ሚትሮቪች ያስቆጠራት ጎል ሦስቱን ነጥቦች ሰርቢያ ለመውሰድ የቻለች አስመስሏት ነበር። በካሜሮን በኩል ተቀይሮ የገባው ቪንሰንት አቡበከር የጨዋታውን መልክ ቀየረው። አቡበከር አንድ ጎል በስሙ ሲያስመዘግብ ኤሪክ ማክሲም ቹፖ-ሞቲንግ ያስቆጠራትን ኳስ ደግሞ አመቻችቶ አቀብሏል። በዚህም ጨዋታው ሦስት አቻ ተጠናቋል። ለዋንጫው ትልቅ ግምት የተሰጣት ብራዚል ከስዊዘርላንድ ጋር ያደረገችው ጨዋታ ቅዝቅዝ ያለ ነበር። በፊፋ ሃገራት ደረጃ ቀዳሚ የሆነችው ብራዚል ያለ ኮከብ ተጫዋቸዋ ኔይማር ነበር ወደ ሜዳ የገባችው። ብራዚል በ83ኛው ደቂቃ ጎል ለማስቆጠር ችላለች። የማንቸስተር ዩናይትዱ አማካይ ካሰሚሮ ብቸኛዋን ጎል ከመረብ አሳርፏል። ጨዋታው በዚሁ ውጤት ሲጠናቀቅ ብራዚል ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋግጣለች። ብራዚል በስድስት ነጥብ ምድቡን ትመራለች። ስዊዘርላንድ ሦስት ነጥብ አላት። ካሜሮን እና ሰርቢያ በአንድ ነጥብ ሦስተኛ እና አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። የኳታር የዓለም ዋንጫ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዎች ዛሬ መከናወን ይጀምራሉ። ምድብ አንድ ሁለት ጨዋታዎች በተመሳሳይ 12 ሰዓት ይከናወናሉ። አዘጋጇ ኳታር ኔዘርላንድስን አል ባይት ስታዲየም ትገጥማለች። ኻሊፋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ላይ ኢኳዶር እና ሴኔጋል ይገናኛሉ። ኔዘርላንድስ ምድቡን በአራት ነጥብ ስትመራ ኢኳዶርም በተመሳሳይ ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ሴኔጋል ሦስት ነጥብ አላት። ኳታር ያለምንም ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዛለች። በምድብ ሁለት እንግሊዝ ከዌልስ እና ኢራን ከአሜሪካ ምሽት አራት ሰዓት ይጫወታሉ። ምድቡን እንግሊዝ በአራት ነጥብ ትመራለች። ኢራን በሦስት ነጥብ ትከተላለች። አሜሪካ ሁለት ነጥብ ሲኖራት ዌልስ አንድ ነጥብ አላት። | ጋና ወደ ድል ስትመለስ ሮናልዶ አስቆጠርኩት ያለው ጎል ለፈርናንዴዝ ተቆጥሯል ደቡብ ኮሪያ ከጋና ያደረጉት ጨዋታ በጎሎች የተንበሸበሸ፣ የስሜት መለዋወጥ እና ካርድ ያስመዘዘ ሆኖ አልፏል። በመጀመሪያው ጨዋታ በፖርቹጋል የተሸነፈችው ጋና በ24ኛው ደቂቃ በሞሐመድ ሳሊሱ ጎል ቀዳሚ ሆነች። ሞሐመድ ኩዱስ ያስቆጠራት ሁለተኛ ጎል ጋናዊያን በቀላሉ አሸነፉ አስብሎ ነበር። የደቡብ ኮሪያ ሊግ ኮከብ ጎል አስቆጣሪው ቾ ጉ-ሱንግ በተከታታይ ያስቆጠራቸው ጎሎች ጨዋታውን ቀየሩት። ደበብ ኮሪያ 2-2 ጋና። ጋናዎች በፍጥነት በኩዱስ ባስቆጠሩት ጎል ምላሽ ሰጡ። ደበብ ኮሪያ 2-3 ጋና። ደቡብ ኮሪያ አቻ ለመሆን ያደረገችውን ተደጋጋሚ ጥረት ግብ ጠባቂው አቲ ዚጊ አክሽፎታል። ጨዋታው በዚሁ ውጤት ተጠናቀቀ። ጋናዎች ሲጨፍሩ የደቡብ ኮሪያው አምበል ሰን ሁንግ-ሚን ሲያለቅስ ታይቷል። የኮሪያው አሰልጣኝ ፓውሎ ቤንቶ ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ ከዳኛው ጋር በነበራቸው እሰጥ አገባ ቀይ ካርድ ተመልክተዋል። በምድቡ ሌላኛ ጨዋታ ፖርቹጋል ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋግጣለች። የጨዋታው መልክ የተቀየረው 54ኛው ደቂቃ ላይ ነው። ቡርኖ ፈርናንዴዝ ያሻማው ኳስ ከመረብ ላይ ያርፋል። ክርስቲያኖ ሮናልዶ ኳሱን ማስቆጠሩን በመተማመን ከቡድን አጋሮቹ ጋር ደስታውን ገልጿል። ጎሏ ሮናልዶን በዓለም ዋንጫ ታሪክ ለፖርቹጋል በርካታ ጎል ካስቆጠረው ኡሴቢዮ የምታስተካክለው ነበረች። በኋላም ሮናልዶ ኳሷን አልነካትም በሚል ጎሏ በፈርናንዴዝ ስም እንድትመዘገብ ተደርጓል። ውሳኔው ሲገለጽ አጥቂው በምጸት ፈገግ ሲል ታይቷል። ጨዋታው መገባደጃ ላይ የተገኘችውን ፍጹም ቅጣት ምትም ፈርናንዴዝ አስቆጥሯል። ምድቡን በስድስት ነጥብ የምትመራው ፖርቹጋል ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋግጣለች። ጋና በሦስት ነትብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ደቡብ ኮሪያ እና ኡራጓይ አንድ አንድ ነጥብ አላቸው። በምድብ ሰባት ጨዋታ ካሜሮን እና ሰርቢያ 3 ለ 3 በሆነ ውጤት አቻ ተለያይተዋል። ጂን-ቻርለስ ካስቴሌቶ በ29ኛው ደቂቃ ካሜሮንን ቀዳሚ ያደረገች ጎል አስቆጠረ። ስታርሂንጃ ፓቭሎቪች እና ሰርጌይ ሚሊንኮቪች-ሳቪች በተከታታይ ባስቆጠሯቸው ጎሎች ሰርቢያ 2 ለ 1 እየመራች እረፍት ወጡ። አሌክሳንደር ሚትሮቪች ያስቆጠራት ጎል ሦስቱን ነጥቦች ሰርቢያ ለመውሰድ የቻለች አስመስሏት ነበር። በካሜሮን በኩል ተቀይሮ የገባው ቪንሰንት አቡበከር የጨዋታውን መልክ ቀየረው። አቡበከር አንድ ጎል በስሙ ሲያስመዘግብ ኤሪክ ማክሲም ቹፖ-ሞቲንግ ያስቆጠራትን ኳስ ደግሞ አመቻችቶ አቀብሏል። በዚህም ጨዋታው ሦስት አቻ ተጠናቋል። ለዋንጫው ትልቅ ግምት የተሰጣት ብራዚል ከስዊዘርላንድ ጋር ያደረገችው ጨዋታ ቅዝቅዝ ያለ ነበር። በፊፋ ሃገራት ደረጃ ቀዳሚ የሆነችው ብራዚል ያለ ኮከብ ተጫዋቸዋ ኔይማር ነበር ወደ ሜዳ የገባችው። ብራዚል በ83ኛው ደቂቃ ጎል ለማስቆጠር ችላለች። የማንቸስተር ዩናይትዱ አማካይ ካሰሚሮ ብቸኛዋን ጎል ከመረብ አሳርፏል። ጨዋታው በዚሁ ውጤት ሲጠናቀቅ ብራዚል ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋግጣለች። ብራዚል በስድስት ነጥብ ምድቡን ትመራለች። ስዊዘርላንድ ሦስት ነጥብ አላት። ካሜሮን እና ሰርቢያ በአንድ ነጥብ ሦስተኛ እና አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። የኳታር የዓለም ዋንጫ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዎች ዛሬ መከናወን ይጀምራሉ። ምድብ አንድ ሁለት ጨዋታዎች በተመሳሳይ 12 ሰዓት ይከናወናሉ። አዘጋጇ ኳታር ኔዘርላንድስን አል ባይት ስታዲየም ትገጥማለች። ኻሊፋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ላይ ኢኳዶር እና ሴኔጋል ይገናኛሉ። ኔዘርላንድስ ምድቡን በአራት ነጥብ ስትመራ ኢኳዶርም በተመሳሳይ ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ሴኔጋል ሦስት ነጥብ አላት። ኳታር ያለምንም ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዛለች። በምድብ ሁለት እንግሊዝ ከዌልስ እና ኢራን ከአሜሪካ ምሽት አራት ሰዓት ይጫወታሉ። ምድቡን እንግሊዝ በአራት ነጥብ ትመራለች። ኢራን በሦስት ነጥብ ትከተላለች። አሜሪካ ሁለት ነጥብ ሲኖራት ዌልስ አንድ ነጥብ አላት። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c3g53x5d2dlo |
0business
| በፍራሹ ስር 137ሺ ብር ያስቀመጠው ኬንያዊ ገንዘብ ከመቀየሩ ጋር ተያይዞ ከሰረ | ኬንያ የመገበያያ ገንዘብ መቀየሯን ተከትሎ አንድ ግለሰብ 137 ሺ ብር (4ሺ 800 ዶላር) ከጥቅም ውጭ ሆኖበታል። ጁሊየስ ኦዲንጋ ምቦጋ የተባለው ግለሰብ 137 ሺ ብር የሚገመት ባለ አንድ ሺ የኬንያ ሺልንግ ገንዘብ ፍራሹ ስር አስቀምጦ የነበረ ሲሆን ገንዘብ ለመቀየር የተቀመጠበት ቀነ ገደብም በማለፉ ነው ለዓመታት ያጠራቀመው ገንዘብ ከጥቅም ውጪ የሆነበት። •ኬንያ ገንዘብ ከመቀየሯ ጋር ተያይዞ ከሰባት ቢሊዮን ሺልንግ በላይ ጥቅም አልባ ሆነ •ጃፓን ያለ መሬትና ያለ አርሶ አደሮች የፈጠረችው የግብርና አብዮት የገንዘብ ቅየራው በሃገሪቷ ውስጥ የተንሰራፋውን ሙስና ለማስቀረትና ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርንም ለመቆጣጠር እንዲያስችል እንደሆነ ተገልጿል። ግለሰቡ ከመንደሩ ሲያያ ግዛት ስልሳ ኪ.ሜትር ርቀት በሚገኘው የማዕከላዊ ባንክ በመገኘት አሮጌ የመገበያያ ገንዘቡን በአዲስ መልኩ ለመቀየር ሙከራ ቢያደርግም የገንዘብ መቀየሪያ ቀነ ገደቡ መጠናቀቁን ተከትሎ ለኪሳራ ተዳርጓል። •"የተርባይኖች መቀነስ በሚመነጨው ኃይል ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም" የህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ በመካኒክነት ስራ ሲተዳደር የነበረው ግለሰብ ለጡረታ ብሎ ያጠራቀመው ገንዘብ እንደሆነም ለደይሊ ኔሽን ተናግሯል። የማዕከላዊ ባንክ አስተዳደር እንዳሳወቁት አዲስ የመገበያያ ገንዘብ የታወጀው ሰኔ አንድ ቀን ሲሆን ከመስከረም ሃያ ጀምሮ አሮጌው የመገበያያ ገንዘብ ከጥቅም ውጭ ሆኗል። •"ሰልፍ የዜጎች መሰረታዊ መብት ነው" መስፍን ነጋሽ አፍሪካ ታክስ ጀስቲስ ኔትወርክ የተባለ ድርጅት እንዳሳወቀው በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ምክንያት ኬንያ በየአመቱ 400 ሚሊዮን ዶላር እንደምታጣ አስታውቋል። ባንኩ እንዳስታወቀውም የገንዘብ ቅይይሩ መሳካቱንና ከዚህ በኋላ ስርአት ባለው መንገድ የገንዘብ ዝውውር እንደሚከናወን ነው። | በፍራሹ ስር 137ሺ ብር ያስቀመጠው ኬንያዊ ገንዘብ ከመቀየሩ ጋር ተያይዞ ከሰረ ኬንያ የመገበያያ ገንዘብ መቀየሯን ተከትሎ አንድ ግለሰብ 137 ሺ ብር (4ሺ 800 ዶላር) ከጥቅም ውጭ ሆኖበታል። ጁሊየስ ኦዲንጋ ምቦጋ የተባለው ግለሰብ 137 ሺ ብር የሚገመት ባለ አንድ ሺ የኬንያ ሺልንግ ገንዘብ ፍራሹ ስር አስቀምጦ የነበረ ሲሆን ገንዘብ ለመቀየር የተቀመጠበት ቀነ ገደብም በማለፉ ነው ለዓመታት ያጠራቀመው ገንዘብ ከጥቅም ውጪ የሆነበት። •ኬንያ ገንዘብ ከመቀየሯ ጋር ተያይዞ ከሰባት ቢሊዮን ሺልንግ በላይ ጥቅም አልባ ሆነ •ጃፓን ያለ መሬትና ያለ አርሶ አደሮች የፈጠረችው የግብርና አብዮት የገንዘብ ቅየራው በሃገሪቷ ውስጥ የተንሰራፋውን ሙስና ለማስቀረትና ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርንም ለመቆጣጠር እንዲያስችል እንደሆነ ተገልጿል። ግለሰቡ ከመንደሩ ሲያያ ግዛት ስልሳ ኪ.ሜትር ርቀት በሚገኘው የማዕከላዊ ባንክ በመገኘት አሮጌ የመገበያያ ገንዘቡን በአዲስ መልኩ ለመቀየር ሙከራ ቢያደርግም የገንዘብ መቀየሪያ ቀነ ገደቡ መጠናቀቁን ተከትሎ ለኪሳራ ተዳርጓል። •"የተርባይኖች መቀነስ በሚመነጨው ኃይል ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም" የህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ በመካኒክነት ስራ ሲተዳደር የነበረው ግለሰብ ለጡረታ ብሎ ያጠራቀመው ገንዘብ እንደሆነም ለደይሊ ኔሽን ተናግሯል። የማዕከላዊ ባንክ አስተዳደር እንዳሳወቁት አዲስ የመገበያያ ገንዘብ የታወጀው ሰኔ አንድ ቀን ሲሆን ከመስከረም ሃያ ጀምሮ አሮጌው የመገበያያ ገንዘብ ከጥቅም ውጭ ሆኗል። •"ሰልፍ የዜጎች መሰረታዊ መብት ነው" መስፍን ነጋሽ አፍሪካ ታክስ ጀስቲስ ኔትወርክ የተባለ ድርጅት እንዳሳወቀው በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ምክንያት ኬንያ በየአመቱ 400 ሚሊዮን ዶላር እንደምታጣ አስታውቋል። ባንኩ እንዳስታወቀውም የገንዘብ ቅይይሩ መሳካቱንና ከዚህ በኋላ ስርአት ባለው መንገድ የገንዘብ ዝውውር እንደሚከናወን ነው። | https://www.bbc.com/amharic/50084810 |
2health
| ፋይዘር የኮሮናቫይረስ ማከሚያ መድኃኒቱን ታዳጊ አገራች እንዲያመርቱት ፈቀደ | ፋይዘር በሙከራ ደረጃ ያለውን የኮሮናቫይረስ ማከሚያ እንክብል መድኃኒቱን ታዳጊ አገሮች እንዲሠሩት እና እንዲያከፋፍሉት ፈቀደ። የአሜሪካው መድኃኒት አምራች ፋይዘር በ95 ታዳጊ አገራት እንክብል መድኃኒቱ እንዲመረት የተስማማው የተባበሩት መንግሥታት ከሚደግፈው ሜድስንስ ፔሸንት ፑል ድርጅት ጋር በመጣመር ነው። ድርጅቱ የኮሮናቫይረስ ማከሚያ መድኃኒቱን ከሠራ በኋላ 53 በመቶ ለሚሆነው የዓለም ሕዝብ ያዳርሳል ተብሎ ይጠበቃል። ስምምነቱ እንደ ብራዚል ያሉ በከፍተኛ ሁኔታ ቫይረሱ የተስፋፋባቸው አገራትን አያካትትም። መድኃኒቱ ለሕመም ተጋላጭ የሆኑ ጎልማሶች በጽኑ በሽታ እንዳይያዙ እንደሚከላከል ፋይዘር አስታውቋል። መድኃኒቱ በታዳጊ አገራት እንዲመረት መፍቀዱ "የመድኃኒቱን ተደራሽነት ያሰፋዋል" ሲል ገልጿል። በታዳጊ አገራት ከሚመረተው መድኃኒት ፋይዘር የባለቤትነት (ሮያሊቲ) ክፍያ አይወስድም። ወረርሽኙ ለዓለም አስጊ ሆኖ እስከቀጠለ ድረስ በሁሉም አገራት ትርፍ እንደማይሰበስብም ይፋ አድርጓል። ፋይዘር ለኮቪድ-19 ማከሚያ እየሠራ ያለው ፓክሎቪድ የተባለ መድኃኒት ነው። ይህም በከፍተኛ ሁኔታ ለሕመም ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን ሞትና ሆስፒታል የመግባት እድልን በ89 በመቶ ይቀንሳል ተብሏል። የሜድስንስ ፔሸንት ፑል ኃላፊ ቻርልስ ጎሬ እንዳሉት መድኃኒቱ በታዳጊ አገራት እንዲመረት ፍቃድ መሰጠቱ መልካም ነው። "ይህ መድኃኒት በተለይም አነስተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገራት ሕይወት ያድናል" ብለዋል። መድኃኒቱን እንዲሠሩ ፈቃድ ካገኙ አገራት አብዛኞቹ በአፍሪካ እና እስያ ይገኛሉ። እንደ ብራዚል፣ ቻይና፣ ሩስያ፣ አርጀንቲና እና ታይላንድ ያሉ ክፉኛ በወረርሽኙ የተጎዱ አገራት በስምምነቱ አልተካተቱም። የኮሮናቫይረስ ሕክምና እንዲሁም ክትባቱን ተደራሽ ለማድረግ ይህ እርምጃ በቂ እንዳልሆነ ባለሙያዎች ተችተዋል። ፋይዘርን ጨምሮ ሌሎችም የኮቪድ-19 ክትባት አምራቾች የባለቤትነት መብታቸውን አንስተው፤ ክትባቱ በሌሎች አገራት እንዲመረት ፈቃድ እንዲሰጡ ቢጠየቁም አሻፈረኝ ብለዋል። ዶክተርስ ዊዝአውት ቦርደርስ ባወጣው መግለጫ፤ ፋይዘር ለታዳጊ አገራት የሰጠው ፈቃድ የኮሮናቫይረስ መድኃኒት በመላው ዓለም እንዲደርስ እንደማይረዳ ተችቷል። "ወረርሽኙን መግታት ከፈለግን የኮሮናቫይረስ ማከሚያ መድኃኒት ለሁሉም ሰው፣ በሁሉም አገር መዳረስ አለበት" ሲሉ የድርጅቱ የሕግ አማካሪ ዩአንክዮንግ ሁ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም መርክ የተባለው መድኃኒት አምራች ድርጅት ሞልኑፒራቪር የተባለ የኮሮናቫይረስ መድኃኒቱ ከሜድስንስ ፔሸንት ፑል ጋር በጥምረት ለማምረት ተስማምቷል። | ፋይዘር የኮሮናቫይረስ ማከሚያ መድኃኒቱን ታዳጊ አገራች እንዲያመርቱት ፈቀደ ፋይዘር በሙከራ ደረጃ ያለውን የኮሮናቫይረስ ማከሚያ እንክብል መድኃኒቱን ታዳጊ አገሮች እንዲሠሩት እና እንዲያከፋፍሉት ፈቀደ። የአሜሪካው መድኃኒት አምራች ፋይዘር በ95 ታዳጊ አገራት እንክብል መድኃኒቱ እንዲመረት የተስማማው የተባበሩት መንግሥታት ከሚደግፈው ሜድስንስ ፔሸንት ፑል ድርጅት ጋር በመጣመር ነው። ድርጅቱ የኮሮናቫይረስ ማከሚያ መድኃኒቱን ከሠራ በኋላ 53 በመቶ ለሚሆነው የዓለም ሕዝብ ያዳርሳል ተብሎ ይጠበቃል። ስምምነቱ እንደ ብራዚል ያሉ በከፍተኛ ሁኔታ ቫይረሱ የተስፋፋባቸው አገራትን አያካትትም። መድኃኒቱ ለሕመም ተጋላጭ የሆኑ ጎልማሶች በጽኑ በሽታ እንዳይያዙ እንደሚከላከል ፋይዘር አስታውቋል። መድኃኒቱ በታዳጊ አገራት እንዲመረት መፍቀዱ "የመድኃኒቱን ተደራሽነት ያሰፋዋል" ሲል ገልጿል። በታዳጊ አገራት ከሚመረተው መድኃኒት ፋይዘር የባለቤትነት (ሮያሊቲ) ክፍያ አይወስድም። ወረርሽኙ ለዓለም አስጊ ሆኖ እስከቀጠለ ድረስ በሁሉም አገራት ትርፍ እንደማይሰበስብም ይፋ አድርጓል። ፋይዘር ለኮቪድ-19 ማከሚያ እየሠራ ያለው ፓክሎቪድ የተባለ መድኃኒት ነው። ይህም በከፍተኛ ሁኔታ ለሕመም ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን ሞትና ሆስፒታል የመግባት እድልን በ89 በመቶ ይቀንሳል ተብሏል። የሜድስንስ ፔሸንት ፑል ኃላፊ ቻርልስ ጎሬ እንዳሉት መድኃኒቱ በታዳጊ አገራት እንዲመረት ፍቃድ መሰጠቱ መልካም ነው። "ይህ መድኃኒት በተለይም አነስተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገራት ሕይወት ያድናል" ብለዋል። መድኃኒቱን እንዲሠሩ ፈቃድ ካገኙ አገራት አብዛኞቹ በአፍሪካ እና እስያ ይገኛሉ። እንደ ብራዚል፣ ቻይና፣ ሩስያ፣ አርጀንቲና እና ታይላንድ ያሉ ክፉኛ በወረርሽኙ የተጎዱ አገራት በስምምነቱ አልተካተቱም። የኮሮናቫይረስ ሕክምና እንዲሁም ክትባቱን ተደራሽ ለማድረግ ይህ እርምጃ በቂ እንዳልሆነ ባለሙያዎች ተችተዋል። ፋይዘርን ጨምሮ ሌሎችም የኮቪድ-19 ክትባት አምራቾች የባለቤትነት መብታቸውን አንስተው፤ ክትባቱ በሌሎች አገራት እንዲመረት ፈቃድ እንዲሰጡ ቢጠየቁም አሻፈረኝ ብለዋል። ዶክተርስ ዊዝአውት ቦርደርስ ባወጣው መግለጫ፤ ፋይዘር ለታዳጊ አገራት የሰጠው ፈቃድ የኮሮናቫይረስ መድኃኒት በመላው ዓለም እንዲደርስ እንደማይረዳ ተችቷል። "ወረርሽኙን መግታት ከፈለግን የኮሮናቫይረስ ማከሚያ መድኃኒት ለሁሉም ሰው፣ በሁሉም አገር መዳረስ አለበት" ሲሉ የድርጅቱ የሕግ አማካሪ ዩአንክዮንግ ሁ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም መርክ የተባለው መድኃኒት አምራች ድርጅት ሞልኑፒራቪር የተባለ የኮሮናቫይረስ መድኃኒቱ ከሜድስንስ ፔሸንት ፑል ጋር በጥምረት ለማምረት ተስማምቷል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59315766 |
2health
| 'በኮሮናቫይረስ ምክንያት የማስታወስ ችሎታዬን አጥቻለሁ' | በኮሮናቫይረስ ለረጅም ጊዜ ከተሰቃዩ ሚሊዮን የዓለማችን ሰዎች መካከል ሮቼሌ ዴቪድ አንዷ ነች። ሮቼሌ ከቫይረሱ ካገገመች 10 ወራት ቢቆጠሩም አንድን ነገር ለማስታወስ ከአንድ ክፍል ወደ ሌላ ክፍል እየተራመደች መሆኗን ሐኪሟ ይናገራሉ። የኮቪድ-19 ሕመም የሚያስከትለው ጉዳት ለረጅም ጊዜ የሚቆይበት አንደኛው ምክንያት ድካም ነው። የራስ ምታት፣ የፀጉር መሳሳት፣ የትኩረት ማጣት፣ ጠረን እና ጣዕም መለየት አለመቻል የመሳሰሉት ምልክቶቹ ናቸው። | 'በኮሮናቫይረስ ምክንያት የማስታወስ ችሎታዬን አጥቻለሁ' በኮሮናቫይረስ ለረጅም ጊዜ ከተሰቃዩ ሚሊዮን የዓለማችን ሰዎች መካከል ሮቼሌ ዴቪድ አንዷ ነች። ሮቼሌ ከቫይረሱ ካገገመች 10 ወራት ቢቆጠሩም አንድን ነገር ለማስታወስ ከአንድ ክፍል ወደ ሌላ ክፍል እየተራመደች መሆኗን ሐኪሟ ይናገራሉ። የኮቪድ-19 ሕመም የሚያስከትለው ጉዳት ለረጅም ጊዜ የሚቆይበት አንደኛው ምክንያት ድካም ነው። የራስ ምታት፣ የፀጉር መሳሳት፣ የትኩረት ማጣት፣ ጠረን እና ጣዕም መለየት አለመቻል የመሳሰሉት ምልክቶቹ ናቸው። | https://www.bbc.com/amharic/news-59206703 |
3politics
| ፕሬዝዳንት አል ሲሲ በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ከስምምነት እንዲደረስ ጥሪ አቀረቡ | ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው ባለው የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ በቅን ልቦና በሚካሄድ ንግግር ከስምምነት እንዲደረስ የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አል ሲሲ ጥሪ አቀረቡ። ፕሬዝዳንቱ ይህንን የተናገሩት ሳዑዲ አረቢያ ሪያድ ውስጥ በመካሄድ ላይ ባለው የቻይና-አረብ አገራት ጉባኤ ላይ ባደረጉት አገራቸውን እና የአረቡን ዓለም በሚመለከተው ንግግራቸው ነው። ወደ መጠናቀቁ የተቃረበውን የታላቁ ሕዳሴ ግድብን የውሃ ሙሌትና የሥራ ሂደት በሚመለከት ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ በተለይ ባለፉት አምስት ዓመታት ድርድር ቢያደርጉም ከስምምነት ላይ ሳይደርሱ መቅረታቸው ይታወሳል። ግድቡ ከዓባይ ወንዝ የማገኘውን የውሃ መጠን ይቀንስብኛል የሚል ስጋት ያላባት ግብፅ ፕሬዝዳንት አል ሲሲ በተለያዩ መድረኮች እንደሚያደርጉት ሁሉ አሁንም ከኢትዮጵያ ጋር ከስምምነት መድረስ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል። አል ሲሲ የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ እና የአረብ አገራት መሪዎች በታደሙበት ስብሰባ ላይ ባድረጉት ንግግር፣ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ላይ በኢትዮጵያ፣ በግብፅና በሱዳን አስገዳጅ ሕጋዊ ስምምነት እንዲደረስ ጠይቀዋል። “ለአሁኑ እና ለመጪው ትውልድ የመልማት መብትን የሚያረጋግጥ እና ትብብራቸውን፣ መረጋጋታቸውን እንዲሁም ደኅንነታቸውን ከስጋት የሚጠብቅ በቅን ልቦና ላይ የተመሠረተ ንግግር በማድረግ አሳሪ ሕጋዊ ስምምነት ላይ እንዲደረስ ለኢትዮጵያውያን ወንድሞቼ በድጋሚ ጥሪዬን አቅርባለሁ” ብለዋል ፕሬዝዳንት አል ሲሲ። በተያያዘ ዜና የግብፅ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት እንዳሳወቀው ከቻይና-አረብ አገራት ጉባኤ ጎን ለጎን አል ሲሲ የስብሰባው ተሳታፊ ከሆኑት የሱዳን የሽግግር ሉአላዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ጄኔራል አብደል ፋታህ አል ቡርሐን ጋር ተወያይተዋል። በሁለቱ መሪዎች ንግግር ወቅት ውሃ የሕዝባቸው ብሔራዊ ደኅንነት ዋነኛ ጉዳይ መሆኑን በመጥቀስ፣ በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ አሳሪ ሕጋዊ ስምምነት መድረስ አስፈላጊ መሆኑን አንስተው አል ቡርሐን የሱዳንን አቋም ማንጸባረቃቸው ተመልክቷል። ይህ የፕሬዝዳንት አል ሲሲ ጥሪ ከዚህ ቀደምም በራሳቸውን በበርካታ የግብፅ ከፍተኛ ባለሥልጣናት አማካይነት ሲቀርብ የቆየ ከመሆኑ በተጨማሪ፣ የግድቡ ጉዳይ አስከ መንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ድረስ ቀርቦ ነበር። ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን በሕዳሴው ግድብ ላይ ከስምምነት እንዲደርሱ ለማድረግ በአሜሪካ መንግሥት እና በአፍሪካ ኅብረት አማካይነት ተከታታይ ድርድሮች ሲካሄዱ ቢቆዩም፣ በግብፅ በኩል አስገዳጅ ሕጋዊ ስምምነት እንዲደረስ ያለው ፍላጎት በዓባይ ውሃ የመጠቀም ተፈጥሯዊ መብቴን የሚጋፋ ነው በሚል ኢትዮጵያ ሳትቀበለው ቆይታለች። ግንባታው አሥር ዓመታትን ያስቆጠረውና ከአራት ቢሊዮን ዶላር በላይ ኢትዮጵያን ያስወጣው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት ከስምምነት ሳይደረስ እንዳይካሄድ ከግብፅና ከሱዳን ከፍተኛ ተቃውሞ ቢገጥመውም ባለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ እንዲይዝ ተደርጓል። በአፍሪካ ከውሃ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጭት ከተገነቡ ግድቦች ሁሉ ግዙፉ እንደሆነ የሚነገረው ይህ የኢትዮጵያ ግድብ ካለፈው ዓመት ጀምሮ በተወሰነ ደረጃ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ይታወቃል። ቢሆንም ግን ግብፅ አሁንም ከወንዙ የምታገኘውን የውሃ መጠን ለማስጠበቅ የሚያስችላትን በግድቡ አጠቃላይ የሥራ ሂደት ላይ ከኢትዮጵያ ጋር ሕጋዊ ስምምነት እንዲደረግ ትፈልጋለች። አል ሲሲ ለመጀመሪያ ጊዜ በቻይና እና በአረብ አገራት መካከል በሚካሄደው ጉባኤ ላይ ባድረጉት ንግግር ላይ የውሃ ደኅንነት ጉዳይ ከአገራቸው በተጨማሪ ሌሎች የአረብ አገራትንም የሚመለከት መሆኑን ጠቅሰዋል። በዚህም ወደፊት በቻይና እና በአረብ አገራት መካከል በሚኖረው ትብብር ውስጥ የአረብ አገራት የውሃ ደኅንነት ጉዳይ ቅድሚያ ከሚሰጠቸው ጉዳዮች መካከል ከፊት ሊሆን እንደሚገባው አል ሲሲ ተናግረዋል። የግብፁ ፕሬዝዳንት ንግግር ያደረጉበት በሳዑዲ አረቢያ ውስጥ የሚካሄደው የቻይና እና የአረብ አገራት ጉባኤ፣ ቻይና በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ካሉ አገራት ጋር ያለትን ምጣኔ ሀብታዊ እና ፖለቲካዊ ትስስሯን ለማጠናከር ከምታካሂደው ዘመቻ ጋር የተያያዘ ነው። | ፕሬዝዳንት አል ሲሲ በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ከስምምነት እንዲደረስ ጥሪ አቀረቡ ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው ባለው የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ በቅን ልቦና በሚካሄድ ንግግር ከስምምነት እንዲደረስ የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አል ሲሲ ጥሪ አቀረቡ። ፕሬዝዳንቱ ይህንን የተናገሩት ሳዑዲ አረቢያ ሪያድ ውስጥ በመካሄድ ላይ ባለው የቻይና-አረብ አገራት ጉባኤ ላይ ባደረጉት አገራቸውን እና የአረቡን ዓለም በሚመለከተው ንግግራቸው ነው። ወደ መጠናቀቁ የተቃረበውን የታላቁ ሕዳሴ ግድብን የውሃ ሙሌትና የሥራ ሂደት በሚመለከት ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ በተለይ ባለፉት አምስት ዓመታት ድርድር ቢያደርጉም ከስምምነት ላይ ሳይደርሱ መቅረታቸው ይታወሳል። ግድቡ ከዓባይ ወንዝ የማገኘውን የውሃ መጠን ይቀንስብኛል የሚል ስጋት ያላባት ግብፅ ፕሬዝዳንት አል ሲሲ በተለያዩ መድረኮች እንደሚያደርጉት ሁሉ አሁንም ከኢትዮጵያ ጋር ከስምምነት መድረስ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል። አል ሲሲ የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ እና የአረብ አገራት መሪዎች በታደሙበት ስብሰባ ላይ ባድረጉት ንግግር፣ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ላይ በኢትዮጵያ፣ በግብፅና በሱዳን አስገዳጅ ሕጋዊ ስምምነት እንዲደረስ ጠይቀዋል። “ለአሁኑ እና ለመጪው ትውልድ የመልማት መብትን የሚያረጋግጥ እና ትብብራቸውን፣ መረጋጋታቸውን እንዲሁም ደኅንነታቸውን ከስጋት የሚጠብቅ በቅን ልቦና ላይ የተመሠረተ ንግግር በማድረግ አሳሪ ሕጋዊ ስምምነት ላይ እንዲደረስ ለኢትዮጵያውያን ወንድሞቼ በድጋሚ ጥሪዬን አቅርባለሁ” ብለዋል ፕሬዝዳንት አል ሲሲ። በተያያዘ ዜና የግብፅ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት እንዳሳወቀው ከቻይና-አረብ አገራት ጉባኤ ጎን ለጎን አል ሲሲ የስብሰባው ተሳታፊ ከሆኑት የሱዳን የሽግግር ሉአላዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ጄኔራል አብደል ፋታህ አል ቡርሐን ጋር ተወያይተዋል። በሁለቱ መሪዎች ንግግር ወቅት ውሃ የሕዝባቸው ብሔራዊ ደኅንነት ዋነኛ ጉዳይ መሆኑን በመጥቀስ፣ በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ አሳሪ ሕጋዊ ስምምነት መድረስ አስፈላጊ መሆኑን አንስተው አል ቡርሐን የሱዳንን አቋም ማንጸባረቃቸው ተመልክቷል። ይህ የፕሬዝዳንት አል ሲሲ ጥሪ ከዚህ ቀደምም በራሳቸውን በበርካታ የግብፅ ከፍተኛ ባለሥልጣናት አማካይነት ሲቀርብ የቆየ ከመሆኑ በተጨማሪ፣ የግድቡ ጉዳይ አስከ መንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ድረስ ቀርቦ ነበር። ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን በሕዳሴው ግድብ ላይ ከስምምነት እንዲደርሱ ለማድረግ በአሜሪካ መንግሥት እና በአፍሪካ ኅብረት አማካይነት ተከታታይ ድርድሮች ሲካሄዱ ቢቆዩም፣ በግብፅ በኩል አስገዳጅ ሕጋዊ ስምምነት እንዲደረስ ያለው ፍላጎት በዓባይ ውሃ የመጠቀም ተፈጥሯዊ መብቴን የሚጋፋ ነው በሚል ኢትዮጵያ ሳትቀበለው ቆይታለች። ግንባታው አሥር ዓመታትን ያስቆጠረውና ከአራት ቢሊዮን ዶላር በላይ ኢትዮጵያን ያስወጣው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት ከስምምነት ሳይደረስ እንዳይካሄድ ከግብፅና ከሱዳን ከፍተኛ ተቃውሞ ቢገጥመውም ባለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ እንዲይዝ ተደርጓል። በአፍሪካ ከውሃ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጭት ከተገነቡ ግድቦች ሁሉ ግዙፉ እንደሆነ የሚነገረው ይህ የኢትዮጵያ ግድብ ካለፈው ዓመት ጀምሮ በተወሰነ ደረጃ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ይታወቃል። ቢሆንም ግን ግብፅ አሁንም ከወንዙ የምታገኘውን የውሃ መጠን ለማስጠበቅ የሚያስችላትን በግድቡ አጠቃላይ የሥራ ሂደት ላይ ከኢትዮጵያ ጋር ሕጋዊ ስምምነት እንዲደረግ ትፈልጋለች። አል ሲሲ ለመጀመሪያ ጊዜ በቻይና እና በአረብ አገራት መካከል በሚካሄደው ጉባኤ ላይ ባድረጉት ንግግር ላይ የውሃ ደኅንነት ጉዳይ ከአገራቸው በተጨማሪ ሌሎች የአረብ አገራትንም የሚመለከት መሆኑን ጠቅሰዋል። በዚህም ወደፊት በቻይና እና በአረብ አገራት መካከል በሚኖረው ትብብር ውስጥ የአረብ አገራት የውሃ ደኅንነት ጉዳይ ቅድሚያ ከሚሰጠቸው ጉዳዮች መካከል ከፊት ሊሆን እንደሚገባው አል ሲሲ ተናግረዋል። የግብፁ ፕሬዝዳንት ንግግር ያደረጉበት በሳዑዲ አረቢያ ውስጥ የሚካሄደው የቻይና እና የአረብ አገራት ጉባኤ፣ ቻይና በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ካሉ አገራት ጋር ያለትን ምጣኔ ሀብታዊ እና ፖለቲካዊ ትስስሯን ለማጠናከር ከምታካሂደው ዘመቻ ጋር የተያያዘ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cv270n6lpzvo |
2health
| ኮሮናቫይረስ ፡ "ኮቪድ-19 የሚያስከትለው የአእምሮ ጤና ችግር ለብዙ አስርት ዓመታት ሊቀጥል ይችላል"- ፕ/ር መስፍን አርዓያ | እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ከሆነ ከኮሮናቫይረሰ ወረርሽኝ መከሰት በኋላ በአፍሪካ የአእምሮ ጤና መታወክ እየተከሰተ መጥቷል። ድርጅቱ ባለፈው ሐሙስ እለት በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተባለው፤ በአፍሪካ የአእምሮ ጤና መታወክ ከኮቪድ-19 በኋላ መጨመር አሳይቷል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የሕክምና አገልግሎቶችን በማስተጓጎሉ ሁኔታውን የበለጠ ፈታኝ አድርጎታል። በዛምቢያ የአእምሮ ጤና ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ሪም ዳላል እንዳሉት፤ በአህጉሪቱ ከወረርሽኙ በኋላ የአእምሮ ጤና ችግሮች ስለመባባሳቸው መረጃዎች አሉ። በዚህ ሳምንት በአፍሪካ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1.5 ሚሊዮን ያለፈ ሲሆን ቢያንስ ከ36,787 በላይ ሰዎች ደግሞ ሞተዋል። በኢትዮጵያም በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 82,662 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,271 ደርሷል። ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአእምሮ ህክምና ትምህርት ክፍል መምህር እና ሐኪም ናቸው። ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ሊከሰቱ የሚችሉ የአእምሮ ህመሞች በጣም ሰፊ መሆናቸውን ይናገራሉ። ወረርሽኙ በራሴ፣ በቤተሰቤና በአካባቢዬ ላይ ይከሰታል የሚለው ስሜት ከፍተኛ ፍርሃት፣ ጭንቀት፣ ድብርት እንዲያም ከፍተኛ ወደ ሆነ የአእምሮ መረበሽ ሊያደርስ ይችላል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ኮቪድ-19 በአካል ላይ በሚያደርሰው ጉዳት ምክንያት በአካባቢያችንና በቤተሰባችን ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል። ከዚህም ጋር በተያያዘ የሚከሰተው ሰርቶ ያለማደርና ቤት ውስጥ ተዘግቶ መዋል ከፍተኛ ጭንቀትና ድብርት እንደሚያስከትል ይናገራሉ። ሕጻናትና ሴቶች በቤት ውስጥ ወይንም በአንድ አካባቢ ብቻ መዋላቸው ከሚያደርስባቸው የአእምሮ ጤና ችግር በላይ በተቃራኒ ጾታ የሚደርስባቸው ጥቃት መስተዋሉን ፕሮፌሰሩ ያነሳሉ። ላለፉት ሰባት ወራት ከመዋዕለ ሕጻናት ጀምሮ እስከ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ድረስ ከትምህርት ገበታ ርቀው በቤት ውስጥ መቆየታቸውን በማስታወስም፤ ይህ የአእምሮ ጤና ላይ ጫና እንዳለው ያብራራሉ። ልጆች እየተሯሯጡ፣ ከእኩዩቻቸው ጋር ሲጫወቱ አካላቸው ብቻ ሳይሆን ማኅበራዊ መስተጋብራቸውም እያደገ እንደሚመጣ የሚያስረዱት ፕሮፌሰሩ፤ እነዚህ ሕጻናት በጋራ ሲጫወቱ አንዳቸው ከሌላኛቸው የሚማሩት እውቀትና ክህሎት ከፍተኛ መሆኑን በማንሳት፤ ለረዥም ወራት በአንድ አነስተኛ ግቢ ወይንም ቤት ውስጥ ተገድቦ መቀመጥ ለሕጻናቱ ከፍተኛ ጫና መሆኑን ያነሳሉ። ከዚህም የተነሳ ሕጻናቱ በከፍተኛ ሁኔታ ሊሰላቹ፣ ሊጨናነቁ፣ ሊወጣጠሩ ይችላሉ ብለዋል። ሕጻናቱ እንደ አዋቂዎች የሚሰማቸውን መናገር አለመቻላቸው ሌላው ችግር በመሆኑ ለተለያዩ የሕጻናት የአእምሮ ጤና ችግር ሊጋለጡ እንደሚችሉ ተናግረዋል። በተለይ በከተማ የሚኖሩ እና የተማሩ የሚባሉት ወላጆች ልጆችን ከኤሌክትሮኒክስ ጋር ስለሚያጋፍጧቸው ለኮምፒውተር ጌም ሱስ እንደሚያጋልጧቸው ይገልፃሉ። በዚህም የተነሳ ትምህርት በሚከፈትበት ወቅት ከእኩዮቻቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት በከፍተኛ ሁኔታ ሊጎዳ እንደሚችል ጨምረው አብራርተዋል። ወረርሽኞች የአእምሮ ጤና ችግር ያስከትላሉ? "የሚገድሉ ሕመሞች በጣም ያስጨንቃሉ" የሚሉት ፕሮፌሰር መስፍን፤ ተላላፊ በሽታዎች ግለሰቦች ላይ ባይደርስ እንኳን ገና ለገና 'ይመጣብኛል' የሚለው ስጋት እንደሚያሳቅቅ ይናገራሉ። እንደ ኮሌራና ኢቦላ ያሉ ወረርሽኞች ተመሳሳይ ተጽዕኖ እንዳላቸው የሚገልፁት ፕሮፌሰሩ፤ የኮሮናቫይረስ ባህሪ በየጊዜው ይበልጥ በታወቀ ቁጥር የሚፈጥረው ስጋትና ጭንቀት እየጨመረ እንደሚመጣ ገልፀዋል። መጀመሪያ ላይ በእድሜ የገፉ ሰዎች ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው የሚለው መረጃ ከተሰማ በኋላ፣ ወጣቶችና ሕጻናትም ተጋላጭ መሆናቸው መታወቁ፣ ተጓዳኝ በሽታ ያለባቸው ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው የሚለው መረጃ ከተሰራጨ በኋላ፣ የሌለባቸውም ተጋላጭ መሆናቸው መታየቱ፤ "ጭንቀት በሰው ላይ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ እንዲመጣ" ማድረጉን ይናገራሉ። ገና ለገና በሽታው ይመጣብኛል የሚለው አስጨናቂ መሆኑን ተናግረው፤ ጭንቀትን የሚያባብሰው ከራስ አልፎ ለቅርብ ቤተሰብ የሚኖረው ስጋት ነው ይላሉ። ቤተሰቦቼ ይያዙ ይሆን? ምልክት ሳላሳይ ቫይረሱን ይዤ እየዞርኩ ይሆን? በእድሜ የገፉ ወላጆቼን፣ ታማሚ ቤተሰቦቼን፣ ልጆቼን አስይዝ ይሆን? የሚሉት የበለጠ ያስጨንቃሉ። ከዚህ በሽታ ጋር ተያይዞ መጀመሪያ የሚከሰተው የጤና ችግር ጭንቀት የሚባለው መሆኑን ፕሮፌሰር መስፍን ይናገራሉ። ይህ ከቀላል ጭንቀት ጀምሮ እስከ ከፍተኛው እንደሚደርስ ፕሮፌሰሩ ተናግረዋል። በኮቪድ-19 የተያዘ ሰው በቤተሰብ ውስጥ ሲገኝ ደግሞ ሕመሙ በመከሰቱ ለበለጠ ጭንቀት መጋለጥ እንደሚኖር እንዲሁም ሊባባስ እንደሚችልም ያብራራሉ። በቫይረሱ የተያዘ የቤተሰብ አባል በሞት ሲታጣ ደግሞ ወደ ተራዘመ ሐዘንና ጭንቀት፣ ባስ ሲልም ወደ ድብርት ሊያስገባ ይችላል ይላሉ። ፕሮፌሰር መስፍን፤ ቫይረሱ በአካል ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት በተጨማሪ አንጎል ላይ የሚያደርሰው ተጽዕኖና ሊከሰቱ የሚችሉ አእምሮ ጤና ችግሮች ገና እየተጠኑ መሆኑን ይናገራሉ። አንዳንድ ጊዜ አንጎል ሲመረዝ ከፍተኛ የሆነ የመርሳት ችግር (ዲሜንሺያ) ወይንም ከፍተኛ የአእምሮ ሕመሞች ሊከሰቱ የሚችሉበት እድል አለ ይላሉ ፕሮፌሰሩ። እንደ አእምሮ ጤና ባለሙያ፤ "ኮቪድ 19 በአካል ላይ ከሚያደርሰው ችግር በላይ፤ ከወረርሽኙ መረጋጋት በኋላ የሚመጣው የአእምሮ ጤና ችግር ለብዙ ዓሥርት ዓመታት ይቀጥላል ብለን እናምናለን" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በኮቪድ -19 ተይዘው ሕመም የጠናባቸውና የትንፋሽ ማገዣ መሣሪያ ላይ ያሉ ሰዎች በአብዛኛው የመትረፍ እድላቸው አነስተኛ መሆኑን ያስታወሱት ፕሮፌሰር መስፍን፤ በመተንፈሻ ታግዘው ጤናቸው ሲመለስ ደግሞ ለከፍተኛ ጭንቀት እንደሚዳረጉ ማስተዋላቸውን ገልፀዋል። እነርሱ በመሣሪያ እየታገዙ ተንፍሰው ሲድኑ፤ ሌሎች ግን ከጎናቸው በመሣሪያ እየተረዱም መትረፍ ሳይችሉ ቀርተው ሲመለከቱ የሚደርስባቸው ሥነ ልቦናዊ ጫና እንዳለ ገልፀዋል። እነዚህ ሰዎች በመትረፋቸው ተመስገን ቢሉም ጭንቀትም ሆነ ድብርት ሊታይባቸው እንደሚችል ከልምዳቸው በመነሳት ያስረዳሉ። ፕሮፌሰሩ አክለውም በተለይ የሕክምና ባለሙያዎች ራሳቸውን መስዋዕት አድርገው ስለሚሠሩ ከራሳቸው አልፎ በእድሜ ለገፉ ወላጆቻቸው፣ ለቅርብ ቤተሰቦቻቸው ተጨንቀው ማስተዋላቸውንም ገልፀዋል። በኮሮናቫይረስ ዘመን ጭንቀትን መቆጣጠር አለመቻል፣ መቼም ቢሆን እርግጠኛ አለመሆን በሰዎች ዘንድ ተፈጥሯል። ጥርጣሬው የሚጀምረው "ንፁህ ነኝ?" ከሚል ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ትንሽ ቆይቶ "ወደ ቀደመው ሕይወቴ መመለስ እችል ይሆን?" ወደሚለው ያመራል። አካላዊ ርቀታችንን መጠበቅ ከቻልን፣ በተደጋጋሚ እጃችንን ከታጠብን፣ አገራት ያሳለፏቸውን ቤት የመቀመጥ መመሪያዎች ከተከተልን በቫይረሱ እንደማንያዝ እርግጠኛ ነን። ነገር ግን አእምሯችንን የሚነዘንዘን ጥርጣሬና እርግጠኛ አለመሆን፤ ከዚያም ጋር ተያይዞ የሚመጣው ጭንቀት ሕይወታችንን ሞልቶታል። የሚመላለሱት ሐሳቦች መጥፎ ስሜቶች ናቸው። ምናልባት ጭንቀቱ በትንሹም ቢሆን እንድንጠነቀቅ ያደርገን ነበር፤ ችግሩ ግን ከቁጥጥራችን ውጪ ይሆናሉ። "ከመጠን በላይ መፍራት ለተለያዩ የእምሮ ጤና ችግሮች ይዳርጋል" ያሉት ፕሮፌሰር መስፍን፤ አንዳንድ ሰዎች ከልክ ባለፈ ፍርሃት ተውጠው ማስተዋላቸውንም ጠቅሰዋል። ቤታቸውን ዘግተው የተቀመጡ እና እንቅስቃሴያቸውን የገደቡ፣ በተደጋጋሚ እጃቸውን በሳሙናና በውሃ የሚታጠቡ አልያም ሳኒታይዘር የሚጠቀሙ ሰዎች ከኮቪድ-19 በኋላ በሕክምና ቋንቋ ኦሲዲ (Obsessive-compulsive disorder) ለሚባለው ችግር እንደሚጋለጡ ይተነብያሉ። የማይፈለግና ለመቆጣጠር የሚያስቸግር ሐሳብ በሰዎች አእምሮ ሲመላለስ ኦሲዲ (ኦብሰሲቭ ኮምፐልሲቭ ዲስኦርደር) ይባላል። አንድን ነገር ሱስ በሚባል ሁኔታ በተደጋጋሚ ከማድረግ ጋር ይገናኛል። ከፍተኛ ፍርሃት የሚመጣው ስለ ቫይረሱ ያለው ግንዛቤ እና እውቀት አነስተኛ ወይንም ቁንጽል ከመሆኑ የተነሳ ነው በማለት በየጊዜው የሚሰጡ የጤና መረጃዎችን ባለሙያዎች ማዳረስ እንዳለባቸው ይመክራሉ። ሐዘንን እና መረበሽን የመቋቋም አቅም ከሰው ወደ ሰው ስለሚለያይ ስለኮሮናቫይረስ የሚተላለፉ መረጃዎች በማያስፈራራና በማይረብሽ መንገድ በአግባቡ መሰጠት እንደሚኖርበት ይናገራሉ። ሰዎች በሚሰሙት መረጃ ተረብሸው ወደ ጭንቀት፣ ድብርት፣ ራስን ወደመጥላት እና ከዚያም ወደ ከፋ እርምጃ እንዳይሄዱ የመገናኛ ብዙኀን፣ የኃይማኖት ተቋማት፣ ወጣቶች ትክክለኛውን መረጃ ማድረስ እንደሚያስፈልጋቸው ይመክራሉ። የአእምሮ ጤናን መጠበቅ የሚቻለው ልክ ሌላው የአካል ክፍል ጤና እንደሚጠበቀው መሆኑን ፕሮፌሰር መስፍን ያስታውሳሉ። ንጹሕ አየር መተንፈስ፣ አመጋገብን ማስተካከል፣ መንፈሳዊ ሕይወትን ማጠናከር፣ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ፣ ጥሩ እንቅልፍ መተኛት፣ ከሱስ መጠበቅ ጠቃሚ መሆናቸውን በማንሳት፤ ለአካላዊ ጤና የሚጠቅሙት እነዚህ ነገሮች ለአእምሮም እንደሚያስፈልጉት ይገልፃሉ። በዚህ ወቅት ከጭንቀት እና ውጥረት ራስን መጠበቅ ወሳኝ መሆኑን ይናገራሉ። እርስ በእርስ መተሳሰብ እንዲሁም መደጋገፍ አስፈላጊ መሆኑንም ያስታውሳሉ። | ኮሮናቫይረስ ፡ "ኮቪድ-19 የሚያስከትለው የአእምሮ ጤና ችግር ለብዙ አስርት ዓመታት ሊቀጥል ይችላል"- ፕ/ር መስፍን አርዓያ እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ከሆነ ከኮሮናቫይረሰ ወረርሽኝ መከሰት በኋላ በአፍሪካ የአእምሮ ጤና መታወክ እየተከሰተ መጥቷል። ድርጅቱ ባለፈው ሐሙስ እለት በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተባለው፤ በአፍሪካ የአእምሮ ጤና መታወክ ከኮቪድ-19 በኋላ መጨመር አሳይቷል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የሕክምና አገልግሎቶችን በማስተጓጎሉ ሁኔታውን የበለጠ ፈታኝ አድርጎታል። በዛምቢያ የአእምሮ ጤና ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ሪም ዳላል እንዳሉት፤ በአህጉሪቱ ከወረርሽኙ በኋላ የአእምሮ ጤና ችግሮች ስለመባባሳቸው መረጃዎች አሉ። በዚህ ሳምንት በአፍሪካ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1.5 ሚሊዮን ያለፈ ሲሆን ቢያንስ ከ36,787 በላይ ሰዎች ደግሞ ሞተዋል። በኢትዮጵያም በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 82,662 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,271 ደርሷል። ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአእምሮ ህክምና ትምህርት ክፍል መምህር እና ሐኪም ናቸው። ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ሊከሰቱ የሚችሉ የአእምሮ ህመሞች በጣም ሰፊ መሆናቸውን ይናገራሉ። ወረርሽኙ በራሴ፣ በቤተሰቤና በአካባቢዬ ላይ ይከሰታል የሚለው ስሜት ከፍተኛ ፍርሃት፣ ጭንቀት፣ ድብርት እንዲያም ከፍተኛ ወደ ሆነ የአእምሮ መረበሽ ሊያደርስ ይችላል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ኮቪድ-19 በአካል ላይ በሚያደርሰው ጉዳት ምክንያት በአካባቢያችንና በቤተሰባችን ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል። ከዚህም ጋር በተያያዘ የሚከሰተው ሰርቶ ያለማደርና ቤት ውስጥ ተዘግቶ መዋል ከፍተኛ ጭንቀትና ድብርት እንደሚያስከትል ይናገራሉ። ሕጻናትና ሴቶች በቤት ውስጥ ወይንም በአንድ አካባቢ ብቻ መዋላቸው ከሚያደርስባቸው የአእምሮ ጤና ችግር በላይ በተቃራኒ ጾታ የሚደርስባቸው ጥቃት መስተዋሉን ፕሮፌሰሩ ያነሳሉ። ላለፉት ሰባት ወራት ከመዋዕለ ሕጻናት ጀምሮ እስከ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ድረስ ከትምህርት ገበታ ርቀው በቤት ውስጥ መቆየታቸውን በማስታወስም፤ ይህ የአእምሮ ጤና ላይ ጫና እንዳለው ያብራራሉ። ልጆች እየተሯሯጡ፣ ከእኩዩቻቸው ጋር ሲጫወቱ አካላቸው ብቻ ሳይሆን ማኅበራዊ መስተጋብራቸውም እያደገ እንደሚመጣ የሚያስረዱት ፕሮፌሰሩ፤ እነዚህ ሕጻናት በጋራ ሲጫወቱ አንዳቸው ከሌላኛቸው የሚማሩት እውቀትና ክህሎት ከፍተኛ መሆኑን በማንሳት፤ ለረዥም ወራት በአንድ አነስተኛ ግቢ ወይንም ቤት ውስጥ ተገድቦ መቀመጥ ለሕጻናቱ ከፍተኛ ጫና መሆኑን ያነሳሉ። ከዚህም የተነሳ ሕጻናቱ በከፍተኛ ሁኔታ ሊሰላቹ፣ ሊጨናነቁ፣ ሊወጣጠሩ ይችላሉ ብለዋል። ሕጻናቱ እንደ አዋቂዎች የሚሰማቸውን መናገር አለመቻላቸው ሌላው ችግር በመሆኑ ለተለያዩ የሕጻናት የአእምሮ ጤና ችግር ሊጋለጡ እንደሚችሉ ተናግረዋል። በተለይ በከተማ የሚኖሩ እና የተማሩ የሚባሉት ወላጆች ልጆችን ከኤሌክትሮኒክስ ጋር ስለሚያጋፍጧቸው ለኮምፒውተር ጌም ሱስ እንደሚያጋልጧቸው ይገልፃሉ። በዚህም የተነሳ ትምህርት በሚከፈትበት ወቅት ከእኩዮቻቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት በከፍተኛ ሁኔታ ሊጎዳ እንደሚችል ጨምረው አብራርተዋል። ወረርሽኞች የአእምሮ ጤና ችግር ያስከትላሉ? "የሚገድሉ ሕመሞች በጣም ያስጨንቃሉ" የሚሉት ፕሮፌሰር መስፍን፤ ተላላፊ በሽታዎች ግለሰቦች ላይ ባይደርስ እንኳን ገና ለገና 'ይመጣብኛል' የሚለው ስጋት እንደሚያሳቅቅ ይናገራሉ። እንደ ኮሌራና ኢቦላ ያሉ ወረርሽኞች ተመሳሳይ ተጽዕኖ እንዳላቸው የሚገልፁት ፕሮፌሰሩ፤ የኮሮናቫይረስ ባህሪ በየጊዜው ይበልጥ በታወቀ ቁጥር የሚፈጥረው ስጋትና ጭንቀት እየጨመረ እንደሚመጣ ገልፀዋል። መጀመሪያ ላይ በእድሜ የገፉ ሰዎች ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው የሚለው መረጃ ከተሰማ በኋላ፣ ወጣቶችና ሕጻናትም ተጋላጭ መሆናቸው መታወቁ፣ ተጓዳኝ በሽታ ያለባቸው ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው የሚለው መረጃ ከተሰራጨ በኋላ፣ የሌለባቸውም ተጋላጭ መሆናቸው መታየቱ፤ "ጭንቀት በሰው ላይ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ እንዲመጣ" ማድረጉን ይናገራሉ። ገና ለገና በሽታው ይመጣብኛል የሚለው አስጨናቂ መሆኑን ተናግረው፤ ጭንቀትን የሚያባብሰው ከራስ አልፎ ለቅርብ ቤተሰብ የሚኖረው ስጋት ነው ይላሉ። ቤተሰቦቼ ይያዙ ይሆን? ምልክት ሳላሳይ ቫይረሱን ይዤ እየዞርኩ ይሆን? በእድሜ የገፉ ወላጆቼን፣ ታማሚ ቤተሰቦቼን፣ ልጆቼን አስይዝ ይሆን? የሚሉት የበለጠ ያስጨንቃሉ። ከዚህ በሽታ ጋር ተያይዞ መጀመሪያ የሚከሰተው የጤና ችግር ጭንቀት የሚባለው መሆኑን ፕሮፌሰር መስፍን ይናገራሉ። ይህ ከቀላል ጭንቀት ጀምሮ እስከ ከፍተኛው እንደሚደርስ ፕሮፌሰሩ ተናግረዋል። በኮቪድ-19 የተያዘ ሰው በቤተሰብ ውስጥ ሲገኝ ደግሞ ሕመሙ በመከሰቱ ለበለጠ ጭንቀት መጋለጥ እንደሚኖር እንዲሁም ሊባባስ እንደሚችልም ያብራራሉ። በቫይረሱ የተያዘ የቤተሰብ አባል በሞት ሲታጣ ደግሞ ወደ ተራዘመ ሐዘንና ጭንቀት፣ ባስ ሲልም ወደ ድብርት ሊያስገባ ይችላል ይላሉ። ፕሮፌሰር መስፍን፤ ቫይረሱ በአካል ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት በተጨማሪ አንጎል ላይ የሚያደርሰው ተጽዕኖና ሊከሰቱ የሚችሉ አእምሮ ጤና ችግሮች ገና እየተጠኑ መሆኑን ይናገራሉ። አንዳንድ ጊዜ አንጎል ሲመረዝ ከፍተኛ የሆነ የመርሳት ችግር (ዲሜንሺያ) ወይንም ከፍተኛ የአእምሮ ሕመሞች ሊከሰቱ የሚችሉበት እድል አለ ይላሉ ፕሮፌሰሩ። እንደ አእምሮ ጤና ባለሙያ፤ "ኮቪድ 19 በአካል ላይ ከሚያደርሰው ችግር በላይ፤ ከወረርሽኙ መረጋጋት በኋላ የሚመጣው የአእምሮ ጤና ችግር ለብዙ ዓሥርት ዓመታት ይቀጥላል ብለን እናምናለን" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በኮቪድ -19 ተይዘው ሕመም የጠናባቸውና የትንፋሽ ማገዣ መሣሪያ ላይ ያሉ ሰዎች በአብዛኛው የመትረፍ እድላቸው አነስተኛ መሆኑን ያስታወሱት ፕሮፌሰር መስፍን፤ በመተንፈሻ ታግዘው ጤናቸው ሲመለስ ደግሞ ለከፍተኛ ጭንቀት እንደሚዳረጉ ማስተዋላቸውን ገልፀዋል። እነርሱ በመሣሪያ እየታገዙ ተንፍሰው ሲድኑ፤ ሌሎች ግን ከጎናቸው በመሣሪያ እየተረዱም መትረፍ ሳይችሉ ቀርተው ሲመለከቱ የሚደርስባቸው ሥነ ልቦናዊ ጫና እንዳለ ገልፀዋል። እነዚህ ሰዎች በመትረፋቸው ተመስገን ቢሉም ጭንቀትም ሆነ ድብርት ሊታይባቸው እንደሚችል ከልምዳቸው በመነሳት ያስረዳሉ። ፕሮፌሰሩ አክለውም በተለይ የሕክምና ባለሙያዎች ራሳቸውን መስዋዕት አድርገው ስለሚሠሩ ከራሳቸው አልፎ በእድሜ ለገፉ ወላጆቻቸው፣ ለቅርብ ቤተሰቦቻቸው ተጨንቀው ማስተዋላቸውንም ገልፀዋል። በኮሮናቫይረስ ዘመን ጭንቀትን መቆጣጠር አለመቻል፣ መቼም ቢሆን እርግጠኛ አለመሆን በሰዎች ዘንድ ተፈጥሯል። ጥርጣሬው የሚጀምረው "ንፁህ ነኝ?" ከሚል ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ትንሽ ቆይቶ "ወደ ቀደመው ሕይወቴ መመለስ እችል ይሆን?" ወደሚለው ያመራል። አካላዊ ርቀታችንን መጠበቅ ከቻልን፣ በተደጋጋሚ እጃችንን ከታጠብን፣ አገራት ያሳለፏቸውን ቤት የመቀመጥ መመሪያዎች ከተከተልን በቫይረሱ እንደማንያዝ እርግጠኛ ነን። ነገር ግን አእምሯችንን የሚነዘንዘን ጥርጣሬና እርግጠኛ አለመሆን፤ ከዚያም ጋር ተያይዞ የሚመጣው ጭንቀት ሕይወታችንን ሞልቶታል። የሚመላለሱት ሐሳቦች መጥፎ ስሜቶች ናቸው። ምናልባት ጭንቀቱ በትንሹም ቢሆን እንድንጠነቀቅ ያደርገን ነበር፤ ችግሩ ግን ከቁጥጥራችን ውጪ ይሆናሉ። "ከመጠን በላይ መፍራት ለተለያዩ የእምሮ ጤና ችግሮች ይዳርጋል" ያሉት ፕሮፌሰር መስፍን፤ አንዳንድ ሰዎች ከልክ ባለፈ ፍርሃት ተውጠው ማስተዋላቸውንም ጠቅሰዋል። ቤታቸውን ዘግተው የተቀመጡ እና እንቅስቃሴያቸውን የገደቡ፣ በተደጋጋሚ እጃቸውን በሳሙናና በውሃ የሚታጠቡ አልያም ሳኒታይዘር የሚጠቀሙ ሰዎች ከኮቪድ-19 በኋላ በሕክምና ቋንቋ ኦሲዲ (Obsessive-compulsive disorder) ለሚባለው ችግር እንደሚጋለጡ ይተነብያሉ። የማይፈለግና ለመቆጣጠር የሚያስቸግር ሐሳብ በሰዎች አእምሮ ሲመላለስ ኦሲዲ (ኦብሰሲቭ ኮምፐልሲቭ ዲስኦርደር) ይባላል። አንድን ነገር ሱስ በሚባል ሁኔታ በተደጋጋሚ ከማድረግ ጋር ይገናኛል። ከፍተኛ ፍርሃት የሚመጣው ስለ ቫይረሱ ያለው ግንዛቤ እና እውቀት አነስተኛ ወይንም ቁንጽል ከመሆኑ የተነሳ ነው በማለት በየጊዜው የሚሰጡ የጤና መረጃዎችን ባለሙያዎች ማዳረስ እንዳለባቸው ይመክራሉ። ሐዘንን እና መረበሽን የመቋቋም አቅም ከሰው ወደ ሰው ስለሚለያይ ስለኮሮናቫይረስ የሚተላለፉ መረጃዎች በማያስፈራራና በማይረብሽ መንገድ በአግባቡ መሰጠት እንደሚኖርበት ይናገራሉ። ሰዎች በሚሰሙት መረጃ ተረብሸው ወደ ጭንቀት፣ ድብርት፣ ራስን ወደመጥላት እና ከዚያም ወደ ከፋ እርምጃ እንዳይሄዱ የመገናኛ ብዙኀን፣ የኃይማኖት ተቋማት፣ ወጣቶች ትክክለኛውን መረጃ ማድረስ እንደሚያስፈልጋቸው ይመክራሉ። የአእምሮ ጤናን መጠበቅ የሚቻለው ልክ ሌላው የአካል ክፍል ጤና እንደሚጠበቀው መሆኑን ፕሮፌሰር መስፍን ያስታውሳሉ። ንጹሕ አየር መተንፈስ፣ አመጋገብን ማስተካከል፣ መንፈሳዊ ሕይወትን ማጠናከር፣ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ፣ ጥሩ እንቅልፍ መተኛት፣ ከሱስ መጠበቅ ጠቃሚ መሆናቸውን በማንሳት፤ ለአካላዊ ጤና የሚጠቅሙት እነዚህ ነገሮች ለአእምሮም እንደሚያስፈልጉት ይገልፃሉ። በዚህ ወቅት ከጭንቀት እና ውጥረት ራስን መጠበቅ ወሳኝ መሆኑን ይናገራሉ። እርስ በእርስ መተሳሰብ እንዲሁም መደጋገፍ አስፈላጊ መሆኑንም ያስታውሳሉ። | https://www.bbc.com/amharic/54485207 |
5sports
| በአውሮፓ የቦክስ ሻምፒዮና የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊው ትውልደ ኢትዮጵያዊ | በዚህ ዓመት አርሜኒያ ውስጥ በተካሄደው የአውሮፓ የቦክስ ሻምፒዮና ላይ አየርላንድን ወክለው በቡጢው መድረክ ለመፎካከር ከተሰለፉ መካከል ጋብርኤል ዶሰን አንዱ ነበር። ትውልደ ኢትዮጵያዊው ጋብርኤል በዚህ ስፖርት በአየርላንድ ውስጥ ዝናው ከፍ ያለ ነው። በአርሜኒያ በተካሄደው የቦክስ ሻምፒዮና ላይም ስለብቃቱ መገናኛ ብዙኃን በአንድ ድምጽ ተርከዋል። የዶሰን ፈጣን ቡጢዎች፣ ተጋጣሚዎቹን ለመከላከልም ሆነ ለማጥቃት ፋታ ነስተው መታየታቸው ተመስክሯል። እነርሱ ጋብርኤልን፣ ጋቢ እያሉ ያቆላምጡታል። የጋልዌዩ ቡጢኛም የሚሉትም አሉ። መኖሪያ አካባቢውን በማጣቀስ። ጋብርኤል ለአገሩ አየርላንድ ወርቅ በማምጣት ባንዲራዋ ከፍ ብሎ አንዲውለበለብ፣ ስሟ በቡጠኞች እና በሻምፒዮናው አዘጋጆች ዘንድ እንዲናኝ አድርጓል። የ22 ዓመቱ ጋቢ፣ የወርቅ ሜዳልያውን ያጠለቀው እንግሊዛዊው ሉዊስ ሪቻርድሰንን አሸንፎ ነው። ሉዊስ ከጋቢ በቀኝ በኩል የሚሰነዘርበትን ፈጣን ቡጢ መቋቋም አለመቻሉን በቦክስ ሜዳው ላይ እና ዙሪያ የነበሩ ሁሉ ታዝነበዋል። ቢቢሲ ጋብሬል ዶሰንን ስለ ድሉ ሲጠይቀው፣ “ጥቁር አፍሪካዊ የኢትዮጵያ ልጅ፣ ሆኜ በቦክስ የአውሮፓ ሻምፒዮና በመሆኔ ከፍተኛ ኩራት ይሰማኛል” ብሏል። በዚህ ድል በኩራት ልባቸው ሐሴት ካደረገ ሰዎች መካከል ደግሞ እናቱ ምሥራቅ ተስፋዬ አንዷ ነች። “ልጄ እኔን እና ቤተሰቦቼን ብቻ ሳይሆን፣ . . .አጠቃላይ ጥቁር አፍሪካውያንን አኩርቷል። የአውሮፓ ሻምፒዮና መሆኑ ለየት ያለ ስሜት አለው” ትላላች። ጋብርኤል በዚህ ውድድር ላይ የወርቅ ሜዳልያ በማጥለቅ ሻምፒዮና ለመሆን በመጀመሪያ የስፔን ተወዳዳሪውን፣ በመቀጠል የቡልጋርያን፣ ወደ ፍጻሜ ለማለፍ ደግሞ የኖርዌይ ተጋጣሚዎቹን በዝረራ አሸንፏል። “አሁን እኔ በቦክስ የአውሮፓ ሻምፕዮን ነኝ። ነገር ግን ያሸነፍኩ ቀን ለማመን ደቂቃዎች ፈጅቶብኛል። ጥቁር አፍሪካዊ፣ የአየርላንድ ዜጋ ሆኜ፣ ደግሞም ከኢትዮጵያ የተገኘሁ ሆኜ በአውሮፓ መድረክ ላይ ሻምፒዮና መሆኔ፣ በጣም አስገርሞኛል። በዚያ ቅጽበት የተሰማኝን መግለጽ ከባድ ነው” ይላል ጋብርኤል። እናቱ ምሥራቅ ተስፋዬ ደግሞ፣ ውድድሩ መክፈቻ ላይ ጋብርኤል ከተጋጣሚው ጋር ሲገናኝ አየርላንዳውያን በአጠቃላይ በጉጉት ሲጠብቁ እንደነበር አስታውሳለች። ሲያሸንፍ የተሰማቸውንም ስትናገር “ዜጎቻቸውን በሙሉ ይወዳሉ። ጥቁር ነጭ ሳይሉ። እርሱ ሲያሸንፍ መላ አገሪቱ ላይ ትልቅ ደስታ ነበር” ብላለች። ጋብርኤል የተወለደው አይቮሪኮስት ውስጥ ነው። አባቱ የላይቤሪያ ዜግነት ያለው ሲሆን በእናቱ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ነው። ከዓመታት በፊት እናቱ በአይቮሪኮስት በስደተኝነት ትኖር ነበር። ያኔ ነው የዶሰን አባት እና ምሥራቅ የተገናኙት። ዶሰን እና ምሥራቅ ተጋብተው ጋብርኤል በተወለደ በሁለት ዓመቱ ወደ አየርላንድ አመሩ። ጋብርኤል ዘጠኝ ዓመት ሲሞላው ደግሞ የቦክስ ሥልጠና መውሰድ ጀመረ። በ16 ዓመቱ ለአየርላንድ ታዳጊ ቡድን ተመርጦ፣ በአውሮፓ መድረክ አገሩን አየርላንድን በመወከል ለንደን ላይ ተወዳደረ። እኤአ በ2019 የአየርላንድ ብሔራዊ ቦክስ ውድድር ላይ ተሳትፎ በአንደኝነት ማሸነፍ ችሏል። ጋቢ ገና ስፖርት ሲጀምር ‘በኪክ ቦክሲንግ’ እንደነበረ ይናገራል። ከቦክስ በተጨማሪ ዋና፣ እግር ኳስ እንዲሁም ቴክዋንዶ የእርሱ የስፖርት ምርጫዎች ናቸው። በቴክዋንዶ ስፖርትም የጥቁር ቀበቶ ማግኘቱን ለቢቢሲ ገልጿል። እድሜው 19 ሲሞላ፣ ወደ ቦክስ አመዝኖ ለብሔራዊ ቡደን ተመረጠ። ጋብርኤል በቦክስ ቡድን ውስጥ ታቅፎ ሥልጠና ሲያደርግ መቆየቱን ይናገራል። ከአየርላንድ ብሔራዊ ቡድን ጋር በመሆን ደግሞ ከማክሰኞ እስከ አርብ ልምምድ ያደርግ ነበረ። ጋብርኤል ለቤቱ የመጀመሪያ ልጅ ሲሆን፣ አረን ዶሰን የሚባል ታናሽ ወንድም አለው። አረን በእግር ኳስ ብቃቱ ይታወቃል። የእንግሊዙ ቼልሲ እግር ኳስ ቡድን ለታዳጊ ክለቡ መልምሎት እንደነበር እናቱ ምሥራቅ ከቢቢሲ ጋር በነበራት ቆይታ ወቅት ተናግራለች። “እኔም ከእርሱ ጋር መሄድ ስለነበረብኝ ለሌሎች ልጆቼ ብዬ መሄድ አልቻልኩም። በዚህ ምክንያት ይህ ዕድል አመለጠው። ለሌሎቹ በማሰብ ነው እዚህ የቀረሁት” ትላለች። ነገር ግን አረን፣ በአሁኑ ወቅት ለጎልዌይ ከተማ ስለሚጫወት “አሁንም ዕድል አለው ብዬ አምናለሁ” ስትል ተስፋዋን ተናግራለች። የጋብርኤል እህት ኢቭ ዶሰን ደግሞ 17 ዓመቷ ሲሆን፣ በእግር ኳስ ለአየርላንድ ከ19 ዓመት በታች የእግር ኳስ ቡድን ተመርጣለች። አንድ የስኮትላንድ እግር ኳስ ቡድን ሊያስፈርማት ጠይቋት የነበረ ሲሆን፣ ትምህርቷን መጨረስ እንዳለባት ቤተሰቡ በመወሰኑ እናቷ ወደ ስኮትላንድ እንዳትሄድ እንደከለከለቻት ለቢቢሲ ተናግራለች። እናታቸው ምሥራቅ ልጆቿ ለስፖርት ስላላቸው ፍቅር ስትጠየቅ፣ “በአንድ ሳምንት ሰባቱንም ቀን መኪና ውስጥ ነው ውለን የምናድረው፣ መኪናችንን እንደ ቤት ነው የምንጠቀመው፣ ቀን ቀን ትምህርት ቤት ይውላሉ። አድርሼያቸሁ እመልሳቸዋለሁ። “ከዚያ በኋላ ደግሞ ለሥልጠና ወደ ተለያዩ ቦታዎች አደርሳቸዋለሁ። በየሁለት ሳምንቱ ደግሞ ወደ ተለያዩ ቦታዎች እወስዳቸዋለሁ። እኔ ደግሞ እነርሱን ለማሳደግ እና ለማስተማር ሥራ እሰራለሁ። ሕይወታችን ይህንን ነው የሚመስለው” ትላለች። ጋብርኤል እዚህ ስኬት ላይ ለመድረስ ከ10 ዓመት በላይ ወስዶበታል። አሁን የልፋቱን ውጤት በማየታቸው ቤተሰቡ ደስተኞች ናቸው። ጋቢ ከአርሜኒያ ወርቅ አሸንፎ ወደ አየርላንድ ሲመለስ ቤተሰቦቹ እና የእግር ኳስ ቡድኑ ደማቅ አቀባበል አድርጎለታል። ይህ ግን ለእናቱ ምሥራቅ ተስፋዬ ስሜት የሚበርዝ ነበር። ኢትዮጵያ ወገኖቹ መካከል ቢሆን ይሄኔ ደስታውና ሆታው የተለየ ነበር ስትል አስባ እንደ ከፋት ለቢቢሲ ተናግራለች። እናት ምሥራቅ ለላለፉት 11 ዓመታት ልጆቿን ብቻዋን ማሳደጓን ትናገራለች። “የልጆቼን ሕልም ለማሳካት ቀንና ሌሊት ነው የምሰራው። አንዳንዴ ማሽን አልያም ሰው መሆኔን እጠራጠራለሁ፤ እራስ ደካማ ሆኖ ልጆችን በርቱ ማለት አይቻልም። ሰርቶ ለልጆችህ ማሳየት ያስፈልጋል።” ከአየርላንድ ምንም እርዳታ እንደሌላት የምትናገረው ምሥራቅ፣ ከፍተኛ ሥራ ዕድል ስላለ ሰርታ ያሰበችው ደረጃ መድረስ እንደምትችል ትናገራለች። ጋብርኤል ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ የእናቱን የትውልድ ስፍራ ማየት ሕልሙ ነው። “የእናቴ ትውልድ ቦታ ሐረጌ ስለሆነ አንድ ቀን ሄጄ ብጎበኝ ብዬ አስባለሁ።” ጋብርኤል በቶኪዮ ኦሊምፒክ በቦክስ ውደድድር ለመሳተፍ እየተዘጋጀ ሳለ በደረሰበት ጉዳት የተነሳ ሳይሳካለት ቀርቷል። ቀጣዩ የኦሊምፒክ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ግን ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ለቢቢሲ ገልጿል። | በአውሮፓ የቦክስ ሻምፒዮና የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊው ትውልደ ኢትዮጵያዊ በዚህ ዓመት አርሜኒያ ውስጥ በተካሄደው የአውሮፓ የቦክስ ሻምፒዮና ላይ አየርላንድን ወክለው በቡጢው መድረክ ለመፎካከር ከተሰለፉ መካከል ጋብርኤል ዶሰን አንዱ ነበር። ትውልደ ኢትዮጵያዊው ጋብርኤል በዚህ ስፖርት በአየርላንድ ውስጥ ዝናው ከፍ ያለ ነው። በአርሜኒያ በተካሄደው የቦክስ ሻምፒዮና ላይም ስለብቃቱ መገናኛ ብዙኃን በአንድ ድምጽ ተርከዋል። የዶሰን ፈጣን ቡጢዎች፣ ተጋጣሚዎቹን ለመከላከልም ሆነ ለማጥቃት ፋታ ነስተው መታየታቸው ተመስክሯል። እነርሱ ጋብርኤልን፣ ጋቢ እያሉ ያቆላምጡታል። የጋልዌዩ ቡጢኛም የሚሉትም አሉ። መኖሪያ አካባቢውን በማጣቀስ። ጋብርኤል ለአገሩ አየርላንድ ወርቅ በማምጣት ባንዲራዋ ከፍ ብሎ አንዲውለበለብ፣ ስሟ በቡጠኞች እና በሻምፒዮናው አዘጋጆች ዘንድ እንዲናኝ አድርጓል። የ22 ዓመቱ ጋቢ፣ የወርቅ ሜዳልያውን ያጠለቀው እንግሊዛዊው ሉዊስ ሪቻርድሰንን አሸንፎ ነው። ሉዊስ ከጋቢ በቀኝ በኩል የሚሰነዘርበትን ፈጣን ቡጢ መቋቋም አለመቻሉን በቦክስ ሜዳው ላይ እና ዙሪያ የነበሩ ሁሉ ታዝነበዋል። ቢቢሲ ጋብሬል ዶሰንን ስለ ድሉ ሲጠይቀው፣ “ጥቁር አፍሪካዊ የኢትዮጵያ ልጅ፣ ሆኜ በቦክስ የአውሮፓ ሻምፒዮና በመሆኔ ከፍተኛ ኩራት ይሰማኛል” ብሏል። በዚህ ድል በኩራት ልባቸው ሐሴት ካደረገ ሰዎች መካከል ደግሞ እናቱ ምሥራቅ ተስፋዬ አንዷ ነች። “ልጄ እኔን እና ቤተሰቦቼን ብቻ ሳይሆን፣ . . .አጠቃላይ ጥቁር አፍሪካውያንን አኩርቷል። የአውሮፓ ሻምፒዮና መሆኑ ለየት ያለ ስሜት አለው” ትላላች። ጋብርኤል በዚህ ውድድር ላይ የወርቅ ሜዳልያ በማጥለቅ ሻምፒዮና ለመሆን በመጀመሪያ የስፔን ተወዳዳሪውን፣ በመቀጠል የቡልጋርያን፣ ወደ ፍጻሜ ለማለፍ ደግሞ የኖርዌይ ተጋጣሚዎቹን በዝረራ አሸንፏል። “አሁን እኔ በቦክስ የአውሮፓ ሻምፕዮን ነኝ። ነገር ግን ያሸነፍኩ ቀን ለማመን ደቂቃዎች ፈጅቶብኛል። ጥቁር አፍሪካዊ፣ የአየርላንድ ዜጋ ሆኜ፣ ደግሞም ከኢትዮጵያ የተገኘሁ ሆኜ በአውሮፓ መድረክ ላይ ሻምፒዮና መሆኔ፣ በጣም አስገርሞኛል። በዚያ ቅጽበት የተሰማኝን መግለጽ ከባድ ነው” ይላል ጋብርኤል። እናቱ ምሥራቅ ተስፋዬ ደግሞ፣ ውድድሩ መክፈቻ ላይ ጋብርኤል ከተጋጣሚው ጋር ሲገናኝ አየርላንዳውያን በአጠቃላይ በጉጉት ሲጠብቁ እንደነበር አስታውሳለች። ሲያሸንፍ የተሰማቸውንም ስትናገር “ዜጎቻቸውን በሙሉ ይወዳሉ። ጥቁር ነጭ ሳይሉ። እርሱ ሲያሸንፍ መላ አገሪቱ ላይ ትልቅ ደስታ ነበር” ብላለች። ጋብርኤል የተወለደው አይቮሪኮስት ውስጥ ነው። አባቱ የላይቤሪያ ዜግነት ያለው ሲሆን በእናቱ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ነው። ከዓመታት በፊት እናቱ በአይቮሪኮስት በስደተኝነት ትኖር ነበር። ያኔ ነው የዶሰን አባት እና ምሥራቅ የተገናኙት። ዶሰን እና ምሥራቅ ተጋብተው ጋብርኤል በተወለደ በሁለት ዓመቱ ወደ አየርላንድ አመሩ። ጋብርኤል ዘጠኝ ዓመት ሲሞላው ደግሞ የቦክስ ሥልጠና መውሰድ ጀመረ። በ16 ዓመቱ ለአየርላንድ ታዳጊ ቡድን ተመርጦ፣ በአውሮፓ መድረክ አገሩን አየርላንድን በመወከል ለንደን ላይ ተወዳደረ። እኤአ በ2019 የአየርላንድ ብሔራዊ ቦክስ ውድድር ላይ ተሳትፎ በአንደኝነት ማሸነፍ ችሏል። ጋቢ ገና ስፖርት ሲጀምር ‘በኪክ ቦክሲንግ’ እንደነበረ ይናገራል። ከቦክስ በተጨማሪ ዋና፣ እግር ኳስ እንዲሁም ቴክዋንዶ የእርሱ የስፖርት ምርጫዎች ናቸው። በቴክዋንዶ ስፖርትም የጥቁር ቀበቶ ማግኘቱን ለቢቢሲ ገልጿል። እድሜው 19 ሲሞላ፣ ወደ ቦክስ አመዝኖ ለብሔራዊ ቡደን ተመረጠ። ጋብርኤል በቦክስ ቡድን ውስጥ ታቅፎ ሥልጠና ሲያደርግ መቆየቱን ይናገራል። ከአየርላንድ ብሔራዊ ቡድን ጋር በመሆን ደግሞ ከማክሰኞ እስከ አርብ ልምምድ ያደርግ ነበረ። ጋብርኤል ለቤቱ የመጀመሪያ ልጅ ሲሆን፣ አረን ዶሰን የሚባል ታናሽ ወንድም አለው። አረን በእግር ኳስ ብቃቱ ይታወቃል። የእንግሊዙ ቼልሲ እግር ኳስ ቡድን ለታዳጊ ክለቡ መልምሎት እንደነበር እናቱ ምሥራቅ ከቢቢሲ ጋር በነበራት ቆይታ ወቅት ተናግራለች። “እኔም ከእርሱ ጋር መሄድ ስለነበረብኝ ለሌሎች ልጆቼ ብዬ መሄድ አልቻልኩም። በዚህ ምክንያት ይህ ዕድል አመለጠው። ለሌሎቹ በማሰብ ነው እዚህ የቀረሁት” ትላለች። ነገር ግን አረን፣ በአሁኑ ወቅት ለጎልዌይ ከተማ ስለሚጫወት “አሁንም ዕድል አለው ብዬ አምናለሁ” ስትል ተስፋዋን ተናግራለች። የጋብርኤል እህት ኢቭ ዶሰን ደግሞ 17 ዓመቷ ሲሆን፣ በእግር ኳስ ለአየርላንድ ከ19 ዓመት በታች የእግር ኳስ ቡድን ተመርጣለች። አንድ የስኮትላንድ እግር ኳስ ቡድን ሊያስፈርማት ጠይቋት የነበረ ሲሆን፣ ትምህርቷን መጨረስ እንዳለባት ቤተሰቡ በመወሰኑ እናቷ ወደ ስኮትላንድ እንዳትሄድ እንደከለከለቻት ለቢቢሲ ተናግራለች። እናታቸው ምሥራቅ ልጆቿ ለስፖርት ስላላቸው ፍቅር ስትጠየቅ፣ “በአንድ ሳምንት ሰባቱንም ቀን መኪና ውስጥ ነው ውለን የምናድረው፣ መኪናችንን እንደ ቤት ነው የምንጠቀመው፣ ቀን ቀን ትምህርት ቤት ይውላሉ። አድርሼያቸሁ እመልሳቸዋለሁ። “ከዚያ በኋላ ደግሞ ለሥልጠና ወደ ተለያዩ ቦታዎች አደርሳቸዋለሁ። በየሁለት ሳምንቱ ደግሞ ወደ ተለያዩ ቦታዎች እወስዳቸዋለሁ። እኔ ደግሞ እነርሱን ለማሳደግ እና ለማስተማር ሥራ እሰራለሁ። ሕይወታችን ይህንን ነው የሚመስለው” ትላለች። ጋብርኤል እዚህ ስኬት ላይ ለመድረስ ከ10 ዓመት በላይ ወስዶበታል። አሁን የልፋቱን ውጤት በማየታቸው ቤተሰቡ ደስተኞች ናቸው። ጋቢ ከአርሜኒያ ወርቅ አሸንፎ ወደ አየርላንድ ሲመለስ ቤተሰቦቹ እና የእግር ኳስ ቡድኑ ደማቅ አቀባበል አድርጎለታል። ይህ ግን ለእናቱ ምሥራቅ ተስፋዬ ስሜት የሚበርዝ ነበር። ኢትዮጵያ ወገኖቹ መካከል ቢሆን ይሄኔ ደስታውና ሆታው የተለየ ነበር ስትል አስባ እንደ ከፋት ለቢቢሲ ተናግራለች። እናት ምሥራቅ ለላለፉት 11 ዓመታት ልጆቿን ብቻዋን ማሳደጓን ትናገራለች። “የልጆቼን ሕልም ለማሳካት ቀንና ሌሊት ነው የምሰራው። አንዳንዴ ማሽን አልያም ሰው መሆኔን እጠራጠራለሁ፤ እራስ ደካማ ሆኖ ልጆችን በርቱ ማለት አይቻልም። ሰርቶ ለልጆችህ ማሳየት ያስፈልጋል።” ከአየርላንድ ምንም እርዳታ እንደሌላት የምትናገረው ምሥራቅ፣ ከፍተኛ ሥራ ዕድል ስላለ ሰርታ ያሰበችው ደረጃ መድረስ እንደምትችል ትናገራለች። ጋብርኤል ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ የእናቱን የትውልድ ስፍራ ማየት ሕልሙ ነው። “የእናቴ ትውልድ ቦታ ሐረጌ ስለሆነ አንድ ቀን ሄጄ ብጎበኝ ብዬ አስባለሁ።” ጋብርኤል በቶኪዮ ኦሊምፒክ በቦክስ ውደድድር ለመሳተፍ እየተዘጋጀ ሳለ በደረሰበት ጉዳት የተነሳ ሳይሳካለት ቀርቷል። ቀጣዩ የኦሊምፒክ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ግን ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ለቢቢሲ ገልጿል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cpdn44d94klo |
3politics
| ተቃዋሚዎች 'ስላቅ' ነው ያሉት ምርጫ በሶሪያ እየተካሄደ ነው | በሶሪያ በመንግሥት ቁጥጥር ስር ባሉ አካባቢዎች ላይ እየተደረገ ባለው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በሽር አል አሳድ ለ4ኛ ጊዜ ለ7 የስልጣን ዓመታት ለመምራት አሸናፊ እንደሚሆኑ እርግጥ እየሆነ ነው። የፕሬዝዳንት አሳድ ተፎካካሪዎች ሆነው የቀረቡት ብዙም የማይታወቁ አብደላ ሳልሙንና ማህመድ አህመድ የተባሉ ፓለቲከኞች ናቸው። ምርጫው ከተካሄደባቸው በመንግሥት ቁጥጥር ስር ያሉ አካባቢዎችን የተቆጣጠሩ ተቃዋሚዎች ምርጫውን ቀልድ ነው ያሉት ሲሆን የአሜሪካና አውሮፓ ፓለቲከኞች ደግሞ ፍትሀዊና ነፃ ያልሆነ ምርጫ ነው ሲሉ ገልፀዋል። ፕሬዝዳንት አሳድ ድምፃቸውን በሰጡበት ወቅት በሰነዘሩት አስተያየት የምዕራባውያን አስተያየት "ዜሮ" ተብሎ ተቆጠረ ብለዋል። በአውሮፓውያኑ የዘመን ስሌት በ2011 ዲሞክራሲን እንፈልጋለን ያሉ ተቃዋሚዎች ላይ የበሽር አል አሳድ መንግስት የኃይል እርምጃ መውሰዱን ተከትሎ የተቀሰቀሰ ግጭት 10 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን ሶሪያን 'እንዳልነበረች' አድርጓታል። የ55 ዓመቱ በሽር አል አሳድ እንደ አውሮፓውያኑ 2000 ላይ ነበር ከሩብ ምዕተ ዓመት ለሚልቅ ጊዜ ሀገሪቱን የመሩትን አባታቸውን ተክተው ፕሬዝዳንት የሆኑት። ከሰባት ዓመታት በፊት ሀገሪቱ በግጭት ውስጥ ሆናና ተቃዋሚዎች ለመሳተፍ ባልተስማሙበት ምርጫ ፕሬዝዳንት አሳድ 88 በመቶ የሚሆነውን ድምፅ በማሸነፍ ለ3 ጊዜ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠው ነበር። | ተቃዋሚዎች 'ስላቅ' ነው ያሉት ምርጫ በሶሪያ እየተካሄደ ነው በሶሪያ በመንግሥት ቁጥጥር ስር ባሉ አካባቢዎች ላይ እየተደረገ ባለው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በሽር አል አሳድ ለ4ኛ ጊዜ ለ7 የስልጣን ዓመታት ለመምራት አሸናፊ እንደሚሆኑ እርግጥ እየሆነ ነው። የፕሬዝዳንት አሳድ ተፎካካሪዎች ሆነው የቀረቡት ብዙም የማይታወቁ አብደላ ሳልሙንና ማህመድ አህመድ የተባሉ ፓለቲከኞች ናቸው። ምርጫው ከተካሄደባቸው በመንግሥት ቁጥጥር ስር ያሉ አካባቢዎችን የተቆጣጠሩ ተቃዋሚዎች ምርጫውን ቀልድ ነው ያሉት ሲሆን የአሜሪካና አውሮፓ ፓለቲከኞች ደግሞ ፍትሀዊና ነፃ ያልሆነ ምርጫ ነው ሲሉ ገልፀዋል። ፕሬዝዳንት አሳድ ድምፃቸውን በሰጡበት ወቅት በሰነዘሩት አስተያየት የምዕራባውያን አስተያየት "ዜሮ" ተብሎ ተቆጠረ ብለዋል። በአውሮፓውያኑ የዘመን ስሌት በ2011 ዲሞክራሲን እንፈልጋለን ያሉ ተቃዋሚዎች ላይ የበሽር አል አሳድ መንግስት የኃይል እርምጃ መውሰዱን ተከትሎ የተቀሰቀሰ ግጭት 10 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን ሶሪያን 'እንዳልነበረች' አድርጓታል። የ55 ዓመቱ በሽር አል አሳድ እንደ አውሮፓውያኑ 2000 ላይ ነበር ከሩብ ምዕተ ዓመት ለሚልቅ ጊዜ ሀገሪቱን የመሩትን አባታቸውን ተክተው ፕሬዝዳንት የሆኑት። ከሰባት ዓመታት በፊት ሀገሪቱ በግጭት ውስጥ ሆናና ተቃዋሚዎች ለመሳተፍ ባልተስማሙበት ምርጫ ፕሬዝዳንት አሳድ 88 በመቶ የሚሆነውን ድምፅ በማሸነፍ ለ3 ጊዜ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠው ነበር። | https://www.bbc.com/amharic/news-57264684 |
3politics
| የተመሠረተው አዲሱ መንግሥት ከከዚህ ቀደሞቹ በምን ይለያል? | ዛሬ ሰኞ መስከረም 24/2014 ዓ.ም አዲሱ የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሥራውን በመጀመር ለቀጣይ አምስት ዓመታት አገሪቱን በጠቅላይ ሚኒስትርነት የሚመራውን ግለሰብ ይሰይማል። ይህንንም ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራው የሥራ አስፈጻሚ መዋቅርና በካቢኔው ውስጥ ሆነው በሚኒስትርነት የሚያገለግሉ ዕጩዎችን በምክር ቤቱ አስሹሞ በይፋ ሥራውን ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል። ባለፈው ዓመት ሰኔ 14 በተካሄደው ምርጫ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሊቀመንበርነት የሚመራው የብልጽግና ፓርቲ ምርጫው በተካሄደባቸው አከባቢዎች ከፍተኛ የበላይነትን በፌደራልና በክልል ምክር ቤቶች ውስጥ ለማግኘት ችሏል። ይህም ለጠቅላይ ሚኒስትሩና ለፓርቲያቸው ተጨማሪ አምስት የሥልጣን ዘመናትን የሚጨምር ሲሆን፤ ዛሬ ሥራውን በሚጀምረው ምክር ቤት ውስጥም ይኸው ይንጸባረቃል ተብሎ ይጠበቃል። በሁለት ዙር ተከፍሎ በተካሄደው ምርጫ ውስጥ ሰኔ 14/2013 ዓ.ም የተደረገው የመጀመሪያው ዙር በአብዛኞቹ የአገሪቱ ከፍሎች ድምጽ የተሰጠበትና ውጤቱም የታውቆ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት አዲሱን አስተዳደር ዛሬ ይመሰርታሉ። ባለፈው ሳምንት የተካሄደው ሁለተኛው ዙር የምርጫ ውጤት በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጸድቆ ይፋ ባይደረግም፤ ቀደም ባለው ምርጫ አብዛኞቹ የምክር ቤት መቀመጫዎች ውጤት በመታወቁ በሕጉ መሠረት በመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት አዲሱ መንግሥት ይመሰረታል። ዛሬ የመጀመሪያ ጉባኤውን የሚያካሂደው ስደስተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካሉት 547 መቀመጫዎች ውስጥ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፓርቲ 410 ወንበሮችን እንዳሸነፈ ይፋ መደረጉ ይታወሳል። ባለፉት ሁለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዘመናት ገዢው ኢህአዴግ ከ547ቱ መቀመጫዎች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ሁኔታ ፓርላመውን ተቆጣጥሮት እንደነበር ይታወሳል። ምርጫው ዘግይቶ በተካሄደባቸው ክልሎችና አካባቢዎች የሚገኘው ውጤት ገና የሚታወቅ ቢሆንም፤ ምንም እንኳን የተጠበቀውን ያህል ባይሆንም በተወሰነ ደረጃ ተቃዋሚዎችና የግል ዕጩዎች ምክር ቤቱን ተቀላቅለዋል። በአዲሱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ ብልጽግና ፓርቲ ግልጽ የበላይነትን በመያዝ አብዛኛውን መቀመጫ ይያዝ እንጂ፤ አሁን ባለው መረጃ መሠረት 11 መቀመጫዎችን የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ሲያሸንፉ፣ አራት መቀመጫዎች ደግሞ በግል በተወዳደሩ ዕጩዎች ተይዘዋል። በምርጫው ከተሳተፉት 47 ተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ሦስቱ አስራ አንድ መቀመጫዎችን ያገኙ ሲሆን እነሱም የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) 5፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) 4 እና የጌዲዮ ሕዝብ ዴሞክራሲኣዊ ድርጅት (ጌህዴድ) 2 መቀመጫዎችን አግኝተዋል። በተጨማሪም በግል ቀርበው ከተወዳደሩት 125 በዕጩነት መካከል አራቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውክልናን አግኝተዋል። እነዚህም የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ የኦነግ ቀደምት መስራቾችና አባላት የነበሩት አቶ ዲማ ነገዎና አቶ ገላሳ ዲልቦ እንዲሁም ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ናቸው። ምርጫው ዘግይቶ በተደረገባቸው የሶማሌና የሐረሪ ክልሎች አጠቃላይ ውጤት ገና ባለመታወቁ በአዲሱ ምክር ቤት ምስረታ ላይ እንደራሴዎቻቸው አይገኙም። እንዲሁም ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር ጦርነት በተቀሰቀሰበት ትግራይ ክልል ውስጥ ምርጫው ባለመካሄዱ የክልሉ 38 ውክልናዎች ባዷቸውን ይቆያሉ። ዛሬ በሚመሰረተው ምክር ቤት ውስጥ ከፍተኛውን የበላይነት የያዘው የብልጽግና ፓርቲ ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚኒስትሩን ይሰይማል። በዚህም መሠረት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጠቅላይ ሚኒስትርነት ሥልጣን ላይ እንደሚቆዩ ይጠበቃል። ከዚህ በተጨማሪ ባለፈው ሳምንት አስተዳደራቸውን የመሰረቱት ክልሎች ላይ እንደተስተዋለው በአዲሱ የፌደራል መንግሥቱ ካቢኔ ውስጥ ተቃዋሚዎች ቦታ እንደሚያገኙ ይጠበቃል። በኦሮሚያ፣ በአዲስ አበባ፣ በአማራና በደቡብ ምክር ቤቶች ምስረታ ወቅት እንደታየው በተወሰነ ደረጃ ተቃዋሚዎች ሥልጣን እንዲጋሩ ተደርገዋል። ቀደም ሲል ብልጽግና ፓርቲ ሲል እንደነበረው አዲስ በሚመሰረተው ካቢኔ ውስጥ ተቃዋሚዎች ሊካተቱ ይችላሉ። አንዳንዶች እንደሚገምትቱም ብልጽግና ከተቃዋሚ ፓርቲዎችም ሆነ በግል ከሚሳተፉ ግለሰቦች መካከል ጉልህ የሚባሉ የሥልጣን ቦታዎችን ሊያጋራ ይችላል። ከእነዚህ መካከልም በምርጫው ከፍ ያለ ውጤትን ያገኛል ተብሎ የተጠበቀው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ከፍተኛ ግምት ተሰጠው ተቃዋሚ ነው። ከመንግሥት ምስረታው ቀናት ቀደም ብሎ ጉባኤውን ያካሄደው ኢዜማ ከብልጽግና ፓርቲ አብሮ የመስራት ጥያቄ እንደቀረበለት የገለጸ ሲሆን፤ ይህንንም ጥያቄ ተወያይቶበት መቀበሉን አሳውቋል። ምናልባትም ይህ ጥያቄ በፓርቲው ውስጥ ካሉ ፖለቲከኞች መካከል መሪውን ጨምሮ አንዳንዶቹን በፌደራል መንግሥቱ የተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ለመሾም ዕድል ሳይፈጥር እንደማይቀር ተገምቷል። በተመሳሳይም በግል ተወዳድረው የምክር ቤት መቀመጫዎችን ካገኙት እንደራሴዎች መካከልም በአዲሱ መንግሥት ካቢኔ እና በሌሎች የሥልጣን ቦታዎች ላይ ሊመደቡ የሚችሉበት ዕድልም አለ። ይህ ሁሉ የሚሆነው ዛሬ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተሰብስቦ ከአባላቱ መካከል ቀጣዩን ጠቅላይ ሚኒስትር ከሰየመ በኋላ የተለያዩ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችን የሚመሩ ሚኒስትሮችን አቅርቦ ይሁንታን ሲያገኝ ነው። በምክር ቤቱ የሚመረጠው ጠቅላይ ሚኒስትር አገሪቱ አሁን ያለችበትን ሁኔታ እንዲሁም በቀጣይ አምስት ዓመታት የሚያከናውናቸውን ዋነኛ ተግባራቱን በተመለከተ ንግግር ያደርጋል። ዛሬ የሚመሰረተው አዲሱ የፌደራል አስተዳደር ከዚህ ቀደም ከነበሩት የተለየ የሚያደርገው ሥነ ሥርዓት እንደሚኖር እየተነገረ ነው። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ ከሚካሄደው የመጀመሪያው የእንደራወሴዎች ስብሰባ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር መሰየምና የካቢኔ ሚኒስትሮች ሹመት በኋላ በመስቀል አደባባይ ሌላ ዝግጅት እንዳለ የአገር ውስጥ መገኛኛ ብዙኃን እየዘገቡ ነው። ከዚሁ ጋር ተያይዞም በአዲሱ መንግሥት ምስረታ ላይ ለመታደም የውጪ አገራት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ወደ አዲስ አበባ እየገቡ መሆናቸውን ከቅዳሜ ጀምሮ እየተነገረ ነው። | የተመሠረተው አዲሱ መንግሥት ከከዚህ ቀደሞቹ በምን ይለያል? ዛሬ ሰኞ መስከረም 24/2014 ዓ.ም አዲሱ የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሥራውን በመጀመር ለቀጣይ አምስት ዓመታት አገሪቱን በጠቅላይ ሚኒስትርነት የሚመራውን ግለሰብ ይሰይማል። ይህንንም ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራው የሥራ አስፈጻሚ መዋቅርና በካቢኔው ውስጥ ሆነው በሚኒስትርነት የሚያገለግሉ ዕጩዎችን በምክር ቤቱ አስሹሞ በይፋ ሥራውን ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል። ባለፈው ዓመት ሰኔ 14 በተካሄደው ምርጫ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሊቀመንበርነት የሚመራው የብልጽግና ፓርቲ ምርጫው በተካሄደባቸው አከባቢዎች ከፍተኛ የበላይነትን በፌደራልና በክልል ምክር ቤቶች ውስጥ ለማግኘት ችሏል። ይህም ለጠቅላይ ሚኒስትሩና ለፓርቲያቸው ተጨማሪ አምስት የሥልጣን ዘመናትን የሚጨምር ሲሆን፤ ዛሬ ሥራውን በሚጀምረው ምክር ቤት ውስጥም ይኸው ይንጸባረቃል ተብሎ ይጠበቃል። በሁለት ዙር ተከፍሎ በተካሄደው ምርጫ ውስጥ ሰኔ 14/2013 ዓ.ም የተደረገው የመጀመሪያው ዙር በአብዛኞቹ የአገሪቱ ከፍሎች ድምጽ የተሰጠበትና ውጤቱም የታውቆ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት አዲሱን አስተዳደር ዛሬ ይመሰርታሉ። ባለፈው ሳምንት የተካሄደው ሁለተኛው ዙር የምርጫ ውጤት በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጸድቆ ይፋ ባይደረግም፤ ቀደም ባለው ምርጫ አብዛኞቹ የምክር ቤት መቀመጫዎች ውጤት በመታወቁ በሕጉ መሠረት በመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት አዲሱ መንግሥት ይመሰረታል። ዛሬ የመጀመሪያ ጉባኤውን የሚያካሂደው ስደስተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካሉት 547 መቀመጫዎች ውስጥ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፓርቲ 410 ወንበሮችን እንዳሸነፈ ይፋ መደረጉ ይታወሳል። ባለፉት ሁለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዘመናት ገዢው ኢህአዴግ ከ547ቱ መቀመጫዎች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ሁኔታ ፓርላመውን ተቆጣጥሮት እንደነበር ይታወሳል። ምርጫው ዘግይቶ በተካሄደባቸው ክልሎችና አካባቢዎች የሚገኘው ውጤት ገና የሚታወቅ ቢሆንም፤ ምንም እንኳን የተጠበቀውን ያህል ባይሆንም በተወሰነ ደረጃ ተቃዋሚዎችና የግል ዕጩዎች ምክር ቤቱን ተቀላቅለዋል። በአዲሱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ ብልጽግና ፓርቲ ግልጽ የበላይነትን በመያዝ አብዛኛውን መቀመጫ ይያዝ እንጂ፤ አሁን ባለው መረጃ መሠረት 11 መቀመጫዎችን የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ሲያሸንፉ፣ አራት መቀመጫዎች ደግሞ በግል በተወዳደሩ ዕጩዎች ተይዘዋል። በምርጫው ከተሳተፉት 47 ተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ሦስቱ አስራ አንድ መቀመጫዎችን ያገኙ ሲሆን እነሱም የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) 5፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) 4 እና የጌዲዮ ሕዝብ ዴሞክራሲኣዊ ድርጅት (ጌህዴድ) 2 መቀመጫዎችን አግኝተዋል። በተጨማሪም በግል ቀርበው ከተወዳደሩት 125 በዕጩነት መካከል አራቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውክልናን አግኝተዋል። እነዚህም የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ የኦነግ ቀደምት መስራቾችና አባላት የነበሩት አቶ ዲማ ነገዎና አቶ ገላሳ ዲልቦ እንዲሁም ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ናቸው። ምርጫው ዘግይቶ በተደረገባቸው የሶማሌና የሐረሪ ክልሎች አጠቃላይ ውጤት ገና ባለመታወቁ በአዲሱ ምክር ቤት ምስረታ ላይ እንደራሴዎቻቸው አይገኙም። እንዲሁም ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር ጦርነት በተቀሰቀሰበት ትግራይ ክልል ውስጥ ምርጫው ባለመካሄዱ የክልሉ 38 ውክልናዎች ባዷቸውን ይቆያሉ። ዛሬ በሚመሰረተው ምክር ቤት ውስጥ ከፍተኛውን የበላይነት የያዘው የብልጽግና ፓርቲ ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚኒስትሩን ይሰይማል። በዚህም መሠረት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጠቅላይ ሚኒስትርነት ሥልጣን ላይ እንደሚቆዩ ይጠበቃል። ከዚህ በተጨማሪ ባለፈው ሳምንት አስተዳደራቸውን የመሰረቱት ክልሎች ላይ እንደተስተዋለው በአዲሱ የፌደራል መንግሥቱ ካቢኔ ውስጥ ተቃዋሚዎች ቦታ እንደሚያገኙ ይጠበቃል። በኦሮሚያ፣ በአዲስ አበባ፣ በአማራና በደቡብ ምክር ቤቶች ምስረታ ወቅት እንደታየው በተወሰነ ደረጃ ተቃዋሚዎች ሥልጣን እንዲጋሩ ተደርገዋል። ቀደም ሲል ብልጽግና ፓርቲ ሲል እንደነበረው አዲስ በሚመሰረተው ካቢኔ ውስጥ ተቃዋሚዎች ሊካተቱ ይችላሉ። አንዳንዶች እንደሚገምትቱም ብልጽግና ከተቃዋሚ ፓርቲዎችም ሆነ በግል ከሚሳተፉ ግለሰቦች መካከል ጉልህ የሚባሉ የሥልጣን ቦታዎችን ሊያጋራ ይችላል። ከእነዚህ መካከልም በምርጫው ከፍ ያለ ውጤትን ያገኛል ተብሎ የተጠበቀው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ከፍተኛ ግምት ተሰጠው ተቃዋሚ ነው። ከመንግሥት ምስረታው ቀናት ቀደም ብሎ ጉባኤውን ያካሄደው ኢዜማ ከብልጽግና ፓርቲ አብሮ የመስራት ጥያቄ እንደቀረበለት የገለጸ ሲሆን፤ ይህንንም ጥያቄ ተወያይቶበት መቀበሉን አሳውቋል። ምናልባትም ይህ ጥያቄ በፓርቲው ውስጥ ካሉ ፖለቲከኞች መካከል መሪውን ጨምሮ አንዳንዶቹን በፌደራል መንግሥቱ የተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ለመሾም ዕድል ሳይፈጥር እንደማይቀር ተገምቷል። በተመሳሳይም በግል ተወዳድረው የምክር ቤት መቀመጫዎችን ካገኙት እንደራሴዎች መካከልም በአዲሱ መንግሥት ካቢኔ እና በሌሎች የሥልጣን ቦታዎች ላይ ሊመደቡ የሚችሉበት ዕድልም አለ። ይህ ሁሉ የሚሆነው ዛሬ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተሰብስቦ ከአባላቱ መካከል ቀጣዩን ጠቅላይ ሚኒስትር ከሰየመ በኋላ የተለያዩ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችን የሚመሩ ሚኒስትሮችን አቅርቦ ይሁንታን ሲያገኝ ነው። በምክር ቤቱ የሚመረጠው ጠቅላይ ሚኒስትር አገሪቱ አሁን ያለችበትን ሁኔታ እንዲሁም በቀጣይ አምስት ዓመታት የሚያከናውናቸውን ዋነኛ ተግባራቱን በተመለከተ ንግግር ያደርጋል። ዛሬ የሚመሰረተው አዲሱ የፌደራል አስተዳደር ከዚህ ቀደም ከነበሩት የተለየ የሚያደርገው ሥነ ሥርዓት እንደሚኖር እየተነገረ ነው። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ ከሚካሄደው የመጀመሪያው የእንደራወሴዎች ስብሰባ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር መሰየምና የካቢኔ ሚኒስትሮች ሹመት በኋላ በመስቀል አደባባይ ሌላ ዝግጅት እንዳለ የአገር ውስጥ መገኛኛ ብዙኃን እየዘገቡ ነው። ከዚሁ ጋር ተያይዞም በአዲሱ መንግሥት ምስረታ ላይ ለመታደም የውጪ አገራት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ወደ አዲስ አበባ እየገቡ መሆናቸውን ከቅዳሜ ጀምሮ እየተነገረ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/news-58756172 |
0business
| ሎተሪ በአንድ ጀንበር ሚሊዬነር ያደረጋቸው ሰዎች ምን አሉ? | ይበለውና ዛሬ ድንገት ዝሆን ሎተሪ ቢደርስዎ ምን ያደርጉበታል? የሀብታሞች አገሮቹ ዝሆን ሎቶሪ። ምናልባት እንደ ዝሆን ጎምለል እያሉ ዓለምን ይዞሩ ይሆናል። ምናልባት ቀሪ ሕይወትዎን በተድላ ይመሩ ይሆናል። ምናልባት ከዚያ በኋላ በደስታ ሕንድ ውቅያኖስ ጠልቀው በሐሴት ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ብቅ የሚሉ ይመስልዎት ይሆናል። ነገሩ እንደዚያ ላይሆን ይችላል ብለው አስበው ያውቃሉ? በዚህ ጉዳይ ላይ አንድ መናጢ ጋዜጠኛ ከሚዘባርቅ የደረሳቸው ቢናገሩት ሳይሻል አይቀርም። አዲ ጉድቻይልድ ባለፈው ዓመት የ71 ሚሊዮን ፓውንድ ሎተሪ አሸነፈ። ዩሮ ሚሊዮንስ የሚባለውን ዝሆን ሎቶሪ ነበር ያሸነፈው። ከዚህ በኋላ ጡረታ ወጥቼ ቁጭ ብዬ እበላለሁ ብሎ ነበር። ቁጭ ብሎ መብላት ደስታን የሚያመጣ ነገር እንዳልሆነ የተረዳው ግን ዘግይቶ ነው። አዲ ብቻውን አይደለም። ጄን አለች። "ሎተሪ ማሸነፌ ሕይወቴን አተራማምሶታል" ጄን ሬስቶሪክ ሎተሪ ሳይደርሳት በፊት ጄን ፓርክ ነበር ስሟ። ስሟን እንድትቀይር ብቻም ሳይሆን ሕይወቷም እንዲቀየር ያደረጋትን ሎተሪ ያሸነፈችው የዛሬ 4 ዓመት ግድም ነበር። በብሪታኒያ ታሪክ ሎተሪን በማሸነፍ ልጅ አግሯ እሷ ናት፤ ጄን። ሎተሪው ሲደርሳት የሆነ አስተዳደር ቢሮ ውስጥ ትንሽዬ ሥራ ነበረቻት። በኤደንብራ በትንሽዬ አፓርታማ ውስጥ ከእናቷ ጋር ትኖር ነበር። ጄን አንድ ሚሊዮን ዶላር ሎተሪው እንደደረሳት በፌስቡክ አወጀች። ከዜናው ጋር የመደነቅ ኢሞጂ የሚሉትን (እኛ ለዚህ የሎቶሪ አዝናኝ ታሪክ ደቂቀ ገጽታ ብለን የምንጠራውን የማኅበራዊ ሚዲያ አሻንጉሊት ሳቅ) አስከተለች። መጀመሪያ ያደረገችው ውድ የቺኋሄ ቡችላ ዝርያን (Chihuahua dog) የሳሎን ውሻ መግዛት ነበር። ፕሪንሰስ ብላ ጠራቻት። ከዚያ ውድ የንግድ ስም ያለውን አንድ ቦርሳ መግዛት ህልሟ ነበር። እንዳሰበችውም የሉዊ ቪቶ (Louis Vuitton) ቅንጡ ፋሽን የእጅ ቦርሳ ገዛች። በእነዚህ ሁለት ወጪዎች ብቻ 10 ሺህ ፓውንዶች እልም ብለው ሄዱ። ከዚያ በኋላ ግን ግራ ገባት። ሕይወቴ እላዬ ላይ ሲፈርስ ነበር የሚታየኝ ብላለች ከሦሰት ዓመት በፊት በሰጠችው አንድ ቃለ ምልልስ። በየቀኑ ስነሳ የማስበው ከገንዘብ ጋር የተያያዘ ነገር ነበር። ያ ስሜት ደስ አይልም ትላለች። ይህን ሐሳቧን ከአእምሮዋ ማውጣት ግን አልቻለችም። "ምነው ይሄ ሎተሪ ጭራሽ ባልደረሰኝ" ብላ እስከመመኘት ደርሳም ነበር። የአንድ ሚሊዮን ፓውንድ ሎተሪ ለ17 ዓመት ልጅ አደገኛ ነገር ነው። ይሄ ምንም አጠራጣሪ አይደለም። "ምን ማድረግ ነው ትክክል የሚለውን ነገር የሚመራኝ ሰው አልነበረም" ትላለች። ሎተሪው ከደረሳት በኋላ ወዳጅ ዘመዶቿ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ዓይን ዓይኗን ማየት ጀመሩ። ይቺ ልጅ "የገንዘብ ችግራችንን የምትቀርፍልን" በሚል መነጽር ብቻ ያይዋት ጀመረ። "ሰዎች እኔን የሚፈልጉኝ ከሎተሪ ገንዘቡ ጋር በተያያዘ ብቻ መሆኑን ስረዳ ጭንቀት ውስጥ ገባሁ" ትላለች። የሎተሪው ድርጅት ኃላፊ ካሜሎት በበኩላቸው "ለልጅቷ የሥነ ልቦና ደጋፍ ብቻም ሳይሆን ገንዘቧን እንዴት ማስተዳደር እንዳለባት የሚያማክራት ሰው በነጻ አቅርበንላት ነበር" ሲሉ ጥፋቱ ከእነሱ እንዳልሆነ ያስረዳሉ። "ሚሊየነር ብሆንም ሥራዬን እወደዋለሁ" ሱ ሪቻርድስ በ2016 ወደ ቤት እየሄደች ነበር። እግረ መንገዷን ሱፐር ማርኬት ገብታ ፈጣን ሎተሪ ገዛች። ነገሩን ከቁብም አልቆጠረችውም ነበር። እንደጨዋታ ነበር የገዛችው። ቤት ገብታ ፋቀችው። 3 ሚሊዮን ፓውንድ አሸናፊ አደረጋት። ደስታዋ ወደር አልነበረምው። ከባሏ ጋር ወደ ኢሴክስ ከተማ ሄደው ቤት ገዙ። አራት መኪኖችን እላዩ ላይ መረቁበት። ከዚያ በኋላ ደግሞ ዓለምን ዞር ዞር ብለው ማየት ጀመሩ። ለልጆቻቸውም የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ አሟሉ። ባለፈው ዓመት ሚስ ሪቻርድ ከባለቤቷ ጋር ሆና ሎተሪ ያሸነፉበትን አራተኛ ዓመት አከበሩ። የቤታቸው ግቢ አፀድ ውስጥ በርከት ያለ ብር አውጥተው በሻምፓኝ ነበር ያከበሩት። ሚስ ሪቻርድስ ሚሊየነር ብትሆንም ቅሉ በሳምንት 90 ሰዓት አዛውንት ተንከባካቢ ሆና ትሰራለች። ምን በወጣሽ ትለፊያለሽ? ስትባል "ሥራዬን እወደዋለሁ" ነው መልሷ። ምናልባት ከሚሊዮን ዶላሩ ባሻገር የደስታዋ ምንጭ ሥራዋ ሳይሆን አልቀረም። "ሚሊየነር መሆን ያን ያህልም አልደነቀኝም" በታኅሣስ 2017 ሜሊሳ ኤድ ወደ ሐል ነዳጅ ማደያ ገባች። እሷም እንዲሁ የሚፋቅ ሎተሪ ገዛች። ፈጣኑን። በሦስተኛው ቀን ባንክ ደብተሯ አብጦ ሊፈነዳ ደርሶ አገኘችው። 5 ሚሊዮን ፓውንድ ገብቶበታል። "በአንድ ጀንበር የባንክ ደበተሬ ከአንደ ፓውንድ ወደ 5 ሚሊዮን ፓውንድ ተመነደገ" ብላ ነበር ለቢቢሲ። ሜሊሳ ሚሊየነር ከመሆኗ በፊት ማታ ማታ የታክሲ ሾፌር ነበረች። ቤሳ ቤስቲን አልነበራትም። "ሕይወት በጣም ፈተና ሆናብኝ ነበር። አንዳንድ ጊዜ ገንዘብ ስለማይኖረኝ እራት እንኳን የማልበላበት ጊዜ ነበር" ትለላች። ካሸነፈች በኋላ 3 ሚሊዮን ፓውንዱን ኢንቨስት አደረገችው። ቤት ገዛች። የቤተሰቧንና የጓደኞቿን እዳቸውን ከፋፈለች። ሕይወታቸውን ለወጠች። ይህን ሁሉ አሳክታም እንዲህ ትላለች። "ሰዎች ሎተሪ ሁሉን ነገር የሚቀይር ይመስላቸዋል። ያን ያህልም የሚያስደንቅ ነገር አይደለም። ከጊዜ በኋላ ሁሉም ነገር ወደነበረበት ይመለሳል" ትላለች። "ብዙ ሰዎቸ ገንዘብ ሁሉንም ችግር የሚቀርፍ ይመስላቸዋል። ውሸት ነው። ሚሊየነር መሆን ደስተኛ መሆን ማለት እንዳልሆነ እኔ ህያው ምስክር ነኝ" ብላ ነበር ለቢቢሲ። "በኬክ ላይ የተንሸራተትኩ ያህል ተሰማኝ" ሪቻርድና ካቲ ብራውን ጋዜጠኞች ነበሩ። ሳያስቡት 6 ሚሊዮን ፓውንድ አሸነፉ። ለነገሩ ሎተሪ ማን አስቦት አሸንፎ ያውቃል። እነ ሪቻርድ ወዲያውኑ ዓለምን መዞር ጀመሩ። በበረዶ ወደተሸፈነው የአንታርክታካ አህጉር ሄደው በረዶ ሸርተቴ ተጫውተዋል። ህልማቸውም እሱ ነበር። "በኬክ ላይ የመንሸራተት ያህል ነው" ይላሉ የሕይወታቸውን መቃናት ሲያሰምሩበት። ባልና ሚስቱ አሁን ጡረታ ወጥተዋል። በሰሜን ዋልታ በባህር ቀዘፋ እየተጫወቱ ዓመቱን ሙሉ ሽር ብትን እያሉ ለማሳለፍ ነው ያቀዱት። "በሎተሪ ያገኘነው ገንዘብ በሕይወታችን ከሚያስፈልገን የገንዘብ መጠን እጅግ የበዛ ነው። ስለዚህ በተቻለ መጠን ቤተሰባችን ከእኛ መልካም ዕድል ተጋሪ ማድረግ ነው የምንሻው" ብለዋል ለቢቢሲ። ሚሊየነር መሆን የገንዘብ ችግርን ይቀርፍ ይሆናል እንጂ በራሱ የደስታ ምንጭ እንዳልሆነ ግን ያሰምሩበታል። ባልና ሚስቱ። | ሎተሪ በአንድ ጀንበር ሚሊዬነር ያደረጋቸው ሰዎች ምን አሉ? ይበለውና ዛሬ ድንገት ዝሆን ሎተሪ ቢደርስዎ ምን ያደርጉበታል? የሀብታሞች አገሮቹ ዝሆን ሎቶሪ። ምናልባት እንደ ዝሆን ጎምለል እያሉ ዓለምን ይዞሩ ይሆናል። ምናልባት ቀሪ ሕይወትዎን በተድላ ይመሩ ይሆናል። ምናልባት ከዚያ በኋላ በደስታ ሕንድ ውቅያኖስ ጠልቀው በሐሴት ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ብቅ የሚሉ ይመስልዎት ይሆናል። ነገሩ እንደዚያ ላይሆን ይችላል ብለው አስበው ያውቃሉ? በዚህ ጉዳይ ላይ አንድ መናጢ ጋዜጠኛ ከሚዘባርቅ የደረሳቸው ቢናገሩት ሳይሻል አይቀርም። አዲ ጉድቻይልድ ባለፈው ዓመት የ71 ሚሊዮን ፓውንድ ሎተሪ አሸነፈ። ዩሮ ሚሊዮንስ የሚባለውን ዝሆን ሎቶሪ ነበር ያሸነፈው። ከዚህ በኋላ ጡረታ ወጥቼ ቁጭ ብዬ እበላለሁ ብሎ ነበር። ቁጭ ብሎ መብላት ደስታን የሚያመጣ ነገር እንዳልሆነ የተረዳው ግን ዘግይቶ ነው። አዲ ብቻውን አይደለም። ጄን አለች። "ሎተሪ ማሸነፌ ሕይወቴን አተራማምሶታል" ጄን ሬስቶሪክ ሎተሪ ሳይደርሳት በፊት ጄን ፓርክ ነበር ስሟ። ስሟን እንድትቀይር ብቻም ሳይሆን ሕይወቷም እንዲቀየር ያደረጋትን ሎተሪ ያሸነፈችው የዛሬ 4 ዓመት ግድም ነበር። በብሪታኒያ ታሪክ ሎተሪን በማሸነፍ ልጅ አግሯ እሷ ናት፤ ጄን። ሎተሪው ሲደርሳት የሆነ አስተዳደር ቢሮ ውስጥ ትንሽዬ ሥራ ነበረቻት። በኤደንብራ በትንሽዬ አፓርታማ ውስጥ ከእናቷ ጋር ትኖር ነበር። ጄን አንድ ሚሊዮን ዶላር ሎተሪው እንደደረሳት በፌስቡክ አወጀች። ከዜናው ጋር የመደነቅ ኢሞጂ የሚሉትን (እኛ ለዚህ የሎቶሪ አዝናኝ ታሪክ ደቂቀ ገጽታ ብለን የምንጠራውን የማኅበራዊ ሚዲያ አሻንጉሊት ሳቅ) አስከተለች። መጀመሪያ ያደረገችው ውድ የቺኋሄ ቡችላ ዝርያን (Chihuahua dog) የሳሎን ውሻ መግዛት ነበር። ፕሪንሰስ ብላ ጠራቻት። ከዚያ ውድ የንግድ ስም ያለውን አንድ ቦርሳ መግዛት ህልሟ ነበር። እንዳሰበችውም የሉዊ ቪቶ (Louis Vuitton) ቅንጡ ፋሽን የእጅ ቦርሳ ገዛች። በእነዚህ ሁለት ወጪዎች ብቻ 10 ሺህ ፓውንዶች እልም ብለው ሄዱ። ከዚያ በኋላ ግን ግራ ገባት። ሕይወቴ እላዬ ላይ ሲፈርስ ነበር የሚታየኝ ብላለች ከሦሰት ዓመት በፊት በሰጠችው አንድ ቃለ ምልልስ። በየቀኑ ስነሳ የማስበው ከገንዘብ ጋር የተያያዘ ነገር ነበር። ያ ስሜት ደስ አይልም ትላለች። ይህን ሐሳቧን ከአእምሮዋ ማውጣት ግን አልቻለችም። "ምነው ይሄ ሎተሪ ጭራሽ ባልደረሰኝ" ብላ እስከመመኘት ደርሳም ነበር። የአንድ ሚሊዮን ፓውንድ ሎተሪ ለ17 ዓመት ልጅ አደገኛ ነገር ነው። ይሄ ምንም አጠራጣሪ አይደለም። "ምን ማድረግ ነው ትክክል የሚለውን ነገር የሚመራኝ ሰው አልነበረም" ትላለች። ሎተሪው ከደረሳት በኋላ ወዳጅ ዘመዶቿ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ዓይን ዓይኗን ማየት ጀመሩ። ይቺ ልጅ "የገንዘብ ችግራችንን የምትቀርፍልን" በሚል መነጽር ብቻ ያይዋት ጀመረ። "ሰዎች እኔን የሚፈልጉኝ ከሎተሪ ገንዘቡ ጋር በተያያዘ ብቻ መሆኑን ስረዳ ጭንቀት ውስጥ ገባሁ" ትላለች። የሎተሪው ድርጅት ኃላፊ ካሜሎት በበኩላቸው "ለልጅቷ የሥነ ልቦና ደጋፍ ብቻም ሳይሆን ገንዘቧን እንዴት ማስተዳደር እንዳለባት የሚያማክራት ሰው በነጻ አቅርበንላት ነበር" ሲሉ ጥፋቱ ከእነሱ እንዳልሆነ ያስረዳሉ። "ሚሊየነር ብሆንም ሥራዬን እወደዋለሁ" ሱ ሪቻርድስ በ2016 ወደ ቤት እየሄደች ነበር። እግረ መንገዷን ሱፐር ማርኬት ገብታ ፈጣን ሎተሪ ገዛች። ነገሩን ከቁብም አልቆጠረችውም ነበር። እንደጨዋታ ነበር የገዛችው። ቤት ገብታ ፋቀችው። 3 ሚሊዮን ፓውንድ አሸናፊ አደረጋት። ደስታዋ ወደር አልነበረምው። ከባሏ ጋር ወደ ኢሴክስ ከተማ ሄደው ቤት ገዙ። አራት መኪኖችን እላዩ ላይ መረቁበት። ከዚያ በኋላ ደግሞ ዓለምን ዞር ዞር ብለው ማየት ጀመሩ። ለልጆቻቸውም የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ አሟሉ። ባለፈው ዓመት ሚስ ሪቻርድ ከባለቤቷ ጋር ሆና ሎተሪ ያሸነፉበትን አራተኛ ዓመት አከበሩ። የቤታቸው ግቢ አፀድ ውስጥ በርከት ያለ ብር አውጥተው በሻምፓኝ ነበር ያከበሩት። ሚስ ሪቻርድስ ሚሊየነር ብትሆንም ቅሉ በሳምንት 90 ሰዓት አዛውንት ተንከባካቢ ሆና ትሰራለች። ምን በወጣሽ ትለፊያለሽ? ስትባል "ሥራዬን እወደዋለሁ" ነው መልሷ። ምናልባት ከሚሊዮን ዶላሩ ባሻገር የደስታዋ ምንጭ ሥራዋ ሳይሆን አልቀረም። "ሚሊየነር መሆን ያን ያህልም አልደነቀኝም" በታኅሣስ 2017 ሜሊሳ ኤድ ወደ ሐል ነዳጅ ማደያ ገባች። እሷም እንዲሁ የሚፋቅ ሎተሪ ገዛች። ፈጣኑን። በሦስተኛው ቀን ባንክ ደብተሯ አብጦ ሊፈነዳ ደርሶ አገኘችው። 5 ሚሊዮን ፓውንድ ገብቶበታል። "በአንድ ጀንበር የባንክ ደበተሬ ከአንደ ፓውንድ ወደ 5 ሚሊዮን ፓውንድ ተመነደገ" ብላ ነበር ለቢቢሲ። ሜሊሳ ሚሊየነር ከመሆኗ በፊት ማታ ማታ የታክሲ ሾፌር ነበረች። ቤሳ ቤስቲን አልነበራትም። "ሕይወት በጣም ፈተና ሆናብኝ ነበር። አንዳንድ ጊዜ ገንዘብ ስለማይኖረኝ እራት እንኳን የማልበላበት ጊዜ ነበር" ትለላች። ካሸነፈች በኋላ 3 ሚሊዮን ፓውንዱን ኢንቨስት አደረገችው። ቤት ገዛች። የቤተሰቧንና የጓደኞቿን እዳቸውን ከፋፈለች። ሕይወታቸውን ለወጠች። ይህን ሁሉ አሳክታም እንዲህ ትላለች። "ሰዎች ሎተሪ ሁሉን ነገር የሚቀይር ይመስላቸዋል። ያን ያህልም የሚያስደንቅ ነገር አይደለም። ከጊዜ በኋላ ሁሉም ነገር ወደነበረበት ይመለሳል" ትላለች። "ብዙ ሰዎቸ ገንዘብ ሁሉንም ችግር የሚቀርፍ ይመስላቸዋል። ውሸት ነው። ሚሊየነር መሆን ደስተኛ መሆን ማለት እንዳልሆነ እኔ ህያው ምስክር ነኝ" ብላ ነበር ለቢቢሲ። "በኬክ ላይ የተንሸራተትኩ ያህል ተሰማኝ" ሪቻርድና ካቲ ብራውን ጋዜጠኞች ነበሩ። ሳያስቡት 6 ሚሊዮን ፓውንድ አሸነፉ። ለነገሩ ሎተሪ ማን አስቦት አሸንፎ ያውቃል። እነ ሪቻርድ ወዲያውኑ ዓለምን መዞር ጀመሩ። በበረዶ ወደተሸፈነው የአንታርክታካ አህጉር ሄደው በረዶ ሸርተቴ ተጫውተዋል። ህልማቸውም እሱ ነበር። "በኬክ ላይ የመንሸራተት ያህል ነው" ይላሉ የሕይወታቸውን መቃናት ሲያሰምሩበት። ባልና ሚስቱ አሁን ጡረታ ወጥተዋል። በሰሜን ዋልታ በባህር ቀዘፋ እየተጫወቱ ዓመቱን ሙሉ ሽር ብትን እያሉ ለማሳለፍ ነው ያቀዱት። "በሎተሪ ያገኘነው ገንዘብ በሕይወታችን ከሚያስፈልገን የገንዘብ መጠን እጅግ የበዛ ነው። ስለዚህ በተቻለ መጠን ቤተሰባችን ከእኛ መልካም ዕድል ተጋሪ ማድረግ ነው የምንሻው" ብለዋል ለቢቢሲ። ሚሊየነር መሆን የገንዘብ ችግርን ይቀርፍ ይሆናል እንጂ በራሱ የደስታ ምንጭ እንዳልሆነ ግን ያሰምሩበታል። ባልና ሚስቱ። | https://www.bbc.com/amharic/news-55156381 |
0business
| ሕንዳውያን የስኳር ምርት ስለተትረፈረፈ አብዝተው እንዲጠቀሙ ተነግሯቸዋል | ሕንድ በጣም የበዛ ስኳር በማምረቷ ሕዝቧ ስኳር አብዝቶ እንዲጠቀም እየመከረች ነው። የሕንድ ስኳር ምርት ማሕበር ስኳር ጤና ላይ ጉዳት ያመጣል የሚባለውን ችላ ብለው ሰዎች አብዝተው እንዲጠቀሙ መክሯል። ሕንዳውያን በአማካይ በዓመት 19 ኪሎ ግራም ስኳር ይጠቀማሉ። ይህ ደግሞ ከተቀረው ዓለም ሲነፃፀር አነስተኛ ነው። ቢሆንም ሕንድ ካላት ሕዝብ አንፃር ከፍተኛ ስኳር ተጠቃሚዋ ሃገር ናት። . ሕንዳውያን ከልጅና የልጅ ልጆቻቸው ጋር የሚኖሩት ለምንድን ነው? . ትራምፕ ስለ ሕንድ የአየር ብክለት የተናገሩት በርካቶችን አስቆጣ . የቶልስቶይ መፅሐፍ ህንዳውያን 'አክቲቪስቶች' ላይ መዘዝ አምጥቷል የሕንድ የስኳር ምርት መጠን በዚህ ዓመት በ13 በመቶ አድጎ 31 ሚሊዮን ቶን ምርት እንደሚመረት ይጠበቃል። ነገር ግን መንግሥት እንደ ሌላ ጊዜው በገፍ ለውጭ ገበያ ማቅረቡን ትቶ ለሕዝብ ሊያከፋፍል ይችላል ተብሏል። የስኳር ምርት ማሕበሩ ድረ-ገፁ ላይ ስኳር መጠቀም እንደማይጎዳ የሚጠቁም ማስታወቂያ ለቋል። ማሕበሩ ሰዎች ለሚሰሯቸው ምግቦች ሌላ ዓይነት ማጣፈጫ ከሚጠቀሙ ስኳር ቢጠቀሙ የተሻለ እንደሆነ የሚጠቁሙ ማስታወቂያዎች እየለቀቀ ነው። የሕንድ የምግብ ሚኒስቴር ሱዳንሹ ፓንዴይ የሕንድ ማሕበረሰብ ለስኳር ያለው አስተሳሰብ የተዛባ ነው ሲሉ ተደምጠዋል። እርግጥ ነው በሌሎች ሃገራት ሰዎች የስኳር አጠቃቀማቸውን እንዲያስተካክሉና ቀነስ እንዲያደርጉት ነው የሚመከሩት። ስኳር ከመጠን ላለፈ ክብደትና በተለምዶ ስኳር በሽታ ተብሎ ለሚታወቀው ዳያቢቲስ ሊያጋልጥ ይችላል ይላሉ ባለሙያዎች። የዓለም ጤና ድርጅት የተለያዩ ምግቦች ውስጥ፤ በተለይ ደግሞ ማርና የፍራፍሬ ጭማቂ ላይ የሚታከል ስኳር ለጤና አሳሳቢ ነው ይላል። ሕንድ ውስጥ 50 ሚሊዮን ገደማ ገበሬዎች ሸንኮራ አገዳ ያመርታሉ። ሚሊዮኖች ደግሞ ስኳር በሚያመርቱ ፋብሪካዎች ውስጥ ተቀጥረው ይሠራሉ። ሕንድ የተረፈ የስኳር ምርቷን ወደ ውጭ ለመላክ ማቀዷ በሌሎች ስኳር አምራች ሃገራት ዘንድ ቅራኔ ፈጥሯል። ሌላኛው የተረፈ የስኳር ምርትን ማስወገጃ መንገድ ወደ ኢታኖል ቀይሮ መጠቀም ነው። የሕንድ ስኳር ምርት ማሕበር የኢታኖል ምርት አሁን ካለው 1.9 ቢሊዮን ሊትር ምርት በሚቀጥለው ዓመት ወደ 3 ቢሊዮን ሊያድግ እንደሚችል ገምቷል። | ሕንዳውያን የስኳር ምርት ስለተትረፈረፈ አብዝተው እንዲጠቀሙ ተነግሯቸዋል ሕንድ በጣም የበዛ ስኳር በማምረቷ ሕዝቧ ስኳር አብዝቶ እንዲጠቀም እየመከረች ነው። የሕንድ ስኳር ምርት ማሕበር ስኳር ጤና ላይ ጉዳት ያመጣል የሚባለውን ችላ ብለው ሰዎች አብዝተው እንዲጠቀሙ መክሯል። ሕንዳውያን በአማካይ በዓመት 19 ኪሎ ግራም ስኳር ይጠቀማሉ። ይህ ደግሞ ከተቀረው ዓለም ሲነፃፀር አነስተኛ ነው። ቢሆንም ሕንድ ካላት ሕዝብ አንፃር ከፍተኛ ስኳር ተጠቃሚዋ ሃገር ናት። . ሕንዳውያን ከልጅና የልጅ ልጆቻቸው ጋር የሚኖሩት ለምንድን ነው? . ትራምፕ ስለ ሕንድ የአየር ብክለት የተናገሩት በርካቶችን አስቆጣ . የቶልስቶይ መፅሐፍ ህንዳውያን 'አክቲቪስቶች' ላይ መዘዝ አምጥቷል የሕንድ የስኳር ምርት መጠን በዚህ ዓመት በ13 በመቶ አድጎ 31 ሚሊዮን ቶን ምርት እንደሚመረት ይጠበቃል። ነገር ግን መንግሥት እንደ ሌላ ጊዜው በገፍ ለውጭ ገበያ ማቅረቡን ትቶ ለሕዝብ ሊያከፋፍል ይችላል ተብሏል። የስኳር ምርት ማሕበሩ ድረ-ገፁ ላይ ስኳር መጠቀም እንደማይጎዳ የሚጠቁም ማስታወቂያ ለቋል። ማሕበሩ ሰዎች ለሚሰሯቸው ምግቦች ሌላ ዓይነት ማጣፈጫ ከሚጠቀሙ ስኳር ቢጠቀሙ የተሻለ እንደሆነ የሚጠቁሙ ማስታወቂያዎች እየለቀቀ ነው። የሕንድ የምግብ ሚኒስቴር ሱዳንሹ ፓንዴይ የሕንድ ማሕበረሰብ ለስኳር ያለው አስተሳሰብ የተዛባ ነው ሲሉ ተደምጠዋል። እርግጥ ነው በሌሎች ሃገራት ሰዎች የስኳር አጠቃቀማቸውን እንዲያስተካክሉና ቀነስ እንዲያደርጉት ነው የሚመከሩት። ስኳር ከመጠን ላለፈ ክብደትና በተለምዶ ስኳር በሽታ ተብሎ ለሚታወቀው ዳያቢቲስ ሊያጋልጥ ይችላል ይላሉ ባለሙያዎች። የዓለም ጤና ድርጅት የተለያዩ ምግቦች ውስጥ፤ በተለይ ደግሞ ማርና የፍራፍሬ ጭማቂ ላይ የሚታከል ስኳር ለጤና አሳሳቢ ነው ይላል። ሕንድ ውስጥ 50 ሚሊዮን ገደማ ገበሬዎች ሸንኮራ አገዳ ያመርታሉ። ሚሊዮኖች ደግሞ ስኳር በሚያመርቱ ፋብሪካዎች ውስጥ ተቀጥረው ይሠራሉ። ሕንድ የተረፈ የስኳር ምርቷን ወደ ውጭ ለመላክ ማቀዷ በሌሎች ስኳር አምራች ሃገራት ዘንድ ቅራኔ ፈጥሯል። ሌላኛው የተረፈ የስኳር ምርትን ማስወገጃ መንገድ ወደ ኢታኖል ቀይሮ መጠቀም ነው። የሕንድ ስኳር ምርት ማሕበር የኢታኖል ምርት አሁን ካለው 1.9 ቢሊዮን ሊትር ምርት በሚቀጥለው ዓመት ወደ 3 ቢሊዮን ሊያድግ እንደሚችል ገምቷል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54791680 |
3politics
| አሜሪካ በአፋር ክልል አዲስ ጦርነት መቀስቀሱ እንዳሳሰባት ገለጸች | የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በሰሜን ኢትዮጵያ በአፋርና በትግራይ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች አዲስ ጦርነት መቀስቀሱ አሳስቦኛል አለ። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ትናንት ሐሙስ ጥር 18/2014 ዓ.ም ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ "በአፋር ክልል ጦርነት እንደ አዲስ መቀስቀሱ እጅግ አሳሳቢ ነው" ብለዋል። ከቀናት በፊት የህወሓት ኃይሎች ከትግራይ ክልል አዋሳኝ የሆኑ በአፋር ክልል ዞን ሁለት ውስጥ የሚገኙ ሦስት ወረዳዎችን መቆጣጠራቸውን የአፋር ክልል መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ለቢቢሲ መናገራቸው ይታወሳል። የህወሓት ኃይሎች ደግሞ ከአፋር ኃይሎች በኩል የሚሰነዘርባቸውን ጥቃት ሲከላከሉ መቆየታቸውን በመግለጽ ሰኞ ጥር 16/2014 'ጠንካራ ወታደራዊ እርምጃ' መውሰዳቸውን ገልጸዋል። ኔድ ፕራይስ በመግለጫቸው፤ የአሜሪካ መንግሥት ግጭት እንዲቆም እና በሁሉም አካላት ተፈጽመዋል የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከ ገለልተኛ የሆነ ምርመራ እንዲካሄድ ጥሪ ሲያቀርቡ መቆየታቸውን ተናግረዋል። ከቀናት በፊት አዲሱ የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ እና ከሌሎች የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ኔድ ፕራይስ ገልጸዋል። በተጨማሪም ቃል አቀባዩ፤ ጦርነቱ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ቀንድ ደኅንነት እና ፀጥታ ስጋት መሆኑን በመጥቀስ፣ በግጭቱ አካባቢ ላሉ ሰዎች ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት እንዲመቻች እና ግጭቱ በድርድር እንዲጠናቀቅ የመንግሥታቸው ፍላጎት መሆኑን አመልክተዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኔድ ፕራይስ ጨምረውም የኢትዮጵያ መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከቀናት በፊት ላለፉት ሦስት ወራት ያህል በመላው አገሪቱ ተጥሎ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ ውሳኔ ማሳለፉ የአሜሪካ መንግሥት በበጎ እንደሚመለከተው ገልጸዋል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባለፈው ረቡዕ ጥር 17/2014 ዓ.ም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ ያሳለፈው ውሳኔ ጸድቆ ተግባራዊ እንዲሆን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመርቷል። "ይህ ውሳኔ [የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ መወሰኑን] በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይጸድቃል ብለን ተስፋ እንዳርጋለን" ሲሉ ኔድ ፕራይስ ተናግረዋል። በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደው ጦርነት ተባብሶ በበርካታ የአማራ እና የአፋር አካባቢዎች በሚካሄድበት ወቅት ነበር በአገሪቱ ሉዓላዊነት ላይ የተደቀነውን አደጋ ለመከላከል በሚል ነበር ሚኒስትሮች ምክር ቤት ጥቅምት ወር ማጠናቀቂያ ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የደነገገው። ኔድ ፕራይስ ጨምረውም ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ሥር ውለው የነበሩት ሰዎች እንዲፈቱም በመግለጫቸው ጠይቀዋል። ቃል አቀባዩ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን እና መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ማስቆም የሚቻለው በድርድር ግጭት ሲቆም፣ የታሰሩ ሰዎች ሲፈቱ፣ የሰብዓዊ እርዳታ ሲፈቀድ እና ሁሉን አካታች የሆነ ብሔራዊ ምክክር ለማድረግ መሠረት ሲጣል ነው ብለዋል። አሜሪካ በትግራይ ክልል ውስጥ ተጀምሮ ወደ አጎራባቾቹ የአፋርና የአማራ ክልሎች የተዛመተው ጦርነት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ መንግሥት ከአማጺያኑ ጋር ድርድር አድርጎ ጦርነቱ እንዲቋጭ ግፊት ስታደርግ የቆየች ሲሆን፣ ልዩ መልዕክተኛ ሰይማም ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣንት ጋር ውይይት ሲደረግ ቆይቷል። | አሜሪካ በአፋር ክልል አዲስ ጦርነት መቀስቀሱ እንዳሳሰባት ገለጸች የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በሰሜን ኢትዮጵያ በአፋርና በትግራይ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች አዲስ ጦርነት መቀስቀሱ አሳስቦኛል አለ። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ትናንት ሐሙስ ጥር 18/2014 ዓ.ም ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ "በአፋር ክልል ጦርነት እንደ አዲስ መቀስቀሱ እጅግ አሳሳቢ ነው" ብለዋል። ከቀናት በፊት የህወሓት ኃይሎች ከትግራይ ክልል አዋሳኝ የሆኑ በአፋር ክልል ዞን ሁለት ውስጥ የሚገኙ ሦስት ወረዳዎችን መቆጣጠራቸውን የአፋር ክልል መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ለቢቢሲ መናገራቸው ይታወሳል። የህወሓት ኃይሎች ደግሞ ከአፋር ኃይሎች በኩል የሚሰነዘርባቸውን ጥቃት ሲከላከሉ መቆየታቸውን በመግለጽ ሰኞ ጥር 16/2014 'ጠንካራ ወታደራዊ እርምጃ' መውሰዳቸውን ገልጸዋል። ኔድ ፕራይስ በመግለጫቸው፤ የአሜሪካ መንግሥት ግጭት እንዲቆም እና በሁሉም አካላት ተፈጽመዋል የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከ ገለልተኛ የሆነ ምርመራ እንዲካሄድ ጥሪ ሲያቀርቡ መቆየታቸውን ተናግረዋል። ከቀናት በፊት አዲሱ የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ እና ከሌሎች የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ኔድ ፕራይስ ገልጸዋል። በተጨማሪም ቃል አቀባዩ፤ ጦርነቱ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ቀንድ ደኅንነት እና ፀጥታ ስጋት መሆኑን በመጥቀስ፣ በግጭቱ አካባቢ ላሉ ሰዎች ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት እንዲመቻች እና ግጭቱ በድርድር እንዲጠናቀቅ የመንግሥታቸው ፍላጎት መሆኑን አመልክተዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኔድ ፕራይስ ጨምረውም የኢትዮጵያ መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከቀናት በፊት ላለፉት ሦስት ወራት ያህል በመላው አገሪቱ ተጥሎ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ ውሳኔ ማሳለፉ የአሜሪካ መንግሥት በበጎ እንደሚመለከተው ገልጸዋል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባለፈው ረቡዕ ጥር 17/2014 ዓ.ም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ ያሳለፈው ውሳኔ ጸድቆ ተግባራዊ እንዲሆን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመርቷል። "ይህ ውሳኔ [የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ መወሰኑን] በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይጸድቃል ብለን ተስፋ እንዳርጋለን" ሲሉ ኔድ ፕራይስ ተናግረዋል። በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደው ጦርነት ተባብሶ በበርካታ የአማራ እና የአፋር አካባቢዎች በሚካሄድበት ወቅት ነበር በአገሪቱ ሉዓላዊነት ላይ የተደቀነውን አደጋ ለመከላከል በሚል ነበር ሚኒስትሮች ምክር ቤት ጥቅምት ወር ማጠናቀቂያ ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የደነገገው። ኔድ ፕራይስ ጨምረውም ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ሥር ውለው የነበሩት ሰዎች እንዲፈቱም በመግለጫቸው ጠይቀዋል። ቃል አቀባዩ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን እና መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ማስቆም የሚቻለው በድርድር ግጭት ሲቆም፣ የታሰሩ ሰዎች ሲፈቱ፣ የሰብዓዊ እርዳታ ሲፈቀድ እና ሁሉን አካታች የሆነ ብሔራዊ ምክክር ለማድረግ መሠረት ሲጣል ነው ብለዋል። አሜሪካ በትግራይ ክልል ውስጥ ተጀምሮ ወደ አጎራባቾቹ የአፋርና የአማራ ክልሎች የተዛመተው ጦርነት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ መንግሥት ከአማጺያኑ ጋር ድርድር አድርጎ ጦርነቱ እንዲቋጭ ግፊት ስታደርግ የቆየች ሲሆን፣ ልዩ መልዕክተኛ ሰይማም ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣንት ጋር ውይይት ሲደረግ ቆይቷል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60133594 |
0business
| በማዳበሪያ ዋጋ መናር “መሬታችን ጦም ሊያድር ይችላል” ሲሉ አርሶ አደሮች ስጋታቸውን ገለጹ | በማዳበሪያ ዋጋ መናር ምክንያት " መሬታችን ምንም አዝዕርት ሳይዘራበት ሊከርም ይችላል" ሲሉ አርሶ አደሮች ስጋታቸውን ለቢቢሲ ገለጹ። የአፈር ማዳበሪያ ዋጋ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ዘንድሮ ከ150 በመቶ በላይ ጨምሯል። ይህም ለአርሶ አደሩ ራስ ምታት ከሆነ ሰነባብቷል። በባለፈው ዓመት በኩንታል 1700 ብር ይሸጥ የነበረው ማዳበሪያ ዘንድሮ ዋጋው ከእጥፍ በላይ ጨምሮ 4200 ብር ገብቷል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው አርሶ አደሮች የዋጋ ንረቱ በምርታቸው ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ይናገራሉ። "የእኔ እቅድ በዚህ ዓመት ለማዳበሪያ እስከ 25 ሺህ ብር ድረስ አወጣለሁ የሚል ነበር። አሁን ግን ከእጥፍ በላይ ሆኖ ከ50 ሺህ ብር በልጧል። ታዲያ እንዴት አድርጌ እዘራለሁ?!" ሲሉ ይጠይቃሉ አርሶ አደር ጌቴ። የዋጋ ንረቱ ማዳበሪያ የማይፈልጉ እና ዋጋ የማያወጡ ሰብሎችን መዝራትን እንደ አንድ አማራጭ እንዲያስቡም አስገድዷቸዋል። አርሶ አደር ጌቴ "እስካሁን አንድም ማዳበሪያ አልገዛሁም፤ ለበጋ መስኖ ቀደም ብሎ ከሰው ተበድሬ የዘራሁትንም እንዴት እንደምከፍል ጭንቅ ሆኖብኛል" ይላሉ። የሌላኛው አርሶ አደር ሹመት ጭንቀትም ተመሳሳይ ነው። "የመንደራችን የማለዳና የምሽት ወግም የማዳበሪያ ጉዳይ ከሆነ ሰንብቷል" ይላሉ። መሬታቸውን በአዝዕርት ለመሸፈን ቢያንስ 8 ኩንታል ኤንፒኤስ እና 4 ኩንታል ዩሪያ ማዳበሪያ እንደሚያስፈልጋቸው የገለፁት አርሶ አደሩ፣ ይህንን ለመግዛት አቅማቸው ስለማይፈቅድ የተሻለ መፍትሔ ካልተሰጠ ጭራሽኑ ማምረት እንደማይችሉ ይናገራሉ። "እኔ ደሃ አርሶ አደር ነኝ። በተባለው ዋጋ ገዝቼ ማምረት አልችልም። እንደው ልጄቼ የሚቆርጡት እሸት እንዳያጡ ጥቂት በቆሎ እዘራ እንደሁ እንጂ ሌላማ ምኑን አመረትኩት" ይላሉ። ኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት 12.8 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ግዥ መፈፀሟን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል። እስካሁን ወደ አገር ውስጥ መግባት የቻለውንም ለክልሎች የማሰራጨት ሥራ መጀመሩን በሚኒስቴሩ የኢንቨስትመንትና ግብዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት ዶ/ር ሶፊያ ካሳ ለቢቢሲ ገልጸዋል። የማዳበሪያ ዋጋው ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ከ150 በመቶ በላይ መጨመሩን የገለጹት ዶ/ር ሶፊያ፣ የግዥ ስምምነቱ ቀድሞ ስለተፈፀመ እንጂ አሁን ባለው የገበያ ዋጋ ጭማሪው ከዚህ የበለጠ ሊሆን ይችል ነበር ብለዋል። ለመሆኑ የማዳበሪያ ዋጋ ለምን ጨመረ? ሚኒስትር ዲኤታዋ ለዋጋ ጭማሪው እንደ ዋና ምክንያትነት የሚያነሱት በዓለም አቀፍ ደረጃ የማዳበሪያ ዋጋ መናርን ነው። " እንደ አገር ቀድመን ጨረታ አውጥተን ውል ስለገባን ነው አሁንም የተሻለ የሚባል ዋጋ ያገኘነው" ይላሉ። ትላልቅ የማዳበሪያ አምራች አገራት በኮቪድ-19 ምክንያት ምርታቸውን በመቀነሳቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ እጥረት መከሰቱን ሚኒስቴር ዲኤታዋ ያስረዳሉ። በተለይ ደግሞ ዩሪያ ለተባለው ማዳበሪያ ማምረቻ የሚያገለግል የተፈጥሮ ጋዝ ዋጋ በመጨመሩ እና ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚያመርቱት አገራት ከምርት ውጭ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። እንዲሁም ቻይና እና ሩሲያ ወደ ውጭ የሚልኩትን ማዳበሪያ ውስን አድርገውት ስለነበር በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ሆነ እጥረት መከሰቱን ሚኒስቴር ዲኤታዋ ለዋጋው መናር አስተዋጽኦ ያደረጉ ነገሮችን በምክንያትነት ይዘረዝራሉ። በግዥ አፈጻጸሙ መዘግየት የተስተዋለውም በዚሁ ምክንያት ተደጋጋሚ ጨረታ ለማውጣት በመገደዳቸው እንደሆነ ያክላሉ። ይሁን እንጂ አሁን እየገባ ያለውን ማዳበሪያ ቀድመው የሚዘሩ አካባቢዎችን በመለየት ክልሎች በአግባቡ እንዲያደርሱ እየተሰራ መሆኑን ሚኒስትር ዲኤታዋ ተናግረዋል። ከዚህም በተጨማሪ አርሶ አደሮች የሰው ሰራሽ ማዳበሪያ ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮ ማዳበሪያ እየተጠቀሙ ማምረት እንዲችሉ ክልሎች በከፍተኛ ንቅናቄ እየሰሩም ነው ብለዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው አርሶ አደሮች ግን የተፈጥሮን ማዳበሪያ እምብዛም እንደማይጠቀሙ እና መሬታቸው ሰው ሰራሽ ማዳበሪያ እንደተለማመደ በመግለጽ ያለውን ችግር ያስረዳሉ። በመሆኑም መንግሥት የሚራዘሙ ፕሮጀክቶችን እያራዘመ አርሶ አደሩ በተመጣጣኝ ዋጋ ማዳበሪያ እንዲያገኝ ድጎማ እንዲያደርግ የተሻለ ነው ያሉትን የመፍትሔ ሃሳብ ሰንዝረዋል። ይህንኑ የአርሶ አደሮቹን ጥያቄ ያቀረብንላቸው ሚኒስትር ዲኤታዋ "በቀጣይ ታይቶ መንግሥት የሚወስደውን አቅጣጫ እናሳውቃለን። አሁን መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ያለው አቅርቦት ላይ ነው" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ሚኒስትር ዲኤታዋ አክለውም ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ከፈፀመችው 17 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ግዥ የዘንድሮው ከ5 ሚሊየን ኩንታል በላይ ያነሰ መሆኑን ጠቅሰው "አጠቃላይ ከነበረው ፍላጎት 70 በመቶ ግዥ ነው የተፈፀመው ፤ በበልግ ወቅት ተጨማሪ ግዥ ሊኖር ይችላል " ብለዋል። ኢትዮጵያ በዋናነት የማዳበሪያ ግዥ የምትፈጽመው ከአፍሪካዊቷ አገር ሞሮኮ መሆኑንም ዶ/ር ሶፊያ ገልጸዋል። | በማዳበሪያ ዋጋ መናር “መሬታችን ጦም ሊያድር ይችላል” ሲሉ አርሶ አደሮች ስጋታቸውን ገለጹ በማዳበሪያ ዋጋ መናር ምክንያት " መሬታችን ምንም አዝዕርት ሳይዘራበት ሊከርም ይችላል" ሲሉ አርሶ አደሮች ስጋታቸውን ለቢቢሲ ገለጹ። የአፈር ማዳበሪያ ዋጋ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ዘንድሮ ከ150 በመቶ በላይ ጨምሯል። ይህም ለአርሶ አደሩ ራስ ምታት ከሆነ ሰነባብቷል። በባለፈው ዓመት በኩንታል 1700 ብር ይሸጥ የነበረው ማዳበሪያ ዘንድሮ ዋጋው ከእጥፍ በላይ ጨምሮ 4200 ብር ገብቷል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው አርሶ አደሮች የዋጋ ንረቱ በምርታቸው ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ይናገራሉ። "የእኔ እቅድ በዚህ ዓመት ለማዳበሪያ እስከ 25 ሺህ ብር ድረስ አወጣለሁ የሚል ነበር። አሁን ግን ከእጥፍ በላይ ሆኖ ከ50 ሺህ ብር በልጧል። ታዲያ እንዴት አድርጌ እዘራለሁ?!" ሲሉ ይጠይቃሉ አርሶ አደር ጌቴ። የዋጋ ንረቱ ማዳበሪያ የማይፈልጉ እና ዋጋ የማያወጡ ሰብሎችን መዝራትን እንደ አንድ አማራጭ እንዲያስቡም አስገድዷቸዋል። አርሶ አደር ጌቴ "እስካሁን አንድም ማዳበሪያ አልገዛሁም፤ ለበጋ መስኖ ቀደም ብሎ ከሰው ተበድሬ የዘራሁትንም እንዴት እንደምከፍል ጭንቅ ሆኖብኛል" ይላሉ። የሌላኛው አርሶ አደር ሹመት ጭንቀትም ተመሳሳይ ነው። "የመንደራችን የማለዳና የምሽት ወግም የማዳበሪያ ጉዳይ ከሆነ ሰንብቷል" ይላሉ። መሬታቸውን በአዝዕርት ለመሸፈን ቢያንስ 8 ኩንታል ኤንፒኤስ እና 4 ኩንታል ዩሪያ ማዳበሪያ እንደሚያስፈልጋቸው የገለፁት አርሶ አደሩ፣ ይህንን ለመግዛት አቅማቸው ስለማይፈቅድ የተሻለ መፍትሔ ካልተሰጠ ጭራሽኑ ማምረት እንደማይችሉ ይናገራሉ። "እኔ ደሃ አርሶ አደር ነኝ። በተባለው ዋጋ ገዝቼ ማምረት አልችልም። እንደው ልጄቼ የሚቆርጡት እሸት እንዳያጡ ጥቂት በቆሎ እዘራ እንደሁ እንጂ ሌላማ ምኑን አመረትኩት" ይላሉ። ኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት 12.8 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ግዥ መፈፀሟን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል። እስካሁን ወደ አገር ውስጥ መግባት የቻለውንም ለክልሎች የማሰራጨት ሥራ መጀመሩን በሚኒስቴሩ የኢንቨስትመንትና ግብዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት ዶ/ር ሶፊያ ካሳ ለቢቢሲ ገልጸዋል። የማዳበሪያ ዋጋው ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ከ150 በመቶ በላይ መጨመሩን የገለጹት ዶ/ር ሶፊያ፣ የግዥ ስምምነቱ ቀድሞ ስለተፈፀመ እንጂ አሁን ባለው የገበያ ዋጋ ጭማሪው ከዚህ የበለጠ ሊሆን ይችል ነበር ብለዋል። ለመሆኑ የማዳበሪያ ዋጋ ለምን ጨመረ? ሚኒስትር ዲኤታዋ ለዋጋ ጭማሪው እንደ ዋና ምክንያትነት የሚያነሱት በዓለም አቀፍ ደረጃ የማዳበሪያ ዋጋ መናርን ነው። " እንደ አገር ቀድመን ጨረታ አውጥተን ውል ስለገባን ነው አሁንም የተሻለ የሚባል ዋጋ ያገኘነው" ይላሉ። ትላልቅ የማዳበሪያ አምራች አገራት በኮቪድ-19 ምክንያት ምርታቸውን በመቀነሳቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ እጥረት መከሰቱን ሚኒስቴር ዲኤታዋ ያስረዳሉ። በተለይ ደግሞ ዩሪያ ለተባለው ማዳበሪያ ማምረቻ የሚያገለግል የተፈጥሮ ጋዝ ዋጋ በመጨመሩ እና ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚያመርቱት አገራት ከምርት ውጭ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። እንዲሁም ቻይና እና ሩሲያ ወደ ውጭ የሚልኩትን ማዳበሪያ ውስን አድርገውት ስለነበር በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ሆነ እጥረት መከሰቱን ሚኒስቴር ዲኤታዋ ለዋጋው መናር አስተዋጽኦ ያደረጉ ነገሮችን በምክንያትነት ይዘረዝራሉ። በግዥ አፈጻጸሙ መዘግየት የተስተዋለውም በዚሁ ምክንያት ተደጋጋሚ ጨረታ ለማውጣት በመገደዳቸው እንደሆነ ያክላሉ። ይሁን እንጂ አሁን እየገባ ያለውን ማዳበሪያ ቀድመው የሚዘሩ አካባቢዎችን በመለየት ክልሎች በአግባቡ እንዲያደርሱ እየተሰራ መሆኑን ሚኒስትር ዲኤታዋ ተናግረዋል። ከዚህም በተጨማሪ አርሶ አደሮች የሰው ሰራሽ ማዳበሪያ ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮ ማዳበሪያ እየተጠቀሙ ማምረት እንዲችሉ ክልሎች በከፍተኛ ንቅናቄ እየሰሩም ነው ብለዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው አርሶ አደሮች ግን የተፈጥሮን ማዳበሪያ እምብዛም እንደማይጠቀሙ እና መሬታቸው ሰው ሰራሽ ማዳበሪያ እንደተለማመደ በመግለጽ ያለውን ችግር ያስረዳሉ። በመሆኑም መንግሥት የሚራዘሙ ፕሮጀክቶችን እያራዘመ አርሶ አደሩ በተመጣጣኝ ዋጋ ማዳበሪያ እንዲያገኝ ድጎማ እንዲያደርግ የተሻለ ነው ያሉትን የመፍትሔ ሃሳብ ሰንዝረዋል። ይህንኑ የአርሶ አደሮቹን ጥያቄ ያቀረብንላቸው ሚኒስትር ዲኤታዋ "በቀጣይ ታይቶ መንግሥት የሚወስደውን አቅጣጫ እናሳውቃለን። አሁን መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ያለው አቅርቦት ላይ ነው" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ሚኒስትር ዲኤታዋ አክለውም ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ከፈፀመችው 17 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ግዥ የዘንድሮው ከ5 ሚሊየን ኩንታል በላይ ያነሰ መሆኑን ጠቅሰው "አጠቃላይ ከነበረው ፍላጎት 70 በመቶ ግዥ ነው የተፈፀመው ፤ በበልግ ወቅት ተጨማሪ ግዥ ሊኖር ይችላል " ብለዋል። ኢትዮጵያ በዋናነት የማዳበሪያ ግዥ የምትፈጽመው ከአፍሪካዊቷ አገር ሞሮኮ መሆኑንም ዶ/ር ሶፊያ ገልጸዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60985422 |
3politics
| የፈረንሳዩ ማክሮን 'ፑቲን ሁኔታዎችን ለማርገብ ቃል ገብተውልኛል' አሉ | ለከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጥረት ወደ ሩሲያና ዩክሬን ያቀኑት የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ቭላድሚር ፑቲን ሁኔታዎችን እንደሚያረግቡ ቃል እንደገቡላቸው ተናገሩ፡፡ "ድንበር አካባቢ ሁኔታዎች እንደማይባባሱ፣ አዳዲስ ትንኮሳዎች እንደማይኖሩ ማረጋገጫ አግኝቻለሁ" ብለዋል ማክሮን ለጋዜጠኖች፡፡ ኢማኑኤል ማክሮን ይህን ያሉት የዩክሬንኑን አቻቸውን ከማግኘታቸው ቀደም ብሎ ነው፡፡ ሩሲያ ዩክሬን ድንበር ላይ መቶ ሺህ ወታደሮቸን ማስፈሯ ሲነገር ነበር፡፡ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ሩሲያ ወረራውን ለመፈጸም ከሚያስፈልጋት ኃይል 70 ከመቶው በዩክሬን ድንበር ላይ መስፈሩን አረጋግጠናል ያሉት ባለፈው ሳምንት ነበር፡፡ ይህ በዩክሬን፣ ሩሲያና ምዕራብ አገራት መካከል ከፍተኛ የጦርነት ስጋትና ውጥረት የተከሰተው ሩሲያ በደቡብ ዩክሬን የክሪሚያን ባሕረ ገብ በኃይል ከያዘች ከ8 ዓመት በኋላ ነው፡፡ ሞስኮ፣ ዩክሬን የሚንስክ ስምምነትን ልታከብርልኝ አልቻለችም ስትል ትወቅሳታለች፡፡ የሚንስክ ስምምነት የሚባለው ጀርመንና ፈረንሳይ ያሸማገሉትና በሩሲያና ዩክሬን መካከል የተደረሰ የሰላም ስምምነት ነው፡፡ ሩሲያ የምትደግፋቸው አማጺያን በሚቆጣጠሩት አካባቢ ከፈረንጆቹ 2014 ጀምሮ 14ሺህ ሰዎች መገደላቸው ይነገራል፡፡ ማክሮን ትናንት ማክሰኞ በዩክሬን ዋና ከተማ ኪያቭ የተገኙ ሲሆን ወደዚያ ያመሩት ሰኞ ዕለት ከፑቲን ጋር ቢያንስ ስድስት ሰዓታትን የፈጀ ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው፡፡ ይህ የተራዘመ ውይይት የተደረገው በእራት ግብዣ ታጅቦ ነበር፡፡ ማክሮን ከፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ጋር በሰጡት የጣምራ መግለጫ ይህን ውጥረት ለማርገብ ወደ ተጨባጭ መፍትሄ ማምራት አለብን ብለዋል፡፡ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በበኩላቸው ፑቲን በተጨባጭ ጦርነቱን የማርገብ እርምጃዎችን እንዲወስዱ አሳስበዋል፡፡ "ቃላትን ብዙም አላምናቸውም፤ ፖለቲከኞች የሚጨበጥ እርምጃዎችን በግልጽ ሲወስዱ ነው የሚሻለው" ሲሉ ከባላንጣቸው ፑቲን የሰላም ተግባር እንደሚጠብቁ ጠቁመዋል፤ ዘለንስኪ፡፡ ማክሮን ከዚህ በኋላ ወደ ጀርመን ያቀኑ ሲሆን በዚያ ጀርመንና ፖላንድ ለዩክሬን ሉአላዊነት ያላቸውን ቀናኢነት ገልጠውላቸዋል፡፡ እነዚህ መሪዎች በጀርመን የተገኙት የዌይማር ትሪያንግል ቡድን ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ለመገኘት ነው፡፡ ይህ ቡድን የተመሠረተው የዛሬ 31 ዓመት ገደማ ሲሆን የቀዝቃዛው ጦርነት ማብቃትን ተከትሎ አውሮጳን የሚገጥማትን አዳዲስ ፈተናዎች ለማርገብ የተፈጠረ ስብስብ ነበር፡፡ የአሜሪካው ጆ ባይደን በበኩላቸው ከትናንት በስቲያ ሰኞ አንጌላ መርክልን የተኩትን የጀርመኑን መራሒ መንግሥት ሾልዝን በዋሺንግተን ተቀብለው አነጋግረዋቸዋል፡፡ ሁለቱ መሪዎች ዋንኛ አጀንዳ ያደረጉት የሩሲያን የወረራ ስጋት ሲሆን ፑቲን እንደተፈራው ዩክሬንን የሚወሩ ከሆነ ወደ ጀርመን የተዘረጋውና ከፍተኛ መዋእለ ነዋይ ፈሶበታል የሚባለውን የኖርድ ስትሪም2 የጋዝ መስመርን ለመዝጋት ዝተዋል፡፡ ይህ የሚፈራው ጦርነት ከተቀሰቀሰ ጀርመን ወታደር እንደማታዋጣ ቀደም ብላ ማሳወቋ በወዳጅ አገራትን ዘንድ ቅሬታን ፈጥሮ ነበር፡፡ ቭላድሚር ፑቲን ይህ የጦርነት ስጋት ጨርሶውኑ እንዲቀለበስ ያቀረቡት ቅድመ ሁኔታ በብዙ የምዕራብ አገራት ዘንድ ውድቅ ተደርጓል፡፡ ሞስኮ፣ የሰሜን ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ዩክሬንን አባል ላለማድረግ እንዲወስን፣ እንዲሁም በምሥራቅ አውሮጳ አካባቢ ዝር እንዳይል ትፈልጋለች፡፡ አሁን በማክሮን የዲፕሎማሲ ሩጫ የሩሲያና የዩክሬን የድንበር ጦርነት የረገበ ቢመስልም ዘለንስኪ ግን ጥርጣሬ እንዳላቸው ተስተውሏል፡፡ ዘለንስኪ ከማክሮን ጋር በሰጡት የጋራ መግለጫ ላይ ፑቲን የሚናገሩትን እምብዛምም እንደማያምኑ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡ "ግልጽነት በመሪዎች ዘንድ ሲታይ ጥሩ ነው፤ ነገር ግን ማዘናጊያ ቁማር መሆን የለበትም" ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡ በዚህ መግለጫ ላይ ያልተጠበቀ ሐሳብ የሰነዘሩት ማክሮን የዩክሬንና የኔቶ ግንኙነት የፊንላድን ሊመስል እንደሚችል ጥቁምታን ሰጥተዋል፡፡ "ፊንላንድ የኔቶ አባል ባትሆንም ቅርብ ናት" ብለዋል፡፡ ይህ ሐሳብ ዘለንስኪን ቅር ሳያሰኛቸው አልቀረም፡፡ ማክሮን በዲፕሎማሲ ጥረታቸው ከፑቲን ቃል አግኝቻለሁ ቢሉም ክሬምሊን ይህን ሐሳብ ለማስተባበል ጊዜ አልወሰደበትም፡፡ "ማክሮን የኔቶ መሪ አይደሉም፡፡ የተደረሰ ስምምነትም የለም" ሲል መግለጫ አውጥቷል፡፡ አሁንም በአገራት መካከል በየአቅጣጫው ንግግሩ የቀጠለ ሲሆን ሩሲያም ወደ ድንበር ወታደሮችና ቁሳቁስ ማስጠጋቷን ገፍታበታለች፡፡ ኔቶም ወደ ምሥራቅ አውሮጳ መስፋፋቱንና ለጦርነት የተጠንቀቅ መሰናዶ ማድረጉን ቀጥሎበታል፡፡ | የፈረንሳዩ ማክሮን 'ፑቲን ሁኔታዎችን ለማርገብ ቃል ገብተውልኛል' አሉ ለከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጥረት ወደ ሩሲያና ዩክሬን ያቀኑት የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ቭላድሚር ፑቲን ሁኔታዎችን እንደሚያረግቡ ቃል እንደገቡላቸው ተናገሩ፡፡ "ድንበር አካባቢ ሁኔታዎች እንደማይባባሱ፣ አዳዲስ ትንኮሳዎች እንደማይኖሩ ማረጋገጫ አግኝቻለሁ" ብለዋል ማክሮን ለጋዜጠኖች፡፡ ኢማኑኤል ማክሮን ይህን ያሉት የዩክሬንኑን አቻቸውን ከማግኘታቸው ቀደም ብሎ ነው፡፡ ሩሲያ ዩክሬን ድንበር ላይ መቶ ሺህ ወታደሮቸን ማስፈሯ ሲነገር ነበር፡፡ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ሩሲያ ወረራውን ለመፈጸም ከሚያስፈልጋት ኃይል 70 ከመቶው በዩክሬን ድንበር ላይ መስፈሩን አረጋግጠናል ያሉት ባለፈው ሳምንት ነበር፡፡ ይህ በዩክሬን፣ ሩሲያና ምዕራብ አገራት መካከል ከፍተኛ የጦርነት ስጋትና ውጥረት የተከሰተው ሩሲያ በደቡብ ዩክሬን የክሪሚያን ባሕረ ገብ በኃይል ከያዘች ከ8 ዓመት በኋላ ነው፡፡ ሞስኮ፣ ዩክሬን የሚንስክ ስምምነትን ልታከብርልኝ አልቻለችም ስትል ትወቅሳታለች፡፡ የሚንስክ ስምምነት የሚባለው ጀርመንና ፈረንሳይ ያሸማገሉትና በሩሲያና ዩክሬን መካከል የተደረሰ የሰላም ስምምነት ነው፡፡ ሩሲያ የምትደግፋቸው አማጺያን በሚቆጣጠሩት አካባቢ ከፈረንጆቹ 2014 ጀምሮ 14ሺህ ሰዎች መገደላቸው ይነገራል፡፡ ማክሮን ትናንት ማክሰኞ በዩክሬን ዋና ከተማ ኪያቭ የተገኙ ሲሆን ወደዚያ ያመሩት ሰኞ ዕለት ከፑቲን ጋር ቢያንስ ስድስት ሰዓታትን የፈጀ ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው፡፡ ይህ የተራዘመ ውይይት የተደረገው በእራት ግብዣ ታጅቦ ነበር፡፡ ማክሮን ከፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ጋር በሰጡት የጣምራ መግለጫ ይህን ውጥረት ለማርገብ ወደ ተጨባጭ መፍትሄ ማምራት አለብን ብለዋል፡፡ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በበኩላቸው ፑቲን በተጨባጭ ጦርነቱን የማርገብ እርምጃዎችን እንዲወስዱ አሳስበዋል፡፡ "ቃላትን ብዙም አላምናቸውም፤ ፖለቲከኞች የሚጨበጥ እርምጃዎችን በግልጽ ሲወስዱ ነው የሚሻለው" ሲሉ ከባላንጣቸው ፑቲን የሰላም ተግባር እንደሚጠብቁ ጠቁመዋል፤ ዘለንስኪ፡፡ ማክሮን ከዚህ በኋላ ወደ ጀርመን ያቀኑ ሲሆን በዚያ ጀርመንና ፖላንድ ለዩክሬን ሉአላዊነት ያላቸውን ቀናኢነት ገልጠውላቸዋል፡፡ እነዚህ መሪዎች በጀርመን የተገኙት የዌይማር ትሪያንግል ቡድን ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ለመገኘት ነው፡፡ ይህ ቡድን የተመሠረተው የዛሬ 31 ዓመት ገደማ ሲሆን የቀዝቃዛው ጦርነት ማብቃትን ተከትሎ አውሮጳን የሚገጥማትን አዳዲስ ፈተናዎች ለማርገብ የተፈጠረ ስብስብ ነበር፡፡ የአሜሪካው ጆ ባይደን በበኩላቸው ከትናንት በስቲያ ሰኞ አንጌላ መርክልን የተኩትን የጀርመኑን መራሒ መንግሥት ሾልዝን በዋሺንግተን ተቀብለው አነጋግረዋቸዋል፡፡ ሁለቱ መሪዎች ዋንኛ አጀንዳ ያደረጉት የሩሲያን የወረራ ስጋት ሲሆን ፑቲን እንደተፈራው ዩክሬንን የሚወሩ ከሆነ ወደ ጀርመን የተዘረጋውና ከፍተኛ መዋእለ ነዋይ ፈሶበታል የሚባለውን የኖርድ ስትሪም2 የጋዝ መስመርን ለመዝጋት ዝተዋል፡፡ ይህ የሚፈራው ጦርነት ከተቀሰቀሰ ጀርመን ወታደር እንደማታዋጣ ቀደም ብላ ማሳወቋ በወዳጅ አገራትን ዘንድ ቅሬታን ፈጥሮ ነበር፡፡ ቭላድሚር ፑቲን ይህ የጦርነት ስጋት ጨርሶውኑ እንዲቀለበስ ያቀረቡት ቅድመ ሁኔታ በብዙ የምዕራብ አገራት ዘንድ ውድቅ ተደርጓል፡፡ ሞስኮ፣ የሰሜን ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ዩክሬንን አባል ላለማድረግ እንዲወስን፣ እንዲሁም በምሥራቅ አውሮጳ አካባቢ ዝር እንዳይል ትፈልጋለች፡፡ አሁን በማክሮን የዲፕሎማሲ ሩጫ የሩሲያና የዩክሬን የድንበር ጦርነት የረገበ ቢመስልም ዘለንስኪ ግን ጥርጣሬ እንዳላቸው ተስተውሏል፡፡ ዘለንስኪ ከማክሮን ጋር በሰጡት የጋራ መግለጫ ላይ ፑቲን የሚናገሩትን እምብዛምም እንደማያምኑ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡ "ግልጽነት በመሪዎች ዘንድ ሲታይ ጥሩ ነው፤ ነገር ግን ማዘናጊያ ቁማር መሆን የለበትም" ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡ በዚህ መግለጫ ላይ ያልተጠበቀ ሐሳብ የሰነዘሩት ማክሮን የዩክሬንና የኔቶ ግንኙነት የፊንላድን ሊመስል እንደሚችል ጥቁምታን ሰጥተዋል፡፡ "ፊንላንድ የኔቶ አባል ባትሆንም ቅርብ ናት" ብለዋል፡፡ ይህ ሐሳብ ዘለንስኪን ቅር ሳያሰኛቸው አልቀረም፡፡ ማክሮን በዲፕሎማሲ ጥረታቸው ከፑቲን ቃል አግኝቻለሁ ቢሉም ክሬምሊን ይህን ሐሳብ ለማስተባበል ጊዜ አልወሰደበትም፡፡ "ማክሮን የኔቶ መሪ አይደሉም፡፡ የተደረሰ ስምምነትም የለም" ሲል መግለጫ አውጥቷል፡፡ አሁንም በአገራት መካከል በየአቅጣጫው ንግግሩ የቀጠለ ሲሆን ሩሲያም ወደ ድንበር ወታደሮችና ቁሳቁስ ማስጠጋቷን ገፍታበታለች፡፡ ኔቶም ወደ ምሥራቅ አውሮጳ መስፋፋቱንና ለጦርነት የተጠንቀቅ መሰናዶ ማድረጉን ቀጥሎበታል፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/news-60314312 |
3politics
| ሩሲያ የኔቶ አባል በሆነችው ሊቱዌኒያ ላይ ጠንካራ ዛቻ ሰነዘረች | ሩሲያ የቀድሞዋ ሶቪየት ሕብረት ግዛትና የኔቶ አባል በሆነችው ሊቱዌኒያ ላይ ጠንካራ ዛቻ ሰነዘረች። ሩሲያ ዛቻውን የሰነዘረችው ሊቱዌኒያ የጭነት ዕቃዎች በድንበሯ በግዛቷ በኩል የሩሲያ ይዞታ ወደ ሆነችው ካሊኒንግራድ እንዳያልፉ ካገደች በኋላ ነው፡፡ ሊቱዌኒያ በበኩሏ ለሩሲያ ዛቻ ምላሽ ሰጥታለች፡፡ "እኛ የአውሮፓ ሕብረትን ማዕቀብ መሠረት አድርገን ነው ክልከላ የጣልነው" ብለዋል የሊቱዌኒያ ባለሥልጣናት፡፡ ካሊኒንግራድ፣ በፖላንድና በሊቱዌኒያ መካከል ያለ አንድ የሩሲያ ግዛት ነው፡፡ ግዛቱ የሩሲያ ይሁን እንጂ ከዋናው የሩሲያ ፌዴሬሽን ጋር ድንበር አይጋራም፡፡ ሆኖም ካሊኒንግራድን የአውሮፓ አባል የሆኑት ፖላንድና ሊቱዌኒያ ያዋስኑታል፡፡ ይህ ግዛት ለሩሲያ ወሳኝ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ነው፡፡ ሩሲያ ለሊቱዌኒያ ባስተላለፈችው በዚህ ማስጠንቀቂያ ሊቱዌኒያ ጭነቶቹ እንዲያልፉ የማታደርግ ከሆነ "ብርቱ ቅጣት" ይጠብቃታል ብለዋል፡፡ "ሩሲያ ለዚህ ጸብ አጫሪነት ሊቱዌኒያን ትቀጣለች" ብለዋል ኒኮሊያ ፓትሮቭ የተባሉ አንድ ከፍተኛ የሩሲያ ባለሥልጣን፡፡ ሊቱዌኒያ በበኩሏ የእኔ ሚና የአውሮፓ ሕብረትን የማዕቀብ ውሳኔ ተፈጻሚ ማድረግ ብቻ ነው ብላለች፡፡ ከባልቲክ ባሕር ኩታ ገጠም የሆነው ካሊኒንግራድ ግዛት ከሩሲያ ርቆ የሚገኝ የሩሲያ ስትራቴጂክ ግዛት ከመሆኑ ባሻገር የሩሲያ የጦር ሰፈር የሚገኝበት ነው፡፡ ይህ የምዕራብ ግዛት የ2ኛው የዓለም ጦርነትን ተከትሎ ከጀርመን ለሩሲያ የተሰጠ ሲሆን፣ በኔቶ አባል አገራት የተከበበ ነው፡፡ አንድ ሚሊዮን ሰዎች የሚኖሩበት ካሊኒንግራድ በብዛት ከሩሲያና ከአውሮፓ ሕብረት በሚመጡ ጥሬ ዕቃዎች ላይ ጥገኛ የሆነ አካባቢ ነው፡፡ ትናንት ማክሰኞ ካሊኒንግራድን የጎበኙት ሚስተር ፓትሮቭ "ይህ ምዕራቡ ዓለም የተነኮሰው ተግባር ነው፤ …ዓለም አቀፍ ሕግን የሚጻረር ተግባር ነው፤ …ሊቱዌኒያ ለዚህ ድርጊቷ ትቀጣለች" ብለዋል፡፡ ይህ ሩሲያ ደጋግማ የምትሰነዝረው የቅጣት ዛቻ ምጣኔ ሃብታዊ ይሁን ወታደራዊ የተባለ ነገር የለም፡፡ ሆኖም የሊቱዌኒያ ዕቀባ ተከትሎ ሩሲያ በአገሯ የሚገኙትን የአውሮፓ ሕብረት አምባሳደርን ጠርታ ማብራሪያ ጠይቃለች፡፡ ምናልባት ሩሲያ እንደዛተችው ሉቲኒያ ላይ ወታደራዊ ጥቃት ከሰነዘረች የኔቶ አባል አገራት ምላሽ እንደሚሰጡ ይጠበቃል፡፡ የኔቶ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 5፣ 'የየትኛውም አባል አገር ጥቃት የሁሉም አገር ጥቃት ነው' ይላል፡፡ አሜሪካ በሊቱዌኒያ ላይ የሚሰነዘር ማንኛውም ጥቃት አጸፋ እንደሚኖረው ይፋ አድርጋለች፡፡ | ሩሲያ የኔቶ አባል በሆነችው ሊቱዌኒያ ላይ ጠንካራ ዛቻ ሰነዘረች ሩሲያ የቀድሞዋ ሶቪየት ሕብረት ግዛትና የኔቶ አባል በሆነችው ሊቱዌኒያ ላይ ጠንካራ ዛቻ ሰነዘረች። ሩሲያ ዛቻውን የሰነዘረችው ሊቱዌኒያ የጭነት ዕቃዎች በድንበሯ በግዛቷ በኩል የሩሲያ ይዞታ ወደ ሆነችው ካሊኒንግራድ እንዳያልፉ ካገደች በኋላ ነው፡፡ ሊቱዌኒያ በበኩሏ ለሩሲያ ዛቻ ምላሽ ሰጥታለች፡፡ "እኛ የአውሮፓ ሕብረትን ማዕቀብ መሠረት አድርገን ነው ክልከላ የጣልነው" ብለዋል የሊቱዌኒያ ባለሥልጣናት፡፡ ካሊኒንግራድ፣ በፖላንድና በሊቱዌኒያ መካከል ያለ አንድ የሩሲያ ግዛት ነው፡፡ ግዛቱ የሩሲያ ይሁን እንጂ ከዋናው የሩሲያ ፌዴሬሽን ጋር ድንበር አይጋራም፡፡ ሆኖም ካሊኒንግራድን የአውሮፓ አባል የሆኑት ፖላንድና ሊቱዌኒያ ያዋስኑታል፡፡ ይህ ግዛት ለሩሲያ ወሳኝ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ነው፡፡ ሩሲያ ለሊቱዌኒያ ባስተላለፈችው በዚህ ማስጠንቀቂያ ሊቱዌኒያ ጭነቶቹ እንዲያልፉ የማታደርግ ከሆነ "ብርቱ ቅጣት" ይጠብቃታል ብለዋል፡፡ "ሩሲያ ለዚህ ጸብ አጫሪነት ሊቱዌኒያን ትቀጣለች" ብለዋል ኒኮሊያ ፓትሮቭ የተባሉ አንድ ከፍተኛ የሩሲያ ባለሥልጣን፡፡ ሊቱዌኒያ በበኩሏ የእኔ ሚና የአውሮፓ ሕብረትን የማዕቀብ ውሳኔ ተፈጻሚ ማድረግ ብቻ ነው ብላለች፡፡ ከባልቲክ ባሕር ኩታ ገጠም የሆነው ካሊኒንግራድ ግዛት ከሩሲያ ርቆ የሚገኝ የሩሲያ ስትራቴጂክ ግዛት ከመሆኑ ባሻገር የሩሲያ የጦር ሰፈር የሚገኝበት ነው፡፡ ይህ የምዕራብ ግዛት የ2ኛው የዓለም ጦርነትን ተከትሎ ከጀርመን ለሩሲያ የተሰጠ ሲሆን፣ በኔቶ አባል አገራት የተከበበ ነው፡፡ አንድ ሚሊዮን ሰዎች የሚኖሩበት ካሊኒንግራድ በብዛት ከሩሲያና ከአውሮፓ ሕብረት በሚመጡ ጥሬ ዕቃዎች ላይ ጥገኛ የሆነ አካባቢ ነው፡፡ ትናንት ማክሰኞ ካሊኒንግራድን የጎበኙት ሚስተር ፓትሮቭ "ይህ ምዕራቡ ዓለም የተነኮሰው ተግባር ነው፤ …ዓለም አቀፍ ሕግን የሚጻረር ተግባር ነው፤ …ሊቱዌኒያ ለዚህ ድርጊቷ ትቀጣለች" ብለዋል፡፡ ይህ ሩሲያ ደጋግማ የምትሰነዝረው የቅጣት ዛቻ ምጣኔ ሃብታዊ ይሁን ወታደራዊ የተባለ ነገር የለም፡፡ ሆኖም የሊቱዌኒያ ዕቀባ ተከትሎ ሩሲያ በአገሯ የሚገኙትን የአውሮፓ ሕብረት አምባሳደርን ጠርታ ማብራሪያ ጠይቃለች፡፡ ምናልባት ሩሲያ እንደዛተችው ሉቲኒያ ላይ ወታደራዊ ጥቃት ከሰነዘረች የኔቶ አባል አገራት ምላሽ እንደሚሰጡ ይጠበቃል፡፡ የኔቶ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 5፣ 'የየትኛውም አባል አገር ጥቃት የሁሉም አገር ጥቃት ነው' ይላል፡፡ አሜሪካ በሊቱዌኒያ ላይ የሚሰነዘር ማንኛውም ጥቃት አጸፋ እንደሚኖረው ይፋ አድርጋለች፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/articles/clmxg0vn0x4o |
2health
| የዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ዶ/ር ቴድሮስን ዳግም ዕጩ አድርጎ አቀረበ | የዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ድርጅቱን ዳግም ለቀጣይ አምስት ዓመታት በዳይሬክተርነት እንዲመሩ ዕጩ አደረገ። ድርጅቱን ለሁለተኛ ዙር ለመምራት ዶ/ር ቴድሮስ ያለተፎካካሪ ብቸኛ ዕጩ ሆነው የቀረቡ ሲሆን የመጨረሻው ውጤትም ግንቦት 2014 ዓ.ም. ላይ ይፋ ይደረጋል ተብሏል። ዶ/ር ቴድሮስ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ኃላፊነታቸውን ከአምስት ዓመት በፊት ከመረከባቸው ቀደም ብሎ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የጤና ሚኒስትር ሆነው ማገልገላቸው ይታወሳል። ዶ/ር ቴድሮስ ከአምስት ዓመታት በፊት ድርጅቱን በዋና ዳይሬክተርነት እንዲመሩ የኢትዮጵያ ድጋፍ አልተለያቸውም ነበር። ይሁን እንጂ የትግራዩን ጦርነት ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት ዶ/ር ቴድሮስ ኃላፊነታቸውን ተጠቅመው ለህወሓት ድጋፍ ያደርጋሉ ሲል በተደጋጋሚ ከሷቸዋል። የዓለም ጤና ደርጅት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ በጄኔቭ ለስበሰባ ከመቀመጡ በፊት የኢትዮጵያ መንግሥት በዶ/ር ቴድሮስ ገለልተኝነት ላይ ምርመራ እንዲያካሂድ ጥያቄ ማቅረቡ ይታወሳል። ይሁን እንጂ ቦርዱ በዳይሬክተሩ ላይ ምርመራ እንዲደረግ የቀረበውን የኢትዮጵያ ጥያቄ ወደ ጎን በመግፋት ሳይመለከተው ቀርቷል። ዶ/ር ቴድሮስ ለሁለተኛ ጊዜ የዓለም ጤና ድርጅትን ለመምራት ዕጩ በሆኑበት ጉዳይ ላይ ለመወያየት በተጠራ የሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ስብሰባ ላይ የድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሰብሳቢ ፓትሪክ አሞት አቤቱታውን ያልተመለከቱበትን ምክንያት ገልጸዋል። "ይህ ጉዳይ በጣም የተወሳሰበና ፖለቲካዊ አንድምታ ያለው፤ ከዚህ ኮሚቴ የአስራር ማዕቀፍ ውጪ ነው" አሞት ያሉ ሲሆን፤ የቦርዱ 34 አባላት በሙሉ የምርመራ ጥያቄውን ሳይቀበሉት ቀርተዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ በጉዳዩ ላይ በተወያየበት ጊዜ የኢትዮጵያ መንግሥት ተወካይ የአገራቸውን አቤቱታ ለማብራራት በመከሩበት ጊዜ እንዲያቋርጡ ተደርገው ነበር። ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ በድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ንግግር እንዳያደርጉ መከልከሉ ተቀባይነት የሌለው ነው ሲል ተቃውሞውን ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ ለገሰ ቱሉ ውሳኔው የዓለም ጤና ድርጅት በጉዳዩ ላይ ገለልተኛ አለመሆኑን ማሳያ ነው ሲሉ መናገራቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። ቃል አቀባዩ የዓለም ጤና ድርጅት በዶ/ር ቴድሮስ ላይ ምርመራ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ መንግሥት በተደጋጋሚ ይጠይቃልም ሲሉ ለሮይተርስ ጨምረው ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር የተሳሳቱ መረጃዎችን በማሰራጨት የድርጅቱን ነፃነት፣ ገለልተኝነት መርህ ጥያቄ ውስጥ እንደከተቱት በመጠየቅ ምርመራ እንዲደረግ አቤቱታ አቅርቦ ነበር። በትግራይ ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሲቪልና ወታደራዊ ባለሥልጣናት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ለዓመታት አባልና አመራር የነበሩበትን ህወሓት የሚደግፉ ተግባራት ላይ ተሳትፈዋል ሲሉ ሲከሱ ቆይተዋል። ዶ/ር ቴድሮስ እና የዓለም ጤና ድርጅት የቢቢሲ የጄኔቭ ዘጋቢ ኦሞጂን ፉክስ እንዳለችው የትኛውም የከዚህ ቀደም የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር እንደ ዶ/ር ቴድሮስ አልተፈተነም። የኮቪድ-19 ወረርሸኝ፣ ቻይና ስለ ወረርሽኑ መረጃ እንድታጋራ ጫና ማድረግ፣ ከቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር የተፈጠረው እሰጣገባ፣ የአሜሪካ ድጋፍ ማቆም እና ከድርጅቱ አባልነት መውጣት በቀዳሚነት የሚወጠቀሱ ሲሆን። ለአንድ ዓመት የዘለቀው የትግራዩ ጦርነት በግል ያደረሰባቸው ጫና እና ከትውልድ አገራቸው መንግሥት ጋር የገቡት ቅሬታ የዶ/ር ቴድሮስ ፈተናዎች ከነበሩት መካከል ተጠቃሽ ናቸው። አሁንም ቢሆን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዝርያውን እየቀረ ዓለም ማሸበሩን አላቆመም፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አሁንም የኮቪድ ክትባትን አልወሰዱም። የዓለም ጤና ድርጅት ሠራተኞች በዲሞክራቲክ ኮንጎ ፈጽመውታል በተባለው የጾታ ጥቃት የድርጅቱን የከበረ ስም አጉዱፏል። በሌላ በኩል ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የትራምፕን ውሳኔ በመቀልበስ አሜሪካን ወደ የዓለም ጤና ድርጅት አባልነት መልሰዋል። አሜሪካ ለድርጅቱ የምታደርገው ከፍተኛ ድጋፍም ቀጥሏል። በውጣ ውረዶች ውስጥ ያለፉት ዶ/ር ቴድሮስ ግዙፉን የጤና ድርጅት ለሌላ አምስት ዓመታት የመምራት ጽኑ ፍላጎት አላቸው ተብሏል። | የዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ዶ/ር ቴድሮስን ዳግም ዕጩ አድርጎ አቀረበ የዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ድርጅቱን ዳግም ለቀጣይ አምስት ዓመታት በዳይሬክተርነት እንዲመሩ ዕጩ አደረገ። ድርጅቱን ለሁለተኛ ዙር ለመምራት ዶ/ር ቴድሮስ ያለተፎካካሪ ብቸኛ ዕጩ ሆነው የቀረቡ ሲሆን የመጨረሻው ውጤትም ግንቦት 2014 ዓ.ም. ላይ ይፋ ይደረጋል ተብሏል። ዶ/ር ቴድሮስ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ኃላፊነታቸውን ከአምስት ዓመት በፊት ከመረከባቸው ቀደም ብሎ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የጤና ሚኒስትር ሆነው ማገልገላቸው ይታወሳል። ዶ/ር ቴድሮስ ከአምስት ዓመታት በፊት ድርጅቱን በዋና ዳይሬክተርነት እንዲመሩ የኢትዮጵያ ድጋፍ አልተለያቸውም ነበር። ይሁን እንጂ የትግራዩን ጦርነት ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት ዶ/ር ቴድሮስ ኃላፊነታቸውን ተጠቅመው ለህወሓት ድጋፍ ያደርጋሉ ሲል በተደጋጋሚ ከሷቸዋል። የዓለም ጤና ደርጅት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ በጄኔቭ ለስበሰባ ከመቀመጡ በፊት የኢትዮጵያ መንግሥት በዶ/ር ቴድሮስ ገለልተኝነት ላይ ምርመራ እንዲያካሂድ ጥያቄ ማቅረቡ ይታወሳል። ይሁን እንጂ ቦርዱ በዳይሬክተሩ ላይ ምርመራ እንዲደረግ የቀረበውን የኢትዮጵያ ጥያቄ ወደ ጎን በመግፋት ሳይመለከተው ቀርቷል። ዶ/ር ቴድሮስ ለሁለተኛ ጊዜ የዓለም ጤና ድርጅትን ለመምራት ዕጩ በሆኑበት ጉዳይ ላይ ለመወያየት በተጠራ የሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ስብሰባ ላይ የድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሰብሳቢ ፓትሪክ አሞት አቤቱታውን ያልተመለከቱበትን ምክንያት ገልጸዋል። "ይህ ጉዳይ በጣም የተወሳሰበና ፖለቲካዊ አንድምታ ያለው፤ ከዚህ ኮሚቴ የአስራር ማዕቀፍ ውጪ ነው" አሞት ያሉ ሲሆን፤ የቦርዱ 34 አባላት በሙሉ የምርመራ ጥያቄውን ሳይቀበሉት ቀርተዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ በጉዳዩ ላይ በተወያየበት ጊዜ የኢትዮጵያ መንግሥት ተወካይ የአገራቸውን አቤቱታ ለማብራራት በመከሩበት ጊዜ እንዲያቋርጡ ተደርገው ነበር። ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ በድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ንግግር እንዳያደርጉ መከልከሉ ተቀባይነት የሌለው ነው ሲል ተቃውሞውን ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ ለገሰ ቱሉ ውሳኔው የዓለም ጤና ድርጅት በጉዳዩ ላይ ገለልተኛ አለመሆኑን ማሳያ ነው ሲሉ መናገራቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። ቃል አቀባዩ የዓለም ጤና ድርጅት በዶ/ር ቴድሮስ ላይ ምርመራ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ መንግሥት በተደጋጋሚ ይጠይቃልም ሲሉ ለሮይተርስ ጨምረው ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር የተሳሳቱ መረጃዎችን በማሰራጨት የድርጅቱን ነፃነት፣ ገለልተኝነት መርህ ጥያቄ ውስጥ እንደከተቱት በመጠየቅ ምርመራ እንዲደረግ አቤቱታ አቅርቦ ነበር። በትግራይ ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሲቪልና ወታደራዊ ባለሥልጣናት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ለዓመታት አባልና አመራር የነበሩበትን ህወሓት የሚደግፉ ተግባራት ላይ ተሳትፈዋል ሲሉ ሲከሱ ቆይተዋል። ዶ/ር ቴድሮስ እና የዓለም ጤና ድርጅት የቢቢሲ የጄኔቭ ዘጋቢ ኦሞጂን ፉክስ እንዳለችው የትኛውም የከዚህ ቀደም የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር እንደ ዶ/ር ቴድሮስ አልተፈተነም። የኮቪድ-19 ወረርሸኝ፣ ቻይና ስለ ወረርሽኑ መረጃ እንድታጋራ ጫና ማድረግ፣ ከቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር የተፈጠረው እሰጣገባ፣ የአሜሪካ ድጋፍ ማቆም እና ከድርጅቱ አባልነት መውጣት በቀዳሚነት የሚወጠቀሱ ሲሆን። ለአንድ ዓመት የዘለቀው የትግራዩ ጦርነት በግል ያደረሰባቸው ጫና እና ከትውልድ አገራቸው መንግሥት ጋር የገቡት ቅሬታ የዶ/ር ቴድሮስ ፈተናዎች ከነበሩት መካከል ተጠቃሽ ናቸው። አሁንም ቢሆን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዝርያውን እየቀረ ዓለም ማሸበሩን አላቆመም፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አሁንም የኮቪድ ክትባትን አልወሰዱም። የዓለም ጤና ድርጅት ሠራተኞች በዲሞክራቲክ ኮንጎ ፈጽመውታል በተባለው የጾታ ጥቃት የድርጅቱን የከበረ ስም አጉዱፏል። በሌላ በኩል ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የትራምፕን ውሳኔ በመቀልበስ አሜሪካን ወደ የዓለም ጤና ድርጅት አባልነት መልሰዋል። አሜሪካ ለድርጅቱ የምታደርገው ከፍተኛ ድጋፍም ቀጥሏል። በውጣ ውረዶች ውስጥ ያለፉት ዶ/ር ቴድሮስ ግዙፉን የጤና ድርጅት ለሌላ አምስት ዓመታት የመምራት ጽኑ ፍላጎት አላቸው ተብሏል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60133588 |
3politics
| የጋዜጠኞቹ እስርና በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለው ዘመቻ | በማህበራዊና በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ የኢትዮጵያ መንግሥትን በመተቸት የምትታወቀው መስከረም አበራ ቅዳሜ እለት፣ ግንቦት 13 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ በቁጥጥር ስር መዋሏን ባለቤቷ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በአዋሳ ዩኒቨርስቲ መምህር የነበረችው መስከረም በቁጥጥር ስር የዋለችው በአዲስ አበባ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲሆን ያለችበትንም ስፍራ እንደማያውቁ ባለቤቷ ተናግረዋል። ይህም በሳምንቱ የታሰሩትን የጋዜጠኞች እና የሚዲያ አካላት ቁጥር ሰባት ያደረሰው ሲሆን ሁኔታውም የተችዎን ድምጽ በማፈኑ ረገድ አዲስ እርምጃ ሊኖር ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል። በያዝነው ሳምንት ሐሙስ ግንቦት 11፣ 2014 ዓ.ም በአማራ ክልል ተቀማጭነቱን ያደረገውና የቅርብ ዘገባቸው በፋኖ ላይ ያተኮረው አሻራ ሚዲያ አምስት ጋዜጠኞቹ በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጿል። ጋዜጠኞቹ የአማራ ልዩ ኃይል፣ የአማራ ፖሊስና የአድማ በታኝ የደንብ ልብስ በለበሱ የጸጥታ አካላት እንደተወሰዱ "ሽንት ቤት ውስጥ ተደብቄ ነበር" ያለ የስራ ባልደረባቸው ለሮይተርስ ተናግሯል። ግለሰቡ በባህርዳር ከተማ የሚገኘው የአሻራ ጽህፈት ቤት መዘጋቱንም ተናግሯል። በተጨማሪም በሃገሪቱ የተካሄደውን ጦርነት በመቃወምና የሰላምና ድርድር መንገዶች የተሻሉ አማራጮች እንደሆኑ በተደጋጋሚ አፅንኦት በመስጠት የሚታወቀው ጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬም መታሰሩ ተዘግቧል። ቢቢሲ የአዲስ አበባን ሆነ የፌደራል ፖሊስን ለማግኘት ቢሞክርም ባለመሳካቱ ምላሻቸውን ለማካተት አልተቻለም። ጋዜጠኞቹ በቁጥር ስር የዋሉት መንግሥት በተለያዩ ክልሎች ህግን የማስከበር ዘመቻ እያካሄደ መሆኑን ባስታወቀ ማግስት ነው። የፌደራል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አርብ ምሽት በአማራ ክልልና በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች እየተወሰደ ያለውን እርምጃ በተመለከተ ባወጣው መግለጫ፣ የሕግ የበላይነትን ማስከበር የዜጎችን ሰላምና ደኅንነት እንዲሁም የአገርን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ብቸኛው መፍትሔ ነው ብሏል። በተለያዩ አካባቢዎች የሚታየውን ሕገ ወጥነትና የሰላም መደፍረስን መንግሥት እንዲቆጣጠር ሕዝቡ በተደጋጋሚ ሲጠይቅ ነበር ያለው መግለጫው፣ ብሔራዊ የፀጥታ ምክር ቤት አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድ መወሰኑን አስታውሷል። የተቃዋሚው አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ዘጠኝ አባላትም እንዲሁ በያዝነው ሳምንት ግንቦት 10፣ 2014 ዓ.ም በሁለት ከተሞች መታሰራቸውን ሮይተርስ በአሜሪካ የሚገኘውን የአማራ ማህበር ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። በተጨማሪም የአብን ፓርቲ አባላትና አመራሮች እስር ተጠናክሮ መቀጠሉን የተለያዩ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ይህንንም ተከትሎ በኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አምስት የአብን አባላት አርብ ዕለት፣ ግንቦት 12፣ 2014 ዓ.ም ባወጡት መግለጫ "መንግሥት እገታና ስወራ" እየፈጸመ ነው ሲሉ ከሰዋል። "በአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን አባላትና አመራሮች፣ በፋኖ አባላት፣ በሕጋዊ ታጣቂዎችና ወጣቶች እንዲሁም አገራቸውንና ሕዝባቸውን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ያገለገሉ የጦር መኮንኖችንና የጸጥታ አመራሮች ላይ የሚፈጸመው መንግስታዊ እገታና ስወራ በአስቸኳይ እንዲቆምና በዚህ ሰበብ በማንነታቸው ብቻ የታገቱ አካላትም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቀቁ እንጠይቃለን፡፡" ብሏል። ከቀናት በፊት አዲስ አበባ ውስጥ መሰወራቸው የተነገረው የቀድሞ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ኃላፊ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ ሞክረዋል በሚል ተጠርጥረው እንደተያዙና በባህርዳር ጠቅላይ ፍርድ ቤት አርብ እለት መቅረባቸው ይታወቃል። ሮይተርስን ጨምሮ ሌሎች ሚዲያዎች ከሰሞኑ ባወጡት ዘገባ በተለያዩ ከተማዎች የሚገኙ የፋኖ አባላት መታሰራቸውንና ሌሎቹንም በቁጥጥር ስር ለማዋል ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑን ዘግበዋል። መግለጫው አክሎም "ህግ ማስከበርን ሰበብ በማድረግ የፌደራል የፀጥታ መዋቅር በሕገ መንግሥቱ ለክልልና ለፌድራል ተለይቶ የተሰጠውን ኃላፊነት እና ሚና በደፈጠጠ መልኩ ክልሉን በሕገ-ወጥ መንገድ ለመቆጣጠር የሚያደርገውን ሙከራ እንዲያቆም" ጠይቋል። የአማራ ክልል ባለስልጣናት በግለሰቦች እጅ የሚገኝ የጦር መሳሪያ እንዲመዘገብ ያደረጉት ጥሪ ትጥቅ ለማስፈታታት ነው ከሚሉ ወጣቶች ጋር ለግጭት መነሻ ሆኗል። "መነሻው ፋኖዎችን ትጥቅ እናስፈታለን በሚሉ የፀጥታ አካላት የተጀመረ ነው። በዚያ ውጥረት ሳቢያ ፋኖዎቹም ትጥቅ አንፈታም በሚል ቦታ ይዘው ነበር" ነበር ያሉት ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ነዋሪ እማኝነታቸውን ሰጥተው፣ ነዋሪዎችም ፋኖ ትጥቅ መፍታት የለበትም በሚል ተቃውሞ አሰምተዋል ብለዋል። በሞጣ ከተማ በጸጥታ ኃይሎች እና በአካባቢው ወጣቶች መካከል በተፈጠረ ግጭት በትንሹ ስድስት ሰዎች መሞታቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይህንንም ተከትትሎ የከተማው አስተዳደር በእንቅስቃሴዎች ላይ ገደብ ከመጣል በተጨማሪ የሰዓት እላፊ አዋጅ ጥሏል። ከዚህም ጋር ተያይዞ የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ቅዳሜ በሰጠው መግለጫ "የሕግ ማስከበር ሥራውን ለማደናቀፍ የሚደረጉ ማንኛውም ድርጊቶች ላይ አስፈላጊው የሕግ እርምጃ" እንደሚወሰድ አስታውቋል። ቢሮው በመግለጫው ካለፉት ቀናት ጀምሮ ተጠርጣሪዎች ያለምንም ግጭት እጃቸውን ለህግ እንዲሰጡ እየተደረገ እንደሆነና ፈቃደኛ ባልሆኑ ግለሰቦች ላይ ጉዳት የመቀነስን ስራ ከህዝቡ ጋር እየተሰራ ነው ብሏል። ህግ ማስከበር ብሎ የጠራው ተግባር ለህዝቡ ሰላም እና ደህንነት፣ ለክልሉ እና ሃገሪቱ የሰላም ዋስትናን ዓላማ አድርጎ እየተከናወነ ባለበት ወቅት የተለያዩ ግለሰቦች "ዋና ጠላቶች" ብሎ ከጠራቸው ጋር በመተባበር ክልሉንና ሃገሪቱን ለማፍረስ የሚሰሩ አካላት እንቅፋት እየሆኑ ይገኛሉ ብሏል። "በአሁኑ ወቅት ከዋና ጠላቶታችን ጋር በማበር ክልላችንን እና ሀገራችንን ለማፍረስ የሚሠሩ አንዳንድ የማኅበራዊ ሚዲያ ባለቤቶች እና ግለሰቦች በአንዳንድ የክልላችን አካባቢዎች ሰልፍ መጥራት እና ለሰላም ማስከብር ሥራው እንቅፋት የኾኑ ቅስቀሳዎችን እያደረጉ ይገኛሉ" ያለው መግለጫው በክልሉ የትኛውም አካባቢ ህጋዊ ጥያቄ ያቀረበም ሆነ ለሰልፍ ፈቃድ ያገኘ እንደሌለም ገልጿል። የክልሉ መገናኛ ብዙኃን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአሥተዳደር ጉዳዮች ክላስተር አስተባባሪ ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር)ን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው "ህግ ማስከበሩ ዋና ዓላማው የክልሉ ህዝብ በሰላም ወጥቶ የመግባትና የመስራት መብት ለማረጋገጥ ነው" ብለዋል። አክለውም "ክልሉ ከወንጀለኞች የፀዳ ኾኖ እና አንድነቱ የተጠበቀ ሕዝብ ኖሮት ሊመጣ የሚችልን ጠላት ኹሉ በብቃት ለመመከት ነው" ማለታቸውን አስፍሯል። በክልሉ አፈና፣ ዝርፊያ፣ ግድያ፣ በሃይማኖት ሰበብ ግጭት ቀስቃሽነት እና ሌሎችም ወንጀሎች በርከት ብለው እንደተስተዋሉና ይህንንም ለመቅረፍ ወደተቀናጀ የሕግ የበላይነት የማረጋገጥ ስራ መገባቱንም ተናግረዋል። ክልሉ የሕግን የበላይነት እንዲረጋገጥና በክልሉ ሰላም እንዲሰፍን እያደረግኩ ነው ባለው ዘመቻም የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ እና ፋኖ በተቀናጀ አሠራር እየተሳተፉ መሆኑንም አስረድተዋል። የአማራ ክልል በግለሰቦች እጅ የሚገኝ የጦር መሳሪያ ምዝገባ እንዲካሄድ ባዘዘው መሰረት ከግንቦት 9፣ 2014 እየተካሄደ ይገኛል። ይህንንም ጥሪ ተከትሎ በርካቶች የጦር መሳሪያ ማስመዝገባቸውን የገለጹት ሰማ ጥሩነህ ምዝገባው በተሰጠው ቀነ ገደብ መጠናቀቅ ባለመቻሉ እስከ ረቡዕ ግንቦት 17፣ 2014 ዓ.ም በሁሉም አካባቢዎች እንዲቀጥል መወሰኑንም አስረድተዋል። | የጋዜጠኞቹ እስርና በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለው ዘመቻ በማህበራዊና በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ የኢትዮጵያ መንግሥትን በመተቸት የምትታወቀው መስከረም አበራ ቅዳሜ እለት፣ ግንቦት 13 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ በቁጥጥር ስር መዋሏን ባለቤቷ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በአዋሳ ዩኒቨርስቲ መምህር የነበረችው መስከረም በቁጥጥር ስር የዋለችው በአዲስ አበባ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲሆን ያለችበትንም ስፍራ እንደማያውቁ ባለቤቷ ተናግረዋል። ይህም በሳምንቱ የታሰሩትን የጋዜጠኞች እና የሚዲያ አካላት ቁጥር ሰባት ያደረሰው ሲሆን ሁኔታውም የተችዎን ድምጽ በማፈኑ ረገድ አዲስ እርምጃ ሊኖር ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል። በያዝነው ሳምንት ሐሙስ ግንቦት 11፣ 2014 ዓ.ም በአማራ ክልል ተቀማጭነቱን ያደረገውና የቅርብ ዘገባቸው በፋኖ ላይ ያተኮረው አሻራ ሚዲያ አምስት ጋዜጠኞቹ በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጿል። ጋዜጠኞቹ የአማራ ልዩ ኃይል፣ የአማራ ፖሊስና የአድማ በታኝ የደንብ ልብስ በለበሱ የጸጥታ አካላት እንደተወሰዱ "ሽንት ቤት ውስጥ ተደብቄ ነበር" ያለ የስራ ባልደረባቸው ለሮይተርስ ተናግሯል። ግለሰቡ በባህርዳር ከተማ የሚገኘው የአሻራ ጽህፈት ቤት መዘጋቱንም ተናግሯል። በተጨማሪም በሃገሪቱ የተካሄደውን ጦርነት በመቃወምና የሰላምና ድርድር መንገዶች የተሻሉ አማራጮች እንደሆኑ በተደጋጋሚ አፅንኦት በመስጠት የሚታወቀው ጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬም መታሰሩ ተዘግቧል። ቢቢሲ የአዲስ አበባን ሆነ የፌደራል ፖሊስን ለማግኘት ቢሞክርም ባለመሳካቱ ምላሻቸውን ለማካተት አልተቻለም። ጋዜጠኞቹ በቁጥር ስር የዋሉት መንግሥት በተለያዩ ክልሎች ህግን የማስከበር ዘመቻ እያካሄደ መሆኑን ባስታወቀ ማግስት ነው። የፌደራል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አርብ ምሽት በአማራ ክልልና በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች እየተወሰደ ያለውን እርምጃ በተመለከተ ባወጣው መግለጫ፣ የሕግ የበላይነትን ማስከበር የዜጎችን ሰላምና ደኅንነት እንዲሁም የአገርን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ብቸኛው መፍትሔ ነው ብሏል። በተለያዩ አካባቢዎች የሚታየውን ሕገ ወጥነትና የሰላም መደፍረስን መንግሥት እንዲቆጣጠር ሕዝቡ በተደጋጋሚ ሲጠይቅ ነበር ያለው መግለጫው፣ ብሔራዊ የፀጥታ ምክር ቤት አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድ መወሰኑን አስታውሷል። የተቃዋሚው አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ዘጠኝ አባላትም እንዲሁ በያዝነው ሳምንት ግንቦት 10፣ 2014 ዓ.ም በሁለት ከተሞች መታሰራቸውን ሮይተርስ በአሜሪካ የሚገኘውን የአማራ ማህበር ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። በተጨማሪም የአብን ፓርቲ አባላትና አመራሮች እስር ተጠናክሮ መቀጠሉን የተለያዩ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ይህንንም ተከትሎ በኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አምስት የአብን አባላት አርብ ዕለት፣ ግንቦት 12፣ 2014 ዓ.ም ባወጡት መግለጫ "መንግሥት እገታና ስወራ" እየፈጸመ ነው ሲሉ ከሰዋል። "በአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን አባላትና አመራሮች፣ በፋኖ አባላት፣ በሕጋዊ ታጣቂዎችና ወጣቶች እንዲሁም አገራቸውንና ሕዝባቸውን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ያገለገሉ የጦር መኮንኖችንና የጸጥታ አመራሮች ላይ የሚፈጸመው መንግስታዊ እገታና ስወራ በአስቸኳይ እንዲቆምና በዚህ ሰበብ በማንነታቸው ብቻ የታገቱ አካላትም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቀቁ እንጠይቃለን፡፡" ብሏል። ከቀናት በፊት አዲስ አበባ ውስጥ መሰወራቸው የተነገረው የቀድሞ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ኃላፊ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ ሞክረዋል በሚል ተጠርጥረው እንደተያዙና በባህርዳር ጠቅላይ ፍርድ ቤት አርብ እለት መቅረባቸው ይታወቃል። ሮይተርስን ጨምሮ ሌሎች ሚዲያዎች ከሰሞኑ ባወጡት ዘገባ በተለያዩ ከተማዎች የሚገኙ የፋኖ አባላት መታሰራቸውንና ሌሎቹንም በቁጥጥር ስር ለማዋል ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑን ዘግበዋል። መግለጫው አክሎም "ህግ ማስከበርን ሰበብ በማድረግ የፌደራል የፀጥታ መዋቅር በሕገ መንግሥቱ ለክልልና ለፌድራል ተለይቶ የተሰጠውን ኃላፊነት እና ሚና በደፈጠጠ መልኩ ክልሉን በሕገ-ወጥ መንገድ ለመቆጣጠር የሚያደርገውን ሙከራ እንዲያቆም" ጠይቋል። የአማራ ክልል ባለስልጣናት በግለሰቦች እጅ የሚገኝ የጦር መሳሪያ እንዲመዘገብ ያደረጉት ጥሪ ትጥቅ ለማስፈታታት ነው ከሚሉ ወጣቶች ጋር ለግጭት መነሻ ሆኗል። "መነሻው ፋኖዎችን ትጥቅ እናስፈታለን በሚሉ የፀጥታ አካላት የተጀመረ ነው። በዚያ ውጥረት ሳቢያ ፋኖዎቹም ትጥቅ አንፈታም በሚል ቦታ ይዘው ነበር" ነበር ያሉት ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ነዋሪ እማኝነታቸውን ሰጥተው፣ ነዋሪዎችም ፋኖ ትጥቅ መፍታት የለበትም በሚል ተቃውሞ አሰምተዋል ብለዋል። በሞጣ ከተማ በጸጥታ ኃይሎች እና በአካባቢው ወጣቶች መካከል በተፈጠረ ግጭት በትንሹ ስድስት ሰዎች መሞታቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይህንንም ተከትትሎ የከተማው አስተዳደር በእንቅስቃሴዎች ላይ ገደብ ከመጣል በተጨማሪ የሰዓት እላፊ አዋጅ ጥሏል። ከዚህም ጋር ተያይዞ የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ቅዳሜ በሰጠው መግለጫ "የሕግ ማስከበር ሥራውን ለማደናቀፍ የሚደረጉ ማንኛውም ድርጊቶች ላይ አስፈላጊው የሕግ እርምጃ" እንደሚወሰድ አስታውቋል። ቢሮው በመግለጫው ካለፉት ቀናት ጀምሮ ተጠርጣሪዎች ያለምንም ግጭት እጃቸውን ለህግ እንዲሰጡ እየተደረገ እንደሆነና ፈቃደኛ ባልሆኑ ግለሰቦች ላይ ጉዳት የመቀነስን ስራ ከህዝቡ ጋር እየተሰራ ነው ብሏል። ህግ ማስከበር ብሎ የጠራው ተግባር ለህዝቡ ሰላም እና ደህንነት፣ ለክልሉ እና ሃገሪቱ የሰላም ዋስትናን ዓላማ አድርጎ እየተከናወነ ባለበት ወቅት የተለያዩ ግለሰቦች "ዋና ጠላቶች" ብሎ ከጠራቸው ጋር በመተባበር ክልሉንና ሃገሪቱን ለማፍረስ የሚሰሩ አካላት እንቅፋት እየሆኑ ይገኛሉ ብሏል። "በአሁኑ ወቅት ከዋና ጠላቶታችን ጋር በማበር ክልላችንን እና ሀገራችንን ለማፍረስ የሚሠሩ አንዳንድ የማኅበራዊ ሚዲያ ባለቤቶች እና ግለሰቦች በአንዳንድ የክልላችን አካባቢዎች ሰልፍ መጥራት እና ለሰላም ማስከብር ሥራው እንቅፋት የኾኑ ቅስቀሳዎችን እያደረጉ ይገኛሉ" ያለው መግለጫው በክልሉ የትኛውም አካባቢ ህጋዊ ጥያቄ ያቀረበም ሆነ ለሰልፍ ፈቃድ ያገኘ እንደሌለም ገልጿል። የክልሉ መገናኛ ብዙኃን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአሥተዳደር ጉዳዮች ክላስተር አስተባባሪ ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር)ን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው "ህግ ማስከበሩ ዋና ዓላማው የክልሉ ህዝብ በሰላም ወጥቶ የመግባትና የመስራት መብት ለማረጋገጥ ነው" ብለዋል። አክለውም "ክልሉ ከወንጀለኞች የፀዳ ኾኖ እና አንድነቱ የተጠበቀ ሕዝብ ኖሮት ሊመጣ የሚችልን ጠላት ኹሉ በብቃት ለመመከት ነው" ማለታቸውን አስፍሯል። በክልሉ አፈና፣ ዝርፊያ፣ ግድያ፣ በሃይማኖት ሰበብ ግጭት ቀስቃሽነት እና ሌሎችም ወንጀሎች በርከት ብለው እንደተስተዋሉና ይህንንም ለመቅረፍ ወደተቀናጀ የሕግ የበላይነት የማረጋገጥ ስራ መገባቱንም ተናግረዋል። ክልሉ የሕግን የበላይነት እንዲረጋገጥና በክልሉ ሰላም እንዲሰፍን እያደረግኩ ነው ባለው ዘመቻም የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ እና ፋኖ በተቀናጀ አሠራር እየተሳተፉ መሆኑንም አስረድተዋል። የአማራ ክልል በግለሰቦች እጅ የሚገኝ የጦር መሳሪያ ምዝገባ እንዲካሄድ ባዘዘው መሰረት ከግንቦት 9፣ 2014 እየተካሄደ ይገኛል። ይህንንም ጥሪ ተከትሎ በርካቶች የጦር መሳሪያ ማስመዝገባቸውን የገለጹት ሰማ ጥሩነህ ምዝገባው በተሰጠው ቀነ ገደብ መጠናቀቅ ባለመቻሉ እስከ ረቡዕ ግንቦት 17፣ 2014 ዓ.ም በሁሉም አካባቢዎች እንዲቀጥል መወሰኑንም አስረድተዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-61540238 |
0business
| ኢትዮጵያ ኢንትርኔትን ስታቋርጥ በየቀኑ 4.5 ሚሊዮን ዶላር ታጣለች | ኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎትን በምታቋርጥባቸው እያንዳንዱ ቀናት በትንሹ ከአራት ሚሊዮን ዶላር በላይ እንደምታጣ የኢንተርኔት ነጻነትና ተደራሽነትን የሚቆጣጠረው ኔትብሎክስ የተባለው ድርጅት ዳይሬክተር ለቢቢሲ ገለጹ። ዳይሬክተሩ እንዳሉት "ኢትዮጵያ ኢንትርኔትን ለአንድ ቀን ስታቋርጥ ከገቢ አንጻር ቢያንስ 4.5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ታጣለች።" ይህም ሌሎች ኪሳራዎችን ሳይጨምር የሚከሰት ጉዳት ሲሆን በተጨማሪ ደግሞ ለኢኮኖሚያዊ እድገት ወሳኝ የሆኑት የመዋዕለ ነዋይ አፍሳሾች ዘንድ እምነት ማጣትን ያስከትላል። ከሁለት ዓመታት በፊት ኢትዮጵያ በኢንትርኔት መቋረጥ ሳቢያ በቀን 500 ሺህ ዶላር ታጣ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በኢንተርኔት የሚንቀሳቀሰው የኢኮኖሚ ክፍል እየሰፋ በመሆኑ የኪሳራው መጠን ከፍ እንዲል እንዳደረገው ይታመናል። • 'የማለዳ ወፍ' ነዎት ወይስ 'የሌሊት'? • ባቡር ላይ የተወለደችው ህጻን ለ25 ዓመታት ነጻ የባቡር ትኬት ተሰጣት • የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፊቱን ወደ ቻይና እያዞረ ይሆን? የኢንተርኔት አገልግሎትን የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች በዋናነት የሚጠቀሙ በመሆኑ በርካታ የአፍሪካ ሃገራት በዚሁ ቴክኖሎጂ ላይ ጥገኛ እየሆኑ እንደሆነ የኢንተርኔት ነጻነትና ተደራሽነትን የሚቆጣጠረው ኔትብሎክስ የተባለው ድርጅት ዳይሬክተር አልፕ ቶከር ተናግረዋል። የአፍሪካ ሃገራት በግለሰብ ደረጃ የሚደረግ የገንዘብ ዝውውርን ጨምሮ ከፍ ያሉ ቁልፍ እንቅስቃሴዎችን ኢንተርኔትን በመጠቀም የሚከውኑ በመሆናቸው ኢትዮጵያን ጨምሮ የአገልግሎቱ መቋረጥ በሚከሰትባቸው ሃገራት ላይ ከፍ ያለ ኢኮኖሚያዊ ጫና እንዳለው አልፕ ይናገራሉ። ኢትዮጵያ ከሁለት ዓመታት በፊት በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ተከስቶ የነበረውን ጸረ መንግሥት ተቃውሞ ለመግታትና የፈተና መሰረቅን ለመቆጣጠር ስትል ለ36 ቀናት ያህል የኢንተርኔት አገልግሎትን በማቋረጧ ከ130 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንዳጣች የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ዓለም አቀፍ የመረጃ ቴክኖሎጂ ፖሊሲ ትብብር የተሰኘው ተቋም አሳውቆ ነበር። በተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት ውስጥ የተለያዩ ችግሮች በተለይ ደግሞ ፖለቲካዊ ቀውሶች ሲያጋጥሙ መንግሥታት በቀዳሚነት የኢንተርኔት አገልግሎት በማቋረጥ ችግሮችን ለመቆጣጠር ጥረት ያደርጋሉ። • ኢትዮጵያ ኢንተርኔትን በመዝጋቷ ከ130 ሚሊዮን ዶላር በላይ አጣች ከሁለት ዓመት በፊት ጀምሮ ኢትዮጵያ ኢንተርኔትን በመዝጋት ከሚታወቁ የአፍሪካ ሃገራት መካከል አንዷ ለመሆን ችላለች። የኢትዮጵያ መንግሥት ለውጥ እንዲያደርግ ያስገደደው ሕዝባዊ ተቃውሞ ካበቃ በኋላ ሆን ተብሎ የተደረገ ሃገር አቀፍ የኢንተርኔት መቋረጥ አላጋጠመም ነበር። በዚህ ሳምንት ግን ሃገር አቀፉ ፈተና ከተጀመረ ከአንድ ቀን በኋላ የኢንትርኔት አገልግሎት በመላው ሃገሪቱ ተቋርጧል። ብልጭ ድርግም እያለ ቆይቶ ባለፉት ሁለት ቀናት ሙሉ ለሙሉ ተቋርጧል። ይህንን በተመለከተም ብቸኛው የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢው መንግሥታዊው ኢትዮቴሌኮምም ሆነ ሌላ የሚመለከተው የመንግሥት አካል የኢንተርኔት አገልግሎት የተቋረጠበትን ምክንያት በይፋ ለመናገር አልደፈሩም። አሁንም ድረስ ለአገልግሎቱ መቋረጥ በርካቶች የሚጠቅሱት ሀገር አቀፉን ፈተና ነው። ቀነኒ ሂኮ በአሰላ ዩኒቨርስቲ የሁለተኛ ዓመት የፋርማሲ ተማሪ ነች። በዩኒቨርስቲ ውስጥ ትምህርት ነክ መረጃዎችን ለመለዋወጥ ያስችላለቸው ዘንድ የትምህርት ክፍሏ ተማሪዎች የቴሌግራም ቡድን አቋቁመው ነበር። በዚህ ቡድን መምህሩ ክፍለ ጊዜ ቢሰርዝ፣ የቤት ሥራ ቢሰጥ ወይንም የተከታታይ ምዘና መምህሩ ቢያቅድ መልእክት ይለዋወጡበታል። አሁን ግን የኢንተርኔት አገልግሎቱ ስለተቋረጠ ምንም ዓይነት መረጃ መለዋወጥ አልቻሉም። ይህ በጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ለሆነው መሐመድ ቃሲምም ተመሳሳይ ነው። የመማር ማስተማሩን ሂደት ያለ ያለኢንትርኔት አገልግሎት ማሰብ ከብዶታል። መረጃ ለመለዋወጥ፣ የተለያዩ የሚሰጡ ሙከራዎችን ለመስራትና በአጠቃላይ ከኢንተርኔት መኖር የሚያገኛችው ጥቅሞች፣ መፅሀፍት ከኢንተርኔት ለማግኘት እንዲሁም የሌክቸር ቪዲዮዎችን ማየት ስላልቻለ ከእለት እቅዱና ትምህርቱ መደናቀፉን ይናገራል። ቀነኒም አክላ በመምህራንና በተማሪዎች መካከል የነበረው ግንኙነት ስለተቋረጠ መቸገራቸውን ትናገራለች። በኢንተርኔት እና የሞባይል አጭር መልዕክት መቋረጥ በባንኮች ላይ ያደሳደረውን ተፅዕኖ ለመጠየቅ የደወልንባቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የኦሮሚያና የዳሸን ባንኮች ስልኮች ባለመስራታቸው ምላሽ ማግኘት አልቻልንም። የአቢሲኒያ ባንክ የማርኬቲንግ፣ የኮሙኑኬሽንና ኦፕሬሽን ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አስቻለው ታምሩ የኢንተርኔት መቋረጡ የእኛ አገልግሎት ላይ ያሳደረው ተፅዕኖ የለም ሲሉ ነግረውናል። "ኢንተርኔቱን በተመለከተ ባንኩ የሚጠቀምበት ቲ24 የተባለ የተለየ የኢንተርኔት መስመር ስላለ እርሱ በአግባቡ እየሰራልን ነው" ብለዋል። ነገር ግን ከባህር ማዶ ገንዘብ ለሚላክላቸው ሰዎች ገንዘቡን በባንካቸው ቅርንጫፍ እንደገባ የሞባይል አጭር መልዕክት የእጣ ቁጥር ይልኩ እንደነበር ያስረዳሉ። አሁን ግን ይህንን ማድረግ ተቸግረናል በማለት የሞባይል የአችር መልዕክት ባለመስራቱ መቸገራቸውን ነግረውናል። | ኢትዮጵያ ኢንትርኔትን ስታቋርጥ በየቀኑ 4.5 ሚሊዮን ዶላር ታጣለች ኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎትን በምታቋርጥባቸው እያንዳንዱ ቀናት በትንሹ ከአራት ሚሊዮን ዶላር በላይ እንደምታጣ የኢንተርኔት ነጻነትና ተደራሽነትን የሚቆጣጠረው ኔትብሎክስ የተባለው ድርጅት ዳይሬክተር ለቢቢሲ ገለጹ። ዳይሬክተሩ እንዳሉት "ኢትዮጵያ ኢንትርኔትን ለአንድ ቀን ስታቋርጥ ከገቢ አንጻር ቢያንስ 4.5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ታጣለች።" ይህም ሌሎች ኪሳራዎችን ሳይጨምር የሚከሰት ጉዳት ሲሆን በተጨማሪ ደግሞ ለኢኮኖሚያዊ እድገት ወሳኝ የሆኑት የመዋዕለ ነዋይ አፍሳሾች ዘንድ እምነት ማጣትን ያስከትላል። ከሁለት ዓመታት በፊት ኢትዮጵያ በኢንትርኔት መቋረጥ ሳቢያ በቀን 500 ሺህ ዶላር ታጣ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በኢንተርኔት የሚንቀሳቀሰው የኢኮኖሚ ክፍል እየሰፋ በመሆኑ የኪሳራው መጠን ከፍ እንዲል እንዳደረገው ይታመናል። • 'የማለዳ ወፍ' ነዎት ወይስ 'የሌሊት'? • ባቡር ላይ የተወለደችው ህጻን ለ25 ዓመታት ነጻ የባቡር ትኬት ተሰጣት • የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፊቱን ወደ ቻይና እያዞረ ይሆን? የኢንተርኔት አገልግሎትን የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች በዋናነት የሚጠቀሙ በመሆኑ በርካታ የአፍሪካ ሃገራት በዚሁ ቴክኖሎጂ ላይ ጥገኛ እየሆኑ እንደሆነ የኢንተርኔት ነጻነትና ተደራሽነትን የሚቆጣጠረው ኔትብሎክስ የተባለው ድርጅት ዳይሬክተር አልፕ ቶከር ተናግረዋል። የአፍሪካ ሃገራት በግለሰብ ደረጃ የሚደረግ የገንዘብ ዝውውርን ጨምሮ ከፍ ያሉ ቁልፍ እንቅስቃሴዎችን ኢንተርኔትን በመጠቀም የሚከውኑ በመሆናቸው ኢትዮጵያን ጨምሮ የአገልግሎቱ መቋረጥ በሚከሰትባቸው ሃገራት ላይ ከፍ ያለ ኢኮኖሚያዊ ጫና እንዳለው አልፕ ይናገራሉ። ኢትዮጵያ ከሁለት ዓመታት በፊት በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ተከስቶ የነበረውን ጸረ መንግሥት ተቃውሞ ለመግታትና የፈተና መሰረቅን ለመቆጣጠር ስትል ለ36 ቀናት ያህል የኢንተርኔት አገልግሎትን በማቋረጧ ከ130 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንዳጣች የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ዓለም አቀፍ የመረጃ ቴክኖሎጂ ፖሊሲ ትብብር የተሰኘው ተቋም አሳውቆ ነበር። በተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት ውስጥ የተለያዩ ችግሮች በተለይ ደግሞ ፖለቲካዊ ቀውሶች ሲያጋጥሙ መንግሥታት በቀዳሚነት የኢንተርኔት አገልግሎት በማቋረጥ ችግሮችን ለመቆጣጠር ጥረት ያደርጋሉ። • ኢትዮጵያ ኢንተርኔትን በመዝጋቷ ከ130 ሚሊዮን ዶላር በላይ አጣች ከሁለት ዓመት በፊት ጀምሮ ኢትዮጵያ ኢንተርኔትን በመዝጋት ከሚታወቁ የአፍሪካ ሃገራት መካከል አንዷ ለመሆን ችላለች። የኢትዮጵያ መንግሥት ለውጥ እንዲያደርግ ያስገደደው ሕዝባዊ ተቃውሞ ካበቃ በኋላ ሆን ተብሎ የተደረገ ሃገር አቀፍ የኢንተርኔት መቋረጥ አላጋጠመም ነበር። በዚህ ሳምንት ግን ሃገር አቀፉ ፈተና ከተጀመረ ከአንድ ቀን በኋላ የኢንትርኔት አገልግሎት በመላው ሃገሪቱ ተቋርጧል። ብልጭ ድርግም እያለ ቆይቶ ባለፉት ሁለት ቀናት ሙሉ ለሙሉ ተቋርጧል። ይህንን በተመለከተም ብቸኛው የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢው መንግሥታዊው ኢትዮቴሌኮምም ሆነ ሌላ የሚመለከተው የመንግሥት አካል የኢንተርኔት አገልግሎት የተቋረጠበትን ምክንያት በይፋ ለመናገር አልደፈሩም። አሁንም ድረስ ለአገልግሎቱ መቋረጥ በርካቶች የሚጠቅሱት ሀገር አቀፉን ፈተና ነው። ቀነኒ ሂኮ በአሰላ ዩኒቨርስቲ የሁለተኛ ዓመት የፋርማሲ ተማሪ ነች። በዩኒቨርስቲ ውስጥ ትምህርት ነክ መረጃዎችን ለመለዋወጥ ያስችላለቸው ዘንድ የትምህርት ክፍሏ ተማሪዎች የቴሌግራም ቡድን አቋቁመው ነበር። በዚህ ቡድን መምህሩ ክፍለ ጊዜ ቢሰርዝ፣ የቤት ሥራ ቢሰጥ ወይንም የተከታታይ ምዘና መምህሩ ቢያቅድ መልእክት ይለዋወጡበታል። አሁን ግን የኢንተርኔት አገልግሎቱ ስለተቋረጠ ምንም ዓይነት መረጃ መለዋወጥ አልቻሉም። ይህ በጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ለሆነው መሐመድ ቃሲምም ተመሳሳይ ነው። የመማር ማስተማሩን ሂደት ያለ ያለኢንትርኔት አገልግሎት ማሰብ ከብዶታል። መረጃ ለመለዋወጥ፣ የተለያዩ የሚሰጡ ሙከራዎችን ለመስራትና በአጠቃላይ ከኢንተርኔት መኖር የሚያገኛችው ጥቅሞች፣ መፅሀፍት ከኢንተርኔት ለማግኘት እንዲሁም የሌክቸር ቪዲዮዎችን ማየት ስላልቻለ ከእለት እቅዱና ትምህርቱ መደናቀፉን ይናገራል። ቀነኒም አክላ በመምህራንና በተማሪዎች መካከል የነበረው ግንኙነት ስለተቋረጠ መቸገራቸውን ትናገራለች። በኢንተርኔት እና የሞባይል አጭር መልዕክት መቋረጥ በባንኮች ላይ ያደሳደረውን ተፅዕኖ ለመጠየቅ የደወልንባቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የኦሮሚያና የዳሸን ባንኮች ስልኮች ባለመስራታቸው ምላሽ ማግኘት አልቻልንም። የአቢሲኒያ ባንክ የማርኬቲንግ፣ የኮሙኑኬሽንና ኦፕሬሽን ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ አስቻለው ታምሩ የኢንተርኔት መቋረጡ የእኛ አገልግሎት ላይ ያሳደረው ተፅዕኖ የለም ሲሉ ነግረውናል። "ኢንተርኔቱን በተመለከተ ባንኩ የሚጠቀምበት ቲ24 የተባለ የተለየ የኢንተርኔት መስመር ስላለ እርሱ በአግባቡ እየሰራልን ነው" ብለዋል። ነገር ግን ከባህር ማዶ ገንዘብ ለሚላክላቸው ሰዎች ገንዘቡን በባንካቸው ቅርንጫፍ እንደገባ የሞባይል አጭር መልዕክት የእጣ ቁጥር ይልኩ እንደነበር ያስረዳሉ። አሁን ግን ይህንን ማድረግ ተቸግረናል በማለት የሞባይል የአችር መልዕክት ባለመስራቱ መቸገራቸውን ነግረውናል። | https://www.bbc.com/amharic/news-48633098 |
2health
| የአውሮፓ ዕለታዊ የኮቪድ ሞት ካለፈው ሳምንት አንጻር 40 በመቶ ከፍ ብሏል | በአውሮፓ በየቀኑ የሚመዘገበው የሞት መጠን ካለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር በ40 በመቶ መጨመሩን የዓለም ጤና ድርጅት ለቢቢሲ ገለጸ። የድርጅቱ ቃል አቀባይ ዶ/ር ማርጋሬት ሃሪስ እንደተናገሩት ፈረንሳይ፣ ስፔን፣ እንግሊዝ፣ ኔዘርላንድስ እና ሩሲያ በአንድ ሦስተኛ ባደገው ቁጥር ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ ይዘዋል። "በሆስፒታሎች ውስጥ የጽኑ ህሙማን የህክምና ክፍሎች በጣም በታመሙ ሰዎች መሞላት ጀምረዋል" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ሩሲያ በቀን 320 የሆነ ከፍተኛ ሞት በማስመዝገብ በአጠቃላይ በቫይረሱ ህይወታቸው ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ26ሺህ በላይ አድርሶታል። ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በ 221 ሰዎች ሞት ምክንያት በጣሊያን ውስጥም እንዲሁ ከፍተኛ ጭማሪ ታይቷል። በአጠቃላይ በኦስትሪያ የሟቾች ቁጥር ማክሰኞ ከ 1000 በላይ ሆኗል። ጣሊያን ውስጥም ቁጥሩ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮ በሃያ አራት ሰዓታት ውስጥ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ወደ 22,000 ደርሰዋል። አዲስ የተጣለውን ገደብ በመቃወም ሰኞ አመሻሽ ላይ የተቃውሞ ሰልፎች በጣሊያን ተካሂደዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ምን አለ? ከቢቢሲ ወርልድ ጋር ቆይታ ያደረጉት ያደረጉት ዶ/ር ሃሪስ "በመላው አውሮፓ የከፋ እና አስደንጋጭ በሆነ መልኩ በቫይረሱ የሚያዙ እና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ጭማሪ እያየን ነው" ብለዋል። ከቀደመው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር በየቀኑ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአንድ ሦስተኛ ሲጨምር የሚመዘገበው የሞት መጠን በ40 በመቶ ከፍ ብሏል። "የሆስፒታሎችን አቅም በተሻለ መንገድ ማስተዳደር ቢቻልም በበርካታ አገራት የሚገኙ ሆስፒታሎች አልጋዎች በፍጥነት እየተያዙ ነው" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። "በተወሰኑ የአውሮፓ አገራት ውስጥ የተጣሉ አዳዲስ ገደቦች ውጤታማነት የሚታወቀው በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ነው" ብለዋል። ሩሲያ ከዛሬ ጀምሮ ሰዎች በሚበዙባቸው እንደ ትራንስፖርት አገልግሎት፣ ታክሲ እና አሳንሰር ያሉ ቦታዎች ላይ የአፍና አፍኝጫ መሸፈኛዎችን ማድረግን አስገዳጅ አድርጋለች። የፈረንሳይ መንግሥት በፓሪስ እና በሌሎች ከተሞች ውስጥ ቀድሞ የተጣሉትን እገዳዎች ማራዘምን ጨምሮ ጥብቅ እርምጃዎችን በመተግበር ላይ እየተወያየ ነው። ጣሊያን ካለፈው አርብ ጀምሮ ምግብና እና መጠጥ ቤቶች፣ የስፖርት መዝወተሪያ ስፍራዎች ና ሲኒማዎች ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ መዘጋታቸውን በመቃወም በቱሪን ሰልፍ ያደረጉ ዜጎች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተው ፖሊስ በሰልፈኞች ላይ አስለቃሽ ጭስ ለመተኮስ ተገዷል። | የአውሮፓ ዕለታዊ የኮቪድ ሞት ካለፈው ሳምንት አንጻር 40 በመቶ ከፍ ብሏል በአውሮፓ በየቀኑ የሚመዘገበው የሞት መጠን ካለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር በ40 በመቶ መጨመሩን የዓለም ጤና ድርጅት ለቢቢሲ ገለጸ። የድርጅቱ ቃል አቀባይ ዶ/ር ማርጋሬት ሃሪስ እንደተናገሩት ፈረንሳይ፣ ስፔን፣ እንግሊዝ፣ ኔዘርላንድስ እና ሩሲያ በአንድ ሦስተኛ ባደገው ቁጥር ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ ይዘዋል። "በሆስፒታሎች ውስጥ የጽኑ ህሙማን የህክምና ክፍሎች በጣም በታመሙ ሰዎች መሞላት ጀምረዋል" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ሩሲያ በቀን 320 የሆነ ከፍተኛ ሞት በማስመዝገብ በአጠቃላይ በቫይረሱ ህይወታቸው ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ26ሺህ በላይ አድርሶታል። ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በ 221 ሰዎች ሞት ምክንያት በጣሊያን ውስጥም እንዲሁ ከፍተኛ ጭማሪ ታይቷል። በአጠቃላይ በኦስትሪያ የሟቾች ቁጥር ማክሰኞ ከ 1000 በላይ ሆኗል። ጣሊያን ውስጥም ቁጥሩ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮ በሃያ አራት ሰዓታት ውስጥ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ወደ 22,000 ደርሰዋል። አዲስ የተጣለውን ገደብ በመቃወም ሰኞ አመሻሽ ላይ የተቃውሞ ሰልፎች በጣሊያን ተካሂደዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ምን አለ? ከቢቢሲ ወርልድ ጋር ቆይታ ያደረጉት ያደረጉት ዶ/ር ሃሪስ "በመላው አውሮፓ የከፋ እና አስደንጋጭ በሆነ መልኩ በቫይረሱ የሚያዙ እና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ጭማሪ እያየን ነው" ብለዋል። ከቀደመው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር በየቀኑ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአንድ ሦስተኛ ሲጨምር የሚመዘገበው የሞት መጠን በ40 በመቶ ከፍ ብሏል። "የሆስፒታሎችን አቅም በተሻለ መንገድ ማስተዳደር ቢቻልም በበርካታ አገራት የሚገኙ ሆስፒታሎች አልጋዎች በፍጥነት እየተያዙ ነው" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። "በተወሰኑ የአውሮፓ አገራት ውስጥ የተጣሉ አዳዲስ ገደቦች ውጤታማነት የሚታወቀው በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ነው" ብለዋል። ሩሲያ ከዛሬ ጀምሮ ሰዎች በሚበዙባቸው እንደ ትራንስፖርት አገልግሎት፣ ታክሲ እና አሳንሰር ያሉ ቦታዎች ላይ የአፍና አፍኝጫ መሸፈኛዎችን ማድረግን አስገዳጅ አድርጋለች። የፈረንሳይ መንግሥት በፓሪስ እና በሌሎች ከተሞች ውስጥ ቀድሞ የተጣሉትን እገዳዎች ማራዘምን ጨምሮ ጥብቅ እርምጃዎችን በመተግበር ላይ እየተወያየ ነው። ጣሊያን ካለፈው አርብ ጀምሮ ምግብና እና መጠጥ ቤቶች፣ የስፖርት መዝወተሪያ ስፍራዎች ና ሲኒማዎች ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ መዘጋታቸውን በመቃወም በቱሪን ሰልፍ ያደረጉ ዜጎች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተው ፖሊስ በሰልፈኞች ላይ አስለቃሽ ጭስ ለመተኮስ ተገዷል። | https://www.bbc.com/amharic/54708506 |
3politics
| የሱዳንን 'አደገኛ' ፖለቲካዊ ቀውስ ለማርገብ አብደላ ሐምዶክ ኮሚቴ አቋቋሙ | ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ በሱዳን ለተከሰተው ፖለቲካዊ ቀውስ መፍትሄ ለመፈለግ የሚያስችል "የቀውስ ጊዜ ኮሚቴ" ማቋቋማቸው ተነገረ። ኦማር ሐሰን አል ባሽር ከሁለት ዓመት በፊት ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አገሪቱን የገጠማት "በጣም አደገኛ" ፖለቲካዊ ቀውስ ነው ያሉትን ችግር ለመፍታት ነው ቡድኑን ያዋቀሩት ሲል የአገሪቱ ዜና ወኪል ሱና ዘግቧል። ትናንት ሰኞ ካርቱም ውስጥ በተካሄደው አስቸኳይ የካቢኔ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ነው የቀውስ ጊዜ ኮሚቴውን ማቋቋማቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ሐምዶክ ያስታወቁት። ሱዳን ለገጠማት ከባድ ፖለቲካዊ ቀውስ መፍትሄ ለማፈላለግና የተጀመረውን የሽግግር ሂደት ለማሳካት በተዋቀረው ኮሚቴ ውስጥ የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካዮችም መካተታቸው ተገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አገሪቱን ወደ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለማሸጋገር የሚደረገውን ጥረት ወደኋላ የመመለስ ስጋትን ፈጥሯል ያሉትን ለሳምንታት የዘለቀ ፖለቲካዊ ውጥረትን ለማርገብ ሁሉም ችግሩን ከሚያባብሱ እርምጃዎች ተቆጥበው ውይይት እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል። ሐምዶክ ይህንን ያሉት በአገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ጠንካራ ተጽእኖ ባለውን የአገሪቱ ጦር ሠራዊት የተደገፈና የሽግግር አስተዳደሩ እንዲወገድና ጦሩ አገሪቱን እንዲመራ የሚጠይቁ ሰልፍ በፖሊስ መበተኑን ተክትሎ ነው። ባለፈው ቅዳሜ የጀመረው የተቃዋሚዎቹ ሰልፍ በርካታ የጦር ኃይሉ ደጋፊ የሆኑ ሱዳናውያን የተሳተፉበት ሲሆን፣ በፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት አካባቢ በመሰባሰብ ጦር ሠራዊቱ ሥልጣን እንዲጨብጥ ጥሪ አድርገው ነበር። ከኦማር አልበሽር ከሥልጣን መወገድ በኋላ በአሁኑ ጊዜ ሱዳን በሲቪልና በወታደሮች ጥምረት በተመሰረተ ሉአላዊ ምክር ቤት አማካይነት በሽግግር መንግሥት እየተመራች ትገኛለች። ባለፈው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ የአገሪቱን የሽግግር ሂደት ለማደናቀፍ ሙከራ የሚያደርጉ ያሏቸውን አካላት አስጠንቅቀው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማስጠንቀቂያውን የሰጡት የአገሪቱን የሽግግር አስተዳደር በሚመራው ሉአላዊ ምክር ቤት ውስጥ ባሉ ወታደራዊና ሲቪል መሪዎች መካከል ያለው አለመግባባት እየተባባሰ ባለበት ጊዜ ነው። ነገር ግን አገሪቱን በሚመራው ሉአላዊ ምክር ቤት ውስጥ ሱዳን በታቀደው መሰረት ወደ ሲቪል አስተዳደር ለመሸጋገር የምታደርገውን ጥረት ለመቀልበስ ከፍተኛ ጥረት የሚያደርጉ የጎላ ተጽእኖና ተሰሚነት ያላቸው የሠራዊቱ አባላት መኖራቸው ይነገራል። ባለፈው መስከረም ወር በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ላይ ተሞክሮ ከከሸፈው መፈንቅለ መንግሥት በኋላ የሽግግር አስተዳደሩን በሚመራው ሉአላዊ ምክር ቤት አባላት መካከል ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል። አገሪቱን ለረጅም ዓመታት በበላይነት የመሩት ኦማር ሐሰን አል ባሽር ከሥልጣን መወገዳቸውን ተከትሎ ከሁለት ዓመት በፊት በአገሪቱ ሠራዊት፣ በሲቪሎች እና ተቃውሞውን በመሩት ቡድኖች መካከል የሥልጣን ክፍፍል መደረጉ ይታወሳል። በዚህም ሲቪሉን በመወከል የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታውን አብደላ ሐምዶክ የያዙ ሲሆን ከሠራዊቱ በኩል ደግሞ የአገሪቱ ሉአላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር በመሆን ሜጀር ጄነራል አብዱል ፋታህ አልቡርሐን ከፍተኛውን ቦታ ይዘዋል። ነገር ግን የሱዳንን የሽግግር አስተዳደር በሚመሩት ወታደራዊና የሲቪል ባለሥልጣናት መካከል ያለው ግንኙነት የሰከነ ሳይሆን ቆይቷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገሪቱ ውስጥ ያለው የደኅንነት ሁኔታ እየተዳከመ የመጣ ሲሆን፣ ምክንያቱም ወታደራዊ መሪዎቹ ሥልጣን የሚያስረክቡበት ወቅትን ለማስተጓጎል ነው ሲሉ ተቺዎች ይናገራሉ። በሜጀር ጄነራል አብዱል ፋታህ አል ቡርሐን የሚመራው ኃያሉ የሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት ለሲቪሎች ሥልጣኑን በመጪው ኅዳር እንዲያስተላልፍ የጊዜ ሰሌዳ ወጥቶለታል። | የሱዳንን 'አደገኛ' ፖለቲካዊ ቀውስ ለማርገብ አብደላ ሐምዶክ ኮሚቴ አቋቋሙ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ በሱዳን ለተከሰተው ፖለቲካዊ ቀውስ መፍትሄ ለመፈለግ የሚያስችል "የቀውስ ጊዜ ኮሚቴ" ማቋቋማቸው ተነገረ። ኦማር ሐሰን አል ባሽር ከሁለት ዓመት በፊት ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አገሪቱን የገጠማት "በጣም አደገኛ" ፖለቲካዊ ቀውስ ነው ያሉትን ችግር ለመፍታት ነው ቡድኑን ያዋቀሩት ሲል የአገሪቱ ዜና ወኪል ሱና ዘግቧል። ትናንት ሰኞ ካርቱም ውስጥ በተካሄደው አስቸኳይ የካቢኔ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ነው የቀውስ ጊዜ ኮሚቴውን ማቋቋማቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ሐምዶክ ያስታወቁት። ሱዳን ለገጠማት ከባድ ፖለቲካዊ ቀውስ መፍትሄ ለማፈላለግና የተጀመረውን የሽግግር ሂደት ለማሳካት በተዋቀረው ኮሚቴ ውስጥ የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካዮችም መካተታቸው ተገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አገሪቱን ወደ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለማሸጋገር የሚደረገውን ጥረት ወደኋላ የመመለስ ስጋትን ፈጥሯል ያሉትን ለሳምንታት የዘለቀ ፖለቲካዊ ውጥረትን ለማርገብ ሁሉም ችግሩን ከሚያባብሱ እርምጃዎች ተቆጥበው ውይይት እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል። ሐምዶክ ይህንን ያሉት በአገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ጠንካራ ተጽእኖ ባለውን የአገሪቱ ጦር ሠራዊት የተደገፈና የሽግግር አስተዳደሩ እንዲወገድና ጦሩ አገሪቱን እንዲመራ የሚጠይቁ ሰልፍ በፖሊስ መበተኑን ተክትሎ ነው። ባለፈው ቅዳሜ የጀመረው የተቃዋሚዎቹ ሰልፍ በርካታ የጦር ኃይሉ ደጋፊ የሆኑ ሱዳናውያን የተሳተፉበት ሲሆን፣ በፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት አካባቢ በመሰባሰብ ጦር ሠራዊቱ ሥልጣን እንዲጨብጥ ጥሪ አድርገው ነበር። ከኦማር አልበሽር ከሥልጣን መወገድ በኋላ በአሁኑ ጊዜ ሱዳን በሲቪልና በወታደሮች ጥምረት በተመሰረተ ሉአላዊ ምክር ቤት አማካይነት በሽግግር መንግሥት እየተመራች ትገኛለች። ባለፈው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ የአገሪቱን የሽግግር ሂደት ለማደናቀፍ ሙከራ የሚያደርጉ ያሏቸውን አካላት አስጠንቅቀው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማስጠንቀቂያውን የሰጡት የአገሪቱን የሽግግር አስተዳደር በሚመራው ሉአላዊ ምክር ቤት ውስጥ ባሉ ወታደራዊና ሲቪል መሪዎች መካከል ያለው አለመግባባት እየተባባሰ ባለበት ጊዜ ነው። ነገር ግን አገሪቱን በሚመራው ሉአላዊ ምክር ቤት ውስጥ ሱዳን በታቀደው መሰረት ወደ ሲቪል አስተዳደር ለመሸጋገር የምታደርገውን ጥረት ለመቀልበስ ከፍተኛ ጥረት የሚያደርጉ የጎላ ተጽእኖና ተሰሚነት ያላቸው የሠራዊቱ አባላት መኖራቸው ይነገራል። ባለፈው መስከረም ወር በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ላይ ተሞክሮ ከከሸፈው መፈንቅለ መንግሥት በኋላ የሽግግር አስተዳደሩን በሚመራው ሉአላዊ ምክር ቤት አባላት መካከል ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል። አገሪቱን ለረጅም ዓመታት በበላይነት የመሩት ኦማር ሐሰን አል ባሽር ከሥልጣን መወገዳቸውን ተከትሎ ከሁለት ዓመት በፊት በአገሪቱ ሠራዊት፣ በሲቪሎች እና ተቃውሞውን በመሩት ቡድኖች መካከል የሥልጣን ክፍፍል መደረጉ ይታወሳል። በዚህም ሲቪሉን በመወከል የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታውን አብደላ ሐምዶክ የያዙ ሲሆን ከሠራዊቱ በኩል ደግሞ የአገሪቱ ሉአላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር በመሆን ሜጀር ጄነራል አብዱል ፋታህ አልቡርሐን ከፍተኛውን ቦታ ይዘዋል። ነገር ግን የሱዳንን የሽግግር አስተዳደር በሚመሩት ወታደራዊና የሲቪል ባለሥልጣናት መካከል ያለው ግንኙነት የሰከነ ሳይሆን ቆይቷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገሪቱ ውስጥ ያለው የደኅንነት ሁኔታ እየተዳከመ የመጣ ሲሆን፣ ምክንያቱም ወታደራዊ መሪዎቹ ሥልጣን የሚያስረክቡበት ወቅትን ለማስተጓጎል ነው ሲሉ ተቺዎች ይናገራሉ። በሜጀር ጄነራል አብዱል ፋታህ አል ቡርሐን የሚመራው ኃያሉ የሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት ለሲቪሎች ሥልጣኑን በመጪው ኅዳር እንዲያስተላልፍ የጊዜ ሰሌዳ ወጥቶለታል። | https://www.bbc.com/amharic/news-58966846 |
5sports
| እግር ኳስ ፡ ለጡረታ እየተዘጋጁ ያሉት የ80 ዓመቱ እግር ኳስ ተጫዋች | ለእግር ኳስ ጥልቅ ፍቅር ያላቸው የ80 አመቱ የእድሜ ባለፀጋ እግር ኳስ ተጫዋች ከሰሞኑ የመጨረሻ ጨዋታዬን አደርጋለሁ ብለዋል። በአውስትራሊያ ነዋሪነታቸውን ያደረጉት እንግሊዛዊው ፒተር ዌብስተር ለጡረታም መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል። በባለፉት ጥቂት አመታት አቅማቸው ደክሞ ከዚህ ቀደም በነበራቸው የሰውነት አቋም ባለመሆናቸውም ከሚወዱት የእግር ኳስ ጨዋታ ለመገለልም ምክንያት ሆኗቸዋል። "ለባለፉት ጥቂት አመታት በእንደዚሁ አይነት ሁኔታ የነበርኩት። የምለብሰውንም ማልያ እያባከንኩ መሰለኝ" በማለትም ለቢቢሲ ተናግረዋል። ፒተር ዌብስተር የተወለዱት በጎሮጎሳውያኑ አቆጣጠር 1948 በእንግሊዟ ፕሬስተን ነው። በህፃንነታቸው ራግቢና እግርኳስ ይጫወቱ የነበረ ሲሆን በተለይም ከአስራ አምስት አመታቸው በኋላ ዝንባሌያቸው ወደ እግር ኳስ ሆነ። በፕሮፌሽናል ተጫዋችነትም በዌልስ ለሚገኙ ክለቦች በሃያዎቹና በሰላሳዎቹ እድሜያቸው ተጫውተዋል። በ1981ም ከባለቤታቸውና ከሶስት ልጃቸው ጋር ወደ አውስትራሊያ የሄዱ ሲሆን እዚያም ባለው የእግር ኳስ ደረጃ ከፍተኛ መሆን አድናቆትን እንደፈጠረባቸውም ከሰሞኑ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል። ለአስርት አመታትም በአውስትራሊያ ፊግትሪ የእግር ኳስ ክለብም ተጫውተዋል። የመጨረሻ ጨዋታቸውንም በያዝነው ሳምንት አርብ እለት እንዳደረጉም ተዘግቧል። በክለቡም ሆነ በአካባቢው ከፍተኛ ዝናን ያተረፉት ፒተር በሳቸውም ስም ውድድር ተሰይሞላቸዋል- ፒተር ዌብስተር ካፕ የሚባል። "እንዲህ አይነት ውድድሮች በስም የሚሰየሙት አንድ ሰው ገንዘብ ከከፈለ ወይም ከሞተ ነው። እኔ አልሞትኩምም አልከፈልኩም፤ እስቲ በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ እሞክራለሁ" ብለዋል። ለረዥም አመታት በእግር ኳስ ተጫዋችነታቸው ለመቆየት ሚስጥሩ ሳያቋርጡ መጫወታቸውና ከፍተኛ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረጋቸው ነው። ለአመታትም ሩጫ፣ ሳይክል መንዳትን ያዘወትሩ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ግን ከእድሜ ጋር ተያይዞ የልጅ ልጃቸውን ውሻ ይዘው ለመራመድ ይወጣሉ። ምንም እንኳን እግር ኳስ ከመጫወት ራሳቸውን ቢያገሉም የልጅ ልጆቻቸው እግር ኳስ ሲጫወቱም እመለከታለሁ ብለዋል። ከዚህ ቀደም ራሳቸው ጨዋታ ስለነበራቸው የነሱን ጨዋታ መመልከት አልቻሉም ነበር። ባለቤታቸውም በቤት ስራዎች እንዲያግዙዋቸው ጡረታ የሚወጡበትን ቀን በጉጉት እየጠበቀች እንደሆነም ተናግረዋል። የፊግ ትሪ የእግር ኳስ ክለብ ፕሬዚዳንት ማይክ ዶድ የእድሜ ባለፀጋው እግር ኳስ ተጫዋች አስተዋፅኦ "ከቃላት በላይ ነው" በማለትም አሞግሰዋቸዋል። | እግር ኳስ ፡ ለጡረታ እየተዘጋጁ ያሉት የ80 ዓመቱ እግር ኳስ ተጫዋች ለእግር ኳስ ጥልቅ ፍቅር ያላቸው የ80 አመቱ የእድሜ ባለፀጋ እግር ኳስ ተጫዋች ከሰሞኑ የመጨረሻ ጨዋታዬን አደርጋለሁ ብለዋል። በአውስትራሊያ ነዋሪነታቸውን ያደረጉት እንግሊዛዊው ፒተር ዌብስተር ለጡረታም መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል። በባለፉት ጥቂት አመታት አቅማቸው ደክሞ ከዚህ ቀደም በነበራቸው የሰውነት አቋም ባለመሆናቸውም ከሚወዱት የእግር ኳስ ጨዋታ ለመገለልም ምክንያት ሆኗቸዋል። "ለባለፉት ጥቂት አመታት በእንደዚሁ አይነት ሁኔታ የነበርኩት። የምለብሰውንም ማልያ እያባከንኩ መሰለኝ" በማለትም ለቢቢሲ ተናግረዋል። ፒተር ዌብስተር የተወለዱት በጎሮጎሳውያኑ አቆጣጠር 1948 በእንግሊዟ ፕሬስተን ነው። በህፃንነታቸው ራግቢና እግርኳስ ይጫወቱ የነበረ ሲሆን በተለይም ከአስራ አምስት አመታቸው በኋላ ዝንባሌያቸው ወደ እግር ኳስ ሆነ። በፕሮፌሽናል ተጫዋችነትም በዌልስ ለሚገኙ ክለቦች በሃያዎቹና በሰላሳዎቹ እድሜያቸው ተጫውተዋል። በ1981ም ከባለቤታቸውና ከሶስት ልጃቸው ጋር ወደ አውስትራሊያ የሄዱ ሲሆን እዚያም ባለው የእግር ኳስ ደረጃ ከፍተኛ መሆን አድናቆትን እንደፈጠረባቸውም ከሰሞኑ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል። ለአስርት አመታትም በአውስትራሊያ ፊግትሪ የእግር ኳስ ክለብም ተጫውተዋል። የመጨረሻ ጨዋታቸውንም በያዝነው ሳምንት አርብ እለት እንዳደረጉም ተዘግቧል። በክለቡም ሆነ በአካባቢው ከፍተኛ ዝናን ያተረፉት ፒተር በሳቸውም ስም ውድድር ተሰይሞላቸዋል- ፒተር ዌብስተር ካፕ የሚባል። "እንዲህ አይነት ውድድሮች በስም የሚሰየሙት አንድ ሰው ገንዘብ ከከፈለ ወይም ከሞተ ነው። እኔ አልሞትኩምም አልከፈልኩም፤ እስቲ በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ እሞክራለሁ" ብለዋል። ለረዥም አመታት በእግር ኳስ ተጫዋችነታቸው ለመቆየት ሚስጥሩ ሳያቋርጡ መጫወታቸውና ከፍተኛ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረጋቸው ነው። ለአመታትም ሩጫ፣ ሳይክል መንዳትን ያዘወትሩ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ግን ከእድሜ ጋር ተያይዞ የልጅ ልጃቸውን ውሻ ይዘው ለመራመድ ይወጣሉ። ምንም እንኳን እግር ኳስ ከመጫወት ራሳቸውን ቢያገሉም የልጅ ልጆቻቸው እግር ኳስ ሲጫወቱም እመለከታለሁ ብለዋል። ከዚህ ቀደም ራሳቸው ጨዋታ ስለነበራቸው የነሱን ጨዋታ መመልከት አልቻሉም ነበር። ባለቤታቸውም በቤት ስራዎች እንዲያግዙዋቸው ጡረታ የሚወጡበትን ቀን በጉጉት እየጠበቀች እንደሆነም ተናግረዋል። የፊግ ትሪ የእግር ኳስ ክለብ ፕሬዚዳንት ማይክ ዶድ የእድሜ ባለፀጋው እግር ኳስ ተጫዋች አስተዋፅኦ "ከቃላት በላይ ነው" በማለትም አሞግሰዋቸዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54406746 |
5sports
| ኢትዮጵያዊው የእግር ኳስ ኮከብ አቡበከር ከደቡብ አፍሪካ ክለብ ጋር ከስምምነት መድረሱ ተነገረ | ወጣቱ ኢትዮጵያዊ የእግር ኳስ ኮከብ አቡበከር ናስር ለደቡብ አፍሪካው ክለብ ለመጫወት ከስምምነት መድረሱ ተነገረ። ያለፈው ዓመት የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ኮከብ ግብ አግቢ የሆነው የኢትዮጵያ ቡና አጥቂው አቡበካር ናስር ከስምምነት የደረሰው ከደቡብ አፍሪካው ኃያል ቡድን ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ጋር ነው። አቡበካር በኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ለታዋቂው ኢትዮጵያ ቡና ቡድን ከመጫወቱ ባሻገር ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተመርጦ ካሜሩን እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ በሦስት ጨዋታዎች ተሰልፏል። የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ፕሬዝደንት የሆኑት ፈቃደ ማሞ ትናንት ምሽት በአንድ ዝግጅት ላይ አቡበከር 'ብራዚላውያኑ' በሚል ቅጽል ስያሜ ወደ ሚታወቁት ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ክለብ ዝውውር ያደርጋል የተባለውን ዜና አረጋግጠዋል። አቡበካር ወደ ደቡብ አፍሪካው እግር ኳስ ክለብ በምን ያህል ክፍያ እንደሚያቀና አስካሁን የተባለ ነገር የለም። የክለቡ ዋና ሥራ አስኪያጅ ገዛኸኝ ወልዴ ተጫዋቹ የተዘዋወረበትን የገንዘብ መጠን ይፋ ባያደርጉም ክፍያው ከፍተኛ እንደሆነ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል። የደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ ፕሪሚዬር ሊግን እየመራ የሚገኘው ኃያሉ ክለብ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ስለአቡበካር ዝውውርና ሌሎች ጉዳዩን የሚመለከት ዝርዝር መረጃ አስካሁን አላወጣም። 'ብራዚላዊያኑ' አቡበከርን እስከውድድር ዓመቱ መጨረሻ ድረስ ለቡና በውሰት መልሰው ሊሰጡት እንደሚችሉም ተዘግቧል። የ21 ዓመቱ ወጣት እግር ኳስ ተጫዋች አቡበከር ናስር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ጨዋታ መሰናበቱን ተከትሎ ከደቡብ አፍሪካው ቡድን ጋር የሙከራ ጊዜ ማሳለፉ ይታወሳል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት ጎል የተሰኘው ታዋቂ የእግር ኳስ ድረ-ገፅ ሌላኛው የደቡብ አፍሪካ ቡድን ካይዘር ቺፍስ አቡባካርን ለማስፈረም እንደሚፈልግ አስነብቦ ነበር። ከዚህ በፊት ጌታነህ ከበደና ፍቅሩ ተፈራ ለደቡብ አፍሪካ ክለቦች መጫወታቸው አይዘነጋም። | ኢትዮጵያዊው የእግር ኳስ ኮከብ አቡበከር ከደቡብ አፍሪካ ክለብ ጋር ከስምምነት መድረሱ ተነገረ ወጣቱ ኢትዮጵያዊ የእግር ኳስ ኮከብ አቡበከር ናስር ለደቡብ አፍሪካው ክለብ ለመጫወት ከስምምነት መድረሱ ተነገረ። ያለፈው ዓመት የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ኮከብ ግብ አግቢ የሆነው የኢትዮጵያ ቡና አጥቂው አቡበካር ናስር ከስምምነት የደረሰው ከደቡብ አፍሪካው ኃያል ቡድን ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ጋር ነው። አቡበካር በኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ለታዋቂው ኢትዮጵያ ቡና ቡድን ከመጫወቱ ባሻገር ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተመርጦ ካሜሩን እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ በሦስት ጨዋታዎች ተሰልፏል። የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ፕሬዝደንት የሆኑት ፈቃደ ማሞ ትናንት ምሽት በአንድ ዝግጅት ላይ አቡበከር 'ብራዚላውያኑ' በሚል ቅጽል ስያሜ ወደ ሚታወቁት ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ክለብ ዝውውር ያደርጋል የተባለውን ዜና አረጋግጠዋል። አቡበካር ወደ ደቡብ አፍሪካው እግር ኳስ ክለብ በምን ያህል ክፍያ እንደሚያቀና አስካሁን የተባለ ነገር የለም። የክለቡ ዋና ሥራ አስኪያጅ ገዛኸኝ ወልዴ ተጫዋቹ የተዘዋወረበትን የገንዘብ መጠን ይፋ ባያደርጉም ክፍያው ከፍተኛ እንደሆነ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል። የደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ ፕሪሚዬር ሊግን እየመራ የሚገኘው ኃያሉ ክለብ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ስለአቡበካር ዝውውርና ሌሎች ጉዳዩን የሚመለከት ዝርዝር መረጃ አስካሁን አላወጣም። 'ብራዚላዊያኑ' አቡበከርን እስከውድድር ዓመቱ መጨረሻ ድረስ ለቡና በውሰት መልሰው ሊሰጡት እንደሚችሉም ተዘግቧል። የ21 ዓመቱ ወጣት እግር ኳስ ተጫዋች አቡበከር ናስር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ጨዋታ መሰናበቱን ተከትሎ ከደቡብ አፍሪካው ቡድን ጋር የሙከራ ጊዜ ማሳለፉ ይታወሳል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት ጎል የተሰኘው ታዋቂ የእግር ኳስ ድረ-ገፅ ሌላኛው የደቡብ አፍሪካ ቡድን ካይዘር ቺፍስ አቡባካርን ለማስፈረም እንደሚፈልግ አስነብቦ ነበር። ከዚህ በፊት ጌታነህ ከበደና ፍቅሩ ተፈራ ለደቡብ አፍሪካ ክለቦች መጫወታቸው አይዘነጋም። | https://www.bbc.com/amharic/news-60227690 |
2health
| ኢንስታግራም 'ክብደት ጨማሪ ክኒን' በማስተዋወቁ ውግዘት ገጠመው | ኢንስትግራም ክብደትን የሚጨምሩ መድሃኒቶችን በሚያስተዋውቁ ተጠቃሚዎቹ ላይ እርምጃ እንዲወስድ ተጠየቀ። ኢንስታግራም ወጣት ሴቶችን አላማ አድርገው ፍቃድ የሌላቸውና 'አደገኛ' የሆኑ ክብደት ለመጨመር የሚያግዙ መደሃኒቶችን የሚሸጡ ተጠቃሚዎቹን አደብ እንዲያስገዛ የእንግሊዝ ብሄራዊ የጤና አገልግሎት አሳሰበ። 'አፒታሚን' የተሰኘው የሰውነትን ክብደት የሚጨምር እንክብል በእንግሊዝ ምድር የታገደ ቢሆንም በበይነ መረብና ሱቆች ውስጥ እንደሚሸጥ ቢቢሲ 3 አጋልጧል። እናም የሀገሪቱ የጤና አገልግሎት እንክብሎቹ ማስተዋወቅ አካላዊና አዕምሯዊ ጤንነት ላይ ያለውን ስጋት ይፋዊ በሆነ ደብዳቤ ገልፃል። ኢንስታግራም ደግሞ ህመሞችን ለመፈወስ ከሚውሉ በስተቀር መድሃኒቶችን መሸጥ 'ከፓሊሲያችን ጋር በእጅጉ የሚቃረን ነው' ብሏል። የምግብ ፍላጎትን በመጨመር የሰውነት ክብደትን የሚየጨምረው 'አፒታሚን' የጉበት ስራ ማቆምን ጨምሮ ለተለያዩ የጤና እክሎች እንደሚዳርግ የጤና ባለሙያዎች ያስረዳሉ። ሆኖም ይህ መድሃኒት በርከት ያሉ ተከታዮች ባሏቸው የኢንስታግራም ተጠቃሚዎች በቋሚነት እየተዋወቀ ይገኛል ተብሏል። ኢንስታግራም በበኩሉ ይህን መድሃኒት ያስተዋወቁና የሸጡ ተጠቃሚዎቹን አካውንት ዘግቻለሁ ሲል ይህንን ጉዳይ ላጋለጠው ቢቢሲ 3 ገልጿል። ሆኖም የእንግሊዝ የጤና አገልግሎት በርከት ያሉ አካውንቶች አሁንም አሉ ያለ ሲሆን ሪፓርት ቢደረግም ኢንስታግራም እርምጃ አይወስድም ነበር ሲል ከሷል። | ኢንስታግራም 'ክብደት ጨማሪ ክኒን' በማስተዋወቁ ውግዘት ገጠመው ኢንስትግራም ክብደትን የሚጨምሩ መድሃኒቶችን በሚያስተዋውቁ ተጠቃሚዎቹ ላይ እርምጃ እንዲወስድ ተጠየቀ። ኢንስታግራም ወጣት ሴቶችን አላማ አድርገው ፍቃድ የሌላቸውና 'አደገኛ' የሆኑ ክብደት ለመጨመር የሚያግዙ መደሃኒቶችን የሚሸጡ ተጠቃሚዎቹን አደብ እንዲያስገዛ የእንግሊዝ ብሄራዊ የጤና አገልግሎት አሳሰበ። 'አፒታሚን' የተሰኘው የሰውነትን ክብደት የሚጨምር እንክብል በእንግሊዝ ምድር የታገደ ቢሆንም በበይነ መረብና ሱቆች ውስጥ እንደሚሸጥ ቢቢሲ 3 አጋልጧል። እናም የሀገሪቱ የጤና አገልግሎት እንክብሎቹ ማስተዋወቅ አካላዊና አዕምሯዊ ጤንነት ላይ ያለውን ስጋት ይፋዊ በሆነ ደብዳቤ ገልፃል። ኢንስታግራም ደግሞ ህመሞችን ለመፈወስ ከሚውሉ በስተቀር መድሃኒቶችን መሸጥ 'ከፓሊሲያችን ጋር በእጅጉ የሚቃረን ነው' ብሏል። የምግብ ፍላጎትን በመጨመር የሰውነት ክብደትን የሚየጨምረው 'አፒታሚን' የጉበት ስራ ማቆምን ጨምሮ ለተለያዩ የጤና እክሎች እንደሚዳርግ የጤና ባለሙያዎች ያስረዳሉ። ሆኖም ይህ መድሃኒት በርከት ያሉ ተከታዮች ባሏቸው የኢንስታግራም ተጠቃሚዎች በቋሚነት እየተዋወቀ ይገኛል ተብሏል። ኢንስታግራም በበኩሉ ይህን መድሃኒት ያስተዋወቁና የሸጡ ተጠቃሚዎቹን አካውንት ዘግቻለሁ ሲል ይህንን ጉዳይ ላጋለጠው ቢቢሲ 3 ገልጿል። ሆኖም የእንግሊዝ የጤና አገልግሎት በርከት ያሉ አካውንቶች አሁንም አሉ ያለ ሲሆን ሪፓርት ቢደረግም ኢንስታግራም እርምጃ አይወስድም ነበር ሲል ከሷል። | https://www.bbc.com/amharic/news-56972154 |
5sports
| የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በቶኪዮ አየር ማረፊያ ያጋጠመው ምን ነበር? | በቶኪዮ ኦሊምፒክ ለመሳተፍ ወደ ጃፓን ያመራው የመጀመሪያ ዙር የኢትዮጵያ ቡደን ቶኪዮ አየር ማረፊያ ከደረሰ በኋላ ለሰዓታት በአየር ማረፊያ እንዲቆይ መደረጉ ተገልጿል። በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ማክስኞ አመሻሽ ወደ ቶኪዮ የበረረው ቡድኑ፤ የኮቪድ-19 ምርመራ ሰርተፊኬቶች ሲመረመሩ እና በአየር ማረፊያ የተደረገው ፈጣን የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤት እስኪመጣ ድረስ ለሰዓታት በአየር ማረፊያ ለመቆየት መገደዱ ተነግሯል። ከቡድኑ ጋር አብራ የተጓዘችው ጋዜጠኛ አርያት ራያ የኢትዮጵያ ልዑክ በበረረበት አውሮፕላን ውስጥ ተሳፋሪ ከነበሩት አትሌቶች መካከል የአንጎላ ዜግነት ያለው አንድ አትሌት በኮቪድ-19 መያዙ መረጋገጡን ተከትሎ ለሌላ ተጨማሪ ሰዓት በአየር ማረፊያው ለመቆየት መገደዳቸውን ለቢቢሲ አስረድታለች። በረራው ረዥም ነበር የምትለው ጋዜጠኛ አርያት፤ በደቡብ ኮሪያ በኩል ትራንዚት አድርገው ቶኪዮ ለመድረስ ከ15 ሰዓታት በላይ መውሰዱን ታስረዳለች። "ብዙ ነበርን። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ብቻ አልነበረም። የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ቡድን፣ የማደጋስካር፣ የታንዛኒያ፣ የአንጎላ ብሔራዊ ቡድን አባላትም ከእኛ ጋር ነበሩ። ብዙ ስፖርተኛ ነበር። ያ ሁሉ የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረግ ነበረበት" ያለችው አርያት፤ የኤርፖርቱ ኃላፊዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ እያደረጉ ስለነበረ የኮቪድ-19 ምርመራውን በፍጥነት እያከናወኑ አልነበረም ትላለች። "ፓስፖርት አይተው እስኪያጣሩ፤ ይዘን የሄድነውን የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤት እስኪያረጋግጡ እና የኮቪድ-19 ውጤታችን እስኪመጣ ድረስ ረዥም ሰዓት ነው የወሰደው። ወደ ሰባት ሰዓት ያህል አየር ማረፊያ ውስጥ ቆይተን ነበረ። ምርመራ ጨርሰን፤ ውጤታችንን አይተን ልንወጣ ስንልን አንድ የአንጎላ አትሌት ውጤቱ ፖዘቲቭ ሆነ ተብሎ እንደገና ትንሽ ቆይታ አድርገን ነው የወጣነው" ብላለች። በመጀመሪያ ዙር ወደ ቶኪዮ ካቀኑት መካከል የኢፌድሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ሂሩት ካሳው (ዶ/ር)፣ የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ኤሊያስ ሽኩር፤ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት አሸብር ወልደጊዮርጊስ (ዶ/ር) እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ይገኙበታል። | የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በቶኪዮ አየር ማረፊያ ያጋጠመው ምን ነበር? በቶኪዮ ኦሊምፒክ ለመሳተፍ ወደ ጃፓን ያመራው የመጀመሪያ ዙር የኢትዮጵያ ቡደን ቶኪዮ አየር ማረፊያ ከደረሰ በኋላ ለሰዓታት በአየር ማረፊያ እንዲቆይ መደረጉ ተገልጿል። በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ማክስኞ አመሻሽ ወደ ቶኪዮ የበረረው ቡድኑ፤ የኮቪድ-19 ምርመራ ሰርተፊኬቶች ሲመረመሩ እና በአየር ማረፊያ የተደረገው ፈጣን የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤት እስኪመጣ ድረስ ለሰዓታት በአየር ማረፊያ ለመቆየት መገደዱ ተነግሯል። ከቡድኑ ጋር አብራ የተጓዘችው ጋዜጠኛ አርያት ራያ የኢትዮጵያ ልዑክ በበረረበት አውሮፕላን ውስጥ ተሳፋሪ ከነበሩት አትሌቶች መካከል የአንጎላ ዜግነት ያለው አንድ አትሌት በኮቪድ-19 መያዙ መረጋገጡን ተከትሎ ለሌላ ተጨማሪ ሰዓት በአየር ማረፊያው ለመቆየት መገደዳቸውን ለቢቢሲ አስረድታለች። በረራው ረዥም ነበር የምትለው ጋዜጠኛ አርያት፤ በደቡብ ኮሪያ በኩል ትራንዚት አድርገው ቶኪዮ ለመድረስ ከ15 ሰዓታት በላይ መውሰዱን ታስረዳለች። "ብዙ ነበርን። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ብቻ አልነበረም። የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ቡድን፣ የማደጋስካር፣ የታንዛኒያ፣ የአንጎላ ብሔራዊ ቡድን አባላትም ከእኛ ጋር ነበሩ። ብዙ ስፖርተኛ ነበር። ያ ሁሉ የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረግ ነበረበት" ያለችው አርያት፤ የኤርፖርቱ ኃላፊዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ እያደረጉ ስለነበረ የኮቪድ-19 ምርመራውን በፍጥነት እያከናወኑ አልነበረም ትላለች። "ፓስፖርት አይተው እስኪያጣሩ፤ ይዘን የሄድነውን የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤት እስኪያረጋግጡ እና የኮቪድ-19 ውጤታችን እስኪመጣ ድረስ ረዥም ሰዓት ነው የወሰደው። ወደ ሰባት ሰዓት ያህል አየር ማረፊያ ውስጥ ቆይተን ነበረ። ምርመራ ጨርሰን፤ ውጤታችንን አይተን ልንወጣ ስንልን አንድ የአንጎላ አትሌት ውጤቱ ፖዘቲቭ ሆነ ተብሎ እንደገና ትንሽ ቆይታ አድርገን ነው የወጣነው" ብላለች። በመጀመሪያ ዙር ወደ ቶኪዮ ካቀኑት መካከል የኢፌድሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ሂሩት ካሳው (ዶ/ር)፣ የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ኤሊያስ ሽኩር፤ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት አሸብር ወልደጊዮርጊስ (ዶ/ር) እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ይገኙበታል። | https://www.bbc.com/amharic/57931331 |
2health
| አዘውትሮ ምሽት አራት ሰዓት አካባቢ መተኛት ለልብ ችግር የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል- ጥናት | ከምሽቱ 4 ሰዓት እስከ 5 ሰዓት ባለው ጊዜ አዘውትሮ መተኛት ለተሻለ የልብ ጤንነት እንደሚረዳ በ88 ሺህ በጎ ፈቃደኞች ላይ ጥናት ያደረጉ ተመራማሪዎች አስታወቁ። በዩናይትድ ኪንግደም ባለ አንድ ቡድን በተደረገ ጥናት እንቅልፍ ከውስጣዊው የሰውነት ክፍላችን የጊዜ አቆጣጠር ጋር እንዲጣታም ማድረግ ለልብ ድካም እና ለስትሮክ የመጋለጥ እድልን እንደሚቀንስ ጠቁሟል። የሰውነት ተፈጥሯዊ የ24-ሰዓት ምት ለደኅንነት እና ንቁ ለመሆን አስፈላጊ መሆኑን የሚገልጸው ጥናቱ እንደ የደም ግፊት ባሉ ሂደቶች ላይም ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል ይላል። በአውሮፓ የልብ ጤና ጆርናል ላይ በታተመው በዚህ ጥናት ተመራማሪዎቹ በሰባት ቀናት ውስጥ በእንቅልፍ እና በእንቅልፍ ጊዜ ላይ ከጥናቱ ተሳታፊዎች መረጃን ለማሰባሰብ የእጅ ሰዓት የሚመስል መሳሪያ እንዲያጠልቁ አድርገዋቸዋል። በመሳሪያው አማካኝነት በአማካይ በስድስት ዓመታት ውስጥ በልብ እና በደም ዝውውር ጤና ላይ ያለውን ሁኔታ ተከታትለዋል። በዚህም ከ3,000 በላይ የሚሆኑ ተሳታፊዎች የልብ ችግር [የካርዲዮቫስኩላር] በሽታ ተገኝቶባቸዋል። በጥናቱ መሰረት ለዚህ ችግር የተጋለጡት ከምሽቱ 4 ወይም 5 ሰዓት ቀደም ብለው ወይም ዘግይተው ወደ አልጋ የማምራት ልምድ ያላቸው ሰዎች ላይ ነው። ተመራማሪዎቹ እንደ ዕድሜ፣ የሰውነት ክብደት እና የኮሌስትሮል መጠን ያሉ የአንድን ሰው ለልብ ስጋት የሆኑ ሌሎች ነገሮችን ለማየት ሞክረዋል። ነገርግን ጥናታቸው መንስኤውንና ውጤቱን ማረጋገጥ አልቻለም። ተመራማሪዎቹ እንደ ዕድሜ፣ የሰውነት ክብደት እና የኮሌስትሮል መጠን ያሉ አንድን ሰው ለልብ ችግር የሚያጋልጡ ሌሎች ነገሮችን ለማየት የሞከሩ ሲሆን ጥናታቸው መንስኤና ውጤቱን ማረጋገጥ እንዳልቻለ አስረድተዋል። "በጥናታችን መንስኤው ላይ መደምደሚያ መስጠት ባንችልም በውጤቱ መሰረት ከመደበኛው የመኝታ ሰዓት ቀደም ብሎ ወይም ዘግይቶ መተኛት የሰውነትን አቆጣጠርን ሊያስተጓጉል ስለሚችል የልብና የደም ሥር ጤና ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያስከትል ጥናቱ አመላክቷል" ሲሉ አጥኚው ዶ/ር ዴቪድ ፕላን ገልጸዋል። "በጣም ችግር የማስከተል ዕድል ያለው የእንቅልፍ ጊዜ ከእኩለ ሌሊት በኋላ ያለው ነው። ምክንያቱ ዘግይቶ የተኛው ሰው የጠዋት ብርሃንን የማየት እድሉን ሊቀንስ ስለሚችል የሰውነት አቆጣጠር እንደገና ይጀምራል" ሲሉም አክለዋል። በብሪቲሽ የልብ ፋውንዴሽን ከፍተኛ የልብ ነርስ የሆኑት ራይጃና ጊብሊን "ይህ ትልቅ ጥናት እንደሚያመለክተው ከምሽቱ 4 እስከ 5 ሰዓት መተኛት ለብዙ ሰዎች ልባቸው ለረጅም ጊዜ ጤናማ እንዲሆን ምቹ ሊሆን ይችላል" ብለዋል። "ሆኖም ይህ ጥናት መንስኤውን እና ውጤቱን ማረጋገጥ እንዳልቻለ ማስታወስ አስፈላጊ ነው። የእንቅልፍ ጊዜ እና ቆይታ ከልብ እና ደም ዝውውር በሽታዎች ጋር ስላለው ተያያዥነት ምርምሮች ያስፈልጋሉ" ሲሉ ገልጸዋል። ነርሷ በቂ እንቅልፍ ማግኘታችን ለአጠቃላይ ጤንነታችን ብሎም ለልባችን እና ለደም ዝውውር ጤናማነት ጠቃሚ ነው። አብዛኞቹ ጎልማሶች ከሰባት እስከ ዘጠኝ ሰዓታት መተኛት ይጠበቅባቸዋል ሲሉም አስረድተዋል። "ይህ ማለት ግን እንቅልፍ የልብ ጤና ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር የሚችል ብቸኛው ምክንያት ነው ማለት አይደልም። የደም ግፊት እና የኮሌስትሮል መጠንን ማወቅ፤ ጤናማ ክብደትን መጠበቅ እና በመደበኛነት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፤ የጨው እና አልኮል መጠጦችን በመቀነስ የአኗኗር ዘይቤን ማጤን በጣም አስፈላጊ ነው። በተጨማሪም የተመጣጠነ ምግብ መመገብ የልብን ጤንነት ለመጠበቅ ይረዳል" ሲሉ ነርስ ራይጃና ጠቅሰዋል። | አዘውትሮ ምሽት አራት ሰዓት አካባቢ መተኛት ለልብ ችግር የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል- ጥናት ከምሽቱ 4 ሰዓት እስከ 5 ሰዓት ባለው ጊዜ አዘውትሮ መተኛት ለተሻለ የልብ ጤንነት እንደሚረዳ በ88 ሺህ በጎ ፈቃደኞች ላይ ጥናት ያደረጉ ተመራማሪዎች አስታወቁ። በዩናይትድ ኪንግደም ባለ አንድ ቡድን በተደረገ ጥናት እንቅልፍ ከውስጣዊው የሰውነት ክፍላችን የጊዜ አቆጣጠር ጋር እንዲጣታም ማድረግ ለልብ ድካም እና ለስትሮክ የመጋለጥ እድልን እንደሚቀንስ ጠቁሟል። የሰውነት ተፈጥሯዊ የ24-ሰዓት ምት ለደኅንነት እና ንቁ ለመሆን አስፈላጊ መሆኑን የሚገልጸው ጥናቱ እንደ የደም ግፊት ባሉ ሂደቶች ላይም ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል ይላል። በአውሮፓ የልብ ጤና ጆርናል ላይ በታተመው በዚህ ጥናት ተመራማሪዎቹ በሰባት ቀናት ውስጥ በእንቅልፍ እና በእንቅልፍ ጊዜ ላይ ከጥናቱ ተሳታፊዎች መረጃን ለማሰባሰብ የእጅ ሰዓት የሚመስል መሳሪያ እንዲያጠልቁ አድርገዋቸዋል። በመሳሪያው አማካኝነት በአማካይ በስድስት ዓመታት ውስጥ በልብ እና በደም ዝውውር ጤና ላይ ያለውን ሁኔታ ተከታትለዋል። በዚህም ከ3,000 በላይ የሚሆኑ ተሳታፊዎች የልብ ችግር [የካርዲዮቫስኩላር] በሽታ ተገኝቶባቸዋል። በጥናቱ መሰረት ለዚህ ችግር የተጋለጡት ከምሽቱ 4 ወይም 5 ሰዓት ቀደም ብለው ወይም ዘግይተው ወደ አልጋ የማምራት ልምድ ያላቸው ሰዎች ላይ ነው። ተመራማሪዎቹ እንደ ዕድሜ፣ የሰውነት ክብደት እና የኮሌስትሮል መጠን ያሉ የአንድን ሰው ለልብ ስጋት የሆኑ ሌሎች ነገሮችን ለማየት ሞክረዋል። ነገርግን ጥናታቸው መንስኤውንና ውጤቱን ማረጋገጥ አልቻለም። ተመራማሪዎቹ እንደ ዕድሜ፣ የሰውነት ክብደት እና የኮሌስትሮል መጠን ያሉ አንድን ሰው ለልብ ችግር የሚያጋልጡ ሌሎች ነገሮችን ለማየት የሞከሩ ሲሆን ጥናታቸው መንስኤና ውጤቱን ማረጋገጥ እንዳልቻለ አስረድተዋል። "በጥናታችን መንስኤው ላይ መደምደሚያ መስጠት ባንችልም በውጤቱ መሰረት ከመደበኛው የመኝታ ሰዓት ቀደም ብሎ ወይም ዘግይቶ መተኛት የሰውነትን አቆጣጠርን ሊያስተጓጉል ስለሚችል የልብና የደም ሥር ጤና ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያስከትል ጥናቱ አመላክቷል" ሲሉ አጥኚው ዶ/ር ዴቪድ ፕላን ገልጸዋል። "በጣም ችግር የማስከተል ዕድል ያለው የእንቅልፍ ጊዜ ከእኩለ ሌሊት በኋላ ያለው ነው። ምክንያቱ ዘግይቶ የተኛው ሰው የጠዋት ብርሃንን የማየት እድሉን ሊቀንስ ስለሚችል የሰውነት አቆጣጠር እንደገና ይጀምራል" ሲሉም አክለዋል። በብሪቲሽ የልብ ፋውንዴሽን ከፍተኛ የልብ ነርስ የሆኑት ራይጃና ጊብሊን "ይህ ትልቅ ጥናት እንደሚያመለክተው ከምሽቱ 4 እስከ 5 ሰዓት መተኛት ለብዙ ሰዎች ልባቸው ለረጅም ጊዜ ጤናማ እንዲሆን ምቹ ሊሆን ይችላል" ብለዋል። "ሆኖም ይህ ጥናት መንስኤውን እና ውጤቱን ማረጋገጥ እንዳልቻለ ማስታወስ አስፈላጊ ነው። የእንቅልፍ ጊዜ እና ቆይታ ከልብ እና ደም ዝውውር በሽታዎች ጋር ስላለው ተያያዥነት ምርምሮች ያስፈልጋሉ" ሲሉ ገልጸዋል። ነርሷ በቂ እንቅልፍ ማግኘታችን ለአጠቃላይ ጤንነታችን ብሎም ለልባችን እና ለደም ዝውውር ጤናማነት ጠቃሚ ነው። አብዛኞቹ ጎልማሶች ከሰባት እስከ ዘጠኝ ሰዓታት መተኛት ይጠበቅባቸዋል ሲሉም አስረድተዋል። "ይህ ማለት ግን እንቅልፍ የልብ ጤና ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር የሚችል ብቸኛው ምክንያት ነው ማለት አይደልም። የደም ግፊት እና የኮሌስትሮል መጠንን ማወቅ፤ ጤናማ ክብደትን መጠበቅ እና በመደበኛነት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፤ የጨው እና አልኮል መጠጦችን በመቀነስ የአኗኗር ዘይቤን ማጤን በጣም አስፈላጊ ነው። በተጨማሪም የተመጣጠነ ምግብ መመገብ የልብን ጤንነት ለመጠበቅ ይረዳል" ሲሉ ነርስ ራይጃና ጠቅሰዋል። | https://www.bbc.com/amharic/59230351 |
2health
| ኮሮናቫይረስ: 'ልጆቼ እናታቸው በኮቪድ እንደሞተች ስለማያውቁ ትመጣለች ብለው ይጠብቃሉ' | ሕንድን ያመሰው ሁለተኛው የኮቪድ ሞገድ በሺህዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦችን የማይነገር ሃዘን ጥሎባቸዋል። መከራ፣ ቸልተኝነት፣ አለመዘጋጀት እና በደንብ ያልታሰበበት የክትባት ዕቅድ ለብዙዎች ሞት ምክንያት ሆኗል። አልቱፍ ሻምሲ ሐዘንም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕንዳውያ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ከገጠማቸው ልብን የሚሰብር ሐዘን መካከል አንዱ ነው። ሚያዝያ መጀመሪያ ላይ ቤተሰቤ እንደተለመደው ደስተኛ ነበር። እኔና ባለቤቴ ሪሃብ ሦስተኛ ልጃችንን እየጠበቅን ነበር። የማህጸን ሐኪሟ ከሚያዝያ 22 በፊት ሆስፒታል እንድንመጣ መክሮናል። ሪሐብ በእርግዝናዋ 38ኛ ሳምንት ውስጥ ስለነበረች በሚቀጥለው ቀን ለማዋለድ ነበር ዕቅዱ። ነፍሰጡር ሴቶች ከመውለዳቸው በፊት ኮቪድ እንዲመረመሩ መመሪያ ወጥቷል። ተመረመረች። ኮሮና እንዳለባት ስናውቅ ደነገጥን። ሆስፒታሉ ኮሮና ያለባቸውን አይቀበልም። ሪሃብ ጊዜ ስለነበራት ሐኪሟ ሌላ ቀጠሮ ሰጠን። ኮቪዱ ላይ እንድናተኩርም ነገረችን። ከጥቂት ቀናት በኋላ ሪሃብ ከፍተኛ ትኩሳት አጋጠማት። ሚያዝያ 28 በሐኪሟ ምክር መሠረት የኮቪድ ህክምና ወደሚሰትበት ሆስፒታል አስገባናት። ሆስፒታል ከገባች ሁለት ቀን ሆናት። ሪሃብ ጠንካራ መድኃኒት እየወሰደች በመሆኑ ህጻኑን እንደምናጣ ሐኪሙ ነገረን። አመሻሹ ላይ ህመሟ ተባብሶ የኦክስጂን ድጋፍ አስፈለጋት። ዶክተሮችም ህጻኑን በድንገተኛ ቀዶ ጥገና እንዲወለድ ወሰኑ። ሆስፒታሉ በከፍተኛ ደም መፍሰስ ምክንያት እስከሞት የሚደርስ ከፍተኛ ዕድል እንዳለ የሚገልጹ ሰነዶችን እንድንፈርም አደረገ። ከገደል አፋፍ ዘሎ በሠላም የማረፍ ተስፋ ዓይነት ነው። ከቀዶ ጥገናው በኋላ ሪሃብ ከፍተኛ የህክምና ክትትል ስለሚያስፈልጋት ሌላ ሆስፒታል የጽኑ ህሙማን አልጋ እንድፈልግ ተነገረኝ። የተሟላ የኮቪድ ህክምና ቢያስፈልጋትም እነሱ ሊያሟሉ አልቻሉም። በዚህ ጊዜ ልጅ እንደወለድን ረስቻለሁ። በአዕምሮዬ የሚመላለሰው ብቸኛው ነገር ሪሃብን ማዳን ነበር። ለቀዶ ህክምናው አእምሮዬን እያዘጋጀሁ እያለ መጥፎ ዜና መጣ። ባለቤቴ ኮሮና እንዳለበት ያወቅነው አባቴም ዴልሂ በሚገኝ ሌላ ሆስፒታል የገባ ጊዜ ሲሆን ጤንነቱ እያሽቆለቆለ ነበር። እናቴም ኮሮና የተገኘባት ሲሆን በአነስተኛ የኦክስጂን ድጋፍ በቤት ውስጥ ነበረች። ባለቤቷ እና የልጇ ሚስት ህይወታቸውን ለማትረፍ እየታገሉ እንደሆነ እንኳን አታውቅም። ዓለም በዙሪያዬ ሊፈርስ ከጫፍ የደረሰ መሰለ። እንዲድኑ እየጸለይኩኝ የጽኑ ህሙማን አልጋ ፍለጋዬን አጧጡፍ ጀመር። ሚያዝያ 29 ሴት ልጄ ተወለደች። አልጋ ማግኘት ስላልቻልኩ ሪሃብ ወደ ጊዜያዊ የጽኑ ህሙማን ክፍል እንድትዛወር ተደረገ። ሆስፒታሉ በቂ ነርሶች አልነበሩትም። እኔም በኮሮና ተያዝኩኝ። የራሴን ትቼ ከሪሃብ ጎን ለመቆም ወሰንኩ። ስለመድኃኒቷ ያለማቋረጥ ነርሶችን ማሳሰብ ነበረብኝ። እነሱ ደግሞ ወደ ሌላ ቦታ እንድወስዳት በተደጋጋሚ ይነግሩኛል። አጋዥ መተንፈፈሻ መሣሪያ (ቬንትሌተር) ያለው አልጋ ካገኘሁ በሚል የማውቃቸው ሰዎች ሁሉ ጋር ደዋወልኩኝ። በመጨረሻም የየጽኑ ህሙማን አልጋ አገኘሁላት። እሷን የሚወስዳት የህይወት ድጋፍ መሣሪያ ያለው አምቡላንስ ግን አልነበረም። ሆስፒታሉ ህክምናውን እንዲቀጥልላት ተማጸንኩኝ። እነሱም እሷን ለማዳን የቻሉትን ሁሉ አደረጉ። ግንቦት አንድን መቼም አልረሳውም። በርካታ ሆስፒታሎች ከፍተኛ የኦክስጂን እጥረት እንደገጠማቸው ይገልጹ ነበር። ሪሃብ የምትታከምበት ሆስፒታል ያሉ ሠራተኞችም ኦክስጂን ሊያልቅባቸው እንደሆነ ነግረውኝ ሲሊንደሮችን እንዳዘጋጅ ጠየቁኝ። አመሻሹ ላይ አባቴ ከሚታከምበት ሆስፒታል ተደውሎልኝ ጤንነቱ በፍጥነት እያሽቆለቆለ እንደሆነ ተነገረኝ። እዚያ ስደርስ አባቴ ህይወቱ አልፏል። ደንዝዤ ነበር። አስከሬኑን እያየሁ ከሪሃብ ሆስፒታል ስለኦክስጅን እጥረት የሚደርሰኝን መልዕክት እያነበብኩ ነበር። እናቴም በጥሩ ሁኔታ ላይ አይደለችም። የሰባት እና የአምስት ዓመት ሴት ልጆቼ እናታቸው እና አዲሷ እህታቸው ቃል በተገባው መሠረት ለምን ቤት እንዳልመጡ ይጠይቁ ነበር። ለእናቴ የ42 ዓመት የትዳር አጋሯን ሞት መንገር ከባድ ነበር። እሱ የቤተሰቡ ጠባቂ ነበር። የእሱ ማለፍ የበለጠ ተጋላጭ እንደሆንኩ እንዲሰማኝ አደረገኝ። እሱን ቀብሬ በፍጥነት ወደ ሪሃብ ሆስፒታል ተመለስኩ። የእሷም ጤንነት አሽቆልቁሏል። በቀጣዮቹ 11 ቀናት በተስፋ እና በተስፋ መቁረጥ መካከል ስወዛወዝ ቆየሁ። ሪሃብ በየቀኑ በመጠኑ እየተሻላት እንደሆነ ቢነገረኝም በከፋ ሁኔታ ውስጥ ነበረች። ከሁለት ቀናት በኋላ ኩላሊቶቿ ድጋፍ አስፈለጋቸው። በማሽን የተደገፈ የደም እጥበት [ዲያሊሲስ] ጀመረች። የኦክስጂን መጠኗ መሻሻል ሲጀምር ከህክምና ክፍሉ እንድወጣ ተነገረኝ። ከሁለት ቀን በኋላ ቬንትሌተሩን ሲነቅሉላት እንደማያት ተነግሮኛል። የዚያኑ ዕለት ምሽት 2 ሰዓት ገደማ ሪሀብን እንድትንከባከብ የቀጠርኳት የግል ነርስ ጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳለች ነገረችኝ። እናቴን እና ሴት ልጆቼን ለማየት ወደ ቤት ተመለስኩኝ። ከምሽቱ 5 ሰዓት ገደማ ከሆስፒታሉ ተደውሎ በፍጥነት እንድመለስ ተጠራሁኝ። ተጣድፌ ሆስፒታል ስደርስ ልቤ በአፌ ልትወጣ ደረሳ ነበር። ሪሃብ ግን በህይወት አልቆየችኝም። የሆስፒታሉ ሠራተኞች "የልብ ችግር" እንደነበር ነግረውኛል። ሙሉ በሙሉ ተሰበርኩኝ። እኔ ጠንካራ ለመሆን እየሞከርኩ ነበር። ቤተሰቦቼን ተንከባክቤ በሚቀጥለው ቀን ባለቤቴን ለማየት እና ላወራት ተስፋ አድርጌ ነበር። ሊደረመስ ከቋፍ ደርሶ የነበረው ዓለሜ ፈረሰ። የነበረኝ ብቸኛው ጭንቀት እናታቸው ወደ ቤት መቼም እንደማትመለስ ለልጆቼ እንዴት እንደምነግራቸው ነው። እስካሁንም አልነገርኳቸውም። እንዴት ማድረግ እንዳለብኝም አላውቅም። በየቀኑ ስለ እሷ ይጠይቁኛል። አሁንም ሆስፒታል መሆኗን እነግራቸዋለሁ። እህቴ አዲሷን ሕፃን በመጠበቅ እየረዳችኝ ነው። ሪሃብ አስደናቂ ሴት ብቻ አይደለችም። አፍቃሪ እና አሳቢ እናት፣ ሚስት፣ ሴት እና ምራትም ነበረች። ደፋር እና በራስ መተማመን የነበራት ስለነበረች ነው የታገለችው። አዲስ የተወለደችውን ልጃችንን ለማየት አልታደለችም። የሪሃብ ስጦታ አድርጌ ስለምወስዳት እንከባከባታለሁ። ለልጆቼ አባት እና እናት ለመሆን እየሞከርኩ ነው። ሪሃብ በህይወታችን የፈጠረችው ክፍተትን ግን በጭራሽ መሙላት አልችልም። እሷን ለማዳን ከዚህ በላይ ማድረግ የምችለው ሌላ ነገር ይኖር ይሆን? እያልኩ አስባለሁ። የተሻለ ሆስፒታል ባገኝ ኖሮ በህይወት ትኖር ነበር? እላለሁ። ቀላል መልሶች የሉትም። በእርግጠኝነት ግን የኮቪድ ክትባቶች እንደ ሪሃብ ያሉ ብዙ ሴቶችን ማዳን ይችላሉ የሚል እምነት አለኝ። ክትባት ብታገኝ ኖሮ በሕይወት ትኖር ይሆናል። ለእርሷ ምንም ክትባት አልተገኘም። በከባድ የኮቪድ በሽታ ለተያዙ እርጉዝ ሴቶች መንግሥት ክትባቱን ገና አላጸደቀም። የህይወቴን አንጸባራቂ ብርሃን አጥቻለሁ። ባለፍኩበት መንገድ ሌላ ሰው እንዲያልፍ አልፈልግም። በሌኛው ዓለም እስከማይሽ ደህና ሁኚ ሪሃብ። | ኮሮናቫይረስ: 'ልጆቼ እናታቸው በኮቪድ እንደሞተች ስለማያውቁ ትመጣለች ብለው ይጠብቃሉ' ሕንድን ያመሰው ሁለተኛው የኮቪድ ሞገድ በሺህዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦችን የማይነገር ሃዘን ጥሎባቸዋል። መከራ፣ ቸልተኝነት፣ አለመዘጋጀት እና በደንብ ያልታሰበበት የክትባት ዕቅድ ለብዙዎች ሞት ምክንያት ሆኗል። አልቱፍ ሻምሲ ሐዘንም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕንዳውያ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ከገጠማቸው ልብን የሚሰብር ሐዘን መካከል አንዱ ነው። ሚያዝያ መጀመሪያ ላይ ቤተሰቤ እንደተለመደው ደስተኛ ነበር። እኔና ባለቤቴ ሪሃብ ሦስተኛ ልጃችንን እየጠበቅን ነበር። የማህጸን ሐኪሟ ከሚያዝያ 22 በፊት ሆስፒታል እንድንመጣ መክሮናል። ሪሐብ በእርግዝናዋ 38ኛ ሳምንት ውስጥ ስለነበረች በሚቀጥለው ቀን ለማዋለድ ነበር ዕቅዱ። ነፍሰጡር ሴቶች ከመውለዳቸው በፊት ኮቪድ እንዲመረመሩ መመሪያ ወጥቷል። ተመረመረች። ኮሮና እንዳለባት ስናውቅ ደነገጥን። ሆስፒታሉ ኮሮና ያለባቸውን አይቀበልም። ሪሃብ ጊዜ ስለነበራት ሐኪሟ ሌላ ቀጠሮ ሰጠን። ኮቪዱ ላይ እንድናተኩርም ነገረችን። ከጥቂት ቀናት በኋላ ሪሃብ ከፍተኛ ትኩሳት አጋጠማት። ሚያዝያ 28 በሐኪሟ ምክር መሠረት የኮቪድ ህክምና ወደሚሰትበት ሆስፒታል አስገባናት። ሆስፒታል ከገባች ሁለት ቀን ሆናት። ሪሃብ ጠንካራ መድኃኒት እየወሰደች በመሆኑ ህጻኑን እንደምናጣ ሐኪሙ ነገረን። አመሻሹ ላይ ህመሟ ተባብሶ የኦክስጂን ድጋፍ አስፈለጋት። ዶክተሮችም ህጻኑን በድንገተኛ ቀዶ ጥገና እንዲወለድ ወሰኑ። ሆስፒታሉ በከፍተኛ ደም መፍሰስ ምክንያት እስከሞት የሚደርስ ከፍተኛ ዕድል እንዳለ የሚገልጹ ሰነዶችን እንድንፈርም አደረገ። ከገደል አፋፍ ዘሎ በሠላም የማረፍ ተስፋ ዓይነት ነው። ከቀዶ ጥገናው በኋላ ሪሃብ ከፍተኛ የህክምና ክትትል ስለሚያስፈልጋት ሌላ ሆስፒታል የጽኑ ህሙማን አልጋ እንድፈልግ ተነገረኝ። የተሟላ የኮቪድ ህክምና ቢያስፈልጋትም እነሱ ሊያሟሉ አልቻሉም። በዚህ ጊዜ ልጅ እንደወለድን ረስቻለሁ። በአዕምሮዬ የሚመላለሰው ብቸኛው ነገር ሪሃብን ማዳን ነበር። ለቀዶ ህክምናው አእምሮዬን እያዘጋጀሁ እያለ መጥፎ ዜና መጣ። ባለቤቴ ኮሮና እንዳለበት ያወቅነው አባቴም ዴልሂ በሚገኝ ሌላ ሆስፒታል የገባ ጊዜ ሲሆን ጤንነቱ እያሽቆለቆለ ነበር። እናቴም ኮሮና የተገኘባት ሲሆን በአነስተኛ የኦክስጂን ድጋፍ በቤት ውስጥ ነበረች። ባለቤቷ እና የልጇ ሚስት ህይወታቸውን ለማትረፍ እየታገሉ እንደሆነ እንኳን አታውቅም። ዓለም በዙሪያዬ ሊፈርስ ከጫፍ የደረሰ መሰለ። እንዲድኑ እየጸለይኩኝ የጽኑ ህሙማን አልጋ ፍለጋዬን አጧጡፍ ጀመር። ሚያዝያ 29 ሴት ልጄ ተወለደች። አልጋ ማግኘት ስላልቻልኩ ሪሃብ ወደ ጊዜያዊ የጽኑ ህሙማን ክፍል እንድትዛወር ተደረገ። ሆስፒታሉ በቂ ነርሶች አልነበሩትም። እኔም በኮሮና ተያዝኩኝ። የራሴን ትቼ ከሪሃብ ጎን ለመቆም ወሰንኩ። ስለመድኃኒቷ ያለማቋረጥ ነርሶችን ማሳሰብ ነበረብኝ። እነሱ ደግሞ ወደ ሌላ ቦታ እንድወስዳት በተደጋጋሚ ይነግሩኛል። አጋዥ መተንፈፈሻ መሣሪያ (ቬንትሌተር) ያለው አልጋ ካገኘሁ በሚል የማውቃቸው ሰዎች ሁሉ ጋር ደዋወልኩኝ። በመጨረሻም የየጽኑ ህሙማን አልጋ አገኘሁላት። እሷን የሚወስዳት የህይወት ድጋፍ መሣሪያ ያለው አምቡላንስ ግን አልነበረም። ሆስፒታሉ ህክምናውን እንዲቀጥልላት ተማጸንኩኝ። እነሱም እሷን ለማዳን የቻሉትን ሁሉ አደረጉ። ግንቦት አንድን መቼም አልረሳውም። በርካታ ሆስፒታሎች ከፍተኛ የኦክስጂን እጥረት እንደገጠማቸው ይገልጹ ነበር። ሪሃብ የምትታከምበት ሆስፒታል ያሉ ሠራተኞችም ኦክስጂን ሊያልቅባቸው እንደሆነ ነግረውኝ ሲሊንደሮችን እንዳዘጋጅ ጠየቁኝ። አመሻሹ ላይ አባቴ ከሚታከምበት ሆስፒታል ተደውሎልኝ ጤንነቱ በፍጥነት እያሽቆለቆለ እንደሆነ ተነገረኝ። እዚያ ስደርስ አባቴ ህይወቱ አልፏል። ደንዝዤ ነበር። አስከሬኑን እያየሁ ከሪሃብ ሆስፒታል ስለኦክስጅን እጥረት የሚደርሰኝን መልዕክት እያነበብኩ ነበር። እናቴም በጥሩ ሁኔታ ላይ አይደለችም። የሰባት እና የአምስት ዓመት ሴት ልጆቼ እናታቸው እና አዲሷ እህታቸው ቃል በተገባው መሠረት ለምን ቤት እንዳልመጡ ይጠይቁ ነበር። ለእናቴ የ42 ዓመት የትዳር አጋሯን ሞት መንገር ከባድ ነበር። እሱ የቤተሰቡ ጠባቂ ነበር። የእሱ ማለፍ የበለጠ ተጋላጭ እንደሆንኩ እንዲሰማኝ አደረገኝ። እሱን ቀብሬ በፍጥነት ወደ ሪሃብ ሆስፒታል ተመለስኩ። የእሷም ጤንነት አሽቆልቁሏል። በቀጣዮቹ 11 ቀናት በተስፋ እና በተስፋ መቁረጥ መካከል ስወዛወዝ ቆየሁ። ሪሃብ በየቀኑ በመጠኑ እየተሻላት እንደሆነ ቢነገረኝም በከፋ ሁኔታ ውስጥ ነበረች። ከሁለት ቀናት በኋላ ኩላሊቶቿ ድጋፍ አስፈለጋቸው። በማሽን የተደገፈ የደም እጥበት [ዲያሊሲስ] ጀመረች። የኦክስጂን መጠኗ መሻሻል ሲጀምር ከህክምና ክፍሉ እንድወጣ ተነገረኝ። ከሁለት ቀን በኋላ ቬንትሌተሩን ሲነቅሉላት እንደማያት ተነግሮኛል። የዚያኑ ዕለት ምሽት 2 ሰዓት ገደማ ሪሀብን እንድትንከባከብ የቀጠርኳት የግል ነርስ ጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳለች ነገረችኝ። እናቴን እና ሴት ልጆቼን ለማየት ወደ ቤት ተመለስኩኝ። ከምሽቱ 5 ሰዓት ገደማ ከሆስፒታሉ ተደውሎ በፍጥነት እንድመለስ ተጠራሁኝ። ተጣድፌ ሆስፒታል ስደርስ ልቤ በአፌ ልትወጣ ደረሳ ነበር። ሪሃብ ግን በህይወት አልቆየችኝም። የሆስፒታሉ ሠራተኞች "የልብ ችግር" እንደነበር ነግረውኛል። ሙሉ በሙሉ ተሰበርኩኝ። እኔ ጠንካራ ለመሆን እየሞከርኩ ነበር። ቤተሰቦቼን ተንከባክቤ በሚቀጥለው ቀን ባለቤቴን ለማየት እና ላወራት ተስፋ አድርጌ ነበር። ሊደረመስ ከቋፍ ደርሶ የነበረው ዓለሜ ፈረሰ። የነበረኝ ብቸኛው ጭንቀት እናታቸው ወደ ቤት መቼም እንደማትመለስ ለልጆቼ እንዴት እንደምነግራቸው ነው። እስካሁንም አልነገርኳቸውም። እንዴት ማድረግ እንዳለብኝም አላውቅም። በየቀኑ ስለ እሷ ይጠይቁኛል። አሁንም ሆስፒታል መሆኗን እነግራቸዋለሁ። እህቴ አዲሷን ሕፃን በመጠበቅ እየረዳችኝ ነው። ሪሃብ አስደናቂ ሴት ብቻ አይደለችም። አፍቃሪ እና አሳቢ እናት፣ ሚስት፣ ሴት እና ምራትም ነበረች። ደፋር እና በራስ መተማመን የነበራት ስለነበረች ነው የታገለችው። አዲስ የተወለደችውን ልጃችንን ለማየት አልታደለችም። የሪሃብ ስጦታ አድርጌ ስለምወስዳት እንከባከባታለሁ። ለልጆቼ አባት እና እናት ለመሆን እየሞከርኩ ነው። ሪሃብ በህይወታችን የፈጠረችው ክፍተትን ግን በጭራሽ መሙላት አልችልም። እሷን ለማዳን ከዚህ በላይ ማድረግ የምችለው ሌላ ነገር ይኖር ይሆን? እያልኩ አስባለሁ። የተሻለ ሆስፒታል ባገኝ ኖሮ በህይወት ትኖር ነበር? እላለሁ። ቀላል መልሶች የሉትም። በእርግጠኝነት ግን የኮቪድ ክትባቶች እንደ ሪሃብ ያሉ ብዙ ሴቶችን ማዳን ይችላሉ የሚል እምነት አለኝ። ክትባት ብታገኝ ኖሮ በሕይወት ትኖር ይሆናል። ለእርሷ ምንም ክትባት አልተገኘም። በከባድ የኮቪድ በሽታ ለተያዙ እርጉዝ ሴቶች መንግሥት ክትባቱን ገና አላጸደቀም። የህይወቴን አንጸባራቂ ብርሃን አጥቻለሁ። ባለፍኩበት መንገድ ሌላ ሰው እንዲያልፍ አልፈልግም። በሌኛው ዓለም እስከማይሽ ደህና ሁኚ ሪሃብ። | https://www.bbc.com/amharic/news-57534543 |
3politics
| ኢሰመኮ በኮንሶ ያሉ ተፈናቃዮች የሰብዓዊ መብት አያያዝ የከፋ ነው አለ | የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኮንሶ ያሉ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሰብዓዊ መብት አያያዝ የከፋ ነው አለ። ኢሰመኮ ይህን ያለው በደቡብ ክልል በኮንሶ ዞን እና በሦስት ልዩ ወረዳዎች በሚገኙ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታን በተመለከተ ይፋ ባደረገው ሪፖርት ነው። የሰብዓዊ መብት ኮሚሽኑ በኮንሶ ዞን፣ በአሌ ልዩ ወረዳ፣ በደራሼ ልዩ ወረዳ እና በአማሮ ልዩ ወረዳ በአጠቃላይ የተመዘገቡ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ከ145 ሺህ በላይ መሆኑን ገልጿል። ኮሚሽኑ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮቹ ሰብዓዊ ድጋፍ እንደማያገኙ እና በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚኖሩ ገልጿል። የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ተቋሙ ክትትል ባደረገባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ተፈናቃዮች “በቂ የሰብዓዊ ድጋፍ ባለማግኘታቸው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ከመሆኑም ባሻገር፣ በተለያዩ ጊዜያት በዚህ አካባቢ የሚያገረሹ ግጭቶች የተፈናቀሉ ሰዎችን ለተደራራቢ ጉዳት እና መፈናቀል እየዳረጉ ነው” ብለዋል። ስለዚህም የሚመለከታቸው አካላት ለመፈናቀል መንስዔ የሆኑ ግጭቶችን ማስወገድ፣ በቂ የሰብዓዊ ድጋፍ ማቅረብ እና ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር ላይ ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው አመልክተዋል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ይህን ሪፖርት ያወጣው የአገር ውስጥ ተፈናቃዮቹ በሚገኙባቸው መጠለያ ጣቢያዎች እና ተቀባይ ማኅበረሰብ ጋር በመዘዋወር ተፈናቃዮችን፣ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎችን እና ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት በማነጋገር እና የሰነድ ማስረጃዎች በማሰባሰብ ነው። ተፈናቃዮች ቀያቸውን ጥለው እንዲሄዱ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል አንዱ እና ዋነኛው ግጭት መሆኑን ኮሚሽኑ ጠቁሟል። የአካባቢውን ነዋሪዎች ለግጭት ከሚዳርጉ ምክንያቶች መካከልም የእርሻ፣ የግጦሽ መሬት እና የደን ሃብት ይዞታ ይገባኛል የሚለው ምክንያት አንዱ ነው። ሌሎች ጉዳዮች ደግሞ የአስተዳደር መዋቅር በሚጠይቁ እና መዋቅሩን በሚቃወሙ እንዲሁም የአስተዳደር ወሰን ግጭት በምክንያት ነት ይጠቀሳል። ኢሰመኮ የክልሉ እና ብሔራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለተፈናቃዮች በቂ እና ጊዜውን የጠበቀ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያቀርቡ እና እንዲያስተባብሩ ጠይቋል። ለመፈናቀል መንስኤ የሆኑ የአስተዳደር መዋቅር እና የአስተዳደር ወሰን ጥያቄዎችን የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ባሳተፈ መልኩ አፋጣኝ መፍትሔ ሊሰጥ ይገባልም ብሏል። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮንሶ አካባቢ ባለፉት ዓመታት በተለያዩ ምክንያቶች በማኅበረሰቦች መካከል በተደጋጋሚ በሚከሰቱ ግጭቶች ከሚፈናቀሉት በተጨማሪ፤ የበርካታ ሰዎች ሕይወት የጠፋ ሲሆን፣ ከፍተኛ መጠን ያለው ንብረትም ለውድመት ተዳርጓል። | ኢሰመኮ በኮንሶ ያሉ ተፈናቃዮች የሰብዓዊ መብት አያያዝ የከፋ ነው አለ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኮንሶ ያሉ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሰብዓዊ መብት አያያዝ የከፋ ነው አለ። ኢሰመኮ ይህን ያለው በደቡብ ክልል በኮንሶ ዞን እና በሦስት ልዩ ወረዳዎች በሚገኙ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታን በተመለከተ ይፋ ባደረገው ሪፖርት ነው። የሰብዓዊ መብት ኮሚሽኑ በኮንሶ ዞን፣ በአሌ ልዩ ወረዳ፣ በደራሼ ልዩ ወረዳ እና በአማሮ ልዩ ወረዳ በአጠቃላይ የተመዘገቡ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ከ145 ሺህ በላይ መሆኑን ገልጿል። ኮሚሽኑ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮቹ ሰብዓዊ ድጋፍ እንደማያገኙ እና በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚኖሩ ገልጿል። የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ተቋሙ ክትትል ባደረገባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ተፈናቃዮች “በቂ የሰብዓዊ ድጋፍ ባለማግኘታቸው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ከመሆኑም ባሻገር፣ በተለያዩ ጊዜያት በዚህ አካባቢ የሚያገረሹ ግጭቶች የተፈናቀሉ ሰዎችን ለተደራራቢ ጉዳት እና መፈናቀል እየዳረጉ ነው” ብለዋል። ስለዚህም የሚመለከታቸው አካላት ለመፈናቀል መንስዔ የሆኑ ግጭቶችን ማስወገድ፣ በቂ የሰብዓዊ ድጋፍ ማቅረብ እና ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር ላይ ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው አመልክተዋል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ይህን ሪፖርት ያወጣው የአገር ውስጥ ተፈናቃዮቹ በሚገኙባቸው መጠለያ ጣቢያዎች እና ተቀባይ ማኅበረሰብ ጋር በመዘዋወር ተፈናቃዮችን፣ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎችን እና ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት በማነጋገር እና የሰነድ ማስረጃዎች በማሰባሰብ ነው። ተፈናቃዮች ቀያቸውን ጥለው እንዲሄዱ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል አንዱ እና ዋነኛው ግጭት መሆኑን ኮሚሽኑ ጠቁሟል። የአካባቢውን ነዋሪዎች ለግጭት ከሚዳርጉ ምክንያቶች መካከልም የእርሻ፣ የግጦሽ መሬት እና የደን ሃብት ይዞታ ይገባኛል የሚለው ምክንያት አንዱ ነው። ሌሎች ጉዳዮች ደግሞ የአስተዳደር መዋቅር በሚጠይቁ እና መዋቅሩን በሚቃወሙ እንዲሁም የአስተዳደር ወሰን ግጭት በምክንያት ነት ይጠቀሳል። ኢሰመኮ የክልሉ እና ብሔራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለተፈናቃዮች በቂ እና ጊዜውን የጠበቀ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያቀርቡ እና እንዲያስተባብሩ ጠይቋል። ለመፈናቀል መንስኤ የሆኑ የአስተዳደር መዋቅር እና የአስተዳደር ወሰን ጥያቄዎችን የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ባሳተፈ መልኩ አፋጣኝ መፍትሔ ሊሰጥ ይገባልም ብሏል። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮንሶ አካባቢ ባለፉት ዓመታት በተለያዩ ምክንያቶች በማኅበረሰቦች መካከል በተደጋጋሚ በሚከሰቱ ግጭቶች ከሚፈናቀሉት በተጨማሪ፤ የበርካታ ሰዎች ሕይወት የጠፋ ሲሆን፣ ከፍተኛ መጠን ያለው ንብረትም ለውድመት ተዳርጓል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/ckv27jv55xjo |